አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሶስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// በእቅዷ መሰረት ኩሪፍቱ ይገኛሉ….ትናንትና ከመሸ ነው የገቡት፡፡ከጥዋቱ ሁለተ ሰዓት አካባቢ ሆኗል..መኝታውን ለቆ ተነስቶ ክፍል ውስጥ ሲንጎራደድ ከጀመረ 30 ደቂቃ ያህል አልፎታል አንዴ መታጠቢያ ቤት ይገባል…አንዴ ወደበረንዳ ይወጣል…እኔ እየሰማው ቢሆንም አንቅልፍ ውስጥ እንዳለ ሰው አድፍጣ ዝም….መታጠቢያ ቤት ሲገባ ፈጠን…»
#ባል_አስይዞ_ቁማር
:
:
#ክፍል_ሀያ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

በማግስቱ ነው…እሷ ገንዳ ውስጥ ገብታ ትዋኛለች እሱ እየሠረቀ ይመለከታታል..
‹‹ለምን ገብተህ አብረሀት አትዋኝም?"
"አብረሀት ማለት?"ስኳር ሲሰርቅ እንደተያዘ ህፃን በርግጎ ጠየቃት፡፡

"እንዴ በአይንህ እኮ ዋጥካት"

"ስርዓት ያዢ እንጂ… የራስሽው ጓደኛ መስላኝ?"

"እሱማ እዚህ ከመምጣታችን በፊት ነዋ ..አሁንማ ቀማሀኝ..ለማንኛውም ይመቻችሁ"አለችውና ከተቀመጠችበት ተነሳች፡፡ጉንጩን ሳመችውና መራመድ ጀመረች፡፡
ደንግጦ"እንዴ! ወዴት ነው?"

"እግሬን ላፍታታ"
‹‹ልከተልሻ"አለ ከመቀመጫው እንኳን ለመንቀሳቀስ ሳይሞክር

"አይ ብቻዬን ይሻለኛል ››

‹‹ እሺ እዚሁ እንጠብቅሻለን›› ብሎ ሸኛት...ደስ አለት።ደስ ያለት ተንኮል ስላሠበች ነው።

ትንሽ እራቅ እንዳለች እንዳያዮት ተጠንቅቃ በዛፍ ተከልላ ተጠማዘዘችና ወደመኝታ ክፍል አመራች፡፡ ...እንደደረሰች  ልብሷን ቀያየረች ።ሻንጣዋን አዘጋጅታ ።ከቦርሳዋ  ዘወትር እንደምታደርገው እነዛን የድመት አይን የመሰሉ ካሜራዎችን ድብቅ ቦታ አስተካክላ አስቀመጠች..ወደጊፊቲ ክፍል ስትሄድ ፅዳቷ እያጸዳች ነበር፡፡

‹‹…ይሄንን ቻርጅ ከጎደኛዬ ተውሼ ልመልስላት ነበር..››አለችና ዝም ብላ ገብታ ኮመዲኖ ላይ ቻርጁን አስቀመጠች… የእሷን እይታ በሰውነቷን ጋርዳ እዛው ኮመዲኖ አጠገብ ካለ የቴሌቪዥን ጠርዝ ላይ የካሜራውን አይን ለጠፈችው….መልሳ ቻርጀሩን አነሳችና‹‹እንደውም ሀሳቤን ቀየርኩ እስክትመጣ ብጠቀምበት ይሻላል›› ብላ ወጥታ ሄደች….ቀጥታ የመኪናውን ቁልፍ እያወዛወዘች ወደ መድሀኔ መኪና ነው ያመራችው..ከፈተችና ገባች… መኪናውን አስነስታ ኩሪፍቱን ለቃ ወጣች ።30 ደቂቃ ከነዳች በኃላ ስልኳን አወጣችና…፡፡
‹‹መኪናህን ይዤ ከጊቢ ወጥቼያለሁ ከሁለት ሰዓት በኃላ እመለሳለሁ ››ብላ መልዕክት ላከችለትና ስልኳን አጠፍችው።
////
አዲስአበባ ገብታ እቤቷ ከደረስች በኃላ ነበር. ስልኳን ስትከፍት ሰዓቱ አንድ ሰዓት አልፎ ነበር ..ከከፈተች ከአስር ደቂቃ በኃላ ተደወለላት።

‹‹አንቺ የት ነሽ?››

"እቤቴ›››

‹‹ ማለት?"

"እቤቴ ነዋ.. አዲስአበባ..."
" ግን ጤነኛ ነሽ...?ምን ሆንኩኝ ብለሽ ነው?"ከንዴቱ ብዛት ድምፁ እየተቆራረጠ እና እየተርገበገበ ነበር..፡፡
"ምንም ..አሰኘኝ አደረኩት ..ለማንኛውም ለሹፌርህ ነግሬልሀለው...አሁን እቤት መጥቶ መኪናህን ወስዷል …ጥዋት እስከሁለት ሰዓት ይደርስልሀል፡፡"

"በጣም ታበሳጪያለሽ…  እኔስ ይሁን አንዴ ፈርዶብኛል.. የሠው ሠው ከቤቷ አክለፍልፈሽ አምጥተሽ  ባዶ ሜዳ ላይ ጥለሻት ትሄጂያለሽ?››

"ባዶ ሜዳ ላይ አይደለም  አንተ ላይ ነው ጥያት የመጣሁት...አንተ ማለት ደግሞ እኔ ነህ...ምነው ተሳሳትኩ እንዴ?››
"አሽሟጠጥሽ ማለት ነው...በይ ቻው"ብሎ ጠረቀመባት ።

እሷ ግን ሁሉም ነገር በእቅዷ መሠረት እየሄደ ስለሆነ  ደስ አላት።
///
"ሶስት ሰዓት የጀመረች ይሄው እስከአራት ሰዓት ተኩል ላፓቶፖን  አስተካክላ ወደክፍላቸው እስኪገብ እየጠበቀች ነው። ‹‹ውይ ተመስገን››አለች…
የጊፍቲ ክፍል ተከፈተና ገባች ...የእሱም ተከፈተ ገባና ዘጋው።ልዩ መልሳ ተበሳጨች…፡፡እቅዴ አልሰራም ወይም ግምቶ ትክክል አልነበረም፡፡ በተለይ እስከእዚህን ሰዓት ድረስ ወደ ክፍላቸው ሳይመለሱ መቆየታቸው ተስፍ ሰጥቷት ነበር ፡፡እነሱ ግን ይሄው ጨዋነታቸውን እንደጠበቁ በየክፍላቸው ገቡ..፡፡ይሄ ጉዳይ ደግሞ ልዩን ተስፋ ሲያስቆርጣት …የእሷን ላፕቶፕ ሀክ በምድረግ እሷንም ሰደሬ ያሉትን እነጊፍቲንም እየተመለከተ ያለው ቃል ደግሞ ፈገግ አለ፡፡
ልዩ‹‹ቆይ ቆይ እስኪ… ››ብላ ትኩረቷን መድሀኔ ክፍል ውስጥ ትኩረት ደረገች፡፡ እሱ ላይ ምንም የመረጋጋት መንፈስ አይታይበትም፡፡ ዝም ብሎ ወለሉ ላይ ከወዲህ ወዲያ እየተመላለሠ ደቂቃዎችን አሳለፈ... ጊፍቲ ምንም የሚነበብባት የተለየ ስሜት የለም፡፡ ልብሷን አወለቀችና በፓንት ብቻ እርቃኗን ቆመች‹‹...ዋው ሰውነቷ ለእኔ ለሴቷም ያጓጓል..፡፡እርግጥ ከመጠን ትንሽ ተረፍረፍ ያለ ውፍረት ይታይባታል ቢሆንም ታምራለች፡፡››በማለት አድናቆቶን ተናገረች …ቃል ደግሞ በግማሽ ትኩረት የሚያውቀውን ገላ እየተመለከተ በገማሽ ቀልቡ ደግሞ የልዩን ጉሩምሩምታና መቁነጥነጥ እየታዘበ ቀጣዩን ትዕይንት ለማየት በጉጉት መከታተሉን ቀጠለ...
ጊፍቲ ከሻንጣዋ ውስጥ ሙሉ ቢጃማ ቀሚስ አወጣችና ለበሰች..ከዛ ሎሺን አወጣችና አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ ብላ ከባቷ ጀምሮ ወደታች እግሮቾን መቀበባት ጀመረች...
መድህኔ  አሁንም ክፍሉ ውስጥ ሆኖ መንጎራደድን አላቆመም ..በውስጡ ከፍተኛ የሀሳብ ፍጭት እየተደረገ ይመስላል.. ድንገት እንደመባነን አለና ወደ ጠረጰዛው ሄደ ..ብዙም ያልተጠጣለት ብላክ ሌብል ውስኪ ነበር ..አንስቶ ያዘው..ትናንት ማታ ልዩ ይሄን መጠጥ ስለምትወድ  ለእሷ ብሎ ነበር  የገዛላት። ሊያንደቀድቀው ነው ብላ ስትጠብቅ ሁለት ብርጭቆ ይዞ ከክፍሉ ወጣ...የቃልም ሆነ የልዩ ልብ በየአሉበት ተንጠለጠለ… ሁለቱም የሚቀጥለውን ትዕይንት ለማየት ተነቃቁ ..የጊፍቲ ክፍል ተንኳኳ

"ማነው?"

"ጊፍቲ መድህኔ ነኝ"
ያለምንም ማቅማማት ቀልጠፍ ብላ ሄዳ ከፈተችለትና በራፍን ይዛ ቆመች..ከካሜራው ስለራቁ የሚያወሩት እየተሠማቸው አይደለም .ከደቂቃዎች ብኃላ ከበራፉ ገለል አለችና እሱን አስገባችው፡፡ በራፍን ዘግታ ወደነበረችበት የአልጋ ጠርዝ ተመልሳ ተቀመጠች...እሱ ውስኪውን ከነጠርሙሶቹ እንደያዘ ቆሟል።

‹‹እንዴ ቁጭ በል እንጂ?››

"እሺ"አለና በሁለቱም ብርጭቆ ቀዳና አንዱን አቀብሏት አንዱን ይዞ ከፊት ለፊቷ ያለ ደረቀ ወንበር ላይ ተቀመጠ...፡፡

"የጠጣሁት ወይን እራሱ አድክሞኛል..."

"አይዞሽ ምንም አይልሽ...ደግሞ አልጋሽ ላይ ነው ያለሽው ከደከመሽ ወደኃላ ክንብል ብሎ መተኛት ነው፡፡"

"እኔስ ክፍሌ ነኝ ክንብል ብዬ ተኛው...አንተስ በሰለም ወደቤትህ መግባትህን ቅድሚያ ማረጋገጥ የለብኝም?።››አለችው፡፡
"ለዛ አታስቢ  ..ከእዚህ ክፍሌ እስከሚደርስ ምን ያጋጥመዋል ብለሽ የምትሰጊ ከሆነ እዚሁ ከእግርሽ ስር እጥፍጥፍጥፍ ብዬ እተኛለሁ›› አላት፡፡
ጊፍቲ ከት ብላ የመገረም ሳቅ ሳቀች ."ይህቺ ጠጋ ጠጋ እቃ ለማንሳት ነው ...ሰውዬ በል ጠጣ ጠጣ አድርግና ወደ ክላስህ" አለችው ….
መልስ ሊመልስላት አፉን ሲከፍት የእሷ ስልክ ጠራ…እርብትብት አለች….መድህኔ  እየተከታተላት ነው…ስልኩን አላነሳችውም፡፡ ስልኩም እስከመጨረሻው ድረስ አልጠራም…በመሀከል ተቋራጠ፡፡ስልኩን የደወለው ቃል ነው..ይሄንን ያደረገው ሆነብሎ ስሜቱ እንደዛ እንዲያረግ ስለገፋፋው ነው፡፡
‹‹ወይ….በፈጣሪ!!›አለች፡፡
‹‹ምነው ?ማነው የደወለልሽ?››
ልዩም በላችበት ሆነ የዚህን ጥያቄ መልስ ለማወቅ ፈልጋ ነበር
‹‹ጓደኛዬ ነው፡፡››መለሰች ጊፍቲ፡፡
‹‹ጓደኛሽ ማለት ፍቅረኛሽ?››
‹‹በለው.. አዎ ፍቅረኛዬ››
‹‹ይሄን ያህል አደገኛ ነው እንዴ;?››
‹‹አዎ….ማለቴ ምንም ብታደርግ ምንም አይናገርህም…አያኮርፍህም ..አይቆጣህም..በቃ ዝም ብሎ ነው የሚያልፍህ››
👍6311👏1
‹‹አልገባኝም…ታዲያ ይሄ ምኑ  ያስፈራል?››
‹‹ወይ ጉድ!! ስላላየኸው ነው…የሚናገር ሰው እኮ አሪፍ ነው ፡፡ጥፋትህን ወዲያውኑ ያወራርድልሀል..ይሄ ግን ውስጥህን በፀፀት ያከሰለዋል፡፡››
‹‹እሱማ አይቼዋለው እኮ በቀደም አብረን እንዳመሸን እረሳሺው እንዴ?››
‹‹አይ አረሳሁትም..ግን ቃልዬን ለማወቅ አንድ ምሽት አይደለም አንድ አመትም በቂ አደለም›› አለችው…
ልዩ ባለችበት ማጉረምረሟን ጀመረች‹‹በዚህ ንግግርሽ አልስማማም…እኔ ለምሳሌ ቃልዬን ነፍሱ ድረስ ዘልቄ ያወቅኩት አንድ ሰዓት በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ ነው….በዛን ቀን እዛ ታክሲ ውስጥ ሞባይሉን ሰርቄ ከተያዝኩበት ጊዜ አንስቶ ሆስፒታል ወስዶኝ እስኪያሳክመኝ ባለው ጊዜ አብዛኛውን የቃልዬን ስብዕና የተረዳሁበት አጭር ግን ዘላለማዊ ያህል ዋጋ ያላቸው መጠነ ጊዜ ናቸው ፡፡ከዛ ወዲህ ያሉት ቀናትና ወራት በሙሉ እነዛን ስብዕናዎቹን ሚያወፍሩና የሚያዳብሩ ብቻ ናቸው……እና ቃልዬን ለመረዳት አመት እንዳማይፈጅ እኔ ምስክር ነች..ይሄን አንድ ቀን ለራስሽ እነግርሻለሁ፡፡›› ስትል ቃል ሰማትና ተደነቀ….ሁለቱ ሴቶች እሱን የሚረዱበት መንገድ እንዲህ መለያየቱ ፈገግ የሚያስብል ነው…‹‹የትኛዋ ነች ግን ትክክል?››ሲል እራሱን ጠየቀ..መልሱ ቀላል ስላልሆነ ጥያቄውን ብቻ በልብ ሰሌዳ ላይ  መዝግቦ ወደሁለቱ የምሽት ጫወታን ወደማመጥ  ተመለሰ፡፡
‹‹አሁን ስልኩን ለምንድነው ያላነሳሽለት?››
‹‹አንስቼ ምን እለዋለሁ….መኝታ ቤቴ ገብቼ  ተኝቸያለሁ ብዬ እዋሸዋለሁ ወይስ  ክፍሌ ውስጥ የጓደኛዬ ባል አስገብቼ አብሬው   ውስኪ እየጠጣሁ ነው ብዬ እውነቱን ነግዋለሁ?››
‹‹እሱን አላውላቅም ደግነቱ እሱም እኮ ከልቡ የደወለ አይመስለኝም….ስልኩ ጠርቶ ሳይጨርስ ነው ያቋረጠው፡፡››
‹አይ እሱ ኮዳችን ነው….ስልክ ደውሎ አራት ጥሪ ድረስ ካልተነሳ አልተመቸኝም ማለት ነው፡፡መልሼ እስክደውልለት ድረስ አይደውልልኝም፡፡››
‹‹እስከነገም ቢሆን?›
‹‹እስከ ሳምንትም ቢሆን አይደውልልኝም..ምን አልባት ድህንነቴ ካሳሰበው  መልዕክት ይልክ ይሆናል?››
ልዩ ፈገግ አለች..ፈገግ ያስባላት..አሁን ከተናገረችው ጋር  የመድህኔ የስለክ አጠቃቀም ልዩነት ትዝ ብሏት ነው የፈገገችው..፡፡ መድሀኔ  አንዴ መደወል ከጀመረ እስከምታነሳለት  ወይም ስልኩን ሙሉ ለሙሉ ዘግታ እስከምትገላገለው አያቆምም…በአንድ ቀን ውስጥ 98 ሚስኮል ስልኳ ላይ የተመዘገበበት ቀን አለ…..አስርና ሀያ…የተለመደ ነው፡፡ ይሄ ማለት ደግሞ ከቃል የስልክ አጠቃቀም ጋር የሰሜን ፖል እና ደቡብ ፖልን ያህል ተቃርኖ አለው ማለት ነው ስትል በንፅፅሩ ተገረመችና ትኩረቷን ወደነጊፊቲ መለሰች፡፡
‹‹ፍቅረኛሽ ነው ግን... ማለት አርግጠኛ ነሽ?››
‹‹እንግዲህ  እንደዘዛ እላለሁ››
በመልሷ በመገረም መሰለኝ መድሀኔ ከትከት ብሎ ሳቀና ‹‹እሱሱ  እንደዛ ይላል?›
‹‹ያው ለሁለተኛ ቀን ስትገናኙ   እራስህ ትጠይቀዋለህ››አለችው እንደማኩረፍ ብላ፡፡
በቃ ከዚሀ ወሬ እንውጣ አሁን ተኚ… ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳና ጎንበስ ብሎ ጉንጯን ስሞት በራፍን ከፍቶ ወጣ….
በዚህ አይነት ሁኔታና እንዲህ በቀላሉ ከዛ ክፍል ይወጣል ብለው ቃልም ሆነ ልዩ አላሳቡም ነበር.. ጊፍቲም እራሷ  የመድህኔ ስንብት ከግምቶ ውጭ የሆነባት እንደሆነ ያስታውቃል… የሳማትን ጉንጮቾን በእጇ መዳፍ እያሻሸች….ከተቀመጠችት ተነሳችና በራፉን ቆለፈች..አልጋዋ ላይ ወጣችና አንሶላውን ገልጣ ገባች..ከዛ መብራቱን አጠፋች..ልዩም በንዴት ላፕቶፕን ስታጠፋ በዛኑ ቅፅበት ከቃል ኮምፒተር ጋር የነበረው ግንኙነት ተቋረጠ፡፡ ልዩ ለመተኛት መዘጋጀት ጀመረች፡፡በተመኘችው መጠን ጭን እስከመፈላቀቅ የሚደርስ ግንኙነት ላይ ባይደርሱም   ጥሩ መቀራረብና የስሜት መፈታተሸ ስላደረጉ ለመፅናናት ሞከረች፡፡

