አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሮዛ


#ክፍል_አስር (🔞)



የረሱት ነገር ታወሳቸውና ተመለሱ። በንግግር ስላስደሰትናቸው ይሁን በሌላ
እላውቅም እኔን ጨምሮ ከአጠገባቸው ለምንገኝ አምስት ሴቶች በግምት ከኪሳቸው ዘግነው በርካታ ዶላሮችን ሳይቆጥሩ ሰጡን ሁላችንንም ለሁለተኛ ጊዜ ተሰናብተውን ወደ ክፍት መኪናቸው አመሩ ቅድም ግራና ቀኝ ከአጠገቤ ተቀምጠው የነበሩት ሴቶች ቀረቡኝ

ነገሩ ምንድ ነው?ምንም የተሰጠን ቀጠሮ የለም፤እስካሁን ምንም እይነት መደበኛ የሆስቴስነት ምዝና እላየንም፣በቃ ይሔው ነው?"

ጥቁር ቱ ፒስ የለበሰችው ጠየቀችኝ፡፡

አንቺማ ተመችተሻቸዋል፣ዶላርም አንበሽብሸውሻል፣እሁን ቀጣይ ቀጠሮ መቼ ነው?ምንም የሰጡን ፍንጭ እኮ የለም” ሌላኛዋ ጠየቀችኝ፤
አሁን እኮ ሁሉም ሄደዋል ጋዳፊም አስተርጓሚውም፣ቪዲዮ ቀራጮቹም…ቀጣይ ቀጠሮ ቢኖር እስካሁን
ይነግሩን ነበር" ባለ ጥቁር ፒሷ ሴት መለሰችላት፡፡
“ምናልባት ከመጀመሪያው አንስቶ በቪዲዮ ስለቀረጹን አገራቸው ገብተው የሚፈልጉትን ከመረጡ በኋላ
ቅድም በመዘገቡት በአድራሻችን ሊያግኙን አስበው ይሆናል”

ግምቴን ገለጽኩላቸው፡፡

“እንዴ ጠባሳ፣ንቅሳት፤የተሸረፈ ጥርስ፣የእግር ክፍተት፣የጥርስ ውበት፣ጥፍር፣መልክ፣ተከለቁመና ምናምን የሚባሉ ነገሮች አይታዩም ማለትነው?”ሌላኛዋ ሴት ጠየቀች፡፡

ንግግሯ የንዴት ድምጸት አለበት፣ውብ መልክ እና ማራኪ የሰውነት ቅርጽ አላት፡፡

እኔ መልማይ የሆነኩ ይመስል ሁሉም እየመጡ ቀጣዩ ምን እንደሆነ ይጠይቁኛል፡፡ አንዲት ሴት አስተናጋጅ
ኩኪስ በባህላዊ የአረብ ሰፌድ ይዛ ለሁላችንም አደለችን፡፡ ብዙዎቻችን እየሆነ ስላለው ነገር በትከከል
አልተገለጸልንም፡፡
ድንኳኑ ውስጥ ያለን ሴቶች በዚህ ውዝግብ ላይ እያለን አስተርጓሚው ከሁለት ሴት ፕሮቶኮሎች ጋ ወደ
ድንኳኑ ተመልሶ መጣና ሁላችንም አሁን ወደየ ቤታችን መሄድ እንደምንችል ነገረን፡፡ ሆኖም በሆቴሉ
መቆየት የሚፈልግ ካለ የሚፈልገውን በልቶና ጠጥቶ መስተናገድ እንደሚችል፣ ወጪው ሙሉ በምሉ በታላቁ መሪ በሙአመር ጋዳፊ እንደተሸፈነ ነገር ግን መጠጥ ክልከል እንደሆነ ነግሮን በጥድፊያ ሲል…ሁሉም ሴቶች ተንጫጫንበት፡፡

“የሆስተስነቱ ጉዳይ ከምን ደረሰ?” አለችው እንዲት ቀይ ቀጭን ከጥግ በኩል የተቀመጠች ልጅ
ስትናገር ብስጭትጭት እያለች ነወ፡፡ መጀመርያ ፊቱ ግር ያለው መሰለ፡፡ ከዚያ ከረዳቶቹ አንዱ ነገሩን ሊያብራሩለት
ብዙም ስለጉዳዩ መረጃ እንደሌለውና ሆኖም ትሪፖሊ ላይ ምርጫውን እካሄደው ውጤቱን እንደሚያሳውቁ እርግጠኝነት በሚያንሰው ድምጽ ተናገረ።

ሁላችንም ወደ ውጪ ስንወጣ አስተርጓሚው በምልከት ጠራኝ፡፡በድጋሚ የልቤ ምት ጨመረ፡፡ከሁለት አጃቢዎች
እሱ ወዳለበት ቀረብኩ፡፡” ታላቁ መሪያችን ነገ ምሽት 4፡30 ላይ ትሪፖሊ ከመሄዳቸው በፊት በቪላቸው የስንበት ግብዣ ያደርጋሉ፡፡ እዚያ እንድትገኚ እንፈልጋለን፡፡ሰአት እከብሪ፡፡ " ይህንን
ብሎኝ ከፕሮቶኮሎቹ ጋ ተፈተለከ፡፡የደስታና የጭንቀት ድብልቅልቅ ስሜት ወረረኝ፡፡የኡስማን ምከርሰምሯል፡፡

hሁለቱ ሴት ጓደኞቼ ጋር እንደተለየሁ ቅድም ሳልቆጥረው ቦርሳዬ ውስጥ ሞጅሬው የነበረውን ዶላር
ቆጠርኩት፡፡ 2200 የአሜሪካን ዶላር ከሊቢያው መሪ ኮሌኔል ሙአመር ጋዳፊ እጅ ተቀብያለሁ፡፡
የተደበላለቀ ስሜት ተሰማኝ፡፡ እጠገቤ ቆሞ የነበረን ላዳ ታክሲ ዋጋ ሳልጠይቅ ከኃላ ገብቼ ዘፍ አልኩበትና
ደረቴን ነፍቼ “ንዳው!” አልኩት፡፡ እሱ ሞቱሩን ሲያስነሳ እኔ ወደ ኡስማን ዘንድ እየደወልኩ ነበር፡፡

ሀሙስ ጥር 28 ፣ 2001

እንዳይደርስ የለም ሀሙስ ደረሰ፤ ማታ እሳቸው በሰጡኝ ስጦታ ኡስማንና ማኪን ጨምሮ ወድ ጓደኞቼን ሳዝናናቸው ነበር ያመሸሁት፡፡ ሆኖም ለዛሬ ንቁ ሆኖ ለመገኘት እነሱ ዊስኪ ሲጠጡ እኔ ሀይላንዴን ይዤ ነበር ምሽቱን ያጋመስኩት፡፡ ኡስማን እንደትናንት ሌሊት አቅርቦኝ አያውቅም፡፡ ብዙ ከዚህ በፊት ስለራሱ ነግሮኝ የማያውቃቸውን ነገሮች አጫወተኝ፡፡ ከኔ ጋር የሆነ የፍቅር ስሜት ጀማምሮት እንደነበር ሲነግረኝ
ግን ደነገጥኩ፡፡ በፍጹም ያልጠበቅኩት ነገር ነው፡፡ ቢሮው የተገናኘን ቀን ጠረጴዛ አስደግፎ ያደረገኝን አስታውሼው በሳቅ ሞተ፡፡ እሳቸው ዘንድ ስቀርብ እንዳልፈራ ይልቁንም በራስ መተማመኔ ይበልጥ
ሊማርካቸው እንደሚችል አስረዳኝ፡፡ እኔ በበኩሌ ሶስና ስለ ጓደኛዋ ሄርሜላና እንዴት ጋዳፊ ህይወቷን እንደለወጡት ኩሪፍቱ ያወራችልኝን ለኡስማን ነገርኩት፡፡ በጣም ገረመው፡፡ ይህንን ታሪክ
ሰምቶት እንደማያውቅም ነገረኝ፡፡

ከሰዓት ላይ ትንሽ ድካም ስለተጫጫነኝ ናፕ ነገር ወሰድኩኝ፡፡ ፍሬሽ ሆኜ ነቃሁ፡፡ ሆኖም ህልሜ በሙሉ
ከጋዳፊ ጋር የተያያዘ ሆነብኝ፡፡ ምን ያህል ስለነገሩ እንደተጨነቅኩ የገባኝ ያኔ ነው፡፡ ራሴን ዘና ለማድረግ ዋይን ቀማመስኩና አንዳይሸትብኝ ማስቲካ ማኘክ ጀመርኩ፡፡

ሸራትን እስከደርስ ድረስ ስልኬ እረፍት አልነበራትም፡፡እነ ራኪ መልካሙን ሁሉ እየተመኙልኝ ነበር ።ራኪ የምር ጋዳፊ ሊቢያ ይዘውኝ እንደሚሄዱ ስለጠረጠረች ከፍቷት ነበር፡፡ «እመቤቴን! እስላም ሁኚ ካሉሽ
የፈለገ ለምን መቶ ሺ ዶላር እይሰጡሽም እሺ እንዳትያቸው» ትለኛለች አስሬ፡፡ ለምን የኔ ኃይማኖት እንዳሳሰባት አልገባኝም፡፡

ወደ ሸራተን እያመራሁ እያለ የሆነ ለብሔራዊ ቡድን ተሰልፌ ለአለም ዋንጫ የምታሳልፈንን ፍጹም ቅጣት
ምት የመምታት ኃላፊነት የተጣለብኝ አይነት ሰው ሆኜ ተሰማኝ፡፡ የሆነ ያልተጠበቀ ነገር እንዳይከሰት
ፈጣሪዬን ከልቤ ተማጸንኩት፡፡ እስከ ዛሬ ምሽት ድረስ ለገንዘብ ያን ያህል የተጋነነ ጉጉት አውቅም ነበር፡፡ ምናልባት ያን ያህል ፍጹም ሀብታም የሚያደርግ ብር አገኛለሁ ብዬ ስላልጠበኩ
ይሆናል እንደዚያ ተስምቶኝ የማያውቀው አሁን ግን ድንገት ሚሊየነር ለመሆን እድል ያለኝ ሰው ነኝ
የሸራተንን ቅጥር ግቢ አልፌ ስገባ ጋዳፊ ገጠር በረሃ ላይ ያገኟት የቤኒኗ ሴት በአእምሮዬ ጓዳ ድንቅን አለችብኝ፡፡ አማተብኩኝ፡፡

ከምሽቱ 4:15

በሸራተን ቅጥር ግቢ ውስጥ ተገኘሁ፤ከቀጠሮዬ ሰአት 15 ደቂቃዎች ብቻ ቀርተውኛል፣ጋዳፊ ወዳረፉበት
ቪላ የሚወስደውን መንገድ ይዤ ስጓዝ የአንድ አጃቢያቸው ድምጽ አስቆመኝ፤አጃቢያቸው የሊቢያን
የሚሊተሪ መለዮ ሰብሷል፤ድምጹ የቁጣና የብስጭት ቃና አለው

አይነ ተዝሀቢ ቢሀዚል ለይል?”(አንቺ ሴት! በዚህ ሌሊት ወዴት ነው የምትሄጂው?)

“ኢንዲ መውሊድ መእ ረእሰል አፈሪቃ ሙአመር ጋዳፊ” (ከአፍሪካው መሪ ሙአመር ጋዳፊ .ጋ ቀጠሮ አለኝ) አልኩት፡፡ ደነገጠ፡፡ በጥርጣሬ አገላብጦ ከተመለከተኝ በኃላ በስልክ የሆነ ነገር ተናገረና…ባለሁበት እንድቆም አዘዘኝ፡፡ይህ ጠባቂ ከጋዳፊ ቪላ እጅግ ርቆ ነው የሚገኘው፤መልሴ ትንሽ ሰከን እንዲል
ሳያደርገው አልቀረም፡፡ከይቅርታ ጋር ጥቂት እንድታገስ ነገረኝ፡፡የሬዲዮ መገናኛውን(ሆኪ ቶኪውን በድጋሚ ወደ አፉ አስጠጋ፡፡ከኔ ራቅ ብሎ የማይሰማኝን ነገር አወራ፡፡ከእፍታ በኋላ ወጣቱ አስተርጓሚ ከሁለት ሴት ፕሮቶኮሎች ጋ መጣ፡፡ደማቅ ፈገግታውን ለገሰኝ፡፡

“መርሀባን ቢኩም፡አህለን ወሳህለን!ከይፈ ሀሉኪ?ኢንተዚሪኒ!Follow me, follow me please (እንኳን
ደህና መጣሽ አንዴት ነሽ?ተከተይኝ ተከተይኝ እባክሽን!”

እግረ መንገዴን ግራናቀኝ በርካታ ወንድ የጋዳፊ ጠባቂዎችን በየተወሰነ ሜትር ርቀት ተመለከትኩ፤ሁለተኛ
ደረጃ የጋዳፊ ጠባቂዎች መሆናቸው ነው፤ከጋዳፊ በቅርብ ርቀት የማይጠፉት 40ዎቹ ግዙፍ ደናግላን ግን የመጀመሪያ ደረጃ ጠባቂ ናቸው፡፡ይህን ወደ ቪላው ውስጥ ስገባ አረጋግጬያለሁ፤ቪላው
እንደገባን አንዲት የምስራቅ አውሮፓ ገጽታ ያላት ውብ ሴት
👍5
ተቀበለችኝ፡፡ወደ አንድ ክፍል ወሰደችን የክፍሉን በር ከፈተች በተሰባበረ እንግሊዝኛ እንዳንድ ጥንቃቄዎችን ነገረችኝ፤

ጋዳፊ ሰኞና ሀሙስ በግል ክፍላቸው ውስጥ የተገለጠችን ሴት አያናግሩም ሂጃብ ልበሽ ማስቲካ የምታኝክ ሴት ይፀየፋሉ ማስቲካ ከያዝሽ ካሁኑ ጣይው…እሳቸው ሳይፈቅዱ እጃቸውን ለመጨበጥ አትሞክሪ ምናልባት ካስነጠሰሽ አፍሽን በመሐረብ ሸፍኚ፣ ምግብ ከቀረበ እሳቸው ሳይጀምሩ መመጠብ እንዳትጀምሪ ሺ ማስጠንቀቂያዎችን ዘረዘረችልኝ፡፡ ፈራሁ፡፡

ከእፍታ በኋላ ጥቁር ሂጃብ ለብሼ ወጣሁ፤ሴቷ ወደ ሌላ ከፍላ ወሰደችኝ፤ እዚያ ክፍል የሆነ ሳጥን በሚመስል
የመፈተሻ ክፍል ውስጥ እንዳልፍ ተደረኩኝ። ከበሩ በስተግራና በስተቀኝ ሁለት ሴት ወታደሮች
ከወንዶቹ የሚሊተሪ መለዮ የተለየ የደንብ ልብስ ለብሰው ተራርቀው እንደ ሀውልት ቅንጣት ሳይንቀሳቀሱ ቆመዋል ሴቷ
ሁለቴ በዝግታ በሩን ካንኳኳች በኋላ ማንነቴን እና መድረሴን ነግራ ወደመጣችበት ተመለሰች።

