አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
🍃👁በ'ነሱ ቤት👁🍃
🍓ክፍል አስራ ሦስት🍓
🍀🍓🍀🍓🍀🍓🍀
እንየው አንድ ወሬ ተጀምሮ ካልተጨረሰ ደስ አይለውም ።ጌታነህ ደሞ ማጓጓት እና ትኩረት ማግኘት ይወዳል ስለዚ አንድ ወሬ ጀምሮ ቶሎ ተናግሮ አይጨርስም ። አጭሯን ነገር መጎተት ልማዱ ነው ። ሰመረ የጌታነህ ወሬ የተለመደ ስለሆነ ብዙምስሜት አይሰጠውም እንዲሁም አንዳንዴ የሚስቀው በነገሩ ተገርሞ ሳይሆን በጌታነህ በሚረባውም በማይረባውም ጉዳይ መደነቅና በዛ ደሞ እራሱን እንደጀብደኛ አድርጎ በማውራቱ ነው ።
"ስሙ ማሚና ዳዲ እንዴት ክው እንዳሉ "አለና ሳቀ እንየው አብሮ ሳቀ ግን ከልቡ አይደለም ጓደኛው እንዳይቀየመው እንጂ በእናትና በአባት ፊት ነውር ስራ መስራት ተገቢ ነው ብሎ አያምንም ። ሰመረ በጓደኛው ወሬ ብዙም ደስተኛ ባለመሆኑ እንደሌላው ጊዜ በሳቅ ከማጀብ ይልቅ ኮስተር ብሏል ። ጌታነህ እረጅም ሳቅ ከሳቀ በዋላ ።
"ከዛ ልክ እንደ በደለኛ ተነስቼ ሁለቱም ላይ ብጮኽባቸውስ !" አለ እንየውን እያየ
"ምንብለህ ደሞ ሆሆሆ ካንተም ብሶ!?"አለው እንየው
"እንዴ ለምን ክፍሌ ዘው ብላቹ ትገባላቹ ።እኔ እናንተ ክፍል ዘው ብዬ እገባለው ወይ?ቢያንስ አታንኳኩም ብዬ ነው ኪኪኪ ከዛ ዳድ ሙድ የገባው ነው እኮ ድንጋጤውን እንደያዘ ይቅርታ ጩኽት ስንሰማ ጊዜ ነው ብሎ ተጨማሪ ነገር ሳይናገር ተመለሰ ።ማም ግን እንዴት በንቀት ሁለታችንንም እንዳየችን ።ያቺ በቀቀን እኔን አስበልታኝ ልክ እንደ ቤቷ ብርድልብሱን ተጠቅልላ ፀጥ ብላ ተጋድማለች እናቷን ደግሜ ላግኛት እራቅ ያለ ቦታ ወስጄ እሷንማ ካልሰራውላት ። በሷ የተነሳ እስካሁን ከማም ጋር አናወራም ፊቴን እንኳ ዞራ አታየኝም ። ዳድ ግን በነጋታው ቁርስ ልጋብዝህ ብሎ ወስዶኝ ብዙ ምክር መከረኝ ኪኪኪኪ ወይ ዳድ ጉርምስናዬን እንደሚረዳ ነገር ግን ቤት ድረስ ሴት ይዞ መምጣት ቤተሰቡንመናቅ እንደሆነ በመንገር የእናቴንም ክብር ዝቅ እንደማድረግ እንደሚቆጠር ,,,,ብቻ ብዙ ብዙ አለኝ እና ላቹ ምክሬን ተቀብዬ ይቅርታ ጠይቄ ከዳድ ጋር ችግሩን በዚሁ ፈታነው ።ከማም ጋር ግን እንደተኮራረፍን ነው ጋይስ እናትህ ስትቆጣ ከባድ ነው ኪኪኪኪኪ ግን ይሄን ነገር ምን እናርገው ኪኪኪኪ"ብሎ ወደታች እያሳየ ሳቀ ።እንየው አጀበው
"በነገራችን ላይ እስካሁን የነገርከን ነገር የሚያስቅ አይደለም በጣም የወረደ ተግባር ነው የፈፀምከው ።ለቤተሰብህ ንቀት ካለብህ በሌላ መልኩ ብታደርገው ይመረጣል ።በእናትና በአባት ፊት ግን ሽርሙጥና ማካሄድ ይበል የሚያስብል ጉዳይ አይደለም ጓደኛዬ ።ስለዚህ ዛሬ መሳቅ ሳይሆን ያለብህ መፀፀት ነው ላደረከው ነገር አላፊነቱን ወስደህ ማስተካከል አለብህ ። በምን? በመጀመሪያ እናትህን ይቅርታ መጠየቅ አለብህ የሰራኽው ሁሉ በመጠጥ ተገፋፍተህ መሆኑን ! በመንገር በመቀጠል ያቺ በቀቀን ያልካት ልጅ ምን አልባት አንተን ተከትላ የሄደችው ደካማጎን ስላላት ነው ወይ ቤተሰብ ታሞባት ገንዘብ አስፈልጓት ይሆናል ክብሯን የምታጣው ስለዚህ እንደ ባለጌ ብቻ ባታያት እና ይቅርታ ብትጠይቃት ይሻላል እንጂ እሷላይ ዳግም መዛት አያስፈልግም ። "አለው ሰመረ በአዋቂነት ።ጌታነህ ሰመረን በመገረም ሲያየው ቆይቶ የለበጣ ሳቅ ሳቀ "ስማ ደሞ መካሪም ሆነህልኛል ዘንድሮእንደው ለየት እያልክ ነው ። በመጀመሪያ ማም በራሷ ሰአት ነገሩ ሲገባት ትተወዋለች ትልቁ ቤት እንደው ለምዶበታል ሴትልጅን አስደስቶ መላክ ኪኪኪኪኪ ምን ልላቹ ነው ማም አዲሷ አይደለም ከዚ በፊት የወንድሜ መስፍንን ዕፀፅ እየሸፈነች ኖራለች ሰራተኛ አስረግዞ ከቤት አባራት ታውቃለች ስለዚ ታሪክ ነግሬአቹሃለው አይደል መቼም ከእናንተ ከጓደኞቼ ሚስጥር መደበቅ አልችልም ። እና እናቴ የኔ እንዲማድረግ ለጊዜው ቢያናድዳት እንጂ ቂም አትይዝብኝም ። መስፍን ያንን ሁሉ አድርጎ እንዴት ከኔ አስበልጣ እንደምትንከባከበው ።አይታችዋል ለኔ እንኳ የመጨረሻ ልጄ ነው ብላ ቦታ ሰጥታኝ አታውቅም ሳምንቱን ሙሉ እሷ እንዳትጎዳ ብዬ ጠብ እርግፍ እያልኩ ድርጅታችን ወስጥ ብሰራም ትኩረቷን ስቤ አላውቅም የፈለገውን ለሚያደርገው ለጡረተኛ ልጇ ታደላለች እና የማም ውለታ የለብኝም ባይዘዌ"ብሎ ወደዋላው ለጠጥ ብሎ ተቀመጠ ።ሰመረ የጓደኛው ቂመኝነት እና ግዴሌሽነት እያሳሰበው ። በራሱመንገድ ሊያስረዳው አፉን ከፈት ሲያደርግ ።ጌታነህ "በቃ በቃ አፍህን ዝጋው እኔን ለመምከር እንዳትሞክር እኔ ህይወቴን በራሴ መንገድ ነው የማስኬደው የግድ አንተን ወይም እንየውን መምሰል አይጠበቅብኝም ።እሺ ይሄንን እርዕስ ዘግቼዋለው ።አለው ሰመረ በምንቸገረኝ ትከሻውን ነቅንቆ ዝም አለ እንየው ሁለቱ ሲነጋገሩ አቅጣጫው መቀየር ስለጀመረ ለማንም ሳይወግን የቀረበውን እየበላ ዝም ብሏል ። ጌታነህ ሰመረ ከቅርብ ጊዜ ወዲ በንግግሩ ሁሉ ከመዝናናት ውጪ ልክ አይደለህም የሚል ሙግት ስለጀመረው አካሄዱን አልወደደለትም ። ወደዋላው ለጠጥ ብሎ ማሰብ ጀመረ ምንአልባት ልቡ የሻከረበት ባለፈው የእህቱ ቬሮኒካ አስራ ስድስተኛ አመት ሲከበር አብሯት በጣም ሲዝናና ነብር ያሁኔታ አስከፍቶት ይሆን ብሎ አሰበ ። ሰመረ ታናሽ እህቱ ቬሮኒካ ገና ከአሁኑ ቀውጢ ልጅ ናት ማንንም አትሰማም የመሰላትን ነው የምታደርገው ።ስለዚ በቀላሉ ችግር ውስጥ ልትገባ ትችላለች ተብሎ በሰመረ አማካኝነት እሷ በማታውቀው መልኩ ጠባቂ ተቀጥሮላታል ።ጓደኞቿበሚደግሱት ድግስ ሳይቀር በቅርብ ሆኖ ነው የሚከታተላት ጠባቂዋ ዳዊት ። ሰመረ ለዳዊት ሁሌም ትህዛዝእንደሰጠው ነው ከአይንህ አትራቅ ይለዋል ።እሱም ትህዛዙን በሚገባ እየተወጣ ነው እስካሁን የተለየነገር አላየባትም ከእብደቷ በቀር ችግሯ አጥብቆ መዝናናትን መውደድ ነው ።
ጌታነህ ልጥጥ ብሎ እንደተቀመጠ ወደ ባሻገር ሲመለከት ቆይቶ የሆነ ነገር ያስታወሰ ይመስል ድንገት ወደ አስተናጋጁ ሰሚር በምልክት ተጣራ
"አቤት ምን ይምጣ "አለው አስተናጋጁ ሰሚር
"አንተ ለዛች ለክስሞቲክሷ ልጅ ስልኬን በትክክል ሰጥተሃታል የዛን ለት "አለው ቆጣ ብሎ
"አዎ እንዴ አልደወለችም"አለ ሰሚር ።በልቡ ባትደውል ደስ እንደሚለው እየተናገረ
"አልደወለችም ይላል እንዴ ሂድና አሁን እሷ ካልቻለች እኔ ልደውልላት ስለምችል ስልኳን ተቀብለሃት ና "አለው በትህዛዝ መልክ ።
"እሺ እሺ "አለና በፍጥነት ተንቀሳቀሰ ።ሰመረ አንገቱን ነቀነቀ እንየው ፈገግ አለ ። ጌታነህ የሰሚርን አሯሯጥ ሲያይ ሊስቅ ከጀለው ,,,,,,,,,,,,,


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍888😁3👎2🔥1
​​#ተአምረተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
//
በማግስቱ….
ከምሽቱ 1 በሰዓት አካባቢ ነው ሰሚራም ሆነች ዶ/ር እስክንድር የእለቱ የማታ ተረኛ ሆነው ስራቸው ላይ ተስማርተዋል፡፡
ሰሚራ ለመላኩ ዘመዶች ደወለችላቸው…ሰሎሞን ነበር  ስልኩን ያነሳው

‹‹ሄሎ››

‹‹ሄሎ..ሰላም ነሽ?››

‹‹አዎ ሰላም  ነኝ …እንድትመጡ ፈልጌ ነው››

‹‹ማን…..? ››

‹‹እናንተ ናችሁ…. ሁለታችሁም››

‹‹ለምን…..? ምን ተፈጠረ…..?››

‹‹ላደርገው ነው…ማድረግ የምፈልገው ደግሞ እያያችሁ ነው..እናንተ ባላችሁበት››

‹‹አረ ችግር የለውም ..ሁሉን ነገር ካጠናቀቅሽ በኃላ ብትደውይልን ይሻላል››

‹‹እንደዛ አላደርግም…በቃ አሁን በነፍስ ነው ብዬ እንደደወልኩላችሁ አስቡትና  እቤትም ሆነ መንገድ ላይ ለገኛችሁት ሰው እንዲሁም ለሌሎች ዘመዶቻችሁ እየደወላችሁ በነፍስ ነው ተብሎ ተደውሎልናል እያላችሁ ንገሩ ፣እናንተም በ20 ደቂቃ ውስጥ ድረሱ›

‹‹አዎ… በቃ ገባኝ እንመጣለን..ትክክል ነሽ››ስልኩ ተዘጋ 

ሁለቱ ብቻ ሳይሆኑ በሌሎች ከስድስት በማያንሱ ሰዎች ታጅበው ለመምጣት ከ15 ደቂቃ በላይ አልፈጀባቸውም…..ሰላም ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት ሆስፒታሉን አተረማመሰችው….ሰሎሞንም እንባውን እየዘራ ወንድሜን እያለ በማጎራት ግቢውን መዞር ጀመረ…
ለስድስት ቀን በኮማ ውስጥ የሰነበተው መላኩ ምን እንደነካው ከዶክተሩና ከሰሚራ ውጭ ማንም በማያውቀው ምክንያት በጣር ነፍስ ጊቢ ነፍስ ውጭ እያቃተተ ነው…ዶ/ር እስክንድር ሲስተር ሰሚራ እና ሌሎች ሁለት ነርሶች ዙሪያውን ከበው  ሊረዱት እየሞከረ ነው..

‹‹ሲስተር ሰሚራ ቶሎ ብለሽ ይሄንን መድሀኒት ውጊው ››ብሎ በወረቀት ላይ የመድሀኒቱን ስም ጽፎ ሰጣት… እሷም ተቀብላ ቶሎ ብላ ወጥታ ሄደችና በሶስት ደቂቃ ውስጥ ይዛ መጣች… መዳሀኒቱን በተንጠለጠው ግሉኮስ ከረጢት ውስጥ በስሪንጅ መጣ ለቀቀችበት ..ቀስ እያለ በቱቦ ውስጥ በመንጠባጠብ ከደም ስሩ ተቀላቀለ…. ከደቂቃዎች በኃላ የበሽተኛው ጣር  እየቀነሰ …መንፈራገጡም እያቆመ መጣ….ከዛ ፀጥ አለ …ሰው ሲሸነፍ ወይም ሲያፈገፍግ ፀጥ ይል የለ….ዶ/ር እስክንድር በማዳመጫ ትንፋሹ አዳመጠው…እጆቹና እያወናጨፈ አንገቱና ቀብሮ በብስጭት ክፍሉን ለቆ ወጣ …ኮሪደር ላይ እነ ሰሎሞን እና አጃቢዎቻቸው ከበቡት.

‹‹ዶክተር..እንዴት ነው በሽተኛው…..?››

‹‹ዶክተር ይሻለዋል ..ፍቅሬ ይድናል…..?››

ለበራካታ ሰከንዶች ተገትሮ ሰላምን አፍጦ ከማየት ውጭ ምንም መናገር አልቻለም፣‹‹….….ይቺን ላየ ሰው እነ ሰላም እና መሀደር ምኑን አክተር ተባሉት ?››ሲል በውስጡ አሰበ…መለስ ብሎም ስለራሱ አሰበ …ወየው ጉድ እኔም ለካ ሌላ ተዋናይ ሆኜያለሁ…አለም ሰፊ መድረክ እኛም ኑሪዎቾ  ተዋናዬች ነን ያለው ማን ነበር …..? ለካ እውነት ነው…›አለና ወደቀልብ በመመለስ ለእነሱ ጥያቄ  መልስ መስጠት ጀመረ 

‹‹አዝናለሁ የተቻለንን አድርገናል…ግን አልተሳካልንም..አርፏል ››ብሎ በተገተሩበት ጥሎቸው እግሮቹን አንቀሳቀሰ  … ግቢውን በጩኸት እና በለቅሶ ሲያደበላልቁት  በውስጡ እየተጠየፋቸው እና እየረገማቸው ጥሎቸው ወደ ቢሮው ሄደ

ሰላም…
..ፍቅሬ ፍቅሬ…
እንጋባለን ብለሀኝ አልነበረ ወይ…
ሙሽራዬ ነሽ አላልከኝም ነበር ወይ..
ለማን ተውከኝ..ለማን ተውከኝ 

ሰሎሞን……
ወንድም ጋሻዬ ….ወንድም ጋሻዬ
የእኔ ብቸኛ..የእኔ ብቸኛ
የአባቴ ምትክ ..የአባቴ ምትክ 
የዓይን ማረፊያዬ….
/////
ከደቂቃዎች በኃላ ሬሳው እየተገፋ ተመላካቹን በእንባ በሚያራጭ እንግሩጉሮአዊ ዜማ እና አንጀት በሚበላ  ሁኔታ በሚያለቅሱት እና ኩርምት ጭብጥ በሚሉት  በወንድሙ  ሰሎሞን እና በፍቅረኛው ሰላም መካከል አልፎ ወደሬሳው ክፍል ተወሰደ…..ሰሚራም እየተንቀጠቀጠች እና እየዘገነናት እራሷን ለማረጋጋት  በትርምሱ መሀል ተሹለክልካ ከሁሉም ነገር በመሸሽ  ቢሮዋ ገብታ ተሸጎጠች
እስከአሁን የሰራችው ስራ እና የፈጠረችው ተግባር ትልቅ ድንጋጤ ውስጥ ከቷት እየተንቀጠቀች  ነው..የሚገርመውና ይበልጥ የሚጨንቀው ግን ከአሁን በኃላ የምትሰራው ስራ ነው…
በበቀልም ሆነ በጥላቻ ተነሳስቶ ሰውን ድፍት አድርጎ መግደል በጣም ቀላል ነው…ሳያስበው በሆነ ብረት ማጅራቱን መጠቅለል እና ዝርግፍ ብሎ ሲወድቅ ጭንቅላቱን በድልዱም ብረት መድገም ነው…አዎ እንደዛ ማድረግ ቀላል ነው… የሚከብደው ከገደሉት በኃላ ያለው ነገር ነው፡፡ሬሳውን ምን ላድርገው…?ግቢው ውስጥ ቆፍሬ ልቅበረው..….?ረሀብ ያንገላታው ውሻ ቆፍሮ አውጥቶ ቢያጋልጠኝስ…?በጆንያ አድርጌ ከከተማ አውጥቼ ራቅ ያለቦታ በመውሰድ ጫካ ውስጥ ልጣለው…?.መንገድ ላይ ፖሊስ ለፍተሻ ቢያስቆመኝስ……..?እንደዛ ሳደርግ ሰው ቢያየኝስ……..?ስቃይ ነው….በዛን ቅጽበት ከሟቹ በላይ ገዳዩ ያሳዝናል…በተለይ  ገዳዩ እንደእሷ አማትር ገዳይ ሲሆን ......ሁኔታው  እንደቅዣት ሆኖባት፤ በውስጧ ስትብሰለሰል  ስልኳ ተንጫረረ….
ከፈጣሪ የተደወለባት ነው የመሰላት….በርግጋ ከተቀመጠችበት በመነሳት ተፈናጥራ ቆመችና የደዋዩን ማንነት ለደቂቆች አትኩራ ተመለከተች…. በፈራ ተባ ስሜት አነሳችው