ይቀጥላል
👍9316🤔5🥰3👏3👎1
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር : : #ክፍል_ሀያ_አራት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// በማግስቱ ነው…እሷ ገንዳ ውስጥ ገብታ ትዋኛለች እሱ እየሠረቀ ይመለከታታል.. ‹‹ለምን ገብተህ አብረሀት አትዋኝም?" "አብረሀት ማለት?"ስኳር ሲሰርቅ እንደተያዘ ህፃን በርግጎ ጠየቃት፡፡ "እንዴ በአይንህ እኮ ዋጥካት" "ስርዓት ያዢ እንጂ… የራስሽው ጓደኛ መስላኝ?" "እሱማ እዚህ ከመምጣታችን በፊት ነዋ ..አሁንማ ቀማሀኝ..ለማንኛውም…»
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

ከምሽቱ 5 ሰዓት እቤት ክፍሌ አልጋዬ ላይ ተኝቼ ስለቃል እያሰብኩ ነው….መቼስ ቃል ቃል ብዬ እናንተንም አሰለቸዋችሁ አይደል  ምን ላድርግ..ተለክፌ እኮ ነው….እንቅልፌ መጥቷል ግን ከመተኛቴ በፊት አሱን ማየት ፈለኩ…ማለቴ በተለያየ ቀን ከመተኛቱ በፊት የፀለያቸውን ያልተለመዱ አይነት ፀሎቶችን እሱ ቤት በቀበርኩት ስውር ካሜራ አማካይነት ቀድቼ ላፕቶፔ ውስጥ አሉ..ከእነሱ መካከል አንድ ሁለቱ ማድመጥ ፈለኩ በዛውም ለእኔም እንደፀሎት ሀኖ ይቆጠልርልኝ ይሆናል…
ይሄ ከዛሬ አስር ቀን በፊት የፀለየው ነው፡፡
///

የዛሬ ሳምንት የፀለየው ደግሞ በእኔ ላይ እየሆነ  ያለው ሁሉ ትክክል ነው…በዙሪዬ ምንም  ገደል የለም…የመታኝ እንቅፋት በንቃት እየተራመድኩ እንዳልሆነ ሊያስታውሰኝ እንጂ ሊያደማኝ ፈልጎ አይደለም፡፡ እየበሰበሰ ያለው ነገር ከመበስበስ ቡኃላ ህይወት መስጠት ስላለ ነው…እየረገፈ ያለው የጠወለገና ደረቅ ቅጠል ለአዲሱና እንቡጠቹ ቅጠሎች ይበልጥ እንዲያቡብና እንዲያፈሩ ነው፡፡በዚህ አለም ላይ  ምንም አይነት የተዘበራረቀ ነገር የለም..እሆነ ያለውነገር ሁሉ አንተ ስለፈቀድክና መሆን ስለሚገባው የሆነ  ነው…ለምለሰሙ ዝናብ ከሰመይ በመርገፍ ምድርን ከጥሞና እንዴያረካት ቀድሞ ሰማዩ በጥቁር ደመና መሸፈንና መዝጎርጎር አለበት…ጨለማው ከሌለ ብሩሆ ጨረቃ የምትተፋውን ብርሀን ፈፅሞ ማየትም ማድነቅም አንችልም….ሁሉ ነገር ድንቅ ነው..ሁሉ ነገር ብሩህ ነው፡፡
አሜን.ብዬ ላፕቶፔን ዘጋሁና መብራቱን አጥፍቼ ተኛሁ፡

///
ከሶደሬ ከተመለሱ ሀያ  ቀን አልፏቸዋል፡፡ዛሬ ለሳምንታት ያቀደችውን ነገር የምትፈፅምበት ቀን ነው፡፡አዎ የምትፈፅመው  ነገር የጽድቅ ስራ አይደለም…አእምሮ የሚጨመድድ ከሳጥናኤል አእምሮ ካልተቀዳ በሰው ሀሳብ የማይታሰብ ነገር እንደሆነ ታውቃለች….ግን ደግሞ በነፃ ሚገኝ  ነገር የለም በሚል እራሷን ለማፅናናት ገፍታበታለች….፡፡‹‹አዎ    ቃልን የራሷ ለማድረግ እሷም መክፈል የሚገባትን መስዋዕትነት በፍቃደኝነት ለመክፈል ቆርጣለች….የልጅነት ጓዳኛዋን፤ የረጅም ጊዜ እጮኛዋ የሆነውን መድህኔን በፍቃደኝነት አሳልፋ ልትሰጥ ነው….አዎ ያንን ለማድረግ ደግሞ የመጨረሻውን ማስፈንጠሪያ የምትጫንበት ቀን ነው…ብቻ እንዲቀናትና ነገሮች በእቅዷ መሰረት እዲከወኑ ለማን መፀለይ እንዳለባት አታውቅም ‹‹እግዚያብሄርን እርዳኝ ብዬ እንዴት ጠይቀዋለሁ….?አረ ያሳፍራል፡፡››አለች ..ብቻ እንዲሁ እንዲቀናት ለራሷ ስኬትን ተመኘች…..በዛው ቅፅበት መኝታ ቤቴ ተንኳኳ፡፡

‹‹ማን ነው?››

‹‹እኔ ነኝ ልዩ..››አለች ከሰራተኛቸው አንዷ፡፡

‹‹እ ..ምን ፈለግሽ?›››

‹‹መድህኔ መጥቷል››

‹‹መጣው ጨርሼያለሁ በይው››

‹‹እሺ….››ብላ ተመልሳ ሄደች፡፡በጣም ተጨንቃ ዝንጥ ብላ ነው የጠበቀችውኩ፤የሚያስፈልጋትን ነገር ሁሉ በቦርሳዋ መጨማመሯን አረጋግጣ ክፍሏን ለቃ ወደታች ወደሳሎን ስትወርድ መድህኔና እናቷ ልክ እንደወትሮቸው አፍ ለአፍ ገጥመው ሲያወሩ ደረሰች፡፡….
እናትዬው ገና እንዳዮት‹‹ወይ ልጄ መልአክ መስለሻል …››አለቻት … መድህኔም ዞር ብሎ ከስር እስከላይ በገምጋሚ አይኖቹ ቃኛትና ፈገግ አለ…..

ከተቀመጠበት ተነሳና‹‹…በቃ ማሚ ሰሞኑን እመጣና በዝርዝር እናወራበታለን›› አላቸው፡፡

‹‹እሺ የእኔ ልጅ..ነገ ተነገ ወዲያ ቢሆን ደስ ይለኛል…ጊዜ የለንም፡፡››አሉት፡፡
..ምንም እንዳልገባው ሆና‹‹ለምኑ ነው ጊዜ የሌላችሁ?›› ብላ ጠየቀች ..ስለሰራጋቸው እንደሚያወሩ ግልፅ ሆኖላታል፡፡..በዚህ ወቅት በእሷም ሆነ በእሱ ቤተሰቦች ቤት ከእነሱ ሰርግ ውጭ ሌላ አንገብጋቢ አጀንዳ እንደሌለ ታውቃለች፡፡

‹‹አይ የአዋቂ ወሬ ነው….››አላትና አቅፏት ይዟት ወጣ…
ሲሸኞቸው ከኃላ የተከተሏቸው እናቷ‹‹ካደራችሁ ደውሉ››አሏቸው…
‹‹አንደውልም  …ከአሁኑ እወቂው እድራናል›››መለሰችላቸው፡፡
በእሱ መኪና ውስጥ ገብተው ገና ከጊቢ እንደወጡ‹‹በል ጊፍቲ እስቴዲዬም እየጠበቀችን ነው››አለችው..
‹‹እነሱም አብረውን ያመሻሉ እንዴ ..?እኔና አንቺ ብቻ ምንሆን መስሎኝ ?››አላት..ቅር ባለው ፊት፡፡
‹‹አዎ እኔም እንደዛ ነበር እቅዴ ..አሁን ከሀያ ደቂቃ በፊት ደውላ ደብሯት እስቴዲዬም ብቻዋን እዳለች ነገረችኝ ››
‹‹እንዴ  ፍሬንዷ ጋር አትደውልም…?››ሙግቱን ቀጠለ
‹‹ፍሬንዷ ማን ?››
‹‹እያሾፍሽ ነው..?ቃል ነዋ››
‹‹ፍሬንዷ ስትል እኮ ዝም ብሎ ጓደኛዋ የምትል መስሎኝ ነው..ቃልማ ለስራ ክፍለሀገር ወጥቷል….ለዛ እኮ ነው እምቢ ማለት የከበደኝ …አንተ በስራ ቢዚ ሆነህ ችላ በምትለኝ ጊዜ የምታዳብረኝ እሷ አይደለች..አሁን ውለታዬን ልመልስ ነዋ…››አለችው፡፡
‹‹አቤት አቤት..አሁን እኔ መቼ  ነው አንቺ ልታገኚኝ ፈልገሽ ቢዚ የሆንኩት…..ደግሞ የድሮ ጓደኞችሽን እርግፍ አድርሽ  ግንኙነትሽን ጠቅላላ ከእነዚህ ባልና ሚስት ጋር እድርገሻል ምንድነው ?አልገባኝም?…››አላት

በመርማሪ አይኖቹ ፡፡
‹‹ምነው አልተመቹህም እንዴ..?እንደዛ ከሆነ ….››
‹‹እንደዛ ከሆነ ምን…?››
‹‹ካልተመቹህ ቀስ በቀስ አቆማለኋ…››
‹‹አዎ አልተመቹኝም›› ቢል እንደማታቆም በውስጧ ታውቃለች..ግን ደግሞ ማስመሰል አለባት፡፡  አቁሚ ቢላት እንደውም እልክ ይዞት ጨርቋን ጠቅልላ እነሱ ጋር የምትገባ ሁሉ ይመስላታል፡፡እሱም አመሏን በጥልቀት ስለሚያውቅ እንደእዛ አይነት ቅብጠት አይቃብጥም፡፡
‹‹ኸረ..እንደውም ከእነሱ ገር መዋል ከጀመርሽ በኃላ  አሪፍ ሆነሻል፡፡››
‹‹አሪፍ ስትል?››ተበሳጭች
‹‹በቃ ደስተኛ ሆነሻል..በረባ ባረባው መነጫነጭ ትተሻል ባልልም በጣም ቀንሰሻል .ለምትጠየቂው ጥያቄ ቀና መልሶች  መመለስ እየተማርሽ ነው..አረ ከሁሉም በፊት እንድንጋባ ፍቃደኛ የሆንሽው ከእነሱ ጋር ጓደኛ ከሆንሽ በኃላ እኮ ነው፡፡››ብሏት የቅርብ ጊዜ ለውጧቾን ዘረዘረላት….ምንም የተሳሳተው ነገር የለም…ሁሉንም በአስተውሎት ታዝቦል….ችግሩ ከለውጦቹ ጀርባ የሸሸገችውን ድብቅ ሚስጥራዊ ተልዕኮ አለማወቁ ነው፡፡

