‹‹እሱን መቼም አልረሳውም። ያ አሁንም ዳኛው ከጀርባዬ ሆኖ ካንተ ጋር እንዲዶልትብኝ ሰበብ ሊሆን አይችልም… ለምን የአስከሬኑን መውጣት እንዲህ ፈራው? የፎረንሲክ ምርመራው ያጋልጥብኛል ብሎ የሰጋው የደበቀው ወንጀል አለ እንዴ ?››
‹‹ያቀረብሽው ጥያቄ ችግር ገጥሞታል።››
"ምን አይነት ችግር…. ያ የሬሳ ሣጥን የታሸገው ማንን ለመጠበቅ ነው?››
"አንቺን።"
"እኔን?"
"አዎ ፣የሰሎሜ አስከሬን ከመቃብር ሊወጣ አይችልም…. ተቃጥሏል"
‹‹ምን?››የሰማችውን ነገር ማመን አልቻለችም፡፡አፏን መረራት፡፡
‹‹አዎ ..ሞታ አስከሬኗ ለምርመራ ወደሆስፒታል ከተወሰደ በኃላ ድንገት ባልታወቀ ምክንያት በሆስፒታሉ እሳት ተነስቶ ስለነበረ የሬሳ ማስቀመጫ ክፍሉን ጨምሮ የተወሰኑ የሆስፒታሉ ክፍሎች ወድመው ነበር….እና የእናትሽም ሬሳ ተቃጥሏል …ለመታሰቢያ እንዲሆን እንዲሁ ከቃጠሎ አመድ ወስደን ነው በሳጥን አድርገኝ የቀበርነው፡፡››
‹‹ቢያንስ አጥንቷ አልተገኘም ነበር?፡፡››
‹‹የተወሰኑ አጥንቶች ተገኝተው ነበር..ግን በወቅቱ ከስምንት በላይ ሬሳ ነበረ..የትኛው አጥንት የማንኛው እንደሆነ በዛን ዘመን ለመለየት በጣም አስቸጋሪ ስለነበረ…እንደዛ ማድረግ አልቻልንም››
ለተወሰኑ ደቂቃዎች ደንዝዛ ዝም አለች….ከዛ ድንገት እንደመባነን አለችና‹አሁን ይበልጥ እያመንኩ መጣሁ››ስትል ተናገረች፡፡
‹‹ማለት? ምኑን ነው ያመንሽው?››
‹‹የእናቴ ገዳይ አሁንም ተገቢውን ቅጣት እንዳላገኘ..እና እሱን ከቅጣት ለማዳን ሆስፒታል እስከማቃጠል ድረስ የሚያደርስ ጭካኔ ያለው ደጋፊ ቡድን መኖሩን››
‹‹አእምሮሽ ግን እንዴት ነው የሚሰራው….?››
‹‹በትክክል ነዋ….እናቴ ሬሳ ሆስፒታል በገባበት ቅፅበት እሳት መነሳቱ ያጋጣሚ ነው ብለህ እንዳታስቀኝ..ደግሞስ ይሄንን ጉዳይ አያቴ እንዴት ሳትነግረኝ….?.››
‹‹እኔ እንጃ…ለምን እንዳልነገረችሽ እሷኑ መጠየቅ ነው…ምን አልባት ገምት ካልሺኝ ግን ይሄንን ነገሮችን ባልተገባ መንገድ የመፈትፈት ፀባይሽን ስለምታውቅ ይመስለኛል፡፡››
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

👍34❤12
#አሜን_በይ_አደራ
ያየሽ አይኑ ይጥፋ
እግርና እግሩን ያርግበት ወልካፋ።
ቡዳ እንደበላዉ ልጅ አይኑ ፈጦ ይቅር አንቺኑ ያየበት
አናቱ ቅል ይሁን አንቺን ያሰበበት
ልቡ ስራ ታቁም ካንቺ የከጀለበት።
ፍቅርሽ እስክመጣ
ፍቅር የተባለ ከወንድ መኖ ይዉጣ
ጠንጋራ ያድርገዉ አንቺን ሊያይ የመጣ።
በፈገግታ ማርኮ ቀልብሽን ለሻተ
ጥርሶቹን አግጥጦ ለተንከራተተ
መጋኛ አግኝቶልኝ ከንፈሩን ያጣመዉ
ጥርሶቹን አርግፎ በድዱ ያስቀረዉ።
እኔ ያንቺዉ መዉደድ ስቃይ እንዳይገባኝ
ቅናት እንዳይገባኝ
ፍርሀት እንዳይገባኝ
ችግር እንዳይገባኝ
የሀገሬዉ ተባዕት በርሀብ ይቀጣ
ሆዱን እያሰበ ወዳንቺ እንዳይመጣ።
የሚበላዉ ይጣ
የሚጠጣዉ ይጣ።
በቃላት ሊያጠምድሽ አንደበቱ ናፍቆ ስምሽን የጠራ
ያሰበዉም ቢሆን ከኔ ፍቅር ጋራ።
ሀረግ ሊደረድር ተፈጥሮ የሰራዉ
ጉሮሮ፣ትናጋ፣ምላስ ከከንፈሩ
ላንቃዉም ሳይቀሩ
የጨዉ ሀዉልት ሆነዉ እዛዉ ደርቀዉ ይቅሩ።
ብቻ ግን አደራ ይሄ ሁሉ ሲሆን
አንዱን አያሳይሽ እንዳይገባሽ ሀዘን
ሲከፋሽ አልወድም።
🔘ትዝታ ወልዴ 🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ያየሽ አይኑ ይጥፋ
እግርና እግሩን ያርግበት ወልካፋ።
ቡዳ እንደበላዉ ልጅ አይኑ ፈጦ ይቅር አንቺኑ ያየበት
አናቱ ቅል ይሁን አንቺን ያሰበበት
ልቡ ስራ ታቁም ካንቺ የከጀለበት።
ፍቅርሽ እስክመጣ
ፍቅር የተባለ ከወንድ መኖ ይዉጣ
ጠንጋራ ያድርገዉ አንቺን ሊያይ የመጣ።
በፈገግታ ማርኮ ቀልብሽን ለሻተ
ጥርሶቹን አግጥጦ ለተንከራተተ
መጋኛ አግኝቶልኝ ከንፈሩን ያጣመዉ
ጥርሶቹን አርግፎ በድዱ ያስቀረዉ።
እኔ ያንቺዉ መዉደድ ስቃይ እንዳይገባኝ
ቅናት እንዳይገባኝ
ፍርሀት እንዳይገባኝ
ችግር እንዳይገባኝ
የሀገሬዉ ተባዕት በርሀብ ይቀጣ
ሆዱን እያሰበ ወዳንቺ እንዳይመጣ።
የሚበላዉ ይጣ
የሚጠጣዉ ይጣ።
በቃላት ሊያጠምድሽ አንደበቱ ናፍቆ ስምሽን የጠራ
ያሰበዉም ቢሆን ከኔ ፍቅር ጋራ።
ሀረግ ሊደረድር ተፈጥሮ የሰራዉ
ጉሮሮ፣ትናጋ፣ምላስ ከከንፈሩ
ላንቃዉም ሳይቀሩ
የጨዉ ሀዉልት ሆነዉ እዛዉ ደርቀዉ ይቅሩ።
ብቻ ግን አደራ ይሄ ሁሉ ሲሆን
አንዱን አያሳይሽ እንዳይገባሽ ሀዘን
ሲከፋሽ አልወድም።
🔘ትዝታ ወልዴ 🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
❤5😁1
#ትናንትና_ማታ
ላሟሟሽ ሲገባኝ፣እንዳሞሌ አጥቤሽ
በመጨረስ ፋንታ
ለነገ ቆጥቤሽ
አስተርፌሽ ለሰው
የጸጸት ሱናሚ ፤ዓለሜን አመሰው፡፡
ምነው ቢቻል ኖሮ
ፈገግታሽን ቋጥሮ
ሙዳይ ውስጥ መደበቅ
ጃንደረባ ቀጥሮ
ጭንሽን ማስጠበቅ
ክፍት ልቤን ይዤ፤ ዝግ ደጅሽን ጠናሁ
በሰበብ ወድጄሽ ፤ያለሰበብ ቀናሁ፡፡
ፍቅር በተባለ፤ ግራ ገቢ ነገር
ከጨመተው አገር
ከሰከነው ቀየ
መናፍቅ ይመስል፤ ባዋጅ ተነጥየ
እንደካፖርቴ ቁልፍ፤ ልቤን የትም ጥየ
የትም ስከተልሽ
የትም ሆኖ እድልሽ፤
ሁሉ ያንች ወዳጅ
ሁሉ ባላንጣየ
መፈቀር ሆኖ ጣሽ፤ መቅናት ሆኖ ጣየ
ላንቺ ብስል ፍሬ፤ ለኔ ገለባ ግርድ
ላንቺ እቅፍ አበባ፤ ለኔ እቅፍ ሙሉ ብርድ
ማነው የበየነው ፣ይህን ግፈኛ ፍርድ፡፡
🔘በዕውቀቱ ሥዩም🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ላሟሟሽ ሲገባኝ፣እንዳሞሌ አጥቤሽ
በመጨረስ ፋንታ
ለነገ ቆጥቤሽ
አስተርፌሽ ለሰው
የጸጸት ሱናሚ ፤ዓለሜን አመሰው፡፡
ምነው ቢቻል ኖሮ
ፈገግታሽን ቋጥሮ
ሙዳይ ውስጥ መደበቅ
ጃንደረባ ቀጥሮ
ጭንሽን ማስጠበቅ
ክፍት ልቤን ይዤ፤ ዝግ ደጅሽን ጠናሁ
በሰበብ ወድጄሽ ፤ያለሰበብ ቀናሁ፡፡
ፍቅር በተባለ፤ ግራ ገቢ ነገር
ከጨመተው አገር
ከሰከነው ቀየ
መናፍቅ ይመስል፤ ባዋጅ ተነጥየ
እንደካፖርቴ ቁልፍ፤ ልቤን የትም ጥየ
የትም ስከተልሽ
የትም ሆኖ እድልሽ፤
ሁሉ ያንች ወዳጅ
ሁሉ ባላንጣየ
መፈቀር ሆኖ ጣሽ፤ መቅናት ሆኖ ጣየ
ላንቺ ብስል ፍሬ፤ ለኔ ገለባ ግርድ
ላንቺ እቅፍ አበባ፤ ለኔ እቅፍ ሙሉ ብርድ
ማነው የበየነው ፣ይህን ግፈኛ ፍርድ፡፡
🔘በዕውቀቱ ሥዩም🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
❤7😁1
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////
ኩማደሩ በቤት ውስጥ ምርጥ የተባለ ውስኪ እያለው በአውራ ጎዳናው ላይ ወደሚገኝ ግርግር ወደሚበዛበት መጠጥ ቤት ገብቶ ለመጠጣት ለምን እንደመረጠ ማወቅ አልቻለም። ምናልባት አዕምሮው ስለተጨናነቀ የተጨናነቀ ቦታ ፈልጎ ሊሆን ይችላል…እሾህን በእሾህ ለማክሰም ።የቡና ቤት አስተናጋጅ መጠጥ እንዲያመጣለት በምልክት ነገረው።ውስኪውን ወደ ብርጭቆው ሲቀዳ እያየ"አመሰግናለሁ" አለ ብቻውን እየቆዘመ ውስኪውን መሳብ ጀመረ፡፡
የጠጣው ውስኪው ቀስ በቀስ በሆዱ ውስጥ እሳት እንዲንቀለቀል እያደረገ ነው። ሲጠጣ ጨጓራውን በጣም ያመዋል….በዛም ምክንያት እርግፍ አድርጎ ለማቆም ሁሌ ይወስናል
..ግን ደግሞ ምክንያት ፈልጎ መጠጣቱን አይተውም…ቢሆንም እስኪሰክር ጠጥቶ አያውቅም በፍጽም የአባቱን ስህተት መድገም አይፈልግም…።ይህ የሌሊቱ የመጨረሻ መጠጥ እንደሚሆን ወሰነ …አዘዘ ፡፡ገና ህጻን ሳለ ነው እንደአባቱ መሆን እንደሌለበት ወስኖ የነበር ።የወህኒ ቤት ወፍ ወይም መነኩሴ፣ የጠፈር ተመራማሪ ወይም የመቃብር ጉድጓድ ቆፋሪ፣ የእንስሳት ጠባቂ ወይም ትልቅ አዳኝ ሆኖ ሊያድግ ይችላል፣ ነገር ግን አንድ መሆን የማይፈልገው ነገር ሰካራም መሆን ብቻ ነበር። ቀድሞውኑ በቤተሰቡ ውስጥ አንዱ ፕሮፌሽናል ጠጪ ነበራቸው እና ያ ደግሞ በጣም በቂ እንደሆነ ያምናል፡፡
"ሂይ ኩማንደር " የሚል ንግግር ከሀሳቡ አናጠበው፡፡
አንገቱን ቀና ሲያደርግ የለበሰችው ጅንስ ሱሪ የጠበባት እና ፊቷን በሚካፕ ያደመቀች ውብ ሴት ፊት ለፊቱ ቆማለች፡፡ይህቺን ሴት ከረጅም ጊዜ በፊት ጀምሮ ያውቃታል….፡፡
‹‹ሰላም ሮዛ።››
"ቢራ ትጋዘኛለህ ብዬ በማመን ነው ከጓደኞቼ ተነጥዬ የመጣሁት?"አለችው በተቃራኒው ኮሪደር ጥግ ከላይ ተቀምጠው ቢራ እየጠጡ ወደ ሚሳሳቁ ሁለት ሴቶች እየጠቆመችው፡፡
"ይቻላል።" አለና እንድትቀመጥ ካደረጋት በኃላ ትዕዛዙን ወደ አስተናጋጁ አስተላለፈ። ትኩር ብላ እያየችው ነው…ብቻውን ከእሷ ጋር መቀመጡ ምቾት ስላልሰጠው..‹‹ከፈለግሽ ጓደኞችሽን ጥሪያቸው››አላት፣ ከአንድ ሴት ጋር ለብቻ ከመሆን ከሶስት ሴት ጋር መሆን የተሻለ መስሎ ስለተሰማው ነው ሶስት ሴቶችን ለመጋበዝ ፍቃደኛ የሆነው፡፡
"አይ እነሱ የሞቀ ጫወታ ይዘዋል …አታስቸግራቸው" አለችው በማሽኮርመም ፡፡
"እየተዝናናችሁ ነው?››
"አዎ..እኛ ሴቶችም አንዳንዴ ወጣ ማለት አያስፈልገንም ትላለህ ?"
"አይ ጥሩ ነው፡፡"
ያዘዘችው ቢራ መጣላትና እየተጎነጨች ማውራቷን ቀጠለች‹‹ከቤት ተያይዘን ስንወጣ ፊልም ቤት ለመግባት ነበር..ግን እንደአለመታደል ሆኖ ፊልሙ ያየነው ስለሆነ ሀሳባችንን ቀየርንና ወደእዚህ ጎራ አልን…እና ደግሞ ደስ የሚለው አንተን አገኘሁህ››
‹‹ጥሩ ነው››ብሎ በአጭሩ መለሰላት፡፡
ሮዛ በቀላሉ የምትተወው አይነት ሴት አልነበረችም። "አይ ኩማንደር ሁል ጊዜ በራስህ ዙሪያ የምትሽከረከር ብቸኛ ፍጡር ነህ።"የሚል አስተያየት ጣል አደረገችበት
" ብቸኝነት ምርጫዬ ነው."ሲል መለሰላት
"አውቃለሁ ግን አሁንም…" እጇን አንቀሳቀሰችና ታፋው አካባቢ አስቀመጠች…በድንጋጤ ግራና ቀኙን አየና..ቀስ ብሎ እጇን አንሸራቶ ነፃ ወጣ፡፡
"ምናልባት አንተን ማስደሰት እችል ይሆናል፡፡ " አለችው ፡፡ " እስቲ እናያለን››አላት፡፡
"ሰባተኛ ክፍል እያለሁ ጀምሮ በጣም ወድጄህ ነበር። መቼስ ያንን አታውቅም አይደል?"
"አይ ያንን አላውቅም ነበር."
"እሺ አሁን ነገርኩህ ። በወቅቱ አብዬት ፍሬ ትምህርት ቤት እየተማርን እያለ አፈቅርህ ነበር…..ግን ያኔ ተነጠቅኩ። የዚያች ልጅ ስም ማን ነበር? በእነ ጁኒዬር የከብቶች በረት ውስጥ የተገደለችው?"
"ሰሎሜ."
