አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
መጠጡን አንስታ በርከት እያደረገች ከተጎነጨችለት በኋላ ባዶውን ብርጭቆ እባንኮኒው ላይ ስታኖር መዳብማ ቀለም በያዘው ለስላሳ ቆዳዋ ላይ እጁ ቀስ ብሎ ሲሰፍ ተሰማት ። በየሳምንቱ እሁድ እጓሮዋ ቁጭ ብላ ፀሐይ ሲመታት ስለሚውል የቆዳዋ መልክ መዳብማ ሆኗል ። እንዲህ ከኋላዋ መጥቶ ሲዳብሳት ዝም ብላ ባለችበት ቆመች ። የገላው ግለት ተሰማት በጣም በጣም ፈለገችው ። ይህን ፍላጐቷን አስቀድሞ ማወቁን ብታውቅም ይህን ማወቋ ሰልችቷት ነበረና ። ልታስበው አቅም አጣች ። ብትችል ኖሮ ገላዋን መከልከል ነበረባት ። ብትችል ያን ለማድረግ ጊዜው አሁን ነበር ።
« ዌንዲ በጣም ታስፈልጊኛለሽ » አለ ። ቃሉን ስትሰማው መላ አካሏን ፍትወት አቅበጠበጣት ። ግን ደግሞ ይህ መሆኑ እንዳይታወቅባት ራሷን መቆጣጠሯም አልቀረም ። ፊቷን እንዳዞረች ፤ በጀርባዋ ላይ ቀስ እያሉ እየደባበሱ የሚወርዱትን እጆቹን ልስላሴ ጠላች ።
« እና ልበልሀ ቅድም አንተ እንዳልከው» አለች ። በጣም ታስፈልጊኛለሽ ላላት ስትመልስ ።
« ፍላጐቴን መቆጣጠር እንደማልችል ታውቂያለሽ ማለቴ ነው» አለ ። ድምጹ እንደገላው ልስልስ ያለና የላመ ነበር ።
«ማይክል የፍላጐቴ ግለት ሳይሆን ፍቅር ነው ። ዳሩ አንተ በፍቅርና በባዶ የፍላጐት ግለት መካከል ያለውሰን ልዩነት አታውቀውም ። ከሷም ጋር ሳለህ እንዲሁ ነበርክ ? » ይሀን ስትል የሚዳስሷት እጆች ቀጥ አሉ ። ክንዱም ጥንክር ሲል ተሰማት ። አደጋ አለ ። ሆኖም ራሷን ተቆጣጥራ ዝም ልትል አልቻለችም ። ልትጐዳውም ፈልጋለች ። «እሷንም ለማፍቀር ለመውደድ ትፈራ ነበር ? ዛሬ ማንንም መውደድ ስለሌለብሀ ፤ እሷን በማጣትህ የተነሣ በደረሰብህ ሀዘን ጀርባ ተከልለህ እንድትኖር ስለረዳህ ፤ ሞቷ ችግርህን ቀላል አድርጐልሀል ልበል ? የሷ ሞት ከፍርጃም ፤ ከንትርክም ነፃ አድርጐሃል ፤ አይደለም ? » ይህን ብላ ዞረችና ፊት ለፊት ተጋፈጠችው። በዓይኑ ውስጥ
የጥላቻ ጥንስስ ሲፈላ ተመለከተች ።


ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍10
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ

...‹‹ሪሌይ ለኔ ታማኝ ነው›› አለችው ሃሳቡን ውድቅ በማድረግ
ፒተር አልለቀቃትም ‹‹ማበረታቻ ካገኘስ?››
ይሄ ነው ለካ የፒተርን ልብ እንዲህ ያሳበጠው አለች ናንሲ በሃሳቧ ዳኒ ሪሌይ ጉቦ በልቷል፡፡ አሁን የምር ጭንቅ ጭንቅ አላት፡ ራሊይ እልም ያለ ሙሰኛ ስለሆነ ጉቦ ከመብላት እንደማይመልስ ታውቃለች፡፡ ፒተር ምን ቢሰጠው ነው ሪሌይ እንደዚህ የተንበረከከለት?› ይህን ማወቅ አለባት፡ ይህን"
ጉቦ ሳይበላው ከአፉ ትነጥቀዋለች ወይም ፒተር ከሰጠው የበለጠ ጉቦ
ታቀርብለታለች፡
‹‹ዕቅድህ ዳኒ ሪሌይ ላይ ላንተ ባለው ታማኝነት ላይ የተንጠለጠለ
ከሆነ እኔን አያስጨንቀኝም›› አለችና በንቀት ሳቀችበት፡

‹‹አዎ ዕቅዴ ዳኒ ሪሌይ በሚሰጠኝ ድጋፍ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ዳኒ
ምን ያህል ገንዘብ እንደሚወድ ታውቂ የለም›› አለ በድል አድራጊነት
መንፈስ፡፡

ናንሲ ወደ ናት ፊቷን አዞረችና ‹‹እኔ አንተን ብሆን ኖሮ ይሄን እውነት ነው ብሎ መቀበል ይከብደኝ ነበር›› አለችው፡፡

‹‹ናት በዚህ በኩል ምንም ጥርጥር የለበትም›› አለ ፒተር ፈርጠም ብሎ፡፡

ናት በወንድምና እህቱ እሰጥ አገባ ውስጥ ከመግባት ተቆጥቧል፡
ፒተር ቀጠለና ‹‹ናት ለሪሌይ ከጄኔራል ቴክስታይል ኩባንያው ጠቀም
ያለ የአክሲዮን ድርሻ ሊሰጠው ነው፡፡››

ፒተር በመጨረሻ የተናገረው ለናንሲ አቅል እንደሚያስት ምት ነበር፡
ናንሲ በንዴት ጉሮሮዋ ተዘግቶ መተንፈስ አቃታት፡፡ ለዳኒ ሪሌይ ጄኔራል
ቴክስታይልስን በመሰለ ግዙፍ ኩባንያ ውስጥ እግሩን ከመትከል በላይ
የሚያጓጓ ነገር አይኖርም፡፡ ኒውዮርክ ውስጥ ከሚገኝ ትንሽ የህግ ጥብቅና
ተቋም ጋር ሲነጻጸር ይሄ በሳህን የቀረበለት ስጦታ የዕድሜ ልክ ገቢ
የሚያስገኝ በመሆኑ ሪሌይ ይህን ስጦታ ላለመቀበል ወደ ኋላ አይልም፡፡
ሪሌይ እንደዚህ አይነት እጅ መንሻ ከቀረበለት እናቱን ከመሸጥ አይመለስም፡፡

የፒተር 40 በመቶና የሪሌይ 10 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ በድምሩ 50 በመቶ ነው፡፡ የናንሲ 40 በመቶ ከአክስታቸው 10 በመቶ ጋር ሲደመር እንደዚሁ ሃምሳ በመቶ ነው፡፡ ሆኖም የቦርድ አባላት ድምጽ እኩል በእኩል በሚሆንበት ጊዜ አሸናፊውን ለመለየት የኩባንያው ኃላፊ (ሊቀመንበሩ)
የሚሰጠው ድምጽ ወሳኝነት አለው፡፡ የኩባንያው ኃላፊ ደግሞ ፒተር ነው፡

ፒተር ናንሲን መደፍጠጥ በመቻሉ በኩራት ፈገግ አለ፡፡

ናንሲ ገና እጇን አልሰጠችም፡ አጠገባቸው ያለውን ወንበር ሳበችና
ቁጭ አለች፡ ፊቷንም ወደ ናት አዞረች፡ ከወንድሟ ጋር ይህን ያህል ስትከራከር የእሷን አባባል እንዳልወደደ አውቃለች፡፡ ፒተር በድብቅ ነገር ሲጎነጉን ናት ያውቅ ነበር ስትል አሰበች፡፡ ስለዚህ ነገር ናትን ልትጠይቀው ወደደች፡

‹‹ፒተር የሚለው እውነት ይመስልሃል?››
በአንድ ወቅት ፍቅረኛው የነበረችው ሴት ላይ ዓይኑን ተከለ፡፡ እሷም በጸጥታ ምንም ሳትናገር ምላሹን ጠበቀች፡፡ በመጨረሻም የዓይኗን ፍጥጫ መቋቋም አቅቶት ‹‹እኔ አልጠየቅሁትም፡፡ ደግሞ በቤተሰባችሁ ጠብ ውስጥ
እኔን ምን ያገባኛል? እዚያው በጠበላችሁ፡ እኔ የንግድ ሰው እንጂ የእርዳታ
ድርጅት ሰራተኛ አይደለሁ›› አላት፡

‹‹ናት አንተ እውነተኛ የንግድ ሰው ነህ?

‹‹እንደሆንኩ ታውቂያለሽ›› አላት ፈርጠም ብሎ፡፡

‹‹ከሆንክ አንተ
እንደዚህ ያለ ሸፍጥ ቢፈጸምብህ ዝም ብለህ
ታልፋለህ?››

ናት ትንሽ አሰብ አደረገና ይሄ የአንድን ኩባንያ ባለቤትነት ለሌላ
የማዛወር ሂደት እንጂ የሻይ ግብዣ አይደለም›› አለ፡፡
ናት ብዙ ሊል ፈልጎ አቋረጠችውና በወንድሜ እምነተ ቢስነት
እጠቀማለሁ ብለህ አስበህ ከሆነ አንተም እምነተ ቢስ ነህ ማለት ነው የአባታችን ምክትል ሆነህ በመስራትህ
ነው ዛሬ እዚህ ደረጃ የደረስከው››አለችና ናት መልስ ከመስጠቱ በፊት ወደ ፒተር ዞረችና ‹‹ለሁለት ዓመት ያህል የኔ ዕቅድ ተግባራዊ እንዲሆን ብትረዳኝ አሁን
በመሸጥ ከምታገኘው እጥፍ እንደምታገኝ አታውቅም?›› አለችው::

‹‹ይሄን እቅድሽን አልቀበለውም፡፡››

‹‹ኩባንያው የአወቃቀር ለውጥ እንኳን ባይደረግበት በጦርነቱ ምክንያት
የአክሲዮን ዋጋው ሰማይ ሊነካ ይችላል፡ የወታደር ጫማ በማቅረብ በኩል
የሚስተካከለን የለም፡፡ አሜሪካ ጦርነቱ ውስጥ ብትገባ ደግሞ የምናገኘው ገቢ የትየሌለ ነው›› አለች፡፡

‹‹አሜሪካንን ደግሞ ጦርነቱ ውስጥ ምን ይጨምራታል?››

‹‹ባይሆንስ? አሁን አውሮፓ ውስጥ የሚካሄደው ጦርነት ብቻ እንኳን ለእኛ ንግድ ጥሩ ገቢ ያስገኝልናል›› አለችና ወደ ናት ዞር ብላ ‹‹ይሄን ታውቃለህ አይደለም? ለዚህ አይደል የእኛን ኩባንያ መግዛት
የምትፈልገው?›› ስትል አፋጠጠችው፡፡

ናት ምንም አልተነፈሰም፡፡

ቀጥሎ ወደ ወንድሟ ዞር ብላ ‹‹ትንሽ ብትቆይ ትልቅ ቢዝነስ ፊታችን ይጠብቀናል፡፡ አድምጠኝ ወንድምዬ፧ የምለው ሁሉ ስህተት ነው? የኔን
ምክር በመከተልህ የከሰርክበት ጊዜ አለ? የኔን ምክር ገሸሽ በማድረግህ
ደግሞ ገቢ ያገኘህበት ጊዜ አለ?›› ስትል በጥያቄ አጣደፈችው፡፡

‹‹አንቺ ምንም አይገባሽም›› አለ ፒተር፡፡

አሁን ቀጥሎ ምን እንደሚመጣ አታውቅም፡፡

‹‹ምንድነው የማይገባኝ?››

“ለምን ኩባንያው ከናት ሪጅዌይ ኩባንያ ከጄኔራል ቴክስታይልስ ጋር እንዲዋሃድ እንደፈለኩ? ለምን እንደዚህ እንደማደርግ አይገባሽም፡፡››

‹‹እሺ ለምንድነው?››
ፒተር አንድ ነገር ሳይተነፍስ ትክ ብሎ ተመለከታት፡፡ እሷም መልሱን
ከዓይኑ አይታ አገኘች::

ለእሷ ከፍተኛ ጥላቻ አለው፡:

በጣም ደነገጠች፡፡ ልክ ከማይታይ ግድግዳ ጋር የተጋጨች መሰላት፡
ይህን ሃቅ በእጅጉ ማመን አልፈለገችም:: ሆኖም ይህን በፊቱ ላይ ያየችውን
እንግዳ የሆነ የጭካኔ ገጽታ እንደሌለ አድርጋ መቀበል አስቸገራት፡፡ በታላቅና
በታናሽ መካከል ያለው ተፈጥሮአዊ ባላንጣነት ድሮም አለ፡፡ ይሄኛው ግን
ከዚያ ይለያል። ይሄ አስፈሪ፣ ለመግለጽ አስቸጋሪና እንግዳ የሆነ የጥላቻ
ገጽታ ነው፡፡ ይህን ከዚህ ቀደም ጠርጥራ አታውቅም፡፡ ታናሽ ወንድሟ
በጣም ይጠላታል፡ ልክ ከሆነ ነገር ጋር የተጋጨች ይመስል ደነዘዛት፡ ይን
እውነታ አምኖ ለመቀበል ትንሽ ጊዜ ይፈጃል።

ፒተር ጅል ወይም ስስታም ወይም ንፉግ ስለሆነ አይደለም ይህን
የሚያደርገው፡፡ እህቱን ለማጥፋት ሲል ራሱን ከመጉዳት አይመለስም፡ ይሄ ደግሞ የለየለት ጥላቻ ነው፡፡ ወንድሟ ትንሽ አዕምሮው ሳይነካ አይቀርም፡

ትንሽ ማሰብ ፈለገች፡ ንጹህ አየር ለማግኘት ብላ በጭስ ከታፈነው ቡና ቤት ወጣች፡ ከቡና ቤቱ እንደወጣች ቀለል አላት፡፡ ከባህር የሚወጣው ቀዝቃዛ ንፋስ ተቀበላት፡፡ መንገዱን አቋረጠችና ወደ ወደቡ ሄደች፡

የሰማይ በራሪው ጀልባ ወደቡ ጥግ ተኮፍሷል፡ አይሮፕላኑ ከጠበቀችው
በላይ ግዙፍ ነው፡፡ የአይሮፕላኑን ነዳጅ የሚሞሉት ሰዎች ከሩቅ ሲታዩ ጉንዳን ያካክላሉ፡፡ ግዙፎቹ ሞተሮች በአይሮፕላኑ ላይ እምነት እንድትጥል አድርገዋታል፡፡ በዚህ አይሮፕላን ላይ ፍርሃት አይሰማኝም› ስትል አሰበች፡ በዚያች ሚጢጢ አይሮፕላን እንኳን ህይወቷን ሸጣ መጥታ የለም፡፡

አገሯ ስትደርስ ምንድነው የምታደርገው? ፒተር ይህን እቅዱን እንዲለውጥ ማሳመን አይቻልም: አሁን ካሳየው ባህሪ በስተጀርባ ለረጅም ዓመት አምቆ የያዘው ድብቅ ጥላቻ እንዳለ አውቃለች፡፡ ለወንድሟ አዘነችለት፡፡ ይህን ያህል ዓመት ከቅናት የተነሳ ጥላቻ በሆዱ ሲያስታምም ቆይቷል፡፡ እጇን ልትሰጥ አልፈለገችም፡፡ የተወላጅነት መብቷን ለማስከበር
‹ሌላ መንገድ ይኖር ይሆን?› ብላ አሰበች፡፡
👍16
ዳኒ ሪሌይ መንፈሰ ደካማ ሰው ነው፡፡ በአንድ ሰው በጉቦ የተደለለ ሰው
በሌላ ሰው መደለሉ አይቀርም፡፡ ናንሲ ድምፁን ለእሷ እንዲሰጥ የሚያደርገው ትልቅ ስጦታ
ማሰብ አለባት: የጄኔራል
ቴክስታይልስ ኩባንያ የህግ ጠበቃነት ከሚያስገኘው ጥቅም ካልበለጠ ግን
ለማቅረብ ድካሟ ሁሉ መና መቅረቱ ነው፡፡

ምናልባት የሰራኸውን ወንጀል አጋልጣለሁ ብላ ማስፈራራት ሳያዋጣት አይቀርም፡፡ ይሄ እንደውም ብዙ ገንዘብ አያስወጣትም፡፡ ግን
እንዴት? ምናልባትም ለቤተሰቡና ለእሷ ጥብቅና እንዳይቆም ማገድ ትችል
ይሆናል፡ ይህም ቃል ከተገባለት የጥብቅና ስራ ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ
የሚባል አይደለም፡፡ ዳኒ በጣም የሚወደው በቀጥታ ጥሬ ገንዘብ ቢሰጠው
ቢሆንም አሁን በእጇ ያለው ጥቂት ሺህ ብር ብቻ ነው፡ አብዛኛው ገንዘቧ
በብላክ ጫማ ኩባንያ ውስጥ ታስሯል፡፡ ብዙም ሳይታወቅ ከኩባንያው ጥቂት ገንዘብ አውጥታ መስጠት ትችል ይሆናል፡ ነገር ግን ዳኒ ብዙ ገንዘብ
መጠየቁ አይቀርም፤ ምናልባትም አንድ መቶ ሺ ዶላር፡፡ ይህን ያክል ገንዘብ
ደግሞ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከየት ታመጣለች?

ይህን በአዕምሮዋ ስታወጣ ስታወርድ ስሟ ሲጠራ ሰማችና ዞር ስትል
ያ የፓን አሜሪካ አየር መንገድ ሰራተኛ እጁን ሲያውለበልብ አየች
ሌኔሃን›› ሲል ጮኸ ‹‹ከቦስተን ስልክ ይፈልግሻል ወይዘሮ
ማክብራይድ የሚባል ሰው፡፡››

ድንገት የመጣው የማክብራይድ የስልክ ጥሪ ትንሽ ተስፋ አጫረባት፡፡
ምናልባትም ማክብራይድ አንድ መላ ይነግራት ይሆናል፡፡ ዳኒ ሪሌይን እንደ
እጁ መዳፍ ያውቀዋል፡፡ ሁለቱም ሰዎች እንደ አባቷ አይሪሾች ሲሆኑ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮችን ሁልጊዜ ይጠራጠራሉ አይሪሾችም
ቢሆኑ፡ ማክብራይድ ሃቀኛ ሲሆን ዳኒ ግን አይደለም፡፡ በሌላው ነገር ግን
አንድ ናቸው፡፡ የናንሲ አባት ሃቀኛ ቢሆንም አይሪሻውያንን የሚጠቅም ከሆነ የተጭበረበረ ተግባር ቢሆንም እንዳላየ ነው የሚያልፈው፡፡

ናንሲ ወደ ስልኩ እየሮጠች አባታቸው አንድ ጊዜ ዳኒን ከገባበት ማጥ ውስጥ እንዳወጡት አስታወሰች፡፡ ከጥቂት ዓመት በፊት ነው፡፡ አባቷ ሊሞቱ አካባቢ፡፡ ዳኒ አንድ ጥብቅና የቆመለት ጉዳይ ነበረው: ቢያሸንፍ ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኝለት፡፡ ይህን ጉዳይ እንደማያሸንፍ ሲያውቅ ለዳኛው ጉቦ
ሊሰጥ ሞከረ፡፡ ዳኛው ደግሞ በጉቦ የሚደለሉ አይነት ስላልነበሩ ‹‹ዳኒ ወይስራህን ልቀቅ አሊያም ከጥብቅና ስራ ትታገዳለህ›› የሚል ምርጫ ሰጡት፡፡
በዚህ ጊዜ የናንሲ አባት ዳኛው እግር ላይ ወድቀው ምህረት አሰጡት፡፡ ናንሲ
ይህን ታውቃለች፡፡ አባቷ ሊሞቱ ሰሞን በሆዳቸው የቋጠሩትን ምስጢር
ሁሉ ይነግሯት ነበር፡፡

ዳኒ ማለት እንግዲህ እንዲህ ያለ ሰው ነው እንደ ተልባ ሙልጭልጭ፣ እምነት የማይጣልበት፣ እጅግ ሲበዛ ጅልና በቀላሉ
ሊጠመዘዝ የሚችል ሰው፡፡ የእሷ ደጋፊ እንደምታደርገው ጥርጣሬዋ ጠፋ፡

ሆኖም ቦስተን ለሚደረገው የቦርድ ስብሰባ የቀራት ሁለት ቀን ብቻ ነው፡፡

ህንጻው ውስጥ እንደገባች ወጣቱ ሰው የስልኩን እጀታ አቀበላት። ስልኩን ጆሮዋ ላይ ስታደርግ በቀጭኑ ሽቦ የማክብራይድ ድምጽ ተንቆረቆረ ማክብራይድ ሲያናግራት ለእሷ ፍቅር እንዳለው ያስታውቅበታል፡፡ ‹‹የሰማይ በራሪው ጀልባ ላይ ደረሽበት የኔ ጀግና!›› አላት የማታ ማታ ልፋቷ ፍሬ
ሲያፈራ ስላየ ደስ ብሎት፡፡
‹‹የቦርዱ ስብሰባ ላይ እገኛለሁ፡ መጥፎነቱ ፒተር የዳኒን የድጋፍ ድምጽ አግኝቷል›› አለች

