አትሮኖስ
282K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
489 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

//////

ራሄል ፀጋን ስታበረታታ‹‹ነይ የኔ ማር ..አንድ ነገር መጠጣት አለብሽ››አለች ። እሷ ግን ከራሔል ደረት ጋር እንደተለጠፈች  ጭንቅላቷን ወደ ጎን አዞረች። ራሄል ትንሿን ህፃን በምቾት መያዝ አልቻለችም ሰውነቷ በጣም ሞቃት እና የሚፋጅ ነበረ….ራሄል ዔሊያስ ባሳየት ዘዴ በመጠቀም የሙቀት መጠኑን ለመቀነስ ሞክራ ነበር፣ነገር ግን ለልጁቷ ጊዜያዊ እፎይታ ቢያስገኝላትም፣ የሙቀት መጠኑ ብዙም ሳይቆይ ከደቂቃዎች በኃላ እንደገና  ይጨምሯል። ራሄል ደፍራ ለዔሊያስ  ደውላ ሁኔታውን ልትነግረው አሰበችና  ስልኩን ተመለከተች። ወዲያው ግን ትላንት ቤቱ በሄደች ጊዜ እንዴት እንዳስተናገዳትና ከህይወቱ ጭምር አሽቀንጥሮ እንዳስወገዳት  ትዝ ሲላት እጇን ሰበሰበች፡፡ እንደገና መዋረድ ስላልፈለገች ከዔሊያስ ለመራቅ ወሰነች ። ከዛ ምንም ምርጫ ስለሌላት.. የሚሆነውን መጠበቅ ጀመረች፡፡

ከአንድ ሰዓት በኃላ  ፀጋ ለውጥ እያሳየች መጣች…ከዛም በላይ እራሷን ችላ መቀመጥና በአሻንጉሊቶች መጫወት ጀመረች…ራሄል በጣም ደስ አላት..ከእሷ እቅፍ ላይ ወረደቻና ግዙፉ ሶፋ ላይ ሆና መጫወት ጀመረች…ራሄልም በተወሰነ መንገድ ስለተረጋጋችላት ተደስታ እዛው አጠገቧ ቁጭ ብላ  አንዳንድ ሰነዶችን ማየት ጀመረች…ግን ብዙም ሳይቆይ አስጠሊታ ነገር ተከሰተ ፡፡ፀጋ ከተቀመጠችበት ተነስታ ከእሷ የሸሸውን አሻንጉሊት ለመያዝ እግሯን ስታነሳ የሶፋው ቆዳ አዳለጣትና ወደኃላዋ ወደቀች…ወደኃላዋ ስትወድቅ የሶፋው እጄታ ጭንቅላቷን መታት…ለሌላ ልጅ ቢሆን ምንም አይነት ጉዳት የሚያስከትል አይነት አልነበረም…ፀጋ ግን ልትቋቋመው አልቻለችም፡፡

ራሄል እዛው አጠገቧ ስለነበረች በእጇ የያዘችውን ወረቀት በትና ተንደርድራ ሄዳ አነሳቻት…ክንዷ ላይ ዝልፍልፍ ብላ ዝርግትግት አለች..አይነቾ ግልብጥብጥ አሉ….ራሄል እሪታዋን ስታቀልጠው..ከኪችን አለምና ረዳቷ ከውጭ አትክልተኛውና ዘበኛው እያለከለኩ መጥተው ከበቧት..አለም ፀጋን ከራሄል እጅ ላይ ተቀበለች…‹‹ቶሎ በሉ አምፑላንስ ደውሉ..አንፑላንስ ደውሉ….››ተንጫጩ..ራሄል ራሷን መቆጣጠር አቃታት…ልቧ መጥታ ጉሮሮዋ ላይ እንደተወተፈች እርግጠኛ ነች…መተንፈስ ሁሉ አቃታት..በእንብርክክ ሳሎኑና ታስሰው ጀመር ..…ከ30 ደቂቃ በኃላ አምፑላንሷ ቀፋፊ የሆነ ሳይረኗን እያስጮሐች ደረሰች…ባለሞያዎቹ ከአለም እጅ ጸጋን ተቀብለው በጥንቃቄ ወደውስጥ አስገብተው አልጋው ላይ አስተኞት..ከዛ ወዲያው የመተንፈሻ መሳሪያዎቹን ይሰካኩላት ጀመር… ራሄል በደመነፍስ ተከትላ ገባች…የአምፑላንሱ በራፍ ተዘጋና ተንቀሰቀቀሱ ፡፡

ሆስፒታል ከደረሰችና ፀጋን ለሀኪሞቹ ካስረከበች ከአንድ ሰዓት በኃላ ግን ነገሮች በብዙ እጥፍ እየተባባሱ እንደመጡ መታዘብ ቻለች፡፡ወደ ውስጥ ገብታ ከሚስኪን እህቷ ጎን መሆን ፈለገች…እግሯን ስታንቀሳቅስ ግን  ‹‹እመቤት ፣ ወደእዛ  መሄድ አትችይም።››ስትን  ነርሷ አገደቻት  ፡፡

መሄድ አለባት፣ ከፀጋ ጋር መሆን ነበረባት።ነርሷ ‹‹ሀኪሞቹ  ሰራቸውን መስራት አለባቸው ልጅሽ  በጥሩ ሁኔታ ላይ ነች››አለቻት፡፡

ልጅሽ የሚለው ቃል አእምሮዋን በጦር ወጋት‹‹..አዎ የአደራ ልጄ ነች››ስትል አሰበች….‹‹ግን አንድ እናት ከማህፀኗ የወጣ ልጅ ሊሞትባት ሲያጣጥር ስታይ ምን አይነት ስሜት ይሰማት ይሆን …?እንዴትስ መቋቋም ትችላለች?››እራሷን ጠየቀች…መልሱን ማሰብ እንኳን ዘገነናት፡፡  ቃላቱ በራሔል አእምሮ ውስጥ ከላይ እንደተወረወሩ  ጠጠሮች ወደቁ።ነርሷ ያለችው ገብቷታል.. ግን አልተዋጠላትም።

‹‹ለምን ዶክተሩ ራሱ መጥቶ ምን እየተፈጠረ እንዳለ አያሳውቀኝም ?።››

ነርሷን ስታያት ወጣት እና ከእሷ በላይ አጭር ነች፣ ነገር ግን ክንዷን የጨበጠው  እጇ በሚገርም ሁኔታ ጠንካራ ነው።ራሄል ፀጋን ወደ ወሰዱበት ቦታ በጨረፍታ ተመለከተች፣ በተጨናነቀው ክፍል ዞር ብላ ስትመለከት በድንገት የጠፋች አይነት ስሜት ተሰማት። እንዴት እዚህ ደረጃ  እንደደረሰች አታውቅም። የሚወዛወዘውን አምቡላንስ በድንጋጤ አስታወሰች፣ ሁለቱ ሰዎች በፀጋ ላይ ሲያንዣብቡ፣ ወደ ኋላ እና ወደ ፊት መመሪያ ሲሰጡ ድምፃቸው ጥርት ብሎ ይሰማት ነበር።  መመሪያው በግልፅ ምትረዳቸው አልነበሩም ፡፡ከቤት ተነስተው ሆስፒታል እስኪደርሱ ነገሮች ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ አይነት ነበር…

ነርሷ በእርጋታ እየመራች ወደአንድ ክፍል ይዛት ገባችና ወንበር ስባ  አስቀመጠቻት ..እሷ ከኮምፒዩተር ባሻገር ባለው ሌላ ወንበር ላይ ተቀመጠች፡፡ ከዛ ራሄል በጥያቄዎች ዝርዝር ታጣድፋት ጀመር ። አለርጂዎች የለባትም?ምን ምን  መድሃኒቶች ነው የምትወስደው?. የሚከታተላት  ዶክተር ማን ነው?።እነዚህንና መሰል ጥያቄዎችን ጠየቀቻት፡፡ቢያንስ ለነርሷ አስፈላጊውን መረጃዎች መስጠት ፀጋን በተወሰነ መጠንም ቢሆን መርዳት እንደሆነ በማሰብ በተቻላት መጠን በትኩረትና በትዕግስት መለሰችላት፡፡ በመጨረሻ ተጠናቀቀ ።

ራሄል ከነርሷ የቀረበላትን ውሃ  አልተቀበለችም። ‹‹እህቴን መቼ ማየት  እችላለሁ?›› ስትል ጠየቀች።

ነርሷ ተነሳች እና በፍጥነት ወደ ክፍሉ ሄደች፣ ራሄል በቁጣ እና በንዴት ተከተለቻት ። ብዛት ያላቸው   የማታውቋቸው ዶክተሮች  ፀጋ ህክምና ላይ እየሰሩ ነበር፣ ቢሆንም የገዛ እህቷን ፣የአደራ ልጇን  እንዳታይ ተከልክላለች..ያ ደግሞ በጣም ያበሳጫል።ዓይኖቿን በመጠባበቂያ ክፍል ውስጥ ካሉት ሌሎች ሰዎች ራቅ አድርጋለች። አእምሮዋም ስቃያቸውንና ጭንቀታቸውን ሊቀበል አልቻለም።በመጨረሻ ነርሷ ተመለሰች።

‹‹አሁን የተረጋጋች ነች። ወደ ህፃናት ህክምና አይሲዩ አስተላልፈዋታል።››ራሄል ደረቷ ላይ ቀዝቃዛ ክብደት  ያለው ብረት የተቀመጠባት መስሎ ተሰማት ።

‹‹ተረጋጊ ያልሽኝ መስሎኝ ነበር?።››ስትል ነርሷ ላይ አፈጠጠችባት።

‹‹ትክክል ነሽ  ተረጋጊ ብዬሻለው…ግን ጥብቅ ክትትል ሊደረግላት ይገባል።›› ነርሷ ጥንቃቄ የታከለበት ፈገግታ ፈገግ አለችላትና ። ‹‹ለአሁን… ደህና ነች ።››የሚል ንግግር አከለችበት፡፡

‹‹ለአሁኑ?››

‹‹ከፈለግሽ ወደ እሷ ልወስድሽ እችላለሁ።››

‹‹በጣም እፈልጋለው።››ራሄል ነርሷን ተከትላ ተራመደች።ሰውነቷ ኤሌክትሪክ እንደጨበጠ ሰው እየተንዘረዘረ ነው፡፡ ሰዎች ወደ ሞሉበት ኤሊቬተር ውስጥ ገቡ፣ እና ራሄል እጆቿን ተመለከተች…በቀደም በወላጆቾ ቤት ለተዘጋጀው ዝግጅት ብላ  የተቀባችው የጥፍር ቀለም ተፋፍቆ ነበር።…አለባበሷን ስታይ የበለጠ ገረማት…ለቀናት ከላዮ ላይ ያልወለቀ  የቆሸሸ እና የተጨማደደ ቲሸርት የሆነ እንዴት እንደለበሰችው እንኳን ማታውቀው አመድማ የነተበ ጅንስ ለብሳለች።በህይወቷ እንደዚህ እራሷን ጥላ እና ሙሉ በሙሉ ዘንግታ እንዳማታውቅ እርግጠኛ ነች፡፡ከመቼ ወዲህ ነው ይህቺን ልጅ እደዚህ የወደደቻት….?

ሊፍቱ ቆመና ፣ በሮቹ ተንሸራተው ተከፍቱ.. ራሄል ነርሷን ተከትላ   ወደ አንድ ክፍል ገባች
… ወደ ማጠቢያ ገንዳ ተወሰደች እና እጇን እንድትታጠብ ታዘዘች። እጆቿን በማድረቅ ነርሷ አገዘቻት ‹‹ጋውን እና ጭንብል  ማድረግ አለብሽ››አለችና አቀበለቻት ።ከዛ ነርሷ በተቆጣጣሪዎች የተከበበ አራት ትናንሽ አልጋዎችን ወደያዘ ክፍት ክፍል መርታ ወሰደቻት።
54
የራሄል  አይኖች ግን ፀጋ ላይ ብቻ ነበር የተሰኩት። ከአንድ ትከሻዋ ላይ የወረደ የሆስፒታል ጋዋን ለብሳ አልጋው ላይ እንዳለች ትንሽ አሻንጉሊት ትመስላለች። ሌላ ነገር ማየት አልቻለችም። በፀጋ አፍ ውስጥ የገባውን ቱቦ ያስፈራል፣ የምትተነፍስበት የመተንፈሻ አካል ጩኸት ሰቅጣጭ ነው፣ ህይወቷን ህልውና የሚቆጣጠሩ የተለያዩ ማሽኖች የሚያሰሙት ድምፅ ለራሄል በጣም ቀፋፊ የሚባል ነው  ፡፡ ከደረቷ እና ክንዷ በሌሎች ማሽኖች አማካኝነት በአልጋዋ ላይ ተንጠልጥለው ከከረጢት ፈሳሽ እየመጠጡ ወደሰውነቷ ያስገባሉ...ከጥቂት ሰዓታት በፊት ይህቺ ምስኪን  በራሄል እቅፍ ውስጥ ነበረች፡፡፡አሁን ግን ህይወቷ በበርካታ  መሳሪያዎች ተደግፎ ይገኛል ...አንድ የታወቀ ድንጋጤ ደረቷን ሲሰነጣጥቃት  ታወቃት። ‹‹እዚህ መሆን አልቻለችም። በዚህ የተደራጁ የቧንቧ እና የመቆጣጠሪያ መሳሪያዎች የታጠረችውን  ተወዳጇን ይህችን  ትንሽ  አቅመቢስ ህጻን  ማየት አልቻለችም። የዚችን ትንሽ ልጅ ነፍስ ከደካማ አካሏ ስትለይ ማየት አልቻለችም።››…ኪሩቤል ልክ እንደእሷ በማሽን ቁጥጥር ስር ሆኖ  ሲያጣጥር  ‹‹በቂ አየር እያገኘሁ አይደለም…መተንፈስ እያቃተኝ ነው።››እንዳላት ታስታውሳለች….ይህቺ ትንሽ ፍጡርም አንደበቷን አላቃ መናገር ባትችልም…ምን አልባት መተንፈስ በጣም ከብዷት ሊሆን ይችላል ስትል አሰበች፡፡

ራሄል ከእይታዋ እየጨለመባት መጣ ..ቀስ ብላ  በእጇ የወንበሩን ጀርባ ያዘች እና እራሷን ዝቅ አደረገች።ቀስ ብላ ተንበረከከች…እጇን በዝግታ ዘረጋች ፣የፀጋን እጅ ስታገኝ አቆመች፣ ከፀጋ አውራ ጣት ጋር የተጣበቀውን የኦክስጂን መቆጣጠሪያ እንዳትነቅል እየተጠነቀቀች  ጣቶቿን በዙሪያው አንሸራተተች።ከእጇ ጋር ያለው ቅጽበታዊ ግንኙነት በልቧ ውስጥ የተስፋ ጭላንጭል ፈነጠቀባት።

‹‹ኃይሌ በድካም ፍጹም ነው›› የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ወደ አእምሮዋ ገባ እና ራሄል ደጋግማ ደጋግማ አነበነበችው፣ የቀረውን ክፍል ብታስታውስ ደስ ይላት ነበር፣ መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ ረገድ  እሷ በጣም ከልምምድ ውጪ ሆና ቆይታለች ፣ ቢሆንም ግን አሁን ማድረግ የምትችለው ብቸኛው ነገር  መፀለይ ነው።ለዛ ነው ሰራተኛዋ አለምን ከቤት መፅሀፍ ቅዱስ እንድታመጣላት ያደረገችው፡፡ምን አልባት የምታደርገው ፀሎት ያቺን ሚስኪን ህፃን ሊጠቅም ይችላል?የሚል ከፊል እምነት በውስጧ በቅሏል… የምትወደው ሰው አልጋ አጠገብ ተቀምጣ በሀዘን በተሰበረ ድምፅ  ስትፀልይ ይሄ የመጀመሪያ ጊዜዋ አልነበረም ።ነገር ግን ሀሳቡ በአእምሮዋ ውስጥ ሲንሸራሸር ውስጧ ሙሉ በሙሉ አልተቀበለውም. ፀጋን ወደቤተክርስቲያን ይዛት ከሄደች ቀን ጀምሮ እግዚአብሔርን ዳግመኛ በልቧ ውስጥ የማግኘት ስሜት ተሰምቷት ነበር። ሕልውናውን መካድ አልቻለችም። የምትኖርበት የሱ አለም እንደሆነ  ታውቀዋለች።

