አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
"የለም : አይደለም ! የዚያን ጊዜ ማታ ትዝታ ነው መቸም ልትረሳው አትችልም በኔም አእምሮ ውስጥ በእሳት ፊደሎች ተጽፋል " ራሴን እንደዚያ አጋልጬ እሰጣለሁ ብዬ አስቤው አላውቅም " አንተም ያን ጊዜ በተፈጸመው ሁኔታ እንኳን
ዛሬ ልትጠይቀኝ አይገባህም ነበር "

ባርርባራ ቀና ብላ አየችውና ያነጋገሩ ቃና በሠራ አካላቷ ሠርጾ ገባ "

“ እንደምወድሽ ታውቂያለሽ ? ካንቺ በቀር ሌላ ማግባት ፍላጎትም ምርጫም እንደ ሌለኝ ታውቂያለሽ ?
አይሆንም : ደስታ በጃችን ሲገባልን በስሜት አንሥተን አንጣለው ! " ክንዱን ተደገፈችና እንባዋን ለቀቅ አደረገችው “ ደስታ? ላንተ
ደስታ ይሰጥሃል ?”

እጅግ በጣም ጥልቅ የሆነ ደስታ ይስጠኛል " "

ሐቅ ገጽታው ላይ አነበበችው " ፀሕይ በመሰለው ፊቷ ልብን ወከክ የሚያደርግ ፈገግታ ፈካበት ።

“ እንደ ዱሮው ታፈቅሪኛለሽ ... ባርባራ ? ”

“ ከዱሮው በበለጠ ' በጣም በበለጠ ” ስትል በሹክሹhታ
እቅፍ አድርጎ ሲይዛት ' ፊቷን ሳብ አድርጎ ወደሱ ሲያስጠጋው
በመጮረሻ እፎይታ አገኘ "

ሪቻርድ ሔር ጠርማሳ ባርኔጣውን ሳይሆን ፊቱን ከታዛቢ ዓይኖች እንዲከልለት ሚስዝ ካርላይል የሰጠችውን ጥላ ዘርግቶ በበረዶው መኻል ጃንጥላው ከሌላ ሰው ጋር ተጋጨ ከሱ ጋር የተጋጠመው ጥላ ጨርቁ መኳንንት ብቻ ሊያገኙት የሚችል ልዩ ሐር ሆኖ እጀታው ደግሞ እንዳለ የማይቈጠር ነበር "
የሁቱም ጥላዎች ተገፋፍተው ወደ ጐን ሲገፋተሩ ሁለቱ ተላላፊዎች ተፋጠጡ "

“ እንዴት እንደዚህ ትደፍራለህ ... ሰውዬ ? ለመሆኑ መንገድህን አይተህ መሔድ አትችልም ? ሲለው ሪቻርድ ተዝለፍልፎ የሚወድቅ መሰለው " ከሱ ጋር የተፋጠጠው ሰውዬ አባቱ መሆኑን ሲያይ በኪሱ ያለውን ግፈገንዘብ ሁሉ በስጠና
መሬት ተከፍታ በዋጠችው ደስ ይለው ነበር "

ሪቻርድ ሳይታወቀው የድንጋጤ ጩኸት አመለጠውና እንደ ቀስት ተወርውሮ በረረ » ጀስቲስ ሔር በዚያ ሪዙ ቸምቸም ያለው ሁኔታው ሁሉ ልዩ የሆነ ሰውዬ ተገርሞ ፡ የእግሩ ዳና ከርቀቱ የተነ ለጆሮ እስኪጠፋ ድረስ ቆሞ ተመለከተው

💫ይቀጥላል💫
👍14🥰21
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ስምንት


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ጀርመን በእንግሊዝ ላይ የምታወርደው የቦምብ ናዳ እስኪቆም ድረስ መንግስት ትያትር ቤቶችን፣ ሲኒማ ቤቶችንና ዳንስ ቤቶችን ቢዘጋም ዳንስ ቤቶች ግን ህጉን ተጋፍተው የሌሊት ስራቸውን እየሰሩ ነው፡፡ ሄሪም በአንድ ዳንስ ቤት ውስጥ ተወሽቆ የአሜሪካን ሙዚቃ በጆሮው እየተንቆረቆረ ውስኪውን ይጨልጣል፡ ሬቤካን እንዴት ሸውዶ ጥሏት እንደሄደ እያሰበ እያለ ወንድሟ ድንገት ከች አለበት፡፡

እዳውን ሳይከፍል ከምግብ ቤቱ በመውጣቱ የጅል ስራ ሰርቷል ሬቤካ ደግሞ ክብሯን ሽጣ ገንዘብ የምትከፍል ዓይነት ሴት አይደለችም፡ ትንሽ
ስታስቸግር የምግብ ቤቱ ኃላፊ ፖሊስ ጠራ፡ ቤተሰቦቿም ፖሊስ ጣቢያ
ተጎተቱ፡፡ እንዲህ አይነቱን ችግር ሄሪ ዘወትር ሲሸሽ ነው የኖረው፡፡ ዛሬ ፍርድ ቤት ከሚቀርቡ ሰላሳ ያህል እስረኞች ጋር ጣቢያ ተዘግቶበታል፡፡ ክፍሉ
መስኮት የሚባል ነገር የሌለው ከመሆኑም በላይ በሲጋራ ጢስ ታፍኗል፡

ሬቤካ ሄሪ የቀረበበት ክስና ማስረጃ የሚያከራክር አይደለም፡፡ ለመሰረተችበት ክስ የምግብ ቤቱ ኃላፊ ምስክር ሆኖ የሚቀርብ ሲሆን ጌታ ሞንክፎርድም የጠፋውን የሸሚዝ ማያያዣ በተመለከተ ከሰውታል፡ ከዚህም የከፋ ነገር አለ፡ በወንጀል ምርመራ መምሪያ ሲመረመር ነው የዋለው
ከሁለት ወይም ከሶስት ዓመት ወዲህ ጌጣጌጥ ጠፍቶብናል የሚሉት
አመልካቾች በርክተዋል፡ አመልካቾቹ ጌጣጌጦቹ ተሰርቀዋል የሚል ግምት
የላቸውም ምክንያቱም ለመውሰድ ዕድሉ ያላቸው እንግዶቻቸው ብቻ ናቸው ለፖሊስ የሚያመለክቱትም እንዲያው ከተገኙ በማለት ነው፡፡

በምርመራው ወቅት ሄሪ አይናገር አይጋገር መልስ ለመስጠት አሻፈረ ብሏል፡፡ ሆዱ ግን ታምሷል፡፡ እስካሁን የፈጸመው ስርቆት እንዳልታወቀበት እርግጠኛ ቢሆንም በተቃራኒው የሰማው ነገር ፍርሃት ለቆበታል፡

መርማሪው አንድ የጠበደለ ዶሴ አውጥቶ እስካሁን ጠፉ የተባሉትን
ጌጣጌጦች ዘረዘረና ‹‹ይሄ ሰው ከፍተኛ የጌጣጌጥ ፍቅር የተጠናወተው ብቻ
ሳይሆን ጌጣጌጥም ያውቃል አለ። ፋይሉ እሱ በተለያዩ ጊዜያት የመነተፋቸውን ጌጣጌጦች ጉዳይ የያዘ ሳይሆን አይቀርም ሲል ገመተ።
ስርቆቶቹ በተፈጸሙበት ጊዜ ሄሪ በነዚህ ቦታዎች ላይ እንደነበር የሚመሰክ
ምስክሮችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ ቤቱም በፖሊስ
መበርበሩ አይቀርም:
አብዛኛዎቹን ጌጣጌጦች ቢሸጣቸውም ጥቂቶቹን አስቀምጧቸዋል፡ የሽሚዝ
ማያያዣውን የሰረቀው አንድ ፓርቲ ላይ ሰክሮ ከሚያንቀላፋ ሰው ላይ ነው: እናቱ ያደረጉትን የአንገት ጌጥ ደግሞ የወሰደው አንድ ሰርግ ላይ ከአንዲት ሀብታም ሴት ላይ ነው፡፡ በተጨማሪም ስራህ ምንድነው ብለው ቢጠይቁት ምን ብሎ ሊመልስ ነው?

ለረጅም ጊዜ እስር ቤት ይወረወር ይሆናል፡፡ እስሩን አጠናቆ ሲወጣ ደግሞ ውትድርና ውስጥ ይከቱታል፡፡ ይሄ ደግሞ ከእስር ቤት አይሻልም።
ይህን ሲያስበው ብርድ ብርድ አለው።

መርማሪው የሸሚዙን ኮሌታ ጨምድዶ ከግድግዳ ጋር ቢያላጋውም ትንፍሽ አልል አለ፡፡ ዝምታው ግን የትም አያደርሰውም፡፡ሄሪ ነጻ
ለመውጣት ያለው አንድ እድል ብቻ ነው፤ ደኛው በዋስ እንደለቁት
ማድረግና ከአገር መጥፋት፡፡ ልክ በሰዓታት
ዳኛው በዋስ እንዲለቁት
ለዓመታት እንደታሰረ ሰው ያህል ነጻነቱን ተመኘ፡፡

ሀብታሞችን እየዘረፈ አኗኗራቸውን እየተላመደው መጥቷል፡፡ ጧት ዘግይቶ ከእንቅልፉ ይነሳል፤ የሚያማምሩ ልብሶች ይለብሳል፡፡ አንዳንድ ጊዜ
ደግሞ እንደ መሰሎቹ አነስተኛ ቡና ቤት ሄዶ ወይም እናቱን ይዞ
መዝናናቱንም አልተወም፡፡ ነገር ግን የእስር ቤት ኑሮ ለጠላቱ አይስጠው ቆሻሻ ልብስ፣ አሸር ባሽር ምግብ፣ መተፋፈጉ ከሁሉም በላይ ደግሞ ትርጉም የሌለው ኑሮ፡፡

በዋስ እንዴት ሊወጣ እንደሚችል ማሰብ ጀመረ፡፡ ፖሊስ የዋስ መብቱ እንዲከበርለት ባይፈልግም ዳኞቹ መወሰን አለባቸው፡፡ ሄሪ እስር ቤት ገብቶ
ባያውቅም ከየስዉ አፍ እንደሰማው የዋስ መብት የሚከለከለው ለግድያ
ወንጀል ብቻ ነው፡ ይሄን ደግሞ ሁሉም ሰው ያውቀዋል፡፡ ባብዛኛው ዳኞች ፖሊስ የጠየቀውን ነው የሚያደርጉት፡ ሁልጊዜም ባይሆን ተከሳሾች አሳዝነው ከነገሯቸው ሆዳቸው ሊራራ የሚችልበት አጋጣሚ ይኗራል አንዳንዴ ደግሞ ጋጠወጥ ፖሊስ ሲገጥማቸው የበላይነታቸውን ለማሳየት
ሲሉ ዋስ የሚፈቅዱበት ጊዜም አለ፡፡ የዋስ መብቱን ለማስከበር የሚያሲዘው
ገንዘብ አያጣም፡፡ ለዚህ ችግር የለበትም፡፡ ረብጣ ገንዘብ አለው፡፡ ስልክ
እንዲደውል ስለተፈቀደለት እናቱ ጋ ደውሎ ‹‹የዋስ መብቴን ሊያከብሩልኝ
ነው እማማ›› አለ ሄሪ

‹‹አውቃለሁ የኔ ልጅ›› አሉ ‹‹እናቱ አንተ ሁልጊዜ ዕድለኛ ነህ››

ብዙ ጊዜ ከችግር አምልጫለሁ አሁን ግን እንጃልኝ ሲል አሰበ፡፡

የእስር ቤት ዘበኛው ‹‹ማርክስ›› ሲል ተጣራ
ሄሪ ተነስቶ ቆመ ዳኞቹ ሲጠይቁት ምን እንደሚል ያቀደው ነገር የለም፡ እንደመጣለት የመናገር ችሎታ ያለው ቢሆንም ለዚህ ጊዜ ግን ተዘጋጅቶ ቢሆን በወደደ፡፡ ክራቫቱን አጠባብቆ ኮቱን ቆላለፈ፡ አገጩን አሻሽና ጢሙን እንዲላጭ ቢፈቅዱለት ተመኘ፡፡ በመጨረሻ አንድ ሃሳብ ብልጭ አለለትና የሸሚዙን ማያያዣ አምባር ከክንዱ ላይ አንስቶ ኪሱ ከተተው፡፡

ችሎቱ ውስጥ ሲገባ ፊት ለፊት የዳኞቹ መንበር ጉብ ብሏል፡ ህዝብ የተቀመጠበትን ቦታ ሲያማትር እናቱ የክት ልብሳቸውን ለብሰው ራሳቸው ላይ ቆብ ደፍተው ተቀምጠዋል፡ የዋስ ገንዘብ እንዳለ ለማመልከት ይመስላል አስር ጊዜ ደረታቸውን ይደባብሳሉ፡ ከአንዷ ሀብታም ላይ የመነተፈውን የኮት ማያያዣ ጌጥ አድርገውት ሲያይ ፍርሃት ጨመደደው፡፡ እጁ
እንዳይንቀጠቀጥበት የተከሳሽ መቀመጫውን ፍርግርግ ለቀም አድርጎ ያዘ፡፡

አፍንጫው አለቅጥ የረዘመው አቃቤ ህግ ‹‹ክቡር ፍርድ ቤት፣ ተከሳሹ
የሎርድ ሞንክፎርድ የሆነ ሃያ ፓውንድ ጥሬ ገንዘብና ጥንድ ከወርቅ የተሰሩ የሸሚዝ ማያያዣዎች ስርቆትና አንድ ምግብ ቤት ውስጥ ተመግቦ ሳይከፍሉ የመውጣት ጥፋት በመፈጸም ተከሷል፡ ፖሊስ የበርካታ ገንዘብ ስርቆት ጉዳይ እየመረመረ ስለሆነ ይህ ተከሳሽ በማረፊያ ቤት እንዲቆይ ይጠይቃል›› አለ፡፡

ሄሪ ዳኞቹን ሲመለከት ሁለቱም በንቀት ያዩታል፡ እነሱም ፊታቸው የቀረበ ሁሉ ጥፋተኛ ነው የሚሉ ይመስላሉ፡ ፍርሃት ፍርሃት አለው፡፡እንግዲህ የመሃል ዳኛው ናቸው ወሳኙ፡፡ ሰውዬው ሪዛቸው የሸበተ ሲሆን ገፅታቸውን ላነበበ በስራ ዘመናቸው በርካታ የክስ ጉዳይ ሲዳኙ የኖሩ
መሆኑን ያሳያል፡፡ እሳቸውን ነው መጠንቀቅ ሲል አሰበ ሄሪ፡፡

የመሃል ዳኛውም ‹‹የዋስ መብት ትጠይቃለህ?›› አሉት

ሄሪ ግር አለው ‹‹ወይ አምላኬ፤ አዎ ጌታዬ›› አለ፡፡

የትልቅ ሰው ንግግሩን ሶስቱም ዳኞች አስተዋሉ፡
ሄሪም ይህን ተገንዝቧል፡፡ የሰዎችን ግምት ማስለወጥ በመቻሉ ይኮራል፡ የዳኞቹ ሁኔታ ስላበረታታው አሞኛቸዋለሁ ሲል አሰበ፡፡

‹‹ምን ትላለህ?›› ሲሉ ጠየቁት።

‹‹አንድ ችግር ሳይፈጠር አይቀርም ጌታዬ›› ሲል ጀመረ፡ በዚህ ጊዜ ዳኞቹ ለመስማት በማቆብቆብ ወንበሮቻቸው ላይ ሲቁነጠነጡ ታዩ፡፡

‹‹እውነቱን ለመናገር በዚያ ምሽት ካርልተን ቡና ቤት
አንዳንዶቹ ሰዎች በጣም ጠጥተው ነበር›› አለና ዳኞቹን አማተረ፡

‹ካርልተን ክለብ ነው ያልከው?››

ሄሪ ከሚገባው በላይ የሄደ መሰለው፡፡ ምናልባትም የዚህ ክለብ አባል ነኝ ማለቱን ሊያምኑ ይችላሉ፡፡

ከዚያም ፈጠን ብሎ ‹‹በእውነት በጣም ያሳፍራል፡፡ ነገር ግን አሁኑኑ
እቦታው ድረስ ሄጄ ሁሉንም ሰዎች ይቅርታ እጠይቃለሁ›› ልክ የምሽት
ልብስ መልበሱን ድንገት እንዳስታወሰ ለመምሰል ‹‹ይህን የለበስኩትን ልብስ
ለውጬ›› አለ።
👍18
‹‹ሃያ ፓውንድና የእጅ አምባር አልሰረቅሁም እያልክ ነው?›› ዳኛው
ድምፃቸው ለስለስ ያለ ሆንዋል፡፡ ሆኖም ጥያቄ መጠየቅ መጀመራቸው ጥሩ ጅምር ነው፡፡ የፈጠረውን ታሪክ አልጣሉበትም ማለት ነው፡፡ ያለውን ካልተቀበሉት ዝርዝሩን ለመጠየቅ አይቸገሩም ነበር፡፡ ልቡ ተስፋ አቆጠቆጠ፡
ምናልባትም ፍርድ ቤቱ ይለቀው ይሆናል፡፡

‹‹የሸሚዝ ማያያዣዎቹን እንኳን ተውሼ ነው እንጂ አልሰረቅሁም የኔን እቤት ትቼ ነበር የወጣሁት።›› በኮቱ እጅጌ ስር ብቅ ያሉትን በሸሚዝ
ማያያዣ ያልተያያዙትን የሸሚዙን እጅጌዎች ከፍ አደረጋቸው፡፡ የራሱን
የሸሚዝ ማያያዣዎች ኪሱ ከቷቸዋል፡፡

‹‹ሃያ ፓውንዱስ?›› አሉ ሽማግሌው ዳኛ፡፡

ከባድ ጥያቄ መጣበት፡፡ መልስ አልመጣለት አለው፡ ‹‹የሸሚዝ ማያያዣህን ረስተህ ብትመጣ ከሰው መዋስ አንድ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን የሰው ገንዘብ ከወሰድክ እንደ ሰረቅክ ነው የሚቆጠረው፡፡››

‹‹ከመጀመሪያውም ጌታ ሲሞን ቦርሳቸው ምን ያህል ገንዘብ እንዳላቸው
የሚያውቁ አይመስለኝም›› ፍርድ ቤቱ ውስጥ ያሉ ተራ ሰዎች ቀጥሎ የሚለውን እንዳይሰሙ የፈለገ ይመስል ድምጹን ዝቅ አደረገ፡፡ ‹‹ጌታዬ
እሳቸው ሀብታቸው የተትረፈረፈ ባለፀጋ ናቸው››

መሃል ዳኛው ‹‹ምን ያህል ገንዘብ እንዳላቸው በመርሳት መቼም
ሀብታም አልሆኑም ጌታ ሲሞን›› አሉ፡፡ ሰዉ በሳቅ አውካካ፡፡ ቀልድ ጣል
መደረጉ አበረታች ቢሆንም መሀል ዳኛው ፈገግም አላሉም፧ፊታቸው ቅጭም እንዳለ ነው፡፡ ‹በምግብ ቤቱስ ሂሳብህን ሳትከፍል ለምን ወጣህ? ሲሉ ጠየቁት፡፡
‹‹ለዚህ በጣም አዝኛለሁ፡፡ ከራት ተጓዳኜ ጋር ብርቱ ጥል ተጣልቼ ነበር፡፡›› ሄሪ ከማን ጋር እራት እንደበላ መግለፁን ሆን ብሎ ተወው፡ የሴት ጓደኛውን ስም ሰው ፊት መግለፅ ተገቢ አይደለም፡፡ ዳኞቹም ይህን
ያውቃሉ፡ ‹‹ስለ ክፍያው ሳላስብ እብስ ብዬ ከምግብ ቤቱ ወጣሁ፡››

መሃል ዳኛው አፈጠጡበት፡፡ ሄሪ አንድ የማይገባ ነገር እንደተናገረ
ተሰማው፡፡ ልቡ በድንጋጤ ዘለለች፡፡ ምን ብሎ ይሆን? ዕዳውን (ሂሳቡን)
አለመክፈሉን እንደ ቀላል ነው ያየው፡፡ ይህ ደግሞ በትልቅ ሰዎች ዘንድ
ብዙም ትኩረት የሚሰጠው ነገር አይደለም፡፡ በአባባል ስህተት የገነባው ውሽት ሁሉ የሚናድ መሰለውና ሰውነቱን ፍርሃት ወረረው፡፡ ወዲያው ‹‹ጌታዬ፣ በእውነት ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው የፈፀምኩት፡፡ ምሳ ሰዓት አካባቢ ሄጄ እዳዬን እከፍላለሁ፤ የሚለቁኝ ከሆነ›› አለ፡፡

መሃል ዳኛው ጥያቄውን ይቀበሉ አይቀበሉ እርግጠኛ አልሆነም፡
‹‹ይህን በማለትህ ባንተ ላይ የቀረበው ክስ ሁሉ ውድቅ የሚደረግ መሰለህ?›› አሉት፡፡

አንተ ጉረኛ ሽማግሌ ዳኛ› ሲል ሄሪ በሆዱ ተሳደበ፡፡ ዳኞቹ ብዙ የሚሰድቡት ከሆነ ወህኒ የማውረዳቸው ዕድል ያነሰ ነው፡፡

‹‹ሌላ የምትለው አለህ?›› ሲሉ ዳኛው ጠየቁት፡

ሄሪ ደከም ባለ ድምፅ ‹‹ያደረኩት ነገር አንገቴን አስደፍቶኛል፡››

‹‹ህም›› መሃል ዳኛው በጥርጣሬ አጉተመተሙ፡ ሆኖም በመቀበል
ራሳቸውን ነቀነቁ፡፡

ሶስቱ ዳኞች እርስ በእርስ አንሾሾኩ፡፡ ሄሪም ትንፋሹን ውጦ ቆይቶ በረጅሙ ለቀቀው፡፡ የወደፊት እጣ ፈንታው በእነዚህ ደደብ ዳኞች እጅ መውደቁ አበሳጨው፡፡ ፈጥነው ተስማምተው ውሳኔያቸውን እንዲያሳውቁት ተመኘ፡ ነገር ግን ወዲያው በአንድነት ራሳቸውን ሲነቀንቁ ሲያይ
ውሳኔያቸውን ለሌላ ጊዜ እንዲያሰሙ ፍላጎት አደረበት፡፡

