#የወድያነሽ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል
....የማለዳዋ የጥር ወር ፀሐይ በመሬት ወለል አካባቢ ከየሚዳው! ከየተራራው፣ ከየዛፉ፣ ከየቤቱ፣ ከየጉራንጉሩ ቀዝቃዛ አየር ጋር ትንቅንቅ ገጥማለች። ተፈጥሮ ራሷን በራሷ የምታስተካክልበትና የምትለዋውጥበት ተፈራራቂ ኃይል ስላላት ቀዝቃዛው አየሩ ቀስ በቀስ ተረታ። ለውጥ የተፃራሪ ኃይሎች የግብግብ ውጤት ነው::
በእኔ ሕይወት ውስጥ ግን ጎልቶ የሚጠቀስ ለውጥ ባለመገኘቱ ሕሊናዩ
እየቀዘቀዘ ከመሔድ በቀር የብርታት ለውጥ አልታየብኝም፡፡ ከመኝታዬ ተነሥቼ
ልብሴን ስለባብስ ሰውነቴ ቀነቀነኝ፡፡ እውነተኛዎቹ የሐሳቤ ቅንቅኖች ግን አንጎሌ ውስጥ ይርመሰመሳሉ። የሥራ ቀን ነበር፡፡
መንገዱ የሚያልቅልኝ ስላልመስለኝ ቀደም ብዬ ተነሣሁ፡፡ ወደ ሕጋዊ ፍርድ ቤት ሳይሆን ወደ ግፈኞች የመከራ ሽንጎ የምገሠግሥ መሰለኝ፡፡ ከአራት ኪሎ እስከ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያለውን ርቀት በሁለት ታክሲ አጠቃለልኩት፡፡
ጠበቆች፣ ዳኞች፣ ጸሐፊዎች፣ ነገረ ፈጆችና ወኪሎች፣ ተሟጋቾችና አማላጆች፣ “ጫማ ጠራጊዎችና ሥራ ፈቶች፣ እንደየ ኑሮ ደረጃቸው ለብሰው ተራ በተራ ሁለትና ሦስት እየሆኑ በመምጣት የፍርድ ቤቱን አካባቢ የበጋ ወራት ገብያ
አስመሰሉት፡፡ አንዳንዶቹ ሰዎች የለበሱት ነጠላና ጋቢ በጣም ከመቆሸሹ የተነሣ
ዳግመኛ ታጥቦ የሚነጣ አይመስልም፡፡ ጥለቱ የተንዘለዘለ፣ ዐልፎ ዐልፎ አይጥ
የበላው ይመስል የተቀዳደደ፣ እንደ አረጀ ሻሽ አለቅጥ የሳሳ ልብስ፣ በተለያየ
የጨርቅ ዐይነት የተጣጣፈ ኮትና ሱሪ፣ ከታጠበ ብዙ ዓመታት ዐልፈውት እድፉ
እንደ ማሰሻ የተላከከበት ሱፍ ኮት፣ ከተወለወለ ወራት ያለፉትና የቆዳው ቀለም የተገጣጠባ ከወደ አፍንጫው በእንቅፋት አልቆ ቀዳዳው የደረቀ የዓሣ አፍ የመሰለ፡ ከወደ ተረከዙ ወይም ከወደ ጎኑ ባንድ ወገን ተበልቶ የተንጋደደ ጫማ፣
በፀሐይ ሐሩርና በውርጭ፣ በአቧራና በእንክርት ቀለሙ ጠፍቶ የነተበ ባርኔጣ፣
የለበሱ ያደረጉና የደፉ ሰዎች በተስፋ መቁረጥ ስሜት እዚህም እዚያም
ቆመዋል፡፡ ለአያሌ ወራትና ዓመታት የተንገላቱና የተጎሳቆሉ ባለጉዳዮች ናቸው::በረሃብና በጥማት በርዛትና በንዴት በመጎዳታቸው አብዛኛዎቹ ውርጭ ላይ ያደረ አንጋሬ ይመስላሉ፡፡ ሕይወታቸው በትካዜ በመሞላቱ የገጽታቸው ፈገግታ ደርቋል፡፡
ወዛቸው እንደ ቅቤ ቅል የሚቅለጠለጥ ፊታቸው በዶሮ ጮማ እንደተወለወለ የወይራ በትር የሚያበራ፣ ቦርጫቸው የመንፈቅ ርጉዝ መስሎ ሱሪያቸው መታጠቂያው ላይ የሪቅ አፍ የሚያህል፣ አለባበሳቸው ሁሉ በጣም ያማረና የተዋበ ደንደሳሞች፣ በየደቂቃው በሚረባና በማይረባው ሁሉ የሚሥቁ በጣም መሠሪ ሰዎች ከየቢጤዎቻቸው ጋር ሰብሰብ ከምችት ብለው አፍ ለአፍ
ገጥመው ያወራሉ። የያዙት የሰነዶች መያዣ ኮሮጆ እንደ ባለቤቶቹ የፀዳ ሲሆን
የልፋት እንክርት አልነካውም፡፡ የተሰበሰበውን ሰው በዝርዝር ሲያዩት እያንዳንዱ ብቻውን ቆሞ እጁን እያወራጨ ከራሱ ጋር ይሟገታል።
አብዛኛው ጨርቅ ለባሽ በሌላ ሰው ወረቀት እያስነበበ ይኽ ልክ ነው
የለም ይኽ ሐሰት ነው! ለዚህ በቂ ነቃሽ አለኝ! ያያት የቅድመ አያቴ ነው ይግባኝ እላለሁ፡ ከዳኛው ጋር ተዋውለው ነው። ወላዲተ አምላክን!” እያለ እሰጥ
አገባ ይላል። ሁሉም ከሕይወት ወዲያ ማዶ በውሸት ዓለም ውስጥ የሚንቀሳቀሱ እንጂ በርግጠኛ ሕይወት በእውነተኛ ዓለም የሚኖሩ አልመሰሉኝም
የመጥፎ ነገር ጥቀርሻ በጥብጠው የጋቱኝ ይመስል አእምሮዩ ተጨነቀ፡፡
የማያቋርጠው የጊዜ ጎርፍ እየጋፈረ መጓዙን ቀጠለ። ደቂቃ የደቂቃ ርካብ ረግጣ እየተፈናጠጠች ላትመለስ ትጋልባለች።
ጎነ ረጂሙ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ግዙፍ ሕንፃ ታላቅ የመከራ ተራራ መስሎ ፊት ለፊት ተገትሯል። የማደርገውን ጥንቃቄ አሟልቼ አካባቢዬን ገልመጥ እያልኩ እያየሁ መለስ ቀለስ አልኩ፡፡ ጭንቀቴና ጥበቴ እንደ ሐምሌ ጥቁር ደመና ከብዶ አንጎሌ ውስጥ አንዣሰሰ። በውስጤ የነበረው ሥጋት በድኃ ገበሬዎች አዋሳኝ እንዳለ የከበርቴ እርሻ መስፋቱን ቀጠለ። ረፈደ።
በወታደሮች ታጅበው በእግራቸውና በመኪና የመጡ አያሌ እስረኞች
በተለየ ቦታ ሰብሰብ አጀብ ብለው ቆሙ። ገር ገጭ ገጭ ገጭ፣ ሲጢጢጢጢጢ !
ካካካካካኪ! የሚል ድምፅ የምታሰማ ቮልስዋገን መጥታ አጠገቤ ቆመች፡፡ ጉልላት ነው። የየወዲያነሽ ቀነ ቀጠሮ በመሆኑ እኔና እርሱ ከፍተኛው ፍርድ ቤት
ለመገናኘት ተነጋግረን ነበር። ድክምክም ባለ እንቅስቃሴ የመኪናይቱን ቋቋቲያም
“በር ከፍቶ ወጣና ጨበጠኝ፡፡
ለአራት ሰዓት ሩብ ጉዳይ እኮ ሆኗል እስካሁን አላመጧትም እንዴ?»
