አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
486 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የፍቅር_ሰመመን


#ክፍል_ሃምሳ_አራት


#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን


#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው


...“ያ ጥቁር ልጅ እኮ የማይረባ የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪ እና ነፍሰ ገዳይ ነበር።ስሙ ኤስሊ ጄምስ ይባላል” ብሎ አፉን እየመረረው ስሙን ከተናገረ በኋላ በመቀጠል “ ጄሪ ግን በጣም ድንቅ እና ጨዋ መርማሪ ፖሊስ ነበር። ምን ይሄ ብቻ ምርጥ ባል እና አባትም ነበር፡፡ ሚስቱ ስትሞት ግን በጣም ስሜት ውስጥ ሆኖ ነበር። አንቺ ግን በእሱ ላይ መሰከርሽበት ጤነኛ ነው ብለሽ ለዳኛዋ ነገርሻት። ያቺ ሸርሙጣ ዳኛም ሃያ ዓመት ፈረደችበት። ይሄዐደግሞ እሱን ሙሉ በሙሉ ነበር ያጠፋው።” አላት፡፡

ኒኪም በጆንስን ፊት ላይ የሚታየውን ንዴት እና የፀፀት ስሜት አስተዋለችና ይህ ሰው በእርግጥም ፍርድ ተዛብቷል ብሎ ያስባል ማለት ነው? ብላ አሰበች እና በመቀጠልም “አስታውሳለሁ በጣም አሳዛኝ ነገር ነበር” አለችው፡፡

“ሊያሳዝንሽ አይገባም ዶክተር ምክንያቱም አንቺ ነበርሽ ጩቤ አቀባይዋ”

ኒኪም አይኑን እያየችው “ሀዘኑ ለሁለቱም ነበር ማለቴ ነው፡፡ ማለትም ለጓደኛህ፣ እንዲሁም ለተደበደበው ልጅ ቤተሰብም ጭምር”

“እውነትሽን ባልሆነ ብቻ?” አላት ጆንሰን፡፡

ኒኪም ኮስተር ብላ “አዎን እውነቴን ነው ምክንያቱም እኔ ከማንም በላይ የሀዘን ስሜት ይገባኛል፡፡ በሀዘን ምክንያት ግን አንድን ሰው እስከሞት ድረስ የሚያደርስ ድብደባን አልፈፅምም፡፡ ይሄ የሀዘኔታ ስሜት አይደለም” አለችው፡፡

ጆንሰንም ፍጥጥ ብሎ አያት እና “አንዴ ኬስሊ እኮ ሰው አይደለም። ምን ኬስሊ ብቻ ዕፅ አዘዋዋሪዎቹ ጎረቤቶቹ እና ጓደኞቹም ጭምር ቆሻሻ የሰው መጨረሻዎች ናቸው! እነርሱ እኮ የህብረተሰቡን ኑሮ እና የእኛን ህግ
የማስከበር ሥራዎችን ሁሉ ገደል የሚከቱ ጭራቆች ናቸው።”

ኒኪ በሀሳቧ በቃ ከዚህ ሰው ጋር ምንም የምንግባባ አይመስለኝም። እሱ እኔ የማሳየውን መንገድ አይቀበልም፡፡ እኔ ደግሞ የእሱን መንገድ በፍፁም
መቀበል የምችል ሰው አይደለሁም እያለች በውስጧ ስታስብ ቆየች እና “እሺ
ለምንድነው ስለ ጄሪ ኮቫክ የጠየቅከኝ?” አለችው፡፡

“ህይወትሽን አትርፌልሻለሁ አይደል? ለዚህ ለዋልኩልሽ ውለታ አንቺም
ውላታ እንድትደውይልኝ እፈልጋለሁ”
“የምችለው ከሆነ ምን ችግር አለው ንገረኝ?” አለችው፡፡

ጆንሰንም ትኩር ብሎ እያያት ነገሩን እንዴት አድርጎ ሲያቀርብላት ሊያሳምናት እንደሚችል ሲያስብ ቆይቶ “ጄሪ ከወር በኋላ ይግባኙን ያቀርባል! እናም አንቺ ይግባኝ ችሎቱ ላይ ቀርበሽ ለእሱ እንድትመሰክሪለት እፈልጋለሁ።” አላት፡፡

ኒኪም ኮስተር ብላ “ችሎቱ ላይ መገኘት እችላለሁ ግን ለእሱ ልመሰከርለት አልችልም፡፡ አሁንም የበፊት አቋሜን ልቀይር አልችልም፡፡ ጄሪ ልጁን በሚደበድብበት ጊዜ ፍፁም ጤነኛ ነበር።” አለችው፡፡

ጆንስንም ራሱን በሀዘኔታ እየነቀነቀ “በቃ ለእናንተ ሁሉ ነገር ጥቁር እና ነጭ ነው አይደል? የእኛ የፖሊሶች ሥራ ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ? ማለቴ እናንተ በሰላም ወጥታችሁ እንድትገቡ በየቀኑ በሎስ አንጀለስ ጎዳናዎች ላይ ከእነዚህ ቆሻሻዎች ጋር የምናደርገው የዕለት ተዕለት ግብግባችን ይገባሻል? አየሽ ለእኛ ህይወት ግራጫ ናት።” አላት በጣም በስሜት ተሞልቶ፡፡

“ይቅርታ አዝናለሁ፤ ይህንን ላደርግልህ አልችልም” አለችው፡፡

“ህምም" አለና ጆንስን ትንሽ ቅሬታን እያሳየ “ይህንን እንደምትይኝ ጠብቄ ነበር። እንደርሱ ከሆነ እንግዲህ እኔም የ ኤፍ ቢ.አይ እርጉዟ ውሽማ የሚል ርዕስ የያዘውን የባልሽን ውሽማ ፋይል ላሳይሽ አልችም ማለት ነው” አላት እና አስተናጋጁን ጠርቶ 20 ዶላር ጠረጴዛ ላይ ካስቀመጠ በኋላ ጥሏት ወደ ካፌው በር መራመድ ጀመረ

ኒኪም “ቆይ አንዴ!” አለችው፡፡
ጆንሰን ግን ዝም ብሎ መራመዱን ቀጠለ፡፡

“እንዴ መርማሪ ጆንሰን እባክህን አንዴ!” ብላ ጮሃ ለመነችው።

እሱም ቆም አለና ወደ እሷ ዞሮ ፈገግ እያለ “እንዴ ምን ተፈጠረ? እሺ አሁን ህይወት ግራጫ መስላ ታየችሽ ደግሞ?” አላት በሹፈት ድምፅ፡፡

አሁን አግኝቷታል፡፡ መናደድ ወይም መሳቅ ይኑርባት አይኑርባት ግራ ገብቷታል፡፡ መሳቅን መረጠች እና ትንሽ ከሳቀች በኋላም

“እሺ የይግባኝ ችሎቱ ላይ እመጣና እመሰክራለሁ።”

“ጓደኛዬን ሙሉ በሙሉ ነፃ በሚያደርገው መልኩ ነው ምስክርነትሽን ለእሱ የምትሰጪው?” ብሎ ጆንሰን ጠየቃት፡፡
ሁሉም ነገር ዋጋ አለው፡፡ ምንም ነገር ደግሞ ማድረግ አትችልም። የጣውንቷን ሌንካ ጎርዴቪስኪ ማንነትን እና እንዴትስ ከባሏ ዶውግ ጋር እንደተዋወቀች፣ ለምንስ ብሎ ባሏ ዶውግ ከእሷ ምንም ሳያጣ ከሌንካ ጋር ሊተኛ የቻለበትን ምክንያት ለማወቅ ነፍሷንም ቢሆን ከመሸጥ ወደ ኋላ የማትመለሰው ኒኪ በጆንሰን ሀሳብ ተስማማች፡፡
እሱ በሌንካ ጎርዶቪስኪ ዙሪያ ኤፍ.ቢ.አይ ያጠናቀረውን ፋይል ሰጣት፡፡
ሌላ ፓን ኬክ አዝዞ እየበላ እያለ ኒኪ በአስር ደቂቃ ውስጥ ፋይሉን አንብባ ጨረሰች።

ቀና ብላ እያየችውም “ይሄ እኮ እኔ ማወቅ የምፈልጋቸውን ነገሮች ሁሉ አይነግረኝም አለችው።

“እንዴ ብዙ ነገር አለው እንጂ” አላት እና አፉን በናፕኪን ከጠረገ በኋላም “ሌንካ ለፊድሪጌዝ መጄመሪያውን የክሮክ ንጥረ ነገር ከሞስኮ የዕጭ ከበርቴ ነው ሰርቃ ያመጣችለት፡፡ የዛሬ አምስት ዓመትም በአንድ ፒተር በርግ ውስጥ በሚገኝ የአደንዛዥ ዕፅ አምራች ላይ መስክራ ስለ ነበር በፌድራሉ ፍርድ ቤት የምስክርነት ከለላ ተሰጣት እና ስሟን ለውጣ አሜሪካ
ውስጥ ገባች። ለዚያ ነው ያንቺ ዊሊያምስ ስለእሷ ማወቅ ያልቻለው። ስሟን ከመለወጧ በፊት ትጠራ የነበረው ናታሊያ ድሮቭስኪ በሚል ሥም ነበር።”
አላት፡፡

“እኔ ስለ ሥሟ ግድ የለኝም፡፡ እኔ ማወቅ የምፈልገው ከባሌ ጋር ስለነበራት ግንኙነት ነው::” ብላ በብስጭት ጠየቀችው፡፡

“ነገሩ እኮ ይገናኛል” አላትና ቀጠለ “ሌንካ ሮድሪጌዝን ከሩሲያ የአደንዛዥ ዕፅ አምራች እና አከፋፋዮች ጋር አስተዋወቀችው። ሎስ አንጀለስ ውስጥ
በዚህ የአደንዛዥ ዕፅ ዙሪያ የሚሰሩ ሰዎችን ታውቅም ስለነበር ቀላል ነገር
ሆኖላት ነበር፡፡ በሁለቱም በኩል ሆኖ መጫወት በጣም አደገኛ ነው።
ሩሲያኖቹ ቢዝነሳቸውን የሚያበላሽ ማንኛውንም ነገር አይወዱም።

“እና ሩሲያውያኖች ናቸው የባሌን መኪና አበላሽተው ሌንካን አብራው እንድትሞት ያደረጉት? ባሌም ከእሷ ጋር ስለነበረ ብቻ ነበር የሞተው እያልከኝ ነው?” ብላ እያፈጠጠች ጠየቀችው፡፡

“ያው ፋይሉን እንዳነበብሺው ነው ነገሩ እንግዲህ፡፡ ምናልባትም ባልሽ ከእሷ ጋር ስለነበረ ብቻ ይሆናል ለመሞት የበቃው። እኔ ግን አደጋውን ያደረሱት ሩሲያኖች ሳይሆኑ ሮድሪጌዝ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡” አላት፡፡

“እንዴ ሌንካ ለሮድሪጌዝ የምትሰራለት ከሆነ ለምን ይ...?” ብላ ኒኪ
ተናግራ ሳትጨርስ ጆንሰን አቋረጣት እና
“በቃ የአገልግሎት ጊዜዋ ስላበቃ እና ሮድሪጌዝም ክሮኩን በበቂ ሁኔታ
ማምረት ስለቻለ ነው:: ልክ ዊሉ ባደንን እንዳደረገው ማለት ነው እንግዲህ
ነገሩ፡፡ እሱን እንዴት እንዳስወገደው አይተሻል አይደል?”