ጭንቅላቷን በአልጋው ሀዲድ ላይ ባለው ቀዝቃዛ ብረት ላይ አስደገፈች፣ ዓይኖቿ ፀጥታ ባለው የታናሽ እህቷ አካል ላይ እንደተተከሉ ነው ፣ ፍፁም እርዳታ የለሽ፣ ድካም እና ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ስሜት እየተሰማት ነው።መፅሀፍ ቅዱስን ከፍታ እያነበበች መጸለይ ጀመረች።

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
56👍9
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

////

ተደግፋ በተቀመጠችበት   ወንበር ላይ ተኮራምታ ነው ያደረችው፡፡በጥዋቱ ተረኛ ዶክተሮች መጥተው እህቷን ቢመለከቷትም ምንም የተቀየረ ነገር አላገኙም…..ይህ  መሆኑ ደግሞ ራሄልን  ይበልጥ ተስፋ ቢስና ረዳት አልባ ስሜት እንዲሰማት አደረጋት፡፡መፅሀፍ ቅዱሷን አነሳችና …አነስተኛ ወንበር  እህቷ አልጋ አጠገብ በማድረግ የፀጋን ትንሽዬ ጣት ይዛ መፀለይ ጀመረች…አምላክ ለሁለተኛ ጊዜ ልቧን እንደማይሰብራት ተስፋ አድርጋለች፡፡ ድንገት ቀና ስትል ዔሊያስ  የሕፃናት ሕክምና አይሲዩ  በር ላይ ቆሞ ተመለከተችው፣ ልቡ ከብዷል። ስለ ፀጋ እንዳወቀ ወደ ሆስፒታል በፍጥነት ነው የመጣው።

ኤልያስ ወደ ክፍሉ ከመምጣቱ በፊት የህክምና ቻርቱን  አንብቦ መድሃኒቱን ሁለት ጊዜ ፈትሾ ነበር ….የፀጋን  አሁናዊ ሁኔታ እና እየተደረገላት ያለውን እንክብካቤ ከህፃናት ሐኪም ጋር ተወያይቷል. ሁሉም ምርመራዎች ታዝዘዋል እና ረፋድ ላይ ሌላ ሲቲ ስካን ማድረግ እንደሚያስፈልጋት ተወስኗል።ፀጋ ለጊዜው ራሷን ስታለች ግን የተረጋጋች ነበረች።በአሁኑ ጊዜ ኤልያስን  በጣም ያሳሰበው ከፀጋ እጅ ጋር የተጣበቀችው እና የገረጣችው ሴት ሁኔታ ነው፣ በመጋረጃዎቹ ክፍተት መሀል   አልፎ የሚመጣው የጠዋት ብርሃን  ጭንቅላቷ ላይ አርፎ ይታያል .. መጽሃፍ ላይ አቀርቅራ እያነበነበች ነው ። ራሔል  አንድ ጊዜ  ስልክ ለመደወል ከፀጋ ጎን ከመነሳቷ ውጭ  ሌሊቱን ሙሉ  ከጎኗ ሳትንቀሳቀስ እንዳሳለፈች ነርሷ ነግራዋለች፡፡

ለመጨረሻ ጊዜ እሱ ቤት መጥታ በመጥፎ ሁኔታ ካስተናገዳት በኋላ ከእርሷ ጋር የመነጋገር መብት እንደሌለው ተሰማው። በወቅቱ ባለበት ንዴት ተነስቶ በሰራው ስህተት በጣም ተቆጭቶ ስህተቱን ለማረም  በመፈለግ ለእሷን ለመደወል ፈልጎ ነበር ..እሷን ማስቀየሙ እንዴት ህይወቱን እንዳመረረበት ሊነግራት ፈልጎ ነበር ። ለምን በእሷ ላይ እንደዛ እንደሆነ እና ስለወላጆቹ ማንነት ያወቀው አዲስ መረጃ  ውስጡን እንዴት እንደሰባበረው ሊያስረዳትና አዝናለት ይቅር እንድትለው ለመጠየቅ ፈልጎ ነበር…ግን አንዱንም ማድረግ ሳይችል  ነው.. ቆይ በኋላ ..ቆይ ትንሽ ልቆይ ሲል ድንገት ዛሬ ጥዋት ከሆስፒታል ተደውሎለት ስለፀጋ በአደገኛ ሁኔታ መታመም እና ለሊቱን ሙሉ ሆስፒታል እንዳደረች  የተነገረውና ሲሮጥ የመጣው፡፡

አዎ አሁን ትልቅ ሰው ነው… አዎ እሱ የበለጠ ጥበበኛ ነው። አዎን፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ ጠንካራ ቦታ አለው።ያ ሁሉ ቢሆንም ግን ከወላጆቹ የተቀዳ ተመሳሳይ ድክመት  በደም ሥሩ ውስጥ ሊፈስ እንደሚችል  መገመቱ አልቀረም ። ብዙውን ጊዜ አንድ ልጅ ከወላጆቹ የሚወርሳቸው ጥሩም ሆነ መጥፎ የባህሪ ውርሶች  እንደሚኖሩ ለማወቅ በቂ የታካሚ ታሪኮችን አንብቧል.፡፡ራሄል በቤቱ ልትጠይቀው ስትመጣ መረጃውን ለመቀበል እየሞከረ ነበር…በህይወቱ ውስጥም የት ቦታ ሊያስቀምጠው እንደሚችል  ለማወቅ በመጣር ላይ ነበር…. በዛ ምክንያት ነበር እሷን ሊያስቀይማት የቻለው፡፡

በጸጥታ ወደ ክፍሉ ገባ፣ አይኑ ወደ ተቆጣጣሪ  ማሽኖቹ ተመለከተ፣ እየፈተሸ፣ እየለካ። ወደ አልጋው አጠገብ ሲደርስ ራሄል .ተስፋ ቆርጣ ታነብ ከነበረው መጽሐፍ ቀና ብላ ተመለከተችው። ፊቷ እርብሽብሽ ብሏል  እና ስታለቅስ ተመለከተ።

ፊቷ ላይ ያለው ህመም በግልፅ ይነበባል። ለሌሎች ታካሚ  ወላጆች እንደሚያደርገው አይነት በርህራሄ የተሞላ እንክብካቤ ሊያደርግላት ከጎኗ ቆመ። ማድረግ የፈለገው ግን ወደ እቅፉ ጎትቶ ደረቱ ላይ ለጥፎ ግንባሯን ደጋግሞ ለመሳም ነበር፡፡ ሊያበረታታት እና  ሊያፅናናት ነበር ሚፈልገው ።

‹‹ደህና ትሆናለች?››አላት፡፡

ራሔል ቀና ብላ ተመለከተችው፣

‹‹ለአሁን የተረጋጋች ናት›› ሲል አከለበት፡፡ 

በዝምታ እያዳመጠችው ነው፡፡

‹‹ሲቲ ስካን ሰርተንላታል እና ስለ ደም ዝውውሯ ከላቦራቶሪ ውጤት በኋላ እናውቃለን ።››

የራሄል እንባ ዝርግፍ አለ…ከተቀመጠችበት ተነሳችና  ቆመች ፡፡በእጇ ይዛ ነበረውን መፅሀፍ አጠፈችውና ማውራት ጀመረች

‹‹ጉንፋን ብቻ ነበር ያመማት..ድንገት በዚህ ደረጃ እንዴት አቅም ልታጣና እራሷን ልትስት ቻለች?››ስትል ጠየቀችው፡፡

ዔሊያስ ራሱን ነቀነቀ።

‹‹አናውቅም… ከዚህ በፊት እንደነገርኩሽ የፀጋ የጤና ችግር ተደራራቢና የተወሳሰበ ነው….. አንዱ በሽታ ሲጀምር ሌላውም ይከተላል…አሁን በጣም አደገኛ የሆነው በአእምሮዋ ውስጥ የተፈጠረው ችግር ነው፡፡

‹‹ከዚህ ስቃይ  ትወጣለች?››

‹‹በአጠቃላይ ያቺ  ትንሽ ልጅ ሳንባዋ ጥሩ ነው፤ልቧ ጠንካራ ነው። ከዚህ በሽታ እንደምታገግም አምናለሁ።››

ራሄል በሚናገርው ነገር ላይ እርግጠኛ እንዳልሆነ ተረዳች፡፡ ‹‹እግዚአብሔር በእርሱ እንድንታመን እንዴት እንደሚነግረን እና የልባችንን መሻት እንዴት እንደሚሰጠን እያነበብኩ ነበር…ይህን ታምናለህ?››ዔሊ ወደ ፀጋ ከዚያም ደግሞ  ወደ ራሄል እያፈራረቀ ተመለከተ፡፡

‹‹እኔ በዚህ ወቅት  ምን ማመን እንዳለብኝ አላውቅም። ለፀጋ የምንችለውን ሁሉ እያደረግን እንደሆነ አውቃለሁ። እና እሷን በሕይወት ለማቆየት ባለን ቴክኖሎጂ ላይ እምነቴን ማሳረፍ እመርጣለው።››

ራሄል የደከመ ፈገግታ ፈገግ አለችለት‹‹ከዚህ በፊት አንድ ጊዜ እግዚያብሄርን  አመንኩኝ እና አሳዘነኝ. ..ማለቴ ስለ ኪሩቤል እያወራሁ ነው?››ራሷን ነቀነቀች፣ ከዚያም ቀና ብላ ተመለከተችው…በዛ ቅፅበት  ነርሷ ወደ ፀጋ አልጋ መጣች።

‹‹ነርሷ ለሰዓታት እዚህ እንደተቀመጥሽ ነገረችኝ…ሄደን ቡና ብንጠጣ ምን ይመስልሻል? እስክንመጣ እዚህ ያለውን ነገር ነርሷ  ትከታተለዋለች?›› አለና  በቀስታ እጇን ጎተታት።

‹‹እኛ ስንሄድ ፀጋ ደህና ትሆናለች?።››ስትል ጠየቀች፡፡

ነርሷ እያስተካከለችው ያለውን መቆጣጣሪውን ቀና ብላ ተመለከተች..ወደ ዶ/ር ኤልያስ ተመለከተችና ‹‹አንድ ነገር ከተቀየረ ወዲያውኑ አሳውቅሃለሁ››አለችው ።

‹‹ለአሁን ነገሮች ደህና ሆነው ይታያሉ።››ራሄል ወደ ፀጋ  ተመለከተች፣ ፡፡ጥላት መውጣቷ ብዙም ምቾት አልሰጣትም፡፡

በለሆሳሳ‹‹እሺ ..እንዳልክ እንሂድ››አለች ።ኤሊያስ መጽሐፍ ቅዱስን ከእጇ ወስዶ ከፀጋ አልጋ አጠገብ ባለው ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠው። ከዚያም ከክፍሉ ይዟት ወደ ካፍቴሪያ ሄደ፡፡ወንበር ስበው ፊት ለፊት እየተዩ ተቀመጡ፡፡የሚፈልጉትን አዘዙ፡፡

አሁንም ከፀጋ ውጭ ምንም ነገር በአእምሮዋ የለም..‹‹ትናንት ከሰዓት ነው፡፡ትንሽ እንደመሻል ብሏት ነበር… ከእኔ በቅርብ ርቀት ሶፋው ላይ ሆና ስትጫወት ነበር…ድንገት አንሸራተታት እና ለስላሳ የቆዳ ሶፋ ላይ ወደቀች እና በጭንቅላቷን ወደኋላ ተኛች… ከዛ ተዝለፍለፈችብኝ..ጮህኩ..ወዲያው አምቡላንስ ተጠራ…ወደዚህ ይዘውን መጡ…..ይሄው እየባሰ ከመሄድ  ውጭ ምንም መሻሻል አላየሁም፡፡››

‹‹አይዞሽ……ሁሉም ነገር ሰላም ይሆናል››

ያዘዙት ነገር መጣላቸው…..እሷ ጥቁር  ቡና ብቻ ነበር ያዘዘችው፡፡

ትኩር ብሎ ሲያያት ያዘችው….ፀጉሯን ከፊቷ ላይ ገፋች እና ‹‹የባቡር አደጋ  የደረሰብኝ መስያለው አይደል?››

ከዚህ በፊት አይቷት ከነበረው በተለየ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ እየተመለከታት ነው ፡፡የለበሰችው ልብስ የተዘበራረቀ እና የተዝረከረከ አይነት ነው… ምንም አይነት ሜካፕ አልተጠቀመችም እና ፊቷ ተጎሳቅሏል እና ደክሟታልል።
49👍1🥰1
‹‹ቆንጆ ትመስያለሽ.››አላት… ቃላቶቹ ከሱ አምልጠው ነው የወጡት… ሊያቆማቸው አልቻለም።ራሄል ጭንቅላቷን ቀና አደረገች…፣  በግንባሯ ላይ  ብስጭት ይታያል። አልወቀሳትም። ከሁለት ቀን በፊት ወደ እሱ መጥታ የልቧን ልትገልፅለት ፈልጋ ነበር…በምላሹም እሷን ከቤቱ አስወጥቶ ነው ያባረራት ፡፡

ግን ሌላ ምን ማድረግ ይችል ነበር?በወቅቱ የራሱ ህይወት ተዘበራርቆበት ነበር፣ ትዝታው ከእሱ ተሰርቋል፣ ባወቀው ነገር ተበሳጭቷል ፡፡እሱ ተራ ሆኖ ሳለ እንዴት እንደ ራሄል ያለችን ሴት እንዴት ሊጠይቅ ይችላል?

ራሄል እሱ እያሰበ ካለው ሀሳብ ፍፅም ተቃራኒ  የሆነ ጥያቄ ድንገት ጠየቀችው፡፡

‹‹ግልፅ ሆነህ…ምንም ሳትደብቀኝ…ፀጋ ምን ችግር እንዳለባት ልትነግረኝ ትችላለህ?›› የንግግሩን ርዕሰ ጉዳይ ወደ ጋራ ጉዳያቸው ቀየረችው…።

ዔሊያስ እጁን ዘርግቶ ጣቱን ከንፈሯ ላይ በማሳራፍ ከአፏ የሚወጣውን የጥፋተኝነት ፍሰት አቆመ።

‹‹ አሁን ማድረግ የምንችለው መጠበቅ ብቻ   ነው….ከዛ ውጭ ምንም የሚጠቅምሽን  ነገር ልነግርሽ አልችልም ››

አላት….ዝም አለች…በሀሳብ ርቃ እንደሄደች ከሁኔታዋ ማወቅ ችሏል…ሊያቋርጣት አልፈለገም…ከዚህ በፊት እላፊ ቀርቧት በሁለቱ  መካከል የሆነ ነገር እንዳለ እንድታስብ አደረጋት።እና አሁን? ምን እንደሚያስብ እርግጠኛ አልነበረም። በአንድ ወቅት በደንብ ይቆጣጠረው የነበረ   ህይወቱ አሁን  ተገለባብጦበታል ።ነገሮችን ወደቦታቸው ለመመለስ ጊዜ ያስፈልገዋል። ቢሆንም ግን አሁን ከፊት ለፊቱ የተቀመጠችውን ሴት በጣም እንደሚፈልጋት እርግጠኛ ነው፡፡

ድንገት መናገር ጀመረች‹‹ለአመታት በፀሎት ማመን አቁሜ ነበር ።››

‹‹ታዲያ አሁን  ምን ተለወጠ?››

‹‹ህይወቴ.›› በጥንቃቄ ፈገግታ ሰጠችው። ‹‹ሁሉንም ነገር የምቆጣጠር መስሎኝ ነበር፣ እና ለተወሰነ ጊዜ  ነገሮች እኔ በምፈልገው መንገድ እያስኬድኳቸው መስሎኝ ነበር። የምፈልገው አይነት  ስራ እና የምወደው አይነት የመኖሪያ ቦታ እና ትክክለኛ ህይወት ነበረኝ። የኪሩቤልን ሞት ለመርሳት ለማደርገው ጥረት መሸሸጊያ አግኝቼ ነበር። አሁን ግን ፀጋ  ታማለች።›› ራሄል ተነፈሰች። ‹‹አዎ. እና ፈራሁ. እና አዝኛለሁ. ወደ ህይወቴ ባትገባ ኖሮ ብዬ እመኛለሁ እና አጣብቂኝ ውስጥ ገብቼያለው… በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆኜ በራሴ ኩራት የምኮፈስበት ምንም አይነት አቅም የለኝም….እና እግዚያብሄር እጅ ላይ ወድቄለው….ይህንንም በግልፅ ማወጅ የምችለው ቀጥታ ከእሱ ጋር በመነጋገር ነው….በፀሎት››