‹‹ታዲያ አመንሽው?››

‹‹ድምጹን ለፒተር የሚሰጥ ከሆነ ከጄኔራል ቴክስታይልስ ኩባንያ
የጥብቅናውን ስራ ሊሰጠው ተስማምቷል፡፡››

‹‹እርግጠኛ ነሽ?›› አለ ማክብራይድ በተስፋ መቁረጥ፡፡

‹‹ናት ሪጁዌይ ከፒተር ጋ ነው አሁን››

‹‹ይሄ እባብ›› አለ ማክ፡፡
ማክ ናት ሪጅዌይን አይወደውም፡፡ ናንሲን በፍቅር ያጠመደ ጊዜ ደግሞ በጣም ጠላው፡፡ ማክ የሞቀ ትዳር ቢኖረውም ናንሲን ከመውደዱ የተነሳ
እሷን በፍቅር የሚፈልግ ወንድ ሲገጥመው በቅናት ይንጨረጨራል፡

‹‹ጄኔራል ቴክስታይልስ ኩባንያ የጥብቅና ስራውን እንዲሰራለት ዳኒን መምረጡ ያሳዝናል›› አለ ማክ፡፡

‹‹ምናልባትም ትንሽ የጥብቅና ስራ ይሰጡት ይሆናል፡ ነገር ግን
የእሱን ድምጽ ለማግኘት ሲሉ የጥብቅና ስራውን መስጠታቸው ህግ መጣስ
አይደለም?›› ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ህግ መጣስ ነው: ነገር ግን ህግ መጣሱን በማስረጃ ማረጋገጡ
አስቸጋሪ ነው፡፡››
‹‹ስለዚህ መቀመቅ መውረዴ ነው ማለት ነው?›› አለች፡

‹‹ሳይሆን አይቀርም፤ አዝናለሁ ናንሲ››

‹‹አመሰግናለሁ የጥንቱ ጓደኛዬ፡ ድሮም ፒተር ኃላፊ እንዳይሆን አስጠንቅቀኸኝ ነበር፡››

‹‹አዎ››

‹‹ከዚህ በላይ ላለፈ ነገር መጨነቅ አያስፈልግም፤ ዳኒ ከሆነ ቁልፉ አሁን መጨነቅ ስለእሱ ነው፡፡››

‹‹እውነትሽን ነው፡፡››

‹‹የሚያስጨንቀው ነገር ዳኒ አቋሙ መለዋወጡ ነው፡፡ ባላንጣዎቻችን እኛ ከምንሰጠው የበለጠ መደለያ ከሰጡት ወደ እነሱ መሄዱ አይቀርም
ስለዚህ ምን ያህል ብንሰጠው ነው ወደ እኛ ልናመጣው የምንችለው?››
ስትል ጠየቀችው፡፡

ማክ ለጥቂት ደቂቃዎች ጸጥ አለና ‹‹ምንም ሃሳብ አልመጣ አለኝ አላት፡፡

‹‹ዳኒ አንድ ወቅት ላይ ለዳኛ ጉቦ ሊሰጥ ሲል ተይዞ አባባ እንዴት
አድርጎ ከችግር እንዳወጣው ታስታውሳለህ?›› ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹በደምብ አስታውሳለሁ፡››
‹‹እሺ ይህን ጉዳይ እሱን ለማስፈራራትና ለእኔ ድምጽ እንዲሰጥ ለማድረግ መጠቀም አንችልም?››

‹‹እንችላለን››
‹‹ከፒተር ስር ስር የምትለውን ነገር ካላቆምክ እናጋልጥሃለን ብንለውስ?››

‹‹የሰነድ ማስረጃ አለን?››

‹‹አባባ ካስቀመጣቸው ወረቀቶች መሃል ሳይኖር አይቀርም፡›››

‹‹ሁሉም ሰነዶች አሉ? አልጠፉም ናንሲ?››
ቦስተን ናንሲ መኖሪያ ቤት ውስጥ የአባቷ ወረቀቶች የታጨቁባቸው
ካርቶኖች አሉ፡፡
‹‹ምን እንዳለባቸው አላውቅም›› አለች።
‹‹ቢኖሩስ አሁን ምን ጊዜ አለን?››
‹‹ሰነዱን አውጥተን እናጋልጥሃለን ብንለውስ?››
‹‹አልገባኝም ያልሽው?››
‹‹አባባ ካስቀመጣቸው ሰነዶች መካከል ያንተን ጉድ የሚመለከቱ ሰነዶች
አግኝተናል ብለን እናስፈራራው፡፡ አንዴ አድምጠኝ ማክ፡፡ ይሄ ሃሳብ ነው›› አለች፡፡ ናንሲ አንድ ሃሳብ ብልጭ አለላትና ደስ አላት፡፡

የጠበቆች ማህበር ወይም ሌላ አካል ዳኒ የሰራውን ህገወጥ ስራ ሊቀሰቅሰው እንደተነሳ አድርገን ሹክ ብንለውስ? አንድ የሆነ አጠራጣሪ ነገር
እንደተገኘበት እንዲነግረው አንድ ሰው እንላክበት››

‹‹እሺ ሆነ እንበል፡፡ ቀጥሎስ?››

‹‹አንድ ሊታመን የሚችል ነገር እንፍጠር፡፡ ለምሳሌ ማህበሩ በአባባ ሰነዶች ውስጥ አንድ ዋና ማስረጃ እንዳለ ሰምቷል ብንለውስ?››

‹‹ሰነዶቹን እንመርምር ብለው ሊጠይቁሽ ይችላሉ››
‹‹ከጠየቁ መስጠት ግዴታ አለብኝ?››
“ቀላል ምርመራ ከሆነ ላይጠይቁሽ ይችላሉ፡፡ የወንጀል ምርመራ ከሆነ
ግን ፍርድ ቤቱ ለምስክርነት ሊጠራሽ ይችላል፡ ያኔ ምርጫ አይኖርሽም››
አለ ማክ፡፡

መስራቱ ቢያጠራጥራትም በናንሲ አዕምሮ ውስጥ አንድ ውጥን ተቀረጸ፡፡ ‹‹ስማኝ ማክ! ዳኒጋ ደውልና የሚከተለውን ጥያቄ አቅርብለት›› አለች ፈጠን ብላ
‹‹ናንሲ ቆዪ ልጻፈው›› አለና ትንሽ ቆይቶ ‹‹ቀጥይ›› አለ፡፡
‹‹ብዚህ ጉዳይ የጠበቆች ማህበር ሰነዶች ጠይቆኛል ልስጣቸው እንዴ?
ብለህ ጠይቀው፡፡››

ማክ ግራ ገባው ‹‹አይ አትስጪብኝ ሊልሽ ነው?››

‹‹እንደኔ ግምት በፍርሃት ሱሪው ላይ ይቀዝናል ማክ፡፡ እዚያ ካርቶን ውስጥ ምን ምን እንዳለ አያውቅም ማስታወሻ ይኑር ደብዳቤ ይኑር ወይም ሌላ ነገር ይኑር የሚያውቀው ነገር የለም፡፡››
👍6
‹‹አሁን ትንሽ ግልጽ እየሆነልኝ መጣ›› ሲል ማክ ናንሲም ካነጋገሩ ተስፋ አጫረች፡፡ ‹‹ዳኒ አንድ ነገር ሳይኖራት አይቀርም ብሎ ይገምታል››

‹‹አባባ እንዳደረገው መረጃውን እንድደብቅለት ይማጸነኛል፤ ሰነዶቹን
ለማህበሩ እንዳልሰጥበት ይለምነኛል፤ እኔ ደግሞ እስማማለሁ፤ ለኔ ድምጽ
የሚሰጥ ከሆነ፡፡››

‹‹ቆይ እስቲ አትቸኩይ፡፡ ዳኒ ገንዘብ ይወዳል እንጂ ደደብ አይደለም: ምናልባትም እሱ ላይ ግፊት ለማድረግ ስንል ይህን ሁሉ እንደምናደርግ
ሊጠረጥር ይችላል፡››

‹‹መጠርጠሩ አይቀርም›› አለች ናንሲ ‹‹እርግጠኛ መሆን ግን አይችልም፡ ነገር ግን የማሰቢያ ጊዜ አንሰጠውም››

‹‹አዎ፡፡ አሁን ለጊዜው ሌላ ምርጫ የለንም››
‹‹እንሞክረው?››
‹‹እሺ›› አለ ማክ፡፡
ናንሲ አሁን ቀለል ብሏታል፡፡ ተስፋዋ ለምልሟል፡ እንደምትረታ ታውቋታል፡፡
‹‹አይሮፕላኑ የሚያርፍበት የሚቀጥለው ቦታ ስደርስ ደውልልኝ ማክ››
አለች::
‹‹የት ነው?››
‹‹ቦት ውድ ኒው ፋንድላንድ (ካናዳ)፡፡ እዚያ ከአስራ ሰባት ሰዓት በረራ
በኋላ እንደርሳለን››
‹‹ስልክ አለ እዚያ?››
‹‹ሳይኖራቸው አይቀርም አይሮፕላን ማረፊያ ካለ፡ አስቀድመህ ለመደወል መመዝገብ አለብህ››
‹‹እሺ ናንሲ፤ መልካም ጉዞ››

‹‹ባይ ማክ›› አለችና ስልኩን ዘጋች፡፡ አሁን ስሜቷ ተነቃቅቷል ዳኒ በዚህ ስራ እጁን ላይሰጥ ይችል ይሆናል፡፡ ሆኖም አንዳች ውጥን መፍጠር መቻሏ አስደስቷታል፡፡

አሁን ሰዓቱ አስር ሰዓት ከሃያ ሆኗል፡ የመሳፈሪያው ሰዓት ደርሷል። ከስልክ መደወያው ኪዮስክ ወጣችና መርቪን ስልክ ወደሚነጋገርበት ክፍል ሄደች።.....

ይቀጥላል
👍11🥰1
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሀያ ሁለት (22)

« እንዴት እንዲህ ትይኛለሽ? እንዴት ይህን የመሰለ ነገር ደፍረሽ ትናገርያለሽ ? አለ ። ለቅፅበት ያህል የእናቱን ገፅታ እየችበት ። ልክ እንደማሪዮን ጨካኝ ፤ ልክ እንደማሪዮን ስሜት አልባ አረመኔ ሁኖ ታያት ። ሆኖም አልቆየም ። ሆኖም ይህ ገፅታው የእናቱን ያህል የፀና አልነበረም ። በዚሀ በኩል ከማሪዮን ሂልያርድ ጋር የሚወዳደር ሰብዓዊ ፍጡር አይገኝም ። «የነገርኩሽን ነገር እንዴት እንዴት አድርገሽ ጠመዘዝሽው! ምን ያህል ብትጨክኝ በዚህ መልክ ተረጐምሽው ?» አለ።! «መጠምዘዘም መተርጐሜም ሳይሆን መጠየቄ ነው። ጥያቄው የማይገባ ከሆነ ስሀተት ነው። በመሳሳቴ ቅር ስላሰኘሁህ ይቅርታ። እውን ተሳስቼ ይሆን ማለትም ጀምሬአለሁ ባንኮኒውን ደገፍ ብላ ቆማ ፊት ለፊት አይኗን ሳትሰብር ስትመለከተው ድንገት ትከሻዋን ይዞ አፈፍ አድርጐ ወደ ገላው አስጠጋት ። « ማይክል » አለች ። ካስር ደቂቃ በኋላ እዘመናዊው ኩሽና ወለል ላይ ተጋድመው ከላይ ከላይ ሲቃትቱ ያለነሱ ትንፋሽ በስተተር ሌላ ድምፅ አልነበረም ። ትንፋሻቸው ደርሶ ፀጥ ሲል እኩሽናው ውስጥ የተቀመጠው የጠረጴዛ ሰዓት ትክ ፣ ትክ ፣ትክ የሚል ድምፅ ጥርት ብሎ ተሰማት ። ማይክል ግን በመስኮቱ አሻግሮ የአትክልት ቦታውን ይመለከት ነበር ፤ በገፅታው ላይ ጥልቅ የሆነ ሀዘን ተስሎ ።

« ማይክል ደህና ነህ ? » አለችው። ወዲያው ነገሬ ሁሉ የእብደት ነው ። እሱ መጠየቅ የሚገባውን እኔ ጠየቅኩት ስትል አሰበች ። ግን ሁሉም የተገላቢጦሽ ሆኗል ። ላይሆንም ይችላል ። እሷ ግን አትችልም።አልቻለችም ። አንድ ቀን ይኸ ሁሉ ያበቃል ። ያኔ ምን ይውጣት ይሆን ? ምን ይደርስባት ይሆን ? ምናልባትም ቤን አቭሪን ጠርቶ ከስራ እንድታባርራት ብሎ ትዕዛዝ ይሰጠው ይሆናል። ይህ ሁሉ በሀሳቧ መጣባት ።
«ማይክ» አለች ድንገት ።
«እእ!--አ... አቤት። በ. . . በጣም ይቅርታ ዊንዲ አንዳንዴ መላ ቅጡ የጠፋኝ ወደር የሌለኝ ወደል አህያ እሆናለሁ» አለ
«እዚህ ላይ ነህ እይደለህም ብዬ ልከራከርህ እንደማልችል ርግጠኛ ነኝ ። አለችና በመከፋት ፈገግታ አየችው ። ከዚያም ጉንጩን ሳም አድርጋ ፤ « የምወድህ ግን ይመስለኛል ፤ ምንም ብትሆን » አለች።
«ሌላ ብዙ ነገር ማድረግ ትችይ ነበር ። መውደድ ብቻ አይደለም ። ግን ፍሬ ቢስ ነገር ነው » አለና ቀና ብላ ስታየው ቁልቁል ተመለከታት ። እንዲህ ሙሉ በሙሉ ካያት ስንት ጊዜ ሆነ። ሩቅ. . . ሩቅ ነው። « አንዳንዴ የምሰራውን ስራ ሳስበው ፤ በተለይ አንችን የማስቀይምሽ ትዝ ሲለኝ ራሴን እጠላለሁ ። እንዲያውም አንድ ነገር ሁን .. .» ሊቀጥል አልቻለም ። ዝም ። አትናገር ! ስትል አመልካች ጣቷን እተገጠመ ከንፈሯ ላይ በማስቀመጥ አሳየችው። « አውቃለሁ» አለ አንገቱን በአዎንታ እየነቀነቀ ። ከተጋደመበት ተነስቶ ቆመ ። እወለሉ ላይ እንደተዘረጋች ሽቅብ ተመለከተችው ። በፊቱ ላይ የነበረው ሀዘን ቀንሷል ። ቢያንስ ቢያንስ ስጋዋን በመስጠት ትንሽ ሰላም ፈጠረችለት ።
« ማይክል››
« ወይ››
«ማይክል ፤ አሁንም እሷን ብቻ ነው እምታስበው ? አሁንም ሴላ ሴት አታምርሀም ? » መልስ አልሰጠም ። ፀጥ ብሎ ለረጅም ጊዜ ቆይቶ በመጨረሻ አዎንታውን በአንገቱ ገለፀ ። ዓይኑ ውስጥ ግን ከፍተኛ ስቃይ ተስሎ ይታይ ነበር ። ይህን ብሎ ሌላ ቃል ሳይጩምር ወደ መኝታ ቤት ገባ። ዌንዲ ቀስ ብላ ከተጋደመችበት ወለል ላይ ተነሳች ። በኩሽናው ውስጥ ከሚገኙ ረጅም ብርጩማዎች ባንዱ ላይ ተንጠላጥላ ባንኮኒውን ተደግፋ ከተቀመጠች በኋላ በዓይኑ ውስጥ ተስሎ ስላየችው ስቃይ ማሰላሰል ጀመረች ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከመኝታ ቤት ወጥቶ ወደ ኩሽና ሲገባ እዚያው ጋ በሀሳብ ተውጣ እንደ ተቀመጠች አገኛት ። ከሀሳቧ ባንና ነቃች ። ቀና ብላ ስታየው ልቧ በኃዘን ተሰበረ ። ምክንያቱም ጂንሱን ታጥቆ ፤ ስፖርት ሸሚዝ ለብሶ በአንድ እጁ ሳምሶናይት የእጅ ቦርሳ ይዞ በሌላው ክንዱ ላይ ደግሞ ሹራቡን አንግቦ ነበር ። አለባበሱ ሊወጣ መሆኑን ነገራት ። ቦርሳዉን ይዞ ስታይ ምንም እንኳን ቀኑ እሁድ ቢሆንም ወደ መስሪያ ቤት ሊሄድ እንደሆነ ተረዳች ። ሹራቡን መያዙ ደግሞ እዚያው ቢሮው ሊያመሽ መወሰኑን ገለፀላት ።

« ትመጣለህ ? እንገናኛለን ?››
ይህን የተናገረውን እሷን ጠላችው ። ይህ መናገርም እይደለም ። መጠየቅ ። መለመን ነው አለች በሀሳቧ ። መልሱ ቢያምር መለመኗ ባልክፋ ። ግን ለጥያቄዋ የሰጣት መልስ በአሉታ ራሱን በመነቅነቅ ነበር ። አፈር ይብላ ! «እስከ ምሽቱ ስምንት ወይም ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ቢሮዬ ቆይቼ እሰራ ይሆናል ። ከዚያ ከቻልኩ ወደ ቤቴ ብደርስ አይከፋም ። ልብስ መቀየርም አለብኝ ፤ አደል » አለ ። ያ ለጥቂት ሰዓት ያህል ብቅ ብሎ የነበረው ለስላሳ ባህርይ ደብዛው ጠፍቶ ሰውየው ማይክል ሂልያርድ ሆነ። መሸሹን ጀመረ ። ሩካቤ ስጋ ካደረጉ በኋላ ባሉት አስር ወይም አሥራ አምስት ደቂቃዎች ውስጥ አንዴ አግኝታው አጣችው ። ሁኔታው ሁሉ የሚያፈናፍን አይደለም ። ማግኘት የሚሉት ነገር ተስፋ የሌለበት ባዶ ነው ። ሆኖም . . . ሆኖም ተስፋ መቁረጥ የሚሉት ነገር ያስጠላታል ። እንዲህ ሲገፏት ፤ ችላ ሲሏትማ ይበልጥ እንድትሞክር የሚወተውት ነገር አለባት ።

«ያው ነገ እቢሮ ነህ አይደለም… እዚያ እንገናኛለና» አለች መከፋቷን ፣ መስቃየቷን ድምጺ እንዳያውጅባት ልትጠነቀት እየሞከረች እበር ድረስ ስትሸኘውና ቻዎ ስትለው እንዲያውም ፈገግታ ቢጤ ሞክራ ነበር ፤ ይሳካም አይሳካም ። ደግነቱ እሱ ይህን ሁሉ ለማየት ጊዜ አልነበረውም ። እግንባሯ ላይ በከንፈሩ ትንሽ ነካ አድርጓት ዞሮ ሳይመለከታት መሄዱ አስደሰታት ። ምክንያቱም ገና በሩን ዘግታ ሳትሸጉረው ማልቀስ ፤ መንሰቅሰቅ ጀምራ ነበርና ። የማይክል ሂልያርድ ነገር ሊሳካ የማይችል መሆኑ ገብቷታል ።

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

በመንገዱ ላይ አንዳች ነገር አልነበረም ። ዝር አይልም። ይህን ሲገነዘብ የቤንዚን መስጫውን እስከ መጨረሻው ረገጠው። ጥቁር ቀለም ያለው ፖርሽ አውቶሞቢል ከነፈ ። የገጠሩ ምድርና በላዩ ላይ የተሸከመው ነገር ሁሉ እየሰፈሰፈ ያልፋቸዉ ነበር ። ልባቸው በደስታ ተሞላ ። በመኪና የመጓዝ ሳይሆን የመንሳፈፍ ስሜት ተሰማቸው ። በአምስት ሰዓት አካባቢ ረፋዱ ላይ እቤቷ ድረስ መጥቶ በአውቶሞቢሉ ከተሳፈረች በኋላ ከሳንፍራንሲስኮ ተነስተው ወደ ደቡብ ጉዞአቸውን ቀጠሉ። ሁልጊዜም እሁድ እሁድ በመጀመሪያ እንዲሁ ይጓዛሉ ። መድረሻቸውን አያውቁትም ። ሲሰለቻቸው ወይም ሲርባቸው ከመኪናቸው ወርደው ምሳ ይበላሉ ። ካረፉ በኋላ እጅ ለእጅ ተያይዘው እየተንሸራሸሩ ፤ ስላለፈው ሕይወታቸው እያወሩ ፤ ባለፈው ስላጋጠማቸው አስቂኝ ሁኔታ እያነሱ ከልባቸው ይስቃሉ። ሽርሽሩ ሲበቃቸው ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ ። ይህ የተለመደ እንደ ጸሎት ሥርዓቱን ጠብቆ የሚደጋገም ነገር ነውና ለምዳዋለች ፤ ወዳዋለች ። ይህን ድርጊት ብቻ ሳይሆን ፒተርንም በተዘዋዋሪ መንገድ ማፍቀር ጀምራለች ።
👍20
ፒተር ግሬግሰን ተዝቆ የማያልቅ ችሎታ ያለው ሰው ነው። ባንደኛው ችሎታው አካሏን እየመለሰላት ነው። ምንም እንኳ ገና ኦፕራሲዮኑን ባይጨርስም ዛሬ የናንሲ ፊት ቁልጭ ብሎ ወጥቷል ። ፋሻው ዓይኗ አካባቢ ብቻ ሲሆን የሚገኘው ፣ ሌላውን ፊቷንም ያደረገችው ሰፊ ጥቁር መነፅር ሙሉ በሙሉም ባይሆንም ሸፍኖታል ። ግንባሯ ላይ ያለውን ፋሻም ባርኔጣዋ ጋርዶታል ። ያም ባይሆን ከፒተር ጋር ስትሆን ይህ ሁሉ ኦይሰማትም፡፡ ፒተር ይህ ሁሉ እንዳይሰማት የሚያደርግ ኃይል አለው ። ይህን ሁሉ የሚያደርግላትን ፤ ምቾቷንና ሕልሟን እውን ያደረገላትን ፒተር ላለመውደድ ችሎታ ይኖራታልን? አንዲት ትንሽ ምግብ ቤት ሲያዩ መኪናቸውን አቁመው ምሳ ለመብላትና ዕረፍት ለማድረግ ወሰኑ ። ምግብ ቤቷ በፈረንሳይ የመንገድ ዳር ማረፊያና መመገቢያ ቤቶች ዕቅድ የተሠራችና የተሽሞነሞነች ነበረች ። በውስጧም የፈረንሳይ ምግቦችና ነጭ ደረቅ የወይን ጠጅ የሚሸጥባት ነበረች ። ምሳቸውን በሉ። ነጭ፤ደረቅ የወይን ጠጃቸውን ጠጡ ። ይህ ደግሞ ናንሲን ያስደስታታል ። ለምዳዋለች ። እዚህ እንደመጣችበት ምሥራቃዊው ግዛት ያሉ መዝናኛዎች የሉም ። ባዛሮች በብዛት አይገኙም ። የሚያብለጨልጩ ሰማያዊ ያንገት ጌጥ መቁጠሪያዎችም አይገኙም ። ስለዚህ እንደ ሀገሩ ያገሩን መዝናኛ መቀበልና መልመድ አለባት ። አንድን ነገር መልመድ በግዴታ የሚቻል ነገር ባይሆንም በውዴታ ለምዳ ወዳዋለች።