መሃል ዳኛው ‹‹አንድ ሌሊት እስር ቤት ማደርህ ከጥፋትህ እንድትማር
ያደረገህ ይመስለኛል›› አሉ፡፡

ኦ አምላኬ ዳኛው ሊለቁኝ ነው ሲል አሰበ፡፡ ምራቁን ዋጥ አደረገና
‹‹እርግጥ ነው ጌታዬ እዚያ መመለስ አልፈልግም›› አለ፡፡

‹‹ለወደፊቱ ተጠንቀቅ››

ዳኛው ወደ ተሰበሰበው ህዝብ እየተመለከቱ ‹‹የሰማነውን በሙሉ
አምነን ተቀብለናል ማለት አይደለም›› አሉ፡፡
ሄሪ በእፎይታ ጉልበቶቹ ሲብረከረኩ ተሰማው፡፡

መሃል ዳኛው ‹ብዋስ ተለቀሃል፡ የሃምሳ ፓውንድ ዋስ አቅርብ›› አሉ፡፡
ከእስር ቤት እንደወጣ ለተወሰኑ ስዓቶች ሳይሆን ልክ አንድ አመት የታሰረ ያህል መንገዱ ሁሉ አዲስ ሆነበት፡ ለንደን ለጦርነት ተፍ ተፍ እያለች ነው፡፡

ይቀጥላል
👍20👏1😱1
👉👉👉የጠንቆዩ ዋሻ👉👉👉
🗾🗾ክፍል 18🗾🗾🗾

መሳይ የኤዛ ያልተገደበ ስሜት ከበደው የዚች ሴት ሕይወት በሱ እጅ ያለች ያህል ተሰማው ትንሽ ጭንቅ አለው እሱ ወደትክክለኛ ኑሮው ሲመለስ ኤዛን መንከባከብ ይችል እንደሆነ እርግጠኛ መሆን አቃተው ፣ እውነት ለሷ የተገባው ሰው እሆን ይሆን ፣ በመካከላችን ያለው የዕድሜ ልዩነትስ የውጭውን ሕይወት ስታየው ቢሰማትስ እኔስ ብሆን ይሄ የጉርምስና ስሜቴን በምን መጠን መገደብ እችላለው ፣ ....በኤዛ እቅፍ ውስጥ ያለውን ሰውነቱን ደካማነት እየታዘበ ፣ በችግርና በጭንቀት የከረመውን አይምሮውን ሰብሰብ አድርጎ
"ኤዛ ውዴ ? የኔ ቆንጆ በቃ ተነሽ ፡ከዚ አካባቢ እንሽሽ ቃጠሎውን አይተው በአካባቢው ሰውም ካለ ወዲ መምጣቱ አይቀርም እኔና አንቺ ደግሞ ድንገት ብንታይ ጥሩ አይሆንም እሺ ፍቅር " ብሎ ረጅም ፀጉሯን በጣቶቹ እንደማበጠር አደረገላት ፣ ኤዛ መሳይን ከእቅፏ በማውጣት ትላልቅ አይኖቿን አይኖቹ ውስጥ በፍቅር አንከራተተቻቸው ፣ መሳይ የጎረምሳ ልቡ ፍርፍር እያለበት ፣ ተቸገረ የኤዛ እይታ ደሞ ያስተላለፈለት 'በዚች ምድር ላይ ካላንተ ማንም ሰው የለኝምና እባክህ ጠብቀኝ 'የሚል ለዛ ያለው መሰለው
"የኔ ቆንጆ ፈራሽ እንዴ አይዞሽ ፣ ቤተሰቦቼ ጋር ነው የምወስድሽ አንቺ ከሞት እንዳተረፍሽኝ ከነገርኳቸው በጣም ነው የሚወዱሽ በተለይ እናቴ "ብሎ በማባበል ከንፈራን በማበረታታት ሳማት ፣ መለሱን ሰጠችው ፣ እናም እቅፍ አድርጎ አነሳትና ልብሷን አስተካከለላት ፣ እሷም የለበሰውን ልብስ ስታራግፍለት ፈገግ አለ ፣ ምክንያቱም እሱ የሚራገፍ ነገር አልነበረበትም ፣ ከፍቅሯ የተነሳ እየተንከባከበችው እንደሆነ ገብቶታል ፣
እጇን ይዞ አካባቢውን በጥንቃቄ እያስተዋለ ተጓዘ ፣ መንገድ ለማግኘት ብዙ አስቸጋሪ ነበር በትላልቅ ዛፎች የተከበበ ስፍራ ነው በግልፅ መውጫ እንዳለው እንኳ አያስታውቅም ፣ ድክክም እስኪላቸው ነው ለመውጣት የተሽከረከሩት አመሻሹ ላይ ግን አንድ መንገድ አገኙና በግልግል ተነፈሱ ፣ ስለ አስባልት መንገዱ ኤዛ የምታውቀው ነገር ባይኖርም በመሳይ ደስታ ጥሩ ነገር እንደሆነ አስባ ተደሰተች ፣ በቀጭኑ አስባልት ላይ እየተጓዙ ሳለ ትላልቅ መኪኖች አልፈዋቸው ሲሄዱ ለኤዛ አዲስ ነገር ነውና ፈንጠዝ ስትል መሳይ እየሳቀ ያረጋጋታል ፣አልፎ አልፎም ከርቀት ሰዎችን እያየችም በመገረም ለመሳይ ትጠቁመዋለች ፣ መሳይ ከዚ የበለጠ በሰዎች የተሞላ ከተማ ሊሄዱ እንደሆነ እየነገረ ለዛ እንድትዘጋጅ ነገራት ፣ ኤዛ ለሁሉም ነገር እሱ አጠገቧ እስካለድረስ ፍራቻ እንደሌለባት ነገረችው እቅፍ አድርጓት በልበ ሙሉነት ተጓዘ ....በነፃነት በጀግንነት በፈቅር በብርሃን መንፈስ ታጅቦ ቆንጆና ማራኪ ልጅ ይዞ ወደ አዲስ አበባ ወደ እናቱ ቤት ፣ የአቢያራን የጥንቆላ እርኩሰት ድራሹን አጥፍቶ ፣ ጓደኞቹን ምን ያክል በእምነት በፅናት በአላማ እንሚበልጣቸው ጥግ ድረስ አሳይቷቸው ፣ አፍረው እንዲሸሹት አድርጎ ፣ .......
መሳይ ከኤዛ ጋር ከአንድ የጭነት መኪናላይ ለምኖ በመውጣት ወደ አዲስ አበባ ተጓዘ ፣ የኤዛ ውበት ከብዙ ሰዎ ጋር እንደሚያታግለው እያሰበ ግን ለማንም አሳልፎ እንደማይሰጣት ፣እንደሚጠብቃት ከልቡ ቃል እየገባ ፣ ወደራሱ አስጠግቶ ፣እቅፍቅፍ እንዳደረጋት ወደፊት አየ፣ የጭነት መኪናው ፣ ይዟቸው ከነፈ................................

ተ ፈ ፀ መ ።

ሙና መሀመድ

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍39👎87🥰5🤔5😁3
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ዘጠኝ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ


የጀርመንን ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች ለማሳሳት በርካታ ትላልቅ ብርማ
ቀለም ፊኛዎች ሰማዩ ላይ ያንዣብባሉ፡ ሱቆችና የመንግስት ህንፃዎች
ከቦምብ ናዳ ለመጠበቅ በአሸዋ በተሞሉ ጆንያዎች ዙሪያቸውን ተከበዋል፡
በየመናፈሻው የቦምብ
መከላከያ የተዘጋጀ ሲሆን ሁሉም ሰው በእጁ የጋዝ
ጭስ መከላከያ ጭምብል አንጠልጥሏል ሰዎች በማንኛውም ደቂቃ በቦምብ
ናዳ እንደሚያልቁ ያስባሉ፡፡

ሄሪ ስለ አንደኛው የአለም ጦርነት ምንም ትዝታ የለውም፡ ጦርነቱ
ሲያልቅ የሁለት አመት እምቦቃቅላ ነበር፡፡ ነፍስ እያወቀ ሲመጣ ጦርነት
ምን ያህል አሰቃቂ እንደሆነ አወቀ፡፡ በኋላም ፋሺስቶች በለንደን መንገዶች
ያደረጉትን ወታደራዊ ሰልፍ አዛውንት ይሁዳውያን በፍርሃት ሲመለከቱ
ሲያይ የጦርነትን አስፈላጊነት ተረዳ፡ሆኖም ሂትለር ሶቭየት ህብረትን
ይደመስስልኛል ብሎ የአንግሊዝ መንግስት የሆነውን ሁሉ እንዳላየ ሲያልፍ ጥላቻው ነገሰ፡፡

ሄሪ ከእስር ቤት ከወጣ በኋላ ቤቱ መሄድ እንደሌለበት ወስኗል።
ፖሊሶች በዋስ በመለቀቁ ስለተበሳጩ በማንኛውም አጋጣሚ ሊያስሩት
አቆብቁበዋል፡፡ ለትንሽ ጊዜ መደበቅ ያዋጣዋል፡፡ ተመልሶ እስር ቤት መግባት
አይፈልግም፡፡ ታዲያ ስንት ጊዜ ፖሊስ መጣ እያለ ሲበረግግ ሊኖር ነው?
ሁልጊዜስ ፖሊስን መሽወድ ይቻላል? ካልሆነስ ምን ማድረግ ይኖርበታል?

እናቱ በሃዘን ፊታቸው ጠቁሯል፡ ገንዘብ እንዴት እንደሚያገኝ ቢያውቁም አንስተውበት አያውቁም፡፡ ‹‹በእናትነቴ ምንም አድርጌልህ አላውቅም›› አሉት ‹‹እማማ ያለሽን አድርገሽልኛል›› ሲል መለሰላቸው፡፡

‹ሃሰት፤ ምንም አላደረኩልህም፤ ለዚህ አይደለም መስረቅህ››
ሄሪ ለዚህ መልስ አጣ፡፡

ከአውቶብስ እንደወረዱ ጋዜጣ ሻጩ በርኒን እናቱን በስልክ ስለጠራለት
እንደውለታ ቆጥሮት ጋዜጣ ገዛው፡፡ የጋዜጣው የፊት ሽፋን ጀርመን ፖላንድን በቦምብ ደበደበች ይላል፡ ወዲያውም አንድ ፖሊስ በብስክሌት ሲመጣ ተመልክቶ በደመነፍስ ተርበተበተ፡፡ እግሬ አውጪኝ ሊል ሲያስብ ሰው ለማሰር ሁለት ሆነው የሚመጡ መሆኑን ሲያውቅ አደብ ገዛ፡፡

እንደዚህ እየሰጋሁማ እንዴት እኖራለሁ› ሲል አስበ፡፡

እቤት ሲገባ እናቱ ሻይ ጥደው ‹‹ሰማያዊ ሱፍ ልብስህን ተኩሼልሃለሁ፤ መለወጥ ትችላለህ›› አሉት

እስካሁንም ልብሱን የሚያጥቡለትና የሚያዘገጃጁለት ካልሲውንም የሚሰፉለት እናቱ ናቸው፡፡ ሄሪ መኝታ ቤት ገባና ከአልጋው ስር ሻንጣውንዐአውጥቶ ገንዘቡን ቆጠረ፡፡ ሁለት ዓመት በስርቆት ተሰማርቶ ሁለት መቶ አርባ ሰባት ፓውንድ አጠራቅሟል፡፡ የአሜሪካ ፓስፖርት እጁ ገብቷል በሃሳብ ተውጦ ፓስፖርቱን እያገላበጠ ተመለከተው፡፡ ከአንድ አሜሪካዊ ላይ እንደመነተፈው አስታወሰ፡ የሰውየው ስም ሃሮልድ መሆኑን ሰውየውም
እሱን እንደሚመስል ተገነዘበና ኪሱ ከተተው፡

የአሜሪካውያንን የአነጋገር
ቅላጼ ይችላል፡፡ በአሜሪካ ውስጥ የእንግሊዛውያን የአነጋገር ቅላጼ ካለህ የከበርቴ መደብ አባል እንደሆንክ ተደርጎ ይቆጠራል፡ አሜሪካ ውስጥ በርካታ በፍቅር ልታሳብዳቸው የምትችላቸው ኮረዶች አሉ፡፡

እንግሊዝ ውስጥ የሚቀርበት እስር ቤትና ውትድርና ብቻ ነው፡፡
አሁን ፓስፖርትና ኪሱ ሙሉ ገንዘብ አለው፡ እናቱ ቁም ሳጥን ውስጥ ንፁህ ሱፍ ልብስ ያለው ሲሆን አንድ ሁለት ሸሚዝ መግዛት ይችላል።

ከሳውዝ ሃምፕተን 75 ማይል ነው የሚርቀው

ዛሬውኑ መሄድ ይችላል።

ሁሉም ነገር እንደ ህልም መሰስ ይላል።

እናቱ ‹‹ሄሪ ሳንድዊች ትፈልጋለህ?›› ሲሉ ጠየቁት

‹‹እሺ እማ››

ኩሽና ሄዶ ተቀመጠ፤ እናቱ ሳንድዊቹን ፊቱ ቢያደርጉለትም ንክች
አላደረገውም፡፡‹‹እማ አሜሪካ እንሂድ›› አላቸው
እናቱ በሳቅ ፈነዱ ‹‹እኔ አሜሪካ?!››
‹‹እውነቴን ነው፡ እኔ ልሄድ ነው፡››
አሁን ፈገግታቸው ጠፋ ‹‹ለኔ አይሆንም ልጄ፡፡ በዚህ እድሜዬ ስደት
ለኔ አይሆንም››

‹‹እዚህ እኮ ጦርነት ሊጀመር ነው፡፡››

‹‹አንድ ጦርነት፣ የስራ ማቆም አድማና የኢኮኖሚ መዳሸቅ አሳልፌያለሁ፡››

ጠባብዋን ማድቤት አማተሩና ‹‹የኔ ዓለም ይሄ ነው›› አሉ።

ሄሪ እናቱ በዚህ እንደማይስማሙ ቢያውቅም ቁርጡን ሲነግሩት ተስፋው ተሟጠጠ፡፡

በዚህ አለም ላይ ያሉት እናቱ ብቻ ናቸው፡፡

‹‹እዚያስ ምን ልትሰራ አስበሃል?›› ሲሉ ጠየቁት፡፡

‹‹የሌብነት ስራዬ ያሳስብሻል?››

‹‹ሌብነት የትም አያደርስም፡ በሌብነት ያለፈለት ሰው አላውቅም›› አሉት፡፡

‹‹እዚያ አየር ኃይል ገብቼ አብራሪ መሆን እፈልጋለሁ፡ አሜሪካ ውስጥ ጭንቅላት ካለሽ የሰራተኛው መደብ ብትሆኝም ግድ የላቸውም።››

እናቱ በመጠኑ ፈገግ አሉ፡ እሳቸው ሻይ ሲጠጡ እሱ ሳንድዊቹን ይገምጣል።

በልቶ እንደጨረሰ ገንዘቡን ከኪሱ አወጣና ሃምሳ ፓውንድ ቆጥሮ ለየ
‹‹ይሄ ለምንድን ነው?›› ሲሉ ጠየቁ፡፡ ይህ ገንዘብ ሁለት አመት ልብስ አጥበው የሚከፈላቸውን ገንዘብ ያክላል

‹‹ይጠቅምሻል እማ ውሰጂው›› አለ፡፡

እናቱ ገንዘቡን ተቀበሉና

‹‹እውነት ልትሄድ ነው?›› ሲሉ ጠየቁት።

‹‹ወደ ሳውዝ ሃምፕተን በሞተር ሳይክል እሄድና መርከብ ላይ እሳፈራለሁ»
እጃቸውን ሰደዱና የልጃቸውን እጅ ለቀም አደረጉ፡፡ ‹‹ልጄ መልካም
ዕድል ይግጠምህ፡››

እሱም የእናቱን እጅ ጨበጥ አደረገና ‹‹ከአሜሪካ ገንዘብ እልክልሻለሁ አለ።

‹‹አያስፈልግም፡፡ ከዚያ ደብዳቤ ቶሎ ቶሎ ስደድልኝና ጤንነትህን
ልወቅ፡፡››

‹‹እሺ እፅፍልሻለሁ፡››

አይናቸው በእንባ ተቆረዘዘ ‹‹አንድ ቀን ናና አሮጊት እናትህን እያት››

እጃቸውን ጨበጥ አደረገ፡፡ ‹‹እመጣለሁ እንጂ እማ፡፡ እመለሳለሁ፡››
ሄሪ በመስታወት ከላይ እስከ ታች ራሱን አየ፡፡

ሰማያዊው ሱፍ ልብስ ያማረበት ሲሆን ከሰማያዊው የአይኑ ቀለም ጋ ሄዷል፡፡

ሸሚዙ የአሜሪካ ሽሚዝ ይመስላል፡ ፁጉር አስተካካዩ የባለ ሁለት
ደረት ኪስ ኮቱን ትከሻ በቡሩሽ ሲጠርግለት ሄሪ ጉርሻ ሰጠውና ወጣ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የሳውዝ ሃምፕተን ወደብ በሰው ተጥለቅልቋል። ከዚህ ቦታ ነው የአትላንቲክ አቋራጭ ጉዞ የሚነሳው፡፡ በመሆኑም በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች
ከእንግሊዝ ለመውጣት ይተራመሳሉ፡፡

ሄሪ መርከብ ለማግኘት ሲጠያይቅ የሁሉም መርከቦች ቦታ ለመጪዎቹ
ሳምንታት ጉዞ አስቀድመው እንደተያዙ አወቀ፡ አንዳንዶቹ የመርከብ ትራንስፖርት ድርጅቶች ባዶ ቢሮ ታቅፈው ለሰራተኛ ደመወዝ ከመክፈል በራቸውን ዘግተዋል፡ ለተወሰነ ጊዜ ምንም ቦታ የማይገኝ መሰለው።

በመርከብ መሄዱን ትቶ ሌላ አማራጭ መጓጓዣ ሲያፈላልግ አንድ የጉዞ ወኪል ባህር ላይ የሚያርፍና ከባህር ላይ የሚነሳ የፓን አሜሪካን
አውሮፕላንን እንዳለ
አበሰረው፡፡ ስለዚህ አይሮፕላን በየጋዜጣው ላይ
አንብቧል፡ መርከብ ወደ ኒውዮርክ ከተማ ለመሄድ አራትና አምስት ቀን
የሚፈጅበት ሲሆን አይሮፕላኑ ከ30 ሰዓት ባነሰ ይደርሳል፡ ታዲያ የአንድ
ጊዜ ጉዞ ትኬት ዋጋ 90 ፓውንድ አዲስ መኪና ይገዛል።

ሄሪ በርካታ ገንዘብ አባክኗል፡፡ እብደት ነው፡፡ ታዲያ ከአገር ለመውጣት
ሲል የፈለገውን ያህል ዋጋም ቢሆን ለመክፈል ወስኗል፡፡ አይሮፕላኑ ምቾቱ
ያጓጓል፡ ኒውዮርክ እስክትደርስ ድረስ ሻምፓኝ መጨለጥ ነው፡፡ እንዲህ
አይነት ቅንጦት ደግሞ ለሄሪ ነፍሱ ነው፡፡

ፖሊስ ባየ ቁጥር መደንበሩ ሊቀር ነው፡፡ ሳውዝ ሃምፕተን ውስጥ
ደግሞ ስለ እሱ ሌብነት የሚያውቅ ፖሊስ የለም፡፡ ከዚህ ቀደም በአይሮፕላን
በርሮ ስለማያውቅ ግን አዕምሮው ተረብሿል፡፡

ሰዓቱን አየ፤ከቤተመንግሥት አንጋች ላይ የመነተፈው ነው፡፡
👍30
የተገላበጠ ሆዱን ለማስከን አንድ ሁለት ሲኒ ቡና ለመጠጣት የሚበቃ
ጊዜ ስላለው ወደ ቡና ቤት ሄደ፡፡

ቡናውን ፉት ሲል ልብ የምትሰርቅ ሴት ወደ ቡና ቤቱ ዘው አለች።
ያማረ ልብስ ለብሳለች፡ እድሜዋ ወደ ሰላሳዎቹ መጀመሪያ ላይ የሚገመት
በመሆኑ ከሄሪ አስር አመት ብትበልጥም አየት ስታደርገው ፈገግ አለ፡፡

ሴትዬዋ ከሄሪ ቀጥሎ የሚገኝ ጠረጴዛ ይዛ ቁጭ አለች። ባለ ነጠብጣቡ
ልብስ እንዴት ሰውነቷ ላይ ልክክ እንዳለ አስተዋለ፡ ፈዘዝ ያለ ብጫ ጫማ
የተጫማች ሲሆን የሰሌን ባርኔጣ አናትዋ ላይ ደፍታለች፡ ጠረጴዛው ላይ
ትንሽ ቦርሳ አስቀምጣለች፡፡
ወዲያው ጃኬት የለበሰች ሰው መጥቶ አጠገቧ ተቀመጠ፡፡ ሲነጋገሩ ሰማና
ሴትየዋ እንግሊዛዊት ሰውየው አሜሪካዊ መሆናቸውን አወቀ፡፡ የሴትየዋ ስም ዳያና የሰውየው ደግሞ ማርክ እንደሆነ አረጋገጠ ሰውየው ክንዷን ሲደባብስ
ደረቱ ላይ ልጥፍ አለች። በፍቅር ስለታወሩ ለማንም ቁብ የላቸውም፡፡ ቡና
ቤቱ ለእነሱ ማንም የለበትም፡

ሄሪ በቅናት ተንጨረጨረ፡፡

ሄሪ ፊቱን አዞረ፡ ሆዱ አሁንም በፍርሃት እየታወከ ነው: አትላንቲክን በሙሉ በአየር ሊያቋርጥ ነው፡፡ ከስር ምንም መሬት ሳያዩ ረጅም ጉዞ ማድረግ ሲታሰብ ያስጨንቃል፡፡ ሄሪ የአየር ጉዞ ሳይንስ አይገባውም፡፡የአይሮፕላኑ ሞተሮች ይሽከረከራሉ፤ ታዲያ አይሮፕላኑ ወደ ሰማይ የሚመነጠቀው እንዴት ነው?!

