አትሮኖስ
282K subscribers
112 photos
3 videos
41 files
497 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
🍁🍁ዲያሪው 📝

ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_9


በሌላ በኩል ደግሞ ይህ የምታወራው ሁሉ እውነት ከሆነ በደለኛው እሷ ሳትሆን እኔ ነኝ ማለት ነው:: ምናልባት ሳላውቀው ደብዳቤ ጽፌ ይሆን? በማለት ራሴን ጠየቅሁ። እርግጥ ነው በዓለማችን ላይ አንዳንድ ሰዎች አንድ ነገር ማድረጋቸውን ወይም መፈጸማቸውን ሳያውቁ በእንቅልፍ ላይ ሆነው የተለያዩ ድርጊቶችን ፈጽመው ተመልሰው የሚተኙ እንዳሉ ሰምቻለሁ፣ አውቃለሁ:: አዎ ትዝ ይለኛል አንዳንድ ጊዜ የእኔም ወንድም በእንቅልፍ ላይ እያለ ተነስቶ በር ከፍቶ ለመውጣት ይታገል ነበር:: ግን የሰራውን ሁሉ ጠዋት የምንነግረው እኛ እንጂ እሱ አያስታውሰውም ነበር። እናቴ ሁል ጊዜ ኦሽ ባለ ቁጥር በር ከፍቶ የወጣ ስለሚመስላት ተኝታም ቢሆን እሱን መጠበቋ የተለመደ ነው:: አንድ ቀን በእንቅልፍ ልቡ ሲሄድ አንድ ነገር ይገጭና ጉዳት ያደርስበታል ወይም ገደል ይገባል ብላም ትዕጋለች:: ይህ ነገር ከቤተሰብ የሚጋባ ከሆነ እኔም ምናልባት አንድ ቀን ተነስቼ ደብዳቤውን ጽፌ ሊሆን ይችላል ብዬም አሰብኩ:: ግን ይኸ ደግሞ የማይቻል ነው:: መጻፉን ልጻፈው ፖስታ ቤት መቼም ወስጄ ላስገባው አይቻለኝምና፡፡ ይህንን ሳወጣና ሳወርድ ራሴ ሊፈነዳ ደረሰ:: በዚህ ሁኔታ ማንበብ እንደማልችል በመረዳቴና ከመጠን በላይ ስለደከመኝ ሃምሳ አለቃውን ጠርቼ ታስሬ ካልሆነ፣ ወደ ቤቴ ወስጄ እንዳነበው እንዲፈቅድልኝ በሩን ከፍቼ ብጣራ የሚሰማኝ አልነበረም። ያለሁበት ቢሮ ባይዘጋም የተቀረው ቢሮ ሁሉ ተዘጋግቷል:: ሰዓቴን አየሁት፡፡ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ሆኗል:: ጭር ብሏል:: እኔ በዲያሪው ውስጥ ሰጥሜ ሳለ ሰው ሁሉ ጥሎኝ ሄዶ ነበር፡፡ እዚያው አካባቢ _ ሃምሳ _ አለቃውን ፈለግሁት፡፡ ላገኘው ግን አልቻልኩም፡፡ እኔ ከነበርኩበት ከምርመራ ክፍል በስተቀር የሁሉም ክፍሎች መብራቶች ጠፍተዋል። በዚህ ላይ የኮሪደሩ መብራት ስላልበራ ፀጥታው ከጭለማው ጋር ተደምሮ እጅግ ያስፈራል። ቶሎ መውጣት ስለነበረብኝ ዲያሪውን ሰው እንዳያየው በሆዴና በሱሪዬ መሐል አጣብቄና ደብቄ እየተጣደፍኩ ወጣሁ:: ከቢሮ ወጣ ስል ግን በር ላይ ዘብ ቆሞ በማየቴ እስረኛ መሆኔን ተረዳሁ:: ዛሬ ሳነብ እንዳድር እንደተፈረደብኝ ገባኝ:: ከዛ በኋላ ደግሞ ምናልባት ነገ ምርመራ ሊኖር ይችላል፡፡ ምን ይኸ ብቻ! አልማዝም እንደተመኘችው ሞታ ከሆነና በእኔ ምክንያት መሞቷን ከፃፈች ደግሞ የእኔ ነገር አከተመ ማለት ነው፡፡ መለቀቅም ተረት ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ አልፌው ስሄድ ጥበቃው አረማመዴን ከማየት ውጪ "ተመለስ" ወይም "ወዴት ነው?" ባለማለቱ በዚሁ ተደፋፍሬ ወደ ውጪው በር አመራሁ፡፡ ነገር ግን እውጪው በር አጠገብ እንደደረስኩ፤

"ወዴት ነው አቶ አማረ?" የሚል ድምፅ በመስማቴ ዞር ብዬ አየሁ፡፡ ሃምሳ አለቃው ጥግ ላይ ራቅ ብሎ ከአንድ ፖሊስ ጋር ፊት ለፊት ቆሟል፡፡ ወደ እኔ እየመጣ ፤ "ለመሆኑ ማን እንዲወጡ ፈቀደልዎት? ዲያሪውን ይዘው ሊጠፉ ነበር ማለት ነው?" አለኝ፡፡ ምን ብዬ እንደምመልስለት ግራ ገብቶኝ ለአጭር አፍታ ዝም ካልኩ በኋላ፤ "ሃምሳ አለቃ፣ ለመጥፋት ፈልጌ አይደለም፡፡ እርስዎን ተጣርቼ ላገኝዎት ባለመቻሌና ዲያሪውን ስላልጨረስኩት አንብቤ ለመመለስ ይዤው ወጣሁ እንጂ ለመውሰድ ፈልጌ አይደለም" አልኩት፡፡ እንድከተለው በእጁ እያመለከተኝ እንደገና ተያይዘን ወደ ቢሮው አመራን፡፡ እንደገባን ወንበሩ ላይ ተለጥጦ ተቀመጠና ቁጭ በል እንኳን ሳይለኝ፤ "እንግዲህ ዲያሪውን መጨረስ ከፈለጉ ያለው አማራጭ እዚህ ግቢ እሥር ቤት ውስጥ አድረው ማንበብ ይችላሉ፡፡ በተረፈ ከዚህ ግቢ ዲያሪውን ይዘው መውጣት አይችሉም" አለኝ፡፡ እንደ ወንጀለኛ እስር ቤት ማደር እንደሌለብኝና ዲያሪውን እቤት አንብቤ እንደጨረስኩ እንደምመልስ ቃል ገብቼ እንዲፈቅድልኝ ተማፀንኩት፡፡ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ያህል ምን እንደሚያደርግ እንደተቸገረ ሰው በዝምታ ሲመለከተኝ ከቆየ በኋላ ዲያሪውን ተቀበለኝና፤ "መጣሁ ይጠብቁኝ" ብሎኝ ወጣ፡፡ ይኸ የማይጨበጥ ሰውዬ አሁን ደግሞ ምን ሊያደርግ ነው እያልኩ በስጋት ስጠብቅ አንድ ሌላ መጽሐፍ ይዞ ተመለሰና ምንም ሳያናግረኝ ወረቀት አውጥቶ መጻፍ ጀመረ፡፡ እንደጨረሰም፧ "አቶ አማረ ይህ የዲያሪው ፎቶ ኮፒ ነው፡፡ ዋናውን ዲያሪ ወስደው እንዲያነቡት ልንሰጥዎ አንችልም፡፡ ይህንን ግን ወደ ቤትዎ ወስደው እንደጨረሱ _ አምጥተው መመለስ ይችላሉ፡፡ ለማንኛውም እዚህ ላይ ይፈርሙ" አለኝ፡፡ እንድፈርምበት የተሠጠኝ ጽሑፍ የሚያትተው፤ የአልማዝን ዲያሪ ላነብ መውሰዴንና ባለበት ሁኔታ ለመመለስ መስማማቴን፣ እንዲሁም አንድ ገፅ ባጎድል፣ ብደልዝና ዲያሪውን በወቅቱ ባልመልስ በሕግ ልጠየቅ ወድጄ መፈረሜን የሚገልፅ ስለነበር ምንም ተጨማሪ ጥያቄ መጠየቅ ሳያስፈልገኝ ፈርሜ መለስኩለት፡፡ ሃምሳ አለቃው ወረቀቱን ተቀብሎ መሳቢያ ውስጥ ከተተና ከመቀመጫው ተነስቶ፣ የቀኝ እጁን መዳፍ ደረቱ ላይ ለጥፎ፣ ከአንገቱ ጎንበስ በማለት፤

