አትሮኖስ
268K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
433 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
🍁🍁ዲያሪው 📝

ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_9


በሌላ በኩል ደግሞ ይህ የምታወራው ሁሉ እውነት ከሆነ በደለኛው እሷ ሳትሆን እኔ ነኝ ማለት ነው:: ምናልባት ሳላውቀው ደብዳቤ ጽፌ ይሆን? በማለት ራሴን ጠየቅሁ። እርግጥ ነው በዓለማችን ላይ አንዳንድ ሰዎች አንድ ነገር ማድረጋቸውን ወይም መፈጸማቸውን ሳያውቁ በእንቅልፍ ላይ ሆነው የተለያዩ ድርጊቶችን ፈጽመው ተመልሰው የሚተኙ እንዳሉ ሰምቻለሁ፣ አውቃለሁ:: አዎ ትዝ ይለኛል አንዳንድ ጊዜ የእኔም ወንድም በእንቅልፍ ላይ እያለ ተነስቶ በር ከፍቶ ለመውጣት ይታገል ነበር:: ግን የሰራውን ሁሉ ጠዋት የምንነግረው እኛ እንጂ እሱ አያስታውሰውም ነበር። እናቴ ሁል ጊዜ ኦሽ ባለ ቁጥር በር ከፍቶ የወጣ ስለሚመስላት ተኝታም ቢሆን እሱን መጠበቋ የተለመደ ነው:: አንድ ቀን በእንቅልፍ ልቡ ሲሄድ አንድ ነገር ይገጭና ጉዳት ያደርስበታል ወይም ገደል ይገባል ብላም ትዕጋለች:: ይህ ነገር ከቤተሰብ የሚጋባ ከሆነ እኔም ምናልባት አንድ ቀን ተነስቼ ደብዳቤውን ጽፌ ሊሆን ይችላል ብዬም አሰብኩ:: ግን ይኸ ደግሞ የማይቻል ነው:: መጻፉን ልጻፈው ፖስታ ቤት መቼም ወስጄ ላስገባው አይቻለኝምና፡፡ ይህንን ሳወጣና ሳወርድ ራሴ ሊፈነዳ ደረሰ:: በዚህ ሁኔታ ማንበብ እንደማልችል በመረዳቴና ከመጠን በላይ ስለደከመኝ ሃምሳ አለቃውን ጠርቼ ታስሬ ካልሆነ፣ ወደ ቤቴ ወስጄ እንዳነበው እንዲፈቅድልኝ በሩን ከፍቼ ብጣራ የሚሰማኝ አልነበረም። ያለሁበት ቢሮ ባይዘጋም የተቀረው ቢሮ ሁሉ ተዘጋግቷል:: ሰዓቴን አየሁት፡፡ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ሆኗል:: ጭር ብሏል:: እኔ በዲያሪው ውስጥ ሰጥሜ ሳለ ሰው ሁሉ ጥሎኝ ሄዶ ነበር፡፡ እዚያው አካባቢ _ ሃምሳ _ አለቃውን ፈለግሁት፡፡ ላገኘው ግን አልቻልኩም፡፡ እኔ ከነበርኩበት ከምርመራ ክፍል በስተቀር የሁሉም ክፍሎች መብራቶች ጠፍተዋል። በዚህ ላይ የኮሪደሩ መብራት ስላልበራ ፀጥታው ከጭለማው ጋር ተደምሮ እጅግ ያስፈራል። ቶሎ መውጣት ስለነበረብኝ ዲያሪውን ሰው እንዳያየው በሆዴና በሱሪዬ መሐል አጣብቄና ደብቄ እየተጣደፍኩ ወጣሁ:: ከቢሮ ወጣ ስል ግን በር ላይ ዘብ ቆሞ በማየቴ እስረኛ መሆኔን ተረዳሁ:: ዛሬ ሳነብ እንዳድር እንደተፈረደብኝ ገባኝ:: ከዛ በኋላ ደግሞ ምናልባት ነገ ምርመራ ሊኖር ይችላል፡፡ ምን ይኸ ብቻ! አልማዝም እንደተመኘችው ሞታ ከሆነና በእኔ ምክንያት መሞቷን ከፃፈች ደግሞ የእኔ ነገር አከተመ ማለት ነው፡፡ መለቀቅም ተረት ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ አልፌው ስሄድ ጥበቃው አረማመዴን ከማየት ውጪ "ተመለስ" ወይም "ወዴት ነው?" ባለማለቱ በዚሁ ተደፋፍሬ ወደ ውጪው በር አመራሁ፡፡ ነገር ግን እውጪው በር አጠገብ እንደደረስኩ፤

"ወዴት ነው አቶ አማረ?" የሚል ድምፅ በመስማቴ ዞር ብዬ አየሁ፡፡ ሃምሳ አለቃው ጥግ ላይ ራቅ ብሎ ከአንድ ፖሊስ ጋር ፊት ለፊት ቆሟል፡፡ ወደ እኔ እየመጣ ፤ "ለመሆኑ ማን እንዲወጡ ፈቀደልዎት? ዲያሪውን ይዘው ሊጠፉ ነበር ማለት ነው?" አለኝ፡፡ ምን ብዬ እንደምመልስለት ግራ ገብቶኝ ለአጭር አፍታ ዝም ካልኩ በኋላ፤ "ሃምሳ አለቃ፣ ለመጥፋት ፈልጌ አይደለም፡፡ እርስዎን ተጣርቼ ላገኝዎት ባለመቻሌና ዲያሪውን ስላልጨረስኩት አንብቤ ለመመለስ ይዤው ወጣሁ እንጂ ለመውሰድ ፈልጌ አይደለም" አልኩት፡፡ እንድከተለው በእጁ እያመለከተኝ እንደገና ተያይዘን ወደ ቢሮው አመራን፡፡ እንደገባን ወንበሩ ላይ ተለጥጦ ተቀመጠና ቁጭ በል እንኳን ሳይለኝ፤ "እንግዲህ ዲያሪውን መጨረስ ከፈለጉ ያለው አማራጭ እዚህ ግቢ እሥር ቤት ውስጥ አድረው ማንበብ ይችላሉ፡፡ በተረፈ ከዚህ ግቢ ዲያሪውን ይዘው መውጣት አይችሉም" አለኝ፡፡ እንደ ወንጀለኛ እስር ቤት ማደር እንደሌለብኝና ዲያሪውን እቤት አንብቤ እንደጨረስኩ እንደምመልስ ቃል ገብቼ እንዲፈቅድልኝ ተማፀንኩት፡፡ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ያህል ምን እንደሚያደርግ እንደተቸገረ ሰው በዝምታ ሲመለከተኝ ከቆየ በኋላ ዲያሪውን ተቀበለኝና፤ "መጣሁ ይጠብቁኝ" ብሎኝ ወጣ፡፡ ይኸ የማይጨበጥ ሰውዬ አሁን ደግሞ ምን ሊያደርግ ነው እያልኩ በስጋት ስጠብቅ አንድ ሌላ መጽሐፍ ይዞ ተመለሰና ምንም ሳያናግረኝ ወረቀት አውጥቶ መጻፍ ጀመረ፡፡ እንደጨረሰም፧ "አቶ አማረ ይህ የዲያሪው ፎቶ ኮፒ ነው፡፡ ዋናውን ዲያሪ ወስደው እንዲያነቡት ልንሰጥዎ አንችልም፡፡ ይህንን ግን ወደ ቤትዎ ወስደው እንደጨረሱ _ አምጥተው መመለስ ይችላሉ፡፡ ለማንኛውም እዚህ ላይ ይፈርሙ" አለኝ፡፡ እንድፈርምበት የተሠጠኝ ጽሑፍ የሚያትተው፤ የአልማዝን ዲያሪ ላነብ መውሰዴንና ባለበት ሁኔታ ለመመለስ መስማማቴን፣ እንዲሁም አንድ ገፅ ባጎድል፣ ብደልዝና ዲያሪውን በወቅቱ ባልመልስ በሕግ ልጠየቅ ወድጄ መፈረሜን የሚገልፅ ስለነበር ምንም ተጨማሪ ጥያቄ መጠየቅ ሳያስፈልገኝ ፈርሜ መለስኩለት፡፡ ሃምሳ አለቃው ወረቀቱን ተቀብሎ መሳቢያ ውስጥ ከተተና ከመቀመጫው ተነስቶ፣ የቀኝ እጁን መዳፍ ደረቱ ላይ ለጥፎ፣ ከአንገቱ ጎንበስ በማለት፤

