#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ለሀለቃዋ ትብለጥ ፍቅረኛዋ መሞቱ ድብርት ውስጥ እንደከታት ተናግራ የአንድ ወር ፍቃድ ወሰደች፡፡እረፍቷን ጨርሳ ተመልሳ ከመግባቷ በፊት መጽሀፉም አልቆ እስከወዲያኛው ይገላግላት ይሆናል፡፡አዎ ተስፋዋ ያ ነው፡፡
ሳባ እረፍት ከወሰደች በኋላ ቤት መዋል ጀመረች፡፡ራሷን መቆጣጠር እስኪያቅታት ድረስም ኃይለኛ መደበትና ጭንቀት ውስጥ ገባች፡፡እርግጥ ይሄ
የመደበት ችግር አሁን ፍቅረኛዋ ስለሞተ ወይም እሷ ራሷ ስላስገደለችው ድንገት የተከሰተባት በሽታ አይደለም…ከእሷ ጋር ሶስት አራት አመት በደባልነት ኖሯል…ቢያንስ በስድስት ወር አንዴ የሆነ ምክንያት ፈልጎ ይቀሰቀስባታል፡፡
ይተወኛል ብላ ለ15 ቀን ከቤቷ ሳትወጣ እረፍት ለማድረግ ብትሞክርም ነገሮች ግን እየባሱባት መጡ..በዚህም ምክንያት የስነ-ልቦና ባለሞያ እንድታናግር አንድ ወዳጇ ጨቀጨቃትና በሀሳቡ ተሰማምታ የጠቆማት ሆስፒታል ሄደች፡፡
በተቻላት መጠን ጥሩ አለባበስ ለብሳ ፤ከወትሮዋ በተሻለ ነቃ ለማለት፤ የተቻላትን ጥረት አድርጋ በጠዋት ተነስታ መኪናዋን አስነስታ በተሰጣት አድራሻ ሄደች፡፡ቀድማ ደውላ ቀጠሮ አስይዛ ስለነበረ.እንደሄደች ነበር ነርሷ የተወሰኑ ፎርሞችን እንድትሞላ በማድረግ ወደ ዶክተሩ እንድትገባ ያደረገቻት፡፡
ብዙ ጊዜ ለህክምና ወደተለያዩ የከተማዋ ስመጥር ሆስፒታሎች ሄዳ አገልግሎት አግኝታ ታውቃለች…አሁንም የገባችበት የዶክተሩ ምርመራ ክፍል ከዚህ በፊት ከምታውቃቸውና ከጎበኘቻቸው ብዙም የተለየ አይደለም…ግን በራፉን ከፍታ ወደውስጥ እንደገባች ፈዛለች፡፡ለውስጧ ጥልቅ ድረስ እስኪሰማት ድረስ ደንዝዛለች፡፡
‹‹ጤና ይስጥልኝ አረፍ በይ›› ሲላት ሁሉ አልሰማችውም.አይኗን አይኖቹ ላይ ተክላ በቆመችበት ቅዝዝ ብላ እየተመለከተችው ነው፡፡
እጁ ላይ ያለውን የእሷን ካርድ እየተመለከተ ‹‹ወይዘሪት ሳባ….አረፍ በይ››ሲላት እንደምንም ከመደንዘዝ ለመንቃት እየሞከረች እግሯን የመጎተት ያህል አንቀሳቀሰችና እንድትቀመጥ በተነገራት ወንበር ላይ ተቀመጠች፡፡
‹‹እሺ ሳባ ዶ/ር ጀማል እባላለሁ.››ሲል ራሱን አስተዋወቃት፡፡
ዝም አለችው
‹‹እስኪ ስለራስሽ ጥቂት ንገሪኝ›› አላት፡፡
‹‹ግራ ገባት..ሀኪም ቤት ለስነ-ልቦና ህክምና የመጣች ሳይሆን የሆነ ካፌ ውስጥ ቁጭ ብላ የሆነ አማላይ ወንድ ወንበሯን ተጋርቶ ሊጀነጅናት ሙከራ እያደረገ እሷ ደግሞ እየተግደረደረችና እየተሸኮረመመች ያለች ነው የመሰላት፡፡
‹‹ስለእኔ ምን?››
‹‹ስለ ማንኛውም ነገር….ሳባ ማን ነች?ምንድነው የምትወደው? ምንድነው የምትሰራው? ፡፡››
‹‹ስራዬ የሆነ የግል ድርጅት ውስጥ ተቀጥሬ ነው ምሰራው…ተቀጥሬ እንኳን ማለት ይከብዳል…በኮሚሽን ነው የምሰራው፡፡የምኖረው ብቻዬን ነው…ማለት አንድ ዘበኛ እና ተመላላሽ የቤት ሰራተኛ አለኝ... ጥሩ ኑሮ እኖራለው፡፡ግን ደግሞ ብቸኛ እና ደስታ የራቀኝ ሰው ነኝ..ሁሉ ነገር እየሰለቸኝ ነው…ለምን እንደምኖር እራሱ ግራ እየጋባኝ ነው፡፡››ሁሉን ነገር ተወችና ቀጥታ ወደ መደምደሚያው በመሻገር አሁን ሰላለችበት ሁኔታ ወደማብራራቱ ተስፈነጠረች፡፡
‹‹ጥሩ…. እንዲህ አይነት ስሜት ይሰማሽ የጀመረው ከመቼ ጀምሮ ነው?››
‹‹ሶስት አራት አመት..ግን የከፋ የሆነው ከሀያ ቀን በፊት ጀምሮ ነው፡፡፡››
‹‹በቅርብ በህይወትሽ የተከሰተ ጠንከር ያለ ነገር ነበር?››
‹‹አዎ ለአንድ አመት ፍቅረኛዬ የነበረ ሰው ቀለበት እያሰረልኝ ሳለ እኔ የማላውቃት ልጅ ፍቅረኛው ሆና በጠርሙስ ጭንቅላቱን ከፈለችውና ሞተ…ከዛ ወዲህ ይመስለኛል ነገሮች እየባሱ የሄዱት፡፡››የታሪኩን ግማሽ እውነት ነገረችው፡፡
‹‹ገባኝ….ግን የትኛው ነው በጣም ያመመሽ…?››ሲል ጠየቃት
‹‹ከምንና ከምኑ?››
‹‹ከፍቅረኛሽ ሞትና….ከመከዳትሽ?››
ደነገጠች…እንዲህ ፈፅሞ አስባ አታውቅም..‹‹መከዳት…ስለፍቅረኛው ማለትህ ነው?››
‹‹አዎ››
ዝም አለች..ምን እንደምትመልስ ግራ ገባት፡፡ሳባ ልክ እንደጓደኛሽ ቁጠሪኝ ….ነፃ ሁኚ፡፡
‹‹አይ ፋሲልን .ማለቴ ፍቅረኛዬን በተመለከተ የሚሰማኝ ስሜት ግራ የተጋባ ነው…ሞቱ ይሄን ያህል ይረብሸኛል ብዬ ፈፅሞ አስቤ አላውቅም ነበር….የእኔና የእሱ ግንኙነት በተወሰኑ የጋራ ጥቅሞች ላይ የተመሰረተ ነበር…ፍቅረኛውን በተመለከተ ምንም የሚሰማኝ ነገር የለም..በእርግጥ እስከመጨረሻው ቀን ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም..ባውቅም በእኔ ላይ ማግጦብኛል ብዬ የምበሳጭበት ምክንያት አይታየኝም...እኔም ታምኜለት አላውቅም እሱም ይታመንልኛል የሚል እምነት አልነበረኝም..እውነቱን ለመናገር እንዲታመንልኝም ፍላጎቱ አልነበረኝም.. በአጠቃላይ ስለፍቅረኛው ማወቄ ምንም ትርጉም የሰጠኝ አይመስለኝም፡፡››
‹‹ምን አልባት ትዳሩን ትፈልጊው ነበር…?በእሱ ሞት ምክንያት በመበላሸቱ ተበሳጭተሻል?››
‹‹በተአምር እንደዛ አይነት ፍላጎት አልነበረኝም...ቀለበቱን ሲያደርግልኝ ድንገት ሳያማክረኝ ነበር ያደረገው...ማማከር ሳይሆን ስለወደፊታችን አውርተን እንኳን አናውቅም...እንዳገባው ሲጠይቀኝ በጣም ብዙ በሚያውቁት ሰዎች ፊት ስለሆነ እሱን ላለማሸማቀቅ እና ግርግር ላለመፍጠር ነበር ጣቴን የዘረጋሁለት..እና መቼም ላገባው እቅድ አልነበረኝም፡፡ግን የገረመኝ በመሞቱ በውስጤ ቅሬታ ተፈጥሯል …ፈፅሞ ልረሳው አልቻልኩም…ከእሱ የማጣው አንድ ብቸኛ ነገር ወሲብ ነው….ያንን ደግሞ ካሰብኩበት ከሌላ ሰው በቀላሉ ማግኘት እችላለሁ…ያው የእሱን ያህል ሊሆን ባይችልም ማለቴ ነው..እና ለምን ከአዕምሮዬ ላወጣው እንዳልቻልኩ አልገባኝም፡››
‹‹ግን እሱ ብቻ ነው የሚያስጨንቅሽ? ማለቴ እሱ በህይወት እያለስ ሌላ ምቾት የሚነሳሽ ጉዳይ ነበር?››
‹‹እየተጠነቀቀች እራሷን ከመጠን በላይ ላለማጋለጥ እየጣረች ከሁለት ሰዓት በላይ ከዶ/ሩ ጋር አወራች….በጊዜያዊነት የሚያረጋጓትን ሁለት መድሀኒቶችን መውሰድ ከሚገባት የተወሰነ ምክር ጋር ለግሷት ለሳምንት ሌላ ቀጠሮ ሰጥቷት አሰናበታት….
በመምጣቷ ተደስታለች …በዶ/ሩ መስተንግዶ ተደስታለች..ልቧ ለምን እንደደነገጠባት አልገባትም…ያምራል…ከአይኖቹ የሚረጫቸው ብርሀን የሰውን ልብ በቀላሉ ይሰረስራሉ፡፡ንግግሩ እርጋታ የተለባሰና እንዲያወሩ የሚያበረታታ ነው፡፡ በዛ የተነሳ በቆይታዋ ተደስታለችም…የተወሰነ ቀለል የማለት ስሜትም እየተሰማት ነው..ትንሽ ቅር ያላት ቀጠሮ ከሳምንት በኋላ መሆኑ ነው፡፡ ከሁለት ወይም ከሶስት ቀን በኋላ መልሳ ብታገኘው ደስ ይላት ነበር.ደግነቱ ችግር ካለና የተለየ ስሜት ከተሰማት እንድትደውልለት ነግሯት ቁጥሩን ሰጥቷታል፡፡መኪናዋን ራሷ እያሽረከረች ቀጥታ ወደቤቷ ሄደች..አዲሱ ዘበኛዋ በራፉን ከፈተና ወደ ውስጥ አስገባት..፡፡ይሄንን ዘበኛ ከቀጠረች አስር ቀን ቢሆነው ነው፡፡የመጀመሪያውን ዘበኛ ያሰናበተችው የመጀመሪየውን ዘበኛ ከእሷ ጋር አስተዋውቋት ያስቀጠረው ፋሲል ስለነበረ ነው፡፡ከእሱ ጋር የሚያገናኛት ምንም አይነት ትዝታ አትፈልግም፡፡ደግሞ ምን አይነት ሚስጥራዊ ግንኙነት እንዳላቸው ስለማታውቅና በዛም ጥርጣሬ ስለነበራት ያልሰራበትን የሶስት ወር ደሞዙን ሰጥታ አሰናበተችው፡፡
ከዛም እንደተለመደው መኝታ ቤቷ ገባችና ራሷን ሸሸገች..