የሚላት ሌላ ነገር ስለጠፋው‹‹ ጥሩ ነገር  ያደረግሽ ይመስለኛል…ግን ዳግመኛ እንድትጎጂ አልፈልግም?››አላት፡፡

‹‹አንዳንዴ መጎዳት ጥሩ ነው… ስጎዳ በህይወት መኖሬን አውቃለሁ። ኪሩቤል ከሞተ በኋላ ስብርብር ስል ሁሉም ሰው ነገሮችን እያጋነንኩ እንደሆነ ነበር የሚያስቡት ። አውቃለው እንደዛ ልጎዳ አይገባም ነበር ። አየህ  ችግሩ ለኪሩቤል ሞት እራሴን ነበር ተጠያቂ ያደረኩት… የዛን ቀን  ባንጣላ ኖሮ በብስጭት ጥሎኝ አይሄድም ነበር …ባይበሳጭ ኖር ደግሞ በተሻለ ትኩረት ያደርግ ነበር፣ እናም በዛ ሰካራም ሹፌር አይመታም ነበር፣ ….አይገርምም .. ከእኔ አንደበት የሰማቸው የመጨረሻ ቃላቶች  ስለዛ ሞተር ሳይክል የተሰነዘረ  ትችት እና ቁጣ ነበር…. ‹‹ሞተር እየነዳህ ሁለተኛ ወደእኔ እንዳትመጣ ››ነበር ያልኩት….፡፡

‹‹ራሄል እንደዚያ አታስቢ። ጥፋቱ ያንቺ አልነበረም።››

‹‹ አሁንማ አውቃለሁ,… ግን ለዓመታት, እንደዛ ነበር የማስበው … እሱን አፈር ውስጥ እንዲገባ አድርጌ እኔ ግንኙነት የመጀመር መብት የለኝም   ብዬ እራሴን ስቀጣ ነበር የኖርኩት … ከዚያም ባላሰብኩት አጋጣሚ ድንገት  ፀጋ ወደ ህይወቴ ገባች….ተስፋዬን አደሰችው …ጨለማ ጎኔን ሸንቁራ ብርሀን እንዲፈስበት አደረገች …ከእንደገና በጣም እንዳፈቅር አበረታታችኝ…ነገን እንድናፍቅና  ከስራ ውጭ ስላለ ህይወቴ እንዳሰላስል አደረገቺኝ…እንደገና እየወለደችኝ እንዳለ ነው የሚሰማኝ…አንድ ነገር ከሆነችብኝ እንዚህን ሁሉ በጎ ስሜቶች መልሼ እንዳላጣቸው ፈራለሁ…ስጋቴ ዳግመኛ እንዳልሞት ነው ››በእንባ እየታጠበች ቢሆንም   ፈገግ አለች፣ የእፎይታ ትንፋሽ ወሰደች።‹‹ እናም ለዛም ነበር ከአንተ የራቅኩት እና ስለፈራሁ ይቅርታ።››

‹‹ ራሄል እባክሽ ለዚህ ይቅርታ አትጠይቂ››በነገረችው ነገር ልቡ አዘነ። የሆነ ነገር ለመናገር አስባ ..ተወችው…ከንፈሯ እየተንቀጠቀጠ ነው። ዔሊያስ ከዚህ በላይ ሊቋቋመው አልቻለም። ጠጋ ብሎ ወደ እቅፉ አስገባት።ደረቱ ላይ ለጠፋት፣ እንባዋ በገላው ላይ ሲንጠባጠብ  ሙቀት ተሰማው።

‹‹ ፈራሁ ኤሊ። በጣም ፈርቻለሁ። እና እንደዚህ አይነት ስሜት እንደገና እንዲሰማኝ አልፈልግም ነበር። ›› ድምጿ ተሰባበረ እና ወደ እሱ ተጣበቀች።

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
67👍14
አትሮኖስ pinned «#የእግዜር_የአደራ_ልጅ… ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አምስት ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ /// ቢንያም እና ዔሊያስ አዲሱ ቤት ውስጥ ሆነው አንዳንድ ነገሮችን እያስተካከሉ ነው፡፡ ‹‹እነዚህ ክፍሎች ከተጠናቀቁ በኋላ የሚቀጥለው ፕሮጀክት የሳሎኑን ሴራሚክ ማሰራት ነው›› አለ ዔሊ፡፡ ቢኒያምም ‹‹አዎ..እኔም እንደዛ ነው ያሰብኩት ››ሲል ለሀሳቡ ድጋፍ ሰጠው፡፡ ‹‹ሰሞኑን በቤቱ የፊኒሽንግ ስራ ላይ ያለህ…»
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
//////

ዔሊያስ በፀጋ አልጋ ጥግ ላይ ቆሟል፡፡ማንኛውም ሕፃን ከማሽን ጋር ተጣብቆ ማየት ሁል ጊዜ ጥልቅ ሀዘን ውስጥ ይጨምረዋል ፡፡እንደፀጋ አይነት የሚያውቃትና የሚቀርባት ልጅ ስትሆን ደግሞ ነገሩ ከባድ ነው የሆነበት ..በዛም ምክንያት እሱ ዛሬ ጠፍቷል፣ ግን ለማንኛውም  ከልምዱ ወጥቶ ወደ ተቆጣጣሪ ማሽኖቹ  ተመለከተ። ምንም ለውጥ የለም።በአንድ በኩል ማመስገን ያለበት ነገር ነበር።በሌላ በኩል፣ አሁን ለሃያ አራት ሰአታት ራሷን ስታ ቆየች ማለት ነው። እና ለምን እንደሆነ አላወቀም. ተአምር እስኪፈጠር ድረስ ከመጠበቅ ውጭ  ምን ማድረግ እንደሚችል   ምንም ሀሳብ አልነበረውም።

ከዚያን ቀደም  ብዙ ነገር ሲከሰት አይቷል። ልክ እንደ ራሄል በልጁ አልጋ አጠገብ ሲያንዣብቡ ለነበረሩ ወላጆች አሳዛኝ ዜና አቅራቢ ሆኖ ያውቃል ።የወንድሙ ሚስት  በካንሰር ስትሞት በዛ ምክንያት ወንድሙ ሲሰቃይ ተመልክቶ ነበር።
የፀጋ ወላጅ እናት ትዝ አለችው፡፡ጽጌረዳ፡፡አሁን በዚህች ደቂቃ ልጇ ያለችበትን ሁኔታ ሰምታ ብትመጣና ለመጨረሻ ጊዜ  ብትሰናበታት ደስ ይለው ነበር፡፡ግን አድራሻዋን ካልታወቀ ምን  ማድረግ ይቻላል?፡፡አንድ ቀን ከአመት ወይም ከአስር አመት በኋላ ካለችበት መጥታ‹‹ ልጄስ የት ነው ያለችው? ››ብላ ስትጠይቀው…መቃብር ቦታ ወስዶ ሲያሳያት በአእምሮው ሳለና ዝግንን አለው፡፡‹‹እግዚያብሄር ሆይ እባክህ እርዳኝ››ሲል ለአምላኩ ተማፅኖ አቀረበ፡፡

‹‹እንዴት ነች?›› የራሄል ድምፅ  ነበር ከሀሳቡ የመለሰው።

‹‹ ..ምንም ለውጥ የለም …ነገሮች ባሉበት እየሄዱ ነው.›› ወደ እሷ ዞረ፣ በዓይኖቿ ውስጥ  ፍርሀት ይነበባል፡፡

‹‹ተኝተሻል?››

‹‹ትንሽ ›› ራሄል ፈገግ አለችለት፣
ከዚያም አንገቷን በቀስታ ዞረች፣

‹‹ሴቶቹ ሄዱ?››ሴት ጓደኞቾ  ሊጎበኟቸው መጥተው ነበር፣ እና በእሱ እርዳታ ራሄልን ለጥቂት ጊዜ መተኛት ችላለች ። እሷ በተኛችበት ጊዜ ጓደኞቾ በፀጋ አልጋ አጠገብ ተንበርክከው ሲፀልዩላት አይቶ  ነበር።

‹‹አዎ ሄደዋል…ብዙ ቆዩ እኮ››

‹‹ደህና …በመምጣታቸው በጣም ደስ ብሎኛል….እንደዚህ አይነት ጥሩ ጓደኞች ስላለሽ እድለኛ ነሽ››የሚል አስተያየት ሰጣት ፡፡

ራሄል በቀስታ ጉንጯን እየዳበሰች ‹‹አዎ ልክ ነህ…ለጸሎታቸው በጣም አመስጋኝ ነኝ።››አለችና ወደ ፀጋ ሄደች።
በቀስታ መዳፏን  ግንባሯ ላይ አሳረፈች ‹‹ስነካት ይታወቃታል እንዴ?›› ብላ ጠየቀችው፡

‹‹አንዳንድ የአካላቷ ክፍል ሴንስ ሊያደርግ ይችላል ። ግን ያንን የምንለካበት ምንም መንገድ የለንም።››

‹‹ግን ከዚህ ኮማ ትነቃለች አይደል? ስትነሳ እንደበፊቱ  እራሷን ትሆናለች አይደል?››ጥያቄዎቾ ሁሉ ጭንቀት የወለዳቸው ናቸው፡፡
እሱም ከእሷ ባልተናነሰ በመጨነቅ‹‹ሁሉም ነገር ደህና መሆኑን ብነግርሽ ደስ ይለኝ ነበር››አላት፡፡

በዚህ ሆስፒታል ውስጥ በህፃናት ሀኪምነት ካሳለፈው ከማንኛውም ጊዜ በላይ  አቅመ ቢስነት  ተሰማው።‹‹ፀጋ የራሷ የሆነ ችግር አለባት ፤ ነገር ግን የምንችለውን ሁሉ እያደረግን ነው።››አለና ወደራሄል ተጠግቶ  እጇን በእጁ  ያዘው።

‹‹ዶክተሯ ስለሆንክ ደስ ብሎኛል››አለችው።

‹‹እዚህ በመሆናችሁ ደስ ብሎኛል.››እጇን  ጨመቀ ፣ -ጸጋ በእሱ  እጅ ፈውስ ታገኝ ዘንድ ተመኘ። እሷን ከኮማ እንድትወጣ ለማድረግ ትክክለኛውን መድሃኒት በፀጋ ደም ስር  ማስገባት ይችል ዘንድ  ተመኘ። በራሔል ፊት ላይ ፈገግታ መመለስ ይችል ዘንድ ተመኘ… ያን ሁሉ ነገር ማድረግ ቢችል ተመኘ።ስለ ወላጆቹ ሊነግራት ፈለገ, ለምን እንደገፋት ሊያስረዳት ፈለገ. ነገር ግን ከመናገሩ በፊት አንዲት ነርስ ወደ በሩ መጣች።

‹‹ራሄል ቸርነት? ወላጆችሽ እዚህ ናቸው።››አለቻት፡፡

ድንጋጤ  የተቀላቀለበት ብስጭት በእሱ ውስጥ ፈሰሰ።.ራሄል እጁን የበለጠ ጨመቀች፡፡

ነርሷ ራሔልን ‹‹በአንድ ጊዜ ሁለት ጎብኝዎች ብቻ ናቸው ወደ ውስጥ መግባት የሚችሉት  …ስለዚህ እነሱ ከገቡ መውጣት አለብሽ።››ስትል አስጠነቀቀች።
ወደ ፀጋ ዞር ብላ ተመለከተች እና ‹‹ገባኝ።››አለቻት።

ደ/ር ኤልያስ የአቶ ቸርነት እና የትርሀስ  ጸጥ ያሉ ድምጾችን እና የራሄልን ዝቅተኛ ምላሽ እስኪሰማ ድረስ በአልጋዋ አጠገብ ቆየ።የራሄል እናት  አቶ ቸርነት  እየገፏቸው  በዊልቸር ላይ ነበሩ፣ ። ሀኪሞቹ  ለልጃቸው ምን እየሰሩ እንደሆነ  በአጭሩ አስረዳቸው እና… የተሻለ ዜና ሊነግራቸው ቢችል ደስተኛ ይሆን እንደነበረ በፀፀት ስሜት ነገራቸው፡፡

‹‹በሰው የሚቻለውን ሁሉ እንደምታደርጉ እናምናለን›› አሉ አቶ ቸርነት፡፡የሚያጽናና እጃቸውን በዔሊያስ ትከሻ ላይ ዘረጉና።

‹‹እኛ ከትንሿ ልጃችን  ጋር ስለምንቆይ  ለምን ራሄልን ለጥቂት ሳዕታት ማረፍ ወደምትችልበት ቦታ  አትወስዳትም.››አሉት
እሱም መስማማቱን ጭንቅላቱን በመነቅነቅ አረጋገጠላቸው፡፡
‹‹ይቅርታ እማዬ…አደራችሁን መወጣት እልቻልኩም››አለች እና እንባዋ እርግፍ አለ!! ከዛ እናቷን ለመሳም ጎንበስ አለች፡፡

እናትዬው የልጇን ፊት በእጆቿ አሻሸች‹‹ልጄ እህትሽን በአደራ አልሰጠሁሽም..እሷ ለሁላችንም የእግዚያብሄር አደራ ነች…የተቀበልናት ከእግዚያብሄር ነው….አይ እፍልጋታለው ብሎ  መልሶ ከወሰደብንም ከእሷ ጋር ስላሳለፍናቸው ጣፋጭ ወራቶች ከማመስገን ውጭ ምንም ማለት አንችል ..ብቻ በዚህ አይነት ጉዳይ ዳግመኛ ወደዚህ ሆስፒታል  እንድትመጪ ስላደረኩሽ አዝናለሁ።››

ራሄል እንባዋን ዘረገፈችው‹‹እማዬ እኔ እኮ እምነቴ እንደእናንተ ጠንካራ ቢሆን ደስ ይለኝ ነበር..ግን አልችልም››

ወ.ሮ ትርሀስ‹‹ልጄ፣ትቺያለሽ ልብሽን ብቻ አለስልሺው… ይሄ የእኔ ስህተት ነው ብለሽ ለአንድ ደቂቃ እንኳን እንዳታስቢ…እሷን ለመርዳት በአቅራቢያዋ ስለነበርሽ ደስ ብሎኛል. እግዚያብሄር ይሁን ያለው ነገር  ማንም ከመሆን ሊያግደው አይችልም.››በማለት የራሔልን ጭንቅላት ወደ ታች ጎትተው ግንባሯ ላይ ሳሟት።
ቀጥለው የተናገሩት አቶ ቸርነት ናቸው‹‹ አሁን ሄደሽ ቡና ጠጪ። ትንሽ እርፍት ውሰጂ እኛም ከናፈቀችን ልጃችን ጋር ትንሽ እንቆይ ።››ራሄል ደካማ ፈገግታ ሰጠቻቸውና, ክፍሉን ለቃ ስትቀወጣ  ኤልያስ ከኋላዋ ተከተላት፡፡

‹‹ከእኔ ጋር መምጣት የለብህም››

‹‹አይ መምጣት ስለምፈልግ ነው፣…እንደውም ተከተይኝ ቆንጆ እርፍት የምታደርጊበት ያልተያዘ ክፍል አውቃለው፡፡››አለና ክንዷን ይዞ እየመራ ወሰዳት…ክፍሉን ከፍተው ሲገቡ ግን እንደጠበቁት ባዶ አልነበረም ፡፡ ሲገቡ አንድ ወጣት ባልና ሚስት  ከአልጋው ተነሱ..እና ለመውጣት ወደበሩ ተንቀሳቀሱ።

‹‹እባካችሁ በእኔ ምክንያት አትውጣ››አለችው ራሄል።

ሴትየዋ በከፍተኛ ፈገግታ ‹‹እኔና ባለቤቴ እየሄድን ነበር፣እዚህ ያለንን ቆይታ ጨርሰን ወደቤታችን እየሄድን ነው…››አለች

‹‹ለዚያ አመሰግናለሁ.››ወጣቱ እጁን በሚስቱ ትከሻ ላይ አድርጎ አቀፋት፡፡ እሷን ዘና ብላ ራሷን በትከሻው ላይ አስተኛች።ዔሊያስ የቅናት ስሜት ተሰማው። ደስተኛ ሆነው ይታዩ ነበር። እሱ እና ራሄል እንዲኖራቸው  የሚፈልገው እንዲህ አይነት ፍቅር እና መፈቃቀድ ነው ።በሩ ከኋላቸው ተዘግቶ ሳለ፣ ፊቷ የናፍቆት መልክ ይዞ ራሄልን እያያቸው ያዘ።

