አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አርባ_አምስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ናንሲ ባህሩ ዳር ቁጭ ብላለች፡፡ መርቪን ላቭሴይ አጠገቧ ተቀምጧል፡፡
የባህሩ ውሃ በማዕበል እየተገፋ ይመጣል፣ ይመለሳል፡፡ ናንሲ ዓይኗን
ጨፍናለች፡ ሌሊት በደምብ አልተኛችም:: መርቪንና እሷ
እሷ ማታ መጋጨታቸው ትዝ አላትና ፈገግ አለች ከእሱ ጋር የምር ግንኙነት
አለመመስረቷ ደስ ብሏታል፡ ለወሲብ መቻኮሉ ጥሩ
አይደለም፡፡የመጣችበትን ዓላማ ከግብ ማድረስ አለባት፡፡

ሼዲያክ የዓሳ ማጥመጃ ፤መንደርና የባህር ዳር መዝናኛ ከተማ ናት፡፡
በባህሩ ዳርቻ ላይ የዓሳ
ማጥመጃ ጀልባዎች፣ መርከቦች፣ ሌሎች ሁለት
አይሮፕላኖችና እነሱ የመጡበት አይሮፕላን ይታያል፡፡ ብዙዎቹ የአይሮፕላኑ ተሳፋሪዎች በባህሩ ዳርቻ ላይ ወዲያ ወዲህ ይላሉ፡፡

ሁለት የፖሊስ መኪኖች እየበረሩ መጥተው ጎማቸውን ሲጢጥ
አድርገው ሲቆሙ የአካባቢው ፀጥታ ታወከ፡፡ ከመኪኖቹም ውስጥ ሰባት
ስምንት ያህል ፖሊሶች እየዘለሉ ወጡ፡፡  በቀጥታ ወደ ተሳፋሪዎቹ
ማስተናገጃ ሲያመሩ የሆነ ሰው ሊይዙ የመጡ ይመስላል›› አለች ናንሲ፡
እሱም በመስማማት ራሱን ነቀነቀና ‹‹ማንን ይሆን?›› አለ፡፡
‹‹ምናልባትም ፍራንኪ ጎርዲኖን››
‹ሊሆን አይችልም እሱ እንደሆነ እንደታሰረ ነው፡፡››
አይሮፕላን ውስጥ ሲገቡ ሁለቱ ወደ ባህሩ ዳርቻ ሲያመሩ ሁለቱ ደግሞ
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ፖሊሶቹ ከመናኸሪያው ወጡና ሶስቱ መንደሩ ውስጥ መንጎራደድ ጀመሩ፡፡

ፖሊሶቹ የሆነ ሰው እንደሚፈልጉ ያስታውቅባቸዋል፡ አንዱ
የአይሮፕላኑ ሰራተኛ ከአይሮፕላኑ ሲወጣ አየችና ናንሲ ‹ፖሊሶቹ ማንን ነው የሚፈልጉት?›› ስትል ጠየቀች:

ሰውየው ምስጢር ለማውጣት እየተጠራጠረ ሄሪ ቫንዴርፖስት
የተባለውን ሰው ነው የሚፈልጉት፤ ስሙ የሀሰት ነው›› አለ፡፡

ናንሲ ግንባሯን ከሰከሰችና ይሄ ልጅ ከኦክሰንፎርድ ቤተሰብ ጋር ተቀምጦ የነበረው ነው፡ ልጁ የማርጋሬትን ልብ ሳይሰርቅ አልቀረም›› ስትል
ገመተች ናንሲ፡

መርቪን ‹‹ከአይሮፕላኑ ወጥቶ ሄዷል እንዴ? እኔ ከአይሮፕላኑ ሲወጣ
አላየሁትም›› አለ፡፡

‹‹እኔም አላስተዋልኩም›› አለች ናንሲ፡

‹‹ልጁ አጭበርባሪ ይመስላል››

‹‹እውነት?›› አለች ናንሲ፡ እሷ ልጁ ከጥሩ ቤተሰብ የተገኘ ነበር የመሰላት፡ ‹‹ጥሩ ባህሪ አይቼበታለሁ: ማርጋሬት ከልጁ ጋር ፍቅር ሳይዛት አልቀረችም፡፡ ፖሊስ እንደሚፈልገው ስታውቅ ታዝናለች›› አለች

‹‹ወላጆቿ ፖሊስ እጅ መውደቁ ደስ ሳያሰኛቸው አይቀርም›› አለ
መርቪን፡፡ናንሲ ስለወላጆቿ ግድ የላትም፡ በአይሮፕላኑ መብል ክፍል ውስጥ
ሎርድ ኦክሰንፎርድ ያሳዩት የነበረው ጋጠወጥ ባህሪ መርቪንና ናንሲ
ያስታውሳሉ፡ ለእንደዚህ አይነት ሰው ውርደት ሲያንሰው ነው ናንሲ ከእንደዚህ አይነት ወመኔ ጋር ማርጋሬት ፍቅር ስለያዛት አዘነችላት፡

መርቪንም ቀጠለና ‹‹እኔ ስለሌላ ሰው ማውራት አልፈልግም›› አለ፡
ናንሲ ጆሮዋን ቀሰረች፡
መርቪን ቀጠለና ‹‹የተገናኘነው ከጥቂት ሰዓታት በፊት ስለሆነ በደምብ ላውቅሽ እፈልጋለሁ፡›› ናንሲም እርግጠኛ መሆን አትችልም አንተ ደደብ አለች በሆዷ
ሆኖም ይህን ማለቱ አስደስቷታል፡ ምንም መልስ አልሰጠችውም፡፡

‹‹ብፊት አንቺን ኒውዮርክ አድርሼ ወደ ማንቼስተር መመለስ ነበር የማስበው፡፡ አሁን ግን አላደርገውም›› አላት፡

ናንሲ ፈገግ አለች ይህን እንዲል ነበር ስትጠብቅ የነበረው:፡ እጇን ሰደደችና እጁን ያዝ አደረገች፡፡ ‹‹ይህን ስላልክ ደስ ብሎኛል›› አለችው፡

‹‹ደስ ብሎሻል? ችግሩ ከዚህ በኋላ አትላንቲክን ማቋረጡ የሚቻል አይሆንም፡፡ የጦር መርከቦች ብቻ ናቸው ይህን ማድረግ የሚችሉት፡››ናንሲ በመስማማት ራሷን ነቀነቀች፡
አሁን ከተለያየን ምናልባትም የምንገናኘው ከብዙ ጊዜ በኋላ ነው፡፡።
እኔ ግን ላጣሽ አልፈልግም›› አለ መርቪን፡፡

‹‹እኔም እንደዚያው›› አለች ናንሲ፡፡

‹‹ከእኔ ጋር ኢንግላንድ ትሄጃለሽ?›› ሲል ጠየቃት፡፡
ናንሲ ፈገግታዋ ከፊቷ ላይ ጠፋ፡፡ ‹‹ምን አልክ?››
‹‹ከእኔ ጋር ወደ ኢንግላንድ እንመለስ፡፡ ሆቴል ውስጥ ትቆያለሽ ወይም ቤት ትገዣለሽ ወይም አፓርትማ ትከራያለሽ››

ናንሲ ያቀረበላት ሃሳብ በጣም አስቆጣት፡፡ ጥርሷን በንዴት አፋጨች፡፡
‹‹አብደሃል እንዴ?›› አለችው፡፡ መርቪንን ፊት ለፊት ማየት ጠልታ
ፊቷን አዞረች፡፡ በእጅጉ አዘነችበት፡፡
መርቪን አባባሏ አስደነገጠው ግራ አጋባው፡፡ ‹‹ምነው?›› ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹እኔ አሜሪካ ውስጥ የራሴ ኑሮ፣ ቤት፣ ሁለት ልጆችና በሚሊዮንዐየሚቆጠር ዶላር ገቢ የሚያስገኝ ፋብሪካ አለኝ፡፡ አንተ እንዴት ይህን ሁሉ እርግፍ አድርጌ ትቼ በማንቼስተር ሆቴል እንድቀመጥ ትጠይቀኛለህ?››

‹‹ይህን ካልፈለግሽ ከእኔ ጋር ተጠቃለይ››

‹‹እኔ እኮ ባገሬ የተከበርኩ ሴት ነኝ እንደ ቅምጥ ልኖር አልችልም፡››

‹‹ይኸውልሽ ልንጋባ እንችላለን፤ ይህን አረጋግጥልሻለሁ፧ እኔ አሁን
በዚህ ደቂቃ ውስጥ እንድትወስኚ አይደለም የጠየቅሁሽ››

‹‹ይህ አይደለም ዋናው ነጥብ መርቪን›› አለች ‹‹እኔን የገረመኝ ሁሉን
ጣጥለሽ ተከትለሽኝ ኢንግላንድ ነይ ያልከኝ ነው፡፡››
‹‹ታዲያ እንዴት ነው አንድ ላይ ልንኖር የምንችለው?››
‹‹ታዲያ ጥያቄውን መጠየቅ ሲገባህ ወደ መልሱ ሄድክ››
‹‹አንድ መልስ ስላለ ብቻ ነው ይህን ያልኩት››
‹‹ሶስት መልሶች ናቸው ያሉት፤ አንተ እንዳልከው አንተን ተከትዬ ወደ
ኢንግላንድ መመለስ ወይም አንተ ወደ አሜሪካ መጥተህ ከእኔ ጋር መኖር
ወይም ሌላ ቦታ ለምሳሌ ቤርሙዳ እንኖራለን›› አለች፡፡
በአባባሏ አልተደሰተም፡፡ ‹‹አገሬ ጦርነት ላይ ነች፤ እኔም የድርሻዬን ማበርከት አለብኝ፤ ጦርነት ውስጥ ገብቼ ለመዋጋት እድሜዬ ቢያልፍም ለአየር ኃይሉ የአይሮፕላን ሞተሮች ሰርቼ አቀርባለሁ፡፡ በእዚህ መስክ ከእኔ የተሻለ እውቀት ያለው የለም፡፡ አገሬ በጣም ትፈልገኛለች››

አሁን ያላት ነገሩን አባባሰው፡ ‹‹ለምንድነው የእኔ አገር እኔን
እንደማትፈልገኝ አድርገህ የምታስበው?›› አለች እኔ የወታደር ጫማ አመርታለሁ፡፡ አሜሪካ ጦርነቱ ውስጥ ከገባች ብዙ የወታደሮች ጫማ
ያስፈልጋታል››
‹‹እኔ ማንቼስተር ውስጥ ፋብሪካ አለኝ››
‹‹እኔ ደግሞ ቦስተን ውስጥ ካንተ የበለጠ ፋብሪካ አለኝ››
‹‹ታዲያ ሴት እንደ ወንድ እኮ አይደለችም››
‹ሴት ከወንድ እንዴት ታንሳለች አንተ ጅል!›› ብላ ጮኸችበት፡፡
ጅል› ማለቷ ወዲያው ጸጸታት፡፡ ፊቱ ቅጭም ሲል ታያት፡፡ በጣም
እንዳበሳጨችው ገባት፡፡ ከወንበሩ ተነሳ፡፡ እንደከፋው እንዳይሄድ አንድ ነገር
ማለት ብትፈልግም ትክክለኛው ቃል አልመጣላት አለ፡፡ እሱም አፍታም ሳይቆይ ጥሏት ሄደ፡፡

