አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
460 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰባ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ሚስ ሉሲ ከአክስቷ ከኮርኒሊያ ቤት ሔዳ አንድ ጥፋት ፈጸመች ከቤት እንደተመለሱ ጥፋቷ ከሚስዝ ካርላይል ጆሮ ደረሰ " እሷም እስኪመሽ ድረስ ከልጆች ቤት እንዳትወጣና ምግብም ከዳቦና ከውሃ በቀር ሌላ እንዳይሰጣት አዘዘች "

የዚያን ለት ማታ ኢስት ሊን ውስጥ የራት ግብዣ ነበር ባርባራ ከመልበሻ
ክፍል ገብታ የራት ልብስ ለብሳ አዲስ የተቀጠፉ ቀይና ወይን ጠጅ አበባዎች
ከጸጉሯ ሰካች " ከደረቷም ተመሳሳይ ቀለም ያለው አበባ አድርጋ ፀሐይ መስላ
አሸበረቀች " ራት የሚበላው በአንድ ሰዓት ነው " አሁን 0ሥራ ሁለት ተኰል ቢሆንም ከሚጠብቁት እንግዶች አንድም ብቅ አላለም " ባርባራ አሁንም ሰዓቷን በጉጉት ትመለከታለች "

ማዳም ቬን ቀስ አድርጋ በሩን መታ መታ አደረገችው " ራት ተበልቶ
ከበቃ በኋላ ወይዛዝርቱ ወደ ሳሎን ሲመለሱ ' አብራቸው ለግማሽ ስዓት እንደትቆይ ቃል ተገብቶላት የነበረችው ሉሲ በተወሰነባት ቅጣት የተገባላት ቃል ሊቀርባት ስለሆነ በጣም ተጨነቀች " ማዳም ቬን ጭንቀቷን አይታ ይቅርታ ልትለምንላት መጣችና እየፈራች እየቸረች በሩን መታ መታ አድርጋ ገብታ ለሚስዝ ካርላይል ነገረችላት "

“ ማዳም .ይህችን ልጅ ልቅ ሰደሽ አበላሸሻት የምትቀጭያትም
አይመስለኝም » ስታጠፋም መታረም አለባት ” አለቻት ባርባራ

“ በጥፋቷ ተጸጽታለች ” አለች ማዳም ቬን " “ እንግዲህ ምንም ላታጠፋ ቃል ትገባለች " አሁንም በልቅሶ ፈርሳ ልትሞት ነው።

“የምታለቅሰው በሠራችው ጥፋት ተጸጽታ ሳይሆን ከሳሎን መግባቱ እንዳያመልጣት ፈርታ ነው "

“ አባክዎን ይቅር ይበሏት ” ብላ ለመነች ማዳም ቬን "

“ እስኪ አስብበታለሁ " እይውማ ማዳም ቬን ይኽ አሁን ተሰበረብኝ ' አያሳዝንም ? አለችና ባርባራ አንድ የወርቅ ሥራ ያለበት ጌጥ አሳየቻት "

ማዳም ቬን ተቀብላ መረመረችው አጣብቆ ሊይዘው የሚችል ማጣበቂያ ከላይ ከፎቅ አለኝ " በሁለት ደቂቃ ውስጥ አላቅቀዋለሁ” አለቻት "

“ ኧረ እንግዲያውስ በይ እስቲ ማጣበቂያውን እዚህ አምጪና ሥሪው " ጉቦ ልስጥሽ ” አለቻት እየሣቀች
እሱን መልሰሽ እንደ ነበረው አድርጊውና ለሉሲ ምሕረት መልእክት ይዘሽላት ትሔጃለሽ " መቸም ልብሽ የቆመው ለዚሁ ነው።

ማዳም ቬን ሔዳ ማጣበቂያውን አመጣችና ስባሪዎቹን አንሥታ እንዴት
ሊገጣጠሙ እንደሚችሉ እያየች ስታስብ ባርባራ ተመለከታለች "

“በፊትም ተሰብሮ ነበር ብላ ጆይስ ነግራኛለች” አለች ባርባራ ነገር ግን እንደማይታወቅ ሆኖ ተገጣጥሞ ይመስለኛል የት ላይ ተሰብሮ እንደ ነበር
እንኳን ለማግኘት አልቻልኩም " ይህ ዕቃ ሚስተር ካርይል የመጀመሪያ ሚስቱን ያገባ ጊዜ ለንደን ሳሉ የገዛላት ነበር " ኋላም እሷ ሰበረችው "እንዴ ምን ነካሽ ማዳም ቬን ? እጅሽ እንደሱ ከተንቀጠጠ ምንም ልትሠሪው አትችይም „

መጀመሪያም የት እንደተሰበረ ልትነግራትና ልታሳያት ስትል የሚያስከትለው ጥያቄም ወዲያው ትዝ አላትና ቃሉን ካፏ አድርሳ ተወችው » ቀጥሎም ይህን ዕቃ መጀመሪያ የሰበረችው ጊዜ እንዴት እንዳዘነችና ሚስተር ካርላይልም አብሮ ስለ ነበር ከዚሁ ክፍል ሆነው እያባበለና እየሳመ እንዴት እንዳጽናናት ስታስታውስ አሁን ደግሞ የጌጡ ዕቃም የካርላይል መሳምም የሷ መሆናቸው ቀርቶ
የባርባራ መሆናቸውን ስታስበው ቆጫት እጆቿም ተንቀጠቀጡ "

“ስሚንቶውን ከፎቅ ሳመጣ በጣም ስለ ሮጥኩ ነው እጆቼ የሚንቀጠቀጡት”
ብላ አመካኘች » በዚህ ጊዜ ሚስተር ካርላይልና እንግዶቹ ሲመጡ ተሰሙ
ሚስተር ካርይል ወደ ሚስቱ መልበሻ ክፍል ሲመጣ ማዳም ቬን ተነሥታ ልትሔድ ፈለገች

“የለም ! የለም !” አለች ባራባራ " “ጀምረሽዋል እኮ ጨርሺው አንጂ !
ሚስተር ካርላይል ወደ ክፍሉ ይሔዳል " ጉዴን አየኸው .... አርኪባልድ ? ይኸውልህ ተሰበረብኝ ”
ሚስተር ካርላይል የማዳም ቬንን ነጫጭ እጆችና የምትጠግነውን ዕቃ
እንደ ዋዛ አየት አድርጎ ወደ ራሱ መልበሻ ክፍል ሔደና በሩን ከፍቶ ባርባራን በጁ ጠቅሶ ጠራት ስትመጣ ሳብ አድርጎ አስገባት " ማዳም ቬን ሥራዋን
ቀጠሰች።

ባርባራ ቶሎ ተመልሳ ማዳም ቬን አጆቿን ከጓንቲዎ ስትከት ቁማበት
ወደ ነበረው ጠረጴዛ መጣች ዐይኖቿ ረጥበው ነበር "

“ዐይኖቼ የደስታ እንባ ሲያለቅሱ መግታት አልቻልኩም” አለቻት ባርባራ ምልክቱን እንዳየችባት ስትገነዘብ “ሚስተር ካርሳፈላይል ወንድሜ ነጻ መሆኑን ተከሳሾቹ አርስ በርላቸው መወነጃጀላቸውን ሎርድ ማውንት እስቨርንም ከችሎቱ መኖራቸውን ' አባባም ሰብሳቢ ሆኖ መዋሉን ነው አሁን የሚነግረኝ" አለቻት ' ለማዳም ቬን "

ማዳም ቬን ይበልጡን ወደ ያዘችው ሥራ አቀረቀረች "

“ማረጋገጫ ተገኘባቸው ? አለች ዝግ ባለ ደካማ ድምጿ "

“ የሌቪሰን ጥፋተኛነት ምንም አያጠራጥርም " ኦትዌይ ቤቴል ግን ምን
ያህል በነገሩ እንደ ገባ እስካሁን ገና አልታወቀም ግን ሁለቱም ለፍርድ እንዲቀርቡ ተወስኗል " በተለይ ያ እርኩስ ያ መናጢ ! በደሉ ሁሉ ባደባባይ ተገለጠበት” እያለች የደስታው ሲቃ ሲተናነቃት' ማዳም ቬን ቀና ብላ አየት አደረጋቻት

“ከሁሊ የሚገርመው ደግሞ ” አለች ባርባራ ድምጿን ዝቅ አድርጋ ''ያቺ
ክልፍልፍ አፊ ድፍን ዌስት ሊንና እኛ ሳንቀር ( ከሪቻርድ ጋር ኮበለለች ስንል
እሷ ግን ይህን ያህል ጊዜ ' ከፍራንሲዝ ሌቪሰን ጋር አንደ ነበረች ገና ዛሬ ሚስተር ቦል ሲያናዝዛት ታወቀባት ”

“መቸም እኔ ሚስተር ካርይል ቢሰማው ደስ አይለም እንጂ እሱም ልክ
እንደ ሎርድ ማውንት እስቨርን በጣም ነው የሚሰማው " ምንም ቢሆን ሚስቱ ነበረች » ይህን ታውቂያለሽ አይደለም ? ልጆቹም ሁሉ የሷ ናቸው " አሁን የተመሰገነና የተከበረ ነው • ወይዘሮ ሳቤላ የጣለችበትን የመሰለ : ውርደት ሊጠጋውና ሊነካው የማይችል ንጹሕ ሰው ነው ”

የመጀመሪያው እንግዳ ሠረገላ ሲገባ ተሰማ " ባርባራ በረረችና ከሚስተር
ካርላይል ክፍል አንኳኰታ “ አርኪባልድ ... ትሰማለህ ? አለችው "
“እሺ እመጣለሁ ደሞ እኮ አዲስ የሕዝብ እንደራሴ ለሆነ ሰው ትንሽ ጊዜ
አላት እየሣቀ

ባርባራ ያችን መከረኛ ሴትዮ በማጣበቂያው የተሰበረን የሽክላ ጌጥ
እየጠጋገነች : ጭንቀቱ ካላለቀለት ልቧ ጋር የቻለችውን ያህል እንድትታገል ትቴት ወደ ሳሎን ወረደች " ሁልጊዜ በማንኛው አጋጣሚ በነገር ስለት መወጋቱ አላቋርጥ አለ " ጠቅ ጠቅ በጊዜው በየምክንያቱ ጠቅ « መቸም እሷም ኢስት ሊን ለመመለስ የወሰነች ጊዜ ለቅጣቷ መቆሚያ እንዳይኖረው አድርጋዋለች " ዘለዓለም በትዝታ ' በነገር መወጋት ' በጸጸት አለንጋ መገረፍ ልማድ ሆነ።

ከሚስተርና ከሚስዝ ሔር በሸር እንግዶቹ ሁሉ ገቡ " ጆስቲስ ሔር ጤንነት
ስለ አልተሰማው ሁለቱም መቅረታቸውን የሚገልጽ ማስታወሻ ለባርባራ ደረሳት

ሳቤላ በሠራችው ሥራ ቅጣቷን እጅግ በከፋ አጠፌታ እንደ ተቀበለችው
ሁሉ ጀስቲስ ሔርም በመጠኑ የሥራ ዋጋ ሳይደርሰው አልቀረም " ስለዚህ ጤንነት ባይሰማው የሚያስግርም አይሆም " በማንኛው ነገር አንድ ጊዜ ተስቶት ከአፊ ፍቅር ሲይዘው በቀር ምንም የማያስቀይመውን ልጁን በድሎታል አንገላቶታል " የሱን ሥራ ዌስት ሊን አይዘነጋውም " ያ በልጁ ላይ ያሳየው ጥላቻ
አሁን ደግሞ መልኩን ለውጦ ደስ የማይል ኃይል ሆኖ ተመልሶበታል ሀይሉ
ከሕሊናው ጋር የመረረና የከረረ ጦርነት ገጥሟል "

“እእ...እኔ እኮ አሳድኜ አስገድየው ነበር ! አየሽ ' አን” አለ ጀስቲስ
ሔር ከወንበሩ ላይ ተቀምጦ ላቡን ከግንባሩ እየጠረገ ፥
👍122👏1
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰባ_አንድ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

ፀደይ ዐለፈ " በጋ ተተካ " እሱም ያልፋል : አሁን ሞቃቶቹ የሰኔ ቀኖች
ገብተዋልና መውጫቸውም ይደርሳል " ሚስተር ካርላይል ከተመረጠበት ከሚያዚያ ወር ጀምሮ ወሮች ሲለዋወጡ ምን ክሥተቶች ታይተውባቸዋል ?