💫ይቀጥላል💫
ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

👍89❤15🤔3👏1
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
:
:
#ክፍል_አራት
:
:
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ፔሩ/ኢኩኤቶስ
ኑሀሚ በተኛችበት አጨንቁራ በመስታወቱ አሻግራ እያየችው ነው፡፡የህይወት አዙሪት ከየት ወስዶ የት ላይ እንደወረወራት አሰበችና እጅግ ተገረመች፡፡ስለእሱ እና ስለገጠመኞቾ እያመላለሰች በማሰብ ላይ ሳለች ድንገት ወደሀገር ቤት የሚያበር የሀሳብ ሀዲድ በአእምሮዋ ተዘረጋ….ጭንቅሏቷን ትራሷ ላይ አመቻቸችና በተዝናኖት ተኝታ በተዘረጋው ሀዲድ ወደሀገር ቤት በትዝታ ፍስስ አለች፡፡ ኑሀሚ የተደላደለ እና የተረጋጋ የሚባል ህይወት የኖረችው እስከ 9 ዓመቷ ድረስ ብቻ ነበር፡፡ ከዛ በጥምቀት ሰሞን በእለተ ከተራ የዘጠኝ አመቷን የልደት በአል ሊከበርላት ድግስ ተደግሶ፤ ኬክ ታዞ፤ ሻማ ተገዝቶና ፤እቤቱ በዲኮሬሽን አሸብርቆ ባለበት ቀን እናትና አባቷ ተቃቅፈው በተኙበት ሞተው ተገኙ፡፡በምትወዳት የልደት ቀኗ በጥምቀት ቀን ጥር 11 በህይወቷ በጣም ልብ ሰባሪው ሀዘን ደረሰባት፡፡ከዛ በኃላ ህይወት ለእሷ ቀላል ሆና አታውቅም፡፡ከዛ በኃላ በአለም ላይ በ10 ደቂቃ ታላቋ ከሆነ ከመንትያ ወንድሟ በስተቀር ምንም ነገር አልነበራትም….ከዛ በኋላ አመት በመጣ ቁጥር በጥምቀት ወቅት ህዝበ- ክርስቲያኑ በየጎዳናው ተቦት ተከትለው ሲዘምሩና ሲጨፍሩ የወላጆቾን ሬሳ ተከትለው ሙሾ የሚያወርዱ ለቀስተኞች ነው የሚመስሏት…በቃ ከዛ በኃላ ሕይወት በአጠቃላይ ሁሉ ነገር አስከፊ ሁሉ ነገር አስጠዩ ነበር የሆነባት፡፡ይህ በጥልቅ ሀዘንና ብቸኝነት አጥንት የሚሰነጣጥቅ ችግር ለእሷ ብቻ ሳይሆን ለወንድሟም ጭምር ነበር፡፡ስለወንድሟ ትዝ ሲላት ከተጋደመችበት ተስፈንጥራ ተነሳችና ስልኳን በማንሳት ወደ ሀገር ቤት ደወለች…ወንድሟ ጋር፡፡
‹‹ሄሎ ናኦል…እንዴት ነህ?››
‹‹አለሁልሽ እህቴ…እንዴት ነሽ…?.ሁሉ ነገር አሪፍ ነው?፡፡››
‹‹ሰላም ነኝ.. ዛሬ ከፔሩ አንተ ወደምትወዳት ብራዚል እየበረርኩ ነበር… ግን የአየር ፀባዩ ተበላሸና ሳንደርስ አንድ የምታምር ለብራዚል ድንበር ቅርብ የሆነች የፔሩ ከተማ ለማረፍ ተገደድን፡፡››
ወንድሟ በሰማው ዜና በጣም ደነገጠ‹‹እንዴት ….?ምን አይነት ቦታ ነው ያረፋችሁት ..?ፕሌኑ ሰላም ነው?››
‹‹አረ ሁሉ ነገር አሪፍ ነው…፡፡››
‹‹እና እንዴት ልትሆኑ ነው?››
‹‹በቃ ምን እንሆናለን..አሁን ቤርጎ ይዤ አረፍ ብዬ ነው እየደወልኩልህ ያለሁት፡፡ነገ የአየር ፀባዩ ከተሻሻለ እንቀጥላለን፡፡ከለበለዚያ የዝግጅቱ አስተባባሪዎች በሚሰጡት ትዕዛዝ መሰረት የምናደርገውን እናያለን፡፡››
‹‹አህቴ እራስሽን ጠብቂ ደግሞ በጣም ናፍቀሺኛል….ጨርሰሽ እስክትመጪ ቸኩያለሁ፡፡..ሶስት ወር እንደዚህ ረጂም መሆኑን አላውቅም ነበር››ሲል ተናዘዘላት፡፡
‹‹ለምን ይዋሻል..ከዚህ በፊት እኮ ሶስት አመት ሙሉ ተለያይተን ነበር››
‹‹የዛን ጊዜ እኮ እኔ ራሴ ሀይለኛ ወከባ ላይ ነበርኩ…የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት አለ..በዛ ላይ በምታውቂው ስራ ሀለቃችን ምስራቅ ከወዲህ ወዲያ ታሽከረክረኝ ነበር…ከዚህ ሁሉ መዋከብ በተረፈቺኝ ብጣቂ ጊዜ ብቻ ነበር አንቺን መናፈቅ የምችለው፡፡አሁን ግን ስለአንቺ ከማሰብ ውጭ ሌላ ምን ስራ አለኝ?››ሲል ተናዘዘላት፡፡
‹‹ስለናፈቅኩህ ደሰስ ብሎኛ፤ቻለው ከአንድ ወር በታች ነው የቀረኝ…እና ደግሞ እንዲህ ዞር ስል የምናፍቅህ ከሆነ ስርህ እያለው አታበሳጨኝም ማለት ነው፡፡››
‹‹አረ አንቺ ብቻ ነይልኝ እንጂ ቀና ብዬም አላይሽም፡፡››ሲል ቃል ገባላት፡፡
‹‹ነግሬሀለው… አሁን የተናገርከውን ሪከርድ አድርጌዋለው፡፡››
‹‹ችግር የለውም እውነቴ ነው፡፡››
‹‹ምስራቅ ደህና ነች..?››ስትል ሌላ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹ያው ታውቂያለሽ ..እሷ ካልፈለገች አላገኛትም..ግን ደህና መሆኗን አውቃለሁ፡፡››ሲል እሷ ብቻ ሳትሆን ምስራቅም እንደናፈቀችው በሚያሳብቅ የድምፅ ቅላፄ መለሰላት፡፡ምስራቅ ማለት በሁለቱም ህይወት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያላት…የደህንነት መስራቤት ውስጥ የምትሰራ ሲኒዬር ሰላይና ለአመታት ሀለቃቸው የነበረች የ43 ዓመት ሴት ነች፡፡
‹‹በል ቸው ..ልተኛ ደክሞኛል ነገ ደውልልሀለው፡፡››አለችው፡፡
‹‹ቸው እህቴ …ውድድ ነው የማደርግሽ››ስልኩ ተዘጋ፡፡
አልጋውን ለቃ ወረደችና ወደ ፍሪጁ በመሄድ ሌላ የቆርቆሮ መጠጥ አወጣችና ከፍታ እየተጎነጨች ወደውጭ ወጣች፡፡ዳግላስ አሁንም ላፕቶፑ ላይ አቀርቅሮ ውዝግብ ውስጥ እንደገባ ነው፡፡የአማዞን ወንዝ ከበረንዳው አሻግረው ሲያያዩ እንደእባብ ተጠምዝዞ ሽብልል እያለ ሲፈስ ይታያል፡፡ትኩረቷን ወደዳግላስ መለሰችና‹‹እሺ አዲስ ነገር አለ?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹የተወሰነ ነገር እየገባኝ ነው፡፡ሳይንቲስት ነኝ፡፡አዎ ኬሚስት ነኝ፡፡እዚህ አማዞን ጫካ ውስጥ በሚገኝ የኮኬይ መቀመሚያ ላብ ውስጥ እሰራ ነበር፡፡አሁንም እንዴት እንደሚቀመም ፕሮሰሱን ሁሉም ትዝ ብሎኛል፡፡ግን ከዛ በፊት የት ነበርኩ..?የት ነው የተማርኩት? ቤተሰቦቼ የት ናቸው…?ሚስትና ልጆች አሉኝ…?እንዴት እዚህ ነገር ውስጥ ልገባ ቻልኩ?አሁንስ ፔሩ ምን ስሰራ ነበር..?የተሸከምኩትን ሻንጣ ሙሉ ዶላር ከየት አመጣሁት? ለምንስ ተሸከምኩት?አሁንስ ወደብራዚል ለምንድነው እየሄድኩ ያለሁት?ቀደም ብለሽ አንቺ ለጠይቅሺኝ ለእነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች ሚሆን መልስ ግን እስከአሁን አላገኘሁም፡፡››
‹‹በቃ ላፕቶፑን ዝጋና ተነስ… ወደ ውስጥ እንግባ …ምን አልባት ለጠየቅካቸው ጥያቄዎች ሁሉ የሚሆኑ መልሶችን አረፍ ብለህ እንቅልፍ ከተኛህ በኃላ ትዝ ሊሉህ ይችላሉ፡፡ዶላሩ ላልከው ግን ምን አልባት ለአመታት ለሰራህላቸው ስራ የከፈሉህ ደሞዝ ሊሆን ይችላል፡፡ምን አልባት ከእነሱ ጋር በሰላም ተለያይተህ ሰላማዊና ኖርማል ህይወት ለመኖር ወደ ሀገርህና ቤተሰቦች በመጓዝ ላይ ትሆናለህ፡፡በል አሁን እኩለ ለሊት ሆነ ፤አረፍ እንበልና ነገ ከነገወዲያ የሚሆነውን እናያለን..ምን አልባትም እኮ ለእነዚህ ሁሉ ጥቄዎችህ መልስ የሚሰጥህ ሰው አየር ማረፊያ ቆሞ እየጠበቀህ ሊሆንም ይችላል፡፡››
‹‹አዎ እኔም ተስፋ ማደርገው እንደዛ ነው፡፡››አለና እንዳለችው ላፕቶፑን በመዝጋት መቀመጫውን ለቆ ተነሳ፡፡ ..ተያይዘው ወደ ውስጥ ገቡን ወደበረንዳ የሚያስወጣውን በራፍ በመዝጋት በየአልጋቸው ላይ ተቀመጡ፡፡
‹‹ታውቂያለሽ ከሌላ ፕላኔት ድንገት ተንሸራትቼ የወደቅኩና ያለቦታዬ ከማላውቃቸውና ከማይመስሉኝ ፍጡሮች ጋር የተቀላቀልኩ እየመሰለኝ ነው፡፡››አላት
በንግግሩ አሳዘናት‹‹አይዞኝ…..እንዳልኩህ አሁን መጨነቁን አቁምና ለማረፍ ሞክር…ጥዋት የሚሆነውን እናደርጋለን፡፡›› ብላ አልጋዋ ላይ ወጣችና ተሸፋፍና ለመተኛት መከረች፡፡ፈፅሞ እንቅልፍ ይወስደኛል ብላ አላሰበችም ነበር፡፡ግን ወዲያው ነበር ጭልጥ ያለ እንቅልፍ የወሰዳት፡፡ማለዳ 12፡40 አካባቢ ከእንቅልፏ ባና አይኗን ስትገልጥ ዳግላስ ስትተኛ ተቀምጦበት በነበረበት ቦታ ተቀምጦ ነው ያገኘችው፡፡
‹‹ምነው አልተኛህም እንዴ?››ስትል በመገረም ጠየቀችው፡፡
