አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የተቃጠለ_ልብ
:
#ክፍል_ሰላሳ_አንድ ( #የመጨረሻ_ክፍል )
:
ድርሰት:-በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
:
:
ከአንደኛው መጽሀፍ መሀል ያየቻቸው ሁለት ፎቶዎች ግን ተስፈንጥራ አልጋዋን ለቃ ወለሉ ላይ እንድትቆም አደረጋት…፡፡.ሰውነቷ እየተንቀጠቀጠ ነው..የምታየውን ማመን አልቻለችም..የኮማንዳሩና የወላጅ እናቷ ፎቶ ነው…አንዱ ፎቶ ሁለቱም በዋና ልብስ ሆነው ሙሉ በሙሉ አቅፎት መዋኛ ገንዳ ውስጥ ሆነው የተነሱት ነው…ሌላው ደግሞ ከንፈር ለከንፈር እየተሳሳሙ…… ይሄን ያህል ሄደዋል ብላ አታስብም ነበር ..ስልኮን አነሳችና ደወለች..እሮዝ ጋር ነው..ተነሳ..?
‹‹አሁኑኑ እፈልግሻለው››
‹‹ምነው ልጄ ምን ሆንሺብኝ..?››
‹‹መቀባጠሩን ተይና በአስቸኮይ ኩማደሩ ቤት ነይ››ስልኩን ጠረቀመችው
ሮዝ የለበሰችውን የለሊት ቢጃማ እንኳን ለመቀየር ጊዜ ማባከን አልፈለገችም…ብን ብላ ነው ግቢውን ለቃ ወደኩማንደሩ ቤት የበረረችው ..ልጄን… ልጄን ምን አደረክብኝ....?የሳሎኑን በር በርግዳ ከፈተችና ወደውስጥ ገባች…
‹‹ምን አደረገብኝ ..?ምነ ሆንሺብኝ ..?ተንደርድራ ልትጠመጠምባት ስትል ገፍትራ ከላዬ አራቀቻት….››
‹‹ይሄ የመቼ ፎቶ ነው....?››ሄለን ነች ጠያቂዋ
‹‹የቱ..? እኔጃ..››ግራ ተጋብታ መለሰች
በእጇ የያዘችውን ፎቶ ወረወረችላት .ደረቷ ላይ አርፎ ወደመሬት ወደቀ… ጎንበስ ብላ አነሳችውና ተመለከተችው..
‹‹እሺ መንም አልጀመርንም ብለሽኝ አልነበር..?››ሄለን ነች በሽሙጥ የጠየቀቻት
‹‹ያው ድሮ እኮ ነው…ግን ከተለያየን ብዙ አመት አልፎናል..?››
‹‹በቀደምለታ የመጣሽው እንታረቅ ልትይው ነበር....?››
‹‹አረበፍጽም ..ስንለያይ ተጣልተን ስለነበረ ቂም ይዞብኛል..አንቺን በማጥቃት እንዳይቀለኝ ስለፈራው ከአንቺ እንዲርቅ ልለምነው ነው…››
‹‹ኦኬ አሁን በጣም ገባኝ….ለመሆኑ ኩማደሩን እንደማፈቅረው ታቂያለሽ..?››
‹‹አታደርጊውም ልጄ..እኔ በህይወት እያለው አታደርጊውም››
‹‹አትጠራጠሪ አደርገዋለው..እንደውም ማግባት ሁሉ የምፈልገው እሱን ነው››
‹‹አረ ተይ ልጄ…እራስሽን ወጥመድ ውስጥ ለምን ትከቺያለሽ....?እሱ እኮ ውስጡ በቀል እንጂ ፍቅር የለበትም…..››
እሱ እኔን አይመለከተኝም…እንደውም እኔም አንቺን ለመበቀል ስለምፈልግ ጥሩ አጋጣሚ ነው…ለመሆኑ ምን ያል ብትበድይው ነው .. ..?ለነገሩ አንቺ አይደለሽ ምንም ብታደርጊው አይደንቀኝም….ለማንኛመው ከዛሬ ጀምሮ በመሀከላችን እንዳትገቢ ልነግርሽ ነው..አሁን የድሮ ፎቶሽን ይዘሽ ወጭልኝ…;››
‹‹በፈጠረሽ ልጄ›› እግሯ ላይ ተደፋች..
‹‹ምንም ብታርጊ ሀሳቤን አታስቀይሪኝም…ምን አልባት በአንድ ነገር..››
‹‹ምንድነው ልጄ …የፈለግሽውን ጠይቂኝ..ከዚህ ሰይጣን ራቂለኝ እንጂ ያልሺኝን ሁሉ አደርጋለው››
‹‹ያው የእኔን ጥያቄ ታውቂያለሽ… ተመሳሳይና የማይቀየር ነው…የአባቴን ማንነት ከነገርሺኝ እተወዋለው…››
‹‹አባቴን....?››ከተደፋችበት ተነሳችና መቀመጫ ይዛ ተቀመጠች
‹‹አዎ ንገሪኝ..ከእሱ እንድርቅ ከፈለግሽ ንገሪኝ››
‹‹እሺ ቁጭ በይ….ነግርሻለው››
ሁለቱም ፊት ለፊት ተፋጠው ተቀመጡ
‹‹እንግዲያው ንገሪኝ ካልሽ ምርጫ የለኝም ነግርሻለው….ግን ለምትሰሚው ነገር እራስሽን አዘጋጂ››
‹‹ግድ የለሽም መግቢያውን ተይና ወደዋናው ታሪክ በቀጥታ ግቢልኝ››
‹‹ይሄውልሽ ልጄ ግማሽ ዕድሜዬን ይሄንን ታሪክ ለሌላ ሰው ይቅርና ለእኔው ለእራሴው ለመናገር ስሸሸው የኖርኩትን ነገር ነው፡፡ይሄው ዛሬ ሳልወድ በግድ ለመናገር ተገድጄያለው፡፡እስከዛሬ ነገሩን ሚስጥር አድርጌው የኖርኩት ለእናቴ ስል ነበር..አሁን ደግሞ ለመናገር የተገደድኩት ለአንቺ ለልጄ ስል ነው..ከእናቴ ስሜትና ደህንነት ይልቅ የልጄን ስሜት እና ደህንነት አስቀድሜ ነው..መቼስ አናቴ ልጅ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ስለምታውቅ ይቅር ትለኛለች ብዬ አስባለው፡፡
ማንኛውም የሰው ልጅ በትዝታ ፈረስ ፊቱን ወደ ኃላው አዙሮ ትናንትናውን ሲያይ መዝለል የሚፈልገው ወይም አለማሰብ የሚመኘው ወይም ምነው ባልኖርኩት ኖሮ ብሎ የሚጠየፈው በጊዜዎች ክፍተት መሀከል የተከወነ ጨለማ ታሪክ ይኖረዋል፡፡የእኔን የተለየ የሚያደርገው ግን ያለፈ ህይወቴ ውስጥ የተከሰተው ጠባሳ አይደለም መሰረዝ እንዲደበዝዝ ማድረግ እንኳን የማይቻል ስለሆነ ዕድለኛ አይደለውም፡፡
ልጄ አንቺ ለእኔ ማለት የበደሌ ምልክት፤ የክስረቴ ትርፍ ነሽ፡፡ሰው ህይወቱን የሚያሳጣው …ማንነትን የሚያወድመው ነገር ከስሮ በዛው ልክ ህይወቱን የሚያለመልምለት እና ለመኖሩ ምክንያት የሆነ ነገር ያተርፋል…እኔ ማለት እንዲያ ነኝ..የነገ ተስፋዬን፤ለመኖር የሚረዳኝን ሞራሌን፤ማንነቴን አጥቼ በምትኩ ግን አንቺን አገኘው፡፡
‹‹አረ የምትይው ነገር ምንም እየገባኝ አይደለም…››መለሰችላት ሄለን
‹‹የእኔ ህይወት ለእኔም ለእራሴ ብዙ ጊዜ አይገባኝም፡፡ግን ቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ልግባ፡፡አንቺን የወለድኩሽ ተደፍሬ ነው፡፡መቼ? ገና 15 ዓመት ሳይሞላኝ፡፡ማን የደፈረኝ ይመስልሻል..?የምትወጂው አጓቴ ነው፡፡ላስተምርሽ ብሎ ከእናቴ በአደራ ተቀብሎ አዲሳባ ወስዶ ደፈረኝ ..አስረገዘኝ …››
‹አጎቴ!!!!.. አጎቴ ማለት የማዬ ወንድም … አንቺን››
‹‹አዎ አጎቴ እኔን …ያ ማለት ደግሞ አንቺ የእሱ ልጅ ነሽ… አባትሽ ነው፡፡
‹‹እኔ አላምንም…››ሄለን ምትሆነው ምትናገረው ነገር ጠፋት
‹‹ልጄ ነፍስ ካወቅሽበት ጊዜ አንስቶ አባቴ ማን ነው ?ብለሽ ስትጠይቂኝ..የተለያየ ሰበብ እየፈጠርኩ ልነግርሽ ያልቻልኩት ነገሩ ለሰሚውም ግራ ሰለሆነብኝ ነው፡፡ ልጄ እስቲ አስቢው በገዛ አጐቴ ተደፍሬ አንቺን እንደወለድኩሽ ስትሰሚ በአንቺ ሰነ-ልቦና ላይ የሚያደርሰውን መረበሽና ተፅዕኖ በምን ማረጋገጥ እችላለው? እንደእኔ ስብርብር ብትይብኝስ.?.ከሁሉም በላይ ደግሞ ይሄ ጉዳይ እናቴ ጆሮ ይሄ ዜና ቢደርስስ ?የገዛ መንትያ ወንድሟ ከመሀጸኖ ፈልቅቃ አምጣ የወለደቻትን እና አደራ አሳድግልኝ ብላ ያስረከበቻትን ጨቅላ ልጆን በድልዱም ቢላዎ ገዝግዞ እንዳረዳት እና ህይወቷን እንዳበከተባት ብትረዳ በድንጋጤ ህይወቷ ባያልፍ እንኳን ጨርቋን ጥላ ማበዶ ይቀራል ብለሽ ታስቢያለሽ…?.ለዚህ ነው ከአንቺ ጋር ስጋጭ እና ስጣላ የኖርኩት፡፡ ለዚህ ነው እራሴን እንደ ጥፋጠኛ አስቆጥሬ ስባልግ እና ስንዘላዘል በገዛ ስህተቴ እደወለድኩሽ እዲታሰብ አድርጌ ግማሽ ዕድሜዬን እንደጋጠወጥ እና እንደ አለሌ ሸርሙጣ እየታሰብኩ በመኖር እራሴን ያሰቃየውት...እርግጥ አልዋሽም ሸርሙጣ የሚለው ስም አይገባኝም አልልሽም..በደንብ ይገባኛል..፡፡ግን በሽታ ሆኖብኝ ነው፡፡ከመደፈሬ ጋር የተፀናወተኝ እኔ እራሴ የምጠየፈው እና የምፀፀትበት ክፉ በሽታዬ ነው፡፡
ልጄ እንግዲህ እውነቱ ይሄ ነው፡፡አባትሽ የምትወጂው አጐትሽ ነው..ከአሁን ቡኃላስ እሱን መውደድሽን ትቀጥያለሽ…?እንግዲህ እሱ የአንቺ ጉዳይ ነው፡፡እኔን ግን ካጠፋውት በላይ ስቀጣ የኖርኩ ሚስኪን እናት ነኝና እባክሽ ይቅር በይኝ እና ቀሪ ህይወቴን ትንሽም ቢሆን ተስፋ እንዲኖራት እርጂኝ፡፡ከእዚህ ሰውዬ ራቂ..እሱን በጣም በድዬዋለው….ሊያገባኝ ሲዘጋጅ ነው ጥዬው ወደአዲስ አበባ የገባውት ..ስለዚህ ለአመታት ሊበቀልኝ ሲጥር እደነበረ አውቃለው..እና ልጄ ….
…ሄለን ከተቀመጠችበት ተነስታ ተንደርድራ ነው እግሯ ላይ የተደፋችባት….‹‹እማዬ የምትችይ ከሆነ ይቅር በይኝ..ባክሽ ይቅር በይኝ››እየነፈረቀች ተማፀነቻት
ሮዝ ከገባችበት መደንዘዝ ውስጥ እንደምንም ነቃችና እሷም ተከትላት ቁጢጥ በማለት ልጆን ከተደፋችበት አንስታት አቀፈቻት… አገላብጣ ሳመቻት ‹‹ልጄ ….ልጄ
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#በክፍለማርያም

