#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አራታ
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///
ስርጉት ወደአባቷ የጥናት ክፍል ስትገባ ። አባቷ ጠረጴዛው ላይ አቀርቅሮ አንድ ፋይል እያነበበ ነበር ››
"ዛሬ እረፍት የሆንክ መስሎኝ ነበር››
" አዎ ነበርኩ ግን አንዱ ማየት የሚገባኝ ጉዳይ ስለነበረ ይሄው እንደምታይኝ ፋይል እያገላበጥኩ ነው፡፡››
"በቅርብ በጣም ጠንክረህ እየሰራህ ነው.. ግን ደግሞ በጣም መጨናነቅ ይታይብሀል…ምነው ችግር አለ እንዴ."
"ያቺ የሰሎሜ ልጅ ነች"
"የሰሎሜ ሴት ልጅ? አሁንም እያስቸገረችህ ነው?"
‹‹የእናቷ አስከሬኑ እንዲወጣ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ፈልጋ ትናንት ቢሮዬ መጥታ ነበር።››
"አምላኬ!"
ስርጉት ባለማመን በሹክሹክታ ተናገረች።
"እና ምን አልካት?."
"ጥያቄዋን ውድቅ አደረኩታ."
"መልካም አድርገሀል "
"ምንም አማራጭ አልነበረኝም። አስከሬኑ ተቃጥሎል …ብትከፍትም በትንሽ የእንጨት ሳጥን የተቀመጠ አመድ ነው የምታገኘው››
"እና የእናቷ ሬሳ እንደተቃጠለ ስትሰማ ምን አለች?"
"አላውቅም …ኩማንደሩ ነው የነገራት ።, ሙሉ በሙሉ እንዳላመነችበት እገምታለሁ."
"ጋሽ ፍሰሀ እና ጁኒዬር ስለዚህ ጉዳይ ያውቃሉ?"
"እስከአሁን ድረስ እንደሚያውቁ እርግጠኛ ነኝ። ኩማንደሩ ይነግራቸዋል።"
ስርጉት"ምናልባት" ስትል አጉረመረመች። ለአንድ አፍታ በፀጥታ ማሰላሰል ጀመረች. "ታዲያ ምን ላመጣልህ..ሻይ ወይስ ቡና ..ቁርስ በልተሀል??"
"ስርጉቴ ፣ አመሰግናለሁ ምንም አልፈልግም….አሁን ይሄንን ፋይል መመርመሬን መቀጠል አለብኝ..ብቻዬን ተይኝ።"
" ይቅርታ ስላስጨነቅኩህ..አባዬ…በቃ ቻው " ብላ ግንባሩን ሳመችና ቢሮውን ለቃ ወጣች፡፡
ስርጉት የጥናት ክፍሉን በጸጥታ ዘጋችለትና ወደ መኝታ ቤቷ አመራች፡፡ ጥሩ ስሜት አልተሰማትም።ስርጉት ሆዷን እየቆረጣት ነው ፡፡ዛሬ ጥዋት ነበር የወር አበባዋን የጀመረው።ምንም እንኳን እነዚህን ወርሃዊ ፍሰቶች በየወሩ መቀበል እና መሸኘት የግድ ቢሆንም የአርባዎቹ አጋማሽ ዕድሜዋ ልክ እንደ ታዳጊ ልጅ የሚያሰቃያት ቁርጠት የሚያሰለች ብቻ ሳይሆን አስቂኝ ሆናባታል። ይሄ ግማሽ እድሜዋን ያስተናገደችው የወርአበባ ሴት መሆኗን ማሳሰቢያ ብቻ ነበር። አንድም ልጅ መውለድ አልቻለችም፡፡