ምን ማለቴ ነው? አለች ምርር ብሏት፡ አባባሉ  ቢያበሳጭም ስላስከፋችው ደግሞ ተናደደች፡፡ በዚህ ሁኔታ እንዲርቃት አልፈለገችም ወዳዋለች፡ ወንዶችን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ለውጥ ማምጣት እንደማይቻል
እያደር ገብቷታል፡፡ ወንዶች ከወንዶች በኩል
የሚመጣውን ጠብ ለምደውታል፡ ከሴቶች የሚመጣውን ግን መቀበል ይከብዳቸዋል፡፡ በንግድ
ስራዋ ላይ ከሰራተኞች የሚመጣ ችግር ሲገጥማት ድምጿን አለስልሳና
አለዝባ ትመልሳቸዋለች እንጂ አታካሮ አትገጥምም፡፡ አሁን ግን ያ ባህሪዋ ሸሽቷት በአስር ዓመት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ልቧን የወሰደውን ሰው
አበሳጭታ አባረረችው፡
👍19
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አርባ_ስድስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


መጋዘኑ ውስጥ አምጥቶ ሲወረውራት ክርኗና ጉልበቷ በመጎዳቱ ቁስሉ ጠዘጠዛት፡፡ ‹‹አንተ አሳማ!›› ብላ ፒተርን በሌለበት ተሳደበች፡፡
ጫማዋን አጠለቀችና ቦርሳዋን አንስታ ዙሪያውን ቃኘች። ሌላ በር አገኘችና ለመክፈት ብትሞክርም በጥብቅ የተዘጋ በመሆኑ መክፈት አልቻለችም::

ቤቱ ከባህር ዳርቻው የራቀ ቢሆንም የአይሮፕላኑ ተሳፋሪዎች ወይም
ሌላ ሰው በዚያ በኩል ሊያልፍ ይችላል፡፡ ናንሲም ጉሮሮዋ እስኪሰነጠቅ
‹‹የሰው ያለህ!›› ስትል ጮኸች፡

ጉሮሮዋ ደርቆ ድምጿ እንዳይዘጋ በየአንድ ደቂቃ ልዩነት አንድ ጊዜ
መጣራቷን ቀጠለች፡
ሁለቱም በሮች በወፍራም እንጨት የተሰሩና ግጥም ያሉ በመሆናቸው
ዲጂኖ ወይም ሌላ ብታገኝ ሰብራ ወይም ፈልቅቃ ትከፍተው ነበር፡፡
ምናልባትም አንድ የሆነ የእጅ መሳሪያ አገኝ ብላ አካባቢውን ቃኘች፡፡ የቤቱ
ባለቤት ዕቃውን በስርዓት የሚይዝ ኖሮ የእጅ መሳሪያዎቹን መጋዘኑ ውስጥ አልተዋቸውም፡፡ መጋዘኑ ውስጥ አንድም የሚታይ የአትክልት መኮትኮቻም ሆነ አካፋና ዶማ የለም፡፡

እንደገና ‹‹የሰው ያለህ!›› መልስ የለም፡፡

ቁጭ ብላ መተከዝ ሆነ ያላት አማራጭ፡ ኮቷን ይዛ በመምጣቷ ብርዱ
ብዙም አላስቸገራትም፡፡ መጣራቱን ባታቆምም ጊዜ እያለፈ ሲሄድ ተስፋዋ
እየተሟጠጠ ሄደ፡ ይሄን ጊዜ ተሳፋሪዎቹ አይሮፕላኑ ላይ እንደገና እየገቡ
ይሆናል፡፡ ጥቂት ቆይቶ እሷን ጥሎ ይበራል፡፡
በአሁኑ ሰዓት እያስጨነቃት ያለው ኩባንያውን ማጣቱ አይደለም፡፡አይበለውና ለሳምንት ያህል ሰው ወደ መጋዘኑ ዝር ባይል ምን ይውጣታል፡ እዚሁ ልትሞት አይደል፡፡ ይህም ጭንቀት ላይ ስለጣላት ያለማቋረጥ
ጩኸቷን አስነካችው፡፡

ጥረቷ ሁሉ አለመሳካቱን ስታውቅ ዝም ብላ ቁጭ አለች፡፡ ፒተር ክፉ
ሰው ቢሆንም ነፍሰ ገዳይ ስላልሆነ እዚህ እንድሞት አይተወኝም ብላ ገመተች፡፡ ሼዲያክ ፖሊስ መምሪያ ስልክ ደውሎ ከመጋዘኑ እንዲያወጧት ይነግራቸው ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከቦርድ ስብሰባው በፊት
አይነግራቸውም፡፡ ያለችበት ቦታ የማያሰጋ ቢሆንም ስጋት መፍጠሩ አልቀረም፡ ፒተር ካሰበችው በላይ ጨካኝ ቢሆንስ! ቢረሳትስ? ቢያመውስ?
ወይም የሆነ አደጋ ቢገጥመውስ? ታዲያ ከዚህ ማጥ ውስጥ የሚያወጣት
መቼም ማነው?

የአይሮፕላኑ ሞተሮች ሲያስገመግሙ ስትሰማ የነበራት ተስፋ ሁሉ ጨለመ  የገዛ ወንድሟ ለክፉ እንደዳረጋት መርቪንም ሊደርስላት እንደማይችል አወቀች፡፡ መርቪን ይህን ጊዜ አይሮፕላኑ ውስጥ ቁጭ ብሎ የአይሮፕላኑን መነሳት እየጠበቀ ይሆናል፡፡ አይሮፕላኑ ውስጥ ሲያጣት ‹ምን ሆና ይሆን?› ማለቱ ባይቀርም በመጨረሻ የተለያዩት ‹‹አንተ ጅል!›› ብላ ሰድባው ስለሆነ ከእሷ ጋር አብቅቷል ብሎ ያስብ ይሆናል፡፡እንግሊዝ አገር ተከትለሽኝ  ነይ ማለቱ ብልግናውን ያሳያል፡ ሆኖም
ማንም ወንድ ይህን ስለሚል መናደድ አልነበረባትም፡፡ የተለያዩት በጥል ስለሆነ ካሁን በኋላ እንደማታገኘው ተገነዘበች፡፡ ‹‹ኩባንያዬንም ተነጠቅሁ፣
መርቪንንም ተነጠቅሁ፣ በረሃብም እሞታለሁ›› ስትል አላዘነች፡፡

ጉንጯ ላይ የፈሰሰውን እንባ በእጅጌዋ ጠረገች፡፡ ከእዚህ ችግር ለመውጣት ወገቧን ጠበቅ ማድረግ እንዳለባት ተገነዘበች፡፡ ከዚህ መውጪያ መንገድ መኖር አለበት፡፡ በዙሪያዋ በሩን ለመስበር የሚጠቅም አንዳች መሳሪያ ካለ ቃኘች፡ ግድግዳውን በጥፍሮቻቸው ፍቀው ከእስር ያመለጡ እስረኞች እንዳሉ  አስታወሰች፡፡ እሷ ደግሞ የዓመታት ጊዜ
የላትም፡፡ ከጥፍር የጠነከረ መሳሪያ ያስፈልጋታል፡፡ ቦርሳዋን ፈታተሸች፡፡
ከዝሆን ጥርስ የተሰራ ማበጠሪያ፣ ሊፒስቲክ፣ መሃረብ፣ የባንክ ቼክ ቡክ፣
ገንዘብ፣ ከወርቅ የተሰራ ብዕር አላት፡፡ ሁሉም በር ለመክፈት አይጠቅሙም
የለበሰችውን ልብስ ተመለከተች፡፡ ቀበቶ ታጥቃለች: የቀበቶ ማያያዣው
ምናልባት በሩን ለመቦርቦር ሊጠቅም ይችል ይሆናል፡ ቡርቦራው ረጅም ጊዜ
ሊወስድ ይችላል ነገር ግን ከዚህ ሌላ አማራጭ የለም፡፡

ወደ በሩ አመራች፡፡ በሩ ከወፍራም እንጨት የተሰራ ነው፡፡ በሩን በሙሉ መቦርቦር አይኖርባትም፡፡ የተወሰነ ጥልቀት ከቦረቦረች ሊሰበር ይችላል፡፡ እንደገና ለእርዳታ ተጣራች፡፡ የሚሰማ የለም፡፡ቀበቶዋን ስትፈታ ቀሚሷ ወለቀ፡  ከዚያም ቀሚሷን አጠፈችና
አስቀመጠችው፡ የሚያያት ሰው ባይኖርም የሚያምር ፓንት አድርጋለች፡፡

በአራት ማዕዘን ቅርጽ ቦረቦረች፡ የቀበቶው ማያያዣ ጠንካራ ባለመሆኑ
ተጣመመ: ቢሆንም ቡርቦራዋን ቀጠለች፡፡ በመሃል በመሃል የድረሱልኝ
ጥሪዋን ታሰማለች፡፡ በትዕግስት ስትፈቀፍቅ የእንጨት ፍግፋጊ መሬቱ ላይ መርገፍ ጀመረ፡፡ እንጨቱ ለስለስ ያለ ነው፡፡ አየሩ እርጥበት ስላለው
ቡርቦራዋን በተስፋ ቀጠለች፡፡ ስትቦረቡር የቀበቶው ማያያዣ እየወለቀ
ያስቸግራታል፡፡ እያነሳች ትቀጥላለች፡፡  አምስት  ስድስት ጊዜ እየወደቀ
እያነሳች ብትቦረቡርም ስራው ፈቀቅ አልል ሲላት ለቅሶዋን ለቀቀችው፡
በሲቃ በሩንም በጡጫ ደበደበች፡፡

ከውጨው ድምጽ ተሰማ፡፡ ‹‹ሰው አለ እዚህ›› አለ ድምጹ፡፡

ድምጹን ስትሰማ በሩን መደብደቧን አቆመች፡፡ በትክክል ድምጽ
ሰምታለች፡፡ ‹‹የሰው ያለህ! ከዚህ አውጡኝ›› አለች፡፡
‹‹ናንሲ አንቺ ነሽ?››
ናንሲ ልቧ በደስታ ዘለለ፡፡ የሰማችው ድምጽ የእንግሊዛውያን ቅላጼ
ያለው ነው፡፡ ድምጹንም አወቀችውና ‹‹መርቪን! ተመስገን አምላኬ!›› አለች፡፡
‹‹አንቺን ያልፈለግሁበት ቦታ የለም፡፡ እዚህ ምን ትሰሪያለሽ?››
‹‹ከዚህ ማጥ አውጣኝ መርቪኔ››