...ያንቺ ነዉ ሲል አፋጠጣት
ቤዛዊት አንዴ ፍፁምን አንዴ አባቷን አፈራርቃ እያየች
የተረገመ ፍቃዱን በዉስጧ እየረገመች መሬት ላይ የወደቀዉን
ጡት ማስያዣ አንስታ እና ንዴቷ እየተቀሰቀሰ አይኗን
እያጉረጠረጠች
"ያንተ ነዉ ልስጥህ ...አንተ ሴታሴት ወረኛ" ጥፍሮቿን አሹላ ወደ ፍቃዱ ተጠጋችዉ
ፍቃዱ አዋረድኳቸዉ ብሎ መዋረዱ እየታየዉ አመጣጧ እያስፈራዉ ወደ አባቷ ቀስ እያለ መጠጋት ጀመረ
"አረ ተረጋጊ ሴትዮ"
አፉ ላይ የመጣለትን ቃል እያወራ
ፍፁም ለመገላገልም አልተነሳም አልጋዉ ጠርዝ ላይ ተቀምጦ
የጥፋተኝነት እና ደግ አረኩ በሚል ሁለት የተቃረኑ ሀሳቦች
ተዉጦ ከሀሳቡ ያነቃዉ ብርጭቆ ከግድግዳ ጋር ሲጋጭ
የሚያሰማዉ ድምፅ ነበር
"ኳኳ ከሽሽሽሽሽ"
ፍቃዱ በሩን በርግዶ እየተንደፋደፈ ወጣ አባቷ በድንጋጤ ተዉጠዉ አንገታቸዉን አቀርቅረዉ እና ፍጥርጣሪዉን ፈርተዉ።

አይናቸዉን ጨፍነዉ ቆይተዉ
ልጃቸዉን በልመና አስተያየት እያዩዋት
"ተረጋጊ ልጄ በቃ"
እያሉ መለመን ጀመሩ መታመሟ እየመሰላቸዉ እየፈሩ
በንዴት የጦፈችዉ ቤዛዊት የወረወረችዉ ብርጭቆ
ፍቃዱን ስላላገኘዉ እና እልኋ ስላሎወጣላት ግላ
"ሁለተኛ ይሄን የተረገመ ሰዉ ማየት አልፈልግም"
እጆቿ እየተንቀጠቀጡ እና የታችኛዉን
ከንፈሯን ወደ አፍዋ ዉስጥ ስባ በጥርሶቿ ነክሳ።
በትክክለኛዉ ስዓት አንዳንዴ ጥፋትን ለመሸፈን ሌላ ጥፋት
ማጥፋት የመጀመርያዉ ጥፋትን ያደበዝዝልናል
ሰዓቱን ካልጠበቀ ደሞ በሁለት ስህተት ቅጣት ያስጠይቀናል
መልካም ነገርም እንደዚህ ነዉ በትክክለኛዉ ስዓት
ጥሩ ነገር ላይ ሌላ ጥሩ ነገር ማስራት እና ድጋሜ ጥሩ ማሰብ
የመጀመርያ ደስታችንን አስረስቶ ወደ እጥፍ ድርብ ወደ ሆነ ደስታ ዉስጥ ይከተናል።

አባቷ ልጃቸዉ ቤዛዊትን እየለመኗት ይዘዋት እየወጡ ነዉ
ዞራ ፍፁምን ተመለከተችዉ ምን ማረግ ይችላል ከአባቷ ነጥቆ ማስቀረት አይችል እየከፋዉ እና እያዘነ ለመሰናበት
እጆቹን አየር ላይ አነሳ እስዋም በአይኖቿ እንባ እየቀረሩ እያየችዉ
አባቷ አቅፈዉ እንደያዟት ወደ ዉጪ ወጣች የቤዛዊት አባት እግሬ
አዉጭን ብሎ የሮጠዉን ፍቃዱን በአይናቸዉ እየፈለጉት ነበር
ቤዛዊት የአባቷ መኪና ዉስጥ ገብታ ስትቀመጥ ወረቀት እና
እስኪርቢቶ ስላገኘች ፊቷ ፈገግ እያለ የሆነ ነገር ሞነጫጭራ ፅፋ
ኪሷ ዉስጥ አባቷ እንዳያዩዋት ከከተተች በኋላ
"የረሳሁት እቃ አለ መጣሁ.."
አባቷን ብላቸዉ ከመኪናዉ ወርዳ ወደ ፍፁም ቤት መሮጥ ጀመረች።

ፍፁም ቤዛዊት እንደወጣች ብቸኝነት ቀንድ አዉጥቶ መልክ ኖሮት
ሰፈረበት ከፋዉ
ወራቶች እያለፉ ስለሆነ በዚህ ወቅት የትም ትምህርት ቤት
ተቀጥሮ ማስተማር እንደማይችል ሲያስበዉ ከአልጋ ወደ አልጋ
ቦታ እየቀያየረ እየመሰለዉ አዘነ
ቤዛዊትም የእሱ ትሁን አትሁን ግራ በገባዉ ሁኔታ ስትታመም
ሲሻላት አብሯት ከጎኗ እንዳይሆን መሰናክል ሲበዛበት
ይባስ ብለዉ ቤተሰቦቿ ጣልቃ እየገቡ እረፍት እና ደስታ ስለነሱት
ተስፋ ወደ መቁረጥ እየሄደ እየተጨነቀ ሲያስብ በሩ ተበርግዶ
ተከፍቶ ቤዛዊት እየፈጠነች ገብታ ሀይሏን በሙሉ ትከሻዉ ላይ
ጥላበት ካቀፈችዉ በኋላ እና ከንፈሩን በፍጥነት ለኮፍ አርጋ
ስማዉ እንደለመደችዉ ከኪሷ የተጣጠፈ ወረቀት አዉጥታ
ሰጥታዉ በገባችበት እየፈጠነች ወጣች።
ከወጣች በኋላ ወረቀቱን ገልጦ አነበበዉ የቦታ ስም ተፅፎበታል
አቅጣጫዉን እና ነገ ሶስት ሰአት እንገናኝ ይላል
አንብቦት ሲጨርስ ደስ እያለዉ በጀርባዉ ጋደም አለ።