"አዎ. በእሷ ላይ ተመስጠህ ነበር አይደል? ወደሀይስኩል ስንገባም በግልፅ ፍቅረኛማቾች መሆናችሁን በይፋ አሳወጃችሁ…ከዚያም እኔም ተስፋ ቆርጬ አግብቼ ልጆች ወለድኩ." ለንግግሯ ፍላጎት እንደሌለው አላስተዋለችም።
"'በእርግጥ አሁን ባሌ ሞቷል፣ እና ልጆቼም እራሳቸውን ችለው ከቤት ወጥተዋል….አንተ ግን በዚ ሁሉ ዘመን ትራስ ታቅፈህ ታድራለህ…ነው ወይስ ሳልሰማ አገባህ?››
"አይመስለኝም።"
‹‹እስካሁን ››ወደ ፊት ቀረበችው፣
"ምናልባት እኔን እየጠበቅከኝ ይሆናል፡፡››ብላ ወንበሯን አንሸራታ ወደእሱ አቀረበችውና እላዩ ላይ ተለጠፈች፣እሱም ቀኝ እጁን ሰነዘረና"ጡቶቿን በእጁ እያሻሸ ምላሽ ሰጣት፡፡ የጡት ጫፎቿ በቲሸርትዋ ላይ ጠንካራ እና የተለየ ስሜት ፈጠሩበት። የሆነ ሆኖ፣ ግልጽነቷ ልክ እንደ አለም ንፁህ እና ባዶ ጣቶች ከነጭ ጋወን ውስጥ አጮልቆ እንደሚወጣ የሚያማልሉ አልነበረም።
በአለም ነጭ ካባ ስር ምን አለ? ብሎ እንዲያስብ ስለተገደደ አላስደሰተውም። ለምን ብሎ አሰበ።አለም በጣም ቆንጆ ነበረች. ከንፈሮቿ ተከፍለው እርጥብ ነበሩ። ሳይፈልግ ከአለም ከሜካፕ ነፃ ከሆኑ ከንፈሮች ጋር አነጻጽሯቸዋል፣ ነገር ግን አሁንም ሞቃት እና እርጥብ፣ የሚሳም እና ሴሰኛ፣እንደሆኑም እርግጠኛ ቢሆንም ምንም አይነት ሙከራ ሳያደርግ የቢራዋን ዋጋ የሚሸፍን ብር ከጂንስ ኪሱ ውስጥ በማውጣት ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠና
‹‹መሄድ አለብኝ"በማለት ከተቀመጠበት ተነሳ፡፡
"ግን እኔ ያሰብኩት…."
"ወደ ጓደኞችሽ ብትመለሺ ይሻላል፣ አለበለዚያ ፓርቲው ያመልጥሻል ።"አላት፡፡ ከጓደኞቾ ጋር በፊት ያልነበሩ አራት የሚሆኑ ወንዶች ተቀላለቅለዋቸው ሞቅ ያለ ቡድን መስርተው ነበር….፡፡
‹‹ሮዛ ስለየሁሽ ደስ ብሎኛል›› አለና ኩማንደር ኮፍያውን ዝቅ አድርጎ ፊቱን በከፈል ሸፈነና ወጥቶ ሄደ፣ ፡፡
እና ስለአለም መብሰልሰሉን ቀጠለ..ትናንት ማታ የእናቷ አስከሬን እንደተቃጠለ ሲነግራት ፊቷ ላይ የተመለከተው ሀዘን አሁንም ትዝ ይለዋል፡፡
"ዳኛ ዋልልኝ ያውቅ ነበር?" ስትል ጠየቀችው፡፡
"እነሆ እኔ የማውቀው ነገር ቢኖር እሱ ጠርቶኝ የፈለጋችሁት ነገር የማይቻል ነው ማለቱን ነው፣ "
"የእናቴ አስከሬን መቃጠሉን የሚያውቅ ከሆነ ለምን እራሱ አልነገረኝም?"
"የእኔ ግምት አንቺ ለዜናው የምታሳይውን ትዕይንት ማየት ስለማይፈልግ ይመስለኛል "
"አዎ" ብላ ትኩረቷን ሳትከፋፍል አጉረመረመች፣
"ሁከትን አይወድም። ››
በዝምታ ተመለከተችው። "ቆሻሻ ስራውን እንድትሰራለት ነው አይደል የላከህ ?። ››ነበር ያለችው፡፡
ኩማንደሩ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ጓንቱን አንስቶ አጠለቀ…ኮፍያውንም መልሶ አደረገ ።
"አሁን ደንግጠሻል ..ግን አይዞሽ ደህና ትሆኚያለሽ?"
"ደህና ነኝ።"
"ጥሩ ››
ጥቋቁር አይኖቿ በእንባ ተሞሉ እና አፏ በትንሹ ተንቀጠቀጠ። ድንገት ወደእሱ ተንቀሳቀሰችና እጆቿን ከወገብዋ ጋር አጣበቀች..እና ተሸጎጠችበት። ያን አጥር እንደገና ከመገንባቷ በፊት፣ እጆቹን አንሸራትቶ ወደ እሱ ጎተታት። እሷ ሞቃት ትንፋሽ እና ጥሩ መዓዛ ነበራት በሀዘኗ ውስጥ ደካማ ሆናለች. እጆቿ ሳይጨነቁ ወደ ጎን ተንጠልጥለዋል።
"ኦ አምላኬ እባክህ በዚህ ፈተና ውስጥ እንዳልፍ አታድርገኝ" ስትል በሹክሹክታ ተናገረች እና ጡቶቿ ሲንቀጠቀጡ ተሰማት። እንባዋን ሲንጠባጠብ በልብሱ አልፎ እስኪሰማው ድረስ ጭንቅላቷን ወደ እሱ አስጠጋች። ፀጉሯን የጠቀለለችበት ፎጣ ተንሸራቶ መሬት ላይ ወደቀ። ፀጉሯ እርጥብ ነበር። በወቅቱ እሷን መሳም እንደሌለበት ለራሱ እየተናገረ ነው… ነገር ግን ከንፈሩ ፀጉሯን ከዚያም የአንገቷ ስር ሽታን ወደውስጡ እየማገ ስለሆነ እየደነዘዘ ነበር፡።በዚያን ጊዜ፣ ከባድ የፍትወት ስሜት አቅበጠበጠው፣ እናም በጣም

❤42👍6
ኃይለኛ ስለነበር መቋቋም መቻሉ ለእሱ ድንቅ ነበር።ይልቁንስ ከእንደዚያ አይነት መቃተት በኋላ እንደ እባብ ፈልቅቆ ከስሯ መውጣቱ እንደ ቂም እየተሰማው ሄደ። ከእሷ ጋር መቆየት መፈለጉ ምንም ጥያቄ አልነበረውም. ግን ደግሞ እሱ ለራሱ ማመን እስኪያቅተው ድረስ ራሱን መቋጣጠር ቻለ። በጠንካራ ስሜት እሷን መሳም ፈልጎ ነበር።ነጭ ጋወኗን ከላዮ ላይ ገፎ ጥሎ እርቃኗን ሊያስቀራት ፈልጎ ነበር፡፡፡ወገቧን ጨምቆ ይዞ በአየር ላይ ሊያንሳፍፍፋት ፈልጎ ነበር….በትከሻው ተሸክሞ ወደመኝታ ቤቷ ይዞት ሊገባ ፈልጎ ነበር…..ብዙ ብዙ ነገር ማድረግ ፈልጎ ነበር…ግን ምንም ነገር አላደረገም፡፡
ከእሷ ጋር በፍቅር ለመቋራኘት በጣም አርጅቷል ። አስደሳች የወሲብ ቅዠቶች እንደሆነ አሰበ ….ጠንካራ, ብስል ቀይ የጡት ጫፎች ለስላሳ ፣ ጥቁር ፀጉር። ጭኖቿ ለስላሳ ይሆናሉ….እና ….. ለአፍታ ዓይኑን ጨመቀ።
እሷ ከእሱ በአሥራ ስምንት ዓመት የምታንስ ሴት ነች፡፡በዛ ላይ የሰሎሜ ልጅ ነች፣ እና በዕድሜው አባቷ ሊሆን ይችላል፣፡፡ አባቷ የመሆን አጋጣሚም ነበረው ። ያንን ማወቁ ሆዱ ትንሽ እንዲረበሽ አድርጎት ነበር ።ብቻ እንደምንም ያለ የሌለ አቅሙን አጠራቅሞ ተሰናብቷት ወደቤቱ መሄድ ቻለ…ልቡ ግን ይሄው ዛሬ በሁተኛ ቀኑም እዛው እሷ ቤት እንደተቸነከረ ነው፡፡
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ከእሷ ጋር በፍቅር ለመቋራኘት በጣም አርጅቷል ። አስደሳች የወሲብ ቅዠቶች እንደሆነ አሰበ ….ጠንካራ, ብስል ቀይ የጡት ጫፎች ለስላሳ ፣ ጥቁር ፀጉር። ጭኖቿ ለስላሳ ይሆናሉ….እና ….. ለአፍታ ዓይኑን ጨመቀ።
እሷ ከእሱ በአሥራ ስምንት ዓመት የምታንስ ሴት ነች፡፡በዛ ላይ የሰሎሜ ልጅ ነች፣ እና በዕድሜው አባቷ ሊሆን ይችላል፣፡፡ አባቷ የመሆን አጋጣሚም ነበረው ። ያንን ማወቁ ሆዱ ትንሽ እንዲረበሽ አድርጎት ነበር ።ብቻ እንደምንም ያለ የሌለ አቅሙን አጠራቅሞ ተሰናብቷት ወደቤቱ መሄድ ቻለ…ልቡ ግን ይሄው ዛሬ በሁተኛ ቀኑም እዛው እሷ ቤት እንደተቸነከረ ነው፡፡
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍41❤11
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////
አለም መተኛት አቅቷት እየተገለበጠች ባለችበት ጊዜ ነበር ስልኩ የጮኸው፡፡ሰዓቱ እኩለ ለሊት በመጠጋቱ የተነሳ ጥሪው በጣም ነበር ያስደነገጣት ። የራስጌ መብራቱን በማብራት የስልኩን እጄታ አነሳችና ጆረዋ ላይ ለጥፋ ጎላ ባለ ድምፅ "ጤና ይስጥልኝ" አለች፡፡ቀደም ብሎ ስታለቅስ ስለቆየች ድምጿ የሻከረ ነበር
"ሰላም ››መለሰላት፡፡
"አወቅሽኝ ወ.ሪት አለም "
ልቧ በደስታ ዘለለ፣"አንተ እንደገና? በዚህ ውድቅት ለሊት ከእንቅልፍ ያስነሳኸኝ ደህና ነገር ልትነግረኝ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ" አለችው።እምቢተኛ ምስክሮች ብዙ ጊዜ የሚናገሩትን ነገር አስፈላጊነት ሲጠቀስላቸው ለመናገር እንደሚበረታቱ ከልምድ ታዝባለች፡፡
"ከኔ ጋር ድብብቆሽ አትጫወቺ …. ማወቅ የምትፈልጊውን በጠቅላላ አውቃለሁ። "
"ለምሳሌ ምን?"
"ለምሳሌ እናትሽን ማን እንደገደላት››
አለም አተነፋፈስዋን በመቆጣጠር ላይ ትኩረት አደረገች።
" ይመስለኛል ዜናው አስደምሞሻል››
"ታዲያ ንገረኝ ማን ነበር?"
"እመቤት ደደብ እመስልሻለሁ እንዴ? ኩማንደሩ ቀደም ሲል ስልክሽን አለማስጠለፉን በምን አውቃለው ?"
"ይመስለኛል….በጣም ብዙ ፊልሞችን አይተሃል?››
‹‹ተረቡን አቁሚና ይልቅ በፅሞና አድምጪኝ ….ነገ ማታ አንድ ሰዓት ሸዋበር የሚገኘው ደንበል ሆቴል እንገናኝ" በማለት ሰዓቱንና ቦታውን ነገራት፡፡
"እንዴት ላውቅህ እችላለሁ?"
"እኔ አውቅሻለሁ"
ሌላ ነገር ከመናገሯ በፊት ስልኩን ዘጋው። አለም በአልጋው ጠርዝ ላይ ለጥቂት ጊዜ ተቀምጣ ጨለማውን እያየች ደርቃ ቀረች። ልትጎዳ እንደምትችል የነገራትን የኩማንደሩ ማስጠንቀቂያ አስታወሰች። የእርሷ ምናባዊ አእምሮ በሴት ላይ ብቻ ሊደርስ የሚችለውን አሰቃቂ ነገር ሁሉ አስተናገደ። በተኛችበት ሆና በላብ ተጠምቀው ነበር።
///
የከተማው የፖሊስ አዛዥ እንፋሎት የሚትገለግበትን ቡናውን አንስቶ ጠጣ። ምላሱን አቃጠለው። ግን ግድ አልነበረውም። በጣም በከፋ መንገድ የካፌይን ማነቃቂያ ያስፈልገዋል
‹‹ስለማን ነው የምናወራው?›› ሲል በግል ቢሮው ደጃፍ ላይ ቆሞ የነበረውን ምክትሉን ጠየቀ ..
" ስለአቃቢ ህግ ፅ/ቤት ነው››
"ስለ ወ.ሪት አለም እያወራህ ነው ?" ምክትሉ መለሰ " አዎ ጌታዬ ስለእሷ ነው።" "እሺ ምን አዲስ ነገር አለ?"
" የእናቷን የሬሳ ምርመራ መዝገብ አስወጥታ ዠለመመርመር ወደ ተክለሀይማኖት ቤ/ክርስቲያን ሄዳለች ››
"ምን?"
"አዎ ጌታዬ እንዲከታተሏት የመደብናቸው ፖሊሶች ናቸው ደውለው የነገሩኝ፡፡››
‹‹በል አሁኑኑ ደውልላቸውና ወደእነሱ እየመጣሁ እንደሆነ ንገራቸው››
ገመዶ ኮቱን ከተሰቀለበት አንስቶ ቢሮውን ለቆ ወጣ…፡፡ ትምህርት ቤቶችን እና አብዛኛዎቹን የንግድ ድርጅቶች እንዲዘጉ ያደረጋቸውን የፀጥታ ችግር ቢኖርም ግድ አል ነበረውም። ሰልፈኛውን እየሰነጠቀ እና ወንበር እያሳበረ ወደሆስፒታል ነዳው፡፡
"የት ነው ያለችው?" እንደደረሰ ኩማንደሩ ጮኸ፣..አንድ አነስተኛ ቢሮ መሰል ክፍል ውስጥ ቁጭ ብላ ከአስተዳዳሪው ጋር ስታወራ ተመለከታ…ወደእዛው ተንደርድሮ ሄደ፡፡
ምንም ፍቃድ ሳይጠይቅ ሰተት ብሎ ገባና " ምን እየሰራሽ ነው ?"አንቧረቀባት፡፡ "እንደምን አደርክ ኩማንደር"አለችው ለስለስ ብላ፡፡
"ጥያቄዬን መልሺልኝ?"
‹‹ምን እያደረኩ እንደሆነማ በደንብ ታውቃለህ?››
"በአንቺ ምክንያት ሴትዮዬ ስራዬን መስራት አልቻልኩም….ከተማዋ በበጥባጭ ጎረምሶች ተረብሻ ያንን ማረጋጋት ሲጠበቅብኝ እኔ አንቺን በየመቃብር ቤቱ እከታተልሻል። ለማንኛውም እንዴት እዚህ ደረስሽ?"
" እየነዳሁ።"
በንዴት በጠረጴዛው ላይ የተበተኑትን ፋይሎች አያመለከተ"ይህ ሁሉ ምንድን ነው?"ሲል ጠየቃት፡፡
" መዛግብት ነዋ…..እናቴ ስትቀበር ለአገልግሎት የተከፈሉ ካርኒዎች እና መሰል መረጃዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ ያንን እያዩልኝ ነው፣ ፡፡
"አስገድደሽው ነው?::"
‹‹እኔ እንደዚህ ያለ ነገር አላደረኩም..እንዴት ነው ምታስበኝ…?ደፍሬ አባቶቼን የማስገድድ ይመስልሀል?."
" ታዲያ የፍተሻ ማዘዣ ፍቃደሽን አልጠየቁሽም?"
ካህኑ‹‹ልጆቼ ይቅርታ እስኪ እናንተ አውሩ እኔ መጣሁ››ብለው ከመቀመጫቸው ተነሱና ክፍሉን ለቀውላቸው ወጡ … ገመዶ ወደሷ ቀረበና በንዴት ክንዷን ጨምድዷ ያዘ፡፡
‹‹ምን እያደረክ ነው?››
‹‹ቄሱን የሆነ ነገር ብዬ ከማስቀየሜ በፊት ቀጥ ብለሽ ቦታውን ለቀሽ ውጪ››
‹‹ለምንድነው እንደዛ የምታደርገው?››
‹‹ነገርኩሽ እኮ..አሁን ተከትለሺኝ ትሄጂያለሽ ወይስ…የማደርገውን ቆመሽ ትመለከቻለሽ?››
ትኩር ብላ አየችው … ፊቱ እንደ ተራራ ሰንሰለታማና ወጣ ገባ ነው፣በአጭሩ ቋጥኝ ይመስላል፣ ነገር ግን እስካሁን ካጋጠሟት በጣም ማራኪ ወንዶች ውስጥ አንዱ ነው።አብረው በሚሆኑበት ጊዜ ሁሉ፣ ስለ እሱ፣ ስለ ሰውነቱ ታስባለች፡፡ የእሷ ለእሱ ያላት መስህብ ሥነ ምግባር የጎደለው እና ከዛም አልፎ እንዝላልነት እንደሆነ ታውቃለች። መጀመሪያ የእናቷ ፍቅረኛ ነበረ።ያንን በደንብ ታውቃለች ..ሆኖም ብዙ ጊዜ እሱን ለመንካት ትፈልግ ነበር። ትናንት ማታ በምታለቅስበት ጊዜ እንዲያባብላት ትፈልግ ነበር። ወደመኝታ ቤቷ ተከትሏት እንዲገባም ፈልጋ ነበር…ደግነቱ እሱ በተሻለ ብቃት እራሱን የመቆጣጠር ችሎታ ነበረው እና ምንም ሳያደርግ ትቷት ሄደ።
‹‹የሰሎሜ ሬሳ እንደተቃጠለ ነግሬሻለሁ።››
"አንተ እና ዳኛው ጭንቅላታችሁን አንድ ላይ አድርጋችሁ እያሻጠራችሁ መሆኑን ማወቄ የተመቸኝ ይመስልሀል?።››
"ነገሮችን መገመት ያስደስትሻል?."