ማርክና ዳያና የሚነጋገሩትን እያዳመጠ የተረጋጋ ለመምሰል ጣረ፡ ሌሎቹ የአይሮፕላኑ ተሳፋሪዎች መጨነቁን እንዲያውቁበት አልፈለገም
‹እኔ ቫንዴርፖስት ነኝ ሲል አሰበ፡፡ አውሮፓ ጦርነት ስለሆነ ወደአሜሪካ የሚመለስ ወጣት አሜሪካዊ ነኝ አሁን ስራ ባይኖረኝም አንድ ገገር መስራት አለብኝ አባቴ ኢንቬስተር ሲሆን እናቴ ነፍሷን ይማረው እንግሊዛዊት ናት ዩኒቨርሲቲ አልገባሁም፧ እንግሊዝ አገር ብዙ ስለቆየሁ የአካባቢው ቋንቋ ተዋህዶኛል፡፡ ጥቂት ጊዜ በአይሮፕላን ሄጃለሁ አተላንቲክ አቋራጭ

የመጀመሪያዬ ነው፡፡ ጉዞዬን
በጉጉት እየተጠባበቅሁ ነው፡›
ቡና ጠጥቶ ሲጨርስ ፍርሃቱ ውልቅ ብሎ ሄደለት፡፡

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ኤዲ ዲኪን ስልኩን ዘጋና ዙሪያውን ቃኘ፡፡ የተነጋገረውን ማንም የሰማ የለም ችግር ውስጥ የከተተው ስልክ ላይ አፈጠጠ፡ ጠላው፡፡ የቀን ቅዠቱን የሚያጠፋለት ይመስል ስልኩን ሊሰባብረው ተመኘ፡፡ ከዚያም ቀስ ብሎ ዞሮ ሄደ፡፡

‹‹እነማን ናቸው? ካሮል አንን የት ነው የወሰዷት? ምንድነው ከሱ
የሚፈልጉት?›› ልክ ደንበጃን ውስጥ እንደገባ ዝምብ ጥያቄዎቹ አእምሮ ውስጥ ጥዝዝ አሉ፡ ለማስታወስም ሞከረ፡ በአንድ ጊዜ አንድ ጥያቄ ብቻ ማተኮር ፈለገ፡፡

«ማናቸው? እንዲያው እብዶች ናቸው? አይደሉም: የተደራጁ ናቸው
ኤዲ የት እንደሚሆን አውቀው ካሮል አንን አግተው ይዘው በተገቢ
ሰዓት ከሚስቱ ጋ እንዲነጋገር ለማድረግ በጥንቃቄ አቅደዋል፡ ሰዎቹ ቀላል ሰዎች አይደሉም፡፡ ለዚህ ደግሞ ህግ ለመጣስ ዝግጁ ናቸው፡፡ ከወሮበሎች ጋር እንደተጋፈጠ ተረድቷል፡፡

ካሮል አንን የት ነው የወሰዷት? ቤት ውስጥ ነው ያገቱኝ› ብላለች።
የአንዱ አፋኝ ቤት ይሆናል፤ ወይም ቤት ተከራይተው ይሆናል፡ አሊያ
ሰው የሌለበት ቦታ ወስደዋታል፡፡
ካሮል እንዳለችው ያገቷት ከሁለት ሰዓት በፊት ነው፡፡ ከባንጎር ከሰላሳ
ወይም ከሰባ ማይል አይርቅም፡፡

«ለምን አገቷት? አንድ ነገር ከሱ ፈልገዋል በፈቃደኝነት
የማይሰጣቸው ነገር ለገንዘብ ሲል የማያደርገውን አንድ ነገር፡፡ ገንንዘብ የለውም፡፡ ምንም የሚያውቀው ምስጢር የለም፡ በእሱ ቁጥጥር ስር ሰው የለም፡፡ ስለዚህ ጉዳያቸው ባህር ላይ እሚያርፈው አይሮፕላን "
የተያያዘ መሆን አለበት፡፡

መመሪያ ቶም ሉተር ከሚባል አይሮፕላኑ ላይ ከተሳፈረ
እንደሚሰጠው ተነግሮታል፡፡ ሉተር ስለ አይሮፕላን አንቀሳቃሽ ክፍሎች
በሚያውቅ ሰው የተቀጠረ ሰው ይሆናል፡ ሌላ በዚህ አይሮፕላን ላይ
ሊኖረው የሚችለው የአየር መንገድ መስሪያ ቤት ምናልባትም የውጭ አገር መስሪያ ቤት ይሆናል፡፡ ነገር ግን የዲዛይኑን ኮፒ ማግኘት የሚችሉበት ቀላል መንገድ አለ፤ እንደዚህ አይነቱን ሰነድ ብዙ ሰው ሊሰጣቸው ይችላል! የፓን
አሜሪካን አየር መንገድ ሰራተኞች፣ የቦይንግ ኩባንያ ሰራተኞች፣ እዚህ
ያሉት የኢምፔሪያል አየር መንገድ መካኒኮች፡፡ የቴክኒክ ዝርዝሮች ደግሞ በየመጽሔቱ ላይ ይወጣል፡፡ ሰው ማገት አያስፈልግም ነበር።

ወይስ አንድ ሰው አይሮፕላኑን ከነነፍሱ ሊወስደው ያስባል፡

ሌላ ሊሆን የሚችለው ምክንያት ኤዲ አንድ ሰው ወደ አሜሪካ
ለማስገባት እንዲያግዛቸው ነው፡:
ለጊዜው ሊገምት የቻለው እነዚህን ብቻ ነው፡፡

ስለዚህ ምንድነው ማድረግ ያለበት?

ኤዲ ለህግ ተገዥ ሰው ነው፡፡ አሁን የወንጀል ሰለባ ሆኗል፧ እናም
ፖሊስ መጥራት ፈለገ፡፡ ነገር ግን ፈራ፡፡ በህይወቱ እንዲህ ፈርቶ
አያውቅም፡፡ በልጅነቱ አባቱንና ሰይጣንን ብቻ ነበር የሚፈራው፡፡ ከዚያ ወዲህ ግን የሚያስፈራው ነገር አልነበረም፡፡ አሁን አቅመ ቢስ ሆኗል፡፡ሰውነቱ ደነዘዘ፤ ከቆመበት መንቀሳቀስ አቃተው፡፡

እንግሊዝ ውስጥ ስላለ ለእንግሊዝ ፖሊሶች የሚያሳውቅበት ምክንያት
የለውም፡፡ ወደ አሜሪካ ፖሊስ ወይም ኤፍ ቢ አይ ስልክ ደውሎ በቅርቡ የተከራየ ገንጠል ያለ ቦታ ላይ ያለ ቤት በሙሉ እንዲያስሱ ሊነግራቸው ተመኘ።

‹‹ለፖሊስ ስልክ እንዳትደውል፤ አይረባህም›› ብሎታል በስልክ
የተንቆረቆረው ድምጽ፡ የምትደውል ከሆንክ ምን ያህል ክፉ እንደሆንኩ
እንድታውቅ፤ ሚስትህን እደፍራታለሁ!›› ብሎታል፡፡ ኤዲም አመነው ማድረጉ እንደማይቀር ከድምጹ አውቋል፡ የሆዷ ሞላ ማለትና የጡቷ መወጣጠር ካሮል አንን የምታማልል አድርጓታል፡፡ እጁን ቡጢ ጨበጠ፤ ነገር ግን ከግድግዳው በስተቀር የሚመታ ነገር የለም፡፡

ኤዲ ተራ ሰው ነው፤ የተወለደው ከባንጎር ወጣ ያለ ገጠር ውስጥ
ነው፡፡ አባቱ አርሶ አደር ሲሆኑ የበሬ ግምባር የምታክል የድንች ማሳ፣
በጣት የሚቆጠሩ ዶሮዎች፣ አንዲት ላምና የጓሮ አትክልት ነበራቸው፡ ኒው ኢንግላንድ ስቴት አሜሪካ ውስጥ በድህነት መኖር ከባድ ነው፡፡ ክረምቱ አለቅጥ ረጅም ሲሆን በጣም ይበርዳል፡ አባቱና እናቱ እግዚአብሔር ያመጣው ነው ይላሉ፡፡ የኤዲ ታናሽ እህት በሳምባ ምች ስትሞት እግዚአብሔር እኛ የማይገባን ምክንያት ስላለው ነው ብለዋል፡ በልጅነቱ ጫካ ውስጥ የተቀበረ ሃብት አገኛለሁ እያለ በቁሙ ያልም ነበር፡ ያ የገጠር
ቤታቸው ምቾት ወደ ተሞላበት እና ደስታ ወደነገሰበት ቦታ ሲለወጥ በዓይነ ህሊናው ይታየው ነበር፡ የተመኘውን ሀብት ባያገኝም በየቀኑ በእግሩ እየኳተነ የተማረበትን ዕድል አላጣም፡፡ ትምህርት ቤቱ ከቤቱ ይልቅ ይሞቅ ስለነበር ይወደው ነበር፡፡ አስተማሪው ደግሞ
መሳሪያዎች እንዴት እንደሚሰሩ ይጠይቃት ስለነበር ትወደው ነበር፡፡

ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ አናፖሊስ ባህር ኃይል ማስጠኛ ገባ
ማሰልጠኛው ለእሱ ገነት የመግባት ያህል ነበር፡፡ መኝታው የተሟላ ምግቡ ለሱ ጥሩ ነው። እንዲህ አይነት ቅንጦት በህይወቱ ሙሉ አልሞ አያውቅም የማሰልጠኛው ጥብቅ ደምብ ለእሱ ቀላል ነበር፡ በመጠኑ በትምህርት
ያጋጠመው መዋከብ ከአባቱ ነጋ ጠባ ድብደባ ጋር ሲነጻጸር እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም፡፡
👍16😁1
መጀመሪያ ማሰልጠኛ የገባ ጊዜ ነበር ሰዎች ስለእሱ ያላቸውን
አስተሳሰብ ማወቅ የጀመረው፡ ቀስ በቀስ ሃቀኝነትን፣ ደምብ ማክበርን
ለፍቶ አዳሪነትንና አቋመ ጽኑነትን እየተላበሰ መጣ፡፡ ቀጫጫ ቢሆንም ጉልበተኞች አይደፍሩትም ነበር፡፡ አባቱና አስተማሪው አንድ ነገር የሚገኘው በስራ ብቻ መሆኑን ደጋግመው ነግረውታል፡፡ እሱም የሚገባው ይኸው መንገድ ብቻ ነው።

ስልጠናውን አጠናቆ እጩ መኮንንነት ማዕረግ እንደተቀበለ በራሪ ጀልባዎች ላይ ስልጠና እንዲወስድ ተመደበ፡፡ ባህር ማሰልጠኛው ተመችቶት ስለነበር ለወላጆቹ ገንዘብ ይልክላቸው ነበር፡ እነሱ ልጃቸው በሚልክላቸ
ገንዘብ ጎጇቸውን ያጠባብቁበት ነበር፡፡

ባህር ኃይል አራት አመት ያህል እንደቆየ እናቱ አረፉ፡፡ አባቱ ደግሞ
ከአምስት ወር በኋላ ተከተሉ ወላጆቹ ከሞቱ በኋላ የአባቱን መሬት ሰው ወሰደው፡ ኤዲ ግን ቤቱንና መሬቱን በትንሽ ገንዘብ ገዝቶ መልሶ ተረከበው ከባህር ኃይልም ለቀቀና ፓን አሜሪካን አየር መንገድ በጥሩ ደመወዝ ተቀጠረ

በረራ በሌለበት ጊዜ የአሮጌውን ቤት ቧንቧ፣ ኤሌክትሪክና ቤት
ማሞቂያውን ራሱ ይጠግናል፡ ለቤቱ የኤሌክትሪክ ማሞቂያ፣ ሬዲዮና ስልክ አስገባ፡፡ ከዚያም ካሮል አንን ተዋወቀ፡ ቤቱ ልጅ በልጅ ሲሆን ታየው ህልሙ እውን የሆነ መሰለው።

ወዲያውኑ ግን ሁሉም ነገር የቀን ቅዠት ሆነበት፡፡....

ይቀጥላል
👍111
አትሮኖስ pinned «#ጠላፊዎቹ ፡ ፡ #ክፍል_ዘጠኝ ፡ ፡ #በኬንፎሌት ፡ ፡ #ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ የጀርመንን ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች ለማሳሳት በርካታ ትላልቅ ብርማ ቀለም ፊኛዎች ሰማዩ ላይ ያንዣብባሉ፡ ሱቆችና የመንግስት ህንፃዎች ከቦምብ ናዳ ለመጠበቅ በአሸዋ በተሞሉ ጆንያዎች ዙሪያቸውን ተከበዋል፡ በየመናፈሻው የቦምብ መከላከያ የተዘጋጀ ሲሆን ሁሉም ሰው በእጁ የጋዝ ጭስ መከላከያ ጭምብል አንጠልጥሏል ሰዎች…»
😘😘 ቃል 😘😘
ዳንኤላ ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አንድ (1)

በሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ የኢሊየት ቤት እየተባለ ከሚጠራው ፊት ለፊት የማለዳ ፀሐይ ጀርባቸውን እየዳሰሰቻው ፤ ብስክሌቶቻቸውን ለጉዞ አዘጋጁ ። እና ሁለቱም ድንገት ቀና አሉ አንዳቸው ከአንዳቸው የሚፈነጠቀውን የፈገግታ ብርሃን በመሻት ። ወሩ ግንቦት ነበር የጸደይ ወራት መዳፊያ፤ የወጣትነት ፤ የአበባነት ተምሳሌት ፤ ግንቦት ። እነሱም አፍላ ወጣቶች ነበሩ ። በጥቁር ፀጉሯ ላይ የማለዳዋ ፀሐይ ጨረሮቿን ስላሳረፈችበት እንደንፁሀ ጥቁር ሀር ሲያንጸባርቅ ይታያል ። ዓይኖቹ ላይ ያረፉ አይኖቿም በደስታ ብርሃን ይረጫሉ እንዲያ ብርሃንን በሚረጩ ዓይኖቿ እያየችው ፍንድቅ ፤ ፍልቅልቅ ብላ ሳቀች ።

« እሺ የኛ ዶክተር ለመሆኑ ምን ይሰማሃል ?» ስትል ጠየቀች .፡፣ ፍልቅልቅ ሳቋን አቁማ ፤ በፈገግታ ጎልታ ።የሚሰማኝን እንድነግርሽ ከፈለግሽ ሁለት ሳምንት ያህል መታገስ ይኖርብሻል ። ዲግሪየን እስክቀበል ማለቴ ነው አለ ። እሱም እንደሷው በፈገግታ በርቶ ፤ በግንባሩ ላይ ዘፍ ያለውን ነጣ ያለ ወርቅማ የጸጉር ቱባ ራሱን ነቅንቆ ወደ ኋላ እየመለሰ “
« ዲግሪ !? » አለች « ብትፈልግ ከዲግሪህ ጋር እንጦሮጦስ ውረድ ! እኔ ያልኩህ ስላለፈው ሌሊት ምን ይሰማሃል ነው» ይህን ብላ እንደገና በፈገግታ ተበረገደች
ምን እንደሚሰማው ለጠየቀችው ጥያቄ መልስ ከመስጠቱ በፊት ኋላዋን በመቃበጥ መልክ ቸብ አደረጋት ።

« ወደር የለሽ ነው » አለ ኋላዋን እየተመለከተ ። ቀጥሎም «የአንችስ ስሜት እንዴት ነው ? ለመሆኑ ለሽርሽር የተረፈ አቅም አለሽ?» ይህ ሲሆን ብስክሌቶቻቸው ላይ ወጥተው በየፊናቸው ፔዳል አስተካክለው በመርገጥ ላይ ነበሩ ። « አንተስ ፤ አቅሙ የተረፈህ ይመስልሃል ? » አለች ። ይህን ተናግራ ብስክሌቷን አስነስታ ጥላው ነጐደች ። ትንሷን ብስክሌት…ከጥቂት ወራት በፊት የተወለደችበትን ቀን ሲያከብሩ የገዛላትን ብስክሌት… አስነስታ ጥላው ነጐዶች ። ከልቡ ያፈቅራታል ሕይወቱን በሙሉ እሷኑ ሲያፈቅር ነው የኖረው። እሷን የመሰለች ልጅ ጸንሶ ፤ እሷኑ ሲያልም ፤ እሷኑ ሲያፈቅር ኖሯል ። በልቡ ቢጸንሳትም በግዘፈ አካል ካገኛት ከተዋወቁ ግን ይኽው ሁለት ዓመት ሞላ።

ከመገናኘታቸው በፊት የእሱም የእሷም ኑሮ የብቸኝነት ኑሮ ነበር። በእርግጥ ድንግል ሆኖ ኖረ ልንል አንችልም ። ግን የሚያገኛቸው ሴቶች ደግሞ ያችን በልቡ የቀረፃትን ፤ ሙሉ ብሎ የሚያስባትን ሴት ሆነው አላገኛቸውም ።

በሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ የከፍተኛ ትምህርቱን ለመከታተል ከኒውዮርክ ስቴትስ ወደ ማሳቹሴትስ ስቴት ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን ብናሰብ እንኳ በዚህ ጊዜ ውስጥ ከተለያዩ ከተሞች ከመጡ ልጃገረዶች ለዓይኑ የገቡለትን ቀርቦ ከማነጋገር አልተቆጠበም ። ግን ገና የመጀመሪያ ዲግሪውን ሳያገኝ ተስፋ ቆረጠ ። የመጀመሪያ ዲግሪውን ይዞ የማስተርስና የዶክትሬት ዲግሪውን ለመቀበል በዚያው በሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ቀጠለ ። በዚህ ጊዜ ግን ተስፋ ቆርጦ ነበርና ማንኛዋንም ሴት አይሞክርም ነበር። እነዚያ ከተለያዩ ከተሞች የሚመጡ ልጃገረዶች ወይ ዕውቀት ወይ ንጹህ ነፍስ ወይ ታማኝነት ይጐድላቸው ነበረና ደጋግሞ መሞከሩን ከንቱ ነገር ብሎ ተወው" የድህረ ምረቃ ትምህርቱን በመከታተል ሁለቱን አመታት በዚህ ሁኔታ በብቸኝነት አሳለፋቸው ።
የሁለተኛው ዓመት መዳፊያ ብቸኝነቱን የሚሰርዝ ነገር አበረከተለት ። ገና በአካል ሳያያት ስእሎቿን በማየት ብቻ ደነገጠ። ስእሎቿ በቦስተን ከተማ በአንድ አዳራሽ ለኤግዚቢሽን ቀርበው ነበር ያንን ኤግዚቢሽን ሲያይ ሰዓሊዋ አንድ የተለየ ኃይል እንዳላት ገባው

የመልክዓ ምድር ቅብ ስእሎቿ በልቡ ውስጥ የጸጥታን ሰላም ፈጠሩበት ። እውጭ ሆኖ የሚያያቸው ሳይሆን እውስጣቸው ገብቶ የሚኖር መሰለው ። በስእሎቿ ላይ ያቀረበቻቸው (የሳለቻቸው) ሰዎችም በሸራ ላይ በቀለም የተሰሩ ግዑዝ ምስሎች ሳይሆኑ ነፍስ ያላቸውና አብረን እንኑር የሚሉ ሕያውና ተግባቢ ሰዎች ሆነው አገኛቸው። የተለየ ስሜት ተሰማው ። ከነዚህ ሰዎች ጋር በነዚያ ቦታዎች ላይ የመኖር ጉጉት አደረበት ።ይልቁንም እነዚህን ሰዎችና እነዚያን ቦታዎች ከፈጠረችው ሰዓሊ ጋር የመኖር ጉጉቱ የበረታ ሆነ ። ሰዓሊዋን ለማየት ፈለገ ።

ተቀምጣ አያት ፤የሱፍ ኮፍያ አድርጋ ፤ የቆዳ ኮት ለብሳ። ወደ ኤግዚቢሽኑ አዳራሽ የመጣችው በቅርብ እንደሆን ያስታውቃል ። ላቧ አልደረቀም ደክማለች ። እንዲያ ደክሟትም የገጽታዋ ብሩህ መሆንና ከዓይኖቿ የምትረጨው ረቂቅ ብርሃን ደምቀው ታዩት ።
ሲያያት ደነገጠ ። ሲያያት ሰውነቱ ተሸበረ። ብቻም አልነበረም ። ገና እንዳያት ተመኛት ። ለሌላ ነገር፤ ለስጋ ጉዳይ ሳይሆን የሱ ሊያደርጋት ተመኘ። ይህ ስሜት ግን ለሱ አዲስ ነበር ። ማንም ትሁን ማን… ከዚህ በፊት አንዲት ሴት አይቶ ወዲያው ተመኝቷት አያውቅም ነበር። ለእለት የስጋ ፍላጐት እንኳ ቸኩሎ አያውቅም ነበር ።" ምንም እንኳ ስሜቱ እንግዳ ቢሆንም ይህ እንግዳ ስሜቱም አላስፈራውም ።
ያኑ እለት ለኤግዚብሽን ከቀረቡት ስእሎችዋ መካከል ሁለቱን ገዛ ። ያኑ እለት ተዋወቁ ። ያኑ እለት ራት ሊጋብዛት እንደሚፈልግ ገለፀላት ። እሷም ግብዣውን ተቆበለች ። እና ያኑ እለት ወዳንድ በጣም ታዋቂ ወደሆነ ምግብ ቤት ሄደው ራት በሉ ። ሌላው ሌላው ነገር ግን ቀስ እያለ ነበር የሆነው ።

