#አላገባህም
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ
፡
፡
#ዴርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///
ፀደይና ዘሚካኤል ዶ/ሩን ለማግኘት ቦንጋ ከተማ ይገኛሉ፡፡ይሄ ጉዞ እንደዚህ አልነበረም የታሰበው፡፡ሚካኤልና እሷ ነበሩ ለሳምንታት አብረው ለመሄድ ሲዘጋጁ የነበሩት፡፡ከዛ ዝግጅቱ ሁሉ ተጠናቆ…ሚካኤል ቻርተር አውሮፕላን ተከራይቶ ወደቦንጋ ለመብረር ከአዳማ ተነስተው አውሮፕላኑ ወደሚገኝበት አዲስ አበባ ሲደርሱ ዘሚካኤል ጠበቃቸው፡፡
ሁለቱም ያልጠቁት ነገር ስለሆነ በጣም ነበር ግራ የተጋቡት፡፡ዘሚካኤል እንደአጋጣሚ ከአዲስአለም ጋር ሲደዋወል ነበር ስለጉዞው የነገረችው፡፡
ለማናቸውም ሰላምታ ሳይሰጥ‹‹ፀዲ ከእኔ ጋር ነው መሄድ ያለብሽ?››አላት፡፡
‹‹ማለት…?ለምን ሲባል?››
‹‹በቃ ካንቺ ጋር መሄድና አብሬሽ መሆን እፈልጋለው››
ሚካኤል እጁን አጣጥፎ በገረሜታ እና በትዝብት እየተከታተላቸው ነው፡፡ፀደይን በተመለከተ እንዲህ ሲሪዬስ በመሆኑ ደስታ ተሰምቶታል፡፡
‹‹አይ…ከሚኪ ጋር ነው የምንሄደው…..አንተን ማስቸገር አልፈልግም››ኮስተር ብላ ተቃወመችው፡፡
እሱም ከእሷ በጠነከረ መኮሳተር‹‹እኔ ደግሞ አልስማማም….በችግርሽ ጊዜ አብሬሽ መሆን እፈልጋለው….የአባትሽን አድራሻ ብታገኚም ባታገኚም አብሬሽ ሆኜ ደስታሽንም ሆነ ሀዘንሽን መካፈል አለብኝ››ብሎ ግግም አለ፡፡
ሚካኤል ፀአዳ ስለ/ዶሩ እንደዋሸችው ስለሚያውቅ በውስጡ ፈገግ እያለ‹‹ፀዲ አንዴ ላናግርሽ?››አላት፡፡
‹‹ቆይ ጠብቀኝ መጣው››ብላው ከዘሚካኤል ተለየችና ወደሚካኤል ሄደች፡፡
‹‹ፀዲ እሱ አንዴ ከጠመመ እሺ አይልም..››አላት፡፡
‹‹እና ከእሱ ጋር ሄጄ እንዴት ልሆን ነው?››
‹‹አሪፍ ነው እንደውም…ይሄ የእግዚያብሄር የራሱ እቅድ ይሆናል…ሁኔታዎችን እንዳመጣጣቸው ትወጫቸዋለሽ… ከሰውዬው የሆነ ጠቃሚ መረጃ ብናገኝ እንኳን እሱን አስረድቶ ማሳመን ከባድ ነው የሚሆንብን .. በኃላ እንዲህ ነው የተፈጠረው..እንደዛ ነው የሆነው ከምንል ቀጥታ ከፈረሱ አፍ ቢሰማ ነው የሚሻለው››
‹‹አረ ተው ሚኪ..››
‹‹ግድ የለሽም ባንቺ እተማመንብሻለው፡፡››አለና ጉንጮን ስሞ በፈገግታ በመጣበት መኪና ተመልሶ ሄደ፡፡
///
እንግዲህ በዚህ ሁኔታ ነው ሁለቱ ቦንጋ ከተማ ሊገኙ የቻሉት፡፡እንደደረሱ ፀደይ ከዘሚካኤል ዞር አለችን የዶ/ሩ ነው ተብሎ በተሰጣት ስልክ ደውላ ነበር፡፡የዶ/ር ወንድም ነኝ የሚል ሰው ነበር አንስቶ ያዋራት፡፡‹‹ለምን እንደመጣችና ዶ/ርን ለምን ጉዳይ እንደፈለገችው በአጭሩ ነገረችው፡፡
‹‹ላናግረውና መልሼ ልደውልልሽ ››አለና ስልኩን ዘጋ፡፡ሰውዬው መልሶ እስኪደውል ለሀያ ደቂቃ ተጨንቃ ነበር፡፡‹‹አይ ማግኘት አልፈልግም ቢል ምን አደርጋለው?››የሚልው ሀሳብ ትንፋሽ እስኪያጥራት ድረስ ነበር ያስጨነቃት፡፡ደውሎ ግን አስደሳች ነገር ነው የነገራት፡፡ በፈለጉት ሰዓት መምጣት እንደሚችሉ እና ሊያናግራቸው ፍቃደኛ እንደሆነ ነገራት፡፡ጊዜ ሳያባክኑ ወዲያው ነበር ባጀጃጅ በመከራየት ከከተማው የአንድ ሰዓት መንገድ ወደሚርቅ ገጠር ጉዞ ጀመሩ፡፡
እየሄዱ ሳሉ በገጠሩ ውበት ተደምማ..ዶዶላ ሆኜ አልፎ እልፎ ገጠር ሄድ ነበር..እዛም እንዲህ ውብ ነበር….እና በጣም ነበር ደስተኛ የምሆነው፡፡››
‹‹ገጠር ዘመድ ነበረሽ?››
‹‹አይ የጎደኛዬ ቤተሰቦች ገጠር ነበሩ.. እሱ ነበር ይዞኝ የሚሄደው››
‹‹ጓደኛዬ ስትይ…?››
‹‹የምስር አባት››
ወደራሱ ጎትቶ እያቀፋት‹‹በጣም ነው አይደል የጎዳሽ?››አላት ፡፡
‹‹አዎ!!በፊት በጣም የምጠላውና ባገኘው የምገድለው ይመስለኝ ነበር፡፡››
‹‹አሁንስ?››
‹‹…አሁን ግን ሙሉ በሙሉ ይቅር ብዬዋለው››አለችው፡፡
‹‹ግን እንዴት በዛ መጠን የምትጠይውን ሰው እንዲህ በቀላሉ ይቅር ማለት ቻልሽ?››ሲል በገረሜታ ጠየቃት፡፡ይህንን ጥያቄ የጠየቃት እሱ በቤተሰቦቹ ላይ የቋጠረውን ቂምና ጥላቻ አሁንም በልቡ ውስጥ ቋጥኝ ሆኖ እያስጨነቀው በመሆኑ እሷ የነገረችውን ነገር ማመን ስላቃተው ነው፡፡
እሷ ግን እርግጠኛ በመሆን ታስረዳው ጀመር….‹‹ምን መሰለህ..በእኔና በእሱ መካከል የተፈጠረው ችገር የዛሬ ስድስት አመት የሆነ ነው››
‹‹እና ጊዜ ቁስልን ይፈውሳል በሚለው ብሂል ሄደሽ ነው?››
‹‹አይ እንደእሱ አይደለም…ሳስበው የዛሬ ስድስት አመት የነበረችው ፀደይ አሁን ካለችው ፀደይ ጋር በብዙ ነገር እንደምትለይ ገባኝ..እንደውም አንዳንዴ ያቺ ፀደይ ልክ እንደአንድ የምወዳት ዘመዴ ትናፍቀኛለች…››
እያወራች ያለችው መጀመሪያ ከተነሱበት ሀሳብ ጋር ምንም አልገጣጠም አለው…ቢሆንም በትግስት ማደመጡን ለመቀጠል ወሰነ..
እሷም ቀጠለች‹‹እና አሁን ያለሁት ፀደይ የዛን ጊዜ ባለፍኩበት ሁኔታ ላይ ብሆን ተመሳሳይ ችግር ላይ እወድቃለው..?ብወድቅስ ተመሳሳይ ምላሽ ነው የምሰጠው..?ማለቴ ራሴን ስለማጥፋት አስባለው….?ቤተሰቦቼንና ሀገሬን ጥዬ ወደማላውቀው ከተማ እሰደዳለው…?አንዱንም አላደርግም…፡፡ችግሩን በተለየ መንገድ ነበር የምፈታው…ይሄንን ወደ እሱ ቀየርኩት…አሁን እሱ በህይወት ካለ የሆነች ሴት አፍቅሮ ካስረገዘ በኃላ ደምፁ አጥፍቶ ይሸሻል…?እርግጠኛ ነኝ ቢያንስ እናትዬውን እንኳን ለማግባት ባይፈልግ ልጁን የራስሽ ጉዳይ ብሎ ዞር አይልም፡፡ታዲያ ዛሬ ባገኘውና ጥላቻዬን ባሳውቀው ካዛም አልፌ ልበቀለው ብሞክር ትርጉም ይሰጣል…አይሰጥም..፡፡ምክንያቱም ያ እኔ ማውቀው ልጅ ጠፍቶል… በብዙ ነገር ተቀይሮ በብዙ መከራ ውስጥ አልፎ ብዙ ህይወት ልምዶችን ቀስሞ ሌላ ሰው ሆኖ ነው ማገኘው..እና ሌላ ሰው ባጠፋው ሌላ ሰው የመቅጣት ያህል ነው….ለዛ ነው ይቅር ልለው የወሰንኩት፡፡››
ዘሚካኤል ዝም ነው ያላት…የነገረችውን ጠቅላላ ወደራሱ ህይወት ወስዶ ነው ማሰላሰል የፈለገው…፡፡ከዛሬ ሰባት በፊት የነበረው ዘሚካኤልና አሁን ካለው ዘሚካኤል ፈፅሞ የማይመሳሰል… የተለያየ ፍላጎት ..የተለየ አላማና አመለካከት ያለው ነው ፡፡እና መቶ ፐርሰንት የሚመሳሰሉበት ነገር ቢኖር በስማቸው ነው፡፡እሱንም ቢሆን የአባቱን ስም ስላስቀየረ….መቶ ፐርሰንት ሊባል አይችልም፡፡
//
ከቦንጋ ከተማ የአንድሰዓት እግር መንገድ ሄደው ነው ሰውዬውን ያገኙት፡፡ግዙፉ የሆነ በአረንጎዴ ዛፎችና ተክሎች ተሞላ ውብ ግቢ ነው የገቡት፡፡የሰውዬው ወንድም ነው የተቀበላቸው፡፡ ‹‹ወደማሳ ሄዶል አሁን መምጫው ደርሶል ግቡና ጠብቁት ››ብሎ ወደግዙፉ የሳር ጎጆ ቤት ይዞቸው ገባ ፡፡ቤቱ ፅድት ያለ ነው፡፡ጥግ ላይ በለአንድ ሜትር የተነጠፈ አልጋ አለ..ከአልጋው አጠገብ ከእንጨት የተሰራ መደርደሪያ አለ..መደርደሪያው ግማሽ በመፅሀፍ ተሞልቷል፡፡ከስር በኩል አንድ መለስተኛ ቴፕ ይታያል፡፡
‹‹ግቡ ››አላቸውን የሚቀመጡበት ወንበር ሰጣቸው፡፡እና መቀመጣቸውን ካረጋገጠ በኃላ ተመልሶ ወጣ፡፡
‹‹አይ ሰውዬው ጥሩ ሁኔታ ላይ ሳይሆን አይቀርም››አላት ዘሚካኤል፡፡
‹‹በምን አወቅክ?››
‹‹አንድ ሰውን እኮ በቤቱ ሁኔታ መገመት ትቺያለሽ..አታይም እንዴ ምንም የቆሸሸ ምንም የትዝረከረከ ነገር የለም….››
‹‹እንደአፍህ ያድርግልኝ.››አለችው፡፡
ድንገት ዘሚካኤል ከተቀመጠበት ተስፈንጥሮ ተነሳ..ሁኔታው ፀአዳን በጣም አስደነገጣት…እና አብራው ብድግ አለች…የሆነ እባብ ያየ ነው የመሰላት….ተንዳርድሮ ወደአልጋው ተጠጋ ..ከአልጋው በግራ በኩል ባለ መለስተኛ ጠረጴዛ ላይ ብዛት ያላቸው በፍሬም ያሉ ፎቶዎች ተደርድረውበታል…ቀጥታ ሔደና ተራ በተራ እያነሳ ያያቸው ጀመር….ፀደይ ያልጠበቀችው ነገር ነው ያጋጠማት…ፎቶውን እያየ ወደእሷ ዞረና አፈጠጠባት›
‹‹ይሄ ምንድነው?››

👍49❤6👏2
‹‹ፎቶ ነዋ››
‹‹እሱማ ፎቶ ነው…..የእናቴና የእህቴ ፎቶ እዚህ ሰውዬ ቤት ምን ይሰራል?››አንቧረቀባት
‹‹ተረጋጋ..አስረዳሀለው››
‹‹እንዴት ነው የምታስረጂኝ……?››የያዘውን ፎቶ አስቀመጠና ሌላ ፎቶ አነሳ‹‹እያት ይህቺ እናቴ ነች…ሌላ የማላውቀው ሰው እየሰማት ነው….ሰውዬው ማን ነው?››
‹‹ዶ/ሩ ነው… ልናገኘው የመጣናው፡፡››
‹‹ምን እየተካሄደ ነው..ይሄ ነገር ፈጽሞ ከአንቺ አባት ጋር የሚገናኝ አይደለም አይደል….?ይሄ የቤተሰቦቼ ጉዳይ ነው?››
ጭንቅላቷን ከፍ ዝቅ በማድረግ አረጋገጠችለት
‹‹እናቴ እንዴት በማላውቀው ሰው ትሳማለች…?.እንዴት ይሄን ሰውዬ ልትስመው ቻለች?››
‹‹በጣም ታፈቅረኝ ስለነበር››የሚል መልስ ከወደ በራፉ ሰሙ..ሁለቱም ዞር ሲሉ እሱን ለማግኘት የመጡት ዶ/ር ለሜቻ በቀለ ሙሉ ገበሬ መስሎ የሰሌን ኮፍያ እና ቦት ጫማ አድርጎ በራፍ ላይ ቆሟል….
