አትሮኖስ
284K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
518 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ከጎራው ዘልቄ እስኪ ልነጋገር ካለ ሰው ቢወዱት ምን ያደርጋል አገር?

የኔ ውብ ከተማ -

ሕንጻ መች ሆነና የድንጋይ ክምር፤

የኔ ውብ ከተማ -

መንገድ መች ሆነና የድንጋይ አጥር፣

የኔ ውብ ከተማ የኔ ውብ አገር የሰው ልጅ ልብ ነው

ሕንጻው ምን ቢረዝም፣ ምን ቢፀዳ ቤቱ

የሌለው ዳርቻ የሌለው ድንበር፡፡ መንገዱ ቢሰፋ ቢንጣለል አስፋልቱ ሰው ሰው ካልሸተተ ምንድነው ውበቱ?

🎴በዓሉ ግርማ🎴


#Share and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍19🥰61
#ትንግርት


#ክፍል_ሰላሳ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ፎዚያ ኤልያስን ደውሎ መልዕክቱን እንደነገራት ጥዋት ወደ ሀዋሳ ለመሄድ መያዝ ያለባትን ዕቃዎች ካሰናዳች በኃላ በለሊት ለመነሳት በጊዜ መተኛት ስላለባት ወደ መኝታዋ አመራች፡፡ ግን አንድ የረሳችው ነገር ትዝ አላት፡፡ ለሰሎሞን ደውላ ትንግርት መታሰሯን ልትነግረው ይገባል፡፡ካለዛ ይቀየማል፡፡ በቤት ስልክ ደወለችለት፡፡

‹‹እሺ ሰሎሞን እንዴት ነህ?››

‹‹ሰላም ነኝ..ምነው በምሽት ደወልሽ?››

‹‹አይ በሰላም ነው ፡፡አንተ ግን ቤት አይደለህም መሰለኝ ..የሆነ ንፋስ ነገር ይሰማኛል ፡፡››

‹‹ሆስፒታል ነኝ ባክሽ፡፡››

‹‹ምነው? ምን ትሰራለህ?››በድንጋጤ ጠየቀችው፡፡

‹‹ኤደንን አሟት ጋንዲ ነው ያለነው፡፡››

‹‹እንዴ!! ቀኗ ደረሷል እንዴ?››

‹‹ኧረ እንደኛ አቆጣጠር አንድ ወር ገደማ ይቀራታል፡፡››

‹‹ታዲያ ምነው?››

‹‹እኔ እንጃ ባክሽ.. ገና ምርመራ ላይ ነች... ውጤቱን አላወቅንም፡፡››

‹‹አይዞህ ምንም አትሆንም፡፡ እግዚር ይማርልህ፤ነገ እጠይቃታለሁ፤ደህና እደር፡፡››

‹‹እንዴ ..ለምን እንደፈለግሺኝ እኮ አልነገርሺኝም?››

‹‹ምንም ጉዳይ የለኝም፤ ዝም ብዬ ለሰላምታ ነው የደወልኩልህ›› አለችው... እንዲህ በችግር ላይ እያለ ስለትንግርት ነግራው ይበልጥ ልታስጨንቀው አልፈለገችም፡፡

‹‹በዚህ ሰዓት ለሰላምታ ..?አድርገሽ የማታውቂውን፤.ይልቅ ቶሎ ንገሪኝ…?ምነው ችግር አለ ?ሁሴን ደውሎ ነበር እንዴ?››

<<ችግር የለም ሁሉም ነገር ሰላም ነው፤በል ቻው፡፡››ብላ ዘጋችበት እና የስልኩን እጄታ ወደ ቦታው መልሳ ወደ መኝታዋ አመራች፡፡

ሰሎሞን ትከሻውን ቀፈፈው፡፡የሆነ ነገር እንደተከሰተ ጠረጠረ፣ ‹በሰላምማ በዚህ ሰዓት አትደውልልኝም፡፡ ቀድሜ የእሷን ጉዳይ መስማት ሲገባኝ የራሴን ችግር ስነግራት ነው ሀሳቧን የቀየረችው፡፡››ሲል አሰበ፡፡ ለማጣራት ትንግርት ጋር ደወለ …ጥሪ አይቀበልም ይላል…፡፡

መልሶ ፎዚያ ጋ ደወለ ...አታነሳም ፤ በቤቱ ስልክ ሞከረ አይነሳም፡፡ለጊዜው ሀሳቡን ሰበሰበና ሚስቱ ወደ ተኛችበት ክፍል አመራ.. እንዴት እንደሆነች ለማየት፡፡

ፎዚያ እንቅልፍ እንዲወስዳት ብትመኝም ከመገላበጥ ውጭ ሊሳካላት አልቻለም፡፡ሰባት ሰዓት ላይ ሞባይሏ ጮኸ ...ሰሎሞን መስሏት ችላ ልትለው ነበር ፡፡በተጨናበሰ ዓይኗ አጨንቁራ ስታየው ግን የውጭ ስልክ ነው ..ተስፈንጥራ አነሳችው፡፡

‹‹ሄሎ ፎዚ፡፡››ሁሴን ነበር የደወለላት፡፡

‹‹ሄሎ ሁስን..እንዴት ነህ?››

‹‹ሰላም ነኝ፡፡ የትንግርት ስልክ አይሰራም… እስቲ አገናኚኝ?››

ደነገጠች ምን ትበለው‹‹የለችም፡፡››

‹‹የት ሄደች?››

‹‹ለስራ..ማለቴ... ከኤልያስ ጋር ሀዋሳ፡፡›› ተንተባተበችበት፡፡

‹‹ፎዚ እኔ በደንብ አውቅሻለሁ፤አንቺ ውሸት አትችይበትም...የሆነውን ንገሪኝ?››

‹‹እውነቴን ነው ሀዋሳ ነው የሄደችው፡፡››

‹‹ታዲያ ስልኳን ለምን ዘጋች?››

አመለጣት‹‹ታስራ ነው››

<<ምን!?>>

‹‹አዎ..እኔም ግራ ገብቶኛል...የሆነች አንድ ሴት በጠርሙስ ፈንክታ ነው አሉ የታሰረችው፡፡››

‹‹የምን ሴት…? በምን ተጣልተው?››

‹‹በምን እንደተጣሉ እስከአሁን አልታወቀም፡፡››

‹‹ማነች ሴትዬዋ?››

‹‹አላወቅኳትም...በቅርብ ከአሜሪካ የመጣች ዲያስፖራ ነች አሉ፡፡የሆነ የእርዳታ ድርጅት ውስጥ እንደምትሰራም ሰምቼያለው፡፡››

‹‹ስሟ ማን ነው?››

‹‹ውይ ስሟን አላውቅም?››

‹‹በይ ከአስር ደቂቃ በኃላ ደውላለሁ.. አጣርተሸ ጠብቂኝ፡፡›› ብሎ ስልኩን ዘጋው፡፡ እንዳለው በ11 ደኛው ደቂቃ ደወለ፡፡

‹‹እሺ ፎዚ ምን አገኘሽ?››

‹‹ዶ/ር ሶፊያ ይድነቃቸው ትባላለች፡፡››መረጃውን ከኤልያስ ነው ያገኘችው፡፡

‹‹ዶክተር ሶፊያ!!!?››

ይበልጥ አርበተበታት‹‹ አዎ ዶ/ር ሶፊያ… ምነው ታውቃታለህ?››

‹‹አዎ... ትንግርት ስለእሷ ነግራኛለች፡፡››

‹‹የት ነው የሚተዋወቁት?››

‹‹በጣም የሚዋደዱ ጓደኛሞች ነበሩ››አለ ፃረሞት ባረበበበት የሰለለ ድምፅ፡፡

ፎዚያ ከድንጋጤው የተነሳ መቃዠት የጀመረች መሰላት ‹‹ዶ/ር ሶፊያ እኮ ነው ያልኩህ ...፤የምን......................

‹‹ተይው ፎዚ፤ ከባድ አደጋ ላይ ነን ያለነው፤በቃ ቻው ነገ እደውልልሻለሁ›› ብሎ ስልኩን አቆረጠው፡፡

ፎዚያም እንደፈዘዘች ከድምፅ አልባው ሞባይሏ ጋር ተፋጣ ቀረች፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ 5 ሰው #subscribe ካደረገ ቀጣዩ ክፍል ማታ 3 ሰአት ላይ ይለቀቃል ዛሬ ከተሳካ እሞክራለው !!

#Share and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍10713🤔6👎2👏1😁1
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  አስር


“በቃ ጨረስን!'' አለ ዶክተሩ፡፡ ያ ቃል በዚያ ቅጽበት እፎይታ የሚሰጥ ቃል ነበር። ሲቆይ ግን ምንጊዜም ጆሮዬ ላይ የሚያቃጭል ረባሽ ቃል ሆኖ ቀረ... እስከ ዛሬ! ምንድን ነው መጨረስ?...ጨረስን! ...እኛ ማነን? ...እኔና ዶክተሩ ...ምን የጋራ ጉዳይ ኖሮን ነው “ጨረስን” የሚለኝ?... በሕይወታችን ውስጥ እንዲህ ዓይነት አጋጣሚዎች አሉ፤ ችግሮቹ፣ ጠባሳዎቹ የእኛ ሆነው ሌሎች በሙያቼው አልያም በገንዘባቼው ብቻ አግዘውን እጃቼውን ታጥበው ሲሄዱ እኛ ዕድሜ ልካችንን ተሸክመናቼው የምንኖራቼው፡ ዶክተሩ እንዳለው አላለቀም ነበር፤ እንዲያውም ጀመረ። በዶነት ከአእምሮዬ ወደ ሰውነቴ ወረደ፣የተሟላ ባዶነት! በአካልም በመንፈስም! ውስጤ እንደ ፊኛ በአየር የተሞላ ይመስል ቀለለኝ።ሰዎች ሁሉ የሆነውን የሚያውቁ ባደረግሁት ነገር የናቁኝ መስሎ ይሰማኝ ጀመር። በሬዲዮ ይሁን በጋዜጣ ወይም በጨዋታ መኻል ስለ ማስወረድ ስለ እርግዝና ሲወራ፣ የአገር ድብርት ይጫነኛል፣ መንፈሴ ይረባበሻል፡፡ በመንፈሳዊ ትምህርትም ሆነ ስብከት፣ ስለማስወረድ ኃጢያትነት ሲነገር ነፍሴ በእሳት ጅራፍ ትገረፋለች፤ ደግሞ ማድመጥ ስለጀመርኩ ነው መሰል ወሬው ሁሉ፣ ስብከቱ ሁሉ፣ የሬዲዮና ቴሌቪዥን ፕሮግራሙ ሁሉ ማስወረድ የሚል ቃል የተሞላ ሆነብኝ፡፡ የሆነ ከባድ ሚስጥር እንደያዘ ሰው ወሬዬ ሁሉ በጣም በጥንቃቄ ሆነ፡፡ እንኳን ወሬ ሳወራ ስስቅ በጥንቃቄ ነበር፡፡ ምንድን ነው ከውስጤ ያወጡት? እስከምል ሁሉም ነገሬ ተወስዶ ነበር፡፡ እንደሆነ ባዶ በርሚል ምናምን፣ ወደ ውስጤ ብጮኽ የገደል ማሚቱ የሚያስተጋባ እስኪመስለኝ ኦና ሆኜ ነበር! ሃይሚ በብዙ ልታጽናናኝ ትሞክራለች “እንትናን ታውቂያታለሽ? ያቺ እንኳን የእንትና ገርል ፍሬንድ? እንትን እንኳን የምትሠራው?...እሷ ሦስት ጊዜ ነው ያስወረደችው፣ ተራ ነገር'ኮ ነው፡፡ እንትናስ? አሁን አግብታ እንግሊዝ የሄደችው? በአራት ወሩ አስወጥታለች ...'' አንዳንድ ነገሮች አሉ ዐሥር ጊዜም ተሠሩ፣ አንድ ጊዜ ዋጋቼው እኩል የሚሆን፤ ሃይሚ ያልገባት ይኼ ነው። ቁጥር ምንድነው? ሁለት ወር ይሁን፣ ዘጠኝ ወር ፅንስ ምን ልዩነት አለው? ሰኞ ልሙት ዓርብ፣ ሟች ያው ማኅደረ ሰላም ነኝ፡፡ የመሞቻ ቀን መቅደምና መዘግዬት የሟችን ማንነት አይቀይረውም።

ብደጋግመው እላመደው ይሆናል እንጂ፤የነገሩን መሠረታዊ እውነት አልቀይረውም:: እውነቱ ግን ተፈጥሮ፣ ወላ እግዚአብሔር ውስጤ በአደራ ያስቀመጡትን ፅንስ ገድዬዋለሁ፡፡ ምክንያቴ ምን ነበር?... ማሳደግ ስለማልችል?...አይደለም! የጤና እክል ስላለብኝ?... አይደለም!... ራስ ወዳድነት ነው፡፡ ሳላገባ ወለድኩ እንዳልባል፣ ከማያፈቅረኝ ሰው ወለድኩ እንዳልል ...አባቴ እንዳያዝን!...አዎ አባቴ እንዳያዝን ልጄን መግደል! ወይም እኔ እንጃ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በሬዲዮ፣ በቴሌቪዥንና በጋዜጣ፣ በየመድረኩ “በሕገ-ወጥ መንገድ ፅንስን ማስወረድ ...በሕጋዊ መንገድ ፅንስን ማስወረድ ..." እየተባለ ሲነገር ግርም ይለኛል፡፡ የተፈጥሮን ሕግ የሚጻረር ሕጋዊነት እንዴት ያለ ነው? ከዚህ አጋጣሚዬ የተረዳሁት የትኛውም ሕጋዊነት ከከፋ የጤና ስጋት ሴቷን ይታደግ ይሆናል፤ ከማስወረድ በኋላ ከሚኖረው የሥነ-ልቦና ጉዳት የሚታደግ ሕግ ግን የለም።ነገሩን ቀለል ለማድረግ የሚጠቀሙበት ብዙ መንገድ በኋላ የደረሰብኝን ከባድ የሥነ-ልቦና ጉዳት እንዳልገምት አድርጎኝ ነበር፡፡ ከማስወረዴ በፊት ጓደኛዬ ሃይሚ ስታጽናናኝ ያለችኝን አልረሳም “ፅንስ እንጂ፣ ልጅ አይደለ!?...'' ፅንስ ማስወረድ የሚለው አገላለጽ፣ ልጅ ማስወረድ ሆኖ እንዳይታዬኝ ማን ነበር የቃል ጨዋታ የቀመረው...? እንዲያዉም ፅንስ ማቋረጥ እኮ ነዉ ያሉኝ፡፡ እንግዲህ ሰዉ ሳይሆን ሰዉ የሚሠራበትን ሂደትን ነዉ ያቋረጥነዉ አይዟችሁ መሆኑ ነዉ፡፡ፊልም ወይንም “ሶፍትዌር' ምናምን ስንጭን ሳይጨርስ ብናቋርጠዉ “አቦርት' ሆነ እንደሚለን የኮምፒዩተር ቋንቋ፣ ከመሐፀንናችን ልጆቻችንን ስናስወርድ አንድ ቀላል ሂደት ያቋረጥን እንዲመስለን “አቦርሽን' የሚል ተመሳሳይ ቃል አስታጠቁን፡፡ ተቀብለን ፅንስ ማቋረጥ እንላለን፡፡ እንኳን ፅንስ ጠብታ ደማችን ዉስጥ ሙሉ ባይሎጂካል ማንነታችን እንዳለ የነገሩን እነሱ አልነበሩም? ሙሉ ማንነቴ ነዉ የተወሰደዉ፡፡ ከዚያን ጊዜ በኋላ የሃይማኖት ሰዎችን እና የመንፈሳዊ ወሬ በሩቁ መሸሽ ጀመርኩ፡፡ እግዚአብሔር ብዬ መጥራት አፌ ላይ ከበደኝ፡፡ በምድር ላይ እንደ እኔ ዓይነት ኃጢያተኛ ያለ መስሎ እስከማይሰማኝ ራሴን ተጸዬፍኩት፣ ጠላሁት፡፡ ከሁሉም

ልቤን የሰበረው፣ ከሕፃንነቴ ጀምሮ አንድ ዓመት እንኳን አልፎኝ የማያውቅ ልማድ ነበረኝ፣ አባቴ ጋር ሆነን ለጥምቀት የልደታን ታቦት መሸኜት “ለልደታ ሴት ልጅ ከሰጠሽኝ በየዓመቱ ላንቀር ብዬ ተስያለሁ" ይላል የአንድ ዓመት ልጅ ሆኜ ነው አቅፎ የወሰደኝ፤ ያኔ ነበር የጀመርነው፡፡ ወንድሞቼ ጋር እንኳን አይሄድም። የሁሉም ዓመት ፎቶ አለን፤ ለአባቴ የተለዬ ትርጉም የሚሰጡ ፎቶዎች፡፡ አቤት እነዚያን ፎቶዎች ሲመለከት ፊቱ ላይ የሚበራው ብርሃን! ...ያ የአባቴ ኩራት ነበር፡፡ በዚያ ዓመት የጥምቀት በዓል ሊከበር ቀናት ሲቀሩት፣ ከባድ የመንግሥት ሥራ አለብኝ በሚል ሰበብ አባቴን አሳምኜ የዕለቱ ዕለት ሃይሚ ቤት ሳለቅስ ውዬ፣ ሳለቅስ አደርኩኝ፡፡ ያን ያኽል ሃይማኖተኛ ባልሆንም ልደታን እወዳታለሁ፡፡ ስመለስና የልደታን ጉልላት ሳይ፣ ማረፊያ ሜዳው ላይ የትም ዞሬ ወደ ሰፈሬ እንደ ደረሰ አውሮፕላን መንፈሴ ለእረፍት ይንደረደራል፡፡ አንዳንዴ በዚያ በኩል ሳልፍ፣ ዝም ብዬ ገብቼ ግቢው ውስጥ ቁጭ ስል ይሰማኝ የነበረው ሰላም ልዩ ነበር። ያጣሁትን ሰላም የምፈልገው እዚያ ልደታ ግቢ ነበር፣ ያንን ሁሉ ነው ከውስጤ ፅንስ ነው ብዬ ያስወጣሁት፤ ከነኃጢያታችሁ፣ ከነሸክማችሁ ኑ! መባሉን እየሰማሁ ባድግም፣የራሴ ሸክም ክፉኛ ወደ ኋላ ጎትቶኝ ልደታን በሯን መርገጥ ፈራሁ፡፡ በዚያ ሳልፍ ጉልላቷን ቀና ብዬ ማዬት እንኳን ከበደኝ። ፍርሃቴ ቀላል አልነበረም፤ ጭል ጭል የሚል እምነቴ ከማሕፀኔ በግዴለሽነት በነፈሰ ነፋስ ድርግም ብሎ ጠፋ። ጨለማ ነበር የዋጠኝ፡፡ ይኼ ሁሉ ዶክተሩ “ጨርሰናል!'' ካለባት ቅጽበት የጀመረ የነፍሴ ረብሻ ነበር።

ማቄን ጨርቄን ሳልል ...