በህይወቷ ውስጥ ለልጅ የሚከፈል መስዋዕትነትና እና ከልጅ የሚገኝ ፍቅር ተቋዳሽ ባለመኗ በየቀኑ ታዝናለች። አንዳንድ ሰዎች አዘውትረው እንደሚጸልዩ ሁሉ፣ ስርጉትም ለፈጣሪዎ ስለት ሁሉ ተስላ ነበር…ለዛውም ደጋግማ ..ግን ምንም ለውጥ እልነበረውም፡፡በቤቱ ውስጥ የሚሯሯጡ የሕጻናት ትናፍቃለች። ባሏ በለሊት ወደመኝታ ክፍሏ ገብቶ ጡቶቿን እየነካካ እና እረፍት ያጣ ገላዋን ረሀብ እንዲያረካላት ትፈልጋለች።ሶስተኛውን መሳቢያ ከፈተች እና የፎቶ አልበሙን አወጣች።በአክብሮት ከፈተችው። አንድ በአንድ እየገለጠች ማየት ጀመረች፡፡ ውድ ትዝታዎችን - ቢጫ ቀለም ያለው ጋዜጣ ከፎቶዋ ስር አለ፣አወጣችና አየችው….ስለሰሎሜ ግድያ የሚያትት ነው፡፡ .. ጨው ጨው የሚል እንባ ከአይኖቿ ፈሰሰ። በማህፀኗ ውስጥ ያለውን የባዶነት ህመም ለማስታገስ የእጇን ጭኖቾ መካከል ጨመረችና ጭብጥብጥ ብላ ተኛች፡፡
…///
አለም ከስራ ቀደም ብላ ወጣችና ለጁኒዬር ደወለችለት…
‹‹እንዴት ነሽ አሌክስ?››
ለስላሳና ማራኪ ድምፅ ነው …በዛ ላይ አሌክስ ብሎ ሲጠራት የተለየ ስሜት ነው የተሰማት፡፡
‹‹ሰላም ነኝ..ላገኝህ ፈልጌ ነበር››
‹‹ምነው? መክሰስ ልትጋብዢኝ ነው?››
‹‹ብጋብዝህ ደስ ይለኝ ነበር…ግን ደግሞ አጣዳፊ ጉዳይ ነበረኝ…አንተን እና አባትህን ማግኘት ፈልጌ ነበር››
‹‹ምነው በሰላም?››
‹‹አይ በሰላም ነው ማለት እንኳን አልችልም..ግን ላገኛችሁ እፈልጋለው፡፡››
‹‹እንግዲው ሁለታችንም ቢሮ ነው ያለነው…የሶሌ ኢንተርፕራይዝ ህንፃን የት እንደሆነ ታውቂያለሽ?፡፡››
‹‹አዎ ..ወደዛው ልምጣ?››
‹‹ጥሩ… ነይ.. እጠብቅሻለው››
ስልኳን ዘጋችና ቀጥታ ወደእዛው ነው የሄደችው፡፡ከህንፃው ውጭ ጠብቆ ተቀበላትና ቀጥታ ወደ አባትዬው ቢሮ ይዞት ሄደ፡፡ጠረጴዛውን ከበው ከተቀመጡ በኃላ የንግግሩን ቅድሚያ ወሰደች…ቀጥታ ወደመጣችበት ጉዳይ ነው የገባችው፡፡
"ትናንት ዳኛ ዋልልኝን በድጋሚ አናግሬቸው ነበር።" አለም ሁለቱም ሰዎች ንግግሯን ተከትሎ ውጥረት ውስጥ ሲገቡ ተመለከተች፡፡
"ለምን ጉዳይ… ?" አቶ ፍሰሀ ጠየቀ።
"የእናቴን አስከሬን ለማውጣት ፈልጌ ነበር.››
"አምላኬ ሆይ፣ ለምን እንደዚህ አይነት ነገር ማድረግ ፈለግሽ? ››አቶ ፍሰሀ ደነገጠ።
" ለማንኛውም የጠየቅኩት ነገር የማይቻል ነው።ያንን እንደምታውቁት ደግሞ እርግጠኛ ነኝ… የእናቴ አስክሬን ተቃጥሏል።"
"ልክ ነው" አለ አቶ ፍሰሀ።
ጁኒዬር በስቃይ አይኖቹን ጨፈነ…
"አቶ ፍሰሀ በዛን ወቅት ሁሉን ነገር የወሰንከው አንተ ነበርክ ? በየትኛው መብትህ? አያቴ በህይወት እያለች አንተ እንዴት? ››
" አስከሬኗ የተቃጠለው ማስረጃ ለማጥፋት መስሎሽ ነው እንዴ?"