አለኝ፡፡ ከንፈሬ ተጣብቆና ምላሴ አልላወስ ብሎ ቢያስቸግረኝም የለም እስካሁን አላመጧትም» ብዬ ዝም አልኩ። ውካታ በበዛበት አካባቢ ጥቂት ዝም ብለን ቆምን። ትላንት ማምሻዬን ሦስት ባለሙያ ጠበቆች አነጋግሬ ነበር። ሁሉም የሰጡኝ መልስ በጣም ተቀራራቢ ነበር፡፡ ቢበዛ አምስት ዓመት” አሉኝ። እንተስ ምን ይመስልሃል?» ብሎ ዐይኔን ማየት ጀመረ።
«እኔ ምን ዐውቃለሁ፡፡ ማንም ቢሆን ከራሱ ላይ ይልቅ በሌላው ላይ
መፍረድ ይቀልለዋል። የፍርድ ሰጪዎቹን ማንነት ስታየው ግን አምስት ዓመት
የሚበዛ አይመስልም፡፡ ቢሆንም ለእኔና ለእርሷ እያንዳንዱ ደቂቃ የሕይወታችን
ማሻከሪያ ክፍለ ጊዜ መሆኗ ነው» ብዬ ዝም አልኩ፡፡
«መቼም ቢሆን» አለ ጉልላት ወደድክም ጠላህም ምን ጊዜም ቢሆን ሕግ አለ። በሕጉም የሚጠቀሙና ጥቅማቸውን የሚያስጠብቁ አሉ። አህያና ጅብ
ባንድ ላይ ሕግ አያረፉም፡፡ ለጨቋኝና ለተጨቋት በአንድ ጊዜ በእኩልነት
የሚያገለግል ሕግ የለም፣ አልነበረምም፡፡ ሕግ ስለተፃፈ ብቻ ሕጋዊ አሠራር አለ
ማለት አይቻልም። እኔና አንተ ባለንበት ሥርዓተ ማኅበር ውስጥ እጀግ በጣም
አያሌ ባለሥልጣኖችና አጫፋሪዎቻቸው በልዩ ልዩ የእሠራር ስልትና ሥልጣን
ፈጠር ከለላ ከሕግ በላይ የሆኑበትና የሚሆኑበት ሁኔታ እንዳለ መዘንጋት
የለበትም፡፡ ስለሆነም ሕግ በትክክለኛው መንገድ በሥራ ላይ እስካልዋለ ድረስ
የሌለ ያህል ነው፡፡ ይህ ጉዳይ በስፋት የሚያነጋግግር ስለሆነ አሁን ከመጣንበት
ጉዳይ ጋር በቀጥታ ተያያዥነት የለውም። ወደ መጣንበት ጉዳይ እንመለስ፡፡
ስለዚህ በሚሰጠው ፍርድ እንዳትገረም፡፡ የበዛ ወይም ያነሰ ሊሆን ይሆናል» ብሎ
ወደፊት ተራመደ፡፡ ርምጃዬን ከርምጃው ጋር አስተካክዩ ተከተልኩት።
ከእኛ ትንሽ ራቅ ብሎ አንድ ብረት ሽፍን ባለ ጥቁር ሰሌዳ አረንጓዴ መኪና ቆሟል፡፡ ጉልላት መኪናውን አሻግሮ እየተመለከተ «ለምንድን ነው አልመጣችም ያልከኝ? ያ እኮ ነው የወህኒ ቤቱ መኪና» ብሎ ጥሎኝ ሔደ፡፡
አልተከተልኩትም፡፡
መኪናው ውስጥ ከተቀመጠው ሰው ጋር ምን እንደተባባሉ ባይሰማም ጉልላት ትንሽ ራቅ ብሎ ተነጋገሩ። ወዲያው ወደ እኔ ዞር ብሉ ና ቶሉ በሚል አኳኋን ጠቀሰኝ እና ሄድኩ፡፡ እስረኞቹ ወደሚገኙበት አካባቢ እንደ ደረስን ዐይኔ
ያካባቢው የብርሃን መጠን ያነሣት ይመስል የውበት ሃያ መስኮቶቿ ተሸጎሩ።
አጠርጠር ያሉና በሰፊ የካኪ ጨርቅ ስልቻ ውስጥ የቆሙ የሚመስሉ
የወህኒ ቤት ሴት ወታደሮች እያንዳንዳቸው አጠር ያለ ዱላ ይዘው ቆመዋል። በአቅራቢያቸው አምስት ሴቶች ሰብሰብ ብለው ተቀምጠዋል። የትካዜ እሳት ያነኮታቸው ይመስላሉ። ንዳድ እንደ ተነሣበት ሰው መላ ሰውነቴ ጋየ፡፡
የሕይወቴ ክፋይ የሆነችውና የማፈቅራት የወዲያነሽ አንገቷን ሰበር አድርጋና ጀርባዋን ለረፋዷ ፀሐይ ሰጥታ መሬት ትቆረቁራለች። ጉልላት ከሴቷ ወታደር ትንሽ ራቅ ብሎ በትሕትና እጅ ነሣ ራመድ ብዬ ከጎኑ ቆመኩ
በተከዘ ፊቱ ላይ ለማስደሰት የሚፍጨረጨር ፈገግታ እያሳየ «ከነዚህ

👍3❤1
#ያልታበሱ_እንባዎች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ
አአድን
....ከቀኑ ዘጠኝ ሠዓት አካባቢ መርዕድ ከአንድ የሥራ ባልደረባው ጋር በመሆን በቀድሞው የዲላ ከተማ አውቶብስ መናኸሪያ ፊትለፊት ጥቂት ሜትሮች ወረድ ብሎ ከሚገኝ (አባይ ፏፏቴ ተብሎ በሚታወቅ ሆቴል በረንዳ ላይ ቁጭ ብለው ሻይ ይጠጣሉ። ፊታቸውን ወደ መናኸሪያው አድርገው ስለተቀመጡ አካባቢ ወለል ብሎ ይታያቸዋል፡፡ በጨዋታቸው መሀል ዓይንና
ቀልባቸው ወደ መናህሪያው ወርወር ሲያደርጉ አካባቢው ለየት ያለ ሁኔታ እየተፈጠረ መሄዱን፣ ሁለቱም በየግላቸው ያጤኑ ኗሯል ሰው በርከትከት እያለ መሄዱን ወንዶች ጋቢ ፣ ሴቶች ደግሞ ነጠላ እየለበሱ እጅብ እጀብ እያሉ መቆማቸው ያያሉ።
«ዛሬ ምን ችግር አለ?» ሲል የመርዕድ ጓደኛ ጠየቀ፡፡
እኔ እንጃ! ምናልባት ከሌላ አገር የሚመጣ አስክሬን ይኖር እንደሆነ፡፡» አለ መርዕድ ወደ መናኸሪያው እየተመለከተ፡፡
ከትንሽ ቆይታ በኋላ ከርቀት የሚሰማ የለቅሶ ድምፅ ከጆሮአቸው ጥልቅ አለ። የድምጹ አቅጣጫ ከተቀመጡበት ሆቴል በስተጀርባ ነው፡፡ መርዕድ
ከተቀመጠበት ብድግ ብሎ የለቅሶ ድምጽ ወደተሰማበት መንገድ ወጣ በማለት ቁልቁል ሲመለከት አንዲት ሴት በሌሎች በርካታ ሰዎች ታጅባ ክንፏን ዘርግታ እያለቀሰች ወደ ላይ ወደ መናኸሪያው ስትገሰግስ አያት፡፡ወንድሜ ወንድሜ! እኔ
አፈር ልብላ! ወንድሜ እኔ ልደፋ! ወንድሜ…!» ስትል ይሰማዋል።
«አረ ወደዚህ ወደ መናኸሪያው እየመጣች ነው» ሲል መርዕድ ያየውን ሴትዮዋ ብዙም ሳትቆይ እነመርዕድ የነበሩበትን ሆቴል አልፋ ወደ መናኸሪያው ተጠጋች፡፡ በአካባቢው የነበሩ ስዎችም እየተላቀሱ ሲቀበሏት መርዕድና
ጓደኛው ተመለከቱ፡፡ «እስቲ ጠጋ ብለን እንጠይቅ!» ተባባሉና መርዕድና ጓደኛው ወደ መናኸሪያው አቀኑ። የመርዕድ ጓደኛ ወደ አንድ ትክዝ ብሉ ቆሞ የነበረ ሰው ጠጋ በማለት ችግር አለ እንዴ የኔ ወንድም?» ሲል ጠየቀው፡፡
«ስው አለቀ ይላሉ።» አለው ስውየው እዝን ባለ አነጋገር።
«ምን ሆኖ?
«በመኪና አደጋ፡፡
«የት?»
"ዝዋይ ያሜዳ በረሃ ላይ::» አለና «ከዚህ ከዲላ ወደ አዲስ አበባ ይሄድ የነበረ አንደኛ በራሪ አውቶቡስ ከሌላ መኪና ጋር ተጋጭቶ ነው አሉ። አለ ጉንጩን በመዳፉ ደግፎ ዘመም በማለት፡፡
«እንዴ!» አለ መርዕድ፡ ጓደኛው ዞር ብሎ መልከት ሲያደርገው የመርዕድ ፊት ልውጥውጥ ብሏል።
«የሄደ ዘመድ እለህ እንዴ?» ሲል ጠየቀው::
አንድ ጓደኛዬ ሄዷል፡፡
«በአንደኛው በራሪ?»
«እሱን እንኳ አላውቅሁም ጠዋት የሸኘው ሌላው ጓደኛችን ነው።» አለና መርዕድ እንዴት ይሻለኛል?» ሲል ጠየቀ ለጊዜው ምላሽ ባይጠብቅም::
«ጠዋት የሸኘውን ጓደኛህን ጠይቀዋ!» አለው ጓደኛው::
«ለመስክ ሥራ እንደሚሄድ ማታ ነግሮኛል። አሁን ከተማ ውስጥ
አይኖርም፡፡» አለ መርዕድ። ትናንት ምሽት ላይ የአስቻለውንም የበልሁንም የወጪ ግብዣ ጠጥቷልና በልሁ ከተማ ውስጥ እንደማይኖር ያውቃል።
አካባቢው በፍጥነት እየተለዋወጠ ሄደ:: ከዲላ ከተማ አራቱም ማዕዘን ወደ መናኸሪያው ሰው ይጎርፍ ጀመር፡፡ የዚያኑ ያህል አልቃሹ በዛና ጩኸት በረከተ
ድብልቅልቁ ወጣ፡፡ እንዳንዶቹ የዘመዶቻቸውን ዕጣ ፈንታ አውቀው አስከሬን ለማምጣት የኮንትራት መኪና ፍለጋ ይሯሯጡ ጀመር። አብዛኛው ግን ከአዲስ አበባ ወደ ዲላ በሚመጣው አውቶቡስ የሚመጣውን ሰው ይጠባበቃል፤ ሁኔታውን አይቶ
ወይም አውቆ ከሆነ ብሎ መረጃ ለማግኘት።
ወደ አስር ሠዓት አካባቢ ድንገት የአውቶብስ ጡርንባ እሩቅ ተሰማ። ልክ "አልቅሱ" የሚል ፊሽካ የተነፋ ይመስል ያ ሁሉ ሰው በአንዱ ጮኹ፡፡ እሪታና ኡኡታው ቀለጠ። በዚያ አላበቃም፣ ወደ አውቶብሱ መምጫ መንገድ ሩጫና
እሽቅድምድም ተጀመረ፡፡ አውቶቡሱ ከታች ከአዲስ አበባ መግቢያ በሆነው አስፋልት
መንገድ ላይ ገስግሶ ወደ መናኸሪያ መታጠፊያ በሆነችው አደባባይ ላይ ሲደርስ በህዝብ ተከበቀ፡፡ መሄጃ አጥቶ ቆመ:: በተሳፋሪና በጠባቂው ህዝብ መካከል መጯጯህ ተጀመረ። መኪና ወስጥ ያለው አንገቱን በመስኮት እያወጣ ምነው?
ምንድነው?» ይላል። ከውጭ ያለው ደግሞ እንዴት ነው? ሰው ተርፏል ወይ! ወዘተ» እያለ ይጮሀል። መሰማማትም መግባባትም አልተቻለም:: እንደ ምንም መግባባት ሲጀመር ደግሞ ለካ መኪኖቹ ተላልፈው ኖሮ ከአዲስ አበባ የመጣው
መንገደኛ ስለ አደጋው ምንም አልሰማም፡፡ እንደውም ከአውቶቡሱ ላይ እየወረደ
ቀድሞ ከነበረው መረጃ ፈላጊ ሕዝብ ጋር እየተቀላቀለ አብሮ ወለሌ ይል ጀመር።
ቀጣዩ አማራጭ በአለታ ወንዶ በኩል የሚመጣውን ሁለተኛ በራሪ መጠበቅ ብቻ መርዕድ በዚያ ጭንቀት ውስጥ ሆኖ መቆየት አልቻለም፡፡ ይህን ሁኔታ ለታፈሡ መንገር እንዳለበት አስበ:: ጊዜ አላጠፋም፣ ወዲያው ወደ ቤቷ በረረ። በሩጫው ወቅት ከቤቷ ስለ መድረሱ እንጂ ታፈሡ ትኑር ወይም አትኑር ምንም
የሚያስበው ነገር አልነበረም:: ብቻ ሲደርስ ምን ብሎ እንደሚነግራት ያስባል፡፡ ከታፈሡ ቤት ሲደርስ ልክ አሥር ሰዓት ሆኗል። ያገኛት ግን ታፈሡን ሳይሆን ያላሰባትን ሔዋንን ነው።
«ታፈሡ የለችም እንዴ?» ሲል እያለከለከ ሔዋንን ጠየቃት።
ምነው? አለችው ሔዋን ከሶፋ ላይ ብድግ ብላ፡፡ የመርዕድ ሁኔታ
አስደንግጧታል፡፡ ከማለክለኩም በተጨማሪ ፊቱን አልቦታል፡፡ ዓይኑም ፈጥጧል።
«አይ ብቻ- ደህና ነኝ::አለና መርዕድ ሶፋው ላይ ቁጭ አለ::
«አትመስለኝም መርእድ!»