መርቪን በሩን ነቀነቀው፡፡ ‹‹ተዘግቷል!›› አላት
‹‹በጎን በኩል ና››
‹‹መጣሁ››
‹‹መርቪን?!››
‹‹በሩ ተቀርቅሯል፡፡ ትንሽ ጠብቂኝ›› አለ መርቪን፡፡
‹‹በፓንትና በስቶኪንግ ብቻ መሆኗ ትዝ አላትና ገላዋን በኮቷ ሸፈነች፡
ጥቂት ደቂቃ ቆይቶ በሩ ወለል ብሎ ተከፈተ፡፡ ሮጣ መርቪን ደረት ላይ
ተለጠፈች፡፡ ‹‹እዚህ ሞቼ እቀር ነበር›› አለችና ለቅሶዋን ለቀቀችው::
መርቪንም ደረቱ ላይ እንደተለጠፈች ጸጉሯን እያሻሽ ‹‹አይዞሽ
አይዞሽ!›› አላት፡፡
‹‹ፒተር ነው እዚህ የዘጋብኝ›› አለች ዓይኗ እምባ አቆርዝዞ::
‹‹ይሄ ወንድምሽ የሆነ በድብቅ የሚሰራው ነገር ሳይኖር አይቀርም፡፡
ወንድምሽ ርጉም ሰው ነው፡፡››
በአሁኗ ደቂቃ ናንሲ  ስለወንድሟ ሳይሆን ስለመርቪን ነው
የምታስበው፡፡ በእምባ በተንቆረዘዙ ዓይኖቿ መላ አካላቱን ቃኘችና ጊዜ
ሳታጠፋ ፊቱን አገላብጣ ሳመችው፡፡ ለጠቀችና ከንፈሮቹን በስሜት
ጨመጨመቻቸው፡ በዚህ ጊዜ የወሲብ ፍላጎቷ በእጅጉ ተነሳሳ፡፡ እሱም
አላሳፈራትም፡፡ እጆቹን ሰደደና ደረቱ ውስጥ ከቶ እቅፍ አደረጋት፡ እሷም
የእሱን ገላ ስለተራበች ከእቅፉ ውስጥ መውጣት አልፈለገችም፡: እጆቹን ወደ
ቂጧ ሲሰድ ፓንቷን ነካና ደንገጥ ብሎ አቆመ:

‹‹ቀሚስሽ የት ሄደ?›› ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹በሩን ለመፈግፈግ ብዬ ቀበቶዬን ፈትቼው ስለነበር ቀሚሴም ያለቀበቶ
ወገቤ ላይ መቆም ስላልቻለ አሽቀንጥሬ ጣልኩት›› አለች እየሳቀች፡፡
‹‹እንዴት ጥሩ አጋጣሚ ነው›› አለና እጁን ሰዶ ቂጧንና ጭኗን መደባበስ ያዘ፡፡ በዚህ ጊዜ ብልቱ ቆሞ ሆዷን ሲነካካት ታወቃት፡ እሷም ሱሪው ውስጥ እጇን ከታ ብልቱን ታሻሸው ጀመር፡
👍191🥰1
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አርባ_ሰባት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ከሼዲያክ ወደ ቤይ ኦፍ ፈንዲ

አይሮፕላኑ ከካናዳ ወደ ኒውዮርክ ሲያቀና ማርጋሬት በጭንቀት ተወጥራለች ሄሪን ምን ዋጠው?› እያለች ታስባለች፡፡

ፖሊሶች ሄሪ በሃሰት ፓስፖርት እንደሚጓዝ አውቀዋል፡፡ ተሳፋሪዎቹም
ይህን ነው የተገነዘቡት፡ ፖሊሶቹ እንዴት እንደደረሱበት አልገባት ብሏታል ከያዙት ምን እንደሚያደርጉት ነው ያልታወቀው:: ምናልባትም ወደ እንግሊዝ አገር ይመልሱትና ጌጣጌጦቹን በመስረቁ እስር ቤት ይወረውሩት ይሆናል፤ ወይም ወደ ጦር ሰራዊት ውስጥ ይጨምሩታል። ታዲያ እንዴት ልታገኘው ነው?

እስካሁን እንዳልያዙት ግን አውቃለች፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ ያየችው ሼዲያክ ላይ አይሮፕላኑ ሲያርፍ ወደ መታጠቢያ ቤት ሲገባ ነው፡ ታዲያ ያኔ ይሆን ያቀደው? ችግር እንደደረሰበት አውቋል ማለት ነው፡፡
ፖሊሶቹ አይሮፕላኑን በሙሉ ቢያስሱም አላገኙትም፡፡ አይሮፕላኑ ሲያርፍ ሾልኮ ጠፍቷል ማለት ነው:: ታዲያ የት ሄደ? ምናልባትም
ከአይሮፕላኑ ወርዶ ጫካ ጫካውን እያሳበረና ሊፍት እየጠየቀ ሄዶ ይሆናል፡
ታዲያ ከዚህ በኋላ በዓይነ ስጋ ታየው ይሆን?

በዚህ ተስፋ መቁረጥ እንደሌለባት ተገንዝባለች፡፡ ሄሪን በማጣቷ ብትጎዳም ናንሲ አለችላት፡፡

አባቷ  ዓላማዋን ከማሳካት አያግዷትም፡ ለራሳቸው  ሁሉ ነገር የጠመመባቸውና ስደተኛ ስለሆኑ የማስገደድ ኃይላቸው ተዳክሟል፡ ሆኖም እንደ ቆሰለ አውሬ እንደገና አገርሽቶባቸው ዓላማዋን የሚያሰናክል ነገር ያደርጉ ይሆናል፡፡
አይሮፕላኑ ሽቅብ መጎኑን ጨርሶ የመቀመጫ ቀበቶዋን ፈትታ ናንሲን ለማነጋገር ሄደች።

አስተናጋጁ ለምሳ ጠረጴዛ እያዘጋጀ ነው፡፡ አባቷ ቦታቸው ላይ ቁጭ
ብለዋል ኦሊስ ፊልድ ከፍራንክ ጎርደን ጋር በካቴና ተጠፍሮ ቁጭ ብሏል፡
ማርጋሬት ወደ ሙሽሮቹ ክፍል ሄዳ ደጋግማ አንኳክታ ምላሽ ስታጣ በሩን
ከፈተች፤ ማንም የለም፡፡

በድንጋጤ ክው አለች፡፡

ምናልባትም ናንሲ መታጠቢያ ክፍል ውስጥ እየተቆነጃጀች ይሆናል፡
መርቪን ላቭሴይ የት ሄደ? ወደ መታጠቢያ ክፍል የሄደ ከሆነ ታየው ነበር ክፍሉ ውስጥ አንድ ቦታ ተደብቀው እንደሆን ቃኘች፡፡ ነገር ግን ምንም መደበቂያ የለም፡፡

የናንሲ ወንድም ፒተርና ጓደኛው የሙሽሮቹ ክፍል አጠገብ ተቀምጠዋል፡ ‹‹ሚስስ ሌኔሃን የት ነች?›› ስትል ጠየቀችው ፒተርን

‹‹ሼዲያክ ላይ ነው የወረደችው››

‹‹ምን አልክ?›› ስትል ጠየቀችው ‹‹አንተ እንዴት አወቅህ?››

‹‹ነግራኛለች››

‹‹ለምን ግን?›› ስትል ጠየቀችው ‹‹ለምንድነው የወረደችው?››

ፒተር የተሰደበ ያህል ተሰማው፡ ‹‹እኔ እንጃ›› ሲል መለሰላት፡ ‹‹ወደ ኒውዮርክ እንደማልሄድ ለፓይለቱ ንገርልኝ ነው ያለችኝ›› አላት ፊቱን አኮሳትሮ፡፡

ማርጋሬት ፒተርን በጥያቄ ማጣደፍ ነውር መሆኑን ብታውቅም አጥብቃ መጠየቁን አላቋረጠችም:፡ ‹‹ናንሲ የት ሄደች?››

ፒተር በዚህ ጊዜ አጠገቡ ያለውን ጋዜጣ አነሳና ‹‹እኔ የማውቀው ነገር የለም›› ሲል መልስ ሰጥቷት ማንበቡን ቀጠለ

ማርጋሬት ሆድ ባሳት፡ ናንሲ እንዴት እንዲህ ታደርጋለች አለች ምን ያህል በእሷ ላይ ተስፋዋን እንደጣለች ታውቃለች፡ ሆኖም
ነገር ሳይገጥማት ከመንገዷ አልተስተጎለችም መልእክት ትታ ይሆናል።

ከአስተያየቱ የነገራት ውሽቱን እንደሆነ ጠረጠረች ማርጋሬት እንደ ፖሊስ ስለመረመረችው ደስ አላለውም፡፡ በደመነፍስ ‹‹እውነቱን አይደለም
የነገርከኝ›› ስትል አፈጠጠችበት፡፡ አባባሏ ትክክል ባይሆንም ምላሹን ግን ትጠብቃለች፡፡

ፒተር ፊቱ በንዴት ቲማቲም መስሏል፡ ‹‹እንደ አባትሽ ጋጠወጥ ነሽ ከፊቴ ጥፊ!›› አላት፡

የፒተር ስድብ አንገቷን አስደፋት። ያባትሽን መጥፎ ባህሪ ይዘሻል ከሚል ስድብ በላይ የምትጠላው ነገር የለም፡፡ ምንም ሳትተነፍስ ውልቅ ብላ ሄደች፤ በዓይኗ እንባ እንደሞላ አልፋ ስትሄድ ውቧን የመርቪንን ሚስት ዳያና ላቭስሌይን አየቻት። አይሮፕላኑ ውስጥ ያለው ተጓዥ በሙሉ ባሏን
ከድታ ከፍቅረኛዋ ጋር ስለኮበለለችው ሚስትና መልሶ በእጁ ለማስገባት አገር አቋርጦ ስለተከተላት ባሏና ቦታ አጥቶ ባሏ ከሞተባት ሴት ጋር በሙሽሮች ክፍል ውስጥ ለመዳበል የመገደዱን ወሬ በደስታ እየተቀባበለ ሲያወጋ ነው የሰነበተው፡፡ ማርጋሬት ባሏና ናንሲ የት እንደገቡ ዳያና ታውቅ እንደሆን መጠየቅ ፈለገች፡፡ በርግጥ ይህን ጥያቄ መጠየቅ የሚያሳፍር ቢሆንም መጥፋታቸው አሳስቧታል፡፡ ዳያና አጠገብ ተቀመጠችና ‹‹ይቅርታ መርቪንና ናንሲ የት እንደገቡ ታውቂ ይሆን?›› ስትል ጠየቀቻት፡ ዳያና ጥያቄው አስገርሟት ‹‹ምን ሆኑ? በሙሽሮች ክፍል ውስጥ የሉም እንዴ?››