‹‹ምን አልባት በእነሱ ፍቅር ቀንቼ ይሆናል…››

‹‹አረ እንኳን  ቀናሽ..እኔ ተጠቃሚ ሆኜያለሁ፡፡››
‹‹ዛሬ እንደውም እንዲህ ተቆነጃጅቼ የወጣሁት የሆነ ነገር ሰጥቼ ሰርፕራይዝ ላደርግህ ነበር..ግን አሁን ፀባይህን ሳየው አይገባህም››

‹‹አይኖቹ በሩ…ምንደነበር ልትሰጪኝ ያሰብሽው…?››
‹‹እስከዛሬ ሰጥቼህ የማላውቀውን››
በደስታ ተፍነከነከ …‹‹በአንድ አፍ….አንዴ አስበሽ ወስነሻል……. ትሰጪኛለሽ፡፡››
‹‹እስኪ እስከምሽቱ ያለህ ፀባይ ታይቶ …ምን አልባት?››አንጠልጥላ ተወችው፡፡
…በዚህ ጊዜ ስቴዲዬም ደርሰው ነበር ..ጊዬን ሆቴል በራፍ አካባቢ መኪናቸውን አቆሙና ደወሉላት..ቅርብ ስለነበረች መጥታ ተቀለቀለቻቸ….  ወደፒያሳ ነበር የነዳው፡፡


ይቀጥላል
👍11313😁3🤔3🔥1🤩1
#ባል_አስይዞ_ቁማር››


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

‹‹ምነው…ፒያሳ ይሻላል እንዴ?››ልዩ ነች የጠየቀችው፡፡

‹‹አይ የሆነች ጉዳይ ሳላለችብኝ ነው… ደረስ እንልና እንደውም እዛው ኢሊሊ ራት በልተን ከዛ ወደምትፈልጉበት ጭፈራ ቤት እንሄዳለን..››

ጊፍቲ ፈገግ አለች….ቀጥታ ፒያሳ ወደሚገኙ መደዳ ወርቅ ቤቶች ነበር ይዟቸው የሄደው..ልዩ እራሱ ያልጠበቀችው ነገር ስለሆነ ግራ ተጋባች…እሱ ራሱ ቀድሞ ያሰበበት ጉዳይ አልነበረም..ሰጥሀለው የምትለዋ ቃል ከአንደበቷ ተስፈንጥራ ስትወጣ በውስጡ በተፈጠረ ፍንጠዛና በምርቃና ድንገት ብልጭ ያለለት ሀሳብ ነው፡፡

‹‹ምነው ምን መጣ..?››ጠየቀችው፡፡

‹‹ቀለበታችን ሳንመርጥ የቀለበቱ ቀን ደረሰ እኮ?››

‹‹እንዴ ገና ሁለት ወር ይቀረናል እኮ››

‹‹ሁለት ወር ምን አላት….አይደል ጊፍቲ፡፡›› አለ ወደ እሷ ዞሮ ድጋፍ እድትሰጠው በሚፈልግ ንግግር…

እሷ የሰማችው አይመስልም ቅዝዝ ብላ ጭልጥ ያለ ሀሳብ ውስጥ ገብታለች

‹‹ጊፍቲ፡፡››

‹‹እ..ታድላችሁ…አዎ ትክክል ነው..ሁለት ወር በጣም አጭር ጊዜ ነው…››አለችና ተያይዘው ወደ ውስጥ ገቡ…ተገቢውን ቀለበት አማርጦ ለመግዛት ከሰላሳ ደቂቃ በላይ ነው የፈጀባቸው….በመጨረሻ እንደውም ጊፍቲ አሪፍ ነው ብላ ያሳየቻቸውን የዳይመንድ ፈርጥ ያለበት ቀለበትን ነው ሁለቱም በአንድ ድምፅ ተስማምተው የተገዛው..የሁለቱንም ቀለበት ሰጣትና ቦርሳዋ ውስጥ በመክተት እየተሳሳቁ ተያይዘው ወጡ…

እንዳአለውም ኢልሌ ሆቴል ጎራ አሉና እራታቸውን በልተው ሲወጡ ሶስት ሰዐት አልፎል…

‹‹አሁን ጭፈራ ቤት ለመሄደ ትክክለኛው ሰዓት ነው››አለ መድሀኔ…ፍንድቅድቅ ባለ ድምፅ፡፡
‹‹አዎ ግን እናንተ ብትሄዱ ይሻላል ..ከዚህ በላይ ካመሸው አከራዬቼ የውጭ በራፍ አይከፍቱልኝም…››አለች ጊፍቲ
‹‹እኛም አይከፍቱልንም››ሲል መለሰላት መድህኔ

‹‹አይ ቢሆንም እናንተ የራሳችሁ ማለቴ የወላጆቻችሁ ቤት ነው..ጨክነው አይጨክኑባችሁም እኔ ግን ኪራይ ቤት..››
ክንዷን ያዘችና ‹‹ነይ ባክሽ እስከአራት እስከ ከአምስት ሰዓት ዘና እንልና አዲሱ ቤታችን ሄደን ነው የምናድረው…አይደል መድህኔ?››

‹‹እ አዎ..ጥሩ ሀሳብ ነው….››አለ…..እሱም ያላሰበው አዲስ ሀሳብ ነው ያመጣችው፡፡
መኪና ውስጥ ገብተው መድሀኒ መንዳት ከጀመረ በኃላ…‹‹እንዴ አዲስ ቤት ተከራያችሁ እንዴ ?›› ስትል ጠየቀች

‹‹ አይ የእኔ ፍቅር አሪፍ ቤት ገዝቶ ሰርፕራይዝ አደረገኝ፣››አለችና መልስ ሰጠቻት፡፡ ለቤት ያላትን ፍቅር እሷም ሆነች ቃል ደጋግመው ነግረዋታል፡፡ለዛም ነው አይን አይኗን እያየች አድምቃ እያወራች ያለችው፡፡

‹‹ለእናንተ እኔ ደስ ብሎኛል አለች››የንግግሯ መዝረክረክ ግን ደስ እንዳላላት ያስታውቅባታል፡፡
‹‹ሰዎች የተለየ ሀሳብ አለኝ››ልዩ ነች ተናጋሪዋ፡፡

‹‹ምንድነው?››

‹‹ለምን የሚስፈልገውን መጠጥ ገዝተን ቀጥታ ወደቤታችን አንሄድም…..ግርግሩ ብቻ ነው የሚቀርብን …ሙዚቃው እንደሆነ እቤት አለ …እንቀውጠዋለን…››
መድህኔ ሁለቱንም እያፈራረቀ አያቸው…

‹‹ወይ በቃ ለካ ጊፍትዬ ጭፈራ ቤት ትወዳለች…››አለች ልዩ..አውቃነው እሷን ይሉኝታ ውስጥ ለመጨመር አስባ ይህቺን አረፍተ ነገር የሰነዘረችው፡፡

‹‹አረ በፍፅም.. አሪፍ እና የተለየ ሀሳብ ነው ያመጣሽው..እንደውም ጭፈራ ቤት አድሬ ነገ ጥዋት ተነስቼ ቢሮ መግባት ይከብደኛል.. እያልኩ እያሰብኩ ነው…››

መድህኔ ‹‹እንግዲያው ወደቤት ነዳሁት…››አለና አቅጣጫውን አስተካከለ…

ከሀያት ሪል እስቴት ወደተገዛው ግዙፍ ቪላ ነው የነዳው..መንገድ ላይ ቆሞ ሴቶቹን መኪና ውስጥ አስቀምጦ መአት አይነት መጠጦችንና የተወሰኑ የሚበሉ ነሮችን ገዝቶ ተመለሰ….እቤት ሲደርሱ አራት ሰዓት ተቃርቦ ነበር..የመኪናውን ጡሩንባ ቢያንጣጣም በቀላሉ ሊከፈት አልቻለም..ወርዶ በእጁ ጭምር መቀጥቀጥ የግድ ሆኖበት ነበር..ከዛ ዘበኛው በድንጋጤና በማለክለክ መጥቶ ከፈተና በተደናገጠ ደምፅ..‹‹ጋሺዬ ይመጣሉ ብዬ ስላላሰብኩ እንቅልፊቱ ጣለችኝ፣እንደው ይቅርታ››ተሽቆጠቆጠ፡፡

‹‹…ችግር የለውም…››ብሎ አረጋጋው…ኮፈኑን ከፈተና
‹‹ይህቺን እቃ ወደሳሎን ውሰድልኝ›› አለው…ዘበኛው በታዛዥነት አንከብክቦ ወደሳሎኑ ከነፈ…ጊፍቲ በግቢው ውበት ፈዛ ከግራ ወደቀኝ አይኗን እያስወነጨፈች ታያለች…የምታደርገውን እየተካታተለ እንዳልሆነ ሰው ችላ ብላ ክንዷን ያዘችና ወደቤት ይዛት ገባች…ከሳሎኑ ጀምራ እያንዳንዱን መኝታ ቤት…መታጠቢያ ቤቶችን… ኪችኑን አስጎበኘቻት….

‹‹እንግዲህ ልጅ እስኪመጣ ድረስ ለእኛ ይበቃናል?››አለቻት
‹‹ትቀልጂያለሽ አይደል?››
‹‹ምን እቀልዳለው..እኔና እናቴ ከሰራተኞቻችን ጋር የምንኖርበት ቤት እኮ የዚህን ሶስት እጥፍ ይሆናል…ከዛ ወጥቶ እዚህ መኖር..ብቻ ይሁን አሪፍ ነው››
‹‹እና ከሁለት ወር በኃላ ልትጋቡ ነዋ››ጠየቀቻት፡፡

‹‹አይ ከሁለት ወር በኃላ ምርቃቴ ስለሆነ ቀለበቴ ነው በደባልነት የሚደረገው ሰርጋችን ከሶስት ወር ነው….ምን ይታወቃል… አብረን አንሞሸር ይሆናል?››

‹‹አይ!! ብለሽ ነው?››አለቻት… ትክዝና ቅዝዝ ብላ….፡፡አዎ የፈለገችውም እንዲህ ውስጧን መበጣጠስና ተስፋ ማስቆረጥ ….ወይንም ማስጎምዠት ነበረ…‹.እርግጠኛ ነኝ ይሄኔ ስንቴ ምን አለ ይሄ ቤት የግሌ በሆነ ብላ ተመኝታለች..እንግዲህ ይሄን ቤት ከፈለገች..የቃልዬን እጅ ለቃ የመድህኔን እጅ መያዝ አለባት ማለት ነው…ያንን እንደምታደርግ ደግሞ ከዛሬ ጀምሮ ምልክት ልትሰጠኝ ይገባል….ጊዜ የለንም፡፡››ስትል እሷን ከጎኗ አቁማ በውስጧ አብሰለሰለች፡፡

ጉብኝታቸውን ጨርሰው ወደሳሎን ሲመለስ መድህኔ ጠረጳዛውን በመጠጥና በሚበሉ ቀለል ባሉ ምግቦች ሞልቶት ግዙፍ እስፒከር ያለውን ቴፕ አዘጋጅቶ ጠበቃቸው…
‹‹የእኔ ፍቅር ምርጥ እኮ ነህ›› ብላ ተንጠልጥላበት ጉንጩን ሳመችው፡፡ ‹‹መቼስ ዛሬ ከወትሮ በተለየ ሁኔታ ቁልትልት ብዬበታለሁ……››ስትል እራሷን ታዘበች
ጊፍቲ ሶፋ ላይ ቁጭ አለች……

‹‹ምን ልቅዳለችሁ?›› መድሀኔ ጠየቀ፡፡

‹‹ወይን ቢሆን ደስ ይለኛል…››መረጠች ጊፍቲ፡፡…
‹‹አዎ ከቀላል እንጀምር ለእኔም ወይን››ልዩም ከጊፍቲ ምርጫ ጋር ምርጫዋን አስማማች፡፡
እንግዲያው ቆንጆ የፈረንሳይ ወይን አለኝ….አለና ከተኮለኮሉት ጠርሙሶች መካከል አንዱን መዞ በእያንዳንዳቸው ብርጭቆ ቀዳላቸው …እና የራሱንም ይዞ ከፊት ለፊታቸው ቁጭ አለ፡፡
መጠጡ በወይን ቢጀመርም..ወደውስኪ ሲሸጋገር አንድ ሰዓት አልፈጀበትም። ስድስት ሰዓት ላይ ተኪላ ነበር ሻት እየተደረገ የነበረው ...ዳንስ ..ጭፈራው ቅውጥ ያለ ነበር፡፡ ልዩም ዛሬ እንደው የእነሱን ያህል ችሎታው እንደሌላት ብታወቅም ቁብ ሳይሰጠት ከእነሱ እኩል ስትቀውጠው አመሸች...ልዪነቱ መጠጡ ላይ እየጠጣች በማስመሰል ስትደፍው ..አንዳንዴ ወደእነሱ ስትገለብጥ በተቻለኝ መጠን የሰከረች በመምሰል ግን ሳትሰክር እራሷን ለማቆየት የተቻላትን ጣረች..እናም ተሳክቶላት ሰባት ሰዓት ሲሆን ሁለቱም በዳንስ ብዛት ውልቅልቅ ብለው በላብ ወርዝተው ከላይ የለበሱትን እያወለቁ ጥለው እሱ በነጭ ፓክ አውት እሷ ደግሞ በጥቁር ጡት ማስያዣ ነበሩ...ልዩም ያው እነሱን ለማበረታት በጡት መያዠ ብቻ ቀርታለች...በዳንሱ ሞቅታ መካከል ሁለቱንም አቅፍቸውና አንድላይ አጣብቃ ወዳራሷ ትጨምቃቸዋለች…እንደዛ ሲሆን እርስ በርስ አንዲፍተጉ እያደረገች ቅርበታቸውን እያጠናከረች ነው፡፡..አንዳንዴ ሞቅ ብሏቸው የጋለ የእርስ በርስ
👍847😁5🥰3👎1🔥1
ዳንስ ሲደንሱ ‹‹ሽንቴ መጣ›› ብላ ጥላቸው ትሄድና ጭልጥ ብላ ትቆያለች...፡፡

ስምንት ሰዓት አዘጋጅታ የመጣችውን ሀሺሽ በሁለቱም መጠጥ ውስጥ ጨመረች ..ሁለቱም ድንብዝ ብለው ስለሰከሩ እንዳያዩት ለማድረግ ብዙ መጨነቅ አይጠበቅባትም።..ሀሺሽ የነሠነስችበትን መጠጥ ለሁለት ዙር ከተጋቱ በኃላ ሁለቱም አቅላቸውን ሳቱ ...
መድህኔ"አፈቅርሻለው..የእኔ ልዩ በጣም አፈቅርሻለሁ"እያለ እየቦጨቃትና እየሳመት መጮህ ጀመረ...
ልዩም በእሱ ሪትም በተመሳሳይ እየጮኸች..‹‹.እኔም በጣም አፈቅርሀለሁ››

"ካፈቀርሺኝ አሁን ስጪኝ"

"እሺ ትንሽ ታገስ ሰጥሀለሁ"

‹‹ጊፍቲ ፓካአውቷን አውልቃ ወረወረች"እኔም ቃልዬ አሁን ቢመጣ ኖሮ ሰጠው ነበር..."