ግን አንቺ በአሁኑ ሠዓት እንዴት እዚህ ልትገኝ ቻልሽ?» ሲል ጠየቃት መርዕድ እሱም በበኩሉ የሔዋንን ሁኔታ ሰለል እያደረገ። ሲያያት ሁኔታዋ ሁሉ አላማረውም፡፡ ስታለቅስ እንደ ዋለች ሁሉ ዓይኖቿ ቀልተው እንዲያው ያበጡ ይመስሳአሉ ። ከፊቷም ላይ ደስታ አይነበብም፡፡! ይቺ ልጅ ስለ አስቻለው ምን ሰምታ ይሆን? እያለ በልቡ ያስብ ጀመር፡፡ «ድንገት መጥቼ ነው፡፡» አለችው ሔዋን። ለጊዜው በዚያ ሠዓት እዚያ ቤት የተገኘችበትን ሁኔታ መዘርዘር አልፈለገም።
“ታፈሡ ስራ ሄዳ ነው?» ሲል ጠየቃት።
«አዎ፡፡» አለችና ሔዋን ግን ደህና እትመስለኝም መርዕድ ስትል
ሁኔታውን ሁሉ በዓይኗ እየሰለለች ጠየቀችው፡፡መርዕድም ልክ እንደ ሔዋን የሆዱን ምስጢር መዘርዘር አልፈልገምና የቻለውን ያህል ራሱን እያረጋጋ «ደህና ነኝ ስልሽ!» ዝምብሉ ጣሪያ ጣሪያውን
ይመሐት ጀመር፡፡ በመሀላቸው ፀጥታ ሰፈነ። በየሆዳቸው ግን የየግላቸውን ጉዳይ በመሀል ከውጭ በኩል የሰው ኮቴ ተሰማቸው። ሁለቱም ጆሮአቸውን
አቁመው ሲያዳሃምጡ ኮቴው እየቀረባቸው መጣ፡፡ አሁንም እርስ በእርስ እየተያዩ ሲያዳምጡ ታፈሡ ከቤት ውስጥ ዘው ብላ ገባች። የቸኮለችና የተጣደፈች ትመስላለች፡፡ ያ ብርቱካን የመሰለ ቀይ ፊቷ የባሰ ደም መስሏል፡፡ ዓይኗም ፈጧል።ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ ይላል። በዚሁ ስሜት ውስጥ ሆና ሳታስበው መርዕድን በዚያ ሠዓት እዚያ ቤት ውስጥ ማግኘቷ የበለጠ እስደነገጣትና
«አንተ መርዕድ!» አለችው ጮክ ባለ ድምጽ።
«ወይ» መርዕድም ደንግጦ ብድግ አለ::
«ምንድነው ከተማ ውስጥ የሚወራው?»
«አደጋ ደረሰ ይላሉ። አንቺም ስማሽ እንዴ?» አላት በድንጋጤ አስተያየት

👍8
#ምንትዋብ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ
...“ቁስቋም ብዙ ነገር ሰጥታኛለች፣ ወንድ ልዥ ደሞ ብትሰጠኝ።”
“ትሰጥሻለች። ምን ይሳናታል? አሁን ስለሱ አታስቢ።”
ሆዷ እየገፋ ሲመጣ፣ ጭንቀቷ በረታ። ሴት በመውለዷ ባትከፋም፣ ወንድ አለመውለዷ ቤተመንግሥት ውስጥ ሊኖረኝ ይችላል ብላ ያሰበችውን ቦታ የሚያሳጣት መሰላት።
ይበልጡንም ደግሞ ወህኒ
አምባ ያሉ የነገሥታት ዘሮች የሚወለደው ወንድ ቢሆን ሐዘናቸውን፣ ሴት ብትሆን ደግሞ ደስታቸውንና የበካፋን ተስፋ መጨናገፍ እያሰበች መንፈሷ ተበጠበጠ። የጐንደርን ታቦታት ሁሉ ተማጸነች። የእሷ
ቋረኝነት ያብከነከናቸው መሣፍንትና መኳንንት ደግሞ በካፋ ሲሄዱ ቋረኛ አልጋው ላይ የመውጣቱ ጉዳይ ሲያሳስባቸው፣ ሲያነጋግራቸውና ልባቸውን ሲሰቅለው እሷ የበለጠ ጭንቀት ውስጥ ገባች።
የቤተመንግሥት ባለሟሉ፣ የበካፋ ደጋፊ መኳንንትና ሕዝቡ ግን
በእነሱ ዘንድ ተወዳጅነትን እያተረፈች ለመጣችው፣ ለእሷ... ለምንትዋብ ወንድ ልጅ እንድትወልድ ተመኙላት።
ለወራት ቤተመንግሥት ግቢ ውስጥ፣ በየቤቱና በየመንደሩ ወሬው ተጋጋለ፤ ሞኝ መቆሚያ ላይ ተሟሟቀ፤ ጃን ተከል ላይ ተፋፋመ።የጃን ተከል ደንበኞች ወደ ሞኝ መቆሚያ ተጨማሪ ወሬ ለማሳደድ አሽቆለቆሉ። የሞኝ መቆሚያዎቹ ወደ ጃን ተከል በጥድፊያ አሻቀቡ።
መጽሐፍ ገላጩና ኮከብ ቆጣሪው ገሚሱ ወንድ፣ ሌላው ሴት ነው
ሲል ተነበየ። ገበሬው በየእርሻው፣ ነጋዴው በገበያው ላይ፣ ሴቶች ወንዝ ዳር፣ ሽማግሌና ወጣት በየጎጡ እሰጥ አገባ ያዙ፤ ተወራረዱ። የንግርት
ዓይነቶች ተወሱ። የቆራጣ ገዳም እመምኔቷ፣ የወለተጴጥሮስ ትንቢት ተወራ፣ የሰማው ላልሰማው አስተላለፈ። ወሬው ጐንደርን ተሻግሮ በየግዛቱ ተናፈሰ። ቀድሞ ስለነገሥታት የተነገሩ ሌሎች ንግርቶች
ሁሉ ለማመሳከሪያነት ቀረቡ፣ ተመረመሩ፣ ተተነተኑ።
ሃገር በወሬ ታመሰች። ወንድ ነው ሲሏት ጮቤ ስትረግጥ፣ ሴት ናት
ሲሏት ስትተክዝ ከረመች።
ምንትዋብ በበኩሏ ቀናቱ ሲያዘግሙባት፣ ወራቱ እንደ ገመድ ሲጎተቱባት ቆይታ አንድ ሌሊት ምጥ ያዛት። እናቷና አያቷ የነገሥታቱ አዋላጅ የሆኑትን ሴት በፍጥነት አስመጡ። ምንትዋብ ሌሊቱን በሙሉ ስታምጥ፣ ሴቱ “ማርያም”፣ “ማርያም” ሲል፣ በካፋ በጭንቀት ቁጭ
ብድግ ሲሉ፣ ሲጸልዩ፣ ካህናት ምህላ ሲያወርዱና የቤተመንግሥት ባለሟሎች ሲንቆራጠጡ ቆይተው ንጋት ላይ የመጀመሪያው ዕልልታ ተሰማ። በሰላም የመገላገሏ ዜና በመኾኑ ለአፄው የአፍታ እፎይታ
ቢሰጣቸውም የሕጻኑን ጸታ ለመለየት ዕልልታውን መቁጠር ጀመሩ።
ዕልልታው ተደገመ፤ የበካፋ ጭንቀትም ናረ፤ ሦስተኛውና የመጨረሻው ዕልልታ ይሰማና ወሽመጤን ይቆርጠው ይኾን ወይስ ይቀጥላል? የሚለው ጭንቀት በእያንዳንዱ ዕልልታ መሃል ያለችዋን ቅጽበት ዝንተዓለም እስክትመስል ድረስ ለጠጣት። ሦስተኛው ዕልልታ
ተሰማ። እዚኸ ላይ የበካፋ የልብ ትርታ ፀጥ አለ፤ ሌላ ዕልልታ ካልተሰማ አልቦ አልጋ ወራሽ የሚለው ሥጋት ሰቅዞ ይዟቸዋል። የጠላቶቻቸውን መደሰት፣ የወዳጆቻቸውን መሳቀቅ እየቃኙ ሳለ፣ አራተኛው የዕልልታ
ድምጽ መጣ። ወንድ ልጅ! አምስተኛውን፣ ስድስተኛውንና ሰባተኛውን ዕልልታ መስማት አላስፈለጋቸውም፤ ወንድ ልጅ ተወልዶላቸዋል! ዜናውን በመላ ቤተመንግሥቱ ግቢ ውስጥ ሲያስተጋቡት፣ ግቢው
ትርምስምሱ ወጣ።
ምንትዋብ ድካም ላይ ብትሆንም ደስታዋ ወሰን አጣ፣ በጭንቀት
የተኮማተረው ግንባሯ ተፍታታ፤ ቁስቋም ማርያምን አመሰገነች።
አፄ በካፋ በጭንቀት የሙጥኝ ይዘውት የነበረውን የጸሎት
መጽሐፋቸውን አስቀምጠው ከመኝታ ክፍላቸው ወጡ።
ምንትዋብ ወዳለችበት ገሰገሱ። ምንትዋብ እስክትጸዳዳ ጠብቀው
ሲገቡ፣ እየደጋገሙ፣ “እንኳን ማርያም ማረችሽ” አሏት። እንኰዬ
ህጻኑን ኣቅፈው ሲያሳይዋቸው የደስታ እንባ ተናነቃቸው። አልጋ ወራሽ በማግኘታቸው ሩፋኤልንና ከአንገርብ ወንዝ በስቲያ ደፈጫ የተከሏትን ኪዳነ ምሕረትን አመሰገኑ፤ ውለታቸውን በወርቅ እንደሚከፍሉ ቃል ገቡ።
ቤተመንግሥቱ ውስጥ ታላቅ ፈንጠዝያ ሆነ። ወዲያው ስፍር ቁጥር የሌለው የግባት ነፍጥ ወደላይ ተተኮሰ። የአካባቢው ሰው “ወንድ ነው!
ወንድ ነው!” እያለ ጃን ተከል ግልብጥ ብሎ ወጣ። ሴቶች ዕልልታቸውን አቀለጡት። ጐንደር የምሥራቹ ደረሳት፤ ፈነደቀች። ራቅ ካሉ ቦታዎች ሳይቀር ጐንደሬዎች እየከነፉ ጃን ተከል ደረሱ።
እቴጌ ወንድ ልዥ ተገላገሉ! ሰባት ግዝየ ሲተኮስ ቆጥሬያለሁ።
ወንድ ነው። ንጉሡ አልጋ ወራሽ አገኙ!” ይላል አንዱ።
“ሦስት ቆጥሬ ሴት ትሆን? ስል ዐራት ሲደገም እንግዲያማ ሰባት
ነው ሚሆን። ወንድ ነው ብየ ስሮጥ መጣሁ” ይላል ሌላው።
የዕጣና የውርርድ አሸናፊዎች የድል ዋጋቸውን ጠየቁ።
ንግርቶች ሁሉ እንደገና ተነገሩ። የቅድስት ወለተጴጥርስ ትንቢት
ተነሣ። “የሷ ንግርት መሬት አይወድቅም” ተባለ። በየደብሩ ካህናት ደወል አሰሙ። ዘመሩ፣ አሸበሸቡ። መነኮሳት ሕልማቸውን ተለወዋጡ: ደስታ በደስታ ሆኑ።
የበካፋ የሥልጣን ተቀናቃኞች ወሬውን ሲሰሙ ደነገጡ፤ ተስፋቸው እንደ እንፋሎት ተነነ። የማስመሰል ካባ የደረቡ አንጀታቸው ያረረ፣ወንድ ልጅ በመወለዱ ከልብ የተደሰቱ መኳንንት፣ ካህናትና ሊቃውንት
ከቅርብና ከሩቅ ደስታቸውን ለመግለፅ ወደ ቤተመንግሥት ጎረፉ።
ለሕጻኑም መልካም ምኞታቸውን አዥጎደጎዱ። ሕጻኑ በአያቱ፣ በአፄ ኣድያም ሰገድ ኢያሱ ስም ተጠራ። ግብር በየቀኑ ገባ። ኢያሱ፣ በወጉ መሠረት በአርባ ቀኑ ክርስትና ተነሣ።
ኢያሱ ከተወለደ በኋላ፣ የመጀመሪያው መስቀል ነው። ለአፄ በካፋ ዓመታዊ ሠራዊት ግባት ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ ነው። እንደ ጎጃምና ትግራይ ካሉ ራቅ ካሉ ግዛቶች የሚመጡ አስተዳዳሪ መኳንንት
ክረምቱ ሳይገባ ግንቦት ወር ላይ እያንዳንዳቸው ሠራዊታቸውን
ይዘው ጐንደር ሲገቡ፣ እንደ ስሜንና ቤገምድር ካሉ ቅርብ ቦታዎች የሚመጡት ደግሞ ዐዲስ ዓመትን ቤታቸው ውለው ሠራዊታቸውን ይዘው ጐንደር ገብተዋል። ቤተመንግሥት ዙርያ ለየግላቸውና ይዘውት
ለመጡት ሠራዊት ድንኳን ተተክሎላቸው እዚያው አርፈዋል።
ምንትዋብና አያቷ ስለ ሠራዊት ግባቱ አስፈላጊነት ሲነጋገሩ
አያትየው፣ ነገሥታቱ እኼን በዓል ሚያደርጉት አንድም እንግዲህ
ወታደራዊ ጉልበታቸውን ለማሳየት...” ብለው ሲጀምሩ አቋረጠቻቸው።
“ለማን ነው ሚያሳዩት?”
“ለሁሉም። እሱ ብቻ ማዶል። የመኳንንቱን ታማኝነት ለማረጋገጥም ሲሉ ነው። ሌላ ደሞ... ደንብ ሲያወጡ ወይም አዋጅ ሲነግሩ መኳንንቱ
በየግዛታቸው ያነን ደንብና አዋጅ በተመሳሳይ መንገድ እንዲያስከብሩ ጭምር ነው። ሌላው ደሞ መቸም ንጉሡ መኳንንቱ እንዳያምጹባቸው...
ተቀይመዋቸው ከሆነ ደሞ ለማረጋጋትና ሰላም ለመፍጠር በጋብቻ ሚተሳሰሩበትም ግዝየ ነው። በዝኸ ግዝየ አንድ የተቀየመ መኰንን አሞኛል ብሎ ሊቀር ይችላል። እናም እኼ ግዝየ ጃንሆይ አለ ነገር ሚሉበት፣ ብዙ ነገር ሚያውቁበትና ሚስተካከል ኻለም ተሎ ብለው ሚያስተካክሉበትም ግዝየ ነው” አሏት።
የበዓሉ ዕለት፣ ምንትዋብ ከአፄ በካፋ ጎን ድባብ ተይዞላት አደባባይ ወጣች። ሥርዐቱን ለማየት እጅግ ጓግታለች። ከንጉሠ ነገሥቱ ጎን ተቀመች። ጐንደሬዎችም ይህን ታላቅ በዓል ለመታደም ሥራቸውን
ነቅለው ወጥተዋል። ፎካሪዎች በየተራ እየወጡ ወደላይ ወደታች እያሉ ፎከሩ፣ ሽለሉ። ንጉሠ ነገሥቱን አወደሱ፤ አመሰገኑ።ሽለላውና ፉከራው ሲቆም፣ በአጋፋሪ መሪነት ታላቁ ስልፍ ተጀመረ።

👍13
#ትኩሳት
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር
....ከዚሀ ከሽጉጥ ፍጥጫ በኋላ ጀምሺድና ሉልሰገድ ብዙ ጊዜ፤
ብዙ ቦታ አብረው ይታዩ ጀመር፡፡ ማታ ሁለቱ በጀምሺድ መኪና
ይሄዱና፣ ኒስ፣ ካን ወይም ሞንቴካርሎ ቁማር ሲጫወቱ ሰንብተው ሰኞ ጧት ይመለሳሉ። ከውጭ ለሚያየው ሰው ጓደኝነታቸው እየጠበቀ ሄዴ..
ክረምት እየተንፏቀቀ መጣና፣ ከወርቃማው በልግ ጋር ተቃቅፋ
የነበረችውን የኤክስ ከተማ እንደ ቀናተኛ ሌላ ውሽማ በብርድ
ይገርፋት ጀመር፡፡ ሽማግሌዎቹንና አሮጊቶቹን ከየመንገዱና
ከየመናፈሻው አባረሯቸው። ልጃገረዶቹ ቆንጆ ስስ ቀሚሳቸውን
ትተው ወፍራም ሱፍ ቀሚስ፣ ሱሪና ወፍራም ሹራብ፣ ካፖርት
እየለበሱ፣ ውብ ቅርፃቸውን ከክረምቱ አይን እየሽሽጉ በበጋ ቀያይ ወይም ብር መሳይ የጥፍር ቀለም ተቀብተው ሲውለበለቡ የነበሩትን ጣቶቻቸውን በወፍራም ጓንቲ ውስጥ እየደበቁ፤ ከክፍል ወደ ምግብ ቤት፣ ከምግብ ቤት ወደ መኝታ ቤት በፍጥነት ኩስ ኩስ ይሉ ጀመር። ውብ ዳሊያቸውን እያወዛወዙ በዝግታ መራመድ፣ ፅጌረዳ ጉንጫቸውን እያሳዩ፣ በቀያይ ከንፈራቸው እየሳቁ፣ በተኳላ አይን
ጎረምሳውን መቃኘት ቀረ፡፡ (ኩሉንና የከንፈር ቀለሙን ብርድ
ስለሚሰነጣጥቀው ለአይን ደስ አይልም።) ደም የሽሽውን ነጭ
ጉንጫቸውን ግራጫ ብጤ የጎሽ ፀጉር ወረረው በየመንገዱ ዳር በተርታ የተተከሉት ዛፎች ራቁታቸውን ቆመው
የኤክስን ንፁህ ሰማይ በጭራሮዋቸው ይቧጥጡታል። ቅጠሎቹ በሙሉ ረግፈው የባቡር መንገዱን ዳርና የሰው መተላለፊያውን ሞልተውታል። ሰው በፍጥነት ሲራመድ በቡት ጫማው ይፈጫቸዋል
አንዳንድ ቀን በረዶው እንደ ጥጥ በዝግታ ይወርድና ኤክስን
በንፁህ ነጭ ሻሽ ይገንዛታል። በሱፍ የተከናነቡት ልጃገረዶችና
ጎረምሶች ሜዳ ወጥተው በረዶውን እያድቦለቦሉ ይፈነካከታሉ ይሳሳቃሉ። ትንፋሻቸው እንደ ጉም ከአፋቸው ቡልቅ ቡልቅ! ሲል ይታያል። ጥቁሮቹ በረዶው ላይ እየሆኑ ፎቶግራፍ ይነሳሉ የኤክስ ሰማይ አብዛኛውን ጊዜ ብሩህ ሰማያዊ ነው። አንዳንድ ጊዜ ውሀ አረንጓዴ ይሆናል፣ ወደ ማታ ሰአት እንደ ልጃገረዶች ጉንጭ ይቀላል። የኤክስ ሰማይ ደመና አይለብስም፡ ሁልጊዜ ራቁቱን ነው፣ ሁልጊዜ ውብ ነው፤ ሁልጊዚ ሰሳማዊ ነው። ማታ ማታ የአልማዝ ከዋክብትና የፀጥታ ሰላም ይለብሳል
ክረምት ሲሆን ሌሊቶቹ ይረዝማሉ፣ ቀኖቹ ያጥራሉ፤ ፀሀይዋ ጧት ወደ አንድ ሰአት ተኩል ላይ ትወጣና ከሰአት በኋላ ወደ አስር ተኩል ላይ መጥለቅ ትጀምራለች፤ በሽታ እንደያዘው እየማቀቀች እየደከመች ትሄዳለች። ሩቅ፣ ሩቅ ሩቅ በጣም ሩቅ ሆና ኮሳሳ ብርሀን ትልካለች። እቺ ፀሀይ በበጋው የሙቀት ምንጭ ነበረች፡ለኤክስ አሮጊቶችና ሽማግሌዎች የህይወት ተስፋ ነበረች፣ አሁን ግን
ሰማዩ ተበስቶ ከውጭ የብርድ ጮራዎች የሚያስገባ ይመስላል
ብርዱ መላውን ፍጥረት ጨብጦ ያዘ፡፡ የሁላችንም ህይወት
በክረምቱ ብርድ ታሰረ፣ በቆፈን ተቋጠረ፡፡ ፀደይና ፀሀይ መጥተው
እስኪያስፈቱንና እስክንንቀሳቀስ ድረስ፣ የህይወታችን ታሪክ በያለበት ረጋ:: ተካና ጀርመኗ እኔ የማላውቀውን ግንኙነታቸውን ቀጠሉ፡፡ጀምሺድና ሉልሰገድ በኒኮል የፍትወት ገመድ ተሳስረው መለያየት አቅቷቸው፣ ጤና የለሽ ጓደኝነታቸውን ቀጠሉ፤ ለገና እረፍት ባህራም ወደ ኤክስ ሲመለስ ጊዜ፤ ኒኮልን ትተውለት ሁለቱ ተያይዘው ወደ ሞንቴ ካርሎ ሽሹ። እኔና ሲልቪ አልፎ አልፎ
እየተገናኘን፣ የቀረውን ጊዜ ስንፅፍ እንሰነብት ነበር በብርዱ ምክንያት የህይወታችን ታሪክ መፍሰሱን መለዋወጡን ትቶ፣ በያለበት ረጋ
አዳሞ የተባለው ዘፋኝ
"Tombe la neige
Tu ne viendras pas ce soir
Tombe la neige
Me crie mon desespoir..."
(በረዶው ይወርዳል
እንግዲህ ዛሬ ማታ አትመጪም
በረዶው ይወርዳል
ተስፋ መቁረጤ ይነግረኛል .. .»)
እያለ የክረምት እንጉርጉሮውን ያዜማል ..
ፀሀይዋ ቀስ በቀስ የሸሸችንን ያህል ቀስ በቀስ ትጠጋን
ጀመር። አየተቀነሰ የሚሄደው ብርድ፣ ቀጥሎም እየበረታ የሚሄደው ሙቀት፣ ረግቶ የነበረውን የፍጥረት ደም ቀስ በቀስ ያፍታታው ጀመር። መጀመሪያ አንዳንዷ ደፋር ቅጠል ብርዱን አሽንፋ አንገቷን
ብቅ ታደርጋለች፣ ራቁታቸውን የከረሙት ጭራሮ ቅርንጫፎች ላይ ስትታይ ታስደንቃለች፡ ታስደስታለች፤ የድል አድራጊው ህይወት ፊታውራሪ ነች፡ ምስጢራዊ ተአምር ነች። እንግዲህ ሌሎቹ ቅጠሎች
ይከተሉዋታል፡ የኤክስ ዛፎች በራቁት ጭራሮዋቸው ሰማዩን
መቧጨር ትተው፣ በለምለም አረንጓዴ ልብሳቸው ይወለውሉታል፣ ያፀዱታል። የኤክስ ጎረምሶችና ኮረዳዎች መጀመሪያ ካፖርትና
ጓንቲያቸውን አወለቁ፤ ቀጥሎ ሹራባቸውን አውልቀው መሳሳቅ
ጀመሩ። አንዳንድ ደፋር አሮጊት ወይም ሽማግሌ ካፖርቱን
እንደለበሰ መንገድ ላይ ይታይ ጀመር፡፡ ክረምቱ አለፈ ..
ፀደይ መጣ፡፡ የኤስ ልጃገረዶች ከባድ የክረምት ልብሳቸውን ገፈው ጥላው፣ ክረምቱ አልብሷቸው የነበረውን
አስቀያሚ ነጭ ጎሽ ፀጉር ኣራግፈው፤ የተፈጥሮ ውበታቸውን
መልበስ አመጡ፡፡ ፀጉራቸው ጭንቅላታቸው ላይ ተቆልሎ ወይም ወደ ኋላቸው እየፈሰሰ፣ ቆዳቸው ልስልስ ብሎ የፅጌረዳ ቀለም እየለበሰ፣ በቀይ ከንፈራቸው የተከበበ ጥርሳቸው በፈገግታ እያብለጨለጨ፡ ተሸሽጎ የከረመው ወጣት ቅርፃቸው እየፋፋ፣ ሹል ጡታቸው
ከፊት እየተንቀጠቀጠ፣ ያበጠ ዳሌያቸው ከኋላ እየተወዛወዘ፣ ይሄ ሁሉ ፀጋ የፀደይን መልካም ብርሀን ለብሶ በየመንገዱ እየተዘዋወረ፣ የኤክስን ጎረምሶች ምራቃቸውን ያስውጣቸው ጀመር። በብርድ ተኮራምተው የከረሙት ኮረዳዎች አሁን በሙቀት ተዝናኑ፤ እየተጯጯሁ በሳሩ ሜዳ ይፈነጩ
ይንከባለሉ ጀመር። ከጎረምሶቹ ጋር ልፊያና መተቃቀፍ ተጀመረ
ሽማግሌዎቹና አሮጊቶቹ እየወጡ የኩር ሚራሶንና የመናፈሻውን
አግዳሚ ወምበሮች ሰፈሩባቸው። እርጅና ከወጣትነት ጋር እየታከከ
የኤክስን መንገዶች በጎባጣ ጨምዳዳ እርምጃው ይንፏቀቅባቸው ጀመር የክረምቱ ብርድ ገድቦ ይዞት የነበረው ታሪካችን አሁን በፀደይ
ውቀት እንደገና መፍሰስ ጀመረ
ፀደይ ለኤክስ ብርሀንና ሙቀት ከአረንጓዴ ቀሚስ ጋር ይዞላት
ሲመጣ፤ ለተካ ችግር ይዞለት
መጣ። ባለውስታሿ ጀርመን
ታስቸግረው ጀመር። ከአንድ ያገሯ ልጅ ጋር መውጣት አመጣች፡፡
ታዛ ምን ትሽረሙ@ያለሽ? አላት። መሸርሞጥ አይደለም ማማረጥ ነው» አለችው:: እና የትኛችን ይሻላል?» አላት::በአንዳንድ ነገር እሱ ይሻላል፤ በሌላ ደሞ አንተ ትሻላለህ»አለችው። ተካን ቅናት ይሞረሙረው ጀመር
ጥፍሩን እየነከሰ «አሁን ምን ማድረግ ይሻለኛል እባክህን?»
አለኝ
«ትወዳታለህ?» አልኩት
«አዎን። ብዙ ነገር ይገባታል፡»
እሷስ ትወድሀለች?»
«አዎን»
«እንግዲያው አግባታ»
“አብደሀል? ነጭ ሚስት ይዤ ብመለስ አባቴ አይታነቅም?»
«እንግዲያው ተዋት»
እንዴት አድርጌ ልተዋት? በፊት እንኳ ቢሆን ልተዋት እችል
ነበር። አሁን ግን፣ ከዚያ ከንፍጣም ጀርመን ጋር መውጣት
ከጀመረች ወዲህ፡ ከምተዋት ብገድላት እመርጣለሁ፡፡»
«የሀበሻ ምቀኝነት ነው?» አልኩት
«አይደለም፡፡»
«ታድያስ?»
«እህ! ስለቅናት አታውቅም እንዴ? እንግዲያው ልንገርህ፡፡
አየህ፣ ስትቀና ልጅቷን በሀይል ትጠላታለህ። ብትገድላት ፈቃድህ
ነው፡፡ ግን በዚህ አለም ላይ ምን ትፈልጋለህ ቢሉህ፤ እሷን ነው
ምትፈልገው ሁሉ ነገር ይቅር ብቻ እሷ ትምጣ፡፡ ገባህ የምልህ?
ለምሳሌ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሱ ጋር የወጣች ጊዜ፣ ቤቷ ወሰድኳትና አንድ ጥፊ አላስኳት፡፡ ወዳ እስክትጠላ ልደበድባት ቆርጬ ኮቴን አወለቅኩ። ታዲያ ዳግማዊ ጥፊ ላወርድባት ስል

👍16❤2
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
አጸፋ
ምሽቱ አልቆ ሊነጋጋ ስለነበር የምሥራቅ ፀሐይ ውጋጋን ታየ፡
ፋንቲን በኃይል እያተኮሳትና እንቅልፍ ሳይወስዳት ነበር ያደረችው::አስታማሚዋ ሴር የፋንቲንን ሁኔታ በማየት መድኃኒት ለመፈለግ ሄዱ፡፡መድኃኒቱን እየፈለጉ ሳለ ዞር ሲሉ መሴይ ማንደላይንን በድንገት
በማየታቸው ሳያስቡት ይጮሃሉ:: መሴይ ማንደላይን እርሳቸው ከነበሩበት ክፍል ገና መግባቱ ነበር፡፡
«መጡ እንዴ ጌታዩ!» አሉ፡፡
«ያቺ ምስኪን እንዴት ናት?
«አሁን ትንሽ መለስ ብሉላታል:: በጣም ሲያማት ጊዚ ተጨንቀን
ነበር፡፡ ፋንቲን ግን ክቡር ከንቲባ ከዚህ የጠፉት ልጄን ሊያመጡ ቢሄዱ ነው ብላ በማመንዋ ነው መለስ ያለላት በማለት ለመሴይ ማንደላይን ሴርዋ አስረዱ:: ሴርዋ ምንም እንኳን ወደ ልጅትዋ አለመሄዱን ቢያውቁም ጥያቄ
መጠየቅ ኣልደፈሩም::
“ደህና ናታ!›› አለ፡፡
“ታዲያ አሁን ልጅዋን እለማምጣትዎን እንዴት እድርገን ነውዐየምንነግራት? » ሲሉ ሴርዋ ጠየቁ፡፡
ጥቂት አሰበና «እሱ ይመራናል» አላቸው::
ግን መዋሸት የለብንም» አሉ ሴርዋ በዝግታ፡
መስኮት ስለተከፈተ የመሴይ ማደላይን ገጽታ በጉልህ ታየ
«እንዴ፣ ምን ሆነዋል!» አሉ አስታማሚዋ:: (ገጸዎ በጣም
ተለዋውጧል::»
«ተለዋውጧል!» አለ፡፡
መስታወት አነሱ:: እርሱም መስታወቱን ተቀብለ መልኩን ከየ::
«እውነትም ተለዋውጫለሁ!» ሲል አረጋገጠ፡: ግን ይህን ያለው
አሳቡ ለሁለት ተከፍሎ እንደሆነ ያስታውቅበት ነበር::
ሴርዋ አነጋገሩና ጠቅላላ ሁኔታውን ሲያዩ ቀፈፋቸው:: መሴይዐማንደላይን ሊከፍተው ሲል አልከፈት ስላለህ በር አስተያየት እየሰጠ
ፋንቲን ከነበረችበት ክፍል ገባ፡፡ የመስኮት መጋረጃዎችን ገለጠ፡፡ ወደ ፋንቲን ጠጋ ብሎ አያት፡፡ እንቅልፍ ወስዷት ነበር፡፡ ስትተነፍስ እያቃሰተች ነው:: ፊትዋ ፍም መስሎአል፡፡ ቆዳዋም ገርጥቶአል::
መሴይ ማንደላይን ሳይነቃነቅ ከአልጋዋ አጠገብ ቆሞ አተኩሮ
ተመለከታት፡፡ አንዴ ወደ እርሱ አንዴ ደግሞ ከግድግዳ ላይ ተሰቅሎ ወደ ነበረውና ክርስቶስ ወደ ተሰቀለበት መስቀል ተመለከተ፡፡ ከሁለት ወር
በፊት ፋንቲን አሞአት ከዚያች ክፍል ውስጥ ስትተኛ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊጠይቃት ሲሄድ እንቅልፍ ወስዷት እንደተመለከታት ዓይነት ነበር አሁንም ያያት:: አሁንም እንደዚያኑ እለት እርሱ ሊጸልይላት እርስዋ እንቅልፍ ወስዷት ተኝታለች:: ልዩነቱ ከሁለት ወር በኋላ የእርስዋ ፀጉር በይበልጥ
ሽበት ጣል ጣል ሲያደርግበት የእርሱ ፀጉር በሽበት ተሸፍኖ ነጭ ሆኖአል።
ሴርዋ አብረው ወደ ክፍሉ አልገቡም:: ሰውዬው በአንድ እጁ
ከንፈሮቹን ይዞ ነው የቆመው:: ፋንቲን ዓይኖችዋን ስትገልጥ አየችው::
ፈገግ ብላ፡
«ኮዜትስ?» ስትል ጠየቀችው::
«ኮዜትስ» ብላ ስትጠይቀው ልክ ይዞአት እንደመጣ አረጋግጣ በማመን ስለነበር ምን ብሎ እንደሚመልስላት ባለማወቁ ዝም ብሉ ተገትሮ ቀረ።
ይህን ጊዜ እርስዋ ንግግርዋን ቀጠለች፡፡
«ልጄ ጋ እንደሄዱ ተስፋ አደርጋለሁ:: እንቅልፍ ወስዶኝ ነበር፤ ግን አይቼዎታለሁ:: ብዙ ጊዜ አይቼዎታለሁ:: ሌሊቱን በሙሉ ዓይኔ እርስዎ
ተከትሎ ነው የሄደው:: መላዕክትም እርስዎን ተከትለው ሲሄዱ ነበር ግርማ ሞገስዎ ደግሞ በጣም... በጣም ደስ ነበር የሚለው፡፡
ቀና ብሎ ከሴትዮዋ ራስጌ የተንጠለጠለውን መስቀል አየ፡፡
‹ግን ንገሩኝ እስቲ፣ ኮዜት የት አለች? ከእንቅልፌ ስነቃ እንዳያት
ለምንድነው ከአጠገቤ ያላስተኛችሁዋት?»
ሳያስበው በድንገት አንድ ነገር ተናገረ፡፡ ደግነቱ ምን እንዳለ በትክክል ሳይሰማ ሐኪሙ በር ከፍተው ገቡ::
«የእኔ ልጅ» አሉ፤ «ረጋ በይ! ልጅሽ መጥታለች፡፡»
የፋንቲን ዓይን እንደ ብርሃን በራ:: በደስታ ብዛት መላ ሰውነትዋ
ተቅበጠበጠ፡፡ እጇን በኃይል አሻሸችው::
«ወይ ልጄ! አምጡልኝ ልያት?» ስትል ጠየቀች፡፡
ያኔ እንደተወቻትና እሽሩሩ እንደምትባል ፉልቁ ሕፃን እንደሆነች አድርጋ በመገመት ልታቅፋትና እሽሩሩ ልትላት ፈለገች::
«አትቸኩይ» አሉ ሐኪሙ፤ «ሰውነትሽ እንደዚህ ደክሞ ከእርስዋ ጋር መጫወት አትችይም፡፡ ከልጅሽ ጋር አሁን በድንገት ብትገናኙ ሲቃ
ይዞሽ ክፉ ነገር ላይ ሊጥልሽ ስለሚችል ትንሽ ብትታገሽ፡፡ መጀመሪያ እኛ አንቺን በቅጡ ማዳን አለብን፡፡
መሴይ ማንደላይን ከአልጋው አጠገብ ወንበር ላይ ተቀምጦአል፡፡
ፋንቲን ወደ እርሱ ዞር ብላ «ግሩም ድንቅን ኣለች:: ስታየው መንፈስዋን
በጣም አረጋግታ ስለነበር ምናልባት «አሁንስ ተሽሉአታል፤ ልጅዋን ብታይ ምንም አትሆንም» ብሎ ያስባል ብላ ከእርሱ ጋር ጨዋታ ቀጥላ በጥያቄ
አጣደፈችው::
«ታዲያ መንገዱ ደህና ነበር? እንዴት የተባረኩ ሰው ቢሆኑ ነው
ለልጄ ብለው ከእዚያ ድረስ መልፋትዎ? መቼም እኔን እንኳን ሳትረሳኝ አትቀርም:: ልጆቹ እኮ ቀላል ፍጡሮች አይደሉም:: የለበሰቻቸው ልብሶች ንጽህናቸው የተጠበቀ ነው? እነሚስተርና ሚስስ ቴናድዬ በንጽህና ነበር
የያዝዋት? ሰውነትዋስ እንዴት ነው? እንዴት ነው የናፈቀችኝ! ቆንጆ ልጅ አይደለችም ክቡር ከንቲባ? በጨለማ ስትጓዘ መንገድ ላይ እኮ ብርድ ሳይጉዳችሁ አልቀረም:: አንድ ጊዜ ብቻ እንዳያት ለአንድ አፍታ ልታስጉቡዋት አትችሉም? ወዲያው ትሄዳለች፡፡ የቤቱ ጌታ- እርስዎ ኖት ፤ ታዲያ ይህን
አይፈቅዱልኝም? መሴይ ማንደላይን እጅዋን ያዘ፡፡ «ኮዜት በጣም ቆንጆ ናት» አለ:
“ጤነኛ ናት ፤ አትቆዩም ፤ ታያታላሽ:: አሁን ግን ብዙ አትናገሪ ! ይደክምሻል:: ደግሞም ሳልሽ እንዳይቀሰቀስ አትገለጭ::
እርሱ ይህን እንዳለ በሃይል አሳላት:: እጅዋን እንደያ፤ በጭንቀት ዓይን ተመለከታት:: አባበ የደረሰበትን ሊነግሪ ት ነበር፡፡ ግን በዚህ ሁኔታ እንዴት ብሎ ይንገራት! ሐኪሙ ካያት በኋላ ወጥቶ ሄደ:: ሰርዋ ከክፍሉ ውስጥ አብራቸው ቆዩ:: ሁሉም ዝም፣ ዝም ተባብለው ነበር
ፋንቲን በድንገት ጮኸች::
«ድምፅዋን ሰማሁት፤ ወይኔ ልጄ! ድምፅዋን ሰማሁት!»
በአካባቢው የጎረቤት ልጅ ነበረች፡፡ ያጋጣሚ ነገር ይህች ልጅ፤ብቻዋን እያወራች ትሮጣለች:: ትምህርት ቤት የተማረችውን ዘፈን እያዜመች
ነበር የምትሮጠው:: ፋንቲን የሰማችው የዚህችን ልጅ ድምፅ ነበር፡፡
«ውይ. ይ፧ የእኔይቱ ኮዜት እኮ ናት! ድምፅዋንኮ አውቀዋለሁ
አለች::
የልጅትዋ ድምፅ እየራቀ ሄደ:: ድምፆዋ ቢርቅም ፋንቲን ለመስማት ሞከረች:: ድምፁ ጨርሶ ሲጠፋ ጥላ የተጠለለባት መሰላት፡፡ «ምን የተረገሙ
ሐኪም ናቸው፤ ልጄን እንዳላይ የሚከለክሉኝ» አለች በማጉረምረም።
ሆኖም ውስጥ ውስጧን ደስ ብሎአታል፡፡ ትራስዋን በእጅዋ አቅፋ ይዛ እርስ በራስዋ መነጋገርዋን ቀጠለች፡፡ «እንዴት ደስ ብሎኝ ነው የምኖረው
የአትክልት ቦታ ይኖረኛል፡፡ መሴይ ማንደላይን እንደሚሰጡኝ ቃል ገብተውልኛል፡፡ ልጄ ከሳሩ ላይ እየፈነደቀች ትጫወታለች፡፡ ከዚያ ቁጭ ብለን ደግሞ
«ተረት ተረት» እያልን እንጫወታለን፡፡ ኮዜት ቢራቢሮ ለመያዝ ስትሮጥ እኔ ቁጭ ብዬ አያታለሁ፡፡ ታዲያ ይሄ መቼ ይሆን የሚሆነው?»
በጣቶችዋ መቁጠር ጀመረች:: «አንድ፣ ሁለት፣ ሦስት፣ አራት፡፡
ሰባት ዓመት ይሆናታል ማለት ነው:: ከአምስት ዓመት በኋላ እኮ አንገትዋን መስበር ትጀምራለች:: ያኔማ እህትዋ ናት ነው የምትባለው::»
በአሳብዋ ተገርማ መሳቅ ጀመረች፡፡

👍17
#ገረገራ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#በታደለ_አያሌው
...“ጥሩ” አሁኑኑ ወደ ፊንፊኔ የባህል ሆቴል መሄድ ትችያለሽ: በዚያ ያሉ
የእኛ ሰዎች ሽፋን እንዲሰጡሽ ተነግሮልሻል። ከመግቢያዉ በር ገባ ብሎ (ቀለወ) ብሎ ሰላምታ የሚያቀርብልሽ አስተናጋጅ ተከተዪዉ: አደራሽን ቸኩለሽ ነገር እንዳታበላሺ። ጃሪም አንቺ እዚያ ካየሽ መደንበሩ ነዉ። በፍጹም ሊያይሽ አይገባም”
“ገብቶኛል”
በይ እንግዲህ ልጅ ወልደሽ እስከምንስማት ድረስ፣ ይኼኛዉ
የመጨረሻ ተልእኮሽ ይሆናል”
“እሺ”
“መልካም ዕድል”
“ለማኅበራች!” ብዬ ስልኩን ዘጋሁት፣ ሁልጊዜም ተልእኮ ስንቀበል እንደ አመቺነቱ እንደምናደርገዉ ሁሉ ማተቤን እየጨበጥሁ፡
ባልቻ እንዳለኝ ልክ ከባህል ሆቴሉ የዉጪ በር ገባ እንዳልሁ፣ አንድ
ወጣት አስተናጋጅ መጥቶ ንግሥት እንደሚያገለግል ሰዉ ተሽቆጥቁጦዐበፊቴ እጅ ነሳ ቀጥሎ ምንም ፋታ ሳይሰጠኝ፣ “የባህሎች ሁሉ መታያ
ወደ ሆነዉ ሆቴላችን እንኳንም በደህና መጡልን ቀለዘ እባላለሁ፤
ምሽትዎ እንደ ፈቃድዎ ለማድረግ እጅግ ጓጉቻለሁ” አለኝ፣ ነፍስ
በሚያረካ ፈገግታ እና ትሕትና
“እንኳን ደህና ቆያችሁኝ፣ አመሰግናለሁ ወንድሜ” ስል ፈገግታዉን ተጋራሁት።
“ይከተሉኝ እባክዎ”
“በደስታ” ብዬ ተከተልሁት እንግዳ መቀበያዉ ያለበትን በግራ በኩል
ትቶ ወደ ጀርባ በር መራኝ ትኩረት ላለመሳብ የሚያደርገዉን ጥንቃቄ
ሳይ አደነቅሁት
“በዚች በኩል ይምጡ እባክዎ። የመጡት የባህል ቤት ነዉ: በባህላችን ደግሞ ንግሥት እና ነፍሰ ጡር የፈቃዳቸዉ ልናሟላላቸዉ ግዳችን ነዉ።
እኔ በበኩሌ፣ እርስዎ የሚፈልጉትን ማንኛዉም ነገር ሁሉ ለማሟላት
የማልሰንፍ መሆኔን ይወቁልኝ እመቤቴ”
“እዉቃለሁ: ግን እኮ፣ ለቤታችሁ ያን ያህል እንግዳ አይደለሁም
“አይደል?”
“አዎ አልፎ አልፎ ብቅ እላለሁ”
“ልክ ነዉ፤ አንድ ጊዜ ቤታችንን ያዩ ሁሉ አዘዉትረዉ እንደሚመለሱ እናዉቃለ። ስለ ደበኝነትዎ ሞልቶልን ሽልማት ባናዘጋጅልዎ፣ ቢያንስ
ደህና መስተግዶ ግን ይገባዎታል እንኳስ ንጉሥ ይሁን ንግሥት
በሆድዎ ይዘዉ!”
ለብ ያለ ሳቅ ሳቅሁለት በጀርባ በር ከወጣን በኋላ፣ ትንሽ እንደ ሄድን
በተለየ ክፍያ የተለየ መስተንግዶ የሚሰጥበት ልዩ (VIP) ቤት ይዞኝ ገባ:: የገጠሩን ድባብ ለመፍጠር ይመስላል፣ ክፍሉ ጭልጭል የሚሉ ኹለት ፋኖሶች በግራና በቀኝ በኩል ባለዉ ግድግዳ ላይ ተለኩሰዉበታል፡ ያም ሆኖ ግን በቤቱ ያሉትን ሰዎች ቀርቶ፣ ራሳቸዉን ፋኖሶቹን ለማየት የጅብ
ዓይን ሳይቀር ይፈትናሉ በቤቱ አማካይ የሆነ ቦታ ላይ በተሠራዉ
መድረክ፣ ኹለት ወጣቶች ከዘፋኟ እና ከሙዚቀኞች ጋር እየተናበቡ
ቅልቅል ባህላዊ ጭፈራ እያቀረቡ ናቸዉ፡ እነሱ ብቻ እንደ ልብ ይታያሉ ከእነሱ በቀር ጥላ የሚመስል ነገር ነዉ የሚታየኝ፡፡ በዚያ ላይ የመድረኩ አሸሸ ገዳሜ ድምፅ ስለዋጠዉ፣ ጥላ የሚመስሉት የቤቱ ተስተናጋጆች
የሚያወሩትን አንዱንም መስማት አልቻልሁም
መጀመሪያ እንዲያዉም ትርኢት ለመመልከት ወደ ብሔራዊ ቴአትር አርፍጄ የገባሁ ነበር የመሰለኝ፡ ቴአትር ከተጀመረ በኋላ የመድረኩ መብራት ብቻ ስለሚቀር፣ ቴአትር ቤት አርፍጄ ስገባ መቀመጫ ለማግኘት የማየዉን ፍዳ አስታወሰኝ፡፡
ከበር ጀምሮ ያመጣኝ አስተናጋጅ፣ ወደ ወንበር ባይመራኝ ኖሮ ስደናበር የሆነ ተስተናጋጅ ላይ መከመሬ አይቀርም ነበር፡ ደግነቱ እሱ የቤቱን ዐመል በዳበሳ ያዉቀዋል፡ በመሆኑም እጄን ይዞ እየጎተተ ወሰደኝና ክብ ሠርተዉ ለተቀመጡ ጥላዎች ጀርባዬን እንድሰጥ አድርጎ አስቀመጠኝ።
ጨለማዉን እየለመድሁት ስመጣ ከአጠገቤ ክብ ሠርተዉ ተቀምጠዉ የሚነጋገሩት ሰዎች ጥላ እንደ መድመቅ እያለልኝ መጣ፡፡ በመጠኑም ቢሆን ወገግ አለልኝ፡፡ ጆሮዬን አቁሜ እየተቀባበሉ የሚናገሩትን ማዳመጥ ስጀምር፣ አንደኛዉ በድንገት የጃሪምን ስም ጠርቶ የሠራ አካላቴን አቀለጠብኝ
“ጃሪም ካነሳቸዉ ነጥቦች ላይ” ብሎ ጀመረ፡ ጀርባዬን እንደ ሰጠሁ
በተወዛዋዦቹ ላይ ጥዬ፣ ቁጭ
ብዬ፣ የመድረኩን ትዕይንት እንደሚከታተል ሰዉ ዓይኖቼን
ከተወዛዋዦች ላይ ጥዬ ተናጋሪዎችን ማዳመጡን ተያያዝሁት ጃሪም አነሳቸዉ የተባሉት ነጥቦች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ለመስማት ቸኮልሁ
ጀሪም ካነሳቸዉ ነጥች ላይ ምንም የሚወድቅ ነገ አላገኘሁም: ነገ ዛሬ ሳንል፣ ነገሮችን ማዕከላዊ እና መስመራዊ ማድረግ አለብን ያለበዚያ እንዲህ እያቦጫረቅን ከማደፍረስ ያለፈ የትም ማድረስ አንችልም። አዛዥ ያስፈልገናል። መስመር መያዝ አለብን። ለምንወስዳቸዉ እርምጃዎች ሁሉ ግብ የሚሰጠን አካል ያስፈልገናል ኪሳራዎቻች ዜሮ ማድረስ ባንችልም፣ መቀነስ ግን አያቅተንም ለዚያ ደግሞ ለሁሉም
መግቢያዎቻችን መዉጫ የሚያበጅልን አካል ያስፈልገናል። ሕመም እና ሕልማችንን የሚጋሩን ብዙ እንደሆኑ ባዉቅም፣ ተበታትነን ስለምታገል ጉዟችንን አርዝሞብናል: ስለዚህ በአንድ እዝ ሥር የሚያደርገን አካል
ያስፈልገናል። ያለበዚያ መድረሻችን አንድ ሆኖ ሳለ፣ ባለመተዋወቅ እና የጋራ መሪ በማጣት ብቻ ራሳችን የራሳችን እንቅፋት እየሆንን መቀጠላችን ነዉ: አንድ አካል ያስፈልገናል። ያን አካል ደግሞ አሁኑኑ መሠየም አለብን በበኩሌ ሙሉ ሆነን እስከምንመርጥ ድረስ፣ ጃሪም
ጊዚያዊ አዛዥ ቢሆነን…
“ቆይ ቆይ!” አለች ሌላኛዋ፣ የቀደማትን ተናጋሪ ከአፉ ቀምታ
“ቆይ እንጂ! መጀመሪያ ሐሳቡን እንስማማበት እና ምርጫዉን
እንደርስበታለን” አለ ሌላኛዉም፣ ተቀብሏት “በእርግጥ እንደተባለዉ
ነዉ። እስከ አሁን ግብ አልነበረንም ማለት ሳይሆን፣ የነጠረ ለማድረግ እና
እርስ በእርስ ለመናበብ ግን የተደራጀን መሆን እንዳለብን እኔም አምንበታለሁ”
“ከዚያ በፊት” ሲል ተቀበለ ሌላኛዉ፣ ምን እንደሆነ ያላየሁትን መጠጥ ገርገጭ አድርጎ ተጎንጭቶለት: ጉሮሮዉ ፏፏቴነት አለዉ እንዴ ብያለሁ በልቤ፣ የተጎነጨዉን ሲዉጥ ያወጣዉ ድምፅ አስገርሞኝ፡ “ከዚያ በፊት
ስለ እህቱ አንድ ነገር ማለት የለብንም ወይ?”
እህቱ? ስለ ማን እህት? ስለ ጃሪም እህት፣ ስለ እኔ እንዳይሆን ብቻ!
“እ..ህ..ቴ አይደለችም!” አለ ጃሪም፣ እጅግ በተቆጣ እርጋታ፡ እፍን ባለ ንዴት… “ዉብርስት የሚባል እህት አላውቅም ብያችኋለሁ: እኔ እህት የለኝም! ማንም ሰዉ እህትህ እንዲለኝ አልፈልግም ከዚህ በኋላ::
ማንም!”
“ከልብህ መሆኑን አሳየና”
“ምን አድርጌ ነዉ የማሳይህ በል? አትመና ከፈለግህ! ምን ይላል ይኼ?” አለ ንዴቱ እየተገለጠበት፡ እንዲያዉም ለድብድብ የሚነሱ ነበር
የመሰለኝ፡ “ና ሆዴ ዉስጥ ግባ: ግባና በልቤ ዉስጥ እሷን እህት፣ እናቷ ደግሞ እናቴ ሆና ካገኘኻት ፈልጋታ! ና በላ!”
ከእሱ በኋላ ደፍሮ የተናገረ የለም፡
ረዥም ዝምታ ሆነ፡
“ቀን ነዉ የምጠብቅላት: አንተ እንድታምን ስል ግን የማደርገዉ ነገር የሚኖር እንዳይመስልህ! አንድ የሚያጠራጥር ነገር ስላየሁባት እሱን እያጣራሁ ነዉ: የሆነ ቡድን ከጀርባዋ ያለ ይመስለኛል: ወጣ ወረደ
ከዚህ በኋላ የእናት የአባቴ ቤት ላይ እንዳሻቸዉ እንዲሆኑ
አልፈቅድላቸዉም: አፈር ነዉ የማገባት! አለብሳታለሁ!”