‹‹ጭራሽ አይሮፕላኑ ውስጥ የሉም፡፡ እኛ ስንሳፈር እነሱ ቀርተዋል››

‹‹እውነት?›› ዳያና ደነገጠች አጠፋፋቸውም እንቆቅልሽ ሆኖባታል፡
‹‹እንዴት ሊሆን ይችላል? አይሮፕላኑ አመለጣቸው እንዴ?››

‹‹የናንሲ ወንድም ጉዞውን ለማቋረጥ ወስነዋል ቢልም አላመንኩትም›› አለች ማርጋሬት፡፡

ሁለቱም ለኔ የነገሩኝ ነገር የለም›› አለች ዳያና፡፡ ‹‹ብቻ ክፉ ነገር.አይድረስባቸው::››

‹‹ምን ማለትሽ ነው ማርዬ?›› ሲል ጠየቃት ፍቅረኛዋ፡፡

‹‹ክፉ አይንካቸው ነው ያልኩት?››

ማርጋሬትም የዳያናን ሃሳብ መቀበሏን ራሷን በመነቅነቅ ገለጸች፡

‹‹ወንድምየውን ግን አላመንኩትም፡፡ የተናገረው ውሸት ይመስለኛል››

ማርክም ቀበል አደረገና ‹‹እኔም ይመስለኛል፡፡ አሁን አየር ላይ ስለሆንን የሚሆነውን ከመጠበቅ በስተቀር ማድረግ የምንችለው ነገር የለም››
‹‹ከዚህ በኋላ የሚያደርገው ነገር አያገባኝም›› አለች ዳያና መናደዷ በግልጽ እየታወቀባት፡፡ ‹‹የአምስት ዓመት ባሌ ስለሆነ ግን ክፉ እንዲያገኘው አልፈልግም፤ ያስጨነቀኝ ደግሞ ይኸው ነው››

‹‹አሜሪካ ስንደርስ ከእሱ መልእክት እናገኝ ይሆናል›› አለ ማርክ በማስተዛዘን አይነት፡፡

‹‹እስቲ እሱ ይሁነና›› አለች ዳያና፡፡

አስተናጋጁ የማርጋሬትን ክንድ ነካ አደረገና ‹‹ክብርት ማርጋሬት ምሳ ደርሷል፧ ቤተሰቦችሽ ለመብል ተሰይመዋል›› አላት

‹‹አመሰግናለሁ›› አለች ማርጋሬት ‹የምግብ አፒታይቴ ተዘግቷል፡፡››

ማርጋሬት ለመሄድ ስትነሳ ዳያና ‹‹ከናንሲ ጋር ወዳጅ ናችሁ?›› ስትል ጠየቀቻት፡፡
በፋብሪካዋ ውስጥ ስራ ልትቀጥረኝ ቃል ገብታልኝ ነበር›› አለች ማርጋሬት በምሬት፡፡ ከንፈሯን እንደነከሰች ዞራ ሄደች፡፡

እናትና አባቷ እንዲሁም እንዲሁም ፔርሲ የመጀመርያው ዙር ምግብ
ቀርቦላቸዋል፡ ማርጋሬትም እንደተቀመጠች ‹‹ይቅርታ አባባ ስለዘገየሁ››
አለች፡፡ የቀረበላትንም ምግብ ትቆነጣጥራለች፡ አልቅሽ አልቅሽ አላት፡ ሄሪና
ናንሲ ሳይነግሯት እብስ ብለዋል፡ አሁን የሚረዳት የለም፡ እንደ እህቷ
ኤልሳቤት ለመኮብለል አስባ ነበር አሁን ግን ሁሉ ነገር ተበላሽቶባታል፡

ሁለተኛው ዙር ምግብ ቀረበ፡፡ ሾርባ ነው፡፡ ሾርባውን አንድ ጊዜ ፉት
አደረገችና ተወችው: ድካምና ንዴት በአንድ ላይ ተሰማት አሟታል፡ የምግብ ፍላጎቷ ተዘግቷል፡ ምቹው አይሮፕላን እስር ቤት
ሆኖባታል፡ ለሃያ ሰባት ሰዓት ስለበረሩ ጉዞው ሰልችቷቸዋል፡ እናቷ
👍22
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አርባ_ስምንት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ድንገት የሞተሩ ድምጽ ተለወጠ፤ሁሉም ተሳፋሪ የሆነውን ሁሉ ባለማወቁ በፍርሃት ረጭ አለ፡፡ አይሮፕላኑ ተንቀጠቀጠና ወደ ታች መውረድ ጀመረ፡

አራቱም ሞተሮች በአንድ ጊዜ ሲጠፉ የኤዲም ዕጣ ፈንታ አብሮ ተዘጋ።

ችግር ከመከሰቱ በፊት ሃሳቡን ቢለውጥ ኖሮ ይሄ ችግር አይመጣም፡፡
ሃሳቡ በውጥን ላይ ብቻ ቢቀር አይሮፕላኑ ሰላማዊ መንገዱን ይጓዝ ነበር
አሁን ግን ምንም ሆነ ምን ችግሩ ዓይኑን አፍጥጦ ጥርሱን አግጦ መጥቷል፡፡ ከዚህ በኋላ እንደተሳፋሪ መብረር ካልሆነ በስተቀር የበረራ መሀንዲስ መሆን አይችልም፡፡ አልቆለታል። በንዴት ስህተት እንዳይሰራ
መጠንቀቅ አለበት፡ ይህን ዕቅድ በርጋት መከወን አለበት፡፡ ከዚያ በኋላ
ህይወቱን ያመሰቃቀሉበት ርጉሞች ላይ ይዘምታል።

አይሮፕላኑ በድንገት ባህር ላይ ማረፍ ሊገደድ ነው: ሚስቱን ያገቱበት ወሮበሎች አይሮፕላኑ ላይ ይወጡና ፍራንክ ጎርዲኖን ያስፈታሉ፡ ከዚያ በኋላ የሚሆነው አይታወቅም:፡ ካሮል አን ደህና ስለመሆኗ ምንም ማረጋገጫ የለም፡፡ ወሮበሎቹ ወደ አይሮፕላኑ ሲመጡ የጠረፍ ጠባቂ
ፖሊሶች አደጋ ይጥሉባቸው ይሆናል፡፡ ኤዲ በዚህ ስራ ውስጥ ለፈጸመው እስር ቤት ይወረወር ይሆናል፡፡ እሱ እጣ ፈንታው ሆኖ እዚህ ውስጥ በመግባቱ ነው
ለእስር  የሚበቃው።ካሮል አንን በደህና እጁ እንዳስገባ ሌላ የሚፈልገው ነገር የለም::

የአይሮፕላኑ ሞተሮች ቀጥ ካሉ ከአፍታ በኋላ የካፒቴን ቤከር ድምጽ በጆሮ ማዳመጫው መጣና ‹‹ምንድነው ነገሩ?›› ሲል ጠየቀ፡፡

ኤዲ በድንጋጤ አፉ ስለደረቀበት ከመናገሩ በፊት ሁለት ጊዜ ምራቁን ዋጥ አደረገ ‹‹ገና አላወቅሁትም›› አለና  መለሰ፤ ነገር ግን መልሱን ያውቃል፡ ሞተሮቹ መስራት ያቆሙት ነዳጅ ስላለቀ ነው፡፡ እሱ ነው ነዳጅ
ወደ ሞተሮቹ እንዳይደርስ ሆን ብሎ ያደረገው። አይሮፕላኑ ስድስት የነዳጅ
ታንከሮች ያሉት ሲሆን ነዳጅ ወደ ሞተሮቹ የሚያደርሰው ክንፉ ላይ ባሉት
ታንከሮች አማካይነት ነው፡፡ ወደ ሞተሮቹ ነዳጅ
የሚያመጡትን ፓምፖች ሆን ብሎ እንዳይሰሩ አድርጓቸዋል፡፡ ሌላ ኢንጂነር
ቢያየው ሆን ብሎ እንዳይሰሩ እንደተደረጉ ያውቅበታል፡

ረዳት ኢንጂነሩ ሚኪ ፊን ተራው ባይደርስም ድንገት ሊመጣ ይችላል ብሎ ተጨንቋል፡ ነገር ግን ሚኪ እንቅልፉን እየለጠጠ ይሆናል ይህን ጊዜ፡
በረራው ረጅም ጊዜ የሚወስድ በሚሆንበት ጊዜ ከስራ ውጭ ያሉ
የአይሮፕላኑ ሰራተኞች ይተኛሉ፡

ሼዲያክ ላይ ሁለት ጊዜ አስፈሪ የፖሊስ ምርመራዎች ነበሩ፡
የመጀመሪያው ፖሊሶች አይሮፕላኑ ላይ የተሳፈረውን የፍራንኪ ጎርዲኖ
ግብረ አበር ስም ማወቃቸውን ገልጸው ነበር፡፡ ኤዲ ሉተርን ማለታቸውን
ገምቷል በዚህም ምክንያት ሉተር  አልቆለታል ብሎ  ካሮል አንን የሚያስለቅቅበትን ሌላ ስልት ማውጠንጠን ጀምሮ ነበር፡፡ በኋላ ደግሞ
ፖሊሶቹ ሄሪ ቫንዴርፖስትን እንደሚፈልጉ ሲገልጹ ኤዲ ጮቤ ረገጠ፡፡ከድንጋጤው መለስ ሲል ከሃብታም ቤተሰብ የተወለደ የሚመስለው ቫንዴርፖስት ለምን በሀሰት ፓስፖርት እንደሚጓዝ ገርሞታል፡የፖሊሶችን ትኩረት ከሉተር ወደ ራሱ እንዲዞር በማድረጉ ቫንዴርፖስትን በሆዱ እግዚአብሔር ይስጥህ  ብሎታል፡።
ፖሊሶችም በምርመራው  ብዙም ሳይገፉበት ርግፍ አድርገው ተዉት፡ ስለዚህ ሉተር ተረዳና በዕቅዱ መሰረት እነ ኤዲ የጀመሩትን ሊያከናውኑ ተነሱ፡፡
የፖሊሶችን

ለካፒቴን ቤከር ግን የተፈጸመው ሁሉ ጥርጣሬን የሚቀሰቅስ ሆኖበታል፡፡ ኤዲ ገና ከድንጋጤው ሳያገግም አንድ ድንገተኛ ሃሳብ ይዞ ብቅ አለ፡፡ አይሮፕላኑ ላይ ጎርዲኖ
ተባባሪ አለው ማለት እሱን ነጻ ለማውጣት የተዘጋጀ ሰው አለ ሲል ደመደመ፡፡ ስለዚህ ጎርዲኖን ከአይሮፕላኑ ላይ ማስወረድ ፈለገ፡፡ ይህ ማለት ደግሞ የኤዲ እቅድ ውሃ በላው ማለት ነው፡፡

ህግ እንዳይከበር በማድረጉ በህግ እንደሚጠይቀው የኤፍ.ቢ.አዩ ኦሊስ ፊልድ ካፒቴን ቤከር ላይ ዝቶ ነበር፡፡ በመጨረሻ ካፒቴኑ ኒውዮርክ ለሚገኘው ለፓን አሜሪካን አየር መንገድ መስሪያ ቤት ስልክ ደውሎ ለችግሩ መፍትሄ እንዲሰጡ ነገራቸው፡፡ አየር መንገዱም ጎርዲኖ በአይሮፕላኑ
መጓዙን እንዲቀጥል ሲፈቅድለት ኤዲም በእፎይታ ተነፈሰ፡፡