‹‹አቤት››

‹‹የት ገባሽ…..?››

‹‹አለው ፈርቼ ቢሮዬ ቁጭ ብዬ ነው››

‹‹ምን ያስፈራሻል.…..?.››

‹‹እንዴ ድመት እኮ አይደለም ሰው ነው ያስገደላችሁኝ…..››

‹‹ማለቴ መግደልሽን  ማን ያውቃል..…..?እንደውም ስትፈሪና ስትንቀጠቀጪ የስራ ባለደረቦችሽ እንዳይጠረጥሩሽ…በተለይ ዶክተሩ እንዴት ሞተ ……..?ይሞታል ብለን አልገመትንም ነበር ሲል ሰምቼዋለሁ››

‹‹እ!! እንደዛ  አለ እንዴ…..? ››

‹‹አዎ ብሏል…ለማንኛውም አሁን ምን እናድርግ.››

‹‹ምን ለማድረግ አሰባችሁ?››

‹‹ሬሳውን አሁኑኑ ብትሰጡንና በጥዋቱ ቶሎ ብለን ብንቀብረው ጥሩ ነው፡፡››

‹‹ሬሳውንማ ላሰጣችሁ አልችልም …ጥዋት ነው መውሰድ የምትችሉት››

‹‹አይ አሁኑኑ መውሰድ አለብን… አሁን ሬሳ ሳጥን ገዝተው እንዲመጡ ሰዎች ልኬያለሁ…አንቺ ብቻ ደክተሩን አሳምነሽ እንዲፈርምልኝ አድርጊ…››

‹‹ዶክተሩ እኮ መሞቱን ብቻ ነው የሚያረጋግጥልህ….ሬሳውን በዚህ ምሽት እንድታወጣ የመፍቀድ ስልጣን ያላቸው  ግን ሌሎች ናቸው››

‹‹ሌሎቹን ተያቸው ..ዶክተሩ ብቻ ካስፈረምሽልኝ ካንቺ ምንም አልፈልገም…..ወደቤትሸ ሄደሽ ተረጋግተሸ በድል መተኛት ትችያለሽ…የስራ ኮንትራታችንን እዛ ላይ ይጠናቀቃል….››

‹‹እዛ ላይማ አይጠናቀቅም … መቶ ሺ ብር ጨምርልሻለው ብለኸኝ ነበር››

‹‹ሀይለኛ ብር ወዳድ  ልጅ ነሽ… አይዞሽ አረሳሁትም ግን እንደምታይኝ አሁን ሀዘን ላይ ነኝ ፡፡ ከሶስት ቀን በኃላ ያው እንደምንም መጽናናቴ  ስለማይቀር  አቀብልሻለሁ…››

‹‹ዋ እንዳትረሳ››

‹‹አረሳም አሁን ያልኩሽን ጨርሺና ደውይልኝ››

ስልኩ ተዘጋ……

ይቀጥላል
👍12214👎9👏4🔥1🥰1
አትሮኖስ pinned «​​#ተአምረተ_ኬድሮን ፡ ፡ #ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ // በማግስቱ…. ከምሽቱ 1 በሰዓት አካባቢ ነው ሰሚራም ሆነች ዶ/ር እስክንድር የእለቱ የማታ ተረኛ ሆነው ስራቸው ላይ ተስማርተዋል፡፡ ሰሚራ ለመላኩ ዘመዶች ደወለችላቸው…ሰሎሞን ነበር  ስልኩን ያነሳው ‹‹ሄሎ›› ‹‹ሄሎ..ሰላም ነሽ?›› ‹‹አዎ ሰላም  ነኝ …እንድትመጡ ፈልጌ ነው›› ‹‹ማን…..? ›› …»
#ተአምረተ_ኬድሮን


#ክፍል_አርባ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
//

አንቺ ወደሬሳ ማቆያው ቀድመሽ ሂጂና ሁኔታውን አመቻቺ… እኔ ቀስ ብዬ በጓሮ በኩል  ሄጂ የግቢውን መብራት አጠፋለሁ…ጄኔሬተሩንም አቶማቲኩን ስላበላሸሁት ሄደው አስተካክለው እስከሚያበሩት 10 ደቂቃ ይኖረናል..በዛ ጊዜ ውስጥ ይዘነው እንሄዳለን››

‹‹እሺ ግን ተጠንቀቅ…. ሰው እንዳያይህ››

‹‹እጠነቀቃለሁ..እንቺ ልክ መብራቱ እደጠፋልሽ ቶሎ አዘጋጂውና ከጋሽ ተካ ጋር ይዛችሁት በጎሮ በኩል መኪና መቆሚያው ድረስ ይዛችሁት ኑ..እኔ የመኪናዬን  ሞተር አስነስቼ ዝግጁ ሆኜ እጠብቃችኋለው…››

ተስማምተው እሱ ወደጎሮ  መብራቱን ሊያቆርጥ እና ግቢውን በጨለማ እንዲዋጥ ሊያደርግ እሷ ደግሞ በሽተኛውን ልትረከብ ወደሬሳ ማቆያ ክፍል ሄደች
መብራቱም ጠፍቶ እነሱም ሬሳውን(በሽተኛውን ) ይዘው  በመምጣት በመኪና ውስጥ አድርገው የውጭ ጥበቃዎችን በጥበብ አልፈው ግቢውን ለቀው ለመውጣት 8 ደቂቃ ብቻ ነበር የፈጀባቸው..

ደ/ር እስክንድር ቀጥታ የነዳው ለዚሁ ጉዳይ ታስቦ ወደተዘጋጀ  ዛሬ ጥዋት ወደተከራዩት አፓርታማ ነበር….ይህን ቤት የተከራዩበት ዋና ምክንያት የሰሚርን ቤት የበሽተኛው ዘመዶች ያውቁታል..እሱ ቤት እንደይወስዱት ደግሞ ከቤተሰቦቹ ጋር ነው የሚኖረው…. በዚህ ምክንያት የግድ   ማንም የማያውቀው እና ሰወር ያለ ቦታ ቤት መከራየት ነበረባቸው….
እንደደረሱ….ያው እንደሬሳ ድርቅርቅ ያለውን በሽተኛ ለሁለት እንደምንም ተጋግዘው ከመኪናው አወረዱትና ከሆስፒታል ባመጡት ተሸከርካሪ ጋሪ እየገፉ ወደቤት  አስገቡትና  …መኝታ ቤት የሚገኝ  አልጋ ላይ  ዘረሩት….

ይሄንን ሁሉ እስኪያደርጉ በመካከላቸው በስሜት ከመግባባት እና በምልክት መልእክት ከመለዋወጥ ውጭ ቃላት አልወጣቸውም ነበር….ሁለቱም በተመሳሳይ ሁኔታ በድን ሆነዋል

‹‹በይ ቶሎ መድሀኒቶቹን አምጪልኝ…››ለመጀመሪያ ጊዜ የተናገረው ዓ.ነገር ነበር

ሮጣ ሄደችና ካስቀመጠችለት በማምጣ ፊቱ ያለው ጠረጵዛ ላይ ዘረገፈችለት…

ሁለት መድሀኒቶችን ቀላቅሎ በመርፌ ክንዱ ላይ ወጋው….እና ከጎን ያለ ወንበር  ሳብ በማድረግ አልጋውን ተጠግቶ በመቀመጥ የሚሆነውን መጠበቅ ጀመረ..ሰሚራ ተገትራ  አይኖቾን የተዘረረው ሬሳ ላይ እንደሰካች ነው…ዶክተርም  ቁና ቁና እየተነፈሰ በየሰከንዶች ልዩነት ሰዓቱን እያየ ይቁነጠነጣል..ሰዓቱ ደግሞ መንቀርፈፉ….

‹‹ምነው ዝም አለ…..?››ሰሚራ ጠየቀች

‹‹እኔ እንጃ …መድሀኒቱ በመላ ሰውነቱ እስኪሰራጭና እስኪሰራ 5 ደቂቃ ይወስድበታል››

‹‹ታዲያ ከሰጠሀው እኮ ቆየ…..?››
‹‹መስሎሽ ነው …ገና ሁለት ደቂቃ ነው››

‹‹ሁፍ!!! ሁለት ደቂቃ ማለት ግን ስንት ነው…..?››

‹‹ሁለት ደቂቃ ማለትማ  ያው ሁለት ደቂቃ ነው..ግን አንዳንዴ  እንደዚህ ይበረክታል››አላት በደመነፍስ

…አይደርስ የለ 5 ደቂቃ ሞላ በሽተኛው ንቅንቅ አልል አለ….

‹‹ምን ይሻላል..…..?የሆነ ምልክት ማሳየት ነበረበት››ደ/ር እስክንድር ነው ግራ በመጋባት ለራሱ ይሁን ለሰሚራ በማያስታውቅ ስሜት ያወራው

‹‹አረ የሆነ ነገር አድርግ..ወይኔ ተዋረድን››

‹‹ቆይ እስቲ ተረጋጊ …ይበልጥ ግራ አታጋቢኝ..››አለና ፊት ለፊቱ ካለ ጠራጴዛ ላይ ከተዘረገፉት መድሀኒቶች ውስጥ አንዱን መርጦ በፊት  ከወጋው በተቃራኒ ባለው ክንዱ ላይ ወጋውና በተመሳሳይ ሁኔታ ውጤቱን መጠበቅ ጀመረ….
አንድ ደቂቃ..ሁለት ደቂቃ…ሶስት ደቂቃ…ምንም የለም..በድን ሬሳ…

‹‹ወይኔ ተበልተናል…ምንድነው የተሸወድኩት…..?››

‹‹እኔ ምን አውቃለሁ…መድሀኒቱ አስተማማኝ ነው …አውቀዋለሁ ብለህኝ ነበር…..?››

‹‹አዎ ብዬሽ ነበር..ግን  አልሆነም››

‹‹ግን አልሆንም ትለኛለህ እንዴ……?ስለሰው ህይወት እኮ ነው እያወራን ያለነው..ገና አለምን በቅጡ መኖር ስላልጀመረ ወጣት››

‹‹መቼስ ይሄ እንዲሆን ፈልገን አይደለም..እንደውም በተቃራኒው የእሱን ህይወት ለማትረፍ ነው እዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ ውስጥ የገባነው..ሞክረናል  ግን አልቻልንም››

‹‹መቻል ነበረብን …››ከ20 ደቂቃ በላይ ተገትራ ከቆመችበት ቦታ ተነቃነቀችና ወደእሱ ቀረበች ….እሱም ምን ሊፈጠር ነው በሚል ስጋት ከተቀመጠበት ተነሳና ፊት ለፊቷ ቆመ
እንባዋን እያዘራች….‹‹ልታድነው ይገባ ነበር …መሞት አልነበረበትም…ከባድ  ስህተት ነው የፈፀምነው…››ደረቱን እየመታች  በመንሰቅሰቅ እቅፉ ውስጥ ገባች፡

‹‹አንቺ ምን አደረግሽ..…..?ከምትችይው በላይ ልትረጂው እየሞከርሽ ነበር›››

‹‹አይ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ነበር መሄድ የነበረብኝ…የማይሆን  ነገር ነው የሞከርኩት …..››

‹‹የት ነው ያለሁት…..?››ያልታሰበ ከሩቅ የሚመስል ድምጽ ተሰማ…. ሁለቱም በድንጋጤ ፈዘው  ወደአልጋው መመልከት ጀመሩ ....መላኩ በተኛበት እልጋ ላይ አይኖቹን ቁልጭ ቁልጭ እያደረገ ዙሪያ ገባውን ሲቃኝና በጥያቄ አስተያየት ሲያይ ተመለከቱት

‹‹ወይኔ በአላህ ነቃ ..አደረከው ..አደረከው..››ደ/ር ላይ ተጠመጠመችበት….ለቅሶዋን ማቋረጥ አልቻለችም….ከሳቅ ጋር የተቀላቀለ የደስታ እንባ

‹‹የት ነው ያለሁት…..?››በሽተኛው ጥያቄውን ደገመው

‹‹አይዞህ… እኔ ሲስተር ሰሚራ እባላለሁ…እሱ ደግሞ ጎደኛዬ ነው ዶ/ር እስክንድር ይባላል…ያንተን ጤንነት የምንከታተለው እኛ ነን››

‹‹ምን ሆኜ ነው…..?››

‹‹አይዞህ ጥቂት ጉዳት ደርሶብህ ነበር.. አሁን ተርፈሀል….››

‹‹ሰላሜስ…..?ሰላምን ጥሪልኝ..››
‹‹አይዞህ ጠራታለሁ .አሁን ራስህን አታድክም .››

‹‹ጥሩ…ልኝ..››እያለ ወደ እንቅልፍ አለም ገባ 

‹‹መተኛቱ ጥሩ ነው….ይገርማል የሰጠነው መድሀኒት ከሞት ብቻም ሳይሆን ሰሞኑንም ከነበረበት ኮማ ጭምር ነው መንጭቆ ያወጣው….እንዲህ ይሆናል ብዬ አልጠበቅኩም ነበር….ግን አሁን መልሶ ከእንቅልፉ ሲነቃ  ስለፍቅረኛው እና  ስለወንድሙ እንዴት ታስረጂዋለሽ…..?››

‹‹አታስብ ዋናው ወደ ህይወት መመለሱ ነው… ሌላው እዳው ገብስ ነው… የሆነ ዘዴ አላጣም..አንተ ግን ድንቅ ሰው ነህ››

‹‹አረ ድንቅነት በአፍንጫዬ ይውጣ ..ሁለተኛ እንዲህ አይነት ቅብጠት አይዳዳኝም …እንዴ ነፍሴ በአፍንጫዬ ልትወጣ እኮ ነበር››

‹‹ይቅርታ አጨናነቅኩህ አይደል…..?››

‹‹አጨናነቅኩህ ብቻ..ልትውጪኝ እኮ ነበር…ይሄ ልጅማ እንዲህ በቃላሉ ከዚህ ቤት የሚወጣ አይመስለኝም››

‹‹ምን ማለት ነው…..?››

‹‹እኔ እንጃ አይነ ውሀሽ አላማረኝም…ለማንኛውም በየስድስት ሰዓት ልዩነት ይሄንን መድሀኒት ስጭው…ችግር ካለ ደውይልኝ አሁን እኩለ ለሊት ከማለፉ በፊት ወደቤቴ ልሒድ››

‹‹ስላደረክልኝ ነገር በጣም አመሰግናለሁ..ና ልሸኝህ››

‹‹አረ ግድ የለም….ነገ መቼስ ስራ አትመጪም››

‹‹አረ የዓመት ፍቃድ እጠይቃለሁ..እስኪሻለው  ለማን ጥዬው እሔዳለሁ…?››

…ፈገግ ብሎ እየሳቀባት ቤቱን ለቆላት ሄደ 

.በደንብ እስኪሻለው 15 ቀን ፈጀበት..የሆነውን ነገር እና ፍቅረኛውና ወንድሙ ምን እንዳደረጉት የነገረችው እቤቷ በወሰደችው በ3ተኛ ቀን ነበር..የመከዳቱን ነገር ከሰማ በኋላ ለቀጣዬቹ ሶስት ቀናት ህመሙ አገርሽቶበት ለምን ነገርኩት…..? ብላ እስከምትፀፀት ድረስ ነበር እንዲቆጫት ያደረገት..በኋላ ግን ቀስ በቀስ እያገገመ መጣ ..ሲቆይ በእሷ እንክብካቤ እና ማበረታታት ተሻለው….
👍9218🥰5😁4
በአስራ አምስተኛው ቀን እራሱን ለዋውጦ ጨለማን ተገን አድርጎ ሰፈሩ አካባቢ ሆነ ድርጅቱ ጋር ሄዶ  ለማየት ሞክሮ ነበር….ወንድሙ ሆነ ፍቅርኛው የየራሳቸውን ቤት ጥለው በቅርብ አስርቶት በነበረው  ባለአንድ ፎቅ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተጠቃለው መግባታቸውን አረጋገጠ…
ውስጡ በጥላቻ እንኩትኩት አለ…ይህን ቤት እኮ ከመሰረቱ አንስቶ አጠናቆ እስኪያጠናቅቅ ድረስ ሰላምን ሙሽራ ሆና እቤቱ ስትገባ እያሰበ እና እያለመ ያም ሞራል ሆኖት ነበር ያገባደደው…እስከሚያውቀው ድረስ በጣም ነበር የሚያፈቅራት ….ከልብ ነበር የሚንከባከባት….መኪና ገዝቶ እስከመስጠት ድረስ ደርሷል..
ወንድሙንስ ቢሆን እራሱን እንዲችል እና የራሱ የሆነ ስራ እንዲኖረው ምን ያላደረገለት ነገር አለ.‹‹.ደግሞ ምንም ባላደርግለትስ…?ወንድሙ አይደለው እንዴ …..?ወንድምነት እንዲህ ቀላል ነገር ነው እንዴ……..?እንዴት ደጋግሞ ይገለኛል……..?ህይወቴን ነጥቆ…ንብረቴን ወርሶ… እጮኛዬን አግብቶ ምን አይነት ህሊና ነው ያለው…?
እንዲሁ ሲብሰለሰል ሰሚራም ስታፅናናው ቀናቶች እየነጎዱ እሱም ጥንካሬም እያገኘ ልብም ወደ ሰሚራ እየተሳበ መጣ…..
ሰሚራን ከሰላም ጋር  ሲያነፃፅራት  ግራ ግብት ይለዋል‹‹ያቺ እያወቀችኝ ስትስመኝ እና ስታቅፈኝ ኖራ ገደለችኝ..ይህቺ ምኔንም ሳወታውቀኝ ህይወቷን አደጋ ላይ ጥላ አዳነችኝ…ወይ የሰው ነገር…ሰው አኮ !! የሚባለው ለካ ለዚህ ነው…ሰውን እንዲህ ነው ተብሎ ቁርጥ ያለ ድምዳሜ ልንሰጠው አይቻልም..ሰው ደግ ነው ሰው ክፍ ነው፡፡ሰው መላዕክ ነው፤ ሰው ሰይጣን ነው፤ሰው ሞኝ ነው፤ ሰው ብልጥ ነው፤ሰው አዳኝ ነው ፤ሰው ገዳይ ነው…..››

