አትሮኖስ
286K subscribers
117 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሮዛ_2


#ክፍል_ሀያ_ሶስት( 🔞)
(የመጨረሻ ክፍል)


#የሰው_ ልጅ_ዓለምን_ አትርፎ #ነፍሱን_ቢበድል....

ቤይሩት፣ ራፊቅ ሀሪሪ አየር መንገድ

አርብ ሌሊት

በምድር ላይ እጅግ ከምጠላቸው ሕዝቦች መሀል እገኛለሁ፤ ሊባኖስ ቤይሩት አየር መንገድ ውስጥ፤
ወደ አቡዳቢ ለመብረር። አየርመንገዱ በአረቦች ታፍኗል። አረብ አረብ ይሸታል። የተቀቡት ሽቶ አልተስማማኝም፤ እነሱን እንዲህ በጅምላ ማየት ራሱ ያቅለሸልሻል። አመመኝ።

ክትፎ የሚወድ ሰው ጣባውን ሲከፍተው የሚዝለገለጉ ትላትሎች ታጭቀው ቢያይ ሊሰማው የሚችለው ስሜት እኔ አረቦችን እንዲህ ብዙ ሆነው በማየቴ ተሰምቶኛል። አዲስ አበባ በተናጥል አገኛቸው ስለነበር
ለነሱ ያለኝ የጥላቻ ስሜት የዛሬውን ያህል አልበረታብኝም ነበር። አሁን አንድ ሙሉ ተርሚናል በሺ በሚቆጠሩ አረቦች ተሞልቶ ብመለከት ምግብ አልረጋ አለኝ። አመመኝ።

ከአረቦቹ መሀል ብዙ መልካምና ደጋግ ሊኖሩ እንደሚችሉ እረዳለሁ፤ የበርካታ ሺህ ወገኖቼ ህይወት በነሱ ላይ እንደተመሰረተም አውቃለሁ፤ ወላጅ አልባ ህጻናት የሚያሳድጉ ደጋግ አረቦች ብዙ አሉ፤ ይህንንም አልከድም። በሀገሬም ሆነ በሀገራቸው ከወገኖቼ ጋ ፍቅር መስርተው የወለዱና የከበዱ አረቦች
እንዳሉም አልክድም።ለወደዱት ሰው ቤት ንብረታቸውን በሙሉ የሚሰጡ፣ ሀበሻ ሰራተኞቻቸው ሲታመሙ ሚሊዮን ብር ከስከሰው ያሳከሙ አረቦች እንዳሉም ከዚያ የተመለሱ ጓደኞቼ ሲያወሩ
ሰምቻለሁ። እርግጥ ነው፤ የትኛውም ህዝብ ሰናይና እኩይ ሰዎች አሉት፤ አረቦቹም ከዚያ የተለዩ እንዳልሆኑ ጠንቅቄ አውቀዋለሁ።ይህን ሁሉ እየተረዳሁ ግን ለአረቦች ስር የሰደደ ጥላቻ ደሜ ዉስጥ ገብቷል፤ ምን ላድርግ?

ህሊናዬን በብርቱ ከፈተነ ማሰላሰልና መብሰልሰል በኋላ የህይወቴ ቀጣዩ ምእራፍ በአረብ ምድር እንዲሆን ወሰንኩ። በተባበሩት ኢምሬትስ ርእሰ መዲና አቡዳቢ ሬስቶራንትና የውበት ሳሎን ያላትን የአብሮ አደጌን የቢዝነስ አጋርነት ግብዣ ለአመታት አሻፈረኝ ብልም ሰሞኑን ውሳኔዬን ከብዙ የአእምሮ
ጂምናስቲከ በኋላ ቀየርኩ፤ ከዚህ በኋላ እንዴትም ብዬ የህይወት አቅጣጫዬን መለወጥ እንዳለብኝ ተሰምቶኛል።

#ተርሚናሉ_ዉስጥ
.
አረብ ወንዶች ያለመጠን የተርከፈከፉት ሽቶ ራሴ ላይ ወጣ። ተርሚናሉ ዉስጥ እየተዝለገለጉ ወዲያ ወዲህ ሲሉ ሆዴ ታወከ። መታጠቢያ ቤት ሄጄ ፊቴን በቀዝቃዛ ዉኃ ነከርኩ። ትንሽ ሻል ያለ
ስሜት ሲሰማኝ በወርቅ የተለበጠ ከሚመስል አግዳሚ ወንበር ላይ አንድ ጥግ ይዤ አረፍ አልኩኝ።
ለጊዜው በዙርያዬ የሚሆነውን ከማየት ዉጭ ሌላ እድል አልነበረኝም። አይኔን ብጨፍንም አረቦችን አያለሁ። አይኔን ብገልጥም አረቦችን አያለሁ። አማራጭ አልነበረኝም። ለካንስ አይንን መጨፈን ማየት የሚፈልጉትን ከማየት አይጋርድም። ዳያሪዬን ከእጅ ቦርሳዬ ዉስጥ ብታቀፈውም አእምሮዬ ባልተለመደ ሁኔታ ደንዝዞብኛል። በአየር መንገዱ አግዳሚ ቁጭ ብዬ ወጪ ወራጁን ስሜት አልባ ሆኜ አያለሁ።
የአረብ ጎታታ ወንዶች፣ በዚያ በሚዝለገለግ ነጭ ቀሚሳቸው ዉስጥ ሆነው አውሮፕላን ለመሳፈር እንደ
ግመል ይጎተታሉ። የቀሚሳቸው መጎተት ላያንስ በሩዝ የተወደረ ከርሳቸውን ይጎትታሉ፤ የከርሳቸው ሳያንስ ኩንታል ሻንጣቸውን ይጎትታሉ። የሻንጣቸው ሳያንስ ነጠላ ጫማቸውን ይጎትታሉ፤ የነጠላ ጫማቸው ሳያንስ ከረፈፍ ሚስቶቻቸውን ይጎትታሉ፣ የሚስቶቻቸው ሳያንስ ያልተቆነጠጡ አስራ ምናምን ልጆቻቸውን ይጎትታሉ። አራት ሚስቶቻቸውን እየነዱም ቢሆን አምስተኛ ሴት ከማየት አይመለሱም። ከአንድም ሁለት ሦስት አጁዛ አረቦች ከወዲያኛው የተርሚናሉ ሬስቶራንት ሆነው

እየሰረቁ ሲመለከቱኝ ዐይቻለሁ፡፡

በድጋሚ መታጠቢያ ቤት ሄጄ ተመለስኩ። ዛሬ ምግብ አልረጋ ብሎኛል።

ቀልቤ አይወዳቸውም። በተለይ እንዲህ ነጭ ቆብ በነጭ ቀሚስ ለብሰው ሳያቸው፣ በነጭ ኩባያ ወተት ከአናታቸው እየፈሰሰባቸው ስለሚመስለኝ የዝንብ አየር ማረፍያዎች እንጂ ሰዎች ሆነው አይታዩኝም።ሰው ነጭ ለብሶም ንፁህ ሆኖ ካልታየኝ መቼስ የሆነ ችግር አለበት ማለት ነው። ለምንድነው ፈጣሪ እኛን
ድሐ እነሱን ሐብታም ያረገው? እግዜር ምናቸው ማርኮት ይሆን አሻዋቸውን የባረከው? በረሃቸውን ያረጠበው?!