"ጁኒየር እናቴ ሬሳ መቃጠሏን ለምን አልነገረኝም?እንደተቀበረች ነበር የነገረኝ ››
‹‹እኔ እየዋሸሁሽ ይምስልሻል….?ለምን ብዬ?" " አስከሬኑ እንዳይወጣ ስለምትፈልግ ነዋ።"
"ሬሳው እንዳይወጣ ለምንድነው የምፈልገው? በእኔ ላይ ምን ለውጥ ያመጣል?"
ፍርጥም ብላ "የእድሜ ልክ እስራት" በማለት መለሰችለት፡፡ "የፎረንሲክ ሪፖርቱ አንተን ነፍሰ ገዳይ መሆንህን የሚያመለክት ፍንጭ ከሰጠን ወደወህኒ መወርወርህ የማይቀር ነው።››
" “አህ...” አለ..ደም ስሯቹ ሲግተረተር እየታዘበች ነው፡፡ "አንቺ ጠበቃ አይደለሽም, ጠንቋይ አዳኝ ነሽ."
"ወንጀል ባይኖር ኖሮ ያ እውነት ሊሆን ይችላል….ግን አንድ ሰው ወደዚያ በረት ውስጥ ገብቶ እናቴን ወግቶ ገድሏታል..እና እስከአሁን ለጥፋቱ የሚመጥን ቅጣት አላገኘም።››
"በእስክሪፕት ደረጃ ትክክል ነሽ" አለ እየተሳለቀ።
"ጋሽ ፍሰሀ ፣ ጁኒየር ወይስ እኔ የቀዶ ጥገና መሳሪያ ይዘን እናትሽን እንደወጋናት ነው ግምትሽ? ለምን በባዶ እጃችን አንገቷን አንቀን አንገድላትም??"
"ሁላችሁም ጎበዝ ስለሆናችሁ።ከመካከላችሁ ወንጀሉን የፈፀመው ሰው እንደዛ ያደረገው ወንጀሉን የአእምሮ ሚዛናዊ የተዛባ ሰው ያደረገው እንዲመስል ፈልጎ ነው።››
‹‹አመንሽም አላመንሽም …እኔ አላደረግኩም
"በብስጭት መለሰላት፡፡
"ታዲያ ማን እንዳደረገው ማወቅ አትፈልግም? ወይስ ነፍሰ ገዳዩ የምትወደው ሌላ ሰው እንዳይሆን ትፈራለህ ?"ስትል ሞጋች ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹አይ ማወቅ አልፈልግም" ሲል በአጽንኦት መለሰላት፡፡
"እኔ ግን ገዳዩን እስካገኝ ድረስ ምርመራዬን አላቋርጥም..››
ሊመልስላት አፉን ሲከፍት አንድ ግራ እግራቸው ሸንከል የሚል አዛውንት አንድ ያረጀች መዝገብ ይዘው ወደውስጥ ሲገቡ ሲመለከት አፉን መልሶ ከደነ፡፡

❤43👍1
"ይመስለኛል ይህን ነው የምትፈልገው? የድሮ ፋይሎች ካሉበት በመከራ ነው ፈልጌ ያገኘሁት….በዛን ወቅት ካርኒ አንጠቀምም ነበር…ግን የሞች ስምን …የተቀበረበትን ቀን እና የከፈለውን ብር የመሳሰሉትን መረጃዎች በዚህ መዝገብ እንመዘግብ ነበር›› በማለት
የሚሰነፍጥ አይነት ሽታ ያለውን መዝገብ አቀበሏት….ኩማንደሩ መዝገቡን ተቀብሎ ቀዳዶ ለመጣል ነበር ፍላጎቱ… ግን እንደምንም ራሱን ተቆጣጠረ እና በዝምታ የሚሆነው ያይ ጀመር..በመስገብገብ ተቀበለችን እየገለጠች እያንዳንዱ ገፅ ላይ ማየት ጀመረች ፡፡
አገኘሁት..ይሄውና…..ስሟ የተቀበረችበት ቀን……ምርምር በሚለው ቦታ ላይ ..ሬሳው ተቃጥሎ ስለነበረ ቀብሩ የመታሰቢያ ነው››ይላል፡፡በድንጋጤ ጭንቅላቷን ያዘች፡፡
በብስጭት ሰውነቷ እየተቃጠለ ነበር፣…
"አያቴ ለምን ይህን አልተናገረችም?"ይህንን ጥያቄ ለሁለተኛ ጊዜ ስትጠይቀው ነው፡፡ "ምናልባት ጠቃሚ ነው ብላ አላሰበችም ይሆናል."
በድንገት ወደ ፊት ቀረበች፣ ክርኖቿን ጠረጴዛው ላይ አሳርፋ አገጮን በሁለት እጆቿ ደገፈች። ሆዷ በጣም ተንቦጫቦጨ። ትኩስ እንባ ከአይኖቾ ረገፉ
"እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህ በሽታ ነው፣ ግን ማወቅ አለብኝ።አዎ እውነቱን ማወቅ አለብኝ።"ትንሽ ትንፋሽ ከወሰደች በኋላ መዝገቡን እንደገና ከፈተች እና የተለያዩ ቅጾችን ማገላበጥ ጀመረች። አንዱን እያነበበች ትንፋሿን በደንብ ወሰደች።
"ምንድነው ይሄ?፧"
"ምኑ ?"
"በመጨረሻ ላይ ያለው ያስቀባሪ ፊርማውን ተመልከት." "ጋሽ ፍሰሀ ነው"
"ይህ ማለት በወቅቱ ሁሉንም ወጪዎች ሆነ የቀብር ስርአቱን ይቆጣጠርና ክፍያውን ሁሉ ይከፍል የነበረው እሱ ነው ማለት ነው…እና ይሄ አይገርምህም?››
"ለምን ይገርመኛል።
‹‹እናቴ የእሱ ንብረት በሆነ መሬት ላይ ነው የሞተችው…ከዛ ጀምሮ ሆስፒታል ገብታ
..ከዛም እስክትቀበር ድረስ እያንዳንዱ በሆነው ነገር ሁሉ በእሱ እይታ ውስጥ ነበር….ወይ የሆነውን ነገር ሁሉ ያደረገው እራሱ ነው ወይንም ደግሞ ማን ምን እንዳደረገ በትክክል ያውቃል፡››
‹‹ምን አይነት ቆሻሻ ጭንቅላት ነው ያለሽ…?በአንቺ ቦታ ሌላ ሰው ቢሆን ኖሮ እናቴን ስላስቀበረልኝና አስፈላጊውን ነገር ሁሉ ስላደረገ እግዚያብሄር ይስጠው ብለው ነበር የሚያመሰግኑት››

👍27❤16
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አራታ
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///
ስርጉት ወደአባቷ የጥናት ክፍል ስትገባ ። አባቷ ጠረጴዛው ላይ አቀርቅሮ አንድ ፋይል እያነበበ ነበር ››
"ዛሬ እረፍት የሆንክ መስሎኝ ነበር››
" አዎ ነበርኩ ግን አንዱ ማየት የሚገባኝ ጉዳይ ስለነበረ ይሄው እንደምታይኝ ፋይል እያገላበጥኩ ነው፡፡››
"በቅርብ በጣም ጠንክረህ እየሰራህ ነው.. ግን ደግሞ በጣም መጨናነቅ ይታይብሀል…ምነው ችግር አለ እንዴ."
"ያቺ የሰሎሜ ልጅ ነች"
"የሰሎሜ ሴት ልጅ? አሁንም እያስቸገረችህ ነው?"
‹‹የእናቷ አስከሬኑ እንዲወጣ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ፈልጋ ትናንት ቢሮዬ መጥታ ነበር።››
"አምላኬ!"
ስርጉት ባለማመን በሹክሹክታ ተናገረች።
"እና ምን አልካት?."
"ጥያቄዋን ውድቅ አደረኩታ."
"መልካም አድርገሀል "
"ምንም አማራጭ አልነበረኝም። አስከሬኑ ተቃጥሎል …ብትከፍትም በትንሽ የእንጨት ሳጥን የተቀመጠ አመድ ነው የምታገኘው››
"እና የእናቷ ሬሳ እንደተቃጠለ ስትሰማ ምን አለች?"
"አላውቅም …ኩማንደሩ ነው የነገራት ።, ሙሉ በሙሉ እንዳላመነችበት እገምታለሁ."
"ጋሽ ፍሰሀ እና ጁኒዬር ስለዚህ ጉዳይ ያውቃሉ?"
"እስከአሁን ድረስ እንደሚያውቁ እርግጠኛ ነኝ። ኩማንደሩ ይነግራቸዋል።"
ስርጉት"ምናልባት" ስትል አጉረመረመች። ለአንድ አፍታ በፀጥታ ማሰላሰል ጀመረች. "ታዲያ ምን ላመጣልህ..ሻይ ወይስ ቡና ..ቁርስ በልተሀል??"
"ስርጉቴ ፣ አመሰግናለሁ ምንም አልፈልግም….አሁን ይሄንን ፋይል መመርመሬን መቀጠል አለብኝ..ብቻዬን ተይኝ።"
" ይቅርታ ስላስጨነቅኩህ..አባዬ…በቃ ቻው " ብላ ግንባሩን ሳመችና ቢሮውን ለቃ ወጣች፡፡
ስርጉት የጥናት ክፍሉን በጸጥታ ዘጋችለትና ወደ መኝታ ቤቷ አመራች፡፡ ጥሩ ስሜት አልተሰማትም።ስርጉት ሆዷን እየቆረጣት ነው ፡፡ዛሬ ጥዋት ነበር የወር አበባዋን የጀመረው።ምንም እንኳን እነዚህን ወርሃዊ ፍሰቶች በየወሩ መቀበል እና መሸኘት የግድ ቢሆንም የአርባዎቹ አጋማሽ ዕድሜዋ ልክ እንደ ታዳጊ ልጅ የሚያሰቃያት ቁርጠት የሚያሰለች ብቻ ሳይሆን አስቂኝ ሆናባታል። ይሄ ግማሽ እድሜዋን ያስተናገደችው የወርአበባ ሴት መሆኗን ማሳሰቢያ ብቻ ነበር። አንድም ልጅ መውለድ አልቻለችም፡፡
በህይወቷ ውስጥ ለልጅ የሚከፈል መስዋዕትነትና እና ከልጅ የሚገኝ ፍቅር ተቋዳሽ ባለመኗ በየቀኑ ታዝናለች። አንዳንድ ሰዎች አዘውትረው እንደሚጸልዩ ሁሉ፣ ስርጉትም ለፈጣሪዎ ስለት ሁሉ ተስላ ነበር…ለዛውም ደጋግማ ..ግን ምንም ለውጥ እልነበረውም፡፡በቤቱ ውስጥ የሚሯሯጡ የሕጻናት ትናፍቃለች። ባሏ በለሊት ወደመኝታ ክፍሏ ገብቶ ጡቶቿን እየነካካ እና እረፍት ያጣ ገላዋን ረሀብ እንዲያረካላት ትፈልጋለች።ሶስተኛውን መሳቢያ ከፈተች እና የፎቶ አልበሙን አወጣች።በአክብሮት ከፈተችው። አንድ በአንድ እየገለጠች ማየት ጀመረች፡፡ ውድ ትዝታዎችን - ቢጫ ቀለም ያለው ጋዜጣ ከፎቶዋ ስር አለ፣አወጣችና አየችው….ስለሰሎሜ ግድያ የሚያትት ነው፡፡ .. ጨው ጨው የሚል እንባ ከአይኖቿ ፈሰሰ። በማህፀኗ ውስጥ ያለውን የባዶነት ህመም ለማስታገስ የእጇን ጭኖቾ መካከል ጨመረችና ጭብጥብጥ ብላ ተኛች፡፡
…///
አለም ከስራ ቀደም ብላ ወጣችና ለጁኒዬር ደወለችለት…
‹‹እንዴት ነሽ አሌክስ?››
ለስላሳና ማራኪ ድምፅ ነው …በዛ ላይ አሌክስ ብሎ ሲጠራት የተለየ ስሜት ነው የተሰማት፡፡
‹‹ሰላም ነኝ..ላገኝህ ፈልጌ ነበር››
‹‹ምነው? መክሰስ ልትጋብዢኝ ነው?››
‹‹ብጋብዝህ ደስ ይለኝ ነበር…ግን ደግሞ አጣዳፊ ጉዳይ ነበረኝ…አንተን እና አባትህን ማግኘት ፈልጌ ነበር››
‹‹ምነው በሰላም?››
‹‹አይ በሰላም ነው ማለት እንኳን አልችልም..ግን ላገኛችሁ እፈልጋለው፡፡››
‹‹እንግዲው ሁለታችንም ቢሮ ነው ያለነው…የሶሌ ኢንተርፕራይዝ ህንፃን የት እንደሆነ ታውቂያለሽ?፡፡››
‹‹አዎ ..ወደዛው ልምጣ?››
‹‹ጥሩ… ነይ.. እጠብቅሻለው››
ስልኳን ዘጋችና ቀጥታ ወደእዛው ነው የሄደችው፡፡ከህንፃው ውጭ ጠብቆ ተቀበላትና ቀጥታ ወደ አባትዬው ቢሮ ይዞት ሄደ፡፡ጠረጴዛውን ከበው ከተቀመጡ በኃላ የንግግሩን ቅድሚያ ወሰደች…ቀጥታ ወደመጣችበት ጉዳይ ነው የገባችው፡፡
"ትናንት ዳኛ ዋልልኝን በድጋሚ አናግሬቸው ነበር።" አለም ሁለቱም ሰዎች ንግግሯን ተከትሎ ውጥረት ውስጥ ሲገቡ ተመለከተች፡፡
"ለምን ጉዳይ… ?" አቶ ፍሰሀ ጠየቀ።
"የእናቴን አስከሬን ለማውጣት ፈልጌ ነበር.››
"አምላኬ ሆይ፣ ለምን እንደዚህ አይነት ነገር ማድረግ ፈለግሽ? ››አቶ ፍሰሀ ደነገጠ።
" ለማንኛውም የጠየቅኩት ነገር የማይቻል ነው።ያንን እንደምታውቁት ደግሞ እርግጠኛ ነኝ… የእናቴ አስክሬን ተቃጥሏል።"
"ልክ ነው" አለ አቶ ፍሰሀ።
ጁኒዬር በስቃይ አይኖቹን ጨፈነ…
"አቶ ፍሰሀ በዛን ወቅት ሁሉን ነገር የወሰንከው አንተ ነበርክ ? በየትኛው መብትህ? አያቴ በህይወት እያለች አንተ እንዴት? ››
" አስከሬኗ የተቃጠለው ማስረጃ ለማጥፋት መስሎሽ ነው እንዴ?"
