አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
‹‹አይደለም…እንደውም አጋንኜዋለሁ..እንቁላል  መጥበስ ብቻ ነው የምችለው….›› እውነቱን ተናዘዘች….ግን ደግሞ የቤታቸው ሰራተኛ ይሄንን ንግግሯን ብትሰማ ትቃወማት ነበረ.ምንያቱም እንቁላሉንም ቢሆን ሰው አጠገቧ ሆኖ እንዲህ አድርጊ ይሄንን ጨምሪ ካላሏት በስተቀር በቅጡ ማድረግ እንደማትችል ታውቃለችና፡፡

እኚህንና የመሳሰሉትን ወሬዎች እያወሩ በጣም ጣፍጭና እጣት የሚያስቆረጥሙ የሚባሉ  ምግቦችን በልተው  ተነሱ። ከዛ መዳኒቷን እንድትውጥ    ውሀ አቀረበላትና‹‹  በይ ዋጪና ተመልሰሽ መኝታ ቤት ገብተሽ ተኚ ››አላት፡፡

‹‹መድሀኒቱን ውጠሸ ወደቤትሽ ሂጂ ምትለኝ ነበር የመሰለኝ››አለችው››

በንግግሯ ደንገጥ ብሎ‹‹አረ አይወጣኝም፡፡ ለምን መጣሽና ?ልታርፊ  እኮ ነው››

‹‹ስቀልድ ነው››አለችው…የሰጣትን መድሀኒት  ዋጠች…ይሄኔ መድሀኒቱን ዋጪ ያለቻት እናቷ ብትሆን ፊቷ ላይ በትናባት ነበር….ትህትና የተለበሰ ማራኪ ፀባዮ ለራሷም አስደመማት፡፡ከዛ  ልክ እንደለማዳ ድመት  አንገቷን አቀርቅራ ወደመኝታ ቤቱ ገባችና  አልጋ ልብሱን ተከናንባ ተኛች ።

የአንሶላውና የብርድልብሱ ጠረን ሳታስበው በጥልቀት ወደውስጧ ሳበችው …ከመቼ ወዲህ ነው የሌላ ሰው ጠረን በማቅለሽለሽ ፋንታ የደስታ ቅመም በውስጧ መበተን የጀመረው፡፡? አልገባትም.. ደስ የሚል ጭልጥ ያለ እንቅልፍ  ወሰዳት።

ይቀጥላል
👍10314🥰8
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_ሶስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ እየተከታተለን ያለ ሠው ቢኖር ሁለቱም ፊት ላይ የደስታ ካፊያ እንደተርከፈከፈባቸው የፊታቸው በድንገት ማብረቅረቅ በመመልከት   በቀላሉ ይረዳ ነበር፡፡ላዳ አስቆሙና ይዟት ገባ...በስድስት ደቂቃ ውስጥ እቤቱ ደረሱ። ግቢ ከፍቶ ወደ ውስጥ ሲያስገባት የቤቱ አካራይ በረንዳ ላይ ቆመው ነበር.. …ልትጠፋ ደርሳ ጭልጭል እያለች ባለች አይናቸው…»
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ስንት ሰዓት   እንደተኛች አታውቅም፡፡ ፍፁም ሰላማዊና ህልም አልባ እንቅልፍ ነበር። ነቃች።ከአልጋ ወረደች።ቀለል ብሏታል። ወደፊት ለፊተኛው ክፍል ስትገባ ባዶ ነው፡፡ እንደውም ተዘግቷል። ‹‹ባዶ ቤት ጥሎኝ የት ሄደ...?፡፡››ቅር አለት፡፡የቤቱን ዙሪያ ገባ ስትቃኝ መሀል ጠረጴዛ ላይ ወረቀት አየች፡፡ ወደእዛ ሄደችና አነሳችው… አነበበችው"
                         

ይቅርታ ስምሽን አላወቅኩትም ለማንኛውም
አስቸኮይ ስራ ስላጋጠመኝ ወጥቼያለሁ..
ሳልመጣ የምትሄጂ ከሆነ መኝታ ቤት ኮመዲኖ ላይ የታክሲ ብር አስቀምጪልሻለሁ።
ቤቱን ቆልፊና ፊት ለፊት ለአከራዮ ስጪልኝ።
በይ እግዜር ይማርሽ...አመሰግናለሁ።

አንብባ ስትጨርስ‹‹በቃ..? ››ስትል ጠየቀች፡፡

‹‹አይ እስክትመጣ አልሄድም..››ስትል ቃል አውጥታ ተናገረች… .አጠገቧ ያገኘችው ወንበር ላይ ተቀመጠች፡፡

‹‹ስሜ ልዩ ነው፡፡››ይሰማት ይመስል  በድጋሚ ጮክ ብላ ተናገረች፡፡

"ደግሞ እንዴት ይሄን ሁሉ ነገር አድርጎልኝ ሳላመሰግነው እሄዳለሁ..?እንደውም ጥሩ ምክንያት አገኘሁ ለእማዬ ደውዬ እንግራተና እዚሁ አድራለሁ..ከዛ የሚፈጠረውን አያለሁ››አለች ድንገት ከመቀመጫዋ ተነሳችና….ወደመኝታ ቤት ተመልሳ ገባች.. እንዳለው ኮመዲኖው ላይ ብር አስቀምጦላታል…አነሳችውና ቆጠረችው፡፡ ሶስት መቶ ብር ነው። ኮመዲኖ የታችኛው ቁልፍ እላዩ ላይ እንደተንጠለጠለ ነው፡፡ የምታውቀወ ግን የምትጠላውና የመትጠየፈው ቢሆንም ደግሞ ልትቆጣጠረው የማትችለው ኃይል በውስጧ ሲሰርግ ታወቃት.... የተጣባት የሌብነት መንፈስ አንበረከካት፡፡ ቁልፉን አሽከረከረችው… ተከፈተላት፡፡ ውስጡ ብዙ ሰነዶችና አንድ ላፕቶፕ አለ."ያለምንም ማቅማማት ላፕቶፑን አነሳችውና ፤300ብር በእጇ ጨምድዳ ይዛ መኝታ ቤቱን ለቃ ወጣች….እንዳለት ቤቱን ቆለፈችና ቁልፉን ለአሮጊቷ ሰጥታቸው ሰፈሩን በላዳ ለቃ ወጣች፡፡

መሄድ የነበረባ ወደጦር ኃይሎች ነበር ..ከዛ ወደትምህርት ቤቷ ሄዳ ግቢው ወስጥ ያቆመቻትን መኪና ይዛ ነበር ወደሳሪስ መሄድ የሚገባት ግን አሁን እንደዛ ማድረግ አልቻለችም ቀጥታ…ላፕቶፑን በደረቷ ላይ ለጥፋ ከካሳንቺስ እስከሳሪስ እያለቀስች ነበር የደረስችው...ልክ ላፕቶፕ ካልሰረቅሽ ህይወትሽን ታጪያለሽ ብለው በግዳጅ እንዳሰረቋት ነገር ነው ሁኔታዋ የሚመስለው፡፡

‹‹አሁን ለዚህ ልጅ በዚህ ደግነቱ እንዲህ መዘረፍ ይገበዋል…?.እኔስ ዘራፊና ሌባ መሆን ይገባኝ ነበር…?አረ ጌታ ሆይ እውነት በመንበርህ ካለህ አንድ ነገር አድርግ..ነው ወይስ የሌባ ፀሎት አንተ ጋር ምንም እርባን የለውም…ምንም ሌባ ብሆነ እኮ ያው አንተው ነህ የፈጠርከኝ››ስትል አምርራ ወደፈጣሪዋ አጉረመረመች፡፡
///
እቤት እንደደረሰች በራፍን የከፈተላት ዘበኛ በድንጋጤ ጭንቅላቱን ያዘ፡፡ በረንዳ ስታፀዳ የነበረችው የቤት ሰራተኛም  መወልወያዋን በቁማ ጥላ‹‹  እትዬ..ልዩ ተጎድታለች..እትዬ ልዩ ተፈንክታልሽ መጣች....››እያላች ወደግዙፍ ባለሁለት ፎቅ ህንፃ ገባች..እሷ የሳሎን በረንዳ ላይ ስደርስ እቤት ውስጥ የነበሩት ቤተሰቦቾ በጠቅላላ በእናቷ ፊት መሪነት እየተንጋጉ ዙሪያዋን ከበቧት፡፡
…እናቷ እሪታዋን ለቀቀችው..‹‹ወይኔ ልጄን ይሄው ገደሏት…ወይኔ ምነው እመቤቴ ..?ምነው አንቺም ልጅ አለሽ …የአንድ ብቸኛ ልጅ እናት መሆን ፈተናውና መሳቀቁ ምን ያህል ጥልቅ እንደሆነ ካንቺ በላይ የሚያውቀው የለም… ታዲያ ምን አለ ብትሰሚኝ   ››ልክ የሞተችና  ሬሳዋን ተሸክመውላቸው የመጡ ነው ያስመሰሉት፡፡
አዛኙም አሽቃባጩም በአንድነት ከበቧትና  አፋፍሰው ልክ መራመድ እንደማትችል ወደውስጥ ይዘዋት ገቡ፡፡ እሷም ሲደጋግፏት ያልነበረ ህመሟ ከያለበት ተሰብሰቦ ሰፈረባት፡፡ ጭንቅላቷ ላይ የሆነ ቋጥኝ የተጫነባት  ይመስል ውጥርጥር አድርጓታል፡፤ የጭንቅላቷ እብጠት ጥዝጣዜ ነርቯን ነካት
‹‹….እዛ ልጅ ጋር ይሄን ያህል ያለመመኝ እቤቴ ስገባ ለምን ተደበላለቀብኝ፡፡››እራሷን ጠየቀች፡፡
‹‹በሉ እዛ ደክተር ጋ ደውሉለት….በአስቸኮይ መጥቶ ይያተና ካልሆነ ሆስፒታል እንወስዳታለን.››እናቷ ናቸው በለቅሶ የታጀበ ትዕዛዝ የሚየዥጎደጉዱት፡፡
አንደኛ ፎቅ ላይ ወደሚገኘው የተንጣለለው መኝታ ቤቷ አስገቧት
….‹‹.ዞር በሉላት በቃ አታጨናንቋት….››ብለው አስተኞት፡፡
‹‹ለመሆኑ መንግስት ባለበት ሀገር ከማን ተጣልተሸ ነው..?››በቀጣይ የጠየቋት ጥያቄ ነው
‹ግን በአሁኑ ወቅት ኢትዬጵያ ውስጥ እንዲህ አይነት ጥያቄ ይጠየቃል..? መንግስት እያለ ምን የማይደረግ ነገር አለ..?ግድያ ፣አስገድዶ መድፈር፣ከገዛ መንደር መፈናቀል…ነገሩ እንዚህ ሁሉ ወንጀሎች መንግስት ባለባቸው በማንኘኛቸውም ሀገሮች ይፈፀማሉ… በአሜሪካም ጭመር….አንዳንዴ እንደውም መንግስት እራሱ በእጅ አዙር ያስፈፅማቸዋል  …አንተ እያለህልን እንዴት እንዲባል?እናቴ ግን ምን ታደርግ  ሳሪስ  ላይ ተቀምጣ ስለእነዚህ ነገሮች በወሬ እንኳን ብትሰማ ከምታየው የቱርክ ፊልም ጋር ስለሚምታታባት እውነት ይሁን ውሸት ትዝም አይሏት….ለነገሩ እኔም እንደእሷው ነኝ…አሁን እራሱ ስለእንደዚህ አይነት ጠንከር ያለ ነገር እንዴት ማሰብ እንደቻልኩ አላውቅም...ምን አልባት ጭንቅላቴን ሲነርቱት  የሆኑ አንቀላፍተው የነበሩ ነርቮችን አነቁብኝ ይሆን እንዴ…?ኸረ አያድርገው…ጌታ ሆይ ስለፖለቲካና ዲሞክራሲ ሚበሉ ህልሞች የሚያስብ የእምሮዬን ክፍሎችን መቼም ንቁ እንዳይሆኑ እማፀንሀለሁ›› ስትል ፀለየች..መቼስ ይሄንንንም እንደሌሎች ፀሎቶቿ ችላ እንደማይልባ አየተማመነች፡፡
እናቷ እሷን መጨቅጨቃቸውን ቀጥለዋል‹‹ዩኒቨርሲቲ አመፅ ተነስቶ ነው…? ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተሸ ነበር እንዴ?ምን  ተከስቷ ነው?›
እናቷ የማትመልሳቸውን አያሌ ጥያቄዎች ያዥጎደጉድባታል…. ዩኒቨርሲቲ ያሏት.. ጥዋት ከቤት ቁርስ በልታ ዩኒቨርሲቲ ክላስ አለኝ ብላ በመውጣቷ ነው ፡፡ደግሞም ሄዳ ነበር….ልዩ የምትማረው ዪኒቲ ዪኒቨርሲቲ ነው..መኪናዋን ይዛ ወደእዛ ነበር የተጎዘችው..አንድ ክላስ እንደተማረች ግን የተለመደ ድብርቷ ተቀሰቀሰባትና መኪናዋን እዛው ግቢ ውስጥ እንዳቆመች፤ስልኳን እንኳን እዛው መኪናዋ ውስጥ ቻርጅ እንደሰካች  በእግሯ ከግቢው ወጣች ፡፡
በተክሲ ስትዲዬም ድረስ ከስቴዲዬም ደግሞ መገናኛ ሄዳ ነው እንግዲህ ያ ታክሲ ላይ ያጋጠማት ታሪክ የተፈጠረው..እንደዛም ስለሆነ ከወትሮ በተለየ ፀፀትና  ንዴት አልተሰማትም ነበር፡፡በጣም ልዩ በሆነ አጋጣሚ ከተለየ እና ተአምራዊ ከሆነ ልጅ ጋር ነበር ያገናኛት.. ምን ያደርጋል? አፈፃፀሙን አበላሸችው… የማትፈልገውን ላፕቶፕ ሰርቃ ያንን የመሰለ አጋጣሚ በማጨመላለቋ እራሷን ተጠይፋለች፡፡አሁን በሰውነቷ ካለው ቁስል በላይ ክፉኛ እየጠዘጠዛት ያለው ይሄ ነው፡፡
..‹‹ግን ወድጄ ነው እንዴ  እንደዛ ያደረኩት?››ስትል እራሷን ለማፅናናት ሞከረች፡፡
ሁሉም መኝታ ቤቷን ለቀው እንዲወጡ ተደረገና በክፍሉ እናቷና እሷ ብቻ ቀሩ፡፡
👍80🥰43🔥1
‹‹እንደው ልጄ እስኪ ማን ነው እዲህ ያደረገሽ..?ንገሪኝና  ለኩማንደር ልደውልለት….››
ኩማንደር ማለት ፌዴራል ፖሊስ ውስጥ ትልቅ ስልጣን ያለው ዘመዳቸው ነው…ልዩ ሁሌ እናቷ ስላላቸው የዘመድ ብዛት ስታስብ ትገረማለች....በእያንዳንዱ ዘርፍ ትልልቅ ቦታ ሚሰሩ ሁለት ሶስት ዘመዶች አሏቸው..እና ምክንያት በተገኘ ቁጥር ይደወልላቸዋል..የሆነ ነገር ያረጉና ከእሳቸውም በምላሹ የሆነ ነገር ይደረግላቸዋል፡፡
‹‹ደውይለት››አለቻቸው፡፡
‹‹እኮ መጀመሪያ የሆነውን  ንገሪኛ?››
‹‹ታክሲ ውስጥ ገብቼ ሞባይል ከሰው ስሰርቅ እጅ ክፍንጅ ያዙኝና ቀጠቀጡኝ..አይገርም? በይ ደውይለትና ለቃቅሞ ይሰራቸው፡፡››
‹‹ልጄ እንደው ምን አይነት ልክፍት ነው…?ህክምናው ካላደነሽ… ፀበሉ ካልፈወሰሽ  ምንድነው የሚሻለው?›› የተለመደ ምሬታቸውን በለቅሶ አጅበው  ቀጠሉ፡፡
‹‹ምን አልባት እስር ያስተካክለኝ ይሆናል…አንድ ሁለት አመት እየገረፍ ወህኒ ቢያቆዩኝ በደንብ ታርሜና ሌብነትን እርም ብዬ ልወጣ እችላለሁ…እማ ግድ የለሽም እንሞክረው.››
ያው እንደዛ የምትላቸው ከአንጀቷ መታሰር ፈልጋ አይደለም..የሚሉትን ለመስማት እንጂ…፡፡እንደውም እንደእስር የምትፈራው ነገር የለም…ይሄ ባህሪዋ ሁሌ ይስገርማታል?‹‹.ሌባ ሆኖ እስር ፈርቶ እንዴት ይዘለቃል?›ስትል በራሷ ታሾፋለች፡፡
እናቷ ሌላ ነገር ለመናገር ከንፈራቸውን ለማነቃነቅ ሲሞክሩ  በራፉ  ተቆረቆረ …እጃቸው ላይ ባለው ናፕኪን  እንባቸውን እያበሱ ሄዳው ሲከፍቱ ዶክተሩና መድህኔ ተከታትለው ወደውስጥ ገቡ…፡፡