ይህ ብቻ ሳይሆን ናንሲ አዲስ ሰውነቷን ፤ አዲስ ገፅታዋንም ተቀብላ ወዳዋለች ። አዲስ ድምጺን በመቃኘት አዲስ እሷን መሆን ጀምራለች ። «ፒተር ስሜን ለመለወጥ እንዳሰብኩ ነግሬሃለሁ!» አለች። ይህን ያለችው ምሳቸውን በልተው ጨርሰው ወይን ጠጃቸውን እየጠጡ ሲዝናኑ ከቆዩ በኋላ ጠርሙሱን ሲያጠነፍፉት አካባቢ ነበር ።። ነገሩን ከፌ አሊሰን ጋር ተወያይተውበታል ። ያኔ ግን ይህን ያህልም የሚያስፈራ መስሎ አልተሰማትም ። ለፒተር ስትነግረው ዕፍረቷ በገፅታዋ ላይ ተስሎ ታዬ። ምነው ባላነሳሁት ኖሮ ስትል አሰበች። ግን ፒተር ዕፍረቷን ሁሉ በፍጥነት ከለላት ። « እንዲያ ስትይ ፈፅሞ አላስገረመኝም ታውቂያሽ ። ምክንያቱም አንቺኮ የድሮዋ ናንሲ አይደለሽም ። አዲስ ሰው ነሽ ሌላ ቆንጆ ። ያሰብሽው ደስ የሚል ስም አለ! » አለ ፒተር፡፡ ይህን ብሎ ምርጥ ሲጋራውን አቀጣጠለ ። በፍቅር ዓይን አያት የሲጋራውን ሽታ መውደድ ጀምራለች ። በተለይ ከምግብ በኋላ ሽታው ያስደስታታል ። ፒተርም ይህን የተረዳ ይመስላል ። ዓላማው ደግሞ ግልፅ ነው። በሕይወት ውስጥ አንድ ነገር ከተደረገ ጥራት ያለው መሆን አለበት ። ነገሩ ለናንሲ አዲስ ስለሆነ ይህንንም እንድትለማመድ ይፈልጋል ። ከፍ ከፍ እንደማለት የሚያስደስት ምን ነገር ሊኖር ይችላል ?።

« ታዲያ አዲሷ ወዳጃችን ማን ትባላለች ? ስሟን ትንገረና »አለ። «ለጊዜው ሜሪ አዳምሰን የሚል ስም ነው የመጣልኝ ። እንዴት ነው ይስማማል ?» ትንሽ አሰበና አንገቱን በስምምነት እየነቀነቀ… « መጥፎ ስም አይደለም ። እንዲያውም ወድጀዋለሁ ። ግን... ግን ለምንድነው ሜሪ አዳምሰንን የመረጥሽው ?››
« የናቴ ስም ማለት ከማግባቷ በፊት ሜሪ አዳምሰን ነበር። እንዳጋጣሚ ሆኖ ዕጓለማውታን ማሳደጊያው ውስጥ እወዳቸው የነበሩ መነኩሲትም ሜሪ አዳምሰን ይባሉ ነበረ››

« አረ በስላሴ ፤ እንዴት የሚያስደንቅ ጉድ ነው እባክሽ » ሁለቱም በጉዳዩ ሳቁ ....» ሜሪ አዳምሰን ። ይህን ስም ስታስበው በጣም ወደደችው ። «ከመቼ ጀምሮ ነው ባዲሱ ስም መጠራት የምትፈልጊው?»
« እኔንጃ. . . ገና አልወሰንኩም »
«እኔ ምለው ከወደድሽው ምን ዛሬ ነገ ማለት ያስፈልጋል። ዛሬ ፤ ከአሁን ጀምረን ለምን ሜሪ አንልሽም? እስራዎችሽ ላይም ሜሪ አዳምሰን እያልሽ ብትፅፊ ጥሩ ነው ። አይመስልሽም ?» ፒተር ይህን የተናገረው በከፍተኛ ስሜትና የልብ ሲቃ ነበር ። ሁልጊዜም ስለሷ ወይም ስለራሱ ሥራ ሲያነሳ የሚናገረው በከፍተኛ ሲቃ ነበር ። « ናንሲ እውነቴን ነው ፤ ለምን እሁኑኑ ሜሪ እትባይም እስራሽ ላይም ይህንኑ ስም አስገቢ »
« እንዴት ማለት እሰራሽ ላይ ? ፎቶግራፎቹ ግርጌ ፎቶ በሜሪ አዳምሰን ብዬ ልፅፍ ? »
‹‹ይመስለኛል ። ማለት ስራሽ እኔንና ፌ አሊሰንን ብቻ አስደስቶ መቅረት የለበትም ። ትንሽ ወጣ ማለት ፤ አድጣስሽን ማስፋት ያለብሽ መሰለኝ » በፒተርና በናንሲ መካከል አለመግባባት አለ ቢባል የማይግባቡበት አንደኛው ጉዳይ ይኸ ነው.። ፒተር ግሬግሰን ናንሲ ማክአሊስተር ትልቅ እንድትሆን ፤ ታዋቂ እንድትሆን ይፈልጋል ። ስራሽን ዓለም ሊያየው ይገባል ይላል ። ናንሲ ግን ለጊዜው ይህን አትሻም ።ሁሌም ይከራከራሉ ። « እንደገና ይህን ነገር እንስተን ባንጨቃጨቅ ይሻላል አለች። መዳፏን «ታገድ» በሚል መልክ እያሳየችው ። «ካልሽ ይሁንልሽ። ለጊዜው ማለቴ ነው። ግን ባጠቃላይ አነጋገር ካልን ይኸ የጋን መብራት ሆኘ ልቅር የምትይው ነገር አይስማማኝም ። ይህን የመሰለ ሥራ ተሠርቶ ማንም ሳያየው ይቅር ብትይኝ እሺ ማለት የሚቻለኝ አይመስሰኝም ። ስራሽ መውጣት ፤መታየት አለበት ።»
‹‹የማይሆነውን !»
« ስሚ ናንሲ ። ደግሜ ልንገርሽ ። አንቺ ወጥ የሆንሽ የኪነጥበብ ሰው ነሽ። እንደፊልም ተዋናይ ይሁን እንደ ፎቶግራፈር ወይም ሌላ ፤ ስራሽም አንችም በአደባባይ መታየት አለባችሁ። ይህ የኔ እምነት ነው። ፅኑ ዕምነቴ ነው »
« አትልፋ ፒተር » አለችና ከወይኑ ተጎነጨች ። ከዚያም ቡዝዝ ብላ በመስኮት ወደወጭ እየተመለከትች « ቅር አይበልህ» ግን ከእንግዲህ አደባባይ መውጣት የማይቻለኝ ሰው ነኝ››
« ለምን ናንሲ? ለምን?››
« ላለም ላሳየው የምፈልገውን ያህል ፤ ዓለም ሊያየኝ የሚፈልገውን ያህል አሳይቻለሁ ። አይቶኛል ። በቃኝ ። ካሁን በኋላ የሚታይ ነገር የለኝም »
« በጣም ጥሩ ፣ የተቻለኝን ያህል ለፍቼ ገፅታሽን የሰጠሁሽ ለካ ዕድሜ ልክሽን እማጀት ተደብቀሽ በኔ ብቻ የሚታዩ ድንቅ ፎቶግራፎችን እንድታነሺልኝ ኖሯል?»
« ይህ ታዲያ በጣም የሚያምር ነገር ነው እንዴ ?»
«ለኔ. . . ለኔ ብቻ ቢሆን ድንቅ ዕድል ነው። ላንች ግን ከዚህ የከፋ ፅጣ ሊኖር ኦይችልም። ናንሲ ፤በጣም ትልቅ ሰው ነሽ እኮ ! ተዝቆ የማያልቅ ችሎታ አለሽ ። ታዲያ ይህን ችሎታሽን መደበቁ ምን ይጠቅማል ? ስምሽ እንዲወጣ ካልፈለግሽ ሜሪ አዳምሰን በሚለው ስም ኤግዚብሽን ማሳየት ትችያለሽ አንዴ ብቻ ለሙከራ ያህል ። አየሽ ፣ ግሬታ ጋርቦም ወደ ምናኔዋ ከመግባቷ በፊት ድንቅ ተዋናይ ተብላለችኮ ። አንዴ ብቻ ምን እንደሚሆን ለማየት ዕድልሽን ሞክሪ » አለ ፒተር በልመና ፣ በማግባባትና በመለማመጥ ድምፅ።

ፒተር በዚህ ሁኔታ ከልቡ በነገራት ቁጥር ልቧ ይዋልላል ። ልሞክረው ? ትላለች ። በተለይ በሌላ ስም መሞከሩ አይከፋም ልበል ? አለች። ግን እንደገና ታዋቂ መሆን ፤እንደገና ኤግዚብሽን ማሳዬት የማይሞከር ሆኖ ተሰማት ። ስትታወቅ ፤ ለክፉ ነገር ስትጋለጥ ፤ መጥፎ ነገር ሲደርስባት ታያት ። ከዚህ በፊት ይሀን ሳትሆን የተጓዘችበት መንገድ ስለሆነ ወዶዚያው ብትመለስ አዲስ መሆን እንደማትችል ተገነዘበች ። ብዙ ነገር እንደሚያሳስባት ማይክል አሳሰባት ።
«እሺ አስብበታለሁ» አለች ።
👍14
በዚህ ጉዳይ ላይ በተነጋገሩ ቁጥር ይህን ያህል ወደ እሺታ የቀረበ መልስ ሰጥታው አታውቅም ነበረና ደስ አለው፡፡
«አዎ በሚገባ አስቢበት ፤ሜሪ » አለ ።
ሜሪ ብሎ በሰፊው ፈገግ አለ። እሷም የልጅ ዕፍረት ላቅ ሳቀች ። እና…. « ካደግክ በኋላ በአዲስ ስም ስትጠራ የቀልድ የቀልድ ይመስላል » አለች።
« ግንኮ ፊትሽም አዲስ ነው ። እሱም የቀልድ ይመስላል ?» አለና ጠየቃት ።
« ፊቴ እንኳ አይመስለኝም ። አሁን አሁን ለምጄዋለሁ። ዕድሜ ለፌ አሊሰንና ላንተ እንጂ ፊቴ የራሴ ሆኖ ነው የሚሰማኝ »አለች። « ሁልጊዜ ፤ካሁን ጀምሮ ሜሪ እያልኩ ልጥራሽ !? »
«ደግ ። ቢያንስ ስሙ ማጠሩንና መጥበቡን ለመለካት ይረዳኛል ፤ ባደባባይ ከመልበሴ በፊት » አለች ። ሁለቱም ደስ ብሏቸዋል ። ሁለቱም የሆነ የመደባበቅ ስሜት ይታይባቸዋል ። ሁለቱም»


ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍8👎1
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰባ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ሚስ ሉሲ ከአክስቷ ከኮርኒሊያ ቤት ሔዳ አንድ ጥፋት ፈጸመች ከቤት እንደተመለሱ ጥፋቷ ከሚስዝ ካርላይል ጆሮ ደረሰ " እሷም እስኪመሽ ድረስ ከልጆች ቤት እንዳትወጣና ምግብም ከዳቦና ከውሃ በቀር ሌላ እንዳይሰጣት አዘዘች "

የዚያን ለት ማታ ኢስት ሊን ውስጥ የራት ግብዣ ነበር ባርባራ ከመልበሻ
ክፍል ገብታ የራት ልብስ ለብሳ አዲስ የተቀጠፉ ቀይና ወይን ጠጅ አበባዎች
ከጸጉሯ ሰካች " ከደረቷም ተመሳሳይ ቀለም ያለው አበባ አድርጋ ፀሐይ መስላ
አሸበረቀች " ራት የሚበላው በአንድ ሰዓት ነው " አሁን 0ሥራ ሁለት ተኰል ቢሆንም ከሚጠብቁት እንግዶች አንድም ብቅ አላለም " ባርባራ አሁንም ሰዓቷን በጉጉት ትመለከታለች "

ማዳም ቬን ቀስ አድርጋ በሩን መታ መታ አደረገችው " ራት ተበልቶ
ከበቃ በኋላ ወይዛዝርቱ ወደ ሳሎን ሲመለሱ ' አብራቸው ለግማሽ ስዓት እንደትቆይ ቃል ተገብቶላት የነበረችው ሉሲ በተወሰነባት ቅጣት የተገባላት ቃል ሊቀርባት ስለሆነ በጣም ተጨነቀች " ማዳም ቬን ጭንቀቷን አይታ ይቅርታ ልትለምንላት መጣችና እየፈራች እየቸረች በሩን መታ መታ አድርጋ ገብታ ለሚስዝ ካርላይል ነገረችላት "

“ ማዳም .ይህችን ልጅ ልቅ ሰደሽ አበላሸሻት የምትቀጭያትም
አይመስለኝም » ስታጠፋም መታረም አለባት ” አለቻት ባርባራ

“ በጥፋቷ ተጸጽታለች ” አለች ማዳም ቬን " “ እንግዲህ ምንም ላታጠፋ ቃል ትገባለች " አሁንም በልቅሶ ፈርሳ ልትሞት ነው።

“የምታለቅሰው በሠራችው ጥፋት ተጸጽታ ሳይሆን ከሳሎን መግባቱ እንዳያመልጣት ፈርታ ነው "

“ አባክዎን ይቅር ይበሏት ” ብላ ለመነች ማዳም ቬን "

“ እስኪ አስብበታለሁ " እይውማ ማዳም ቬን ይኽ አሁን ተሰበረብኝ ' አያሳዝንም ? አለችና ባርባራ አንድ የወርቅ ሥራ ያለበት ጌጥ አሳየቻት "

ማዳም ቬን ተቀብላ መረመረችው አጣብቆ ሊይዘው የሚችል ማጣበቂያ ከላይ ከፎቅ አለኝ " በሁለት ደቂቃ ውስጥ አላቅቀዋለሁ” አለቻት "

“ ኧረ እንግዲያውስ በይ እስቲ ማጣበቂያውን እዚህ አምጪና ሥሪው " ጉቦ ልስጥሽ ” አለቻት እየሣቀች
እሱን መልሰሽ እንደ ነበረው አድርጊውና ለሉሲ ምሕረት መልእክት ይዘሽላት ትሔጃለሽ " መቸም ልብሽ የቆመው ለዚሁ ነው።

ማዳም ቬን ሔዳ ማጣበቂያውን አመጣችና ስባሪዎቹን አንሥታ እንዴት
ሊገጣጠሙ እንደሚችሉ እያየች ስታስብ ባርባራ ተመለከታለች "

“በፊትም ተሰብሮ ነበር ብላ ጆይስ ነግራኛለች” አለች ባርባራ ነገር ግን እንደማይታወቅ ሆኖ ተገጣጥሞ ይመስለኛል የት ላይ ተሰብሮ እንደ ነበር
እንኳን ለማግኘት አልቻልኩም " ይህ ዕቃ ሚስተር ካርይል የመጀመሪያ ሚስቱን ያገባ ጊዜ ለንደን ሳሉ የገዛላት ነበር " ኋላም እሷ ሰበረችው "እንዴ ምን ነካሽ ማዳም ቬን ? እጅሽ እንደሱ ከተንቀጠጠ ምንም ልትሠሪው አትችይም „

መጀመሪያም የት እንደተሰበረ ልትነግራትና ልታሳያት ስትል የሚያስከትለው ጥያቄም ወዲያው ትዝ አላትና ቃሉን ካፏ አድርሳ ተወችው » ቀጥሎም ይህን ዕቃ መጀመሪያ የሰበረችው ጊዜ እንዴት እንዳዘነችና ሚስተር ካርላይልም አብሮ ስለ ነበር ከዚሁ ክፍል ሆነው እያባበለና እየሳመ እንዴት እንዳጽናናት ስታስታውስ አሁን ደግሞ የጌጡ ዕቃም የካርላይል መሳምም የሷ መሆናቸው ቀርቶ
የባርባራ መሆናቸውን ስታስበው ቆጫት እጆቿም ተንቀጠቀጡ "

“ስሚንቶውን ከፎቅ ሳመጣ በጣም ስለ ሮጥኩ ነው እጆቼ የሚንቀጠቀጡት”
ብላ አመካኘች » በዚህ ጊዜ ሚስተር ካርላይልና እንግዶቹ ሲመጡ ተሰሙ
ሚስተር ካርይል ወደ ሚስቱ መልበሻ ክፍል ሲመጣ ማዳም ቬን ተነሥታ ልትሔድ ፈለገች

“የለም ! የለም !” አለች ባራባራ " “ጀምረሽዋል እኮ ጨርሺው አንጂ !
ሚስተር ካርላይል ወደ ክፍሉ ይሔዳል " ጉዴን አየኸው .... አርኪባልድ ? ይኸውልህ ተሰበረብኝ ”
ሚስተር ካርላይል የማዳም ቬንን ነጫጭ እጆችና የምትጠግነውን ዕቃ
እንደ ዋዛ አየት አድርጎ ወደ ራሱ መልበሻ ክፍል ሔደና በሩን ከፍቶ ባርባራን በጁ ጠቅሶ ጠራት ስትመጣ ሳብ አድርጎ አስገባት " ማዳም ቬን ሥራዋን
ቀጠሰች።

ባርባራ ቶሎ ተመልሳ ማዳም ቬን አጆቿን ከጓንቲዎ ስትከት ቁማበት
ወደ ነበረው ጠረጴዛ መጣች ዐይኖቿ ረጥበው ነበር "

“ዐይኖቼ የደስታ እንባ ሲያለቅሱ መግታት አልቻልኩም” አለቻት ባርባራ ምልክቱን እንዳየችባት ስትገነዘብ “ሚስተር ካርሳፈላይል ወንድሜ ነጻ መሆኑን ተከሳሾቹ አርስ በርላቸው መወነጃጀላቸውን ሎርድ ማውንት እስቨርንም ከችሎቱ መኖራቸውን ' አባባም ሰብሳቢ ሆኖ መዋሉን ነው አሁን የሚነግረኝ" አለቻት ' ለማዳም ቬን "

ማዳም ቬን ይበልጡን ወደ ያዘችው ሥራ አቀረቀረች "

“ማረጋገጫ ተገኘባቸው ? አለች ዝግ ባለ ደካማ ድምጿ "

“ የሌቪሰን ጥፋተኛነት ምንም አያጠራጥርም " ኦትዌይ ቤቴል ግን ምን
ያህል በነገሩ እንደ ገባ እስካሁን ገና አልታወቀም ግን ሁለቱም ለፍርድ እንዲቀርቡ ተወስኗል " በተለይ ያ እርኩስ ያ መናጢ ! በደሉ ሁሉ ባደባባይ ተገለጠበት” እያለች የደስታው ሲቃ ሲተናነቃት' ማዳም ቬን ቀና ብላ አየት አደረጋቻት

“ከሁሊ የሚገርመው ደግሞ ” አለች ባርባራ ድምጿን ዝቅ አድርጋ ''ያቺ
ክልፍልፍ አፊ ድፍን ዌስት ሊንና እኛ ሳንቀር ( ከሪቻርድ ጋር ኮበለለች ስንል
እሷ ግን ይህን ያህል ጊዜ ' ከፍራንሲዝ ሌቪሰን ጋር አንደ ነበረች ገና ዛሬ ሚስተር ቦል ሲያናዝዛት ታወቀባት ”

“መቸም እኔ ሚስተር ካርይል ቢሰማው ደስ አይለም እንጂ እሱም ልክ
እንደ ሎርድ ማውንት እስቨርን በጣም ነው የሚሰማው " ምንም ቢሆን ሚስቱ ነበረች » ይህን ታውቂያለሽ አይደለም ? ልጆቹም ሁሉ የሷ ናቸው " አሁን የተመሰገነና የተከበረ ነው • ወይዘሮ ሳቤላ የጣለችበትን የመሰለ : ውርደት ሊጠጋውና ሊነካው የማይችል ንጹሕ ሰው ነው ”