የጋዳፊ እኩያ የሆነ ሰው በሩን
ከፈተልኝና ገባሁ፤አረቢያን መጅሊሱ ላይ እንድቀመጥ በእጁ ምልከት
ጋበዘኝ፡ “መርሀባን ቢኩም!አጅሊሲ” (እንኳን ደህና መጣሽ፣ ተቀመጭ)
ጋዳፊ ከአፍታ በኋላ ሲያነቡ የነበረውን ቅዱስ መጸሐፍ ከድነው በከብር ቦታው ላይ ካስቀመጡ በኋላ በፈገግታ ተመለከቱኝ፣ባልደረባቸው ከግዙፉ ፔርሙዝ ሻይ ቀዳልኝ፤ከኔ በኋላ ለጋዳፊና ለሱ ቀዳ፡፡ፈረስ ከሚያስጋልብ ሰፊ አልጋ ከክፍሉ ጥግ ላይ ከነግርማ ሞገሱና ከነቅንጦቱ ይታያል፡፡አረብና ሻይ የማይለያዩ የልብ ወዳጆች ናቸው ሲባል ሰምቻለሁ፡፡ ንጉስ ቤትም ሻይ ይጠጣል ለካ፡፡

ከሻዬ አንዴ እንደተጎነጨሁ ጋዳፊ ማንነቴን ጠየቁኝ፡፡ ትናንትና ከሌሎች ሴቶች ጋር መጥቼ እንደነበረ
እስታወስኳቸው፡፡ ወዲያው ትዝ አልኳቸውና ሳቁ፡፡ « አንቺ ባለብሩህ አእምሮ ሴት! አልረሳሁሽም፡፡
አሉኝ በአረብኛ፡፡ የሳቸው እኩያ የሆነው ሰው የሚሉኝን ነገር ጥርት ባለ የእረብ በማይመስል እንግሊዝኛ በፍጥነት ይተረጉምልኛል፡፡አረንጓዴውን መጽሀፋቸውን መቼ፣ለምንና እንዴት እንዳነበብኩት ጠየቁኝ፤መጽሀፋቸውን ማንበቤ ብርቅ የሆነባቸው ይመስለኛል፡፡ አንገቱና ደረቱ አካባቢ ውብ ጥለትና
አፍሪካዊ ዲዛይን ያለው ቡኒ ጀለቢያና ጥቁር የበደዊኖች አይነት የበረሀ ጥምጣም አድርገዋል፡፡ እስክረጋጋ
ድረስ ልብሳቸውን እንኳ በደንብ አላየሁትም ነበር፡፡

በኮሌኔል መንግስቱ የስልጣን ዘመን ሟቹ አባቴ ተወዳጅ ጋዜጠኛ እንደነበር፤የሳቸው ፖለቲካዊ አመራር
ከፍተኛ አድናቂ እንደነበረ፣ስለእሳቸው ስብእናና ፖለቲካዊ ህይወት በየእለቱ ይነግረኝ እንደነበር፣ቤት
ቁምሳጥን ላይ የነበረውን የመጽሀፋቸውን የአማርኛ ቅጂ በአባቴ ትእዛዝ እንዳነበብኩ ነገርኳቸው፡፡
ይህን በከፊል እውነት የሆነውን ታሪከ ትናንትና በጥንቃቄ የተዘጋጀሁበት ነገር ነው፡፡ ጋዳፊ ይህን ጊዜ
ፊታቸው በደስታ ፈካ፡፡ አባቴን «ይርሃመኩላህ!» ፈጣሪ ነፍሱን ይማር! ብለው ጸለዩለት ፡፡ መጽሀፋቸው
በኢትዮጲያ ቋንቋ መተርጎሙን እንደማያውቁ ነገሩኝ፡፡እኔም በጥቂት ኮፒ ብቻ ለአንድ ጊዜ ታትሞ
እንደነበር ከአባቴ እንደሰማሁ ነገርኳቸው፡፡የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በሆነችው አገር ውስጥ መጽሀፉ
በሚሊዮኖች ቅጂ እንዲታተም ከሳቸው የሚፈለገውን እገዛ እንደሚያደርጉና ብዙ ህዝብ ሲያነበው በርካታ
ቁምነገሮችን እንደሚያገኝበት ተናገሩ፡፡

የገረመኝ ነገር ቢኖር በየመሃሉ ከኔ ጋር ንግግራቸውን ሳይጨርሱ ይሄ ከሳቸው ጋር ካለው ሰውዬ ጋር የጦፈ ወሬ ይጀምራሉ፡፡እኔን መፈጠሬንም ይረሱኛል፡፡ ሻይዬን እንዳልጠጣሁትና እየቀዘቀዘብኝ እንደሆነ
አብረዋቸው የተቀመጡት ሰውዬ አስገነዘቡኝ፡፡

በድርጊቴ አፍሬ ጨለጥኩት፡፡ ሰውየው ሳቁብኝ፡፡

ጋዳፊ ወርቃማ ፔርሙዙን አንስተው በድጋሚ ሻይ ሊቀዱልኝ ሲሉ እንደሚበቃኝ ነግሬ ተከላከልኳቸው፤
ጨዋነቴን ማሳየቴ ነበር፡፡ አብረዋቸው ያሉት ሰው ግን በእይናቸው ገሰጹኝ፡፡ ወደ ጆሮዬ ጠጋ ብለው ለሳቸው በቃኝ ማለት እንደማልችልና ንጉስ እያስተናገደ በቃኝ ማለት ነውር እንደሆን አስገነዘቡኝ፡፡ ይሄኔ ድንብርብሬ ወጣ፡፡ ራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩ፡፡ ራሴን ለማረጋጋት በመኳርኩ ቁጥር ይበልጥ መረበሽ ጀመርኩ፡፡ በዚህ ቅጽበት ከእንድ አገር መሪ ሻይ እየተቀዳልኝ እንደሆነ ሳስብ ነገሩ
ህልም መሰለኝ።

አብሯቸው ያለውና ፈንጠር ብሎ የተቀመጠው ሶስተኛው ሰው እስካሁን ምንም አላወራም፤የሱ ሚና መስማት
ብቻ ይመስላል፤ማንነቱን ለማወቅ በውስጤ ብፈልግም አጋጣሚው እስካሁን አልተፈጠረልኝም፤ጋዳፊ
ሰውዬውን ለማስተዋወቅ ያደረጉት ጥረት የለም፤እሱን ቀርቶ እኔንም እስካሁን በስሜ አልጠሩኝም፤መልኬን
እንጂ ስሜን አላስታወሱትም ማለት ነው፡፡ለነገሩ እንዴትስ እንዲያስታውሱት እጠብቃለሁ? ምኗ ደፋር ነኝ በናታችሁ! ከዚያ ሁሉ ሴት ተወዳዳሪ መሀል የኔን ስም በተለየ ሁኔታ ሊይዙት አይችሉም የ6 ሚሊዮን ሊቢያዊ ዜጎቻቸው እንዲሁም አሁም ደግሞ በአዲሱ ሹመታቸው አንድ ቢሊዮን የሚጠጋው የእህጉራች
ሀላፊነት ያለባቸው ሰው ናቸው፡፡ በዚህ ሁሉ መሀል እንደኔ አይነቷን ተራ ሴት ስም በተአምር ካልሆነ በቀር ሊያስታውሱ አይችሉም፡፡እኔም ቂልነቴ እንጂ ይህን ማሰብ አልነበረብኝም፡፡

የዛሬዋን ምሸት ጨምሮ ባለፉት ሶስት ቀናት ካገኘኋቸው ሴቶች የኔን ያህል ያስተወሱት ሰው ያለ እንደማይመስላቸው አብረዋቸው ያሉት ሰው ነገሩኝ፡፡ ያን ሲነግሩኝ ጋዳፊ አጠገባችን ነበሩ፡፡ ግን የሰሙ አይመስለኝም፡፡ ትንሽ ግራ ያጋባል የጋዳፊ ፊት፡፡ እያዳመጡ እንደሆነ በእርግጠኝነት ለመናገር ፊታቸው
ግልጽ አይደለም፡፡ ሌላ ሰው እያወራ ድንገት ንግግር ይጀምራሉ፡፡ ወይም ፊታቸውን ወደሌላ አቅጣጫ
ያዞራሉ፡፡ ምን እያሰቡ እንደሆነ በእርግጠኝነት ማወቅ አይቻልም፡፡ እኔ ኡስማን ደጋግሞ በነገረኝ መሰረት
ራስ ወዳድነታቸውንና ውዳሴ አምላኪነታቸውን ከግንዛቤ በማስገባት ከሌሎቹ በተሻለ የግልና የፖለቲካ
ህይወታቸው ላይ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ትኩረት ስለሰጠሁ እንጂ ከተወዳዳሪዎቹ መሀል በስራ
መደብ፣በሙያም ሆነ በእውቀት የሚያስከነዱኝ በርካታ ተወዳዳሪዎች ነበሩ፡፡ጋዳፊ ስለሳቸው የፖለቲካ
ህይወትና አህጉራዊ አስተዋጽኦ ባለኝ እውቀት ደስተኛ እንደሆኑ ግዴለሽነት ስሚንጸባረቅባት አኳኋን
ከተናገሩ በኋለ ያልጠበኩትን ጥያቄ አቀረቡልኝ

“ማ ሚህነቱኪ?እንቲ ሷሀፊ፣ሙተርጂም ፣ካቲብ አው አዲብ?” (ሙያሽ ምንድ ነው ጋዜጠኛ ፣ተርጓሚ ፣ጸሀፊ ወይም ደራሲ ነሽ”

አዎ!ግምቴ ትክክል ነበር፤ጋዳፊ ስሜንም ሙያዬንም ረስተውታል፤ትላንት ምሽት ሁላችንም ንግግራችንን ከማቅረባችን በፊት ስማችንን፣እድሜያችንን እና ስራችንን መናገራችን ግዴታ ነበር፡፡ጋዳፊ እኔን በተመለከተ ሁሉንም ዘንግተውታል፡፡ትላንት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ እንደሆንኩ ነበር የተናገርኩት፡፡

መልሴን ሳይሰሙ ሰእታቸውን ተመለከቱ፡፡ ግራ የሚያጋቡ ሰው ናቸው፡፡የማይሰሙኝ ከሆነ ለምን ጠየቁኝ ታዲያ፡፡ ደግሞ እኔን ረሱኝና አብረዋቸው ካሉት ሰው ጋር ስለ ትናንቱ ስብሰባው ይሠስለኛል
የጦፈ ወሬ ያዙ፡፡ ጋዳፊ እልፎ አልፎ ይስቃሉ፡፡ ሲስቁ አይናቸው ፍጹም ይጨፈናል፡፡ ፊታቸው ሳይተኮስ
ቅርጫት ውስጥ እንደተረሳ ሸሚዝ እጥፍጥፍ ይላል፡፡ ሌላው ደግሞ ሲስቁ ከትከሻቸው ይገፈጠፋሉ
እኚህ አብረዋቸው ያሉት ሰው ቀልደኛ ቢጤ ሳይሆኑ አይቀሩም:: እኔ ከገባሁ በኃላ እንኳንከ ከአሁኑ ጋር ለሶስተኛ ጊዜ ሲያስቃቸው። ፈንጠር ብሎ የተቀመጠው ሰው ግን ምንም አይስቅም፡፡ጋዳፊ ሲናገሩ ብቻ ግንባሩን ያለማቋረጥ በእውነታ ሲነቀንቅ አስተውያለሁ።

በስብሰባው ዙርያ ይመስለኛል ፈጠን ባለና ልረዳው ባልቻልኩት አረብኛ ማውራት የያዙት
👍3
እኔን መፈጠሬንም እረሱኝ
መፈጠሬንም ረሱኝ፡፡እጄን የቱ ጋር እንደማደርገው ግራ ገባኝ፡፡ ከንዶቼ ረዘሙብኝ፡፡ አንድ ጊዚ ሻሼን አንድ ጊዜ ፀጉሬን እነካካለሁ፡፡ ግራ ሲገባኝ የተቀዳልኝን ሻይ ቀስ እያልኩ ማጣጣም ጀመርኩ፡፡ "ግሪንቲ" የሚባለው አይነት ሻይ መሰለኝ፡፡ ጣዕሙ ይለያል፡፡ እኚህ ሰው "ግሪፊ" በሚባል ነገር ሳይለከፉ አይቀርም።

በፈጣን አረብኛ ወሬያቸው መሀል «ረእሰል ሀበሻ ዜናዊ» የሚል ነገር አልፎ አልፎ ይሰማል ጆሮዬ ቆመ፡፡ ለወሬ እንዳቆበቁብኩ ሲገባቸው ነው መሰለኝ አብረዋቸው ያሉት ሰውዬ
We have been discussing your leader Mr. Zenawi, You guys have such a smart leader finally
afer Hailesilasie ካሉ በኃላ ረዥሙን ጺማቸውን ቁልቁል እየሳቡና አይን አይኔን
እየተመለከቱ what do you think of him? አሉኝ፡፡ ሁለቱም የምለውን ለመስማት አቆበቆቡ፡፡
ሆኖም የምለውን ማሰብ ገና ከመጀመሬ ጋዳፊ ምላሼን እንኳ ሳይሰሙ ስለ መንግስቱ ኃይለማርያም
ማውራት ጀመሩ፡፡ ጥሩ መሪ ነው ብለው ያስቡ እንደነበረና አገሩን ጥሎ ኩባ ከገባ በኃላ ግን አድናቆታቸው
እንደከሰመ በግማሽ እንግሊዝኛና በግማሽ አረብኛ ተናገሩ፡፡ Mengistu shame leader not good
leader የሚለውን ቃል ደጋግመው ተናገሩ፡፡

እኔ ቀልጠፍ ብዬ መንግስቱ ወደ ኩባ ሳይሆን ወደ ዚምባቡዌ እንደሄደ ገለጽኩ፡፡ጋዳፊ ሳቁብኝ፡፡ No..no that is what Americans are saying. Mengistu is now in Cuba. ብለው
ድርቅ እሉ፡፡

ጋዳፊ እንደተሳሳቱ ለመግለጽ መናገር ስጀምር ሽማግሌው ሰውዬ እንዲሁም ዝም ብሎ የሚያዳምጠው
ጎልማሳ በአይናቸው ገሰጹኝ፡፡ቅድም ጋዳፊ ሻይ ሲቀዱልኝ ለመከላከል ስሞከር በተመሳሳይ መልኩ
በአይናቸው ተቆጥተውኛል እኚህ ሽማግሌ የጋዳፊ ጓደኛ፡፡ በጣም ተገረምኩ፡፡ ጋዳፊ ተሳስተዋል አይባሉም
ማለት ነው፡፡ እግዚኦ አልኩ በሆዴ፡፡

ቅድም መምጣቴን የገለጸችላቸው ሴት ድንገት ገባችና ዝም ብሎ ያዳምጥ ለነበረው ሰው የሆነ ምልክት አሳየችው
እሱ ደግሞ ሊጋዳፊ በጆሯቸው አንሾካሾከላቸው፡፡ ተነስተው ሶላት መስገድ ጀመሩ። እሳቸው
መስገድ ሲጀምሩ ዝምተኛው ሰውዬ ወደ ደጅ እንድወጣ በምልከት ነገረኝና ተከትሎኝ መጣ፡፡

ማአሳላማ ያ ኡኽቲ !ኢለሊቃወዳአን በድጋሚ እስከምንገናኝ ደህና ሁኚ እህቴ

ደነገጥኩ፡፡ ፈርጠም ብዬ እሳቸውን በትክክል እንዳልተሰናበትኩ ነገርኩት፡፡ በእጁ "እሸሽ" የሚል ምልክት
ሰጠኝ፡፡ እየሰገዱ ማውራት ከልክል ነው አለኝ፡፡ “ጸሎት ከጀመሩ በኃላ ሰው አያናግሩም፤ ይቅርታ አሁን መሄድ ይኖርብሻል፡፡ ሸራተን ሆቴል ውስጥ መስተናገድ ከፈለግሽ ግን ማንኛውም ወጪ ይሸፈንልሻል መሪያችን የሚፈልጉሽ ከሆነ በአድራሻሽ የኛ ሰዎች እንዲያገኙሽ እናደርጋለን፡፡ ስለመጣሽና አብረሽን ስለቆየሽ ሹከረን ጀዚለን፡፡” ብሎ አሰናበተኝ፡፡ በአረብኛና በእንግሊዝኛ ነው የሚያወራው፡፡

ሰማይ ምድሩ ተገለባበጠብኝ፡፡ አንዳች የመከዳት ስሜት ተሰማኝ፡፡ ሁሉም ነገር የሆነው በጥቂት ሰከንዶች ውስጥ ነው:: ራሴን ለመከላከል እንኳ እድል አልነበረኝም፡፡

ሂጂ ዉጪ ስባል ኣልሄድም አይባል ነገር!