‹‹አይ አልተኛሁም፡››
‹‹እና እዛው የተቀመጥክበት ቦታ አነጋኸው …. ?››

👍88❤8
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
በፀሎት ከጠፋች ከአንድ ሰዓት በኃላ ነበር አባትዬው ዜናውን የሰሙት፡፡በመጀመሪያ የቤቱ ሰው ሁሉ ያሰበው የተለመደው የልብ በሽተዋ ተነስቷባት ተዝለፍልፋ የሆነ ቦታ ወድቃ ይሆናል ተብሎ ነበር ፡፡ለአንድ ሰዓት ያህል ጋርዶቹ ፤ ዘበኞቹና አስተናጋጆቹ ሳይቀር የቤቱ ጥጋጥግ ከ50 በላይ ክፍሎች አንድ በአንድ እየከፈቱ አንድም ቦታ ሳይቀር ፈልገው ጅባት ካሉ በኃላ ነበር የጋርዶቹ ሀላቃ ፈራ ተባ እያለ የአቶ ኃይለመለኮትን መኝታ ቤት ያንኳኳው….በለሊት ልብሳቸው ሆነው የልጃቸውን የልደት በዓል ምክንያት በድካም የዛለ ሰውነታቸውን አልጋ ላይ አሳርፈው ገና እንቅልፍ እንዳሸለባቸው ነበር በራፋቸው የተንኳኳው…በመጀመሪያ በህልማቸው መስሏቸው ነበር፡፡ በኋላ ግን የምርም ክፍላቸው እየተንኳኳ መኆኑን ገባቸውና እየተነጫነጩ አልጋቸውን ለቀው በንዴት ውስጥ ሆነው በራፉ ሊከፍቱ እየሄዱ ባሉበት ቅፅበት ከመኝታ ቤታቸው ቀጥሎ ካለው ከፍል ውስጥ ያሉት ወ.ሮ ስንዱ ድምፅ ሰምተውና ደንግጠው ክፍላቸውን ከፍተው እየወጡ ነበር፡፡ ሁለቱም በአንድ ጊዜ እያንኳኳ ያለው ጋርድ ላይ አፈጠጡበት፡፡
‹‹ምን ተፈጥሮ ነው?››
‹‹ጋሼ..እንዴት እንደሆነ አናውቅም…..ልጆቹ እየተከታተሏት ነበር….››ለማስረዳት አስቦ መንተባተብ ጀመረ..፡፡
‹‹ምን እያወራህ ነው?››
‹‹በፀሎት..››
‹‹በፀሎት ..ልጄ ምን ሆነች..?አመማት እንዴ…?የልብ ህመሟ ተቀሰቀሰባት?››እናትዬው በመርበትበት በጥያቄ አጣደፉት፡፡
‹‹አይ አላመማትም…ላለፉት አንድ ሰዓት ውስጥ ስንፈልጋት ነበር…የለችም…››
‹‹የለችም ማለት…….?››
‹‹ጓደኞቾ ደብቀው ይዘዋት ሄደው መሰለኝ…. ግቢው ውስጥ የለችም፡፡››
‹‹እንዴ ..ይሄ ምን ማለት ነው..?ያን ሁሉ ጠብደል ጎረምሳ በጠባቂነት የቀጠርኩት እንዲህ አይነት ነገር እንዲከሰት ነው እንዴ…?ሰውዬ የእያንዳንዳችሁን ግንባር በሽጉጥ ሳልነድልላችሁ ልጄን ካለችበት ፈልጉና አስረክቡኝ…፡፡››በመራር ንግግር ቀድሞም የደነገጠውን ሰውዬ ይበልጥ ፍርሀት ለቀቁበት፡፡
‹‹እሺ ጌታዬ… ሁሉም ሰው እየፈለጋት ነው፣ይሄንን ነገር እርሶም በሰዓቱ መስማት አለቦት ብዬ ነው ቀድሜ ያሳወቅኳት…››
‹‹ወይኔ ልጄን..ይሄ የእነሱ ሳይሆን ያንተ ጥፋት ነው…››እናትዬው ቁጣቸውን ወደባላቸው አዞሩት፡፡
‹‹ይሄ ደግሞ ምን ማለት ነው?››ባልና ሚስቶች የተለመደውን ጭቅጭቃቸውን ቀጠሉ፡፡
‹‹ልጄን እንደከብት እረኛ ቀጥረህባት ስታጨናንቃት ነው ለዚህ ያበቃችው፡፡››
‹‹ሴትዬ እስኪ አሁን ተይኝ….እኔ ለራሴ ግራ ገብቶኛል ይበልጥ ግራ አታጋቢኝ.››አሉን ፊት ለፊት እየሄደ ያለውን ጋርድ ተከትለው ኮሪደሩን አቆርጠው መሄድ ጀመሩ..፡፡ወ.ሮ ስንዱም ማጉረምረማቸውን በለቅሶ አጅበው የለበሱትን ቢጃማ እንኳን ሳይቀይሩ ከኋላ መከተል ጀመሩ…፡፡በፀሎት ግን ለሊቱን ሙሉ ብትፈለግ ..በየወዳጅ ዘመድ ቤት ቢደወል…በከተማ አውራ ጎዳናዎች ከሰላሳ በላይ መኪኖችን ተሰማርቶ ብትፈለግ ድኩዋን ለማግኘት አልተቻለም…
በስተመጨረሻ የግቢው ካሜራ ቅጂ ለሁለተኛ ጊዜ በዝግታ ሲታይ ነው እራሷን በአለባበሶ ቀይራ ብቻዋን በሞተር ሳይክል ግቢውን ለቃ እንደወጣች የታወቀው፡፡ይሄ ደግሞ በቤተሰቡ ላይ የነበረውን ድንጋጤና ፍራቻ ይበልጥ አናረው..ምክንቱም አወጣጧ አስባባት መሆኑን ስለተረዱ….፡፡ከዛ አባትዬው አቶ ኃይለመለኮት ያላቸውን ተሰሚነትና ከመንግስት ሰዎች ጋር ያላቸውን ትስስር በመጠቀም ለእያንዳንዱ ፖሊስና ትራፊክ ፖሊስ ፎቶዋና የሞተር አይነትና ታርጋ ቁጥሩ ተበትኖ እንድትፈለግ መመሪያ እንዲተላለፍ ተደረገ ፡፡
በማግስቱም ምንም ፍንጭ ሳይገኝ በመንጋቱ እቤቱ ሁሉ በወዳጅ ዘመድ ተጨናነቀ፡፡..ወላጆቹ በስጋትና ፍራቻ ብቻ ሳይሆን በሰው ትንፋሽም መፈናፈኛ አጣ…አቶ ኃይለመለኮት ሲጨንቃቸው ከአጀቡ ተነጥለው ቀጥታ ወደልጃቸው መኝታ ቤት ገቡና ከውስጥ ዘግታው አልጋዋ ጠርዝ ላይ ቁጭ ብለው ግድግዳው ላይ የተለጠፈውን ግዙፍ የልጃቸውን ፎቶ እየተመለከቱ በትካዜ መንሳፈፍ ጀመሩ....እንባቸው መቆጣጠር አልተቻላቸውም…እንደህፃን ልጅ ነው ተንሰቅስቀው ያለቀሱት….በህይወታቸው እንዲህ አይነት ለቅሶ መቼ እንዳለቀሱ ፍጹም ትዝ አይላቸውም….አዎ ልጃቸው የልብ ንቅለተከላ በተደረገላት ጊዜ በህይወታቸው በጣም ያዘኑበትና የተጨናነቁበት ጊዜ ነበር…በቀሪ ህይወታቸውም መቼም ተመሳሳይ ሀዘን ውስጥ እገባለሁ የሚል ግምት አልነበራቸውም….ግን ተሳስተው ነበረ..አሁን ያሉበት ጭንቀትና ስጋት ከዛን ጊዜም ከፍ ያለ ነው…. ፡፡ልጃቸው አንድ ነገር ብትሆን ምን እንደሚሆኑ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም..፡፡ግን በእርግጠኝነት ሌላ ኃይለመለኮት እንደሚሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው..ምን አልባት አብደው ጨርቃቸውን ሊጥሉ ይችሉ ይሆናል...ወይንም ንዴታምና አውሬ አይነት ሰው ሊሆኑ ይችላሉ ….ልባቸው ፍስስ እያለባቸው ነው….አይናቸውን ከወዲህ ወዲያ እያሽከረከሩ የልጃቸውን እቃዎች በስስት ሲቃኙ አይናቸው አንድ ፖስታ ላይ አረፈ..በድንጋጤ ተነሱና ወደእዛው ተራመድ፡፡ አነሱት… ሁለት ነው…፡፡ከላዩ ላይ የተፀፈውን አነበቡት..፣አንደኛው ለአባዬ ይላል…ሁለተኛውን አዩት ለእማዬ ይላል…እሱን ጠረጴዛው ላይ መልሰው አስቀመጡና ለእሷቸው የተጻፈውን ይዘው ወደአልጋ ጠርዝ ተመላሱና ፖስታውን ቀደው ወረቀቱን በማውጣት ማንበብ ጀመሩ፡፡
አባዬ….እንዴት እንደምወድህ ታውቃለህ አይደል? በጣም ነው የምወድህ..ግን ሁሌ ትናፍቀኛለህ…፡፡ሁሌ እሩቅ ውጭ ሀገር ያለህ ነው የሚመስለኝ….እቤት እያለህ እራሱ የሌለህ መስሎ ነው የሚሰማኝ…እርግጥ አንተ ሁሉ ነገር ተሟልቶልኝ በቅምጥል የምኖር ደስተኛ
ልጅ ነው የምመስልህ…እየቀያየርኩ ምነዳችወ ከሶስት በላይ ዘማናዊ መኪናዎች አሉኝ፣በወር ከመቶ ሺ ብር በላይ በእጄ ይሰጠኛል….በየሄድኩበት እየሄዱ የሚጠብቁኝ ቁጥራቸውን የማላውቃቸው ጋርዶች አሉኝ……በአመት ሁለትና ሶስት ጊዜ የፈለኩትን ውጭ ሀገር ሄጂ እዝናናለሁ…በአጠቃላይ ኑሮዬ ለአብዛኛው ኢትዬጵያዊ በተረት አለም እንኳን ሰምቶት የማያውቀው የህልም አለም አይነት ነው…ግን እኔ በእድሜዬ እናትና አባቴ ሲሳሳሙ አይቼ የማላውቅ ልጅ እንደሆኑክ ማንም አያውቅም..አረ መሳሳሙ ይቅር አንድ መኝታ ቤት ውስጥ አብረው ሲያድሩ አይቼ አላውቅም… አይገርምም…..፡፡
አባዬ ልጅ ሆኜ እርግቤ እያልክ ነበር የምትጠራኝ..እርግቤ ስትልኝ እንዴት እንደምደሰት አታውቅም ፡፡የእውነትም ያንተ ነጭ እርግብ ሆኜ አድማሱን ሰንጥቄ በሰማይ መብረር የምችልና ጨረቃ ጋር ደርሼ ከዋክብቶችን ጨብጬ ምጫወትባቸው ይመስለኝ ነበር…በቃ ትንሽ መልአክ እንደሆንኩ እንዲሰማኝ ነበር የምታደርገው..ግን አባዬ አንተ ያልተረዳኸውነ ነገር እኔ ከ19 ዓመቴ በኋላ ማለቴ የሌላ ሴት ከሰውነቴ ካወሀድኩ ጀምሮ እኔ እኔን አይደለሁም…..ትዝ ይልሀል እርግቤ አትበለኝ በስሜ ጥራኝ ብዬ ያስተውኩህ እራሴው ነኝ..ለምን ብለህ ጠይቀኸኝ ግን አታውቅም..ምን አልባት ዝም ብዬ እርግቤ የሚለው ሰም ደስ ስለማይለኝ መስሎህ ሊሆን ይችላል እንደዛ ግን አይደለም….ከልብ ነቅለ-ተከላ ከተደረገልኝ በኃላ ክንፏ የተሰበረባት መብረር የማትችል እና በየጓሮ የምትንፏቀቅ እርግብ እንደሆንኩ እየተሰማኝ ስለመጣ ነው ያስቆምኩህ..ለአንድ ልጅ እኮ በሰማይ እንዳሻት እንድትበር የሚያደርጋት የአባቷ ፍቅር ቀኝ ክንፍ እና የእናቷ ፍቅር ግራ ክንፍ ሲሆናት ነው….የወላጆቾ ፍቅር ነው እንድትበር የሚያደርጋት….ያ እንደሌለኝ ስረዳ ነው ስሙ ያስጠላኝ፡፡ለምን