‹‹እና ስጪው እያልሺኝ ነው?"ጠየቀቻት

"አዎ ስጪው...መስጠት እኮ ደስ ይላል..›› በማለት ሁለቱንም ከያሉበት ጎትታ እርስ በርስ አስተቃቀፈቻቸው።መድህኔ ከንፈሯ ላይ ተጣበቀ..አልተቃወመችውም፡፡እንደምንም እራሷን ከከንፈሯ አላቀቀችና"ተቃጠልኩልሽ .."አለና ቀኝ እጅን በሱሪዋ ውስጥ ሰርስሮ በማስገባት ቀኝ መቀመጫዋን በመዳፉ ጨብጦ ጨመቃት ...በሰውነቷ ገሀነማዊ ሙቀት ተራወጠ"ልዩ ተልዕኮሽን እንዳትረሺ...ዛሬ ለዚህ አልመጣሽም"አለችና እራሷን ለመቆጣጠር ሞከረች፡፡ ጊፍቲ ፊትለፊቷ ወዳለው ሶፍ እየተንገዳገደች ሄደችና ከታች የለበሰችው ቀሚስ ተሰብስቦ የውስጥ ፓንቷ ለእይታ እስከሚጋለጥ ድረስ ተበለቃቅጣ ተቀመጠች…‹‹ ልዩ"ስትል ከጣሪያ በላይ በሚባል የድምፅ ተጣራች

"ወይ ጊፍቲ"

"ባልሽን ከዚህ ይዘሺልኝ ወደመኝታ ክፍልሽ ግቢ...ፊቴ ስትላላሱ በጣም እያማረኝ ነው .."አለች፡፡

መድሀኔም ከእሷ ተቀብሎ"እኔም በጣም አምሮኛል...እንግባ."እያለ ወደመኝታ ቤታቸው ጎተታት… ከወዲህ ወዲያ ሲንገዳገድ አንደምንም እየደግፈችና እያስተካከለች መኝታ ቤት አደረሰችው..አልጋው ላይ ተዘረረ ..በመንቃትና በመተኛት መሀከል ነው ያለው..፡፡

‹‹ልዪዬ ነያ ስጪኝ..ሰጥሀለው አላልሺኝም?"


ይቀጥላል
👍67🤔158👎5
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር›› ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ስድስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// ‹‹ምነው…ፒያሳ ይሻላል እንዴ?››ልዩ ነች የጠየቀችው፡፡ ‹‹አይ የሆነች ጉዳይ ሳላለችብኝ ነው… ደረስ እንልና እንደውም እዛው ኢሊሊ ራት በልተን ከዛ ወደምትፈልጉበት ጭፈራ ቤት እንሄዳለን..›› ጊፍቲ ፈገግ አለች….ቀጥታ ፒያሳ ወደሚገኙ መደዳ ወርቅ ቤቶች ነበር ይዟቸው የሄደው..ልዩ እራሱ ያልጠበቀችው ነገር…»
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///

"ሰጥሀለው መጀመሪያ ልብስህን አውልቅ ..፡፡››አለችና ጎንበስ ብላ ጫማዋን አወለቀችለት ..ከዛ የሱሪውን ቀበቶ ፈታችና ቁልፍን ከፍተች… ዚፑን ወደታች በማንሸራተት ሁለቱን እግሮቹን ከታች በመያዝ እንደምንም እየጎተተች ከላይ እየሳበች ሱሪውን ከፓንቱ ጋር አንድ ላይ ሞሽልቃ አወለቀች…..እንዲህ ጨርቅ ሆኖ እንትኑ አደባባይ መሀል የቆመ የነፃነት ሀውልት ይመስላል....‹‹ልዩ ይሄን የመሰለ ዕቃ ለሌላ አሳልፈሽ ከመስጠትሽ በፊት አንዴ ብትጠቀሚው?››የሚል ሴጣናዊ ምክር የሆነ መንፈስ በጆሮዬ ሹክ አለባት። ጆሮዋን ደፈነችና ተልዕኮዋን ላይ አተኮረች...አሁን የቀረው ፓካውቱን ማውለቅ ነው ሙሉ በሙሉ አልጋው ላይ ወጣችና እንደምንም ታግላ አወለቅችለት.. አሁን ሙሉ እርቃኑን ቀርቷል..አልጋ ላይ ቆማ ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ፀጉሩ በትኩረት አይኖቾን እያመላለስች አየችው፡፡ ወንድ ልጅን እንዲህ መለመላውን በአካል ስታይ የመጀመሪያ ጊዜዋ ነው። ጥሩ የተባለ የእስፓርተኛ ሰውነት ከተመጠነ ውፍረትና ቁመት ጋር ነው ያለው ..እንዲያም ሆኖ ግን የወንድ አካላዊ ቁመና እንደሴት ማራኪ አይደለም ስትል አብሰለሰለች። ‹‹አሁን ይሄን ማሰቢ ጊዜ ነው ?››እራሷን ገሰፅችና ወደሳሎን ተመለሰች...ጊፍቲ አሁን ድረስ ሙሉ በሙሉ እጅ አልሰጠችም" አሁንም የመጠጥ ብርጮቆዋን በእጇ እንደያዘች... እያላዘነች ነው፡፡

"ቃልዬ አሁን ናልኝ...ናና ሰውነቴን ዳብሰው...ናና ከንፈሬን ምጠጠው...ናና ጡቶቼን ጭመቃቸው...ናና ጭኖቼን ገነጣጥላቸው...ናና ..››

‹‹..ቃልዬን ፈልገሽው ነው?"

"አዎ ...ቃልዬን አምጪልኝ "

"ቃልዬን እንዳመጣልሽ...መጀመሪያ የያዝሽውን መጠጥ ጠጪ"

"መጠጥ ይሄው"

በአንድ ትንፋሽ ግልብጥ አደረገችው" ይሄው ጨረስኩ በያ አምጪልኝ"

"አመጣዋለሁ ..ግን ከአመጣሁት ትሰጪዎለሽ"

"ለቃልዬ..በደንብ ነዋ ...ለዛውም እንደፈለገው፡፡"

"እንቢ አልፈልግም ካለስ?"

"አንቺ ብቻ አምጪልኝ እንጂ በግድ ነው የምሰጠው..?"

‹‹እንግዲህ ተነሽ...ቃልዬ ልብሱን አወላልቆ ዝግጅ ሆኖ እየጠበቀሽ ነው...››

የእውነት ፈጥና መቀመጫዋን ለቃ ለመነሳት ብትሞክርም መቀመጫዋን ከሶፍው መላቀቅ አልቻለችም...ክንዷን ይዛ በመጎተት አስነሳቻትና እየጎተተች ማለት ይቻላል..ወደራሳቸው መኝታ ቤት ይዛት ገባች... መድህኔን ጠቅልላ እንዳስተኛችው ተኝቷል።

"የተኛ ሰው በማየቷ "ቃልዬ ነው እንዴ?"ስትል በተኮለታተፈ እና በተሰባበረ አረፍተ ነገር ጠየቀች፡፡

‹‹አዎ ግን በመስከርሽ እንዳይበሳጭ ድምፅሽን ቀንሺ አለቻት...በሁለት እጇ አፏን ፡አፈነች...አልጋው ጫፍ አስቀመጥኳት ‹‹...አሁን ልብስሽን ላውልቅልሽ..ተስማማሽ?›› ልክ እንደ መድህኔ እንዳደረገችው እያንዳንድን በሰውነቷ ላይ ያለውን ልብስ አወለቀችላትና መለመላዋን አስቀረቻት‹‹...ፐ ቅርፅ...›› በሚል አድናቆት እየጎተተች ከውስጥ አስገባቻት …እና ወደ ጆሮዋ ጠጋ ብላ ‹‹እንግዲህ እኔ ሄድኩልሽ ..ያው ቃልዬ በደንብ ስጪው" አለቻት፡፡፡

መዲህኔ ላይ እየተጣበቀችበት‹‹ እ…ሺ ››.አለችን

መብራቱን አጠፍችና ከአልጋው ወረደች ..ተራመደችና ከክፍሉ አልወጣችም፤ እዛው መግቢያ ላይ ወዳለ ሶፍ ሄደችና ጋደም አለች...ከዛ የሚፈጠረውን ነገር መከታተል ጀመረች...

"ቃል አንተ ተኛህ እንዴ...?››ጊፍቲ ነች መድሀኔን እየወዘወዘች ያለችው፡፡

"አለው ....ልዪዬ"በሰመመን ውስጥ ሆኗ መለሰላት፡፡

"ከዛ የመተሻሸት ድምፅ ተሰማ ..ልዩ የሞባይሏን መብራት አበራችና ወደእነሱ አተኮረች ..ጊፍቲ እላዪ ላይ ወጥታበት ጎንበስ ብላ ከንፈሩን እየላሰችው ነው...ወገቧን ጨምቆ ይዞታል‹‹...ከደቂቃዎች በፊት ሁለቱም ተዝለፍልፈው እሬሳ መስለው አልነበረ እንዴ?›› ስትል በመገረም በውስጧ ጠየቀች፡፡ እንዲህ ልትል የቻለችው አንደኛው አንደኛውን ሲጨምቅና አንደኛው አንደኛውን በጥንካሬ ሲያንከባልል በማየቷ ነው....ከላይ አልብሳቸው የነበረ አልጋ ልብስም ሆነ ብርድ ልብስ ከላያቸው ተንሸራቶ ወደመሬት ወደቀ...አሁን ሁሉ ነገር በግልፅ ይታያት ጀመር...ሲተሻሹ..ሲሳሳሙ እና ሲዋሰብ በቂ የሆነ ፎቶም ቪዲዬም ቀረፀቻቸው፡፡.

ከዛ እነሱ እስኪረኩ መታገስ ከብዷት መሬት ካዝረከረኩት ልብስ ብድርብሱን ትታላቸው አልጋልብሱን ወሰደችና እሱን ተከናንባ እዛው ሶፋ ላይ ተኝች‹‹..እስቲ ሌሎች ሶስት መኝታ ክፍሎች ነበሩ ለምን እዛ ሄጄ አልተኛሁም..?››ስትል ጠየቀች…ምክንያቱን ግን አታውቀውም ነበር፡፡ወዲያው ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰዳት… ከእንቅልፏ ባና ሰዓቷን ሳታይ 12.10 ሆኖ ነበር..አይኗን አሻሽታ አልጋውን ስትመለከት ማመን አልቻለችም… ጊፍቲ መድሀኔ ክንድ ላይ ተንተርሳ አንደኛውን እግሩን ጭኖቾ መካከል ሰንቅሮ አንደኛውን ደግሞ ከላዬ ጭኖባት ጭልጥ ያለ እንቀለፍ ውስጥ ገብተው ያንኮራፋሉ… ማንኮራፋታቸው እራሱ ተራ በተራ ስለሆነ የራሱ የሆነ ስልተ ምት አለው….ከሶፋዋ ተነሳችና ቆመች.. .መኝታው ሰላልተመቻት ሰውነቷ ድቅቅ ብሏል…ተራመደች…ወደአልጋው ተጠጋችና እሪ ብላ ጩኸቷን ለቀቀችው……በመበርግ ሁለቱም ከእንቅልፋቸው ባነኑና ከተጣበቁበት ተላቀቁ፤ አንዴ እሷን አንዴ እርስ በረስ መተያየት ጀመሩ…፡፡

እሷ እንደድንቅ ብሄራዊ ተያትር ቤት ተዋናዬች ባጠናችውና በተዘጋጀችው መሰረት መድረኩን ተቆጠጣጠረችው፡

‹‹እንዴት እንዲህ ታደርጉኛላችሁ…ሰክራለች ብላችሁ እኔን ሶፋላ ላይ አስተኝታችሁ…?መድሀኒ ይሄ ለእኔ ይገባል.?››እራሷን ነጨች..ኸረ እንባዋ ሁሉ እየረገፈ ነው..መድሀኔ ተነስቶ ከአልጋው ወረደ… መለመላውን ሁለት ሴቶች ፊት ተገተረ….ጊፍቲ አንሶላውን ሰበሰበችና እርቃኖን ሸፈነች…ፊቷ በእፍረትና ግራ በመጋባት በአንዴ ሲገረጣ እየታየ ነው..
‹‹ልዩ ተረጋጊ …ምን እንደተፈጠረ በእውነት አላውቅም..››ወላል ላይ የተበታተነውን ልብሱን መሰብሰብ ጀመረ…ከመሀከል ፓንቱን እነሳና ለበሰ..፡፡
‹‹ሁለታችሁንም ከዛሬ ጀምሮ በአይኔ ማየት አልፈልግም….ያው ከመሀከላችሁ ወጥቼለሁ....እቤቱንም ተጋብታችሁ ልትኖሩበት ትችላላችሁ፡፡››
‹‹አረ ልዩ እንደዛ አይደለም…ይሄ ስህተት ነው››ጊፍቲ ነች እራሷን እንደምንም አበረታታ መናገር የጀመረችው፡፡

‹‹ምንም ስህተት አይደለም...እንደውም አሁን ሳስበው ይሄ ጉዳይ ከእኔም ሆነ ከቃል ጀርባ ሆናችሁ ስትፈፅሙት ዛሬ የመጀመሪያችሁ አይመስለኝም.››ነገሩን አንቦረቀቀችው፡፡
እንደ እብድ እየተወራጨችና እየተራገመች መኝታ ቤቱን ለቃ ወጣች፡፡ ሊለብስ ያዘጋጀውን ሱሪ በእጁ እንዳንከረፈፈ ሊከተላት ሞከረ….አልሰማችውም፡፡ ተንደርድራ ግቢውን ለቃ ወጣችና .ወዲያው ታክሲ ውስጥ ገባችና ከአካባቢው ተሰወረች…ስልኳን አጠፋችው፡፡

ቀጥታ ወደቤቷ ነው የሄደችው…..እናቷን እንኳን በቅጡ ሰላም ሳትል ወደ ክፍሏ ገባችና ከውስጥ ቀርቅሬ አልጋዋ ላይ ወጣች፡፡ድንግርግር ያለ ስሜት ነው እየተሰማት ያለው፡፡ ያሰበችውን ያህል ደስታ አልተሰማትም…ግን ቢሆንም ያሰበችውን በእቅዷ መሰረት ፈፅማዋለች....አሁን የሚቀራት ስህተቱን ተከትሎ መድህኔና ጊፊቲ ግንኙነታቸውን በዛው እንዲቀጥሉ ማድረግ ሲሆን በቀጣይነት ደግሞ ብቻውን የሚቀረውን ቃልን ብቻዋን ወደአለችው ወደራሷ ማምጣት…አዎ የመጨረሻ ግቧ ያ ነው፡፡አሁን መተኛት ስለፈለገች በአልጋ ልብሱ ሙሉ አካሏን ሸፈነች፡፡