እሷ ናንሲ ማክአሊስተር ትባላለች እሱ ደግሞ ማይክል ሂልያርድ ይባላል ። ወሩ ግንቦት ነበር ። እነሱም አፍላ ወጣቶች ።
ናንሲ ማክአሊስተር ገና የአሰራ ዘጠኝ ዓመት ጉብል ነበረች ። ከማይክል ሂልያርድ ጋር ሲተዋወቁ ከሁለት ዓመት በፊት ። ናንሲ ለማይክል ልቧንም ሆነ አካሏን በአጭር ጊዜ ልትሰጠው አልቻለችም ። የሚቻላትም አልነበረችም ። ያደገችው በእጓለማውታን ማሳደጊያ ውስጥ ነበር። አሳዳጊዎችዋ መነኩሲቶች ነበሩ ። ወደ እጓለማውታን ማሳደጊያው ወስዳ ያስረከበቻት እናቷ እንደነበረች በሰሚ ሰሚ ብታውቅም ናንሲ ግን እናት የሚባል ነገር ኖሯት አያውቅም ። እናቷ ትዝ አትላትም።
👍251
የምታስታውሰው ጭንቀት ጭንቀቱን ብቻ ነው ። ቀዝቃዛውን የእጓለማውታን መመገቢያ አዳራሽ ! ያ አዳራሽ ዛሬም ትዝ ባላት ቁጥር ይቀዘቅዛታል የማታውቀው ፤ያለመደቻቸው ሰዎች ጠረን ዛሬም ይሸታታል ፤ ያስፈራታል ። እንቅልፍ የወሰዳት መሰላ አልጋዋ ላይ ተኝታ ትሰማቸው የነበሩ የተለያዩ እንግዳ ድምጾች ዛሬም እንግዳ ሆነው ትሰማቸዋለች ። ዛሬም ወደ አንድ የማታውቀው ዓለም የተጣለች ብቸኛ ፍጡር የሆነች ይመስላታል በጠቅላላ ናንሲ አባቴ ወይም እናቴ የምትለው ሰው ሳይኖራት ፡ ልጄ ብሎ እቅፎ የሚስም ወላጅ ሳታይ የእናት.. አባት ፍቅር ሳታገኝ ያደገች ልጅ ናት ። ታዲያ ይህች ልጅ ምን ሆና ምንስ አድርጋ ለማይክል ሂልያርድ በቶሎ ልቧን ከፍታ ትስጠው ? የማይቻላት ነገር ነበረና ፍቅሯንም ፤ አካሏንም የሰጠችው ቀስ እያለች ነበር ።

ናንሲ ማክአሊስቶር ማይክል ሂልያርድን እሰክታገኝ በነፍሷ ውስጥ አንድ ትልቅ ክፍት ቦታ እንዳለ አዘውትራ ታስብ ነበር። ያን ክፍት ቦታ ሊሞላ የሚችል ሰው አገኛለሁ የሚል ሕልም እንኳን አልነበራትም ። ግን አገኘች ዛሬ ያንን ባዶ ማይክል ሞልቶታል ። ዛሬ ያ ባዶ የለም ። የኔ እምትለው ሰው አላት ።

የማይክልና የናንሲ ፍቅር የአንድ ሰሞን ሽር ብትን ፤የአንድ ሰሞን የስጋን ትኩሳት ለማብረድ የታለመ ተራ ፍቅር አልነበረም አይደለም ። የነዚህ የሁለቱ ፍቅር በጠንካራ ስሜት ላይ የተመሰረተ ፍቅር ነው። ይህ ፍቅር ስላለም እሷ በሱ የተሟላና የተደላደለ አስተዳደግ የበታችነት አይሰማትም፡፡ እሱ የሷን ተራ አስተዳደግ ተመልክቶ እንደ ዝቅተኛ አያያትም ። በዚህ ፈንታ አንዳቸው ካንዳቸው አስተዳደግ እየተማሩ የኖሩትንና ከዚያ ኑሮ ያገኙትን ልምድ አዋጥተው በመቀየጥ ውብና እጹብ ድንቅ የሆነ እዲስ ኑሮ ፈጠሩ ። ስለዚህ እሷ ለሱ አዲስ አይደለችም ፣እሱም ለሷ አዲስ አይደለም ።
የማይክል እናት ማሪዮን ሂልያርድ የማይክልና የናንሲን ፍቅር ስትሰማ «ለየት ካለ ሰው ጋር ፍቅር ሲይዝህ ደግ አይደለም» ስትል ለልጅዋ እንደማስጠንቀቂያም እንደምክርም አድርጋ ነግራው ነበር ። ማሪዮን ነገሯን የጀመረችው «ከሆነች ሰዓሊ ጋር ፍቅር ያዘኝ ብሎ ይንዘላዘላል ብለው ነገሩኝ» በማለት ነበር ።

ይቀጥላል...

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍21
#ሳቤላ


#ክፍል_አርባ_ዘጠኝ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ከበረዶው ማዕበል በኋላ ብራ የሆነ ጧት ተተካ ሰማዩ ፍንትው ብሎ ጠርቶ
ፀሐይ ደምቃ ስታበራ ሲጥል ያደረው በረዶ ግን ከመሬት እንደ ተቆለለ ነበር
ሚስዝ ሔር በወንበር ተቀምጣ የቀኑን ድምቀት እያየች ትደሰታለች የማስተር ካርላይልም
አጠገቧ ቆሟል ከባርባራ ጋር የመለያየቷን ነገር ስታስበው ኀዘኑ ለሷ አቻዋ የሆነ ባል በማግኘቷ ደስታው ሁለቱ ስሜቶች ተጋጭተው ሲያስጨንቋት ዐይኖቿ የኀዘንና የደስታ እንባ አቀረሩ ።

“አርኪባልድ . . . ይህች ልጅ ከኛ ጋር ሁና ደስተኛ ነበረች አንተ ዘንድም የለመደችውን ደስታ ታገኘው ይመስልሃል ?

“ እኔ በምችለው ሁሉ።"

“ ታዝንላታለህ ? ትንከባከባታለህ ?

ሚስዝ ሔር ... ደኅና አድርገው
ስለሚያውቁኝ የሚጠራጠሩኝ አይመስለኝም ነበር " አሁንም ባለኝ አቅም ሁሉ በሙሉ ልቤ እሷን ለማስደሰት እሞክራለሁ " "

“ አንተን አልጠረጥርህም ! በደንብ አምንሃለሁ ዓለም ሁሉ ከባርባራ እግር ቢወድቅ አንተን እንድትመርጥልኝ እጸልይ ነበር ግን አርኪባልድ የኮርንሊያ ነገርስ እንዴት ይሆናል ? እኔ እንኳን ባንተ ጉዳይ ወይም አንተና ባርባራ ተስማምታችሁ በምትፈጽሙት ለመግባት ሳይሆን ባልና ሚስት ብቻቸውን ቢሆኑ የማሻል መስሎኝ ነው "

"እሷ የፊተኛዋ ሚስቴ ሳለችም ብዙ ጊዜ ጣልቃ እየገባች ታስቸግራት እንደ ነበረ ለማወቅ ችያለሁ ይህን ነገር በጊዜው ብሰማ ኖሮ አንድ ቀን አላሳድራትም ነበር " አሁን ግን ይህ ነገር አይደገምም " በርግጥ ገና አልነገርኳትም እንጂ ኮርኒሊያ ከኢስት ሊን ለቃ ከቤቷ ትገባለች " በዚህ ምንም አያስቡ "

“ኧረ ለመሆኑ ባርባራ ስንቱን ሰው ስትመልስ ኖራ አንተን እንዴት እሺ አለችህ ? አለ ቀደም ሲል በነገሩ መደስቱንና ስምምነቱን የገለጸው ሚስተር ጀስቲስ ሔር "

“ ምናልባት መስተፋቅር አድርጌባት ይሆናል ” አለ ሣቅ ብሎ "
“ እንዲያውም ይኸው መጣች ” አለና አባትየው።

“ ኧረ እንዲያው ለነገሩ ካርላይልን ከሌሎች የተለየ ምን ብልጫ አየሽበት ? አላት "

ጉንጮቿ ፍም በመምሰል መልሱን ተናገሩላት “ “ አባባ .... ሚስተር ኦትዋይ ቤቴል ከደጅ ሊያነጋግርህ ይፈልጋል " ጃስፐር እንዶፈደ ነገረኝ ከሆነ ለመግባት አልፈለገም አለችው።

“ እኔም ብሆን በዚህ ብርድ አልወጣለትም " ሚስተር ኦትዌይ ... ግባ እንጂ
ምን አስፈራህ ? አለው
“ቀጠሯችሁ ከሰባት ሰዓት ወደ ስምንት ሰዓት ቢለወጥ የሚመችዎ እንደሆነ ኮሎኔል ጠይቅ ብለውኝ ነው የመጣሁት " አንድ ያልታሰበ እንግዳ ስለ መጣባቸውና እሱም ዛሬ በስምንት ሰዓቱ ባቡር ተመልሶ ስለሚሔድ ነው ” አለው "

“ እኔምን ከፋኝ ! በሰባትም ሆን በስምንት ግድ የለኝም ” አለው ሚስተር ሔር"

“እሺ! እንግዲያው ይኸንኑ ለሔርበትና ለፒነር ልንገራቸው " ለመሆኑ ሙቶ ስለ ተገኘው ሰውዬ ሰምተዋል ?

" የምን ሰው ነው ?

“ እንግዲህ አንዱ መንገድ የጠፋው ወይም ደክሞት ከበረዶው የወደቀና በዚያው እንዳለ የቀረ ይሆናል እንጂ ከሆሊጀን ቤት መዞሪያ አጠገብ ካለው ጐድጓዳ ሥፍራ ነው ከመንገዱ ዳር ሞቶ የተገኘው "
ብዙ ስዎች ወደዚያ ሲጎርፉ
አየሁና እኔም ሄጄ አየሁት" አለው።

“ ማነው እሱ ?” አለ ጀስቲስ ሔር ።

“ የሚታወቅ ሰው አልመሰለኝም ! ፊቱን አይቸ ላውቀው አልቻልኩም "
የሥራ ካፖርት ለብሷል ። በጣም ጢማም የሆነ ልጅ እግር ነው ” አለ ኦትዌይ ቤቴል »

“ ትናንት ጃንጥላውን በስተፊቱ ገትሮ እየተደናበረ ሲያልፈኝ ጃንጥላዬን
ሊሰብርብኝ የነበረው ሰው ሳይሆን አይቀርም » አንድ
የሥራ ካፖርት የደረበ ሪዙ ችምችም ያለ ልጅ እግር ነበር ሰውዬው ጤነኛ አልመሰለኝም " ተናደድኩና
ስጮህበት ጊዜ የድንጋጤውን ያህል ጮኸና እንደ ጥይት ሽው ብሎ ሔደ እና ኦትዌይ ይህ የምትለው ሰው እሱ ይሆናል ” አለ ሚስተር ሔር ።

“ ሊሆን ይችላል ጌታዬ " አለው ።

የሚስተር ሔር ገለጻ ' ከሪቻርድ ጋር የሚመሳሰል ስለ ነበር ባርባራ በበኩሏ
ሪቻርድ ይሆናል ብላ ተጨነቀች ሚስተር ካርላይልም ገባው "
ሚስተር ካርላይል ክፍሉን አቋርጦ ወደ በሩ ሲያልፍ እንደ ምንም ብሎ አንድ
ነገር በጆሮዋ ሹክ አላት "
ሔጄ አይቸ ወሬውን አመጣልሻለሁ እስከዚያው ቻይው የኔ ፍቅር"

“መሔድህ ነው አርኪባልድ ? አለችው ሚስዝ ሔር "

ይህን ቤቴል የሚለውን ሰውዬ አይቸ ለመምጣት ነው " መቸም ለወሬ መጓጓት ነው "

ሚስተር ካርላይል በአትክልቱ ቦታ አቋርጦ ወርዶ ሔደ ባርባራ በዐይኗ እስከ በሩ ተከተለችው
በጣም ተጨነቀች ካርላይል ተመልሶ ነው ወይም አይደለም የሚል መልስ እስኪሰጣት ድረስ እንዴት ትቆይ በጣም ተቸገረች ሪቻርድ ነው ብሎ አንድ ነገር እንደነገራት ተሰማት ኦትዌይ ቤቴልም ሔዶ ጀስቲስ ሔርም ሰው ሠራሽ ጸጉሩንና ኮቱን ማለፈያ ማለፊያውን መርጦ ለባበስና ተከትሎት ወጣ እሱም ሞተ የተባለውን ሰውዩ ለማየት ፈለገ ዌስት ሊንን በመሰለ ትንሽ ከተማ
ጥቃቅኑ ነገር ሁሉ እንደ ብርቅ ይታያል በትልልቅ ከተሞች ከቁም ነገር የማይገባው ሁሉ እዚህ ሲሆን በጣም ይጋነናል " ሕዝቡ ያደንቀዋል "

ባርባራ ከበረንዳ ቁማ በጭንቀት በጕጕት ስትጠባበቅ ካርላይልን ሲመለስ ከሩቅ አየችው ዶርሶ እስኪነግራት መቸኮሏን ተረድቶ ጥቂት ቀረብ አንዳለ ራሱን በመነቅነቅ የፈግታ ምልክት አሳያት ልቧ መምታቱን ባይቀንስላትም በፈገግታው ትንሽ ጠንከር አለች
«እንዲያው ነው የተደናገጥነው .... ባርባራ » አንድ መንግድ ጠፍቶት ይንከራተት የነበረ ማንም የማያውቀው መንገደኛ ነው " ሪዙ ቀይ ነው » በምኑም ሪቻርድን አይመስልም።

«ያን ለት ማታ ሚስ ካርላይል ጉንፋኗ ቀሏት ነበር " ራት ተበላና ሚስተር ካርላይል ስለ ጋብቻው ሊያጫውታት ጀመረ።

“ ኮርኒሊያ... እመቤት ሳቤላ ቬንን ሳገባ አስቀድሜ ስለአልነገርኩሽ በጣም ተቆጥተሽ ነበር "

« ማንም ሰው ድረግ እንደሚገባው አስቀድመህ ብታማክረኝ ኖሮማ
የደረሱት ነገሮች ሁሉ ሌላ መልክ ይኖራቸው ነበር " በዚህ ቤት ላይ የወረደው ውርደትና ፈተና አይደርስም ነበር ” አለችው እየተቆጣች "

“አሁንም ያለፈውን ትተን ስለ ወደፊቱ እናስብ " እንደ ከዚህ ቀደሙ በተሣሣመሳሳይ ሁኔታ ዳግመኛ ላስቀይምሽ ሐሳብ እንደሌለኝ ልነግርሽ ፊልጌ ነው " እንደ ሚመስለኝ ከልብሽ ይቅር አላልሽኝም"

“ ወደፊትም ከልቤ ይቅር አልልህም ” አለችው “እንደዚህ መናቅ አይገባኝም ነበር "

ስለዚህ እኔ ራሴ በቁርጥ እንዳወቅሁት ወዲያው ከሐቁ ጋር ላስተዋውቅሽ
እፈልጋለሁ " ኮርኒሊያ አሁን ሁለተኛ ላገባ አስቤአለሁ ”

ሚስ ካርላይል ክው ብላ ደነገጠችና ቀና ስትል መነጽሯ ከአፍንጫዋ ወደቀ
ስትሠራው የነበረውን ክር የያዘችበት ባኮ ከጉልበቷ ላይ ስለ ነበር ተንሸራትቶ ከመሬት ዐረፈ ።

ምን ምን ” አልክ ?”
“ አሁን በቅርቡ ማግባቴ ነው ”

“አንተ !?

“ አዎን እኔ ... ምነው ? ምን የሚያስገርም ነገር አገኘሽ ?”

“ በል በል አሁን ደግሞ በገዛ እጅህ ገብተህ አትጃጃል " አንድ ጊዜ ያየኸውዐአይበቃህም ? አሁን ደግሞ ዐይንህ እያየ ባንገትህ ሸምቀቆ ታስገባለህ ?

“ ኮርኒሊያ ... እኔ የምነግርሽን ሁሉ አንቺ በዚህ ዐይነት ስትቀበይው
እያየሁ እንዲህ ያሉትን ነገሮች ባልነግርሽ ሊገርምሽ ይገባል ? አንቺ እኔን ልክ እንደ ሕፃንነቴ ጊዜ ነው የምታይኝ " ይኸ ደግሞ ከፍተኛ የዋህነት ነው”
👍13🥰1
“ ትልቆችም ቢሆኑ የልጅ ሥራ ከሠሩ እንደ ልጆች መታየት አሰፈለባቸው "
ከዚህ በፊት ስታገባ ጊዜ አበድክ ብዬ ሳስብ ኖርኩ " አሁን ደግሞ ዕብደትህ በእጥፍ እንደ ጨመረ እቁጥረዋለሁ ። ”

አንቺ ለራስሽ ብቸኛና ነጠላ ሆነሽ መኖርን ስለ መረጥሽ እንዴት እንደ እኔ አድርግ ብለሽ ትፈርጅብኛለሽ ? አንቻ ብቻሽን በመሆንሽ ደስተኛ ነሽ " እኔ ደግሞ
የበለጠ ደስ የሚለኝ ከትዳር ጓደኛዬ ጋር ስሆን ነው " "

“ ልክ የፊተኛይቱ ሚስትህ እንዳደረገችው እንድታዋርድህ ነው የፈለግኽው''

' የለም " አላት ረጋ ብሎ!“በአሁኑ ምርጫዬ አንቺ የምትይው ችግር ይደርስብኛል ብዬ ምንም አልሠጋም
ኮርኒሊ እየሰራች ያለውን
ሥራዋን ሰበሰበች ካርላይል ባኮውን አነሳላት
እጆቿ ሲንቀጠቀጡ የግንባሯ ሥሮች ደግሞ ቁጥር ፈታ ይሉ ነበር" ይህ ወሬ ልክ እንደ ፊተኛው ጋብቻ የበትር ያህል ተስማት።

“ አገር ምድሩ ዐይን ዐይንህን ሲያይ ለመሆኑ ማንን ልታግባ ነው?

“ ምን ያዶርጋል ማንም ትሁን ማን አንቺ እንደሆነ ልዕልትም ትሁን የገበሬ ልጅም አንድ እንከን ለማውጣት ምክንያት አታጭላትም "

አዎን ፤ማድረግ አለብኝ ማን እንደ ሆነችም ዐውቄያታለሁ " ያቺ ትአቢተኛ ሎዊዛ ዶቢዴ ናት።

“አይደለችም እኔ ሚስት የማግባው ለደስታ ነው "ስለዛህ የምፈልገውን
ደስታ ከሷ ስለማላግኘው እኔ እሷን ለማጨት'እም እኔን ለመምረጥ ሐሳብ አልነበረንም

“ ልክ ባለፈው ጊዜ እንዳደረግኸው ” አለችው እያሽሟጠጠች »

አዎን ልክ ባለፈው እንዳደረግሁት

“ ግን ማን መሆኗን ለመናገር አትችልም ?
“ ባርባራ ሔር ናት "

“ ማን?” ብላ ጮኸችና “ አን† ከብት ነህ ” አለችው እጆንና ዐይኖቿን ሽቅብ አንሥታ በመጮህ “ስትከታተልህ ስታጠምድህ ስታደባህ ስትዞርሀ ኖራ
ኖራ በመጨረሻ በጂዋ አስገባችህ » አትረባም ከብት ነህ አርኪባልድ"

አመሰግናለሁ አላት ከፊቱም ምንም ቅሬታ ሳያሳይ እሷ ምንም አላጠመደችኝም እንደዚህ አድርጋ ቢሆን ኖሮ ሚስዝ ካርላይል ለመሆን አትችልም ነበር " እንዲያውም በዚህ በሁለተኛው ጊዜ ጋብቻዬ እሷን እንደምጠይቃት ምንም አልጠረጠረችም”

ልታይ ባይ ራስ ወዳድና ትዕቢተኛ ናት "
ሌላስ በሷ ላይ የምትሰጪው አስተያየት አለሽ ?
“ እኔ ብሆን ካገባሁ ላይቀር ጥቁር ነጥብ የሌለባትን ነበር የማገባው "

የምን ጥቁር ነጥብ ?”
“ የሪቻርድ ሔርን እኅት ስታግባ ' ላንተ ክብር መሆኑ ነው ?ፀ

" ሆነም አልሆነም ይህ የባርባራ ጥቁር ነጥብ አይደለም » ሪቻርድም ቢሆን ንጹሕነቱን የሚያረጋግጥበት ቀን ይመጣ ይሆናል »

“ አዎ እንጂ ይቀራል ? ዓሣሞችም ባየር ይበሩ ይሆናል " እስከ ዛሬ ግን ሲበሩ አላየሁም

አሁን ሌላው ነገር የመኖሪያሽ ጉዳይ ነው ከቤትሽ ተመልሰሽ መግባት
ሊኖርብሽ ነው "

ሚስ ካርላይል የገዛ ጆሮዋን ማመን አቃታት “ እኔ ከዚህ ወጥቼ ከቤት ተመልሸ ልገባ ! እንደዚያ ያለውን ነገር ጭራሽ አልሞክረውም ኢስት ሊን ለመቀመጥ ምን ያግደኛል ?”
ሚስተር ካርላይል ራሱን ነቀነቀና ( እንዶሷ ሳይጮU ዝግ ባለ ድምፅ'' ሊሆን
አይችልም አላት።

“ማነው ያለው ?

እኔ ነኝ ያን ጊዜ ሌሊት እሷ የኮበለለች ጊዜ ጆይስ የተናገረችውን ረሳሽው
ኮርነሊያ ... ጆይስ ያላችው እውነት ቢሆንም ባይሆንም ያሁኒቱ ሚስቴንም ለዚህ እድል አልዳርጋትም።

መልስ አልሰጠችም ከንፈሮቿ እንዶ መከፈት አሉና መልሰው ግጥም አሉ"የጆይስን ንግግር ሲያስታውሳት ኩምሽሽ አለች » ተሰማት

“ እኔ ስሳንቺ መጥፎ አስተያየት የለኝም አንቺ ለብዙ ዘመን የቤት አስተዳሪ
ሁነሽ ኑረሻል » አሁንም በዚያው ብትቆይ ደስ የሚልሽ ቢሆን አያስደንቅም "ግን በአንድ ቤት ሁለት እመቤቶች ኖረው እንደማያውቁ ሁሉ ወደፊትም አይኖሩም ” አለና ቁርጡን ነገራት ።

“ ታዲያ አንተስ ይህን ስታስብ መጀመሪያ ወደ ኢስት ሊን ስመጣ ለምን አትነግረኝም ነበር ?

