ክሪስ የእውነት ያስደነገጠኝን አንድ ነገር አደረገ፡ ትልቅ ስጋ በሹካ ያዘና
ሙሉውን ወዳፉ ከተተው ምን ነክቶታል!
“እንደዚያ አትብላ ክሪስ። ለልጆቹ መጥፎ ምሳሌ ትሆናለህ” አልኩት።
በአፉ ሙሉ ምግብ እንደያዘ “እነሱ እያዩኝ አይደለምº በዚያ ላይ እርቦኛል።በህይወቴ እንደዚህ ርቦኝ አያውቅም: ምግቡ ደግሞ በጣም ይጣፍጣል” አለ፡
እኔ በመቀማጠል አይነት በትንሹ ቆረጥኩና አፌ ውስጥ ከተትኩ። እግረ መንገዴን በትክክል የሚበላው እንዴት እንደሆነ እያሳየሁት ነበር በመጀመሪያ
ዋጥኩኝና “ለምታገባት ሚስት አዘንኩላት፡ በአመት ውስጥ ትፈታሀለች " አልኩት።
ከመደሰት በቀር ለሁሉም ነገር ዲዳና ደንቆሮ ሆኖ መብላቱን ቀጠለ፡
“ካቲ… ክሪስ ላይ ክፉ አትሁኝበት፤ እኛም ቀዝቃዛ ምግብ ስለማንወድ መብላት ስለማንፈልግ ነው:: አለች ኬሪ
“ሚስቴ በጣም ትወደኛለች፤ የቆሸሹ ካልሲዎቼን ማንሳት ያስደስታታል።
ኬሪ፣ አንቺና ኮሪም ቀዝቃዛ ምግብ ትበላላችሁ:"
ምግቡ አልቆ ጠረጴዛውን ማፅዳት ስጀምር ክሪስ ያግዘኝ ጀመር፡ ላምን አልቻልኩም! በመረታት አይነት ፈገግ አለና ጉንጬን ሳመኝ፡ ከዚያ ወደ እኔ መጥቶ ሳህኖችን ሳጥብና ሳደራርቅ ከማገዙ በፊት ካልሲዎቹን ሳይቀር
አነሳ፡ አሪፍ ምግብ አንድን ወንድ እንዲህ ሊያደርግ ከቻለ፣ ምግብ ዝግጅት መማር ያዋጣል።
ክሪስና እኔ ሁሉንም ነገር አፅድተን በንፁህ ፎጣ ሸፍነን ጠረጴዛው ስር አስቀምጠን ከጨረስን ከአስር ደቂቃ በኋላ መንትዮቹ በአንድ ላይ “እርቦናል ሆዳችንን አመመን፡" እያሉ ጮሁ።
ክሪስ ወንበሩ ላይ ተቀምጦ እያነበበ ነበር፡ እኔም ጋደም ብዬ ከማነብበት ተነሳሁና ምንም ሳልናገር በለውዝ ቅቤ ሳንድዊች ሰርቼ ሰጠኋቸው።
ወለሉ ላይ ተቀምጠው እየበሉ ሳለ ራሴን አልጋ ላይ ወረወርኩና ግራ በመጋባት ተመለከትኳቸው፡ እንዴት ይህንን የማይረባ ምግብ ወደዱት? ወላጅ መሆን ለካ እገምተው እንደነበረው ቀላል ወይም ደስ የሚል አይደለም።
“ኮሪ ወለሉ በጣም ይቀዘቅዛል ወለሉ ላይ አትቀመጥ።” አልኩት።
በሚቀጥለው ቀን ኮሪን ሀይለኛ ብርድ አመመው: ትንሽዋ ፊቱ ፍም መስላ በጣም ያቃጥላል ሰውነቱን ሁሉ እያመመው እንደሆነ ተናገረ ካቲ እናቴ የታለች? እውነተኛዋ እናቴ?” እናቱን ነው የፈለገው: በመጨረሻ መጣች።
ወዲያውኑ የኮሪን የጋለ ፊት ስትመለከት ፈጠን ብላ የሰውነት ሙቀት መለኪያ አመጣች: ደስ ሳይላት የምታስጠላውን አያታችንን ተከትላ ዞር
አለች::
ኮሪ የሙቀት መለኪያውን አፉ ውስጥ እንደያዘ በጭንቀቱ ጊዜ ልታድነው የመጣች ወርቃማ መልአክ ትመስል እናቱን አተኩሮ እየተመለከተ ነበር።የእናትነት ቦታ ተክታ የነበረችው ግን ተረሳች:
“የምወድህ ውዱ ልጄ” እሹሩሩ ልትለው ከአልጋው ላይ አንስታ አቅፋው የሚወዛወዘው ወንበር ላይ ተቀመጠችና ቅንድቦቹን እየሳመች “አለሁልህ የኔ ልጅ እወድሀለሁ እንከባከብህና ህመምህን እናጠፋዋለን፡ እንደ ጎበዝ ልጅ ምግብህን ብላ፣ የብርቱካን ጭማቂህንም ጠጣ ከዚያ ቶሎ ትድናለህ" አለችው::
እንደገና አልጋ ላይ አስተኛችውና አስፕሪንና ውሀ ሰጥታው እንዲውጥ አደረገች: ሰማያዊ አይኖቿ በእምባ ረጥበዋል። ቀጫጭን እጆቿ በደመነፍስ
ይሰራሉ፡ አይኖቿን ጨፍና ፀሎት የምታደርግ ይመስል ከንፈሮቿ ሲንቀሳቀሱ እያየሁ ነው።
ከሁለት ቀናት በኋላ ኬሪም ከኮሪ አጠገብ አልጋ ላይ ሆነች: እሷም
እያስነጠሰችና እያሳላች የሰውነቷ ሙቀት በሚያስፈራ መጠን ከፍ አለ፡ ክሪስም የፈራ ይመስላል ፍዝዝ ብለውና ገርጥተው ሁለቱም ትልቁ አልጋ ላይ ጎን ለጎን ተኝተዋል።
ከሸክላ የተሰሩ ይመስሉ ነበር፡ ሰማያዊ አይኖቻቸው ወደ ውስጥ እየጎደጎዱ በመሄዳቸው ትልቅ መሰሉ: አይኖቻቸው ስር ጥቁር ጥላ አጠላባቸው እናታችን አጠገባችን በሌለች ጊዜ አይኖቻቸው በፀጥታ እኔና ክሪስ ላይ ተተክለው የሆነ ነገር እንድናደርግና ስቃያቸውን ማጥፋት እንድንችል ይማፀኑናል፡
እናታችን ከትምህርት ቤቷ ተመልሳ ከልጇ ጋር ለመሆን ሳምንት ወሰደባት በጣም ያስጠላኝ ነገር አያትየው እናታችን በመጣች ቁጥር ተከትላ የመምጣቷ አስፈላጊነት ነው ሁልጊዜ አፍንጫዋን በማያገባት ቦታ መክተት፣ የእሷን ምክር የማንፈልግበት ጊዜ ላይ ምክር መስጠት ትወዳለች አስቀድማ
እንዳልተፈጠርን፣ እግዚአብሔር በፈጠራትና እንደሷ ፃድቅና ንፁህ ለሆኑ ያዘጋጃት ምድር ላይ በህይወት ለመኖር መብት እንደሌለን ነግራናለች።
የምትመጣው የበለጠ ልታሰቃየንና እናታችንን ለራሳችን በማድረጋችን ያገኘነውን ምቾት ለመንጠቅ ነው።
የግራጫ ቀሚሷ መንኮሻኮሽ፣ ድምፅዋ፣ የከባድ እግሮቿ እርምጃ ድምፅ፣በአልማዝ ቀለበቶች የተንቆጠቆጡ፣ ቡናማ ነጠብጣብ የሞላባቸው የገረጡ፣
ለስላሳ፣ ወፍራምና ትልልቅ እጆቿ! አምላኬ እሷን ማየት እጅግ ያሰለቻል፡
ከዚያ እናታችን በአብዛኛው እየፈጠነች ትመጣና መንትዮቹን ወደ ጤንነታቸው ለመመለስ የቻለችውን ሁሉ ታደርጋለች: ለመንትዮቹ መጀመሪያ አስፕሪንና
ውሀ፣ በኋላ ደግሞ የብርቱካን ጭማቂና ትኩስ የዶሮ ሾርባ ሰጠቻቸው።
አንድ ጠዋት እናቴ ራሷ ጨምቃ ያዘጋጀችው የብርቱካን ጭማቂ የያዙ ሁለት ትልልቅ ፔርሙዞች ይዛ መጣች: “ከቀዘቀዘው ወይም በቆርቆሮ ከታሸገው ይሻላል፤ በቫይታሚን ሲ እና ኤ የተሞላ ስለሆነ ለብርድ በጣም ጥሩ ነው::” ስትል አብራራችልን፡፡ ከዚያ እኔና ክሪስ ቶሎ ቶሎ የብርቱካን ጭማቂውን እንድንሰጣችው ነገረችን፡
እናታችን ከኬሪ ከንፈሮች ላይ ያነሳችውን የሙቀት መለኪያ ስትመለከት ደነገጠች: “አምላኬ! ወደ ዶክተር ልወስዳት ይገባል፡ ወደ ሆስፒታል!”