በዚያ ስቃይ ውስጥ እያለፍኩ አብርሃምን አልራቅሁትም። በደወለልኝ ቁጥር ተንደርድሬ እቤቱ ነበርኩ፡፡ ወደ ቤቱ ስሄድ እንደ አክርማ ልቤ ለሁለት ይሰነጠቃል፣ ወደ ኋላዬ በመመለስና ወደሱ በመሄድ፤ ስቃዩ በአካል በስለት የመሰንጠቅ ያኽል

የሚያም ነበር፡፡ አስታውሳለሁ አንድ ቀን በጭራሽ ቤቱ መሄድ የለብኝም ብዬ ወሰንኩ፤ በደወለልኝ ቁጥር እሱ አልጋ ላይ የምገኘው ሴተኛ አዳሪ ነኝ ወይ አልኩን እልኽ ከእግር ጥፍሬ ጀምሮ እስከ ራስ ጸጉሬ አንቀጠቀጠኝ... በጭራሽ! አልኩ! ሲደውል ግን ወደ ላፍቶ የሚሄድ ታክሲ ላይ ራሴን አገኜሁት... ወደ እሱ ቤት፡ ከራሴ ጋር ትግል ጀመርኩ። እዚሀ ወርጄ መመለስ አለብኝ...እዚያጋ...እያልኩ ላፍቶ ደርሽ ወረድኩ፡፡ ቆሜ የኮንዶሚኒዬሙን ግራጫ ሕንጻ ለደቂቃዎች ተመለከትኩ፣ ምንድነው እዚያ ብሎኬት ክምር ውስጥ ያለው? ተመለከትኩ! ራሴ ጋር ግብግብ ገጠምኩ፤ እናም ለመጀመሪያ ጊዜ ራሴን አሸንፌ የሚመለስ ታክሲ ውስጥ ዘልዬ ገባሁ። አቤት የተሰማኝ እርካታ!...ከሆነ አውሬ ያመለጥኩ ያኽል፣ ከንፈሬ እየተንቀጠቀጠ ዕንባ ተናንቆኝ ነበር፡፡ ልክ ሜክሲኮ ደርሼ ስወርድ ግን ስልኬ ጮኸ፣ አብርሃም ነበር፣
👍359
አነሳሁት...ደግሞ የአነሳሴ ፍጥነት፤ በቃ ምን እንደተፈጠረ የማወቅ ጉጉት:: እንዳንዴ ውስጣችን የሚደረግ ጦርነት ዓለምን ሁሉ የገለባበጠ የሚመስለን ነገር አለ አይደል!? ....በተረጋጋ ድምፅ “ማሂ ሰላም ...በደሀናሽ ነው? ስትቆይ...'' አለኝ፣ አላስጨረስኩትም..."እየመጣሁ ነው ታክሲ አጥቼ ነው አብርሽዬ'' የሚል ምላሽ ነበር ከእፌ የወጣው። ዙሪያዬን ቃኜሁ፣ መንገድ ተሻግሮ ከተደረደሩት የኮንትራት ላዳ ታክሲዎች ውስጥ ወደ አንደኛው የሩጫ ያኽል ገሰገስኩ፡፡ እናም ልክ እንደምርኮኛ በዝምታ ከራሴ ፈቃድ ውጭ ወደ ላፍቶ መንገዴን ጀመርኩ- ወደ እሱ ቤት፣ ወደ እሱ አልጋ፡፡ እዚያ ሌላ ምን አለ? ምንም! ...አልጋ ብቻ! በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ በዚህ ፍጥነት ያለቀ ጦርነት ይኖር ይሆን?! ከዚህ አዙሪት ለመውጣት ብቻዬን ስወድቅ ስነሳ ኖሬ፣ አልሆን ሲለኝ ዓይኔን ጨፍኘ ትዳር ውስጥ ለመግባት ወሰንኩ። በቃ ማንም ይሁን አንዱን ማግባት፡፡ ከዚያ በፊት ግን ለማንም ያልተናገርኩት ውሳኔዬ የነበረው ራሴን ማጥፋት ነበር፤ ድንገት ነው ሐሳቡ የመጣብኝ፣ እሑድ ቀን አባቴ ጋር ቁጭ ብለን አንድ በቴሌቪዥን የሚተላለፍ ተከታታይ ድራማ እየተመለከትን ነበር፡፡

ከተለያዩ ሰዎች ብዙ ብድር ተበድሮ መክፈል ያቃተው ገጸ- ባሕሪ ነው...ምርር ብሎት “ በቃ ከዚህ ሁሉ ጭቅጭቅ ራሴን ባጠፋ፣ አበዳሪ እንጂ እኔ ምን እሆናለሁ? መሞትን የመሰለ ነገር ምናለ? ማቄን ጨርቄን ሳልል በዝምታ ይህችን ምድር ትቼ እብስ ...ከዚያ የለሁም፣ ስቃይ የለም፣ጭንቀት የለም፣ አበዳሪ የለም፣ ሆድ የለም ..ምንም የለም'' ይላል፡፡ አባቴን ዞሬ አዬሁት እየሳቀ ነበር፤ እኔ ግን “ማቄን ጨርቄን “ቃሉ ራሱ ደስ አለኝ ...ይህች ማቃምና ጨርቃም ዓለም ምኗ ይቀራል? አልኩ ለራሴ... ማኅደረ ሰላም ትታት ስለሄደች በምድሩ “አዲተር ሊጠፋ ነው?...ወይስ ለአንድ ደመ ቀዝቃዛ አብርሃም ቀሚሷን የምትገልብ ሴት ልትጠፋ? ማን ምን ይቀርበታል?... እኔስ ምን ይቀርብኛል? በጣም ውስጤ በሚያስገርም ሁኔታ ሐሳቡን ለሳምንታት ሲያመነዥክ፣ ከዚያም አልፌ ሐሳቡ አድጎ አሟሟቴን ስመርጥ ሰነበትኩ፡፡ ግን በብዙ ብዙ ምክንያቶች በተለይ ያለ እናት ላሳደገኝ አባቴ ስል ሐሳቤን ቀዬርኩ። ራሴን ማጥፋት ያለጥርጥር ወደዚህ ምስኪን አባቴ አነጣጥሮ እንደመተኮስ ነበር፤ በስንቱ ይጎዳ!? እኔን ማዬት ነውና ተስፋው አባቴን ለምን በቁሙ ልግደለው? እንዲህ ሳስብ ድንገት አንድ ቀን “ማኅደሬ ምነው ሰሞኑን ትክ ብለሽ ታይኛለሽ?... አረጄሁ እንዴ? ...ገና ነኝ፣ ገና የልጅ ልጆችሽን ሳላይ የምን እርጅና?....” ብሎ ፈገግ አለ፡፡ ውስጤ ተንሰፈሰፈ፣ ድንገት አቅፌው ዕንባዬ ተዘረገፈ። ሌላም ሰበብ፣ ላለመሞት ሰሚ ፈርታ ነው ቢለኝም፤ እንደ እናቱ ለሚወደኝ እኔም እንደ ነፍሴ ለምወደው ለወንድሜ ልጅ ስል ሐሳቤን ቀዬርኩ (እናቱ እስክትወስደው ድረስ ያኔ እኛ ጋር ነበር የሚኖረው) ምናልባትም በግልጽ አልበለው እንጂ ጥልቅ በሆነው የነፍሴ ክፍል ሐሳቤን መቀዬሬ ከማፈቅረው ሰው የመለዬት ፍራቻም ይመስለኛል፡፡ መሞትም መኖርም የማልችል ከንቱ ሆኜ ቀረሁ፡፡ ዝርዝሩ ብዙ ነው፤ ሰርጌ ሁለት ቀን እስኪቀረው ድረስ ፍቅረኛዬ አብርሃም አልጋ ውስጥ ነበርኩ ብል ማን ያምነኛል!? ፍቅረኛዬ ስልና ስነጫነጭ መቼም ሰው የሚያስበው፣ የማይታመን ወይም መጥፎ ባሕሪ ያለው (የሚጠጣ፣ የሚሰክር፣

የሚቀና ወይም የማይታመን) ወንድ ያፈቀርኩ ነው፤ በየቀኑ ጋን ሙሉ ቢጠጣና ሒሳቡን እኔ ብከፍል ደስታውን አልችለውም ነበር፡፡ ጓደኛዬ “አስደግሞብሽ ነው!" ትለኛለች፡፡ ብዙ ጊዜ እሷ ጋር አብረን ምሳ እየበላን ሲደውልልኝ ወደ አፌ የሚጓዘውን ጉርሻ ከእጄ ርግፍ አድርጌ፣ እጄን እንኳን ሳልታጠብ ወደ እሱ ስሮጥ ትበሳጭ ነበር፡፡ አትወደውም፡፡ ተንበርክኮ የረገጥሽውን አፈር በምላሱ እየላሰ፣ እመቤቴ ሊልሽ የሚገባው ነው... ትበዥበታለሽ ትለኛለች፡፡ እውነታው ግን አውቆም ይሁን ሳያውቀው በሥጋም፣ በነፍስም ከሚረግጠው አፈር በታች ትቢያ አድርጎ ሞራሌን መሰባበሩ ነው። ምን ለውጥ አለው? ተንበርክኬለት ነው የኖርኩት፡፡ ምንም ምክንያት የለኝም ፍቅር ብቻ፡፡ ዝቅ ያደረገኝ፣ ከፍ ያደርጋል የሚሉት ፍቅር ነበር፡፡ ሕይወት ከስብከትና ከጥቅስ ፈጽሞ ይለያል፤ እንጃ የተሳካለት ካለ!? ለእኔ ግን ስሰማው የኖርኩትና የገጠመኝ ፈጽሞ የተለያዬ ነበር፡፡ ስለ እሱ ሳወራ ዕንባ ይቀድመኛል፣ እሱ ፊት ግን ለዓመታት ላለማልቀስ ታግያለሁ፤ የፈረደባት ጓዳኛዬ ላይ መጥቼ እነፋረቃለሁ፣ “ይኼ መተታም፣ የመተታም ልጅ አስደግሞብሻል'' እያለች ታባብለኛለች። የኔ ምስኪን! ለክፉም ለደጉ ጸበል እንሂድ ብላ በስንት ልመና ወስዳኝ፣ እውነትም ሰይጣን ሹክ ያለው ይመስል ቤተክርስቲያኑ በር ላይ ስደርስ ደወለ ...ነጠላዬን እንደ ክንፍ እያውለበለብኩ ለጸበል የታሰብኩት ልጅ እሱ አልጋ ላይ ተገኜሁ። ድግምት የሚባለው ኖረስ አልኖረስ ከዚህ የተለዬ ምን ያደርጋል!? እፈራው ነበር ዓይኖቹን ትክ ብዬ ማዬት እፈራ ነበር፣ ውስጤ ይሸበራል፡፡ ስልኩ ሲጠራ እጄ ለማንሳት ሲንቀጠቀጥ ይታወቀኛል። ልቤ በደስታ እየዘለለች ጉሮሮዬ ላይ የተወተፈች እስኪመስለኝ በደስታ እታፈናለሁ፡፡ ነፍሴም፣ ሥጋዬም በንቃት የሚጠብቁት የእሱን ስልክ ብቻ ነበር፡፡ ግን ምንድን ነው ፍቅር?...አንዱ ለአንዱ አስደገመ ማለቱ ይቆዬንና፣ ፍቅር በራሱ ሁለት ሰዎች ላይ ተፈጥሮ ያዞረችባቼው መተት ሳይሆን ይቀራል? ለነገሩ ያን ያኽል ሃይማኖተኛ ባልሆንም፣ ፍቅር ግን ከእግዚአብሔር አልመስልሽ ካለኝ ቆይቷል፡፡ በተለይ የእኔ ዓይነቱ እግር እጅ የሌለው ፍቅር፡፡ በምን የተረገመ ቀን ነው ይኼንን ሰው ያወቅሁት!? እላለሁ፡፡

ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍2910
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ:
እባክሽ አትሂጂ…..
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አንድ
///
ልዕልት ትባላለች።እንዲህ አይነት ውብ መልክና ውብ ስም ካላት ሴት ጋር ስተዋወቅ ምን አልባት ይሄ የመጀመሪያ የህይወት ገጠመኜ መሰለኝ፡፡የተዋወቅነው ከአመት በፊት ነው:: ባሏ እኔ በምሰራበት ሆስፒታል የፁኑ ህመምተኛ ታካሚ ነው፡፡ በየጊዜው ስለሚመላለስና ቀጥታም የምከታተለው እኔ ስለሆንኩ ከእሷ ጋርም በተደጋጋሚ ጊዜ (ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን)የመገናኘት እድል አለን።ባለፈው አንድ ወር ደግሞ ባሏ ሙሉ በሙሉ አልጋ ይዞ ስለተኛ  ቀኑን ሙሉ፤ ተረኛ ስሆን ደግሞ ለሊትም ጭምር የመተያየት እና የመገናኘት ወርቃማ አጋጣሚ አለን።
ልዕልት እሷ ባትነግረኝም እድሜዋ ስገምት ከ35-40 ይሆናታል።በዛ ላይ ባለትዳር ብቻ ሳትሆን የሦስት ልጆችም እናት ነች።ትልቁ ልጇ አስር አመት፤ ቀጥሎ ያለው ስድስት አመት ሲሆነው ሶስተኛዋና ዘወትር ደረቷ ላይ ያለው ጡቷን ጎርሳ ስትመጠምጥ የማያት የመጨረሻዋ ልጅ ለሁለት አመት ጥቂት ወራት የቀራት ነች።
ልዕልት እውነት እንደስሟ በመልኳም ሆነ በፀባዮ ልዩ አይነት የነገስታት ዝርያ ያለባት የምትመስል ልዩ  ሴት ነች።ንፁህ ጥርት ያለ ውበት..ትንሽ ቢጫኗቸው ተመንቅረው የሚወድቁ የሚመስሉ ተንከባላይ አይኖች...ሁል ጊዜም በቅጡ ባይሰሩም ደማቅ ጥቁር ሉጫና ግንባሯ ላይ ድፍት የሚል ፀጉር ያላት ጠይም ባለ ቸኮሌት ቀለም ..ቁመተ -ለግላጋ  ለእናትነት ስቃይ ሳይሆን ለቤተ-መንግስት ምቾትና መሞላቀቅ የተፈጠረች የምትመስል ሴት ነች።
ደግሞ ከልዕልት ነገሮች ሁሉ የሚገርመው ለአመታት የአልጋ ቁራኛ ሆኖ ለህይወቱ ለሚታገለው ባሏ ያላት የፍቅር ግለት ከሰው ልብ የሚመነጭ አለመምሰሉ ነው።እንዴት አንድ ቀን ችላ አትለውም?እንዴት ለሆነ ሰዓታት ቱክረቷን ከእሱ ላይ አንስታ አካባቢው ላይ አታንከራትትም....?እንዴት የከሳ ሰውነቱ እና ያገጠጠ አጥንቱን አይታ ፊቷን አትቋጥርበትም...?እንዴት በየቀኑ እየከሳችና እየሠለለች በመሄድ ላይ ያለችውን ነፍሱን ታዘባ ተስፍ መቁረጥ አትጀምርም...?በየቀኑ ስለእሷ ባሰብኩ ቁጥር ራሴን የምጠይቀው ጥያቄ ነው።ጥያቄውን ደጋግሜ ስጠይቅ በሰውዬው ቦታ እራሴን ወደማስቀመጥና በእሱ ወደመቅናት ተሸጋገርኩ..፡፡በሂደት አስደንጋጭ ቅርቃር ውስጥ ገብቼ እራሴን የፍቅር ወጥመድ ውስጥ እንዳስገባሁ ተረዳሁ፡፡
የታካሚዬ ባለቤት የሀነችውን ሴት… የሦስት ልጇች እናት የሆነችውን ሴት…. ቢያንስ በአስር አመት የምትበልጠኝን ሴት… ክፉኛ እንዳፈቀርኳት ተገለፀልኝ..፡፡ያ ደግሞ ክፉኛ አስገረመኝም፤ አስደነገጠኝም፡፡
በከሳና በገረጣ ሰውነቱ የቱቦ መአት ተሰክቶለት በህይወትና በሞት መካከል ተጣብቆ የሚቃትት ባሏን በማስታመም እየቃተተች ያለች ሚስኪን ግራ የገባት ሴት እንዴት ላፈቅር ቻልኩ...?ኸረ እንዴት ቀድሞውንስ ሀሳብ ወደአእምሮዬ ተሰነቀረ..?ማፍቀሬስ እሺ ይሁን አፈቀርኩ...ይሄንን እብደት ለእሷ እነግራታለሁ..?መች? ባሏ ድኖ ሲወጣ ጠብቄ ወይሰ አሁኑኑ...?ምን ምላሽ ትሰጠኛለች...?ምንስ ምላሽ ብትሰጠኝ   ለውጥ ይኖረዋል..?ግራ ገብቶኛል ።
ልክ እሷ በባሏ ህመምና ለእሱ ህክምና በምታወጣው ወጪና ልጆቾን ለማኖር በምታደርገው መንፈራገጥ ጭንቅ ውስጥ እንዳለችው ሁሉ እኔም እሷ ላይ ባለኝ ስሜት  እንደዛው ግራ ተጋብቼያለሁ።
እርግጥ የምናፈቅረው  ከሌላው የበለጠ ውበት እና  እውቀት ያለውን ሰው መርጠን    አይደለም፡፡የምናፈቅረው ምክንያት አልባው ልባችን የደነገጠበትን ሰው  ነው፡፡ ጓደኞቻችንን በአእምሮችን አስልተን ..መስፈርት ደርድረን  በጥንቃቄ እንመርጣለን…ፍቅረኞቻችንን ደግሞ በቅፅበታዊ  ውሳኔ በስሜት ላይ ተመስርተን ብቻ በልባችን እንመርጣለን፡፡አእምሮአችን  ምክንያታዊነትን ሲያደንቅ..ልብ ደግሞ ለስሜት  እጅ ይሰጣል ፡፡እና እሷም ለባሏ ያለት ፍቅር እኔም ለእሷ ያለኝ ስሜት በዚህ ስሌት ውስጥ የሚታይ ነው፡፡
አሁን ላናግራት ፈልጌ ቢሮዬ አስጠርቼያት እየጠበቅኳት ነው።ቢሮዬ በስሱ ተንኳኳ….. በተቀመጥኩበት ተሽከርካሪ ወንበር የማደርገው ግራ ገብቶኝ እየተቁነጠነጥኩ በተሰባበረ ድምፅ ‹‹ይግብ›› አልኩ፡፡በራፉ በዝግታ ተከፈተ..ያሰገገ ሰንደቅ አንገት አየሁ...እራሷ ነች።ትንሿን ሴት  ልጅ በደረቷ ታቅፋለች ፤ሌለኛው ልጅ ቀሚሷን አጥብቆ እንደጨበጠ ተከትሏታል።ትልቁ ልጅ ብቻ ነው ስሯ የሌለው።
ከመቀመጫዬ ተነሳሁና ..‹‹ግቢ ልዕልት››  አልኳት፡፡
ዝግ እና ቅስስ ባለ እርምጃ‹‹እሺ ዶክተር አመሰግናለሁ፡፡›› አለችና የከፈተችውን በራፍ ዘግታ ወደ ውስጥ በመዝለቅ የጠቆምኳት ወንበር ላይ ተቀምጣ ህፃኗን ጭኗ ላይ አስቀመጠችና የዛኛውን ጭንቅላት በእጆቾ እያሻሸች የምላትን ለመስማት ዝግጅ ሆነች።
‹‹እሺ እንዴት ነሽ?››
‹‹ይመስገነው ዶ/ር ...፡፡››
‹‹ስለባለቤትሽ ህመም እንድንነጋገር ነበር የጠራሁሽ፡፡››ንግግሬን ሳልጨርስ በእነዛ አሎሎ አይኖቾ የእንባ እንክብል ግጥም ሲልባቸው እኔ የምገባበት ጠፋኝ።
‹‹ዶ/ር ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ..?ይድንልኛል አይደል?በፈጣሪ እርዳታ ታድኑልኛላችሁ አይደል?››ተንሰፈሰፈች፡፡ወንድ ልጇ አንዴ እናቱም አንዴ እኔን እያየ ይቁለጨለጭ ጀመር፡፡ልጁ ፊት በቀጣይ የምነግራትን ነገር እንዴት እንደምነግራ ግራ ገባኝ…፡፡
‹‹ልዕልት ተረጋጊ...አሁን ለጊዜው ምንም የተፈጠረ የተለየ ነገር የለም...ይሁን እንጂ ባለፉት ሶስት ሳምንታት ምንም አይነት የመሻሻል ምልክትም እየታየ አይደለም።››
‹‹እና ምንድንነው መፍትሄው?"
‹‹እንድንማከርም የፈለኩት ለዛ ነው….ባለቤትሽ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ለተራዘመ ጊዜ ከቀጠለ አንቺም ከነልጆችሽ ትሰቃያለሽ...በየቀኑ  የህክምና ሆነ የመድሀኒት ወጪውን አትቺይውም››
‹‹እና ምን አድርጊ ነው የምትለኝ?››
‹‹ቀዶ ጥገና ለማድረግ ቢያንስ እጢው  የተወሰነ ማደግ አለበት፡፡ ለዛ ደግሞ ቢያንስ ስድስት ወር መጠበቅ የግድ ይለናል።ለስድስት ወር ሙሉ ደግሞ እዚህ ልታቆዪው አትቺይም..››
‹‹ታዲያ ዶክተር ምን ትመክረኛለህ?››
‹‹እንደእኔ ወደቤት ወስደሽ እንድትንከባከቢው ነው የምመክርሽ ..እቤት ከሆነ የመድሀኒት ወጪ ብቻ ነው የሚኖርብሽ...በሶስት ቀን አንድ ቀን እየመጣሁ አይልሻለሁ..ድንገት ካመመውም እንደደወልሺልኝ ቶሎ መጥቼ ላይልሽ ቃል እገባልሻለሁ።››
አይኖቾን ጎልጉላ በአድናቆት አፍጥጣ አየችኝ።ብዙ  ጥያቄዎች በውስጧ እየተተረማመሱ እንደሆነ በግልፅ ተረድቼለሁ።
‹‹ከእነዚህ ልጆች ጋር ከዚህ በላይ ስትንገላቺ ዝም ብሎ ማየት ስላላስቻለኝ ነው››አልኳት፡፡
እስከአሁን በመከራ ከትራው የነበረውን እንባዋን ለቀቀችው።በጉንጫቾ  ተንኳሎ ያቀፈቻት ህፃኗ ግንባር ላይ ይነጥር ጀመር..፡፡ወንዱ ልጇ ተጨንቆ ተንቆራጠጠ፡፡
ፍፅም ትህትና በተላበሰ ድምፅ‹‹ዶ/ር በእውነት በጣም መልካም ሰው ነህ..እስከዛሬ ድረስ ባሌን በመንከባከብ ያደረክልኝን ነገር ዕድሜዬን ሙሉ አረሳውም...ከዚህ በላይ ላስቸግርህ አልፈልግም...እንዳልከው ግን ወደቤት ወስጄው እየተመላለሰ የሚያይልኝ ሌላ ሰው ፈልጋለሁ።አንተን ከዚህ በላይ ማስቸገር አልፈልግም፡፡››
👍4611🔥1😱1
‹‹አይ ያማ አይሆንም ..ይሄንን የማደርገው ለአንቺ ብዬ ሳይሆን እራሴ ስለፈለኩ ነው።ጥሩ ነገር ለመስራት ልቤ ሲነሳሳ አንቺ ደግሞ እንቅፋት ስትሆኚብኝ እግዜሩስ ምን ይልሻል?››ይሄንን የመሰለ የታሰበበት ወርቃማ እድል እንዳታበክንብኝ ስለሰጋሁ ቀባጠርኩ፡፡ተሳካልኝና ፈገግ አስባልኳት...ልጇን አቅፋ ከተቀመጠችበት ተነሳችና››እግዜር ይባርክህ...እንዳልከኝ አደርጋለሁ፡፡››ብላኝ እንዳአመጣጧ ሹልክ ብላ  ወጣችና.. በራፉን ዘጋችልኝ።እኔም በረጅሙ የእፎይታ ትንፋሽ ተነፈስኩና በቀጣይ ስለሚሆነው ነገር ማሰብ ጀመርኩ።


ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
21👍17😱3
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ:
እባክሽ አትሂጂ…..
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-ሁለት
///


በሶስተኛው ቀን የሆስፒታሉን ኘሮሰስ ሁሉ ጨርሳ   ባሏን ይዛው ወደቤት ሄደች ።በማግስቱ ከስራ እንደወጣሁ ደወልኩላት።
‹‹ሄሎ ልዕልት ዶ/ር ሳሙኤል ነኝ፡፡››
‹‹አውቄሀለው ዶ/ር ...እንዴት ነህ?››
"ሰላም ነኝ ..ቀጠሮ ነበረን… ለዛ ነው የደወልኩልሽ››
‹‹አዎ ዶክተር.. ስራ በዝቶብህ ምትዘነጋው መስሎኝ ነበር፡፡››
‹‹አይ ፈፅሞ አልዘነጋውም...ያንቺም ጉዳይ ከዋና ስራዎቼ ውስጥ አንዱ  ነው...አሁን ሰፈርሽን ንገሪኝ፡፡››
ደስ በሚል በረጋና ዝም ብሎ ፍስስስ በሚል ድምፅ  የቤቷን አድራሻ በዝርዝር ነገረችኝ...መኪናዬን ወደእዛው አንቀሳቀስኩ…የነገረችኝ ሰፈር እንደተቃረብኩ አንድ ሱፐር ማርኬት ጎራ አልኩና ለትልልቆቹ ልጆቹ ቸኮሌት ለትንሿ ልጅ አሻንጉሊት..ለእናትዬው አዲስ የተቀነጠሰ ትኩስ እንቡጥ ፅጌረዳ አበባ ገዛሁና ጉዞዬን ቀጠልኩ፡፡
እቤቷ አካባቢ ደርሼ ደወልኩላት። ወጥታ ተቀበለችኝ፡፡ መኪናዬን ወደ ጊቢ ውስጥ አስገባሁና አቆምኩ።እቤታቸው ግዙፍ የሚባል የድሮ ቢላ ነው።ጊቢውም ቢያንስ ከ300 ካ.ሜትር በላይ ይሰፋል። ከቢላው ጀርባ አምስት የሚሆኑ  ሰርቢስ ቤቶች ይታዩኛል።ሰው ገባ ወጣ ሰለሚልባቸው ለኪራይ የተዘጋጅ እንደሆነ ገመትኩ።ለልጆቹ የገዛሁትን ቸኮሌትና መጫወቻ አሻንጉሊቱን ከነፔስሉ ይዤ ወረድኩ።በሰላምታ ተቀበለችኝ።አለባበሷ እንደወትሮ ብዙም ያልታሰበበት ቢሆንም ውበቷ ግን ያው እንደተለመደው አስደንጋጭ ነው።
‹‹እንኳን በሰላም መጣህ ዶክተር...ና ግባ፡፡››ብላ ቀድማ ትመራኝ ጀመር..፡፡
በትህትና እየተከተልኳት‹‹እቤታችሁ ግዙፍ ነው..ግቢያችሁም ያምራል አልኳት፡፡››
‹‹ከአያቶቼ የወረስኩት ነው...እነሱ ነበሩ ያሳደጉኝ..አሁን ሁለቱም በህይወት የሉም››አለችኝ፡፡
‹‹አዝናለሁ...ነፍሳቸውን ይማር››አልኳት..በውስጤ እያሰብኩ ያለሁት ግን ጭራሽ ባልሽን በራስሽ የውርስ ቤት እያኖርሽ ነው?ብዬ እያማኋት ነበር፡፡
‹‹አረ ችግር የለም..የቆየ ታሪክ ነው።ግባ ቁጭ በል።››አለች፡፡
ግዙፍ ሳሎን ገብቼ በግራ በኩል ያለው ሶፋ ላይ ልቀመጥ ወይስ በቀኝ ያለው ላይ እያልኩ በመወዛገብ ላይ እያለሁ ሁለቱ ልጆቾ ከውስጠኛው ክፍል እየተሽቀዳደሙ‹‹ዶ/ር መጣ ….ዶ/ር …››እያሉ ሮጠው በመምጣት በግራና በቀኝ ተከፋፍለው ተጠመጠሙብኝ።እኔም እንደጥሩ አጎት ሁለቱንም ግንባራቸውን እያሸሁና ጉንጫቸውን እየሣምኩ አፀፋውን መለስኩ፡፡
‹‹እስቲ ዞር በሉለት ቁጭ ይበል፡፡››ተከላከለችልኝ።ቁጭ ስል በግራና በቀኜ ተቀመጡ...ምን አልባት ይሄ ከልጆቹ ጋር የጀመርኩት መቀራረብ  ትልቅ ውጤታማ እስትራቴጂ ሊሆን ይችላል የሚል ሀሳብ ብልጭ አለልኝ፡፡...በልጆቹ ልብ ውስጥ በጥልቀት ከገባው እዛ ውስጥ የናትዬውንም ልብ ማግኘቴ ስለማይቀር ነገሮችን ያቀልልኝ ይሆናል።
የያዝኩትን ፔስታል ከፈትኩና ሱፐርማርኬት ጎራ በማለት የሸመትኩትን ቸኳሌትና ብስኩት እኩል እኩል አካፈልኳቸው …በደስታ ፈነጠዙ...መጫወቻ አሻንጉሊት አውጥቼ ‹‹ይሄ ደግሞ የሚጡ ነው..የታለች?"
‹‹ተኝታለች፡፡››
‹‹በሉ.. ስትነሳ ስጡልኝ፡፡››
‹‹በሉ አሁን ስጦታቸውን ይዛችሁ ወደክፍላችሁ ሂድ፡፡››እናትዬው ትዕዛዝ አስተላለፈች፡፡
ስጦታቸውን በእቅፋቸው ሰብስበው‹‹ዶ/ር እናመሰግናለን.. ››እያሉ ተከታትለው ወደውስጠኛው ክፍል በመግባት ተሠወሩ።
ከዛ እናትዬው በተቀመጠችበት ትኩረቷን ወደእኔ ሰበሰበችና ‹‹ዶ/ር ለምን እንደዚህ ታደርጋለህ?››ስትል የሀዘኔታ ይሁን የቁጣ ባለየሁት ድምፀት ጠየቀቺኝ፡፡
‹‹ምን አደረኩ..?››
‹‹ይሄ ሁሉ ወጪ..አስፈላጊ አልነበረም እኮ...ለማንኛውም ቡና ላፍላ ወይስ ሻይ?››
‹‹አይ ትኩስ ነገር ላይ እስከዚህም ነኝ.....በቀን አንዴ ብቻ ነው የምጠጣው..››
‹‹ቢራስ...?››
‹‹አይ ካለ ውሀ?››
ወደፍሪጅ ሄደችና አንድ ሊትር የታሸገ ውሀ አምጥታ ፊቴ በማስቀመት ቀድሞ በነበረችበት ቦታ   ተቀመጠች።
‹‹ባለቤትሽ እንዴት ነው?››ጠየቅኳት፡፡
‹‹ያው የተለየ ነገር የለም..አልፎ አልፎ ወደቀልብ እንደመመለስ ይልና መልሶ ደግሞ ጥፍት ይላል።››
‹‹መድሀኒቱስ?››
‹‹መድሀኒቱን ባልከኝ መሰረት እራሴው በሰአቱ እየተከታተልኩ እየሰጠሁት ነው…የተወሰነ ለውጥ እያመጣለት ይመስለኛል፡፡››አለችኝ፡፡
በፈጥረት ታሪክ እንደ ኦክቶፐስ መስዋዕት የምትከፍል ቁርጠኛ የሆነች የእናቶች ተምሳሌት የለችም።አንድ የኦክቶፐስ እናት በአንድ ጊዜ 50 እንቁላል ትጥልና ያለምንም እረፍት ፣ መዘናጋትና እንቅስቃሴ ለ6 ወር ትጠብቃቸዋለች..ከስድስት ወር በኃላ እንቁላሎቹ ሲፈለፈሉ እናት ከጥበቃው ትገላገላለች ።ይሁን እንጂ ለስድስት ወራት ባጋጠማት   መጎዳትና ረሀብ ምክንያት  ህይወቷ ወዲያውኑ  ያልፋል።ይህቺም ፊት ለፊቴ ያለችው ሴት በዚሁ ከቀጠለች በእናትነቷ እና በሚስትነቷ ፍጽም መስዋዕት ሆና ልክ እንደኦክቶፐሷ የመጨረሻ ዕጣዋ መክሰምና መጥፋ እንዳይሆን ፈራለሁ…የእውነት በጣም ፈራለሁ፡፡
እንደምንም ወደ ቀልቤ ተመለስኩና ‹‹አሁን ላየው እችላለሁ?››አልኳት
‹‹ደስ ይለኛል›› ቀድማ ተነሳች፡፡ተከተልኳት፡፡ኮሪደሩን እየሰነጠቅን ብዙ ክፍሎችን  ካለፍን በኃላ አንድ ግዙፍ ክፍል ውስጥ ይዛኝ ገባች።ባልዬው በስርአት በተነጠፈው ግዙፍ አልጋ ላይ ስትር ብሎ ተኝቶል። በቀኝ በኩል ባለ ግድግዳ ላይ የተንጠለጠለ ጉሉኮስ ቱቦ ከክንድ ጋር ተገናኝቷል።ፊቱ ሲታይ ፀጥ ያለ ነው።አይኖቹን እየገላለጥኩና  አንገቱንን እየዳበሰኩ  ተመለከተኩና...‹‹አይ ጥሩ ነው...ዛሬ ዝም ብዬ ሁኔታውን ለማየት ነው የመጣሁት፡፡ነገ ግን መሳሪያ ይዤ መጣና አንዳንድ  ነገሮችን አይቼ  ተጨማሪ መድሀኒትም የሚያስፈልገው ከሆነ አዝለታለሁ።››አልኳት፡፡
‹‹እሺ በቃ ዶ/ር ..በል ና አትቁም፡፡›› አለችና..አይኔ እያየ በድን ሆኖ የተሠተረውን ባሏን ግንባሩን ስማ‹‹የእኔ ጀግና ለእኔ ያድርገው፡፡››በማለት አሁንም ቀድማኝ መኝታ ክፍሉ ለቃ መውጣት ጀመረች ...ተከተልኳት ፡፡ሳሎን ስመለስ የምግብ ጠረጴዛው የቤቱ ሰራተኛ በመሰለችኝ ሴት በምግብ እየተሞላ ነበር።ለመቀመጥ ወደ ሶፋው ስራመድ...‹‹ዶ/ር ወደ ማዕድ ጠረጴዛው ቅረብ››አለችኝ።
‹‹ኸረ ይቅርብኝ››በመሽኮርመም ተግደረደርኩ።
ፍስስ ብሎ ወደውስጥ በሚሰርግ አዚማም ድምፅ‹‹የማይሆነውን...የሚመጥንህ ባይሆንም ያው ለአንተ ብለን የፍቅራችንን ነው የዘጋጀነው።››አለችኝ፡፡
‹‹የፍቅራችንን ›› የምትለዋን ቃል ስሰማ ተንደርድሬ መቀመጫ ያዝኩ።የእጅ ውሀ በተቀመጥኩበት መጣልኝ..ጣፍጦኝ በላሁ።መአድ ተነሳ፡፡ ወደሶፋው ተመልሰን ፊት ለፊት ተቀመጥን።
‹‹ቆንጆ እራት ነበረ ፣አመሠግናለሁ ››አልኳት።
‹‹ስለወደድከው ደስ ብሎኛል...አብዛኛው ግን የሠራተኛዬ ሞያ ነው፡፡››
‹‹እንግዲያው ይህቺን ሰራተኛ እንዳላስኮበልልብሽ ተጠንቀቂ፡፡››አልኳት
‹‹ውይ እንደዛማ አይሆንም..ባይሆን ምግቧን  ሲያምርህ እዚሁ እየመጣህ ብትበላ ይሻላኛል።››
‹‹የወር አስቤዛህን ጭነህ አምጣ እያልሺኝ ነው?››
👍598👎1
ከት ብላ ሳቀች...እንደ እናት ሳይሆን እንደሴት ነው የሳቀችው..እንደሴት መሳቅ ግን እንዴት ነው?
‹‹አይ አስቤዛው እንኳን ከቤቱ ነው፡፡››
‹‹በኃላ ከሰርኩ እንዳትሉ››
‹‹ግድ የለህም...ይልቅ ወደቁም ነገሩ እንመለስ?ምን ያህል ነው ምታስከፍለኝ?››አለችኝ..ፍፁም ያልጠበቅኩት ጥያቄ ነው፡፡ደነገጥኩ...፡፡ምን ለማለት እንደፈለገችም አልገባኝም።
‹‹ለምኑ ነው የምትከፍይኝ?››
‹‹ያው  ተመላልሰህ ለምታይልኝ ነዋ..ጊዜህ አለ…. የመኪና ነዳጅ አለ››ዘረዘረችልኝ፡፡