‹‹ወደ ቤታቸው መሄድ በመቻላቸው ደስ ብሎኛል››አለች በለስላሳ።
ክፍሉ ውስጥ ግድግዳ ተጠግቶ ካለ ሶፋ ላይ ተቀመጠና በረጅሙ የእፎይታ ትንፋሽ ተነፈሰች፡፡
50👍3🥰1
ዔሊያስ ‹‹ፀጋ አሁን ደህና ናት…ወላጆችሽ አሁን አሉ እና ነርሶች ሁል ጊዜ አጠገቧ ናቸው.››

‹‹አውቃለሁ።››አጠገቧ ያለውን መቀመጫ እየደበደበች ቀና ብላ ተመለከተችው።

‹‹እባክህ መጥተህ እዚህ ተቀመጥ …አንድ ነገር ልነግርህ እፈልጋለሁ ››አለችው፡፡
በጣቷ ላይ ያለውን ቀለበት እያሽከረከረች  በጎን  ተመለከተችው። በወቅቱ ያጠለቀችው  ብቸኛው ጌጣጌጥ እንደሆነ ተገነዘበ።የሚገርመው እጁን በራሷ ያዘች።

ፈራ ተባ እያለ ወደእሷ ተጠጋና ግማሽ ሜትር ያህል ክፍተት ትቶ ከጎኗ ተቀመጠ፡፡ጥቂት የፅሞና ጊዜ ወሰደችና  መናገር ጀመረች‹‹ዛሬ ጥዋት አንተ ባልነበርክበት ጊዜ  አንድ ሰው  ጎብኝቶኝ  ነበረ - ወንድምህ ቢንያም። ስለ ወላጇችህ  ነገረኝ። በቅርብ ስለእነሱ ያወቅከው ነገር እንደጎዳህ አስረዳኝ።››
በኤልያስ ፊት  ላይ ብስጭት ታየ።‹‹ወንድሜ ሚስጥር መጠበቅ የማይችል ወንፊት  መሆኑን አላውቅም ነበር.››

‹‹አንተን ፈልጎ  ነበር የመጣው…እድሉን ሳገኝ ላናግረው ፈለኩ..እኔ ነኝ የወተወትኩት።››ራሄል ፣እጇን ወደእሱ   ዘረጋችና በእጁ ላይ ያለውን ጠባሳ በትንሹ ተጫነችው። ያለፈውን ጊዜ የሚያስታውሰው ምልክት ነው፡፡
‹‹ስለ አንተ ልጠይቀው ፈልጌ ነበር።››

‹‹ለምን?››

‹‹ያን ቀን ልጠይቅህ የመጣሁት  በዝግጅቱ ቀን  ስለእኛ  ስህተት እንደሰራሁ ልነግርህ ነበር ። እንዳልኩት በህይወቴ ውስጥ ሌላ ሰው ላለመፍቀድ በጣም ፈርቼ ነበር። ኪሩቤልን ማጣት ከባድ ነገር ነበር፤ ነገር ግን እነዚያ ቀናት ከአንተ የሰማሁት ነገር የበለጠ ከባድ ነበር፣ እናም ከዚህ በኋላ መጎዳት አልፈልግም - ምናልባት ወንድምህ ሊያውቅ ይችላል ብዬ አስቤ ነበር።

‹‹ለሕይወቴ እቅድ ነበረኝ›› አለ ኤሊያስ። ጣቶቹን ከጣቶቾ አቆላለፈ። ሊለቃት አልፈለገም።

‹‹ቤት ለመስራት  ብድር መበደር ነበረብኝ  ፡፡እዳዬን አስክከፍል ድረስ ቢያንስ ለአንድ ወይም ለሁለት አመት የምጨነቅለትን ሰው  ወደህይወቴ ማስገባት አልፈልግም ነበር ።›› በለሆሳስ ሳቀ፣ ‹‹ከዚያም አየሁሽ፤ ቀድመሽ መጣሽ።››የራሄል የጨለማ አይኖች እየፈኩ ቢሄዱም  ዞር ብላ አላየችም።‹‹ኤሊ ምን እያልክ ነው?››

‹‹ራሄል ላንቺ አስባለሁ:: ከማንም በላይ ህይወቴን ቀይረሽዋል:: ግን ስለ ወላጆቼ ካወቅኩ በኃላ ነገሮች ተገለባበጡብኝ… ምን ማሰብና ምን ማድረግ እንዳለብኝ  አላውቅም. ››

‹‹ወላጆችህ ከእኛ ጉዳይ ጋር ምን አገናኛቸው?››

‹‹... ሌሎች ወላጆች እንዳሉኝ እያወቅኩ ነው ያደግኩት እድሜዬን ሙሉ ወላጆቼ ድንቅ ሰዎች ናቸው ብዬ ነበር የማስበው ›› አለና የተገናኙትን እጆቻቸውን እያየ።
‹‹እርግጥ ያደኩት በሚያስደንቅና እንክብካቤ እና  በፍቅር በተሞላ ቤት ውስጥ ነው፣ነገር ግን ሁልጊዜ የማስታምማቸው ሌሎች ትዝታዎች ስለነበሩኝ፣ለአሳዳጊ ቤተሰቦቼ  በቀላሉ ሊረዱት የሚከብድ አስቸጋሪ  ልጅ ሆንባቸው ነበር።ቢንያም በማደጎ የተወሰደው በጣም ህፃን ሆኖ ስነበር  ወደኋላ ሚጎትተው የስጋ ወላጆቹ ምንም ትዝታ ስላልነበረው ለእነሱ መልካም ልጅ ሆኖ ማደግ ችሏል፡፡እና አሁን ድንገት ስጓጓለት ስለኖርኩት ስለስጋ  ወላጆቼ ታሪክ ካወቅኩ በኃላ በጣም ተናደድኩ  …የተከዳው አይነት ስሜት ነው ተሰማኝ ።"

‹‹ለዛ ነው የዛን ቀን ፎቶዎቹን የጣልካቸው፡፡››

‹‹አዎ…››

‹‹አሳዳጊ ወላጆችህ   ስለስጋ ወላጆችህ ታሪክ ያውቁ ነበር ብለህ ታስባለህ?››

‹‹አይ. አሁን አንኳን እንደዛ  ለማሰብ ይከብደኛል ..ምናልባት እነሱ ለእኔ ውለታ እየሰሩኝ እንደሆነ አድርገው እያስቡ ይሆናል. ነገር ግን እኔ ወላጆቼ ዙሪያ  ህልም  ፈጠርኩ. እኔ ከእውነተኛ ወላጆቼ ጋር ብሆን ኖሮ የተሻለ ህይወት እንደምኖርና የተሻለ ፍቅር እንደማገኝ አስብ ነበር ስለዚህ ፎቶዎቹን ድንገት ሳገኝ  በጣም አስፈላጊ ከሆነው የሕይወቴ ክፍል ጋር የተገናኘሁ ያህል ተሰማኝ። ፍለጋዬ ግን በቀላሉ እራሴን ጎትቼ ማውጣት ወደማልችልበት ቅርቃር ውስጥ ነው ያስገባኝ -በወላጆቼ ላይ ባለኝ ንዴት አሳዳጊዎቼ ላይ  በማመፅ ስጎዳቸው እንደኖርኩ መገንዘቤ ሌላ ፀፀት ላይ ነው የጣለኝ…››
‹‹ከአሳዳጊዎችህ ጋር ያለህን ግንኑኙነት ለማሻሻልና እንሱን ይቅርታ ለመጠየው እኮ አሁንም ጊዜው አረፈደም… እነሱ ድንቅ ወላጆች ናቸው፣አንተን አሳድገው ለዚህ ደረጃ አብቅተውሀል..ስለዚህ መመስገንና የሚገባቸውን የአንተን ፍቅር ማግኘት ይገባቸዋል፡፡ ›› አለችኝ ቀና አድርጋ ጉንጩን እየዳሰሰች።

‹‹ትክክል ነሽ…እንደዛ ነው የማደርገው…››አላት

‹‹ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ እግዚአብሔር ከእኔ የሚፈልገውን ለማወቅ በመጸለይ ብዙ ጊዜ አሳልፌአለሁ፣ እና አላውቅም። ፀጋን ሊራራላት ወይም ሊወስዳት እንደሆነ አላውቅም። ታገልኩት። በቃ ጠንክሬ ከጸለይኩ፣ ነገሮች በፈለኩት መንገድ ይከሰታሉ ብዬ በማሰብ የምችለውን ሁሉ እያደረኩ ነው…እኛ የሰው ልጆች በወቅቱና በሰዓቱ ማድረግ የምንችለውን ነገር ሁሉ ማድረግነው የሚጠበቅብን …ፀፀትና ቁጭት  ነፍሳችንን የሚያከሳ በሽታ ነው….እንደዛ ይመስለኛል፡፡››

‹‹‹ሙሉ በሙሉ ትክክል ትመስይኛለሽ.››አላትና አቅፎ ጉንጮን ሳማት፡፡ፊቷ ቀላ፡፡
ለተወሰኑ ደቂቃዎች ዝም ተባባሉ፡፡ከዛ እንደምንም አማጠና‹‹ታዲያ ይህን እንዴት እናደርጋለን ራሄል?ማለቴ የእኔና የአንቺ ጉዳይ …በፀጋ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ነው ?››ሲል ስጋቱን ጠየቃት፡፡
በጥንቃቄ ፈገግ  አለችና ‹‹አሁንም በእሷ ላይ ስለሚደርስባት  ነገር እፈራለሁ፣ ምንም እንድትሆንብኝ አልፈልግም… ነገር ግን በዝግታም ቢሆን መልቀቅን እና በእግዚአብሔር እጅ ማስቀመጥን እየተማርኩ ነው። እናቴ ቅድም የተናገረችው ነገር ልቤ ላይ አርፏል፡፡ ፀጋ  ለእኔ ለአንተ ፤ለአባቴ እና ለእናቴ ለሁላችንም  ከእግዜር የተሰጠችን አደራችን ነች፣ከእኛ የሚጠበቀው አብራን እስካለች ድረስ እሷን መንከባከብ፤መጠበቅና ምቾት እንዳይጓደልባት ማድረግ ነው…ሌላውን ለእሱ ለባለቤቱ መተው አለብን…አዎ እንደዛ ማድረግ የሚገባን ይመስለኛል…ወደጥያቄህ ስመለስ የእኔ እና የአንተ ጉዳይ ላይ ምንም ችግር እንደማያመጣ ነው የማስበው፡፡  ››ዔሊያስ በዚህች አስደናቂ ሴት እየተደመመ ፊቷን በጣቶቹ ዳሰሰ። ከዚያም ሳያስበው፣ ጠጋ ብሎ ሳማት። ተጣበቀችበት።

‹‹እዚህ ስላመጣሀኝ ደስ ብሎኛል››አለች ..ወዲያው መልሷ ይስማት ጀመር…ድንገት በሩ ተከፍተ …በድንጋጤ ተለያዩ::
አንድ  ነርስ ነበረች ‹‹ይቅርታ ደ/ር  ፀጋ በጭንቀት ላይ ነች።››ሁለቱም በምን ፍጥነት ተፈትልከው ፀጋ ወደተኛችበት ክፍል  ደደረሱ እነሱም አያውቁትም፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
93👍16
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_ሀያ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

//
ራሄል የእናቷ የቀዘቀዙ  እጆቿን ይዛ በሆስፒታሉ የእንግዳ መቀበያ   ክፍል ውስጥ ባለው የሶፋው ጠርዝ ላይ ተቀምጣለች። ቄሱ  በአጠገባቸው ተቀምጦ፣ መዝሙር 46ን ሲያነብ አቶ ቸርነት ከመግቢያው በራፍ ጋር ቆመው በትካዜ ጎብጠው ይታያሉ፡፡


‹‹ እግዚአብሔር መጠጊያችንና ኃይላችን ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው፥ ስለዚህ ምድር ብትናወጥ ተራሮቸም ወደምድር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም፡፡
።››ራሄል ቃላቷ በተዳከመ እና በዛለ አእምሮዋ ላይ እንዲያርፍ እየሞከረች ነው፡፡

"ቸርነት  ከእኛ ጋር ትቀላቀላለህ?" ቄሱ ጠየቁ።

አቶ ቸርነት  እንደመባነን አሉና  ጭንቅላታቸውን በአውንታ በመነቅነው ወደእነሱ ተንቀሳቀሱ…ከራሔል አጠገብ ተቀመጡ።ቄሱ የአቶ  ቸርነትን እና የወ.ሮ ትርሀስን  እጅ ያዙ፣ ቸርነት ደግሞ የራሄልንን፣ ራሄል የእናቷን  ያዘች፣ ክቡኑ  ዘጉት ።ቄስ   መጸለይ ጀመሩ። እሱ ፈቃዱ ከሆነ ፀጋን እንዲወስድ ሲጸልይ፣ ራሄል ተቃውሞዋን በጮኸች አሰማች።ግን የእናቷ እና የአባቷ እጆች እጆቿን ሲጨምቋት የተከፈተ አፏን መልሳ ዘጋች፡፡ እግዚያብሄር የሚፈልገው ያንን ከሆነ ፀጋን  መልቀቅ እንዳለባት አወቀች፣ሲጨርሱ፣ ወደ ቄሱ   ቀና ብላ ተመለከተች።

‹‹ አመሰግናለሁ…እዚህ መገኘትዎ በጣም አስፈላጊ ነበር.››አለች፡፡

ቄሱ ፈገግ አሉላት እና‹‹እኛ ቤተሰብ ነን ራሄል ..እርስ በርሳችን እንረዳዳለን።››

‹‹አውቃለሁ እናም ለዚህም አመሰግናለሁ.››

ከሶፋው ተነሳች፣ ድንገት እረፍት ማጣት ተሰማት።እህቷን ማየትም ፈልጋለች። ነገር ግን ኤሊያስና  እና ነርሶቹ ትኩረት የሚከፋፍሉ ነገሮች አያስፈልጋቸውም። የአይሲዩ ተከፋች በሮች መስኮቱን እየተመለከተች በሩ አጠገብ ቆመች። ከእነሱ ቀጥሎ አንድ  ነርስ በችኮላ ጋሪ እየገፋች ወደ ፀጋ ክፍል ስትሮጥ ተመለከተች፣ እና ልቧ ወርዶ  የጎድን አጥንቷ ውስጥ የተሰነቀረ መሰላት፡፡ …

‹‹ምን እየሆነ ነው?ጌታ ሆይ እባክህ እሷን ከእኛ ጋር አቆይ… እባክህ…ትንሽ እንንከባከባት። ›› ፀሎቷን ሳታቆርጥ   ወደበሩ ቀረበች ።አንገቷን አስግጋ እና አይኖቾን አጨንቁራ በመስኮቱ ወደውስጥ ለማየት ሞከረች..ነገሮች ጥሩ እየሄዱ እንዳልሆነ ያስታውቃል..ሁሉም ከወዲህ ወዳያ ይሯረሯጣሉ….ሚስኪኗን ፀጋን ከበዋታል…

‹‹ቢ.ፒ. እየወረደ ነው›› አለ ‹‹ፈሳሽ ቦልስ ስጧት.›› ሌላ ማሽን ጠፋ።ሌላ ነርስ ‹‹የኦክስጅን መጠን እየቀነሰ ነው›› .ከማሽነቹ የሚወጣው ሲጥሲጥታ ይሰቀጥጣል….ሁሉም ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ እንደሆነ ነው የሚያወራው…ራሄል በምታየውና በምትሰማው ነገር እራሷን መቆጣጠር አቅቷት ጩኃቷን ስትለቀው በኮሪደሩ አካባቢው የነበሩ ሰዎች  ሁሉ ትኩረት ወደእሷ ዞረ…ሁኔታውን የተረዳች አንድ ነርስ ፈጠን ብላ መጣችና የመስታወቱን መጋረጃ ከውስጥ በመሳብ ዘጋችው፡፡

…በሁሉም ፊት ላይ  ድንጋጤ እና ተስፋ መቁረጥ ነው የሚነበበው…ከኤልያስ በስተቀር ሌሎች ያከተመ ነገር አድርገው በመውሰድ እጃቸውን ሰብስበዋል…እሱ  ወደጆሮዋ ጎንበስ አለና ‹‹የእኔ ቆንጆ መልአክ …ከእኛ ጋር ቆይ። ራሄል ትፈልግሻለች። ሁላችንም እንፈልጋግሻለን።››አላት..እሱ ሊደርግ ሲገባው ያላደረገው ምንም ነገር ስለሌለ  ..አምላክ ጥንካሬ እንዲሰጠው  ጸለየ፣ ጥበብ ለማግኘት ጸለየ እና ይህች ትንሽ ልጅ እንድትቆይ እንዲፈቀድላት ተማጸነ።ከዛም ወደፀጋ ተመለሰና  በደመነፍስ ሚችለውን ነገር ሁሉ መሞከር ጀመረ…ከ10ደቂቃ ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ ትግል በኃላ መቆጣጠሪያ ማሽኖቹ ድንገት የምስራች ማሰማት ጀመሩ….ሁሉም ማመን አልቻሉም…

