አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ትንግርት


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


እሁድ ከቀኑ ዘጠኝ ሠዓት

ሁሴን ከነጋ ከትንግርት ጋር አልተያዩም፡፡ ማታ ሲጠጡና ሲጫወቱ እስከ ስምንት ሠዓት ነበር የቆዩት፡፡ ከዛ በኋላ ነው ብቻውን መሆን እንደሚፈልግ የተናገረው ነገር ከምሩ ሳይሆን በወቅቱ ተበሳጭቶ ስለነበር ገልፆላት ይቅርታ እንድታደርግለት ከለመናት በኋላ የመጨረሻ ዕድሉን የመሞከሪያ ቀኑንም አብራው እንድትሆን አሳምኗት ሊተኛ ወደ መኝታ ክፍሉ እየተንገዳገደ የሄደው፡፡

ከእንቅልፉ ሲነቃ ሠባት ሠዓት ሆኖ ነበር፡፡ በርግጎ በመነሳት ከክፍሉ ወጥቶ የትንግርትን ክፍል ሲያይ እሷም አልተነሳችም፡፡ ከዛ ያደረገው ነገር ቢኖር አስተናጋጁን ጠርቶ ምግብ እና የምትጠጣው ነገር ክፍሏ ድረስ እንዲወስዱላት ማድረግ ነበር፡፡ እሱም ለራሱ ሻወር ከወሠደ በኋላ ምሳውን በልቶ ወደ ከተማ ወጣና ዞር ዞር ብሎ ሲመለስ ትንግርት እንደተኛች አገኛት፡፡ ክፍሉ ገብቶ የተዝረከረኩና የተበታተኑ የግል ዕቃዎቹን ሠብስቦ በሻንጣው ውስጥ ጨመራቸው፡፡ ወደ ሆቴሉ እንግዳ መቀበያ ክፍልም ሄዶ ያለበትን ሂሳብ ዘጋ፡፡ ዛሬ ከበፊት ቀናት ይልቅ የመዝናናት የደስታ ስሜት እየተሠማው ነው፡፡ ሠዓቱን ተመለከተ፤ ዘጠኝ ተኩል ሆኗል፡፡

በመካከለኛ ኃይል የትንግርትን በር አንኳኳ፡

ኳ..ኳ..ኳ..ኳ..ኳ

‹‹ማነው?"

‹‹በሕይወት አለሽ? የበከትሽ መስሎኝ ነበር፡፡››

‹‹አንተም አልበከትክ .. ጠብቀኝ መጣሁ፡፡››

ከውጭ እንደተገተረ የተወሠኑ ደቂቃዎች አስጠበቀችው፡፡በዝግታ በሩ ተከፈተና ‹‹ግባ›› አለችው፡፡ ገባ፡፡ መልሳ በራፉን ዘጋችው፡፡ ከሻወር ነው የምትወጣው፡፡ገና ልብሷን
አለበሰችም፡፡ መሀከላዊ ሠውነቷን በፎጣ ጠቅልላዋለች፡፡አብዛኛው የላይና የታች አካሏ እንደተራቆተ ነው፡፡ ለመጀመሪያ ቀን ያያት ይመስል ዓይኖቹን ተከለባት፡፡ ከእሷ ጋር ያሳለፋቸው የፍቅር ጊዜያቶች፣የቆዳዋ ልስላሴ፣የሠውነቷ ጠረን፣የከናፍሮቿ ጣዕም፣ጠቅላላ ትዝታው የፍቅር ረሃቡን ቀሠቀሱበት፡፡ የቡና ቤት ሕይወቷን ካቋረጠች ስምንት ወር ሞላት ያ ማለት ከእሱ ጋርም ጾታዊ ግንኙነት ማድረግ ካቆሙ ስምንት ወር አለፏቸዋል ማለት ነው፡፡ያ የሆነው ደግሞ እሷም ፊት ስለነሳችው እሱም ስለፈራት ነው!፡፡

‹‹ምነው አትናገርም እንዴ?››

‹‹እንዲህ ቆንጆ ሆነሽ አይቼሽ አላውቅም..›› አላት አስቦበት አይደለም በድንገት ነው ቃላቶቹ ከአንደበቱ ተስፈንጥረው የወጡት ፡፡

ተንጨፍርሮ ውሃ የቋጠረ ፀጉሯን በፎጣ እያደረቀች‹‹ምን አልባት ያየኸኝም ዛሬ ገና ብቻ ሳይሆን አይቀርም!!›› መለሠችለት ፡፡

‹‹አይደለም፤ካገኘሁሽ ቀን ጀምሮ በጥልቀት አይሻለሁ፤ ቆንጆ እንደሆንሽም
አውቃለሁ፤አሁን ለማለት የፈለኩት ግን የተለየሽ ሆነሻል ማለቴ ነው፡፡ዞማ ፀጉርሽ ተንጨፍርሮ ወዲህና ወዲያ መዘበራረቁ፤የአይኖችሽ ቅንድቦች አበጥ…
አበጥ ማለታቸው፣የፊትሽ ወዝ ጥራቱ፣ደረትሽ
ላይ ያለው ሀብል፣የጡቶችሽ
መቀሰር፣ያገለደምሽው ፎጣ፣ ወጣ ወጣ ያሉ
ዳሌዎችሽ፣በትንሹ የተጋለጠው ባትሽ፣ የእግሮችሽ ጣቶች፣በቃ እነዚህ ሁሉ በአንድ ላይ በግልፅ ሳያቸው ምን ዓይነት ስሜት እንደፈጠሩብኝ ታውቂያለሽ? ምነው
ሠዓሊ በሆንኩ ነው ያሰኘኝ፡፡›› ያለ ምንም
ፍራቻና መሳቀቅ ፊት ለፊቱ ልብሶቿን እየለበሠች ንግግሯን ቀጠለች
<<አቶ ጋዜጠኛው! እነዚህን የመሰሉ ውብ የፍቅር
ዓረፍተ ነገሮች ያለቦታቸው አታባክናቸው፡፡ ነው
ወይንስ በኋላ እሷን ስታገኛት ምን ማለት
እንዳለብህ እየተለማመድክብኝ ነው? >>
‹‹ካገኘኋትማ አትበይ! ለምን እንደዚህ ደስ ያለኝ ይመስልሻል፤ ዘጠና ዘጠኝ ፐርሠንት ያቺ ጠይም አንባቢ የእኔዋ ምስጢር እንደሆነች እርግጠኛ ነኝ፡፡ ግን አመንሽም አላመንሽም ስለ አንቺ የተናገርኩት ከምሬ ነው››

ቀሚሷን ከስር አጥልቃ ዳሌዋን ካለበሰች በኋላ ከላይ ያለውን ፎጣ አንስታ አልጋ ላይ ወረወረችና በገረሜታ ቆሞ የሚያወራትን ሁሴንን ተመለከተችው፤እናም ከወገቧ በላይ እንደተራቆተች አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ አለችና እሱንም ስባ ከጎኗ አስቀመጠችው፡፡ ግራ በመጋባት ዝም ብሎ ተጎተተላት፡፡

‹‹እስቲ ንገረኝ... ቆይ እኔ ላንተ ምንህ ነኝ?››

‹‹አልገባኝም?››

‹‹ብዙ ጊዜ የእኔ ነገር በቀላሉ እንደማይገባህ አውቃለሁ፡፡ ለማለት የፈለግኩት እኔ ላንተ የድሮ የቡና ቤት የወሲብ ደንበኛህ ነኝ? ... የድሮ ፍቅረኛህ ነኝ? ... ወይስ ጓደኛህ ነኝ?...

ወይንስ በቃ ዝም ብሎ በሆነ አጋጣሚ የምታውቀኝ አንድ ተራ ግለሠብ ነኝ?››

ዝም ብሎ የጎንዬሽ ተመለከታት፡፡ በመጀመሪያ ጥያቄዎቿ እንደወትሮው የቀልድና የሽሙጥ መስለውት ነበር፡፡ አይኖቿን ሲያነባቸው ግን ትናንትና ማታ ስላለፈ የፍቅር ሕይወቷ ስትተርክለት ያስተዋለውን አይነት ስቃይ አነበባቸው እናም ጥያቄዎቿን በጥሞና አጤናቸው፡፡

‹‹ትክክለኛ መልስ ነው የምትፈልጊው?››

‹‹ለስሜቴ ቅንጣትም ሳትጨነቅ ትክክለኛ የሚሠማህን››

ለደቂቃዎች እንደመቆዘም አለና መናገር ጀመረ፡፡ ‹‹እንግዲያው እውነቱን ንገረኝ ካልሽ አንቺ ምኔ እንደሆንሽ ከአሁን በፊት አስቤው አላውቅም፡፡ ግን በእርግጠኝነት የማውቀው አንድ ነገር ቢኖር ዘወትር ካንቺ ጎን መሆን መፈለጌን ነው፡፡ሁል ጊዜ ስበሳጭ፣በሕይወቴ
የሆነ ነገር ሲመሠቃቀልብኝና ማደርገው ነገር ግራ ሲገባኝ፣መጨፈር ወይም ማልቀስ ሲያሠኘኝ፣አጠገቤ ማግኘት የምፈልገው ብቸኛዋ ሠው አንቺ መሆንሽን በእርግጠኝነት አውቃለሁ፡፡ይሄ ስሜቴና ፍላጎቴ የጓደኝነት ይሁን የፍቅር ... ብቻ ትክክለኛ ስሜቱን አላውቅም፡፡ በቃ ይሄው ነው፡፡›› በማለት ንግግሩን ጨርሶ ቀና ሲል ከሚንከባለሉ ዓይኖቿ እንባዋ እየተንጠባጠበ ደረቷ ላይ አርፎ በጡቶቿ መሃከል ሲንኳለል ተመለከተ፡፡

‹‹ምን ያስለቅስሻል ... ምን የሚያስለቅስ ነገር ተናገርኩ?›› በማለት ይበልጥ ተጠጋትና ቀኝ እጁን ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጎ ሊያባብላት ፈለገ፡፡

‹‹ምንም ክፉ ነገር አልተናገርክም፡፡ እንደውም በተቃራኒው መስማት የምፈልገውን ነገር ስለነገርከኝ ደስ ብሎኝ ነው ያለቀስኩት፡፡ እኔም ስላንተ የሚሠማኝን ነገር ሁሉ ዝርግፍ አድርጌ ብነግርህ ደስ ይለኝ ነበር ...ግን አልችልም በፍፁም አልችልም›› ሠዓቷን ተመለከተች ፡፡

ዘጠኝ ሠዓት ሆኗል፡፡

‹‹ይሄውልህ አሁን ዘጠኝ ሠዓት ነው፡፡ ወደ ቀጠሮህ ቦታ ለመሄድ የቀረን አንድ ሠዓት ብቻ ነው፡፡ ከዛ በኋላ ነገሮች ሁሉ መልካቸውን ይቀይራሉ ፤እንዳልከው እሷ ሆና ካገኘሀት እንደዚህ እንደዛሬው አንድ ቤርጎ ጎን ለጎን ለዛውም ግማሽ እርቃን ሆኜ ማውራት ይቅርና በአደባባይና በካፌ እንኳን የመገናኘት ዕድላችን በእሷ በጎ ፍቃደኝነት የሚወሰን ይሆናል፡፡ ባታገኛትም የተለየ ታሪክ አይኖረውም፤ምክንያቱም እኔ ከዚህ በፊት ደጋግሜ በፍቅር እጦት እንደተሠባበርኩ አንተም ትሠበራለህ፤ከዛ በኃላ አንተ ትጠፋና በድንህ ብቻ ይቀር ይሆናል፤ከበድንህ ጋር
ደግሞ እንደከዚህ ቀደሙ ያለ ግንኙነት ሊቀጥል አይችልም ...>>

‹‹ምን እያወራሽ ነው?የሲኦል ፍራቻ በልቤ ውስጤ እየበተንሽ እኮ ነው

‹‹እኔም በጣም ስለፈራሁ ነዋ፡፡ ከፍራቻዬ ጥልቀት የተነሳ እየተንቀጠቀጥኩ አይታይህም?››

‹‹መንቀጥቀጥሽ ይሠማኛል፤ግን ተረጋጊ በእኛ ግንኙነት መካከል ምንም የሚቀየር ነገር አይኖርም፡፡›› እርግጠኛ ባይሆንም በወቅቱ ማለት የሚችለው እንደዚህ ነበር፡፡

‹‹እንድረጋጋ...ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ.... ማለት ከዛሬ ወዲህ መቼም የማይደገም… በቃ...መሠናበቻ ...›› ንግግሯን መጨረስ አልቻም ሳግ አቋረጣት፡፡

‹‹የመሠናበቻ ምን? ... ንገሪኝ፡፡››
👍11111😁1🤔1🎉1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


"ውይ ለመክሰስ ሆቴል...?ሰርቼ ልጋብዝሽ የምትለኝ መስሎኝ ነበር።"
‹‹ደስ ይለኝ ነበር...ግን ካገዝሽኝ ነው..."

