#መምሰል_እና_መኖር
፡
፡
#በሕይወት_እምሻው
፡
፡
“ሴትን ልጅ ለማብቃት ቁልፉ ነገር ትምህርት ነው፡፡ ካልተማረች
ምርጫ ታጣለች፡፡ በኢኮኖሚ ጥገኛ፣ ሂጂ ባሏት ሂያጅ ፣ ነይ ባላ
ተከታይ ትሆናለች፡፡ ካልተማረች ሁሌም እስረኛ ነች፡፡
ስለዚህ ለእኔ ከሁሉም በላይ አንገብጋቢው ነገር ማንኛዋም ሴት
የትምህርት ዕድልን አግኝታ ራሷን እንድትለውጥ ማገዝ ነው፡፡
ለዚህ ደግሞ ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል፡፡”
እንዲህ የተሰተረ ንግግር የተናገረችው ከምመካባቸው ሴት ወዳጆቼ መሀል አንዷ ናት፡፡ ታወራ የነበረው በአንድ ሰሞን ለማርች ስምንት ተሰናድተው ከነበሩት ከጸጉር የበዙ ዝግጅቶች በአንዱ መድረክ ላይ ነበር፡፡
እንደተለመደው ኮርቼባት ሳላበቃ ፕሮግራሙ አበቃና አዳራሹ በር
ላይ ተገናኘን፡፡
“ተናገርሽው መቼም...! ደስ ይል ነበር” አልኳት አጥብቄ ካቀፍኳት፤ ሞቅ አድርጌ ከሳምኳት በኋላ፡፡
“ታንኪው ፤ ታንኪው.... አወራሽ ነበር ግን መሮጥ አለብኝ..." አለችኝ ጥድፍ ጥድፍ እያለች፡፡
“ምነው ከመሽ ወዴት ነው የሚያሮጥሽ?” አልኳት ጥድፊያዋ ተጋብቶብኝ እኔም እየፈጠንኩ፡፡
ገና ገብቼ እገረዳለሁ... እራት መስራት አለብኝ...." ፊቷ ቅጭም አለ።
"ምነው ሠራተኛ የለሽም እንዴ...?”
"የለኝም ባክሽ... እነሱ መች ይቀመጣሉ? በናትሽ እስቲ ከሰማሽ
ኤፈላልጊልኝ... ሥራ ውዬ ወደ ሥራ... መሞቴ ነው እኮ...”
ሳቅ አልኩና፣ “ደርግ እንዳለው ድርብ ጭቆና ገደለሽ አይደል?..
ከሰማሁ እነግርሻለሁ” ብዬያት ተለያየን፡፡
ከሦስት ቀናት በኋላ ሥራ ስለምትፈልግ ልጅ ስሰማ ፈጠን ብዬ ደወልኩላት፡፡
ሰላምታ ስንጨርስ፣
“ስሚ... ሰው አላገኘሽም አይደል?” አልኳት፡፡
“ኸረ ሰጭራሽ... በናትሽ የኔ ቅመም አገኘሽልኝ እንዴ...?" ጉጉቷ
ግልጽ ሆኖ ይሰማል፡፡
"አዎ...."
“ምን ዓይነት? ”
“አነስ ያለች ልጅ ናት፡፡... ገና መምጣቷ ነው አሉ ከክፍለ ሀገር.. ምስኪን... ታማኝ ልጅ ናት፡፡”
“ወይኔ ታድዬ! ታማኝ ሰው እኮ ነው የቸገረን ዘንድሮ! መቼ ትመጣለች ታዲያ?”
"ነገ ወይ ከነገ ወዲያ፡፡ የዘመዷን ስልክ አሁኑኑ ቴክስት አደርግልሻለሁ.... እዛ ነው ያለችው ተብያለሁ፡፡”
“ወይ ተመስገን.! ምሳ አለብኝ የኔ ቅመም... ኃይለኛ ምሳ ነው የምጋብዝሽ፡፡”
“ችግር የለውም... በነገርሽ ላይ...”