ይቀጥላል
👍13323🤔14👏9😱5👎3🔥3😁1
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሰባት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// "ሰጥሀለው መጀመሪያ ልብስህን አውልቅ ..፡፡››አለችና ጎንበስ ብላ ጫማዋን አወለቀችለት ..ከዛ የሱሪውን ቀበቶ ፈታችና ቁልፍን ከፍተች… ዚፑን ወደታች በማንሸራተት ሁለቱን እግሮቹን ከታች በመያዝ እንደምንም እየጎተተች ከላይ እየሳበች ሱሪውን ከፓንቱ ጋር አንድ ላይ ሞሽልቃ አወለቀች…..እንዲህ ጨርቅ ሆኖ እንትኑ አደባባይ…»
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

ጊፍቲ ሕይወት ቀፏታል.. ሁሉ ነገር ጭልምልም ካለባትና ክፉ በሆነ በሀይለኛ እራስ ምታት በታጀበ ድባቴ ውስጥ ከገባች ሳምንት ሞላት

…..በዚህ ሀዘን ላይ በጣላት ክስተት ማንን ተወቃሽ እንደምታደርግ አለማወቋ ነው ይበልጥ ህመሟን ያጠነከረባት…ሰው ሰውን ሲቀየምና ሲጠላ ምንም አይደል…ሰው አምላኩን ቢቀየምም ምንም አይደል(ምክንያቱም አምላክ ለምን ተቀየማችሁኝ ብሎ እልክ በመጋባት ጥበቃውን አያቋርጥም)…. ሰው ራሱን ከተቀየመና ከጠላ ግን አደገኛ ነው…እራሱን የጠላ ሰው ለምንም ነገር ደንታ አይኖረውም.. እራሱን የጠላ ሰው ነገሮችን በቀና ሁኔታ  የማስተካከል ተነሳሽነቱ ዜሮ ነው…. እራሱን የጠላና የተጠየፈ ሰው አለምን እንዳለ ለማጥፋት እና ለማውደም ዝግጁ ነው፡፡ ጊፍቲም  በአሁኑ ጊዜ እንደዛ ነው የሆነችው..እራሷን ነው የጠላችው..እራሷን ነው የተጠየፈችው፡፡

ጊፍቲ ከደነዘዘችበት መቀመጫ ላይ ተስፈንጥራ ተነሳችና  ወደ መኝታ ክፍሏ አመራች፡፡ አልጋው ላይ በጀርባው ተዘርራ አይኗን ጣሪያዋ ላይ ተክላ ምስቅልቅል ሀሳቧቾን ታስብ ጀመር ..ደግሞም ተነሳችና  ኮሞዲኖ ላይ የተቀመጠውን የውስኪ ጠርሙስ አነሳችና ከእነ ጠርሙሱ አፏ ላይ ደቅና አንደቀደቀችው………. የንዴት እና ሽንፈት አጠጣጥ ነበር፡፡እሩብ ያህሉን አጋምሳና ቀሪውን ይዛ ወደ መስኮቱ ተጠጋችና በጨለማው እየተሸነፈ ያለውን ውጭ እየቃኘች ምን ማድረግ እንዳለባት ማሰብ ቀጠለች‹‹ህይወቷን እንዴት ማስተካከል ትችላለች…?ከቃልስ ጋር እስከወዲያኛው ተለያይታ እንዴት ትችለዋለች? …. ሰውነቷ በላብ ወረዛ‹‹መሆን የለበትም በፍጹም አይደረግም ቃልዬን አጥቼ መኖር የለብኝም አዎ እራሴን ማጥፋት አለብኝ.. እናቴ ወደላችበት መቃብር እራሴን እልካለሁ ››በውሳኔዋ ረካች…. እና ከት ብላ ሳቀች..የንዴት ሳቅ…..የመበለጥ ሳቅ….የተሸናፊነት ሳቅ…ተስፋ የመቁረጥ ሳቅ..የእብደት ሳቅ ››
በዚህ ወቅት እቤቷ ተንኳኳ…ዝም ባለች ቁጠር የማንኳኳቱ ኃይል እየጨመረ ሲመጣ እንደምንም እግሯን እየገተች ሄዳ ከፈተችው…ስትከፍት ያገኘችው ሰው ግን ፍፅም ያልጠበቀችውና ስትሸሸወ የነበረ ሰው ነው፡፡

‹‹ውይ ምነው? ምን አደረኩህ?››

‹‹እኔስ ምን አደረኩሽ…?››
‹‹በራፉን ትታ ፊቷን ወደውስጥ መለሰችና እንዳመጣጧ እግሯን በመጎተት  ተራምዳ መቀመጫ ይዛ ተቀመጠች.እሱም ወደውስጥ በመግባት በራፉን ዘጋና ተከትሏት ከፊት ለፊቷ ተቀመጠና ማውራት ጀመረ…
‹‹ስልክ አይሰራም…ስትረጋጊ ትደውያለሽ ወይም ወደቤት ትመጪያለሽ ብዬ ጠበቀኩ ጠበቅኩ..ሲያቅተኝ መጣሁ .
‹‹ስልኬን የዘጋሁት እኮ ሰው ማግኘት ስለማልችል ነው…በተለይ አንተን››አይኖቹን ማየት አቅቷት አንገቷን ደፍታ የቤቱን ወለል እያየች መለሰችለት፡፡

‹‹ተይ እንጂ ጊፍቲ…እራስሽን መቅጣትስ ሳያንስሽ እኔንም ለምን ትቀጪኛለሽ..በጣም እኮ ነው የናፈቅሺኝ››

‹‹ቃል አይገባህም እንዴ ?እንዴት ብዬ ነው አንተን ለማግኘት ድፍረቱ ሚኖረኝ…?በጣም እኮ ነው የቆሸሽኩት …›
‹‹ሰው ሊሰራ የማይችለውን ምን የተለየ ተአምር ስራሸ …በዛ ላይ እንደሰማሁት በወቅቱ ሁላችሁም በጣም ጠጥታችሁና እስከመጨረሻው ሰክራችሁ ነበር….ለወደፊቱ ተመሳሳይ ስህተት ላለመስራት ከክስተቱ ትምህርት መውሰድ እንጂ እንዲህ እቤት ውስጥ እራስን እስረኛ በማድረግና አምርሮ በመቆዘም የሚቀየር ነገር የለም፡፡››
‹‹አሁን ጥፋቴን ቀለል አድርጎ በማቅረብ የምትደልለኝ ይመስልሀል?››

‹‹አይ እየደልኩሽ  አይደለም..የሚሰማኝን እውነት እየነገርኩሽ ነው…በውስጥሽ ያለውን ጨላማ ሀሳብ አስወግጂ
….በመሀከላችሁ ስር የሰደደ ጥላቻ መቼም ሊኖር አይችልም..እስኪ ነገሩን በራስሽ ገልብጠሸ አስቢው …አሁን አንቺ የሰራሁት የምትይውን ስህተት እኔ ሰርቼው ቢሆን ኖሮ አይንህ ላፈረ ብለሽ እስከወዲያኛው ፊትሽን ታዞሪብኝ ነበር፡፡ ምንስ ነገር ብበድልሽ አምርረሽ ልትጠይኝ ትችያለሽ.?ለዛ አቅሙ አለሽ?››

‹‹ቃል እንዲሁ አትድከም….ምንም ብትል መፅናናት አልችልም….በሰራሁት ቀሺም ስህተት ምክንያት በውስጤ የሚሰማኝ  ህመምና .ህሙም ያሳደረብኝን  ቁስለት ሊረዳልኝ የሚችል  አንድ ሰው በዚህ አለም ላይ አይኖርም…?ከአሁን በኃላ ህመሜን ብቻዬን ስታመም እኖራለሁ..ምን አልባት የመከራዬ መግል ሽታ የእኔ የሆኑትን ሰዎች እየከረፋቸው ስለሚቸገሩ ቀስ በቀስ ከጎኔ ሊጠፉ ይችላሉ….››ንግግሯን አቋረጠችና  እየተንሰቀሰቀች መነፍረቅ ጀመረች……ቃል መቀመጫውን ለቆ ተነሳና ከጎኗ ተቀመጠ...ቃላት ሳይጠቀም ወደደረቱ ጐተታትና አቀፎ ግንባሯን በመሳምና   ፀጉሯን በማሻሸት  ያጽናናት ጀመረ፡፡
‹‹ቃልዬ›› ለስለስ ባለ ድምጽ ጠራችው

‹‹ወዬ ጊፍቲ››

‹‹በፈጠረህ አንድ ነገር ላስቸግርህ፡፡››

‹‹ምንደነው  የፈለግሺውን››አላት

በውስጡ ግን አሁን ይቅር በለኝና ዛሬውኑ እንጋባ ብትለኝ ምን መልስ እሰጣታለሁ? እያለ መሳቀቅ ጀምሮ ነበር፡

‹‹እስቲ ስደበኝ…ሸርሙጣ ነሽ፤ከዳተኛና አዋራጅ ሴት ነሽ… ብለህ ስደበኝ ..ከተቻለህም በጥፊ አጠናግረኝ…ምራቅህንም ሀክ እንትፍ ብለህ ግንባሬ ላይ በመትፋት ጥለኸኝ ሂድ..ያዛን ጊዜ ትንሽ ቀለል ይለኝ ይሆናል፡፡››በማለት ያልጠበቀውን ንግግር ተናገረች፡፡አሳዘነችው፡በውስጡም የጥፋተኝነት ስሜት ያሰቃየው ጀመር፡፡
‹‹እንደዛ መቼም እንደማላደርግ ታውቂያለሽ…አንቺ ለእኔ እኮ ፍቅረኛዬ ብቻ አይደለሽም እህቴም ጭምር ነሽ…››
‹‹ይሄው እንደገመትኩት ክፉ እኮ ነህ..ሰውን የምትቀጣበት መንገድ መራር ነው…ያንተ ቅጣት ነፍስ ላይ ነው ጠባሳ ሚጥለው፡፡››
‹‹ስለተበሳጨሽ ነው እንዲህ የምትይው…ጊዜ የውስጥን ቁስል ይፈውሳል…ለራስሽ ጊዜ ስጪና ለመረጋጋት ሞክሪ…ሰው ስለሆንሽ ሰው ሚሰራውን ነገር ነው የሰራሽው ስህተት ቢሆን እንኳን ይቅር የማይባልና የማይስተካከል ስህተት የለም፡፡››
‹‹እንዴት ..?እስኪ ንገረኝ ብልቴ ውስጥ ሲዋኝ ያደረውን ብልቱን እንዴት አድርጌ እንዳልተፈጠረ ማድረግ እችላለሁ…?ዕድሜ ልኬን ላንተ እንኳን ከመስጠት ሰስቼ ሳሽሞነሙነው የነበረውን ድንግልናዬንስ እንዴት አድርጌ ወደቦታው ልመልሰው እችላለሁ..?ነው ወይስ ሰርጀሪ ላሰራው?፡፡››
‹‹ጊፍቲ ኮ… ተይ እንጂ.. አንቺ እኮ በጣም ጠንካራ ልጅ ነሽ ፡፡ በህይወትሽ ብዙ ከዚህ በጣም የከፉ አስቸጋሪ  መከራዎች አጋጠጥመውሽ በትግስትና በብልሀት አልፈሻቸዋል…አሁንም ንም ትወጪዋለሽ…ታውቂያለሽ እኔም ከጎንሽ ነኝ፡፡››

‹‹ተው ቃል ….በዚህ ልክ የህይወቴን መስመር ድብልቅልቁን የሚያወጣ መከራ ገጥሞኝ አያውቅም ወደፊትም አይገጥመኝም…ልፋ ሲልህ የማይሰራ ምክር ነው እየመከርከኝ ያለኸው...ተመልከተኝ እስኪ ክስተቱ ልቤን አድቅቆታል፤ ውስጤን  በታትኖታል…፡፡አዎ ሞራሌን ተሰባብሯል …ሰባአዊነቴንም አክስሞብኛል…  የሚቧጥጥ ጥፍርና..ያገጠጡ ስል ጥርሶች ያሉት   የሚዘነጣጥልና የሚሸረካክት አውሬ በውስጤ እየተፈጠረ ይመስለኛል….እኔ በጣም መጥፎ ሰው ነኝ  …? መጥፎነት ፈፅሞ አይግልጻውም..ፈፅሞ…››መለፍለፎን ማቆረጥ አልቻለችም፡፡
👍86😢128🔥2👏1
‹‹ተገናኝታችሁ ታውቃላችሁ…ማለቴ ከክስተቱ በኃላ››
ደንግጣ አይን አይኑን እያየች‹‹ከማን ጋር?››ስትል መልሳ ጠየቀችው፡፡
‹‹ከመድሀኔ ጋር››
እንዴት ልንገናኝ እንችላለን›››ይሄው ሳምንቴ ነው ከዚህ እቤት አልወጣውም…የአመት ፍቃድ እንኳን የወሰድኩት በስልክ በመደወል ነው፡፡እንደምታውቀው ስልኬም አይሰራም…ከዛ የተረገመ ቀን በኃላ ሰው ሳገኝ አንተ የመጀመሪያው ነህ….ከእሱ ጋር ዳግመኛ ምገናኝበት ምክንያት የለም….ከእሷም ጭምር…ደግሞ እኮ የሚገርመው የራሴን ህይወት ድብልቅልቁን ማውጣቴ ሳያንስ ለመጋባት ሁለት ወር የቀራቸውን ፍቅረኛሞች ህይወት ማበላሸቴ  ነው፣››
ቃል የጊፍቲ ሀዘን ከጠበቀው በጣም የመረረ ስለሆነ በጣም አዘነ…እውነቱን ሊነግራት ቢችልና እሷ ሰውን በዳይ ሳትሆን ተበዳይ እንደሆነች በመረጃ አስደግፎ በማስረዳት ከዚህ ቆሻሻ ህመም ቢያክማት ደስ ይለው ነበር ፤ግን እንደዛ ማድረግ አይችልም…ለእሷም ሆነ ለእሱ የወደፊት ህይወት እውነቱ እንደተዳፈነ መቅረት አለበት….ልዩ ጊፍቲ ላይ ባደረሺው ሀዘን በቅርብ አንቺም ላይ ይደርሳል››ሲል በውስጡ  ፎከረ.‹‹ግን እኔስ….?በቀጥታ ያደረኩት ነገር ባይኖርም  ነገሮችን ከመጀመሪያው ጀምሮ የልዩን እቅድ አውቃለሁ.. ልዩን ላስቆማት ወይም ጊፍቲን ላስጠነቅቃት እችል ነበር፤ ግን አላደረኩትም..የእኔስ ቅጣት ምንድነው?›› ሲል እራሱን ጠየቀ…የእሱ ቅጣት ከልጅነት ጀምሮ  ከጎኑም በልቡም ውስጥ ያለችውን ጊፍቲን እስከወዲያኛው ማጣት ነው፡፡‹‹ይሄ ቅጣት ካልሆነ ሌላ ምን ቅጣት ይሆናል›› ሲል በውስጡ አሰበ፡፡
እዛው አድሮ ጥዋት ተሰናብቶት ወደ ስራው ሊሄድ ሲል ደውሎ ሁኔታውን ለልዩ ነገራት፡፡