ይቀጥላል
🥰56👍4412😁2
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_አራት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ስንት ሰዓት   እንደተኛች አታውቅም፡፡ ፍፁም ሰላማዊና ህልም አልባ እንቅልፍ ነበር። ነቃች።ከአልጋ ወረደች።ቀለል ብሏታል። ወደፊት ለፊተኛው ክፍል ስትገባ ባዶ ነው፡፡ እንደውም ተዘግቷል። ‹‹ባዶ ቤት ጥሎኝ የት ሄደ...?፡፡››ቅር አለት፡፡የቤቱን ዙሪያ ገባ ስትቃኝ መሀል ጠረጴዛ ላይ ወረቀት አየች፡፡ ወደእዛ ሄደችና አነሳችው… አነበበችው"…»
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


እናቷ ሌላ ነገር ለመናገር ከንፈራቸውን ለማነቃነቅ ሲሞክሩ  በራፉ  ተቆረቆረ …እጃቸው ላይ ባለው ናፕኪን  እንባቸውን እያበሱ ሄደው ሲከፍቱ ዶክተሩና መድህኔ ተከታትለው ወደውስጥ ገቡ…፡፡

‹‹ደግሞ ለእሱ ማን ደወለ…?››ልዩ ነች በውስጧ ያልጎመጎመችው፡፡  ወዲያው መልሱን አገኘችው..መድህኔ  እነሱ ቤት ውስጥ  ከዘበኛ አንድ ከቤት ሰራተኛ አንድ  የእሷን የቤት ውስጥ እቅስቃሴ የሚሰልሉ ጆሮ ጠቢዎች እንዳሉት በእርግጠኝነት ታውቃለች…..በዚህም አልተሳሳተችም አሁን ደውለው የነገሩት እነሱ ናቸው..መድህኔ የልጅነት ጓደኛዋ ብቻ ሳይሆን እጮኛዋ ነው…፡፡

‹‹ልዩ..ምን ተፈጥሮ ነው..?እንዴት ሳትደውይልኝ….?ማሚስ ብትደውይልኝ..ምን አለበት…?››
‹‹ያው ተደውሎልህ መጣህ አይደል?›› መሽቆጥቆጡ አበሳጭቷት የመለሰችለት ልዩ ነች፡፡
‹‹አረ እኔ ስልክሽ  ከጥዋት ጀምሮ አልሰራ ስላለኝ ግራ ገብቶኝ ለማጣራት ስመጣ ነው በራፍ ላይ ያለው ዘበኛ የነገረኝ››አላት….
ቀኑን ሙሉ ስለእሷ ሲያስብና ሲጨነቅ መዋሉን አልዋሻትም…ግን አሁን እዚህ ሊገኝ የቻለበት ምክንያት እሱ እንዳለው ሳይሆን ልዩ እንደገመተችው ዘበኛው ደውሎ የልዩን መጎዳት ነግሮት ነው በድንጋጤ እያለከለከ ካለበት በሮ የመጣው፡፡

ዶክተሩ ይዟቸው በመጣቸው ዕቃዎች አገላብጦ መረመራትና ቀድሞ የተደረገላት ህክምና እና የተሰጣትን ኪኒን ካየ በኃላ‹‹ወ/ሮ ጥሩነሽ  ተገቢው ህክምና ስለተሠጣት ለጊዜው ሌላ ተጨማሪ ነገር አያስፈልግም… ምግብ ትውሰድ ፤እረፍት ታግኝ….ነገ ተመልሼ መጥቼ አያታለሁ››ብሎ እቃውን ሰብስቦ ወጥቶ ሄደ፡፡  ሶስቱ ብቻ ቀሩ፡፡

‹‹ምን ሆነሽ ነው ፍቅር ?››ቅልስልስ ባለ ንግግር ጠየቃት፡
እሷ ልትመልስለት አፏን ከመክፈቷ በፊት እናቷ  ጣልቃ ገብተው ይመልሱላት  ጀመር…‹‹ጓደኞቾ ሲጣሉ ለማገላገል መሀከል ገብታ እንደዚህ ሆነች..እስኪ ቢጫረሱ ምን አገባሽ…?››
እናቷ ገመና ከታች መሆቸው ነው….እጮኛዋ በድርጊቷ እንዳይከፋው ለመከለላከል ነው እንደዛ ያደረጉት…ልጃቸው ስለተፀናወታት መጥፎ ልክፍት ከእሱ በላይ ደግሞ የእሱ ቤተሰቦች እንዳይሰሙ አብዝተው ይጨነቃሉም፤ ይሳቀቃሉም..
የመድሀኔ ቤተሰቦች ከእሳቸው በላይ ወግ አጥባቂና ለክብራቸው አብዝተው ሚጨነቁ ናቸው..አባትዬው እኔ የቀኝ አዝማች ገ/እግዚያብሄር ሀጎስ ልጅ…›› የዘወትር ፉከራቸው ነው…የልዩ እናት  አባታቸው ፊት አውራሪ ቢሆንም በግልፅ ሲፎክሩበት ሰምታ አታውቅም….ግን ነገረ ስራቸውና ተግባራቸው ያው በአጥንት ቆጠራ ታሪክ ውስጥ እናቷም እንዳሉበት ታውቃለች፡፡ …አንዳንዴ ሰዎች ሲያበሳጯቸው‹‹ እኔ ከማንም ወፍ ዘራሽ ጋር ዝቅ ብዬ አፍ አልካፈትም›ሲሉ ብዙ ጊዜ ሰምታለች…‹‹አረ ተው የአባቴ መንፈስ ይታዘበኛል›› የሚሉትም  ነገር አላቸው.. .እንግደህ ልዩና መድህኔ የሁለት ፊውዳል ቤተሰቦች ውጤት ናቸው…ጥምረታቸውም ፍቅርን ብቻ መሰረት ያደረገ  ሳይሆን የቤተሰብም የእጅ አዙር ፍላጎት ያለበት ነው….፡፡›
መድህኔ ወቀሳውን ቀጠለ‹‹ፍቅር እንዴት እንዲህ ታርጊያለሽ.. ? ቀጥታ አይንሽን አግኝተውት ቢሆንስ? ››
‹‹አሁን የእውነት የሆነ የማላውቀው ወንድ መኝታ ቤቱ ድረስ ሰተት ብዬ ገብቼ አልጋው ላይ ስተኛ ውዬ እንደመጣሁ ቢያውቅ እንዲህ በመንሰፍሰፉ ይቀጥልበት ይሆን…?››ስትል በውስጧ አብሰለሰለች…‹‹አሁን አውቆ ነው አይደል እንዲህ የሚሆነው? እኔን በፀፀት ለመለብለብ… በአንድ ቀን ውስጥ በልቤ ገብቶ እየተገለባበጠ ያለው ልጅ ላይ የሰራሁት ግፍ መች አነሰኝ…››በማለት በውስጧ አሰበችና ተበሳጨች፡፡
አናም በንዴት ውስጥ ሆና መልስ ትሰጠው ጀመረች‹‹ቢሆንም ይጠፋላ.. ሌላ ምን ይሆናል…?›› መለስችለት፡፡

‹‹የአይን መጥፋት ቀላል አደረግሽው?››

‹‹ምን ችግር አለው..አንተም እማዬም ብር አላችሁ… ይገዛል… ይቀየራል..አሁን ደክሞኛል ልተኛ ነው፡፡›› አለችውና ተሸፋፍነች፡፡

‹‹ና ልጄ ደሙ ጭንቅላቷ ላይ ወጥቷል መሰለኝ ብስጭትጭት ትላለች..አረፍ ብላ ስትረጋጋ እናነጋግራታለን፡፡››

‹‹አረ ካልሆነ  ዊክ ኢንድ ላይ ኢስትአንቡል ወይም ዱባይ ወስዳትና ትንሽ ሪላክስ አድርጋ ትመጣለች…እኔ በህይወት እያለሁም እሷ እንዲህ ድብርት ውስጥ አትገባም፡፡››

‹‹እስቲ ትረጋጋና …እንማከራለን›››ብለው ይዘውት ወጡ…እሷም ወደጥልቅ ሀሳብ ወስጥ ገባች፡፡
//
በማስመሠል ብቃቷ እልል የተባለለትን አርቲስት ታሰንቃለች።በጓደኞቾ መካከል ስትሆን ፈገግታዋ  ከጨረቃ የሚፈነጠቅ ብርሀን በሉት  ፤ቤተሠቦቼ ሲያገኙት ጥርሷ እንደጥርስ ኪኒሊክ አስተዎዎቂ ያለገደብ ይፈለቀቃል። አለባበሷ የታሰበበትና ሽክ ያለ ነው።ከእሷ ላይ አንድ እንከን ማውጣት  ፀጉር መሠንጠቅ  ነው ሚሆነው...ታዲያ የትኛው ስል እይታ ያለው ሰው ነው ወደ ውስጧ ዘልቆ የተሰባበረው እሷነቷን በመገንዘብ ሊያዝንላት የሚችለው...?የትኛውስ ጠንቋይ ነው የነፍሷን መሠንጠቅ በራዕይው አይቶ ፈውስ የሚሆን ቅድስ ዘይት የሚሰጣት?።የትኛውስ የልብ ጓደኛ ነው ውስጧ የተንጣለለውን የሀዘን ባህር አይቶ እንዴ ይህቺ ሴትና ደስታ አይተዋወቁም ብሎ በድፍረት መናገር የሚችለው?።ልቧ ላይ ያረፈውንስ አለምን የሚያህል ጥቁር ጠባሳ የትኛው ምጡቅ ሀኪም ነው  አክሞ ሊያድነው  የሚችለው?

