#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ቤት እንደገባች ስልኳን ከፈተችና አሰላ ስንዱ ጋር ደወለች "እንዴት ነሽ ሳባ...? ሀኪሙ ጋር ሄድሽ?" ማውራት ስለማትፈልገው ርዕስ ብታወራላትም እንደምንም እራሷን ተቆጣጥራ መለሰችላት
"አዎ ሄጄ ነበር..መድሀኒት ቀይሮ አዞልኛል.. ግን አሁን የደወልኩት አንድ ጓደኛዬ ሱባኤ ልትገባ ወደ ደብረሊባኖስ ገዳም ልትሄድ ነበር. ለተወሰነ ጊዜ በፆምና በፀሎት ብናሳልፍ ጥሩ ነው አለቺኝ"
"እና ምን አሰብሽ?"
"እኔ እንጃ ..ውስጤ ግን ሂጂ ሂጂ እያለኝ ነው፡፡"
"ብትሄጂ ጥሩ ነው ብቻ እንዳይከብድሽ ነው የምፈራው"
"ግድ የለሽም ስንድ.. እንደምንም ልሞክረው"
‹‹ታዲያ መች አሰባችሁ?"
‹‹ነገ ጠዋት"
"ስንቅ ምናምን ሳለዘጋጅልሽ?"
"ስንዱ ደግሞ ሁሉ ነገር ሱፐር ማርኬት አለ...›› "ዳቦ ቆሎ፤ኩኪስ፤በሶም እንዳትረሺ.."
"በቃ ስንዱ አታስቢ….ምን አልባት ስልክ ካልተፈቀደ ላልደውልልሽ እችላለሁ"
"እሺ የአባትሽ አምላክ ከአንቺ ጋር ይሁን...እኔም ፀልይልሻለሁ"
"ቻው ስንድ ..ለራጂ ንገሪው" ስልኩን ዘጋችው፡፡ ወዲያው ሙሉ በሙሉ አጥፍታ ኮመዲኖ መሳቢያ ውስጥ ከተተች። ተወዳጅ የእንጀራ እናቷን ስለዋሸቻት ፀፅቷታል.. ግን ምንም ማድረግ አትችልም።ላልተወሰነ ቀናተሰ ከሰው ጋር በአካል መገናኘትም ሆነ በስልክ ማውራት አትፈልግም፡፡ ለዚህም ዘዴ መዘየድ ነበረባት
..መጥሪያውን አንጣረረች፡፡ታች ምድር ቤት ኪችን ያለችው..ሰራተኛዋ አለም እየሮጠች መጣች
"ምነው ሳባ ፈለግሺኝ?" "አዎ ቁጭ በይ"
በእንደዚህ አይነት ሁኔታ አውርታት ስለማታውቅ ደነገጠች...ሽምቅቅ ብላ በራፋ አጠገብ ያለው ወንበር ላይ ተቀመጠችና የምትነግራትን ነገር ለመስማት ዝግጅ ሆና መጠበቅ ጀመረች።
"አሁን የምነግርሽን..ለልጁም ንገሪው፤ ከዛሬ ጀምሮ ማንም መጥቶ በራፍ አንኳኩቶ ቢጠይቃችሁ የለሁም ..ፀበል ሄጃለሁ.. እዚህ መኖሬን ማንም በስህተት እንኳን እንዲያውቅ አልፈልግም።ማንም እንዲረብሸኝ አልፈልግም። ጫጫታ ኳኳታ እንዳልሰማ። ስራሽን እስከአሁን እንደምትሰሪው መስራትሽን ቀጥይ፤ ግን መቶ ፐርሰንት ራስሽን ችለሽ በመሠለሽ መንገድ ነው የምትሰሪው.. በየቀኑ ደግሞ አንድ አንድ ጠርሙስ ውስኪ እዚህ ጠረጴዛ ላይ ታስቀምጪልኛለሽ... ለጊዜው መጋዘን አለ፡፡ እሱ ሲያልቅ ያው ከተለመደው ቦታ ታስመጪያለሽ...የምትፈልጊውን ነገር ከደንበኛችን ሱፐር ማርኬት ሄደሽ እያስመዘገብሽ ትወስጂያለሽ... ከእነሡ ጋር ስለተነጋገርኩ ሂሳቡን እኔ ነኝ የምዘጋው። እዛ የማይገኝ እቃ የምትፈልጊ ከሆነ እዛ ቁም ሳጥኑ የታችኛው ኪስ ውስጥ ብር አለልሽ፡፡እኔን መጠየቅ አያስፈልግሽም ..ቀጥታ የምትፈልጊውን ያህል ትወስጂያለሽ..ደሞዛችሁ ያው እንደተለመደው ከባንክ ጋር አጀስት ስላደረኩ ቀናችሁ ሲደርስ በደብተራችሁ ይገባል። ልጁ ቁርስ ምሳ ራቱን እንዳታጎይበት፡፡የሚፈልገው ነገር ካለም እንዳትከለክይው። ጨርሻለሁ በቃ ወደ ስራሽ ተመለሽ።"
"ሳባ ሰላም ነሽ ግን ?አስፈራሺኝ እኮ"
"ጨረስኩ አልኩሽ እኮ" ወደአልጋው ወጣችና ብርድልብሱን ጥቅልል ብላ ተኛች። አለምም ግራ መጋባቷን በልቧ እንደያዘች ሹክክ ብላ ወጥታ ወደ ስራዋ ተመለሠች። ከዛ በማግስቱ ጠዋት ስትመጣ የተለየች ሳባ ነበረች የጠበቀቻት፤
//////
ሳባ ክፍሏ ውስጥ ከተከተተች 35 ቀን ሞላት
ከሆስፒታል የዶክተሯ ምርመራ ክፍል ውስጥ ድንገት ከተገናኘችው ኤፍሬም የተባለ ሰው ጋር አጓጉል ነገር አድርጋ ከተመለሰችበት ቀን አንስቶ ከበፊቱ በባሰ መልኩ መኝታ ቤቷ ውስጥ ራሷን ደበቀች፡፡ ሰራተኛዋ በቀን ሁለት ጊዜ ምግብ ወደ ክፍሏ አስገብታ ከአልጋው ጎን ባለው ኮመዲኖ ላይ ታስቀምጥላትና ሹክክ ብላ ተመልሳ ትወጣለች፡፡እሷም ከቀረበላት ምግብ 20 ፐርሰንቱን ብቻ ስትጠቀም ከመጠጡ ግን እንጥፍጣፊ ጠብታ አታስተርፍም፡፡
ይህ ድባቴ እስከመቼ እንደሚዘልቅ ማብቂያው የት ጋር እንደሆነ ማንም አያውቅም፡ እሷም እያስጨነቃት አይደለም፡፡ከአስር አመት በፊት ከአዲስአባ ዩኒቨርሲቲ በአካውንቲንግ ተመርቃ ስራ ፍለጋ በየቢሮው የምትንከራተት፤ የታክሲ የሚቸግራት፤ ካፌ ግብቶ ማኪያቶ ለመጠጣት ድፍረት ያልነበራት፤ ሚስኪን ንፅህና ፤ባለብሩህ ተስፋ ወጣት ነበረች፡ዛሬ ከአስር አመት በኃላ የተንጣለለ ባለ10 ክፍል ቢላ ቤት ያላት፤ ምርጥ የተባለ ሴቶች ሁሉ አይናቸውን የሚያንከራትቱበት መኪና ምታሽከረክር ፤የባንክ ደብተሯ ላይ አስራ ምናምን ሚሊዬን ብር ያላት የ33 ዓመት አማላይ ግን ደግሞ አባቷን ጨምሮ የአራት ሰዎችን ህይወት ያመከነች ከዚህም በኃላ በአጠቃላይ የህይወት አላማው ትርጉሙም ውሉም የጠፋባት ስብርብረ ያለች ሴት ነች፡፡
በተኛችበት አልጋ ላይ ሳትነሳ እጇን ሰደደችና ኮሚዶኖ ላይ የተቀመጠ ውስኪ ጠርሙስን እንደምንም ጎትታ አነሳች፡፡ገርገጭ ገርገጭ እያደረገች ጠጣችና ክዳኑን በመከራ አሽከርክራ በመዝጋት እዛው ቅርቧ ትራሱ ስር አስቀመጠችና ወደድባቴዋ ተመለሰች፡፡
አለም እንደመጣች ወደሳባ ክፍል በመሄድ ሰላም ማደሯን ከተለመለከተች በኃላ ወደኪችን ሄዳ በተቻላት መጣን አጣፍጣ ቁርስ ሰራችና እንደጨረሰች ከዳድና በማስቀመጥ ተመልሳ ወደሳባ ክፍል ሄደች ፤ስትገባ ሳባ ተዘርራ በተኛችበት አይኖቾን ኮርኒሱ ላይ ሰክታ በሀሳብ ጠፍታ ነው ያገኘቻት ፤ቀጥታ ወደ ቁም ሳጥኑ ሄደችና ከፈተች.. ልብስ መምረጥ ጀመረች…ፎጣ፤ፓንት…ቢጃማ ከያሉበት መረጠችና አወጣች…..ወደሻወር ቤት ይዛ ገባች.የሻወሩን ሙቅ ውሀ ለኮሰችው…ገንዳውን በውሀ ሞላችው..
ከዛ ተመልሳ ወደመኝታ ቤት ገባችና ወደሳባ ተጠግታ ጎንበስ አለችና ወዝውዛ ከገባችበት ሀሳብ በግድ መነጭቃ በማውጣት ‹ሳቢ ተነሽ ሰውነትሽን ታጠቢና ልብስ ቀይሪ››አለቻት፡፡
‹‹ምን? ››
‹‹ሰውነትሽን ታጠቢ. ..ውሀውን ለኩሼልሻለሁ….ቀለል ይልሻል››
‹‹ምነው ሰውነቴ ሸተተሸ እንዴ?››
አለም ያላሰበችውን ነገር ስለተናገረቻት ደነገጠች‹‹ኸረ ሳቢ እንደዛ ለማለት ፈልጌ አይደለም››
‹‹በቃ ውጪልኝ››ሰሞኑን ከነበራት ኃይል በመቶ እጥፍ በበለጠ ኃይል አንቧረቀችባት…አለም በጣም ተከፍታ ወደሻወር ቤት ተመልሳ ገባችና የለኮሰቸችውን ውሀ አጠፋፍታ ያወጣችውን ልብስ ወደቁምሳጥኑ መልሳ ሹክክ ብላ ክፍሉን ለቃ ወጣች፡
ሳባ ልጅቷን እንዲህ ለማበሻቀጥ ምንም ፍላጎት አልነበረትም፡፡እንደዛም ስላደረገች እፍረት ተሰምቷታል..የጮኸችው በእሷ ላይ ይሁን እንጂ እውነታው ግን በራሷ ላይ ነበር ለመጮኸ የፈለገቸው፡፡በገዛ ማንነቷ ነው የተበሳጨችው፡፡
ለመሆኑ እንዲህ ከንቱ ከሆንኩ ቀድሞውንስ ለምን ተፈጠርኩ..?ለምንስ እኖራለሁ? ህይወት ምንድነው? ሞትስ..?በመኖሬ ምን አተርፋለሁ.?.በሞቴስ የማጣው ነገር አለ?ያለፈትን አንድ ወር ሙሉ በእምሮዋ ሚጉላሉ ግን ደግሞ ቁርጥ ያሉ መልሶችን ልታገኝላቸው ያልቸለች ግትልትል በህይወት ትርጉም ላይ ሚያጠነጥኑ ጥያቄዎች ናቸው፡፡
እንዲሁ በድን ሆና ተዝለፍልፋ እንደተኛች..ቀኑ ነጎደ መሸ..አራት ሰዓት ሆነ

👍67❤8👏2🔥1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት
፡
፡
#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
እሷ እየተንደረደረች ወደቤቷ ገባችና ፎቁን ወጣች መኝታ ቤት ገባች፡፡ የሆነ ነገር አደናቅፎት እንዳትወድቅ እንኳን መብራቱን ማብራት አልፈለገችም።በዳበሳ ከልጋዋ ላይ ወጣችና ጠርዙን ያዘች፡፡ ወደ ኮመዲኖ ተንጠራራች ቀን በጅምር ያቆመችውን የውስኪ ጠርሙስ አነሳችና ክዳኑን ከፍታ አንደቀደቀችው።
"እስኪ ይሄ ምስኪን ልጅ ምን አደረገኝ?"እራሷን እረገመች። ምነው እግሬን በሠበረው በማለቱ ወደእሱ በመሄዶ እራሷን ወቀሰች፡፡
….////…
ሳባ አሁን በዚህን ሰዓት 80ሺ ብር የተገዛ ባለ 2 ሜትር የተንጣለለ ግዙፍ አልጋ ጠርዝ ላይ ተኝታ ያቺን ከዛሬ 10 ዓመት በፊት የነበረችዋን የዋህ ንፅህ ጉጉ ተስፈኛ ወጣት አብዝታ እየናፈቀቻት ነው፡፡አሁን ያላትን ሀብትና ንብረት ሁሉ ከፍላ ይቺን ሚስኪን ወጣት ከነሙሉ ክብሯ፤ ንፅህናዋና፤ የዋህነቷ እንዲውም ከሙሉ ተስፋዋ ጋር ቢመልሱላት ዓይኗን ሳታሽ ነበር የምትስማማው፤ ግን ያንን ማድረግ እንደማይቻል ስታውቅት ተስፋ ቆርጣ ይበልጥ አንገት ያስደፋታል፡፡
ደግሞ ይህ ተስፋ መቁረጧ ጫፍ ላይ አድርሶ እርሷን እንድታጠፋ እና ካለችበት ቅዠት እንድትገላገል ቢያግዛት ደሰተኛ ትሆን ነበር፡፡ግን ህይወትን በአዲስ መንፈስ አድሳ ከድባቴ እራሷን አላቃ ከሚወቅራት እራስ ምታትና ከሚያኮረማምታት የመንፈስ መሰበር ተላቃ አዲስ ህይወት ለመጀመር የሚያስችላት አቅም ለማግኘት ሆነ እስከዛሬ ባለፈችበት የሀጥያት መንገድና የተበላሸ የህይወት መስመር የተነሳ እራሷን ተጠይፋ ከህይወት መዝገብ ላይ በፍቃዷ እራሷን ለማሰናበት የሚያስችል ብቃትና ፅናት ማግኘት አልቻለችም፡፡ያ ደግሞ በአየር ላይ አንገትን በገመድ ታንቆ እንደመንጠንጠል አይነት የሚያቃትት ስሜት ነው እንዲሰማት እያደረጋት ያለው፡፡
አሁን እንደዚህ ምስቅልቅል ባለ ህይወት ላይ ሆና ለሚያያት ሰው ምን ሆነሽ ነው
?ብለው ቢጠይቋት እንዲህ ሆኜ ነው ብላ በድፍረት አንገቷን ቀና አድርጋ የምትመልሰው ለሰሚው ሚዛን የሚደፋና ለእሷም እንዲያዝኑላት የሚያደርግ ምንም ምክንያት የላትም… ምክንያቱም ትክክለኛ ምክንያቷን(ነፍስ ገዳይነተዋን)መናገር አትችልም…ብትናገር ማረፊያዋ እስር ቤት ነው፡፡
እነዛን ሚስጥሮች የማያውቁ ሰዎች ደግሞ‹‹ባፈቀረችውና ልቧን አሳልፋ በሰጠችው ሰው የመከዳት ችግር አልገጠማትም ..የገንዘብ እጥረት ወይም ኪሳራ ፍፅም የለባትም..የሆነ ወንጀል ሰርታ የተከሰሰችበት ጉዳይ ፈፅሞ የለም..የህክምና ምርመራ አድርጋ እንዲህ አይነት ቋሚ የጤና ችግረ አለብሽ ተብሎ አልተነገራት…ታዲያ ምንድነው እንዲህ የሚሰባብራት?›› ብሎ ቢያስብና ቅብጠት ነው ብሎ ፍርድ ቢሰጥ አይገርምም፡፡
እውነታው ግን አሁን በዚህ ወቅት የሳባ መንፈሶ ተሰብሯል ፤የመኖር ጉጉቷ ተንቆሻቁሾል፤በውስጧ ምንም አይነት የደስታ ቅመም መመረት ካቆመ ሰነባብቷል፡፡ የመኖርም ሆነ የመሞት ፍላጎቷን አጥታለች፡፡ማፍቀርም ሆነ መፈቀር ሳይቀር ትርጉመ ቢስ ሆኖባታል፡፡በአጠቃላይ ስሜተ ቢስ እየሆነች ነው፡፡እንደሚታወቀው ስሜት ማለት የሠው ልጅ መንፈሳዊ ወዝ ነው። የሰው ልጅ ህይወትን ጣፍጭና ወዝ ያለው የሚያደርገው የስሜቱ ውጣ ውረድ ነው ። ሰው ሲከፍው ከላለቀሰና ሲደሰት ካልሳቀ ከፍተኛ የስሜት መሠበር እንዳለበትና ጠንካራ ህክምና እንደሚያስፈልገው በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል።ጠንካራ ስሜት ያላቸው ሰዎች ህይወታቸው ደማቅና ከሩቅ ትኩረት የሚስብ ናቸው።ግን ደግሞ እንደነዚህ አይነት ሰዎች ሲሰበሩም በትልቁና በቀላሉ ነው፧፡ለዚህ ነው የሠውን ስሜት መስበር አስጠሊታ ሀጥያት የሚባለው።
እለቱ ማክሰኞ እኩለቀን አካባቢ ነው።ሰራተኛዋ አለም የምትሰራውን ሰርታ ወደቤት ለመሄድ ስትወጣ ቀናውን በራፍ ላይ ቁጭ ብሎ እንደወትሮው ሲያነብ አገኘችው፡፡ኮቴዋን ሲሰማ ቀና ብሎ ‹‹ልትሂጂ ነው?››አላት፡፡
‹‹አዎ ልሄድ ነው….ግን አንድ ነገር ላማክርህ ነበር፡፡›› ከመቀመጫው ተነሳና ፊት ለፊቷ ቆመ‹‹ምንድነበር?››ጠየቃት፡፡
‹‹የዚህች ልጅ ነገር በጣም አሳስቦኛል…ይሄው መኝታ ቤቷ ከተሸሸገች ሁለት ወር ሊደፍናት ነው..ምግብ አትበላ፤ መጠጣትና ..መተኛት ብቻ ነው ስራዋ…፡፡አሁንማ ሰውነቷ አልቆ አልቆ ስንጥር አክላለች..በዚሁ ከቀጠለች በጥቂት ሳምንታት ውስጥ መሞቷ አይቀርም፡››
‹‹የእሷ ነገር እኔንም አሳስቦኛል…..አንቺ ምን አሰብሽ?››
‹‹እንዴ ግራ ገባኝ ..ከቤት መውጣት እምቢ ካለች፤ ህክምናዋና ካቆረጠች፤ መብላትና መጠጣት ካቆመች..እራሷን ቀስ በቀስ እየገደለች እኮ ነው….አንድ ነገር ከሆነች ደግሞ እኔና አንተ መጠየቃችን አይቀርም.. በተለይ እኔ……በጣም አሳስቦኛል፡፡››
‹‹ቆይ ዘመዶች የሏትም እንዴ?››
‹‹አላት …አሰላ ናቸው እንጂ ዘመዶች አሏት ፡፡እሷ ግን ያለችበትን ሁኔታ ለማንም እንዳንናገር በጥብቅ ነው ያስጠነቀቀችኝ…ግን አሁን አሁን ምርጫ የለኝም..ግፋ ቢል ስራውን መልቀቅ ነው፣ እስር ቤት ከመግባት ስራዬን ባጣ ይሻለኛል…እንደምንም የእንጀራ እናቷን ስልክ አግኝቼያለሁ…ልደወልላት ነው፡፡››
‹‹እኔ የሆነ ነገር አስቤ ነበር››አላት ቀናው፡፡
‹‹ምን?››
‹‹አሁን አልነግርሽም…ግን አንድ ሳምንት ይፈጅብኛል..እንደምንም አንድ ሳምንት ጊዜ ስጪኝና ልሞክር… እስከዛ ምንም ለውጥ ካላሳየች እንዳልሺውም ትደውይላቸዋለሽ፡፡››
ለተወሰነ ደቂቃ እንደማሰብ አለችና‹‹..እሺ ካልክ…እስከዛሬ ያልሞተች መቼስ በአንድ ሳምንት ውስጥ አትሞትም ››ብላ ተሰናበተችውና ወጥታ ሄደች፡፡ቀናው ወደ ነበረበት መቀመጫ ተመልሶ ተቀመጠና ማሰላሰል ጀመረ..ምን አድርጎ ቀጣሪው ከገባችበት የመደበት ስሜት ሊያወጣት እንደሚችል አሰበ …ቢያንስ የተወሰነ ቀና ብላ ወደህክምና ክትትሏ እንድትመለስ ማድረግ እንዳለበት ወሰነና ከተቀመጠበት ተነሳ፡፡ ግቢውን ቆላለፈና አነስተኛ ምንጣፋና አንድ መፅሀፍ ይዛ ወደ ትልቁ ቤት ገባ።
የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለበት ውስጡ እየገፋፋው ነበር የከረመው ዛሬ ደግሞ የአለም ንግግር በአፋጣኝ ወደ ተግባር እንዲሸጋገር አስገደደው…እርግጥ ከእሷ የሚያጋጥመውን መልስ ምን እንደሚሆን አያውቅም ግን ምንም ሆነ ምንም ለመጋፈጥ ወስኗል......ሳሎኑን አልፎ ወደፎቅ የሚወስደውን ደረጃ ተያያዘው... መኝታ ቤቷን ቀስ ብሎ ገፍው፡፡ አንገቱን አሰገገና ወደ ውስጥ ተመለከተ... እንደዚህ ባለ ቅርበት ካያት ብዙ ቀናት አልፈዋል....ፀጉሯ ተንጨፍርሮና እርስ በርሱ ተቆጣጥሮ አስፈሪ ሽፍታ አስመስሏታል፡፡ ሆዷ ከጀርባዋ የተጣበቀ ነው የሚመስለው ፤በጣም ከስታለች፤ አይኖቾ ኮርኒሱ ላይ እንደተሰካ ነው ወደ ውስጥ ዘልቆ ገባና መልሶ ዘጋው።በዚህ ጊዜ አይኖቾን አንከባለለችና ወደእሱ ተመለከተች
..የሆነ ነገር እንድትለው ፈልጎ ባለበት ተገትሮ ቆመ...፡፡
ምንም አላለችውም..ወደጥግ ሄደና ግድግዳውን አስጠግቶ ምንጣፉን አነጠፈ... እንደብዲስት መነኩሴ እግሩን አጣምሮ ቁጭ አለ።መፅሀፍን ከፊት ለፊቱ አስቀመጣና እጇቹን አቆላለፈ...ከዛ ልክ እንደእሷ ፀጥ አለ...ልዩነቱ የእሷ ፀጥታ በድንዛዜ ሲሆን የእሱ ፀጥታ በንቃት ነበረ...