ብሎ ሲነግራት ትውስታው መጣባት እና ዝግንን አላት፡፡

“ሮድሪጌዝ በምዕራብ ዳርቻ ያለውን የክሮክ ገበያ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮታል።” አላት እና ጆንሰን በመቀጠልም ጉድማን ደግሞ
የሩሲያውያኑን የክሮክ ቢዝነስ ጥርግ አድርጎ ከዚህ ከተማ ስላስወጣለት
ማንንም ክሮክ አቅራቢ አይፈልግም፡፡ ሜክሲኮ ሲቲ ውስጥ ኮኬይን
የሚያመርትበት የራሱ ትልቅ ላብራቶሪ አለው። በነገራችን ላይ ቻርሎቴ ክላንሲ ለመገደል የበቃችው ይህንን ላብራቶሪ ስላወቀች ነው፡፡ በመሆኑም ይህንን ላብራቶሪ ሙሉ በሙሉ ወደ
1👍1
#የተወጋ_ልብ


#ክፍል_ሃምሳ_አራት


#ድርሰት_በትክክል_ገና


...ባሏ ታደስ የሰውን የማይመኝ ከሰው የማይጠብቅ በራሱ የሚተማመን ኩሩ ባል መሆኑን ብቻ ነው፡፡ እንደዚህ ዛሬ በአይኗ እንዳየችውና ከአንደበቱ እንደምትሰማው የተበደለውን፣ የቆሰለውንና የደማውን ሰላማዊ
ህዝብ ለመካስ ቆርጦ የተነሳ ስለመሆኑ ምልክቱን ያየችው ገና ዛሬ ነው።

ታደሰ ብዙውን ጊዜ ይህንን ጉዳይ ሊገልጽላት እየፈለገ ህይወትህ አደጋ ላይ ትወድቃለች ይቅርብህ” ትለኛለች በሚል ሥጋት ነው የደበቃት፡፡ዛሬ ግን አጋጣሚው በተወሰነ መልኩ ራሱን እንዲያስተዋውቅ አደረገው።

“ይህ ሰው ምናልባት እኔ ሳላውቀው የመጽሐፍ ቅዱስ ሰባኪ ይሆን እንዴ?"አለች በልቧ። መደበኛ ስራው ድለላ መሆኑን ተጠራጠረች።
“ታዴ ከድለላ ሌላ የምትሰራው ስራ አለ እንዴ? ድለላ አንዱን እየጎዱ ሌላውን የመጥቀም ነገር የለበትም? ሸፍጥ የለበትም? ለመሆኑ በዚህ ፀባይህ የድለላ ስራን እንዴት ልትመርጠው ቻልክ?” ከሚነግራትና በተግባርም ካየችው ባህሪው የተነሳ የድለላ ስራው የሚያሳድርበትን ተፅእኖ
ለማወቅና ከዚያ ጣፋጭ አንደበቱ የሚወጡ ተጨማሪ ቃላትን ለመስ
ማት ጥያቄ ጫና አደረገችበት።

“ስላምዬ ስራዬ የምታውቂው ድለላ ነው። የድለላ ስራዬ ሻጭና ገዥ በሚያዋጣቸው ዋጋ እንዲገበያዩ በማድረግ ሁለቱንም ወገኖች አስደስቼ ለኔም የሚገባኝን ጥቅም ማግኘት ነውና በሽተኛን የሚፈውሰው ዶክተር፣
የእውቀት ጮራ የሚፈነጥቀው መምህር፣ የአገር ድንበር የሚጠብቀው ወታደር ሥራቸውን የሚወዱትን ያክል እኔም በእኔ የእውቀት ደረጃ የደላላነት ስራዬን እወዳታለሁ፡፡ ያልተገባ የድለላ ስራን በመስራት ሰዎችን መጉዳት ግን ለበጎ ህሊና ተቃራኒ ከመሆን አልፎ ከሰዎች ጋር የሚያጋጭ ነውና እንዳልሽው ጥንቃቄን የሚጠይቅ ስራ ለመሆኑ ጥርጥር
የለውም። ድለላን የመረጥኩት ግን በማንበብና በመፃፍ የትምህርት ደረጃ ዶክተር መሆን ስለማልችል ነው” እየሳቀ መለሰላት። ሰላማዊት ባሏ
ታደስ በማንበብና በመፃፍ የእውቀት ደረጃው የርቱእ አንደበት ባለቤት መሆኑ እያስደነቃት የበለጠ እንዲያወራላት ስሜቱን በመኮርኮር ልትሞግተው ፈለገች፡፡
“ታዴ ገዥና ሻጭ በድለላ ስራህ ሁሌም ደስተኛ ሊሆኑ አይችሉም::
እያየህ ዝም አትልም፡፡ በመሃል ገብተህ በተሻለ ዋጋ አገበያያለሁ ማለት የማይቀር ይሆናል፡፡ ያንን ስታደርግ ደግሞ በውድ ዋጋ ሊገዛ የነበረው ሰው ሲደሰትብህ በውድ ዋጋ ሊሸጥ የነበረው ሻጭ ባንተ ቅር ይሰኝብሃል አይደለም?” አለችው። ታደሰ የሚስቱን የመከራከሪያ ነጥብ ስለወደደው
ለጠየቀችው ጥያቄ መልስ በመስጠት ሊያሳምናት ፈለገ፡፡

“በእርግጥ ሁሉም አይነት ስራ ሁሉንም ወገን እኩል የሚያስደስት ነው ብዬ ልከራከርሽ አልችልም፡፡ በጣም በርካሽ ዋጋ የሚገዛ ሰው ሻጨን ጎድቶ ነው የሚገዛው። በውድ ዋጋ የሚሸጠውም ገዢውን ጎድቶ ነው የሚሽጠው። በዚህ ጊዜ ሚዛን ማስጠበቅና ማካካስ ያስፈልጋል። በጣምም
ሳይወደድ፣ በጣምም ሳይረክስ፡፡ የኔ ስራ ሰዎች ተካክሰው ሳይጎዳዱ እንዲጠቃቀሙ ማድረግ ነው። ስራዬ ሻጭና ገዢ አሸናፊ የሚሆኑበትን መንገድ በማመቻቸት ሚዛኑን ማስጠበቅ ነው። የድለላ ስራ የሚያስጠላው ተዋዋይ ወገኖችን የሚጎዳ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ሲባል
ሽፍጥ የተቀላቀለበት ሲሆን ነው። አይመስልሽም ?" አላት።

“ታዴ ሁሉንም ወገን እኩል የሚያስደስት ስራ እንደዚህ በቀላሉ የሚገኝ ይመስልሃል? ዳኛው ፍርድ ሲፈርድ እንኳ የተፈረደለት የሚደሰተውን
ያክል የተፈረደበት መከፋቱ የማይቀር ነው። ጠበቃው የሚጣላ፣ የሚደባደብ፣ የሚፋታ፣ የሚፈናከት በአጠቃላይ የሚካሰስ የጠፋ እንደሆነ አዝኖ ገበያዬ ቀዘቀዘ ይላል፡፡ የሬሳ ሳጥን ሻጩም ሰው ሞቶ የሰራው
ሳጥን ቶሎ ቶሎ ካልተሽጠለት ገበያ ጠፋ ብሎ ማዘኑ አይቀርም፡፡ እንዲያውም በነገራችን ላይ ስለ ሬሳ ሳጥን ሻጩ የሰማሁትን የሚያስቅ ነገር ልንገርህ፡፡ ስውዬው ዘመድ ሲሞትበት ሁል ጊዜ የሬሳ ሳጥን የሚገዛው
ከአንድ ቋሚ ደንበኛው ነበር አሉ፡፡ የሬሳ ሳጥን ሻጩ የዚህ የቋሚ ደንበኛው ውለታ ይከብደውና ሊክስው ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሀል እናት ይሞቱበትና ሳጥን ለመግዛት ሲመጣ የሬሳ ሳጥን ሻጩ ውለታውን ለመክፈል አስቦ በትልቁ ሳጥን ላይ አንድ ትንሽ የሬሳ ሳጥን ያስቀምጥለታል።
ሰውዬው ግራ ተጋብቶ ይሄ ደግሞ ምን ያደርግልኛል? ብሎ ቢጠይቀው ግድ የለም ጋሽዬ የዚህን ያክል ዘመን ደንበኛዬ ሆነው አንድ ቀን እንኳ
ክሼዎት አላውቅምና እሷን ደግሞ ለልጅዎ እንዲያደርጓት ምርቃት ነች አለና መለሰለት" ታደሰ በሳቅ ፍርስ አለ። “ሰላምዬ በጣም ያስቃል። ግን ምን ታደርጊዋለሽ የዓለም ነገር ይኸው ነው። ሳጥን ሻጩ ውለታ መክፈሉን እንጂ ልጅህን ይግደልልህ ማለቱን አላሰበውም። እሱ የታየው
በልጁ ሞት ምክንያት ደንበኛው የሚደርስበትን ሀዘን ሳይሆን ቋሚ ደንበኛውን መካሱንና ደንበኛነቱን ማጠናከሩን ብቻ ነው"እንደዚህ እየተጨዋወቱ ከቆዩ በኋላ ተቃቅፈው ወደ ጓዳ ገቡ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ያቺ በናፍቆት የተጠበቀችው የፋሲካ በዓል ደረሰች። ታደሰና ሰላማዊትም በደስታ ሊቀበሏት ሽር ጉድ ሲሉ የከረሙላት፣ በለሊት ተነስተው የሚጐራረሱባት ዕለት ከተፍ አለች።
“ታድዬ...ተነስ...ዶሮ ጮኋል” አለችው። እስከ እኩለ ለሊት ዶሮ
ወጡን ስትስራ ቆይታ እንቅልፍ ሳይወጣላት ነበር የመፈሰኪያው ስዓት የደረሰው።
“ከምንጊዜው ሰላምዬ? ትንሽ እንኳን ሳንተኛ?" እሱም በቂ እንቅልፍ አላገኘም ነበር። በአንዳንድ ነገር ሲያግዛት ነው ያመሸው። ከአልጋቸው ላይ ተነስተው እየተጉራረሱ ፆም ይፈቱ ጀመር።
“ይሄኔ..” አለ ታደሰ።
“ይሄኔ ምን?” ወደ ጐን በፍቅር እያየች ጠየቀችው።
“እንትን...” ሳቅ አለና ሆዷን ተመለከተ።
“ገባኝ” እሱን ተከትላ እየሳቀች።
አንድ አድማቂ የመሀል አጫዋች፣ሌላ ፍቅርን የሚጨምር ፀጋ በመካከላችን ቢኖር ኖሮ ፋሲካው የበለጠ ፋሲካ ደስታው የበለጠ ደስታ ፍቅሩም የበለጠ ፍቅር ይሆን ነበር ማለቱ እንደሆነ ገባት ።
“እሱማ የዛሬ ዓመት ነዋ ታዴ?”
በሚቀጥለው ዓመት በዛሬዋ ቀን ፋሲካን ሲፈስኩ ድንቡሽቡሽ ያለ ልጅ ወልደው መጪዋን ፋሲካ በድምቀት እንደሚቀበሏት በምኞት ተጨዋወቱ፡፡ ሰላማዊት የወር አበባዋ ከቀረ ውሎ አድሯል። ማቅለሽለሽና ማስመለስ እያዘወተራት ነው። ታደሰ ይሄ ሁኔታ እርግዝና መሆኑን ካወቀ
በኋላ ልጅ የማግኘት ጉጉቱ በጣም ከፍተኛ ሆኗል። ዛሬም ይሄኔ...
የሚላት አንድ ልጅ በመካከላችን ቢኖር ደስታው ድርብ በአሉም በእጥፍ ደማቅ ይሆንልን ነበር ማለቱ ነበር፡፡
“ታዴ ወንድ ነው ወይንስ ሴት ብወልድ ደስ የሚልህ?“
“ስላምዬ ማሚቱም ማሙሽም ተወዳጅ የአምላክ ስጦታዎች
ናቸው። ሰው ነንና አንዳንድ ጊዜ ማሙሽን ከማሚቱ ማሚቱን ከማሙሽ የምንመርጥበት ጊዜ ይኖራል። ብዙውን ጊዜ እናት ሴት ልጅ ለመውለድ ትፈልጋለች፡፡ አባት ደግሞ ለወንድ ልጅ ያደላል ለምን እንደሆነ ግን አይገባኝም።
እኔ እንጃ ታዴ እኔ ግን አሁን አንተ እንዳልከው ሴት ልጅ ብወልድ ደስታውን አልችለውም”
እንደሱ ካልሽ እኔ ደግሞ ወንድ ልጅ ብትወልጅልኝ ደስታውን
👍53
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ሃምሳ_አራት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

