አትሮኖስ
284K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
523 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
🌻በ'ነሱ ቤት🌻
🍀ክፍል ሠላሳ አንድ🍀
🍀🌻🍀🌻
የጌታነህ እናት ወይዘሮ ገነት የምትሰራው ነገር ግራ እስኪገባት ድረስ ሆነች። አንዴ በቴሌቭዥን የምታያት የቀድሞ የቤት ሰራተኛዋ መሳይ በዕንባ ታጅባ የምታደርገውን የእርዳታ ጥሪ ልቧ ተሰብሮ ታያለች ቀጥላ ባለቤቷ ከወዲያወዲ እያለ ።'አይ ውርደት አይ መዋረድ ሰሞኑን ያለምክንያት አደለም እዚ ቤት እሳት እየነደደ ያለው ፈጣሪ የሰራነውን ስራ እንድናይ ሊያደርገን ነው ተመልከች አጥያታችን ፈጦ ወጣ "አላት ። ወይዘሮ ገነት ባለቤቷ ከሚናገረው ነገር ይልቅ ። መሳይን ስታባርራት የነበረውን ሁኔታ በአይምሮዋ እያመጣች ማመላለስ ጀመረች ፣በወቅቱ ምን ያክል ጭካኔ እንዳሳየች ሲሰማት በራሷ አፈረች፣የልጇን ብልግና ለመሰወር ብላ አንዲት ቆንጆና ምስኪን ታዳጊ ልጅ ውሻ አድርጋ ከልጇ ዞር እንዳደረገች የታሰባት ዛሬ ነው ። አጠገቧ ባገኘችው ሶፋ ላይ ዘጭ ብላ በመቀመጥ ጭንቅላቷን በሁለት እጆቿ ይዛ በፀፀት ተንገበገበች ፣  ባለቤቷ ቁጣ ቁጣ እያለው"ይሄ የማይረባ ልጅሽ ምን ያክል ወንጀል ሲያሰራን እንደነበር አስተዋልሽ ዛሬ ፣እ ሁሌም ዕፀፁን ለመደበቅ ትታገይለት ነበር ተመልከች እንዳልጠቀምሽው ። በአርባ አመቱ እንኳን ሰው መሆን አቅቶት ዛሬም ጥፋት እያጠፋ ቀሚስሽ ውስጥ ለመደበቅ ይሞክራል ።እውነቱን ነው ጌታነህ ዘላለሙን የማያድግ ልጅ ነበር ስታሳድጊ የነበርሽው "ብሎ ጣቱን ወደሷ ቀሰረ። ወይዘሮ ገነት በንዴት ተነስታ ቆመች"ምን እያልክ ነው አንተ እራስህን ነፃ ማውጣትህ ነው።አንተ አይደለህ እንዴ ወንዶች ልጆችህን መክረ ዘክረህ እንደ አባትነትህ ማስተካከል የነበረብህ ፣ ነገር ግን ያንን እያደረክ ነበር ወይ ?በፍፁም ፣ ከዛ ይልቅ ባጠፉ ቁጥር ከመገሰፅ ይልቅ ምን ነበር የምትለኝ 'ልጅሽን ስርሃት አሲዢ 'ልክ ያንተም አላፊነት እንዳልሆኑ ሁሉ !እንግዲ እኔ የጠቀምኳቸው መስሎኝ ራርቼላቸው ይሆናል ፣ አንተ ግን በነሱም ሆነ በኔም ሕይወት ላይ ትልቁን ድርሻ መውሰድ ነቀረብህ !ታውቃለህ እኔም ብሆን አንተን ሳገባ ያን ያክል በዕድሜ የበሰልኩ አልነበርኩም"ብላ ተንጣጣችበት ። ባለቤቷ የራሱን አሳብ በንዴት ሊናገር ሲል ። ልጃቸው መስፍን ድምፅ ሰማው ብሎ ወደሳሎን መጣ "እማዬ ምንድነው ጩኽቱ ሰላም አይደላችሁም?!"ብሎ ጠየቀ
"ምን ሰላም አለ አንተ እያለህ"አለው አባቱ ቱግ ብሎ
"ስርሃትህን ያዝ አንተ ሰው አትጩኽበት አንዴ የፈሰሰ ውሃ ይታፈስ ይመስል ይልቅ መፍቴሄ ብታመጣ ይሻላል"አለች ወይዘሮ ገነት ለልጇ እየተከላከለች ።መስፍን ድንብርብር ብሎ አባቱን አየው ።ሰሞኑን ደሞ ሁሉም ነገር እኔላይ ነው እንዴ የተነሳው አለ ለራሱ።
"ምን አጠፋው ደሞ ሳምንቱን ሙሉ ከቤት አልወጣውም ...."ብሎ ሊቀጥል ሲል
"በመጀመሪያ ደረጃ አንተ ለጥፋት መውጣት አይጠበቅብህም እዚሁ የምታጠፋቸው ስላሉልህ ። ሲቀጥል ደሞ ቀድሞ ያጠፋሃቸው ጥፋቶች ቤትህ ድረስ ሊመጡልህ ስለሚችሉ ውጪ መውጣት አይጠበቅብህም! ችግሩ ያንተን ስእተት ችግር ማስተካከል ያለብን ዛሬም እኛ መሆናችን ነው እንጂ!"ብሎ ተቀመጠ። ወይዘሮ ገነት በባሏ እየተናደደች ።መስፍንን እጁን ይዛ ወደክፍሉ ሄደች እራሴው አረጋግቼ የተፈጠረውን እነግረዋለው ፣ አለዛ ልጄ በሰሞኑ ሁኔታው እራሱን ሊያጠፋም ይችላል አለች..........
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
መሳይ አስተናጋጁ ሰሚርም የአብላካት ጓደኞችም አሰባስበው አምጥተው የሰጧትን ገንዘብ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆና ደጋግማ ትቆጥራለች ፣ የገንዘቡ አለመሙላት ልጇን በየቀኑ እንደሚገልባት ተሰምቷታል። አብላካትን ዞራ ተመለከተች በፀጥታ ተኝታለች ትንፋሿ እንኳን ጎልቶ አይሰማም ። መሳይ አዘነች ምነው ፈጣሪ ይሄን ሁሉ ነገር በኔ ላይ አመጣህብኝ ? ከልጅነቴ ጀምሮ አንድም ቀን ከአሳብ እና ከችግር ከአዘን እንዳልላቀቅ ማነው የረገመኝ ምንስ ባጠፋ.....
አብላካት ተኝታ እያለመች ነው ፍፁም ፀጥ ያለ ና ማንም የማይታይበት አውላላ ሜዳ ላይ ቀስ እያለች እያዘገመች 'ሰው ሁሉ የት ሄዶ ነው ፡እሺ ሰውስ ባይኖር አንዳንድ እንስሳቶች እንኳ አይታዩም እንዴ ኡፍፍፍፍ እንዴት ደክሞኛል ደሞ  'እያለች ትጓዛለች ሄዳ ሄዳ አንድ ወንዝ ጋር ደረስች ለመጠጣት አስባ ዝቅ ስትል በውሃው ውስጥ የሚርመሰመሱ ትላትሎች አይታ በድንጋጤ አፈገፈገች ። እናም በሌላ አቅጣጫ መጓዝ ስትጀምር ደረቅ እና ቢጫ ሰአር የወረረው ስፍራ ደረሰች የሰአሩ መጠውለግ አሳዘናት በቃ እዚ አካባቢ ዝናብ አይጥልም ማለት ነው ብላ አሰበች ። መንገዷን ቀጥላ ወደፊት ስትሄድ ቢጫው ሰአር እየረዘመ እየረዘመ መጣ ለመራመድ ሲያስቸግራት ከፊቷ የተጋረደውን ሳር ገለል ስታደርገው ፊትለፊቷ ሰመረ ቆሞ አገኘችው ። በዚ ጊዜ በደስታ ተፍለቀለቀች ።ሰመረ ግን ምንም አይነት ፈገግታ ሳያሳያት  ወደዋላዋ እየጠቆመ
"የት እየሄድሽ ነው ተመለሺ "አላት
"እንዴ ወደቤቴ ነዋ"
"አይ አይ ቤትሽ ወደዚ አይደለም በይ ተመለሺ"
"ግንኮ "
"ነገርኩሽ ነይ እኔው እወስድሻለው "ብሎ እጇን እየጎተተ ወደዋላ መለሶ ይዟት መሄድ ጀመረ
"እሺ አትጎትተኝ ቀስ እያልን መሄድ አንችልም ?በዛላይ የምነግርህ ነገር ነበረኝ "
"ንገሪኝ እሰማሻለው"
"እሺ ግን አንዴ መቆም እንችላለን "
"እሺ ነይ ብሎ ወደራሱ አስጠጋት"
"እ እኔ በጣም በጣም አፈቅርሃለው ይሄንን ሳልነግርህ ሩቅ ቦታ ልሄድ ነበር እኮ"
"እንዴ እኔን ጥለሽማ በፍፁም አትሄጂም ።ደሞ እኔም አፈቅርሻለው እኮ ሚጣ"
"ሚጣ አይደለውም !አብላካት ነው ስሜ !ድጋሚ ሚጣ እንዳትለኝ "
"እሺ በቃ "ብሎ እቅፍ አድርጎ ሊስማት ጠጋ ጠጋ ሲላት አንዲት አሞራ መጥታ በመሃላቸው ብር ብላ ስትገባ 'ዋይ 'ብላ ብንን አለች
  መሳይ በፍጥነት ወደልጇ ተጠግታ ግንባራን እያሻሸችላት "የኔ ውድ አይዞሽ ህልም ነው ፣መጥፎ ህልም አይተሽ ነው እኔን  እኔ ልሳቀቅ ዓለሜ አይዞሽ እስከመጨረሻው አልለይሽም "አለቻት
"እማ የኔ ውድ እናት ያን ያክል የሚያሳስብ አይደለም ህልም ህልም እላለው "አለቻት እና ወደ እናቷ አቅጣጫ በመዞር ጥቅልል ብላ ተኛች ።ወዲያው በአሳቧ ወደ ሰመረ ገሰገሰች በህልሟ የተሰማት የተለየ ስሜት ገርሟታል እውነት ከሰመረ ጋር በውንም እንዲ ይሰማኝ ይሆን ?  ልቧ እንደ አዲስ ለሰመረ ሲመታ አዘነች ።ሰመረን እንደፈለገችው ሳታገኘው ስሜቷን ሳታጋራው ወደ ማይቀረው መሄዷን ስታስበው በአልጋዋ ላይ እንዳለች ተቁነጠነጠች ።ሁኔታዋንስትከታተላት የነበረችው መሳይ ይህንን ከማይ ብላ እናም ዕንባዋም ሊመጣ ሲታገላት መጣው ብላት ወጣች።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ጌታነህ በስንት ጊዜው እንየውን አግኝቶ የጦፈ ወሬ ይዘዋል ።ጌታነህ ስላሳለፈው ነገር እየነገረው እንየውን በሚያስቀውም በማያስቀው ያስቀዋል ። ስለሰመረም ትንሽ አሜት መሰል አውርተው ቦጨቁት ።ሰመረ የተቀየረባቸው ያቺን ትንሽ ልጅ አብላካትን ካገኘ ጀምሮ እንደሆነ አወሩ መልሰው ደሞ መራራቃቸው ከዛ ቢጀምርም ።ልጅቷናት ለማለት አይቻልም በሚለው ደሞ ተስማሙ ። በዛውአጋጣሚ  እንየው እሷን ልጅ እጅህ ማስገባቱ አልሆን አለህ አይደል ብሎ ጀመረው ይሄን ጊዜ የጌታነህ በህልህ የተሞላ ልብ ድጋሚ ተነሳሳ እናም የሆነ ያልሆነ ውሸት ከነገረው በዋላ ።ወደ አብላካት ደወለ ይጠራል ብዙ ጊዜ ሞክሮ ስልኳ ዝግ ነበረ ዛሬ ስለሰራለት ደስ አለው 'አንሺው አንቺ ትንሽዬ በቀቀን "አለ ስልኩ ቢጠራም አልተነሳም አቅበጠበጠው  በጣም ስሜታዊ ሆኖ  ሚሴጅ ፃፈላት "አንቺ ፈልፈላ ለምንድነው ስልኬን የማታነሽው ካንቺ ምን ፈልጌ መስሎሽ ነው 
👍8610🔥1👏1
አመዳም የደሃ ልጅ አመድሽን ላራግፍልሽ ነው እኮ ያልኩሽ " ብሎ ሴንድ አለው እና ተመልሶ እንየው ጋር ሄዶ ተቀመጠ ፣በጣም ስለተናደደ እንየው የሚለውን መስማት አቆመ ። በዚ አጋጣሚ አስተናጋጁ ሰሚር መጥቶ አጠገባቸው ሲቆም ጌታነህ አይቶት "ደብል ውስኪ "አለው
"እንዴ ሳንበላ ደሞ በቀን"አለው እንየው
"ፈለኳ ተሎበል አንተ ደሞ "አለው አስተናጋጁ ሰሚር እነ ጌታነህ በመምጣታቸው ተደስቶ ነበር የመጣው ይምጣ ስለ አብላካት ሁኔታ ነገሮ እርዳታቸውን ለመጠየቅ ቆርጦ ነበር ።ከሁኔታው ግን ሲረዳ ጌታነህ ተናዷል በዚ ሁኔታ ለማናገር በመፍራቱ ተወው  እናም ወደ ትህዛዙ ሄደ ።
ጌታነህ በንዴት ውስጥ ሆኖ ስልኩን ጠረቤዛው ላይ ሲያሽከረክር ሳለ ሜሴጅ ገባ አቢ ይላል በደስታ ሚሴጁን ሊያነብ ሲል ስልኩ ጠራ እናቱ ነበረች የእናቱን ጥሪ ዘግቶ የአብላካትን መልስ ማንበብ ጀመረ " አትጨነቅ እኔ መንገደኛ ነኝ ያንተ ገንዘብ አያስፈልገኝም መልካም ነገር ሁሉ እመኝልሃለው ለስድቡ አመሰግናለው ትልቁ"ይላል ጌታነህ ግራ ገባው  ። የእናቱ ስልክ መልሶ ጠራ አነሳው
"አቤት ማሚ"
"ማታ እንዳታመሽ የምናወራው ነገር አለ "
"ሰላም ዋልክ ልጄ ?አይቀድምም ማሚ"
"ድምፅህን ስሰማ መዋልክን አረጋገጥኩ እኮ አሁን ቁም ነገር ነው በፍፁም እንዳታመሽ እጠብቅሃለው"
"እሺ እንደፈለግሽ እኔም የትም የመሄድ ስሜት አልነበረኝም "
"ጡሩ "አለችና ስልኩን ዘጋችው ።ጌታነህ መልሶ ለአብላካት ሚሴጅ ፃፈ
"የት ልትሄጂ ነው አረብ አገር እንዳይሆን ብቻ"ብሎ ሴንድ አደረገ መልሱ እረዘመበት ቢያይ ቢያይ ዝም ሆነ አስተናጋጁ ሰሚር መጥቶ ትህዛዙን አስቀመጠ። እናም ለመናገር ሲል ።ጌታነህ ሚሴጅ ገባለት
"አረብ አገር አይደለም መንገዴ ወደ አባቴ ነው ለመጨረሻ ጊዜ ነው የፃፍኩልህ እባክህ መልሰህ አትፃፍ " ይላል ።ጌታነህ እቺ ትንሽ በቀቀን ምንድነው የምታወዛግበኝ ብሎ ውስኪውን ጎንጨትአድርጎ አስቀምጦ ቆም አለ መልሶ ተቀመጠ ።አጠገባቸው እንደጅብራ የቆመውን አስተናጋጅ አየው በእጁ አነስተኛ የእርዳታ ጥሪ ወረቀት ይዟል
"ምንድነው አንተ ደሞ !"አለው
"እቺን እንድትቀበሉኝ ነው "
"ምንድነው እርዳታ ነው "
"አዎ"
"በቃ እዛው ወረቀትህን የምትፈልገውን እንሰጥሃለን አለው "እንየው
"እስኪ ላንተ ነው "አለና ጌታነህ ተቀበለው ወረቀቱ ላይ ለማመን የከበደው ስም ተፅፏል  የኩላሊት ታማሚዋን የአስራ ስምንት አመቷን ታዳጊ እናትርፋት ..........
"ምንድነው አንተ ይሄ"ብሎ አፈጠጠበት ።አስተናግዶ ጁ ሰሚር  ስለሁሉም ነገር አንድም ሳያስቀር ነገራቸው ጌታነህ ደነገጠ ።ከአብላካት ጋር ሲፃፃፍ የነበረውን ሚሴጅ መልሶ አነበበው ። ለምን እንደው ባያውቅም ከወትሮ በተለየ ልቡ አዘነበት ....