የመጀመሪያው እንግዳ ሠረገላ ሲገባ ተሰማ " ባርባራ በረረችና ከሚስተር
ካርላይል ክፍል አንኳኰታ “ አርኪባልድ ... ትሰማለህ ? አለችው "
“እሺ እመጣለሁ ደሞ እኮ አዲስ የሕዝብ እንደራሴ ለሆነ ሰው ትንሽ ጊዜ
አላት እየሣቀ

ባርባራ ያችን መከረኛ ሴትዮ በማጣበቂያው የተሰበረን የሽክላ ጌጥ
እየጠጋገነች : ጭንቀቱ ካላለቀለት ልቧ ጋር የቻለችውን ያህል እንድትታገል ትቴት ወደ ሳሎን ወረደች " ሁልጊዜ በማንኛው አጋጣሚ በነገር ስለት መወጋቱ አላቋርጥ አለ " ጠቅ ጠቅ በጊዜው በየምክንያቱ ጠቅ « መቸም እሷም ኢስት ሊን ለመመለስ የወሰነች ጊዜ ለቅጣቷ መቆሚያ እንዳይኖረው አድርጋዋለች " ዘለዓለም በትዝታ ' በነገር መወጋት ' በጸጸት አለንጋ መገረፍ ልማድ ሆነ።

ከሚስተርና ከሚስዝ ሔር በሸር እንግዶቹ ሁሉ ገቡ " ጆስቲስ ሔር ጤንነት
ስለ አልተሰማው ሁለቱም መቅረታቸውን የሚገልጽ ማስታወሻ ለባርባራ ደረሳት

ሳቤላ በሠራችው ሥራ ቅጣቷን እጅግ በከፋ አጠፌታ እንደ ተቀበለችው
ሁሉ ጀስቲስ ሔርም በመጠኑ የሥራ ዋጋ ሳይደርሰው አልቀረም " ስለዚህ ጤንነት ባይሰማው የሚያስግርም አይሆም " በማንኛው ነገር አንድ ጊዜ ተስቶት ከአፊ ፍቅር ሲይዘው በቀር ምንም የማያስቀይመውን ልጁን በድሎታል አንገላቶታል " የሱን ሥራ ዌስት ሊን አይዘነጋውም " ያ በልጁ ላይ ያሳየው ጥላቻ
አሁን ደግሞ መልኩን ለውጦ ደስ የማይል ኃይል ሆኖ ተመልሶበታል ሀይሉ
ከሕሊናው ጋር የመረረና የከረረ ጦርነት ገጥሟል "

“እእ...እኔ እኮ አሳድኜ አስገድየው ነበር ! አየሽ ' አን” አለ ጀስቲስ
ሔር ከወንበሩ ላይ ተቀምጦ ላቡን ከግንባሩ እየጠረገ ፥
👍122👏1
“አሁን እኮ ሁሉ ነገር ዐለፈ ...የኔ ሪቻርድ " አለችው ባሏን ወዳድ ደግ
ሚስቱ ዕንባዋ በአራት መዕዘን እየወረደ "

“እኔ ግን እሱ ከዚህ ግድም መጥቶ ቢሆን ኖሮ አልተወውም ነበር " በውነት አሳልፌ ለሞት እሰጠው ነበር !”

“አትዘን ሪቻርድ I ያለፌውን አታስብ ፤ እሱንም አንድ ቀን ከመኻከላችን አከቀምጠነው እናየው ይሆናል " ያን ጊዜ ሁለታችንም እንክሰዋለን „”

“እንዴት አድርገን እናገኘዋለን ? የት እንዳለስ ማን ያውቃል ? ምናልባት
ሞቶ ይሆናል።

“አለ አልሞተም " ጊዜው ሲፈቅድ እናግኘዋለን ሚስተር ካርይል ያለበትን ያውቃል ”

“ግን አሁንም እውነት መሆኑን እጠራጠራለሁ...አን " እውነት ጥፋት
ከሌለበት ለምን እስከ ዛሬ ቀርቦ ነጻነቱን እንዲያግኝ አልሞከረም ከወንጀሉ
ንጹሕ ነው ብለሽ ታስቢያለሽ ?

“ሪቻርድ ... ንጹሕነቱንስ ዐውቃለሁ” አለችው ፈግግ ብላ : “ እኔ ግና በፊት ነበር ያወቅሁት " ሚስተር ካርላይልም ደኅና አድርጎ ያውቃል ”

“በይ እንደዚህ ከሆነስ ደግ ነው " ሚስተር ካርላይልም ካመነበት ጥሩ ነው " ለመሆኑ መኝታውና ሌላውም የሚያስፈልገው ነገር ተዘጋጀለት ?

“ለማን ? አለች ሚ0ዝ ሔር

“ለሪቻርድ እንጂ ደሞ ለማን?”

“ምን ነካህ የኔ ፍቅር ? ነገር እየረሳህ ሔድክሳ ? ዛሬኮ ገና ምስክርነት ነው
የተሰማው ስለዚህ የከፍተኛው ፍርድ ቤት በሱም በነዚያም የሚሰጠው ፍርድ
ሳይታወቅ ሊመጣ አይችልም ”

“እህም እውነትሽ ነው ልጄ ” አለ ጀስቲስ ሔር "

ኢስት ሊን ላይ ግሩም የሆነ የራት ግብዣ ተደርጎ ነበር " የመጨረሻው እንግዳ ከመውጣቱ በፊት ዕኩለ ሌሊት ተደወለ ከዚያ በኋላ ሁለት ሰዓት ያህል ቆይቶ ሁሉ ነገር ጸጥ አለ " ሰው ሁሉ በየመኝታው ገብቶ እንቅልፍ ወሰደው
ጨረቃ ፀሐይ መስላ ወጣች " ብርሃኗ ቤቱን ሁሉ አጥለቀለቀው " የመተላለፊ
ያው ኮሪደሩ ደወል ጮኸ "

ከዚያ ሁሉ ቀድማ በንቃት ዊልሰን አንገቷን በመስኮት ብቅ አድርጋ ወደ ውጭ ተመለከተች „ “ እሳት ነው እንዴ ?” አለችና በጣም ጮኻ ጠየቀች "ዊልሰን እሳት የመፍራት ጠባይ ነበራት " ብዙ ጊዜ እንዲያው ከመሬት ተነሥታ
“እሳት ሸተተኝ እያለች ራሷ ደንግጣ ሌላውን ሁሉ ታስደነግጥ ነበር ።

ከዚያ ዊልስን አንድ ዓመት እንኳን ያልሞላው ልጅ በአንድ እጅዋ አንጠልጥላ
እሳት ! እሳት ! እያለች ትጮህ ጀመር " ከዊልያምና ከሎሲ መኝታ ቤቶች እየገባች ከየአልጋቸው እየጎተተች አወረደቻቸው » ቀጥላም የማዳም ቬንን
መዝጊያ ደበደበችው " ይኸን ሁሉ ስታደርግ “ እሳት ! እሳት ! ተቃጠልን
ነዶድን!” እያለች መጮኹዋን አላቆረጠችም ነበር" ሁሉም እየተደናገጡ የሌሊት ልብሶቻቸውን እንደ ለበሱ ወጡ " ማዳም ቬንም ቤቱ ግማሽ በግማሽ በእሳት የተያያዘ መሰላትና ባጠገቧ ያግኘችውን መደረቢያዋን አንሥታ ወጣች ከሷ ቀጥላ
ጆይስ ብቅ አለች ዊልሰን አሁን ግን ኧረ እሳት ! " እያለች ጩኸቷን ቀጠለች » ሰዎች ሕይወታቸውን ለማዳን ሲሉዐበሚሯሯጡበት ጊዜ በእጃቸው የገባላቸውን ከማንጠልጠል በቀር የሚያስፈልጋቸውንና የማያስፈልጋቸውን የልብስ
ዐይነት ሊመርጡ አይችሉም » ስለዚህ ባርባራም የሌሊት ፒጃማዋን እንደ ለበሰች ወጣች "

ቀጠለና ሚስተር ካርላይል ወጣ " ወደ ደረጃው ቢመለከት ምንም እሳት
አልነበረም " ገና ባይደርስበት ነው አለና በዚያ በኩል ለማምለጥ የተመቸ ሆኖ ሲያገኘው ጊዜ ሮጠና ዐለፈ " በዙሪያው ከበው የነበሩት ሁሉ " አሳት ” እያሉ
በአንድ ድምፅ ይጮኻሉ - ነገር ግን ፍንትው ብላ ወጥታ ከነበረችው ጨረቃ
ብርሃን በቀር ሌላ ብርሃን አልታየም "

“እሳቱ የት አለ ? አለ ሚስተር ካርላይል " " እኔ እስካሁን ምንም አይታየኝም " ማነው መጀመሪያ እሳት ብሎ የጮኸው ?

አሁን ደወል ተደወለ " ሚስተር ካርላይል በአንድ መስኮት በኩል ወደ
ውጭ ተመለከተና “ ማነው? አለ " ማዳም ቬን ሕፃኑን አርኪባልድን አቅፋ ይዛ ነበር።

“እኔ ነኝ ..ጌታዬ ” አለ አንድ ሰው ከውጭ " ሚስተር ካርላይል ሰውየው የሚስተር ጆስቲስ ሔር አሽከር ጃስፐር መሆኑን በድምፁ ዐወቀው "ጌቶች
በድንገት ስለ ታመሙ ለናንተ እንድነግር እሜቴ ልከውኝ ነው » ጌታዬ... በነፍሳቸው ለመድረስ ቶሎ ብትመጡ ይሻላል ”

“ስማ ጃስፐር!” አለው ሚስተር ካርላይል. “ይህ ቤት በእሳት ተያይዟል?”

“ እኔ እንጃ . . . ጌታዬ እሳት የሚል ጩኸት እሰማለሁ ”

ሚስተር ካርላይል መስኮቱን ወግቶ ወደ ዊልስን ዞር በማለት: “ማነው እሳት ነው ያለሽ ? አላት

“ ይኽ ከበር ሆኖ የደወለው ሰውዬ አለችውና አየተንሰቀሰቀች “ ተመስገን
አምላኬ ! ልጆቹን ከመቃጠል አተረፍኳቸው " አለች "

ሚስተር ካርላይል በተፈጠረው ስሕተት በጣም ተበሳጨ » ሚስቱ የሌሊት ልብሷን እንደ ለበሰች ካጠገቡ ሁና ከግር እስከ ራሷ ትንዘፈዘፍ ጀመር እሱ ደግሞ በማንኛውም ምክንያት ቢሆን መደንገጥ በሌለባት ሁኔታ ላይ እንደ ነበረች ያውቅ ነበር » አሷም እንደ ደነገጠች ከሱ ላይ ልጥፍ አለች

ባርባራ ግና ከድንጋጤዋ ስላልተመለሰች እሱን ለቃ ባጠገባቸው የነበረውን
መሰኮት ልትከፍተው ሞከረች ሚስተር ካርይል ብርድ እንዳይመታት ሰግቶ
ይንደረደርና በአንድ እጁ እሷን ይዞ ቀሌላው እጁ መስኮቱን ዘጋው ከዚያ ወደ
መኝታ ቤት ወስዶ ጃስፐር የመጣበትን ነገር አለሳልሶ ነገራት " እሷ ማመን አቃታት በእውነት አባቷ በሕይወት ያለ አልመስላትም " የሆነ ሆኖ ለመሔድ መዘጋጀት ጀመሩ "

በዚህ ጊዜ ዊልያም ትዝ አላትና ባርባራ ወደ ኮሬደሩ ስትሮጥ ብትሔድ ቁሞ
ሲንቀቀጥ አገኘችው ከሷ ሌላ ማንም ያሰበው አልነበረም " “ ወይ ጕድ
ሙቶ ነበር እንጂ ” አለችና ከቆመበት አፈፍ አድርጋ አነሣችው “ ዊልሰን ምነው እንደዚህ ታደርጊያለሽ? የሌሊት ልብሱ ብስብስ ብሎ ረጥቦ በረዶ ሆኗል”
ብላ ጮኸችባት "

ልጁን አቅፋ ከመኝታ ቤቱ ልታደርሰው ዐቅም ስለ አጣች ወደ መኝታዋ ወሰደችው " ዊልሰን በበኩሏ ወቀሳና ተግሣጽ ለመስማት ጊዜ አልነበራትም "በረንዳ ማገር ተደግፋ ከጃስፐር ጋር የቃሳት ጦርነት ጀምራ ነበር

“ እኔ መቸ እሳት ተነሳ ብዬ ነገርኰሽ ? አላት ቆጣ ብሎ

ነግረኽኛል " ምነው መስኮት ከፈትኩና “እሳት ነወይ” ብዬ ብጠይቅህ
አዎን አላልከኝም

"ጃስፐር ነህ ወይ ብለሽ ስትጣሪ አዎን” ኤልኩሽ ሌላ ምን ልል ኖሯል?

እሷ እሳት ነወይ' ስትል 'ጃስፐር ነህ ወይ ያለችው መስሎት 'አዎን እንዳላት ግልጽ ሆነ "

ዊልሰን ልጆቹን አስተኚያቸው " አለ ሚስተር ካርይል ጠበቅ ባለ ትዛዝ … " ጆን..ዝጉን ሠሪገላ ቶሎ ጫነው " አባክሺን ፈጠን በይ " ማዳም ቬን " መደፊት ይህንን ከባድ ልጅ አንሥተሽ መያዝሺን ተይ ጆይስ. . .ምናለ ብትቀቢያትና ብታሳርፊያት ?”

ሚስተሮ ካርይልም ወደ መኝታ ቤቱ ሲመለስ በማዳም ቬን አጠግብ ዐለፈ ክፉኛ ስትንቀጠቀጥ አያት " እስካሁን የሁከቱ ምክንያት አልግባትም ከድንጋጤዋም አልተመለሰችም " ጆይስም ብትሆን ነገሩ እንደሷው አልገባትም"እሷም
ከድንጋጤዋ አልተመለሰችም ከራሷ አስጠግታ ይዛት ቁማ የነበረችውን ሎሲን
ትታ አርኪባልድን ለመቀበል ሔደች " ሚስተር ካርላይል ሚስቱ ዘንድ ገባ ሚስዝ ካርላይል የሌሊት ልብሷን አውልቃ ዊልያም ላይ ጣል አደረገችበትና መብራት አብርታ መልበስ ጀመረች "
👍11👏1
“ የሌሊት ልብሱን በጅህ ንካውማ አርኪባልድ | ይህች ዊልሰን ” ስትል ሌላ ጩኽት ነገሯን አቋረጣትና ሚስተር ካርላይል ዘሎ ወጣ " ባርባራ ተከተለችው " ዊልሰን ሕፃኑን መተላለፊያው ላይ የጣለችው መሰላት " ነገሩ ግን ሌላ ነበር ዊልሰን ሕፃኑን አቅፋ ሉሲን ይዛ በደረጃው ወጥታ ወደ መኝታቸው ከወሰደቻቸው ቆየት ብላ ነበር " ማዳም ቬንም በመግባት ላይ ነበረች » አርኪባልድ ከኮሪደሩ ሥጋጃ ላይ ተጋድሟል " ጆይስ ልጁን አንሥታ ለመውስድ ብድግ ስታደርገው አንድ ነገር ድንገት አስደነገጣትና በቁሟ ለቀቀችው » የበረንዳውን ማገር ተደግፋ ፊቷን በጣር የተያዘች አስመስላ አፋን ከፍታ ዐይኖቿን አፍጥጣ
ቆመች " አርኪባልድ ከወደቀበት ቀስ ብሎ ተነሥቶ በጠንካራ እግሮቹ ቀጥ ብሎ ቆመ።

“ምነው ጆይስ .. .ምን ነካሽ ? ጣረምት ያየሽ ትመስያለሽ ?” አላት
ሚስተር ካርላይል አዬ ጌታዬ ! አለች እየተርበተበተች !“ አይቸማ ነው ! ”

“ሁላችሁም ባንድነት ማበዳችሁ ነው ? አላት በቤቱ ምን ዐይነት ግራ
መጋባት እንደ ወረደበት እየተገረመ „ “ ጣረሞት አየሁ ? ጆይስ

ጆይስ መቆም ያቃታት ይመስል ተንበረከከች - የሚንቀጠቀጡት እጆን
ከደረቷ ላይ አመሳቀለች » በቤቱ ልበኛና ታማኝ በቀላሉ የማትበገር የረጋች
ሠራተኛ ነበረች » ሚስተር ካርላይል ፈዞ በጣም ተገርሞ ተመለከታት "

ጆይስ..ምን ሆነሽ ነው ? ” አላት ወደሷ ጐንበስ ብሎ በርኅሩህ አነጋግሩ "

እግዚኦ ጌታዬ ... ሁላችንም ይቅር በለን !” ብቻ ነበር መልሷ"

ጆይስ . . . ምን ሆንሽ እኮ ነው የምልሽ ?”

“መልስ አልሰጠችውም እየተንቀጠቀጠች ተነሳች " የአርኪባልድን እጅ ይዛ
ቀስ እያለች ወደ ፎቅ ወጣች

“ ምን አግኝቷት ይሆን ?” አለች ባርባራ በዐይኗ እየተክታተለቻት "
ጣረሞት ስትል ምን ማለቷ ነው ?” አለች በጆሮው "

" የጣረሞት ታሪክ ስታነብ ቆይታ ይሆናል” አለ ሚስተር ካርላይል »

“የዊልሰን መንቀዥቀዥ እኮ ቤቱን አተረማመሰው ቶሎ በይ ባርባራ እንሒድ!”....

💫ይቀጥላል💫
👍15👎1
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰባ_አንድ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

ፀደይ ዐለፈ " በጋ ተተካ " እሱም ያልፋል : አሁን ሞቃቶቹ የሰኔ ቀኖች
ገብተዋልና መውጫቸውም ይደርሳል " ሚስተር ካርላይል ከተመረጠበት ከሚያዚያ ወር ጀምሮ ወሮች ሲለዋወጡ ምን ክሥተቶች ታይተውባቸዋል ?

የሚስተር ሔር በሽታ ከመሰለል አደረሰው " ሰዎች ልጅን ያለአግባብ
ሲበድሉ ኖረው መሳሳታቸውን በሚገነዘበቡት ጊዜ ' ' ተሳስቼ ኖሯል በማለት ብቻ የጃቸውን ሳያገኙ ይቀራሉ ማለት ዘበት ነው " ይህ ሁኔታ በሚስ ጀስቲስ ሔር
ላይም ታይቷል ። ከበሽታው በጎ እየሆነ ሔዷል " ነገር ግን የበፊቱ ጀስቲስ ሄር መሆን አይችልም : ጃስፐር የጌታውን መታመም ሊነግር ኢስት ሊን ሔዶ በነበረ ጊዜ የተፈጠረው የእሳት ድንጋጤም ከዊልያምና ከጆይስ በቀር ማንንም አልጐዳም " ዊልያምን ብርድ መታውና የሳንባ በሽታውን አባባሰበት ጆይስ ከዚያ ወዲህ ፍራት አደረባት " በውኗ እያለች በሕልም ያለች ትመስላለች " ድንገት ሲናገሯት ትበረግጋለች አንዳንድ ጊዜ አንድ ሰዓት
ሙሉ ሐሳቧ ይዟት ጭልጥ ይላል።

ሚስተር ካርላይልና ሚስቱ የሚስተር ሔር በሽታ ለክፉ እንደማይሰጠውዐእንዴረጋገጡ ወዲያውም ወደ ለንደን ሔዱ : ዊልያም አባቱ ከሱ እንዲለየው ስላልፈለገና የለንደን ሐኪሞች እርዳታ ይጠቅመው ይሆናል በማሉት አብሮ ሄዷል " ጆይስ ከሌሎች ሠራተኞች ጋር ተከትላ ሔዳለች "

ለንደን ሲደርሱ የስር ፍራንሲዝ ሌቪሰን መያዝ አፍላ ወሬ ሆኖ አገኙት "
ነገሩ ለለንደን ስዎች ሊገባቸው አልቻለም : ብዙ የማይመስሉና የማይሆኑ ነገሮች ሲወሩ ዜናው ለዘጠኝ ቀኖች ያህል ብርቅና ድንቅ ሆኖ ሰነበተ እነሱ ለንደን የገቡ ዕለት ማታ አንዲት ልጅ እግር ቆንጆ ሴት፡ ንገሩልኝ ብላ እነሱ ከነበሩበት ክፍል ገባች ስሟን መግለጽ ባትፈልግም ሚስተር ካርላይል ሲያያት
የመጀመሪያ ሚስቱ ባልንጀራ የነበረችው የብላንሽ ሻሎነር መልክ ትዝ አለው እሷ ግን ብላንሽ አልነበረችም "

እንግዳይቱ ባርኔጣውን በጁ ይዞ ሊወጣ ቁሞ ያገኘችውን ሚስተር ካርላይልን እያየች ' “ በአጉል ሰዓት በማስቸገሬ ይቅርታ ያድርጉልኝ " የመጣሁት አንድ የሰው ልጅ ከሌላው ለማግኘት የሚፈልገውን እርዳታ ለመለመን ነው " እኔ
አመቤት ሌቪሰን ነኝ ” አለችው"

ባርባራ ፊቷ ደም መስለ ። ሚስተር ካርላይል እንግዳይቱን በአክብሮት
ወንበር ላይ አስቀምጦ እሱ ቈሞ ዝም አለ ። እሷም ትንሽ ተቀምጣ ከመጨነቋ የተነሳ ተመልሳ ብድግ አለች

“ኣዎንታ እኔ ያን ሰው ባሌ ለማለት የተገደድኩት እመቤት ሌሺሰን ነኝ " ክፋቱን በፊትም ዐውቀዋለሁ አሁን ደግሞ ወንጀለኛ ሆነ ይባላል ትክክለኛነቱን ግን የሚያረጋግጥልኝ አጣሁ " ሎርድ ማውንት እስቨርን ዘንድ ሑጄ ብጠይቃቸውም ሊነግሩኝ አልፈቀዱም " ስለዚህ ሚስተር ካርላይል ዛሬ ለንደን ይገባሉ ሲባል ስምቸ ለመጠየቅ መጣሀ "
ስትናገር ሰውነቷ እየተርገፈገጸ ድምጿ እየተቆራረጠ ስለ ነበር ከውስጧ የሚገነፍልባት የስሜት ግፊት ይታወቅባት ነበር "

“ ይህ ሰው ሁለታችንንም በድሎናል ...ሚስተር ካርላይል ሰውየው እንዲበድለኝ ያደረግሁ እኔ በገዛ እጄ ነው እርስዎ ግን አይደሉም « የሱ በደል
የደረሰባት እኅቴና አሁን ዘጠና ዓመት የሚጠጋቸው አያቱ ሚስዝ ሌቪሰን አስ
ጠንቅቀውኝ ነበር ከማግባቴ አንድ ቀን ቀደም ብለው አያቱ እኔ ድረስ ለዚ
ሲሉ መጥተው ፍራንሲዝ ሌቪስን ባገባ ዕድሜ ልኬን ሳለቅስ አንደምኖር አሁንም የገባሁትን ቃል ለማጠፍ በቂ ጊዜ እንደ ነበረኝ ሲነግሩኝ አልተቀበልኳቸውም " ጊዜ ነበረኝ ፍላጎት ግን አልነበረኝም " በግብዝነት ' በሞኝነት በተለይም ለመካር እኅቴ እልክ ስል አገባሁት የሱን ስም የሚወርስ ልጅም ወልጃለሁ ... ይፈርድበት ይሆን ሚስተር ካርላይል ?”