‹‹አይ ምንም እየገባኝ አይደለም….?››
‹‹ቁጭ በል አስረዳሀለው..››አለና ወደውስጥ ገብቶ ቀድሞት ተቀመጠ…በፀደይ ዘሚካኤልን እየጎተተች ይዛው መጣችና አስቀመጠችው…እሷም ተቀመጠችን ስልኳን አውጥታ ሪከርድ ላይ አደረገችና ሰውዬው የሚናገረውን ለመስማት ዝግጁ ሆነች፡፡
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe ቤተሰቦች ይሄን የምታነቡ ምንያህላቹ subscriber አድርጋችኋል???
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

👏60👍30❤8😱4
#መሃልይ
ይኅው
ይኅው መጣች
መጣችልኝ
ይህቺት....
...
እሷ ናት
የዝምታዬ አባራሪ
የመዝሙሮቼ ባለቤት
እሷ ናት...
የ ሁከቶቼ እረኛ
የሰላሞቼ ባለቤት
እሷ ናት.....
አይኗ ውስጥ ጣት አለ
ትጫወተኛለች
ጣቷ ውስር አይን አለ
ታባብለኛለች
የኔ ልብ ፒያኖ
የ'ሷ ሙዚቀኛ
ስትጫወትብኝ
እንቅልፍም አይወስደኝ
ስሜቴ ሲነካ
የመጣች እንደሆን
ዘማሪ ናት ነፍሴ
የመጣች እንደሆን
አቀንቃኝ ነው ልቤ
ገላዬም ዳንሰኛ
ነቃ ቀና ካለ አይሆንም ዳተኛ። ያየችኝ እንደሆን፤
ዓይኗ ጣት ያበቅላል
የበቀለው ጣቷ
ዓይኔ ውስጥ ይሰርጋል
የሰረገው ጣቷ
የልቤን ፒያኖ
ሲጫወተው ያድራል።
ይህን እሷ አታውቅም፤
ታአምሯን አታውቅም
እኔም አልነገርኳት፤
ምስጢሩን አላውቅም
እየመጣች ብቻ ትጫወተኛለች
እየመጣች ብቻ
እኔ ፒያኖ ነኝ እሷ ሙዚቀኛ...
🔘እንዳለ ጊታ ከበደ🔘
ይኅው
ይኅው መጣች
መጣችልኝ
ይህቺት....
...
እሷ ናት
የዝምታዬ አባራሪ
የመዝሙሮቼ ባለቤት
እሷ ናት...
የ ሁከቶቼ እረኛ
የሰላሞቼ ባለቤት
እሷ ናት.....
አይኗ ውስጥ ጣት አለ
ትጫወተኛለች
ጣቷ ውስር አይን አለ
ታባብለኛለች
የኔ ልብ ፒያኖ
የ'ሷ ሙዚቀኛ
ስትጫወትብኝ
እንቅልፍም አይወስደኝ
ስሜቴ ሲነካ
የመጣች እንደሆን
ዘማሪ ናት ነፍሴ
የመጣች እንደሆን
አቀንቃኝ ነው ልቤ
ገላዬም ዳንሰኛ
ነቃ ቀና ካለ አይሆንም ዳተኛ። ያየችኝ እንደሆን፤
ዓይኗ ጣት ያበቅላል
የበቀለው ጣቷ
ዓይኔ ውስጥ ይሰርጋል
የሰረገው ጣቷ
የልቤን ፒያኖ
ሲጫወተው ያድራል።
ይህን እሷ አታውቅም፤
ታአምሯን አታውቅም
እኔም አልነገርኳት፤
ምስጢሩን አላውቅም
እየመጣች ብቻ ትጫወተኛለች
እየመጣች ብቻ
እኔ ፒያኖ ነኝ እሷ ሙዚቀኛ...
🔘እንዳለ ጊታ ከበደ🔘
😁26👍10❤4😢2
#አላገባህም
፡
፡
#ክፍል_ሀያ
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///
ዘሚካኤል እንግዳው ላይ አፍጥጦ
‹‹አይ ምንም እየገባኝ አይደለም….?››አለ
ሰውዬውም ዘሚካኤል‹‹ቁጭ በል አስረዳሀለው..››አለና ወደውስጥ ገብቶ ቀድሞ ተቀመጠ…
ፀደይ ዘሚካኤልን እየጎተተች ይዛው መጣችና አስቀመጠችው…እሷም ተቀመጠችን ስልኳን አውጥታ ሪከርድ ላይ አደረገችና ሰውዬው የሚናገረውን ለመስማት ዝግጁ ሆነች፡፡
‹‹ምን ድረስ ታውቃላችሁ?››
‹‹እኔ ምንም የማውቀው ነገር የለም››ዘሚካኤል በትግስተ የለሽነት መለሰ፡፡
ፀደይ ዝም አለች‹‹ጥሩ ከመጀመሪያው ብጀምርላችሁ ችግር የለውም..እኔ እና እናትህ የልጅነት ጓደኛሞች ማለት ፍቅረኛሞች ነበርን…በጣም ነበር የምንዋደደው…..ምንጊዜም ስለመጋባትና ዕድሜ ዘመናችንን ሙሉ አብሮ ስለመኖር ነበር የምናስበው…ከዛ ድንገት አባቴ ወደአሜሪካ መሄድ አለብህ አለኝ…ብዙ ወንድሞቹ እዛ ስላሉ ሀሳቡን ላስቀይረው አልቻልኩም….አባቴን በጣም ነበር የምፈራው..ከዛ ጥያቄውን ተቀብዬ ወደአሜሪካ ሄድኩ…ለካ እሷ በወቅቱ እህትህን ፀንሳ ነበር..፡፡››
‹‹ፀንሳ ማለት …ከማን?››
‹‹ከማን ይሆናል ከእኔ ነዋ››
‹‹እና እህቴ የአንተ ልጅ ነች…?.ምንድነው የምትቀባጥረው?››
‹‹አልቀባጠርኩም..ከፈለክ አባትህን ጠይቀው …ያውቃል…እናትህ እኔ ጥያት ስለሄድኩ በጣም ተበሳጭታብኝ ስለነበር እና በዛ ላይ አርግዛ ስለነበር…ወዲያው አባትህን አገባችው…ስታገባው..ለልጇ አባት ለማግኘት አንጂ አፍቅራው አልነበረም…እሱም ይወዳት ስለነበረ ተንከባከባት….እህትህም በሰባት ወር እንደተወለደች ነበር ያሰበው…የገዛ ልጁ ነበር የምትመስለው….ስለዚህ ትርሲትን እንደልጁ አሳደጋት..ከዛ አንተ እና ወንድምህ ተወለዳችሁ፡፡እኔም ከሀያ አመት ቆይታ በኃላ ከአሜሪካ ተመለስኩ፡፡ለእሷ የነበረኝ ፍቅር ከውስጤ ስላልበረደ ፈልጌ አገኘኋት…በጣም ተበሳጭታብኝ የነበረ ቢሆንም ታፈቅረኝ ስለነበረ በሂደት ይቅር አለቺኝ…አባትህን ፈታ እኔን እንድተገባኝ እጨቀጭቃት ጀመር…እሷም ምንም እንኳን ከእኔ ጋር ለመጋባት በጣም ፍላጎት ቢኖራትም እናንተን መበተን ስላልፈለገች በሀሳቤ ልትስማማ አልቻለችም፡፡
እኔም እሷን ትቼ ሌላ ሴት ማግባት ብሞክርም አልቻልኩም..አቃተኝ…ከዛ በቃ አንቺ እሺ ብለሽ ባልሽን ፈተሸ ማታገቢኝ ከሆነ ቢያንስ ልጄን የማግኘት መብት አለኝ..ለልጄ አባቷ እኔ እንደሆንኩ ንገሪያት እያልኩ በዚህ መጨቃጨቅ ጀመርን፡፡እሷም ያንን ማድረግ አልችልም እያለች መከላከል ጀመረች፡፡በዚህ ሁሉ ጊዜ ግን በድብቅ እየተገናኘን ፍቅራችንን እንወጣ ነበር…
‹‹ለምን ያህል ጊዜ ከአባቴ እየተደበቃችሁ ..እንደዛ አደረጋችሁ?››ግሽግሽ ባለና ጥላቻ በተጫነው ስሜት ጠየቀው፡፡
‹‹አራት ወይም አምስት አመት››መለሰለት
‹‹እና አባቴ ይሄን ሁሉ ታሪክ ሲያውቅ ነዋ ..ቀልቡን ነስቶት ያንን ወንጀል የፈፀመው?››
‹‹አይ አይደለም…ስለዚህ ጉዳይ ሳስብ እስከዛሬ ድረስ ራሴን መቆጣጠር እስኪያቅተኝ አዝናለው..እመነኝ በጉዳዩ በጣም መፀፀት ብቻ ሳይሆን ብዙ ነገሬን አጥቼበታለው….፡፡ ስራዬን፤ ጤናዬን …ብዙ ብዙ ነገር…ብዙ ጊዜም ራሴን አጥፍቼ ከልጄ ትርሲት እና ከእናትህ ጎን ለመተኛት ሞክሬ ነበር..ግን በሆነ መንገድ እተርፋለው…መጨረሻ ይሄው እንደምታየኝ የአያቴ መንደር መጥቼ በዚህ አይነት ሁኔታ መኖር ጀመርኩ..ትንሽም ወደእዚህ ከመጣሁ ነው ጤነኛ የሆንኩት››
‹‹ሰውዬ እኔ ያንተን ፀፀት ለመስማተ ምንም አይነት ፍላጎት የለኝም..ስለዋናው ጉዳይ ንገረኝ››
‹‹ትዝ ይለኛል ቀኑ እሁድ ነበር….በእለቱ አባትህ ሞጆ የጓደኛው ለቅሶ ስለነበረ መሄዱን እናትህ ስትነግረኝ..መኪናዬን ከአዲስአበባ አስነስቼ አዳማ ሄድኩ ፡፡እናትህን ተቀጣጥረን ስለነበር ቡቲክ አገኘኋት …እሁድ በዛ ላይ ጥዋት ስለሆነ የገበያ ግር ግር አልነበረም.. ከዛ የተወሰነ ከቆየን በኃላ የተለመደ ጭቅጭቃችንን ጀመርን‹‹ …ለልጄ አባቷ መሆኔን ወይ ቀድመሽ ንገሪያት ወይ እነግራታለው››አልኳት፡፡
‹‹እሷ ቅጣውን በልዩ ሁኔታ ነው የምትወደው …አባትሽ ቅጣው አይደለም ብላት ልጄ በጣም ነው ምትጎዳው››አለቺኝ፡፡
‹‹ብትጎዳም ለጊዜው ነው…ከውሸት ጋር ለዘላለም ከምትኖር እውነቱን አውቃ ለትንሽ ጊዜ ብትጎዳ ይሻልል››አልኳት
በዚህ ጉዳይ ላይ ለ30 ደቂቃ ለበለጠ ጊዜ በከረረ ሁኔታ ስንከራከር ቆየን….ከዛ የስልክ ንግግር ድምፅ ነው ሁለታችንንም ያነቃን….