‹‹እ እሱን ነው...ያው ብዙውን ጊዜ ምመጣው ማታ ከስራ መልስ ነው..እናም በመጣሁ ቁጥር የቅድሙን አይነት እራት እፈልጋለሁ፡፡››
‹‹አትቀልድ ዶ/ር፡፡››
‹‹የቀለድሽው አንቺ ነሽ...እኔ ከአንቺ ክፍያ ምቀበል ከሆነ ከሆስፒታል እንድትወጪ ማድረጌ ምንድነው ጥቅሙ..?እዛው አስተኝተሽ ብትከፍይ አይሻልሽም ነበር?››
‹‹ምን ነካህ ዶ/ር… እቤት በመሆኑ እኮ መአት ነገር ነው የማተርፈው..ቢያንስ ቢያንስ እሱንም ልጆቼንም በተሻለ መንከባከብ እችላለሁ።እና ለአንተ የሚገባህን ከፍዬም ብዙ ነገር አተርፋለሁ፡፡"
ከመቀመጫዬ ተነሳሁ...‹‹በይ አሁን ሸኚኝ...ክፍያ ምትይ ከሆነ ሌላ ሰው መፈለግ ይኖርብሻል…ለእኔ ክፍያ መክፈል ሎጂካል አይደለም››አልኳት..በፈጣሪ አሁን ልክ ያልሆነው እሷ ለእኔ የአገልግሎት ክፍያ መክፈል ነው ወይስ እኔ ከመሬት ተነስቼ በነጻ ካለገለገልኩሽ ማለቴ ነው?
‹‹አስጨነቅከኝ እኮ››
‹‹በቃ እንደወንድምሽ እይኝ...የቤተሠብ አንድ አካል እንደሆንኩ ቁጠሪ...ወይም ደግሞ ጥሩ የድሮ ጓደኛሽ እንደሆንኩ ..ብቻ እንደተመቸሽ ..ግን ልክፈልህ አትበይኝ፡፡››
በዚህን ጊዜ መኪናዬ ጋር ደርሼ ነበር..ከፍቼ ስገባ ወደበሩ ተጓዘችና ከፈተችልኝ። አንቀሳቀስኩና  ከግቢው ወጥቼ ቆምኩ ፡፡መጣችና አጎንብሳ በተከፈተው መስኮት አንገቷን አስግጋ...በፍፅም ፈገግታና በፍፁም ትህትና‹‹በጣም አመሠግናለሁ...ደህና እደር፡፡››አለችኝ፡፡
ተንጠራርተህ የሚንቀሳቀሱ ከንፈሮቾ ላይ ተጣበቅባቸው የሚል ስሜት ተናነቀኝ...እንደምንም እራሴን ተቆጣጥሬ  ‹‹ደህና እደሪልኝ …እነሚጣን ቸው አላልኳቸውም… ሳሚልኝ፡፡››
‹‹እሺ እስምልሀው፡፡››ብላ ቀና አለችና ከመኪናዋ ሁለት እርምጃ ወደኃላ ሸሸት በማለት ቆመች...ሌላ ነገር ቀባጥሬ ሳልዋረድ ብዬ ሞተሩን አስነሳሁና ተንቀሳቀስኩ….  በእስፖኪዬ እያየኋት ነው፡፡ በቆመችበት በፋዘት ሆና ሸኘችኝ...እኔ ደግሞ መላ እሷነቷን በልቤ ተሸክሜ ተሸበለልኩ።ለእሷ ለመስጠት የገዛውት እንቡጥ ፅጌረዳ አበባ አሁንም ኃላ ወንበር እንደተቀመጠ ነው፡፡ምን ብዬ በምን ድፍረት ልሰጣት ነበር የገዛሁት?ማሰቤ እራሱ በጣም አሳፈረኝ።

ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍404
#ትንግርት


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ትንግርት ያታሰረችበት ክፍል ሌሎች አራት ሴቶቸ አብረዋት ታስረዋል፡፡አንድ የ18 ዓመት ወጣት ...ሁለቱ ከ25-30 የሚገመት ዕድሜ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡ከሁለቱ አንደኛዋ ቀጫጫ ቢጤ ስትሆን ስትታይ የቢሮ ሰራተኛ ነገር ትመስላለች.. ሌላኛዋ ግን ደልደል ያለች የተንጨፈረረ ፀጉር ያላት ወንዳወንድ ነገር ነች …አራተኛዋ 4ዐ ዓመት የሚጠጋት ገዘፍ ያለች ሴትዬ ነች፡፡ከእሷና ከልጅ እግሯ ወጣት በስተቀር ሌሎቹ እስር ሲታሰሩ ዛሬ የመጀመሪያቸው እንዳልሆነ ከሁኔታቸው መገንዘብ ይቻላል፡፡

‹‹አቦ አትቆዝሙብን ...እስቲ ወሬ አምጡ ..እናውራ፡፡ ካለዛ የእስር ቤት ተባዬች ደማችንን ሲመጡን በዝምታ ምናዳምጣቸው ከሆነ ስቃዩ ከፍተኛ ነው ሚሆንብን..፡፡ወሬ ግን ማደንዘዣ ነው ..ቀልባችን ወደ ወሬው ከላክን እነሱ ደማችንን ብቻ ነው ሚመጡት፡፡ ካለዛ
ደማችንንም ቀልባቸንንም ምጥጥ ነው የሚያደርጉት፡፡›› ቀጫጫዋ ወጣት ተናገረች

‹‹ተስማምተናል..…እስቲ ከተማሪዋ እንጀምር ..ምን አጥፍተሸ ታሰርሽ?››

‹‹ምንም?›› አለች ፈራ ተባ እያለች፡፡

‹‹ባክሽ አትሽኮርመሚ.. ዝምብለውማ አምጥተው እዚህ አያጉሩሽም... የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነሽ አይደል?››ትልቋ ሴትዬ ጠየቀቻት፡፡

‹‹አዎ... ዋናው ግቢ ነው የምማረው..የሶስተኛ አመት ተማሪ ነኝ፡፡››

‹‹የየት ሀገር ልጅ ነሽ…?››

‹‹የደብረማርቆስ፡፡››

‹‹እሺ ምን ሰርተሸ ታሰርሽ?››

‹‹ፖሊሶቹ ጭፈራ ቤት ለሊት ይዘውኝ፡፡››

‹‹አቦ አትፎግሪ.…ፋራ አረግሺን እንዴ ?››አለቻት ወንዳወንዷ ወጣት፡፡

‹‹እሱማ ዕቃ ይዘውብኝ ነው ፡፡››

‹‹የምን ዕቃ?››

‹‹ሀሽሽ ሚሉትን ዕፅ….፡፡››

‹‹ሀሽሽ !!አይ የዘንድሮ ተማሪ ስትጦዢ ይዘውሽ ነዋ?››

‹‹ወላዲቷን እኔ ነክቼውም አላውቅ ..፡፡ጓደኞቼ ናቸው ቦርሳሽ ውስጥ አስቀምጪልን ፤ የስጦታ ዕቃ ነው አሉኝ፤እውነት መስሎኝ እሺ አልኳቸው፤ከዛ ስንዝናና ስንጠጣ ቆይተን ከሰከርን በኋላ ወደ ጓሮ ይዘውኝ ሄደው ቦርሳዬን ተቀብለው ከውስጡ ያስቀመጡትን ቆንጥረው ወስደው የተቀረውን እዛው በመመለስ የራሴኑ ቦርሳ ለእኔው ካስያዙኝ በኃላ እነሱ እየተቀባበሉ ሲያጬሱ በስካር መንፈስ ናውዤ ቢሆንም በድርጊታቸው ግራ ገብቶኝ ስገረምባቸው ድንገት ከየት እንደፈለቁ
ያላወቅናቸው ፖሊሶች መጥተው ከበቡን..ከዛም አፈሱንና ሲፈትሹን እነሱ ምንም አልተገኘባቸው እኔ ቦርሳ ውስጥ ግን ተገኘ‹‹ካመጣሽበት ጠቁሚ፡፡ ››ተብዬ ይሄው ታስሬያለሁ፡፡

‹‹እና ጓደኞችሽ ምን አሉ?››ትንግርት ጠየቀቻት፡፡

‹‹እንጃላቸው...ምናቀው ነገር የለም መሰለኝ ያሉት..ለዛም መሰለኝ የለቀቋቸው፡፡››

‹‹ታዲያ ምን ይሻልሻል?››

‹‹እንጃልኝ…እቤተሰቦቼ ከሰሙ በቃ ማጣፊያዬ ነው የሚያጥርብኝ... አባቴ ቀጥታ ይገድለኛል..፡፡››

‹‹ቆይ ያልገባኝ ፖሊሶቹ በዛ ሰዓት እንዴት ሊገኙ ቻሉ?›› ትንግርት ነች ግልፅ ስላልሆነላት የጠየቀችው፡፡

‹‹እሱማ ከመካከላችን ሜሪ የሚሏት የዱከም ልጅ በጣም የሚወዳትን ተማሪ ፍቅረኛዋን ችላ ብላ ትልቅ ሀብታም ሰውዬ ጋር ነበር ስትጨፍር ያመሸችው.. ልጁ መጥቶ አብራው ወደ ካምፓስ እንድትመለስ ሲለምናት ነበር..እሷ ግን አልሰማህም ነፍስያዬን ማስደሰት እፈልጋለሁ አለችው፤እያለቀሰና እየፎከረ ነበር ጥሏት የሄደው.....እሱ ይመስለኛል ለፖሊሶች የጠቆመው፡፡››

‹‹እናንተ ፖሊስ እጅ ስትወድቁ ሰውዬው አብሮችሁ ነበር?››

‹‹ነበር ግን ፖሊሶቹ ምንም አላሉትም አልፈተሸትምም..የሚያውት መሰለኝ… ሳስበው ሳስበው ዕፁን እራሱ ለእነሚሪ ያመጣላቸው እሱ ይመስለኛል፡››

‹‹በይ ነገ ይሄንን ሁሉ ለፖሊሶቹ በዝርዝር ንገሪያቸው..ሀሽሽ አለመጠቀምሽንም በምርመራ ማረጋገጥ የሚችሉ ይመስለኛል፡፡››
‹‹እስቲ እግዜር ቢረዳኝ እሞክራለሁ፡፡››ብላ መነፍረቅ ጀመረች፡ሁሉም አባበሏት..ስትረጋጋ ቀጣዩን ባለታሪክ ለማዳመጥ ተዘጋጁ፡፡ቀጣዪ ባለተራ በዕድሜ ከሁሉም አንጋፋ የሆነችው ሴትዬ ነበረች‹‹እሺ ያንቺስ ታሪክ?›› ቀጫጫዋ መጠየቅ ጀመረች፡፡

‹‹የእኔ እንኳን ከበድ ይላል..ከሁለት እስከ አምስት ዓመት ተፈርዶብኝ ወደ ወህኒ መውረዴ አይቀርም፡፡››

‹‹እንዴ !!!እራስሽ ወንጀለኛ እራስሽ ዳኛ ሆነሽ አረፍሺው ?ለማንኛውም እስኪ እንስማው?››

‹‹የባሌን እንትን የማስወገድ ሙከራ አድርጌ ነው፡፡››

‹‹እንትን ምንድነው?››ነገሩ ግራ ገብቷት ጣልቃ በመግባት ሳታስበው ጥያቄ የሰነዘረችው ትንግርት ነበረች፡፡

<< የሚመጠጠው ጀላቲ››አሾፈችባት ወንዳወንዷ፡፡

‹‹አልገባኝም?››

‹‹ባክሽ ሽሮ መብያውን ማለቷ ነው?››ቀጫጫዋ እስረኛ አስረዳቻት፡፡

‹‹በስመአብ ...!!!የባልሽን?››ተማሪዋ ጠየቀች... ሰቅጥጧት፡፡

ትንግርትም...የሴትዬዋ ጭካኔ አንዘርዝሯት‹‹ምነው አንደኛውኑ ብትገይው?››አለቻት፡፡
‹‹ጠላትን ለመበቀል ግድያ የመጨረሻው ቀሺሙ ዘዴ ነው?››መለሰች፡፡