የሚስተር ሔር በሽታ ከመሰለል አደረሰው " ሰዎች ልጅን ያለአግባብ
ሲበድሉ ኖረው መሳሳታቸውን በሚገነዘበቡት ጊዜ ' ' ተሳስቼ ኖሯል በማለት ብቻ የጃቸውን ሳያገኙ ይቀራሉ ማለት ዘበት ነው " ይህ ሁኔታ በሚስ ጀስቲስ ሔር
ላይም ታይቷል ። ከበሽታው በጎ እየሆነ ሔዷል " ነገር ግን የበፊቱ ጀስቲስ ሄር መሆን አይችልም : ጃስፐር የጌታውን መታመም ሊነግር ኢስት ሊን ሔዶ በነበረ ጊዜ የተፈጠረው የእሳት ድንጋጤም ከዊልያምና ከጆይስ በቀር ማንንም አልጐዳም " ዊልያምን ብርድ መታውና የሳንባ በሽታውን አባባሰበት ጆይስ ከዚያ ወዲህ ፍራት አደረባት " በውኗ እያለች በሕልም ያለች ትመስላለች " ድንገት ሲናገሯት ትበረግጋለች አንዳንድ ጊዜ አንድ ሰዓት
ሙሉ ሐሳቧ ይዟት ጭልጥ ይላል።

ሚስተር ካርላይልና ሚስቱ የሚስተር ሔር በሽታ ለክፉ እንደማይሰጠውዐእንዴረጋገጡ ወዲያውም ወደ ለንደን ሔዱ : ዊልያም አባቱ ከሱ እንዲለየው ስላልፈለገና የለንደን ሐኪሞች እርዳታ ይጠቅመው ይሆናል በማሉት አብሮ ሄዷል " ጆይስ ከሌሎች ሠራተኞች ጋር ተከትላ ሔዳለች "

ለንደን ሲደርሱ የስር ፍራንሲዝ ሌቪሰን መያዝ አፍላ ወሬ ሆኖ አገኙት "
ነገሩ ለለንደን ስዎች ሊገባቸው አልቻለም : ብዙ የማይመስሉና የማይሆኑ ነገሮች ሲወሩ ዜናው ለዘጠኝ ቀኖች ያህል ብርቅና ድንቅ ሆኖ ሰነበተ እነሱ ለንደን የገቡ ዕለት ማታ አንዲት ልጅ እግር ቆንጆ ሴት፡ ንገሩልኝ ብላ እነሱ ከነበሩበት ክፍል ገባች ስሟን መግለጽ ባትፈልግም ሚስተር ካርላይል ሲያያት
የመጀመሪያ ሚስቱ ባልንጀራ የነበረችው የብላንሽ ሻሎነር መልክ ትዝ አለው እሷ ግን ብላንሽ አልነበረችም "

እንግዳይቱ ባርኔጣውን በጁ ይዞ ሊወጣ ቁሞ ያገኘችውን ሚስተር ካርላይልን እያየች ' “ በአጉል ሰዓት በማስቸገሬ ይቅርታ ያድርጉልኝ " የመጣሁት አንድ የሰው ልጅ ከሌላው ለማግኘት የሚፈልገውን እርዳታ ለመለመን ነው " እኔ
አመቤት ሌቪሰን ነኝ ” አለችው"

ባርባራ ፊቷ ደም መስለ ። ሚስተር ካርላይል እንግዳይቱን በአክብሮት
ወንበር ላይ አስቀምጦ እሱ ቈሞ ዝም አለ ። እሷም ትንሽ ተቀምጣ ከመጨነቋ የተነሳ ተመልሳ ብድግ አለች

“ኣዎንታ እኔ ያን ሰው ባሌ ለማለት የተገደድኩት እመቤት ሌሺሰን ነኝ " ክፋቱን በፊትም ዐውቀዋለሁ አሁን ደግሞ ወንጀለኛ ሆነ ይባላል ትክክለኛነቱን ግን የሚያረጋግጥልኝ አጣሁ " ሎርድ ማውንት እስቨርን ዘንድ ሑጄ ብጠይቃቸውም ሊነግሩኝ አልፈቀዱም " ስለዚህ ሚስተር ካርላይል ዛሬ ለንደን ይገባሉ ሲባል ስምቸ ለመጠየቅ መጣሀ "
ስትናገር ሰውነቷ እየተርገፈገጸ ድምጿ እየተቆራረጠ ስለ ነበር ከውስጧ የሚገነፍልባት የስሜት ግፊት ይታወቅባት ነበር "

“ ይህ ሰው ሁለታችንንም በድሎናል ...ሚስተር ካርላይል ሰውየው እንዲበድለኝ ያደረግሁ እኔ በገዛ እጄ ነው እርስዎ ግን አይደሉም « የሱ በደል
የደረሰባት እኅቴና አሁን ዘጠና ዓመት የሚጠጋቸው አያቱ ሚስዝ ሌቪሰን አስ
ጠንቅቀውኝ ነበር ከማግባቴ አንድ ቀን ቀደም ብለው አያቱ እኔ ድረስ ለዚ
ሲሉ መጥተው ፍራንሲዝ ሌቪስን ባገባ ዕድሜ ልኬን ሳለቅስ አንደምኖር አሁንም የገባሁትን ቃል ለማጠፍ በቂ ጊዜ እንደ ነበረኝ ሲነግሩኝ አልተቀበልኳቸውም " ጊዜ ነበረኝ ፍላጎት ግን አልነበረኝም " በግብዝነት ' በሞኝነት በተለይም ለመካር እኅቴ እልክ ስል አገባሁት የሱን ስም የሚወርስ ልጅም ወልጃለሁ ... ይፈርድበት ይሆን ሚስተር ካርላይል ?”

እስከ አሁን በደንብ የተረጋገጠበት ነገር የለም” አላት ሁኔታዋ እያሳዘነው

“አሁን ከሱ የምፋታበትን መንገድ ባገኘሁ " አለች ራሷን መቈጣጠር እንደ ተሳናት በግልጽ እየታየባት “ የልጄን ስም መለወጥ ብችል እንግዲህ ይህን የገባሁበትን ዘንቅ ለማረም የቀረኝ ዕድል ይኖር ይሆን ?”

ምንም አልነበራትም ። ሚስተር ካርላይልም መላ መናገር አልሞከረም "
ጥቂት የማስተዛዘኛ ቃላት ተናግሮ ሊወጣ ሲል ዐለፈችና ከፊቱ ቆመች

ለዚህ መፍትሔ ሳይነግሩኝ አይውጡብኝ ። እርስዎን አምኘ መልስ እንዶገማኝ ተስፋ አድርጌ ነው የመጣሁት

“ከባድ ቀጠሮ አለብኝ " ባይኖረኝም በራሴም ሆነ ባንቺ ምክንያት መልስ
ልስጥሽ አልፈቅድም ነበር " ነገርሽን እንዳቃለልኩብሽ አድርገሽ አትይው
እመቤት ሌቪሰን ስለ ሰውዬው ግን ላንቺ እንኳን ስናገር ስሙ ራሱ ከንፈሮቼን
ያቆስልብኛል

እርስዎ የሚናገሩት እያንዳንዱ የጥላቻ ቃል ' ቃሌ ነው የርሶዎን የንቀት አባባል ሁሉ ተቀብዬ አስተጋባለሁ ”

ባርባራ ዘገነናት ምንም ቢሆን እኮ ባልሽ ነው ! " አለቻት "ባርባራ

“ባሌ ! የበደለኝን በደልሳ ዐውቀሺዋል ? እሱ ራሱ ምን እንደ ነበርና ምን
እንዳደረገ እያወቀ ለምን ሚስት እንድሆን አሳሳተኝ ? አንቺም እንደኔ ሚስትም
እናትም ስለሆንሽ
እንደገና...ሚስዝ ካርላይል በደሌ ሊገባሽና ልታዝኝልኝ ይገባል" እነዚህ መጥፎ ሰዎች ለምን ያገባሉ ? ወንጀሉ ሕሊናውን እያኘከው
እኔን ለማግባት ሰብኮ ሰብኮ ያሳሳተኝ! ያለፈው ኃጢአቱ አነሰው የማይቴረም ከባድ ግፍ ውሎብኛል " በልጄም ላይ ተፍቆ የማይጣል አሳፋሪ ውርደት ጥሎ
በታል ”

“ ቢሆንም ባልሽ ነው
አለቻት ባርባራ "

“ እታሎኝ እኮ ነሙ ባሌ የሆነው " ስለዚህ በአደባባይ ብጠላው የሚያግደኝ የሞራል ግዴታ የለብኝም " በኔና በልጁ ይህ ነው የማይባል ጥፋትና ክፋት አድርሶብናል ኧረ ለመሆኑ” አለች ወደ ሚስተር ካርላይል ዞር ብላ' “ከእርስዎ ጋር ለመወዳደር ዌስት ሊን ሲመጣ እንዴት አስቻለዎትና ዝም አሉት

“እሱን ልነግርሽ አልችልም » ለራሴም ብዙ ጊዜ ሳስበ ገርሞኛል” አላትና በትሕትና አነጋግሮ ከሚስቱ ጋር ትቷት ሔደ " ሁለቱ ሴቶች ብቻቸውን ሲቀሩ' ባርባራ የሚስዝ ሌቪሰንን ጥያቄ ባጠቃላይ መልኩ ባጭሩ ገለጸችላት

“አንቺና ሚስተር ካርላይል በጥፋተኛነቱ አምናችሁበታል ? አለቻት "
“ አዎን ” ያንቺ የመጀመሪያ ሚስቱ ሳቤላ ቬን ዕብድ ነበረች ?
"ዕብድ ? አለች ባርባራ በመገረም "

' አዎን ' ሚስተር ካርላይልን በሱ መለወጧ!እሱን ለዚያኛው መለወጧ
ዕብዶት እንጂ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል ? አንዲት ሴት ከቪሰን ከድታ ሚስተር ካርላይልን አፍቅራ ብትሔድ ሊገባኝ ይችላል ? አሁን ያንቺን ባል ሳየው በተለይ እሱን ጥሎ ወደ ሌቪሰን የሚሔድበት ምክንያት ሊገባኝ አይችልም”
አለቻት » ከዚያ ጥቂት ተነጋግረው አሊስ ሌቪሰን ወጥታ ሔደች "

በርባራ ' ሦስት ሳምንት ያህል ለንደን ቆይታ ለጤንነቷ ለምቾቷ ተብሎ ወደ ኢስት ሊን ተመለሰች ሚስተር ካርላይልም ለንደን ከቆየ በኋላ በሐምሌ ጠቅልሎ ሲመጣ አንድ ወር የሞላት ሴት ልጅ ተወልዳ ቆየችው :

የዊልያም ሁኔታ አሽቆልቁሎ ሔደ " የዶክተር ማርቲን አባባል የለንደኑ
ሐኪምም አረጋግጦ ደገመው " ስለዚህ መጨረሻው ብዙ እንደማይቆይ ግልጽ
እየሆነ ሔደ"
👍16
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰባ_ሁለት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


