አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሴቷ_እመቤት

#በብርክቲ

ይህን አጭር ድርሰት የላከችልኝ የቻናሉ ተከታታይ ናት እናንተም አንብቡና አስተያየታችሁን በ @Bruktiaug ላይ አድርሷት ሌሎችም የራሳችሁ ፅሁፍ ካለ ላኩልኝ እያየን እናስተናግዳችኋለን።
----------------------------------------------------

"አቤት የኔ እድል እግዚኦ....!! አሁን እኔም ቆሜ እሄዳለሁ? እበላለሁ? እጠጣለሁ? እስቃለሁ? ኧረ ለስንቱ ቆየሁት መድሀኒያለም ኧረ በቃሽ በለኝ"
ፀሀይ ሁለት እጆቿን ጭንቅላቷ ላይ አድርጋ የእምባ ዶፍ ታወርዳለች።የልብ ስብራቷን መደበቅ ተስኗት ለቀናት; ለወራት; ብሎም ለአመታት አምቃ የያዘችው የማይጠፍ ቁስል ከአቅም በላይ ሆኖባት ሳታቋርጥ ትንሰቀሰቃለች።ሳግ እየተናነቃት ሽንፈትን የማይቀበለው ማንነቷ ሲይዛት በእንባ ታጅባ ፈገግ ለማለት ትሞክራለች። ወ/ሮ ሰብለም አይኖቿን ወደ መሬት አቀርቅራ የምትለውን ከመስማት ውጭ አንድም ቃል አልተነፈሰችም። ምንስ ልትል ትችላለችና? ፀሀይ አምቃ የያዘችውን መከራ ፀጥ ብሎ ከመስማት ውጭ ምንም ልታደርግላት የምትችለው ነገር አልነበረም።
"ሰብልዬ አስታሞ መቅበር ምነኛ መታደል መሰለሽ። ሰው አስታሞ ሲቀበር ሳይማ ቅናት ነው የሚለቅብኝ።ምናለ ትንሽ ቀን የሆነ ምልክት ቢያሳዩኝና አንዴ ከህክምናው አንዴ ከፀበሉ ይዤ በዞርኩ እላለሁ።ቢይንስ መልፍቴ ህመሙን ይቀንሰው ይሆን? እህህ!! ኧረ እንደው ቢጨንቀኝ ነው።" ፀሀይ እንባ የሞሏቸውን አይኖቿን ከዚያ እዚ እያንከራተተች "ሰብልዬ እናቴን እንዴት እንዳጣኋት ታውቂያለሽ? አንድም ቀን የህመም ምልክት ሳላይባት ምስኪኗ እናቴ በእርጎ አብልታ ስማ መርቃ ተከራይቼ ወደምማርበት ከተማ ሸኝታኝ በሳምንቱ እናትሽ ሙታለች ነይና ቅበሪ ተብሎ ሰው ተላከብኝ"

"አህህ እናትዬ እኔን.. እኔ አፈር ልብላልሽ" ሰብለ እናትነትን ታቃለችና ከልቧ አለቀሰችላት። የሰብለን ልብ መሰበር ያየችው ፀሀይ አይኖቿ እንባ ቋጥረው ፈገግ አለችና አይ ሰብልዬ የኔ ጉድ እንዲ በቀላሉ የሚያበቃ መስሎሻል።

"አባቴ ደግሞ....."
ገና ሳትጀምረው ጉሮሮዋን ዝግት አድርጎ አንደበቷን አሳሰረው።እንደምንም ተነፈሰችና ስቅ ስቅ ብላ አለቀሰች።
"አባቴ ...ለንግድ ስራ ወደ ከተማ በሄድኩበት ዛሬ አንዳትቀሪ ቤት መጠሽ ነው 'ምታድሪው ብሎ ለሰው ላከብኝ።እኔም በጊዜ ስራየን ጨርሼ ምግብ እንኳ ሳልቀምስ ጉዞ ጀመርኩ። እንዳሁኑ መኪና አልነበረም ወደ ቤት በእግሬ እየሄድኩ እያለ ልደርስ ትንሽ ሲቀረኝ አንድ የሰፈር ሰው መጣና 'ኧረ ፀሀይ ኧረ ጩሂ ኧረ ጩሂ' አለኝ። ምንነቱን ሳላውቅ ልቤ ስለተረበሸብኝ እየጮኩ ወደ መንደር ገባሁ። ምንድን ነው ኧረ ምን ሆናችሁ ስላቸው........"
ፀሀይ ትንፍሿ ቁርጥ ቁርጥ እያለ ; ሳግ እየተናነቃት
" አባትሽ ሙቷል አሉኝ።.......
ሙቷል።.......
ቀለል አድርገው ሙቷል አሉኝ ሰብልዬ። ከእናት በላይ የሆነው አባቴ... የምሳሳለት...ከጠላት እንደ ወንድ ሳልተኛ የምጠብቀው አባቴ ጠዋት አይቼው ማታ ስመጣ ሞቶ ጠበቀኝ።"