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍9417😢8😱4😁1
#በኔ_ቤት

በኔ ቤት……
ፍየል ቅጠል አይታ
ሳትበላ ታድራለች
ዶሮ ጥሬ ረግጣ
ልፆም ነው ትላለች
ውሻ ስጋ እያየ
በረሀብ ይሞታል
ሰው እህል ቀርቦለት
ባዶ ድስት ይከፍታል

በኔ ቤት……
አንበሣ ሚዳቋን
አቅፎ ይስማታል
ጅብ ስጋ ላይበላ
ምሎ ይገዘታል
ዕባብ ሰውን አይቶ
አይተናኮልም
ነብር ጎሽ አይጥልም

በኔ ቤት……
አንድ ብር ላይ ያለው
ትንሹ እረኛ መሳቁን ያቆማል
የሰፌዱም ስፌት
ሳንቲም ላይ ይሆናል
ወተት የጠጣ ህፃን
ሰክሮ ተንገዳግዶ
የአስር ዓመት ልጅ
አስር ልጆች ወልዶ
የሰፈር አዛውንት
ሰፈር ይቦርቃል
ሩቅ ያለው ቀርቦ
ቅርብ ያለው ይርቃል


አሁንም…
ከጣልሺኝ ቦታ ላይ
ብቻዬን ቁጭ ብዬ
ታምራዊ ስዕል
በአይምሮዬ ስዬ
ሀሳቤን ጥጃለሁ
ማይበስል ማይመስል
ዳግም በህይወቴ
አገኝሽ ይመስል

ልዑል ሀይሌ

#YouTube Subscribe እያረጋቹ ቤተሰቦች👇

https://www.youtube.com/@atronose
👏30👍2712🥰2😁1
እመኚኝ !!

ነይ ግቢ በሞቴ
እቤት ማንም የለም
የለችም እናቴ
እመኚኝ ግዴለም
ምንም አናደርግም
ወደ ውስጥ ገብተሽ
በሩን ብዘጋውም
አንድ ላይ ተቀምጠን
አብረን ብናወጋም
ከንፈርሽን ልስም
ወዳንቺ ብጠጋም
ብስምሽም እንኳን
ስጋት እንዳገባሽ ምንም አናደርግም... በፀጉሮችሽ መሃል
ጣቴን ባንሸራሽር
ጠረንሽን ቢሸተኝ
ገብቼ አንገትሽ ስር
እጄ ሚይዘው አጥቶ
ጡትሽን ቢነካካ እየጨባበጠ
መጠኑን ቢለካ
እንዳትጠረጥሪኝ ለሌላ
እንዳይመስልሽ ውዴ
ሙች እመኚኝ...
.
.
.
በዚህ ሁሉ መሃል በስሜት
ገንፍዬ ልብስሽን ባወልቅም
ልብሴን ወዲያ ጥዬ
እርቃንሽን ሆነሽ እርቃኔንም ሆኜ
አልጋው ላይ ብጥልሽ
በክንዴ ዘግኜ በሚገርም ሁኔታ
ፍቅር ብንሰራም እመኚኝ አለሜ
እኔ ልሙትልሽ
ምንም አናደርግም😂


#YouTube Subscribe እያረጋቹ ቤተሰቦች👇

https://www.youtube.com/@atronose
😁68👍366👎4
👁በ'ነሱ ቤት👁
🌻ክፍል ሠላሳ ሁለት🌻
🌻🌻🌻
ጌታነህ በኪሱ የያዘውን ገንዘብ እንዳለ ዘርግፎ ለአስተናጋጁ ሰሚር እያስረከበ ወደ እንየው በመዞር እሱም ልክ እንደሱ እንዲያደርግ ነገረው ። እንየው የጌታነህ ሁኔታ የጤና አልመሰለውም ዝምብሎ እያየው ነበር ።ጌታነህ በእንየው መረጋጋትና የጥርጣሬ አስተያየት ተቆጣ ። አስተናጋጁ ሰሚር አረጋጋውና እርዳታው የግድ ዛሬ መሆን እንደሌለበት ነገም ተነገ ወዲያም ይደርሳል ብቻ የእርዳታ እጃችሁን ዘርጉላት እባካቹ አላቸው ። ሁለቱም ተስማሙ  ።ጌታነህ ከሬስቶራንቱ እንደወጣ በቀጥታ ወደቤቱ ነበር የሄደው አይለኛ ድብርት ተጫጭኖታል ።ስለ አብላካት የሰማው ነገር  ምቾት ነስቶታል ቤት ሲገባ ወላጆቹ እናም ወንድሙ ሳሎን ሰብሰብ ብለው ተቀምጠዋል ።ሁኔታቸው ግን ያስፈራ ነበር በከባድ ዝምታ ውስጥ ነበሩ ሁኔታቸው ደስ ስላላለው ወደክፍሉ ሊገባ መንገድ ጀመረ  በዚጊዜ እናትየው ሶፋው ላይ እንዲቀመጥ በትህዛዝ ተናገረችው ። ጌታነህ እየደበረው ተቀመጠ በውስጡ ምነው ወደቤት ባልመጣው የሚል አሳብ መጣበት ።እናቱን ቀናብሎ ሲያያት አንድ ነገር ለመናገር ስታምጥ አስተዋለ ።ወደአባቱ ሲያይ  ወደ መስፍን ፊቱን አጨፍግጎ ዞሯል መስፍን በዕንባ የራሱ አይኖቹን እየጠራረገ እና በተደጋጋሚ በአፍንጫው የሚወጣድምፅ እንዳለ አስተዋለ ። ጌታነህ አሁን ይበልጥ ተረበሸ ። ከረጅም ዝምታ በዋላ እናት እያማጠች መናገር ያለባትን ነገር ሁሉ ከስር መሰረቱ አፈረጠረጠችው ። መስፍን ተነፋረቀ ጌታነህ የሚሰማውን ሁሉ ለማመን ከበደው ።  ጭራሽ እያወሩ ያሉት ስለአብላካት መሆኑን ሲያውቅ አፉን ያዘ የሚሆነው ጠፋው  በተደጋጋሚ ምን አይነት አገሮች ጣሚ ነው ምን አይነት አጋጣሚ ነው .....እያለ ጮኽ
እናት ከመስፍን የጌታነህ ባሰባት ...
"ተረጋጋ ጌታነህ ምን ሆነሃል መስፍን እንኳ እንዳንተ አላበደም ። ልጅቷ በዚ ሰአት ችግር ውስጥ ናት እናቷን አፈላልገን ልንረዳት ይገባል "አለችው
"ማሚ አልገባሽም እኮ ልጅቷን .."ብሎ ጭንቅላቱን ያዘ
"ልጅቷን ምን?"አለችው እናት ደንገጥ ብላ
"ልልጅቷን አውቃታለው ማለቴ..."ብሎ ሊቀጥል ሲል
"አምላኬ የት ነው የምታቃት "ብላ እናት ተነሳች እሷን ተከትሎ አባትየውም ብድግ አለ
"ተው ጌታነህ በሌላ መልኩ ነው እንዳትለን ተው !!"አለ አባትየው በድንጋጤ
መስፍን የሚገባበት ጠፋው
"አይ እንደዛ ነገር አልተፈጠረም ግን ሊሆን ነበር ።ምን እንደሰራቹ ተመልከቱ ልጅቷን በተደጋጋሚ የፍቅር ጥያቄ አቅርቤላት ነበር በእርግጥ አንድ ቀን ነው ያገኘዋት ከዛ በዋላ በስልክ ልቀርባት ሞክሬ አለው ላገኛት ብዙ ቀጠሮ አስዣታለው ነገርግን ፍቃደኛ አልነበረችም እልህ ውስጥ ከታኝ ነበር በአካል ባገኛት ነገር ይበላሽ ነበር ።ወይ ፈጣሪዬ ለካ ለዚነበር የጠበቅከኝ አመሰግናለው አምላኬ "ብሎ ተንበረከከ
"ልጅቷእኮ ገና ታዳጊ ናት እንዴት ሌላ ነገር አሰብክ "ብሎ መስፍን ድንገት ጮኽ
"ምን ታወራለህ ደሞ አፍ አለኝ ብለህ ዝም በል "አለ አባት በብስጭት ። የጌታነህ እናት ። ጌታነህ ሌላ ግንኙነት አለን የሚላት መስሏት ደንግጣ ነበር ።ያ ባለመፈጨሩ ቅልል አላት ።እናም እርስ በእርስ መነታረካቸውን ትተው ልጅቷን ማዳን እንዳለባቸው አፅኖት ሰጥታ ተናገረች ።ሁሉም በእሷ አሳብ ተስማሙ እናም አብላካትን በፍጥንት ወደ ውጪ ወስደው ማሳከም እንዳለባቸው  እናም የአብላካትን እናት መሳይን  ማግኘት እና ላደረጉት ነገር ይቅርታ ጠይቀው መካስ ያለባትን ሁሉ ለመካስ ቃል ተገባ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አስተናጋጁ ሰሚር ከጌታነህ ያገኘውን በርካታ ገንዘብ ይዞ ወደነ አብላካት የሄደው ከስራ እንደወጣ ነበር ። አስባልቱን ጨርሶ ቅያስ ውስጥ ሲገባ አንድ አሳብ መጣለት እነገታነህ ይሄን ሁሉ ገንዘብ ከሰጡት ሰመረ ደሞ የተሻለ ነገር እንደሚያደርግ ተማመነ አብላካት እንዳትነገርው ያለችውን ነገር ወደጎን በመተው የሞባይል ስልኩን ከኪሱ አውጥቶ ወደ ሰመረ ደወለ ..........

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍11319😁10🥰3👏1
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሃምሳ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
/////

ወደቀልቧ እስክትመለስ እና መኝታ ቤቷ ውስጥ ያልጋበዘቻችው ሰዎች እንደገቡ ለመገንዘብ ከአንድ ሰዓት በላይ ወሰደባት ….

‹‹እንዴት ብትደፍረኝ ነው ግን ሰተት ብለህ መኝታ ቤቴ ድረስ  ሚስትህን ይዘህ የገባኸው……?.›

ኤርሚያስ ግራ ተጋባ … ተርበተበተ……‹‹ይቅርታ..ማለት ሚስቴ አይደለችም…. አላውቃትም..ይቅርታ ማለቴ አውቃታለሁ ግን ይሄውልሽ እሷ….››
አቋረጠችው ‹‹…ውጣልኝ …ውጡልኝ..››ጭንቅላቷን በእጆቾ ይዛ ጩኸቷን ለቀቀችው….

‹‹እሺ እንወጣለን..አንቺ ብቻ ተረጋጊ… እንወጣለን…ይሄው እየወጣን ነው…››የሚያደርገው ጠፍቶት ክፍሉን ለቆ ለመውጣት ወደበራፉ ፊቱን አዞረ…

ኬድሮን‹‹አባትሽን ላገናኝሽ ነው የመጣሁት››አለቻት

ከተቀመጠችበት ወንበር ንቅንቅ ሳትልል
ከትከት ብላ ሳቀች..የምፀት ሳቅ…..የእብደት ሳቀ..የንዴት ሳቅ

‹‹እንዴት አድርገሽ ነው ከሞተው አባቴ ጋር ምታገናኚኝ….…?ነው ወይስ ከበድኑ ነው ልታገኛኚኝ ያሰብሺው…..አመሰግናለሁ በድኑ በእጄ ስለሆነ አትልፊ  ….››

‹‹አይ እዲያናግርሽ ማድረግ እችላለሁ››

‹‹እንዲያናግረሽ አልሽ…..ኤርሚያስ ምን በድዬሀልው..…?››አለችው ወደእሱ ዞራ

እየተርበተበተ‹‹..ሰላም አንቺ ምን በወጣሽ.. አረ ምንም አልበደልሺኝም  …ለምን እንደዛ ልትይ ቻልሽ…?››

‹‹እንዴ ያንተ ሳያንስ ሌላ ሰው ይዘህ መጥተህ እድታሾፍብኝ ታደርጋለህ……?በሀዘኔ እንዴት ታላግጣላችሁ….…?በቁስሌ እንዴት ጨው ትነሰንሳላችሁ…?ይሄ ምን አይነት ጭካኔ ነው …?…››

‹‹አረ በፍፅም እንደዛ አይደለም….አንቺን ለመርዳት እንጂ ሌላ ምንም አላማ የለንም››

‹‹እና ታዲያ እንዴት ነው ከአባቴ የምታገናኘኝ……?.››

‹‹እሱን አንዴት እንደሆነ አላውቅም ..ግን ታደርገዋለች ››አለ አንዴ ኬድሮንን አንዴ ሰላምን በማፈራረቅ እያየ
ልታስረዳት ሞከረች‹‹እመኚኝ  የሙት መንፈስ ማናገር እና ከሚወዶቸው ሰዎች  ጋር የማገናኘት ችሎታ አለኝ…መቼስ ስለዚህ ጉዳይ ሰምተሸ አታውቂም  ለማለት አቸገራለው….››

‹‹ሰምቼማ አውቃለው..በመጽሀፍ ቅዱስ ላይም አንብቤያው..ግን ..››>

‹‹ምንም ግን የለም…››ብላ ንስሯን እንዲመጣ በአዕምሮዬ መልዕክት አስተላለፍችለት ….. ክንፉን እየማታ መጣና  አልፎን ፈሪጁ ላይ ጉብ  ሲል  ሰላም  በድንጋጤ ተንደርድራ ልትሰፍርበት ስትል ቦታ ቀየረና አመለጣት….

‹‹አባቴን ..አግዙኝ…. አባቴን አንዳይነካብኝ››

‹‹አይዞሽ የእኔ ንስር ነው ..ምንም አያደርግም…››

‹‹እርግጠኛ ነሽ ……?አባቴን አይነካውም…?››አለች… በእሷ ግምት የኬድሮን ንስር  የአባቷን በድን አካል ለመዘንጠል ይዳዳል ብላ ነው

‹‹እንዴ ንስር የሞተ ነገር እንደማይነካ አታውቂም…››

‹‹አላውቅም››አለች

‹‹እኔም አላውቅም ››በማለት ድጋፍ ሰጣት  ኤልያስ

ማብራሪያዬን በኩራት ቀጠልኩ ‹‹ንስር ኩሩ ነው…እራሱ አባሮ… እራሱ ታግሎ …እራሱ ገድሎ ካልሆነ ነክች አያደርግም…ለማንኛውም አሁን ተዘጋጂ ቁጭ በይ ››….ቁጭ አለች…
‹‹ይሄሁልሽ አሁን ንስሬ ያግዘኝና ከአባትሽ መንፈስ ጋር አገናኝሻለሁ...ማለት የእኔን አንደበት ተጠቅመው አባትሽ ቀጥታ ያናግሩሻል..በእኔ አንደበት በራሳቸው ድምፅ››

‹‹እሺ››

‹‹ኤርምያስ አንተ ደግሞ ካለህበት እንዳትነቃነቅ..ምንም የሚረብሽ ነገር ካለ ትኩረቴን ስለሚበታን መሀል ላይ ግንኙነቱ ሊቋረጥ ይችላል››

‹‹አረ በፍጽም ይሄው ንቅንቅ አልልም..ትንፋሼ እራሱ አይሰማም››አለና በተቀመጠበት ጭብጥብጥ አለ

ሁሉም ነገር ዝግጁ መሆኑን ሳታረጋግጥ አዕምሮዋን ከንሰሯ ጋር አገናኘቸው..ለደቂቃዎች ተመሰጠች …ይሄን ነገር ከዚህ በፊት አድርጋው አታውቅም ‹‹..ግን ማድረግ አያቅተኝም›ስትል በራሷ ተማመነች….አዎ ንስሯ የአባቷን ነፍስ ካለችበት እንድትመጠ እየጋበዘ  ነው..ወይ ብዙም አላስቸገራትም ….ቀጥታ አባትዬው በኬድሮን አንደበት ልጃቸውን ማናገር ጀመሩ……

‹‹ልጄ ሰላሜ…››

ባለማመን መለሰች‹‹ወይ አባዬ..››ተንደርድራ ሬሳውን እያየች
‹‹እዛ ለምን ትፍልጊኛለሽ….…?አይ ልጄ ስጋዬ ውስጥ አይደለሁም.. …ግን ደግሞ ወደዘላለም ማረፊያዬም መሄድ አልቻልኩም..ከሁለቱም ሳልሆን በአየር ላይ ተንጠልጥዬ አለሁልሽ፡፡

‹‹ምነው አባዬ……? እኔ ልሰቃይልህ…..እኔ በአየር ላይ ለዘላለም ተንጠልጥዬ ልቅር››

‹‹አይ ለምን ልጄ…? ለምን..…?ለአንቺማ ይሄ አይገባም…ትቼሽ ስለሄድኩ ይቅርታ ልጄ..ምን ላድርግ የአማላክ ጥሪ ነው….እባክሽ ልጄ ከዚህ በላይ እንድሰቃይ አታድርጊኝ…››

‹‹እንዴ አባዬ እኔ አንተን ማሰቃየት…?››

‹‹አዎ እናቴ… እዚህ እቤቴ ውስጥ በድን አካሌን ታቅፈሽ እንደዚህ ሆነሽ እንዴት እፎይ ብዬ ወደዘላለም የሚወስደኝን  መንገዴን እቀጥላለሁ..…?አልችልም ልጄ ..አካሌ መሬት ሳይገባ ነፍሴ ወደአምላኮ ልትሄድ ይከብዳታል..ልጄ እባክሽ በአምላክ  ስራ ጣልቃ አትግቢ..››