“የአረብ ጥላቻ የተፈጠረብኝ መቼ ነው?” ብዬ ለማስታወስ ሞከርኩ። ትዝ የሚለኝ ነገር የለም። ምናልባት ኡስማን ዘ ፒምፕ ስለሚጠላቸው እሱ ሳያውቀው አጋብቶብኝ ይሆን? አይደለም። ኡስማንን
ሳላውቀው በፊት አረብ የሚባል ፍጥረት ያስጠላኝ ነበር። ልጅ እያለሁ የጀመረኝ ይመስለኛል። አያቴ በነበረችበት ሰፈር። ባደኩበት ሰፈር፣ በነእማማ ዙበይዳ ሰፈር።

ልጅ እያለሁ ለተወሰነ ጊዜ ሴት አያቴ ታሳድገኝ ነበር። በሰፈራችን የምንወዳቸው፣ እማማ ዙበይዳ
የሚባሉ ሴት ነበሩ። የሆኑ ደርባባ አሮጊት ሴትዬ። ሰው ዝም ብሎ ይወዳቸው ነበር። ጎመን መንገድ ላይ ይሸጣሉ። በክረምት ደግሞ በቆሎ ይሸጣሉ። እማማ ዙበይዳን ሰፈሩ ሁሉ ለምን ይወዳቸው እንደነበር ግን በትክክል አላውቅም። እኔም እወዳቸው ነበር። ለምን እንደነበር ግን አላውቅም። “ነይ እስቲ አንቺ
ጎራዳ!" እያሉ ግንባሬን ይስሙኝ እንደነበር ብቻ ነው ትዝ የሚለኝ።

እማማ ዙበይዳ ባልም ዘመድም የላቸውም። በምድር ላይ ያለቻቸው ፋጤ ቀጮ ናት። የሳቸው ብቸኛ ልጅ ፉጤ ቀጮ ጅዳ ሄደች ተባለ። ሰፈሩ ሁሉ እማማ ዙበይዳ በቃ ሻሩ፣ አሁን ወርቅ በወርቅ ሊሆኑ ነው ብሎ ተነበየ። እሳቸውን ያገኘ ሰው ሁሉ “ፋጤ ቀጮ ጅዳ ነው አይደል የሄደችው?”፣
ትደውላለች”፣ “ደህና ናት ታዲያ፣ “አሁን ለመድኩ አለችፖ፣ ግህም፣ “በርቺ በሏት እንግዲህ!
ይለመዳል.ይለመዳል”፣ “ዋናው መበርታት ነውታዲያ”፣ “እ!” እያለ ከእማማ ዙበይዳ የበቆሎ እሸት
ወይ ጎመን ገዝቷቸው ያልፋል። በበጋ ጎመን በከረምት የበቆሎ እሸት በመሸጥ ነበር የሚተዳደሩት።
በዚያ ሁሉ የሰፈር ሰው ሳይታክቱ በዚያ እናታዊ ፈገግታቸው ታጅበው ስለ ልጃቸው ደኅንነት ምላሽ ይሰጣሉ። “እላሙዲሊላ አላሂ ወላሂ ደህና ናት!ዱዋ አርጉላት." ይላሉ፤ መልሰው መላልሰው።

ሲኖሩ ሲኖሩ.…የሆነ ጊዜ ላይ ልጃቸው ስልክ ደውላ አለቀሰች ተባለ። “ምን ሆንሽ” ሲሏት አትናገርም
ሲኖሩ ሲኖሩ…የሆነ ጊዜ ላይ ደግሞ መደወል አቆመች ተባለ። ደህንነቷን የሚነግራቸው ጠፋ። ጎመን ወይ
በቆሎ ለሚገዛቸው የሰፈር ሰው ሁሉ “አረብ አገር ስልክ ማድረግ ታውቅበታለህ?” እያሉ ይጠይቃሉ።
የተማረ የሚመስል ወጣት ሲመለከቱ ደግሞ “ልጄ! እስኪ ባክህ የጅዳ ስልክ ቁጥር ጽፈህ አምጣልኝ? ልጄ ናፈቀችኝ ይሉታል። የሷ ስልክ ቁጥር ግን የላቸውም። አንዳንድ ሰው ነገሩን ሊያስረዳቸው ሞከረ።ኾኖም ሊገባቸው አልቻለም። የሰፈሩን ሰው መሄጃ መቀመጫ አሳጡት። እርስዎ ስልኳን ፈልገው ያምጡ! እኛ እንደውልሎታለን” ሲባሉ እኔ ቁጥሯን ከየት አዉቄ” ነው መልሳቸው። እሷ ካልደወለች
እሳቸው ወደየት ብለው ይደውላሉ? አድራሻዋ አይታወቅ ነገር።

የሰፈሩ ሰው በሙሉ እማማ ዙበይዳ ሲያዝኑ አይቶ አዘነ። እማማ ዙበይዳ የደግነት ምሳሌ ነበሩ። ፋጤ
ቀጮ እጅግ ስትናፍቃቸው ግን ሰው ሰላም ሳይሉ ማለፍ ሁሉ ጀመሩ። የሚሸጡት ጎመን ጠወለገ።
ወዲያው ደግሞ ወገባቸው ጎበጠ። ከመቼው በእድሜያቸው ላይ ምዕተ ዓመት እንደጨመሩ። ሰው የልጁ ናፍቆት እንደ ኤድስ አመንምኖ ሊገድለው እንደሚችል ያየሁት በእማማ ዙበይዳ ነው።

ከ5 ዓመታት በኋላ ልጃቸው ፋጤ መጣች ተባለ። በዊልቸር ላይ ሆና። በጣም ከመወፍሯ የተነሳ ዊልቸሩ ጠበባት። ፋጤ ቀጮ ትባል የነበረችው የሆነች ሲንቢሮ በረሮ ስለበረች ነበር።ታዲያ ለምን ወፈረች? ተስማምቷት ነበር ማለት ነው?
👍4
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#በክፍለማርያም

...ወደ ሆስፒታል ገሰገሰች
ፍፁም የህክምና ሰወች ተረባርበዉ ትንሽ ነብሱ መለስ አለች
ህመሙን የሚቀንስ መድሀኒት ተሰጥቶት ከዋጠ በኋላ
ከትራሱ ጋር ድጋሜ ጭንቅላቱን አገናኘዉ
እንደ ህመም ከባድ ወቅት የለም በጤነኝነት ስንኖር ዋጋ ሰጥተን
ባናስበዉም ስንታመም እና ስቃይ ዉስጥ ስንሆን ግን ሁሉ ነገራችን ተወስዶ ጤናችን ቢመለስ እንለምናለን
አብዛኞቻችን ለጤናችን አስበን አናዉቅም ጥንቃቄም የለንም
ምኞታችን ብር ላይ ያተኮረ ይሆናል ይለፋል ይለፋል በስተመጨረሻ ጤና ጠፍቶ ስንሰቃይ በህመም እጅ ዉስጥ
ስንወድቅ ብራችንን በሙሉ ለጤናችን መልሰን እናዉላለን
እንደ ፍፁም በአደጋ ህመም ላይ ሲወደቅ ግን ምን ይደረጋል
ሳያስበዉ እና ሳይጠብቀዉ ለዚህ በቃ የዚህ ሁሉ ጦስ ደግሞ
የፍቃዱ ተንኮል በተጨማሪም የቤዛዊት ማገናዘብ አለመቻል ናቸዉ።

እንቅልፍ መተኛት ባይፈልግም አልጋዉ ላይ ጋደም ብሎ
አይኖቹን ያንከራትታል
"እግሬ ለወደፊቱም መራመድ ባይችልስ?"
በድን እግሮቹን ለማንቀሳቀስ እየሞከረ
በፊት ልጅ እያለ ከጉዋደኞቹ ጋር እሩጫ ሲወዳደሩ አንደኛ እንደሚወጣ አስታዉሶ ፈገግ አለ ወደ አሁኑ ያለበት ህይወት ሲያስብ ግን እንባ እና ተስፋ መቁረጥ
ስለሚከቡት ላለማሰብ በብርድ ልብሱ ተጠቅልሎ ተኛ።

ቤዛዊት ብቻዋን እንድትሄድ ቤተሰቦቿ አልፈቀዱላትም ነበር
እህቷ አብራት ነበረች የተኛበትን አልጋም ስለምታዉቀዉ ልታሳያት ተከተለቻት።

ከቦታዉ ደርሰዉ አልጋዉ አጠገብ ቆሙ ተጠቅልሎ የተኛ አካል
በብርድ ልብሱ ቅርፅ ሰርቶ ይታያል ፍፁምን ለማየት የጓጓችዉ
ቤዛዊት እንዲነሳ እግሩን በእጆቿ ነካ ነካ ነረገችዉ አልሰማ አላት

"ፍ ፁ ም ..."