የሊንበረ የችሎት አዳራሽ በጣም ሰፊ ባይሆን ኖሮ ሰር ፍራንሲዝ ሌቪሰን
በጆርጅ ሆሊጆን ማድያ የተከሰሰበትን ፍርድ ለመስማት ከመጣው ብዙ ሕዝብ አብዛኛው ቦታ ባለ ማግኘት ሳይሰማ ይቀር ነበር "

ጕዳዩ ከተከሳሹ ማዕረግ ጋር በማነጻጸር ተከሳሹ ቀደም ሲል ከነበረው ታሪክና በተለይም እመቤት ሳቤላ ካርላይልን ከሚመለከተው ሥራው ጋር በማገናዘብ
በሪቻርድ ሔር የተላለፈው ፍርድ ወንጀሉ የተፈጸመበት ዘመን መርዘም አፊ የተጫወተችው ሚና የኦትዌይ ቤቴልን ትክክለኛ ድርጊት ለማወቅ ከፍተኛ ጕጕት ነበረ የድርጊቱን ዝርዝር ትክከለኛ ገጽታ የመረዳት ፍላጐት ሁሉ
የሕዝቡን ጉጕት አራገበው » ከጠቅላላው ሕዝብ ውስጥ የሚስተር ካርላይል :
የሔር ቤተሰቦችና ወዳጆች : የሻሎነር የእስረኛው ቤተሰቦችና ወዳጆች ጭምር ነበሩ ኮሎኔል ቤቴልና ጀስቲስ ሔር ግልጽ ከሆነ ቦታ ላይ ተቀምጠው ነበር ።

ዳኞቹ ከሦስት ስዓት ጥቂት ቆይተው ተሠየሙ ኦትዌይ ቤቴል የዐቃቤ ሕግ
ምስክር እንዲሆን ተደረገ የሚል ዳኞቹ ገና ሳይሠየሙ ወሬው ካፍ ወደ አፍ ሲሸጋግር ቆይቶ ነበር " የዚህንም ወሬ ትክክለኛነት ለመስማት የጓጉ ሁሉ አንገታቸውን እያስገጉ ለማዳመጥ ይጠብቁ ጀመር

ቀደም ሲል የሰጡትን ምስክርነት መድገም አላስፈለገም ነበር " የጎደለ
ቢኖር አንዳንዶቹ እየተጠየቁ ካስተካከሉ በኋላ'ያልተሰሙ ምስክሮች እንዲስሙ
ተደረገ።

“ሪቻርድ ሔርን ጥራ ” አለ ዳኛው

ሚስተር ሔርን የሚያውቁ ሁሉ ስሙ እየተጠራ ለምን እንደማይነሣ ራሳቸውን እየጠየቁ ሲደነቁ ሪቻርድ ሔር ትንሹ” ብቅ አለ "
በፍርድ ቤቱ አዳራሽ የነበረው ሕዝብ ሲንሾካሾክ ተሰማ " የተሰደዶው ሞተ የተባለው አሁንም ሕይወቱ በአጠራጣሪ ሁኔታ ያለው ሪቻርድ ሔር ሲዘልቅ አጫጭሮች ደኅና አድርገው ለማየት እየተንጠራሩ በግሮቻቸው ጫፍ ቆሙ።ሰብሳቢው ሁሉም ጸጥ እንዲል ጠየቀ ሁለት መኮንኖች ቀስ ብለው መጥተው ከኋላ ቆሙ እሱ ሊያቀው ባይችልም በጥበቃ ሥር ዋለ በደንቡ መሠረት ምሎ ማንነቱን ሁሉ ተናግሮ ምስክርነቱን ቀጠለ

“እስረኛውን ዞር በልና ደህና አድርገህ ተመልከተው
“ታውቀዋለህ ?

“ አሁን ስር ፍራንሲዝ ሌቪሰን መሆኑን ዐወቅሁት እስካለፈው ሚያዝያ
ድረስ ግን ስሙ ቶርን መሆኑን ነበር የማውቀው

እስኪ የግድያው ዕለት ማታ እስከምታውቀው ድረስ የሆነውን ንገረን ።”
“ ያን ዕለት ማታ ከአፊ ጋር ቀጠሮ ስለ ነበረኝ ወደ ቤታቸው ሔድኩ "
ቀጠሮህ በምስጢር ነበር ?”

"በከፊል ከዎን » ከአፊ ጋር የመቃረቤን ነገር ወላጆቼ ስለማይወዱልኝ
እኔም መሔዴን እንዲያውቁ አልፌልግም ነበር " ስለዚህ ከራት በኋላ ጠበንጃ ይዤ
ስወጣ አባቴ የምሔድበትን
ቢጠይቁኝ ቦሻ ዘንድ ብዬ ዋሽቼ ሔድኰ እኔ ግን ለሆሊጆን ላውሰው ቃል ገብቸለት የነበረውን ጠበንጃ ይዠ ከቤቱ ስደርስ
አፊ ሥራ አለብኝ ብላ እንዳልገባ ከለከለችኝ " እኔም ቶርን ከቤት መኖሩ
ገባኝ " ከዚያ በፊትም እሷ በሰጠችኝ ቀጠሮ እየሔድኩ ከአንድ ጊዜ በላይ ከውጭ
መልሳኝ ነበር እኔም እንቅፋት እየሆነ ከደጅ እንድመለስ ያደረገኝ የቶርን
ከቤት መኖር መሆኑን ደጋግሜ ደርሸበት ነበር " "

“ከቶርን ጋር ትቀናኑ ነበር ማለት ነው ?

“የሱን አውቅም እኔ ግን በርግጥ እቀና ነበር ” አለ ሪቻርድ

“ እሺ ቀጥል የምሽቱን ሁኔታ "

“ከሷ ጋር ብጨቃጨቅም እንዳላስገባችኝ ቁርጡን ሳውቅ ጠበንጃው መጕረሱን ነግሬያት ለአባቷ እንድትሰጥ አስረክቤያት ተመለስኩ "ቶርን ከቤት
መኖሩን ስለ ካዶች እውነቷን መሆኑን በዐይኔ አይቸ ለማረጋገጥ ወደ ዱር ገባ ብዬ ተሸሽጌ እመለከት ጀመር " ሎክስሌይ አየኝና ለምን እንደ ተሸሽግሁ ቢጠይቀኝ ምንም ሳልመልስለት ዝም አልኩ ግማሽ ሰዓት ሳልቆይ ከሆሊጆን ቤት በኩል
ተኩስ ሰማሁ " እንግዲህ ሆሊጆንን የገደለው ያ ተኩስ ነበር "

“ ተኩስ በኦትዌይ ቤቴል ሊተኮስ የሚችል ይመስልሃል ?

አይችልም " እሱ ከነበረበት ራቅ ብሎ ነበር የተተኮሰው ቤቴል ከነበረበት ጠፋ " ወዲያው አንድ ሰውዬ ፊቱ ጭው ብሎ ገርጥቶ • ዐይኖቹን አፍጦ ቁና ቁና እየተነፈሰ ልቡ እስኪወልቅ እየበረረ መጣና ሽው ብሎ ዐልፎኝ ሲሔድ ቶርን መሆኑን አየሁት " ከኔ ዐልፎ እንደ ሔዶ ወዲያው የፈረስ ኮቴ ሰማሁ "ከዱሩ አስሮት ነበር "

“ተከተልከሙ ?

“ የለም " ምን እንደዚያ እንዳደረገው እየገረመኝ አፊ ለሁለታችንም አለው
እያለች ስለ አታለለችኝ ልሰድባት እየሮጥኩ እንደ ገባሁ አነቀፈኝና ከተዘረረው
የሆሊጆን ሬሳ ላይ ወደቅሁ " ነፍሱ ወጥቶ ከመዝጊያው ሥር ወድቆ ነበር" ጠበንጃዬ ጥይቱ ተተኰሶ ቀፎው ብቻ ከወሉሉ ተጥሉ አገኘሁት "

በአዳራሹ ውስጭ ጸጥታ ስፈነ "

“ከቤቱ ውስጥ ማንም አልነበረም አፊንም ብጠራት አልመልስልኝ አለች”
ጠበንጃዬን አነሣሁና ከቤቱ ወጥቼ ስሮጥ ሎክስሌይ ከዱሩ ወጥቶ አየኝ ግራ
ገባኝ ፈራሁ " ጠበንጃውን መልሼ ከነረበት ጣልኩና ሮጥኰ "

“ ስሸሽ ቤቴልን አገኘሁት ተኩሱ እንደ ተሰማ ወዶ ሆሊጆን ቤት ከሔደ በኋላ ተመልሶ ወደ ዱሩ ስለ ገባ ማንንም አለማየቱን " ሲነግረኝ አመንኩትና
ጥየው ሄድኩ።

“ታዲያ ዌስት ሊንን ለቀህ ሔድክ ?”

በዚያው ሌሊት ለአንድ ሁለት ቀን ዘወር ብዬ ቆይቸ ሁኔታውን ለማየት ነበር አሳቤ "

ምርመራው ቀጠለ " በመጨረሻ ጥፋቱ በኔ ላይ ተጣለ " ስለዚህ ካገር ጠፋሁ።

ቀጥላ አፊ ሃሊዮን እንደገና ተጠራች « የሰጠችው ምስክርነት ከሬቻርድ
አነጋግር ጋር አንድ ሆነ "

ከዚያ ኦትዌይ ቤቴል ተጠራና የምስክርነት ቃሉን ሰጠ።

"ሆሊጆን የተገለ ማታ አይ ጫካ ውስጥ ነበርኩ " ሪቻርድ ሔር ከወደ
ቤቱ ጠበንጃ ይዞ ሲወርድ እየሁት "

" ሪቻርድሳ አይቶህ ነበር?”

የለም " ከጫካው ገባ ብዬ ስለ ነበር ሊያየኝ አይችልም ነበር " ከቤቱ በር እንደ ተጠጋ አፊ ቶሎ ወጣችና መዝጊያውን በስተኋላዋ ይዛ ካነጋረችው በኋላ ጠበንጃውን ተቀብላው ገባች ራቅ ብዬ ስለ ነበር የተነጋገሩትን አልሰማሁም እሱም ከዚያ ቤት ተመልሶ እኔ ከነበርኩበት ርቆ ሔደ ሲደበቅ አየሁት ምን እንዳስደበቀው ሳስብ ከሆሊጆን ቤት በኩል ተኩስ ሰማሁ "

“ የተተኮሰው በሪቻርድ ሊሆን ይችላል ?

አይችልም » ተኩሱ የተሳማበት አካባቢ ከሪቻርድ ሔር ይልቅ ለእኔ
ይቀርብ ነበር "

"ቀጥል ”

“የተኮሰው ማን እንደሆነ ለመገመት እንኳን አልቻልኰም » ነገሩን ይበልጥ ለማወቅ ተኩሱን ወደ ሰማሁበት ቦታ ሳመራ ካፒቴን ቶርን እያለከለከ ሲሮጥ መጣ በጣም መደንገጡና መረበሹ ከገጽታው በግልጽ ይታይ ነበር " ዐልፎኝ ሊሔድ ሲል ክንዱን ያዝኩና፡“ምን ሆነሃል ? የተኮስከው አንተ ነበርክ? ” አልኩት

“ቆይ ለምን ጠረጠርከው ?