አንድ ነርስ ‹‹ቢ.ፒ. እየወጣ ነው›› አለች.፣ኤሊያስ ቀና ብሎ ማሽኑን   ተመለከተ፣ ትንሽም ቢሆን ምላሽ የመስጠት ምልክት ማሳየቷ የተስፋ ጭላንጭል በልቡ ፈነጠቀ፡፡

በመቀጠልም ‹‹ የኦክስጅን መጠን እየጨመረ ነው››አለች ነርሷ ።

ሁሉም በደስታ ተሳሳቁ…ፀጋ  አምልጣ እንደነበር ሁሉም ባለሞያዎች ተቀብለው ነበር…ተአምሩን በደስታ በመተቃቀፍ ተቀበሉት… እናም እሷን ቀስ በቀስ  ለማረጋጋት አስፈላጊውን ሁሉ አደረጉ፡፡ዔሊያስ የተረጋጋች መሆኗን በደንብ እስኪያረጋግጥ ጥቂት ጊዜ ቆየ። ከዚያም ለራሔልና ወላጆቿ ሊነግራቸው ወጣ።

ፍፅም በድካም ዝሎ እና መላ ሰውነቱ በላብ ተጠምቆ ነበር…የዛሬው ህክምና በእሱ እውቀት ሳይሆን  በአምላክ ጥበብ  ነው የተሳካው።ምን ተጠቅሞ ምን አድርጎ ከሞት ወደህይወት እንደመለሳት የሪፖርት መዝገቡ ላይ አስታውሶ መፃፍ አይችልም….ብቻ  በመጨረሻ ተቆጣጣሪው እግዚአብሔር  ነበር።ለእሱ ብሎ ሳይሆን ያቺን ሚስኪን ልጅ ተጨማሪ ጊዜ በምድር እንድትኖር ስለፈለገና ለእሷ ሚሆን እቅድ ስላለው ነው..አዎ እንደዛ ነው የገባው፡፡ በኮሪደሩ ላይ ወደ ቤተሰቧ ሲሄድ እያሰበ የነበረው ይሄን ነበር  ፡፡

ራሔል ሲመጣ አይታ ወደእሱ ተንደረደረች… እሱም ወደ እሷ ሮጠ፣

‹‹ደህና ትሆናለች?››

‹‹ጌታ ይመስገን..አስቸጋሪውን ጊዜ አልፈነዋል››

ራሄል ተነፈሰች። ተጠምጥማ አቀፈችው…ከዚያም እንባ አፈሰሰች።ከዛ እህቷን እንድታያት ወደውስጥ ይዞት ገባ ፡፡

የፀጋ  አልጋ ጋር ቆማ ቁልቁል በስስት እያየቻት‹‹ጥሩ ትመስላለች››ስትል በሹክሹክታ ተናገረች። ወላጆቿ ከአንድ ሰአት በፊት ነበር ፀጋ እየተዳከመች ስትሄድ ሞቷን ቁጭ ብለው ላለማየት ወደቤተክርስቲያን ለመፀለይ ተያይዘው የሄዱት፡፡

ራሄል ጸጋ ከኮማዋ እስክትነቃ ድረስ ከአልጋዋ ጎን መነጠል እንደማትፈልግ ተናገረችው..እሱ ግን እንደዛ ማድረግ እንዳማትችልና ለ5 ደቂቃ አይኗን አይታ እንድትረጋጋ ብቻ አስቦ እንደፈቀደላት በትህትና አስረዳት፡፡

ኤሊያስ ከ ጀርባ ቆሞ እጆቹን ትከሻዋ ላይ አደረገ እና ‹‹አሁን ደህና ትሆናለች..አታስቢ ››አለ

‹‹አመሰግናለሁ…አንተ ድንቅ ዶክተር ነህ.››አለችው

‹‹እኔ ዶክተር ብቻ ነኝ…የዳነችው በተአምር ነው›› አለ.

ራሔል ከዔሊ አጠገብ ተነስታ ወደ እኅቷ ቀረበችና  ጎንበስ ብላ ጭንቅላቷን  በስሱ ሳመቻት  ።‹‹ጥሩ እንቅልፍ ተኚ  የእኔ ውድ ››አለች።  ከዚያም ወደ ዔሊ ዞረች።

‹‹እዚህ መቆየት አይቻልም ካልክ… አሁን ለመሄድ ዝግጁ ነኝ.››አለችው…ራሄልን አልፎ ሄዶ የፀጋን  ጉንጭ  በአንድ ጣቱ ነካ።

‹‹ጌታሆይ አመሰግናለሁ››ብሎ በሹክሹክታ አመሰገነ። ከዚያም  አብረው ከክፍሉ ወጡ በኮሪደሩ ላይ ወደ አሳንሰሮች ሄዱ። ሲከፈት ተያይዘው ገቡ፡፡   ድክምክም ብሏታል…ደረቱ ላይ ደገፍ አለችበት፡፡

እጆቹን በደረቷ ዘርግቶ አቀፋትና  ወደታች  ተመለከታት እና ቀስ ብሎ ወደታች ጎንበስ በማለት  ከንፈሯን ሳመ።‹‹ሁሉንም የታካሚዎችህን  ዘመዶች  እንደዚህ ነው የምትስመው?›› ብላ በፈገግታ ጠየቀችው።

‹‹በጣም የሚያስጨንቁኝን እና የምወዳቸውን ብቻ ነው የምስመው››

ራሄል የሚንቀጠቀጡ ጣቶቿን አነሳችና  ጉንጯ  ነካች፣ እይታዋ አሁንም በሱ ተጋርዷል።

‹‹እና እነዚያ ስንት ናቸው?››

‹‹አንድ ብቻ›› አገጮን ቀና አድርጎ  በድጋሜ   ሳማት።መልሳ ሳመችው፡፡

‹‹እወድሀለው  ዶ/ር ኤሊ ። ››

‹‹መቼም ቢሆን እነዚህን ጣፋጭ ቃላት ከአንደበትሽ ታወጪያለሽ ብዬ አስቤ አልውቅም ነበር››በማለት ፈገግ አለና እንደገና ሳማት… እና እንደገና።
47👍8
‹‹እየወጣህ ነው?››ዔሊ በትከሻው አሻግሮ ወደ ኋላ ተመለከተ። ሊፍቱ ቆሞ ነበር እና በሮቹ ክፍት ነበሩ። አንድ ትልቅ ወንድ እና ሴት በዋናው ፎቅ ኮሪደሩ ላይ ቆመው በፈገግታ እየተመለከቷቸው ነበር። ራሄል እራሷን አላቀቀችና   ‹‹ይቅርታ›› ስትል አጉተመተመች።

‹‹ይህ ይቅርታ የሚያስጠይቅ ነገር አይደለም›› አለ ሰውዬው… ሚስቱን መስማማቷን በፈገግታዋ ገለፀች፡፡

ራሄል ሳቀች፣ ከዛ ዔሊን እጁን ይዛ ከአሳንሰሩ አወጣችው። በዝግታ ጎን ለጎን መራመድ ጀመሩ፡፡ግራ መጋባቱን አየችና ‹‹ምን ፈልገህ ነው?›› ብላ  ጠየቀችው።

‹‹ለብቻችን ሆነን በአግባቡ የምንነጋገርበት ቦታ ››

ራሄል እግሩ ላይ ቆማ በፍጥነት እና ጠንክር ያለ ስሞሽ  ሳመችው። ‹‹ኤሊ እወድሃለሁ። እና ማንም ቢያውቅ ወይም ቢያየን  ግድ የለኝም። ለትክክለኛው ነገር ግድ የለኝም እና  ከየት እንደመጣህ ግድ የለኝም። ወዴት እንደምንሄድ ግድ የለኝም ከአንተ ጋር መሆን ብቻ ነው የምፍልገው።››ዔሊ ራሱን በአግራሞት  ነቀነቀ እና እጁን በወገቧ ዙሪያ ጠመዘዘ እና አቀፋት።

‹‹እኔም እንዲሁ። ግን ያለ ተመልካቾች አንዳንድ ተራ ውይይት ማድረግ እመርጣለሁ።››ራሄል ወደ እሱ ተጠግታ ቃተተች።‹‹ የዚያህን  ቃል ድምፅ ወድጄዋለሁ።ታዲያ ወዴት እንሂድ?››

‹‹የወላጆችሽ ቦታስ? ያን ያህል ሩቅ አይደለም››

‹‹ይህ የግል ጉዳያችን አይመስልህም..ለእኛ የሚሆን ድብቅ ቦታ እዛ የምናገኝ ይመስልሀል? ›› አለች ራሄል ፡፡

‹‹እየቀለድሽ ነው? በዚያ ቦታ ቢያንስ 20 ክፍሎች አሉ…።››

‹‹ሀያ አይደለም  …አስራስምንት  ብቻ ነው››ስትል አረመችው፡፡  ‹‹ከእነዚያም አንዳንዶቹ የአገልጋዮች መኖሪያ ናቸው።››ስትል አከለችበት

‹‹ይቅርታ አድርጊልኝ››አለ ኤሊ እየሳቀ። ‹‹ግን  ለመነጋገር  ልንጠቀምበት የምንችለው ጸጥ ያለ ቦታ ከአስራስምንቶቹ  ክፍሎች በአንዱ ውስጥ እንደምናገኝ እርግጠኛ ነኝ።››

‹‹እንደምንችል እገምታለሁ..የራሴ መኝታ ቤት እስከአሁንም ባለበት እንዳለ አትርሳ" አለችው እና እጇን ከእጁ ጋር አቆላልፋ ወደእሷ መኪና ገብታው  ከሆስፒታሉ ወጡ።

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍4217
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

//
ራሄል በወላጆቿ ቤት ከመዋኛ ገንዳ አጠገብ ከእናትና አባቷ ጋር ተቀምጣ የጥዋት ፀሀይ እየሞቀች ነው፡፡

ፀጋ   ‹‹ አበባ ስጪኝ?››ስትል እህቷን ጠየቀች፡፡

ራሄል ከተቀመጠችበት ተነሳችና   የፀሐይ መነፅሯን ወደ ጭንቅላቷ ገፋ በማድረግ   እህቷ የፈለገችውን  አበባ ቀነጠሰችና በትናንሽ እጆቾ ውስጥ አስቀመጠችላት…ፀጋ በደስታ ፈነጠዘች፡፡
ሮቤል እና አዲሷ ረዳት የፋውንዴሽኑን ስራ ከአሰበችው በላይ  በጥሩ ብቃት እየመሩላት እንደሆነ ለሁለት ቀን ወደቢሮ ተመልሳ ባደረገችው የስራ ግምገማ መረዳት ችላለች፡፡
…እህቷን ለማስታመም በሆስፒታል ባሳለፈቻቸው አስር ቀናት ውስጥ ምንም የጎደለ እና ሳይሰራ የተወዘፈ ስራ አልነበረም…እና አሁንም ለሌላ አንድ ሰምንት ታናሽ እህቷ በደንብ እስክታገግም አብራት እንድትሆንና ቀለል ያሉ  ስራዎችን እዛው እቤት ሆና እንድትሰራ ፈቅደውላት እሷም ተስማምታ  ወላጇቾ ቤት ነው ያለችው፡፡

‹‹ኤሊ እመጣለሁ ያለው መቼ ነው?››ወ.ሮ ትርሀስ  መጽሃፏቸውን  ከጎኗቸው  ባለ የመስታወት ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠው ራሄልን  ጠየቋት።

‹‹ከሶስት እስከ  አራት ሰዓት እመጣለሁ ነበር ያለው ፡፡ ››መለሰች…ጸጋ  ራሷ ቀጥፋ የሰጠቻትን አበባ  ፀጉሯ መካከል ሻጠችላት…ራሄል  በፈገግታ እህቷን ወደራሷ ሳበችና ጉንጮን በመሳም‹‹ትንሿ እህቴ ..እንዲህ ስላሳመርሺኝ አመሰግናለው››አለቻት፡፡
በዛው ቅፅበት ወደግዙፉ ግቢ እየቀረበ የሚመጣ የመኪና ድምፅ ተሰማ ፡፡

‹‹የምትጠብቂው ጓደኛሽ  አለ እንዴ?››አቶ ቸርነት ጠየቁ፡፡

‹‹ አይ አይመስለኝም?››ራሄል እርግጠኛ ባለመሆን ጠየቀች፡፡

‹‹እንግዲያው አለም መጥታ ማንነቱን እስክታሳውቀን እንጠብቅ  ?››በማለት እናቷ ሳቁ።

አለም ወዲያው እየተፍለቀለቀች መጣች…‹‹ራሄል  ነይ እንግዳሽን ተቀበይ››

‹‹ማን ነው?››

‹‹አትንገሪያት ተብያለው…እራስሽ መጥተሸ እይው››አለችና ወደኪችኗ ተመለሰች፡፡

ራሄል.‹‹ማነው በወላጆቼ ቤት ከእኔ ጋር እንዲህ አይነት ጫወታ ለመጫወት የደፈረው?››በማለት ተነስታ ፀጋን ይዛ   ሄደች።ራሄል እና ፀጋ  ወደ ግቢው የመኪና ማቆሚያ አካባቢ ሲሄዴ ኤሊ ወደ ውስጥ ሲገባ ተመለከቱት  ።ራሄል እንዳየችው  በውስጧ የደስታ ማዕበል አጥለቀለቃት።

ባለመኪና ስትጠብቅ ባለሞተር ሰው በማየቷ ተደንቃ ‹‹ሄይ፣ እንዴት እዚህ ደረስክ? የሞተር ሳይክልህን ድምፅ አልሰማሁም።››አለችው…

ዔሊ ጎንበስ ብሎ በቀስታ ሳማት እና ፀጋን አንስቶ ካቀፋት በኃላ‹‹ሌላ አይነት  የመጓጓዣ ዘዴ ነው የተጠቀምኩት.››ሲል መለሰላት፡፡

‹‹ሞተርህ ተበላሸች እንዴ ?›› አለችና አይኖቾን ወደመኪና ማቆሚያ አዞረች  ከእሷ   ቀይ መኪና  አጠገብ የቆመ ባለ ሰማያዊ ቀለም  መኪና እያየች ግራ ተገባች።

‹‹ ያን መኪና  ከማን ነው የተዋሰከው? ወንድምህ እንደዚህ አይነት መኪና የለውም።››

ዔሊ ተነፈሰ። ‹‹እነሆ፣ ወ.ሮ ራሄል  ሞተሬን ሸጥኩት።››

ራሄል መኪናዋን በድጋሜ  ተመለከተች፣ ‹‹ሞተር ሳይክልህን አስወገድከው !አየህ እኔ ስለ አንተ የምወደው ያን  ነው ። ቆንጆ እና ፈጣን ተማሪ ነህ….ግን ለምን?››

…‹‹ደህና፣ በአንድ ወቅት አንድ ሰው እንዴት አንድ ኃላፊነት የሚሰማው ለዛውም የህፃናት ሀኪም የሆነ ሰው ሞተር ሳይክል ይነዳል ? የሚል  ጥያቄ ጠየቀኝ። እና ለእሱ መልስ ለመስጠት ብዬ ነው መኪና የገዛሁት፡፡››

ራሄል ወደ መኪናው ሄዳ እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ  ትንሽ ነካችው፣ ከዚያም ወደ ዔሊ ተመለሰች፣ ››

‹‹አስደንቀኸኛል ››አለችው

‹‹ስለሞተር ሳይክሎች ያለሽን ስሜት ስለማውቅ  እናም የፍራቻሽም ምክንያት በከፊል ትክክል መሆኑን ስላመንኩበት  ነው...››

እዛው የሳሎኑ በረንዳ ላይ ካሉ ወንበሮች አንዱን እንዲቀመጥ ሳበችለት ፀጋን በክንዱ እንዳቀፈ ተቀመጠ….ከጎኑ ሌላ ወንበር ስባ ተቀመጠች፡፡

ከዛ ሳታስበውና ምንም ሳትዘጋጅበት ትልቅ  ቁም ነገር ከአንደበቱ አፈትልኮ ወጣ  ‹‹ይህን ሁሉ  በትክክለኛው መንገድ ይፋ   ማድረግ ፈልጌ ነው …ራሄል፣ ላገባሽ እፈልጋለሁ።››አላት፡፡