....በቀድሞው የዲላ ከተማ አውቶብስ መናኸሪያ ፊትለፊት በግምት በሀምሳ ሜትሮች ርቆ ከታች በስተምዕራብ በኩል የሚገኘው «አባይ ፏፏቴ ሆቴል በዕለተ እሁድ ምሽት ለዘወትር ደንበኞች ዝግ ሆኖ ለየት ያሉ እንግዶች ሊስተናገዱበት ተዘጋጅቷል፡፡ ለክብር እንግዶች የተዘጋጀው መድረክ የተለያዩ
ቀለማት ባሏችው መብራቶች አጊጧል፡፡የድግሱ ታዳሚዎች ከመድረኩ ፊትለፊት በተዘጋጀላቸው ወንበርና ጠረጴዛ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ ከታዳሚዎቹ
መሀል የሚበዙት የፖሊስ ሰራዊት አባላት ናቸው። መለዮ የለበሱት
ይበልጣሉ፡፡ ጠረጴዛዎቻቸው በነጭ ጨርቅና በላስቲክ ተሸፍነው ያልተከፈቱ
የቢራ ጠርሙሶች ተደርድረውባቸዋል አስተናጋጆች የመስተንግዶ ስራቸውን
ለማከናወን ጥግ ጥግ ይዘዋል:: በትላልቅ ድምጽ ማጉያዎች የሚለቀቀው ሙዚቃ አዳራሹን ያነቃንቀዋል፡፡ የድግሱ ታዳሚዎች ፊትለፊት በመድረኩ
ላይ የተዘረጋውን ልዩ ሶፋ እየተመለከቱ የክብር እንግዶችን ይጠባበቃሉ፡፡ልክ ከምሽቱ አስራ ሁለት ሠዓት ተኩል ላይ
ሙዚቃው ድንገት ቆመ:: በሙዚቃው ጩኸት ውስጥ እየተጨዋወቱ ይሳሳቁ የነበሩ እንግዶች ዝም ዝም አሉ፡፡ ቤቱ ፀጥ ረጭ አለ፡፡ ወዲያው አንድ የዝግጅት አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሳይሆን የማይቀር ጠየም ያለ ልጅ እግር ሰው ከሆቴሉ ጓዳ በኩል ወጥቶ ወደ መድረኩ ወጣ።
«እንዴት ዋላችሁ እንግዶቻችን?» አለ ፈገግ ባለ ሁኔታ እጆቹን
እያፍተለተለና በሆቴሉ ውስጥ የታደሙ እንግዶችን በሙሉ በዓይኑ እየቃኘ፡፡
«እግዚአብሔር ይመስገን!» የሚል ምላሽ ተሰጠው ከታዳሚዎቹ፡፡
«በቅድሚያ ጥሪያችንን አክብራችሁ ጊዜያችሁን መስዋት አድርጋችሁ በዚች ሰዓትና ቦታ ስለተገኛችሁልን በዕለቱ የክብር እንግዳና በዝግጅት አስተባባሪ ኮሚቴ ስም ምስጋናዬን ማቅረብ እወዳለሁ፡፡»
ከታዳሚዎቹ በኩል ሞቅ ያለ ጭብጨባ ተቀበለው::
«አመሰግናለሁ፡፡» አለና «ዛሬ በዚች ሠዓትና ቦታ የመገናኘታችን
ዓላማ ለሁላችንም ግልጽ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ሰዎች በአንድ ወይም በሌላ አጋጣሚ ይተዋወቃሉ:: የትውውቁ መሰረት በአንድ አካባቢ መኖር፡ የስራ
ባህሪና ቦታ፣ ወይም ሌላ ሌላም ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን መተዋወቅና መግባባት ወይም መዋደድ እንዳለ ሁሉ በሆነ አጋጣሚ መለያየትም ይኖራል፡፡
የመለያያው መንገድና ዓይነትም እንደዚሁ ብዙ ነው፡፡ በጠብና በጥላቻ፣ በሞት በስራ ዝውውር... ወዘተ ሊሆን ይችላል፡፡ በአጠቃላይ በደስታም በሀዘንም
የተዋወቁና የተዋደዱ ሰዎች ሊለያዩ ይችላሉ::
«ዛሬ ልናከብረው የተዘጋጀነው የመለያየት በዓል ግን የሰላምና የደስታ ነው፡፡ አንድ የስራ ባልደረባችን ዕድገትና ሹመት አግኝቶ ከመካከላችን
በመለየት ወደ ሌላ አካባቢ ሊሄድ ስለመሆኑ ሁላችንም እናውቃለንና እስቲ ስለወንድማችን ደስታ መግለጫ ይሆን ዘንድ ሁላችንም እንዴ እናጨብጭብ»
ሲል በፈገግታ ዓይን እያየ ታዳሚዎቹን ጠየቃቸው።
አሁንም ሞቅ ያለ ጭብጨባ ተቀበለው::
“አመሰግናለሁ፡፡ ከዚህ ቀጥሉ የክብር እንግዳችን ከቅርብ ዘመድ
ወዳጆች ጋር በመሆን እየመጣ ስለሆነ ወደ መድረኩ በሚያልፍበት ሰዓት ሁላችንም ከተቀመጥንበት ብድግ በማለት በጭብጨባ እንድንቀበለው እያሳሰብኩ በኔ በኩል የመክፈቻ ንግግሬን እዚህ ላይ አበቃለሁ፡፡አመሰግናለሁ፡፡» በማለት እጅ ነስቶ ወደ መጣበት አቅጣጫ ተመለሰ፡፡
የድግሱ ታዳሚዎች የክብር እንግዳውን በዓይናቸው የሚጠብቁት ከውጭ በር በኩል ነበር፡፡ ነገር ግን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በዚያ የመክፈቻ
ንግግር ባደረገው ሰው እየተመራ ከወደ ጓዳ በኩል ድንገት ብቅ አለ፡፡ የክብር እንግዳው የሀምሳ አለቃ መኮንን ዳርጌ ነው፡፡ የምክትል መቶ አለቅነትና
የወላይታ አውራጃ ፖሊስ አዛዥነት ሹመት እግኝቶ ሊሄድ ነው፡፡ ድግሱም እሱኑ ለመሸኘት ነው።
የቀድሞው የሀምሳ አለቃ፡ ዛሬ ግን የምክትል መቶ አለቅነት ማዕረጉን
መለዮ ለብሶ ከአስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢው ኋላ ተከትሎ ብቅ ሲል ታዳሚዎች በሙሉ ከተቀመጡበት ብድግ በማለት በማያቋርጥ ጭብጨባ ተቀበሉት፡፡
ከእሱ ኋላ ነጫጭ የሀገር ልብሷን ለብሳ እንቁጣጣሽ የመሰለችው ታፈሡ እንግዳሰው! ቀጥላ ሔዋን: ከእሷ ኋላ ደግሞ መርዕድ እሽቱ በመሆን ተከታተሉ፡፡ ሁሉም ለታዳሚዎች የጭብጨባ አቀባበል እጅ እየነሱ ወደ
መድረኩ አመሩ፡፡ ምክትል የመቶ አለቃ መኮንን ዳርጌ እና ታፈሡ ጎን ለጎን እንዲሁም ሔዋን ከታፈሡ ቀኝ በኩል፣ መርዕድ ደግሞ ከምክትል መቶ አለቃ
መኮንን ዳርጌ ግራ ጎን በመቆም ታዳሚዎች እንዲቀመጡ ጋበዙ፡፡ ታዳሚዎች ጭብጨባቸውን አቁመው ሲቀመጡ የክብር እንግዶችም በየቆሙበት አቅጣጫ ተቀመጡ፡፡ ሙዚቃው ተለቀቀ፡፡ አስተናጋጆችና የድግሱ አስተባባሪዎች በታዳሚዎች ፊት ተቀምጠው የነበሩ ጠርሙሶችን መክፈት ጀመሩ፡፡ መስተንግዶው ጦፈ፡፡
በርካታ የድግሱ ታዳሚዎች ታፈሡንና መርዕድን በከተማ ውስጥ ያውቋቸዋል፡፡ ሔዋንን ግን እንኳንስ በውል የሚያውቃት በዓይኑም ዓይቷት የሚያውቅ ስለመሆኑ ኣንድም ታዳሚ እርግጠኛ አልነበረም፡፡ ከሁሉም በላይ ታዳሚዎቹን ያስደነቃቸው በምን ምክንያትና ሰበብ ታፈሡና መርዕድ የምክትል መቶ አለቃ መኮንን ዳርጌ የቅርብ ዘመድ ወዳጆች ሊሆኑ እንደቻሉ
ነው፡፡ ያም ሆኖ ሁሉም በየሆዳቸው 'ወይ ጉድ! የሰው ዘሩና የግንኙነት መስመሩ እኮ አይታወቅም በማለት በግርምት አለፉት፡፡
የግብዣው ሥነ-ሥርዓት ቀጠለና በምክትል መቶ አለቃ መኮንን ዳርጌ ቀዳሚነት፡ በእነታፈሡ ቀጣይነት የብፌ ምግብ መነሳት ጀመረ፡፡ ታዳሚዎችም
በየአቀማመጥ ቅደም ተከተላቸው ተከታትለው ምግብ አነሱ፡፡ እራት መበላት ተጀመረ፡፡ የመጠጡ ግብዣም ተከታተለ፡፡ ምግብ ተበልቶ አብቅቶ፡ ሳህኖች
ከየጠረጴዛው ላይ ተነስተው: ጠረጴዛዎች በአስተናጋጆች ተወልውለው ካበቁ በኋላ መጠጡ ጭውውቱና የመዚቃው ጩኸት በቀጠለበት ሰዓት አሁንም
ለሁለተኛ ጊዜ ሙዚቃው ድንገት ቆመ፡፡ የታዳሚዎችም ወሬና ጫጫታ ወድያው ቆመና አዳራሹ ፀጥ ረጭ አለ ሰዓቱ በግምት ከምሽቱ ሁለት ተኩል አካባቢ ይሆናል፡፡ አሁንም ያ የመክፈቻ ንግግር ያደረገው ሰው ወደ መድረኩ ሲራመድ ታየ፡፡ ቀድሞ እንዳደረገው ሁለ ከታዳሚዎች ፊትለፊት በመቆም ታዴሚዎችን በፈገግታ እያየ።
«የተከበራችሁ እንግዶቻችን» ሲል ጀመረ፡፡ «ቀደም ሲል በመክፈቻ
ንግግሬ ላይ እንደጠቀስኩት የዛሬው ጉዳያችን የስራ ባልደረባችን የሆነው የቀድሞው የሃምሳ አለቃ ዛሬ ደግሞ...» እያለ ንግግሩን ጎተት በማድረግ ወደ
ኋላው ዞሮ ምክትል መቶ አለቃን ሳቅ እያለ ሲያይ ታዳሚውም ምክትል መቶ አለቃ መኮንን ዳርጌና እነታፈሡም ሳቁ።
«አፍሬም ፈርቼም ነው እኮ» አለ በመቀለድ ዓይነት::
ሳቅና ጭብጨባ ከታዳሚዎች ተቸረው፡፡
«አመስግናለሁ።» ብሎ እጅ ከነሳ በኋላ «በቀጣይ ሁለት ፕሮግራሞች አሉን፡፡ በመጀመሪያ የምንወደውና የምናከብረው ጓደኛችንና የስራ ባልደረባችን
ከመካከላችን ተለይቶ ሲሄድ ማስታወሻችን ያደርጋት ዘንድ ያዘጋጀንለትን ስጦታ ማበርከትና ከዚያ ቀጥሎም ምክትል መቶ አለቃ መኮንን ዳርጌ ስለ አግኘው
የማዕረግ ዕድገትና ሹመት እንዲሁም ከእኛ ከወዳጆቹ በመለየቱ ያደረበትን ስሜት አጠር ባለ ሁኔታ የሚገለጽበት ፕሮግራሞች ናቸው። በዚሁ ቅደም ተከተል ማከናወን እንዲቻል የአውራጃችን ፖሊስ አዛዥ የሆኑት መቶ አለቃ ብዙአየሁ አስራት ስጦታዋን እንዲያበረክቱልንና ምክትል መቶ አለቃም ወደ መድረኩ ጫፍ ቀረብ ብሎ እንዲቀበልልን ሁለቱንም እጋብዛለሁ። አመሰግናለሁ፡፡» ብሎ ከመድረኩ ወረደ።
👍113🔥1
#ምንዱባን