ሌላ ረዳታቸው ወደኔ መጥቶ መኪና ካልያዝኩ እንዲሸኘኝ እፈልግ እንደሆነ ጠየቀኝ፡፡ በብስጭት እንደማልፈልግ ነገርኩት፡፡ መበሳጨቴን ሲያይ ደነገጠ፡፡ ጋዳፊ ሰድበው ያስቀየሙኝ ሳይመስለው
አልቀረም፡፡
ከሳቸው ክፍል ስወጣም ሆነ የሸራተን ሆቴል ቅጥር ግቢን ስለቅ ልበሺ የተባልኩትን ሂጃብ አላወለቅኩትም
ነበር፡፡ሰአቴን ተመለከትኩ፤ 4፡55 ይላል፤በሊቢያው መሪ የመኝታ ክፍል ለ15 ደቂቃዎች ቆይቻለሁ፡፡
ጥቁሩን ሂጃብ እንደለበስኩ በእግሬ ወደ አምባሳደር አቅጣጫ ቁልቁል ማዝገም ጀመርኩ፡፡ አሁን ማን ያምናል ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ከሊቢያው ፕሬዝዳንት ጋር ሻይ ቡና ስትል የነበረች ልጅ በእግር ወደቤቷ ለመሄድ እየኳተነች እንደሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ቢያውቅ፡፡ ጋዳፊን ማግኘቴ ለራሴም አልዋጥልሽ አለኝ፤
እውነት እውነት አልመስልሽ አለኝ፡፡ የከሰዓት እንቅልፍ ላይ የማያቸውን ህልሞች አይነት ሆነብኝ፡፡
የማይጨበጥ ነገር፡፡
ድንገት የተለየ ነገር ካለ በሚል ፊቴን ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ሸራተን በር አቅጣጫ ሳዞር ከሁለት ቀናት በፊት
በሸራተን ሎቢ ውስጥ አይቼው የነበረውና ደህንነት እንደሆነ የጠረጠርኩት ከረፈፍ ጎልማሳ በቅብ
ርቀት እየተከተለኝ እንደሆነ አስተዋልኩ፡፡

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍71👏1
አትሮኖስ pinned «#ሮዛ ፡ ፡ #ክፍል_አስር (🔞) ፡ ፡ የረሱት ነገር ታወሳቸውና ተመለሱ። በንግግር ስላስደሰትናቸው ይሁን በሌላ እላውቅም እኔን ጨምሮ ከአጠገባቸው ለምንገኝ አምስት ሴቶች በግምት ከኪሳቸው ዘግነው በርካታ ዶላሮችን ሳይቆጥሩ ሰጡን ሁላችንንም ለሁለተኛ ጊዜ ተሰናብተውን ወደ ክፍት መኪናቸው አመሩ ቅድም ግራና ቀኝ ከአጠገቤ ተቀምጠው የነበሩት ሴቶች ቀረቡኝ ነገሩ ምንድ ነው?ምንም የተሰጠን ቀጠሮ የለም፤እስካሁን…»
#የምትመር_ፀበል

የግዱን ቢቀምሳት
የምትመር እውነት
ቋቅ ብሎት ወጣ
የደበቀው እብለት፡፡
#የዋህ

‹‹አባይን ያላየ
ምንጭ አመስገነ>>
ተመስገን እያለ
ራሱን ታለለ
ባገሩ መሬት ላይ
ጎበዝ ደባል ሆነ፡፡
1👍1
#መምሰል

ሆዳም በበዛብት
በዚህች ከንቱ አለም
ስለ ፍቅር ማውራት
ለፍቅር መመስከር
በይምሰል መባደር
ኧረ እንዲያው አናፍርም ...!?
በቀለበት ታስረን
በፊርማ ተጣምረን
ተፋቀርን ብሎ
እራስን ማታለል፤
በገንዘብ ተጋብተው
በገንዘብ ተዋደው
ፍቅር አለን ቢሉ
ማነው የሚሰማው?
ካንቺ ወዲያ ለኔ
ካንተ ወዲያ ለኔ
እንዳልተባባሉ
እንዳልተማማሉ
ቃልኪዳን አክብረው
በጥምረት የታሉ፤
የጥቅም ላይ ፍቀር
ፍቅር ነው እያልን
ፍቅርን ስንቀብር
ማን ይሆን አልቃሹ
ማን ይሆን ሙሾ አውራጅ
ቀብሩንም እያየ
አይተቶም እንዳላየ
በሰፈሩ ወራጅ...፤
ኧረ እንደው...
የይምስል ከመኖር
ቢቀር ባንወዳጅ.!
#ሮዛ


#ክፍል_አስራ_አንድ(🔞)


#አሌክስ_የልጅ_ሐብታም

አሌክስ ዑስማን ካገናኘኝ ደንበኞቼ ሁሉ የሚገርመኝ ፍጡር ነው፡፡እድሜው 30 እንኳን አይሞላም፡፡ የልጅ ሃብታም ነው፡፡ አባቱ በከተማዋ 3 ጽድት ያሉ ፎቆችን ሰርተው ለውጭ ድርጅቶች አከራይተዋል።በዚያ ላይ የታወቁ የሴራሚክ እቃዎች አስመጪ ናቸው፡፡ ሳር ቤት ገብራል አካባቢ ለኢምባሲ 120ሺ ብር የሚያከራዩት ቤታቸው ገቢው ሙሉ በሙሉ ለእሌክስ ይሰጠዋል፡፡ እሱ እቲ ገንዘብ ምኑም አይደለም በስዕል ፍቅር ተለክፏል፡፡ ብሩን የሚጨርሰው ጋለሪ እየሄደ የወደደውን ስዕል በመግዛት ነው።
አንድ ቀን ለገጣፉ ወደሚገኘው ቤቱ ይዞኝ ሄዶ የሆነ ህጻን የቸከቸከበት የሚመስል ነገር አሳይቶኝ
የምወደው ስዕል ነው አለኝ፡፡ መጀመርያ ከቁብም አልቆጠርኩትም ነበር፡፡ አሁን ይሄ ምኑ ይወደዳል በእግዚሃብሔርም አልኩት እንደቀልድ፡፡ የምሬን ነበር ደሞ፡፡ ዋጋውን ሲነግረኝ ግን አዙሮ ሊደፋኝ ሆነ፡፡
እምስት መቶ ሺ የኢትዮጵያ ብር ነው የከሰከሰበት፡፡ እንዲያውም ሰአሊው "ይህንን ስራዬን አልሸጥልህምም"
ብሎት በስንት አማላጅ ደጅ ጠንቶ እንደገዛው ሲነግረኝ ገርሞኝ ልሞት እኔ ምን አስዋሸኝ እማማ ትሙት ይህን ስዕል መሬት ወድቆ ባየው ኩስ እንዳየ ሰው ተስፈንጥሬ እሄዳለሁ እንጂ ዞሬም የማየው አይመስለኝም፡፡

አሌክስ እና እኔ በጂና ተበጂ፣ሸሌና ደንበኛ ብቻ አይደለንም፡፡ አንዳንድ ጊዜ እንደ ባልና ሚስትም ይሰራራናል፤እንደ ፍቅረኛሞች ለምሳሌ ከዕለታት አንድ ቀን በለገጣፎ ቤቱ አሪፍ የጣልያን ፓስታ ሰርቶልኝ እየበላን ሳለ በማይረባ ነገር ተጨቃጨቅንና አናደደኝ፡፡ ስናደድ አንዳንድ ጊዜ የማደርገውን አላውቅም፡፡ጮህኩበት በያዝኩት የፓስታ ሹካ ፊቱን ቡጭቅጭቅ ላደርገው ወደድኩኝ፡፡ እሱን የመቦጫጨቁ ሀሳብ የሚተገበር እንደማይሆን ሲታወቀኝ ቤቱ ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ መሰባበር ጀመርኩ፡፡ አሌክስ ምንም ሳይመስለው ዝም ብሎ ያየኛል።ይባስ ብሎ ሞባይሉን አወጥቶ ቪዲዮ ይቀርጸኝ ጀመረ፡፡ ብልጭ
አለብኝ፡እኔን ማብሸቅ በመቻሉ ደስ ሳይሰኝ የቀረ አይመስለኝም፡፡ ነገሩ ይበልጥ አናደደኝና ዙርያ ገባውን
እየቃኘሁ እርሱን ሊያናድ የሚችል ነገር ማሰብ ጀመርኩ፡፡ ድንገት ሳሎኑ ግድግዳ ላይ የተሰቀለው ያን መከረኛ ስዕሉን አየሁት፡፡ በያዝኩት ሹካ ልቦጫጭቅ ተንደርድሬ ስሄድ አሌከስ ይሆንልኛል ብዬ
ባልጠበኩት መልኩ ተንበርክኮ ለምነኝ፡፡ ከልቡ ሲለምነኝ አሳዘነኝ፡፡ ልጅ ስለሆነ ያሳዝነኛል፡፡ ልጅ ስለሆነ ብቻም ሳይሆን የሆነ የተለየ ፍጡር ስለሆነ አሌክስን እወደዋለሁ መሰለኝ፡፡ ብቻ የራሱ ጉዳይ፡፡ እንደዚያ ተናድጄ እንኳ በአሌክስ መጨከን ለምን አቃተኝ? ሹካውን ጣልኩትና ተንሰቅስቄ አለቀስኩ፡፡ ከንዱ ላይ አቅፎኝ ያባብለኝ ጀመረ፡፡ ሲያባብለኝ ይበልጥ ሆድ ባሰኝ፡፡ ወንድ ልጅ ገላዬን እንጂ እንዲህ በፍቅር
አባብሎኝ አያውቅም መሰለኝ፡፡ ድንገት እንደተቃቀፍን ከንፈሬን ሳመኝ፡፡ ከዚያም እምባዬን በምላሱ እየላሰ ጠረገልኝ ሁሉንም ቦታዬን ይስመኝ ጀመረ፡፡ ከረዥም ጊዜ በኃላ ለመጀመርያ ጊዜ በከፍተኛ የወሲብ ስሜት ተናጥኩኝ፡፡ምን እንደተፈጠረብኝ ለኔም ግራ ነው የሆነብኝ፡፡ ለካንስ እሱም ቅንዝሩ አፍንጫው ጋ ደርሷል፡፡ የለበስኩትን ቀሚስ በእጁ ተረተረው፡፡ ደስ አለኝ፡፡ የርሱን ቲሸርት በያዝኩት ሹካ

ቡጭቅጭቅ አረኩለት፡፡ እየተደባደብን እያለቀስን ሴከስ አደረግን፡፡ የማልረሳው ሸሌነቴን ያስረሳኝ ሴክስ አሌክስ እንዲህ ነው፡፡ አንዳንዴ ያቀብጠኝና ማንነቴን ያስረሳኛል፡፡

ያን ቀን እንደተለመደው ሲሸኘኝ 20 ሺ ብር ቼክ ቦርሳዬ ውስጥ አኖረልኝ፡፡
አልተቀበልኩትም፡፡ ያንን የወደድኩትን ወሲብ ሸቀጥ ሆኖ ማሰብ ስላልፈለኩ ቼኩን ፊቱ ላይ ቀዳደድኩት
ድርጊቱ በጣም ሳይገረመው አልቀረም፡፡መኪናውን ዳር አስይዞ ፊንገር ያደርገኝ ጀመረ ብልቴን ነዘረኝ፡፡ እንደዚህ ቀን በወሲብ ልሞት ደርሼ አላውቅም፡፡ ከዚያን ቀን በኃላ ፍቅር እንዳይዘው
ፈርቶ ነው መሰለኝ ቶሎ አልደወለልኝም፡፡ እኔ ግን በጣም ናፈቅኩት፡፡ሌሎች ደንበኞቼ በሙሉ አስጠሉኝ ስራዬ ሸሌነት ቢሆንም ከሌሎች ወንዶች ጋ መውጣት እሱ ላይ «ቺት ማድረግ መስሎ ተሰማኝ እንዲህ ነው፣ ያቀብጠኝና ማንነቴን ያስረሳኛል፡፡

ከስንት ሳምንት በኃላ ቆይቶ ደወለልኝ፡፡ ምነው ጠፋህ ስለው አገር ውስጥ እልነበርኩም ምናምን ብሎ ዘባረቀ፡፡ አመንኩት፡፡ ምን ቤት ነኝና ነው ግን እንደዚህ ብዬ የምጠይቀው? ብዙ ጊዜ ዉጭ አገር ለስራ ይሄዳል፤ ቅዳሜና እሁድ ዱባይ ወይም ባንኮክ ተዝናንቶ ይመጣል፡፡ በዚህ ለጋ እድሜው ከአንድ
ስዊድናዊት ሰዓሊ ፈረንጅ የምትመስል ሴት እንደወለደ ነግሮኛል፡፡እባቱ ይሄንን ቢሰሙ ይገድሉታል አንድም የቤተሰቡ አባል ይህንን ሚስጢር አያውቅም፡፡ አባቱ የተማሩ አይደሉም፡፡ ሆኖም በትምህርት በጣም ያምናሉ፡፡ ስዊድን በግድ ልከውት ዶላራቸውን እየቀፈቀፉ ትምህርቱን እንዲከታተል አድርገውታል
እሱ ግን እግሩ ስዊድንን እንደረገጠ አማተር የስዕል ትምህርት ቤት እየሄደ ነበር አብዛኛውን ጊዜው
የሚያጠፋው፡፡ እንደምንም ብሎ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ዲግሪ ይዞ ተመለሰ፡፡ አባቱ በደስታ ሊሞቱ
ደረሱ፡፡አሁን ይኸው ዉጭ ስለተማረ ብቻ ሁለት አማካሪዎች ተቀጥረውለት በወጣትነቱ ብዙዎች የአባቱን ድርጅቶች በበላይነት ኮስተር ብሎ ያስተዳድራል፡፡

