አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሀያ አራት (24)


«አሁን ለምን ተለያያችሁ?» አለች ናንሲ ። ጥያቄውን እንደጠየቀች አልተለያዩ እንደሆነስ? የሚል ሀሳብ ብልጭ አለባት። ይህ ሐሳብ ብልጭ ሲል አፈረች፡፡ በሰው ነገር እየገባሁ ይሆን እንዴ? አለች፤ በሀሳቧ ምኑ ይታወቃል። ስለፒተር የማታውቃቸው በርከት ያሉ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ያ ብቻ ሳይሆን መጠየቅ የማይገባት ነገርም ሊኖር ይችል ይሆናል። ከዚህ በፊት እንዲሀ ያለ ነገር እስባ አታውቅም ነበረና ከላይ ለምን ተለያያችሁ ብላ ጠየቀች።
ልክ ላይሆን ይችላል። ይህን ለመጠየቅ ለመሆኑ እሷ ማን ናት? ምኑ ናት? «ይቅርታ ፒተር እንደዚያ እይነት ጥያቄ መጠየቅ አልነበረብኝም» አለች። «ጅል አትሁኝ» አለ ፒተር አይኑም እሷን ማየት፤ ሀሳቡም እሷን ማጤን እየጀመረ። «የፈለግሺውን ነገር ልትጠይቂኝ መብት አለሽ ፤ እንዳትጠይቂኝ የምትከለከይ ሰው አይደለሽም። እና አየሽ ጠብ ወይም ሌላ ነገር አይደለም የለያየን። የለያየን ሞት ነው ። ሞትች። ካራት ዓመት በፊት ካንሰር ገደላት ።

«ከተገናኘንበት ቀን ጀምሮ ተለያይተን እናውቅም ነበር። አብዛኛውን ጊዜ አብረን ነበርን፤ ከመጨረሻዋ ቀን በስተቀር። ወደ መጨረሻውማ አንለያይም ነበር ልልሽ እችላለሁ ። ከዚያች ቀን በስተቀር። እንደሚመስለኝ ሪቻርድም ነገሩን አውቆት ነበር ባሏ ማለቴ ነው። አወቀም ቀረም ዋጋ አልነበረውም ። እሷ እንደሁ የሁለታችንም እትሆንም ። አልሆነችም ። ካመማት በኋላ በሚገባ አውቆ ነበር ይመስለኛል ። ይህን አልሽ ይህን ሰራሽ አላለም። ምናልባት የፍቅራችንን ጥልቀት ተገንዝቦ ይህን ያህል ጊዜ ጥላው ባለመኮብለሏ ልፍታህ ባለማለቷ ይህን እንደውለታ ቆጥሮ ሊሆን ይችላል ። ሁለታችንም አዘንላት ። ሁለታችንም እልቀሰን ቀበርናት።

«ሳስባት ግርም ይለኛል ። በጣም ጠንካራ ሰው ነበረች በጣም ። ልክ እንዳንቺ!» ይህን ብሎ ቀና አለ ። አያት አየችው፡፡ እንባው ተንቀርዝዟል። ሲያያት ኮለል ብሎ በጉንጩ ላይ ወረደ ። እሷም እንባ ተናነቃት። ሳታስበው ፤ ምን እንደነካት ሳታውቀው ተጠጋችው ። እና እጅዋን ሰደድ አድርጋ እጉንጩ ላይ የፈሰሰውን እንባ ጠረገችለት ። እጅዋን ከፊቱ ላይ ሳታነሳ ጠጋ ብላ ሳም አደረገችው ፤ በለሆሳስ እከንፈሩ ላይ ። ፀጥ ላለ በጣም ረጂም ለሆነ ቅፅበት ባሉበት እንደቆሙ ቆዩ ። ከዚያም ፒተር እጁን በጀርባው አዙሮ እቅፍ ሲያደርጋት ታወቃት ። ይህም ሲሆን ከአንድ ዓመት ወዲህ ተሰምቷት የማያውቅ ስሜት ተሰማት ። ሙሉ የመሆን ፣ የጤነኝነት ፤የደህንነት ስሜት ተሰማት ። አይን ለአይን ገጥመው እጅግ ቅርብ ለቅርብ ልባቸው ተሳስሮ ፤ እሱም እጆቹን እጀርባዋ ላይ አስሮ እንዲያ እንደያዛት ዘለአለምን ለሚያህል ጊዜ ባሉበት ቆዩ።

«እንደምወድሽ እንደማፈቅርሽ ታውቂያለሽ ?›» አለ ፤ ወደኋላው ለጠጥ ብሎ። ይሀን ሲልም በፊቱ ላይ ከዚህ በፊት አይታው የማታውቀው አይነት ፈገግታ ተግ ብሎ በርቶ ነበር ። ያ ፈገግታ ከነገራት ነገር ይልቅ በልቧ ውስጥ ባንድ ጊዜ ሁለት ስሜት አሳደረባት ፤ ደስታም ሀዘንም ። ምክንያቱም ርግጠኛ አልነበረችም ። ምክንያቱም እሱ በዚያ ፈገግታ አማካይነት የሰጣትን ልትሰጠው ዝግጁ እንዳልሆነች ገብቷታል ። ትወደዋለች! ታፈቅረዋለች ። ግን አይኖቹ የሚነግሯትን ፤ በፈገግታው የነገራትን… ያን አይነት ፍቅር በዚያ አይነት መንገድ አትወደውም ርግጠኛ አይደለችም ።

‹‹እኔም እወደዋለሁ አፈቅረዋለሁ ፤ ፒተር ። በኔው መንገድ የኔ በሆነ ፡ በተለዬ መንገድ»አለች
«ደግ ለጊዜው በቂ ነው» ይህን ብሎ ፊቱ ጥቁር አለ ። የናንሲ መልስ አስከፍቶት አልነበረም ። የሟችቲ ፍቅረኛው የመጀመሪያ ቀን መልስ ትዝ ስላለው እንጂ ። አሷም ልክ እንደናንሲ ነበር ያለችው ። ሰው ሁለት ሆኖ ተፈጥሮ ይህን ያህል ይመሳሰላል ! ሲል አሰበ። ናንሲ ሁኔታውን ስታይ በመጨነቅ «ፒተር ስትጨነቅ ደስ አይለኝም» አለች ።« ልዋሽህ አልፈልግም። ... ምን ብዬ ልንገርህ!? አየህ ፒተር እወድሀለሁ ፤አፈቅርሃለሁ ። ግን ታውቃለህ አደል፣ ያለፈው ሕይወቴን አላመለጥኩትም ። ቀስ በቀስ ... በትንሽ በትንሹ ላስወግደው በመሞከር ላይነኝ። ስለዚህ አየህ ስለሁሉም ነገር ርግጠኛ አይደለሁም»

«እኔም ደግሞ አልቸኮልኩም ትልቅ ትእግሥት የታደለኝ ሰው ነኝ ። እና ተይው አያስጨንቅሽ » አመነችው ። ቃላቱ ብቻ ሳይሆኑ እነዚህን ቃላት የተናገረበት ድምፅ የሚያሳምን ነበረ። ይህም አስደሰታት። ልቧ በፍስሀ ሞቀ። ፒተር ልዩ ሰው ነው ብላ አሰበች ። ምናልባትኮ ከማምነው በላይ ይሆናል የምወደው ፤ የማፈቅረው አለች በሀሳቧ ።

ወደ መኖሪያቸው ወደ ሳንፍራንሲስኮ ለመመለስ መኪናቸውን ወዳቆሙበት ሲሄዱ ድንገት አንድ ነገር አሰበች ። ድንገት ያሰበችው ነገር አስፈራት። በደስታም አቅበጠበጣት። ነገር ግን ትፍራ ትቅጥበጥ እንጂ ልታደርገው እንደምትፈልግም ወድያውኑ ታወቃት ይህን ስታስብ ስሜቷን አይኖቿ አውጥተውት ኖሮ ያይኖቿን መንቅልቀል የተመለከተው ፒተር «አሁን ደግሞ ምን ሚስጥር ተገለጠ›› ሲል ጠየቃት። መልሷ «ምንም» የሚል ሲሆንበት «በእግዚኣብሔር እንዲያ አትበይ ። ምንድነው ነገሩ!?» አለ። አንዲህ ድንገት የሚመጣባት ነገር ያስገርመዋል ። ከወራት በፊት አንድ ቀን ጧት ከእንቅልፉ ቀስቅሳ « እፁብ ድንቅ የሆነ ስሜት ሊሰማህ ከፈለክ አሁኑኑ ተነስተህ የዛሬዋን ፀሐይ አወጣጥ ተመልክት » ያለችውን አስታወስ ። «ናንሲ» አለና «የለም ናንሲ አይደለም ሜሪ… ካሁን ጀምሮ ናንሲን አናውቃትም…. ሜሪ ፤ ይቺ ሜሪም እንደናንሲ ደፋርና አስቸጋሪ ፍጡር ናት እንዴ?»
«እንዲያውም ትብሳለች። ብታውቃት ሜሪ አዳዲስ ሀሳቦችን በየደቂቃው የምታፈልቅ ነገር ናት»አለች ።
«ያንተ ያለህ ! እንግዲያስ በቃ ይቅርብኝ» አለ ። ግን ደግሞ ይቅርብኝ ያለው ነገር እንዲቀርበት የሚፈልግ አይመስልም ነበር ። ፈፅሞ አይመስልም ነበር ። እመኪናው ውስጥ ከገቡ በኋላ «ግን ካሰበችው ትንሽ ጨረፍ ብታረግልን ? ትንሽ?» አለ። አይቻልም በሚል ራሷን እየነቀነቀች ፈገግታ አጎረሰችው ። ይህ ሲሆንም ፍሬድ ውሻው በተከፈተው በር ገብቶ እንጣጥ ብሎ ጭኗ ላይ ተቀመጠ ። ፒተር መኪናውን አስነሳ።


«እንግዲያስ እኔ አንድ ሀሳብ አለኝ ። አዲስ ዓመት እንደባተ ሜሪ አዳምሰን የፎቶግራፍ ትርኢት ብታቀርብ ምን ይመስልሻል ? አትስማሚም ? »
«እስማማ ይሆናል» አለች ነፃ የመሆን አዲስ ስሜት እየተሰማት ነበር ። «ግን መጀመሪያ ላስብበት » ‹‹አንዴ ላስብበት ... ምን የለም ። ቃል ቃል ነው ። ቃል እንድትገቢልኝ እፈልጋለሁ። እንዲያውም…» አለና ሞተር አጥፍቶ ቁልፉን ነቀለ ። ተቀመጠበት ። ከዚያም ምን ትሆኝ ከሚል ፈገግታ ጋር እየተመለከታት « እንዲያውስ ምን አለማመነኝ ! እቤትሽ መድረስ ከፈለግሽ ተስማሚ ። አይ ካልሽ እዚሁ መቅረትሽ ግድ ይሆናል ። ታግሎ ቁልፉን ለመውሰድ ደግሞ ጉልበት ያስፈልጋል›› አላት፡፡ ትንሽ የምታስብ መሰለችና « እሺ ተሸንፈናል» አለች ፍሬድን እየደባበሰች « ለዛሬ ለዚህ ጉዳይ በአሸናፊነት ወጥተዋል ። ትርኢቱን ላቀርብ ተስማምቻለሁ››

« እንዲህ በቀላሉ ?» አለ የዕውነት ተገርሞ ። ብዙ ጊዜ ይህን ጉዳይ ሲያነሳ ጭራሽ የማይሞከር ነገር ነው ትለው ነበርና። « እንዲህ በቀላሉ » አለችና የምር በሆነ ድምፅ «ግን እትርኢቱ ላይ የምገኝ ከሆነ በዚህ ሁኔታ… የሚቻል ይመስልሀል ?» ስትል ጠየቀችው ። ፈቷን እያሳየችው ። « እሱን ለኔ ተይው ። ከዚያ በፊት አንዲት ፋሻ እፊትሽ ላይ አትኖርም » አለ ።
👍211
«ሌላው ነገር ትርኢቱን ለማቅረብ ብዙ ነገር ያስፈልጋል። ሰው፤አዳራሽ . . . ያንንሳ ምን እናድርገው ? « እሱንም ለኔ ተይው ። አንቺ ተስማሚ ። ሌላውን ሁሉ በኔ ላይ ጣይው ። ተስማማን ? »
« አዎን ጌታዬ ። በፊርማ›› ይህን ስትል ያለውን ሁሉ በመተማመን ነው። ታምነዋለች። ፒተር ምንም ነገር ያደርጋል ። ትርኢቱን ሊያዘጋጅ እንደሚችል ታምንበታለች ። በስራው ሁሉ ታምንበታለች ። ፊቷን በቀዶ ጥገና ሙያው ሊያስውበው እንደሚችል ታምንበታለች ። ለኑሮዋ ፤ ለጤናዋ ፤ ለህይወቷ ቤዛ እንደሆነ ታምንበታለች ። «የኔ ውድ ፤ የፎቶግራፍ ትርኢቱ ከቀረበ በኋላ ለምን አደረኩት ብለሽ እንደማትፀፀች ርግጠኛ ነኝ» አለና ሳማት ። መኪናውን አስነሳ ። ጉዞ ቀጠሉ ።


እቤቷ እንደገባች ወደ መኪናው እየሄዱ ሳለ ያሰበችው ነገር ትዝ አላት ። ኮመዲኖ ከፍታ የተለያዩ ንድፎችን ፤ ስዕሎችን አወጣች ። በመጨረሻ የፈለገችውን አገኘች ። አየችው ። ቃል ገብታ ነበር ። ይህን ስዕል ለማይክል እንደምትሰጠው… የሰርጋቸው ዕለት እንደምታበረክትለት ቃል ገብታ ነበር ። የገፀ ምድርን ምስል የያዘ ሲሆን አንደኛው ዛፍ ቅርንጫፍ ላይ አንድ ልጅ ተቀምጦ የሚያሳየው ስዕል ነው ። ገና ስታየው እንባዋ ዝርግፍግፍ ብሎ ፊቷን አለበሰው ። ይህን ስዕል አውጥቶ ለማየት፣ ለመጨረስ ስትፈራ ነበር ። ይህን ለማድረግ ይኸወና ዓመት ከሰባት ወር ፈጀባት ። አሁን ግን ደፈረች ። አንዴ ደፍራዋለች። ገና አላለቀምና ትጨርሰዋለች ። ለፒተር ።

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍71
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰባ_ሦስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

ሳቤላ ዊልያም ካርላይል ከሚያጣጥርበት አልጋ ጎን ተንበርክካለች ያች የማትቀረው የመጨረሻ ሰዓት ደርሳለች " ልጁም ቁርጡን ዐውቆ ከመራራዋ
ዕድሉ ጋር ታርቆ መንፈሱን አርግቶ ዟ ብሎ ተዘርግቶ ይጠብቃል "

በጉንጮቹ ይታይ የነበረው ደማቅ የትኩሳት ቅላት ለቋል ፊቱ ነጥቷል
አጥንቱ ወጥቷል " ዐይኖቹ ትልልቅና ደማቅ ሆነዋል ቅላት የቀላቀለው ሐርማው ጸጉሩ ወደ ኋላ ተቀልብሶ ተኝቷል " እንደ እሳት የሚፈጁት ትናንሽ እጆቹ
ከአልጋው ውጭ ተዘርግተዋል "

“ እንግዲህ ብዙ የምትጠብቅ አይመስለኝም አይደለም ማዳም ቬን ”?

"ለምኑ ነው የኔ ልጅ ? ”

“ሁሉም እስኪመጡ" አባባ እማማና ሉሲ ሁሉም „”
ግንባሯን ( ድርቅ ብሎ ከከሳው ክንዱ ላይ አንተርሳ ከላዩ ላይ ተደገፈችና
እንባዋን አፈሰሰች "

ዊልያም ጥቂት ካሰበ በኋላ “ አየሽ . . '' ድምፁ ወደ ውስጡ ሰጠመ ምልስ ሲልለት እያመነታ ስለ ወላጅ እናቱ አየሽ . . ደግ ሰውኮ አልነበረችም ለኛም ላባባም ክፉ ስው ነበረች እንዲያውም ተጸጽታ ይቅርታ የለመነች አይመስለኝም "

“ ዊልያም” አለች እየተንሰቀሰቀች “ከናንተ ከተለየች የነበረው ሕይወቷን በጸጸትና በኅዘን ነው ያሳለፈችው ጸጸቷ ኀዘኗ ከምትችለው በላይ ነበር " ሁል ጊዜ ስለናንተ ስለ አባታችሁ ስታስብ ነበር መንፈሷ የተሰበረ » ”

"እንዴ ማዳም ቬን ! ይህንን ነገር እማማ ካልነገረችሽ ማወቅ እትችይም አይተሻት ታውቂያለሽ ? ባሕር ማዶ ሳለች ታውቂያት ነበር ?

“ አዎን ባሕር ማዶ ዐውቃት ነበር "
“ አዬ ! ታዲያ ለምንድነው ነግረሽኝ የማታውቂ ? ምን አለችሽ ? ምን ትመስል ነበር?”
“ ከልጆቿ መለየቷን ስትነግረኝ ነበር " ነገር ግን አንድ ቀን እንደምታገኛቸውና ለዘለዓለም አብራቸው እንደምትኖር ትነግረኝ ነበር

"ፊቷ ምን ይመስል ነበር ? ”

“ ያንተን ይበልጡን ደግሞ የሉሲን ይመስል ነበር ”
"ቆንጆ ነበረች ? ”
ትንሽ ዝም አለችና ' ' አዎን ” አለችው "

“ አ ... ዬ ! ወይኔ ! አመመኝ ! ያዥኝ እስቲ ! ” አለ » ቀና ብሎ የነበረው ራሱ ዝቅጥቅጥ ከፊቱ ላይ ላቡ ክንብል ሲል ያ አንዳንድ ጊዜ የሚነሣበት
የሰውነት ዝለት የተቀሰቀሰበት መስሏት ነበር " ሳቤላ ደወለችና ዊልሰን መጣች "
ብዙ ጊዜ ከዊልያም የማትለይና አንድ ችግር ሲኖር የምትቀርብ
ጆይስ ነበረች "የዚያን ዕለት ግን የነበረውን አሳሳቢ ሁኔታ አልተገነዘበችውም ቀኑ ሪቻርድ ነጻ በተለቀቀበት ማግሥት ነበር " ሚስዝ ካርላይል ለሁለተኛ ጊዜ የታመመው አባቷን በባሏ መታመም ደንግጣ በልጅዋ ነጻ መውጣት ተደስታ የነበረችው እናቷን
ከብዙ ዘመን ስደት በኋላ ከወላጆቿ ጋር የተጨመረው ወንድሟን ለመጠየቅና አብራ ለመዋል ወደ ወላጆቿ ቤት ሔደች " ጆይስንም አስከትላ ወስዳት ነበር " በዚያ ጊዜ እግረኛው ሳይጨመር አምሳ የሚሆኑ ሠረገሎች በጀስቲስ ሔር ቤት ተሰብስበዋል " 'ይኽ ሁሉ ሰው ኮ አንተን ለማየት ነው . . ሪቻርድ” ብላው ነበር እናቱ ዐይኖቿ የደስታና የፍቅር እንባ እያቀረሩ ሉሲንና ትንሹን አርኪባልድን
ሣራ ይዛቸው ወደ ሚስ ኮርኒሊያ ቤት ሔደዋል ስለዚህ ከቤት የቆየችው ዊልሰን ብቻ ስለ ነበረች ማዳም ቬን ስትደውል ከች አለች።

"ምነው ? አሁንም ድካሙ ተነሣበት ? ” አለች ስትገባ "
“ መሰለኝ እስኪ እርጂኝና ቀና እናድርገወ ” አለቻት ሳቤላ ።
ዊልያም ግን ነፍሱን አልሳተም " ይዞታው ከተለመደው የተለየ ነበር » እንደወትሮው አቅሉን በመሳትና በመዝለፍለፍ ፈንታ ማዳም ቬንና ዊልሰንን ግጥም አድርጎ ይዞ ወባ እንደ ተነሣበት ተንቀጠቀጠ

ያዘኝ ኧረ እንዳልወድቅ ያዙኝ ደግፉኝ ” እያለ ይቃትት ጀመር ትንሽ ቆየና ጭንቀቱና እንቅጥቃጤው እልፍ አለለት ። ላቡን ከግንባሩ ጠረጉለትና ዐይን ዐይኑን ይመለከቱት ጀመር ዊልስን አንድ ማንኪያ ለስሳሳ ምግብ ካፉ ስታደርግለት ዋጠው " ልትደግመው ስትል ራሱን ነቀነቀ » ፊቱን ወደ ትራሱ
መለሰና ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ እንቅልፍ ሽልብ አደረገው "

“ ምን ነገር ነው ልጄ ?” አለች ሳቤላ ቀስ ብላ ወደ ዊልሰን እየተመለከተች
“ ነገሩን ዐውቀዋለሁ ከዚህ በፊትም የዚህ ዐይነት ሕመም አንድ ጊዜ
አይቻለሁ "