“ደንግጦ ነበር መጨነቁንና መርበትበቱን በቀላሉ ዐወቅሁበት እንዲያም ስይዘሙ ጊዜ በጣም ተጨነቀ " ነጥቆኝ ሊሔድ ሞከረ አልሆነለትም ።
ስለዚህ ነግሩን ማለስለስ ፈለገ“ ዝም እንድል ነገረኝ “የዝምታሀን ዋጋ እሰጥሃለሁ » ሳይታሰብ በንዴት ያደረግሁት ነው ሰውየው ሁልጊዜ ይሰድበኛል ልጂቱን " ምንም አላደረግኋትም” አለኝና የሃምሳ ፓውንድ ኖት በእጄ ሸጎጠልኝ » የሆነ ነግር ያልሆነ ማድረግ አይቻልም " ስለዚህ እኔን ማየትህን መናገር ለምንም አይጠቅምህም ሲለኝ ፡ እኔም ያንን ገንዘብ ወሰድኩና እንደማልናገር
ነገርኩት " ነገር ግን ሰው መግደሉን አላወቅሁም !አልጠረጠርኩም ነበር »

“ ታዲያ ምን ተደርጓል ብለህ አሰብh ?”
👍17👎1
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰባ_ሦስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

ሳቤላ ዊልያም ካርላይል ከሚያጣጥርበት አልጋ ጎን ተንበርክካለች ያች የማትቀረው የመጨረሻ ሰዓት ደርሳለች " ልጁም ቁርጡን ዐውቆ ከመራራዋ
ዕድሉ ጋር ታርቆ መንፈሱን አርግቶ ዟ ብሎ ተዘርግቶ ይጠብቃል "

በጉንጮቹ ይታይ የነበረው ደማቅ የትኩሳት ቅላት ለቋል ፊቱ ነጥቷል
አጥንቱ ወጥቷል " ዐይኖቹ ትልልቅና ደማቅ ሆነዋል ቅላት የቀላቀለው ሐርማው ጸጉሩ ወደ ኋላ ተቀልብሶ ተኝቷል " እንደ እሳት የሚፈጁት ትናንሽ እጆቹ
ከአልጋው ውጭ ተዘርግተዋል "

“ እንግዲህ ብዙ የምትጠብቅ አይመስለኝም አይደለም ማዳም ቬን ”?

"ለምኑ ነው የኔ ልጅ ? ”

“ሁሉም እስኪመጡ" አባባ እማማና ሉሲ ሁሉም „”
ግንባሯን ( ድርቅ ብሎ ከከሳው ክንዱ ላይ አንተርሳ ከላዩ ላይ ተደገፈችና
እንባዋን አፈሰሰች "

ዊልያም ጥቂት ካሰበ በኋላ “ አየሽ . . '' ድምፁ ወደ ውስጡ ሰጠመ ምልስ ሲልለት እያመነታ ስለ ወላጅ እናቱ አየሽ . . ደግ ሰውኮ አልነበረችም ለኛም ላባባም ክፉ ስው ነበረች እንዲያውም ተጸጽታ ይቅርታ የለመነች አይመስለኝም "

“ ዊልያም” አለች እየተንሰቀሰቀች “ከናንተ ከተለየች የነበረው ሕይወቷን በጸጸትና በኅዘን ነው ያሳለፈችው ጸጸቷ ኀዘኗ ከምትችለው በላይ ነበር " ሁል ጊዜ ስለናንተ ስለ አባታችሁ ስታስብ ነበር መንፈሷ የተሰበረ » ”

"እንዴ ማዳም ቬን ! ይህንን ነገር እማማ ካልነገረችሽ ማወቅ እትችይም አይተሻት ታውቂያለሽ ? ባሕር ማዶ ሳለች ታውቂያት ነበር ?

“ አዎን ባሕር ማዶ ዐውቃት ነበር "
“ አዬ ! ታዲያ ለምንድነው ነግረሽኝ የማታውቂ ? ምን አለችሽ ? ምን ትመስል ነበር?”
“ ከልጆቿ መለየቷን ስትነግረኝ ነበር " ነገር ግን አንድ ቀን እንደምታገኛቸውና ለዘለዓለም አብራቸው እንደምትኖር ትነግረኝ ነበር

"ፊቷ ምን ይመስል ነበር ? ”

“ ያንተን ይበልጡን ደግሞ የሉሲን ይመስል ነበር ”
"ቆንጆ ነበረች ? ”
ትንሽ ዝም አለችና ' ' አዎን ” አለችው "

“ አ ... ዬ ! ወይኔ ! አመመኝ ! ያዥኝ እስቲ ! ” አለ » ቀና ብሎ የነበረው ራሱ ዝቅጥቅጥ ከፊቱ ላይ ላቡ ክንብል ሲል ያ አንዳንድ ጊዜ የሚነሣበት
የሰውነት ዝለት የተቀሰቀሰበት መስሏት ነበር " ሳቤላ ደወለችና ዊልሰን መጣች "
ብዙ ጊዜ ከዊልያም የማትለይና አንድ ችግር ሲኖር የምትቀርብ
ጆይስ ነበረች "የዚያን ዕለት ግን የነበረውን አሳሳቢ ሁኔታ አልተገነዘበችውም ቀኑ ሪቻርድ ነጻ በተለቀቀበት ማግሥት ነበር " ሚስዝ ካርላይል ለሁለተኛ ጊዜ የታመመው አባቷን በባሏ መታመም ደንግጣ በልጅዋ ነጻ መውጣት ተደስታ የነበረችው እናቷን
ከብዙ ዘመን ስደት በኋላ ከወላጆቿ ጋር የተጨመረው ወንድሟን ለመጠየቅና አብራ ለመዋል ወደ ወላጆቿ ቤት ሔደች " ጆይስንም አስከትላ ወስዳት ነበር " በዚያ ጊዜ እግረኛው ሳይጨመር አምሳ የሚሆኑ ሠረገሎች በጀስቲስ ሔር ቤት ተሰብስበዋል " 'ይኽ ሁሉ ሰው ኮ አንተን ለማየት ነው . . ሪቻርድ” ብላው ነበር እናቱ ዐይኖቿ የደስታና የፍቅር እንባ እያቀረሩ ሉሲንና ትንሹን አርኪባልድን
ሣራ ይዛቸው ወደ ሚስ ኮርኒሊያ ቤት ሔደዋል ስለዚህ ከቤት የቆየችው ዊልሰን ብቻ ስለ ነበረች ማዳም ቬን ስትደውል ከች አለች።

"ምነው ? አሁንም ድካሙ ተነሣበት ? ” አለች ስትገባ "
“ መሰለኝ እስኪ እርጂኝና ቀና እናድርገወ ” አለቻት ሳቤላ ።
ዊልያም ግን ነፍሱን አልሳተም " ይዞታው ከተለመደው የተለየ ነበር » እንደወትሮው አቅሉን በመሳትና በመዝለፍለፍ ፈንታ ማዳም ቬንና ዊልሰንን ግጥም አድርጎ ይዞ ወባ እንደ ተነሣበት ተንቀጠቀጠ

ያዘኝ ኧረ እንዳልወድቅ ያዙኝ ደግፉኝ ” እያለ ይቃትት ጀመር ትንሽ ቆየና ጭንቀቱና እንቅጥቃጤው እልፍ አለለት ። ላቡን ከግንባሩ ጠረጉለትና ዐይን ዐይኑን ይመለከቱት ጀመር ዊልስን አንድ ማንኪያ ለስሳሳ ምግብ ካፉ ስታደርግለት ዋጠው " ልትደግመው ስትል ራሱን ነቀነቀ » ፊቱን ወደ ትራሱ
መለሰና ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ እንቅልፍ ሽልብ አደረገው "

“ ምን ነገር ነው ልጄ ?” አለች ሳቤላ ቀስ ብላ ወደ ዊልሰን እየተመለከተች
“ ነገሩን ዐውቀዋለሁ ከዚህ በፊትም የዚህ ዐይነት ሕመም አንድ ጊዜ
አይቻለሁ "

“ ምክንያቱ ምንድነው . . . ዊልሰን? አለች ሳቤላ።

"ያየሁት ባዋቂ እንጂ በልጅ አልነበረም ። ግን ልዩነት የለውም " ሁሉም በተመሳሳይ ምክንያት ነው የሚነሣው ሊሞት ይመስለኛል "

"ምን መሆንሽ ነው .. ዊልሰን ? እስከዚህኮ አልታመመም " ደሞ ዛሬ
ጧት ሚስተር ዌይንራይት አይቶት አንድ ወይም ሁለት
ሳምንት ይቆይ ይሆናል
ብሏል"

ዊልሰን ከምቹ ወንበር ላይ ተደላድላ ቁጭ አለች አስተማሪቱን እንኳን
የማክበር ልምድ አልነበራትም » አስተማሪቱም ቢሆን ደረጃዋን ጠብቃ እንድትቀመጥ እንዳትነግራት ትፈራት ነበር ሚስተር ዌይንራይትን እንዳለ አትቁጠሪው እዚህ ግባ የሚባል ሰው አይደለም ” አለች ዊልሰን " የልጁ
ትንፋሽ እየቀነሰ መሔዱን ቢያይና ትንሽ ቆይቶ ደግሞ የመጨረሻው የሚሆን ቢሆን እንኳ ከዐሥራ ሁለት ሰዓት በላይ እንደሚቆይ ለሁላችንም እየማለ ይነግረን ነበር " ዌይንራይትን እኔ የማውቀውን ያህል አታውቂውም ማዳም ። ከናቴ ቤት ሐኪማችን እሱ ነበር ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከተቀመጥኩባቸው ቦታዎች ሁሉ ሲያክም ዐውቀዋለሁ " ከስኳየር ስፒነር ቤት ዋና ሞግዚት ሆኜ አምስት ዓመት
የሚስዝ ሔር ደንገጡር ሆኘ አራት ዓመት ሠርቻለሁ " ክዚህ ቤትም ሚስ ሉሲ
አራስ ልጅ ሳለች ነበር የገባሁ " ታድያ ከነዚህ ቦታዎች ሁሉ እንደ ጥላ እየተከተለኝ ሠርቷል እመቤት ሳቤላ በሱ ላይ ከፍተኛ እምነት እንደ ነበራቸው ትዝ ይለኛል እኔ ከማስበው በላይ ይገምቱት ነበር።

ሳቤላ ምንም ሳትመልስ ዊልያምን ዐይን ዐይኑን እያየች ዝም አለች "

የትንፋሹ ድምፅ እየጐረነነና እየከበደ ሔደ »

" ያቺ ሣራ ” አለች ዊልሰን “ መቸም ከብት አይደለች ! ከየትኛው የወንድ አያቱ አጠገብ ይቀብሩት ይሆን ? " አለችኝ " “ እኔ ደግሞ እናቱ
የሚስተር ካርላይል ሚስት እንደሆነች ብትሞት ኖሮ እሷ ካባቷ አጠገብ ስለምትቀበር እሱም ከናቱ ጎን ይቀበር ነበር " አሁንማ ከአባቱ አባት ጎን ነው መቀበር ያለበት አልኳት።

ሳቤላ የልጁን ማንቋረር ብቻ እያዳመጠች ዝም አለቻት ዊልስን ርዕስ ቀየረች

“ አዪጉድ ! አሁን ያ መልከ መልካም ጎበዝ ምን ይመስለው ይሆን ?” አለቻት በማሾፍ » ሳቤላ ሙሉ ሐሳቧ በልጁ ላይ ስለ ነበር ስለሱ የተናገረች መሰላትና እሷም በመገረም ቀና ብላ አየቻት "

“ ያንኮ ሊንበራ ወህኒ ቤት የገባውን ሽቅርቅር ማለቴ ነው " መቸም ከትናንት ጀምሮ ያለው መኖር መኖር' አይሆንም " አቤት!እሱ በሚሰቀልበት ቀን ስንት ባቡር ሙሉ ሕዝብ ለማየት ይሔድ ይሆን ? ”

“ ተፈረደበት እንዴ ? ” አለች ሳቤላ ስልል ባለው ድምጿ "

“ተፈረደበት ሚስተር ኦትዌይ ቤቴል ተለቀቀ » ሪቻርድ ሔርም በነጻ ተለቀቀ መቸም አምሮበታል ይባላል " እሱ በነጻ ሲለቀቅማ ከፍርድ ቤቱ ሙስጥ
ጭብጨባው ውካታው ቀለጠ ዳኛው እንኳን መቆጣጠር አልቻለም ነበር ይላሉ ”