"አላውቅም!" ጮኸች እና ከተቀመጠችበት ተነሳች። ወደ መስኮቱ ሄደች እና ባዶውን ሰማይ ትኩር ብላ ተመለከተች።ከዛ ተመልሳ ወደእነሱ መጣችና ወንበሯ ላይ ተቀመጠች እና"ያደረግከው ያልተለመደ ነገር ነው..ማብራሪያ እፈልጋለው።"አለችው
"እኔ የፈለኩት አያትሽን ከኃላፊነት ለማላቀቅ ብቻ ነበር። ልጇ በእኔ መሬት ላይ ስለተገደለች ቢያንስ ማድረግ የምችለውን ማድረግ አለብኝ ብዬ አሰብኩ።አያትሽ በሀዘን አእምሮዋ ስለተጎዳ ልንከባከባት ብቻ ነበር የፈለኩት። ያደረኩት ነገር አጠራጣሪ ከመሰለኝ፣ ያ በጣም መጥፎ ነው ፡፡ ወጣቷ ሴት ፣ ዛሬም እንደገና ተመሳሳይ ሁኔታ ቢያጋጥመኝ የማደርገው ተመሳሳዩን ነው ››
‹‹እርግጠኛ ነኝ አያቴ በወቅቱ ላደረከው ነገር አድንቃህና አመስግናህ ነበር..እንደውም ሳስበው ይሄንን ሀገር ላቃ ወደአዲስአበባ መግባት እንደምትፈልግ ስትነግርህ ገንዘብ ሰጥተሀታል፡፡››
‹‹እሷ ነች የነገረችሽ….?አዎ አምስት ሺ ብር ሰጥቼት ነበር…››
‹‹በዛን ጊዜ 5 ሺብር እኮ ማለት የዛሬ መቶ ሺብር ነው፡፡››
‹‹አዎ በትክክል..ለዚህ ነው መመስገን እንጂ መወቀስ አይገባኝም የምልሽ፡፡››
ጁኒዬር ምንም ጣልቃ ሳይገባ የሁለቱን ምልልስ በትግስትና በጭንቀት እያዳመጠ ነው፡፡አለም ንግግሯን ቀጥላለች‹‹ይገርማል ….ቆይ እናቴ ምን ያህል ብትበድላችሁ ነው ትዝታዋንም ሆነ እሷን የሚያስታውሳችሁን ነገሮች ሁሉ ከከተማዋ ለማስወገድ ያንን ሁሉ መስዋዕትነት መክፈል የፈለጋችሁት?››
‹‹ነገ የምታፍሪበትን ነገር አትናገሪ..አያትሽ በወቅቱ በጣም አመስጋኝ ነበረች…ብዙ ?‹‹ታዲያ አሁን ከአመታት በኃላ እናቴን እናንተ እንደገደላችኋት ለምን ነገረችኝ?››
‹‹እሱ እኛንም ግራ ያጋባን ጉዳይ ነው…ምን አልባት በእርጅናዋ የተነሳ አእምሮዋ ሚዛኑን አጥቶ ነገሮችን በትክክል ማሳታወስ ተስኗት ይሆናል..አዎ ከዛ ውጭ ሌላ ማብራሪያ ሊኖረው አይችልም፡፡››
‹‹ቆይ እኔ ያልገባኝ…እንደምትሉት የእናቴ ሬሳ ከተቃጠለ..አመዱን በሳጥን አድርጎ መቅበሩ ለምን አስፈለገ…..?ምን ሊረባ?››
"መቼስ ሰሎሜ ዘሞዶች አሏት …ከዛ በላይም ልጅ አለቻት…ልጅቷ አድጋ እናትሽ ሞታለች ስትባል..የት ነው የተቀበረችው…?መቃብሯን ማየት እፈልጋለው ብትል ለእሷ ለማሳየት ታስቦ ነው…ይሄው እንደፈራነውም የእናቴ መቃብር የት ነው ብለሽ መጠየቅሽ አልቀረም፡፡››
‹‹በእውነቱ አርቆ አሳቢነታችሁ በጣም እያስደነቀኝ ነው፡፡››ስትል በምፀት ተናገረች፡፡

❤33👍9🥰1
"ለማንኛውም መቃብሩን አስከፍቼ ሬሳውን ለማስወጣት አስቤ ነበር ። የፎረንሲክ ምርመራ በማድረግ የእናቴን ገዳይ ምንነትን በተመለከተ የተወሰነ ፍንጭ ይሰጠኛል ብዬ አስቤ ነበር።››ለተወሰነ ሰከንድ ድምጿ ጠፋ።የአቶ ፍሰሀ ማብራሪያ የማያሳምን አይነት ነው የሆነባት ። ሁሉንም የቀብር ወጪዎችን መክፈል፣ ሁሉንም ዝግጅት ማድረግ፣ የሴት አያቷን ሃላፊነት መሸከምና እና የገንዘብ ስጦታ መስጠት። እርግጥ ያደረገው ነገር እንደ ሰሎሜ ልጅ ሆና ስትመለከተው ውስጧን ጥሩ ስሜት እንዲሰማት አድርጎታል። እንደ አቃቤ ህግ ግን የበለጠ እንድትጠራጠር አድርጓታል።
ለጊዜው ከዛ በላይ ምንም የሚታናግራቸው ነገር ስላልነበራት ተሰናብታቸው ወጣች
…ጁኒዬር ልሸኝሽ ብሏት ሲነሳ ..‹‹ቆይ እኔ ልሸኛት›› ብሎ አቶ ፍሰሀ ተነሳ እና ከኋላዋ ተከተላት፡፡
‹‹አረ ችግር የለውም ነበር እኮ››
"ግድ የለም፡በዛውም እግሬን ላፍታታ ብዬ ነው…የሽማግሌ ሰውነት በቀላሉ ነው የሚተሳሰረው››
‹‹አረ አንተ ሽማግሌ..?ከልጅህ የተሻለ ሞቃት ደምና የጋለ ፍላጎት የሚንተከተክብህ ጎረምሳ ነህ››አለችው፡፡
በንግግሯ ከት ብሎ ሳቀና"ለአነቃቂው አስተያየትሽ አመሰግናለው››አላት፡፡
‹‹ምንም አይደል?››
"ስለ አያትሽ መረጃ አለሽ?"ሲል ሌላ ያልጠበቀችውን ጥያቄ ጠየቃት፡፡
"በየቀኑ ወደ ሀኪም ቤት ስልክ እደውላለሁ …ምንም ለውጥ እንደሌለ ነው የሚነግሩኝ….ሰሞኑን ብቅ ብዬ አያታለው ብያለው"
"እግዚያብሄር ቀላሉን እንዲያደርግላቸው ምኞቴ ነው… የሆነ ነገር ከፈለግሽ ምንም ሳታቅማሚ ንገሪኝ?"በዚህ ጊዜ ህንፃውን ለቀው ወጥተው ነበር፡፡
አለም በመገረም በትኩረት ተመለከተችውና ‹‹አቶ ፍሰሀ… ለምን ለእኔ እንደዚህ ደግ ልትሆንልኝ ትሞክራለህ ?"ስትልየገረማትን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
"ስለምወድሽ እና በዋናነት በእናትሽ ምክንያት ነው ።ማወቅ ያለብሽ እኛ ከአንቺ የምንደብቀው ምንም ነገር የለም።"
‹‹ለማንኛውም አመሰግናለው…››ብላ ለመሰናበት እጇን ዘረጋች.. ሲጨብጣት ተንጠራራችና ጉንጩን ስማ ፈዞ በቆመበት ወደመኪናዋ ሄደች……ወደቢሮው ሲመለስ ልጁ ጁኒዬር አሁንም ከመቀመጫው አልተንቀሳቀሰም ነበር…ቀጥታ ወደወንበሩ ሄደና ተቀመጠ፡፡
ጁኒየር ከተቀመጠበት ተነሳና የቢሮውን በር ከውስጥ ዘጋውና ወደውስጠኛው ክፍል ገብቶ የመጠጥ ጠርሙስና ብርጭቆ ይዞ መጣና "ቦድካ ለመጠጣት ዝግጁ ነህ አባ?"ሲል ጠየቀ፡፡
አባትዬውም በልጁ ሁኔታ ግራ እየተጋባ"እስካሁን አይደለሁም ….ጠንካራ መጠጥ ለመጠጣት ቀኑ በጣም ገና ነው።"ሲል መለሰለት፡፡
"ከመቼ ጀምሮ ነው መጠጥ ለመጠጣት ጊዜውን ከግምት ውስጥ ማስገባት የጀመርከው? "ከዛሬ"
ዝም ብሎ በራሱ ፍላጎት መጠጡን በሁለት ብርጭቆ ቀዳና አንዱን አባቱ ፊት ሌላውን ለራሱ ይዞ ቁጭ አለና ‹‹አባዬ…ላናግርህ እፈልጋለሁ።" አለው፡፡
"ስለምንድን ነው? ስለስራ እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ ። ›› "ስለአለም ነው ."
" ስለአለም ምን?››
‹‹ወዴት እያመራች ነው….?ይሄንን ጉዳይ እስከምን ድረስ ነው የምትቆፍረው? ››
"የወንጀሉ ፍንጭ ላይ ለመድረስ በቁርጠኝነት እየሰራች ያለች ሴት ነች። ቆንጆ ሴት ብትሆንም ችኮ ነገር ነች። ለስላሳ ትመስላለች ነገር ግን አይደለችም። እሷ ጭቃ ሰብስቦ እንደያዘ ቦት ጫማ ከባድ ነች። ››አለው
ጁኒየር በቁጭት "ይህን አውቃለሁ" አለ።
" ታውቃለህ ግን ደግሞ እሷን ለማስቆም ምንም ነገር ስትሰራ አላየሁም።" "ምን እንዳደርግ ትፈልጋለህ?››
‹‹በፍቅር አንበርክካት››
‹‹እንዴት አድርጌ? ልክ እንደ ጎረምሳ አፍቃሪ ወደፍርድ ቤት የምትሄድበትን መንገድ በአበቦች …የቢሮዋን ጠረጴዛ በቸኮሌት ልሸፍነው…ለዛውም ገደብ ያለበት ፍቅር እንዴትነው የሚሰራው?"
"አዎ …ማድረግ ያለብህን ሁሉ አድርግ .. ትሰማለህ የእኔ ልጅ ። ጥሩ ሕይወት አለህ። በየዓመቱ አዲስ ሞዴል መኪና ትነዳለህ፣ ትልቅ በአልማዝ ያሸበረቀ ሮሌክስ ሰዓት ታስራለህ። ረብጣ ብር እያሲያዝክ ቁማር ትጫወታለህ።ግን ህይወት ማለት ያ ብቻ አይደለም..አሁን ትልቅ ሰው ሆነሀል…..እያንዳንዱ እንቅስቃሴህም የተለካ መሆን አለበት..አስብ… ለምርጫውም ከአንድአመት ብዙም ያልበለጠ ጊዜ ነው የቀረህ››
‹‹ግን ዝም ብንላት …..የት ድረስ ትጓዛለች?››
"ምንም በተጨባጭ ልታቀርበው የምትችለው ማስረጃ የላትም። ይህን የምታውቅ ይመስለኛል። ወደ ጨለማ ቀስቷን እየወረወረች በአጋጣሚ አንዱን አህያ ልመታው እችላለው ብላ እድሏን እየሞከረች ነው ያለችው። ይዋል ይደር እንጂ፣ ክንዷ ይደክማል። ቢሆንም ግን ገና ለገና እንደዛ ይሆናል በሚል ተስፋ እጅና እግራችንን አጣጥፈን ቁጭ ማለት የለብንም፡፡››
"ስለዚህ ምን እንደሚሰማኝ ታውቃለህ አባዬ። እንደዚህ አይነት ጩኸት አልወድም። ሴቶች በፍርድ ቤት ውስጥ ባይገቡ ጥሩ ነበር።"
"ወዴት ታስቀምጣቸዋለህ? በመኝታ ክፍልህ?"ተሳለቀበት፡፡
ጁኒየር ሳቀ። "እንደዛ ቢሆን ምንም ስህተት የለውም."
"ስለ ዋናው አቃቢ ህግ ግርማ በደንብ ነው የማውቀው….እሱ ለሀቅ እሞታው የሚል አደገኛ ሰው ነው፣ ማንኛውም ሰው ተገቢውን ፍርድ ማግኘት እንዲችል ነው ወንበሬ ላይ የተቀመጥኩት ብሎ የሚመፃደቅ ሰው ነው..እናም ይህቺ የእሱ ምክትል የሆነች አማላይ ወጣት ምንም ነገር ብታደርግ ከጓኗ ሆኖ ያግዛታል እንጂ አድቢ አይላትም››
"ሁሉንም ነገር ላይ በጥልቀት እያሰብክበት እንደሆነ አይቻለሁ" ሲል ጁኒየር በደረቅ አስተያየት ተናገረ።
"ምክንያቱም ካንተ በተለየ መልኩ ነገሮችን ለአጋጣሚ አልተዋቸውም።የማጣራት ስራ ሰርቼያለው፣እሷን በዙረያዋ ያሉትን ሰዎች ታሪክ በጥልቀት ፈትሻለው።››
ጁኒየር በሹክሹክታ "አባዬ አንተ እኮ ሁሌ እንዳስገረምከኝ ነው"አለው በአድናቆት ።
"ሁሌ ሊያጠቃህ የሚፈልገው ሰው ምን አይነት ካርዶች እንደያዘ ማወቅ አለብህ።ልጄ ሆይ አሸናፊ እጅ መያዝህ ምንም አይጠቅምህም።ይህቺን ልጅ በፍጥነት ተቆጣጠራት..ግን ደግሜ አስጠነቅቅሀለው በምንም አይነት ተአምር አልጋ ላይ ይዛሀት እንዳትወድቅ..”
‹‹ ይህ እኮ ነው የማይገባኝ አባዬ….ካፈቀርኳት ለምን አይሆንም..እንደውም ለምን አላገባትም፡፡››
አቶ ፍሰሀ የጁኒየርን ጉልበት መታ መታ አደረገና "እንደዛ ከሆነ በጣም መጥፎ ችግር ነው ሚያጋጥምህ….ምን አልባትም እድሜ ልክህን እስር ቤት እንድታሳለፍ ነው የማደርግህ?"አለው
ጁኒዬር በአባቱ ማስጠንቀቂያ ፍርሀት ተሰማው፡፡
‹‹ሰሎሜ ባሏ ከሞተባት በኃላ… ‹ ለእኔ ተስማሚ ሚስት ነሽ ..አፈቅርሻለው …እንጋባ›› ብዬት ነበር….ግን መልሷ የሚያሳምም ነበር….እናትዬውን በዛ ወቅት ማሳመን ያልቻልኩ አሁን እንዴት ብዬ ነው ልጅዬውን ማሳመን የምችለው…ላድርገው ብልም አይሳካልኝም፡፡››
‹‹ ያኔ የአሥራ ስምንት አመት አፍላ ጎረምሳ ነበርክ ልጄ!..ሰሎሜ ደግሞ ሕፃን ያላት መበለት ነበረች።ባለፈው ነገር አትዘን….አሁን ግን የምልህን ስማ ››
‹‹ሰሎሜ ባታበላሸው …ዛሬ አለም የእንጀራ ልጄ ልትሆን ትችል ነበር "

❤28👍5
"ሌሎች ከግምት ውስጥ የሚገቡ ነገሮች ነበሩ."
ጁኒየር ዙሪያውን ዞረ። "እንደ ምን አይነት?"
"ያ ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት ነበር፣ሌላ ጊዜ፤ሌላ ሰው. አለምን እንደ እናቷ አይደለችም. የበለጠ ውብ ነች ,…የማሰብ ብቃቷም በጣም የተሻለ ነው ፡፡ አንተ መሆን ካለብህ ሰው ግማሹን ከሆንክ በህይወትህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከልብህ ይልቅ በጭንቅላትህ ማሰብ ከቻልክ ያሳብከውን ታሳከዋለህ….እሷም ካንተ ፍቅር ከያዛት በኃላ የእናቷን ገዳይ ማሳደድ ትረሳውና አንተን ማሳደድ ትጀምራለች››
" እንደዛ እንዲሆን ተስፋ አደርጋለው። ከእሷ ጋር የፍቅር ጫወታ ከመጀመሬ በፊት እርግጠኛ ለመሆን ፈልጌ ነበር ።አመንክም አላመንክም ሰሎሜን በጣም እወደት ነበር። እና ምን አልባትም ልጇንም ልክ እንደእሷ መውደድ እችል ይሆናል። ››
"አትተኛት እንጂ… በፈለከው መጠን ልትወዳት ትችላለህ?"
በቃ አባዬ ከዚህ በላይ ካንተ ጋር ማውራት አልችልም..በጣም እየተጨናነቅኩ ነው….››በማለት መቀመጫውን ለቀቀና ወደበሩ መራመድ ጀመረ፡፡
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ጁኒየር ዙሪያውን ዞረ። "እንደ ምን አይነት?"
"ያ ከሃያ አምስት ዓመታት በፊት ነበር፣ሌላ ጊዜ፤ሌላ ሰው. አለምን እንደ እናቷ አይደለችም. የበለጠ ውብ ነች ,…የማሰብ ብቃቷም በጣም የተሻለ ነው ፡፡ አንተ መሆን ካለብህ ሰው ግማሹን ከሆንክ በህይወትህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከልብህ ይልቅ በጭንቅላትህ ማሰብ ከቻልክ ያሳብከውን ታሳከዋለህ….እሷም ካንተ ፍቅር ከያዛት በኃላ የእናቷን ገዳይ ማሳደድ ትረሳውና አንተን ማሳደድ ትጀምራለች››
" እንደዛ እንዲሆን ተስፋ አደርጋለው። ከእሷ ጋር የፍቅር ጫወታ ከመጀመሬ በፊት እርግጠኛ ለመሆን ፈልጌ ነበር ።አመንክም አላመንክም ሰሎሜን በጣም እወደት ነበር። እና ምን አልባትም ልጇንም ልክ እንደእሷ መውደድ እችል ይሆናል። ››
"አትተኛት እንጂ… በፈለከው መጠን ልትወዳት ትችላለህ?"