  ከታክሲው ገጠመኝ በኃላ ይሄው ዛሬ ሶስተኛ ቀኗ ቢሆንም ደፍራ ከቤቷ  አልወጣችም...አይደለም ከቤቷ ከክፍሏም አልወጣችም…ዶክተሩ ዛሬ ጥዋት መጥቶ የተለባበዱት ፕላስተሮችን  አላቆላት ፤ባንዴጁን ከላዮ ላይ ጥሎ ንፁህ ሰው መሆኗን አረጋግጦል  ‹‹ለሚያቁነጠንጣሽ ደብርት የሚሆን መድሀኒት››ብሎ የሆኑ ኪኒኖች  ሰጥቷት ሄዷል፡፡
አዎ ዶክተሩ እንዳለው ፊቷ ላይ የነበረው እብጠትና ቁስለት ጠፍቷል.. ያንንን መታጠቢያ ክፍል  ባለ  ትልቅ መስታወት ፊት ለሳዕታት  ቆማ በመመልከት አረጋግጣለች..፡፡ነገር ግን  ልቧ ላይ ያለው ቋጥኝ የሚያህል እብጠት አሁንም ባለበት እንደተነረተ ነው….ልቧ ላይ የተሞነጫጨረው ቁስለትም እንዳለ ነው...እንደውም መግል ይዟል …፡፡ ሲያመረቅዝ የሚለቀው መጥፎ  ጠረን በአፍንጫ እየመጣ እየረበሻት  ነው…፡፡ክፋቱ ደግሞ እናቷን ጨምሮ ሁሉም ሰው ለሶስት ቀን ሙሉ ሲረባረብ የነበሩት ፊት ለፊቷ  ማንም የሚያየውን አካሏ ላይ የሚገኘውን ጭረት ለማዳን ነው…ስለውስጥ ድማቷ  ግን ማንም ቁብ የሰጠው የለም… ዶክተሯንም ጨመሮ…አረ ፍቅረኛዋም ጭምር፡፡
‹‹አሁን ምን ይሰማሻል..?እብጠቱ አካካቢ  ያምሻል…?ፊትሽ ላይስ? ›› እነዚህንና  መስል ጥያቄዎችን ነው  በመጠየቅ የሚያደነዝዟት፡፡
‹‹አሁን ስለ እዛ ልጅ ምን ላድርግ? ››ስትል አሰበች፡፡ከእቤቱ ይዛው የመጣችው  ላፐቶፕ ኮመዲኖዋ  ላይ ቁጭ ብሎ እያፈጠጠባት  ነው… .. እዛ ሀሳብ ውስጥ ከገባች እራስ ምታቷ  መቀስቀሱ የታወቀ ስለሆነ ችላ አለችውና የራሷን  ላፕቶፕ  ወደሚገኝበት አልጋዋ  ላይ ወጥታ  ከፈተችው..ዩቲዩብ ትንሽ አየችና ወደ ፌስ ቡክ  ቀየረችው….ቻት ውስጥ ገባችና ከክላስ ጎደኞቾ  ጋር እያወራች ሰላ ድንገት ትናንት ተልኮላት የነበረ የማታውቀን  ሚሴጅ አገኘች፡፡
👍8911🥰2👎1👏1
ላኪው  ቃል እንደሆነ ይገልፃል… ተስፈንጥራ ለፕቶፖን በእጇ እንደያዘች  ከአልጋው ወረደችና የሚለሰልሰው የቱርክ ሰራሽ ምንጣፍ  ለይ በእግሮቾ  አረፍች፡፡ በቆመችበት ሚሴጁን ማንበብ ጀመረች፡፡
ልዩ እንዴት ነሽ..?እንደተሻለሽ ተስፋ አደርጋለሁ…
ስሜን እንዴት አወቀ ብለሽ ተገርመሽ ይሆናል…
(የእውነትም እንዴት አወቀ…?በማለት እየተገረመች ስለነበር እዕምሮዋን ቀድሞ ስላነበበ አስገረማት)
ትናንትና ኪኒሊክ የሄድን ጊዜ ለካርድ ክፍሏ ስትነግሪያት
እንደድንገት በአዕምሮዬ መዝግቤው ነበር፡፡
እና እሱን ይዤ  ፌስ ቡክ ላይ ስፈልግሽ አገኘሁሽ…
ልዩ እባክሽ አንድ ነገር ላስቸግርሽ ነበር…
አንቺ ጋር ያለው ላፕቶፕ ላይ ዴሰክቶፕ ላይ የተቀመጠ
ቃል የሚል ፎልደር አለ..የስራ ፋይል ነበር…አሱን ካላገኘሁ
ትንሽ ሚበላሽብኝ ነገሮች ስላሉ በሲዲ ገልብጪልኝና  የሆነ የሚመችሽ ሱቅ ወይም ካፌ ብቻ አንድ ቦታ ብታስቀምጪልኝና በደስታና በምስጋና ሄጄ ወስዳለሁ…
ስለመልካም ትብብርሽ እግዜር ይስጥልኝ፡፡

አንብባ ስትጨርስ ንዴቷ ካለችበት ፎቅ ቤት ጣሪያ በላይ ሆኖባት ነበር…‹ላፕቶፖን አሽቀንጥራ ከግድግዳ ጋር አላተመችው
‹‹..ምንድነው እንዲህ ክንፍ የሌለኝ ፃድቅ ልሁን አለ…? እንደሌላው  ሰው ለምን አይሰድበኝም…?.ምን አይነት ውለታ ቢስ ሰው ነሽ ብሎ አይወቅሰኝም…? ቅሌታም መሆኔን እስከዶቃ ማሰሪያዬ ድረስ አይነግረኝም..››ተንጨረጨረች፡
ሞባይሏን አወጣችና ፌስብኳን ከፈተች ..ቻት ውስጥ ገበች፡፡አዎ ኦን ላይን ነው‹አንተ ምን ለማለት ፈልገህ ነው…?ላፕቶፔን ሰርቀሻል  እያልከኝ ነው?››..ብላ በመፃፍ ላከችለት፡፡
አይገርምም ‹የሌባ አይነደረቅ መልሶ ልብ ያድርቅ›በማለት የራሷን ድርጊት በትዝብት ተቸች፡፡
‹‹አረ ልዩ እንደዛ አላልኩም..ይቅርታ አንቺ ጋር ያለ መስሎኝ ነው…››
‹እሺ አለ ፡፡ታዲያ ምን ይጠበስ? ወስጄዋለሁ .ማለት ሰርቄ ወስጄዋለሁ…ግን የሰረቅኩት ከነፋይሉ ነው...ምንም ነገር አልሰጥህም፡፡››
ላፕቶፑን እሷ እንደወሰደች በትክክል ያውቃል…በጥርጣሬ አይደለም…እቤት ጥሏት በሄደ ቀን እቤቱን ቆልፋ ቁልፉን ለአከራዬ ልታስቀምጥለት ስትሄድ ላፕቶፑን በግልፅ ፊት ለፊት በእጇ ይዛው ነበር…ያንን ደግሞ አሮጊቷ በግልፅ አይታዋታል… ያንንም ሳይጠይቃቸው ነግረውታል፡፡
ቢሆንም ግን …ከዚህ በላይ ሊከራከራትና ወደብስጭት ውስጥ ሊከታት አልፈለገም፡፡‹‹በቃ እርሺው ጥያቄዬን ትቼዋለሁ…. ፋይሉን ከሌላ ቦታ በሌላ መንገድ ለማግኘት ሞክራለሁ..ባይገኝም ችግር የለውም..ሁሉን ነገር  እርሺው..አንቺ ብቻ ሰላም ሁኚ››ብሎ በመፃፍ መለሰላት፡
‹ምን  ያስቀባጥርሀል..?››እየጻፍች ያለችውን ሳትጨርስ ከኦላይን ሲወጣ ተመለከተችው፡፡
መፅፏን አቆመችና ስለእሱ ማጣራት ፈለገች..ወደእሱ ፕሮፋይል ለመግባት መከረች..‹‹ ከመቼው.. ዴአክቲቪት አድርጎታል…ወይኔ ልጅት..ምን እየሆንኩ ነው…..?እንዴት አንድ ሰው በእሱ ልክ ቁጥብ ፤በጣም  የተረጋጋ ሲሆን በተቃራኒው  ደግሞ በእኔ ልክ ቅብዝብዝ ተነታራኪ እና ደግሞ  ምግባረ ብልሹ ሊሆን ይችላል?››በማለት ለፈለፈች….በራፉን ከፈተችና ወጣች…በረንዳ ላይ ቆመችና ጩኸቷን ለቀችው፡፡
‹እማዬ…አንቺ እማዬ……››

ይቀጥላል
👍106🥰1610👎2
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_አምስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ እናቷ ሌላ ነገር ለመናገር ከንፈራቸውን ለማነቃነቅ ሲሞክሩ  በራፉ  ተቆረቆረ …እጃቸው ላይ ባለው ናፕኪን  እንባቸውን እያበሱ ሄደው ሲከፍቱ ዶክተሩና መድህኔ ተከታትለው ወደውስጥ ገቡ…፡፡ ‹‹ደግሞ ለእሱ ማን ደወለ…?››ልዩ ነች በውስጧ ያልጎመጎመችው፡፡  ወዲያው መልሱን አገኘችው..መድህኔ  እነሱ ቤት ውስጥ  ከዘበኛ አንድ ከቤት…»
ፍቅር❤️ ና ጦርነት

ክፍል 1

ጳጉሜ 3    2013ዓ.ም

ከቀን ወደቀን ቢሻለኝም የክረምቱ ብርድ ህመሜን ጨምሮታል ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያለሠው ድጋፍ መንቀሳቀስ ችያለሁ ሠፈር ውስጥ ዞር ዞር ማለት ጀምሬያለሁ ። እንዲያውም ከሞት ያተረፈኝን ለቤቴ ያበቃኝ አምላክን ለማመስገን ወደ ቤተ-ክርስቲያን እየሄድኩ ነው ። ለዚህ እበቃለሁ እግሮቼ እንዲህ መንቀሳቀስ ይችላሉ ብዬ አላሰብኩም ነበር ከ 2 ወር በላይ ከተቀመጥኩበት ዊልቸር እነሳለሁ እንዳሁኑ እንቀሳቀሳለሁ እንደ ሰው ቆሜ እሄዳለሁ ሚል ምንም ግምት አልነበረኝም ታዲያ እኔ አምላኬን ያላመሰገንኩ ማን ሊያመሰግን ከሞት መንጋጋ ያተረፈኝ ያላመሰገንኩ ማን ሊያመሰግን ማንም ለዛነው ወደ ቤተክርስቲያን በመሄድ ለማመስገን ማሰቤ።

ዝናቡ ሚያቆም ባይሆንም ለብርዱ ልብስ ደራርቤ ከቤት ወጣሁ ፧ ከቤታችን በቅርብ የሚገኘው መድሀኒአለም ቤተክርስቲያን ነው ። ከልጅነቴ ጀምሮ ያደኩት ቤተክርስቲያን ስለሆነ ስምልም ረሱ መድዬን ብዬ ነው ለቤታችን ቅርብ ነው 20ደቂቃ ቢፈጅ ነው አሁን ግን ለኔ ከ 45_60 ደቂቃ ሳይፈጅብኝ አይቀርም   እራሴን ጠንክር በል ብዬ ጉዞዬን ጀመርኩ ።

መንገድ ላይ ብዙ ሰው ጋር አልተገናኘሁም በዝናቡ ና ገና ጥዋት በመሆኑ ምክንያት ግን ያገኘሁት ሰው ሁሉ ከንፈራቸውን እየመጠጡ ነው ሚያልፉት ሀዘኔታ ይሁን መገረም ባይገባኝም ምንም ምቾት አልሰጠኝም ። ወደ ቤተክርስቲያን እየደረስኩ ስመጣ ሠውነቴ በጣም ዛለ ድካም ተሰማኝ እንደምንም ብዬ የ ቤተክርስቲያኑን መግቢያ ተሳልሜ ለምእመናን ወደ ተሰራው መጠለያ ገብቼ አረፍኩኝ ። የተጎዳችው እግሬ ህመም መቋቋም አቃተኝ ስልኬን አውጥቼ ስመለከት ከቤት ከተነሳው 50 ደቂቃ ሆኖኛል በጣም አዘንኩ 50 ኪ/ሜ በምጓዝበት እግሬ 50 ደቂቃ ተጓዝኩ ብሎ እንዲህ መሆኑ አናደደኝ አይሰው መሆን ከንቱ በተፈጥሮ ተገረምኩኝ ግን ምንም ቢሆን መጠንከር እንዳለብኝ ለራሴ ነገርኩት ። በመጠለያው ትንሽ እንደቆየው ያላስተዋልኩትን ነገር አስተዋልኩ ያለሁበት በሴቶች ቦታ ነበር ድካሜ ሲጠፋልኝ  ቦታ ለመቀየር ከተቀመጥኩበት ስነሳ እግሬ አቅም አቶ ወደድኩኝ ። ከየት መጣች ያልተባለች ልጅ "እኔን " ብላ እጇን ዘረጋችልኝ እኔ ማየው አፍዞኛል መላክ ያየው መሰለኝ ክንፉን የዘረጋ ግን ሴት መላክ ከየት መቶ  ፤ ደሞ ማነው መላክን ወንድ ያረገው ብቻ ግራ ገባኝ አምላክ ለኔ የላካት መሰለኝ ባይኔ አካሏን ስቃኘው እንደኔው ፍጡር ናት ፈራሽ ገላ ነው የያዘችው በዛችው ደቂቃ አዘንኩላት ከገነት ተባራ ምድር ላይ ምደክም እንጂ እንደ ሰው የሁለት ሠዎች ውጤት አትመስልም ግን ምን መድረግ ይቻላል እንደኔው ፍጡር ናት ........