አያትየውን አየት አደረግኳት፤ ለዚህ ነገር ያላትን ምላሽ ማወቅ እየሞከርኩ ነው: አያትየው ለእንደዚህ አይነት ከቁጥጥር ውጪ መሆንና መርበትበት
ምንም ትዕግስት አልነበራትም “ሞኝ አትሁኚ ኮሪን: ልጆች ሁሉ ሲያማቸው ትኩሳት ይኖራቸዋል ምንም ማለት አይደለም አሁን ያንን ማወቅ አለብሽ ብርድ በቃ ብርድ ነው” አለች
ክሪስ ከሚያነበው መፅሀፍ ላይ ጭንቅላቱን ቀና አደረገ:፡ መንትዮቹ ኢንፍሉዌንዛ
ይዟቸው እንደሚሆን አምኗል: ያልገባው ቫይረሱን ከየት እንዳገኙት ነው::
አያትየው ቀጠለች “ዶክተሮች ብርድን ስለማዳን ምን ያውቃሉ? እኛ ብዙ እናውቃለን፡፡ ማድረግ የሚያስፈልጉ ሶስት ነገሮች አሉ᎓ አልጋ ውስጥ መቆየት፣
ብዙ ፈሳሽ መጠጣትና አስፕሪን መውሰድ ሌላ ምን ያስፈልጋል? እና እነዚያን ነገሮች ሁሉ አላደረግንም?” በክፉ አይን ተመለከተችኝና “እግሮችሽን
ማወዛወዝ አቁሚ አንቺ! እየረበሽኝ ነው:" አለች እንደገና አይኖቿንም፣
ቃላቶቿንም ወደ እናታችን መለሰች ለእናታችንም “ብርድ ለመያዝ ሶስት ቀን ህመሙ ሶስት ቀን ይቆያል በሶስት ቀን ውስጥም ይለቃል” አለች
“ኢንፍሉዌንዛ ቢሆንስ?” አለ ክሪስ አያትየው ጥያቄውን ችላ ብላ ጀርባዋን አዞረች በጣም አባታችንን ስለሚመስል መልኩን አትወደውም አያትየው እንደገመተችው መንትዮቹ ተሻላቸው፤ ግን በዘጠኝ ቀን ሳይሆን በአስራ ዘጠነኛው ቀን ነበር፡ ደህና የነበሩ ጊዜ ብዙ ጥያቄ የማይጠይቁት
ከታመሙ በኋላ ግን ጥያቄዎች መጠየቅ አበዙ።
የሚያነጫንጯቸውንና የሚያስጨንቋቸውን ነገሮች ሁሉ በቃላት መግለፅ ባለመቻላቸው የፈሩ አይኖቻቸው አስተያየት ልብ የሚያደማ ነበር።
“ለምንድነው ሁልጊዜ እዚህ ፎቅ ላይ የምንሆነው?”
“ምድር ቤቱ ጠፍቷል?"
“ፀሀዩዋ ወደተደበቀችበት ሄዶ ነው?"
“እናታችን ከአሁን ወዲያ አትወደንም?”
“ግድግዳዎቹ ለምንድነው የፈዘዙት?”

👍28🥰1
“ፈዘዋል እንዴ?” በምላሹ ጠየቅኩ
“ክሪስም የፈዘዘ ይመስላል”
ክሪስ ደክሞት ነው::”
ክሪስ ደክሞሀል?”
“ሁላችሁም ጥያቄዎች መጠየቅ አቁማችሁ ትንሽ እንድትተኙ እፈልጋለሁ! ካቲም ደክሟታል እኛም መተኛት እንፈልጋለን” አለ ክሪስ፡
ከዚያ ኮሪን ብድግ አደረገና ወደሚወወዘው ወንበር ወሰደው፡ ኬሪና እኔም ተhትለነው ወንበሩ ላይ ሲቀመጥ እኛም ጭኑ ላይ ተቀመጥን፡፡ ከሌሊቱ ዘጠኝ
ሰዓት ነው፡ ወደፊትና ወደ ኋላ እየተወዛወዝን ታሪክ እናወራላቸው ጀመር።በሌሎቹም ምሽቶች እስከ ሌለቱ አስር ሰዓት ድረስ ተረት እያነበብንላቸው ነበር። እናታቸውን ፈልገው ሲያለቅሱ ክሪስና እኔ እንደ እናትና አባት ሆነን
በቀስታ እሹሩሩ እንላቸዋለን፡፡ ወለሉ ድምፅ እስኪያሰማ ድረስ ወንበሩ ላይ አድርገን እናወዛውዛቸዋለን፡ በእርግጠኝነት ምድር ቤት ያለ የሆነ ሰው
ሊሰማን ይችላል፡
ወዲያው ከኮረብታው በኩል ንፋስ ሲነፍስ ሰማን፡፡ ነፋሱ ሀይለኛ ከመሆኑ የተነሳ በሁሉም መንገዶች ደህንነታችን የተጠበቀ እንዳልሆነ እንድናውቅ
እያደረግን ይመስላል
ከመፍራታችን የተነሳ ጮክ ብለን ማንበብና ብዙ መዘመር ቀጠልን፡፡ እኔና ክሪስ ድምፃችን ከመዘጋቱና ከድካም የተነሳ ራሳችንን በግማሽ ታመምን። ሁልጊዜ ማታ በጉልበቶቻችን ተንበርክከን እግዚአብሔር መንትዮቻችንን እንደገና ደህና እንዲያደርጋቸው በመጠየቅ እንፀልያለን፡፡ “እባክህ እግዚአብሔር በፊት እንደነበሩት አድርገህ መልሰህ ስጠን” እንለዋለን፡፡
ከዚያ ሳሉ የቀነሰበት፣ የአይኖቻቸው ሽፋሎች በእንቅልፍ የከበዱበትና በመጨረሻ በሰላማዊ እንቅልፍ የተዘጉበት ቀን መጣ፡ ወደ መንትዮቹ ተዘርግተው የነበሩት አጥንታማ የሞት እጆች በቀስታ ተሰበሰቡና መንትዮቹ
ወደ ጤናቸው ተመለሱ ሲሻላቸው ግን በፊት እንደነበሩት አይነት ጠንካራ አልሆኑም። ኮሪ በፊትም የሚያወራው ትንሽ ነበር አሁን ደግሞ የበለጠ ያነሰ ሆነ የራሷ የማያቋርጥ ጩኸት የሚያስደስታት ኬሪ አሁን እንደ ኮሪ ዝምተኛ ሆነች፡ ለረጅም
ጊዜ ፀጥታ እንዲኖር የተመኘሁ ቢሆንም አሁን ግን ድምፃቸው ናፈቀኝ፡፡
ምላሷን ሳየው ነጭ የሆነ ይመስላል እየፈራሁ ትራሱ ላይ አጠገብ ለአጠገብ ጋደም ያሉት ሁለቱ ትንንሽ ፊቶች ላይ አተኮርኩ። ለምንድነው እንዲያድጉና ትክክለኛ ዕድሜያቸው ላይ እንዲሆኑ የምፈልገው? ይህ ለረጅም ቀናት የቆየ በሽታ ትልልቅ ሰማያዊ አይኖቻቸው ስር ጥቋቁር ክብ በማድረግ ጤናማ ቀለማቸውን ሰረቀ ትኩሳቱና ማሳሉ ቅፅበታዊ የእድሜ ለውጥ አምጥቶ
ፀሀዩዋ ብትወጣ ባትወጣ ግድ የሌላቸው የደከሙ የአዛውንቶች አይነት እይታ ሰጣቸው አስፈሩኝ፡ አሳዛኝ ፊታቸው ወደ ሞት ህልም ወሰደኝ.....
✨ይቀጥላል✨

👍22❤17
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
ሕፃኗ በሕይወት መኖሯን ቀጥላለች " እንግዲህም ቢሆን የሚያሠጋት ነገር የሚኖር አይመስለኝም " የሚቀጥለው ሐሳብ ደሞ ሞግዚት መፈለግ ነው ሳቤላ አልጠነከረችም ትኩሳትና ድካም እየተጋገዙ ያጠቋታል " አንድ ቀን ለባብሳ ከምቹ ወንበር ላይ እንደ ተቀመጠች ሚስ ካርላይል ገባ።
«ባካባቢው ካሉት የቤት ሠራተኞች ሁሉ ለሞግዚትነት ትበቃለች የምትባል ታስቢያለሽ ?» አለቻት
« ኧረ እኔ እገሊት ለማለት አልችልም »
« እንዴ ዊልሰን አለች ሚስዝ ሔር ዘንድ የነበረች ከነሱ ጋር ሦስት ዓመት ካምስት ወር ተቀምጣለች አሁን ከባርባራ ጋር ስለ ተጣላች ነው የምትወጣው ትምጣና ታያት ? »
« የምትሆን ትመስላለች ? ጥሩ ሠራተኛ ናት ? »
« በሠራተኛነቷ እንኳን አትከፋም " ሥራዋን አክባሪ ቁም ነገረኛ ናት "
ነገር ግን ከዚሀ እስከ ሊምበራ ' የሚደርስ ምላስ አላት»
« ምላሷ ሕፃኗን አይጐዳትም ግን በደንገጡርነት ስለኖረች የልጅ አያያዝ ልምድ ያጥራት እንዶሆነ ነው እንጂ " »
« ልምዱስ አላት ከሚስዝ ሔር ቤት ሳትገባ ስኳየር ስፒነር ቤት ዋና ሞግዚት ሆና አምስት ዓመት ተቀምጣ ነበር " »
« እንግዲያው ትምጣና ልያት »
« በይ እልክልሻለው ግን ካነጋገርሻት በኋላ ለመልሱ ቀጠሮ ስጫት።
እኔ ከሚስዝ ሔር ዘንድ ሔጀ ስለሷ አጥንቸ ከመጣሁ በኋላ መልሱን ትነግሪያታለሽ”»
አባባሏ ትክክል ነበር ። ሳቤላም ተስማማችና ሠራተኛይቱ ስትመጣ ተነገረላት " የደስ ደስ ያላት ዐይነ ጥቋቁር ረጅም ሴት ገባች ሳቤላ ከሚስዝ ሔር ቤት
ለምን እንደ ወጣች ጠየቀቻት "
« የባርባራን ጠባይ አልችለው ብዬ ነው የወጣሁት ... እመቤቴ " በተለይማ ከዓመት ወዲህ ያመጣችው ዐመል አንዱም ነገር አያስደስታትም " ከዚህ በላይም
ዕብሪቷ ልክ እንዳባቷ ነው " ብዙ ጊዜ ለመውጣት እያሰብኩ መልሸ ስተወው ኑሬ ትናንት ደግሞ ተጣላን " ዛሬ ጠዋት ጨርሸ ወጣሁ " ስለዚህ እርስዎ ሊቀጥሩኝ ከፈቀዱ በደስታ እቀበላለሁ » አለች ዊልሰን "