"መልካም ንባብ እንዲሆንልዎ እመኛለሁ" አለኝ በፌዝ መልክ። ለፌዙ ቁብ ሳልሰጥ፣ “አመሰግናለሁ ሃምሳ አለቃ" በማለት ቶሎ ቶሎ እየተራመድኩ ከቢሮው ወጣሁ:: ጥበቃው ተመለስ እንዳይለኝ ብሰጋም፣ በዝምታ አሳለፈኝ: እኔ ግን ከመፍራቴ የተነሳ ወደ ኋላ ዞር ብዬ እንኳ ማየት አልደፈርኩም:: ታክሲ ውስጥ ገብቼ ወደ ቤቴ ስጓዝ፤ "ከዚህ በኋላ መቼም ቢሆን ሃምላ አለቃው አያገኘኝም" በማለት ተፅናናሁ:: ግን ደግሞ ዲያሪው የአልማዝን የመጨረሻ ሁኔታ የማያሳውቀኝ ከሆነ የግዴታ ቀሪውን ታሪክ ለማወቅ ተመልሼ መምጣት እንዳለብኝ ሳሰብ ተመልሶ ፍርሀት ወረረኝ:: ቤቴን እንደቆለፍኩት አገኘሁት:: ሠራተኛዬም ዘመዶችዋን ለመጠየቅ እንደሄደች አልተመለሰችም:: በሩን ከፍቼ እየተጣደፍኩ ወደ አልጋዬ አመራሁ:: ልብሴን እንኳን ለማውለቅ አቅም በማጣቴ ጫማዬን ብቻ አውልቁ አልጋው ላይ ዘፍ አልኩ፡፡ ድካም ይኑርብኝ እንጂ እንቅልፌ ግን ወዲያው አልመጣም፡፡ እንቆቅልሹን መፍታት ስላልቻልኩ እንዴት እንዲህ ሊሆን ቻለ? አልማዝ እየዋሸች ነው ወይስ እውነት ነው የምታወራው? ወይስ እሷ ከሞተች በኋላ ዲያሪውን ያ እርኩስ ዶ/ር አግኝቶት ሆን ብሎ ያልሆነ ነገር ጽፎበት ይሆን? እያልኩ ራሴን ደጋግሜ ስጠይቅና መልሼ ለራሴ የማያሳምን መላ ምት ሳስቀምጥ እኩለ ሌሊት ሆነ፡፡ በመሀሉ እንቅልፍ ይዞኝ ጭልጥ አለ። “ታዲያ አልሚና እንደነገርኩሽ አባቴን በጣም እወደው ነበር፡፡ እሱም እኔን ከልጆቹ ሁሉ አብልጦ እኔን ይወደኝ ነበር፡፡ አባቴ እንደእኔ ጨዋ አልነበረም፣ ማለቴ መጠጥ ነፍሱ ነበር። ሳይጠጣ መግባትን እኔ እስከማውቅ ድረስ ሞክሮት አያውቅም:: ግን የሚገርመው ነገር፣ ሰክሮ ቢገባም ይበልጥ ቤተስቡን የሚያጫውትና የሚያዝናና እንጂ እንደተለመዱት ሰካራሞች አይጨቃጨቅም :: ይልቁንም የሚጠጣበት አጥቶ ቤት የዋለ ዕለት ጭቅጭቁ የሚቻል አልነበረም:: በዘመኑ አራዶች ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ስለነበር ሞቅ ባለው ቁጥር ቯልስ እንደንስ እያለ እናቴን ያስጨንቃት ነበር፡፡ እሷ ደግሞ ገራገርና ምንም የማታውቅ ስለነበረች ከአጠገቧ እንዲሄድላት መጨቅጨቅ እንጂ ሞክራው አታውቅም:: እርግጥ ሠርግ ሠፈር ውስጥ ሲኖር የሠፈሩ ድግሥ አድማቂ ነበረች:: እስክስታ ስትወርድ የተቀመጠው ሁሉ ነሽጦት እንዲነሳ ታደርግ ነበር። ታዲያ አባቴ ቯልስ የሚያዳንሰው ሲያጣ ትንሹን
👍354
ወንድሜን አልያም ወንበር ይዞ እግሩን በቯልስ አደናነስ ወዲህና ወዲያ እያወራጨ በመደነስ ያዝናናን ነበር:: ከሁሉም የማይረሳኝ ግን አባቴ የሰከረ ቀን በጣም ደግ ይሆናል:: እኔ ካለሁ ችግር የለም ባይ ይሆናል:: የደብተር መግዢያ፣ የጤፍ መግዢያ፣ የእድር መዋጮ ወዘተ የሚጠየቀው በዚህ ወቅት ነው:: ካልጠጣማ ያበደ ወይም ለመሰደብ የፈለገ ካልሆነ በስተቀር ገንዘብ የሚጠይቅ የለም:: ገንዘብ ከተጠየቀም፣ “አንቺ ሴትዮ አሁንስ አላበዛሽውም እንዴ! ገንዘብ የማርስ እኮ አደረግሽኝ! ባለፈው የገዛሁትን ከምኔው ጨርሰሽ ነው አሁን ደግሞ ገንዘብ አምጣ የምትዪኝ? እኔ እንደሆን ቤሳ ቤስቲን የለኝም! እንደምታደርጊው አድርጊ" ማለቱ የተለመደ ነው፡፡ ግን ያው ተጨቃጭቆም ቢሆንም መጨረሻ ላይ ግን መስጠቱ አይቀርም፡፡ ደግነቱ ሁሌ ስለሚስክር ችግር የለም:: ማታ ያለጭቅጭቅ "እኔ እያለሁ ባለቤቴና ልጆቼማ አይቸግራችሁም" እያለ ገንዘብ ሲያድለን ያመሽና ጠዋት ሲነሳ ገንዘቡን ቆጥሮ መጉደሉን ከተጠራጠረና እኛም አቅብጦን ገንዘብ ማታ እንደሰጠን ከነገርነው ሁሌ የማትረሳኝ ቃሉ፤ “እናንተ ሰዎች፤ እኔ ስሰክር ገንዘብ አትጠይቁኝ አላልኩም!" የሚለው ነበር። ያም ሆነ ይህ ሳይሰክር ጠይቆ ከመስደብ የተሻለው አማራጭ ያኛው በመሆኑ እኛም መጠየቃችንን አይቀርም፣ እሱም ያቺኑ ቃል መናገሩን አይተውም፡፡ ታዲያ አልሚና አባቴ ጥቁር መሆናችንን አይቀበልም ነበር። ጥቁር የሚባል ነገር አይወድም:: ጥቁር ስልሽ ከሱ በመጠነ- ጠቆር ያለውን ማለቴ ነው፡፡ በእርሱ አስተሳሰብ ጥቁር ሰው አይሆነውም፡፡ ለሱ ጥቁር በግ ወይም ዶሮ ገደቢስ ነው፡፡ ምን አለፋሽ ከለበሰው ሱፍ በስተቀር ጥቁር የተባለ ነገር አይስማማውም:: አንዴ ትዝ የሚለኝ የስፖርት አስተማሪያችን ዴስክ ሰብረሃል ብለው ከተቀመጥነው ልጆች መሃል እኔን ወላጅ አምጣ ብለው አባረሩኝ፡፡ አባቴ አስተማሪው ጥቁር መሆኑን እንዳየ ሊያናግረው አልፈለገም፡፡ እንደመመለስ ሲል፤ “ምነው አባዬ አናገራቸው እንጂ” አልኩት፤ “አይ! እኔ ጥቁር ሰው አይሆነኝም፣ በኋላ አናደውኝ መጥፎ ነገር ከምናገር ዝም ብዬ ክፈል የሚሉኝን ብከፍል ይሻላል ብሎ ሊመለስ ሲል እኔ እንደምንም አግባብቼ ጥሩ ሰው ስለሆኑ እንደማያስከፍሉኝ ነገሬ ሳይወድ

በግድ መለስኩት:: አስተላለቡ ባጋጣሚ ተሳካና እንዳለውም ሰውዬው ምንም ያሀል ቢለመኑ ፍንክች የሚሉ ስላልነበሩ እየተናደደ ክፈል የተባለውን ከፍሎ ተገላገለ፡፡ ታዲያ ሁል ጊዜ እኔም ጥቁር ሴት እንዳላጋባና ጥቁር ጓደኛ እንዳይኖረኝ ይመክረኝ ነበር:: ለምን ቢባል ለሱ ገዱ አይደሉምና፡፡ ለእኔ ግን ነገሩ ከማሳቅ አልፎ ደንታም አይሰጠኝም ነበር፡፡ አንቺ ደግሞ የቀይ ዳማ እንጂ ጥቁር አይደለሽም:: ነገር ግን ያደረግሽኝን ሳስታውስ ድንገት የአባቲ አስተሳሰብ ትዝ ይለኝና የቀይ ዳማም ከጥቁር ይመደብ ይሆን እንዴ እላለሁ? ሳምንሽ ስለከዳሽኝና ይህም በደል ሳያንስ አንቺው ጥፋተኛ ሆነሽ እኔን እንደበደለኛ መቁጠርሽ አናዶኛል:: ግን ለምን? አንቺ በእኔ ብቻ ህያውነት እንደሚሰማሽ፣ አለ እኔ ግን የሰውነት ሳይሆን ተጥሎ የተገኘ ዕቃ ያህል ራስሽን እንደምትቆጥሪ ደግመሽ ደጋግመሽ ነግረሽኝ ነበር፡፡ ዛሬ ግን ምን ተገኘና ከእኔ ተለይተሽ ህያው ሆነሽ መቆየት ቻልሽ? ለጊዜውስ ቢሆን እንዴት እኔን በትምህርት ለውጥሽኝ? አብረን ሆነንስ መማር አትችይም ነበር?" “አማረ ይቅርታ አድርግልኝ፤ ያለፈውን እርሳው:: አንተን ውድ ፍቅሬን እኔ በምንም አልለውጥህም፡፡ እንካ ሁለት እጆቼን ያዛቸው፣ ና ጠጋ በልና እቀፈኝ፣ አዎ እንደሱ፣ በል እንደድሮ ሳመኝ፣ ምጊዜም ቢሆን እወድሃልሁ፣ አሁንም ቢሆን እኔ ያለአንተ በድን፣ ግዑዝ አካል ነኝ" ልቤ አልጨከነም፤ ያለፈውን በደሏን ሁሉ እረስቼ እቅፍ አድርጌ ልስማት ስገላበጥ ከአልጋው ላይ ተንሸራትቼ በመውረዴ ደንግጬ ከእንቅልፌ ባንኜ ተነሳሁ:: ከእንቅልፌ እንደነቃሁ ያየሁት ህልም እንጂ በውን የሆነ ነገር አለመሆኑን ስረዳ ተደሰትኩ፡፡ ግን ምን ያደርጋል? በአካል ርቄያታለሁ ብዬ ባስብም ልርቃት አለመሌቻሌን ሳስብ ደግሞ አዘንኩ:: በቀን ልርቃት ብሞክርም እሷ ግን ሌሊት አድብታ መምጣቷን አልተወችም:: እኔስ ብሆን ፎቶዋ ራስጌዬ ተቀምጦ እንዴት ልረሳት እችላለሁ? ከመቅጽበት ተነሰቼ ፎቶዋን እነሳሁና መሬት ላይ ከሰከስኩት:: መስታወቱ ወለሉ ላይ እንደጠጠር ደቀቀ፡፡ አልማዝ ግን አሁንም በጀርባዋ ወለሉ ላይ ተንጋልላ ትስቅብኛለች:: መጨከን ስላልቻልኩ ፎቶዋን አንስቼ ሁለተኛ እንዳላያት በማለት ኮመዲኖ ውስጥ ቆለፍኩበት:: የተሻለው አማራጭ ግን መቅደድ ወይም ማቃጠል ነበር፡፡ ለዚህ ደግሞ የሚሆን ጭካኔም ሆነ ወኔ አልነበረኝም:: ያም ሆነ ይህ ያን ጭንቅላቴ ውስጥ ተቀርፆ ማታ ማታ