👍92❤8👏4😁1
#የጣት_ቁስል
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ
ተመስገን
ከጠፋች በኋላ፤ ብቻ ሳይሆን ከእድላዊት ጋርም ከትምህርት ቤት መጥተው ምሳቸውን ከበሉበት ቀን አንስቶ ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ አይደለም አስቦትም አያውቅም፡፡
ወደ ትምህርት ቤትም አልሄደም፡፡ ትዳር የሚባል ሳያስብ እናት አባቱን እየረዳ የግብርና ስራውን ሌት ከቀን እየተጋ መዋሉን ተያይዞታል፡፡
ከሚወዳት እህቱ እድላዊት ውጪ የቅርብ ጓደኛዬ የሚለው ሴትም ይሁን ወንድ ለግዜው አልነበረውም፡፡ አንድ ቀን በስራ ምክንያት ከሰፈሩ ልጅ ያሬድ ጋር ይገናኛል፡፡ ታዲያ ተመስገንና ያሬድ ከዚህ በፊት ከእግዚአብሔር ሰላምታ በስተቀር የጠበቀ ግንኙነት አልነበራቸውም፡፡
ያሬድ ተመስገንንም ይሁን ቤተሰቦቹን በደንብ ጠንቅቆ ያውቃቸዋል፡፡ በጥሩ ቤተሰብ ያደገና ከቤተሰቦቹ ጋር የሚኖር ገና ታዳጊ ወጣት ሆኖ በራሱ ፈቃድ
ትምህርቱን አቋርጦ ወደ ግብርናው ከተሰማራ ሰንበትበት ብሏል፡፡
ከተመስገን ጋር ግንኙነታቸው ከእግዚአብሔር ሰላምታ አልፎ ወደ መቀራረብ ደረሰ ፤ አልፎ አልፎም ስራ በመተጋገዝ መረዳዳት ጀምረዋል፡፡
ተመስገን እንደ እህቱ የሚሆንለት ባያገኝም ለእሱ የሚሆንና የሚያበረታታው የቅርብ ጓደኛ በማግኘቱ ደስተኛ አድርጎታል፡፡
ከእለታት አንድ ቀን እነያሬድ ቤት የሽንብራ ቆሎ እየፈጩ ፤ ከስንዴው ጠላ ጎንጨት እያሉ የወደፊት ምኞታቸውና አላማቸውን ይጫወታሉ፡፡
"ለወደፊት ምን ለመስራት አስበሃል?" ብሎ ጠየቀው ተመስገን፡፡
"እኔ ለቀጣይ ያስብኩት አሁን የጀመርኩትን ቤት ስጨርስ ቤተሰቦቼ ትምህርትህን ከተወህ ማግባት አለብህ እያሉኝ ስለሆነ ለማግባት አቅጃለሁ፡፡ ብሎት አንተስ ምን አስበሃል? አለው ያሬድ፡፡
ተመስገን የወደፊት ምኞትና እቅዱ ከጓደኛው ያሬድ የተለየና ተቃራኒ ነው፡፡ "እኔ እንኳን እህቴን እስከማገኝ ድረስ ትዳር የመያዝ ሃሳብና ፍላጎት የለኝም"፡፡
ቤተሰቦቸን እየረዳሁ ለራሴም ትንሽ እያጠራቀምኩ ለመኖር ነው የማስበው አለ፡፡
ያሬድ የተመስገንን እቅድ ሲሰማ እህቱን በፊትም እደሚወዳት ስለሚያቅ ለምን አታገባም ብሎም አልጠይቀውም..፡፡
አርምዴ
ባለቤታቸው ከሞተ በኋላ፤ ሌላ ባል አላገቡም፡፡ ወደ ውጭ ወጥተው ጎንበስ ቀና ብለው መስራት አይችሉም፡፡
ልጃቸው ሰርቶ የሚሰጣቸውን እህል አብስለው ለመብላት ያልተቸገሩ የስልሳ ዓመት የእድሜ ባለፀጋ ናቸው፡፡ የአርምዴ እናት ወ/ሮ በሰልፏ፡፡
ቀኑ እንደመምሸት ብሎ ለዓይን ያዝ አድርጓል፡፡ ኩራዝ ለመለኮስ ከምድጃቸው እሳት ለማቀጣጠል ይታገላሉ፡፡
አይናቸው ተርገበገበባቸው፡፡ ዛሬ ደግሞ በምሽት ምን ሊያሳየኝ ነው ፡፡ አይኔ የሚርገበገበው እያሉ የውጭ በር ተንኳኳ
እሳት ማቀጣጠሉን ተወት አርገው ወደ ውጭ ወጡ፡፡ ልጃቸው አርምዴ እድላዊትን አዝሎ ገባ፡፡ ደነገጡ፡፡
"ውይ! በሞትኩት ልጄ ምን ሆና ነው? ብለው ጠየቁት፡፡
እረኞች ጫካ ውስጥ መሬት ለመሬት ጎትተዋት ነው፡፡
"እና በጣም ጎድተዋታል" ?
"አዎ! ይዣትም ስመጣ ለማናገር ብሞክርም ማናገር አልቻለችም"፡፡
"ታዲያ ከየት እንደመጣችም አልነገረችህም"?
"አልነገረችኝም ፡፡ ጩኸት ሰምቼ እየሮጥሁ ሲሄድ ጥለዋት ተበታተኑ፡፡ እሷም ተጎድታ ስለነበር አላናገረችኝም፡፡ እንዴው እግዚአብሔር ድረስላት ሲለኝ ነው እንጂ ዛሬ አደን የሔድኩት ይገሏት ነበር፡፡
"አሁን ምን እንስጣት? ነው ትንሽ ትተኛ? ድካሟ እስከ ሚያልፍላት አሉ ወ/ሮ በሰልፏ፡፡
ወደ አስተኛት ፍራሽ ላይ ተጠጋ፡፡ እድላዊት አይኖቿን አንከራተተች፡፡ ግራና ቀኝ ተቁለጨለጨች፡፡
አርምዴ የእድላዊትን አይኖች መንከራተትና በእንባ መሞላት አየ፡፡ እሱም ከየት መጣ ሳይባል አይኖቹ በእንባ ተሞሉ፡፡
እድላዊት አርምዴን የምትመለከተው ውሃ ስጠኝ ለማለት ነበር፡፡ ግን መናገር አቅቷታል፡፡
አቶ አርምዴ ውሃ መፈለጓን የተረዳት አይመስልም፡፡ አንጀቱ እንደነብሰጡር ተላወሰ፡፡ እንባ እየተናነቀው "ምን ልስጥሽ " አላት፡፡
እድላዊት መናገር አልቻለችም፡፡ በእጇ ውሃ እንደ ጠማት አመለከተችው፡፡
አቶ አርምዴ በምልክት የገለፀችውን ሳያደናግረው ተረዳት፡፡ ውሃ ቀድቶ ሰጣት፡፡
ውሃው ወደ ውስጥ መግባቱን ትቶ ግራና ቀኝ በአፏ ወደ ውጭ ፈሰሰ፡፡
እድላዊት በውሃ ጥም የተነሳ ቶንሲሏ ወርዷል፡፡ አቶ አርምዴ የባሰ ተጨነቀ
"ውይ በሞትኩት ልጄን ውሃ አልወርድላት አለ ? ቶንሲሏ ወርዶ ይሆናል አሉ፤ ወ/ሮ በሰልፏ፡፡
"እና ምን ይሻላል? መድሃኒት በቅርብ አይገኝም? አለ ፤ አቶ አርምዴ፡፡
ወ/ሮ በሰልፏ የሃበሻ መድሃኒት ሊያቀምሷት መድሃኒቱን እንዲያመጣላቸው ልጃቸውን እንዳይልኩት መድሃኒቱ ሲቆረጥ ስሙ መጠራት የለበትም፡፡ እራሳቸው ለመቁረጥ ቆይ እስቲ መጣሁ ብለው ወደ ጓሮ ሄዱ፡፡
ለቶንሲል መድሃኒት የሚሆነውን ሰባት የጌሾ ቀንበጥ ቆርጠው አመጡ፡፡ ለእድላዊት እንድታኝከው ሰጧት፡፡
እድላዊት መናገር ቢያቅታትም መስማት ትችላለች፡፡ የተሰጠችውን የቶንሲል መድሃኒት አኝኪው ስለተባለች ብቻ
እየመረራት ቢሆንም ጨክና አኘከችው፡፡
በውሃ ጥም ምራቋ ደርቋል፡፡ ከንፈሮቿም ኩበት መስለዋል፡፡ ምላሷ ብቻ ብቅ ጥልቅ ይላል፡፡ ነብሷ ልትወጣ ደረሰች፡፡ ሰውነቷ በላብ ተዘፈቀ፡፡ ልቧ ተጨነቀች፡፡ በጀመረችው የምልክት ቋንቋ ውሃ ስጡኝ ብላ በእጇ አመለከተች፡፡
አቶ አርምዴ የእድላዊት ነገር አሁንም ግራ ገባው፡፡ ከሸንበቆ ላይ ቀጭን ሸንበቆ ተከርክሞ እድላዊት በሸንበቆው አማካኝነት ውሃ እንድትቀምስ ተደረገ፡፡
ለእድላዊት እንጀራ እንዳይሰጧት ችላ አትበላም፡፡ ምን እንደሚሰጧት ጨነቃቸው፡፡ የእድላዊት ነገር አንጀታቸውን በላው፡፡
በደከመ አቅማቸውም ቢሆን ትንሽ ገንፎ አገንፍተው እንድትቀምስ አደረጉ ወ/ሮ በሰልፏ፡፡
እድላዊት የተሰራላትን ገንፎ ለመድሃኒት ያህል ቀመሰች፡፡ ወ/ሮ በሰልፏ ለቶንሲሏ ሌላ መዳኒት ዝንጅብል እንድታኝክበት ሰጧት፡፡
"ለቶንሲል ጥሩ ነው፡፡ ለነገ በደንብ ይሻልሻል፡፡ አይዞሽ እያሉ ልጃቸው ያሰረላትን ጨርቅ ከቁስሏ ላይ ፈቱላት፡፡ ለብ ባለ ውሃ አጠቡላት፡፡ ያበጠውን እግርና እጇንም በቅባት አሹላት፡፡ የተላላጠውን ቁስሏንም በነጠላ ጨርቅ ተኩሰው መኝታ ላይ ጋደም እንድትል አደረጉ፡፡
አቶ አርምዴ የሚደረግላትን ካደረገ በኋላ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ አድሮ በነጋታው ጥዋት እድላዊት እንዴት እንዳደረች ለመጠየቅ ከመኝታው ተነስቶ ሲመጣ እናቱ የቤቱን በር ከፍተው ሲወጡ ደረሰ፡፡
የእግዚአብሔር ሰላምታ ተለዋውጠው "ደግሞ ማታ እመለሳለሁ ብለህ ሳትመጣ ቀረህ በሰላም ነው ያልተመለስከው? አሉት ወ/ሮ በሰልፏ፡፡
"ለመምጣት አስቤ ነበር፡፡ ግን ቤቱንና ከብቶቹን ትቼ እንዳልመጣ አውሬ እንኳን ቢገባ የሚሰማ ስላልነበረ ቀረሁ"፡፡ እንዴት አደረች ልጅቷ?ተሸሏት አላደረችም? አለ፡፡
የእድላዊት ስቃይና መከራ ከአንጀቱ ገብቶ ሳይወጣ አንጀቱ እያለቀሰላት እህል እንኳን አልወርድ ብሎት ለአደን ሲሄድ በቀመሰው ቁራሽ እንጀራ ነበር፡፡ እራት ሳይቀምስ ያደረው፡፡
ከአሁን አሁን ያማት ይሆን ? እያሉ ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፍ ሳይወስዳቸው አይደለም በዓይናቸው ሳይዞር ነበር ያደሩት ወ/ሮ በሰልፏም፡፡