ያን ጊዜ ይህን ሁሉ አላውቅም " በኋላ ከኑሮ ልምድ ያገኘሁት ነው
“ ቤትህን እኔ ይዠልህ ከነበረው ሁኔታ አብልጣ የምትይዝልህ አታገኝም

“ እኔም ይህን ለማድረግ አላሰብኩም " የቤትሽ ኪራይተኞች በመጋቢት አይ አይደለም የሚለቁት ? ”

“ በል እንግዲያው እኔ ከባርባራ ጋር ብቀመጥ መርዝ የማበላት መስሎ ከታየህ እለቃለሁ ግን ኢስት ሊን ለናንተ በመጠኑም በዐይነቱም በጣም ስለሚበዛባችሁ
አከራዩትና እናንተ ከኔ ቤት ግቡ እኔ ደግሞ እንዳቅሜ አነስ ያለች ቤት ፈልጌ
ልከራይ ”

“ እኔ ደግሞ ኢስትሊን በምኑም አይበዛብኝም ስለዚህ ልለቀው አልፈልግም'

“ግን ሚስተር አርኪባልድ . . . ካንተ ቤት ወጥቸ ስሔድ የራሴን ገቢ ይዤ መሔዴን ዐወቀኸዋል ?”

“እንዴታ ! ገቢሽማ ለራስሽ ነው !! ለራስሽ ጣጣ ያስፈልግሻል " እኔ ለግንዘብሽ ፍላጐትም መብትም የለኝም "

“ የኔ መጣት በገቢህ ላይ በቀላሉ የማይደፈን ቀዳዳ ያበጅብሃል ዕወቀው
አንተም ኢስት ሊንም ተያይዛችሁ እንዳትወድቁ ።

“ አንቺ እንደምትዪ ብዙ ገንዘብ ባወጣም የዚያን ያህልም ተቀማጭ አላጣም
" አንቺም ታውቂያለሽ " "

“ አየህ ወጭህን ቀነስ ብታደርገው ከዚህ የበለጠ ማስቀመጥ ትችል ነበር"
"እኔ ኮ እንደ ስስታም ወይም እንደ ባሕታዊ ለመኖር አልጸልግም ተበሳጨች “

በዚህ ጊዜ አንድ እንግዳ መምጣቱ ተነገረ ሆድ የባሳት ሚስ ካርላይል በዚወያው ተበሳጨች
ደሞ ዛሬ ሌሊት መጥቶ የሚረብሸው ማነው ?” አለች "

ወድያው አሽከሩ ፒተር ገባና “ሻለቃ ቶርን ነው ከሳሎን አስገባሁት" አለው

ሚስተር ካርላይልም ገረመው እሱ ወደ ሳሎን ሲገባ እሷ ደግሞ ጆይስ እንድ ትመጣላት ጥሪያውን ደወለች » የሚርመው ግን በወንድሟ ውሳኔ የታሰበውን
ያህል አልተቃወመችም
ሚስተር ካርላይል የግባ እንደሆነ መውጣቷ እንደማይቀር በልቧ ዐውቃውና አስባበት የተቀመች ይመስል ነበር ኤስት ሊን የሱ ነበር አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ከተናገረው ቃል ፍንክች እንደማይልም ታምን ነበር "

ጆይስ...ይኽ ጌታሽ ተጃጃለ " አሁን ደግሞ ሁለተኛ ላግባ ይላል "ስለዚህ ከሱም መለየቴ ኢስት ሊንንም መልቀቄ ነው አንቺስ ከአኤ ዘንድ መጥተሽ የሠራተኞች አዛዥ ትሆኛለሽ ?”

እኔ ከእርስዎ ጋር ለመሔድ እፈልግ ነበር ነገር ግን እመቤት ሳቤላ አንድ ጊዜ ታመው በደከሙ ጊዜ የሚሞቱ ስለ መሰላቸው ከልጆቻቸው እንዳልለይ አስምለውኛል " በርግጥ ያኔ በሞት ባይለዩዋቸውም ዙሮ ዙሮ መጨረሻው ልጆቹ እናታቸውን አላገኙም ? "

“ግን በቤቱ ሌላ እመቤት ስትመጣበት ከዚህ እንድትቀመጭ ይፈቅድልሻል?”
አለቻት እንደ ማሾፍ እያለች

ጆይስ ትንሽ አሰበችና አስተማማኝ መልስ ስታጣ ( “ይታገሡኝና አስቤ እነግርዎታለሁ " አለቻት "

“ እንዲህ ያለ መንገድ ! አለው ሻለቃ ቶርን ደግሞ ለሚስተር ካርላይል
“ መንገድ ስወጣ ዕድሌ ሆኖ መጥፎ አየር አያጣኝም ዝናብ የበረዶ ጠጠር ነጎድጓድ የሚያቃጥል ሙቀት አንድም አይቀርም " እኔ ከወጣሁ በረዶው ሐዲዱ
ላይ ተቆልሏል ። ከአንድ ጣቢያ ላይ ሁለት ሰዓት ሙሉ ቆምን ።
“ ዌስት ሊን ለመሰንበት ሐሳብ አለህ እንዴ ?”

“ ነገ እሔዳለሁ የዛሬው ፈቃዴን ከእናቴ ጋር ላሳልፈው ነው ያቀድኩት
ቢሆንም ለዌስት ሊንም ሳምንት ያህል እሰጠው ይሆናል " አሁን እንኳን ወደዚህ ያመጣችኝ አንዲት ሴት ናት ካርላይል ” አለው "

“ እውነት ? እንዴት ነው? ”

“ ከባርባራ ሔር ጋር ፍቅር ይዞኛል = እሷ ግን አይሆንም ብላ ደብዳቤ ጻፈችልኝ " አሁን ሔርበርትም በግንባር ቀርቤ አጥብቄ እንድጠይቃት ስለ መከረኝ
ለዚሁ ስል መጣሁ።
👍9😁2
ሚስተር ካርላይል ነገሩን በሐሳቡ አውጥቶ አውርዶ አሰበ » ባርባራ ለሁለተኛ
ጊዜ እምቢ ብላ ከምትመልሰውና ነገሩን ከሌላ ሰው ከሚስማው እውነቱን ገልጾ ሊነግረው ወሰነ ።

“ ሻላቃ ባርባራን እንግዲህ ደግመህ መጠየቅ ምንም ፋይዳ የሌለው ልፋት
መሆኑን ብነግርህ አይከፋህም "

“ መቸም አልተያዘችም ' አይደለም ? አለ ሻለቃ ቶርን ፈጠን ብሎ "

“ ማግባት አላግባችም " ግን በቅርቡ ታገባለች "

ይኸማ የዕድሌ መጥመም ነው " እንዴት ያለ ዕድለኛ ስው አገኛት በል ?

ስሙን ብገልጽልU ላትጮህብኝ ቃል ግባልኝ "

"" ካርላይል ! አንተን አንዳይሆን አንጂ ?

" አንተው ተናገርከው " "

ትንሽ ጸጥ ብለው ከቆዩ በኋላ “ቶርን . . መቸም ይኸ ወዳጅነታችንን ሊቀንሰው አይገባም አለው "

ሻለቃው እጁን ዘርግቶ የሚስተር ካርይልን እጅ ያዘና “ በምንም አይነት አይቀንሰውም ሁሉም የዕድል ጉዳይ ነው ለኔ ካልሆነች ከሌላ ዘንድ ከማያት ያንተ ሁና ባያት ው የምመርጠው ገና በፊት ጠይቄያት የነበረ ጋዜም አጭተሃት ነበር ? ”

" የለም አሁን በቅርቡ ነው የተጨነው " "
"ግን እኔ ጠይቄያት እንደ ነበረ ነገረችህ ?

በጭራሽ !አባቷ ናቸው አንድ ቀን ተናደዱና ነግሩን ያወጡት „

" ልጃቸውን ለማግባት ስለ ጠየቅሁ ነው የተናደዱት ? ”

የለም ጥያቄህን ባለመቀበሏ እንጂ አንተን ብቻ ሳይሆ የጠየቋትን ሁሉ
መመለስ ልማድ ስለ አደረገችው ነበር የተናደዱት

“ አንተስ አይሆንም ብላህ ነበር ?

“ የለም ” አለ ካርላይል ሣቅ ብሎ“ ስጠይቃት ተቀበለችኝ

“ምን ይደረግ ዕድል ያስፈልጋል " መቸም ልጂቱ ለጥሩነቷ ጓዶኛ አይገኝላትም " ባገኛት ኖሮ ጥሩ ነበር "

“ አንዱን ለቆ ሌላውን አይሁንብኝና ቶርን ... ሁለተኛ ብንግናኝ እጠይቅሃለሁ ብዬ ሳሰላስለው የኖርኩት አንድ ጥያቄ ነበረኝ አንተ ስዌንስ መጥተህ የተቀመጥከው መቼ ነበር ?

ሻለቃ ቶርን ጊዜውን ሲያስታውስ ሆሊጆን በሞተበት ዘመን ሆነ "
“ ታዲያ በዚያን ጊዜ ቶርን የሚባል ሌላ የስም ሞክሸህ የነበረ ሰው ታስታ
ሳለህ ?

አንድ ሰው ያየሁ ይመስለኛል » አንድ ቀን ብቻ ስላየሁት አላውቀውም እንያውም በከተማው ነዋሪ አይመስለኝም ከከተማ ውስጥ አይቸው አላው
ቅም "

“ ታዲያ የት አየኸው ?”

“ ከስዌንስን ሁለት ማይል ያህል ወጣ ይላል " አንድ የመንገድ ዳር መጠጥ
ቤት ነበር ያየሁት " አንድ ቀን በፈረስ ስሔድ በጣም የሚያስፈራ ነፋስ የቀላቀለ
ዝናብ ያዘኝና ከዚያ መጠጥ ቤት ተጠለልኩ " ወዲያው አንድ አለባበስ መልካም
የትልቅ ሰው ወገን የመሰለ ረጂም ፈረሰኛ ተከትሎኝ ገባ " ዝናቡ ሲያባራ ቀድሞ
ወጣና ሔደ። ማን መሆኑን ጠየቅኩ " ሰዎች ሁልጊዜ በፈረስ እየሆነ ሲያልፍ ቢያዩትም ስሙን እንደማያውቁት ነገሩኝ » አንድ ሲጠጣ የነበረ ሰው ብቻ ካፕቴን ቶርን እንደሚባልና ከወደ ዌስት ሊን እንደሚመጣ የነገረኝን አስታውሳለሁ" ሆኖም
ሰውዬው የካፕቴን ቶርንን ስም ከማወቅ በቀር ሌላ የሚያውቀው ዝርዝር አልነበረም

ብታየው የምታውቀው ይመስልሃል ?” አለው ሚስተር ካርላይል "

“ አዎን ይመስለኛል መልኩ አንድ የሆነ ልዩ ገጽታ ስለነበረው ዛሬም በደንብ ትዝ ይለኛል ”

ምናልባት ባጋጣሚ ብታየው እኔም እንዳውቀው ለማድረግ ትረዳኛለህ
ቶርን የውሸት ስሙ ሳይሆን አይቀርም እኔ ትክክለኛ ስሙን ለማወቅ እፈልግ ነበር”
"ያለሁበት ቦታ ከሌሎች ረጅመንቶች የተለየ እሩቅ በመሆኑ ለዚህ አጋጣሚ
አይመችም እጂ ካጋጠመኝ በደስታ እፈጽማለሁ "

ሻለቃ ቶርንን ከሸኘ በኋላ ፡ እኅቱን ወደ ተወበት ከፍል ሊመለስ ሲል ጆይስ
"ጌታዬ ” አለችው “ ኢስት ሊን ውስጥ አንድ ለውጥ እንደሚኖር ሚስ ካርላይል ነገሩኝ እኔም አብሬአቸው ለመሐድ እፈልግ እንደሆነ ጠይቀውኛል"እርስዎን እስካማክር እንዲታገሠኝ ነርኩዋቸው "

“ አናስ ?”

እኔማ ሟቺቷ እመቤቴ አንድ ጊዜ ታመው የደከሙ ጊዜ ያኔውኑ የሚሞቱ
መስሏቸው እንደ ኑዛዜ አድርው ከልጆቻቸው እንዳልለይ አደራ ብለውኝ ነበር » እኔም ለመኖር እስከ ተፈቀደልኝ ድረስ እንደማልለይ ቃል
ገባሁላቸው" ስለዚህ
የሚደረገሙ ለውጥ የኔንም ኢስት ሊን ውስጥ የመቆየቴን ነገር የሚነካ እንዴሆነ ልጠይቅዎ ፈልጌ ነው ።

“ የለም ጆይስ . . . እኔም ከልጆቼ ጋር እንድትቆይ እፈልጋለሁ ” አላት።

ጥሩ ነው ጌታዬ ” አለችውና ፊቷ በደስታ ተሞልቶ ከሳሎን ወጥታ ሔዶች።...

💫ይቀጥላል💫
👍143😁1
😘😘 #ቃል 😘😘
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሁለት (2)


የማይክል እናት ማሪዮን ሂልያርድ የማይክልና የናንሲን ፍቅር ስትሰማ «ለየት ካለ ሰው ጋር ፍቅር ሲይዝህ ደግ እይደለም» ስትል ለልጅዋ እንደማስጠንቀቂያም እንደምክርም.-አድርጋ 'ነግራው ነበር ።* ማሪዮን ነገሯን የጀመረችው «ከሆነች ሰዓሊ ጋር ፍቅር ያዘኝ ብሎ ይንዘላዘላል ብለው ነገሩኝ» በማለት ነበር ።

ማሪዮን ያለችውን ትበል እንጂ ማይክል ናንሲን ያውቃታል ። ናንሲን ከማፍቀር የበለጠ ነገር እንደሌለ ያውቃል ። ናንሲ አፈቀረችው መባል ደግሞ ራሱን የቻለ ጽድቅ እንደሆነ ያምናል።
ማይከል ልጅም ጅልም ስላይደለ መጥፎና ጥሩን ለራሱ አሳምሮ ያውቃል ። እናቱ ልዩ ስላለችውም ቢሆን ናንሲ ከሰው የተለየች ፍጡር አይደለችም ። ልዩ የሚያደርጋት ነገር ግን አታጣም ። አንደኛው ናንሲ እንደሌሎች በሷ እድሜ እንዳሉ ልሻገረዶች ገና ተማሪ ፣ ገና እምትሆነውን ያልመረጠች ልጅ አይደለችም ሙያዋን መርጣለች ። ሰአሊ ናት ። ናንሲ እምትወደውን ሰው ለመምረጥ አንድ ቀን አንዱን ፤ በሌላ ቀን ሌላውን እየቆያየረች በመፈተንና በመፈታተን ላይ ያለች ልጅ አይደለችም ። የምትወደውን ወንድ ለማግኘትም በመባዘን ላይ አይደለችም ፤ መርጣለች ። ከምታፈቅረው ወንድ ጋር መኖር ጀምራለች ፤ ችኖራለች ። ዛሬ ለናንሲ ከማይክል ሌላ ወንድ አይታያትም። ናንሲ የተለየች ሴት ከተባለች ጠንካራ ፍጡር ፤ ንጹህ ልጅ በመሆኗ ብቻ እንደሆነ ይገባዋል ። ይህ ደግሞ ጉድለት አይደለም ። እንዲያውም ማይክል ምንም እንኳ ዛሬ ዛሬ የሚወደው ሙሉ እሷነቷን እንደሆነ ቢታወቅ በመጀመሪያ የወደዳት በዚህ ልዩ በሚያደርጋት ባህሪዋ እንደሆነ ያስባል ።

ማይክል ናንሲን ይወዳታል ። ናንሲም ማይክልን ታፈቅረዋለች ። የሁለቱ ፍቅር ሚዛኑ የተስተካከለ ነው። ከተገናኙ ሁለች ዓመት ሞላቸው ። ይህን ያህል ጊዜ አብረው ሲኖሩ መሰልቸት የሚሉት ስሜት አይታበት አታውቅም ። ዛሬማ ተዋውቀዋል ።

የልጅነት አጉል ምኞቱን ፤ የልጅ ሸረኝነቱን ፤ አስቂኝ ምስጢሮቹን፤ መሰረት የለሽ ስጋቱንና ፍርሃቱን ይህንን ሁሉ አካፍሏታል። የሷንም አካፍላዋለች ። ዛሬ ደግሞ ምኞታቸውም ፤ ስጋታቸውም፤ ደስታቸውም ፤ ሐዘናቸውም የጋራ ነው። ማይክል የሚባል አዲስ ሰው የለም ። ርግጥ ነው ከእናቱ ጋር አላስተዋወቃትም ። ቤተሰቤ የሚለውን ነገር በዓይኗ አላየችውም ። ግን ደግሞ እናቱም ሆነ ቤተሰቡን ቁልጭ አድርጋ ታውቃችዋለች፡፡ ያን ቤተሰብ በሚገባ ከማወቋ የትነሳ በታላቅነታቸው ታከብራቸዋለች ። ስለሷ ያላትን አስተያየት እያወቀች ማሪዮንን ሳይቀር ታከብራታች።

ማሪዮን ሂልያርድ በመላው የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት ውስጥ ታዋቂነትንና ዝናን ያተረፈው «ኮተር ሂልያርድ የሕንፃ ንድፍ ጥበብ (አርክቴክቸር) ሥራ ተቋራጭ ድርጅት » ዋና ሥራ አስኪያጅ ናት ። ማይክል «ኮተር ሂልያርድን» ለመምራት ብቁ ሲሆን «ዙፋኑን» ይረከባል ። ሥራውን በሚገባ እንዲያካሂድ « ኮተር ሂልያርድን» በይበልጥ እንዲያገዝፍ እየተኮተኮተ ነው ያደገው ።የተማረውም ድርጅቱ የሚፈልገውን ዓቢይ ሙያ ነው… የሕንፃ ንድፍ ጥበብ ። በቅርቡ ከታወቀው የሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ በዚሁ ሙያ የዶክሬት ዲግሪውን በመቀበል ይመረቃል ።

ታዲያ የማይክል ስጋት «ለዚህ ታላቅ ኃላፊነት ብቁ ሆኘ አልገኝ ይሆን ?» የሚል ነው። ናንሲ ግን ያላንዳች ጥርጥር ታውቃለች ። ማይክል «ኮተር ሂልያርድን» በሚገባ ሲመራ ይችላል ። ያም ብቻ ሳይሆን «ኮተር ሂልያርድ» በማይክ «ዘመነ መንግሥት» እጅግ ይበለፅጋል ። ማይክ ጠንካራ ሰው ነው። ግትርም አይደለምና ሁሉን ልፍጀው ባይ አይደለም ለአመራሩ ከማይክ የተሻለ ሰው ከየት ሊመጣ ትላለች ።

ማይክም ቢሆን ይስጋ እንጂ ... ያለውን ኃይል ሁሉ በሚገባ ከተጠቀመ አደራውን የማይወጣበት ምክንያት እንደማይኖር ያምናል ። ሆኖም ገና አልገባበትምና… ሰው ደግሞ የማያውቀው ፤ ያልገባበት ነገር ያስፈራዋልና ይፈራል ፤ ይገነግናል ።
ምክንያቱ ? በቂ ምክንያት አለው ።

« ኮተር ሂልያርድ » ባንድ ትውልድ የተገነባ ድርጅት አይደለም ። ማይክል ሦስተኛው ትውልድ ነው ። በዛሬ ስሙ ሳይሆን «በኮተር» ብቻ ይህን ድርጅት የጠነሰሰው የማይክል አያት የማሪዮን አባት ሪቻርድ ኮተር ነበር ። ሪቻርድ ኮተር የሕንፃ ንድፍ ጠቢብ (አርክቴክት) ነበርና ድርጅቱን መሠረተ ። ይህ ከሆነና ድርጅቱ እያደገ በመሄድ ላይ እንዳለ የማይክል አባትና እናት ተዋወቁ; ተፋቀሩ ። ሊጋቡ ወሰኑ። የኮተርና የሂልያርድ ቤተሰብ በጋብቻ ተሳሰሩ ። የእነዚህ የሁለቱ መጋባት የዛሬውን ታዋቂ ድርጅት ፈጠረ… “ኮተር ሂልያርድን”። የማይክል አባት ሚስተር ሂልያርድም እንደ አማቱ እንደ ሪቻርድ ኮተር የሕንፃ ንድፍ ጠቢብ ነበረ። የሂልያርድ ቤተሰብ የታወቀ ሀብታም ቤተሰብም ስለነበረ ድርጅቱ የደለበ ገንዘብ በገፍ አገኘ ።ትልቅ ስሙን ተከለ ።

እንግዲህ ይህን በሁለት ታላላቅ ቤተሰቦች ኃይልና ጥረት የተመሠረተ ግዙፍ « መንግሥት» መቀበል በቸልታ የሚታይ አልነበረም ።

ከላይ እንዳልነው ናንሲ ሙሉ በሙሉ ትተማመንበታለች ይህንንም ትነግረዋለች ። እሱም ያምናታል ። እሱም በበኩሉ በሷ ይተማመናል ። ምንም እንኳ አስተዳደጓ አመቺ ባይሆን ናንሲ ብዙ ትረዳኛለች ይላል በልቡ ። ይህን በልቡ የሚያደርገውን ጭውውት በመቀጠል… ባንድ በኩል በጣም ታላቅ ሰዓሊ ስለሆነች «ኮተር ሂልያርድ» ደግሞ ሰዓሊዎች ስለሚያስፈልጉት በሙያዋ ታግዘኛለች ። በሌላ በኩል ደሞ ንቁና አስተዋይ ናትና ቤቴን በሚገባ ትመራልኛለች ። አስተዳደጓ? ያ! ለናንሲ ምንም አይደለም ይላል ። ተገናኝተው ከተካፈሏቸው ሐሳቦች ብቻ በመነሳት ስለበለጸገ ቤተሰብ አኗኗርና አስተዳደር ያላት አስተያየት ዛሬ እንኳ የሚያኮራ እንደሆነ ተገንዝቧል ።

ናንሲ ፊት ፊት እየጋለበች ማይክልም ቢስክሌቱን በፍጥነት እያሽከረከረ ፣በየፊናቸው ሐሳባቸውን እያውጠነጠኑ መንገዱን ተጋትረውታል ። ስለ ናንሲ አእምሮ ክፍትነት እያሰበ በኩራት ተሞልቶ ሲያያት ፤ ዞር ብላ አገጩን በትከሻዋ ላይ አሾልዳ አየችውና «በል ድረስብኝ» በሚል መልክ ስቃ የቢስክሌቱን መርገጫ በኃይል ትመታ ጀመር ። በፍጥነት ሊነዳና ሊደርስባት ከጀለ ። ሆኖም በርቀት ሲያያት የተስተካከለ ቅርጽ ፤ ፈጣን ውብ እግሮቿ ልዩ የሆነ ስሜት አሳደሩበት ። ዞራ ፈገግ ስትል ደስታው ከመጠን እለፈ ። ሰውነቱን ወረረው ሂድ ... ሂድ ድረስባት የሚል ጉትጐታ ተሰማው ። ከደረሰባት በኋላ … ከዚያ በኋላ ብስክሌቷን ይዞ ከብስክሌቱ ላይ ወርዶ ከብስክሌቷ ላይ ያወርዳትና እመስኩ ላይ… እዚያ ደስ እሚል አረንጓዴ ምንጣፍ ላይ . . . እዚያ ላይ ይጥላትና ከዚያ በኋላ ልክ እንደትናንት ማታ !.... እንደ ማታው ! ልክ እንደ...