#ክፍል_ሃምሳ_አራት


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

ደክሞ የጨለመው ውጋጋን ሲፈካ

በሚቀጥለው ቀን ዣን ቫልዣ ከነኮዜት ቤት ሲሄድ ዘበኛው ትእዛዝ የተሰጠው ይመስል ከበራፍ ቆሞ ጠብቆት ወደ ምድር ቤት ይዞት ሄደ:: ዣን ቫልዣ በጣም ደክሞታል ባለፉት ጥቂት ቀናት እህል አልቀመሰም፤ብዙም እንቅልፍ አልተኛም:

ከጥቂት ጊዜ በኋላ ኮዜት መጥታ ‹ሰላምታ» ስትሰጠው ዞር ብሎ
በማፍጠጥ አያት
‹‹ምነው አባባ፣ ሰሞኑን ደስ አላለህም? ምነው ይህን ጨለማ ቤት መረጥክ! ከዚህ ለመሆን እንደፈለግህ ማሪየስ ነግሮኛል »
«አዎን፣ ነግሬዋለሁ፡፡››
«ትስመኛለህ ብዬ ጉንጬን ሳቀርብ ፊትህን አዞርክብኝሳ? እስቲ አሁን
ሳመኝ:»
እንደመጀመሪያው አሁንም ፊቱን አዞረባት እንጂ አልሳማትም::
«አሁን የከበደው መጣ» አለች ኮዜት እንደመቀለድ ብላ:፡ «ምን አደረግሁ? ግራ ነው የገባኝ፡ ለዚህ ማካካሻ እራት ከእኛ ጋር መብላት አለብህ::››
«በልቼአለሁ:»
«ውሸት ነው፡፡ ና እባክህ፤ አሁኑኑ ወደ ምግብ ቤት እንሂድ»
«አልችልም »
ኮዜት ጨነቃትና በትእዛዝ መልክ ከማናገር ቆጠብ አለች
ለምንግን? እንድንገናኝበት የመረጥከው ክፍል አስቀያሚ ክፍል
ስለሆነ አስጠላህ?»
«ሰማሽ እመቤቴ፧ ታውቂኛለሽ‥ ጠባዬ ከሰው አይገጥምም::›
«እመቤቴ! ይሁና!»
«እመቤቴ መባልን ፈለግሽ: ይኸው አገኘሽው:»
«እመቤትነቴ ለአንተ አይደለማ!»
«ከአሁን በኋላ አባባ እያልሽ ባትጠሪኝ መልካም ነው»
«ምን?»
«መሴይ ዣን ቫልዣ ብለሽ ጥሪኝ፤ ከፈለግሽ ዣንም ይበቃል»
«በቃ ከአሁን በኋላ አባቴ አይደለህም ማለት ነው? እኔም ከአሁን
ወዲያ ልጅህ ኮዜት አይደለሁም ማለት ነው? ይህ ምን ማለት ነው? ምነው
ጠላኸኝ? መከራ ውስጥ ነው የዘፈቅኸኝ:»

በድንገት ኮስተርተር ብላ ዣን ቫልዣ ላይ አፈጠጠችበት:

እያፈጠጠችም የሚከተለውን ቀጥላ ጠየቀችው::
«እኔን ደስ ሲለኝ አትወድም ማለት ነው?»
አንዳንድ ጊዜ አንድ ሰው የአነጋገር ዘይቤ ሳያውቅ ቀርቶ እንዳመጣለት ሲናገር ንግግሩ አጥንት ሰብሮ ይገባል፡ ይህ ጥያቄ ለኮዜት ቀላል ቢመስልም
ለዣን ቫልዣ ከአሜከላ የበለጠ የሚዋጋ ነበር፡ ኮዜት እሰፋለሁ ብላ ተረተረች:: የዣን ቫልዣ ፊት በድንጋጤ አመድ መሰለ፡፡ ለጥቂት ጊዜ ለጥያቄው መልሰ ሳይሰጥ ዝም አለ፡፡ በመጨረሻ በቃላት ሊገልጽ በማይቻል የአነጋገር ስልት በጣም ዝግ ብሎ እርሱ በራሱ ይነጋገር ይመስል
በማጉረምረም ተናገረ::

«የእርስዋ ደስታ የሕይወቴ ግብ ነበር፡ አሁንስ እግዜር ቢወስደኝ ይሻላል፡ ኮዜት ደስ ብሎሻል፡ ከአሁን በኋላ በቃኝ»

«ጎሽ 'ኮዜት ብለህ ነው እኮ የጠራኸኝ: 'እመቤት አላልክም» ስትል ጮኸች:: ዘልላ ከአንገቱ ላይ ተጠመጠመች::
ዣን ቫልዣ የሚያደርገውን ቢያጣ ጭምቅ አድርጎ አቀፋት፡፡ ወደ ቤቱ መልሶ የሚወስዳት መሰለው
«እግዚአብሔር ይስጥልኝ፣ አባዬ» አለችው፡፡
ዣን ቫልዣ ቀስ ብሎ ራሱን ካላቀቀ በኋላ ቆቡን አነሳ፡
«እና!» አለች ኮዜት
«ልሂድ» አለ ዣን ቫልዣ ፧ «ይጠብቁሻል ኮዜት» በሩ አጠገብ ሲደርስ መለስ ብሎ ኮዜት ብዬ ጠራሁሽ እኮ ሁለተኛ እንደማይደገምና ይቅርታም እንደጠየቅሁ ለባልሽ ንገሪው፡፡›
ዣን ቫልዣ ወጥቶ ሄደ ኮዜት ከቆመችበት ፈዝዛ ቀረች በሚቀጥለው ቀን በዚያቹ ሰዓት ዣን ቫልዣ ተመልሶ መጣ: ኮዜት
ግን ነገር አላበዛችበትም: መሴይ ዣን» ወይም «አባባ» ብላ ላለመጥራት
ጥንቃቄ አደረገች የፈለገውን እንዲናገር እድል ሰጠችው፡ ማዘንዋንም ላለማሳየት ሞከረች