ይቀጥላል
👍84😢65🥰5🤔2🤩2
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ስምንት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// ጊፍቲ ሕይወት ቀፏታል.. ሁሉ ነገር ጭልምልም ካለባትና ክፉ በሆነ በሀይለኛ እራስ ምታት በታጀበ ድባቴ ውስጥ ከገባች ሳምንት ሞላት …..በዚህ ሀዘን ላይ በጣላት ክስተት ማንን ተወቃሽ እንደምታደርግ አለማወቋ ነው ይበልጥ ህመሟን ያጠነከረባት…ሰው ሰውን ሲቀየምና ሲጠላ ምንም አይደል…ሰው አምላኩን ቢቀየምም ምንም አይደል(ምክንያቱም…»
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

ከክስተቱ በኃላ መድህኔ ልዩ ቤት ድረስ አይኑን በጨው አጥቦ ሊያናግራትና ይቅርታ ሊጠይቃት መጥቶ ነበር..የመኝታ ቤቷን በራፍ ግን ልትከፍትለት አልፈቀደችም…ለእናቷም የሰርግ ዝግጅቱን እንዲያቆሙና ከመድህኔ ጋርም  ፍፅም እንደማትጋባ ስትነግራቸው. መጀመሪያ በጊዜያዊ ንዴት ተገፋፍታ የተናገረችው ነው ብለው ትኩረት አልሰጡትም ነበር…ውሎ አድሮም ምንም አይነት የመርገብም ሆነ የመረጋጋት ሁኔታ ስላልታየባት እየደነገጡ ሄዱ….ከዛ ምክንያቱን እንድትነግራቸው አምርረው ጨቀጨቋት…‹‹ከጓደኛዬ ጋር ሲማግጡ አንድ አልጋ ላይ ያዝኳቸው›› ብላ እቅጩን ነገረቻቸው…ባለማመን እራሱ መድህኔ ጋር ደውለው ጠየቁት…አላደረኩትም ብሎ ሊክዳቸው አልቻለም...ከዛ እሷቸውም እጥፍ በሆነ ምሬት መድሀኔን ተቀየሙት… እሷን መጨቅጨቁንም ሆነ የሰርጉን ወሬ እርግፍ አድርገው በመተው ልጃቸው ብቻ በብስጭት አንድ ነገር እንዳትሆንባቸው  በስስት መከታተላቸውን  ቀጠሉ፡፡

ስለጊፍቲ ሁኔታ ደግሞ ቃል አንድ ሁለት ቀን  እቤቷ ድረስ በመሄድ እንዳገኛትና ያለችበት ሁኔታ የከፋ የሚባል እንደሆነ ነገሯታል….መድሀኔና ጊፍቲም ተገናኝተው እንደማያውቁ ሲነግራት ስጋት ውስጥ ገብታለች።

‹‹በዚህ የቃል ሀዘኔታ  ጊፍቲ እግሩ ላይ ወድቃ ይቅርታ ብትጠይቀው አይኑን ሳያሽ ነው ይቅር የሚላት።››ስትል ስጋት ውስጥ ነች፡፡ምን ማድረግ እንዳለባት ግራ ተጋብታለች፡፡

ጊዜ ተለዋዋጭ ነው…በተለያ ሁኔታ ውስጥ ሊለጠጥና ሊኮማተር ሊረዘምና ሊያጥር ይችላል፡፡ጊዜ በተለያዩ የሰማይ አካላት ላይ ባላቸው ፍጥነት መጠን ልክ የተለያየ መጠን አለው፡አንድ ዓመት ርዝመት  በምድር ላይ እና በማርስ ላይ በጠጣም የተለያየ ነው…
በፍጥነት በሚጓዙ .የሰማይ አካላት  ላይ ሰዓት ሲኮማተር ዝግ በሚሉ ብለው በሚጓዙት ላይ ደግሞ ጊዜ ይለጠጣል ወይም ይረዝማል፡፡
አልበርት አንስታይን በቴኦሪ ኦፍ ሪላቲቪቲ መሰረት  የአንድ ቁስ ጉዞ ከብርሀን ፍጥነት በላይ በሚሆንበት ጊዜ ወደ ትናንና  ይጓዛል የሚለውን አረጋግጧል..ይሄ ማለት   የታይም ትራቭለር ሀሳብ  በዚህ ስሌት የሚሰላ ነው ፡፡
ይሄን ያሰበችው ቃልን ከማግኘቷ በፊት ያሳለፈችው ጊዜ ሲቆጠር ረጅም አሰልቺ አይነት ሲሆን አሱን  ካገኘች በኃላ ያሳለፈችው በሚዛኑ የቀኝና የግራ ሰሀን ላይ ቢቀመጥ  የትኛው በልጦ ይገኛል? ፡፡
ከቃል ጋር እያወራች ነው..እራሱ ደውሎ ነው ከቤት እንድትወጣ ያደረጋት..ምክንያቱም በጣም ልቧ ተሰብሯል…ምክንያቱም የእሱ ጓደኛና እጮኛ የእሷን እጮኛ አማግጣባታለች...ወይንም እርስ በረሻቸው ተመጋግጠዋል….ስለዚህ አፅናኝ ትፈልጋለቸ፡፡ይሄው አሁን ቃል እያደረገ ያለውም ያንን ነው፡
‹‹ልዩ የምሬን ነው በጣም ነው ያዘንኩት ..ልብሽ እንዲሰበር ስላደረኩ ይቅርታ›› አላት አንጀት በሚበላ  አሳዛኝ ንግግር፡፡
"አንተ ምን አደረክ...?እንደውም ከእኔ እኩል ተጠቂ ነህ።"
"አይ የእኔና ያንቺ አንድ አይደለም .›አላት፡፡
.‹‹ምን? የእኔ የራሴ ጥፍት ነው"ምን ለማለት እንደፈለገ ግልፅ አልሆነላትም‹ምን ማለትህ ነው?›ስትል ጠየቀችው፡፡
"ኃላፊነቴን ባለመወጣቴ ምንም ነገር ብታደርግ በእሷ ላይ ጣቴን የመቀሰር ሞራል የለኝም..ብቻ ከአንቺ  እጮኛ ጋር ለምን እንዳደረገችው ነው ሊገባኝ ያልቻለው?"
"ከእኔ እጮኛ ጋር ሆነ ከሌላ ጋር ምን ለውጥ አለው ..ክህደት ያው ክህደት ነው?"

"አይ እኔ ከድታኛለች ብዬ አላስብም...ጊፍቲ መቼም እኔን ልትከዳኝ አትችልም...ግን ከእኔ የምትጠብቀውን ለዘመናት ጠብቃ ስላጣች..ያደረገችውን ማድረጓ  ያንስባት እንደሆነ እንጂ  አይበዛባትም፡፡"

"እና አሁን ወደአንተ መጥታ ይቅርታ የምትጠይቅህ አይመስልህም"
"ይቅርታ..."
የመደነጋገር ስሜት ታየበት..‹‹ጊፈቲና መድህኔ ተበዳይ እእጂ በዳይ እይደሉም..ይቅርታ መጠየቅ ያለብን እኔና አንቺ ነን..››በማለት በውስጡ አያሰበ በአንደበቱ ግን"አይ ይቅርታ  የምጠይቃት እኔ ነኝ...... ጥፋተኛው እኔ ስለሆንኩ ላባከንኩት ጊዜዋ፤ላልከሰከስኩት ተስፋዋ፤ለሁሉም ነገር  ይቅርታ እጠይቃታለሁ።"አላት፡፡
ልዩ ሰውነቷ ሁሉ በፍርሀት መንዘርዘር ጀምሯል...ያ ሁሉ ልፋቷ ያ ሁሉ ጥረቷ   በዚህ ሰው አጉል የዎህነት ገደል  ሊገባባት እንደሆነ ታሰባትና ውስጧ በንዴት ተቃጠለ።እንዲህማ አያደርገኝም....፡፡
"እና ይቅርታህን ከተቀበለች በኃላ እንደድሯችን እንሁን ብትልህ እሺ ትላለህ?"
"ምን አልሽ? እንደውም እንደድሯችን መሆን አንችልም  ካለቺኝ  ነው እሺ ማልላት...እንደዛ መቼም አይሆንም፡፡"
"እንዴ ይሄ ምን የሚሉት ግራ የተጋባ ነገር ነው...ከእኔ ባል ጋር ፍቅር ይዞት ከሆነስ ...?እሱን ለማግባት ፈልጋለሁ ብትልህስ?›› ስትል ጭርጭር በሚያደርግ የንዴት  ጠየቀችው፡፡
"እሱን ማለቴ አይደለም... እንዳልሽው እሱን ታፍቅረውም ለማግባት ትሞክርም.. የእሷ  የራሷ መብቷ ነው። ያንን ምርጫዋን ሆነ ውሳኔዎን አከብርላታለሁ።ግን እሺ ማልላት ጓደኝነታችንን እናበላሽ ካለቺኝ ነው።…አዎ ሲሆን ሲሆን ይቅር ብላኝ ብታገባኝ ደስ ይለኛል.ከልሆና እንዳልሺው አሱን ወዳውም ከሆነ ችግር የለም ዋናው የእሷ ምቾት ነው››አላት…ቃል ንግግሩን ሆነ ብሎ የልዩን የአሸናፊነትና የስኬት ስነልቦና ለመናድ አልሞ ነው እየሰነዘረ ያለው.. እናም ደግሞ ተሳክቶለታል..ልዩ በተሸናፊነት መንፈስ እየተናጠችና በፍርሀት ስሜት እየተንቀጠቀጠች ነው፡፡

‹‹እና አንተን ጥላ መድሀኔንም አግብታ ቢሆን እንደበፊቱ ጓደኛዋ ሆነህ የመቀጠል ፅናቱ ይኖርሀል።››
"እንደዛ ካላደረኩ እኮ መጀመሪያውኑ  አልወዳትም ነበር ማለት ነው"አለትና አስደመማት።
ዝም አለች..."እኔ አሁን የመድህኔ መሳሳት የእኔ ስውር እጅ ስላለበት ይሉኝታ ይዞኝ ትንሽ ቀዝቀዝ አልኩ እንጂ ከእኔ እውቅና ውጭ  ወስልቶብኝ ቢሆን ኖሮ  ዘልዝዬ አልበላውም ነበር?›ስትል በውስጧ እራሷን ጠየቀች..፡፡
" እኔ ግን   መቼም ቢሆን መቼም ይቅር ልለውና  መልሼ እንደድሮችን ልቀበለው አልችልም።››ስትል ፍርጥም ብላ አቋሟን ለቃል ነገረችው፡
"እንደእጮኛ  ተቀበይው ብዬ  ላስገድድሽ አልችልም...ግን ከእዚህ በፊት እንዳጫወትሺኝ ከሆነ መድህኔ ፍቅረኛሽ ከመሆኑ በፊት የልጅነት ጓደኛሽ ነው። በጓደኝነት ህይወታችሁ  ብዙ መልካም ቀናትን… ብሩህ የሆኑ ትዝታዎችን አሳልፋችኋል...እና እሱን ከውስጥሽ እስከወዲያኛው ፈንቅለሽ ስትጥይ የራስሽንም መልካም ትዝታዎችንና ወርቃማ ትናንቶችሽን ነው አብረሽ የምትደመስሼያቸው... እሱን በጎዳሽው መጠን አንቺም ተጎጂያለሽ፡፡.››
"እና ምን እያልከኝ ነው?"
ከደረት ኪሱ እስኪረሪብቶና ብጣሽ ወረቀት አወጣና ሰጣት.::ግራ በመጋባት‹‹ምን ላድርገው?››ብላ ጠየቀችው፡፡
‹‹የምነግርሽን ነገሮች ለመፃፍ ተዘጋጂ››አላት፡፡
ምን ሊለኝ ነው በሚል ጉጉት እስኪርብቶውን ወረቀቱ ላይ ቀስራ መጠባበቅ ጀመርረች፡፡
‹‹መድህኔ በህይወት ጉዞዬ ጎደኛዬ በነበርክ ጊዜ…››
ቀና ብላ አየችው..
‹‹ፃፊው…፡፡››
‹‹መድህኔ በህይወት ጉዞዬ ጎደኛዬ በነበርክ ጊዜ››ብላ  ፃፈች፡
👍6711🥰2🤔1
‹‹እሺ ከዛስ?››
ከዛ አንድ ሁለት እያልሽ በጓደኝነት ግንኙነታችሁ በሀቀኝነት የነበረውን ጥሩ ጎኖቹን ፃፊ፡፡
‹‹አሺ›› ብላ መፅሀፍ ጀመረች፡
1/በተበሳጨሁና በምንም ነገር በከፋኝ ወቅት ሁሉ ከጎኔ በመገኝት ሊያፅናናኝና ሳቄን ሊመልስልኝ የተቻለውን ያህል ይጥራል፡፡
2/በየአመቱ በልደቴ ቀን ከእናቴ  ቀድሞ እንኳንም ተወለድሽ የሚል የመልካም ምኞት መግለጫ ከምርጥ ሰጦታ ጋር የሚያደርሰኝ እሱ ነው፡፡በዛም ሁሌ ጥሩ ስሜት እንዲሰማኝ ያደርጋል፡፡
3/ ለምንም ጉዳይ ስፈልገው ይገኛል…ፍላጎቴን ለማሟላት ሁሌ እንደተጋ ነው፡
4/ሁል ጊዜ እኔ አስቀይመዋለሁ .እሱ ይቅርታ ይጠይቀኛል፡፡ለምን በዛ መጠን እንደሚያሞላቅቀኝ አይገባኝም፡፡
5/ቤተሰቦቼን በተለይ እናቴን በጣም ያከብራል፡፡
ዝርዝሩን በመፃፍ ተመሰጠች‹‹ …ለጊዜው ይበቃል›› አለና የፃፍችውን ከእጇ ነጥቆ ማንበብ ጀመረ…እንደሚያነበው ብታውቅ ኖሮ እንደዚህ ግልፅ ሆና በዝርዝር አትፃፍም ነበር…
‹ዝም ብልሽ ይሄ ወረቀት አልቆ ሌላ ወረቀት ጨምርልኝ ልትይ ትችይ ነበር….ዋናው ልንግርሽ የፈለኩት ነገር…የቅርባችን ስለሆኑ ሰዎቸ በጊዜያዊ እልክ ምክንያት መጥፎ ስሜት ሲሰማን እንዲህ ወረቀት አውጥተን ያሳለፍናቸውን መልካም ነገሮች ብቻ በማሰብ  ያደረጉለንን ጥሩ ነገር  ዘርዝረን በመፃፍ ስሜታችንን ለማስተካከል ሞከር ጥሩ ዘዴ ነው…..እንሱን እስከወዲያኛው ለማጣት ከመወሰናችን በፊት አብረን የምናጣቸውንም ነገሮች ቀድመን እንድናስብ  ያደርገናል፡ትልቁ ተጓጂዎች እኛም ጭምር አንደሆን እንድናውቀ ያግዘናል፡፡ ››
‹‹እና››አለች እሷን  ለማሳመን የሄደበትን መንገድ አስገርሟት….
"እናማ ቢያንስ ይቅር በማለት ከሁለት አንድን አትርፊ እያልኩሽ ነው…ልክ እኔ ለማድረግ እንዳሰብኩት...፡ደግሞ እኛ ከእነሱ ጋር ያለንን የጓደኝነት ግንኙነት አተረፍን ማለት  እርስ በርሳችንም ያለን ግንኙነት ጭምር አዳን ማለት ነው..ማለቴ እኔ ከመዳኔ ጋር አንቺ ከጊፍቲ ጋር ..››.
"እሱስ እውነትህን ነው...አንተ እንደዛ እንዲሆን ከፈለክ ተስማምቼያለሁ...ይቅርታ ከጠየቁኝ ሁለቱንም ይቅር እላቸዋለሁ።›አለችው፡
"አመሰግናለሁ.  መልካም እርምጃ ነው..."