👍55❤9🔥1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_አራት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ተገለበጣና ፊቱን ወደእሷ አዞረ…‹ከደፈረኝ በኃላ እዚሁ ሲጥ አድርጎ በጨረሰኝ››ስትል ተመኘች…
እሱ ግን ማውራት ጀመረ‹‹ስሜ አይያዝልሽም አይደል…እረስተሸው ከሆነ ዛሬም መልሼ ላስታውሽ፣፣ ቀናው ይመር እባላለሁ፡፡ይገርምሻል ብዙውን ጊዜ ስምህን እረሳሁት ብለሽ ደጋግመሽ ስትጠይቂኝ በደስታ ነው የምነግርሽ..እና ሁሌ ባገኘሁሽ ቁጥር ስሜ ጠፍቶባት ብትጠይቀኝ እያልኩ አመኛለሁ…ያው ምን አልባት ካንቺ ጋ ማውራት የተለየ ስሜት ይፈጥርብኛል መሰለኝ…..ሰባ አሁን ያለሽበትን ሁኔታ በጣም እረዳዋለሁ፡፡ እንዴት አድርጌ እንደማግዝሽ ግን ስለማላውቅ ነው ዝም ብዬ ማይሽ...ምክንያቱም እኔም እንደአንቺ ቁስለኛ..እኔም እንደአንቺ በሽተኛ ነኝ፡፡እኔ የወሎ ልጅ ነኝ…ቤተሰቦቼ ገጠር ኑዋሪ ገበሬዎች ናቸው፡፡ሀይስኩል ደሴ ወ.ሮ ሰህን ነበር የተማርኩት፡፡ ከ9 ዓመት በፊት ነው ማትርክ የወሰድኩት ፡፡በወቅቱ እንደ ኢትዬጵያ ትልቁ ውጤት የእኔ ነበር….ወዲያው እስኮላር አገኘሁና ወደአሜሪካ ወጣሁ፡፡በቃ በዛን ጊዜ የነበረኝ ደስታ…በውስጤ የተፈጠረው ፈንጠዝያ አለምን በእጄ የጨበጥኩ ነበር የመሰኝ..ከአንዲት መንደር ተነስቼ የልዕለ ሀያሎ አሜሪካ ሜትሮፖሊቲያን ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዴንቨር ተማሪ ስሆን…ይህቺን ደሀ ሀገር ተመልሼ እንደምመራና ልዕለኃያል ኃያል ላደርጋት ባልችል እንኳን ኃያል እንደማደርጋት እየፎከርኩ ወጣሁ…እዚህ ላይ አንድ አዛውንት የተናገሩትን ልጥቀስልሽ.. ወጣት ሳለሁ እኔ አስብና
እግዚያብሄርን በፀሎት ጠይቅ የነበረው ..እግዚያብሄር ሆይ አለምን ጠቅላላ የምቀይርበትና ምስቅልቅሏን የማስተካክልበት ኃይል ስጠኝ "ብዬ ነበር።ትንሽ በሰል ስል ደግሞ "ጌታ ሆይ አለምን መቀየር በጣም ከባድና ለእኔ አቅም የሚሰፋ ዕቅድ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።እስከአሁን አንድ ነጠላ ሰው እንኳን ሳልቀይር ዕድሜዬ እየነጎደ ነው።ቤተሰቤ ለእኔ በቂ ነው።ቤተሰቤን የምቀይርበት ኃይልና ጥበብ ስጠኝ"ብዬ ወደመፀለይ ተሸጋገርኩ አሁን ሳረጅ ደግሞ እቤተሰቦቼ ራሱ በጣም እንደሚበዙ ተረዳው"..እራሴን መቀየርና ማስተካከል ከቻልኩ በቂ ነው...አሁን ወደትክክለኛው መስመር ተመልሼያለሁ ..ስለዚህ ይሄንን እንዳደርግ የሚያግዘኝ ኃይልና ጥበብ ስጠኝ "ብዬ የመጨረሻ ፀሎቴን ፀለይኩ።አምላክም መለሰልኝ"አሁን የቀረህ ምንም አይነት እንጥፍጣፊ ጊዜ የለህም።ይሄንን መጠየቅ የነበረብህ ከአመታት በፊት በጉልምስና ወራትህ ላይ ነበር..አሁን ግን ረፍዶብሀል"አለኝ።እና ልጄ የእኔ እጣ እንዳያጋጥምህ ዛሬውኑ ንቃ...ፀሎትህን አስተካክል...ምኞትህን አርቅ...ብለው የመጨረሻ ምክራቸውን ለገሱ…
ሽማግሌው እንዳሉት አለም ምስቅልቅል ያለች የሚመስለን ምስቅልቅሎን የሚያስተካክል ሰው ስለጠፋ ሳይሆን እራሱን ለማስተካከል የሚጥር ሰው ጥቂት ስለሆነ እንደሆነ ለመረዳት እኔም ረጅም ጊዜ ወስዶብኛል፡፡ለማንኛውም ወደ ታሪኩ ልመለስልሽ፡፡
እዛ እንደደረስኩ ሁሉ ነገር አሪፍ ነበር…ልጅ ስለነበርኩ ሁሉን ነገር በፍጥነት ነበር አዳብት የደረኩት…ትምህርቴን እንደጨረስኩ. ወደ ሚኒሶታ ሙቭ አደረኩና ፍላይንግ ክላውድ አየር ማረፊያ አካባቢ ዋና ቢሮውን ያደረገ ኬ.ቢ ኢንተርናሽናል ኮስሞቲክ ካምፓኒ ውስጥ ስራ ያዝኩ፡፡ ወዲያው ከአንዲት አሜሪካዊት የካምፓኒ ሰራተኛ ጋር ወዲያው ፍቅር ያዘኝ…ትዝ ይለኛል…የተያየነው ሰኞ ቀን ነው…ማክሰኞ ፍቅር እንደያዘኝ ገባኝና ከስራ
መውጫችን ላይ ከስሯ ኩስ ኩስ እያልኩ ተከትዬ አዋራኋት…በሁለተኛው ቀን እራት አብረን በላን…ይሄንን ያዩ አብረውኝ ሚሰሩ ወንዶች በአድነቆት ፈዘው ሲያዩኝ ግራ ገባኝ…‹‹ምንድነው ቆንጆ ስለሆነች እሺ አትለውም ብለው እስበው ነበር ማለት ነው?››ስል ማሰላሰል ጀመርኩና በጥረቴ ገፋሁበት..ከሁለት ሳምንት በኃላ እፍ ያለ ፍቅር ውስጥ ያሉ ፍቅረኛሞች ሆን…ከአንድ ወር በኃላ የሚገርም ዜና ሰማሁ..ለካ በድፍረት የጠበስኩት የስራ ባለደረባዬን ብቻ ሳይሆን የተቀጠርኩበት ካምፓኒ ብቸኛ ልጅ እና የወደፊት ወራሽ የሆነችውን ልጅ ነው…ወንዶቹ ሁሉ በድፍረቴ ለምን እንደተደመሙ ቆይቶ ነው የገባኝ..እኔም ቀድሜ ባውቅ ያንን አይነት ድፍረት አይኖረኝም ነበር፡፡
ሳባ ከትንፋሹ ጋ ተደባልቆ የሚወጣው ሙቅ አየር ጉንጮቾ ላይ ሲያርፍ እየተሰማት በፀጥታና በተመስጦ እያዳመጠችው ነው፡፡
ካትሪና በጣም ቆንጆ፤ንፅህ ደፋር ቀጥተኛን ፤ልታይ ልታይ ማትል፤የተለየ ስብዕና ያላት ልጅ ነበረች..እኔ ግን ይሄንን ሁሉ አይቼና መዝኜ ሳይሆን ዝም ብዬ ድንገት ሳያት ድንገጥ ስላልኩባት ነው ያፈቀርኳት፡፡ የመጀመሪያ እይታ ስንተያይ ከአይኖቾ የተረጩ ብርሀን ልቤን ሰንጥቆት ስለነበረነው፡፡ከስድስት ወር በኃላ ተጋባን፡፡በሁለት አመት ውስጥ የተደራጀ ቤትና ኑሮ ኖረን..ሁሉነገር እስደሳችና የገነት ኑሮ መሰለ…ከትሪን ሌላ ካትሪንን አረገዘች፣፣በቃ በደስታ አቅሌን ልስት ደረስኩ፡፡ ወደኢትዬጵያ ተመልሶ ለዚህ ህዝብ መሲ የመሆን እቅዴ እየደበዘዘ ሙሉ በሙሉ በአሜሪካ ኑሮ እየተሰባኩ በአሜሪካኖች ስነልቦና እየተዋጥኩ ሄድኩ፡፡
ከኢትዬጵያ ጋር የሚያገናኙን ወላጆቼ ነበሩ፡፡ ለእነሱ በሶስት ወርም ሆነ በስድስት ወር ለእኔ ትንሽ የሚባል ለእነሱ ግን ህይወታቸውን ሊቀይር የሚችል አይነት ብር እልክላቸዋለሁ…በቃ
ከዛ ሱዛና ተወለደች…የእኔ ሱዛና ትንሽዬ መልአክ ነበር የምትመስለው፤እጆቾ ድንብሽብሽ ያሉ አይኖቾ የተቁለጨለጩ…አቤት ሁሉ ነገር እንዴት ፐርፌክት እንደነበረ….ሱዛና ተወልዳ ስድስት ወር ሳይሞላት የካትሪና እናት ሞተችና ወደ 5 መቶ ሚሊዬን ዶላር ሀብት ያለውን ያን ካማፓኒ ወረሰች በዛን ጊዜ ካትሪን ስራዋን ሙሉ በሙሉ ለቃ የቤት እመቤት ሆና ነበር ፡፡እዛው እቤት ሆና የእድሜ ልክ ታለንቶ የሆነው ሙዚቃ ላይ ትሰራ ስለነበረ ወደስራ ተመልሶ ካምፓኒውን የማስተዳደሩ ፍላጎት ምንም አልነበራም..በዛ ምክንያት እኔ የካማፓኒው ዋና ሰው ሆንኩ…ከዛ ካትሬን ሌላ ልጅ አረገዘችልኝ…ታዲያ የዛ ሁሉ የተትረፈረፈ የቤተሰብ ደስታ፤ የዛ ሁሉ የተትረፈረፈ ሀብት ባለቤት የሆንኩት ያ ሸራ ጫማ መግዣ ይቸግረው የነበረው?ያ በሶ እየበጠበጠ በመጠጣት ረሀቡን በማስታገስ የተማረው ቀናው ነኝ...ብዬ በመደመም ሰው ከለፋና ከጣረ.. የት ድረስ መድርስ እንደሚችል እና እድልም ለእሱ አጎብድዳ እንደምታገለግለው ላገኘሁት ሰው ሁሉ ልክ እንደሞቲቬሽናል እስፒከር በመጎረር ስተርክ የምውል በራስ መተማመኔ ጣራ የነካ ሰው ሆንኩ…..፡፡
ታዲያ ምን ሆነ ዳቢሎስ ቁጣውን በምድር ላይ አዘነበ….እግዚያብሄርም ተባባሪው ነበር…ወይንም መጀመሪያውኑ ዋናው እቅድ የራሱ የእግዚያብሄር ይሆናል፡፡ ጃንዋሪ 2020 አካባቢ ከካምፓኒው ጋር ለተያያዘ ስራ ቻይና ለአንድ ወር ቆይቼ ነበር…በወቅቱ ቻይና አዲስ ቨይረስ መከሰቱን እየተወራ ነበር.ወደአሜሪካ በተመለስኩ በቀናት ውስጥ ቨይረሱ በቻይና ምድር እየተስፋፋ መሆኑን መንግስት ግን የደበቀ መሆኑን ሀኪሞች መረጃውን እያሾለኩ ማውጣት ጀመሩ የቻይና መንግስትም አመነ፣ብዙ ሰዎች እየሞቱበት እነደሆነ ተናገረ..ከዛ ሌሎች ሀገሮችም ተዛመተ አሜሪካ ገባ ተብሎ ሶስት ቀን ሳይሞላው ካትሪን ያተኩሳት ጀመር፤ወዲያው ትንፋሽ አጠራት …ጉሮሮዋ ቆሰለ..… ዶክተራችን መጥቶ አያትና

👍94❤5🥰2👏2
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_አምስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
የተንታራሰችው ትራስ የሌላ ሰው ጠረን ይዞል…ደስ የሚል ተፈጥሯዊ ጠረን…እዚህ አልጋ ላይ አብሯት የተኛ ወንድ ፋሲል ብቻ ነበር ፤እሱንም ጨክና አስገድለዋለች….ትናንት ሌላ ወንድ በራሱ ፍቃድ ሰተት ብሎ ገብቶ ከጎኗ በመተኛት አስደምሟታል፡፡ማስደመም ብቻም ሳይሆን ልቧንም ሸርሽሮባታል… ሚኒዬነሩ ዘበኛዋ….ታሪኩ ራሱ ህልም ነው የሆነባት….ስለእሱ እያሰበች የመኝታ ቤቷ በራፉ ተከፈተ …አለምን ነበር የጠበቀችው….ወደውስጥ እየገባ የነበረው ግን ቀናው ነበር…የሼፎችን አይነት አለባበስ ለብሷል…በእጁ ላይ ባለ ሰፋ ያለ ትሪ ላይ ትናንሽ ሳህኖች ተደርድረው በዛ ያሉ ምግቦችን ይዘዋል፡፡
ምግቡን መኝታ ቤት የምትገኘው አነስተኛ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠና መኝታ ክፍል ውስጥ ወዳለ አነስተኛ ፍርጂ በመሄድ ውሀ አወጣ… አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠ…ከዛ ከምግቡ ጠቀለለና በተኛችበት ወደአፏ አስጠጋላት… በጣም ከመደንገጧና ከመደመሟ የተነሳ ያለምንም ተቃውሞ አፏን በጠባቡም ቢሆን ከፈተች…አጎረሳት…፡፡እንደምንም አላምጣ ስትወጥ እየጠበቀ ያጎርሳታል.. በመሀከል ለራሱም አንድ ሁለቴ ይጎርሳል… እደምንም ብላ አንድ ስምንት የሚሆን ጉርሻ ጎረሰችና ከአቅሟ በላይ ሲሆንባት በቃኝ አለችው፡፡
ያ ምግብ ትብለጥን ወደ ወህኒ ልካ በክፍሏ ከተከተተች በባለፈው ሁለት ወር ውስጥ ወደሆዷ የገባ ብዛት ያለው ምግብ ነው። እሱም ለራሱ የተወሰነ ከጎራረሰ በኃላ ምግብ የተቀመጠበትን ጠረጴዛ ከአልጋው ራቅ አድርጎ አስቀመጠና የታሸገ ውሀውን በማንሳት ክዳኑን ከፈተና አቀበላት። ከትራሷ በመጠኑ ቀና ብላ የተወሰነ ጠጣችለትና መልሳ ሰጠችው።
"ሌላ የምትፈልጊው ነገር ከሌለ መሄዴ ነው? "አላት። "እስኪ ቁጭ በል"አለችው።
ጥያቄዋን ተቀብሎ ከአልጋው ጠርዝ ላይ መልሶ ተቀመጠ"ደህና ነህ አይደል..? ማለቴ ትናንት ህመምህን ለእኔ ስትል ..."
"አታስቢ ሰላም ነኝ"
"ጥሩ..ጥያቄ ብጠይቅህ ቅርይልሀል?"