‹‹እንዴት?››ግራ ገብቷት፡፡

‹‹ገደልኩት ማለት እኮ ገላገልኩት ማለት ነው ፤ከሞት በኃላ ፀፀት የለ.... መከራ የለ….ምን ይቀርበታል፡፡ ስለፅድቅና ኩነኔው እንደሆነ ማን እርግጠኛ መሆን ይችላል፡፡እንደውም እኔ ነኝ መከራውን የምቀበለው..እሱን የሰላም ዕንቅልፉ ወደሚያገኝበት ስፍራ ሸኝቼ እራሴን

ለዕድሜ ልክ የእስር ስቃይ አሳልፌ ሰጣለሁ..?ምን በወጣኝ፡፡እኔም እሰቃያለሁ እሱም በቁሙ እየኖረ ይሰቃይ...>>
‹‹ሰማንሽ ...እስቲ ያረግሺውን በዝርዝር አስረጂን?››

‹‹ባሌ ቀለም ቀቢ ነበረ፡፡ ከዛሬ ሁለት አመት
በፊት አንድ ፎቅ ሲቀባ ከሁለተኛ ፎቅ ላይ
መሰላል አንሸራቶት ይፈጠፈጥና የቀኝ እግሩ
ስብርብሩ ይወጣል ይታያችሁ.. እኔ እና ታናሽ
እህቴ በኪራይ ቤት እሱ በሚያመጣው ገቢ
ነበር የምንተዳደረው፡፡እሱ ስብርብሩ ወጥቶ
ቤት ሲቀር የሆነ ነገር ማድረግ የሚጠበቀው
ከእኔ ነው፡፡እራሳችንን መቀለብ ብቻ ሳይሆን
እሱንም አሳክሞ ማዳን የእኔ ኃላፊነት ስለነበር መጣር ጀመርኩ፤ብዙ ነገር ለመስራት ሞከርኩ… ሰው ቤት ፅዳት..ቀን ስራ
ያልሞከርኩት ነገር የለም ፡፡ግን ሁሉም ከልፋት
በስተቀር ለቤተሰቡ የሚበቃ ጠብ የሚል ገንዘብ ሊያስገኝልኝ አልቻለም፡፡ቀለባችንን ችዬ የቤት ኪራይ ከፍዬ ከዛ ተርፎኝ እሱን
ለማሳከም አቅም አነሰኝ…እግሩ ከህክምና እጦት የተነሳ የተነፋፋ ቆሰለ ..ትል ሁሉ ማፍራት ጀመረ፤ምን ላድርግ ?ተሳቀቅኩ፡፡ ሲቸግረኝ ሌላ ዘዴ ቀየስኩ፡፡››

‹‹ምን ዓይነት ዘዴ?››

‹‹የለሊት ስራ ... ፋብሪካ ውስጥ አገኘሁ ብዬ አስወራሁ?››

‹‹ሳታገኚ?››

‹‹ስራውንማ አግኝቼያሁ ...ግን ፋብሪካ ውስጥ አልነበረም፤ ሽርሙጥና ነበር ለመስራት የወሰንኩት፡፡››

ቀጫጫዋ በገረሜታ‹‹ባል እያለሽ?››አለቻት ፡፡

‹‹ባሌማ እኮ ….ዓይኔ እያየ የተሰባበረ እግሩ ከህክምና እጦት የተነሳ መትላት ጀመረ፤ምንበላው አጣን፣የቤት ኪራይ መክፈል አቃተን፣እህቴም ትምህርቷን ልታቋርጥ ጫፍ ደረሰች..እና ምን እንዳደርግ ትጠብቂያለሽ…?

አንዳንዴ ይህቺ አስቀያሚ ህይወት ሁሉንም በራፎች ትከረችምብሽና አዋራጅ እና አስቀያሚ የሆነውን ጭላንጭል የዕድል ቀዳዳ ብቻ ትተውልሻለች፡፡››
‹‹እሺ ቀጥይ ባክሽ፡፡››አለቻት ትንግርት ታሪኳ አጓጉቷት፡፡
👍609👏1😢1
‹‹ከዛ ለሊት ሽርሙጥናዬን እየሰራው ለአንድ አመት ቤቱን ለብቻዬ አስተዳደርኩ፡፡ ባሌንም ከአንድ አመት አስቸጋሪ ህክምና በኃላ እራሱን ችሎ ቆሞ መሄድ ጀመረ፤ትንሽ ሸንከል ቢልም ዳነ ፤ስራ መሞካከር ጀመረ፡፡.እኔም ቀስ በቀስ ሽርሙጥናውን አቆምኩ፡፡በዚህ ጊዜ ሁኔታዎች የተስተካከሉ ሲመስሉ ሌላ ችግር ተከሰተ… እህቴ አረገዘች…፡።

ስጠይቃት ካንድ የትምህርት ቤት ጓደኛዋ ከሆነ ጎረምሳ እንደሆነ እና አሁን ጥሏት እንደጠፋ አረዳቺኝ..፡፡ምን ላድርግ ብቸኛ እህቴ ነች..የእናት እና አባቴ አደራ ነች..አንጀቴ ቢቃጠልም ቻልኩት ፤ጭራሽ እሷን አፅናና
አባብል ጀመር፤ምክንያቱም በብስጭት እራሷ ላይ የሆነ እርምጃ ትወስድና ጉድ ታደርገኛለች ብዬ ሰለሰጋሁ፡፡..በዛ ላይ እኔ ልጅ የለኝም ፡፡ ከዚህ ባለቤቴ ጋር እንኳን ባሳለፍናቸው 5 የትዳር አመታት ልጅ ልወልድለት አልቻልኩም ፡፡መሀን ሳልሆን አልቀርም..ታዲያ እግዚያብሄር በእህቴ በኩል ልጅ ሊሰጠኝ ፈልጐ እንደሆነ ብዬ ሁሉንም በፀጋ ተቀብዬ የመውለጃ ቀኗን በጉጉት እየጠበቅኩ ሳለው ከሶስት ቀን በፊት ጉዴን ሰማሁ፡፡››

‹‹እንዴት?››

<<የሆነ የጓደኛዬ አባት ሞቶ ስለነበር አዳር ብዬ ባለቤቴንም እርጉዟን እህቴንም ተሰናቼ ከቤት ወጣሁ፤ለቅሶ ቤት ስደርስ ግን ጠጠር መጣያ አልነበርም..ድንኳኑ በሰው ተጨናንቋል፡፡በኃላ ሀሳቤን ለወጥኩና አስከ 5 ሰዓት ብቻ አመሻሽቼ ወደ ቤት ተመለስኩ፡፡ስደርስ መብራቱ እንደበራ ነው..ወደ በራፉ ተጠጋሁ… የባሌ እና የታናሽ እህቴ ተንከትካች ድምፅ በጆሮዬ ተሰነቀረ፡፡

‹‹እንዴት እስከ እዚህ ሰዓት ድረስ ሳይተኙ?››በአዕምሮዬ የተሰራጨ ጥያቄ ነበር፡፡ የሆነ ነገር ሸከከኝና ላንኳኳ የዘረጋሁትን እጄን አንከርፍፌ ጆሮዬን አስቀደምኩ፡፡

‹‹የእኔ ቆንጆ ልጃችን መቼ ነው የሚወለደው?››የባሌ ድምፅ ነው፡፡

‹‹አይዞህ ዓይንህን በዓይንህ ለማየት አንድ ወር ብቻ ነው መጠበቅ የሚገባህ፡››

‹‹አቤት አንቺ እኮ ነፍስ ነሽ ....እህትሽ በ5 ዓመት ያልሰጠችኝን ፀጋ አንቺ በአንድ አመት ፍቅር አሻርሺኝ፡፡››ሲላት ሰማሁ፡፡

‹‹አንተ እኮ አሳሳች ሴይጣን ነህ ..እህቴ ላይ ግፍ እንድሰራባት አደረግከኝ፡፡››በ15 ዓመት የምታንሰኝ የታናሽ እህቴ ድምፅ ነው፡፡

‹‹ምን ግፍ አለው… ?ድንገት ተፋቀርን በቃ፡፡››

‹‹በመጀመሪያማ ተፋቅረን አይደለም...ምነው እረሳኸው እንዴ..? የጀመርነው አስገድደህ
ደፍረኸኝ ነው፡፡››አለችው፡፡

‹‹ከዛ በኃላ ግን ፈልገሽ ነው?››

‹‹እሱማ ስትደጋግመው ጣመኝ ምን ላድርግ..?እህቴ ብታሳዝነኝም... ማቆም ግን አልቻልኩም፡፡››

‹‹እንደእኔ እንደኔማ ብንጋባ ሁሉ ደስ ይለኛል..አሁን እኮ እንደምታይው ድኜያለሁ ስራም ጀምሬያለሁ፡፡ የእህትሽ እርዳታ አያስፈልገንም..እውነቱን እንንገራት እና የራሳችንን ህይወት እንቀጥል፡፡››ሲላት ቀጥታ በጆሮዎቼ ሰማሁ ፤.መቼስ ጆሮ ማይሰማው የለም፡፡

‹‹ያንንማ…..ፍፅም አታስብ፡፡ ልጅህን እወልድልሀለው… ሶሰት ወር አጠባልሀለው፤ ከዛ ለአንተ እና ለእህቴ አስረክቤ አገር ጥዬ ጠፋለሁ…፡፡ለእህቴ ከዚህ በላይ ክህደት አይገባትም፤ደግሞ እወቅ እህቴም ብቻ ሳትሆን እናቴም ነች፡፡››
በወቅቱ ከዛ በላይ መስማት አቅሙ አልነበረኝም..ወደ ኋላዬ ተመለስኩ…ድሮ ወደ ምሰራበት ሆቴል በመሄድ ስጠጣ አንግቼ እዛው ውዬ ሲመሽ ወደቤት መጣሁ፡፡ሁለቱም የት እንደቆየሁ ቢጠይቁኝም የረባ መልስ አልመለስኩላቸውም፡፡

ከዛ እህቴን ምክንያት ፈጥሬ አንድ ጓደኛዬ ጋር ሄዳ እንድትድር አደረግኩ፤ሥጋ ገዝቼ ችክን ያለች ወጥ ሰራሁና ቆንጆ እራት አበለሁት፡፡ አረቄም ገዝቼ ነበር ...በላይ በላዩ እንዲጠጣ አስገደድኩት፡፡ ሰውነቴን ታጠቤ ሽቶ በላዬ አርከፍክፌ ወደመኝታ ይዤው ሄድኩ፤ልክ እንደተገናኘን ጊዜ እንደነበረው እስኪያለከልክ ድረስ ሰጠሁት..ምክንያቱም የመጨረሻው ስለሆነ ይገባዋል ብዬ ነው እንደዛ ያደረግኩት፡፡ ከዛ በወሲብም በስካርም ተዝለፍለፎ ሲዘረርልኝ...ስዬና ሞርጄ ባዘጋጀሁት ቢላዋ ያንን የቅንዝሩን መሳሪያ ገዘገዝኩለት፡፡››

‹‹ግን ቁርጥ ቁርጥ አደረግሺው?››

‹‹አይ ግማሽ እንደደረስኩ ሆዴ ባባ መሰለኝ ተውኩት..ምንም ቢሆን የበላ አንጀት ሆኖብኝ መሰለኝ፡፡››

‹‹ታዲያ አሁን እንዴት ሆነ?››

‹‹ምን አውቃለሁ በወቅቱ ጮኸ ..አጓራ ..ወሬኛ ጐረቤቶች ተሰበሰቡ እና እሱን ወደ ሀኪም ቤት እኔን ወደእዚህ አምጥተው ወረወሩኝ…..ግን ሙሉ በሙሉ ስላልተለያየ ሊመልሱለት እየሞከሩ ነው አሉ፡፡››

‹‹እንዲህ በማድረግሽ ግን ተበቅዬዋለሁ ብለሽ ታስቢያለሽ?››ትንግርት ጠየቀቻት፡፡

‹‹መቼስ ከመግደል ይሻላል..ማለቴ ብገድለው በቃ ተገላገለ..አሁን ግን የእንትኑን ጠባሳ ወይም ከዛ እየተነሳ የሚጠዘጥዘውን የህመም ስሜት በተሰማው ቁጥር በእኔ ላይ የሰራውም ግፍ አብሮ ይታሰበዋል..ቅጣቱ ለአመታት ህሊናው ሲቆጠቁጠው ይኖራል፡፡ >>
‹‹እኔ ግን እንደዛ አይነት በቀል ውጤታማ አይመስለኝም >>አለች ቀጫጫዋ እስረኛ፡፡

‹‹ታዲያ ንገሪና..… አንቺ ብትሆኚ ምን ታርጊያለሽ?››ወንዳወንዷ ጠየቀቻት፡፡

‹‹እህቴን ከባሌ ጋር አጋባና እኔ ከመካከላቸው እወጣለሁ...ያ ሁለቱንም ከፍተኛ ፀፀት ላይ የሚጥል...ከስህተታቸው እንዲማሩ እና እንዲለወጡ..ቀሪ ህይወታቸውን መልካም ሰው እንዲሆኑ የሚያደርግ እርምጃ ይመስለኛል፡፡አሁን አንቺ ባልሽንም እህትሽንም አጥተሸ እስር ቤት ገባሽ…ባልሽ ዕቃውንም አንቺንም አጣ..እህትሽም እንደዛው ሁለታችሁንም አጣች….አየሽ እነሱ አንድ ስህተት አንቺ ላይ ሰሩ ...አንቺ ደግሞ ሁሉንም ነገር ድብቅልቅ የሚያደርግ አውዳሚ ስህተት ሰራሽ፡፡

ባልሽ ከአሁን ወዲህ መዳን ቢችል እንኳን ጠቅላላ ሴቶች ላይ ምን አይነት ጥላቻ እንደሚያድርበት አስበሽዋል.?.እንኳን እሱ
ቀጥታ ተጠቂው ይቅርና ይህንን ታሪክ የሰማ የአዳም ልጅ ጠቅላላ እንዴት የሴትን ጭካኔ እንደሚያራግብበት አስቢው፡፡እንደእኔ ምልከታ በደል አድርሶብናል ብለን የምናስበውን ሰው በመግደል ወይም እሱና የእሱ የሆኑትን ነገሮች ላይ ጉዳት በማድረስ መበቀል ቀሺምና እርካታ የሌለው ወይም ጥም የማይቆርጥ በቀል ነው፡፡››

‹‹እስቲ እንደአንቺ ጥም ሚቆርጠው በቀል ምን አይነት ነው?››ትንግርት ነች የልጅቷን ፍልስፍና ይበልጥ ለመረዳት የጠየቀቻት፡፡
‹‹እንድሞት አስባ ምግቤን የመረዘችብኝን ጎረቤቴን ..አንድ ቀን ቀን ጥሏት ታማ በህይወት እና በሞት መካከል ወድቃ ባገኘኋት ጊዜ ወደ ህይወት የሚመልሳትን የመጨረሻውን ፈዋሽ መድሀኒት ባለኝ ጥሪት ሁሉ ገዝቼ በመስጠት እንድትድን በማድረግ ነው ልበቀላት የምፈልገው፡፡እንደዛ አይነት በቀል ነው የእኔን ጥም የሚቆርጥልኝ፤ከበዳዬ በልጬ በመገኘት..፡፡››

ሁሉም ፀጥ አለ፡፡ ትንግርትም እሷ በደለችኝ.. ከዳችኝ የምትላት ዶ/ር ሶፊያ ላይ የወሰደችውንና ለመውሰድ ያሰበችውን የበቀል መንገድ ዳግም መከለስ እንዳለባት በድንገት ከእስርቤት ጓደኞቿ በዚህች ጠባብ ክፍል በዚህ ጨለማ ውስጥ የሰማችውን ታሪክ ለአዕምሮዋ መልእክት አስተላለፈላት፡፡‹‹መማር ለፈለገ ለካ ሲዖል ውስጥም ቢሆን ዕውቀት ይገኛል››በማለት አሰበች…፡፡
‹የተቀራችሁትን ታሪክ ነገ እንደበርበታለን… አሁን እንተኛ›› ተባባሉ፡፡ሁሉም በያሉበት አዕምሮአቸውን በሀሳብ ሰውነታቸው በተባዬቹ እየተቦጠቦጠ ቢሆንም ለእንቅልፍ ተመቻቹ፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች አረ #subscribe እያደረጋቹ 5 ሰው ብዬ 3ሰው አድርጎ ቆመ እስቲ አሁንም #subscribe እያደረጋቹ

#Share and #subscribe my #YouTube 
👍10017👏3🔥1😁1
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👏14👍1👎1
አትሮኖስ pinned «#ትንግርት ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_ስድስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ትንግርት ያታሰረችበት ክፍል ሌሎች አራት ሴቶቸ አብረዋት ታስረዋል፡፡አንድ የ18 ዓመት ወጣት ...ሁለቱ ከ25-30 የሚገመት ዕድሜ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡ከሁለቱ አንደኛዋ ቀጫጫ ቢጤ ስትሆን ስትታይ የቢሮ ሰራተኛ ነገር ትመስላለች.. ሌላኛዋ ግን ደልደል ያለች የተንጨፈረረ ፀጉር ያላት ወንዳወንድ ነገር ነች …አራተኛዋ 4ዐ ዓመት የሚጠጋት…»
እባክሽ አትሂጂ…..
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-ሶስት