"ሰላም አድራለች፡፡ ብቻ ሌሊቱን ሲያቃዧት ነው ያደረው፡፡ አሟት ይሆን ብየ ሌሊት ተነስቼ ሳያት ከቅዠት በስተቀር ምንም አላየሁባትም፡፡ ከነጋም አልቀሰቀስኳትም፡፡ ቅዝቃዜ ስላለ ትንሽ ትተኛ ብየ ነው፡፡ እስኪ አሁን አንተ ከመጣህ ቀስቅሳትና እንዴት እንዳደረች ጠይቃት አሉ፡፡ ቤታቸውን ለመጥረግ የቤት መጥረጊያ ቅጠል ለማምጣት ወደ ውጭ እየወጡ፡፡

👍88❤13🥰3👎1
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================
አለማየሁ ልቡ ላይ አዲስ እና ያልተጠበቀ ፍቅር በቅሏል…የአስካለ ምስልም በተለይ ወሬዋና ሳቋ ከምናቡ ለደቂቃም ሊሰወር አልቻለም፡፡ለዘላለም ከሰሎሜ ውጭ ሌላ ሰው ሊያፍቀር ሚችል አይመስለውም ነበር…ግን ሆነ፡፡እርግጥ ለሁለቱ ያለው ፍቅር ፍፅም ተመሳሳይ አይደለም….ይሄኛው አዲሱ ፍቅሩ የሚያንቀዠቅዝ አይነት ነው፡፡የወሲብ ርሀብ ያለበት የተክለፈለፈ ፍቅር፡፡የሰሎሜ ግን የተረጋጋና ጥልቅ ነው፡፡ስስትና እና ተስፋ ያቆሙት ዘላለማዊ መሳይ ነው፡፡
ከአስካለ ጋር ባሳለፈ በሁለተኛው ቀን ወደአላዛር ሄደና‹‹አባትህ እንዴት ናቸው?››ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹ያው ድኖ አይደል ወደቤት የገባው…ምን ይሆናል?››ሲል ድርቅ ያለ መልስ መለሰለት፡፡
‹‹አሁን እንዴት እንደሆኑ ደውለህ ጠየቅክ?››
‹‹ለምን ብዬ ጠይቃለሁ?››
‹‹በትክክል መጠየቅ ይገባሀል…›››
‹‹የትናንቱንም እንዴት እንዳደረኩት ግራ እየገባኝ ነው››
‹‹እንደውም ተነስ እንሂድና አይተናቸው እንምጣ፡፡››
አላዛር ግራ በመጋባት አፍጥጦ ሲያየው ከቆየ በኃላ፡፡‹‹ሰላም ነህ ግን?››ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹ምነው…ምኔ ነው ሰላም አልመስል ያለህ ?››ሲል መልሶ ጠየቀው፡፡
‹‹ የምናገረው አይገባህም እንዴ? ትናንት በዛ ለሊት ለእሱ ስል ራሴም ተንከራትቼ እናንተንም ሳንከራተት ማደሬ እራሱ እየቆጨኝ ነው ..ጭራሽ ዛሬም ደግሜ ቤት ሄጄ እንድጠይቀው ትፈልጋለህ?፡፡››
‹‹ተወው በኃላ እንዳትፀፀት …ላንተው ብዬ ነው፡፡እኔ አባቴ ጠጪም ሌባም ፤ቁማርተኛም ..ምንም ሆኖ ምንም በህይወት ቢኖርልኝ እንዴት እንደምደሰት ልትገምት አትችልም፡፡በዚህ አለም ላይ እንደቤተሰብ ወሳኝ ነገር የለም፡፡ከፋም ለማም በጨለማ ቀናቶችህ አብረውህ የሚንከራተቱት እነሱ ናቸው፡፡..ቤተሰብ በህይወት መንገድ ወሳኙ አጋር እንደሆነ አውቃለው፡፡የገንዘብ ችግር ቢኖርብህ ቤተሰብ ካለህ ታልፈዋለ…ክፉኛ ብትታመም ቤተሰብ ካለህ ህመምህን ቻል አድርገህ በቀላሉ ማገገም ትችላለህ …ሀገርህ ፈርሳ ስደት ላይ ብትሆን እራሱ ቤተሰብህ ከጎንህ ካለ እንደምንም እየተደጋገፍክ ያንን ክፉ ቀን ታልፈዋለህ፡፡››
‹‹ገባኝ…የእኔ ቤተሰብ እናቴና እህቶቼ ናቸው፡፡በተጨማሪ ደግሞ እናንተ ወንድሞቼ አላችሁልኝ…እርግጥ እናቴ የለችም….ሁለት እህቶቼ ግን አሁንም አሉልኝ..እነሱ በቂዬ ናቸው፡፡ለእኔ አባቴ ከእናቴ ቀድሞ ነው የሞተው…አሁን እሱን ሳይ በድን አካሉ ብቻ ነው ሲንቀሳቀስ የማየው..ነፍሱ ውስጡ የለችም፡፡››
አለማየሁ ሊያሳምነው ስላልቻለ ተበሳጨ‹‹በቃ ቸው..ድሮም አንተ ከጠመምክ መመለሻ የለህም››አለውና ፊቱን አዙሮ መራመድ ጀመረ፡፡
‹‹ቆይ አትሂድ..ና እንካ››አለና እጁን ወደባንኮኒው በመስደድ ብር በእጁ አስጨበጠው፡፡
‹‹ምንድነው?››
‹‹ማኪያቶ ልጋብዝህ ነበር …መውጣት አልቻልኩም..ስለዚህ ብቻህን ጠጣ››አለው፡፡
አለማየሁም‹‹አመሰግናለሁ፡፡››ብሎት የሰጠውን ብር በእጁ እያሻሸ አካባቢውን ለቆ ሄደ ..የእሱ ሀሳብ አላዛርን አሳምኖ አባቱ ቤት አብሮት መሄድ ነበር፡፡፡ያንን የፈለገው ያችን ውብ የጓደኛውን አባት ሚስት ዳግመኛ ለማየት ነው፡፡ከትናንትናው ምሽት ጀምሮ ፈፅሞ ከምናቡ ሊያሸሻት አልተቻለውም፡፡የአላዛር መገገም ግን እቅዱን ሁሉ ገደል ከተተበት፡፡
ከአላዛር ሱቅ ከራቀ በኃላ መዳፉን ፈልቅቆ ሲያየው ድፍን መቶ ብር ነው፡፡ስልኩን አወጣ ..ሰሎሜ ጋር ለመደወል ነው የፈለገው፡፡መቶ ብር ካለው ወይ ይዟት ሲኒማ ቤት ይገባል ወይ ደግሞ አንድ ካፌ ቁጭ ብለው ማኪያቶ እየተጎነጩ ዘና ይላሉ፡፡እቅዱ እንደዛ ነው፡፡
‹‹ሄሎ ››
‹‹ምነው? አሁን ተለይተሀኝ ሄደህ አሁን ናፈቅኩህ እንዴ?››
‹‹ውይ ሰው ጠፍቶ አንቺ ትናፍቂኛለሽ…..?ጉረኛ ነሽ››
‹‹እመን …..››
‹‹ለምን ብዬ ነው የማምነው?››
‹‹እሺ ለምን ፈለከኝ?››
‹‹ምን እየሰራሽ ነው…?አመድ በኪሴ ስላለ ዘና ላድርግሽ ብዬ ነው…››
‹‹አንድ ጥብስ የማይገዛ ብር ይዘህ..ዘና ላድርግሽ ብዬ ነው ስትል ትንሽ አይሸምምህም?››
‹‹አንቺ ምስጋና ቢስ…ይሄኔ በኪስሽ አምስት ብር የለም…አሁን ትወጪያለሽ ወይስ አትወጪም?››
‹‹አዝናለሁ እቴቴ...ዘመዶቾ ጋር እንሂድ ብላኝ ለመሄድ እየተዘጋጀን ነው፡፡››
‹‹የት ?ሰንዳፋ?››
‹‹አዎ…ምነው መሄድ ትፈልጋለህ እንዴ?››
‹‹አይ ይለፈኝ…ግን ታድራላችሁ እንዴ?››
‹‹አዎ… ነገ ነው ምንመጣው፡፡››
‹‹እሺ መልካም መንገድ፡፡››
‹‹አንተ ደግሞ በጊዜ ወደቤት ግባ …እቴቴ እንዳታዘርፈኝ እያለች ነው ፡፡››
‹‹እሺ …አታስቢ በያት፡፡››ብሎ ስልኩን ዘጋውና ተቀያሪ ሀሳብ ማብላላት ጀመረ…ወዲያው ነው መሳጭ የሆነ ሀሳብ ብልጭ ያለለት‹‹ መንገድ ተሻገረና ወደአትክልት መሸጫ ሱቅ ሄደ ..አንድ ኪሎ ሙዝ ገዛ፡፡ ታክሲ ውስጥ ገባ ፡፡ቀጥታ ወደአላዛር አባት ሰፈር ነው የሄደው፡፡ደረሰና የውጪውን በራፍ አንኳኳ…፡፡
ከተወሰነ ጥበቃ በኃላ ተከፈተለት…
ይህቺን ሴት ለሁለተኛ ጊዜ ሲያያት ይበልጥ አምራና ውብ ሆና ነው የታየችው፡፡አስካለ ፈፅሞ አየዋለሁ ብላ ያልጠበቀችው ስለሆነ በጣም ነው የደነገጠችው፡፡
በዝምታ አፍጥጣ ስታየው ግራ ተጋባና ‹‹ምነው አላወቅሺኝም እንዴ?››ሲል ጠየቃት፡፡
በራፉን ጋርዳ እንደቆመች‹‹ይቅርታ እንዲህ በቅርቡ ደግሜ አይሀለው ብዬ ስላልገመትኩ ነው…እንጂማ አንተን እንዴት እረሳሀለው፡››አለችው ፡፡
በጥቁር ፔስታል የያዘውን ሙዝ እንድታይ እያወዛወዘ፡፡‹‹ጋሼን ለመጠየቅ ነው የመጣሁት››አላት፡፡
‹‹ግባ…ና ግባ››አለችና በራፉን ለቀቀችለትና ቀድማው ወደውስጥ መራመድ ጀመረች ፡፡ከኃላዋ ተከተላት፡፡ገቡ፡፡
‹‹ቁጭ በል፡፡››ሙዙን አቀበላትና ፈራ ተባ እያለ ቁጭ አለ፡፡
‹‹አሁን የእውነት ሰውዬው እሷቸውን ልጠይቅ እንደመጣው ያምኑኛል?››ሲል ከዚህ በፊት ያላሰበውን ነገር አሰበ‹‹አይ አላዛር ነው የላከኝ ..ስራ ላይ ስለሆንኩ ሰላም መሆኑን እይልኝ ሳለለኝ ነው የመጣሁት፡፡››እለዋለው ሲል ወሰና ተረጋጋ፡፡ሙዙን ተቀበለችውና ጠረጴዛ ላይ አስቀምጣ..ከፊት ለፊቱ ሄዳ ተቀመጠች፡፡
‹‹ጋሼ ተኝተዋል እንዴ?››ፈራ ተባ እያለ ጠየቃት፡፡
‹‹‹የሉም ስራ ገብተዋል››
በረጅሙ ተነፈሰ‹‹እንደዛ ነው…በደንብ ተሻሏቸዋል ማለት ነው?››
‹‹አዎ በደንብ ተሽሏቸዋል፡፡አተነፋፈስህ ግን ባለመኖራቸው ደስ ያለህ ይመስላል››አለችው፡፡ የውስጡን ስላነበበችበት አፈረ፡፡
‹‹አይ..ያው አለ አይደለ..ከድሮም ጀምሮ እፈራቸዋለው…ለዛ ነው፡፡››
‹‹ታዲያ ይሄን ያህል የሚያጨናንቅህ ከሆነ ለምን መጣህ?››ብላ ሲፈራው የቆየውን ከባድ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹ያው አላዛር ስራ ላይ ስለሆነ መጥቶ ሊጠይቃቸው አልቻለም…እይልኝ ብሎ ስላስቸገረኝ ነው››ከደቂቃ በፊት ያቀናበረውን ምክንያት ነገራት፡፡
ፈገግ አለች….
