የሚያስጸዳውም (የሚበዛው ቆሻሻ የራሱ ቢሆንም)ይኼው ክፍሌ ነበር፡፡ ታዲያ እኔም ጋር ጥሩ የእህትና ወንድማዊ ቅርርብ ነበረን፣ እንደ እናትሽ ጠይም ሰይጣን ይለኛል። ደፍሬ ሰው ቀና ብዬ ማዬት የምፈራ እኔ... ክፍሌ ጋር ምላሴን የማረዝመው ነገር አለ፤ እንዲሁ እወደው ነበር፡፡ አለ አይደል ንጹህ ልብ ያለው የሥራ ሰው እንደዚያ ነው፡፡ በዚያ ላይ አባቴን ሲወደው ለጉድ ነው፡፡ታዲያ በየዓመቱ የኦዲት ሪፖርት የምሠራለት እኔ ነበርኩ “እነዚህ ገቢዎች ሲኦል ያስገባቼውና..." እያለ የደረሰኝ መዓት ፊቴ ይከምርልኛል፡፡ የምወደውን “ፒዛ” ልጅ ልኮ ያስመጣል፤ እንደ ታላቅ ወንድም ነበር የምቀርበው፤ ሚስጢረኛዬ ነበር፡፡ “መኪና ከገዛሽ ለጥገናው የዕድሜ ልክ ዋስትና በእኔ ጣይው'' ይለኛል .... ከልቡ ነው ደግሞ። “አንተ ቤት የሚጠገን መኪናማ አልገዛም...” “መናቅሽ ነው ...ዶሮ የሌላት ላም አማረረች አሉ!'' “አህያ የሌላት በቅሎ ታማርራለች ነው የሚባለው!" “የዛሬ ልጆች ሥራ አትወዱም እንጂ፣ የተረት ቡለን ፍቱ ...” ይላል፡፡
“...እና ደንበኞችህ በሙሉ ሰካራሞች ናቸው ... እየተጋጩ ነው የሚመጡት ... የከተማዋን አጥርና ምሰሶ የጨረሱት የአንተ ደንበኞች ናቸው።'' “ምናለ ታዲያ.ወንድ ልጅ ካልጠጣ፣ ካልተጋጨ ምኑን ወንድ ሆነ ...? ከመቼ ነው አንቺ እንዲህ ምላሳም የሆንሽው!?”... ታዲያ አብርሃም ጋር የተጣላን _ ሰሞን ጸብም ባይባል ወደ መጨረሻው አካባቢ፣ በጭንቀት ልፈነዳ ስደርስ ፍቅር እንደ መኪና ጋራዥ ይጠገን ይመስል፣ የሆንኩትን ሁሉ ነገርኩት ... አሰበ አሰበና፣ “እናስደብድበው ይሆን!?'' አለኝ ሳቄ አመለጠኝ፡፡ “ምን ያስቅሻል? ጥርሳም... ይኼ ሸርሙጣ ... መቅመስ አለበት! ለመሆኑ ምንድን ነው ሥራው?'' “ደራሲ!”
“ያው “ሸርሙጣ” ማለት'ኮ ነው! አንቺ ስንት ሰው እያለ ምን አልከሰከሰሽ? እኔ ወርቅ እጅ ያለው ሜካኒክ እድርሽ አልነበር? እውነቴን'ኮ ነው በዚህ ስታልፊ ስንት ሠራተኞቼ ናቸው አንችን እያዩ አአአአአአ ብለው ሥራ የሚፈቱት የነበር ... !? ሴቶች ስትባሉ ሕዝብ መኻል ካለ ንብ፣ መድረክ ላይ የሚዘል ዝንብ ትወዳላችሁ.... ሚስቴም ጥላኝ የሄደችው እዚያ ከበሮ የሚደልቅ ዘፋኝ ወዳ ነው ... “ሸርሙጠ'' ሆና እንጂ ከበሮ ምኑ ይወደዳል? ደግሞ ደራሲ ትላለች ...ሁለተኛ አጠገቡ እንዳትደርሺ ....ሆሆ'' በብስጭት የሚይዝ የሚጨብጠውን አጣ፡፡ ግን ምክሩን አልሰማሁም፡፡ እዚህ ድረስ እየወደድኩት፣ እየቀረብኩት ሰፈሬን ያስጠላኝ ረብሻ ግን ከዚህ ሰው ጋራዥ ነበር የሚመነጨው፡፡ ዕድሌ ይሆን ፍቅርና ረብሻ አንድ ላይ የሚሰጠኝ፡፡
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️

ይቀጥላል...
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍35❤1
እባክሽ አትሂጂ…..
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አራት
ባሏን አይቼላት …መመርመር የሚገባኝን ሁሉ መርምሬ ከሚወስዳቸው መድሀነቶች መካከል አንድን ቀንሼ ሌላ አንድ ተጨማሪ መድሀኒት በቅያሬ አዝዤ አሁን እየሸኘችኝ ነው፡፡ቆይቼ እራት እንድበላ ብትጠይቀኝም አልተስማማሁም፡፡ሳልፈልግ ቀርቼ ሳይሆን ትናንት ከኖሮዌይ በደወለችልኝ የቀድሞዋ እጮኛዬ እርግበ ምክንያት ጠቅላላ መንፈሴ እርብሽብሽ ብሎ ስለዋለና አሁንም ያ ስሜት አብሮኝ ስላለ ድብርቴን ወደ እሷ ላጋባባት ስላልፈለኩ ነው፡፡
‹‹ደ/ር ግን ቢያንስ አንድ ሲኒ ብና ሳትጠጣ ቅር አሰኝተሀኛል፡፡››
‹‹ምን ነካሽ እቤቴ እኮ ነው…ብፈልግ እራሴ ጠይቄ አፍይልኝ እልሽ ነበር..ስለቸኮልኩ ነው፡፡››
‹‹ይሁን….››አለቺኝ፡፡
እኔ ወደ መኪናዋ ሳመራ እሷ የውጩን በራፍ ልትከፍትልኝ ሄደች፡፡መኪናዬን በማሰነሳት ከግቢው ወጣሁና ዳር አሲዤ አቆምኩ፡፡መኪናዋን ሳላቆም እጄን በማውለብለብ ተሰናብቼያት መቀጠል እችል ነበር..አሁን ማቆሜ ግን ነይና ቀርበሽ ሰላም በይኝ የሚል ምልክታዊ መልዕክት ማስተላለፌ እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡፡ ..አላሳፈረችኝም ወደ መኪናው ቀረበችና ጎንበስ አለች….
‹‹በይ እንግዴ ..ከነገ ወዲያ እንገናኝ….ችግር ካለ በማንኛውም ሰዓት ደውይልኝ››
‹‹እሺ ዶክተር…ደውልለሀላሁ…››በማለት አረጋገጠችልኝና ቀና አለች፡፡››
‹‹ ቆይ አንዴ››አልኩና ወደኃላ ዞሬ ከኃላ መቀመጫ ወዳለው እቃ ተንጠራራሁ…ቀዩን እንቡጥ ፅጌረዳ ተውኩና በካርቶን ያለውን ቸኮሌት አንስቼ ሰጠኋት››
‹‹ምንድነው?››
‹‹ላንቺ አይደለም…ለነዳኒ ስጪልኝ››
‹‹ኸረ ዶክተር ተው..፡፡››
‹‹በይ ደህና ሁኚ…››ሌላ መልስ ከእሷ ሳልጠብቅ መኪናዬን አንቀሳቀስኩ…፡፡የሰጣኋትን አነስተኛ ካርቶን እንደያዘች ወደ ውስጥ ገባች፡፡ በእስፖኪያ ወደ ኃላ ወንበሬ እያየሁ ነዳሁት፡፡ፅጌረዳ አበባዋ ዛሬም ለሁለተኛ ጊዜ መባከኗ ነው፡፡ ቅድም ስገዛው ከቸኮሌቱ ጋር አብሬ እንደምሰጣት ባለ ሙሉ ወኔ ነበርኩ፡፡አሁን የእውነቱ ሰዓት መጥቶ ከእሷ ጋር ስፋጠጥ ግን ወኔዬ ተሰለበ፡፡ደግሞም ይሄንን ለማድረግ በጣም ፈጥኜያለሁ፡፡ከዚህ ማለቴ አበባ ከመስጠት በፊት የሚቀድሙ ገና ብዙ ሂደቶች አሉ፡፡እንዴ ቢያንስ አንድ ቀን ካፌ ቁጭ ብለን ማኪያቶ በመጠጣት የግል ወሬ አውርተን አናውቅም…ለእኔ ጭላንጭል እንኳን የሆነ ፍላጎት ይኑራት አይኑራት አላውቅም፡፡ብዙ ብዙ ነገር አላውቅም፡፡ስለዚህ ነገሮች ድብልቅልቃቸው ወጥተው የቤቷን በራፍ ዘግታብኝ ከቤቷም ከባሏም አካባቢ ልታርቀኝ ትችላለች፡፡፡ እንደዚህ አይነት ሪስክ መውሰድ አልፈለኩም.. ለዛነው ይዤ የመጣሁትን እንቡጥ ፅጌረዳ መልሼ ይዤ እየሄድኩ ያለሁት፡፡
ቀጥታ ወደ መጠጥ ቤት ነው ያመራሁት፡፡ይህ የዘወትር ባህሪዬ አይደለም.. ግን ዛሬ መጠጣት እና ውስጤና ማረስረስ አምሮኛል፡፡ሰዓቱ ገና 12፡15 ቢሆንም ግድ አልሰጠኝም፡፡.አልፎ አልፎ ጎራ የምልበት ከሰፈሬ ቀረብ ያለ አንድ ሆቴል ገባሁና ሰወርና ነጠል ያለ ቦታ መርጬ በመቀመጥ ቀዝቃዛ ቢራዬን አዘዤ ከትካዜ ጋር መማግ ጀመርኩ፡፡
አእምሮ ግን ምን አይነት እረፍት አልባ ተፈጥሮአዊ ማሽን ነው?እንኳን ላስብ ብለው አስበውበት ይቅርና እንዲሁም ሀሰሱንም ገሰሱንም ጨምሮ በቀን ከ60 ሺ በላይ ቁርጥራጭ ሀሳቦችን እንደሚያስብ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ይታያችሁ 60 ሺ ሀሳብ፡፡ ከዛ ውስጥ ጎጂው ስንት ነው…? ጠቃሚውስ… ?አስደሳቹ ምን ያህል ነው…? ሀዘን ላይ የሚጥለንስ የትኛው ነው…? ሰው አስተሳሰብን በምን ያህል መጠን መቆጣጠር ይችላል? ከመቀባዠሬ ሳልወጣ ስልኬ ቨይብሬት ስታደርግ በኪሴ ውስጥ ስለተሰማኝ አውጥቼ አየሁት፡፡ወይ እየሸሸሁት ከነበረ ሰው የተላከ መልእክት ነው፡፡
‹‹ነገ ማክሰኞ በኢትዬጵያ ሰዓት
አቆጣጠር ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ ቦሌ እንደርሳለን
ያንተው ፍቅር እርግበ ነኝ፡፡››ይላል፡፡
በንዴት ግማሽ የነበረውን የቢራ ጠርሙስ አነሳሁና ተጋትኩት፡፡ሙሉ በሙሉ አጋብቼ አስቀመጥኩት፡፡አስተናጋጁን ጠራሁና ጅን እንዲቀይርልኝ ነገርኩት፡፡አመጣልኝ፡፡
አዎ ከበሰበሱ አይቀር መብከት ይሻላል፡፡ሁለት ሰዓት ሲሆን በደንብ ግዬ ነበር፡፡ሳልዋረድ እንደምንም እራሴ ገሰፅኩና ሂሳቤን ከፍዬ መኪናዬን በዝግታ እየነዳሁ ወደ ቤቴ ገባሁ፡፡የምኖረው አፓርታማ ላይ ተከራይቼ ስለሆነ መኪናዬን ፓርክ አደረኩና እንደምንም እግሮቼን እየጎተትኩ ሁለተኛ ወለል ላይ ወደ ሚገኘው ባለሁለት መኝታ ክፍል ቤቴ አመራሁ፡፡ከፍቼ እንደገባሁ የቤቱ ስልክ ሲጠራ እኩል ሆነ፡፡ እየተንገዳገድኩ ሄድኩና በመነጫነጭ አነሳሁት፡፡
‹‹ሄሎ ..ማን ልበል?››
‹‹ሳምዬ ምነው? ስልክህ እኮ አይሰራም፡፡››
‹‹እንዴ እማዬ፡፡አረ ይሰራል፡፡››ስልኬን አውጥቼ ሳየው ዘግቷል፡፡
‹‹ወይ እማዬ ቻርጅ ዘግቷል.. አላየሁትም ነበር፡፡››
‹‹ምንድነው? ሰላም አይደለህም እንዴ?››
‹‹ኸረ ሰላም ነኝ? ምን ሆንኩ፡፡››
‹‹ኸረ ወዲያ…. አፍህ ተሳስሮ የለእንዴ?
‹‹እኔ ትንሽ ከጓደኞቼ ጋ ቆይቼ አንድ ሁለት ቢራ ጠጥቼ ነው፡፡››
‹‹በል ..ነገ እርግበን መቀበሉን እንዳትረሳ፡፡››ትዕዛዛዊ የሆነ ጠንከር ያለ አረፍተ ነገር ነው፡፡
‹‹እርግበን….እኔ ጋር እኮ አይደለም ሀገሯ ነው የምትመጣው፡፡››
‹‹እና ሀገሯ ሄዳ ትቀበላት እያልከኝ ነው?››እማዬ እያሽሞጠጠቺኝ ነው እንዴ?፡፡
‹‹እኔ እንጃ?››
‹‹በል አትጨማለቅ፡፡ሄደህ በስነስርአት ተቀበላት፡፡ቅሬታም ካለህ ውላ ካደረች በኃላ ትነጋገራላችሁ፡፡ልጄን ገና ከመምጣቷ እንድታስቀይምብኝ አልፈልግም፡፡››
እርግበን በተመለከተ ከእማዬ ጋር ተከራክሬ ላሳምት እንደማልችል ስለማውቅ ነገሩን ማንዛዛት አልፈለኩም፡፡ እማዬ እርግበ ከእኔ ጋር ተጋብታ ምራቷ እንደምትሆን በእርግጠኝነት ለዘመድ ወዳጁ ሁሉ አዋጅ በሚመስል ሁኔታ ዜናውን ነዝተዋለች፡፡እርግበም የእማዬን እንዴት አንጀት መብላትና ማስደሰት እንደሚቻል ገብቷታል….፡፡
‹‹እማዬ..እሺ እንዳልሽ፡፡ስራ ከሌለኝ እቀበላታለሁ፡፡››
‹‹አይ እንግዲህ ..ስራ ካለኝ ምናምን አይሰራም፡፡ማትችል ከሆነ ከአሁኑ ንገረኝ፡፡››
‹‹ብነግርሽ ምን ልታደርጊ ነው?››
‹‹እንዴ ልጄንማ አላሳቅቃትም፡፡በከዘራ እያነከስኩ ቢሆንም ሄጄ እቀበላታለሁ፡፡››
‹‹እንዴ….አንቺ?››
‹‹ጅሎ …ታዲያ አንተ ከፈዘዝክ ምን ላድርግ?››
‹‹እሺ በቃ እማዬ እኔ እቀበላታለሁ፡፡.በይ ደህና እደሪ፡፡››
‹‹ደህና እደር….››ስልኩ ተዘጋ፡፡ወደ ኃላ ተመለስኩና በራፉን ቆልፌ ቀጥታ ወደ መኝታ ቤቴ በመሄድ ከነልብሴ ተዘረርኩ፡፡

👍57❤9👎2👏1
ለቅሶ ቤት ሄድኩና…
እንባዬ ደርቆብኝ ፡ ለማልቀስ ስቸገር
በድንገት ትዝ አለኝ ፡ ያደረግሺኝ ነገር
ትውስ ያለኝ ጊዜ : የሰራሺኝ ስራ
ሚፈሰው እንባዬ : እንደምን ያባራ
አልቅሼ አላቀስኩኝ : ሳላዝን በሟቹ
ድሮም ያንቺ ፍቅር ፡ ለሀዘን ነው ምቹ
🎴 እንደልቡ🎴
ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ
#Share #like and #subscribe my #YouTube
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
እንባዬ ደርቆብኝ ፡ ለማልቀስ ስቸገር
በድንገት ትዝ አለኝ ፡ ያደረግሺኝ ነገር
ትውስ ያለኝ ጊዜ : የሰራሺኝ ስራ
ሚፈሰው እንባዬ : እንደምን ያባራ
አልቅሼ አላቀስኩኝ : ሳላዝን በሟቹ
ድሮም ያንቺ ፍቅር ፡ ለሀዘን ነው ምቹ
🎴 እንደልቡ🎴
ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ
#Share #like and #subscribe my #YouTube
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍31😁10❤2🔥1👏1
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
✍ አሌክስ አብርሃም
ክፍል አስራ ሁለት
ረብሻ ሁለት!