እስከ አሁን በደንብ የተረጋገጠበት ነገር የለም” አላት ሁኔታዋ እያሳዘነው

“አሁን ከሱ የምፋታበትን መንገድ ባገኘሁ " አለች ራሷን መቈጣጠር እንደ ተሳናት በግልጽ እየታየባት “ የልጄን ስም መለወጥ ብችል እንግዲህ ይህን የገባሁበትን ዘንቅ ለማረም የቀረኝ ዕድል ይኖር ይሆን ?”

ምንም አልነበራትም ። ሚስተር ካርላይልም መላ መናገር አልሞከረም "
ጥቂት የማስተዛዘኛ ቃላት ተናግሮ ሊወጣ ሲል ዐለፈችና ከፊቱ ቆመች

ለዚህ መፍትሔ ሳይነግሩኝ አይውጡብኝ ። እርስዎን አምኘ መልስ እንዶገማኝ ተስፋ አድርጌ ነው የመጣሁት

“ከባድ ቀጠሮ አለብኝ " ባይኖረኝም በራሴም ሆነ ባንቺ ምክንያት መልስ
ልስጥሽ አልፈቅድም ነበር " ነገርሽን እንዳቃለልኩብሽ አድርገሽ አትይው
እመቤት ሌቪሰን ስለ ሰውዬው ግን ላንቺ እንኳን ስናገር ስሙ ራሱ ከንፈሮቼን
ያቆስልብኛል

እርስዎ የሚናገሩት እያንዳንዱ የጥላቻ ቃል ' ቃሌ ነው የርሶዎን የንቀት አባባል ሁሉ ተቀብዬ አስተጋባለሁ ”

ባርባራ ዘገነናት ምንም ቢሆን እኮ ባልሽ ነው ! " አለቻት "ባርባራ

“ባሌ ! የበደለኝን በደልሳ ዐውቀሺዋል ? እሱ ራሱ ምን እንደ ነበርና ምን
እንዳደረገ እያወቀ ለምን ሚስት እንድሆን አሳሳተኝ ? አንቺም እንደኔ ሚስትም
እናትም ስለሆንሽ
እንደገና...ሚስዝ ካርላይል በደሌ ሊገባሽና ልታዝኝልኝ ይገባል" እነዚህ መጥፎ ሰዎች ለምን ያገባሉ ? ወንጀሉ ሕሊናውን እያኘከው
እኔን ለማግባት ሰብኮ ሰብኮ ያሳሳተኝ! ያለፈው ኃጢአቱ አነሰው የማይቴረም ከባድ ግፍ ውሎብኛል " በልጄም ላይ ተፍቆ የማይጣል አሳፋሪ ውርደት ጥሎ
በታል ”

“ ቢሆንም ባልሽ ነው
አለቻት ባርባራ "

“ እታሎኝ እኮ ነሙ ባሌ የሆነው " ስለዚህ በአደባባይ ብጠላው የሚያግደኝ የሞራል ግዴታ የለብኝም " በኔና በልጁ ይህ ነው የማይባል ጥፋትና ክፋት አድርሶብናል ኧረ ለመሆኑ” አለች ወደ ሚስተር ካርላይል ዞር ብላ' “ከእርስዎ ጋር ለመወዳደር ዌስት ሊን ሲመጣ እንዴት አስቻለዎትና ዝም አሉት

“እሱን ልነግርሽ አልችልም » ለራሴም ብዙ ጊዜ ሳስበ ገርሞኛል” አላትና በትሕትና አነጋግሮ ከሚስቱ ጋር ትቷት ሔደ " ሁለቱ ሴቶች ብቻቸውን ሲቀሩ' ባርባራ የሚስዝ ሌቪሰንን ጥያቄ ባጠቃላይ መልኩ ባጭሩ ገለጸችላት

“አንቺና ሚስተር ካርላይል በጥፋተኛነቱ አምናችሁበታል ? አለቻት "
“ አዎን ” ያንቺ የመጀመሪያ ሚስቱ ሳቤላ ቬን ዕብድ ነበረች ?
"ዕብድ ? አለች ባርባራ በመገረም "

' አዎን ' ሚስተር ካርላይልን በሱ መለወጧ!እሱን ለዚያኛው መለወጧ
ዕብዶት እንጂ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል ? አንዲት ሴት ከቪሰን ከድታ ሚስተር ካርላይልን አፍቅራ ብትሔድ ሊገባኝ ይችላል ? አሁን ያንቺን ባል ሳየው በተለይ እሱን ጥሎ ወደ ሌቪሰን የሚሔድበት ምክንያት ሊገባኝ አይችልም”
አለቻት » ከዚያ ጥቂት ተነጋግረው አሊስ ሌቪሰን ወጥታ ሔደች "

በርባራ ' ሦስት ሳምንት ያህል ለንደን ቆይታ ለጤንነቷ ለምቾቷ ተብሎ ወደ ኢስት ሊን ተመለሰች ሚስተር ካርላይልም ለንደን ከቆየ በኋላ በሐምሌ ጠቅልሎ ሲመጣ አንድ ወር የሞላት ሴት ልጅ ተወልዳ ቆየችው :

የዊልያም ሁኔታ አሽቆልቁሎ ሔደ " የዶክተር ማርቲን አባባል የለንደኑ
ሐኪምም አረጋግጦ ደገመው " ስለዚህ መጨረሻው ብዙ እንደማይቆይ ግልጽ
እየሆነ ሔደ"
👍16
አንድ ሌላ ሰውም እየከሰመ ይሔድ ነበር ሳቤላ የተሸከመችው የሥቃይ መስቀል ከመጠን ያለፈ ሆኖ ስለ ከበዳት ቁልቁል እየሰጠመችና በሥቃይ ጭነት እየደቀቀች ትሔድ ጀመር። ወደ ኢስት ሊን ልትመለስ ስትል እንዳሰበችው ያን ክብደት
በትግሥት ለመሸከም ብትጥር ኖሮ ነገሩ ሊለወጥ ይችል ነበር " እሷ ግን አስባ
ለራሷ የገባችውን ቃል ማክበር አልቻለችም " የሽክሟን ክብደት በዝምታ አልተቀበለችውም " ታገለችው !ዐመፀችበት " ይህም ከዐቅም በላይ የሆነ ከባድ ትግል ሕይወትን ያህል ዋጋ የሚጠይቅ ሆኖ ተገኘ" ወደ ኢስት ሊን ከተመለስች ጀምሮ በየሰዓቱ በየቀኑ ልዩ ልዩ ሰበቦች በማየትና በመስማት ልቧን እያነጠረ አንጀቷን እያሳረረ " ፊቷን አየቀያየረ ሲያስጨንቃትና ሲያንገበግባት ይውል
የነበረው ስሜት ሚስተርና ሚስዝ ካርላይል ወደ ለንደን ሲሔዱ ጋብ ብሎላት
ነበር ከዚያ በኋላ ደግሞ ከፊተኛው ስሜቷ ጋር የሚፃረር አዲስ ስሜት አደረባት መቁረጫ የሌለው የአእምሮ መትከንከን ስሜትና ትንቅንቅ ሁሉ ለቆ በቦታው ተስፋ መቁረጥና ደንታ ቢስነት ተተካበት " ስሜቷ ተግ እያለ ብስጭትጭት ያደርጋት የነበረው ቀረና በሚያስደነግጥ ፍጥነት መስጠም ጀመረች የሚያሠጋ በሺታ አልታየባትም እሷ ግን ከቀን ወደ ቀን እየመነመነችና እየሰለስለች ሔደች ይሁንና አዲሱን የአካልና የመንፈስ ለውጥ የተነገነዘበ አልነበረም " አንዳንድ ጊዜ ዊልያም ዘንድ ብቅ እያለች ጥቂት ጊዜ ብታሳልፍም ሎሲን የማስተማር ተግባሯን በሚገባ ትፈጽም ነበር "

አንድ ቀን ፀሐዩ እንደ እሳት በሚቃጥልበት በሐምሌ ውስጥ አፊ ሆሊጆን ከምን ጊዜም የበለጠ ሽክ ብላ ለብሳ በመንግዱ እየተሽከረhረች ትጓዛለች » አፊ በተለይ ከምርመራው በኋላ በብዙ ሰው ዘንድ
ከበፊቱ የበለጠ ተንቃ ነበር
ሚስዝ ላቲመር እንኳን በሷ ላይ የነበራትን እምነት ለወጠች " የአንድ ወር የማስጠንቀቂያ ጊዜ ስጥታ አሰናበተቻት "

በያቅጣጫው ዐይንሽ
ላፈር በተባለችበት ጊዜ ሚስተር ጂፊን ፊት ግን ደፍሮ ስለሷ ክፉ የሚያነሳ ሰው ቢግኝ እንኳን ምንም
ቢደረግ አይሰማውም አይቀበለውም " ዌስት ሊኖችን ቅጣፊዎች ለራሷ መልአክ ናት” ይላቸው ነበር

በመንገዱ እየተንሳፈፈች በሚስተር ጂፊን ቤት አጠገብ ስታልፍ እሷን ለመቀበል ይደረግ የነበረውን የቤት እድሳት ተመልክታ ደስ አላት " ሁልጊዜ በዚያ በኩል ባለፈች ቁጥር አንዳንድ ነገር እንዲሟላ ስትጠቁመው በደስታ የሚፍነከነከው የወደፊቱ ሙሽራ ወዲያው ይፈጽማል ባቡር በመጣ ቁጥር ልዩ ልዩ የቤት ዕቃዎች በጥቅል በጥቅል እየሆኑ ይመጡለታል “

እዕድገቱ እኮ በደንብ ቀጥሏል.. ሚስ አፊ በዚህ ሳምንት ያልቃል የሳሎኑ ጌጥ ብታይው መቸም ሌላ ነው " እንግባና እይው እስቲ ” አላት

"እንዴ ! ከአንተ ጋር ልገባ ? ዌስት ሊን ምን ይለናል ?”

“ የሚከፋሽ ከሆነስ ይቅር :ይቅርታ አድርጊልኝ ሚስ አፊ

“ እንዲያው በፈጠረህ ይህን ነጭ ሽርጥህን ብትጥለው ምነው ?

“ ይህ አስቸጋሪ ነገር ነው " የጠየቅሺኝን ሁሉ እንደምፈጽምልሽ ታኸ
ዉቂያለሽ » አሁን ይህን ባወልቀው ግን ከሥሩ ያለው ልብሴ እንዴት እንደሚበላሽ
ጠፋሽ ? የሰደርያየን ነገርማ ተይው አየሽ ቅቤ ከመያዣው እየከፈልኩ
ስሸጥ የዓሣማውን ሥጋ ስቆርጥ ዓይቡን ስለካ የዓሣማው ሥጋ በበርሜል
የተነከረበት ሆምጣጤ ሲረጨኝ ሌላም ሌላም ብዙ አስቸጋሪ ሥራዎች አሉ "
ስለዚህ ሚስ አፊ ሽርጤን ካወለቅሁ በየሳምንቱ አዲስ ልብስ ብለብስም ንጹሕ
ልሆን አልችልም ” ብሎ ገለጸላትና የንግግራቸውን ርዕስ ለመለወጥ ሲል
ብቻ ነገ ጧት ወደ ሊንበራ ትሔጃለሽ ?” አላት ።

“ የታወቀ አይደል ብዙዎቻችን እንሔዳለን ። ፍርዱ የሚጀመረው በሦስት ሰዓት ነው " ስለ ሪቻርድ ሔር የሚወራውን ሰምተሃል ?”

“የለም ” አለ ጃፊን “ ምን ወሬ ነው እሱ ?”

" እሱም ለፍርድ ሊቀርብ ነው እያለ ዌስት ሊን ያወራል

“ ለመሆኑ አለ እንዴ ? አለ ሚስተር ጂፊን "

“እኔ ስለሱ ምንም አላውቅም " በቅርቡ ሙቷል እየተባለ ሲወራ ታውቃለህ ጥፋተኛው እሱ ወይም ሌቪሰን ቢሆኑ ግድ የለኝም " ምንጊዜም አነሱ
እንደማይረቡ ዐውቃቸዋለሁ " እነሱን ላስጠጋቸው ቀርቶ በረጂም አንጨት
እንኳን አልነካቸውም
አለችው

ከጂፊን ተሰነባብታ ጥቂት እንደ ሔዶች ከሚስተር ካርላይል ጋር ተገናናኙ "

“ ታዲያስ አፊ . . .ልታገቢ ነው አሉ ”አላት "

ጀፊን ያስባል እኔ ግን ምናልባት ሐሳቤን እለውጥ ይሆናል . ገና እርግጠኛ አደለሁም እርሱም ደሞ እንደኔ ያለች ሴት የተፈጠረች አይመለውም
ብርና ወርቅ የምበላ ብሆን ያቀርብልኝ ነበር " ሰውዬው እንደ ነዱት ነው „

“ላንቺ ነው እንደ ነዳሺው የሚሆንልሽ እንጂ እሱ በኔ አስተያየት ሥነ ሥርዓት ያለውና የተወደደ ሰው ነው

“እኔ ከመጀመሪያ ክብር ያለው ከፍ ያለ ሰው እንጂ ከሱቅ ተቀምጦ ሲቸረችር የሚውል ባል ለማግባት ሐሳብ አልነበረኝም " እንዲያውም . . ነጭ ሽርጥ አስሮ የሚውል ባል።

"ይገርማል ! አላት ሚስተር ካርላይል ፊቱን ቁጥር አድርጎ

" ቢሆንም ከፍቶም አይከፋ ” አለችው መልሳ . “ ቤቱን ዘመናዊ አድርጎ እያሠራ ነው " ሁለት ጥሩ ጥሩ ሠራተኞች እቀጥርና እኔ ቁጭ ብዬ ልብስ
መቀየር ' ከቤተ መጻሕፍት ማኅበርተኛ ሁኜ መመዝግብ "ገንዘብ እንደሆነ ሞልቶታል
አለች አፊ።

“ገንዘቡን እንዳትጨርሽበት ተጠንቀቂ . : .አፊ ” አላት

“ለዚያ ግድ የለም እጠነቀቅበታለሁ .....

💫ይቀጥላል💫
👍151🥰1
😘 #ቃል 😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሀያ ሶስት (23)

«ደግ ። ቢያንስ ስሙ ማጠሩንና መጥበቡን ለመለካት ይረዳኛል ፤ ባደባባይ ከመልበሴ በፊት » አለች ። ሁለቱም ደስ ብሏቸዋል ። ሁለቱም የሆነ የመደባበቅ ስሜት ይታይባቸዋል ። ሁለቱም»
ሂሣባቸውን ከፍለው ከሆቴሉ ወጡ። መኪናው ዘንድ ሲደርሱ ፍሬድ አይቷቸው ሲጨፍር ተመለከቱት ። ፍሬድ በእሁድ እሁድ ሽርሽር ላይ ተካፋይ ነው። ሁሌም በምሳ ሰዓት እመኪናው ውስጥ ይጠብቃቸዋል ። ሽርሽር ሲሄዱ ግን አብሯቸው ይሄዳል። የመኪናው በር ተከፍቶለት ከወጣና የውሻ ሰላምታውን ካቀረበላቸው በኋላ ተከተላቸው ። «እንዴት ነው ፤ ደከመሽ!? » አለ ፒተር ፤ ለአንድ ሰዓት ያህል በእግራቸው ከተጓዙ በኋላ ። «እንመለስ? ወይስ እንቀጥል?»
«እንመለስ ማለቱ ትንሽ ቢያሳፍርም መመለሱ አይከፋም» አለች። «ምን አሳፈረሽ ሜሪ? እስከ አመት ድረስ እኔና አንች የሩጫ ውድድር ብንጋጠም ጥለሺኝ እንደምትሄጂ እያወኩት» አለ ፒተር፡፡ ትቀድሚኛለሽ ስላላትም፤ በአዲስ ስሟ ሲጠራት ዘላለም በዚያ ስም ሲጠራት የኖረ ያህል ስለጠራትም ተገርማ ሳቀች። «የሩጫውን ውድድር ተቀብያለሁ» አለች። «እትጠራጠሪ ታሸነፊኛለሽ። ከኔ የምትሻይበት ነገር አለሻ»
‹‹ምን ? »
«ወጣትነት ፤ ጥንካሬ»
«አንተስ? አንተም ገና ወጣት ነህ» ይህን ያለችው ከልቧ ነበረና ራሱን በአሉታ እየነቀነቀ ሳቅባት። «እንዲህ አፅናኚኝ እንጂ። ምን ጊዜም ይህን አይንሽን አይቀይርብኝ፤ የኔዋ ተወዳጅ» አለ ። እንዲህ ብሎ አይኑን እወዲያ ላይ ተከለ ። እንዲያ ወዲያ ወዲያ ሲያይ በፊቱ ላይ አንድ አይነት የትካዜ ጥላ ያንዣብበት ነበር ። የትካዜውን ጥላ ናንሲ ያየችው እንደ ውልብታ ብቻ ቢሆንም አይታዋለች ። የተከዘበት ምክንያቱም ገብቷታል ። የዕድሜው ጉዳይ ነበር ። ምንም እንኳን በመካከላቸው ያለውን የ24 ዓመት የእድሜ ልዩነት እንዳለ ባትቆጥረው ልዩነቱ ግን እንዳለ ገባት። ይግባት እንጂ አልተከፋችም። እንዲያውም የልዩነቱን መኖር የምትወደው ይመስላታል። ይህንንም ደጋግማ ለፒተር ነግራዋለች። አንዳንድ ቀን ይቀበላትና ደስ ይለዋል ። አንዳንድ ቀን ግን ይከፋዋል ። እንደተነገረበት እለት የባህርይ ይዞታው ይለዋወጣል ። ይህ ደግሞ ለፒተር አዲስ አይደለም ። ከዚህ በፊትም አጋጥሞታል ። ስንት ጊዜ ነው አስር ወይም ሃያ ዓመት ያህል እድሜው ዝቅ ቢል የተመኘው ?

«ናንሲ» አለ ፒተር አዲሱን ስሟን ፈፅሞ ዘንግቶ ።
«አቤት»
«ናንሲ. . . እስቲ ንገሪኝ. . . ማለት. . . አሁንም. . . ማለት እስከ ዛሬ ታስታውሺዋለሽ? . . . ማለት ይናፍቅሻል ?» እፊቱ ላይ የተሳለውን ጭንቀትና ስቃይ ስታይ አዘነችለት። አንገቱን እቅፍ አድርጋ በአሉታ ልትመልስለት ፈለገች፣ ለማፅናናት ። ግን ደግሞ ከበዳት ። ለፒተር ውሸት መንገሩ ከማንኛውም ነገር የከበደ ሆኖ ታያት ። «አዎ አንዳንዴ... ሁልጊዜ ግን አይደለም» አለች፡፡ «አሁንም ፍቅሩ አልለቀቀሽም?»