ይቀጥላል
👍11016👏6🔥3
አትሮኖስ pinned «#ተአምረተ_ኬድሮን ፡ ፡ #ክፍል_አርባ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ // አንቺ ወደሬሳ ማቆያው ቀድመሽ ሂጂና ሁኔታውን አመቻቺ… እኔ ቀስ ብዬ በጓሮ በኩል  ሄጂ የግቢውን መብራት አጠፋለሁ…ጄኔሬተሩንም አቶማቲኩን ስላበላሸሁት ሄደው አስተካክለው እስከሚያበሩት 10 ደቂቃ ይኖረናል..በዛ ጊዜ ውስጥ ይዘነው እንሄዳለን›› ‹‹እሺ ግን ተጠንቀቅ…. ሰው እንዳያይህ›› ‹‹እጠነቀቃለሁ..እንቺ ልክ መብራቱ…»
🍀🍃በ'ነሱ ቤት🍃🍀
❤️ክፍል አስራ አራት❤️
👁👣👁👣👁👣👁
አብላካት የእናቷን እመም ካወቀች በዋላ ትንሽም ቢሆን ቀለል ብሏታል ቢያንስ ህመሟ መዳኒት ያለው መሆኑ አንድ መፍትሄ ነው ብላ አምናለች ።ዶክተሩ አንደኛው ሳንባሽ በከፊል ተጎድቷል ነገርግን እክምናሽን በትክክል ከተከታተልሽና እራስሽን ከተንከባከብሽ መዳን ይችላል ሲላት ።በጆሮዋ ሰምታለች ። የዚህን መፍቴሄም ነግሯቸዋል ከብርድ መጠንቅ እንዳለባት ትንሽ እረፍት እንደሚያስፈልጋት መመገብ ስላለባት ጭምር ሁሉንም አብራት ዶክተሩ ጋር ገብታ ሰምታለች ።ስለዚህም እናቷን ለጊዜው ጤናዋ እስኪመለስ ልታሳርፋት ወስና ። ጉሊት መሄዱን የሷ ድርሻ አድርጋዋለች ። ምንም እንኳ እንደ እናቷ ከደንበኞቿጋር ለመግባባት ቢከብዳትም ። ይህንን መወጣት እንዳለባት አምናለች ። በጠዋት ተነስታ አትክልት ተራ በመሄድ የተለያዩ አትክልቶችን በማምጣት ያቅሟን ትግሏን ጀምራለች ።እናቷ መሳይ የልጇ ድካም ስሜቷን ቢነካውም ።ተይ ብትላት ደሞ ከልጇ ጋር መጣላት እንደሚሆን ስለገባት ተሳቃ የልጇን ድካም ከማየት በቀር ምንም የማለት ጉልበት አጣች ።አብላካት የራሷ ድካም አልታያትም የሷ ፍላጎት እናቷ በፍጥነት ድና ማየት ብቻ ነው ።
አልፎ አልፎ ከአስተናጋጁ ሰሚር ጋር ይደዋወላሉ ።ሰሚር ስራ እንዳገኘላት በተደጋጋሚ ቢነግራትም ።ለጊዜው የእናቷን መደብ ጥሎ መምጣት ስለማትችል ስራው እንደማያስፈልጋት ነግራዋለች ። አስተናጋጁ ሰሚርም ተረድቷት በሀሳብ ግን እያገዛት ነው ያለው ። በወሬ አቸው መሃል ስለነ ሰመረ ይነግራታል እንዴት ያሉ ስርሃተ ቢስ እንደሆኑ ለሴት ልጅ ያላቸውን ንቀት ደሃ እንደማይወዱ በተለይ ደሞ ወፍራሙ ልጅ ጌታነህ ስልክሽን የተቀበለሽ ልጅ ጥሩ ልጅአይደለም አደራ እንዳያታልልሽ ይላታል ሰሚር እንደ ወንድም ። አብላካት ማንም አያታልለኝም የኔ ትልቁ ፍላጎቴ እናቴን መርዳት ብቻ ነው ። ብላዋለች እናም እሱም ይህን ጥንካሬዋን ማስቀጠል እንዳለባት ይመክራታል ።
*አብላካት የጉሊት ስራዋን ጨርሳ የሸጠቻትን ብር ቦርሳዋ ውስጥ ጨምራ ።ለእናቷ ወተት ገዝታ ወደቤቷ እየተጣደፈች ሳለ ስልኳ ጮኽ
"አቤት "አለች በእጇ የያዘችውን እቃ መሬት ላይ አስቀምጣ
"አቢ እንዴት ነሽ አስታወሺኝ የኔ ቆንጆ"አለ ድምፁ
"አላወቅኩህም ማን ልበል "አለችው እየተጠራጠረች
"እንዴ ይሄ ድምፅ ይረሳል በይ በይ ጌታነህ ነኝ ከሳምንት በፊት መንገድ ላይ ጫማሽ ተበላሽቶ እንዲሁም ጓደኛዬ የረዳሽ ጊዜ ኪኪኪኪ "አላት። አብላካት አወቀችው ነገር ግን አነጋገሩ አልተመቻትም
"እእ አወቁኩ ሰላም ነው"አለችው ተረጋግታ
"ጎበዝ እንደሱነው የሚባለው ።እኔ መረሳት የማልወድ ልጅ ነኝ እሺ የኔ ቆንጆ "አላት ለማግባባት እየሞከረ
"እሺ ለማንኛውም ስለደወልክልኝ አመሰግናለው መንገድ ላይ ነኝ ብዙእቃ ይዣለው ስለዚ ቆይቼ ልደውልልህ "አለችው ፍላጎት ባጣ ስሜት
"እውነት ደክሞሻላ !እኔን ይድከመኝ አቢዬ የኔ ቆንጆ በቃ በዋላ መደወልሽን እንዳትረሺ ።እሺ አቢዬ በጣም ነው ካየውሽ ጀምሮ ትናፍቂኝ ነበር "አላት ተለሳልሶ
"እሺ እደውላለው "አለች አብ ላካት ለመገላገል
"እሺ እወድሻለው እሺ "አላት ።አብ ላካት ሳቋ ልትለቅ ምንም አልቀራትም ድንገት ተነስቶ እወድሻለው ዕፃን አደረገኝእንዴ የሚያታልለኝ አለች ለራሷ
"ለማንኛውም አመሰግናለው መልካም ምሽት "ብላ መልስ ሳትጠብቅ ስልኩን ዘጋችው ። እናእቃዋን ሰብስባ እየፈጠነች ወደቤቷ ሄደች ,,,,,,,
👁ጌታነህ አስተናጋጁ ሰሚር መጥቶ ሲፈራ ሲቸር
"ይቅርታ የኮስሞቲክሷ ልጅ ስልክ ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለችም"ሲለው በመገረም አየው ።ሰመረ እና እንየው ተያይተው ተሳሳቁ ።ጌታነ ሽንፈት ስለማይወድ በንዴት አስተናጋጁ ሰሚር ላይ አፍጥጦ
"ማነኝ ነው የምትለው ?!ደሞስ ባለፈው ተቀብላ እደውላለው ብላለች አላልክም "አለው
"አዎ ባለፈው ብላ ነበር "አለው ሰሚር
"እና ዛሬ ምን ብለሃት ነው?"አለው ሽንፈቱ እየቆጨው
"አይ እንደውም ስላንተ አግባብቼ ነግሬያት ነበር ።ነገርግን ባለ ትዳር እና የሁለት ልጆች እናት ነኝ ይቅርታ ደግመህ እንዳትመጣ ።አለመደወሌ እኮ አለመፈለጌን ያሳያል ለምን ይጨቃጨቃል አለችኝ "አለው ሰሚር በውስጡ እየሳቀ
"ምን እንደዛ ነው እንዴ ውይ እኔም አልፈልጋትም አሮጊት "አለ ጌታነህ ።አለመሸነፉን ለራሱ እየነገረ ።ሰመረ ከት ብሎ ሲስቅበት ነበር ሰመረን የሚያናድደው ነገር ሲፈልግ ።የአብላካት ስልክ ትዝ አለው እናም በፍጥነት ወደ አብላካት ደወለ የሰመረ ፊት ሲቀያየር ሲያይ ደስ እያለው ነበር ,,,,,,,,,, ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍6910👎1👏1
🍃🍓በ'ነሱ ቤት🍓🍃
👁ክፍል አስራ አምስት👁
🍃🍓🍃🍓🍃🍓🍃
እንየው የጌታነህ ፍጥነትና በቀላሉ ያለመሸነፍ ስሜት ሁሌም ስለሚያስገርመው ምነው እሱን ቢያረገኝ ይላል በውስጡ ። እሱ ከሴቶች ጋር የማውራቱ ነገር ላይ ብዙም አይደለም ።ምንም እንኳ አቋሙ የተስተካከለ አይነግቡ ቢሆንም ተናግሮ የማሳመን ነገር ላይ የለበትም ። እንዲሁ ከጓደኞቹ ጋር በየ ናይት ክለቡ የሚያገኛትን ሴት በገንዘቡ ከመቃረም ውጪ ።በትክክለኛው መንገድ ሴትን ልጅ አግባብቶ ወደራሱ አምጥቶ አያውቅም እንደተራራ ነው የሚከብደው ። ጌታነህ ሴቶቹን ከቤት ልጅ እስከ ...... በሚባል ደረጃ በቀላሉ አግባብቶ የፈለገውን ማድረግ ሲችል ሲያይ ይቀናበታል ። ሰመረ ደሞ መናገርም ሳይጠበቅበት የተለያዩ ሴቶች የፍቅር ጥያቄ እንደሚያቀርቡለት ያውቃል ሰመረ ግን ፍላጎት የለውም እኔ ሳልወድ የሚከተሉኝ ሴቶች አይመቹኝም ይላል ።እንየው በሰመረ አይቀናም ምክንያቱም ሰመረ ግድ የለውም ።ጌታነህ ግን ነፃ ሰው ነው ብሎ የሰው ስባል ።በተቃራኒው ደሞ ጌታነህ በሰመረ ይቀናል ። ሰመረ መልከመልካም ስለሆነ ሴቶቹ በቀላሉ ይጠመዱለታል ሳይለፋ እና ጌታነህ እሱን ባረገኝ ከላይ እስከታች ነበር ማሯሩጣቸው ብሎ ያስባል ።
ጌታነህ ለአብላካት ደውሎ አውርቶ ስልኩን ሲዘጋው ። እንየው መገረሙ እንዳለ ሆኖ
"እንዴ ለዛች ትንሽ ልጅ እየደወልክ ነው እንዴ?"አለው
"እና እንዴ እኔ እኮ ነኝ "ብሎ ሳቀ
"ገራሚ ነህ ኪኪኪኪ "አለ እንየው
"ትቀልዳለህ ቆንጆ በቀቀን እኮ ናት"አለው ጌታነህ
"ስማ በየናይት ክለቡ እንደምታገኛቸው ሴቶች በቀቀን እያልክ ልትጠራት አይገባም በጣም ልጅ እኮ ናት "አለው ሰመረ እየደበረው
"ተው እንጂ !ታዲያ ምን ችግር አለው ሁሌም እሷ ስትመጣ በአንድ እጄ ጡጦ ይዤ በሌላኛው ደሞ ......እንትን ይዤ አጫውታታለዋ "አለው እየሳቀ
"መቀለድህ ነው ! ቆይ እኔን ለመቃረን ፈልገህ ነው ወይስ የእውነት በዛች ትንሽ ልጅ ላይ ፍላጎት አሳድረህ ነው ?"አለው ሰመረ ፊቱን አጨፍግጎ
"ኧረ በናታቹ እንዴ ስለዝች ልጅ ሲነሳ ሁለታቹ መናቆር ጀምራችዋል እንዴ ሰሙ ምንድነው ይቺን ልጅ ፈልገሃታል እንዴ "አለው ለጌታነህ በመቆርቆር
"አንተም እንዲ ታወራለህ? ልክ ነው እያልክ ነው ?ለነገሩ አንተ ምን ታውቃለህ መከተል ብቻ የራስህ አቋም የለህ ። "አለው ሰመረ ብልጭ ብሎበት
"ኧረ አብርድ እንዴ ይህውልህ ምንም አልክ ምንም በቅርቡ ታየኛለህ የሷን ጉዳይ ሳፋጥነው "ብሎ የሚያናድድ ረጅም ሳቅ ሳቀ ጌታነህ ።ሰመረ በንዴት መልስ ሊሰጥ ሲል ። የጌታነህ ስልክ ጮኽች ። ጌታነህ ስልኩን አየና ሳቀ ወደ ሰመረ እያየ "ተመልከት ሴቶች ቀልብ የላቸውም የኔቆንጆ ማለት ብቻ ነው የሚጠበቅብህ ኪኪኪ "ብሎ ስቆ ስልኩን አንስቶ ማውራት ጀመረ ።ሰመረ ልቡ ተሸበረበት እንዴ የእውነት ያቺ ልጅ ደውላለት ነው ።ኤጭ እንዴት ያናድዳል ። በቃ ችግር ውስጥ መግባቷ ነው ለዚ ደሞ እኔ ነኝ ተጠያቂው ።ምን አለ የዛን ለት ባላወራዋት አለ። እንየው የጌታነ የጅንጀና ወሬ ይጠቅመው ይመስል አፉን ከፍቶ ያዳምጠዋል ።ጌታነህ ብዙ የፍቅር የሚመስሉ ወሬዎችን ካወራ በዋላ ቀጠሮ ይዞ ስልኩን ዘጋው እናም እንደተለመደው እረጅም ሳቅ ሳቀ ።
"ታውቃላቹ ባለፈው ሐሙስ ለት ገቢዎች ሄጄ ነበር ዳድ ስላልተመቸው አመታዊ ግብር እንድከፍል ። ከዛ አንዷ እንደኔው ክፍያዋን ልትፈፅም የመጣች ተለቅ ያለች ሴት አይኗን ብትጥልብኝስ ኪኪኪ እኔስ ምኔ ሞኝ ስርስ ብዬ ተጠግቼ ያዋቂ ወሬ እያወራው ልባን አልነሳዋትም መሰላቹ ኪኪኪ ከዛስ ጉዳይዋን ፈፅማ ስትጨርስ ።በጣም ስለተመቸኽኝ እንደዋወል ብላ ከአንዳንድ ስልኬን አልተቀበለችኝም ዋው ተለቅ ብትልም ለየት ያሉ ነገሮች አሏት መደበቂያ የሚሆኑ ኪኪኪኪኪ እና ከሷ ጋር ነው ያወራውት ።እኔ እረስቻት ነበር እንግዲ ከመጣች ምን ይደረጋል ኪኪኪኪ"ብሎ የሰመረን ሁኔታ መከታተል ጀመረ
"እና እሺ ከአንዱ ወዳንዱ ሆነብህ እኮ ፈንድተህ እንዳትሞት ተረጋጋ "አለው ሰመረ ።በውስጡ እፎይ ብሏል አብላካት የደወለች መስሎት አሳስባው ነበር
"ይመችህ ጌቾ እሱን እርሳው እንጫወት ካሉ አጫውታቸው ላንተ የዘነበው ለኛም ያካፋልን "አለው እንየው እየሳቀ
"ሰሙ ሰሞኑን ለየት ብለሃል ወይ ማፊ አወዛግባሃለች ወይ ወይ አንድ የደረሰብህ ነገር ይኖራል አይዞህ እንግዲ ወደጤናህ እንድትመለስ እንፀልያለን "አለው
"ለራስህ ፀልይ ባክህ አሁን ለምን አንወጣም "አለ ሰመረ እየሰለቸው
"እእ የት ነን ዛሬ "አለ እንየው በጉጉት
"እህ የተለመደው ቦታ ነዋ ያችን በቀቀንማ ማግኘት አለብኝ እንደዛ በነ ማሚ ፊት አዋርዳኝማ አለቃትም ዛሬ አግባብቼ ይዣት ወጥቼ ልክ ነው የማስገባት "አለ ጌታነህ ።እንየው ሳቀ ።ሰመረ የራስህ ጉዳይ ቀሚል ተሰላችቶ ቆመ እናም"ይቅርታ ዛሬ የክለብ ነገር ይቅርብኝ በጊዜ መተኛት እፈልጋለው ። በዛላይ ማፊም ሰፈር እንገናኝ ብላኛለች ።እሷን ካገኘው በዋላ በቀጥታ ወደቤት ነኝ "አላቸው ።ሁለቱም ተያይተው በመከፋት ስሜት አዩት ።የሰመረ አካሄድ ደስ አላላቸውም ።ከዚ በፊት እንዲ ተለያይተው አያውቁም ።ምን ተፈጠረ ብለው አሰቡ ። ማፊ ናት ፀባዩን የቀየረችው ወይስ ያቺ ትንሽ ልጅ,,,,,,,,,,,,,, ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍1294👏4😁4🥰2👎1
#ተአምረተ_ኬድሮን