እየታየ የሚረብሸኝን ፎቶዋን ካራቅሁት ከአሁን በኋላ ሰላም አገኛለሁ ብዬ ተፅናናሁ፡፡ ይሁን እንጂ እንቅልፍ የሚባል ነገር የማይታሰብ እየሆነ መጣ፡ ሸለብ ባደረገኝ ቁጥር የማያት አልማዝ ብቻ ሆነች:: ቤቱም፣ ጭንቅላቴም በሷ ምስል ተሞላ፡፡ ከዚህ ሲዖል እንዴት እንደምወጣ ግን አላውቅም:: አሁንም እንደ አካሌ ጥላ እየተከተለች አዕምሮዬን ትበጠብጠዋለች። በለመደችው ቀላማጅ አፏ ዛሬም ትቀላምዳለች:: አልማዝ እንደሆን ብሸሻትም የምትለቀኝ አልሆነችም:: "እየተከተለ የሚያጠቃ ባለጋራ ሲሸሹለት ሳይሆን መልሰው ሲያጠቁት ነው ጋብ የሚለው" እንደተባለው ከእሷ ከመሸሸ ይልቅ መጋፈጥን መረጥኩ፡፡ ዲያሪውንም አንስቼ ማንበብ ሳይሆን ከእሷ ጋር መጫወት ጀመርኩ:: "ከእንቅልፌ ስነቃ በሰው እጅ ታቅፌ በሰው ደረት ላይ መተኛቴን አወቅሁ፡፡ ግን ዶ/ር አድማሱ ደረት ላይ መተኛቴን ያወቅሁት ብዙ ሰዓት አስቤ ህሊናዬ መለስ ሲልልኝ ነው:: ተስፈንጥሬ ልነሳም ፈለግሁ፡፡ ግን በምን አቅሜ ልነሳ፣ መላ ሰውነቴ ዝሏል፡፡ እሱም መንቃቴን እንዳወቀ ፀጉሬን በእጆቹ እያሻሸ፤ “አልሚ! አይዞሽ እንደ ቤትሽ ይሰማሽ፣ አትፍሪ፡፡ ከእኔ ጋር ከሆንሽ ምንም አይደርስብሽም፡፡ ደግሞም ስለምወድሽ ምንም እንዲያጋጥምሽ አልሻም፡፡ ለብዙ ጊዜ ስሜቴን ተቆጣጥሬዋለሁ፡፡ ለብዙ ጊዜ ራሴን እንደአስተማሪ አንቺን እንደ ተማሪ ለማየት ሞክሬአለሁ፡፡ ዛሬ ግን ትምህርትሽን ለመጨረስ ትንሽ ቀርቶሻል፡፡ እኔ ከእንግዲህ የምጠላውን ያን የአንቺ አስተማሪ መሆንን ብቻ ሳይሆን አስተማሪ እንደነበርኩ ማሰብንም አልሻም፡፡ እስቲ አስቢው! እጅግ የምታፈቅሪያትን ተማሪ እያስተማርሽ ነገር ግን እንደምትወጂያት ለመንገር ሥርዓቱ እንደማይፈቅድልሽ በመረዳት ስሜትሽን አፍነሽ የምትወጂያት አበባ ስትጠወልግ፣ የምታፈቅሪያት ብርሀን የተሳሳተ መንገድ ተከትላ ጨለማውን ከማጥፋት ይልቅ በጭለማ ተውጣ ስትጠፋ ማየት፡፡ እጅግ የምታምር ውብ ቢራቢሮሽ በተሳሳተ መንገድ ሄዳ እሳት ውስጥ ገብታ ስትቃጠል ማየት አያሳዝንም:: ይህንን በዝምታ ለማየት የሚያስችል ልብ የለኝም፡፡ ከአሁን በኋላም ስሜቴን አፍኜ እንድቀመጥ የሚያስገድደኝ ሕግ ሊኖር አይችልም:: ብርሀኔ ስትጠፋ፣ አበባዬ ስትጠወልግና ቢራቢሮዬ ስትቃጠዪ ማየት አልሻም:: እኔ ከማንም በላይ ለአንቺ የተፈጠርኩ መሆኔንም እንድታውቂ እፈልጋለሁ፡፡ ሁሌም ለዘላለምም ከአንቺ ጋር መሆንን እሻለሁ፡፡ እጅግ በጣም እወድሻለሁ፡፡" ብሎ ጉንጬን ሳመ::
👍303🔥2
ነገሩ ግራ ቢያጋባኝም የቀረኝ አንድ ተስፋና አለኝታዬ እሱ ብቻ በመሆኑና ሌላ አማራጭ ስላልነበረኝ እሱንም ማስቀየም ስላልነበረብኝ ምንም ሳልናገር ደረቱ ላይ ልጥፍ ብዬ ተኛሁ:: እንባዬ ግን ማቆሚያ አልነበረውም:: ደረቱን በእምባዬ አጠብኩት:: እሱም ፀጉሬን እያሻሽና ጉንጬን እየሳመ ያባብለኝ ጀመር።" ዲያሪውን መቀጠል አልቻልኩም:: ድርጊቱ አሁን የተፈፀመ መሰለኝ:: ለካስ ያ እርኩስ ላስጠናሽ የሚለውና የእኔን ስም የሚያራክሰው ለጤናው አልነበረም:: አንዴቴ የተነሳ አጠገቤ የለም እንጂ አግኝቼው ቢሆንና አንቂ ብገድለው ደስተኛ ነበርኩ:: ግን ጊዜውን ሳየውና ከሶስት ዓመት በፊት የተፈፀመ ድርጊት መሆኑን ስረዳ መናደዴ ቂልነት መሆኑን በመረዳቴ ላለመናደድ ጣርኩ፣ ውስጤ ግን መብከንከኑን ሊያቆም አልቻለም፡፡ በጣም የገረመኝና ያናደደኝ ግን አልማዝ ለምን ዲያሪዋ በሙሉ በውሸት የተሟላ እንዲሆን መፈለጓን አለማወቄ ነው፡፡ ዲያሪ ማለት ሰው ካለፈ በኋላ ታሪኩን ለትውልድ የሚያስተላልፍበት ሰነድ ሆኖ ሳለ የእሷ እውነትን ሳይሆን ውሸትን አውርሶ መሄድ ጠቀሜታው ሊገባኝ አልቻለም:: ነገር ግን አልማዝ ፅፋ ለትውልድ የምታስተላልፈውና ለወዳጅ ዘመድ የምታወርሰው እንደ አርአያ የሚቆጠር ጥሩ ታሪክ ስለሌላት፣ እሷ ከዳተኛ ሆና እንደተከዳች አድርጋ መዋሸቷ የሚገርም ላይሆን ይችላል፡፡ እኔ ግን የእሷን የውሸት ታሪክ እያነበብኩ ጭንቅላቴ የሚፈነዳበት ምክንያት አልነበረምና ዲያሪውን ጠረጴዛ ላይ ወርውሬው ወደ አልጋዬ አመራሁ:: ግን ትንሽ ሄድ እንዳልኩ አንድ ነገር ከነከነኝ:: አልማዝ ጠላቴ ደረት ላይ ተኝታ መጨረሻው ምን እንደሆነ ሳላውቅ መሄዴ ማንበቤን ቀጠልኩ፡ አላስችል ስላለኝ ተመልሼ “ሌሊቱን ያሳለፍኩት ከአድማሱ ጋር ነበር፡፡ ሰውነቴ ለፍቅራዊ ግንኙነት ዝግጁ ስላልነበር በሰላም ሳልረበሽ መተኛት ነበር የፈለኩት፡፡ እሱም ይህንን አልነፈገኝም:: ጉንጬን እየደጋገመ ከመሳም፣ ፀጉሬን ከማሻሸትና እምባዬን ከመጠራረግ ውጪ ምንም አላስቸገረኝም ነበር። ባልሰማውም እንደሚያፈቅረኝና እንደሚወደኝ እየደጋገመ ይነግረኝ ነበር። ንግግሩ ውስጤ ዘልቆ ባይገባም አንድ የሚወደኝ ሰው በማግኘቴ ቀለል እያለኝ መጥቷል፡፡ አሁን የሆነውን ልረሳው ባልችልም ቢያንስ መሞት አልፈልግም፡፡ ከእናትና አባቴ ውጪ እንድ የሚያስብልኝና የአማረን ቦታ ባይተካም ማፅናኛ ሊሆን የሚችል ሰው ያገኘሁ መስሎም ተሰማኝ፡፡ ግን የማፈቅረው መስሎ አልታይሽ አለኝ፡፡ ግፋ ቢል ከብቸኝነት ለመሸሸጊያ እጠቀምበት ይሆናል እንጂ እኔማ ለተቃራኒ ፆታ ያለኝ ፍቅር ከአማረ ጋር

አብሮ በንኗል:: ከእንግዲህ ሰው እወድ ይሆናል እንጂ እንደማላፈቅር ግን እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ንዴቴ ከቁጥጥር ውጪ በመሆኑ ዲያሪውን ወረወርኩት፡፡ ግን ጨክኜ አልጨከንኩም ትንሽ ቆይቼ አነሳሁት:: በዓለም ላይ ማንኛውም ሰው ሊሸከመው ከሚችለው በላይ በደል ያደረሰችብኝ ሴት ዛሬ ከእኔ ውጪ ፍቅር ላሳር እንደሆነ ልትነግረኝ ትሞክራለች:: ምናልባት ይህንን ጽሑፍ እኔ ብጽፈው እውነት ይሆን ነበር። ፍቅር ለእኔ ከአልማዝ ጋር አክትሟል:: ለእኔ የተፈጠረች፣ እንደ አምላክ የማመልካት ሴት ዛሬ የለችም:: የማያቸው ሁሉ አርቴፊሻል የሆኑ አሻንጉሊት ሴቶች ናቸው:: ስለሆነም ከእንደዚህ ዓይነት ሴቶች ጋር መቼም ቢሆን ፍቅር ሊይዘኝ አይችልም፡፡ ከእንግዲህ ወዲያ ከአልማዝ ጋር የነበረኝን የፍቅር ዓይነት የሚተካ ፍቅር የሚይዘኝ አይመስለኝም፡፡ ይልቁንም ለሴት ያለኝን ጥላቻ ይበልጥ እያዳበርኩ በመምጣቴ እኔን የሚያዝናናኝ ሥራዬ ብቻ ሆኗል፡፡ ከሴት በመራቄ፣ ጊዜዬን ለንባብና ለጽሑፍ በማዋሌና በመጽሔቶች ላይ የተለያዩ ጽሑፎችን በማቅረብ ታዋቂ እየሆንኩ መጥቼያለሁ:: ታዲያ ጽሑፎቼ ሳላስበው ለሴት ያለኝን ጥላቻ የሚያንፀባርቁ በመሆናቸው በሴቶች ዘንድ እምብዛም የተወደዱ አልነበሩም:: አንዳንድ ስለ ሴት ልጅ ጥላቻ ያለኝ ትምክህተኛ መሆኔን እየጠቀሱ ጽሑፌን የሚተቹ አሉ፡፡ ፍቅር ይዞት የማያውቅ፣ ፍቅር የማይገባው፣ በጽሑፉ ጥሩ ነገርን ከመግለፅ ይልቅ ሴትን ለማጣጣል የሚጠቀም በማለት የሰው ሳይሆን የአውሬ መንፈስ የተጠናወተኝ ዓይነት አድርገው የሚያቀርቡኝም ነበሩ፡፡ ያም ሆነ ይህ እኔ ግን አልፈርድባቸውም:: አልገባውቸውም እንጂ እኔ ስለፍቅር ከማንም በላይ ጠንቅቄ የማውቅ ነበርኩ:: የኔ ሕይወት ታሪክ በፍቅር ገመድ ተተብትቦ በመጨረሻ እኔንም ጠልፎና ሽባ አድርጎ ከትምህርት ቤት አባሮኛል፡፡ በትምህርቴ ከአንደኛ በታች ወጥቼ የማላውቀውን ልጅ እንደሰነፍ ተማሪ ግቢውን በሀፍረት ለቅቄ እንድወጣ አድርጎኛል:: ሌላው ቀርቶ ዛሬም ጥላ ሆኖ እየተከተለኝና እንቅልፍ እየነሳ አእምሮዬን ሊያስተኝ ደርሷል:: ታዲያ ፍቅርን ብሸሽ እንዴት በእኔ ይፈረዳል? ፍቅርንና ከዳተኛ ሴትን ብጠላና ስለ ከዳተኛ ፍቅረኛና ሴት ብተርክ፣ ብጽፍና ባብጠለጥል ለምን የማይሆን ስያሜ እየተለጠፈብኝ እወቀሳለሁ?፡፡ በመሀሉ የቤቴ በር ተንኳኳ፡፡ ከገባሁበት የሐሳብ ባህር ደንግጬ ወጣሁ:: በሌሊት የመጣው ማነው በማለት ሰዓቴን ተመለከትኩ፡፡ ከንጋቱ አስራ ሁለት ስዓት ሆኗል። ለካስ ሌሊቱን በሙሉ አንዴ ሳነብ ሌላ ጊዜ በሐሳብ ባህር ውስጥ ሰጥሜ ሳሰላስል ሳይታወቀኝ ነግቶ ኖሯል::