ይህን ሐሳብ በግድ አስወጣው ፤ ከአእምሮው ውሰጥ ። ሐሳቡ ሊመለስ ሲታገለው ፤ ብስክሌቱን በኃይል እየነዳ በጥሪ ድምፅ እንዲህ አለ፤ «የኛ ሐሳበ ቢስ … ይህን ያህል… ›› አለ ዞራ ሳቀችና ፍጥነት ጨመረች። እሱም ፍጥነት እየጨመረ… ‹‹ጠብቂኝ እንጂ! ጅል» አለ ። ብዙ ጊዜ ሳይፈጅ ደረሰባት ። ሁለቱም በጣም ደክመው ነበረና መነጋገር አልቻሉም ። ስለዚህም ፍጥነት ቀንሰው ፤ ጸጥ ብለው ጎን ለጎን በመሆን ጉዟቸውን ቀጠሉ ። በዚህ ሁኔታ ሲጓዙ ሳለ ድንገት ተያዩ ። እጁን ዘረጋላት እጅዋን ዘርግታ ጣቱን ነካ አድርጋ ለቀቀችው ። ትኩር ብሎ እያያት የደስታና የአድናቆት ሲቃ በተሞላ ድምፅ
👍262
«ናንሲ» አላት
«ናንሲ ዛሬ ደሞ እንዴት ቆንጅዬ ልጅ የሆንሽ መሰለሽ?» አላት ።

ድምጹ ነፋሻውን የመጸው ወራት እየር እየሰነጠቀ ሲደርሳት የሰራ አካላቷ ተፍነከነከ ። በአካባቢያቸው ያለው አለም ምንም ነገር ያልበከለው ፤ ንጹህ ወላንሳ በመሆን ደስታዋን ፤ ደስታውን ፤ ደስታቸውን አደመቀው ።

«ናንሲ !» አላት በዚያው ድምፅ «ናንሲ ! ምን ያህል እንደምወድሽ ብታውቂ !» «እይጠፋኝም !፤ አይጠፋኝም ሚስተር ሂልያርድ» አለች ናንሲ በውሸት ጠብ ድምፅ ፤ ማይክል በማለት ፋንታ እንደ ሩቅ ሰው ሚስተር ሂልያርድ እያለችው ።

«አይጠፋኝም ! ግን ፍቅርህ የእኔን ፍቅር ከፊሉን እንኳ አይሆንም» አለች ። የውሸት ብሽቀት በሽቆ፣ «ባትናገሪ ይሻልሽ ነበር ። ስትናገሪ ነገር የማይገባሽ መሆንሽ ቁልጭ ብሎ ይታያል» ሲል ተናገረ። ይህን የብሽሽቅ ጨዋታ በመሻት ነበር ያን መልስ የሰጠችው እንጂ እንደሚወዳትማ ታውቃለች ። ምን ያህል እንደሚወዳት ያወቀችው ፤ ወደኋላ ስታስበው ፤ በመጀመሪያ የተገናኙ እለት ነበር።. . . ያን ለት «ወይ ለኤግዚብሽን ያቀረብሻቸውን ስዕሎች ሁሉ ሽጭልኝ ፤ እምቢ እምትይኝ ከሆነ ዶግሞ የለበስኩትን ልብስ ሁሉ አውልቄ ጥየ ባደባባይ በጸሐይ ራቁቴን እሄዳለሁ» ሲል ኩስተር ብሎ የዛተው ትዝ አላት ። እንዲያ ያላት እለት ነበር እንደሚወዳት የተረዳችው ።
«ብስል ሰው ብትሆኚ ፍቅሬ ያንችን ሰባት እጥፍ እንደሆነ ይገባሽ ነበር» አለ ።
«ሰባት እጥፍ ? »
«አዎ!»
«አትዋሽ ! በጭራሽ የሌለ ነገር !»
«ያንችን...»

ነገሩን ሳይጨርስ ፍጥነት ጨምራ ፈትለክ አለችና ዞራ ከሳቀች በኋላ ኮስተር በማለት «ማይክል ! ያንተ ፍቅር መጠን አለው ። የኔ ግን መጠን ስለሌለው ፤ ሰባት ጊዜ ፤ መቶ ጊዜ፣ተብሎ አይለካም» አለች ። «እንዴት አወቅሽ ? » አላት ፤ እሱም ቢስክሌቱን በኃይል እየነዳ … ሊደርስባት እየተቃረበ ። ዞራ አየችውና…
«ዛር ነገረኝ |» ብላው እንደገና ፍጥነት ጨምራ ራቀችው” ርቀታቸው ሳይቀንስም ሳይጨምርም ፊትና ኋላ ሆነው ጉዞ ጀመሩ ። በመካከላቸው ያለው ርቀት አካሏን ለሁለተኛ ጊዜ እንዲማትር አደረገው ። እንደገና ሰውነቱ በደስታ ተሞላ ሆኖም አሁን እመስኩ ላይ ሊጥላትና . . . አላሰበም ። ለዘለአለም የሱ እንድትሆን ግን ተመኘ ። የኔ ማድረግ አለብኝ አለ… ይህ ሐሳብ ወደ ዛሬ ጧት ውሳኔው መራው ።

ፍጥነቱን ጨመረና ደረሰባት ። ቢስኪሌቶቻቸው ተጠጋግተው መንገዱን ተያያዙት ። እንደደረሰባት ስታውቅ ፍጥነቷን ጨምራ ልታመልጠው ከመርገጫው ጋር መታገል ጀመረች። እግሮቿ እንደመቂናጥ ብቅ ጥልቅ ይላሉ ። ጥረት ላይ ነበረችና ዞር ብላ አላየችውም ። እሱም ወደ ኋላ ላለመቅረት ፍጥነቱን ጨመረ ። በዚህ ሁኔታ ሲጓዙ ከቆዩ በኋላ መንገዱ ተጠመዘዘ ። መጠምዘዣውን እንዳዩ ፍጥነት ቀነሱ ። መጠማዘዣውን እንደጨረሱ ገና ፍጥነትም ሳትጨምር መሪውን ባንደኛው እጅ ብቻ ይዞ በሌላኛው እጅ ጀርባዋን መታ መታ እያደረገ
«ሚስዝ ሂልያርድ !» አላት «ሚስዝ ሂልያርድ እንዴ ይቅርታ አድርጊልኝ»

እንዲህ ሲላት እፍረት ቢጤ ተሰማት ። የምንተ እፍረቷን ፈገግ አለች ። መልስ አልሰጠችውም ። እየቆየ የምንተ እፍረት ፈገግታዋ ወደ ተስፋ ፈገግታ እየተለወጠ ሔደና ፊቷ በራ ። ምክንያቱም እሱ ማይክል ሂልርድ ሲሆን ፤ እሷን ሚስዝ ሂልያርድ ብሎ መጥራት ማለት ባልና ሚስት ሆነናል ፤ ተጋብተናል ማለት ነው ። ዞራ አየችው ።
« ምነው አየሽኝ ? ያልኩትን አልሰማሽም እንዴ ሚስዝ ሂልያርድ? »
«ልጅ ሳይወለድ ለልጁ ስም ማውጣቱ አጉል ችኮላ አይመስልህም ማይክ ?» አለች ። ፍቅራቸውን አትጠራጠርም ። ግን ደግሞ ስጋት አለባት ። ስጋቷ የማይክል እናት ማሪዮን ሂልያርድ ናት ። «ማሪዮን እንድንጋባ ትፈቅድልን ይሆን ?» የሚለው ጥያቄ ሁልጊዜም በናንሲ ማክአሊስተር አእምሮ ውስጥ እንዳለ ነው ። «ምንም ያቻኮልኩት ነገር ያለ አይመስለኝም» አለ ማይክል። ዝም አለች ። «ልጅ አይደለሁም ። እልቸኮልኩም ። ውሳኔ ላይ የደረስኩት ነገሩን አውጥቼ አውርጄ ነው » አለ ፤ነገሩን በመቀጠል ። የለም የለም ከመወሰኑ በፊት ቢያንስ ቢያንስ ከእናቱ ጋር መመካከር አለበት አለች በሐሳቧ።

«እሰብኩበት ። ወሰንኩ ። ናንሲ በጣም ታስፈልጊኛለሽ » አለ ። ማይክል ይህን ቢል አዲስ ነገር አልተናገረም ። ሁለቱማ እንደሚጋቡ ከወሰኑ ቆይተዋል ። የሰርጉን እቅድ ሁሉ አውጥተዋል ። ይህ የታወቀ ነገር ነው ። የናንሲ ሐሳብ ቀጠለ ። « የስርጋችን ቀንም» አለ ማይክል « የዛሬ አስራአምስት ቀን እንዲሆን ወስኛለሁ ። ያም ማለት ዲግሪየን የምቀበልበት ቀን መሆኑ ነው

እሷ ቤተሰብ ስለሌላት ድግሱ የአንድ ወገን ብቻ እንደሚሆን ካሰበበት በኋላ የሱ ድግስም ቻቻታ የሌለበት ፤ የልብ ጓደኞቹ ብቻ የሚገኙበት እጥር ምጥን ያለ ሰርግ እንደሚሆን ነገራት
«ለምን ማይክ ?» አለችው ።
«ምክንያቱም በጫጫታ የምናሳልፈው ጊዜ የለንም ። ብቻችንን መሆን ያስፈልገናል » ብሎ መለሰላት ። ሁለቱም ዝም አሉ። «ዛሬ ጧት አንድ ነገር እነግርሻለሁ ብዬ ረሳሁትና እስካሁን ሳልነግርሽ ቆየሁ።... ኒው ዮርክ ልሄድ አስቤአለሁ ። ከማሪዮን ጋር ስለሰርጋችን ለመመካከር » አለ ፤ ድንገት ። ናንሲ ዝም አለች ። «ዛሬውኑ ልሄድ ነው የወሰንኩት
«ዛሬውኑ! »
« አዎ !... ዛሬ ማታ ። እደርሳለሁ »
ይህን ሲል የብስክሌቷን ፍሬን ያዘች ። በአላምንህም አስተያየት እያየችው
«ዛሬ?... ዛሬ ማታ ፤ ዛሬ ማታ ?» አለች ። ራሱን በአዎንታ ነቀነቀ። ሁለቱም ቆሙ።
«ማሪዮን እምትስማማ . . . ይመስልሃል ?» አለች በመጠራጠር… መልሱን ለመስማት በመፍራት።
«አትጠራጠሪ ። ትስማማለች ።» አለ። በጥርጣሬ አይን አየችው።የተናገረውን እሱም እራሱ ያመነበት
አልመሰላትም ።
«ጋብቻውን ላትፈቅደው ትችላለች ።ግን ደሞ ሚስት ልምረጥልህ ለማለትም አትደፍርም ። ይህን ያህል አውቃታለሁ ። ስለዚህ አታስቢ ።»
ነገሩ እንኳ እሷን ብቻ አይደለም ራሱን ማይክልንም ያሳስበዋል ። ሴትዮዋ ማሪዮን ሂልያርድ ናታ ! ማሪዮን የማይክልንና የናንሲን ጋብቻ ካልፈቀደችው እንዳይጋቡ ከመከልከል አትመለስም ። ምክንያቱም ለማሪዮን ከራሷ እምነት ውጪ ምንም ነገር የለም። ይህንን ደግሞ ከናንሲ ይበልጥ የሚያውቀው ማይክል ነው ። ማሪዮን ሲጀመር ጀምሮ የሁለቱን በፍቅር መተሳሰር አልወደደችውም ።

ለረጅም ጊዜ ማሪዮን ያችን ሰአሊ ካልተውክ እረግምሃለሁ ፤ እክድሃለሁ ፤ ውርስህን አፈርሳለሁ ስትልና ስታስፈራራው፤ ማይክል የመጣው ፤ይምጣ የቻልሽውን ሁሉ አድርጊ ናንሲን ግን አልተውም ፤ ሲል ደብዳቤም መፃፍ፡ ስልክም መደወል ሲያቆም ፤ ጠርታ ስታባብለው ፤ የተለያዩ ምርጫዎች ስታቀርብለት ፤ቆንጆ ከሚባሉት የደህና ቤተሰብ ሴቶች ልጆች ጋር ስታስተዋውቀው ማይክል ግን ሁሉን ችላ ብሎ ወደናንሲ ሲመለስ ፤ ናንሲን እንደሚወድ ደጋግሞ ሲነግራት ስታስፈራራው ዛሬ ፤ ዛሬ ያ ሁሉ የለም … ዛሬ፤ ዛሬ ማሪዮን ፤ ናንሲን ተቀብያለሁ አስተዋውቀኝም አትል ፤ ናንሲን ካልተውክ ! ብላም እታስፈራራው ፤ ያለፈው ስህተትም አይነሳ ፤ የዛሬው ሁኔታም አይወጋ፣ ዝም ዝም ሆኗል።
👍23😱21
ይህ ደግም ናንሲን ያናድዳታል ። የማሪዮን ዝምታ ናንሲ የለችም የማለት ያህል የገነነ ነበርና ። እያሉ እንደሌሉ መቆጠርን ያህል ደግሞ የሚያናድድ ነገር የለም ። ግን መቼም ቢሆን ፤ምንም ዓይነት ሀኔታ ቢፈጠር፤ የሰው ልጅ አንድ ቀዳዳ ፈልጐ ተስፋ ማየት ይወዳልና ናንሲ አንዳንዴ ተስፋ ታደርጋለች ። የማሪዮንን ዝምታ ፤ መቀበል ነው ብላ ታስባለች ። መቀበሏን እንዳትገልፅ ባለፈው የፈፀመችውን ድርጊት እያስታወሰች ስለምታፍር ነው ትላለች ። ይህ ሃሳብ ሲመጣ ክፉ ነገርን ሁሉ በመጣስ መልካም ራእይ ታያለች።. … ማሪዮንና እሷ ተስማምተው ፤ ማይክል ሲደሰት ፤ ማይክል የሚፈልገውን ሁሉ እየተማከሩ ሲያደርጉለት… የሚወደውን ልብስ ሲገዙለት ፤ የሚወደውን ምግብ ሲያበስሉለት... ይታያታል ። ሃሳብ በዚህ በኩል ወደውስጣዊ ቁስሏ ይመራታል ። ያለ እናት ማደጓን ታስታውሳለች ። ከማሪዮን ሂልያርድ ጋር ከተስማሙ ግን ችግሩ ሁሉ አይኖርም ። ማሪዮን የማይክል ብቻ ሳይሆን የናንሲም እናት ትሆናለች ። ተፈጥሮ ናንሲን የነፈገቻችን የእናት ፍቅር ማሪዮን ትሰጣታለች ።

ወዲያው ጨለማ ሃሳብ. . . እንደ ልጅ መፈቀር ቀርቶብኝ እንደሰው ባስታወሰችኝ ! ማይክል ግን የማሪዮንን ዝምታ እንደመቀበል ነው የቆጠረው። ከዚህ በፊት ይህንኑ ለናንሲ ነግሯት ነበር ። «ታዳያ ለምን ተቀብያለሁ እትልም» ብላው ነበር ናንሲ ። «አፍራ ነው... አየሽ ስንጀምር ባደረገችው ነገር አፍራለች ። ስለዚህ ይቅርታ ከመጠየቅ የጋብቻ ፈቃድ ሲጠይቁ ፈቅጃለሁ ማለት ይቀለኛል ብላ ነው ፀጥ ያለችው» ሲል መለሰላት ።
«እኔም አንዳንዴ እንደሱ ይመስለኛል» አለች ናንሲ « ግን አላምንም ››
« አልፈቅድም ብላ ምን ትፈይዳለች ? » አላት ማይክ እያቋረጣት ።
« ካልፈቀደች ልንጋባ አንችልማ !»
«ለምን ? ልትነግሪኝ ትችያለሽ ? ለምን ?»
«ካልፈቀደች !? . . .» ብላ ምን ማድረግ ይቻላልን ትከሻዋን ነቀነቅ በማድረግ ገለፀችለት ። «ሞኝ አትሁኝ ናንሲ» አላት ። « እኔም አንችም ለአካለ መጠን ደርሰናል ። ሕጋዊ የሆነ ነገር ሁሉ በፈቃዳችን ልንፈጽም መብት ያለን ሰዎች ነን ። ስለዚህ አይሆንም ካለች መኪናችን ውስጥ ገብተን ወደ አንድ ፍርድ ቤት መጓዝ ነው። በሕግ እንጋባለን አየሽ » ያንለት ያነጋገሩን ገራገርነት በማጤን ብቻ ሳቀች። ይህ እንዲህ ቀላል አድርጐ ያቀረበው ሃሳብ ግን ከማንኛውም ሰው ይበልጥ አስቸጋሪ ሆኖ የሚታየው ለሱ ለራሱ ለማይክል ነበር። ለማይክል ግማሽ ሕይወቱ « ኮተር ሂልያርድ » አይደለምን ።

እጅዋን ያዝ ሲያደርጋት ክሐሳቧ ተመለሰች ። «እንዴት ቆንጆ ነሽ!» አላት አይን አይኗን እየተመለክተ። ደካማ ፈገግታ አሳየችው ። «በጣም እወድሻለሁ!.. . የኔ እመቤት !» አለ። «ማይክ . .. በጣም እወድሀለሁ» አለችው ። ከብስክሌቷ ወርዳ ቆመች ። እሱም ወረደ ። ገጽታዋም ፤ አይኗም ጥያቄ ይታይባቸዋል ። ጭንቀት ይነበብባቸዋል ። አቅፎ ሳማት ። የገፅታዋና የዓይኖቿ ጥያቄ ተሰረዘ ። በሁለቱም ልብ ውስጥ የሰፈረው ጥያቄና ጭንቀትም በልባቸው ውስጥ ተዳፈነ ። ያን ጥያቄ ሊያጠፋ የሚችል የለም… ካላንድ ሰው ፤ ካለማሪዮን ሂልያርድ ። ያች ሴት ካልራራች የሁለቱም ልብ በተዳፈነው ጥያቄ ይግላል ። ከብስክሌቷ ወርዳ ብስክሌቷን ለቅቃ እቅፉ ላይ አረፈች ።

‹‹ ማይክል የማሪዮንን ሆድ ቢያራራልን … ቢረዳን » አለች ። «አይዞሽ ! ይረዳናል ። ሁሉ ነገር ቀላል ሆኖ ነው የምናገኘው እመኝኝ» አላት ። ይህን ብሎ በቀልድ ቁጣ ፤ «ምንድነው ነገሩ ፤ አሁን ጉዞ እንቀጥላለን ፤ ወይስ እዚህ ቆመን ማደር ሊኖርብን ነው ? » አለ ። ገዟቸውን ሲቀጥሉ ማሪዮን ሂልያርድን የረሷት ይመስላሉ ። ሆኖም ማሪዮን ከነፍሳቸው አልተሰረዘችም ። ማሪዮን አንድ ሰው ብትሆንም ትልቅ ተቋምም ናት ። በቀላሉ አትሰረዝም ። ማሪዮን በማይክል ሕይወት ውስጥ የቆመች ትልቅ ምሶሶ ናት ። ዛሬ ዛሬ ደግሞ በናንሲ ሕይወት ውስጥም ጎልታ መታየት ጀመረች ።

በብስክሌታቸው ላይ ሆነው ለሙን መሬት እያቋረጡ እሽቅድምድሙን ተያያዙት ። አንዴ ስትቀድመው ወዲያው ሲደርስባት ጎን ለጎን ሲጓዙ እንደገና ስትቅቀድመው ዞራ ስታሾፍበት ሊደርስባት ሲያባርራት ። እንደለቆ ጥጃ ሲፈነጥዙ … » በሌላ ጊዜ ፀጥ ብለው ጎን ለጎን ሲጓዙ . . . እነሱም ገሰገሱ ፤ ፀሐይም የሰማዩን ዳገት እየተንፏቀቀች ወጣች ። ወደ ሪቨር ቢች ሲቃረቡ ተሲያት ተቃርቦ ነበር ። ከፊት ለፊታቸው የመጣው መኪና ፍጥነቱን ሲቀንስ ቤን አቭሪ መሆኑን ተመለከቱ ።
‹‹ ታዲያስ?» አለ ቤን ።
«ሃይ ቤን ! » አለች ናንሊ። ሰላምታ ተለዋወጡ። ከቤን አቭሪ ጎን አንዲት ልጅ ተቀምጣለች-። ናንሲም ሆነች ማይክል ይህችኛዋን ልጅ አይተዋት አያውቁም ። ግን ከየት አገኛት ? ብለው አልተደነቁም ። ቤን አቭሪ ዛሬ አብሯት ከወጣት ልጅ ጋር ነገ ተመልሶ አይወጣም ። ይህን ባህሪውን ናንሲም ማይክልም ያውቃሉ ።
«ወዴት ነው?ወደ ባዛሩ የምትሔዱ ይመስላል» አለ ቤን። ሁለቱም ዝም አሉ ። ሀሳባቸው እልጅቷ ላይ ነበር ። ይህን የተገነዘበው ቤን ቶሎ ብሎ አስተዋወቃቸው ፡፡
«ጃኒት ትባላለች … ናንሲና ማይክል ይባላሉ » አለ።
‹‹ ባዛሩ እንዴት ነው ? » አለ ማይክል ከትውውቁ በኋላ። እንግዲህ እንደየሰዉ ነው ። ግን » አለና እባዛሩ ውስጥ ያለውን ነገር ይዘረዝርሳቸው ጀመር “ በጫወታ አሸንፈው ያመጧቸውን ዕቃዎች ፣ የገዟቸውን ምግቦችና መጦችም ነገራቸው … ገለጻውን ሳይጨርስ … «በቃ በቃ … እንሔዳለን ። በቂ አድርገህ እንድንሔድ ገፋፍተኽናል » አለ ማይክል ። ከዚያም ወደ ናንሲ ዞሮ « ምን ይመስልሻል ደረስ ብለን ብንመለስ ›› ሲል ጥያቄ እቀረበላት ።

