አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
481 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ከሰል እና ፌሮ ተሸካሚ ልወድ አልችልም፤ሰፈራቸው ደብተራ ይበዛል?

"ወንድ ሁሉ ውሻ ነው፤ሮዝ ሙች፤ሰራተኛዬ እኮ የሆነ መጋጫ ነገር ነች፤መልከ ጥፉ አይገልጻትም፤ ግራ
ቂጤ ከሷ ፊት ይነጻል፡፡ ከኔ በምን ተሸላ ነው ከሷ ጋር የሚባልገው?

ፍቅርተ በአሹ የተነሳ ህዝበ አዳምን አምርራ ጠላች፤ለመበቀልም ዛተች፤ለአሹ ስትል የከሰከሰችው
ሀብትና ንብረት የእግር እሳት ሆኖ ያቃጠላት፤ከብስጭቷ ለመገላገል ከዚህ ቀደም የሌለባትን አመል እመጣች፤ አልኮል አብዝታ መጠጣት ጀመረች፤ማርቲ እንደነገረችኝ ፍቅርተ ስትጠጣ
አያምርባትም፤ከሁሉም ጋር ትላተማለች፡በተለይ ከሆቴሉ ደምበኞች ጋር ወንዶችን በስድብ ዶፍ ታጥረገርጋቸዋለች፡በዚሁ ተናካሽ ጸባይዋ ብዙ ጊዜ ከሆቴሉ ደምበኖች ዱላ ተቃጥቶባት ገላጋዮች
አትርፈዋታል፡፡ይኸው ክፉ አመልዋ ለአመታት ተከትሏት ከትላንት በስቲያ ለቀመሰቸው የሞት ጽዋመንስኤ ሆነ፡፡

ትዳር ሁለት፣የፍቅርተ ገዳይ

ፍቅርተ በደበበ ተክሌ ለአመት ያህል ከሰራች በኋላ እንደገና ፍቅር አገረሽባት፤አሁን ግን ፍቅር የጀመረችው እንደ አሹ ካለ መናጢ ጋር አልነበረም፣ይሄኛው ሀብታም ነው፤የክፍለ ሀገር ሀብታም፡፡ በተደጋሜ ጎበዝ
ገበሬ ተብሎ በቲቪ ሲሸለም ታይቷል፡፡ ከአንድም ሁለት አይሱዞዎች አሉት፡፡ አንድ ቅጥቅጥ ካቻማሊ አለው፡፡ መንግስት ስለሚወደው ገጠር ብዙ መሬት ሰጥቶታል፡፡ የኢህአዴግ አባል ስለሆነ ጉዳይ ቶሎ ይፈጸምለታል፡፡ በስራው ታታሪ ነው፣ እረፍት አያውቅም፡፡ ጎልማሳ ነው፤ፍቅርተ እንደነገረችኝ በአስራ
አራት አመት ይበልጣታል፡፡ሸሌነቱን አስትቷት በትዳር ጠቀለላት፡፡ፍቅርተ ከኛም ራቀች፡፡ከዘጠኝ ወራት በኋላ ደውላ ከማርታ ጋር አገኘችን፣ከምሳ ጀምሮ አብረን ዋልን፤ነፍሰጡር ናት፡፡

በዚያን ወቅት በትዳር ህይወቷ መማረር ጀምራ ነበር፤ባልዋ ከነመኖራ ረስቷታል፣እንደሷ አባባል ወሲብ
ከፈጸሙ ወራት ተቆጥረዋል፣ እሱ ሁልጊዜ ለመሸለም እና በቲቪ ለመታየት ነው የሚሰራው፡፡ እኔን ረስቶኛል እያለች ታማራለች፡፡

ከባሌ ጋር በአንድ ቤት እየኖርን ከተፋታን ቆይተናል፤ትዳር አትበሉት!ቀን ስለ ቢዝነሱ ሲብሰለሰል እና የፓርቲ ስብሰባ ሲመራ ይውላል፤ማታ በአልኮል ድንብዝ ብሎ ከእኩለ ሌሊት በኋላ ይመጣና ጀርባው
ሰጥቶኝ ይተኛል"

ማርቲ በፍቅርተ ሀዘን በግና ነበር፤

ታዲያ ምን እየጠበቅሽ ነው?ለምን አትፈቺውም?ገንዘቡ ለምን ጥንቅር ብሎ አይቀርም! ፍቅርተ ከሺሻው
አንዴ ከማገችለት በኋላ ማርቲን በአትኩሮት ተመለከተቻት፤
“ማርቲ!ወንዶች ሲባሉ አንድ ናቸው፤በቁጥጥራቸው ውስጥ እስከትወድቂ ነው የሚንከባከቡሽ የእነሱ
እንደሆንሽ ሲያረጋግጡ ይረሱሻል፤ መጀመሪያ ከኔ ፍቅርና ወሲብን ይፈልግ ነበር፤አሁን በሆዴ ያለውን ልጅ ብቻ ነው የሚፈልገው፤እኔም ልጄን እስከገላገል ነው የምታገሰው፣"