ያ ሃምሳ አለቃ እንዳይሆን እየተመኘሁ ከአልጋዬ ላይ ተነስቼ በሩን ለመክፈት እግሬን ለማነሳት ስሞክር አልቻልኩም፡፡ ሰውነቱ ሁሉ ሽባ ሆኗል:: እንደምንም እየተንገዳገድኩ በሩን ከፈትኩ:: አለሚቱ ነበረች:: ዛሬ ደግሞ ብላ ብላ እያደረች መምጣት ጀመረች? እንደገባች ፊቴን ትኩር ብላ አየችኝና፣ “ምነው ጋሼ! ደህና አይደሉም እንዴ? ፊትዎት ሁሉ አብጧል:: እንቅልፍ የወሰደዎት አይመስልም:: መቼም አንቺ ውጪ በማደርሽ ተናድጄ አልተኛሁም እንዳይሉኝ' አለችኝ :: በቁጣ፤ “እኔስ ደህና ነኝ፣ ይልቁንስ ደህና ያልሆንሺው አንቺ ነሽ፡፡ ለመሆኑ የት ሄደሽ ነው?'' ብዬ አምባረቅኩባት :: “ጋሼ፣ ሳልነግርዎት በማደሬ ይቅርታ አድርጉልኝ፡፡ ከልጅነቴ ጀምሮ ያሳደጉኝ ጎረቤታችን የነበሩ አንድ ደግ አሮጊት ነበሩ። ዘመዶቼ መታመማቸውን ነግረውኝ ብሄድ እጁ ላይ ግጥም አሉ፡፡ እኔም ጥዬ መምጣት ስለማልችል ያው ትላንት ቀብር ውዬና ከዛ መልስ አሰተዳድሬ መምጣቴ ነው:: መቼም ጥዬ ከመምጣት እርሶ ቢቆጡኝ ይሻላል ብዬ ነው" ብላ ወደ ጓዳ ገባች። የሚበላ ነገር ከቀመስኩ ቆይቼ ስለነበርና ረሀቡም ስለጠናብኝ በመምጣትዋ ደስ ብሎኛል:: በዚህ ላይ ደግሞ ሠራተኛዬም ብቻ ባለመሆኗ እንዲህ ስረበሽ የሷ መኖር አስፈላጊዬ ነው:: ግን ሳያት ለምን ያን ያህል እንደተናደድኩ አልገባኝም፡፡ መቼም ቅናት መሆን የለበትም፡፡ አለሚቱ በእኔ ንዴት ብዙም ሳትጨነቅ እንቁላል ጠብሳ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠችልኝ፡፡ በጣም ከመራቤ የተነሳ ከምኔው እንደጨረስኩት እንኳን ትዝ አይለኝም፡፡ ያቀረበችልኝንም ወተት ጠጥቼ ወደ አልጋዬ አመራሁ:: ከድካም የተነሳ ሰውነቴ ዝሏል:: ከዚህ በኋላ አንዲት ገፅ እንኳን ማንበብ እንደማልችል እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ አለሚቱ ልብሴን እያወላለቀች፤ “ምነው ጋሼ ዛሬ ልክ አይደሉም፡፡ እደጅ አድሬ ነው ብቻ እንዳይሉኝ:: እኔ እንደሁ ደግሜ ደጋምሜ መክሬዎታለሁ፡፡ ኋላ አንድ ቀን ማጅራት መቺ እዛው እንዳያስቀሮት:: በኋላ አለሚቱ የነገረችኝን ብሰማ ምን ነበር? ብለው ቢፀፀቱ ዋጋ የለውም፡፡ ሚካኤልን ነግሬወታለሁ ኋላ!" እያለች ልብሴን አወላልቃ አንሶላና ብርድልብስ አልብሳኝ ልትወጣ ስትል እጇን ያዝ አድርጌ አብራኝ እንድትተኛ ነገርኳት፡፡ አብዛኛውን ጊዜ አብራኝ የምትተኛው ሌሊት ስክሬ ስገባ ስለነበርና የዛሬው
👍234
ግን ያልተለመደ ነገር ስለሆነባት፤

ዛሬ ደግሞ በቀኑ ነው ያማሮት፡፡ ኧረ ሰው ቢመጣ ምን ይላል? እያለችና እንደመግደርደርም እየቃጣት ልብሷን አወላልቃ አቅፋኝ ተኛች:: እኔ የፈለኩት ሙቀቷን እና ከጭንቀት እንድታወጣኝ ብቻ ስለነበር፣ ሰውነቷና አጎጠጎጤ ጡቷ ገላዬን ቢነኩትና በእጆቿ ብትደባብሰኝም አንዳችም የመነሳሳት ስሜት አልተፈጠረብኝም። በሥጋም ሆነ በመንፈስ ለፍቅር የተዘጋጀሁ አልነበርኩምና አለሚቱ የምትጠብቀውን ላደርገው አልቻልኩም:: አለሚቱ በመዳበስና በመሳም አልሳካ ሲላት፣ ስሜቴ እንደቀዘቀዘ ማረጋገጥ በመቻሏ ተስፋ ቆርጣ ደረቷ ላይ አስተኝታ እንደልጅ ፀጉሬን ትደባብስ ጀመር፡፡ በመሀሉ ሳላስበው እንቅልፍ ይዞኝ ጭልጥ አለ:: ከእንቅልፌ ስነቃ አለሚቱ አጠገቤ አልነበረችም:: እኔ የምፈልገው ከሐሳብ ባህር ወጥቼ እንቅልፍ እንዲወሰድኝ ነበርና የፈለኩትን አግኝቼአለሁ፡፡ እሷ ግን የምትፈልገውን ስላላገኘች እንዳበሳጨኋት እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ከአልጋዬ ወርጄ ልብሴን መለባበስ እንደጀመርኩ አለሚቱ ምሳ ሰርታ ትጠብቀኝ ኖሮ የፊት ውሀ ይዛ መጥታ፤ “ጋሼ ምነው ዛሬስ በቀኑ ተኝተው ቀሩ። ምሳ እንዲበሉ ብቀሰቅሶት እንኳን አልሰሙኝም፣ ደህና አይደሉም እንዴ?" እያለች መልስ በዓይኔ የምሰጣት ይመስል ዓይን ዓይኔን ማየት ጀመረች፡፡ እኔም ሌላ ጫን ያለ ጥያቄ እንዳይከተል በማለት፤ “ደህና ነኝ” ብዬ አጠር ያለ መልስ ሰጠኋትና ወደ ጠረጴዛው አመራሁ:: እሷ ግን የምትለቀኝ አልነበረችም፣ “አይ ጋሼ ደብቀውኝ ነው እንጂ አንድ ያጋጠሞት ነገር እማ አለ፣ ቅዝቅዝ ብለዋል፣ ነው ወይስ በእኔ ማደር ተቀይመው ነው?” ብላ ፍትር አድርጋ ያዘችኝ:: የተቀየምኩ ቢመስላትም አልፈርድባትም፡፡ ምክንያቱም የምትፈልገውን ፍቅር ባልተለመደ መልኩ ነፍጌያታለሁና:: ስለዚህ ያልተቀየምኩ መሆኔን የሚያሳምን ምክንያት መፍጠር ነበረብኝ፡፡ “ደህና ነኝ፤ ትንሽ አመም አድርጎኝ ነው" አልኳት :: ምክንያቴ ባያረካትም ከዚህ በላይ የመከራከር መብት ስለሌላት በሰጣኋት መልስ ባትረካም ምሳ ለማምጣት ሄደች:: ከምሳ በኋላ ቀሪውን ታሪክ ለማንበብ ተጨማሪ ጉልበት ያለኝ መስሎ ስለተሰማኝ የመኝታ ቤቴን በር ቆልፌ ንባቤን ተያያዝኩት፡፡ የቆምኩበትን ቦታ ለማስታወስ ጊዜ አልፈጀብኝም፡፡ ያ እርኩስ ያቺን የምወዳትንና የማፈቅራትን አበባዬን እንዳትቀጠፍ የሚከላከል መስሎ

ለመቀንጠስ እጁን ሲያሾል ነበር ያቆምኩት:: ንባቤም ቀጠልኩ፡፡ የኔዋ ቀባጣሪም መቀባጠሯን ቀጠለች፤

ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍39🤔1
አትሮኖስ pinned «#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_አራት ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ ================ ኩማንደር ሆስፒታል በረንዳ ላይ ከወዲህ ወዲያ ሲንገዋለል አንዴ እናቷን እቴቴን ሲያፅናና..ቆይቶ ደግሞ ያለመደበትን ፀሎት ለመፀለይ ሲሞክር…ሰለሰሎሜ መጥፎም ሆነ ጥሩ ዜና ሳይሰማ ነጋ፡፡አንድ ሰዓት ነበር ከዶክተሩ አሰቃቂውን መርዶ የሰማው…፡፡‹‹ሰሎሜ የደም ካንሰር በሽተኛ ነች፡፡ለጊዜው ኬሞትራፒ…»
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሰላሳ_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
===================

የሰሎሜ ህክምናው በሰላም ተጠናቆ ወደ ቤት ተመልሳለች፡፡እናትዬው ብቻ ሳትሆን ሁሴን እና አለማየሁም ከስሯ ሳይለዩ  ልክ ልጅ ሆነው ታማ ሆስፒታል በገባች ጊዜ እንዳደረጉት በትኩረትና በሙሉ ጥረት ሲንከባበከቦት ነበር የከረሙት፡፡በዛ ምክንያት የማገገም ፍጥነቷ ተአምር የሚባል ነበር፡፡