አሴክስ ከስዊድን ዲግሪ ብቻ ይዞ አልተመለሰም፡፡ በሁለት ሱሶች ተለክፎ ነበር ፡፡ የመጀመርያው ሱስ
"ናርኮቲክ" የሚባል ቀለል ያለ በትንፋሽ ከሚወሰድ ዕፅ ጋር የተያያዘ ነው፤ እርሱን ሳይጠቀም አይደለም ስራ መስራት አይኑን መግለጥም አይችልም :: ይህንን ዕጽ ያስጀመረችው ስዊድናዊቷ ሚስቱ ናት፤ ዕፅ በአፍንጫዋ ሳትምግ ምንም ስዕል የመሳል ንሸጣ ውስጥ መግባት አትችልም ብሎኛል፡፡ እርሷ ይህንን
የምትገዛው ኮፐንሃገን ከተማ ውስጥ ማንኛውንም ዕጽ ለመግዛት ህጋዊ ከሆነችው እና ከሪስታኒ ከምትባል መንደር ውስጥ ነበር፡፡ አሌክስ ከዚች ስዊድናዊት ጋር ሁልጊዜ አርብ ማታ ወደ ከርስታኒ አብሯት ይሄድ ነበር፡፡ የኋላ ኋላ አንድ ሁለት እያለ እርሱም በሱሱ ተለከፈና አረፈው እንጂ፡፡

አሌክስ እንደነገረኝ ከሆነ እፁ ለጉሮሮ ካንሰር ህመምተኞች መጠኑ አነስ ተደርጎ እንዲወስዱት የሚፈቀድ ስለሆነ ዋጋው ውድ ይሁን እንጂ ጉምሩክ አካባቢ መጠነኛ ጉቦ በመስጠት አገር ውስጥ ማስገባት አይከብድም፡፡ ለዚህም ሲል በታናሽ እህቱ ስም የመድኃኒት አስመጪ ድርጅት አቋቁሞ እግረ መንገዱን
ጠቀም ያለ ትርፍ ያገኝበታል፡፡ ይህንን ሚስጢሩን ያካፈለኝ ከሁለት ዓመታት የደንበኝነት ዘመናችን በኋላ ነው፡፡

አሌክስ የአደገኛ እጽ ተጠቃሚ ይሁን እንጂ የሚገርም ባህሪ ያለው ልጅ ነው፡፡ሲበዛ ደግ፣ ሰው የሚወድ፥ህግ አክባሪና
ትሁት ነው፡፡ አምስት አረጋዊያንን ቤት ተከራይቶላቸው ተንከባካቢ ቀጥሮላቸው ያስተዳድራቸዋል፡፡ ታዲያ ማንም ይህን ተግባሩን እንዲያውቅለትም ሆነ እንዲያውቅበት አይፈልግም፡፡ለእኔም
የነገረኝ በአጋጣሚ ነው፤ ከእለታት አንድ ቀን ከሚጦራቸው አዛውንት አንዱ ሞተውበት ሙዱ ተከንቶ አግኝቼው ነው
ነገሩን ያወራልኝ፡፡ ከነገረኝ በኃላ ግን ራሱን በፀፀት ሊገድል ምንም አልቀረውም የረከስኩ ያህል ነው የተሰማኝ አለኝ በነገታው ሲያገኘኝ፡፡ ወይ አሌክስ!

የአሌክስ ነገር ግራ ይገባኛል፡፡ እንድ ጢጥ የሚነፋና ሸሌ የሚበዳ ወጣት እንዲህ እግዚያብሄር የሚወደውነገር ሲሰራ ግራ ያጋባል
የአሌክስ እውነተኛ ማንነት ይሄ ነው ብሎ ለመናገር የሚከብደውም ለዚያ ነው፡፡ ለምሳሌ አሌክስ ጥሩ ሰው ቢሆንም ለየት ያለ የወሲብ ባህሪ ያለው ሰው ነው፤
👍41🥰1
ሁሉም ሰው እንደጨረቃ የማይታይ መልከ እለው» የሚለው አባባሉ የገባኝ ስለአሌክስ ብዙ ነገር እያወቅኩ ስመጣ
ነው፡፡ እውነቱን ሳይሆን አይቀርም፡፡

የአሌክስ ሁለተኛው ሱስ ያፈነገጠ የወሲብ ባህሪው ነው፡፡ ከኔ ጋር ያገናኘንም ይኸው ልክፍቱ ይመስለኛል፤
የአሌክስ የወሲብ ስሜቱ የሚነቃቃው ህዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ብቻ ነው፡፡ ለምሳሌ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ፣ ብዙ መኪና በቆመበት ፓርኪንግ ላይ፣ አውቶቡስ ዉስጥ፣ የህዝብ መጸዳጃ ቤት ውስጥ፣ ሲኒማ ቤት ፡፡ በስነ ስርዓት ከኔ ጋር ሴክስ እድርጎ የሚያውቀው ያኔ ስዕሉን በሹካ ልሸከሽክለት ስል ያስጣለኝ
ጊዜ ብቻ ነው፡፡ እንደማንኛውም ሰው መኝታ ቤት ቆልፎ፣ መብራት አጥፍቶ ወይም ሆቴል እልጋ ይዞ መባዳት እይሆንለትም፡፡ በእንደዚህ አይነት ወቅት ምንም የወሲብ ፍላጎት እለማሳየት ብቻ ሳይሆን ወንድነቱ ይሟሽሻል። አይቆምለትም፡፡

ሐመር መኪና ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ የገባሁት ከአሌክስ ጋር ነው፡፡ ከተማዋ ውስጥ ከሚነዱት ጥቂት ሐመር መኪናዎች አንዱ የአሌክስ ነው፡፡ አባቱ ይህንን መኪና እንደሚነዳ ቢያውቁ ከቤት ያባርሩታል፡፡ በፍጹም ታይታ የሚወዱ ሰው አይደሉም፡፡ ለነገሩ አሌክስም ብዙ ታይታ አይወድም፡፡ ሐመር የሚነዳበት
የራሱ ያልገባኝ ምስጢር ሳይኖረው አይቀርም፡፡መኪናውን በድብቅ በታናሽ እህቱ ስም አስመጥቶ ነው የሚነዳው፡፡ የምሬን ነው አሌክስ ሐመር ያስመጣው ለጉራ አይመስለኝም፡፡ ብዙዉን ጊዜ ለገጣፎ በድብቅ በተከራየው ቤቱ ውስጥ አቁሞት ነው የሚውለው፡፡ ምናልባት ለስንፈተ ወሲቡ ማካካሻ ይመስለኛል
የሚፈልገው፡፡ ኖርማል ሴከስ ብዙም አይሳካለትም፡፡ሴከስ ላይ ለየት ያለ ባህሪ አለው፡፡ ለኔ ግልጽ ባይሆንልኝም ምናልባት ከዚህ መኪና ጋር የተገናኘ አንዳች የወሲብ ዛር ሰፍሮበት ይሆናል፡፡ ይህንን የምለው ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ለምሳሌ ለገጣፎ ወዳለው ቪላ ቤቱ ከወሰደኝ ሐመር መኪናውን
አስደግፎ ግቢ ውስጥ ሴክስ ያደርገኛል፡፡ ቤት ውስጥ ገብቶ ግን ብዙዉን ጊዜ ሴክስ ማድረግ እይችልም፡፡

በሌላ ጊዜ ደግሞ መብዳት ሲያምረው ካለሁበት ቦታ በሐመር ፒከ ያደርገኝና ብዙ ፓርኪንግ ወዳለው ሰፈር ይዞኝ ይሄዳል፡፡ ኦፔራ የሚባል ለኔ ምኑም የማይገባኝ ሙዚቃ ይከፍታል፡፡ መኪና ፖርክ ተደርጎ የሚጠጣባቸው ቦታዎች ወይ ፒኮከ፣ወይ ኤርፖርት ሞቴል አካባቢ ይዞኝ ይሄዳል፡፡ ከዚያ ሁለት አፕሬ ያዝና
እየተሳሳቅን እንጫወታለን፡፡ ኦፔራውን ድምጹን ከፍ አድርጎ ከከፈተው በኃላ ናርኮቲካውን ከሐመር መኪናው የሲዲ ማጫወቻ ኪስ ውስጥ መዞ ያወጣዋል፡፡ ለተወሰነ ደቂቃ በዝምታ ይመሰጣል፡፡ ከዚያ የመኪናውን መስታወት ይዘጋዋል፡፡ የሐመሩ መስታወት ቲንትድ ስለሆነ ሰው አየኝ አላየኝ አይልም
እጁን ወደ ጭኖቼ ይሰድና የመሐል ጣቱን እምሴ ውስጥ ከቶ ይጎረጉረኛል፡፡ እኔ መኪና ውስጥ በቀን እንደዚህ መሸፋፈድ መልመድ እያቃተኝ ሰው የሚያየኝ እየመሰለኝ እሳቀቃለሁ፡፡ እሱ ግን ይበልጥ ደስ ይለዋል። ብዙም አይቆይም ግን፡፡ እዚያው ጣጣውን ጨርሶ እዚያው የውስጥ ሱሪውን ቀይሮ፣ እዚያው በኦፔራ ሙዚቃው ለሁለተኛ ጊዜ ተመስጦ መኖሬን የረሳ እስኪመስለኝ ድረስ የወንበሩን መደገፊያ ዘርግቶ ለጥ ይላል፡፡ ናርኮቲካዋ ስትበርድለት ነው መኖሬ ትዝ የሚለው፤ ይቅርታ ጠይቆኝ ወደ ቤቴ ይሸኘኛል። እኔም ነገሩን ስለለመድኩት ምንም አልልለውም፡፡ እነ ራኪ አንድ ጊዜ ሎሌ ህንፃ ጋር ሸኝቶኝ ከሐመር መኪናው ስወርድ አይተውኝ ባለ ሐመር የጠበስኩ መስሏቸው አንድ ሰሞን 'በኮንግራ'
አጨናንቀውኝ ነበር፡፡ እኔና አሴከስ ያለንን ግንኙነት ግን ለማንም ተናግሬው አላውቅም፤ ወላ ለራኪ።

አሌከስ ቢያንስ በሁለት ሳምንት አንድ ቀን ደውሎ «ፊልም ልጋብዝሽ» ይለኛል፡፡ ሲኒማ ቤት ሳይሆን በሀመር መኪናው ውስጥ በተገጠመ ስከሪን ነው ፊልም የምናየው፡፡ በዚህን ጊዜ እርሱ ራሱ ከአምስተርዳም
"ሬድ ላይት ዲስትሪክት» ገዝቶ ያመጣልኝን ሦስት ነገሮች መያዜን አልዘነጋም፡፡ ነጭ ለስላሳ የእጅ ፎጣ፤
ዶሼ የሚባል ሉብሪካንት ቅባት እና ከከፋይ ሀር ጨርቅ የተሰራ የእጅ ጓንት፡፡ መኪናውን ምቹ ቦታ ወይም መንገድ ዳር ካቆመው በኃላ የሆነ ቁልፍ ሲጫን የሱ ወንበር እንደ አልጋ ይዘረጋል፡፡የሚከፍተው ፊልም ምን አይነት እንደሆነ ከልምድ አውቀዋለሁ፡፡ ሴቶች ብቻ የሚሳተፉበት ህዝብ ፊት የተቀረጹ
የወሲብ ፊልሞችን ነው ዘወተር የሚያሳየኝ፡፡ ፈረንጆች በሆነ ጋራዥ በሚመስል ጋለሪ ውስጥ ስእል
እየሳሉ፣ በድራግ እየጦዙ የሚባዱበት ፊልም ይከፍትልኝና እሱን እያየነው በመሐል በመሐልይነካካኛል
ይላፋኛል…ከዚያ ደግሞ አስጨርሽኝ ይለኛል፡፡አስጨርሰዋለሁ፡፡ጣጣውን ሲጨርስ ያው እንደተለመደው
ኦፔራ ሙዚቃውን ከፍቶ ለተወሰነ ደቂቃ ይመሰጥና በሀሳብ ጥሎኝ ይነጉዳል፡፡ አንድ ቀን ግን ያልጠበኩትነገር ሆነ፡፡ የፊልሙን ድምጽ እንደጠፋ ኦፔራውን ከፍቶ በሀሳብ አይኑን ጨፍኖ ሳለ አይኔ ፍጹም ማየት የማይፈቅደውን ነገር አየ፡፡ እንደዚያ ቀን በፍርሃት ተንቀጥቅጬ አላውቅም፡፡ አሌክስ በቪዲዮው ላይ
ይታያል፡፡ ሁለት ፈረንጅ ሴቶች እጁን የፊጢኝ በብረት አስረው የሆነ ጋራዥ ውስጥ ሲያስገቡትና አንድ
ጥቁር ጠብደል ቦርጫም ሰውዬ ራቁቱን ወደርሱ ሲመጣ፡፡ ጩኸቴን ለቀቅኩትና ከመኪናው ወረድኩ፡፡ከዚያ በኃላ አግኝቼው አላውቅም፡፡እሱም ደውሎ አያውቅም፡፡ አሌከስ የልጅ ሀብታም፡፡

#ድንግል_የሚጸየፍ_ትውልድ

ቀን 11:20

ጸጉሬን ቦስተን ስፓ ቢኒ ጋ ለመሰራት ከፒያሳ ሚኒባስ ታክሲ ውስጥ ገብቼያለሁ፡፡ከኋላዪ ሶስት ታዳጊ ሴቶች
እንዲት ጓደኛቸውን በሀሜት እየቦጨቋት ነው፡፡ምን እንዳደረገቻቸው አላውቅም!
ሶስቱም በየተራ ይዘነጣጥሏታል፡፡ከንግግራቸው እንደተረዳሁት የሀይስኩል ተማሪዎች ናቸው፡፡የቦሌ ሀይስኩል ዩኒፎርም ለብሰዋል፤ አቦ እንርሳት ጋይስ!ይህን ያህል ከተቦጨቀች ይበቃታል፣ ደሞ እሷም ሰው ሆና
ኤሚ ሙች እውነትሽን ነው!ሙደ ገዳዳ ብቻ ሳትሆን ገገማም ጭምር ነች
ሶስተኛዋ ልጅ ቀጠለች) ስምረትን ፋራ የሚለው እይገልጻትም፥በድንግልናዋ የምትኮራ ግግም ያለች ቆምጬ ናት እኮ እታባ ትሙት! ትላንት ለመቶኛ ጊዜ ምን እንዳለቾኝ ታውቂያለሽ?

(እሺ! ምናለች በናትሽ) አለቻት ከጥግ በኩል የተቀመጠችዋ ጓደኛቸው።

ከብረንጽህናዬን እስከ ሰርጌ ቀን ድረስ አላስነካም አትለኝ መሰለሽ?!