"ይቻላል"
ሁለቱም  የየራሳቸውን  ቢራ  ይዘው  በእሱ  መሪነት  ወደ  ኪችን.አመሩ።
ኪችኑ በእጅጉ የተደራጀና የሚያምር ነው። ፍሪጁን ከፈተና ተመለከተ...
"ምን እንስራ"በራሱ መወሰን አቅቶት ጠየቃት።
"እኔ እንጃ...ምን አለህ?"አለችና ወደእሱ ተጠግታ ያለውን ነገር ተመለከተች...ብዙ ምርጫ አላቸው...የምትፈልገውን ነገር እየመረጠች ከፍሪጁ ማውጣት ጀመረች፡፡ እሱም ወደውጭ ሊወጣ አስቦ የለበሰውን ጃኬት አወለቀና ሽርጥ ለበሰ..ለእሷም ተመሳሳይ ሽርጥ ሰጣት።በ30 ደቂቃ ውስጥ ሶስት የተለያየ የምግብ አይነት ተጋግዘው በመስራት ሳሎን የምግብ ጠረጴዛ  ላይ  አቀረቡ..በልተው  ሲጨርሱ አንድ ሰዓት አልፎ ነበር።

"አሁን በላሁ ጠጣሁ...ወደማድርበት ቤርጎዬ ልትመልሰኝ ትችላለህ?›› አለችው። ሞባይሉን በማውጣት ሰዓቱን አየና"እንዴ ገና አንድ ሰዓት  እኮ  ነው...ባይሆን አንድ ወዳጄ ከፈረንሳይ ያመጣልኝ ልዩ ወይን አለኝ...እሱን ላምጣና መጠጥ እንቀይር››አለና እሺታዋንም ሳይጠብቅ መቀመጫውን ለቆ ወደመኝታ ቤቱ በመሄድ ይዞ መጣና የቢራ ጠርሙሶችን ከፊታቸው በማንሳት በወይን ብርጭቆ ተካውና ተደላድሎ ቁጭ አለ፡፡:

"በቀደም  ለታ  ግን  ማደሪያ  ቦታ  ስጠይቅህ  ለምን  ቤትህን  አራተኛ  ምርጫ አድርገህ አላቀረብክልኝም ነበር?"ስትል.ያላሰበውን ድንገተኛ ጥያቄ ጠየቀችው።
"እኔ  እንጃ...ምን  አልባት  እንደዛ  ብልሽ  ሌላ  ነገር  ታስቢያለሽ  ብዬ.ፈርቼ ይሆናል"አላት፡፡
"እንዴት ሌላ ነገር አስባለሁ?"
"ብታስቢም እኮ አይፈረድብሽም...በጥልቀት አታውቂኝም"
"ለነገሩ እውነትህን ነው፤እሺ አሁን ብዙ ብር ከምትዝቅበት የማሳጅ ስራ ራስህን ለምን እንዳገለልክ ንገረኝ? "ቅድም ጀምረው ወዳቋረጡት የጫወታ ርእስ መለሰችው፡፡
የወይኑን ብርጭቆ አነሳና ውስጡ ያለውን ከጨለጠ በኃላ መልሶ አስቀምጦ አንገቱን አቀረቀረ፡፡››
"ምነው ከባድ ጥያቄ ነው እንዴ የጠየኩህ?" በረጅሙ ተነፈሰ፡፡
"ከከባድም በላይ..አየሽ ቅድም ስለስራው ሳስረዳሽ ልክ እንደሀሺሽ ነው ብዬሽ ነበር አይደል። በመጀመሪያ ሁሉ ነገር አስደሳችና ልብን ስውር የሚያደርግ ነበር። አገልግሎቱን ለማግኘት የሚመጡት ሴቶች ሊነኳቸው የሚያሳሱ  የሰውነታቸው ቆዳ እንደሀር ጨርቅ የለሠለሠ፤ የፊታቸው ውበት የመላእክት የመሰለ ፤ጠረናቸው ጭንቅላት አዙሮ ጭናቸው ስር የመድፋት ኃይል ያለው፤ የህልም አለም ንግስቶች ናቸው። ታዲያ እነሱን እርቃን አስወልቀሽ ከላይ ከጭንቅላታቸው እስከታች የእግር ጥፍራቸው መላ ሰውነታቸውን አፍተልትለሽ ዳብሰሽና አሽተሽ፤በስሜት ሲወራጩና በደስታ እንባቸው ሲንጠባጠብ አይተሽ...ለምነውና በአይናቸው ተለማምጠው እርቃንሽን ከእርቃናቸው እንድታዋህጂ ለምነውሽ...አርክተሻቸውና.ረክተሽ፤አስደስተውሽና ተደስተሽ፤ አስለቅሰሻቸውና አልቅሰሽ  ከዛ  ደግሞ  ረብጣ ብር የእጅሽ መዳፍ ላይ አስጨብጠው..በመፍለቅለቅ ጉንጭሽን ወይም ከንፈርሽን ስመው በሳምንቱ እንደሚመለሱ ምለውና ተገዝተው ይሄዳሉ...;
‹‹ስራው እስከዚህ ይሄዳል ማለት ነው"

"አዎ ምነው የፈረምሽውን ውል በቅጡ አላነበብሽውም እንዴ...ደንበኛ ምንም ነገር ጠይቆ መከልከል የለበትም ይላል እኮ.ያ ማለት ደግሞ ስራው ከነገርኩሽም በላይ ይሄዳል ማለት ነው.."
"እና አሁን አንድ የማላውቀው ሰው መጥቶ እንድትወጪልኝ እፈልጋለሁ  ካለኝ..ዝም ብዬ እከፍትለታለሁ ማለት ነው።"

‹‹አይ ዝም ብለሽማ አትከፍቺለትም ...አንቺ ያለሽበት ቦታ አገልግሎትሽን ፈልጎ የሚመጣው ግለሰብ በየሄደበት ዝም ብለው የሚከፍቱለት ቁጥር ስፍር የሌላቸው አንዳንዴም ካንቺ በላይ ለጋ፤ ካንቺ በላይ ፀሀይ የመሰሉ ውብ የሆኑ ሴቶች አሉት...እንደዛ ካደረግሽ ደብሮት የመጣውን ሰውዬ ጭራሽ አሳብደሽ ነው የምትልኪው››

‹‹እና ምንድነው ማድረግ የሚጠበቅብኝ ?››በከፍተኛ መገረም ጠየቀችው።
እጅሽ ሰውነቱ ላይ ሲያርፍ ልስላሴውና ሙቀቱ ቆዳውን ሳይሆን ልቡ ላይ ሊሰማው ያስፈልጋል....መሳም ኖሮብሽ ከሳምሽው ከከንፈሮችሽ የሚመነጨው ሙቀት ወደ ጭንቅላቱ ሄዶ በቢሊዬን የሚቆጠሩትን የኒሮን ሴሎችን ከተኙበት መቀስቀስና መደነስ እንዲችሉ ማድረግ አለብሽ... ልብሶችሽን  ፊቱ  ስታወልቂ አይኖቹ ቆዳሽን ሰንጥቀው ውስጥሽ በመግባት ነፍስሽን ጭምር ለመቆረጣጠም እስኪመኝ መቃተት መቻል  አለበት። ጭንሽን  ከፍተሽለት  ብልቱ ብልትሽን ሰንጥቆ ከገባ አካሉ መጥፋት፤አእምሮ መሰወር፤ነፍሱ በአየር ላይ እየተንሳፈፈች ትዕይንቱን መታዘብ አለባት።ሰውዬው ካንቺ በፊት ከመቶ ሴቶች ጋር ለአንድ ሺኛ ጊዜ ወሲብ አድርጎ የሚያውቅ ከሆነ .. እንዴ ከዚህ በፊት ወሲብ አድርጌ አውቅ ነበር እንዴ ..?ብሎ እስኪጠይቅና እስኪወነባበድ ድረስ ህልም ውስጥ እንዲገባ ማድረግ ይጠበቅብሻል... የስራው ከባድነት ደግሞ ሰውዬው በሳምንት ወይም በወራት ልዩነት ደጋግሞ ቢመጣ በተመሳሳይ ብቃት ግን ደግሞ ፍፁም ባልተደጋገመ 10 የተለያየ መንገድ ማስተናገድ ይጠበቅብሻል፡፡
"የሚያወራውን ሁሉ የምታዳምጠው ሁሉንም የስሜት ህዋሳቶቿን ከፋፍታ ነበር...እየጠጣችው ያለው መጠጥ እየሠማችው ካለው ወሬ ጋር ተዳምሮ ሙቀትና ንዝረት ለቀቀባት
"የምትነግረኝ ነገር ሁሉ ግን እውነት ነው?ማለቴ እንደዚህ አይነት ነገር አለ?"
"አዎ አለ"
"ወይ በፈጣሪ..ታዲያ እኔ ምን  ላደርግ  ነው?  እንደው  ፍቃደኛ  ሆኜ የተጠየቅኩትን ለማድረግ ፈለኩ ልበል…ግን በየትኛው ብቃቴ ነው አንተ ባወራህልኝ መጠን በአየር ላይ የሚያንሳፍፍ ወሲብ መፈፀም የምችለው..?
"አይዞሽ ...አንቺ ብቻ ከልብሽ ተቀባይ ሁኚ እንጂ…በቂ ስልጠና ይሰጥሻል...ከዛ የተወሰነ የስራ ልምድ በኋላ እርግጠኛ ነኝ ከነገርኩሽም በላይ የተካንሽ ትሆኚያለሽ"
"እንዴት እርግጠኛ ሆንክ?"ብላ ልትጠይቀው ፈለገችና ብዙ በተናገረች  ቁጥር ይበልጥ ራሷን እያጋለጠችና ወደ ሽብር ውስጥ እየገባች ስለመጣች መልሳ ዋጠችው።
"እሺ ይሄን ለጊዜው ተውና ..የጀመርክልኝን የራስህን ታሪክ ቀጥልልኝ"
"አጠር ላድርገውና በተደጋጋሚ ጊዜ ከሚመላለሱ ደንበኞቼ መካከል ከአንዷ ጋር የተለየ ግንኙነት ነበረኝ፣ለነገሩ ከአንዷ ጋር ብቻ አልነበረም ከአምስት ከስድስቱ ጋር በይው። ግን ስራ እንዳቆም ስላስገደደቺኝ አንዷ ብቻ ላውራሽ።
የባለስልጣን ሚስት ነች። ባሏ የሆነ መስሪያ ቤት ሚኒስትር ዲኤታ ነው። ያው በስራውም በራሱ ጉዳይም በጣም እረፍት የሌለው ከወር ውስጥ ግማሹን ቤቱ
የማያድር...በሚያድርባቸው ጥቂት ቀናትም እኩለ ለሊት ገብቶ ወፍ ሲንጫጫ የሚወጣ አይነት አባወራ ነው። ሚስቱ የፈለገችውን ያህል ብር ይሰጣታል። በዛ ላይ በእሷ ስም የተከፈተ ግዙፍ ድርጅት አላቸው። የት ገባህ የት   ወጣህ እንዳትለው ያንን በማስተዳደር ቢዚ ሊያደርጋት ሞክሮ ነበር። ይሄ  እቅድ ለተወሰነ አመት ቢሰራለትም ቀስ በቀስ ሴትዬዋን ለድብርትና   ለጭንቀት እያጋለጣት መጣ ...ከዛ በአንድ ወዳጇ ገፋፊነት እኛ ጋር ትመጣለች..አጋጣሚ ሆኖ እኔ ጋር ተላከች። በመጀመሪያዎቹ ሶስት አራት   ዙሮች እንደማንኛውም ኖርማል  ማሳጅ  የተለመደውን  አገልግሎት  እያገኘች   ነበር የምትሄደው...ከዛ ነገሮች በሂደት እድገት ሲያሳዩ ከስድስት ወር የደንበኝነት መመላለስ በኃላ ጥልቅ የሆነ ፍቅር ውስጥ ገባች...
👍68😱54
ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ልጅም ቶሎ ያንጠለጠለውን የእጅ ቦርሳ ጠረጴዛ ላይ አደረገና ከብር የተሠራ የሚመስል ሁለት የእጅ ብራስሌት መጀመሪያ ምስራቅ እጅ ላይ ቀጥሎ ናኦል እጅ ላይ አጠለቀና ከኪሱ ስልኩን አውጥቶ በማብራት ሲነካካ እጃቸው ላይ ያጠለቀላቸው ብራስሌት ቀለሙን ከብራማነት ወደ ደማቅ ሰማያዊነት ቀየረ።ዝም ብሎ ሁኔታውን ሲከታተል የነበረው ዳግላስ መናገር ጀመረ
"አሁን እንግደህ እህታችሁን እኔ ሳልሆን ለእናንተ ማመጣላችሁ ..እናንተ ናችሁ ለእኔ የምታመጡልኝ..." ብሎ ኑሀሚ የእሱን ሰው ገድላ ከሌላ ከእሱ ሰው ጋር እንደኮበለለች...እስከአሁንም በመላው አማዞን ደን ውስጥ ቢያስፈልጋት ሊያገኛት እንዳልቻለ...እሷን መሞቷን ካላረጋገጠ ወይም በህይወት እጅ ካላስገባት የሰላም እንቅልፍ እንደማይወስደው..ወንድሟን ያስመጣበት ምክንያት ተሳክቶላት እንኳን ማምለጥ ብትችል ለወንድሟ ደህንነት ስትል በፍቃዷ መልሳ እጅ እንድትሰጥ አቅዶ ያደረገው እንደሆነ አብራርቶ ከአሁን ሰዓት በኃላ እዛው እሱ የሚኖርበት ወለል ላይ የራሳቸው ክፍል እንደሚሰጣቸው እና እጃቸው ላይ በተጠለቀላቸው አንባር ሙሉ የ24 ሰዓት ክትትል እንደሚደረግላቸው ነገራቸው። እሷ መጥታ በፍቃዷ እጇን እስክትሰጥ ወይንም መሞቷ እስኪረጋገጥ ድረስ ከክፍላቸው መውጣት እንደማይችሉ...ፀባያቸውን እስካሳመሩና ችግር ለመፍጠር እስካልሞከሩ ድረስ የሚፈልጉት ነገር እንደሚያሟላላቸው አብራርቶላቸው.. ወደክፍላቸው እንዲወስዳቸው አዘዘ...።የታዘዘውም ታጣቂ እየጎተ ወሰዶ አንድ ለቀቅ ያለ ሻወርና ማንበቢያ ክፍል ያለው ባለአንድ ክፍል ቤት ውስጥ አስገብቶ ከውጭ ዘጋባቸው..
እቤት ውስጥ ከገብ በኃላ እንኳን ናኦል እና ምስራቅ  ለረጅም ደቂቃ ደንዝዘውና ፈዘው ማህል ወለል ላይ በዝምታ ተገትረው ነበር።