‹‹ምነው?››
‹‹አይ …እኔ ደግሞ እኔን ለማየት የመጣህ መስሎኝ ደስ ብሎኝ ነበር?››ስትል ያልጠበቀውን አማላይ አይነት መልስ ሰጠችው፡፡
‹‹እሱማ ..ያው እግረመንገዴን አንቺንም ማየትና እንዴት እንደሆንሽ ማወቅ ስለፈለኩ ነው የመጣሁት፡፡››ሲል በከፊል አመነላት፡፡
‹‹ስለመጣህ ደስ ብሎኛል…መጣው ተጫወት›› ብላ ወደውስጥ ገባችና ..ሻይ ጥዳ….ተመለሰች፡፡
ሞባይሉን አወጣና ሰዓቱን ተመለከተ..5፡20 ይላል፡፡‹‹ምሳ ሰዓት እየቀረበ ነው….››አላት፡፡
‹‹አዎ ..ምነው እርቦሀል ላቅርብ እንዴ?››
‹‹አይ!! ማለቴ ጋሼ አሁን ለምሳ ይመጣሉ ለማለት ነው፡፡››

👍56❤14
#አላገባህም
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////
ዘሚካኤል ተገትሮ በቆመበት የክፍሉ መሀከላዊ ስፍራ እንደደነዘዘ ነው፡፡ልጅቱ አስር ለማይሞሉ ደቂቃዎች ብቻ አብራው ብታሳልፍም….ግን ደግሞ ለቀናት ያህል ያቀፋትና ለሳዕታት ሲስማት የቆየ አይነት ስሜት ነው እየተሰማው ያለው…‹‹.ለምን ጉዳይ መጣች ምን ሰርታ ሄደች?››ብሎ ሲያስብ ሳይወድ ፈገግ አለ…ከቆመበት ተንቀሳቀሰና እጁ ላይ ያለውን የሰርግ የጥሪ ካርድ የያዘውን ፖስታ በራፉ አጠገብ በሚገኘው ቆሻሻ ማጠረቀሚያ ቅርጫት ውስጥ ጨምድዶ ወረወረው፡፡
ለዛች ስሟን እንኳን ላልነገረችው ሴት ልጅ እንደነገራት በዚህ አለም ምንም አይነት ወንድም ሆነ ቤተሰብ አያስፈልገውም እና ወደ የትኛውም ሰርግ የመሄድ ፍላጎት የለውም። እንደውም ከተቻለው ስለቤተሰብ በውስጡ የቀረውን እንጥፍጣፊ ትዝታ ከልቡ አሟጦ መሰረዝ ነው ፍላጎቱ፡፡
ከወገብ በላይ ራቁቱን መሆኑን ትዝ ሲለው ወደጠረጴዛው ሄደና ያወለቀውን ልብስ መልሶ ለበሰው..መጀመሪያ እቅዱ ቀጣይ የሙዚቃ ማቅረቢያ ሰዓቱ እስኪደርስ ድረስ ሻወር ገብቶ ከተለቃለቀ በኃላ 30 ወይም 40 ደቂቃ መተኛትና እረፍት መውሰድ ነበር፡፡አሁን ግን ሻወር የመውሰድም ሆነ የመተኛት ፍላጎቱ ከውስጡ በኖ ጠፍቷል…ቀጥታ ሶፋው ላይ ሄደና ተቀመጠ፡፡ፊትለፊት ካለው ጠረጴዛ ላይ ያለውን የውስኪ ጠርሙስ አነሳና ከፍቶ በብርጭቆ ቀድቶ እየተጎነጨ ማሰላሰል ጀመረ….
‹‹ይህቺ ልጅ ምኑን ነክታ እንዴት ስሜቱን ድፍርስርስ አድርጋ እንደሄደች አያውቅም…ወንድሙ ላይ የያዘበት ቂምና የተበሳጨበት ብስጭት አሁንም ትኩስ ነው፡፡
‹‹ግን የዛን ጊዜ ፈቅዶልኝ አባቴን በዛ ቢላዋ ጨቅጭቄ ብገድለው ኖሮስ…?››ሁል ጊዜ እራሱን የሚጠይቀው ጥያቄ ነው፡፡
አዎ ወንድሙ በድብድብ እና በትግል ባያስቆመው ኖሮ እሱም ይሄን ጊዜ የእድሜ ልክ ፍርድ ተፈርዶበት በአባቱ ምትክ እስር ቤት ውስጥ ተቆልፎበት ተስፋ የሌለው ህይወት ይኖር እንደነበረ…እርግጠኛ ነው፡፡
‹‹ታዲያ እኮ ሚካኤል ወንድምህ የእድሜ ልክ ባለውለታህ እንጂ ጠላትህ አይደለም?››አለው አእምሮው፡፡
‹‹ለምን..ያማ እውነት አይደለም….እሱ እኮ እንደዛ ያደረገው እኔን ከመከራ ለማትረፍ አስቦ ሳይሆን ለዛ ጨካኝ እና ገዳይ አባቱ ለማገዝ ፈልጎ ነው››
‹‹አይ እሱ የአንተ አእምሮ አንሻፎ የተረጎመው ትርጉም ነው…እንደዛም ቢሆን እንኳን በዛ ታሪክ ውስጥ ዋናው ተጠቃሚ አንተ ነህ፡፡በወቅቱ ዝም ብሎህ ያሰብከውን እንድታደርግ ቢፈቅድልህ ኖሮ ዛሬ በዚህ ጊዜ ዝነኛው ድምፃዊና ተዋናዩ ዘሚካኤል የለም ነበር…ሀመር መኪና የሚነዳው…የተንጣለለ ውድና ውብ ቪላ ቤት ውስጥ የሚኖረው…ከአደባባይ እስከቤተመንግስት የሚታወቀውና የሚጋበዘው የመገናኛ ብዙሀኖች የዜና ማጣፈጫ የሆነው ዘሚካኤል አይኖርም ነበር፡፡››ሲል እራሱን በራሱ በዝርዝር አስረዳ፡፡
የአእምሮው የእርስ በርስ ጭቅጭቅ ከዚህ በላይ ማስቀጠል አልቻለም..ምክንያቱም በንዴትና በቁጭት አእምሮው ብቻ ሳይሆን መላ ሰውነቱ እየጋለበት ነው፡፡ጠረጴዛው ላይ ያለውን ብርጭቆ አነሳና ጠቀም አድርጎ ተጎነጨለት እና መልሶ አስቀመጠው፡፡
ከዛ ስለሌላ ነገር ለማሰብ ሞከረ ..ግን አሁንም አእምሮውን የሞላችው ያቺ ከደቂቃዎች በፊት ከሰውነቱ ለጥፎ ያቀፋትና ለሁለት ሰከንድ ሲስማት የነበረችው ሴት ነች፡፡‹‹ቆይ ይህቺ ልጅ ምን የተለየ ነገር ቢኖራት ነው ከአእምሮዬ ልትወጣ ያልቻለችው ?››እራሱን ጠየቀ…‹‹ከንፈሯ ላይ አስማት አለ መሰለኝ…››አለና ፈገግ አለ….‹‹ምን አለ ስሟን እና የሞባይል ቁጥሯን ብጠይቃት ኖሮ…?››በጣም ተቆጨ፡፡
ደግሞ እሷም እሱን በምንም አይነት ሁኔታ ደግማ የማግኘት ፍላጎት እንደሌላት በሚያሳይ ሁኔታ ነው የመጣችበትን ጉዳይ ተናግራ የጥሪ ካርድን እጁ ላይ አስቀምጣ ነው ውልቅ ብላ የሄደችው፡፡
‹‹ባለትዳር ትሆን እንዴ?››የሚል ሀሳብ በአእምሮ ብልጭ አለበት፡፡
ሀሳብን መቋጫ ሳያበጅለት በራፉ በስሱ ተቆረቆረ…ብርጭቆ ውስጥ የቀረችውን ውስኪ ጨለጠና ሶፋውን ለቆ ወደበራፉ ሄደ ..ቀጣይ ዝግጅቱን የሚያቀርብበት ጊዜ መድረሱን ለማሳወቅ በራፉን እንደቆረቆሩ ያውቀል..በራፉን ከፍቶ ሲወጣ ንቁ ሆነው የሚጠብቁት ሁለት ወጠምሻ ጋርዶች ከግራና ከቀኝ ከበቡት፡፡ ሁለት እርምጃ ከተራመደ በኃላ የሆነ ነገር ወደኃላ ሳበው…መልሶ ፊቱን ዞረና ወደክፍሉ ተመለሰ….ከውስጥ በኩል ከበራፉ በስተቀኝ ወዳለው የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ባስኬት አጎነበሰና አጣጥፎ የጣለውን የሰርግ ጥሪ ወረቀት አነሳ ፡፡የሱሪ ኋላ ኪስ ውስጥ ጨመረውና መልሶ ወጣ..ለምን እንዲህ እንዳደረገ ቢጠየቅ ምንም አይነት መልስ የለውም …እንዲሁ በደመነፍስ ያደረገው ነገር ነው፡፡
////
አሁን የዘሚካኤል ምስል ከሙሉ አቋሙ ጋር በአእምሯዋ እየተራወጠ ነው፡፡ሁለቱ ወንድማማቾች ከቁመትና ከፀባይ ውጭ በሌላው ነገር በሚያስደንቅ ሁኔታ ይመሳሰላሉ። የሚካኤል ባህሪያት ከዘሚካኤል ትንሽ ደብዘዝ ያሉ ነበሩ እና የዓይኑ ቀለም ንፁህ ፣ ጠንከር ያለ ሰማያዊ ነበረ ፣ ግን ሁለቱም ሰዎች ተመሳሳይ ውብ ፈገግታ፣ ክብ የፊት ቅርፅ እና ሰልካካ አፍንጫ.. ወተት ከመሰሉ ነጫጭ ድርድር ጥርሶች ጋር አላቸው፤››
እየሾፈረች ያለችውን ቪታራ መኪና ኤክስፐረስ መንገድ ውስጥ አስገብታ ወደ አዳማ እያሽከረከረች ሲሆን አሁንም ስለዛ ዘ-ሚካኤል ስለሚባለው ድምጻዊ ነው የምታሰላስለው፡፡ለሊት 8 ሰዓት ላይ ከእሱ ተለይታ እዛው በአቅራቢያው ወደተከራየችው ፕንሲዬን ሄዳ ለመተኛት ብትሞክርም ምንም እንቅልፍ በአይኗ ሳይዞር እንዲሁ ስትበሳጭና ስትገላበጥ ነው ያደረችው፡፡
ስለእሱ ማሰብ የጀመረችው ቀደም ብላ ታሪኩን ከየጋዜጦችና ከዪቲዩብ ቻናሎች እየሰበሰበች በምታዳምጥበት ጊዜ ነው፡፡እርግጥ ታውቀለች በዩቲዩቭ የቀረበ ዜና ሁሉ በተለይ ስለፍቅርና ፃታዊ ግንኙነት የሚነዙት አብዛኞቹ ተመልካች ለማግኘት የታስቡ…በውሸት የሚፈበረኩ እንደሚሆን ታምናለች..ግን ቢሆንም‹‹ እሳት በሌለበት ጭስ አይጨስም….››በማለት ለሰው ስሜት የማይጨነቅ ጋጠወጥ ወሲባም አድርጋ ስላው ነበር፡፡እና ደግሞ ለሊት እንዳየችው አልተሳሳተችም…በዛ ለሊት እዛ ክፍል ውስጥ ሲያገኛት መጀመሪያ ያደረገው ወደራሱ ስቦ ከንፈሯ ላይ መጣበቅ ነው…..ስለዛች ቅፅበት ስታስብ ከንፈሯ ተንቀጠቀጠባት….የሚያበሳጨው ደግሞ ለማንም ሴት ግርማ ሞገሱንና ውበቱን ለመቋቋም አስቸጋሪ የሆነ ሰው መሆኑን በራሷ ማረጋገጧ ነው…ባለፉት ስድስት አመታት በጣም ብዙ ከሆኑ ወንዶች በብዙ የተለያዩ አጋጣሚዎች ሊፈታተኗት ሞክረው ሾልካና አሳስቃ ..አንዳንዱንም ተኮሳትራና አስፈራርታ እራሷን ማትረፍ ችላለች..ከእሱ ጋር ግን በአንድ እይታ ነው ተዝለፍልፋ እቅፉ ውስጥ የወደቀችው፡፡
እንደምንም ከእቅፉ ወጥታ ለማምለጥ ወደበራፉ በምትራመድበት ጊዜ እንኳን ተንደርድሮ መጥቶ እጇን ይዞ ጎትቶ እንዲያስቀራት እና ተሸክሞ ሶፋው ላይ እንዲጥላት በውስጧ እየተመኘች ነበር፡፡ግን በተመሳሳይ ጊዜ እንደዛ በመመኘቷ እራሷን ስትወቅስና ስትራገም ነበር፡፡