ሶስቱም በሳቅ አሽካኩ፤ ወያላው የልጆቹ ድርቅና ከዚህ ቀደም ገጥሞት በማያውቅ ሁኔታ አፉን ከፍቶ ያያቸዋል፡፡ ጥቂት በእድሜ ጠና ያሉ ተሳፋሪዎች ወደ ኃላ ፊታቸውን በማዞር በግልምጫ ሶስቱን
ሴቶች አንደበታቸው እንዲታረም ገረመሟቸው፡፡

ታዳጊዎቹ ላይ ሰው እየሰማን ነው የሚል ይሉኝታ ሲያልፍም አይነካቸው፡፡ሶስቱም ለሁሉም የታከሲው ተሳፋሪ በሚሰማ ድምጽ በከፍተኛ ስሜት ተውጠው ነው የሚያወሩት፡፡ የኔን የተማሪነት ጊዜ እያሰብኩ፣ ሀፍረተ ሆይ ሀገርሽ የት ነው ?እያልኩ ጆሮዬን ተማሪዎቹ ላይ ጥዬ ጉዞዬን እቀጥላለሁ፤ እንደዚህ አይነት
ወሬ ቺቺኒያ ስሰራ ቢራ እየጠጣን ካልሆነ በሌሊቱ አለሜ እንኳ ገጥሞኝ አያውቅም፡፡በርግጥ በነርሱ እድሜ
እያለሁ የወሲብ ፊልሞችን በድብቅ
👍94🥰1👏1
እመለከት እንደነበር አስታውሳለሁ፤12ኛ ከፍል ተፈትኜ መሠለኝ ያየሁት፡፡ ኾኖም በዚህ መልኩ ህዝብ ባለበት አፌን እልከፍትም፡፡ ከጓደኞቼም ማንም
በዚህ ልቅ ሁኔታ ያደገ አላስታውስም፡፡ አረጀሁ ማለት ነው?
ከታክሲው ከወረድኩ በኋላም ቢሆን የታዳጊዎቹ አነጋገር በአእምሮዬ ጓዳ መመላሱ አልቀረም፡ከ7 እና 8 አመት በፉት ክብረ ንጽህና ያላት ሴት በማህበረሰባችን የሚሰጣት ከብር ትልቅ ነበር፡፡ ከዚያ ደግሞ እኔ በሬ አራጅ ይመስል ደም አላፈስም ድንግልናሽን አስወስደሽ ካልሆነ በጫት እንጨት አልነካሽም የሚሉ ቦይፍሬንዶች ተወለዱ፡፡ በታዳጊ ሴቶች ዘንድ ድንግልና እንደ ቆምጬነት እንደሚያስቆጥር ግን ዛሬ ገና መረዳቴ ነው፡፡ከግማሽ ከፍለዘመን በፊት ታዳጊ የሆንኩ ያህል ተሰማኝ፡፡

የሚገርም ነው፡፡ በወግ አጥባቂው እና ለክብረንጽህና ከፍተኛ ክብር በሚሰጠው ባህል ያለፈ ጎልማሳ ደምበኞች ታወሱኝ፡፡ በተለይ መሿለኪያ ጋር ቁርጥ ቤት ያላቸው ጋሽ በረደድ እስቲ ድንግል ሴት አምጪልኝ ያንቺን ኮሚሽን ሳይጨምር 5000 ብር እከፍላለሁ» የሚሉን ታውሶኝ ሳቂ መጣ
ጋሽ በሪደድ ሰባት ሴት ልጆችን ወልደውም ድንግል ፍለጋ ላይ ናቸው፡፡ ራኪ 'ሰውየው የቁራጭ ስጋ ነገር
አይሆንላቸውም፡ ቁርጥ ነጋዴ ስለሆኑ ነው ድንግል የሚወዱት" እያለች ታሾፍባቸዋለች። ዘመድኩን ደግሞ የድንግል ስጋ እየበጠሱ ቁዝሚ እያሰሩ ነው ሼባው የቁርጥ ቤቱ ስራ የደራላቸው” እያለ ይምላል
አንድ ቀን ራሄል ቤት እየጠጣን « እስኪ ድንግል ፈልጉልኝ 500 ሺ ብር እከፍላለሁ…» ሲሉ የራሄል በጂ
የነበረው ዘካሪያስ « ጋሽ በረደድ ቁራጭ ስጋ ካማረዎ ቄራ ሄደው ይጠይቁ፡ ይሄ መጠጥ ቤት ነዉ
ብሎ ቀሌያቸውን ገፈፋቸውና ሳምንት ሳይመጡ ቀሩ፡፡ እኛ ደሞ እኚህ ሰውዬ ጠዋት ጠዋት ዱለት እያሉ የሚሸጡልን ቁርጥራጭ የድንግል ስጋ ሳይሆን አይቀርም ብለን በመጠርጠር እሳቸው ጋ ቁርስ መብላት አቆምን።

ከወር በፊት ቁልቢ ገብርኤልን ለማከበር ድሬዳዋ የሄድኩ ጊዜ ከዚሁ ከድንግልና ጋር የተያያዘ አጋጣሚዬ ተመሳሳይ መደነቅን ፈጥሮብኝ ነበር፡፡ለቁልቢ በተሳሉት መሰረት ጉዳያቸው ከተሳካ ከብረንጽህናቸውን ለቁልቢ እንደሚያስረከቡ ቃል የገቡ ጥቂት ሴቶች ድንግልናቸው ቤተክርስቲያኑ አካባቢ ለሚኖሩ ጎረምሶች እንደሚያስረከቡ ሰምቻለሁ፤በእምነቴ እንዲህ አይነት ስእለት መኖሩን ለመጀመሪያ ጊዜ ያወቅኩት በዚህ አስደናቂ ጉዞዬ ነበር፡፡

ከዚህ ጉዞዬ በአውቶቡስ ወደ አዲስ አበባ ስመለስ ከጎኔ ተቀምጦ የነበረው የድሬዳዋ ነዋሪ ትዝ አለኝና ፈገግ አልኩኝ፡፡ ቆንጆ ጎልማሳ ቢሆንም ጥርሶቹ በጫት ተጎድተዋል፤ የጫት አጎራረሱ ያስፈራል፤በርካታ ቅጠሎችን በቶሎ በቶሎ ወደ አፉ ይልከና በሀሳብ ይመሰጣል፤ገና ብዙ ሳንጓዝ አይኑ በምርቃና ፈጠጠ፤

እህቴ አብሽር!ተጫወች

ሰውዬው በተደጋጋሚ እንዲህ ቢልም ምንም የሚያጫውተኝ ነገር የለም ከጫቱ ጋር ብቻ ነው ጨዋታው፤ ስለ ድሬዳዋ ብዙ ለማወቅ እና ጓደኛዬ ራኒን ለማስደነቅ ሰለምፈልግ ብዙ እንዲያወራ
ፈልጌያለ፤እሱ ግን ወይ ፍንክች፤በመረቀነ ቁጥር ቀና ሲል፤ «እህቴ አብሽር!ተጫወች» ከማለት ውጪ
ቃል አልተነፈሰም ቆቦ እልበረከቴ ሂርና፣አሰበ ተፈሪ እና ሜኤሶ ላይ ይህን አሰልቺና ተደጋጋሚ ጥያቄ
ሲጠይቀኝ በይሉኝታ እና በስልቹነት ስሜት አብሽር እየተጫወትኩ ነው!» ብዬዋለሁ፡፡ሁኔታው እንግዳ
ባዶ ቤት አስቀምጠው ተጫወት!! » የሚሉትን አዲስ አበቤዎች እስታወሰኝ፡፡በመሐል ራኪ ከዚህ በፊት የነገረችኝ ቀልድ ትዝ አይለኝም? ሲገርም! አጋጣሚው ገርሞኝ ለሷ ልነግራት ስልክ ልደውል እያሰብኩ ጎልማሳው ጫት ቃሚ አሁን አብሽር ተጫወች» ብሎ ካሰለቸኝ የራኪን ቀልድ እንደምተገብረውና አፉን
እንደማሲዘው አሰብኩ፤እንደጠበቅኩትም አዋሽ ላይ ደገመው፤

«እህቴ አብሽር!ተጫወች

ወንድሜ እየተጫወትኩ ነው!ግን በቃ እስከ አዲስ አበባ አንተ ራስህ አብሽር»አልኩት፡፡

ከጎናችን ቁጭ ብሎየኔንና የቃሚውን ነገር ሲከታተል የነበረ ወጣት በሳቅ ተንከተከተ፡፡ ቦርጫሙ ሹፌራችን
ቦርጩ እስኪቀንስ ድረስ እጁን ከመሪው አንስቶ እየነጠረ አስካካ፡፡ ሌሎች ከኋላችን የነበሩ ሴቶችም
በኔ መልስ ተገርመው መቅረሚያቸውን ሸፍነው በሳቅ ተንፈራፈሩ፡፡ እኔም ያልጠበኩት የተሳፋሪው የማያቋርጥ ሳቅ መልሶ አሳቀኝ፡፡ ቃሚው ሰውዬ በመልሱ ተገርሞ የቀሩት ጥርሶቹ እስኪረግፉ ይስቃል ብዬ ስጠብቅ…« እህቴ አብሽር ተጫወች»ብሎኝ አረፈው፡፡

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍5
አትሮኖስ pinned «#ሮዛ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አንድ(🔞) ፡ ፡ #አሌክስ_የልጅ_ሐብታም አሌክስ ዑስማን ካገናኘኝ ደንበኞቼ ሁሉ የሚገርመኝ ፍጡር ነው፡፡እድሜው 30 እንኳን አይሞላም፡፡ የልጅ ሃብታም ነው፡፡ አባቱ በከተማዋ 3 ጽድት ያሉ ፎቆችን ሰርተው ለውጭ ድርጅቶች አከራይተዋል።በዚያ ላይ የታወቁ የሴራሚክ እቃዎች አስመጪ ናቸው፡፡ ሳር ቤት ገብራል አካባቢ ለኢምባሲ 120ሺ ብር የሚያከራዩት ቤታቸው ገቢው ሙሉ በሙሉ ለእሌክስ…»
#ሀገሬ_ከየት_ነው?

ከከረን ነች እሷ የኔ ቤት ባድማ
ፍሬ ሰቶን ጌታ ከባዕድ አውድማ
ጠየቀን በጊዜው ማደግ አይቀርማ
ሀገራችን የትነው ልጠይቅሽ እማ?
ልጄም አይጠረጥር መልካችንን ቢያየው
ነጠላ ለብሳለች ጃኖ ደርቤያለሁ
ውዳሴ ማሪያምን እሷም ታነባለች
እኔም እደግማለሁ
የት ብዬ ልናገር ሀገሬ ከየት ነው??

ቶናና በረካን አቦሉን ሳናስቀር
ቡና ጠጡ ማለት ባህላችን ነበር፤

መውጫዬ ከሷ ቤት ጓዳዋ ከኔ ጋር
ለብዙ አመት ባንድ ላይ ስንኖር
ሁለት ቁማርተኞች እጣ ተጣጣሉ
ነብሳችን ይዘው ይዋጣልን አሉ፤
እኔም ወንድሜ ላይ ጥይቱን ተኩሼ
ያሸነፍኩኝ መሰለኝ እራሴን አፍርሼ ፤

ልጄስ ምን ይለኛል ለማን ይነገራል
ሀገሬ ሁለት ነው ገና ስል ያመኛል
ያመኛል ያመኛል........……
አልናገር ነገር እምባ ይቀድመኛል !
ዛሬ ግን......
ነገን በመናፈቅ ስቆጥር ዘመኑን
ፀፀት እየፈጀኝ ሳላቀው ሀገሬን
ይኸው አፉን ፈታ የት ብዬ ልናገር
መላው ካንቺ ጋር ነው ተናገሪ ምድር
ድምፅሽን አሰሚኝ የ ት ነ ው የ ኛ ሀ ገ ር
#ሮዛ


#ክፍል_አስራ_ሁለት (🔞)


#እንዲህችም_አይነት_ሚስት
#እንዲህም_አይነት_ፍቅር
#እንዲህም_አይነት_ትዳር_አለ

ህዳር 8 ፣2007

ፈረንጆች Sometimes real life is more fictious than fiction and more filmic than a Hollywood film የሚሉት አባባል በህይወቴ ውስጥ ተከስቶብኛል፤ለዚያውም በተደጋጋሚ፡፡ እውነቴን ነው! በህይወቴ የሆኑት አንዳንድ ነገሮች ከልቦለድ ድርሰት በላይ ልቦለድ፣ ከፊልም በላይ ፊልም መስለው ይታዩኛል፡፡
ለምሳሌ በትላንትናው ውሎዬ እና አዳሬ የተከሰቱት ከስተቶች ልቦለድ ድርሰት እያነበብኩ ነው ወይስ ፊልም
እያየሁኝ እስከምል ድረስ ብዥታ ውስጥ ከተውኛል፤የብዥታው ስሜት አሁንም አለቀቀኝም፡፡

ከሊሊቱ 8፡30 ቦሌ አትላስ ውስጣ ውስጥ በአንድ ገስት ሀውስ ሳሎን ቤት እገኛለሁ፡፡ ከሳዲቅ ጋር ነኝ፣በእናቱ
በኩል የመናዊ በአባቱ በኩል ደግሞ ሳኡዲ አረቢያዊ ነው፤ በቅርቡ ቢልየነሩ ሸከአላሙዲ ኢትዮጵያ ውስጥ
የሩዝ እርሻ ላይ እንዲሰማሩ በማሰብ በሚሌንየም አዳራሽ ከባለስልጣናት ጋር ከሰበሰቧቸው የሳኡዲ መልቲሚልየነር ኢንቨስተሮች የአንዱ ተላላኪ ሆኖ ነው የመጣው ተብያለሁ፣ሳዲቅን ደውሎ ያገናኘኝ ዑስማን ዘ ፒምፕ ነው፤ከራሱ አንደበት እንደሰማሁት ሳዲቅ የ33 ዓመት ጎልማሳ ነው፡፡

እዚህ ገስት ሀውስ ውስጥ የተገኘሁት ከምሽቱ 2፡30 ጀምሮ ቢሆንም ሳዲቅ እረፍት አልሰጠኝም፤ከረጅም
አመታት እስር በኋላ ወሲብ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደፈጸመ ሰው የአልጋ ላይ አውሬ ሆኖብኛል፡፡በጥድፊያ እና በከፍተኛ የመንገብገብ ስሜት ነው ሶስት ዙር ወሲብ የፈጸመው፡፡ ይሄ አይነት ባህሪ ብዙውን ጊዜ የጥቁር አሜሪካዊ እንጂ ከአረብ አይጠበቅም፡፡ ሁለት ሀሳቦች በእእምሮዬ ተመላለሱ፤

አንድ ይህ ሰው በሳኡዲ አረቢያ ውስጥ ሴት ነከቶ አያውቅም፤የበረሃው ንዳድ ከረጅም አመታት የወሲብ ጥማቱ ጋር
ተደምሮ የወሲብ አውሬ አድርጎታል፡፡ ምኑም ለወሲብ አዲስ አይመስልም ድንግል እና አዲስ ወንድ የመደናገር እና ያለመረጋጋት ነገር ስለሚታይበት አያያዙን አይቶ መለየት አይከብድም፤ሳዲቅ ላይ እነዚህን ስሜቶች በፍጹም አላየሁም፡፡ ይልቁንም ኮርማ ሆኖብኛል፡፡ ጀማሪ ቢሆን አንዱ ሻወር ቤት አንዴ
ወለል ላይ፣አንዴ ሶፋ ላይ፣አንዴ አረቢያን መጅሊስ ላይ እያለ ነፍሴን አያወጣትም ነበር፡፡ ምን አልባት ቀን ከሌት ሲወጥቅ የከረመው የአረብ ሩዝ ነው እንዲህ ኮርማ ያደረገው፡፡ ይሄንን ሩዝ
ተሳክቶላቸው እዚህ ቤኒሻንጉል ከተከሉት ሴቶች አለቀልን” አልኩ በሆዴ፡፡