ዋና ስራዬ ስለእሷ ማሰብ ሆነ።ከብዙ ድካም በኃላ ማታ አልጋዬ ላይ ተንጋልዬ በእንቅልፍ እጦት እየተንከባለልኩ  አዲስ አይነት ሰይጣናዊ ሀሳቦች ማሰብ ሁሉ ጀመርኩ።‹‹ሰውዬው ማለት ባሏ ምን አለ ቢሞት፡፡ሞት ማለት…በህይወት ለቆየንባቸው ለእያንዳንዷ ቀን የምንከፍለው ውዝፍ ዕዳ ነው፤ታዲያ እሱስ ብዙ ወለድ ሳይወልድበት ምን አለ ብድሩን አሁኑኑ ቢከፍልና ከህይወትም ከእኔ ፊትም ገለል ቢል?››አሁን እስኪ ከእንደእኔ አይነት ሰውን ለማዳን አመታትን ለፍቶ ከተማረ እና መሀላ ገብቶ ወደስራ ከተሠማራ ዶ/ር የሠውን ሞት ለዛውም እራሱ የሚያክመውን ሰው ሞት መመኘት  የጤንነት ነው?።እርግጥ ሰውዬው ይዋል ይደር እንጂ የመሞት  እድሉ ከሰማንያ ፐርሰንት ዘለግ ያለ ነው።  (ይሄ አባባል  ትክክል አይደለም ፤ለመዳን ያለው ተስፋ 20 ፐርሰንት ነው ተብሎ ቢገለፅ ይሻላል)ምክንያቱም የማንኛውም ሰው የእኔንም ጨምሮ የመሞት እድላችን መቶ ፐርሰንት ነው...ታመምንም አልታመምንም እውነታው ይሄ ነው...ከእሱ ቀድሜ እኔም ልሞት እችላለሁ፡፡ ለማንኛውም ወደ ታማሚው ስመለስ መቼ ነው ሊሞት የሚችለው ?የዛሬ አመት ?የዛሬ ሁለት አመት...?በሁኔታዋች ላይ የሚወሰን ነው?እና እኔ ያን ሁሉ ለመጠበቅ የሚያስችል ትእግስት አለኝ?አይመስለኝም።ከሞተ በኃላስ እሷን የራሴ ለማድረግ ያለኝ እድል ምን ያህል ነው?ምንም ብርሀን አይታየኝ አይደለም ፡፡ቢሆንም ግን ተስፋ የመቁረጥ ምንም አይነት ሀሰብ የለኝም።ሀሳቤን ሳልጨርስ ስልኬ አንቃጨለ  ...በዚህ ሰዓት ማን ነው? ተንጠራራሁና አየሁት...የውጭ ቁጥር ነው። እየተጠራጠርኩ አነሳሁት...፡፡
‹‹አንተ ሰውዬ ለመሆኑ በህይወት አለህ?››
ተንዘርዛሪ ቃጭል ድምፅ...አልተሳሳትኩም እርግበ ነች።እርግበ ማለት የረጅም ጊዜ ጓደኛዬና የሶስት አመት ፍቅረኛዬ የነበረች ሴት ነች።የተዋወቅነው ሁለታችንም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምና ለማጥናት እንደተመደብን ፍሬሽማን ላይ ሆነን ነበር...ለመመረቅ አንድ አመት ሲቀረን ጀምሮ የጠበቀ የጓደኝነት ቀረቤታችንን ወደ ፍቅር ለወጥነው ።አራት አመት በስራ ካሳለፍን በኃላ እኔ አዲስአበባ ሁለተኛ ዲግሪዬን መስራት ስጀምር እሷ ደግሞ የውጭ እድል አግኝታ ሁለተኛ ዲግሪዋን በስነ-ልቦና ልትሰራ ኖሮዌይ ሄደች።እርግጥ ለእኔም ችምር በራሷ ጥረት ተሯሩጣና ተፃፅፋ አብሬያት በመሄድ ውጭ የምማርበትን እድል አመቻችታልኝ ነበር፡፡እኔ ግን ግግም አልኩባት፡፡‹‹እናቴንና አሀገሬን ጥዬ አልሄድም፡፡››የሚል አቋም ያዝኩ፡፡ብትለምነኝ ብታስለምነኝ እሺ አላልኩም፡፡ከዛ የራስህ ጉዳይ ብላ በከፊል ኩርፊያና በከፊል ንዴት ጥላኝ ሄደች፡፡ትምህርቷን እየተማረች ባለችባቸው ለሁለት አመታት ግንኙነታችን በስልክና በቪዲዬ ኮል ቢሆንም   በተስፋ የተሞላና በናፍቆት የታጠረ ነበር፡፡ከተመረቀች በኃላ በገዛ ውሳኔዋ ቆይታዋን ስታራዝም ግን ጭቅጭቆች በመሀከላችን መፈጠረ ጀመሩ...እዛ ካሉ አንዳንድ ጓደኞቼም የምሰማቸው ወሬዋች በወደፊታችን ተስፋ እንዳደርግ የሚያበረታቱ ሆነው አላገኘኋቸውም እና ቀስ በቀስ መደዋወሉን እየቀነስን በቆይታ ማለት ከስድስት ወር በፊት ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በማቋረጥ ከስልኬ ውስጥ ሲሜን አውጥቼ ጣልኩና አዲስ ቁጥር ያዝኩ።
እርግበ ኑግ ታውቃላችሁ? ልክ እንደዛ ወዙ ችፍ ያለ እንደውም  እስፕረይ የተነፋበት የሚመስል የሚያብረቀርቅ አይነት ወዛም መልክ፣  ከዋክብት  የመሰሉ ግዙፍና ጉልህ ተንከባላይ አይኖች ያሏት እንቁላል መሠል ኦቨል የፊት ቅርፅ ከእሱ ጋር በሚቃረን መልኩ ቀጭን ቅንጥስ የምትል የሚመስል ሰንደቅ መሳይ  ቁመት ያላት  ወጣት ነች።የእኔ ብቻ ሳይሆን የብዙ ወንዶች ምኞት ናት።ግን የተረጋጋ መንፈስ የላትም።ሁሌ ተቅበዝባዠና እራሷ ተሸብራ ሌላውን የምታሸብር አይነት ነች።ሁሉንም ነገር በአንዴ የራሷ ለማድረግ የምትጥር መኪናውንም፣ ቤቱንም፣ድርጅቱንም ለምን በአንዴ ላገኝ አልቻልኩም ባይ አግበስባሽ ነገር ነች፡፡ልክ እንደስሟ እርግብ ነች..ሁሌ ለመብረር ዝግጁ ሆና ክንፎቾን ስታማታ ነው የምታገኟት።ወይንም እኔ እንደዛ እንደሆነች ነው የማስበው፡፡እኔ ደግሞ ነገሮች ሂደታቸውን ጠብቀው ተግባራዊ እንዲሆኑ የምመኝ ነኝ። በዚህ ክፍተት የተነሳ በጣም ብወዳትም የግድ መቁረጥ እንዳለብኝ ወሰንኩና አደረኩት...እንግዲህ ግንኙነታችን ሙሉ በሙሉ  ከተቋረጠ ከአምስት ወይም ከስድስት ወራት በኃላ መደወሏ ነው።
‹‹እሺ እርግበ…እንዴት ነሽ?››
‹‹እራስህን ብትሰውርም...አገኘሁህ››ንግግሯ የፉከራ ወዘና ያለው ነው፡፡
‹‹ጎበዝ ነሽ...ግን ስልኬን ከማን አገኘሽ?››
‹‹እናትህ እንደአንተ አይደለችም...ሰላም ልላት ደውዬ ነበር ...ሰጠችኝ፡፡››
‹‹ጥሩ...ሁሉ ነገር ሰላም ነው አይደል?››
‹‹አዎ በጣም ሰላም ነው...ልመጣ መሆኑን ልነግርህ ነው፡፡››
‹‹ልመጣ...መቼ?...እንዴት?››ድንግርግሬ ወጣ፡፡
‹‹አረ ተረጋጋ ..በደስታ ልብህ ቀጥ እንዳትል››መመፃደቋን ቀጠለች።
‹‹ቀልድን ተይና ....ማውራት የፈለግሽውን አውሪ፡፡››
‹‹አትቆጣአ.. አሁን ምን የሚያስቆጣ ነገር ተናገርኩ፡፡ኤኒዌይ ከሶስት ቀን በኃላ ሸገር ነኝ።ኤግዛክት ሰዓቱን በሚሴጅ ልክልሀለው፡፡››
‹‹ምን እንዲያደርግልኝ?››ብልጭ አለብኝና ጠየቅኳት፡፡
‹‹እንዴ ፍቅር...እንድትቀበለኝ ነዋ...ሌላ ለማንም ሰው አልደወልኩም...፡፡››
‹‹አልገባኝም፡፡››
‹‹በቃ ከቻልኩ ነገ ደውልልሀለው...አሁን መሄድ አለብኝ።››ስልኩ ተቋረጠ፡፡
አሁን ምን ላደርግ ነው? የተበጠሰውን ፍቅር  እቀጥላለሁ? ከቀጠልኩ በኃላስ የልዕልተ ጉዳይስ?ለገዛ አእምሮዬ ያቀረብኩለት ጥያቄ ነው።‹‹የልዕልተ ጉዳይ ምን?››አእምሮዬ መልሶ ጠየቀኝ።በህይወቴ እንዲህ ተወዛግቤና ግራ ገብቶኝ አያውቅም። ሁለቱን ሴቶች በምናቤ ጎን ለጎን ሳልኳቸውና ለማወዳደር ሞከርኩ፡፡ ቅንጥስጥስ ያለች ዘናጭ ፤ ጋዋን የለበሰችና ኮንፊደንሶ ሰማይ ላይ የተንጠለጠለው እርግበ..በሌላው ጎን ደግሞ ዙሪያዋን በሶስት ልጆች የተከበበችው አንገቷ ተሰብሮ አይኖቾ አልጋ ላይ የተኛው ባሏ ላይ የተሰካው እና እንደነገሩ የለበሰችውን ልዕልት...፡፡
በፈጣሪ ልቤ ሄዶ እዚች ሚስኪንና ጣጣ-ብዙ የሆነች ሴት ላይ ነው የተጣበቀው.፡፡ታዲያ አሁን እኔ ጤነኛ ነኝ?... አይመስለኝም፡፡ በህክምና የማይድን አይነት በሽታ መጋኛ አይነት ነገር ሳያጠናግረኝ አይቀርም፡፡እንደምንም ሊነጋጋ ሲል እንቅልፌ መጣ።


ይቀጥላል...

ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍5410👎1🔥1
#ትንግርት


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ከ8 ሰዓት እራስን የመሳት ሂደት በኃላ ዶ/ር ሶፊያ ስትነቃ ከአንደበቷ ሾልኮ የወጣው የመጀመሪ ቃል <<ትንግርት››የሚል ነበር፡፡ በወቅቱ አጠገቧ የነበረው ታዲዬስ ነበር፡፡ ግንባሯ በቀኝ በኩል በከፊል በፋሻ ተሸፍኗል፡፡ እንደምንም ተረጋግታ ያለችበትን ሁኔታ አጣራችና በደከመ ድምፅ << ታዲ >> ብላ ተጣራች ፡፡

‹‹አቤት…ምን ፈለግሽ?››

‹‹ትን..ግር ትስ?››

‹‹ሰላም ነች..አንቺ እራስሽን አረጋጊ፡።››

‹‹ንገረኝ ..የት ነው ያለችው..?ጥራልኝ በናትህ..ላገኛት እፈልጋለው፡፡››

‹‹አሁን እኮ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ነው..ነገ ታገኚያታለሽ››

‹‹አሁን ነው የምፈልጋት.. ታዲ በፈጠረህ ደውልላት፡፡››

‹‹ሞባይል ቁጥሯ የለኝም፡፡››

‹‹እኔ ሞባይል ውስጥ አለ፡፡››

ሊነግራት ባይፈልግም ስላስጨነቀችው ምንም ማድረግ አልቻለም ‹‹ታስራለች፡፡››አላት ፡፡

‹‹ወይኔ በጌታ ..!!!ማን አሰራ..ት?››አለች... ከተኛችበት ለመነሳት ብትጣጣርም ተራራ በጭንቅላተቷ የተሸከመች ይመስል የገዛ ራሷን ማነቃነቅ እንኳን አልተቻላትም፡፡

‹‹ህግ ነዋ ያሰራት...ልትገልሽ ሁሉ ትችል ነበር.::>>

‹‹ብትገድለኝም ይገባኛል..በፍፅም መታሰር የለባትም፡፡››

‹‹እሱ ያንቺ ፍላጎት ሊሆን ይችላል…ህግ ደግሞ እንደዛ አይልም፡፡››

‹‹ወይኔ ታዲ..አሁን ምን ይሻለናል?››

‹‹ስለምኑ?››

‹‹እንድትታሰር አልፈልግም፡፡››አለችው ደግማ፡፡

‹‹እንግዲ ሲነጋ የሚሆነውን እናያላን..ክስ ልትመሰርቺባት ካልፈለግሽ ምን አልባት በሽምግልና እንጨርሳለን ብለን ልናስፈታት እንችል ይሆናል፤አሁን ግን አንቺ ገና አላገገምሽም አረፍ በይ ፡፡››

‹‹ታዲ ...አንተ ግን ለምን ወደ ቤት ሳትሄድ…? ልጆችህስ?››

‹‹እንዲህ ሆነሽ እንዴት ጥዬሽ እሄዳለሁ…? ለልጆቹም ደውዬ ነግሬያቸዋለው፤ በጣም ነው ያዘኑት ፡፡ቶሎ እንድታገግሚ መልካም ምኞታቸው እንዳደርስላቸው ጠይቀውኛል፡፡ በገዛ እንግዳ እንዲህ በመሆንሽ አዝናለሁ፡፡››

‹‹ፍፅም ማዘን የለብህም...ይሄ የማንም ስህተት አይደለም፤ ለማንኛውም አብረኸኝ
ስለሆንክ ደስ ብሎኛል... አመሰግናለሁ፡፡››አለችውና አይኖቿን በድካም ከደነቻቸው.... እሱም የጀመረውን መጽሀፍ ማንበቡን ቀጠለ፡፡

ከለሊቱ 11 ሰአት ላይ ፎዚያ ተነስታ እየለባበሰች ሳለ ከውጭ የመኪና ጡሩንባ ጩኸት ሰማች... በጣም ነው የደነገጠችው፡፡ ‹‹በዚህን ሰዓት ማን ነው የመጠው..?››ሰውነቷ ሁሉ ተንቀጠቀጠባት፡፡‹‹የምን መርዶ ይዘውብኝ መጡ...?::>>

የመኝታ ቤቷን መስኮት ከፍታ ወደውጩ ስታማትር ዘበኛው የውጩን በር እየከፈተ ነበር፡፡ከዛ መኪናዋ ወደ ውስጥ ዘልቃ ገባች .. የሰሎሞን መኪና ነች፡፡ሮጣ ወደ ውጭ ወጣች፡፡እሱ ሞተሩን አጥፍቶ ከመኪናው ከመውረዱ በፊት እሷ ስሩ ደርሳ ‹‹ምን ተፈጠረ…? ምን ሆንክ..?ኤዲስ ደህና ነች…?››

‹‹አረ ተረጋጊ .…ሁሉም ሰላም ነው፡፡››

‹‹ታዲያ ምነው በዚህን ሰዓት?››

‹‹አብሬሽ ሀዋሳ ልሄድ ነው፡፡››

«ለምን?»

‹‹ለሽርሽር፡፡››አሾፈባት፡፡

‹‹ማለቴ ማን ነገረህ?››

‹‹አንቺ ብትደብቂኝም ሁሴን ደወለልኝ..ይገርማል ሀገር ውስጥ የተሰራ ታሪክ በአሜሪካ ዞሮ ስሰማው››

‹‹እኔ እኮ ኤደን አሟታል ስትለኝ ላስጨንቅህ ስላልፈለኩ ነው፡፡››

‹‹ቢሆንም መስማት ነበረብኝ..አሁን በይ ተዘጋጂና እንሂድ፡፡››

‹‹እሺ ጨርሻለሁ ...አምስት ደቂቃ ብቻ፡፡››አለችውና ወደ ውስጥ ተመልሳ ገባች፡፡

ዝዋይ ሲደርሱ ከጥዋቱ 1፡4ዐ ነበር፡፡‹‹ቁርስ እንሞክር እንዴ?››አላት ሰሎሞን፡፡

‹‹ኧረ ገና ጥዋት ነው… እንቀጥል፡፡›› አለችው..ተስማማና ነዳው፡፡

‹‹ግን ኤደን ታማ እያለ ጥለሀት ስትመጣ አልከፋትም?›› ጠየቀችው... ፎዚያ ፡፡

‹‹ከፍቷታል... ግን ምንም ማድረግ አልችልም፡፡ ሁሴን ሂድና እያት ብሎኝ ምክንያት ፈጥሬ እምቢ ልለው አልችልም፡፡ በዛ ላይ እኔ ኖርኩም አልኖርኩም ለውጥ የለውም፤ቤተሰቦቿ ዙሪያዋን ከበዋታል፡፡››

‹‹ቢሆንም.... ቤተሰብ ሌላ ባለቤት ሌላ፡፡››

‹‹ጉረኛ ...ስለባል ደግሞ ምን ታውቂያለሽ?››

‹‹ለምን አላውቅም፤ ስለባለትዳሮች ለማወቅ እኮ የግድ ባለትዳር መሆን የለብኝም፡፡››

‹‹መስሎሻል.. እኛም ሁለት ጊዜ ያገባነው እንኳን አሁንም ስለትዳር ምንም አልገባንም፡፡››

‹‹ምን ማለት ነው?››

‹‹ባክሽ ሴቶችን ማወቅ በጣም ነው እየከበደኝ ያለው፡፡››

‹‹ይህቺ ነገር..!!!!ምነው ከኤደን ጋር ሰላም አይደላችሁም እንዴ?››

‹‹እኔ እንጃ ባክሽ.. ከባለፉት ሁለት ወራቶች ወዲህ ንጭንጯን ልቋቋመው እየከበደኝ ነው....?»