« ግን እንደ ተረዳሁት አንቺ ከሚስዝ ሔር ቤት የገረዶች አለቃ ነበርሽ እኛ ዘንድ ደሞ አለቃይቱ ጆይስ ናት ምናልባት እኔ ወጣ ብል ወይም ብታመም አዛዧ እሷ ስለሆነች አንቺን የከፋሽ እንደሆነስ ? »
«እኔ ለዚህ ግድ የለኝም ጆይስን ሁላችንም እንወዳታለን ሳቤላ ጥቂት ከጠያየቀቻት በኋላ ለመልሱ ወደ ማታ እንድትመጣ ነግራ ሰደደቻት ኮርነሊያ ወደ ዐጸዱ ሔዳ ስለ ዊልሰን ጠባይ ሚስዝ ሔርን አንድ ባንድ ጠየቀቻት ሚስዝ ሔርም
ዊልሰን በባርባራ አመካኝታ ቸኰላ ከመልቀቋ በቀር ይህ ነው የምትለው ጥፋት እንደሌላት በግልጽ ነግረቻት " ስለዚህ ዊልሰን ተቀጠረች " አዲሱን ሥራዋን በበነጋው ጧት መጥታ እንድትጀምር ተደረገ።
ሳቤላ ከመኝታ ቤቷ ውስጥ የእንቅልፍ ሰመመን ተጫጭኗት ሶፋ ላይ ተጋድማለች።
አዲሲቱ ሞግዚት ጧቱን መጥታ ሥራ ጀመረች በዚሁ ዕለት ከሰዓት በኋላ ሳቤላ ከመኝታ ቤቷ ውስጥ የእንቅልፍ ሰመመን ተጫጭኗት ሶፋ ላይ ተጋድማለች
የዚህ ዐይነቱ መስለምለም እንዴት እንደሚያደርግ በትክክል የሚያውቁት አንደ ሳቤላ በሰውነት ድካምና ትኩሳት የሚሠቃዩት ብቻ ናቸው ። ከሷ መኝታ ቤት ቀጥሎ ካለው ክፍል ዊልሰን የተኛ ሕፃን ከጉልበቷ ላይ ይዛ ጆይስ ልብስ ስትሰፋ ተቀምጠው ያወጋሉ " በሩ ጎርበብ ብሏል " ሳቤላ በእንቅልፍና በንቃት መካከል ሆኖ ስትስለመለም ስሟ ሲጠራ ድንገት ትሰማና ትነቃለች።
« እንዴት ተደይነዋል ! በጣም የታመሙ ይመስላሉ » አለች ዊልሰን "
« ማን ? » አለቻት ጆይስ "
« እሜቴ » እስከ መቼም በጐ የሚሆኑ አይመስሉም»
« አሁን እኮ በጣም እየተሻላቸው ነው " ባለፈው ሳምንት አይተሻቸው ቢሆን ኖሮና ካሁኑ ሁኔታቸው ጋር ብታነጻጽሪው ገመምተኛ ይመስላሉ አትይም ነበር"
« አሁን አይበለውና እሳቸው አንድ ነገር ቢሆኑ የአንድ ሰው ተስፋ አያንሰራራም ብለሽ ነው ? »
« ወጊጅ ወድያ !ሌላ ወሬ አምጨ»
« አንቺ ያልሺውን ብትይ አይቀርም» ቀጠለች ዊልሰን ።
« ለሁለተኛ ጊዜ እንዲያመልጧት አትፈልግም " በአንድ ጊዜ ነው የምትነጥቃቸው እሷ እንደሆነች ዛሬም ልክ እንደ ድሮዋ ስቅቅ ብላ ነው የምትወዳቸው»
« ይህ ሁሉ የዌስት ሊን ሰው ሥራ ሲፈታ የሚያናፍሰው ወሬ ነው ሚስተር ካርላይል እንደሆኑ ስለሷ ቅንጣት ደንታ የላቸውም»
« ጆይስ አንቺ አታውቂም እኔ ያየሁት ነገር አለኝ " ሲስሟት በዐይኔ አይቻለሁ»
« መንጋ ወሬኛ ! » አለች ጆይስ " « ይኸ እሳቸው እሷን ለማግባት መፈለ?ቸውን አያስረዳም»
« እኔ ያስረዳል አልወጣኝም " ብቻ አሁን የምታስረውን ባለሙዳይ ያንገት ሐብል የሰጧት እሳቸው ናቸው»
« ማናት የምታስረው ? እኔ ስለዚህ ነገር መስማት አልፈልግልም » አለች
« ሚስ ባርባራ እንጂ ደግሞ ማን ! ካንገቷ አውልቃው አታውቅም እኔስ ስትተኛም የምታስቀምጠው አይመስለኝም »
« እሷ አትረባም» አለች ጆይስ "
« እመቤት ሳቤላን ለማግባት ከዌስት ሊን ማለዳ ሊነሡ ማታውን ሚስ ባርባራ
ከሚስ ካርላይል ቤት አምሽታ ስለነበር ሚስተር ካርይል ወደ ቤቷ ይዘዋት መጡ"ገና በመንገድ እያሉ እንዴት እንደሆነ አላውቅም ጃንጥላዋን ሰበሩት ከዋናው
በር ሲዶርሱ የፍቅር ትርዒት ታየ»
« አንቺ ሦስተኛ ሆነሽ አብረሽ ከቦታው ነበሮሽ ? »
« አዎን ሳላስበው እዚያው ተገኘሁ " ያ ገብጋባ አሮጌ ዳኛ አንድም ሰው አስከትለን እንድንገባ አይፈቅድም ካበባ ጐመን የረዘመ አትክልት በሌለው በገላጣው
የማድ ቤት አታክልት ቦታ ውስጥ ማንንም በምስጢር ማነጋገር አይቻልም " ስለዚህ ጠያቂ ወዳጅ ሲመጣ የነበረው ዕድል ወደ ዐጸዱ ገባ ብሎ ለግማሽ ሰዓት ተጫውቶ መመለስ ነው " ያን ዕለት ማታ የምጠብቀው ሰው ስለነበረኝ ወደ ዐጸዱ ወጣሁ።
ወዲያው ሚስተር ካርላይል ሚስ ባርባራ መጡ " እንዲገቡ ብጠይቃቸውም አልፈለጉም ስለዚህ ሁለቱም እዛው ቆሙ ። ስለ መታሰቢያ መያዣው ያንገት
ሙዳይ ጸጉሩን ለማስታወሻ ስለ መስጠታቸው አንዳንድ ነገር ይነጋገሩ ነበር እንዳይሰሙኝ ስለፈራሁ hቆምኩበት አልተነቃነቅሁም የጦፈ የፍቅር ጭውውት ቀጠለ ጠቅላላ አነጋሯ ሁሉ ልክ እንደ ሚስት ነበር ።
« እንቺ ወሬኛ ሊያገቡ ከመሔዳቸው በፊት ማታውን አላልሺም ? »
« እና ቢሆንስ ? እሷ መቸም ዕብድ ሆነች ተሰናብተዋት ከሔዱ በኋላ እጆቿን ወደ ሰማይ ዘረጋች አግብተው እስኪያዩዋት ድረስ ምን ያህል እንደምትወዳቸው ሊገባቸው እንደማይችል ብቻዋን ታወራ ጀመር » አየሽ ጆይስ « በሁለቱ መኻል ብዙ የፍቅር ገድል መፈጸሙን አትጠራጠሪ በመጨረሻ ሚስተር ካርላይል እሜቴን ሲያገኙ ጊዜ በቁንጅናቸውና በትውልዳቸው ማረኳቸው የፊቱ ፍቅር ተረሳ ወንዶች ሲባሉ በተለይ እንደ ሚስተር ካርላይል በመልካቸው የሚመኩ ከሆነ ወረተኝነት ባሕሪያቸው ነው ። »
« ሚስተር ካርይል ወረተኛ አይደሉም ... አንቺ ! »
« አሁንም ሌላ ልንገርሽ » አለችና ጆይስ ማብራራቷን በመቀጠል ሚስተር ካርላይል ማግባቱን ለእኅቱ በጻፌላት ጊዜ ' ኮርነሊያ ለባርባራ ስትነግራት ከመኝታ
ቤቷ ገብታ ያለቀሰችውን ሁሎ እያሳመረችና እየኳኳለች ነገረቻት
« በምንም ለማይወዳት ሰው ይሀን ያህል መጨነቋ ምን ያህል ደንቆሮ ብትሆን ነው ? » አለች ጆይስ

👍21👎1🥰1
« ነገርኩሽ ኮ ... ጆይስ " የማይወዳት መሆናቸውን ማወቅ አትችይም "ዝም ብለሽ እንዶ ዳኛው ሔር ድርቅ አትበይ " በሚስተር ካርላይል ጋብቻ
መልካም ምኞታቸውን ለመግለጽ አባቷ እናቷና እሷ ወደ ኢስት ሊን መጥተው ነበር በትክክል ካስታወስሽ ወላጆቿ ቀድመው ሲሔዱ እሷ ኢስት ሊን እየተጫወተች ለማምሸት ወደኋላ ቀረች "
« አስታውሳለሁ »
« ጃ ስፐር ወጥቶ ስለነበር እኔ እንድቀበላት ተላክሁ ከአጥሩ አጠገብ ስደርስ ምን አየሁ መሰለሽ ? »
ጆይስ ቀና ብላ አየቻት « እንጃ ምናልባት እባብ አይተሽ እንደሆነ ? »
« ሚስ ባርባራንና ሚስተር ካርላይልን አገኘኋቸው " እኔ ከመድረሴ በፊት ምን ያደርጉ እንደነበር እነሱ ይወቁ " እሷ ከአጥሩ ተደግፋ እየተንሰቀሰቀች ታለቅስ ነበር " ሁኔታው ከቀድሞ የተነገራት ነገር እንደ ነበር ለዚያ የወቀሳ መልስ የምትመልስላቸው ይመስል ነበር » እሳቸውም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ወንድምና እህት ብቻ መሆን እንደሚችሉ ሲነግሯት ሰማኋቸው " እኔም ያዩኝ እንደሆነ ብዬ ፈራሁና ተናገርኩ " ሚስ ባርባራ እንዲመለሱ ነግሬአቸው ነበር " እሳቸው ግን ክንዳቸውን ዘርግተው ክንዷን አቅፈው በጓሮ በኩል እስከ በሩ አብረዋት ወጡ " እኔ በሩን ለመክፈት አልፌያቸው ስሔድ ሁለት እጆቿን ይዘው ራሳቸውን ወደሷ አጐንብሰው አየኋቸው " በመኻላቸው ያለውን ነገር አናውቅም»