ክፍል  2 ይቀጥላል

    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ                                     ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍104🥰41😁1
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

‹እማዬ…አንቺ እማዬ……››
እታች ምድር ቤት ሁሉም ከየክፍሉ እየወጣ እሷ ወደአለችበት የመጀመሪያ ፎቅ የሚያስወጣውን መወጣጫ  ግር ብለው በመምጣት መክበብ ጀመሩ…. እናቷ ከእሷ ፊት ለፊት ካለው መኝታ ቤቷ  ልብሳቸውን እንኳን በቅጡ ሳይለብስ በተለመደ ድንጋጤዋ እያለከለከች
‹‹ምን ተፈጠረ ልጄ.?ደግሞ ምን  ሆነሽ ነው?››
‹‹እንዴት አድርገሽ ነው ያሳደግሺኝ?››ጮህችባቸው፡፡
‹‹አረ ተረጋጊ ልጄ …እሱ ደግሞ ምን ማለት ነው.?››

‹‹እኔ ለምንድነው እንደሌላው ሰው ጥሩ መሆን የማልችለው…? እኔ ለምንድነው ስርዓት የሌለኝ? አለሌ የሆንኩበት ምክንያት ምንድነው›?

እናቷ የምትለፈልፈውን  ሌሎች ሰራተኞች እንዳይሰሙ በመጨናነቅ  ይመስላል እቅፍ አረጓትና የሚወራጩ  እጆቾን አንድ ላይ በዛ ግዙፍ ሰውነታቸው በመጭመቅ  አንጠልጥለው ወደመኝታ ቤታቸው አስገቧትና  አልጋዋ  ላይ በማሳረፍ በራፍን ሄደው ዘጉት…እሷም ከንዴቷ እንደመብረድ ብላ ሹክክ ብላ ተነሳችና ሙሉ በሙሉ ወደ አልጋዋ ላይ ወጣች..፡፡ከውስጥ ገባችና ተኛች…፡፡በቃ ደከማት..እናቷም እንደእሷው አደረጉ፡፡ ቀስብላው ወደአልጋው ላይ ወጡና ከጎኗ በመተኛት ክንዳቸውን አንተርሰው ከራሳቸውጋር ልጥፍ አደረጓት፡፡
ሰው ሲከፋው እንዲህ እንደእሷ ሮጦ የሚወሸቅበት ጉያ ወይም ተንተርሶ  የሚተኛበት ክንድ ወይም እቅፋ ውስጥ ገብቶ የውስጥ ቁጣውንና ለቅሷውን የሚያቀዘቅዘዝዝት ምሽግ ካላው እድለኛ ነው። ሲከፍ ወደ  መጠጥ ቤት ሮጦ አልኮል ከመጎንጨት የሚያፈቅሩት ሰው እቅፍ ውስጥ ኩርምትምት ብሎ በማልቀስ የመረጋጋት አማራጭን መጠቀም ውጤታማና ብልሀት የታከለበት ውሳኔ  ነው።በተለይ ያ ክንድ እንዲህ እንደልዩ የእናት ሲሆን የቀጥታም ሆነ የጎንዬሽ ጉዳቱ ለዜሮ የቀረበ ነው።

‹‹የእኔ እርግብ…. አንቺን የሚስተካከል ደግ የለም እኮ…ከአንቺም እኩል  ለሰው አዛኝ እና ሰናይ ምግባር ያለው ልጅ ማግኘት ከባድ ነው….ይሄን  እኔ ብቻ  አይደለሁም ሀገር ምድሩ ነው የሚያወራው…እዚህ ቤት የሚርመሰመሱ ሰራተኞች አንቺ ሲያምሽ አብረው ሚታመሙት፤ ፈገግ ስትይ ሲገለፍጡ የሚውሉ ናቸው እኮ...የሰፈሩ አሮጌት ምረቃትን  ካንቺ እኩል የተመረቀ ማን አለ..?ከአኔ ከእናትሽ ቦርሳ እየመዠረጥሽ ለሰፈር አሮጊትና ሽማጊሌ ብሬን ስታድይ፤ የተመመ ችግረኛ ስታሳክሚ ፤መማር ላቃተቻው ህፃናት ደብተርና ዩኒፎርም እየገዛሽ ስታድይ አይደል እንዴ የኖርሽው?
ልጄ እኔ እንደውም ይሄ ሁሉ ደግነትና ቸርነት ከየት አምጥታው ነው ?እያልኩ ዘወትር እንደተደምኩብሽና እንደኮራሁብሽ ነው..አንቺ ይሄ ክፍ አመል ባይጠናወትሽና ባይለክፍሽ እንከን አልባ መልአክ እኮ ነበርሽ..ልጄ ታዲያ ምን ላድርግሽ እንድትፈወሺልኝ ያልሞከርኩት ህክምና የላጠጣሁሽ ጠበል የለም..የእኔ ቆንጆ ሰው ሲቸገር ምንም ነገር ለመሞከር ይደፍራል፤አጣብቂኝ  የትኛውንም የተነገረውን ነገር ያምናል፤ የትኛውንም መጥፎ የተባለ ስምምነት ይፈርማል፤የትኛውንም የሚወደውን ነገር  አሳልፎ ይሰጣል።አዎ ችግር እንደዛ ያደርጋል።እኔም በዚሁ በአንቺ ችግር ምክንያት የሰራሁትን ዛሬ ልንገርሽ…ሚስጥር አድርጌ ይዤው ነበር.. እግዜር ይቅር ይበለኝና ይሄውልሽ ጠንቆይ ቤት ሁሉ እኮ መፍቴ ይሰጠኝ መስሎኝ ሄጄ ጠይቄያለሁ….ግን መፍትሄ አልተገኘም፡፡
‹‹እጄን አስቆርጪው…በእጄ አይደለ ምሰርቀው…በቃ አልፈልጋቸውም.. ሁለቱ እጆቼ ይቆረጡ፡፡››
‹‹በስመአብ በይ ልጄ ..በስመአብ…የሚነሳው በእጅ ቢሆንም ቀድሞ  የሚሰርቀው  እኮ እዕምሮ ነው..እምሮሽን አላስቆርጥ?››
›‹‹እማዬ  ብቻ እኔ አንዲህ እየተዋረዱ መኖር ሰልችቶኛል…ትንሽ ጊዜ ነው የምሰጥሽ ….ካለበለዚያ..››
‹‹ካበለዚያ ምን?››
‹‹እራሴን አጠፋልሻለሁ..ከዛ ግልግል ነው፡፡››
‹‹አረ ተይ ልጄ…. ተይ እኔ እናትሽ እንኳን አላሳዝንሽም..?ሌላ ትርፍ ልጅ እንዳለው ሰው እንዲህ ትያለሽ..? አንቺ እኮ ከታችም ከላይም የሌለሽ ብቸኛ ልጄ የአይኔ ማረፊያ ነሽ…እኔ ባለኝ ሀብት በአለም በየትኛውም ጥግ ለዚህ ፈውስ ቢኖር የምሰስት ይመስልሻል ?ለምን ብዬ…ከሰባራ ሳንቲም አንስቶ ሙሉ ካማፓኒው ያንቺው ነው..እኔ ከአሁን ወዲህ የምኖረው እራሴን ለማስደሰት ሳይሆን አንቺ በሁሉ ነገር የተሳካልሽ ሆነሽ ስትስቂ ለማየት ነው…፡፡››
‹‹እና ታዲያ ምን አድርጊ እያልሺኝ ነው?››
‹‹ካልሆነ ለሁለተኛ ጊዜ እዛው አሜሪካ ሂጂና ትሞክሪ ይሆን ?››
‹‹እማዬ እኔ የትም ሀገር መሄድ አልፈልግም..ደግሞ የፈረንጆች የቅዠት ሀሳበ መሞከሪያ መሆን ሰልችቶኛል፡፡››
‹‹እሺ.በቃ ከመድህኔ ጋር ተማከሬ የሆነ ነገር አደርጋለሁ፡፡›› 
‹‹ከእሱ ጋር አትማከሪ በራስሽ ከቻልሽ አድርጊ ካለበለዚያ…፡፡››
‹‹በቃ በቃ. እሱን ለእኔ ተይውና ተኚ.›
እጃቸውን ፀጉሯ ውስጥ ከተው ሲዳብሷት የሆነ ፀጥ ያለ ውቅያኖስ ውስጥ እየዋኘች ያለች መሰላት…ወዲያው እንቅልፍ ይዞት ጭልጥ አለ፡፡

  ይቀጥላል
👍10217👏3😁3
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_ስድስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// ‹እማዬ…አንቺ እማዬ……›› እታች ምድር ቤት ሁሉም ከየክፍሉ እየወጣ እሷ ወደአለችበት የመጀመሪያ ፎቅ የሚያስወጣውን መወጣጫ  ግር ብለው በመምጣት መክበብ ጀመሩ…. እናቷ ከእሷ ፊት ለፊት ካለው መኝታ ቤቷ  ልብሳቸውን እንኳን በቅጡ ሳይለብስ በተለመደ ድንጋጤዋ እያለከለከች ‹‹ምን ተፈጠረ ልጄ.?ደግሞ ምን  ሆነሽ ነው?››…»
ፍቅር ና ጦርነት
ክፍል 2
"ወንድም ተጎዳህ እንዴ.. ወንድም " ብላ እጄን ስትይዘው ከሀሳቤ ነቃው እንደምንም በሷ እገዛ አመቺ ቦታ ተቀመጥኩኝ እግሬን እንደ ፈለኩኝ ማንቀሳቀስ እንደማልችል ስትረዳ " እግርህን ሚያምህ ከሆነ ለምን  መደገፊያ ክራንች ወይም ሚደግፍህ ሰው ሳትይዝ መጣህ " እንዳ ቀረቀረች ጠየቀችኝ "አይ ተሽሎኝ ነበር እኮ ትንሽ ስንቀሳቀስ ነው ያመመኝ  " የእግሬ ህመሙ ሲብስብኝ በእጄ ጠበቅ አርጌ ያዝኩት "አይዞህ አምላክ ይርዳህ" ብላ ለመሄድ ስትዘጋጅ መንቀሳቀስ እንደማልችል ና ከሷውጭ ሊረዳኝ ሚችል ሰው እንደ ሌለ የቤተክርስቲያኑ መውጫ ደረጃውን ለመውጣት እንድትረዳኝ ስጠይቃት እሺታዋን ገልጻልኝ አስከምረጋጋ አብራኝ ቁጭ አለች ።

ለደቂቃዎች ሳናወራ ብንቆይም አለባበሷን አይቼ በዚህ በብርድ እንዲህ መልበሷን ና ቤተክርስቲያን ውስጥ መሆኑ ገርሞኝ "ይህ አለባበስ ለቤተክርስቲያን ይፈቀዳል" ብዬጠየኳት እንዳቀረቀረች ፀጉሯን እያስተካከለች "ሰው ነው እንጂ አምላክ ልብስን አያይም የልቤን ችግር ደሞ እሱ ያቃል " ብላ ለይስሙላ ፈገግ አለች ፈገግታዋ ውስጥ ሀዘን አለው ፈገግታዋ ውስጥ መጎዳት አለው ፈገግታዋ ውስጥ ብቸኝነት አለው ።