#ክፍል_አርባ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
//

በ25ኛው ቀን ጥዋት ቁርስ ከበሉ በኃላ

‹‹ዛሬማታ ልሄድ ነው››

‹‹የት ነው የምትሄደው…..?››ደንገጥ ብላ ጠየቀችው ሰሚራ

‹‹ከከተማ ወጣ ብዬ  ትንሽ ራቅ ብዬ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ማሰብ እፈልጋለሁ….››

‹‹ስለምንድነው የምታስበው..…..?ክፉ ነገር አይደለም አይደል…..?››

‹‹እኔ እንጃ …ለጊዜው ምንም የመጣልኝ ነገረ የለም..እንደገደሉኝ ልግደላቸው…ወይስ ይቅር ልበላቸው …..?የማውቀው ነገር የለም…ገንዘቤን ግን ልጅነቴን የሰዋሁበትና ብዙ ፈተና ያየሁበት ስለሆነ ሰባራ ሳንቲም እንደማልተውላቸው እርግጠኛ ነኝ..ምን አልባት እስከዛው በደንብ ቢደሰቱበት  ጥሩ ነው››

‹‹እንዴት አድርገህ ታስመልሳቸዋለህ……..?አሁን እኮ ንብረትህ በእነሱ እጅ ነው..በህይወት መኖርህን ካወቁ ባለ በሌለ  ኃይላቸው ነው አሳደው የሚያስገድሉህ››

‹‹አይዞሽ አታስቢ… እጠነቀቃለሁ….ለዛም ነው ከዚህ ከተማ ራቅ ብዬ በጽሞና ምን ማድረግ እንደምችል ማሰብ አለብኝ የምልሽ››

‹‹ካልክ እሺ ..ቆይ መጣሁ›› ብላ ከነበሩበት ሳሎን ተነስታ ወደመኝታ ቤቷ ከሄደች ከ5 ደቂቃ በኃላ ተመልሳ መጣችና ቼክ እጁ ላይ አስቀመጠችለት፣..ግራ ገብቶት አንዴ የሰጠችውን ቼክ አንዴ ደግሞ እሷን በማፈራረቅና በመገረም ሲያያት  ከቆየ በኃላ

‹‹ምንድነው ይሄ…..?››ጠየቃት

‹‹የራስህ ብር ነው..አንተን እንድገድልላቸው የከፈሉኝ ነው…ሁኔታዎችን እስቲስተካከሉልህ ለመንቀሳቀሻ ይሆንሀል››

‹እንዴ ምን አይነት ሰው ነሽ….?እንዲህ አይነት ሰው እኮ በዚህ ጊዜ አይገኝም››

‹‹አይ እንደምታስበኝ ደግ ሴት ሆኜ አይደለም..ለአንተ ብቻ ነው እንዲህ የሆንኩት..››

በንግግሯ ውስጡ ተነካና‹‹ለእኔ ለምን…..?››ጠየቃት

‹‹እኔ እንጃ….. ›አለችው
..ከተቀመጠበት ተነሳና ስሯ ተንበረከከ..ደነገጠች፡፡ አቀፋት …አንገቷ ሰር ገብቶ ሳማት…. ውርርር አደረጋት፣..አላቆመም… ወደታች አስጎንብሶ ግንባሯን …አይኖቾን… ጉንጮቾን በመጨረሻ ከንፈሯ ላይ ተጣበቀባት…አይኗን ከመጨፈን እና ከንፎሯን ከማነቃነቅ ውጭ ምንም ተቃውሞ አላሰማችም…ደስ የሚሉ እልፍ መሰል ሁለት ደቂቆች አለፉ….

የሚያደርገውን አድርጎ ከተቀመጠበት ተነስቶ ሲቆም እሷ አፍራ  አቀረቀረች…
የሰጠችውን ቼክ መልሶ ጉልበቷ ላይ እያስቀመጠላት..ይሄ ምን አልባት እኔን ለገደልሽበት ቢከፍሉሽም.. አንቺ ግን እኔን ለማዳን ለህክምና ይሄን ቤት ለመከራየት ላወጣሽው ወጪ መሸፈኛ ይሁንሽ…ውለታሽ ግን በዚህ ብር የሚመለስ ወይም የሚጣጣ ፍጽም አይደለም…በሕወቴም ጭምር ከፍዬ አልጨርሰውም››

‹‹ህይወትህን ስፈልግ ያኔ  ትከፍለኛለህ …አሁን ግን ከእኔ ይልቅ አንተ ነህ ችግር ላይ ያለህው …  ደግሞ ከራሴ ገንዘብ ምንም ያወጣሁት ነገር የለም…ከዚህ በተጫማሪ መቶ ሺ ብር ቦነስ ብለው ሰጥተውኝ ነበር…እርግጥ ከላዩ ላይ አንተን ለማሸሽ እና የሬሳ ሳጥኑን ቀይረው ለሰጡኝ አቶ ተካ 50 ሺ ብር ከፍያለሁ..ሌላውን 50 ሺብር   ደግሞ እስከአሁን እየተጠቀምኩበት ነው ፡፡››

‹‹አይዞሽ ለእኔ አትስቢ አልኩሽ እኮ …እነሱም ሆነ ማንም የማያውቀው 5 ሚሊዬን ብር ባንክ አለኝ…..በዛ እጠቀማለሁ፡፡››

‹‹ግን ባረብሽህ ምትሄድበት ይዘህኝ ብትሄድ …..?››

‹‹አረ ደስ ይለኛል..ስራሽን ብዬ እኮ ነው…..?››

‹‹ስራው ይደርሳል››

‹‹በያ ተዘጋጂ….መኪና እንከራይ ››

‹‹ወደየት ነው ግን ምንሄደው…..?››

‹‹እግራችን ወደመራን….››

ይቀጥላል
👍11210👎5👏2
#ተአምረተ_ኬድሮን


#ክፍል_አርባ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


//
የጊቢዋ አጸድ ውስጥ ባለ ወንበር ላይ ቁጭ ብላ የወፎችን ዝማሬ እና የዛፎችን ሽውሽውታ እየታዘበች በሀሳብ እየናወዘች ነው፡፡ያው በህይወቷ አዲስ ክስተት ተከስቷል … አንድ ሰው ላይ ለቀናቶች ሀሳቧ እንደተጣበቀ ነው….ያ ባሪያ ልጅ ልቧን ቅልጥ ሀሰቧን ውስውስ ነው ያደረገባት፡፡ሰሚራ ከምትባለው ፍቀረኛው ጋር ያለውን ታሪክ እና የፍቅር ትስሰር  ሙሉውን ታሪክ ለመጨረስ እራሱ አቅም አነሳት...ስለሱ ከማሰብ የሚያሰንፋት መስሎ እየተሰማት ነው….‹‹ለማንኛውም እስቲ  ታሪኩን ልጨርስ›› ብላ ተቀመጠች …ግን ታሪኩን ለመጨረስ  ንስሯ ያስፈልጋታል..እንደምታየው ደግሞ አሁን ጊቢ ውስጥ  ንስሯ አይታያትም …ብዙም ሳያስጠብቃት ከሄደበት ተመልሶ መጣ 

ቀጥታ ወደዛ ወደተለከፈችበት ታሪክ አመራች …አእምሯዋን ከንስሯ አዕምሮ ጋር በተለመደው መንገድ አቆራኘችው..አዎ አገኘዋቸው…ከከተማ እንውጣ ብለው ላንጋኖ ነው የሄድት …በሀይቁ ዳር በታነፀ ላውንጅ  የተዘጋ መኝታ ክፍል ውስጥ ናቸው፡፡
//////
ህይወት ልክ እንደካርታ ጫወታ ነች…ይበወዝና ተጫዋች ለሆኑት  ኗዋሪዎቾ የሚታደል ዕጣ ፋንታ በሚሉት ምናባዊ ሀዲድ  የምትሸረብ…አጋጣሚ በተባለ የህይወት ሰንሰለታማ  ጉዞ ላይ በትክክለኛው ቦታ በትክክለኛው ጊዜ አንዱ ካንዱ በመገጣጠም መላተም እና በሌላ ገጽ ላይ  በሰከንድ ሽርፍራፊ ሰከንድ መዘግየት ተፈጥሮ ተፈላልጎም ሳይገናኙ  መተላለፍን በውስጧ የያዘች….

በጣርነው መጠን ማናገኝባት…ባመረትነው መጠን ማንሰበስብባት…በተመኘነው መንገድ ማንጓዝበት..እንደሎተሪ ዕጣ ብዙዎቻችን የምንከስርባት…የተወሰነው በማስተዛዘኛ የምንፅናናባት..ጥቂቶች ደግሞ እንደው ጠብታ  ላባቸውን በአልማዝ ተመንዝሮ እጃቸው ላይ የሚቀመጥላቸው …ውጥናቸውን አለም ጠቅላላ ተረባርቦ ከግብ የሚያደርስልቸው ከእርጥብ እድል ጋር የተፈጠሩ…ንግግራቸውን በደቂቃ አለም የሚያደምጥላቸው…እነሱ ለተከዙት አለም ተንሰቅስቆ የሚያለቅስላቸው …እንዲሁ መርቆ የፈጠራቸው አሉ፡፡ … እና ህይወት የካርታ ጫወታ ነች…የጫወታውን ህግ ግን ተፈጥሮዊ ብቻ አይደለም..ሰው ሰራሽም ጭምር ነው … 
ይሄንን ሀሳብ ያሰበችው ሰሚራ ነች ..ፍቅረኛዋ  መላኩ ደረት ላይ ጋደም ብላ እያሰላሰለች የምትገኘው፡፡እንዴት እንዲህ ልሆን ቻልኩ....?እንዴት ከበሽተኛዬ ጋር ፍቅር ውስጥ ገባሁ…...?አጋጣሚው ነው ወደዛ የገፋኝ ወይስ እራሴ ነኝ ፈቅጄ እና አስቤ ወደዚህ ደረቱ ላይ ወደተጋደምኩት ልጅ ልብ ውስጥ የገባሁት…...?

‹‹ምን እያሰብሽ ነው..?››ድንገት በጠየቃት ጥያቄ ለውስጥ ጥያቄዋ መልስ ሳታገኝ  አቋረጠችው፡፡

‹‹መቼ ጥለህኝ እንደምትሄድ እያሰብኩ ነው››አለችው…ለምን እንደዛ እንዳለችው ለራሷም አልተገለጸላትም… ..ምክንያም እያሰበች ያለችው ያንን እንዳልሆነ እሷና እግዚያብሄር ያውቃሉ….ሳታስብ ከንፈሯ ላይ የመጣላት ድንገታዊ መልስ የእውነት ስጋቷ አይደለም ማለት ግን አይቻልም…

‹‹የት ነው ጥዬሽ የምሄደው..?››

‹‹ወደኑሮህ ነዋ››

‹‹ኑሮ ማለት እኮ  የህይወት ደስታሽ የሚመረትበት ቦታ ነው….ማንም ሰው በህይወቱ የሚባክነው ያንን ቦታ ፍለጋ ነው…የደስታው ምንጭ የሚፈልቅበትን ጥግ ለማግኘት …የሰው ልጅ ስኬትም የሚለካው በዚህ ነው…እና እኔ እድለኛ ነኝ .ብዙም ሳለፋ በተዐምራዊ አጋጣሚ አንቺን አግኝቼያለሁ….እንዳገኘውሽ ያወቅኩት ደግሞ በአሁኑ ጊዜ በቃ ስትስቂ ልቤ ትቀልጣለች…ትንፋሽሽን ወደውስጤ ስስበው በሰውነቴ ውስጥ በስብሰው  ያበቃላቸው ሴሎቼ እንኳን መልሰው ህይወት ሲዘሩ ራሱ ይታወቀኛል…..ከጎኔ መኖርሽን ሳይ ዓለም ጠቅላላ ተሰብስባ ከእጄ የገባች ይመስለኝና ልቤ በኩራት አብጣ ልትፈነዳ ትደርሳለች..እና ከአንቺ ተለይቼ መሄድ ማለት ወደባዶነት ሸለቆ ተወርውሮ መከስከስ ማለት እንደሆነ ሚጠፋኝ ይመስልሻል …...?አሁን ባለሁበት ሁኔታ ከንቺ ውጭ ኑሮ ማለት ሲም ካርድ የሌለው ባዶ የሞባይል ቀፎ መሆን ማለት ነው…..››

ከትከት ብላ ሳቀች..ኪ…ኪ..ኪ…እንዴ ‹‹ነገሩን ሁሉ እኮ ስነጽሁፋዊ አደረከው…ከእኔ ከመገናኘትህ በፊት ነጋዴ ነበርኩ ብለሀኝ አልነበር እንዴ..?››

‹‹አዎ በጣም ጎበዝ ነጋዴ ነበርኩ…ምን ተፈጠረ..?››

‹‹አይ ንግግርህ የደራሲ እንጂ የነጋዴ አልመሰለኝ አለኛ…..››

‹‹አታውቂም እንዴ..? ፍቅር እና ችግር ያፈላስፋሉ እኮ….!!!››

‹‹አይ ጥሩ….ለማንኛውም የቀልድህንም ቢሆን በሰማሁት ነገር ደስ ብሎኛል….ምነው በተናገረው መጠን ሊያፈቅረኝ በቻለም ብዬ ተመኝቼያለሁ››

ከደረቱ ላይ ቀና አድርጎ አነሳትና እሱም ከተጋደመበት ቀና ብሎ ተቀመጠ… ወደእሷ ዞሮ አይን ዓይኗን እያየ‹‹አላመንሺኝም እንዴ ..? የምሬን ነው የተናገርኩት….በጣም ነው ያፈቀርኩሽ ..ወደፊት ማግባት የምፈልገው አንቺን ነው….የልጆቼ እናት ላደርግሽም እፈልጋለሁ….. ››
አንገቷን ወደእሱ ዘንበል አድርጋ እጆቾን በመዘርጋት ተጠመጠመችበት ..‹‹በጣም ነው የማፈቅርህ አንተን ስላገኘው እድለኛ ነኝ››
…..
‹‹እሺ አሁን ወጣ ብለን  ቢች ዳር ዘና እንበል…..››አላት በሀሳቡ ተስማማችና ተያይዘው ወጡ…
ላንጋኖ ሀይቅ ላይ ያረፈችው የማታዋ ጀንበር ልዩ ህብረቀለም እየረጨች ስትታይ ለአካባቢው ልዩ ውበት አልብሳዋለች…. ቢች ዳር ኳስ የሚጫወቱ አሉ..ሀይቅ ውስጥ ገብተው የሚዋኙን የሚንቦጫረቁም ጥቂት አይደሉም…… በአካባቢው ደስታ ተመርቶ የሚታደል ወይንም ከንፋሱ ጋር ተቀላቅሎ አየሩን እየሞላው በስፍራው ያለው ሰው ሁሉ እየማገው የሚፈግና የሚደሰት ይመስላል፡፡

‹‹ትዋኚያለሽ …..?››

‹‹አረ ይቅርብኝ …ዝምብለን እዚህ ሳሩ ላይ ቁጭ እንበልና  በማየት እንደሰት..ባይሆን ቆይቶ ከነሸጠኝ አብረን እንገባለን›› አለችውና ቁጭ አለች ..ተከትሎት ከጎኗ ቁጭ አለ…….