“ ማነው ሪቻርድ ሔር ወደ ቤቱ ተመለሰ ያለው” አለ ዊልያም ድክም ባለና
እንደ ልብ በማይሰማ ድምፁ "
👍10
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰባ_አራት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ሚስተር ካርይል ምልስ ብሎ ልጁን ከደረቱ እቅፍ ሲያደርገው እንባው ፈሰሰ
አየወረደ የልጁን ፊት አራሰው “ የኔ ልጅ ... አባባ አሁን ይመለሳል " አማማን
እንድታይክ ሊያመጣት ነው


"አናም አብራ ትመጣለች ? ደስ የምትል ልጅ ናትኮ”

"አዎን ከፈለግሃት ሕፃኒቱ አናም ትመጣለች » እነሱን ካመጣኋቸው በኋላ
ካጠግብህ ንቅንቅ አልልም

“ በል እንግዲያሙስ አስተኛኝና ሒድ "

ሚስተር ካርላይል እንባው እየወረደ ልጁን ከሚመታው ልቡ አስጠግቶ
እ.... ቅ ....ፍ ካደረገው በኋላ ትራሱን አመቻችቶ አስተኛው አሁንም
እንድ ማንኪያ የንጆራ ጭማቂ ሰጥቶት እየተጣደፈ ሔዶ "

“ ደኅና ሁን .. አባባ ” አለ ልጁ በደካማው ድምፁ » እሱ ግን አልሰማውም " ሳቤላ ከተንበረከከችበት ብድግ ብላ እጇን ወደ ሰማይ ሰቅላ እንባዋ
ዝርግፍ ዝርግፍ ብሎ እየወረዶ ትንሰቀሰቅ ጀመር

"ዊልያም . . የኔ ዓለም ፡ በዚች የሞት ሰዓት እናት ልሁንልህ " ስትለው
እንደ ገና የደከሙት ዐይኖቹን ገለጠ " ነገሩ እሷ ካለችው ዐይነት አልገባውም

“ አባባ ኮ ሊያመጣት ሔዷል ”

“ እሷን አይደለም የምልህ " እኔ እኔ ” አለችና አቋረጠችው " ከአልጋው ላይ ተደፍታ ዝም ብላ ትንሰቀሰቅ ጀመር " በዚያች በመጨረሻ ስዓት እንኳን እኔ እናትህ ነኝ ' ልትለው አልደፈረችም "

ዊልሰን ተመልሳ መጣችና “ እንቅልፍ የወሰደው ይመስላል ” አለቻት "
“ አዎን ” አለች ሳቤላ “ግድየለም ሒጅ አንድ ነገር ሲያስፈልገው እጠራሻለሁ

ዊልሰን ክፉ ሰው ባትሆንም ከዚያ የጭንቀት ክፍል መቆየቱን ስላልወደደች ወጣች " ሳቤላ ብቻዋን ቀረች " እንደገና ተንበረከከችና..... ወዲያው የዱሮው ትዝታ መጣባት " የሚስተር ካርይል ሙሽራ
ሆና ኢስት ሊን ከጎባችበት ጀምሮ እስከ ዛሬ የነበረውን ታሪኳን አሰበች "
ይህ የዱሮ ታሪኳ በየመልኩ ስታስበው አንዱ እያለ ሌላው እየተተካ እስካሁኑ ሁኔታዋ ድረስ በሐሳብ እንደ ተዋጠች አንድ ስዓት ዐለፈ " ልጁም አላስቸገረም » ሚስተር ካርላይልም ኤልተመለሰም በዚህ ሁኔታ ላይ እንዳለች ጆይስ ደረሰች ሳቤላ ከተንበረከከችበት ብድግ አለች " ጆይስ ቀጥታ መጣችና ዊልያምን
ለማየት ልብሱን ገለጥ አደረገች ዊልያም እንደሚፈልገኝ ጌቶች ነገሩኝ አለችና ስታየው ክው አለች " ማዳም ቬንም አደናገገጧን አይታ ወደ ጀይስ ጠጋብላ
እየች » ጢስ የለበሰው ለጋ ፊት ጸጥ ብሎ ተኝቷል - ያች ሁልጊዜ ዲም -ዲሞ
ስትል የኖረችው ትንሽ ልብም ሥራ አቁማለች "

ራሷን መቆጣጠር አቃታት " እንደሚሞት ተረድታ ሞቱንም በጸጋ በእርጋታ እንደምትቀበለው አምናና ዐውቃ ተቀምጣ ነበር ግን እንደዚያ ቶሎ የሚሞት እልመስላትም " ቢያንስ በጥቂቱ ሰዓት ዕድሜ እንደሚኖረው ገምታ ነበር "
አሁን ሳታስበው እንደ ደራሽ ጎርፍ ቀደማት " ጮሽች ተንሰቀሰቀች : ተጣራች
እላዩ ላይ ወደቀች ጥምጥም አድርጋ ይዛ አቀፈችው " መነጽሯንና ዐይነ ርግቧን ወረወረች » የድሮ መልኳ እንደ ነበረው ቁጭ አለ ፊቷን ከፊቱ አድርጋ አንድ ጊዜ ወደሷ ምልስ እንዲልላት ለመነችው ወደሷ ወደምትወደው ወላጅ እናት
ምልስ ብሎ ስማ እንድታስናብተው ጠራችው።

ጆይስ ከልጁ ሞት ይልቅ የሷ ሁኔታ አስደነገጣት » እንድታስብ ልብ እንድትል ያለችበትን ሁኔታ እንድትግነዘብ ለመነቻት በመጨረሻ ያለ የሌለ ጉልበቷን ተጠቅማ ካቀፈችው የልጁ ሬሳ አለያየቻት "

"ኧረ እመቤቴ ይተዉ ! ይተዉ !

'እመቤቴ ስትላት ነገሩ ልብ ራሷን መታት በዚህ አኳኋን ነበር ዱሮ ጆይስ የምትጠራት ድርቅ ብላ ደነገጠች » ስታብድ የነበረው ኩምሽሽ አለች "
ጆይስን ትክ ብላ አየቻትና የኋሊት አፈፈገች ;

“ እሜቴ . . ይበሎ እንግዲህ ወደ ክፍለዎ ልመሰድዎ " ሚስተር ካርላይል ሚስታቸውን ይዘው እየመጡ ነው " ከፊታቸው እንደዚህ ሆነው አይቆዬዋቸው እባክዎን ቶሎ ይምጡ ”

"አንቺ . . እንዴት ዐወቅሽኝ ?

“እሜቴ . . እሳት ተነሣ ተብሎ ሌሊት ተበራግገን የተነሳን ዕለት ነበር ያወቅኦ " ሕፃኑን አርኪባልድን ከዕቅፍዎ ለመቀበል ስጠጋ ሳይዎ በመንፈስ እንጂ በአካል የተገናኘን አልመሰለኝም " ፊትዎ አልተሸፈነም " በጨረቃው ብርሃን እንደ ፀሐይ ቁልጭ ብሎ ታየኝ ትንሽ ቆይቼ ድንጋጤዬ ለቀቅ ሲያደርገኝ ከእሜቴ ሳቤላ ጋር በአካል መግናኘቴን ተረዳሁ " ይበሉ አሁን እንውጣ ሚስተር ካርላይል ሊገቡ ነው " አለቻት ጆይስ

“ጆይስ . . እዘኝልኝ አታጋልጭኝ ለቅቄ እሄዳለሁ እስካለሁ ድረስ ምሥጢሬን ጠብቂልኝ አደራሽን "

“እሜቴ አይሥጉ " እስከ ዛሬ ድረስ ችዬው ኖሬአለሁ አሁንም እችለዋለዑ"
በርግጥ ወደዚህ በመምጣትዎ ተሳስተዋል " እኔም ካሁን አሁን ምን ይፈጠር ይሆን ? እያልኩ የልብ ሰላም የሌት እንቅልፍ አጥቻለሁ "

"ሰማሽ ጆይስ . . ከነዚህ ካልታደሉት ልጆቼ ተለይቼ መኖሩ አቃተኝ እኔ ግን ወደዚህ በመምጣቴ የተቀጣሁ አይመስልሽም ? እሱን ባሌን የሌላ ባል
ሆኖ ማየቱ ቀላል ነገር ነው ? ይኸ ራሱ አየገደለኝ ነው።

“ ኧረ ይምጡ እባክዎ ! ይኸው ሲመጡ ሰማኋቸው

አንደ ማባበልም እንደ
መጎተትም አድርጋ ከክፍሏ አስገባቻትና እየሮጠች
"ተመለሰች " ልክ ሚስተር ካርሳይል ከልጁ ክፍል ሲገባ አብራ ገባች ከእግር
እስከ ራሷ ተንቀጠቀጠች "

' ጆይስ ! ምን ነካሽ ? አመመሽ ? ” አላት

ጌታዬ ይዘጋጁ ! ዊልያም–– ዊልያም
ጆይስ ! ሞተ እንዳትይኝ ? ”
መቸስ ጌታዬ ምን ይደረጋል? ከዚህ የሚቀር የለም ።

ሚስተር ካርላይል ወደ ወስጥ ገብቶ መዝጊያውን በስተውስጥ ቀርቅሮ ወደ
የመነመነው የሕፃን ፊቱ ልጁ ተጠጋ " ከትራሱ ዝንጥፍ ብሎ ወድቆ አየው

" ልጄ ! ልጄ ወይ ልጄ ! ” እያለ “ጌታ ሆይ ያቺን ያልታደለች እናቱን ተቀ
ብለሃታል ብዬ እንደማምነው ሁሉ የዚህንም ሕፃን ነፍስ ታርፍ ዘንድ ተቀበላት” ብሎ ጸለየ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሎርድ ማውንት ስቨርን ከዊልያም ካርላይል ቀብር ላይ ለመግኘት ከልጁ ጋር
መጣ ዊልሰን እንዳሰበችው ዊልያም ካባቱ አባት ጎን ተቀበረ » መቃብሩ ላይ !
ዊልያም ቬን ካርላይል የኢስት ሊኑ አርኪባልድ ካርላይል የመጀመሪያ ወንድ ልጅ የሚል ዕብነበረድ አቆመበት " ዐይን ካረፈባቸው ኀዘንተኞች አንዱ
ሪቻርድ ሔር ትንሹ ነበር "

ሳቤላ በአእምሮም ሆነ በአካልም ይዞታዋ በጣም የሚያሠጋ ሆነ ነገር ግን
ሐኪም እንዲያያት ስለ አልፈለገች የሕመሟ መጠን አልታወቀላትም ይታይባት
የነበረ የበሽተኝት ምልክት ዊልያምን ያለ ዕረፍት ስታስታምም ከድካም ብዛት
የመጣ ስለመሰለ በቤተሰብ ዘንድ አሳሳቢ ሆኖ አልታየም " ከክፍሏ መውጣት
ስትተው ጆይስ ታስታምማት ጀመር " እሷ ግን የሰው ልጆች ኃይልና ጥበብ
ሊመልሰው የማይችል ሞት በመምጣት ላይ እንደ ነበር ዐውቃው ነበር ነገር
ግን ኢስት ሊን ሆና ለመሞት አልፈለገችም ሐሳቧን በሙሉ አሰባስባ ከኢስት
ሊን የምትወጣበትን መንገድ ማውጣት ማውረድ ተግባሯ አደረገችው " እንዳትታወቅ የነበራት ሥጋት እንደ ወትሮው ማስጨነቁን እየቀነሰላት ሔደ መታወቋ ሊያስከትለው ለነበረው ውጤት ማሰቡንም ተወችው " ወደ መቃብር ሲቃረቡ ማንኛቸውም ዐይነት የዚህ ዓለም ፍራቶችና ተስፋዎች ሁሉ ኃይላቸውን ያጣል
👍15
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰባ_አምስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