የለበሰችው ልብስ ስስ የሌሊት ልብስ ሲሆን ሰውነቷን በከፊል ያሳያል ፀጉሯ ፊቷን ካልሸፈንኩ ካልሸፈንኩ ሚል ይመስላል እርዝመቱ መጋረጃ እንጂ ፀጉር አይመስልም እግሮቿ በጭቃ ተበላሽተዋል ውበቷን ግን አልቀነሱትም ትኩር ብዬ ከተመለከትኳት በኋላ እንደበረዳት ገባኝና የለበስኩትን ሹራብ አውልቄ ሰጠኋት ፧ ትንሽ ብትግደረደርም ተቀብላኝ ለበሰችው ሰውነቷ ተፍታታ እንደንጋት ጮራ ፊቷ አበራ "ስምሽ ግን ማነው " ድንገት ጠየኳት ፈገግ ብላ " ፀጋማርያም እባላለሁ " አለችኝ እውነትም የማሪያም ፀጋ በግርምት ላይ ግርምት ጨመረችብኝ አድናቆቴን በሆዴ ደብቄ መሄድ እንደምንችል ነግሬያት ብድግ ስል እሷ ቀድማ ተነስታ ደግፋ አነሳችኝ እጄን ትከሻዋ ላይ አድርጌ መንገዳችን ጀመርን ።

የቤተክርስቲያኑን መውጫ አልፈን ዋና መንገዱ ላይ ስንደርስ ካልቸኳለች ቤቴ ቅርብ ስለሆነ እንድታደርሰኝ ጠየኳት ችግር እንደሌለው ነግራኝ መንገዳችንን ቀጠልን ፤ ቤት እስክንደርስ ስለብዙ ነገር አወራን ። በብዛት ስለራሷ ባትነግረኝም ችግር ውስጥ እንደሆነች ነገረችኝ እኔም ምን ሆኜ እንደተጎዳው ብጠይቀኝም በጦርነት ተጎድቼ እንደሆነ ብነግራት ትፈራለች ብዬ በቀልድ አድርጌ አለፍኩት የተለያዩ ነገሮችን እያነሳን እየተጨዋወትን ቤት ደረስን።

የጊቢውን በር ከፍቼ ወደውስጥ ገባን ቤቱን ከቤተሰብ የወረስኩት እንደሆነና ሁሉንም ክፍሎች ዋናውን ቤት ጨምሮ አከራይቼ እኔ ጥግ ላይ ያለችው ቤት ውስጥ እንደምኖጋ እያስረዳኋት እያለ ስልኬ ጠራ ቤቱ ክፍት እንደሆነና አውርቼ እስክጨርስ ገብታ እንድትጠብቀኝ ነግሬያት ስልክ ማውራት ጀመርኩኝ ። በጣም አስፈላጊ ስልክ ስለነበር ሳላስበው ብዙ ደቂቃ አወራው ስልኩን ጨርሼ ወደቤት ስገባ እንደ ህፃን ልጅ ጥቅልል ብላ ተኝታለች መላክ ይተኛል እንዴ ? ደሞ ማማሯ ውበት ማለት አንቺ ብሎ የተዘፈነው ለሷ ይሁን እንዴ ........

ክፍል 3 ይቀጥላል ......

Tsiyon Beyene:
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ                                     ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍725👏2
ፍቅር ❤️ና ጦርነት


ክፍል 3


እናት ልጇ ተኝቶ በስስት እንደምትመለከተው እኔም ፀጋን በስስት አይን አይኗን እያየኋት በአምላክ አፈጣጠር እየተገረምኩ ቀኑም ሳላስበው መሸ .... ደመናማ ቀን ስለነበር መምሸቱን ያወኩት ሁሌም እራት ምታመጣልኝ ለምለም ስትመጣ ነው ። ለምለም የእናቴ የቅርብ ጓደኛዎ ነበረች እናቴ ከሞተች ወዲህ እንደ እናትም እንደ ዘመድም እንደ ጓደኛዬ እየሆነተች ምታፅናናኝ ናት ።

እናቴ በእድሜ ብትበልጣትም ለምለም በሂወት ብዙ ያየች ሴት ናት  በኢትዮ_ኤርትራ ጦርነት ምክንያት ኤርትራውያን ወደሀገራቸው ሲባረሩ እናቴ ናት ጓደኛዬ የትም አትሄድም ብላ መታወቂያ አውጥታ ያስቀረቻት ፤ አንዳንዴ እናቴ ትዝ ስትላት ...."ጦርነት መጥፎ አባረረኝ ፍቅር ደጉ አስቀረኝ " ትላለች ከህክምና ከመጣሁ ጀምሮ ከለምለም ውጪ ሴት ቤቴ ገብቶ  ስለማያውቅ ለምለም ፀጋን ተኝታ ስታያት  እንደ ሌላ ቀን ሳትቀልድ ሳትጫወት

  "በል እኔ ልሂድ ስለዚህ ነገር ግን ነገ እናወራለን "  ብላ እየተገረመች ትታኝ ሄደች የለምለም ድርጊት አላስገረመኝም ምክንያቱም ቤቱ የሴት ጠረን ና ወዝ ከራቀው አመታት አልፈውታ እናቴ ካረፈች ወዲህ ከለምለም ውጪ ሴት አያቅም ግን ምን ቤቱ ብቻ እኔ እራሱ ከሄዋን ዘር ከራኩኝ ዘመናት ሆኖኛል ምናልባት ያ ነገር ቦታው ተቀይሯል ቢሉኝ ራሱ  ደረቴን ነፍቼ ለመከራከር አልደፍርም ለምለምም ይህን ስለምታቅ ነው እንዲህ የገረማት ።

አይኔን ከፀጋ ላይ መንቀል አልቻልኩም ሙሉ አካሏን ቃኘሁት ትንሽ ቆይቼ ደገምኩት ደጋገምኩት በፈጣሪ ስራ ተገረምኩኝ እንኳን ችግር ገጥሟት ይቅርና አተኩረው ቢመለከቷት ምትሰበር ነው ምትመስለው ። አይኔን ለሰከንድ ከሷ ነቅዬ የእናት ና አባቴ ፎቶ ላይ ጣል አደረኩ በሂወት ቢኖሩ ብዬ ተመኘው ብቸኝነቴ ተሰማኝ ከልብ የሳኩበት ቀን የተደሰትኩት ቀን ትዝ አልልህ አለኝ አይኔን ጨፍኜ ለማስታወስ ሞከርኩ የታየኝ ግን ሳቅ ሳይሆን ለቅሶ ደስታ ሳይሆን ሀዘን ጨዋታ ሳይሆን የድረስልኝ አትርፈኝ ዋይታ የተኩስ እሩምታ የደም ጭቃ..... ነበር

ፀጋ ከእንቅልፋ ስትነቃ እኔም ከሀሳቤ ተመለስኩ በአይኖቿ ቤቱን ቃኘች ግራ መጋባት ና ማፈር አንድ ላይ ባንድነት ከፊቷ ይታያል ፀጉሯን እያስተካከለች " በጣም ይቅርታ ሳላስበው እንቅልፍ ወስዷኝ ነው " ትህትናዋ ልብን ያቀልጣል ሞት ፍርድ ያስቀይራል

ችግር እንደሌለው ና ቤቷ ድረስ እደምሸኛት ስነግራት ተረጋጋች እኔም ተረጋጋው ለሰዓታት ይሁን ለደቂቃዎች ባላቅም ከሷ ጋር ያለኝን እድሜ በማስረዘሜ እፎይ አልኩኝ ምላሴን ግን ዋጥኩኝ ምናገረው ጠፋኝ ጭንቅላቴ ግን እረፍት አላገኘም ብሎ ብሎ ይሰድበኝ ጀመር " አንተ ደነዝ ፈሪ ቆይ በየትኛው ልብህ ነው ወታደር የሆንከው ቆይ አሁን ቻው ልሂድ በቃ ብትል ምን ሊውጥህ ነው አታፍርም እኮ እንደ ደካማ ሰው ልትቆጭ ነው እንዳትለቃት ዋ ዋ ዋ " ብሎ እረፍት ቢነሳኝም ድፍረት ከዳኝ ቀጥሎ ሚሆነው ግራ ቢገባኝም እጄን አጣምሬ መጠበቅ ጀመርኩ ።ዝምታ በቤቱ ሰፈነ ዝምታውን የሚያጠፋ አንዳች ነገር ስጠብቅ አንድ ድምፅ ሰማው የውሀ ጠብታ ድምፁ አዲስ ሆነብኝ ለመለየት ተቸገርኩ ስረዳ ግን ያምላክ ስጦታ ነው ። ዝናቡ ቀስ በቀስ መጠንከር ጀመረ በሂወቴ ለመጀመሪያ በዝናብ ተደሰትኩኝ በ ሁለት ምክንያቶች ዝናብ አልወድም  የመጀመሪያው ለጎዳና ተዳዳሪዋች በማሰብ ነው ሁለተኛው ግን ከስራዬ ጋር የተገናኘ ነው ወታደር ዝናብ አይወድ የኛን ከጎዳና ተዳዳሪ ሚለየን እና ዝናብ እንድንጠላ ያረገን ወዴትም አንሸሽም ስራ ላይ ሆነን ከዘነበ ወዴትም መንቀሳቀስ የለም ቤት አጠገባችን ቢሆንም እንኳን ሚደረብ ልብስ ቢኖረንም እንኳን ሲያምረን ይቀራል እንጂ ንክች አናደርግም ስለዚህ ወታደሮች ዠናብ አንወድም እንደውም አንድ የውጪ ዜጋ የኢትዮጵያን ወታደር ካየ በኋላ .."የኢትዮጵያ ወታደር ዝናብ ሲዘንብ ወደቤት ጥይት ሲዘንብ ወደ ሜዳ " ያለው እስካሁን አረሳውም ። አሁን ግን አስፈላጊ ሰዓት የሰማይ ቀዳዳዋች ተከፍተው ሀይለኛ ዝናብ ዘነበ በዚ ዝናብ እሄዳለሁ እንደማትል ገመትኩ ።ጉሮሮዬን እየጠረኩኝ " ፀጋ ለምን እዚህ አታድሪም " ልቤ እየመታ ጠየኳት ካቀረቀረችበት ቀስብላ ቀና ብላ " አይ ላስቸግርህ አልፈልግም ባይሆን ዣንጥላ አለህ " አለች በሚያምር ድምጿ እንኳን ሰውን እንስሳትን በሚያራራ ቃና እኔን ግን ልቤን አደነደነው ...." የለኝም ያለሽ አማራጭ እዚህ ማደር ነው ደሞዝናብ ነው በዛላይ መሽቷል አንቺ የዛን ያህል ረድተሽኝ አንቺን በዚህ ጨለማ ለጅብ አልሰጥሽም ባይሆን ነይ እራት እንብላ " ሳላስበው ስሜታዊ ሆንኩኝ የበፊቱ መቶ አለቃ አብርሃ ወኔ መጣብኝ
ሳላስበው የተቆጣኋት መሰለኝ ግን በዚህ ጊዜ ያለኝ አማራጭ እሷን እዚህ ማቆየት ብቻ ነው ፤ በማላቀው መንገድ ልቤ እንዳትለቃት እንዳትለቃት ይለኛል ልብን መስማት አደጋ ቢኖረውም ምንም አማራጭ የለኝም ፤ በረጅሙ ተንፍሳ ምንም አማራጭ እንደሌላት እና ባረኩላት ነገር አመስግና እራታችንን መብላት ጀመርን እርቧት እንደነበር ለመረዳት አልተቸገርኩም ከኔ ጋር እራሱ ከተገናኘን 11 ስዓታት ተቆጥረዋል ከዛ በፊት ምግብ ሳትበላ ምንያህል እንደቆየች አምላክ ብቻ ነው ሚያቀው ፍሪጅ ላይ ከነበረ ምግብ ጨምሬ ተመስገን እስክትል ተመገበች ። የበላንበትን አነሳስታ ስልክ እንዳስደውላት ጠየቀችኝ ስልኬን ሰጥቻት በረንዳ ላይ ሆና ማዋራት ጀመረች ባላሰብኩት መንገድ ንግግሯ ሳበኝ የደወለችው ለሴት ጓደኛዎ ነበር እንዳልሰማት በትግርኛ ነበር ያዋራቻት ። እድሜ ለእናቴ ጓደኛ ለምለም ና አብዛኛውን የውትድርና ጊዜዬን ያሳለፍኩት ትግራይ ስለነበር ትግርኛ እችላለሁ ። አውርታ ስትጨርስ መኝታዋን አዘጋጅታ ተኛች እኔ ግን እንቅልፍ እንቢ አለኝ እንዴት ይህን ነገር ሰምቼ እንቅልፌ ይምጣ የአንድ ሰው ሂወት እየተበላሸ እያየው እናት ና አባት ልጅ እየሸጡ ፣ በቤተሰብ ችግር ልጅ ሲበደል እያየው እንዴት ብዬ እቺን ነብስ እንዴት እንደማተርፍ እያሰብኩ እንቅለፍ ወሰደኝ ......