"መልካም ንባብ እንዲሆንልዎ እመኛለሁ" አለኝ በፌዝ መልክ። ለፌዙ ቁብ ሳልሰጥ፣ “አመሰግናለሁ ሃምሳ አለቃ" በማለት ቶሎ ቶሎ እየተራመድኩ ከቢሮው ወጣሁ:: ጥበቃው ተመለስ እንዳይለኝ ብሰጋም፣ በዝምታ አሳለፈኝ: እኔ ግን ከመፍራቴ የተነሳ ወደ ኋላ ዞር ብዬ እንኳ ማየት አልደፈርኩም:: ታክሲ ውስጥ ገብቼ ወደ ቤቴ ስጓዝ፤ "ከዚህ በኋላ መቼም ቢሆን ሃምላ አለቃው አያገኘኝም" በማለት ተፅናናሁ:: ግን ደግሞ ዲያሪው የአልማዝን የመጨረሻ ሁኔታ የማያሳውቀኝ ከሆነ የግዴታ ቀሪውን ታሪክ ለማወቅ ተመልሼ መምጣት እንዳለብኝ ሳሰብ ተመልሶ ፍርሀት ወረረኝ:: ቤቴን እንደቆለፍኩት አገኘሁት:: ሠራተኛዬም ዘመዶችዋን ለመጠየቅ እንደሄደች አልተመለሰችም:: በሩን ከፍቼ እየተጣደፍኩ ወደ አልጋዬ አመራሁ:: ልብሴን እንኳን ለማውለቅ አቅም በማጣቴ ጫማዬን ብቻ አውልቁ አልጋው ላይ ዘፍ አልኩ፡፡ ድካም ይኑርብኝ እንጂ እንቅልፌ ግን ወዲያው አልመጣም፡፡ እንቆቅልሹን መፍታት ስላልቻልኩ እንዴት እንዲህ ሊሆን ቻለ? አልማዝ እየዋሸች ነው ወይስ እውነት ነው የምታወራው? ወይስ እሷ ከሞተች በኋላ ዲያሪውን ያ እርኩስ ዶ/ር አግኝቶት ሆን ብሎ ያልሆነ ነገር ጽፎበት ይሆን? እያልኩ ራሴን ደጋግሜ ስጠይቅና መልሼ ለራሴ የማያሳምን መላ ምት ሳስቀምጥ እኩለ ሌሊት ሆነ፡፡ በመሀሉ እንቅልፍ ይዞኝ ጭልጥ አለ። “ታዲያ አልሚና እንደነገርኩሽ አባቴን በጣም እወደው ነበር፡፡ እሱም እኔን ከልጆቹ ሁሉ አብልጦ እኔን ይወደኝ ነበር፡፡ አባቴ እንደእኔ ጨዋ አልነበረም፣ ማለቴ መጠጥ ነፍሱ ነበር። ሳይጠጣ መግባትን እኔ እስከማውቅ ድረስ ሞክሮት አያውቅም:: ግን የሚገርመው ነገር፣ ሰክሮ ቢገባም ይበልጥ ቤተስቡን የሚያጫውትና የሚያዝናና እንጂ እንደተለመዱት ሰካራሞች አይጨቃጨቅም :: ይልቁንም የሚጠጣበት አጥቶ ቤት የዋለ ዕለት ጭቅጭቁ የሚቻል አልነበረም:: በዘመኑ አራዶች ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ስለነበር ሞቅ ባለው ቁጥር ቯልስ እንደንስ እያለ እናቴን ያስጨንቃት ነበር፡፡ እሷ ደግሞ ገራገርና ምንም የማታውቅ ስለነበረች ከአጠገቧ እንዲሄድላት መጨቅጨቅ እንጂ ሞክራው አታውቅም:: እርግጥ ሠርግ ሠፈር ውስጥ ሲኖር የሠፈሩ ድግሥ አድማቂ ነበረች:: እስክስታ ስትወርድ የተቀመጠው ሁሉ ነሽጦት እንዲነሳ ታደርግ ነበር። ታዲያ አባቴ ቯልስ የሚያዳንሰው ሲያጣ ትንሹን