"የፈለግሽውን"
" ካምፓኒው ማለቴ የባለቤትህ ነበር..አሁን ማን ወረሰው?"
"ማንም ..አሁንም የእኔ ንብረት ነው..አሁንም በጥሩ ሁኔታ እየሠራ ነው..የእሷ ስም የያዘ ካምፓኒ በመሆኑ የበለጠ እንዲያድግ ነው የምፈልገው.."
"እና የአንተ በቅርብ አለመኖርህ ችግር አይፈጥርም"
"በፍፅም… ያ ካምፓኒ ከቤተሰብ ሲዎረስ የመጣና ከ80 ዓመት በላይ እድሜ ያለው ነው..እዛ ደግሞ እንደእኛ ሀገር አይደለም ..ነገሮች በህግና በስርዓት ስለሚመሩ በተለይ የደረጀ ድርጅት ባለቤቱ ቢኖርም ባይኖርም ልዩነቱ ያን ያህል ነው።ደግሞም እንደእቅዴ ከዛሬ 15 ቀን በፊት ተመልሼ ስራዬ ላይ የመሆን እቅድ ነበረኝ››
‹‹እና ታዲያ ለምን ሳትሄድ…?ደግሞስ እንደዛ ሚኒዬነር ሆነህ እዚህ ዘበኝነት ለምን ?አልገባኝም።››
‹‹እኔም አልገባኝም..በነገራችን ላይ እስከአሁን የካምፓኒው ወስጄ የተጠቀምኩት ብር የለም… እንደዛ ለማድረግ እቅድ የለኝም..እኔም የራሴ የሆነ የተወሰነ ብር አለኝ።ትናንት እንደነገርኩሽ እዚህ የመጣሁት ለስድስት ወር ነበር… እንደመጣሁ ለሁለት ወር ሆቴል ነበር ያረፍኩት.. ግን ሰለቸኝ። አፓርታማ ተከራይቼ ልወጣ አስብኩና ድንገት የእብደት የሚመስል ሀሳብ መጣብኝ።..ለምን መልሼ እንደድሀ አልኖርም..ምን አልባት ያ ሁሉ ቅጣት የመጣብኝ የማይገባኝ የድሎት ቆጥ ላይ ስለተንጠለጠልኩ ይሆናል ..እስኪ ለትንሽ ወራትም ቢሆን ድህነትን መልሼ ላጣጥመው ብዬ አሰብኩና ከክፍለ ሀገር ስራ ፍለጋ እንደመጣሁ ተናግሬ ቄራ አካባቢ አንድ ክፍል ቤት ተከራይቼ ገባሁ።እና በሰላም አንድ ወር ያህል እንደኖርኩ ከጎኔ ተከራይቶ የሚኖር አንድ ደላላ ነበር ሲገባ ሲወጣ ሰላም መባባል ጀመርን… ተግባባን በወሬ በወሬ ስራ አጥ መሆኔን ነገርኩት። እንደዛ የነገርኩት ስራ እንዲፈልግልኝ አልነበረም።እሱ ግን ዘበኝነት ካላስቀጠርኩህ..አሪፍ ቤት ነው ሴተ-ላጤ ነች..ካልተመቸህ ወዲያው ትለቃለህ ብሎ ድርቅ አለብኝ።ወደአሜሪካ ለመመለስ ከሶስት ወር ያነሰ ጊዜ ቢቀረኝም እንደአድቨንቸር ለምን አልወስደውም አልኩና እሺ አልኩት፡፡ አመጣና ካንቺ ጋር አስተዋወቀኝ..ስራ ጀመርኩ ..ይሄው አራተኛ ወር ልደፍን ነው።
ፈገግ አለችና ‹‹እና እንዴት ነው ስራው ተመቸህ?"ስትል ጠየቀችው፡፡
"አዎ..በጣም እንጂ ...ከመልመዴና ከመደላደሌ የተነሳ የራሴ ቤት ሁሉ እየመሠለኝ ተቸግሬለሁ።››
ዝም አለች‹‹...አመሠግናለሁ..እንዲህ እንዳወራ ስላደረከኝ አመሠግናለሁ።››
"አንቺም ዳግመኛ ለሌላ ሰው መጨነቅ እንድጀምርና ...አሁንም እስትንፋሴ ያልተቋረጠ ሰው እንደሆንኩ እንዲሰማኝ ስላደረግሺኝ በጣም አመሠግናለሁ"
‹እና አሜሪካ መሄዱንስ?›
‹‹በሁለት ወር አራዘምኩት››
‹‹ለምን እንደሆነ መጠየቅ እችላለሁ?››
‹‹ሳይሽ ባለፉት አመታት ያሳለፍኩትን መከራ ነው የምታስታውሺኝ..እንደዚህ ሆነሽ ብሄድ የሆነ ግማሽ ማንነቴን እዚሁ አንቺ መኝታ ቤት ቆልፌበት እንደሄድኩ ነው የምቆጥረው..እንደዛ ከሆነ ደግሞ ሄጄም ሰላም ማገኝ አይመስለኝም››
‹‹እና መቼም ከዚህ ካልተነሳሁስ?ምን ልታደርግ ነው?››
‹‹ሳባ በዚህች ሶስት ወር ስላንቺ እንደተረዳሁት አንቺ ደጋ ላይ በቅላ ያደገች ..ግን ንፋስ ድንገት አንገዋሎ በረሀ መሀከል የጣላት ...ያንንም መልመድና መቀበል አቅቷት የደነገጠች የፅጌረዳ አበባ ነሽ...ያቺ አበባ ባለመደችው የውሀ ጥም ጉሮሮዋ ተሰነጣጥቆ እየሟሸሸች ነው። ...ያቺን ማራኪ ፅጌረዳ አበባ በፀሀይ ንዳድ ስትነድ የህይወት ፈሳሿ ከውስጧ ተሟጦ ሲያልቅ እያየሁ በከፍተኛ ትዕግስት እና በጥልቅ ሀዘን ስታዘብ ቆይቼያለሁ።ማየት ብቻም ሳይሆን ምን አልባት ላድናት እችል ይሆን ?በሚል ተስፋ ዙሪያዋን በመኮትኮት በኮዳዬ ለክፍ ቀን ብዬ ያኖርኩትን የውሀ ጠብታ በስሯ ዙሪያ ለማንጠባጠብ በጥቂቱም ቢሆን እየሞከርኩ ነው ፡፡ስሯ ግን በራሱ ሀዘን ጨልሞ መምጠጫ ቀዳዳውን ፅልመት ስለደፈነበት የዕንቁ ያህል ዋጋ ያላቸው ህይወት አድን የውሀ ጠብታዋቼን በከንቱ የበረሀው ንዳድ በላቸው።እና እኔ ከንቱው ከዚህ በላይ እዚህ ቆይቼ የፅጌረዳዋ ቅጠሎች ከመወየብና ከመጠውለግ አልፈው እስኪረግፋ ማየት አልችልም፡፡ደግሞ በቅጠል መርገፍ ብቻ የሚያበቃ መስሎ አልታየኝም...የግንድ መሞሸሽና ሙሉ በሙሉ መፍረስ ሊያጋጥም ይችላል...እኔ ታዲያ በየትኛው ብረት ልቤ ይሄንን እስከፍፃሜው ጠብቄ ማየት እችላለሁ..አይ እኔ ለዛ የተሰራሁ አይነት ሰው አይደለሁም..
እና ለእኔ ስትይ ይህቺን ፅጌረዳ አድኚያት ...ወይ የሚበቃትን ያህል የህይወት ውሀ ያለችበት በረሀ ድረስ በመውሰድ ስሯ እስኪረሰርስ፤ሙሽሽ ብሎ የተኛው ቅጠሏ እስኪነቃና እስኪቃና አጠጪያት… ወይ ደግሞ ቀስ ብለሽ ስሯን ሳትነኪ ዙሪያዋን በመቋፈር ከነስሯ ንቀያትና ቀድሞ ወደበቀለችበትና ወዳደገችበት ስፍራ... ወደለመደችውና ወደምትናፍቀው ቀሄ በመውሰድ መልሰሽ ትከያት።...ለዛ 15 ቀን

👍82❤11👏2🥰1😁1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት
፡
፡
#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ባለፋ ሶስት ወር ውስጥ ተሰምቷት የማያውቅ ደስ የሚልና የሚያፅናና ስሜት ተሰማት…..እናም ለመጀመሪያ ጊዜ ሰውነቷን ለመታጠብ ወደ ሻወር ቤት ገባች፡፡ግዙፉ መስታወት ፊት ቆማ የለበስችውን ቢጃማ በቁሟ አወለቀችና እዛው ከእግሯ በታች ወለሉ ላይ ረገጠችው…መላ እሷነቷን በፅሞና ተመለከተች…. ፀጉሯ በዛ ርዝመቱና ብዛቱ ጭብርር ብሎ ከመንግስት ተሰውሮ ዋሻ ውስጥ ለአመታት ተደብቆ የኖረ ሽፍታ አስመስሏታል፡፡ ….አማላይ የነበረው የሠውነቷ ቅርፅ አሁንም እንዳለ ቢሆንም የሰውነቷ ክብደት ግን በተጋነነ ሁኔታ መቀነሱ ወደፊት ወጥተው በጉልህ የሚታዩት አጥንቶቾና ወደ ውስጥ ጎድጉደው ጭል ጭል የሚሉ አይኖቾ ምስክር ናቸው፡፡ከሁሉም በላይ ያስደነገጣት ግን የብልት ፀጉሯ ነው…ከስራዋ ባህሪ አንጻር ለአመታት በሶስት ቀን አንዴ ስትላጭ የኖረች ሴትዬ ለወራት ችላ የተባለው የብልቷ ፀጉር በአስፈሪ ሁኔታ አድጎና ተንጨፍርሮ እርስ በርሱ ተቆጣጥሮ በመሀከል ስንጥቅ መኖሩን እራሱ በእጅ ዳብሰው ካልበረበሩት ማወቅ የማይቻልበት ደረጃ ላይ በመድረሱ አስደነገጣት….
….የቀኝ አጇን ዘረጋችና አንገቷን ጠምዝዛ ብብቷን ተመለከተች ..ተመሳሳይ ነው፡፡ በፀጉር ከመሸፈኑም በተጨማሪ ሽታ ከሩቁ ይገፋተራል፡፡ይሄ ሁኔታ ደግሞ ይበልጥ አስገረማት፡፡
‹‹ለምንድነው ግን በቁማችንም እያለን ጭምር ለጥቂት ቀናት ትኩረታችንን ከራሳችን ላይ ስናነሳ እንዲህ በፍጥነት የምንሸተው..?››ስትል ጠየቀች፡፡መልሱን ለመመለስ ግን ብዙም አላስቸገራትም፡፡ ምክንያቱም ከማሳጅ ስራዋ ጋ ተያይዞ ከወሰደቻቸው ኮርሶች አንደኛው የሰው ልጅ አመጋገብ ስርዓት በተመለከተ ነበር ፡፡ ከሺ አመታት በፊት የሞቱ ሰዎች መቃብር ተቆፍሮ ሲገኝና የጥርሳቸው ጤንነትና ጥንካሬ ሲፈተሸ አሁን ካለው የሰው ልጅ ጋር የማይነፃጸር እጅግ ንጹህና ጠንካራ እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡ምክንያቱም ደግሞ አመጋገባችን ሆኖ ነው የተገኘው፡፡አሁን አብዛኛው ምግቦች ከኬሚካል ጋ ንክኪ ያላቸው… ስኳርነት የበዛባቸውንና ጤንነትን ሳይሆን ጥፍጥና መሰረት ያደረጉ ናቸው…ስለዚህ እነዚህ ገብተው ተፈጥአዊ ሰውነታችንን በክለዋል….በዛ ላይ ምንቀባቸው ቅባቶች የምንረጫቸው ሽቶዎች፤ የምንታጠብበት ሳሙና በጠቅላላ እንዲህ በቀናት ውስጥ በቁማቸንን እንድንሸት ዋና ምክንያቶች መሆናቸው ለመረዳት ብዙ ምርምርም አያስፈልግም፡፡ ወደመኝታ ቤቷ ተመለሰችና የቁም ሳጥኗን ኪስ ከፈተችና የፀጉር መላጫ ማሽኗንና መቀስ አውጥታ በመያዝ ወደ ሻወር ቤት ተመለሰች፡፡ምንም ማሰብ እና መጨነቅ አላስፈለጋትም፡፡ከፀጉሯ ጀመረች…..ከርዝመቱ ወጥራ ወደፊት እየያዘች…..ወገብ ላይ ትጎምደው ጀመር፡፡ ወለሉ በተንጨባረረ እና በተቆጣጠረ
ፀጉር ተሞላ፡፡ ባለከመከም ጎፈሬ ሆነች፡፡በመስታወቱ የተለየች አይነች እስከዛሬ እሷ ራሷ ማታውቃት አይነት ሳባን ተመለከተች፡፡መቀሷን አስቀመጠችና ማሽኗን አመቻቸችና ወደብልቶ ጎንስ ብላ እግሯን ፈርከክ በማድረግ ታጭደው ጀመረ…..ሁሉን ነገር ጨርሳ ሰውነቷን ታጥባና ፀድታ ከሻወር ለመውጣት ከ2 ሰዓት በላይ ነው የፈጀባት፡፡
ከዛ ወደመኝታዋ ተመልሳ የተወሰነ እረፍት አደረገች.. ከተኛበት ብንን አለችና ስልኳን አነሳች፡፡ እንዲህ አይነት ጥንካሬ እና ፍላጎት በደቂቃ ውስጥ ከየት እንዳመጣች አታወቅም፡፡ደወለች..ከሶስት ጥሪ በኃላ ተነሳ፡፡
‹‹ሄሎ ዶክተር››
‹‹ሳባ ለመሆኑ በህይወት አለሽ…?ምን ነካሽ…?ሌላ ሌላው ይቅር እሺ ህክምናሽን ግን እንዴት ታቋርጪያለሽ…ያልተመቸሽ ነገር ካለም እኮ ተነጋግረን ማስተካከል እንችል ነበር..››
‹‹ምን አልተመቻትም ብለህ አሰብክ…ያደረኩት ነገር አግባብ ነበር እንዴ?›ስትል መልሳ ጠየቀችው፡፡
‹‹እሱን ከህክምናሽ ጋር ምን አገናኘው..ምን አልባት በእኔ ህክምናውን መከታተል የሚከብድሽ ከሆነ እኮ በሀገሪቱ ያለሁት የስነ-ልቦና ሀኪም እኔ ብቻ አይደለሁም
… ተነጋግረን ሁኔታዎችን መስመር ማስያዝ እንችል ነበር››
‹‹ኖኖ ዶክተር እንደዛ አስቤ አይደለም…እኔ እንደውም አንተ ካላከምከኝ ማንም ሊያክመኝ አይችልም››አለችው፡፡
የተናገረችው ትክክል ይሁን አይን እራሷም እርግጠኛ አይደለችም…እርግጥ ከእሱ ውጭ በሌላ ሀኪም መታከም አትፈልም….ደግሞም በእሱም ቢሆን መታከሙን የምትችል መስሎ አልተሰማትም፡፡ህመሟ አካላዊ ቢሆን ችግር የለውም፡፡ ጉበቷ ወይም ኩላሊቷ ቢሆን ወይም ማህፀኗን አሟት ልብሶቾን አወላልቃ እግሮቾን አንፈርክካ መላ ሚስጥሯን ለእሱ ማሳየት ቢሆን ምንም አይመስላት ነበር፡፡…..እሱ ፊት ስትቀርብ ከኤፍሬም ጋር በገዛ ምርመራ ክፍሉ የሰራችው ነውር ነው ትዝ የሚለው የገዛ ወንድሙን ስታማግጥበት…ዝግንን አላት፡፡
‹‹እና ታዲያ ለምን እራስሽን ሰወርሽ….?እንዴት እዲህ ይጠፋል…..?ደግሞ ለህክምና ፋይል ላይ ያስመዘገብሽ መረጃ በጠቅላላ የተሳሳተ ነው….አድራሻሽን ጭምር ..አንድ ትክክል የሆነው ስልክ ቁጥርሽ ቢሆንም እሱንም ጠርቅመሽው ይሄው ስንት ወር፡፡››
ደስ አላት…ስለእሷ እንዲህ ሲጨነቅና ሲብሰለሰል መክረሙ ደብዝዞ እና ሊከስም ጫፍ ላይ ደርሶ የነበረ ተስፋዋ በጥቂቱም ቢሆን ቢል ቢል እያለ እንዲነቃቃ ተጨማሪ ነዳጅ ሆኖ ሲያነቃቃት ተሰማት፡፡
‹‹እና አሁን እንዴት ነሽ…?የት ነሽ..?ሀገር ውስጥ ነሽ?››
‹‹አዎ እዚሁ ነኝ፡፡››
‹‹እና እንዴት ነሽ?፡፡››
‹‹እኔ እንጃ ..ምን ላይ እንደሆንኩ አላውቅም…እንዴት እንደሆንኩ አላውቅም….. መኖሬን እራሱ አላውቅም….ለምን አሁን አንተ ጋ እንደደወልኩም አላውቅም….
››አለችው፡፡
ከንግግሯ አሁን ያለችበት ሁኔታ ከወራት በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ካገኛት እጅጉኑ የከፋ እንደሆነ ወዲያው ተረዳ….ስለእሷ ሲያስብና ሲጨነቅ የከረመው ግን ከዚህም የከፋ ነገር ላይ እራሷን ትጥላለች ብሎም ጭምር ስለሰጋ ነበር…እራሱን ያጠፋ ሰው ዜና በሶሻል ሚዲያም ሆነ በሜን እስትሪም ሚዲያ ሲሰማ ደንግጦ በንቃት ዜናውን እስከመጨረሻው ለማየት ሲጥር የነበረው እሷን አስቦ ነው፡፡አሁን ግን በከፋ ሁኔታ ላይም ሆና ቢሆን በህይወት መኖሯ ብቻ አስደሰተው፡፡
‹‹አይዞሽ ይሄ በማንኛውም ሰው ላይ በሆነ ጊዜ ላይ የሚከሰት ነው..አንቺ ደግሞ ከዕድሜሽ በላይ ብዙ ነገር ያየሽና ብዙ ነገር ምታውቂ ጠንካራ ልጅ ነሽ...እኔም ደግሞ በፈለግሽኝ ጊዜና መንገድ ከጎንሽ ነኝ፡፡››
‹‹አንተ ከጎኔ መሆንህን በመስማቴ ተደስቼያለሁ…አመሰግናለሁ፡፡››
‹‹እና መች ብቅ ትያለሽ?›
‹‹እኔ እንጃ››አለችው የምትለው ግራ ገብቷት…
‹‹እኔ እንጃ ማለት ምን ማለት ነው…ህክምናው ቢቀር አንኳን ናፍቀሺኝል… ሆስፒታል መምጣት ካስጠላሽ የፈለግሺው ቦታ መገናኘት እንችላለን፡፡››
‹‹ካልክ ነገ ስንት ሰዓት ይመችሀል?››
‹‹እንቺ የሚመችሽን ሰዓት ነገሪኝ እኔ ፕሮግራሜን አሬንጅ ማድረግ እችላለሁ›› እሷን ከማግኘት የሚቀድምበት ምንም ጉዳይ የለውም፡፡
‹‹በቃ 10 ሰዓት እንገናኝ..››
ደስ አለው….‹‹እሺ የት እንገናኝ?›› ነገረችው
‹‹ችግር የለም….እንገናኛለን…››
‹‹እሺ ዶ/ር ….አመሰግናለሁ››

👍69❤7👏4🥰2
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ለ15 ቀን ያህል በሶስት ቀን አንዴ እየተመላለሰች ህክምናዋን መከታተልና የታዘዘላትን መድሀኒት በመጠቀም ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ከጀመረች በኃላ... ቀናውና ሳባ እሷ መኝታ ቤት አንድ አልጋ ላይ ጎን ለጎን ተኝተው እያወሩ ነው።
‹‹እንግዲህ አሁን ጥሩ ሁኔታ ላይ ነሽ ...ቀጣይ እቅድሽ ምንድነው?›› "ቀጣይ እቅዴ አንተን ማግባት"አለችው ፍርጥ ብላ
"እውነቴን እኮ ነው"
""ወደአሰላ እመለሳለሁ...እዛ የእንጀራ እናቴ የጀመረችልኝ በጣም እስፔሻል የሆነ ስራ አለ …እሱን በሰፊው መስራት ነው የምፈልገው።››
"ምንድነው ስራው?"