እህትህ ትርሲት ከባንኮኒው ማዶ … ፊቷ በእንባ ታጥቦ…አይኖቾ ፈጠውና አውሬ መስላ ቆማለች..ሱቁ ውስጥ ገብታ እዛ የቆመችበት ቦታ መች እንደቆመች አናውቅም..ምን ያህሉን እንደሳማችንም አናውቅም….ከሁኔታዋ እንደሚታው ግን የሚበቃትን ያህል እንደሰማችን ያስታውቃል…ሁለታችንም በርግገን ጎን ለጎን ተጣብቀን ከተቀመጥንበት ተነሳን….
‹‹ለማን እየደወለች ነው?››ሁለታችንም ግራ ተጋባን፡፡ወዲያው ስልኩ ተነሳላትና ማውራት ጀመረች፡፡
‹‹አባዬ ….ያንተ ልጅ አይደለሁም እንዴ…?እማዬና ውሽማዋ ሲያወሩ ሰማው…አባዬ እኔ ያንተ ልጅ ካልሆንኩ መኖር አልፈልግም…የሌላ ሰው ልጅ መሆን በጣም ነው የሚቀፈኝ…አይ አልጠብቅህም ..በጣም ነው የምወድህ….››አለችና ስልኩን ግድግዳው ላይ ወርውራ ከሱቁ ወጥታ ተፈተለከች፡፡ልንደረስባት ሞከርን ግን ወዲያው ተሰወረችብን፡፡
‹‹ወይኔ ልጄ….ወይኔ ልጄ…››እናትዬው ተርበተበተች....እኔም የምይዝው የምጨብጠው ግራ ገባኝ….ሱቁን ዘጋንና….
‹‹ወደየት ነው የሄደችው?››ስል እናትህን ጠየቅኳት፡፡‹‹እኔ ምናውቃለው..ወደቤት ከሄደች…ሄጄ ልያት››አለችኝ
‹‹በቃ ነይ መኪና ውስጥ ግቢ››ስላት
‹‹እንዴ ..አንድ ላይ ስንሄድ..?››
‹‹አሁን እኮ ነገሮች ተደበላልቀዋል…ምንፈራው ሳይሆን የምንጋፈጠው ነው››አልኳትና እየጎተትኩ መኪናዬ ውስጥ ይዣት ገባው፡፡በየመንገዱ እየፈለግናት…ልትሄድ ትችልበታለች ብላ እናቷ የጠረጠረችበት አንድ ሁለት ቦታ አቁመን አይተን መጨረሻ ወደቤት ሄድን…መኪናውን ራቅ አድርጌ እንዳቆም አደረገችኝና…‹‹እኔ ገብቼ ልያትና ካለች እነግርሀለው..ከሌለችም ሌላ ቦታ ሄደን እንፈልጋታለን›› ብላኝ ገባች፡፡እኔም በጭንቀት እየተንቆራጠጥኩ መጠበቅ ጀመርኩ…5 ደቂቃ ..10 ደቂቃ አለፈ..ስልኬን አውጥቼ ስደውል እናትህ ሞባይል አይነሳም…ራሴን መቆጣጠር አቃተኝና የሆነው ይሁን ብዬ ወደግቢው ገባው፡፡ሳሎኑ በራፍ እንደተከፈተ ነበር…ስገባ ልጄ ኮርኒሱ ላይ ተንጠልጥላለች..እናትህ ደግሞ የገዛ ሆዷን ላይ ቢላዋ ሽጣ ተዘርራለች፡፡ይመስለኛል እናትህ ወደቤት ስትገባ እህትህ ተሰቅላ እራሷ አጥፍታ ስታያት ወዲያው አካባቢው ላይ ያገኘችውን ቢላዋ ሆዷ ውሰጥ የሻጠችው ይመስለኛል፡፡
ከዛ ደንዝዤ የምሆነው ጠፋኝ…ምን ላድርግ ..?ልጄን ከተሰቀለችበት ለማውረድ ገመድ መቁረጫ ለመፈለግ ወደውስጥ ገብቼ መቁረጫ ይዤ ስመለስ አባትህ ከውጭ ከሳሎኑ ሲገባ አየሁት፡፡በደመነፍስ ወደ ጎሮ በራፍ ሄድኩ…ዞሬ ከግቢው ወጣሁና መኪናዬ ውስጥ ገብቼ ደም እንባ እያለቀስኩ ሁኔታዎችን መከታተል ጀምርኩ፡፡ ከዛ አንተና ወንድምህ አንድ አይነት ሰማያዊ የስፖርት ልብስ ለብሳችሁ ወደቤት ስትገቡ ተመለከትኩ፡፡ ከደቂቃዎች በኃላ ፖሊሶች ሰፈሩን ወረሩት…እናንተንም አባታችሁንም ፖሊሶች ይዘዋችሁ ሲሄድ የእናትህንና የእህትህን አስከሬን በአንብላንስ ሲወሰድ ከመንገድ ማዶ መኪናዬ ውስጥ ተቀምጬ እየተመለከትኩ ነበር፡፡ ሁለቱም እራሷቸውን እንዳጠፉ እርግጠኛ ነኝ፡፡

👍64❤15
እና በጣም የማስጠላ ፈሪ ሰው ነኝ አይደል…በወቅቱ ትልቅ ስልጣን ላይ ነበርኩ..ከዚህ ወንጀል ጋር ስሜ ቢያያዝ ምንድነው የሚገጥመኝ? ብዬ ፈራው…አባትህ እንደገደለ ሲያምን ..የሞት ፍርድ ሲፈረድበት ሁሉ ዝም ብዬ ተመለከትኩ…ከሰውዬው አይኖች እንባ እየረገፈ ነው፡፡‹‹እና ምን መሰለህ….››ዶ/ሩ የዘሚካኤልን መቀያየር ሲመለከት ንግግሩን አቆመ፡፡
ዘሚካኤል ወደኃላው ክንብል ብሎ ወደቀ…ፀአዳ እና ዶክተሩ በድንጋጤ ተባብረው አነሱትና አልጋ ላይ አስተኝተው ውሀ በተነከረ ጨርቅ ጭንቅላቱንና ልቡን ያቀዘቅዙለት ጀመረ….ቀስ በቀስ ከገባበት ጭልጥ ያለ ሰመመን እየነቃ መጣ…ራሱን በደንብ ሲያውቅ በመጀመሪያ ያደረገው ነገር…ከተኛበት ተስፍንጥሮ በመነሳት የሰውዬውን አንገት አንቆ በቴስታ መነረት ነበር…..
ከአንድ ሰዓት በኃላ ፀአዳና ዘሚካኤል ወደአዲስ አበባ የመልስ ጉዞ ለማድረግ በተከራዩት የቻርተር አውሮፕላን ውስጥ ገብተው ፓይለቱ የአውሮፕላኗን ሞተር አስነስቶ አየር ላይ አስኪሰቅላት ድረስ እየተጠባበቁ ነው…ዘሚካኤል አሁን ድረስ በድኑ ነው ያለው….እንደጣኦት ያመልካትና ይወዳት የነበረችው እናቱ እንደዛ አይነት ሰው መሆኗን ሲያውቅ ከመሸማቀቁ የተነሳ የሚደበቅበት ጥጋት ነው ያጣው….በእናቱ ከመመካቱ የተነሳ ሀጥያተኛና ጨካኝ ነው ብሎ የሚያስበውን የአባቱን ስም ከስሙ ቀጥሎ መጠራቱን ተጠይፎ እንዲፋቅ በማደረግ የእናቱ ስም እንደአባት አድርጎ መጠቀም ከጀመረ አመታት አልፎታል፡፡
ምንም ጥፋት የሌለበትን እና የዚህ ሁሉ በደል ዋና ተጠቂ የሆነው አባቱን በዛን ወቅት ሊገድለው ሁሉ ነበር… ከዛ በኋላም ወንድሙንና አባቱን ሲጠየፍና ሲራገም ነው የኖረው..‹‹ አሁን እኔ ምን አይነት ፍጡር ነኝ?››ሲል እራሱን ተጠየፈው፡፡‹‹እንዴት የወንድሜን ያህል ማስተዋልና መረጋጋት ያቅተኛል…?››ለራሱ ያለው ግምት ወረደበት፡፡
ፀአዳ ….ሚካኤልና አዲስ አለም በየተራ እየደወሉ እያጨናነቋት ነው….አንስታ ምን እንደምትላቸው ስላልገባት ለማንሳት አልደፈረችም….ከዛ ይልቅ አሁን ወደ አዲስአበባ ሊመለሱ ሄሊኮፍረተር ውስጥ መግባታቸውና እና ስልኩን ማናገር እንደማትችል ገልጻ
ከዶ/ር ጋር ያደረጉትን ውይይት የሰውዬውን ንዛዜ የመሰለ አስገራሚ ትያትራዊ ገለፃ በቴሌግራም ለሚካኤል ላከችለትና ስልኳን ዘጋችው፡፡
‹‹ፀዲ …እኔን እንዳትወጂኝ እሺ……የማንም ሰው ፍቅር አይገባኝም››አላት እየነፈረቀ፡፡
ወደእሱ ይበልጥ ተጠጋችና.. አቀፈችው፡፡እየነፈረቀ ንግግሩን ቀጠለ‹‹እኔ ሁል ጊዜ ከእኔ ለመሸሽ ስትሞክሪና እንድተውሽ ስትጨቀጭቂኝ…ይህቺ ልጅ ያማታል እንዴ? እንዴት ጨክና እኔን የመሰለ ሰው አልፈልግም ልትል ቻለች ? ››እያልኩ እገረም ነበር..ለካ አንቺ ብልህ ስለሆንሽ ደካማነቴና እንጭጭ የሆነ አስተሳሰቤን በግልፅ ስላወቅሽ እንደማልመጥንሽ ተረድተሸ ነው፡፡›
‹‹አረ አንተ ሰው ምኑን ከምን እያገናኘህ ነው….?እባክህ የእኔ ቆንጆ ራስህን አታሰቃይ..የሆነው ሁሉ ሆኗል….ይልቅ ራስህን አረጋጋና በቀጣይ የሚስተካከሉ ነገሮችን ማስተካከሉ ላይ ትኩረት ማድረግ ነው››
‹‹አልገባሽም እንዴ..?ምንም የሚስተካከል ነገር የለም….ይሄንን ዜና ወንድሜ ካወቀ በኃላ እንዴት እንደሚጠየፈኝ አስበሽዋል..?አባቴንማ ተይው ይሄኔ ልጁ መሆኔንም ዘንግቷል..››
‹‹አይ …ይሄንን ጉዳይ እንድናጣራ እኮ ፍንጩን ለሚኪ የሰጡት አባትህ ናቸው…. ምክንያታቸው ደግሞ ከመሞቴ በፊት ልጄ እንደጠላኝ መሞት አልፈልግም…..ከመሞቴ በፊት እውነቱን አውቆ አንዴ አይኑን አይቼውና አቅፌው ልሰናበተው እፈልጋለው…ብለው ነው፡፡አንተን ለማግኘት ስለሚፈልጉ ነው፡፡››
‹‹ተይ ፀዲ.. አኔን ለማፅናናት ብለሽ ነው፡፡››
‹‹አይደለም…እውነቴን ነው…ለማንኛውም አሁን ሁሉንም ረስተህ ለመረጋጋት ሞክር፡፡››ስትለው የሂሊኮፕተሯ ሞተር መንኳኳት ጀመረ፡፡
///