ናኦል እንባ እየተናነቀው"ምስራቅ ምን ውስጥ ነው የገባነው..?ይሄ ሰውዬ ተጫወተብን"አላት ።
ምስራቅም ወደእሱ ተንደረደረችና  አቀፈችው ።አንገቱ ስር ሽጉጥ ብላ በጆሮው "አትደንግጥ...እቅድ አለኝ"አለችው።

ዝም አለ...ከዚህ ለመውጣት ምን አይነት ተአምራዊ ዕቅድ ሊኖራት እንደሚችል ምንም ሊገለፅለት አልቻለም።ቢሆንም ከሞስራቅ ጋር ባሳለፋቸው በርካታ አመታት ብዙ ተአምር መሳይ ነገሮችን ስትከውንና ደጋግሞም ሲሳካላት ታዝቦልና የተናገረችው ነገር ንቆ ሊያልፈው አልደፈረም።...
ብራዚል/አማዞን ደን ውስጥ
አካባቢው ድቅድቅ ጨለማ ነው፡፡ጨረቃዋም በሰማይ ላይ ብርሀን አልፈነጠቀችም፡፡ከዋክብቱም የከሰሙ መስለዋል ፡፡ኑሀሚ ካርሎስ የሰራላት የአንጨት ርብራብ አልጋ ላይ ተኝታ የእጇ ጥዝጣዜ ታዳምጣለች፡፡እርግጥ ከትናንቱ የተሻ ጤንነት ላይ ብትገኝም ሰውነቷ ግን ሙሉ በሙሉ እደዛለ ነው፡፡በህይወቷ በእንዲህ አይነት ደካማንትና አቅመ ቢስነት ተሰምቷት አያውቅም፡፡ ካርሎስ በሶስት ቀን ውስጥ ሙሉ በሙሉ እደምታገግም ነግሯት ነበር ፡፡ አሁን አሁን ያለችበት ሁኔታ ስታስበው በሶስት ወር ተሽሏት ከዚህ አካባቢ የምትንቀሳቀስ እየመሰላት አይደለም፡፡ያም ሆኖ ግን ትናንትና ጉሮሮዋን ፈጥርቆ ነፍሷን ሊነጥቃት የነበረው ሲኦላዊ ህመም ዛሬ በሙሉ አቅሙ የለም፡፡ያ የሆነው ደግሞ ካርሎስ እጇ ላይ ባሰረለት የባህል መድሀኒት ምክንያት ነው፡፡
እንደምንም አንገቷን ወደ ዳር ሸርተት አድርጋ አየችው፡፡ እዛው ርብራብ አልጋ ጎን ባለ ጠፍጣፍ ድንጋይ ላይ ተቀምጦ አንገቱን በካኔቴራው ሙሉ በሙሉ ሸፍኖ የእንጨት አልጋውን ቋሚ ተደግፎ ጨልጥ ያለ እንቅልፍ ተኝቷል፡፡ አሳዘናት፡፡ቢቻላት ኩርምት ብሎ በተቀመጠበት እንቅልፍ የወሰደውን ይሄን መልካም ሰው ጎትታ ወደራሷ ስባ እሷ የተኛችበት የእንጨት ርብራብ ላይ ከጎኗ ሽጉጥ አድርጋው ብትተኛ ደስ ይላት ነበር ፡፡
ወዲያው ሀሳቧን ሳትጨርስ ነጎድጓድ በሰማዩ አንፀባራቂ ብርሀን እየረጨ ያንቧርቅ ጀመር፡፡የሚያስፈራ ደራጎናዊ ድምፅ አካባቢውን ያናጋው ጀመር፡፡ ኑሀሚ እንኳን በእንደዚህ አይነት ሁኔታ እንደዚህ አይነት ቦታ ሆና ይቅርና በሀገሯ ሰማይ ስር በገዛ ቤቷ እያለች ሳይቀር እንዲህ አይነት ነጎድጎድ በጣም ነው የሚያስፈራት፡፡፡እንደምንም ደካማ እጃን አንቀሳቀሰችና ትከሻው ላይ አኑራ በመወዝወዝ..‹‹ካርሎስ ካርሎስ›› ስትል ጠራችው፡፡

በርግጎ ተነሳ‹‹..ምን …አመመሽ እንዴ?››
‹‹አይ ነጎድጎድ ፈራለሁ››
ከተቀመጠበት ተነሳና ወደእሷ ተንቀሳቀሰ….ርብራቡ ጠርዝ ላይ ከጎኗ ተቀመጠና እጆቿን በእጆቹ ውስጥ አስገብቶ ያሻሽላት ጀመር፡፡ከእሱ ሰውነት ወደእሷ እየተላለፈ ያለው ሙቀት ብቻ ሳይሆን ብርታትና ጥንካሬ ጭምር ነው፡፡
በድጋሚ‹‹በጣም እኮ ነው የፈረሁት››አለችው፡፡
‹‹አይዞሽ…ስጋታችን፤ፍረሀቶችንና እና ጥርጣሬዎቻችን ሰው በመሆናችን የተሰጡን ፀጋዎች ናቸው፡፡ካለበለዚያማ እህያና በቅሎ መሰል አይነት ስሜቶች ስለሌላቸው ከእኛ የተሻሉ እደለኞች ናቸው ልንል መሆኑ ነው?፡፡››
‹‹እሱስ እውትህን ነው››አለችና ይበልጥ ተለጠፈችበት

ወዲያው ሰማዩን አግቶ ይዞ የነበረውን ዝናብ ዘረገፈው፡፡የተሰራችው ጊዜያዊ ጎጆ ሙሉ በሙሉ በዛ ድቅድቅ ጨለማ የሚወርደውን የዝናብ ውሀ አግዳ ለማስቀረት ጥንካሬው አልነበራትም፡፡ሁለቱም በ5 ደቂቃ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በዝናብ ራሱ፡፡እሷ ከህመሙና የሰውነት ጥንካሬዋ በመዳከሙ የተነሳ ዝናቡንና ቅዝቃዜውን መቋቋም ስላልቻለች ትዘፈዘፈች፣ካርሎስ የሚያደርገው ጠፋበት፡፡ ሙሉ በሙሉ ወደእንጨት አልጋው ወጣና ከእሷ ተስተካክሎ ተኛ…አቀፋትና ወደራሱ አስጠግቶ ከሰውነቱ ለጠፋት፡፡የናፈቀውን የእናቱን ጡት እንዳገኘ ህፃን ልጥፍ አለችበት፡፡የተሻለ ምቾት ተሰማት፡፡ከዝናብ ውርጅብኝ የምትሸሸግበት መጠለያ ዋሻ ያገኘች አይነት ስሜት ተሰማት፡፡ እጆቹን በረጠበ ልብሷ ስር ሰቅስቆ በማስገባት ሰውነቷን ላይ አሳረፈና ይዳብሳት ጀመር..፡፡ከዛ ቀስ እያለ ከንፈሩን ከንፋሯ ላይ አሳረፈና በቀስታ ይመጣት ጀመር፡፡አሁን ከውስጧ እየተቀጣጠለ ያለው ሙቀት ወደላይኛው የሰውነት ቆዳ በመድረስ ከላይ የሚያርፋባትን ዝናብ የሚያስከትልባትን ቅዝቃዜ እያተነ የሚያስወግድላት እየመሰላት ነው፡፡ጭልጥ ያለ ምናባዊ ህልም ውስጥ ነው የገባችው፡፡ከንፈራቸው ሳይላቀቅ ዝናቡም ከመቆሙ በፊት እሷ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰዳት፡፡