"ልነግርህ አልችልም...የዛሬ ሳምንት አብረን እንሄዳለን ..የምወዳት እናቴን አስተዋውቅሀለው..ትንሹ ወንድሜም እርግጠኛ ነኝ ይወድሀል... እናም የምወዳትን እትብቴ የተቀበረባትን ከተማዬን አስጎበኝሀለው...ከዛም የምሰራውን ስራ አሳይሀለው።››
"በጣም ደስ ይለኝ ነበር...ግን እኮ የዛሬ ሳምንት የምበርበት ቀን ነው፡፡"
"ምን?"ብላ ከተቀመጠችበት ተነሳችና ቁጭ አለች።
ጭራሽ ትዝ ብሏት አስባበት የማታውቀው ነገር ነው፡፡
ቅዝዝ እና ክፍት ብሏት፡፡"የእውነት ጥለኸኝ ልትሄድ ነው...?."ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹ምን ማድረግ እችላለሁ...?እሺ ብትይኝማ ወደአሜሪካ ብወስድሽ ደስ ይለኛል "
‹‹እንደዛማ ማድረግ አልችልም...ለስንድ ቃል ገብቼላታለሁ....አባቴን የሚያስደስት ስራ መስራት ነው የምፈልገው፡፡ሀገሬን ለቆ የመሄድ እቅድ የለኝም"
"ይገባኛል....ግን የእኛ ነገርስ?"
"እኳ አትሂድ ምልህ እኮ ለእኛ ብዬ ነው።...አሜሪካ ምን አለህ ?ገንዘብ ብቻ ነው ያለህ። እዚህ ለዛውም አሰላ ለመኖር ያንተ ብር አያስፈልገንም።እኔ ሁሉንም ነገር አስተካክላዎለው።ይሄንን ቤት እንሸጥና ጥሩ ብር እናገኛለን፡፡ ከዛ አሪፍ የሆነ ገቢ ሚያስገባ ድርጅት እናቋቁማለን..፡፡››
"መሄድ እኳ የምፈልገው ለገንዘብ አይደለም...የካትሪንና የሱዛና ስም ከስሞ እንዲጠፋ ስለማልፈልግ ነው።በካምፓኒው አመታዊ ትርፍ የሚንቀሳቀስ ካትሪን ኤንድ ሱዛና ፋውንዴሽን የሚባል የእርዳታ ድርጅት ለማቋቋም አስቤ ነበር።
"የሚገርምና ደስ የሚል ሀሳብ ነው።.....ግን ፍውንዴሽኑ ምን ላይ ነው የሚሰራው..?ሀሳብህ እንዴት ነው?።››
"እሱን ገና አልወሰንኩም...ይሄን አይነት ሀሳብ እራሱ ወደ አእምሮዬ የመጣው እኮ አሁን በቅርብ እዚሁ አንቺ ቤት ሆኜ ነው።"
"አትለኝም...እየቀለድክ መሆን አለበት?"
"የእውነቴን ነው፡፡ ወደ ኢትዬጰያ ስመጣ የምኖርበት የህይወት አላማ የሚኖር ከሆነ በስክነትና በመረጋጋት ውስጥ ሆኜ ለመፈለግ ነበረ...እና የዛሬ ወር አካባቢ
እዚሁ አንቺ ቤት ሆኜ ሳውጠነጥን ነው ሀሳብ የመጣልኝ። ስለዚህ ዝርዝሩን ገና አሜሪካ ከሄድኩ በኃላ ነው የተወሰኑ ጥናቶችን በማድረግ የምወስነው።"
‹‹እሺ ገባኝ ..ግን ለእኔ ስትል አንድ ነገር አድርግ...››
‹‹ጠይቂኝ".
‹‹ ..ወደአሜሪካ የመሄድ ቀንህን በአንድ ወር አራዝመው..."
የተወሰነ እንደማሰብ አለና‹‹ጥሩ እሺ አራዝመዋለሁ...እና ለአንድ ወር እንዴት አድርገሽ ልትንከባከቢኝ ነው ያሰብሽው?››
‹‹እርግጠኛ ሁን …አሪፍ የሚባል ጊዜ እንድታሳልፍ አደርጋለሁ…››
‹‹እኮ እንዴት እንዴት አድርገሽ..?››
‹‹በመጀመሪያ አሰላ ወስድሀለሁ...ከምወዳት እንጀራ እናቴና ከወንድሜ ጋር አስተዋውቅሀለው...ቀጥሎ ደሴ እንሄዳለን?"
የደሴን ድምፅ ሲሰማ ደነገጠ "ምን ..?ደሴ? ምን ለመስራት?"
"ቤተሠቦችህን ሳታይ በምንም አይነት መንገድ መሄድ የለብህም..እነሱ በአሁኑ ጊዜ በምድር ላይ የቀሩህ የቅርብህ የሆኑ ሰዎች ናቸው።እንዳልከው እነሱን ማግኘት የማትፈልገው የሚጠይቁህን ጥያቄ መመለስ ፈርተህ ብቻ አይመስለኝም?"
በገረሜታ አፍጥጦ እያያት ‹‹›.እና ለምን ይመስልሻል?"
"ዳግመኛ የእኔ የምትላቸውን ሰዎች ስትነጠቅ ላለማየት ከለህ ፍራቻ ነው። ጨለማውን እየሸሸህ ነው።በጭለማው ሰንጥቀህ ካላለፍክ ደግሞ ብርሀን የሚባል ነገር አታይም…"
"ዋው...የስነ-ልቦና ባለሞያዎችን ታስንቂ የለ እንዴ?"
"አዎ... በበሽታዬ የተነሳ ከእነሡ ጋር አመታትን አሳለፍኩ እኮ ..አሁን አሁን እንደእነሡ ማሰብ ጀምሬለሁ።"
‹‹..እሱን በደንብ እያየሁ ነው…ግን ነገሩ እንዳልሽው ቀላል አይደለም.."
‹‹ይሄውልህ ቀናው እኔ ካንተ አላውቅም… አንድ ጓደኛዬ ‹ሁሉም ድርጊቶች የአምላክን ፍቃድ ያገኙ ናቸው::››የሚል እምነት ነበረወ… ይሄ ጓደኛዬ ሀይማኖተኛ አይደለም…ማለቴ ማንኛውንም ሀይማኖት አይከተልም….ግን በእግዚያብሄር ያምናል..መንፈሳዊ ሰው እንደሆነም ይናገራል፡፡እና እሱ እኛ የሰው ልጆች የእግዚያብሄር ህልውና አንድ ቅንጣት ሴሎች ነን፡፡ከመወለዳችን በፊት የእግሩ ሴል ከሆንን ከተወለድን በኃላ ምን አልባት የእጆቹ ሴል ሆነን ሊሆን ይችላል.. ከሞትን በኃላ ደግሞ የጭንቅላቱ ወይም የፀጉሩ አንድ ቅንጣት ሴል ነው የምንሆነው…ስለዚህ ለእግዚያብሄር ከመወለዳችን በፊትም በተወለድን ጊዜም ሆነ ከሞታችን በኃላም ተመሳሳይ ዋጋ ነው ያለን… ቦታችን እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸን ካልሆነ በስተቀር ምንም የሚቀየር ነገር የለም…››
‹‹ይመስለኛል ጓደኛሽ ለማለት የፈለገው…ሞት በእግዚያብሄር ዘንድ ያለው ትርጉም እኛ እንደምናስበው አይደለም ለማለት መሰለኝ››
‹‹በትክክል….በቃ አሁን እንተኛ"
‹‹እሺ… ከመተኛታችን በፊት ግን አንድ ጥያቄ መልሺልኝ?›› "ምንድነው?"
"እናትሽ..ማለቴ እንጀራ እናትሽ ላንቺ ብላ የጀመረችውን ስራ ምንድነው?እስቲ ንገሪኝ"
"ምነው ሄደህ እስክታየው መጠበቅ አቃተህ..?እኔስ እንደሰርፕራይዝ እንዲታይልኝ ፈልጌ ነበር...ያው ከዚህ በፊት ታሪኬን ስተርክልህ ስለአባቴ አደጋ ነግሬህ ነበረ.. በመኪና አደጋ ሁለቱም እጀግሮቹን አጥቶ በዊልቸር ለአመታት ሲገፍ ኖሮ እንደሞተ...እና ድንቋ እናቴ ስንድ በተለያየ ምክንያት አደጋ ደርሷባቸው አካል ጉዳት ላይ የወደቁ ግን ደግሞ ለመታከምና ለማገገም የፋይናንስ አቅም የሌላቸውን ጉዳተኞች እቤት በመከራየት ተንከባካቢ ቀጥራ ሀኪም ቤት እያመላለሰች ትንከባከባቸዋለች ፡፡ሙሉ በሙሉ ድነው ህክምና የማይፈልጉበት ደረጃ ላይ ሲደርሱ የተሻለ ነገር ካገኙ መርቀዋትና ተሰናብተዋት ይሄዳሉ። እርግጥ ካላት አቅም አንፃር ለጊዜው አስር የሚሆኑ ሰዎችን ነው የያዘችው..እኔ አቅሜን አጠናክሬ ስሄድ እስከመቶ ሰው መቀበልና መንከባከብ ምችል ይመስለኛል..በሂደት ደግሞ ፈንድ በማፈላለግ…እያስፋፋሁት ሄዳለሁ…..ያን በማድረጌ ምን አልባት ባለፉት አስር አመታት ውስጥ የሰራዋቸውን ቆሻሻ ስራዎች እግዚያብሄር ይቅር ይለኝ ይሆናል፡፡በዛ ላይ ደግሞ ከአባቴ የሙት መንፈስ ጋር ያለኝን ቀረቤታ
አጠብቅበታለሁ…እያንዳንዱን አካል ጉዳተኛ ስንከባከብ አባቴን እንደተንከባከቡኩ ነው ሚሰማኝ..እሱም ባለበት ሰማይ ቤት ሆኖ ይደሰትብኝ ይሆናል፡፡››
‹‹የሚገርም ነው..ምን አልባት እኔና አንቺ መገናኘታችን እንዲሁ በዘፈቀደ የሆነ ነገር አይመስለኝም…የሆነ ታላቅ ህይወት ምስጢራዊ ተልዕኮ ያለው ሊሆን ይችላል፡፡››
‹‹አልገባኝም››

👍106❤8👎1😁1
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================
ጥዋት አንድ ሰዓት ተኩል ሲል ሁሉም ከእንቅልፋቸው ተነስተው ሳሎን በረንዳ ላይ ቁርስ ለመብላት ጠረጴዛ ከበው ተቀምጠዋል፡፡
ሰሎሜ ከሰራተኛዋ ጋር ተጋግዛ ቁርስ ለመስራት 11፡30 ላይ ነበር አልጋዋን ለቃ የተነሳቸው፡፡እርግጥ ማታ ሰባት ሰዓት አካባቢ ወደመኝታዋ እንዳመራች ቀኑን ሙሉ ስትደክም ስለዋለች ወዲያው ነበር እንቅልፍ የወሰዳት…ቢሆንም ከ3 ሰዓት በላይ መተኛት አልቻለችም፡፡አስር ሰዓት ላይ ሙሉ በሙሉ ነቅታ ግን ደግሞ እዛው አልጋዋ ላይ ጀርባውን ሰጥቷት ከተኛው ባሏ ጎን በጀርባዋ ተንጋላ በመተኛት…የባጥ የቆጡን ስታብሰለስል ነበር፡፡ አንድን አውጥታ ሌላውን ስታወርድ ከቆየች በኃላ 11፡30 ሲሆን ተነስታ ወደኪችን ገባች፡፡ሰራተኛዋ ቀድማት ተነስታ ቁርስ ለመስራት ሽንኩርት ስትከታትፍ ነበር ያገኘቻት፡፡ከዛ እየተጋገዙ ሰሩና የሚፈልጉትን ቁርስ አንድ ሰዓት ላይ ጥንቅቅ አድርገው ሰርተው ጨረሱ…፡፡ወንዶቹ ተነስተው እና ተጣጥበው ጠረጴዛው ዙሪያ አስኪቀርቡ አንድ ሰዓት ተኩል ሆኖ ነበር፡፡ …ሁለት ሰዓት ላይ የቁርስ ፕሮግራሙ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ፡፡
‹‹ምድረ ስራ ፈት….እኔ እንግዲህ የመንግስት ኃላፊነት ያለብኝ ሰው ነኝ ፣ወደስራ ልሔድ ነው፡፡››አለ አለማየሁ፡፡
‹‹ስማ ሀገሪቱ እያደገች ያለችው በመንግስት ሰራተኞች ብቃትና ትጋት አይደለም እኮ…››አላዛር ነው የመለሰለት፡፡
‹‹ታዲያ በማን ነው?››
‹‹በእኛ በግል ባለሃብቶች ትጋትና ልፋት ነው፡፡›› አላዛር መለሰ፡፡
‹‹ታዲያ ምን ይሁን እያልክ ነው?››
‹‹ስራ ያለብህ አንተ ብቻ አይደለህም..እኔም ስራ አለብኝ ለማለት ነው››
‹‹አውቃለሁ…አንተ ግን አረፋፍደህ ባሰኘህ ሰዓት መግባት ትችላልህ ብዬ ነው››
‹‹አይ …ማርፈድ የስፍና ምልክት ነው ይባል የለ..አብረን እንውጣ፣ቢሮህ አድርሼህ ወደስራ ገባለሁ፡፡››
‹‹እንዴ የእኔ ቢሮ ቄራ ያንተ ቢሮ አራትኪሎ ዙሪያ ጥምዝ እኮ ነው››
‹‹ችግር የለውም…››ብሎ ከመቀመጫው ተነሳ..አለማየሁም ተከትሎት ተነሳ፡፡
‹‹እና ጥላችሁን ልትሄዱ ነው?››ሁሴን ጠየቀ
‹‹ምንም ማድረግ አንችልም..ሁለት ሁለት ተካፈልን ማለት ነው…››
‹‹ምሳ ሰዓት ትመጣላችሁ እንዴ?››ሰሎሜ ሁቱም ላይ ተራ በታራ አይኖቾን እንከባለለች ጠየቀች፡፡
እኔ እየዞርኩ ሳይቶችን የማይበት ቀን ስለሆነ ምመጣ አይመስለኝም..ምን አልባት ኩማንደር››
‹‹አይ እኔም አልችልም…ዲያስፖራው እሷ ካስደበረችህ ግን ራይድ ታክሲ ተሳፍረህ ቢሮ ድረስ ከች በል››
‹‹አንተ ፣እንዴት እንዴት ነው የምታስበኝ …?እኔ የማስደብር ሰው ነኝ?››
‹‹አይ ነገሩን ነው ያልኩት››
አላዛር‹‹በሉ ሄደናል…ማታ ተያይዘን እንመጣለን››አለና ፊቱን አዙሮ መንገዱን ቀጠለ
‹‹እሺ ሞቅ ሞቅ አድርገን እንጠብቃችኃለን››አለች ሰሎሜ ፡፡
አላዛር እና ኩማንደሩ መኪና ውስጥ ገብተው የጊቢውን በራፍ ዘበኛው ከፍቶላቸው ወጥተው ሲሄዱ ሁለቱም በትኩረት እየተመለከቷቸው ነበር፡፡?
‹‹የማየው ነገር ሁሉ ህልም ህልም እየመሰለኝ ነው››አለ ሁሴን
‹‹ምኑ?››
‹‹የአራታችን ከአመታት በኃላ እንዲህ አንድ ላይ መሰባሰብ››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው…መቼም ይሆናል ብዬ አስቤው አላውቅም ነበር….በተለይ አንተ ወደሀገር ተመልሰህ ትመጣልህ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር››
ትኩር ብሎ እያያት‹‹ለምን?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹ወደዚህ እንድትመጣ የሚያደርግ ምክንያት የለህማ››
‹‹ተሳስተሻል…አንቺ እስካለሽ ምክንያት አለኝ ማለት ነው››
ያሰበችውን መልስ ከአንደበቱ አውጥቶ እንዳይነግራት በመፍራትና ደግሞም በተመሳሳይ ጊዜ የሚለውን ለመስማት መጓጓት በሚታይበት ግራ በተጋባ ስሜት ‹‹አንቺ ስትል…ሶስታችንንም ለማለት ነው አይደል…?የልጅነት ጓደኞችህን?››
‹‹አዎ ..የአንቺ ግን በተለየ ነው…ሶስታችንም እናፈቅርሽ እንደነበር ታውቂያለሽ አይደል?››
‹‹ይሄ ነገር እውነት ነው እንዴ…?በቀደም አሌክስ እንደዚህ ሲለኝ ሙሉ በሙሉ አላመንኩትም ነበር…ዛሬ አንተ ደገምከው››
‹አይ እወነቱን ነው..ህፃን ሆነን ጀምሮ የሶስታችንም የወደፊት ምኞታንና እቅዳችን አንቺን ማግባት ነበር..››
‹‹የህፃንነት ምኞታችሁ ነዋ..ስትጎረምሱ ግን ተዋችሁት..እንደዛ ነው አይደል?››
‹‹አይ ተሳስተሻል..ስንጎረምስ እንደውም የበለጠ እያፈቀርንሽ..የበለጠ እየተራብንሽ ነው የሄድነው…፡፡››
የምትመልሰው መልስ ስለጠፋት ዝም አለች…..