አሁን ሁለቱ ጓደኛሞች አለማየሁ እና ሁሴን በዛሬው ቀን ከውጭ የሚመጣውን ጓደኛቸውን ሊቀበሉ ቦሌ ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡አላዛር ሰሎሜ ለመቅኔ ንቅለ ተከላ የሚያደርስ ህመም ታማ እንደነበረ አልሰማም፡፡ ኬሞትራፒ እክምና  ላይ እያለች ይሁን ከዛ ወጥታ ኮማ ውስጥ ገብታ ሳለ በስልክ እንድታናግረው በሚጠይቅበት ጊዜ ኃይለኛ ጉንፋን ይዟት ድምፆ ተዘግቷል ብለው ሸውደውታል፡፡እንደዛ ያደረጉት የሄደበትን ጉዳይ ያለምንም እንቅፋት እንዲያጠናቅቅ ስለፈለጉ ነው፡፡ይሄ ውሳኔ የአለማየሁ ነው፡፡ሌሎቹንም ያሳመናቸው እሱ ነው፡፡
‹‹ተሳክቶለት የሚመጣ ይመስልሀል?››ሁሴን ነው ፈራ ተባ እያለ አለማየሁን የጠየቀው፡፡

‹‹ይመስለኛል..በስልክ ሳወራው እሱም ሙሉ በሙሉ እንደዳነ እርግጠኛ ነው››ሲል መለሰለት፡፡

‹‹ደስ ይላል ….እርግጠኛ ነኝ አሁን አንተም ሙሉ በሙሉ እንዲሳካለት ነው የምትፈልገው››በማለት የሚያስገርም ነገር ነገረው፡፡

‹‹ማለት ?››

‹‹ያው አሁን ወንድሟ መሆንህን አውቀሀል…ከትዳሯ መፍረስ ምንም ምታተርፈው ነገር የለም…እንደውም በተቃራኒው ታዝናለህ››
‹‹በፊትስ ቢሆን ምን አተርፍ ነበር?››

‹‹ባክህ ምን ያደባብቅሀል፡፡ እድሜ ልካችንን እኮ እርስ በርስ እንተዋወቃለን….ባይሳካለት ያንን ክፍተት ተጠቅመህ የሆነ ነገር ለማድረግ አሰፍስፈህ በመጠባበቅ ላይ ነበርክ….››ብሎ የሚያምንበትን ነገር ያለምንም ይኑኝታ ፍርጥ አድርጎ ተናገረ፡፡

አለማየሁም ያልገባው በመምሰል‹‹የሆነ ነገር ማለት?››ሲል ተጨማሪ ማብራሪያ ጠየቀው፡፡

‹‹ከአላዛር ልታፋታትና እራስህ ልታገባት…ተሳሳትኩ?ደግሞ ይሄንን አቋምህን ቀጥታ ለእሱም ነግረሀዋል…››

‹‹እሱ ነው እንደዛ ብሎ የነገረህ?››

‹‹ማን እንደነገረኝ ማወቁ ምን ያደርግልሀል..?ብቻ እንደዛ ለማድረግ እቅድ እንደነበረህ አውቃለው››

‹‹አሀ..አሁን አንተም እኔ ማድረግ አቅጄ እንደነበረው ለማድረግ እያሰብክ ነው ማለት ነው?››ሲል በገረሜታ ጠየቀው፡፡

‹‹መጀመሪያ ያንተን መልስልኝ››
‹‹አሁን እዚህ ጉዳይ ላይ ማውራት ምን ይረባል?››

‹‹በጣም ይረባል…አሁን አንተ ወንድሟ ስለሆንክ ስለእሷ ወደፊት መጨነቅና ማሰብህ የሚጠበቅብህ ሁኔታ ላይ  ነው ያለኸው…ከአላዘር  ጋር ካልተሳካላትና የሚፋቱ ከሆነ እኔን እንድታገባኝ ታግዘኛለህ…?.››

‹‹ይሄ ሁሉ ዙሪያ ጥምዝ ….ይሄን ለማለት ነው?››

‹‹አዎ…ታውቃለህ ልክ አንተ ታፈቅራት በነበረው መጠን አፈቅራታለው…እሷ ለሁላችንም የእድሜ ልክ ህልማችን ነች፡፡እሱ እድሉን ተጠቅሟል…ካልሆነለት  ቀጣይ የእኔ እድል ነው፡፡እኔ ደግሞ በምንም አይነት ተአምር እድሌን ማባከን አልፈልግም…ቀሪ ዘመኗን እንደሳቀች እንድትኖር ነው የማደርጋት፡፡››

አለማየሁ ምን ሊመልስለት እንደሚገባ መወሰን አልቻለም..ዝም ብሎ ትካዜ ውስጥ ገባ….ሁሴን እየተናገረው ያለው ነገር ደረቅና የሚያሳቅቅ አይነት ቢሆንም  ግን ደግሞ እሱም ወንድሟ መሆኑን ከማወቁ በፊት ለማድረግ ሲያስብ እና ሲመኘው የነበረ ነገር ነው አሁን እሱ እያወራ ያለው፡፡እሱ ሲያደርገው ትክክል ሌላ ሲያደርገው ደግሞ አፀያፊ የሚሆንበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ደግሞም ለእሱም ቢሆን  የአላዛር ህክምና የማይሳካለት  ከሆነ እህቱ ከዚህ በላይ ከእሱ ጋር እየተሰቃየችና እየተሳቀቀች እንድትቀጥል አይፈቅድም…ከአላዛር ከተለያየች ደግሞ ከሁሴን የተሻለ ሰው ታገኛለች ቡሎ አያስብም…ወደደም ጠላም በእሱ ሀሳብ ተስማምቶ ሊረዳው ግድ ነው፡፡

‹‹ጥሩ …ባልከው ነገር እስማማለሁ..፡፡በመጀመሪያ ግን የአላዛር ውጤት በግልፅ ከመታወቁ በፊት ምንም አይነት እንቅስቃሴ አታደርግም፡፡እሱ በግማሽ እንኳን ለውጥ አሳይቶ ከመጣ ሙሉ በሙሉ እንዲያገግም እንረዳዋለን እንጂ  ተስፋውን ለማጨለም ምንም አይነት አሻጥር አንሰራም፡፡››

‹‹እስማማለሁ…ሰሎሜን አፈቅራታለሁ ስልህ እኮ የእውነት ነው የማፈቅራት…ደግሞ እሷን ብቻ ሳይሆን እሱንም በጣም የምወደው ወንድሜ ነው፡፡ የመጀመሪያ ምርጫዬ በመሀከላቸው ያለው ችግር ተቀርፎ ትዳራቸውን አጣፍጠው መኖር እንዲቀጥሉ ነው…..፡፡ትዳሩ እንደማይቀጥል እርግጠኛ እስክሆን ድርስ ምንም አይነት እንቅስቃሴ አላደርግም..ለዛ ቃል ገባልሀለው፡፡››

‹‹ጥሩ ..ሌላው…ነገሮች የማይሆኑ ሆነው..እሷን የማግባቱ እድል ያንተ ከሆነ ከውጭ ጓዝህን ጠቅልለህ ትመጣለህ…ይዣት ልሂድ የምትል ከሆነ ..አልስማማም›

‹‹የእሷ ፍላጎት ከሀገር ውጭ ሄዶ መኖር ከሆነስ?››

‹‹ነገርኩ እኮ…ከአሁን በኃላ ከእህቴ ተለይቼ መኖር አልችልም…እዚሁ በቅርቤ እንድትሆን ነው የምፈልገው፡፡››

‹‹.ጥሩ …ለእኔ ችግር የለውም ..እሷን እስከአገኘሁ ድረስ የትም ብኖር ደስተኛ ነኝ፡፡››

ስምምነታቸውን አገባደው ወደ ግል ትካዜያቸው ተመልሰው ገቡ..የአላዛርን መምጣት ሲያዩ ነበር ከትካዜያቸው ባነው የተንቀሳቀሱት፡፡የሞቀ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ…ወደመኪና ይዘውት እየሄዱ ሳለ አላዛር ‹‹ሰሎሜስ…?አብራችሁ ትመጣለች ብዬ ነበር?››ሲል ቅሬታውን አሰማ፡፡

አለማየሁ ፈጠን አለና ‹‹አልቻለችም…አንተን በደመቀ ቤት ለመቀበል ሽር ጉድ እያለች ነው፡፡››የሚል የውሸት ምክንያት ነገረው፡

‹‹እኔን ለመቀበል የምን ሽርጉድ ያስፈልጋል…?አንድ ወር ብቻ እኮ ነው የቆየሁት››እያለ በመነጫነጭ መኪና ውስጥ ገባ፡፡በአለማየሁ ሹፌርነት ወደቤት ጉዞ ጀመሩ…፡፡
አላዛር እቤት ሲደርሱ ሰሎሜን አግኝቶ ናፍቆቱን ለመወጣት ባለው ጉጉት  ቀጥታ ተንደርድሮ ወደሳሎን ነው የገባው ፡፡እቴቴና ሰራተኞቹ የምግብ ጠረጴዛው ላይ ምግብን ለመደርደር  ሽር ጉድ እያሉ ነው… ሰሎሜን ማየት አልቻለም፡፡ውስጡን ፋራቻ ወረረው፡፡ ግን ወዲያው ሶፋው ላይ ጋቢ ለብሳ ተኝታ ተመለከታት፡፡ተንደረደረና ስሯ ደርሶ  ተንበረከከ‹‹እንዴ የእኔ ፍቅር እስከዛሬ እያመመሽ ነው እንዴ?››ብሎ ተጠመጠመባት፡፡

‹‹ቀስ ቀስ…ሰውነቷ ገና በቅጡ አላገገመም››ሲሉ እናትዬው አስጠነቀቁት፡፡

‹‹ማለት››

‹‹የመቅኔ ንቅለተከላ ተደርጎላት ነበር..?››እናትዬው ነች ተናጋሪዋ
አላዛር ሚስቱን አፍጥጦ ተመለከታት፡፡ሰሎሜም ‹‹ትንሽ አሞኝ ነበር..››ስትል ጠቅላላ ሁኔታውን በአጭሩ አስረዳችው፡፡

‹‹ማለት ..?እንዴት ይሄ ሁሉ ሲሆን እኔ ሳልሰማ…?ለምን ልትደብቁኝ ፈለጋችሁ?የሆነ ነገር ሆናስ ቢሆን ?››ወደኃላ ዞሮ ጓደኞቹ ላይ አፈጠጠባቸው፡፡…ዘራፍ አለ ..ተንሰቅስቆ አለቀሰ..