« እሷ ግን አሁንም ትወዳቸው እንደሆነ ሞኝ ናት » አለች ጆይስ ቆጣ ብላ "
« በርግጥ ሞኝነት ነው ! ግን ትወዳቸዋለች ሁልጊዜ እሳቸው በነሱ በር አጠገብ በሚያልፉበት ሰዓት እየጠበቀች እንዳያዩዋት ትደበቅና ታያቸዋለች ጆይስ በዚህ ባለፈው ዓመት ባርባራ ጠባይዋ ከዱሮው ተለወጠ " ቁጣ ቁጣ ይላታል ። የዚህ ሁሉ ምክንያቱ ግን በወይዘሮ ሳቤላ ስለምትቀና ብቻ ነው አሁንም ሚስተር ካርላይል እሜቴን ቸለል ቢሏቸው. »
« ዊልሰን » አለቻት ጆይስ ነገሯን አቋርጣ « እባክሽን የምትይውን ዕወቂ። »
« እንዴ አሁን እኔ ምን አልኩ ? ሐቁን ነው ኮ የተናገርኩ " ወንዶች በተለይም ባሎች ከፍቅረኞች የበለጡ ወረተኞች ናቸው " አሁን እሜቴ አንድ ነገር ቢያገኛቸው ሚስ ባርባራ በእግራቸው ጥልቅ ማለቷ የማይቀር ነው»
« እሳቸው ምንም ነገር አይደርስባቸውም» አለቻት ጆይስ
« ለዚች በጭኔ ለታቀፍኳት ምንም ለማታውቅ ሕፃን ሲል ምን ጊዜም እንዳፍሽ ያድርግላቸው " ከክፉ ይሰውራቸው » አለችና ዊልሰን ነገሯን በመቀጠል
« የመጀመሪያይቱ ሚስት ከተጠላች ልጆቿም እንደማይወደዱ የተረጋገጠ ነው
ስለዚህ ሚስ ባርባራ ከገባች ጥሩ የእንጀራ እናት አትሆንም " እንዲያውም ሚስተር ካርላይል እንዲጠሏቸው ታደርጋለች »
« ስሚ ዊልሰን ... ኢስት ሊን ሁነሽ የዚህ ዐይነት ወሬሺን የማታቆሚ ከሆነ ለዚህ ቤት እንደማትስማሚ ለእሜቴ እነግራለሁ»
« አንቺ ደግሞ ጥብቅነቱን ታበዥዋለሽ . . . ጆይስ » አለች ዊልሰን እየሣቀች"
« እኔ ግን ያለውን ነር ተናግሬአለሁ እንግዲህ በቃኝ " ደሞም ይኸንኑ ጉዳይ ለቤትኣሽከሩ ሁሉ የምለፈልፈው አይምሰልሽ »
ሳቤላ የዊልስንን ንግግር ቃል በቃል ልቅም አድርጋ ሰማችው " ጥሩ ጤነኛ ብትሆን ኖሮ ከቁም ነገር አትጽፈውም ነበር " አሁን ግን ሰውነቷ ደከመ የማያቋርጥ ትኩሳት እንደ እሳት ይፈጃታል ከዚህ የተነሣ ዐልፎ ዐልፎ ልቧን እየሳተች ትቃዣለች ይህ አሳዛኝ ሁኔታዋ የሚስተር ካርላይልን ይዞታ እንድትጠራጠር
የተወራውን ነገር አንድታተነትን አስገደዳት " ሚስተር ካርይል ያገባት እውነተኛ ፍቅር ኖሮት ሳይሆን የዝና ፍላጐቱን ለማርካት እንደሆነ አድርጋ አሰበችው
ልቡ ከባርባራ እንጂ ከሷ ጋር እንደሆነ ለማመን አልቻለችም "
በገመምተኛነቷ ላይ ይህን ብስጭት አከለችበትና ይበልጡኑ ደካክማ ተኛች "አእምሮዋን በቅናት በትኰሳት በፍቅር ነገር በጠበጠችው " ሚስተር ካርላይል ሲገባ የራት ሰዓት ተቃርቦ ነበር " ጉንጮቿ ዐመድ ለብሰው በትኩሳት ሲቃጠሉ ዐይኖቿ ተበርዘው ቀልተው ሲያያት ደነገጠ "
« ሳቤላ . . .ዛሬ ደግሞ ብሶብሻል ! » አለ ወደሷ እየተንደረዶረ ሔዶና " ከተቀመጠችበት ሶፋ እንደ መነሣት ብላ እየተርበተበተች ግጥም አድርጋ ያዘችው "
« አርኪባልድ !...አርኪባልድ ! . . . እንዳታግባት - ካገባሃት ከመቃብር
ሁኘም ዕረፍት አላገኝም »
ሚስተር ካርላይል ባነጋገሯ ተገረመና ግራ ተጋባ " ነገሩ ከሰውነት መድከም የመጣና ቶሎ ብሎ እልፍ የሚል ቅዠት መስሎት ሊያረጋጋት ሞከረ " ነገር ግን
ሁኔታዋ በቀላሉ የሚመለስ አልመሰለም " ዕንባዋን እንደጐርፍ እያወረደች ነገሯን ቀጠለች "
“ልጄን ታንገላታብኛለች " ያንተን ፍቅር ለራሷ ወስዳ ለሕፃኗ እንዳታስብ እኔንም እንዳታስታውስ ታደርግሃለች እንደማታገባት ቃል ግባልኝ "
“ አግባብ ላለው ለማንኛውም ነገር ቃል እገባለሁ ” አላት በአነጋገሯ እየተገረመ ።
አሁን የምትዪው ነገር ግን አልገባኝም " እኔ ማንንም የማግባበት ምክንያት የለኝም : አግብቻለሁ ! ሚስቴ አንቺ ነሽ ።
“ የሞትኩ እንዴሆነሳ ? እሞት ይሆናል " ብዙዎቹ ትሞታለች አትተርፍም ይሉኛል " እሷ ያንተ ሚስት መሆኗን ሳስበው ሊገድለኝ የሚችል ሕመም ይሰማኛል "
እሷ በኔ እግር እንዳትግባ "
“የምትያት ሴትዮ ማንም ትሁን ማን ምንም ቢሆን ባንቺ እግር አትገባም ምን ስታልሚ ነበር ? ከጭንቅላትሽ ገብታ እንደዚህ የበጠበጠችሽ ማናት ? ”
“ አርኪባልድ እንዴት ትጠይቀኛለህ ? እኔን ከማግባትህ በፊት የምትወዳት አልነበረችህም ? ምናልባትም እስካሁን ትወዳት ይሆናል ”
“ ስለማን ነው የምትናሪው ... ሳቤላ? አላት ፊቱን ኮስተር አድርጎ
“ ስለ ባርባራ ሔር ”
ሚስተር ካርላይል ግንባሩን ቋጠረ ተበሳጨ ብሽቅ አለ ደግፋት ተቀምጦበት ከነበረው ሶፋ ብድግ አለና ፈንጠር ብሎ ከፊት ለፊቷ ቆመ » ሳቤላ .. በኔና በባርባራ ሔር እንደዚህ ያለ ሐሳብ መኖሩን ኧንዴት አወቅሺው ሊገባኝ አልቻለም እኔ ባርባራ ሔርን በፊትም ሆነ አሁን ለፍቅር ለጋብቻ አስቢያት አላውቅም " ይህሐሳብ እንዴት አድርጎ ከጭንቅላትሽ እንደገባ እንድትነግሪኝ እፈልጋለሁ "
"እሷ ግን ትወድ ነበር "
በዚህ ጊዜ ትንሽ ወላወለ " እንደምትወደው ያውቃል " ይኸንንም እንዴት ሊያውቀው እንደቻለ ያስታውሳል " ነገር ግን ይኸን ሁኔታ ለሚስቱም ሊያምንላት አልቻለም “ እኔ የምትወደኝ መሆኗን አላውቅም " ያንቺ በባርባራ መቅናት ግን በእኅቴ በኮርነሊያ ከመቅናት ለይቸ አላየውም "
ሳቤላ በረጅሙ ተነፈሰች የእፎይታ ትንፋሽ " ትንፋሿም ተስተካከለ ተረጋጋ በአስተማማኝ ሁኔታ አረጋገጠች " ሚስተር ካርላይል ወደሷ ጐንበስ ብሎ በቅሬታና በአዘኔታ አነጋገር “ እኔ ያለፈው ዓመት በከንቱ እንጠጠፋ አድርጌ አላሰብኩትም ነበር ስለ እውነተኛ የልብ ፍቅር አንድ ወንድ ሊሰጠው ከሚገባው ማረጋገጫ ምን አጐደልኩብሽ ?” አላት " ቀና ብላ ስታየው እንባዋ ቅርር አለ " የጸጸት ለቅሶ ተናነቃት " እጁን በሁለት እጆቿ መኻል ያዘችና'' አትቆጣኝ አርኪባልድ እኔ ላንተ ብዙ ባልሳሳና ባልጨነቅ ኖሮ ይህ ሁሉ መጠራጠርና የመንፈስ መረበሽ አይመጣብኝም ነበር "

👍19
ሣቅ አለና አሁንም ወደሷ ዝቅ ብሎ''ይህን ነገር ምን ሰይጣን ከጭንቅላትሽ ከተተው ? አላት ።
የሰማችውን ሁሉ ዝክዝክ አድርጋ ልትነግረው አሰበች ! ከዓመት በፊት ሱዛንና ጆይስ የተናገሩዋቸው ጥቂት ቃላትና አሁን የሰማችውን የጆይስን ንግግር ሁሉ ልትገልጽለት ከቆረጠች በኋላ የገረዶች ወሬ ማዳመጡ ውርደት ነው ከቁም ነገር መቁጠሩም የዋህነት ነው” ብላ እንዶገና አሰበችና ተወችው "
አንቺ በኔ የተዛባ አስተሳሰብ እንዲኖርሽ የሚያደርግ ሰው አለ ? አላት
አርኪባልድ .... ማንም የለም " እንዲህ ያለውን ወሬ ማን ደፍሮ ይነግረኛል
እንግዲያ ተኝተሽ ያየሺው ሕልም ስትነቂም አልለቅሽ አለ ?