‹‹መነሻውን አታውቅም? >>

‹‹ውሀ ቀጠነ ነው…ግን ቅዳሜ እና ዕሁድን ከልጆቼ ጋር ማሳለፍ ከጀመርኩ ወዲህ ይመስለኛል ነገሩ የጀመረው፡፡››

‹‹ከልጆቼ ጋር ስትል..ወደ ድሮ ሚስትህ እየሄድክ ማለት ነው?››

‹‹ኖ..ኖ ቅዳሜ እኔ ጋር ይመጣሉ. አብረውኝ አድረው እሁድ ማታ እመልሳቸዋለሁ.. ከእናታቸው ጋር ምንም የሚያገናኘኝ ነገር የለም፡፡››

‹‹ታዲያ እሷን ምኑ ነው የደበራት?››

‹‹እኔም ያልገባኝ እሱ ነው፡፡እንግዲህ መጀመሪያም ልጆች እንዳሉኝ እያወቀች ነው ያገባችኝ...ከሚስቴ ተፋተው እንጂ ከልጆቼ አልተፋታውም፤ ምኑ ቅር እያሰኛት አንደሆነ አልገባኝም፡፡››

‹‹ቆይ ያልገባኝ...ልጆቹን መተው የሚያሳልፉት አብረዋችሁ ቤት አይደል..?››

‹‹በፊት ነበር…በኃላ ግን ቅዳሜና እሁድን መጥተው ከእኛ ጋር ሲያሳልፉ ቅር እያላት ፊቷን እያጠቆረችባቸው ስታሳቅቃቸው ..ነገርኳትና ውጭ ማለቴ ሶደሬ ፤ላንጋኖ ካልተቻለም ደግሞ እዛው አዲስ አበባ ሆቴል አብሬያቸው ማሳለፍ ጀመርኩ፡፡

በነገራችን ላይ በሳምንት ሁለቱን ቀን ከልጆቼ ጋር ማሳለፍ እንዳለብኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳሰበኝ ሁሴን ነው ፤ ከመሄዱ በፊት ሊሰናታቸው ቤት ሄዶ በናፍቆት በጣም ተጎድተውና ተሳቀው ስላገኛቸው እኔም ኤደንም ባለንበት ሁኔታውን በማስረዳት አሳምኖን ሄደ፡፡እኔም ሁኔታውን መለስ ብዬ ሳስበው በጣም ነበር የፀፀተኝ ‹‹እንዴት ልጆቼን ችላ ልል እንደቻልኩ ድንቅ ነበር ያለኝ….በአጠቃላይ ሁኔታው ሁሉ እንደዛ ነው እልሻለው፡፡››

‹‹አይ ቢሆንም ተነጋገሩበት…እሷም ነገሩን መቀበል መቻል አለባት፡፡ ቅሬታም ካላት በግልፅ ትንገርህና መፍትሄ ፈልጉለት፡፡››

‹‹እስቲ እሞክራለሁ....ምን አልባት የራሷን ልጅ ስትወልድ ልጅ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በቅጡ ስለሚገባት ያን ጊዜ ትረዳኛለች ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡››

‹‹እንድትረዳህ እመኝልሀለው...ካለበለዚያ ስታገባ ሰትትፈታ መኖርህ ነው፡፡››ብላ አሾፈችበት፡፡

‹‹እጣ ክፍሌ ከሆነ ምን አደርጋለሁ፡፡››

3 ሰዓት ሀዋሳ ደረሱ፡፡ኤልያስ ሲጠብቃቸው ስለነበረ ወዲያው ወደ ትንግርት ይዞቸው ሄደ፡፡

‹‹ተራማጆቹ ፀሀፊዎች በፖለቲካ በሚታሰሩበት ዘመን አንቺ በፈንካችነት ትቀላቀያቸዋለሽ..? ምነው ምነው?››አላት ሰሎሞን ገና ከፖሊሶቹ ፍቃድ አግኝተው ፊት ለፊት እንደተገናኙ፡፡

‹‹ምን ይደረግ ....ይህቺ ሀገር ፀሀፊ ሳይሆን ጀግና ነው ያጣችው ብዬ ነዋ!!››ብላ መለሰችለት፡፡

የሚነጋገሩት ፖሊሶቹ ጆሮ ይደርሳል... አይደርስም የሚለውን ለማጣራት ግራ ቀኙን ተገለማመጠ

‹‹ምነው ፈራህ እንዴ?››አለችው፡፡

‹‹ልጄ ለምን አልፈራ..በስህተት እንኳን አንድ ቀን እስር ቤት ባድር ፈንድቼ የምሞት ነው የሚመስለኝ፡፡››

‹‹ለመሆኑ እንዴት ነሽ…?ምን አሉሽ?›› አለቻት ፎዚያ በጭንቀትና በሀዘኔታ፡፡
👍819😁4
‹‹ያው ዛሬ እሁድ ነው ....ማንም ምንም አይለኝም፡፡››

‹‹እንዴ ዛሬም እዚህ ልታድሪ?››ፎዚያ ነች፡፡

‹‹እዚሁ ልሰነብትም እኮ እችላለሁ ..አይዞሽ የምታስቢውን ያህል አስፈሪ አይደለም..ለማንኛውም ሁኔታዎች የሚታወቁት ነገ ነው፡፡››

‹‹በቃ እስቲ ተሯሩጠን የሆነ ነገር እናደርጋለን..ልጅቷንም ክስ እንዳትከፍት በሽማግሌ ይዘን ይቅርታ እንድታደርግልሽ እናግባባታለን፡፡›› አለ ሰሎሞን፡፡

‹‹አትሞክሩት፤ እሷን ይቅርታ ከምጠይቅ መቶ አመት በእስር ብበሰብስ ይሻለኛል፡፡››

‹‹ቆይ ግን ይሄን ያህል ያዳረሳችሁ ምንድነው?››ፎዚያ ነች በአእምሮዋ ሲጉላላ ያደረውን ጥያቄ ያቀረበችላት፡፡

‹‹እሱ ሆድ ይፍጀው ነው፤ለመሆኑ አምጪልኝ ያልኩሽን ዲያሪ አመጣሽልኝ?››

‹‹አዎ እኚው፡፡››ብላ ከቦርሳዋ ውስጥ አውጥታ ልታቀብላት ስትል ፡፡

‹‹ለእኔ አይደለም…. ለኤልያስ ስጪው..ሁለቱንም ዲያሪ አንድ ላይ በፖስታ አሽግና ከትንግርት ብለህ ከላይ ፃፍበት እና ስጣት፡፡››

‹‹ለማን? >>

‹‹ለዛች ሰይጣን፡፡››

‹‹ለዶ/ር ሶፊያ ማለትሽ ነው?››

‹‹አዎ… ስሟን ቄስ ይጥራውና፡፡››

‹‹ያመጡላትን ቁርስ በፖሊሱ አማካይነት ከላዩ አንዲቀምሱ ተደረገና አስረከቧት፤ለነገ ሁኔታዎችን ሊያመቻቹ ሶስቱም የፖሊስ ጣቢያውን ግቢ ለቀው ወጡ፡፡

ይቀጥላል


ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ

#Share and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍4618
እግዜር ከፋው መሰል
እሺ ነው የሚልልኝ :

ቀንሶ መስጠት አቆመ
ሁሉንም ተወልኝ።

መመላለሴን ወደዋለሁ
አትስጠኝ ጠቅልለህ

:

ቀንስብኛና ልበል ወዴት አለህ?

ሰጥተህ አትተወኝ
አርገህ አትተወኝ

:

በማግኘት ገረጣሁ በማጣቴ ወዛሁ ከልክለኝ ልጠይቅ እንዳገኝህ በዛው።

🎴ኤልያስ ሽታኹን🎴


ቤተሰቦች #subscribe እያደረጋቹ

#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍357🔥3👏2🥰1
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል  አስራ አንድ


በገጽ 113 እና 114 መካከል ምን ተደብቋል?

ጓደኛዬ ሃይሚ የማታውቀው ገጣሚና ደራሲ የለም (ገጣሚና ደራሲ ይለያያል ወይስ አንድ ነው? እኔ እንጃ! ብቻ እንደዚያ ነው የሚሉት) እንደ እሷ ድንገት ተነስቶ ግጥም የወደደ ሰው አላጋጠመኝም፡፡ የግጥም ዝግጅት አለ በተባለበት ሁሉ አዲስ ጸበል ፈልቋል እንደተባለ በሽተኛ መሮጥ ነበር ሥራዋ፤ ወደ እንደነዚህ ዓይነት ቦታዎች ስትሄድ የምትዘንጠው አዘናነጥ ሰርግ ቤት ያስንቃል፡፡ አጭር ናት፣ ራሷም እንደምትለው መልክ አላደላትም፤ ውበቷ ዓይኖቿ፣ጥርሷና እግሯ ላይ ያቆማል፤ ሳቋ በግድ ያስቃል፣ ዓይኖቿ አያርፉም፡፡ ሁልጊዜ ነፍሷ የሆነ ነገር እንደፈለገ ነው፡፡ ትውውቃችን ገና ከሕፃንነታችን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነበር፤ አውቃታለሁ እላለሁ፡፡ ብዙ ጊዜ የሥነ-ጽሑፍ ምሽት የሚሉት ጋብዛኝ እዚያው በጸበልሽ ብያታለሁ። ግጥም፣ ልብ-ወለድ የሚሉት ነገር ምኑም አይስበኝም፡፡ ነገሩ ማንበብ ላይ ሰነፍ ሆኜ አልነበረም፤ እንዲያዉም ግለ-ታሪኮችንና በሙያዬ ዙሪያ የተጻፉ መጽሐፍትን፣ አሳድጄ ነበር የማነበው። ልብ-ወለድ፣ በአጋጣሚ እንኳን በሬዲዮ ሲተረክ ከሰማሁ ለወራት _ ከአእምሮዬ_አይወጣም፡፡ ታሪኩን ሳወጣና ሳወርድ፣ በቁም ነገር ሳዝንና ስደሰት እሰነብታለሁ፡፡ እንደ ፈጠራ ሥራ ቀለል አድርጌ ማዬት አልችልም። ያንን ስሜት ደግሞ አልወደውም። ሃይሚም ብትሆን ከእኔ ብዙም አትለይም ነበር፤ እንዲያውም እውነቱን ለመናገር ንባብ ላይ ብዙም አልነበረችም፡፡ ይኼ የግጥም ፍቅሯ ድንገት የሆነ ጊዜ የጀመረ ነበር። ከ “ኤለመንተሪ” እስከ “ሀይስኩል” በኋላም አብረን ኮሌጅ ስንማር ስለ ልብስ እና ጌጣጌጥ እንጂ ስለ ግጥም ስታወራ ሰምቻት አላውቅም ነበር። ታዲያ እንዲህ እንዲህ ያለው ቦታ ጋብዛኝ አልሄድም ስላት “ኋላ ቀር” ትለኛለች፡፡

አንድ ሁለት ጊዜ የሙዚቃ ዝግጅት እንድንሄድ ለምኛት እንቢ ስላለችኝ “ኋላ ቀር እዚያ ሄደሽ የሽማግሌዎች ተረት ስሚ" ብያታለሁ።አንዳንዴ ጓደኝነታችን ይገርመኛል፡፡ በጋራ የምንወደው ነገር “ፒዛ” ብቻ ይመስለኛል፡፡ እኔ ወድጄው ያልጠላችው፣ እሷ ወዳው ያልጠላሁት ነገር የለም። ከሆነ ጊዜ ጀምሮ እቤቷ ከሰበሰበቻቼው መጽሐፎች የሚበዙትን የደራሲያኑ ፊርማ ያለባቼው ስለነበሩ እንደ ቅርስ ነበር የምታያቼው፡፡ ለሰው አታውስም፣ በበኩሌ መጽሐፍ የደራሲው ፊርማ ኖረበት የመጽሐፍ አዟሪው፣ ልዩነቱ አይገባኝም ነበር። ሃይሚ ስለ ማንበብ ጥቅም ብዙ ብዙ ስትለኝ ምን እንዲህ ቀዬራት? እያልኩ በግርምት አያታለሁ፡፡ በተለይ አንድ ሰሞን ወደ ስብከት የሚቀራረብ “ዲስኩር† ነበር _ የምትደሰኩርብኝ፡፡ _ ታዲያ በአንገቴ ገመድ ቢገባ ከቤቴ አይወጡም የምትላቼውን መጽሐፍት፣ ካላነበብሽ እያለች ስትሰጠኝ ጉዱን ልዬው ብዬ ልብ ወለድ ማንበብ ጀማመርኩ። አንዳንዱን በጣት የሚቆጠር ገጽ እንኳን ሳላነብ እመልስላታለሁ፤ አንዳንዶቹን በስንት ትግል ዐሥራ አምስት ቀንም፣ ወርም ወስዶብኝ እጨርሳቼዋለሁ። እንዲህ ስንነታረክ ነበር አንድ መጽሐፍ ያዋሰችኝ፡፡ ያንን መጽሐፍ በጣም ነበር የወደድኩት፤ ታሪኩን ከመውደዴ የተነሳ በሦስት ቀናት ነበር አንብቤ የጨረስኩት። ሃይሚ ያንን መጽሐፍ ስታውሰኝ በጣም እንደወደደችው እና ሁለት ጊዜ እንዳነበበችው አጋና ነግራኝ ነበር፡፡ የመጽሐፉ የመጀመሪያ ገጽ ላይ የደራሲው ፊርማ እና “ከአክብሮት ጋር ለሃይማኖት ዳኛቸው የተሰጠ” የሚል ጽሑፍ በጥቁር እስክርቢቶ ተጽፎበታል፤ ማንበብ ጀመርኩ፡፡ ስለ አንዲት በአደጋ ምክንያት የማስታወስ ችሎታዋን ስላጣች ሴት ነበር፡፡ ይህቺ ሴት የአምስት ዓመት ልጇንም _ ነበር _ የረሳችው፤ ልጅቱ ሕፃን ናትና ችግሩን አትረዳም፡፡ እናቷን እንደወትሮው ለመቅረብ የማታደርገው ጥረት የለም፡፡ እናት ግን በየቀኑ ትረሳታለች ፤ በዚያ ላይ በጣም ቁጡ እናት ሆና ነበር...መጽሐፉ ሲበዛ አሳዛኝ በመሆኑ ላለማልቀስ እየታገልኩ ነው ያነበብኩት፡፡ እስካሁን ያ ታሪክ ድርሰት

ነው ቢሉኝ አላምንም፤ የሆነ ነፍሴ ውስጥ ተሰንቅሮ ቀርቷል።ያቺ ሕፃን እኔ ነኝ፤ የተረሳሁ፣ የሚገፋኝን፣ የረሱኝን ሁሉ እግራቼው ሥር እየወደቅሁ እንዲወዱኝ የመማጸን፤ እኔ ነኝ። ሰልነግረው የተረዳኝ ሰው ያገኜሁ መሰለኝ፡፡ ደራሲዉ እኔ ራሴ የሆንኩ መሰለኝ፤ የሆነ ተናግሬም፣ አልቅሸም ልገልጸው የማልቾል ነገሬ ላይ ደርሶ ነክቶኛል። መቼም ትንሽ ማወቅ ዕዳ ነው፤ ከዚያ በኋላ ስለ መጽሐፍ በተወራ ቁጥር የማነሳው ያቺን መጽሐፍ ሆነ፡፡ እንድ ነገር ግን ገረመኝ ፣ ስለመጽሐፉ ሳይሆን ስለጓደኛዬ ሃይሚ ... ያዋሰችኝ መጽሐፍ ገጽ 113 እና 114 ከላይ የተጣበቁ ነበሩ፣ ሕትመት ላይ የሚፈጠር ነገር ነው፡፡ ብዙ አዳዲስ “ሪፈረንስ' መጽሐፍት ስገዛ አጋጥሞኝ ያውቅ ስለነበር የገጾቹ መያያዝ አላስገረመኝም፤ የገረመኝ ሃይሚ እንዳለችው ይኽን መጽሐፍ ሁለት ጊዜ ካነበበችው እንዴት ገጾቹን አላላቀቀቻቼውም...?ያላነበበችውን መጽሐፍ ለምን ታደንቃለች....? አራት ጣቶቼን በመኻል አስገብቼ እንደ ክብ ትቦ በተጣበቁት ገጾች መኻል አጨነቆርኩ፤ ምናልባት ሌላ ኮፒ ይኖራት ይሆናል ብዬ በቀስታ በምላጭ አላቅቄ ማንበቤን ቀጠልኩ። ለሃይሚ መጽሐፉን እንደወደድኩት ነገርኳት ስለ ታሪኩ ብዙ አወራኋት “አዎ! አስገራሚ ነው'' ከማለት ውጪ ብዙም ዝርዝር አላወራችኝም። እኔ ግን ማውራቴን ማቆም አልቻልኩም፤ የጥያቄ መዓት አዥጎደጎድኩባት መልስ የለም፡፡ እንዲያውም ለአባቴ ሰጥቼው አንብቦ ወደደው... ብዙ ብዙ አወራንበት፡፡ ለሃይሚ መጽሐፉን ከመለስኩላት በኋላ ሥራዬ ብዬ ሔጄ ለራሴ ገዛሁ፡፡ ልብ-ወለድ መጽሐፍ ስገዛ የመጀመሪያዬ ነበር፤ ምናልባት የመጨረሻዬም!! አንድ ዓርብ ቀን ታዲያ ጓደኛዬ ሃይሚ ደወለችልኝና... “የምትወጂው ደራሲ ነገ ጧት የመጽሐፍ ምረቃ ፕሮግራም ላይ ይመጣል ለምን አንሄድም?'' አለችኝ...