ምናልባት ከማሪየስ ጋር ስለ ዣንቫልዣ ተነጋግረ ይሆናል:: ሆኖም የሚወዱት ወንድ ቢቀባጥርና ያፈቀደውን ቢናገር ብልጫና ፍሬ ያለው ንግግር እንደተናገረ በመቁጠር በቀላሉ እንደሚረኩበት ሁሉ ያፈቀረችውም ሴት እንዲሁ በቀላሉ ስለምትታለል እርስ በርስ በመተማመን በንግግራቸው ብዙም አልተጨቃጨቁ ይሆናል የፍቅረኞች የማወቅ ጉጉት ከፍቅራቸው አያልፍምና::

በዚህ ዓይነት ብዙ ሳምንቶች አለፉ ዣን ቫልዣ በየቀኑ እየመጣ ዓይንዋን ብቻ አይቶ ይሄዳል: ኮዜት ግን ሀዘንዋ እየቀለላት መጣ እንጂ
ለዣን ቫል የነበራት ፍቅር አልተቀነሶም ዓይንዋን ማየት ዣን ቫልዣን
ያረካዋል አንድ ቀን እንደለመደው ከነኮዜት ቤት ሲመጣ ኮዜት በመርሳት
«አባባ» ስትል ጠራችው:: እርሱ መልሶ «ዣን ይላታል፡ «ይቅርታ፣
መሴይዣን» ትለዋለች እየሳቀች: «ልክ ነሽ» ብሎ ከመለሰላት በኋላ
እንባው ሲወርድ እንዳታየው ፊቱን ወደ መስኮት አዙሮ እንደመናፈጥ
በማለት እንባውን ይጠራርጋል
ዣን ቫልዣ በመጣ ቁጥር ዘወትር ከሚገባበት ክፍል እሳት ተቀጣጥሎ
ነበር የሚጠብቀው: አንድ ቀን ሲመጣ እሳቱ ሳይቀጣጠል ይቀራል: ቆይቶ
ደግሞ በሌላ ቀን ሲመጣ ይቀመጥበት የነበረው ወንበር ከቦታው ይነሳል
በሌላ ቀን ከክፍሉ ውስጥ ጨርሶ ወንበር አይቀመጥም፡ በዚህ ጊዜ
እንዳልተፈለገ ገባው፡ ኮዜት «ለምን እሳቱ አልተያያዘም? ወንበሮቹስ የት ሄዱ? ብላ ስትጠይቅ ዣን ቫልዣ እኔ አዝዤ ነው» ይላታል በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ከነኮዜት ቤት ሳይመጣ ቀረ፡ ኮዜት ሰው
ከቤቱ ላከች::
‹‹ምነው ትናንት ሳትመጣ ቀረህ?» ብለዋል እመቤቴ
«ከትናንት ወዲያም አልመጣሁም» አለ ሳቅ እያለ ሠራተኛዋ አልገባትም፡ ስትመለስ ከ ዣን ቫልዣ ደኅንነት በስተቀር
ለኮዜት ሌላ ነገር አልነገረቻትም


በ1833 ዓ.ም መጀመሪያ አጋማሽ ፓሪስ ከተማ ውስጥ ማሬይ ከተባለ ቀበሌ አካባቢ የሚኖሩ ባለሱቆችና ቦዘኔዎች አንድ ነገር ያያለዘሉ:: አንድ ከወገቡ የጎበጠ፣ ከፀጉሩ የሸበተ ሽማግሌ በየቀኑ በተወሰነ ሰዓት ሽርሽር ይወጣል:: የሚሄድበት መንገድ አንድ ሆኖ ሳለ የሚሸፍነው ርቀት ግን በየቀኑ በትንሽ በትንሹ ይቀንሳል የሚራመደው በጣም ዝግ ብሉ ሲሆን አንድም ቀን ግራና ቀኝ ሳያይ እንዳቀረቀረ ወደፊት ነው የሚጓዘው
አንድ ከተወሰነ ስፍራ ሲደርስ ፊቱ ወገግ ይልና እርስ በራሱ ብቻውን ያወራል ማውራቱን ለማወቅ የሚቻለው ከንፈሮቹ ሲነቃነቁ ነው: ካልቬር ከተባለ ጎዳና ላይ ከሚገኝ አደባባይ ሲደርስ ቆም ይልና አካባቢውን ይቃኛል
" አካባቢውን ቃኝቶ ከጨረሰ በኋላ በአሳብ ተውጦ ዓይኑ እንባ ያቀርራል:
ጥቂት ካለቀሰ በኋላ በመጣበት መንገድ ይመለሳል

ቀን እያለፈ ሲሄድ አደባባዩን በሩቁ ማየት እንጂ ከእዚያ ለመድረስ አልቻለም፡ ሰውነቱ እየደከመ ሄደ:፡ ወደኋላማ ወደ አደባባዩ መጠምዘዣ መድረስ እንኳን ተሳነው፡፡ በየቀኑ በዚህ ዓይነት በተወሰነ ሰዓት ከቤቱ እየወጣ ጉልበቱ እስከፈቀደለት ድረስ ተጉዞ ይመለሳል፡፡ ዝናብ ሲሆን ጥላ ይይዛል፡ ብርድ ሲሆን ካፖርት ይለብሳል፡ የሚሸፍነው ርቀት ባጠረ ቁጥር ከደረሰበት ቆም ይልና አንገቱን ከነቀነቀ በኋላ ግራ ቀኙን ተመልክቶ ይመለሳል፡፡ ከጊዜ በኋላ የተቀነሰው መንገዱ ብቻ አልነበረም፤ የእንባውም ዘለላ ተቀነሰ፡ በመጨረሻ እስከነአካቴው ዓይኑ ደርቆ ለማልቀስ ቢፈልግም እምባ አይወጣውም:፡ በየእለቱ ሽማግሌው ብቅ ሲል አንዲት አሮጊት «የሚገርም ነው‥ ሰዓቱን ጠብቆ ይመጣል፣ አይቀራትም መቼም» ይላሉ፡
ከተወሰነ ነጥብ ሲደርስ ደግሞ ልጆች እየሳቁ ይከተሉታል

አንድ ቀን ዣን ቫልዣ ከቤቱ ወጥቶ ከዋናው ጎዳና ሲደርስ ሦስት
እርምጃ ወደፊት ከተራመደ በኋላ ከድንጋይ ላይ ቁጭ አለ፡፡ ሰኔ 5 ቀን
ከዚህች ድንጋይ ላይ ቁጭ ብሎ ነው ጋቭሮችን ያነጋገረው:፡ ጥቂት አወጣ፣
አወረደና ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ ከዚያ በኋላ ለሽርሽር መውጣት አልቻለም::
በሚቀጥለው ቀን ከክፍሉም አልወጣም:: አሁንም በሚቀጥለው ቀን ከአልጋው አልተነሳም::
👍16
#ሳቤላ


#ክፍል_ሃምሳ_አራት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ትናንት ማታውን ሚስተር ካርላይል ትክ ብሎ ሲያስተውላት ነበርና አሁን
እንዳያውቃት ሰጋች " በበነጋው ጧት ሳቤላ ወደ ሳሎኑ የሚወስደውን መንገድ ከሚስተር ካርላይል ነጻ መሆኑን ለማረጋገጥ ከመኝታ ቤቷ በር ቁማ ታዳምጥ ጀመር
ሚስተር ካርላይልን ከምንጊዜም የበለጠ ወደደችው » እሱ ደግሞ የሌላይቱ ባል ስለሆነ ተንግዲህ እሱን አጥብቆ ማየቱ ከነውር የሚቆጠር መሆኑን በማሰብ ጭምር
ነበር እንዳታየው የፈራችው

እሷ በዚህ ሁኔታ ቁማ ሳለች መደ አምስት ዓመት የሚገመት አንድ ቆንጆ ልጅ
መጣ" የማድ ቤት መጥረጊያ በሁለቱ ጭኖቹ መኻል አድርጎ እንደ ፈረስ እየጋለበ በኮሪዶሩ በኩል ደረሰ ልጅዋ አርኪባልድ ለመሆኑ አስተዋዋቂ አላስፈለጋትም ሚስተር ካርላይልን ቁርጥ ነው መልኩ ልትቋቋመው ባልቻለችው የስሜት ግፊት
ተደፋፍራ እንዲያ ሶምሶማ እየረግጠ ዐልፋት ሊሔድ ሲል ከነመጥረጊያው እቅፍ
አድርጋ ወደ ክፍሏ ወሰደችው።

“ከአንተ ጋር እንድተዋወቅ ያስፈልጋል” አለችው እንደ ማባበል አድርጋ ትንንሽ ልጆችን እወዳለሁ።

ከአንድ ትንሽ ወንበር ላይ ተቀመጠች » ልጁን ጭኗ ላይ አስቀምጣ መላልሳ
ሳመችው " እንባዋ እንደ ምንጭ ውሃ መውረድ ጀመረ " በምንም መንገድ ልትገታው አልቻለችም መሳሙንም መተው አልሆነላትም ቀና ብላ ስታይ ዊልሰንን አየቻት " ስትገባ አልሰማቻትም » ሳቤላ ልክ ራሷን እንዳጋለጠች ሆኖ ተሰማት አሁን እንግዲህ አንድ የሆነ ምክንያት መስጠት ነበረባት

ልጆቼን አስታውሶኝ እኮ ነው አለቻት ለዊልሰን ይተናነቃት የነበረውን የስሜት ፍላት ለመዋጥ እየታገለች በተቻላት መጠን እንባዋን ለመደበቅ ተጣጣረች » ነገሩ የገረመው አርኪባልድ ጣቱን እየጠባ ዐይኖቹን አፍጥጦ ትልቁን ሰማያዊ መነጽሯ ይመለከት ጀመር።

“የወለድናቸውን ስናጣ ካጠገባችን የምናያቸውን ለመውደድ እንገደዳለን”
አለች ሳቤላ "

ዊልሰን ይህች አዲሲቱ የልጆች አስተማሪ ድንገተኛ ዕብደት ያልደረሰባት
መሆኑን ለማረጋገጥ ብላ አስተዋለቻት ከዚያ ወደ አርኪባልድ መለስ ብላ አንተ
ባለጌ እንዴት አባክ ብትደፍር ነው የሳራን መጥረጊያ ይዘህ የምትሮጠው ? የለም
የለም ዕብደቱን እያበዛኸው መጥተሃል ቆይ ለእእማማ ባልናገርልህ ” አለችና ጭምድድ አድርጋ ይዛ ደጋግማ ናጠችው " ሳቤላ እጆቿን ሽቅብ አንሥታ እያራገበች “ተይ ተይ እባክሽ አትምቺው ! ሲመታ ላየው አልችልም !” ብላ በሚያሳዝንና ልብ
በሚነካ ድምፅ ቁማ ለመነቻት "