‹‹ምነው ሶስታችንም እንደምናፈቅርሽ ስላወቅሽ ደበረሽ….?ማለት ከዳተኛ ጓደኞች መስለን ታየንሽ?››
‹‹አይ ..ማንኛዋም ሴት እኮ በመፈቀሯ አይደብራትም..እንደውም ኩራትና ደስታ ነው የሚሰማት…ግን ያልተዋጠልኝ የምትሉትን ያህል የምታፈቅሩኝ ከሆነ ለምን ጥላችሁኝ ተበታተናችሁ…አብሮኝ አስከመጨረሻው ከጎኔ የነበረው አላዛር ነው…እናም አፈቅርሻለው ቢለኝ የማምነው እሱን ነው፡፡››ስትል በእውነት የምታምንበትን ነገር ነገረችው፡፡
‹‹እዛ ላይ ትክክል ነሽ…የአሌክስን አላውቅም …እኔ ግን ያው እንደምታውቂው ከዩኒቨርሲቲ ልመረቅ ጥቂት ወራት ሲቀረኝ አንድ የቀረችኝ ብቸኛ ዘመድ እናቴ ሞተች..ያ በጣም ነበር ያበሳጨኝ..እና በዛ ስሜት ላይ እያለው ነበር እስኮላሩን ያገኘሁት…ያ ለእኔ ታላቅ እድል ነበር..አሻፈረኝ ብዬ የማልገፋው እድል..ምክንያቱም ምንም የሚረዳኝ ሌላ ይቅር የኮፒ ሳንቲም የሚሰጠኝ ዘመድ አልነበረኝም፡፡ለትምህርቴ ያለኝን ፍቅር ደግሞ የምታውቂው ነው…እና እድሉን ሳገኝ በደስታ ነበር የተቀበልኩት..ያንን ስቀበል አንቺን ያሳጣኛል የሚል ምንም አይነት ጥርጣሬ አልነበረኝም…መጀመሪያውኑ እኔ ከሁለቱ ጓደኞቼ በትምህርት የተሻልኩ በመሆኑ እኔን እንደምትመርጪ በእርግጠኝነት አምን ነበር..የውጭ እድል ሳገኝ ደግሞ በራስ መተማመኔ የበለጠ ጨመሮ ነበር፡፡››
‹‹ይገርማል ..ወንዶች ስትባሉ ሁላችሁም ጅሎች ናችሁ ማለት ነው?እንዴት እንደዛ ልታስብ ቻልክ… ?ከሄድክ በኃላ እኮ ለረጅም ጊዜ ግንኙነት አልነበረንም..ተመልሰህ እንደምትመጣ እንኳን አላውቅም ነበር…እንደው እንደምታፈቅረኝ አውቄ ላንተ ፍላጎት ቢኖረኝ እንኳን እንዴት ልጠብቅህ እችላለሁ?፡፡
‹‹ነይ እስኪ የሆነ ነገር ላሳይሽ?››ብሎ ከተቀመጠበት ..ተነሳ፡፡
‹‹ምንድነው?››ግራ በመጋባት ጠየቀችው፡፡
‹‹ዝም ብለሽ ተከተይኝ›› አለና እጇን ይዞ እየጎተተ ወዳረፈበት መኝታ ክፍል ወሰዳት…‹‹በገዛ ቤትሽ ልጋብዝሽ ተቀመጭ››አላት፡፡
አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠች፡፡
ግድግዳውን ተጠግተው ከተቀመጡ ሁለት ሻንጣዎች ወደአንደኛው ሄደና ዚፑን ከፈተው…አንድ አነስተኛ መጠን ያለው ላፕቶፕ አወጣና ወደእሷ ቀረበ ከጎና ተቀመጠና ላፕቶፑን ከፈተው…. ከዛ ኤሜል ከፈተና
‹‹አየሽ ይሄን ኤሜል››
ወደእሱ ጠጋ ብላ አየችው
salome2013@gmail.com ይላል
ግራ በመጋባት በትኩረት አየችው፡፡
‹‹ምንድነው ..?አልገባኝም››
‹‹ወደ እንግሊዝ ከሄዱክ ከተረጋጋው በኃላ ደውዬ ላገኝሽ ሞክሬ ነበር..ስልክሽ ግን አይሰራም..አላዛርን ስጠይቀው..ስልኳ ጠፍቶባታል ..አዲስ ቁጥር ደግሞ ገና አላወጣችም አለኝ፡፡ከዛ ኢሜልሽን እንዲልክልኝ የጠየቅኩት…እና ይሄንን ኤሜል ላከልኝ››
‹‹ግን እኮ ይሄ የእኔ ኢሜል አይደለም››

👍82❤11🤔7🔥5😱1
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
==================
....‹‹አሁንማ ያንቺ እንዳልሆነ አውቄያለሁ…በወቅቱ ግን የእሷ ነው ብሎ ስለላከልኝ ..ያንቺ በመሆኑ ምንም ጥርጣሬ አልነበረኝም..እናም በየጊዜው ደብዳቤ እፅፍልሽ ነበር፡፡ከአንቺም መልስ ለማግኘት አመታትን በናፍቆት ጠብቄያለሁ፡፡
‹‹ታዲያ ኢሜሉ የእኔ እንዳልሆነ እና ምትፅፍልኝ ደብዳቤዎች እንዳልደረሱኝ እንዴት ልታውቅ ቻልክ፡፡››
‹‹ከአላዛር ጋር ከተጋባችሁ ከአንድ ወር በኃላ በዚሁ ኢሜል መልስ ፃፈልኝ..መጀመሪያ ያንቺ መስሎኝ ፈንጥዤ ነበር …ሳነበው ግን የእሱ ነበር .. እንቺ አንብቢው››አለና ከፍቶ ሰጣት ፡፡
በጣም በመገረምና ምን ብሎ እንደፃፈለት ለማወቅ በመጎጎት ላፕቶፑን ተቀበለችውና ጭኗ ላይ አስቀምጣ ማንበብ ጀመረች፡፡
የልጅነት ጎደኛዬ ሁሴን እንዴት ነህ…?.የሰው ሀገር ኑሮ እንዴት ይዞኸል?እኔ በጣም ደህና ነኝ፡፡
ይሄንን ደብዳቤ ልፅፍልህ የተነሳሁት ይቅርታ እንድታደርግልኝ ለመጠየቅ ስለፈለኩ ነው፡፡የሰራሁት ነገር አግባብ ይሁን አይሁን አላውቅም፡፡ግን ደግሞ ደጋግሜ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ብገባ ተመሳሳዩን ነው የማደርገው፡እሰክዛሬ ለሰሎሜ እንዲደርሳት ስትልካቸው የነበሩ ኢሜሎች በአጠቃላይ ለእሷ አልደረሷትም….ምክንያቱም የምትልክበት አድራሻ የእሷ ነው ብዬ ብልክልህም እውነታው ግን በእሷ ስም የከፈትኩት እኔ ነኝ..እሷ ስለዚህ የኢሜል አድራሻ ምንም የምታውቀው ነገር የለም ፡፡ወንድሜ የምትፅፍላትን ደብዳቤ እንድታነበው ኢሜሉን ልሰጣት ያልቻልኩት ላወዛግባት ስላልፈለኩ ነው፡፡አየህ አንተም ሆንክ አሌክስ እዚህ አጠገቧ የላችሁም፡፡ስለዚህ እሷን በተመለከተ ከአመታት በፊት እርስ በርስ የገባነው ቃልኪዳን ተፈፃሚ ሊሆን አይችም…ከህፃንነታችን እስከዚህን ቀን ድረስ አብሬያት በብቸኝነት መዝለቅ የቻልኩት እኔ ብቻ ነኝ..የዚህንም ፍሬ አሁን ልቆርጥ ነው፡፡በቀደም እቴቴ ጋር እሷን ለማግባት ሽማግሌ ልኬ እሺ ተብያለሁ…ምን አልባትም ይሄ የኢሜል መልዕክት በምታነብበት ጊዜ እኔና እሷ ታጋብተን ባልና ሚስት በመባል አንድ ቤት ገብተን ይሆናል፡፡ለዛ ነው አሁን እውነታውን ልነግርህ የፈለኩት፡፡ይሄንን ጉዳይ ሰሎሜ አታውቅም፡፡ከፈለክ ግን ደስ ባልህ ጊዜ ልትነግራት ትችላለህ፡፡ከአሁን በኋላ የእኔ ስለሆነችም እንዳታገኛት እንቅፋት ልሆንህ እልፈልግም…ቢያንስ ጓደኛዋ ሆኖ የመቀጠል መብት አለህ፡፡ለዛ ነው ቀጥታ ስልክ ቁጥሯን በዚህ የኢሜል መልዕክት ላይ የላኩልህ፡፡
በል ወንድሜ ቅር በተሰኘህብኝ ነገር ሁሉ ይቅርታህን ጠይቃለው….የዘላለም ጓደኛህ አላዛር ነኝ፡፡››ይላል፡፡
የምታነበውን ማመን ነው ያቃታት፡፡ምን አይነት ምላሽ ሁሉ መስጠት እንዳለባት ማወቅ አልቻለችም፡፡
‹‹እነዚህ በዚህ የኢሜል አድራሻ ላንቺ የላኳቸው መልዕክቶች አሁን ጥቅም የሌላቸው ና ጊዜያቸውም ያለፈባቸው ቢሆኑም ያንቺው ናቸው…ቢያንስ በወቅቱ ስለአንቺ ምን አስብ እንደነበረና ምን ብዬሽም እንደነበረ ያስረዳሉ….ላፕቶፑን ውሰጄና ለማንበብ ዝግጁ በምትሆኚበት ጊዜ አንብቢያቸው››› አላት፡፡
ዝም ብላ እጇ ላይ ያለውን የተከፈተ ላፕቶፕ አጥፋ ዘጋችና ከተቀመጠችበት ተነሳች….‹‹አራት ሰዓት አካባቢ ወጣ እንላለን….እስከዛ አረፍ በል….››ብላው ከእሱ መልስ ሳትጠብቅ ላፕቶፑን ይዛ ቀጥታ ክፍሉን ለቃ ወጥታ ወደ ራሷ መኝታ ክፍል አመራች…ክፍሉን ከፍታ በቁሟ ነው አልጋዋ ላይ የተዘረረችው፡፡ኢሜሎቹን አሁን ከፍታ ለማንበብ እና ሌላ አይነት ውዥንብር ውስጥ እራሷን ለመሰንቀር አልፈለገችም…ተንጠራራችና ላፕቶፑን ኮመዲኖ ላይ አስቀመጠችው፡፡
‹‹በወቅቱ ሶስትም እንደሚያፈቅሩኝ ባውቅ ኖሮ ማንኛቸውን መርጥ ነበር?››እስከዛሬ አስባ የማታውቀውን ጥያቄ እራሷን ጠየቀች፡፡
‹‹ሶስቱንም በወጣትእናታቸው ምን እንደሚመስሉ …አቋማቸውን፤ ፀባያቸውን ፣የወደፊት ተስፋቸውንና ጉድለታቸውን መዘነች…..ልቧ አልማየሁ ላይ ተንጠልጥሎ ቀረባት…ግን ያ የሆነው በምክንያት ተመዘዝኖ በልጦ ስለተገኘ አይደለም….ብቻ በማታውቀው ምክንያት አንጀቷ በተለየ ሁኔታ ከልጅነታቸው ጀምሮ ለእሱ እንደሚንሰፈሰፍ ታውቃለች…ከሶስቱም ጋር ስትሆን ደስታና ምቾት እንደሚሰማት ታውቃላች ከእሱ ጋር ስትሆን ግን የበለጠ ድልቅቅ ያለ የመዝናናት ስሜት ነው የሚሰማት፡፡በሌላ ቋንቋ ለመግለፅ…ሶስቱም ጓደኞቾ ለእሷ ቤቷ ናቸው፡፡ግን ደግሞ አላዛርና ሁሴን ሳሎኗ ሲሆኑ..አላዛር ግን ጋደም ብላ እራሷን የምታድስበት….እርቃኑዋን ሆና ልብሷን የምትቀይርበትና የምትዋዋብበት የምቾቷ መጨረሻ ምሽግ የሆነው መኝታ ቤቷ ማለት ነው…እሱን እንደዛ ነው የምታስበው….ለዛም ነው እንደሚያፈቅራት እንኳን ሳታውቅ ጥሏት በመሄዱና ለስድስት አመት ከእሷ ጋር ያለውን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ስላቆረጠ..ክፉኛ ተቀይማው ነበረው….፡፡
አላዛር 12 ሰዓት ሲሆን ለአሌክስ ደወለለት›
‹‹ሄሎ ኮማንደር›››
‹‹ሄሎ አላዛር››
‹‹የት ነህ..ስራ ቦታ ነህ ወይስ ወጣህ?››
‹‹አይ ስራ ቦታ ነኝ….ምነው በሰላም?››
‹‹አይ ስራ ከጨረስክ መጥቼ ልውሰድህ ልልህ ነው፡፡››
‹‹ወደ የት?››
‹‹እንዴ ጥዋት ተነጋገርን አልነበር እንዴ..?ወደቤት ነዋ››
‹‹ዛሬ ቢያልፈኝ አይሻልም…?››
‹‹ኖኖ…እንደዛማ አይሆንም..አሁን ሰሎሜ ደውላልኝ አብረን እየመጣን ነው ብያታለው…ዲያስፖራውም ይጠብቀናል::››
‹‹በቃ እሺ…በቢሮ መኪና እራሴ መጣለሁ››
‹‹ለምን ..ሜክሲኮ አካባቢ ነው እኮ ያለሁት..ልምጣና አብረን እያወራን እንሄዳለን…..››
‹‹እሺ በቃ ና››አለና ስልኩን ዘጋው፡፡
‹‹ይሄ ሰውዬ ለምንድነው እንዲህ ሙጭጭ ያለብኝ?››ሢል ጠየቀ፡፡ነገረ ስራው ሁሉ ግራ እያጋባው ነው..መቼስ እንደዚህ የሚያደርገው የድሮ ጓደኛሞችን በአንድ ላይ በመሰብሰብ የድሮ ፍቅራችውን እንዲያገኙ ለማድረግ አይደለም..የሆነማ የተደበቀ ተልዕኮ አለው››ሲል አብሰለሰለ፡፡‹‹ይሄንንማ ፈልፍዬ እቅዱን ማግኘት ካልቻልኩ ምኑን ፖሊስ ሆንኩ?›› ሲል ፎከረ፡፡ከተቀመጠበት ተነሳና ከመስቀያ ላይ ጃኬቱን በማንሰት ለብሶ ከቢሮው ወጣ…የፖሊስ ጣቢያው ግቢ ውስጥ ወዲህ ወዲያ እየተንቀሳቀሰ አላዛርን መጠበቅ ጀመረ…ብዙ አላስጠበቀውም ..እንደደወለለት ፈጠን ብሎ ሄደና ገቢና ከጎኑ ተቀመጠ …ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤቱ መንዳት ጀመረ….
‹‹ውሎ እንዴት ነበር?››አለማየሁ ነበር የጠየቀው፡፡
‹‹ያው እንደተለመደው ነው..አንተ ጋስ?››
‹‹እኔ ጋርም እንደዛው…››
ለተወሰነ ደቂቃ በሁለቱ መካከል ጥልቅ የሆነ ዝምታ ሰፈነ..በኋላ ግን ኩማንደሩ ዝምታው ሰበረው
‹‹ዛሬ ቤቴ ለማደር ነበር እቅዴ››
‹‹ቤት ብቻህን ምን ትሰራለህ…?አብረን ተሰብስበን ስንጫወት እናመሻለን››
‹‹እሺ እንዲህ ተሰብስበን መጫወት ለምደን በኃላስ…?