ቀና ብላ አየችው፤ ከመመለሷ በፊት ። አይኑን ትኩር ብላ ተመለከተች። ከዚያም እንዲህ ስትል ጥያቄውን መለሰችለት ። «እኔ እንጃ ። በቅጡ እማውቀው ነገር የለም. . .ግን ምን መሰለህ… አንዳንዴ ሳስበው ሁሉ ነገር ህልም መስሎ ይታየኛል። ለምን ብትለኝ፤ ዛሬ እሱም እሱ አይደለ ። እኔም እኔ አይደለሁ። ተለውጠናል ። አደጋው እሁለታችንም ላይ ምልክት ጥሎ ያለፈ ይመስለኛል ። ማለት እሱም ጠባሳ ይኖርበት ይሆናል ። ምናልባት እኮ አየህ ያ ጠባሳ ያጠፋውን ይሆናል እወደው የነበረው፡፡ እሱም እኔ ላይ ይወደው የነበረውን ነገር ሊያጣ ይችላል ። ያ የሚወደው ነገር ተሰርዞ ይሆናል ። እና ብንገናኝ ፤ ብንተያይ የሚያስተሳስረን የነበረውን ነገር ልናጣው እንችል ይሆናል ። ስለዚህ አሁንም ማይክልን አፈቅረዋለሁ ማለት ይከብደኛል ። ህልም ነው። ያለፈ ጊዜ ትዝታ የዛሬ እውነት ሊሆን አይችልም ። ይህን ሳስብ ምነው አንዴ በተገናኘንና ባየሁት ፤ በወጣልኝ እላለሁ ። አሁን አሁን ግን ገብቶኛል ። ላገኘው... . ፤ ላየው እንደማልችል ገብቶኛል» አለች ቃላቱን ለመናገር እየተቸገረች ።
ዝምታ…..

«ህልም ነው» አለች ቆይታ «እና ወዳሁኑ ፤ህልሙን ራሱን ላለማሰብ ቆርጫለሁ»
«ያማ ... እንዲህ በቀላሉ መቼ ይቻላል» አለ ፒተር። ይህን ሲናገር አይኖቹ በሀዘን ተሰብረው ነበር ። የነገረችው ሁሉ እንደገባው ስለተረዳች ገረማት። ምናልባት እሱም የኔ አይነት ችግር ደርሶበት ነበር ይሆን? መሆን አለበት ። ያ ባይሆን የምነግረው ነገር እንዲህ በቀላሉ ሊገባው፤ ይህን ያህል ሊሰማው አይችልም ነበር፡፡ አለች በሀሳቧ እና ፣ «ፒተር» አለች ። «ፒተር ለምንድነው ሚስት ሳታገባ የኖርከው?» ጎን ለጎን በፀጥታ ጉዟቸውን ቀጠሉ ። ፍሬድ ኋላ ኃላቸው ቱስ ቱስ ይላል ። ፈፅመው ዘንግተውታል ። ፀጥታው ሲገን ጊዜ «ወይስ መጠየቅ አልነበረብኝም ? » አለች ናንሲ ። «መጠየቅሽ ምንም ጥፋት የለበትም ። መልሱን ግን በቅጡ እማውቀው አይመስለኝም» ሲል መለሰላት። ቀጥሎም ‹‹ምክንያቱም ብዙ ነገር አለ» አለ ። «ምናልባት ራሴን በጣም ስለምወድ ሊሆን ይችላል ። አየሽ ሚስት አግብቼ ለሷ ማሰብ ይከብደኝ ይሆናል። ምናልባትም ስራዬን ስለምወድ ይሆናል። ምርምሬን ለማካሄድ ስፈልግ ሴት መሰናክል ትሆናለች ብዬ በማሰብ ማለቴ ነው፡፡ አይታወቅም ። ምናልባትም ረግቼ መቀመጥ የምችል ሰው ስላልሆንኩ . . .ወይም ያልኩሽ ሁሉ ባንድነት ሆነው...»

«የተባለው ሁሉ ግን ለኔ እውነት ሊመስለኝ አልቻለም» አለች ናንሲ በአቅርቦት እያየችውና የነቅቸብሀለሁ… ዋሽትሀል ፈገግታ እያሳየችው። «ልክ ነሽ። የነገርኩሽ ሁሉ የምገምተው ነው እንጂ እኔም ራሴ እማምንበት አይደለም ። ያም ሆኖ ግን አንዳንድ እውነትም አይጠፋበትም » ይህን ብሎ ለረጂም ጊዜ ቆየና በረጅሙ ተንፍሶ የሚከተለውን አጫወታት ።

«ሌሎች ምክንያቶችም አሉ» አለና እንደገና በረጂሙ ተነፈሰ «አንደኛው ምክንያት ፍቅር ነው ። እስራ ሁለት ዓመት የወሰደ ፍቅር ። የወደድኳትን ሴት የተዋወቅኋት ሐኪም ቤት በታካሚነት ገብታ ነው ። እንዳየኋት ልቤ ትርትር እለ ። ግን ልቤን ተው አልኩት ። ተው እንጂ እንዲህ ዝም ብሎ መፍሰስ ምን ይባላል ? አልኩት ። እሷ ደግሞ ይህ መሆኑን ያወቀችው በኋላ ነው። በጣም ዘግይቶ ።››

«ሕክምናዋን ከጨረሰች በኋላ ይህ ነው የማትይው አጋጣሚ እየተፈጠረ ዘወትር እንገናኝ ጀመር ። ፓርቲ ተጠርቼ ስሄድ ፓርቲው ላይ እሷም አለች። ምሳ ግብዣ እዚያም አንኛታለሁ። ምን ይኽ ብቻ አንዳንድ የስራ ጉዳይም ያገጣጥመን ጀመር እንጂ።››

«እሷ እንኳ ሕኪም አይደለችም ። ግን ባሏ ሐኪም ነው ያልነገርኩሽ ነገር ሴትዮዋ እኮ ባለትዳር ነበረች። በዚህ ሁኔታ ወደ ፈትናም አታግባኝ እያልኩ አንድ አመት ሙሉ ከስሜቴ ጋር ታገልኩ። ከዚያ በኋላ ግን አልሆነልኝም።ተሸነፍኩ ። ስሜቴን ነገርኳት ። ምን ልበልሽ፡፡ ሆነ… ሁለታችንም በፍቅር ቀንበር ተጠመድን ። እይከፋኝም ። ሳስበው ለምን ሆነ አልልም ። በጣም ያሚጥም ፍቅር መስረትን በጣም የሚጣፍጥ ጊዜ እሳለፍን ።
👍14😁21
«በየቀኑ ስለመኮብለል፤ ስለመጋባት፤ ልጅ ስለመውለድ እናወራ ነበር ። ፕላን እናወጣ ነበር። እንዘጋጃለን። ግን አንዱም አይፈጸምም። እሷም ከባሏ ጋር ፣ እኔም ብቻዬን እንዳለን ፍቅራችንን እየኮመኮምን መኖር ቀጠልን። አስራ ሁለት ዓመት ሙሉ አንድ ነገር አልተለወጠም። ዛሬ ዛሬ ያን ያህል ዓመት በዚያ ሁኔታ እንዴት አድርገን ልንቆይ እንደቻልን ሳስበው ይገርመኛል፡፡ ሆኖም ኑሮ የራሱ መንገድ ይኖረዋል ። ኑሮ በዘልማድ በራሱ መንገድ ሲቀጥል፤ ሲጓዝ ፤ ሲቀጥል ይኖራል ። አንድ ቀን ከዘልማድ እንቅልፍሽ ብንን ብለሽ ስታስቢው ለካ አስር ዓመት ቡን ብሏል፡። ወይም አስራ አንድ ዓመት ወይም እስራ ሁለት ።

«በመጀመሪያ ጋብቻውን ሰርዘን ምክንያት ፈጠርንለት። ባሏን መፍታት እንደሌለባት ተስማማን ። ምክንያቱም ባሏን ከፈታች ብዙ ችግር አለ ። አንደኛ ነገር ፍቅሯ ለኔ ይሁን እንጂ ባሏ እንዲጎዳ፤ እንዲጎሳቆል አልፈለግንም ። ሁለተኛ ለእኔም ቢሆን የሰው ሚስት አስኮብልሎ አገባ ሲባል ለስሜ ጥሩ አይደለም ። ሶስትኛ የሷን ቤተሰቦችም ክብር ሊነካ ይችላል… ይህ ሁሉ ተብሎ ጋብቻው ተሰረዘ ። ብቻ ከጀመርነው መንገድ ውጪ አንድ እቅድ ከመጣ ምክንያት አይጠፋለትም ። ሲመስለኝ ሁለታችንም ፣ በልባችን ፍቅራችንን ከጀመርንበት መንገድ ውጭ ልናየው አንፈልግም ነበር ይመስለኛል። እርግጠኛውን ነገር በርግጥ አላውቀው፡፡››

ስለዚህ ጉዳይ ነግሯት አያውቅም ነበርና ናንሲ ሁለመናዋ ጀሮ ሆኖ ታዳምጠው ነበር፡፡ እሱም ይህን የሚናገረው አይኑን አድማስ ላይ ተክሎ ፤መንፈሱ በትዝታ ጎዳና ርቆ ሄዶ ቅዝዝ ብሎ ነበር፡፡

«እሁን ለምን ትለያያችሁ?» አለች ናንሲ ። ጥያቄውን እንደጠየቀች አልተለያዩ እንደሆነስ? የሚል ሀሳብ ብልጭ አለባት። ይህ ሐሳብ ብልጭ ሲል አፈረች፡፡ በሰው ነገር እየገባሁ ይሆን እንዴ? አለች፤ በሀሳቧ ምኑ ይታወቃል። ስለፒተር የማታውቃቸው በርከት ያሉ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ ። ያ ብቻ ሳይሆን መጠየቅ የማይገባት ነገርም ሊኖር ይችል ይሆናል ። ከዚህ በፊት እንዲሀ ያለ ነገር እስባ አታውቅም ነበረና ከላይ ለምን ተለያያችሁ ብላ ጠየቀች።

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍21
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰባ_ሁለት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


የሊንበረ የችሎት አዳራሽ በጣም ሰፊ ባይሆን ኖሮ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን
በጆርጅ ሆሊጆን ማድያ የተከሰሰበትን ፍርድ ለመስማት ከመጣው ብዙ ሕዝብ አብዛኛው ቦታ ባለ ማግኘት ሳይሰማ ይቀር ነበር "

ጕዳዩ ከተከሳሹ ማዕረግ ጋር በማነጻጸር ተከሳሹ ቀደም ሲል ከነበረው ታሪክና በተለይም እመቤት ሳቤላ ካርላይልን ከሚመለከተው ሥራው ጋር በማገናዘብ
በሪቻርድ ሔር የተላለፈው ፍርድ ወንጀሉ የተፈጸመበት ዘመን መርዘም አፊ የተጫወተችው ሚና የኦትዌይ ቤቴልን ትክክለኛ ድርጊት ለማወቅ ከፍተኛ ጕጕት ነበረ የድርጊቱን ዝርዝር ትክከለኛ ገጽታ የመረዳት ፍላጐት ሁሉ
የሕዝቡን ጉጕት አራገበው » ከጠቅላላው ሕዝብ ውስጥ የሚስተር ካርላይል :
የሔር ቤተሰቦችና ወዳጆች : የሻሎነር የእስረኛው ቤተሰቦችና ወዳጆች ጭምር ነበሩ ኮሎኔል ቤቴልና ጀስቲስ ሔር ግልጽ ከሆነ ቦታ ላይ ተቀምጠው ነበር ።

ዳኞቹ ከሦስት ስዓት ጥቂት ቆይተው ተሠየሙ ኦትዌይ ቤቴል የዐቃቤ ሕግ
ምስክር እንዲሆን ተደረገ የሚል ዳኞቹ ገና ሳይሠየሙ ወሬው ካፍ ወደ አፍ ሲሸጋግር ቆይቶ ነበር " የዚህንም ወሬ ትክክለኛነት ለመስማት የጓጉ ሁሉ አንገታቸውን እያስገጉ ለማዳመጥ ይጠብቁ ጀመር

ቀደም ሲል የሰጡትን ምስክርነት መድገም አላስፈለገም ነበር " የጎደለ
ቢኖር አንዳንዶቹ እየተጠየቁ ካስተካከሉ በኋላ'ያልተሰሙ ምስክሮች እንዲስሙ
ተደረገ።

“ሪቻርድ ሔርን ጥራ ” አለ ዳኛው

ሚስተር ሔርን የሚያውቁ ሁሉ ስሙ እየተጠራ ለምን እንደማይነሣ ራሳቸውን እየጠየቁ ሲደነቁ ሪቻርድ ሔር ትንሹ” ብቅ አለ "
በፍርድ ቤቱ አዳራሽ የነበረው ሕዝብ ሲንሾካሾክ ተሰማ " የተሰደዶው ሞተ የተባለው አሁንም ሕይወቱ በአጠራጣሪ ሁኔታ ያለው ሪቻርድ ሔር ሲዘልቅ አጫጭሮች ደኅና አድርገው ለማየት እየተንጠራሩ በግሮቻቸው ጫፍ ቆሙ።ሰብሳቢው ሁሉም ጸጥ እንዲል ጠየቀ ሁለት መኮንኖች ቀስ ብለው መጥተው ከኋላ ቆሙ እሱ ሊያቀው ባይችልም በጥበቃ ሥር ዋለ በደንቡ መሠረት ምሎ ማንነቱን ሁሉ ተናግሮ ምስክርነቱን ቀጠለ

“እስረኛውን ዞር በልና ደህና አድርገህ ተመልከተው
“ታውቀዋለህ ?

“ አሁን ስር ፍራንሲዝ ሌቪሰን መሆኑን ዐወቅሁት እስካለፈው ሚያዝያ
ድረስ ግን ስሙ ቶርን መሆኑን ነበር የማውቀው

እስኪ የግድያው ዕለት ማታ እስከምታውቀው ድረስ የሆነውን ንገረን ።”
“ ያን ዕለት ማታ ከአፊ ጋር ቀጠሮ ስለ ነበረኝ ወደ ቤታቸው ሔድኩ "
ቀጠሮህ በምስጢር ነበር ?”

"በከፊል ከዎን » ከአፊ ጋር የመቃረቤን ነገር ወላጆቼ ስለማይወዱልኝ
እኔም መሔዴን እንዲያውቁ አልፌልግም ነበር " ስለዚህ ከራት በኋላ ጠበንጃ ይዤ
ስወጣ አባቴ የምሔድበትን
ቢጠይቁኝ ቦሻ ዘንድ ብዬ ዋሽቼ ሔድኰ እኔ ግን ለሆሊጆን ላውሰው ቃል ገብቸለት የነበረውን ጠበንጃ ይዠ ከቤቱ ስደርስ
አፊ ሥራ አለብኝ ብላ እንዳልገባ ከለከለችኝ " እኔም ቶርን ከቤት መኖሩ
ገባኝ " ከዚያ በፊትም እሷ በሰጠችኝ ቀጠሮ እየሔድኩ ከአንድ ጊዜ በላይ ከውጭ
መልሳኝ ነበር እኔም እንቅፋት እየሆነ ከደጅ እንድመለስ ያደረገኝ የቶርን
ከቤት መኖር መሆኑን ደጋግሜ ደርሸበት ነበር " "

“ከቶርን ጋር ትቀናኑ ነበር ማለት ነው ?

“የሱን አውቅም እኔ ግን በርግጥ እቀና ነበር ” አለ ሪቻርድ

“ እሺ ቀጥል የምሽቱን ሁኔታ "

“ከሷ ጋር ብጨቃጨቅም እንዳላስገባችኝ ቁርጡን ሳውቅ ጠበንጃው መጕረሱን ነግሬያት ለአባቷ እንድትሰጥ አስረክቤያት ተመለስኩ "ቶርን ከቤት
መኖሩን ስለ ካዶች እውነቷን መሆኑን በዐይኔ አይቸ ለማረጋገጥ ወደ ዱር ገባ ብዬ ተሸሽጌ እመለከት ጀመር " ሎክስሌይ አየኝና ለምን እንደ ተሸሽግሁ ቢጠይቀኝ ምንም ሳልመልስለት ዝም አልኩ ግማሽ ሰዓት ሳልቆይ ከሆሊጆን ቤት በኩል
ተኩስ ሰማሁ " እንግዲህ ሆሊጆንን የገደለው ያ ተኩስ ነበር "

“ ተኩስ በኦትዌይ ቤቴል ሊተኮስ የሚችል ይመስልሃል ?

አይችልም " እሱ ከነበረበት ራቅ ብሎ ነበር የተተኮሰው ቤቴል ከነበረበት ጠፋ " ወዲያው አንድ ሰውዬ ፊቱ ጭው ብሎ ገርጥቶ • ዐይኖቹን አፍጦ ቁና ቁና እየተነፈሰ ልቡ እስኪወልቅ እየበረረ መጣና ሽው ብሎ ዐልፎኝ ሲሔድ ቶርን መሆኑን አየሁት " ከኔ ዐልፎ እንደ ሔዶ ወዲያው የፈረስ ኮቴ ሰማሁ "ከዱሩ አስሮት ነበር "

“ተከተልከሙ ?

“ የለም " ምን እንደዚያ እንዳደረገው እየገረመኝ አፊ ለሁለታችንም አለው
እያለች ስለ አታለለችኝ ልሰድባት እየሮጥኩ እንደ ገባሁ አነቀፈኝና ከተዘረረው
የሆሊጆን ሬሳ ላይ ወደቅሁ " ነፍሱ ወጥቶ ከመዝጊያው ሥር ወድቆ ነበር" ጠበንጃዬ ጥይቱ ተተኰሶ ቀፎው ብቻ ከወሉሉ ተጥሉ አገኘሁት "

በአዳራሹ ውስጭ ጸጥታ ስፈነ "

“ከቤቱ ውስጥ ማንም አልነበረም አፊንም ብጠራት አልመልስልኝ አለች”
ጠበንጃዬን አነሣሁና ከቤቱ ወጥቼ ስሮጥ ሎክስሌይ ከዱሩ ወጥቶ አየኝ ግራ
ገባኝ ፈራሁ " ጠበንጃውን መልሼ ከነረበት ጣልኩና ሮጥኰ "

“ ስሸሽ ቤቴልን አገኘሁት ተኩሱ እንደ ተሰማ ወዶ ሆሊጆን ቤት ከሔደ በኋላ ተመልሶ ወደ ዱሩ ስለ ገባ ማንንም አለማየቱን " ሲነግረኝ አመንኩትና
ጥየው ሄድኩ።

“ታዲያ ዌስት ሊንን ለቀህ ሔድክ ?”

በዚያው ሌሊት ለአንድ ሁለት ቀን ዘወር ብዬ ቆይቸ ሁኔታውን ለማየት ነበር አሳቤ "

ምርመራው ቀጠለ " በመጨረሻ ጥፋቱ በኔ ላይ ተጣለ " ስለዚህ ካገር ጠፋሁ።

ቀጥላ አፊ ሃሊዮን እንደገና ተጠራች « የሰጠችው ምስክርነት ከሬቻርድ
አነጋግር ጋር አንድ ሆነ "

ከዚያ ኦትዌይ ቤቴል ተጠራና የምስክርነት ቃሉን ሰጠ።

"ሆሊጆን የተገለ ማታ አይ ጫካ ውስጥ ነበርኩ " ሪቻርድ ሔር ከወደ
ቤቱ ጠበንጃ ይዞ ሲወርድ እየሁት "

" ሪቻርድሳ አይቶህ ነበር?”

የለም " ከጫካው ገባ ብዬ ስለ ነበር ሊያየኝ አይችልም ነበር " ከቤቱ በር እንደ ተጠጋ አፊ ቶሎ ወጣችና መዝጊያውን በስተኋላዋ ይዛ ካነጋረችው በኋላ ጠበንጃውን ተቀብላው ገባች ራቅ ብዬ ስለ ነበር የተነጋገሩትን አልሰማሁም እሱም ከዚያ ቤት ተመልሶ እኔ ከነበርኩበት ርቆ ሔደ ሲደበቅ አየሁት ምን እንዳስደበቀው ሳስብ ከሆሊጆን ቤት በኩል ተኩስ ሰማሁ "

“ የተተኮሰው በሪቻርድ ሊሆን ይችላል ?

አይችልም » ተኩሱ የተሳማበት አካባቢ ከሪቻርድ ሔር ይልቅ ለእኔ
ይቀርብ ነበር "

"ቀጥል ”

“የተኮሰው ማን እንደሆነ ለመገመት እንኳን አልቻልኰም » ነገሩን ይበልጥ ለማወቅ ተኩሱን ወደ ሰማሁበት ቦታ ሳመራ ካፒቴን ቶርን እያለከለከ ሲሮጥ መጣ በጣም መደንገጡና መረበሹ ከገጽታው በግልጽ ይታይ ነበር " ዐልፎኝ ሊሔድ ሲል ክንዱን ያዝኩና፡“ምን ሆነሃል ? የተኮስከው አንተ ነበርክ? ” አልኩት

“ቆይ ለምን ጠረጠርከው ?