ይቀጥላል
👍1095👏5👎4🥰2😢1
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// ከክስተቱ በኃላ መድህኔ ልዩ ቤት ድረስ አይኑን በጨው አጥቦ ሊያናግራትና ይቅርታ ሊጠይቃት መጥቶ ነበር..የመኝታ ቤቷን በራፍ ግን ልትከፍትለት አልፈቀደችም…ለእናቷም የሰርግ ዝግጅቱን እንዲያቆሙና ከመድህኔ ጋርም  ፍፅም እንደማትጋባ ስትነግራቸው. መጀመሪያ በጊዜያዊ ንዴት ተገፋፍታ የተናገረችው ነው ብለው ትኩረት አልሰጡትም…»
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሰላሳ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///
ይሄን ሁሉ ወሬ ያወሩት አንድ ሬስቶራንት ገብተው እራት እየበሉ ነው።ሰዓቷን ስታይ 2:30 ሆኗል።መኪና ስለያዘች ወደቤት ለመሄድ ሰዓቱ ገና ነው..ግን መሄድ አልፈለገችም.....፡፡
"ቃልዬ ...ዛሬ አንተ ጋር ማደር እችላለሁ?"ስትል ጠየቀችወ፡፡
"ችግር የለውም ...ግን እቤት ቅር እንዳይላቸው፡፡››አላት፡፡
‹‹አይ .እሱን እኔ አስተካክላለሁ… ችግር የለውም››አለችው፡፡
ከሆነ እሺ ›አለና ተያይዘው ወደ ቃል ቤት አመሩ፡፡
እራታቸውን ውጭ ስለበሉ ቀጥታ ወደ መኝታ ቤት ነው ያመሩት።ያው እንደ ለማዳነቷ አልጋው ላይ ተቀመጠች.. ቃል ቀጥታ ወደ ቁምሳጥኑ ሄደና ከፍቶ ልብሶችን እያነሳ እየጣለ‹‹ ...የእኔን ቢጃማ ብሰጥሽ ይደብርሻል...ከታጠበ በኃላ አለበስኩትም" አለት.፡፡.
ግን.‹‹ወይ አለመተዋወቅ›አለች በውስጧ ቃል ያላወቀው እንደውም ለብሶት ሙሉ በሙሉ ጠረኑ እንደተጣበቀበት ቢሆን እርካታዋ ወሰን አልባ ይሆን እንደነበረ ነው...‹‹ምን ያደርጋል ይሄንን ግን እሱ አይረዳለኝም›ስትል በውስጧ አማረች፡፡በጣም በጥልቀት እንደሚረዳትና ግን ደግሞ አውቆ ያልተረዳት እያስመሰለ እንደሆነ ቢገባትስ ምን ትል ይሆን?፡፡
"አረ ችግር የለውም ..ስጠኝ ደስ ይለኛል"አለችው..ነጭ ቢጃማ ሱሪ ከነአላባሹ አቀበላት ...ተቀበለችና ጎኗ አስቀመጠችው"አሁን እንዴት ነው የለበስኩትን አውልቄ ይሄን የምለብሰው ...ቀሚስ ለብሼ ቢሆን እንኳን ቀላል ነው ...ግን አሁን የለበስኩት ሱሪ ነው...ቃል ፊት ሱሪዬን አውልቄ በፓንት ቆሜ ቢጃማ መልበስ...‹አይ ወደ መታጠቢያ ክፍል ልግባና እዛ ልቀይር›ብላ በማሰብ ወሰነችና...መልሳ ሀሳቧን ሰረዘችው፡፡
‹‹እዚሁ እሱ ፊት ነው መቀየር ያለብኝ...እኔ በገዛ እጮኛው ባሌን የተነጠቅኩ እና ልቤ የተሠበረ ንክ ነኝ ...ቢያንስ እሱ እንደዛ ነው የሚያውቀው እና ምንም ነገር ባደርግ በሀዘኔታ ከማየት ውጭ ምን ማለት ይችላል...?ለዛውስ እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች እየተጠቀምኩ ልብን ካልሸራረፍኩ እንዴት ነው ትልቁ እቅዴ ጋር የምደርሰው፡፡››በማለት እራሷን አበረታታችና ተነሳች፡፡ ቆመች፡፡ በአንድ ሜትር ርቀት ፊት ለፊቷ ነው ያለው...የጂንስ ሱሪዋን ቁልፍ ፈታ ዚፑን ወደታች ሳታንሸራትት እሱ እጅ ላይ ያለውን ሌላ ሰማያዊ ቢጃማ ይዞ ፊቱን አዙሮ ወደሚቀጥለው ክፍል ገባ....እንግዲህ ይሄ ማለት አልማችሁ ልትተኩሱ ቃታውን ስትስብ ቃ..ቃ ብቻ ብሎ ሲከሽፍባችሁ የሚሠማችሁን ስሜት በሉት።‹‹አይ ቃል አሁን የእኔን ከፊል እርቃን ላለማየት ካልሆነ በስተቀር የአንተንማ...እያንዳንድን የሠውነት አካሉን ማንም ሌላ ሰው ካየው በላይ አገላብጪ አይቼዋለሁ...እድሜ እዚህ ክፍል ለቀበርኳት ስውር ካሜራ ...የማርያም ስሞሽ ጥቁር ነጥብ ምልክት የት የት ጋር እንዳህ...በሰውነትህ ላይ ያለው ፀጉር የት ጋር እንደሚበዛ እና የት ጋር እንደሚሳሳ... የደረትህን መጠነ ስፋት እና የእንብርትህን ጉዶጓድ ጥልቀት ጭምር አውቃለሁ....እናም ይበልጥ ሚስጥራዊ ስለሆኑ የሠውነት ክፍሎቹም ርዝመትና እጥረት፤ ውፍረትና ቅጥነት በዝረዝር መናገር እችላለሁ...ቃል ግን ይሄንን ቢያውቅ ምን ይላል..." እያለች ስለራሷ የሚስጥር ጎተራነት በኩራት እያሰበች ባለችበት በዛው ደቅቃ ቃልም የእሷን እያንዳንዷን እርቃን የሰውነት ክፍሏን በተለያየ ቀን ክፍሉ ተቀምጦ ላፕቶፐ ላይ እየመጣለት ደጋሞ ያየውንና ያጠናውን በምልስት እየከለሰ በፈግታ ተሞልቶ ነበር ልብሱን እየለበሰ ያለው..
ሲጨርስ የመኝታ ቤቱን በራፍ አንኳኳ..
"ቃል ግባ ጨርሼያለሁ"አለችው፡፡ከፍቶ ገባ...ጨርሳ ከውስጥ ገብታ ተኝታ ነበር...
"ተኛሽ እንዴ?"
‹‹አዎ…ምነው?›› ምነው አባባሎ .ከመተኛቷ በፊት እንድታደርግለት ወይም እንድትሰጠው የሚፈልገው ነገር ካለ ብላ ነው፡፡
"አይ ምንም›› አለና እሱም እንደእሷው ተኛ .. በመሀከላችን የአንድ ክንድ ክፍተት ቢኖርም እሷም ወደ እሱ ዞራ እሱም ወደእሷ ዞሮ ፊት ለፊት እየተያየን ነበር የተኙት፡፡
"እንዴት ነው አሁን ተረጋጋሽ?›
‹‹ አዎ..ዕድሜ ላንተ ምንም አልል "አለችው…
‹‹ እጅሽን ስጪኝ ?››አለት.
ለምን እንደፈለገው ግራ ቢገባትም ቀኝ እጇን ሰጠችው.. በግራ እጅ ጨበጠው…‹‹ ያኛውንም›› አላት …በተመሳሳይ ሰጠችው… በሌለኛው እጅ ጨበጠው....ሰውነቷን ውርር አደረገው....ዛሬ ነገሮች መልካቸውን ሊቀይሩ ነው ስትል በውስጧ አሰበች ..ግን ወዲያው ነበር ሀሳቧ የተወላገደና የተሳሳተ መሆኑን የተረዳችው..."ከመተኛታችን በፊት በቀን ውሎችን ስላተሰጠን በጎ ነገር ሁሉ እንድናመሠግን ፈልጌ ነው"አለ
"ተኝተን?"
"ችግር የለውም …ዎናው ልባችን አለመተኛቱ ነው"
‹‹እሺ እንዳልክ ››አለችና እራሷን ዝግጅ አደረገች...አይኖቹን ጨፈነና ማነብነብ ጀመረ.. ከተወሰኑ ደቂቆች በኃላ የሚላቸውን ነገሮች በግልፅ መስማት አቁማ ነበር ... የሆነ የሚያንሳፍፍ አይነት መመሰጥ ውስጥ ገብታ እየቀዘፈች ነው። ሰውነቷ ሲላቀቅና ሲፍታታ፤ እናም ክብደት አልባ ሲሆን እየታወቀት ነው።አእምሮዋ ውስጥ የሆኑ የብርሀን ፍንጥርጣሪዎች ሲደንሱ ይሰማታል፡፡
...ቃል የምስጋና ፀሎቱን አጠናቆ እጆቾን ቢለቃቸውም እሷ ግን ቀጥላለች...አይኖቾ እንደተጨፈኑ አንደበቶም እንደተዘጋ ቢሆንም ውስጧ ግን እያነበነበ ነው።
‹‹…ቃልዬ አንተን መተዋወቄን እንደመባረክ ነው የምቆጥረው..አንተ ውስጤ ተደፍኖ የኖረውን እሳት የምታወጣልኝ የፍቅሬ ነዳጅ ነህ..አሁን እየተነፈስክ ያለኸው ትንፋሽህ ወደ ውስጤ ሰርጎ ሲገባ ኃይለኛ የኤሌክትሪክ ሞገድ በውስጤ ፈጥሮ ሲያንዘፈዝኝ ይታወቀኛል...ከንፈርህ ከንፈሬ ላይ ባይጣበቅም በጥልቀት ነፍስህ ድረስ ጠልቄ እየሳምኩህ ነው።እጆችህ እርቃን ሰውነቴ ላይ አርፈው እየዳበሱኝ ባይሆንም እኔ በፍቅርህ ቅልጥልጥ ብዬ እየተዝለፈለፍኩ ነው... ቢጃማዬንና ፓንቴን አውልቀህ ጥለህ ጭኔን ፈልቅቆ ውስጤ ለመግባት ባትሞክርም እግሮቼ ተከፋፍተው ሴትነቴ ረጥቦልህ እየቃተትኩ ነው...እንዲህ አይነት ፍቅር ማንንም አፍቅሬ አላውቅም.. እንዲህ አይነት ወሲብ ከማንም ተዋስቤ አላውቅም ...እንዲህ አይነት ስጋንም ነፍስንም በአንዴ ከፀባኦት አድርሶ የመመለስ አይነት የጦዘ እርካታ ማንም እንድረካ አድርጎኝ አያላውቅም..ወደፊትም ማድረገግ አይችልም…፡፡አንተ ግን..አንተ ግን...አንተ ግን ለስንት ጊዜ እንደደጋገመችው አታውቅም…ሰውነቷን ተርገፈገፈ..ጭው አለባት...ለአስር ደቂቃ በኃላ አይኖቾን መግለጥ ቻለች ...ቃል ርቀቱን እንደጠበቀ ጭልጥ ያለ ሠላማዊ እንቅልፍ ውስጥ ነው...እሷ ግን ምን ውስጥ ገብታ ነው የወጣችው ?የምታውቀው ነገር አልነበረም‹‹ቆይ አንድ የሚወድትን ሰው አጠገብ ተኝተው ግን ደግሞ ጫፍን ሳይነኩት በሀሳብ እያለሙ ብቻ ፍቅር መሰራት…ከዛም በተግባር የመጨረሻውን እርካታ መርካት ይቻላል እንዴ?እንዲህ አይነት ተአምር የትኛውም የፍቅር ፊልም ላይ ሆነ መፅሀፍ ሊይ አላነበብኩም….አሁን ቃል ምን አስቤ ምን እንደሰራው ቢያውቅ እንዴት ይታዘበኛል...?››ስትል ራሷን ጠየቀች…ፊቷን ከእሱ መለሰችና ጀርባዋን ሰጥታው ጥቅልል ብላ ተኛች...ደስ የሚል ሠላማዊ እንቅልፍ።


ይቀጥላል
👍14219👎5🤔3🥰2
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// ይሄን ሁሉ ወሬ ያወሩት አንድ ሬስቶራንት ገብተው እራት እየበሉ ነው።ሰዓቷን ስታይ 2:30 ሆኗል።መኪና ስለያዘች ወደቤት ለመሄድ ሰዓቱ ገና ነው..ግን መሄድ አልፈለገችም.....፡፡ "ቃልዬ ...ዛሬ አንተ ጋር ማደር እችላለሁ?"ስትል ጠየቀችወ፡፡ "ችግር የለውም ...ግን እቤት ቅር እንዳይላቸው፡፡››አላት፡፡ ‹‹አይ .እሱን…»
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