ቤዛዊት ቤቷ ስትደርስ መሳቅ መጫወት አበዛች ቤተሰቦቿ
ደስ እያላቸዉ መሽቷ ለእንቅልፍ ወደየአልጋቸዉ ተለያዩ
እስዋ ግን ስለነገዉ እያብሰለሰለች የባንክ ደብተሯን ኪሶ ዉስጥ
ከትታዉ በለበሰችዉ ሱሪ አልጋዋ ላይ ወጣች።

ነፋሻማ አየር ከአዲስ አበባ ወደ ክፍለ ሀገር መዉጫ መስመር
በአካባቢዉ የበቀሉት ዛፎች በንፋስ ይወዛወዛሉ ዛፎቹ ላይ ያሉት
የወፍ ዝርያወች ቢንጫጩም ዜማ አላቸዉ
እማማ ስንቅነሽ ቤዛዊትን በራቸዉ ላይ ቆማ ሲያገኟት
የሞተች ልጃቸዉ መቃብር ፈንቅላ እንደወጣች ተደስተዉ እያዩዋት
"ልጄ ልጄ የምትመጪ አልመሰለኝም
የኔ የዋህ የኔ ምስኪን"
እያሉ አቀፏት

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ (የመጨረሻ ክፍል)


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

#ድህረ_ታሪክ

አራት አመት አለፈኝ፡፡ የህክምና ክትትል አደርጋለሁ፡፡ እድሜ ለነ ሃብትሽ፣ አደራ የሰጠኋቸውን የዶሮ እርባታ በቅንነትና በታማኝነት ሰርተው ከነ ፍሬው ጠበቁኝ፡፡ መልሼ ለመቋቋም በቃሁኝ፡፡ ለዶክተር
ለህክምናዬ ያወጣውን ግማሹን ቢሸፍን እንኳ ብዬ የተወሰነ ገንዘብ ላኩለት፡፡ አሁን ውስጤ በጣም የተረጋጋ ስሜት ይሰማኛል። የግል ስራዬን አስፋፍቼ ንሮዬን አዲስ አበባ አድርጌያለሁ፡፡ ነገሮች እንደበፊቱ ቶሎ አይረብሹኝም እንደውም፣ አሁን የሰዎችን ህመም አዳማጭና
መካሪ ሆኛለሁ፡፡ አንዳንዴማ፣ እንደ ዶክተርም ሊቃጣኝ ይሞክራል፡፡ሰዎች
በማይረባው ነገር ተረብሸው፣
ስራቸውን መስራት እስኪያቅታቸው፣ የማትረባዋን ነገር አግዝፈው ሲያኝኩ፣ ሲያብሰለስሉ ሳይ፣ ሰዎች ሁሉ ተደራጅተው ሊያጠቁኝ ነው ብለው እያሰቡ ሲጨነቁ ሳይ፣ ወደራሳቸው ማየት ሲያቅታቸው፣ ወላፈኑ እየለበለባቸዉ
ሲመስለኝ፣ ከነበልባሉ፣ ከእረመጡ ውስጥ ገብተው ሳይቃጠሉ፣ መፍትሄ
እንዲያገኙ ሃኪም እንዲያማክሩ እመክራለሁ፡፡

አሁን ዐይኔ በርቶልኛል፡፡ በአጠገቤና በአካባቢዬ በጣም ብዙ ሰዎች ላይ ምልክቱን አያለሁ፡፡ በተቻለኝ መጠን ልረዳቸው አዳምጣቸዋለሁ፡፡ አሁን ግን፣ ይሄ ብቻ በቂ እንዳልሆነ እየተሰማኝ ነው።
ቁጭ ብዬ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እያሰላስልኩ ነው፡፡ ከጎረቤት የተከፈተው የዳንኤል አምደሚካኤል መዝሙር ይሰማኛል፡፡ አብሬ ማንጎራጎር ጀመርኩ፡፡

“ዐይኔ በርቶልኛል፣ ሁሉን አይቻለሁ፡፡

ከዚህ የበለጠ ምን እፈልጋለሁ..::

እናገራለሁኝ...፣ አልታክትም ሁሌ..
.
ስለዚህ ሳወራ..አ..ሃ..ሃ፣ ከቶ አልደክምም እኔ።”

ከዶ/ር ሄኖክ ጋር እየተደዋወልን እንጠያየቃለን፡፡ በእድሜም ስለምንቀራረብ ነው መሰለኝ፣ ግንኙነታችን ጠብቋል፡፡ ከሳምንት በፊት፣
ደውሎልኝ ወደ አዲስ አበባ እንደተዘዋወረና ሊመጣ እንደሆነ ሲነግረኝ በጣም ደስ አለኝ፡፡ ውለታው የሚመለስ ባይሆንም፣ ለሱ ያለኝን ክብርና ፍቅር የምገልጥበት አጋጣሚ እንዳገኘሁ ተሰማኝ፡፡ ሲመጣ እኔ ጋር
እንዲያርፍ ተቀበልኩት፡፡ ተከራይቼ ምኖርበት፣ ሳር ቤት መቻሬ ኮንዶሚኒየም ወሰድኩት::


“ዶክ ተዋወቃት ባለቤቴ ናት፡፡”

“እንኳን ደህና መጣህ፡፡ ግባ፡፡ ማሂ እባላለሁ፡፡” አለችው ባለቤቴ
እየጨበጠችው፡፡

“እንኳን ደህና ቆየሽኝ፡፡ ሄኖክ፡፡ እንዴት ነሽ?"

“ዶክ ይህንንም ጎረምሳ ተዋወቀው፡፡ ልጄ ነው፡፡”

‹‹እንዴ! ከመቼው ይሄን አደረስክ?” ልጄን እየሳመው በመገረም ጠየቀኝ፡፡

ሁሌም ከአምናችን ይዘን ምንሻገረው ጥሩም መጥፎም ነገር ይኖራል፡፡ አንድ ጥሩ ነገር ቤቢ ነው፡፡ ይህ ትልቅ የፊቴ ጠባሳ ደግሞ ሌላው፡፡” ማሂ በፈገግታ ታስተናግደናለች፡፡

ዶክተርን ከማሂ ጋር ሆነን በምንችለው አቅም በደንብ አስተናገድነው፡፡ በህይወቴ ባሳየሁት ለውጥ በጣም ደስተኛ እንደሆነ
ደጋግሞ ነገረኝ፡፡ ለሳምንት የራሱን ቤት እስኪያመቻች ከኛ ጋር ቆየ፡፡ደስ የሚል ግዜን አሳለፍን፡፡ ቤት አፈላለኩለት፣ እቃዎችን አጋዛሁት፣ባገኘሁት አጋጣሚ ያለኝን ፍቅርና ክብር ለማሳየት ሞከርኩ፡፡ ያለኝን ትርፍ ሰዓት አብረን እናሳልፋለን፡፡ ወክ እናደርጋለን፣ ሃሳብ እንለዋወጣለን፡፡ ነገ ወደ ተከራየው አዲሱ ቤት ይገባል፡፡ ዛሬ የሰፈራችንን የመጨረሻውን ወክ ልናደርግ ወጣን፡፡

“ያቤዝ...”

“ወዬ ዶክ፡፡”

“ሰሞኑን አንተ ላይ ባየኋቸው ለውጦች ምን ያህል ደስተኛ እንደሆንኩ ስነግርህ ቆይቻለው፡፡ ዛሬ ግን፣ እንደ አዲስ ሙሉ የህይወት ታሪክህን እንድትነግረኝ እፈልጋለሁ።”

“ማለት? አልገባኝም ዶክ፡፡”

“በቃ ህይወትህን፣ ከልጅነትህ ጀምረህ እንድትተርክልኝ እፈልጋለሁ።”

“እንዴ! ለምን?”