“ደንግጦ ነበር መጨነቁንና መርበትበቱን በቀላሉ ዐወቅሁበት እንዲያም ስይዘሙ ጊዜ በጣም ተጨነቀ " ነጥቆኝ ሊሔድ ሞከረ አልሆነለትም ።
ስለዚህ ነግሩን ማለስለስ ፈለገ“ ዝም እንድል ነገረኝ “የዝምታሀን ዋጋ እሰጥሃለሁ » ሳይታሰብ በንዴት ያደረግሁት ነው ሰውየው ሁልጊዜ ይሰድበኛል ልጂቱን " ምንም አላደረግኋትም” አለኝና የሃምሳ ፓውንድ ኖት በእጄ ሸጎጠልኝ » የሆነ ነግር ያልሆነ ማድረግ አይቻልም " ስለዚህ እኔን ማየትህን መናገር ለምንም አይጠቅምህም ሲለኝ ፡ እኔም ያንን ገንዘብ ወሰድኩና እንደማልናገር
ነገርኩት " ነገር ግን ሰው መግደሉን አላወቅሁም !አልጠረጠርኩም ነበር »

“ ታዲያ ምን ተደርጓል ብለህ አሰብh ?”
👍17👎1
“ ምንም ነገር አልጠረጠርኩም " ጥድፊያና ድንግርግር ስለ ነበር አንድም የተወሰነ ሐሳብና ጥርጣሬ ለማስተንተን ሳልችል ቶርን ዘቅዝቆ ሮጠ ቀጠለና
ሪቻርድ ከዱሩ ወጥቶ ወደ ሆሊጆን ቤት ሲሔድ አየሁት" እሱም ከቶርን ባላነሰ ሁኔታ ደንግጦ ወዲያውኑ ተመለሰና ያንን ሶለግ ውሻ አይቸው እንደሆነ ጠየቀኝ”

“ የምን “ሶለግ ውሻ ? ብዬ ስጠይቀው ' ' ቶርን ነዋ አለኝ » አለማየቴን
ስነግረው መንገዱን ቀጠለ " ኋላ ሆሊጆን መገደሉን ሰማሁ "

ይኸን አሠቃቂ ወንጀል ለመደበቅ ነው ገንዘቡን የተቀበልከው ?

“ ንዘቡን ተቀበልኩ I ይኸንኑ ስናዘዝም ኃፍረት ይስማኛል " ግን ሳላስብ ነው ያደረግሁት የተቀበልኩት ግድያውን ለመደበቅ መሆኑን ባውቅ ኖሮ አልነካውም ነበር" ያን ጊዜ የገንዘብ ችግር ስለ ነበረብኝ ተሳሳትኩ"

ኋላ ምን ነገር እንደ ተሠራ ሪቻርድም እንደ ተከሰሰ ሳቅ በሠራሁት ሥራ ደነገጥኩ " የተቀበልኩትን ገንዘብ እስከ ዛሬ ስረግመው እኖራለሁ " በሪቻርድ የደሪሰው መከራም የሕሊና ሸክም ሆኖብኝ ቀረ ”

“የደበቅኸውን ምስጢር በመናገር ሸክሙን ልታወርዴው አትችልም ነበር?”

“እንዴት አድርጌ ? የምናግርበት ጊዜ ቀድሞ ዐለፈ " ቶርን አሁን በቅርቡ
ከሚስተር ካርላይል ጋር ለመፎካከር ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ተብሎ እስከ መጣ
ድረስ ፈለጉ ጠፋኝ ሪቻርድ ሔርም እንደሱ ጠፋ " የደረሰበትን ያየም የሰማም
" እንዲያውም ሞተ እየተባለ ተወራ ስለዚህ ማንም ተጠያቂና መስካሪ በሌለበት ብናገር ራሴን ማስጠርጠር ብቻ መስሎ ስለ ታየኝ ዝም ማለቱን መርጬ ተውኰት ”

" በዚያ ዘመን ስለ ቶርን ምን የምታውቀው ነገር ነበር?”

“ምንም አፊን ፍለጋ የአይን ጫካ ከማዘውተሩ ቶርን እየተባለ ከመጠራቱና እሱም እኔን ቤቴል” ብሎ ስለጠራኝ የኔንም ስም ያውቅ የነበረ ከመምሰሉ በቀር ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም " "

የምስክሮቹ ቃል እንዳበቃ ' የሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን ጠበቃ ሰፋ ያለ ጥልቅ' የሆነ የመከላከያ ሐተታ አሰማ „ “የደረሰው አደጋ በድንገተኛ አጋጣሚ
ያልተፈጸመ ለመሆኑና ተከሳሹ ትክክለኛ ጥፋተኛ ሆኖ ለመኘቱ የቀረበ ማረጋገጫ የለም " ከዚህም ሌላ በአንዲት ጠባብ ክፍል የጎረሰ መሳሪያ ማስቀመጥ
ለአደጋ ማመቸቱን አመልክቶ የተከበረው ፍርድ ቤት ይህን ያልተጋገጠ መረጃ ይዞ ቸኩሎ ከመፍረዱ በፊት በነገሩ አጠራጣሪነት ምክንያት እስረኛው በነጻ
ዠ እንዲለቀቅ ለመነ ጥያቄውን ምክንያት በመስጠት ሲያብራራው ተከሳሹ ስለ መልካም ጠባዩ ምስክር እንደማያሻው ጠቅሶ ያን ሁሉ በማገናዘብ እንዲታይለት አመለከተ " የጠባዩ ነገር ሲነሣ ከሰብሳቢው ዳኛ በቀር ሁሉም ሳይወዱ
ፈገግ አሉ ።

ችሎቱ በዐሥር ሰዓት ተነሳና ከሩብ ሰዓት በኋላ ተመልሶ ተሠየመ

“ክቡራን የሕዝባዊ ፍርድ ሸንጎ አባላት .. ምን ትላላችሁ ? ጥፋተኛ ነው
ወይስ አይደለም ?” አለ ዋናው ዳኛ " ሁሉም ጸጥ አለ " ' ጥፋተኛ ነው ማለት
እንደ ነበረ በስሜት ይታወቅ ነበር “ ነገር ግን” አለ አንዱ ከግንባር ከተቀመጡት ' ' ምሕረት ቢደረግለት ነው አስተያየታችን ”

በምን ምክንያት ?” አለ ዳኛው "

ወንጀሉ አስቀድሞ የታሰበ ሳይሆን ከድንገተኛ ንዴት ተነሥቶ የተፈጸመ በመሆኑ

ዳኛው ትንሽ ዝም ብሎ ቆየ ከኪሱ ውስጥ አንድ ጥቁር ነገር አወጣ "

“ተከሳሽ ! የሞት ቅጣት እንዳይፈረድብህ ለፍርድ ቤቱ የምትሰጠው ምክንያት አለህ ?”

እስረኛው የቆመ0ትን ሳጥን ጨምድዶ ያዘ » የተጫነውን አሠቃቂ ፍራት ለማራገፍ የፈለገ ይመስል ራሱን ወዘወዘ " ዕብነ በረድ መስሎ ነጥቶ የነበረ
ፊቱ ተለውጦ እንደገና ደም ለበሰ "

ምሕረት እንዲደረግልኝ ያሳሰቡልኝ የጁሪዉ አባላት መልካም ገልፀውታል
የሰውዬው ሕይወት በእጄ ለመጥፋቱና ዛሬ የተሰጠውን ምስክርነት
መካዱ ዋጋ የለውም " ልጂቱን ከውጭ ትቻት ባርኔጣዬን ልወስድ ከቤት ብገባ ሟቹን አገኘሁት " ስድብ ጀመረኝ " ተጨቃጨቅን " ከዚያ እንደዚያ የመሰለ
አደጋ ሊዴርስ ቻለ እንጂ አስቀድሜ አስቤ የፈጸምኩት ግድያ አልነበረም” አለ"

ዳኛው ጥር ቆብ ከራሱ ደፍቶ እጆቹን አንዱን በሌላው ላይ አመሳቀለ "

“ ተከሳሽ” አለ ዳኛው : “ሆን ብለህ በፈጸምከው የግድያ ወንጀል በማያጠራጥር ግልጽ በሆነ ማስረጃ ተመስክሮብሃል የጁሪዉ አባላት ወንጀለኛ ነህ
ብለውሃል እኔም በነሱ ሐሳብ እስማማለሁ " የዚያን ያልታደለ ሰውዬ ሕይወት ለማጥፋትህ አንዳችም የጥርጥር ጥላ እንኳን የለበትም አንተም ራስህ ተናዘሃል » አድራጎትህ ጭካኔ ግፍና ክፋት የተሞላበት ነው "ለዚህ ያደረሰህ የተለየ ሁኔታ ምንም ይሁን " በአነጋገሩ አበሳጭቶህ ሊሆን ይችላል " ነገር ግን ጠበንጃ አንሥተህ ምላጭ እንድትስብበት የሚያበቃህ አልነበረም የብሪታኒያ
ታላላቅ መኳንንት ወገን ስለ ሆንክ ጠበቃህ አስተያየት እንዲደረግልህ አመልክቶልሃል እንዶዚህ የመስለ አባባል ከአንደበቱ ሲወጣ በመስማቴ ደንቆኛል
በኔ አስተያየት ደግሞ በኅብረተሰቡ ዘንድ ያለህ ደረጃ ጥፋትህን የበለጠ ያጠነክረዋል " በኔ እምነት አንድ ኑሮ የተሟላለት ሰው ሲያጠፋ የሚደረግለት አስተያየት ለድሆች ለተራና ላልተማሩ ሰዎች ከሚደረገው ያነስ መሆን አለበት ዛሬ የተሰማብህ ምስክርነት ጥፋተኛነትህን በጉልህ አሳይቶብሃል " የዚህን ሰውዬ ልጅ ክብር በሌለው ርካሽ ፍላጎትህ ታሳድዳት ነበር " በዚህ ረገድ እንኳን ጠባይህ ከሪቻርድ ሔር ጋር ይነጻረራል " እሱ ለጋብቻ ሲያስባት አንተ ደግሞ ለዕለት ፍላጎትህ ነበር የምትከታተላት " በዚህ ፍላጎትህ አባቷን ገደልክ ይኸው አልበቃህ ብሎ ደግሞ ወንጀልህን ደብቀህና በሌላ ለጥፈህ ልጂቱን እያታለልክ ወደ ጥፋት መራሃት አባቷ ሳያስበው ሳይዘጋጅበት አንተም ሳታዝንለት ቆርጠህ ጣልከው አሁን ከሠራኸው ግፍ ለመንጻት ሕይወትህን መክፈል አለብህ ። የጁሪዉ አባሎች ምሕረት እንዲደረግልህ ሐሳብ አቅርበዋል " ሐሳባቸው በወቅቱ ለሚመለከተው ይቀርባል " ነገር ግን ይህ ሐረግ ምን ጊዜም ከፍርዱ ውሳኔ ጋ ተያይዞ ለመጨረሻው ውሳኔ መቅረቡ የተለመደ ነገር ቢሆንም የሚፈለገው ትክክለኛ ፍትሕ ስለሆነ እምብዛም እንደ ማይተኮርባቸው ልታውቀው ይገባል ያለፈ የሕይት ዘመንህ ምን ይመስል እንደ ነበር ዓለምም በመጠኑ የሚያውቀ ስለሆነ በዚህ ምድር ለመኖር የቀረን አጭር ጊዜ ባጉል ተስፋ ከምታሳልፈው
የበደልካቸውን ይቅርታ ከልብህ ለመለመን ብትጠቀምበት የበለጠ ይሆናል " እንግዲህ በኔ በኰል የቀረኝ መራራውን የፍርድ ውሳኔ ባንተ ላይ ማሳለፍ ብቻ ነው "
እርሱም አንተ ፍራንሲዝ ሌቪሰን መጀመሪያ ወደ መጣህበት ቦታ ከተወሰድክ
በኋላ • ከዚያ ወደ መገደያው ሥፍራ ተወስደህ ትሞታለህ ኃያሉ ጌታ ለማት
ሞተው ነፍስህ ምሕረት ይስጥ "

“ አሜን !

ከዚያም የሪቻርድ ሔር ጉዳይ ቀረበና በሱ ላይ የቀረበ መረጃ ባለመኖሩ
በነጻ እንዲለቀቅ ዳኛው አዘዘ"የተንገላታና የተታለለው ምስኪኑ ሪቻርድ እንደ ገና ነጻ ሰው ሆነ "

ሆሊጆንን ግዪለ ተብሎ በተነገረበትና እርሱም ካገር በተሰደደበት ጊዜ ቢገኝ
ኖሮ ምንም እንኳን ተወልዶ ባደገበት ቦታ ሰሃ የማይወጣለት የዋህና የተባረከ ልጅ እንደ ነበር የማያውቅ ባይኖርም ድንጋይ የማይወረውርበት እርግማን የማያወርድበት ሰው አልነበረም አሁን ደግሞ በሕግ በአደባባይ ከወንጀሉ ነጻ መሆኑ
👍7
ተነግሮለት ሲወጣ ደስታውን የሚገልጽለት ሕዝብ ትንፋሽ እስኪያጥረው ድረስ
ከበበው " አንድ መቶ እጆች ቢኖሩት ኖሮ እንኳን ለመጨበጥ አያደርስም
ሪቻርድ እንደ ምንም ብሎ ከከበበው ሕዝብ መሐል ወጣና ወደ አባቱ ተጠጋ "
ሽማማሌው ዳኛ ያንን ሁሉ ኩራቱን ያንን ሁሉ መንቀባረሩን ረሳና እንደ ልጅ ተንሰቅስቆ አለቀሰ "

“ አባባ” አለው ልጁ የእርሱም ዐይኖች እንባ እንዳንቆረዘ''ያለፈው
ነገር ተረስቷል " የቂም ትዝታው ተፍቋል " አሁን አንተ! እኔና እናቴ አብረን
የምናገኘውን ደስታ ብቻ አስብ።

በልጁ ተጠምጥመው የነበሩት የጀስቲስ ሔር እጆች ለቀቁት በሚያሠቅቅ
ሁኔታ ተሸማቀቁ " ፊቱም ተኮማተረና ጡንቻዎቹ ለሁለተኛ ጊዜ ስልል አሎ "
ዝልፍልፍ ብሎ ከኮሎኔል ቤቴል ትከሻ ላይ ድግፍ አለ....

💫ይቀጥላል💫
11👍6👎1
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


...አሁን ሰዓቱ አስር ሰዓት ከሃያ ሆኗል፡ የመሳፈሪያው ሰዓት ደርሷል። ከስልክ መደወያው ኪዮስክ ወጣችና መርቪን ስልክ ወደሚነጋገርበት ክፍል ሄደች።ስታልፍ እንድትቆም የእጅ ምልክት ሰጣት በመስታወት አሻግራ
ስታይ ተሳፋሪዎች ወደ አይሮፕላኑ የሚወስዳቸው ጀልባ ላይ ሲወጡ አየች፡፡
ሆኖም መርቪን ቁሚ ስላላት ቆመች፡ መርቪን በስልክ አሁን በዚህ ነገር
አታስቸግረኝ፡፡ ሰራተኞቹ የጠየቁህን ክፈልና ስራው እንዲቀጥል አድርግ›› ሲል አዘዘ፡፡

በመርቪን ፋብሪካ ውስጥ ሰሞኑን የአሰሪና ሰራተኛ ውዝግብ እንደነበር
ነግሯታል፡ ከእሱ ባህሪ በተቃራኒ ሲታይ አሁን ለሰራተኞቹ ጥያቄ እጁን
የሰጠ ይመስላል፡

ስልኩን የደወለው ሰው በመርቪን አነጋገር ሳይደነቅ አይቀርም፡፡
‹‹አዎ እንዳልኩህ አድርግ፤ የምሬን ነው፡፡ ከማንም ቀጥቃጭ ጋር
ለመጨቃጨቅ ጊዜ የለኝም፡ ደህና ሁን›› አለና ስልኩን ዘጋ፡፡ ከዚያም
‹‹ስፈልግሽ ነበር?›› አላት ናንሲን፡፡

‹‹ተሳካልህ? ባለቤትህ አብሬህ እመጣለሁ አለች?›› ስትል ጠየቀችው፡
‹‹ገና በቀጥታ እንሂድ አላልኳትም››
‹‹አሁን የት ነው ያለችው?››
በመስኮት አየና ‹‹ያቻትልሽ ቀይ ኮት የለበሰችው››
ናንሲ በእድሜ በሰላሳዎቹ መጀመሪያ ላይ የምትገኝ ቃጫ የመሰለ ጸጉር
ያላት ሴት አየች፡ ‹‹መርቪን ባለቤትህ በጣም ቆንጆ ናት!›› አለች፡ ናንሲ
በመርቪን ሚስት ቁንጅና ተደንቃለች፡፡ እሷ የገመተቻት እንዲህ አልነበረም፡
‹‹ይህቺ ሴት ከእጅህ እንዳትወጣ ለምን እንደፈለግህ አሁን ገባኝ›› አለች፡ዳያና አንድ ሰማያዊ ሱሪ የለበሰ ሰው ሶቶ ይዛለች፡፡ ማርክ እንደ መርቪን አያምርም፡ ቁመቱ አጠር ያለ ሲሆን ፀጉሩ ከግንባሩ እየሸሸ ነው፡፡ ነገር ግን ፎልፎላ እና ተጫዋች ይመስላል ሲያዩት፡፡ ናንሲ የመርቪን ሚስት የባሏን
ተቃራኒ የሆነ ሰው መያዟን አስተዋለች፡፡ ለመርቪን አዘነችለት።
‹‹እግዚአብሔር ጽናቱን ይስጥህ›› አለችው፡፡

‹‹ገና እጅ አልሰጠሁም›› አለ፡፡ ‹‹ኒውዮርክ ድረስ ተከትያት እሄዳለሁ››
ናንሲ የመርቪን አባባል አሳቃት፡ ‹‹ደግ አደረግክ! ባለቤትህ ማንም ወንድ ልጅ አትላንቲክን አቋርጦ የሚከተላት አይነት ሴት ናት፡››

‹‹የችግሩ መፍትሄ አንቺ እጅ ውስጥ ነው ያለው›› አላት ‹‹አይሮፕላኑ ሞልቷል ቦታ የለም››

‹‹እውነት ነው ታዲያ ኒውዮርክ ድረስ በምን ትሄዳለህ? ደግሞ
ምንድን ነው በእኔ እጅ ውስጥ ያለው መፍትሄ?››
‹‹አንቺ ነሽ ቀሪውን ትርፍ ወንበር የያዝሽው፡፡ የሙሽሮችን ክፍል
መያዝሽን ሰምቻለሁ፡ ትርፏን ወንበር ለኔ ሽጭልኝ››

ናንሲ ከት ብላ ሳቀችና ‹‹የሙሽሮችን ክፍል ከወንድ ጋር መጋራት
አልችልም፡፡ እኔ የተከበርኩ ሴት ነኝ እንጂ የሆነች ዳንሰኛ አይደለሁም››
‹‹እኔ ግን ማንም ያላደረገልሽን ውለታ አድርጌልሻለሁ›› አላት ፍርጥም ብሎ።
‹‹ውለታህ ሊኖርብኝ ይችላል ክብሬን መሸጥ ግን አልችልም ናንሲ ያለችውን እንዳልተቀበለ ይመሰክራል ‹‹በአይሪሽ ባህር ላይ ከኔ ጋ
ስትበሪ ስለክብርሽ አልተጨነቅሽም››

‹‹እዚያ ላይ እኮ አብረን አላደርንም›› አለች፡፡ ብትረዳው በወደደች
ውቧን ሚስቱን ለማስመለስ ቁርጠኛ መሆኑ ልቧን ነክቷታል፡

‹‹ይቅርታ አድርግልኝ በዚህ እድሜዬ ካንተ ጋር አንድ ክፍል አድሬ የሰው መሳቅያ
መሆን አልፈልግም

‹‹ስለሙሽሮች ክፍል ጠይቄያለሁ። ከሌሎች ክፍሎች የሚለየው ነገር
የለም፡ ባለሁለት አልጋ ነው፡፡ ማታ ማታ በሩን ብንከፍተው ሁለት የማይተዋወቁ ሰዎች ፊት ለፊት የያዟቸው ትይዩ ወንበሮች መሆናቸው ይታያል፡››

‹‹ሰው ምን እንደሚል አስብ መርቪን››

‹‹ለማን ነው የምትጨነቂው? ባል የለሽ? ቤተሰቦችሽ ሞተዋል እዚህ
ለምታደርጊው ነገር ማን ግድ አለው?››

መርቪን አንድ ነገር ከፈለገ ፊት ለፊት ነው የሚናገረው፡
ይቀየመኛል ብሎ አያስብም፡፡

‹‹ሁለት ትልልቅ ወንድ ልጆች አሉኝ›› ስትል አነጋገሩን ተቃወመች።
‹‹ልጆችሽ ይህን ሲሰሙ ቀልድ ነው የሚመስላቸው››
ሊመስላቸው ይችላል አለች በሆዷ ሃዘን እየተሰማት፡ ‹‹እኔን የጨነቀኝ የድፍን ቦስተን ከተማ ሰው ምን እንደሚል ነው፡፡ እኔ ታዋቂ ሴት በመሆኔ ወሬው እንደ ቋያ እሳት በአንዴ ነው የሚዳረሰው››

‹‹ተመልከች! እንግሊዝ አገር እዚያ አይሮፕላን ጣቢያ ላይ ሆነሽ ምን ያህል ተቸግረሽ እንደነበር እንድወስድሽ ምን ያህል ፈልገሽ እንደነበር
አስታውሺ፡፡ ያኔ ከጉድ ነው ያወጣሁሽ፡፡ አሁን በተራዬ እኔ የማልወጣው ችግር ላይ ወድቄያለሁ፡ የኔ ጭንቀት አልገባሽም ማለት ነው?›› አላት

‹‹ይገባኛል››

‹‹ስለዚህ ችግር ላይ ስላለሁ ከጉድ አውጪኝ፡፡ ትዳሬን ለማዳን ያለኝ
የመጨረሻ እድል ይሄ ብቻ ነው፡፡ ይህን ማድረግ ደግሞ ትችያለሽ፡፡ እኔ በችግርሽ ጊዜ ደርሼልሻለሁ፡ አሁን ብድር የምትመልሽበት ጊዜ መጥቷል።ሰው እንደሆነ አምቶ አምቶ ሲደክመው ይተዋል፡፡ የአንድ ሰሞን ሀሜት ደግሞ ሰውን አይገድልም፡፡››