እህቷ የፍፁም እግሮች እንደማይሰሩ እንደማይሰሙ
ብታዉቅም ለመንገር ግን
ከብዷት እህቷ የምታረገዉን በሀዘኔታ ታያለች።

"ፍ ፁ ም ፍፁም..."

የሚሉ ቃላቶች የእዉነት እየሆኑ በቅዠት መልክ ስለተሰሙት
አቤት ለማለት አይኖቹን ከፍቶ ከብርድ ልብሱ ተገለጠ
ፊት ለፊቱ ቤዛዊት ቆማለች የጠቆረች የከሳች የተጎዳች መሰለዉ
ለማማተብ የዘረጋዉን እጁን አይኑን ባለማመን ጠራረገበት
እሷ ፊት ላይ ለስለስ ያለ ፈገግታ እየታየ ቀረበችዉ
ወደ ጉንጮቹ ከመጠጋቷ በፊት እህቷን አየት አርጋት ሳመችዉ
እህቷም ስለገባት እንዲያወሩ ጥላቸዉ ወደ ዉጪ ወጣች
የደረቀ እና የተጣበቀ ከንፈሩን እያለያየ
"እንዴት ነሽ ቤዚ..."
"ደህና ነኝ አንተስ አልተጎዳክም አደል ..."
በእጆቿ እየደባበሰችዉ
"ምንም አልተጎዳሁም..."
ህመሙን ዋጥ እያረገ እሷ ስለመጣች ደስ እያለዉ
ፊቷን አተኩሮ እያየ ፈግታዋ እንደድሮዋ አልደምቅልህ አለዉ
ደህንነቷ አሰጋዉ ጠፍታ ነበር የተባለዉን አስታዉሶ ልጠይቃት
አልጠይቃት እያለ በዉስጡ ማሰብ ጀመረ።

በእስዋ በኩልም ፍፁምን ታሞ አልጋ ላይ ስታየዉ ዉስጧ እርብሽ ብሏል ከትምህርት ቤት እንደተባረረ ወሬ
ስለሰማች በእሷ ምክንያት መሆኑን ገምታለች
የተገጨዉም ይሄኔ እኔን ለማዋራት ትምህርት ቤት ሲመጣ
ነዉ እያለች ሁለቱም በራሳቸዉ ሀሳብ ሰምጠዉ ቆይተዉ
"ቀሚስሽ ደሞ እንዴት ያምራል .."
ጨዋታ ለመጀመር አስቦ ለየት ስላለበት አለባበሷ
"የእማማ ስንቄ ነዉ እንዴት ጥሩ ሰዉ መሰሉክ የሆነ ቀን አብረን ሄደን አስተዋዉቅሀለዉ..."
መራመድ እንደማይችል ትዝ ስላለዉ ማዉራት እየከበደዉ
በመስማማት አንገቱን ነቀነቀ
"ምግብ በልተሀል ለምን ከአልጋ ወርደህ አትቀመጥም "
ፈጠን ያለ ጥያቄ ጠየቀችዉ
"በልቻለሁ.."
ተስፋ በቆረጠ አነጋገር
ቤዛዊት መቀመጥ ብቻ ሳይሆን ተነስቶ ተቃቅፈዉ
የሆድ የሆዳቸዉን እያወሩ ከሚጨንቀዉ ሆስፒታል
ፍፁምን ይዛዉ ብትወጣ ደስታዋ ነዉ
ነገር ግን ፍፁም መንቀሳቀስ የፈለገ አልመሰላትም
"ተቀይመሀኛል እንዴ መጥቼ ስላልጠየኩህ"
ከንፈሯን እያጣመመች
"አረ አልተቀየምኩሽም"
እጆቹን ሰዶ እጆን ያዛት
"እሺ ተነስ..."
አይኖቹን እስዋ ላይ ተክሎ እግሮቹን ለማንቀሳቀስ መታገል ጀመረ
"እ ህ ..........አ"
እየከበደዉ እልህ እየተናነቀዉ በእጆቹ ታግዞ
አልጋዉ ጠርዝ ላይ በመከራ ተቀመጠ
ቤዛዊት ግራ ተጋብታ እያየችዉ ነዉ ልታግዘዉ እየሞከረች
እንዳትረዳዉ በእጆቹ ምልክት ስላሳያት ፈዛ በሀዘኔታ ታየዋለች
በደንብ አልተሻለዉም በማለት እንባዋን ለመቆጣጠር እየታገለች
ከጀርባዋ ያለዉን ዊልቸር እየጠቆማት
"እሱን ጠጋ አርጊልኝ"
አዘዛት
ላለ ማልቀስ እየታገለች አስጠጋችለት ከአልጋዉ ወርዶ
ዊልቸሩ ላይ ሊቀመጥ ሲል ግን
የዊልቸሩ ጎማወች ስለሚንቀሳቀሱ ለመቀመጥ ሲታገል
ሚዛኑን ሳቶ ከመዉደቅ ቤዛዊት በእጆቿ ደግፋ አተረፈችዉ
ተደናግጠዉ ተያዩ ወድያዉ እንዲቀመጥ ካገዘችዉ በኋላ መሳቅ ጀመሩ።

የቤዛዊት እህት ተመልሳ ወደ ፍፁም እና ቤዛዊት ተጠጋች
ልብ አላሏትም ሁለቱም የሞቀ ጨዋታ ላይ ናቸዉ
እስከ አሁን ይነግራታል ብላ በማሰብ
"እግርህ አሁን ለዉጥ አለዉ..."
ወሬያቸዉን አቋርጠዉ ተመለከቷት
"ጥሩ ነዉ ለዉጥ አለዉ "
አላት እና ፈገግ አለ ቤዛዊት ባትኖር መዉደቁ እንደ ነበር
እያስታወሰ የቤዛዊት እህትም ፊቱ ላይ ፈገግታ ስታይ ሳቀች
ፈገግታዋ ከቤዛዊት ጋር ይመሳሰላል ፍፁም ተገርሞ አያት በልቡ
"ቁጭ ቤዛዊትን" እያለ
ቤዛዊት የእህቷን አሳሳቅ አልወደደችዉም ደስ አላላትም
ዉስጧ ንዴት እየተቀጣጠለ ነዉ ህመሟ መንስኤ ነዉ የሚፈልገዉ
በተለይ የፍፁምንም እህቷን እያየ መሳቁን ስታይ
"እገላታለሁ"
ስትል በታመዉ ህሊናዋ እህቷ ላይ ዛተች።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍5
​​#ልጩህበት!!


