#ፈገግታ_ነው_የሚቀድመኝ
የድሜ ነፋስ በገላየ ተረማምዶ ኮበለለ
ልቤን ክንዴን እያዛለ
ያቀፍኩትን እየቀማ፣ የያዝኩትን እያስጣለ።
እድል በኔ ጨከነ ስል፣ በምረት እጅ ደባበሰኝ
አንቺን ነጥቆ ከቅፌ ላይ፣ በትውስታ ደሞ ካሰኝ።
አስታወሰኝ
አስታወሰኝ
ወድያው ታይቶ፣ ጠፊ ኩርፍያሽ
ገራም ሳቅሽ፣ ልዝብ ልፍያሽ
ያለም ዘፋኝ የማያውቀው
የግልሽ ዳንስ ውዝዋዜ
ትውስ ትውስ ባለኝ ጊዜ
ከግር ጥፍሬ
እስከ ጠጉሬ
ደስታ ነው የሚያቀልመኝ
ያንቺን ነገር ባሰብሁ ቁጥር፣ ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ።
በሰጠሽኝ ጸጋ መጠን፣ የሰራሽኝ ጉድ አያልቅም
እኔ ባንች ትዝታ እንጂ፣ በተራቢ ቀልድ አልስቅም
ማፍቀር ማለት ለካ ፍቺው፣ መጃጃል ነው አውቆ ፈቅዶ
ከገደል ላይ መወርወር ነው፤ ተጨፍኖ በራስ ፈርዶ፡፡
እፈቀርኩሽ በየቀኑ፣ ተጃጃልሁኝ ደጋግሜ
ከገደል ላይ ተከስክሼ ፣ ሞተ ሲሉኝ አገግሜ
ያጥንቶቼን ርጋፌ እንደዛጎል ለቃቅሜ
እንደ ቆሎ፣ ጥርሴን ቅሜ
ያደረኩሽ ሲደንቀኝ፣ ያደረግሺኝ ሲገርመኝ
እፍረት ፀፀት አይደለም፡ ፈገታ ነው የሚቀድመኝ
አውቃለሁኝ ጊዜ ሂዷል፣ ታሪካችን ተጠቅልሏል።
በሄድንበት ጎዳና ላይ፤ የመለየት ዝናብ ጥሏል
በርምጃችን ምልክት ላይ፣ ረጃጅም ሰርዶ በቅሏል
ብቻ ሙሾ ቢደረደር፣ የሆነውን ላይለውጠው
ለንባየማ ፊት አልሰጠው።
ያሳሳምሽ ለዛ ቀርቶ፣ እንደ እንጎቻ እሚጥመኝ
የነከሽኝ የቧጨርሽኝ፣ አገርሽቶ ቁስሉ ሲያመኝ
ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ!!
🔘በእውቀቱ ስዩም🔘
የድሜ ነፋስ በገላየ ተረማምዶ ኮበለለ
ልቤን ክንዴን እያዛለ
ያቀፍኩትን እየቀማ፣ የያዝኩትን እያስጣለ።
እድል በኔ ጨከነ ስል፣ በምረት እጅ ደባበሰኝ
አንቺን ነጥቆ ከቅፌ ላይ፣ በትውስታ ደሞ ካሰኝ።
አስታወሰኝ
አስታወሰኝ
ወድያው ታይቶ፣ ጠፊ ኩርፍያሽ
ገራም ሳቅሽ፣ ልዝብ ልፍያሽ
ያለም ዘፋኝ የማያውቀው
የግልሽ ዳንስ ውዝዋዜ
ትውስ ትውስ ባለኝ ጊዜ
ከግር ጥፍሬ
እስከ ጠጉሬ
ደስታ ነው የሚያቀልመኝ
ያንቺን ነገር ባሰብሁ ቁጥር፣ ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ።
በሰጠሽኝ ጸጋ መጠን፣ የሰራሽኝ ጉድ አያልቅም
እኔ ባንች ትዝታ እንጂ፣ በተራቢ ቀልድ አልስቅም
ማፍቀር ማለት ለካ ፍቺው፣ መጃጃል ነው አውቆ ፈቅዶ
ከገደል ላይ መወርወር ነው፤ ተጨፍኖ በራስ ፈርዶ፡፡
እፈቀርኩሽ በየቀኑ፣ ተጃጃልሁኝ ደጋግሜ
ከገደል ላይ ተከስክሼ ፣ ሞተ ሲሉኝ አገግሜ
ያጥንቶቼን ርጋፌ እንደዛጎል ለቃቅሜ
እንደ ቆሎ፣ ጥርሴን ቅሜ
ያደረኩሽ ሲደንቀኝ፣ ያደረግሺኝ ሲገርመኝ
እፍረት ፀፀት አይደለም፡ ፈገታ ነው የሚቀድመኝ
አውቃለሁኝ ጊዜ ሂዷል፣ ታሪካችን ተጠቅልሏል።
በሄድንበት ጎዳና ላይ፤ የመለየት ዝናብ ጥሏል
በርምጃችን ምልክት ላይ፣ ረጃጅም ሰርዶ በቅሏል
ብቻ ሙሾ ቢደረደር፣ የሆነውን ላይለውጠው
ለንባየማ ፊት አልሰጠው።
ያሳሳምሽ ለዛ ቀርቶ፣ እንደ እንጎቻ እሚጥመኝ
የነከሽኝ የቧጨርሽኝ፣ አገርሽቶ ቁስሉ ሲያመኝ
ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ!!
🔘በእውቀቱ ስዩም🔘
👍2❤1