ይቀጥላል
👍12915👎15👏6😁2🔥1
አትሮኖስ pinned «#ተአምረተ_ኬድሮን ፡ ፡ #ክፍል_አርባ_ሁለት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ // የጊቢዋ አጸድ ውስጥ ባለ ወንበር ላይ ቁጭ ብላ የወፎችን ዝማሬ እና የዛፎችን ሽውሽውታ እየታዘበች በሀሳብ እየናወዘች ነው፡፡ያው በህይወቷ አዲስ ክስተት ተከስቷል … አንድ ሰው ላይ ለቀናቶች ሀሳቧ እንደተጣበቀ ነው….ያ ባሪያ ልጅ ልቧን ቅልጥ ሀሰቧን ውስውስ ነው ያደረገባት፡፡ሰሚራ ከምትባለው ፍቀረኛው ጋር ያለውን ታሪክ…»
👁በ'ነሱ ቤት👁
ክፍል አስራ ስድስት
👁👁👁👁
የአብላካት እናት መሳይ ጤንነቷ እየተመለሰ ሲመጣ ልጇን ለማሳረፍ ብላ ወደስራ ለመመለስ ወሰነች ።አብላካት በእናቷ አሳብ አልተስማማችም ።ምክንያቱም ዶክተሩ አስጠንቅቋታል ። እራሷን ከቅዝቃዜ እና ከሆነ ላስፈላጊ ድካም እንድትጠብቅ ።ስራው ደሞ በጠዋት ተነስቶ መንቀሳቀስን ይጠይቃል ማምሸትም ጭምር ። ስለዚ ከእናቷ ጋር ክርክር ገጠመች ።
"እናቴ ለምን ታስቸግሪኛለሽ ? የእኔ እናት ሆነሽ መኖር አትፈልጊም ?"አለቻት ምርር ብላ ።መሳይ ጨነቃት እንዲ ትከፋለች ብላ አላሰበችም ።የሷ ዋነኛ አላማ ልጇ የማይገባትን ስራ እየሰራች እንዳትደክምባት ነው በተጨማሪ ደሞ እኩዮቿ በተለያየ የትምህርት ስልጠናውስጥ ገብተው እሷ ግን በኑሮ ተቸግራ ገሊት ላይ አትክልት ደርድራ ከአሁን አሁን ገዢ መጣ እያለች ስትጨነቅ ማየት ስላላስቻላት ነው ። ጤንነት ሲሰማት ካላሳረፍኩሽ ያለቻት።
"የኔ ትንሽዬ አበባ እኔ እኮ ብቻሽን ስትለፊ ማየት ስለጨነቀኝ ነው ።በዛላይ በጣም ደና ነኝ "አለቻት እቅፍ አድርጋት ።
"ተይ እናቴ ለኔ ካንቺ ጤንነት በላይ የሚያሳስበኝ ነገር የለም ።ለኔ ሞራል መጠንቀቅ ፈልገሽ ነው ይገባኛል ነገር ግን እኔ ማንነቴን ጠንቅቄ የማቅ ሰው ነኝ ሌሎችን ለመሆን አይደለም አላማዬ እራሴን በሁለት እግሮቼ ማቆም እና ያንቺን የኑሮ ጫና መቀነስ ነው ። የሰፈር ጓደኞቼ ስላሉበትና ስለሆኑት ነገር እያሰብሽ ለኔም ተመኝተሽልኝ ይሆናል ነገር ግን እኔ እራሴን ከማንም ጋር አላወዳድርም እኔ ማድረግ ያለብኝ የምችለውን ነው ። እና ደሞ ታያለሽ ሁሉም ነገር አንቺ ደና ሁኚልኝ እንጂ ይቀየራል እሺ እናቴ "አለቻት እናቷ ላይ ልጥፍ ብላ ።መሳይ የልጇ አዋቂነት ሁሌም እንዳስገረማት ነው ። ልዩ ናት አብ ላካት ምንም ነገር ባልተሟላላት ሁኔታ ላይ ብትሆንም ። ቅሬታ አቅርባ አታውቅም ። እሷ የምታዝነው እናቷ ስታዝን ስታይ ነው የምታለቅሰው እናቷ ያለቀሰች ቀን ነው ። መሳይ በልጇ እንደኮራች ነው ።ነገርግን የሁሌም ጭንቀቷ አንድ ወንድ ልጇን እንዳያሰናክልባት ነው ።
*ቀን በቀን እየተተካ ጊዜው ወደፊት ገሰገሰ የአብላካትም እናት ተሽሏት ወደስራዋ ተመለሰች አብላካትም አንዲት አነስተኛ ፑቲክ ቤት ተቀጥራ መስራት ጀመረች ። በዚ አሳብ እናቷ ባትስማማም አብላካት ግን ትምህርቷን በማታው ክፍለጊዜ እንደምትማር በጭራሽ እንደማታቋርጥ ነገረቻት በስንት ጉትጎታ አመነችላት ። ይህንን ስራ ያገኘላት አስተናጋጁ ሰሚር ነበር ። መጀመሪያ ላይ እሱ የሚሰራበት ሬስቶራንት ሊያስቀጥራት ነበር በዋላላይ ግን አሳቡን ቀየረ ።ሰሚር አሳቡን ያስቀየረው ምክንያት ።ጌታነህ በስልክ እንደሚያወራት ስትነግረው ነበር ። አስተናጋጁ ሰሚር አብላካትን እሬስቶራንቱ ማስቀጠር ።ለጌታነህ አሳልፎ እንደመስጠት ነው የቆጠረው ስለዚ ተወው ።
አንድ ቀን አስተናጋጁ ሰሚር ከስራ እንደወጣ አብላካት የምትሰራበት ፑቲክ ቤት በቀጥታ ሄደ ። አሳቡ የሷም ሰአት ስለደረስ በዛው ስለ ጌታነህ እያወራት ሊሸኛት በማሰብ ነው ቀኑም ቅዳሜ ስለሆነ ትምህርት እንደማትገባም ያውቃል ።
አብላካት ሰሚርን ስታየው ደስ አላት መንገድ ስትሄድ ከሰው ጋር ብትሆን ትመርጣለች በተለይ አሁን ላይ እራሷን መጠበቅና አለባበሷም ስለተቀየረ ቁንጅናዋ ይበልጥ ስለጨመረ ። የወንዶቹ ለከፋ ምቾት ይነሳታል ስለዚ አብዛኛውን ጊዜ ከጎኗ ከምትሰራ ልጅ ጋር ነው የምትሄደው ። በእርግጥ የመጣባትን ጥያቄ ሁሉ በአግባቡ መመለስ የሚከብዳት አልነበረችም ። እሷ የሚረብሻት ጥግ ጥግ ተቀምጠው እያፏጩ የሚላከፉ ወንዶች ሁኔታ ነው ። ዛሬ አስተናጋጁ ሰሚር ስለመጣላት ተደሰተች። እናም አብረዋት የሚሰሩትን የስራ ባልደረቦቿን ቻዎ ብላ ከሰሚር ጋር እያወራች ወደ ሰፈሯ በእግር ወክ እያረጉ ሄዱ ። አስተናጋጁ ሰሚር ጥቂት እንደተጓዙ "አቢ እኔ የምልሽ እነዛ ልጆች አሁንም ይደውሉልሻል እንዴ?"ብሎ ጠየቃት
"እ እነዛ?.."
"እማለት ይሄ ጌታነህ "አላት
"እእ አዎ ኧረ ትላንት ደውሎ ምን ቢለኝ ጥሩ ነው ለዛሬ ማታ ላግኝሽ ኪኪኪ የሚገርም ምላሳም ነው "አለች
"እና አንቺ ምን አልሺው"አላት ሰሚር
"በሆዴ እያማረህ ይቅር ኪኪኪ በአፌ ደሞ በማታ አይፈቀድልኝም ከስራ የምወጣው ደሞ አስራ አንድ ተኩል ነው አልኩት "አለችው
"ጎበዝ በፍፁም አንዳቸውንም እንዳታገኛቸው "አላት
"እሺ ግን ምን ድነው የፈራኽው"አለችው
"ልክ አይደሉም ይጎዱሻል "አላት ጭንቅ እያለው አብላካት ቀና ብላ አይታው ሳቅ አለች ። በዚጊዜ አንዲት መኪና አጠገባቸው ደርሳ ሲጢጥ ብላ ቆመች ሁለቱም ደንግጠው ፈንጠር አሉ,,,,,,,


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍758🥰1👏1
👁በ'ነሱ ቤት👁
ክፍል አስራ ሰባት
🍃🍓🍃🍓🍃🍓🍃
አስተናጋጁ ሰሚር አጠገባቸው ድንገት የቆመችውን መኪና ሲያይ ደነገጠ።እናም ወደውስጥ አይኑን ወረወረ እንደ ጠበቀው ነው ። ከመኪናው ውስጥ ሰመረ በመገረም ሲያየው የሚገባበት ጠፋው ። አብላካት ቆጣ ብላ ወደመኪናው እያየች "በሽተኛ ነህ እንዴ ገጭተኽን ነበር እኮ ! ማን ሰቶክ ነው መኪናውን!"ብላ ተንጣጣችበት ። ሰሚር ዝም እንድትል ምልክት እያሳያት ነበር ። ሰመረ መኪናውን ከፍቶ ሲወጣ አብላካት ለማስታወስ ሞከረች ።
"እሺ አንተ ጉደኛ አስተናጋጅ እቺን ልጅ ከየት አገኘሃት ? ባክህ "አለው ፊቱን ቅጭም አድርጎ እያየው
"እእ እኔ ,,,"ብሎ ሲንተባተብ
"እንዴ ይመለከትሃል ሰሚር ጓደኛዬ ነው "አለች ለማስታወስ እየሞከረች
"ምን እሺ እኔን አስታወሺኝ ሰመረ እባላለው አንድ ወቅት መንገድ ዳር ችግር......"ብሎ ሊያስታውሳት ሲጥር
"እንዴ በፈጣሪ አስታወስኩህ በጣም ይቅርታ ሰመረ መቼም ያንተ ውለታ የሚረሳ አይደለም !"አለችው እጇን እየዘረጋች
"ያን ያክል የሚካበድ ባይሆንም ስላስታወሺኝ ግን ደስ ብሎኛል እንዴት ነሽ ግን ?"አላት አስተናጋጁ ሰሚርን እየገላመጠው ። ሰሚር ምንም እንኳ ሰመረ ስላገኘው ቢደነግጥም ።የአብ ላካት ሁኔታ ግን አላስደሰተውም ።ሰመረን የምታናግረው በጣም ተደስታ ነው ሰሚር ደሞ እነሰመረን በጣም ነው የሚፈራቸው ልክ አይደሉም ብሎ ነው የሚያስበው ሲሰበሰቡ የሚያወሩት ስለሴት ብቻ ነው በዛላይ እያወራረዱ ።በተለይ ጌታነህ ።ከሰመረ ብዙ መጥፎ ነገር ባይሰማም ነገር ግን አብሮአቸው እስካለ ።ከነሱ የተሻለ ነገር እንደማያስብ ነው የሚሰማው ። እናም አብላካት ከነሱ መራቅ አለባት ብሎ ያምናል ።
"ደና ነኝ አካበድሽ ላልከው ነገር ደሞ ሲያንስ ነው። አንተ በሰጠኸኝ ገንዘብ ተጠቅሜ የእናቴን ጤንነት መልሼበታለው ።እናቴን አትርፈህልኛል ይህ ለኔ ትልቅ ነገር ነው "አለችው ።ሰመረ እንዲ ከፍያለ ችግር ውስጥ በዚ ዕድሜዋ ትገኛለች ብሎ አላሰበም ።ስለዚ ከበፊቱ በባሰ አዘነላት ።
"እኔ ግን እንዲ አገኝሻለው ብዬ አላሰብኩም ይገርማል "አላት
"እንዴ እኔም ሁሌም ሳስብህ እንዳመሰገንኩ ነው ። "አለችው ስታናግረው ትላልቅ አይኖቿን ከአይኖቹ ሳትነቅል ነበር ። ሰመረ ውስጡ አንዳች ነገር ሲነካካው ተሰማው እና ያንን ስሜት ላለማዳመጥ ጥረት አደረገ ።በል በል ልቤ ተው ።ገና ታዳጊ ናት በዛላይ በጣም ምስኪን ይችን ልጅ ንፁ ጓደኛ አድርጎ ከጎኗ በመቆም ከክፉ አሳቢ ሁሉ መጠበቅ ነው የሚያስፈልገው አለ በውስጡ።
"ግን አንድ ነገር ቅር ብሎኛል ጓደኛዬ አንድ ሁለቴ ሲደውልልሽ ሰምቻለው እና ግን በዛ መሃል ስለኔ አንስተሽ አታውቂም "አላት በቅሬታ
"ኧረ እኔ ስለ አንተ ጠይቄው አውቃለው ነገር ግን እንደማያገኝህ ነው የነገረኝ "አለችው
"በእውነት ?!"አላት
"እውነት ስለሰሚር ደሞ ተገርመሃል አውቃለው እሱም ያው እንዳንተ እየረዳኝ ነበር እና ረጅም ጊዜ ሆነን ።አሁን እማ በጣም ተግባብተን እንደ ታላቅ ወንድሜ ሆኗል ሰሚር ወንድሜ ነው እሱ ከጎኔ ባይኖር እንዲ ጠንክሬ ባልቆምኩ በርግጥ ያን ያክል ሰነፍ ባልሆንም የሚመክር ሰው ግን ያስፈልገኝ ነበር "አለችው ።ሰሚር አንገቱን ወዝውዞ አረጋገጠ
"ይሁን እሺ ታዲያ ለምን እራት አልጋብዛችሁም "አላቸው ሰሚር "አይ እናቷ ስትቆይ ታስባለች "አለው
ሰመረ ኮስተር አለበት
"አዎ ሰመረ ሌላ ጊዜ ይሻላል "አለችው
"እሺ ካልሽ በቃ እ ለማንኛውም ግን መልሰን ስንገናኝ አንቺ ትጋብዢኛለሽ መቼም አሁን ስራ ገብተሻል አይደል "አላት ቅር እያለው
"ችግር የለውም ግን ስራ መጀመሬን በምን አወቅክ "አለችው ፈገግ ብላ
"ያስታውቃል ትልቅ ሴት ሆነሻል በዛላይ በዚሰአት ከስራ ነው መቼም የምትመለሺው እና ደሞ በስልክ ለጊታነህ ስትነግሪው ሰምቻለው "አላት
"አዎ እሱስ ልክ ነህ ጓደኛህ እየደወለ ያደርቀኛል ኪኪኪ "ብላ ሳቀች ።አስተናጋጁ ሰሚር ቅር አለው ለነዚ ሀብታሞች መሳቅ ትርፉ ችግር ነው ።ብሎ ያስባል
"በነገራችን ላይ እራስሽን ጠብቂ በፍፁም ለማንም እራስሽን አሳልፈሽ እንዳትሰጪ የፈለገ ቢሆን በይሉንታ በውለታ እንዳትሸነፊ እሺ "አላት
"እሺ አታስብ ሰመረ በድጋሚ አመሰግናለው "አለችው
"ችግር የለም እ በሉ እንግዲ ሰላም አምሹ " ብሎ ሁለቱንም ጨብጦ ከተሰናበተ በዋላ ወደ መኪናው ተራመደ ።አብላካት ሰመረን ከዋላው እያየችው በቅሬታ ቆመች ሰሚር እንሂድ እስከሚላት ድረስ ።ሰመረ መኪናው ውስጥ ከገባ በዋላ እጁን አውለብልቦላት ነንገድ ጀመረ ። እሷ ፈዛ ቀረች ።ሰሚር እጇን ጎተት ሲያደርጋት እንደመባነን አለች
"ምነው ወሬው ከምር ተመቸሽ እንዴ?"አላት እያለመጠ
"እእ አይ ገርሞኝ ነው ማለት ለምንድነውእንዲ እየተጨነቀልኝ ነገርግን ስልኬን የማይጠይቀኝ "አለችው በቅሬታ
"እንዴ እሱም እንዲነተርክሽ ፈልገሽ ነው እንዴ ?!"አላት ሰሚር ።
"አይ እሱ ይለያል ሰሚር እንደዛ እብድ ልጅ አይደለም ላደረገልኝ ነገር እንኳ ውለታ አልፈለገም "አለችው ተክዛ ሰሚር በዝምታ ስለ ሰመረ እና ስለጓደኞቹ ልዩነት እያሰበ ከአብላካት ጎን መሄድ ጀመረ ።አብላካት ጭንቅላቷን የሰመረ አነጋገር እርጋታ ቁጣ ሁሉ ነገር ሞላው ።አሰበችው ,,,,,,,,


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍1044👎4🥰2😁1
#ታምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አርባ_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

////
ሁለቱ ፍቅረኛሞች ከአካባቢው ተነስተው የተንቀሳቀሱት ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ ነበር…እያመሩ ያሉት ወደመኝታ ቤት ነበር..ልብስ ቀይረው ራት ለመብላት እና ምሽቱን ዘና ብለው ለማሳለፍ ወደ ሬስቶራንት ለመሄድ..ግን  መንገድ ላይ ያላሰቡት ሰው በዛፎችና በጭለማ የተሸፈነውን  ጠባብ  የእግር መንገድ ዘግቶ ሽጉጥ ደቅኖ ጠበቃቸው… መላኩ ቶሎ ብሎ የሰሚራን ክንድ ጨምድዶ ያዘና ጎትቶ ከጀርባው በማድረግ አሱ የግንብ ግድግዳ ሆኖ ከፊቷ ተገተረ…..