ከሰርጋችን በኋላ ባለቤቴ ረፍቱን ጨርሶ ወደ አሜሪካ ሲመለስ ቤተሰቦቹ ቤት ነበር አስቀምጦኝ የሄደው። የሚያምር ትልቅ ግቢ፣ በአበቦች የተዋበ፣ ከዋናው “ሺላ ነጠል ብሎ በሰርቪስ ስም የተሠራ ሌላ ባለ ሦስት ክፍል 'ቪላ' ውስጥ ለብቻዬ ነው የምኖረው፡፡ ቤተሰቦቹ (እናቱና ሁለት እህቶቹ) ሲበዛ ጥሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ዋና ሥራቼው እኔን መንከባከብ እስኪመስለኝ አፈር አይንካሽ ብለው ነበር የያዙኝ። ከገባሁ በኋላ ሥራ አቁሜ ስለነበር ውሎዬ ቤት ነው። “ምን ጎድሎ በየገጠሩ ትንከራተቻለሽ?'' ብሎ ነበረ ባሌ ሥራ ያስቆመኝ፡፡ በዚያ ላይ ወደ አሜሪካ ለመሄድ ወዲያው “ፕሮሰስ'' እንደሚጀምርልኝ ስለነገረኝ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሥራ ማቆሜ አይቀርም በሚል የቤት እመቤት ሆንኩ። እውነቱን ለመናገር እኔም ወደ ውጭ መውጣት፣ ሰው ጋር መገናኜት በራሴ ምክንያት ጠልቼ ነበርና ሥራዬን ማቆሜ አላስከፋኝም። ታዲያ በሰበብ አስባቡ (እነሱ በፍጹም ቅንነት ብቼኝነት እንዳይሰማኝ በማሰብ) እሀቶቹ፣ አልያም እናቱ ከአጠገቤ አይጠፉም ነበር፡፡ በጭራሽ ብቻዬን መሆን አልቻልኩም፡፡ እሱም ባልከፋ፤ ሰብሰብ ሲሉ በአንድም በሌላም መንገድ “የሴት ልጅ ሙያ'' ስለሚሉት ነገር ሳያነሱ ያልፋሉ ማለት ዘበት ነበር። ስለ ጠላ መጥመቅ፣ ስለ ዶሮ ወጥ ጣዕም፣ ስለ እንጀራ ዓይን፣ ስለ ዳቦ ኩፍ ማለት፣ ስለ በርበሬ መቀንጠስ፣ ስለምናምን መደለዝ ይኼ ትንሽ ሳያማርረኝ አልቀረም፡፡ በተለይ የባለቤቴ እናት! ከሃያ ዓመት በፊት ሰው ቤት ሄደው ስለቀመሱት የማይረባ ዶሮ ወጥ ሳይቀር አንስተው ያማርራሉ «ሴት ልጅ እንዴት የግዜር ዶሮ ወጥ መሥራት ያቅታታል? አሁን ማን ይሙት ዶሮ እንደዚያ ይበለታል?» ይላሉ በግርምት። ጉድዎትን አልሰሙ፣ እላለሁ በውስጤ! ይህች ጥሩ ሴትዮ እንጀራ መጋገር አላውቅበትም ብላቼው ራሳቼውን ስተው የሚወድቁ ነው የሚመስለኝ፤ እጄን ታጥቤ ሲቀርብልኝ ከመብላት ባለፈ ዶሮ ይገንጠል፣ ይፈጭ ግድ አይሰጠኝም ብላቼው ደግሞ በቀጣዩ ቀን ቀብር የምንውል ይመስለኛል።
እውነቴን ነው፤ እኛ ቤት ምግብ በሕይወት ለመሰንበት ከመበላቱ ውጭ እንዲሀ ትልቅ ርዕስ ሆኖ አያውቅም። ሠራተኛችን ጽጌም ብትሆን ከእናቴ ብትሻልም ምግብ ላይ ያን ያኽል የምትደነቅ አልነበረችም። ምስኪን የገጠር ሴት ናት። ከተማ እንደገባች እኛ ቤት ተቀጠረች፤ የከተማ ምግብ የሚባለውን ሙያ እናቴ ናት እንግዲህ ያሰለጠነቻት። ይኼን ሳስብ ሳቅ ይቀድመኛል። ጓደኛዬ ሃይሚ እግር ጥሏት ስበላ ከደረሰች አንዴ ጎርሳ ትተወውና “ከእናንተስ ቤት ምግብ የእኛ ቤት ርሃብ ይሻላል'' ትለኛለች። በተለይ በሠራተኛችን ጽጌ እንጀራ እንደቀለደች ነው “ጽጌ እኮ እንጀራ ሆኖባት ነው እንጀራ የምትጋግረው'' ትልና እንስቃለን። የሆነ ሆኖ የባሌ ቤተሰቦች ከዬት እንዳገኟት እንጃ በደግ ቀን የቀጠሩልኝ ሠራተኛ በዚህ ባለሙያ ቤተሰብ መኻል ከመዋረድ አድናኛለች። ይኼንንም ችዬ ታዲያ በጣም ያማረረኝ ሲበዛ ሃይማኖተኞች መሆናቼው ነበር። ጧት ማታ ቤተክርስቲያን እንሂድ ንዝናዚያቼው ማቆሚያ የለውም፡፡መጀመሪያ እማማ (የባለቤቴ እናት)... “ያይኔ አበባ!” ይሉኛል (እንደዚያ ነው ሲጠሩኝ፣ አቤት ይኼ ስም ሲያስጠላኝ! የሆነ ሰው አምጥቶ እዚህ ግቢያቼው ውስጥ የተከለኝ፣ ከትንሽ ጊዜ በኋላ የምጠወልግና ጠርገው የሚጥሉኝ የሆነ ከንቱ አበባ የሆንኩ መስሎ ነው የሚሰማኝ፡፡) “ነገ የዓመቱ ሚካኤል ነው በጧት ይቀሰቅሱሻል ልጆቹ፤ ቤተስኪያን እንሄዳለን" “አይ! እኔ አልሄድም እማማ'' ደንገጥ ብለው አዩኝ፡፡ አደነጋገጣቼው ጾታዬ'ኮ ወንድ ነው ያልኳቸው ዓይነት ነበር ፡፡ “ምነው! ያውም ለክብረ በዓሉ ከቤተስኪያን የሚያስቀር ...?'' ድንገት የመጣልኝን ሰበብ ወረወርኩ “ፔሬድ ላይ ነኝ'' አልገባቼውም፡፡ ትልቋ ልጃቼው እየሳቀች “ንጹሀ አይደለሁም! ማለቷ ነው" አለች፡፡ የዚያን ቀን በዚህ አለፍኩ፡፡ ከዚያ በኋላ የነበረው የዬቀን ጥያቄ ግን ማቆሚያ አልነበረውም፡፡
ቤታቼው ውስጥ መንፈሳዊ መዝሙር ካልሆነ ምንም ዓይነት ዘፈን አይከፈትም፡፡ ሬዲዮ እንኳን ሲከፍቱ ሰምቼ አላውቅም፡፡ ታዲያ አፍ አውጥተው ባይናገሩትም እኔ ዘፈን ስከፍት ፊታቼው ላይ የማዬው ግራ መጋባት ይረብሸኝ ነበር፡፡ የሆነ መብረቅ ላስመታቼው የተላክሁ ዓይነት ዓይናቼው ማረፊያ ያጣል፡፡ ቀስ በቀስ የራሴን ፍላጎት ቶቼ፣ የእነሱን ለማክበር ከሙዚቃ እየራቅሁ፣ ከመዝሙሩም ሳልቀረብ ዝምታ ውስጥ እየተነከርኩ መጣሁ። ይኼ ደግሞ ድብርቴን አባብሶት ግቢው እስር ቤት እስኪመስለኝ በጭንቀት ልሞት ደረስኩ፡፡ አንዳንዴ አባቴ ጋር ሄጄ አድር ነበር፡፡ በተለይ የባሌ እናት ይኼ ነገር ፈጽሞ ደስ አይላቼውም፡፡ ምንድን ነው ይኼ ሁሉ ነገር? እላለሁ ለራሴ... ምን ውስጥ ነው የገባሁት? ታዲያ አባቴ ቤት ስሄድ እዚያ ሜክሲኮ “ላፍቶ ላፍቶ” የሚል የታክሲ ረዳት ጥሪ “ማኅደረ ሰላም'' ከሚለው ስሜ እኩል ይጎትተኛል፡፡ አምላኬ ርዳኝ ስንቴ አልኩ!
ረብሻ ሦስት!
የስልክ ሰው አይደለሁም፡፡ ሰው በስልክ ዐሥር ደቂቃ ከሚያወራኝ፣ በአካል ሙሉ ቀን ቢያወራኝ እመርጣለሁ፡፡ባለቤቴ፣ በየቀኑ አንዳንዴም በቀን ሁለትና ሦስት ጊዜ ከአሜሪካ ይደውልና ረዢም ሰዓት ሊያወራኝ ይሞክራል... ቀን፣ ሌሊት፣ ጧት፣ ማታ አይልም፤ ይገባኛል...ሚስቱ ነኝ፣ ሌላ የሚያገኝብኝ አማራጭ የለውም፣ ይናፍቅ ይሆናል፣ ግን ሁሉም ነገር ዞረብኝ፤ ስልክ አልወድም።ይኼን ባህሪዬን የሚያውቁኝ ሁሉ ያውቃሉ፣ “ውይ እሷና ስልክ'' ነው የሚባለው፡፡ ሌሊት ከእንቅልፌ መንቃት አልወድም፣ አባቴ እንኳን እኔ ከተኛሁ እንዳይቀሰቅሰኝ ቤት ውስጥ በጥፍሩ ነበር የሚራመደው፣ ረዘመ ከተባለ ያውም የሥራ ጉዳይ ከሆነ ዐሥር ደቂቃ ካወራኹ ራስ ምታት ይጀምረኛል፡፡ ጓደኛቼ “ቴክስት" ቢልኩልኝ እመርጣለሁ፡፡ የሆነ ጊዜ ባለቤቴ አንድ ሰዓት ሙሉ ያወራኝ ቀን ሲዘጋው አለቀስኩ፤ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ። ፊቴን የጋለ ጆርዬን በቀዝቃዛ ፎጣ ሸፍኜ አለቀስኩ ጩኺ! ጩኺ! አለኝ፣ ርግማን ነው ይኼ! ምንም ምንም በነፍስም በሥጋም የሚቀራረብ ነገር የሌለን ሰዎች ምን ዓይነት ነገር ነው ያገናኜን? ባሕሪው ጥሩ ይሁን አይሁን የራሱ ጉዳይ።
ለምሳ ወጥቼ ነው ብሎ በደረቅ ሌሊት ይደውላል፤ አእምሮዬ ሌሊት ነውና ስለምሰ ማሰብ አይችልም። ባሌ በሌሊት ምሳ የሚበላ ፍጥረት ነው? አይ! አሜሪካ የምለ ሰዓት ነው እላለሁ ለራሴ፣ ይሁና በዚህ ሰዓት የሆነ ነገር እያላመጠ የሚያወራ ሰው በእንቅልፍ ልብ መስማት ያቅለሸልሻል፡፡ ስልኬን ከዘጋሁ በቤት ስልክ ዋናው ቤት ደውሎ ደህና አይደለችም እንዴ? ይላል እየተንጋጉ መጥተው በደረቅ ሌሊት በሬን ያንጓጓሉ፡፡ የሩቅ ትዳር ርግማን ነው፣ ዝም ብሎ ሲያወራ ሬዲዮ ይመስለኛል፡፡ ስሜን የሚጠራ የሆነ ዜና አንባቢ…“ማሂዬ የኔ ማር!” አጠራሩ ይዘጋኛል፡፡ የAND3 መራራቅ በወሬ ሊሞሉ መጣር፤ እንዲያውም ሌላ ነገር ያምረዋል፣ በስልክ ስለ ሴክስ ማውራት ምናምን፤ በራሴ አዝናለሁ በምርጫዬ ድድብና ራሴን ረግመዋለሁ። አዲስ አበባ የተቀመጠ የከሰል _ ፍም፣ _ አሜሪካ በረዶ ላይ ተቀምጦ ሊሞቅ እንደሚታገል ሰው ምን ምስኪን አለ? እንዲህ ዓይነት ሕይወት...

👍35❤3
የእሱ ችግር አይደለም ድድብናዬ ነው። ከአንድ አብርሃም ለመሸሽ አሜሪካ ድረስ መሮጥ ምንድን ነው? ፈረስ ጭኖ፣ ጦር አሰልፎ አሳደደኝ? ቆይ ባላገባስ?...እዚህ መሥሪያ ቤቴ ስንት የሚመኙኝ ወንዶች ነበሩ፣ አንድ ወንድ ስለገፋኝ ስንት ሚሊዮን ሕዝብ የሚኖርባት አገሬን፣ ሥራዬን፣ ፀሐዬን፣ ሰፈሬ ሜክሲኮን፣ አዲስ አበባዬን ትቼ መፈርጠጥ አልተጋነነም? ምን ዓይነት ፈሪ ብሆን ነው? አስባለሁ...ስለ አብርሽ አስባለሁ፤ ከፍተኛ በስልክ ያወራብኝ ያውም ረጅሙ አሞኝ ሊጠይቀኝ የደወለ ጊዜ ነበር፡፡ አምስት ደቂቃ ቢሆን ነው፡፡ ከፊልድ ስመለስ ታመምኩ፣ በአጋጣሚ ሲደውል መታመሜን ነገርኩት።
“ሆስፒታል ሄድሽ?''