‹‹እንዴት አባ……? እንዴት ጣልቃ ገባሁ……?.››

‹‹እንዴ ሞትን የፈጠረውን አምላክ  እኮ እየተቃወምሽው ነው..ተሳስተሀል እያልሺው ነው››

‹‹አዎ ተሳስቷልማ..እንዴት አንድ አባቴን ይነጥቀኛል..…?እንዴት ባዶዬን ያስቀረኛል….…?.››

‹‹አየሽ ልጄ …ሞት እርግጥ በጥፋታችን ምክንያት የተሸለምነው ቅጣታችን ነው…ይሁን እና በዚህ ምድር ለመኖር እስከመጣን  ድረስ   ሞታችንም በጣም አስፈላጊ ነው..››

‹‹እንዴት አባ .. …?ሞት ደግሞ እንዴት ነው ጠቃሚ የሚሆነው.?››

እግዜር ፈጥሮ ምድር ላይ ቢረሳንስ ምን ይውጠናል….…?አርጅተን መንቀሳቀስ አቅቶን እቤት እስክንቀር…. ቆዳችን እስኪጨማደድ እና  ወበታችን እስኪረግፍ ድረስ አልወስዳችሁም ቢለን ማነው የሚጎዳው……?.ጥርሳችን ረግፎ ገንፎ እንኳን  ማኘክ እስኪያቅተን ቢተወን …አይናችን ለግሞ  የልጅ ልጆቻችንን ከጎረቤቶቻችን ልጆች መለየት እስኪያቅተን ..መኝታ ቤታችን ከሽንት ቤታችን መለየት እስኪሳነን ድረስ ኑሩ ብንባል ሽልማት ነው ቅጣት…ዕርግማን ነው ምርቃት…?››

‹‹እንዴ አባዬ.. …!!!አንተ እኮ ገና ነህ …ሰባ አመት እንኳን አልሆነህም..…?››

‹‹እኮ እግዚያብሄር ይወደኛል ማለት ነዋ..…?ምላሴ ጣዕም መለየት ሳይሳነው፤አይኖቼ ማንበብ ሳያቆሙ ፤እግሮቼ ላምሸው ከዘራ ሳልይዘ አስታወሶኛል…››

‹‹ግን እኮ አባ እኔን ጥለህ ነው የሄድከው…?››

‹‹የሞት መጥፎው ክፍል ያ ነው….አዎ ሁልግዜ የሆነ ነገር ጥለሽ መሄድሽ አይቀርም…ማንም ቢሆን ከዚህ ምድር ሲሰናበት የሆነ ነገር በጅምር ጥሎ መሄዱ የሆነ የሚወደውን ሰው ሳይሰናበት ማምለጡ ያለ እና ግዳጅም ነው….እና ልጄ አንቺ አፈር ካላቀመሺኝ እና በሀዘን መቆራመድሽን እስካላቆምሽ ድረስ ጉዞዬን መጀመር አልችልም… ብጀምርም ቶሎ አልደርስም..ሀዘንሸ ወደኃላ ይስበኛል….ለቅሶሽ  መንገዴን እያጨቀየው ያዳልጠኝ እና አላላውስ ይለኛል…..››

‹‹አባ አረ እኔ እንዲህ የበደልኩህ አልመሰለኝም…?››

‹‹በደልሺኝ እኮ አላልኩም.. ግን  በቃ..አንዳንዴ መሆን ያለበት ነገር እንዲሆን መተው ነው..ታግለሽ ልታሸኝፊው ከማትችይው ነገር ጋር መታገል  ከድካም ውጭ እርባን ያለው ውጤት አያስገኝም ››

‹‹እና ምን ላድርግ አባ…?››
👍8910🥰3👎1🔥1😁1
‹‹በቃ አልቅሰሽ ቅበሪኝ….ከዛ በኃላ ሞተ የእያንዳንዱ ሰው ዕጣ ፋንታ መሆኑን አምነሽ ተቀበይና ወደ ህይወትሽ ተመለሺ…የራስሺኝ ሰው ፈልገሽ ኑሮሽን  ኑሪ….የእኔ በድን ታቅፈሽ እዚህ ቤት ባሳለፍሽው ስድስት ቀናት ውስጥ ስራ ላይ ብትሆኚ ኖሮ ሰንት ነፍስ  እንደምታታርፊ አስበሽዋል….… ?ስንት ያንቺን ክትትል የሚፈልጉ ህመምተኞችን እርግፍ አድረግሽ በመተውሽ  በያሉበት ምን ያህል እየተሰቃዩ እንደሆኑ ታውቂያለሽ….…?ያባትሽን መንፈስ ለዘላለም ለማስደሰት እውነታውን ተቀብለሽ  ፈገግ በይ ..በእኔ ስም የአዛውንቶችን ጤንነት ተንከባከቢ…እኔን እያሰብሽ ሞያሽን በጥንቃቄ እና በታማኝነት ስሪ..እያንዳንዱ ሰው ባንቺ እጅ ታከሞ በመዳኑ ተደስቶ ፈገግ ሲል  እኔም ባለሁበት  ፈገግ እንዳልኩ በማሰብ ውስጥሽ ሀሴት ታድርግ….›.

‹‹አዎ አባ እውነትህን ነው..እንዳልከው አደርጋለሁ››

‹‹ስለዚህ ተስማምተናል››

‹‹አዎ አባ ..ተስማምተናል››

‹‹በቃ ደህና ሁኚ ልሄድ ነው

‹‹አባ ከመሄድህ በፊት ››

‹‹እሺ ምንድነው…?››

‹‹ግን ገነት ነው ምትገባው አይደል…?››

‹‹አይ ልጄ..መች ሄድኩና አውቀዋለሁ ..ግን ምንም አይት ፍራቻ እየተሰማኝ አይደለም….እረፍትና እፎይታ ነው ዙሪያዬን የከበበኝ….የሚታየኝ  አንፀባራቂ ብርሀን እንጂ ፅልመት አይደለም….እና ፈጥኜ የመሄድ ፍላጎት ነው ያለኝ…ባከሽ ልጄ እንድዘገይ አታድርጊኝ..››

‹‹እሺ አባ ..አንድ የመጨረሻ ጥያቄ››

‹‹ምን ልጄ…?››

‹‹እማዬን ታገኛታለህ…?››

‹‹አዎ ልጄ ተስፍ አደርጋለሁ..በጣም መቸኮሌ አንድም ለዛ ይመስለኛል››

‹‹እንደምወዳትና በጣምም እንደናፈቀቺኝ ንገርልኝ››

‹‹እሺ ነገርልሻለሁ››
ደግሞ ቀኔ ደርሶ ወደእናንተ  ስመጣ ከእናንተ ጋር አብሬያችሁ መኖር ነው የምፈልገው››

‹‹እሺ ልጄ  እንዳልሽ…ደህና ሁኚልኝ…››

‹‹እሺ አባ ደህና ሁን››

ይቀጥላል

#YouTube ላይ subscribe
እያደረጋችሁ ቤተሰቦች ከ110,000 እዚ ካላችሁት ሩቡ እንኳን subscribe ቢያደርግ አስባችሁታል ይሄን ድርሰት ያነበበው ሁሉም ቢያደርግም ቀላል አደለም ግን አብዛኞቻችን አንብበን ነው የምንወጣው ስለዚህ አንብባችሁ ስትጨርሱ ወደ #YouTube ሄዳችሁ Subscribe
እያደረጋቹ #አመሰግናለው
👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍12122😢15👎6😁4
👁በ'ነሱ ቤት👁
ክፍል ሠላሳ ሦስት
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
አስተናጋጁ ሰሚር ደጋግሞ የሰመረን ስልክ ሞከረ ይጠራል አይነሳም  በጣም ጓጉቶ ስለነበር ሰመረ ባለማንሳቱ ቅር አለው ። ለአብላካት አንድ የተሻለ ነገር እንደሚፈጥርላት ተማምኗል ፣ የተለየ ነገር ባያደርግ እንኳ ብዙ ገንዘብ ሊረዳት ይችላል ።
እነ አብላካት ቤት ሲደርስ ቆም ብሎ በረጅሙ ተነፈሰ ፣አብላካት ፊት ሲቀርብ ጭንቀት ማሳየት አይፈልግም ልክ እንደወትሮው  እየቀለደ ዘና ሊያደርጋት ነው የሚፈልገው ።
   እናም በር ከፍቶ ሲገባ መሳይ ቡና እያፈላች ከአብላካት ጋር እየተጫወቱ አገኛቸው ይህንን ስሜት ሲያይ የአብላካትን እናት አመሰገናት ፣ በዚ ጉዳይ ላይ ደጋግሞ መክሯታል ልጇን ማዳን ከፈለገች በፊትለፊቷ ማልቀስና ደካማነቷን ማሳወቅ ሳይሆን ፣ በተቻላት መጠን ስለህመሟ እንዳታስብ ማዝናናት ጠንካራመሆኗን መንገር ከፈጣሪ ጋር ሁሉ ነገር እንደሚቀየር መንገር ነው ብሏታል።እና ዛሬ እንደዛ ስታደርግ ስላየ ተደሰተ ። ሁለቱንም ጉንጫቸውን ስሞ ተቀመጠ እና አብላካትን ፣ በቀልድ
"አንቺ ሚጣ ምንድነው እንደዚ የሚያስቅሽ"አላት
"ስነስርሃት ሚጣ እንዳትለኝ ፣ደሞ ያሰመረን ተገላገልኩ ስል አንተም ሚጣ ትለኛለህ ዋ.."አለች
"አውቄ ነው ኪኪኪኪ የኔ ትልቅ ገና ትልቅ ትሆኛለሽ አምናለው ሀላ ያውቃል አንቺ ብቻ ፈገግ በይ"አላት በሰአን ላይ የቀረበውን የቡና ቁርስ ፈንዲሻ እየዘገነ
"አይ ሰሚ ምላስህ እኮ "አለች አብላካት የሆዷን በሆዷ ይዛ ለነሱ ስትል እየሳቀች
"ሰሚሬ አንተ እኮ እንደታናሽ ወንድሜ ነህ አንተ ባትኖር ምን ይውጠኝ ነበር ፈጣሪ ይጠብቅ "አለች መሳይ። ሰሚር ፈገግ ብሎ መልስ ሊሰጥ ሲል ስልኩ ጮኽ በፍጥነት አንስቶ
"ሃሉ "አለ
"ሃሉ ማን ልበል ወንድም ደውለህልኝ ነበር"አለው
"አዎ አዎ"ብሎ ተነስቶ ወደደጅ ወጣ ።
"እኮ ማን ልበል "
"ሰሚር እባላለው የአብላካት ጓደኛ ነኝ አስታወስከኝ"አለው
"እህ አዎ አዎ ሰሚር አስተናጋጁ "
"አዎ እንደቴ ነህ ሰላም ነው"አለው ሰሚር
"ደና ነኝ እንዴት ናቹ እናንተ ፣"
"ደና ነን"
"ሚጣ እንዴት ናት ማለቴ አብላካት"
"ደና ነች እእ ያው..."ብሎ ሰሚር ዝም አለ
"ያው ምን አብላካት ደና አደለችም እንዴ ?"አለው ሰመረ
"ያው ትንሽ ታማለች እእ ብቻ አስቸጋሪ ሁኔታላይ ነው ያለችው "አለው ሰሚር እየተጠነቀቀ
"ምንድነው እሱ የት ነው ያለችው ስልኳን ደጋግሜ ብሞክር የማታነሳው ለዛ ነው የት ነው ያለችው ሆስፒታል ናት"ሰመረ ተርበተበተ። አስተናጋጁ ሰሚር የሰመረን ድምፅ መለዋወጥ ሲሰማ ገባው በቃ ሰመረ ይወዳታል ስለዚህ ልነግረው ይገባል ምናልባትም ፈጣሪ የአብላካትን መጪ ሁኔታ ተመልክቶ ቢሆንስ ሰመረን ያዘጋጀላት ብሎ አሰበ
"ሆስፒታል አደለችም ለጊዜው ነገር ግን በሳምንት ሦስት ቀን ሆስፒታል የሚያስኬዳት ህመም ነው ያለባት በጣም አሳዛኝ ሁኔታላይ ነው ያለችው"አለው
"ምን ምን እያልክ ነው ?!የምትለውን ታውቃለ ይሄን ያክል ምንድነው እየቀለድክብኝ ነው እንዴ"አለው ሰመረ በቁጣ
"ከምሬን ነው ዛሬም ልደውልልህ የተገደድኩት እርዳታ ስለሚያስፈልጋት ነው በፍጥነት የኩላሊት ንቅለተከላ ካላደረገች ቅስሟ ተሰባብሮ ቶሎ ትሞታለች "አለ ሰሚር እንባ እያነቀው
"ምን ምምን ኩላሊቷ...."ብሎ ዝም አለ ስልኩም ተቋረጠ ። ስልኩን አየው ተዘግቷል ።ጠበቀ ጠበቀ እና መልሶ ደወለ ካገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ነው ይላል ። ቅር እያለው ወደቤት ገባ ። መሳይ አየቸው እና ቀስብላ መጥታ እርዳታ አገኘን እንዴ አለችው ። አስተናጋጁ ሰሚር ከነ ጌታነህ ያገኘውን ገንዘብ አውጥቶ ዘረገፈው ፣ ብዙ ነው ነገር ግን ለጊዜው ነው ። አብላካት የናቷ ፊት ሲፈካ ስታይ ።ልቧ ተነካ  ፈጣሪ ለሷ ሲል ቢምራት ተመኘች ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ጌታነህ ምሽቱን ሙሉ ከቤተሰቦቹ ጋር አንዴ በቁጣ አንዴ በተረጋጋ መንፈስ ሲማከር ነው የቆየው ፣ በመጨረሻ የተስማሙበት ጉዳይ መሳይን እንደምንም ብሎ ማናገርን ነው ከዛ በዋላ በፍጥነት ልጅቷን ወደውጪ ሄዳ የምትታከምበትን መንገድ ማመቻቸት ።ከዛ በዋላ ሁሉንም ነገር እንድታውቅ ማድረግ በዚ አሳብ ተስማምተው ሁሉም እያብሰለሰሉ ወደመኝታቸው ሄዱ ። ጌታነህ ነገሩ ሁሉ ሌላ ሰው አድርጎታል ልቡ በጭራሽ አላርፍ አለው ፣አስተናጋጁ ሰሚር የሰጠውን የእርዳታ ወረቀት አውጥቶ ተመለከተው ስልክ ቁጥሮች አሉት ። ነገ ደውሎ አድራሻቸውን እንዲያሳውቁት ሊጠይቃቸው ወሰነ ።እንቅልፍ መተኛት እስኪያቅተው ድረስ ስለ አብላካት አሰበ ፣ፈጣሪ ያቺን ልጅ እንዳላገኛት ስላላደረገኝ አመሰግነዋለው እሺ ብትለኝ ኖሮ ትልቅ ስህተት ውስጥ ገብቼ ነበር ። ይሄ የተረገመ ወንድሜ አጥፍቶ አጥፍቶኝ ነበር ። እንደስራዬ ያልከፈልከኝ ፈጣሪ አመሰገናለው ።አለ ደጋግሞ ።ስለ ጓደኞቹም አስቦ ይህንን ጉድ ሲሰሙ ምን ይሉ ይሆን ። ብሎ አሰበ ። ብቻ እንድቺው ሲገለባበጥ ሲጨነቅ አደረ...