በርግጥ ከቀትር በኋላ ስተኛ በተለይ በሚያተኩሰኝ ጊዜ ብዙ እንግዳ ሕልሞችን አያለሁ » አንዳንድ ጊዜ ቅዠቱ ልቤን ያጠፋወና እውነቱንና ሕልሙን መለየት ይሳነኛል "
መልሱ የማምለጫ መሆኑ ቢገባውም አጥብቆ አልጠየቃትም "
በይ እንግዲህ ቢቻልሽ እንደዚህ ያለ ሕልም ይቅርብሽ " ላንቺ ደግ አይደለም " ለኔም ያን ያህል ስወድሽና ሳስብልሽ አለስሜ ስም የሚሰጥ ነው እኔ ከአንቺ ጋር በፍቅር በሕግ ማሰሪያዎች ተሳስሬያለሁ " ስለዚህ ልብ በይ ሳቤላ ባርባራ ሔር ይህን አልፋ በሁለታችን መኻል ለመግባት ኃይል የላትም በዚህ ዓለም ቅናትን የሚያህል አሳሳች የማይታመንና ኃይለኛ ነገር አልነበረም አይኖርምም ሚስተር ካርላይል ነገሩ በቅዠት የመጣ እንደ መሰለው ሁሉ አሁንም ይህ ትዝታ እንዶ ቅዠቱ የሚጠፋና የሚረሳ መሰለው ።
ነገር ግን አይደለም ። የባሏን ቃል ወዲያውኑ አመነችበት » ጥርጣሬ ከልቧ በማስገባቷም አፈረችበት " ከዚያ በኋም ይህ ደስ የማይለው ሥጋት እንደገና እንዳያንሰራራባትና እንዳያብታት መጨነቅ ጀመረች በአጉል አጋጣሚ የሰማችው
የዊልሰን ወሬ የሚስተር ካርላይልን ማስተባበያ አሸንፎ በማለፍ ከዐውደ ሕሊናዋ
ገብቶ ይወቃት ጀመረ "።
ሼክስፒር ቅናትን ቢጫና አረንጓዴ ይለዋል እኔ ግን ጥቁርና ነጭ ተብሎ ሊጠራ የሚችል ይመስለኛል ምክንያቱም ነጩን ጥቁር ጥቁሩን ነጭ አድርጎ ያሳያልና " ሊታመኑ የማይችሉትን ግምቶች የእውነተኝነትን መልክ ያለብሳቸዋል " ፍጹም ሊሆኑ የማይችሉ ነገሮችን ተጨባጭ እውነታዎች አስመስሎ ያቀርባቸዋል " ሳቤላ ለባሏ ሌላ ምላሽ አልሳጠችም የቅናቷን ነገር ስታስበው ባሏን ከምን ጊዜም በበለጠ እንድትቀርበውና ለፍቅሩም እንድትሳሳ አድርጓታል ባርባራ ሔር ግን ከልቧ ልትወጣለት አልቻለችም....
💫ይቀጥላል💫

👍17❤6
ሁሌም በየዘመን ፣ ጎልያድ ነን ባዮች በጉልበት ሲነሱ ፣ አይጠፉም ልባሞች
እግዜርን ተማምነው ፣ ጠጠር የሚያነሱ።
እግዜርን ተማምነው ፣ ጠጠር የሚያነሱ።
❤64👍54🥰7👏3
ጊዜን በቃሉ ያፀና ፣ ሳያጎል የሰራ
ባለጊዜ አምላክ ነው ፣ ታድያ ጊዜው የኔነው ባይ የሰው ልጅ ምን ቤት ነው።

🥰57👍33😢5🎉5🤔4👏3
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
...ምላሷን ሳየው ነጭ የሆነ ይመስላል እየፈራሁ ትራሱ ላይ አጠገብ ለአጠገብ ጋደም ያሉት ሁለቱ ትንንሽ ፊቶች ላይ አተኮርኩ። ለምንድነው እንዲያድጉና ትክክለኛ ዕድሜያቸው ላይ እንዲሆኑ የምፈልገው? ይህ ለረጅም ቀናት የቆየ በሽታ ትልልቅ ሰማያዊ አይኖቻቸው ስር ጥቋቁር ክብ በማድረግ ጤናማ ቀለማቸውን ሰረቀ ትኩሳቱና ማሳሉ ቅፅበታዊ የእድሜ ለውጥ አምጥቶ
ፀሀዩዋ ብትወጣ ባትወጣ ግድ የሌላቸው የደከሙ የአዛውንቶች አይነት እይታ ሰጣቸው አስፈሩኝ፡ አሳዛኝ ፊታቸው ወደ ሞት ህልም ወሰደኝ
በዚህ ሁሉ ንፋሱ መንፈሱን ቀጥሏል።
በመጨረሻ አልጋቸውን ለቀው በዝግታ መራመድ ቢጀምሩም፣ በአንድ ወቅት ጠንካራ፣ ለመዝለልና ለመሮጥ ይችሉ የነበሩ እግሮቻቸው አሁን ደካማ;
እንደ ሳር የቀጠኑ ሆነዋል አሁን የሚችሉት በመብረር ፋንታ መዳህ፣ በመሳቅ ፋንታ ፈገግ ማለት ብቻ ሆኗል።
በድካም አልጋው ላይ በፊቴ ተደፍቼ የልጅነታቸውን ውበት ለመመለስ እኔና ክሪስ ምን ማድረግ እንችላለን? እያልኩ ደጋግሜ እያሰብኩ ነበር
የእነሱን ጤና መመለስ ለማገዝ ሲል ለእኛ ጤና የሰጠን ቢሆንም፣ እኔም ሆንኩ እሱ ማድረግ የምችለው ነገር አልነበረም።
እኔና ክሪስ በመንትዮቹ መካከል ያለውን ጤናማ ያልሆነ ልዩነት ለማስተካከል እየታመምን ባለንበት ወቅት “ቫይታሚኖች!” ስትል እናታችን ጮኸች።
“የሚያስፈልቸው ቫይታሚኖች ናቸው፡ እናንተም ያስፈልጋችኋል: ከአሁን ጀምሮ እያንዳንዳችሁ በየቀኑ የቫይታሚን ኪኒኖች መውሰድ አለባችሁ” ይህንን ስትነግረን እንኳን ቀጭኑና ረጅሙ እጇ በሚስብ ሁኔታ የተያዘውን
የሚያንፀባርቅ ፀጉሯን እየነካ ነበር።
አቅራቢያዬ ባገኘሁት አልጋ ላይ አረፍ እያልኩና ችግሩን ለማየት ፈቃደኛ ያልሆነችው እናት ላይ እያፈጠጥኩ “ንፁህ አየርና የፀሀይ ብርሃንም በኪኒን
መልክ ይመጣሉ?” ስል ጠየቅኳት “እያንዳንዳችን በየቀኑ የቫይታሚን ኪኒኖች መዋጣችን አብዛኛውን ጊዜያችንን ውጪ በምናሳልፍባቸው ቀናትና ትክክለኛ ህይወት እንመራ በነበረበት ጊዜ የነበረንን መልካም ጤንነት ይሰጠናል?”እናታችን በንቀት እይታ ገረፍ አድርጋኝ “ካቲ፣ ለምንድነው ያለማቋረጥ
ነገሮችን ሁሉ ከባድ የምታደርጊብኝ? የቻልኩትን እያደረግኩ ነው እውነቴን
ነው እና አዎ እውነቱን ከፈለግሽ በምትውጧቸው ቫይታሚኖች ውስጥ የውጪው አየር የሚሰጣችሁን መልካም ጤንነት ይመለስላችኋል፡ ለዚያ
ነው ብዙ ቫይታሚኖች የሚሰሩት:" አለች:
ግዴለሽነቷ ልቤ ውስጥ ተጨማሪ ህመም ፈጠረብኝ አይኖቼን ወደ ክሪስ ወረወርኩ፤ ምንም ሳይናገር አንገቱን አቀርቅሮ ሁሉንም ያዳምጣል
“እስረኝነታችን መቼ ነው የሚያበቃው እማዬ?”
በአጭር ጊዜ ውስጥ ካቲ፣ አጭር ጊዜ! ብቻ እመኚኝ
“ሌላ ወር?”
“ሊሆን ይችላል‥”
“እንደምንም ተደብቀሽ መንትዮቹን ለጥቂት ጊዜ በመኪናሽ ወደ ውጪ
ልታወጫቸው ማመቻቸት ትችያለሽ? ሰራተኞቹ በማያዩበት ጊዜ ልታደርጊው ትችያለሽ፡ ትልቅ ልዩነት ይፈጥራል ብዬ አስባለሁ። እኔና ክሪስ መሄድ የለብንም:”
ታላቅ ወንድሜ እዚህ ሴራ ውስጥ ይኑርበት አይኑርበት ለማየት ተሽከርክራ ተመለከተችው፤ ነገር ግን መገረሙ ፊቱ ላይ በግልፅ ይነበብ ነበር፡ “አይሆንም፣
በፍፁም አይቻልም! እንደዚያ አይነት አደጋ አልጋፈጥም! እዚህ ቤት ውስጥ ስምንት ሰራተኞች አሉ ማደሪያቸው ደግሞ ከዋናው ቤት ቀጥሎ ነው:ሁልጊዜም የሆነ ሰው በመስኮት ይመለከታል እና መኪናውን ሳስነሳ ሊሰሙኝ
ይችላሉ: ከዚያ በየትኛው አቅጣጫ እንደምሄድ ያጣራሉ።" አለች።
ድምጼ ቀዘቀዘ፡ “እባክሽ ትኩስ ፍራፍሬ ማምጣትስ ትችይ ይሆን? እባክሽ? በተለይ ሙዝ፡ መንትዮቹ ሙዝ እንደሚወዱ ታውቂያለሽ እዚህ ከመጣን ጀምሮ በልተው አያውቁም::”
“ሙዝ ነገ አመጣላችኋለሁ አያታችሁ እንደሆነ ሙዝ አይወድም:"
“hሱ ጋር ምን ያገናኘዋል?”