“ለምን እንደሆነ ባላውቅም፣ ካየሁህ፣ ካገኘሁህ ቀን ጀምሮ ስላንተ በጥልቀት ማወቅ ፈልጌያለሁ፡፡ ስላንተ ብዙ አስባለሁ፤ እገምታለሁ፡፡ እስከዛሬ ግዜው እንዳልነበር ይሰማኝ ነበር፡፡ ሰሞኑን ግን፣
ከመቼውም ግዜ በላይ ደስተኛና የተረጋጋህ እንደሆንክ አይቻለው፡፡
ስለዚህ ብትነግረኝና ብሰማኸ ደስ ይለኛል፡፡

“ዶክ፣ አንተን ይህን ያህል ካስደሰትህ፣ እንኳን ይሄን ሌላም
አደርግልሃለው፡፡ መቼም ከፍዬው ማልጨርሰው ውለታህ አለብኝ፡፡”

“ኧረ በፍፁም! እንደዛ ሁለተኛ እንዳትለኝ፡፡ እኔ ምንም አላደረኩልህም፡፡ አንተ ጎበዝና ጠንክራ ሰው ስለሆንክ ነው፡፡”

“እሺ እንዳልክ፡፡ ብቻ ግን ውለታህን ለመመለስ ያብቃኝ፡፡”

“አሁን የጠየኩህን፣ ታሪክህን ንገረኝ፡፡”

“እሺ! ያቤዝ እባላለሁ፡፡ ሰላሳ ስምንት አመቴ ነው። በልጅነቴ ዝምተኛም፣ አስቸጋሪም ልጅ ነበርኩ፡፡ ደግሞም ጎበዝ ተማሪ፡፡.” ከመቻሬ ኮንዶሚኒየም ወጥተን የጦር ሀይሎች አጥርን ታከን ቁልቁል
የካርል አደባባይን እየወረድን ነው፡፡ ዶ/ር ሄኖክ ዝም ብሎ ያዳምጠኛል፡፡ገብርኤልን አልፈን፣ በቶታል ማዞሪያ ቁልቁል ወደ መካኒሳ እየወረድን፣ከልጅነት እስከ ዩኒቨርስቲ፣ ከመመረቅ እስከ ከፍተኛ ሀላፊነት፣ ደስታና ሃዘን መውጣትና መውረዶች፣ ከእሱ ጋር እስከተዋወቅንበት ያለውን የማስታውሰውን ያህል ነገርኩት፡፡ በየመሀሉ የሚሰማኝን የጥፋተኝነትና
የቁጭት ስሜቶች ከፊቴ እንዳያነብብኝ፣ ቀና ብዬ ሳላየው በተመስጦ ተረኩለት፡፡ ስጨርስ ዝም አልኩኝ፡፡

“እንዙር፡፡” አለኝ፡፡ እርቀን ሄደናል፡፡ እሺ ሳልለው ዝም ብዬ ዞረኩኝ፡፡ ምንም እያወራ አይደለም፡፡

“በቃ ይኸው ነው፡፡ ከዛ ህይወቴን አንተ ቀጠልከው:: አሁን ደስተኛ ነኝ፡፡ ቀድሜ ህክምና ብጀምር ብዙ ጉዳቶቼን ማስቀረት እችል ነበር፡፡ ግን፣ ባለፈ ክረምት ቤት አይሰራም፡፡ እንዴት እንደምመልስው ባላውቅም፣ ውለታህ በህይወት ዘመኔ ሁሉ አልረሳውም፡፡”

“የምን ውለታ ነው ምትለው ያቤዝ፣ መልስህ እንዲህ ደስተኛና ስኬታማ ሆነህ በማየቴ ብቻ፣ በምንም ከፍዬ ማላገኘው ደስታ ነው::ታሪክህ ደግሞ ከጠበኩት በላይ ይገርማል፡፡ መፅሀፍ እየተረክልኝ
እስኪመስለኝ፣ ተመስጬ ነበር ያዳመጥኩህ፡፡”

“እንዴት..?”

“በህይወትህ የባይፖላር ምልክቶችን በተደጋጋሚና በተለያየ ጊዜ ተፈራርቀውብሃል፡፡በማህበረሰባችን የስነ አዕምሮ የግንዛቤ እጥረት ሰፊ ስለሆነ እንጂ፣ ይሄን ሁሉ ቀውስ ሳታሳልፍ በቀላሉ መቆጣጠር ይቻል ነበር፤” ብሎ ትክዝ አለ፡፡

“እውነትህን ነው፡፡ አሁን፣ እኔም የቀድሞ እኔን ካሁኑ ጋር ሳነፃፅረው እንደዛ ይሰማኛል፡፡ ግን ምን ማድረግ ይቻላል፡፡ ለበጎ ነው ብሎ ከማለፍ ውጪ፡፡”

“ማድረግማ መቻል አለብን፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣በሃገራችን ከአራት ሰዎች አንዱ የሆነ አይነት የአዕምሮ ችግር አለበት፡፡በዚህ ሰዐት እንዳንተ ብዙ ሴ ሰዎች፣ በስራቸው፣ በማህበራዊ ህይወታቸው ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው፡፡ ባለው የመረጃ እጥረትና የተዛባ አመለካከት፣ ብዙ ሰዎች ችግሩ እንዳለባቸው አይገነዘቡም፣ ችግሩም ህክምና እንዳለው አያውቁም፣ ማህበረሰባችን በዚህ ጉዳይ ሃኪም ማናገር ይፈራል፡፡ በዚህ ምክንያት ስንቶች፣ ከሚገባቸው ስኬት በታች ሆነው፣መድረስ ካለባቸው ከፍታ በታች ወርደው፣ በሚገፉት ህይወት
የሚሰማቸውን ቁጭትና ህመም ሳይ፣ ማድረግ ያለብኝን እያደረኩ እንዳልሆነ ይሰማኛል። በጣም አዝናለሁ፡፡ የችግሩን መጠንና ስፋት ስመለከት ደግሞ፣ ነብሴን ትጨነቃለች። የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለብኝ ይሰማኛል፤” አለኝ አሁንም በትካዜ ውስጥ ሆኖ፡፡ እነዛ አስጨናቂና አስፈሪ፣ ላቆማቸው የማልችላቸው የባዶነት፣የተስፋ ቢስነት፣ ሀሳቦች ትዝ አሉኝ፡፡ አሁን የሉም፡፡ ጠፍተዋል።
ውስጤ ስላምና የተረጋጋ ነው፡፡ አሁን፣ ለእኔ አለም ጨለማ
👍2🥰2🔥1
#ሰመመን


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ድርሰት_በሲሳይ_ንጉሱ

በሩ ላይ ያለው ግርግር ሳያብዱ ያሳብዳል ። ቂቅ ብሎ ሙሉ ሱፍ ከነከረባቱ የለበሰ ሰውዬ በሌሎች ሰዎች ክንዶቹን ተይዞ እየጮኽና እየተሳደበ ይገባል ። ማንን እንደሚሳደብ እይታወቅም ፤ ብቻ ይሳደባል ያነበንባል እንደ ሕፃን የሚቦርቁ • ዕርቃናቸውን የሚንፏቀቁ ና የሚዘባርቁ እንደ ምሁር የሚፈላሰፉ በያይነቱ የተለያዩ ሰዎች ከውስጥ ብቅ እያሉ ሲጋራና ፍራንክ ይለምናሉ ። ዘበኛው እንዴ እንባርቆ ወደ ውስጥ ይወድሳቸዋል ። እነሱ ሳይ
ሲጮህ " ዘበኛው ራሱ ያበደ ይመስላል ። ያስደነግጣል ።

“ እዚሁ ይውረድ ወይስ ወደ ውስጥ ይግባ ? ” አለ አቤልን ያመጣው ሹፌር ፡ መኪናውን በሩ ላይ አቁሞ ።

“ እ ምንም አይል እዚሁ ይውረድ ” አለ አብሯቸው የመጣው አንድ የዩኒቨርስቲው የማኅበራዊ ሥራ ክፍል ባልደረባ ።

መኪናውን ውጭ አቁመዉ አቤልን
ግራና ቀኝ ደግፈው ወደ ዕብዶቹ ሐኪም ቤት ገቡ ።

“ እረ እባካችሁ ልቀቁኝ ፡ እኔ “ ኮ ደኅና ነኝ ” አላችው አቤል ፍጹም ጤናማ በሆነ ድምፅ።

እርስ በርሳቸው ተያይተው ዝም አሉት ።
“ ይልቅ እጄን ፍቱኝ ። አታሥቁብኝ ።
“ እሺ ቆይ ደርሰናል ፤እንፈታሃለን ” አሉት

አቤል እጁን ታስሮ ወደ ዕብዶች ሐኪም ቤት እንዲመጣ ያደረገው ነግር ምን እንደሆን በውል አያውቅም ።ከሚስተር ሆርስ ጋር ከተናነቁ በኋላ • እየጮኸና እየተንፈራገጠ አስቸግሯቸው ነው እጆቹን ያሰሩት ። በስሜቱ ሚስተር ሆርስ ትእግስትን ይዟት ሲሄድ የተሰበሰበው ሰው ሁሉ ያገዘው መስሎት ነበር የጮህው ሆኖም” ድርጊቴ ከተመስጦ
የመነጨ የቅዠት ያህል እንጂ የጸና ቀውስነት አልነበረም።አሁንም በጣጋ ደኅና ነው ። ጌና በመኪና ግማሽ መንገድ ሳይጓዙ ራሱ አውቆ ፥ “ አሁን ደኅና ነኝ ፣ ወደ ካምፓስ መልሱኝና ከፈለጋችሁ ልጁን ይቅርታ ልለምነው ” ብሎአቸው
ነበር ። ነግር ግን ሊያምኑት አልቻሉም ።