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍14715😁4😢4
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሃምሳ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////

ቫይብሬት ላይ የተደረገ ሞባይል ስልክ ላይ ሲደወል እንዳለ ንዝረት ተንቀጠቀጥችና አዕምሮዋን ከንስሯ ጋር አላቀቀች…
ሰላም ወደኬድሮን ተንደርድራ መጥታ እግሯ ሰር ድፍት አለችና‹‹በጣም አመሰግናለሁ….እግዜር ይስጥሽ››

‹‹ተነሺ ..እኔን አታመስግኚ…እሱ በጣም ስለለመነኝ ነው እንዲህ ያደረኩልሽ…››አለቻት

‹‹ኤርሚ እግዜር ይስጥልኝ….አንተንም በጣም  ነው የማመስግንህ..ምን አይነት ሰላም በውስጤ እንደተሰራጨ አትገምትም››አለች ወደመቀመጫዋ ተመልሳ በመቀመጥ

‹‹በነጋራችን ላይ በጣም ነው የሚያፈቅርሽ …እንደነገረኝ ከሆነ ከልጅነቱ ጀምሮ አንቺን ሲያፈቅርሽ ነው የኖረው….አንድም ቀን አንቺን ማፍቀር አቁሞ አያውቅም..ግን በኑሮ ደራጃ ስለምትለያዩ እሺ አትለኝም የሚል ፍራቻ በውስጡ ስላለ  ካንቺ ሲሸሽ ነው የኖረው››አፈረጠችለት

ባለማመን አንዴ ኬድሮንን አንዴ እሱን በማፈራረቅ ማየት ጀመረች..ኤርምያስም የተቀመጠበት ወንበር ላይ አንገቱን ወደወለሉ እንደደፋ ሚገባበት ጠፍቶታል እጆቹን እያፍተለተለ ነው…

‹‹አላውቅም ነበር…ኤርምያስ እኔን ማፍቀር….…?››

‹‹አዎ….ኤርምያስ አንቺን…››

‹‹እሺ ጥሩ ነው…አሁን ምን እናደርግ …ኤርሚ እርዳኝ ለእድር ሰዎች ንገራቸው…አባቴ ዛሬውኑ እንዲቀበር እፈልጋለሁ….››

‹‹አረ እሺ… ችግር የለውም… አሁኑኑ ነግሬያቸው ልምጣ …ስልካቸውን ስለማላውቅ እናቴ ጋር ሂጄ …››ብሎ ተነሳ 

ኬድሮን የተለየ ሀሳብ አመጣች‹‹ቆይ መጀመሪያ የሬሳ ሳጥን እንግዛና አባትሽኝ  በሳጥኑ ውስጥ በማድረግ  ማዘጋጀት አለመብን..አሁን ዕድርተኛው መጥተው ጓደኞቸው ተሰብስበው እንገንዝ ማለታቸው አይቀርም …እንደዛ ከሆነ ደግሞ ሌላ ሀሚት ላይ ይጥልሻል…በህግም ሊያስጠረጥርሽ ይችላል››

‹‹ታዲያ ምን እናድርግ››አለች ግራ ገብቷትና ያለሳበችውን ነገር ስላነሳው ደንግጣ

‹‹ግድ የለም እኔና ኤርሚ ሳጥኑን ይዘን እንምጣ..ሁሉንም ከጨረስን  ብኃላ ለሌላው ሰው እንናገራለን….››

‹‹አስቸገርኮችሁ አይደል…?›› 

‹አረ አትጨነቂ …እኔን እንደእህትሽ ቁጠሪኝ… ኤሪሚም  ያው ያንቺው ነው..››አለችና ምትናገረው ጠፍቷት በመቁለጭለጨ ላይ ሳለች የደነዘዘውን ኤርሚያስን ይዛው ወጣች…

መኪናው ውስጥ ገብተን የሬሳ ሳጥን ወደሚሸጥበት ቦታ  እያመሩ ሳለ…

‹‹ምን አይነት ተአምር ነው ያደረግሽው……?.››ሲል ጠየቀት

‹‹ያው ላንተ ስል ነው››

‹‹በጣም ነው የማመሰግንሽ….ግን  እንደማፈቅራት ለእሷ ባትነግሪያት ጥሩ ነበር››

‹‹ለምን…?››

‹‹ያው አንደኛ መንገሩ ምንም ውጤት አይኖረውም ሁለተኛ እኔ እና አንቺ……››

‹‹አይ እኔና አንቺ የሚባል ነገር የለም…አኔን እርሳኝ…እኔ ሁለት ቀን ብቻ ነው የቀረኝ..››

‹‹ምን ለመሆን…?››

‹‹ለመብረር…››

‹‹እንዴ የት አሜሪካ ወይስ አውሮፓ……?››

‹‹በለው ከሁለት አንዱ….ስለዚህ እሷኑ ጠበቅ አድርግ.ደግሞ በትክክል ይሳካልሀል….

እንደምታፈቅራት ስነግራት የልቧን ምት በደንብ ታዝቤያለሁ. ዋናው ከዚህ ሀዘን እስክትወጣ ከስሯ አትለይ …….

‹‹እንዴ ወዴት ነው የምለየው….ከእሷ የሚበልጥ ምን ሌላ ጉዳይ ይኖረኛል››

‹‹ምንም ››

‹‹አንቺ ልትበሪ መሆንሽን መስማቴ  ግን ቅር አሰኝቶኛል››

‹‹እኔን እርሳኝ አልኩህ እኮ››

‹‹እኮ እንዴት አድርጌ ልርሳሽ…?››
/////

የሰላምን አባት የቀብር ሁኔታ ካመቻቸችና ከተጠናቀቀ በኃላ ሁለቱንም አንድ ላይ ከለቀስተኞች ጋር ጥላቸው እናም በውስጧ ለመጨረሻ ጊዜ ተሰናብታቸው መልካሙን ሁሉ እየተመኘችላቸው ወደቤቷ ነው የተመለሰችው…ድክምክም ብሏት ነበር…ግቢውን አስከፍታ ስትገባ ግን ድካሟን ሁሉ ከላዮ የሚያበንላት አስደሳች ሁኔታ ነው የጠበቃት…

ግቢው መሀል ላይ ባለች ክፍት ቦታ ጠራጴዛ እና ወንበር ወጥቷል፤…ጠረጵዛው በልዩ ሌዩ ምግቦችና መጠጦች ተሞልቷል …ከዛ አልፎ ዙሪያው በየጥጋጥጉና በየቦታው የዛፍ ቅርንጫፎች ላይም ሳይቀር የተለያዩ የምግብና የፍራፍሬ አይነቶች ተቀምጠዋል…የተለያዩ ጥራጥሬዋች በየቦታው ተበትኗል….በጊቤዋ ውስጥ ያሉ እንስሳት ብቻ ሳይሆኑ እንግዳ የሆኑ ወፎች ሳይቀሩ ግቢውን ወረውት የተበተነላቸውን ጥራጥሬ በደስታ ይለቅማሉ… ጦጣና ዝንጆሮዎቾም ሙዙን እየላጡ ይውጣሉ …የማይፈነጭ እና የማያስካካ ፍጥረት በግቢው አይታይም..  የሆነ እንስሳት አግብቶ ሌሎቹ ሠርግ ተጠርተው አሼሼ ገዳሜ ላይ ያሉ ነው የሚመስለው….ሌላው ይቅር እያንዳንዱ  ተክል   ስሩ ተኮትኩቶና አፈር ታቅፎ ውሃ ጠግቦ እስኪተፋ ድረስ ጠጥቶ ይታያል….በቃ በግቢው አንድም ያልተደሰተ ፍጥረት አልነበረም..ይሄ ሁሉ በፕሮፌሰሩ የተደረገው እነሱ በተደሰቱበት መጠን እኔ እንደምደሰት በደንብ ስለሚያውቁ ነው፡፡

‹‹አትመጪም…  ይሆን ብዬ በስጋት ላይ ነበርኩ …እንኳን በሰላም መጣሽ››አሏት ከእድሜ ጫና የተነሳ ያጎበደድት ፕሮፌሰር…

‹‹አይ እፈልግሻለሁ ብለውኝ የለ..…….?በዛ ላይ  አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረኝ …ማታ ወደ እናቴ  እሄዳለሁ.አዎ ነገ ሙሉውን ቀን ከእሷዋ ጋር ነው ማሳለፍ የምትፈልገው………››

‹‹ጥሩ ጥሩ..ነይ እዚህ ጋር ቁጭ በይ›› ብለው ምግብ በሞላበት ጠረጴዛ ዙርያ ከበው ከተቀመጡ ወንበሮች ውስጥ አንድን ሳቡላት… አመስግና ተቀመጠች፡፡

የእጅ ውሀ አመጡላት …‹‹አረ እራሴ እታጠባለሁ›› ብላ በራሷ ተጣበች… ሳሀን ስባ ምንም እንኳን የምግብ ፍላጎት ባይኖራትም እሷቸውን ለማስደሰት ስትል ብቻ መብላት ጀመረች… እሳቸውም ከፊት ለፊቷ ተቀምጠው በስስት እያዮት መመገብ ጀመሩ…

‹‹የሚጠጣ ምን ልቅዳልሽ…….?››

‹‹ውሀ ››

‹‹ወይን ወይም ሌላ ነገር አይሻልሽም…….?››ካለወትሮዋ ዉሀ ማለቷ አስገርሞታል

‹‹አይ ውሀ ነው የምፈልገው….››

‹‹እሺ ካልሽ ››ብለው ውሀ ቀዱላት፡፡

‹‹ጋሼ በዚህ ምድር በኖርኩበት ዓመት የተረዳሁት ነገር ቢኖር  ምድር መተኪያ የሌላቸው ሁለት ነገሮች መታዳሏን ነው ….አዎ  እናትና ውሃ የዚህ ዓለም ሁለት ልዩዎች  ናቸው…››

‹‹እንዴት ልጄ..…….?እንዴት እንደዛ ተረዳሽ…?››

‹‹እናታችን መጀመሪያ ገነታችን ነች..ከተፈጠርንበት ቀን አንስቶ እስክንወለድበት ቀን ድረስ በእናታችን መሀፀን ውስጥ ገነታዊ ኑሮ ነበር የምነኖረው… ያ ስፍራ ሁሉ ነገር በፍፅምና  እንከን አልባ  ስፍራ  ነበር..ሁላችንም ከዛ ያለፍላጎታችን ተገፍትረን ስንወጣ(ስንወለድ) እሪ ብለን ለቅሶችንን የምንለቀው  ምን እንዳጣን በደመነፍስ ስለሚገባን ነው…አዳም እና ሄዋን በሰሩት ሀጥያት ከገነት ወደምድር ተባረሩ የሚባለው ሌላ አይደለም ከእናት መህፀን ወደምድር ተገፍትሮ መውጣት ነው…ከዛ በኋላም ቢሆን  እናት ምን ጊዜም እናት እንደሆነች ነው ምትቀጥለው… እንዳላረጀን እና እንዳላበቃልን የሚሰማን እናታችን በሰላሳ አመታችንም እንደ ህፃን ስትቆጣን ስናይ ነው..ጭንቅላታችንን ስትዳብስልን…ተይ አንቺ ልጅ ብርድ ይመታሻል ስትለን  ነው፡፡
👍918👏4😢4🔥2🥰2🤔1
ግን ክፋቱ በፈለግናት  ጊዜ ስለምናገኛት…በጣራናት ጊዜ ሮጣ ስራችን ስለምትገኝ ዋጋዋን ብዙም አናውቀው…. እንደድንገት ስትነጠለን  እና ከእጃችን ተንሸራታ ስናጣት ግን  አንድ ሰው ብቻ እንዳልነበረች ይገለጽልናል…መላ ዓለም እሷን እንደማይተካልን  ትምህርት እናገኛለን…ግን ትምህርት ቀድሞ ያጣኸው ነገር ወደፊት ዞሮ መጥቶ እንድታስተካክለው እድሉን ካላገኘህ ጥቅም የለውም..በደንብ ስትፀፀት እድትኖር ብቻ ነው የሚያግዝህ፡፡

ውሃም በቀላሉ ነው የምናገኘው..እኛ እራሱ በዋናነት የተሰራነው ከውሀ ነው ..ምድርም ሶስት እጆ ውሀ ነው….በቀላሉ ብቻ ሳይሆነ በርካሽም እናገኘዋለን.. ሰውነታችን ከየትኛውም መጠጥ በተሻለ በውሀ ይረካል…በውሃ ጤነኝነት ይሰማዋል…የውስጥ መጠማታችንን ብቻ ሳይሆን በአካልም መዛላችንን በውሀ ነው የምናክመው….ሰውነታንን የምንታጠበው የቆሸሸ ሰውነታችንን ለማጽዳት ብቻ አይደለም ውኃው በሰውነታችን ላይ ሲያርፍ መነፍስን የማረጋጋት እና የአዕምሮ ውጥረትን የማከም ኃይል ስላለው ነው…ግን ‹‹ወይ ስታጠብ ቀለል ይለኛል›› በማለት ያገኘነውን ጥቅም እናቃልለዋለን እንጂ ውሀ መድሀኒት ነው ብለን ዕውቅና መስጠት አንፈልግም ..ወሃ የደም ግፊት መድሀኒት ነው..ውሀ የኩላሊት መድሀኒት ነው…ውሃ የራስ ምታት መድሀኒት ነው…..ወሃ የበሽታዎች ሁሉ ፈውስ ነው…
‹‹የእኔ ውሃ ግን  አንቺ ነበርሽ…››አሏት እዝን እንዳሉ፡፡
‹‹ማለት……….?››አለቻቸው አሳዝነዋት፡፡
‹‹አዎ እኔ ጡረታ እስክወጣ ድረስ በዚህች ሀገር ላይ በጣም ስኬታማ ከሆኑ ጥቂት ሰዎች መካከል አንድ  ነኝ ብዬ አስብና እመፃደቅ ነበር….አምስት ስድስት ዲግሪዎች ስላሉኝ አንቱ የምባል ፕሮፌሰር ስለሆንኩ በቃ እታበይ ነበር….ልክ ጡረታ ስወጣ ግን ግማሽ ህይወት ብቻ ስኖር እንደነበር ተገለጽለኝ..እንደው ወደኃላ ተመልሶ የኖሩትን ህይወት ማስተካከል ቢቻል ካሉኝ ዲግሪዎች መካከል አንድን ብቻ አስቀርቼ ሌሎቹን በልጆች እና የልጅ ልጆች መቀየር ብችል ደስ ይለኝ ነበር..ከዛሬ 40 አመት በፊት አግብቼ ዛሬ የ35 ዓመት ልጅ እና የአምስት አመት የልጅ ልጅ ኖሮኝ ቢሆን ኖሮ በጣም ስኬታማ እና ሙሉ እሆን ነበር..ይሄን ቁጭቴን ባንቺ ነበር እየተፅናናው ለመኖር እውተረተር የነበረው…አሁን ግን….››
‹‹እንዲህ እማ አይዘኑ››
‹‹ተይኝ ልዘን…እነዛ ሁሉ ያገኘዋቸው ግኝቶች …እነዛ ሁሉ የተሸለምኮቸው ሽልማቶች እኔ ካለፍኩ በኃላ ማን ይረከባቸዋል..ማን ነው ሊኮራባቸው የሚችል የእኔ ሰው  ……….?
‹‹አሁን ወደኃላ ተመልሰው አድሉን ቢያገኙ እኮ መልሰው ተመሳሳዩን ነው የሚያደርጉት››
‹‹በፍጽም አላደርገውም..ህይወት ሚዛን መጠበቅ አላባት…እድሜሽን ሙሉ ገንዘብ ለማካበት ሰትባክኚ ቆይተሽ ካረጀሽ እና ጥርስሽ ከረገፈ በኃላ ልዝናና ብትይ አያምርብሽም… ደስታ ሚያመነጨው የሰውነትሽ ዕጢም እንዘይሙን ማምረት ስለሚያቆም አትቺይም….ወንደላጤ ሆነሽ ስትንዘላዘይ ኖረሽ በእኔ ዕድሜ ላግባ ብትይ እንዴት ተደርጎ..እንደው ሚስትዬዋ ተገኝታ ማግባት ቢቻል እንኳን እንዴት መውለድ ይቻላል..…….?ቢወለድ እራሱ የማያሳድጉትን ልጅ  እንዴት ….?ሁሉ ነገር በጊዜው ነው የሚያምረው››
‹‹እና እንዴት መሆን አለበት ይላሉ…….?››ጠየቀቻቸው
‹‹የተወሰነ መማር..የተወሰነ ገንዘብ መስራት… የተወሰን ቁጥር ያለው ቤተሰብ መመስረት…በቃ ከሁሉም የሚያስፈልገውን እና የምትጠቀሚበትን ያህል መውሰድ ነው…አየሽ አኔ አሁን ተማርኩ ከምላቸው ትምህርቶች መካከል ሁለቱን ዲግሪዎች ለአንድ ሰምንት እንኳን አልሰራሁባቸውም…እንዲሁ ለጉራ ካልሆነ በስተቀር  ያን ያህል ፋይዳ አልነበራቸውም …
በልተው እንደጨረሱ እጇን ታጥባ  እሳቸው ቢራቸውን እየጠጡ እሷ ደግሞ ወኃዋን ይዛ ወሬውን ቀጠሉ
‹‹እቤቱን እንግዲህ  ሰጥቼዎታለሁ…..››
‹‹አይ እንደዛማ አይሆንም ….እኔ እኮ ለራሴ የሚበቃ የጡረታ ብር አለኝ..ተከራይቼ ሌላ ቦታ እኖራለሁ..ቤቱ የሚገባወ ለዘመዶችሽ ነው..››
‹‹አይ ይሄ ቤት የሚገባው ለእናቴ ነበር..ግን እናቴ ከተወለደችበት አካባቢ ንቅንቅ ማለት አለትፈልግም….››
‹‹እንደዛ ከሆነ ይሸጥና ብሩን ይጠቀሙበታ››
‹‹አይዞት ለእሷ አያስቡ …በቂ የሆነ ብር ሰጣታለሁ..ይሄ ቤት ግን የሚሸጥ አይደለም…እሺ ጣሪያና ግድግዳው መሸጥ ቀላል ነው…እነዚህ ግቢውን የሞሉትን ዛፎች በስንት ብር ተምኜ ልሽጣቸው…?እነዚህ ዛፎቹን የወረሯቸውን በሺ የሚቆጠሩ ወፎች ስንት ስንት ብር ያወጣሉ...?ዝንጀሮዬን ስንት ልሽጠው..…?ጉሬዛዬንስ….?አዩ አንዳንድ ነገሮች ከሚሰጡት ጥቅም አንፃር ብቻ ሳይሆን ካለቸው ትርጉም  በመነሳት ዋጋ ሊወጣላቸው አይቻልም….አሁን ለአንድ ሀብታም ብሸጠው እኚ አሁን የጠቀስኩሎትን ሁሉ አንድ ሰምንት የሚያቆያቸው ይመስሎታል….?.ዛፎቹን ጨፍጭፎ መሬቱን ነፃ በማድረግ ፎቅ ነው ሚገነባበት…ወፎችስ እድሜ ለክንፋቸው በስደት  በመሸሽ  ነፍሳቸውን ለማቆት ይሞክራሉ..፤ሎሎቹስ….?