ሆኖም ፍቅርተ ያለችውን አላረገችም፤ ወልዳ ወራት እና አመታት ከተቆጠሩ በኋላም ከሱ ጋር ኑሮዋን ቀጠለች፣ እንደበፊቱ ግን ነጻነቷን አልገታችም፣ ፍቅርተ እንደገና ፈነዳች፡ከኛ ጋር በየቀኑ መገናኘት ጀመረች፤ምሳ ከበላን በኋላ እየቃምንና እየጠጣን እንውላለን፤ማታ ከባልዋ ጋር ሁለቱም በስካር ቅኝት ላይ
ሆነው ይሰዳደባሉ፡፡
ፍቅርተ ሰከረች

ማርታ እንዳጫውተኝ የፍቅርተ ባል ቢሰከርም የመሳደብ ልማድ አልነበረውም፡የፍቅርተን ባህሪ
የወረሰው ከአንድ አጋጣሚ በኋላ ነበር፡፡ባል ሊጠጣ ሲፈልግ ፒያሳ ከሚገኛው እና ከሃያ በላይ ሸሌዎች በአይነት በአይነቱ ከሚርመሰመሱበት ናሽናል ሆቴል ይገባል፣ያዘዘውን መጠጥ እየጠበቀ አይኑን ሲያማትር
ፍቅርተን ከአንድ ወንድ ጋር እየጠጣች ያያታል፤በመጀመሪያ አይኑን ተጠራጠረ ህልም ይሁን እወን ግራ ተጋብቷል፡እሷ አይታው ፈግግ ስትል በብርሀን ፍጥነት ከተቀመጠበት ተነስቶ አንገቷን አንቆ ከሆቴሉ አስወጣት፣መኪናው ውስጥ ወርውሯት ነጎደ፡፡

“ጥፋተኛው እኔ ነኝ!ሸርሙጣ ሁሌም ሸርሙጣ ናት!ደሞ እዚህ ቤት ምን ልትሰሪ መጣሽ?"

"ደበበ ተከሌ ሆቴል አብረውኝ ይሰሩ የነበሩት ማርቲና ዝናሽ እዚህ ስለገቡ ላገኛቸው ነው የመጣሁት፤በጣም
ናፍቀውኛል' ባል አላመናትም፤
አንቺ ደደብ ሸርሙጣ ደድበሽ እንደ ደደብ አትመልከቺን እኔ የተከበርኩ ሰው ነኝ፡፡ እንኳን አንቺ መንግስት ያከበረኝ ሰው ነኝ፡፡ ያገኘሁሽ እኮ ከምትያቸው ሴቶች ጋር አይደለም ከወንድ ጋር እየጠጣሽ
ስትገለፍጪ ነው ያገኘሁሽ!"

"የድሮ ደምበኛዬ ነው!በአጋጣሚ ነው እዚህ ቤት ያገኘሁት!ከመጫወት ውጪ ያደረግነው ነገር የለም

ቀጣፊ ሸርሙጣ ስለሆንሽ አላምንሽም..ጓደኞቼን ምክር አልሰማ ብዬ ነው ያገባሁሽ.ሰው ላደርግሽ
ነበር

ፍቅርተ እሳት ለበሰች፤ በሞቅታ መለሰችለት፤

ታዲያ አንተም ልትሸረሙጥ ስለመጣህ ምኑ ያስገርማል…?”

በማግስቱ ማርቲ የፍቅርተን ፊት አባብጦና በላልዞ አገኘችው፤ባል ከፉኛ ደበደባት፡፡

በሽማግሌዎች ተታርቀው የትዳር ጥምረታቸውን ቀጠሉ፤ሁለቱም ሰከረው እየመጡ መሰዳደባቸው ግን
ቀጠለ፤በዚህ ሁኔታ ወራት አለፉ…

ፍቅርተ በመጨረሻዋ ሰአት

ለቀስተኛው ስለ ፍቅርተ አሟሟት ብዙ ሲያወራ ሰምቼያለሁ፤ሁሉም ጎረቤቶቿ ገዳዩ እጁን ለፖሊስ ሲሰጥ እየጮኸ በተደጋጋሚ የተናገረውን በደንብ ሰምተዋል፡፡
ከትናንት በስቲያ ምሽት ባል ምንም ሳይጠጣ ገብቶ ልጁን ያጫውታል፡፡4፡30 አካባቢ ፍቅርተ ሰክራ ገባች፤አቅሏን እስክትስት ጠጥታለች፣ባል ላይ የተለመደ የስድብ ናዳዋን ታወርደው ጀመር፡፡ባል ሆደ ሰፊ ሆኖ በሰላም ክፍሏ ገብታ እንድትተኛ በተደጋጋሚ ተማጸነ፡፡ፍቅርተ በስድቧ ቀጠለችበት፡፡በስካር
እንደምታወራ የተገነዘበው ባል ምንም መልስ አልሰጣትም፡፡ቢጨንቀው ለልጇ ስትል መኝታ ከፍሏ ገብታ
እንድትተኛ ጠየቀ፤

እባክሽ ፍቅርተ፡ባንቺ ሁኔታ ልጃችን ይረበሻል፤ምናለ ገብተሸ ብትተኚ!"

የተከተለው የፍቅርተ መልስ ባልን በንዴት ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ሽጉጡን እንዲመዝ አስገደደው፡፡

እንዴት አፍህን ሞልተህ ልጃችን ትላለህ?ያንተ ልጅ እንደሆነ በምን እርግጠኛ ሆንከ?”

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 Share እያደረጋችሁ #MUTE ያደረጋችሁ #UNMUTE አድርጉ እባካችሁ ሁሌ የምለጥፈውን ለመከታተል ቻናሉን #Favorites ውስጥ አስገቡት #አመሰግናለው

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍81
አድራ ስለምትመጣ ቀን ላይ ብርሃን ልትጠይቀኝ ብቅ ስትል “ብርሃን በእናትሽ ቶሎ ቶሉ ነይ” አልኳት፤ ልመና ነበር ውስጤ!

“ደህና ነሽ?” አለችኝ ግራ ገብቷት፤ ዝም አልኩ፡፡

ይቀጥላል

Like 👍 Share እያደረጋችሁ #MUTE ያደረጋችሁ #UNMUTE አድርጉ እባካችሁ ሁሌ የምለጥፈውን ለመከታተል ቻናሉን #Favorites ውስጥ አስገቡት #አመሰግናለው

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍1
‹‹በቃ አልቅሰሽ ቅበሪኝ….ከዛ በኃላ ሞተ የእያንዳንዱ ሰው ዕጣ ፋንታ መሆኑን አምነሽ ተቀበይና ወደ ህይወትሽ ተመለሺ…የራስሺኝ ሰው ፈልገሽ ኑሮሽን  ኑሪ….የእኔ በድን ታቅፈሽ እዚህ ቤት ባሳለፍሽው ስድስት ቀናት ውስጥ ስራ ላይ ብትሆኚ ኖሮ ሰንት ነፍስ  እንደምታታርፊ አስበሽዋል….… ?ስንት ያንቺን ክትትል የሚፈልጉ ህመምተኞችን እርግፍ አድረግሽ በመተውሽ  በያሉበት ምን ያህል እየተሰቃዩ እንደሆኑ ታውቂያለሽ….…?ያባትሽን መንፈስ ለዘላለም ለማስደሰት እውነታውን ተቀብለሽ  ፈገግ በይ ..በእኔ ስም የአዛውንቶችን ጤንነት ተንከባከቢ…እኔን እያሰብሽ ሞያሽን በጥንቃቄ እና በታማኝነት ስሪ..እያንዳንዱ ሰው ባንቺ እጅ ታከሞ በመዳኑ ተደስቶ ፈገግ ሲል  እኔም ባለሁበት  ፈገግ እንዳልኩ በማሰብ ውስጥሽ ሀሴት ታድርግ….›.

‹‹አዎ አባ እውነትህን ነው..እንዳልከው አደርጋለሁ››

‹‹ስለዚህ ተስማምተናል››

‹‹አዎ አባ ..ተስማምተናል››

‹‹በቃ ደህና ሁኚ ልሄድ ነው

‹‹አባ ከመሄድህ በፊት ››

‹‹እሺ ምንድነው…?››

‹‹ግን ገነት ነው ምትገባው አይደል…?››

‹‹አይ ልጄ..መች ሄድኩና አውቀዋለሁ ..ግን ምንም አይት ፍራቻ እየተሰማኝ አይደለም….እረፍትና እፎይታ ነው ዙሪያዬን የከበበኝ….የሚታየኝ  አንፀባራቂ ብርሀን እንጂ ፅልመት አይደለም….እና ፈጥኜ የመሄድ ፍላጎት ነው ያለኝ…ባከሽ ልጄ እንድዘገይ አታድርጊኝ..››

‹‹እሺ አባ ..አንድ የመጨረሻ ጥያቄ››

‹‹ምን ልጄ…?››

‹‹እማዬን ታገኛታለህ…?››

‹‹አዎ ልጄ ተስፍ አደርጋለሁ..በጣም መቸኮሌ አንድም ለዛ ይመስለኛል››

‹‹እንደምወዳትና በጣምም እንደናፈቀቺኝ ንገርልኝ››

‹‹እሺ ነገርልሻለሁ››
ደግሞ ቀኔ ደርሶ ወደእናንተ  ስመጣ ከእናንተ ጋር አብሬያችሁ መኖር ነው የምፈልገው››

‹‹እሺ ልጄ  እንዳልሽ…ደህና ሁኚልኝ…››

‹‹እሺ አባ ደህና ሁን››

ይቀጥላል

#YouTube ላይ subscribe
እያደረጋችሁ ቤተሰቦች ከ110,000 እዚ ካላችሁት ሩቡ እንኳን subscribe ቢያደርግ አስባችሁታል ይሄን ድርሰት ያነበበው ሁሉም ቢያደርግም ቀላል አደለም ግን አብዛኞቻችን አንብበን ነው የምንወጣው ስለዚህ አንብባችሁ ስትጨርሱ ወደ #YouTube ሄዳችሁ Subscribe
እያደረጋቹ #አመሰግናለው
👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍12122😢15👎6😁4