የሆንሁትን አላዉቀዉም፡ ብቻ ግን፣ ጭዉ የሚል ድምፅ ይሰመኛል።

👍42🤔2
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
ሎርድ ማውንት እስቨርንና ባለቤቱ ወይዘሮ ኤማ ከለንዶን ወደ ካሰል ማርሊንግ ሲመለሱ ሳቤላ ቬን ከአዲሱ መኖሪያዋ ከመጣች ዐሥር ቀን ሆኗት ነበር ።ካስል ማርሊንግ የከተማ እንጂ የግንብ ስም እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል የሬይሞንድ ቬን አዲሱ የማውንት እስቨርን ኧርል መኖሪያ ከካስል ማርሊንግ ከተማ አጠገብ ነበር ደርሰውም ሎርድ ማውንት እስቨርን በደስታ †ቀብሎ ሲያነጋግራት የማውንት እስቨርኗ ወይዘሮ ግን እንደ ዐመሏ በንቀትና በኩራት ገጽታ አየቻት የሳቤላ ጉንጮችም ደም መሰሉ ። እያደርም በዚህ ዐይነት የተጀመረው ግንኙነት የሚያበሳጩ የንቀት ንግግሮች የሚያበግኑ ጥቃቅን ድርጊቶች እየተጠራቀሙ ትዕግሥቷን እስከ መጨረሻ ተፈታተኑት " ብቻዋን በምትሆንበት ጊዜ እጆቿን እያፋተገች ወዴትና እንዴት አድርጋ ሌላ መጠጊያ እንደምታገኝ ታወጣና ታወርድ ጀመር።
ኤማ ቬን እየተደነቀችና እየተወደሰች መኖር ትወድ ስለነበር ይኸንኑ ፍላጐቷን የሚያራግቡላትንና የሚያረኩሳትን በዙሪያዋ ሰብሰባ ስትቃበጥና ስትዳራ ለሰውነቷና ለመልካም ስሟ በመጠበብ ረገድ ግድ አልራትም " ድርጊቷና ጠባይዋ
ሁሉ እሷን ከምታህል አገር ያወቃትና ክብር ያላት ወይዘሮ የሚጠበቅ አልነበረም።
የራስ ወዳድነትና የምቀኝነት ምንጭ ነበረች መልከ ቀና ልጅ እግር ሴት እቤቷ ጠርታ አታውቅም " ይኸን ከማድረግስ ክፉ ገላ የያዘውን ወንድ ብትጋብዝ
ትመርጥ ነበር ።
ሳቤላ ቬንም ያንን የመሰለ መልክና ለጋነት ይዛ ለዘለቄታ አብራት ለመኖር መምጣቷን ገና ስትሰማ ያናደዳት ይኸው ዐመሏ ነበር " በገና በዓል እንግዶች መጡባቸወ ከነሱም አብዛኞቹ ወጣት ወንዶች ነበሩ " እነዚያ ሰዎች ስለሚፈጠረው
ስሜት ሳያስቡ አፋቸው እንዳመጣቸው ማን አህሎኝ ከምትለው የቤቱ እመቤት
ይልቅ ወጣቷ ቆንጆ በጣም እንደምትበልጥ ሲናገሩ ባለቤቲቱ ሰማች ። ሕሊናዋን ለመሳት እስክትቃረብ ድረስ ተናደደች ከንዴቷ በስተቀር ሌላውን ሥነ ምግባር ጨርሳ ረሳችው ሳቤላን ለብቻዋ ጠርታ የተጠላች ቀላዋጭ ሳትፈለግ የመጣችባት መሆኗን ነገረቻት " ወትሮውንም ተግዳ እንጂ ወዳ እንዳላስገባቻት እየነገረች ሙልጭ አድርጋ ሰደበቻት " ኧርሉና ባለቤቱ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩዋቸው : አንዱ የብዙ ጊዜ ታማሚ ስለነበር በየካቲት ሞተ ። ፋሲካ እንደዋለ
ወደ ለንደን በመሔድ የነበራቸው ዕቅድም በኀዘኑ ምክንያት ተለውጦ ወደ ግንቦት ተሳበ ሬይሞንድ ቬን በልጁ ሞት ከእናቲቱ የበለጠ አዝኖ ነበር ። ጊዜውን ከፊሉን በዚያን ጊዜ በመታደስ ላይ የነበረውን የማውንት እስቨርንን ዕድሳት በመቆጣጠር ካሳለፈው በኋላ በመጋቢት ወደ ፓሪስ ሔደ ።
ፋሲካ ሚያዝያ ውስጥ ዋለ ። እመቤቲቱ ወደ ለንደን ለመሔድ ተዘጋጅታ ቀን ስትቆጥር አያቷ ሚስዝ ሌቪዞን ፋሲካን አብራት ለመዋል ወደ ካስል ማርሊንግ
እንደምትመጣ ጻፈችላት " አንጀቷ እርር አለ ። እንድትቀር ገልጻ አትጽፍላት ችግር ሆነባት " ባልቴቷን እንዳትመጣባት ለማድረግ በገንዘብ የሚለወጥ ነገር ቢሆን ኖሮ አይከፍሉ ከፍላ ታስቀራት ነበር ነገር ግን የማይሆን ነገር ሆነና ሚስዝ ሌቪ
ዞን ፍራንሲዝ ሌቪዞንን ብቻ አስከትላ የሕማማት ሰኞ ካስል ማርሊንግ ገባች "
ነገሩ ተከድኖ እበሰለ ላይ ላዩ ሰላም እየመስለ እስከ ዓርብ ስቅለት በደህና ሰነበቱ » ካፒቴን ሌቪሰን ዐይኑን ሳቤላ ላይ ጣለ "
የማውንት እስቨርን እመቤት
የካፒቴኑን አዝማሚያ እያየች ልታብድ ተቃረበች በቅናት ተቃጠለች " በፊት መጥቶ የነበረ ጊዜም ሳቤላ ልቡን እንደ ማረከችው አይታ ልታብድ ነበር" ያሁኑ ደግሞ በጣም ባሰ። ይህ Oይኖቹን በሳቤላ ይ የጣለው ስው ፍሬንሲዝ ቪን ባይ ሆን ኖሮ ! ለእመቤት ሳቤላ ከእሱ በቀር ዓለሙ ሁሉ ቢስግድላትና ቢረግፍላት ሚስዝ ቬን ደስታን አትችለወም ነበር።
ምክንያቱም ወጣቱ መኮንን ምንም እንኳን ያክስቷ ልጅ ቢሆንም ክፉኛ ከልቧ ገብቶ ነበር እንዲያውም ሴትዮዋ ገመናዋን ለመሸፈን ባትጠነቀቅ ኖሮ ውርደት
ላይ ትወድቅ ነበር ።
ዓርብ የስቅለት ዕለት ከሰዓት በኋላ ሳቤላ ሕፃኑን ዊልያም ቬንን ይዛ በእግሯ ለመንሽርሸር ወጣች " ካግቴን ሌቪሰንም ከነሱ ጋር ተጨመረና አብሮ ሔደ የራት
ሰዓት ሊደርስ ጥቂት ሲቀረው ተመለሱ ሚስዝ ቬን አያቷን ሚሲስ ሌቪሰንን ከቤት ጥላ ከነሱ ጋር መወት ባለመቻሏ በንዴት ስታር ስትተክን አመሸች ሦስቱም ተያይዘው እንደግቡ የራት ሰዓት ደርሶ ስለ ነበር ሳቤላ ልብስ ለመቀየር ቀጥታ ወደ መኝታ ቤቷ ገባች ልብሷን አውልቃ የመቆያ ቀሚሷን አጥልቃ ተቀመጠችና ማርቨል ጸጉሯን ስትሠራላት ዊሌም መጣ ከጉልበቷ ተደግፎ ሲለፈልፍ መዝጊያው ድንገት ብርግድ ብሎ ተከፈተ እመቤቲቴ ጥልቅ አለች።
ጀየት ነበርሽ ? ” አለቻት በቁጣ እየተንቀጠቀጠች "
ሳቤላ ምልክቱ ገባት።
“ በመስኩና በቁጥቋጦቹ ስንንሸረሸር ቆይተን መጣን " "
· እንዴት ራስሽን እንደዚሀ ከመሰለ ውርደት ትጥያለሽ ? ”
“ የምትይው አልገባኝም ” አለቻት እሷም የልቧ ምት እየጨመረ
“ተይ እንጂ" ቀስ በይ ማርቨል ጸጉሬን እኮ ነጨሺኝ " አለቻት "
“ ከቤቴ መጠጊያ ማግኘትሽ አነሰና ታስደፍሪው ? ሦስት ሰዓት ሙሉ ፍራንሲዝ ሌቪሰን ጋር ተያይዘሽ እንደዚህ ትጠፊያለሽ?ከመጣሽ ጀምሮ ከሱ ጋር ከመዳራት በቀር ምንም ነገር አልሠራሽም ። የገና ጊዜ እንዶሁ ከሱ ጋር እንደ ተቃበጥሽ እንደተዳራሽ አሳለፍሽው "
ዘለፋ ከዚህ የበዛ ቢሆንም ፍሬ ነገሩ ይኸው ነበር " ሳቤላም ከሰዳቢዋ ያላነሰ ንዴት ተናነቃት በተለይም እሷን ሳቤላ ቬንን የታላቁ መኮንን የሎርድ ማውንት እስቨርን ልጅ ባባትም ከኤማ ማወንት እስቨርን የምትበልጠን ከገዛ ገረዴ ከማርቨል ፊት ስለ ሰደበቻት ይቅርታ የሌለው ድፍረት አድርጋ ቆጠረችውና ነገሩ
ጥቂት በሐሳቧ ካገላበጠችው በኋላ ራሷን ስትሠራላት ከነበረችው መንጭቃ ብድግ
አለችና ከቤቱ እመቤት ጋር ተፋጠጠች "
ባለቤቲቱ የንዴቷን ያሀል ስትንጨረጨር ድምጿን ገትታ በትዕግሥትና በዕርጋታ
ስትሰማት ቆየችና “ እኔ አልዳራም ” አለቻት “ተዳርቸም አላውቅም። እንደዚህ ያለውን ሥራ ከባለትዳች ይልቅ ያላገቡ ሴቶች ቢፈጽሙት ጥፋቱ ቀለል ሊል ሊችል ቢመስልም እኔ ለእነሱ ትቸዋለሁ እኔ ከዚህ ከመጣሁ ጀምሮ ሁልጊዜ ስትዳራ የማያት አንዲት ሴት ብቻ ናት " እሷም እኔ ሳልሆን አንቺ ነሽ " '
ኤማ ቬን ፊቷ ልውጥውጥ አለ " የምታደርገው የምትሆነው ጠፋት በእጅዋ አንድ ጊዜ በጥፊ ጉንጯ ላይ አጮለቻት " ድንጋጤዋ ሲለቃት በግራ እጅዋ መታቻት " ሳቤላ እርር ብላ ጮኸችና ራሷን ስትሠራበት ከነበረው ወንበር ላይ ጥቅልል አለች ማርቨል ደነገጠችና እጅዋን ወደላይ ዘረጋች ዊልያምም ሳቤላ ስለተመታች አለቀሰ " ራሱ ተገርፎ ቢሆን ኖሮም ከዚያ የበለጠ አያለቅስም ነበር "
ወይዘሮ ማወንት እስቨርን ልጅዋን በቡጢ አንድ ጊዜ አፍንጫው ላይ ካለችው በኋላ አንገቱን ይዛ ወዶ ውጭ ገፈተረችው " እሷም ወጥታ ሔዶች ሳቤላ ሌሊቱን ሙሉ እንዳለቀሰች አደረች " ከዚያ ቤት ለመኖር አልቻለችም "በዚህ ጭካኔ ሌላ ሰውም ቢሆን ሊኖር አይችልም ግን የት ትድረስ ? እስኪነጋ ድረስ ሙታ ብታርፍና ከአባቷ ጐን ብትቀበር ብዙ ጊዜ ተመኘች መንፈሷ ሲረጋጋ

👍16