ከምዝገባው ክፍል ሲደርሱ ሰንሰለቱ ተፈትቶለት አስፈላጊውን ፎርማሊቲ እንዲያስሞላ ተጠየቀ ። ስሙን ዕድሜውንና አድራሻውን በትክክል ተናገረ ይዘውት የመጡት የዩኒቨርስቲ ሰይራተኛ ጤናማ መሆኑን ቢገምቱም። ሳያስመ
ረምሩት ለመመለስ ኣልደፈሩም ።

“ተራውን ጠብቆ ወደ ሐኪሙ ዘንድ ቀረበ ገና የሐኪሙን ፊት ሲመለከት፡እዕምሮው ውስጥ የማያጣበት ነገር የኤሌክትሪክ ሾክ ነበር ሰዎች አዕምሮአችውኝ ታመው
ወደ አማኑኤል ሆስፒታል ሲገቡነ ጭንቅላታቸውን በኤሌክትሪክ ጠዝጥዘው ያደነዝዟቸዋል ፤ ኤሌክትሪኩ ደሞ ኃይለኛ ነው ሲባል ይሰማ ነበር ። ይህን የኤሌክትሪክ ሾክ የሚጠቀሙት ለምን ዐይነት የዕብደት ደረጁ እንደሆን ጠንቅቆ ስለማያውቅ " በእሱም ላይ የሚጠቀሙበት መስሎት ፈራ ።
ሐኪሙ አጠገብ ያን አይነት የሚያስፈራ ግዙፍ መሳሪያ የለም ። ይልቅ አቤል “ ማሰቃያ ነች ” ብሎ የፈራት ከዚሁ ከሐኪም ክፍል ጋር የተያያዘችውን ጓዳ ነው ። ከሐኪሙ ፊት ቁጭ እንዳለ በዐይኑ እየሰረቀ ጓዳዋ ውስጥ ያለውን ነገር ለማየት ይሞክር ነበር።

ሐኪሙ ራሱ አንድ ሐሙስ የቀረው ሕመምተኛ ይመስላል ። የታወቀ ሳይካቲሪስት ነው ። የለበሰው ነጭ የሥራ
ካቦርት እንደ ኽብዛኛዎቹ ሐኪሞች ክብደት አልሰጠውም ።ተራ የጤና ረዳት አስመስሎታል ። በየዕለቱ ከሚቀርበለት
በርካታ ታካሚዎች የሚሰማው የተዘበራረቀ የችግር ዐይነት ወስፋቱን እየዘጋው ከእህል የተራራቀ ይመስላል ። ሺ ቀውስ ማነጋጎሩ ራሱ አያስቀውስም ? በየቦታው ፡ በየጎሬው ስንት ዐይነት መሥዋዕትነት የሚከፈልበት ሥራ አለ ! እንኳንስ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ችግር የአንድን ሰው ችግር ስቃይ መስማት ያስጠላል ። መንፈስን ይረብሻል ። ችግሩ
በሕያውነት ስሜት ተላልፎ ያቃጥላል ። አቤል ይህን ሲያስብ ለሐኪሙ ከልብ አዘነለት ።

ሐኪሙ የማንበቢያ መነጽሩን አውልቆ ከጠረጴዛው ላይ ቁጭ ሲያደርግ ፡ ትናንሽ ዐይኖቹ ከጉድጓዶቻቸው
ውስጥ ብቅ ብቅ አሉ ።

አቤል በሐሳቡ ዮናታን ትዝ አሉት ። ዕብዶቹ ሐኪም ቤት መድረሱን ቢሰሙ ምን ይሉ ይሆን ?

ሐሳቡን ለመቀጠል ሐኪሙ ጊዜ አልሰጠውም
“ እሺ ፥ ስምህ ማን ይባላል ? ”
አቤል ሙሉዬ ።
"የት ነው የምኖረው ? ”

“ እ ሀገሬ ጎንደር ነው ፤ አሁን ግን ያለሁት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስድስት ኪሎ ነው
“ ተማሪ ነህ ? ”
አቤል ራሱን በአዎንታ ነቀነቀ ።
« ስንተኛ ዓመት ደርሰሃል ? ”
“ በፍልስፍና ትምህርት አራተኛ ዓመት ።
“ ኦ! መጨረሻህ ነው? ” አቤል ዝም አለ

ይህ ሁሉ መግባቢያ ነው ። ሐኪሙ የታካሚውን ማንነት ወይም ችግር የሚረዳበት ጥያቄ አለ ፦ ። የአመላለስ
ሁኔታቸው በፍርሀት ፡ በጩህት በግዴለሽነት ወይም በአነጋገር ደረጃ ይለያይ እንጂ ፡ ብዙ ታካሚዎች የመግባቢያውን ጥያቄ በትክክል ይመልሳሉ ።

መልካም ነው አቤል ! ኧ፡ ወደዚህ ቦታ ለምን እንደመጣህ ታውቃለህ?

ሐኪሙ የዚህን ጥያቄ መልስ የሚጠብቀው በጉጉት ነው ። የሕመምተኞቹን ደረጃ ይገመግምበታል ። መቼም በተለያየ ጊዜ ከተለያየ ሕመምተኛ የሚቀርበው መልስ በየአይነቱ ነው።

ዝነኛ ሐኪም ነህ ሲባል ሰምቼ ነው ።
ፍቅረኛዬ ነች ለዚህ ያበቃችኝ ።
ያመጡኝን ሰዎች ጠይቅ ፥ እኔ ምን ዐውቃለሁ።
እንጃልህ የሚል መልስ የሚሰም አሉ ።

ታካሚዎቹ ከጥያቄው ጋር ፍጹም ያልተያያዘ ወይም የሚያሥቅ ወይም የሚያሳዝን መልስ ሊሰጡ ይችላሉ። ሆኖም ሐኪሙ አይሥቅም ። ረዳቶቹ አንዳንዴ ያመልጣቸውና ይሥቃሉ በሥራው ዓለም በሕመምተኛው መልስ መሣቅ ክልክል ነው ።

“ ግቢ ውስጥ ከአንድ ተማሪ ጋር በቼስ ጨዋታ ወጣላቴን ነው የማስታውሰው ” አለ አቤል ፥ ቀጥ ባለ ድምፅ ።

ምነው ? ምን አጣላችሁ ? ”
“በጨዋታው ሊያሸንፈኝ ሲል ተጣላን ለጊዜው ተመስጦ ውስጥ ነበርኩ ... አለና ሊናገር ያሰበውን አቋረጠ

አይኑን ከሐኪም ወደ ጠረጴዛው ወደ ሐኪሙ አንቀዋለለ ዳኛ ፊት የቀረበ ወንጀለኛ ይመስል አንገቱን ደፋ ።
ቼስ ጨዋታው ላይ ጸብ የፈጠረው በዓይኑ ያፈቅራት ልጅ የተመስጦ የቼስ ንግሥት ተመስላ ስሜቱ ውስጥ መጥታበት መሆኑን መናገር አልፈለገም ስለ ትዕግሥት ምንም ነገር ማለት አልፈለገም” ።ጸቡ የተፈጠረው መሸነፍ በሚያስከትለው ብስጭት ብቻ እንደሆነ አድርጎ ሊናገር አሰበ ።

በሌላ በኩል ደግሞ ዘመናዊ የማናዘዣ ዘዴ ( ሂፕኖቲዝም) መኖሩን ሲነገር በወሬ ሲለሚሰማ፥ ልቡ ምስጢሩን ለመደበቅ ፈራ በዚህ ዘዴ ሐኪሙ ምስጢሩን አንድ ሳይቀር ጎልጉሎ የሚያስወጣ መሰለው ። ዐይኑን እያስለመለመ ልቡ ምስጢሩን በማውጣትና በመደበቅ መሐል ተከፋፍሎ ቆየ " " ምነው ይህን ያህል ? ፍቅር ወንጀል ነው እንዴ ?” አለ በሐሳቡ ብናገርስ ምን ይመጣብኛል? ?

አቤል መደበቅ የፈለገው ወይም ያስጨነቀው ነገር እንዳለ ፡ ሐኪሙ ከገጽታውና ከሚስለመለሙት ዐይኖቹ
መረዳት ቻለ "

አይዞህ አቤል ነጻ ሁን !እዚህ እኔ ፊት የቀረብከው እንድረዳህ ነው ። ማናቸውንም ነገር እንደ ወንድምህ ወይም እንደ ባልንጀራህ ወይም እንደ ምስጢር ጓደኛህ ወይም እንደ ... እ... እንደ ሴት ጓደኛህ አርገህ አጫውተኝ ። ”

“ እሺ ” አለ አቤል እሁንም እየተቅለሰለሰ
“ ፍቅረኛ፡ የት ነው ያለችው ? ”
ሐኪሙ ይሆን የጠየቀው በአንድ በኩል ስለ ሴት ጓደኛ ሊያነሣበት ፥ በአቤል ፊት ላይ ያነበበምን ለውጥ አስቦ ሲሆን፥
በሌላ በኩል ደግሞ፡የፍቅር ትኩሳት የወጣትነት ዕድሜ አንዱና ዋናው ችግር መሆኑን ከሥራ ልምድ በማውቁ ነበር

አቤል ተደናግጦ ጭጭ አለ ፡ ምንም መልስ ሊሰጥ አልደፈረም”

“ እ እሷም ዩኒቨርስቲ ውስጥ ናት?”

ይህም ከገጠመኝ የመነጨ
👍1🔥1
#በፍቅር_ላይ_ሾተላይ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ድርሰት_በትክክል_ገና

...ድሮ የሰማችው የንፁሁ የአቢላዛር ታሪክ ትዝ አላት፡፡ኤቢላዛር በሀሰት ውንጀላ በአባቱ ዘንድ እምነት ያጣና፤ባልሰራው ወንጀል፡ ከባድ ስቃይና ቅጣት የደረሰበት እናቱ በህጻንነቱ የሞተችበት ወጣት ነበር፡፡አቢላዛር በቁንጅናው ምክንያት በሕይወቱ ላይ ታላቅ ስቃይና
መከራ ደርሶበታል፡፡የአቢላዛር አባት ባትሮሊዮ ሕጻን ልጁን እናትም አባትም ሆኖ አሳደገው፡፡ አቢላዛር ዕድሜው ለአቅመ አዳም ሲደርስ አባቱ ባትሮሊዮ
ሚስት ለማግባት ፈለገ፡፡ሚስት ቢያገባ ለእሱም፤ ለልጁም፤ ረዳት - እንደምትሆን
በመገመት በዕድሜዋ ወጣት የሆነችውን ውቧ ጉቲኤራን አገባት፡፡ጉቲኤራ በቁንጅናዋ እዚህ ጉደለሽ የማትባል ብትሆንም፤ በራሷ ቁንጅና ላይ የነበራት ኩራት ወደታች የወረደው ፤ የባሏን ልጅ አቢላዛርን ያየችው ዕለት ነበር፡፡ በዚያን ዕለት በፍቅር የተነደፈ ልቧን ሐኪምም፤
ፀበልም፤ ማንም እንደማያድነው አወቀች፡፡ መድሃኒቱ አንድ ነው፡፡ እሱም
አቢላዘር ብቻ! ስሜቷን አምቃ እየተሰቃየች፣ በአንድ ወገን የእንጀራ ልጂ
የመሆኑ ጉዳይ ቢያስጨንቃትም፤ ፍቅሯን መቋቋም አልቻለችምና፤የእንጀራ ልጅነቱን ጉዳይ ችላ በማለት፤በፍቅር ልታጠምደው ቆርጣ ተነሳች፡፡
ጉቲኤራ በፍቅር የተረታችለት መሆኑን እንዴት አድርጋ እንደምትገልጽለት ጨንቋት ውስጥ ውስጡን ስትሰቃይ ኖረች።ቀስ በቀስ ውስጥ ውስጡን የሚያብሰለስላት፣ የሚያብከነክናት፤
የፍቅር መጋዝ፤ በአካሏም ላይ ለውጥ እያስከተለ ሄደ፡፡
አፏን ከፍታ ፍዝዝ፣ ድንዘዝ፣ ብላ የምትቀርበት ጊዜ ጥቂት አልነበረም፡፡ ይህ ሁኔታ ለአቢላዛር በፍፁም አልተገለጠለትም ነበር፡፡በእርግጥ አቢላዛር ማንም በቀላሉ አይቶት የሚያልፈው ልጅ አይደለም፡፡ ያጓጓል፡፡ በዚሁ መሀል ለጉቲኤራ አንድ አጋጣሚ ተፈጠረላት። በጣም አስደሳች አጋጣሚ፡፡
ባሏ ባትሪሊዮ ግመሎቹን በሙሉ እየነዳ
የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ለማምጣት ድንበር ጥሶ የሚሄድበት ቀን ደረሰ፡፡
ባትሮሊዮ ቢያንስ ከሁለት ወራት በፊት አይመጣም፡፡ በቃ በዚህ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ የሚያለቅሰው ልቧ ፈውስ ሊያገኝ ነው፡፡ እሺ አለም እንቢ፤ በውድም ይሁን በግድ፤ አቢላዛርን ማግኘት አለባት፡፡ እንቢ ቢል ልታስገድደው ወሰነች፡፡
አቢላዛር እናትም አባትም ሆኖ ላሳደገው ለአባቱ ያለው ፍቅር የተለየና በአለም ላይ ከሚያፈቅራቸው ነገሮች ሁሉ በላይ ነው፡፡
የአባቱ የጉዞው ቀን ደረሰ፡፡ አቢላዛር አባቱን በፍቅር ተሰነባበተው፡፡ ጉቲኤራ ደግሞ በቶሎ አይመልስህ ብላ ሸኘችው፡፡ ከዚያም ባትሮሊዮ በሄደ በሳምንቱ ጉቲኤራ ተቅበጠበጠች፡፡ ከዚህ በላይ ብትቆይ የምትፈነዳ መሰላት፡፡ከዚህ በላይ መቆየት መታገስ አቃታት፡፡ አቢላዛር
ደግሞ እስከአሁን ድረስ ቅንጣት ታክል ችግሯን አልተረዳላትም፡፡
በሣምንቱ መጨረሻ፤ ያ ምሽት፤ እንደወትሮው ሁሉ፤ አቢላዛር የመኝታ ክፍሉን በር ቀርቅሮ የተኛበት ምሽት ነበር፡፡ ጉቲኤራ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት አካባቢ ሲሆን የውስጥ ሱሪዋን ብቻ እንደለበሰች ወደ መኝታ ክፍሉ መጣች፡፡
“አቢላዛር! አቢላዛር ድረስልኝ! እባክህ በሩን ቶሎ ክፈትልኝ!”
እያለቀሰች በሩን በሃይል መታቸው፡፡
አቢላዛር በዚያን ሰዓት በሆነ ቅዠት ላይ ነበረ፡፡ በሩ በሃይል ተንኳኳ፡፡ ተንጓጓ፡፡ በዚህ ጊዜ ከእንቅልፉ ባኖ ቢያዳምጥ፤ የእንጀራ እናቱ በእንባ ሲቃ በታፈነ ድምጽ ስትጣራ ሰማ፡፡ በሁኔታው በጣም
ተደናገጠና በሩን ከፈተው፡፡
የሚያየውን ነገር ማመን አቅቶት፤ አሁንም በህልሙ እንዳይሆን ተጠራጠራና፧ አይኖቹን አሻሽ፡፡ በርግጥም በህልሙ አልነበረም፡፡ በውኑ ነው፡፡