“በዚያ ምክንያት ነው ሙዝ የማይገዛው፡”
“ወደዚያ ትምህርት ቤት በሳምንቱ ቀናት ሁሉ ትሄጃለሽ፡፡ ቆም በይና ሙዝ፣ተጨማሪ የለውዝ ቅቤና ዘቢብ ግዢ አንዳንዴ እንኳን ለምንድነው የካርቶን
ፈንዲሻ የማያገኙት? በእርግጠኝነት ጥርሳቸው እንዳይበላሽ አይደለም!”
ደስ በማይል ሁኔታ ጭንቅላቷን ነቀነቀችና ተስማማች: “ለራስሽስ ምን ትፈልጊያለሽ?” ስትል ጠየቀችኝ፡
“ነፃነት! መውጣት እንዲፈቀድልኝ እፈልጋለሁ፡ በተቆለፈ ክፍል ውስጥ መኖር ደክሞኛል። መንትዮቹም እንዲወጡ እፈልጋለሁ። ክሪስ እንዲወጣ
እፈልጋለሁ ቤት ተከራይተሽም ይሁን ሰርተሸ ወይም ሰርቀሽ ብቻ ከዚህ ቤት እንድታስወጪኝ እፈልጋለሁ!
“ካቲ…” ትለምነኝ ጀመር። “የምችለውን ሁሉ እያደረግኩ ነው: በመጣሁ ቁጥር ስጦታ አላመጣሁላችሁም? ከሙዝ ሌላ ምንድነው የጎደላችሁ? ንገሪኝ
“እዚህ የምንቆየው ለጥቂት ጊዜ ነው ብለሽን ነበር አሁን ወራት አለፉ::
እንደሚፀልይ ሰው እጆቿን አነሳችና “አባቴን እንድገድለው ትጠብቂያለሽ? አለችኝ፡ በዝምታ ጭንቅላቴን ነቀነቅሁ
የእሱ አማልክት ወጥታ በሩ እንደተዘጋ ክሪስ “ለምን አትተያትም?!” ሲል ጮኸ፡ “ለሁላችንም የምትችለውን እያደረገች ነው፡ አትጨቅጭቂያት
ልክ እንደማታምኛት ሁሉ የማያልቁ ጥያቄዎችሽን እየደረደርሽና ከጀርባዋ
አልወርድ እያልሻት ልታየን መምጣቷ ራሱ የሚገርም ነው: ምን ያህል እንደተሰቃየች እንዴት ታውቂያለሽ? አራቱ ልጆቿ አንድ ክፍል ውስጥ ተቆልፎባቸውና ጣራ ስር ያለ ክፍል ውስጥ ብቻ እንዲጫወቱ መደረጋቸውን
እያወቀች ደስተኛ ነች ብለሽ ታምኛለሽ?”
እንደ እናታችን ስላለ ሰው መናገር ከባድ ነው፡ ምን እንደምታስብ፣ ምን እንደሚሰማት ማወቅ አይቻልም: አንዳንድ ጊዜ ብቻ የደከማት ከመምሰሏ በስተቀር ስትታይ ሁልጊዜ ረጋ ያለች ናት ልብሶቿ አዲስና ውድ ሲሆኑ አልፎ አልፎ አንድን ልብስ ሁለት ጊዜ ለብሳ እናያታለን፡ ለእኛም
አዳዲስና ውድ ልብሶች ታመጣልናለች: ግን የምንለብሰው ልብስ ልዩነት አልነበረውም: ከአያታችን በስተቀር ማንም ስለማያየን ፊቷ ላይ የደስታ
ፈገግታ የሚያመጣላትን የነተቡ ቡትቶዎችንም መልበስ እንችላለን
ሲዘንብና በረዶ ሲጥል ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል አንሄድም: ዝናብ በሌለ ቀን እንኳን በሀይል እያፏጨ በአሮጌው ቤት ስንጥቅ በኩል የሚገባ ከባድ
ንፋስ አለ።
አንድ ሌሊት ኮሪ ከእንቅልፉ ባኖ ጠራኝና ካቲ ንፋሱን አባሪው" አለ
አልጋዬንና ኬሪን ትቼ ከኮሪ አጠገብ ብርድ ልብስ ውስጥ ገባሁና ጥብቅ አድርጌ አቀፍኩት ምስኪን ቀጫጫ፣ የሚነፍሰው ንፋስ ይዞት የሚሄድ ነው የሚመስለው፡ በእናቱ በጣም መወደድን ቢፈልግም ያለሁት እኔ
ብቻ ነኝ፡ ፊቴን ዝቅ አድርጌ ንፁህና ቆንጆ ሽታ ያለውን ፀጉሩን ሳምኩት
ልጅ ሆኖ አሻንጉሊቶቼን በእውነተኛ ልጆች የተካሁ ጊዜ እንዳደረግኩት እቅፍ አደረግኩት፡ “ንፋሱን ማባረር አልችልም ኮሪ ያንን ማድረግ የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው''
“ታዲያ ለእግዚአብሔር ንፋሱን እንዳልወደድሽው አትነግሪውም? አለ።
“ለእግዚአብሔር ንፋሱ የመጣው ሊወስደኝ ፈልጎ እንደሆነ ንገሪው::”
እንደገና አስጠጋሁትና የበለጠ ጥብቅ አድርጌ አቀፍኩት ... በጭራሽ ንፋሱ ኮሪን እንዲወስደው አልፈቅድለትም: በጭራሽ!
“ንፋሱን እንድረሳው ታሪክ ንገሪኝ ካቲ"

👍34🥰2
ኮሪን ለማስደሰት የፈጠርኩት በጣም የሚወደው ታሪክ አለ፡ በሀሳብ ስላለ አለም ነበር ትንንሽ ልጆች በትንሽዬ ቆንጆ ቤት ውስጥ የሚያስፈራሩ ነገሮችን ማባረር ከሚችሉ ሀይለኛ እናትና አባት ጋር የሚኖሩበት፣ ስድስት ሰዎችን ያሉበት ቤተሰብ፣ ከቤታቸው ጓሮ ትልልቅ ዛፎች የሚወዛወዙበት፣
የአትክልት ስፍራ ያላቸው በዚያ የአትክልት ስፍራ ውስጥ፣ በበልግ ወቅት የሚሞቱና በፀደይ የሚነሱ እውነተኛ አበቦች፣ ክሌቨር የሚባል ውሻ ካሊኮ የምትባል ድመት፣ ቀኑን ሙሉ በወርቃማ ጎጆዋ ውስጥ ሆና የምትዘምር
ቢጫ ወፍ ያለችበት፣ ሁሉም ሰው ሁሉንም የሚወድበት፣ ማንም ሰው የማይገረፍበት፣ የማይመታበት፣ የማይጮህበት፣ መጋረጃዎች የማይዘጉበት፣
በሮች የማይቆለፉበት
“መዝሙር ዘምሪልኝ ካቲ፣ እየዘመርሽልኝ ስተኛ ደስ ይለኛል።"
ኮሪ ደጋግሞ ሲያንጎራጉር የሰማሁት ዜማ ላይ ራሴ ግጥም ጨምሬበት መዘመር ጀመርኩ፡ ኮሪን ከንፋሱ ፍርሀት ለማውጣት፣ ምናልባት ራሴንም ካለብኝ ፍርሀት እንዲያላቅቀኝ የታለመ መዝሙር ነው
እና የኔው ትንሹ ደህንነት ተሰምቶት በትክክል እየተነፈሰ ክንዶቼ ላይ አንቀላፋ
ከእሱ ቀጥሎ ክሪስ አይኖቹን በሀይል ከፍቶ ኮርኒሱ ላይ አፍጥጧል
መዝሙሩ ሲያልቅ ወደኔ ዞሮ ተመለከተኝ፡ አስራ አምስተኛ አመቱ መጣ ሄደ: ቀኑን ለየት ለማድረግ የተገዛ ኬክና አይስክሬም አድርገን ነበር።
ስጦታዎች በየቀኑ ይመጣሉ ማለት ይቻላል አሁን ካሜራና አዲስና የተሻለ ሰዓት አለው፡ ጥሩ ነው ግን እንዴት እንዲህ በቀላሉ ደስ ሊለው ቻለ?
እናታችን በፊት እንደነበረችው አይነት እንዳልሆነች አላየም? እንደ በፊቱ በየቀኑ እንደማትመጣ አላስተዋለም? የምትለውን ሁሉና የምታቀርባቸውን ሰበቦች ሁሉ የሚያምን ድልል ሆኗል?