ስትነቃ ጎጆዋ በጥዋት የደመቀ የፀሀይ ፈንጣቂ አድምቋታል፡፡ሁሉ ነገር ብሩህ ፣ ሁሉ ነገር ዳማቅ ሆኖ ነው እየታየ ያለው፡፡እራሷን ለማንቀሳቀስ ሞከረች፡፡ አሁንም ሰውነቷ እንደተሳሰረ ነው፡፡ወደ ጎን አንገቷን መልሳ ተመለከተች፡፡ ለሊት ጎኗ ተኝቶ የነበረው ጉብል አሁን የለም፡፡አይኖቾን ብታንከራትትም ጎጆው ባዶ ነው፡፡ አንደምንም እራሷን አበረታታ ከተኛችበት ተነሳች፡፡ ዱላ መሰል እንጨት ተደግፋ እንደምንም እግሮቾን እየጎተተች ወደጎጆዋ በራፍ ሄደች፡፡ፊት ለፊቷ ያለው አማዞን ወንዝ እየተገማሸረ ጥሩ አቋም ላይ አንዳለ የማራቶን ራጭ ወደፊት እየገሰገሰ ነው፡፡አካባቢውን የሞሉት ውብና ማራኪ ወፎች ወዲህና ወዲያ አክሮባት እየሰሩ ይዝናናሉ.. አይኖቾን አሩቅ ስታማትር ካርሎስ በ500 ሜትር ርቀት በፓንት ብቻ አማዞን ወንዝ ውስጥ ጠልቆ ገብቶ ዓሳ ላመስገረ ሲዳክር ተመከተችው፡፡ፈገግ አለችና ወደ ውስጥ ተመለሰች፡፡ወደ ሻንጣቸው ተጠጋች ፡፡ውሀ የማያሳገባውን የሻንጣ ዚፕ ከፍታ ውስጥ ያለውን የካርሎስን ማስታወሻ ደብተር ከእነእስኪሪብቶው አወጣች፡፡እዛው መሬት ይዛ ተቀመጠችና ለመፅሀፍ ተዘጋጀች፡፡
👍867👎1😁1
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)
:
:
#ክፍል_ሀያ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ተካ አቶ ኃይለልኡል ባዘዙት መሰረት ሽጉጡን ሙሉ ጥይት ሞልቶ ወገቡ ላይ ከሸጎጠ በኃላ አጉሊ መሳሪያ ያዘና  ማንን ሳያስከትል ቀጥታ መኪና ውስጥ ገብቶ ወደ ቃሊቲ ነዳው….የሰውዬውን ጥርጣሬ ምንም አልተዋጠለትም…‹‹ልጅቷ ስንት አማራጭ እያላት እንዴት እዛ ጭንቁርቁስ ቤት ከጭርቁስቁስ ሰዎች ጋር ለመቆየት ታስባለች? ››ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡ ሊዋጥለት አልቻም…፡፡

በፀሎት ከጠፋችበት ቀን አንስቶ በመላ ሀገሪቱ ፍላጋ የተሰማሩትን በመቶ የሚቆጠሩ ግለሰቦችን የሚመራው ..መረጃ የሚቀበለው አዲስ ቦታ ስምሪት የሚሰጠው እሱ ነው፡፡እና የእሱ እቅድ የሆነ ቦታ መኖሯን በሆነ መንገድ ቀድሞ ቢደርስበት እንደምንም ብሎ የራሱ ሰው በሚስጥር እንዲያገኛት አድርጎ በእጅ አዙር 5 ሚሊዬኑን የሽልማት ገንዘብ ለመቀባበል አቅዶ ከልቡ እየሰራ ነበር...እርግጥ እንደዚህ እያደረገ መሆኑን ቀድመው ቢደርሱበት ያለምንም ማቅማማት ግንባሩን በጥይት እንደሚነድሉት እርግጠኛ ነው…ግን በህይወት የተሻለ ነገር ማግኘት ሪስክ መውሰድ የግድ እንደሆነ የሚያምን ስለሆነ ነገሩን ልክ እንደቁማር ነው ያየው..‹‹ወይ በላለሁ..ወይ ደግሞ እበላለው››ብሎ ነበር ውሳኔ ላይ ደርሶ በተግባር ሲንቀሳቀስ የከረመው፡፡…አሁን ሰውዬው እንደሚሉት ልጅቷ የገመቱት ቦታ የምትገኝ ከሆነ ያ ሁ እቅዱ ውሀ በላው ማለት ነው፡፡ቦታውን ራሳቸው ቀድመው አውቀው ስለነገሩት ሽልማት የሚሰጡበት ምንም ምክንያት የለም….መኪናውን ወደእዛ ሲያሽከረክር በውስጡ በፀሎት የተባለው ቤት በፍፅም እንዳትገኝ እየፀለየ ነበር፡፡እንደደረሰ ከመንገድ ማዶ አስፓልት ጠርዝ ላይ መኪናውን ፓርክ አደረገና የመኪናው መስኮት በከፊል ከፍቶ ማጊሊያ መነፅሩን ወደእነ አቶ ለሜቻ ግቢ አነጣጠረና ገቢ ወጪውን መመልከትና በመሀከልም የተለየ ነገር ያገኘ ሲመስለው በሞባይሉ ፎቶ ማንሳት ጀመረ…
ስራ የጀመረው ከጥዋቱ 5 ሰዓት አካባቢ ቢሆንም እሰከ 10 ሰዓት ሁለት ሶስት ጊዜ አሮጊት ሴት ስትወጣ ስትገባ ከማየት ውጭ በግቢው ውስጥ አይን የሚስብ ምንም አይነት እንቅስቃሴ አልነበረም…ሰዓቱ እየረዘመ ሲሄድ ተስፋ እየቆረጠና እየተሰላቸ መጣ…ለዛሬ ይበቃኛል ብሎ 11 ሰዓት ላይ አካባቢውን ለቆ ወደቤቱ ሄደ ..
በማግስቱ በጥዋት ማለዳ አንድ ሰዓት ላይ ነበር የመጣው፣እና ሁለት ሰዓት ላይ የሚፈልገውን አገኘ ..ደጋግሞ ፎቶ አነሳው…በቤቱ አንድ ሴት ልጅ ብቻ እንዳላቸው አጣርቷል ..አሁን እየገቡ እየወጡ ያሉት ግን በተቀራራቢ እድሜ ላይ የሚገኙ ሁለት ወጣቶች ናቸው፡፡አንደኛዋ የቤቱ ልጅ እንደሆነች እርግጠኛ ነው…ሁለተኛዋ ግን የሚፈልጋት የባለፀጋው ቅምጥል ልጅ ትሁን አትሁን መለየት አልቻለም…የለበሰችው ልብስ የተለመደ አይነት ነው..በዛ ላይ ፊቷን ጭንቅላቷን ጭምር በሻርፕ ሸፍናለች…ዝም ብሎ ከመኪናው በመውረድና በእግሩ ወደ አጥሩ በመጠጋት ከቅርብ ርቀት በርከት ያለ ፎቶ አነሳና ለአቶ ኃይለ ልኡል ላከላቸው፡፡

አቶ ኃይለልኡል በዚህ ጊዜ ከባለቤታቸው ጋር በሰለሞን በሚሾፈር መኪና ከቢሾፍቱ ወደአዲስ አበባ እየተመለሱ ነበር፡፡ስልካቸው ድምፅ ሲያሰማ ከኪሳቸው አወጡና ተመለከቱት..መልዕክት መሆኑን ሲያዩ ከፈቱት…አይናቸው ተጉረጠረጠ….
‹‹እራሷ ነች ..ልጄ እራሷ ነች….ከጎናቸው ያለችው ሚሳታቸው ላይ ተጠመጠሙና ጉንጮቾን አገላብጠው ይስሙ ጀመር››
‹‹እንዴ ኃይሌ ምን ተፈጠረ..?ምን ተገኘ..አረ ንገረኝ?››
‹‹ይሄውልሽ..እንቺ እይው..ፊቷን ብትሸፋፈንም እራሷ ነች፡፡››ወይዘሮ ስንዱ ስልኩን ከባላቸው እጅ ተቀበሉና አፍጥጠው ተመለከቱ…..ከባላቸው በበለጠ በመደነቅ ኡኡ.አሉ…መኪናዋን በእልልታ አደባላለቁት…ሰለሞን የነገሩ ውል ስላልገባው መሪውን ጠመዘዘና የመንገዱን ዳር አስይዞ መኪናዋን አቆማት…በራፉን ከፍተው ወረዱ….እሱም ተከትሏቸው ወረደ‹‹አረ ለእኔም ንገሩኝ ምንድነው? እንዲህ የሚያስፈነጥዝ ደስታ፡፡››
‹‹ልጃችን የት እንዳለች አወቅን..እያት ተመልከት››ስልኩን ከሚስታቸው ተቀበሉና ለሰለሞን አቀበሉት..አንድ ፊቷ በቅጡ የማይታይ ወጣት ፎቶ ነው…ግን በፀሎት እንደሆነች ወዲያው ነው ያወቃት..ሙሉ ፊቷን ሳያይ እሷ እንደሆነች አንዴት እንዳወቀ አልገባውም…››
‹‹አየህ …ልጃችን እራሷ ነች…ሰው እንዳይለያት ነው ፊቷን የሸፋፈነችው……››
‹‹ለመሆኑ የት ነው ያለችው?››ጠየቀ ሰሎሞን፡፡
‹‹የት እዳለች ቆይ ነግራችኃላው››ብለው ስልኩን ተቀበሉና ደወሉ
‹‹ሄሎ….ፎቶው ደርሶኛል፡፡››
‹‹አዎ ሳስበው እሷ ትመስለኛለች››
‹‹አዎ እሷ እራሷነች…ከቦታው እንዳትንቀሳቀስ..እዛው ጠብቀን…ከቢሾፍቱ እየተመለስን ስለሆነ ከ15 ደቂቃ በኃላ ያለህበት እንደርሳለን››
‹‹ወጥታ ከሄደችስ…?ላስቁማት››
‹‹አይ..ልጄን ቀጥታ እኔው ነኝ የማገኛት..እንዳታስቆማት ትደነግጥብኛለች…ከቤት ከወጣች ዝም ብለህ በርቀት እየተከታተልክ ያለችበትን ታሳውቀኛለህ፡››

‹‹እሺ..ጌታዬ እንዳሉት አደርጋለው››
‹‹ጎበዝ ..እንዳስደሰትከኝ አስደስትሀለው…ቆንጆ ጉርሻ ይጠብቅሀል ››
‹‹እሺ ጌታዬ››ስልኩን ዘጉና‹‹በሉ ጊዜ አናባክን ..ግቡና እንሂድ››
‹‹እንዴ የት አንዳለች ንገረን እንጂ……?››ወ.ሮ ስንዱ ጠየቁ
‹‹ስንድ ልጃችን ሰዎቹ ጋር ነው ያለችው….››
‹‹የትኞቹ ሰዎች››
‹‹እነአቶ ለሜቻ ጋር..ማለቴ የልብ ለጋሾ ቤተሰብ ጋር ነው ያለችው››
‹‹ወይ ጉዴ….አሁን ምንድነው የምናደርገው?››እያሉ ወደመኪናው ገቡ፡፡ አቶ ኃይለልኡልም ተከትለዋቸው ገቡ….ሰለሞን በሰማው ያልተጠበቀ ነገር ግራ እንደተጋባና ምን ማድረግ እንዳለበት እያሰላሰለ ገቢና ገባ፡፡ መኪናውን አንቀሳቀሳት…ባልና ሚስቶቹ በደስታ ሰክረው እሱን ከቁብ ሳይቆጥሩት እርስ በርስ በፈንጠዝያ ሲጎሻሸምና ሲሳሳሙ እሱ ምን ማድረግ እንዳለበትና ይሄንን ያለጊዜው ያጋጠመውን ነገር እንዴት እንደሚፈታ እያሰላሰለ ነበር የሚነዳው….
አቃቂ አቶ ለሜቻ ቤት ለመድረስ 500 ሜትር ያህል ሲቀራቸው የመኪናውን መሪ ወደግራ ጠመዘዘና ፊት ለፊት ከሚታየው ሆቴል ይዞቸው ገባ..ባልና ሚስቶቹ በድንጋጤ እርስ በርስ ተያዩ
‹‹ሰለሞን…ምን እያደረክ ነው?››አቶ ኃይለልኡል ጠየቁ፡፡
‹መነጋገር አለብን››
‹‹ስለምን?››
‹‹አሁን ልጃቹህ ጋር ከመሄዳችሁ በፊት አረፍ ብለን መነጋገር አለብን››
‹‹ምን መነጋገር ያስፈልጋል…?በቃ እኔና እናቷ ሄደን ልጃችንን ወደቤት ይዘን እንሄዳለን….እንደምታየው  አሁን  ሁሉ  ነገር  ውብ  እና  የተስተካለከለ  ነው..አይዞህ