ልዩ ከመድህኔም ሆነ ከጊፍቲ ጋር በአካልም ሆነ በሰልክ  ከተገናኘች ሁለት ወር ተቆጠረ፡፡ሰሞኑን የምርቃት ሽር ጉድ ላይ ስለሆነች ሀሳቧን ለጊዜውም ቢሆን ከእነሱ ላይ አንስታለች…

የሚቀጥለው እሁድ የምረቃ ፕሮግራም አለባት…ነገሩ በገዛ ሴራዋ ድብልቅልቅ ባታደርገው ኖሮ ቀለበቷም ጭምር የሚደረግበት ቀን ነበር፡፡በዚህ ሀሳብና ሁኔታ ላይ እያለች ነበር ትናንት ማታ ቃል ደውሎ ነገ በስድስት ሰዓት እሱ ቤት እንድትመጣ የነገራት።ምክንያቱን ስትጠይቀው ‹‹ስትመጪ ትደርሺበታለሽ›› አላት። በዚህም የተነሳ ልቧ እንደተንጠለጠለ መሽቶ ነጋ።

ሁል ጊዜ ቃል ፈልግሻለሁ ባላት ቁጥር ለምንድነው ልቧ   የምትቅበዘበዘው? ሁሌ የማይገባት ጉዳይ ነው… አምስት  ተኩል ሲሆን ነው አምራና ተሸቀርቅራ እቤት የደረሰችው....እቤቱ የቀጠራት የፍቅር ጥያቄ ሊጠይቃት እንደሆነ 90 ፐርሰንት እርግጠኛ ነች...እሱ ደፍሮ ባይጠይቃት እንኳን ትንሽ ፍንጭ ካሳያት እሷ ገፍታበት የውስጧን ዘክዝካ ልትነግረውና የዘላለም ፍቅረኛዋ እንዲሆን ልትጠይቀው አስባበትና ተዘጋጅታበት ነው የመጣችው፡፡ ስትደርስ ቤቱ በምግብ ሽታ ታውዷል "ስትገባ በሞቀ ፈገግታና  ሠላምታ ተቀበላት የሚሰራውን ምግብ ገና ስለነበረው ታግዘው ጀመር..እየተዘጋጀ ያለው የምግብ ብዛት ግን ለሁለቱ ብቻ አልመስል አላትና ደባሪ ስጋት በእምሮዋ ሽው አለባት…እሱን ጠይቃ ለማረጋገጥ ግን አልፈለገችም፡፡ስድስት ሰዓት ሲሆን በራፍ ተቆረቆረ..‹‹ ሂጂና ክፈቺ ››አለት፡፡ የቃል የቤት አከራዮ ናቸው በሚል ግምት ቂው ቂው እያለች ሄዳ ስትበረግደው  ፊቷ የተጋረጠው ሰው ያልጠበቀችው ነበር..ልክ እንደናፈቀ ሰው  ተንደርድራ ልትጠመጠምባት ነበር.. ለጥቂት ነው ትውስታው በአዕምሮዋ ብልጭ ሲል  እራሷን የገታችውና..እንደመመናቀር ብላ በራፋን በመልቀቅ ወደውስጥ የተመለሰችው...፡፡እሷ ካለች ቃላ ላሰበችው ነገር እንዳልጠራት አወቀችና በጣም ተከፋች….

"ማነው?"ጠየቃት ቃላ..አልመለሰቸለትም ዝም አለችው   ..ቃል ግን ወዲያው ገባውና  የሚሰራውን ምግብ አቋሞ ወጣ ""ጊፍቲ..እንኳን በሰላም መጣሽ" "ብሎ ተጠመጠመባት ..አገላብጦ ሳማት...ጊፍቲ ቅዝቅዝና ቅዝዝ ባለ ስሜት አፀፋዋን መለሰች ..ወስዶ ምግብ የተደረደረበት ጠረጴዛ አካባቢ አስቀመጣትና ትኩር ብሎ አያት ..ባለፈው ካያትም በላይ ጉስቁልና ጥቁርቁር ብላለች…ውስጡ አዘነ..ፊቱን አዙሮ ወደ ልዩ እየተራመደ ሳለ  በራፉ ዳግመኛ ተቆረቆረ...ልዩ ባለችበት ግራ ተጋባች ‹‹ዛሬ ምንድነው .? ›ስትል አጉረመረመች….ሄዶ ከፈተው።

"ኦ መድሀኔ ...እንኳን በሰላም መጣህ… ግባ›› ሲል ልዩ ሠማች ባለችበት ሽምቅቅ ነው ያለችው፡፡

‹‹ወይ ጉዴ ጭራሽ ያን ሁሉ የለፋሁበትን ነገር ገደል ከተተው..ይሄ ልጅ ምን እየሠራ ነው? ። እንዲህ በድንገት አንድ  ቤት የሠበሰበን ሊያቧቅሰን ነው ወይስ ሊያስታርቀን?ሊያስታርቀን ከሆነ በምን መልኩ።እንደድሮችን እንድንጣመር ወይስ በአዲስ አሰላለፍ...?››በደቂቃ ውስጥ አእምሮዋ ውጥርጥር አለ።
ከዛ የተሰራው ምግብ ሁሉ ጠረጴዛው ላይ ቀረበ...ሁሉም በተኳረፈ ስሜት ቢሆኑም ጠረጴዛውን ከበው ተቀመጡ.የቀረበውን ምግብ በልተው አጠናቀቁና የተበላበትን ሰሀኖች ተገጋዘው በማንሳት መልሰው በጠረጴዛው ዙሪያ ተቀመጡ።በዛ በውጥረት ውስጥ የመናገር  ቅድሜያውን የወሰደው  ቃል ነው።

ያው እንግዲህ  ሁላችንንም  እዚህ  ለምን እንድንገናኝ እንደፈለኩ ታውቃላችሁ።ባታውቁም መገመት አይከብዳችሁም፡፡ በመካከላችን ደስ የማይል ነገር ተፈጥሯል። እንደድሮችን እርስ በርስ አንገናኝም፤አንደዋወልም ይሄ ከዛሬ ጀምሮ በዚህ አይነት ሁኔታ መቀጠል የለበትም።

ልዩ ጣልቃ ገባች"ቃል እነሱ በእኛ ላይ የፈፀሙት በደል እኮ መቼም ይቅርታ የሚያሰጥ አይደለም" ተንዘረዘረች.አዎ በተቻላት አቅም ነገሩን ከመጀመሩ በፊት ልታስቆም እየጣረች ነው፡፡

ቃል ግን ቀድሞውንም ይሄን ገምቶ የተዘጋጀበት ጉዳይ ስለነበር በጥንካሬ ተጋፈጣት‹‹አይ… ይቅርታ የማያሰጥ አንድም በደል  የለም...ደግሞ በግንኙነት ውስጥ አንድ በአንድ ነገር ሲበድል  ሌላው ደግሞ በሌላ መበደሉ አይቀሬ ነው...ስለዚህ እሱ የበደለው ይቅር እንዲባልለት እሱ ቀድሞ  የጓደኛውን በደል  ይቅር ማለት አለበት።ጊፉቲ  አንቺ ለእኔ በጣም አስፈላጊ ሰው እንደሆንሽ ታውቂያለሽ  ።ለሁለታችንም ግንኙነት ብዙ ብዙ መስዋአትነት ከፍለሻል..አንቺ በጣርሺው መጠን እኔ አልጣርኩም.. በዛም በጣም አዝናለሁ...እባክሽ  በውስጥሽ ለፈጠርኩት መጥፎ ስሜት በአጠቃላይ ከልብሽ ይቅር እንድትይኝ እፈልጋለሁ"በማለት ከመቀመጫው ተነሳና በተቀመጠችበት እዛው ይዞ ጉልበቷ ላይ ተደፋ...እሷም እጇን ጭንቅላቱ ላይ አድርጋ ፀጉሩን እያሻሸች ትነፈርቅ ጀመር..

መድሀኔ እንደፈዘዘ ነው። ልዩ ግራ ገብቶታል‹‹ ምንድነበር የተፈጠረው?ማን ነው ማንን ይቅርታ መጠየቅ ያለበት.....?እኔም ተነስቼ መድሀኔ እግር ስር ልደፋ እንዴ?›እያለች ስትብሰለስል በድንገት መድሀኔ ከተቀመጠበት ተነሳና መጥቶ እግሯ ስር ድፍት አለ"እባክሽ ልዩ በተፈጠረው ነገር በጣም አፍሬለሁ።እንዴት እንደዛ እንዳደረኩ አላውቅም ።በእውነት በዛ ስካርና የእብደት ቀን ከተፈጠረው ውጭ እምልልሻለሁ በእኔና በእሷ መካከል ምንም የለም...አንቺ መስለሺኝ እሷንም ያሳሳትኳት እኔ ነኝ።በዚህም ሶስታችሁም ይቅር እንድትሉኝ እፈልጋለሁ።

"በቃ ተነስ ይቅር ብዬሀለው ....ከአሁን ጀምሮ ግን ንፅህ ጓደኛሞች ነን"አለችው ፈርጥም ብላ..ፈጥና ይቅር ያለችው ሆነ ብላ የቃልን ትኩረት ለመሳብ ስለፈለገች ነው፡፡ባለፈው ከቃል ጋር ስለዚህ ጉዳይ ሲያወሩ እንዲ እንድታደርግ ስለነገራት ምን ያህል የእሱን ቃል አክባሪ እንደሆነች እንዲያቅላት ስለፈለገች ነው

መድሀኔ ግን ከፊል በሆነው ይቅርታዋ እርካታ አልተሰማውም.በልመናው ገፈበት"እባክሽ ልዩ እኔ እኮ በጣም ነው የማፈቅርሽ በዛ ላይ የሁለታችንም ቤተሠቦች ለሠርጋችን እየተዘጋጅ እኮ ነው።ይቅር ብለሺኝ እንደበፊቱ ካልሆን ምን ልንላቸው ነው።"

"አይ እንደዛማ ፍፅም አይሆንም...እኔ ለቤተሠቦቼ አንተን እንደማላገባ ነግሬቸው ዝጎጅታቸውን አቋርጠዋል...አንተም ጊዜውና ሳይረፍድ ዛሬውኑ ለቤተሠቦችህ ንገራቸው።

"ምን ብዬ.ቀለበቱን እንኳን እንዲቀር ለማድረግ ስንት ነገር ቀባጥሬ ነው…ከእነጭራሹ ሰርጉም ጭምር ቀርቷል ብላቸው ኸረ በስመአብ?"ዘገነነው

"እሱ ያንተ ችግር ነው..."

"ቃል አረ አንድ ነገር በላት...ቆይ አንተ ጊፍቲን በፍቅረኝነት አትቀበላትም።"ሲል አንጀት በሚበላ ድምፅ ጠየቀው

ልዩ የቃልን መልስ ለመስማት አይኖቾን አፍጥጣበት በጉጉት ትጠብቅ ጀመር..የፈራችውን አይነት መልስ መለሰ"ለምን አልቀበላትም የይቅርታ ግማሽ የለውም እኮ"

በቃል ንግግር ወሽመጧ ብጥስ አለ‹‹...ምን አይነት ሀሞት የሌለው ሰው ነው...የወራት ልፋቴን በጠቅላላ ገደል ሊከተው እኮ ነው.. አሁን እሺ ምን ላድርግ?።›በውስጧ አብሰለሰለች.ሀሞትና ከርቤ ቀላቅላ እንደተጋተ ሰው .አፏን መረራት…፡፡መድህኔ ተፍለቀለቀ...ግን የልዩ ብስጭት ሆነ የመድሀኔ ደስታ ለሽርፍራፊ ሰከንድ ብቻ ነው መቆየት የቻለው።ድንገት የመብረቅ ብልጭታ በሚመስል ክስተት ታአምር መሳይ ዜና ከጊፊቲ አንደበት ዱብ አለ"አርግዤለሁ"አለች...መድህኔ በተንበረከከበት ዝርፍጥ ብ ሎ መሬት ያዘ
👍712😱2😁1
‹‹ምን አልሺ ጊፍቲ…?››ልዩ ነች ጠያቂዋ
‹‹ሰሞኑን ጥሩ ያልሆኑ ስሜቶች እየተሰሙኝ ስለነበረ ወደእዚህ ከመምጣቴ በፊት ሆስፒታል ሄጄ ተመርምሬ ነበር….እንዳረገዝኩ ነገሩኝ››ብላ ከኪሷ የተሰጣትን የማስረጃ ወረቀት አውጥታ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠችው…..ከዛ በኃላ ማንም መናገር የደፈረ አልነበረም…‹‹.ወይኔ ጉዴ መድህኔ ቀድሞኝ በአቆራጭ የልጅ አባት ሊሆን ነው፡፡›ልዩ በውስጧ  በደስታ እየተፍለቀለቀች ያሰበችው የሽሙጥ መሳይ ሀሳብ ነበር ፡፡‹‹ይሄ ለእኔ ያልጠበቅኩት ቦነስ ነው፡፡እነዚህ ሰዎች ከአሁን ወዲህ ከመጋባት ውጭ ምንም ምርጫ የለቸው…፡፡ቃልም ከእኔ ውጭ ሌላ አፅናኝ ከወዴት ያገኛል….?ከየትም፡፡›ስትል በውስጧ በማሰብ በስኬቷ ተመፃደቀች፡፡

ቃልም አውጥቶ አይናገረው እንጂ በሰማው ዜና በውስጡ ተደስቶል ፤‹‹አሁን የጊፍቲን የወደፊት ህይወት በትክክለኛው አይሮፕላን ላይ መሳፈሩን እርግጥ ሆኖል ››አለ..አሁን እነሱን ገፋፍቶ ወደትዳር እንዲገቡ ማድረግ ለእሱ በጣም ቀላል ስራ ነው…ከዛ በገባው ቃል መሰረት እራሱን ሙሉ ለሙሉ ከመሰወሩ በፊት ልዩን ከሌብነት አመሏ ማላቀቅ ብቻ ነው የሚቀረው ለዛ ደግሞ በቂ የሚባል ጊዜ አለው…‹‹ጊፍቲና መደህኔ ላይ በሰራችው የብልጠት ሴራ  ቅጣቷን የምተታገኝ ቢሆንም በእሷ ስህተት ባልሆነ ጉዳይ ከገባችበት የሌብነት  ጣጣ ግን መፈወስ አለባት›› ሲል በማሰብ ቀድሞ ውሳኔውን ዳግም አፀደቀ ፡፡
ጊፍቲና መድሀኔ ግን ዜናውን ተከትሎ ምን እየተሰማቸው እንደሆነ ?እያዘኑ ይሁን ወይስ እየተደሰቱ? እራሳቸውም አያውቁትም…ሁለቱም ደንዝዘው እርስ በርስ በፍዘት  እየተያዩ ነው፡፡

ይቀጥላል
👍10011👎6🤔6😢6