ሼዲያክ ላይ አንድ አስደሳች መልዕክት ደረሰው፡፡ የመጣው የኮድ
መልዕክት ከጓደኛው ስቲቭ አፕል ባይ መሆኑ አያጠራጥርም፡ መልዕክቱም አንድ የባህር ኃይል ጀልባ አይሮፕላኑ የሚያርፍበት አካባቢ ጥበቃ እያደረገ መሆኑንና እንዳይታወቅ ከእይታ ውጭ ሆኖ ወደ አይሮፕላኑ የሚጠጋ ማንኛውንም ጀልባ ለመምታት የተዘጋጀ መሆኑን ይገልጻል፡

ይሄ ለኤዲ ትልቅ ነገር ነው፡፡ በኋላ ወሮበሎቹ ከህግ እንደማያመልጡ
ማረጋገጫ ቢሰጠውም ዕቅዱ ግን ያለምንም እንከን ባሰበው መልኩ
እንዲጠናቀቅ እንቅፋት እንዳይፈጠር ምኞቱ ነው፡፡
ካፒቴን ቤከር ወደ ኤዲ መጣ፡፡ ኤዲ እጁ እየተንቀጠቀጠ ለሞተሩ ነዳጅ የሚመግበውን ፓምፕ ከፈተውና ‹‹ታንከሩ ባዶ ስለሆነ ሞተሩ አልነሳ አለ›› አለው::

‹‹ለምን?›› ሲል ካፒቴኑ ተቆጣ፡፡

ኤዲ መልስ አልነበረውም፡፡
የአይሮፕላኑ መሳሪያዎች በመጠባበቂያ ነዳጅና በመጋቢ ቧንቧዎቹ
መካከል የነዳጅ እንቅስቃሴ ወይም ግፊት መኖሩን አያሳዩም፡ ፓይለቶቹ ጋ
ግን የነዳጅ ሁኔታን የሚያሳዩ የነዳጅ መቆጣጠሪያዎች አሉ ካፒቴኑ ሁሉንም በየተራ አየና ‹‹ምንም ነዳጅ የለም›› አለ፡፡ ‹‹በክንፉ ላይ ባለው
ታንከር ውስጥ ምን ያህል ነዳጅ አለን?›› ሲል ጠየቀ፡፡
‹‹ትንሽ ነው የቀረው - የተወሰኑ ኪሎ ሜትሮች ብቻ የሚያስኬድ››
‹‹እንዴት ነው ይህን ያላስተዋልከው?›› ሲል ጠየቀ በቁጣ፡

‹‹እኔ ፓምፕ እያደረገ ነው የመሰለኝ›› አለ ኤዲ በተቆራረጠ ድምጽ
ይህ መልስ ግን ካፒቴኑን አላጠገበውም፡፡

‹‹ሶስቱም ፓምፖች እንዴት ባንድ ጊዜ ስራ ሊያቆሙ እንደቻሉ አልገባኝም›› አለ ካፒቴኑ።

‹‹ቶሎ ባህር ላይ ካላረፍን የቀረው ነዳጅ ተንጠፍጥፎ አይሮፕላኑ ሊወድቅ ይችላል›› አለ ኤዲ፡፡

‹‹ባህር ላይ ልናርፍ ስለሆነ ሁላችሁም ተዘጋጁ›› አለ ቤከር፡፡ ጣቱንም ኤዲ ላይ እያወዛወዘ ‹‹አንተ አታስፈልገኝም አላምንህም›› አለው፡

ኤዲ ሞቱን ተመኘ፡፡ ካፒቴኑ ላይ ክህደት ለመፈጸም በቂ ምክንያት እንዳለው ቢያውቅም የፈጸመውን ድርጊት አልወደደውም፡ ህይወቱን በሙሉ
ሃቀኛ ሆኖ ነው የኖረው:: አጭበርባሪዎችንና አታላዮችን አጥብቆ ይጠላ
ነበር፡፡ አሁን ግን የሚጠላውን ነገር ለማድረግ ተገዷል፡
ካፒቴኑ ናቪጌተሩ ጋ በመሄድ ቻርቱ ላይ ዓይኑን ተከለ፡፡ ናቪጌተሩ ጃክ
አሽፎርድ ኤዲን በግርምታ ገረመመውና ‹‹አሁን ያለነው እዚህ ላይ ነው››
ብሎ ቻርቱ ላይ በመጠቆም ለካፒቴኑ አሳየው፡፡

የኤዲ ዕቅድ ሊሳካ የሚችለው አይሮፕላኑ እሱ ባሰበው ቦታ ከወረደ
ነው፡፡ ወሮበሎቹ እዚህ ቦታ ላይ ነው የሚጠብቁት፡፡ ነገር ግን ድንገት
የሚፈጠር ነገር ካለ ከታሰበው ውጭ ሊደረግ ይችላል፡፡ ካፒቴኑ ሌላ ቦታ
ከመረጠ ግን ኤዲ እሱ ያለው ቦታ የተሻለ ስለሆነ እዚያ ማረፍ እንዳለበት
ካፒቴኑን ማሳሰቡ አይቀርም፡፡ ካፒቴኑ ሊጠረጥር ቢችልም እዚህ ቦታ ከማረፍ የተሻለ ነገር እንደሌለ በሎጂክ መቀበል ይኖርበታል፡ ሌላ ቦታ
እንዲያርፍ የሚያደርግ ከሆነ ግን ትክክል የማይሆነው እሱ ነው፡፡ ስለዚህ የእሱ ጣልቃ ገብነት አያስፈልግም ማለት ነው፡፡ ትንሽ ቆየና ‹‹እዚህ ጋ ነው የምናርፈው›› አለ ካፒቴኑ፡
👍19
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_አርባ_ዘጠኝ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

‹‹እሺ›› አለ ቪንቺኒ ወደ ጀልባዋ ፊቱን አዞረና ‹‹ጆ መጀመሪያ አንተ ና
ቀጥሎ ትንሹ ልጅ በመጨረሻ የኤዲ ሚስት፡፡›› ወደ ውስጥ ሲያዩ ካፒቴኑ ወደ አይሮፕላን መንጃው ክፍል ሲሄድ አየው፡፡ በዚህ ጊዜ ቪንቺኒ ሽጉጡን
መዘዘና ‹‹አንተ ባለህበት ቁም›› ሲል አዘዘው ቤከርን፡፡
ኤዲም ካፒቴን እንደሚልህ አድርግ እባክህ እነዚህ ሰዎች ቀልድ አያውቁም›› አለ ቤከር ባለበት ቆመና እጁን ወደ ላይ አነሳ፡፡

ጆ የተባለው ወሮበላ ‹‹እዚህ ውስጥ ብወድቅ መዋኘት አልችልም›› አለ
ከጀልባው ወደ አይሮፕላኑ መዝለል ፈርቶ፡፡

‹‹መዋኘት አያስፈልግም›› አለ ኤዲ እጁን ዘረጋለት፡፡

ጆም እንደምንም ዘለለና አይሮፕላኑ ውስጥ ገባ፡፡
ከእሱ በፊት ሁለት ሰዎች በደህና መዝለላቸውን አይቶ ትንሹ ልጅ ኮራ ብሎ ዘለለ፤ ነገር ግን ሲዘል ሚዛኑን ሳተና ወደኋላው ሊወድቅ ሲል ኤዲ የልጁን ቀበቶ ይዞ አዳነው ‹‹አመሰግናለሁ›› አለ ልጁ፡፡

አሁን የካሮል አን ተራ ደረሰ ለመዝለል ፈርታ የኤዲን አይን አይን ታያለች በተፈጥሮዋ ፈሪ ሆና ሳይሆን ከእሷ በፊት ትንሹ ልጅ ተንገዳግዶ ባህር ውስጥ ሊገባ ሲል ስላየች ነው የፈራችው፡፡ ኤዲም ፈገግ አለና
‹‹እንደነሱ ዝለይ ማርዬ›› አለ ‹‹አይዞሽ ውሃ ውስጥ አትወድቂም::››

ኤዲ በፍርሃት ልቡ እየደለቀ በጉጉት ጠበቀ ሚስቱ እስክትዘል፡፡ ካሮል
አን መዝለል መቻሏን ተጠራጠረች፡፡ ‹‹ተዘጋጂና ዝለይ!›› አላት እሱም የእሷ
ፍርሃት ተጋብቶበት፡፡

ካሮል አን ጥርሷን ነክሳ እንደ ምንም ዘለለች፤ ነገር ግን ግማሽ አካሏ ባህሩ ውስጥ ሆኖ ገመዱን ለመያዝ ተፍጨረጨረች፤ ‹‹ገመዱን አጥብቀሽ
ያዥ አይዞሽ›› አለ ወደ ባህሩ የምትወድቅ ከሆነ ለመዝለል ተዘጋጅቶ
ኤዲ ተንበረከከና እጇን ለመያዝ እጁን ሰደደ፤ ሆኖም ሚዛኑን ሳተና ወደ
ባህሩ ሲወድቅ እጇን መያዝ አልቻለም፤ የባህሩ ሞገድ ጎትቶ ውሃ ውስጥ
ሲያስቀራት በተስፋ መቁረጥ ጮኸች፡፡

ያለ የሌለ ሀይሏን ተጠቅማ ወደ ኤዲ እየዋኘች ተጠጋች፤ ኤዲ ጥርሷ
ሊንገጫገጭ አየ፧ እንደ ምንም ብሎ እግሯን ያዘ፤ ሆኖም የባህሩ ሞገድ
ሃይለኛ በመሆኑ ከእጁ አፈተለከችና እንደገና ባህሩ ላይ ወደቀች፤ ካሮል አን
እየሰመጠች ነው እሱም እጁን ሰደደና ወገቧን ያዘ፡፡

‹‹አይዞሽ የኔ ማር ይዤሻለሁ›› አለና እንደምንም ተሸክሞ ወደ
አይሮፕላኑ አስገባት፡፡ ካሮል አን ባሏ  እቅፍ ውስጥ ገብታ ማንባቷን ቀጠለች፡፡ እምባ ቢተናነቀውም እንደምንም ዋጥ አደረገው፡፡የምትንቀጠቀጠውን
ሚስቱን ለማረጋጋት አጥብቆ ደረቱ ላይ ለጠፋት
‹‹ደህና ነሽ የኔ ማር? እነዚህ ሰዎች አንገላቱሽ?›› ሲል ጠየቃት