‹‹አይ አይ ….ካንተ በፊትማ እሷን ነው መግደል  የምፈልገው››

‹‹አይ እንደጀመርከኝ እኔኑ ጨርሰኝ….››

‹‹አይ መጀመሪያማ እንደህጻን ያታለለቺኝን ይቺን ጊንጥ ፊትህ ደፋትና አንተን አስከትላለሁ..››

‹‹ለመሆኑ እዚህ ድረስ እንዴት ተከትለኸን መጣህ..?››መላኩ  ነው ድንጋጤውን እንደምንም   ተቆጣጥሮ  በጣም የገረመውን እና ያልጠበቀው ነገር እንዴት ሊሆን እንደቻለ ለማወቅ የጠየቀው፡፡

‹‹እግዜር ነው እጄ ላይ የጣላችሁ..እኔማ ሀገር ሰላም ነው ብዬ ልዝናና ነበር እዚህ የመጣሁት
…ግን ሞቶ አልቅሼ በእጄ አፈር
አልብሼ ቀብሬዋለሁ ያልኩት ወንድሜ እዚህ ዘና ብሎ አለሙን ሲቀጭ አገኘሁት…..ለዛውም ገደልኩልህ ብላ 6መቶ ሺ ብሬን ቅርጥፍ አድርጋ ከበላች ቀጣፊ ሴት ጋር…››መለሰለት ሰሎሞን
መላኩ እየተንቀጠቀጠ መናገር ጀመረ‹‹ገራሚ ነህ …አንደኛ በዚህ አፍህ የእግዜያብሄርን ስም ማንሳትህ ትልቅ ድፍረት ነው..እግዚያብሄር እኮ ፍትህ ነው..እግዚያብሄር ፍቅር ነው..እግዜያብሄር የበጎነት የመጨረሻው ጥግ ነው…ታዲያ በምን ስሌት  እግዚያብሄር አንትን ረድቶህ እኛን አንተ እጅ ላይ ይጥለናል ብለህ ታስባለህ …..?ማይሆነውን…..!!!ደግሞ ገንዘቤን የምትለው…ገንዘቡ እኮ የእኔው ነው…ደግሞ እሷ እንደአንተ እና እንደዛች ሴት ከንቱ አትምሰልህ….ገንዘቡን የእኔ መሆኑን በመረዳት ሳትሰስት ሰታኛለች…››
‹‹በቃ ከዚህ በላይ ልፍለፋህን ልስማ  አልፈልግም …..አሁን አይኔ እያየ ሁለታችሁም በአንድ ሳጥን ተዳብላችሁ ትቀበራላችሁ..እዚህ የጀመራችሁት ፍቅር እዛ ያለከልካይ ትኮመኩሙታላችሁ…››ብሎ ወደነሱ የቀሰረውን ሽጉጡን ቀጭ ቀጭ አድርጎ አቀባበለ….ይሄ ቅጭልጭልታ ቀድሞ የተሰማው ለሰሚራ ጆሮ ነበር..ያው ሴት ከወንድ በላይ ንቁ አይደለች….ከሰማችው ድምጽ ጋር እኩል ተሸከርክራ መላኩን  ገፍታር ከፊቱ ተደቀነች.. ሞቱን ቀድማ ልትሞትለት….ተሳካላት…..በዛ ቅፅበት   ዶ..ዶ..የሚል አደንቋሪ ድምጽ ተሰማ  …ወዲያው የብዙ ሰው ጩኸት እና  የሚሮጡ የሰው ኮቴ …ከዛ ሰሚራ ዝልፍልፍ ብላ መላኩ  እጁ ላይ ገንደስ ስትል ይዟት ወደመሬት ሲወርድ ..ሁሉ ነገር የሚሆነው በደመነፍስ ነበር….
////
…ሰሚራ ድንገተኛ እና ያልታሰበ ከነበረው ከዛ አደጋ ከወራት  ህክምና በኃላ ዳነች…መላኩም ወንድሙንና  እና የበፊት ሚስቱን በግድያ ሙከራ እና በእምነት ማጉደል ከሶ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ በማድረግ  ወህኒ እንዲወረወር አድርጎ ንብረቱን መልሶ ተቆጣጥሯል….አዎ እዚህ ድረስ ያሉ ነገሮች ጥሩና መልካም የሚመስሉ ነገሮች ነበሩ…እንግዲህ ይህ  ድርጊት የተከወነው ከአምስት አመት በፊት ነበር…

በመላኩ ወንድም በሰለሞን  ሽጉጥ ተተኩሶባት ፍቅረኛዋን ቀድማ በተመታችበት ወቅት ከተተኮሱባት ሁለት ሽጉጦች መካከል አንዱ ሽጉጥ በደረቷ ሌላው ደግሞ በጭነቅላቷ ነበር የገባባት…እና በወቅቱ በደረቷ የገባቸውን የጥይት ቀላሀ በቀላሉ ማውጣት ቢቻልም የጭንቅላቷን ማውጣት ግን በጣም አስቸጋሪ ሆኖ ነበር…፡፡
አስቸጋሪነቱ ጭንቅላቷን ቀዶ ጥይቷን  መዞ ማውጣቱ አይደለም….የከበደው ጥይቷ የተቀረቀረችበት ቦታ እንጂ… ጥይቷ ከወጣች የሰሚራ የጤና ሁኔታ በቋሚነት እንደሚበላሽ ….ትውስታዋ ሙሉ በሙሉ ሊጠፋ ከዛም አልፎ የማሰብ አቅሞንም እንደሚጎዳው ከፍተኛ ስጋት ስለጣለባቸው….ለጊዜው  ባለበት እንዲቆይ… በየጊዜው የቅርብ የህክምና ክትትል እንድታደርግና በሂደት የሚሆነውን ለማድረግ ተወሰኖ ነበር..
ለአንድ አመት  በየወሩ እየተማመላለሰች ህክምናዋ በመከታል በጥንቃቄ  ካሳለፈች በኃላ ምንም የሚሰማት እና የሚለወጥ ነገር ስላልነበረ ቀስ በቀስ እየተዘናጋችና ምንም አይፈጠረም በሚል እምነት ክትትሉን አቆመች ….
በዛን የጊዜ ክፍተት ውስጥ…መላኩ በንግዱ አለም ከበፊቱ የበለጠ ተሳክቶለት ከሰሚራ ጋር ያየነበረው የፍቅር ትስስር ይበልጥ እየጎመራ ሄዶ ወደጋብቻ ሊሸጋገር ወራቶች ሲቀሩት….ግን ከሁለት አመት ቆይታ በኃላ ድንገት ወድቃ  ሀኪም  ቤት ዳግመኛ ለመግባት ተገደደች…  ምርመራ ባደረገችበት ጊዜ በጭንቅላቷ መሀከላዊ ስፍራ የተቀረቀረችው ጥይት ብቻ ሳትሆን በፊት ያልነበረ ጎን ላይ  አስደንጋጭ እጢ ተፈጥሮ  ታየ..ሀኪሞቹ ተደናገጡ ..ተስፋ እንደሌላት እና ማድረግ የሚችሉት ብዙም ነገር እንደሌለ ለመላኩ ሲነግሩት አንጠልጥሎ ወደውጭ ሀገር ይዞት ሄደ….ግን የረፈደ ውሳኔ ነበር…ጥይቷ እንዲወጣላት ማድረግ ተቻለ ..እጢውም በጨረር ህክምና እንዲሞሞ ማድረግ ብዙም ከባድ አልነበረም…ይ ሁሉ ቢሆን ግን በህይወት ልትቆይ የምትችለው በዛ ቢባል ለቀጣዩ አንድ ወይም ሁለት አመት እንደሆነ አስምረው ነገረዋቸዋል…ከዛ በኃላ ወይ ትሞታለች ወይ ደግሞ በድን ሆና በህይወት እና በሞት መካከል ተንጠልጥላ ለአመታት ትኖራለች…..ሚሻለው ግን ወዲያው ብትሞት ነው…. የሀኪሞቹ ምክር ነበር፡፡ …የምርመራው ወጤቱ ለሁለቱም  ሰቅጣጭ ነበር…

እንግዲህ እነዚህ ፍቅረኛሞች …ሳቃቸው ከእንባ የተቀላቀለ፤ደስታቸው ከፍራቻ የተጋባ፤ተስፋቸው ጨለማ የገደበው ከሆነ እና በዚህ ሰቀቀን ውስጥ መኖር ከጀመሩ አመት አልፏቸዋል እና ንስሯ ባመጣላት ታሪክ መሰረት በቀደም የዋና ገንዳ ውስጥ ያገኘችው ፤የፈተነችው እና የፎከረችበት ወጣት ታሪክ እንደዚህ ነው…ታማኝ የሚሆነውም ለዚህች ፍቅረኛው ነው…..አግቢኝ እና ውለጂልኝም የሚላት ይችኑ በጀርመናዊዎቹና በአሜሪካኖቹ ሀኪሞች የ አመት ጊዜ ብቻ የተቆረጠላትን ወጣት  ነው….
ኬድሮን አሰበች‹‹እና ምን ላድርግ ….?እንዳለች ልተዋት….? ትውለድለትና ትሙት…. ከዛ እኔ ለእሱ ሚስት ለልጁ ደግሞ እናት ልሁን…..?ነው ወይስ ላድናት……..?›ከህሊናዋ ጋር ከባድ ፈተና ገባች፡፡በእርግጠኝነት   ንስሯ ከረዳት ለእሷ መዳኛ የሚሆን መድሀኒት ሌላ የአለም ጥግ ማሰስ ሳያስፈልጋት …ከዚህችው ከቅድስቲቷ የኢትዬጵያ ምድር  ቆፍር ቆፈር አድርጋ  ስር ማስ ማስ ፤ ቅጠል በጠስ በጠስ በማድረግ  ልታድናት ትችላለች..፡፡ግን  ለምን ታደርገዋለች…..?ለማንኛወም ጊዜ ወስዳ ልታሰብበት ከራሷ ጋር ተስማማች….

ይቀጥላል….
👍12821👎4😁2🔥1👏1
አትሮኖስ pinned «#ታምራተ_ኬድሮን ፡ ፡ #ክፍል_አርባ_ሶስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ //// ሁለቱ ፍቅረኛሞች ከአካባቢው ተነስተው የተንቀሳቀሱት ከምሽቱ 2 ሰዓት አካባቢ ነበር…እያመሩ ያሉት ወደመኝታ ቤት ነበር..ልብስ ቀይረው ራት ለመብላት እና ምሽቱን ዘና ብለው ለማሳለፍ ወደ ሬስቶራንት ለመሄድ..ግን  መንገድ ላይ ያላሰቡት ሰው በዛፎችና በጭለማ የተሸፈነውን  ጠባብ  የእግር መንገድ ዘግቶ ሽጉጥ ደቅኖ ጠበቃቸው……»
🍓🍃በ'ነሱ ቤት🍃🍓
🍃ክፍል አስራ ስምንት🍃
🍓🍓🍓🍓🍓🍓🍓🍓
አብላካት ሰፈሯ እስክትደርስ ምንም መናገር አልቻለችም ።አስተናጋጁ ሰሚር ብቻውን እያወራ መሆኑን ልብ ብሏል ነገር ግን ወሬውን አላቋረጠም ።ድንገት ግን በወሬው መሃል "ሰመረ ግን ብዙ ጊዜ ከኪሱ ገንዘብ አውጥቶ ሲከፍል አይቼው አላውቅም ሁሌም የሦስቱንም ሒሳብ የሚዘጋው ጌታነህ ነው ።ምን አልባት የሰመረ እጅ የተፈታው ላንቺ ብቻ ሳይሆን አይቀርም ሃሃሃሃ ሂሂሂ "ብሎ ሲስቅ ።አብላካት የዚን ጊዜ ጆሮዋን ቀስራ ለመስማት ጓጓች ለምንደው ባታውቅም የሰመረን ስም ስለጠራ ደስ አላት "ትቀልዳለህ እና ሰመረ የተጠቀመበትን አይከፍልም ለማለት ነው ?"አለችው ቆም ብላ ።
"ሃሃሃሃ እሺ የሰመረ ስም ሲነሳ ቤትሽ መድረስሽንም እረስተሽ ቆምሽ "አላት እየታዘባት አብላካት እጁን ቆነጠጠችው እና"ስነስርሃት ቤሌላ አቅጣጫ አትውሰደኝ ።እኔ የአንተ አነጋገር ገርሞኝ ነው ሰመረ እንደምታየው በዚ ዕድሜው ራቫ ፎር መኪና የሚነዳ ሀብታም ነው ያንተን የስምንት መቶብር ምሳ በልቶ ለመክፈል የሚቸገር ይመስልሃል? አይመስለኝም ምን አልባት ጌታነህ እንደነገረኝ ከሆነ ሌላቦታም ያመሻሉ ማለት ክለብ ምናምን እና እዛ ያለው ወጪ ደሞ የሰመረ ይሆናል እኔ እንደዛ ነው የማስበው "አለችው ።አስተናጋጁ ሰሚር ሳቀ ትክክል ነሽ በሚልም ጭንቅላቱን ነቀነቀ ። የአብላካት የሰፈር ጎረምሶች ሲያልፉ እንደማፋጨት እያሉ ዞረው አይዋቸው ። አብላካት ፈገግ አለች አሳባቸው ስለገባት አስተናጋጁ ሰሚር ሁኔታቸው ደስ ስላላለው እጇን ይዞ በርሽ ላይ ነው የማደርስሽ አላት ።
"ምነው ፈራሃቸው እንዴ? ውይ ተዋቸው ባክህ ለምጃቸዋለው ደሞ ያን ያክል አልፈው የሚሄዱም አይደሉም ሰፈር ቁጭብለው እየጦዙ በምኞት የሚኖሩ ናቸው ።ከሴት ይልቅ ሱሳቸውን አብለጠው የሚወዱ ናቸው "አለችው
"ቢሆንም ለእናትሽ አስረክቤሽ ነው የምሄደው ዛሬ "አላት
"ኧረ  ሌላ ቀንስ?አጉል ልምድ አታስለምደኝ ይልቁንስ "አለችው
"ችግር የለም ታናሽ እህቴ ሁሌም ከጎንሽ ነኝ "አላት
"አመሰግናለው ሰሚ "አለችው
"በይ ተንቀሳቀሽ "ብሎ እየጎተተ በሯላይ አደረሳት
"በል እዚ ከደረስክ ግባና እናቴንም ሰላም በላት ቡና አፈላለው መክሰስ በልተ ጠጥተህ ትሄዳለህ "አለችው
"አይ አመሰግናለው "ብሎ ተከራከራት
"አይ እንግዲ አታስቸግር ፣በሀላ ይዤሃለው ና"ብላ ስትጎትተው።ከወደውስጥ በሩ ተከፍቶ የአብላካት እናት መሳይ ብቅ አለች ።እና ሁለቱንም ሰላም ካለችበዋላ"ሰሚሬ ምነው አልገባም ብለሃት ነው ?"አለችው ፈገግ ብላ
"አዎ መሳይ የሆነ የምደርስበት ጉዳይ ስላለ ነው "አላት
"አይ ትደርሳለህ ና ግባ ተጫውተህ ትሄዳለህ በርደርሰህማ አትመለስም "ብላ ወደውስጥ እንዲገባ አስገደደችው። ሰሚርን እንደ ታናሽ ወንድም ትወደዋለች ልጇን ልክ እንደሷ ሲጠብቅላት ሲንከባከባት ልክ እንደ ቤተሰብ ነው ።
"እሰይ ቁጭ የምን መሽከርከር ነው ኪኪኪኪኪ"ብላ ሳቀችቀት አብላካት ሰሚር ገብቶ ሲቀመጥ ።የአብላካት እናት እስቶቭ ለኩሳ ወጥ ማሞቅ ጀመረች አብላካት ወደውስጥ ከለል ብላ ልብሷን ቀያይራ ማንደጃ ይዛ ወጣች ከጎረቤት ቡና የምታፈላበት እሳት ለማምጣት ,,,,,,,,,,,,
👁ሰመረ ጓደኞቹን አግኝቶ አንድ ትልቅ ሆቴል ራት እየበሉ ነው ። ሰመረ ከወትሮው በተለየ ምንም ሳያወራ ጎረስ ጎረስ ሲያደርግ በመገረም ቀና እያሉ ያዩትና እየተያዩ ፈገግ ይሉበታል ። እሱ አሳቡ እዛ አልነበረም ።አብላካትና አስተናጋጁ ሰሚር ላይ ነው ።አብላካት ከሚገባው በላይ ቆንጆ ሆና ተለውጣለች በዛላይ በአመት ውስጥ ትልቅ ሆናለች ።ማንንም አሰሮ የሚያስቀር ውበት ነው ያላት ።እና ደሞ አስተናጋጁ ለምንድነው እንደዚ የቀረባት ችግር ውስጥ ሊጨምራት ይሆን ተለሳልሶ ገብቶ ። ግን እንደዛአይነት ልጅ አይመስልም ይላል መልሶ ።ሰመረ ስለዚች ልጅ ጭንቅላቱ ዳግም ይወጠርበት ጀመር ።
"ሰሙ ዛሬ አልተቻልክም ቀኑን ሙሉ አልበላህም እንዴ"ብሎ ጠየቀው ጌታነህ እያሾፈ
"ውይ በላውብህ እንዴ "አለው ሰመረም እያሾፈ
"አይ የሆነ የሚያስበላ ነገርማ ገጥሞታል "አለ እንየው እየሳቀ
"ምን የሚያስበላ ነገር አለ ደሞ "አለው ጌታነ
"ለምሳሌ ማፊ ቢሮህ ድረስ መጥታ አጫውታህ ከሆነስ እሱ እራሱ እኮ ያስበላል ሉዝ ታደርግ የለ ኪኪኪኪ ማፊ እንደው ቦታ አትመርጥም ተጫዋች ናት "ብሎ ሳቀ። ሰመረ መልስ ከመስጠት ይልቅ ገላምጦት ወደምግቡ ተመለሰ
"እኔኮአላምንም  ማፊ ስራ ቦታ እየመጣች ታጫውትሃለች እንዴ ዋውው የቢሮው ጠረቤዛ ላይ ታየኝ እኮ ኡኡኡኡ ስንት ላፕ ቶፕ ድንገት እንደሚሰበር ከፍ አድርገህ እዛላይ እእእእ ኪኪኪኪኪኪ"ብሎ ረጅም ሳቅ ሳቀ ጌታነህ
"ኧረ ለሰው ክብር ይኑርህ ትላልቅ ሰዎች አሉ ድምፅህን ቀንስ "አለው ሰመረ በሆቴሉ የነበሩ ተስተናጋጆች ወደነሱ ዞር ዞር እያሉ ሲያዩ ጨንቆት
"ተወው አበሻን ወግ ልማድ ሲያጠብቅ ነው ግንባሩ በጊዜ የሚቋጠረው ፈታ በል ከፈለጉ ይውጡ አዘግቼ እጋብዛችዋለው "አለ ደረቱን እየነፋ ።ሰመረ ዝምብሎ ሲያየው ቆይቶ ጭንቅላቱን ነቀነቀበት ።አይምሮው መልሶ ወደ አብላካት ሄደበት ስለሷ አለማሰብ አልቻለም ። ጌታነህ እሱን ማብሸቁን ተወት አድርጎ ስልኩን በማውጣት ደወለ ። እናም
"ሃሉ አቢዬ እና ምን አልሺኝ በቃ አልመጣም ነው በናትሽ እንዴ እኔ እኮእንዲ እረጅም ጊዜ ሰው ለምኜ አላውቅም የኔ ቆንጆ አላሳዝንሽም እሺ ሰፈር ልምጣና አቅጣጫውን ነገረሺኝ ይዤሽ ልውጣ ደሞ ሳይመሽ ነው የምመልስሽ የኔ ውድ እሺ በይኛ "እያለ በስልኩ ሲለማመጥ ። ሰመረ ልቡ ፍስስ አለበት በጭራሽ አብላካትን ጌታነህ መንካት የለበትም ብሎ ወሰነ ,,,,,,,,,,,,,,