"ሲመታ !” ብላ ጮኽች ዊልሰን በደንብ ቢገረፍማ ይሻለው ነበር" እስከ ዛሬ ትንሽ ቸብ ቸብ ከማድረግ ወይም ከመወዝወዝ በቀር ገርፌው አላውቅም እሱ ደሞ ይህን አምንም አልቆጠረውም አልጠቀመውም ብልግናውና አስቸጋሪነቱን ብነግርሽ አታምኚም " ሌሎቹ የሱን ያህል አያስቸግሩኝም"
አሁን ወዲህ ና አንተ ከይሲ ! ከልጆች ክፍል አስግብቸ ነው የምዘጋብህ" አሁን ብዘጋበትም እኮ በጉበኑ ተንጠልሎ ወጥቶ ለመክፈት ከመሞከር አያርፍም ” አለቻት " ልጁን እየገፈተረች ከገባበት ክፍል አስወጥታ በኮሪደሩ እያዳፋች ወደ ልጆቹ ክፍል ወሰደችው ፤ሳቤላ መንፈሷ እየተፋጨ ፡ ልቧ ታጥቦ እንደሚሰጣ ጨርቅ እየተጠመቀ ቁጭ አለች የገዛ ልጅዋን ሠራተኛይቱ ስታንገላታው ዐይኗ እያየ ልትከለክላት አልቻለችም "

ወደ ግራውጫው ሳሎን ወረደች "
ቁርስ ቀርቦ ሁለቱ ትልልቅ ልጆች ተቀምጠው ሲጠብቋት ገባች እሷ ስትገባ አብራቸው የነበረችው ጆይስ ወጣች

አንዲት የስምንት ዓመት ደርባባ ሴት ልጅና ከሷ አንድ ዓመት የሚያንስ
አንድ ስልል ያለ ደካማ ወንድ ልጅ ነበሩ ። ሁለቱም ልጆች የዱሮው የናታቸውን ቅርጽ ስልክክ ያለ መልክና ትልልቅ ለስላሳ ዐይኖችን በሚገባ ወርሰዋል እንደ እናትነቷና እንደ ናፍቆቷ ስሜቷን ለመግለጽ ብትችል ኖሮ ብዙ ማየትና መስማት ይቻል ነበር ። ሆኖም ብሶቷን በግድ እምቅ አድርጋ ይዛ ጐንበስ ብላ ሁለቱንም ሳመቻቸው ሉሊ ምንጊዜም የረጋችና ዝምተኛ ነበረች ዊልያም ግን ለፍላፊ ብጤ ስለ ነበር ወሬ ጀመረ ።

“አንቺ አዲሷ አስተማሪያችን ነሽ ? ” አላት
“ አዎን ፤ ጥሩ ወዳጆች መሆን አለብን ።

“ እንሆናለን አለ ልጁ ከሚስ ማኒንግ ጋርም ጥሩ ወዳጆች ነበርን አሁን ያለብኝ ሳል በቅርቡ እንደ ለቀቀኝ ላቲን መማር እጀምራለሁ አንች ላቲን
ታውቂያለሽ ?”

“የለም ለመምሀርነት የሚያስችል ዕውቀት የለኝም "

“አባባም እንደማታውቂ ነግሮኛል " ሴቶች እምብዛም ላቲን አያውቁም ። ስለዚህ ሚስተር ኬን እየመጣ ላቲን እንደሚያስተምረኝ ተነግሮኛል ”

ሚስተር ኬን ? ”አለች ሳቤላ ያ ስም ትዝ አላትና “ ሚስተር ኬን የሙዚቃ አስተማሪው ? ”

የሙዚቃ አስተማሪ መሆኑን በምን ዐወቅሽ ? ” አላት ብልሁ ልጅ ።እመቤት ሳቤላ ሳታስበው ስለ አመለጣት ነገር በመደንገጧ ፊቷ ፍም መሰለ የምትለው ጠፍቷት ጥቂት ግራ ከተጋባች በኋላ ከሚስዝ ላቲመር መስማቷን ነገረችው "

“ አዎን የሙዚቃ መምህር ነው ። ግን ብዙ ገንዘብ አያገኝበትም " ሚስ ማኒንግ ከሔደች ወዲህ እየመጣ ሙዚቃ ያስተምረናል " እማማም ተጠንቅቀን አንድንማር ትነግረናለች

“ ሁልጊዜ በቁርስ የምትመገቡት ዳቦና ወተት ነው ? አለች የቀረበላቸውን አይታ።

አንዳንድ ጌዜ ሲሰለቸን ወተትና ውሃ ዳቦና ቅቤ ወይም ማር ይሰጠናል
ከዚያ እንደገና ወደ ዳቦና ወተት እንመለሳለን አክስት ኮርኒሊያ ናት አባታችሁም
በልጅነቱ ሌላ ቁርስ አግኝቶ አያውቅም እያለች ዳቦና ወተት እንዲቀርብልን የም
ትናገር ።

ሉሲ ቀና ብላ አየቻትና ቁርሴን ከአባባ ጋር ስበላ በነበረ ጊዜ አንድ አንድ
ዕንቁላል ይሰጠኝ ነበር " አክስት ኮርኒሲያ ዕንቁላል ለኔ ጥሩ አይደለም ብትለውም ዝም ብሎ ዕንቈላሉን ይሰጠኝ ነበር ሁልጊዜ ከሱ ጋር ነበር ቁርሴን የምበላው ”

ታዲያ ዛሬስ ለምን አብረሺው አትበይም ?
እንጃ እማማ ከመጣች ወዲህ ቀርቤ አላውቅም "

የንጀራ ናት የሚለው ቃል ትውስ ሲላት ሳቤላ ልቧ ተንደፋደፈባት ሚስዝ ካርላይል ልጆቹን ካባታቸው እየለየቻቸው መሆኑን ተገነዘበች

ቀርስ ተበልቶ አቐቃና ስለ ትምህርታቸው ስለ መዝናኛ ስአታቸው ስለ ዕለት ከዕለት ኑሮዋቸው ስትጠይቃቸው ይኸ ኮ መማሪያ ክፍል አይደለም ” አላት
ዊልያም መማሪችን እላይ ነው እፎቅ ይህ ምግብ ቤታችን ማታ ማታ ደግሞ • ያንቼ ማፊያ ገው "

ከደጅ የሚስተር ካርይል ድምፅ ተሰማ ሉሲ ድምፅ ወደ ሰማችበት ልትንደረደር
ብድግ አለች » ሳቤላም ልጂቱን በበራፉ ስትዘልቅ ካየ እንዳይገባ ፈራችና
እጅዋን ለቀም አድርጋ አቆመቻት "

“ እዚህ ቆይ ሳቤላ
“ ሉሲ እኮ ነው ስሟ ” አለ ዊልያም ቶሎ ቀና ብሎ እያያት '“ ለምን ሳቤላ
ትያታለሽ?”

እኔማ - እኔማ ሳቤላ ብለው ሲጠሯት የሰማሁ መስሎኝ ነበር ” ብላ ተንተባተበች "

“ስሜ ሳቤላ ሎሲ ነው ” አለቻት ልጂቱ“ ግን ሳቤላ ተብዬ ስለማልጠራ ማን እንደ ነገረሽ ገርሞኛል
እ... እ..ልንገርሽ ? . . . እማማ ጥላን ከሔደች
ወዲህ ተጠርቸበት አላውቅም " ዱሮ የነበረችው እማማ ማለት እኮ ነው »"

“ ሔደች ? አለቻት ሳቤላ በስሜት ፍላት ስለ መልሱ ሳታስብ
"ተጠለፈች ” አለቻት በሹክሹክታ
“ ተጠለፈች ?” አለቻት አሁንም በመገረም "
“ አዎን ባትጠለፍማ መች ትሔድ ነበር አንድ ክፉ ሰው የአባባ እንግዳ ሆኖ መጥቶ ሰረቃት እማማ ስሟ ሳቤላ ነበር ከያኔ ጀምሮ ሳቤላ ተብዬ እንዳልጠራ አባባ ከለከለ "

“ ግን አባባ መከልከሉን በምን ዐወቅሽ ? አለቻት "
👍15🔥1
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሃምሳ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

የንስሯ ጭንቅላቷ ላይ ማረፍ ነበር ከእንቅልፏ ያባነናት….በመከራ አይኗን ገልጣ ዙሪያዋን ስትቃኝ እራሷን  እዛው ቅድም የተዘረረችበት ወለል ላይ እርቃኗን አገኘችው….ባለ ላደውም የሞተ እስኪመስል ድረስ ትንፋሹ ጠፍቶ እግሮቾ  መካከል ጭንቅላቱን ቀብሮ በተመሳሳይ እርቃኑን ተዘርሯል ….ቀስ ብላ ከላዮ ላይ ገልበጥ  አደረገችውና እና እራሷን በማላቀቅ  ሾልካ ወደ ሻወር በመሄድ ለ5 ደቅቃ ውሃ በላይዋ ላይ አፈሰሰችና..
ከዛ ወደመኝታ  ቤቷ ተመልሳ ቢጃማ ለበሰችና ባለ ላዳውን እንደምንም እየጎተተችም እየደገፈችውም ወስዳ አልጋው ላይ በማስተኛት ብርድልብስ ካለበስችው በኋላ ወደሳሎን አመራች…..ንስሯም ተከተላት..፡፡
አዎ ሊነጋ  መሆኑን ከውጭ የሚሰማውን የወፎች  ዝማሬ በማዳመጥ ተረዳች …ሳሎኖ እንደደረሰች ተስተካክላ ከተቀመጠች በኋላ ንስሯ ያየውን  እንዲያሳየት… ያወቀውን እንዲያሳውቃት አዕምሮዋን ከእሱ ጋ አቆራኘችው…
ሰላምና አባቷ…ፍቅራቸው ከአባትና ከልጅም የዘለል አይነት ነው..ኤርምያስ እንዳለው እናትም አባትም ወንድምም እህትም ሆነው ነው ያሳደጎት…ግን አሁን ስላለችበት ሁኔታ ብቻ ያለውን ታሪክ ከንስሯ በተረዳችው የሚከተለውን ነው
ቀጥታ ቤታቸው ገባች… መኝታ ቤት ወደመሰላት ክፍል ተጓዘች… አዎ ትክክል ነች ያልተነጠፈ እና የተዝረከረከ አልጋ … አልጋው ላይ የተዘረረች ውብ ለጋ  ሀዘን የሰበራት ወጣት ተኝታለች…..ወለሉ ጠቅላላ በመጠጥ ጠርሙሶች እና በተበታተኑት ልብሶች ተሞልቷል..አንድ ግዙፍ  አራት መአዘን  ፍሪጅ አልጋውን ተደግፎ   ይታያል…ትኩረቷን ወደፍሪጁ አመዘነበት… ውስጡን አየችው… .ህልም ውስጥ ነኝ እንዴ ያስብላል… …ነጭ ሱፍ ለብሶ ነጭ ሸሚዝና ቀይ ከረባት ያደረገ  እንቅልፍ የተኛ የሚመስል ሰው ፍሪጅ ውስጥ ይታያል.. ..አባቷ ነው ….የሰላም አባት..አሁን የሆነ ነገር የገባት ነው..ልጅቷ እንደጠረጠረችውም  አደጋ ላይ ነች…ሰላም አባቷን አጥታለች..ሰላም አባቷን መሬት ውስጥ ቀብራ ለዘላላም ለመለየት ድፍረቱንም ጭካኔውንም ለማግኘት አልቻለችም….
/////
ነገሩን በዝርዝር ለመረዳት  አምስት ቀን ወደኃላ እንመለስ 
እንደማንኛውም ቀን እየተጎራረሱ እራት በሉ…እያተሳሳቁ ዜናና ፊልም አዩ…አራት ሰዓት አካባቢ ወደመኝታቸው አመሩ….ሰላም አባቷን መኝታ ቤት አስገብታ እንዲተኙ ካደረገች  በኃላ ግንባራቸውን ስማ ተሰናብታ ወደመኝታዋ ልትሄድ ስትል