“ኧረ! ባክሽ?'' አልኩ ሰፍ ብዬ... በመሠረቱ ደራሲውን እወደዋለሁ የሚል ቃል ከአፌ አልወጣም ነበር! የት አውቄው? “እውነት! ቶማስ ጋር “ቤስት' ናቸው ያስተዋውቀናል እንዲያውም እኔን ትጠይቂዋለሽ”... ቶማስ ከምታደርቂኝ ስለዚያ መጽሐፍ ያለሽን ጥያቄ ሁሉ የሃይሚ ፍቅረኛ ነበር፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሥነ-ጽሁፍ ተመርቆ እስካሁን አንድ ስንኝ እንኳን ያልጻፈ ነጭናጫ ልጅ፣ በሕሪው ስለሚያስጠላኝ አልወደውም፤ ሃይማ ምኑን እንደወደደችው እስከ ዛሬ ይገርመኛል፡፡ ለወትሮው እንዲህ ዓይነት የሥነ-ጽሑፍ ዝግጅት ይሁን፣ ስብሰባ የሚባል ነገር ባልወድም፣ የዚያን ቀን ግን ደራሲውን ለማዬት ጓጓሁ፤ ምናልባት ውስጤ አድንቆት ይሆናል እንጃ! ብቻ ውስጤ ሊያገኜው ፈለገ፡፡ በቀጣዩ ቀን ቅዳሜ ጧት ከሃይሚ ጋር ተያይዘን ሄድን፡፡ እዚህ ራስ ሆቴል፣ አዳራሹ ካፍ እስከገደፉ በሰው ተሞልቷል። መድረኩ ላይ የባሕል የሙዚቃ ተጫዋጮች የባሕሩ ቃኜን ዘፈን ይጫወታሉ(ይልቅ ይኼ ደስ አለኝ) እንደፈራሁት አልነበረም፡፡ እንዲያውም ደስ የሚል ዝግጅት ነበር፡፡ የተለያዩ ሰዎች መድረክ ላይ እየወጡ ግጥም ያነባሉ፡፡ መጽሐፍ ያሳተመውን ሰውዬ እንኳን ደስ ያለህ ይላሉ፡፡ ፕሮግራሙ ወደማለቁ ሲቃረብ ወጣትና ንጹህ ልብስ የለበሰ፣ በሥርዓት ፂሙን የተስተካከለ ልጅ ወደ መድረክ ሲወጣ ሃይሚ በክንዷ ጎሼም አድርጋኝ “እሱ ነው!!' አለችኝ፡፡ ሰው እንደዚያ አፍጥጨ ዓይቼ አላውቅም፡፡ ትልቅ _ ሰውዬ ነበር የጠበቅሁት፣ መላጣ መነጽር የሚያደርግ ምናምን፡፡ ግጥም አነበበ፣ እውነቱን ለመናገር ግጥሙ አልገባኝም። የአዳራሹ ሰው ሲያጨበጭብ አብሬ
👍355
አጨበጨብኩ። የጓደኛዬ ሃይሚ ፍቅረኛ ቶማስ “አጨብጫቢ ሕዝብ” እያለ ይነጫነጫል፤ ይኼን ነገሩን ነበር የማልወደው ከመተቼትና ከመዝለፍ ውጭ ምንም ሲሠራ አይቼው አላውቅም፡፡ የሆነ የሚያሳፍር ዓይነት ባሕሪ ነበር ያለው፣ እርሜን ባጨበጭብ “አጨብጫቢ ...” ሆሆ!

ዝግጅቱ አልቆ ሰው መውጣት ሲጀምር፣ የአንድ እግር ጫማዬ ወንበሩ ሥር ገብቶ ጠፋኝ፤ አውልቄ ነበር የተቀመጥኩት፤ አልተው ያለኝ ዓመል። አጎንብሽ ለፍለጋ ስንደፋደፍ ሃይሚ “ኤጭ! አሁንም ጫማሽ ጠፋሽ?'' እያለች አብራኝ ማፈላለግ ጀመረች “ምን የአንድ ዓመት ሕፃን ነሽ እንዴ? በዚህ ዕድሜ ጫማሽን በየቦታው መጣል?" ሁልጊዜ የሚያማርራት ይኼ ነገሬ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ እያለን ቶማስ ስሜን ጠርቶ፣ “ተዋወቂው!'' አለኝ፡፡ ቀና ብል ደራሲው አጠገቤ ቆሟል፤ በአንድ እግር ጫማ እንደቆምኩ ተዋወቅን (ተመስገን ይኼ ቶማስ የሚባል ገልቱ ይኽችን እንኳ ጥሩ ነገር ይሥራ ብያለሁ በውስጤ) በሥርዓት ሰላም ብሎኝ ትክ ብሎ እያዬኝ “ምን ጠፍቷችሁ ነው?'' አለ፡፡ “ጫማ!'' አልኩ በእፍረት ወደ አንድ እግሬ እያሳዬሁ፤ እግሬን እያዬ... “እንኳን ጠፋ ይኼን ቆንጆ እግር የማዬት ዕድል ፈጠረልን፡፡ ለማንኛውም ዕቃ መፈለግ አይሆንልኝም ግን እስቲ በፍለጋው ልሳተፍ" አለና ወደ ወንበሩ ሥር ::חחלל “ኸረ! እኛ እንፈልገዋለን”... አልኩ ተሳቅቄ፤ አብሬው ጎንበስ ብዬ ቀና ላደርገው እየሞከርኩ፡፡ ሰዎች ጉልበታቸውን ሊስሙ ያጎነበሱ ሰዎችን ትከሻቼውን ይዘው ቀና እንደሚያደርጓቼው ዓይነት ነበር ሙከራዬ፡፡ “ኸረ! ችግር የለውም!'' አለና፣ ትንሽ ቆይቶ ከተቀመጥኩበት ሦስት መደዳ አልፎ የወደቀ ጫማዬን አገኜው፣ እንደ ዋንጫ ከፍ አድርጎ እዬሳቀ መጣና ጎንበስ ብሎ እግሬ ሥር አስቀመጠልኝ፤ “ሰዎች በእግራቼው እየገፉ ወደዚያ ወስደውት መሆን አለበት አለ!'' በዚያ እየተሳሳቅን ወደ ውጭ ወጥተን እንደቆምን፣ አሁንም ዓይኑን ከእኔ ላይ ሳይነቅል፣

“የሚገርም ጠይምነት!'' አለኝ። አፈርኩ። ብዙ ሰው ከዚያ በፊት እንደዚያ ብሎኛል፤ የእሱ አስተያዬት ግን ለምን የተለዬ እንደመሰለኝ እስከዛሬ አይገባኝም፡፡ ፊቱን በመስተወት ባዬሁ ቁጥር ይኼ አስተያዬቱ ነው የሚያቃጭልብኝ፡፡ ጠይምነቴን ሳስብ፣ እሱ እንደግድግዳ የቀባኝ ይመስል እሱን ነው የማስታውሰው።

“በነገራችን ላይ አልተዋወቅንም፣ አብርሃም'' አለና እጁን ለሰላምታ ዘረጋልኝ፡፡

“ማኅደረ ሰላም'' አልኩ እጁን እየጨበጥኩ፡፡

“ሌላ አስገራሚ ነገር'' ብሎ ሳቀ፡፡

“ምኑ?''አልኩ፡፡

“ስምሽ!"

“ረዘመ?”

“አዎ! ግን በጣም ነው ደስ የሚለው!”

“...የአባቴን ቀንሼልህ ነው፡፡'' ተሳሳቅን፡፡ ለሁሉም ሰው የምለው ነበር፡፡

ሃይሚ በወሪያችን መኻል ጣልቃ ገብታ “መጽሐፍህን አንብባ የአገር ጥያቄ ስታዘንብብኝ፣ ራሱን ጠይቂው ብዬ አመጠኋት፤ በጣም ነው የወደደችው" አለችው፡፡

“እና ዛሬ ችሎት መቅረቤ ነዋ? ...ለምን በእኔ ግብዣ ቡና እየጠጣን አናወራም ታዲያ?'' ብሎ ሁላችንም ተያይዘን እዚያው አካባቢ ያለ ካፌ ገባን፡፡ በግርምት አዬዋለሁ፤ ቡና አዘዘ፣ ልክ እንደመጣለት በሚገርም ፍጥነት መጠጣት ጀመረ። እያወራን ሌላ ቡና አዘዘ ...እና ሦስተኛ ቡና ሲያዝ፣ ሳላስበው ቀና ብዬ አዬሁት! እሱም ቀና ብሎ አዬኝ፡፡ ዓይኖቻችን ሲገጣጠሙ የማደርገው ነገር ጠፋኝ። የእፍረቴን “ቡናው አልበዛም?'' አልኩት፡፡ እየሳቀ ወደ አስተናጋጁ ዞረና “በቃ ውሃ

አምጣልኝ ቡናውን ተወው” አለ፡፡ እያንዳንዱን ቅጽበት አልረሳውም፡፡ የዚያን ቀን በሕይወቴ ደራሲ የሚባል ፍጥረት ጋር ተዋወቅሁ ... ያው ሰው ናቸው፤ ከዬት ነው የሚያመጡት ታሪኩን!?... ለምንድን ነው ብዙ ቡና የሚጠጣው!? ... ሲጋራ ያጨስ ይሆን!? እያልኩ አዬዋለሁ፡፡ አልፎ አልፎ ዓይኖቻችን ይጋጫሉ፤ ሃይሚ፣ ቶማስ እና እሱ ስለ _ ግጥም ምናምን ሲያወሩ በየመኻሉ ተጫዋች ይለኛል፡፡ ስለ መጽሐፉ አላነሳንም። ቆይቶ...

“እና ምን ትሠሪያለሽ ልገምት ?'' አለ፡፡

“ገምት፣”

"ነርስ?"

“አይይይ!”

“ሥራ አጥ ነርስ?'”

“እንዴዴዴ፣'” ተሳሳቅን “አካውንታት.. ኦዲተር ...ነኝ'' አልኩት፡፡

“ኦ! ግምት ላይ ቀሽም ነኝ፣''

“አዬሁህ'ኮ!” ረዘም ያለ ሳቅ።

“በቃ! ለስሕተቴ ቅጣት...ቅዳሜ የግጥም ምሽት አለ፤ በእኔ ወጭ ልጋብዝሽ''አለኝ፡፡

“ግጥም _ አልወድም!'” አልኩት፡፡ ሊሰጠኝ፣ ከሆነ መጽሐፍ ውስጥ ያወጣውን የመግቢያ ትኬት ለሃይሚ አቀበላትና ሌላ ትኬት አውጥቶ ባትወጂም ነይ ብሎ ሰጠኝ ተሳሳቅን፡፡ ስትደርሽ ደውይልኝ ብሎ ትኬቱ ላይ ስልኩን ጻፈልኝ፡፡ ለምን እንደሆነ እንጃ፣ እንደ ሕፃን ነበር “ትሪት' የሚያደርገኝ፡፡ አላስታውስም ሰዎች እንዲህ ያናገሩብኝን ጊዜ፤ እንደዚያ ተዋወቅን፡፡በዚያው ሰበብ መደዋወል እና መገናኜት ጀመርን፡፡

የዚያች ካፌ የቡና ጠረን፣ የሰዎች ጫጫታ፣ በነጭ ድንክ የቡና ስኒ ቡና አጠጣጡ፣ አስተያዬቱ፣ እያንዳንዷ ድርጊት፣ ድምፅ እና ዝምታ ጭምር ነፍሴ ውስጥ ታትሞ ቀርቷል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ተቀጣጥረን የተገናኜን ጊዜ ጨንቆኝ ነበር፡፡ ወንድ ጋር ከሥራ ጉዳይ ውጭ ስቀጣጠር የመጀመሪያዬ ነበር፡፡ ቀድሜው ደረስኩ፤ እንደ ደረሰ ሰላም ብሎኝ ተቀመጠና ካዘዝኩት ለስላሳ የእኔን ብርጭቆ አንስቶ ተጎነጨ፡፡ ከዚያ ቡና አዘዘ፤ ይኼ ድርጊቱ ውስጤ የነበረውን መጨናነቅ ቀንሶ በጓደኝነት ስሜት አንድናወራ አድርጎኝ ነበር፡፡ አብርሃም ጋር እንዲህ ነበር ትውውቃችን፡፡ አልዋሽም ጥሩ ልጅ ነበር፡፡ ነገሮች የት ላይና ለምን እንደተበላሹ እስከዛሬ አይገባኝም፡፡ በብዙ ነገር ከተረባባሼ ሕይወቴ የማርፈው እሱ ጋር ስሆን ብቻ ነበር፡፡ ለምንድን ነው ግን ሕይወቴ እኔ ባልፈጠርኩት ረብሻ የተከበበ የሚሆነው? ደግሞ ክፋቱ ሁሉም ረብሻዎች በፍቅር፣ በደግነት፣ በትህትናና በበጎነት የተጠቀለሉ መሆናቼው ነበር፡፡ አቤት ያለፍኩባቼው ረብሻዎች መዓት....!

ረብሻ አንድ!

ጋራዡ ስም የለውም፣ በቃ ጋራዡ ነው የሚባለው፡፡ ከቤታችን መቶ ሜትር ያኽል ቢርቅ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ እዚህ ጋራዥ ሊጠገኑ የሚመጡ መኪናዎች የጋራዡ ጠባብ ግቢ ስለማይበቃቼው ቤታችን መስኮት ጥግ ድረስ ይሰለፋሉ፡፡ ከእነዚህ መኪናዎች የሚንጠባጠብ ዘይት፣ ግራሶና ነዳጅ ባጠቆረው ወዛም ቆሻሻ ሰፈር መኖር ቢለመድም፣ የሚያስመርር ነገር ነበረው፡፡ የተለመደ ምሬት። ከዚህም በላይ ከጧት እስከ ማታ የከባድና ቀላል መኪና ሞተር ሲያጓራ፣ እንደ ማዕድቤት ጭስ የጠቆረ፣ እንደ ደመና የነጣ፣ የመኪና ጭስ አየሩን ሲሞላው፣ የተሰረጎደ የመኪና አካል እንዲቃና በመዶሻ ሲቀጠቀጥ፣ የብረት መበዬጃና መቁረጫ ሲንጫረርና ሰፈሩ በሊድ ሽታ ሲቀረና፣ የማያቋርጥ የመበዬጃ ጨረር በርና መስኮት ተዘግቶ እንኳን በሆነ ቀዳዳ አልፎ እንደ ካሜራ ፍለሽ ሲንቦገቦግ፣ በዚህ ሁሉ መኻል ነው ያደግሁት...ለምጄዋለሁ ግን ያስመርረኛል፤ ወይም

አብሬው እኖራለሁ ግን አለመድኩትም፡፡ እኔ እንጃ! በሕይወቴ ብዙ ምኞት አልነበረኝም ቢያንስ ሰላምና ሙዚቃ ያለባት አንዲት ክፍል ቤት ነበር ምኞቴ። ከዚሀቹ ምኞት ብሶ እንደ ሰማይ ስትርቅብኝ አይገርምም? በለ ጋራዡ አንዳንዴ ክፉኛ ይሟዘዛል እንጂ የተመሰከረለት ጥሩ ሰው ነው፡፡ ክፍሌ ይባላል፤ ኤርትራዊ ነው። ሰው ታመመ ከተባለ መኪናው ከአንቡላንስ ቀድሞ ሆስፒታል የሚያደርስ፣ ሰርግ _ ከተባለ እንኳን የራሱን ሊሰሩ ጋራዡ የቆሙ መኪኖቹን አሰልፎ የሚያደምቅ፣ የሰፈር ሰው ሁሉ የሚወደው ሰው ነው። በየዓመቱ ጥምቀት ሲከበር የሰፈራችን ታቦት የሚያልፍበትን መንገድ ከፍሎ
👍3210