ማለት ስንበታተን…?አንተ ሚስትህን አቅፈህ በሞቀ ቤትህ ትቀራለህ..እኔ ሚስኪኑ ወደወንደላጤ ቤቴ ስመለስ በፊት ከማውቀው በተለየ ሁኔታ ቀዝቅዞ ደባሪ ሆኖ እንደሚጠብቀኝ አታውቅም?››
‹‹ሚስትህን አቅፈህ በሞቀ ቤትህ ነው ያልከው?››
‹‹አዎ …ምነው››
‹‹አሽሙር አይደለም አይደል?››
‹‹እንተ ሰው ከመቼ ወዲህ ነው እንዲህ ተጠራጣሪና የሰው ንግግር መንዛሪ የሆንከው?››
‹‹እኔን እኮ የቆሰለ ነበር በለኝ…ማንኛውም ኮሽታ ያስደነብረኛል….››
‹‹አይዞኝ….ቁስልህ በቅርብ እንደሚጠግ እርግጠኛ ነኝ፡፡››
‹‹ልሄድ ነው››

👍56❤5
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================
‹‹እሺ በቃ ..እንዳልክ ይሁን ….እኔ እንዳግዝህ የምትፈልገው ነገር ካለ ምንም ሳታቅማማ ንገረኝ››አለው አለማየሁ ከልብ ለአላዛር ከፍተኛ ሀዘኔታ ተሰምቶት፡፡
‹‹እሺ….ለጊዜው እኔ እስክመጣ ቤት እንድትሆን ነው የምፈልገው..ማለቴ አንተና ሁሴን እኔ ቤት እንድትሆኑ እፈልጋለው››
ኩማንደሩ‹‹ያ ግን ምንድነው የሚጠቅምህ?››ሲል በገረሜታ ጠየቀው፡፡
‹‹ሁለት ጓደኞቾ አብረዋት ከሆኑ …ምንም ሳይታወቃትና ሳይደብራት ነው ህክምናዬን ጨርሼ የምመጣው…ብቻዋን ከሆነች ግን ማብሰልሰሏና መበሳጨቷ አይቀርም…ያ እንዳይሆን አግዙኝ››
‹‹ቀላል ነው..አንተ ብቻ ተረጋግተህ ችግርህን ለመቅረፍ ሞክር ››ሲል ቃል ገባለት፡፡
‹‹እሺ ሞክራለው››እርግጠኝነት በማይነበብበት የድምፅ ቅላጼ መለሰለት፡፡
‹‹ካልተሳካም ምንም ተስፋ አትቁረጥ..አየህ ትልቁ ነገር የችግርህ መነሻ ምን እንደሆነ በግልፅ አውቀሀል..ስለዚህ ምንም ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር አይኖርም…እዛ ካልተሳካ እዚህ መልሰን አንሞክራለን››
‹‹አመሰግናለሁ….››
//////
አላዛር ወደቱርክ በበረረ በሁለተኛው ቀን ሰሎሜ አለማየሁና ሁሴን እራት በልተው ቢራ እየተጎነጩ እስከምሽቱ ሰባት ሰዓት ሲጫወቱና ሲሳሳቁ ከቆዩ በኋላ ፤አለማየሁ ድንገት ሞባዩሉን አወጣና ስልኩን ካየ በኃላ ‹‹ሰዎች ነገ ሰኞ ነው..እኔ ደግሞ ስራ አለብኝ….እና ጥያችሁ ልገባ ነው››አላቸው፡፡
ሰሎሜም ‹‹አረ..ሁላችንም እንተኛ..ነገም እኮ ሌላ ቀን ነው››ስትል ለቀረበው ሀሳብ ድጋፍ ሰጠችው፡፡
ሁሴንም ‹‹እንደዛ ከሆነማ እንነሳ›› አለና የቀረችውን ቢራ ጨልጦ ቀድሞ ከመቀመጫው ተነሳ…ሁለቱም ተከትለውት ተነሱ፡፡
መራመድ ሲጀምሩ እሷን ከመሀከል አደረጓት….የሁሉም መኝታ ክፍል አንደኛ ፎቅ ላይ ሚገኝ ሲሆን የፎቁን መወጣጫ እንደወጡ በተከታታይ የሁለቱ መኝታ ክፍል ይገኛል…የእሷ መኝታ ክፍል ግን የግራውን ኮሪደር ይዞ መጨረሻ ላይ ነው የሚገኘው..መለያያቸው ላይ ሲደርሱ ‹‹‹እንግዲህ ስለያችሁ በእንባ ነው..ደህና እደሩ››አለቻቸው፡፡
‹‹አይ…እንሸኝሻለን…ክፍልሽማ ሳናደርስሽ አውላላ ሜዳ ላይ ጥለንሽ ወደቤታችን ብንገባ ቀልባችን አርፎ አይተኛም››አላት አሌክስ፡፡
ሁሉም በአንድነት ተሳሳቁ‹‹አይመሽባችሁም?››ስትል ቀልዱን በቀልድ መለሰች፡፡
‹‹ግድ የለም…ከመሸብንም እዛው እናድራለን››መለሰላት ሁሴን፡፡
‹‹እንግዲያው ሸኙኝ ደስ ይለኛል፡፡››ፈቀደችላቸው፡፡
መሀከላቸው እንዳደረጎት የግራውን ኮሪደር ያዙና ወደመኝታ ቤቷ መራመድ ጀመሩ…አስራአንድ ወይም አስራሁለት እርምጃ እንደተራመዱ መኝታ ቤቷ በራፏ ላይ ደረሱ፡፡
በራፉን ገፋችና ከፈተችው፡፡
‹‹አሁን ደህና እደሪ››ሁሴን ነው ተናጋሪው፡፡
‹‹አይ እዚህ ድረስ ለፍታችሁማ የሆነ ነገር ሳትቀምሱ አትሄዱም ..ግቡ››ብላ ቀድማ ገባችና የመኝታ ቤቱን በራ ወለል አድርጋ ከፍታ እንዲከተሏት ትጠብቅ ጀመር፡፡
ሁለቱ ወንዶች እርስ በርስ ተያዩ፡፡
‹‹እንዴ…ግቡ አይዟችሁ …አትፍሩኝ …መቼስ አቅም ኖሮኝ ሁለት ወንድ በአንድ ላይ አልደፍርም፡፡››
ሁለቱም በየልባቸው ሲፈልጉት የነበረ ነገር ስለሆነ ተጣብቀው እየተገፋፉ ገቡ፡፡በራፉን መልሳ ዘጋችና እየመራች ወሰደቻቸው፡፡መኝታ ቤቱ ግዙፍና ሳሎን መሳይ ነው..ከአልጋው በሶስት ሜትር ርቀት ያለ አነስተኛ ጠረጴዛን የከበቡ አራት ዘመናዊ ውብ ደረቅ ወንበሮች አለ፡፡እነሱን ከጠረጴዛው ስር እየጎተተች እንዲቀመጡ አመቻቸችላቸው፡፡ተቀመጡ፡፡
ወደኮመዲኖ ሄደችና ከስር ያለውን መሳቢያ ከፈተች፡፡ውብ ጥቁር እና አብረቅራቂ ካርቶን አወጣችና አምጥታ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠችው፡፡ሶስት ብርጭቆ አመጣችና ከፊት ለፊታቸው ደረደረች፡፡
‹‹ልብስ ልቀይር እስከዛ እራሳችሁን አስተናግዱ፡፡››
‹‹ወደ ክፍሌ ግቡ ስትይ እኮ ሻይ ወይም ቡና ልታቀርቢልን መስሎኝ ነበር፡፡››አላት ኩማንደሩ፡፡
‹‹ያው በለው…..እስኪ ካርቶኑን ክፈትና እየው .ቁርጥ ሻይ ነው የሚመስለው፡፡››.አለችና እየሳቀች ወደቁምሳጥኑ ሄዳ በመክፈት የለሊት ልብስ መራርጣ ይዛ ወደመልበሻ ክፍል ገባች፡፡
ኩማንደሩም‹‹ሰውዬ እንግዲህ ምን እናዳርጋለን እራሳችሁን እናስተናግድ፡፡›› አለና ካርቶኑን ከፍቶ የውስኪ ጠርሙሱን አወጣው፤ ክዳኑን ከፈተ፡፡ሁለቱ ብርጭቆ ውስጥ ቀዳ…አንዱን ለሁሴን አስጠጋለትና የራሱን ብርጭቆ አንስቶ ተጎነጨለትና ጣዕሙን አጣጥሞ መልሶ አስቀመጠው፡፡
‹‹ነገ ስራ ገባለው መሸብኝ ያልክ መስሎንኝ?››ሲል ጠየቀው ሁሴን፡፡
‹‹አዎ..እና ››
‹‹እናማ አሁን ወደክፍልህ ሄደህ ብትተኛ ምን ይመስልሀል?››
‹‹አንተስ?››
‹‹እኔማ ነገም ተኝቼ መዋል እችላለሁ…ከሰሎሜ ጋር አንድ ሁለት ብርጭቆ ተጎንጭቼ ወደ ክፍሌ እሄዳለው፡፡››
‹‹አይ አመሰግናለሁ…እንደውም ስላመመኝ ነገ ስራ አልገባም….››
‹‹ተው እንጂ!! አሞኛል በሚል ተልካሻ ምክንያት ከስራ ገበታ ላይ መቅረት ለዛውም እንደአንተ ሀላፊነት ላይ ላለ ሰው ሲሆን ትልቅ ሙስና ነው እኮ››
‹‹ይሁን ችግር የለውም..በሀገሪቱ ያለሁት ሙሰኛ ባለስልጣን እኔ ብቻ አይደለሁም…በዛ ላይ …የአላዛር አደራ አለብኝ…ጠብቃታለሁ፡፡››
‹‹ከምንድነው የምትጠብቃት?››
‹‹ከማንኛውም ትንኳሳ ሆነ ጥቃት…ምንም አልከኝ ምንም አይጧን ድመቱ እቅፍ ውስጥ ጥዬ አልሄድም፡፡››
‹‹የተረገምክ ነህ››አለው ፡፡
ሁለቱም ተሳሳቁ…..
በዚህ ጊዜ ሰሎሜ ውብ የሆነ ስስ ሀመራዊ ቀለም ያለው ቢጃማ ቀሚስ ለብሳ ከመልበሻ ክፍል ወጥታ ወደእነሱ ስትመጣ ተመለከቱ፡፡ሁለቱም መሳሳቃቸውን አቁመው አፋቸውን በመክፈት አይኖቻቸውን ተከሉባት፡፡የለበሰችው ቢጃማ ስስ ስለሆነ የሰውነቷን ቅርፅ እና ከውስጥ የለበሰችውን ፓንት ሳይቀር በግልፅ ያሳያል፡፡
የተነጋገሩትን ሳትሰማ ፈገግታቸው ተጋብቶባት እሷም እየፈገገች ‹‹ምንድነው እንዲህ የሚያሳስቃችሁ?››ስትል ጠየቀቻቸው፡፡
ኩማንደሩ‹‹የሻይ ግብዣሽ አስደስቶን ነው…ነይ ቁጭ በይ፡፡›› በማለት ከተቀመጠበት ተነሳና ወንበር ሳበላት፡፡ ተቀመጠች..ባዶውን ብርጭቆ ወደእሷ አስጠጋና ከውስኪው ቀዳላት፡፡
‹‹እኔም ልጠጣ እንዴ?››
‹‹መጠጣት ፈልገሽ አይደል..ሶስት ብርጭቆ ያመጣሽው?››
‹‹አሁን እራሱ እኮ ሰክሬለሁ….ይሄንን ስጨምርበት ደግሞ..››
‹‹አንቺማ ስከሪ….የገዛ ክፍልሽ ነው ያለሽው..ምን አሰጋሽ?››
‹‹እናንተም ሳትሰጉ ጠጡ..እንደምታዩት አልጋው ሰፊ ነው…አንግዳ በአጉል ሰዓት ከቤታችን አናባርርም፡፡››
አለማየሁ ከአንደበቷ ነጥቆ‹‹በአንድ አፍ….››አላት፡፡
‹‹..ችግር የለውም …ዘና ብላች ጠጡ!!››
‹‹ምን እደሚገርመኝ ታዊቂያለሽ?››ሲል ድንገት ጠየቃት፡፡
‹‹ምንድነው የሚገርምህ?››
‹‹በፊት እኮ መጠጥ በጣም ነበር የምትጠይው..ሽታው እራሱ ያምሽ ነበር..አሁን ግን ይሄው ከእኛ እኩል ትቀመቅሚያለሽ?››
‹‹አዎ…እኔም ገርሞኝ በውስጤ ሳማሽ ነበር››ሁሴን የአለማየሁን አስተያየት ደግፎ ተናገረ፡፡
‹‹አይ የወንደላጤ ነገር!››ስትል በሽሙጥ መለሰችላቸው፡፡
‹‹እንዴ ይሄ ደግሞ ከወንደላጤና ከትባለትዳር ጋር ምን አገናኘው?፡››
‹‹አንድ ሰው ከትዳር በፊትና ከትዳር በኃላ በብዙ ነገር የተለያየ ሰው ነው የሚሆነው…ከለውጦቹ ውስጥ አንድ.. ባልትዳር የሆነ ሰው ወይ ጠጪ ወይ ፈላስፋ ወይ ደግሞ ወፈፌ የመሆን እድሉ ሰፊ ነው፡፡››
‹‹እና አታግቡ እያልሺኝ ነው፡፡››

👍56❤6🥰1
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================
ኩማንደሩ ቢሮ ቁጭ ብሎ እያሰበ ነው…የሚያስበው አዲስ ነገር አይደለም፡፡እድሜ ልኩን ሲያስበው ስለኖረው ነገር ነው..ስለ ሰሎሜ፡፡
ጥዋት ላይ አላዛር ከቱርክ ደውሎለት ነበር፡፡ምንም የሚያስደስት ነገር አልነገረውም፡፡ለዛም ነው ቀኑን ሙሉ ሲጨፈግገው የዋለው፡፡
‹‹አሌክሶ እድሜ ለአንተ ሳልፈወስ አልቀርም››የሚለው ንግግሩ ደጋሞ በጆሮዎቹ ላይ እያንቃጨለበት ነው፡፡
‹‹ሳልፈወስ አልቀርም ነው.ወይስ ተፈውሼለው?››
‹‹በቃ ተፈውሼለሁ ማለት ይቻላል..እርግጥ ቀሪ የአንድ ሳምንት ክትትል አለኝ….ከዛ በኋላ በእልልታ ወደሀገሬ እመለሳለሁ..አዎ እርግጠኛ ነኝ ድኜ እመለሳለሁ››
‹‹በጣም ደስ የሚል ዜና ነው የምትነግረኝ…እንኳን ደስ ያለህ››
‹‹እንኳን አብሮ ደስ ያለን…እንደውም ምን እንደአሰብኩ ታውቃልህ..የእውነትም ድኜ ከሆነ ..አንተና ሁሴን እንደአዲስ ደግሳችሁ ትድሩኛላችሁ፡፡››
‹‹ማለት?››
‹‹የመጀመሪያው ሰርጌ የእናንተ ምርቃት ስለሌለበት ጎዶሎ ነበር..አሁን ግን ሙሉ እንዲሆን እፈልጋለው..መልሳችሁ ከእንደገና ትድሩኛላችሁ››
‹‹አንተን የሚያስደስትህ ከሆነ እናደረርገዋለን..ለመሆኑ ዜናውን ለሰሎሜ ነገርካት፡››
‹‹እንዴት ምን ነካህ …?ለዚህ ጉዳይ እዚህ እንደመጣሁ እኳ ከአንተ ውጭ ማንም ሰው አያውቅም…እንዴት ልነግራት እችላለው…?
ከሳምንት በኃላ ስመጣ በህይወቷ አይታ የማታውቀውን ትልቅ ሰርፕራይዝ ነው የማደርጋት››
‹‹ደስ የሚል ነገር ነው..በቃ የምትመጣበትን ትክክለኛ ቀን ደውለህ አሳውቀኝ››
‹‹እሺ አሳውቅሀለው..ደህና ሁን››
በዚህ ሁኔታ ነበር የስልክ ንግግራቸው የተቋጨው፡፡የአላዛር የምስራችና ፈንጠዝያ ለእሱ ሀዘንና የውስጥ ቅዝቃዜ ነው የፈጠረበት፡፡
‹‹እሺ አሁን ምን ላድርግ?››እራሱን ጠየቀ፡፡አእምሮው‹‹ በህይወትህ ለሁለተኛ ጊዜማ አትሸነፍ…ለፍቅርህ ታገል…አላዛር ከችግሩ ተላቆ መጥቶ ከሰሎሜ ጋር የነበረውን ስንጥቅ ሙሉ በሙሉ ከመድፈኑ በፊት ተንቀሰቀስና የሆነ ነገር አድርግ…ስንጥቁን አስፋውና ሸለቆ ይሁን …ንጠቀውና የራስህ አድርጋት››ይለዋል..፡፡ልቡ ደግሞ ‹‹ተው እንጂ ..አላዛር እኮ ለአንተ በህይወት ውስጥ ከተከሰቱ በጣም መልካም ሰዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ደግሞ ከዚህ በፊትም የእንጀራ አባቱን ሚስት በማማገጥ አባቱ ገዳይ እንዲሆን ምክንያት ሆነሀል…ለዚህ የስንፈተወሲብ ችግር የተጋለጠበት ዋናው ምክንያትም አንተ ከሰራሀው ስህተት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ከበቂ በላይ ጎድተሀዋል..አሁን ደግሞ ሚስቱን ከነጠቅከው ምንድነው የሚሆነው…?በዛ ላይ ለእሷስ ቢሆን አሁን ከእሱ በላይ የተሻለ ባል እሆናታለው ብለህ ታስባለህ…?.በመንግስት ደሞዝ ምን አይነት የተመቻቸ ኑሮ ልታኖራት ነው?የምትወዳት ከሆነ ባለችበት ተዋት››እያለ ይሞግተዋል፡፡
የስልኩ ድምፅ ነው ከሀሳቡ ውስጥ መዞ ያወጣው..አየው ሰሎሜ ነች..ፈጠን ብሎ አነሳው፡››
‹‹ሀይ ቢራቢሮዋ››
‹‹አለሁልህ…..እየመጣህ ነው?››
‹‹አይ ቢሮ ነኝ…ምነው?››
‹‹ለመድኳችሁ መሰለኝ ደበረኝ…ትቆያለህ እንዴ?››
‹‹አይ ..ጨርሼለው፡፡ በቃ መጣሁ….ምነው ግን ሁሴን የለም እንዴ?›
‹‹ፕሮጀክቱን በተመለከተ የሚያገኛቸው ሰዎች ስላሉ ቡራዩ ሄዶል፡፡››
‹‹እሱናማ አውቃለሁ እስከአሁን አልተመለሰም እንዴ.?.››
‹‹አይ አሁን ደውሎ ስላልጨረስኩ አድራለሁ ብሎኛል…ለዛ ነው የደወልኩልህ››
‹‹በቃ መጣሁ››ስልኩን ዘጋውና ከተቀመጠበት ተነሳ…ቢሮውን ቆልፎ ወጣ..ሞትሩን አስነሳና ወደሰሎሜ መብረር ጀመረ…
‹‹ዛሬ .የመጨረሻ እድሌ ነው….የሆነ ነገር ማድረግ አለብኝ››ሲል በውስጡ ወሰነ…ሲደርስ በረንዳ ላይ ቁጭ ብላ ስልኳን እየጎረጎረች ነበር…ስታየው ተነሳችና ጉንጩን አገላብጣ በመሳም ተቀበለችው፡፡
ሊቀመጥ ሲል…‹‹ወደውስጥ እንግባ ..ውጩ ይቀዘቅዛል…እ ››የሚል ሀሳብ አቀረበች፡፡
‹‹እሺ…››አለና ተከተላት…
ሳሎን መሀል እንደደረሱ ‹‹መክሰስ ላቅርብ ..እስከዛ እጅህን ታጠብ››አለችው፡፡
‹‹ምነው ልጅቷ አታቀርብም እንዴ››
‹‹ዛሬ የረፍት ቀኗ ነው…ብቻዬን ስለሆንኩ እኮ ነው የደወልኩልህ››
ልዩ አይነት ደስታ በውስጡ ሲፈስ ታወቀው….እሷም እኔ ያሰብኩትን አስባ ይሆን እንዴ?››ሲል አሰበና እየፈገገ ወደመታጠቢያ ክፍል ሄደ…ታጥቦ ሲመለስ የምግብ ጠረጴዛው በምግብ ደምቆ ነበር…
‹‹የሚጠጣ ምን ይሁንልህ?›
‹‹ወይን ቢሆን ደስ ይለኛል….አንቺ ከጠጣሽ ማለት ነው?››
‹‹እኔ እንኳን ድክምክም እያለኝ ነው..ቢቀርብኝ››
‹‹እንደዛ ከሆነ አልጠጣም››
‹‹ችክ ያልክ ሰው እኮ ነህ..በቃ ትንሽ ጠጣለሁ..ብላ ሔደችና ወይንና መጠጫ ብርጭቆ አምጥታ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠች፡፡፡አነሳና ክዳኑን ከፍቶ ለሁለቱም ቀዳ…ከፊት ለፊቱ ተቀመጠችና እራት መብላት ጀመሩ….