ዘሚካኤል አፓርታማ ሲደርሱ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሆኖ ነበር፡፡አሳንሱሩን ተጠቅመው ወደላይ ወጡ…ሲደርሱ በራፉ ክፍት ነው፡፡መጥሪያውን ተጭነው ሲከፈት አዲስ አለም ሚካኤልና ቅድስ እየጠበቋቸው ነበር….ሁሉም ዘሚካኤል ላይ ተጠመጠሙበት…ሁለቱ ወንድማማቾች ለመላቀቅ በርካታ ደቂቃዎች ወሰደባቸው…ህፃኑ ቅዱስ ተጨንቆ እስኪያለቅስ ሁሉም እየተንሰቀሰቁ ተላቀሱ…ቤቱ አዲስ ሬሳ የወጣበት ቤት ነው የመሰለው፡፡
///
ዘሚካኤል ስቲዲዬ ቆይቶ ገና ወደቤት እንደገባ ነበር ስልኩ የጠራው፡፡የደወለችለት አዲስ አለም ነበረች፡፡የጠበቀው ሚካኤል ይደውልልኛል ብሎ ነበር ፡፡ከአባቱ ጋር የሚገናኙበትን ቀን ከወህኒ ቤቱ አስተዳዳሪ ጋር ተነጋግሮ እንደሚደውልለት ነገሮት ነበር፡፡እና ይሄን ቀን በፍርሀትና በጉጉት ነበር እየጠበቀ ያለው፡፡ስለአባቱ ዜና ለመስማት፡፡ስልኩን አነሳው፡፡
‹‹ሄሎ አዲስ እንዴት ነሽ?››
‹‹ሰላም ነኝ አንተስ?››
‹‹እኔ በጣም ደህና ነኝ…ሚካኤል ይደውልልኛል ብዬ እየጠበቅኩ ነበር፡፡››
‹‹ይደውልልሀል..አሁን ኩማንደሩ ቀጥሮት ሊያገኘው ሄዶል …ከእሱ እንደጨረሰ እርግጠኛ ነኝ ይደውልልሀል፡፡…አታስብ ኩማንደሩ ደግሞ ያንተ አድናቂ ስለሆነ ከአባታችሁ እንድትገናኙ ሁኔታውን ያመቻቻል….በዛ እርግጠኛ ነኝ፡፡››አለችው
‹‹ጥሩ ታዲያ አንቺ ሰላም ነሽ?››
‹‹በጣም ሰላም ነኝ…ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ ነበር››
‹‹ምን?››
‹‹ከፀዲ ጋር እንዴት ናችሁ?››
ያልጠበቀውን ጥያቄ ነው የጠየቀችው‹‹በጣም አሪፍ ነን…ከቦንጋ ከተመለስን በኃላ በአካል ባንገናኝም በስልክ ግን በቀን ሁለት ሶስት ጊዜ እንደዋወላለን…እንደውም የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ከከተማ ወጣ ብለን ለማሳለፍ ተነጋግረናል፡፡ግን ምነው ጠየቅሺኝ?››
‹‹ግልፅ ሆነህ ንገረኝ…ስለእሷ ምን ታስባለህ..ማለቴ አሁንም በፊት እንደነገርከኝ ታፈቅራታለህ?››
‹‹እንዴ!እንዴት በአንድ ወር ፍቅሩ ይተናል ብለሽ አሰብሽ? እንደውም ጥሩ ነገር አነሳሽልኝ…የሆነ ቀን አመቻችቼ ካንቺ ጋር መነጋገር እፈልግ ነበር..እኔ ላገባት እፍልጋለው..በቅርብ ቀን..እና እንዴት ጠይቄ ላሳምናት የሚለውን ከእኔ ይልቅ አንቺ ስለምታውቂ እንድታማክሪኝ እፈልጋለው፡፡››
‹‹እንግዲያው እንደዛ ከሆነ ሳይረፍድብህ ፍጠን››
‹‹አልገባኝም?››
‹‹ያንተን ልጅ አርግዛለች..››
የሰማውን ነገር ማመን አልቻለም…በደስታ ጮኸ…‹‹ማለት…በፈጣሪ እየዋሸሺኝ አይደለም አይደል? ››
‹‹አርግዛለች..ለእኔም አልነገረችኝም ፡፡በአጋጣሚ አንድ የግል ሆስፒታል ካርድ ክፍል የምትሰራ ወዳጅ ነበረችኝ …አሁን ከደቂቃዎች በፊት ደውላ ጓደኛሽ ፀንሳ እኛ ሆስፒታል ለማስወረድ መጥታ ነበር…ብላ ነገረችኝ፡፡
መጀመሪያ አላመንኩም ነበር..በኃላ ግን ሆስፒታሉ ድረስ ሄጄ በሌላ መንገድ እራሷ መሆኗን አረጋግጬያለው…ልታስወርደው ለተነገወዲያ ቀጠሮ አሲይዛለች….ቀጥታ ላናግራት ፍልጌ ነበር….ጭራሽ እልክ ትጋባለች ብዬ ስለፈራሁ ምንም ልላት አልቻልኩም…አንተ ምታደርገው ነገር ካለ ሞክር››
‹‹ወይኔ በፈጣሪ..ለእኔ አረገዘችልኝ…..››በቃ ቻው አዲስ አንቺ አትጨነቂ እኔ አስተካክለዋለው፡፡
የአዲስን ስልክ ከዘጋ በኃላ ቀጥታ ልብሶቹ በሻንጣ መክተት ነው የጀመረው፡፡ሁለት ሻንጣ ልብስና በወሳኝ የሚፈልጋቸውን ነገሮች ሰበሰበና አፓርታማውን ለቆ ወጣ …ቀጥታ ወደአዳማ ነው የነዳው፡፡

👍132❤17👏3
#አላገባህም
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
/////
ዘሚካኤል ስቲዲዬ ቆይቶ ገና ወደቤት እንደገባ ነበር ስልኩ የጠራው፡፡
የደወለችለት አዲስ አለም ነበረች፡፡የጠበቀው ሚካኤል ይደውልልኛል ብሎ ነበር ፡፡ከአባቱ ጋር የሚገናኙበትን ቀን ከወህኒ ቤቱ አስተዳዳሪ ጋር ተነጋግሮ እንደሚደውልለት ነገሮት ነበር፡፡እና ይሄን ቀን በፍርሀትና በጉጉት ነበር እየጠበቀ ያለው፡፡ስለአባቱ ዜና ለመስማት፡፡ስልኩን አነሳው፡፡

ያልጠበቀውን ጥያቄ ነው የጠየቀችው‹‹በጣም አሪፍ ነን…ከቦንጋ ከተመለስን በኋላ በአካል ባንገናኝም በስልክ ግን በቀን ሁለት ሶስት ጊዜ እንደዋወላለን…እንደውም የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ከከተማ ወጣ ብለን ለማሳለፍ ተነጋግረናል፡፡
ግን ምነው ጠየቅሺኝ?››

የሰማውን ነገር ማመን አልቻለም…በደስታ ጮኸ…
‹‹ማለት…በፈጣሪ እየዋሸሺኝ አይደለም አይደል? ››
‹‹አርግዛለች..ለእኔም አልነገረችኝም ፡፡
በአጋጣሚ አንድ የግል ሆስፒታል ካርድ ክፍል የምትሰራ ወዳጅ ነበረችኝ …አሁን ከደቂቃዎች በፊት ደውላ ጓደኛሽ ፀንሳ እኛ ሆስፒታል ለማስወረድ መጥታ ነበር…ብላ ነገረችኝ፡፡መጀመሪያ አላመንኩም ነበር..በኋላ ግን ሆስፒታሉ ድረስ ሄጄ በሌላ መንገድ እራሷ መሆኗን አረጋግጬያለው…ልታስወርደው ለተነገወዲያ ቀጠሮ አሲይዛለች….ቀጥታ ላናግራት ፍልጌ ነበር….ጭራሽ እልክ ትጋባለች ብዬ ስለፈራሁ ምንም ልላት አልቻልኩም…አንተ ምታደርገው ነገር ካለ ሞክር››
‹‹ወይኔ በፈጣሪ..ለእኔ አረገዘችልኝ…..››በበቃ ቻው አዲስ አንቺ አትጨነቂ እኔ አስተካክለዋለው፡፡
የአዲስን ስልክ ከዘጋ በኃላ ቀጥታ ልብሶቹ በሻንጣ መክተት ነው የጀመረው፡፡ሁለት ሻንጣ ልብስና በወሳኝ የሚፈልጋቸውን ነገሮች ሰበሰበና አፓርታማውን ለቆ ወጣ …ቀጥታ ወደአዳማ ነው የነዳው፡፡
ፀአዳ ቤት ሲደርስ በራፏ ዝግ ነበር..ሊደውልላት አልፈለገም ፡፡ሻንጣውን አወረደና በራፏ በረንዳ ላይ አድርጎ እሱ መኪናው ውስጥ ሆኖ መጠበቅ ጀመረ…ከምሽቱ አንድ ሰአት ስትመጣ እሱ መኪና ውስጥ ሻንጣው በረንዳ ላይ ሆኖ ስታየው ፍፁም ነው ግራ የተጋባችው…ምስር እሱ መሆኑን ስታውቅ ከእናቷ ተነጥላ ወደእሱ መሮጥ ስትጀምር እሱም ፈጥኖ ከመኪናው ወረደና እጇቹን እንደክንፍ ዘርግቶ ጠበቃት…ተጠምጥማበት በደስታ ጉንጩን ትስመው ጀመር…
ወደቤት እንደገቡ ፀደይ‹‹ምንድነው ጉዱ?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹ምንም ..ለጥቂት ሳምንታት እረፍት ስለሆንኩ እዚህ ከእናንተ ጋር ለመቆየት ወስኜ ነው፡፡››
‹‹እዚህ ከእኛ ጋር?››
‹‹አዎ ከእናንተ ጋር››
ህፃኖ ምስር ‹‹ታድለን…ታድለን›› እያለች መጨፈር ጀመረች፡፡
ፀአዳ ልጇ ምስር ፊት ምንም ማለት አልቻለችም.‹‹እንግዲያው እደቤትህ ዘና በል…እኔ ልብስ ልቀይር ››አለችና መኝታ ቤት ገባች፡፡ከዛ እራት ሰርታ በሉና ከሶስት ሰዓት በኃላ ምስርን አስተኝተው ነበር እንደአዲስ ጭቅጭቁን የጀመሩት፡፡
‹‹ምን እየሰራህ ነው?››
‹‹እንደምታገቢኝ ቃል ገብተሸ ቀለበት እስክታስሪልኝ ድረስ ከዚህ ቤት ወጥቼ ወደቤቴ አልመለስም››ሲል ቁርጡን ፍርጥም ብሎ ነገራት፡
‹‹ጭራሽ ማግባት? እየቀለድክ ነው፡፡››
‹‹በፍፅም …ብቀልድ ነው እንደዚህ አይነት እርምጃ የወሰድኩት፡፡››
‹‹ስማ..እኔ ካንተ ጋብቻ ፍቅር ምናምን አልፈልግም››
‹‹ታዲያ ምንድንው ምትፈልጊው?››
ትኩር ብላ አየችው….