ጆሮዎቾን ማመን አልቻለችም…ልቧን  ደረቷን ሰንጥቆ እንዳይወጣ የፈራች ይመስል ደግፋ ያዘችው ። በውስጧ የሚንተከተከው ደስታ እና ፍቅር እና ምስጋና መውጫ ለማግኘት እየሞከሩ በአንደበቷ ላይ ተንገዋለሉ….ማልቀስ ብቻ ነው የቻለችው፡፡

‹‹ሄይ እኔ ያን ያህል መጥፎ ነገር አልተናገርኩም….ለምን ታለቅሻለሽ?››

‹‹በጣም ደስ ብሎኝ ነው…..››ስትል በለሆሳሳ መለሰችለት፡፡‹‹እወድሀለሁ ኤሊ›› ወደ እሱ ተሳበችና ጉንጩን ሳመችው..ታፋው  ላይ የተቀመጠችው ፀጋ  በደስታ እጆቿን እያጨበጨበች በሳቅ ተንከተከተች። የእሷ ሳቅና ደስታ ወደ እነሱም ተጋባ፡፡

‹‹መጀመሪያ ዝም ብዬ ለአንቺ ምንም ሳልነገርሽ ወደቤተሰቦችሽ ሽማግሌ ለመላክ አቅጄነበር …››

‹‹እንዴ የእኔን ሀሳብ ሳታውቅ ሽማግሌ ልከህ እምቢ ብልህስ?››

‹‹ያው ምን አደርጋለው የተሰበረ ልቤን  ይዤ  የብቸኝነት ኑሮዬን ቀጥላለዋ !!››ብሎ ትከሻውን ነቀነቀ።ራሄል ጣቷን ከንፈሩ ላይ አድርጋ ሳቀች።

‹‹ ስለነርከኝ ደስ ብሎኛል፣ደግሞ ስትነግረኝ  ፀጋ በመሀከላችን መገኘት በመቻሏ  ደስታዋ ድርብ  ሆኗል … ለነገሩ እኛን አንድ ያደረገች እሷ ነበረች.››

‹‹እሺ ስላልሽኝ ደስ ብሎኛል…:በዚህ ምክንያት በህይወቴ ለሆነው ነገር እግዚአብሔርን በየቀኑ አመሰግነዋለሁ:: በአንቺ ምክንያት ህይወቴ መሉ ሆኗል››

‹‹አንተ ስጦታዬ ነህ ኤሊ ›› አለችና አቀፈችው።

‹‹አሁን እናትና አባትሽን እንፈልግ።››

ተስማሙና …ተያይዘው በአረንጓዴ ተክሎች ወደተሸፈነው ግዙፉ ጊቢ  ተያይዘው እየተሳሰቁ ሄዱ፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
84👍18
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

////
ዶ/ር ኤልያስ ዛሬ ምን አልባትም በህይወቱ ፍፁም የሆነ ደስታ የተሰደሰተበት ቀን ስለሆነ ስሜቱን መቆጣጠር አቅቷት ጥንቅቅ ብሎ ባለቀ ውብ ቤቱ ውስጥ ከክፍል ክፍል እየተመላለሰ  እንደህፃን እየቧረቀ ነው፡፡ስልኩን አነሳና ደወለ…፡፡ከአራት ጥሪ በኃላ ተነሳ፡፡

‹‹ውድ ባለቤቴ እንዴት አለሽልኝ››

‹‹አንተ ያንን ቃል መጠቀም የምትችለው እኮ ሰማንያ ፈርመህ ቤትህ ስታስገባኝ ነው››አለችው እየሳቀች፡፡፡

‹‹ያው በይው..ዜናውን አልሰማሽም እንዴ…..?ሽማግሌዎቼ እኮ ወላጆችሽ ልጃቸውን ሊሰጡኝ በደስታ መስማማታቸውን አሁን ነግረውኝ በደስታ እያበድኩ ነው፡፡››

‹‹ከአንተ ቀድሜ ሰማሁ…ምነው ይከለክሉኛል ብለህ አስበህ ነበር እንዴ?››

‹‹እንዴ ምን ይታወቃል…..ምን አልባት ቅድሞ እደጅ እየጠና ያለ  ብረት መዝጊያ አማች ኖሮ ሀሳባቸው ወደእሱ ቢያጋድልስ?››

‹‹እሱስ እውነትህን ነው …ለአሁኑ ግን ተርፈሀል››

‹‹እኔም መትረፍ የምፈልገው ለአሁኑ  ብቻ ነው…የማገባው አንዴ ብቻ እኮ ነው…››ተሳሳቁ፡፡

‹‹እና ይሄንን ደስታ አብረን ማክበር የለብንም ትያለሽ…?››

‹‹አንተ ..ከአሁን ወዲህ እኮ እስከሰርጌ ቀን ድረስ ልታየኝ አይገባም…››

‹‹እንደዛ ከሆነማ ሰርጉን ነገውኑ ደግስ በይኛ››

‹‹አዎ ..ያን ያህል ከቸኮልክ አድርገው››
‹‹እሺ..አስበብበታለው..እውነት ግን በጣም ላገኝሽ ፈልጌለሁ…››

እሷም ከአንደበቷ አውጥታ አትናረው እንጂ በጣም ልታገኘው ፈልጋለች፡፡‹‹ ይቻላል..የትና መቼ?፡፡››

‹‹ምሳ ልጋብዝሽ …ሰባት ሰዓት ስካይ ላይት እንገናኝ፡፡››

‹‹ሰባት ሰዓት ..አሁን እኮ አራት ተኩል ሆኖል…..ለመዘጋጃጀት በቂ ጊዜ አይኖረኝም፡፡››

‹‹አንቺ ደግሞ..እንደውም ምንም መዘገጃጀት አያስፈልግሽም… እዛ ሆስፒታል በነበርሽበት ጊዜ ያለምንም ዝግጅት ምን እንደምትመስዬ እኮ አውቃለው…ለእኔ ብለሽ ለመቆነጃጀት ከሁለት ሰዓት በላይ ማጥፋት የለብሽም…ከዛሬ ወዲህ ባልሽ ነኝ፡፡ማለቴ ለጊዜው እጮኛሽ ነኝ..ግን ለጥቂት ጊዜ ብቻ ነው፡፡››

‹‹‹ይሁንልህ እሺ…..ግን  ቅር ካላለህ አንድነገር ልጠይቅህ ››

‹‹ምን ጠይቂኝ››

‹‹ጸጋን ይዣት ብመጣ ቅር ይልሀል?››

‹‹አረ በፍፅም   ..እንደውም በተቃራኒው ደስ ነው የሚለኝ …እሷ ከመጀመሪያው ጀምሮ የፍቅራችን ብቸኛ ምስክር ነበረች..ዛሬ መገኘት ይገባታል….ጫጉላ ቀናችን ላይ አብራን ወደመኝታ ትግባ እንዳትይ እንጂ ለዛሬው ደስ ይለኛል››

ስለጫጉላ ሲያወራ እፍረትም ሙቀትም ተሰማት‹‹አንተ ምን እያልክ ነው..?በል ቸው››ብላ ስልኩን ዘጋች፡፡

እሱም ወዲያው ወደሻወር ቤት ገባና ሰውነቱን በፍጥነት ተለቃለቀ…ከዛ ፂሙን ላጨ…ሙሉ ሱፍ ለበሰና ዝንጥ አለ…፡፡ለመውጣት ዝግጁ ሆነ…፡፡ሰዓቱን ሲያይ 5 .ከሩብ ይላል….ከራሄልና ከፀጋ ጋር ወደሚገናኝበት  ቀጠሮ ከመሄዱ በፊት ማግኘት የሚገባው አንድ ሰው አለ…ከአመት በፊት በሆስፒታል አብራው ትሰራ የነበረች የህጻናት ሀኪም ነች ትናንትና ደውላ ላገኝህ እፍልጋለው ያለችው፡፡ለዚህች ዶ/ር የስራ ባለደረባው ነበር…ያለፈውን አንድ አመት ተጨማሪ ትምህርት እድል አግኝታ ኖሩዌይ ነበር ያሳለፈችው፡፡አሁንም ለሁለት ሰምንት ረፍት እንደመጣች እና መመለሻዋ እንደደረሰ እናም ከመሄዶ በፊት አንድ እቃ ልትሰጠው እንደምትፈልግ ነግራው ነው እግረመንገዱን ሊያገኛት የወሰነው፡፡

ሀያ ሁለት ነበር ቀጠሮቸው…እሷም ቸኩላ ስነበረ ቀጥታ ወደጉዳዩ ነበር የገባችው፡፡አንድ የታጠፈ ነጭ ፖስታ አውጥታ እጁ ላይ አደረገች፡፡ግራ ገብቶትም ደንግጦም‹‹ምንድነው ሲል?››ጠየቃት፡፡

‹‹ትዝ ይልሀል ከመሄዴ በፊት አብረን የምንከታተላት አንድ ታማሚ ልጅ ነበረች…እናቷ ከአንተ ጋር ትግባባለች…እንደውም የልጅነት ጓደኛዬ ነበረች ብለሀኛል››

‹‹ኦኬ ትክክል ነሽ..ስለፀጋ ነው…ማለቴ የዛን ጊዜ ስሟ ትሁት ነበር..ስለእሷ ነው የምታወሪው››

‹‹አዎ ስለእሷ ነው…ለመሆኑ እንዴት ነች…?አሁንም በህይወት አለች?››

‹‹አዎ በጣም ጥሩ ሁኔታ ላይ ነች…ግን ፖስታው ምን እንደሆነ አልገባኝም››

‹‹ፖስታውማ እናትዬው እዛ ሆስፒታል ውስጥ ህጻኗን ጥላ ከመሄዶ በፊት ይህንን ፖስታ ለአንተ እንድሰጥ አደራ ብላ ሰጥታኝ ..ነበር….እርግጥ በወቅቱ ልጇን ጥላ እንደምትሄድ አልገመትኩም እና እሺ ብዬ ተቀበልኮት….ግን በዛው ሰሞን አንተም ለሆነ ስራ ወደክፍለሀገር ወጥተህ ነበር..እኔም  ውጭ ለመሄድ በጣም እየተዋከብኩ ስለነበረ  እቤቴ ወስጄ እንደቀልድ እንዳስቀመጥኩት እረሳሁት እና ሳልሰጥህ ሄድኩ ..በቀደም ነው የድሮ ወረቀቶቼን ሳስተካክል ድንገት አገኘሁት..አድራሻውን ሳነብ ትዝ አለኝ….መጀመሪያ አፍሬ እንደተረሳ ልተወው ነበር›..በኃላ ሳስበው ግን ምን አልባት በጣም አስፈላጊ ነገር ቢሆንስ ብዬ…አይኔን በጨው አጥቤ አግኝቼ ልሰጥህ ወሰንኩ….ይቅርታ እሺ››

‹‹አረ ችግር ለውም…ያው ልጄን አደራ..ተከታተላት ምናምን የሚል መልዕክት ነው የሚሆነው….ያንን ደግሞ እሷ ባትለኝም አደርገዋለው››በማለት ፖስታውን ኪሱ ውስጥ ከተተና  ከእሷ ተሰናብቶ  መኪናው ወደ እስካይ ላይት አዞረ፡፡

ከቀጠሯቸው 10 ደቂቃ ቀድሞ ነበር የደረሰው፡፡ ወንበር ይዞ በጉጉት ይጠብቃቸው ጀመር..፡፡ድንገት ፖስታው ትዝ አለው፡፡ አወጣና አየው…፡፡ከጀርባው  ለማከበርህ ደ/ር ኤልያስ ከፅጌረዳ ይላል፡፡
እነ ራሄል እስኪመጡ ቀዶ ሊያነበው ፈለገ…መቅደድ ከመጀመሩ በፊት ፖስታውን ጠራጴዛው ላይ አስቀምጦ  ስልኩን ከኪሱ አወጣና ተመለከተው…ራሄል ነች፡፡አነሳው፡፡

‹‹እሺ የእኔ ፍቅር››

‹‹ቀድመንህ ደርሰናል መሰለኝ››

‹‹አረ እንዴት ተደርጎ…››አለና ያለበትን ቦታ ነገራቸውና እስኪያዩት ቆሞ ጠበቃቸው…. ራሄልን ሲያያት ልቡ ትርክክ አለ….ወደፊት ተራምዶ  ፀጋን ከእቅፏ ተቀበለና..ጉንጭ ለጉንጭ ተሳሳሙ…. ወደ ጠረጴዛቸው ሄደው ተቀመጡ….ምሳ ታዘዘ እና እስኪመጣ ሞቅ ያለጫወታ ጀመሩ…..ራሄል ድንገት ፊት ለፊቷ የተቀመጠ ፖስታ አየችና በመገረም አነሳችና አየችው…፡፡

‹‹ፅጌረዳ ማን ነች?››ኮስተርተር አለች፡፡

‹‹ቀናሽ እንዴ?››

‹‹በኢንተርኔት ዘመን ፖስታ በምትልክልህ ሴት እንዴት ብዬ ነው የምቀናው?››

‹‹በፖስታው አድራሻ ላይ የተጠቀሰችው ፅጌረዳ ማለት የፀጋ እናት እንደሆነችና ፖስታው ከተፃፈ ከአመት በኃላ እንዴት እንዳገኘው… በእንግሊዘኛ ነገራት››ይሄንን  ያደረገው ፀጋ ፊት ስለእናቷ በምትሰማው ቋንቋ ለማውራት ስላልደፈረ ነው፡፡

‹‹እና..አልተከፈተም እኮ››

‹‹አዎ…አሁን ስለፀጋ እኔን ብቻ ሳይሆን አንቺንም ስለሚመለከት አብረን እናነበዋለን››

‹‹እርግጠኛ ነህ?››

‹‹ አዎ እርግጠኛ ነኝ››

‹‹እና እናንብበዋ››ብላ ልትቀደው ስትዘጋጅ፡፡

‹‹አይ …ይሄንን ጊዜያችንማ ለሌላ ጉዳይ አንጠቀምበትም…››ብሎ ፖስታውን ከእጇ ተቀበለና ከጎኗ ካለው ወንበር ላይ የተቀመጠው የራሷ ቦርሳ ውስጥ ከተተው፡፡

‹‹በቃ አንቺ ጋር ይሁንና ..ሰሞኑን አንድ ላይ ሆነን እናነበዋለን፡፡››ተስማማች…ምሳ ቀረበላቸው በሉ…ከዛ ወጥተው ወደአለም ሲኒማ ጎራ አሉና ፊልም አዩ….አሪፍና ጣፋጭ ቀን አሳለፉ….
41👍3👏1
ራሄል ደስ የሚል ቀን ብታሳልፍም ድክም ብሎታል…ገና ሁለት ሰዓት ሳይሆን ነው መተኛት እንደምትፈልግ ለወላጆቾ ተናግራና እነሱን ተሰናብታ ወደመኝታ ክፍሏ የገባቸው…የለሊት ልብሷን ቀይራ ለመተኛት አልጋዋ ላይ ከወጣች በኃላ ….የፀጋ እናት ፃፈች ተባለው ደብዳቤ ትዝ አላት….፡፡ለምን እንደሆነ ባታውቅም ውስጡ ያለውን ደብዳቤ ማንበብ ፈልጋለች….ግን ኤልያስ አብረን እናነበዋለን ነው ያለው..እራሷን ገሰጸች እና ተኛች፡፡እንቅልፍ ሊወስዳት  ግን አልቻለችም…መልሳ ተነሳችና ከአልጋው ወርዳ   ከቦርሳዋ ውስጥ ያለውን ፖስታ አወጣችና ወደአልጋዋ ተመለሰች….ቀደደችውና ውስጡ ያለውን ደብዳቤ አወጣችው…ማንበብ ጀመረች፡፡.