‹‹ሰላሜ››ሲሉ ጠሯት

‹‹አቤት አባ›››

‹‹አብረሺኝ ተኚ››
ዘላ አልጋው ላይ ወጣችን ብድርብሱን ገልጣ ከውስጥ በመግባት እቅፋቸው ውስጥ ገባች…..ይህ አዲስ ነገር አይደለም..ተለያይተው ከሚተኙበት ይልቅ አንድ ላይ የሚተኙባቸው ቀናቶች የበዙ ነበሩ..ሁለቱም ትንሽ ሲከፋቸው ወይንም አመም ሲያደርጋቸው..ወይንም እንዲሁ ለብቻ መተኛት ሲደብራቸው ዛሬ እኔ ጋር ትተኚ..?ዛሬ አብረሀኝ ትተኛ..? እየተባባሉ አንድ ቀን እሷ ክፍል አንድ ቀን እሳቸው ክፍል ይተኛሉ..እና የተለመደ ነው፡፡
ችግሩ ንጊ ላይ ከእንቅልፏ ባና ከእቅፋቸው ስትወጣ ነበር የተፈጠረው….እጃቸውን ከሰውነቷ ላይ ሳታነሳ በተለየ ሁኔታ ቀዘቀዛት…..ቀስ ብለ ወጣችና አየቻቸው..ጸጥ ያለ ፊት ነበር..ዝም ያለ ፊት…እጇን ወደ አንገታቸው ላከች ….ትንፋሽ አልባ ሆነዋል..

‹‹አባዬ ..አባዬ›› ወዘወዘቻቸው…ጮኸች……..ወደመኝታ ቤቷ  በሩጫ ሄደችና የልብ ማዳመጫ መሳሪዋን አመጣች…ምንም  የለም..?…ጮኸች…ሁሉ ነገር ረፍዶ ነበር..ፀሀይ በጠለቀችበት ቀርታ ነበር…ጨረቃ በደመናው ሙሉ በሙሉ ተሸንፋ ከስማ ነበር…ምጽአት ደርሶ  ነጋሪት እየተጎሰመ እና መለከት እየተነፋ ነበር…..
አባቷ እርግጥ ህመም ላይ ከነበሩ ወራት አልፏቸዋል….ግን እየተንከባከበቻቸው እና በትክክል የህክምና ክትትል እያደረገችላቸው ነበረ…ምንም የተለየ እና ለሞት የሚያሰጋ ምልክት አልተመለከተችም….የት ጋር ነው የተሸወደችው…..?ማወቅ አልቻለችም…፡፡ ለሳዕታት እሬሳውን ላይ ተኝታ ስትነፈርቅ ቆየች…ስልክ ደውላ ለወዳጆቾ ልትናገር ፈለገችና መደወል ከጀመረች በኃላ መልሳ ተወችው

‹‹አባቴን ልቀብር…..?አባቴንም ፈጽሞ አልቀብርም…….ለሳዕታት ካሰበች በኃላ ወሰነች‹‹..አብሬው እሞታለሁ..ግን ለመሞት እስክቆርጥ ድረስ እሱም አይቀበርም›› አለችና…ባላት የህክምና እውቀት በመጠቀም ሬሳው እንዳይበሰብስ አድርጋ በባለመስታወት ፍሪጅ ውስጥ በማድረግ መኝታ ቤት ውስጥ ሬሳውን ደብቃ አስቀመጠች….እና ይሄ ነው የሚያስጨንቃት…እና በዚህ ጊዜ ነበር ኤርምያስ ላዳ ውስጥ የገባችው….ይሄን ችግር ነበር እሱ ሊያውቅና ሊረዳላት ያልቻለው…..በዚህ ከቀጠለች  በጥቂት ቀናት ውስጥ ወይ አዕምሮዋ ተነክቶ ጨርቋን ጥላ ይለይላታል ወይንም እዛው መኝታ ቤት ውስጥ እራሷን አጥፍታ ከአባቷ ጋር ወደመቃብር ትጓዛለች..ከሁለቱ የተለየ የነገ ዕጣ ፋንታ የላትም….
ንስሯ ይዞላት የመጣው ታሪክ ይሄ ነው..በእውነት ልብ የሚነካ ታሪክ ነው…‹‹እና እንዴት ልረዳት እችላለሁ…...?›ስትል እራሷን ጠየቀች፡መቼስ ምንም  ተአምረኛ ብትሆን ከሞተ  አራት ቀን የሆነው እና በፍሪጅ ውስጥ በቅዝቃዜ የደረቀ ሬሳን  ህይወቱን ካሄደችበት መልሳ በማዋሀድ ነፍስ  ልትዘራበት አትችልም…ይሄ የማይቻል ነው… ቢሆንም ቢያንስ ልጅቷ የአባቷን ሞት አምና እንድትቀበል እና እንድትቀብረው…ከዛም እንድትጽናና የሚያስችል አንድ ዘዴ መዘየድ እንዳለባት ተሰማት…አዎ ያንን ማድረግ ትፈልጋለች…
ሀሳቧን ሰብስባ ውሳኔ ላይ ሳትደርስ በፊት የሳሎኗ  በራፍ ተንኳኳ..ግራ ገባት …በዚህ ጥዋት ማን ነው የሚያንኳኳው .. ..?ገና አንድ ሰዓት እንኳን አልሆነም፡፡

‹‹…ማነው..?››ከተቀመጠችበት ሳትነሳ

‹‹እኔ ነኝ ..››

የፕሮፌሰር ድምጽ ነው..ተነሳችና ከፈተችላቸው‹‹እንዴ ፕሮፌሰር..በጥዋት እንዴት ተነሱ..?››

‹‹አረ ጨርሶውኑም አልተኛሁም…ከሰው ጋር ስለሆንሽ ነው እንጂ  ለሊቱን አብሬሽ ስጫወት ማደር ነበር የፈለግኩት››

‹‹ምነው በሰላም..?››

‹‹እኔ እንጃ ብቻ  ትናፍቂኛለሽ…ከፍቶኛል››

‹‹እንዴ ፕሮፌሰር..እስቲ ግቡ››

‹‹አሁን አልገባም.. በኋላ ግን እፈልግሻልሁ››

‹‹ለምን አይገቡም..?››

‹‹አይ አሁን እንግዳ ይፈልግሻል››

‹‹ማንን እኔን....?››ግራ ገብቷት 

‹‹አዎ አንቺን››ብለው ከበራፍ ላይ ገለል ሲሉ ከጀርባቸው በአዕምሮዋ ውስጥም የሌለ ሰው ብቅ አለ…አንድ ጥቁር ሻንጣ በእጁ አንጠልጥሎ አንገቱን ደፍቶ ቋማል..ፕሮፌሰሩ  ወደክፍላቸው ተመለሱ….

‹‹እንዴ መላኩ ..ምነው ሰላም አይደለህም እንዴ....?ሰሚራን አመማት እንዴ..?››

‹‹አረ እሷስ ደህና ነች››

‹‹ታዲያ ምነው በለሊት....?››እስቲ ግባ ብላ ወደውስጥ ገብቶ እንዲቀመጥ አደረገችው…

‹‹ምን ሆንክ..?››ፊት ለፊቱ ቆማ በገረሜታ እያየቸችው ዳግመኛ የመጣበትን ምክንያት ጠየቀችው፡፡

‹‹ምን ያልሆንኩት ነገር አለ..አሸንፈሻል …ሰሚርን አስመርምሬያታለሁ..ሙሉ በሙሉ ጤነኛ ሆናለች..››

‹‹አሪፍ ነዋ .ታዲያ ደስ አላለህም..?››

‹‹አዎ ብሎኛል…››
‹‹እና ታዲያ አሁን ለምን መጣህ..?››

‹‹ስምምነታችንን ላከብር ነዋ..በሶስት ቀን ውስጥ ትተሀት ካልመጣህ ብለሽ ፎክረሻ አድራሻሽን ሰጥተሸኝ ነበር  እኮ..የሆነ ነገር ለማድረግ ኃይል እንዳለሽ አሳይተሸኛል…እንቢ ብዬ በዛው ብቀር ደግሞ ፍቅሬን  መልሰሽ በሽተኛ ብታደርጊብኝስ..?››
👍12010🥰1👏1🎉1
#ትንግርት


#ክፍል_ሃምሳ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


..ከአንዱ ለምኖ ለአንዱ በመስጠት ብልጽግናን ማምጣት አይቻለም::

ለታዲዬስ ፣ትንግርት፣ሁሴን፣ዶ/ር ሶፊያ፣ፎዚያ እና ኤልያስ ዛሬ ልዩ ቀን ነች፡፡ለስድስት ወር የለፉበትን ...እንቅልፍ አጥተው ገንዘባቸውንም ዕውቀታቸውንም ያፈሰሱበት የድርጅታቸው የመጀመሪያ ፍሬ እነሱም የሚያዩበት ለማህበረሰቡም የሚያስተዋውቁበት ቀን ነው፡፡

ዝግጅቱ በሸራተን አዲስ የሚካሄድ ሲሆን የህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ዲኤታ፣የተለያዩ ሀይማኖት አባቶች፣የኤንባሲ ሰዎች፣ታዋቂ ሙዚቀኞች፣የፊልም አክተሮች፣አትሌቶች፣ነጋዴዎች፣
ለዚህ ድርጅት ከምስረታው እሰከአሁን ከፍተኛ እገዛ ካደረጉት ከየተለያዩ የፌስ ቡክ ግሩፖች የተወከሉ ወጣቶች፣ከተለያዩ ሚዲያዎች የተሰበሰቡ ጋዜጠኞች እና ካሜራ ማኖች..አዳራሹን
ሞልተውታል፡፡