...ባርባራ ማዳም ቬንን ከኢስት ሊን ሳትወጣ እንድትቆያት አጥብቃ በለመነቻት ጊዜ በልቧ በጣም ደስ እንዳላት ባትገልጸውም ላለመቀበል አልጨከነችም "
ይህች አስተማሪ ጠባይዋ ከብዙዎቹ ብጤዎቿ ለየት ያለች ከትልቅ ቤተስብ
የተወለዶች በጨዋ ደንብ
ያደገች መሆኗን ባርባራ ጠቅላላ ሁኔታዋን በመገምግም ዐወቀቻት " ሁለተኛዉ ለሉሲ ስትል ብቻ ደሞዟን የምትፈልገውን ያህል አሳድጋላት እንድትቀመጥላት ፈለገች ነገር ግን ባርባራ ለሉሲ ስትል ብቻ እንጂ በግል ስሜቷ ማዳም ቬንን አትወዳትም ነበር በአርግጥ ሰውነቷ ቢነግራት ይሆናል እንጂ የምትጠላበት ይኸ ነው የምትለው ምክንያት አልነበራትም "

ወይም መልኳ ከሳቤላ ጋር በመመሳሰሉ ሊሆን ይችላል " ባርባራ ራሷም የማዳም ቬን መልክ ከሳቤላ ጋር መመሳሰል በድምፅ ይሁን በመልክ ይሁን በጠባይ
ይሁን ግልጽ ሊሆንላት ባይችልም ብዙ ጊዜ የሚገርም መመሳሰል ሰትል ነበር
ሳቤላ ቬን ትሆናለች ብላ ግን በጭራሽ አልጠረጠረችም እንደማትወዳትም ለማንም ተናግራ አታውቅም " የሰማይ ወፎች የየብስ እንስሶችና የባሕር ዓሦች ሁሉ አንድ ነገር ከመድረሱ በፊት የማወቅ ተሰጥኦ እንዳላቸው ሁሉ ሰውም የራሱ የሆነ ተሰጥኦ አለው " ስለዚህ በዚህ ተሰጥዎው ሰውነቷ ነግሯት ይሆናል " ከላይ እንዳልነው ባርባራ ለሉሲ ስትል ብቻ ማዳም ቬን ከኢስት ሊን እንድትለቅ ባትፈልግም ሞተች ቢባል ግን አንዲት ዘለላ እንባ እንኳን እንደማታፈስላት ታውቅ ነበር ።

እነዚህ የተለያዩ አሳቦችና ትዝታዎች በሁለቱ ሴቶች ናላዎች ሲመላለሱባቸው
ቆዩና " ማዳም ቬን ለመሔድ ከወንበሯ ተነሣች
ልጄን ለአንድ ደቂቃ ያህል ትይዥልኝ .. ማዳም ቬን ? ” አለቻት ባርባራ " ማዳም ቬን ያላሰበችው ጥያቄ ሲሆንባት ጊዜ ደነገጠችና “ ይችን ሕፃኗን ! ” ስትላት ባርባራ ሣቀች

“ ይቻትልሽ ከጎኔ ተኝታለች

ማዳም ቬን ጠጋ ብላ ልጂቱን አሣቻት " ከዚያ በፈት በክንዷ ልታቅፋት
ቀርቶ ለዐይኗም በወጉ አይታት አታውቅም " አንድ ቀን ይሁን ሁለትቀን ያህል
ሚስዝ ካርላይልን ለማየት ገብታ ወንፊት በመሰለ ልብስ የተሸፈነች ትንሽ ፊት ከህፃን አልጋዋ ላይ እንደተኛች አሳይታት ነበር » ከዚያ በቀር አይታት አታውቅም።

“ አመሰግንሻለሁ አሁን መነሣት እችላለሁ " አየሽ ልጅቱ እዚሁ እንዳለች ለመነሣት ብሞክር ኖሮ ላፍናት እችል ነበር " አለቻት ባርባራ እየሣቀች "
“ እዚህ ጋደም ካልኩ ብዙ ቆይቻለሁ አሁን ድካሜ ደኅና ወጣልኝ እንደተኙ
ስለሚታፈኑት ሕፃናት ጉዳይ ከሚስተር ካርላይል ጋር አሁን ስንጫወት ነበር "
በየሳምንቱ በሚወጣው የጤና ዜና ይህን ያህል ልጆች እንደተኙ ተደርቦ ተተኛባቸው ይህን ያህል ልጆች እንደተኙ እየታፈኑ ሞቱ እየተባለ ይገጻል" በየሳምንቱ እስከ አሥር ይደርሳሉ" ሚስተር ካርላይልማ ሆነ ተብሎ ነው የሚደረገው ይላል ”

“ ኧረ ሚስዝ ካርላይል !

እሱ አንደዚህ ብሎ ሲነግረኝ እኔም እንዳንቺ ጮኩበትና እጄን ከንፈሮቹ ላይ ጣልኩበት እሱም ሥቆብኝ ሲያበቃ የዓለምን ክፋት ግማሹን አንኳን አለማወቄን ነገረኝ " አመሰግንሻለሁ " አለቻት ሚስዝ ካርላይል ልጂቱን ከማዳም ሼን እየተቀበለች ቆንጆ ልጅ አይደለችም ? አና የሚለውን ስምስ ወደድሽው ?

ቀላል ስም ነው ቀላል ስሞች ሁልጊዜም ደስ ይላሉ” አለች ሳቤላ "
አርኪባልድ ልክ እንዳንች ረጅም ስም አልወድም አለና የኔን የእኅቱንና የራሱን ስም ምሳሌ አድርጐ ነገረኝ " አሁን “ባርባራ የሚለውን ስም እወደዋለሁ ብሎ ልጂቱን ባርባራ ብሎ ስም አወጣላት » ስለዚህ አን ባርባራ ትባላለች የመጀመሪያው መጠሪያዋ ሁለተኛው ደግሞ ሙሉ ስሟ ሲመዘገብ የምትጠቀምበት
ነው ...

“ ክርስትና ገና እልተነሣችም ...አይደለም ? " አለች ማዳም ቬን "

ጥምቀት ብቻ ነው ዊልያም ባይሞት ኖሮ ቀደም ብለን እናስነሳት ነበር።
ሌላው ደግሞ የመንድሜ የሪቻርድ ጉዳይ የሊንበራው ፍርድ ቤት የሚለው እስኪ
ለይለት ስንል ነበር የቆየን " በርግጥ ለክርስትና ድግስ አናደርማፈግም ”

"ሚስተር ካርላይል ' ኮ ለክርስትና መደግስ አይወዱም ”አላች ሳቤሷ .

በምን አወቅሽ ? ” ጠየቀች ባርባራ ዐይኖን አፍጣ " ምስኪን ማዳም ቬን ፊቷ ልውጥ አለ » የኢስትሊን ባለቤትነቷ ቅዠት እንዲህ ዐልፎ ዐልፎ ልቧን ስውር ያደርገ ነበር" ለባርባራ ጥያቄ ክው ብላ ደነገጠችና " ሰዎች ሲሉ ስምቾ ነሙ ” አለች "

“እውኑት ነው አለች ባርባራ » “ ለማንኛውም ልጅ የክርስትና ድግስ አድርጎ አያሙቅም በጸሎት በሚፈጸመው ሥነ ሥርዓትኖ በአንድ ላይ ተሰባስቦ መብላት መጠጣትና ዓለማዊ ፈንጠዝያ በማድረግ ያለው ልዩነት ሊገናኝለት አልቻለም

ማዳም ቬን፡ ከባርባራ ዘንድ ወጥታ ወደ ክፍሏ ስትሔድ ወጣቱ ሎርድ ቬን
በየማእዘኑ አንገቱን እያሰገገ በመቃኘት“ ሎሲ! ሎሲ! ” እያለ የተንከለከአለ
እየተጣራ መጣ።

“ ለምን ፈለግኻት ?” አለችው ማዳም ቬን "

“እሱን ልነግርሽ አልችልም” አላት በፈረንሳይኛ „ “ የኢትን ተማሪ ስለ ነበር አጋጣሚ ሲያመቸው የፈረንሳይኛ ችሎታውን ማሳየት ደስ ይለው ነበር »

“ ሉሲ አሁን እያጠናች ስለሆነ ልትመጣ አትችልም ” አለችው " ለምን
እንደ ፈለጋት አሁንም መልሶ በፈረንሳይኛ ሲነግራት ሳትወድ ሣቅ ኤለችና “ከፈረንሳይኛ አርቲ ቡርቲ የእንግሊዝኛ ቁም ነገር? ምነው ብትናግር " አለችው

“ እንግዲያው የግድ ማወቅ ከፌለግሽ ቁም ነገሩ ሎሲን እፈልጋታለሁ እሷን ማግኘት አለብኝ " በትንሹ ሠረገላ ሽሮሽር ልወስዳት እፈልጋለሁ እሷም ተስማምታለች " ጆን ሠረገላውን እያዘጋጀ ነው ”

“ የለም አልፈቅድልሀም " አንተ ሠረገላ ላይ ከወጣች በኋላ ልታስፈራራራ
ልትረብሻት ነው የፈለግኸው ?

“ግድ የለሽም " እኔ በጣም ነው የማስብላት " ሠረገውን ዝግ አድርጌ እነዳለሁ " እሷኮ ሚስቴ ልትሆን ነው ... ታውቂያለሽ? ”

ማዳም ቬን ልጁን ክንዱን ይዛ ወደ መስኮቱ ወስዳ“ ስለ ሎሲ ካርላይል
እንደዚህ ብለህ የምትናግር እናቷ በሠራችው አጢአት እንክን እንዳለባት ረስተህው ነው?

“ እናቷ ሎሲ ማለት አይደለችም "

“ላንተ ባይመስልህም ሎርድ ማውንት እስቨርንና ወይዘሮ ማውንት እስቨርን
ቢሰሙ አይወዱልህም "

“ አባቴ ምንም አይልም !እናቴን ግን አሳምናለሁ" የእርቅ ፍልሚያ እፉለማታለሁ .... ገባሽ ጠላትን ማሳመን።

ማዳም ቬን ሰውነቷ ተረበሽ መሐረቧን አውጥታአፏ ላይ አደረግች።

ልጁም እጆቿ እንዴት እንደሚንቀጠቀ አየ "

“ሉሲን ክፉኛ ለመድኳት አብሬአት ባሳለፍኰዋቸው ጥቂት ወሮች ውስጥ
አንደ እናትና ልጅ ሆነን ነው የቆየን " ዊልያም ቬን . . እኔ በቅርቡ ምድራዊ ልዩነቶች ወደሌሉበት በደልና ኀዘን ወደማይታዩበት ዓለም እሔዳለሁ " ምናልባት እንዳሳብህ ሆኖልህ ከዘመናት በኋላ ሎሲ ካርላይል ሚስትህ ለመሆን ብትበቃ የናቷን ጥፋት እንዳታነሣባት አደራህን " ካነሳህባት ያሠቅቃታል
አለጥፋቷ ትጨነቃለች » የዚያች የዕድለ ቢስ እናቷ በደል የሷም በደል ነው » ስለዚህ የናቲቱ ኃጢአት ከናቲቱ ጋር እንደ ተቀበረ ቁጠረው » ለሎሲ ስለናቷ እንዳታነሳባት” አለችው .