“ ምክንያቱ ምንድነው . . . ዊልሰን? አለች ሳቤላ።

"ያየሁት ባዋቂ እንጂ በልጅ አልነበረም ። ግን ልዩነት የለውም " ሁሉም በተመሳሳይ ምክንያት ነው የሚነሣው ሊሞት ይመስለኛል "

"ምን መሆንሽ ነው .. ዊልሰን ? እስከዚህኮ አልታመመም " ደሞ ዛሬ
ጧት ሚስተር ዌይንራይት አይቶት አንድ ወይም ሁለት
ሳምንት ይቆይ ይሆናል
ብሏል"

ዊልሰን ከምቹ ወንበር ላይ ተደላድላ ቁጭ አለች አስተማሪቱን እንኳን
የማክበር ልምድ አልነበራትም » አስተማሪቱም ቢሆን ደረጃዋን ጠብቃ እንድትቀመጥ እንዳትነግራት ትፈራት ነበር ሚስተር ዌይንራይትን እንዳለ አትቁጠሪው እዚህ ግባ የሚባል ሰው አይደለም ” አለች ዊልሰን " የልጁ
ትንፋሽ እየቀነሰ መሔዱን ቢያይና ትንሽ ቆይቶ ደግሞ የመጨረሻው የሚሆን ቢሆን እንኳ ከዐሥራ ሁለት ሰዓት በላይ እንደሚቆይ ለሁላችንም እየማለ ይነግረን ነበር " ዌይንራይትን እኔ የማውቀውን ያህል አታውቂውም ማዳም ። ከናቴ ቤት ሐኪማችን እሱ ነበር ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከተቀመጥኩባቸው ቦታዎች ሁሉ ሲያክም ዐውቀዋለሁ " ከስኳየር ስፒነር ቤት ዋና ሞግዚት ሆኜ አምስት ዓመት
የሚስዝ ሔር ደንገጡር ሆኘ አራት ዓመት ሠርቻለሁ " ክዚህ ቤትም ሚስ ሉሲ
አራስ ልጅ ሳለች ነበር የገባሁ " ታድያ ከነዚህ ቦታዎች ሁሉ እንደ ጥላ እየተከተለኝ ሠርቷል እመቤት ሳቤላ በሱ ላይ ከፍተኛ እምነት እንደ ነበራቸው ትዝ ይለኛል እኔ ከማስበው በላይ ይገምቱት ነበር።

ሳቤላ ምንም ሳትመልስ ዊልያምን ዐይን ዐይኑን እያየች ዝም አለች "

የትንፋሹ ድምፅ እየጐረነነና እየከበደ ሔደ »

" ያቺ ሣራ ” አለች ዊልሰን “ መቸም ከብት አይደለች ! ከየትኛው የወንድ አያቱ አጠገብ ይቀብሩት ይሆን ? " አለችኝ " “ እኔ ደግሞ እናቱ
የሚስተር ካርላይል ሚስት እንደሆነች ብትሞት ኖሮ እሷ ካባቷ አጠገብ ስለምትቀበር እሱም ከናቱ ጎን ይቀበር ነበር " አሁንማ ከአባቱ አባት ጎን ነው መቀበር ያለበት አልኳት።

ሳቤላ የልጁን ማንቋረር ብቻ እያዳመጠች ዝም አለቻት ዊልስን ርዕስ ቀየረች

“ አዪጉድ ! አሁን ያ መልከ መልካም ጎበዝ ምን ይመስለው ይሆን ?” አለቻት በማሾፍ » ሳቤላ ሙሉ ሐሳቧ በልጁ ላይ ስለ ነበር ስለሱ የተናገረች መሰላትና እሷም በመገረም ቀና ብላ አየቻት "

“ ያንኮ ሊንበራ ወህኒ ቤት የገባውን ሽቅርቅር ማለቴ ነው " መቸም ከትናንት ጀምሮ ያለው መኖር መኖር' አይሆንም " አቤት!እሱ በሚሰቀልበት ቀን ስንት ባቡር ሙሉ ሕዝብ ለማየት ይሔድ ይሆን ? ”

“ ተፈረደበት እንዴ ? ” አለች ሳቤላ ስልል ባለው ድምጿ "

“ተፈረደበት ሚስተር ኦትዌይ ቤቴል ተለቀቀ » ሪቻርድ ሔርም በነጻ ተለቀቀ መቸም አምሮበታል ይባላል " እሱ በነጻ ሲለቀቅማ ከፍርድ ቤቱ ሙስጥ
ጭብጨባው ውካታው ቀለጠ ዳኛው እንኳን መቆጣጠር አልቻለም ነበር ይላሉ ”

“ ማነው ሪቻርድ ሔር ወደ ቤቱ ተመለሰ ያለው” አለ ዊልያም ድክም ባለና
እንደ ልብ በማይሰማ ድምፁ "
👍10
ዊልሰን ወደ ተኛበት አልጋ ተንደርድራ ሔዳ “እንዴ ዊልያምI በል ዝም ብለህ
ተኛ አባትህ ከሊንበራ ሲመለሱ እንደዚህ ደክሞህ ሲያገኙሀ እኔን ነው የሚቆ
ጡኝ " በል አሁን ዐይኖችህን ሸፍንና ተኛ " ጥቂት ፈሳሽ ምግብ ትፈልጋለህ ? አለችው "

ዊልያም ስለ ፈሳሹ ምግብ ምንም ምላሽ ሳይሰጥ ከትራሱ ላይ ሽብልል ብሎ
ተኛ ሚስተር ካርላይል ለሥራ ጉዳይ ብዙ ጊዜ ወደ ሊንበራ ይመላለስ ነበር "
በዚያን ዕለትም እዚያው ሔዶ ውሎ በአንድና በሁለት ሰዓት መካከል ወደ ቤቱ
ተመለሰ ወዲያው እንደ ደረስ ወደ ዊልያም ክፍል ገባ " ልጁ ያባቱን ድምፅ
ሲሰማ ፊቱ በራ "

“ አባባ!” አለ "

ሚስተር ካርላይል አልጋው ላይ ተቀመጠና ሳመው ልትጠልቅ ማሽቆልቆል
የጀመረችው ጀንበር ጨረሯ ከክፍሉ ቦግግ ብሎ ስለነበር ሚስተር ካርላይል
በልጁ ፊት የሞት ጥላ እንዳጀበበት በግልጽ ታየው

“ ባሰበት እንዴ ? " አላት ማዳም ቬንን "

ዛሬ ማታ የባሰበት ይመስላል ” አለችው ከምን ጊዜም የበለጠ ድክም
ባለ ድምፅ

"አባባ አለ ዊልያም እየቃተተ : “ ፍርዱ አበቃ ? ”

የምን ፍርድ የኔ ልጅ ? ”
“ የሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን"

“ ትናንት አበቃ " አሱን ራስህን ልታስጨንቅለት የሚገባው ሰው አይደለም አታሰብ "
“ ለማወቅ እኮ ፈልጌ ነው ' ይሰቅሎታል ? ”
“ ሞት ተፈርዶበታል
ሆሊጆንን ገድሎታል ?”

“አዎን ስለዚህ ጉዳይ ማን ነገረው ? ” አላት ማዳም ቬንን " ነገሩ ቅር እንዳለው ከድምፁ ይታወቅ ነበር "

"ዊልሰን ነገሩን አንሥታው ነበር ... ጌታዬ !
የኔ ልጅ . . . ምነው ዕረፍት አጣህ ? ”

“ አንድ ቦታ ላይ መርጋት አልቻልኩም " አልጋ ትክክል አይደለም ማዳም ቬን እስኪ ወደ ትራሱ ሳቢኝ "

ሚስተር ካርላይል ራሱ ከፍ አደረገው : “ማዳም ቬን ድካምን የማታውቅ
አስተማሚህ ናት” አለው ማዳም ቬን ሔዳ ወደ ተጠጋችበት የመስኮት መጋረጃ በለውለታነት እየተመለከተ።

"ረስቼው ረስቼው ! " ዊልያም አልመለስለትም " አንድ ነጀር ለማስታወስ በመጣር ያለ ይመስል ነበር

" ምን ረሳህ የኔ ልጅ ? ” አለው አባቱ "

“ አንድ ልጠይቅህ ወይም ልነግርህ የፈለግሁት ነገር ነበር " ሎሲ አልመጣችም ?

የመጣች አልመሰለኝም ” አለው "

“ ጆይስን እፈልጋታለሁ " "

“ከራት በኋላ እናትህ ዘንድ እሔዳለሁ » እንደ ደረስኩ ወደ አንተ እልካታለሁ

“ እማማ ዘንድ ? አሃ አሁን አስታወስኩ » አይደለም እንጂ አባባ እማማን
ከሰማይ እንዴት ላውቃት እችላለሁ ? ይህችኛዋን እማማን አይደለም ”

ሚስተር ካርላይል • ምናልባት በጥያቄው ግራ ተጋብቶ ሊሆን ይችላል
ቶሎ አልመለሰለትም "

" ከመንግሥተ ሰማያት እኮ ትግኛለች ” አለ ልጁ ራሱ "
"አዎን አዎን ልጄ! ከዚያ እንደምትገኝ ማዳም ቬንም ታውቃለች " ውጭ አገር ተገናኝተው ነበር " ያውም አንድ ነገር ምን ነበር ማዳም ቬን ? ” አላት "

ማዳም ቬን ከልክ በላይ ደነገጠች » ሚስተር ካርላይል በድንጋጤ በርበሬ
የመሰለ ፊቷን ትክ ብሎ አያት " ቢቻላት ኖሮ ወጥታ እልም ብትል አትጠላም ነበር "

“ እማማ በጣም ' በጣም ታዝን ነበር አሉ” አለ ዊልያም የጠየቀውን
እርዳታ አለማግኘቱን ሲያውቅ " አንተንም ፈልጋ እኛንም ፌልጋ ፈልጋ
ሁላችንንም ስታጣ ልቧ በኀዘን ፈርሶ ሞተች ” ”

ሚስተር ካርላይል ፊቱ ደም መሰለና አሁንም ወደ ማዳም ቬን ተመለከተ »

ጌታዬ ይቅርታ እንዲያደርጉልኝ ” አለችው ድክም ባለ አነጋገሯ
“ ስለዚህ ጉዳይ በማንሣት በቤተሰብዎ ጉዳይም መግባት አልነበረብኝም
ልጁ የናቱን ነገር እያነሣ ተወዝውዞ ሊሞት ሲሆን ጊዜ ትንሽ ያረጋጋሁት መስሎኝ ነው የተናገርኩ

ሚስተር ካርሳይል ግራ ገባው “ ነግሩ ሊገባኝ አልቻለም " ለመሆኑ እናቱን ባሕር ማዶ አይተሻት ነበር ?

አጅዋን አንሥታ ደም መስሎ የቀላውን ፊቷን ጋርዳ “ኧረ የለም ጌታዬ
አለችው " የተጨነቀች ልብ ያረገችው ጸሎት ደረሰ ከተባለ የሷ ነበር ሚስተር ካርላይል ሳይታስብ ርእሱን ለወጠላት "

ሚስተር ካርይል ወደሷ ጠጋ አለና ' “የመልኩን መለዋወጥ ልብ ብለሽ
አየሽው ? ” አላት ቀስ ብሎ
“ አዎን ጌታዬ ዛሬ ከቀትር በኋላ አዲስ ዐይነት እንቅጥቃጤ ካንቀጠቀጠው ወዲህ መልኩ እንደዚህ ሆነ ዊልሰን ከእንግዲህ በሕይወት እንዳለ አይቆጠርም ትላለች " እኔም ከኻያ አራት ሰዓት በላይ የሚቆይ አይመስለኝም "

ሚስተር ካርይል ክንዱን ከመስኮቱ ጠርዝ አሳርፎ ግንባሩን እጁ ላይ አስደግፎ ! “ ኧረ እሱን ማጣትስ አያምጣው ! ከባድ ነገር ነው ! ” አላት "

“ይሻለዋል ጌታዬ” አለችው ይተናነቃት የነበረውን እንባና ጭንቀት አምቃ ለመያዝ እየታገለች " ሞት በዚህ ዓለም ከታዩት የመለያየት ዐይነቶች ሁሉ የከፋ
አይደለም ሞትን እንችለዋለን " እሱም ከዚህ ዓለም ጭካኔ ይላቀቃል "

አንዲት ሠራተኛ መጣችና ራት መቅረቡን ነገረችው " ሚስተር ካርላይል
ተነሥቶ ሔደ ተመልሶ በሽተኛው ወደ ተኛበት ክፍል ሲመጣ ፀሐይ ጠልቃ
ጨረሯ በነበረበት አንድ ሻማ ተተክቶ ደረሰ " የልጁ ፊት እንደ ጨረሩ ጊዜ በደንብ ሊታየው አልቻለም ሻማውን አንሥቶ ፊቱን ጠጋ ብሎ ለማየት ቀረበ "
ብርሃኑ ከፊቱ ሲያርፍ ልጅዋ ዐይኖቹን ገለጥ አደረገ ።

ተወኝ እባክህ ... አባባ ! ጨለማው ይሻለኛል "

“አንድ ጊዜ ብቻ ልይህ የኔ ልጅ” አለው " ፊቱ ጢስ እንደ መሰለ ነበር
ሞት እየቀረበ መሆኑን በግልጽ ተግነዘበው

በዚያ ሰዓት ሉሲና አርኪባልድ አክስታቸው ሚስ ኮርኒሊያ ዘንድ ውለው
ገቡ ከሞት አፋፍ የነበረው ልጅ ዐይኖቹን በናፍቆት ገለጥ አደረጋቸው "

“ ደህና ሁኝ . . ሉሲ አለ ላብ ያረጠበው ቀዝቃዛ እጁን ለመዘርጋት እየሞከረ ።

“ እኔኮ ከውጭ ቆይቸ መምጣቴ ነው " እየወጣሁ አይደለም ” አለችው ሎሲ " “ገና አሁን መግባታችን ነው

“ ደኅና ሁኝ .. ሎሲ ” አለ ዊልያም መልሶ።

የዘረጋላትን እጅ ተቀብላ ሳመችው "በል ደህና ሁን ! እኔ ግን የትም እየሔድኩ እንዳይመስልህ :እዚሁ አለሁ አለችው "

“ እኔ መሔዴ ነው ” አላት " " ወደ ሰማይ እየሔድኩ ነው :አርኪባልድ የት አለ ? ”

ሚስተር ካርላይል አርኪባልድን ወደ አልጋው ከፍ አደረገለት » ሉሲ ደነገጠች » አርኪባልድም ግራ ተጋባ "

“ደኅና ሁን አርኪባልድ ደኅና ሁን የምወድህ " እኔ መሔዴ ነው ወደዚያ ወደ ጠራው ሰማይ " እዚያ ሔጄ እማማን አግኛታለሁ » አንተና ሉሲ በቅርቡ እንደምትጡ እነግራታለሁ "

ሉሲ ወትሮውንም ሆደ ባሻ ነበረች " ስለዚህ ጦሽ ብላ አለቀሰች እሷ ስትጮህ ክፍሉ ተረበሽ " ዊልሰንም ልቅሶ ሰምታ ከሌላ ክፍል ሮጣ ደረሰች » ሚስተር ካርላይል ልጆቹን ! “ ተሽሎት ካደረ ደግሞ ነገ ጧት ታዩታላችሁ " ብሎ አባብሎ እንዲወጡ አደረጋቸው"

ሳቤላ ከአልጋው ጎን ተንበርክካ በጩህት ለመውጣት የሚተናነቃትን
የናትነት ጭንቀት ለማፈን ፊቷን ከአልጋው ልብስ አድርጋ አንዱን ያልጋ ልብስ ጠርዝ ከአፏ ውስጥ ወተፈችው ውጥረቱ ከመታገስ ዐቅሟ በላይ
ሆኖ ሔደ " የገዛ ልጅዋ የሱም ልጅ ' ሁለቱም ' አባትና እናቱ ሚጠራሞትበት አልጋ ዙሪያ ሆነው ተጨነቁ » የልጅዋን ጣርና ስቃይ እያየች አንዲት የአይዞታ አንዲት የማጽናኛ ትንፋሽ ለመናገርም ለመቀበልም አልቻለችም " አንጀቷ እየተንሰፈሰፈ ' ውስጧ እያረረ እየተቀቀለ
በውጭ ለሚያይ የናት ባዕድ ሆና ተከድና ትበስል ጀመር "
👍18
ሚስተር ካርላይል ' ድምጿን አፍና ስትንሰቀሰቅ ሰምቶ ዞር ብሎ አንደ ማንም አዛኝና ደግ ቅጥር ሠራተኛ አያት " ለሱም ለደከመ ልጁም ምናቸውም
አይደለችም » ጐንበስ ብሎ ወደ ልጁ ተጠጋ “ ዐይኖቹ እንባ አቀረሩ ።

" አታልቅስ አባባ ! ” አለው ዊልያም በለሆሳስ ደካማ እጁን ብድግ አድርጎ ያባቱን ጐንጭ እየዳበሰ " " እኔ እኮ ለመሔድ አልፈራም "

“ለመሔድ መፍራት ! የኔ ልጅ እሱንስ እንደማታደርገው አምናለሁ አንተ እየሔድክ ነው ወደ ደስታ ከጥቂት ዓመት በኋላ እኛም ሁላችንም ወደ አንተ
እንመጣለን "

“ አዎን እንደምትመጡ በደንብ ዐውቃለሁ ።

ለእማማም ይኸኑ እነግራታለሁ።ምናልባትም ከወንዙ ዳር ቁማ ነፍሶችን የሚያጓጉትን ጀልባዎችን እየተመለከተች ትጠብቀኝ ይሆናል ።”

“ አባባ .. እናቴ ቅስሟ ተሰብሮ መሞቷን ታውቃለህ ? ”

ዊልያም እናትሀ ቅስሟ የተሰበረው ከመሞቷ በፊት ይመስለኛል አሁን
ስለሷ ሳይሆን ስለ አንተ እንጫወት ሕመም ይስማሀል ? ”

“መተንፈስ አቃተኝ " መዋጥ ከለከለኝ « ጆይስ እዚህ ብትኖር እወድ ነበር”
ሚስተር ካርላይል ቀስ አድርጎ ትራሱ ይ አሳረፈውና አስተውሎ ከተመለከተው
በኋላ ሊወጣ ዞር ሲል " እንዴ ! አባባ ! አባባ !” ብሎ ጠራው የናፍቆት ዐይኖቹን ገልጦ “ ደህና ሁን በለኝ እንጂ ” አለው »

ሚስተር ካርይል ምልስ ብሎ ልጁን ከደረቱ እቅፍ ሲያደርገው እንባው ፈሰሰ
አየወረደ የልጁን ፊት አራሰው “ የኔ ልጅ ... አባባ አሁን ይመለሳል " አማማን
እንድታይክ ሊያመጣት ነው....

💫ይቀጥላል💫
👍11
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ

‹‹አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ግድ የለኝም፡፡ ጦርነት አውድማ ውስጥ ገብቼ ፋሺዝምን ከሀገሬ ለማባረር እዋጋለሁ›› አለች በልበ ሙሉነት፡ ፊቷ ላይ
የሚነበበው ገፅታ ለህይወት ግድ እንደሌላት ያሳያል፡ ሄሪ ይህን ሲያይ ጎበዝ ናት› አለ በሆዱ፡፡

‹‹የቆረጥሽ ትመስያለሽ››

‹‹በዚህ እምነቱ የተነሳ የስፔን ፋሺስቶችን ሊዋጋ ሄዶ አፈር በልቶ የቀረ ፍቅረኛ ነበረኝ፡፡ የእሱን አርማ አንስቼ አላማውን ዳር ለማድረስ እታገላለሁ››ደ አለች በወኔና በሀዘን፡

‹‹ትወጂው ነበር?»