👍61❤13👏1
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
እሁድ የእረፍት ቀን ስለሆነ ኤልያስ ከወንድሙና ከጓደኛው ጋር ካፌ ቁጭ ብለው ቁምነገሩንም ቀልዱንም ሲጫወቱ አረፈድና ሌላ የሚሄዱበት ቦታ ስለነበር ተያይዘው ወጡ፡፡ሶስቱም የቢኒያም መኪና ወዳቆመችበት ቦታ እየተለፉ እየሄዱ ሳለ ድንገት ኤልያስ ከወንድሙ ከቢኒያም ጉሽሚያ ለማምለጥ ወደኃላው ሲሸሽ ከአንድ ውብ ሴት ጋር ተላተመ ፡፡ሴትዬዋ በእጇ የያዘችው ወረቀቶቿ ከእጆቿ ተንሸራተው ወደቁ እና ቦርሳዋ ከተከሻዋ ተንሸራቶ ሊወድቅባት ነበር…እሷም ተነገዳግዳ ሚዛኗን ለመሳት ስትጥር ኤልያስ በፍጥነት ተስፈነጠረና ክንዷን ያዛት ። ተረጋግቶ ሲያያት አይኖቹን ማመን ነው ያቃተው ።፡ራሄል ነች፡፡ ሞባይል ስልኳ አንድ ጆሮዋ ላይ ተጣብቆል…ስልክ እያወራች እንደነበር ተገነዘበ፡፡
አቀርቅራ የተበተኑ ወረቀቷቾን እያየች‹‹ምንድነው…አይንህ አያይም እንዴ? አብደሃል?››ስትል ጮኸችበት ።ከዚያም ቀና ብሎ አያት።ሀዘን ያረበባቸው አይኖቿ እሱን ሲያዩት ፣ ንዴቷ በጥልቀት ወደ ውስጡ ዘልቆ ሲገባ ተሰማው። በልቡ ክልል ውስጥ የሆነ ቦታ ላይ የብርሃን ብልጭታ ፈነጠቀ።ድንገት ወደጎን ዞር ብላ እሱ መሆኑን ስታውቅ በንግግሯ አፈረች፡፡‹‹እባክህ ይቅርታ አድርግልኝ››ብላ አጉተመተመች፣ክንዷን ወደኋላ ጎተተች። አሁንም እንደያዛት ረስቶት ነበር። ፈጠን ብሎ ለቀቃት። ርቀቱን ጠብቆ በጉጉት እያዩ ወደነበሩት ወንድሙ እና ጓደኛው እየተመለከተ። ‹‹ይቅርታ አላየሁሽም….ከወንድሜ ቢኒ ጡጫ እራሴን ለማራቅ እየሞከርኩ ነበር.››አላት፡፡
‹‹ምንም አይደለም፣ እኔም ቀልቤ የማወራው ስልክ ላይ ስለነበር መጠንቀቅ አልቻልኩም ።›› በማለት ወረቀቶቿን ለማንሳት ጎንበስ አለች።
‹‹ቆይ እኔ ላንሳልሽ›› ብሎ እሱም ጎንበስ አለ… ሁለቱም በአንድነት እጇቸውን ወደወረቀቱ ሲሰዱ እርስ በርስ ተነካኩ ፡፡በመሀከላቸው የኤሌክትሪክ ንዝረት አይነት ቅፅበታዊ ብልጭታ ተፈጠረ፡፡
‹‹እባክህ አትጨነቅ›› የውስጥ ስሜቱን የሚቆሰቁስ አይነት እንደገና የሚያነቃቃ ፈጣን ፈገግታ ሰጠችው።
ወረቀቶቹን ሰብስበው ከተነሱ በኋላ‹‹ለመሆኑ እዚህ ሰፈር ምን እግር ጣለሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹ለስራ ጉዳይ››ስትል አፏ ላይ የመጣላትን ምክንያት ሰጠችው፡፡
‹‹ በእረፍት ቀን ትሰሪያለሽ እንዴ?››
ራሄል ፊቷን አኮሳትራ‹‹ስራ እስካለኝ ድረስ ቀን ሳልመርጥ ነው የምሰራው..ታውቃለህ …ሥራዬ በጣም አስፈላጊ ነው።››ስትል መለሰችለት፡፡
‹‹ደህና፣ በቃ እንገናኛለን።››
‹‹ተስፋ አደርጋለው።›› አለችና መንገዷን ቀጠለች ፡፡
‹‹አሁንም አለሽ ራሄል?›› ከያዘችው የሞባይል ስልክ የአንድ ወንድ ድምፅ ተሰማ። እናም ራሄል እስከአሁን ስልኳ እንዳልተቆረጠ ስትረዳ ‹‹ ሮቤል በቃ ቆይቼ ደውልሀለው … መንገድ ላይ ያልሆነ ነገር አጋጥሞኝ ነው›› ብላ ስልኩን ዘጋችው፡፡
ከዛም እርምጃዋን ሳታቋርጥ ወደ ዔሊያስ ዞር ብላ ተመለከተች …በተገተረበት ቆሞ እያያት ነበር ..የሆነ ውርር የሚያደርግ ስሜት ተሰማት ፡፡መንገዱን አቋርጣ ወደካፌው ታጠፈችና ከእይታው ተሰወረች፡፡
ሁኔታውን በትኩረት ሲከታተሉ የቆዩት ቢንያም እና ጓደኛው ወደ እሱ ሮጠው ከጎኑ ቆመ
‹‹በቀጣዬቹ አመታት ውስጥ ያለህ የሕይወት እቅድ ውስጥ ሴት እንደሌለችበት ደጋግመህ ነግረኸኝ ነበር? ››አለው ቢኒያም፡፡
‹‹እና ታዲያ?››
‹‹እናማ ይህቺ ሴት ማን ነች?።››
ዔሊያስ ለወንድሙ ‹‹የህይወት እቅዴ ላይ ምንም ማስተካከያ አልተደረገበትም..ያንን ካወቅክ ይበቃል።››ብሎት ወደመኪናው ጉዞውን ቀጠለ፡፡
ወንድሙም ከኋላው ተከትሎት‹‹እቅድህን ማስተካከል ትችላለህ …በቅድሚያ ግን ብድርህን ክፈል፣ ሞተርህን ሽጥና ትክክለኛ መኪና ግዛ፣ ከዛ ኑሮህን የምትጋራ ሴት መፈለግ ትችላለህ››አለው
ዔሊያስ ሕይወት ሁል ጊዜ እንደማይተነበይ ከግል ተሞክሮ ያውቃል ። ዔሊ በስድስት ዓመቱ ወደ ማደጎ ቤት ለመግባት ተገዶ ነበር፡፡ በወቅቱ ጮርቃ ልጅ ነበር እና ስለ ተፈጥሮ ወላጆቹ የሚያውቀው ብቸኛው ነገር አባቱ ሉቃስ እናቱ ደግሞ ትእግስት እንደምትባል ብቻ ነው፡፡ስለ እነሱ ያለው የመጨረሻ ትዝታ ቤተሰቡ በአንድ ላይ ሆነው እየተጓዙ እያለ አባቱ መኪናውን መቆጣጠር ተስኖት ሲጯጯሁ ነበር፡፡አንድ አመት ሙሉ በህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ተጣለ፡፡በዛን ተመሳሳይ ወቅት ቢኒያምም የአንድ አመት ህፃን ሆኖ በወላጇቹ ተጥሎ እዛ ማደጎ ቤት ከእሱ ጋር ነበር፣ እንደእድል ሆኖ አሳዳጊዎቻቸው ለሁለቱም ልባቸው ራራና አንድ ላይ ወደቤታቸው ወስደው እንደገዛ ልጇቻቸው ተንከባክበው አሳደጓቸው..እነሱም እርስ በርስ የሚዋደዱና የሚደጋገፉ ወንድማማቾች ሆነው አደጉ፡፡ አሳዳጊ ወላጆቻቸው ሁለቱንም በፍፁም ፍቅር እና …በስርዓት አስተምረው ለዚህ ደረጃ አበቁዋቸው፡፡
ቀጥታ ጓደኖቾ ይጠብቋት ወደነበረው ካፌ ገባች፡፡በጠረጴዛ ዙሪያ እየተጨዋወቱ እና እየሳቁ ካሉት ከጓደኞቿ ጋር ተቀላቀለች፡፡
‹‹ደህና ናችሁ ፣ ውድ ጓደኞቼ››
እንዴት ነሽ ንግስቲቷ›› ሜሮን ነች ቀድማ ለሰላምታዋ መልስ የሰጠቻት፡፡ከዛ ያሬድና ሌንሳ ተከተሉ፡፡እነዚህ ሶስቱ የልጅነት የትምህርት ቤት ጓደኞቾ ናቸው፡፡ራሄል ልጅ ሆና ፈጣን እና ጎበዝ ተማሪ ነበረች እና በዚህ ምክንያት ሁለት ክፍል በመዝለሏ ትምህርት ቤት ከገባችባቸው ልጆች ትንሿ ነበረች። አንድ ቀን በክፍሏ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ልጃገረዶች በመጫወቻ ስፍራው ላይ ወደ ጥግ ወስደው ይሳለቁባት ጀመር። እንደአጋጣሚ ሶስቱ ጓደኛሞች በአካባቢው ሲያልፉ ሁኔታውን ተመለከቱ ..ዝም ብለው ሊያልፉ አልፈለጉም…ጣልቃ ገብተው ራሄልን በክንፋቸው ስር ከልለው ታደጓት። ከዛን በኃላ ቋሚ ጓደኞቾ ሆኑ..ይሄው እስከዛሬ በህይወት ውጣ ውረዶች ውስጥ፣ የእርሷ ምስጢረኞች አማካሪዎች እና ውድ ጓደኞቿ ሆነዋል።እና ከአራት አመት በፊት ሌንሳና ያሬድ የጓደኝነት ግንኙነታቸውን ወደፍቅር ቀይረው በመጋባት መንታ ልጆችን ለመውለድ ችለዋል፡፡
ያሬድ የራሄልን የተዘበራረቀ ሸሚዞን እና የተበታተነ ወረቀቷን ተመለከተና ‹‹ደህና ነሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹አዎ..ደህና ነኝ››
‹‹ቆይ ምን ሆንሽ?››ሜሮን ተቀበለችው፡፡
‹‹ከመኪናዬ ወርጄ ወደእዚህ ስመጣ ..፣ከአንድ ጓረምሳ ዶ/ር ጋር ተጋጨው ››
‹‹ምን…!ከጎረምሳ…?ወይስ ከዶክተር?››ሌንሳ ጠየቀቻት፡፡
‹‹ጓረምሳ የሆነ ዶ/ር ..ምነው ግልፅ አይለም እንዴ?››
‹‹እኔ ያልገባኝ..ጎረምሳ መሆኑን በእይታ አወቅሽ እንበል..ዶክተር መሆኑንስ?››ሜሮን ጠየቀች፡፡
‹‹ባክሽ የማውቀው ሰው ነው …የእህቴ የፀጋ ዶክተር ነው፡፡››ሸሚዙ እንደተከፈተ፣ እና ፀጉሩ በግንባሩ ላይ ተደፍቶ እንደነበረ ላለማሰብ ታገለች።
ሁሉም በአንድ ላይ አስካኩባት፡፡
‹‹ስሙ ማን ነበር?››ሌንሳ በማሾፍ ጠየቀች፡፡
ራሄል ግን ጥያቄዋን በቁም ነገር ወስዳ‹‹ዓሊ››ስትል መለሰች፡፡
‹‹ኤሊ ማለት?››ያሬድ በገረሜታ ጠየቀ፡፡
‹‹ማለቴ ኤልያስ….ዶ/ር ኤልያስ››
ሌላ የህብረት ሳቅ ተከተለ፡፡
‹‹ተመልከቷት ነገሩ ስር የሰደደ ይመስላል ። የዔሊን ስም ሲነሳ መልኳ በደቂቃ ተለወጠ›› ሜሮን ጮኸች።
‹‹እንዴት ነው ግን…?››ለሊሴ ጠየቀቻት፡፡
‹‹ እሱ ቆንጆ ነው ማለት ይቻላል...›› ቡድኑን ዞር ብላ ተመለከተች እና በራሷ ሳቀች።‹‹እንደ ያሬድ ወንዳ ወንድ ነው›› ስትል አከለችበት፡፡