የአንድ ሰሞን ሀሜቱን አሰበች፡፡ አንዲት የአርባ አመት እድሜ ላይ የምትገኝ ባሏ የሞተባት ሴት በግድ የለሽነት እንዲህ አይነት ነገር ብታደርግ ምን ችግር አለው፡፡ ይህን በማድረጓ አትሞት! መርቪን እንዳለው ክብሯንም አይቀንሰውም፡፡ አሮጊቶች ምነው ቀበጠች› እንደሚሏት ጥርጥር የለውም:፡
የእድሜ እኩዮቼ ግን ድፍረቴን ያደንቃሉ አለች በሃሳቧ የመርቪን የተጎዳና አቋመ ፅኑ ፊት ስታይ ልቧ ከእሱ ጋርሄደ የቦስተን ህዝብ ገደል ይግባ፡፡ ይህ ሰው ችግር ላይ ወድቋል፡ እኔ ተቸግሬ በነበረበት ሰዓት ለችግሬ ደርሷል፡ እኔ ባላመጣሽ ኖሮ ዛሬ እዚህ አትገኝም ነበር› ያለው እውነት ነው።

‹‹ናንሲ የያዝሽው ክፍል ውስጥ ታስገቢኛለሽ? የመጨረሻ ተስፋዬ አንቺ ነሽ"

‹‹አዎ አስገባሀለሁ›› አለች፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የሄሪ ማርክስ የመጨረሻ አውሮፓ ትውስታ ለመርከበኞች ምልክት የሚሰጠውን የፓውዛ ማማ የአትላንቲክ ውቅያኖስ ሞገድ እየመጣ
ሲለትመው ያየው ብቻ ነው፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የሚታይ መሬት
አልነበረም፧ ዳርቻ ከሌለው ባህር በስተቀር፡፡

አሜሪካ ስገባ ሀብታም እሆናለሁ› ሲል አሰበ፡፡

በሌዲ ኦክሰንፎርድ ሻንጣ ውስጥ የተሸጎጠው ጌጥ የወሲብ ያህል የሚያጓጓ ነው፡፡ ይህ እንቁ በዚህ አይሮፕላን ውስጥ አንድ ቦታ ይገኛል ዕንቁውን በእጁ ለማስገባት ቋምጧል፡

ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ እንቁ ከሌባ እጅ በመቶ ሺህ ብር ይገኛል።በዚህ ገንዘብ ጥሩ መኪና ምናልባትም የቴኒስ መጫወቻ ያለው ቤት እገዛለሁ ወይም ገንዘቡን ኢንቨስት አደርግና በወለዱ ብቻ እኖራለሁ፡ ስራ
ባልሰራ ደልቀቅ ብዬ እኖራለሁ› ሲል ተመኘ፡፡
በመጀመሪያ ግን እንቁውን በእጁ ማድረግ ይኖርበታል፡ ጌጡ በሌዲ ኦክሰንፎርድ አንገት ላይ አይታይም፡ ስለዚህ ሊኖር የሚችለው በእጅ ቦርሳቸው ውስጥ ወይም እዚህ አጠገባቸው ባለው ማስቀመጫ ወይም ደግሞ ሻንጣ የሚቀመጥበት ቦታ እኔ ብሆን ካጠገቤ አለየውም ነበር ከአይኔ ከራቀ እንቅልፍም አይዘኝም› ሲል አሰበ ሄሪ፡

መጀመሪያ የእጅ ቦርሳቸውን ይበረብራል፡ እንዴት እንደሚበረብር ግን
አልመጣለትም፡፡ ምናልባትም የሚሻለው ማታ ሰው ሁሉ ከተኛ በኋላ ነው።
👍13
እንቁውን በእጁ ለማድረግ አንድ የሆነ መንገድ መፈለግ አለበት፡፡ ሊያዝ
ይችላል፡ ስርቆት አደገኛ ተግባር ነው፡፡ ሆኖም ሁልጊዜ ሳይያዝ ከክፉ ነገር
እንዳመለጠ ነው፡ ‹እስኪ ተመልከቱኝ አለ ለራሱ ከሰረቅኩት የወርቅ
አምባር ጋር እጅ ከፍንጅ ተይዤ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ሌሊቱን ወህኒ
አደርኩ፡ አሁን ደግሞ በፓን አሜሪካ አየር መንገድ አይሮፕላን እየበረርኩ
ነው፡፡ እድለኛ አይደለሁም?› አለ በልቡ፡፡

አንድ ከአስረኛ ፎቅ ላይ ወደ መሬት የሚወረወር ሰው ቀልድ ሰምቶ ነበር፡፡ ሰውዬው አምስተኛ ፎቅ ላይ ሲደርስ እስካሁን ችግር የለም› ሲል ተደምጧል።

አስተናጋጁ ኒክ የሚጠጣ አመጣለትና ሜኑ ሰጠው፡ መጠጥ መጠጣት
ባይፈልግም ጥሩ ነው ብሎ ስላሰበ ሻምፓኝ አዘዘ፡፡ ህይወት እንግዲህ
እንዲህ ናት ሄሪ› አለ ለራሱ፡ በአለም ምቹው አይሮፕላን ላይ መሆኑ የሰጠው ደስታ ውቅያኖስን ማቋረጡ ከፈጠረበት ፍርሃት ጋር
ተደባልቆበታል፡ ሻምፓኙን ሲጎነጭ ፍርሃቱ ለሀሴት ቦታውን ለቀቀ።

የቀረበለት ሜኑ በእንግሊዝኛ የተፃፈ በመሆኑ ገርሞታል፡ ውድና
በአለም ተቀባይነት ያላቸው ምግቦች የፈረንሳይ ምግቦች መሆናቸውን
አሜሪካውያን አያውቁም፡፡ ቢሆንም ካሁኑ አሜሪካንን ወዷታል፡

‹‹የመብል ክፍሉ በአንድ ጊዜ አስራ አራት ሰው ብቻ ነው የሚይዘው::ስለዚህ ራት የሚበላው ተሳፋሪዎችን በሶስት ቡድን በመክፈል ነው›› በማለት
ገለፀ አስተናጋጁ፡፡ ‹‹ስለዚህ ከ12 ሰዓት፣ ከአንድ ሰዓት ተኩልና h3 ሰዓት በየትኛው ሰዓት ነው መብላት የምትፈልገው ሚስተር ቫንዴርፖስት?›› ሲል ጠየቀው ሄሪን፡፡

አሁን ጌጡን ለመውሰድ የምችልበት ዕድል ሊፈጠር ነው አለ በሆዱ፡ የኦክሰንፎርድ ቤተሰብ ከእሱ በፊት ወይም በኋላ የሚበሉ ከሆነ እሱ
ብቻውን የሚቀርበትን ዕድል ያገኛል፡፡ ነገር ግን እነሱ በስንት ሰዓት መብላት
እንደሚመርጡ አያውቅም፡፡ አስተናጋጁ ከእሱ በመጀመሩ በሆዱ ረገመው
እንግሊዛዊ አስተናጋጅ ቢሆን በመጀመሪያ የሚጠይቀው ትልልቅ ሰዎችን ነበር‥ ይሄ ዲሞክራቲክ አስተሳሰብ የተላበሰው ሰው ግን ጥያቄውን በወንበር
ቁጥር ነው የጀመረው፡፡ የኦክሰንፎርድ ቤተሰብ በስንት ሰዓት ሊበሉ እንደሚችሉ መገመት ይኖርበታል፡፡ ሀብታም ሰዎች በሀገሩ እንደሚያውቀው ምግባቸውን ቆየት ብለው ነው የሚመገቡት፡፡ ሰርቶ አዳሪ ቁርሱን ጠዋት
በአንድ ሰዓት ምሳውን ቀትር ላይ እራቱን ደግሞ በጊዜ አስራ አንድ ሰዓት
አካባቢ ነው የሚበላው፡፡ ባለሀብት ግን ቁርሱን ጠዋት በሶስት ሰዓት ምሳውን በስምንት ሰዓት እራቱን ደግሞ ማታ በሁለት ሰዓት ተኩል ነው፡፡ እንግዲህ የኦክሰንፎርድ ቤተሰብ ምግባቸውን የሚመገቡት ዘግየት ብለው ነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሄሪ የመጀመሪያውን የራት ሰዓት መረጠ፡፡ ‹‹ስለራበኝ ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት ላይ እበላለሁ›› አለ፡፡

አስተናጋጁ ወደ ኦክሰንፎርድ ዞር አለና በስንት ሰዓት መብላት
እንደሚፈልጉ ሲጠይቃቸው ሄሪ ትንፋሹን ውጦ አዳመጠ፡፡

ሎርድ ኦክሰንፎርድ ‹‹ሶስት ሰዓት ቢሆን ይሻላል› አሉ፡
ሄሪ ይህን ሲሰማ በእርካታ ፈገግ አለ፡፡
ሌዲ ኦክሰንፎርድ “ፔርሲ እስከ ሶስት ሰዓት መቆየት አይችልም ይርበዋል ቀደም ቢል ይሻላል›› አሉ፡
ሄሪ ተቁነጠነጠ 12 ሰዓት እንዳይባል ሰጋ
‹‹እንግዲያው አንድ ሰዓት ተኩል ይሁን›› አሉ ሎርድ፡
ሄሪ ይህን ሲሰማ ልቡ በደስታ ሞቀ፡፡ ለሌዲ ኦክሰንፎርድ እንቁ ቅርብ
መሆኑ ተሰማው፡

አሁን አስተናጋጁ ከሄሪ ፊት ለፊት ወደተቀመጠው ሰው ዞረ ሰውዬው ወይን ጠጅ ሰደርያ የለበሰ ሲሆን ፖሊስ ይመስላል፡፡ ስሙ ክላይቭ
መምበሪ ነው፡ ሄሪ እራት የምበላው አንድ ሰዓት ተኩል ነው በልና
ቦታውን ልቀቅልኝ አለ በሆዱ፡፡ ሆኖም ክላይቭ ‹ያሰብከው አይሳካ የሚል
ይመስል ስላልራበው ሶስት ሰዓት ተኩል ላይ መብላት እንደሚፈልግ ተናገረ፡፡

‹ምን አይነት ስቃይ ነው› አለ ሄሪ በሆዱ የኦክሰንፎርድ ቤተሰብ እራት በሚበላበት ጊዜ መምበሪ እዚህ ነው ማለት ነው፡

ምናልባት ለጥቂት ደቂቃ መጸዳጃ ቤት ወይም ሌላ ቦታ ይሄድ ይሆናል ሰውዬው እረፍት የለሽ ቢጤ ነው፡፡ ገባ ወጣ ያበዛል፡፡ ነገር ግን
ሰውዬው በራሱ ፍላጎት ተነስቶ ካልሄደ እንዲሄድ ማድረግ ሊኖርበት ነው፡
አይሮፕላን ላይ ባይሆኑ ኖሮ ከቦታው ለማስነሳት ምክንያት አይጠፋም
ነበር፡ ሌላ ክፍል እንደሚፈልግ ወይም ስልክ እንደሚፈልገው ወይም
መንገድ ላይ ራቁቷን የቆመች ሴት አለች ማለት ይቻላል፡፡ እዚህ ግን
ይህን ማለት አይቻልም:
አስተናጋጁ ተመልሶ መጣና ‹‹ሚስተር ቫንዴርፖስት የበረራ ኢንጂነሩና
ናቪጌተሩ ካንተ ጋር እራት ይበላሉ ከፈቀድክ›› ሲል ጠየቀው
‹‹እስማማለሁ›› አለ ሄሪ ከአይሮፕላኑ ሰራተኞች ጋር መጨዋወቱን አይጠላም፡፡ ሎርድ ኦክሰንፎርድ ሌላ መለኪያ ውስኪ አዘዙ፡፡ ሌዲ ኦክሰንፎርድ ፊታቸው ገርጥቷል፡ምንም አይናገሩም፡፡ ጭናቸው ላይ
መጽሐፍ ቢኖርም ሲያነቡ ግን አይታዩም፡፡ ሀዘን ገብቷቸዋል፡፡

ፔርሲ ተረኛ ካልሆነው የአይሮፕላን ሰራተኛ ጋር ለማውራት ስለሄደ
ማርጋሬት ሄሪ አጠገብ መጥታ ተቀመጠች፡፡ የተቀባችው ሽቶ አፍንጫውን አወደው፡፡

ኮቷን ስታወልቅ የእናቷን ቅርፅ መያዟን አየ፡፡ ትከሻዋ ሰፋ ያለ ሲሆን
ቅልጥማም ናት፡፡ የለበሰችው ልብስ አልተስማማትም፡፡ ሄሪ ረጅም የመኝታ ልብስ ለብሳ በአንገትና በጆሮ ጌጥ ተሸልማ ቢሆን ኖሮ እንዴት እንደምታምር ገመተ፡፡ እሷ ግን እንደ ባላባት ልጅ መምሰል አትፈልግም፡፡ ሀብታም ሆኖ መታየት ያሳፍራታል፡፡ ስለዚህ አለባበሷ የቄስ ሚስት አስመስሏታል፡
የባላባት ዘር በመሆኗ ደፈር ብሎ ሊጠጋት ፈራ፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከማንም ሰው ለመቀላቀል መፈለጓን ወደደው፡፡ ነገር ግን የሚወደድ ባህሪ
ቢኖራትም አደጋ ልትፈጥርበት ስለምትችል ተጠንቀቅ ሄሪ አለ ለራሱ!
ስለዚህ ልጅቷን ቀስ ብሎ መለማመድ እንዳለበት ተረዳ፡፡

ከዚህ ቀደም በአይሮፕላን ሄዳ ታውቅ እንደሆን ጠየቃት።

‹‹ከእናቴ ጋር አንድ ጊዜ ፓሪስ ሄጃለሁ›› አለችው:

የእሱ እናት ወደ ፓሪስ ሊሄዱ ወይ በአይሮፕላን ሊበሩ ቢመኙ አያገኙትም እንዳማራቸው ይቀራል

‹‹የባላባት ልጅ በመሆንሽ ምን ይሰማሻል ወይም እንዴት አገኘሽው?››

‹‹ወደ ፓሪስ ያደረግነውን ጉዞ አልወደድኩትም›› አለች፣ ‹‹ከአስልቺ
የእንግሊዝ ሰዎች ጋር ነበር የሄድኩት፡ እኔ የምፈልገው የኔግሮ ሙዚቀኞች
የሚጫወቱበት ትርምስ የበዛበት ሆቴል ነበር››

‹‹እናቴ ባህሩ ዳርቻ ትወስደንና ባህሩ ላይ እየቀዘፍን እንጫወታለን
አይስክሬም ዓሳና ድንች ጥብስ እንበላ ነበር›› አላት፡
ይህን እንደተናገረ መዋሸት እንደነበረበት በማወቁ ፍርሃት ፍርሃት አለው፡፡ ከዚህ ቀደም የሀብታም ልጆች ሲያጋጥሙት አዳሪ ትምህርት ቤት እንደሚማርና ቤተሰቦቹ ከተማ ውስጥ ካላቸው ቤት በተጨማሪ የገጠር
መዝነኛ ቤት እንዳላቸው አድርጎ ይናገር ነበር አሁን ግን የሚዋሽበት
ምክንያት የለም፤ ማርጋሬት ሚስጥሩን ሁሉ አውቃለች አሁን እውነቱን የተናገረው ድምጹን የአይርፕላኑ ሞተር ድምጽ ስለሚውጠው የሚሰማበት ስለሌለ ነው፡፡

‹‹እኛ ባህሩ ዳር ለመጫወት ሄደን አናውቅም›› አለች ማርጋሬት የተመኘችውን ማግኘት ባለመቻሏ እያዘነች፡፡ ባህር ዳር ሄደው የሚጫወቱ የተራ ሰው ልጆች ናቸው፡ እኔና እህቴ በደሃ ልጆች ነፃነት እንቀና ነበር፡ እነሱ የፈለጉትን ማድረግ ቢፈልጉ የሚከለክላቸው የለም፡››

ሄሪ ማርጋሬት ያለችውን ሲሰማ ደስ አለው፡፡ እሱ ሲወለድም እድለኛ
ነበር፡ በትልልቅ መኪና የሚሄዱት፣ ያማረ ልብስ የሚለብሱትና በየቀኑ ስጋ
የሚበሉት የባለሃብት ልጆች በእሱ ነፃነት ያለው የድህነት ኑሮ ይቀናሉ
👍13
‹‹በምሳ ሰዓት በኬክ ቤት በር ላይ ሳልፍ የኬኩ ሽታ ያውደኛል። በቡና ቤት በር ሳልፍ የቢራውና የትንባሆው ሽታ በአፍንጫዬ ይገባል፡፡ ሰዎች በነዚህ ቦታዎች እንደልባቸው ይዝናናሉ፤ እኔ ቡና ቤት ገብቼ አላውቅም፡››

‹‹ምንም ያመለጠሽ ነገር የለም አለ›› ሄሪ ቡና ቤት ስለማይወድ።
‹‹በትልልቅ ሆቴሎች የምግቡ ጥራት የበለጠ ነው››
‹‹እኛ የእናንተን ህይወት እንመኛለን እናንተ የእኛን›› አለች

‹‹እኔ ግን ሁለቱንም ህይወት አውቀዋለሁ›› አለ የተሻለው የቱ እንደሆነ አውቃለሁ››

የወደፊት እቅድህ ምንድ ነው?››

‹‹መዝናናት›› አለ፡፡

‹‹ህይወትህን እንዴት ልትመራ ነው ያሰብከው?››

«አሁን ልሰራ ያሰብኩት አለ ሄሪ ለማንም ያልነገረውን አንድ ምስጢር ሊነግራት ፈልጎ ‹‹አንድ ሌባ አለ፤ የሚያጨሰው የቱርክ ሲጋራ
የሚለብሰው ጥሩ ጥሩ ልብስ ነው፡፡ ታዲያ ሰዎች እቤታቸው ሲጋብዙት
ጌጣጌጣቸውን ይሰርቃል፡ እኔም እንደዚህ ሰው ነው መሆን የምፈልገው:››

‹‹ጅል አትሁን እንግዲህ›› አለች፡

በዚህ አባባሏ ትንሽ ቅር ብሎታል፡ አንድ የማይረባ ነገር ሰው ሲናገር ከሰማች በቀጥታ አባባሉን ትቃወማለች፡፡ አሁን የተናገረው ግን ቀልድ
አይደለም፡፡ የወደፊት ህልሙን ነው የነገራት፡፡ እሱ ልቡን ከፍቶ የሆዱን
ዘክዝኮ ነግሯታል፡፡ እንድታምነው ‹‹ቀልዴን አይደለም›› አላት፡፡

‹‹እድሜህን በሙሉ በሌብነት ልትተዳደር አትችልም›› አለች ‹‹ከተያዝክ እስር ቤት ታረጃለህ፡ ሮቢን ሁድ እንኳን በስተመጨረሻ አግብቶ ሰላማዊ ኑሮ መኖር ጀምሮ ነበር፡፡ እውነት ምን ልትሰራ ነው ያሰብከው?››

‹‹ጥሩ ቤት እሰራለሁ ፈረሶች አረባለሁ፡፡ የቆዳ ቦት ጫማ አደርግና
በእርሻዬ ላይ እየተንጎራደድኩ ጭሰኞቼን አናግራቸዋለሁ: እነሱም እኔን እንደ ባለቤት ያዩኛል፡፡ ገንዘቤን በጥሩ የንግድ ስራ ላይ ኢንቨስት አደርግና
የተንደላቀቀ ኑሮ እኖራለሁ፡፡ በበጋ ሰዎችን እየጠራሁ በአትክልት ቦታዬ ላይ ፓርቲ በማድረግ ብሉልኝ ጠጡልኝ እላለሁ፡፡

እናታቸውን የመሰሉ አምስት
ሴት ልጆችም እወልዳለሁ፡››
‹‹አምስት!›› አለች እየሳቀች ‹‹ጠንከር ያለች ሴት ነው ማግባት ያለብህ፡፡
ጥሩ ራዕይ ነው የሰነቅኸው፡፡ የተመኘኸው እንዲሳካልህ እመኝልሃለሁ››
አለችው::

የፈለገውን መጠየቅ እስኪችል ቀስ በቀስ እየተግባቡ መጡ ‹‹አንቺስ
ምንድን ነው አላማሽ?
‹‹እኔ እንኳን ጦሩን መቀላቀል ነው የምፈልገው››
ሴቶች መዝመት እንፈልጋለን ሲሉት ያስቀዋል፡፡ አሁን አሁን በእርግጥ ሴቱ ሁሉ ወታደር እየሆነ ነው፡፡ ‹‹ጦሩ ውስጥ ምን ትሰሪያለሽ?››
‹‹በሹፌርነት አገለግላለሁ፡፡ ወታደርና ስንቅ እንዲሁም ቁስለኛ አመላልሳለሁ››
‹‹አደገኛ አይደለም ጦር ሜዳ?››

‹‹አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ግድ የለኝም፡፡ ጦርነት አውድማ ውስጥ ገብቼ ፋሺዝምን ከሀገሬ ለማባረር እዋጋለሁ›› አለች በልበ ሙሉነት፡ ፊቷ ላይ
የሚነበበው ገፅታ ለህይወት ግድ እንደሌላት ያሳያል ሄሪ ይህን ሲያይ ጎበዝ ናት› አለ በሆዱ፡፡....

ይቀጥላል
👍9