በአዎንታ ራሷን ነቀነቀች፡፡

አይኗ እንባ እንዳቀረረ ተመለከተና በሀዘኔታ ክንዷን ያዝ አደረጋት
‹‹አሁንም ትወጂዋለሽ?›› ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹ምን ጊዜም ከልቤ አይጠፋም›› አለች የሹክሹክታ ያህል ‹‹ስሙ ኢያን ይባላል፡››

ሄሪ አሳዘነችው፡፡ ማርጋሬትን ደረቱ ውስጥ ወሽቆ ሊያፅናናት
ቢፈልግም በየት በኩል። ውስኪያቸውን እየጨለጡ ጋዜጣ የሚያነቡ በርበሬ
ፊት አባቷ ፊት ለፊት ተቀምጠዋል፡ እንደ ምንም እጁን ሰደደና አጇን ጨመቅ አደረገው፡፡ እሷም ለማፅናናት መሆኑ ገብቷት
ፈገግ አለች።

‹‹እራት ደርሷል ሚስተር ቫንዴርፖስት›› አለ አስተናጋጁ፡ ሄሪ አስራ
ሁለት ሰዓት ከምኔው እንደደረሰ ገርሞታል፡ ከማርጋሬት ጋር የጀመረውን
ጭውውት ማቋረጡ አሳዝኖታል፡፡ እሷም የእሱ ጭንቀት ገባትና ‹ብዙ
የምንጫወተው ነገር አለ›› አለች ‹‹ለሚቀጥሉት ሃያ አራት ሰዓታት አብረን
እንሆናለን››

‹‹ልክ ነሽ›› አለና ፈገግ አለ፡፡ እንደገና እጇን ዳበስ አደረገና ‹‹በኋላ
እንገናኝ›› አላት፡፡

ምስጢሩን በሙሉ የነገራት አጋሩ ሊያደርጋት ነው፡፡

ወደሚቀጥለው ክፍል ሲገባ ክፍሉ ከሳሎን ቤት ወደ መብል ቤትነት ተለውጦ ሲያይ ተገረመ እያንዳንዳቸው አራት ሰዎች የሚቀመጡባቸው
ሶስት ጠረጴዛዎች የተዘረጉ ሲሆን ሌሎች ሁለት ትንንሽ ጠረጴዛዎችም ይታያሉ፡፡ የእቃው አደራደር እንደ ምግብ ቤት ሲሆን ጠረጴዛዎቹ ጨርቅ
ለብሰዋል፡፡ በላያቸው ላይ የፓን አሜሪካ አየር መንገድ ስምና ምልክት ያለባቸው ብርጭቆዎች፣ ሰሃኖችና ናፕኪኖች ተቀምጠዋል። የመብል ክፍሉ ግርግዳ የአለም ካርታ ተለጥፎበታል አስተናጋጁ ሄሪን አንድ ሱፍ የለበሰ አጠርና ደልደል ካለ ሰው አጠገብ ወስዶ አስቀመጠው: ሄሪ የሰውዬው አለባበስ አስቀናው፡ ሰውዬው ክራቫት ያደረገ ሲሆን ውድ በሆነ ማያያዣ ጌጥ ከሸሚዙ ጋር አያይዞታል፡ ሄሪ እራሱን አስተዋወቀ፡ ሰውዬውም እጁን ለሰላምታ ዘረጋና ‹ቶም ሉተር እባላለሁ›› አለ፡፡ እጁ ላይ ያለው የወርቅ አምባር ከክራቫት ማያያዣው ጋር ይሄዳል፡፡ ለውድ ጌጣጌጥ ገንዘቡን
መበተን የሚወድ ሰው ማለት ይሄ ነው፡፡

ሄሪ የታጠፈውን ናፕኪን ዘረጋ፡፡ ሉተር አነጋገሩ የአሜሪካዊ ነው።
‹‹ከየት ሀገር ነው የመጣኸው?›› ሲል ሄሪ ጠየቀው ሰውዬውን
‹‹ፕሮቪደንስ ሮድ አይላንድ፧ አንተስ?››
‹‹ፊላደልፊያ›› አለ ሄሪ፡ ፊላደልፊያ የት እንዳለ እንኳን አያውቅም፡፡
አሜሪካ ውስጥ ያልኖርኩበት ቦታ የለም፡፡ አባቴ የኢንሹራንስ ሰራተኛ
ነበር፡››

ሉተር አንገቱን ነቀነቀ፡፡ ነገር ግን ከዚህ በላይ ማውራት አልፈለገም የሰውዬው ዝምተኛነት ለሄሪ ተስማምቶታል፡ ስለአኗኗሩ ሰው እንዲጠይቀው
አይፈልግም: በዝምታ ማለፍ ጥሩ ነው፡
ሁለት የአይሮፕላኑ ሰራተኞች በመጡና ራሳቸውን አስተዋወቁ፡ የበረራዐመሀንዲሱ ኤዲ ዲኪን ትከሻው የሰፋ፣ የደስ ደስ ያለው ፀጉረ ነጭ ሰው
ነው፡ ሁለተኛው ጃክ አሽፎርድ የሚባል ናቪጌተር ነው ፀጉረ ጥቁር ሲሆን
የለበሰው ዩኒፎርም ሄዶበታል።

ሰዎቹ እንደተቀመጡ በሉተርና በመሃንዲሱ መካከል የሆነ ጠብ እንዳለ
ሄሪ አስተዋለ።እራት ቀረበ፤ ሁለቱ የአይሮፕላን ሰራተኞች ኮካ ኮላ ሲመጣላቸው ሄሪ
ነጭ ቪኖ ቀረበለት፡ ቶምሉተር ማርቲኒ አዘዘ
ሄሪ እራት እየበላ ሳ
በአይሮፕላኑ መስኮት እያየ ስለማርጋሬትና ስፔን
ሄዶ ስለቀረው ቦይ ፍሬንዷ ያስባል፡፡ ስለእሱ አሁን ምን ያህል እንደምታስብ ማወቅ ፈለገ፡፡ ከእሷ እድሜ አንጻር አንድ አመት ትንሽ ጊዜ አይደለም፡፡

ጃክ አሽፎርድ ሄሪ በመስኮት እያየ መሆኑን ተገነዘበና ‹‹እስካሁን አየሩ
ጥሩ ስለሆነ እድለኞች ነን›› አለ፡

‹‹ሁልጊዜ እንዴት ነው አየሩ?›› ሲል ጠየቀ ሄሪ

‹‹አንዳንድ ጊዜ ከአየርላንድ እስከ ካናዳ በዝናብ የምንሄድበት ጊዜ አለ፡፡
‹‹አንዳንዴ ደግሞ በረዶና መብረቅ ያጋጥማል፡››

ሄሪ አንድ ጊዜ ያነበበውን አስታወሰና ‹‹በረዶ ከዘነበ ለአይሮፕላኑ አደገኛ አይደለም?›› ሲል ጠየቀ፡

‹‹በተቻለን መጠን ቀዝቃዛው የአየር ንብረት እንዳያገኘን እንጥራለን፡፡ለማንኛውም ተብሎ ግን አይሮፕላኑ ክንፎች ላይ የበረዶ ማቅለጫ ሸራ
ተደርጎለታል፡››

የመጪው የአየር ትንበያ ምን ያመለክታል?››

ጃክ ይህን መልስ ለመስጠት ሲጠራጠር አየና ስለአየሩ ባልጠየቅ ይሻል
ነበር›› ሲል አሰበ፡፡ ‹‹አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ዶፍ ዝናብ ይጠብቀናል››
አለ፡፡

‹‹ይህን ያህል መጥፎ ነው?›› ጠየቀ ሄሪ፡

‹‹ዶፍ ዝናቡ መሃል ከገባን መጥፎ ነው፡ ሆኖም እኛ ከዶፍ ዝናቡ ራቅ ብለን እንበራለን›› አለ በሰጠው መልስ ብዙም ባለመተማመን፡፡

ቶም ሉተርም ቀጠለና ‹በዶፍ ዝናብ ውስጥ መጓዝ ምን ችግር አለው ሲል ጠየቀ።

ጃክ በዝርዝር አልተናገረም፤ ነገር ግን የበረራ መሀንዲሱ ኤዲ፣ ቶም ሉተርን ለማስፈራራት ሲል ወደ እሱ እያየ ‹‹ልክ ባልተገራ ፈረስ የሚጋልቡ ይመስል ያነጥራል›› አለ፡

ሉተር ኤዲ ያለውን ሲሰማ በድንጋጤ አመድ መሰለ፡፡ ኤዲ በተሳፋሪው
ፊት አፉ እንዳመጣ በመናገሩ ጃክ ገላመጠው:

ተሳፋሪዎቹ ሁለተኛ ዙር የእንቁራሪት መረቅ መጣላቸው:🤮

አሁን የሚያስተናግዱት ሁለቱ አስተናጋጆች ኒኪና ዴቪ ናቸው፡ ኒኪ ድብልብል ሲሆን ዴቪ ደግሞ ከአፍ የወደቀች ጥሬ ነው የሚያክለው፡፡

ሄሪ ሁለቱም ወንዳገረዶች ሳይሆኑ አይቀሩም› ሲል ገመተ፡ ታዲያ ቅልጥፍናው አስደስቶታል፡፡

ሄሪ በድብቅ እንደተከታተለው የበረራ መሀንዲሱ አዕምሮው በአንድ ነገር የተጠመደ ይመስላል፡፡

‹ሄሪ መሀንዲሱ ባህሪው አኩራፊ አይመስልም፡፡ ሲያዩት ተጫዋችና
ግልፅ ይመስላል› ሲል አሰበና እንዲናገር ለማበረታት ‹‹አንተ ምግብ በምትበላበት ጊዜ የበረራ ምህንድስናውን ስራ ማን ይሰራል?›› ሲል ጠየቀው
‹‹ረዳት የበረራ መሀንዲሱ ሚኪ ፊን ነው›› አለ፡ ‹‹በፈረቃ ነው የምንሰራው፡፡ ጃክና እኔ ከሳውዝ ሃምፕተን በረራ ከጀመርንበት ከቀኑ
ስምንት ሰዓት ጀምሮ ስንሰራ ቆይተናል፡፡ ስለዚህ ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት
ላይ እረፍት እናደርጋለን፡፡››

‹‹ካፒቴኑስ?›› ሲል ጠየቀ ቶም ሉተር ሀሳብ ገብቶት።
‹‹እንቅልፍ እንዳይዘው መድሃኒት ይውጣል፡ ከቻለ በተቀመጠበት ትንሽ ያንቀላፋል›› አለ ኤዲ፡ ‹‹ወደኋላ የማንመለስበት ሁኔታ ላይ ስንደርስ
ፓይለቱ ምን አልባት ረጅም እረፍት ያደርጋል፡››

‹‹ስለዚህ በሰማይ በምንበርበት ጊዜ ፓይለቱ ይተኛል ማለት ነው?››
ሲል ጠየቀ ሉተር ሳያስበው ጮክ ብሎ፡

‹‹አዎ›› አለ ኤዲ በፈገግታ:፡ ሉተር ፍርሃት ፍርሃት እንዳለው ያስታውቅበታል፡፡ ሄሪ ጨዋታው ሰላማዊ እንደሆነ በማሰብ ‹‹ወደኋላ
የማንመለስበት ሁኔታ ማለት ምንድን ነው?›› ሲል ጠየቀ፡፡
👍19
‹‹የመጠባበቂያ ነዳጃችንን መጠን ለማወቅ በየጊዜው እንቆጣጠራለን ወደ ፎየንስ አየርላንድ ለመመለስ የሚበቃ ነዳጅ ከሌለን ወደ
ኋላ የማንመለስበት ሁኔታ ላይ ደረስን ማለት ነው,አለ ኤዲ ድርቅ ባለ አነጋገር፡፡ ኤዲ ይህን ያለው ቶም ሉተርን ለማስፈራራት እንደሆነ ተረዳ
ናቪጌተሩ ተሳፋሪዎችን ለማረጋጋት ብሎ ጣልቃ ገባና ‹ብአሁኑ ጊዜ
አሜሪካ አድርሶ የሚመልሰን በቂ ነዳጅ አለን›› አለ፡

ሉተርም ቀጠለና ‹‹አሜሪካ የሚያደርሰን ወይም ወደ ኋላ የሚመልሰን
ያህል ነዳጅ ባይኖርስ?›› ሲል ጠየቀ፡፡

ኤዲ ወደ ሉተር ጠጋ ብሎ እየሳቀ ‹‹እመነን ሚስተር ሉተር፤ ችግር ላይ ከመውደቃችን በፊት ወደ ፎየንስ አየርላንድ እንመለሳለን፡፡ ለተጨማሪ
ጥንቃቄ በማለት የነዳጅ መጠኑን የምናሰላው በአራት ሞተር ሳይሆን በሶስት ሞተር ነው:: l . . . ምናልባት አንዱ ሞተር ላይ የሆነ ችግር ሊከሰት ይችላል ብለን፡፡››

ጃክ ሉተርን ለማረጋጋት ብሎ ስለ ነዳጅ የተናገረውi ነገር በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ የባሰ ፍርሃት ለቀቀበት፡፡

ሉተር የቀረበለትን ሾርባ ለመጠጣት ቢሞክርም እጁ> እየተንቀጠቀጠ
ስላስቸገረው ሾርባው ክራቫቱ ላይ ተንጠባጠበ፡፡
ኤዲ ሉተርን በማስፈራራቱ የረካ ይመስላል፡ ጃክም ርዕስ ለማስቀየር ሌላ ሌላ ነገር ይቀበጣጥራል፡፡ ሄሪም ጣልቃ እየገባ

ጨዋታ ያግዛል፡ ነገር
ግን አንድ የሆነ እንግዳ ነገር እንዳለ ገምቷል፡ ሄሪ ‹ኤዲና ሉተርን ያጣላቸው ምን ይሆን?› እያለ ራሱን ይጠይቃል፡፡የመመገቢያ ክፍሉ ቀስ በቀስ እየሞላ ነው፡፡ ጠቃጠቆ ያለበት ልብስ የለበሰችው ቆንጆዋ ሴት ከአጃቢዋ ጋር መጥታ ተቀመጠች፡ ቆንጆዋ ሴት
ስሟ ዳያና ላቭሴይ ሲሆን አብሯት ያለው ጓደኛዋ ደግሞ ማርክ አልደር
ይባላል፡ ማርጋሬት እንደ ወይዘሮ ላቭሴይ ለብሳ ቢሆን ኖሮ የበለጠ ታምር
ነበር› ሲል አሰበ ሄሪ፡

አስተናጋጆቹ ተፍ ተፍ እያሉ ምግብና መጠጥ የሚያቀርቡ ሲሆን
ምግቡም ጥሩ ነው፡፡ ሄሪ ግን ምንም አልበላም፡፡ መጠጥም ቢሆን ከያዘው
ውጪ መጨመር አልፈለገም፡፡ ንቁ ሆኖ መቆየት ይፈልጋል፡ የሌዲ
ኦክሰንፎርድን እንቁ ሊሰርቅ ተዘጋጅቷል፡፡ ስርቆቱን መፈጸሙ ደግሞ ፍርሃት ፈጥሮበታል፡ በስርቆት ከተሰማራ ጀምሮ የአሁኑ ስርቆት ህይወቱን
የሚለውጥ እንደሆነ ተማምኗል፡ የተቀማጠለ ኑሮ ያስገኝለታል፡፡

ሁለተኛው ዙር ምግብ መጣ፡ ሰላጣ ነው፡፡ በውድ የእንግሊዝ ምግብ
ቤቶች ውስጥ በሁለተኛ ዙር ምግብነት ሰላጣ አይቀርብም በተለይም
ብቻውን፡

በመጨረሻም ቡና ቀረበ፡፡ ኤዲ ብዙም አለመጫወቱን አወቀና ተሳፋሪዎችን ማናገር ጀመረ፡፡ ‹‹ሚስተር ቫንዴርፖስት ወደ አሜሪካ
የምትጓዝበት ምክንያት ምንድን ነው?›› ሲል ጠየቀ፡፡

‹‹ከሂትለር መራቅ እፈልጋለሁ›› አለ ሄሪ ‹‹አሜሪካ በጦርነቱ ውስጥ
እስክትገባ ድረስ፡፡››

‹‹አሜሪካ ጦርነቱ ውስጥ ትገባለች ብለህ ታስባለህ?›› ሲል ጠየቀ ኤዲ፡

‹‹በአንደኛው የአለም ጦርነት ጊዜ አሜሪካ አውሮፓ ድረስ መጥታ
ተዋግታ የለ›› አለ ሄሪ

ቶም ሉተር ቀጠለና ‹‹እኛ ከናዚዎች ጋር ምንም ጠብ የለንም፡ እነሉ ኮሚኒዝምን ይቃወማሉ፡፡ እኛም እንደዚሁ›› አለ፡፡

ጃክም በመስማማት ራሱን ነቀነቀ፡፡

ሄሪ አሜሪካውያኑ ያሉትን ሲሰማ ደነገጠ፡፡ እንግሊዝ ውስጥ ሁሉም የሚያስበው አሜሪካ አውሮፓን ለመርዳት እንደምትዋጋ ነው፡፡ እነዚህ አሜሪካውያን ግን የሚናገሩት ሌላ ነው።
‹ምናልባትም እንግሊዛውያን ራሳቸውን እያሞኙ ይሆናል› ሲል አሰበ በሀዘኔታ፤ ከአሜሪካ ምንም አይነት ድጋፍ አይገኝም ይሆናል፡ ለንደን ያለችው እናቴ ምን ይውጣት?› ሲል
አሰበ ሄሪ።

ኤዲ ቀጠለና ‹‹ምናልባትም አውሮፓ ሄደን ናዚዎችን እንዋጋ ይሆናል፡፡ እነሱ ከወሮበላ አይለዩም›› አለ ቆጣ ብሎ በቀጥታ ወደ ቶም ሉተር እያየ ‹‹እንደነዚህ ያሉትን ሰዎች ደግሞ እንደ አይጥ ልንፈጃቸው
ይገባል፡፡››

ጃክ ከመቀመጫው ምንጭቅ ብሎ ተነሳና ‹‹ኤዲ እራት ከጨረስን ወደ
ማረፊያችን እንሂድ›› አለ ፈርጠም ብሎ፡፡

ኤዲ በጃክ ድንገተኛ አባባል ቢደናገጥም ከመቀመጫው ተነሳና ከጃክ ጋር ተያይዘው ወጡ።
‹‹የበረራ መሀንዲሱ ስርዓት የጎደለው ሰው ነው›› አለ ሄሪ

‹‹እኔ ግን አላስተዋልኩትም›› አለ ሉተር፡

‹ውሽታም! ወሮበላ እያለህ!› አለ ሄሪ በሆዱ፡ ሉተር ብራንዲ አዘዘ፡ ሄሪ
ሉተር ወሮበላ ይሆን እንዴ?›
አለ በሆዱ፡፡ ለንደን ውስጥ
የሚያውቃቸው የከተማ ወሮበሎች እዩኝ እዩኝ የሚሉ ናቸው፡፡ ጣት ሙሉ ቀለበት ፀጉራም ልብሶች እና ከባድ ጫማዎች ያደርጋሉ ሉተር የቢዝነስ ሰው ነው የሚመስለው፡ ‹‹ቶም መተዳደሪያህ ምንድን ነው?›› ሲል ጠየቀው፡፡

‹‹ሮድ አይላንድ ውስጥ በንግድ ነው የምተዳደረው›› አለ ሉተር፡ ሄሪም በሆዱ ሞኝህን ብላ› አለና ‹‹ደህና ሁኑ›› ብሎ ተነስቶ ሄደ።

ወደ መቀመጫው ሲመለስ ሎርድ ኦክሰንፎርድ ‹‹ደህና የሚበላ ነገር አለ?›› ሲሉ ጠየቁት፡፡ ሄሪ ምግቡ ተስማምቶታል፡፡ ከበርቴዎች ስለ ምግብ ብዙም ግድ
የላቸውም፡፡ ‹‹ምንም አይልም፡፡ መጠጥም አይጠፋም›› አላቸው፡፡

ሎርድ ኦክሰንፎርድ አጉተመተሙና ወደ ጋዜጣ ንባባቸው ተመለሱ።
ሄሪ እንደዚህ አይነት ጋጠወጥ ሎርድ ገጥሞኝ አያውቅም› አለ በሆዱ
ማርጋሬት ስታየው ተደስታ ፈገግ አለችና ‹‹እውነት ምግቡ እንዴት ነው?›› ስትል ጠየቀችው፡

‹‹እጅ ያስቆረጥማል›› አላትና ሁለቱም ሳቁ

ማርጋሬት ስትስቅ ውበቷ ይወጣል፡፡ ዝም ያለች ጊዜ አትስብም፡፡ አፏን ከፈት አድርጋ በስርዓት የተደረደሩ ጥርሶቿን ብልጭ ስታደርጋቸውና ጸጉሯን ወደ ኋላ ስታዘናፍለው ልብ ትሰርቃለች፡ ጎርነን ባለ ድምፅ ስታስካካ
ወሲብ ትጭራለች፡ ሄሪ ሊደባብሳት እጁን ሲሰድ ፊት ለፊት የተቀመጠው
ክላይቭ መንበሪ ሲያየው እጁን ሰበሰበ፡፡

‹‹አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ አውሎ ንፋስ የተቀላቀለ ዝናብ ይኖራል›› አላት ሄሪ፡፡

‹‹ይህ ማለት ጉዟችን አስቸጋሪ ነው ማለት ነው›› አለች ማርጋሬት፡፡

‹‹አዎ፣ አውሎ ንፋሱን ለመሸሽ በአውሎ ንፋሱ መሐል ሳይሆን ራቅ
ብለው ይበራሉ፤ የሆነው ሆኖ ጉዞው ሰላማዊ እንዳልሆነ ታውቋል፡›› በሄሪ
እና በማርጋሬት መሐል አስተናጋጆቹ ምግብና ጥቅም ላይ የዋሉ የመመገቢያ እቃዎችን ለማመላለስ ያለማቋረጥ ይንቀሳቀሳሉ