‹‹ደህና ነኝ›› አለች ጥርሷ እየተንገጫገጨ፡፡

የካፒቴኑን ዓይን ለማየት ፈርቶ እየሰረቀ ያየዋል፡፡ ቤከር ወደ ካሮል
አን አማተረና
‹‹ያደረግኸው ሁሉ ለምን እንደሆነ አሁን እየገባኝ መጣ›› አለ፡፡
‹‹ይበቃል የምንሰራው ስራ አለን›› አለ ቪንቺኒም፡፡
ኤዲ ካሮል አንን ለቀቃትና ‹‹እሺ ወደምትፈልጉት ሰው እወስዳችኋለሁ››
‹‹እሺ›› አለ የወሮበሎቹ መሪ፡
‹‹ተከተሉኝ›› አላቸውና ወደ ውስጥ ገቡ፡ ሰራተኞቹ ምንም ነገር ለማድረግ እንዳይሞክሩ ኤዲ አስጠነቀቃቸው:
‹‹ሁላችሁም አደብ ግዙ፡፡ እነዚህ ሰዎች አድርጉ የሚሏችሁን ማድረግ
ብቻ ነው ያለባችሁ አለበለዚያ በጥይት ከመግደል ወደ ኋላ የሚሉ ሰዎች አይደሉም፡ ሰው እንዲጎዳ አልፈልግም፡ ካፒቴኑም ይህንኑ ነው የሚላችሁ አለ ኤዲ፡

‹‹ትክክል ነው›› አለ ካፒቴኑ ‹‹ጎበዝ! እነዚህ ሰዎች መሳሪያ የያዙ ናቸው፤ ብትወራጩ በጥይት ነው የሚሏችሁ ››
ኤዲ ወደ ቪንቺኒ ዞረና ‹‹እንሂድ እንግዲህ፤ ካፒቴን ተሳፋሪዎቹን ማረጋጋት ይኖርብሃል›› አለ፡፡

ቪንቺኒ በኤዲ አባባል መስማማቱን በራሱ ንቅናቄ አሳየ፡
‹‹ካሮል አን ከአይሮፕላኑ ሰራተኞች ጋር ሁኚ፧ እሺ›› አላት፡፡

ኤዲ ሚስቱ ከወሮበሎቹ ጥይት መራቋን ወዶታል፡ በተጨማሪም ባሏ
ለምን እነዚህን ሰዎች ሊተባበር እንደወሰነ ለተሳፋሪዎቹ ታስረዳለታለች፡
ኤዲ ቪንቺኒን ‹‹እባክህ ጠመንጃህን ከተሳፋሪዎች ብታርቅልኝ፧ ይፈራሉ››
‹‹ተነፋ!›› አለ ቪንቺኒ ‹‹እንሂድ›› ሲል አዘዘ ጓደኞቹን፡ ኤዲ ትከሻውን
በንዴት ነቀነቀ፡፡ ሁሉም ቦታ ቦታቸው ላይ እንደተቀመጡ ነው፡፡ ሁለቱ አስተናጋጆች ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ ለማረጋጋት ጥረት እያደረጉ ነው፡፡
ኤዲ አይሮፕላኑ ውስጥ እየተዘዋወረ ሲያይ መብል ክፍሉ ትርምስምስ
ብሏል፡፡ ወለሉ በሸክላ እና በብርጭቆ ስብርባሪ ተሸፍኗል። ምግብ ተበልቶ
ስላለቀና ተሳፋሪዎች እየጠጡ ስለሆነ የተደፋፋ ነገር አይታይም፡:
ተሳፋሪዎቹ የቪንቺኒን ሽጉጥ ሲያዩ በፍርሃት ድምጻቸውን አጠፉ፡፡ ካፒቴን
ቤከር ወደ ፊት መጣና ‹‹ክቡራንና ክቡራት ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ
እጠይቃለሁ፡ ከመቀመጫችሁ እንዳትነሱ፡ አሁን ያለው ችግር ከተወሰነ
ደቂቃ በኋላ መፍትሄ ያገኛል›› አለ፡፡

ኦሊስ ፊልድና ፍራንኪ ጎርዲኖ አብረው ቁጭ ብለዋል አሁን ነፍሰ
ገዳይ እንዲያመልጥ ላደርግ ነው አለ ኤዲ ለራሱ፡ ወደ ጎርዲኖም ጣቱን እየጠቆመ ‹‹ያውልህ ሰውዬህ ውሰደው›› አለ፡፡
ኦሊስ ፊልድ ከተቀመጠበት ተነሳና ‹‹ይሄ የኤፍ ቢ አይ መርማሪ ቶሚ ማክ አርድል ነው›› አለ ‹‹ፍራንኪ ጎርዲኖ ትላንት በመርከብ ኒውዮርክ ደርሶ ወህኒ ገብቷል››
‹‹የአምላክ ያለህ!›› ሲል ኤዲ በግርምት ጮኸ፡፡ ይህን ሁሉ እኩይ ተግባር ሲፈጽም የነበረው ለአስመሳይ ሰው ነው?!

‹‹እኛ ከፍራንኪ ጉዳይ የለንም፡፡ ጀርመናዊው ሳይንቲስት የታለ?›› አለ ቬኒቺኒ

ኤዲ ተገርሞ ቪንቺኒ ላይ አፈጠጠ፡፡ ጎርዲኖን አይፈልጉትም፡፡ ታዲያ
ማንን ነው የሚፈልጉት?ተ

የቶም ሉተር ድምፅ ተሰማ ‹‹እዚህ ነው ያለው፤ በእኔ ቁጥጥር ስር  ነው›› አለ ሉተር ሃርትማን ላይ ሽጉጡን እየደገነ፡፡ተ

ኤዲ የበለጠ እንቆቅልሽ ሆነበት፡፡ የፓትሪያርካ ማፊያ ቡድን ለምንድን ነው ካርል ሃርትማንን ማገት የፈለገው?› ‹‹ሳይንቲስቱን ለምንድን ነው የምትፈልጉት?› ሲል ጠየቀ፡፡

ቀበል አድርጎ ‹‹ተራ ሳይንቲስት እንዳይመስልህ የኒኩሊየር ፊዚስት
ነው›› አለ ሉተር፡

‹‹እናንተ ናዚ ናችሁ?›› ሲል ጠየቀ ኤዲ፡፡

‹‹አይደለንም፧ እኛ ዲሞክራቶች ነን፡፡ እነሱ ሳይንቲስቱን አግተን
እንድንሰጣቸው ስራ አዘውን ነው፡ ረብጣ ገንዘብ ይከፍሉናል›› አለና ቪንቺኒ
ተንከተከተ፡

ሉተርም ‹‹እኔ ዲሞክራት አይደለሁም፡፡ የጀርመን አሜሪካን ትብብር
ማህበር አባል ነኝ፡፡ ይህ ማህበር በናዚ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ
የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነው፡፡ ሂትለር ራሱ ነው ከአገር አምልጦ የወጣውን
ሳይንቲስት አፍኜ ወደ ጀርመን እንዳመጣው ያዘዘኝ›› አለ፡፡ ሉተር ይህን
ሲናገር በኩራት ነው፡፡ ‹‹እነዚህ ሰዎች ከፍዬ የማሰራቸው እኔ ነኝ፡፡ ስለዚህ ዶክተር ፕሮፌሰር ሃርትማንን ወደ ጀርመን መልሼ እወስደዋለሁ፡
ሳይንቲስቱ እዚያ በጣም ይፈለጋል›› አለ፡

ኤዲ ከሃርትማን ጋር ዓይን ላይን ግጥም አለ፡፡ ሰውዬው ፍርሃት
ጨምድዷቸዋል፡ ኤዲ ወዲያው ፀፀት ገባው፡፡ ሳይንቲስቱ ወደ ጀርመን
ሊመለሱ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ የኤዲ ጥፋት ነው፡፡

‹‹ምን ላድርግ ባለቤቴን ስላገቱብኝ ነው የተባበርኳቸው›› አለ፡፡

የሃርትማን አስተያየት ተለወጠ ‹‹ይገባኛል›› አሉ ሳይንቲስቱ ‹‹እንደዚህ
አይነት ክህደቶችን ጀርመን ውስጥ ለምደናቸዋል፡ አንዱን ለማዳን ስትል
ሌላውን አሳልፈህ ትሰጣለህ፡ ምንም ምርጫ አልነበረህም፡፡ በዚህ ራስህን አትውቀስ›› አሉት፡፡
👍12
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሃምሳ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ



ናንሲ ሌኔሃን በተከራየችው አይሮፕላን በካናዳ ጠረፍ ላይ ስትበር ለችግሯ መፍትሄ ታያት፡ ወንድሟን መርታት ብቻ ሳይሆን አባቷ
ካስቀመጡላት የህይወት መርህ መውጣት ትፈልጋለች፡ ከመርቪን ጋር
መሆንም ትፈልጋለች፡ ሆኖም የጫማ ፋብሪካውን ትታ መርቪንን ተከትላ
እንግሊዝ ሃገር ሄዳ ብትኖር እንደ ዳያና የባሏን እጅ መጠበቅ የሰለቻት
ሚስት መሆኗ ነው፡

ናት ሪጅዌይ ኩባንያውን በተሻለ ዋጋ እንደሚገዛና በጄኔራል ቴክስታይል ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ እንደሚሰጣት ነግሯታል፡ ጄኔራል ቴክስታይልስ ደግሞ አውሮፓ ውስጥ ባብዛኛው በተለይም እንግሊዝ ውስጥ በርካታ ፋብሪካዎች አለው፡፡ ናት ሪጅዌይ ደግሞ ጦርነቱ ካላበቃ ፋብሪካዎቹን መጎብኘት አይችልም፡፡ ስለዚህ እሷ የፋብሪካ
ዎቹን የአውሮፓ የበላይ ሀላፊነት ቦታ ይሰጣታል፡፡ ይህ ደግሞ በራሱ
ከመርቪን ጋር ለመሆንና ስራ መስራት የሚያስችላት በመሆኑ ጥሩ ነው፡

መፍትሄው ጥሩ ይመስላል፡፡ አንድ የሚያስፈራ ነገር አውሮፓ ጦርነት ውስጥ ስላለች ልትሞት ትችላለች፡፡ ናንሲ ይህን ስታወጣና ስታወርድ
መርቪን ባህሩ ላይ የቆመውን አይሮፕላናቸውን አሳያት፡፡
መርቪን ከአይሮፕላኑ ጋር በሬዲዮ መገናኛ ለመገናኘት ቢሞክርም ምንም ምላሽ አላገኘም፡፡ ናንሲ አይሮፕላኗ ስታንዣብብ አዕምሮዋ ውስጥ የሚመላለሰውን ነገር ተወችው፡፡ ምንድን
ምንድን ነው የተፈጠረው?
አይሮፕላኑ ውስጥ አሉ? አይሮፕላኑ ሲታይ ምንም አልተጎዳም፡፡ ሆኖም
የሰው ዘር ያለበት አይመስልም፡፡

መርቪን ‹‹ምናልባትም ችግር ደርሶባቸው ከሆነ አርፈን ብናያቸው›› አለ፡፡ ናንሲ በመስማማት ራሷን ነቀነቀች፡፡

‹‹የመቀመጫ ቀበቶሽን በደምብ እሰሪ፡፡ ባህሩ ማዕበል ያለበት ስለሆነ
ስናርፍ ይንገጫገጫል፡››
ፓይለታቸው እንደ ፈረስ የሚጋልበው ባህር ላይ አይሮፕላናቸውን
አሳረፈ፡ ናንሲ እንደገመተችው ማዕበሉ አስቸጋሪ አልነበረም፡፡
አንድ የሞተር ጀልባ ከአይሮፕላኑ ጋር ታስሯል፡፡ ትልቁ አይሮፕላን በር ላይ አንድ ሰው እጁን ያውለበልባል። ከዚያም እነ መርቪን አይሮፕላናቸውን ከግዙፉ አይሮፕላን ጋር አሰሩት፡፡