የዛሬው ዝግጅት ዓለማ በዋናነት ሁለት ሲሆን ሌላም አንድ ንዑስ ዝግጅት አለ፡፡መድረኩን የሚመራው ጋዜጠኛ ሁሴን ነው..ማይኩን ይዞ ወደ መድረክ ወጣና ጉሮሮውን ሞርዶ ንግግሩን
ጀመረ::

‹‹ክቡራን እና ክብሯት ጥሪያችንን ተቀብላችሁ እዚህ የተገኛችሁ ሁላችሁም እንዲሁም በየቤታችሁ ሆናችሁ ዝግጅቱን በቀጥታ በቴሌቨዥን ስርጭት እየተከታተላችሁ ያላችሁ በአጠቃላይ በድርጅታችን ስም ምስጋናችንን እያቀረብን እስከፍፃሜውም በፅሞና እንድትከታተሉን እየጠየቅን በቀጥታ ወደ ዝግጅቱ እንገባለን፡፡በቅድሚያ የድርጅታችን መሪ የሆኑት ዶ/ር ሶፍያ ፕሮግራሙን በንግግር እንዲከፍቱልን እንጠይቃለን… ዶ/ርን ወደ መድረክ ሸኙልን፡፡››ዶ/ር ሶፊያ በጭብጨባ ታጅባ ወደ መድረክ ወጣችና ማይኩን ከሁሴን ተቀብላ ንግግሯን ማሰማት ቀጠለች፡፡

‹‹ክቡራን እና ክቡራት የመንግስት ባለስልጣናት፣የሀይማኖት አባቶች፣ከተለያዩ የማህበራት ዘርፎችን በመወከል
የተገኛችሁ፣በየቤታችሁም በመሆን እየተከታተላችሁን ያላችሁ በአጠቃላይ..እንኳን ለዚህች ቀን አደረሰን አላለሁ፡፡

የዛሬው ፕሮግራማችን ሁለት ዓላማዎች አሉት፡፡ አንደኛው የወላጆች እና ልጆች የምረቃ በዓል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ለድርጅታችን የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ነው..እኔ አሁን አትኩሬ የተወሰነ ማብራሪያ ልሰጣችሁ የምፈልገው በመጀመሪያው ላይ ነው..ሁለተኛውን በተመለከተ አቶ ታዲዬስ ቆየት ብሎ ያብራራላችኋል፡፡

እንግዲህ እንደመነሻ ይሆነን ዘንድ የዛሬ አንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን አካባቢ በበጎ ፍቃደኝነት አሳዳጊ የሌላቸውን ህፃናትን እናሳድጋለን ብለው ከተመዘገቡ በብዙ ሺዋች ከሚቆጠሩ ባለቀና ልቦች መካከል ለጊዜው አቅማችንን መሰረት አድርገን 15ዐ ግለሰቦችንና በቡድን ከመጡት መካከል ደግሞ 5ዐ ዎቹን ወደ ስልጠና አስገብተን ነበር፡፡እንግዲህ በአንድ ወር ስልጠና ውስጥ በድርጅቱ ህግና የስልጠና ማኑዋል የተሰጣቸውን ስልጠና በመከታተል ከ15ዐ ዎቹ ግለሰቦች መካከል 43 በቡድን ሆነው ከመጡት መካከል ደግሞ 31 መስፈርቱን ማሟላት ስላልቻሉ ከይቅርታ ጋር እንደ ፍላጎታቸው ህፃናትን እንዲያሳድጉ ልንፈቅድላቸው አልቻልንም፡፡የተቀሩት እንግዲህ ብቁ ሆነው በመገኘታቸው እንሆ ዛሬ በእናንተ ፊት መርቀን ልጆቻቸውን በአደራ እናስረክባቸዋለን፡፡››

የደመቀ ጭብጨባ ከአዳራሹ...ቀጠለች ዶ/ር ‹‹ዛሬ አሁን ለነገርኳችሁ ወላጆች የምናስረክባቸውን ልጆችም ለ3 ወር በካምፕ በማስገባት ስልጠና ሰጥተናቸዋል፡፡ልዩነቱ ህፃናቱን አንዴ ወደ ማሰልጠኛ ካስገባናቸው:: የምንፈልገውን ብቃት እስክናገኝባቸው ድረስ የፈጀውን ያህል ይፍጅ እንለፋባቸዋለን፡፡ ልጆቹን ከበሸቀጠ የድህነት መንደር እንዲሁም በስነ- ምግባር እና በሞራል ከዘቀጠ ጎዳና ላይ ነው የምንሰበስባቸው፤አመላቸውን ማረቅ፣ ስነ- ልቦናቸውን መገንባት፣ጤንነታቸውን ማስተካከል፣ ተስጥኦቸውን ለይቶ ማወቅ፤ወዘተ እንደሀሳባችን እስክናሳካ 3 ወር ፈጀብንም ሶስት
አመት ተስፋ አንቆርጥባቸውም፡፡ የራሱ ጉዳይም ብለንም እርግጠኛ ባልሆንበት ሁኔታ ለአሳዳጊ ወላጅ አሳልፈን አንሰጣቸውም፡፡ይህ ነው ልዩ የሚያደርገን.. እንጂማ መአት በህፃናት ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች እንዳሉ እናውቃለን...፡፡.››

ወላጅ ለመሆን ስልጠናውን ወስደው መስፈርቱን አላሟላችሁም ብለን ከመለስናቸው ውስጥ የተወሰኑት በጣም ተበሳጭተውብን ነበር፤ላሳድግ ባልኩ መልካም ልስራ ባልኩ እንዴት እከለከላለሁ?የሚል መከራከሪያ ሀሳብ
ነበራቸው፡፡ግን እኛም ያንን ስናደርግ እያዘንን ነው... እየገነባን ያለነው የወደፊቱን ትውልድ
ነው፡፡አንድ ሰው ገንዘብና ፍላጎት ስላለው ብቻ ዝግጁ የሆነ ስነልቦና እንዲሁም የወላጅ ባህሪ
ሳይኖረው ልጅን ያህል ነገር አሳድግ ብለን አንስተን አንሰጠውም..በፍፁም እንደዛ
አናደርግም፡፡በእኛ መአከል ሰልጥነው ልጅ የተረከቡ ሰዎች በስልጠናው ያገኙትን ዕውቀት
ከዚህ ከእኛ ጋር ለወሰዷቸው ልጆችም ብቻ ሳይሆን ከአብራካቸው ለወጡትም
ህፃናት፣ለዘመዶቻቸው ልጆች ፣ለጎረቤቶቻቸው ልጆችም ያገኙትን ዕውቀት እንዲጠቀሙበት
እንፈልጋለን፡፡አርአያ እንዲሆኑበት እንፈልጋለን፡፡ ለዛ ነው ማኑዋሉንም አዘጋጅትን ለእያንዳንዱ ያደልነው፡፡

‹‹ልጅ ማሳደግ ማብላትና ማጠጣት ብቻ ሳይሆን..የወደፊት የህይወት ዓላማቸውን፤ ተሰጥኦዋቸውን ከስር ከመሰረቱ እያጎለበቱ መንገድ ማስያዝን ይጠይቃል፡፡ ይሄንን ነው ጠቅላላ የሀገራችን ወላጆች ሊከተሉት የሚገባው መንገድ፡፡ ህብረተሰቡም እንደህብረተሰብ...መንግስትም እንደመንግስት የየራሳቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ እጠይቃለሁ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡ አሁን ቀጥታ ወደ ምረቃ በዓሉ እንሄዳለን፤ ክብር የህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ዲኤታ ለተመራቂ ወላጅ እና ህፃናት የምስክር ወረቀት ይሰጡልን ዘንድ እንጠይቃለን፡፡››

ሚንስቴሩ በሙሉ ሱፍ ሽክ ብለው በከረባት እንደታነቁ በተጀነነ እርምጃ ወደ መድረክ ወጥተው ከዶ/ር ጎን ቆሙ ፡፡ሁሴን የተመራቂዎቹን ስም ተራ በተራ ሲጠራ ወላጆቹ ከተረከቧቸው ህጻናት ጋር በመምጣት የምስክር
ወረቃታቸውን እየወሰዱ ወደ መቀመጫቸው ይመለሳሉ፡፡ ከነዚህ ተመራቂዎች ውስጥ..ሰሎሞንና የውብዳር አንድ ወንድ ልጅ(እነሱ የጠየቁት ሁለት ቢሆንም በታዲዬስ የሚመራው ቴክኒክ ብድን ግን በዚህ በአንዱ ልጅ ላይ የሚያሳዩት አፈፃፀም ታይቶ ከአመት በኃላ ሌላ ልጅ ሊጨመርላቸው ይችላል እንጂ አሁን ባለው ሁኔታ ከአንድ ልጅ በላይ አይፈቀድላችሁም በማለት ከለከሏቸው) ሌላው..ዶር ሶፊያና ከፕ/ዬሴፍ ጋር አንድ ሴት ልጅ፣ፎዚያ እና ኤልያስ አንድ ሴት ልጅ፣ፅዮን እና ዓላዛር ..ትንግርት እና ሁሴን አንድ ልጅ በመረከብ ከራሳቸው በመጀመር አርዓያነታቸውን አሳይተዋል፡፡

የምስክር ወረቀት የመስጠት ፕሮግራም ሲጠናቀቅ የክብር እንግዳውንና ዶ/ር ሶፊያ መድረኩን ለቀው ወደ መቀመጫቸው ሄዱ.... ሁሴን ቀጣዩን ፕሮግራም ማስተዋወቅ ጀመረ…፡፡

‹‹ክብሯን እንግዶች ወደ ቀጣዩ ፕሮግራማችን ከመሸጋገራችን በፊት የሙዚቃ እረፍት

እናደርጋለን..ድምፃዊ ሀሊማ እና ሄለን ወደ መድረክ፡፡››

በአካልም በየቤቱም እየተከታተሉ ያሉ አይኖቻቸውን ወደ መድረኩ ላኩ፡፡

የተባሉት ሙዚቀኞች ወደ መድረክ ሲመጡ ታዩ …ሀሊማ ጊታሯን ይዛ ወንበር ስባ ተቀመጠችና ማይኩን ወደ አፏ አስተካክላ አመቻቸች፡፡ሄለን ወደ ፒያኖው አመራች፡፡አብዛኛው ህዝብ አስታወሳቸው፡፡ ባለፈውም በቴሌቨዥን ቃለ መጠየቅ የተደረገላቸው ጊዜ ብቃታቸውን አሳይተዋል፤በአይድል ውድድርም እንደዛው…፡፡ ጀመሩ ሄለን ፒያኖውን ስታናግረው ሀሊማ ጊታሯን እየተጫወተች በድምጿም ታንቆረቁር ጀመር..
👍6311