ክፍል 4 ይቀጥላል

    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ                                     ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍98🥰32
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሰባት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///
ብዙ ፍላጎቶች አሏት..ለዛውም ያልተገሩ ፍላጎቶች ።አንደኛውን ለማሟላት በቀኝ ትጓዛለች ..ሌላው ደግሞ ወደግራ ያስፈነጥራታል...እንዲሁ የፍላጎቶቾን ጭራ ተከትላ ከግራ ቀኝ ስትላጋ ትከርምና በስተመጨረሻ እራሷ ከራሷ ትጠፋለች‹‹...የት ነው ያለሁት?ምን እየሠራሁ ነው? ምንድነበር የምፈልገው?››የአንድንም መልስ መመለስ አትችልም.... ፍፅም ድንዛዜ ውስጥ ትገባለች።ነፍሷ በማጥ ተይዛ እዛው ጭቃ ውስጥ መውጣት አቅቷት የምትንቧጫረቅ  ይመስላታል..‹‹.ጭቃ ውስጥ ገብቼ እንደዚህ እየዳከርኩ ያለሁት እኔ ነኝ ሌላ ሰው?›› ግራ ይገባታል...እራሷው ከእራሷ ትጠፋለች።አንድ ሰው እራሱ  ጠፊ እራሱ ደግሞ ፈላጊ ሲሆን የሚፈጠረው ነገር?
ለሊቱ በመከራ ነው የነጋላት..ምን አልባትም በህይወቷ ካጋጠሟት እጅግ አታካችና ደባሪ ለሊቶች ውስጥ አንዱ ነው….አስራአንድ ሰዓት ከሆነ በኃላ ክፍሏ ውስጥ መቆየት አልቻለችም ፡፡ መኝታዋን ለቃ ወረደችና  ቁምሳጥኗን ከፋፍታ ፊት ለፊት ያገኘቻውን ልብስ ያለምንም ማሰብ ለባበሰችና ስልኳንና የቃልን ላፕቶፕ በቦርሳዋ ከተተች፡፡  ከክፍሏ ይዛ ወጣች…በሩን ስትዘጋና ስትከፍት እናቷን እንዳትቀሰቅስና እሄዳለሁ አትሂጂም የሚል አተካራ ውስጥ ላለመግባት ብላ በጥንቃቄና በፀጥታ  ወደታች ወረደች ፡፡ የሳሎኑን በራፍ ከፍታ ወጣች... ግቢው ውስጥ የለሊቱን መንጋት የሚያበስሩ ባለ ብዙ ቀለም ማራኪ  ወፎች ከአንዱ   ዛፍ ወደሌላው ዛፍ እየተሸጋገሩ ሲዘምሩ ከሚሰማው ተፈጥሮዊ  ዝማሬ በስተቀር ሙሉ አካባቢው ፀጥ ያለ ነው፡፡ወደ ዘበኛው ቤት ሄደችና በስሱ አንኳኳች‹‹…..ማነው….?››የሚል ሻካራ ድምጽ ከውስጥ ተሰማ፡፡
‹‹ድምፅህን ቀንስ እኔ ነኝ?››
‹‹እትዬ ልዩ ምነው?››የ50 አመቱ ጎልማሳ እሷን የ23 አመቷን ልጅ እትዬ እያለ ሲጠራት ሁሌ እንዳስፈገጋት ነው…ብዙ ጊዜ ልዩ ብቻ ብሎ እንዲጠራት ነግራውም አስፈራርታውም ነበር..እሺ ይላል እንጂ በተአምር ተሳስቶ ልዩን ከእትዬ ነጠሎ ጠርቷት አያውቅም.. አሁንማ እሷም ለመደችው …
‹‹ድምፅ ቀንስ እኮ አልኩህ…ፈልጌህ ነው?››
‹‹እሺ እሺ..›› እየተደናበረ ወጣ፡፡››
‹‹ምነው…? ፈለግሺኝ….?››
‹‹መኪና ይዤ ልወጣ ነው፡፡››
‹‹ከማ ጋር?››
‹‹ከአንተ ጋር ››
‹‹ምን አልሺኝ እትዬ?››
‹‹ብቻዬን ነዋ…እዚህ አካባቢ በዚህን ሰዓት አብሮኝ ሊሄድ የሚችል ሰው ይታይሀል?..አሁን ክፈትልኝ…እስከዛ ሞተር ላሙቅ ››እለችውና መኪኖች ወደሚቆሙበት ስፍራ ሄደች…
ሶስት ሚኪኖች በተርታ    ተጠጋግተው ቆመዋል፡፡ዝም ብላ የእናቷን ሰማያዊ ኮሮላ መኪና ውስጥ ገባች፡፡ያው በእነሱ ቤት ልምድ መኪኖች ግቢ ውስጥ ከገቡ በኃላ ቁልፋቸው አይነቀልም..ምን አልባት ኢመርጀንሲ ተፈጥሮ ቢፈለጉ ገና ቁልፉን ከቤት ወይም ከሹፌሮች ጋር ከመፈለግ መንዳት የሚችል ሰው ወዲያው ገባ ብሎ ይነዳቸዋል..ይህ ህግ የወጣው በእሷ ምክንያት ነው..፡፡ያው በተለያ ሰበብ ሁሌ አደጋ ስለማያጣት…ሹፌር ፍለጋና ቁልፍ ፍለጋ ህይወቷንም ጭምር ሊያሳጣት የደረሰ አጋጣሚ ተከስቶ ስለነበር ይሄ ውሳኔ ተወሰነ..እና ይሄው ዛሬ ለራሷ ረዳት…፡፡
ላፕቶፑን ያለበትን ቦርሳዋን ከጎኗ አስቀመጠችና ቁልፉን አሽከርክራ ሞተሩን አስነሳችው.‹‹.መቼስ እማዬ የመኪናውን የሞተር ድምፅ ሰምታ በመንቃት መጥታ እንደማትቀውጠው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡››አለች
ዘበኛው በራፉን በልቅጦ ከፈተና እየተጎተተ ወደእሷ መጣ….. በአሳዛኝ ሁኔታ እየተቅለሰለሰ‹‹እትዬ ልዩ ግን አትዬ እንዴት እንደሚቆጡኝ እየታየኝ ሆዴ ተሸብሮብኛል…. ሊያባርሩኝ ሁሉ ይችላሉ፡፡›› አላት፡፡
ኪሷ ገባችና ድፍን ሁለት መቶ ብር በማውጣት በእጁ አስጨበጠችው… ‹‹ከሰደበችህ በዚህ ቻለው…ከባረረችህ  ግን ደውልልኝ እኔ አስቆማታለሁ…›› አለችው፡፡
በደስታ ተፍለቅልቆ‹‹እሺ የእኔ ደግ..ይሁን እችለዋለሁ…በይ  ሂጂ›››አለታ
መኪናውን አስነሳችና ግቢውን ለቃ ወጣች….መንገዱ  ነፃና ምንም አደናቃፊ  ስለሌለበት 25 ደቂቃ ነው የፈጀባት፡፡በራፉ ላይ ደርሳ የመኪናዋን አፍንጫ የግቢ በራፋቸው ላይ አስደግፋ አቆመች ..ሰአቷን ስታይ ሰውነቷ ቀዘቀዘ.. ‹‹በዚህ ሰዓት ለምን መጣሁ? ምንድነው የማደርገው..?›› ግራ ገባት…፡፡
‹‹በዚህ ለሊት እንደመርዶ ነጋሪ የሰው በራፍ አላንኳኳም፡፡የራሱ ቤት እንኳን ቢሆን የራሱ ጉዳይ….የኪራይ ቤት ለዛውም አሮጊት…..ምን አለ የዛን ቀን ስልክ ቁጥሩን ተቀብዬው ቢሆን.. አሁን ደውልለትና ቀጥታ መጥቶ ይከፍትልኝ ነበር….ከዛ ይሄንን ላፕቶፕ አፍንጫው ላይ ወርውሬለት የመኪናዬን መሪ ወደኃላ አዙሬ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ይሄን ሰፈር እለቅ ነበር…ከህይወቴ እስከመጨረሻ አሽቀንጥሬ እወረውረውና ከእነመፈጠሩም እረሳው ነበር፡፡››ስትል አብሰለሰለች፡፡
የመኪናዋ መሪ ላይ ተደፍታ እነዚህንና መሰል ሀሳቦች እያሰበች ሳለ ባልገመተችው ሁኔታ የግቢው ትንሿ በራፍ ከውስጥ መንጓጓት ጀመረች…..ነቃ አለችና, ከተደፋችበት    ተነሳች፡፡ በራፉ ተከፍቶ ነጭ በነጭ የለበሰች አንድ ሰትዬ ወጡ …አሮጊቷ የቃል  አከራይ ናቸው፡፡አለባበሳቸውን ብቻ አይቶ ወደቤተክርስቲያን ሊሄዱ  እንደሆነ መናገር ይቻላል…ከወጡ በኃላ ባልተለመደ ሁኔታ መኪና በራፋቸውን ታኮ መቆም እንዳስገረማቸውም እንዳስደነገጣቸውም ከሁኔታቸው መገመት ይቻላል፡፡…ልዩ ያንን ስለተረዳች ፈጠን ብላ ገቢናውን ከፈተችና በመውረድ ወደ እሳቸው ተጠጋች፡፡
‹‹ደህና አደሩ ማዘር …የቃል ጓደኛ ነኝ፡፡››
‹‹እ…የበቀደሞ ልጅ  ነሽ;››
‹‹ቆቅ አሮጊት ናቸው››ስትል አሰበች… እንዲህ በፍጥነት ያውቁኛል ብላ አልገመተችም ነበር፡፡
‹‹አዎ..አውቀውኛል››
‹‹ታዲያ ሰላምም አይደለሽ…?ገና ለሊት ነው እኮ፡፡››
‹‹‹አዎ ከቃል ጋር 12.30 የሆነ ቦታ ለመሄድ ተቀጣጥረን ነበር …ሳላስበው ትንሽ ቀደም ብዬ መጣሁና ማንኳኳት ደበረኝ፡፡››
‹‹እና አትደውይለትም ነበር?››
‹‹ሞክሬ ነበር..ዘግቶታል መስለኝ አይሰራም››ውሸት መቼስ የተካነችበት ነው..ከልጅነቷ ጀምሮ በብቃት የምትሰራቸው ሶስት ነገሮች ሌብነትና ቅጥፈት እና ወሬ(የሰው ሚስጥር)ማነፍነፍ ናቸው…፡፡
‹‹ግቢያ ….በራፍን ልክፈትልሽና ሚኪናዋን ታስገቢያት?››
የበቀደምለታው ግልምጫ ከዛሬው መሽቆጥቀጥ ጋር አመዛዝና ፈገግ አለች፡፡በቀደም የዱርዬ ገፀ ባህሪ ተላብሳ ነው ፊታቸው የተጋረጠችው ዛሬ ደግሞ የሞጃ ልጅ .ስለዚህ አይፈረድባቸውም፡፡
‹‹…ግዴለም ማዘር እርሶ ይሂዱ እኔ ከፍቼ አስገባዋለሁ››አለቻቸው፡፡
‹‹እሺ ልጄ.ደህና ዋይ ..››.ብለው በራፍን ለቀውላት ወደፊት መራመድ ሲጀምሩ የእሳቸውን ቀልብ ምትማርክበት የሆነች ሸር ነገር ብልጭ አለችላት…ኪሷ ገባችና ድፍን ሁለት መቶ ብር አወጣች፡፡
‹‹ማዘር.. ››
‹‹አቤት ልጄ›› ባሉበት ቆሙና ፊታቸው ወደ እሷ አዞሩ..ሮጣ ሄደችና ተጠጋቻቸው.
.‹‹‹ይቅርታ ይቺን ሙዳይ ምፅዋት ውስጥ ያስገቡልኝና..ያሰበችው ይሳካላት ብለው ይፀሉልኝ፡፡››
ፊታቸው ሲፈካ በግልፅ ይታያታል…‹‹ልጄ ይሳካልሽ…. ተባረኪ… ወይ አንቺም እንደቃልዬ  ነሽ መሰለኝ..ለመሆኑ ስምሽ ማነው?››ሲሉ ጠየቋት፡፡
👍91😁85👎2🔥1👏1🤔1
‹‹ልዩ ይባላል ..ልዩ››
‹‹ልዩ ሸጋ ስም ነው….በይ አትጥፊ ….እኔ እናትሽንም እየመጣሽ ጠይቂኝ …ቃልዬ ማለት ልጄ ነው››አሏት
‹‹እሺ ማዘር አልጠፋም....በሉ አይቁሙ፡፡ ››
‹‹ተባረኪ…››ፊታቸውን አዙረው መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡
እሷም ወደውስጥ ገባችና የትልቁን በር በራፍ ከፈተች ..መኪናዋን አስነሳችና ወደውስጥ አስገባች…. አመቻችታ ካቆመች በኃላ ሞተሩን አጠፋች…ቦርሳዋን በትከሻዋ አንጠልጥላ ከመኪናዋ ወረደች፡፡የከፈተችውን በራፎች ዘጋችና የፊት ለፊቱን ቤት አልፋ ወደጓሮ    ዞረች…‹‹አሁን ያቺ ጊፍቲ የተባለችው ሴት አብራው ብትሆንስ?›› የሚል ድነገተኛ ስጋት እረፍት እልባ በሆነው አእምሮዋ ስንቅር አለባት..ደንግጣ አማተበች…እርምጃዋን ግን አልገታችም… ደረሰች.. ማንኳኳት ጀመረች..
   ‹‹መጣሁ..መጣሁ….››የሚል ጎርነን ያለ ድምፅ ከውስጥ ሰማች..የልቧ ድውድውታ ድምፅ ለእሷም እየተሰማት ነው…..ላፕቶፑን የያዘው ቦርሳዋን ከትከሻዋ አውርዳ በእጇ አንጠልጥላለች… እጇ ደግሞ እየተንቀጠቀጠ ነው… ከእጇ  ተንሸራቶ እንዳያመልጣትና እንዳይከሰከስ በእያለች ስትብሰለሰል በራፉ ተከፈተ..ሙሉ ሰማያዊ ቢጃማ የለበሰ ጠንበለል ጠይም ወጣት ፊቷ ተጋረጠ፡፡ “