‹‹ንገሪኝ ከእኔ ምንድነው የምትፈልጊው….. ?››
‹‹ካንተ ወሲብ ብቻ ይበቃኛል….ማለቴ እስከአሁን የደረግነውን ለማለት ነው …ደግሞ አሁንም እናድረግ እያልኩህ አይደለም፡፡››
በንግግሯ ሆድን እስኪያመው ሳቀ…በመሀል ስልክ ተደወለለት ..ከወንድሙ ነበር…በጉጉት አነሳው‹‹እሺ ሚካኤል ደህና አመሸህ?››
‹‹ሰላም ነኝ…ነገ ጥዋት ሶስት ሰዓት ላይ አዳማ መገኘት ትችላለህ?››
‹‹ምነው ?አባዬን እንድናገኝ ፈቀዱልን እንዴ?››
‹‹አዎ በጣም ደስ የሚለው ደግሞ አንድ ላይ እንድናገኘው ነው ያመቻቹልን ቅር ካላለህ አዲስንና ቅዱስንም ይዘናቸው እንሄዳለን››
‹‹አረ ቅር አይለኝም ጥሩ ሀሳብ …ግን አባዬ እኔን ለማናገር ፍቃደኛ የሚሆን ይመስልሀል?››ሰሞኑን ሲብሰለሰልበት የነበረውን ስጋቱን አንስቶ ጠየቀው፡፡
‹‹ትቀልዳለህ እንዴ…ከመሞቱ በፊት ማግኘት የሚፈልገው ብቸኛ ነገር እኮ አንተን ማናገር ነው…በደስታ ነው የሚያነባው….እንኳን በአካል አግኝተሀው አባዬ ብለህ ስጠራው ሰምቶ ይቅርና ባለፈው ፎቶህን ሳሳየው እንዴት እያገላበጠ ሲስምና ሲያለቅስ እንደነበረ እኔ ነኝ የማውቀው…በል በዛ እርግጠኛ ሁን..ምንም አትጨናነቅ፡፡››
‹‹ምን ያስፈልገዋል…?ማለት ምን ይዤለት ልሂድ?››
‹‹የሚያስፈልገወን ነገር ሁሉ አዘጋጅተናል…አንተ ደግሞ ሚፈልገውን ነገር እንጠይቀውና በሚቀጥለው ዙር ትወስድለታለህ…ደግሞ ደስ የሚለው ከቦንጋ ያመጣችሁትን ከዶ/ሩ ጋር ያደረጋችሁትን ውይይት ለኩማንደሩ አሰምቼው በጣም ነው ያዘነው..እናም አባዬን ከሌሎች እስረኞች ጋር ተቀላቅሎ እንዲኖር ወስነዋል…››
‹‹በጣም የሚያስደስት ነገር ነው እየነገርከኝ ያለሀው..ወንድሜ በጣም ጥሩ ሰው እንደሆንክ ታውቃለህ አይደል… በጣም ነው የምኮራብህ፡፡››
ሚካኤልም እንባ እየተናነቀው‹‹እኔም በጣም ነው የምኮራብህ››አለው
‹‹በቃ እሺ …...ሶስት ሰዓት ነው ያልከኝ አይደል?፡፡››
‹‹አዎ…መድረስ ትችላለህ አይደል…?››
‹‹በደንብ እንጂ ሁለት ተኩል ደርሼ ደውልልሀለው››
‹‹ጥሩ በቃ ደህና እደር››ስልኩን ዘጋ፡፡
ንግግራቸውን ሁሉ በገረሜታ ስትሰማ የነበረችው ፀደይ‹‹እርግጠኛ ነህ ግን ሁለት ተኩል ትደርሳለህ?››ስትል በፈገግታ አሾፈችበት፡፡
‹‹ትቆጪኛለሽ ብዬ ነው እንጂ እዚህ ነኝ ልለው ነበረ››
‹‹ልፋ ቢልህ ነው ….ግን ለእናንተ ደስ ብሎኛል››
‹‹ማለት?››
‹‹አንተና ወንድምህ እንዲህ እየተደዋወላችሁ በሰላም ማውራት መቻላችሁ ትልቅ ነገር ነው…አረ እንደውም ከመነጋጋርም አልፋችሁ መሞጋገስ ጀምራችኃል››
‹‹እድሜ ለአንቺ ….ባንቺ ቀናነትና ጥረት ነው ለዚህ የበቃነው….››
‹‹እኔን ማሞገሱን እንኳን ለሌላ ጊዜ አቆየው..በነገራችን ላይ የአባትህ ጉዳይ ላይ ይግባኝ ለመጠየቅ ሚቻል ከአሆነ አንድ ጎበዝ ጠበቃ አግኝኝቼ ሁኔታውን አስረድቼው ነበር….››
‹‹በእውነት ..ታዲያ ምን አለሽ?››

👍67❤21👎1👏1
‹‹ምንም ነገር ከማለቴ በፊት ዶ/ር ለሜቻን ማናገር አለብኝ..አለኝ..እስኪ የሚቻል ከሆነ በስልክ ላገናኛቸው አስቤለው…ቆይ አንደውም እስኪ ልደውልና ላናግረው››
‹‹ማንን ጠበቃውን..?››
‹‹አይ ዶክተሩን››አለችና ስልኳን አንስታ ቦንጋ የሚገኘው ደ/ር ለሜቻ ቁጥር ላይ ደወለች ፡፡
ከበርካታ ጥሪዎች በኃላ ሰልችቷት ልትዘጋው ስትል ተነሳ‹‹ሄሎ…ፀደይ ነኝ..ባለፈው… ››
‹‹አውቄሻለው….ወንድሙ ነኝ››የሚል መልስ አገኘች፡፡
‹‹እሺ በምሽት ስለደወልኩ ይቅርታ››
‹‹ምንም አይደል?››የደከመ እና የቀዘቀዘ ድምፅ ነው እየሰማች ያለችው፡፡
‹‹አውቀኸኛል አይደል?››
‹‹አዎ አውቄሻለው… የዘፋኙ ጓደኛ አይደለሽ?››
‹‹አዎ ነኝ..ዶ/ርን ለማናገር ፈልጌ ነበር…ከልተኙ ልታገናኘን ትችላለህ…ለብርቱ ጉዳይ ነው የምፈልጋቸው፡፡››
‹‹አዝናለው አልችልም››
‹‹ችግር የለውም በቃ…ነገ ጥዋት መልሼ ደውላለው…እንደደወልኩ ነገርልኝ››
‹‹አልችልም አልኩሽ እኮ››ፀደይ ድግገርግር አላት
‹‹ማለት…ምን ችግር አለው?››
‹‹ወንድሜ ከሶስት ቀን በፊት እራሱን አጥፍቶል…ዛሬ ቀብሩ ነበር››ሲል ሳግ በተናነቀው ድምፅ አረዳት….ፀደይ ስልኩ ከእጇ ተንሸራቶ ወለሉ ላይ ወደቀ…
ሁኔታዋን በንቃት ሲከታተል የነበረው ዘሚካኤል ከተቀመጠበት ተስፈንጥሮ ተነሳና ስሯ ደርሶ ትከሻዋን እየነካካ ምን እንደተፈጠረ ይጠይቃት ጀመር‹‹ዶ/ሩ እራሱን አጥፍቶ እንደሞተ ነው የነገረኝ››ስትል ነገረችው፡፡
ቀስ አለና አጠገቡ የሚገኝ ደረቅ ወንበር ላይ ቁጭ አለ…ይዘን ወይስ ይደሰት ግራ ገባው…እንኳን ሞተም ወይም ነፍስ ይማርም ማለት አልቻለም፡፡
ፀደይ ግን በጣም ነው የደነገጠችው…እንባዋ እስኪረግፍ ድረስ ነው ያዘነችው‹‹ደህና እያገገመ የነበረውን ሰውዬ የተደበቀበት ዋሻ ድረስ ሄደን ቁስሉን ነካካንበትና ለሞት ዳረግነው››ስትል ተፀፀተች፡፡‹‹ለምንድነው ግን አንተ ፍፅም መልካም ነገር ለመስራት በተንቀሳቀስ ቁጥር ሳታውቀው መጥፎ ነገር እንድትሰራ የምትገደደው?››ጥያቄው ለራሷ ይሁን ወይስ ለዘሚካኤል አይታወቅም፡፡
እሱ ግን የመሰለውን መመለስ ጀመረ‹‹ለዛ እኮ ነው የማይሳሳተው የማይሰራ ሰው ብቻ ነው የሚባለው..በእንቅስቃሴ ላይ ካለሽ የግድ መልካሙንም መጥፎውንም ነገር መስራትሽ አይቀርም…ዋናው ልዩነት አንድ ነገር ስትሰሪ ኢንቴንሽንሽ ምንድነው የሚለው ነው…?በመንገድሽ ላይ ክፍ ተግባራትን ላለመስራት ምን ያህል ተጠንቅቀሻል ?..ግን ደግሞ ምንም ብትጥሪ ከቁጥጥርሽ ውጭ በሆነ መንገድ የማትፈልጊው ነገር መፈጠሩ አይቀርም፡፡››
ከሰውዬው ሀዘን ለማገገም ከአንድ ሰዓት በላይ ወሰደባቸው…አምስት ሰዓት ሆነ….‹‹በል አሁን እንተኛ..መቼስ ድንገት ነው የመጣሀው እንደምታየው ያለን አንድ መኝታ ቤት ብቻ ነው››አለችው፡፡
‹‹ችግር የለውም …ምለብሰው ልብስ ብቻ ስጪኝ፣ እዚሁ ሶፋ ላይ እተኛለው››አላት፡፡ያልጠበቀችው መልስ ነበር፡፡ብቻዬን ልታስተኚኝ…ምናምን ››ብሎ ይቀውጠዋል ብላ አስባ ነበር፡፡እሱ ግን ምንም አልተቃወማትም..ጭራሽ መጀመሪያውኑ ከእሷ ጋ ለመተኛት ያሰበ አይመስልም፡፡
‹‹ለምን ከምስር ጋር መኝታ ቤት ገብተህ አትተኛም….እኔ እዚህ…›› አላስጨረሳትም.
‹‹.አይሆንም አልኩሽ እኮ…!!››
ተነሳችና ሚለብሰው ልብስ አምጥታ አስተካከለችለትና ግንባሩን ስማ ወደመኝታ ቤቷ ሄዳች…እጄን ይዞ ጎትቶ ይስመኛል ብላ አስባ ነበር..ግን አላደረገውም….በመገረም ተሞልታ ከልጆ ጎን ተኛችና ስለገጠማት ነገር ማሰላሰል ጀመረች፡፡
‹‹እሺ አሁን ምን ላደርግ ነው?››እራሷን በጥያቄ አስጨነቀች‹‹ምን አደርጋለው…በእቅዴ መሰረት ነው የምሄደው…..ፅንሱን አስወርዳዋለው…ስለዚህ ጉዳይ ማንም እንዲያውቅ አላደርግም..ከዛ ቀስ ብዬ በዘዴ ሻንጣውን ሸክፎ እንደመጣ ሸንጣውን ሸክፎ ወደቤቱ እንዲመለስ አደርገዋለው….››ብላ ወሰነች፡፡
በዚህ ጊዜ ዘሚካኤም እንዴት ከዚህ በላይ እንደሚያጠምዳትና በራሷ ላይም ሆነ በፀነስችው ፅንስ ላይ ምንም እንዳታደርግ ማድረግ እንደሚችል እያሰበ ነው፡፡ሳሎን ተኝቶ መኝታ ቤት ሆና የምትተነፍሰው የእሷ ትንፋሽ የሚሰማው መስሎ እየተሳማው ነው…ሹክክ ብሎ ሄዶ የመኝታ ቤቱን በራፍ ከፍቶ ጉያዋ ውስጥ ተወሽቆ ትንፋሿን ቢሞቅ በጣም ደስ ይለው ነበር…ግን እሷን ለወሲብ ብቻ ሳይሆን ለፍቅርና ለጋብቻ ጭምር እንደሚፈልጋት በተግባር ማሳየት አለበት..ለዛ ደግሞ ይሄ አንዱ አጋጣሚ ነው፡፡
ስልኩን አነሳና መልእክት በመፃፍ ከፎቶ ጋር ለሚያውቃቸው ሶስት ጋዜጠኞች በመላክ ተከናንቦ ለመተኛት ሞከረ፡፡
ጥዋት አስራሁለት ሰዓት ተኩል ነው የባነነው፡፡ሶፋውን ለቀቀና ሳሎኑ ውስጥ እየተዘዋረ ሰውነቱን ሲያፍታታ ከወደኪችን ድምፅ ሰማ ..ቀስ ብሎ ተጠጋና ‹‹ፀዲ››ሲል ተጣራ፡፡
በበራፉ ብቅ አለችና‹‹እንዴ !!ቀሰቀስኩህ እንዴ?››
‹‹አይ በራሴ ነው የተነሳሁት… የተኛሽ እኮ ነው የመሰለኝ፡፡››
‹‹እንዴ የልጅ እናት እኮ ነኝ…ልጄን ቁርስ አብልቼ የምሳ ዕቃዎን ቆጥሬ ወደትምህርት ቤት መላክ አለብኝ..በዛ ላይ ችኮ የሆነ እንግዳ አለብኝ››
‹‹አንቺ እኔ ችኮ…ብሎ ሊይዛት ወደእሷ ሲንደረደር ተፈናጥራ ወደውስጥ ገባች…ተከትሎት ገባ…‹‹አንተ እረፍ ….ምግቡን እንዳታስደፋኝ፡፡››ከኃላ አቀፈና አንገቷን ሳማት…ከንፈሩ እዛው አንገቷ ላይ ተጣብቆ እንዲቆይ ተመኘች…. ግን ‹‹እማዬ ..እማዬ›› ብሎ የሚጣራውን የምስርን ድምፅ ሲሰሙ ሁለቱም በፍጥነት ተላቀቁ….