‹‹እሱስ ከባድ ነው››
‹‹ስለዚህ ቤቱ አይሸጥምም… ለሌላ ዘመድም ቢሆን ተላልፎ አይሰጥም…ይሄ ቦታ የሚገባው ለእርሷ ብቻ ነው..የእያንዳንዶን ዕጽዋት ሚስጥር የሚያውቁትና የሚረዱት እርሶ  ኖት… ስለዚህ የእርሶ ነው››
ፈገግ አሉ..
‹‹ምነው .. …….?ተሳሳትኩ እንዴ..…….?››አለቻቸው ፈገግታቸው የምፀት ስለነበረ ገርሞት
‹‹ስንት ዓመት ልኖር ብለሽ..…….?በተለይ አንቺ በሌለሽበት..ሁለት አመት ሶስት አመት..ከዛስ ያው የፈራሽው  መድረሱ አይቀርም..እነዚህ ሁሉ የለፋንባቸው ነገሮች አጥፊ እጅ መግባታቸው እና መውደማቸው አይቀሬ ነው…››
‹‹ስለዚህ አንድ ነገር እናድርጋ››
‹‹ምን…….?››
ከመቀመጫዋ ተነሳች..ንስሯ ለማድረግ የፈለገችውን ቀድሞ ገብቶታል ፤ ካለበት ዛፍ ላቆ ልክ ትሪኢት እደሚያሳይ የአየር ኃይል የጦር ጄት መገለባበጥ ጀመረ… እንዲህ የሚያደረግው ሲደሰት ነው…በስንት ቀኑ ፈታ አለ….. 
ወደእሳቸው ቀረበች… ግራ ገብቷቸው በዝምታ ያዩታል…. ከጀረባዋ ቆማ  ፀሎት እንደሚያደሰርስ   የፕሮቴስታንን ፓስተር ሁለት እጇን በጭንቅላታቸው ላይ ጫነችና አይኖቾን ጨፈነች…በፍጽም መመሰጥ ውስጥ ገባች….ቀስ እያለ ሰውነቷ ሲግል ይታወቃታል..አዎ ከልቧ ጀምሮ ኃይል እየተሰበሰብ በደምስሯ በመራወጥ ወደ እጆቾ እየፈሰሰ ነው…ከዛ ወደ ፕሮፌሰሩ ጭንቅላት መተላለፍ  ጀመረ…አይኖን የጨፈነች ቢሆንም እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ ይታያታል… ኃይል የሞላው ሀመራዊ ቀለም  ከፕሮፌሰሩ ጭንቅላት አንስቶ ወደ አንገታቸው..ከዛም  ትከሻቸው እያለ ወደመላ ሰውነታቸው ተሰራጨ… መንዘፍዘፍ ጀመሩ….ኦ.. ሽበት የወረረው ነጭ ፀጉራቸው...ከግንባራቸው እየተነሳ ወደ መሬት ይረግፍ ጀመር…በዛው ቅፀበት ሌላ ደማቅ ጥቁር ሉጫ ፀጉር ከእያንዳንዱ የራስ ቅል ቀዳዳቸው በመብቀል ወደ ውጭ በመውጣት ጭንቅላታቸውን ሞላው…

ይቀጥላል

#YouTube ላይ subscribe እያደረጋችሁ ቤተሰቦች #የYou tube subscriber ቁጥር 100 በሞላበት በማንኛውም ሰአት ቀጣዩን እለቃለው ለናንተ ለቤተሰቦቼ ቀላል ነው 1 ደቂቃ ይበቃዋል ወይም ከዛ በታች በሉ አሁን ጀምሩ።
👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍8410😁7👏4👎1
#ተአምረተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሃምሳ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////

ለዓመታት ጎብጦ እና አጎንብሶ የነበረ ትከሻቸው ቋቋቋቋቋ የሚል ድምጽ እያሰማ በመላቀቅ መቃናት ጀመረ…የተጨማደደ እና ተኮመታትሮ የነበረ ቆዳቸው ልክ የሽማግሌ ገፃ-ባህሪ ለመጫወት ጭንብል አጥልቆ እንደነበረ አክተር  ከፊታቸው ተሞሽልቆ በመነሳት መሬት ወደቀ…
ወዲያው መለስተኛ አውሎ ንፋስ ተነሳና እየተሸከረከረ መጥቶ እዚህም እዛም በዙሪያችን የወደቀውን የፕሮፌሰሩን የተወገደ አካል ከአካባቢው ጠራርጎ በአየር ላይ ተሸክሞ ሄደ ..
ከዛ…. ሁሉ ነገር እንዳሰበችው እንደሆነ ካረጋገጠች በኃላ እጆቾን ከጭንቅላታቸው አነሳችና…ወደመቀመጫዋ ተመልሳ ተቀመጠች…

አየቻቸው‹‹…..እንዴት አባቱ የሚያምር ጎረምሳ ሆኖል›ስትል እራሷ በሰራችው ተአምር እራሷ ተደነቀች   …‹‹ውይ እነዛ የአባቴ ዘመዶች መተው ሚወስዱኝ ባይሆን  ኖሮ ይሄን  ፊት ለፊቴ የተቀመጠውን ቆንጅዬ  ጎረምሳ አግብቼ  መኖር ነበር….›ስትል የምፀት ፈግታ ፈገግ አለች፡
ፕሮፌሰሩ ቀስ እያለ ከሰመመኑ ነቃ…
‹‹ወይ ልጄ ምድነው ያደረግሺኝ…….?ራስ ምታቴ እና ጭንቀቴ እኮ ለቆኝ ሄደ››
‹‹አሞህ ነበር እንዴ…….?››
‹‹ምን አልሽኝ…….?››ግራ ተጋብተው
‹‹ ይቅርታ አሞት ነበር እንዴ…….? ለማለት ፈልጌ ነው››
‹‹አንቺን አልረብሽሽም ብዬ ነው እንጂ እንደምትሄጄ ከሰማሁበት ቀን አንስቶ ጤናም የለኝ ነበር..››
‹‹አይ እንኳን ተሸሎት››
‹‹አረ መሻል ብቻ አይደልም …››ንግግራቸውን ሳይጨርሱ አይናቸው እጃቸው ላይ አረፈ..ተጨማዶ ና ተሸብሽቦ የነበረ እጃቸው አሁን በለግላጋ  ጣት እና ለስላሳ ቆዳ ተሸፍኖ ሲያዩት ማመን አልቻሉም… ግራ በመገባት እና  ባለማመን በጃኬታቸው ሸፈኑት..መልሰው ገለጡ…
‹‹ቆይ መጣሁ›› ብለው….ትተዋት ወደቤት በፍጥነት መራመድ ጀመሩ…ከኃላ ተከተለቻቸው…ቀጥታ ወደመኝታ ቤታቸው ሄደው የቁምሳጥናቸው መስታወት ፊት ለፊት  ነው የቆሙት….
‹‹የምን ታአምር ነው.…….?.እኔ የት ሄድኩ……….?ማን ነው ይሄ..…….?እኔ ማነኝ…….…….? ››ፊታቸውን እየዳበሱ ለፈለፉ…
መልስ መስጠት ጀመረች‹‹አሁን የ30 ዓመት ወጣት ሆነዋል..ማለት ሆነሀል፡፡…የሚፀፀቱበት ምንም ነገር የለም..ቀጣይ 45 ዓመት ተሰጥቶታል …. ስዚህ ቅድም እንዳሉት ሚዛናዊ ኑሮ ይኑሩበት..ማለቴ ኑርበት…››
‹‹ምን ጉድ ነው….…….?እኔ ወጣት…አንደገና መወለድ እኮ ነው…….?››
‹‹አዎ ነው..ልክ እንደንስር እንደገና የመታደስ ዕድል..››አለቻቸውና ቤታቸው ለቅቄ ወደራሴ ቤት አመራሁ ..ወደ እናቴ ለመሄድ ልዘጋጅ
////
ንጋት ላይ ነው ጉዞ የጀመሩት፡፡የንጋቱን ቀዝቃዛ አየርን  እየማጉ ሰማዩን ሰንጥቀው ቁልቁል የኢትዬጵያን ደቡባዊዉን መልካ ምድር እየቃኙ እየተጓዙ ነው፡፡እስኪ ትንሽ ከላይ ሆነው ቁልቁል ወደታች ሳያዩ ከፊል ኢትዬጵያ ምን እንደምትመስል አብረናቸው እንመልከት፡

ኢትዬጵያ 12 ታሪካዊ ቅርሶችን በዩኒስኮ በዓለም አቀፍ ቅርስነት አስመዝግባለች፡፡እነዚህም፤ የአክሱም ሀውልቶች፣ የላሊበላ አብያተክርቲያናት፣ የጎንደር ፋሲል ቤተመንግስት፤የሰሜን ብሄራዊ ፓርክ፣ የኮንሶ ሰው ሰራሽ መልካዓ ምድር፣ የጢያ ትክል ድንጋዮች፣የታችኛው አዋሽና የታችኛው ኦሞ ሸለቆ፣ የመስቀል ደመራ፣ የሲዳማ ፊቼ ጨንበላላ፣ የኦሮሞ የገዳ ሥርአት ናቸው። ሌሎችም ለማስመዝገብ   ላይ ያለ አሉ  በዩኔስኮ እንዲመዘገቡ በእቅድ ደረጃ የተያዙ ቅርሶችም እንደ የባሌ ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ፣ የድሬ ሼክ ሁሴን መስጊድ፣ የሶፍ ኦመር ዋሻ፣ የጌዲዩ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ መልከዓምድር፣ የመልካ ካንቱሬ የአርኪዮሎጂ ስፍራዎች ናቸው። በማይጨበጥ ባህላዊ ቅርስነት ደግሞ የአማራና የትግራይ የሻዳይና የአሸንዳ በዓላት የጥምቀት በዓል ይጠቀሳሉ። 
ኢትዬጳያ ግን ለቱሪስት ኢነደስትሪው ግብአት የሚሆኑ ሀብቶቾ እነዚህ ብቻ አይደሉም…ሀገሪቱ እራሱ ሙሉ በሙሉ በዩንሰኮ ቅርስነት ብትመዘገብ አያንስባትም…ግን በዛ መጠን የሚያስብ በዛም መጠን የሚሰሩ ልጆች ወልዳ አለማሳደጎ በጣት የሚቆጠሩትን ብቻ ማስመዝገብ ችላለች፡፡

ይገርማችኋል ይህቺ ሀገር ሙሉ ነች፡፡ሙሉ ስላችሁ ለምሳሌ አየር ፀባዮ  ደጋ ጥቂት ፈቅ ስትሉ ወይና ደጋ ..ብዙም ሳትርቁ ቆላ ታገኛላችሁ፡፡ይሄ ድንቅና መድሎ ያለበት የተፈጥሮ ስጦታ ነው…መልካ ምድሯን ስንመለከት  ለጥ ያለ ሜዳ…ደግሞ ቀጥ ያለ ተራራ..እሱ ሲገርማችሁ ጭው ያለ ገደል…በሌላ ጎኑ እንደጣባ አህያ የተራቆተ መሬት…እንደ ደብረብርሀን የሱፍ በግ ጥቀጥቅ ያለ ጫካ…ኩሬ ሀይቅ ወንዝ….አቤት እነዛ አሜሪካኖቹ ይሄን መልካ ምድር ከዚህ የተመጣጠነ ምግብ ከሆነ አየሯ ጋ ቢያገኙት.. አቤት ይሮፖዎች ያ በቆፈን የሚያኮራምት በረዶ ገላግሎቸው እንዲህ ሚዛኑን የጠበቀ አየር ቢያድላቸው ምን ያህል ተአምራዊ ህይወት ይኖሩ ነበር.. ተፈጥሮ ሚዛኗን የምትጠብቅበት የራሷ ቀመር አለት መሰለኝ ለእነሱ ሀብት ከቆፈን ጋር ስታድል ለእኛ ምርጥ አየር ከችጋር ጋር.. ያስቃል….እነሱ በቱሪስት ሆነው መልካምድሯን አይተው ለመደሰት እና አይሯን ምገው ሀሴት ለማድረግ ምቾት ባለው አይሮፕላን መጥተው ገንዘባቸውን ከስክሰው ከረምረም ብለው ይመለሳሉ..እኛ በስደት መልክ ከችግር ለመላቀቅ በእግር ተጉዘን በባህር ተጉዘን ሀገራቸው እንገባና ጉልበታችንን አንጠፍጥፈን አንገታችንን ደፍተን ስንባዝን ስንባዝን እንኖርና በዛው የውሀ ሽታ ሆነን እንቀራለን የእነሱ አንድ ነፍስ በእኛ ስንት ነፍስ እንደሚመነዘር ስሌቱ አይታወቅም ..ምን አልባት የብራችን ምንዛሬ ወይም ዋጋ ልዩነትን ያህል የነፍሳችንም ዋጋ ልዩነት ይኖረው ይሆናል…

….ይሄን ሁሉ ይምታስበው.ይሄን ሁሉ የምትመኘው በአየር ላይ ሆና ንስሯ ጀርባ ላይ ተጣብቆ ነው እየተጓዙ ያሉት… 

ያው ሰው በተፈጥሮ በመጨረሻው የህይወቱ ማብቂያ ሰዓት ቁጭት ውስጥ መግባቱ እና ፀፀቱን መናዘዙ ተለመደ አይደል..እሷም ያው በግማሽም ሰው በመሆኗ መጠን ከሰውም ኢትዬጵያዊ ስለሆነች ያው ያ ደግሞ ክርስቶስም ለስጋው አደላ የእንደሚባለው ለእሷም ለዘመዶቿ ተቆጭታ ነው እንጂማ የእሷ የአባቷ ዘመዶች በምድራዊ ዕውቀት የማይመዘን ብቃት እንዳላቸው ታውቃለች፡፡

ለማንኛውም አሁን ደሎ ደርሰዋል…ግን ቀጥታ ወደእናቷ ቤት መሄድ አልፈለገችም ..በመጀመሪያ ያደገችበትን ጫካ ልትሰናበት ፈለገች..መቼስ የደሎመና ጫካ ጫካ ብቻ አይደልም …ውስጡ  የቡና ተክል የተሰገሰገበት ነው..ልጅ ሆነው እንጨት ለቀማ ከእኩዬቾ ጋር ስትሰማራ ከቡናው ተክል ድፍኑን ሸምጥጠውን ይመጡት ነበር..የቡና ተክል ጥሬ ሆኖ ድፍን አረንጓዴ ነው …እየበሰለ ሲሄድ ቢጫ እየሆነ ይመጣል በስተመጨረሻ ሙሉ ብስል  ሆኗል የሚባለው ሙሉ ቀይ ሲሆን ነው..ታዲያ በዛን ጊዜ ፍሬውን ቀፈው ይመጣሉ…ቀዩ የቡና ገለፈት በወስጡ የያዘው ፈሳሽ ልዩ ጣዕም አለው….ሌላው የሚገርማት ይሄ አሁን ከላይ ወደታች የማታየው የደሎ ጫካ ወይም ሀራና ደን የመንግስት ነው…በውስጡ ከደኑ ጋ ተሰባጥሮ ሚገኘው የቡና ተክል ደግሞ የግለሰብ ነው….የኢትዬጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲህ ተዋህደው በስምም ሲጠቀሙ በዚህ ደን ብቻ ነው ያየችው፡፡
👍7010😢2😁1🤔1
ንስሯ ያዶት ወንዝ ውስጥ እንዲጥላት ነገረችው….አምዘግዝጎ ወሰደትና ለመዋኘት በሚመች ቦታ ከስምንት ሜትር ርቀት ላይ ስትደርስ ከተጣበቀበት እራሱን አላቀቀና ወደሰማይ ተመልሶ ተንሳፈፈ..  ተምዘግዝጋ በመውረድ ዳይቭ ገባች……ከእነልብሷ ቦጭረቅ..ደግነቱ ገና ጥዋት ስለነበረ ሰው የለም…እንግዲህ ይሄ የመጨረሻ የምትዋኝበት ቀኗ ነው… ከእናቷ እንደሰማችው አሁን የምትዋኝበት ቦታ እናቷና አባቷ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙበት ቦታ ነው…….ደጋግመውም ሲገናኙበት የነበረ ቦታ ነበር …እናም አባቷ እናቷን ወደዘመዶቹ ይዞት የሄደው በዚህ አሁን በምትዋኝበት ቦታ ይዞት በመጥለቅ ነው….አዎ ወደአባቷ መኖሪያ ስፍራ የሚወስደው ስውር መንገድ እዚህ አካባቢ ከዚህ ከያዶት ወንዝ ጥልቅ ወለል ላይ ነበር… አሁንም የአባቷ ዘመዶች ዛሬ ማታ ሲመጡ በዚሁ ቦታ  ሾልከው ይሆናል የሚመጡት እናንም ይዘዋት ሚሄዱት.. በዚሁ መንገድ ሊሆን ይችላል….ሰማየሰማያትን ሰንጥቀውም ይዘዋት ሊመጥቁ ይችላሉ….