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍1108🔥3🤔1
#ታምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አርባ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


////
እየሄደች ነው… ልታናግረው…፡፡ ለምን እሱን ማናገር እንደፈለገች አታውቅም፡፡ ምን አልባት ዳግመኛ አጠገቡ ልትቆምና ያንን ወንዳወንድ ቁመናው እና ቆንጅዬ ባሪያ የሆነ መልኩን በቅርበት ለማየት ፈልጋ ሊሆን ይችላል….ናፍቋትም ሊሆን ይችላል፡፡ 

ንስሯ የት እዳለ በነገራት መሰረት ቀጥታ ቤቱ ነው የሄደችው..የውጩን የጊቢ በር መጥሪያ ስትጫን ዘበኛው ነበር የከፈተላት…‹‹ከመላኩ ጋ ቀጠሮ ነበረኝ ቤት እየጠበኩሽ ነው ብሎ ደውሎልኝ ነበር..?››ብላ ቀላመደች… ዘበኛው ያልተለመደ ነገር ሆኖበት .. ግራ እንደመጋባት አለና በመጠኑ ካቅማማ በኃላ እንድትገባ  ፈቀደላት…
ቀጥታ ቤተኛ እንደሆነ ሰው የተንጣለለውን ግቢ ሰንጥቃ ባለአንድ ፎቅ ከሆነው ዘመናዊ መኖሪያ ቤት  በረንዳው ላይ ደረሰች… የሳሎኑን በር ገፋ ስታደርገው ተከፈተ…የቀኝ እግሯን አስቀድማ ግራዋን አስከትላ ወደውስጥ ከገባች በኃላ  ወደኃላ ዞሯ በራፉን አንኳኳችው…
‹ከገቡ በኃላ ማንኳኳት ከገደሉ በኃላ ማዘን አይነት አይደለም እንዴ…..?››እራሷው በራሷ ነው የጠየቀችው
መላኩ የሳሎኑ መአከላዊ ስፍራ ላይ  ካለችበት ወደውስጥ 4 ወይም 5 ሜትር ያህል ርቆ በመገረም አፍጥጦ እያያት ነበር….
ማንኳኳቷን ስትቀጥል

‹‹አቤት››የሚል ድምጽ አሰማ

‹‹መግባት ይቻላል..?››

‹‹ገብተሻል እኮ ››

‹‹እሺ ካልክ›› ብላ ቀጥታ የሳሎኑን በር መልሳ ዘግታ ወደእሱ አቅጣጫ አመራች ….በተገተረበት ስለማንነቷ በመመራመር ይመስለል ፈዞ እንደቆመ በስሩ አልፋ ልክ እንደቤተኛ ሶፋው ላይ ዘና ብላ ተቀመጠች….መጣና ከፊት ለፊቷ ተቀመጠ

‹‹አውቅሻለሁ ልበል..?››

‹‹እኔን የመሰለች ቆንጆ ልጅ እንዴት ልትረሳ ትችላለህ..?››

‹‹ማለት..?››

‹‹ጎበዝ የዋና ተማሪህ ነበርኩ ብዬ ነዋ››

…ድንገት እንደበራለት ሰው በመደነቅ ‹‹እንዴ አንቺ እብድ ..እቤቴን ደግሞ ማን አሳየሽ..?›› አለት ‹‹ቀላል ሰው  አይደለሁም ብዬህ ነበርኮ..?››

‹‹አረባክሽ.. ፉከራሽን እኮ አየነው..እኔማ አንተን ማሳሳት ካቀተኝ እንጠለጠላለው ብለሽ ስለነበረ..በቃ ይቺ ልጅ አልሆንላት ሲል እራሷን አጥፍትለች ማለት ነው..ምን አይነት ለቃሏ ታማኝ ልጅ ነች ብዬ ሳደንቅሽ ነበር የሰነበትኩት፤ለካ ዝም ብለሽ ጉረኛ ነገር ነሽ..?››

‹‹አንተን ማውጣት አቅቶኝ ሳይሆን አሳዝነኸኝ ነው የተውኩህ ››

ግድግዳውን ሰንጥቆ በመውጣት ውጭ ድረስ ለመሰማት ኃይል ባለው አይነት አንቧራቂ ሳቅ ሳቀ‹‹አሳዘንኩሽ…..?ቀልደኛ ነሽ››

‹‹ቀልድ አይደለም…የዛን ቀን የሄደክው ከፍቅረኛህ ጋር ወደሆቴል አልነበር…..?ስለ ጋብቻ ስታወሩ አልነበር....?እንድታገባህ ስትለምናት አልነበር…..?እሷ መጋባቱ ቀርቶባችሁ እስክትሞት ድረስ የቀራትን ህይወት እንደዚሁ እንድታሳልፉ ስትለምንህ አልነበር…..?ከመሞቷ በፊት ካላገባችህ እና መጽናኝ የሚሆን ልጅም ካልወለደችልህ በሞተች ቀን አብረሀት እንደምትሞት እየነገርካት ስትላቀሱ አልነበር……..?››

ይሄንን ስትነግረው እነዛ የኮከብ ክፋይ የሚመስሉ  ደማቅ አይኖቹን ከወዲህ ወዲያ በመገረም እያሽከረከራቸው ነበር…..

‹‹አንቺ ክፍል ውስጥ ተደብቀሽ ስታዳምጪኝ ነበር እንዴ..?››በንዴት ጡንቻው ውጥርጥር ሲልና … ልነቃት አልነቃት እያለ ከውስጡ ጋር ሙግት እንደገተመ ከሁኔታው ያስታውቃል….

‹‹አይደለም …ክፍል ውስጥ አልነበርኩም…ግን በአካል ባይሆንም ክፍል ውስጥ ገብቼ  እናንተን ምታዘብበት ሌላ ዘዴ ነበረኝ››

‹‹ምን ..?ካሜራ ..?››
‹‹አይደለም…ምንነቱን ቀስ ብዬ ነግርሀለሁ…አሁን ወደመጣሁበት ጉዳይ እንግባ››

‹‹ወደመጣሁበት ጉዳይ .. ..?በይ ሳትዋረጄ በመጣሽበት እግርሽ ሹልክ ብለሽ ቤቴን ለቀሽ ውጪ..››ከመቀመጨው ቀድሞ ተነሳ…

‹‹ሁለተኛ እንኳን እቤቴ እኔ ባለሁበት አካባቢ  በድንገት ባገኝሽ እወነቴን ነው አጠፋሻለሁ…ሲጥ አድርጌ ነው የምገልሽ….››

ዘና ብላ እንደተቀመጠች መልስ መመለሷን ቀጠለች  ‹‹ዝም ብለህ አትፎክር…በቁጣ እያንቧረቁ መናገር እና ፊትን ማጨማደድ የምትለውን አይነት ጭካኔ እንዲኖርህ አያግዝህም››

‹‹ምን ማለት ነው..?››

‹‹እንኳን እኔን ምንህም  ላይ ያልደረስኩትን ልጅ ይቅርና ሰላምን እንኳን እንደዛ በድላህ ፍቅህን ረግጣ የገዛ ወንድምህን በማግባት ስታወድምህ   ለህግ አሳልፎ ከመስጠት ውጭ ምንም ልታደርጋት  አቅም አላገኘህም፡፡››
ተንደርድሮ ወደእሷ ቀረበና  ተንበርክኮ አንገቷን በማነቅ እያረገፈገፋ‹‹ማነሽ …....?አንቺን ማነው የላከብኝ....?ማነው ንገሪኝ..?››

‹‹ማንም …ምን አልባት የምታመልከው አምላክ ሊታረቅህ ፈልጎ ይሆናል…ምን አልባት እስዛሬ የፀለይከው ፀሎት አምላክ መንበር ደርሶ መልስ የማግኛህ ጊዜ ደርሶም ሊሆን ይችላል…››
፣እጁን ከአንገቷ ላይ መንጭቃ በማላቀቅ ገፈተረችውና …ዝርፍጥ ብሎ ወለሉ ላይ በቂጡ ቁጭ አለ …እዛው ባለበት አፍጦ እሷን ከማየት በስተቀር ለመነሳት አልሞከረም

‹‹ሰሚራን ባድንልህ ምን  ታደርግልኛለህ..?››

‹‹ምን  እየቀባጠርሽ ነው…...?ደግሞ በእሷ ልትቀልጂብኝ ነው..?››

‹‹አይደለም ..ካዳንኩልህ ምን ታደርግልኝለህ..?››

‹‹ቅጠል አሽተሸ በመቀባት የምታድኚው ቁስል… ምች መድሀኒት ወይንም ጅንጅብል ጨቅጭቀሽ ከሻይ ጋር አፍልቶ በመጋት  የምታድኚው  ጉንፋን በሽታ  ያመማት መሰለሽ  እንዴ..?››
‹‹አውቃለሁ…ለአመታት በጭንቅላቷ ቆይቶ የነበረው ጥይት እና የጭንቅላት እጢ ተከትሎ…….››
አላስጨረሳትም ‹‹…በፈጠረሽ ማን ነሽ ?ምንድነው ምትፈልጊው....?ይሄን ሁሉ ገበናችኝን ስንት አመት ብትሰልይን ነው ማወቅ የቻልሺው..?››

ጥያቄውን ችላ በማለት  የራሷን ጥያቄ ደግማ ጠየቀችው

‹‹ካዳንኩልህ ምን ታርግልኛለህ..?››

‹‹ እኮ እንዴት ነው የምታዲኚያት…..?የጀርመንና አሜሪካ ጠበብቶች ያቃታቸውን አንቺ እንዴት ብለሽ..?››

‹‹እኔ የተለየ መንፈሳዊ ስጦታ አለኝ …››

‹‹አላምንሽም››

‹‹እንድታምነኝ…አንድ አንተ ብቻ የምታውቀው ታሪክ ልንገርህ…እንደውም ለምን ዛሬ ያየኸውን ህልም አልነግረህም ..…››

ንገሪኝም ተይው ማለት አቅቶት በግራ መጋባት ስሜት እየዋለለ ዝም ብሎ እንዳፈጠጠባት ፈዞ ቀረ…

ጣና ሀይቅ መሀል ላይ ያለች ትንሽ ደሴት ትመስልሀለች….እሷን ከብዙ የሀገሪቷ ሀብታሞች ጋር ተወዳደረህ በጫረታ በማሸነፍ ትገዛና …በጣም ውብ የሆነ በባህላዊ መንገድ እጽብ ድንቅ ተደርጎ የታነፀ ቤት ትሰራበታለህ…በዛች ደሴት ላይ አንተ ከሰራሀት ቤት ውጭ ምንም አይነት ሌላ ቤት የለም፤ደሴቱ ሙሉውን በቡና ተክል፣በሙዝ፣በብርቱካን፣በመንደሪን፣በአፕል እና  በመሰሰሉት የሚበሉ ፍራፍሬዋች የተሞላች ነች…አዕዋፍት እና የዱር እንስሳትም  ከደኑ ጋር ስመም ፈጥረው ተፈጥሮን አድምቀው እና በተፈጥሮም ደምቅው የሚኖርበት ቦታ በመሆኑ ልዩ ድስታ ተሰምቶህ ይሄንን ስጦታ ላዘጋጀህላት ለሰሚራ ትሰጣታለህ…

‹‹ሰሚርዬ ቀሪ ህይወትሽን ምንም እንኳን አጭር ብትሆንም በደስታ የተሞላች እድትሆን ፈልጋለሁ…በዛ ላይ እዚህ ከእኔ እና ከተፈጥሮ ውጭ ምንም አይነት የሰው ልጅ ወደ ሌለበትና ወደማይኖርበት ቦታ ሳመጣሽ ቀሪ ዘመንሽን የብቻዬ ብቻ እንድትሆኚ በመፈለግ እና በመሰሰት ነው…ይቺ ስፍራ የእኔ እና የአንቺ ገነት ነች››ትላታለህ፡
👍767😁3🥰2
እሷም በመፍለቅለቅ እና ስጦታህን ከልቧ በደስታ  በመቀበል‹‹የእኔ ውድ….እዚህ ሰፍራ ከንተ ጋር አንድ ሳምንት እንኳን መኖር ዘላለም የመኖር ያህል ጣዕም ይሰጠኛል.. አፈቅርሀለው››ትልሀለች
‹‹ካፈቀርኝማ አግቢኝ››ትላታለህ
‹‹እንዲህ አድረገህልኝማ እንዴት እንቢ ልልህ እችላለሁ…..?ዛሬውኑ አገባሀለሀ…እዚህም ደሴት ላይ ምታምር ልጅ  ወልድልሀለሁ… ስሟንም ዘሀራ ትላታለህ  ..ትርጉሙም አበባ ማለት ነው››ትልህና ያልጠበቅከውን የምስራች ነግራህ ታስፈነድቅሀለች፡፡አንተም በሰማሀው ነገር   ሰክረህ ጮኸህ ስትጠመጠምባት‹‹..አረ አነቅከኝ …ምነካህ  …››ብላ ከጎንህ የተኛችው የእውነቷ አለም ሰሚራ ቀስቅሳ ነው ከእንቅልፍህም ከህልምህም ያፋታችህ…
ከተዘረፈጠበት ወለል..ዝልፍልፍ እንዳለ እየተጎተተ ተነሳና ሶፋው ላይ ተቀመጠ..ድክምክ ባለ እና እጅ የሰጠ በሚመስል  የተሸነፈ ድምጽ‹‹ይህንን እኮ ለሰሚራዬ እንኳን እ
አልነገርኳትም… ለብቻዬ አልሜ በውስጤ ብቻ ቀብሬ አስቀርቼው የነበረ  ፍቺውን በማብሰልሰል ላይ የነበርኩት  ጣፍጭ ህልሜ ነበር….እንዴት ልታውቂ ቻልሽ?››

‹‹ዋናው ማወቄ ነው…..አሁን እንዳድንልህ ትፈልጋለህ..?››

‹‹በጣም…አትቺይም እንጂ ከቻልሽ በጣም እድታድኚልኝ እፈልጋለሁ….››

‹‹ካዳንኩልህ ምን ታደርግልኛለህ…..?››መልሳ ወደ መነሻ ጥያቄዋ 

‹‹ህይወቴንም ከፈለግሽ..አንገቴን ቀንጥሼ ለመስዋዕትነት በሰሐን እንዲቀርብልሽ አደርጋለሁ  ››

‹‹ጥሩ ስጦታ ነው…..ግን አንገትህን አልፈልግም››

‹‹እሺ ሙሉ ንብረቴን ምንም ቤሳ ቤስቲ ሳትቀር ሰጥሻላሁ››

‹‹እሱንም አልፈልግም….እኔ በንብረት የምደሰት አይነት ሰው አይደለሁም››

‹‹እሺ ምን ትፈልጊያለሽ..?››

‹‹ሰሚራን  ከዳነች በኃላ ትተዋታለህ..ትተዋት እና እኔን ታገባለህ››

‹‹ዝም አለ…በቃ ዝም …..በድን የሆነ የሚጮህ ዝምታ….ድምፅ ያለው ዝምታ…..››

‹‹እ ምን አልከኝ..?››አለችው ዝምታው በውስጧ የፈጠረውን  ስቃይ መቋቋም ሲያቅታት ልትረብሸው ፈልጋ…

ይቀጥላል

#አደራ በዛውም YouTube ቻናሌን subscribe እያደረጋቹ አያስከፍልም👇
https://www.youtube.com/@atronose