“አልሄድኩም::''
“ተዘጋጅና ጠብቂኝ መጣሁ እንሄዳለን” በቃ ትዕዛዝ ነበር።
ሆስፒታል የማልወደው ልጅ ተዘጋጅቼ ጠበቅሁት አብሬው መሄዴ ነበር ያስደሰተኝ። በኮንትራት ታክሲ መጣ እና ወሰደኝ፡፡ እንደዚያን ቀን ተደስቼ አላውቅም። ሁልጊዜ
በታመምኩ ብዬ እስከምመኝ። ከእኔም የባሰ ስልክ የማይወድ ሰው ነበር፤ ለምንድን ነው ግን ያላገባኝ? ወይስ የምፈልገውን ለማግኜት እንዴት መዋጋት እንደነበረብኝ አላወቅሁም...?
ሰላም ውልብ ሲል!
መቼም ሁሉም ሰው ለአፍታም ቢሆን ከዚህ ዓለም ሁካታ ራሱን የሚደበቅበት ቦታ ይኖረዋል።ይኼ ደግሞ _ ከሕፃንነታችን የሚጀምር የነፃነት ፍላጎት ሳይሆን አይቀርም። ለዚያ ሳይሆን ይቀራል ሕፃናት በዬአልጋና ጠረንጴዛ ሥሩ የራሳቼውን ዓለም ፈጥረው ቁጭ የሚሉት? ባለቤቴ ዮናስ ከማያቋርጥ የወሬ ጎርፉ በአንዱ ስለ መርካቶ አውርቶኝ ነበር። አባቱ ሳይሞቱ በፊት መርካቶ የጣቃ መሸጫ ሱቅ ነበራቸው። እና በዚያ የመርካቶ ሁካታ መኻል በእነዚያ የጣቃ ጨርቆች መጋረጃ ነገር ሠርቶ ውስጡ ይደበቅ ነበር። ሰላም ይሰማኝ የነበረው በእነዚያ ግርዶሾች ውስጥ ነበር ይላል። ነገሩ የልጅ ዕቃ-ዕቃ ጨዋታ ይምሰል እንጂ ስሜቱ ይገባኛል። እነዚያ የጣቃ ግርዶሾች የኮንክሪት ግድግዳ አልነበሩም፣ዕድሚያቼው አጭር ነበር ወይ ይሸጣሉ አልያም ተጠቅልለው ይደረደራሉ። ግን ለቅጽበት የሰጡት ሰላም እስከአሁን ትዝታው ሆኗል። የአብርሽ ቤት ለእኔ እንደነዚያ የጣቃ ግርዶሾች ነበር። ለጊዜው እራሴን የጋረድኩበት ትዝታው የቀረ ግርዶሽ። አብሮነታችን ከምን እንደተሠራ ስላልገባኝ ነበር ዘላለማዊ ካልሆነ ብዬ ችክ ያልኩት፤ ወይ እሱ በእኔ ውስጥ ተደብቆ ነበር፣ አልያም እኔ በእሱ ውስጥ ተደብቄ ነበር። ዕቃ-ዕቃው ፈረሰ ሲባል የኔ ነፍስ የዕቃ-ዕቃውን ሕግ ጥሳ ተነጫነጨች፤ ፍቅር እፍርታም አደረገኝ። በዚህ ሁሉ የሕይወቴ ረብሻ መካከል በጣት የሚቆጠር የሰላም ጊዜ የነበረኝ እሱ ጋር እዚያ ቤት ነበርና ዛሬም ቢሆን በራሴ አልፈርድም። ለምንድን ነው ማንም በቀላሉ ሊያደርገው የሚችለውን ቀላል ነገር ሁሉ እሱ ሲያደርገው እንደ ትልቅ ተአምር፣ እንደ ትልቅ ታሪክ ነፍሴ ውስጥ ታትሞ የሚቀረው? በእነዚያ አራት ዓመታት የማይረሱኝ እስከ አሁን ሳስባቼው ልዩ ስሜት የሚሰጡኝ ጊዜያት ነበሩ። ጥቂት
ናቸው በጣም ጥቂት። የሆነ ቀን ሲደውልልኝ ፔሬድ ላይ መሆኔን ነገርኩት፤ ፔሬድ ላይ ስሆን በተለይ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት ስቃይ ነበሩ። እሱ ቤት ከሄድኩ የግድ አብረን መተኛት እንዳለብን አእምሮዬ አምኖ ነበርና ፔሬድ ላይ ከሆንሽማ ሌላ ጊዜ እንገናኛለን እንደሚለኝ ነበር ያሰብኩት። “እና መምጣት አትችይም?'” አለ ግራ ገብቶት። “መምጠትማ እችላለሁ ግን . . ." ሳቀና “ችግር የለም ! ነይና እዚህ አርፈሽ፣ ተጫውተሽ ትሄጃለሽ፤ አሪፍ ምሳ ሰርቻለሁ _እንደምታውቂው ሙዚቃም አለ" አለኝ የዚያን ቀን ለምን እንደዚያ ተለማመጠኝ እላለሁ። ምናልባት የሆነ ብቸንነት ተሰምቶት ይሆን? አላውቅም:: እቤቱ እንደደረስኩ ሻወር ወስጄ በቦርሳዬ የያዝኩትን ፒጃማ ለብሼ ጋደም አልኩ። የሚስትነት ስሜት እስከሚሰማኝ ተንከባከበኝ። ምሳ በላን፣ሻይ አፈላልኝ፤ ከዚያ በፊት ሕመሜ ጋር ከመታገል ውጭ ምንም ዓይነት ማስታገሻ መድኃኒት ወስጄ አላውቅም _ ነበር። ሄዶ “አይቦፕሮፊን' የሚባል የሕመም ማስታገሻ መድኃኒት ገዝቶልኝ መጣ። አጠገቤ ቁጭ ብሎ ስለ ጽሁፎቹ አዲስ እዬጻፈ ስለነበረው መጽሐፍ አወራኝ። እንደዚያን ቀን ረዘም ላለ ጊዜ አውርቶኝ አያውቅም። ከምሳ ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሸቱ አንድ ሰዓት አካባቢ ከአጠገቤ አልራቀም። የተሰማኝ ምቾትና ሰላም እስከ አሁን ውስጤ አለ። እንዴት ውብ ስሜት ነበር!! የዚያን ቀን እሱ ጋር ማደር ፈለግሁ። ሁል ጊዜ ቤቱ ማደር እፈልግ ነበር። እሱ ደግሞ በግልጽ “ማሂ ሰላም! አብረሽኝ ብታድሪ በጣም ነው ደስ የሚለኝ፤ ግን ያላገባሽው ሰው ቤት በጭራሸ ማደር የለብሽም''ይለኛል፡፡ “ምንድን ነው ፍልስፍና ነው?'' እለዋለሁ፡፡ “ልትይው ትችያለሽ፤ እንዲሁ የግል እምነቴ ነው። ለአንዳንድ ነገሮች ቦታ መተው አለብን። ለምሳሌ ለትዳር፣ አብሮ ማደር ለትዳር መተው ያለበት ነገር ነው የሚል
ጽኑ እምነት አለኝ። ቢያንስ ስለ ትዳር ስናስብ ልንጓጓለት የሚገባ የሆነ ነገር መተው አለብን. . . ስናገባ ለመጀመሪያ ጊዜ አደረግነው የምንለው ነገር ... ቀላቀል ሐሳብ ይመስላል፣ ግን ለምን እንደሆነ እንጃ ማደር የሚባለውን ነገር በቀላሉ ማዬት እልችልም' ይለኛል። እኔ ግን ቀን አብረን ስንውል ካደረግነው ነገር የተለዬ ሌሊት የሚፈጠር ምን ተአምር ይኖራል እያልኩ ውስጤ በቅሬታ ይሞላል፤እሱ ጋር ማደር እፈልግ ነበር። የዚያን ቀን እንደዚያ በሰላም ውዬ በኮንትራት ታክሲ ወደ ረብሻዬ ተመለስኩ። በአራት ዓመታት ቆይታችን አንድም ቀን አብረን አድረን አናውቅም። ታዲያ ባለቤቴ ዮናስ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ሀዋሳ አብረን ስናድር (ያኔ ገና አልተጋባንም) በነገሮች ብረባበሽም እንደ ትልቅ ተአምር ነበር ያየሁት። እሱ ጋር ማደሬን ሳይሆን ወንድ ጋር ማደሬን። እንደዚህ የመሳሳሉ የሰላም _ ውልብታዎች እንደ ትልቅ ትዝታ በዬቀኑ እእምሮን ይሞሉታል፤ እንደ ጣቃ እየተተረተሩ የሚያልቁ ግርዶሾች።
*።**።*።
አረገዝኩ! ሕይወት ቀልድ አታውቅም፤ የባልዬው ሲገርመኝ ነፍስ አልባ ሥጋዬ ውስጥ ሌላ ነፍስ አደረ፡፡ ካገባሁ ከዓመት በኋላ ነበር ያረገዝኩት፣ ያገባሁት ከሆነ ሰው ለመሸሽ እንደሆነው ሁሉ ያረገዝኩትም ይኼን ሸሽቴን ሙሉ ያደርገዋል በሚል ስሌት ነበር፡፡ ባለቤቴ ከአሜሪካ ተመልሶ መጥቶ እኛ ጋር ወዲያ ወዲህ እያለ ሰርግና ምላሽ ሆኖለታል፤ በጣም ደስ ብሎት ስለነበር የሚይዝ የሚጨብጠውን አያውቅም፤ እኔ ግን __ ብዥዥ እያለብኝ ነበር፡፡ እንደ ሴቶቹ ጧት አላስመለሰኝም፣ ምግብ አልዘጋኝም፡፡ እንዲያውም በሕይወቴ እንደዚያን ሰሞን በልቼ አላውቅም፡፡ በቃ ቁጭ ብዬ ያገኜሁትን ወደ አፌ መላክ ሆነ። እርግዝና _ ከሚለው ቀጥሎ አእምሮዬ ውስጥ የሚያቃጭለው ማስወረድ የሚል ቃል ነበር፡፡ ያስጠላኝ ብቼኛ ነገር ባሌ እና የቡና ሺታ ብቻ ነበር፡፡ ሳወራ ይደክመኛል በሚል ሰበብ ባሌ ጋር ለዛ ቢስ ማስመሰል የሞላው ወሬ ከማውራት ዳንኩ፡፡
እርግዝናው ምቾት አልሰጠኝም በሚል ሰበብ አልጋ ለዬሁ፡፡ ለብቻዬ ሰፊ አልጋዬ ላይ ተኝቼ ያለመሳቀቅ ስለማፈቅረው ሰው ማሰብ፣ የማፈቅረውን ሰው መርገም አንዳንዴም በሹክሹክታ ለብቻዬ _ ማውራት _ ጀመርኩ፡ ደግሞ የክፋቱ ክፋት በመጀመሪያወቹ የእርግዝናዬ ወራቶች መልሼ ለማሰብ እንኳን እስኪከብደኝ የማልቋቋመው የወሲብ ስሜት ይሰማኝ ነበር፡፡ ቤተሰብ የተረገዘው ልጅ ወንድ ነው ሴት? እያለ ይነታረካል፡፡ አባቱን ይመስላል እናቱን እያለ ይተነብያል (ሲወለድ ሊያዩት ምን ሥራ አስፈታቼው?) ወንድ ይሁን ሴት፣ እኔን ይምሰል ይኼን አብሬ

👍33❤4
የምኖረውን ሰውዬ፣ አልያም ሰሞኑን በቴሌቪዥን የሚታዩትን ቬኔዙላ የተባለች አገር ፕሬዚዳንት ግድ አይሰጠኝም፣ እላለሁ ለብቻዬ። ለጊዜው እርግዝናዬ ደስ ያለኝ፣ ለረዥም ጊዜ ረፍት ወስዶ ከአሜሪካ ከመጣው ከዚህ ባል ከተባለ ፍጥረት ፈቀቅ እንድል ዕድል ስለሰጠኝ ነው(ጠልፎ በግዳጅ ያገባኝ ይመስል) ምን ዓይነት እናት እንደምሆን አላውቅም፤ ለምን እናት እንደምሆንም አላውቅም፡፡ ብዙ ጊዜ እርጉዝ መሆኔን እየረሳሁ ለእርጉዝ የማይገባ ነገር ሳደርግ ባሌ ይከለክለኛል፡፡ ዓይኑ እኔ ላይ ነበር፡፡ እርጉዝ ይኼን አታደርግም፣ ያንን አታደርግም ...እና ለስለስ ብሎ ጸጉሬን አየደባበሰ “አንዳንዴ ሰውነትሽ ዘና እንዲል ሴክስም ጥሩ ነው'' ይለኛል... ነበር - ግን እዚያ የተረገመ ልጅ ጋር ቢሆን እንኳን ጸጉሬን ነክቶኝ ገና በዓይኑ ሲያዬኝ ቀሚሴ በራሱ ጊዜ ተንሸራቶ ራቁቴን በተገኜሁ ነበር፡፡ ባሌ ጥሩ ሰው ነውና አይጋፋኝም፣ ያሳዝነኛል፡፡ ያለፍኩትን አያውቅም፣ እንደ ምጠላው አያውቅም፣ ሚስት አለኝ፣ ትዳር አለኝ ብሎ ውቂያኖስ አቋርጦ የመጠ ሚስኪን ፍጥረት፣ ሰውን የሚያስፈቅር መድኃኒት ቢኖር አሁኑኑ ውጨ ባፈቀርኩት ነበር። ፍቅር _ የሚባል የተረገመ ስሜት፣ በውለታ አይመጣ በደግነት ምናባቴ ላድርገው ...? ወለድኩ! ሴት ልጅ፡፡ ቀድሜ እኔ አለቀስኩ፣ ምጡ ለራሴ ልጅ ሳይሆን ባል ለሚባለው ሰው የከፈልኩት ዋጋ መሰለኝ። ልክ መሥሪያ ቤት ከሚከፈለኝ በላይ ከባድ ሥራ እንዳሠሩኝ ዓይነት ስላገባኝ ብቻ ይኼን ሁሉ ዋጋ መክፈል ለምን? አልኩ
ለራሴ። ልጁን ሲያሳቅፉኝ የእውነት ከውስጤ ስለመውጣቷ ተጠራጠርኩ። ግን አንጀቴ ተንሰፈሰፈ፡ ትዳር፣ ልጅ እንደ ቀልድ የተሳፈርኩባት የሕይወት (an በቀስታ እያንሳፈፈች ወደ ውቂያኖሱ መኻል የወሰደች ... ከምወደው ል? ብቆምበት ከምተማመንበት ብዙ አበባና ፍቅር ካለበት ምድር ያራቀችኝ፤ መሰለችኝ ወይስ ሕይወት ውቂያኖሱ ናት?... ትዳሩ መሆን አለበት ጀልባው፡፡ በሌ ልጃችንን በጉጉት እያዬ በላብ የረሰረሰ ግንባሬን ይስመኛል፣ አሁን ደግሞ ምን ይሁን ነው? ...እላለሁ፡፡ “እንዴት የምታምር ልጅ ናት!” ይላሉ ገና እንኳን ምናምኗ ያልታጠበ ሉጫ ጸጉሯ እናቷ ላይ የተለጠፈ አስፈሪ ፍጡር፣ ስታለቅስ የሚበዛውን የፊቷን ክፍል አፏ ይሸፍነዋል፤ አፍንጫ፣ ዓይን ሳይሆን ትልቅ አፍ ያላት ፍጥረት ዓይነት...ሲያሳቅፉኝ ግን ተንሰፈሰፍኩ፡፡ ያኔውኑ ነፍሴ ውስጥ ልጅ የሚባል ነገር ታተመ፤ ዕንባዬን ማቆም አልቻልኩም፡፡ እንቅልፍ ወሰደኝ... ሰመመን... እናም በሐሳብ ደሜ ሳይደርቅ ያ የተረገመ ልጅ ወዳለበት ወደ ነበረበት በረርኩ‐ ወደ ላፍቶ ... ቼልተኛ ፊቱ ፊት፣ ልጄን አቅፌ ቆምኩ፣ ርግማን ነው፡፡
ባለቤቴ ከሥሬ አይጠፋም፡፡ አባባ የኔ ምስኪን አባት፣ ልክ እንደ እናት ልወልድ ሆስፒታል ከገባሁባት ቅጽበት ጀምሮ አልተለዬኝም። ከወለድኩ በኋላ አባባ ሰው ጉድ እንዳይል አፍኖት እንጂ፣ ዕንባ ሲተናነቀው ታዝቤ ነበር። በጣም ነው ደስ ያለው፡፡ በኋላ ነው የገባኝ፣ ልጄ ከእኔም ሆነ ከባለቤቴ አንዲት ዘለላ ጸጉር ሳትይዝ ማደ እናቴን መስላ ቁጭ አለች፡፡ እናቴን ወለድኩ ብል በትክክል ይገልጸዋል፤ የጥቁር ቆንጆ፡፡ይኼ እኔንም ገረመኝ፣ አባባ በቀስታ “ሰላምዬን ቁጭ''አለ፡፡ ዓይኖቼን ጨፍኜ በሰመመን ወደ ኋላ ተጓዝኩ ወደ ኋላ ...