ዋናዋን ስትጨርስ…በእግሯ ነው ወደቤቷ መጎዝ የጀመረች..ንስሯ መምጣቷን ለማብሰር ቀድሞ እናቷ ጉያ ተሸጉጡ ነው ያገኘችው..እናቷ እቤቱን በቡና አጫጭሳ..ቆንጆ የምትወደውን ገንፎ ቁርስ ሰርታላት ..እርጎ በኩባያ አቅርባላት ነበር የተቀበለቻት፡፡

‹ሀርሜ ደህና ነሽ?››

‹‹ደህና ነኝ ልጄ …›.ብላ አገላብጣ ከሳመችኝ በኃላ የረጠበ ልብሷን እንድትቀይር ሌላ የራሷን ቀሚስ አቀበለቻት…ልብሷን ቀይራ የደረበችላትን ነጭ ጋቢ ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጋ ገንፎዋን በቀንድ ማንኪያ እየዛቀችና በቅቤ አየለወሰች መዋጥ እና እርጎዋን በላዩ መማግ ጀመረች፡፡
ቡና ተጠጣ…

‹ሀርሜ…›

‹‹ማልታቴ ገረ ኮ››

‹‹ትኝት ብለን እነዋል›

‹‹ቶሌ››አለችና የዘራጋቸውን ሲኒም ከቦታው ሳታነሳ ከበርጩማዋ ላይ በመነሳት በራፉን ቀርቅራ ወደአልጋ ይዛት ሄደች ፣..ብርድልብሱን ገልጣ ገባች..ተከተላት ገባች..ንስሩም ተክትሎቸው ግን ደግሞ እንደእነሱ ብርድልብሱ ውስጥ ሳይገባ ከላይ ሁለቱ መካከል ጉብ ብሎ አደፈጠ…..

እናትዬው ጉያዋ ውስጥ ሸጎጠቻት….እሷም አንገቷ ስር ሰርሰራ ገባችና ከሰውነቷ ተጣበቀችባት….እናቷ እንደበቀደም ለታው አይነት ስሜት ላይ አይደለችም..በቀደም ወደአባቷ እንደምሄትድ ስትነግራት ጠንካራ ነበረች ..እያጀገነቻትም ነበረ….እስኪገርማት ድረስ ቀለል አድርጋ ነበር ያየችው…ምን አልባት በወቅቱ ስለልጇ መሄድ ሳይሆን ስለዕድሜ ልክ ፍቅረኛዋ ነበር እያሰበች  የነበረው…በወቅቱ ልጇን ስታወራት የነበረውን ነገር ሁሉ ለእሱ ካላት ናፍቆት በተሸፈነ ስሜት ነበር ..አሁን ግን ስብር ብላለች..አስተቃቀፎ ሁሉ የማፈን ያህል ነው…ጨምቆ መልሶ ወደሆድ በመክተት የመደበቅ ያህል..አዎ ድብት ብሎታል..ልጇ ከመጣች ጀምሮ በሁለቱም ዓይኖቾ ያቀረረ የእንባ ዘለላ ይታይ ነበር…ከሆነ አስፈሪ ስሜት ጋር እየታገለች ነው….ስለዚህ ጉዳይ ኬድሮን እያሰበች ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰዳት ..ምንም ጭንቀት የሌለበት ምንም  ህልም ያላለመችበት ዝም ያለ  ነበር..የሆነ የሞቀ ፈሳሽ ግንባሯ ላይ ሲንጠባጠብ ነው ከእንቅፏ የባነነችው.. ባለችበት ምንም እንቅስቃሴ ሳታደርግ አይኗን ገለጠችና እናቷ ከአንገቷ ቀና ብላ አይን አይኖቾን ስታይ በእጆቾ ጉንጮቾን ስትዳብስ….. ተመለከተች.. ለካ ግንባሯ ለይ እየተንጠባጠበ ሲያርሳት  የነበረው የእናቷ እንባ ነበር…

‹‹ሀርሜ ምን ሆንሺብኝ?

‹‹ከሄድሽ በኃላ እንድትመለሺ እፈልጋለሁ››

‹‹እንዴ እማ …አንዴ ከወሰዱኝ እኮ ላይመልሱኝ ይችላሉ››

‹‹ግድ የለሽም ..እንድትመለሺልኝ እንደምፈልግ ብቻ ለአባትሽ ንገሪው ፤እሱ አንድ መላ አያጣም…እኔ ያንቺን መመለስ እንደምፈልግ ካወቀ ያደርገዋል..››

‹‹አይ እማ እንደዛ ማድረግ የሚችል አይመስለኝም…››

‹‹አይ ልጄ አባትሽን የት ታውቂዋለሽ…እሱ እኮ ያለዘመዶቹ ፍቃድ ወደዚህ ምድር ሲመላለስ ነበር..እነሱ ሳይፈቅድ እኔን ማፍቀር ችሏል..ወደ ሀገሩ ይዞኝ መሄድ ችሎል..እና በአባትሽ ተማመኚ››
እንዴት አድርጋ ልታስረዳት እንደምትችል ግራ ገባት፡  እሷ በአባቷ ብቃት ሳትተማመን ቀርታ ሳይሆን አሁንም እስር ላይ እንዳለ ስለምታውቅ ነው…ይሄንን ደግሞ ለእናቷ ልትነግራት እና ጭራሽ ቅስሞን ሰብራ ተስፋ ቢስ ልታደርጋት አልፈለገችም..‹‹ግን ምንድነው እነሱጋም አማባገነንነት አለ እንዴ…?እንዴት በእኔ እድሜ ሙሉ ያራሳቸውን አካል አስረው ያኖራሉ….››ምንድነው ከሁለት አንባገነንና በፍቃድ መኖርን ከማያበረታቱ አፋኝ ፍጡሮች ነው እንዴ የተገኘሁት…››በውስጧ አብሰለሰለች፡፡.ወደ እዛ የመሄድ ፍላጎቷ ቀነሰ…

‹ልጄ አንቺ ግን አባትሽን ካየሽና የተወሰነ ጊዜ ከቆየሽ በኃላ ተመልሰሽ መምጣት ትፈልጊያለሽ አይደል፡፡››

‹‹እንዴ ሀርሜ ትጠራጠሪያለሽ እንዴ..እኔ እኮ ጭሩሱኑ መሄድ አልፈልግም››

‹‹እንደዛማ አይሆንም..መሄድሽን ካንቺ በላይ እኔ ነኝ የምፈልገው….ለአባትሽ ሳፈቅረው እንደኖርኩ አንቺ ካልሄድሽ ማን ያስረዳልኛል…አንቺ ሄደሽ አየሽው ማለት እኮ እኔም አየሁት ማለት ነው..ስያቅፍሽ እኔን እዚህ ሆኜ ይሞቀኛል…ሲስምሽም እዚህ ሆኜ እኔን እንደሳመኝ ስለምቆጥረው እንባዬን በደስታ አፈሳለሁ››

‹‹በቃ ሀርሜ ዝም ብለሽ እቀፊኝ ና እንተኛ …››

‹‹እሺ በማለት ትረሱን ዝቅ አደረገችና ከእሷ ተስተካከለችና አቀፈቻት…››

ለሁለተኛ ጊዜ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ይዞት ሄደ 

አይመሽ የለ መሸ ..ሁለት ሰዓት አካባቢ እናቷ ከመኝታዋ አስነሳቻትና ወደ ሻወር ቤት ይዛት ገባች ..ሻወር ቤቱን ከመዝጋቷ በፊት ንስሩ በራፍን የመገንጠል ያህል በረግዶት ገባና የሻወሩ እጄታ ላይ ተደላድሎ ተቀመጠ..እናት በዝምታ በራፍን ዘጋች..ወደሶፊያ ቀረበችና የለበሰችውን የራሷን ቀሚስ አወለቀችላት ፤ፓንቷንም አወለቀችላት፤ መላመላዋን ቀረቸ፡፡ ትንሽ ከእሷ ፈንጠር ብላ አየችትና ጎትታ ወደሻወሩ አስጠጋቻት..ንስሩ ውሀውን ከላይ ለቀቀው ከፀጉሯ ጀምሮ ሠውነቷ ራሠ ..እናቷ ሳሙናውን ከማስቀመጫው
አነሳችና መላ ሠውነቷን በአረፋው አዳረሰችና ትፈትግላት ጀመር...ልክ እንደልጅነቷ...እያገላበጠች ..ከዛ እንደማሰብ አለችና ሳሙናውን ካነሳችበት ቦታ የሆነ ነገር አነሳችና ስሯ ከፊት ለፊቷ ቁጢጥ አለች ..ከዛ ስትጓበኝ እንደመጣችው  የሀገሯ ደን ተንጨፍርሮ ያደገውን የብልቷን ፀጉር ትላጭላት ጀመር..ኬድሮን ከላይ ቁልቁል እናቷን እያየቻት እንባዋ  ይረግፍ ጀመርን ፡፡የጭንቋ ሰዓት ደረሰች… 
ለሊት ለስድስት አስር ጉዳይ …እቤቱን ለቀው ጊቢ ውስጥ ሶስቱም እርስ በርስ ተጣብቀው ተቀምጠዋል..እሷ እናቷና ንስሯ...አብሮነታቸውን ሊጠናቀቅ አስር ደቂቃ ብቻ ነው የቀረው..እርስ በርሳቸው መነጋገር አልቻሉም…አሷማ ሰውነቷ ሁሉ እየተንቀጠቀጠ ነው….ይሄው ሶስት ቀኑ ወደንስሯ አዕምሮ ዘልቆ ለመግባት እንኳን  ድፍረቱን ማግኘት አልቻለችም..አሁን በዚህች በመጨረሻ ሰዓት ሳይቀር  ልታደርገው  ድፍረቱ የላትም..ምን አይነት ሰቆቃ ላይ እንዳለ..ምን አይነት ሀዘን በውስጡ እንደሚብላላ ለማወቅ የሚያስችል ጭካኔውን ከየት ታምጣው  ....ውይ ደቂቃዎቹ ደግሞ እንዴት ነው የሚበሩት..7 ደቂቃ ቀረው…እናቷ ጉልበቷ ላይ አስደግፋ ጭንቅላቷን ታሻላት ጀመር…5 ደቂቃ ሲቀራው ንስሩ ከስራቸው በተተት ብሎ ተነሳና በቅርብ እርቀት  ካለ ጉቶ መሳይ  እንጨት ላይ አረፈ…ከእናቷ ጉልበት ላይ ቀና አለች….ክንፉን ዘረጋና በመንቁሩ ከክንፉ ስር የሆነ አረንጎዴ ብጣሽ ቅጠል አወጣና በቅፅበት ዋጠው..ገረማት‹‹…ከመቼ ወዲህ ነው ቅጠል በሊታ
👍794👏2
የሆነው…›› ስትል እራሷን ጠየቀች፡ለመሄጃ 3 ደቂቃ ቀረው….ንስሩ ከነበረበት ጉቶ ጥቅልል ብሎ በመንሸራተት  መሬት ላይ ተዘረረ..እናቷም እሷም በደቂቃ ውስጥ ስሩ ደረሱ..አገላበጡት…ከአይኖቹ ደም እየፈሰሰ ነው…‹‹ወይኔ እማ ቅጠሉ….. ቅጠሉ ነው..መርዝ ነው የተጠቀመው..እማ ምን እናድርግ…?››የማሰቢያ ጊዜ ሳያገኙ ግቢያችን በሰማያዊ ብርሀን ተሞላ…ቀና ስትል በሰማይ ላይ ዲስክ መሳይ መንኮራኩር ብርሀን እየረጨች ሰማየ ሰማያትን በመሰንጠቅ እነሱ  ወዳሉበት አቅጣጫ እየወረደች ነው….መጡ ማለት ነው…መጡ መሰለኝ….ወይኔ ንስሬ….

 ተፈፀመ…

ያው አልቋል ብዙ ጥያቄ እንደሚኖራቹ አልጠራጠርም ግን አልቋል ቀጣዩ ድርሰት ደሞ ምንድን ነው ቢያንስ ርእሱን ልንገራቹና YouTube ቻናሉን ከ 100 Subscriber አለፍ ስታደርጉት እንደተለመደው እንጀምረዋለን የቀጣዩ ድርሰት ረዕስ #ትንግርት የተሰኘ ልብ አንጠልጣይ ረጅም ልብ ወለድ መፅሀፍ ነው ስለዚህ ቶሎ እንዲጀመር #YouTube እየገባቹ #Subscribe አድርጉ Link ከታች አለላችሁ አሁኑኑ ከ 100 Subscriber አሳልፉትና እንጀምረው👍

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
😱70👎38👍2216👏8🤔4🎉3😢1
🍃በ'ነሱ ቤት🍃
🍄ክፍል ሠላሳ አራት🍄
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
መሳይ ጌታነህን ስታገኘው  በመጀመሪያ የመጣላት ነገር ከበጎ አድራጊ ዎቹ ጋር አገናኝቷት ጉዳይዋን በማሳዘን እንድትነግራቸው መክሯት ዞር የሚል መስሏት ነበር ።ነገር ግን መኪናው ውስጥ አስገብቷት  እርዳታ ሊያደርጉላት የሚፈልጉት ሰዎች ቤተሰቡ መሆናቸውን እና ይህንን ድጋፍ የመስጠት ግዴታ እንዳለባቸው በመተማመን ሲያወራ ግራ መጋባት ውስጥ ከተታት ። እናም ልቧ ፈራ ይሄልጅ የእውነት ቁም ነገረኛ ነው ወይስ አይምሮው ንክ ነው ሲያወራ እራሱ  ያልተረጋጋ መሆኑ ያሳብቅበታል ብላ ማሰቧን አላቆመችም ። ከረጅም ጉዞ በዋላ ከዚበፊት በምታውቀው መንደር ውስጥ ታጥፎ ገባ እናም አካባቢው ላይ ያላት ትውስታ አንድ በአንድ መጣባት ።ከአስራ ስምንት አመት በፊት በዚ መንደር ውስጥ ተመላልሳበታለች ። በመጨረሻም ልጇን አርግዛ ስትባረር በዚሁ ድንብርብር እያለች ወጥታበታለች ። በጣም በተጠጋች ቁጥር ያ የአብታሞች መንደር የቀለም ለውጥ ከማድረጋቸው በስተቀር እንዳሉ ናቸው ፣ ልቧ መምታት ጀመረ ፊቷን ወደ ጌታነህ አዙራ ተመለከተችው ። በዝምታ ወደፊት ለፊቱ እያየ ነዳ ትንሽ ሄድ ብሎም አንድ ግዙፍ የተንጣለለ ጊቢ ጋር ሲደርስ አቆመ ።የመሳይ ልብ አብሮ የቆመ መሰለ ።ይህንን ጊቢ ታውቀዋለች ።ጌታነህ ከመኪናው ወርዶ እየከፈተላት እንድትወርድ ጠየቃት መንቀሳቀስ አልቻለችም ።እጇን ያዝ አድርጎ እንድትወርድ ለመናት ፣ሰውነቷ መንቀጥቀጥ ጀመረ ።
"እባክህ....."አለች ቃላት እያማጠች
"እባክሽ ውረጂና ከቤተሰቦቼ ጋር ላስተዋውቅሽ እኔ የዛ ባለጌ ወንድም ነኝ የመስፍን ከዚቤት የሚገባሽን እንድታገኚ እስከመጨረሻው ልረዳሽ ዝግጁ ነኝ አትፍሪ "አላት  መሳይ እንደምንም ከመኪናው በመውረድ ጌታነህ ላይ አፈጠጠች "ባቢ አንተ ነህ እንዲ ትልቅ የሆንከው "አለችው
"አንቺ ታውቂኛለሽ እኔ ግን ምንም ነገር አላስታወስኩሽም ነበር "አላት በመገረም እያያት
"እኔ አልረሳም ትንሽ ልጅ ነበርክ ልታስታውሰኝ አትችልም ግን እንዴት አወቅክ "አለችው ተገርማ
ጌታነህ አብላካትን እንዴት መጀመሪያ ከጓደኞቹጋር እንዳገኛት ፣ከዛ ምን ሲፈጠር እንደነበረ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ ፈጠን ፈጠን እያለ ነግሯት በረጅሙ ተነፈሰ ።የአብላካት መጨረሻ ሞት እንዳይሆን ፈርቷል።  መሳይ የሚንቀጠቀጠውን እጇን ማስቆም አቅቷታል ። ጌታነህ ሁኔታዋን ሲያይ ትንሽ ማረጋጋት ያስፈልጋል ብሎ በማሰብ ተመልሰው መኪናውስጥ ገብተው መነጋገር እንደሚችሉ ነግሯት መኪናውስጥ ገቡ እናም ስለቤተሰቦቹ ሁኔታ አወራት አብላካተሸ መታመሟን እና እርዳታ እንደሚያስፈልጋት ስታወራ በቴሌቭዥን ቤተሰቡ ሁሉ እንዳይዋት እና ማንነቷንም እንዳወቁ ከዛ በጣም መደናገጣቸውን ።ከዛ ልጅቷ የራሳቸው ዘር መሆኗን አምነው ለማሳከም እንደፈለጉ አወራት ። መሳይ ያለፈውን አስታውሳ እልህ ያዛት አይሆንም ብላ ጌታነህ ላይ ጮኽች ።
"እንዴት አይሆንም ትያለሽ እኛም እኮ በልጅቷ ላይ መብት አለን ቤተሰባችን ናት ዝም ብለን ስትሞት ልናይ ነው"አላት ተቆጥቶ
"እኛ አትበል አውጥተው ጥለውኛል ከመስፍን አላረገሺም እርሺው ብለው ነው የወረወሩኝ አሁን ምን ተገኘ"ብላ አለቀሰች
"እየነገርኩሽ ነው እንኳን ወላጆቼ መስፍንም ተፀፅቷል ልጁ እንደሆነች አምኗል በወቅቱ የነበረው ነገር አሁን ላይ የለም "አላት ሊያግባባት እየጣረ
"አይ ከነሱ አምሳንቲም አልፈልግም "አለች በደከመ ድምፅ ውስጧ ግን ሲሸነፍ ይታወቃታል
"ላንቺ አይደለም ለአብላካት ነው  መዳን አለባት እኔም ከዚ በዋላ እህት ይኖረኛል  እባክሽ እራስ ወዳድ አትሁኚ "አላት ቀናብላ ስታየው ቆይታ ።አንገቷን በመነቅነቅ ።ውስጧ እያዘነ ተስማማች ። ሌላስ ምን መላ አላት የታመመች ልጅ ይዛ ብትኮራ ምን ሊያዋጣት ። ጌታነህን ተከትላ ወደ ጊቢው ዘለቀች ።ጊቢው ውስጥ እንደገቡ መናፈሻ በመሰለው ስፍራ ላይ ክብ ጠረቤዛ ከበው ተቀምጠው የነበሩት የጌታነህ ወላጆች ቆም ብለው ጠበቋቸው ። ሲቀርቧቸው የጌታነህ እናት የነበረባትን ትምክህት ጣል አድርጋ  ይቅር በይኝ በማለት የመሳይ እግር ላይ ተደፋች መሳይ ያልጠበቀችው ነገር ስለነበር ድንብርብሯ ጠፋ ደጅ ላይ የፎከረችው ነገር ጥሏት ጠፋ የጌታነህን እናት ከመሬት ላይ በማንሳት ፣አቅፋት አለቀሰች ። ጌታነህ ሁኔታው አስለቀሰው ። መሳይን ወላጆቹ ደጋግመው ይቅርታ እየጠየቁ ሲያይ ወላጆቹን እንዲ ተቀይረው በማየቱ ጉድ አለ ። ለማንም ግድ የሌላቸው የሱ ኩሩ ወላጆች ተንበረከኩ ።ይሄ መቼስ ስለ አብላካት ነው ሌላ አይደለም 'ይሄ ቆሞ የቀረ ልጃቸው የልጅ አባት ሊሆን ነው'ብሎ በውስጡ ሳቀ ። ብቻ በፍጥነት ሄዳ ትታከም ......
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨?፨?፨??
አብላካት እናቷ የሄደችበት ጉዳይ ተሳክቶ ሁሉም ነገር ሰላም እንዲሆን በልቧ ደጋግማ ፀለየች ። እናቷን እዚ ምድር ላይ ብቻዋን ጥሎ መሄድ በጣም ያማል ያ እንዲሆን ፈጣሪዋ እንደማይፈቅድ ለራሷ እየተናገረች ትፅናናለች ። ሰሚር ስልኩን እየነካካ አልፎ አልፎ ትክዝ ብላ የተቀመጠችውን አብላካትን ያያል ። ከቆይታ በዋላ ስልኩ ተደወለ አንስቶ ሲያየው ሰመረ ነው ተነስቶ ሊወጣ ፈልጎ ነበር መልሶ ተወው እና አነሳው
"ሃሉ "
"ሰሚር የት ነው ያለኽው እባክህ ልምጣ ሚጣ ጋር ውሰደኝ "አለው ቅስሙ ስብር ብሎ
"እኔ አሁን እሷው ጋር ነኝ እናቷ ስለወጣች አብሬያት ልቆይ ብዬ ነው"
"እሺ አቅጣጫውን ንገረኝ እመጣለው "አለው ሰሚር የሰመረ ሁኔታ አሳዘነው እሱ ከመጀመሪያው ጀምሮ ለአብላካት ጥሩ ነበር ታዲያ ለምን አብሯት እንዳይሆን ይከላከላል ?በጭራሽ!   ።አቅጣጫውን ነገረው ሰመረ እሺ ብሎ ስልኩን ዘጋው ።
"እሺ ለማን ነው ደሞ ቤቴን የምትነግረው ኪኪኪ ስንት ሺብር ይዘን መጣን አሉክ ?"አለችው አብላካት እግሯን እያሻሸች
"ሲመጡ ታያለሽ ምን አስቸኮለሽ "
"ስንት ናቸው"
"አንድ ነው ስታይው የምትወጂው ይመስለኛል"ብሎ ሳቀ
"ማነው "አለች ኮስተር ብላ
"ሲመጣ ማንነቱን እራሱ ያስተዋውቀናል"
"ደረቅ "ብላ ለመነሳት ስትል ወጋት በከባዱ አቃሰተች አስተናጋጁ ሰሚር በድንጋጤ ሄዶ አቀፋት እጆቹ ላይ ልፍስፍስ ስትልበት "አቢ አቢ ደና አይደለሽም አቢ..........."እያለ ተጣራ ,,,,,,,,,,,,

,ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍504
🍄በ'ነሱ ቤት🍄
👁ክፍል ሠላሳ አምስት👁
🌻🌻🌻🌻
አስተናጋጁ ሰሚር አብላካትን ታቅፎ ይዟት ከቤት ወጣ
በፍርሃት ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ አካባቢውን ወዲወዲያ አየ ። የነአብላካት ጎረቤቶች ያለወትሮ ቤታቸው ተከተዋል  አይኖቹን አሻግሮ ሲያይ የሰፈር ጎረምሶች ተቀምጠው ሲጫወቱ አየ እናም ጮክ ብሎ
"እባካቹ እርዱኝ እባካቹ "አለ  ጎረምሶቹ ተሯሯጡ
"ምንድነው፣ ምን ሆነች ?አብላካት ነች ?ምን ተፈጥሮ ነው ?ኧረ በደንብ ያዛት !"  የተለያየ ጥያቄ እያከታተሉ በአስተናጋጁ ሰሚር ዙሪያ ተሰባሰቡ ።
"እባካቹ ልትሞትብኝ ነው ! ድንገት እራሷን ሳተች አኪም ቤት መድረስ አለባት መኪና ጥሩ ልኝ ፍጠኑ እባካቹ "እያለ ወደፊት ተሸክሟት እንደመሮጥ አለ
"እሺ እሺ  ዳንኤል እቤት ካለ መኪና እንዲያመጣ እንንገረው  "አለ አንደኛው ወደ ጎረቤት ቤት እየሮጠ
"እባካቹ ቶሎ በሉ !?አቢዬ ጠንከር በይ አይዞሽ ተንፍሺ ...." እያለ ሰሚር ፈጠን ለማለት ሞከረ 
እንዲ ሲዋከብ የሰፈር ጎረምሶችም ፣በድንጋጤ እርዳታ ፍለጋ ወዲወዲያ እያሉ  ሲከተሉት ከርቀት አንድ መኪና በነሱ አቅጣጫ ሲመጣ አዩት ሦስት ጎረምሶች አስገድደው ሊያሰቆሞቱ ወደሱ ተሯሯጡ እናም አስቆሙት ትንሽ እንደማንገራገር ሲል አስተናጋጁ ሰሚር እጁላይ አብላካትን ታቅፎ ሲመጣ የሰፈር ሰው አጅቦት ሲለቃቀስ አየ ።ከመኪናው በፍጥነት ወጣ ። አስተናጋጁ ሰሚር ሲያየው እንባ ተናነቀው "ሰሚር ምን ተፈጠረ ደና ነች ና ና ልቀበልህ" ብሎ ተጠጋው
"ሰመረ ፍጠን እንኳን መጣህልን ቶሎ አኪም ጋር መድረስ አለባት ትንፋሿ እየተቆራረጠነው "አለ ሰመረ ከእጁ ተቀበለውና የመኪናው የዋላ ወንበር ላይ በጥንቃቄ አስተኛት አስተናጋጁ ሰሚር ገብቶ እግሩላይ ጭንቅላቷን አስደገፋት ። ሰመረ በፍጥነት ገብቶ መኪናውን አስፈነጠራት በጣም ደንግጧል አልቦታል ደጋግሞ ለፈጣሪው ይፀልያል .....
"ምን ተፈጥሮ ነው ስደውል ደናነች ብለኽኝ ነበር"
"አዎ ድንገት ነው ለመነሳት ስትሞክር አቃስታ የወደቀችብኝ "አለ አስተናጋጁ ሰሚር
"ምግብ አልበላችም ?"
"ያን ያክል አልወሰደችም " አለ አስተናጋጁ ሰሚር ።
ሰመረ የልብ ምቱ አስፈራው አብላካት በዚ ዕድሜዋ ያሳለፈችው ፈተና አስጨነቀው የዛሬን ደና ከሆነች ሊጠብቃት ቃል ገባ ብቻ ምንም አትሁን እንጂ የሚከፈለውን መስዋት ከፍዬ አሳክማታለው  ወላጆቼንም ቢሆን አስቸግሬ በነሱ ዙሪያ ያሉትንም ሰዎች አሰባስቤም ቢሆን ፈጣሪ እባክህ እንድትሞት አታድርግ ,,,,,,,,,,,,,


,ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍9921🎉2👏1😁1
👁በ'ነሱ ቤት👁
🍄ክፍል🍄🍄
ሠላሳ ሥድስት
🌻🍃🌻🍃🌻🍃
በነ ጌታነህ ቤት ሰላም የወረደ ይመስላል ፣ ቤተሰቡ ከእንግዳዋ መሳይ ጋር የተረጋጋ ወሬ ይዘዋል ፣ በመሃል በመሃል መሳይ ላይ ቅሬታ ቢታይም ። ግንኙነታቸውን ጤናማ ለማድረግ የበኩላቸውን እየጣሩ ነው የሚገኙት ። ጌታነህ በመሃል ሆኖ ሁለቱንም ወገን ለማስማማት መልካም አሳብ ሲያጋራ ነው የቆየው  በዚ ደሞ ውጤታማ ሆኗል ። በተለይ መስፍን እና መሳይ ሲተያዩ ሊፈጠር የነበረውን የሰላም መደፍረስ እንዲቀር አድርጓል ።  በዚም እናቱ ኮርታበታለች ። ያለውን ቁርሾ ሁሉ ትተው የታዳጊዋን ሕይወት ማትረፉላይ ማተኮር እንዳለባቸው ተመካከሩ እናም ።መሳይ ሁሉን ትታ ስለልጇ ተሸንፋ ተስማማች ፣ ለመጀመሪያ ጊዜም ለልጇ መመኪያ የሚሆናት ግዙፍ ቤተሰብ እንዳላት አስባ ስለልጇ ተፅናናች ። በመጨረሻም ወደቤቷ ለመሄድ ተነሳች ፣ መስፍን ፈጠን ብሎ ሊሸኛት ተነሳ እሷ አያስፈልግም አለች ፣አስራ ስምንት አመታቶችን በሱ ምክንያት አፈር በልታለች ምን እንደሰራት በአጭር ጊዜ ለዛውም በሰአታት ምንም እንዳልተፈጠረ መርሳት አልችል አለች ። ጌታነህ ነገሩ ስለገባው ፣ጠጋብሎ 'መስፍን ተረጋጋ እንዲ በፍጥነት አይሆንም ። ጌዜ ያስፈልጋታል ባንተ የተነሳ ምን እንዳሳለፈች አታውቅም 'አለውና እኔ እሸኛታለው ፣ አብላካትንም በዛው አያታለው ከዶክተሯ ጋርም ስላለው ነገር እነጋገራለው ። እናም በአፋጣኝ ወደውጪ ሄዳ እንድትታከም እናደርጋለን እናንተም ተዘጋጁ አላቸው። የጌታነህ ወላጆች በአንድ ቃል ሁሉንም ነገር ተዘጋጅተናል ጊዜ የለም ልጃችን በሕይወት እንድትቆይ ማድረግ ያለብንን ሁሉ እናደርጋለን ። መስፍን በመሃል ጣልቃ ገብቶ 'እኔ ኩላሊት ልሰጣት ዝግጁ ነኝ እንኳን አንዱን ሁለቱንም ሰጥቻት ብሞት አይቆጨኝም ፣ ልጄን እንደገደልኩ የማነሳትም እኔነኝ እላለው እባካቹ ይህን ማድረግ አትከልክሉኝ 'ብሎ ለመነ ሁሉም በዝምታ አለፉት ። መሳይ ያ ኩሩና ትህቢተኛው የሀብታም ልጅ መስፍን አልመስል አላት ።ወይ ጊዜ ስንት ነገር ይቀይራል ብላ ተገረመች ። በዚ መሃል ስልኳ ጮኾ አነሳችው በፍርሃት ፣ስልኩ ላይ ሰሚር አብላካት ሆስፒታል መግባቷን ሲነግራት ስልኩን በቁሟ ለቀቀችው ሁሉም ደነገጡ ። ጌታነህ በፍርሃት የወደቀውን ስልክ ሲያነሳው የሰሚር ድምፅ መጣ "ሃሉ ምንድነው "አለው ጌታነህ
"ሃሉ ኧረ ደና ነች እኮ አሁን"አለው
"ሰሚር ነህ ምን ተፈጠረ"
"አይ ድንገት እራሷን ስታብኝ አኪም ቤት ወስደናት ነበር እክምና ተደርጎላት አሁን ደና ነች"
"ጥሩ መጣን በቃ"አለው
"እሺ አብሮኝ ሰመረ አለ ጓደኛህ "አለ ሰሚር ድንገት ሲገናኙ ቅሬታ እንዳይፈጥር በማሰብ
"ምን ከየት አወቀ የት አገኘህ ለሱ ደውለህ ነው እንዴ "አለው ግራ በመጋባት
"አይ ልክ እንደ እናንተ ሳገኘው ስለሷ ነግሬው ነበር ባጋጣሚ ሊረዳት ሲመጣ ታማ አገኛት እና አብረን ነው አኪም ቤት ይዘናት የሄድነው ።እሱ መኪና ይዞ ባይመጣ ነገሩ ሌላ ነበር "አለው እንዳይቆጣው እየፈራ
"አንተ ግን እሱ ጋር ማስቸገር አልነበረብህም እኔ እንደምጨርሰው ነግሬህ ነበር ።እሺ ይሁን መጣን"አለውና ስልኩን ዘጋው ።አፋቸውን ከፍተው ሲሰሙት የነበሩት ቤተሰቦቹ ሰላም መሆኑን ሲነግራቸው እፎይ አሉ ከዛም አንድላይ ለመሄድ ተነሱ ።,,,,,,,,,,,,,,,


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍12521👏1
👁በ'ነሱ ቤት👁
🍃🍄ክፍል ሠባት🍄🍃
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
ሆስፒታል ሲደርሱ አስተናጋጁ ሰሚር ነበር የተቀበላቸው ፣እናም በፍጥነት ያለችበትን ክፍል ጠየቁት እሱም አብላካት የተኛችበትን ክፍል ካሳያቸው በዋላ እውስጥ ሰው ስላለ ትንሽ መጠበቅ እንዳለባቸው ሊያስረዳቸው ሞከረ ።
ጌታነህ ማነው ሰው ብሎ ቆጣ አለበት ፣ሰሚር ሲፈራ ሲቸር  ነገረው "አይ ሰመረ ነው ማለት..."
"ሰመረ "አለው እና ዝም አለ ። የአብላካት እናት መሳይ "ማነው ሰመረ ?"ብላ ጠየቀች
"ከዚ በፊት እኮ ስለሱ ነግራሽ ታውቃለች ያ መንገድ ላይ አግኝቷት የረዳት ኧረ እንደውም እኮ የጌታነህም ጓደኛ ነው "አለ አስተናጋጁ ሰሚር ጭንቅ እያለው ።የጌታነህ ቤተሰቦች እርስ በእርስ ተያይተው ።"ሰመረ የኛ እንዴ እሱም ያውቃል "አሉ ። አስተናጋጁ ሰሚር አንገቱን ነቅንቆ አዎ የሚል ምልክት አሳያቸው።
"እና መግባት አንችልም ነው እሱ ካልወጣ "በማለት ጌታነህ እየተመናቀረ ሄዶ አብላካት የተኛችበትን ክፍል አንኳኳ!
ከውስጥ ሰመረ የአብላካትን እጅ በእጁ አቆላልፎ አይኖቹ ዕንባ እንዳዘሉ በቀስታ የምታወራውን ያዳምጣል ፣አብላካት ለራሷ የመጨረሻዬ ነው ብላ ስላሰበች ለሰመረ የሚሰማትን ስሜት ሳትደብቅ ነበር እየነገረችው ያለችው ፣ሰመረ አንዳች ነገር ሳይናገር እጇን እያሻሸ ግንባሯን እየነካካ ያዳምጣታል እናም ደሞ ዕንባው አምልጦት ከፊቷ አልቅሶ ደክሞ እንዳያደክማት እየተጠነቀቀ ነው ።ግን አልችል ብሏል የአብላካት ለሱ ያላት ስሜት ትልቅ መሆኑን ሲያውቅ ልቡ መረበሹን አበዛበት እናም ጎንበስ ብሎ ግንባሯን ሳም ካደረጋት በዋላ"ሚጣ ተይ እሺ እንዳበቃለት ሰው አታውሪ ምንም አትሆኚም "አላት
"ግንኮ ዛሬ አብቅቶልኝ ነበር ነገም ምን ሊፈጠር እንደሚችል አላውቅም ፣ለዚነው እንዲ በፍጥነት ላንተ ያለኝን ስሜት የምነግርህ ፣ጤነኛ ብሆን ኖሮ መቼም የምነግርህ ነገር አልነበረም ፣እንዲሁ ፍቅሬን ይዤው ነበር የምኖረው ፣ አሁንግን ሁሉንም ይዤው ከምሞት ብነግርህ ይሻላል ፣በርግጥ ዛሬ አንተ ባትመጣ አልናገረውም ነበር ግን መጣህ እድሜ ለሰሚር ፣እሱን በጣም ነው የማመሰግነው እኔ አይሆንም ያልኩትን ነገር ሁሉ ቢያደርግም ፣ግን ውጤቱ ክፋት የለውም ፣አንተን በመጥራቱ ሁሉም ነገር ቀሎኛል "አለችው እና ተነፈሰች
"የኔ ሚጢጢ"አላት
"አብላካት ነው ስሜ "ብላ ፈገግ አለች
ጠጋ ብሎ ጉንጯን ሳም አድርጓት ሲመለስ በሩ ተንኳኩቶ ምላሽ ሳይጠብቅ ተከፈተ ። እናም ጌታነህ ገብቶ ሲያፈጥ ሁለቱም እርስ በእርስ ተያዩ ፣አብላካት ተገረመች እና ደሞ የሰሚር ስራ ነው ሁሉንም ሰበሰበ እሺ ይሁን እኔን ለማዳን ካለው ጉጉት የተነሳ ነው ደሞም እናቴ ልታገኘው ሄዳ አልነበር እንግዲ መፍትሄ አገኘው ብሎ ሊያደርቀኝ ይሆናል ።ብላ አሰበች ጌታነህ እራሱን ተቆጣጥሮ ሰመረን ሰላም ካለው በዋላ እሷን ጎንበስ ብሎ አይን አይኗን ሲያይ ቆይቶ
"አይዞሽ ሁሉም ነገር በቅርቡ ያበቃል ደና ትሆኛለሽ እሺ እርዳታ ሊያደርጉልሽ ፍቃደኛ የሆኑት ቤተሰቦቼም አብረውኝ እዚ መጥተዋል አንቺ ብቻ በርቺ እሺ"አላት እና ፀጉሯን ደባበሳት ፣አንገቷን ነቀነቀች በመስማማት ሰመረ በመገረም ሲያየው  ግድ ሳይሰጠው ።
"እባክህ ቤተሰቦቼ እና የአብላካት እናት ቆመዋል አስገባቸው "አለው
"ከልብህ ነው እነሱ ሊረዷት ይፈልጋሉ ሙሉ ወጪ ችለው "አለው
"እሱን በደንብ እናወራበታለን ከነምክንያቱ አሁን ተጨንቀዋል አስገባቸው "አለው ።ግራ የተጋባው ሰመረ ወጣ ብሎ እነሱን አሰገባቸው ለሰላምታ እንኳ ጊዜ ሳይሰጡት ተቻኩለው ወደውስጥ ገቡ ፣እናት ስፍስፍ ብላ ከአልጋው አጠገብ በርከክ ብላ አብላካት ላይ ተደፋች ፣መስፍን ለመጀመሪያጊዜ የካዳት ልጁን ሲያያት ልቡ በፀፀት ዘለለበት የጌታነህ ወላጆች በቁንጅናዋ ለየት ያለችው የልጅልጃቸው አንሰፈሰፈቻቸው ።
አብላካት ግራ እንደገባት ነው ሁሉንም በተራ ተራ እያየቻቸው ነበር ፣በተለይ በሩን ተደግፎ ዕንባውን ኮለል እያደረገ የሚያወርደውን ጎልማሳ አይታ አይኗን መንቀል አቃታት,,,,,,,



ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍13517😱8
🍄በ'ነሱ ቤት🍄
👁ክፍል ሠላሳ ሥምንት👁
🍃🌻🍃🌻🍃🌻
አብላካት የሁሉንም መንሰፍሰፍ ስታይ ሆድ ቢብሳትም ስሜቷን ዋጥ አድርጋ እናቷን ወደሷ እንድትጠጋ አድርጋ በጆሮዋ "እማ ለምንድነው እንዲ ማለቴ የዚህን ያክል ለኔ የሚሆኑት ፣ስለ እርዳታው ሳይሆን እያለቀሱ እኮ ነው ?"አለቻት
"የኔ አበባ አትጨነቂ እነሱ ያው አሳዝነሻቸው ነው የሚሆነው በዛላይ ያው የጌታነህ ቤተሰቦች ናቸው ።እሱን ደሞ ታውቂዋለሽ አይደለ "ብላት ሌላ ነገር ላለመናገር እራቅ አለች ። መስፍን አላስችልህ ብሎታል ።ሄደህ እቀፋት አፅናናት የሚል ስሜት እየገፋፋው ነው ።  የጌታነህ እናት ጠጋ ብላ እጇን በአብላካት እራስ ላይ ጣል አድርጋ እያሻሸቻት፣
"አይዞሽ የኔ ውድ የፈጀው ይፍጅ እንጂ ከነገ ጀምሮ ዝግጅትሽ ይካሄዳል ፣ እሺ "አለቻት አብላካት ሁሉም ነገር ግር ቢላትም እሺ ብላ ዝም አለች ፣ ቀጥሎ መስፍን ጠጋብሎ እጇን በስስት ይዞ ሲነካካት ፣አይኗን ከሱ ላይ መንቀል አቃታት ፣በዚጊዜ የአብላካት እናት ሳግ ስለተናነቃት ቶሎ ብላ ክፍሉን ለቃ ወጣች ፣ ጌታነህም አብሯት ወጣ ፣ከደጅ ሰመረ እና አስተናጋጁ ሰሚር ተቀምጠው ሲጠብቁ አገኟቸው ። ሰመረ እነሱ ሲወጡ ቀረብ ብሎ ችግር እንዳለ ጠየቀ ።"ምንም ችግር የለም ሁሉም ይፈታል እናመሰግናለን "አለው ጌታነህ
"ቀይ ቀይ ቀይ እንዴት እንዴት ነው የምታናግረኝ ደርሰህ ቤተሰብ ልሁን አልክ እኮ "አለው ሰመረ
"ስማ ካንተጋር የምጨቃጨቅበት ጊዜየለኝም ከአኪሟ ጋር መነጋገር እና በአሰቸኳይ ፕሮሰሷን ማስጀመር አለብኝ "ብሎ ጥሎት ሄደ
"በጣም ጎረርክ ጉዳዩን ቀድሜ ብሰማ ይሄን ማድረግ የማልችል ይመስልሃል ?!"አለው ጌታነህ ዝም ብሎት ሄደ ።ወደ አስተናጋጁ ሰሚር ዞሮ
ሰሚር አንተ ነህ ቀድመህ ብትነግረኝ ኖሮ የዚ ጉረኛ እጅ ላይ አትወድቅም ነበር "አለዎ
"ኧረ እኔ የሷን መዳን ነው የምፈልገው "ብሎ አቀረቀረ
"ቢሆንም እሱ ከሷ ምን እንደሚፈልግ እያወቅክ "ሲል የአብላካት እናት ስትሰማ ቆይታ "እባክህ ጌታነህ ከሷ ምንም አይፈልግም ሊሆንም አይችልም"አለችው
"አይ አንቺ ስለማታውቂ ነው "አለ ሳያስበው ቆጣ ብሎ
"ምንም ማወቅ አያስፈልገኝም አይሆንም አልኩ ህ እኮ"አለችው እሷም ኮስተር ብላ
"እንዴት እንዲ ትያለሽ ያብላካት እናት "አለ
"ምክንያቱም እሱ አጎቷ ነው ፣መስፍን ደሞ አባቷ ነው እነዛ እውስጥ ያሉት አያቶቿ ናቸው "አለችው በጩኽት። ሰመረ እና አስተናጋጁ ሰሚር ጆሮ አቸውን ተጠራጥረው እኩል አፍጥጠው እያይዋት
"ምን!!!?"ብለው ጠየቋት ።ደገመችላቸው ሰመረ የዞረበት መሰለው ሄዶ ወንበር ላይ ተቀመጠ
ከራሱ ጋር ማውራት ጀመረ"ጌታነህ የአብላካት አጎት መስፍን የአብላካት አባት በየት በኩል ነው እንዴ ከየት ወደየት ነው  "ጨንቅላቱን በሁለት እጆቹ ማሻሽት ጀመረ ደጋግሞ ሆሆሆሆ ይላል ,,,,,,አስተናጋጁ ሰሚር ከአብላካት እናት ጋር ስለሆነው ነገር ይነጋገራል በጣም ተገርሟል የሕይወት አዙሪት ከየት ወደየት ቤተሰቡን አዙራ አምጥታ እንዳገናኘች ተገርሟል ።
፨፨፨፨፨፨፨፨

ይቀጥላል......
ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍1114
🍄በ'ነሱ ቤት🍄
ክፍል ሠላሳ ዘጠኝ
👁👁👁👁👁
አብላካት ወደ ውጭ ወጥታ በፍጥነት እንድትታከም በስተመጨረሻ ያገኘቻቸው የጣሏት ቤተሰቦቿ ገንዘብ ስራውን ሰራ ። ገንዘብ ካለህ በሰማይ መንገድ አለ እንደሚባለው ፣ አብላካትን ግራ ያጋባትና ሚስጢር ያደረጉባት ነገር ቢኖር የመስፍን ጉዳይ ነው ፣ መስፍን ተመርምሮ ሁለቱም ኩላሊቶቹ ንፁ መሆኑን ካረጋገጠ በዋላ ለልጁ ኩላሊቱን ሊለግሳት በተስማማ ጊዜ ፣ የሱ ቤተሰቦች ለነገሩ አዲስ ሆነው ባይከራከሩትም ፣አብላካት ግን እንዴት 'ማንነቴን ጠንቅቆ የማያውቀኝ ሰው በዚመጠን ሊረዳኝ ፈለገ 'ብላ እናቷን በጥያቄ አፈጠጠች ፣ የአብላካት እናት ግን ምክንያቱን ወደፊት ልትነግራት እንደምትችል እና ለጊዜው ግን በጎ አድራጎቱን አመስግና እንድትቀበል አግባባቻት ፣
የመስፍን ኩላሊት እናም የጤና ጉዳይ መልካም ካልሆነ ፣ሰመረ በድፍረት እሱ ለአበበ ላካት ኩላሊቱን ሊያጋራ ቃል ገብቶ ነበር ። መሳይ የሰመረን ሁኔታ ስታይ ለልጇ ያለውን አመለካከት ወዳዋለች ፣ ልጇ አሁንም ድረስ ለሷ ዕፃን ብትሆንም ፣ የሰመረን አላፊነት የሚሰማው  ሰውነት ግን ስላየች ተማምናበታለች ። ጌታነህ ደሞ አሁን ላይ ከሰመረ ጋር የነበረው ፉክክር ቀርቶ ፣ አላፊነት እንደሚሰማው አጎት ፣ ሰመረ ሌላ ነገር በአብላካት ላይ እንዳይከጅል እየተከላከለ ይመስላል ።
በመጨረሻ አብላካት ከጌታነህ እና ከመስፍን ጋር እንድትሄድ በመወሰኑ ፣ ሁኔታው ባይመቻትም ድና ለእናቷ ልጅ ለመሆን ስለጓጓች ፍቃደኛ ሆነች ፣በሽኝቷ ጊዜ እናቷ አልቅሳ መልካሙን ሁሉ እንዲገጥማት እንደምትፀልይላት ነግራ አቅፋ ተሰናበተቻት ፣አስተናጋጁ ሰሚርም ፣የጌታነህ ቤተሰቦችም ፣በፈረንሳይ ቅር አቅፈው ተሰናበቷት ። ሁሉንም ከተሰናበተች በዋላ ፣በአይኖቿ ሰመረን ፈለገችው ፣ጥግ ላይ ቆሟል ዝምብላ ስታየው ፣ሰውነቱ ቅጥቅጥ እያለበት እንደምንም ቀረባት ፣
"ምንድነው ጌታው መጥቼ ልሰናበተዎት እንዴ"አለችው በቀልድ ። ጌታነህ ሲገላምጠው ቢያይም ፣እጁን የአብላካት አገጭ ላይ አሳርፎ የግዱን ፈገግ እያለ" የኔ ሚጢጢ አንቺ ጠንካራ ራ ልጅ ነሽ በሙሉ ጤንነት እንደምትመለሺ አምናለው ፣"አላት
"በመጀመሪያ ደረጃ ሚጢጢህን ሄደ ፈልግ እሺ ! ስሜን ላስታውስህ እንዴ ?"
"ሚጣ አይደለውም !አብላካት ነው ስሜ ! ልትይኝ ነው አይደል አቢዬ  ይታወሳል ቂያለሽ ይሄን ድምፅሽን ሁሌም እናፍቀዋለው !ደና ሁኚልኝ እሺ !"አላት አይኖቹ እንባ እያቆረዘዙ ። አብ ላካት የማትቆጣጠረውስሜት ገፍቶ ሰመረን እንድታቅፈው አደረጋት እሱም አላስቻለውም ወደራሱ አስጠግቶ አቀፋት ሁሉም ተያይተው ዝም አሉ ፣ ጌታነህ ግን ብዙም አልተደሰተም ፣ ምክንያቱም ጌታነህ የጓደኝነታቸው ጊዜ ላይ በሴቶች ላይ ያላቸውን አመለካከት ስለሚያውቅ በዛ ስሜት የወንድሙ ልጅ እንድትታሰብበት በጭራሽ አይፈልግም ፣እራሱም ታማኝ ስላልነበረ ማንንም አያምንም ። ሁለቱንም ቆጣ እንዳለ ካላቀቃቸው በዋላ ሰመረን የማስጠንቀቅ አይነት እይታ አይቶት አብላካትን ይዟት ሄደ,,,,,,,,,,,,,
👁👁👁👁👁👁👁👁👁👁👁👁
የአብላካት እናት በየቀኑ ስልክ እየተደዋወለች ፣ስላለው ነገር ከጌታነህ ኢንፎርሜሽን ታገኛለች የልጇ ሁኔታ በፍፁም ጤንነት ላይ እንዳለ በማወቋ ደስተኛ ነች ። አልፎ አልፎም እነ ጌታነህ ቤት ሄዳ ተጫውታ ትመለሳለች ፣  ቅዳሜ ቀን ነው የመጨረሻ እክምናዋ የሚደረግበት ፣ተብላ ለሊቱን ሙሉ ስትቃዥ ነበር ያደረች ፣ ሲነጋጋ እንደተጨነቀች ስልክ እየጠበቀች ቆየች ፣ ሰአት በሄደ ቁጥር ልቧ መምታቱን መጨነቁን ከፍ አደረገች ፣ጌታነህ አልደወለም ፣ ተነስታ ቤተ ክርስቲያን ሄደች ፣ፀሎቷን በእንባ ታጅባ አደረገች ፣ከቤተክርስትያን ተመልሳ ወደቤቷ አቅጣጫ ለመሄድ መንገድ ጀምራ ተወችውና ወደነ ጌታነህ ቤት ገሰገሰች ፣እነሱጋር ስትደርስ እነሱም ተጨንቀው አገኘቻቸው ፣ ለረጅም ሰአት ተፋጠው ቆዩ ፣ ጌታነህ አልደወለም ፣የአብላካት እናት ለቅሶ ጀመረች ፣ የጌታነህ እናትም አገዘቻት ሁለቱም ሲለቃቀሱ ፣የጌትነህ አባት መገሰፅ ጀመረ ፣አታሟርቱባት ብሎም ተቆጣ ፣ "እስካሁን መደወል ነበረበት"ብላ ባሰባት ።የጌታነህ እናት"ኧረ እኔ ፈራው  "አለች በመሃል ስልክ ጮኽ ሦስቱም በፍርሃት ተያዩ ፣የሚጮኽው የመሳይ ስልክ ነበር እየተንቀጠቀጠች ስልኳን አነሳችው ,,,,,,,,,,,,,,,


ይቀጥላል......
ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍12214👏3😁3👎1