…..
አንድ ሰዓት ተኩል ሲሆን ምስርን አብረው ወጥተው ሰርቢሶ ድረስ ሸኞትና ወደቤት ተመለሱ…ቁርስ አቀረበችና እየተጎራረሱ መብላት ጀመሩ‹‹ቆይ ስራ የለህም እንዴ?››
‹‹ለአንድ ወር ምንም ስራ ላለመስራት አመቻችቼለው…ያሉኝን የስራ ቀጠሮዎች ሁሉ ሰርዣለው፡፡
ተስፋ ቆረጠች…‹‹ጥሩ ነው…ግን ያው እዚህ እንደምታየው ምንም አይመችህም..ቤታችን ጠባብ ነው..አንድ ምኝታ ቤት ብቻ ነው ያለን…..አባትህን ካየህ በኃላ ቆንጆ ምሳ ጋብዝህና ከዛ ወደ አዲስ አበባ እሸኝሀለው፡፡ባይሆን ቅዳሜ እመጣና አንተ ጋር አድራለው››
‹‹አይ …አታስቢ…ሶፋ ላይ መተኛት እንደዚህ እንደሚመች አላውቅም ነበር……በጣም ተመችቶኛል….ደግሞ ትዳር መስዋዕትነት ይጠይቃል….አንቺ ካለሽ እንኳን እንደዚህ አይነት ቤት ገጠር ጎጆ ቤት ውስጥም ቢሆን ይመቸኛል፡፡››
ከእሱ ጋር መከራከር ልብ የሚያቆስል ተግባር ሆኖ ነው ያገኘችው….በቀጣይ ምን ብዬ ልመልስለት ብላ ስታስብ ስልኳ ጠራ…እሷ ጋር ምትሰራ ልጅ ነች፡፡የስራ ጉዳይ ነው ብላ ችላ አለችው፡፡ደግሞ ተደወለ..አነሳችው፡፡
‹‹ፀዲ እንኳን ደስ ያለሽ››
ግራ ተጋባች‹‹ለምኑ?››
‹‹ምን አገር ምድሩ የሰማውን ነገር እኔን እንዴት ትደብቂኛለሽ?››
‹‹ምኑን ነው የምደብቅሽ?››
‹‹ለማንኛውም..ለባሉም ለልጁም እንኳን ደስ ያለሽ..ግን ድል ያለ ድግስ እፈልጋለን››
ስልኩን ጠረቀመችባት…..ዘሚካኤልን አፍጥጣ አየችው….እሱ እየሆነ የለው ነገር ስለገባው ብዙም አልተደናገጠም….ወዲያው መልሶ ስልኳ ጠራ…ሌላ የምታውቃት ሴት ነች…አነሳችው፡፡
ሰላምም ሳትላት ቀጥታ ወደጉዳዩ ገባች‹‹አንቺ …ያንን የመሰለ አርቲስት አፈሺው አይደል….?አንኳንም ደስ ያለሽ….ሰርጉን እንዳትረሺን››
‹‹ምንድነው ?የምን ሰርግ››
‹‹እንዴ ዪቲዩብና ፌስ ብክ ጠቅላላ በአንቺና በእጮኛሽ ፎቶ ተጥለቅልቆ የለ እንዴ››ስልኩን ጠረቀመችና ፌስ ብኩ ከፈተች..፡፡

👍58❤14😢2
ታዋቂው ዘፋኝና የፊልም አክተር ዘሚካኤል በመጨረሻ ሊያገባ እንደሆነ ተናገረ፡፡
ይህቺ በምስሉ ላይ የምትታየው የአዳማ ልጅ በጠም እንዳፈቀራትና በቅርብ ሊጋቡ እንደሆነ …እንደፀነሰችለት ሲያውቅ በደስታ ሻንጣውን ሸክፎ እቤቷ እንደገባና በቅርብ ከተጋቡ በኋላ ተነጋግረው ኑሮቸውን ወደአዲስአበባ እንደሚያዘዋውሩ ይገልጻል…ከፅሁፉ ጋር የተያያዘው ፎቶ ቦንጋ በሄዱ ጊዜ ተቃቅፈው እየተሳሳሙ እንደቀልድ የተነሱት ፎቶ ነው፡፡
እየተረተረች ስታይ…..ማህበራዊ ሚዲያውን ጠቅላላ አደበላለቆታል፡፡የዜናው ምንጭ የራሱ የገዛ የፌስ ቡክና የኢንስታግራም ገፅ ነው፡፡
‹‹ምንድነው ይሄ…?አንተ እንደዚህ ብለሀል እንዴ..?ብላ ስልኳን አቀበለችው..ተቀብሎ አየት አደረገና .‹‹.አዎ…››ሲል መለሰላት፡፡
‹‹የምን ልጅ ነው?››
‹‹አረባክሽ….?››
ከመበሳጨቷ የተነሳ መናገር አንኳን አቃታት‹‹ግን የእውነት አእምሮ ጤነኛ ነው….ሁል ጊዜ ለምን እራስህን ብቻ ታዳምጣለህ…?ይሄንን ነገር ለማድረግ ከማሰብህ በፊት እሷስ ምን ታስባለች…..?ብለህ አታስብም፡፡››
‹‹አንቺስ ልጄን ለማስወረድ ከመነሳትሽ በፊት ስለዚህ ጉዳይ እሱስ መስማት የለበትም ወይ…?ብለሽ አታስቢም፡፡››
‹‹እና በቀል መሆኑ ነው…?››
‹‹አይ በቀል ሳይሆን ነገሮችን ወደትክክለኛ መስመር እንዲገቡ እያስተካከልኩ ነው፡፡በነገራችን ላይ በሚቀጥለው ሳምንት ወደቤተሰቦችሽ የምልካቸውን ሽማግሌዎች አዘጋጅቼለው..ድንገት እንዳይሆንባቸው አሁኑኑ ደውለሽ ለወላጆችሽ ንገሪያቸው፡፡››
ከተቀመጠችበት ተነሳች…መልሳ ቁጭ አለች…ከንደገና ተነሳች‹‹ይሄውልህ ምን አይነት ክፉ ሰው ያልሆነ ነገር ነግሮህ እንዳሳሳተህ አላውቅም..እኔ ምንም ልጅ አልፀነስኩም…ልጅ ሚባል በማህፀኔ የለም››
‹‹እሺ ቀላል ነው..››ኪሱ ገባና የእርግዝና መመርመሪያ አውጥቶ ጠረጴዛ ላይ አደረገና›› በቃ መሳሳቴን አሳምኚኝ… አይኔ እያየ ያው ተጠቀሚና አለማርገዝሽን አሳይኝ፡፡››
‹‹አላደርገውም….››መመርመሪያውን አነሳችና ሰባብራ ወደውጭ ወረወረች..ተንከትክቶ ሳቀ…‹‹አየሽ እኔ አልተሳሳትኩም…..ልጄን ምንም ነገር ማድረግ አትቺይም…ታፈቅሪኛለሽ አፈቅርሻለው..እናም እንጋባለን››
‹‹እኔ ካንተ ፍቅር አልፈልግም አልኩህ…..››
‹‹እና…››
..ልትመልስለት አፏን ስትከፍት የዘሚካኤል ስልክ ጠራ….ስልኩን አነሳው፡፡
‹‹ደህና አደርክ ወንድሜ?››
‹‹ደህና ነኝ..ደረስክ እንዴ?››
ደርሼለው…..ሰአት ገና ስለሆነ ፀዲ ጋር ጎራ አልኩ..እኔም ከእናንተ ጋር እሄዳለው እያለችኝ ነው››
‹‹በጣም ጥሩ እኔም እንደዛ አስቤ ልደውልላት ነበር……እና አሁን የት ናችሁ?፡፡››
‹‹እሷ ቤት››
በቃ አዲስንና ቅዱስን ይዣ እመጣለው..እዛ ጠብቁኝ.. ከ30 ደቂቃ በኃላ እደርሳለው…ሁላችንም ተያይዘን እንሄዳለን፡፡
ፀደይ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጋ ሶፋው ላይ ሄዳ ተቀመጠች፡፡
‹‹ሰማሽ አይደል..ተዘጋጅታችሁ ጠብቁኝ ብሎል….አንቺም መገኘት አለብሽ…ይልፋትሽን ውጤት ማየት ይገባሻል….በዛ ላይ አባቴ ምራቱንና የወደፊት የልጅ ልጁንም መተዋወቅ አለበት፡፡
‹‹በጣም ሟዛዛ ሰው ነህ ..ታውቃለህ አይደል?፡፡››
‹‹አዎ አውቃለው..››አለና ከጎኗ ተቀመጠ…ፈራ ተባ እያለ ወደራሱ ጎትቶ ደረቱ ላይ ለጠፋት..እጅ በመስጠት መንፈስ ቀና ብላ አይን አይኑን ማየት ጀመረች፡፡ወደታች ዝቅ አለና ከንፈሯ ላይ ተጣበቀ…..እጇቾን በአንገቱ ዙሪያ ጠመጠመች….ከተቀመጠችበት ተነሳችና እላዩ ላይ ተቀመጠችበት…..የለበሰችውን ልብስ ማውለቅ ጀመረ…ሁለቱም ያለቻቸውን ጥቂት ደቂቃ በጥድፊያ ሊጠቀሙባት የቸኮሉ ይመስላሉ….እርስ በርስ እንደተቃቀፉ ወለሉ ላይ ወደቁ….‹‹እኔ እኮ ከአንተ ፍቅር አልፈልግም…..››ስትል ቃተተች
✨ተፈፀመ✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe ቤተሰቦች ይሄን የምታነቡ ምንያህላቹ subscriber አድርጋችኋል??? በቅርብ በሌላ ታሪክ እንገናኛለን እስከዛው #Subscribe

👍113❤26😁13🤔10🥰2
#የሚፈልጉትን_አይፈልጉትም
#አጭር_ታሪክ
ግልጽ ሰው እወዳለሁ አለችው
ህይወቱን ግልጽ ነገራት ጠላችው
ቀላል ሰው ደስ ይለኛል አለችው
ቀለል ሲል ረከሰባት ሸሸችው
ኩሩ ሰው ምርጫዬ ነው ስትለው ኮራ አለ
ጠበርክ ብላው ሄደች።
የተረጋጋ ሰው እወዳለሁ አለችው
ሲረጋጋ ተንቀራፈፍቅ ብላው ሄደች
የማይጨቃጨቅ ሰው ነው ምርጫዬ አለች
ስህተቷን ሲያልፋት ባትወደኝ ነው ግድ ያለሰጠህ አለችው
አስሬ መገናኘት መደዋወል ምናምን አልወድም አልችው።
መደወሉን ሲቀንስ ብትፈልገኝ ኖሮ ይሄንንም ብልህ ገፍተህ ትመጣ ትደውል ነበር። በቃኸኝ አለችው።
ምን እንዳጠፋ አሰበ።
እስካሁን አልገባውም።
ለአባቱ ነገረው ሁሉንም። አባቱ መለሰለት።
"ሰው ወዳለሁ ያለው ሁሉ አይኮንለትም።
ያለውን ሁሉ የምደረግለት ለአምላክህ ነው።
ሰው እኮ የፈለገውን ነገር ገና መፈለጉን አርግጠኛ አደለም።
የሚወደውን ነገር ለይቶ ያልጨረሰ ፍጡር ነው።
በተለይ እነሱ ወጣቶቹ የሚፈልጉትን ራሱ በቅጡ አይፈልጉትም"
"ምን ልሁንላት?"