‹‹ምንም አታስብ አሁን እኮ ሙሉ በሙሉ ድኜለሁ…እየን እስኪ በጣም እኮ ደህና ነኝ፡፡.ስራ ሁሉ እኮ መስራት እችላለው…እነእማዬ ትንሽ አገግሚ ስላሉኝ እኔም ትንሽ ልሞላቀቅ ብዬ ነው ተኝቼ የጠበቅኩህ፡፡››ስትል አፅናናችው፡፡ከብዙ ምክርና ተግሳፅ በኋላ እንደምንም ተረጋጋ፡፡ሁሉም በተደረደረው ምግብ ጠረጴዛ ከበው ተቀመጡ፡፡እየተሳሳቁና እየተጎራረሱ አሪፍ እራት በሉ፡፡ሁሉም ከምግብ ጠረጴዛው  ወደ ሶፋው ተሸጋግረው በመደዳ በመቀመጥ ከሰሎሜ በስተቀር ሁሉም የሚፈልገውን መጠጥ እየተጎነጨ ለሌላ ዙር ጫወታ ዝጉጁ ሆኑ.፡፡
👍555
የተለመደውን የቤተሰብና የጓደኝነት ወግ ሲያወሩ ለአንድ ሰዓት ያህል ከቆዩ በኃላ እቴቴ እጆን አጨበጨበችና መናገር የምትፈልገው ነገር እንዳለ እና ሁሉም በጥሞና እንዲያዳምጣት ጠየቀች፡፡ሁሉም ፀጥ ብለው የምትለውን ነገር ለመሳማት በመጓጓት  ምትፈልገውን ትኩረት ሰጧት፡፡

እቴቴም ትንፋሿን ወደውስጧ በረጅሙ ሳበችና የተወሰነ ለመረጋጋት ከሞከረች በኃላ …ንግግሯን ጀመረች‹‹ይሄንን ነገር ለባለፈው 25 አመት በውስጤ አምቄ ኖሪያለው፡፡ምን አልባትም በውስጤ እንደቀበርኩት ወደመቃብር ይዤው ልወርድ እቅዴ ነበር፡፡ግን እግዚያብሄር በራሱ መንገድ እንደዛ እንዲሆን አልፈቀደም፡፡የሰሎሜን ህመም ተከትሎ የግድ ሚስጥሩን የማወጣበት አስገዳጅ ሁኔታ ተፈጥሮል፡፡

ልጄ ሰሎሜ ይሄንን የምነግርሽን ነገር እንዴት እንደምትቀበይው አላውቅም፡፡ግን ደግሞ እንዴትም ተቀበይው እንዴትም… የግድ ነግርሻለው…ከሆፒታል በወጣሽ ቀን ነበር ልነግርሽ የፈለኩት፡፡ግን ደግሞ ለክፉም ለደጉም ባለቤትሽ ከጎንሽ ባለበት ቀን ነገሩን ብትሰሚው እንደሚሻል ከአለማየሁ ጋር ስለተስማማን እስከዛሬ አቆየሁት…ከዚህ በላይ ግን ማፈንና በውስጤ ቀብሬ ለአንዲት ተጨማሪ ቀንም ቢሆን ማቆየት  አልችልም፡፡

ሰሎሜ በጉጉት ትንፋሽ አጠራት‹‹እማዬ ምን ጉድ ነው? በጣም እስጨነቅሽኝ እኮ ነው?››ስትል እቴቴ ላይ አፈጠጠች፡፡

አላዛርም በተመሳሳይ የታፈነ ስሜት‹‹አዎ እኔም በጣም ተጨንቄለው..ምን ተፈጠረ..?ትዳራችንን የተመለከተ ነገር ነው?››ሲል ጠየቀ፡፡.አእምሮው ተስፈንጥሮ የሄደበት እሱ ቱርክ የሄደበትን ምክንያት በሆነ መንገድ አውቅው የሆነ ውሳኔ ላይ ደርሰው ከልጃቸው ሊያለያዩት  እንደወሰኑ ነው፡፡

እቴቴ የአላዛርን ጥያቄ ችላ በማለት ‹‹ልጄ…..ለአመታት አባቴ ማን ነው..?ንገሪኝ እያልሽ ስትጠይኝ እኔም መልሱን ላለመመለስ ስሸሽ ኖሪያለሁ››

በትልቅ ጉጉትና አድናቆት ‹‹እንዴ!! እማዬ አባቴን አገኘሽልኝ…..?››ስትል ጠየቀች፡፡

‹‹አዎ..ግን ብዙ አትጎጊ ሞቷል››ብስራትና መርዶ የተቀላቀለበትን ዜን በአንድ አረፍተ ነገር አስቀመጡላት፡፡

‹‹ሞቷል….››አለችና ለረጅም ደቂቃ ትክዝ አለች፡፡የሆነ የልብ መቆረስ አይነት ስሜት ነው የተሰማት…ምንም እንኳን በእድሜ ዘመኗ ምን እንደሚመስል አይታ የማታውቀው ሰው ቢሆንም  አባቷ ነው፡፡ማንናቷ ከእሱ ማንነት የተሸረፈ ነው፡፡እና የሆነ የሀዘን ጦር በልቧ ላይ መሰካቱ የማይጠበቅ አይደለም፡፡፡
ከረጅም ደቀቃ ትካዜ በኃላ በሌላ ተስፋ እንደመነቃቃት ብላ ‹‹ግን ዘመዶች ወይም ሌሎች ልጆች አሉት አይደል?››ስትል ጠየቀች፡፡

‹‹ስለዘመዶቹ አላውቅም ልጆች ግን አለው…..››

‹‹የት ናቸው ?አድርሻቸውን ታውቂያለሽ?››በከፍተኛ ጉጉት ጠየቀች፡፡

‹‹አዎ…ወንድም አለሽ.. እሱም ከፊት ለፊትሽ የተቀመጠው በእድሜ ዘመንሽ ሙሉ አብሮሽ የኖረው አለማየሁ ነው፡፡››

የሰማችው ዜና ምንም ትርጉም የሚሰጥ ነገር ሆኖ አላገኘችውም፡፡ጀሮዋን ኮረኮረች..አላዛር ደግሞ ከእሷ በላይ ነው በጉዳዩ ግራ የተጋባው፡፡ሙሉ ታሪኩን ቀድመው ያወቁት አለማየሁና ሁሴን  በዝምታ የሚሆነውን ነገር በፅሞና እየተከታተሉ ነው፡፡

‹‹እማዬ ያልሽው ነገር ምንም  አልገባኝም?››

‹‹አለማየሁ ወንድምሽ ነው፡፡የታሪኩን ዝርዝር ምናምኑን እንዳትጠይቂኝ፡፡አንቺም አለማየሁም ከአንድ አባት ነው የተወለዳችሁት፡፡እስከዛሬ አባቴ ማን ነው? ብለሽ ስትጠይቂኝ በቀላሉ እከሌ ነው ብዬ ልነግርሽ ያልቻልኩት በዚህ ምክንያት ነው፡፡››

‹‹ይሄ ተአምር ነው…..››አለማየሁን በእድሜ ዘመኗ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳየችው ነገር አፍጥጣ እየመረመረችው‹‹አንተ ይሄን ጉድ ታውቅ ነበር?››ስትል ጠየቀችው፡፡

አለማየሁ‹‹ያው በቀደም ታመሽ ሆስፒታል ከገባሽ በኃላ ለህክምናው ለአንቺ የሚሆነውን መቅኔ ለመለገስ ወላጅ ወይም ወንድምና እህት ያስፈልጋል ሲባል ነው..እቴቴ ወንድሟ ነህና ምን አልባት መቅኔያችሁ ከተመሳሰለ ልትለግሳት ትችላለህ ብላ ሙሉ ታሪኩን የነገረችኝ፡፡በወቅቱ እኔም ልክ አሁን አንቺ እንደተደነቅሽውና ግራ እንደተጋባሽው ነው እኔም ተመሳሳዩን  ስሜት የተሰማኝ፡፡››

‹‹እኔ ይሄንን አላምንም..?እንዴት እቴቴ….በመሀከላችን የሆነ ነገር ተፈጥሮ ቢሆን ኖሮስ?››በንዴትና በቁጣ ወደእናቷ ለወቀሳ ዞረች፡፡

‹‹ያ እንዳይሆን ስፀልይና ስከላለከል ነበር የኖርኩት..ትዝ ይልሻል ትምህርት እንደጨረሳችሁ ከሁሴን በስተቀር ሶስታችሁም ተግባረ እድ ሞያ ለመማር ተመዝግባችሁ ነበር፡፡የዛኑ ሰሞን ታዲያ ሶስቱም ጓደኞችሽ  አንድ ላይ ተሰብስበው ስለአንቺ ሲያወሩ ሰማሁ››
በዚህ ጊዜ ሰሎሜ ብቻ ሳትሆን ሶስቱም ወንዶች በቀጣይ ስለእነሱ የሚነገረውን ለመስማት ተነቃቁ፡፡

‹‹ምን እያሉ ነው የሚያወሩት?››

‹‹ሶስቱም ከህፃንነታቸው ጀምሮ እንሚያፈቅሩሽ ተናግረው..በቅርብ ቀን ውስጥ አንቺን ፊት ለፊታቸው አስቀምጠው ሶስታቸውም እንደሚያፈቅሩሽ እና ከመሀከላቸው አንዳቸውን ለፍቅር ጓደኛነት እንድትመርጪ እንደሚያደርጉ  እቅድ ሲያወጡ ሰማሁ…በህይወቴ እንደዛን ቀን ደንግጬ አላውቅም…እንዴ እነዚህ ልጆች እንዳሉት ቢያደርጉና እሷ ደግሞ ከመሀከላቸው አለማየሁን ብትመርጥ ምንድነው የማደርገው? ብዬ ለቀናት በሀሳብ ስንገላታ ከረምኩ፡፡ከዛ አለማየሁን ቤተክርስቲያን ወሰድኩና…ከልጄ ጋር ምንም አይነት ፃታዊ ግንኙነት ማድረግ እንደሌለበትና ያንን ያደረገ ቀን እኔ በህይወት መኖር እራሱ እንደማልችል ነገርኩት፡፡ከዛ እሱም የእኔን ትዕዛዝ መጣስም ሆነ  አንቺን አጥቶ አጠገብሽ መኖር ስላልቻለ መሰለኝ 15 ቀን ሳይሞላው ፖሊስነት ተመዘገበና እኛንም ሀገሩንም ጥሎ ጠፋ፡፡በእውነት በዛን ወቅት ድብልቅልቀቅ ያለ ስሜት ነው የተሰማኝ….የፈራሁት ጥፋት እንዳይደረስ ማድረግ ስለቻልኩ ብደሰትም የምወደውና እንደልጄ ያሳደኩት የልጄ ወንድም ብን ብሎ ጥሎኝ በመሄዱ ቅሬታ አድሮብኝ ነበር..ግን ምንም ምርጫ ስላልነበረኝ ሁኔታውን በፀጋ ነው የተቀበልኩት፡፡››

አሁን ሰሎሜ ሌላ የህይወት እንቆቅልሽ ተፈታላት‹‹አሀ ..ለዛ ነው ለካ ለአመታት ከእኛ ተሰውረህ የኖርከው..እኔ ደግሞ ምን በድዬው የት ጋር አስቀይሜው ነው እንደዛ ያደረገው እያልኩ ለአመታት መልሱን ለማግኘት እራሴን ሳሰቃይ መኖሬ..ለካ ተገደህ ነው?››ስትል የአለማሁን አይን በስስትና በሀዘኔታ እያየች ጠየቀችው፡፡