ማርጋሬት አንብባ ያስቀመጠችውን ‹‹ላይፍ›› መጽሔት ማገላበጥ ጀመረ። ሄሪ የኦክሰንፎርድ ቤተሰብ ቦታውን ለቀው እስኪሄዱለት ተቁነጠነጠ፡ ብዙም አንባቢ ስላልሆነ መጽሔት ወይም መጽሐፍ አልያዘም፡፡ጋዜጣ ማንበብ ባይጠላም ለመዝናናት ፊልም ወይም ሬዲዮ ይመርጣል፡

የመንበሪ ፖሊስነት እንቆቅልሽ ሆኖበታል፡ ካልሆነ ደግሞ በፓን
አሜሪካ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ ምን ሊሰራ መጣ? አንድ ተጠርጣሪ
እየተከተለ ከሆነ አውሮፕላን ላይ እንዲወጣ ያስገደደው የወንጀሉ ከፍተኛነት መሆን አለበት፡ አለበለዚያ 90 ፓውንድ ለማውጣት የሚደፍር ፖሊስ የለም፡

ሄሪ ትዕግስት የሌለው ሰው ነው፡፡ ከእኩል ሰዓት በኋላ መንበሪ ከቦታው አልንቀሳቀስለት ካለ ተነስቶ የሚሄድበትን ብልሃት መፍጠር አለበት፡ ‹የፓይለቶቹን ክፍል ኣይተኸዋል ሚስተር መንበሪ?›› ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹አላየሁትም›› አለ መንበሪ፡፡

‹‹መታየት ያለበት ቦታ ነው፡፡ ውስጡ ሰፋ ያለ ነው፡፡ አይሮፕላኑም በእርግጥም ሰፊ ነው፡፡››

‹‹ይገርማል›› አለ መምበሪ ነገሩ ባያስደንቀውም፡፡ እንዲያው ለትህትና
ብሎ ነው እንጂ እሱ የአይሮፕላን አድናቂ አይደለም፡፡

‹‹ሄደን ብናየውስ?›› ሲል ጠየቀው መምበሪን፡፡
‹‹ተሳፋሪዎች የፓይለቶቹን ክፍል ማየት ይፈቀድላቸዋል?›› ሲል ጠየቀው ኒክን፡፡

‹‹አዎ ጌታዬ ማየት ይቻላል፡››
👍142👎1👏1
‹‹አሁን ይቻላል?›› ሲል ጠየቀ ሄሪ፡
‹አሁን ጥሩ ጊዜ ነው፣ ሚስተር ቫንዴርፖስት፡፡ የአይሮፕላኑ ማረፊያ ጊዜ ገና ነው፡፡ አየሩም ጥሩ ስለሆነ ጉዞው ሰላማዊ ነው፡፡ ከዚህ የተሻለ ጊዜ
አታገኙም:››

ሄሪም ኒክ ይህን እንዲል ነበር የጠበቀው፡፡ ተነሳና
መምበሪን እንሂድ አለው።

መምበሪን መሄድ አልፈለገም፡፡ ከፍላጎቱ ውጪ ‹እንዲህ አድርግ ሲሉት በቀላሉ የሚቀበል ሰው አይደለም፡፡ ሆኖም መሄድ ባይፈልግም የተደረገለተን ግብዣ አልቀበልም ማለት ብልግና ስለመሰለው በይሉኝታ እሺ ብሎ ተነሳ፡

ሄሪ ፊት ለፊት እየመራ ኩሽናውንና የወንዶችን መጸዳዳ ክፍል አልፈው በደረጃው ወጡና ወደ ፓይለቱ ክፍል ሄዱ፡

ሄሪ ዞር ዞር እያለ ተመለከተ፡፡ የአብራሪዎቹ ክፍል ንፁህ ፀጥታ
የሰፈነበትና ምቹ ነው፤ በዘመናዊ ህንፃ ላይ ያለ ቢሮ ይመስላል።

ሄሪ የእራት ተጓዳኞቹ
የበረራ መሀንዲሱና ናቪጌተሩ በቦታው
አይታዩም፡፡ እነሱ እረፍት ላይ ስለሆኑ ሌሎች ተረኛ ሰራተኞች ናቸው
ያሉት፡፡

ፓይለቱ ቦታው ላይ ተቀምጧል፡ እነ ሄሪን አየና በፈገግታ ‹‹እንደምን
አመሻችሁ መኳንንት እየተዟዟራችሁ ማየት ትፈልጋላችሁ?› ሲል
ጠየቃቸው፡፡

‹‹አዎ እንፈልጋለን›› አለ ሄሪ ‹ካሜራዬን ላምጣ ፎቶ ማንሳት ይቻላል?››

‹‹ይቻላል፡፡››

‹‹ይዤ መጣሁ›› አለና ሄሪ ደረጃውን በሩጫ ወረደ፤ ውስጡ በደስታ ተሞልቶ፡ ፍርሃት ግን አልተለየውም፡፡ መምበሪን ለትንሽ ደቂቃ ቢሆንም መለየት ችሏል፡፡ ሆኖም እነ ኦክሰንፎርድ ሳይመለሱ ፈጥኖ ቦርሳዎቹን መበርበር አለበት፡፡
ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡ አስተናጋጆቹ ከርቀት ይታዩታል፡፡ እሱ
የተቀመጠበት ቦታ እየመጡ ብርብራውን እንዳያቋርጡት እራት ለማቅረብ ተፍ ተፍ የሚሉበትን ጊዜ ጠበቀና የሌዲ ኦክሰንፎርድን ቦርሳ አነሳ ቦርሳው በእጅ እንደሚይዙት ቦርሳ ሳይሆን ከባድና ትልቅ ነው፡ ምናልባትም እራሳቸው አይዙት ይሆናል፡ ቦርሳውን ወምበሩ ላይ አስቀመጠና ዚፑን ከፈተው፡፡ ቦርሳው አለመቆለፉ ጥሩ ምልክት አይደለም፡፡ መቼም ባልተቆለፈ ቦርሳ ውስጥ ውድ ጌጥ ይዘው አይሄዱም ወይዘሮዋ፡፡
የሆነ ሆኖ ምናልባት የሆነ ሰው እንዳይደርስበት በመስጋት በዓይኑ ቂጥ
እያየ ብርበራውን ተያያዘው፡ ቦርሳው ውስጥ ሜክ አፕ፣ ሽቶ፣ ከብር የተሰራ ማበጠሪያ፣ የጥርስ ብሩሽና ሳሙና፣ ፒጃማ፣ ስሊፐር፣ የውስጥ ሱሪ፣ ስቶኪንግ፣ የገላ ሳሙናና መጽሐፍ ተጠቅጥቆበታል፡፡
ሄሪ ጌጡን ሳያገኘው ሲቀር እድሉን ረገመ፡ እዚህ ቦርሳ ውስጥ ነው እንቁው ይኖራል ብሎ የገመተው፡፡ አሁን ግን ግምቱ ሁሉ ትክክል እንዳልሆነ አወቀ፡

ፍለጋው ጥቂት ደቂቃ ወስዷል፡፡ ቦርሳውን ዘጋና ካገኘበት ቦታ መለሰው
ሌላ ሃሳብ መጣበት፡፡ ምናልባት ዕንቁውን ባላቸው እንዲይዙት ሰጥተዋቸው ከሆነስ።?

በሎርድ ኦክሰንፎርድ ወምበር ስር ያለውን ቦርሳ በዓይኖቹ ቃኘ፡፡አስተናጋጁ በስራ ስለተጠመደ ይህን እድል ሊጠቀምበት ፈለገ፡፡

የሎርዱን ቦርሳ ከወምበሩ ስር ጎትቶ አወጣው፡ ከቆዳ የተሰራ ነው፡፡ ዚፑ በቁልፍ ተቆልፏል: ሄሪ ለእንደዚህ አይነት ጊዜ የሚጠቀምበት ሰንጢ ከኪሱ መዘዘና ቁልፉን ጎርጉሮ ሰብሮ ዚፑን ከፈተው ቦርሳውን እየፈታተሸ እያለ አጭሩ አስተናጋጅ ዴቭ በትሪ ጠርሙስ ይዞ ሲያልፍ ሄሪ ፈገግ አለ፡፡ ዴቪ ሄሪ ቦርሳውን ሲፈታትሽ አይቷል፡ ሄሪ ቢደነግጥም ፈገግታ አልተለየውም፡፡ ዴቪ መንገዱን ቀጠለ፡ ዴቪ ሄሪ
የያዘው የራሱን ቦርሳ ነው ብሎ ገምቷል፡

ሄሪ ዴቪ ሲሄድ በእፎይታ ትንፋሹን ለቀቀው፡፡ጥርጣሬ የሚያስለውጥ ችሎታ ቢኖረውም ይህን ባደረገ ቁጥር ግን ድንጋጤ ይወረዋል፡

የሎርድ ኦክሰንፎርድ የወንድ ቦርሳ ሊይዝ የሚገባውን ቅራቅንቦ ሁሉ
ይዟል። ምላጭ፣ የፀጉር ዘይት፣ ፒጃማ፣ የውስጥ ሱሪ እና የናፖሊዮን
ታሪክ መጽሐፍ፡ ሄሪ ብርበራውን ካጠናቀቀ በኋላ ዚፑን ዘጋና ቁልፉን
ዘጋው፡ ሎርድ ቁልፉ መሰበሩን ሲያውቁ እንዴት ሊሆን ቻለ?› ማለታቸው
አይቀርም፡ የጠፋ ነገር ካለ ብለው ቦርሳቸውን መፈተሻቸው አይቀርም፡፡
አንድም እቃ እንዳልጠፋ ካረጋገጡ ግን ቁልፉ የተበላሸ ይሆናል ብለው
ይደመድማሉ፡፡

ሄሪ ቦርሳውን ወደነበረበት ቦታ መለሰው፡፡ አሁንም እንቁው ጋር ለመድረስ ብዙ እንደሚቀረው ገመተ፡፡

ልጆቹ የሌዲ ኦክሰንፎርድን እንቁ በቦርሳቸው ይይዛሉ ተብሎ ባይገመትም የእነሱንም ቦርሳ ከመበረበር አልቦዘነም፡፡

ሎርድ ኦክሰንፎርድ እንቁውን በልጆቹ ቦርሳ ወስጥ በሚስጥር መክተት
ካሰቡ በማርጋሬት ቦርሳ ውስጥ ሳይሆን በፔርሲ ቦርሳ ውስጥ ነው ሊከቱት
የሚችሉት፡፡ ምክንያቱም ማርጋሬት የእሳቸውን ሀሳብ የማትደግፍ በመሆኗ።

ሄሪ የፒርሲን የሸራ ቦርሳ አነሳና የኦክሰንፎርድን ቦርሳ ካነሳበት ቦታ ላይ አስቀመጠው፡ የፔርሲን ቦርሳ ከፍቶ ሲያይ ልብሶቹ
ተጣጥፈውና እቃዎቹ በስርዓት ተቀምጠው ሲያይ ሻንጣውን አሽከሮች እንደሸከፉለትገመተ፡፡ የአስራ አራት አመት ልጅ ዕቃዎቹን በዚህ ሁኔታ
ገመተ፡፡ የአስራ አራት አመት ልጅ ዕቃዎቹን በዚህ ሁኔታ አያስቀምጥም፡፡
ሻንጣው ውስጥ የጥርስ ሳሙና፣ የጥርስ ብሩሽ፣ የቼዝ መጫወቻ፣ የህጻናት
መጽሐፍና ፓኬት ብስኩት አለበት፡ ሄሪ የቼዝ መጫወቻውን፣ መጻሕፍቱን
እና የብስኩት ፓኬቱን ከፋፈተና አየ፡፡ ነገር ግን የዕንቁ ዘር አይታይም
ቦርሳውን ቦታው ሲመልስ አንድ ተሳፋሪ ወደ መጸዳጃ ቤት ለመሄድ ባጠገቡ አለፈ፡፡ ሰውየውን ግን ከምንም አልቆጠረውም፡

መቼም ሌዲ ኦክሰንፎርድ በቅርቡ በጠላት እጅ በሚወድቅ አገር ውስጥ
ይህን ከፍተኛ ዋጋ የሚያወጣ ዕንቁ ትተው ይመጣሉ ብሎ ማመን ጅልነት ነው ሲል ገመተ፡ አንገታቸው ላይ እንዳላጠለቁት የታወቀ ሲሆን እዚህ ሻንጣ ውስጥም አለመኖሩን በርብሮ አረጋግጧል፡ ይህ ዕንቁ በማርጋሬት
ሻንጣ ውስጥ ከሌለ የተቀመጠው በአይሮፕላኑ ሻንጣ ማስቀመጫ ቦታ ባለው ሻንጣቸው ውስጥ መሆን አለበት፡ እዚያ ከሆነ ደግሞ ሄዶ መፈለጉ እጅግ
አስቸጋሪ ነው። አይሮፕላኑ አየር ላይ ሆኖ እዚያ ቦታ መግባት ይቻል ይሆን?
ሲል አሰበ፡፡ እንቁውን በእጁ ለማድረግ ሌላው አማራጭ
የኦክሰንፎርድን ቤተሰብ ኒውዮርክ የሚያርፉበት ሆቴል ድረስ እግር በግር
ተከትሎ መግባት ነው፡፡

ሄሪ ካሜራ ይዤ እመጣለሁ ብሎ በዚያው ጭልጥ ብሎመቅረቱ ካፒቴኑና ክላይቭ መምበሪ ሳይገርማቸው አልቀረም
ሄሪ የማርጋሬትን ቦርሳ አነሳና ሲከፍተው የተቀባችው ሽቶ አወደው:
ቦርሳው ውስጥ ከጥጥ የተሰራ ፒጃማና ፓንቶች አገኘ ፓንቶቿ ታዳጊ
ልጃገረዶች የሚለብሱት አይነት በመሆኑ ከዕድሜዋ አንጻር እንዴት ይህን
ታደርጋለች? ልጃገረድ ትሆን እንዴ?› አለ በሆዱ። ቦርሳዋ ውስጥ እድሜው ከሃያ አንድ የማይበልጥ ጸጉሩ የተንዠረገገ መልከ መልካም ወጣት ፎቶ
አገኘ፡፡ ልጁ የኮሌጅ ተመራቂ ጋዋን ለብሶ ይታያል፡ ምናልባትም ስፔን አገር ሄዶ የሞተው ቦይፍሬንዷ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ከእሱጋ ተኝታ ይሆን? ምንም እንኳን ፓንቶቿ የታዳጊ ልጃገረዶች ቢሆኑም ከዚህ ልጅ ጋር አንሶላ ተጋፋለች ብሎ ጠርጥሯል፡ አንድ ልብ ወለድ መጽሐፍም ቦርሳ ውስጥ አለ፡፡ ዕንቁው ግን የለም፡፡

ሄሪ ባዶ እጄን ከምመለስ ብሎ በሽቶ ከታጠኑ መሃረቦች መካከል
አንዱን ለማስታወሻ ብሎ ሲያነሳ ዴቪ በሾርባ የተሞሉ ሰሃኖች በትሪ ይዞ ብቅ አለ፡፡ ዴቪ አሁን ቆም አለ፡፡ ፊቱን ከስክሷል፡ የማርጋሬት ቦርሳ
ከሎርድ ኦክሰንፎርድ ቦርሳ የተለየ መሆኑን ዴቪ አይቷል፡ ሄሪ ደግሞ
የሁለቱም ቦርሳዎች ባለቤት እንዳልሆነ ሳይገምት አልቀረም፡፡ ስለዚህ ሄሪ
የሰው ቦርሳ እየበረበረ ነው ማለት ነው ሲል ገምቷል፡
👍15
ዴቪ ትክ ብሎ ሄሪን አየው፡፡ የሰው ቦርሳ እንደሚበረብር ቢጠረጥርም አንድን ተሳፋሪ ያለ ማረጋገጫ የሰው ቦርሳ ለምን ትበረብራለህ?› ማለቱን
ፈራና ‹‹ጌታዬ ያንተ ቦርሳ ነው እሱ?›› ሲል ጠየቀው፡

ሄሪ ከማርጋሬት ቦርሳ ያወጣውን መሃረብ አሳየውና ታዲያ በሰው
መሀረብ እሷ ሳትፈቅድ ንፍጤን እጠርጋለሁ ብለህ ነው?›› አለውና
ቦርሳውን ዘግቶ አስቀመጠው፡

ዴቪ ሄሪ የሰጠው መልስ አልተዋጠለትም፡ ሄሪ ቀጠለና ‹መሃረቤን
አምጣልኝ ብላኝ ነው›› አለው፡፡

ዴቪ ከጥርጣሬው መለስ አለ፡ በሁኔታው እንደማፈር አለና ‹‹ይቅርታ ጌታዬ፣ መቼም ለተሳፋሪዎች ቦርሳ ደህንነት መቆርቆሬ ትክክል እንደሆነ ሳትረዳ አትቀርም›› አለው:

‹‹አንተም ይህን ማድረግህ ደስ ብሎኛል›› አለው ሄሪ ‹‹ብዚሁ ቀጥል
ዴቭ›› አለና ጀርባውን በማበረታታት መታ መታ አደረገው፡ ሄሪ ድንገት
የፈጠረው ታሪክ እውነተኛነት ለማረጋገጥ ለማርጋሬት መሃረቡን ወስዶ
መስጠት ይኖርበታል፡

ሄሪ መብል ክፍሉ ውስጥ ሲገባ ማርጋሬት ከቤተሰቦቿ ጋር ተቀምጣ አገኛትና ‹‹መሀረብሽን ጥለሽዋል እንቺ›› አላት

‹‹ጣልኩት?! አመሰግናለሁ›› አለች፡

‹‹አዎ›› አለና ወጥቶ ሄደ፡
መቼም ዴቪ ማርጋሬት መሀረብ እንዲያመጣላት ሄሪን መጠየቋን ሄዶ እንደማያረጋግጥ ገምቷል፡ ሄሪ ኩሽናውን አልፎ በደረጃው ወጣ፡
እንዴት ነው የተሳፋሪዎች ሻንጣ ያለበት ክፍል የሚገባው? የት እንዳለም አይታወቅም፡› ሻንጣዎቹ ሲጫኑ አላየም፡ ነገር ግን እዚያ ሻንጣ ማስቀመጫ ክፍል ውስጥ መግባት ይኖርበታል፡

ሄሪ የአይሮፕላኑ ማብረሪያ ክፍል ውስጥ ሲገባ ካፒቴኑ መምበሪን ጭው ካለው ውቅያኖስ በላይ እንዴት እንደሚበሩ እየነገረው ደረሰ፡፡

መምበሪ ሄሪ መምጣቱን አየና ‹ካሜራ የለም?›› ሲል ጠየቀው።

‹መምበሪ እውነትም ፖሊስ ነው› ሲል አሰበ፡፡ ‹ካሜራ ውስጥ ፊልም ሳልጨምር ረሳሁ፡፡ ምን አይነት ጭንቅላት ነው ያለኝ›› አለና ‹‹እዚህ ሆናችሁ እንዴት ነው ኮኮቦቹን የምታይዋቸው?›› ሲል ጠየቀ ካፒቴኑን፡፡

‹‹ናቪጌተሩ ለትንሽ ደቂቃ ጣራው ላይ ይወጣል›› አለ ካፒቴኑ፡
‹‹ስቀልድ ነው›› አለ መልሶ፡፡ ‹‹ኮኮቦቹን የምናይበት ቦታ አለን፡፡ ኑ
ላሳያችሁ›› አለና አንድ በር ከፍቶ ሲሄድ መምበሪና ሄሪ ተከተሉት፡፡ ‹‹ይሄ ነው የኮከብ መመልከቻ ቦታው>> አለ፡፡ ለሄሪ ይህ ቦታ ምኑም አይደለም፡፡
የእሱ ልብ ያለው የሌዲ ኦክሰንፎርድ ዕንቁ ላይ ነው፡ አይሮፕላኑ ኮርኒስ ላይ የአቅጣጫ መጠቆሚያ የኮከብ መመልከቻ መስታወት አለ፡ ወደዚያ
መውጪያ ታጣፊ መሰላል ኮከብ መመልከቻው አጠገብ ቆሟል። ካፒቴኑም
‹‹ጉም በሌለ ጊዜ ናቪጌተሩ እዚህ ላይ ይወጣና መሳሪያውን ይዞ ኮኮቦቹ ላይ ያነጣጥራል፡፡ የሻንጣ መጫኛውም ቦታ ይሄ ነው›› አለ፡፡

ሄሪ ልቡ አቆበቆበ፡፡ ‹ሻንጣዎቹ በጣራው በኩል ነው የሚገቡት?›› ሲል
ጠየቀ፡

አዎ በዚህ በኩል ነው የሚገቡት›› አለ ካፒቴኑ
‹‹ታዲያ የት ነው የሚቀመጡት?››
‹‹እዚያ ክፍል ውስጥ›› አለና አንድ የተዘጋ በር አመለከታቸው ሄሪ የገጠመውን መልካም እድል ማመን አቃተው፡፡ ‹‹ሁሉም ቦርሳዎች እዚህ
ክፍል ነው የሚቀመጡት?›› ሲል ጠየቀ፡፡

‹‹አዎ›› አለ ካፒቴኑ፡

አሻግሮ ሲያይ ሻንጣዎቹ ላይ በላይ ተደራርበውና በበረራ ጊዜ እንዳይወድቁ
በገመድ ተጠፍረው ተመለከተ

ያ የሄሪን ህይወት የሚለውጥ ዕንቁ አንዱ ሻንጣ ውስጥ ተወሽቋል፡
ክላይቭ መምበሪ ‹‹ያስደንቃል አይደል?›› ሲል ጠየቀው፡
ሄሪም ‹‹ምን አልክ?›› አለው.....

ይቀጥላል
👍8🔥1😁1
አትሮኖስ pinned «#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሰባት ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ ‹‹አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ግድ የለኝም፡፡ ጦርነት አውድማ ውስጥ ገብቼ ፋሺዝምን ከሀገሬ ለማባረር እዋጋለሁ›› አለች በልበ ሙሉነት፡ ፊቷ ላይ የሚነበበው ገፅታ ለህይወት ግድ እንደሌላት ያሳያል፡ ሄሪ ይህን ሲያይ ጎበዝ ናት› አለ በሆዱ፡፡ ‹‹የቆረጥሽ ትመስያለሽ›› ‹‹በዚህ እምነቱ የተነሳ የስፔን ፋሺስቶችን…»
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሀያ አምስት (25)


ቀኑ ጭጋጋማና እጅግ ቀዝቃዛ ነው ። ሚሪ ማለትም ናንሲ ማክአሊስተር ወደ ፌ አሊሰን ቢሮ ስትቃረብ የባርኔጣዋን ክፈፍ ቁልቁል ሳበች ። የደማቅ ቀይ ሱፍ ካፖርቷን ኮሌታም ሽቅብ ዘረጋች፤ ፊቷንና አንገቷን እንዲሸፍንላት ። ፍሬድ ውሻዋ እንደ ሁልጊዜው ተከትላታል ። ለፍሬድ የተጠለቀለት የአንገት ዘለበትና መሳቢያውም ልክ ሜሪ (ናንሲ) አንደለበሰችው ካፖርት ደማቅ ቀይ ናቸው ። አንገቷን ሰበር አድርጋ ውሻውን ቁልቁል እየተመለከተች ፈገግ አለች ። መንፈሷ በፌሽታ ሰፍፏል ። ደስተኛ መንፈሷ ጭጋጉና ብርዱም ሊሸፍኑትና ሊያቀዘቅዙት አልቻሉም። ወደ ፌ ቢሮ የሚወስደውን ደረጃ በሩጫ ከወጣችው በኋላ በሩን ከፍታ ገባች ። እና «ቤቶች ! የላችሁም እንዴ ? መጥተናል» አለች ። ከላላ ድምጺ በሞቃቱና ምቹው ቤት ውስጥ እስተጋባ ። ወዲያው ከሌላ ክፍል መልስ መጣ ። ሜሪ ካፖርቷን አወለቀች ። ከስር የለበሰችው ቀለል ያለ ወርቅማ ጌጥ ያለው ነጭ የሱፍ ቀሚስ ነበር። ይህን የገዛላት ፒተር ነው ። ከዚያም በከፊል ልብ ራስዋን በመስታወት ውስጥ ተመለከተች ባርኔጣዋን ወደ ጐን ዘንበል አደረገችና እንደገና አየችው ራስዋን። ምስሏን ተመልክታ ፈገግ አለች ። ደስ አላት ። መነፅር ማድረግ አቁማለች ። ምክንያቱም አይኖችዋ ላይ የነበረው ፋሻ ተነስቷል ። ፊቷ በጠቅላላ ፋሻ አይታይበትም ። ጥቂት ፋሻዎች ብቻ እግንባርዋ ላይ ይታያሉ ። እሱም ካሁን በኋላ ብዙ ጊዜ አይቆይም ። አለቀ ። እድሜ ለዘመናዊ የሕክምና ጥበብ ሜሪ (ናንሲ) ጠባሳ አይታይባትም ። አዲስ ፊት ፤ አዲስ ሰው ፤ አዲስ ስም ፤ አዲስ ሕይወት ።

«እመስተዋቱ ውስጥ ባየሽው ነው እንዲህ የተደስትሽው ናንሲ?» ይህን ድምፅ ስትሰማ ደንገጥ ብላ ዞር አለች ። ፌ አሊሰን ነበረች የተናገረችው፡፡ ፌ በፍቅር በተሞላ ፈገግታዋ ጥያቄውን ደገመችላት ። ራሷን በአወንታ ነቀነቀች ሜሪ ። በቃልም «አዎ። በሱ ነው የተደሰትኩት ብዬ አስባለሁ ። የሚገርምሽ በጠቅላላ የሆንኩትን እኔነቴን ሁሉ ለምጀዋለሁ። አንች ግን አለመድሽልኝም » አለች ። ፊቷ ላይ መቀየምና ቁጣ መሰል ነገር ይታይባት ነበር ። «ምን ማለትሽ ነው ፣ እንዲያ ስትይ ?» አለች ፌ አሊሰን ። «አለስሜ ትጠሪኛለሽ ሁሌ ። ሁሌ ናንሲ ነው እኮ እምትይኝ። ናንሲ አይደለሁም። ነበርኩ ቀረ። አሁን ሜሪ ነኝ ። በፍርድ ቤት ፀድቆ በሕግ ሊታወቅ ምንም ያልቀረው ስሜ ሜሪ አዳምሰን ነው»
«ገባኝ። ይቅርታ » ፌ ይህን ብላ ሁልጊዜም ሁለቱ ሲገናኙ አረፍ ብለው ወደሚጨዋወቱበት ምቹ ወደሆነውና ቅልል ወደሚለው ክፍል አመራች። «ይቅርታ ፤ ሁልጊዜም ናንሲ የሚለው ስም አፌ ላይ ደርሶ ጥልቅ ይላል » አለች ፌ አሊሰን ደግማ ። «ሁልጊዜ» አለች ሜሪ እምትወደው ወንበር ላይ እየተቀመጠች። ግን የተበሳጨች አትመስልም። ትንሽ ካሰበች በኋላ «አንዴ የለመደን ነገር ማስወገድ በጣም ክባድ ነገር ሳይሆን አይቀርም ። ይመስለኛል» አለች ሜሪ። ይህን የተናገረችው ፊቷን ቅጭም አድርጋ ነበረና ፌ አሊሰን ዝም አለች ። ከዚህ ጋር አያይዛ የምታመጣውን ነገር ለመስማት ።

«ይህን ነገር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነው የተረዳሁት ። ሳስብ ሳስብ ገባኝ ። ብዙ ጊዜ ላስወግደው ስሞክር አሻፈረኝ ብሎ እቦታው ላይ ሲገኝ ግን አሁን ሳላራግፈው የቀረሁ አይምስለኝም » አለች ሜሪ ።
«ማይክልን ማለትሽ ነው?» ሜሪ አንገቷን በአወንታ ነቀነቀች እንጂ ምንም አልተና
ገረችም ። «እንዳራገፍሽው እንዴት ልትገምቼ ቻልሽ ?» አለች ፌ። «ወሰንኩ ። ምርጫ ጠፋ። ወሰንኩ ። ለምን ? በይኝ ። ምክንያቱም ያ አደጋ ከደረሰብኝ ይኽው ሁለት ዓመት መሙላቱ ነው፡፡ ዓመት ከዘጠኝን ወር… ሁለት ዓመት በይው ። ይህን ያህል ጊዜ ስቀመጥ ሊፈልገኝ አልሞከረም ። እንዳሰብኩት እናቱን ብትፈልጊ እንጦረጦስ ግቢ ብሏት ወደኔ አልመጣም። ተወኝ ። ረሳኝ ። ስለዚሀ እኔም ልተወው ፤ ልረሳው ይገባኛል ።››

«መርሳት ! መርሳት ቀላል አይደለማ ! በልብሽ ውስጥ ለብዙ ጊዜ ያገነንሽው ሰው እንዲህ በቀላሉ ይረሳል ብለሽ ነው? በልብሽ ያስቀመጥሽው ጊዜ ረጂም ነው እኮ »
«እጅግ በጣም ረጂም ። ያን ያህል ጠብቄውም እንዲህ አድርጐኝ ቀረ ። ጣለኝ… ረሳኝ »
‹‹ጣለኝ… ረሳኝ ስትይ ስለራስሽ ምንነት ምን ይሰማሻል ?»
«ስለኔ ምንም ዓይነት መጥፎ ስሜት የለኝም ። ያጠፋ እሱ ። ያናደደኝ እሱ ። እኔ ምን አጠፋሁ? »
«ማለቴ ባለፈው ትንሽ ራስሽን ጠልተሽ ነበር ። ለምን ከማሪዮን ሂልያርድ ጋር ያን ስምምነት አደረግኩ ? ስትይ ነበር። ያ ስሜት አሁን ፈጽሞ አይሰማሽም? » ፌ አጉል ቁስል እየዘነቆረች እንደሆነ ገብቷታል ። ቢሆንም አለባብሶ ቢያርሱ በአረም ይመለሱ ነውና መሸፋፈኑን አልወደደችውም ።

«ምርጫ… ምንም ምርጫ አልነበረኝም» አለች ሜሪ። «ኖረም አልኖረም ለምን እንዲህ አደረግኩ ብለሽ ራስሽን ወቅሰሽ አታውቂም ?»
«ለማን ብዬ? ለምን ብዬ? ማይክል ለምን አልጠየቅኳትም ብሎ በራሱ የሚናደድ ይመስልሻል ? ሳያስብልኝ በመቅረቱ የህሊና ወቀሳ እንቅልፍ ይነሳዋል ብለሽ ታስቢያለሽ ?»
«ማይክልን እንተወው የሚያሳስበን ያንቺ ነገር ነው አሁንም እሱን በማሰብ ዕንቅልፍ ታጪያለሽ ፤ናንሲ ? »
« ናንሲ አይደለም ሜሪ » አለች ሜሪ እያረመቻት ። «በፍጹም ። አልፏል ያ ቀረ ፤ ይህን የቁም ሕልም ለማስወገድ ወስኜ ተነሳሁ ። ብዙ ስለተሰቃየሁ ዛሬ ቆረጥኩ ። በቃ » አለች ። ድምጺም ቃላቱም ሆዷ የቆረጠ መሆኑን ይናገሩ ነበር ። « በምትኩ ? » አለች ፌ አሊሰን « በማይክል ቦታ ማንን ልትተኪ?» ፒተርን ብላ አሰበች። « በቃ እሠራለሁ ። ሥራ ! በመጀመሪያ ግን ወደ ደቡባዊ ምሥራቅ ግዛቶች ሄጄ ትንሽ መንፈሴን አዝናናለሁ… የገናን በዓል አስመርኩዤ ። እዚያም እየተዝናናሁ አላርፍም ። እሠራለሁ ። ዕቅዴን ነድፌ ጨርሻለሁ ። አሪዞናን ፤፣ ኒው ሜክሲኮን ካየሁ በኋላ ከመሰለኝ ወደ ሜክሲኮም መሻገር አስቤአለሁ ። ሦስት ሳምንት ቆይቼ ስመጣ ፤ ዕረፍት ! በቃ ! »
« ከዚያ በኋላስ ? »
« ከዚያማ መሥራት ፤ ሌት ተቀን መሥራት ። በቃ ! የኔ አእምሮ ካሁን በኋላ እስራ ላይ ብቻ ነው። ልቤ ሥራን ብቻ ነው እሚያስበው ። በነገራችን ላይ የፎቶ ግራፍ ትርኢት እንደማቀርብ ሰምተሻል ። ፒተር ሁሉን ነገር ጨርሶልኛል ። ጥር ወር ላይ ነው የሚሆነው ። እንዳያመልጥሽ ብታስቢበት መልካም ነው።»
« ያመልጣታል ብለሽ ታስቢያለሽ ? »
« እንዳያመልጥሽ እመኝልሻለሁ ። እንዲህ ቀላል አይምሰልሽ። ፎቶ ግራፍ በጣም አድርጐ ፍቅር ያስያዘኝ ሥራ ሆኗል ከምር የማፈቅረው ነው ስልሽ ። እና ደግሞ የሠራኋቸውን ነገሮች አብዛኞቹን አላየሻቸውም ። አንቺ ቀርቶ ፒተር እንኳ ያየው ጥቂት ነው። ኤግዚቢሽኑን ሲመለከት ደስ ቢሰኝልኝ እኔም ደስ ይለኛል ።»
« አትጠራጠሪ ደስ ይለዋል ። አንቺ ከሠራሽው ምንም ይሁን ለሱ ድንቅ ነገር ነው » አለች ፌ ። እና ቀና ብላ አየቻት ሜሪን። ከዚያ ‹‹ነገርን ነገር ያነሳዋል ናንሲ. . . ማነው? ሜሪ.. . ስለ ፒተር አልተነጋገርንም ? ስለ ፒተር የሚሰማሽን እስኪ ንገሪኝ »
👍17
« ስለ ፒተር» አለች በረጅሙ ተንፍሳ « ስለ ፒተር የሚሰማኝ ነገር ብዙ ነው»
‹‹ትወጅ…. ማለት ታፈቅሪዋለሽ ?»
« በራሴ መንገድ »
« በልብሽ ውስጥ በኑሮሽም ቢሆን የማይክልን ቦታ የሚወስድ ይመስልሻል ?»
« ምናልባት… ምናልባት ይቻል ይሆናል ። በበኩሌ ማይክል ወጥቶ እሱ እንዲሆን እየሞከርኩ ነው ። እወደዋለሁ ፤በጣም በጣም እሳሳለታለሁ »
« ያ ከሆነ ስሜትሽን አታስገድጄው ። ማይክልን ከልብሽ ለማውጣት ወስነሻል ። ይህም ልብሽን ነፃ ያደርገዋል ያኔ ይታወቃል »

ፌ ይህን ብላ ሜሪን ተመለከተቻት ። የመንጋጋዋ አጥንት ሲነቃነቅና ጅማቷ ሲወጣጠር እየች ። « ሜሪ › አለች ፌ ና« ሜሪ ምናልባት ሰውን በጠቅላላ ወደ መጥላት ፤ ፍቅርን ወደ መሸሽ እየሄድሽ ይሆን?»
« በፍጹም። ለምን ብዬ? ምን አጣሁ ብዬ ፍቅርን እሸሻለሁ ?››
«እሱ ነው ዋናው ነገር ። ማይክልን ወደድሽ ። እንዳሰብሺው ሳይሆን ቀረ ። ግን ማይክል ብቻ አይደለም በዚች ዓለም ላይ ያለው ወንድ ። ወንድ ሞልቷል ። የሚሆንሽን ምን ጊዜም ቢሆን አታጭውም ። ያ ወንድ ምናልባት ፒተር ይሆን ይሆናል ። ወይም ሌላ ። ወይም ሌላ። አየሽ መርሳት የሌለብሽ ቆንጆ ልጅ መሆንሽን ፤ገና ሃያ አምስት ዓመት ያልሞላሽ ወጣት መሆንሽን ነው። ዓለም ያንቺ ናት ። ኑሮ በሰፊው እምትጠብቅሽ ሰው ነሽ ። እሺ ? »
« ፒተርም ደጋግሞ የሚነግረኝ ይህንኑ ነው » እንዲህ ትበል እንጂ ያለችውን ነገር ያለችው ከልቧ እንዳልሆነ ፌ አሊሰን ተረድታለች ። ሌላ ወንድ የመውደድ ነገር ሜሪ ከባድ ሆኖ እንደሚሰማት ገብቷታል ።

« አንድ ሌላ ነገርም ወስኛለሁ » አለች ሜሪ ፍርሐቷንሩ ሐዘኗን ይሸፍን ዘንድ አጉል ፈገግታ ለብሳ።
«ምን ?”»
« ስለኔና ስላንቺ ። እንደኔ ግምት ከሆነ የሚቻለኝን ሁሉ ለማድረግ የሰጠሽኝን ምክር በተግባር ለማሳዬት ሞክሬአለሁ ተሳክቶልኛልም እላለሁ። ካሁን በኋላ ቢያንስ ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ይህን ሁሉ ትቼ ወደ ሰፊው ዓለም ለመግባት ላቤ ጠፍ እስኪል ለመሥራት እና ሥራዬን ለማሸነፍ ወስኛለሁ »
« ዓለምን ከመታገል ፤ ኑሮን ላብ ጠፍ እስኪል በመሥራት ብቻ ከማሳለፍ በኑሮ ደስታን ለማግኘት ለምን አትሞክሪም !» አለች ፌ። «ስሚ ሜሪ በዓለም ላይ ደስ ብሎሽ ትኖሪ ዘንድ ትልቅ ነገር ተሰጥቶሻል ። ውበትን ለብሰሻታል ። እና ይህችን ትልቅ ጸጋ ለምን በካሜራ ጀርባ ትሸሽጊያታለሽ ? »
« ስጦታ ! ስጦታ ኦልሺው ፌ ። ውበትን በስጦታ አላገኘኋትም ። ውበትን ለማግኘት አለኝ የምለውን ፤የኔ የሆነውን ነገር ሁሉ ከፍዬባታለሁ ። ስጦታ አይደለም » መልካም የገና በዓል ይሆንላቸው ዘንድ መልካም ምኞት ተለዋውጠው ተሰነባበቱ ። የመልካም ምኞት ልውውጡ ግን ከልብ አይመስልም ነበር ። ግልብ ነበር ። ቃላቱ ካፋቸው ሲወጣ ከአፍ የወጡ ሳይሆን ምንጫቸው ሳይታወቅ የገደል ማሚቶ አንጥራ የምትመልሳቸው ይመስሉ ነበር ።

ሜሪ አዳምሰን ካፖርቷንና ባርኔጣዋን ለብሳና አድርጋ የሁለት ዓመት ወዳጅዋንና ሐኪሟን ፤ ፌ አሊሰን እጅዋን በማወዛወዝ ስትሰናበት ወዳጅዋን ሳይሆን እኒያን ሁለት ዓመታት ደህና ሁኑ የምትል ትመስል ነበር። ፌ አሊሰንን ተሰናብታ ስትሄድም ከኒያ ዓመታትና ከነበረችበት ዓለም ተላቃ ወደ ሌላ አዲስ ዘመን ፤ ወደሌላ አዲስ ዓለም የምትሄድ ፤ ያለፈውን ነገር ሁሉ ረስታ ባለፈው የወደደችውን ሁሉ ትታ አዲስ ኑሮ ለመጀምር የተዘጋጀች ትመስል ነበር ።

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍122
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሀያ ስድስት (26)

ሜሪ አዳምስን ከፌ አሊሰን ተሰናብታ እንደወጣች በቀጥጥታ ወደ ዩኒየን ስኩዌር እመራች ፤ በታክሲ ። እዚያም የሄደችበት ምክንያት ቲኬት ለማስቆረጥ ነበር ። በጉዞው አስቀድማ ስላሰበችበት ከሁለት ሳምንት በፊች ቲኬት ለመቁረጥ ተመዝግባ ነበር ስለዚህም ችግር የለባትም ። ገንዘቡን ሰጥታ ቲኬት መቀበል ብቻ ነው ። ሜሪ ስለጉዞው ስታስብ እጅግ ደስ አላት ። ለመዝናናት ካሰበችበት ቆይታለች ። ይህ ጉዞ የመጀመሪያዋ ባይሆንም ብዙ ጊዜ ያደረገችው አይደለም ። አንዴት ነው ይህን ዓይነት ጉዞ ያደረገችው ። ከሜሪ ጋር ። በበዓለ ፋሲካ ።. . . ይህ ሐሳብ ረሰሻት። ማይክልን ማሰብ የለባትም ። ሐሳቡን እንደምንም ታግላ መለሰችው ።

ዩኒየን ስኩዌር እንደደረሰች ወደ ቲኬት መሸጫው ቢሮ ገባች፤ «አስቀድመሽ እንዲያዝልሽ አድርገሽ ነበር?» አለቻት የክፍሉ ሠራተትኛ ።
«አዎ ። ከአሥራ አምስት ቀን በፊት»
«ስምሽን ማን ልበል ?።»
«ሜሪ አዳምስ... ኖ ናንሲ ማክአሊስተር» አለች ሜሪ ። ናንሲ ማክአሊስተር የሚለውን ስም ስትሰማው እንግዳ ነገር ሆነባት። ስሟን ወደ ሜሪ አዳምሰን ቀይራ በዚሁ ስትጠራ ከሁለት ወር አለፍ ይላል ። እዲሱን ስሟን ለመልመድ ስትጣጣር የወትሮውን እየረሳችው እንደሆነ ተገነዘበች፡፡ ቲኬት ለመቁረጥ በናንሲ ማክአሊስተር የተጠቀመችው በከንቱ አልነበረም ። ምንም እንኳን ናንሲ ማክእሊአስተር መባሏ ቆርቶ ሜሪ አዳምሰን እንድትባል በሕግ የተፈቀደላት ቢሆን በወጣላት አዲስ ስም መጠራት የምትጀምረው ከአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ማለትም ከጀንዋሪ ( ጥር) ጀምሮ እንደሆነም ውሳኔ ተሰጥቶ ነበር ። ለዚሀም ነው ከገና በፊት ሜሪ አዳምሰን ተብላ ልትመዘገብ ያልቻለችው ።

ናንሲ ስለስሟና ስለጉዞው ስታስብ ገረማት ። ዛሬ ናንሲ ናት ። የዕረፍትና የመዝናናት ጉዞዋን ጨርሳ ስትመለስ ግን በሕግ ፊት ሳይቀር ሜሪ አዳምሰን ትሆናለች ። አገባሁ ማለትኮ ነው ! አለች በሐሳቧ ። አሁን የምሄደው የጋብቻ እረፍት ለማድረግና ለመዝናናት መሆኑ ነው ማለት ነው አለች ።

ከዚያ ስትመለስ አዳምሰን እንጂ ማክአሊስተር ተብላ እትጠራም። (የፈረንጅ ሴቶች ሲያገቡ የባላቸውን የቤተሰብ ስም ይወርሳሉና የስሟን መቆየር ነው እንደማግባት የቆጠረችው) ሜሪ አዳምሰን ናንሲ ማክአሊስትር አይደለችም ። ነበረች ። ግን አይደለችም ። ሜሪ አዳምሰን በስም ብቻ ሳይሆን በመልክም።
በሰውነት ቅርጽም ፤ በአነጋገርም፤ በድምጽም፤ በአካሄድም፤ ናንሲን አትመስልም ። መልኳን ዶክተር ፒቶሮ ግሬግሰን ቀይሮታል ። ከዚህ በፊት ናንሲን የሚያውቃትን ማንም ሰው የዛሬዋን ሜሪ አሳይቶ ናንሲ ናት ቢሉት አያምንም ። የዛሬዋ ሜሪ ውበቷ የሚያፈዝ ማንም ሴት የሷን መልክ በሰጠኝ ብላ የሚቀናባት ቆንጆ ነች ። ለራሷ ከሆነ ይች ቆንጆ እንግዳ አይደለችም ። ለምዳታለች ። ግን አብራት የኖረችው ናንሲ ማክአሊስተርም አይደለችም ። የምትናገረው ነገር ያው ይሁን እንጂ የእነጋገር ስልቷና ድምጽ አወጣጧ ስለተቀየረ ይህችኛዋ ስትናገር አድማጭን ታፈዛለች ። አፍ ታስከፍታለች ። ሰውነቷ ጠንከር ሲልና የሕክምናው ተግባር ሲገባደድ ፣ ዶክተር ፒተር ግሬግሰን የባሌ ዳንስ እንድትማር ፈቅዶላታል ። ትማራለች ። ይህ ደግሞ በእካሏ ላይ ምን ያሀል ለውጥ እንደሚያመጣ የታወቀ ነው ። የዮጋ ልምምድም ታደርጋለች ። ይህች ናት የዛሬዋ ሜሪ አዳምሰን ፤ የወትሮዋ ናንሲ ማክአሊስትር ። ተለወጥኩ ፡አዲስ ሰው ሆንኩ አለች በሐሳቧ ። ገረማት ። ደርሶ ንዴት ተሰማት ። እንጦሮጦስ ! አለች በልቧ ። ማይክል ረሳኝ ። እኔም ራሴ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እረሳዋለሁ አለች አሁንም በሐሳቧ ።

«እንድ መቶ ዘጠና ስድስት ዶላር ይሆናል ክፍያው»አለች የቲኬት ቢሮ ሠራትኛዋ ፣፤ ሜሪን ከሐሳቧ እየመለሰችና ኮምፒውተሩን እየተመለከተች ። ሜሪ ቼክ ጽፋ ስትሰጣት ልጅቷ አንዴ ኮምፒውተሩን አንዴ ሜሪን ትመለከት ጀመር ። ከዚያም ሜሪን ትኩር፤ ፈገግ ብላ ተመለከተቻች ። ሜሪ እንድ ነገር አላት ። አንዴ ካየሃት ዓይንህን ከሷ ላይ መንቀል ያስቸግርሃል ። ማናት ? ትላለህ ፤ ይህን የሚሉ ደግሞ ወንዶች ብቻ አልነበሩም ። ሴቶችም ቢሆኑ ያው ነው ።

ፍሬድን አቅፋ (መኪና እንዳይገጨው በመፍራት) ከቲኬት መሸጫው ቢሮ ወጥታ ጉዞዋን ቆጠለች ። አንድ በጣም ትልቅ ሱፐር ማርኬት ስታይ ወደዚያው ገባች ። ምን ለመግዛት እንደምትፈልግ ግን አታውቀውም ነበር ። ለራሴ አንድ ስጦታ እገዛለሁ ። ወይም ለጉዞዬ የሚያስፈልገኝ ነገር ሊያጋጥመኝ ይችላል አለች ። በዚያ ግዙፍ ሱፐር ማርኬት ውስጥ ካንደኛው ፎቅ ወደ ሌላው ከልብስ ክፍል ወደ ጫማ ፤ ክዚያም ወደ ጌጣጌጥ ፤ ከዚያም ወደ ሌላው እየተዘዋወረች አንዱን ዕቃ አንስታ እየጣለች ሌላውን አንስታ እየመረመረች ወይም እየሞከረች ብዙ ጊዜ አሳለፈች ። በመጨረሻ አንድ ነጭ የሱፍ ሹራብ ላይ ዓይኗ አረፈ ። ሹራቡን ለብሳ ሞከረችው። ከውብ ገፅታዋና ከጥቁር ሐር መሳይ ጸጉሯ ጋር ሹራቡ የውበት ዳርቻ የሆነችውን ልዕልት አስመሰላት ።ራሷም ይህን አሰበች ። ሃሳቧ አስደመማት ፤ አስደሰታትም፡፡ ሹራቡን አስጠቅልላ ወደ ዋናው አዳራሽ ተመለሰች ያሉትን ዕቃዎች በመደዳ ተመለከተች ። ከዚያም አንድ ታኒካ ቸኮላት ገዛች ። ይህን ቸኮላት ለፌ አሊሰን ነበር የገዛችው ፤የገና ስጦታ ። በታኒካው ላይ በተንጠለጠለው ካርድ ላይ « አመሰግናለሁ፤ ፌ። ከፍቅር ጋር ። ሜሪ» ብላ ጸፈችበት ። ሌላ ምን ብላ ልትጽፍ ፤ ምንስ ልትጨምር ትችላለች ? « ማይክልን እንድረሳው ስለረዳሽኝ ፤ ሁሉን ትቼና ረስቼ መኖር እንድችል ስለመከርሽኝ አመሰግናለሁ » ብላ ትጻፍበት ?

ይህን ሀሳብ እያውጠነጠነችና ከራሷ ጋር እየተጨዋወተች ሳለች ድንገት የሚያስደነግጥ ትዕይንት አጋጠማት ። ዛር ወይም ሰይጣን ያየች ይመስል ባለችበት ክው ብላ ቀረች ። ገንዘብ ተቀባይዋ ደረሰኝ ቆርጣ እጅዋን ሰንዝራ ነበር ። ይህን ስትቀበል እንኳ ዓይኗ ካየችው ነገር ላይ አልተነቀለም። ያየችው ዛር ቤን አቭሪ ነበር ። ቤን አቭሪ እሷ ካለችበት አለፍ ብሎ በጣም ውድ የሆነ የሴቶች የዕቃ ሻንጣ ይመለከት ነበር ። ሜሪ ካለችበት ንቅንቅ ሳትል ለረጂም ጊዜ ቆየች ። ከዚያም ቀስ ብላ ቤን ወዳለበት አካባቢ ጠጋ አለች ። ቀረብ ብላ ልታየው ፤ ቀረብ ብላ ልትነካው ፤ቀረብ ብላ ድምጹን ልትሰማው ፈለገች ። ላንዲት ቅፅበት የሆነውን ሁሉ በመርሳት አፍታ ያስታውሰኝ ይሆን የሚል ስሜት ተቀረጸባት። ያች አፍታ እስክታልፍም ባወቀኝ ፤ ባስታወሰኝ ስትል ተማፀነች ። ሆኖም ያቺ ቅፅበት አለፈች ። ያኔ በምንም ዓይነት መንገድ ሊያስታውሳት እንደማይችል ተገነዘበች ። ይህን ማሰቧ ቢያስከፋትም ፤ እረ እንኳን ያላወቀኝ ስትል ራሷን ወደ ደስታ ገፋፋችው ። እንዲህም ስትል ተፅናናች ። እንኳን ያላወቀኝ ቢያውቀኝ ኖሮ ያናግረኝ ነበር፡፡ ክፉ ሳይናገረኝ እንዲህ ተጠግቼ ልመለከተው እችል ነበር? እንኳን የቀረብኝ አለች ።

እንዲያ አጠገቡ ቆማ እያጤነችው ከማይክል ጋር አሁንም ይገናኙ ይሆን ? ከማይክል ጋር ይሆን የሚሰሩት ? ወይስ ቤን ሌላ መሥሪያ ቤት ገባ ? የሚሉ ጥያቄዎች ይጎርፉ ጅመር በአእምሮዋ ውስጥ ። ሹልክ ብላ አጠገቡ ደርሳ ከሚያገላብጣቸው ዕቃዎች ጎን ያሉትን ከፈይ የመዛግብት ቦርሳዎች ትመለከት ጀመር ። ቦርሳዎቹን የተመለከተች ትምሰል እንጂ ዓይኗስ ከቶም ከፊቱ ላይ አልተነቀለም ። ይህ ሲሆን ሳለ ድንገት ቤን ዞር ብሎ እያትና ያንን የምታወቀውን ገር ፈገግታውን አሳያት ግን . . .
👍22
ግን ቅንጣት ታህል የማስታወስ ምልክት, በፊቱ ላይ አልነበረም ። ፊቱ በውበቷ የተሰማውን አድናቆት ብቻ ነበር የሚገልጸው ። እንዲያ ባድናቆት እንደተሞላ እጁን ሰደድ አድርጐ ፍሬድን ለማጫወት ሞከረ ።

« ታዲያስ ፤ አያ ትንሽ ነገር » አለ ቤን ውሻውን ሊያጫውት የሚሞክር እየመሰለ ። ድምጹን ስትሰማ ሁሉ ነገር ታወሳት ። እና ደርሶ መንፈሷ ተሸበረ ። ደከመች ። አልወደቀችም ። እንዲያውም ውሻውን ለመዳበስ የተሰነዘረው የቤን አቭሪ እጅ ሙቀት እየተሰማት ከተቀመጠችበት ተነሳች ። ሁኔታው ሁሉ ገረማት ። ቤን አቭሪን ስላየች ብቻ ይህ ዓይነት የስሜት ዝብርቅርቅ እንደሚሰማት ገምታ አታውቅም ነበር ። ግን ደግሞ አይፈረድባትም ። ማይክልንና እሷን በቀጥታ የሚያገናኝ ሁኔታ ሲያጋጥማት ይህ
የመጀመሪያው መሆኑ ነው ። ከዚያ ዕንባ ተናነቃት ። ቤንን ቀና ብላ ማየት አልቻለችም ። ስለዚህም ሲመለከተው የነበረውን ሻንጣ አየች ። እጅዋ ወዳንገቷ ሄደና ያኔ ለሙሽርነቷ ቤን ያዋሳትን የወርቅ ሀብል ዳበሰ ። ካንገቷ አውልቃው አታውቅም ከተሻላት ጊዜ ጀምሮ ። « የገና ስጦታ በመግዛት ላይ ነህ መሰለኝ » አለችው ። « አዎ ላንዲት ወጣት እመቤት ከጦታ ለመግዛት አስቤ የቱን እንደምገዛ መወሰን አቃተኝ »
« ምን ዓይነት ናት እመቤቲቱ ?»
« እሳት! እሳተ ነበልባል ናት።». ሜሪ በቤን መልስ ሳቀች ። ቤን ምን ጊዜም ቤን ነው። መልሱ አጭርና ቀልድ የተሞላ ነው ። አሁንስ እንዴት ነው እመቤቲቱ ቋሚ ናቸው ? ልትለው አስባ ነበር ። ግን የማይሞከር ነገር ማሰቧ ወዲያው ገባት። ጸጉሯ ቀያቴ ሲሆን ፤ ቁመቷ እንዲህ አንቺን ታህላለች አለ ቤን። .

ይህን ብሎ ሜሪን ከላይ እስከታች በተጠሙ ዓይኖቹ ጠጣት። ይህን ሲያደርግ ስሜቷ ተደበላለቀባት ። ስለተመኛት ። እና ግንኙነታቸውን ስታስብ መናደድ አማራት ። ስላላወቃትና ቤን ሴት ካየ መጎምዥት ልማዱ መሆኑን ስታስብ ልትስቅበት አማራት ። « ግን ሻንጣ ፤ ቅራቅንቦ የሚያስፈልጋት መሆኑን ርግጠኛ ነህ » አለች። « ይመስለኛል ። ወደ አንድ ቦታ እንድንሄድ አስቤአለሁ። ሳታስበው እንዲሆን ስለምፈልግ ፤ ቲኬቱን እሻንጣ ውስጥ ከትቼ ላስገርማት ብዬ ነው» አለ ። አንድ ትኬት ደብቆ ለመስጠት አምስት መቶ ዶላር መክፈል ይገባል ቤን ? ቤን አቭሪ እንዲህ ገንዘብ በታኝ ሆነ ?

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍9
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ


ማርጋሬት ደስ ደስ ብሏታል፡ ከእውነተኛ ሌባ ጋር መወዳጀቷን ማመን
እያቃታት ነው፡ አንድ ሰው ‹‹እኔ ሌባ ነኝ›› ቢላት አታምነውም፡ ነገር ግን
ሄሪ አንድ ጊዜ ፖሊስ ጣቢያ ተከሶ ስላየችው ‹‹እኔ ሌባ ነኝ›› ቢላት እውነቱን መሆኑን አወቀች።

ከስርዓት ውጭ የሚኖሩ ሰዎች ማለትም ወንጀለኞች ለህግና ለመንግስት የማይገዙ ሰዎች፣ ሴተኛ አዳሪዎችና በረንዳ አዳሪዎች ሁልጊዜ
ያስደንቋታል፡ እነሱ ነጻ ሰዎች ናቸው፡፡ በእርግጥ በህብረተሰቡ የተተፋ ሰው
ጥሩ ነው የሚል አመለካከት የላትም፡፡ ነገር ግን እንደ ሄሪ ያሉ ሰዎች አድርጉ የተባሉትን ሁሉ ለማድረግ አይፈቅዱም፡ይህ ነጻነታቸው ነው ማርጋሬትን የሚያስቀናት፡፡ አንዳንዴ የወታደር ልብስ ለብሶ ጠመንጃውን ታጥቆ በየመንደሩ እየዞረ ህዝብ የሚዘርፍ ሽፍታ መሆን ያምራታል እንደዚህ አይነት ሰዎች ገጥመዋት አያውቁም: አንድ ጊዜ በለንደን ጎዳናዎች
ላይ ሴተኛ አዳሪ መስላቸው ሊደፍሯት የመጡትን ሰዎች ባታይ የምታውቅበት ሁኔታ አልነበረም፡፡

ሄሪ እሷ የምትመኘውን ነገር ሁሉ ያሟላ ሆኖ ነው ያገኘችው የፈለገውን ማድረግ የሚችል ሰው! ዛሬ ጧት አሜሪካ ለመሄድ ወሰነና ዛሬ ከሰዓት በኋላ አይሮፕላኑ ላይ ተገኘ፡፡ ሌሊቱን በሙሉ መደነስና ቀኑን በሙሉ መጋደም ከፈለገ ያደርገዋል፡ ከልካይ የለበትም፡፡ መብላት የፈለገውን ይበላል፧ መጠጣት የፈለገውን ይጠጣል፡ ገንዘብ ከፈለገ ገንዘባቸውን መጣያ
ካጡ ባለጸጎች ይሰርቃል፡ እሱ ነጻ የሆነ ሰው ነው፡
ስለሄሪ በይበልጥ ማወቅ ፈለገች፡ ከእሱ ጋር ራት ሳትበላ ያሳለፈቻቸው
ቀናት ቁጭት ውስጥ ጣሏት፡፡

ባሮን ጋቦንና ካርል ሃርትማን ከኦክሰንፎርድ ቤተሰብ ቀጥሎ ተቀምጠዋል እነዚህ ሰዎች ይሁዲ ስለሆኑ ነው ገና ወደ መብል ክፍሉ እንደገቡ ሎርድ ኦክሰንፎርድ ክፉኛ የገላመጧቸው፡አብረዋቸው
የተቀመጡት ኦሊስ ፊልድና ፍራንክ ጎርደን ናቸው፡፡ ፍራንክ ጎርደን በዕድሜ
hሄሪ ብዙም የማይበልጥ መልከ መልካም ወጣት ነው፡፡ ኦሊስ ፊልድ ደግሞ
ኑሮ የጠመመበት የመሰለ በዕድሜ ገፋ ያለ ራሰ በራ ሰው ነው፡፡

ፎየንስ ላይ አይሮፕላኑ ሲያርፍ ሁሉም ሰው ከአይሮፕላኑ ወጥቶ
በየፊናው ሲበታተን እነዚህ ሁለት ሰዎች አይሮፕላኑ ውስጥ በመቅረታቸው
የለው ሁሉ መነጋገሪያ ሆነው ነበር፡፡

ሶስተኛው የመመገቢያ ጠረጴዛ ላይ ሉሉ ቤልና ሾርባው ጨው የበዛበት ነው እያሉ ሲያማርሩ የዋሉት ልዕልት ላቪኒያ ተቀምጠዋል ከነሱ ጋር ፎየንስ ላይ የተሳፈሩት ሚስተር ላቭሴይና ሚስስ ሌኔሃን ተቀምጠዋል። ወሬ መለቃቀም የሚወደው ፔርሲ እነዚህ ሰዎች ባልና ሚስት ባይሆኑም የሙሽሮቹን ክፍል እንደሚጋሩ ወሬ ለጠማቸው አውርቷል
ባልና ሚስት ያልሆኑ ሰዎች ይህን ክፍል እንዲይዙ ፓን አሜሪካን አየር
መንገድ እንዴት እንደፈቀደላቸው ማርጋሬት ገርሟታል። አየር መንገዱ ብዙ ሰዎች ወደ አሜሪካ መሄድ ስለፈለጉ ህጉን መጋፋት የግድ ሆኖበታል፡

ፔርሲ ጥቁር የይሁዲዎች ኮፊያ አናቱ ላይ ደፍቷል፡ ማርጋሬት ይህን ስታይ በሳቅ ተንፈቀፈቀች፡፡ ከየት ነው ያመጣው! አባቱ ግን ‹‹ጅል!›› ብለው ተሳድበው ኮፍያውን መንጭቀው ወረወሩት፡፡

ሌዲ ኦክሰንፎርድ ኤልሳቤት ተለይታቸው ከሄደች ወዲህ ለመጀመሪያ
ጊዜ ፊታቸው በመጠኑ ፈካ ብሏል፡፡

ሌዲ ኦክሰንፎርድ ‹‹የራት ሰዓታችን ገና ነው›› አሉ፡፡
ሎርድ ኦክሰንፎርድ ደግሞ ‹‹አንድ ሰዓት ተኩል ሆኗል እኮ›› አሉ፡፡
‹‹ለምንድነው ታዲያ ያልጨለመው?››
‹‹እንግሊዝ አገር አሁን ጨለማ ነው፡ አሁን ግን ከአየርላንድ ባህር
ጠረፍ ሶስት መቶ ማይል ርቀት ላይ ነው የምንገኘው ጸሃይዋን እያሳደድን
ነው›› አለ ፔርሲ፡፡

‹‹መቼም መጨለሙ አይቀርም››
‹‹ምናልባት ሶስት ሰዓት ላይ የሚጨልም ይመስለኛል›› አለ ፔርሲ
‹‹ጥሩ›› አሉ እናት፡፡
እንደማይጨልም
‹‹ጸሃይዋን ተከትለን በፍጥነት ብንጓዝ
እንደማይጨልም ታውቃላችሁ? አለ ፔርሲ፡፡

‹‹እንደዚህ አይነት ፍጥነት ያለው አይሮፕላን የሰው ልጅ ይሰራል ብዬ አልገምትም›› አሉ አባት ከኔ በላይ አዋቂ የለም በሚል ግብዝነት፡
ቦትውድ ካናዳ ለመድረስ አስራ ስድስት ሰዓት ተኩል ይፈጃል›› አለ ፔርሲ ‹‹እዚያ በግሪንዊች ሰዓት አቆጣጠር ከጧቱ ሶስት ሰአት እንደርሳለን››
‹‹ካናዳ ስንት ሰዓት ይሆናል ማለት ነው?,,
‹‹የኒውፋንድላንድ ካናዳ የሰዓት አቆጣጠር ከግሪንዊች የሰዓት አቆጣጠር ሶስት ሰዓት ወደ ኋላ ነው›› አለ ፔርሲ፡፡

እናት የፔርሲን ችሎታ አጤኑና ‹‹ወንዶች የቴክኒክ እውቀት ላይ ጎበዞች ናቸው›› አሉ፡፡

ማርጋሬት በእናቷ አነጋገር ተናደደች፡፡ እናት የቴክኒክ ነገሮች ሴቶች አይገባቸውም ብለው ያምናሉ፡፡ ‹‹ወንዶች ሴቶች ጎበዝ ሲሆኑ አይወዱም››
ብለዋታል ብዙ ጊዜ፡ በዚህ ጉዳይ ማርጋሬት ከእናቷ ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ መግባት ባትፈልግም እሷ ግን አታምንበትም፡ ይህን የሚቀበሉ ወንዶች ደደቦች ናቸው ብላ ነው የምትገምተው ጎበዝ ወንድ ጎበዝ ሴት ይወዳል፡

አጠገባቸው ካለው ጠረጴዛ ዙሪያ የተቀመጡት ባሮን ጋቦንና ካርል ሃርትማን ክርክር ገጥመዋል አጠገባቸው ያሉት የጠረጴዛ ተጋሪዎች
ባይገባቸውም በጸጥታ ያዳምጣሉ: ሁለቱ ሰዎች አይሮፕላኑ ላይ ከወጡ
ጀምሮ ጥልቅ ውይይት ሲያደርጉ ይታያሉ፡፡ በዓለም ከታወቀ ሳይንቲስት
ጋር እንደዚህ ያለውን ውይይት የምታደርጉ ከሆነ ውይይቱ ጥብቅ መሆኑ
አያስደንቅም፡፡ በክርክራቸው ውስጥ ፍልስጤምንና እስራኤልን በተደጋጋሚ ያነሳሉ፡ ማርጋሬት የውይይት ርዕሳቸውን ስትሰማ
‹‹አባባ ምን ይል
ይሆን?›› እያለች አስሬ ታያቸዋለች፡፡ እሳቸውም የሁለቱ ሰዎች ውይይት
አልጥም ብሏቸው አኩርፈዋል፡፡ አባቷ ነገር እንዳይጭሩ ርዕስ ለማስለወጥ
‹‹አይሮፕላኑ የሚጓዘው ኃይለኛ ነፋስ በቀላቀለ ዝናብ ውስጥ ነው›› አለች
‹‹እንዴት አወቅሽ?›› አለ ፔርሲ አነጋገሩ ቅናት ያለበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በበረራ መረጃ ከማርጋሬት ይልቅ እሱ ነው ኤክስፐርቱ።
‹‹ሄሪ ነገረኝ››
‹‹እሱ እንዴት ያውቃል?››
‹‹እሱ ዛሬ ራት የበላው ከበረራ መሃንዲሱና ከናቪጌተሩ ጋር ነው፡››
ማርጋሬት ዝናቡ ችግር ይፈጥራል ብላ አልገመተችም፡፡ በእርግጥ
በዝናብ ውስጥ መጓዝ ምቾት ቢነሳም ለክፉ አይሰጥም፡፡

ሎርድ ኦክሰንፎርድ ብርጭቋቸው ውስጥ የቀረውን ቪኖ አጋቡና ሌላ
እንዲጨመርላቸው ቆጣ ብለው ጠየቁ፡፡ ዝናቡ ችግር ያመጣል ብለው ፈሩ
እንዴ? ከተለመደው በላይ እየጠጡ መሆናቸውን ማርጋሬት ተገንዝባለች።
ፊታቸው ከመጠጥ ብዛት ፍም መስሏል: ዓይናቸው ፈጧል፡ ምናልባትም
ነርቭ ሆነዋል፡፡በኤልሳቤት መኮብለል ክፉኛ ተበሳጭተዋል
እናትም ማርጋሬትን ‹‹ሚስተር መምበሪን አጫውቺው›› አሏት፡
ማርጋሬት የእናቷ አባባል ገርሟት ‹‹ለምን?›› ስትል ጠየቀች፡ ሲያዩት
ሰው እንዲያናግረው የሚፈልግ አይመስልም፡

‹‹ምናልባትም አይናፋር ሳይሆን አይቀርም›› አሉ እናት፡፡

እማማ ከመቼ ወዲህ ነው ለአይናፋሮች መቆርቆር የጀመረችው?የሚሆን ነገር አይደለም፡፡ ‹‹ግን ምን ማለትሽ ነው?›› ስትል ጠየቀች ማርጋሬት።
👍13🔥1
‹‹አሜሪካ እስክንደርስ ከዚያ ቫንዴርፖስት ከተባለ ወጠጤ ተጣብቀሽ መዋልሽን አልወደድኩትም›› ሲሉ እናት የሆዳቸውን አፈረጡላት፡

‹‹ለምን እማማ?››
እሱ እኩያሽ ስለሆነ የምትሰጪው ሃሳብ አይኖርሽም››
‹‹ብዙ የምሰጠው ሃሳብ አለኝ፡፡ እሱ መልከ መልካምና ዓይናፋር ልጅ
ነው፡››

‹‹አይሆንም የኔ ማር›› አሉ እናት ፈርጠም ብለው፡፡ ‹‹ደህና ሰው እንዳልሆነ ዓይነ ውሀው ያስታውቃል፡፡ ቀልቤ አልወደደውም:››

እናት ሄሪ የደህና ቤተሰብ ልጅ አይደለም እያሉ ነው፡ ባዶ እጁን መጥቶ ከባላባት ዘር መጋባት የሚፈልግ ሰው ነው› ብለው ገምተዋል። በዚህ በኩል እናት ከእንግሊዞች የበለጠ ደሃ ይንቃሉ፡፡

ሄሪ ሀብታም አሜሪካዊ ወጣት ለመምሰል የሚያደርገው ጥረት
አልተዋጠላቸውም፡ ምኑም አይመስልም፡፡ እሳቸውን መሸወድ አይችልም፡፡
ማን ምን እንደሆነ ያውቃሉ፡

‹‹ፊላዴልፊያ የሚኖሩትን የቫንዴርፖስት ቤተሰቦችን አውቃቸዋለሁ ነው ያልሽው?››

‹‹አዎ አውቃቸዋለሁ ይህ ሰው ግን የእዚያ ቤተሰብ አባል እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ›› አሉ እናት፡፡

‹‹እማማ ይሄ ሰው መናቅ ነው››

‹‹ይሄ ንቀት አይደለም የኔ ማር፡ የዘር ጉዳይ ነው፡፡ ንቀት እኮ ብልግና
ነው:››

ማርጋሬት ከእናቷ ጋር የምታደርገውን ክርክር አቆመች፡ የእናቷ የጌታ
ዘር እምነት አባዜ እንዲህ በቀላሉ የሚናድ እንዳልሆነ ገባት፡፡ hእሳቸው ጋር ከዚህ በላይ መነታረኩ ፍሬ እንደሌለው ተገንዝባለች፡፡ ቢሆንም ያሉትን
አልተቀበለችም፡፡ ሄሪ ልቧን ገዝቶታል፡

ፔርሲም ‹‹ሚስተር መምበሪ ስራው ምን ይሆን? የለበሳትን ቀይ
ሰደርያውን ወድጄለታለሁ፡ መደበኛ የአትላንቲክ አቋራጭ ተጓዥ አይመስልም›› አለ፡

እናትም ቀበል አደረጉና ‹‹አንድ የመንግስት ኃላፊነት የተሰጠው ሰው ይመስላል›› አሉ፡፡

ማርጋሬትም ‹‹ሳይሆን አይቀርም›› አለች፡ እናታችን እንደዚህ አይነት
ነገር ዓይኗ አይስትም› ስትል አሰበች::

አባትም ‹‹ምናልባት የአየር መንገዱ ሰራተኛ ይሆናል›› አሉ።
አስተናጋጁ ዋናውን ምግብ አመጣላቸው። እናትም የመጣውን የተቀቀለ ስጋ አይተው ‹‹እኔ የተቀቀለ ነገር አልበላም›› አሉት ኒኪን ‹‹አትክልት አምጣልኝ፡፡››

በሚቀጥለው ቦታ ላይ የተቀመጡት ባሮን ጋቦን ‹‹የራሳችን የሆነ አገር
ሊኖረን ይገባል፤ ሌላ መፍትሄ የለውም›› አሉ፡

ካርል ሃርትማንም ‹‹ከሆነም ወታደራዊ መንግስት ይሁን እያልክ ነው›› አሉ።

‹‹አዎ ይህን ያልኩት ከጠብ አጫሪ ጎረቤት አገሮች የሚመጣ ጥቃትን
መከላከል እንዲቻል ነው›› አሉ ጋቦን፡፡

‹‹ለእስራኤላውያን ጥቅም ሲል በአረቦች ላይ መድልዎ የሚያደርግ
መንግስት ማለትህ እኮ ነው፡ ይሄ ደግሞ ወታደራዊ መንግስት ከዘረኝነት ጋ ከተዋሃደ ደግሞ ፋሺዝም ይሆናል፡ አሁን እየተዋጋኸው ያለኸው ደግሞ ፋሺዝምን ነው፡››

‹‹ቀስ ብለህ ተናገር ሰው ይሰማል›› አሉ ጋቦን፡፡

ሌላ ቦታ ቢሆን እንደዚህ ያለ ውይይት ማርጋሬት ይጥማታል ከዚ ቀደም ከቦይፍሬንዷ ኢያን ጋር ተወያይታለች፡፡ የሶሻሊስት ፍልስፍና አራማጆች በፍልስጤም ጉዳይ ተከፋፍለዋል፡፡ አንዳንዶቹ ፍልስጤም ለዓለም
ምሳሌ ሊሆን የሚችል መንግስት ሊሆን ይችላል ብለው የሚያስቡም አሉ።ሌሎቹ ደግሞ አንዴ አረቦች የሚኖሩበት አገር በመሆኑ ለይሁዳውያን መሰጠት የለበትም፤ ይሁዳውያን ፍልስጤም አገራቸው እንዳልሆነ ማሰብ አለባቸው ይላሉ፡፡ ታዲያ ብዙዎቹ ሶሻሊስቶች ይሁዲዎች ስለሆኑ ነገሩን
ያወሳስቡታል፡፡

ማርጋሬት አሁን እነዚህ ሰዎች አባባ እንዳይሰማ ስለፍልስጤም
የሚያደርጉትን ክርክር ቢያቆሙ ምናለ ስትል አሰበች። እነዚህ ሰዎች ግን ይህን ርዕስ የሚተዉት አይመስልም፡፡ ከልባቸው ነው የሚወያዩት፡፡

‹‹እኔ ግን በዘረኝነት አገር ውስጥ መኖር አልሻም›› አሉ ሃርትማን
ድምጻቸውን ከፍ አድርገው:

አባትም ጮክ ብለው ‹‹ከይሁዲ መንጋ ጋር እንደምሄድ አላወቅሁም
ነበር›› አሉ፡

ማርጋሬት በአባቷ አነጋገር ክፉኛ አዘነች፡፡ አንዳንድ ጊዜ የፖለቲካ ፍልስፍናቸው ስሜት የሚሰጣት ጊዜ ነበር፡፡ በርካታ ሊሰሩ የሚችሉ ሰዎች ስራ አጥተው ሲራቡ ሲያዩ ደፍረው ካፒታሊዝምም ሶሻሊዝምም የፈየዱት ነገር የለም፡ ዲሞክራሲም ለተራው ሰው ያመጣለት ነገር የለም ይላሉ፡
በኢንዱስትሪ የበለጸገች አገርን የሚመሰርት ጠንካራ አምባገነን መሪ መመኘት በራሱ አንድ ነገር ነው፡ ከዚህ ቀደም አባቷ ያራምዷቸው የነበሩት
እንደዚህ አይነት አስተሳሰቦች ዛሬ ወደ ትርጉም የለሽ ግብዝነት ዘቅጠዋል።

እነዚህ ሁለት ይሁዳውያን ያባቷን አጥንት የሚሰብር ስድብ የሰሙ አይመስልም፡፡ አባቷ አባቷ ለሰዎቹ ጀርባቸውን ስለሰጧቸውና
በክርክራቸው ስለተዋጡ ምን እንዳሉ እንኳን አላወቁም፡ ማርጋሬት አባቷ
የተቆጡበትን ርዕስ ለማስለወጥ ‹‹ብስንት ሰዓት ነው የምንተኛው?›› ስትል
ጠየቀች፡፡

እኔ ቶሎ ነው የምተኛው›› አለ ፔርሲ፡ እሱ ለወትሮው በጊዜ ተኝቶ አያውቅም፡፡ ነገር ግን አይሮፕላን ላይ መተኛት ምን እንደሚመስል ለማወቅ ጓግቷል።

‹‹በተለመደው ሰዓት ነው የምተኛው›› አሉ እናት፡
‹‹በየትኛው የጊዜ ቀመር?›› ሲል ጠየቀ ፔርሲ ‹‹በግሪንዊች ወይስ
በኒውፋውንድላንድ?››

‹‹አሜሪካ ዘረኛ አገር ናት›› አሉ ባሮን ጋቦን ‹‹ፈረንሳይም፣እንግሊዝም፣ ሶቭየት ህብረትም እንዲሁ››

አባትም ይህን ሲሰሙ ‹‹እባካችሁ ስለእግዚአብሔር ብላችሁ እናንተ ሰዎች!›› አሉ።

"ያንተ ተራ ነው አባባ አለ ፔርሲ"

ፔርሲ፡አባት ዝምታ መረጡ፡፡ እነ ማርጋሬት ልጆች ሳሉ አባት ከልጆቹ ጋር ይጫወቱ ነበር፡፡ አሁን ግን ደስታ ርቋቸዋል፡ ሆኖም ፊታቸው በመጠኑም
ፈታ ማለት ሲጀምር ማርጋሬት ጨዋታው ውስጥ ገብተው ሊቀላቀሉ
መሆኑን ገምታ ደስ ብሏት ነበር፡፡

ከዚያም በዚያው ቅጽበት ካርል ሃርትማን ‹‹ለምን ሌላ ዘረኛ መንግስት
ይቋቋማል?›› ሲሉ ተናገሩ፡፡

አሁን ነገር መጣ፡፡ ሎርድ ኦክሰንፎርድ በንዴት የቀላ ፊታቸውን ወደ ሰዎቹ አዙረው ማንም ይናገራሉ ብሎ ባልጠበቀበት ጊዜ ‹‹እናንተ ቆሻሻ
ይሁዲዎች! ድምጻችሁን ብትቀንሱ ይሻላችኋል›› አሉ፡

ሃርትማንና ጋቦን የሎርዱ ንግግር ገርሟቸው አፈጠጡባቸው:
ማርጋሬት በድንጋጤ ፊቷ የበሰለ ቲማቲም መሰለ፡፡ አባቷ የተናገሩት ጮክ ብለው ስለነበር ሰዉ ጸጥ ረጭ አለ ማርጋሬት መሬቱ ተከፍቶ ቢውጣት ወደደች፡ ይህን የተናገሩት ፊት ለፊቷ የተቀመጡት ባለጌ፣ መሆናቸውን ሰው ሁሉ ስላወቀ ተሽማቀቀች።
አስተናጋጁን ኒኪን ቀና ብላ ስታየው መሳቀቋን አይቶ ለእሷ ማዘኑን ከፊቱ አነበበች፡ ይህም የበለጠ እፍረቷን አባባሰባት"...

ይቀጥላል
👍14
አትሮኖስ pinned «#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ስምንት ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ ማርጋሬት ደስ ደስ ብሏታል፡ ከእውነተኛ ሌባ ጋር መወዳጀቷን ማመን እያቃታት ነው፡ አንድ ሰው ‹‹እኔ ሌባ ነኝ›› ቢላት አታምነውም፡ ነገር ግን ሄሪ አንድ ጊዜ ፖሊስ ጣቢያ ተከሶ ስላየችው ‹‹እኔ ሌባ ነኝ›› ቢላት እውነቱን መሆኑን አወቀች። ከስርዓት ውጭ የሚኖሩ ሰዎች ማለትም ወንጀለኞች ለህግና ለመንግስት…»
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰባ_አራት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ሚስተር ካርይል ምልስ ብሎ ልጁን ከደረቱ እቅፍ ሲያደርገው እንባው ፈሰሰ
አየወረደ የልጁን ፊት አራሰው “ የኔ ልጅ ... አባባ አሁን ይመለሳል " አማማን
እንድታይክ ሊያመጣት ነው


"አናም አብራ ትመጣለች ? ደስ የምትል ልጅ ናትኮ”

"አዎን ከፈለግሃት ሕፃኒቱ አናም ትመጣለች » እነሱን ካመጣኋቸው በኋላ
ካጠግብህ ንቅንቅ አልልም

“ በል እንግዲያሙስ አስተኛኝና ሒድ "

ሚስተር ካርላይል እንባው እየወረደ ልጁን ከሚመታው ልቡ አስጠግቶ
እ.... ቅ ....ፍ ካደረገው በኋላ ትራሱን አመቻችቶ አስተኛው አሁንም
እንድ ማንኪያ የንጆራ ጭማቂ ሰጥቶት እየተጣደፈ ሔዶ "

“ ደኅና ሁን .. አባባ ” አለ ልጁ በደካማው ድምፁ » እሱ ግን አልሰማውም " ሳቤላ ከተንበረከከችበት ብድግ ብላ እጇን ወደ ሰማይ ሰቅላ እንባዋ
ዝርግፍ ዝርግፍ ብሎ እየወረዶ ትንሰቀሰቅ ጀመር

"ዊልያም . . የኔ ዓለም ፡ በዚች የሞት ሰዓት እናት ልሁንልህ " ስትለው
እንደ ገና የደከሙት ዐይኖቹን ገለጠ " ነገሩ እሷ ካለችው ዐይነት አልገባውም

“ አባባ ኮ ሊያመጣት ሔዷል ”

“ እሷን አይደለም የምልህ " እኔ እኔ ” አለችና አቋረጠችው " ከአልጋው ላይ ተደፍታ ዝም ብላ ትንሰቀሰቅ ጀመር " በዚያች በመጨረሻ ስዓት እንኳን እኔ እናትህ ነኝ ' ልትለው አልደፈረችም "

ዊልሰን ተመልሳ መጣችና “ እንቅልፍ የወሰደው ይመስላል ” አለቻት "
“ አዎን ” አለች ሳቤላ “ግድየለም ሒጅ አንድ ነገር ሲያስፈልገው እጠራሻለሁ

ዊልሰን ክፉ ሰው ባትሆንም ከዚያ የጭንቀት ክፍል መቆየቱን ስላልወደደች ወጣች " ሳቤላ ብቻዋን ቀረች " እንደገና ተንበረከከችና..... ወዲያው የዱሮው ትዝታ መጣባት " የሚስተር ካርይል ሙሽራ
ሆና ኢስት ሊን ከጎባችበት ጀምሮ እስከ ዛሬ የነበረውን ታሪኳን አሰበች "
ይህ የዱሮ ታሪኳ በየመልኩ ስታስበው አንዱ እያለ ሌላው እየተተካ እስካሁኑ ሁኔታዋ ድረስ በሐሳብ እንደ ተዋጠች አንድ ስዓት ዐለፈ " ልጁም አላስቸገረም » ሚስተር ካርላይልም ኤልተመለሰም በዚህ ሁኔታ ላይ እንዳለች ጆይስ ደረሰች ሳቤላ ከተንበረከከችበት ብድግ አለች " ጆይስ ቀጥታ መጣችና ዊልያምን
ለማየት ልብሱን ገለጥ አደረገች ዊልያም እንደሚፈልገኝ ጌቶች ነገሩኝ አለችና ስታየው ክው አለች " ማዳም ቬንም አደናገገጧን አይታ ወደ ጀይስ ጠጋብላ
እየች » ጢስ የለበሰው ለጋ ፊት ጸጥ ብሎ ተኝቷል - ያች ሁልጊዜ ዲም -ዲሞ
ስትል የኖረችው ትንሽ ልብም ሥራ አቁማለች "

ራሷን መቆጣጠር አቃታት " እንደሚሞት ተረድታ ሞቱንም በጸጋ በእርጋታ እንደምትቀበለው አምናና ዐውቃ ተቀምጣ ነበር ግን እንደዚያ ቶሎ የሚሞት እልመስላትም " ቢያንስ በጥቂቱ ሰዓት ዕድሜ እንደሚኖረው ገምታ ነበር "
አሁን ሳታስበው እንደ ደራሽ ጎርፍ ቀደማት " ጮሽች ተንሰቀሰቀች : ተጣራች
እላዩ ላይ ወደቀች ጥምጥም አድርጋ ይዛ አቀፈችው " መነጽሯንና ዐይነ ርግቧን ወረወረች » የድሮ መልኳ እንደ ነበረው ቁጭ አለ ፊቷን ከፊቱ አድርጋ አንድ ጊዜ ወደሷ ምልስ እንዲልላት ለመነችው ወደሷ ወደምትወደው ወላጅ እናት
ምልስ ብሎ ስማ እንድታስናብተው ጠራችው።

ጆይስ ከልጁ ሞት ይልቅ የሷ ሁኔታ አስደነገጣት » እንድታስብ ልብ እንድትል ያለችበትን ሁኔታ እንድትግነዘብ ለመነቻት በመጨረሻ ያለ የሌለ ጉልበቷን ተጠቅማ ካቀፈችው የልጁ ሬሳ አለያየቻት "

"ኧረ እመቤቴ ይተዉ ! ይተዉ !