"የለም ' የለም ! ሚስቴ ከሆነች በኋላ ስለናቷ ሁልጊዜ ነው የማነሣላት "
በዚህ ዓለም ከራሷ ከሉሲ በቀር እንደ መቤት ሳቤላ የምወደው ሰው እንዳልነበረ
አጫውታታለሁ " ሎሲን የምወዳት በናቷ ስለሆነ የናቷን ጥፋት የሲ መስደቢያ አላደርገውም " ይህ ቃሌ ነው ”
👍156👎1
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰባ_ሰባት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ባርባራ ለዕረፍት ወደ ባሕር ዳርቻ በሔደችበት ቀን ሳቤላ ከመኝታዋ ወድቃ መጠራሞት ጀመረች።

ለመሰናበት ካሰበች በኋላ እንደገና ባርባራ እስክትመለስ ድረስ ልትቆያት የተሰማማችው ከልጆቹ ጋር መሰንበቷን ተስፋ አድርጋ ነበር " ሚስተር ካርላይልም
በሽተኛዪቱ አስተማሪ ከልጆች ጩኸትና ውካታ ተላቃ ከማንኛውም ሥራ ርቃ የተሟላ ጸጥታና ዕረፍት አንድታገኝ በማሰብ ልጆቹን ሎሲንና አርኪባልድን ወደ ሚስ ኮርኒሊያ ዘንድ ሰደደቸው " ሳቤላ ልጆቹ ከእሷ ጋር እንዲሰነብቱ ሆዷ እየፈለገ እንዳይሔዱ ብላ ለመጠየቅ ፈራች ስለዚህ ያሰበችው ነገር
ሲበላሺባት በዝምታ ተቀበለችው የሳቤላ ሁለተኛዉ ሐሳቧ ደግሞ ማንነቷ እንዳይታወቅባት የመሞቻዋ ጊዜ ከመድረሱ በፊት ከኢስት ሊን ሹልክ ብላ ለመልቀቅ ነገር
እንዳይደርስባት የፈራችው ሰዓት ባላሰበችው ፍጥነት ቀደማት " ጊዜ ዐለፈ ልክ እንደ እናቷ እሷንም ሳይታሰብ አጣደፋት " ዊልሰን እመቤትን ተከትላ ስለ ሔደች የምታስታምማት ጆይስ ነበረች።

ባርባራ የሔደችበት ቦታ ከኢስት ሊን ሃምሳ ኪሎ ሜትር ያሀል ይርቃል
ሚስተር ካርላይል ቀን ቀን ከሥራው እየዋለ ማታ ማታ እዚያው ሔዶ ያድር ነበር " በዚህ ምክንያት ወደ ኢስት ሊን ከዘለቀ ዐሥር ቀን ዐለፈው " በነዚያ ጥቂት ቀኖች ውስጥ የሳቤላ ሁኔታ እየባሰ ሔዶ " ቀኑ ሮብ ነው ሚስተር ካርላይል
ከቤቱ ያድራል ተብሎ ይጠበቃል ።

ጆይስ የምታደርገው ነገር ጠፋት " በጣም ተጨነቀች ። ሳቤላ ተዳከመች
ራሷን መቈጣጠር አልችል አለች » ደብቃው የኖረችው ምስጢር ሊገለጽ ሆነ
የሚገለጽበት ጊዜ ደግሞ ጆይስ አስቀድማ ባለመናገሯ ከሳቤላ ጋር ተመሳጥራ አንደ ደበቀችው ተደርጎ እንዳይተረጐምባት ፈራች ባልና ሚስቱ ምን እንደሚሏት አስባው ተጨነቀች » ሚስተር ካርላይልን ጠርታ ሁሉን ነገር ልትገጽላት ብዙ
ጊዜ እያሰበች መልሳ ትተዋለች እሷ በዚህ ነገር ስትዋልል ሰዓቱ ገሠገሠ በተለይ ከእኩለ ቀን በላይ የነበረው ጊዜ ቶሎ መሸ የሳቤላ ሕይትም ከጀንበሪቷ
ጋር የመጥለቅ እሽቅድምድም የያዘች ይመስል ወደ ጥልቀት ገሠገሠች ጆይስ
ከአጠገቧ አልተለየችም
ቀኑን ሙሉ ዛል ብላ ውላ ወደ ማታ ትንሽ ዐለፍ ያለላት
መስለች ከመኝታዋ ላይ እንደ ሆነች በትራሶች ተደግፋ ትንሽ ቀና አለች " ከነጭ ሱፍ የተሠራ ያንን ልብስ ተደረበላት ደኅና አድርጋ አየር እንድታገኝ የሌት ቆቧ ወለቀላት » መስኮቶች ወለል ብለሙ ተከፈቱላት ።

ሞቃቱ የበጋ አየር ጸጥ ብሏል ጆሮዋ እንደነቃ አእምሮዋም እንዶ ሰላ ነበር
ጆይስ ” አለቻት "ዘ
እመት ” መለሰች ጆይስ
' ላየው ብችል ደሰ ብሎኝ እሞት ነበር "
“ ልየው ! " አለች ጆይስ በትክክል መስማቷን ጆሮዋን በመጠራጠር "
" እሜቴ ልየው አሎኝ ... ሚስተር ካርላይልን ?”

“ ምነው ምናለበት ? ያለሁ መስሎኝ ነው ? እኔ እኮ አሁን ሙት ማለት ነኝ "
እሱን ለማየት ብጠይቅ ነውር ሆነብኝ ? እኔ ላነጋግረው በልቤ ከተመኘሁ ብዙ ቀን ሆኖኛል " ይህ ፍላጎቴ ከሞት ፊት ተደንቅሮ አላሳልፍ አላሰቀርብ አለው .
ጣሬ በዛ ጆይስ እባክሺን ላግኘው? አንዴ ላነጋግረውና በሰላም ልሙት ”

ሊሆን አይችልም ... እሜቴ ” አለቻት ፍርጥ አድርጋ " የማይያገባ ነገር ነው " አይቃጣም !አይታሰብም”

ሳቤላ የጆይስን እምቢታ ስትሰማ እንባዋን ባራት ማዕዘን አወረደችው
ምነው ጆይስ ምን በደልኩሽ? በዚህ የተነሣ መሞት እኮ አልቻልኩም
ነፍሴ አልወጣ አለች ልጆቼን ከኔ ወሰድሽብኝ " እኔ እንዳልታወቅብሽ ስለፈራሽ እዚህ ግድም እንዳይመጡ ብለሽ ሰደድሻቸው " አሁን ደግሞ ባሌን እንዳላናግረው ትክለክይኝ ? ተይ .. ጆይስ ተይ ላግኘው! ግድ የለሺም ንግሪው ይምጣ።

ባሏ ! ምስኪን ዛሬም ባሌ ትለዋለች ጆይስ ከውሳኔዋ ፈቀቅ ባትልም ሁኔታዋ በጣም አሳዘናት ዐይኖቿ በእንባ ክድን አሉ ። ነገር ግን ሚስተር ካርላይልን ጠርታ ከዱሮ ሚስቱ ፊት ብታመጣው ባርባራ ላይ የክህደት ሥራ እንዶ
ፈጻመች እንዳይቆጠርባት ፈራች "

በፉ ተንኳኳ " ጆይስ “ ግቡ ” አለች ። ሁልጊዜ ወደዚያ ክፍል ይመጡ የነበሩት ሁሉት ሠራተኞች ሐናና ሣራ ነበሩ ሁለቱም ማዳም ቬንን ወይዘሮ ሳቤላ እንደ ነበረች አያውቁም ሣራ አንገቷን ብቅ አደረገችና
ስሚ ጆይስ ” አለቻት "
ጌቶች ይጠሩሻል .
ሚስ ጆይስ።

''እሺ መጣሁ።

“ ከመብል ቤት ናቸው " አሁን አርተር ካርላይልን ሰጥቻቸው መምጣቴ ነውኀ

“ ማዳም እንንዴት ሆነች . . . ጆይስ ? ” አላት አርተርን በትከሻው ተሸክሞ አገኘችውና ካርላይልን ።
ጆይስ ምን ብላ እንደምትመልስ ድንግር አላት " በሌላ በኩል'ደግሞ ከጥቂት ሰዓት በኋሳ በግድ የሚገለጸውን ነገር ሽፋፍና ልታልፈው አልፈለገችም

“ በጣም አሟታል , , ጌታዬ ” አለችው "

"በጣም ? ''

“ አዎን ' መሞቷ ነው መሰለኝ።

ሚስተር ካርላይል ያቀፈውን ልጅ በድንጋጤ አወረደው "

“ መሞቷ ነው ”
“ አዎን ዛሬ ማደሯንም እንጃ

“ ምነ ? ለሞት የሚያደርስ ምን ነገር አገኛት ? "

"ጆይስ አልመለሰችለትም " አሷም የምትለው ጠፍቷት ፊቷ ዐመድ መስሎ ነበር።

"ዶክተር ማርቲን አይቷት ነበር ? ”

" የለም ... ጌታዬ " ግን ምንም አይጠቅማትም ”

“ አይጠቅማትም ! " ደገመው ሚስተር ካርላይል ቆጣ ብሎ ሊሞቱ ለተቀረቡቃረቡ ሰዎች የምናደርግላቸው ይኸው ነው ? ማዳም ቬን አንቺ እንደምትይው ታማ ከሆነ ዶክተር ማርቲን በቴሌግራም ተጠርቶ ቶሎ መምጣት አለበት » እስኪ
እኔው ራሴ ሔጄ ልያት ” አለና ወደ መዝጊያው አመራ

ጆይስ ጀርባዋን ወደ መዝጊያው ሰጥታ ከበሩ መኻል ቆመችና እንዳይወጣ ከለከለችው
ጌታዬ . . ይቅርታዎን እለምናለሁ " ነገሩ ደግ አይደለም ።እባክዎን ወደሷ ክፍል መግባቱ ይቅርብዎ ”

“ ለምንድነው የማልገባው ?

“ ሚስዝ ካርላይልን ይከፋቸዋል ብላ ተንተባተበች "

“ የማታመጡት የለም " ሚስዝ ካርላይል ባትኖር የግድ አንድ ሰው ሊያያት
ያስፈልጋል። ከቤቴ ውስጥ ስትሞት ላልጠይቃት ነው ? አብደሻል መሰለኝ ጆይስ !
በይ ከራት በኋላ እጠይቃታለሁና በደንብ አዘጋጂያት ”

ራት ቀረበ ጆይስ ሕፃኑን አርተርን ይዛ ወደ ሣራ ሔደች "

ሚስተር ካርላይል ራት ሊበላ ሲጀምር እኅቱ ደረሰች " የመጣችው ከአንዳንድ ቤቶቿን ከተከራዩ ሰዎች ጋር ጭቅጭቅ ስለ ፈጠረች ለወንድሟ ለመንገር ነበር " የመጣችበትን ከመስማቱ በፊት ጆይስ የነገረችውን የማዳ ቬንን ሁኔታ ነገራትና ሔዳ እንድታያት ጠየቃት "

“ልትሞት ነው?” አለች ኮርኒሊያ እሷም ድንግጥ ብላ “ “ግድ የለህም ይህች
ጆይስ ዘንድሮ በጤናዋ አይደለችም " እስኪ አሁን ምን አገኛትና ነው ልትሞት
ነው ብላ የምታወራ ? ”

ኮርኒሊያ ላይኛው ቆቧንና ካባዋን አውልቃ ከወንበሩ ላይ ጣል አደረገች
መልኳን ከግድግዳው ላይ ከነበረው መስተዋት
ቆቧን ነካ ነካ አድርጋ አስተካከለችና በሽተኛዪቱ ወደ ነበረችበት ወደ ፎቅ ሔዳ በር መታች
ጆይስ " ይግቡ የሚል ምላሽ ሰጠቻት ወዲያው ጆይስ ማን መሆኑን ስታይ
ደነገጠችና ' “ ይተዉ እማማ አይግቡ ” አለችና ከበሩ ሒዳ ከፊቷ ተደቀነች

ማነው ደግሞ እኔን የሚከለክለኝ: ' አለች ነገሩ ስለገረማት ትንሽ ተግ ብላ ካሰበች በኋላ።በይ ዘወር በይ ሴትዮ ! ለመሆኑ ጭንቅላትሽ ደህና ነው?
ከዚህ በኋላ ደግሞ ምን ታመጪ ይሆን?