እቴቴ ‹‹እንግዲህ ዋናው ነገር ይሄ ነው….ከአሁን ወዲህ ልትረግሚኝም ልትወቅሺኝም ትቺያለሽ….አሁን ደክሞኛል …ገብቼ ልተኛ››ብላ ከመቀመጫዋ ተነሳችና ወደ ማደሪያ ክፍሏ ሄደች፡፡ሁሉም በዝምታ ሸኞት፡፡
አራቱ ጓደኛሞች ተፋጠው ተቀመጡ፡፡

‹‹እኔ ባስበው ባስበው ወደ አእምሮዬ ዘልቆ ሊገባልኝ አልቻለም››አላዛር ነው ተናጋሪው፡፡
አለማየው ከአንደበቱ ተቀበለና‹‹ምኑ ነው አልዘልቅ ያለህ…? ወንድሟ መሆኔ ቅር አሰኘህ እንዴ?››አለው በንዴት፡፡

‹‹ትቀልዳለህ እንዴ ….?እንደውም በተቃራኒው በጣም ደስ ነው ያለኝ…ለልጆቼ አጎት እኮ ነው የምትሆነው፡፡››

ሰሎሜ በአላዛር ንግግር ተገርማ አፍጥጣ አየችው፡፡እንዲህ ሰው በተሰበሰበት ስለልጅ መውለድ በድፍረት ሲያወራ ሰምታው አታውቅም፡፡እንደውም በተቃራኒው እሷ በምታወራበት ጊዜ እንደተሳቀቀና የሚገባበት እንደጠፋው ነው፡፡‹‹ዛሬ ምን አዲስ ነገር ተገኘ ?››ስትል በውስጧ ጠየቀች፡፡
👍6211
ሁሴን መሀከላቸው ያለው ውጥረትና ግራ መጋባት ከዚህ በላይ እንዲቀጥል ስላልፈለገ…ወደአላዛር ዞረና ‹‹በል አሁን ሚስትህን ይዘሀት ወደመኝታ ቤት ግባ…..ገና ሙሉ በሙሉ ስላላገገመች ከዚህ በላይ መድከም የለባትም..በዛ ላይ አንተም ከመንገድ ነው የገባሀው››የሚል ሀሳብ አቀረበ፡፡

‹‹እውነትህን ነው..ማሬ ተነሽ.››አለና ቀድሞ ተነስቶ ደግፎ አስነሳት….እና መራመድ ጀመሩ ..ከዛ ወደኃላ ዞረችና‹‹ አሌክስ ››ስትል በስስት ተጣራች፡፡

‹ወዬ እህቴ››

‹‹ጥዋት ሳላገኝህ እንዳትሄድ››
‹‹አታስቢ አልሄድም..ደህና አደሪ››
‹ደህና እደሩ››ብላ ፊቷን አዞረችና እግሯን አንቀሳቀሰች፡፡

💫ይቀጥላል💫

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronosem
👍752🤔2
#ካራማራ ኢትዮጵያዊው የድል ቀን

ይህ ነው ምኞቴ እኔ በሕይወቴ
ከራሴ በፊት ለኢትዮጵያ እናቴ...

የካቲት 26 1970 ዓ.ም 🇪🇹
19👍8👏4🤔1
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
=====================

ቤቱ ቅልጥ ያለ ድግስ ላይ ነው፡፡ግቢ ውስጥ ግዙፍና ዘመናዊ ድንኳን ተደኩኖ በዲኮር አሸብርቋል፡፡በዝግጅቱ የሰሎሜ ፤ የእቴቴ የአላዛር እና የአለማየሁ አንድም ወዳጅና የስራ ባለደረቦች አልቀረም…ከ500 በላይ ሰው ነው የተጠራው፡፡እርግጥ ይሄ ድግስ እንዲደገስ ቀጠሮ የተያዘለት ሰሎሜ አለማየሁ ወንድሟ መሆኑን ከሰማች ከሳምንት በኃላ ነበር፡፡ግን ባልተጠበቀ ፕሮግራም ዜናው ከተሳማ ከሦስት ቀን በኃላ አለማየው ለአጭር ጊዜ ስለልጠና ወደ ተባበሩት አረብ ኤሜሪት እንዲሄድ በመስሪያ ቤቱ ስለታዘዘ ድግሱ በሁለት ወር እንዲራዘም ተደርጓል፡፡

ይሄ ድግስ በዋናነት ሰሎሜ አለማየሁ ወንድሟ መሆኑን በማወቋ እና ዘመናት ለማወቅ ስታልመው የነበረው የአባቷን ማንነት በማወቋ የተፈጠረባትን ፈንጠዝያ ለማክበር ነበር..ሌላው ለህይወቷ በጣም አስጊ የሆነውን በሽታ ታክማ መዳን በመቻሏም ለተንከባከቧት ሰዎች ሆነ ለፈጣሪ ምስጋና ለማቅረብ ነው፡፡ለሌላው ሶስተኛ ነገር ደግሞ ትዳር በያዘችባቸው ሶስት አመቷ ውስጥ ስትሰቃይበት የነበረችው ከአላዛር ላይ ተከስቶ የነበረው ስንፈተ ወሲብ ሙሉ በሙሉ ተወግዶ  ልክ እንደአዲስ ሙሽራ ቀንና ለሊት ሳይለዩ በፊት ያበከኑትን ጊዜ ማካካስ በሚመስል መልኩ እልካቸውን እየተወጡበት ስለሆነ በዛ ጉዳይ የተፈጠረባቸውን ደስታ በይፋ ለማክበር ነው፡፡ያም መሆኑ ለሁለቱም ከፍተኛ ደስታና አዲስ የህይወት እርካታ አጎናፅፏቸዋል፡፡ከሁለቱም ልብ እየተበተነ ያለ ደስታ በዙሪያቸው ያለውን ሰው ላይ ሁሉ የሚጋባ አይነት ሆኗል፡፡ይሄም ድግሱ ደማቅና ሰፊ እንዲሆን አንዱ ምክንያት ነው፡፡
ድግሱ ለሁለት ወር በመራዘሙ ምክንያት ሌላም ሊከበር የሚገባው ተደራራቢ ምክንያትና በረከት ተፈጥሮል፡፡

ድግሱ ላይ የታደሙት 500  ያህል የቅርብ ሰዎች ምሳ ከበሉ በኃላ ሰሎሜ የተፍለቀለቀ ፊቷን በፈገግታ አጅባ ወደመድረኩ ወጣች፡፡

ማይኩን ድግሱን በሙዚቃ እያደመቀ ካለው ዲጄ  ተቀብላ ማውራት ጀመረች፡፡

‹‹ወዳጆቼ ዘመዶቼ ይሄ ድግስን አስመልክቶ ጥቂት ነገር መናገር እፈልጋለው፡፡››ስትል ሁሉም የምትለውን ነገር ለመስማት የእርስ በርስ ወሬያቸውን አቁመው ትኩረታቸውን ወደእሷ አዞሩ….ንግግሯን ቀጠለች፡፡

‹‹ንግግሬን ከመጀመሬ በፊት ..እናቴ እቴቴ ..ባለቤቴ አላዛር….ወንድሜ አለማየሁ….ጓደኛዬ ሁሴን ..ሁላችሁም ወደዚህ መድረክ ኑና ከጎኔ ያለው የፊት ፊት መቀመጫ ላይ እንድትቀመጡ እፈልጋለው፡፡የሚል ጥያቄ አቀረበች፡፡

ሁሉም እየተያያዙ መጡና ፊታቸውን ወደእድምተኞች አዙረው መድረክ ላይ በተዘጋጀው መቀመጫ ላይ ተቀመጡ፡፡

ሰሎሜ ንግግሯን ቀጠለች‹‹እንግዲህ እነዚህ አራት ሰዎች ወደእዚህ ምድር ከመጣሁበት ከመጀመሪያዋ ቀን ጀምሮ ከጎኔ ነበሩ…ሰሎሜ ሰሎሜ እንድትሆን ሁሉም የየራሳቸውን ድርሻ ተወጥተዋል፡፡እኔ ማለት የእነሱ ውጤት ነኝ፡፡እናቴ እቴቴ … ከልጅነቴ ጀምሮ ያለአባት  በጀግንነት አሳድጋኛለች፡፡ላደረግሺልኝ ነገር ሁሉ በጣም አመሰግናለሁ፡፡በጣም ነው የምወድሽ፡፡
በህይወቴ ሁለት ጊዜ በከባድ በሽታ ሆስፒታል ገብቻለሁ፡፡ልጅ ሆኜ በታመምኩ ጊዜ ለህክምናው 70 ሺ ብር ተጠይቆ ነበር፡፡በወቅቱ እናቴ የነበራት ከ7ሺ ብር የማይበልጥ ብር ነበር፡፡ቀሪውን ብር በትምህርት ቤትና በየመንደሩ እየዞሩ ለምነው ያሳከሙኝ..እንዚህ ከፊት ለፊት ተቀምጠው የምታዬቸው የልጅነት ሶስቱ ጓደኞቼ ናቸው፡፡ከሶስት ወር በፊትም ተመሳሳይ አይነት ፈታኝ ህመም አሞኝ ነበር፡፡ ከአካሉ አካል ቆርሶ በመስጠት ደግመኛ ዛሬን እንደዚህ ከፊት ለፊታችሁ እንድቆም ያደረገኝ ወንድሜ አለማየሁ ነው፡፡ይሄም ዝግጅት እንዲጋጅ አንዱ እና ዋነኛው ምክንያት ‹‹ወንድሜም ስለሆንክ…ከህመሜም እንድፈወስ ስላደረከኝ››አመሰግናለው ለማለት ነው፡፡

ሌላው የዕድሜ ልክ ጓደኛዬ  ሁሴን በሁለቱም የህይወቴ ጨለማ ቀናቶች ከጎኔ ስለነበርክ አንተንም በጣም አመስገናለሁ፡፡በጣም እንደምትወደኝ አውቃለው….እኔም በጣም እወድሀለው….እናም ከሶስት ቀን በኃላ ተመልሰህ ወደውጭ እንደምትሄድ ስለማውቅ ዳግመኛ ሙሉ ጓዝህን ጠቅልለህ ወደሀገር እስክትመለስ እና አብረሀን መኖር አስክትጀምር ድረስ  ይሄ እንደሽኝት ፕሮግራም እንዲታይልኝ እፈልጋለው፡፡
ከፍተኛ የሞቀ ጭብጨባ ተከተላት…ትንፋሽ ወሰደችና ንግግሯን ካቆመችበት ቀጠለች፡፡
ሌላው የእድሜ ልክ ጓደኛዬ እና አንድም አመት ቢሆን ከስሬ ተለይቶኝ የማያውቀው መከራዬንም ሆነ ደስታዬን አብሮኝ ያሳለፈው የምወደው ባለቤቴ  አላዛር  ..ስለተንከባከብከኝ. .ለአስቸጋሪው ፀባዬ ጠቅላላ ትዕግስት አድርገህ ተስፋ ሳትቆርጥብኝ እስከአሁን አብሬህ እንድኖር ሚስትህ እንድሆን ስላደረከኝ አመሰግናለው..ለዚህም ድንቅ አበርክቶትህ ከእኔ ከሚስትህ በዚህ ሁሉ ወዳጅ ዘመድ ፊት አንድ ስጦታ ላበረክትልህ እፈልጋለው፡፡››አለችና ንግግሯን ገታ አደረገች…አላዛር ግራ ተጋባ..ሌሎችም የሽልማቱን ምንነት ለማወቅ ጉጉት አሳዩ፡፡