የገና ዋዜማ! በፎክስወርዝ አዳራሽ ውስጥ ከታሰርን አምስተኛ ወር ሆኖናል።አንድም ቀን፣ እዚህ ትልቅ ቤት ውስጥ ወዳለው ምድር ቤት እንኳን ሄደን አናውቅም: ከመመገባችን በፊት የማመስገን፣ ሲመሽ አልጋዎቻችን ግርጌ
ተንበርክከን የመፀለይ፣ መታጠቢያ ቤት በጨዋ ደንብ መጠቀም፣ ሀሳቦቻችንን ንፁህና ፅዱ የማድረግ ህጎችን ሁሉ እየጠበቅን ነው: ሆኖም ግን ከቀን
ወደ ቀን ምግባችን ጥራቱ እየቀነሰ እየቀነሰ መጣ
አንድ የገና ገበያ ቢያመልጠን ምንም አይደል። በጣም ሀብታም በምንሆንበት ጊዜ፣ ወደ ሱቅ ሄደን የምንፈልገውን ሁሉ የምንገዛባቸው ብዙ ገናዎች
ይኖራሉ ብዬ ራሴን አፅናናሁ።
በሚያማምሩት ልብሶቻችን፣ ልዩ ተወዳጅና ተፈላጊ ሰዎች መሆናችንን በሚያሳዩ ለስላሳና አባባይ ድምፆቻችን፣ እንዴት
እንደምናምር አሰብኩት።
በገና ወቅት ተቆልፎብንም እንኳን ስራ በዝቶብን ነበር እኔና ክሪስ ምንም የምትፈልገው ነገር ባይኖርም ለእናታችን ስጦታ ሰራንላት። ለመንትዮቹ ደግሞ በእጅ የተሰሩ በጥጥ የተሞሉ አሻንጉሊቶች ሰራን፡ እኔ ደግሞ በግሌ መታጠቢያ ቤት እየተደበቅኩ ለክሪስ ከጥጥ የተሰራ ኮፍያ እየጠለፍኩለት
ነበር ኮፍያው እያደገ መጣ፤ ነገር ግን እናታችን ስለ ልኬት ሳትነግረኝ ረስታዋለች መሰለኝ፡
ከዚያ ክሪስ በጣም አስፈሪና የጅል ሀሳብ ይዞ መጣ: “ለአያትየውም ስጦታ እንስራላት!” የሚል፡ “እሷን ነጥሎ መተው ትክክል አይደለም ሁልጊዜ
ምግብና ወተት ታመጣልናለች: ማን ያውቃል የእሷን ፍቅር ለማግኘት እንደዚህ አይነት ነገሮች ያስፈልጉ ይሆናል። ከእሷ ጋር ሰላም ቢፈጠር ኑሯችን እንዴት አስደሳች ለሆን እንደሚችል አስቡት” አለ ጥሩ ሊሆን እንደሚችል አስቤ ለማትወደን ጠንቋይ አሮጊት ስጦታ በመስራት
ስራ ተጠመድን በነዚህ ሁሉ ጊዜያት አንድ ቀንም እንኳን ስማችንን ጠርታ አታውቅም::
“አያችሁ” አለ ክሪስ “አያታችንንም ለማግባባትና በእኛ ጎን ለማድረግ እድል እንዳለን አምናለሁ ምንም ቢሆን አያታችን ናት‥ ሰዎች ይለወጣሉ። እናታችን የወንድ አያታችንን ለማግባባት ስትሰራ እኛ ደግሞ እናቷን እናግባባለን እኔን
ማየት ባትፈልግም አንቺን ግን ታይሻለች "
“እኔንም አትመለከተኝም ፀጉሬን ነው የምታየው በሆነ ምክንያት ፀጉሬን ወዳዋለች”
ከሰዓት በኋላ ሊመሽ ሲል እናታችን እውነተኛ የገና ዛፍ ይዛ ወደ ክፍላችን መጣች: የእናታችን ቀሚስ አንድ ቀን እንዲኖረኝ ተስፋ የማደርገው አይነት የሚያምር ብሩህ ቀይ ቀሚስ ነው፡ እየሳቀችና እየተደሰተች አብራን ቆይታ
ዛፉን ስናሳምርና መብራት ስናደርግለት በማገዝ እያስደሰተችን ነበር:
“በሚቀጥለው አመት በዚህ ቀን በራሳችን ቤት ውስጥ እንሆናለን::” አለች: አመንኳት:
ፈገግ እያለች ሁላችንንም በደስታ ሞላችን፡ “በሚቀጥለው ዓመት ይህን ጊዜ ህይወት ለሁላችንም በጣም ጥሩ ይሆንልናል᎓ የራሳችን ትልቅ ቤት ለመግዛት ብዙ ገንዘብ ይኖረናል፡ የምትፈልጉት ሁሉ የእናንተ ይሆናል። በአጭር ጊዜ
ውስጥ ይህንን ክፍልና ጣሪያው ስር ያለውን ቦታ ትረሱታላችሁ በጀግንነትና በፅናት የተቋቋማችኋቸው ቀናት ልክ እንዳልተፈጠሩ ሁሉ ይረሳሉ”
ሳመችን፣ እንደምትወደን ነገረችን ስትሄድ ስንመለከት እንደ በፊቱ ባጣናት አይነት ስሜት አልነበረም:: አይኖቻችንን፣ ተስፋዎቻችንንና ህልሞቻችንን
ሞልታው ነበር።
ጠዋት ስነቃ ስጦታዎችን በሙሉ ዛፉ የነበረበት ጠረጴዛ ስር እንዲሁም በሁሉም ባዶ ቦታዎች ላይ ተደርገው ስመለከት እናታችን ማታ ተኝተን መጥታ እንደነበር አወቅኩ:
አይኖቼ ከክሪስ አይኖች ጋር ሲገጣጠሙ ጠቀሰኝና ፈገግ አለ፡ ከዚያ ከአልጋው ተነስቶ ትንሽዋን ቃጭል ያዘና እየነቀነቀ “መልካም የገና በዓል፣ ሁላችሁም ተነሱ! ኮሪ፣ ኬሪ አይኖቻችሁን ግለጡ! የገና አባት ያመጣላችሁን ተመልከቱ!” አለ፡
ኮሪ አልጋው ላይ እንደተቀመጠ ትንንሽ እጆቹን ጨብጦ አይኖቹን እያሻሽ ግራ የተጋባ መሰለ፡
ኬሪ ግን ሁልጊዜም የምትናገረው ታገኛለች። “የገና አባት እንዴት አገኘን?” አለች:
የገና አባት አስማተኛ አይኖች አሉት: አባታችን እንደሚያደርገው ነው ያደረገው” አለ ክሪስ፡ ከዚያ የበሩ እጀታ ሲከፈት ስንሰማ፣ ከረሜላዎቹን አጠገብ ባለው አልጋ ስር ደበቅናቸው᎓ አያትየው ነበረች: የሽርሽር ቅርጫቱን
እንደያዘች በፀጥታ ገባችና ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠችው: “እንኳን አደረሳችሁ" አላለችንም እንዴት አደራችሁም አላለችንም ፈገግም አላለች ወይም ደግሞ በሆነ መንገድ ልዩ ቀን መሆኑን አላሳየችንም:: እኛም ደግሞ ቀድማ ካላናገረችን በስተቀር መናገር አንችልም ነበር።
መጪውን እየፈራሁም ቢሆን እጇ ባዶ ሲሆን ልቀርባት እየጠበቅኩ ነበር። አያትየው ወደ ክሪስ ስለማትመለከትና መንትዮቹ ደግሞ ከመፍራታቸው
የተነሳ እሷ ስትኖር ስለሚንቀጠቀጡ፣ የሰራንላትን ስጦታ መስጠት የኔ ኃላፊነት ነበር... ግን እግሬን እንኳን ማንቀሳቀስ አልቻልኩም: ድንገት ክሪስ.....

👍44❤12🥰1
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_ሀያ
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
....መጪውን እየፈራሁም ቢሆን እጇ ባዶ ሲሆን ልቀርባት እየጠበቅኩ ነበር። አያትየው ወደ ክሪስ ስለማትመለከትና መንትዮቹ ደግሞ ከመፍራታቸው
የተነሳ እሷ ስትኖር ስለሚንቀጠቀጡ፣ የሰራንላትን ስጦታ መስጠት የኔ ኃላፊነት ነበር. ግን እግሬን እንኳን ማንቀሳቀስ አልቻልኩም: ድንገት ክሪስ በክንዱ ጎሸም አድርጎኝ “ቀጥይ” ሲል አንሾካሾከልኝ፡፡ “በሆነው ደቂቃ ከክፍሉ ትወጣለች”
እግሮቼ ከወለሉ ጋር በሚስማር የተጣበቁ መሰለኝ፡ በሁለቱ እጆቼ ረጅም ቀይ እሽግ ይዣለሁ፡ ከቆምኩበት ቦታ ሲታይ መስዋዕት የማቅረብ ነገር ይመስል
ነበር ምክንያቱም እስከዛሬ ስትሰጠን የነበረው ክፋት ስለነበረና አሁንም የባሰ
ህመም ልትሰጠን እድል እየጠበቀች ያለች ስለሆነች ለሷ ስጦታ መስጠት ቀላል አልነበረ።
በዚያ የገና ጠዋት ካለ አለንጋና ካለ ምንም ቃል ለሁላችንም ህመም መስጠት ተሳክቶላት ነበር በትክክለኛው መንገድ “መልካም ገና አያቴ። ትንሽ ስጦታ ልንሰጥሽ ነበር። እንድታመሰግኝን አይደለም:: ችግር የለውም በየቀኑ ምግብ ስለምታመጪልንና መጠለያ ስለሰጠሸን ለማመስገን ያህል ትንሽ ስጦታ ልንሰጥሽ ነው:” ልላት ነበር፡ ግን አይሆንም እንደዚያ ብላት እያፌዝኩባት
ይመስላት ይሆናል፡ የሚሻለው ዝም ብዬ “መልካም ገና፣ ይህንን ስጦታ እንደምትወጂው ተስፋ አለን ኮሪና ኬሪን ጨምሮ ሁላችንም ነን የሰራንልሽ፡”
ገና ስጦታውን ይዤ ስቀርባት ስታይ እጅግ ተደነቀች።
“በቀስታ አይኖቼ በድፍረት አይኖቿን ለማየት ቀና እያሉ የገና መስዋዕታችንን አቀረብኩ፡ በአይኖቼ ልለምናት አልፈለግኩም ግን እንድትወስደው፣
እንድትወደውና ቀዝቀዝ ብላም ቢሆን “አመሰግናለሁ” እንድትል ፈልጌያለሁ።ዛሬ ማታ ወደ መኝታዋ ስትሄድ ስለኛ እንድታስብ መጥፎ ልጆች እንዳልሆንን
እንድትረዳ ፈልጌያለሁ፡ ለእሷ ስጦታ ለመስራት የለፋነውን እንድታስብና እኛን የምታስደናግድበት መንገድ ትክክል ነው ወይስ ስህተት ብላ ራሷን እንድትጠይቅ ፈልጌያለሁ።
እጅግ በከፋ መንገድ ቀዝቃዛና የንቀት አይኖቿን በቀይ ወዳሰርነው ረጅም ሳጥን ዝቅ አደረገች፡ ላዩ ላይ ካርድ አለ ካርዱ ላይ “ለአያታችን ከክሪስ፣
ካቲ፣ ኮሪና ኬሪ” የሚል ተፅፎበታል: በግራጫ ድንጋይ አይኖቿ ካርዱን ረዘም ላለ ጊዜ ተመለከተች። ከዚያ አትኩሮቷን ቀጥታ ወደ እኔ ተስፋ የተሞሉ፣ የሚለምኑ፣ ክፉ አለመሆናችንን ማረጋገጥ የሚሹ አይኖቼ ላይ
አደረገች ከዚያ ወደ ስጦታው፣ ከዚያ ሆን ብላ ጀርባዋን አዞረችና ቃል ሳትናገር ከበሩ ወጥታ በሩን በሀይል ወርውራ ዘጋችና ቆለፈችው: እኔም የብዙ ረጃጅም ሰአታት ውበት የመስጠት ትጋት ውጤት የሆነውን ስጦታ
በእጆቼ እንደያዝኩ ክፍሉ መካከል ቆሜ ቀረሁ።
ጅሎች! የማንረባ ጅሎች!