#ቻናሉም ይቀላቀሉ ለሌላም ያጋሩ👇
https://xn--r1a.website/atronosee
👍8312👏6😢6👎5🥰1
👁🍃በ'ነሱ ቤት🍃👁
🍃ክፍል አስራ ዘጠኝ🍃
🍃🍃🍃
ሰመረ የጌታነህ ልምምጥ ገርሞታል እውነት አብ ላካትን ወዷት ነው ለማለት በፍፁም አልቻለም ምክንያቱም አብላካትን የመጀመሪያ ጊዜ ተቸግራ ያገኟት ጊዜ ያን ያክል ለጌታነህ ልዩ የምትሆን ሴት ሆና አልነበረም ። ይልቁንም ጌታነህ በአለባበስም ሆነ በኮንፊደንስ የሚንቀቸው የሚጠየፋቸው አይነት ሰው አይነት ነበረች ።የአብላካት ብቸኛ እና የሚያስመካ ነገር አላት ከተባለ ቁንጅናዋ ነበር እናም ልጅነቷ ። ታዲያ ጌታነህ እስካሁን ድረስ አብላካትን የሚጨቃጨቃት ለምንድነው ? ከዛንቀን በዋላ አይቷት አያውቅም በስልክ ሊያማልላት ቢሞክርም አልተሳካለትም ።እና ለምን አይተዋትም  ነው ከ'ኔ ጋር እልህ እየተጋባ ነው ? ' ብሎ አሰበ ሰመረ የጌታነህ ጓደኝነት ሲበላሽበት ታየው ።
    "ሰሙ ታውቃለህ እቺ ትንሽ ልጅ በጣም አስቸጋሪ ነች ኪኪኪኪ ነገር ግን በስልክ ስለሆነ ነው እንጂ በአካል ያገኘዋት ለት የአስር ደቂቃ ስራ ነች ኪኪኪ "ብሎ ሳቅም ቀልድም አስከተለ
"አልጠየኩህም !ስለዚ ምንም ነገር ለኔ ለማስረዳት አይጠበቅብህም  "አለው ሰመረ በውሃ የተሞላውን ብርጭቆ አንስቶ ለመጠጣት እየተዘጋጀ
"ኪኪኪኪ አታስመስል ያቺ ልጅ እንድትነካብህ አትፈልግም ያልገባኝ እሷ ላይ ያለህ ፍላጎት ነው"አለው እንየውም እንዲያግዘው እየነካካው
"እኔ በአንዲት ትንሽ ልጅ ላይ ምን ፍላጎት ይኖረኛል አንተን አደረከኝ "አለው። ውስጡ ደሞ ሌላ ወሬ አወራው እውነት አብላካት ቅድም እንዳየዋት ትንሽ ልጅነት ይታይባታል ።በጭራሽ ቀልቤን ገፋው አይደልእንዴ ።በአስተናጋጁ ሰሚርስ አልቀናውም ነበር ።ብሎ አስቦ መልሶ በራሱ እንደማፈር አለ ።ወይጉድ ማፊ 'ወንድ ልጅ 'ጅብ ነው  ያገኘውን ነው የሚበላው 'ያለችው ትዝ አለው ።
"ተወው እኔን አያድርግህ ኪኪኪኪ እኔን ለመሆን ዳግም መፈጠር አለብህ እኔ ለሴቶቹ መዳኒት ነኝ ኪኪኪ ፈዋሽነቴን መደበቅ አይሆንልኝም ለሁሉም አለውላቸው ለሚያቁኝም ለማያቁኝም ።አቢ ደሞ የማታውቀው ዓለም አለ እሱን የማሳየት የኔ አላፊነት ነው ።ታያለ በዚ እሷ በጭራሽ አትከፋም የሚያስፈልጋት ገንዘብ ነው እንዳየውት ከሆነ ።እና እሷ እንትን ትሰጠኛለች እኔ ገንዘብ እሰጣታለው አለቀ ኪኪኪኪኪ"ብሎ አሽካካ ።እንየው አብሮ አሞቀ
"አይ አንተ የተመታህ እኮ ነህ ! ችኮቹ አሳዘኑኝ ኪኪኪኪ"ብሎ እንየውም ሳቀ። ሰመረ ወሬው አልተመቸውም ከጌታነህ ጋር መነጋገር የባስ መቃጠል ሆኖበታል ።አብላካትን ካገኙ ጀምሮ ጓደኝነታቸው ብሽሽቅ የሞላበት ሆኗል ።
ምሽታቸው ብዙም ውበት አልነበረውም ።ጌታነህ ሲያሽካካ እንየው ሲያሽቃብጥ ።ሰመረ ሲቆስል ነበር ያሳለፉት ። በመጨረሻ ሰመረ እንደተለመደው ተሰናብቷቸው ከሆቴሉ ሲወጣ ቅሬታቸው ጨመረ ።ከአስተሳሰባቸውና ከአመለካከታቸው ጋር ባለመሄዱ ሰመረን ማማት ጀመሩ ። ማነኝ ብሎ ነው፣ እሱኮ እንዲ ነው ፣እንዲያነው ፣እንትንም ብዙ አይደለም ፣ ማፊ እየተጫወተችበት ነው፣ አልቻላትም ፣ስራላይም ብዙ አይደለም የቤተሰቡ ሀብት ባይኖር ኖሮ ባዶ ጭንቅላት እኮ ነው፣ ምናምን ምናምን .....እያሉ ሰመረን ማማታቸውን ቀጠሉ .......
👁አብላካት ሰመረን ማሰቧን አላቆመችም ።ዳግም ካየችው ጀምሮ ከአይምሮዋ ሊወጣላት አልቻለም ።ስራም ላይ ሆና ስትተኛም ሰመረን አለማሰብ አልቻለችም ቁመናው እርጋታው ድንገት ቱግ የሚለው ነገር ይመላለስባታል ። በራሷ ተገርማለች በቀን በቀን ባገኘው ምን ልሆን ነው ትላለች ለራሷ ። የሰመረን ስልክ አለመጠየቋም ይቆጫታል ።ደሞ እሱ ስልኳን አለመጠየቁም ትዝ ይላትና ።ምናልባት ንቆኝ ከሆነስ ብላ እዝን ትላለች ።ለነገሩ እኔ ማነኝና ነው ያንን የሀብታም ልጅ የምመኘው እሱ ከኔ በጣም የላቁ ሴቶችን እንደልብ ማግኘት ይችል የለ ። አጉል ምኞት ብላ ትተክዛለች ።
አስተናጋጁ ሰሚር የአብላካት ፀባይ እየተቀየረበት ሲመጣ ይታወቀዋል እንደበፊቱ በቀላሉ አትስቅለትም መተከዝ አብዝታለች ። በሆነ ባልሆነው ድንገት ትቆጣለች ።በዚ ሁኔታዋ ግር ቢሰኝም ።አንዳች ነገር እንዳለ ግን ጠርጥሯል ስለዚህም ።በተለያየ አጋጣሚ የሰመረን ስም እያነሳ እየፈተሻት ነው ።እውነትም የሰመረ ስም ከተነሳ ጆሮዋን አቅንታ ታዳምጠዋለች እናም ። ስለሷ ፈራላት ፍቅር ይዟት ከሆነ ምን ሊፈጠር ነው ......


ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍100🥰148👏3😁2🤔1😱1
#ታምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_አርባ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

////
‹‹ግን ምን አይነት ዳቢሎስ ነሽ..?››ሙትት ባለ ድምጽ

‹‹ዳቢሎስ እንኳን አይደለሁም…. ምን አልባት የዳቢሎስ ልጅ ልሆን እችላለሁ…ግን የምትወዳትን ልጅ ላድንልህ እኮ ነው እያልኩህ ያለሁት .. ..?እንደዚህ አይነት በጎ ተግባር  ዳቢሎስ ያሰኛል እንዴ..?››

‹‹አዎ ዳቢሎስ ፍቅር አያውቅም..ፍቅር የማያውቅ ደግሞ ምንም ነገር በነፃ መስጠት አይችልበትም፤ለሰጠሸ ጥሩ የሚመስል ነገር ሁሉ ተመጣጣኝ የሆነ መከራና ስቃይ ያስከፍሉሻል…››

‹‹አልገባኝም..?››

‹‹ለምሳሌ …ያለፋሽበትን ገንዘብ ተመኝተሸ ስጠኝ ብትይው በደስታ ነው የሚሰጥሽ፤የገንዘብን ባለቤት ግደይና ነጥቀሺው ውስጂ ብሎ መንገድን እና ብልሀቱን ያሳይሻል…ከዛ ትገድይና ገንዘብን ታገኚያለሽ ሀብታም እና በፀፀት የሚሰቃይ ሰው ትሆኚያለሽ፡፡አንቺም ፍቅረኛህን ላድንልህ..እና ልንጠቅህ እያልሺኝ ነው…፡፡ያው እኮ ነው በስጋ ከመሞት ታድኛታለሽ ከዛ ፍቅርን በመንጠቅ በመንፈስ ትገያታለሽ…እኔንም እንደዛው፤ታዲያ አንቺ ዳቢሎስ ካልሆንሽ ማን ይሆናል....?››አላት ምርር ባለ የመጠየፍ ንግግር፡

‹‹እሺ እንግዲያው ይቅርብህ…ሁለተኛ አረብሽህም፤ደህና ሁን››ብላ ከመቀመጫዋ ተነሳችና እንደ አመጣጧ ሳሎኑን ሰንጥቃ  በርፍን ከፍታ ወጣች እና መልሳ ዘግታ መንገዶን ቀጠለች…የግቢው አማካይ ስፍራ ስትደርስ   ነበር የበር መከፈት እና ‹‹ማን ነበር ስምሽ..?››የሚል  ከሙታን  መንፈስ የወጣ የሚመስል ድምጽ  ከጀርባዋ የተሰማው

እርምጃዋን ገታችና ቀኝ ኋላ ዞራ ‹‹ሶፊያ››ስትል መለሰችለት
‹‹ከቻልሽ አድርጊው..አድኚልኝ ፤ተስማም..ቼ…ያ….ለሁ››አላትና ከእሷ ምንም አይነት መልስ ሳይጠብቅ ፊቱን መልሶ ወደውስጥ በመግባት  በራፉን በመዝጋት ከእይታዋ ተሰወረ ..

‹‹እውነትም ዳቢሎስ ነገር ነኝ እንዴ..?….ምን እያረግኩ ነው…...?››ስትል አሰበች፡፡ቅድም እዚህ እሱ ጋር ስትመጣ ይሄንን ለማድረግ አልነበረም…ዝም ብላ ፍቅረኛው እደምታድንለት ልትነግረው እና በተስፋ ልታስፈነጥዘው ብቻ ነበር ፍላጎቷ…ያደረገችው ግን ተቃራኒውን ነው..በደስታ እና ሀዘን መካከል ነፍሱ ተንጠልጥላ እዲሰቃይ ፈረደችበት …

‹‹የእውነት ግን ያልኩትን አደርገዋለሁ…..?እሷን አድኜ እሱን ነጥቄያት አገባዋለሁ…..?.ማግባትስ በእውነት እኔ የምፈልገው ነገር ነው....?ወይስ በስቃዩ ለመደሰት…..?››ብላ ተደራራቢ ጥያቄ እራሷን ጠየቀች፡

ለማንኛውም ዛሬ ማታ ከንስሯ ጋር ለመብረር አቅዳለች….ለልጅቷ የሚሆን መድሀኒት የት እደሚገኝ ፍንጩን አግኝታለች ….ቦረና ባሌ መካከል መዳ ወላቡ አካባቢ ነው ለሰሚራ ፈውስ የሚሆነው መድሀኒት ሚገኘው….፡፡ 
የየትኛውም ሀገር አቨዬሽን  የማይቆጣጠረው በረራ ላይ ነች፡፡ግን ደህንነቱ ፍፅም የተረጋገጠ በረራ ….ከየትኛውም አይሮፕላን ጋር እጋጫለሁ ወይም አሞራና ወፎች ተላትመውብን አቅጣጫ ያስቀይሩናል…ነዳጅ አልቆ ወይም ሞተር ጠፍቶ ችግር ላይ እንወድቃለን  ብላ የማትሰጋበት ዥዋዝዌ የመጫወት ያህል ዘና የሚያደርግ በረራ…. ይሄን አይነት በረራ ሳታካሂድ ሶስት ወራት ስላለፋት ናፍቆት ነበር…
እየሄድ ያለው ከአዲስ አበባ ወደ መዳወላቡ ነው ፡፡መዳወላቡ የት እንደምትኝ መገመት ካቃታችሁ..ኬንያ ድንበር አካባቢ ብትሉት አካባውን ለመገመት ይቀላችኋል ፡፡እየበረሩን ያለነው ከንስሯ ጋር ነው…፡፡እሱ ክንፎች  መሀከል ዘና ብሎ ቁጭ ብላለች….
ከመሬት ያሉበትንን ከፍታ ገምታ ለመናገር አትችልም ..…ግን ትንሽ ግልፅ ለማድረግ  ምሳሌ ለመስጠት ያህል በዚህ ሰዓት ( ከምሽቱ ሶስት ሰዓት አካባቢ ነው) ሻሸመኔ ከተማ አካባቢ ደርሰዋል..እላይ ባሉበት ከፍታ ላይ ሆነው ከተማዋ ቁልቁል ስያዮት ከእሷ ቤት ጊቢ ብዙም ሰፍታ አይታያትም….ጭልጭል የሚሉ አንድ ቦታ የተሰበሰቡ መብራቶች ናቸው እንደምልክት የሚታዩት..
የሚፈልገበት ቦታ ላይ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ነው የደረሱት…ከአውሬ ድምጽ እና ከጥቅጥቅ ጨለማ በተጨማሪ ብዙ ድምጽ ይሰማል..የደረቁ ቅጠሎች በንፋስ ተገፍተው ከዛፍ ሲወድቁ ይሰማል…..ካረፍበት ተራራ ወገብ ላይ እየፈለቀ ቁልቁል ወደ ታች እየተምዘገዘገ የሚወርድው  አረፋ ደፋቂ ፏፏቴ ድምጽ በጣም ይሰማል…የብዙ አውሬዎች መጣራራት እና ማስካካተ ድምጽ ይሰማል…. ….

‹‹የቱ ነው መድሀኒቱ….?››ጠየቀችው ንስሯን 
አንድ ከእሷ ቁመት ብዙም የማትበልጥ ቋጥኝ ላይ ዘና ብሎ ቁጭ በማለት ዝም አለት
የሚያስበውን ማወቅ ስለፈለገች..‹‹አዕመሮህን ክፈትልኝ…..….?››ስትል ጠየቀችው… ቁልፍ አደረገና ችላ አለት ..አንዳንዴ እንዲህ ግግም ብሎ ያስቸግራታል..

‹‹ምን እያሰብክ ነው… ….?ለሊቱን እዚሁ ጫካ ውስጥ ከአውሬ ጋር እናሳልፍ እንዴ…….?››ጠየቀችው
አዕምሮው ውስጥ ሰርስሯ እንዳትገባ እንደከረቸመባት በሹፈት መልክ አንገቱን አሸከረከረባትና ጀርባውን ሰጣት…በቃ ምንም ማድረግ አልችለችም …እስኪለቀው ድረስ መጠበቅ እንዳለባት ስለተረዳች እራሷን አረጋጋች..የሆነ የሚጠብቀው ወይም ለጊዜው ያልጣመው ነገር አለ ማለት ነው ስትል አሰበች..ተወችውና አካባቢውን በመቃኘት ዘና ማለት ጀመረች..
ጥቅጥቅ ያለውን ጫካ ስታይ.. በአካባቢው በቅርብ ርቀት  ከሚገኙ የገጠር መንደሮች ጭል ጭል የሚሉትን  የኩራዝና የፍኖስ መብራቶችን  ..ወደ ላይ አንጋጣ የዘወትር አጫዋቾን ጨረቃን ስትመለከት ሰዓቱ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ሆነ …ንስሯ ፀባይ ላይ ምንም የተለወጠ ነገር የለም …አሁንም የነበረበት ቋጥኝ  ላይ በተመስጦ… አረ እንደውም የፀሎት በሚመስል ሁኔታ ያለእንቅስቃሴ አንገቱን ወደጨረቃዋ አንጋጦ ተደምሟል ..
የተቀመጠችበት የወደቀ የግንድ ጉማጅ ቂጧን ስላሳመመት ተነሳችና ቀስ እያለች እሾህ እንዳይቧጭራ እና አውሬ ጉድጋድ ውስጥ ተንሸራታ እንዳትገባ እየተጠነቀቀች ወደ ፏፏቴው ተራመደች… እንደደረሰች ሙሉ ልብሷን ፓንቷንም ሳታስቀር ውልቅልቅ አድርጋ ገባችበት… ፏፏቴው ከላይ ከአለቱ እየተላተመ መቶ ጭንቅላቷ ላይ ሲያርፍ ያለውን ኃይል መቋቋም አቅቶት ልትወድቅ ነበር.. ለጥቂት ነው በአቅራቢያዋ የጋጠማትን የግንድ ቅርንጫፍ ይዛ የተረፈችው‹‹..ደግሞ ውሀው እንዴት አባቱ ይሞቃል…….?››አለችና ድክም እስኪላት ድረስ ሰውነቷን እየተገለባበጠች አስመታችውና ወጥታ ልብሷን ለብሳ ወደ ንስሯ ተመለሰች፡፡
ስሩ እንደደረሰች  ከፊት ለፊቱ ቆማ በትኩረት አየችው…መልኩ ተለየባት… የሆነ አመድ ላይ የተንከባለለ አህያ መስሏል..እንዴ ምን ላይ ተንከባሎ ነው….?..እዚህ ሰውነት ላይ ነው እንዴ ተጭኜ የመጣሁት…….?ነው ወይስ እኔ ውሀ ውስጥ  ሳለው የሆነ ነገር ከሰማይ አመድ ነፋበት..….?አረ አመድ ብቻ አይደለምል  አንገቱንም መሸከም አቅቶታል…››ስለንስሷ ቴና ሀሳ ገብቷት መነብሰልሰል ጀመረች

‹‹ምን ሆንክ….?››
አዕምሮውን ቀስ እያለ ከፈተላት፡፡እሷም እንደምንም እራሷን ለማረጋጋት ሞከረችና ወደአዕምሮው ገባች…አዎ መድሀኒቷን አየቻት …እሷ ካለችበት በ5 ሜትር ያህል ርቀት ላይ ትገኛለች…የተለየች አይነት ልዩ ተክል ነች ….?የአንድ ሰው የማህል ጣትን ነው የምታክለው…የበቀለችው ሌላ ትልቅ የብሳና ዛፍ ላይ ጥገኛ ሆና ነው….የሆነ ሀመራዊ አይነት የተለየ ብርሀን  ትረጫለች…
👍7113😁1