«በጣም ደስ ይለኛል » አለች ናንሲ ። « እናንተስ አብራችሁን አትመለሱም ቤን? » እንደጠየቀች መልሱን አገኘች ። ቤን አቭሪ ጎምዥቷል ። ጃኒትም ብትሆን ረሀቡን ለማርካት የጓጓች ትመስላለች ። የሁለቱን ሰዎች በሥጋ የመፈላለግ ችኮላ ስትገነዘብ ናንሲ ማክአሊስተር እንደመሳቅ ቃጣት ። ቢሆንም ሳቋ አካሏን ዘልቆ ሳይታይ አፍና አስቀረችው ።
«እኛ እንኳ አረፈድንበት » አለ ቤን « እሁን ወደ ቤት፤ደክመናል ። በስንት ሰዓት የወጣን መሰላችሁ … ጧት ፤ በአሥራ ሁለት ሰዓት » ይህን ብሎ ፤ .
« ግን ማታ ፒዛ መብላት የሚፈልግ ካለ ቤት ድረስ ብቅ ማለት ይችላል › ሲል ጨመረ ። ማይክልና ቤን ጎረቤት ናቸው።
«ለመሆኑ እራት የምትበሉት የት ነው ዛሬ?» ቤን ይህን ሲጠይቅ ናንሲ
‹‹ ሲኛር ፤ ዛፊ እራት የምንበላው የት ነው? » ስትል ማይክልን ጠየቀች ። ማይክል ራሱን በአሉታ ነቀነቀና ፡… «ጉዳይ አለኝ . . - እራት ላይ አንገናኝም» ሲል በደፈናው መልስ ሰጠ ። «ሆኖም» አለ ቀጠለና « በሌላ ቀን ለፒዛው ፕሮግራም ልንይዝ እንችላለን »
ጉዳይ አለኝ ? ቆርጦ ማሪዮንን ሊያነጋግራት አስቧል ማለት ነው ።

‹‹ እሺ እንግዲያ. . . እንዲያ ከሆነ በቸር ይግጠመን ›› አለ ቤን። ጂኒትና ቤን ለስንብት እጃቸውን አወዛወዙ ። ከሄዱ በኋላ ፤ «እውነት ዛሬ ማታ ልትሔድ እስበሀል ? » አለች ናንሲ። «እንዲህ , አይነት ፌዝ የምሞክር ይመስልሻል ባንች ላይ?» አላት ጥያቄዋን በጥያቄ እየመለሰ። ፤ «አይመስለኝም፤ ሆኖም … ››
👍20🎉1
«የኔ እመቤት ምንም የሚያ ስጨንቅሽ ነገር የለም ። እርግጠኛ ነኝ ማሪዮን ትስማማለች። እርግጠኛ ነኝ ሁሉ ነገር እንዳሰብነው ይሆናል» አለና ድምጹን ወደ ደስታ ቅኝት ለውጦ « በነገራችን ላይ ማሪዮን ቤንን ልትቀበለው ነው፣፤ ስራ ለመግባት አመልክቶ እንደነበር ነግሬሻለሁ አደል ?» !
‹‹ ነግረኸኛል።»

«በጣም ጥሩ ሆነ አየሽ። ስራውን የምንጀምረወም ባንድ ቀን ነው። የምንሰራበት ቦታ ግን ይለያያል» ማይክ ይሀን ለናንሲ ሲነግር ጉዳዩ ለራሱ እንጂ ለእንድ ሌላ ሰው የተፈፀመለት አይመስልም ነበር። ቤንና ማይክ የተዋወቁት እዚሁ ሀርቫርድ ውስጥ ነበር … የመጀመሪያ አመት ተማሪ ሆነው ። የኮሌጅ ትምህርታቸውን አብረው ጨረሱ፡፡ ለድህረ ምረቃ ፕሮግራም ሁለቱም ቀጠሉ ። በነዚህ ዓመታት ውስጥ ባህሪ ለባህሪ ተዋውቀዋል ። ዛሬ እንደወንድማማች እንጂ እንደጓደኛ አይደሉም ።

ቤንጃሚን (ቤን) አቭሪን ከማሪዮን ጋር ካስተዋወቀው ቆይቷል ትምህርቱን ጨርሶ ሲመረቅ ቤን ለማሪዮን ማመልከቻ እንዲያስገባ ነገረው። ቤን እንደተባለው አደረገ ። ማይክ ስለቤን ጉብዝና ለእናቱ ተናገረ ። በመጨረሻ ማሪዮን ቤንን እንደተቀበለችው ለማይክል አስታወቀች።
«ቤን ስራውን እንዳገኘ አውቋል አለች ናንሲ። ማይክ በአሉታ ራሱን ነቀነቀና… «ከአሁኑ ቢያውቅ ደስታው ይበላሽበታል ብዩ አልነገርኩትም ። በድንገት ነግሬ ላስፈነድቀው አስቤአለሁ» ናንሲ ገረማት ።
«ምን አይነት ሰው ነህ ማይክ? በጣም ደግ ነህ ። አንተን ስለወደድኩ ምን ያህል የታደልኩ ሰው ነኝ እላለሁ» «አመሰግኖለሁ ሚስዝ ሂልያርድ›› «እባክህ እንዲያ ብለህ አትጥራኝ ማይክ?» «ለምንድነው እንዲያ ብዬ የማልጠራሽ? ምክንያቱን ልትነግሪኝ ትችያለሽ ? ይልቅስ ካሁኑ ተላመጅው ። አዲስ ስም በቀላሉ አይለመድም››
«ሁሉም ነገር ቢሆን ይለመዳል ። ሲሆን የማይለመድ ነገር የለም» አለች ። ቀጥላም «ለጊዜው ግን ናንሲ ማክአሊስተር ነኝ። ሚስ ማክአሊስተር ብትለኝ በቂ ነው» ስትል ጨመረች። « ጊዜ የለንምኮ የኔ እመቤት ። ለአሥራ አምስት ቀን እድሜ ማክአሊስተር ብልሽ ግፍ አይሆንም !» ይሆን ብሎ ድምጹን ወደ ጨዋታ ቅኝት ቀየረና…
«አሁን ወንድና ሴቱ ይለይ!...ባዛሩ በር ድረስ እሽቅድምድም እንገጥማለን። ይለይ!›› አለ ።
«ይለይ!» አለች።

ትንፋሽ እስከሚያጥራቸው ድረስ በፍጥነት መንዳት ጀመሩ ። «ለረጂም ጊዜ ማንም አልቀደመም ። በመጨረሻ ማይክል ከናንሲ ግማሽ ደቂቃ ቀድሞ ደረሰ « ሁለቱም ከላይ የተነጋገሩትን ረስተው ድንገት በተፈጠረው ደስታ ታጥበው ፣ ፀድተው ነበር ። ቢስክሌታቸውን ዛፍ አስደግፈው ወደ ባዛሩ ቅጥር አመሩ ። በዚህ ጭር ባለ ገጠር ማንም ቢስክሴት እንደዶማይሰርቅ እርግጠኛ ነበሩ።
ይህ ሁሉ ከሆነ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ኮርን (ከነቆረቆንዳው ተቀቅሎ በቅቤ የተዘፈዘፈ በቆሎ) ይዘው መጋጥ ጅመሩ ። ቅቤው እጃቸውን አረስርሶ ሲንጠባጠብ ይታይ ነበር ። በቆሎ ቅቅል በቅቤአቸውን ካስገቡ በኋላ « ሆት ዶግ» በብዛት ጎስጎሱ። በላዩ ላይም ቀዝቃዛ ቢራ ቸለሱበት ። ናንሲ በዚህ አላበቃችም ። ጣፍጭ የሆነና እንደ ጀላቲ መያዣ እንጨት ያለው ግን ጠንከር ያለ ሳይሆን ጥጥ የሚመስል ካንዲ ፍሎስ የሚሉት ጣፍጭ ነገርሩ መብላት ቀጠለች፡፡ ካንዲ ፍሎሱን ስትልስ ፊቷና ጉንጯ ፤ ከንፈሯና አፍንጫዋ ተቀባብተው ነበር ።

«ልጅ መሆንሽ ነው?!... አይቀፍሽም› እላት ማይክል «ይጣፍጠኛል እንጂ ለምን ይቀፈኛል ! ትንሽ ብትቀምስ አስሩን ትረሽነው ነበር» አለች ካንዲ ፍሎሱን አፏ ውስጥ እንደያዘች። ስለዚህም ቃላቷ ሁሉ የህፃን ልጅ ይመስሉ ነበር። ሁኔታዋም የህፃን ልጅ ነበር «ምን አይነት ፍጡር እንደሆንሽ አይገባኝም ! ባየሁሽ ቁጥር የበለጠ ቆንጆ የምትሆኝው ለምንድነው" አለ፡፡ ሰፊ ፈገግታ ለገሰችው፡፡ ፊቷ በካንዲ ፍሎሱ ተበካክሏል። መሀረብ አወጣና ጉንጯን ጠረገላት ።፡ ከዚያም ፤ «ፊትሽ እንዲህ ባይበካከልኮ ፎቶ እንነሳ ነበር› አላት ።
‹‹ፎቶ!›› አለች እንደአምስት ዓመት ህፃን እየፈነጠዘች «የት የት ነው እምንነሳዉ›› ይህን እያለች ሌላ ካንዲ ፍሎስ አነሳች ። አንስታ ስትልስ ጥጥ መሰሉ ጣፍጭ ነገር ፊቷን ሸፈናት ። ‹‹ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ ለምን አይበቃሺም ይኸ ነገር››
‹‹የት ነው ፎቶ እምንነሳው!? የት ነው?››
‹‹ እዚያ ጋ››

ፎቶግራፍ ተነሱ ። ፎቶግራፍ አንሺዎቹ የተለያዩ ልብሶች ይሰጣሉ ። ማይክና ናንሲ የርሄት በትለርን የስካርለት ኦ ሀራን አለባበስ መረጡ ። ( ርሄት በትለርና ስካርለት ኦ ሀራን (gone with the wind) በሚል ርእስ አሜሪካዊቷ ማርግሬት ሚቸል በፃፈችው ዝነኛ ልብወለድ መፅሐፍ ውስጥ ዋናዎቹ ገፀ ባህርያት ናቸው።) እንደ ርሄት በትለርና እንደ ስካርለት ኦ ሀራን ለብሰው የተንሱትን ፎቶግራፍ ሲያዬ ተገረሙ ። ናንሲ የደቡባዊ ዩናይትድ ስቴትስን ቆነጃጅት ልብስ ስትለብስ ውባቷ ጎላ። ማይክልም ኮስታራ ወንድ ሆኖ ቁጭ አለ። ይህን ያየው ፎቶግራፍ አንሺ ሳይቶር ገንዘቡን ተቀብሎ ፎቶግራፉን ሲሰጣቸው
«ይህን ፎቶ መስጠት አልነበረብኝም ። አንድ የተለየ ደስ የሚል ነገር አላችሁ ። ይህን ካየሁ ደግሞ ቆየሁ። ስለዚህ ቢያንስ ፎቶግራፋችሁን እያየሁ ዶስ እንዲለኝ ማስቀረት ነበረብኝ» አላቸው። ናንሲ ይህን ስትሰማ ደስ አላት ። ማይክልም ፈገግ አለ ያን ያህል ግን አልተደሰተም፡፡ ምክንያቱም አይቶ እማያደንቃት እንደሌለ ያውቃል። ግን የሱ ናት ።ሙሉ በሙሉ የሱ ትሆናለች። ሁለት ሳምንት . . . የናንሲ ጉትጎታ ከሃሣብ መለሰው።

«ተመልከት. . . እዚያ ጋ… ቀለበት በጠርሙስ አንገት ማስገባት ጨዋታ አለ» አለች። ይህን ጨዋታ ለመጫወት ከልጅነቷ ጀምሮ ትልቅ ጉጉት ነበራት ። ሆኖም እድሉ አጋጥሟት አያውቅም ። ከእጓለማውታን ማሳደጊያው ውስጥ የነበሩ መነኩሴ ሞግዚቶቿን ስትጠይቅ ከፍተኛ ገንዘብን የሚያባክን ጥቅም የሌለው ጨዋታ ስለሆነ አይቻልም ይሏት ነበር።

«መጫወት እንችላለን ? » አለች ገንዘብ ይባክናል እንዳይላት እየፈራች ። «ከፈለግን ደግሞ ማን ይከለክለናል ? ያውም አንች ብለሽ አለና በትያትር ደንብ ለጥ ብሎ እጅ ነሳት ። ከዚያም ክንዱን በክንዷ ታስገባ ዘንድ አዘጋጀላት ። ጅንን እያለ ለመሄድ ሞከረ ። ናንሲ ግን በዚያ የመጀነን ጉዞ ተካፋይ ልትሆን አልተቻላትም። ልክ እንደ እንቦሳ መፈንጠዝ ጀምራ ነበርና ። ይህ ፈንጠዚያ ደግሞ ይበልጥ ደስ አሰኘው።
«አሁኑኑ መጫወት እንችላለን!››
«አሳምረን ነዋ ፍቅሬ» አንድ ዶላር አወጣና ለአጫዋቹ ሰጠ። አጫዋቹም ከተለመደው አራት እጥፍ የሆነ ቁጥር ያላቸው ቀለበቶች ሰጣት ። ሩቡ በቂ ነበር።እሷ ግን ልምድ ስለሌላት ያን ሁሉ ቀለበት ተቀብላ ወደ ጠርሙሶቹ ብትወረውርም ጉዳዩ ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ነበር ።ማይክል ደስ ብሎት ሲያስተውላት ከቆየ በኋላ፣
«ምን ማግኘት ነው እምትፈልጊው?» ሲል ጠየቃት ።
«ያንገት ጌጦቹን ፣ መቁጠሪያ መሰል ጌጦችን» አለች።

በጣም እንደጓጓች ድምጺም አይኗም ጠቅላላ አካላቷም ይናገር ነበር «እንደዚያ አይነት ውብ ጌጥ አጥልቄ አላውቅም» አለች። በህፃንነቷ የምትመኘው አንዱ ትልቅ ነገር ይኽ የአንገት ጌጥ ነበር ። የሚያብረቀርቅ ፤ የሚያምር ጌጥ ስታይ እንደጓጓች ነበር ያደገችው ።
👍19
«የምትፈልጊው ነገር ቀለል ያለውን ነውና ውዴ ። ሌላ ፤ ለምሳሌ ጃኒት የያዘችውን አይነት አትፈልጊም ?» አላት ። አንገቷን በአሉታ ነቀነቀች። «እሺ ተይው። የፈለግሽውን ለማድረግ ታዛዥሽ ነኝ» አለና ወረወረ። ሶስቱም ኢላማቸውን መቱ ። የአንገት ጌጡን ተቀብሎ ለናንሲ አጠለቀላት ። «ይኸው ወጣቷ እመቤት። የፈለግሽውን አምጥቻለሁ። ያንችው ነው። ኢንሹራንስ ልንገባለት ይገባል ብለሽ ትገምቻለሽ»

«አይ ፣ እንግዲህ በአንገት ጌጤ ላይ ማሾፍሀን አቁም ።ደስ አይልም?» ቀስ ብላ ነካ ነካ አደረገቻቸው ። እያንዳንዳቸውን ነቅነቅ ነቅነቅ… ሲያንፀባርቄ ለማየት ። «ጌጡ ሳይሆን ውብና ደስ እምትይ አንቺ ብቻ ነሽ። ስለዚህ ሌላ ልብሽ የሚሻው ነገር ቢኖር ታዛዥሽ እሆናለሁ» የደስደስ የተሞላ ፈገግታዋን አሳየችውና ፣ «ሌላ ካንዲ ፍሎስ ግዛልኝ» አለችው ገዛላት ። ከባዛሩ ወጡ። ቢስክሌቶቻቸውን ወዳቆሙበት ቦታ ሲያመሩ ማይክል… እንዴት ነው፤፣ ደክሞሻል?» ሲል ጠየቃት ።
«በጣምም አልደከመኝም » «ወደ ቤታችን እንመለስ ወይስ ወደ ፊት እንቀጥል ?» «ምን ያሀል እንቀጥል ?» «ቅርብ ነው ፤ ላሳይሽ የምፈልገው ቦታ አለ ። እባህሩ ዳር አካባቢ አንድ ደስ እምትለኝ ቦታ አለች» «ደስ ይለኛል እንሂዳ»
ቀስ ብለው፣ፀጥ ብለው ጉዟቸውን ቀጠሉ ። ድንገት ሁለቱም በየግል ሀሳባቸው ተዋጡ የቅድሙ መቃበጥና መቧረቅ ጥሏቸው የሸሸ ይመስል ነበር ። ወደ ባህሩ ዳር ሲደርሱ ገና ይህ ነው ሳይላት ሊያሳያት የፈለገውን ቦታ አወቀችው። በትላልቅ ዛፎች የተከበበ ለመፋቀርና ትዝታን ለዘላለም አጥምዶ ለማስቀረት ተብሎ የተሰራ የመሰለ ቦታ ነበረ ። ይህን ቦታ እንዳየች ናንሲ እየፈነደቀች ‹‹ እንዴት ደስ ይላል ! እንኳን መጣን» አለች።

‹‹በጣም ደስ ይላል ፤አይደለም ፣» አለ ፤ደስ ሲላት ስላዬ እየተደሰተ ። «በጣም በጣም» አለች እየፈነጠዘች ። « ብዙ ጊዜ እስባለሁ ፤ ላሳይሽ››
«ዛሬ እንኳን ይዘኽኝ መጣህ ። እንኳን አላመለጠኝ» እጅ ለጅ ተያይዘው በጸጥታ ተቀመጡ ። ለተወሰነ ጊዜ በዚህ ሁኔታ ቆዩ። ከዚያም ናንሲ ድንገት ብድግ አለች ። «ምነው?... ሰለቸሽ ?» አለ ማይክል ።
«አይ . - -. አልሰለቸኝም »
«ታዲያ የት መሄድ ፈለግሽ››
«አንድ ጉዳይ አለኝ. . .»
«ነው? ቀላል ነው። ወደጥሻው ገባ ብለሽ...»
«ግን እኔ ያሰብኩት ሌላ ነው » ይህን ብላ ጥላው ሮጠች። ቀስ እያለ ተከተላት ። በልቡ ምን ይሆን ደግሞ አሁን ያሰበችው? የሚል ጥያቄ እየጠየቀ ። ጐንበስ ብላ አንድ ትልቅ ድንጋይ ለመፈንቀል ትታገል ጀመር። ድንጋዩ ግን ንቅንቅም አላለ ።
« ቂል ‹ከድንጋይ ጋር ትታገላለች?» አለ የቀልድ እየናቃት። ቀና አላለችም ። ትግሏን ቀጠለች .።

«በቃ በቃ ። ይህን ያህል ካስፈለገሽ አንዴ ዞር በይልኝ ልሞክረው» አለ። ደካክማ ቀና አለች ። «ግን ለምንድነው የፈለግሽው !? » አላት ፤ ድካሟን በፊቷ ላይ ሲየይ ግራ ተጋብቶ « «ለሆነ ጉዳይ. . . ትንሽ ብቻ ብድግ ካለ ይበቃል» አለች ። ማይክ ሲሞክረው ድንጋዩ በመጠኑ ተነሳ ።
«በቃ | እንደሱ ያዘው » አለች ናንሲ ።
ከዚያም እባዛሩ ላይ ማይክል ተጫውቶ በማሸነፍ የሸለማትን የጌጥ መቁጠሪያ አውልቃ እድንጋዬ ሥር ከተተችው። ይህን ካደረገች በኋላ ፤
«አሁን ልቀቀው » አለች ።
«ምን ? የአንገት ጌጥሽን መቅበር ፈለግሽ »
«አዎ | ልቀቀው » ድንጋዩ ወደ ቦታው ተመለሰ። መቁጠሪያ መሰሉ ጌጥ ተቀበረ። ከዚያም መቁጠሪያው የተቀበረበትን ቦታ እየተመለከተች ፤ «ይህ የአንገት ጌጥ በቃል ኪዳን የመተሳሰራችን ቋሚ ምስክር ነው።ይህ ምስክርም ይህ ድንጋይ ፤ ይህ ወደብና እነዚህ አድባር መሳይ ዛፎች በዚህ ቦታ ላይ ፤እስከ ኖሩ ድረስ ይኖራል ። ትስማማለህ ? » አለች ። «እስማማለሁ ግን...» አለ ፈገግ እያስ « ግን ፍቅራችን የጀማሪ ፍቅር አልሆነም ? »

«ምን ነውር አለበት ? ...ከፍቅር ሁሉ የጀማሪ ፍቅር ንጹህ ፍቅር መሆኑን አታውቅም ? ስለዚህ እንዲያ አይነት ፍቅር ሲያጋጥምህ በደንብ መያዝ ፤ መንከባከብ ፣ መጠለያ ማበጀት አለብህ » አለች ።
«ልክ ነሽ ። በጣም ልክ ነሽ ፍቅሬ ። አሁን ፍቅራችን እዚህ ቦታ ላይ መጠለያ ይኖረዋል» አለ ማይክል"ደስ እያለው።
«አሁን በዚህ ቋሚ ምስክር ፊት እኔ ላንተ፤አንተ ለኔቃል ኪዳን እንገባለን ። እኔ ናንሲ ማክአሊስተር እዚህ ኦማይሞት ድንጋይ ስር ካረፉት መካከል እያንዳንዷን መቁጠሪያ በህይወቴ እያለሁ ላልረሳ ቃል እገባለሁ። እነዚህ መቁጠሪያዎች የፍቅራችን ፤ የመተሳሰራችን ምልክት እንደሆኑ ላልረሳ ቃል እገባለሁ » አለችና ቀና ብላ «አሁን ደሞ ያንተ ተራ ነው» አለች።