በቃ አባዬ ከዚህ በላይ ካንተ ጋር ማውራት አልችልም..በጣም እየተጨናነቅኩ ነው….››በማለት መቀመጫውን ለቀቀና ወደበሩ መራመድ ጀመረ፡፡
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍39❤21
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
፡
///
አለም ወደ አፓርታማዋ እደገባች የእጅ ቦርሳዋን እና ካፖርትዋን ወንበር ላይ አስቀመጠች
ዛሬ ከሰአት በኋላ ለዋናው አቃቢ ህጉ ደውላለት ነበር። እስካሁን እጇ ላይ ባስገባችው ግኝት ደስተኛ ሆኖ አላገኘችውም፡፡ ስራውና እርግፍ አድርጋ ወደ አዲስ አበባዋ እንድትመለስ ወይም እራሷን ካለፈው ታሪኳ ጋር እንድታስታርቅ ምርጫ አቀረበላት።እስከአሁን በሚጠበቀው ልክ ተጨባጭ ውጤት ማግኘት ያለመቻሏ የሱ ቅሬታ አንዱ ምክንያት ነበር። ዛሬ ማታ ባላት ቀጠሮ መሰረት ለዋናው አቃቢ ህግጉ የአይን እማኙን አግኝታ ያገኘችውን መረጃ ስታቀርብለት ስሜቱ ሙሉ በሙሉ እንደሚቀየር እርግጠኛ ነች።
ወደ መጠጥ ቤቱ የመኪና ማቆሚያ ቦታ በገባችበትን ቅጽበት ብዙም ተስፋ እንደማይሰጥ ማወቅ ነበረባት። አምፖሎቹ ቦግ ብልጭ ድርግም ከሚለው የሸዋ በር መጠጥ ቤቶች መካከል በአንዱ ነው የቀጠራት ። ከደረሰች በላ ወደ ውስጥ አልፋ ለመግባት በጣም አመንትታ ነበር።ግን ይሄ የያዘችውን ምርመራ ከስኬት ለማድረስ መክፈል ከሚገባት መስዋዕትነት መካከል አንዱ እንደሆነ ራሷን በራሷ አሳመነችና እግሮቾን እየጎተተች ወደውስጥ ገባች፡፡በክፍሉ ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ሰው ትኩስ ስጋ እንዳየ ጥንብ አንሳ ወደ እሷ ተመለከቷት፡። የተወሰኑ ሴቶች ቢኖርም የእነሱ እይታ እንደውም ከወንዶቹ በተቃራኒ ሻካራ መስሎ ነው የተሰማት ፡፡ወደኋላ ዞራ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጋ ትታ መሮጥ ፈለገች ..ግን ያደረገችው ወደግራዋ ታጥፋ ኮርነር አካባቢ ወንበር ስባ መቀመጥ ነበር፡፡
አስተናጋጆ መጥታ
‹‹ ምን ልታዘዝ ስትላት"
‹‹እባክሽ ነጭ ወይን "ስትል አዘዘች፡፡
በስልክ ያናገራት እና ድምፁን ብቻ የሰማችው ሰው የትኛው እንደሆነ ለማወቅ ዓይኗን ከአንዱ አቅጣጫ ወደሌላው በማወናጨፍ ለመገመት ሞከረች ።ግን ….አይኗ ሲንከራተት እየተካታተሉ የነበሩ አንዳንድ ወንዶች ሁኔታዋን በተለየ መንገድ ትርጉም ሰጥተውት አስፀያፊ ምልክት ሲሰጦት ነው ያወቀችው። ከዛ በኋላ አይኖቾን አደብ አስገዛችና መጠጧን እየተጎነጨች አቀርቅራ ማሰላሰሏን ቀጠለች፡፡ የምትፈልገው ሰው እዛ ሆቴል ውስጥ ካሉት ሰዎች መካከል አንዱ ከሆነ የምትወደው አይነት ሰው ሊሆን እንደማይችል አሰበችና ተረበሸች፡፡
እያጨሰች ባትሆንም በዙሪያዋ ብዙ ሰዎች የተለያየ አይነት ሲጋር እያጬሱ ስለሆነ በጭስ ደመና ታፍናለች። እና አሁንም ብቻዋን እንደተቀመጠች ነው።በመጨረሻ፣ እሷ ስትመጣ ባለጌ ወንበር ላይ ተቀምጦ የነበረ የተጎሳቆለ አይነት ሰው ከመቀመጫው ተነሳና ወደ እሷ አቅጣጫ መጣ። ከእሷ ጠረጴዛ ጋር ከመድረሱ በፊት ካለው ሌለኛው ጠረጴዛ ላይ ወንበር ስቦ ተቀመጠና ይዞ የመጣውን ቢራ ከፊት ለፊቱ አስቀመጠ…የሁለቱ ወንበር መደገፊያ የተደጋገፈ ስለሆነ ጅርባቸው ተጋጥሟል ማለት ይቻላል..በዛ ላይ ሰውዬው ጥቁር ኮፍያ አድርጎ ፊቱን በከፍል ስለሸፈነ ምን እንደሚመስል በትክክል ልትለየው አልቻለችም፡፡፡
አንገቱን ወደኋላ ለጥጦ"ሰው እየጠበቅሽ ነው?"ሲል ተናገረ…ድምፁ የተለየ ይመስላል፣
"እኔ መሆኔን በምን አወቅክ ?ደግሞስ ይህን ያህል ጊዜ የፈጀብህ ለምንድን ነው?"ብላ በቀዝቃዛ ድምጽ መለሰችለት።
"ድፍረቴን እያሰባሰብኩ ነበር" አለ ከቢራው እየተጎነጨለት።
‹‹ጥሩ….ከእኔ ጋር አንድ ጠረጴዛ ለመጋራት ይሄን ያህል ትፈራለህ እንዴ?››
‹‹ህይወት እኮ ነው የያዝኩት… ለምን አልፈራም?››
"ይሁን እሺ…የምትነግረኝ ነገር እንዳለህ ገምታለው…ምንድነው ?።"
"የምትፈልጊውን ሁሉ ማውራት እንችላለን " የቢራ ጠርሙስ ጠረጴዛው ላይ አስቀምጦ ከኪሱ ብር አወጣና አስቀምጦ ‹‹..ግን መጀመሪያ ከዚህ መውጣት አለብን›› አላት፡፡
‹‹ ጥሩ የእኔ መኪና ውጭ ነው …ነጭ ቪታራ ነች"
‹‹አውቃታለው››
‹‹ሂሳብ ከፍዬ መጣሁ.. እዛ ጠብቀኝ››
ቀድሞ መራመድ ጀመረ፡፡ሹክክ ብሎ ሆቴሉን ለቆ ተሰወረ….እሷም አስተናጋጁን ጠርታ ሂሳብን ዘጋችና ግማሽ የቀረውን የወይን ጠርሙስ ባለበት ጥላ ቦርሳዋን ይዛ ወደውጭ ወጣች ..ወደ መኪናዋ ቀረበች ….ምንም ሰው በአካባቢው አይታያትም…..ወደመኪናዋ ውስጥ ገባችና ..የውስጥ መብረቱን አብርታ መጠበቅ ጀመረች…….ምንም ብቅ የሚል ሰው አልነበረም፡፡ ግራ ተጋባች…ተበሳጨች…ሰሞኑን ይደውልላት በነበረው ስልክ ደወለችለት…እንደተለመደው ይጠራል አይነሳም፡፡ማልቀስ ሁሉ አማራት..እዛው መኪናዋ ውስጥ ኩርምት እንዳለች ከአንድ ሰዓት በላይ አሳለፈች..በመጨረሻ ተስፋ ቆረጠችና አዲስ ወደ ተከራየችው አፓርታማ ነዳችው፡፡ከሀሳቧ ያባነናት የስልክ ጥሪ ድምፅ ነው… ከብስጭቷ ሳትወጣ ከአልጋዋ ተፈናጥራ ተነሳችና አነሳችው።
"ሀሎ።"
"እብድ ነው እንዴ ብለሽ አስበሻል አይደል ?"
የምታውቀውና የምትጠብቀው ድምፅ ነው።
"አንተ የት ነበርክ? ከእኔ ጋር ምን አይነት ጫወታ ነው አየተጫወትክ ያለኸው?መኪናዬ ውስጥ ተጎልቼ አንድ ሰዓት ያህል ስጠብቅህ ነበር.."
"ካንቺ ጋር ድብብቆሽ መጫወት ብፈልግ ኖሮ መልኬን እንድታይው አልፈቅድልሽም ነበር….ኩማንደሩ እዛው ነበር?"
"ምንድን ነው የምታወራው? ገማዶ እዚያ አልነበረም"
"የእኔ እመቤት ነበረ፣ በትክክል ነው ያየሁት። በቀጠሯችን መሰረት በቦታው ተገኝቻለሁ ግን ኩማንደር ገመዶ ከጀርባሽ በቅርብ ርቀት ተቀምጦ እያየሁት በአካባቢው መቆየት እና ከአንቺ ጋር ማውራቱን መቀጠል አልችልም… ፡፡››
‹‹ኩማንደሩ እየተከተለህ ነበር እንዴ?"
"እንዴት እንደዛ ያደርጋል….እኔ ምንም አይነት ህግ እልጣስኩም,…በተለይም ከፍሰሀ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች አንገቴ ስር ሲተነፍሱ. ደስ አይለኝም…ኩማንደሩ ደግሞ ከልጅነቱ ጀምሮ ከፍሰሀ ጋር ያበረ ወፍራም ሌባ ነው. የእሱ ዋነኛ ቀኝ እጁ ነው..ለማንኛውም አንቺን ተከትሎ የመጣ ይመስለኛል!!››
"ኩማንደሩ በአካባቢዬ እንዳለ አላውቅም ነበር. ሌላ ቦታ እንገናኛለን. በሚቀጥለው ጊዜ እሱ እንዳልተከተለኝ እርግጠኛ እሆናለሁ."ስትል ቃል ገባችለት፡፡
" እስቲ እናያለን።"
‹‹እናያለን ማለት ምንድነው…?ነው ወይስ የምትነግረኝ ነገር ያን ያህል አስፈላጊ አይደለም፡፡.››
"ወንጀሉን ማን እንደፈፀመው አይቻለሁ እመቤት"
ተፈላጊነቱን ስታሳንስበት ተበሳጨ፡፡
"ታዲያ የት ነው የምንገናኘው?
እና መቼ?"
‹‹አሁን ህዝብ የተሰበሰበበት ቦታ አይደለም መገናኘት ያለብን ….ከቶታል ማደያ በቀኝ በኩል በምታስገባው መንገድ አንድ ሰማያዊ ቀለም የተቀባ ህንጻ አለ…. ከእሱ ፊት ለፊት
አንድ አሮጌ ሰማያዊ ባጃጅ ውስጥ ቁጭ ብዬ እጠብቅሻለው። እኔ ከኃላ ውስጥ አለሁ..ዝም ብለሽ ትገቢያለሽ።"
‹‹ባጃጁ ያንተ ነው ማለት ነው››
‹‹ከየት አባቴ አምጥቼ…የጓደኛዬ ነው..ሰሞኑን ስለታመመ እኔ ደግሞ ስራ ፈት ስለሆንኩ እየሰራሁለት ነው፡፡››
"በቃ በሰዓቱ እገኛለሁ- ግን እስከዛው ቢያንስ ስምህን ልትነግረኝ አትችልም?"
"አይ አልችልም" ስልኩን ዘጋው። አለም ተሳደበች። ከአልጋው ወርዳ ወደ መስኮቱ ሄደች ፣ መጋረጃዎችን ገለጠችና ወደውጭ ተመለከተች…የጠቆረው እና ኮከቦች የተበተሉበት ሰማይን በትኩረት አየች፡፡መጋረጃዎቹን ዘጋች፣ ወደ ስልኩ ተመለሰች፣ እና በቁጣ ውስጥ እንዳለች ሌላ ቁጥር ላይ ደወለች። የዓይን እማኝን በማስፈራራቱ በኩማንደሩ ላይ በጣም ተናደደች፣ እየተንቀጠቀጠች ነበር።ቀጥታ እሱ ላይ ነበር መደወል የፈለገችው…ግን ደግሞ ቁጥሩን አታውቅም…..የሰዓቱ መምሸት ግድ አልሰጣትም ፡፡ስልኩ ተነሳ፡፡

❤49👍2🥰2
"ፖሊስ ጣቢያ ነው ."
‹‹አዎ..ምን ልታዘዝ?››ጎርናና የወንድ ድምፅ፡፡
"ኩማንደር ገመዶን ፈልጌ ነበር."
"ይቅርታ በዚህን ሰዓት አይገኙም" ተባለች።
"አስቸኳይ ነው?"
" ምንም ልረዳሽ አልችልም የእኔ እህት….ችግር ላይ ከሆንሽ ከተረኛ ፖሊስ ጋር ላገናኝሽ?"
‹‹አይ ቀጥታ ኩማንደሩን ነው የፈለኩት››
"እንግዲያው መኖሪያ ቤቱ ነው..በግል ስልኩ ደውይለት፡፡." "እባክህ የቤቱን ቁጥር ትሰጠኛለህ ?"
"እኛ የግል ስልኩን ለመስጠት ፈቃድ የለንም ."
"እኔ የዞኑ ረዳት አቃቢ ህግ አለም ጎበና ነኝ … ። አሁኑኑ ከኩማንደሩ ጋር መነጋገር አለብኝ። በጣም አስፈላጊ ነው። ››
ማብራሪያዋን ተከትሎ ያለምንም ማቅማማት ስልክ ቁጥሩ ተሰጣት። ኩማንደሩ በእሷ ላይ እያደረገ ያለውን ድብቅ ክትትል ወዲያውኑ ለማስቆም አስባ ነበር።ስልኩን አንስቶ ድምፁን ስትሰማ ግን የሷ ውሳኔ ጠፋ።
"አለም ነኝ."
"ምን ፈለግሽ?"
"ዛሬ ማታ ለምን ስትከተለኝ እንደነበር ማወቅ እፈልጋለሁ?." "እየተከታተልኩሽ እንደሆነ እንዴት አወቅሽ?"
".. አየሁህ።"
"አይ፣ አላየሺኝም። በዚያ ሆቴል ውስጥ ከሙስጠፋ ጋር ምን ታደርጊ ነበር?" "ከማንም ጋር አልነበርኩም..እኔ ብቻዬን እየጠጣሁ ነበር."
" አረባክሽ..ካልጠፋ ቦታ የዞኑ አቃቢ ህግ የሆነች ሴት የወንጀለኞች መገናኛ የሆነ ሆቴል ዘና ብላ መጠጥ እየጠጣች ማየት የሚገርም ነገር ነው››በማለት በፌዝ ጠየቀ።
"ለስራ ጉዳይ እዛ ተገኝቼ ቢሆንስ ምን ታውቃለህ ?ለማንኛውም እየተከታተልከኝ እንደነበረ አመንክ ማለት ነው?"
ኩማደሩ በግትርነት ዝም አለ።
"ይህ ነገ ጥዋት ከምንወያይባቸው በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው..መብቴን በህግ እንዳስጠብቅ አትገፋፋኝ።""
‹‹ይቅርታ.. ነገ የዕረፍት ቀኔ ነው።›› "መገናኘታችን የግድ ነው"
"ያ የአንቺ አስተያየት ነው."
"እሺ እርፍትህን የት ነው የምታሳልፈው?"