ከንፈሮቿን በቁጭት እየነከሰች እንባዋን ትዘረግፈዋለች።
"አረርኩ። ከሰልኩ። አበድኩ። ግን ምን አመጣለሁ? ፈጣሪ አንዴ ይሁን ያለውን እኔ በምን አቅሜ እታገለዋለሁ?

"ከዛ ሰብልዬ ቤተሰቦቸን የጨረሰውን ሀገር አያሳየኝ ብዬ ብን ብዬ ጠፍሁ። ያኔ የኔ የምለው አይቼ የማልጠግበው የልጅነት ትዳሬ አብሮኝ ነበርና በሱ የማይቻለውን ቻልኩት። ቀስ በቀስ ቀልብ እየገዛሁ መጣሁ። መከራው ባይቀልልኝም ተላምጀው አብሬ መኖር ጀመርኩ። የውስጤን በውስጤ ይዤ ዋጥ አደረኩት።"

ፀሀይ ሽፋሽፍቷ ረግፈው ያለቀውን አይኖቿን በእጆቿ ይዛ በረጅሙ ተነፈሰች። .....ወደ መሬት አቀርቅራ በሀሳብ ጭልጥ አለች።

"ላያስችል አይሰጥ ፀሀይዬ እኔ እንግዲ ምን ላድርግልሽ ?" ሰብለ የተናገረችው ለሷም ቢሆን ዋጋ ቢስ ስለሆነባት ብዙ ሳትቀጥልበት ዝምታን መረጠች። ከረጅም የጭንቀት ዝምታ በኋላ ፀሀይ ካቀረቀረችበት ቀና አለችና
"ከዛ እርም የለኝ ምንም ቤተሰቦቼን ቢነጥቀኝ ወንድሞቼንና እህቶቼን ለማን ብዬ እተዋለሁ ብዬ በወጣሁ በብዙ አመቴ ተመልሼ ወደ ትውልድ ሀገሬ ዘመድ ጥየቃ ገባሁ። ከዘመዶቼ ጋር ደስ የሚል ጊዜ አሳለፍኩ። ከብቸኛዋ ከእናቴ ልጅ ጋር የሆዴን ስቃየን ብሶቴን ሁሉ አወራሁ። እስከዛሬ ባለመምጣቴ ስንቱ ቀረብኝ ብዬ ሳልጨርስ መቼስ የተረገምኩ አደለሁ ለጥየቃ ሂጄ በተመለስኩ በሁለት ሳምንቱ 'ነይ ብቸኛዋ የእናትሽ ልጅ ሞታለች ' ብለው አረዱኝ።"
ፀሀይ ሰቅሰቅ ብላ አለቀሰች።