👍39❤5👏2
እባክሽ አትሂጂ…..
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አምስት
ቀኑን ሙሉ ሲሸክከኝ ነው የዋለው፡፡ሀሳቤን ሰብስቤ አንድ ውሳኔ ላይ መድረስ አቅቶኝ ስብሰለሰል ዋልኩ፡፡ማታ ሄጄ ከኤርፖርት ‹‹እንኳን ለሀገርሽ በቃሽ ››ብዬ ልቀበላት ወይስ ይቅርብኝ….?የመቀበሉንም ያለመቀበሉንም ትርፍና ኪሳራውን እየተነተንኩ ሳሰላስል ዋልኩና 10 ሰዓት አካባቢ ወሰንኩ፡፡ ወንድ ልጅ ቆረጠ፡፡እግሬን አላንቀሳቅስም፡፡››ስወስን ቀለል እያለኝ መጣና ስራዬ ላይ አተኮርኩ፡፡12 ሰዓት ላይ የእለቱን ስራዬን አጠናቅቄ ከሆሲፒታል እየወጣሁ እያለ…ስልኬ ጠራ፡፡ከኪሴ አወጣሁና አየሁት፡፡ወይ ጣጣ እማዬ ነች፡፡ላለማንሳትም ፈለኩ…ግን አሟት ፈልጋኝ ቢሆንስ? አላስቻለኝም እና አነሳሁት፡፡
‹‹ሄሎ እማ እንዴት ነሽ?›.
‹‹አለሁልህ ልጄ..አንተስ እንዴት ነህ?››
‹‹እኔማ ምን ሆናለው ብለሽ ነው? ሰላም ነኝ፡፡››
‹‹ያው የትናንቱ አንጎበር ከጭንቅላትህ ካልወረደ ብዬ ነዋ››ብላ በአሽሙር ጠቅ አደረገችኝ፡፡
‹‹አይ ደህና ነኝ፡፡››በአጭሩ መለስኩላት፡፡
‹‹አሁንም ወደመጠጥ ቤትህ ጎራ እንዳትል ነው በጊዜ የደወልኩልህ፡፡››
‹‹ማለት?››
‹‹ማለትማ አሁኑኑ ወደቤትህ ሄደህ ተዘገጃጅና በጊዜ ሄደህ ልጅቱን ተቀበላት እያልኩህ ነው፡፡ደግሞ ነገ በጥዋት እቤት ይዘሀት ና፡፡ ቁርስ ሰርቼ እጠብቃችኃለው..››
‹‹እማ …ልጁቷ እዚሁ አዲስ አበባ ቤተሰቦች አሏት እኮ ፡፡አሁን ምትይውን እነሱ ማድረግ ይችላሉ፡፡››
‹‹አይ እንግዴ ተናግሬለሁ፡፡ጥዋት ቁርስ ተዘጋጅቼ እጠብቃችኋላው፡፡በል አሁኑ ወደቤት ሄድ ያልኩህን አድርግ፡፡››ስልኩ ተዘጋ፡፡
ከመናደዴ የተነሳ ጨጓራዬን ለበለበኝ፡፡ወይ እማዬ…አሁን እሺ ምንድነው የማደርገው?፡፡የእማዬን ትእዛዝ አለመተግበርና ከፍቃዷ ማፈንገጥ ማለት ደግሞ እሷን ብስጭት ላይ መጣል ነው፡፡ተበሳጨች ማለት ደግሞ ለተወሰነ ወር እስርስር ብላ አልጋ ላይ ቀረች ማለት ነው፡፡እንግዲህ መምረጥ አለብኝ፡፡ቀጥታ እንደታዘዝኩት ወደቤት ሄድኩ፤ግን ምንም የምዘጋጀው ነገር አልነበረኝም፡፡ሻወር መውሰድ፣ልብስ መቀየር፣ላደርጋቸው የምፈቃዳቸው ነገሮች አይደሉም፡፡ብቻ ሰዓት እስኪደርስ አረፍ ልል ነው፡፡ከቤቴ ቦሌ አየር ማረፊያ ድረስ ከ30-40 ደቂቃ ነው የሚፈጀው፡፡እናም ከቤቴ ሶስት ሰዓት ሲሆን ለመነሳት ቆርጬያለሁ፡፡…አስከዛ እራቴን ሰርቼ ለመብላት የሚበቃኝ በቂ ሰዓት ቢኖረኝም የምግብ አምሮቴ ድራሹ ስለጠፋ ዝም ብዬ በተቀመጥኩበት ሶፋ ላይ ጋደም ብዬ የቴቪዬን ቻናል እየቀያየርኩ በሀሳብ መንጎድ ቀጠልኩ፡፡ ናፍቃኛለች፡፡ ከሰዕታት በኃላ ከኖሮዌዬ የምትመጣው ሽቅርቅሮ እርግበ አይደለችም..በልጆቾ ተከባ ባሏን እየተንከባከበች ስላለችው ልዕልተ ነው የማወራው፡፡
አይደርስ የለ አስጠሊታው ሰዓት ደረሰና ለሶስት አስር ጉዳይ ሲል መኪናዬን አስነስቼ ወደቦሌ ጉዞ ጀመርኩ፡፡ለኣራት 25 ጉዳይ ደረስኩና ጥበቃዬን ቀጠልኩ፡፡ አስር ጉዳይ ሲሆን ግን ስልኬ ጠራ፡፡የእሷ መስሎኝ አነሳሁት፡፡እርብትብት የማውቀው ድምፅ ነው፡፡ሰውነቴ ተብረከረከ፡፡
‹‹ልዕልት ምን ሆንሽ?››
‹‹እኔ እንጃ ዶክተር፡፡ዝም ብሎ ይንቀጠቀጣል፡፡ከአፉም አረፋ ነገር እየወጣ ነው፡፡ጉድ ልሆንልህ ነው መሰለኝ ደክተር፡፡›››
‹‹አይዞሽ ተረጋጊ አሁን መጣሁ፡፡ከእሷ ጋር እያወራው ወደመኪናዬ ገባሁና ሞተሩን አስነሰው፡፡በርሬ እሷ ጋር በመድረስ ትከሻዋን አቅፌና ደረቴ ላይ ለጥፌ እሷን ከማፅናናት ውጭ በዚህ ሰዓት ምንም የሚያስጨንቀኝም ሆነ የሚያሳስበኝ ምድራዊ ጉዳይ እልነበረም፡፡እቤቷ ልደርስ 5 ደቂቃ ሲቀረኝ ስልኬ ጠራ፡፡እሷ መስላኝ አነሳሁት፡፡
‹‹እ..ደርሼለሁ፡፡››
‹‹ምን?››
‹‹ደርሼያለሁ…የታለህ ?››
ድምፁ የልዕልተ እንደሆነ ስረዳ ደነገጥኩ፡፡
‹‹እርግበ አዝናለሁ መጥቼ ነበር …በሽተኛዬ ታሞ ተደውሎልኝ አሁን ወደእዛ እየሄድኩ ነው፡፡››
‹‹አር ዩ ኪዲንግሚ ሚ?››
‹‹ የህይወት ጉዳይ ነው፡፡ስጨርስ ደውልልሻለሁ፡፡ ቸው…፡፡››ዘጋሁትና ስልኩን ሙሉ በሙሉ አጠፋሁት፡፡በራፏ ደርሼ ክላክስ ሳጮህ ተከፈተልኝ፡፡ ከፋቾ ሰራተኛዋ ነበረች፡፡መኪናዬን እንደነገሩ አቆምኩና ወደውስጥ ተንደረደርኩ፡፡ ቀጥታ በሽተኛው ወደሚተኛበት የመኝታ ቤት ነበር ያመራሁት፡፡በርግጄ ስገባ ወለል ላይ በቂጦ ተዘርፍጣ በመቀመጥ ግንባሯን አልጋው ላይ ደፍታ ለበድንነት የቀረበ ሰውነቱን እየዳበሰች ትነፈርቃለች፡፡እንዳየችኝ በርግጋ ከተቀመጠቸብት ተነሳች ቆመች፡፡
‹‹ዶር አየኸው አይደል…?ምን ሆኖ ነው..?በፈጣሪ የሆነ ነገር አድርግ…?›› በአሳዛኝ ሁ..ኔታ ትለምነኝ ጀመር፡፡አብዝታ ከማልቀሷ የተነሳ አይኖቾ ደም ለብሰው አባብጠዋል፡፡እንደው በዚህ ሰዓት መለኮታዊ ስልጣን ቢኖረኝና ‹‹አንተ በሽተኛ ድነሀል ተነስና አልጋህን ተሸክመህ ዝለል፡፡›› ብዬ ባስጨፍረውና ለእሷም ሳቋንም ብመለስላት እንዴት ደስ ይለኝ ነበር መሰላችሁ፡፡.ግን እልችልም …እኔ ሀኪም ነኝ እንጂ መሲህ አይደለሁም..፡፡
‹‹እስኪ ልየው…ውጪና ሳሎን ጠብቂኝ፡፡››
‹‹ይሻላል? እዚህ ብሆንስ..?››
ከእሱ ለመለየት ድፍረቱን አላገኘችም፡፡እንደምንም ተጭኜ ክፍሉን ለቃ እንድትወጣ አደረኩ፡፡ በራፉን ከውስጥ ቀረቀርኩና ከበሽተኛው ጋር ተፋጥጬ ቆምኩ፡፡ እሷ እንምድትወጣ ያደረኩት ለራሴ ብዬ ነው፡፡ የእሷን እንባና ሀዘን ፊት ለፊት እያየሁ በምንም አይነት ተአምር ሰውዬውን መርምሬ ችግሩን ለማግኘትና መፍትሄ ልዘይድለት እንደማልችል ስለገባኝ ነው፡፡
ብቻ ያንንም ይሄንንም አድርጌ ከሰላሳ ደቂቃ በኃላ ቀድሞ ወደነበረበት የመረጋጋት ሁኔታ እንዲመለስ ማድረግ ቻልኩ፡፡መጥታ ስታየው በጣም ተደሰተችና ተጠምጥማ አቅፋ አመሰገነችኝ፡፡ከምታቅፈኝ ብትስመኝ ይሻለኝ ነበር፡፡
ከግቢያቸው ተሰናብቼት ስወጣ አምስት ሰዓት ሆኖ ነበር፡፡ቀጥታ ወደቤቴ ነው ያመራሁት፡፡ ደርሼ ቁልፉን ከኪሴ አውጥቼ ልከፍት ስታገል እምቢ አለኝ፡፡ግራ ገባኝ፡፡ ደግሜ ስታገል ከውስጥ ድምፅ ሰማሁ፡፡ግራ ተጋባሁና ቁልፉን አውጥቼ ተገትሬ ቆምኩ ‹..ቃቃ..››የሚል ድምፅ ከውስጥ ተሰምና ተከፈተ፡፡እርቃን ጋላዋ ላይ ብጣቂ ሰማያዊ ፓንት ብቻ አድርጋ ፊት ለፊቴ ቆማለች ፡፡እየቃዣሁ ሁሉ መሰለኝ፡፡ሰላምም ሳትለኝ እየተምነቀነቀች ፊቷን አዞረችና ቀጥታ ወደመኝታ ክፍሉ ተመልሳ ገባች፡፡ወይ እርግበ፡፡ሳሎን ሙሉ ሰው ጠቅልለው የሚይዙ ግዙፍ ሁለት ሻንጣዋች አሉ፡፡የጎርጥ አየኋቸውና በደመነፍስ ወደ መኝታ ቤት ተከትያት ገባሁ፡፡ ከላይ ምንም ልብስ ሳትለብስ ዝርግትግት እና ብልቅጥቅጥ ብላ ተኛች፡፡

👍49❤6🥰2😁2
#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ዶ/ር ሶፊያ የተኛችበት ሆስፒታል አልጋ ላይ ሆና በኤልያስ በኩል ከትንግርት የተላከላትን ዲያሪ ማንበብ ጀመረች፡፡
ጥቅምት 25 1999ዓ.ም
የሁለተኛ አመት የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ከጀመርን አንድ ወር ሊሞላን ነው፡፡አምና ፍቅረኛ ነበረኝ፡፡ጌዲ ከኔ ጋር ነበር..አሁን ግን ብቻዬን ነኝ፡፡ቢሆንም ምርጥ የሴት ጓደኛ ማግኘት ችያለሁ፡፡ሶፊያ ትባላለች፡፡አንድ ዶርም ነው የምንጋራው፡፡እርግጥ ሌሎች አራት ልጆችም አብረውን ይኖራሉ..በአርባ ምንጭ ሙቀት አንድ ዶርም ውስጥ ስድስት ሰው ታጭቆ መኖር ይከብዳል..ቢሆንም እየኖርን ነው፡፡
ሶፊ የምትገርም ልጅ ነች…የተወለደችውም ያደገችውም አሜሪካ ነው፡፡ በዲሞሽን ወደ
ኢትዬጵያ ከተወረወረች ሶስተኛ አመቷ ነው፡፡ አንድ አመት ሃይስኩል የተቀሩትን ሁለት ዓመት እዚህ ዩኒቨርሲቲ እንዳሳለፈች አጫውታኛለች፡፡
ስለእሷ ሳስብ ሚገርመኝ የኢትዬጵያ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ውጭ ለመላክ አፈር ድሜ ይግጣሉ..የእሷ ወላጆች እሷን ባህሏን እረሳች..ፀባዮ ተበላሸ ...መረን ለቀቀች በሚል ሰበብ ወደ ኢትዬጵያ ላኳት..ልክ እንደ ፀባይ ማረሚያ..አይ ሚስኪኗ ሶፊያ፡፡
ህዳር-5 1999 ዓም
ከሶፊ ጋር ዛሬ ወደ ከተማ ወጥተን ነበር..ሲቀላ ፡፡ ዋናው የሄድንበት ምክንያት አባቷ ከአሜሪካ ዶላር ልኮላት ስለነበር ያንን ለመቀበል ነው፡፡ አንድ ሺ ዶላር ነበር የላከላት፡፡ከዛ ምሳ ጋበዘችኝ..ወይን ጠጣን…ለእሷ አንድ ሱሪ ብቻ ስትገዛ ለእኔ ሁለት ሱሪና ሁለት ቀሚስ ገዛችልኝ፡፡ግርም ነው ያለኝ፡፡ ማነው ለጓደኛው እንዲህ የሚያደርገው…?በዛ ላይ የእሷን ያህል አይሁን እንጂ እኔም ከውጭ በሚላክ ዶላር የምማር ልጅ ነኝ፤ሌላው ደግሞ አንድ ደርዘን የሚያማምሩ ፓንቶች ገዛችና ስድስቱና ለእኔ ስድስቱን ለራሷ ወሰደች፡፡በእውነት የዋህ ነች እንዳልል ለሌሎች ጓደኞቿ እንደዛ ስታደርግ አይቼት አላውቅም፡፡ብቻ እኔ ወደድኳት፡፡ጥሩ ጓደኛዬም አድርጌ ከልብ ተቀብዬታለሁ፡፡
ህዳር 29 1999 ዓ ም
የሚቀርቡን የዩኒቨርቲ የወንድ ጓደኞቻችን ከተማ ካልወጣን አሉን፡፡አስር ሆነን ወጣን.... አራት ሴት ስድስት ወንድ፡፡ከግቢ ስንወጣ እራሱ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ሆኖ ነበር፡፡ከግቢ በታክሲ ሲቀላ... ከሲቀላ ደግሞ ሼቻ አመራን፡፡ በመጀመሪያ ወደ በቀለ ሞላ ሆቴል ነው ያመራነው፡፡፡