‹‹ይሄ ግዙፍ የተንጣለለ ቤት ለብቻ ያስፈራል አይደል?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹አረ እንደውም ብዙ ጊዜ ብቻዬን ስሆን ደስ ነበር የሚለኝ..ዛሬ ግን ምን እንደነካኝ አላውቅም ፍርሀት ፍርሀት ይለኛል››
‹‹አይ ምንም ፍራሀት የለም…ናፍቆት ነው››
‹‹ባልሽን ናፍቀሻል እያልከኝ ነው?››
‹‹አይ እኔን ናፍቀሺኝ ነው እልኩሽ ነው››
‹‹ሂድ ጉረኛ….ምን ስለሆንኩ ነው የምትናፍቀኝ?››
‹‹የዘመናት አፍቃሪሽ ስለሆንኩ ነዋ…›
‹‹ታዲያ አፍቃሪዬ ነህ አንጂ አፍቃሪህ አይደለውም ….ልትናፍቀኝ ትችላለህ እንጂ አኔ አልናፍቅህም፡፡››
‹‹ተይ ተይ ..አይኖችሽ ግን እንደዛ አይደለም የሚሉት፡፡››
ከት ብላ ሳቀችና‹‹‹አንተ እያሽኮረመምከኝ እኮ ነው››
ፈራ ተባ እያለ‹‹ሳሎኑ ለሁለት ሰው በጣም ይበዛል…ወደላይ ሄደን ብንጠጣ አይሻልም›› የሚል ሀሳብ አቀረበላት፡፡
‹‹ውይ አንተንም በርዶሀል ማለት ነው…እኔን ብቻ መስሎኝ ኮ ነበር…ተነስ እንሂድ››ብላ ቀድማ ተነሳች…ደስ አለውና ጠርሙሱን ያዘ….‹‹ብርጭቆቹን ልያዛቸው››
‹‹ተዋቸው..እዛ ሌላ አለ›››አለችና ቀድማ ከፊት ለፊቱ መራመድ ጀመረች...በደስታ እየተፍለቀለቀ ተከተላት..‹‹ዛሬ በቃ እድል ሙሉ በሙሉ ፊቷን ወደእኔ አዙራለች…››ሲል አሰበ‹‹አሌክስ ዛሬ ይሄን ወርቃማ እድልህን ተጠቅመህ የሆነ ነገር ካላደረክ በቃ ለዘላለም ሰሎሜን እርሳት››ሲል እራሱን አስጠነቀቀ፡፡ቀጥታ ወደራሷ ክፍል ነው የሄደችው…ልክ እንደህጋዊ ባሏ ያለምንም ማቅማማት ተከተላት..ከፋታ ስትገባ ተከትሎት ገባ..አልጋው ጠርዝ ላይ ስትቀመጥ ጠረጴዛውን ወደእሷ አስጠጋ…ይዞ የመጣውን የወይን ጠርሙስ አስቀመጠ…ብርጭቆውን ካለበት አመጣና ለሁለቱም ቀዳና ወንበሩን አንሸራተተና ወደእሷ በማስጠጋት ተቀመጠ፡፡የፈለገው አልጋው ላይ ከጎኗ በመቀመጥ ሰውነቷን መነካካት ነበር…ግን ደግሞ ያንን ለማድረግ ለጊዜው ድፍረቱን አላገኘም…
ቀለል ያሉ ጫወታዎችን እያወሩ የድሮ ትዝታዎችን እያነሱ እየተጫወቱ ሰዓቱ ገፋ…
‹‹እንቅልፌ መጣ መሰለኝ ››አለችው፡፡
‹‹እና ወደክፍልህ ሂድልኝ እያልሽ ነው››
‹‹ለምን? ከፈለክ እዚህ ማደር ትችላለህ››
በመልሷ ደነገጠ‹‹እርግጠኛ ነሽ?››ሲል መልሷ ጠየቃት፡፡
‹‹ምነው እራስህን አታምነውም እንዴ?››
‹‹አረ አምነዋለው››

👍57❤6👎3😱3
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================
ኩማንደር ሆስፒታል በረንዳ ላይ ከወዲህ ወዲያ ሲንገዋለል አንዴ እናቷን እቴቴን ሲያፅናና..ቆይቶ ደግሞ ያለመደበትን ፀሎት ለመፀለይ ሲሞክር…ሰለሰሎሜ መጥፎም ሆነ ጥሩ ዜና ሳይሰማ ነጋ፡፡አንድ ሰዓት ነበር ከዶክተሩ አሰቃቂውን መርዶ የሰማው…፡፡‹‹ሰሎሜ የደም ካንሰር በሽተኛ ነች፡፡ለጊዜው ኬሞትራፒ እንዲደረግላት የተወሰነ ሲሆን በቅርብ የአጥንት መቅኔ ንቅለ ተከላ ማድረግ ስለሚያስፈልጋት ዘመዶቾ በአፋጣኝ መጠራት አለባቸው››…ተባለ፡፡
ህመሟ ከፍተኛ ደረጃ ስለደረሰ በቅርብ ቀናቶች ውስጥ ቀዶ ጥገናው ካልተደረገ ህይወቷን ልናጣት እንችላለን የሚል ዜና ነገረው፡፡
‹‹ዶክተር እስኪ የመቅኔ ንቅለ ተከላ ማለት ምን ማለት ነው? እስኪ ትንሽ አስረዳኝ?››ሲል ከፍራቻ ቆፈን ራሱን ሳያላቅቅ ጠየቀው፡፡
‹‹መቅኔ ማለት የደም ህዋሳትን ለማምረት የሚጠቅም በአጥንቶች መሃከል የሚገኝ ዘለግላጋ የሰውነት ክፍል ሲሆን ነጭ የደም ሴሎችን፤ቀይ የደም ሴሎችን እንዲሁም ለደም መርጋት የሚያገለግሉትን የፕላትሌት ንጥረ ነገሮች ለማምረት ይረዳል፡፡እነዚህ ንጥረ ነገሮች አንዴ ከተመረቱ በኋላ ከሰውነት ውጪ ለረጅም ጊዜ የማይቆዩ ሲሆን ይህንንም ለማገዝ እና ሰውነታችን ጤነኛ እድገት እንዲኖረው በመቅኔ አማካኝነት ቶሎ ቶሎ ይመረታሉ ፡፡ከሰውነት በሽታን የመከላከል ስርዓት መታወክ ጋር የተያያዙ ችግሮች የሚመጡት መቅኔ ከሚያመርተው ግድፈት ያለባቸው የደም ህዋሳት ወይም ያልበለጸጉ የደም ህዋሳት ወይም ደግሞ አነስተኛ የደም ህዋሳት መመረት የተነሳ ነው:: ይህም የአዳዲስ የደም ህዋሳት ከቁጥጥር ውጪ ተመርተው በደም ስር ውስጥ እንዲከማቹ በማድረግ ሌሎች ህዋሳትንም ያውካሉ ፡፡ ይህንን ጤነኛ ያልሆነ ሁኔታ ለማከም ልክ አሁን ለሰሎሜ እያደረግን እንዳለነው የኬሞቴራፒ እንዲሁም የጨረር ህክምና ይደረጋል ፡፡በዚህ ህክምና ወቅት ግን ሌሎች በመቅኔ ውስጥ የሚገኙ ጤነኛ የሆኑ የሰውነት ህዋሶችም ሊጎዱ ይችላሉ፡፡የመቅኔ ንቅለ ህክምና ግን ግድፈት ያለባቸው የደም ህዋሳት እና መቅኔ እንዲወገዱ በማድረግና በጤነኛ መቅኔ በመተካት ሀኪሙ የመፈወስ አቅሙ ጠንከር ያለ የኬሞቴራፒ እና የጨረር ህክምናን መጠቀም እንዲችል ያስችለዋል፡፡ ምንም እንኳን የመቅኔ ንቅለ ተከላ ህክምና በሽታው ተመልሶ ላለመምጣቱ ማረጋገጫ ባይሆንም ታካሚው የመዳን እድሉን ከፍ በማድረግ እንዲሁም ከህመም ነጻ ሆኖ የሚቆይበትን ጊዜ ከፍ ያደርገዋል ፡፡ይህ ህክምና ከሌላ ሰው (ለጋሽ ) ወይም ደግሞ ከራሱ ከታማሚው ሊከናወን ይችላል፡፡አለማየሁ የዶክተሩን ማብራሪያ በፅሞና ሲያዳምጥ ከቆየ በኃላ‹‹መቅኔውን ማንኛውም ሰው መለገስ ይችላል?››ሲል ሌላ ጥያቄ ጠየቀ፡፡
‹‹አዎ ማንኛውም ሰው መለገስ ይችላል…ግን ደግሞ ቀላል አይደለም ….የሚወሰደው መቅኔ ውጤታማ እንዲሆን ከታካሚዋ ጋር ቢያንስ ከ50 ፐርሰንት በላይ የሚመሳሰል መሆን አለበት፡፡ይሄንን ማግኘት ብዙውን ጊዜ አስቸጋሪ ነው፡፡ለዛም ነው ወላጆች ወይ እህትና ወንድም የተሻለ የመለገስ እድል አላቸው የሚባለው፡፡እንደዛም ሆኖ ግን አንዳንድ ጊዜ ከአራትና አምስት ወንድሞች አንደኛውም ለመለገስ ብቁ ላይሆን ይችላል፡፡››
የዶክተሩ ገለፃ አለማየሁን የበለጠ ስጋት ውስጥ ጣለው፡፡‹‹አንዴ!! እቴቴ መለገስ ካልቻለች ምንድነው የሚውጥን?››ሲል እራሱን ጠየቀና ሰውነቱ በስጋት ሽምቅቅ አለ፡፡
‹‹ዶክተር..ምንአልባት የሚለግሳት ሰው ከጠፋ ከራሷ መውሰድ ይቻላል ብለሀል፡፡››
‹‹አዎ ብያለው ..አጠቃላይ ሁኔታው እንደዛ ነው፡፡ያ ግን አሁን ሰሎሜ ባለችበት ሁኔታ ለመተግበር ቀላል አይመስለኝም ..እርግጥ ተጨማሪ ዲቴል ምርመራዎች ማድረግ ይገባናል…ቢሆንም ግን ምን አልባትም የማይቻል ሊሆን ይችላል፡፡ስለዚህ አሁን ተሯሩጣችሁ ለጋሽ መፈለጉ ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባችኋል››ሲል ምክር ሰጠው፡፡አለማየሁ ቀስ ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳና ዶክተሩን ተሰናብቶ ወጣ፡፡ቀጥታ ወደሰሎሜ እናት ነው የሄደው፡፡አንገቱን ደፍቶ እየተቅለሰለሰ ዜናውን ነገራት..እንደእብድ እየጮኸች የሆስፒታል ግቢ አመሰችው፡፡
ከሁሴን ጋር በመሆን እንደምንም አረጋጓትና ምረመራውን እንድታደርግ ተደረገ፡፡ቢሆንም ግን ካለባት የጤና ችግር አንፃር ከእሷ መውሰድ እንደማይችሉ ተነገራት..ሌላ ዘመድ አባት ወንድም ወይም እህት ይፈለግ ተባለ፡፡፡፡
አለማየሁ ሆነ ሁሴን ይሄንን ዜና ሲሰሙ ሁሉ ነገር ነው ጭልም ያለባቸው…‹‹ሰሎሜ ወንድምም ሆነ እህት እንደሌላት ያውቃሉ..አባቷንም ቢሆን ለዘመናት መኖር አለመኖሩ የማይታወቅ አባት በሰዓታት ውስጥ ከየት ተፈልጎ ሊገኝ ይችላል?፡፡
አለማየሁ ሁሴንን ከሰሎሜ ጎን እንዲሆን አዘዘውና ምርጫ ስለሌለው ጉዳዩን ለእቴቴ ነግሯት እሷን ይዞ ወደካፌ ወሰደና ከጎኗ ተቀመጠ፡፡
‹‹ልጄ እንዴት ነች…ንቅለ ተከላው መቼ ነው የሚደረግላት?››ስትል በስጋት ጠየቀችው፡
‹‹እቴቴ እንጃ ..አንቺ ካለብሽ በሽታ የተነሳ ለእሷ መለገስ አትችይም ብለዋል…››
በድንጋጤ አይኖቾን አፍጥጣ ‹‹እንዴት ታዲያ ምን ይሻላል?››
‹‹እኔም ግራ ገብቷኛል››ስል ግራ በመጋባት ውስጥ ሆኖ መለሰ፡፡
‹‹የሆነ መፍትሄማ መኖር አለበት?››
‹‹ወላጆች ወይም ወንድምና እህቶች ካሏት በአስቸኳይ አምጡ ነው ያሉን፡፡››ከዶክተሩ የተነገረውን ነገር ቀጥታ ተናገረ፡፡
እቴቴ በድንገት ንቁ ሆና‹‹ወንድምና እህት ነው ያልከው?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹አዎ እቴቴ ወንድምና እህት››ደገመላት፡፡
‹‹ሂድና ወንድሟ ነኝ በላቸውና ..ይመርምሩህ››አለችው፡፡
‹‹እንዴ እቴቴ…ምን ማለትሽ ነው?፡፡››
‹‹ታምነኛለህ አይደል?››
‹‹በደንብ ነው ማምንሽን እቴቴ…በደንብ አምንሻለሁ››
‹‹እንግዲያው አሁኑኑ ተነሳና ወንድሟ ነኝ በላቸው፡፡››
መከራከርም እሺ ለማለትም ግራ ተጋባ..ትኩር ብሎ ሲያየት ኩስትርትር እንዳለች ነው…‹‹ሴትዮዋ ከድንጋጤ የተነሳ እያበደች ይሆን እንዴ? ››ሲል እራሱን ጠየቀና ቀስ ብሎ ተነሳና እሷን እዛው ካፌ ትቶ ወደ ዶክተሩ ቢሮ እግሩን እየጎተተ ሄደ ..፡፡ያለችውን ከማድረግ ውጭ ምንም ሌላ የመጣለት መፍትሄ የለም…እንዳለችው ወንድሟ ነኝ ብሎ ነገራችው…ወዲያው አፈጥነው ሙሉ ምርመራ አደረጉለት…ውጤቷቹ ሁሉ ተሰብስበው ስኪመጡ ከስምንት ሰዓት በላይ ፈጅቷ ነበር…እሱ ጊዜ ማባከን አድርጎ ነው የወሰደው…እቴቴ ፊት ላይ ግን ትልቅ ተስፋ ይነበብ ነበር..ውጤት ደርሶ ወደ ዶክተሩ ቢሮ ተጠሩ…የተነገራቸው ዜና እናትዬውን በእልልታ ያሰከረ ኩማንደሩን እንዴት በሚለው ጥያቄ ያደነዘዘ ነበር፡፡እርግጥ አንዳንዴ ዘመድ ያልሆነ ሰውም ተመሳሳይ አይነት መቅኔ ሊኖረው እንደሚችል ዶክተሩ በደንብ አስረድቶታል፡፡፡ያ ግን እንዲህ በቀላሉ የሚሳካ አይደለም፡፡አልተዋጠለትም፡፡
‹‹በሉ ነገ ጥዋት ተዘጋጅ…..ኦፕራሲዬኑን ጥዋት እናካሂዳለን››ተባለ..እቴቴ አለማየሁን እጁን እየጎተተች ወጣችና ‹‹የሆነ ቦታ ደርሰን እንምጣ ››አለችው፡፡
‹‹የት እቴቴ?››
‹‹ምን ቸገረህ …ተከተለኝ››አለችው ቆፈጠን ብላ፡፡
‹‹ሰሎሜን ትተን?››
‹‹ምንም .. እነሁሴን አሉ አይደል…እነሱ ያዮታል..ደግሞም አንቆይም››

👍62❤11🔥1🥰1😱1
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
===================
የሰሎሜ ህክምናው በሰላም ተጠናቆ ወደ ቤት ተመልሳለች፡፡እናትዬው ብቻ ሳትሆን ሁሴን እና አለማየሁም ከስሯ ሳይለዩ ልክ ልጅ ሆነው ታማ ሆስፒታል በገባች ጊዜ እንዳደረጉት በትኩረትና በሙሉ ጥረት ሲንከባበከቦት ነበር የከረሙት፡፡በዛ ምክንያት የማገገም ፍጥነቷ ተአምር የሚባል ነበር፡፡
አሁን ሁለቱ ጓደኛሞች አለማየሁ እና ሁሴን በዛሬው ቀን ከውጭ የሚመጣውን ጓደኛቸውን ሊቀበሉ ቦሌ ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡አላዛር ሰሎሜ ለመቅኔ ንቅለ ተከላ የሚያደርስ ህመም ታማ እንደነበረ አልሰማም፡፡ ኬሞትራፒ እክምና ላይ እያለች ይሁን ከዛ ወጥታ ኮማ ውስጥ ገብታ ሳለ በስልክ እንድታናግረው በሚጠይቅበት ጊዜ ኃይለኛ ጉንፋን ይዟት ድምፆ ተዘግቷል ብለው ሸውደውታል፡፡እንደዛ ያደረጉት የሄደበትን ጉዳይ ያለምንም እንቅፋት እንዲያጠናቅቅ ስለፈለጉ ነው፡፡ይሄ ውሳኔ የአለማየሁ ነው፡፡ሌሎቹንም ያሳመናቸው እሱ ነው፡፡
‹‹ተሳክቶለት የሚመጣ ይመስልሀል?››ሁሴን ነው ፈራ ተባ እያለ አለማየሁን የጠየቀው፡፡
‹‹ይመስለኛል..በስልክ ሳወራው እሱም ሙሉ በሙሉ እንደዳነ እርግጠኛ ነው››ሲል መለሰለት፡፡
‹‹ደስ ይላል ….እርግጠኛ ነኝ አሁን አንተም ሙሉ በሙሉ እንዲሳካለት ነው የምትፈልገው››በማለት የሚያስገርም ነገር ነገረው፡፡
‹‹ማለት ?››
‹‹ያው አሁን ወንድሟ መሆንህን አውቀሀል…ከትዳሯ መፍረስ ምንም ምታተርፈው ነገር የለም…እንደውም በተቃራኒው ታዝናለህ››
‹‹በፊትስ ቢሆን ምን አተርፍ ነበር?››
‹‹ባክህ ምን ያደባብቅሀል፡፡ እድሜ ልካችንን እኮ እርስ በርስ እንተዋወቃለን….ባይሳካለት ያንን ክፍተት ተጠቅመህ የሆነ ነገር ለማድረግ አሰፍስፈህ በመጠባበቅ ላይ ነበርክ….››ብሎ የሚያምንበትን ነገር ያለምንም ይኑኝታ ፍርጥ አድርጎ ተናገረ፡፡
አለማየሁም ያልገባው በመምሰል‹‹የሆነ ነገር ማለት?››ሲል ተጨማሪ ማብራሪያ ጠየቀው፡፡
‹‹ከአላዛር ልታፋታትና እራስህ ልታገባት…ተሳሳትኩ?ደግሞ ይሄንን አቋምህን ቀጥታ ለእሱም ነግረሀዋል…››
‹‹እሱ ነው እንደዛ ብሎ የነገረህ?››
‹‹ማን እንደነገረኝ ማወቁ ምን ያደርግልሀል..?ብቻ እንደዛ ለማድረግ እቅድ እንደነበረህ አውቃለው››
‹‹አሀ..አሁን አንተም እኔ ማድረግ አቅጄ እንደነበረው ለማድረግ እያሰብክ ነው ማለት ነው?››ሲል በገረሜታ ጠየቀው፡፡
‹‹መጀመሪያ ያንተን መልስልኝ››
‹‹አሁን እዚህ ጉዳይ ላይ ማውራት ምን ይረባል?››
‹‹በጣም ይረባል…አሁን አንተ ወንድሟ ስለሆንክ ስለእሷ ወደፊት መጨነቅና ማሰብህ የሚጠበቅብህ ሁኔታ ላይ ነው ያለኸው…ከአላዘር ጋር ካልተሳካላትና የሚፋቱ ከሆነ እኔን እንድታገባኝ ታግዘኛለህ…?.››
‹‹ይሄ ሁሉ ዙሪያ ጥምዝ ….ይሄን ለማለት ነው?››
‹‹አዎ…ታውቃለህ ልክ አንተ ታፈቅራት በነበረው መጠን አፈቅራታለው…እሷ ለሁላችንም የእድሜ ልክ ህልማችን ነች፡፡እሱ እድሉን ተጠቅሟል…ካልሆነለት ቀጣይ የእኔ እድል ነው፡፡እኔ ደግሞ በምንም አይነት ተአምር እድሌን ማባከን አልፈልግም…ቀሪ ዘመኗን እንደሳቀች እንድትኖር ነው የማደርጋት፡፡››
አለማየሁ ምን ሊመልስለት እንደሚገባ መወሰን አልቻለም..ዝም ብሎ ትካዜ ውስጥ ገባ….ሁሴን እየተናገረው ያለው ነገር ደረቅና የሚያሳቅቅ አይነት ቢሆንም ግን ደግሞ እሱም ወንድሟ መሆኑን ከማወቁ በፊት ለማድረግ ሲያስብ እና ሲመኘው የነበረ ነገር ነው አሁን እሱ እያወራ ያለው፡፡እሱ ሲያደርገው ትክክል ሌላ ሲያደርገው ደግሞ አፀያፊ የሚሆንበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ደግሞም ለእሱም ቢሆን የአላዛር ህክምና የማይሳካለት ከሆነ እህቱ ከዚህ በላይ ከእሱ ጋር እየተሰቃየችና እየተሳቀቀች እንድትቀጥል አይፈቅድም…ከአላዛር ከተለያየች ደግሞ ከሁሴን የተሻለ ሰው ታገኛለች ቡሎ አያስብም…ወደደም ጠላም በእሱ ሀሳብ ተስማምቶ ሊረዳው ግድ ነው፡፡
‹‹ጥሩ …ባልከው ነገር እስማማለሁ..፡፡በመጀመሪያ ግን የአላዛር ውጤት በግልፅ ከመታወቁ በፊት ምንም አይነት እንቅስቃሴ አታደርግም፡፡እሱ በግማሽ እንኳን ለውጥ አሳይቶ ከመጣ ሙሉ በሙሉ እንዲያገግም እንረዳዋለን እንጂ ተስፋውን ለማጨለም ምንም አይነት አሻጥር አንሰራም፡፡››
‹‹እስማማለሁ…ሰሎሜን አፈቅራታለሁ ስልህ እኮ የእውነት ነው የማፈቅራት…ደግሞ እሷን ብቻ ሳይሆን እሱንም በጣም የምወደው ወንድሜ ነው፡፡ የመጀመሪያ ምርጫዬ በመሀከላቸው ያለው ችግር ተቀርፎ ትዳራቸውን አጣፍጠው መኖር እንዲቀጥሉ ነው…..፡፡ትዳሩ እንደማይቀጥል እርግጠኛ እስክሆን ድርስ ምንም አይነት እንቅስቃሴ አላደርግም..ለዛ ቃል ገባልሀለው፡፡››
‹‹ጥሩ ..ሌላው…ነገሮች የማይሆኑ ሆነው..እሷን የማግባቱ እድል ያንተ ከሆነ ከውጭ ጓዝህን ጠቅልለህ ትመጣለህ…ይዣት ልሂድ የምትል ከሆነ ..አልስማማም›
‹‹የእሷ ፍላጎት ከሀገር ውጭ ሄዶ መኖር ከሆነስ?››
‹‹ነገርኩ እኮ…ከአሁን በኃላ ከእህቴ ተለይቼ መኖር አልችልም…እዚሁ በቅርቤ እንድትሆን ነው የምፈልገው፡፡››
‹‹.ጥሩ …ለእኔ ችግር የለውም ..እሷን እስከአገኘሁ ድረስ የትም ብኖር ደስተኛ ነኝ፡፡››
ስምምነታቸውን አገባደው ወደ ግል ትካዜያቸው ተመልሰው ገቡ..የአላዛርን መምጣት ሲያዩ ነበር ከትካዜያቸው ባነው የተንቀሳቀሱት፡፡የሞቀ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ…ወደመኪና ይዘውት እየሄዱ ሳለ አላዛር ‹‹ሰሎሜስ…?አብራችሁ ትመጣለች ብዬ ነበር?››ሲል ቅሬታውን አሰማ፡፡
አለማየሁ ፈጠን አለና ‹‹አልቻለችም…አንተን በደመቀ ቤት ለመቀበል ሽር ጉድ እያለች ነው፡፡››የሚል የውሸት ምክንያት ነገረው፡
‹‹እኔን ለመቀበል የምን ሽርጉድ ያስፈልጋል…?አንድ ወር ብቻ እኮ ነው የቆየሁት››እያለ በመነጫነጭ መኪና ውስጥ ገባ፡፡በአለማየሁ ሹፌርነት ወደቤት ጉዞ ጀመሩ…፡፡
አላዛር እቤት ሲደርሱ ሰሎሜን አግኝቶ ናፍቆቱን ለመወጣት ባለው ጉጉት ቀጥታ ተንደርድሮ ወደሳሎን ነው የገባው ፡፡እቴቴና ሰራተኞቹ የምግብ ጠረጴዛው ላይ ምግብን ለመደርደር ሽር ጉድ እያሉ ነው… ሰሎሜን ማየት አልቻለም፡፡ውስጡን ፋራቻ ወረረው፡፡ ግን ወዲያው ሶፋው ላይ ጋቢ ለብሳ ተኝታ ተመለከታት፡፡ተንደረደረና ስሯ ደርሶ ተንበረከከ‹‹እንዴ የእኔ ፍቅር እስከዛሬ እያመመሽ ነው እንዴ?››ብሎ ተጠመጠመባት፡፡
‹‹ቀስ ቀስ…ሰውነቷ ገና በቅጡ አላገገመም››ሲሉ እናትዬው አስጠነቀቁት፡፡
‹‹ማለት››
‹‹የመቅኔ ንቅለተከላ ተደርጎላት ነበር..?››እናትዬው ነች ተናጋሪዋ
አላዛር ሚስቱን አፍጥጦ ተመለከታት፡፡ሰሎሜም ‹‹ትንሽ አሞኝ ነበር..››ስትል ጠቅላላ ሁኔታውን በአጭሩ አስረዳችው፡፡
‹‹ማለት ..?እንዴት ይሄ ሁሉ ሲሆን እኔ ሳልሰማ…?ለምን ልትደብቁኝ ፈለጋችሁ?የሆነ ነገር ሆናስ ቢሆን ?››ወደኃላ ዞሮ ጓደኞቹ ላይ አፈጠጠባቸው፡፡…ዘራፍ አለ ..ተንሰቅስቆ አለቀሰ..