ኔድ ‹‹እኔ አይሮፕላኔ ውስጥ እቆያችኋለሁ›› አለ ‹‹እናንተ ውጡ አይሮፕላኑ ምን ችግር እንደደረሰበት አጣሩ›› አላቸው፡፡

‹‹እኔም እመጣለሁ›› አለች ናንሲ፡፡

መርቪን መጀመሪያ ወደ አይሮፕላኑ ዘለለና ለናንሲ እጁን ዘረጋላት፡

በሩ ላይ የቆመውን ሰው ‹‹ምንድን ነው የተፈጠረው?›› ሲል ጠየቀው፡

‹‹ነዳጅ ስላለቀባቸው ነው ባህሩ ላይ ያረፉት›› ሲል መለሰ፡፡

‹‹በሬዲዮ መገናኛ ላገኛቸው ሞክሬ ነበር፡፡

ሰውዬውም ‹‹ወደ ውስጥ ግባ›› አለው፡

መርቪን ከገባ በኋላ ‹‹ምንድን ነው ችግሩ?›› ሲል ጠየቀ፡

‹‹አይሮፕላኑ ድንገት ነው ያረፈው›› አለ ወጣቱ ሰው ‹‹እኛ አሳ አጥማጆች ነን ስለዚህ ችግሩን ለማጣራት መጥተን ነው››

‹ካፒቴኑን እጠይቀዋለሁ›› አለ መርቪን፡፡

ወጣቱ ሰው በአለባበሱ አሳ አጥማጅ አይመስልም፡፡ ክራቫት አድርጓል፡፡
ናንሲ ሁኔታው አሳቃት፡፡

ወደ ውስጥ ገብተው ሲመለከቱ መምበሪ በደም ተለውሶ ወለሉ ላይ
ተዘርግቷል፡፡ አፏን ያዘች በድንጋጤ
‹ወይ አምላኬ! ምንድን ነው ችግሩ?›› ሲል መርቪን ጠየቀ ከኋላቸው ያለው ወጣቱ ሰው ‹‹ቀጥሉ ወደፊት›› አለ በቁጣ፡

ናንሲ ዞር ብላ ስታየው ሰውዬው ሽጉጥ ደግኗል፡፡ ‹‹አንተ ነህ እንዲህ ያደረከው?›› ስትል ጠየቀች
‹‹አፍሽን ዝጊና ቀጥ ብለሽ ሂጂ›› አላት፡፡

መብል ክፍል ውስጥ ገቡ፡፡
ሌሎች ሶስት ሽጉጥ የያዙ ሰዎች አሉ፡፡ አዛዣቸው የሚመስል አራተኛ
ሰው ቆሟል፡፡ ትንሹ ልጅ ከመርቪን ሚስት ኋላ ቆሞ ጡቷን ይጎነትላል፡
መርቪን ይህንን ሲያይ ተናደደ፡፡ ሶስተኛው ሰው የአይሮፕላኑ ተሳፋሪ
የሆነው ሉተር ሲሆን በፕሮፌሰር ሃርትማን ላይ ሽጉጡን ደግኗል፡
ካፒቴኑና የበረራ መሀንዲሱ ኤዲ የሚያደርጉት ጠፍቷቸው ዓይናቸውን
ያቁለጨልጫሉ፡ በርካታ ተሳፋሪዎች ወምበራቸው ላይ እንደተቀመጡ
ሲሆን ወለሉ ላይ የብርጭቆና የሰሃን ስብርባሪ ይታያል፡፡ ናንሲ ዙሪያውን ስታማትር በፍርሃት የተዋጠችው ማርጋሬት አይኗ ገባች፡፡
‹‹ላቭሴይ አምላክ ፊቱን አዙሯል፡፡ አይሮፕላን በምንፈልግበት ጊዜ
ደርሰህልናል፡ እኔን ቪንቺኒንና የእሱን ሰዎች በአይሮፕላን ይዘኸን ትሄዳለህ፡ ኤዲ ዲኪንማ ፖሊስ እጅ ሊጥለን ወጥመድ ሲያሰናዳልን ነው
የከረመው›› አለ ሉተር፡
መርቪን ከመገላመጥ በስተቀር ምንም መልስ አልሰጠውም፡፡

ባለመስመር ሱፍ ልብስ የለበሰው ሰው ‹‹የባህር ኃይል ወታደሮች
መጥተው ችግር ከመፍጠራቸው በፊት እንሂድ፡፡ ትንሹ ልጅ አንተ ላቭሌይን ይዘህ ና፡፡ ገርል ፍሬንዱ እዚሁ ትቆይ›› አለ፡፡
‹‹እሺ ቪኒ›› አለ ትንሹ ልጅ፡፡
ናንሲ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ባታውቅም ወደኋላ መቅረት ግን አልፈለገችም፡፡ መርቪን ችግር ውስጥ የሚገባ ከሆነ ከጎኑ ትሆናለች፡፡

ቪንቺኒ ሌላ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ‹‹ሉተር አንተ ሳይንቲስቱን ይዘህ ና፡›› ወደ ጆ ዞር አለና ‹‹በመጨረሻ ቆንጆዋን ሴት ይዘህ ና›› ሲል ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

ሰውየው ዳያና ላቭሴይ ላይ ሽጉጡን ደግኖ ‹‹እንሂድ›› አላት እሷ ግን ከቦታዋ ንቅንቅ አልልም አለች፡፡ ናንሲ ሌላ ጥያቄ ጭንቅላቷ ውስጥ አጫረ፡ ዳያናን ለምንድን ነው የሚወስዷት? በኋላ ግን መልሱ ተከሰተላት
ጆ ቀጠለና በሽጉጡ አፈሙዝ የዳያናን ጡት ወጋ ሲያደርገው ጮኸች፡፡

‹‹ቆይ እስቲ›› አለ መርቪን፡፡

ሁሉም እሱ ላይ አፈጠጡ፡፡

‹ሁላችሁንም በአይሮፕላን እወስዳችኋለሁ። ነገር ግን አንድ ነገር ማሟላት አለባችሁ›› አላቸው

ቪንቺኒም ‹‹አፍህን
ዝጋና ተንቀሳቀስ፡፡ ምንም ቅድመ  ሁኔታ ማስቀመጥ አትችልም›› አለው፡፡

መርቪን እጁን ዘረጋና ‹‹እንግዲያውስ ግደሉኝ›› አለ፡፡

ናንሲ በፍርሃት ጮኸች፡
እነዚህ ሰዎች የሚዳፈራቸውን ሰው
ከመግደል ወደኋላ የሚሉ አይደሉም መርቪን  አላወቃቸውም አለች በሆዷ

‹‹ምንድነው ቅድመ ሁኔታው?›› ሲል ጠየቀ ሉተር

መርቪን ወደ ዳያና
አመለከተና ‹‹እሷ እዚሁ ትቆይ›› አለ ጆ በንዴት መርቪን ላይ አፈጠጠ፡፡

‹‹አንፈልግህም ብዙ የፓን አሜሪን ፓይለቶች ሞልተዋል፡፡ እነሱም
እንዳንተ ማብረር ይችላሉ›› አለ ቪንቺኒ፡

‹‹ሁሉም እንደዚህ አይነት ጥያቄ ሊያነሱ ይችላሉ›› አለ መርቪን፡፡
‹‹ጠይቋቸው ጊዜ ካላችሁ፡፡›› ወሮበሎቹ እነሱን ያመጣው ፓይለት መኖሩን እንዳላወቁ ተገንዝቧል፡

‹‹ሴትዬዋን ተዋት›› አለ ሉተር፡፡

ጆ በንዴት ፊቱ ቀላ፡፡

‹‹ለምን?››

‹‹እሷን ተዋት›› ሲል ጮኸ ሉተር፡፡ ‹‹እኔ ገንዘብ የከፈልኩህ ሃርትማንን እንድታፍንልኝ ነው እንጂ ሴት እንድትደፍርልኝ ነው እንዴ››

‹‹ሉተር ልክ ነው ጆ፡ በኋላ ሌላ ሴት ታገኛለህ›› አለው ቪንቺኒም:

‹‹እሺ›› አለ ጆ፡

ዳያና በእፎይታ አለቀሰች።

‹‹ጊዜ የለንም ከዚህ እንውጣ›› ሲል ቪንቺኒ አዘዘ፡፡

ናንሲ ‹መርቪንን ዳግመኛ አየው ይሆን?› አለች በሃሳቧ
ከውጭ ክላክስ ተሰማ፡፡ የጀልባው ነጂ ነው ክላክስ ያደረገው።
👍192
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሃምሳ_አንድ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ጎረምሳውና ጆ ውሃ ውስጥ እየሰጠሙ ስታይ ጮኸች፡፡
ወጣቱ ልጅ ወደ ላይ ለመውጣት ሲሞክር ጆ ደግሞ ህይወቱን ለማትረፍ ወጣቱን ወደ ታች ይጎትታል፡፡ በጣም አስፈሪ ሁኔታ ነው የሚታየው፡፡
ማርጋሬት መጮኋን ሰምቶ ሉተር በመስኮት ተመለከተና ‹‹ባህሩ ውስጥ ወድቀዋል››› ሲል ጮኸ በጭንቀት፡፡

‹‹እነማ ናቸው?›› አለ ቪንቺኒ፡፡

‹‹ጎረምሳውና ጆ›› አለ ሉተር፡

የጀልባው ነጂ ገመድ ቢወረውርላቸውም ሁለቱ ሰዎች አላዩትም፡፡ እነሱ
የሚይዙትን አጥተው በፍርሃት ውሃ ውስጥ እየተንቦራጨቁ ሲሆን ጆ
ጎረምሳውን ልጅ ወደ ባህሩ ውስጥ እየደፈቀው ነው፡፡

‹‹እባክህ እርዳቸው›› አለ ሉተር እሱም በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ፡፡

‹‹ምን?›› አለቪንቺኒ ‹‹ምንም ልንረዳቸው የምንችለው ነገር ያለ
አይመስለኝም፡ እነሱም ራሳቸውን ለማዳን አቅም የላቸውም፡፡›› በመጨረሻም
ሁለቱን ሰዎች ጨካኙ ባህር ሰለቀጣቸው፡

‹‹እንዴት ሊሆን ቻለ?›› ሲል ጠየቀ ሉተር ‹‹በመጀመሪያ ውሃ ውስጥዐእንዴት ሊወድቁ ቻሉ?››

‹‹ምናልባት የሆነ ሰው ገፍቷቸው ይሆናል›› አለ ቪንቺኒ፡

‹‹ማን?››

‹‹እዚህ አይሮፕላን ውስጥ የሆነ ሌላ ሰው ይሆናል፡›› ማርጋሬት የሁለቱን ሰዎች ንግግር ስትሰማ ስለነበር ሄሪ ሊሆን ይችላል› ስትል
ገመተች፡ ሄሪ ጀልባው ውስጥ ይኖር ይሆን?
ፖሊሶቹ አይሮፕላኑን
ሲፈትሹ እሱ የሆነ ቦታ ተደብቆ አይሮፕላኑ ባህሩ ላይ ሲያርፍ ከተደበቀበት
ወጥቶ ይሆን? ሁለቱን ወሮበሎች ውሃ ውስጥ ገፍቶ የጨመራቸው እሱ
ይሆን? እያለች መልስ የሌለው ጥያቄ በአዕምሮዋ ተጉላላ፡፡