አታስብ…ከንተጋር  ያለንን  ነገር  እንቀጥላለን..ከሶስት  ቀን  በኃላም  ወደአልከው  ቦታ ትወስደናለህ››
መኪናውን  አቆመና  ሞተሩን  አጥፍቶ  ወደኃላ  ዞረ..ፊት  ለፊት  እያያቸው‹‹ይሄ  ነገር እንደምታስብት ቀላል ይመስላችኃላ?››
‹‹ማለት?››
‹‹አሁን ያለችበት ቤት ሄደችሁ በማንኳኳት..ነይ ልጄ በቃ አግኝተንሻል አሁን ወደቤትሽ ተመለሺ ብትሏት ..እሺ ብላ በደስታ ዘላ የምትጠመጠምባችሁ ይመስላችኃላ…እምቢ መሄድ አልፈልግም ብትል ምን ታደርጋላችሁ ?በግድ በጎረምሳ አሳዝላችሁ መኪና ውስጥ በመክተት ወደቤት ትወስዷታላችሁ….?ከዛስ..?አንድ ክፍል ውስጥ ቆልፋችሁባት በራፍ ላይ ሁለት ጠብደል ጠባቂ ታቆማላችሁ?እስኪ ንገሩኝ ምንድነው የምደርጉት?››
👍9311🤔1
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
====================

ኩማንደር አለማየሁ የአላዛርን ስልክ ተቀብሎ እሷን ወደማረፊያ ክፍል ከላካት በኃላ ጥልቅ ትዝታ ውስጥ ነው የተዘፈቀው፡፡ከእሷ ጋር ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ሁለት ጓደኞቹ ጋር የነበረው የልጅነት እና የወጣትነት ትዝታ በብዙ ውጣ ውረዶች የተሞላ፤ደስታንም ሀዘንንም በውስጡ ያጨቀ ነበር፡፡አዎ አለማየሁ እንደሚያስታውሰው ሰሎሜ ለሶስቱ ወንዶች ልክ እንደጨረቃቸው ነበረች፡፡እነሱ ደግሞ በዙሪያዋ እየተሸከረከሩ ውበቷን የሚያጎሉላት ፍንጥርጣሪ ከዋክብቶች፡፡እናም ሰሎሜ ሶስቱንም ጓደኞቾን የምትወድበት የራሷ የሆነ የተለየ ምክንያት እንደነበራት ይገምታል፡፡ለምሳሌ አላዛርን በውበቱና በልስልስ ባህሪው…እሱን በኮሚክነቱና በድፍረቱ ሁሴንን በጉብዝናው እና በብልሀቱ ፡፡

አሌክስ ፤አላዛር እና ሁሴን ከልጅነታቸው ጀምሮ በእሷ ምክንያት ችግር ውስጥ እንደገቡ ነበር፡፡አረ ከእነሱም አልፎ ወላጆቻቸውን ጨምሮ በተደጋጋሚ ጊዜ ችግር ውስጥ ገብተው እንደሚያውቀው ያስታውሳል፡፡አንድ ጊዜ የዘጠኝ አመት ገዳማ ልጆችና የሁለተኛ ክፍል ተማሪ እንደሉ ነበር፡፡ጊዜው የበልግ ዝናብ በሚዘንብበት ወቅት ስለሆነ መስኩ ጠቅላላ ውሀ ባቆሩ መሬቶችና ጭቃ ባላቆጡ መንገዶች የተሞላ ነበር፡፡ታዲያ የትምህርት ቤት የእረፍት ጊዜ ደውል ከተደወለ በኋላ ሰሎሜ ከእነሱ ተነጥላ ሳያዮት ሾልካ ትሔዳች፡፡እደዛ ያደረገችው ሽንቷ ወጥሯት ስለነበረ ወደ ሽንት ቤት ነበር፡፡ስትመለስ ግን ጎረምሳ ጎረምሳ ከሚጫወቱ የስድስተኛ ክፍል ሴት ተማሪዎች እጅ ትወድቃለች፡፡ሴቶቹ እድሜያቸው አስራዎቹ ቤት የገባና በቁጥርም ሶስት ነበሩ፡፡ዙሪያዋን ከበዋት ጆሮዋን እየቆነጠጡ ውሀ ያቆረ ሜዳ ውስጥ በባዶ እግሯቾ ገብታ እያንቦረጨቀች መዝሙር እንድትዘምርላቸው አስገደዷት፡፡
እንዳሏት እየዘለለች ስትዘምር በጭቃ የላቆጠው እና ውሀ ያቆረው መሬት እየተፈናጠረ የለበሰችውን ሙሉ ነጭ ቀሚስ እንዳልነበረ አበላሸባት…፡፡ከዛም አልፏ ፊቷና ጸጉሯ ላይ ሳይቀር ተፈነጣትጥሮባት.. በጭቃ የተሰራች አሻንጉሊት አስመሰሏት ነበር …በንዴትና በፍርሀት እንባዋ እየረገፈ ያሏትን ስታደርግ ቆየች..ልጆቹ የትምህርት ቤት የእርፍት ጊዜ ማለቁን የሚያበስር ደውል ሲደወል ነበር  ጥለዋት የሄዱት …ከዛ ምን ታድርግ ተማሪዎች ሁሉ ወደክፍል ከገቡ በኃላ እያለቀሰች ሄዳ ክፍላቸው ጀርባ  ባለ መቀመጫ ተቀመጠች፡፡እንደዛ ጨቅይታና ልብሷ ጠቅላላ ተበላሽቶ እንዴት ወደክፍል ትግባ..?አስተማሪውስ ምን ይላታል?፡፡ ወደቤት እንዳትሄድ ደግሞ ቦርሳዋ ክፍል ውስጥ ነበር፡፡
በዚያን ቀን እሱን ጨምሮ  ሁለቱ  ጓደኞቾ እረፍትን ጨምሮ  ክፍል ውስጥ ባለመኖሯ እንዴት ተደናግጠው እንደነበረ ትዝ ይለዋል፡፡‹‹የት ሄደች?››የሶስቱም ጥያቄ ነበር፡፡የሚቀርቧትን ሴቶች ሁሉ ቢጠይቁ አይተናታል የሚል ሰው አላገኙም፡፡…አስተማሪ መጥቶ ክፍለጊዜው ከመጀመሩ በፊት እሷን ፍለጋ ክፍሉን ለቀው በመውጣት የትምህርት ቤቱን አጥር ጊቢ በሳምሶማ ሩጫ ማሳስ ጀመሩ፡፡በስተመጨረሻ ከክፍላቸው ጀርባ   እንዳልሆነች  ሆና አገኞት፡፡….ሶስቱም ነበር አብረዋት ያለቀሱት፡፡በዛን ወቅት ሲያያት የተሰማውን ድንጋጤና ንዴት ትዝ አለውና ፈገግ አለ ና ወደ ትዝታው ተመለሰ፡፡
በወቅቱ ወደ ቧንቧ ወሰዷት ..ፊቷንና፤ ፀጉሯን እና እግሮቾንም  በማጣብ  የአንዳቸውን ጃኬት አለበሷት…ሶስቱም ወደክፍላቸው ገብተው የእሷን እና የራሳቸውን ቦርሳ ጭምር በመያዝ ወጡና እሷን መሀከል አድርገው በማፅናናት  ወደቤት ነበር ይዘዋት የሄድት፡፡
ከዛ ምሽቱን ሙሉ በወላጆቻቸው ተገደው ወደቤት  እስኪገቡ ድረስ ‹‹እንዴት አድርገን ነው የእኛን ንግስት ያስለቀሷትን ሴቶች በእጥፍ የምናስለቅሳቸው?›› ብለው ሲማከሩና እቅዶች ሲነድፉ አመሹ ፡፡

የእነሱን ሰሎሜን ያቆሸሾትና  ያስለቀሷት ልጆቹ ሰሚራ፤ ሳራና፤ ሰላም ይባለሉ እንደነበር አሁን ድረስ ስማቸውን ከነመልካቸው ያስታውሰዋል፡፡

‹‹እኛ ሶስት ነን አይደል?››ሲል ነበር አለማየሁ ጓደኞቹን የጠየቀው፡፡

‹‹አዎ››መለሱለት፡፡

‹‹እሺ ሰሎሜን ያስለቀሷትም  ሴቶች ሶስት ናቸው››

‹‹አዎ ትክክል ሶስት ትላልቅ ሴቶች ናቸው››መለሱለት፡፡

‹‹ጥሩ..አንዳ እንድ እንከፋፈላቸዋለን››አለ አለማየሁ፡፡
አላዛር ተቃወመ‹‹አይሆንም እኔ አልስማማም››

‹‹ለምንድነው ማትስማማው?››

‹‹እኔ ከሰሎሜ ውጭ ሌላ ሴት አልፈልግም…..የእኔን ድርሻም ከፈለጋችሁ ተካፈሉና ውሰዷት››ሲል ነበር አቋሙን ያሳወቀው፡፡

‹‹አንተ ጀዝባ የሆንክ ልጅ …የምንካፈላቸው እኮ የእኛ  ልናደርጋቸው አይደለም.. ልናሰቃያቸውና ልናስለቅሳቸው ነው…ለሰሎሜ  ልንበቀልላት ነው፡፡››

ሁሴን ‹‹ገባኝ..ለመበቀል ግን ለምን መከፋፈል አስፈለገ?››ሲል ጠየቀ

‹‹‹ለእያንዳንዳችን የደረሰችንን ሴት የሆነ ዘዴ ፈልገን በተማሪ ፊት እንድታፍር ፤ እንድታለቅስና እንድትፀፀት እናደርጋታላን፡፡ታዲያ ከሶስታችን በጣም በአስቂኝና አስደናቂ መንገድ ተጠቅሞ ማስለቀስ የቻላ የበለጠ ሰሎሜን ያፈቅራታል ማለት ነው፡፡››እንደዚህ አይነት ሀሳብና እቅድ በዛ እድሜ እንዴት ማመንጨት እንደቻለ ዛሬም ሲያስበው በራሱ ይገረማል፡፡

ሁሴን‹‹ተስማምቼለው…እኔ ከሁለታችሁም በላይ ጂኒዬስ ስለሆኑክ ካሁኑ መሸነፋችሁን እመኑ››ሲል ጎረረ፡፡

‹‹ሞኞ በትምህርት ጎበዝ ሆንክ ማለት በእንደዚህ አይነት ነገርም ጎበዝ ነህ ማለት አይደለም?››ሲል ነበር  የመለሰለት፡፡
በክርክራቸው የተሰላቸው አላዘር‹‹እባካችሁ አትጨቃጨቁብኝ. .አሁን እንዴት አድርገን ነው ሴቶቹን ምንካፈላቸው››ሲል ግራ የገባውን ነገር ጠየቀ፡፡