«እኔም. . . እኔ ማይክል ሂልያርድም የመጣው ቢመጣ የሆነው ቢሆን ፤ እነዚህን መቁጠሪያዎች ምስክር በማድረግ ካንቺ ሌላ ላላስብ ቃል እገባለሁ። ቃል ኪዳን ነው » አለ ። በቃል ኪዳን ተሳሰሩ ። በደስታ ፈንደቁ ። የደስታ ሳቅ ሳቁ ። ያን ያህል የሚያስቅ ፤ የሚያስፈነድቅ ምን ነገር አጋጠማቸው ? ወጣት ናቸው ፤ ፍቅር የያዛቸው አፍላ ወጣት መሆናቸው ውብ ፍቅርን መላበሳቸው ደስታ ለኮሰባቸው ። ይህ ደስታ አሳቃቸው ፤ አስፈነደቃቸው። ያን ለት በዚህ ሁኔታ ቀኑን በደስታ አሳለፉት ፤ ሲወዳደሩ ሲደናነቁ ፤ ሲፈነጥዙ ። በመጨረሻ አንዳቸው አንዳቸውን ላይዘነጉ? ሌላ ላያስቡ በቃል ኪዳን ተሳሰሩ ። ቃል ኪዳናቸውን በደስታ ሳቅ አሳረጉ። ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ማይክል «አሁን ወደቤታችን እንድንመለስ ትፈልጊያለሽ ? » ሲል ጠየቃት። ራሷን በአወንታ ነቀነቀች ። ቀስ እያሉ ብስክሌቶቻቸውን ወዳቆሙበት ቦታ አመሩ።

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️❤️
👍233
#ሳቤላ


#ክፍል_ሃምሳ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

ድፍን የዌስት ሊን ሕዝብ ደስ በሚለው የሰኔ ማለዳ አየር ወዲያና ወዲህ ይተ
ራመሳል ሕዝቡ ምንጊዜም በጧት ወጥቶ በመንገድ ሲተላለፍ በብዛት መታየቱ
የተለመዶ ቢሆንም እንደዚያን ዕለት ሆኖ ወጥቶ አያውቅም ዕለቱ ሚስተር ካርይል ከባርባራ ሔር ጋር በጋብቻ የሚተሳሰሩበት ቀን ስለ ነበር ሕዝቡ ንቅል ብሎ ወጥቶ ሥነ ሥርዓቱ ወደ ሚፈጸምበት ቦታ ይጐርፋል
ሚስ ካርላይል ከዚያ ሁሉ ድብልቅልቅ አልገባችበትም " ትልቅ 'ደማቅ የጋብቻ በዓል አይወድልኝም ቢፈልጉ እሷ ሳትኖር በገዛ እጃቸው ግጥም ብለው
መታሰር ይችላሉ ” ብላ አልተጠጋቻቸውም " የካርላይል ልጆች የሁለተኛዋን እናት መምጣት በጸጋ እንዳይቀበሉ በማሰብ አስተማሪያቸውንና ጆይስን ጭምር ከበቷ ጠርታ ወስዳቸዋለች " የቤት ሠራተኞቿን ይዛ ከሚስተር ካርላይል ቢሮ ቀጥሎ ከሚገኘው ቤቷ ለዘለቄታ ከገባች ሰንብታለች ፒተር ብቻ ከኢስት ሊን
ለመውጣት ባለ መፈለጉ ከሷ ተለይቶ ቀረና አስቀየማት "

ሚስተር ዲልም ስለ ጋብቻዉ አከባበር በጣም አሰበበት " እንዳያያዙ ከሆነ
በሚስተር ካርላይል የመጀመሪያ ጋብቻ ጊዜ እንዳደረገችው ሁሉ ዛሬም ኮርነሊያ! አንግቱን ይዛ ሳትንጠው በመቅረቱ ዕድለኛ ነበር " በአራት ሰዓት ገደማ ከሚስ ካርላይል ቤት መጣ " ነባር ሰው በመሆኑ የጥንቱን ባህላዊ ሥነ ምግባር በሚገባ ያውቃል " ስለዚሀ እሷ ዘንድም ጐራ ብሎ ደስታውን ቢገልጽላት እሱን ከመሰለ ሽማግሌና ጨዋ ሰው የሚጠበቅ መልካም ሥራ ነው ብሎ ሔደ ።

ሚስ ካርላይል እጆቿን አጣጥፋ ከምግብ ቤት ውስጥ ተቀምጣለች ያለ ምንም ሥራ እንዳሁኑ ዝም ብላ ተቀምጣ ታይታ አታውቅም ሚስተር ዲል ሲገባ ዞር ብላ አየችው ።

“ ዛሬ ምን አግኝተሃል?” አለችው እሱ ሳይናገር አስቀድማ ' “ ወጣት መስለሀል ሽቅርቅር ብለሃል
“ ወደ ሠርጉ መሔዴ ነው ሚስ ኮርኒሊያ አንቺስ አልሰማሺም እንዴ |
ሚስዝ ሔር ለቁርስ ጠርተውኛል " ሚስተር አርኪባልድ ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንድገኝ አጥብቆ ነግሮኛል" ይህን ያህል ከልክ በላይ አጊጫለሁ እንዴ ? አይመስለኝም" "
ምስኪኑ ሚስተር ዲል ' “ ሽቅርቅር ብለሃል ” የተባለው ' አንድ ባለ ወርቅ
ቁልፍ ነጭ ሰደርያና ደረቱ ላይ የተጠለፈ ሸሚዝ በመልበሱ ነበር " ሚስ ኮርኒሊያ ግን እሱን ለማሽሟጠጥና ለማብሸቅ ተመቻት "

"ማማር ?” ብላ ጮኸችበትና “ ምን እንደምትለው አላውቅም " እኔ መቸም ወርቅ በቁና ቢሰፈርልኝ እንደዚያ መሣቂያ ሁኘ አልወጣም " ከመንገዱ ባፈር የሚ
ፀጫወቱት ሕፃናት አንተን ሙሽራ አድርገው "ሆ” እያሉ ይከተሉሀል ይኸው ነበር የጎደለህ « በዚህ ዕድሜህ በተጠለፈ ሸሚዝ ስታጌጥ አለማፈርህ " በኮትህ ጠርዝ ያበባ ጌጥ ብትጨምርበት ደግሞ የበለጠ ባማረብህ ነበር እንዴ ኮቴን ኮ በምንም ነገር አላስጌጥኩትም ' ሚስ ኮርኒሊያ "

"አላስጌኩትም ? ” አለች ካፉ ነጥቃ ምናልባት ከዙሪያ ያበባ ጉንጉን ልትዘመዝምበት ባንገትያው የነጭ የባሕር አምራ ለስላሳ ላባና ቀይ አበባ ልታስጠልፍበት አምሮህ ይሆን ? ከሱ ሸሚዝህና ሰደርያህ ጋር ይስማማ ነበር !”

“በሰርግ ቀን ኮ ከአዘቦቱ ለየት ያለ ልብስ መልበስ የሚገባ ነው....ሚስ ኮርኒሊያ አንድ ሰው ተጠርቶ ከሔዶ እንደዚህ ለብሶ መሔድ ጠሪዎችን ማክበር ነው ”

“ እኔ እኮ ሰዎች ወደ ሠርግ ቤት ኬሻ ለብሰው ይሒዱ ኘልወጣኝም " ብቻ ለሁሉም ነገር መጠን አለው ። እስቲ አንተ አሁን ዕድሜህን ታውቀለህ ?

“ ልክ ስልሳኛዬን መያዜ ነው

ታዲያ አንድ የስልሳ ዓመት ሰው አንተ አሁን እንደ ተሸለምከው ሆኖ ማጌጥ
የሚገባው ነገር ነው ? የሰበካው ሕዝብ መሣቂያ ነው የሚያደርግህ " ብቻ ልጆች የቆርቆሮ ማንቆርቆሪያ ከልብስህ ጋር ቋጥረው እንዳያንጠሰጥሉብህ ተጠንቀቅ "

ሚስተር ዲል ለኮርኒሊያ የመሰላትን ያህል እንደማይሣቅበት ያውቃል እሷ ለምታቀርብለት ሐሳብ ሁሉ ጥሩ አክብሮት ስላለው ያጠለቃቸውን ነጫጭ የጅ ሹራቧን ሳታየው አውልቆ ከኪሱ ከተተና ገባ ።

አሁን እንኳን የመጣሁት በዚህ ታላቅ ቀን ደስታዬን ልገልጽልሽ ነው ያለኝ ተስፋ ሚስተር አርኪባልድ ሚስቱና አንቺም...."

“ በል በቃህ አትልፋ ” አለችው አቋርጣ " ዛሬ ጥናቱን ይስጣችሁ የምን
ባልበት ቀን ነው " አርኪባልድን ወስደው ሲያንጠለጥሉት ባይ በጣም ደስ ይለኝ ነበር .

ምነው ኮርኒሊያ !

“ አዎን ሁንም ደስ ይለኝ ነበር። አንተም ጉሮሮህን እንደ ተያዝክ አታፍጥጥብኝ እስኪ አሁን እንደገና በገዛ እጁ ከሚስት ጋር በሰንሰለት መታሰርን ምን አመጣው ? ያለፈው አይበቃም ነበር ? እኔማ ጭንቅላቱ ዶኅና አይደለም ማለት ከጀመርኩ
ቆይቻለሁ

ያለፈው ዐለፈ " ሁላችንም ልናወሳው አይገባንም " ጋብቻ ያስደስታል ያስከብራል ። እሱም ቢሆን ነገሩ ከመበላሸቱ በፊት ጥቂት የደስታ ዓመታት አሳልፎበታል " አሁንም ቢሆን ካዲሷ ሚስቱ የበፊቱን የሚያስረሳ እንደሚያገኝ ተስፋ አለኝ " ከሷ የበለጠች ቆንጆ ማግኘት አይችልም " ሚስተር ካርላይል እሷን በማግኘቱ በበኩሌ የተሰማኝ ደስታ ይህ ነው አይባልም "

“ እንዴ ከምን ያገኛል ? እሷን የመሰለች ሥራ ፈት • ስድ ባለጌ ' አውደልዳይ :
አሻንጉት ስለሚመስለው ፊቷና ስለ አርኪባልድ ካልሆነ በቀር ምንም ሐሳብ የሌላት ከንቱ ' የትም አትገኝም ” ብላ ደነፋች "

“ አይ ሚስ ኮርኒሊያ ...
መልከኛ ወጣት ሲቶች ቁንጅናቸውን ያውቃሉ "
ስለ ውበታቸው መታየት ' መሽቀርቀር መወደዳቸውንም ማንም ሊወስድባቸው አይችልም " ነገር ግን እሷ ጥሩ ሚስት እንደምትሆንለት አልጠራጠርም " ያች ያል
ታደለች ከንቱ እንዶ በደለችው አትበድለውም

“ እኔ እሷም እንደዛችኛይቱ እንደምታዋርደው ብሠጋ ኖሮ አሁኑኑ ሥነ ሥርዓቱ ከሚካሔድበት ሔጄ ጋብቻውን እከለክል ነበር " እምቢ ብትል እንኳን
እዚያ እንዳለች አንቃት ነበር
" አለችና ደነፋች "
እያት ደሞ ያቺ ከውካዋ ዐይን አውጣ ! አለች ትንሽ በረድ ብላ ወደ መንገዱ እያየች " ሚስ ካርላይል ከወንበሯ ተንደርድራ ወደ መስኮቱ ሔደች ሚስተር
ዲልም ወደዚያው ዞር ብሎ ተመለከተ።

ራስ ወዳድና ትዕቢተኛዋ አፊ ሆሊጆን ሽቅርቅር ብላ ለብሳ ስታልፍ ሚስተር
ዲልን አየችውና የሰላምታ ምልክት ሰጠችው ። ትሕትና የተሞላው ሽማግሌም
አጸፋውን መለሰላት " ሚስ ካርላይል አሁንም ጮኽችበት "

“ ደግሞ ለሷ ሰላምታ የምትሰጣት ምን መሆንህ ነው? ”
“ አይ ሚስ ኮርኒሊያ ሰላምታ ስትሰጠኝ አንቺም አይተሻታል "

አይቻታለሁ !እሷም አይታኛለች " ግን የብልግናዋ ብልግና አንተን እጅ ነሣችህ አንተም እኔ እያለሁ ቡጢህን ጨብጠሀ ልትነቀንቅባት ሲገባህ አጻፍውን መለስክላት።

“ ሚስ ኮርኒሊያ ያለፈው ዐለፈ ። በርግጥ እሷ አትረባም " ሆኖም ሪቻርድ ሔር ጋ ያለ መሔዷ ተረጋግጧል አሁንም ስክን ብላ ረግታ ተቀምጣለች " ታዲያ ሰላም ብላት ምናለበት ።

“ አንተማ ምናለ! ሰይጣኑ ራሱ ቀንዱን ገትሮ ጅራቱን ቀስሮ ቁሞ ብታየውም ይቅርታ የሚያስደርግ ምክንያት ሳትፈልግለት አትቀርም " አንተም እንደዚያ እንደ አርኪባልድ ነህ " አትረባም ! እስኪ አፊ ሆሊጆንን ልብ ብለህ ተመልከታት " እስኪ የማን ገረድ እንደዚህ ለባብሳ አደባባይ ወጥታ ታውቃለች ? ያደረገችው ዐይነ ርግብ እንዳንተ ሸሚዝ ጥልፍ ያሳፍራል ።

አፊ እኮ የእመቤቷ ደንገጡር ናት እንጂ የቤት ሠራተኛ ልትባል አትችልም"
የወይዛዝርት ደንገጡሮች ኮ በደንብ ነው የሚለብሱት " ለአባቷ ትልቅ አክብሮት ነበረኝ " ከሱ የተሻለ ጸሐፊ ከቢሮአችን አይተን አናውቅም ።
👍142
“ ምናልባት እሷንም አከብራታለሁ እንዳትለኝ ብቻ ! እኔስ ነገሩ ሁሉ የተገላቢጦሽ ሆነብኝ " ዱሮ አመቤቶች ገረዶቻቸውን በሥራ ይጠምዱዋቸው ነበር " ዛሬ ግን ለአጫዋችነት ነው የሚያስቀምጧቸው " ተራ የጥጥ ቀሚሷን አጥልቃ የሥራ ሽርጧን ታጥቃ ከቤት አልጋዎችን ማሰናዳትዋን ትታ ከሰርጉ ሥነ ሥርዓት ተገኝታ ለማፍጠጥ ወደ ቤተ ክርስቲያን እየሔዶች ነው » ደግሞ ያ የምን ሠረገላ ነው?” አለች ሚስ ካርላይል አንድ ሠረገላ ወደ ቢሮ ጠጋ ብሎ ሲቆም አይታ "

“ ሠረገላ ? አለ ዲል መላጣ ራሱን ወደፊት በማሰገግ እንዲመጣልኝያዘ ያዘዝኩት ይሆናል " በይ ደኅና ዋይ ሚስ ኮርኒ ።

“ ሠረገላ ላንተ?” አለችና ጮኸች!“ ምነው? ቤተክርስቲያን በእግርህ የማትሔደው ሪህ አለብህ እንዴ ?

"አሁን እንኳን ወደ እዚያ ሳይሆን ወደ ዐጸዱ ነው የምሔደው ። ይሁን
እንጂ በሠረገላ መሔዱ ለጠሪዎች ክብር መስጠት ስለ መሰለኝ ነው "

'አይጠረጠርም እንደዚያ ሺክ ብለህ መሔድ ያስፈልግሃል ብቻ ለምን የዳንስ ጫማና በጥልፍ ያጌጠ የግር ሹራብ አታክልበትም ?”

ወዲያው ጥሏት ቢወጣ ይወድ ነበር ፤ነገር ግን በንግግሯ ያለመቀየሙን ለመግለጥ መልካም ቃል ተናግሮ ቢለያት መሻሉን አሰበ “ ወደ እዚያ የሚጐርፈውን ሕዝብ ተመልከቺውማ ! መቸም ቤተ ክርስቲያኑ ግጥም ብሎ መሙላቱ ነው ” አላት
“ እኔም መሰለኝ !ምክንያቱም አንድ ሞኝ ብዙ ሕዝብ ይሰበስባል … ”

"ሚስ ኮርኒሊያ ያሁኑን ጋብቻ ከፊተኛው የተሻለ የወደደችው አልመሰለኝም
አለ ሚስተር ዲል ለራሱ “ በሌሎች ነግርች አስተዋይ ሰው ናት » ሚስተር አርኪባልድ በማግባቱ እንደዚህ መቆጣቷ ግን ልክ አይደለችም ኧረ ለመሆኑ
አለ ሐሳቡን በመለወጥ ይህ ሸሚዝ እሷ እንደምትለው አስጠልቶብኝ ይሆን እንዴ !
አኔ ደግሞ ለሚስተር አርኪባልድና ለሚስ ባርባራ አክብሮቴን ለመግለጽ እንጂ
ሌላ ለምን ብዬ ነው ኻያ አምስት ሽልንግ ያወጣሁት ምናልባት በጧቱ እንደዚህ
መልበሱ ከሥነ ሥርዓት ውጭ ይሆን ? ቢሆንም እንግዲህ ወደ ቤት ተመልሼ ለመለወጥ ጊዜ የለኝም ምንም ማድረግ አልችልም "

ቤተክርስቲያኑ ግጥም ብሎ በሕዝብ ሞላ " ከውስጥ ሊገቡ ያልቻሉ ከግቢውና
ከዚያም ተርፈው በመንዱ ቆሙ " የዚያን ቀን የመቃብር ሐውልቶችም አልተከበሩም ደንታ ቢስ እግሮች ብዙዎቹን ደቀደቋቸው ቢንስ አምሳ የሚሆኑ ልጆች እርስ በርሳቸው ተያይዘው
ከሎርድ ማውንት እስቨርን መቃብር ማገሮች ላይ ወጥተው ነበር " ከቀኑ አምስት ሰዓት ሆነ፤ሙሽሮች ግን ገና ብቅ አላሉም " ከደጅ አብርቆ ለብሶ የቆመው ሕዝብም ሆነ ከውስጥ ጥቅጥቅ ብሎ የተቀመጠው ዕድምተኛ ትዕግሥቱ አለቀ አንዳንዶቹ ከሁለት ሰዓት በላይ ጠብቀዋል " በመጨረሻ የሠረገላ ድምፅ ተሰማ" ሕዝቡም ከመቅደሱ አካባቢ ገለል እንዲል ተደረገ "

ወይዛዝርቱ መኳንንቱ አበባ መስለው አምረው ዘለቁ። ከሁሉ በፊት ሚስተር
ካርላይል ረጋ ብሎ ስሜቱን ገዝቶና ተዝናንቶ ወደ ቤተክርስቲያኑ ውስጥ ገባ "
የሙሽራይቱ ወላጆችና እኅቷ አን ከሌሎች እንግዶች ጋር ገቡ ሚስዝ ሔር ስር ጆን ዶቢዴ ክንዷን ይዞ ደግፎ ሲያስገባት የሚያምረው ፊቷ ከመቸም ይበልጥ ግር
ጥት ብሎ ያዩ ሰዎችም እርስ በርሳቸው እየተጠቃቀሱ አዬ ጉድ ! አሁንም የዚያ የተረገመ ልጂዋ ክፉ ሥራ እየመጣባት እኮ ነው” ይባባሉ ነበር " ሚስተር ጀስቲስ ሔር የተዘናፈለ ሰው ሠራሽ ጸጉር አጥልቆ በኮቱ የአዝራር ማስግቢያ ቀዳዳ ነጭ ጽጌረዳ ሰክቶ ፊቱን ኮስተር አድርጎ እየተጀነነ ሲራመድ ሰው ሁሉ እሱን ለማየት አንገቱን ወደ ፊት አሠገገ ።

ባርባራ ለስላሳ ነጭ ሐር ቀሚስ ለብሳ ወለል የሚል ዐይነ ርግብ አድርጋ” በሚዜዎቸ ታጅባ ገባች።

ሚስተር ካርላይል ቀደም ብሎ ከመቅዶዘደሱ ዳር ቦታውን ያዘ " ባርባራ ወደ እሱ ስትጠጋ ' ወደሷ ቀርቦ አጂዋን ያዘና በግራው በኩል አቆማት " የተለመደ ነገር አይመስልም ነገር ግን በፊት ስለገባ ማወቅ ነበረበት " ሌሎችን የሚቆሙበትን ጸሐፊው አመለከታቸው " ከዚያ ሥርዓተ ጸሎቱ ተጀመረ።

ባርባራ ስሜቷ በኃይል እንደሚተናነቃት ባያጠራጥርም ቀጥ አድርጋ መለሰች "ይህን ሰው ቅዱስ በሆነ ጋብቻ አብረሽው ለመኖር ባል ብለሽ ተቀብለሽዋልን ?”
አለ ቄስ ሊትል " ሁለታችሁም በሕይወት
አስካላችሁ ድረስ
በጤናም ሆነ በሕመም ጊዜ በታዛዥነት በአገልጋይነት በፍቅር ትይዥዋለሽን ?

“አዎን ” የባርባራ አነጋገር ግልጽና የማያወላውል ነበር

ሥነ ሥርዓቱ ቶሎ አበቃ " ባርባራ በጣቷ የጋብቻ ቀለበቷን አጥልቃ በክንዷ
የሚስተር ካርላይልን ክንድ ይዛ እየተመራች ዛሬ የሷም ጭምር ወደ ሆነው ሠረገላ
ገባች " የተሰበሰበው ሕዝብ የሙሽራይቱን የደስ ደስ ያለው ፊት ሲያይ ጭብጨባውን አቀለጠው
የሙሽሮቹ ሠረገላ እየመራ አጃቢ ሠረገሎች እየተከተሉ ለቁርስ ወደ 0ፀዱ አመሩ።

" ባርባራ ... " አላት ሚስተር ካርላይል “ ለቄሱ የገባሽልኝን ቃል .
ታከብሪያለሽ ?

እንደ ማፈር አለች " የጠራ ሰማይ የመሰሉት ዐይኖቿን በፍቅር እንደ ተመሉ ወደሱ 0ይኖች ቀና ስታደርጋቸው ከልብ የፈለቀ አውነተኛ ስሜት በእንባ ክድን አደረገቻው።

ሁልጊዜ ! ቃሉንም መንፈሱንም ሞት እስኪጠራኝ ድረስ ! ” አለች....

💫ይቀጥላል💫
👍15