‹‹ምንም አታስብ አሁን እኮ ሙሉ በሙሉ ድኜለሁ…እየን እስኪ በጣም እኮ ደህና ነኝ፡፡.ስራ ሁሉ እኮ መስራት እችላለው…እነእማዬ ትንሽ አገግሚ ስላሉኝ እኔም ትንሽ ልሞላቀቅ ብዬ ነው ተኝቼ የጠበቅኩህ፡፡››ስትል አፅናናችው፡፡ከብዙ ምክርና ተግሳፅ በኋላ እንደምንም ተረጋጋ፡፡ሁሉም በተደረደረው ምግብ ጠረጴዛ ከበው ተቀመጡ፡፡እየተሳሳቁና እየተጎራረሱ አሪፍ እራት በሉ፡፡ሁሉም ከምግብ ጠረጴዛው ወደ ሶፋው ተሸጋግረው በመደዳ በመቀመጥ ከሰሎሜ በስተቀር ሁሉም የሚፈልገውን መጠጥ እየተጎነጨ ለሌላ ዙር ጫወታ ዝጉጁ ሆኑ.፡፡

👍56❤7
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
=====================
ቤቱ ቅልጥ ያለ ድግስ ላይ ነው፡፡ግቢ ውስጥ ግዙፍና ዘመናዊ ድንኳን ተደኩኖ በዲኮር አሸብርቋል፡፡በዝግጅቱ የሰሎሜ ፤ የእቴቴ የአላዛር እና የአለማየሁ አንድም ወዳጅና የስራ ባለደረቦች አልቀረም…ከ500 በላይ ሰው ነው የተጠራው፡፡እርግጥ ይሄ ድግስ እንዲደገስ ቀጠሮ የተያዘለት ሰሎሜ አለማየሁ ወንድሟ መሆኑን ከሰማች ከሳምንት በኃላ ነበር፡፡ግን ባልተጠበቀ ፕሮግራም ዜናው ከተሳማ ከሦስት ቀን በኃላ አለማየው ለአጭር ጊዜ ስለልጠና ወደ ተባበሩት አረብ ኤሜሪት እንዲሄድ በመስሪያ ቤቱ ስለታዘዘ ድግሱ በሁለት ወር እንዲራዘም ተደርጓል፡፡
ይሄ ድግስ በዋናነት ሰሎሜ አለማየሁ ወንድሟ መሆኑን በማወቋ እና ዘመናት ለማወቅ ስታልመው የነበረው የአባቷን ማንነት በማወቋ የተፈጠረባትን ፈንጠዝያ ለማክበር ነበር..ሌላው ለህይወቷ በጣም አስጊ የሆነውን በሽታ ታክማ መዳን በመቻሏም ለተንከባከቧት ሰዎች ሆነ ለፈጣሪ ምስጋና ለማቅረብ ነው፡፡ለሌላው ሶስተኛ ነገር ደግሞ ትዳር በያዘችባቸው ሶስት አመቷ ውስጥ ስትሰቃይበት የነበረችው ከአላዛር ላይ ተከስቶ የነበረው ስንፈተ ወሲብ ሙሉ በሙሉ ተወግዶ ልክ እንደአዲስ ሙሽራ ቀንና ለሊት ሳይለዩ በፊት ያበከኑትን ጊዜ ማካካስ በሚመስል መልኩ እልካቸውን እየተወጡበት ስለሆነ በዛ ጉዳይ የተፈጠረባቸውን ደስታ በይፋ ለማክበር ነው፡፡ያም መሆኑ ለሁለቱም ከፍተኛ ደስታና አዲስ የህይወት እርካታ አጎናፅፏቸዋል፡፡ከሁለቱም ልብ እየተበተነ ያለ ደስታ በዙሪያቸው ያለውን ሰው ላይ ሁሉ የሚጋባ አይነት ሆኗል፡፡ይሄም ድግሱ ደማቅና ሰፊ እንዲሆን አንዱ ምክንያት ነው፡፡
ድግሱ ለሁለት ወር በመራዘሙ ምክንያት ሌላም ሊከበር የሚገባው ተደራራቢ ምክንያትና በረከት ተፈጥሮል፡፡
ድግሱ ላይ የታደሙት 500 ያህል የቅርብ ሰዎች ምሳ ከበሉ በኃላ ሰሎሜ የተፍለቀለቀ ፊቷን በፈገግታ አጅባ ወደመድረኩ ወጣች፡፡
ማይኩን ድግሱን በሙዚቃ እያደመቀ ካለው ዲጄ ተቀብላ ማውራት ጀመረች፡፡
‹‹ወዳጆቼ ዘመዶቼ ይሄ ድግስን አስመልክቶ ጥቂት ነገር መናገር እፈልጋለው፡፡››ስትል ሁሉም የምትለውን ነገር ለመስማት የእርስ በርስ ወሬያቸውን አቁመው ትኩረታቸውን ወደእሷ አዞሩ….ንግግሯን ቀጠለች፡፡
‹‹ንግግሬን ከመጀመሬ በፊት ..እናቴ እቴቴ ..ባለቤቴ አላዛር….ወንድሜ አለማየሁ….ጓደኛዬ ሁሴን ..ሁላችሁም ወደዚህ መድረክ ኑና ከጎኔ ያለው የፊት ፊት መቀመጫ ላይ እንድትቀመጡ እፈልጋለው፡፡የሚል ጥያቄ አቀረበች፡፡
ሁሉም እየተያያዙ መጡና ፊታቸውን ወደእድምተኞች አዙረው መድረክ ላይ በተዘጋጀው መቀመጫ ላይ ተቀመጡ፡፡
ሰሎሜ ንግግሯን ቀጠለች‹‹እንግዲህ እነዚህ አራት ሰዎች ወደእዚህ ምድር ከመጣሁበት ከመጀመሪያዋ ቀን ጀምሮ ከጎኔ ነበሩ…ሰሎሜ ሰሎሜ እንድትሆን ሁሉም የየራሳቸውን ድርሻ ተወጥተዋል፡፡እኔ ማለት የእነሱ ውጤት ነኝ፡፡እናቴ እቴቴ … ከልጅነቴ ጀምሮ ያለአባት በጀግንነት አሳድጋኛለች፡፡ላደረግሺልኝ ነገር ሁሉ በጣም አመሰግናለሁ፡፡በጣም ነው የምወድሽ፡፡
በህይወቴ ሁለት ጊዜ በከባድ በሽታ ሆስፒታል ገብቻለሁ፡፡ልጅ ሆኜ በታመምኩ ጊዜ ለህክምናው 70 ሺ ብር ተጠይቆ ነበር፡፡በወቅቱ እናቴ የነበራት ከ7ሺ ብር የማይበልጥ ብር ነበር፡፡ቀሪውን ብር በትምህርት ቤትና በየመንደሩ እየዞሩ ለምነው ያሳከሙኝ..እንዚህ ከፊት ለፊት ተቀምጠው የምታዬቸው የልጅነት ሶስቱ ጓደኞቼ ናቸው፡፡ከሶስት ወር በፊትም ተመሳሳይ አይነት ፈታኝ ህመም አሞኝ ነበር፡፡ ከአካሉ አካል ቆርሶ በመስጠት ደግመኛ ዛሬን እንደዚህ ከፊት ለፊታችሁ እንድቆም ያደረገኝ ወንድሜ አለማየሁ ነው፡፡ይሄም ዝግጅት እንዲጋጅ አንዱ እና ዋነኛው ምክንያት ‹‹ወንድሜም ስለሆንክ…ከህመሜም እንድፈወስ ስላደረከኝ››አመሰግናለው ለማለት ነው፡፡
ሌላው የዕድሜ ልክ ጓደኛዬ ሁሴን በሁለቱም የህይወቴ ጨለማ ቀናቶች ከጎኔ ስለነበርክ አንተንም በጣም አመስገናለሁ፡፡በጣም እንደምትወደኝ አውቃለው….እኔም በጣም እወድሀለው….እናም ከሶስት ቀን በኃላ ተመልሰህ ወደውጭ እንደምትሄድ ስለማውቅ ዳግመኛ ሙሉ ጓዝህን ጠቅልለህ ወደሀገር እስክትመለስ እና አብረሀን መኖር አስክትጀምር ድረስ ይሄ እንደሽኝት ፕሮግራም እንዲታይልኝ እፈልጋለው፡፡
ከፍተኛ የሞቀ ጭብጨባ ተከተላት…ትንፋሽ ወሰደችና ንግግሯን ካቆመችበት ቀጠለች፡፡
ሌላው የእድሜ ልክ ጓደኛዬ እና አንድም አመት ቢሆን ከስሬ ተለይቶኝ የማያውቀው መከራዬንም ሆነ ደስታዬን አብሮኝ ያሳለፈው የምወደው ባለቤቴ አላዛር ..ስለተንከባከብከኝ. .ለአስቸጋሪው ፀባዬ ጠቅላላ ትዕግስት አድርገህ ተስፋ ሳትቆርጥብኝ እስከአሁን አብሬህ እንድኖር ሚስትህ እንድሆን ስላደረከኝ አመሰግናለው..ለዚህም ድንቅ አበርክቶትህ ከእኔ ከሚስትህ በዚህ ሁሉ ወዳጅ ዘመድ ፊት አንድ ስጦታ ላበረክትልህ እፈልጋለው፡፡››አለችና ንግግሯን ገታ አደረገች…አላዛር ግራ ተጋባ..ሌሎችም የሽልማቱን ምንነት ለማወቅ ጉጉት አሳዩ፡፡
‹‹ውድ ባለቤቴ ወደእኔ ና››ስትል ጠየቀችው፡፡
ከተቀመጠበት ተነሳና ወደእሷ ቀረበ….በእጆ የያዘችውን ፖስታ አቀበለችው፡፡ምን እንደሚያደርገው ግራ ገብቷት ዝም ብሎ እያገላበጠ ያየው ጀመር፡፡
ሁሴን እና አለማየሁ‹‹ይከፈት ይከፈት››አሉ..ሌሎችም እድምተኞች ተከተሏቸው፡፡አላዛር ምርጫ ስላሌለው በቀስታ ፖስታውን ሸረከተው፡፡አንድ ነጠላ ወረቀት ነው ውስጡ ያለው፡፡ አወጣውና ተመለከተው ፡፡ ምንም አልገባውም‹‹ምንድነው ፍቅር?››ሲል እሷኑ መልሶ ጠየቃት፡፡
‹‹አንብበዋ››አለችው፡፡
‹‹እንድምንም ትክረቱን ሰብስቦ ማንበብ ጀመረ…አይኑ ፈጠጠ…‹‹ምንድነው ፍቅር..? የማየው ነገር እውነት ነው…?››ሲል ባለማመን ጠየቃት፡፡ተንደረደረና ተጠጋት፡፡ዝቅ ብሎ ጉልበቷ አካባቢ በእጆቹ ያዛትና ወደላይ አንስቶ አሽከረከራት፡፡ሰው ሁሉ ሽልማቱ ምን ቢሆን ነው በሚል ጥያቄ ራሱን እየጠየቀ መወዛገብን ቀጠለ፡፡እንደምንም እንዲያወርዳት ካደረገች በኃላ ጠረጴዛ ላይ ያለውን ማይክሮፎኑን ወደአፈዋ አስጠጋችና ‹አዎ እውነት ነው..ውድ ባለቤቴ ሽልማትህ ልጅ ነው..እኔ ሚስትህ የሁለት ወር እርጉዝ ነኝ፡፡››በማለት ለእሱ ብቻ ሳይሆን ለመላ ታዳሚው የምስራቹን አበሰረች፡፡መጀመሪያ እልልታዋን ያቀለጠችው እናቷ እቴቴ ነች….ከዛ ሙሉ ዱንኳኑ በእልልታና በጭብጨባ ተደበላለቀ፡፡.አለማየሁም ሆነ ሁሴን ከመጠን በላይ ተደሰቱና ተንደርድረው ባልና ሙስቶቹ ላይ ተጠመጠሙባቸው፡፡ከዚህ በፊት ተደርጎ የማያውቅ ልዩ አይነት ዝግጅት ሆኖ አለፈ…፡፡
እንግዶቹ ከተሸኙ በኋላ ቤተሰቡ ድግሱንና ፈንጠዝያውን ቀጠሉበት፡፡ሁሴን ወደመጣበት እንግሊዝ ተመልሶ እስኪሄድ ድረስ ከዛ ቤት የሄደ ሰው አልነበረም፡፡.እቴቴ ለአመታት ቃል በገባችው መሰረት ብቸኛ ልጆን በእርግዝና ወቅቷ ለመንከባከብና ከወለደችም በኃላ የልጅ ልጆን ለማሳደግ ስትል የራሷን ቤት ዘግታ ሙሉ በሙሉ ባልና ሚስቱ ጋር ተጠቃላ ገባች፡፡አለማሁም ከእንግዳ ክፍሎቹ ውስጥ አንዱ ክፍል ተመርጧ የእሱ ቆሚ ክፍል ሆኖ እንዲደራጅ ተደረገና ቢያንስ በሳምንት ሶስት እና አራት ቀን እየመጣ እነሱ ጋር ማደር ጀመረ፡፡እሱ እንቢ ብሎ እንጂ እነሱማ ቢያንስ የራስህን ሴት አግኝተህ ሚስት እስክታገባ ሙሉ በሙሉ የተከራየኸውን ቤት ልቀቅና እዚሁ እኛ ጋር ተጠቃለህ ግባ ና እንደቤተሰብ አንድ ላይ እንኑር ብለውት ነበር፡፡እሱ ግን ሙሉ በሙሉ በሚለው ሊስማማ አልቻለም፡፡በአጠቃላይ እንደዛ የጭቅጭቅ መናኸሪያ ሆኖ ቀዝቅዞ የነበረው ቤት አሁን ደምቆና በቤተሰብ

👍76❤15👏4🥰3👎1😱1