የጉቲኤራ ራቁት ገላ፣ ያገጠገጡ ጡቶቿ፤ ባለጥንድ አፈሙዝ ድግን መትረየስ መስለው፤ ከፊት ለፊቱ ተወድረዋል፡፡
ዓይኖቿ በማያቋርጥ የእንባ ምንጭ ይዋኛሉ፡፡
“ምን ሆንሽ ጐቲኤራ?” ደንግጦ ጠየቃት፡፡
“አነቁኝ፡፡ መጡብኝ ሊበሉኝ ነው” ወተወተች፡፡
“እነማናቸው? ማን አባቱ ነው ሊበላሽ የመጣው?”
በእንጀራ እናቱ ላይ እጁን የሰነዘረውን ጠላቱን ሊተናነቀው አይኖቹ በንዴት ቀልተው ጠየቃት፡፡
“ግዴለም ቆይ ቁጭ በል፡፡ አሁን ሄደዋል፡፡”
“ጅል፤ ነገር የማይገባህ ደደብ” አለችው በልቧ፡፡ እኒያ የቆሙ ጡቶቿ ያ ውብና ማራኪ ራቁት ሰውነቷ የማይታየው እውር አናደዳት፡፡
“ሰይጣኖች ናቸው፡፡ ሰዎች አይደሉም፡፡ ይኸውልህ እዚህ ላይ ነው በጣም የትጫኑኝ፡፡ ተመልከት እዚህ ጋ” የቀኝ እጁን ይዛ ጡቶቿ መካከል አስቀመጠችው፡፡
አቢላዛር በየዋህነት እዚያ ጡቶቿ ሥር የሚሰማትን ህመም እንዲወገድላት አሻሻት፡፡
በዚያን ሰዓት ጉቲኤራ ጦፋ በሃሣቧ ከዚያ በኋላ በሚፈጠረው
ትርኢትና፤ በትርኢቱ ውስጥ የሚስማትን የእርካታ ስሜት እያጣጣመችው ነበር፡፡
“በቃ እዚሁ እሆናለሁ ከአሁን በኋላ እዚያ ዳፍንታም ክፍል አልመለስም” አለችውና ሄዳ እሱ አልጋ ላይ ቁጭ አለች፡፡
“ብርድ ይመታሻል ልብስ ልበስ” ብሎ የራሱን ሸሚዝ እላይዋ ላይ ጣል ቢያደርገው ፤ ወደዚያ ውርውር አድርጋ...
“ይልቁን እሱን በደንብ አድርገህ እሽልኝ፡፡ ያለበለዚያ ያመኛል
በታዘዘው መሠረት እዚያ ጡቶቿ
ሥር፧ሰይጣኖቹ ያሳመሟትን ቦታ፤ ለማዳን ማሻሸት ቀጠለ፡፡ጉቲኤራ ደግሞ እንደዚያ
ጡቶቿን ሲያሻሽላት የምትሆነውን አጣች፡፡ እንደሰም ቀልጣ መፍሰስ ጀመረች።
ሙሉውን ሌሊት በእንባ እየታጠበች ብትለምነው ንዴቱ እየባሰበት እንጂ ሃሣቡን የመለወጥ አዝማሚያ ሳያሳይ ቀረ። በዚህ ሁኔታ በተደጋጋሚ ፈተነችው፡፡ አቢላዘር ግን ወይ ንቅንቅ! አለ፡፡
በመጨረሻም እንዳልተሳካላት ቁርጧን ስታውቅ፤ ልትበቀለው ቆርጣ ተነሳች፡፡
ሴራዋን ስትጎነጉን ሰነበተች፡፡ ባሏ ከሁለት ወር በኋላ ሲመጣ፣በናፍቆት ከመቀበል ይልቅ፤ እሳት ጎርሳ፤ እሳት ለብሳ፤ ተቀበለችው:: የሁለት ወር ሙሉ ናፍቆት አቃጥሎት ሲስማት አመናጨቀችው፡፡
“የጋብቻ ውላችንን አፍርስልኝ” ስትል ጮኽችበት ባትሮሊዮ በነገሩ ተደናግጦ ምክንያቱን ቢጠይቃት...
“ምንም እንኳን ባልወልደው፤ ልጅህ ፤ ልጄ ይሆናል ብዬ ነበር እዚህ ጣጣ ውስጥ የገባሁት፡፡ እሱ ግን ለሚስትነት ፈለገኝ” ብላ ከፍላጐቷ ውጭ አስገድዶ በግብረ ሥጋ የተገናኛት መሆኑን እያለቀሰች ነገረችው፡፡
ባትሮሊዮ እንደ አይኑ ብሌን የሚያየው አንድዬ ልጁ፣ እናትም አባትም ሆኖ ተሰቃይቶ፣ በሽንት ተጨማልቆ ያሳደገው የሚወደው ልጁ ተመልሶ እጁን ስለነከሰው ፤ ሀዘኑ ጣራውን አለፈና፤ ለዚህ ወደር ለሌለው ጥፋቱ ቅጣቱን ሲያውጠነጥንለት ዋለ፡፡በመጨረሻ የመጣላት ሃሣብ መግደል ቢሆንም፧ መግደል ብቻውን አላረካህ አለው፡፡ ከዚያ በላይ በቁሙ እያለ እንዲቀጣ ፈለገ፡፡
እንደዚያ በጥጋብ እንዲያነጠንጥ፤ እንደዚያ ያለውን አፀያፊ ሥራ እንዲሠራ፤ የገፋፋውን ችግሩን ከላዩ ላይ ሊያስወግድለት ወሰነና፤ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ላይ የመኝታ ቤቱን በር አስከፍቶት ገባ፡፡
አቢላዘር ከእንቅልፉ ባንኖና፤ በሁኔታው ተደናግጦ፡
“ምነው አባባ?” ሲል ጠየቀው፡፡
“ዝም በል!! የምትታዘዘውን ብቻ ትፈጽማለህ!!” ሲል ጠንካራ ትዕዛዝ ሰጠው፡፡አባቱ እሳት ለብሶ፤ እሳት ጉርሶ፤ ሲያይ ልጁ በአባቱ አዲስ ፀባይ ተደናግጦና፤ ግራ ተጋብቶ፤ የታዘዘውን ሁሉ በአክብሮት ይፈጽም ጀመር፡፡ራቁቱን አስቁሞ እጁንም እግሩንም አሰረው፡፡ ያለተቃውሞ
በአባቱ ትዕዛዝ መሠረት እጁንም፤ እግሩንም፤ ለገመድ ሰጠ፡፡
“በሽንትህ ተጨማልቄ፤ ያለ እናት ያሳደግኩህ አባትህ መሆኔን አውቀህ ፤ ቤቴን ትዳሬን አክብረህ ስለቆየኸኝ ፤የረጅም ዘመን ድካሜን ዋጋ ለመክፈል እንቅልፍ አጥተህ ስለጠበቅከኝ፤ ይህንን የዋልክልኝን ከፍተኛ የልጅነት ውለታህን ተቀብዬ፤ እኔም የአባትነት ውለታዬን
🔥21👍1
#ቆንጆዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ



#ድርሰት_ሰርቅ_ዳ


....በጥፊ ጆሮ ግንዷን እናጋው፡፡
ለጥቂት ደቂቃዎች ያለችበት ጠፋት፤ዘሪያዋ ጨለማ ለበሰ፡፡ እዛው
አፓርትመንት ክፍሏ ውስጥ እጆቿንና እግርቿን ከአልጋዋ ጋር በአንሶላ
ጨርቅ ጥፍር አድርገው አስረው እንዳትጮህ አፏ ውስጥ ጨርቅ ጎስጉሰው ለጉመው አጋድመዋታል፡፡

“ንገሪኝ!” አለ ድጋሚ ሊያጣፋት እየተንጠራራ “የት ነው ያለው?
ትነግሪኛለሽ አትነግሪኝም?”
ጭንቅላቷን በጭንቀት አርገፈገፈችው:: ከተለጎመው አፏ ጀርባ ጉሮሮዋ . “የት እንዳለ አላውቅም:: እውነቴን ነው!” አለች:: ድምፅ ግን አላወጣችም፡፡

ውልብ አለባት ድጋሚ፡፡ ጆሮዋ ላይ ሌላ ጥፊ ደወለ፡፡
“ንገሪኝ!”

ዱላው እየጨመረ በመጣ ቁጥር እልኋና ቁጣዋ እንዴት ተደፈርኩ ባያነቷ እንደጨው እየሟመ ለማይታክተው እንባዋ እስረከበዋታል፡፡ ፀጉሯ
ሲጨመደድ ተሰማት::

“ንገሪኝ! የት ነው ያለው?”
ድጋሚ በጥፊ አይኖቿን ከደናቸው፡፡
“ንገሪኝ!”

ተከትሎ ምን እንደተናገረ አልሰማችውም:: ጆሮዋ ላይ የሚደውለውን ስቃይ ተከትሎ ዙሪያዋ ፅልመት ተከናነበ፡፡ አይኖቿን ድጋሚ ስትገልጣቸው ሰውነቷን ክፉኛ ቀዘቀዛት፡፡ለሶስተኛ ጊዜ ውሃ አፍስሰውባታል፡፡
አልጋዋ በየደቂቃው ህሊናዋን በሳተች ቁጥር በሚቸለስባት ቀዝቃዛ ውሃ
ረስርሳል:: የለበሰችው ስስ ቀሚስ እላይዋ ላይ ተጣብቋል፡፡

ዓይኖቿን ግርብብ አድርጋ ተመሰከተቻቸው፡፡ ሶስቱም በአልጋዋ
ዙሪያ ቆመው ቁልቁል ይመለከቷታል፡፡ ሁለቱን አታቃቸውም፡፡ ሶስተኛው
ግን ያው የህዋሷ መሪ ማርቆስ ነበር፡፡ በጠባሳ የተገመሰ ፊቱን ቁልቁል
አንዘርቦ ይመለከታታል፡፡ ደጉን የተወያየችው የገዛ ጓደኛዋ አልመስልሽ
አላት፡፡ አይኖቿን ጭምቅ አድርጋ ጨፈነቻቸው፡፡ በተንጋለለችበት እንባዋ
የገዛ አይኖቿን እንደጨው እየለበለበ ፈሰሰ፡፡

“ከሃዲ!” አለ ሰስተግራዋ የቆመ ሌሊቱን ሲጠፈጥፋት ያደረው ሰው ድንገት ፊቱን መልሶ የመኝታ ክፍሏን በር ከፍቶ እየወጣ፡፡

በክፍሉ ውስጥ የቀሩት ሁለት ሰዎች ለጥቂት ደቂቃዎች ያለ እንቅስቃሴ ቁልቁል ሲመለከቷት ቆዩ፡፡ ወዲያው ማርቆስ ጠጋ ብሎ አፏ የተለጎመበትን ጨርቅ መፍታት ጀመረ፡፡ ሽቅብ ፊቱን ስትመለከተው ከዓመት በላይ የምታውቀው አብራው የቀለደችና የሳቀች ያው የድሮው የህዋሷ መሪ ማርቆስ መሆኑን ማመን አቃታት፡፡