"ራስህን ሁንላት!
የምትልህን ትተህ የማትልህን ሁንላት።
ሴቶች ከንግግራቸው ጋ ሩቅ ናቸው።
ያሉህን ትተህ ያላሉህን ስማቸው"
የልጁ ስልክ ጮኸ። እሷ ናት።
~ ~ ~ ~
💧ኤልያስ ሽታኹን💧

👍55🔥8❤7👏1
"ሁሌ ባገኝህ አይሰለቸኝም" አለችው
"እውነትሽ ነው"
"አዎ ገና መተዋወቃችን ቢሆንም ደጋግሜ ላገኝህ እፈልጋለሁ"
ዝም ተባባሉ ረጅም ሰዓት።
"እኔ ምልህ ህይወት ላንተ ምንድነው አለችው?"
"ቀይሮ መድገም ነው" አላት
"ማለት"
"አሁን የሆነች ተራ ካፌ ቡና ትጠጪያለሽ ሲኖርሽ ሸራተን ነው ራሱን ቡና
አሁን አንድ ክፍል ቤትሽ ውሰጥ ትተኛለሽ
ሲኖርሽ አስር ክፍል ያለው ግን አንዱ ክፍል ብቻ ራሱን እንቅልፍ ትተኛለሽ
ደሀ ሆነሽ አረቄ ነው
ሀብታም ስትሆኚ ውስኪ ነው ቀይሮ መድገም
ሰው ለምን ይመስለሻል አንድ ደብር ደጋግሞ ከመሳለም ደብር የሚቀያይረው ቦታ ቀይሮ ጸሎት ለመድገም ነው።
በፊት የሆነ ልጅ ትወጃለሽ ስትለያይ
ልጅ የሆነ ትወጃለሽ
ያንኑ መውደድ ቀይሮ ነው መድገም ነው
የሆነ ዘፈን በሌላ ዘፈን ዘፋኝ ቀይሮ መድገም
የምታውቂውን ስብከት በሌላ ሰባኪ ወይም ቄስ ቀይሮ መድገም
በኢኮኖሚ ክላስ መሄድ ዝነኛ ስትሆኚ እዛው ፕሌን ውስጥ ቢዝነስ ክላስ ሆኖ ወንበር ቀይሮ በረራ መድገም
ሰው ሁሉ ገንዘብ የሚፈልገው የነበረውን ነገር ቀይሮ ለመድገም ነው።"
የሆነ ነገሯ ተዛባባት።
"በቃ የዘመኑን ከቨር ሙዚቃ ታውቂያለሽ?"
"አዎ" አለችው
"የኛ ሰው ህይወት እንደዛ ነው
የህይወት ከቨር በይው።
የሆነ የሆነ ነገር ቀንጭጮቦ መምጣት ቀጣጥሎ ማዜም
ቀያይሮ መድገም..."
"የሚቀጥለው አመት እደውልልሀለሁ" አለችው
💧ኤልያስ ሽታሁን💧

👍57❤7🔥2
የምታውቁት ሰው ሲጠላችሁ
የማታውቁት ነው የሚያነሳችሁ!
ቅዱስ ዮሴፍ የሚያውቁት
ወንድሞቹ ሸጡት
የማያውቁት ግብፆች አነገሱት!
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
የማታውቁት ነው የሚያነሳችሁ!
ቅዱስ ዮሴፍ የሚያውቁት
ወንድሞቹ ሸጡት
የማያውቁት ግብፆች አነገሱት!
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍50❤6🥰1
እንዴት እንደመጣሁ እንዳትጠይቂኝ
ለምን
ስለምትናፍንቂኝ፡፡
አውቀዋለሁኛ
አንድ የበደለሽ ሰው ናፍቀሺኛል ቢልሽ
ላንቺ
ፌዝ ነው የሚመስልሽ
፡
፡
ግን ናፍቀሽኛል፡፡
፡
አዎ
በድያለሁ በግፍ
ደግሞም
ናፍቀሽኛል በእጥፍ፡፡
ማርያምን የምሬን በዝቷል መናፈቄ
የትም እገኛለሁ
የትም እስቀለሁ ግን ያለቅሳል ሳቄ፡፡
ብራመድ በሀገሩ
ብክንፍ እንኳ ብበር
ተከፍቶ አያለሁ ቆለፍኩት ያልኩት በር፡፡
ቀን የከረቸምኩት
ሌት በምን ከፈትኩት?
በለሊትሽ መጣሁ
አለሜን ስላጣሁ
ከትናንት የባሰ እንደማጣሽ ሳስብ
በደሌን አየሁት እጥፍ መውደድ ሲስብ
አንቺዬዋ ወዴ
የበደለ ሁሉ አይናፍቅም እንዴ...
ማቀፍ እንኳ ባልችል ምረት ባለምንም
አትሳቂብኝ እንጂ
ግጥሙን እያነበብኩ ናፍቀሽኝ አሁንም፡፡
ፀሀይዋን ከተትኳት
አይንሽን ለማየት ከቤቴ እየወጣሁ
የበደለ አይኔን እንዳታይኝ ብዬ
በጨለማ መጣሁ፡፡
ደረስኩኝ ከደጅሽ መፍራቴ በነነ
እሰይ አገኘሁሽ ናፍቆቴ ሰው ሆነ፡፡
እከንፋለሁ ይኸው ስደርስም አልሳምሺኝ
አጃኢብ ሰው መሆን
ሳጠፋ ጊዜ ነው ጭራሽ የናፈቅሽኝ፡፡
አጥፍቻለሁ አዎ መውደዴን ቀብሬ
አትሳቂብኝ እንጂ
ልክ ስበድልሽ ጨመረብኝ ፍቅሬ፡፡
:
:
:
ናፈቅሽኝ፡፡
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
ለምን
ስለምትናፍንቂኝ፡፡
አውቀዋለሁኛ
አንድ የበደለሽ ሰው ናፍቀሺኛል ቢልሽ
ላንቺ
ፌዝ ነው የሚመስልሽ
፡
፡
ግን ናፍቀሽኛል፡፡
፡
አዎ
በድያለሁ በግፍ
ደግሞም
ናፍቀሽኛል በእጥፍ፡፡
ማርያምን የምሬን በዝቷል መናፈቄ
የትም እገኛለሁ
የትም እስቀለሁ ግን ያለቅሳል ሳቄ፡፡
ብራመድ በሀገሩ
ብክንፍ እንኳ ብበር
ተከፍቶ አያለሁ ቆለፍኩት ያልኩት በር፡፡
ቀን የከረቸምኩት
ሌት በምን ከፈትኩት?
በለሊትሽ መጣሁ
አለሜን ስላጣሁ
ከትናንት የባሰ እንደማጣሽ ሳስብ
በደሌን አየሁት እጥፍ መውደድ ሲስብ
አንቺዬዋ ወዴ
የበደለ ሁሉ አይናፍቅም እንዴ...
ማቀፍ እንኳ ባልችል ምረት ባለምንም
አትሳቂብኝ እንጂ
ግጥሙን እያነበብኩ ናፍቀሽኝ አሁንም፡፡
ፀሀይዋን ከተትኳት
አይንሽን ለማየት ከቤቴ እየወጣሁ
የበደለ አይኔን እንዳታይኝ ብዬ
በጨለማ መጣሁ፡፡
ደረስኩኝ ከደጅሽ መፍራቴ በነነ
እሰይ አገኘሁሽ ናፍቆቴ ሰው ሆነ፡፡
እከንፋለሁ ይኸው ስደርስም አልሳምሺኝ
አጃኢብ ሰው መሆን
ሳጠፋ ጊዜ ነው ጭራሽ የናፈቅሽኝ፡፡
አጥፍቻለሁ አዎ መውደዴን ቀብሬ
አትሳቂብኝ እንጂ
ልክ ስበድልሽ ጨመረብኝ ፍቅሬ፡፡
:
:
:
ናፈቅሽኝ፡፡
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
❤39👍18🥰2
(አንቺ ተኝተሽ እስክትነቂ የተፃፈ)
ሰርቄ ልቀፍሽ ሰርቄ ልሳምሽ
ከባልሽ በፊት ነው ልቤ የሚያስብሽ
ወድጄ መሰለሽ
የሳሙትን ከንፈር በሌላ ሲወዛ
ያሳደጉትን ነፍስ በስጋ ሲገዛ
መታዘብ ያበሽቃል
ቱ ቱ ቱ
እኔ ጋር ስትመጪ መብሸቄ ይወድቃል፡፡
ባልሽን እርሺልኝ
መንትፌ ልቀፍሽ
ደብቄሽ እቀፊኝ
ጨለማን ስናስስ
ከብርሀን ስፊኝ፡፡
መስረቅ ቢሆን ሀጢያት በሰው የሚያስነቅፍ
እንዴትም አልሰማ ጆሮዬ ካንቺ እቅፍ፡፡
እቅፍቅፍ ...
እጥምጥም ትጥምጥም
ሞቴ ባንቺ ሲጥም፡፡
አበጀሁ ሰረቅኩሽ
እምጿ!!!!!
ይኸው ሳምኩሽ፡፡
እሰይ እዘርፉለሁ
እሬሳ እስከምሆን
ማነው የሚያውቅልኝ
ባልሽስ ራሱ ከኔ ዘርፎሽ ቢሆን?
እረ....
ትዳር በቀደመ::
ይቀድመኝ
ግድ የለኝ፡፡
የሰው ነሽ እያልኩኝ ኑሪልኝ ከእቅፌ
እንኳንና ሞቴ አይመጣም እንቅልፌ፡፡
ሰርቄ ልቀፍሽ ሰርቄ ልሳምሽ
ከባልሽ በፊት ነው ልቤ የሚያስብሽ
በይ
ደርቢ እንዳይበርድሽ፡፡
----------///////----------
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
ሰርቄ ልቀፍሽ ሰርቄ ልሳምሽ
ከባልሽ በፊት ነው ልቤ የሚያስብሽ
ወድጄ መሰለሽ
የሳሙትን ከንፈር በሌላ ሲወዛ
ያሳደጉትን ነፍስ በስጋ ሲገዛ
መታዘብ ያበሽቃል
ቱ ቱ ቱ
እኔ ጋር ስትመጪ መብሸቄ ይወድቃል፡፡
ባልሽን እርሺልኝ
መንትፌ ልቀፍሽ
ደብቄሽ እቀፊኝ
ጨለማን ስናስስ
ከብርሀን ስፊኝ፡፡
መስረቅ ቢሆን ሀጢያት በሰው የሚያስነቅፍ
እንዴትም አልሰማ ጆሮዬ ካንቺ እቅፍ፡፡
እቅፍቅፍ ...
እጥምጥም ትጥምጥም
ሞቴ ባንቺ ሲጥም፡፡
አበጀሁ ሰረቅኩሽ
እምጿ!!!!!
ይኸው ሳምኩሽ፡፡
እሰይ እዘርፉለሁ
እሬሳ እስከምሆን
ማነው የሚያውቅልኝ
ባልሽስ ራሱ ከኔ ዘርፎሽ ቢሆን?
እረ....
ትዳር በቀደመ::
ይቀድመኝ
ግድ የለኝ፡፡
የሰው ነሽ እያልኩኝ ኑሪልኝ ከእቅፌ
እንኳንና ሞቴ አይመጣም እንቅልፌ፡፡
ሰርቄ ልቀፍሽ ሰርቄ ልሳምሽ
ከባልሽ በፊት ነው ልቤ የሚያስብሽ
በይ
ደርቢ እንዳይበርድሽ፡፡
----------///////----------
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍25❤3👎3🥰1
#አጭር_ታሪክ
አንድ በእድሜ የገፋ አናፂ ፣ ጡረታ ሊወጣ ሲቃረብ የመጨረሻውን ቤት እንዲሠራ ተጠየቀ።
ደክሞት ስለነበረ ለማረፍ ጓጉቶ ርካሽ ቁሳቁሶችን ተጠቅሞ ስራውን በችኮላ ጨረሰ...