ኤሊ ይሄንን ደብዳቤ ለመጻፍ ለበርካታ ቀናት ከራሴ ጋር ስሟገት  ነበር..ብዙ ቀን መፃፍ ጀምሬ ወረቀቱን ቀድጄ ጥያለው…በመጨረሻ ግን ለልጄ ስል ማድረግ እንዳለብኝ ውስጤ ስላመነ አድርጌዋለው፡፡

ኤሊ አንተ የልጅነት የሰፈር ጎደኛዬ ነህ…በጣም እወድሀለው…እርግጥ አውቃለው አንተም በጣም ትወደኛለህ..የእኔ ግን ከዛ ያለፈ ነው..አፈቅርህ ነበር…ሀይስኩል እያለን ህልሜ ወደፊት አንተን ማግባት ነበር…ከአንተ ልጅ መውለድ ነበር…አውቃለው ለአንተ ጓደኛህ ብቻ ነኝ….በእኔ ልብ ውስጥ ያለው መዝሙር ግን ሌላ ነበር….እና ምን ሆነ አንተ አሪፍ ውጤት አምጥተህ ዩኒቨርሲቲ ስትገባ እኔ ወድቄ ሰፈር ቀረሁ..እንደዛም ሆኖ በአንተ ደስተኛ ነበርኩ…እሱ ለሁለታችንም ይበቃል አልኩ…በአንተ ዲግሪ እኔ የራሴን ወደፊት ኑሮ አቀድኩ….ከአንተ ጋር የምሰራውን ቤት አለምኩ…ግን ህይወት ወራጅ ወንዝ ብቻ ሳትሆን ደራሽ ጎርፍ ጭምር ነችና…ሳላስበው ካልሆኑ ልጆች ጋር ገጠምኩ..ድህነቴና የቤተሰቦቼ የገንዘብ አቅም ደካማነት አንዳንድ ያልሆኑ ስራዎችን እንድሰራ አስገደደኝ..

አንተ ዶክተር ሆነህ ተመርቀህ ስትመጣ እኔ የሶስት አመት የሽርሙጥና ልምድ ነበረኝ..ያ ደግሞ በድብቅ ሳደርገው የቆየሁት ሳይሆን ሀገር ዘመድ ያንተም ቤተሰቦች ጭምር የሚያውቁት መራር ሀቅ ነበር፡፡እና በዛ ቆይታ ስለአንተ ያለኝን ህልም ገድዬው ነበር….እና ተመርቀህ መጣህ…በጣም ደስ አለኝ..የቁጭት እንባ አለቀስኩ…፡፡ አረሳሀኝም..አልተጠየፍከኝም…ቤታችሁ በተዘጋጀ የምረቃት ዝግጅት ላይ አፈላልገህ የምሰራበት ብና-ቤት ድረስ መጥተህ ጋበዝከኝ፡፡ለአንተ ስል የሰፈር ሰዎችን አይን ..ችዬ የቤተሰቦችህን ምን ይሉኛል እያልኩ እየተሸማቀቅኩ መጣሁ..ጥሩና ደስ የሚል ዝግጅት ነበር፡፡

ራሄል የምታነበውን ነገር ማመን አልቻለችም…..በጣም አጎጊና አስፈሪ ሆነባት….ማንበቧን ቀጠለች፡፡

…ከዛ መደዋወል አልፎ አልፎ መገናኘትም ጀመርን፡፡ትዝ ይልሀል ስራ ከያዝክ  ከሁለት አመት በኃላ ሚዜ የሆንክበት የዶ/ር  ሰለሞን ሰርግ ላይ ጋበዝከኝ….ደስ አለኝና መጣሁ…አሪፍ ሰርግ ነበር..አንተም በጣም ደስ ብሎህ ነበር…ያለወትሮህ በጣም ጥተህ ነበር… እኩለ ሊሊት ላይ ከሰርጉ ቤት ደግፌህ ተያይዘን ወጣን…ሆቴል አልጋ ያዝኩልህና እንድታርፍ አድርጌ ወደቤቴ ልሄድ ስል ትንሽ አጣጪን አልከኝ..ተው ይበቃሀል ብልህም አልሰማሀኝም..እንደውም ሶፋ ላይ ተኛለው አንቺ አልጋው ላይ ትተኚያለሽ…በለሊት ወዴትም አትሄጂም አልከኝ፡፡ከዛ ተስማማውና እዛው እልጋ ክፍል ውስጥ መጠጥ አዘን መጠጣት ጀመርን…ፈርቼ ነበር…ለእኔ ሳይሆን ለአንተ ነበር የፈራሁት…ከዛ    እንዴት እንደሆነ አላውቅም መሳሳም ጀመርን… ሁሉም ነገር ሆነ   …ካዛ በኃላ ነፍስህን አታውቅም ነበር…በውድቅት ለሊት ቁጭ ብዬ አሰብኩ…ጥዋት የተፈጠረውን ስታውቅ በጣም እንደምትበሳጭ አሰብኩ..ሁለተኛ ስሬ እንዳትደርሺ እንደምትለኝ እርግጠኛ ሆንኩ…ሳልመው የኖርኩትን ፍቅርህን ማግኘት ባልችልም ጓደኛነትህን ማጣት  እንደሌለብኝ  ወሰንኩ፡፡

ሁሉን ነገር አፀዳደው..ያወለቅከውን ፓንትና ሱሪህን በየተራ እንደምንም ብዬ መልሼ አደረኩልህ…ቀበቶህን ሳይቀር አሰርኩልህ፡፡ከዛ በስነ-ስርአት አልጋው ላይ አስተኛውህ… የራሴንም ልብስ ሙሉ በሙሉ ለብሼ አልጋ ልብሱን ተከናንቤ ሶፋ ላይ በመተኛት ስጨነቅና ስፀልይ ነጋ….ጥዋት ስትነቃ አይን አይንህን ሳይ ነበር…እግዜር የተመሰገነ ይሁን አንተ ምን እንደተፈጠረ አላወቅክም..ምንም የተቀየረ ነገር አልነበረም..ከዛ ጓደኝነታችን እንደነበረ ቀጠለ፡፡ደስ አለኝ…ከሁለት ወር በኃላ ሌላ መዘዝ መጣብኝ ..ማርገዜን አወቅኩ..ምን ላድርግ ..ከአንተ ጋር መተኛት  ለአንት ማርገዝ ለእኔ የልጅነት ህልሜ ነበር እናም መደስት ነበረብኝ..ግን በዚህ አይነት ሁኔታ ላይ እያለው የሚሆን እንዳልሆነ  አውቃለው…አንተ ለእኔ አዝነህ ልጅቷን ብትቀበል እንኳን ወላጆችህ ምን ይሉሀል….?ቤተሰቦችህ ምን ያህል ሀይማኖተኛ  እና የተከበሩ ሰዎች እንደሆኑ አውቃለው..በአንተ ምን ያህል እንደሚኮሩብህ በደንብ አውቃለው…እና አንተ በማታውቀው ጉዳይ እንዴት እንዲያዝኑብህ ላድርግ…?ወሰንኩ…ትሁትን ላስወርዳት ወሰንኩ፡፡ብዙ መድሀኒት ተጋትኩ..እሷ ግን ጠንካራ ታጋይ ነበረች..አልወጣም አለች…በመጨረሻ የራሱ ጉዳይ ብዬ ተውኳት.. ተወለደች.. በእርግዝናዬ ወቅትም ሆነ ከወለድኩ በኃላ ከጎኔ ነበርክ…አባቷን ብዙ ጊዜ ጠይቀሀኝ ዋሽቼህ ነበር…እና እስከመጨረሻውም ላልነግርህ ነበር እቅዴ፡፡ ግን…ከስድስተ ወሯት በኃላ ታመመች… ሙሉ በሙሉ ሆስፒታል ገባች…ሳያት  ህመሟ ቀጣይነት ያለውና ምናልባትም የእድሜ ልኳ እንደሆነ ተረዳው…እኔ ጋር ብትሆን ምን ላደርግላት እችላለው? ..እንዴት ልንከባከባትና እንዴት ላሳክማት እችላለሁ..?አሰብኩ..ከዛ ለአንተ እወነቱን ለመናገር ወሰንኩ፣ግን ያው ፊት ለፊትህ ተቀምጬ አይኖችህን እያየው ይሄንን ዜና ልነግርህ አልችልም..ያለኝ ምርጫ ይሄንን ደብዳቤ ፅፌ እኔ ከአካባቢው ከተሰወርኩ በኃላ እንዲደርስህ ማድረግ ነው፡፡

አንተ የትሁት አባት ነህ…ከፈለክ ዲ.ኤን.ኤ ማስመርመር ትችልህ..እኔ ማንም ሊያገኘኝ ወደማይችለው ቦታ ሄጄያለው ..ማለት ከሀገር ውጭ ነው ሄድኩት..መቼም አልመለስም….ልጅህን ወላጆችህን በሆነ መንገድ አሳምነህ ለእነሱ ብትሰጣቸው ደስ ይለኛል..እነሱ ልጅን ለማሳደግ ፍላጎቱም ፍቅሩም፣፣ ብሩም አላቸው…ብቻ የራስህ ልጅ ነች…በፈለከው መንገድ አሳድጋት፡፡
ጽጌረዳ ነኝ…..እስከመጨረሻው ደህና ሁንልኝ፡፡

ራሄል ወረቀቱን ጨመደደች ከእሷ አርቃ ወረወረችው….ከአልጋዋ ወረደችና የወለል ምንጣፉ ላይ እየተንከባለለች እስኪደክማት አለቀሰች…‹‹እሺ አሁን ምድነው የማደርገው?››እራሷን ጠየቀች፡፡‹‹‹ኤልያስ ይሄ ደብዳቤ ሲደርሰው ምንድነው የሚሆነው?››የዚህን መልስ መገመት አልቻለችም፡፡ለመረጋጋት እና ወደአልጋዋ ለመመለስ ከሁለት ሰዓት በላይ ነው የወሰደባት፡፡ ካዛ እስከንጊቱ አስራ አንድ ሰዓት ድረስ ስትገለባበጥና ስታስብ ነበር ያሰበችው፡፡ መጨረሻ የነገሩን ጥሩ ጎን ማየት ቻለች..በተለይ ለፀጋ አባት ማግኘቷ ደስ አላት..ኤልያስ አባቷ ሆነ ማለት ደግሞ እሷም እናቷ ሆነች ማለት ነው፡፡ይሄን ስታስብ ውስጧ ደስ ሚል ስሜት ወረራት፡፡
ግን ኤልያስስ ዜናውን በእንደዚህ አይነት መንገድ ይቀበለዋል…በእፍረት አንገቱን ደፍቶ ቢጠፋባትስ …?‹‹አልመጥንሽም…ጋብቻው ይቅር ቢላትስ?››ስቅጥጥ አላት..ደግሞ ኤልያስ ምን ያህል ስሜታዊ ሰው እንደሆነ ስለምታውቅ አያደርገውም ብላ በእርግጠኝነት ልትተማመንበት አልቻለችም…እና አንድ ውሳኔ ወሰነች፡፡
39
አንደኛ ሰርጋቸውን ከሁለት ወር ባነሰ ጊዜ እንዲደረግ ማድረግ፡፡ሁለተኛ  ደግሞ ሰርጋቸው ተደግሶ ባል እና ሚስት ተብለው አንድ ቤት ተጠቃለው እስኪገቡ ድረስ ይሄንን ፀጋ ልጁ እንደሆነች የሚገልፀውን ደብዳቤ እንዳያገኘው ማድረግ፡፡
እነዚህን ውሳኔዎች ከወሰነች በኃላ ነው የተወሰነ መረጋጋት ስለተሰማት እንቅልፍ የወሰዳት፡፡

ተፈፀመ

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
35👍10🤔5
#የፀሎት_ፉክክር
.
ለረጅም ዘመናት
እግዚአብሔር ይስጥልኝ እየተባለበት፤
በእያንዳንዱ ሠው አፍ እግዜር ዕዳ አለበት፤
እያሉ ሠምቼ
ይኸው መጥቻለሁ
እሱ ይስጥህ እያሉ ሲልኩኝ ወዳንተ፤
በል እግዜር መፅውተኝ
ምሰፍርበት አጣሁ
ምድሩን ዘር ዘርተውት
እንኳን ለኔ ቀርቶ ቦታ የለም ላንተ፤
.
ብዛ ተባዛባት
ምድሪቱንም ሙላት ብለህ ስትልከኝ፤
ምን አስበህ ይሆን?
እንደሚታነቅ ሰው ባዶ ኪስ የላክከኝ?፤
.
ፍቃድ ትዕዛዝህን
ላከብር ልበዛ ኑሮ ልጀምር ስል፤
እንዳልከው አልሆነም
አብስትራክት ሆኗል የዚህች ምድር ምስል፤
.
ፈጣሪ ሆይ ፍረድ!
በደላቸው በዛ ትዕግስትህን አይተው፤
የገዛ መሬትህን
እየሸጡልኝ ነው በስንዝር ለክተው፤
.
ወይ ምድርህን ስጠኝ
ወይ ስንዝሩን ቀማ፤
መሬቴን ብቻ ሆኗል
የዚህች ምድር ዜማ፤
እኔ አላማረኝም
መሬትህን ውሰድ በሠው ሳትቀማ፤

🔘ልዑል ሐይሌ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍2112
#እናትነት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

//////

የእኔ ቅንዝርነት የልጅቷ ድህነት፤እናትነት እና ተስፋ ቢስነት

ስሟ ግን ማን ነበር?

ምን አይነት ችግር ላይ እንዳለሁ ልትገምቱ አትችሉም፡፡  ሀገር አማን ነው ብዬ በእንቅልፍ ዓለም ከተዋጥኩ በኋላ በእኩለ ለሊት ላይ ለመንገድ  መብራት ማቆሚያ እደተተከለ  የእንጨት ምሰሶ ቀጥ ይላል፡፡ ቀጥ ማለቱ ብቻ አይደለም እኮ የሚያበሳጨኝ ቀጥ በማለቱ ውስጥ ጥዝጣዜ ነገር አለው፡፡ የመነዝነዝ ዓይነት እና  ለመግለፅ የሚያስቸግር ግራ አጋቢ ህመም ከእቅልፍ እስከማባበነን ድረስ የሚደርስ ኃይል ያለው ህመም ፡፡እስከአሁን ስለምን እንደማወራችሁ አልገባችሁም አይደል?

እንጠራራ እና ከእንቅልፌ ጋር እየታገልኩ ዓይኔን እያሻሸው በዳበሳ ወደ ሽንት ቤት ሄዳለው… ምን አልባት ሽንቴ ወጥሮኝ እንደሆነ ብዬ…ግን ብጨምቀው ባልበው ጠብ አይለኝም ፡፡

በንጭንጭ ወደ አልጋዬ እመለስና እያተገላበጥኩ እንቅልፍ እስኪያሸንፈኝ  እሰቃያለው፡፡ከሰዓታት በኃላ እንደምንም  እንቅልፍ ያሸንፈኛል፡፡ሊነጋጋ ሲል መለልሶ ይቀሰቅሰኛል፡፡የዚህኛውን ጊዜ እንኳን ፊት አልሰጠውም …ከነ ተረቱ ‹ የጥዋት ቁ› ይባል  የለ …ሽንት እንዲወጠር እድርጎት ይሆን ትክክለኛ አምሮት ይሁን መለየት አይቻልም…ሀሰተኛ መሲ ነገር ነው፡፡

ይሄ ነገር  እየተደጋገመ ሲያስቸግረኝ ህልሜን ሁሉ የከተማዋ ቆነጃጅቶች እና በአካልም በምናብም የማውቃቸው ሴቶች ሲሞሉት የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለብኝ  ወሰንኩ…፡፡ በእኔ ምክር ሳይሆን በተፈጥሮ ህግ የሚመራውን ቅንዝሬን  የሆነ ዘዴ ፈጥሬ ማቀዝቀዝ አለብኝ..ስለዚህ ግዢ ልወጣ ወሰንኩ፡፡

ሰፈሩን ባልነግራችሁም …ለግዢ ምቹ ናቸው ሲባሉ ከሰማዋቸው የከተማዋ ጉድ ሰፈሮች  መካከል ወደ አንዱ ነው የሄድኩት…ቺቺኒያ አይተንሀል  አላችሁኝ…..?ምን  አልባት እኔን የመሰለ ሰው አይታችሁ ይሆናል እንጂ እኔ ወደ እዛ ሰፈር ዝር አላልኩም…ደግሞስ እናንተ ራሳችሁ እዛ ሰፈር ምን ስትሰሩ ነበር? ለማንኛውም ያልኳችሁ ቦታ ሄድኩ …ቀድሜ አልጋ ተከራየው….
ከዛ ወደ ቡና ቤቶቹ ወይም ወደ ጭፈራ ቤቶቹ አልነበረም ጎራ ያልኩት፡፡ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ወደ ጎዳናው ነው የወጣሁት…፡፡ከቤት ውስጥ ግዢ የውጩን ለምን እንደመረጥኩ አልገባኝም…. ብቻ ስሜቴ ወደ እዛ ነው የገፋኝ ፡፡ዞሬ ለመምረጥ… መርጬ ለማነጋገር እና ለመስማማት..ተስማምቶም ይዞ ለመሄድ ..አንድ ሰዓት ገደማ ፈጀብኝ፡፡