" ነገ በእንስሰታ እርባታው ቦታ ፈረሶቼን እየተንከባከብኩ ነው የምውለው ።" " ቀኑን ሙሉ ።"
‹‹አዲስ ነገር ካልተፈጠረ ከ3 ሰዓት 9 ሰዓት እዛው ነኝ››
‹‹ጥሩ.. ደህና እደር ›› ብላ ስልኩን ዘጋችው፡፡
////
ወደእሱ ከመቅረቧ በፊት ባለችበት ቆማ ስለሁኔታው በትዝብት ማየቷን ቀጠለች፡፡ የለበሰው ጂንስ ሱሪ ንፁህ ቢሆንም ፣ ከወደ ጫፎቹ ተቀዳዷል፣ ቢጫ ቀለም ያለው ቦት ጫማ ተጫምቷ.. በጭንቅላቱ ላይ ከሰሌን የተሰራ ሰፊ ኮፍያ አድርጓ ደንበኛ ገበሬ መስሏል፡፡ጓንት ያጠለቀው እጅን በፈረሱ ጀርባ ላይ አድርጎ በፍቅር ያሻሸዋል…‹‹እርግጠኛ ነኝ ሰውን እንኳን በዚህ መጠን አይንከባከብም››ስትል በውስጧ አማችው፡፡
አንደኛውን እጁን በላይኛው የአጥር አግዳሚ እንጨት ላይ ተደግፎ ነበር፡፡ባለፈው ምሽት ቤቷ በመጣ ጊዜ ከሰውነቱ አጣብቆ አቅፎ ሲያስለቅሳት ነበር ። አካሏ ላይ ያሳረፋቸው እጆቹን ከእርቃን ሰውነቷ በቀጥታ እንዳይገናኝ በሰዓቱ ከሻወር ቤት ስትወጣ የለበሰችው ጋወን ነበር የከለከለው፡፡ በወቅቱ በጀርባዋ ላይ ጣቶቹን እያንቀሳቀሰ ስሜቷን ሲቆሰቁስ እንደነበረ ትዝ አለት ፡፡ልክ አሁን እየሆነ እንዳሆነ አሰበችና በሰውነቷ ሙቀት ሲፈስበት ተሰማት፡፡
"እረፍ ..አደብ ግዛ" ብሎ ፈረሱ ላይ ጮኸበት።
ድምፁ ልክ እንደ ባህሪያቱ ሁሉ ወንዳ ወንድ ነው።በአቅራቢያው የሚገኙ ፈረሶች ወደ አራት አካባቢ ተከፋፍለው ይታያሉ፣
ሁሉም ሸኮናቸው መሬቱን እየቆፈሩ ስራቸው ፦፦፦ከቀረበላቸው የሳር ክምር ላይ እያነሱ ይበላሉ። የሚንቀጠቀጡት የፈረሶቹ የአፍንጫ ቀዳዳዎች የእንፋሎት መሰል ጭስ ያወጣል
።ኩማንደሩ አንዱን ፈረስ በተለይ ወደእሱ ስቦ መዳበሱን ቀጥሏል፡፡ ወደእሱ ቀረበችና ‹‹ስሙ ማን ይባላል››አለችው፡፡
የኩማንደሩ ጭንቅላቱን ቀና ብሎ ተመለከታት፡፡ "ሴት ነች።"ሲል መለሰላት፡፡
"ኦ. ነው እንዴ…ወንድ መስላኝ ነው "አለችና ጀርባዋን መዳበስ ጀመረች፡፡" ያንተ ነች?" "አዎ"
‹‹ይገርማል.. አንድ የፖሊስ መኮንን የራሱ ፈረሶች ኖረውት ሲንከባከብ››
‹‹ምን ይገርማል…ፖሊስ ከመሆኔ በፊት በልጅነቴ ጀምሮ እዚህ እሰራ ነበር…የራሴ የሆኑ ከብቶችና ፈረሶች ይኖሩኝ የጀመረው የፖሊስ መኮንን ከመሆኔ በፊት ነው…እንደውም ፖሊስ ባልሆን ኖሮ አሁን ካሉኝ ነገሮች በጣም በበለጠ ይኖረኝ ነበር››
‹‹አዎ..ትክክል ነህ…እኔም እንደዛ ነው የማምነው…ግን ታዲያ ለምን ፖሊስ ለመሆን ፈለክ?››
‹‹ምክንያቴን ለአንቺ ለመናገር ፍቃደኛ አይደለሁም››አለና ከወንዶቹ ፈረሶች መካከል ነጭ እና ጥቁር ቀለም ኖሮት ቡራቡሬ ገፅ ያለውን ውብ ፈረስ ሉጋሙን በአፉ ከቶ ከመሀከል ጎትቶ አወጣው፡፡ፈረሱም እንዳደረገው ሲሆንለት አየችና ተገረመች፡፡
"ከእሱ ጋር እውነተኛ ግንኙነት ያለህ ይመስላል." አለችው አለም።
"ሲወለድ ስሩ ነበርኩ ..ሙሉ እድሜውን በፍቅር ተንከባክቤዋለው….ስለዚህ ቢወደኝ አይገርምም፡፡››
‹‹ለፈረሶች የምታሳየውን ፍቅር ግማሹ ለሰው ብታሳይ እንዴት ጥሩ ነበር….ፈረሶችህን በትህትና ስታናግር ከቆየህ በኃላ ከሰው ጋር ማውራት ስትጀምር ቶንህ ወዲያው ይቀየርና ተናዳፊ ትሆናልህ››

❤50👍12
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////
‹‹ለፈረሶች የምታሳየውን ፍቅር ግማሹ ለሰው ብታሳይ እንዴት ጥሩ ነበር….ፈረሶችህን በትህትና ስታናግር ከቆየህ በኋላ ከሰው ጋር ማውራት ስትጀምር ቶንህ ወዲያው ይቀየርና ተናዳፊ ትሆናልህ››
የምፀት ፈገግታ ፈገግ አለና‹‹ለፈረሶችም ሆነ ለሰዎች የሚገባቸውን ነው ማደርገው….››አለና አጥሩ ላይ የተንጠለጠለውን ኮርቻ በማንሳት ፈረሱ ጀርባ ላይ አድርጎ አሳሰረውና የፈረሱን ሉጋም ይዞ ወደመውጫው መሄድ ጀመረ፡፡
ግራ ተጋብታ
"ወዴት ትሄዳለህ?"ስትል ጠየቀችው
" ትንሽ መጋለብ ፈልጋለው"
ከንዴቷ አንፃር ማልቀስ አማራት ‹‹ላናግርህ እፈልጋለሁ..ለምን እንደመጣሁ እያወቅክ ጥለኸኝ ልትሄድ ነው..?›› አለችው
ፈረሱ ላይ ወጣና ወደእሷ ቀረበ…እጁን ዘረጋላት….ግራ ተጋብትና በቆመችበት አይኖቾን አቁለጨለጨች….
‹‹እጅሽን ስጪኝ››አላት…..ዝምብላ ቀኝ እጇን ወደላይ ሰቀለችለት.. አጥብቆ ያዛትና ወደላይ ጎተታት…ጥንካሬው አስገረማት….እርካብ ላይ እግሯና አኖረችና እንጣጥ ብላ በመውጣት ከጀርባው ፈረሱ ላይ ተፈናጠጠች፡፡ከዛ ለፈረሱ ሉጋሙን ለቀቅ ሲያደርግለት ፈረሱ እየሰገረ ወደፊት ተስፈነጠረ ፡፡በፍራቻ ወገቡን አጥብቃ አቀፈችው….የኮረኮንች መንገዱን ይዞ ወደ ከተማዋ መውጫ ሽምጥ መጋለብ ጀመሩ….፡፡
"ትላንትና ማታ በቡና ቤት ውስጥ ከማን ጋር ነበር የተገናኘሽው?"
"ይሄ የኔ ጉዳይ ነው ኩማንደር …ለምን ተከተልከኝ?"ልትጠይቀው የምትፈልገው ብዙ ጥያቄዎች ነበራት፣ ነገር ግን በእያንዳንዱ የፈረስ እንቅስቃሴ ከተቀመጠችበት እንጣጥ ብላ ጀርባው ላይ ስትለጠፍበት ስለነበር አእምሮዋን በጀመረው ሀሳብ ላይ ፀንቶ እንዲቆይ ማድረግ ከባድ ሆነባት። እንደምንም ወደ አእምሯዋ የመጣውን የመጀመሪያ ጥያቄ ጠየቀችው።
"አንተ እና እናቴ እንዴት የቅርብ ጓደኛሞች ሆናችሁ?"
"አብረን ነው ያደግነው" አለ በንቀት። ተንፋሽ ወሰደና ቀጠለ"ት/ቤት መጫወቻ ሜዳ ላይ ተጀምሮ በእድሜ እየገፋን ስንሄድ ተሻሻለ"
"አስቸጋሪ ሆኖ አያውቅም?"
"አይ አንዳችን ከሌላችን የምደብቀው ምንም ምስጢር አልነበረንም. እንዲያውም ያንቺን ካሳየሺኝ የእኔንም አሳይሻለው እያልን እንጫወት ነበር."አለና ፈገግ አለ።‹‹በአጠቃላይ በእኔ እና እሷ መካከል አይነኬ የተባለ የውይይት ርዕስ አልነበረም ።››ሲል አከለበት፡፡
"ያ አንድ ሴት ልጅ ከሌላ ሴት ጋር የሚኖራት አይነት ግንኙነት አይደለምን?"
‹‹ብዙውን ጊዜ ግን ሰሎሜ ብዙ የሴት ጓደኞች አልነበራትም, አብዛኛዎቹ ልጃገረዶች በእሷ ይቀኑ ነበር."
"ለምን፧"
አለም መልሱን ቀድሞውንም ብታውቅም ከእሱ አንደበት መስማት ፈለገች፡፡ "በአንተ ምክንያት ነበር አይደል? ካንተ ጋር የነበራት ወዳጅነት?"
"ምናልባት ሊሆን ይችላል, ዋናው ጉዳይ ግን እሷ በጣም ቆንጆ ነበረች…በዙሪያዋ ያሉ አብዛኞቹ ልጃገረዶች እንደ አጋር ሳይሆን እንደ ተቀናቃኝ ነበር የሚቆጥሯት፡፡….ቆይ አንዴ።›› ፈረሱን አቅጣጫ ከመቀየሩ በፊት አስጠነቀቃት እና ፈረሱ ጓድጓዳ አካባቢ ሲረግጥ ወደ ፊት ገፋት፣ እሱ ላይ ተለጠፈች። በደመ ነፍስ ወገቡን አጥብቃ አቀፈችው።
"ፈረስ ቁልቁል ሲወርድ ወደፊት መንሸራተቱ የሚጠበቅ ነው….››
ስትረጋጋ“እናቴ ሁሉንም ሚስጥሮቾን እያመጣች ለአንተ ትዘረግፍ እንደነበረ እየነገርከኝ ነው?›› ብላ ጠየቀችው፡፡
‹‹አዎ, እንደዛ ነበር የምታደርገው…እሷ እንደአንቺ አይነት ውስብስብ ሴት አልበረችም…ለምሳሌ አንድ ቀን ምንም ሳትነግረኝ ከትምህር ቤት ቀረች እና የሆነ ችግር እንዳለ አውቄ ነበር...ተጨንቄ ስለነበር በእረፍት ወደ ቤቷ ሄድኩ. አያትሽ በሥራ ላይ ስለነበሩ ሰሎሜን ብቻዋን እያለቀሰች ነበር ያገኘዋት…ፈርቼ ምን እንደሆነች እስክትነግረኝ ድረስ ጨቀጨቅኳት።"
‹‹ጉዳዩ ምን ነበር?"
‹‹ የወር አበባዋን ለመጀመሪያ ጊዜ መቶባት ነበር….አያትሽ የወር አበባን በተመለከተ የሀጥያት ፍሬ እና እርግማን እንደሆነ የሚተርኩ አስፈሪ ታሪኮች ነግረዋት ስለነበር በጣም አዝና ነበር ያገኘኋት ፡፡ እንዴት ነው አያትሽ ለአንቺም እንደዛ አይነት አስፈሪ ታሪኮችን ይነግሩሽ ነበር?››
አለም ወገቡን ሳትለቅ አንገቷን እንደምንም ቀና አደረገችና‹‹ያን ያህል የሚረብሹ አይነት ታሪኮችን ነግራኝ አታውቀኝም… ምናልባት አያቴ እኔን ማሳደግ በጀመረችበት ጊዜ ተሻሽላ ሊሆን ይችላል።ለአቅመ አዳም በደረስኩበት ጊዜ በቀላሉ ነው የተቀበልኩት።››
ፈረሱ ግልቢያውን እስኪያቆም ድረስ አለም ያሉበትን ቦታ አላስተዋለችም ነበር፡፡መኖሪያ ቤቱ ደርሶ ነበር ያቆመው፡፡
" ከዛስ እንዴት ሆነ?"
‹‹አፅናናኋት እና የወርአበባ ማለት ሴትነቷ በይፋ የታወጀበት ድንቅ ቀን እንደሆነ እና መደስት እንጂ ማልቀስ እንደማይገባት ነገርኳት።››
"ሰራ ታዲያ?"
"እንደምገምተው አዎ። ማልቀሷን አቆመች"
'እና...?'' አለም የታሪኩን በጣም አስፈላጊ ክፍል እንዳልነገራ ስላወቀች እንዲቀጥል አነሳሳችው።
"ከዛማ.. በቃ ።››አለና ቀድሞ ከፈረሱ ላይ በቀላሉ በመውረድ ‹‹ እግርሽን አንሺው።" አለና እሷን ለማውረድ እጁን ዘርግቶ በጠንካራ እጁ ወገቡ ላይ አቀፋትና ወደ መሬት አወረዳት።
ከእናቷ ጋር ሲሳሳም ሚያሳየውን ፎቶ መመልከቷን አስታወሰች ። "ለቅሶዋን ካቆመች በኃላ ሳምካት አይደል?"
በትከሻው የማይመች እንቅስቃሴ አደረገ። "ከዚያን ቀን በፊትም ስሜያት ነበር።" "ግን ያ የመጀመሪያው እውነተኛ መሳም ነበር አይደል?"
እሷን በጥልቀት ተመለከታትና ወደ ቤቱ በረንዳ ወጥቶ በሩን ገፋው ። ወደኃላ ዞር አለና
‹‹መግባትም ሆነ አለመግባት የአንቺ ጉዳይ ነው።››አለና ክፍት አድርጎ ተወው… ወደ ውስጥ ገብቶ ጠፋ, ተስፋ የቆረጠች ቢሆንም ግን ደግሞ ተጫማሪ የማወቅ ጉጉት ስላላት ተከተለችው።
መየፊት ለፊት በር በቀጥታ ወደ ሳሎን ተከፈተ። በግራዋ በኩል ባለው በር በኩል የመመገቢያ ቦታ እና ኩሽና ማየት ችላለች። በተቃራኒው በኩል ያለው የመተላለፊያ መንገድ ወደ መኝታ ክፍል ይወስዳል፣ እሱም ሲያወራ ትሰማለች። የሳሎኑን በር ዘጋች፣ መነጽርዋን አውልቃ ዙሪያዋን ተመለከተች።ቤቱ የወንደላጤነት ወዝ ነበረው …ፈሪኒቸሮቹ መጠነኛና ቅልብጭ ያሉ ናቸው፡፡በግራ ግድግዳ ያለው መደርደሪያ ላይ ያሉት መጻሕፍቶች የተዘበራረቁ ነበሩ፣ ፡፡
"ቡና ትፈልጊያለሽ?"
"ባገኝ ደስ ይለኛል።››
ወደ ኩሽና ገባ። የቀዘቀዙ እግሮቿ የደም ዝውውር እንዲስተካከል እያፍታታች በክፍሉ ውስጥ መዞሯን ቀጠለች። ከመጽሐፍ መደርደሪያው በላይ ወደተቀመጠው አንድ ረጅም ዋንጫ ቀልቧ ተሳበ። በላዩ ላይ የኩማንዱሩ ስም እና ቀኑ በግልፅ ፊደላት ተቀርጾበታል።
"ይህ ትክክለኛው ቀለም ነው?" ዘወር ስትል አንድ ኩባያ ቡና ይዞላት ወደ እሷ እየቀረበ ነበር።
"አመሰግናለሁ።" ብላ ተቀበለችውና …ጭንቅላቷን ወደ ዋንጫው በማዘንበል "ይሄ ያንተ ምርጡ አመት አይደል?"ስትል ጠየቀችው፡፡
"ምን አልባት"
"ምነው ?እርግጠኛ አይደለህም?"
ወደ ወንበሩ ሄደና ተቀመጠ ፡፡ "ያኔ እንደዛ ተሰምቶኝ ነበር እና አሁንም ድረስ በወቅቱ የሚደግፈኝ ጥሩ ቡድን እንደነበረኝ ይሰማኛል።ሌሎች በእጩነት የቀረቡት ተጫዋቾችም እንደኔ ዋጋ ያላቸው ነበሩ።"
"ለምሳሌ ጁኒየር?"
"አዎ እሱም ከነሱ አንዱ ነበር " ሲል መለሰ፣
‹‹ሽልማቱን ያሸነፍከው አንተ እንጂ ጁኒየር አይደለም።››ዓይኖቹ ወደሷ አፍጠጠ፡፡
"ውድ አቃቢህግ ከእኔ ጋር የጀመርሽውን ጫወታ አቁሚ እና በአእምሮሽ ያለውን ነገር ቀጥታ ተናገሪ።"

❤40👍4🔥1
እሺ በተሸፈነው የዋንጫ ክንድ ላይ ተደግፋ በጥንቃቄ ተመለከተችው፣ “በወቅቱ ኮከብ ግብ አግቢም ኮኮብ ተጫዋችም መሆን ያለብህ አንተ ነበርክ…..ግን ጁኒየር ኮከብ ተጫዋች ሆኖ እንዲመረጥ አሻጥር ሰራህ.. እንደዛ ለምን አደረክ ?›› ስትል ጠየቀችው።
"እሱን ጠይቂው"
"ምናልባት ጠይቀው ይሆናል… ፍላጎት ካለው አባትዬውንም እጠይቀዋለሁ።ግን የሽልማት ግብዣው በተካሄደበት ምሽት አቶ ፍሰሀ የበለጠ ኩራት ተሰምቶት ነበር አይደል?ለእሱ ኮኮብ ተጫዋች ተብሎ መሸለም ያንተ ሚና ምን ነበር…ለዛ ውለታህ ምን ተከፈለህ
?እርግጠኛ ነኝ ሽልማቱ ለአንተ ነበር የሚገባው."
"የፈለግሽውን እመኚ። ለእኔ ምንም ለውጥ አያመጣም።" የቡናውን ኩባያ ባዶ አድርጎ ከፊቱ ባለው ትሪ ላይ አስቀምጦ ቆመ።
"ለመሄድ ዝግጁ ነሽ?"ሲል ጠየቃት፡፡
እሷም ቡናዋን አስቀመጠች፤ነገር ግን ምንም አይነት እንቅስቃሴ አላደረገችም.
"ይህ ጉዳይ መነሳቱ ለምንድነው የሚረብሽህ ?"አለችው፡፡
"መረበሽ አይደለም፤አሰልቺ ነው." ፊቱን ወደ እሷ አስጠጋ ።… "ያ ዋንጫ ሃያ አምስት አመት ያስቆጠረ የተበላሸ ቆሻሻ ነው… አቧራ ከመሰብሰብ በቀር ምንም የማይጠቅም"
"ታዲያ እነደዚህን ከሆነ ይህን ሁሉ ዓመታት ለምን በክብር አስቀመጥከው?" "አየሽ አሁን ምንም አይነት ዋጋ የለውም.፡፡››
"ግን ያኔ ዋጋ ነበረው።"
‹‹አዎ ..ኮሌጅ ለመግባት የሚያስችለኝን ገንዘብ የማገኝበት መንገድን ለማመቻቸት ይረዳኛል ብዬ አስቢ ነበር፡፡››
‹‹እና እንዴት ሆነ?››
‹‹ያገኘሁት ገንዘብ ለዛ በቂ አልነበረም››
"ምን አረግክ…ኮሌጅ ገብቶ መማሩን ተውከው፧"
‹‹አይ ተማርኩ››
"ክፍያውን እንዴት ሟሞላት ቻልክ፧"
"ብድር"
"የመንግስት ብድር?"
"የለም የግል" ሲል መለሰ። "ገንዘቡን ማን አበደረህ አቶ ፍሰሀ ?"
"አዎ ? ግን ለሶስት አመት ወጪያ ያበደረኝን እያንዳንዱን ሳንቲም መልሼለታለው›› "ለሱ በመስራት?"