‹‹እጣ እንጥላለን›› ብለው ተስማሙና በዛው መሰረት ተከፋፈሉ…ለሁሉም የአንድ ሰምንት ጊዜ ተሰጣቸው፡፡

ይሄ ውይይት በተደረገ በአራተኛው ቀን ሰላም በምትባለው ልጅ ላይ የመጀመሪያው ጥቃት ደረሰባት፡፡ሁሴን ለመጀመሪያ ሁለት ቀናት ልጆቹን ስር ስራቸው እየሄደ የሆነ ቦታ ተቀምጠው ሲያወሩ በሆነ ከለላ እየተደበቀ የሚያወሩትን በመስማት መረጃ ሰበሰበ፡፡በሶስተኛው ቀን እንደምንም ወደስድስተኛ ክፍል ሾልኮ ገባና ከሰላም ቦርሳ ውስጥ አንድ ደብተር በመስረቅ ወደቤቱ ይዞ ሄዳ፡፡ከዛ ለሁለት ሰዓት ያህል  ፊደል   አጣጣሏንና የእጅ ፅሁፏን ሲለማመድ ቆየ..ከዛ እርግጠኛ ሲሆን ያሰበውን ወደማድረግ ተሸጋገረ፡፡

በእሷ ስም ለአንዱ የክፍሏ ልጅ ደብዳቤ ፃፈ፡፡

ውድ ወንድይራድ…..እንዴት ነህ..?እኔ የአንተ ፅጌረዳ ከአንተ ሀሳብና ናፍቆት በስተቀር ሰላም ነኝ፡፡ይሄንን ደብዳቤ የፃፍኩልህ ምን ያህል እንደማፈቅርህ ፊት ለፊትህ ቆሜ  ልነግርህ መድፈር ስላቃተኝ ነው፡፡ታውቃለህ ደግሞ እነዛ አስጠሊታ ሁለት ጓደኞቼ ሁል ግዜ እንደተጣበቁብኝ ነው…ሲያስጠሉ፡፡ውዴ ከአሁን በኋላ አንተን ካገኘሁ እነሱ አያስፈልጉኝም…ድሮውም እንደመደበሪያ ነበር የምጠቀምባቸው፡፡ውዴ በእርግጠኝነት አንተም እንደምታፈቅረኝ አውቃለሁ…እንደእኔ አይነት ቆንጆ እንዴት ላታፈቅር ትችላለህ?፡፡ለማንኛውም መልስህን በጉጉት እጠብቃለው፡፡ደግሞ የመልሱን ደብዳቤ ስትሰጠኝ አነዛ ቅናታም  ጓደኞቼ እንዳያዩህ ተጠንቀቅ፡፡
👍656😁4👏1
#አላገባህም


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

/////
ዘሚካኤል ስቲዲዬ ቆይቶ ገና ወደቤት እንደገባ ነበር ስልኩ የጠራው፡፡

የደወለችለት አዲስ አለም ነበረች፡፡የጠበቀው ሚካኤል ይደውልልኛል ብሎ ነበር ፡፡ከአባቱ ጋር የሚገናኙበትን ቀን ከወህኒ ቤቱ አስተዳዳሪ ጋር ተነጋግሮ እንደሚደውልለት ነገሮት ነበር፡፡እና ይሄን ቀን በፍርሀትና በጉጉት ነበር እየጠበቀ ያለው፡፡ስለአባቱ ዜና ለመስማት፡፡ስልኩን አነሳው፡፡

‹‹ሄሎ አዲስ እንዴት ነሽ?››

‹‹ሰላም ነኝ አንተስ?››

‹‹እኔ በጣም ደህና ነኝ…ሚካኤል ይደውልልኛል ብዬ እየጠበቅኩ ነበር፡፡››

‹‹ይደውልልሀል..አሁን ኩማንደሩ ቀጥሮት ሊያገኘው ሄዶል …ከእሱ እንደጨረሰ እርግጠኛ ነኝ ይደውልልሀል፡፡…አታስብ ኩማንደሩ ደግሞ ያንተ አድናቂ ስለሆነ ከአባታችሁ እንድትገናኙ ሁኔታውን ያመቻቻል….በዛ እርግጠኛ ነኝ፡፡››አለችው

‹‹ጥሩ ታዲያ አንቺ ሰላም ነሽ?››

‹‹በጣም ሰላም ነኝ…ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ  ነበር››

‹‹ምን?››

‹‹ከፀዲ ጋር እንዴት ናችሁ?››

ያልጠበቀውን ጥያቄ ነው የጠየቀችው‹‹በጣም አሪፍ ነን…ከቦንጋ ከተመለስን በኋላ በአካል ባንገናኝም በስልክ ግን በቀን ሁለት ሶስት ጊዜ እንደዋወላለን…እንደውም የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ከከተማ ወጣ ብለን ለማሳለፍ ተነጋግረናል፡፡

ግን ምነው ጠየቅሺኝ?››

‹‹ግልፅ ሆነህ ንገረኝ…ስለእሷ ምን ታስባለህ..ማለቴ አሁንም በፊት እንደነገርከኝ ታፈቅራታለህ?››

‹‹እንዴ!እንዴት በአንድ ወር ፍቅሩ ይተናል ብለሽ አሰብሽ? እንደውም ጥሩ ነገር አነሳሽልኝ…የሆነ ቀን አመቻችቼ ካንቺ ጋር መነጋገር እፈልግ ነበር..እኔ ላገባት እፍልጋለው..በቅርብ ቀን..እና እንዴት ጠይቄ ላሳምናት የሚለውን ከእኔ ይልቅ አንቺ ስለምታውቂ እንድታማክሪኝ እፈልጋለው፡፡››

‹‹እንግዲያው እንደዛ ከሆነ ሳይረፍድብህ ፍጠን››

‹‹አልገባኝም?››

‹‹ያንተን ልጅ አርግዛለች..››

የሰማውን ነገር ማመን አልቻለም…በደስታ ጮኸ…

‹‹ማለት…በፈጣሪ እየዋሸሺኝ አይደለም አይደል? ››

‹‹አርግዛለች..ለእኔም አልነገረችኝም ፡፡

በአጋጣሚ አንድ የግል ሆስፒታል  ካርድ ክፍል የምትሰራ ወዳጅ ነበረችኝ …አሁን ከደቂቃዎች በፊት ደውላ  ጓደኛሽ ፀንሳ እኛ ሆስፒታል  ለማስወረድ መጥታ ነበር…ብላ ነገረችኝ፡፡መጀመሪያ አላመንኩም ነበር..በኋላ ግን ሆስፒታሉ ድረስ ሄጄ በሌላ መንገድ እራሷ መሆኗን አረጋግጬያለው…ልታስወርደው ለተነገወዲያ ቀጠሮ አሲይዛለች….ቀጥታ ላናግራት ፍልጌ ነበር….ጭራሽ እልክ ትጋባለች ብዬ ስለፈራሁ ምንም ልላት አልቻልኩም…አንተ ምታደርገው ነገር ካለ ሞክር››

‹‹ወይኔ በፈጣሪ..ለእኔ አረገዘችልኝ…..››በበቃ ቻው አዲስ አንቺ አትጨነቂ እኔ አስተካክለዋለው፡፡

የአዲስን ስልክ ከዘጋ በኃላ ቀጥታ ልብሶቹ በሻንጣ  መክተት ነው የጀመረው፡፡ሁለት ሻንጣ ልብስና በወሳኝ የሚፈልጋቸውን ነገሮች ሰበሰበና አፓርታማውን ለቆ ወጣ …ቀጥታ ወደአዳማ ነው የነዳው፡፡

ፀአዳ ቤት ሲደርስ በራፏ ዝግ ነበር..ሊደውልላት አልፈለገም ፡፡ሻንጣውን አወረደና በራፏ በረንዳ ላይ አድርጎ እሱ መኪናው ውስጥ ሆኖ መጠበቅ ጀመረ…ከምሽቱ አንድ ሰአት ስትመጣ እሱ መኪና ውስጥ ሻንጣው በረንዳ ላይ ሆኖ ስታየው ፍፁም ነው ግራ የተጋባችው…ምስር  እሱ መሆኑን ስታውቅ ከእናቷ ተነጥላ ወደእሱ መሮጥ ስትጀምር እሱም ፈጥኖ ከመኪናው ወረደና እጇቹን እንደክንፍ ዘርግቶ ጠበቃት…ተጠምጥማበት በደስታ ጉንጩን ትስመው ጀመር…
ወደቤት እንደገቡ ፀደይ‹‹ምንድነው ጉዱ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ምንም ..ለጥቂት ሳምንታት እረፍት ስለሆንኩ እዚህ ከእናንተ ጋር ለመቆየት ወስኜ ነው፡፡››

‹‹እዚህ ከእኛ ጋር?››

‹‹አዎ ከእናንተ ጋር››
ህፃኖ ምስር ‹‹ታድለን…ታድለን›› እያለች መጨፈር ጀመረች፡፡

ፀአዳ ልጇ ምስር ፊት ምንም ማለት አልቻለችም.‹‹እንግዲያው እደቤትህ ዘና በል…እኔ ልብስ ልቀይር ››አለችና መኝታ ቤት ገባች፡፡ከዛ እራት ሰርታ በሉና ከሶስት ሰዓት በኃላ ምስርን አስተኝተው ነበር እንደአዲስ ጭቅጭቁን የጀመሩት፡፡

‹‹ምን እየሰራህ ነው?››

‹‹እንደምታገቢኝ ቃል ገብተሸ ቀለበት እስክታስሪልኝ ድረስ ከዚህ ቤት ወጥቼ ወደቤቴ አልመለስም››ሲል ቁርጡን ፍርጥም ብሎ ነገራት፡

‹‹ጭራሽ ማግባት? እየቀለድክ ነው፡፡››

‹‹በፍፅም …ብቀልድ ነው እንደዚህ አይነት እርምጃ የወሰድኩት፡፡››

‹‹ስማ..እኔ ካንተ ጋብቻ ፍቅር ምናምን አልፈልግም››

‹‹ታዲያ ምንድንው ምትፈልጊው?››

ትኩር ብላ አየችው….
‹‹ንገሪኝ ከእኔ ምንድነው የምትፈልጊው….. ?››

‹‹ካንተ ወሲብ ብቻ ይበቃኛል….ማለቴ እስከአሁን የደረግነውን ለማለት ነው …ደግሞ  አሁንም እናድረግ እያልኩህ አይደለም፡፡››

በንግግሯ ሆድን እስኪያመው ሳቀ…በመሀል ስልክ ተደወለለት ..ከወንድሙ ነበር…በጉጉት አነሳው‹‹እሺ ሚካኤል ደህና አመሸህ?››

‹‹ሰላም ነኝ…ነገ ጥዋት ሶስት ሰዓት ላይ አዳማ መገኘት ትችላለህ?››

‹‹ምነው ?አባዬን እንድናገኝ ፈቀዱልን እንዴ?››

‹‹አዎ በጣም ደስ የሚለው ደግሞ አንድ ላይ እንድናገኘው ነው ያመቻቹልን ቅር ካላለህ አዲስንና ቅዱስንም ይዘናቸው እንሄዳለን››

‹‹አረ ቅር አይለኝም ጥሩ ሀሳብ …ግን አባዬ እኔን ለማናገር ፍቃደኛ የሚሆን ይመስልሀል?››ሰሞኑን ሲብሰለሰልበት የነበረውን ስጋቱን አንስቶ ጠየቀው፡፡

‹‹ትቀልዳለህ እንዴ…ከመሞቱ በፊት ማግኘት የሚፈልገው ብቸኛ ነገር እኮ አንተን ማናገር ነው…በደስታ  ነው የሚያነባው….እንኳን በአካል አግኝተሀው አባዬ ብለህ ስጠራው ሰምቶ ይቅርና ባለፈው ፎቶህን ሳሳየው እንዴት እያገላበጠ ሲስምና ሲያለቅስ እንደነበረ እኔ ነኝ የማውቀው…በል በዛ እርግጠኛ ሁን..ምንም አትጨናነቅ፡፡››