“ምን ማድረግህ ነው?” አለ ከበስተግርጌ የቆመው ጺማም ሰውዬ ማርቆስ አፏ የተለጎመበትን ጨርቅ ሲፈታላት ሲያይ እየተቁነጠነጠ።

ማርቆስ ለሰውየው መልስ ሳይሰጠው አፏን ሞልቶ ተርፎ የነበረውን ቡትቶ ጨርቅ ጎትቶ አወጣላት፡፡ ተበርግዶ የቆየ መንጋጋዋ የራሷ መንጋጋ እንዳልሆነ ሁሉ አልገጥምልሽ አላት፡፡ ደርቆ የቆየ ጉርሮዋ የገዛ ምራቋን አልውጥልሽ አላት፡፡ እንባዋ ብቻ ጉንጮቿን እየተለተለ መውረዱን
ቀጠለ፡፡

“ርብቃ …ለምን ለእኛም ለራስሽም አስቸጋሪ ትሆኛለሽ?” ማርቆስ
ቁልቁል እየተመላከተ ተማፀናት፡፡ “ርብቃ ልለምንሽ የት እንዳለ ንገሪንና
ይህ ሁሉ ያብቃ፡፡” ተለማመጣት፡፡

ለምን አይገባቸውም?! ናትናኤል የት እንደለ ኣላውቅም ስትላቸው ለምን አያምኗትም?! እንዴት አድርጋ ነው እውነቱን እውነት ነው የምትላቸው?

“የት እንዳለ አላውቅም፡፡” ልትል ፈለገችና ጉሮዋ አልታዘዝሽ አላት፡፡ በጀርባዋ በተንጋለለችበት ጭንቅላቷን ነቀነቀች፡፡
“ርብቃ ጊዜ በወሰድሽ ቁጥር ሁኔታው ለራስሽ እየከፋ ነው የሚሄደው፡፡ የምትጋፈጫቸው ሰዎች ትዕግሥታቸው ያለቀና ቁጣቸው ወደ ዕልህ የተቀየረ ራሳቸውን መቆጣጠር የማይችሉ ናቸው:: ርብቃ እነዚህ ሰዎች ሊያደርጉት የሚገፋፉትን ደግሞ ማንም አይወደውም፡፡ አንቺ ሴት ነሽ፡፡ እነዚህን ሰዎች የሚቋቋም የመንፈስ ጠንካራነት የለሽም:: በቀላሉ እንደቀርከሃ ሊሰባብሩሽ ይችላሉ፡፡ በቀላሉ! እባክሽን ንገሪኝ፡፡፡ ናትናኤል የት ነው?” የሌሊት ሁኔታዋን መቋቋም አቅቶት ሲቁነጠነጥ ያደረው
ማርቆስ የባሰ ከመምጣቱ በፊት ሊያሳምናት ታገለ፡፡

አ....አላውቅም፡፡” አለችው እንባዋን እያስተናገደች::
“ጥሩ፡፡ መስሪያ ቤትሽ ደውሉ ሲያጣሽና ስራ ከገባሽ ውሰሽ ማደርሽን ሲረዳ እንዴት እዚህ አልደወለም?”
“ፈርቶ ይሆናል... እኔ ምን አውቃለሁ፡፡” እውነተኛነቷን ይገልፅላት ይመስል ድምጿን አለሰለሰችው::

“ምን? ማንን ነው የሚፈራው?”
“እናንተን፡፡” አለች በለቅሶ መሃል፡፡

“አየሽ ይህ ማለት አንቺ ከእኛ ጋር ግንኙነት እንዳለሽ አውቋል ወይም በፊትም ያውቅ ነበር ማለት ነው፡፡ ይህን ሊያውቅ የሚችለው ደግሞ አንቺ....”

አልነገርኩትም!” አለች አቅጣጫውን ስትረዳ አቋርጣው፡፡ “እኔ አልነገርኩትም፡፡እኔ በእርሱ ላይ መረጃ ስስበስብ መቆየቴንም ጭራሽ አያውቅም፡፡ ግን እዚህ ሲመጣ ልታገኙት እንደምትችሉ ጠርጥሮ ይሆናል፡፡”
ለምን ድጋሚ መሥሪያ ቤትሽ ስልክ አልደወለም? ባለፈው ጊዜ ሲደውል ጓደኛሽ ቢሮ ከገባሽ ዉስሽ ማደርሽን እንድትነግረው አድርገናል፡፡እዚህ መደወል ወይ መምጣት ነበረበት፡፡ አልመጣም፧ አልደወለም:: መሥሪያ
ቤትሽም መልሶ አልደወለም:: ለምን?”

“አላውቅም::” እለች በማስተዛዘን፡፡

“ውሽት አውቋል… ሁሉንም ተረድቶታል:: ለዚህ ነው ሊገናኝሽ ያልሞከረ፡፡ ባያውቅ ኖር..”

“ውሸቴን አይደለም!” አቋረጠችው “እመኑኝ ናትናኤል ምንም የሚያውቀው ነገር የለም ናት…”

“ያውቃል! ያውቃል! ምንም የማያውቅ ሰው በጭካኔ የሁለት ሰው ነፍስ አጥፍቶ አይሰወርም፡፡ ትሰሚኛለሽ? የፈጸመው ወንጀል ምንም የማያውቅ ሰው የሚፈጽመው አይደለም!” ትከሻዋን በሁለት እጆቹ ይዞ ነቅነቃት፡፡

“ናትናኤል ሰው ፡ አይገድልም...ውሸት
ነው፡፡” ለራሷ ፡ ነበር የተናገረችው፡፡

“ርብቃ…. ሰዎቻችን ያውቁታል፡፡ ለይተው ስላወቁትም ነው የተከታሉት፡፡ ይገባሻል? የካልቨርትን አድራሻ ከሴትየዋ ማግኘት ስላልቻለ ምናልባትም አድራሻውን አስገድዶ ካውጣጣት በኋላ ነው ደረቷን በጥይት የበሳው፤ ገድሏት የሄደው፡፡
አስታውሽ እሷን ብቻ አይደለም ያጠፋው!
የኛንም ሰው ነው:: ርብቃ… እባብ ነው ሰውዬሽ፡፡ ሁላችንንም አታሎናል፡፡
ምንም የማያውቅ የዋህ መስሎ አታሎናል፡፡ አንቺንም አታሎሻል፡፡ አብረን
ልናቆመው ይገባናል፡፡ ንገሪኝ፤ የት ነው የተሸሸገው?”

“አላውቀውም አልኩህ፡፡”
ገፁ በንዴት ተኮማተረ፡፡

“ርብቃ” አይኖቹን አጥብቦ ተመለከታት፡፡ “በአንድ ወቅት ከጎናችን መቆምሽን አንዘነጋውም፤ ያ የሩቅ ትዝታ አይደለም፤ ግን ደግሞ መረባችን በከዳተኞች ምላጭ ሲበጣጠስና ውጥናችን በባንዳዎች ራስ ወዳድነት እርቃኑን ወጥቶ እያንዳንዳችን ለስደትና ለሞት ስንዳረግ በዝምታ መመልከት አንችልም፡፡ ይህ እንዳይሆን ደግሞ የምንጠላውንም ነገር ቢሆን ለማድረግ እንገደዳለን፡፡ ርብቃ ትሰሚኛለሽ? መንፈስሽ መኮሳሽት ካለበት እናኮላሽዋለን፤ሰውነትሽ መዋረድ ካለበት እናዋርደዋለን! ህሊናሽ መጨቅየት ካለበት እናጨቅየዋለን… የማታ ማታ የጠየቅንሽን ሁሉ ታወጪዋለሽ፡፡ ይህ ከመሆኑ በፊት አስተውይ፡፡ ናትናኤል አታሎሻል! የስጋ ፍላጎትሽን ተጠቅሞ
ምስጢራችንን ከቀዳ በኋላ አጋልጦሽ ተሰውሯል፡፡ የት ነው ያለው?
ናትናኤል የት ነው?”

“አላውቅም'ኮ” እንባዋ ገና ድሮ በቀደደው ቦይ ያንቆረቆር ጀመር፡፡

የመኝታ ቤቷ በር ተከፍቶ ሦስት ሰዎች ተከታትለው ገቡ፡፡ ሁለቱን አይታቸው አታወቅም አንደኛው ግን ከትላንት ጀምሮ ሲቀጠቅጣት የቆየ ነው ከፊት ቀደም ያለው ሰው በእድሜ ጠና ያለ ይመስላል፡፡ ወደፊት ራመድ ብሎ ወደ አልጋዋ ግርጌ ከተጠጋ በኋላ በክፍሉ ውስጥ ለተሰበሰቡት ሰዎች እንዲፈቷት ምልክት ሰጣቸውና ከማርቆስ ጋር በሹክሹክታ ይነጋገር ጀመር
1👍1