በኋላ ደግሞ ወንድሟ ትዝ አላት ፔርሲ የወሮበሎቹ ጀልባ ከአይሮፕላኑ ጋር በሚታሰርበት ጊዜ ነው የጠፋው፡፡ ‹ምናልባትም መጸዳጃ ቤት ሄዶ ግርግሩ እስኪያልቅ እዚያው ሊቆይ አስቦ ይሆናል› አለች በሆዷ፡
እሱ ደግሞ እንዲህ አይነት ባህሪ የለውም፡፡ እሱ እንደውም ሁሉን ነገር
ለማወቅ ስለሚፈልግ ችግር አይፈራም፡፡

ሉተር ‹‹ሁሉ ነገር ከእጃችን እየወጣ ነው ምን ብናደርግ ይሻላል?›› ሲል ጠየቀ፡

‹‹አሁን በመጣችው አይሮፕላን እንሄዳለን እንዳቀድነው፡፡ አንተ፣ እኔና
ሳይንቲስቱ›› አለ ቪንቺኒ፡ ‹‹መንገዳችንን ሊያሰናክል የሚሞክር ሰው ካለ
በሆዱ ጥይት ልቀቅበት፡ አሁን ረጋ ብለን እንውጣ፡፡››
ማርጋሬት ወሮበሎቹ ፔርሲን ደረጃው ላይ ያገኙትና በሆዱ ጥይት
ይለቁበታል ብላ ሰጋች፡
ሶስቱ ሰዎች ከምግብ ቤቱ ሲወጡ የፔርሲ ድምጽ ከበስተኋላቸው
ተሰማ፡፡ ድምጹንም ከፍ አድርጎ ‹‹እንዳትነቃነቁ!›› አለ፡፡
ፔርሲ ቪንቺኒ ላይ ሽጉጡን መደገኑን ስታይ ማርጋሬት ዓይኗን ማመን አቃታት፡፡ የሽጉጡን አፈሙዝ አይታ ካፒቴኑ ከኤፍ.ቢ.አዩ ሰውዬ
ላይ የነጠቀው መሆኑን ገመተች፡

ቪንቺኒ ቀስ ብሎ ወደ ፔርሲ ዞረ፡፡

ማርጋሬት የወንድሟ ህይወት አደጋ ላይ ቢሆንም በፔርሲ ኮራች፡፡

የመብል ክፍሉ በሰው
ተሞልቷል፡፡ ከቪንቺኒ ኋላ ማርጋሬት ከተቀመጠችበት አጠገብ ሉተር በሃርትማን ላይ ሽጉጡን ደግኗል፡ በሌላኛው በኩል ናንሲ፣ መርቪን፣ ዳያና፣ ኤዲ እና ካፒቴኑ ቆመዋል ቪንቺኒ ፔርሲን ዘለግ ላለ ጊዜ አየውና ‹‹ልጅ ከዚህ ጥፋ›› አለው፡፡

‹‹ሽጉጥህን ጣል!›› ሲል ፔርሲ አዘዘ፡፡

በመሃል አንድ ጥይት ጮኸች፡፡ የጥይቱ ድምጽ ጆሮ ያደነቁራል፡
ማርጋሬት ጩኸቷን አቀለጠችው: ማን ማን ላይ እንደተኮሰ አላወቀችም:: ፔርሲ ምንም አልሆነም፡፡ ትንሽ ቆይቶ ቪንቺኒ ከደረቱ ላይ ደም እየተንፎለፎለ ተንገዳገደና መሬት ዘፍ አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ቦርሳው
ሲወድቅ ተበረገደና ብሮቹ በደም ታጠቡ፡

ፔርሲ ቪንቺኒን ሲያይ ሽጉጡን ጣለ፡፡ ደንግጧል፡
ሁሉም ሰው ሽጉጥ የያዘው የመጨረሻው ወሮበላ ላይ አፍጧል፡

ካርል ሃርትማን በተፈጠረው
ሁኔታ ከተዘናጋው ሉተር መንጭቀው ራሳቸውን ነጻ አደረጉና መሬት ያዙ ማርጋሬት ሳይንቲስቱን ይገድላቸዋል ብላ ሰግታለች ፔርሲንም እንዲሁ፡ ነገር ግን ወዲያው የሆነው ግን
አስደንግጧታል፡፡

ሉተር አፈፍ አድርጎ ያዛት፡ ከወንበሯ ጎትቶ አነሳትና ጭንቅላቷ ላይ ሽጉጡን ደገነባት፡፡ በዚህ ጊዜ ሁሉም በድንጋጤ በድን ሆኑ።

ማርጋሬት ፍርሃት ስለገባት መንቀሳቀስ መጮህ አልቻለችም፡ የሉተር
ሽጉጭ ጭንቅላቷን እየወጋት ነው፡ ሉተር ራሱ ይንቀጠቀጣል፡፡ ከዚያም
ሳይንቲስቱን ‹‹ውጣና ጀልባ ውስጥ ግባ፡፡ ትዕዛዜን ካልፈጸምክ ልጅቷ
ጭንቅላት ላይ ጥይት እቀረቅርበታለሁ›› አለ፡፡
ወዲያው ፍርሃቷ ሲለቃት ታወቃት፡፡ ሉተር  ብልህ መሆኑን ተገንዝባለች፡፡ ሽጉጡን ሃርትማን ላይ ደግኖ ቢሆን ኖሮ ሃርትማን ግደለኝ ጀርመን አገር ከምመለስ ሞቴን እመርጣለሁ› እንደሚሉ እርግጠኛ ሆኗል፡ አሁን ግን የእሷ ህይወት አደጋ ላይ ነው፡ ሃርትማን ምናልባት
ህይወታቸውን ለመስጠት ዝግጁ ይሆኑ ይሆናል፡፡

ሃርትማን ቀስ ብለው ተነስተው ቆሙ፡፡

ሁሉም ነገር በማርጋሬት ላይ የተጣለ ነበር፡ ራሷን ሰውታ ማዳን ትችላለች፡ ሆኖም ይህ አድራጎት ጥሩ አይደለም፡፡ እሷም ይህን አደርጋለሁ ብላ አልጠበቀችም፡፡ ለዚህ ራሴን አላዘጋጀሁም፡፡ ማድረግ አልችልም› አለች
በሆዷ፡
ከአባቷ ጋር ዓይን ላይን ግጥም አሉ፡፡ አባቷ በጣም ደንግጠዋል ሲያበሻቅጧት እንደኖሩ ምን ያህል
አቅመቢስ እንደሆነች ጦሩንም ተቀላቅላ አንድ ቀን እንኳን እንደማትቆይ
የነገሯት ሁሉ ትዝ አላት፡፡
አባቴ ያለው እውነት ይሆን?› አለች ለራሷ፡
ስለዚህ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለባት ወሰነች፡፡ ሉተር ሊገላት ይችላል ነገር ግን አንድ ነገር ከማድረጉ በፊት ሌሎች ሰዎች ዘለው ይረባረቡበታል ጊዜው እየሄደ ነው፤ አንድ ነገር ማድረግ አያቅተኝም, አለች በሆዷ፡

ከዚያም ‹‹ሁላችሁም ደህና ሁኑ›› አለች፡፡ አፍታም ሳይቆይ የሄሪን ድምጽ ከኋላዋ ሰማች፡፡

‹‹ሚስተር ሉተር ጠላቂው መርከብህ ደርሷል›› አለ፡፡

ሁሉም ሰው በአይሮፕላኑ መስኮት ተመለከተ፡፡ ማርጋሬት ሄሪ በተናገረው ነገር ሉተር ልቡ መወሰዱን አወቀች፡፡ ከዚያ አንድ ጥይት ጮኸች፤ እሷ ግን ምንም አልሆነችም፡፡ ሁሉም አንድ ጊዜ ተንቀሳቀሰ፡፡ ኤዲ ዘለለና እንደ ተቆረጠ ዛፍ ሉተር ላይ ወደቀበት፡፡ ሄሪ የሉተርን ሽጉጥ
መንጭቆ ወሰደ፡፡

ፔርሲ ወደ ማርጋሬት ሄደና አቀፈችው፡፡ ‹‹አንተ ግን ደህና ነህ?››ቸ ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹አዎ ይመስለኛል››
‹‹በጣም ጎበዝ ነህ››
‹‹አንቺም እንዲሁ››
‹አዎ እኔ ጎበዝ ነኝ አለች ለራሷ፡
ፀጥ ብሎ የቆየው ተሳፋሪ ሁሉ በአንድ ጊዜ ተንጫጫ፡፡ በዚህ ጊዜ
ካፒቴኑ ‹‹ፀጥታ እባካችሁ ዝም በሉ›› አለ፡፡
ማርጋሬት ዙሪያውን ቃኘች፡፡
ሉተር ኤዲ እና ሄሪ ላዩ ላይ ወጥተውበት ከመሬቱ ላይ እንደተደፋ ነው፡፡ አይሮፕላኑ ውስጥ ያንዣበበው አደጋ ተወግዷል፡ ሃርትማንና
ሉተርን ሊወስድ የመጣው ጠላቂ መርከብ ተንሳፎ ይታያል፡

ካፒቴኑም የባህር ኃይል መርከብ በቅርብ ርቀት ይታያል፡ ‹‹ጠላቂ
መርከብ እዚህ እንዳለ የሬዲዮ መልእክት እናስተላልፋለን፡፡››
‹‹ቤን›› ሲል ተጣራ፡
‹‹አቤት ጌታዬ›› አለ የሬዲዮ ኦፕሬተሩ ‹‹የጠላቂው መርከብ አዛዥ
ሬዲዮ መልእክት ማስተላለፋችንን ካወቀ ወደ እኛ ሊተኩስ እንደሚችል
ተገንዝበኸዋል?›› አለ ቤን፡፡

‹‹ደህና ይቅር›› አለ ካፒቴኑ ‹‹ተሳፋሪዎቻችን እስካሁን የደረሰባቸው መከራ
ይበቃል፡››
ጠላቂው መርከብ መግቢያው እንደተዘጋ ነው አዛዡ  አንድ ነገር
ይሆናል ብሎ እየጠበቀ ነው፡፡

‹‹ቤከር አንድ ያልተያዘ ወሮበላ  ይቀረናል፡ እዚህ እንዲመጣ እፈልጋለሁ፡፡ የጀልባዋ ነጂ፡ ኤዲ ሂድና ቪንቺኒ እንደሚፈልገው ንገረው አለው
👍192🔥2🥰2🤔1