‹‹ምን ያስፈልገዋል…?ማለት ምን ይዤለት ልሂድ?››

‹‹የሚያስፈልገወን ነገር ሁሉ አዘጋጅተናል…አንተ ደግሞ ሚፈልገውን ነገር እንጠይቀውና በሚቀጥለው ዙር ትወስድለታለህ…ደግሞ ደስ የሚለው ከቦንጋ ያመጣችሁትን ከዶ/ሩ ጋር ያደረጋችሁትን ውይይት ለኩማንደሩ አሰምቼው በጣም ነው ያዘነው..እናም አባዬን ከሌሎች እስረኞች ጋር ተቀላቅሎ እንዲኖር ወስነዋል…››

‹‹በጣም የሚያስደስት ነገር ነው እየነገርከኝ ያለሀው..ወንድሜ በጣም ጥሩ ሰው እንደሆንክ ታውቃለህ አይደል… በጣም ነው የምኮራብህ፡፡››

ሚካኤልም እንባ እየተናነቀው‹‹እኔም በጣም ነው የምኮራብህ››አለው

‹‹በቃ እሺ …...ሶስት ሰዓት ነው ያልከኝ አይደል?፡፡››

‹‹አዎ…መድረስ ትችላለህ አይደል…?››

‹‹በደንብ እንጂ ሁለት ተኩል ደርሼ ደውልልሀለው››

‹‹ጥሩ በቃ ደህና እደር››ስልኩን ዘጋ፡፡

ንግግራቸውን ሁሉ በገረሜታ ስትሰማ የነበረችው ፀደይ‹‹እርግጠኛ ነህ ግን ሁለት ተኩል ትደርሳለህ?››ስትል በፈገግታ አሾፈችበት፡፡

‹‹ትቆጪኛለሽ ብዬ ነው እንጂ እዚህ ነኝ ልለው ነበረ››

‹‹ልፋ ቢልህ ነው ….ግን ለእናንተ ደስ ብሎኛል››

‹‹ማለት?››

‹‹አንተና ወንድምህ እንዲህ እየተደዋወላችሁ በሰላም ማውራት መቻላችሁ ትልቅ ነገር ነው…አረ እንደውም ከመነጋጋርም አልፋችሁ መሞጋገስ ጀምራችኃል››

‹‹እድሜ ለአንቺ ….ባንቺ ቀናነትና ጥረት ነው ለዚህ የበቃነው….››

‹‹እኔን ማሞገሱን እንኳን ለሌላ ጊዜ አቆየው..በነገራችን ላይ የአባትህ ጉዳይ ላይ  ይግባኝ ለመጠየቅ ሚቻል ከአሆነ አንድ ጎበዝ ጠበቃ አግኝኝቼ ሁኔታውን አስረድቼው ነበር….››

‹‹በእውነት ..ታዲያ ምን አለሽ?››
👍6824👎1👏1
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

//
ራሄል በወላጆቿ ቤት ከመዋኛ ገንዳ አጠገብ ከእናትና አባቷ ጋር ተቀምጣ የጥዋት ፀሀይ እየሞቀች ነው፡፡

ፀጋ   ‹‹ አበባ ስጪኝ?››ስትል እህቷን ጠየቀች፡፡

ራሄል ከተቀመጠችበት ተነሳችና   የፀሐይ መነፅሯን ወደ ጭንቅላቷ ገፋ በማድረግ   እህቷ የፈለገችውን  አበባ ቀነጠሰችና በትናንሽ እጆቾ ውስጥ አስቀመጠችላት…ፀጋ በደስታ ፈነጠዘች፡፡
ሮቤል እና አዲሷ ረዳት የፋውንዴሽኑን ስራ ከአሰበችው በላይ  በጥሩ ብቃት እየመሩላት እንደሆነ ለሁለት ቀን ወደቢሮ ተመልሳ ባደረገችው የስራ ግምገማ መረዳት ችላለች፡፡
…እህቷን ለማስታመም በሆስፒታል ባሳለፈቻቸው አስር ቀናት ውስጥ ምንም የጎደለ እና ሳይሰራ የተወዘፈ ስራ አልነበረም…እና አሁንም ለሌላ አንድ ሰምንት ታናሽ እህቷ በደንብ እስክታገግም አብራት እንድትሆንና ቀለል ያሉ  ስራዎችን እዛው እቤት ሆና እንድትሰራ ፈቅደውላት እሷም ተስማምታ  ወላጇቾ ቤት ነው ያለችው፡፡

‹‹ኤሊ እመጣለሁ ያለው መቼ ነው?››ወ.ሮ ትርሀስ  መጽሃፏቸውን  ከጎኗቸው  ባለ የመስታወት ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠው ራሄልን  ጠየቋት።

‹‹ከሶስት እስከ  አራት ሰዓት እመጣለሁ ነበር ያለው ፡፡ ››መለሰች…ጸጋ  ራሷ ቀጥፋ የሰጠቻትን አበባ  ፀጉሯ መካከል ሻጠችላት…ራሄል  በፈገግታ እህቷን ወደራሷ ሳበችና ጉንጮን በመሳም‹‹ትንሿ እህቴ ..እንዲህ ስላሳመርሺኝ አመሰግናለው››አለቻት፡፡
በዛው ቅፅበት ወደግዙፉ ግቢ እየቀረበ የሚመጣ የመኪና ድምፅ ተሰማ ፡፡

‹‹የምትጠብቂው ጓደኛሽ  አለ እንዴ?››አቶ ቸርነት ጠየቁ፡፡

‹‹ አይ አይመስለኝም?››ራሄል እርግጠኛ ባለመሆን ጠየቀች፡፡

‹‹እንግዲያው አለም መጥታ ማንነቱን እስክታሳውቀን እንጠብቅ  ?››በማለት እናቷ ሳቁ።

አለም ወዲያው እየተፍለቀለቀች መጣች…‹‹ራሄል  ነይ እንግዳሽን ተቀበይ››

‹‹ማን ነው?››

‹‹አትንገሪያት ተብያለው…እራስሽ መጥተሸ እይው››አለችና ወደኪችኗ ተመለሰች፡፡

ራሄል.‹‹ማነው በወላጆቼ ቤት ከእኔ ጋር እንዲህ አይነት ጫወታ ለመጫወት የደፈረው?››በማለት ተነስታ ፀጋን ይዛ   ሄደች።ራሄል እና ፀጋ  ወደ ግቢው የመኪና ማቆሚያ አካባቢ ሲሄዴ ኤሊ ወደ ውስጥ ሲገባ ተመለከቱት  ።ራሄል እንዳየችው  በውስጧ የደስታ ማዕበል አጥለቀለቃት።

ባለመኪና ስትጠብቅ ባለሞተር ሰው በማየቷ ተደንቃ ‹‹ሄይ፣ እንዴት እዚህ ደረስክ? የሞተር ሳይክልህን ድምፅ አልሰማሁም።››አለችው…

ዔሊ ጎንበስ ብሎ በቀስታ ሳማት እና ፀጋን አንስቶ ካቀፋት በኃላ‹‹ሌላ አይነት  የመጓጓዣ ዘዴ ነው የተጠቀምኩት.››ሲል መለሰላት፡፡

‹‹ሞተርህ ተበላሸች እንዴ ?›› አለችና አይኖቾን ወደመኪና ማቆሚያ አዞረች  ከእሷ   ቀይ መኪና  አጠገብ የቆመ ባለ ሰማያዊ ቀለም  መኪና እያየች ግራ ተገባች።

‹‹ ያን መኪና  ከማን ነው የተዋሰከው? ወንድምህ እንደዚህ አይነት መኪና የለውም።››

ዔሊ ተነፈሰ። ‹‹እነሆ፣ ወ.ሮ ራሄል  ሞተሬን ሸጥኩት።››

ራሄል መኪናዋን በድጋሜ  ተመለከተች፣ ‹‹ሞተር ሳይክልህን አስወገድከው !አየህ እኔ ስለ አንተ የምወደው ያን  ነው ። ቆንጆ እና ፈጣን ተማሪ ነህ….ግን ለምን?››

…‹‹ደህና፣ በአንድ ወቅት አንድ ሰው እንዴት አንድ ኃላፊነት የሚሰማው ለዛውም የህፃናት ሀኪም የሆነ ሰው ሞተር ሳይክል ይነዳል ? የሚል  ጥያቄ ጠየቀኝ። እና ለእሱ መልስ ለመስጠት ብዬ ነው መኪና የገዛሁት፡፡››

ራሄል ወደ መኪናው ሄዳ እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ  ትንሽ ነካችው፣ ከዚያም ወደ ዔሊ ተመለሰች፣ ››

‹‹አስደንቀኸኛል ››አለችው

‹‹ስለሞተር ሳይክሎች ያለሽን ስሜት ስለማውቅ  እናም የፍራቻሽም ምክንያት በከፊል ትክክል መሆኑን ስላመንኩበት  ነው...››

እዛው የሳሎኑ በረንዳ ላይ ካሉ ወንበሮች አንዱን እንዲቀመጥ ሳበችለት ፀጋን በክንዱ እንዳቀፈ ተቀመጠ….ከጎኑ ሌላ ወንበር ስባ ተቀመጠች፡፡

ከዛ ሳታስበውና ምንም ሳትዘጋጅበት ትልቅ  ቁም ነገር ከአንደበቱ አፈትልኮ ወጣ  ‹‹ይህን ሁሉ  በትክክለኛው መንገድ ይፋ   ማድረግ ፈልጌ ነው …ራሄል፣ ላገባሽ እፈልጋለሁ።››አላት፡፡

ጆሮዎቾን ማመን አልቻለችም…ልቧን  ደረቷን ሰንጥቆ እንዳይወጣ የፈራች ይመስል ደግፋ ያዘችው ። በውስጧ የሚንተከተከው ደስታ እና ፍቅር እና ምስጋና መውጫ ለማግኘት እየሞከሩ በአንደበቷ ላይ ተንገዋለሉ….ማልቀስ ብቻ ነው የቻለችው፡፡

‹‹ሄይ እኔ ያን ያህል መጥፎ ነገር አልተናገርኩም….ለምን ታለቅሻለሽ?››

‹‹በጣም ደስ ብሎኝ ነው…..››ስትል በለሆሳሳ መለሰችለት፡፡‹‹እወድሀለሁ ኤሊ›› ወደ እሱ ተሳበችና ጉንጩን ሳመችው..ታፋው  ላይ የተቀመጠችው ፀጋ  በደስታ እጆቿን እያጨበጨበች በሳቅ ተንከተከተች። የእሷ ሳቅና ደስታ ወደ እነሱም ተጋባ፡፡

‹‹መጀመሪያ ዝም ብዬ ለአንቺ ምንም ሳልነገርሽ ወደቤተሰቦችሽ ሽማግሌ ለመላክ አቅጄነበር …››

‹‹እንዴ የእኔን ሀሳብ ሳታውቅ ሽማግሌ ልከህ እምቢ ብልህስ?››

‹‹ያው ምን አደርጋለው የተሰበረ ልቤን  ይዤ  የብቸኝነት ኑሮዬን ቀጥላለዋ !!››ብሎ ትከሻውን ነቀነቀ።ራሄል ጣቷን ከንፈሩ ላይ አድርጋ ሳቀች።

‹‹ ስለነርከኝ ደስ ብሎኛል፣ደግሞ ስትነግረኝ  ፀጋ በመሀከላችን መገኘት በመቻሏ  ደስታዋ ድርብ  ሆኗል … ለነገሩ እኛን አንድ ያደረገች እሷ ነበረች.››

‹‹እሺ ስላልሽኝ ደስ ብሎኛል…:በዚህ ምክንያት በህይወቴ ለሆነው ነገር እግዚአብሔርን በየቀኑ አመሰግነዋለሁ:: በአንቺ ምክንያት ህይወቴ መሉ ሆኗል››

‹‹አንተ ስጦታዬ ነህ ኤሊ ›› አለችና አቀፈችው።

‹‹አሁን እናትና አባትሽን እንፈልግ።››

ተስማሙና …ተያይዘው በአረንጓዴ ተክሎች ወደተሸፈነው ግዙፉ ጊቢ  ተያይዘው እየተሳሰቁ ሄዱ፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
96👍18
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///

ገመዶ እኩለ ለሊት ላይ ስልኩ ጮኸ….