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#ድርሰት_በጥላሁን

ምኑን ከምኑ ነው እምመርጠው?
"ወይ ኤደንን እኔ ሄጄ እንዳናግራት መፍቀድ ካልሆነ ከልጅቷ ጋር ፍቅር ጀምረህ ኤደንን መርሳት!"
ጆሲ አምርሯል ግራ ገባኝ ። ኤዱን እንዲያናግራት በጭራሽ እንደማልፈልግ አውቃለሁ ሁለተኛው ምርጫ ደግሞ ጡጫ ሆነብኝ ቢሆንም•••
ውስጤ እንደማይሆን እያወቀው ከዳኒ ጭቅጭቅ ለመገላገል ስል •እሺ አልኩት
በቃ እሺ!
"በቃ እሺ ምን በየትኛው ሀሳብ?"
"በቃ ካልካት ልጅ ጋር እንቀራረባለና!"
አዋ ዳንዬ አንዳንዴ እንኳን እንደዚህ እሺ በለኝ እስቲ ዳንዬ ዋናው መቀራረባችሁ ነው ከዛ ቡሀላ ሌላው ይከተላል ኤዱንስ ቢሆን ሳትቀርባት አላፈቀርካት!"
እሺ አልኩህ እኮ በቃ አልኩት። ከዛች ሰአት ጀምሮ ጆሲ ስራውን ጀመረ ።
ልጅቷን እቤት ያመጣትና መጣሁ ብሎ በመውጣት ጥሎን ይጠፋል።
መቀራረብ ብንጀምርም እውነቱን ለመናገር እሷን ለብቻዋ ከማገኛት ይልቅ ኤዱን ከልጁ ጋር ሆና ባገኛት እመርጥ ነበር።

ለሶስት ወር ልጅቷ እና ጆሲ ስራ አደረጉኝ የተቀየረ ስሜት አልነበረም በመሀል ድንገት ለተከታታይ ቀናት ጥፍት አለች።
ለስድስት ቀን ያህል ድምጿንም ስልኳንም አጥፍታ ከተሰወረች ቡሀላ በሰባተኛው ቀን እኔና ጆሲ ሰፈር ውስጥ ቁጭ ባልንበት እራሷ ጆሲ ስልክ ላይ ደወለች።
ስልኩን ለሁለታችንም እንዲሰማ አደረገና •••
" ምን ሆነሽ ነው የጠፋሽው?" የጆሲ ጥያቄ ነበር
" ምን ላድርግ ጓደኛህ ኤደን የምትባል ሰይጣን አጠናፍራዋለች መሰለኝ በተገናኘን ቁጥር ወሬው ሁሉ ከሷ አያልፍም እንዴ እኔ ልጅቷን ሳላውቃት ሁላ እንድጠላት ነው ያደርገኝ በጣም ነው የተጎዳሁት ጆሲ ከቻልክ ጓደኛህን ወይ አሳክመው ወይ ፀበል ውሰደው " ብላው እርፍ አለች ።

ጆሲ ዘወር ብሎ ሲያፈጥምኝ ተነስቼ ካጠገቡ ሄድኩ።
ከዛን ቀን ቡሀላ ከጆሲ ጋር ስለምንም ነገር ሳናወራ የኤዱ ምርቃት ሰባት ቀን( ሳምንት) ቀረው ።
ስድስት ቀን ሲቀረው ደውላ ቤተሰቦቿ ለምርቃቷ ከሁለት ቀን ቡሀላ እንደሚመጡ እና ከምርቃቷ ቡሀላ አብራቸው ወደ አዲስ አበባ እንደምትሄድ ነገረችኝ ።
ይህ ንግግሯ መብረቅ በሉት ለኔ ።ጨነቀኝ ።
ያን ቀን ጠጥቼ ብገባም እንቅልፍ እንቢ አለኝ እኩለ ለሊት ላይ አንድ ሀሰብ መጣልኝ።
ተነስቼ ለኤዱ ደብዳቤ መፃፍ ጀመርኩ•••
••••• ለኤደን
ኤዱዬ ህይወትን መራራም ጣፋጭም እንድትሆን ካደረጓት ምክንያቶች አንዱ ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ?
እኛ ሰዎች ስላለፈው እና ስለ አሁኑ እንጂ ነገ ምን እንደሚፈጠር እለማወቃችን ነው ።
ነገን አለማወቅ የራሱ የሆነ ብዙ ጥሩም መጥፎም ገፅታዎች አሉት።
ነገ የሚከሰተውን መጥፎ ነገር ቀድመን ስናውቅ እና ነገ የሚከሰተውን ጥሩ ነገር ቀድመን ስናውቅ የሚሰሙን ሁለት ተቃራኒ ስሜቶች ናቸው።
እንዲህ ያልኩሽ አሁን የሆንኩትን ነገር ያኔ በዛ በብርድ እዛ ሆቴል በር ላይ ቆመሽ ባየሁሽ ሰአት ቀድሜ ባውቀው ምን እወስን ነበር ብዬ ሁሌም እራሴን ስለምጠይቀው ነው
"አሁን ምን ሆንክ? ትይ ይሆኖል። ምንም አታውቂምና ጥያቄሽ ልክ ነው የኔ ስስት ያኔ ካሁን ቡሀላ ወንድምሽ ነኝ ስልሽ አንቺም ተቀብለሽ የእውነት ወንድም አድርገሽኛልና ምን ሆንክ ብትይኝ ባንቺ አይፈረድም እኔ ግን ብዙ ሆኛለሁ አንቺን በማፍቀሬ እንኳን አንቺ እኔ እንኳን የማላውቀው ሌላ ዳኒ እንደሆኑኩ አውቃለሁ።
ኤዱዬ አፈቅርሻለሁ!
ይህን ስታነቢ ምን ትይኝ ይሆን?
በቃሌ የማልገኝ እራስ ወዳድ ነኝ አደል ኤዱዬ?
በጣም ይቅርታ።
ከግዜ ቡሀላ ለኔም ባልገባኝ መንገድ ውስጤ ተቀያይሮ ካቅሜ በላይ ሆኖብኝ እንጂ ያኔ ወንድም እሆንሻለሁ ከጎንሽ ነኝ እንደወንድምሽ እይኝ ያልኩሽ ግን ከልቤ ነበር!።
ሁሌም ቃሌን ያጠፍኩ መስሎ ይሰማኛል ላንቺ ስላልነገርኩሽ ምንም ባትይኝም ብታውቅ ምን ትለኛለች እያልኩ ከመሸማቀቅ አልዳንኩም።
ፍቅር የሻቱትን ማግኘት ብቻ አይደለምና የኔ እንደማትሆኚ እያሰብኩም አፈቅርሻለሁ።
ከምንም ነገር በላይ አንቺን በእውኔም በህልሜም ማየት፣ ስላንቺ ማሰብ ፣ ስላንቺ ማውራት ያስደስተኛል ። ካንቺ ውጪ ሁሉ ነገር አልጥምህ ካለኝ ወራቶች ተቆጥረዋል።
"ታድያ በነበረን ግዜ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ከነበርክ እንዴት አልነገርከኝም?
ወይም እንዴት ከፊትህ መረዳት አልቻልኩም? " ትይኝ ይሆናል
በፍቅር ንዳድ ከመለብለብ በላይ በልብ ውስጥ ያለውን የፍቅር እሳት አውጥቶ ላፈቀሩት ሰው ንዳዱን ማሳየት ለብዙ አፍቃሪዎች ከባድ ነው።
እኔን ግን አውጥቶ ከመናገሩም በላይ ከባድ የሆነብኝ ብነግርሽ የሚሰማሽን ስሜት ማሰብ ነው።
ፍቅረኛሽ ሆኜ ቢሆን አሁን ወንድምሽ በመሆኔ የተደሰትሽውን ያክል እምትደሰቺ መስሎ አይታየኝም ።
ካፌ ሻይ ቡና እያልን ፊት ለፊቴ ቁጭ ብለሽ ከናት ካባቴ ባትወለድም አንተን የመሰለ ወንድም በስጦታ ስለሰጠኝ እያልሽ ፈጣሪን ስታመሰግኚ ስሰማ እንኳን ልነግርሽ ማፍቀሬን የምታውቂብኝ እየመሰለኝ ምክንያት ፈጥሬ ካጠገብሽ እሽሻለሁ ።
ጆሲ ጓደኛዬ ምን እንደሚለኝ ታውቂያለሽ ኤዱዬ?
••••" አንተኮ መፍታት ያቃተህ መጀመሪያ ላይ እራስህ አጥብቀህ ያሰርከውን ቋጠሮ ነው አልፈታ ባለህ ቁጥር ደግሞ በንዴት ለመበጠስ እየሞከርክ የበለጠ ታጠብቀዋለህ!" ይለኛል
እውነቱን ነው ትዝ ይልሻል እዱዬ?
ስለመሲ ስናወራ አንድ ሰው ውለታ ውሎልሽ ውለታውን በመንተራስ ከፍላጎትሽ ውጪ የሚጫንሽ ከሆነ ውለታ ሳያስቀድም ተመሳሳይ ጥያቄ ከሚጠይቅሽ ሰው በላይ እርኩስ ነው ብዬሽ ነበር ።
እኔም የፍቅር ጥያቄዬ ካደረኩልሽ ትንሽ ውለታ ጋር እንዳይያያዝብኝ ፈራሁ።
አንቺንም እኔን ወንድም እንጂ ፍቅረኛ የማድረግ ፍላጎት ውስጥሽ ሳይኖር የምጫንሽ ጥያቄዬን ባለመቀበልና እኔን ባለማስከፋት መሀል ሆነሽ የምትጨነቂ መስሎ ታየኝ ።
በዚህ መሀል እናንተ ባታዩኝም ከልጁ ጋር ሆኖችሁ ብዙ ቦታዎች ታጋጥሙኝ ጀመር።
ያኔ በሱም ባንቺም ሳይሆን በራሴ ይበልጥ መናደድ ጀመርኩ ።
ህመምህ መድሀኒት የለውም አትድንም እንደተባለ በሽተኛ የፍቅር ህመሜ ፈውስ የሆንሽውን አንቺን የኔ እንደማላደርግሽ ተረዳሁ ።
ኤዱዬ በመመረቅሽ እንኳን ደስ አለሽ!
በመመረቅሽ የተሰማሽን ደስታ ትንሽ ሳታጣጥሚውና ከድሬ ሳትወጪ አንብበሽው ሌላ ስሜት ውስጥ እንድትገቢ ስላልፈለኩ ነው ይህን ደብዳቤ በእጅሽ ሳልሰጥሽ ከምርቃቷ ቡሀላ ወደ አዲስ አባባ ስሸኛት ሳታየኝ የልብስ ሻንጣዋ ውስጥ አስቀምጥላታለሁ ባየችው ግዜ ትየው ብዬ የወሰንኩት።
በነበረን ስሜት ወንድምሽ ሆኜ ልሸኝሽ ቀናቶች ቀርተዋል ለዛም ተዘጋጅቻለሁ ።
የኔ ኤደን ዛሬም ቢሆን ስላወኩሽ ደስተኛ ነኝ።
የማንም ሁኚ እኔ ግን አፈቅርሻለሁ። መቼም ቢሆን አረሳሽም። ዝምምምም ብዬ ሳፈቅርሽ እኖራለሁ።
ሰላም ሁኚ!
ዳኒ ነኝ።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍3
#ለኀጥአን_የመጣ