ሆቴሉን ጥለን ወደ ጓሮ አለፍንና ውጭ ወንበር ከበን በመቀመጥ እራት አዘዝን፡፡ከፍታ ቦታ ላይ ያለው የበቀለ ሞላ ሆቴል ወደ ታች የነጭ ሳርን የተንጣለለ ደን፤ በእግዜር ድልድይ የተከፈሉትን አባያና ጫሞ ሀይቅን፤ በግሩም
ሁኔታ ማየት የሚያስችል እስትራቴጂካዊ ቦታ ላይ ነው የታነፀው ..ከዛ ከዝቅታው የተፈጥሮ ሙዚዬም ወደ ላይ ሚነፍሰው ቀዝቃዛና ነፋሻማ አየርም ልብን ስውር ያደርጋል፡፡ እራታችንን በልትን ስናጠናቅቅ እና የበቀለ ሞላን ሆቴል ለቀን ስንወጣ 2፡45 ሆኖ ነበር፡፡ ቀጥሎ ሞቅ ወዳለው ጫሞ ሆቴል ነው የገባነው፡፡በተለያ አጋጣሚዋች ሶስት ቀን እዚህ ቤት መጥቼያለሁ....በተለይ ከጊዲዬን ጋር የመጣሁባቸው ሁለት ቀናት አይረሱኝም፡፡
መጠጥ መጠጣት በቢራ ነው የተጀመረው፡፡ ጨወታው፣ ተረቡ ደስ ይል ነበር፡፡ በተለይ የሶፊ ደስታ ልዩ ነበር፡፡በፊትም እኔ ስለማጣጥልባት እንጂ እንዲህ አይነት ቸበርቻቻ ነፍሷ ነው፡፡ ..አራት ሰዓት አካባቢ መቀመጫው ላይ ማንም አልነበረም፡፡ ሁሉም በሙዚቃ ምት በመታገዝ ጭፈራውን እየቀወጠው ነው፡፡አንዳንዱም መጠጡን ከቢራ ወደ አልኮል ቀይሮታል….. እየሰከረ ያለም አለ፡፡ወንዶቹ የመረጧትን እና ቀልባቸውን የተመኛት ሴት ዙሪያ ይሽከረከራሉ… ይጎነታትላሉ ...ይጀነጅናሉ፡፡
ሁለቱ ሴቶች ከሁለቱ ወንዶች ጋር ተግባብተው እየተላላሱ ነው፡ኃይሌ የሚባል የመቀሌ ልጅ እኔን እየጀነጀነኝ ነው..በጣም ያምራል..፡፡ለምን እንደሆነ አላውቅም ይሄን ልጅ ካወቅኩት ቀን ጀምሮ የሆነ ነገሩ ይመቸኛል፡፡እና እንዲሁ በሴትነቴ እግደረደራለሁ እንጂ ቀልቤ ፈቅዶታል..፡፡እሱም እየተግደረደርኩ መሆኔ ገብቶት መሰለኝ ጥረቱን አጠናከረ..ቀስ በቀስ እየደከምኩለት መጣሁ..<በቃ ዛሬ አብሬው ማደሬ ቁርጥ ነው› ስል አስቤ ነበር በውቅቱ ፡፡ ባዛ ላይ ከጌዲዬን ከተለያየው ስድስት ወር ሆኖኛል ...ስድስት ወር ሙሉ ምንም አላገኘሁም ..በጣም አምሮኛል፡፡
ሶፊያ ሶስት ወንዶች እየተሻሙባት ነው፡፡የሆነ ሙድ እየያዘችባቸው መሰለኝ፡፡እዚህኛው ላይ ትንጠለጠላለች.... ያኛውን ትጠቅሰዋለች.. ደግሞ ከዛኛው ጋር ትጎነታተላለች፡፡በመጨረሻ ጓደኛ የሆኑት ሶስቱ ወንዶች እርስ በርስ
መገለማመጥ ጀመሩ…..ስድስት ሰዓት ሲሆን
ሁላችንም በስካር ጥንብዝ ብለን ሆቴሉን ለቀን
ወደ ቤርጓችን ሄድን ፡፡አምስት ክፍል በመደዳ
ነበር የተያዘው፡፡እንዲህ እንዲሆን የወንዶቹ
ዕቅድ ነው ፡፡ዕድል የቀናቸው አራቱ ወንዶች
አንዳንድ ሴት ይዘው ይተኛሉ ምስኪኖቹ ሁለት ወንዶች የቀረችው አንድ አልጋ ላይ አብረው ያድራሉ.. በሚል ስሌት ነበር የተሰላው፡፡....
.......................
እዚህ ጋር ከደረሲው እውቅና ውጪ ቢሆንም ለአንባቢው የሚጎረብጡ ሐሳቦች የተነሱበት ክፍል ስለሆነ ቆርጬ አውጥቼዋለሁ ለምን ተቆረጠ የሚልም አይጠፋምና ከወዲሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ
........"በየጓዲያችን ቀስ በቀስ እየገባ ያለ ነገር ሆኖ ሳለ ቃሉን አናንሳ ..ጭራሽ በጆሮችን አንስማ ማለት አግባብም አይደለም አያዋጣንምም ብዬ አምናለሁ ፡፡
ይልቅ ችግሩ በቤታችን አለ...? አዎ አለ ፡፡… አግባብ ያልሆነ እና መቅረት ያለበት አካሄድ ነው ወይ..? አዋ ነው፡፡..ስለዚህ ውስጡ ያሉትን እንዴት አግዘናቸው ከህይወቱ እንዲወጡ ማድረግ እንችላለን…?ሊገቡ ቋፍ ላይ ያሉትንስ ሳይቃጠል በቅጠል እንዴት ነው ከገደሉ አፋፍ ልንመልሳቸው የምንችለው…? መልሱ ችግሩ በመሀከላችን መኖሩን በግልፅ ስናምን..በችግሩ ላይ በግልፅ መነጋገር
መወያት እና መግባባት ስንችል ነው መፍትሄውን በእጃችን መጨበጥ የምንችለው፡፡ እራሳችንንም ከችግሩ የምናድንበት መድሀኒት ማግኘት የምንችለው ... መጪውን ትውልድንም መታደግ የምንችለው የዛን ጊዜ ነው፡፡››
ካለበለዚያ እንዲሁ በጭፍን ባህላችን አጎደፉት .... እርኩሶች ናቸው፤ ይጨፍጨፉ….ይመንጠሩ በማለት ቅንጣት ውጤት ማምጣት አንችልም፡፡እንደውም ስለዚህ ነገር ሳስብ
1980ዎቹ ቤት አካባቢ የነበረውን የኤች. አይ ቪ ጥፋት ያስታውሰኛል ፡፡የዛኔ ጊዜም ስለበሽታው በአደባባይ አውጥተን መወያየትና መፍትሔ መፈለግ ሲገባን በየጓዲያው በማንሾካሾክ ....አውሬ መጣላችሁ፣ጭራቅ መጣላችሁ እያልን ለተጠቂዎች ሲኦልን
ስንሸልማቸው..እኛም በፍርሀት ታፍነን በቁም
ስንንዘፈዘፍ ስንት እና ስንት ህይወት ረገፈ ….?
ስንቱ አፍላ ወጣት ለውይይትና ለምክክር ዝግ
በሆነው ባህላችን ምክንያት በየጓዳው ባክኖ ቀረ...?ቤት ይቁጠረው፡፡ዛሬም ከዛ ውድመት አልተማርንም፡፡መቼም እርግማን ሆኖብን አንድ ችግር የህዝባችንን እሩብ ካልጨረሰ በስተቀር መፍትሄው አይገለፅልንም፡፡
‹‹ትክክል ነህ .…እኔም ባንተ ሀሳብ እስማማለሁ፡፡›› አለችው ዶ/ር ሶፍያ፡፡
‹‹ጥሩ.. በይ አሁን ተነሺ እንውጣ፡፡››
‹‹ጨረስክ እንዴ ፕሮሰሱን?››

👍72❤4👎1😁1
‹‹አዎ ታክሲም ጠርቼያለሁ...>> አላት እቃዎችን ከሰበሰበ በኃላ .. ደግፎ ታክሲው ድረስ ወሰዳት ..እና ታክሲው ውስጥ እንድትገባ ረድቷት እሱም ገብቶ ከጎኗ ተቀመጠ፡፡ታክሲዋ መንገድ ጀመረች፡፡አቅጣጫዋ ግን ወደ ሆቴሏ ስላልሆነ ግራ ገባት እና ‹‹እንዴ !ወዴት ነው?፡፡››
‹‹እነ ሰላም ይዘሀት ና…. እናስታምማታለን ብለውኛል፡፡ ተሸሎሽ ወደ አዲስ አበባ እስክትመለሺ ቤት ብትሆኚ ይሻላል ብዬ ነው….አይከፋሽም አይደል?››
‹‹አረ አይከፋኝም..እንዳም በጣም ነው ደስ የሚለኝ፡፡›› አለችው፡፡እዛ ቤት ከእነዛ ጣፋጭ ልጆች ጋር ሶስት ቀን አይደለም እድሜ ልኳንም የመኖር ዕድል ብታገኝ ነፍሷ ሀሴት ታደርግ ነበር፡፡
✨ይቀጥላል✨
ቤተሰቦች #YouTube #subscribe እያደረጋቹ አሁንም #subscribe እያደረጋቹ ከነገ ጀምሮ እስከሚያልቅ በየቀኑ ለመልቀቅ አስቤለሁ እናንተም ግን #subscribe እያደረጋቹ ድርሰቱ እስከሚያልቅ 500 #subscribers እጠብቃለሁ #ሰላም✌️
#Share and #subscribe my #YouTube
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
‹‹እነ ሰላም ይዘሀት ና…. እናስታምማታለን ብለውኛል፡፡ ተሸሎሽ ወደ አዲስ አበባ እስክትመለሺ ቤት ብትሆኚ ይሻላል ብዬ ነው….አይከፋሽም አይደል?››
‹‹አረ አይከፋኝም..እንዳም በጣም ነው ደስ የሚለኝ፡፡›› አለችው፡፡እዛ ቤት ከእነዛ ጣፋጭ ልጆች ጋር ሶስት ቀን አይደለም እድሜ ልኳንም የመኖር ዕድል ብታገኝ ነፍሷ ሀሴት ታደርግ ነበር፡፡
✨ይቀጥላል✨
ቤተሰቦች #YouTube #subscribe እያደረጋቹ አሁንም #subscribe እያደረጋቹ ከነገ ጀምሮ እስከሚያልቅ በየቀኑ ለመልቀቅ አስቤለሁ እናንተም ግን #subscribe እያደረጋቹ ድርሰቱ እስከሚያልቅ 500 #subscribers እጠብቃለሁ #ሰላም✌️
#Share and #subscribe my #YouTube
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍50❤4
#ኑዛዜ
እስኪ ስሙኝ አንዴ ወዳጅ ዘመዶቼ
ምን አልባት ከሄድኩኝ እችን አለም ትቼ
መቸም የአለም ነገር ስለማይታመን
እኔም እንደሌሎች የሞትኩኝ እንደሆን
ሰባት አመት ሙሉ ደም እያነባችሁ
ከሊቅ እስከ ደቂቅ ቆሻሻ ለብሳችሁ
ጥቅርሻ መስላችሁ
የሀገሩን ባንዴራ ግማሽ ላይ ሰቅላችሁ
አመድና አፈር ላይ መሬት ተኝታችሁ
በኔ ሀዘን ሳቢያ ቆሎ እየበላችሁ
አደራ ቅበሩኝ በሰሌን አርጋችሁ::
..የለም....የለም.....የለም
በሰሌን ስቀበር በማይረባ ኬሻ
ምስጦች እንዳይበሉኝ እስከመጨርሻ በሻቦላ ትርዒት ማርሽ ባንድ አርጋችሁ
ጥይት በማይበሳው ሳጥን ቆልፋችሁ
ቅበሩኝ ወገኖች አደራ ልስጣችሁ::
....የለም.....የለም....የለም.....
በቀፋፊ ሳጥን መከርቸም ይጨንቃል
አየሩም ሙቀቱም ሊከብደኝ ይችላል
በስፖንሰር ቴሌቶን ገንዘብ ሰብስባችሁ
የመስታውት ሳጥን እንዲሰራ አዛችሁ
በመሀል ፒያሳ ላይ ሐውልቴን አርጋችሁ
ቅበሩኝ ወገኖች ኑዛዜ ልስጣችሁ
የስፖንሰሮች ብርም ይተርፋል አውቃለሁ
በኪሴ አስቀምጡልኝ እፈልገዋለሁ::
የለም እሄን ተውት ገባኝ አሁን ገና
ሉሲም ታስጠላለች በመስታውት ሁና
ይሄንን ያህል ግን ከምትደክሙብኝ
እስኪ ምን አለበት ሞቴን ብትሞቱልኝ?😁

😁34👍22❤5👎2🤔2🔥1👏1
#የነገው_ነፋስ
ያንን ገለባ ልብ
ከደጅ የወደቀው፣
"አድራሻህ ወዴት ነው?"
ብለህ አትጠይቀው፣
የነገው ነፋስ ነው
መንገዱን የሚያውቀው ።
🎴በዕውቀቱ ስዩም🎴
ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ
#Share #like and #subscribe my #YouTube
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ያንን ገለባ ልብ
ከደጅ የወደቀው፣
"አድራሻህ ወዴት ነው?"
ብለህ አትጠይቀው፣
የነገው ነፋስ ነው
መንገዱን የሚያውቀው ።
🎴በዕውቀቱ ስዩም🎴
ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ
#Share #like and #subscribe my #YouTube
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍18🥰6👏3🔥1
#ጠላቴ
ጠላቴን ስፈልግ ከጎረቤቶቼ
ጠላቴን ስፈልግ ከባልደረቦቼ
ጠላቴን ስፈልግ ከሩቅ ከቅርቦቼ
ለካስ ክፉ ጠላት ደመኛዬ ያለው
ከገዛ እኔነቴ ከራሴ ውስጥ ነው !!