"አዎ …ፖለስ ማሰልጠኛ እስክገባ ድረስ ለእሱ ነበር የምሰራው›› "ፖሊስ ቤት የተቀጠርከው..ከእሱ ስር ራስህን ነፃ ለማውጣት ነው?›› መስመር በለቀቁ ጥያቄዎቾ ተገርሞ ዝም አላት፡፡
‹‹መልስልኝ እንጂ?››
‹‹አይ መጀመሪያ ወታደር ቤት ነው የተቀጠርኩት…በባድመ ጦርነት ለአንድ አመት ተሳትፌለው…ጦርነቱ አብቅቶ እድሉን ሳገኝ ወደፖሊስ ቤት ቀየርኩ፡፡››
‹‹ለዛ ነዋ የፖሊስ ሳይሆን የወታደር ፈርጣማ ሰውነት ያለህ …?ጁኒየርስ እንደ አንተ ወታደር ቤት አገልግሏል?"
"ጁኒዬር ወታደር ? ይህን በዓይነ ሕሊናሽ ማየት ትችያለሽ ?" ብሎ በሀሳቧ ሳቅ ።
"ለምን ታዲያ ዩኒፎርም የለበሱ ፎቶዎች የሉህም?" ግድግዳው ላይ የተሰቀሉትን ስዕል እየተመለከተች ጠየቀችው፡፡
" የጦርነት ጊዜ ምንም ትውስታ እንዲኖረኝ አልፈልግም።"አለና ከእርሷ ወደ ኋላ ተመለሰ፣ ኮፍያውን፣ ኮቱን አነሳ፣ ከዚያም ወደ መግቢያው በር ሄዶ ከፈተው።አለም ባለችበት ቀረች።
"አንተ እና ጁኒየር የጋራ ፎቶ አላችሁ? ››
"ስለ እኔ ምንም አታውቂውም። ››አላት በንዴት
‹‹ምን ያበሳጭሀል..ቀላል ጥያቄ እኮ ነው የጠየቅኩህ… ብዙ ሰዎች ያለፈ ጊዜያቸውን በማስታወስ ደስ ይላቸዋል."
" እኔ ደግሞ እደዛ አይደለሁም… ያለፈውን ትቼ ወደፊት መሄድ እፈልጋለሁ." "ምክንያቱም ያለፈውን ማስታወስ ይጎዳሀል?"
" አንዳንዶቹን ታሪኮቼን ማስታወስ …አዎ ይጎዳኛል..."
"ለምሳሌ እናቴን ለመጀመሪያ ጊዜ የሳምክበትን ጊዜ ማስታወስ ይጎዳሀል?"
ወደ ወስጥ ተመልሶ ተራመደ..ወደእሷ ተጠጋ … ወገቧን በእጆቹ ያዘ.. እና ከሰውነቱ ለጠፋት" አንቺን ብስምሽ በጣም እንደሚያስደስትሽ እርግጠኛ ነኝ፣ አይደል አቃቢት ህግ?"
ምንም ማለት አልቻለችም።"እንግዲህ፣ እናትሽ እንዴት እንደሳምኳት ለማወቅ የምትጓጊ ከሆነ ምናልባት አንቺ በራስሽ ልታጣጥሚው ትችያለሽ። ››አለና አንገቱን ወደታች ዝቅ አደረገና ከንፈሩን ከንፈሯ ላይ አጣበቀ፡፡ በአፍንጫዋ መተንፈስ ጀመረች። እየሆነ ያለውን ነገር ስትረዳ ሁለቱንም እጆቿን ደረቱ ላይ አጥብቃ ያዘች። ጭንቅላቷን ወደ ጎን ልታዞር ብትሞክርም በአንድ እጁ መንጋጋዋን አጥብቆ ያዘው። ከንፈሮቹ በልዩ ሁኔታ አሻሸው፣ ከዚያም ምላሱን በመካከላቸው ሰነቀረው። በደንብ ሳማት፣ ትንሽ የመገረም እና የመደነቅ ጩኸት አሰምታ ሊሆን ይችላል። ሰውነቷ ከሱ ጋር ለመስማማት ተንጠልጥሎ ሊሆን ይችላል።.ነገር ግን በጭኖቿ መካከል ያለውን ስሜት፣ ወይም የጡቶቿ መንቀጥቀጥ፣ መቆጣጠር አልቻለችም። ብርቅዬ እና አስደናቂውን የአፉ ጣዕም፣ በህይወቷ ዘመን የምትረሳው አይነት አይደለም።በተከታታይ ለስላሳ እና ርጥበታማ ከንፈሯን ሳማት… የከንፈሮቿን ጥግ በምላሱ ጫፍ ዳበሳቸው፣ እንደምንም ለቀቃት እና አንገቱን ቀና በማድረግ የደነዘዙ አይኖቿን ተመለከተ።ራሷ ግራ ተጋባችባት። በድጋሚ ወራሪ ምላሱ ወደአፏ ውስጥ አስገባው….ሰውነቷን ንዝረት መቋቋም ስላልቻለች በጥፍሯ ቆመች…..በአንገቷ ዙሪያ የሉትን እጇቾን ይበልጥ ጨመቀችውና ይበልጥ ተለጠፈችበት…። ጡቶቾ ሲጨፈለቁ ከዚህ በፊት ተሰምቷት የማያውቀው ጣፋጭ ህመም ተሰማት ፣ ነገሮች ከዚህ በላይ እዲያድጉ ፈለገች…. እሱ ግን ድንገት ከእንቅልፉ እደነቃ ሰው አይነኖቹን ገለጠና ለቀቃት እና ሰውነቱን ከሰውነቷ አላቆ ወደ ኃላው ጠጋ አለ …በመሀከላቸው ክፍተት ፈጠረ፡፡
"ልክ እንዳታለልኩሽ እንዳይሰማሽ፣ክብርት አቃቢ ህግ.. ከአሁን በኋላ ፣ ያሉሽን ጥያቄዎች በፍርድ ቤት በኩል እንድታቀርቢ እመክርሻለሁ።ያ ለአንቺ የበለጠ አስተማማኝ ነው።"አላት
ምንም ሳትናገር ቤቱን ለቃ ወጣችና መኪናዋን አስነስታ አካባቢውን ለቃ ሄደች፡፡ከእሱ ለመለየት ስለፈገች ብቻ ሳይሆን እናትሽን ማን እንደገደላት አውቃለው… ካላት ሰውዬ ጋርም ለመገናኘት ቀጠሮ ስለላት ነበር፡፡
ቦታው ላይ እንደደረሰች በሩቅ የነገራትን አሮጌ ባጃጅ መኪና ተመለከተች….ውስጡም አንድ ሰው እንዳለ እየታያት ነው፡፡አሁን የእናቷን ትክክለኛ ገዳይ ማን እንደሆነ የምታውቅበት ደቂቃ መቃረብን አሰበችና፣ደስታም ፍርሀትም ተሰማት…፡፡
‹‹የእናቴ ገዳይ ከደቂቃዎች በፊት እላዩ ላይ ተጣብቄ ስስመው የነበረው ሰው ቢሆንስ…?ምንድነው የማደርገው?››ስትል ራሷን ጠየቀች፡፡መልሱን የመገመት ድፍረት እኳን አልነበራትም፡፡መኪናዋን ለቃ ወረደችና አካባቢውን በጥንቃቄ ቃኘች፣ከዛ ወደ ባጇጅ ተራመደች….ሰውዬው ከጀርባ ተቀምጦ ማየት ትችላለች ፣ ጫማዎቿ መሬቱን ሲረግጡ የሚያሰሙት ድምጽ በጇሮዋ ያንቃጭላል ። አካባቢው በጨለማ እንደተዋጠ ነበር… ሌላ ምንም አይነት መኪና በአቅራቢያ አልቆመም።አለም ባጇጆ አጠገብ ስትደርስ ድንጋጤን ተሰማት። ወደውስጥ ገባች…።የአይን ምስክሯ አስቀያሚ ትንፋሽ ወደውስጦ ገባ ። እሱ ደንዝዞ ነበር፣ ።‹‹በተደጋጋሚ ገላውን መታጠብ አለበት››ስትል አሰበች…. አትኩራ አየችው…በጣም ደነገጠች..አንገቱ ወደኃላ ታጥፎ ይታያል…አይኖቹ ፈጠው ያስፈራሉ በአንገቱ ዙሪያ ያለው ገመድ አንገቱ ስር ጠልቆ ገብቷል …እሱ ሞቷል።
ደንዝዛ ለተወሰነ ጊዜ ባለችበት ተቀመጠች….ከዛ በደመነፍስ ባጇጆን ለቃ ወጣች። እግሯ መሬት ላይ ቢያርፍም መንቀሳቀስ ግን አልቻለችም፡፡እየተንቀጠቀጠች ነው…በፍርሃት

❤33👍6
ጮኸች እና. …ጨለማው ውስጥ ሆና ቃተተች…ድንገት ሁለት የፊት መብራቶች ግንባሯ ላይ በራ ፣በሁለት እጆቾ ፊቷን ለመከለል ሞከረች .. መሮጥ ፈለገች.. ምንም ነገር ከማድረጓ በፊት አንድ ሰው ከኃላዋ ተንደርድሮ መጣና ክንዷን ያዛት… ዞር ብላ ስታየው ያልጠበቀችው ሰው ነው "ገመዶ!" እፎይታ እና ሽብር በተቀላቀለበት ስሜት አለቀሰች፡፡
"እዚህ ምን ታደርጊያለሽ?"
"ተመሳሳይ ጥያቄ ልጠይቅህ ነበር። ያ ሰውዬ…ሞቷል" አለች፣ የሚወዛወዝ ጣት ወደ ባጇጆ እየጠቆመች፣
"አዎ አውቃለሁ።"
"ታውቃለህ?"
"ስሙ ሙስጠፋ ደደፎ ይባላል። ለአቶ ፍሰሀ ይሰራ የነበረ ሰው ነው።››
"በኢየሱስ…ምን አይነት ውጥንቅጥ ነው?"
"አይ በነፍስ ግድያ ተጠርጥሪነት የማልወስድሽ ምክንያት ሰውዬው ጉሮሮው ታንቆ መገደሉን ደውሎ የነገረን ምስክር አንቺ ከሞተ በኃላ ወደ ባጇጆ እንደገባሽ ስለነገረን ነው."
"ሲገደል ያየ ሰው አለ?"
"ትክክል"
"ገዳዩ እኔ እሱን ለማግኘት ወደዚህ እንደምመጣ የሚያውቅ ይመስለኛል …አንተ እንዴት በፍጥነት እዚህ ደረስክ?"
"እሱን አንገቱ ላይ ገመድ ጠምጥሜ ያነቅኩት ይመስልሻል?" ብሎ ሳቅ ፡፡ከዛ አንድ ምክትሉን ጠራና። ‹‹ሳጂን አቃቢት ህጓን ወደ ቤቷ መልሷት" ሲል አዘዘው፡" ወደ ቤቷ መግባቷን እርግጠኛ ሁን››ሲል አከለበት፡፡
"እሺ ጌታዪ።"
"እስኪ ነጋ ድረስ በአካባቢው ሆኖ የሚጠብቃት ሰው መድብ የትም እንደማትሄድ እርግጠኛ ሁን."
ምክትሉ ወደ መኪናዋ እንድትመለስ ከመፍቀዷ በፊት አለም እና ኩማንደሩ የጥላቻ እይታ ተለዋወጡ
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
"እዚህ ምን ታደርጊያለሽ?"
"ተመሳሳይ ጥያቄ ልጠይቅህ ነበር። ያ ሰውዬ…ሞቷል" አለች፣ የሚወዛወዝ ጣት ወደ ባጇጆ እየጠቆመች፣
"አዎ አውቃለሁ።"
"ታውቃለህ?"
"ስሙ ሙስጠፋ ደደፎ ይባላል። ለአቶ ፍሰሀ ይሰራ የነበረ ሰው ነው።››
"በኢየሱስ…ምን አይነት ውጥንቅጥ ነው?"
"አይ በነፍስ ግድያ ተጠርጥሪነት የማልወስድሽ ምክንያት ሰውዬው ጉሮሮው ታንቆ መገደሉን ደውሎ የነገረን ምስክር አንቺ ከሞተ በኃላ ወደ ባጇጆ እንደገባሽ ስለነገረን ነው."
"ሲገደል ያየ ሰው አለ?"
"ትክክል"
"ገዳዩ እኔ እሱን ለማግኘት ወደዚህ እንደምመጣ የሚያውቅ ይመስለኛል …አንተ እንዴት በፍጥነት እዚህ ደረስክ?"
"እሱን አንገቱ ላይ ገመድ ጠምጥሜ ያነቅኩት ይመስልሻል?" ብሎ ሳቅ ፡፡ከዛ አንድ ምክትሉን ጠራና። ‹‹ሳጂን አቃቢት ህጓን ወደ ቤቷ መልሷት" ሲል አዘዘው፡" ወደ ቤቷ መግባቷን እርግጠኛ ሁን››ሲል አከለበት፡፡
"እሺ ጌታዪ።"
"እስኪ ነጋ ድረስ በአካባቢው ሆኖ የሚጠብቃት ሰው መድብ የትም እንደማትሄድ እርግጠኛ ሁን."
ምክትሉ ወደ መኪናዋ እንድትመለስ ከመፍቀዷ በፊት አለም እና ኩማንደሩ የጥላቻ እይታ ተለዋወጡ
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍33❤12🤔5
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////
ነጋ አልነጋ ብላ ጥዋት ወደቢሮዋ ከመግባቷ በፊት ቀጥታ ወደኩማንደሩ ቢሮ ነው የሄደችው፡፡እንዳጋጣሚ እሱም በማለዳ እንደገባ ነገሯት፡፡ቀጥታ ወደቢሮ መራመድ ጀመረች፡፡
ኩማንደር ወደቢሮ በጥዋት ቢገባም ከጥቂት ሰኮንዶች በላይ በአንድ ሀሳቡ ላይ ትኩረት አድርጎ ማሰብ አልቻለም። የአለም ምስል በምናቡ ብልጭ ድርግም እያለ እየረበሸው ነው፡፡ወንበሩን ትቶ ወደ መስኮቱ ሄደ። መጋረጃውን ገልጦ ወደ ውጭ መመልከት ጀመረ፣የጥዋቷ ፀሐይ ደማቅና ብሩህ ነች። ትላንትን ከአለም ጋር ያሳለፈውን ጊዜ አስታወሰ
.. እሷን ጎትቶ ፈረስ ላይ ሲያወጣት እና ተፈናጥራ በእጇቾ ወገቡን ጨምድዳ ስትይዝ… ጀርባዋ ላይ ስትለጠፍበት …አናዳጅና አብሻቂ ጥያቄዎቾን ስታዥጎደጉድበት በወቅቱ ያየባት ብልሀትና ብልጠት አስገርሞታል….በተቃራኒው ደግሞ ማታ የሙስጠፋ ሬሳ ጋር በዛ በጭለማ ቦታ ሲያገኛት በጣም የፈራች ፤የምትንቀጠቀጥና ፈሪ ሴት ሆና ነው ያገኛት፡፡
‹‹ምናልባት የሙስጠፋ አሰቃቂ ግድያ ስለእናቷ ግድያ የምታደርገውን ምርመራ ፈርታ እንድታቆም ያስገድዳት ይሆናል። ምናልባት ሻሸመኔን ትታ ወደ ኋላ ላትመለስ ወደ አዲስአባዋ ትመለስ ይሆናል።››ሲል አሰበ፡፡ይህ አጋጣሚ ሊያስደስተው በተገባ ነበር። ግን አላስደሰተውም። በእሷ እና በራሱ ላይ የበለጠ ተናደደ።ትላንትን ከእሷ ጋር መሳሳሙ የደደብ ሰው ተግባር እንደፈፀመ ነው የተሰማው፡፡በወቅቱ ራሱን መቆጣጠር ፈልጎ ነበር። ግን ለስሜቱ ተገዢ ሆኖ ማድረግ የሌለበትን ነገር አድርጎል፡፡በህይወቱ እንዲህ እንዲያደርግ ያስቸለው አንድ ሌላ ሴት ብቻ ነበረች እሷም ሰሎሜ ነች። ገረመው። ለዓመታት አላሰበውም ነበር ፣ ግን አሁን በአእምሮው ውስጥ ግልፅ ሆኖ እየታየው ነው።
ሰሎሜ ትወደው ነበር።እሱም ወዷት ነበር። አንድ ቀን ሊጋቡ ተስማምተው ነበር….ፍቅራቸውን የሚያጨነግፍ ምንም አይነት እንቅፋት በመሀከላቸው እንደማይፈጠር እርግጠኞች ነበሩ….ገመዶ አይኑን በድካም እያሻሸ ወደ ጠረጴዛው ተመለሰ እና ወንበር ላይ
ተቀመጠ ። አለም ለዓመታት ውስጡ የቀበረውን ትዝታ እየቆሰቆሰች እንዲያስታውስ እየደረገችው ስለሆነ ተበሳጨባት ፡፡ትናንት እሷን ሲስማት ሊቀጣት እና ሊያበሳጫት ነበር አላማው ። ነገር ግን ውጤቱ ተገላቢጦሽ ነበር የሆነበት… ።ከንፈሯ ልክ እንደእናቷ በዛ መጠን ይጣፍጣል ብሎ አልጠበቀም ነበር። ያ ጣፋጭነት አሁንም በምላሱ ላይ ቀርቷል. ድድር ጡቶቿ በዛ ልክ ስሜት ቀስቃሽ እና ለስላሳ እንደሚሆኑ እንዴት ሊገምት ይችላል? ለወደፊቱ ሁሉንም እቅዶቹን ማበላሸቷ እንደማይቀር ገመተ። ህልሙን እውን ለማድረግ በጣም ቅርቦ ነበር። ሊደርስ ጥቂት ነበር የቀረው….።ህይወቱን በሙሉ በትጋት የሰራበት ቦታ ለመሆን አንድ የመጨረሻ እርምጃ ነበር የቀረው።በዚህ መጥፎ ጊዜ ነው እንቅፋት ሆና ከፊቱ የተገተረችው፡፡‹እና ምን ያድርግ አንቆ ይግደላት ?›ስለማነቅ ሲያስብ ዘገነነው፡፡ ሀሳቡን ሳያገባድድ የበራፍ መቆርቆር ሰማ….