ሁሉም ሳቃቸውን መቆጣጠር አልቻሉም፡፡

❤63👍3
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
/////
አለም ወደ ዩኒቨርሲቲ መግባቷ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ አያቷ የህግ ሙያ እንድታጠና አጥብቃ ትገፋፋት ነበር..በወቅቱ ምክንያቱ አይገባትም ነበር…እንዲሁ ሰዎች.. የልጅ ልጅሽ ጠበቃ ነች ወይም ዳኛ ነች እንዲሏት ካላት ምኞት ተነስታ የምትገፋፋት ይመስላት ነበር..አሁን ነው ነገሮችን ስታገጣጥም ምክንያቱ ፍንትው ብሎ የተገለፀላት፡፡
አለም በትምህርት ቤት ጎበዝ ተማሪ ነበረች እና በመጨረሻ አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍልም ወርቅ ሜዳሊያ አጥልቃ ነበር የተመርቀችው። የህግ ትምህርት አያቷ የመረጠችለት እና በእሷ ዘንድ በልጅነቷ ያላገኘችውን ሞገስ ለማግኘት ስትል የገባችበት ሙያ ነበር፣ ግን ከተማረችው በኋላ አያቷን ደጋግማ አመሰግናታለች… ምክንያቱም በጣም የሳባት እና ያስደሰታት መስክ ነው። የማወቅ ጉጉት ያለው አእምሮዋ ወደ ውስጡ የህግ ዕውቀቷቹን መጦ ሲያስገባ በደስታ ነው፡፡ ወደስራም ስትሰማራ በሙሉ የራስ መተማመንና በከፍተኛ የስራ ንቃት ነበር፡፡
አቃቢ ህጉ የእጅ ሰዓቱን ተመለከተ.. ከዚያም ሲጋራውን በከንፈሮቹ መካከል አስገብቶ ቆመና ኮቱን ከመስቀያው አነሳ "ያለ በቂ ማስረጃ የግድያ ክስ እንደገና መክፈት አልችልም። ታውቂለሽ። ከሀያአምስት አመት በፊት ተፈፅሞ የነበረ ወንጀልን ወደኋላ ተጉዞ መረጃ ማሰባሰብ ብራንድ ልብሶችን ለብሶ በመዘነጥ የአዳም ዘርን እንደማማለል ቀላል ስራ አይደለም…..እና መጀመሪያ እኔን አሳምኚኝ..ምን አልባት ከዛ በኋላ ስለክሱ ሁኔታ መልሰን እንንጋገርበት ይሆናል››
ልቅ የሆነ ንግግሩን ችላ ብላ በብስጭት ተመለከተችው፡አጠያየቋ በጣም ድፋረት የታከለበትና እና ቅንነት የጎደለው መሆኑን ታውቃለች።እሷ በእሱ ቦታ ብትሆን ከረጂም ደቂቃ በፊት ክፍሉን ለቃ ትወጣ ነበር፡፡
"አየሽ አለም፣ ይህ የምትጠይቀኝ ጉዳይ እንደምትይው ቀላል አይደለም…እነዚህ ሰዎች በደቂቃ ውስጥ ይህንን ቢሮ ወደ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ መቀየር የሚችሉ ናቸው። አንገቴን ልታስቀነጥሺኝ ካልፈለግሽ በስተቀር ይሄንን የአያትሽን ከንቱ ጥርጣሬ መልሰሽ ታነሺብኛለሽ ብዬ አልጠብቅም››ብሎ መንገዱን ቀጠለ፡፡ወደ ቢሮው ደጃፍ ሲያመራ ተከተለችው
"ክቡር አቃቢ ህግ ይሄ ለእኔ ጥልቅ ትርጉም ያለው ጉዳይ ነው። እንዴት እምቢ ትለኛለህ..የምታስበው ስለራስህ ብቻ ነው?።"
"እውነትሽን ነው እኔ እራስ ወዳድ ነኝ።
"ሲል መለሠላት።
"በሌሎች ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረጌን እንዳለ ሆኖ ይህን ግድያ እንዳጣራ ፍቃድ ስጠኝ።"ሙጭጭ አለችበት፡፡
"እኛ ምን አይነት ውዝግብ እንዳለብን ታውቂያለሽ? መአት አንገብጋቢ ጉዳዮች እጃችን ላይ አሉ ፤ሀያ ምናምን አመት የተረሳ...መዝገብ እራሱ በአቧራ የተበላ ጉዳይን በቀላሉ ለፍርድ ማቅረብ አንችልም።"
"እሺ በትርፍ ሰዓቴ እሰራለሁ፣ ሌሎች ኃላፊነቶቼ ላይ በምንም አይነት ተፅዕኖ እንዲያሳድር እላደርግም፣ለዛ ቃል ገባልሀለው ።"
"አለም"
"እባክህ … ግርማ በቅርቡ አንድ ተጫባጭ ፍንጭ ከላገኘሁ ..ጉዳዩን እርግፍ አድርጌ ተወዋለሁ...ከዚያ በኋላ ስለ ጉዳዩ በጭራሽ ከእኔ አትሰማም.››
በትኩረት ተመለከታት እና ፊቷን አጠና ። "ለምን እንዲህ አይነት ውስብስብ ነገር ውስጥ ራስሽን ታስገቢያለሽ ..እንደማንኛውም ወጣት ዘመናዊ ሴት .ዘና ያለ የህይወት መንገድን አትመርጪም፡፡ ።"
ፊቷን አኮስታተረችበት ።
"እሺ፣ እሺ፣ ምርመራውን መጀመር ትችያለሽ፣ ነገር ግን በትርፍ ጊዜሽ ብቻ ነው። ተጨባጭ የሆነ ነገር ይዘሽ ነይ። አለበለዛ ውሳኔዬን ታውቂዎለሽ .አሁን ከቀጠሮዬ አዘግይተሽብኛል።››ብሎ በቆመችበት ጥሏት ሄደ፡፡
በእርካታ ተነፈሰች፡፡ሸክሟ ከባድ ነበር ፡፡ እያቷ በእናቷ ግድያ ላይ ያላት መረጃ የተወሰነ ነበር። በጋዜጣ ላይ እንዳገኘችው መረጃ ከሆነ እናቷን በመግደል የተወነጀለው ሰው የአእምሮ ብቻ ሳይሆን የመስማትም ችግር እንዳለበት ነው፡ ።እነሱ መሠረታዊ እና ቀላል ችግሮች ነበሩ. የአእምሮ ዝግመት ችግር የነበረው ሊቁ የተባለው ሰው በግድያው ቦታ በተያዘበት ጊዜ የሟቾ እናቷን ደም በጠቅላላ ልብሱ ላይ ተነክሮ እንደነበረ ተዘግቦ ነበር።በተጨማሪም በተያዘበት ወቅት ተጎጂዋን ገድሎበታል የተባለበትን የቀዶ ጥገና መሳሪያ በእጁ ይዞ ነበር።በዛ ምክንያት ወዲያው በቁጥጥር ስር ውሎ ታስሯል፣ ተጠየቋል
እና ተከሷል። በቀናት ውስጥ ነበር ችሎት የቀረበው። ወዲያው ዳኛው ካለበት የጤና እክል የተነሳ ለፍርድ የመቅረብ ብቃት እንደሌለው አውጀው በመንግስት የአእምሮ ሆስፒታል ውስጥ አንዲታሰር ትዕዛዝ አስተላለፉ።ተጠርጣሪው ግን ወደአእምሮ ሆስፒታል ተመዘዋወሮ ብዙም ሳይቆይ እራሱን አጠፋ ተባለ፡፡ በውቅቱ ወንጀለኛውን አሳዶ ለመያዝ
..ከዛም ፍርድ ለማስተላለፍና ፋይሉን ለመዝጋት የነበረው ጥድፊያ ያስደነግጣል፡፡ እናም ከፍተኛ ጥርጣሬም በአለም አእምሮ ውስጥ ጭሯል፡፡
በሶስተኛው ቀን ያገኘችውን ተጨማሪ መረጃ ይዛ ዋና አቃቢ ህጉ ፊት ለፊት ቀረበች፡፡መረጃዎቹን ካቀበለችው በኃላ
‹‹የእረፍት ቀን እንዴት ነበር?›››ስትል ለጫወታ መጀመሪያ ጠየቀችው፡፡
"ድንቅ ነበር. ካንቺ የበለጠ ውጤታማ ቀናቶችን አሳልፌለሁ ብዬ አስባለው። ብዙ ነገሮችን የማንበብ እድል ነበረኝ።"
ፋይሉን ገልጦ ይዘቱን መቃኘት ጀመረ። "እህም" የመጀመሪያ ንባቡ ትኩረቱን ለመሳብ በቂ ነበር። ወንበሩ ላይ ተደግፎ በጥንቃቄ በድጋሚ አነበበው።
"ይህ ዶ/ር ታደሰ የተባለው … ሊቁ የታሰረበት የነበረበት የአእምሮ ሆስፒታል ሐኪም ነው?"
‹‹አዎ ነው››
‹‹ታዲያ አግኝተሸ ማነጋገር አልቻልሺም?››
"አልቻልኩም እንዳለመታደል ሆኖ ከጥቂት ወራት በፊት ሞቷል." "አስደሳች ነው."
"አስደሳች?" አለም በንግግሩ ተበሳጨች። ወንበሯን ትታ ዞረች እና ከኋላው ቆመች
"ይሄ ታደሰ የተባለው ዶክተር ሊቁ የግድያ ወንጀል ለመፈፀም ብቃቱ እንዳለው ሙያዊ ውሳኔ ላይ ሲደርስ ለመጨረሻ ጊዜ የተከታተለው ሌላ የስነ አእምሮ ሃኪም ግን ሊቁ የተባለው ግለሰብ የአእምሮ በሽተኛ ቢሆንም ምንም አይነት ሰውን የማጥቃት ዝንባሌ አሳይቶ እንደማያውቅ በሪፖርቱ አስፍሯል.. ምንም አይነት የወሲብ ፍላጎት እንደሌለው እና
አመፀኝነትም ታይቶበት እንደማያውቅ ተናግሯል፡፡ እና በዶክተሩ ሞያዊ አስተያየት መሠረት እሱ እኔን ዋጋ እንዳስከፈለኝ አይነት የግድያ ወንጀል መስራት እንደማይችል ነው ያረጋገጠው።ገደለ በተባለው ሰው ላይ ሁለቱ ባለሞያዎች የተለያ አይነት ምልከታ ነበራቸው…ይሄም ከመዝገቡ ጋር ተያይዞል..ዳኛው የባለሞያዎቹን ውሳኔ ሚዛናዊነት ለመጠበቅ የሶስተኛ ባለሞያ አስተያየት መጠየቅ ሲገባቸው ባልታወቀ ምክንያት የአንደኛውን አስተያየት ውድቅ አድርገው የሌለኛውን ተቀብለዋል፡፡በአጠቃላይ…ሊቁ የተባለው ሰው እናቴን አልገደላትም የሚል በጣም ጠንካራ እምነት አለኝ።›› አቃቢ ህጉ ሌሎች በርካታ አጭር መግለጫዎችን አነበበ፣ ከዚያም አጉተመተመ፡-
"በአጭር ቀናት ከዚህ የበለጠ ተአምራዊ የሆነ ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ አልችልም። ጉዳዩ ሃያ አምስት አመት ያስቆጠረ ነው። ተስፋ የማደርገው ይሄ ጉዳዩን በ ዳኞች ፊት ለማቅረብ በቂ ምክንያት ነው። በተጨማሪም የዓይን እማኝ የማግኘትም ትንሽም ቢሆን እድል አለኝ
።"
አቀቢ ህጉ‹‹አለም.››ሲል ተጣራ "አቤት"

❤44👍5