🎴በሰለሞን ሞገስ🎴
ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ
#Share #like and #subscribe my #YouTube
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ጠላቴን ስፈልግ ከጎረቤቶቼ
ጠላቴን ስፈልግ ከባልደረቦቼ
ጠላቴን ስፈልግ ከሩቅ ከቅርቦቼ
ለካስ ክፉ ጠላት ደመኛዬ ያለው
ከገዛ እኔነቴ ከራሴ ውስጥ ነው !!
🎴በሰለሞን ሞገስ🎴
ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ
#Share #like and #subscribe my #YouTube
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍31🤔8👏5🔥1
#እኔ_ላንቺ_ማለት
ከሬሳዎች መሀል ወድቆ የተገኘ፣
በጣም የረከሰ ሞቱን የተመኘ፣
ሁሉም የጠየፈው ህሊናውን ሽጦ፣
ባዶውን የቀረ መንፈሱ ተሟጦ፣
ተጠሪ የሌለው ትብያ የወደቀ፣
ወኔው እንደከዳው ጉልበቱ የደቀቀ፣
ሳይወለድ ሞቶ ሳይጀምር ያለቀ፣
በጣም ተራ ሰው ነኝ፡
ምንም የማልረባ፣
ላንቺ የማልመጥን ከቁብ የማልገባ፣
...በኔ መጠየቅሽ አካልሽ ተሳቆ፣
ዕርኩስ እንደነካው ውስጥሽ ተሸማቆ፣
እኔን ላለማየት ህይወትሽ ቢርቅም፣
....ጠልቼሽ አላውቅም።
🎴እሱባለው ብዙነሽ…🎴
ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ
#Share #like and #subscribe my #YouTube
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ከሬሳዎች መሀል ወድቆ የተገኘ፣
በጣም የረከሰ ሞቱን የተመኘ፣
ሁሉም የጠየፈው ህሊናውን ሽጦ፣
ባዶውን የቀረ መንፈሱ ተሟጦ፣
ተጠሪ የሌለው ትብያ የወደቀ፣
ወኔው እንደከዳው ጉልበቱ የደቀቀ፣
ሳይወለድ ሞቶ ሳይጀምር ያለቀ፣
በጣም ተራ ሰው ነኝ፡
ምንም የማልረባ፣
ላንቺ የማልመጥን ከቁብ የማልገባ፣
...በኔ መጠየቅሽ አካልሽ ተሳቆ፣
ዕርኩስ እንደነካው ውስጥሽ ተሸማቆ፣
እኔን ላለማየት ህይወትሽ ቢርቅም፣
....ጠልቼሽ አላውቅም።
🎴እሱባለው ብዙነሽ…🎴
ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ
#Share #like and #subscribe my #YouTube
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍22🥰6👏4
#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ትንግርት ዶ/ር ሶፊ ክስ ስላልመሰረተችባት ሰሎሞን እና ኤልያስ ተሯሩጠው ከእስር እንድትፈታ አደረጉ፡፡አሁን ስለቀጣይ እቅዳቸው ያረፉበት ፔንሲዬን ውስጥ ።ቁጭ ብለው እተመካከሩ ነው፡፡
‹‹ቀጣይ እቅዳችን እንዴት ነው?፡፡››ኤልያስ ጠየቀ፡፡ጥያቄው ለትንግርት ነው የተሰነዘረው፡፡
‹‹ሰሎሞንና ሶፊያ ወደ አዲስ አበባ ይመለሱ፤እኔና አንተ የመጣንበትን ስራ መስራት እንቀጥላለን፡፡›› ውሳኔው የትንግርት ነው፡፡
‹‹እኛ ከመሄዳችን በፊት ከልጅቷ ጋር ያለውን ነገር መጨረስ አለብን፡፡›› አለ ሰሎሞን፡፡
‹‹እንዴት አድርጋችሁ ነው የምትጨርሱት?››
‹‹እናስታርቃችኋለና፤ይቅር ተባባሉ፤ከይቅርታ በላይ ምን አለ.?››ሰሎሞን ነው ተናጋሪው፡፡
‹‹እኔና እሷ በራሳችን የጀመርነውን ጊዜው ሲደርስ በራሳችን እንጨርሰዋለን፡፡ለድርድር የሚያመች ችግር አይደለም በመሀከላችን ያለው፡፡››
‹‹እኛ እኮ ኢትዮጵያዊያን ነን፤ምን አልባት ለአቅመ ሽምግልና አልደረሳችሁም ካላልሽን በስተቀር በባህላችን መሰረት በሽማግሌ የማይፈታ ምንም አይነት ችግር የለም፡፡››አላት ኤልያስ፡፡
‹‹ለሽምግልና ብቁ ናችሁ፤እንዳልከውም እኛ ኢትዬጵዊያን በሽምግልና የማይፈታ ችግር የለንም፤ክፋቱ የእኔና የእሷ ችግር ኢትዬጵያዊ አለመሆኑ ነው፡፡››
‹‹ስለዚህ የፈረንጅ ሽማግሌ ካልመጣ አሻፈረኝ እያልሽ ነው?››አላት ሰሎሞን፡፡
በዚህ መካከል የትንግርት ስልኳ ጠራ ..ከውጭ ነው፤ወደ ውጭ ወጣችና አነሳችው፡፡
‹‹ሀይ ማሬ፡፡››
‹‹አለሁ ...ተፈታሽ አይደል?በጣም ተጨንቄ ነበር፡፡››
‹‹አይዞኝ ..አሁን ሁሉ ነገር ተስተካክሏል፡፡ ተፈትቼያለሁ፡፡››
‹‹በዋስ ነው የተለቀቅሽው?››
‹‹አይደለም ..ስላልከሰሰችኝ በነፃ ነው የለቀቁኝ፡፡››
‹‹እሺ በቃ ከአምስት ቀን በኃላ እመጣለሁ፡፡››
‹‹ምን? ወዴት ነው የምትመጣው?››
‹‹ወደ ኢትዮጵያ ነዋ፡፡››
‹‹ለምን ?ትምህርቱስ ?››
‹‹ለጊዜው አቋርጬው፡፡ >>
«ለምን?»
‹‹በቃ ..በዚህ ጊዜ ከጎንሽ መሆን እፈልጋለሁ?››
‹‹አልገባኝም ሁሴን?››
‹‹በቃ ወደ አንቺ መመለስ እፈልጋለሁ፤ከትምህርቱ በላይ አንቺ ታስፈልጊኛሽ፡፡››
‹‹እኔማ አለውልህ..ትምህርትህን ጨርሰህ በመጣህ ጊዜ ታገኘኛለህ፡፡››
‹‹በዛ እርግጠኛ መሆን አልቻልኩም…<ጅብ ካለፈ..... >እንዳይሆንብኝ መምጣት ይሻለኛል፡፡››
‹‹ፈፅሞ እንዳታደርገው፡፡ይሄንን ትምህርት በጣም ትፈልገው እንደነበረ፤ የተሳካልህም ከብዙ ጥረት በኋላ መሆኑን አውቃለሁ፡፡
በምንም አይነት ሰበብ እንድታበላሸው አልፈልግም፤እኔ እኮ ትንግተርት ነኝ አትርሳ፡፡ በጣም አፍቅሬህ ነው ያገባውህ፤ላጣህም አልፈልግም፡፡››
‹‹የእኔ ፍቅር ..እንደምታፈቅሪኝ በጣም አውቃለሁ…ግን?››
‹‹ግን ምን…?››
‹‹እሷንም ከአቅም በላይ xxxx "እንደነበረ አውቃለሁ፡፡››
‹‹እና ስጋትህ ወደእሷ ትመለሳለች ብለህ ?>>
‹‹እኔ እንጃ፤ ብቻ ውስጤን ፍርሀት ፍርሀት ብሎኛል፤ስሜቴ በረህ አጠገቧ ሁን እያለኝ ነው፡፡››
‹‹እንዳታደርገው፡፡እንኳን አንተ በህይወቴ ኖረህልኝ ብቻዬን ብሆን እንኳን አልሞክረውምከጥፋቱ የማይማር ፈንጅ አምካኝ ብቻ ነው። ይባላል፤ ለማንኛውም ማታ ደውልልኝና እናወራበታለን፡፡››
‹‹ማር አትልፊ... ትኬት ሁሉ ቆርጪያለሁ፡፡››
‹‹እብድ እኮ ነህ.... በጣም የማትረባ እብድ፤በል ቻው፡፡››
‹‹ቻው አፈቅርሻለሁ፡፡››
ስልኩን ዘግታ በንዴት ጬሳ፣ደም ስሯ ተወጣጥሮ ወደክፍል ስትመለስ ሁሉም ደነገጡ‹‹ምን ሆንሽ ደግሞ ?››አለቻት ፎዚያ፡፡
‹‹ምን ሆናለሁ….ይሄ እብድ ወንድምሽ ነዋ!!››
‹‹እሱ ደግሞ ምን አረገሽ?››ጠየቃት ሰሎሞን፡፡
‹‹እመጣለሁ እያለ ነው?››
<<ለምን?»
‹‹እኔ እንጃለት?››
ሁሉም ፀጥ አለ፡፡‹‹...በቃ ሁለታችሁ ተነሱና ሂዱ..ኤልያስ አንተ ደግሞ ታዲዬስ ጋር ደውልለት እና ቀጠሮ አሲዝልን፡፡››
‹‹ደውዬለት ነበር ፤1ዐ ሰዓት ይመቸኛል ብሏል፡፡››
‹‹ጥሩ ነው፤በሉ ተነሱ እንውጣ›› ብላ ቀድማ ክፍሉን ለቃ ወጣች፤ ሶስቱም ተከተሏት፡፡
ትንግርትና ኤልያስ በትንግርት መኪና ፣ ፎዚያ እና ሰሎሞን ደግሞ በሰሎሞን መኪና ሆነው የፔኒሲዬኑን ግቢ ለቀው ወጡ፡፡ምሳ በልተው ሊለያዩ ነበር ዕቅዳቸው፤ምሳ ለመብላት የፈለጉበት ሆቴል ከመድረሳቸው በፊት የሰሎሞን ስልክ ጠራ፤ከአዲስ አበባ ነው ፡፡ የኤደን እህት ነች የደወለችለት፡፡መኪናውን ጥግ አስይዞ አቆመውና ስልኩን አነሳው፡፡
‹‹ሄሎ ሂሩት ሰላም ነው?››
‹‹ሰላም አይደለም.፤ኤዲን አሞት ሆስፒታል ተመልሳለች፡፡›››
‹‹ምን ሆነች..?ማለቴ እንዴት አደረጋት?››
‹‹እኔ እንጃ ሶል፤ጠንከር ያለ ይመስለኛል ፤ኦፕራሲዬን መደረግ አለባት ብለዋል››
<<ምን>?>>
‹‹አዎ !!በአንድ ሰዓት ውስጥ ኦፕራሲዬን መደረግ አለባት እያሉ ናቸው፡፡››
‹‹ምነው ? ጽንሱ ሰላም አይደለም እንዴ? >>
‹‹እኔ እንጃ ፤ ስለእሱ ምንም አላሉኝ፤መምጣት ብትችል ?>>
<<እየመጣሁ ነው..ቻው፡፡ እስክደርስ ሁኔታውን እየተከታተልሽ ደውይልኝ፡፡›› ብሎ ስልኩን ዘጋውና መኪናውን አስነሳ፤ እነትንግርትም ከኋላው መኪናቸውን አቁመው ሲጠብቆቸው ነበር ፤መኪናውን ሲያንቀሳቅስ እነሱም አንቀሳቀሱ፡፡
‹‹ሰላም አይደለም እንዴ?››ፎዚያ ጠየቀችው ፡፡
<< አዎ ኤደንን በጣም አሞታል ነው ምትለኝ፤ ለእነ ትንግርት ደውይና ንገሪያቸው.. ምሳው ይቅርብን ፡፡››
‹‹እሺ ችግር የለም፡፡›› ብላ ሞባይሏን አወጣችና ኤልያስ ጋር ደወለችለት፡፡
‹‹ምሳው ይቅርብን ልንወጣ ነው፡፡››
‹‹ምነው ?››
‹‹ኤደን አሞታል ብለው ከአዲስ አበባ ደወሉልን ፤ በቃ ቻው እናንተ ብሉ፡፡››ብላ ተሰናበተችው፡፡
ሰሎሞን በመጨረሻ ፍጥነት እየከነፈ ሻሸመኔ ከተማ ሊገባ 3 ኪሎሜትር ያህል ሲቀረው ድንገት ወደኃላው በአስፖኪዬ ሲመለከት የትንግርትን መኪና ተመለከታት፡፡
‹‹እንዴ እነትንግርት ተከትለውናል፡፡››ብሎ ለፎዚያ እየነገራት የመኪናውን ፍጥነት ዝግ አደረገ ፎዚያም አንገቷን ወደኃላ አዞረችና ተመለከተች ‹‹እውነትም እነሱ ናቸው፡፡››
ጠበቃቸውና አንገቱን በመስኮት በማውጣት‹‹ምን እየሰራችሁ ነው?››ሲል ጠየቃቸው፡፡
‹‹ወደ አዲስ አበባ እየሄድን ነዋ››
«ለምን?»
‹‹ባክህ ቀጥል.. ኤደን ታማለች እያላችሁን እንድንቀር ትፈልጋለህ?››
‹‹ስራውስ... ?››
‹‹ይደርሳል ፤እንደውም ተረጋግተን ሌላ ጊዜ እንመለሳለን ፤ይልቅ ቀጥል ጊዜ አታባክን >> ብላው አልፍው ሄደች፡፡
‹‹አዲስ አበባ ጋንዲ ሆስፒታል ሲደርሱ ከቀኑ 11 ሰዓት ሆኖ ነበር፡፡››
የኤደን እና የእሱ ጓደኞች፤የእሷ ቤተሰቦች ኮርደሩን ሞልተውታል፡፡የሁሉም ፊት ጨልሟል ፡፡የሆነ የተበላሸ ነገር እንዳለ ወዲያው ገባው፡፡
በነትንግርት እንደ ታጀበ ተንደርድሮ ወደ እህቷ ቀረበ‹‹ሂሩት ምንድነው የተፈጠረው? ኤደን ደህና ነች?››
ቃላት ከማውጣቷ በፊት እንባዋ ቀደመ..ሳግ ተናነቃት፡፡
‹‹ምን ሆነች ...?ምን ተፈጠረ ….?ንገሪኝ እንጂ?>
‹‹እሷ ደ..ህና ነች፡፡››
‹‹እና ታዲያ…?››
‹‹አዝናለሁ ሶል..…ልጁ ጠፍቶባታል፡፡››
<<ምን?>>
‹‹አዎ ሶል…፡፡››

👍87❤11
የሆነ ነገር አዕምሮውን ጨምድዶ ያዘው፤ጭልም አለበት፡፡በአካባቢው አግዳሚ ወንበር ላይ አረፍ አለ፡፡…ልጅ ልጅ ነው፤በመልክ እና በአካል የማያውቁትም ቢሆን ያሳዝናል፡፡ከእሱ በላይ ግን ኤደን በጣም እንደምትጎዳ ያውቃል፡፡በ31ኛ ዓመቷ
ላይ በታላቅ ጉጉት ያገኘችው ልጅ ነበር፡፡ይህን
ልጅ ከመወለዱ በፊት መፀነሱ ከታወቀበት ቀን
ጀምሮ ኤደን ያልገዛችው
አሻንጉሊት፣ያልገዛችው መጫወቻ፣ያልገዛችው
የህፃን ልብስ አልነበረም፡፡ኧረ የህጻን አልጋ
ሁሉ አስርታ ነበር፡፡ አቤት እንግዲህ ቤታቸው
ውስጥ የሚበተነው ሀዘን፣የሚፈሰው
እንባ፣ከአሁኑ ሲያስበው ልቡ ደከመችበት፤ነገን
በጣም ፈራት፡፡
ከህመሟ ጨርሳ ሳታገግም እየተነጫነጨችና እየተቃወመችው ጥሏት ትንግርት ጋር ወደ ሀዋሳም መሄዱም አሁን ከተፈጠረው ችግር ጋር ሲያያዝ በመሀከላቸው የነበረውን ስንጥቅ ወደ ሸለቆነት ማስፋቱ አይቀሬ ነው፡፡
ከአንድ ሰዓት በኃላ ወደ ኤደን እንዲገባ ተፈቀደለት፡፡በፍራቻ ፈራ ተባ እያለ ገባ፡፡ ልክ እሱ መሆኑን ስታይ ፊቷን ወደ ግድግዳው
አዞረች፡፡የተኛችበት አልጋ ተጠጋና በጉልበቱ ወለሉ ላይ ተንበረከከ፡፡
‹‹ፍቅር ሰላም ነሽ..?በጣም አዝናለሁ፡፡›› ምንም አልመለሰችለትም….ፊቷንም ወደእሱ ለማዞር ፍቃደኛ አልሆነችም፡፡ …እየፈራ እጆቹን ግንባሯ ላይ አሳረፋቸው‹‹በፈጠረህ ... እ..ጅ..ህን አን..ሳልኝ፡፡››
‹‹እሺ ፍቅር....››ብሎ እጁን ሰበሰበ፡፡ምን ብሎ እንደሚያጽናናት ግራ ገባው ...እራሱን ማጽናናት ያልቻለ ሰው ሌላውን ለማፅናናት እንዴት ይቻለዋል?፡፡
‹‹ፍቅር አይዞሽ፤ የእግዚያብሄር ፍቃድ ከሆነ አሜን ብሎ ከመቀበል ውጭ ምን ማድረግ ይቻላል?ደግሞ ነገም ሌላ ቀን ነው፤ምንም ነገር ማድረግ የማይሳነው እግዚያብሄር ሌላ ልጅ ባርኮ ይሰጠናል፡፡››
ፊቷን ወደ እሱ መልሳ እሳት በሚተፉ ዓይኖቿ እየገፈተረችው ‹‹በፈጠረህ ከፊቴ ጥፋልኝ፤የእኔ እና አንተ ነገር አክትሞለታል…በቃ ተወኝ››አለችው..ይህንን ስትናገረው እንደሰውነቷ ያልተሳሰረው እንባዋ ከምንጩ እየፈለቀ በጉንጮቿ በመንኳለል ወደ ታችኛው ሰውነቷ ይንጠባጠብ ነበር፡፡..እሱም ቅስሙ ተሰብሮና ተስፋ ቆርጦ ክፍሉን በዝግታ ለቆላት ወጣ።

👍56❤9😢4🤔3🥰1😁1
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ:
እባክሽ አትሂጂ…..
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-ስድስት
እርቃን ጋላዋ ላይ ብጣቂ ሰማያዊ ፓንት ብቻ አድርጋ ፊት ለፊቴ ቆማለች ፡፡እየቃዣሁ ሁሉ መሰለኝ፡፡ሰላምም ሳትለኝ እየተምነቀነቀች ፊቷን አዞረችና ቀጥታ ወደመኝታ ክፍሉ ተመልሳ ገባች፡፡ወይ እርግበ፡፡ሳሎን ሙሉ ሰው ጠቅልለው የሚይዙ ግዙፍ ሁለት ሻንጣዋች አሉ፡፡የጎርጥ አየኋቸውና በደመነፍስ ወደ መኝታ ቤት ተከትያት ገባሁ፡፡ ከላይ ምንም ልብስ ሳትለብስ ዝርግትግት እና ብልቅጥቅጥ ብላ ተኛች፡፡
‹‹ቁልፍ ከየት አገኘሽ?››
‹‹አሁን በፈጣሪ እንዴት እዚህ ድረስ መጣሽ? ማለት ይቀላል ወይስ ቁልፌን የት አገኘሽ?››
‹‹እዚህ ድረስማ ዶላርሽ ይጨነቅ ..አንከባክበው ያመጡሻል፡፡››
‹‹አንከባክበውም ሊዘርፉኝም ይችሉ ነበር፡፡››
ካቅም በላይ የሆነ ጉዳይ ስለገጠመኝ ነው፡፡ለአራት አሩብ ጉዳይ ድረስ ቦሌ ደርሼ እየጠበቅኩሽ ነበር.፡፡ሲደወልልኝ ግን ምንም ማድረግ አልቻልኩም፡፡››
‹‹ቆይ በሆስፒታሉ ያለኸው ዶ/ር አንተ ብቻ ነህ እንዴ?››
‹‹እሱስ አይደለሁም፡፡ግን የበሽተኛውን ኬዝ ለረጅም ጊዜ እየተከታተልኩ የነበርኩት እኔ ነኝ፡፡በዛ ላይ ሆሲፒታል አልነበረም፡፡የገዛ ቤቱ ተኝቶ የሚታከም በሸንተኛዬ ነው፡፡››
‹‹እ የሴትዬዋ ባል ነው፡፡››
በዛ ለሊት አመዴ ብን አለ፡፡አመዴ ብን አለ ብሎ ገለፃ ግን ምንድነው?ከየት የመጣ አመድ ነው ከሰው ላይ ብን ሚለው..? አቧራ እንኳዋን ያው ሰው ከጭቃ ስለተሰራ ሲደነግጥ አበዋራው ቡን ቢል ከተሰራበት ጭቃ ነው ይባላል አመድ ግን…..ለማንኛውም በጣም ደነገጥኩ፡፡››
‹‹የቷ ሴት?››
‹‹የሶስት ልጆቾ እናት ነቻ፣ያቺ ሰሞኑን እቤቷ የምትመላለሰባት፡፡››
‹‹አንቺ እያሰለልሺኝ ነበር እንዴ?››
‹‹እንዴ ባሌ አይደለህም እንዴ? ባሰልልህ ምን ይገርምሀል?››
‹‹እርግጠኛ ነሽ ባልሽ ነኝ?››
‹‹አዎ ለእኔ ባሌ ነህ፡፡ባይሆን ላንተስ ሚስትህ ነኝ ወይ? የሚለው ነው እርግጠኛ መሆን ያቃተኝ፡፡››
ዝም አልኳት:: ከሶስት አመት ቆይታ ለሀገር ምድሯ የበቃችን ሴት ከዚህ በላይ በነገር መቀበል አግባብ መስሎ አልተያኝም፡፡››
‹‹እራት ልስራ አርቦሻል?››ስል ጠየቅኳት፡፡
‹‹አመሰግናለሁ…አራበኝም ሚጠጣ ነገር ካለ ግን ቢራ ነገር ባገኝ አልጠላም፡፡››.
‹‹እሺ…አለ››ከተቀመጥኩበት ተነሳሁና ወደሳሎን ሄጄ ከፍሪጅ ውስጥ ሁለት ቢራ በማውጣት ከብርጭቆ ጋር ይዤ ወደመኝታ ክፍል ተመለስኩ፡፡ ከፈትኩና በብርጭቆ ቀድቼ አቀበልኳት፡፡ከተጋደመችበት ተነሳችና እርቃኗን እንዳለች አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀምጣ ተቀበለችኝና አንዴ ተጎንጭታለት በቅርብ ያለች አነስተኛ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠቸና በትኩረት ለደቂቃዎች አፈጥጣ አየቺኝ፡፡ ተንደርድራ መጣታ አንገቴ ላይ ተጠምጥማብኝ ጉንጮቼን፣ አይኖቼን፣ ግንባሬን…ከንፈሬን እያፈራራቀች በመስገብገብ ትሰመኝ ጀመር፡፡እኔም እየሞቀኝና እየጋልኩ ስሄድ በፍቃደኝነት መሳምና አቅፌትና ጨመቄያት መልሼ እስማት ጀመረ፡፡ናፍቃኝ ነበረ እንዴ…?ሙሉ በሙሉ ከውስጤ አላወጣትም ነበር ማለት ነው…?፡፡
‹‹በጣም ነው የናፈቅከኝ…በጣም፡፡››
‹‹እ…ኔ…ምምም፡፡››
በመከራ ተላቀቅን፡፡ ወደ አልጋው ጠርዝ ተመልሳ ቢራችን እየተጎነጨን የሰላም የሚመስል ወሬዎችን ማውራት ቀጠልን፡፡
‹‹ግን የእውነት ቁልፉን ከየት አመጣሽ?››
አብራራችልኝ‹‹አንተን ኤርፖርት ሳጣህ በጣም ነበር ግራ የገባኝ፡፡ ደግሞ ስደውልልህ ንግግሬን ሁሉ ሳታስጨርሰኝ ነው ስልክህን የዘጋኸው፡፡ቀጥታ እዛው እስካይፒ አልጋ ይዤ ማደር ፈለጌ ነበር፡፡ከዛ ድንገት ሀሳብ መጣልኝና ወንድምህ ሶና ጋር ደወልኩለትና ያጋጠመኝን ስነግረው..በአስራአምስት ደቅቃ ውስጥ በሮ መጣልኝ፡፡አመጣኝ ከፍቶ አስገባኝና ተመልሶ ሄደ፡፡››ብላ አብራራችልኝ፡፡
‹‹አሁን ገባኝ፡፡››
‹‹አንተነህ እንጂ ለእኔ ግድ የሌለህ ወንድሞችህ ሆኑ እናትህ በጣም እኮ ነው የሚወዱኝ፡፡››
ዝም አልኳት፡፡የሆነ ነገር ብላት ሌላ መልስ ትመልስልኝና መቆሰል ነው ትርፉ ብዬ ባመሰብ፡፡
‹‹ደክሞሻል አይደል..?እንተኛ፡›› አልኳት፡፡
‹‹ደስ ይለኛል…..ብርጭቆ ውስጥ የቀረችውን ቢራ በአንድ ትንፋሽ ጨለጠቸና ዘላ አልጋ ላይ በመውጣት ቆመች ፡፡ምንም ሳይመስላት ሰውነቷ ላይ ቀርቶ የነበረውን ብጫቂ ጨርቅ(ፓንቷን) አወልቃ ወደ ኮመዲኖ ወረወረችና መለመላዋን ከውስጥ አንሶላዋን ገልጣ ገባች፡፡አይኔን ከፈት ከደን እያደረኩ ውበቷን አደነቅ ጀመርኩ፡፡ …ቆንጅዬ ሰይጣን ነች፡፡ከተቀመጥኩበት ተነሳሁና ቆምኩ፡፡ወደግድግዳው ጠጋ አለችና ሰፊ ቦታ ለቀቀቸልኝ ፡፡በስነ ስራአት ብርድልብሱን አስተካክዬ አለበስኳትና ከላይ አልጋ ልብሱን ገፍፌ አነሳሁና ጠቅልዬ በመያዝ ‹‹ደህና አደሪ፡፡ምትፈልጊው ነገር ካለ ጥሪኝ ፡፡››በማለት ወደኃላም ዞር ብዬ ሳላያት በሩን ዘግቼ መኝታ ቤቱን በመተው ሳሎን ሄጄ ሶፋው ላይ ተመቻችቼ ተኛሁ፡፡..እንደዛ በማደርጌን እኔ እራሴ አላመንኩም፡፡እንዲህ አይነተ ጀግንነት ከየት ነው ያመጣሁት?፡፡በዕርግበ ገላ እንዲህ መንቀባረር….?ከዛሬ አራትና አምስት አመት በፊት ቢሆን ይህ ማይታሰብ ነበር፡፡ከእሷ ጋር አንድ ቀን የማደር እድል ለማግኘት ከአዲስአበባ አዳማ በእግርህ ንካው ቢሉኝ ያለማንገራገረ አደርገው ነበር፡፡ዛሬ ግን ይሄው..የጊዜ እንጂ የሰው ጀግና የለውም የሚባለው ለዚህ አይደል፡፡
እርግበን ፍቅርኛ ያደረኳት በቀላሉ አልነበረም፡፡ እርግጥ ጓደኛሞች የሆነው ሳናስበውና በቀላሉ ነበር.፡፡ያንን ግንኙነት ወደፍቅር ለመቀየር ግን ከአንድ አመት በላይ ፍዳዬን በልቼያለሁ፡፡አረ በእንብርክክ ሄጃያለሁ ብል በተሻለ ይገልፃዋል፡፡አምስተኛ አመት ላይ ሆነን ለተግባራዊ ልምምድ አንድ ሆስፒታል ላይ ተመደብን፡፡አቤት በወቅቱ የተደሰትኩት መደሰት እንዲህ በቀላል ቃላት የሚገለፅ አደለም፡፡ እርግጥ እሷም ተደስታ ዘላ ጉንጬን ስማኝ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ግን የእሷ መደሰት እና የእኔ የተለያየ ትርጉም ነበርው፡፡እሷ በጣም ምትግባባውና ከምትቀርበው ጓደኛዋ ጋር በመመደቦ ደህንነት ተሰምቷት ነው፡፡እኔ ደግሞ በዚህ ሄደት ከዩኒቨርሲቲው ማህረሰብ ተለይተን ብቻችንን እራቅ ብለን በአዲስ ቦታና አትሞስፌር ውስጥ ማሳለፈችን ይበልጥ ያቀራርበንና ጓደኝነታችንን ወደፍቅረኝነት ለመቀየር ሁኔታዎችን ያመቻችልናል በሚል ተስፋ ነው፡፡እና በዛ ሂደት ከስድስት ወራት በኃላ እሷም ደህንነትን ፍለጋ ከወትሮ በበለጠ በእየለቱ በሚደረግ መቀራረብ ይበልጥ ስትጠጋኝና ስትደገፍብኝ..እኔም ልቧን ለማግኘት ከወትሮው በተሻለ መቅረብ ስቀርባት..በተለያየ መልኩ በእንክብካቤ ትንፋሽ ሳሳጣት በስተመጨረሻ የእሷም የእኔም ሀሳብ በየራሳችን ተሳካልን፡፡ከዛ ፍቅረኛሞች ሆነን ወደዩኒቨርሲታችን ተመለስን፡፡ከተመረቅን በኃላ እንደምንም ብለን የተለያየ ሆስፒታል ቢሆንም አዲስ አበባ ስራ ለማግኘት እና ይበልጥ ፍቅራችንን ለማጠንከር እና የነገ ተስፋችንን ብሩህ የማድረግ በጀመርነው መንገድ ገፋንበት ፡፡

👍56❤7
እንዲህ ስላችሁ ከእሷ ጋር በፍቅር መቆየት ቀላል አድርጋችሁ አትዩት…፡፡ቆንጆና ቀበጥ መሆኗ ብቻ አይደለም…የማትጨበት ሙልጭልጭ ነገር ነች፡፡በሆነ ምክንያት ለአንድ ሳምንት ሀሳቤን ከእሷ ላይ አንስቼ ከቆየሁ..በቃ የሆነ ሰው ክንድ ላይ ተዝለፍልፍ ልትወድቅ ስትል ነው የማገኘት፡፡ከዛ መንጭቄ ወደራሴ ለመመለስ አቤት ያለው መከራ….አቤት እሷን ይቅር ያልኳት መጠኑ …ሰባት ጊዜ ሳባ ሰባት አይገልፀውም፡፡አሁን ውጭ ከሄደች በኃላ ግን እየደከምኩና እየሰነፍኩ መጣሁ ..ከዛም አልፎ ይሄው ለዚህ በቃን፡፡
ይቀጥላል...