ሁለተኛው ግምቴ የበለጠ አሳማኝ ሆኖ ታየኝ፡ሳዲቅ አንድ ዙር ከጨረሰ በኋላ ሙቅ ሻወር ወስዶ ይመለስና
አልጋ ላይ ብዙም ሳንቆይ ብልቱ ሲጠጥር በተደጋጋሚ ተመልክቼያለሁ ይሄ ሁሉ ኃይልና ጥንካሬ መቼም
ብዙ ሩዝ አግበስብሶ በመብላት ብቻ ይመጣል ብሎ መገመት ሞኝነት ነው፡፡ ሌላ ሚስጠር መኖር አለበት
ቁላ የሚያቆም ከሩዝ ጋር በደቃ መልክ ተቀቅሎ የሚበላ የወይራ ዘይት አለ ሲባል ሰምቻለሁ፡፡ ዊክኤንድ
ላይ ዱባይ እየሄዱ ቢዝነስ የሚሰሩ ጓደኞቼ ሲያወሩ ነው የሰማሁት፡፡ይህን ግምቴን የሚያጠናክር ሌላ ክስተት 8፡30 ላይ ተፈጠረ፡፡ሳዲቅ ድንገት ብድግ ብሎ ወደ ኪችን ሄዶ ትንሽ ቆይቶ አፉን ተጣጥቦ ተመለሰ፡፡ ምን እንዳረገ ስጠይቀው ትንሽ ስለራበው ፍሪጅ ውስጥ የነበረ የተራረፈ ሩዝ ለመቀማመስ
ማድ ቤት ጎራ ብሎ እንደነበረ ነገረኝና ቶሎ ርእስ ሊያስለውጠኝ ሞከረ፡፡ የሆነ ነገር ጠረጠርኩ፡፡ ከዛ
ከጀለቢያው ባለሰፊ ስክሪን ቅንጡ ሞባይሉን አውጥቶ አበራውና ሰዓቱን ከተመለከተ በኃላ ከሻንጣዉ የምታምር ላፕቶፕ ኮምፒውተር በመከፈት በገመድ ከሞባይሉጋር እገናኛት፡፡ ከዚያ የSkype እካውንቱን ከፈተ እፍታም ሳትቆይ አንዲት አረብ ሴት በሂጃብ እንደተሸፋፈነች ከላፕቶፕ ስከሪን ላይ ተገኘች፤

«ያ ሀቢብቲ ያ ህልዊ!ከይፈ ሀሉኪ?(ፍቅሬ እንዴት ነሽልኝ እያለ ያቆለማምጣታል)

«ቢኸይረን ወልሀምዱሊላህ!ከይፍ አንትያ ሁቢት»ፈጣሪ የተመሰገን ይሁን!አንተ እንዴት ነህ? ትለዋለች)

ከላፕቶፑ ስከሪን በስተቀኝ ሆኜ የሚለዋወጡትን የናፍቆት ቃላት ባለችኝ ሸወያ ሸወያ» የአረብኛ እውቀት
አሰማለሁ፡፡ ሳዲቅ እኔን ከፊት ለፊት ዞር እንድል እንኳ ሳይነግረኝ ሚስቱ ጋር መደወሉ አስገርሞኛል፡፡በራሴ ጊዜ ዞር አልኩለት፡፡
«አይነ ቢንቲ?እይነ ያስሚን?» አላት(ልጄ ያስሚን የት ሄዳ ነው?)
-
እንቅልፍ እንደወሰዳት ነገረችው፡፡

የተለያዩ ቤተሰባዊ ጉዳዮች የሚመስሉ ብዙም ያልገቡኝን ነገሮች ካወሩ በኋላ እርቃን ገላዋን በጣም እንደናፈቀ ነገራት፤ሂጃቧን እንድታወልቅም አዘዛት፤አላንገራገረችም፡፡

ይህን ጊዜ እኔ ልክ እንደ ወንድ ለሀጬ ሊዝረከረከ ምንም አልቀረውም፡፡

«ጠይብያሁቢ!ማፊሙሽኪላህi!» ብላው ማወላለቅ ጀመረች፤ እኔ አሁንም የሷን ገላ ለማየት በጉጉት ልሞት ደረሻለሁ፡፡ አንዲት ህይወቷን ሙሉ እስከ አፍንጫዋ ድረስ ኒንጃ መስላ የምትከናነብ ሴት ራቁቷን ስትሆን ምን ልትመስል እንደምትችል ማየት ማንንም የሚያጓጓ ጉዳይ ይመስለኛል፡፡ ከሞባይሉ ፊት ለፊት ከሆንኩ እርሷ ልታየኝ እንደምትችል በመገመት በቁምሳጥኑ ተከልዬ አይኔን ስከሪኑ ላይ ተከልኩ፡፡ ገላዋ በጣም ስስ
ሆኖ ያምራል፤በጡት መያገዥዋ እና በፓንትዋ ብቻ ቀረች፤ቢጫ ናት፤ኑሮ ሲበዛ የተስማማት፤በአረብ ዲሽ ላይ ከማያቸው አብዛኞቹ ሴቶች በተቃራኒ ሸንቃጣ እና ቦርጭ ያልጎበኘው አማላይ ሰውነት ያላት ልክ እንደ ሀበሻ ሴቶች አብዛኞቹ አረብ ሴቶች ከወለዱ በኋላ የቀድሞውን የሰውነት ቅርጻቸውን ጠብቆ መቆየት
ይከብዳቸዋል፤ውፍረት እና ቦርጭ ያበላሻቸዋል፤ 24 ሰዓት ይበላሉ፡፡ ካዳሚ ስላላቸው ቤት ውስጥ እንኳ
ጉድ ጉድ አይሉም፡፡ ይዘፈዘፋሉ::
አህላም ግን ወልዳም ማራኪ የሰውነት ቅርፅ እንዳላት ተረዳሁ።

እንደ ሁሉም አረብ እየተጯጯሁ ነው የሚያወሩት።

የአህላም ፊት ድንገት ተለዋወጠ ቅድም በፈገግታ ደምቆ እና ብርሃን ተርከፍከፎበት የነበረ ፊቷ አሁን ጨፍግጎል ንግግራቸውን በአትኩሮት እያደመጥኩ ነው፤ሳዲቅ ምን የሚያስቀይም ነገር ቢናገራት ነው እንዲህ በቁጣ ፊቷን ያጨለመችው
በግራ መጋባት ስሜት ውስጥ ለአፍታ ከቆየሁ በኋላ አህላም የንዴት ቃና በተጫነው አረብኛዋ ጥያቄ አስከተለች

ከጀርባ ያለችው ሴት ማናት?

ቁምሳጡና ጋር ብቅ ጥልቅ ስል አይታኛለት ማለት ነው ይቺ ከይሲ አረብ።

ሳዲቅ በታረጋጋ ስሜት ወደርሱ እንድመጣ በምልክት ጠራኝና «ሂያ ዛኒል ሀበሽ በኬ (ሸርሙጣ ናት የሀበሻ
ሸርሙጣ!)ብሏት እቅፍ አደረገኝ፡፡

እኔ በሀፍረት መትነን አማረኝ፡፡ ሳዲቅ የሚያወራው ግን በኩራትና ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ ሆኖ ነው፡፡

«ያ ሳዲቅእየዋሸኸኝ ነው?እስቲ ማልልኝ

“ወላሂ! ወቢላሂ» ብሎ ማለላት፡፡

ምኗም ሸርሙጣ አትመስልም፤ ሳዲቅ እየዋሸኸኝ መሆን አለበት፤ እንተ ተዛብ!” የሸርሙጣ ሴትን ፊት ለየት የሚያቅተኝ መሰለህ?!» አለችው፡፡
ያ ሀቢብቲ!ቁልቱ ወላሂ!!!(ፍቅሬ በአላህ ስም እኮ ምዬልሻለሁ» አለ ትንሽ ቆጣ ብሎ፡፡

«እስካሁን ምንም የሸርሙጣ ሴት ምልከት አላየሁባትም፤ኑሮ የተሟላላት የቤት ልጅ ነው የምትመስለው፤ሳዲቅ ልቤ ከዚህች ልጅ ጋር አዲስ ፍቅር እንደጀመርክ ይንግረኛል ስለጠረጠርኩህና ስላላመንኩህ አትቀየመኝ!»

እንግዲህ ከዚህ በላይ እንድታምኚኝ ምንም የማደርገው ነገር አይኖርም
አረብኛ ትንሽ ትንሽ ስለምትሞከር ከፈለክሽ ከራሷ አንደበት ስሚው አላትና ላፕቶፑን ወደኔ ገፋው፡፡

እኔ በነገሩ በጣም በማፈሬና ለገዛ ሚስቱ “ሸርሙጣ ነኝ" ብሎ መናገር ስለከበደኝ ላ
👍94
ፕቶፑን አረቢያን መጅሊሱ ላይ ጥዬለት ወደ ሳሎን ሄድኩ። ሁለቱም በአረብ የግንፍልተኝነት ስሜት እየተጯጯሁ ቤቱን በአንድ እግር አቆሙት
እርሷ ባለቨ ከሌላ ሴት ማደሩ ጭራሽ አላሳሰባትም እርሷን ያስጨነቃት ሀበሻ

ሴት ወዶ እርሷን እንዳይፈታት ብቻ ነው እንደዚህ አይነት ጉድ ደግሞ ሰምቼም አላውቅም የሳዲቅ ሚስት ጩኸቷን ትታ ማልቀስ ስትጀምር ሳዲቅ ሮዚ ፕሊስ ካም፣ ካም ካም ፕሊስ ብሎ ጠራኝ
በጣም እየከረረ መሆኑን ስረዳ ጣልቃ መግባት እንዳለብኝ ተረዳሁ፤እንደ አቅሚቲ በምችላት አረብኛ ተጠቅሜ እውነቱን ላስረዳት ሞከርኩ

<<..ኢስማእ ሊ እነ ዛኒ በስ» እያልኩ እየጮህኩ አስረዳኋት እኔ እርሷን እያስረዳሁ ሳለ ሳዲቅ እንድታምነው ብሎ ከቆሻሻ መጣያው ውስጥ ከደቂቃዎች በፊት የተጠቀምንበትን ኮንዶም በሶፍት
እንጠልጥሎ ይዞት መጣ፡፡ እኔ በሰቀቀን ሞትኩ፡፡ ኮንዶሙ ስላጸየፈኝ እኔ አሱ ላይ ጮህኩበት። አረብ ድሮም ስነ ስርዓት የሌለው ፍጥረት ነው ቤቱ ተረባበሸ የሳዲቅ ሚስት ትነፉረቃለች፣ እኔ እጮኸለው ሳዲቅ እንደ ጅል ኮንዶም በሶፍት ይዞ ቆሟል በኋላ አንድ ሀሳብ መጣልኝ፡፡ ቦርሳዬን አውጥቼ የከፈለኝን
500 ሪያል ቆጥሬ ማሳየት ካመነች አመነች፣ ካላመነች ባፋንኩሎ! ስራዋ ያውጣት

ሪያሉን አውጥቼ ስቆጥር ና ሳሳያት ቁጣዋ ትንሽ በረደላት

« ሀበሻ እባብ የሆነ ፍጡር ነው፣ እዚህ አሽከር ባሪያ ሆነው እየመጡ ባሎቻችንን ይቀሙናል፣ እዚያ ሸርሙጣ ሆነው እየሰሩ ኑሯችንን ጀሀነም ያረጉታል፣ ናእለቱ አልሐበሻ!! ሐበሻ ላይ እርግማን ይውረድ ያ አላህ» እያለች ተንጣጣች ይሄን ጊዜ ራሴን መቆጠጠር አቃተኝና መልስ ለመስጠት የሚያስችለኝ
የአረብኛ እውቀት ስለሌለኝ ክፉኛ እዝኜ ዉስጥ ዉስጡን ጦፍኩ፡፡ ከዚያ ግን ዝም ማለቱ ስላንገበገበኝ በእንግሊዝኛ ራሷን እስክትስት ሰደብኳት

«You bastard Arab, you don't know what you are talking about. You know what!! you are
the one mentally slaved. My sisters are in a better position than you coz their mind has
never been slaved. You idiot Arabs...you have no moral ground to curse us. Fuck your
morals..fuck your culture...wearing Hijab doesn't make you cleaner...you know what? Clean your heart first. Your mind is dirtier than our clothes. Assholes..fuck you bitch
Arab..fuck you all...Bafankullo!!

እንደ እብድ አደረገኝ ሳዲቅ በኔ ንግግር ከመናናደድ ይልቅ በሳቅ ተንከትከቶ ሊሞት!