‹‹ውድ ባለቤቴ ወደእኔ ና››ስትል ጠየቀችው፡፡

ከተቀመጠበት ተነሳና ወደእሷ ቀረበ….በእጆ የያዘችውን ፖስታ አቀበለችው፡፡ምን እንደሚያደርገው ግራ ገብቷት ዝም ብሎ እያገላበጠ ያየው ጀመር፡፡

ሁሴን እና አለማየሁ‹‹ይከፈት ይከፈት››አሉ..ሌሎችም እድምተኞች ተከተሏቸው፡፡አላዛር ምርጫ ስላሌለው በቀስታ ፖስታውን ሸረከተው፡፡አንድ ነጠላ ወረቀት ነው ውስጡ ያለው፡፡ አወጣውና  ተመለከተው ፡፡ ምንም አልገባውም‹‹ምንድነው ፍቅር?››ሲል እሷኑ መልሶ ጠየቃት፡፡

‹‹አንብበዋ››አለችው፡፡

‹‹እንድምንም ትክረቱን ሰብስቦ ማንበብ ጀመረ…አይኑ ፈጠጠ…‹‹ምንድነው ፍቅር..? የማየው ነገር እውነት ነው…?››ሲል ባለማመን ጠየቃት፡፡ተንደረደረና ተጠጋት፡፡ዝቅ ብሎ ጉልበቷ አካባቢ በእጆቹ ያዛትና ወደላይ አንስቶ አሽከረከራት፡፡ሰው ሁሉ ሽልማቱ ምን ቢሆን ነው በሚል ጥያቄ ራሱን እየጠየቀ መወዛገብን ቀጠለ፡፡እንደምንም እንዲያወርዳት ካደረገች በኃላ ጠረጴዛ ላይ ያለውን  ማይክሮፎኑን ወደአፈዋ አስጠጋችና ‹አዎ እውነት ነው..ውድ ባለቤቴ ሽልማትህ ልጅ ነው..እኔ ሚስትህ የሁለት ወር እርጉዝ ነኝ፡፡››በማለት ለእሱ ብቻ ሳይሆን ለመላ ታዳሚው የምስራቹን አበሰረች፡፡መጀመሪያ እልልታዋን ያቀለጠችው እናቷ እቴቴ ነች….ከዛ ሙሉ ዱንኳኑ በእልልታና በጭብጨባ ተደበላለቀ፡፡.አለማየሁም ሆነ ሁሴን ከመጠን በላይ ተደሰቱና ተንደርድረው ባልና ሙስቶቹ ላይ ተጠመጠሙባቸው፡፡ከዚህ በፊት ተደርጎ የማያውቅ ልዩ አይነት ዝግጅት ሆኖ አለፈ…፡፡

እንግዶቹ ከተሸኙ በኋላ ቤተሰቡ ድግሱንና ፈንጠዝያውን ቀጠሉበት፡፡ሁሴን ወደመጣበት እንግሊዝ ተመልሶ እስኪሄድ ድረስ ከዛ ቤት የሄደ ሰው አልነበረም፡፡.እቴቴ ለአመታት ቃል በገባችው መሰረት ብቸኛ ልጆን በእርግዝና ወቅቷ ለመንከባከብና ከወለደችም በኃላ የልጅ ልጆን ለማሳደግ ስትል የራሷን ቤት ዘግታ ሙሉ በሙሉ ባልና ሚስቱ ጋር ተጠቃላ ገባች፡፡አለማሁም ከእንግዳ ክፍሎቹ ውስጥ አንዱ ክፍል ተመርጧ የእሱ ቆሚ ክፍል ሆኖ እንዲደራጅ ተደረገና ቢያንስ በሳምንት ሶስት እና አራት ቀን እየመጣ እነሱ ጋር ማደር ጀመረ፡፡እሱ እንቢ ብሎ እንጂ እነሱማ ቢያንስ የራስህን ሴት አግኝተህ ሚስት እስክታገባ ሙሉ በሙሉ የተከራየኸውን ቤት ልቀቅና  እዚሁ እኛ ጋር ተጠቃለህ ግባ ና እንደቤተሰብ አንድ ላይ እንኑር ብለውት ነበር፡፡እሱ ግን ሙሉ በሙሉ በሚለው ሊስማማ አልቻለም፡፡በአጠቃላይ እንደዛ የጭቅጭቅ መናኸሪያ ሆኖ ቀዝቅዞ የነበረው ቤት አሁን ደምቆና በቤተሰብ
👍7513👏4🥰3👎1😱1
ተሞልተ ሳቅና ደስታ የሚመረትበት..የተስፋና የብስራት መቅደስ ሆኗል…..በሁሉም ላይ ደግሞ ይሄ ደስታ ቀጣይ እንደሚሆን ልባዊ ምኞት አለ፡፡

💫ተፈፀመ💫

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronosem
👍116🥰2720👏6🔥3
#የሴትነት_ክብር

ከእውነታው ድግስ በሀቅ እንዲታደም
ከሴቶች ቀን በፊት ሴትን ማክበር ይቅደም።

🔘ኢዛና መስፍን🔘
56👍20
#የሴት_ልጅ

የሴት ልጅ ነው በሉኝ ስሜን ተውትና፣ ከፍ ከፍ አድርጉኝ ኩራቴ ናትና። ክብሬ ስለሆነ መጠራት በእናቴ፣ እሷ ስለሆነች ስጋ ደም አጥንቴ፣ ለኔ ልዕልና ነው የሷን ስም ማግኘቴ።

🔘ሀይደር🔘
👍5614🥰1
#የሴት_ልጅ

የሴት ልጅ ይለኛል ያዋረደኝ መስሎት
ስድብ እና ሙገሳ መለየት ተስኖት
አው የሴት ልጅ ነኝ ያውም የጀግናዋ
ጉንበስ ቀና ብላ ለልጅዋ ኗሪዋ
ዘጠኝ ወር ሳልከፍል በሆድዋ ተኝቼ
በጀርባዋ አዝላኝ እሰክሄድ በእግሮቼ
ተደፍታ ስታነድ ምግቡን ለማብሰል
እንጀራ ስትጋግር ፊትዋ መስሎ ከሰል
ሳጠፋ ገስፃ እንዳልኩራ መክራ
በርታ እያለችኝ ሁሌም እንዳልፈራ
አይዞህ አልከፋም ሴት ያሳደገኝ ነኝ
ስድብ ከመሰለህ ደጋግመህ ስደበኝ
አልቀየምህም በስምዋ ስትጠራኝ
እውነቱን ልንገርህ አዎ የሴት ልጅ ነኝ

"መታሰቢያነቱ እናቱን ለሚወድ በሙሉ።"

🔘ሎሬት ፀጋዬ ገ/ መድህን🔘
72👍22🥰2🔥1
#ንግድና_መሐላ

እጅን ለመሀላ

ከፍ አርጎ ዘርግቶ

በድለላ ቋንቋ

አግባብቶና ዋሽቶ

ለመሸጥ ሲታሰብ

የሁለቱን በሃያ፤

የአሥሩን በመቶ

በቀማኞች ጉሊት

በሌቦች ገበያ

ወላሂና እዝጌርን

ወጥ ሆኑ ማባያ ፡፡

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronosem
👍266👏2😱1
አሁን በቀደም'ለት..!

መጣች ተቀበልኳት አወጋች አመንኳት ብዙ ብዙ አለችኝ፣ የትም ከርማ መጥታ የሄደችበትን ምክንያት ነገረችኝ፣

ትክክል ነሽ አልኳት ባትሆንም ግድ የለኝ፣ ከመመለሷ እንጂ፣ ከመሄድ ምን አለኝ!?

🔘ሰሎሞን ሽፈራው🔘
👍22
"ቢደርስብህ ሀዘን ቢደርስብህ በደል ተሸሽገህ አልቅስ ወንድ ልጅ ነህ አይደል?

ሚሉህን አትስማ ተረቱን አፍርሰው
አልቅስ አልቅስ ካለህ፤
መሀል አደባባይ ዕንባህን አፍስሰው።

ግድ የለም ተንሰቅሰቅ፤
በልብህ እያነባህ ስቃይ አታስታምም ይህንን አስታውስ ፤

ውስጥህ ሲፈስ ነው የሚገድለው ደም

🔘እዮብ🔘
👍34
#እኔ_ጠላሻለሁ

እንደ ጫማ ሽታ

ልክ እንደ በሽታ

ጌታ በባርያው ላይ እንደ ሚበረታ

#እኔ_ጠላሻለሁ

እንደ ረጅም መንገድ

ለሀብታም እንደ መስገድ

ከጠጡ በኋላ እንደ መንገዳገድ

#እኔ_ጠላሻለሁ

ገንዘብ እንደ ማጣት

ዳገት እንደ መውጣት

ከያዘ እንደ ማይለቅ እንደ ጨካኝ ቅጣት

#እኔ_ጠላሻለሁ

ልክ እንደ መልከስከስ

እምነት እንደ ማርከስ

ማስቲካ እያኘኩ ምላስ እንደ መንከስ

እኔ ጠላሻለሁ . . . (ወዘተ )

አሁን ግን ፈራሁኝ ጀመርኩኝ መብሰልሰል ጠላሁሽ ያበዛሁ #ወድጄሽ ነው መሰል፡፡

🔘እዮብ🔘
30👍27😁10👏4
#አንቺ. . .

እንደዘመኑ ሴት፤
መኪና ላለው ወንድ ጭንሽን ማትከፍቺ ኑሮን ለማሸንፍ፣
የምትታትሪ የምትሟሟቺ
አንቺ. . !

በአቋራጭ ሄደሽ ቁማር ሳትቆምሪ በጉልበት በላብሽ፤
የራስሽን ህይወት ምታስተዳድሪ ቤተክርስቲያን ብለሽ፤
ከቦርጫም ሰውዬ ጋ ክለብ የማታድሪ
አንቺ .. !

የሄዋን ምሳሌ የሴትነት ልኩ
መልካም ፀባይ ያለሽ የጨዋነት መልኩ

ዘመንሽ ይለምለም ...
በበረከትና በፀጋ ተከቦ
መልካሙ ፈጣሪ ፤
መልካሙን በሙሉ ጀባ ይበልሽ አቦ! ! !

🔘እዮብ🔘
🥰41👍172
አልወድክም በይኝ

   ልቤ ተጨነቀ....

መጥላትም ፍቅር ነው

  ቁርጡ ከታወቀ።😔
23👍11