#ክፍል_ሀያ_ሶስት(የመጨረሻ ክፍል)

#የታዳጊው_ወታደር_ትዝታ

#በኢስማኤል_ቤህ

#ክፍለእየሱስ_አበበ_እንደተረጎመው


አስር ስዓት ሲሆን አውቶብሱ ካምቢያ ከምትባል ከተማ አደረሰን። የመጨረሻ ፌርማታው ነበር። ፍሪ ታውንን ለቀን
ከመጣን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳፋሪዎቹ ፊት ተፈታ። ግን ብዙም አልቆየም! ድንበር ለማለፍ ክፍያ ስንጠየቅ የሁሉም ፊት መልሶ ተኮማተረ አጉረመረምን፡፡ ሁሉም ሰው ከካልሲው
ውስጥ፣ ከውስጥ ሱሪ እና ከረባት ሳይቀር የተረፈ ገንዘብ ካለ ፈለገ። ሶስት መቶ ሊዮንስ (የሴራሊዮን ገንዘብ) ነበር
የተጠየቅነው:: አንድ ሰው ከገዛ ሃገር ለቆ ለመውጣት ለምንድን ነው ሚከፍለው? አሰብኩ ግን መከራከር አልችልም:: ከፈልኩ:: የይለፍ ወረቀቱ ላይ ማህተም እንደተደረገልኝ ወዲያው ወደ ጊኒ
ደንበር ተሻገርኩ። ዋና ከተማዋ ኮናክሪ ለመድረስ ደግሞ ገና ብዙ መንገድ ይቀረኛል። ወደ ከተማው የሚወስድ አውቶብስ ለማግኘት ቶሎ ቶሎ መራመድ ጀመርኩ። ጊኒ ውስጥ የሚነገር
የትኛውንም ቋንቋ መናገር አልችልም ምን ማድረግ እንዳለብኝም አላሰብኩበትም ነበር። ትንሽ አስጨነቀኝ ግን ከሃገሬ በህይወት መውጣቴ ትልቅ ነገር ነው::
ኮናክሪ የሚሄድ አውቶብሶች የጊኒ ወታደሮች ባቆሟቸው ኬላዎች በኩል ነበር የሚቆሙት፡፡ በኬላዎቹ ተጠግተው
በፈለጉት መጠን የጊኒን ገንዘብ የሚመነዝሩ ሰዎች ነበሩ።

ወታደሮቹ ይሄን ጥቁር ገበያ የሚከላከሉ መስሎኝ ነበር ግን ግድ አይሰጣቸውም:: ገንዘቤን ቀይሬ ወደ ኬላው ተጠጋሁ። ደንበሩ ላይ ያሉ ወታደሮች ወይ እንግሊዝኛ መናገር አይችሉም ወይ
ደግሞ እንደሚችሉ ማሳወቅ አይፈልጉም:: መሳሪያቸውን ብቻ
በተጠንቀቅ ይዘዋል፡፡ ቀና ብየ ማየት አልፈለኩም። ከዚህ በፊት ወታደር እንደነበርኩ እና አሁን ግን ትቼው እሸሸሁ መሆኑን ማሳበቅ አልፈለኩም::

አውቶብሱን ለማግኘት ጥቁር ቡናማ የሆኑ የጣውላ ቤቶችን ማለፍ ነበረብኝ። ውስጥ ወታደሮች የሰዎችን ሻንጣ ይበረብራሉ።ሰዎች ደግሞ መረጃዎቻቸውን ለሃላፊዎች ያሳያሉ። የእኔ ተራ ሲደርስ ወታደሮቹ ሻንጣየን ከፍተው በውስ ጡ ያለውን ሁሉ መሬት ላይ ዘረገፉት። ብዙ እቃ ስላልነበረኝ ለመሰብሰብ እና መልሶ ለመክተት ብዙም አያስቸግርም፡፡ ሁለት ቲ ሸርት፣ ሁለት
ዉስጥ ሱሪ እና ሶስት ጥንድ ሱሪዎች ብቻ ነበሩ::