«What makes you laugh, you bitch?» አልኩት በንዴት እንደጦፍኩ

እርሱ ሳቁን እንኳ መግታት ተስኖ....Oh Roza...you are so funny.. Come on ...Don't you
know my wife is deaf to English...oh Roza...you made my day እያለ ተከትክቶ ሳቀ

ይልቅ እኔን የገረመኝ የሚስቱ እንግሊዝኛ አለመቻል ሳይሆን የርሱ ደደብነት ነው ስለ አረብ የተናገርኩት ሁሉ እርሱንም ጭምር እንደሚመለከት ለመረዳት የሚያስችል ጭንቅላትእንኳ አልታደለም አረብ ደደብ ሆኖ የተፈጠረ ፍጥረት ነው

ሚስቱ የኔን ሁኔታ ስታይ እና በንዴት መጦፌን ስትመለከት ነው መሰለኝ የእውነት ሸሌ መሆኔን ተረድታ ሳዲቅን በፍቅርና በደስታ ማነጋገር ጀመረት ስለ ልጃቸው ጥቂት ካወሩ በኋላ ከኔ ሌላ ከሌላ ሴት ፍቅር እንዳይጀምር አስጠንቅቃው የስካይፕ ወሬያቸውን አጠናቀቁ

ከዚህ በኋላ በተከተሉት ደቂቃዎች ከሳዲቅ አንደበት ሁሉንም ጉድ ሰማሁት።

ሰዲቅ በስራው ጠባይ የሪያድ መልቲሚኒየር ዓሚር አለቃውን አጅቦ ከአገር አገር ይዞራል እረፍት የለውም ሚስቱ አህላም የሳውዲ ዜጋ ስትሆን በሪያድ ውስጥ ነው የምትኖረው አልተማረችም፣ ስራ አትሰራም
በአገራቸው ሴቶች የቢሮ ስራ እንዲሰሩ ብዙም አይበረታታም ስራዋ እርሱን መንከባከብ ብቻ ነው ከሄደበት አገር ሁሉ ሲመለስ ረዥም ሂል ጫማዎችንና እጅግ ዉድ አጫጭር ሚኒስከርቶችን፣ወሲብ ቀስቃሽ የተገላለጡ ልብሶችን ይገዛላታል ልብሶቹን ከቤት ዉጭ መልበስ ወንጀል ስለሚሆንባት
በመቶዎች የሚቆጠሩትን ረዣዥም ሂል ጫማዎችንና ሚኒስከርቶቹን ለብሳ ግቢ ውስጥ ወዲህ ወዲያ እያለች ቀኑን ሙሉ ትዘዋወርባቸዋለች እግሯ ከቤት ወጥቶ ሲረግጥ ግን አይኗ ሲቀር ሁሉንም የሰውነት ከፍሏን በጥቁር አባያ የግድ መሸፈን ይኖርባታል መዳፏንም ከሀር በተሰራ ጥቁር ጓንት ትሸፍነዋለች

አህላም በአገሯ መኪና ማሽከርከር እንኳ አትችልም በሳኡዲ አገር ሴቶች መኪና መንዳት አይፈቀድላቸውም ስለዚህ ግቢያቸው ውስጥ ሆና ልጃቸውን በመኪና አድርጋ በተንጣለለው ግቢ
ውስጥ ታንሸራሽረዋለች የመኪና አምሮቷን ለመወጣት እንዳንድ ጊዜ እንደ ወንድ ለብሳ በማታ እዛው ሰፈራቸው አካባቢ መኪና በፍጥነት እሽከርከራ ቤት ትገባለች

ሚስቱ ሲበዛ ቀናተኛ ናት፣መጀመሪያ አካባቢ ሳዲቅ አገር ጥሎ በሄደና ለቀናት/ለሳምንታት/ለወራት በተለያት ቁጥር “ይሄኔ ሌላ ሚስት ይዟል፤ከኔ የበለጠ ታስደስተው ይሆናል፣ ሊፈታኝ ይችላል " እያለች ትብከነከን ነበር በቅናት እና በጥርጣሬ ስሜት ስትንጨረጨር ትከርምና ሲመጣ ያሳለፈችውን ስቃይ
ትተርክለታለች እንደማይፈታት ቅዱስ መጽሐፋቸውን እስይዛ ታስምለዋለች እርሱም እቅጩን ይነግራታል፤ መቼም እንደማይፈታት ሆኖም ግን በሄደበት አገር ከሸርሙጣ ጋር ማደር እንደሚፈልግ
ቅዱስ መጸሐፋቸውን ይዞ መማል ያስቃስፈኛል ብሎ ስለሚያስብ ነው እውነቱን የሚነግራት

አህላም በደስታ ሀሳቡን ትቀበለዋለች አማራጭ የላትም ሶስት ጊዜ ለቀልድ እንኳ ፈታሁሽ ብሎ ቢናገር ህይወቷ
እስከወዲያኛው እንደሚጨልም ታውቀዋለች እስካልፈታት ድረስ ደስ ካለችው ሴት ጋር ማደር እንደሚችል
ኾኖም ማፍቀር እንደማይችል ሸርሙጣም ጋር ቢሆን ከአንድ ሸሌ ጋር ከአንድ ሌሊት ማሳለፍ እንደሌለበት መጸሐፋቸውን ይዘው ተማማሉ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከሸሌ ጋር ሲያድር ካለበት ሃገር ሆኖ ስካይፕ በማድረግ ሪፖርት የማድረግ ግዴታ ተጣለበት

አህላም ባሏ በምንም ሁኔታ ልቡን ለሌላ ሴት የሚሰጥበት አጋጣሚ እና ክፍተት እንዲፈጥር አትፈልግም ለዚህም ነው
ምን ጊዜም አብራው የምታድረውን ሸሌ በ Skype ቪዲዮ እንዲያሳያት የምትፈልገው በዚህም ማረጋገጥ የምትፈልገው ሴቷ እውነተኛ ሸሌ መሆኗን እና ቆይታዋ የአንድ ሌሊት ብቻ መሆኑን
ነው አረብ ወንዶች ለሀበሻ ሴት ያላቸውን ፍቅር ስለምታውቅ ነው ዛሬ እቧራ ያስነሳቸው

እንቅልፍ ሊጫጫነኝ ሲል በሳዲቅ እቅፍ ውስጥ እንዳለሁ ዘወትር በአእምሮዬ ጓዳ የሚመላለሱ ጥያቄዎች ተመላለሱብኝ

"ባሪያ መባል ያለባቸው ኑሮን ለማሸነፍ አረብ አገር የሄዱት እህቶቼ ናቸው? ወይንስ ይህችን አይነት ደንቆሮ የአረብ ሚስቶች?»

ከገንዘብ ባርነት የአእምሮ ባርነት ምንኛ የከፋ እንደሆነ እያሰላሰልኩ እንዲሁም ደግሞ ፈጣሪ ለም የአእምሮ ድሀ የሆንን ህዝብ በነዳጅ ሀብት ሊከሰው እንደፈለገ እየተፈላሰፍኩ ጀርባዬን ለሳዲቅ ሰጥቼ
ተኛሁ የሳዲቅ ወንድነት ቂጤ አካባቢ እንደ እባብ ሲተሻሸኝ እየተሰማኝ ከባድ እንቅልፍ ጣለኝ

💫ይቀጥላል💫

Like 👍ማድረግ ቀንሳችኋል

ከ 160 👍በኋላ ቀጣዩ ክፍል ይቀጥላል

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍112
አትሮኖስ pinned «#ሮዛ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ሁለት (🔞) ፡ ፡ #እንዲህችም_አይነት_ሚስት #እንዲህም_አይነት_ፍቅር #እንዲህም_አይነት_ትዳር_አለ ህዳር 8 ፣2007 ፈረንጆች Sometimes real life is more fictious than fiction and more filmic than a Hollywood film የሚሉት አባባል በህይወቴ ውስጥ ተከስቶብኛል፤ለዚያውም በተደጋጋሚ፡፡ እውነቴን ነው! በህይወቴ የሆኑት አንዳንድ…»
#የፈሪ_ዱላ

ያም ሲል ተነሳ
ይሄም ሲል ተነሳ
ሁሉም ሲል ተነሱ
እኮ ኬት ይነሱ?
ሐምሌ ገብቶ ቢጨልምም
ፀሐይ ወታ ብትገባም
ዛሬም እዛው...አልነቃንም
አንድ መሆን አልጀመርንም.፤
ይብቃን አንነሳ
ከቤትህ ያለውን
መሳሪያህን አንሳ
ይላሉ አስሬ
ተነሳ ተነሳ ...!
ሲለው ወጣ ብሎ
እራሱን ደብቆ
ይጽፋል ሸምቆ
የአገሬው ጎበዝ
ለነፍሱ ተሳቆ ...!
እኮ ማን ይነሳ?
ሁሉም ሲል ተነሳ
ቀኑ እየገፋብን
ማን ነው 'ሚያስነሳን?
ለነጻነታችን
ቀጠሮ ማይስጠን፤
እኮ ማን ይነሳ?
ሁሉም ሲል ተነሳ፡፡
#ይኑር_ጠላቴ

ጠላቴ ሲጠቅመኝ
በጉዳቴ ስቆ
ወዳጄ ግን ጐዳኝ
እንከኔን ደብቆ፡፡
#ሮዛ


#ክፍል_አስራ_ሦስት (🔞)


#ከናንተ_መሐል_ጻድቅ_የሆነ
#መጀመርያዋን_ድንጋይ_ይወርውር

መጋቢት 8፣ 1998

በኮዚ ክለብ መስራት ከጀመርኩ እንድ ዓመት አልፎኛል፤ስጀምር አካባር አርብ፣ቅዳሜ እና እሁድን ብቻ ነበር
በክለቡ ውስጥ የምሰራው፡፡ይህን ያህል ጊዜ የቆየሁበት ሌላ ቤት የለም፡፡ጥሎብኝ በአንድ ቤት ለረጅም ጊዜ መቆየት አልችልም። ስልቹ ነኝ መሰለኝ።
ድሮም ቢሆን እዚህ ህይወት ውስጥ ሳልገባ ከአንድ ወንድ ጋር ሙጭጭ ማለት አይሆንልኝም ነበር፡፡ ወንዶች ቶሎ ይሰለቹኛል። በሕይወቴ መቀየር የምችለውን ነገር ሁሉ መቀየር ብችል ደስ ይለኛል፡፡ ጸጉሬን ደጋግሜ የምቆረጠውም ለዚህ ይመስለኛል፡፡ጓደኞቼ ግን የሚያምረውን ጸጉሬን ስቆርጠው ያበድኩ ይመስላቸዋል፡፡እንኳን ጸጉሬን ቁመቴንም እሰለቸዋለሁ፤
አንዳንድ ጊዜ ቁመቴን መቁረጥ እንደሚያምረኝ ማን በነገራቸው፡፡ ሰው እንደ ግመል ሜትር ከ 75 ሆኖ
ይፈጠራል በማርያም"ይህን ቁመትሽን ወይ ቁንጅና አልተወዳደርሸበት ወይ አውሮፕላን አላበረርሽበት"
ትለኛለች ራኪ፡፡ ብዙ ሀበሻ ወንዶች ከኔ ጋር መቆም ምቾት የማይሰጣቸውም ለዚሁ ነው:: ያነሱ ይመስላቸዋል፡፡ «ይህቺ ቆጥ እምስ» እያሉ ያሙኛል፡፡ ምን ላድርግ…ቁመቴን እኔ ኮትኩቼ አላሳደኩት፡፡

ኮዚ ክለብ ብዙም ሐበሻ ስለማያዘወትረው ተመችቶኛል፤ በዚያ ላይ አሪፍ ቢዝነስ አለ፤አሪፍ አሪፍ ሰዎች
ሚኒስትሮች ከስብሰባ በኃላ"ጌዳውን" ሲያምራቸው በጊዜ ከዚህ ቤት ይሰየማሉ፡፡ እንደ ሌሎች ቤቶች
ተደጋጋሚ እና አሰልቺ ፊቶች አይበዙም፡፡ ለምሳሌ በየምሸቱ አዳዲስ ተጋባዥ ዲጂዎች ይኖራሉ።
በየእለቱ ከአዳዲስ ደምበኞች ጋር እንደመውጣቴ የተለያዩ አገር ስጦታዎች ይመጡልኛል፡፡ ተመሳሳይ ፊት አይቼ አላውቅም፡፡ አዲሳባ ለአጭር ጊዜ ስብሰባ ወይም የስራ ጉብኝት የሚመጡ ሰዎች ናቸው ኮዚን በብዛት የሚያዘወትሩት፡፡

የሰዉ ዓመልም በኮዚ የዛኑ ያህል ለየቅል ነው፤ አንዳንዱ ጡትሽን እንደ ህጻን እየጠባሁ ልደር ይላል፤ሌላው ቂጥሽን ሌሊቱን ሙሉ ልንተራሰውና የፈለግሽውን ልከፈልሽ ይላል፡፡ የኔ መፍሳትአለመፍሳት
አያሳስበውም፡፡አንዳንዱ ሰው የቅንዝር ለሃጭ ጭንቅላቱን ሲጋርደው ሰው መሆኔንም ይረሳል መሰለኝ።
ተንበርከከን እንላስልሽ የሚሉኝ ብዙ ናቸው፡፡በተለይ አረቦች ጭንቅላታቸውን ጭኔ ውስጥ ቀብረውት ማደር ይወዳሉ፡፡ ራኪ ይህን ጉዳይ ስነግራት « አረብ ነዳጅ ካላየ ያን ያህል የሴት ጭን ውስጥ አይደፋም፤ አስቆፍሪው» ትለኛለች፡፡ እሷ ጫወታ አያልቅባትም፡፡ ነዳጅ ቀርቶ አንድ ከርሳም አረብ እዚያው ትንፋሽ
አጥሮት ድብን ብሎ ሰበብ እንዳይሆንብኝ እንጂ ለኔስ ብዙም ከባድ አልነበረም፡፡ በኮዚ የማይገጥመኝ ጉድ የለም፤አንዳንድ ጊዜ የሚገርመኝ ነገር ከመብዛቱ የተነሳ መገረም ሁሉ አቆማለሁ፡፡ ግን ይኸው ለውጥ
ይመስለኛል እዚህ ያከረመኝ፡፡

የኮዚ ክለብ እለታዊ ፕሮግራም ተለዋዋጭ ነው፤ በብዛት ግን ምሽት
2፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 5:00 ሰዓት ድረስ ለስላሳ የጃዝ ሙዚቃ ይቀርባል፤ በዚህ ሰዓት የሚገቡት ባለስልጣናትና ታዋቂ ሰዎች ናቸው ከሰሞኑ ደግሞ እትሌቶች መምጣት ጀምረዋል። አሁን ማን ይሙት በቀደም ስንት ሺ ሜትር ነው ሮጦ ወርቅ ያመጣው ባላገር ልጅ እንዴት ሆኖ ነው ጃዝ ሙዚቃ ገብቶት እዚህ ቤት ማዘውተር የጀመረው ይሄ አትሌት በመጣ ቁጥር ቶሎ ራኪ ጋር እንሰባሰባለን፡፡ በጣም ነው ሙድ የምትይዝበት፡፡ ለነገሩ እሱ ላይ በመቀለድ አፉን ያልፈታ የቤቱ ሰራተኛ የለም፡፡ ደግነቱ ዘወትር ምሽት የሚያዘው ወይ ሃይላንድ ግፋ ቢል
ሬድቡል መሆኑ በጀው እንጂ እንደሌላው ቀምቅሞ ቢለፋደድ ከሰው አፍ ይገባና ያርፈው ነበር፡፡ አትሌቱ አንድ ሳምንት በተከታታይ ይመጣና ከዚያ ለእንድ ለሁለት ወር ይጠፋል፡፡ ባለፈው ወር አምለሰትን ልጋብዝሽ ብሏት አብረው እየተጫወቱ ድንገት ዘሎ ለምን “ከዚህ ስራ አትወጪም… ምናምን ብሎ
ሊመከራት አልዳዳውም? ጌጃ! አምለሰትን እያወቃትም ማለት ነው "ሆድዬ! እንተ ሩጫ ስታቆም ነው
እኔ ይህን ስራ የማቆመው» ብላው አመዱን ቡን አደረገችው፡፡ ከዚያን ቀን ጀምሮ እዚህ ቤት ሴት ጋብዞ አያውቅም፡፡ ብቻውን እዛች ዲጄው መስኮት ጥግ ተቀምጦ ይሄን ዉሃውን ይጋታል፡፡ የጌጃነቱ ጌጃነት እዚህ ቤት የስፖርት ቱታ ለብሶ ይወጣል፡፡ ንክር ባላገር!