"አላውቅም!" ጮኸች እና ከተቀመጠችበት ተነሳች። ወደ መስኮቱ ሄደች እና ባዶውን ሰማይ ትኩር ብላ ተመለከተች።ከዛ ተመልሳ ወደእነሱ መጣችና ወንበሯ ላይ ተቀመጠች እና"ያደረግከው ያልተለመደ ነገር ነው..ማብራሪያ እፈልጋለው።"አለችው
"እኔ የፈለኩት አያትሽን ከኃላፊነት ለማላቀቅ ብቻ ነበር። ልጇ በእኔ መሬት ላይ ስለተገደለች ቢያንስ ማድረግ የምችለውን ማድረግ አለብኝ ብዬ አሰብኩ።አያትሽ በሀዘን አእምሮዋ ስለተጎዳ ልንከባከባት ብቻ ነበር የፈለኩት። ያደረኩት ነገር አጠራጣሪ ከመሰለኝ፣ ያ በጣም መጥፎ ነው ፡፡ ወጣቷ ሴት ፣ ዛሬም እንደገና ተመሳሳይ ሁኔታ ቢያጋጥመኝ የማደርገው ተመሳሳዩን ነው ››
‹‹እርግጠኛ ነኝ አያቴ በወቅቱ ላደረከው ነገር አድንቃህና አመስግናህ ነበር..እንደውም ሳስበው ይሄንን ሀገር ላቃ ወደአዲስአበባ መግባት እንደምትፈልግ ስትነግርህ ገንዘብ ሰጥተሀታል፡፡››
‹‹እሷ ነች የነገረችሽ….?አዎ አምስት ሺ ብር ሰጥቼት ነበር…››
‹‹በዛን ጊዜ 5 ሺብር እኮ ማለት የዛሬ መቶ ሺብር ነው፡፡››
‹‹አዎ በትክክል..ለዚህ ነው መመስገን እንጂ መወቀስ አይገባኝም የምልሽ፡፡››
ጁኒዬር ምንም ጣልቃ ሳይገባ የሁለቱን ምልልስ በትግስትና በጭንቀት እያዳመጠ ነው፡፡አለም ንግግሯን ቀጥላለች‹‹ይገርማል ….ቆይ እናቴ ምን ያህል ብትበድላችሁ ነው ትዝታዋንም ሆነ እሷን የሚያስታውሳችሁን ነገሮች ሁሉ ከከተማዋ ለማስወገድ ያንን ሁሉ መስዋዕትነት መክፈል የፈለጋችሁት?››
‹‹ነገ የምታፍሪበትን ነገር አትናገሪ..አያትሽ በወቅቱ በጣም አመስጋኝ ነበረች…ብዙ ?‹‹ታዲያ አሁን ከአመታት በኃላ እናቴን እናንተ እንደገደላችኋት ለምን ነገረችኝ?››
‹‹እሱ እኛንም ግራ ያጋባን ጉዳይ ነው…ምን አልባት በእርጅናዋ የተነሳ አእምሮዋ ሚዛኑን አጥቶ ነገሮችን በትክክል ማሳታወስ ተስኗት ይሆናል..አዎ ከዛ ውጭ ሌላ ማብራሪያ ሊኖረው አይችልም፡፡››
‹‹ቆይ እኔ ያልገባኝ…እንደምትሉት የእናቴ ሬሳ ከተቃጠለ..አመዱን በሳጥን አድርጎ መቅበሩ ለምን አስፈለገ…..?ምን ሊረባ?››
"መቼስ ሰሎሜ ዘሞዶች አሏት …ከዛ በላይም ልጅ አለቻት…ልጅቷ አድጋ እናትሽ ሞታለች ስትባል..የት ነው የተቀበረችው…?መቃብሯን ማየት እፈልጋለው ብትል ለእሷ ለማሳየት ታስቦ ነው…ይሄው እንደፈራነውም የእናቴ መቃብር የት ነው ብለሽ መጠየቅሽ አልቀረም፡፡››
‹‹በእውነቱ አርቆ አሳቢነታችሁ በጣም እያስደነቀኝ ነው፡፡››ስትል በምፀት ተናገረች፡፡

❤33👍9🥰1