‹‹ይግቡ››
በራፉን ከፈተችና ገባች እና " እንደገባህ ነግረውኝ ነው ቀጥታ ወደእዚህ የመጣሁት››አለችው፡፡
እሷን በማያቱ እንዳልተደሰተ በሚያሳብ የድምፅ ቃና‹‹እ …ዛሬ ደግሞ ምንድነው?››ሲል ጠየቃት ፡፡አለም በሩን ዘጋችና ወደውስጥ ዘልቃ በመግባት ወንበር ይዛ ተቀመጠች፡፡
"ከደቂቃዎች በኋላ ወደ ፍርድ ቤት እንደምሄድ አልነገሩሽም? ››
‹‹አይ…አልነገሩኝም››አለችው ፈገግ ብላ…ከትናንት ማታው ሁኔታ ያገገመች ትመስላለች፡፡ " እሺ ምንድነው ጉዳይሽ?"በመሰላቸት ጠየቃት፡፡
"ስለተገደለው ሰው ልትጠይቁኝ ትፈልጋላችሁ ብዬ ስላሰብኩ ነው…ቃል ልሰጥ የመጣሁት››
"በእርግጥ ተጠርጣሪ አይደለሽም። የተሳሳተ ጊዜ ላይ በተሳሳተ ቦታ ተገኝተሸ ነው ፡፡ይሄ ድግሞ ያንቺ መጥፎ ልማድ ነው።"አላት፡፡
"በእኔ እና በእሱ ግድያ መካከል ግንኙነት ያለ አይመስላችሁም?" "አይ አይመስለንም ››አላት ፍርጥም ብሎ፡፡
‹‹እኔ ደግሞ ይመስለኛል››
"ከሆነ እንስማው" አለ።
"አስቀድመህ የምታውቀው ይመስለኛል። ሙስጠፋ የሰሎሜን ግድያን አይቷል…የአይን እማኝ ምስክር ነበር።"
በበደነ እና በቀዘቀዘ ስሜት "እንዴት አወቅሽ?"ሲል ጠየቃት፡፡
"በስልክ ደውሎ ነገረኝ።"
"እሱ እኮ ውሸታም ሰው እንደሆነ ማንም ያውቃል….ስለባህሪው የሚያውቁትን ሰዎች መጠየቅ ትችያለሽ "
"እኔ አምኜዋለሁ። በጣም የተደናገጠ እና በጣም የፈራ ይመስላል ነበር። በመጨረሻ ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘን ነበር፣ አንተ ስትከተለኝ እንደነበረ የነገረኝ እሱ ነው…በዛን ቀን እዛ ሆቴል ባትገኝ ኖሮ የእናቴን ገዳይ በዝርዝር ይነግረኝ ነበር።"
"ታዲያ ይሄ ዝርዝር.. የሰሎሜ ገዳይ ያደርገኛል?"
"ገዳይ ባትሆን አንኳን ለገደለው ሰው እየሸፈንክለት ሊሆን ይችላል ››
"በንድፈ ሀሳብሽ ላይ ምን ችግር እንዳለ ልንገርሽ?አቶ ፍሰሀ ከስራ ካባረረው ቀን አንስቶ እሱ የበቀል ጉዞ ላይ ነበር፣ ድንገት አንቺ የእናትሽን ገዳይ እያነፈነፍሽ እንዳለ ሲሰማ በዛ ተንኮለኛ ጭንቅላቱ ነገሮችን አገጣጠመና ጥሩ ድረሰት በአእምሮ ቀምሞ ሊያጃጅልሽ ሞከረ…››
" ያ እውነት አይደለም..ሰውዬው የተገደለው. ስለእናቴ አሟሟት ለእኔ እንዳይነግረኝ አፉን ለማዘጋት ነው ፡፡ይህ ሰውዬ የእናቴን መገደል ለማየት የሚችልበት አጋጣሚ ከፍተኛ ነው…እንደሚታወቀው እናቴ የሞተችው በእርባታ ድርጅት ውስጥ በከብቶቹ በረት አካባቢ ነው..እሱ ደግሞ የከብቶቹ ተንከባካቢ ስለሆነ አብዛኛውን ጊዜ ከአካባቢው አይጠፋም፣››
‹‹የፈለግሽውን ማመን ትችያለሽ…ለማንኛውም የእሱን መገደል የተመለከተ የአይን እማኝ እንዳገኘን ነግሬሽ ነበር..እድሜ ለእሱ አሁን የሰውዬውን ገዳይ ይዘነዋል…››
ደነገጠች‹‹ይዘነዋል…..እና አመነ?››
‹‹ትንሽ ቢያቅማማም አምኗል››
‹ለምን ገደልኩት አለ?››
‹‹ሚስቴን አማግጦብኛል ..የሚል ምክንያት ነው የሰጠው…የሰውዬውን ሚስትም አግኝተን አናግረናታል…ከሟቹ ጋር የድብቅ የፍቅር ግንኙነት እንዳላት አልካደችም…..››
‹‹ይገርማል…ለሊቱን ሙሉ አልተኛህም አይደል….?በእውነት በአንድ ለሊት ይሄን ሁሉ አቀናብራችሁና አደራጅታችሁ ማደር በመቻላችሁ በራሳችሁ ልትኮሩ ይገባል….››
‹‹ምን ለማለት ፈልገሽ ነው?››የደፈረሱ አይኖቹን አጉረጠረጠባት፡፡
‹‹አንዲት ሴት የደፈረ ወንጀለኛ ለመያዝ ስድስት ወር የማይበቃችሁ በ12 ሰዓት ውስጥ ለዛውም በለሊት ገዳዩን ይዛችሁ …ምስክር አጠናቅራችሁ እንዲህ ጥንቅቅ ብላችሁ ሳያችሁ ባልደነቅ ነው የሚገርመው…..እርግጠኛ ነኝ በጥዋት መጥቼ እንደማፋጥጥህ እርግጠኛ ስለሆንክ መደረግ ያለበትን ነገር ሁሉ አድርገሀል…አድናቂህ ነኝ፡፡››
ሚመልስላት ስላልነበረው ዝም አላት..
"ሁሉንም ፕሮፌሽናል ሴቶች ትጠላለህ ወይስ በተለይ እኔ ነው የምትጠላው?"ስትል ሌላ ያልጠበቀውን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹በተለይ አንቺ ነው የምጠላው።"አላት ፡፡ድፍረቱ አስነዋሪ ነበር። የትናንት መሳሳማቸውን እንዳልወደደው የሚያሳይ ነገር አላነበበችበትም ፡፡በመሀከላቸው ምንም እንዳልተፈጠረ ለማስመሰል ሞከረች፡፡ ግን መርሳት አልቻለችም። ንግግሩ በጣም ጎድቷታል።
"ለምንድነው ማትወደኝ?"ስትል ጠየቀችው
"ምክንያቱም አንቺ ጣልቃ ገብ ነሽ። በሌሎች ሰዎች ህይወት ውስጥ ጣልቃ የሚገቡ ሰዎችን አልወድም።"
"ይህ ጣልቃ መግባት አይደለም… የእኔ ጉዳይ የእናቴን ገዳይ መፈለግ ነው."

❤31👍5
"እንዴት ሊሆን ይችላል? ሰሎሜ ስትገደል አንቺ በዳይፐር ውስጥ ነበርሽ…ምንም የምታውቂው ነገር የለም" ሲል ጮኸ።
"ይህን በማንሳትህ ደስ ብሎኛል:: ያኔ ገና የሁለት ወር ልጅ ስለነበርኩ ነው…እናቴ በዛ ምሽት በእርባታው ቦታ ምን ትሰራ ነበር?"
ለጥያቄው የሰጠው አስደንጋጭ ምላሽ ።" አላሳታውስም ››የሚል ነበር፡፡
"ልትረሳው አትችልም ። እዛ ምን ታደርግ ነበር? እባክህ ንገረኝ"ተነሳ። አለምም እንዲሁ።
"ከጁኒየር ጋር ቀጠሮ ነበራት መሰለኝ ..አልፎ አልፎ እዛ እርባታ ቦታ ባለው ሰፊ ሜዳ ላይ በጨረቃዋ ድምቀት እሳት አቀጣጥለን…ስጋ እየጠበስንና መጠጥ እየጠጣን የመዝናናት ልምድ ነበረን….በእለቱም ለተመሳሳይ ጉዳይ ነበር የተገኘችው..።"
" በቃ ለዚህ ብቻ ነው የተገኛኙት?"
"ሌላ ነገር አለ ምትይ ከሆነ እሱን ጠይቀው"
"እጠይቅሃለሁ፡ ዝግጅቱ ምን ነበር? የተለየ ትርጉም ነበረው ?።" "ምናልባት አዘኖላት መሰለኝ"
"ይቅርታ? ለምን ያዝንላታል?"
" ካለእድሜዋ ስለወለደች ነዋ!!አንቺን ስትወልድ አስራ ስምንት አመት ብቻ ነበረች፣በዛ ላይ ባሏ ወዲያው ነው ጥሎት ውትድርና የሄደው….በጣም ከፍቷት ነበር።"
‹‹ በዚያ ምሽት እራት ላይ እዚያ ነበርክ? ” "አዎ እዚያ ነበርኩ" እጁን ነጻ አወጣ
"ምሽቱን ሙሉ?"
"አይ ..ከዚህ በፊትም እኮ ይህን ጥያቄ ጠይቀሽኝ መልሼልሻለሁ ….ከእራት በኋላ ተለይቻቸው ሄድኩ."
"ለምን?፧" ዝም አለት
መልስልኝ ገመዶ፣ ‹‹የት ነው የሄድከው?"
‹‹የፍቅር ቀጠሮ ነበረኝ"
"ከማን ጋር? አሁንም እዚህ ከተማ ውስጥ ትኖራለች?" "ኖረች አልኖረች ልዩነት ምንድነው?"
" ላናግራት እፈልጋለሁ።"
" እሷን ወደዚህ ጉዳይ በፍጹም ጎትቼ ማስገባት አልፈልግም።" ". ያን ምሽት ወደ እርባታ ቦታው አልተመለስክም?"
"አይ አልተመለስኩም።ነገርኩሽ የፍቅር ቀጠሮ ነበረኝ" ትንፋሹ እስኪሰማት ድረስ ፊቱን ወደ እሷ አስጠጋ።
///
"እራት እና ጭፈራ ላይ እንዴት ነሽ?››ሲል ጠየቃት ጁኒየር "እንደ ተረት ተረት"
" አይ አይመስለኝም.ሲያዩሽ ደናሽ ነው የምትመስይው››
በ
"እራት እና ጭፈራ እየጋበዝከኝ ነው እንዴ?"
"አዎ ..ዛሬ አመታዊ የነጋዴዎች ህብረት ክብረበዓል የሚከበርበት ቀን ነው…ዛሬ በከተማዋ የሚገኙ ዋና ዋና ሀብታሞች ከነ ሚስቶቻቸውና ከነልጆቻቸው ይገኙበታለል….እና እባክሽ ከእኔ ጋር ትሄጂያለሽ… ?ካልሆነ ግን እንደ ገሃነም አሰልቺ ይሆንብኛል።››አላት፡፡
።
አለም ሳቀች። "ጁኒየር፣ እንደእዚህ አይነት ቦታ ለአንተ መቼም አሰልቺ ይሆናል ብዬ አልጠብቅም ፡፡ በተለይ ሴቶች በዙሪያህ ባሉበት ጊዜ የሚታሰብ አይደለም…አብዛኛዎቹ በአንተ ውበት ይወድቃሉ?"
" ዛሬ ማታ አንቺ አብረሽኝ ከሄድሽ ያለ ምንም ልዩነት ማለት ይቻላል., " "ዛሬ ማታ?"
‹‹አዎ ዛሬ ማታ ››፥
"በእርግጥ አልችልም. ደክሞኛል. ትናንት ምሽት ጥሩ እንቅልፍ አላገኘሁም - "
"አዎ፣ ሙሰጠፋ በዚያ መንገድ ሞቶ እንዳገኘሽው ሰምቼያለሁ።በጣም አስከፊ ምሽት እንዳሳለፍሽ መገመት እችላሁ፡፡ አእምሮሽን ከዛ እንድታወጪ መርዳትና እፈልጋለሁ።"
"አስተያየትህን አደንቃለሁ ግን መሄድ አልችልም." "ተቃውሞ አልቀበልም"
"ጁኒየር በእውነት መሄድ አልችልም።"
"ለምን?"
"ሁሉም የእራት ልብሶቼ ላውንደሪ ሊታጠቡ ሄደዋል ። የምለብሰው የለኝም።"
"እሱ አሳማኝ ምክንያት አይደለም….አንቺን የመሰለች ዘናጭና ሽቅርቅር ሴት አንድ የእራት ልብስ ቤቷ ታጣለች…?ለምሳሌ ትናንት ለብሰሽ የነበረው ሌዘር ቀሚስ..በጣም እኮ ነው የሚያምርብሽ"
አስተያየቱ አሞቃት ‹‹እባክህ ተወኝ..ይቅርብኝ››
"ለምን ?
ምክንያቱም በቅርቡ የእስር ቤት ነዋሪ እንደምሆን ተስፋ ስላደረግሽ?"
"አይ!"
"ታዲያ ምን?"
"ወደ እስር ቤት ልልክህ አልፈልግም… ነገር ግን አንተ በግድያ ጉዳይ ላይ አንዱ ተጠርጣሪ ነህ።"
‹‹አሌክስ ስለ እኔ የሆነ ግንዛቤ ለማግኘት በቂ ጊዜ ያገኘሽ ይመስለኛል …እንደዚህ አይነት አሰቃቂ ወንጀል እንደምሰራ በእውነት ታምኛለሽ?"
ገመዶን ጁኒየር ወታደር ሆኖ ያውቃል ወይ ብላ ስትጠይቀው እንዴት እንደሳቀባት አስታውሰች።
"አይ፣ አላደርገውም" ስትል ለስለስ ብላ መለሰችለት፡፡ "ግን አሁንም ተጠርጣሪ ነህ።ጓደኛሞች መሆናችንን አያዋጣንም።››
"ይህን ቃል ወድጄዋለሁ" አላት፡፡
"ምን?"
"ዛሬ ማታ ከእኔ ጋር ትሄጃለሽ…ማታ አንድ ሰዓት ላይ እወስድሻለሁ።"
"አልችልም።"
“አሌክስ፣ አሌክስ፣” ሲል በሚያስገርም ሁኔታ አቃሰተ፣ “
በዚህ መንገድ ተመልከቺው። ዝግጅቱ ላይ እኔ ሁለት ወይም ሶስት ጠርሙስ እጠጣለሁ፣ ምናልባትም ከዛም በላይ ልጠጣ እችላለው ።ከዛ አንቺ ስለምትፈልጊያቸው መረጃዎች ማስታወስ ልጀምር እችላለሁ፣ ምን አልባትም በውስጤ የቀበርኩትን ሚስጥር ልናገር እችል ይሆናል።ስለዚህ አንቺ በቦታው ተገኝተሸ እድልሽን ብትሞክሪ ጥሩ ይመስለኛል። ምን አይነት አስደናቂ ኑዛዜዎች እንደማሰማሽ ማን ያውቃል? በዛ ላይ በዝግጅቱ ብዛት ያላቸው የአባቴ ወዳጆችና የእኔም ጎደኞች ይገኛሉ…ከብዙ ሰዎች የመተዋወቅ እድል ይኖርሻል፡፡››
እንደገና፣ በአስደናቂ ሁኔታ አቃሰተች። "በቃ እሺ…አንድ ሰዓት."ስትል መስማማቷን ነገረችው፡፡

👍31❤29
#ፍቅር_ሙጀሌ
እየነዘነዘ እንቅልፍ ቢነሳም ፣
ንክሻ ፣ ስቃዩ ፣ረብሻው ይጥማል፣
ፍቅር ሙጀሌ ነው፣
በትዝታ ጥፍር ሲያኩት ደስ ደስ ይላል።
🔘ኑረዲን ዒሳ🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
እየነዘነዘ እንቅልፍ ቢነሳም ፣
ንክሻ ፣ ስቃዩ ፣ረብሻው ይጥማል፣
ፍቅር ሙጀሌ ነው፣
በትዝታ ጥፍር ሲያኩት ደስ ደስ ይላል።
🔘ኑረዲን ዒሳ🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍8❤4😁4