'እመቤቴ ስትላት ነገሩ ልብ ራሷን መታት በዚህ አኳኋን ነበር ዱሮ ጆይስ የምትጠራት ድርቅ ብላ ደነገጠች » ስታብድ የነበረው ኩምሽሽ አለች "
ጆይስን ትክ ብላ አየቻትና የኋሊት አፈፈገች ;

“ እሜቴ . . ይበሎ እንግዲህ ወደ ክፍለዎ ልመሰድዎ " ሚስተር ካርላይል ሚስታቸውን ይዘው እየመጡ ነው " ከፊታቸው እንደዚህ ሆነው አይቆዬዋቸው እባክዎን ቶሎ ይምጡ ”

"አንቺ . . እንዴት ዐወቅሽኝ ?

“እሜቴ . . እሳት ተነሣ ተብሎ ሌሊት ተበራግገን የተነሳን ዕለት ነበር ያወቅኦ " ሕፃኑን አርኪባልድን ከዕቅፍዎ ለመቀበል ስጠጋ ሳይዎ በመንፈስ እንጂ በአካል የተገናኘን አልመሰለኝም " ፊትዎ አልተሸፈነም " በጨረቃው ብርሃን እንደ ፀሐይ ቁልጭ ብሎ ታየኝ ትንሽ ቆይቼ ድንጋጤዬ ለቀቅ ሲያደርገኝ ከእሜቴ ሳቤላ ጋር በአካል መግናኘቴን ተረዳሁ " ይበሉ አሁን እንውጣ ሚስተር ካርላይል ሊገቡ ነው " አለቻት ጆይስ

“ጆይስ . . እዘኝልኝ አታጋልጭኝ ለቅቄ እሄዳለሁ እስካለሁ ድረስ ምሥጢሬን ጠብቂልኝ አደራሽን "

“እሜቴ አይሥጉ " እስከ ዛሬ ድረስ ችዬው ኖሬአለሁ አሁንም እችለዋለዑ"
በርግጥ ወደዚህ በመምጣትዎ ተሳስተዋል " እኔም ካሁን አሁን ምን ይፈጠር ይሆን ? እያልኩ የልብ ሰላም የሌት እንቅልፍ አጥቻለሁ "

"ሰማሽ ጆይስ . . ከነዚህ ካልታደሉት ልጆቼ ተለይቼ መኖሩ አቃተኝ እኔ ግን ወደዚህ በመምጣቴ የተቀጣሁ አይመስልሽም ? እሱን ባሌን የሌላ ባል
ሆኖ ማየቱ ቀላል ነገር ነው ? ይኸ ራሱ አየገደለኝ ነው።

“ ኧረ ይምጡ እባክዎ ! ይኸው ሲመጡ ሰማኋቸው

አንደ ማባበልም እንደ
መጎተትም አድርጋ ከክፍሏ አስገባቻትና እየሮጠች
"ተመለሰች " ልክ ሚስተር ካርሳይል ከልጁ ክፍል ሲገባ አብራ ገባች ከእግር
እስከ ራሷ ተንቀጠቀጠች "

' ጆይስ ! ምን ነካሽ ? አመመሽ ? ” አላት

ጌታዬ ይዘጋጁ ! ዊልያም–– ዊልያም
ጆይስ ! ሞተ እንዳትይኝ ? ”
መቸስ ጌታዬ ምን ይደረጋል? ከዚህ የሚቀር የለም ።

ሚስተር ካርላይል ወደ ወስጥ ገብቶ መዝጊያውን በስተውስጥ ቀርቅሮ ወደ
የመነመነው የሕፃን ፊቱ ልጁ ተጠጋ " ከትራሱ ዝንጥፍ ብሎ ወድቆ አየው

" ልጄ ! ልጄ ወይ ልጄ ! ” እያለ “ጌታ ሆይ ያቺን ያልታደለች እናቱን ተቀ
ብለሃታል ብዬ እንደማምነው ሁሉ የዚህንም ሕፃን ነፍስ ታርፍ ዘንድ ተቀበላት” ብሎ ጸለየ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሎርድ ማውንት ስቨርን ከዊልያም ካርላይል ቀብር ላይ ለመግኘት ከልጁ ጋር
መጣ ዊልሰን እንዳሰበችው ዊልያም ካባቱ አባት ጎን ተቀበረ » መቃብሩ ላይ !
ዊልያም ቬን ካርላይል የኢስት ሊኑ አርኪባልድ ካርላይል የመጀመሪያ ወንድ ልጅ የሚል ዕብነበረድ አቆመበት " ዐይን ካረፈባቸው ኀዘንተኞች አንዱ
ሪቻርድ ሔር ትንሹ ነበር "

ሳቤላ በአእምሮም ሆነ በአካልም ይዞታዋ በጣም የሚያሠጋ ሆነ ነገር ግን
ሐኪም እንዲያያት ስለ አልፈለገች የሕመሟ መጠን አልታወቀላትም ይታይባት
የነበረ የበሽተኝት ምልክት ዊልያምን ያለ ዕረፍት ስታስታምም ከድካም ብዛት
የመጣ ስለመሰለ በቤተሰብ ዘንድ አሳሳቢ ሆኖ አልታየም " ከክፍሏ መውጣት
ስትተው ጆይስ ታስታምማት ጀመር " እሷ ግን የሰው ልጆች ኃይልና ጥበብ
ሊመልሰው የማይችል ሞት በመምጣት ላይ እንደ ነበር ዐውቃው ነበር ነገር
ግን ኢስት ሊን ሆና ለመሞት አልፈለገችም ሐሳቧን በሙሉ አሰባስባ ከኢስት
ሊን የምትወጣበትን መንገድ ማውጣት ማውረድ ተግባሯ አደረገችው " እንዳትታወቅ የነበራት ሥጋት እንደ ወትሮው ማስጨነቁን እየቀነሰላት ሔደ መታወቋ ሊያስከትለው ለነበረው ውጤት ማሰቡንም ተወችው " ወደ መቃብር ሲቃረቡ ማንኛቸውም ዐይነት የዚህ ዓለም ፍራቶችና ተስፋዎች ሁሉ ኃይላቸውን ያጣል
👍15
ሳቤላ ወደ ኢስት ሊን በመመለስ ከፍተኛ ድፍረት ነበር የፈጸመችው » በተግባር ባየችው ጊዜ በጉልበትም ሆነ በመንፈስ ጥንካሬ እንደማይቻል ተረዳችው ።የደረሰባት ከፍተኛ የመልክ ለውጥና የራሷም ጥንቃቄ ተዳምረው እንድትታወቅ እንደማያደርጓት የተሰማት ኤርግጠኝነት በሁሉም ገጽታ አዙሮ የማየት ግንዛቤዋን አጨለመው የፈለጉትን ይበሉ እንጂ የሰዎችን ስሜቶች ከልባቸው ጨርሶ
ማጥፋት ይቻላል ማለት ዘበት ነው አምቆ መያዝ አደንዝዞ ማቆየት ወይም
በቁጥጥር ሥር ማዋል ይቻል ይሆናል " ነቅሎ ማጥፋት ግን አይቻልም ። በዚህ ዓለም የመጨረሻውን የፍጹምነት ደረጃ ደረሰ የሚባል ትልቅ ሰው ቢኖር እንኳን ክፋትን ከሐሳቡ ስሜታዊ ፍላጐቶችን ከተፈጥሮው ላለማስቀረብ ያለማቋረጥ መታገል ያስፈልገዋል ።

ሳቤላ የሚስተር ካርላይል ሚስት በነበረችበት ጊዜ ከልቧ አትወደውም ነበር።
እሱ ለሷ የነበረው ፍቅር ያደርግላት የነበረው እንክብካቤ ይሰጣት የነበረው አክብሮት በሷ ላይ የነበረውን ከፍተኛ ግምት እያየች : እያወቀች አጸፋውን አስተካክላ መልሳለት አታውቅም " አሁን ግን ነገሩ ተለዋወጠ " ዓለም የምትዞረው በቅራኔ ሕጎች ስለሆነ እኛም አብረናት እንዞራለን " በእጃችን የገባውን እንንቃለን የማናገኘውን እንመኛለን " ወደ ኢስት ሊን ተመልሳ ከመጣችበት ማታ
ጀምሮ ለሚስተር ካርላይል ያደረባት ፍቅር ከዚያ በፊት ሆኖ በማያውቅ ኃይልና
ግለት ነደደባት
" ገልጻው የማይለቃት ' ነዶ የማይወጣላት በርዶ የማይይጠፋላት ውስጥ ውስጡን እያቃጠለ የሚፈጃት ሆነ ከድታ ስትወጣ ወዲያው ጀመራት ተመልሳ ስትግባ ጠናባት » ስለዚህም ትታው በሔደችው ባሏ ፍቅር ተብከነከነች
አሁንም አሁንም የሆነውን ነገር ሁሉ ትዘነጋውና ባሉም ባሏ ቤቱም ቤቷ ይመስላታል ከዚህ የቀን ሕልም እየሆነ ከበጠበጣት ተስፋ ቢስ ፍላጎት ለመላቀቅ ቆርጣ እርግፍ አድርጋ ለመተውና ስለሱም ላለማሰብ ትሞክርና ለቀቅ
ሲያደርጋት በገዛ ምኞቷና ሐሳቧ ኃፍረትና ጸጸት ተተክተው ያንገበግቧታል እነሱ ደግሞ ጥቂት ቆይተው ከአአምሮዋ እልም ሲሉላት ወዲያው ተመልሳ ከወጣችበት የአጉል ምኞትና የቀን ቅዠት ባሕር ትግባለች ባሏን ሚስተር ካርላይልን ከነፍቅሩ እራሷ ለባርባራ ማስረከቧን ፈጽማ ትረሳዋስች የሚስተር ካርላይል ፍቅር የባርባራ እንጂ የሷ አይደለም ሚስተር ካርላይልም የሚስቱ የባርባራ እንጂ
የሷ አይደለም ከሁሉ የከው ነገር ደግሞ የሷ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን የሌላ መሆኑ ነበር " በዚህ ጉዳይ ባርባራ ባትኖር ኖሮ እንደ ምንም ትችለው ነበር ነገር ግን ሆነና ከጸጸት ጋር ተደርቦ ከዕድሜዋ በፊት ጣላት ።

በሌላ በኩልም የፍራንሲዝ ሌቪሰን ወደ ዌስት ሊን መምጣትና በከባድ ወንጀል መከሰስ መንፈሷን አወከው ናላዋን በጠበጠው ጸጸቷን አባባሰ " ትዝታዋ ሁልጊዜ በሹል ጦር እንደ ተወጋ ሁል ጊዜ ሳይታሰቡ በሚወረወሩት የነገር
መርዞች እንደ ተነደፈች በየስዓቱ በመታወቅ ሥጋት እንደ ተሸማቀቀች ወደ
ዌስት ሊን ለምን እንደ መጣች ከሕሊናዋ ጋር እንደ ተናነቀች ማብቂያ ባልነበረው ውጥረት ውስጥ ተዘፍቃ ኖረች " ዕድሜዋ ይህን ሁሎ ችሎ ቢረዝም ነበር እንጂ ቢያጥር ምንም አያስገርምም "

ሞቷ እሷ ታስበው ከነበረው በበለጠ ቢቃረብም እሷም የጉልበቷን መድከም
የስሜቶቿን መፍlዝ እየተመለከተች ብዙ እንደማትቆይ ዐውቃው ነበር " እናቷም የሞተችው በተመሳሳይ ሁኔታ ነበር " አንዳንዶቹ እንደ ዶክተር ማርቲን ያሉ በሳንባ በሽታ ነው ሲሉ ባሏ የማውንት እስቨርን ኧርል ደግሞ በኀዘን ብዛት ነው ይል ነበር " ሳቤላም በልጅቱ ይኸ ነው የሚባል በሽታ አልነበራትም " ነገር ግን ጊዜ ሞቷ እንደ ቀረበ ዐወቅችው እሷ ደግሞ ዐይኗ እያየ ለመታወቅ አልፈለገችም
እንዲያወም እስከ ጊዜ ሞቷ ድረስ ኢስት ሊን ለመቆየት ምንም ሐሳብ
አልነበራትም ።

ኢስት ሊንን ሹልክ ብላ በወግ በማዕረግ መልቀቋን እንጂ ከዚያ ወጥታ ወዴት
አንደምትሔድ የት እንደምትገባ የቅድሚያ ትኩረት አልሰጠችውም " ጆይስም ብትሆን ለራሷ ፈርታ አንድትሔድላት በየቀኑ ትወተውታት ጀመር ስለዚህ ከሁሉ በፊት የመሔዷን ነገር ለሚስዝ ካርላይል ልትነግራት ፈለገችና ዊልያም በተቀበረ በበነጋው ወደ አመቤቲቱ መልበሻ ክፍል ሰተት ብላ ገባች "

ባርባራ በሠረገላ ወጣ ብላ ስለ መጣች ድካም ተሰምቷት ከሶፋው ላይ
ጋደም ብላለች ሳቤላ ስትገባ ሚስተር ካርላይል ወጥቶ ሔደ ።

ማዳም ቬን ” አለቻት ባርባራ ለልጆች የምታደርጊው ጥንቃቄ
ከልብ ነው የተሰማን ሚስተር ካርላይል የውለታሽ ነገር ከብዶቷል አንቺን
ማጣቱ በጣም ነው
የሚያሳዝነን ።

“እኔም ከናንተ መለየቱ በጣም አስጨንቆኛል
አለች ሳቤላ እሷማ
ምትፈልገውንና የምትወደውን ሁሉ ትታ ስትሔድ እንዴት አይጨንቃትም »

"አሁንም መሔድ የለብሽም " ዊልያምን ስታስታምሚ ስለሆነ የታመምሽው
በጎ እስክትሆኝ ድረስ ዕረፍት አድርገሽ መቀመጥ አለብሽ በደንብ ካስታመምንሽ ቶሎ ትድኛለሽ"

እርስዎ ለኔ አዝነው መሆኑ ይገባኛል " ነገር ግን እምቢታዬ የዕብደት
አይምሰልብኝ እንጂ እኔ ደክሜአለሁ ጉልበቴ ከእንግዲህ ተመልሶ እንደ
ነበረው አይሆንም
“የለም እንደሱ አትበይ ሲደክመንና ሲያመን ብዙ ሐሳብ ይመጣብናል
አሁን እኔ ለአርኪባልድ ስነግረው እያነጋገረ አበረታታኝ እንጂ ድክም ብሎኝ ነበር ላንቺም ማዳም ቬን .. የምትወጂው ባልሽ በሕይወት ቢኖርልሽ ኑሮ
ባሌ እንደሚያደርግልኝ ይወድሽና ይደግፍሽ ነበር አሁን ግን ማንም እንደሌለሽ
እያወቅን እንዲህ ሆነሽ ከቤት አውጥተን አንጥልሽም " አለቻት "

“ከዚህ ያደረሰኝ ዊልያምን በማስታመሜ አይደለም መሔድ አለብኝ በነገሩ
አስቤበታለሁ ''

“ ወደ ባሕር ዳርቻ መሔድ ደስ ይልሻል ? " አለቻት ባርባራ „ “ እኔ አርኪባልድ ሔደሽ አየር ካልለወጥሽ ብሎ ስለ አስቸግረኝ ሕፃኗን ይዤ በሚመጣው ሳምንት ልሔድ ነው " ለመሔድ ከፈለግሽ ግን ልዩ ፕሮግራም ልናዘጋጅ
እንችላለን " ሊረዳሽ ይችል ይሆኖል ... ማዳም ቬን »

ማዳም ቬን ራሷን ነቀነቀች “ይብስብኛል “ እኔ የምፈልገው ጸጥታን ነው
ስለዚህ የምለምንዎ ይኸው አስቀድሜ ስለ ተናገርኩ ከጥቂት ቀኖች በኋላ እንድለቅ እንዲፈቀድልኝ ብቻ ነው ።

“ ስሚ ” አለች ባርባራ ጥቂት ካስበች በኋላ “ እኔ በሁለት ሳምንት ውስጥ
እመለሳለሁ ። እስከዚያ ድረስ መቆየት አለብሽ " እንዲያውም ሚስተር ካርላይል አብሮኝ ሊስነብት ስለማይችልና ፡ እዚያ ብቻዬን መቀመጡ ቶሎ ሊስለቸኝ ስለሚችል ከዚያ በፊትም እመለስ ይሆናል እንድታስተምሪ ወይም ሌላ ሥራ እንድትሠሪ አልፈልግም ሉሲም ዕረፍት አድርጋ ልትሰነብት ትችላለች ሚስተር ኬን ብቻ እየመጣ ሙዚቃ ያስተምራታል ዋናው ነገር ምን መሰለሽ ልጂቱ ነፍስ እያወቀች እያደገች ነው " ስለዚህ ያንቺ ቁጥጥር ይኖርበት ለቤት ሰራተኛች
ለጆይስ እንኳን ቢሆን ጥያት መሔዱ ደስ አላለኝም " አንቺ ሐሳብሽን ካልለወጥሽ እኔ ስመለስ መሔድ ትችያለሽ " ምን ይመስልሻል ? ''

“ እሺ ” አለች ቶሎ ብላ ከልጆቿ ከሎሲና ከአርኪባልድ ጋር ሌላ ሁለት
👍20
ሳምንት መሰንበቱን በታላቅ ደስታ ተቀበለችው " በርግጥ ያ ክፉ ሞት ሊወስዳት በመምጣት ላይ እንደ ነበር ብታውቅም ከሁለት ሳምንት የበለጠ ጊዜ እንደሚኖራት ታምን ነበር " እሷም ራሷ የሚስተር ካርላይል ሚስት በነበረችበት ጊዜ ወደ
ባሕር ዳርቻ እንድትሔድ መታዘዟን ባሏም መሔድ እንደሚገባትና ጤንነቷንም
ሊሻላት እንደሚችል ምን ያህል እንደ ወተወታት አስታወሰች » በዞ በሆቴል
አያያዝ ስለ ምቾቷ ምን ያህል ይጨኔቅላት እንደ ነበር ተመልሶ ሊጠይቃት በመጣ ጊዜም ምን ያህል አሰቦላትና ናፍቋት እንደ ነበረና ደኅና ተሽሏት ሰውነቷም ተመልሶም ሞልቶና ወዝቶ ባያት ጊዜ የተሰማው ደስታ የሆነላት መሆን ሁሉ ትዝ
አላት » በተለይ ደግሞ አንድ ቀን እሷን ጠይቆ ለመመለስ ከመርከብ ሊሳፈር ሲል አንተ... ከባርባራ ሔር ጋር እንዳትዳራ ያለችው አሁን ድቅን አለባት "
ዛሬ ያ ሁሉ የነበረው ፍቅር ደግነት ባርባራ ባለመብት ሁናበት ምኑም ሳይጓዶል እየተጠቀመችበት ነው "

ባርባራ ማዳም ቬንን ከኢስት ሊን ሳትወጣ እንድትቆያት አጥብቃ በለመነቻት ጊዜ በልቧ በጣም ደስ እንዳላት ባትገልጸውም ላለመቀበል አልጨከነችም "
ይህች አስተማሪ ጠባይዋ ከብዙዎቹ ብጤዎቿ ለየት ያለች ከትልቅ ቤተስብ
የተወለዶች በጨዋ ደንብ
ያደገች መሆኗን ባርባራ ጠቅላላ ሁኔታዋን በመገምግም ዐወቀቻት " ሁለተኛዉ ለሉሲ ስትል ብቻ ደሞዟን የምትፈልገውን ያህል አሳድጋላት እንድትቀመጥላት ፈለገች ነገር ግን ባርባራ ለሉሲ ስትል ብቻ እንጂ በግል ስሜቷ ማዳም ቬንን አትወዳትም ነበር በአርግጥ ሰውነቷ ቢነግራት ይሆናል እንጂ የምትጠላበት ይኸ ነው የምትለው ምክንያት አልነበራትም ".....

💫ይቀጥላል💫
👍13