ከጣውላ ቤቱ ስወጣ መረጃዎቼን ማሳየት ነበረብኝ፡፡ ብዙ ጠረጴዛዎቹ እና ወታደሮች ደግሞ የማንጎ ዛፍ ስር ነበሩ።
መሳሪዎቻቸው ወንበራቸው ላይ ወይም የአንዳንዶቹ ጠረጴዛዎቹ ላይ ተቀምጦ ነበር፡፡ ለማን ማሳየት እንዳለብኝ
አላውቅም::

አንድ ወታደር ወደ እሱ እንደሄድ ምልክት አሳየኝ። እጁን ዘረጋ እና የይለፍ ወረቀቴን ተቀበለኝ። ወታደሩ በማይገባኝ አንድ
ቋንቋ ተናገረ።የይለፍ ወረቀቴን የደረት ኪሱ ውስጥ አስገባው እና እጁን ጠረጴዛ አድርጎ አትኩሮ ተመለከተኝ። አቀረቀርኩ
ወታደሩ አገጩን ቀና አደረገኝ፡፡ የይለፍ ወረቀቴን ከኪሱ አውጥቶ መረመረ። አይኑ ቀላ ፊቱ ላይ ፈገግታ ይታይ ነበር።
እጁን አጥፎ ተደላድሎ ተቀመጠ። ፈገግ አልኩ እሱም ሳቀ።በቋንቋው የሆነ ነገር አለና እጁን እንደገና ጠረጴዛው ላይ አደረገ።ፈገግታው እየጠፋ ሄደ፡፡ የተወሰነ ገንዘብ እጁ ላይ አስቀመጥኩ።
የይለፍ ወረቀቴን ከኪሱ አውጥቶ ሰጠኝ እና በሩ እንዳልፍ ጠቆመኝ፡፡

ብዙ አውቶብሶች ስለነበሩ ወደ ኮናክሪ ለመሄድ አውቶብስ መያዝ እንዳለብኝ አላውቅም ግራ ገባኝ፡፡ ሰዎችን ለመጠየቅ ብሞክርም ማንም ሊረዳኝ አልቻለም:: የማውቀው ፈረንሳይኛ
ቃል bonjour ቦንጁር ብቻ ነበር፡፡

ግራ ገብቶኝ ቁሜያለሁ አንድ አልፎ ሂያጅ በኪሮ ቋንቋ ሲያጉረመርም ሰማሁትና “ ጤና ይስጥልኝ” ብየ ወደ ኮናክሪ
የሚወስደው አውቶብስ የትኛው እንደሆነ ጠየቅኩት። እሱም ወደ ዛው እንደሚጓዝ ነገረኝ እና ወደ ከአፍ እስከ ገደፉ ጢም
ብሎ የሞላ አውቶብስ ውስጥ ገባን፡፡ በየ ሃምሳ ሜትሩ ወደ አስራ አምስት የሚጠጉ ኬላዎች ላይ ወታደሮች ነበሩ እና ወታደሮቹ ምህረት የለሽ ነበሩ። ወታደሮቹ መክፈል የማችሉትን እየደበደቡ
ከአውቶብሱ ያወርዷቸዋል። እኔ ግን እድለኛ ነበርኩ። ከአጠገቤ የነበረው ሰውየ ልጅ ስለመሰልኳቸው ብዙ ኬላዎችን በነፃ አልፌያለሁ። የእሱን መረጃ ያያሉ እና የሁለታችንንም እሱን
ያስከፍላሉ፡፡ ሰውየው የገባው አይመስለኝም:: ገንዘብ ጉዳዩ አይደለም ኮናክሪ መግባት ብቻ ነበር የሚፈልገው:: የመግቢያ ክፍያው ሶስት መቶ ሊዮንስ እንደሆነ ሰዎች ሲያወሩ ሰማሁ።
መቶ ሊዮንስ ብቻ ነበር የቀረኝ፡፡ ምንድን ነው ማደርገው? ብየ ማሰብ ጀመርኩ። ይሄ ሁሉ መንገድ የመጣሁት ለከንቱ ነው? ወደ ፍሪ ታውን መመለስ እንኳ ብፈልግ የምመለስበት ገንዘብ የለኝም:: አይኖቼ እንባ አቀረሩ። ተረበሽኩ ከዚህ መውጫ መንገዱ አልታይህ አለኝ፡፡ አንድ የይለፍ ወረቀቱ የተመታለት ሰው ከኬላ ወደ አውቶብስ ሲመለስ ሻንጣውን ጥሎ አየሁ። የተወሰነ ካመነታሁ በኋላ እድሉን ልጠቀምበት ወሰንኩ። ሰልፉን ትቼ ሻንጣውን ይዤ ተከልኩት:: አውቶብስ ውስጥ ገብቼ መጨረሻ ወንበር ላይ ተደብቄ ተቀመጥኩ። አውቶብሱ ቀስ ብሎ ከወጣ በኋላ ፍጥነቱን ጨመረ። በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሃገሪቱ
ገባሁ በኋላ ግን ችግር ይሆናል፡፡

አውቶብሱ ወደ ኮናክሪ ሲደርስ መጨነቅ ጀመርኩ። ከደረስኩ በኋላ ምን እንደማደርግ አላውቅም:: የሴራሊዮን አምባሳደር ስደተኞች በጊዜዊነት ግቢው ውስጥ እንደሚያሳድር ሰምቻለሁ
ግን ኢምባሲው የት እንደሆነ እንኳ አላውቅም:: ጃሎህ ከሚባል
ፉላኒ በምዕራብ አፍሪካ የሚገኝ አርብቶ አደር ጎሳ) ጋር ነበር የተቀመጥኩት። ጃሎህ ፍሪ ታውን እንደኖረ ነገረኝ፡፡ ስለ ጦርነቱ እና በሃገሪቱ ላይ ስላስከተለው ጉዳት አወራን። በኋላ ስልክ ቁጥሩን ሰጠኝ እና ከተማዋን ስንቀሳቀስ እርዳታ ካስፈለገኝ እንድደውልለት ነገረኝ። ማደሪያ እንደሌለኝ ልነግረው ፈለኩ ግን
ቀድሞኝ ወረደ። አብሮኝ የመጣውን ሴራ ሊዮናዊ ፈለኩ ግን ላገኘው አልቻልኩም። ከደቂቃዎች በኋላ አውቶብሱ ግዙፍ
መናሃሪያ ውስጥ ገባ። ወጥቼ ሁሉም ሲሄድ ተመለከትኩ። ተነፈስኩ እና እጆቼ ራሴ ላይ ጭኜ ወደ አግድም ወንበር ሂጄ
ተቀመጥኩ። ፊቴን በእጆቼ ሸፍኜ “ለሊቱን ሙሉ ከዚህ መቀመጥ አልችልም” ብየ ለራሴ አጉረመረምኩ።