ልጅቷ የተከራየሁት ቤርጎ ገብታ አልጋው ጠርዝ ላይ እንደተቀመጠች  ፊቷን ለማንበብ ሞከርኩ..፡፡ፊቷ ሜካፕ የነከካው ቢሆንም በስርዓቱ አልተዳረሰም… የሆነ መዝረክረክ ይታይበታል፡፡ከቀይ ዳማ መልክ ወደ ግራጫ የተቀየረ የፊት ቀለም ይታየኛል..፡፡የዓይኖቾ ቅንድቦች ቀና ማለት ደክሟቸው መሰለኝ ተደፍተዋል፡፡ጉንጮቾ ወደ ውስጥ ስርጉድ ብለው በረሀ ላይ ውሃ እንዲወጣባቸው የተቆፈሩ ጉድጓዶች ነው የሚመስሉት ...፡፡ከንፈሮቾ ቁርፍድፍድ ብለው የመሰነጣጠቅ ምልክት ይታይባቸዋል፡፡ግን በተቀባችው ቀይ ሊፒስቲክ ልትሸፍነው ሞክራለች፡፡ውጭ ከመብራቱ  ፖል አቅራቢያ ከሚገኝ ግንብ አጥር ጋር ተጣብቃ ግማሽ ብርሀን እና ግማሽ ጨለማ ከቧት ሳነጋግራት ይሄ ሁሉ አሁን የዘረዘርኩላችሁን የመልኳ ሁኔታ አልተገለፀልኝ ነበር.፡፡አቋሟን እና የፊቷን ቅርጽ በከፊል ነበር የገመገምኩት….፡፡ገምግሜም አስፓልቱ ላይ ከተኰለኰሉት መሀከል እሷን የመረጥኳት…መርጬም ያነጋገርኳት …አነጋሬም የተሰመመማነው… ተስማምተን ወደ ተከራየውት ቤርጎ ይዤት የገባሁት፡፡

አሁን ..ከገባችና በመጠኑም ፈንጠር ብላ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀምጣ ሳስተውላት ግን አሁን ከላይ እንደዘረዘርኩላችሁ የተለየች ሆና ነው ያገኘኋት፡፡ ገና ያልበሰለች የ16 ዓመት አካባቢ ጨቅላ ወጣት ነች ፡፡ቢሆንም ውስጧ የ60 ዓመት  …የጎበጠች እና የጨረጨሰች አሮጊት በእሷነቷ ውስጥ ተደብቃ ትታያለች፡፡  ወጣትነቷ  በፍጥነት ወደ መጠውለግ ሲንደረደር  ይታያል፡፡

‹‹ተጫወቺ እንጂ …ምነው ከእኔ ጋር ማደሩ ደስ አላለሽም እንዴ? ››አልኳት፡፡

ፊቷን እንዳጨማደደች አላስፈላጊ ጥያቄ እንደጠየቀ ሰው በግርምት እያየችኝ

‹‹መደሰት እና አለመደሰት እዚህ ጋር ምን  አመጣው›ስትል መለሰችልኝ፡፡

‹‹አልገባኝም››

‹‹እንዴት አይገባህም..እኔ ገንዘብህን ነው የምፈልገው፡፡ ከፍለኸኛል….ከከፈልከኝ ደግሞ ደስ አለኝም  አላለኝም  አብሬህ ማደር ግዴታዬ ነው››አለችኝ እና ልብሶቾን ማወላለቅ ጀመረች፡፡
እኔም አወላለቅኩና ተከተልኳት..ተያይዘን  አንድ አንሶላና ፍራሽ ከስር..አንድ አንሶላና ብርድ ልብስ ከላይ አድርገን ከመሀከል ገባን…፡፡

‹‹እዛ ባዶ ቤት ብቻውን በነበረበት ሰዓት ዘራፍ እያለ  እረፍት  ይነሳኝ  የነበረው አጅሬን‹‹ አሁን እስቲ ጉዱህን እየዋለው….ሜዳውም ፈረሱንም ያው አመቻችቼለታለው… ›› አልኩት.፡፡

ግን ለእኔም ሆነ ለአጅሬው እንደአሰብነውና እደጓጓነው የሆነልን አይመስለኝም ….የሆነ ደስ የማይል ስሜት እየተሰማኝ ነው…እሱም አንዴ ቀጥ ከዛ መልሶ  እንደመልፈስፈስ እያለ ፈራ ተባ  ውስጥ ገብቷል፡፡ወደ እሷ ፊቴን አዞርኩና እጄን ትከሻዋ ላይ ጣል አደረግኩ..ስጠጋት ከሰውነቷ የሚረጨው ጠረን ተምዘግዝጎ ወደ አፍንጫዬ ሲገባ ደስ የማይል ስሜት ነው የተሰማኝ..እርግጥ  ከለበሰችው ልብስ አልፎ ሰውነቷ ላይ የቀረ የሽቶ ሽታ አለ ..፡፡ግን  ከሽቶው ተደባልቆ ና ተዋህዶ የሚበተን ሌላ ጠረን  አለ..ምንነቱን ልለየው ያልቻልኩት ትንሽ የሚረብሽ ጠረን….፡፡

እንደዛም ሆኖ በደንብ ተጠጋኋት ..ሰውነቴን ከሰውነቷ አጣበቅኩ…እዳብሳት እና  አሻሻት ጀመርኩ፡፡..ቀስ በቀስ ሰውነቴ እየጋለ እየሞቀ ቢመጣም ከእሷ ወደ እኔ እየተላለፈ ያለ ምንም አይነት ሙቀት ሊሰማኝ አልቻለም…. አሁንም በረዶ እንደሆነችና ሰውነቷ ከፍሪጅ እደወጣ ስጋ እንደደረ ነው፡፡ማሻሸቴ ቀጥሎ ጡቶቾ ጋር ደረሰ ....ጨመቅ ለቀቅ.. ጨመቅ ለቀቅ ሳደርግ አስደንጋጭ ፈሳሽ ከጡቶቾ  ፊን ብሎ ደረቴ ላይ ተረጨ..ደነገጥኩ ፡፡

በደነገጥኩበት ፍጥነት አሷም ይበልጥ በመበሳጨት ጮኸችብኝ፡፡

‹‹በናትህ ዝም ብለህ ማሻሻቱን ጥለህ ..ማድረግ አትችልም ?››

‹‹ምድነው ከጡትሽ የወጣው?››
‹‹ምን እንዲወጣ ትፈልጋለህ… ነዳጅ…››.በማሾፍ መለሰችልኝ፡፡

‹‹እሱማ ወተት ነው…ግን እንዴት...?እንዲህ ይሆናል እንዴ?››

‹‹እመጫት ስለሆንኩ እና ስለማጠባ ነው››ግዴለሽ እና ስሜት አልባ በሆነ ስሜት መለሰችልኝ፡፡

‹‹ማ….? አንቺ?››

‹‹አዎ …የሁለት ወር አራስ ልጅ ቤት ጥዬ ነው የመጣሁት››
በድንጋጤ ከመኝታዬ ተስፈንጥሬ በመነሳት  ቁጭ አልኩ

‹‹ አቤት ጭካኔ ..የሁለት ወር አራስ ቤት አስተኝቶ  ለሽርሙጥና መሰማራት  ሀጥያት ብቻ ስይሆን ወንጀልም ነው..ምን አይነጠቷ አውሬ ነሽ በእግዚያብሄር…!!!!››አልኳት፡፡

ተንፈቅፍቃ የሹፈት ሳቅ ሳቀችብኝ‹‹ሀጥያት አልክ ..?ማነው እኔን  ወንጀለኛ እና ሀጥያተኛ ነሽ ብሎ ሊፈርድብኝ የሞራል ብቃት ያለው..?ያሳደገኝ ማበረሰብ…? ሚያስተዳድረኝ መንግስት …?ቄሱ..?ፓስተሩ…? አንተ ..
38😢3
?ወይስ እግዚያብሄር…?›› ትንፋሽ ወሰደችና ንግግሯን ቀጠለች….‹‹….ልጄ  ወተት ያስፈልጋታል...እኔም መብላት ባልችልም ቀምሼም ቢሆን ማደር አለብኝ...እናቴም አየር ስባ ብቻ አይደለም የምትኖረው….አንገታችን የምናስገባበትን እና ጎናችንን የምናሳርፍበት ደሳሳ ጎጆም  ከመንግስት በችሮታ የተሰጠን ሳይሆን በ6000 ብር የተከራሁት ነው..ነው ወይስ አራስ ልጄን  እና ደህነት እና በሽታ ተባብረው  ያደቀቋትን እናትኔን  ይዤ ጎዳና በመውጣት መንገድ ጠርዝ ጨርቅ አንጥፌ ልለምን?ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው አሉ….ዳሩ ወንድ አይደለህ.. ማስታቀፍ አንጂ መታቀፍ ምን እንደሆነ ጣጣውን እና መዓቱን የት ታውቃለህ?፡፡››

በንግግሯ ደነዘዝኩ ..ጭንቅላቴን ራስምታት ሲወቅረኝ ይታወቀኛል‹‹ይቅርታ ..ስሜታዊ ሆኜ ነው… አሁን ልጅሽን ማን ነው የሚጠብቀልሽ?››ስል ቀዝቀዝ ብዬ ለስለስ ባለ የድምፅ ቃና ጠየቅኳት፡፡

‹‹እናቴ››

‹‹አይቸገሩም?››

‹‹ታስቸግራለች..ግን ብዙ ጊዜ አዳር አልሰራም… ሁለትም ሆነ ሶስት ሰዎችን አግኝቼ ሾርት ከሳራው በኋላ ያገኘኋትን ብር ይዤ ስድስትም ሳባትም ሰዓት ወደቤቴ እገባ ነበር… ዛሬ ግን እንደዛ ስላልቀናኝ ነገ ደግሞ የግድ የቤት ኪራዬን መክፈል ስላለብኝ እና ለዛ የሚሆን በቂ ብር እጄ ላይ ስለሌለ ነው አዳር ለመስራት የወሰንኩት፡፡››

‹‹ሞባይሌን አወጣሁና ሰዓቴን አየው 5፡25 ይላል..ኪሶቼን በረበርኩና ጥዋት ለታክሲ ይሆነኛል ብዬ ሀምሳ ብር ብቻ አስቀረሁና ሌላውን መዳፎ ላይ አስጨበጥኳት.. ከተስማማንበት ሂሳብ ቢያንስ በእጥፍ ይበልጣል….

‹‹በቃ… ለልጅሽ ሂጂላት››

‹‹ለምን?››

‹‹በቃ ሂጂላት››

‹‹ቢያንስ አንዴ ተጠቀምና  ልሂድ››

‹‹አይ አልችልም ስሜቴ ደፈራርሷል››

ለመጀመሪያ ጊዜ ፈገግ አለች..ለሽርፍራፊ ሰከንድ ቢሆንም ውስጧ ያለችው አሮጊት ስትከሳ እና ከውጭ የሚታየው ወጣትነቷ ሲፈካ ታዘብኩ‹‹ በጣም ነው ማመሰግነው..በእውነት ከጭንቀት እና ከስጋት ነው የገላገልከኝ….፡፡በድኔ ብቻ ነበር እዚ ያለው…፡፡ ስጋዬም  ነፍሴም ልጄ ጋ ነበር፡፡››እየመረቀችኝ ልብሶቾን ለበሰች… ሞባይሌን ተቀብላ ቁጥሯን መዘገበች ና መለሰችልኝ‹‹ቁጥሬ  ነው ብትደውልልኝ ደስ ይለኛል›› አለችኝ፡፡

‹‹እሺ እደውልልሻለው.. ለማንኛውም አንቺ በርቺ››

‹‹ወድጄ እበረታለው..››አለችኝና ንግግሯን ቀጠለች‹‹በጣም ይገርማል ››አለችኝ፡፡

‹‹ምኑ?››

‹‹ወንዶች ስትባሉ  እንደየመልካችሁ  ባህሪያችሁም ብዛቱ ..ስንቱ አውሬ እና ማሰብ የተሳነው የአእምሮ ድኩማን አለ መሰለህ… እነሱን አስበህ በአዳም ልጆች ተስፋ ልትቆርጥ ስትል ደግሞ እንደ አንተ አይነት በግ  ያጋጥማሀል፡፡››

‹‹በግ?››አልኰኳት … ደንግጬም ተገርሜም፡፡

‹‹ይቅርታ በግ ስልህ ሞኝ ለማለት ፈልጌ አይደለም… ፡፡የዋህ እና መልካም ሰው  ለማለት ነው ..ለማኛውም ብትደውልልኝ ደስ ይለኛል ፡፡ቆንጆ እና የምታምር ልጄንም አሳይሀለው››

‹‹እሺ አይልሻለሁ..››

‹‹እሺ ቻው››ብላኝ  በራፉን ከፋታ በመውጣት መልሳ ዘጋችልኝና ሄደች፡፡እርምጃዋ ቀስ እያለ እየደበዘዘ..እየደበዘዘ ለጆሮ እየሳሳ በስተመጨረሻ ጭልም ብሎ ሲጠፋ ተሰማኝ…፡፡

ግን ነገ ወይ በማግስቱ እደውልላት ይሆን? በውስጤ የተጫረ ጥርጣሬ የወለደው ጥያቄ ነበር፡፡ልደውልላትማ ይገባል….ስለዚህች ልጅ ታሪክ ጠለቅ ብዬ ባውቅ ደስ ይለኛል.. ?እንደዛ አይነት ጉጉት በውስጤ ተፀንሷል፡፡

ተፈፀመ

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍3229
#ሞት_አያምም!!!

እኖር ብዬ ብታረድም
ለመኖር ስል ብሰደድም
እኖር ብዬ ብዋረድም
ዘጠኜ ሞቴን ብሞተው…
አንዴ እንደመኖር አይከብድም!
መኖር ከመምት አይልቅም
ሞት እንደሕይወት አይጨንቅም፡፡
………………………………
የሞተ ‹‹እሞታለሁ›› ሲል…
በጭራሽ አያውቅም ፈርቶ፡፡
ያልኖረ አያውቅም ሞቶ።
።።።።
መኖር እንጂ የሚያስፈራኝ
መኖር እንጂ የሚያስገፋኝ
መኖር እንጂ የገደለኝ
መኖር እንጂ የበደለኝ
ሞት አያምም ካቆሰለኝ
ምት አያምም ከገደለኝ!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍126🔥2
#ቀረሽ_እንደዋዛ

እንደ ድመቶቹ
የትም እንደሚያድሩት
እንደ ስልክ እንጨቶች
እንደ ዛፍ ሀረጎች
እንደ ቤት ክዳኖች
ብርድ አቆራመደኝ
ስጠብቅ ስጠብቅ
˝ትመጫለሽ ብዬ ሳይ ማዶ ሳይ ማዶ
የልጅነት አይኔ ሟሟ እንደ በረዶ˝
ትመጫለሽ ብዬ ደቂቃ ስቆጥር
ትመጫለሽ ብዬ ደቂቃ ስቆጥር
ትመጫለሽ ብዬ ባዝን ባንጎራጉር
ትወጫለሽ ብዬ በበራፍሽ ብዞር
ብርድ አቆራመደኝ
የመንገድ መብራቶች አይተው አፌዙብኝ
ውርጩ ቀለደብኝ
ጨለማው ሳቀብኝ
አለመምጣትሽን አውቀዋል ያውቃሉ
መስኮቶች ጨልመው
ቤቶች ተቆልፈው
ከተማው ሲተኛ
አይተዋል ያያሉ
አለመምጣትሽን
አውቀዋል ያውቃሉ፡፡

🔘ገብረ ክርስቶስ ደስታ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍123
አለም ትዞራለች የተባለው ሳይንስ
         አሁን የለው ዋጋ፣
አለም ዛሬ ቆማ ሰው እየዞራት ነው
         እንጀራ ፍለጋ።

🔘ስፍራዬ ጥላዬ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
🔥124
ስትመጪ
ክንዴ በስተራስጌ ክንፍ አቆጠቆጠ
የደጅ አፌ ዳገት፣ ዐይኔ ፊት ቀለጠ

ስትሄጂ
ጸሐዩ ፈረጠ፣ ቁልቁለቱ አበጠ
የቀዬው አብሪ ትል በጽልመት ተዋጠ።

በዳፍንታም አለም፣ ጠባቂ ሲተጋ
እንኳን ቀን ጨልሞ፣ ሌሊቱ ሲነጋ...

መምጣትና መሄድ ቀን ይቀያይራል፥
ምላስሽ ያጎድፋል፣ ምላስሽ ያጠራል
ትንፋሽሽ ያጠፋል፣ ትንፋሽሽ ያበራል።

  🔘ዮሐንስ ሞላ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍7