ግን ክፋቱ በፈለግናት ጊዜ ስለምናገኛት…በጣራናት ጊዜ ሮጣ ስራችን ስለምትገኝ ዋጋዋን ብዙም አናውቀው…. እንደድንገት ስትነጠለን እና ከእጃችን ተንሸራታ ስናጣት ግን አንድ ሰው ብቻ እንዳልነበረች ይገለጽልናል…መላ ዓለም እሷን እንደማይተካልን ትምህርት እናገኛለን…ግን ትምህርት ቀድሞ ያጣኸው ነገር ወደፊት ዞሮ መጥቶ እንድታስተካክለው እድሉን ካላገኘህ ጥቅም የለውም..በደንብ ስትፀፀት እድትኖር ብቻ ነው የሚያግዝህ፡፡
ውሃም በቀላሉ ነው የምናገኘው..እኛ እራሱ በዋናነት የተሰራነው ከውሀ ነው ..ምድርም ሶስት እጆ ውሀ ነው….በቀላሉ ብቻ ሳይሆነ በርካሽም እናገኘዋለን.. ሰውነታችን ከየትኛውም መጠጥ በተሻለ በውሀ ይረካል…በውሃ ጤነኝነት ይሰማዋል…የውስጥ መጠማታችንን ብቻ ሳይሆን በአካልም መዛላችንን በውሀ ነው የምናክመው….ሰውነታንን የምንታጠበው የቆሸሸ ሰውነታችንን ለማጽዳት ብቻ አይደለም ውኃው በሰውነታችን ላይ ሲያርፍ መነፍስን የማረጋጋት እና የአዕምሮ ውጥረትን የማከም ኃይል ስላለው ነው…ግን ‹‹ወይ ስታጠብ ቀለል ይለኛል›› በማለት ያገኘነውን ጥቅም እናቃልለዋለን እንጂ ውሀ መድሀኒት ነው ብለን ዕውቅና መስጠት አንፈልግም ..ወሃ የደም ግፊት መድሀኒት ነው..ውሀ የኩላሊት መድሀኒት ነው…ውሃ የራስ ምታት መድሀኒት ነው…..ወሃ የበሽታዎች ሁሉ ፈውስ ነው…
‹‹የእኔ ውሃ ግን አንቺ ነበርሽ…››አሏት እዝን እንዳሉ፡፡
‹‹ማለት……….?››አለቻቸው አሳዝነዋት፡፡
‹‹አዎ እኔ ጡረታ እስክወጣ ድረስ በዚህች ሀገር ላይ በጣም ስኬታማ ከሆኑ ጥቂት ሰዎች መካከል አንድ ነኝ ብዬ አስብና እመፃደቅ ነበር….አምስት ስድስት ዲግሪዎች ስላሉኝ አንቱ የምባል ፕሮፌሰር ስለሆንኩ በቃ እታበይ ነበር….ልክ ጡረታ ስወጣ ግን ግማሽ ህይወት ብቻ ስኖር እንደነበር ተገለጽለኝ..እንደው ወደኃላ ተመልሶ የኖሩትን ህይወት ማስተካከል ቢቻል ካሉኝ ዲግሪዎች መካከል አንድን ብቻ አስቀርቼ ሌሎቹን በልጆች እና የልጅ ልጆች መቀየር ብችል ደስ ይለኝ ነበር..ከዛሬ 40 አመት በፊት አግብቼ ዛሬ የ35 ዓመት ልጅ እና የአምስት አመት የልጅ ልጅ ኖሮኝ ቢሆን ኖሮ በጣም ስኬታማ እና ሙሉ እሆን ነበር..ይሄን ቁጭቴን ባንቺ ነበር እየተፅናናው ለመኖር እውተረተር የነበረው…አሁን ግን….››
‹‹እንዲህ እማ አይዘኑ››
‹‹ተይኝ ልዘን…እነዛ ሁሉ ያገኘዋቸው ግኝቶች …እነዛ ሁሉ የተሸለምኮቸው ሽልማቶች እኔ ካለፍኩ በኃላ ማን ይረከባቸዋል..ማን ነው ሊኮራባቸው የሚችል የእኔ ሰው ……….?
‹‹አሁን ወደኃላ ተመልሰው አድሉን ቢያገኙ እኮ መልሰው ተመሳሳዩን ነው የሚያደርጉት››
‹‹በፍጽም አላደርገውም..ህይወት ሚዛን መጠበቅ አላባት…እድሜሽን ሙሉ ገንዘብ ለማካበት ሰትባክኚ ቆይተሽ ካረጀሽ እና ጥርስሽ ከረገፈ በኃላ ልዝናና ብትይ አያምርብሽም… ደስታ ሚያመነጨው የሰውነትሽ ዕጢም እንዘይሙን ማምረት ስለሚያቆም አትቺይም….ወንደላጤ ሆነሽ ስትንዘላዘይ ኖረሽ በእኔ ዕድሜ ላግባ ብትይ እንዴት ተደርጎ..እንደው ሚስትዬዋ ተገኝታ ማግባት ቢቻል እንኳን እንዴት መውለድ ይቻላል..…….?ቢወለድ እራሱ የማያሳድጉትን ልጅ እንዴት ….?ሁሉ ነገር በጊዜው ነው የሚያምረው››
‹‹እና እንዴት መሆን አለበት ይላሉ…….?››ጠየቀቻቸው
‹‹የተወሰነ መማር..የተወሰነ ገንዘብ መስራት… የተወሰን ቁጥር ያለው ቤተሰብ መመስረት…በቃ ከሁሉም የሚያስፈልገውን እና የምትጠቀሚበትን ያህል መውሰድ ነው…አየሽ አኔ አሁን ተማርኩ ከምላቸው ትምህርቶች መካከል ሁለቱን ዲግሪዎች ለአንድ ሰምንት እንኳን አልሰራሁባቸውም…እንዲሁ ለጉራ ካልሆነ በስተቀር ያን ያህል ፋይዳ አልነበራቸውም …
በልተው እንደጨረሱ እጇን ታጥባ እሳቸው ቢራቸውን እየጠጡ እሷ ደግሞ ወኃዋን ይዛ ወሬውን ቀጠሉ
‹‹እቤቱን እንግዲህ ሰጥቼዎታለሁ…..››
‹‹አይ እንደዛማ አይሆንም ….እኔ እኮ ለራሴ የሚበቃ የጡረታ ብር አለኝ..ተከራይቼ ሌላ ቦታ እኖራለሁ..ቤቱ የሚገባወ ለዘመዶችሽ ነው..››
‹‹አይ ይሄ ቤት የሚገባው ለእናቴ ነበር..ግን እናቴ ከተወለደችበት አካባቢ ንቅንቅ ማለት አለትፈልግም….››
‹‹እንደዛ ከሆነ ይሸጥና ብሩን ይጠቀሙበታ››
‹‹አይዞት ለእሷ አያስቡ …በቂ የሆነ ብር ሰጣታለሁ..ይሄ ቤት ግን የሚሸጥ አይደለም…እሺ ጣሪያና ግድግዳው መሸጥ ቀላል ነው…እነዚህ ግቢውን የሞሉትን ዛፎች በስንት ብር ተምኜ ልሽጣቸው…?እነዚህ ዛፎቹን የወረሯቸውን በሺ የሚቆጠሩ ወፎች ስንት ስንት ብር ያወጣሉ...?ዝንጀሮዬን ስንት ልሽጠው..…?ጉሬዛዬንስ….?አዩ አንዳንድ ነገሮች ከሚሰጡት ጥቅም አንፃር ብቻ ሳይሆን ካለቸው ትርጉም በመነሳት ዋጋ ሊወጣላቸው አይቻልም….አሁን ለአንድ ሀብታም ብሸጠው እኚ አሁን የጠቀስኩሎትን ሁሉ አንድ ሰምንት የሚያቆያቸው ይመስሎታል….?.ዛፎቹን ጨፍጭፎ መሬቱን ነፃ በማድረግ ፎቅ ነው ሚገነባበት…ወፎችስ እድሜ ለክንፋቸው በስደት በመሸሽ ነፍሳቸውን ለማቆት ይሞክራሉ..፤ሎሎቹስ….?
‹‹እሱስ ከባድ ነው››
‹‹ስለዚህ ቤቱ አይሸጥምም… ለሌላ ዘመድም ቢሆን ተላልፎ አይሰጥም…ይሄ ቦታ የሚገባው ለእርሷ ብቻ ነው..የእያንዳንዶን ዕጽዋት ሚስጥር የሚያውቁትና የሚረዱት እርሶ ኖት… ስለዚህ የእርሶ ነው››
ፈገግ አሉ..
‹‹ምነው .. …….?ተሳሳትኩ እንዴ..…….?››አለቻቸው ፈገግታቸው የምፀት ስለነበረ ገርሞት
‹‹ስንት ዓመት ልኖር ብለሽ..…….?በተለይ አንቺ በሌለሽበት..ሁለት አመት ሶስት አመት..ከዛስ ያው የፈራሽው መድረሱ አይቀርም..እነዚህ ሁሉ የለፋንባቸው ነገሮች አጥፊ እጅ መግባታቸው እና መውደማቸው አይቀሬ ነው…››
‹‹ስለዚህ አንድ ነገር እናድርጋ››
‹‹ምን…….?››
ከመቀመጫዋ ተነሳች..ንስሯ ለማድረግ የፈለገችውን ቀድሞ ገብቶታል ፤ ካለበት ዛፍ ላቆ ልክ ትሪኢት እደሚያሳይ የአየር ኃይል የጦር ጄት መገለባበጥ ጀመረ… እንዲህ የሚያደረግው ሲደሰት ነው…በስንት ቀኑ ፈታ አለ…..
ወደእሳቸው ቀረበች… ግራ ገብቷቸው በዝምታ ያዩታል…. ከጀረባዋ ቆማ ፀሎት እንደሚያደሰርስ የፕሮቴስታንን ፓስተር ሁለት እጇን በጭንቅላታቸው ላይ ጫነችና አይኖቾን ጨፈነች…በፍጽም መመሰጥ ውስጥ ገባች….ቀስ እያለ ሰውነቷ ሲግል ይታወቃታል..አዎ ከልቧ ጀምሮ ኃይል እየተሰበሰብ በደምስሯ በመራወጥ ወደ እጆቾ እየፈሰሰ ነው…ከዛ ወደ ፕሮፌሰሩ ጭንቅላት መተላለፍ ጀመረ…አይኖን የጨፈነች ቢሆንም እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ ይታያታል… ኃይል የሞላው ሀመራዊ ቀለም ከፕሮፌሰሩ ጭንቅላት አንስቶ ወደ አንገታቸው..ከዛም ትከሻቸው እያለ ወደመላ ሰውነታቸው ተሰራጨ… መንዘፍዘፍ ጀመሩ….ኦ.. ሽበት የወረረው ነጭ ፀጉራቸው...ከግንባራቸው እየተነሳ ወደ መሬት ይረግፍ ጀመር…በዛው ቅፀበት ሌላ ደማቅ ጥቁር ሉጫ ፀጉር ከእያንዳንዱ የራስ ቅል ቀዳዳቸው በመብቀል ወደ ውጭ በመውጣት ጭንቅላታቸውን ሞላው…
✨ይቀጥላል✨
#YouTube ላይ subscribe እያደረጋችሁ ቤተሰቦች #የYou tube subscriber ቁጥር 100 በሞላበት በማንኛውም ሰአት ቀጣዩን እለቃለው ለናንተ ለቤተሰቦቼ ቀላል ነው 1 ደቂቃ ይበቃዋል ወይም ከዛ በታች በሉ አሁን ጀምሩ።
👇
https://www.youtube.com/@atronose

👍84❤10😁7👏4👎1