"ምንድን ነው ነገሩ" በማለት እየተነጫነጨ በተኛበት እጁን ዘረጋና ስልኩን ከኮመዲኖ ላይ አንስቶ ጆሮው ላይ ለጠፈና ‹‹ሄሎ››አለ፡፡

‹‹ኮማንደር መስማት አለብህ ብዬ ነው…ድንገተኛ ነገር ተከስቷል."ምክትሉ ነበር፡፡ ከመኝታው ተነሳና አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠ፡፡

"…ምንድነው የተፈጠረው?"

"ከእርባታ. ቦታው …ማለቴ የቤተሰቦችህ እርባታ ቦታ፣ከዛ ነው የተደወለልን"አለው…

ከአልጋው ወርዶ ጂንስ ሱሪውን መልበስ ጀምሮ ነበር፡፡ጭንቅላቱ የፍርሀት ቅዝቃዜ ሲፈስ ታወቀው፡፡

"ምን አይነት ድንገተኛ አደጋ ነው?"
‹‹ገና አልተረጋገጠም..ኃይል ወደእዛው ልከናል፡፡›› ያልተቆለፈ ሸሚዙን ከቆለፈ በኋላ ቆሞ ጫማውን አደረገ፡፡

‹‹በቃ ቶሎ አጣርተህ ደውልልኝ…ወደእዛው እሄዳለው፣ይሄው እየወጣሁ ነው… ››ስልኩን ዘጋና ኮቱንና ኮፍያውን አድርጎ ወደ ኮሪደሩ ሮጠ።
/////

አለም በከባድ እንቅልፍ ውስጥ ነበረች፣ ለዚህም ነው የበሯን መንኳኳት በህልሟ መስሎ የተሰማት…።ህልም ውስጥ ነበረች….በመጨረሻ ተከታታይ የሆነው የጥሪ ድምፅ ከእንቅልፏ ቀስቅሷት።

"ተነሺ እና በሩን ክፈቺ."በቁጣ እየጮኸባት ነው፣ ቁጭ አለችና አልጋው ዳር ያለውን መብራት አበራችው… መብራቱ ሲበራ …. ብርሃኑ ዓይኗን አጭበረበራት።

"ገመዶ ነኝ… ክፈቺ?" ጮኸ ። ዝም አለችው፡፡

"በአስር ሰከንድ ውስጥ ካልተነሳህሽ በሩን ሰብረዋለው››

የግድግዳውን ሰዓት ተመለከተች። ከምሽቱ ስምንት ሰዓት ገደማ ነበር።

‹‹ኩማንደሩ ወይ ሰክሯል ወይም አብዷል።››ስትል አሰበች፡፡ ያም ሆነ ይህ አሁን ባለበት ሁኔታ በሯን ልትከፍትለት አልፈለገችም።

"ምን ፈለክ?"

ከእሱ መልስ ስትጠብቅ በራፉ ላይ ፈንጅ የተጣለበት ይመስል ጎጎጎጎ አለና ተከፈተ….ተንደረደረና መኝታ ቤቷ ገባ፡፡በድንጋጤ እየተንቀጠቀጠች አልጋዋ ላይ ቆመች "ምን እየሰራህ ነው?"ብላ ጮኸችበት በቆመችበት አልጋ ልብሱን እየሰበሰበች እርቃኗን ለመሸፈን እየጣረች ነው››

"አንቺን ለማግኘት ነው የመጣሁ ‹‹
ከአልጋው ላይ ጎተተና ወለሉ ላይ አቆማት፣የተጠቀለለችበትን አልጋ ልብስ ከላዬ ላይ ገፎ ወረወረው፣እርቃኗን በፓንት ብቻ ፊት ለፊቱ ቆመች፣ምን ሊያደርጋት እንደሆነ መገመት ሁሉ አልቻለችም፡፡

"ኩማንደር በሬን ገንጥለህ መኝታ ቤቴ ለመግባትህ በቂ ምክንያት እንዳለህ ተስፋ አደርጋለሁ።"

"ማብራሪያ አለኝ።" አለና መሳቢያውን ከፈተ እና ውስጡ ያሉትን ልብሶች ማተረማመስ ጀመረ።

"ንገረኝ ምን እየፈለክ ነው?."አለችና እርቃኗን ወደእሱ ሄዳ ሚያተራምሰውን  የቁምሳጥን በራፍ በዳሌዋ ገፋችና ዘጋችበት ፡፡

"ምን ፈልገህ ነው?"ዳግመኛ ጠየቀችው፡፡
"ልብስ። እንደዚህ እርቃንሽን  መውጣት ካልመረጥሽ በስተቀር  ምትለብሺው ልብስ ያስፈልግሻል››

‹‹ወደየትም አልሄድም››

" ጂንስሽ የት ነው ያለው?›› በ ወፍራም ድምፁ ጠየቀ ። "የትም አልሄድም። ስንት ሰዓት እንደሆነ ታውቃለህ?››

ድንገት ቀና ሲል ከአልጋው አጠገብ ባለው ግድግዳ ልብሷ ተሰቅሎ አየው፡፡ ጂንሱን ከተሰቀለበት ላይ አወረደና ወረወረላት፣ መያዝ ስላልቻለች ወደ ወለሉ ወደቀ።
ከጫማዋቾ ውስጥ አንዱን መረጠና ወደእግሯቾ አቀረበላት፡፡ ዝም ብላ ፈዛ ታየው ጀመር፡፡ "እሺ.. እንዳለብስሽ ትፈልጊያለሽ?"

እሱን ለማስቆጣት ምን እንዳደረገች መገመት አልቻለችም። እርቃኗን እሱ ፊት ቆማ መከራከሩ ስለደከማት ጆንሱን አነሳችና አጠለቀች ፡፡ከላይ ሹራብ ለበሰች….ከኮመዲኖ መሳቢያ ውስጥ አንድ ካልሲ አወጣችና አራግፋ አጠለቀችና ጫማዋን አደረገች፡፡ በመጨረሻም ዞር ብላ አየችው።

"እሺ ይሄው ልብስ ለብሻለሁ …አሁን ምን እየተካሄደ እንደሆነ ንገረኝ ?"

"እየሄድን  እነግርሻለው  ››አለና  እጆቿን  በመያዝ  እየጎተተ  ይዞት  ወጣ  ፡፡በንዴት እየተንቀጠቀጠች ነበር።

‹‹እንዲህ እንድታደርገኝ ማን ነው የፈቀደልህ?››

"አንገትሽን መስበር አለብኝ…..አላደረገውም››በማለት ወደእሷ ተጠጋና ከንፈሯን ሳማት።ያለተቃውሞ ተሳመችለት፡፡ምላሱን ወደ አፏ ውስጥ አስገባ። በዚህ ጊዜ በቁጣ ስሜት መነጨቀችውና እራሷን አላቀቀች፡፡

ኮትዋን ከሳሎን በራፍ አካባቢ ካለው ማንጠልጠያ አነሳችና ያዘች፡፡ ከቤት ይዞት ወጣ " በሩስ?"ብላ ጠየቀችው ።
"የሚጠግን ሰው እልካለሁ።"

"በዚህ ለሊት?"

"በፈጣሪ … በሩን እርሺው..በአካባቢው ቤትሽን በንቃት የሚጠብቁ ፖሊሶች አሉ" ብሎ ጮኸ።

‹‹የሚጠብቁ ነው ሚሰልሉኝ?››

እጇን ጨምድዶ እንደያዛት ስትጠብቀው ወደነበረ ታክሲ ውስጥ ይዞት ገባ፡፡

"በፈጣሪ ገመዶ…ምን እየተፈጠረ ነው……?ነው ወይስ እያሰርከኝ ነው?››

‹‹እያሰርከኝ ..አንቺን……?ምነው ወንጀል ሰርተሸል እንዴ?›› ፡፡

‹‹እና ምንድነው ንገረኛ….?ወደየት እንደምሄድና ለምን እንደምሄድ የማወቅ መብት አለኝ›› ።

"የእርባታ ቦታው እየተቃጠለ ነው."

‹‹የእርባታ ቦታው.?.የነጁኒዬር?››

‹‹አዎ››

‹‹ወይ..ፈረሶችህ ተረፉ?››

ፈረሶቹን ምን ያህል ይወዳቸውና በምን ያህል መጠን ይንከባከባቸው እንደነበረ ስለምታውቅ ነው ቀድማ ስለፈረሶቹ የጠየቀችው፡፡

‹‹አላውቅም…የወደመውንና የተረፈውን ስንደርስ ነው የምናውቀው፡፡››
////
ሲደርሱ እሳቱ ከፈረሶቹ ጋጣ አካባቢ እየተንቀለቀለ ነው…በአንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሚገኘው የእንጨት ፋብሪካው ከአደጋ ውጭ ነው፡፡ቢሆንም በንፋስ ታግዞ ወይም በሆነ ምክንያት እሳቱ እዛ ቢደርስ ከፍተኛ ውድመት እንደሚያስከትል የታወቀ ነው፡፡

እንደደረሱ መኪናዋ ስትቆም ኩማንደሩ ከመኪናው ወረደና ወደእሳቱ አቅጣጫ ተንቀሳቀሰ…አለም ከኋላው ተከተለችው፡፡ከአንዱ የፈረስ ጋጣ ጭስ ሲትጎለጎል ይታያል…አለም ሆዷ ተገለባበጠባት። የእሳት አደጋ መከላከያ ሰራተኞች፣ የደንብ ልብሳቸውን ለብሰው እሳቱን ለመቆጣጠር እየሞከሩ ነበር።ብዛት ያላቸው የእርባታው ሰራተኞችና የአካባቢው ኑዋሪዎች ቅጠለም አፈርም እየተጠቀሙ እሳቱ እንዳይዛመት ለመቆጣጠር እየተረባረቡ ነው፡፡
አንድ ሰው ወደኩማንደሩ ቀርቦ"በጣም ብዙ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ደርሰውበታል" ሲል ነገረው፡፡

‹‹ሰውስ አልተጎዳም?››

‹‹አንድ የተጎዳ ሰው አለ…››የሚል ድምፅ ሰማ፡፡

"ማንው የተጎድቷል?"

‹‹በጣም አሰቃቂ ትዕይንት ነበር።ከፈረስ ተንከባካቢዎች አንዱ ነው… በቂ አየር ወደ ሳምባዋ መሳብ አልቻለችም። ፈረሶችን ለማዳን ሲሯሯት አንድ እግሩም ተሰብሯል››

በዛ ቅፅበት አንድ ፈረስ እየጮኸ ነበር፣ በግልጽ ህመም ላይ እንዳለ ያስታውቃል። አለም እስካሁን ሰምታ የማያውቀው እጅግ አሳቃቂ ድምፅ ነበር የሰማችው። ገመዶ በፍጥነት ወደእዛው አመራ…ከኃላው ተከተለችው….የአቶ ፍሰሀ ቤተሰቦች በጠቅላላ በለሊት ቢጃማቸው በአካባቢው ነበሩ ፡፡መኖሪያ ቤታቸው ከእርባታው ድርጅት ብዙም ሰላማይርቅ እንደሰሙ በእግራቸው ነው ሮጠው ወዲያው ነው የደረሱት፡፡ ሳራ እያለቀሰች ነበር። ፍሰሀ

እራሱን ተቆጣጥሮ በፅናት ቆሞ ይታያል…ጁኒዬር እናቱን አቅፎ ያፅናናል፡፡ ገመዶ ወደ ጎን ገፋቸው እና እሳቱ ጠፍቶ ጭሱ ብቻ ከሚታይበት ጋጣ ውስጥ ገባ ፡፡
48👍4🔥1