ብዙ ታክሲዎች ነበሩ እና አውቶብሱ መናሃሪያ የደረሱ ሰዎች ሁሉ ይዟቸዎል። እኔም ብቸኛ ሚሄድበት የጠፋው እንግዳ
መስየ መታየት ስላልፈለኩ አንዱ
ታክሲ ውስጥ ገባሁ። ሹፌሩ በፈረንሳይኛ ሲናገር ወዴት እንደምሄድ እየጠቀኝ እንደሆነ ገመትኩ። ሴራ ሊዮን ቆንስላ አ ኢምባሲ” ብየ ነገርኩት።በመስኮት ስመለከት የመብራት ምሶሶዎች ላይ የመንገድ መብራቶቹ ተንበርግገው
ተንጠልጥለዋል። ብርሃናቸው ከጨረቃ ብርሃን ሳይበልጥ አይቀርም። ታክሲው ኢምባሲው ፊት ለፊት ቆመ እና የምፈልገው ቦታ ይዞኝ እንደመጣ
ለማረጋገጥ ወደ አረንጓዴ፣ ነጭ እና ሰማያዊ ባንዴራ ጠቆመኝ፡፡ራሴን በማወዛወዝ ትክክል እንደሆነ ከገለፅኩለት በኋላ ከታክሲው ወረድኩ
በኤንባሲው በር ላይ ጠባቂዎቹ በኪሪዎ የይለፍ ወረቀቴን እንዳሳይ ጠየቁኝ፡፡ አሳየኋቸው እና ወደ ግቢው እንድገባ ፈቀዱልኝ::

በግቢው ውስጥ ከሃምሳ በላይ ሰዎች ሲኖሩ እንደእኔ መጠጊያ ያጡ ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡ አብዛኖቹ ትራስ ብቻ አድርገው ተጋድመዋል። ጓዛቸውን ወይም ሻንጣቸውን ከጎናቸው አስቀምጠዋል። ሰዎቹ ማታ ማታ ከዚህ የሚያድሩ ሲሆን ቀን ቀን ወደ ውጭ ይወጣሉ። ጥግ ላይ ቦታ አገኘሁ እና መሬት ተቀምጨ ጀርባየን ወደ ግድግዳው አስጠጋሁ። ስዎቹን ሳይ
ከጦርነቱ ለማምለጥ ያለፍኩባቸው ሰፈሮች ትዝ አሉኝ።
#የታካሚው_ማስታወሻ


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#ድርሰት_በመለሰ_ታዬ (MD)

“ወደ ዚህ ስትመጣ የመጀመሪያህ ነው?”

“አዎ።”

“ትቆያለህ?”

ሳምንት አካባቢ።”

“እዚያ ማዶ ሚታየው አፄ ዮሐንስ አንገታቸው የተቀላበት ቦታ ነው።” እጁን ከመንገዱ በላይ እየጠቆመ::

“መተማ ዮሐንስ ደረስን ማለት ነው?”

“አዎ፡፡ አሁን ገብተናል፡፡” ልቤ ድንግጥ ድንግጥ አለብኝ፡፡ ሚኒባሱ እየቆመ፣ ሰዎችን ያወርዳል። እስከዛሬ ያልተሰማኝ ፍርሀት እየተሰማኝ ነው፡፡ ዝም አልኩ፡፡ ወደ ስንብት እየተጠጋሁ ነው፡፡
የማውራትም የማወቅም ፍላጎት የለኝም፡፡ ዝም ብዬ በዐይኔ ከተማውን መፈለግ ጀምረኩ፡፡ በግራና በቀኝ የተደረደሩ የጭቃ ቤቶች፣ ጭር ያለ ከተማ ነው፡፡ እንደጠበኩት ግርግር የበዛበት ከተማ አይደለም፡፡ ሰዐቴን አየሁ፤ አስር ተኩል፡፡ አብዛኛው ሰው ወርዶ አልቋል፡፡

“መናኸሪያ ትገባለህ?” ወያላው ፊቱን አዙሮ ጠየቀኝ፡፡

“አይ አልገባም፡፡”

“ካልገባህ መጨረሻው እዚህ ነው።”

“እሺ አውርደኝ!”

በጭራሽ እንደገመትኩት አይደለም፡፡ ለማደሪያ ሚሆን አልጋ ቤት እንኳን እስካሁን አላየሁም፡፡ ከተማዋ ትሞቃለች። አስራ አንድ ሰዓት እየሆነ ቢሆንም፣ በጣም ይወብቃል፡፡ ፍርሀት ነው መሰል፣ በጣም እያላበኝ ነው። ዝም ብዬ ዋና መንገዱን ይዤ፣ አልጋ ቤት ፍለጋ
ተጓዝኩኝ፡፡ ነጋዴ የሚርመሰመስበት፣ አዲስ ሰው፣ ፀጉረ ልውጥ ሰው
ከዐይን የማይገባበት ብዬ የገመትኩት ከተማ፣ ትንሽዬ መንደር ሆና አገኘኋት፡፡ መንገድ ዳር በብሎኬት የታጠረ ሰፊ ግቢ ያለው ሆቴል አየሁ፡፡ ሰላም ሆቴል ይላል፡፡ አላንገራገርኩም፡፡ ዘው ብዬ ገባሁ፡፡ ብቻ
አልጋ በኖረ፡፡

“አልጋ አለ?”

“አለ፡፡”

“እስቲ አሳዩኝ?”

“ባለሻወር ነው፣ ያለሻወር?”

“ባለሻወር፡፡” ቁልፍ አመጣችና አሳየችኝ፡፡

“ስንት ነው?”

“አንድ መቶ ሃምሳ ብር፡፡” ብሩን ሰጠኋትና ቦርሳዬን አስቀመጥኩ።

ሻወር ቤት ገብቼ ሻወር ቼክ ሳደርግ ውሀ የለችም፡፡ ዞር ስል፣ውሀ በባልዲ ተቀምጧል፡፡ በጣም አልቦኛል፣ ተለቃለኩኝ፡፡ እራት በልቼ ቢራ መጠጣት ጀመርኩ፡፡ ሙቀት ስለሆነ ተጠጣልኝ፡፡ ማታ ጥሩ እንቅልፍ ተኝቼ አደርኩ፡፡ ቀን ወጥቼ ከተማውን ዙሪያውን ሳይ ዋልኩ፡፡
በፍፁም እኔ እንዳሰብኩት አይደለም፡፡ የከተማው ዙሪያ ለጥ ያለ ለእርሻ የሚውል ሜዳ ሲሆን፣ ዛፎች በእርቀት ነው የሚገኙት፡፡ ስዞር ውዬ አመሻሹ ላይ፣ ቢራዬን እየጠጣሁ ምን እንደሚችል ሳስብ፣ አርሴማ ገዳም የሚል ሀሳብ መጣብኝ፡፡

#ኑሮ_በገዳም

ሽቅብ ዝግዛግ ሆኖ በተሰራውን የጥረጊያ መንገድረገ፣ በግራና በቀኝ በዛፎች ተከቧል፡፡ ከፊት ለፊቴ፣ አጠር ያለ ወጣት፣ የክርስቲያኖ ሮናልዶ ስዕል ያለበት ጥቁር የጨርቅ ሻንጣ በጀርባው ተሸክሞ በዝግታ ያዘግማል። እየተከታተልን ወደ ገዳሙ ዘልቀን ገባን። ከገዳሙ መግቢያ
በር ትንሽ ፈቅ ብላ ያለች የጭቃ ቤት ጋር ስንደርስ፤

“እንኳን ደህና መጣችሁ። ምዝገባ ቢጤ አለች።” አለን ፊቱ መጠጥ ያለ ጠይም ወጣት፡፡

“እሺ!” ብዬ ቆምኩኝ፡፡ ልጁን መዝግቦ ከጨርሰ በኋላ፣ ትንሽ ቆየኝ ብሎት እኔን መመዝግብ ጀመረ፡፡ ስም፣ እድሜ፣ የመጡበት አድራሻ፣ የአደጋ ግዜ ተጠሪ...፣ ሁሉንም ቀይሬ ነገርኩት፡፡

“ለስንት ግዜ ነው ሚቆዩት?”

“ለሦስት ሳምንት፡፡”

“መታወቂያ ይዘዋል?”