ሲጨርስ አሰሪው
''ይህ ቤትህ ነው ለአመታት ያገለገለልክበት ስጦታ'' ብሎ ቁልፉን ሰጠው። አናፂው ደንግጦ በግዴለሽነቱ ተፀፀተ። የራሱን ቤት የገነባው በደካማ ሁኔታ ነበር።
/////////
ዛሬ የምትሰራው ስራ ነገ የምትኖረውን ህይወት ይቀርፃል። ሁልጊዜ ጥሩውን ነገር ስራ!

👍57
#እቀናለሁ_አዎ
አጥንት ያነቅዛል ሲል ባይገባንም ውሉ
ቅናት ይሉት ነገር ተሰጥቷል ለሁሉ፡፡
#አዎን_እቀናለሁ
ያልቀኑበት ነገር ሲነጠቅ ስላየሁ፡፡
ብቻ ወድሽ የለ እኔ ምን አውቅና
ራሴን የማገኝ በሆንሽው ስቀና፡፡
ይኸውልሽ ጉዴ
ከከንፈርሽ በታች
ባለው ጥቁር ነጥብ ስቀና እያየሽኝ
እንደማላቅ ነገር ማርያም ስማኝ አልሽኝ፡፡
ለምን
ለምን ከንፈርሽ ጋር
ለምን አንቺን መርጣ
ለምን
ለምን
ለምን
ለምን ሳመችሽ ስል ብዬ ደፋ ቀና
አትፍረጂ ፍቅሬ
አፍቃሪ አይመርጥም በፍቅሩ ሲቀና፡፡
ለምን
እኔ ምን አቃለሁ ብቻ ወድሻለሁ!!!
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
አጥንት ያነቅዛል ሲል ባይገባንም ውሉ
ቅናት ይሉት ነገር ተሰጥቷል ለሁሉ፡፡
#አዎን_እቀናለሁ
ያልቀኑበት ነገር ሲነጠቅ ስላየሁ፡፡
ብቻ ወድሽ የለ እኔ ምን አውቅና
ራሴን የማገኝ በሆንሽው ስቀና፡፡
ይኸውልሽ ጉዴ
ከከንፈርሽ በታች
ባለው ጥቁር ነጥብ ስቀና እያየሽኝ
እንደማላቅ ነገር ማርያም ስማኝ አልሽኝ፡፡
ለምን
ለምን ከንፈርሽ ጋር
ለምን አንቺን መርጣ
ለምን
ለምን
ለምን
ለምን ሳመችሽ ስል ብዬ ደፋ ቀና
አትፍረጂ ፍቅሬ
አፍቃሪ አይመርጥም በፍቅሩ ሲቀና፡፡
ለምን
እኔ ምን አቃለሁ ብቻ ወድሻለሁ!!!
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍29🥰16❤5
በውሃ ላይ እርፍ
ያንቺን ገድል ልጽፍ....
(ላይሆንልኝ)
ቀለም ቢሆን ላይጽፍሽ ያንቺን ቁንጅና
የነፍስሸን ፊደል ላይችለው መሬት ብራና....
መታገሌ
መጃጃሌ፡፡
እንደው
ድከም ያለው
አንቺን የወደደ አንቺን የተመኘ
ተሞኘ፡፡
ሁሉን ትቼ ኖሬ ልጽፍሽ ከምጥር
በቃሌ ባጠናሽ እንደመንፈስ ምስጢር፡፡
(ይሻላል)
በቃሌ ወደድኩሽ
በቃሌ ናፈቅኩሽ
አይገርምሽም?
በቃል እየያዙ በቃል አለመጻፍ
ምንም አለማለት እያለ ምላስ አፍ
በቃል ብወድሽም
በቃል ባሰብሽም
ቃል ግን አይጽፍሽም፡፡
(አይገርምሽም?)
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ያንቺን ገድል ልጽፍ....
(ላይሆንልኝ)
ቀለም ቢሆን ላይጽፍሽ ያንቺን ቁንጅና
የነፍስሸን ፊደል ላይችለው መሬት ብራና....
መታገሌ
መጃጃሌ፡፡
እንደው
ድከም ያለው
አንቺን የወደደ አንቺን የተመኘ
ተሞኘ፡፡
ሁሉን ትቼ ኖሬ ልጽፍሽ ከምጥር
በቃሌ ባጠናሽ እንደመንፈስ ምስጢር፡፡
(ይሻላል)
በቃሌ ወደድኩሽ
በቃሌ ናፈቅኩሽ
አይገርምሽም?
በቃል እየያዙ በቃል አለመጻፍ
ምንም አለማለት እያለ ምላስ አፍ
በቃል ብወድሽም
በቃል ባሰብሽም
ቃል ግን አይጽፍሽም፡፡
(አይገርምሽም?)
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍21
ዝም በይ ዝም በይ
ገና ጨለማ ነው በዚህ ምድር ሰማይ
አንቺ ቃል ካወጣሽ ትወጣለች ፀሀይ::
ፀሀይ ወጣች ማለት
ካንቺ ጋር መለየት፡፡
ካንቺ ከመለየት ከመሸሽ ከመልክሽ
ፀሀይ ገብታ ትቅር ቃል አታውጪ ባክሽ፡፡
እንደኤልያስ ቃል ሰማይ እንዳዘዘ
ባንቺ ዝም ማለት ብርሃን ተያዘ፡፡
(እሰይ)
ያዥልኝ ያን ፀሀይ ያዣት ያችን ጀንበር
እስከዛሬስ ቢሆን
አንቺ ባታወሪ መች ታበራ ነበር?
አሁን
በዚህ ምሽት
ከኔ ተደባልቀሽ
ከኔ ተቀላቅለሽ
ከኔ ጋር ተራምደሽ
የሕይወትን ጣጣ ከኔ ጋር ተሻግረሽ
ፀሀይን አታውጫት አንድ ቃል ተናግረሽ፡፡
(ስወድሽ)
ባለችበት ትቅር አይንጋ ዘላለም
አይንጋ ዘላለም ባለችበት ትቅር
ብርሃን አያሻውም ሰው ካወረው ፍቅር፡፡
ዝም በይ ዝም በይ
ገና ጨለማ ነው በዚህ ምድር ሰማይ
አንቺ ቃል ካወጣሽ ትወጣለች ፀሀይ፡፡
(አታውሪ በዝምታሽ አብሪ)
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ገና ጨለማ ነው በዚህ ምድር ሰማይ
አንቺ ቃል ካወጣሽ ትወጣለች ፀሀይ::
ፀሀይ ወጣች ማለት
ካንቺ ጋር መለየት፡፡
ካንቺ ከመለየት ከመሸሽ ከመልክሽ
ፀሀይ ገብታ ትቅር ቃል አታውጪ ባክሽ፡፡
እንደኤልያስ ቃል ሰማይ እንዳዘዘ
ባንቺ ዝም ማለት ብርሃን ተያዘ፡፡
(እሰይ)
ያዥልኝ ያን ፀሀይ ያዣት ያችን ጀንበር
እስከዛሬስ ቢሆን
አንቺ ባታወሪ መች ታበራ ነበር?
አሁን
በዚህ ምሽት
ከኔ ተደባልቀሽ
ከኔ ተቀላቅለሽ
ከኔ ጋር ተራምደሽ
የሕይወትን ጣጣ ከኔ ጋር ተሻግረሽ
ፀሀይን አታውጫት አንድ ቃል ተናግረሽ፡፡
(ስወድሽ)
ባለችበት ትቅር አይንጋ ዘላለም
አይንጋ ዘላለም ባለችበት ትቅር
ብርሃን አያሻውም ሰው ካወረው ፍቅር፡፡
ዝም በይ ዝም በይ
ገና ጨለማ ነው በዚህ ምድር ሰማይ
አንቺ ቃል ካወጣሽ ትወጣለች ፀሀይ፡፡
(አታውሪ በዝምታሽ አብሪ)
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍21❤6
የአምላክን ትዕዛዝ ልቤ እሺ ቢልም
ካንቺ ጋር የሆንኩት ሀጢያት አይባልም፡፡
ደብር የመሳለም ያህል
እንደ ትጉህ ገበሬ እህል
ሙሉ ነሽ
ልክ ነሽ፡፡
እናማ
ነይማ
መሳት
መሳሳት
ባንቺ ካለ
ፅድቅ ይሉት ገነት የት አለ?
ካንቺ አበላልጬ ገነትን ባልሽርም
አንቺን ያህል ቆንጆ ችዬ አለሸሞሽርም፡፡፡
የንፅህናሽ ልክ ገዝፎ ከምሳሌ
ያልታየ ገፄ ነሽ መሀሌ ማህሌይ፡፡
እቴ ባአንቺ መቅደስ
ወረብም አያፀድቅም ካንቺ ከመደነስ፡፡
የአምላክን ትዕዛዝ ልቤ እሺ ቢልም
ካንቺ ጋር የሆንኩት ሀጢያት አይባልም፡፡
(ለኔ)
ነውር እንደሆነ
ነውር እንደሆነ የእብድ እሳትን ማጥፋት
ነውር እንደሆነ ለማኝ ላይ መትፋት
ነውር እንደሆነ መሽናት ቤተስኪያን ዳር
ነውር እንደሆነ ያለእድሜ መዳር
ነውር እንደሆነ
ኪዳነውልድን ትቶ ቃል አውቃለሁ ማለት
ነውር እንደሆነ
ረስቶ መቀመጥ የግሸንን ስለት
ነውር እንደሆነ
በጁምኣ መሀል ሶላትን ማቋረጥ
ነውር እንደሆነ
በቆሞስ ወንበር ላይ ጉብ ብሎ መቀመጥ
እንደዚያ ነውር ነው አንቺን አለመሳም
የወደደ ሲያብድ ለነገው አይሳሳም፡፡
አልሳሳም ለነገ አልሳሳም ለተስፋ
ትዕዛዝ አይባልም
ፅድቅ የሚሉት ምስጢር ፍቅርን ከገፋ፡፡
ናፈቅሽኝ።
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ካንቺ ጋር የሆንኩት ሀጢያት አይባልም፡፡
ደብር የመሳለም ያህል
እንደ ትጉህ ገበሬ እህል
ሙሉ ነሽ
ልክ ነሽ፡፡
እናማ
ነይማ
መሳት
መሳሳት
ባንቺ ካለ
ፅድቅ ይሉት ገነት የት አለ?
ካንቺ አበላልጬ ገነትን ባልሽርም
አንቺን ያህል ቆንጆ ችዬ አለሸሞሽርም፡፡፡
የንፅህናሽ ልክ ገዝፎ ከምሳሌ
ያልታየ ገፄ ነሽ መሀሌ ማህሌይ፡፡
እቴ ባአንቺ መቅደስ
ወረብም አያፀድቅም ካንቺ ከመደነስ፡፡
የአምላክን ትዕዛዝ ልቤ እሺ ቢልም
ካንቺ ጋር የሆንኩት ሀጢያት አይባልም፡፡
(ለኔ)
ነውር እንደሆነ
ነውር እንደሆነ የእብድ እሳትን ማጥፋት
ነውር እንደሆነ ለማኝ ላይ መትፋት
ነውር እንደሆነ መሽናት ቤተስኪያን ዳር
ነውር እንደሆነ ያለእድሜ መዳር
ነውር እንደሆነ
ኪዳነውልድን ትቶ ቃል አውቃለሁ ማለት
ነውር እንደሆነ
ረስቶ መቀመጥ የግሸንን ስለት
ነውር እንደሆነ
በጁምኣ መሀል ሶላትን ማቋረጥ
ነውር እንደሆነ
በቆሞስ ወንበር ላይ ጉብ ብሎ መቀመጥ
እንደዚያ ነውር ነው አንቺን አለመሳም
የወደደ ሲያብድ ለነገው አይሳሳም፡፡
አልሳሳም ለነገ አልሳሳም ለተስፋ
ትዕዛዝ አይባልም
ፅድቅ የሚሉት ምስጢር ፍቅርን ከገፋ፡፡
ናፈቅሽኝ።
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍25❤5👎5🥰2😱2