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
ይቀጥላል...
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍15❤6
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ:
እባክሽ አትሂጂ…..
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-ሰባት
አስራሁለት ሰዓት ከእንቅልፌ ባነንኩ ፡፡ በየትኛው ሰዓት በእንቅልፍ እንደተሸነፍኩ ትዝ አይለኝም፡፡ግን ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ነበር የወሰደኝ፡፡ሶፋውን ለቅቄ ተነሳሁና እየተንጠራራሁና አይኔን እያሻሸው ወደመኝታ ቤት አመራሁ፡፡ገርበብ ያለውን ክፍል ቀስ ብዬ ገፋ አደርጌ በመክፈት ወደውስጥ አሰገግኩ፡፡እርግበ ከወገቧ በታች ለብሳ ከወገቧ በላይ እራቃኗን በመሆን በጀርባዋ ተንጋላ ተኝታለች፡፡ጡቶቾ ወደላይ አፍጥጠው ቀጥታ ኢላማቸውን ወደእኔ ያቀባበሉ ይመሰላሉ፤ፀጉሯ ብትን ብሎ ትራሱን ሞልቶታል፤አይኖቾ ሙሉ በሙሉ ስላልተጨፈኑ በከፊል የምትታይ ይመስላል፤አንጀቴን በላችኝ…ምን አለ እንደመልኳና ውበቷ …ጸባዮና ምግባሯ ሰናይ ቢሆን…..
ፊቴን አዞርኩና ወደኪችን ገባሁ፡፡ለቁርስ እማዬ ጋር መሄድ ግዳጅ ቢሆንም ግን አፋችን ላይ ጣል የምናደርገው ቀላል ነገር ለመስራት ፈለኩ….ፍሪጁን ከፍቼ ያለውን ነገር ተመለከተኩና ምን መስራት እንደምችል አሰብኩ፡፡‹‹ወደ አእምሮዬ የመጣልኝ ጂውስ ነው››ፓፓዬና መንጎ ነበር..እንደውም ጥሩ ነው፡፡በአስራአምስት ደቂቃ ውስጥ ሁሉንም አጠናቀቅኩና…ወደመኝታ ቤት ሄድኩ፡፡አሁንም እንደተኛች ነው፡፡ሻወር ለመውሰድ ፈለኩ፡፡ መቼስ ውዬ ባደርኩበት ልብስ አልወጣም፤ልብሴን አወላለቅኩና ከቁም ሳጥን ውስጥ ፎጣና ፓንት ይዤ ወደ ሻወር ገባሁና ከሰዓቱ የአየር ፀባይ ጋር እንዲስማማ ውሀውን ለብ አድርጌ መታጠብ ጀመርኩ፡፡ የተለቀለቅኩትን ሳሙና ከላዬ ላይ እያስለቀቅኩ እያለው…የሻወሩ በራፍ ተከፈተ….ሳሙናውን ከአይኖቼ ላይ ለማስለቅቅ እያሞከርኩ አየኋት…፡፡
‹‹ደህና አደርክ?››አለቺኝና ወደውስጥ ገብታ በራፍን በመዝጋት ወደእኔ ተጠጋች፡፡እንዲህ አልነበረም የጠበቅኳት፡፡ እንድትሰድበኝ እንድትወቅሰኝና …ከዛም አለፍ ብሎ የሆነ ዕቃ ትወረውርብኛለች ብዬ ነበር ግምቴ፡፡ እሷ ግን በተቃራኒው ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ እና አብሮ ተቃቅፎ ሲላላሱ አንዳደሩ ፍቀረኛሞች ይሄው በለሰለሰ አማላይ ደምፅ እያወራችኝ ነው፡፡
‹‹ደህና..እንዴት ነው ጥሩ እንቅልፍ ተኛሽ?››
‹‹አዎ ደክሞኝ ነበር መሰለኝ ..የት እንዳደርኩ አላውቅም፡፡…ልሽህ እንዴ?››
‹‹ካላስቸገርኩሽ ደስ ይለኛል፡፡››አልኳት፡፡ እንድታሸኝ ፈፅሞ ፍላጎት አልነበረኝም…ግን እንደዚህ ትሁት ስትሆን እኔም ትሁት ለመሆን ፈልጌ ነው፡፡
እሺ ..አለችና ሳሙናውን ከማስቀመጫው ላይ አነሳችና ከጀርባዬ ዞራ ከአንገቴ ጀምሮ መላ ሰውነቴን ሳሙና እየለቀለቀች ታሸኝ ጀመር፡፡የምፈራው አይነት ስሜት ይሰማኝ ጀመር….‹‹ይብቃኝ ሳሙናውን ስጪኝና እራስሽ ታጠቢ›› አልኳት፡፡ያለምንም ክርክር ሳሙናውን እጄ ላይ አስቀመጠችና ቧንቧውን ከላይ ከፍታ ሰውነቷን ታስቀጠቅጥ ጀመረ፡፡እኔም ትንሽ ጠጋ ብዬላት በፍንጣሬው እየተመታውና ፊት ለፊቴን በሳሙና እያደራስኩ አያት ጀመር፡፡ከዛ ጀራባዋን ሰጠችኝና ‹‹በል ውለታ አለብህ፡፡›› አለችኝ፡፡በዝምታ ልክ እሷ እንዳደረገችው ሰውነቷን ሳሙናውን እየለቀለቅኩ በጥንቃቄ አሻት ጀመር…ከሻወር በስሜት ተቃጥለንና ግለን ስንወጣ ለአንድ 20 ጉዳይ ሆኖ ነበር፡፡
እሷ እርቃኗን ሆና ቂጦን እያማታች… እኔ በቀየርኩት ፓንት ሆኜ መኝታ ቤት ጎን ለጎን ቆመናል፡፡ እሷ አነስተኛ ቦርሳዋ ከፍታ ምትለብሰውን ስትፈለልግ እኔም ቁም ሳጥኑን ከፍቼ ምን መልበስ እንዳብኝ መምረጥ ጀመርኩ…
‹‹እማዬ ቁርስ ይዘሀት ና ብላኛለች…እንዴት ነው ይመችሻል እንዴ?››
ፊቷ ሁሉ በራ‹‹እንዴ ትቀልዳለህ እንዴ ?እማዬ ጠርታኝ እንዴት አይመቸኝም…?››
‹‹ያው ምን አልባት ቤተሰቦችሽ ጋር ትሄጂያለሽ ብዬ ነዋ፡፡››
‹‹ባክህ እነሱ ጋር ቀስ ብዬ ነገ ተነገ ወዲያ መሄድ ችላለሁ፡፡ውይ እማዬ እኮ እንደናፈቀቺኝ…››
አውጥቼ አልተናገርኩም እንጂ በንግግሯ ተበሳጭቼያለሁ፡፡….እማዬ እያለች ስታሽቃብጥ እኮ ስለገዛ እናቷ የምታወራ ነው የሚመስለው፡፡
እርግጥ እሷ እናቷ በልጅነቷ ስለሞተችባት የእውነትም እማዬን እንደእናቷ እንደምታያት አውቃለሁ..ግን እኳ እኛ ግንኙነት ካበቃለት የእነሱም እንደዛው ማብቃቱና መራራቃቸው አይቀርም፡፡
‹‹ጥሩ እንደፈለግሽ…ተዘጋጂና እንሄዳለን…አደርስሽና እኔ በዛው ስራ ገባለሁ፡፡››
‹‹ችግር የለውም…..ከእሷ ጋር ስጫወት ውላለሁ፡፡››አለችኝ…ቀድሜያት ለባብሼ ጨርስኩና ወደሳሎን በመሄድ ቅድም የሰራሁትን ጅውስ አዘጋጅቼ ጠበቅኳት …ሽክ ብላ ለባብሳ ስትመጣ አንድ ብርጭቆ ቀዳሁና አቀበልኳት..ያለ ምንም ንግግር ተቀበለችኝና በቁሟ በመጠጣት ብርጭቆውን መልሳልኝ‹‹..አሁን መሄድ እንችላለን…..መኪናህ አለች አይደል?››
‹‹አዎ አለች…›››
‹‹ይሄ ሰማያዊ ሻንጣ ወደእማዬ የሚሄድ ነው፡፡››
‹‹እንዴ…ለእሷ ያመጣሽውን ብቻ ቀንሰሽ በአነስተኛ ሻንጣ አንይዘውም?››
‹‹ሁሉም የእሷ ነዋ፡፡››
‹‹ይሄ ሁሉ ሻንጣ…?››
‹‹ምነው እኔ ከአሜሪካ ለማምጣት ያልከበደኝ አንተ ከዚህ መኪና ድረስ ማስወሰድ ከበደህ?››
እውነትም ምን ማለቴ ነው..?ስልኬን አነሳሁና ደወልኩ..ሰፈር ውስጥ ለሚላላክልኝ አንድ ጓረምሳ ነበር የደወልኩት..ወዲያው እየበረረ መጣና ተጋግዘን ከፎቅ ላይ አውርዳን መኪናዬ ላይ ጫነው…ከዛ እሷን ገቢና ከጎኔ አስቀምጬ ወደእናቴ ጋር እነዳው ጀመር…እዛስ ስደርስ ምን ያጋጥመኝ ይሆን?
መንገድ ላይ እያለን ስልኳ ጠራ…አነሳቸው፡፡
‹‹ሄሎ … እንዴት ነህ?››
ስሜቴ ሁሉ ተነቃቃ፡፡‹‹በዚህ ፍጥነት ቁጥሯን ለማን ሰጥታ ነው የምትደዋወለው..?››እራሴን በውስጤ የጠየቀኩት ጥያቄ ነው፡፡
‹‹ሰላም ነኝ፡፡ አንቺስ…?ሰውዬውሰ መጣልሽ?››
‹‹አዎ ወዲያው እኮ መጣልኝ….ውለታህን ግን አረሳውም፡፡››
‹‹የምን ውለታ ነው …ምንም ቢሆን ምራቴ አይደለሽ?››
ከት ብላ ሳቀችና…‹‹ልስጥልህ?››
ስልኩን አቀበለቺኝ፡፡
‹‹በአንድ እጄ መሪዬን ጨብጬ በአንድ እጄ ስልኩን ተቀበልኳትና‹‹ታናሽ ወንድሜ የት ነህ?››አልኩት፡፡
‹‹የት ሆናው እንዳንተ አድራሻዬን እየሰወርኩ አልደበቅ..እቤቴ ነኝ…››
‹‹እንግዲያው ጥሩ ቁርስ ትፈልጋለህ?››
‹‹አረ ታድዬ …ልትጋብዘኝ እንዳይሆን?››
‹‹አረ መች አበድኩ…ጥሩ ቁርስ የት እንደሚገኝ ጥቆማ ልሰጥህ ፈልጌ ነው፡፡››
‹‹በፈጠረህ..ግን የሚከፈልበት አንዳይሆን፡፡››
‹‹እማዬ ጋር ከመጣህ ያልኩህን ታገኛለህ..በል ቸው ..፡፡ትራፊከ ከፊት ለፊቴ እየታየኝ ነው›፡፡ስልኩን ዘጋሁትና እጄን አንሸራትቼ አቀበልኳት፡፡
‹‹አቤት የኢትዬጵያ ሹፌሮች.. ትገርሙኛላችሁ…ተማራቸሁ አልተማራችሁ አንድ ናችሁ፡፡››
‹‹ይሄ ደግሞ ምን ማለት ነው?፡፡››
‹‹ህግ የምታከብሩት አምናችሁበት ሳይሆን የትራፊክ ቅጣት ፈርታችሁ ነዋ፡፡››
‹‹እንግዲህ እኛም አንድ ሁለት አመት ፈረንጆቹ ጋር ሄደን ባህሪያችንን ካልገሩለን ምን አናደርጋለን …ያደግንበት ነው፡፡››
‹‹አግቦ መሆኑ ነው?›› አለቺኝ፡፡ ዝም አልኳት፡፡እቤት ደርሰን መኪናዋን ሳቆመ እማዬን ነጭ በነጭ ለብሳ በረንዳ ላይ በሰፈር ሴቶች ታጅባ አየኋት፡፡እርግበ ገቢናውን ለቃ ወርዳ ወደ እማዬ መንደርደር ስትጀመር እሷም እጆቾን እንደክንፍ ዘርግታ እያረገፈገፈች ሰፈሩን በእልልታ አደበላለቀችው፡፡እኔ ሰቅጥጦኝ ጆሮዎቼን ደፍኜ በዝግታ እርምጃ መከተል ጀመርኩ፡፡ተቃቅፈው እየተሳሳሙ ሲላቀሱ..ገና ይሁን አይሁን እርግጠኛ ያልሆኑ አማትና ምራት ሳይሆን ለአመታት ሳይተያይ በናፍቆት ሲብሰለሰል የኖሩ እናትና ልጅ ነው የሚመስሉት፡፡

👍50❤5
የእማዬን ጩኸት ሰምተው በረንዳ ላይ በፊት እማዬን አጅበዋት ከነበሩ ሴቶች በእጥፍ ጨመሩ፡፡ እንደምንም እየተሹለከለኩ ሁሉንም አልፌ ሳሎን ስገባ ልዩ ዝግጅት ነው የጠበቀኝ፡፡ቤቱ ውስጥ ለሊቱን ሙሉ የተኛ ሰው ያለ አይመስለኝም፡፡ሳሎን መሀከል ቆሜ በሁኔታው በመገረም ዙሪያ ገባውን እየቃኘሁ ሳለ.. ከኃላዬ‹‹አንተ መልስ ነው ቁርስ ነበር ያልከኝ?››የሚል ድምፅ ሰማሁ ፡፡ማንነቱን ለማወቅ ዞሬ በማየት አላስፈለገኘም ….ሶና ነው፡፡
‹‹አንተ ከምኔው ደረስከ?››
‹‹ትቀልዳለህ እንዴ ..ሁሉ ነገር እንዲ የተትረፈረፈ መሆኑን ባውቅ ማታውኑ መጥቼ ነበር የማድረው….››
‹‹ሆዶ!! አንተ አታደርገውም አይባልም…፡፡››
‹‹እንክት…አሁን እኮ ሀለቃዬ ጋር ደውዬ እህቴ ከአሜሪካ መጥታብኛለች ብዬ የሶስት ቀን ፍቃድ ጠየቅኩ…በሶስት ቀን እንጨርሰዋለን አይደል?››
ሁኔታው አስገረመኝና እየሳቅኩ አጠገቤ ባገኘሁት ወንበር ቁጭ እንዳልኩ፡፡ እማዬና እርግበ እንደተቃቀፉ እየተሳሳቁ ከአስር በላይ ሴቶች ከኃላ አጅበዋቸው በመግባት ሳሎኑን ሞሉት፡፡የቁርስ መስተንግዶ በሳቅና በጫወታ ታጅቦ ቀጠለ፡፡ሁለት ተኩል ሲሆን ለእርገበ ብቻ በጆሮዋ ነግሬያት ከቤት ሹልከ ብዬ ወጣሁና ወደስራዬን አመራሁ፡፡…የዚህ ቅጥአንባሩ የጠፋው ግርግርና ድግስ መጨረሻው ምን ሊሆን እንደሚችል ምንም አልገባኝም፡፡

👍34❤10😁4👏1