ኮዚ ባር ከ5፡30 ጀምሮ ደግሞ ዲጀ ዲክ ከዕለቱ ተጋባዥ ዲጄ ጋር በመሆን በአለም ሙዚቃ ያምነሸንሹናል፡
ክልሱን ዲጄ ዲከን የማያውቀው የለም፡፡ በእንግሊዝኛው ኤፍ ኤም የራሱ የአየር ሰዓት ስላለው ብዙ የዲፕሎማት ሴት ልጆች እርሱን በአካል ለማየት ከዚሁ ሰዓት ጀምሮ ቤቱን ይሞሉታል፡፡ ከሱ ጋር ለማደር የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡ እሱ ሸክላውን ከሚያጫውትበት መስኮት ፊት ሆነው ቂጣቸውን እየቆሉ
ይደንሱለታል፡፡ እሱ ብዙም ግድ አይሰጠውም፡፡ የፈለጋትን ሴት በፈቀደው ሰዓት ማግኘት እንደሚችል
አሳምሮ ያውቀዋል፡፡ ሲኮራ ይበልጥ ያምርበታል፡፡ ለነገሩ የሚያምር ሰውነት ነው ያለው፡፡ እኔ ግን ለምን
እንደሆነ እንጃ እንደ ወንድሜ እንጂ በሌላ ተመኝቼው አላውቅም፡፡ በጣም እንቀራረባለን፡፡ ቀልድ ጫወታ ስለሚችል ደስ ይለኛል፡፡

እኩለ ሌሊት አካባቢ ቢዝነስ እጀምራለሁ ፡አፍሪካውያን፣ አረቦች፣ አውሮፖውያንና አሜሪካውያ ከጥቂት ዲታ ኢትዮጵያዊያኑ ጋር ቤቷን በአንድ እግሯ ያቆሟታል፡፡ በእስካሁኑ ልምዱ እንደዚህ ቤት
የምናማር ሴቶችን ብቻ በብዛትና በጥራት የሚያቀርብ አላውቅም፡፡ ለነገሩ የኛም የሾርትና የአዳር ዋጋ በከተማዋ ሁሉ የማይቀመሰው ነው ይላሉ፡፡ ኮዚ እየሰሩ ሾርትና አዳር እየተልፈሰፈሰ በመጣው የብር ዋጋ መተመን የማይታሰብ ነው፤ ከ5:30 ጀምሮ ቋንቋው ሁሉ በዶላር ይሆናል፡፡ሪያል የምንቀበለው ራሱ አረብ ቂጣችንን እየላሰ ሲለማመጠን ብቻ ነው:: አንኳን ለዜጋ ለሀገር ልጆችም በዶላር ተምነን ነው የምቀበላቸው:: ከዚያ ዶላሩ ጠርቀም ሲልልን ኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ በሳምንት አንድ ጊዜ ሰኞ ሰኞ መንዝረነው እንመጣለን፡፡ ያ ሁሉ ዶላር የት እንደሚገባ በበኩሌ አይገባኝም፡፡ ለምን
ይሆን የማይበረከትልኝ? ለሁላችንም ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ የምናገኘው ብር በረከት ኖሮት አያውቅም፡፡ ሸሌን
ጌታ ረግሞታል፣ ንስሀ ግቡ” ትለናለች ሸሌዋ ጓደኛችን ትርሲት፡፡

በስካሁኑ ቆይታዬ በርካታ ዓለም አቀፍ ደንበኞችን አፍርቼአለሁ። ዜጋ ደንበኛ በማብዛቴ ጓደኞቼ "ኮፊ ሀናን" በሚል ቅጽል ስም ነው የማጠሩኝ።ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ ኮፊ አናን ጋር አያይዞ ዲጄ ዲክ ነው መጀመሪያ ይህንን ቅፅል ስም ያወጣልኝ። በኮዚ እንደ ዲጄ ዲክ ተረበኛ ሰው የለም መቼለታ ስቱዲዮ ጠርቶኝ ተኪላ ከጋበዘኝ በኋላ "ሮዚ ቆንጆ ይሄ ፓስፖርት የመሰለ እምስሽን የስንት አገር ቪዛ ነው የምታስደበድቢው?" ብሎ ተረበኝ። "አንተ ክፉ" ብዬው እየሳኩ ወደ ደንበኛዬ ፋሩቅ
ሄድኩኝ፡፡ ፋሩቅ ግብጻዊ ኦርቶዶክስ አረብ ነው ቀልዱን በእንግሊዘኛ ተርጉሜ ነገርጉትና ሌሊቱን ሙሉ ሲስቅ አደረ፡፡ ቁላው በቆመበት ቁጥር ታድያ..Rozina may i have your passport please? wanna issue my visa....እያለ ተላጠብኝ፡፡

በእኔ በኩል ደንበኛን የማብዛቱ ቀመር አሁንም አልተለወጠም፤ ብዙ ደንበኛ የማፈራበት ምክንያት ብዙ የወንድ ሳይኮሎጂ ላይ የተጻፉ መጻሕፍትን በማንበቤ ይመስለኛል፡፡ ወንድ ሲፈጥረው ጉረኛ ነው። ጉራውን ሲቸረችር
ሳይሰለቹ እህ! ብሎ መስማት ዋናው ቁም ነገር ነው፡፡ ሁልጊዜም ወንዶች ከሌሎች ወንዶች የተለዩ አስደናቂና ስኬታማ እንደሆኑ እነግራቸዋለሁ፡፡ ወዲያው
👍62
ልባቸው ይሞቃል፡፡
ልባቸው ሲሞቅ ቁላቸው መንከላወስ ይጀምራል፡፡ ከንፈሬን አልሰስትም፡፡ የሚያወሩትን የስራ ዝባዝንኬና ቅራቅንቦ
ሁሉ «እህ!» ብዬ እሰማቸዋለሁ፡፡ ጉዳያቸውን ጉዳዬ ብዬ ስሰማቸው ፍቅራቸው ይጨምራል፡፡ በወሲብ
ወቅት በቁምነገር አካላቴን ሲደባብሱኝ የምር ስሜት ውስጥ የገባሁ እንዲመስላቸው እሆናለሁ፡፡ ይህን ጊዜ
ሸሌ መሆኔን ይረሱታል፡፡የብዙ ጓደኞቼ ችግር ደንበኞቻቸው በወሲብ ሲንፈራገጡ እነሱ ምንም ግድ ሳይሰጣቸው ችላ ይሏቸዋል፡፡ በፍጹም እርግጠኝነት የምናገረው ወንዶቹ ከፍተኛ የወሲብ ጡዘት ላይ የሚደርሱት እኛ በምናሳያቸው ነገር መሆኑን ነው፡፡ ለምሳሌ በወሲብ ጊዜ "ወይኔ አንተ ልጅ ስታስጠላ!በጣም ኃይለኛ ነህ እሺ! ማርያምን፣ አልቻልኩህም አቆሳሰልከኝ እኮ ነገ መራመድ የምችል ሁሉ አይመስለኝም እሺ፡እስከንሻፈፍ እኮ ነው የበዳከኝ…ሂድዛ ከፉ! እስቀያሚ» የሚል ቃል በጆሮው ሳንሾካሹክ የትኛውም ወንድ አለመጨረስ አይችልም፡፡ የብዙ ጓደኞቼችግር የሚመስለኝ ወንዶቹ
ወሲብ ላይ ሲቆዩባቸው «እስኪ ጨርስ በናትህ! ምን ይመስላል!» እያሉ ይመነቃቀራሉ፡፡ እንዲህ አይነቱ
ንግግር ሲመስለኝ የወንዱን ስሜት ይበልጥ እንዲጠፋ ያደርገዋል እንጂ እንዲጨርስ እያደርገውም፡፡

አንዳንድ ወንዶች ከጨረሱ በኋላም ቢሆን በሚገርም ሁኔታ እንደበዱኝና በዚህ መልኩ ማንም አርጎኝ እንደማያውቅ ስነግራቸው በደስታ ራሳቸውን ሊስቱ ይደርሳሉ፡፡ ደረታቸው ላይ ስሸጎጥ ደግሞ ለራሳቸው
ያላቸው ስሜት ከፍ ስለሚል ፊታቸው ይበራል፡፡ ጭራሽ ከሸሌ ጋር ያደሩ መሆናቸውን ይረሳሉ፡፡
ሳምንት ሳይቆዩ ካልደገምንሽ እያሉ መከራዬን ያበሉኛል፡፡ ፔሬድ ላይ ሆኜ ክለብ ካልመጣሁ ስልኬ እረፍት የላትም፡፡ መች ተመልሼ እንደምገባ በሚጠይቁ ደንበኞች እጨናነቃለሁ፡፡ ጓደኞቼም አንድ መለኪያ ውስኪ የሚጋበዙት እኔ መቼ እንደምገባ አንዲናገሩ ብቻ ነው፡፡ እኔ ከሌለሁ በጊዜ ወደቤት የሚሄዱ ደንበኞቼ ብዙ ናቸው:: ላግባሽ ያሉኝ ደንበኞች ማዘጋጃ ይቁጠራቸው፡፡ የስፔስ ትዊን ታወር
ባለቤት ዱባይ ቤት ልከራይልሽና ላስቀምጥሸ” ብሎኝ እምቢ ብዬዋለሁ፡፡ በዚህ ኢድሜዬ ብሞት ቅምጥ አልሆንም
ያረፉበት ሆቴል ድረስ እንድመጣ የዲፕሎማት ታርጋ ያለው መኪና ከነሾፌሩ ያለሁበት ድረስ የሚልኩልኝ ዜጎች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ እኔን የቀመሱ ደንበኞቼ በፍጹም የኔን ጓደኞች አያወጡም፡፡
ምንድነው የምታስነኪያቸው? እምስሽ ውስጥ ቁዝሚ አስቀብረሻል እንዴ!» ይሉኛል እነ አምለሰት፣
የወንድ ሳይኮሎጂ መጸሐፍ ቢያነቡ ሚስጢሩን በቀላሉ መባነን ይችሉ ነበር፡፡ ችግሩ ሸሌዎች ስንባል
ፊልም ማየት እንጂ መጸሐፍ ማንበብ እንወድም፡፡ ከልምዴ እንዳየሁት ወንድ በጣም ደካማ ፍጡር ነው ወንድን ማታለል ድመትን በወተት ከማታለል የበለጠ ቀላል ነው፡፡

“ወንዶሎጂ 101” ወንድ ከ "ኢጎ" የተሰራ ተሰባሪ ፍጥረት ነው፡፡ ጉራውን እና ጉጉቱን ማኮላሸት የእርግብ ከንፍ እንደመስበር ነው፡፡ “ወንዶሎጂ 102" ወንድ በሴት ሲናቅ፣ሲገፋ የማንነቱ መሰረት ይናጋል፡፡ ወንዶሎጂ103" ብዙ ወንድ ሸሌ ጋር የሚመጣው ሴትን ማስመጥ እንደሚችል ለራሱ ማረጋገጫ
መስጠት ሲፈልግ ነው፤ እንጂ እኛ ጋር በማር የተለወሰ ጡትና ቂጥ ኖሮ አይደለም፡፡

እንደ መደዴ ሸሌ"ይቅርታ! ከንፈሬን መሳም አልወድም" ብዬ የወንድ ወሲብ ስሜቱ ላይ ቀዝቃዛ ውሃ አልቸልስም፤ከንፈሬን ያለ ስስት እሰጠዋለሁ፡፡ ከንፈርም እምስም የተሰሩት ከቆዳ ነው፡፡ ደንበኛዬ
የጡቶቼን ጫፎች በጣቶቹ ለመዳበስ ሲፈልግም እንደ መደዴ ፤አባቱ! በናትህ ጡቴን አትንካው አልወድም ብዬ የተነሳሳ የቅንዝር ስሜቱን አልገድልም፡፡በወሲብ ወቅት ደምበኛ ንጉስ ነው፤ ቢዝነስ ሳይሰስት እስከሰጠኝ ድረስ ገላዬን ሳልሰስት እሰጠዋለሁ፡፡ የዶላር ከፍሎኝ የብር አላዝናናውም፡፡
ሮዛ ቆንጅዬ ዙሪና ስጪኝ!” ብሎ ሲጠይቀኝም እንደ አብዛኛዎቹ ጌጃ ሸሌዎች፤ሂድና አህያ አስፈንድደህ
ብዳ፤እኔ ሰው እንጂ አህያ አይደለሁም!" ብዬ የደምበኛዬን የቆመ ብልት አላሟሽሽም፤ ክብሬን የማስጠብቀው “የፉ” ባለመስጠት አይደለም፡፡ ይሄ ጭልጥ ያለ ኋላ ቀርነት ነው፡፡ አንዳንዶቹ ጓደኞቼ ይገርሙኛል፡፡ የቁም ተበዱ የቅምጥ፣ አሞራ ግብግብ ተበዱ፣ አሞራ ሲያይሽ ዋለ ተበዱ ዞሮ ዞሮ እምሳቸው
ውስጥ ቁላ መግባቱ ላይቀር ይላላጣሉ፡፡ አሊያ ባሌን ጎዳሁ ብላ እምሷን በእንጨት ከወጋችው የገጠር ሴትዮ በምን ተለዩ ታዲያ፡፡

ወደድንም ጠላንም ስራችን ወንዶችን በወሲብ ማስደሰት አይደለም እንዴ?ወንዱ ፍቅረኛውንና ሚስቱን ትቶ እኛ ጋር የሚመጣው እኮ ከነሱ ያጣውን ወሲባዊ ቅብጠት ለማግኘት ነው?እንጂ የኛ እምስ
ከአይስክሬም ስለተሰራ አይደለም፡፡እኔ ደንበኛዬ የጠየቅኩትን እስከከፈለ ድረስ እንዴትም አድርጎ ቢበዳኝ
ችግር የለብኝም፡፡ ችግር የሚፈጠርብኝ ለኔ አስቦትም ሆነ ሳያስበው በሆነ መልኩ ንቀት ሲያሳየኝ ነው ችግር የሚፈጠረው እኔን ከሰው በታች አድርጎ ማየት ሲጀምር ነው፡፡ ያኔ ሸርሙጣነቴ ይመጣብኛል
በስድብ አስታጥቀዋለሁ፡፡ ለምን ዶላር በጆንያ ይዞ አይመጣም ከሱ ጋር አላድርም፡፡ እውነት እንነጋገር
ከተባለ በጂም ተበጂም ያው ሸሌ ነው፡፡ የሸሌነትን ማዕረግ ለሴት ብቻ ያረገው በወንዶች ዓለም ስለምንኖር ነው፡፡ጂሰስ እኮ ከናንተ ጻድቅ የሆነ የመጀመርያውን ድንጋይ ይወርውር ያለው ሁላችንም ሸሌ እንደሆንን ሊነግረን ፈልጎ መሰለኝ፡፡ ሀበሻ ወንድ ይሄ መች ይገባዋል፡፡ ባፋንኩሎ ሁላ!

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 ማድረግ እንዳይረሳ ዛሬ እስቲ ለጓደኞቿቹ ሼር በማድረግ እንዲሁም 200👍 በማድረግ አስደስቱኝ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍131👏1
አትሮኖስ pinned «#ሮዛ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ሦስት (🔞) ፡ ፡ #ከናንተ_መሐል_ጻድቅ_የሆነ #መጀመርያዋን_ድንጋይ_ይወርውር መጋቢት 8፣ 1998 በኮዚ ክለብ መስራት ከጀመርኩ እንድ ዓመት አልፎኛል፤ስጀምር አካባር አርብ፣ቅዳሜ እና እሁድን ብቻ ነበር በክለቡ ውስጥ የምሰራው፡፡ይህን ያህል ጊዜ የቆየሁበት ሌላ ቤት የለም፡፡ጥሎብኝ በአንድ ቤት ለረጅም ጊዜ መቆየት አልችልም። ስልቹ ነኝ መሰለኝ። ድሮም ቢሆን እዚህ ህይወት…»