ይቀጥላል
👍6911👏11
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_ሰባት ፡ ፡ #ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// ብዙ ፍላጎቶች አሏት..ለዛውም ያልተገሩ ፍላጎቶች ።አንደኛውን ለማሟላት በቀኝ ትጓዛለች ..ሌላው ደግሞ ወደግራ ያስፈነጥራታል...እንዲሁ የፍላጎቶቾን ጭራ ተከትላ ከግራ ቀኝ ስትላጋ ትከርምና በስተመጨረሻ እራሷ ከራሷ ትጠፋለች‹‹...የት ነው ያለሁት?ምን እየሠራሁ ነው? ምንድነበር የምፈልገው?››የአንድንም መልስ መመለስ አትችልም....…»
:
ፍቅርና ጦርነት

ክፍል 4

የማይነጋ ቀን የማያልፍ መከራየለም እንደሚሉት አበው ጨለማ ጊዜውን ለብርሃን ለቀቀ ፀሀይ የክረምቱን ደመና ሰነጣጥቃ ጨረሯን ወደምድር በትናለች ተስፋ ያለው ቀን ይመስላል ፤ ንጋት ላይ የመተኛት ልምድ የለኝም ዛሬም እንደልማዴ በጥዋት ተነስቻለሁ ።

ህመሙ እንዳገረሸበት ሰው ኩርምት ብዬ ቁጭ አልኩኝ ፀጋ ከእንቅልፏ ስትነሳ ያመመኝ እንዲመስላት ገና ካሁኑ እየተዘጋጀው ነው የዛሬውን ቀን አብራኝ እንድታሳልፍ ፈልጊለው ። ስዓት ስመለከት ገና 12:30 ነው ጊዜው አልሄድ አለኝ እንዴት ቀናችንን እንደምናሳልፍ ሳስብ ፀጋም ከእንቅልፏ ነቃች የእግዜር ሰላምታ ሰታኝ ሰውነቷን እያፍታታች መፀዳጃ የት እንደሆነ ጠይቃኝ ሄደች ።

ብዙም አልቆየችም ተመለሳ መታ የተኛችበትን እያነሳሳች እኔ በስስት እያየኋት ውስጤ ማዘን ጀመረ ማጣት ማጣት መሰለኝ ጭራሽ ማንተያይ ቻው ብላ ተለይታኝ በዛው ቀልጣ ምትቀር መሰለኝ ቢቸግረኝ ምነው አምላክ እህቴ ባደረጋት ብዬ ተመኘው አይ የጨነቀው ግራገባኝ እንዲህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ገብቼ አላቅም እንደዚህም ተሰምቶኝ አያውቅም ቤቴን ወደድኩት ፀሀይ እኔ ቤት ብቻ ያለች መሰለኝ አለም ሁሉ ጨለማ የኔ ቤት ብቻ ብርሀን ያለ መሰለኝ እድሜ ለፀጋማርያም የሷ ህይወት ጨልሞ የኔን አበራችው ፤

ድንገት ስራዋን ጨርሳ ወደኔ ስትዞር ግራገባኝ ተደናበርኩኝ ሳስበው የነበረው ያወቀችብኝ መሰለኝ ታማሚዋን እግሬን በእጄ ይዤው ማቃሰት ጀመርኩኝ ያካበድኩት መሰለኝ የዛኔ ስመታ ራሱ እንዲህ ያቃሰትኩ አይመስለኝም ። ፀጋ በፍጥነት መታ " ምነው አመመህ" ብላ ጠየቀችኝ ማቃሰቴን ሳላቆም ምወጋው መርፌ እንዳለኝና ሚወስደኝ ሰው እንደ ሌለ ነገርኳት ፤ አብረን መሄድ እንደምንችል ነግራኝ እሺ ተባብለን መኪና ያለውን አብሮ አደጌን ያሬድን ጠርቼው በሱ መኪና ሄድን ከቤት ጀምሮ ያሬድን እያየሁት ነበር በጣም ተገርሞል ሰረቅ ሰረቅ አርጎ ፀጋን ይመለከታታል እየተገረምኩኝ መኪናውን እንዲያቆም ነግሬው ፀጋን ተከተይኝ ብዬ ወረድኩኝ ፀጋ ምታየው ነገር ግራ አጋብቷታል ከሴቶች ልብስ ቤት ውጪ ህክምና አይታይም እጇን ይዤው ወደአንዱ ሱቅ ገባን ለሻጯ እንድታስወርጣት ነግሪያት እኔ ቁጭ አልኩኝ ። ልብሶች እየለካች ስታሳየኝ ለብቻዬ የውበት ውድድር ( ሞዴሊንግ ) ማይ መሰለኝ የለካችውን የተወሰኑትን ገዝተን ወደመኪናው ተመለስን ።ያሬድ ፀጋን ሲያያት አፉን ከፍቶ ቀረ ፤ መኪና መንዳት እስኪያቅተው ፈዞ ቀረ ፤

አሪፍ ቁርስ ወዳለበት ቤት ወስዶን እሱን ሸኘሁት ፤ ፀጋ ያሬድ ከሄደ በኋላ " ህክምናውስ መርፌ ምትወጋውስ " ብላ ጠየቀችኝ  " ታከምኩ እኮ " ብያት ቦታ ይዘን ቁጭ አለን ።

የሰዓታት ፍጥነት ገረሙኝ ምግቡ ከመቼው ማለቁ እጇን ለመታጠብ ስትነሳ ማትመለስ መስሎኝ ፈራሁኝ ልቤ መታ ሰውነቴ ብርድ ብረድ አለው ግራ ገባኝ አንገቴን ጠረቤዛው ላይ ደፍቼ ሚሆነው መጠባበቅ ጀመርኩ ....

"ምነው በሀሳብ ሄድክ " ከጎኔ መታ ተቀመጠች በጣም ቀረበችኝ እጄን ሰድጄ እጇን ያዝኩት በስሱ ዳበስኩት
" ምነው " አለችኝ አይኔ ላይ አይኗን ተክላ " አይ የበረደሽ ትመስያለሽ " ሞኝ የሆንኩ መሰለኝ መጃጃሌ ገባኝ ምናለ ግልፁን ብነግራት እንደኔው ፍጡር መሆኗን መጠራጠሬን እንደው ሁሉም ነገር ህልም ህልም እየመሰለኝ መሆን ግን እንዴት ምላሴን ማዘዝ አቃተኝ .....

ዝምታዬ ሲበዛባ " አብርሽ "
"አቤት "
" እንዴት እንደማመሰግንህ እንጃ ቃላት ያንሰኛል ምናልባት ውለታህን እመልስ ይሆናል አምላክ ካለ አሁን ግን መሄድ አለብኝ ቤተሰቦቼ ይጨነቃሉ  " ብላ ለመሄድ ተነሳች " እሺ" ከማለት ውጪ ምንም አልተናገርኩም ጨክናብኝ  ጉዞዋን ጀመረች የተሸናፊነት ስሜት ተሰማኝ አግኝቶ የማጣት ይዞ የመልቀቅ እያንዳንዱ የፀጋ እርምጃ ጆሮዬ ላይ አስተጋባ እራሴን አንድ ጥያቄ ጠየኩት " አግኝቶ ማጣት ያለ ቢሆንም ያጡትን ማግኘት አይቻልም ?" እራሴው ጠያቂ እራሴው መላሽ ሆኜ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ " ፀጋማርያም አስመሳይ ነሽ " አልኳት ድምፄን ከፍ አድርጌ ድምፄን ስትሰማ መንገዷን አቁማ ወደኔ ዞራ አይን አይኔን እያየች  "እንዴት " አለች ሲቃ ባለው ድምጽ ዞር ዞር ብዬ ያለንበትን ስመለከት ጥዋት ስለሆነ ከኛ ውጪ ማንም አልነበረም ጉሮሮዬን ጠራርጌ

     " ችግር ውስጥ እንደሆንሽ አቃለው ምትሄጅበት አንድም ቦታ የለም ጓደኛሽም ጋር እንዳትሄጂ ባለቤቷ ደስ እንደማይለው ነግራሻለች ቤተሰብ ጋር እንዳትሄጂ አደጋ ውስጥ መመለስ ነው ታዲያ ይህን እያወቅሽ ምንም ችግር እንደሌለብሽ ቻው ብሎ መሄድ ምን ይሉታል እውነት እውነት እልሻለሁ ስተት ነው የሰራሽው " ውፍፍፍፍፍፍ

በደንብ ተነፈስኩኝ ሆዴ ውስጥ የቀረ ምንም ነገር ያለ አይመስለኝም አሁን ምጠብቀው የሷን ምላሽ ነው አይኔን አይኗ ላይ ተክዬ እሺ የትም አልሄድም እንድትለኝ መጠበቅ ጀመርኩ እሷ ግን
"ይህን ሁሉ እንዴት አወክ " አለችኝ
አይኗ እንባን አዝለዋል ቀስ ብዬ አጠገቧ ሄጄ
" ውሸት ነው "  አልኳት ድምፄን ዝቅ አድርጌ ስሜቷን መቆጣጠር አቃታት እንኳን እናቴ ሞታብኝ እንዲያው አልቅስ አልቅስ ይለኛል አለ የመረረው እንባዋን እንዳላየው ፊቷን አዞረች፤

ማልቀሷን አላቆመችም እጇ ሳብ አድርጌ እቅፊ ውስጥ አስገባኋት እንድትፅናና መቀባጠር ጀመርኩ ግን ህመሟን ሚሽሩ አልነበሩም እንዳቀፍኳት ድምፄን ከፍ አድርጌ እግሬን ብዬ አቃሰትኩ ሀዘኗን ረስታ እንባዋን እየጠራረገች " ምነው አመመህ " አለች በእናትነት ርህራሄ ምንም ብትጎዳም የራሷን ረስታ ሰውን ምትረዳ ምናይነት ፍጡር ናት
" አውቀህ ነው " አለችኝ ዝምታዬን አይታ ፀጥ ስላት ገባትና ህይወት ያለው ፈገግታን ለግሳኝ ና እንቀመጥ አለችኝ ።

በድርጊቴ እየተገረመች

" ምን አይነት ሰውነህ " አለችኝ

"ጠቆር ያልኩ" አልኳት

ጥርሷቿን ለመጀመሪያ ጊዜ አየኋቸው ከምር ሳቀች

" አይ ለሰው ትጨነቃለህ "

ብላ ሁሉን እንድነግርህ ትፈልጋለህ አለች ልሰማት እንደምፈልግ ና ልረዳት እንደምፈልግ ነገርዃ
እሺ ብላ በረጅሙ ተንፍሳ

" እንደምታውቀው በጣም ትልቅ ችግር ውስጥ ነኝ ችግር ውስጥ የገባሁት ደሞ በኔ ስተት አይደለም በቤተሰቤ እንጂ ሙሉ ስሜ ፀጋማሪያም ኪዳኔ ነው አባቴ በቀድሞ መንግስት ብዙ መጥፎ ስራዎችን ሰርቷ ለመዘርዘር ሚያስጠላ ነው በዚህ ስራው ባገኘው ሀብት ቦሌ ላይ ህንፃዎች አሉት ይህ መጥፎ ስራው ጊዜ ሲያጋልጠው ሀብቱን ላለማጣት ከአሁን ካሉት ባለስልጣኖች ጋር የቻለው ቢሞክርብ አልሆነለትም ጦርነቱም እየጠነከረ መጣ በዚህ መሀል ሁለቴ ታስሮ ተፈታ የስኳር ታማሚ ስለ ነበር በጣም ተሰቃየ በዚህ መሀል ነው የሆነ ሀሳብ የመጣለት   እኔን ልጁን ለባለስልጣን ሊድረኝ አስማማኝ እኔም የአባቴን ስቃይ ከማይ ብዬ እያስጠላኝ ተስማማው ግን ከዚህ ሁሉ ሚያስጠላው ሚያገባኝ ሰውዬ virus በደሙ ያለበት መሆኑ ነው ይህን ሁሉ ቤተሰቦቼ እያወቁ ምንም አልመሰላቸውም ከቤት ከወጣሁ 4 ቀን ሆኖኛል ጓደኛዬ ጋር ለማረፍ ብሞክር ሊያገባኝ ያሰበው ሰውዬ  ባለቤቷን አስደበደቡት ጓደኛዬም እያዘነች ቢሆንም ቤቷ መቆየት እንደማልችል ነገረችኝ እኔም ምንም ሳልላት የለበስኩትን ሳልቀይር ወጣሁ ከዛ ካንተ ጋር ተገናኘን  ይሄ ነው ባጭሩ ብቻ በጣም ችግር ውስጥ ነው ያለሁት "