ጆይስ በሥልጣንም በጉልበትም ዐቅም እንዳልነበራት ታውቅ ነበር
ስለዚህ ሚስ ካርላይልን እንድትገባ አሳለፈቻትና ራሷ ወጣች "
👍20
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰባ_ስምንት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ጆይስ ወረደችና ሚስተር ካርላይልን ራት ከሚበላበት አስነሥታ ይዛው መጣች

“ ማዳም ቬን ባሰባት እንዴ . . ኮርኒሊያ ? እኔን ፌለገችኝ ?

“ አዎን ልታነጋግርህ ትፈልጋለች ”

ሚስ ካርላይል እየተናገረች በሩን ከፈተችው "መጀመሪያ እሷ እንድትግባ በጁ አመለከታት “ የለም” አለችው “ ብቻህን ገብተህ ብታያት ይሻላል ”

ሊገባ ሲል ጆይስ ክንዱን ያዘችው “ ጌታዬ ተዘጋጅተው ይግቡ“ እማማ
ለምን አይነግሯቸውም ?”

ሁለቱንም ትክ ብሎ አያቸው ሁኔታቸውን ይኸ ነው ብሎ ለመናገር አልቻለም
አንግዳ ነገር ሆነበት " እንዲያውም ወደ ዕብደቱ ወሰድ ያደረጋቸው መሰለው
ፊቷ ምንም ቢሆን ተለውጦ የማያውቀው ኮርኒሊያ እንኳን ምንም ኮስተር ብላ
ብትቆምም ከንፈሮቿ ሲንቀጠቀጡ መቁጣጠር አልቻለችም " ሚስተር ካርላይል ግንባሩን ቋጥሮ ሲገባ እነሱ በሩን ዘጉበት "

በቀጥታ ወደ በሽተኛይቱ አልጋ ቀስ ብሎ ተጠጋና “በጣም አዝናለሁ ማዳም ቬን...” ብሎ የጀመረውን ሳይጨርስ ቀሪዎቹ ቃላት ምላሱ ላይ ተንከባለሉ"
ሊወጡ አልቻሉም . እሱም እንደ ጆይስ የሳቤላን መንፈስ ያየ መሰለው
ከአልጋው ትንሽ አፈገፈገ ወርዶ አንገቷ ላይ የተቆለለው ጸጉሯ የሚያምሩትና የኀዘን ዳመና የጣለባቸው 0ይኖቿ ሳይቀሩ የሳቤላ ቬንን መልክ ቁልጭ አድርገው አሳዩት

አርኪባልድ ! ” አለችው "

የሚንቀጠቀጠው እጅዋን ዘረጋችና እጁን ያዘችው " ትክ ብሎ አያት» ከሕልም የነቃ ይመስል ዙሪያውንም አስተውሎ አየ "

“ነፍሴ ያንተን ይቅርታ ሳታገኝ ከሥጋዋ መለየት አልቻለችም " አለችው
የሰራችውን በደል ስታስብ ዐይኖቿን ስብር አድርጋ “ ተው ' ፊትህን አታዙርብኝ " ለአንዳፍታ ታገሠኝ ይቅር ብየሻለሁ ብቻ በለኝና በሰላም ልሙት

“ ሳቤላ ! አንቺ ነሽ? አንቺ ነሽ ? ማዳም ቬን የነበርሽው ? " አለ የሚናገረውን አላወቀውም።
ይቅር በለኝ ማረኝ... አርኪባልድ | አልሞትኩም » የደረሰብኝ አደጋ ለወጠኝ እንጂ አልገደለኝም » ነገር ግን ማንም አላወቀም ስለዚህ ማዳም ቬን
ተብዬ ወደዚሁ መጣሁ " ተነጥዬና ርቄ መኖር አልቻልኩም » ማረኝ ... አር
ኪባልድ ማረኝ " "

የሚናገረው የሚያደርገው ቅጡ ጠፋው " አምሮው ጠሮ ነፋስ እንደ ገባበት
ተበጠበጠ ግራ ገብቶት ዝም ብሎ እንደ ቆመ ነገሯን ቀጠለች "

“ ከአንተና ከልጆቼ ተነጥዬ መኖር አልቻልኩም " ያንተ ናፍቆት ሊገድለኝ ሆነ ” አለችው " አነጋግሯ የትኩሳት ቅዠት ይመስል ነበር “ “ እንደዚያ አሳብዶኝ ካን† ከተለየሁ ወዲህ የአንዲት ቅጽበት እንኳን ሰላም አግኝቸ አላውቅም .
መላው ባይጠፋኝ ኖሮ ወዲያው ተመልሸ እመጣ ነበር ከቤት ከወጣሁ አንድ
ሰዓት እንኳን ሳልቆይ ጸጸት ያዘኝ እያደር እየከበደኝ እየጠናብኝ ሔደ ምን እንዳ
ስመሰለኝ ታየዋለህ ? እየው ተመልከተው " ብላ የሸበተው ጸጉሯን የመነመ
ነውን እጁዋን አሳየችው » አንተው ማረኝ ይቅር በለኝ !ጥፋቴ በጣም ከባድ ነው ! የተቀበልኩት ቅጣት ግን ይበልጣል " ለብዙ ዘመን ከባድ መከራ ከባድ
ሥቃይ ተቀብያለሁ " ሕይወቴ ረጅም ዘመን የፈጀ የጻዕረ ሞት ሕይወት ነበር ”

“ እንዲያው ሲጀመር ምን ሆነሽ ሔድሽ?”

“ ለምን እንዶ ሔድኩ አላወቅህም? ”

“ የለም አላውቅም " እስከ ዛሬ ምስጢር እንደ ሆነብኝ ነው ”

“ አንተን ከመውደዴ የተነሣ ነበር የሔድኩት " ከንፈሮቹን በንቀት ቀስቀስ አደረጋቸው " በጣር ላይ ሆናም የምትቀልድበት መሰለው

“ ተው እንደሱ አድርገህ አትየኝ " አቅም የለኝም " ያለው የሌለው ጉልበቴ አልቋል " ከሰውነት ወጥቻለሁ " ዐይንህ ያያል " የምነግርህ እውነት መሆኑን ተረዳልኝ ነገሬ ግልጽ ካልሆነ እንጃ በጣም እወድሀ ስለ ነበር ጠረጠርኩህ፤ እኔን አለሁልሽ ብለህ እያታለልክ ፍቅርህን ለሌላ የሰጠህብኝ መስለኝ » ስለዚህ በጥርጣሬ ቅናት እንደ ቆሰልኩ ከዚያ ክፉ ሰው ወጥመድ ገባሁ " እንድበቀልህ በጆሮዬ ሹክ ይለኝ ነበር ”

“እኔ ግን አንቺን በሐሳብም፡ በቃልም በተግባርም ለማታለል አልሞከርኩም"
ያንጊዜም ታውቂኝ ነበር " ከዚያ ወዲህም ሳታውቂኝ አልቀረሽም

“አርኪባልድ ... አብጀ ነበር " በዕብደት እንጂ በጤንነት እንደዚያ ያለውን ሥራ አልሠራውም ነበር " ስለዚህ እርሳው ' ይቅር በለኝ ”

“ መርሳት አልችልም " ይቅር ካልኩሽ ግን ቆይቻለሁ "

“ ከዚያ ሌሊት ወዲህ ያለፈውን የኀዘንና የብስጭት ጊዜ ለመርሳት ሞክር” አለችው ዕንባዋ በሁለት ጉንጮቿ እየወረደ " ሥጋው አልቆ አጥንቱ ብቻ ቀርቶ በትኩሳት የሚቃጠለውን ክንዷን ወደሱ ዘርግታ : “ በሱ ፈንታ የፍቅር ጊዜአችንን ላለመርሳት ሞክር "
አኔን በመጀመሪያ ወደ ዐወቅህበት ዘመን መልሰው " ከዚህ ቤት ሳቤላ ሼን አየተባልኩ ካባቴ ጋር ደስተኛ ልጅ የነበርኩበትን ዘመን አስታውስ ያኔ ለኔ ባትገልጽልኝም እንዴት ልትወደኝ እንደቻልክ አስታውስ" አባቴ በሞተ ጊዜ የተቸገርክልኝን በዚያች ምናምን ባልነበረኝ ሰዓት አንድ መቶ ፓውንድ የሰጠኸኝን ወደ ካሰል ማርሊንግ የመጣህ ዜ
ሐሳብህን ላንዳፍታ
ላገባህ ቃል የገባሁበትን ለመጀመሪያ ጊዜ ከንፌሬን የሳምከኝን ከተጋባን በኋላ የነበረን ደስታ ትዝ ይልሃል ? አብረን ያሳለፍናቸውን የፍቅር ዘመናት ታስታውሳቸዋለህ ? ሉሲ ስትወለድ ከሞት አፋፍ በመትረፌ የተሰማህን
ሁሉ ትዝ ይልሃል ? ”

“ ታዲያ አሁን እኔን ይህን አጠፋህ የምትይኝ አለሽ ” አላት አሳዛኝ እጅዋን
በእጁ ይዞ ።

አንተን ? በኔ ቀርቶ በአምላክ ዘንድም ጥፋት አይገኝብህም " ከልብህ
ወደከኝ ነበር " ለደኅንነቴ ባያሌ» ስትጨነቅልኝ ነበር » አንተ ደግሞ ምንህ ይወቀሳል? ምን አንደነበርክና ዛሬም እንዴት ያለህ ሰው እንደሆንክ ሳስበውና ከመለስኩልህ ውለታ ጋር ሳነጻጽረው በኃፍረትና በጸጸት መሬት ተከፍታ ብትውጠኝ እወድ ነበር ለራሴም ጥፋት የሚያበቃኝን ቅጣት ተቀብያለሁ ባንተና
በልጆችህ ያመጣሁባችሁን ውርደት ግን ማስለቀቅ አልችልም ”

“ የኔን ፈተና ግን አስበው " አለችው ድምጿ እየደከመ " እሱም እየራቀ የሔደውን ድምፅ ለመስማት ጆሮውን ጠጋ ለማድረግ ተገደደ ። “ በዚህ ቤት ውስጥ ከሚስትህ ጋር ተቀምጬ ምን ያህል እንደምታፈቅራት እኔን ትዳብስኝ እንደ ነበረው ስትዳብሳት እያየሁ ' በቅናት ስንገገብ ኖርኩ አሳልፌ ለሌላ ከስጠሁህ በኋላ ያፈቀርኩህን ያህል አፍቅሬህ አላውቅም ነበር " እስቲ ይታይህ' ዊልያም ልጄ ጉልበቱ እየመነመነ ሰውነቱ እያለቀ ሲሔድ እያየሁ ነፍሱ በምትወጣበት
ሰዓት ካንተ ጋር ብቻችንን ሆነን ስንጠብቀው እናቱ መሆኔን እንኳን ለመናገር
አለመቻሌ እንደ ሞተም ቤተሰቡ ሁሉ ሰምቶ ሲደናገጥ የኔን የወላጅ እናቱን ኀዘን ሳይሆን የስዋን ትንሽ መጠነኛ ኀዘን ነበር የምታጽናኑት " እኔ ባሁኑ ጊዜ ከዚህ ቤት ችየው የኖርኩት ፈተና የሞት ያህል መራራና አስጨናቂ ነበር "

“ለምን ተመልሰሽ መጣሽ ? ” አላት "

“ ነገርኩህ እኮ ካንተና ከልጆቼ ተለይቸ መኖር አልቻልኩም '

“ስሕተት ነበር ! ፍጹም ስሕተት ነበር የሠራሽው
👍10