"አይቻታለሁ እኮ ደህና ነበረች። የተቀቀለ እንቁላል እህቴ ሳትበላ ሄደች ብላ ከተሳፈርኩበት መኪና ድረስ ሮጣ መጣ አብልታኛለች። ሰብልዬ ምንም አልሆነችም ነበር እኮ...... እንገናኛለን ብላኝ ነበር።"
" እህህህ" ፀሀይ አላስችል ቢላት ህመሙ ቢበረታባት ተነስታ ወዲያ ወዲህ ማለት ጀመረች።
"አየሽ ሰብልዬ ከስቃይ ላይ ስቃይ ከመከራ ላይ መከራ ያከናንበኛል። እንደው ምን ሰርቸ ይሆን እንዲ 'ምፈተነው? እንደው ምን በድዬ ነው? አልሰረኩ ጉልበቴን አንጠፍጥፌ አፈር ድሜ በልቼ ነው ምኖረው....አልገደልኩ የሰው ሀቅ አልበላሁ" ፀሀይ እጆቿን እያወናጨፈች የሆዶን ታወራለች።
"ምናለ ደግሞ በዚህ በቃሽ ቢለኝ ሆ!" እንደ መሳቅ አለችና
" አንች የተረገምሽ ብቻሽን ቅሪ ነው መሰለኝ የ ሁለት ልጆቼን አባት;ሁሉን ያየሁበትን ; ፈጣሪን ተመስገን የምልበት ብቸኛውን ምክንያቴን ትንሽ እንኳ ጉብታ በሌለበት መንገድ መኪና በላብኝ። ይመጣል ብዬ ከልጆቸ ጋር ስጠብቀው በወጣበት ቀረ። ደጉ ባሌ በእናትና አባቴ እንኳ የማልቀይረው ባሌ ብቻዬን ትቶኝ ሄደ። ተሰቃይተን ተምረን አድገን እንቁላል ሽጦ ትልቅ ደረጃ የደረሰው ባሌ እፎይ ብሎ ጠግቦ በሚበላበት ጊዜ መኪና ወሰደብኝ። ልጆቹን ናፍቆ ድካም እንኳ ሳይለቀው ወደ ቤቱ ሲመጣ ሳይደርስ በዛው ቀረ።......."ኧረ ያሁኑ ባሰኝ ሰብልዬ" ፀሀይ ምርር ብላ አለቀሰች።
"የገጠር ክንድ ለክንድ በሚባለው ነበር የተጋባነው። ገና በልጅነታችን...። አንድ ላይ ሆነን ቤተሰብ እየረዳን ትምህርታችንን ልንማር...። የምንኖርበት ገጠር ስለሆነ ወደ ሌላ ከተማ ሂደን ዶርም ተከራይተን ነበር የምንማረው። ሰብልዬ አንድ ቀን ቤተሰብ ሳያግዘን ነው የተማርነው። አንድ ዩኒፎርም ለሁለት እየለበስን; ቅዳሜና እሁድ እየነገድን ነበር ለዚህ የደረስነው። ስንት ስቃይና መከራ አብረን አሳልፈናል። እንደ ባልና ሚስት እንኳ አንድ ቀን ተኮራርፈን እንኳ አናቅም።" ፀሀይ ፈገግ አለችና "የሆነ ጊዜ ምን እንዳለኝ ታቂያለሽ? 'ፀሀይዬ ባልና ሚስት ግን ምን ሆነው ነው 'ሚጣሉት? ያውም በገንዘብ? ደሞዙን ታቀዋለች ከልጆቹ ውጭና ከአስፈላጊ ነገር ውጭ ምን ያደርገዋል?'...... ሁሉ ሰው እንደሱ መስሎት....። ስንት ወንድ ሁለት ቤተሰብ እንደሚያስተዳድር አያውቅ።"
" ማታ ማታ ደግሞ በሌሊት ይደውልና ሲያወራይኝ ነው በቃ 'ሚያድረው። አብረውት የሚኖሩ ጓደኞቹ እንደ አፍላ ፍቅረኛ ጀመረው ነበር የሚሉት። ወደ ሌላ ሀገር ለስራ ከተመደቡ ጀምሮ ከ ሁለት ጎደኞቹ ጋር አብረው ነበር የሚኖሩት።" ፀሀይ ሳይታወቃት ፊቷ አበራ። ግን ትንሽም ሳትቆይ እንባዋ መፍሰስ ጀመረ። "ሰብልየ ይህን ባሌን ነው ያጣውት።
ይህን ባሌን........."
ፀሀይ አንድ ትዝታ መቶባት ፈገግ አለች።
"ሰብልዬ ማስተርሱን ዩኒቨርሲቲ ገብቶ እየተማረ እራት ቆንጆ ስጋ ወጥና ጥብስ ተዘጋጅቶላቸው ብቻየን አልበላም ብሎ በላስቲክ ይዞት ማታ ሶስት ሰአት ቤት
👍2