“እ.. "
“ሰባተኛ ክፍል ናት፡፡ ዘንድሮ ያው... እዚህ ስትመጣ አቋርጣ ነው
እንጂ ትማራለች፡፡ የቤተሰብ ችግር ምናምን ነው እንጂ ጎበዝ ተማሪ
ናት አሉ ፤ መሸኛ አምጥታ ለሚቀጥለው ትመዘገባለች፡፡ ዕድለኛ ናት
አንቺ ቤት ከገባች ብዙ ቦታ ልትደርስ ትችላለች፤ እሱን አስቤ ነው
እኔም ቶሎ የደወልኩልሽ” አልኩኝ በተስፈኛ ድምፅ፡፡
“እ... ትማራለች?” ከድምፅዋ የደነገጠች መሰለኝ፡፡
“አዎ... ትማራለች... ትንሽ ልጅ እኮ ናት... እንዳልኩሽ አቋርጣ ነው... ምነው?”
“ኤጭ! በናትሽ እኔ መማር የምትፈልግ ሠራተኛ አልፈልግም፡፡
...ሌላ ...ሌላ ...መማር የማትፈልግ ከሰማሽ ደውይልኝ በቃ...
አሁን ሥራ ቢዚ ነኝ... ቻው..."
ከዐስራ ሦስት ዓመታት ላለፈ ጊዜ በሴት ልጅ ትምህርት ዙሪያ ደከመኝ፣ ታከተኝ ሳትል ስትታትር የኖረችው የሴት ልጆች መብት ተሟጋቿ ወዳጄ..፣ ለስንብት እንኳን ዕድል ሳትሰጠኝ ስልኩን ጆሮዬ ላይ ስትደረግመው ትዝ ያለኝ አንድ ነገር ብቻ ነው።
“ማንኛዋም ሴት የትምህርት ዕድልን አግኝታ ራሷን እንድትለውጥ
ማገዝ ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ ደግሞ ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ
ይገባል፡፡” ብላ በአደባባይ የተናገረችው፡፡
💫አለቀ💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ቀን። 🙏

#መምሰል
ሆዳም በበዛብት
በዚህች ከንቱ አለም
ስለ ፍቅር ማውራት
ለፍቅር መመስከር
በይምሰል መባደር
ኧረ እንዲያው አናፍርም ...!?
በቀለበት ታስረን
በፊርማ ተጣምረን
ተፋቀርን ብሎ
እራስን ማታለል፤
በገንዘብ ተጋብተው
በገንዘብ ተዋደው
ፍቅር አለን ቢሉ
ማነው የሚሰማው?
ካንቺ ወዲያ ለኔ
ካንተ ወዲያ ለኔ
እንዳልተባባሉ
እንዳልተማማሉ
ቃልኪዳን አክብረው
በጥምረት የታሉ፤
የጥቅም ላይ ፍቀር
ፍቅር ነው እያልን
ፍቅርን ስንቀብር
ማን ይሆን አልቃሹ
ማን ይሆን ሙሾ አውራጅ
ቀብሩንም እያየ
አይተቶም እንዳላየ
በሰፈሩ ወራጅ...፤
ኧረ እንደው...
የይምስል ከመኖር
ቢቀር ባንወዳጅ.!
ሆዳም በበዛብት
በዚህች ከንቱ አለም
ስለ ፍቅር ማውራት
ለፍቅር መመስከር
በይምሰል መባደር
ኧረ እንዲያው አናፍርም ...!?
በቀለበት ታስረን
በፊርማ ተጣምረን
ተፋቀርን ብሎ
እራስን ማታለል፤
በገንዘብ ተጋብተው
በገንዘብ ተዋደው
ፍቅር አለን ቢሉ
ማነው የሚሰማው?
ካንቺ ወዲያ ለኔ
ካንተ ወዲያ ለኔ
እንዳልተባባሉ
እንዳልተማማሉ
ቃልኪዳን አክብረው
በጥምረት የታሉ፤
የጥቅም ላይ ፍቀር
ፍቅር ነው እያልን
ፍቅርን ስንቀብር
ማን ይሆን አልቃሹ
ማን ይሆን ሙሾ አውራጅ
ቀብሩንም እያየ
አይተቶም እንዳላየ
በሰፈሩ ወራጅ...፤
ኧረ እንደው...
የይምስል ከመኖር
ቢቀር ባንወዳጅ.!