አለችኝ ከቅድሙ አሁን የቀለላት ትመስላለች

" ጥያቄ ልጠይቅ"አልኳት እሺታዋን ገልፃልኝ
👍585😁2
" መኖሪያ ቤት ካገኘሽ ስራ ካገኘሽ ሚጠብቅሺ ካገኘሽ ምን ታረጊያለሽ " አልኳት
እየሳቀች " ትቀልዳለህ በዚህ ሁኔታ ውስጥ አምላክ እራሱ እንዲህ አያደርግልኝም " አለች
"ቢገኝስ " አልኳት ቀጠል አድርጊ
" ደስ ይለኛል" አለች አቀርቅራ

"ተነሽ በቃ ካሁን በኋላ አንቺን ማንም ምንም አያደርግሽም እኔ እያለሁ ካሁን በኋላ ማዘን የለም እሺ ፀጋ" አልኳት እጇን ይዜ

"ተው ቃል አትግባ ሰዋቹን አታቃቸውም ምንም ከማረግ አይመለሱም እንድትጎዳ አልፈልግም ይቅርብህ "አለችኝ

ፈገግ ብዬ" እሱን ለኔተይው "ብዬ እጇን ይዤ ተነስተን ወደ ቤት መንገድ ጀመርን ለሀገሬ በውትድርና ጊዜ ቃል ከገባሁት በላይ ለፀጋ ቃል የገባሁት ከበደኝ ምክንያቱም ለሀገሬ የገባሁት ቃል ባፈርስ ወይ እኔ ብሰዋ  ከኔ ውጪ ሀገሬን ሚጠብቃት ጀግና ልጆች ሞልተዋል ለፀጋ ግን ከኔ ውጭ ማንም የላትም ማንም እኔ ብቻ .....

ክፍል 5..ይቀጥላል

    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ                                     ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍42🥰4
#ባል_አስይዞ_ቁማር

#ክፍል_ስምንት

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///

‹‹..ለምንድነው በርሬ የመጣሁት…?››እራሷን ጠየቀች… አዎ ላፓቶፑን አስታቅፋው ፊቷን አዙራ ለመሄድ ነበር…እንደዛ ለማድረግ ታዲያ መኪናዋን ለምን ወደጊቢው ውስጥ አስገብታ አቆመች..?‹‹አሮጊቷ ናቸው ሀሳቤን ያዛቡብኝ፡፡››ስትል ለራሷ ሰበብ ሰጠች፡፡

‹‹ልዩ ሰላም አደርሽ…?ግቢ ..አረ ብርድ ላይ …››ተንስፈሰፈ….፡፡

እርግጥ የሆነ ቀን መጥታ በራፉን እንደምታንኳኳ እርግጠኛ ነበር..ማታ ፌስቡኩን ዲአክቲቬት ሲያደርግም ለዛ አላማ እሷን ለማመቻቸት ነበር.. ግን ደግሞ ፈፅሞ በዚህ ፍጥነት በዚህ ለሊት እሷን በደጁ ቆማ አያታለሁ ብሎ አልጠበቀም…በዛም የተነሳ በጣም ነው የደነገጠው..
‹‹ብርዱ ›› ሲላት የእውነት በረዳት….ገባችና ቆመች፡፡ …በራፉን ዘጋና‹‹ ነይ ..››እጇን ይዞ ወደመኝታ ቤቱ ጎተታት…ዝም ብላ ተጎተተችለት…አልጋው ጠርዝ ላይ እንድትቀመጥ አመቻቸላት…፡፡
‹‹ስንት ሰዓት ነው…?እንዲህ ነግቷል እንዴ ?አለና ሞባይሉን ከጠረጴዛ ላይ አንስቶ ተመለከተ …የሰዓቱን ገና ለሊት መሆን ሲያይ ደነገጠ ፡፡
ከእግር እስከፀጉሯ እየመረመራት‹‹ደህና ነሽ ግን ?›› ባለማመን ጠየቃት.፡፡
‹‹ደህና አልመስልም?››
‹‹እሱማ በጣም ደህና ትመስያለሽ..እብጠትሽም ቁስልሽም ከቦታው የለም…..ግን በዚህ ሰዓት ስትመጪ ችግር ከተፈጠረ ብዬ ነው?››
‹‹ለምን ፌስቡክህን ዲአክትቤት አደረከው?››
‹‹ስላበሳጨሁሽ አዝኜ ነው››
‹‹ስለአበሳጨኸኝማ አይደለም..እኔ መርዝ ንግግሮቼን እንዳልክልህና ይበልጥ እንዳላፍር እራሴንም እንዳልጠየፍ ስለፈለክ ነው፡፡››አለችው…ከተናገረችው ውስጥ ምንም ስህተት ስላልነበረበት ዝም አለ፡፡
‹‹እንካ ይሄው ላፕቶፕህ..ከቦርሳዋ አወጣችና ሰጠችው…..ኪሷ ገባችና የተጠቀለለ ብር አውጥታ አንድ በአንድ እየቆጠረች. ይሄ ለህክምና ያዋጠኸው ነው፣ይሄ ደግሞ ለላዳ የከፈልክልኝ ነው፣ይሄ ደግሞ ወደቤት ስሄድ የላዳ ብለህ እዛ ኮመዲኖ ላይ ያስቀመጥክልኝ ነው፣ልክ በአራጣ ተበድሮ ብድሩን አንድ በአንድ እየቆጠረ እንደሚያስረክብ ሰው እጁ ላይ እያስቀመጠች ስትንጣጣበት እሱ ያለምንም ተቃውሞ ተቀበላትና እንደነገሩ ፊት ለፊቱ ጠረጴዛ ላይ ወርወር አደረገው..ላፕቶፕንም አስቀመጠው…
እና በሚያምሩ አይኖቹ ፊት ለፊት እያያት…ብዙ ብዙ ነገር እንዲል ፈልጋለች...እንዲሰድባት..እንዲረግማት ..እንዲያደንቃት.. እንዲያዝንላት… ብቻ አንድ መስመር ይዞ የሚናገራን ነገር ከአንደበቱ መስማት ፈልጋለች..እሱ ግን ንፉግ ነው የሆነባት.. የምትፈልገውን አልሰጣትም…፡፡
‹‹አሁን ለሊት ነው.. አንቺም በርዶሽ እየተንቀጠቀጥሽ ነው… ጫማሽን አውልቂና አልጋ ላይ ውጪ፡፡እኔም ገና እንቅልፌን አልጠገብኩም.. ትንሽ እንተኛና ሲነጋ ማድረግ ያለብንን እናደርጋለን፡፡››አላት፡፡
ለመጮህ ፈለገች…ገፍትራውና ሰድባው እቤቱን ለቃለት ልትወጣም ዳዳት...ግን እንደዛ እየተመኘች ባለችበት ሰዓት ትዕዛዟን አክብራ ጎንበስ ብላ ጫማዋን እያወለቀች ነው…ልብ እና አዕምሮ ሁለቱም የራሳችው የሆነው መደማመጥ አቁመው በየፊናቸው ያሰኛችውን ሲያደርጉ ማለት እንዲህ ነው፡፡ጫማዋን አወለቅችና ልክ እንደለመደች የፍሬንዷ አልጋ ሙሉ በሙሉ ወጣች…እሱ ለሊቱን ሙሉ ተኝቶበት ከወጣበት ቦታ አልጋ ልብሱንና ብርድ ልብሱን ገልጣ ገባች….፡፡
‹‹እሱስ ተከትሎኝ መጥቶ ከጎኔ ይተኛ ይሆን እንዴ.?››ይሄንን ያሰበችው ከተኛች በኃላ ነው….ግን እንዲተኛ ፈልጋለች ወይስ አልፈለገችም..?›ለዚህ ጥያቄ በውስጧ የተቀመጠ አውንታዊም ሆነ አሉታዊ መልስ የለም…፡፡
ቃል ከተቀመጠበት ወንበር ተነሳ.. በግርጌ በኩል ያለውን አልጋ ልብስ እና ብርድ ልብስ ገለጠና ከጎኗ ያለውን አንዱን ትራስ በማንሳት በተቃራኒው ቦታ በማስቀመጥ ከውስጥ ገብቶ ከሰውነቷ እንዳይነካካና እንዳያሳቅቃት ወይም እንዳይፈታተናት እስከቻለው ድረስ ርቀቱን በመጠበቅ ጠርዙን ይዞ ተኛ፡፡እንግዲህ የተመሰቃቀለ አስተኛኘት ተኙ ማለት ነው….
‹‹እንደ እኔ አይነት የተመሰቃቀለ አስተሳሰብ ያለው ሰው የተመሰቃቀለ አስተኛኘት ተኝቶ እንዴት ነው የሚሆነው…?፡፡››በውስጧ አብሰለሰለች፡፡
ሳታስበው ቃላለቶች ከአንደበቷ አመለጧት‹‹ምነው ፈራህኝ እንዴ..?››አለችው፡፡
‹‹..ይህ ማለት እንግዲህ ምን ማለት ነው ?››እራሷን ነው በትዝብት የጠየቀችው፡፡
እስቲ አስቡት…እንድትተኛ የምፈልገው በትክክሉ እንደእኔው ወደላይ ዞረህ ነው እያለችው አይደል…?ይህ ንግግር ደግሞ ጥሩ መንዛሪና ተርጓሚ ካገኘ ከዛም በላይ ስውር መልእክት ሊኖረው ይችላል ፡፡እንድታቅፈኝና ከመንቀጥቀጤ እንድትታደገኝ እፈልጋለሁ የሚል የተለጠጠ መልእክት ያስተላልፋል…አጋኖ ተርጎሚ ካገኘ ደግሞ ከዛም በላይ..፡፡
ጭራሽ ይባስ ብሎ ‹‹አረ በፍፅም….ይልቅስ የፈለኩት ሳሎን መተኛት ነበር…እንደዚህ ታስቢያለሽ ብዬ ነው እዚህ የተኛሁት፡፡››አላት፡፡ይሄ መልስ ደግሞ እሷ ከምታውቃቸው ወንዶች ሁሉ ልታገኘው የማትችል ግራ የሆነ ግን ደግሞ ትክክለኛ ሀሳብ ያዘለ መልስ ነው፡፡
‹‹መተኛትህ ካልቀረ ታዲያ በትክክል ተኛ..››አለችው፡፡
‹‹እሺ››ብሎ ትራሱን ይዞ ከጀርባዋ ዞሮ ተስተካክሎ ተኛ….አቅጣጫውን አስተካከለ እንጂ በመሀከላቸው ያለውን ክፍተት ለማጥበብ እልደፈረም… ፍላጎቱም አልነበረውም፡፡እሷም ከዛ በላይ አልፈለገችም ..አልጠየቀችም.
በመከፋትና በከፍተኛ ብስጭት የመጣችው ልጅ ከስንት ጊዜ በኃላ ደስ የሚል ስሜት ተሰማት..እንደው ደስ የሚል ስሜት ማለት ምን ማለት ነው ካላችሁ…?የሆነ ፍፅማዊ መረጋጋት፤መረበሽም መቆጨትም የሌለበት…በሸለቆ ውስጥ እንደሚንኳለል የምንጭ ውሀ ጥርትና ኩልል ብሎ የሚፈስ የአእምሮ ሞገድ..አዎ እንደዛ ነው እየተሰማት ያለው…እና እንቅልፏ መጣ፡፡

ይቀጥላል
👍116🥰1715🤔12😁2
አትሮኖስ pinned «#ባል_አስይዞ_ቁማር #ክፍል_ስምንት #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ /// ‹‹..ለምንድነው በርሬ የመጣሁት…?››እራሷን ጠየቀች… አዎ ላፓቶፑን አስታቅፋው ፊቷን አዙራ ለመሄድ ነበር…እንደዛ ለማድረግ ታዲያ መኪናዋን ለምን ወደጊቢው ውስጥ አስገብታ አቆመች..?‹‹አሮጊቷ ናቸው ሀሳቤን ያዛቡብኝ፡፡››ስትል ለራሷ ሰበብ ሰጠች፡፡ ‹‹ልዩ ሰላም አደርሽ…?ግቢ ..አረ ብርድ ላይ …››ተንስፈሰፈ….፡፡ …»