“አልያዝኩም፡፡” አልተጫነኝም፡፡
“እሺ፣ እንግዶቻችን፣ እኔ መልካሙ እባላለሁ፡፡ በገዳሙ አስተባባሪ ነኝ፡፡ አሁን ማደሪያ ቦታ እሰጣችኋለው፡፡ ገዳሙን
አስጎበኛችኋለው፤ ስለ ገዳሙ ታሪክ፣ መተዳደሪያ ደንብና ሌሎች መረጃዎችን እነግራችኋለው፡፡ እዚህ ገዳም፣ ማንኛውም አዲስ ሱባኤተኛ ሲገባ እናንተ እንዳደረጋችሁት ተመዝግቦ ነው፡፡ ገዳሙ የአርምሞ ገዳም ነው:: ማውራት ክልክል ነው፡፡ አስገዳጅ ነገር ካላጋጠማችሁ በስተቀር፣ ማውራት አይቻልም፡፡ የግድ ማውራት ካስፈለገ እንኳ፣ ዝግ ባለ ድምፅ፣ በለሆሳስ ነው ማውራት ሚቻለው፡፡ እዚህ መዳን የሚገኘው በአርምሞ ውስጥ ነው፡፡”

ከኛ ውጪ ለሌላ ሰው እንዳይሰማ፣ በሆዱ እንደሚያወራ፣ በጣም ዝግ ባለ ድምፅ ያወራናል፡፡ በአርምሞና በለሆሳስ ማለት እንዲህ ነው' ብዬ አሰብኩ፡፡ የሚያወራው እንዲሰማን፣ አንገታችንን ወደሱ አሰገግን፡፡ እያወራን ወደ ማደሪያችን ወሰደን፡፡ እያንዳንዱ ከሁለት መቶ ምዕመን በላይ የሚይዝ፣ አራት የማደሪያ አዳራሾች አሉ፡፡ ሁለቱ የወንድ፣ ሁለቱ የሴት እንደሆነ ነገረን፡፡ ቦታ ሊሰጠን ወደ አንደኛው አዳራሽ ይዞን ገባ፡፡ በውስጡ ከመቶ ሚበልጡ ምዕመናን አሉ፡፡አሰላሁት። በግምት በገዳሙ አንድ ሺህ የሚጠጉ ሱባኤያተኛ ምዕመናን
እንዳሉ ገመትኩኝ፡፡ ገዳሙ ግን ሰው ያለው አይመስልም፡፡ ዝም፣ ጭጭ፣ ያለ ነው፡፡ ሁሉም በለሆሳስ ፀሎት ላይ ነው፡፡ ሰላምታ እንኳ፣ ጎንበስ ቀና በመባባል ብቻ ነው፡፡ ምንም አይነት የሰው ድምፅ አይሰማም፡፡የወፎች ጭጭታና የዛፎች ሽው ሽውታ ብቻ ነው፡፡ በጣም ደስ ይላል፡፡መንፈስን ያድሳል፡፡ አዕምሮን ያረጋጋል፡፡ ፈውስ በመንፈስ ቅዱስ
ባይላክም እንኳ፣ የቦታው ድባብ ፈውስን ይሰጣል።

“እና ሌላው...” አለ መልካሙ ቦታችንን ሰጥቶን ከአዳራሹ ይዞን እየወጣ፣ “ማንኛውም ምእመን ወደ ገዳሙ ለሱባኤ ሲገባ፤ ፀጉሩን መላጨት፣ ንስሀ መግባትና ስግደት መውሰድ አለበት፡፡” አለን እኔን እኔን እየተመለከተ፡፡

“እሺ፡፡ ማን ነው ሚላጨን?”

“እርስ በእረስ ነው ምትለጫጩት፡፡ ፈራህ እንዴ..? አንተን እኔ ቆንጆ አድርጌ እላጭሃለው፡፡” የከተማ ልጅ መሆኔን አውቆ ነው መሰል፣ ከገባን ጀምሮ እኔን እኔን እየተመለከተ ነው ሲያወራ የነበረው፡፡

“እሺ” አልኩት፡፡ አሁን ስለራሴ ብዙም ግድ የለኝም፡፡ ምላጭ ግቢ ካለው ሱቅ ተገዝቶ ሁለታችንንም ላጨን፡፡ ነብስ ካወኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ፀጉሬን ተላጨሁ፡፡ እየላጨንም ስለ ገዳሙ መተዳደሪያ ደንብ ይነግረናል።

“በገዳሙ፣ በቀን ሁለት ጊዜ ብቻ ነው የሚበላው፡፡ ጥዋት ቅዳሴ እንዳለቀና ማታ አስራ ሁለት ሰዐት። አስራ ሁለት ሰዐት ካለፈ መመገብ አይቻልም፡፡ ገዳሙ መብራት ስለሌለው፣ ማታ ማታ ሻማ ነው
ምትጠቀሙት። ሻማ ከዚህ ሱቅ መግዛት ትችላላችሁ፡፡ የማታ ሦስት ሰዓት ፀሎት ካበቃ ቦሃላ ሻማ ማብራት አይቻልም፡፡ የእንቅልፍ ሰዓት ነው፡፡ እንዳያችሁት፣ የቦታ ጥበት ስላለ አንድ ሰው፣ በአንድ መዳበሪያ በታ ላይ ነው መተኛት ያለበት፡፡ የለሊቱ ዘጠኝ ሰአት ፀሎት ላይ ሁሉም
ምዕመን መገኘት ግዴታ ነው፡፡” ሁለታችንንም ላጭቶ ሲጨርስ አስራ
አንድ ሰዐት ሆኖ የሰርክ ፕሮግራም ተጀመረ።

“በሉ ተነሱ እንሂድ፣ የሚቸግራችሁ ነገር ካለ እዚሁ ስላለን በፈለጋችሁት ሰዓት ጠይቁኝ ፤ ” ብሎ ፕሮግራሙ ወደ ሚካሄድበት ስፍራ ወሰደን፡፡

የገዳም ኑሮዬ ተጀመረ፡፡ ለሊት ዘጠኝ ሰዓት መነሳት በጣም ከባድ ነው፡፡ ግን፣ አማራጭ የለም፡፡ አስተባባሪዎች እየዞሩ ይቀሰቅሳሉ።ያልተነሳ ሰው ላይ ቀዝቃዛ ውሃ ይረጫሉ፡፡ የመጀመሪያ ቀናቶች ላይ
በጣም ከበደኝ፡፡ ከእንቅልፍ ሳልነቃ ውሃ ሲረጩኝ እንደ ኤሌክትሪክ ይነዝረኛል፡፡ ሁለት ሦስት ቀን ሲደጋግሙኝ፣ ገና ድምፃቸውን ስሰማ መነሳት ጀመርኩ፡፡ ፀሎትና ምህላው እስከ ጥዋቱ አስራ ሁለት ሰዓት ይደረጋል፤ ከዛ ወደ ፀበል።

ገዳሙን ቅጥር ግቢ በደንብ ለማማወቅ እየተዟዟርኩ ማየት ጀመርኩ፡፡ የአርሴማ ገዳም በሃገራችን እንዳሉት አብዛኞቹ ገዳማት፣በተራራማ ቦታ ላይ ከየተመሰረተ ነው፡፡ የገዳሙ መስራችና አስተዳዳሪ
የሆኑት መነኩሴ፣ እድሜያቸው ሃምሳ ዓመት ቢሆን ነው፡፡ ገዳሙ በእውቀት እንዲለማ በደንብ አስበውበት እንደመሰረቱት ገዳሙ አፍ አውጥቶ ይናገራል፡፡ ከመሰረቱት
1👍1