አላግባባናትም:: ሁልጊዜም ከሰይጣን የተፈለፈልን አድርጋ ነው የምትቆጥረን!
እሷን በተመለከተ እኛ አልተፈጠርንም ይጎዳል፡ እስከ ውስጥ እግሬ ድረስ ዘልቆ አመመኝ፡ ልቤ ወደ ደረቴ ህመም የሚልክ የተቀደደ ኳስ መሰለኝ፡
ከኋላዬ ክሪስ በፍጥነት ወደ ውስጥና ወደ ውጪ ሲተነፍስና መንትዮቹ ሲነጫነጩ ይሰማኛል።
ይህ ትልቅ የመሆኛ ጊዜዬ ነው፤ እናታችን በትክክልና ውጤታማ በሆነ መንገድ የምትጠቀምበትን ራስን የመቆጣጠር ዘዴ ተግባራዊ የማደርግበት ጊዜ ነው: እንቅስቃሴዬንና ፊቴ ላይ ያለውን ስሜት ከእናቴ ኮረጅኩ።
እጆቼን እሷ እንደምታደርገው አደረግኩ በቀስታና በማታለል አይነት እሷ እንደምታደርገው ፈገግ አልኩ
ከዚያስ? መብሰሌን ለማሳየት ምን አደረግኩ?
ስጦታውን ወለሉ ላይ ጣልኩት! ከዚህ በፊት ጮክ ብዬ ተናግሬያቸው የማላውቃቸውን ቃላት እየተናገርኩ፣ እግሬን አንስቼ ረገጥኩትና መያዣው ሲሰበር እየሰማሁ ጮህኩ! በሁለቱም እግሮቼ ላዩ ላይ ዘለልኩበት ጣሪያው ስር ካለው ክፍል ያገኘነውና ስጦታውን የሰራንበት የሚያምር ፍሬም እንክትክቱ እስኪወጣ ድረስ ላዩ ላይ ጨፈርኩበት ከድንጋይ የተሰራችን ሴት እንድናግባባ የመከረኝን ክሪስን ጠላሁት እንደዚህ አይነት ቦታ እንድንኖር ስላደረገችን እናቴን ጠላኋት!
እናቷን የተሻለ ልታውቃት ይገባ ነበር እዚህ አምጥታን ውርስ ከምትጠብቅ ሱቅ ውስጥ ጫማ መሸጥ ትችል ነበር። አሁን ካደረገችው የተሻለ ነገር
ማድረግ ትችል ነበር።
በአንድ እብድ አውሬ ጥቃት ስር ደረቁ ፍሬም ብትንትኑ ወጣ ልፋታችንም ሄደ፡
“አቁሚ! ለራሳችን እናስቀምጠዋለን፡” አለ ክሪስ
ሙሉ በሙሉ መበላሸቱን ለመከላከል ፈጥኖ ቢደርስም ስዕሉ ግን ተበላሽቶ
ነበር ለዘለዓለም ሄዶ ነበር አለቀስኩ፡
ስንሰቀሰቅ ክሪስ በክንዶቹ አቅፎኝ በአባትነት ቃና “አይዞሽ ምንም አይደል። ያደረገችው ነገር ችግር የለውም፡ እኛ ትክክል ነን፡ የተሳሳተችው እሷ ናት። እኛ ልንቀርባት ሞክረናል፡ እሷ ናት በፍፁም ያልሞከረችው" አለኝ:
በስጦታዎቻችን መካከል ወለሉ ላይ በፀጥታ ተቀመጥን፡ መንትዮቹ ትልልቅ አይኖቻቸው በጥርጣሬ ተሞልተው ፀጥ ብለዋል፡ በአሻንጉሊቶቻቸው
መጫወት ቢፈልጉም፣ የእኛ መስታወቶች በመሆናቸውና ምንም ብንሆን የእኛን ስሜት የሚያንፀባርቁ በመሆኑ መወሰን አልቻሉም: እነሱን የማየት
ሀዘን እንደገና አሳመመኝ።
እናታችን ፈገግ ብላና የገና ሰላምታዋን አስቀድማ ወደ ክፍላችን ስትመጣ ተጨማሪ ስጦታዎች ይዛ ነበር ከነዚያም መሀል ድሮ የእሷና በጥላቻ
የተሞላች እናቷ የነበረ ትልቅ የአሻንጉሊት ቤት ይገኝበታል። “ይሄ ለኮሪ ለኬሪ የኔ ስጦታ ነው:" አለችና ሁለቱንም አቅፋ ጉንጮቻቸውን ሳመች።ከዚያ እሷ የአምስት አመት ልጅ የነበረች ጊዜ ታደርግ እንደነበረው “የውሸት
ወላጆች፣ የውሽት ቤት” እያደረጉ እንዲጫወቱ ነገረቻቸው።
ብታስተውል አንዳችንም በዚያ የአሻንጉሊት ቤት አልተደሰትንም ነበር።አስተያየት አልሰጠችም: በደስታ እየሳቀች ወለሉ ላይ እንደመንበርከክ ብላ
ተረከዟ ላይ ቁጢጥ አለችና ይህንን የአሻንጉሊት ቤት እንዴት ትወደው እንደነበረ ነገረችን
“ካቲ” አለች እናቴ ክንዷን አንገቴ ላይ አድርጋ፣ “ይህንን ትንሽ ጨርቅ ተመልከቺ ከንፁህ ሀር የተሰራ ነው፡፡ በምግብ ቤት ውስጥ ያለው ደግሞ
ኦሪየንታል ምንጣፍ ነው" አለችኝ የአሻንጉሊቱ ቤት ውስጥ ያሉትን ዋጋ ያላቸው ነገሮች በመጥራት፡
“አሮጌ ሆኖ እንዴት አዲስ ሊመስል ቻለ?” ስል ጠየቅኳት።
በእናታችን ላይ ጥቁር ደመና ሲያጠላና ፊቷን ሲሸፍናት አየሁ። “የእናቴ በነበረበት ወቅት በመስተዋት ሳጥን የተሸፈነ ነበር። እንድትመለከተው እንጂ
እንድትነካው አይፈቀድላትም ነበር። ለእኔ ሲሰጠኝ አባቴ የመስተዋቱን ሳጥን በመዶሻ ሰበረውና እጄን መፅሀፍ ቅዱስ ላይ አስደርጎ ምንም ነገር
እንዳልሰብር ካስማለኝ በኋላ በሁሉም ነገር እንድጫወት ፈቀደልኝ
“ከማልሽ በኋላ የሆነ ነገር ሰበርሽ?” ክሪስ ጠየቃት።
“አዎ ከማልኩ በኋላ አንድ ነገር ሰበርኩ" አንገቷን ስላቀረቀረች ፊቷን ማየት አልቻልንም “በጣም ቆንጆ ወጣት ሆኖ የተሰራ ሌላ አሻንጉሊት ነበር እና ኮቱን ላወልቅለት ስሞክር እጁ ወለቀ ከዚያ አሻንጉሊቱን ስለሰበርኩ
ብቻ ሳይሆን ከልብሱ ስር ያለው ምን እንደሆነ ለማወቅ በመፈለጌ ጭምር ተገረፍኩ።"
እኔና ክሪስ ዝም ብለን ስንቀመጥ ኬሪ ግን ቀልቧ የሚያምር ባለቀለም ልብስ የለበሱት ትንንሽ የሚያስቁ አሻንጉሊቶች ላይ አረፈ፡ እሷ ፍላጎት ስላደረባት
ኮሪም በአሻንጉሊት ቤቱ ውስጥ ያሉትን ነገሮች መመርመር ጀመረ:
የዚህን ጊዜ ነው እናታችን ትኩረቷን ወደኔ ያደረገችው ካቲ እኔ ስመጣ ምን ሆነሽ ነው ቅር ብሎሽ የነበረው? ስጦታዎችሽን አልወደድሻቸውም? አለች:

👍43❤1
መልስ ሳልሰጥ ስቀር ክሪስ መለሰላት: “የከፋት አያትየው የሰራንላትን ስጦታ አልቀበልም ስላለች ነው" አለ፡ እናታችን አይኖቼን እየሸሸች ግን ትከሻዬን
መታ መታ አደረገችኝ፡ ክሪስ ቀጠለ፡ “ስለሁሉም ነገር እናመሰግናለን ያላመጣሽልን ነገር የለም፡ ስለ አሻንጉሊት ቤቱም በጣም እናመሰግናለን፡
መንትዮቹ ከሌሎች ነገሮች በበለጠ በዚህ ደስ እንደሚላቸው አስባለሁ" አለ
እናታችን ከተንበረከከችበት ብድግ ብላ ሚስጥራዊ ፈገግታ አሳይታን ወጣች ልክ ከበሩ እንደወጣች በአንድ ወይም በሁለት ሰከንድ ውስጥ እመለሳለሁ አለችንና እጅግ በጣም ምርጥ ስጦታ አመጣችልን ትንሽ ቴሌቭዥን"! “አባቴ መኝታ ቤት ውስጥ እንድጠቀምበት ሰጥቶኝ የነበረ ነው እና ወዲያውኑ ማን
የበለጠ እንደሚያስፈልገው አወቅኩ አሁን አለምን ልታዩ የምትችሉበት ትክክለኛ መስኮት አላችሁ” አለችን፡
ተስፋዎቼን ወደ ሰማይ ከፍ አድርገው የሚያበሩ ትክክለኛ ቃላት! “እማዬ!”ስል ጮህኩ “አባትሽ ውድ ስጦታ ሰጠሸ ይህ ማለት አሁን ወደደሽ ማለት
ነው? አባታችንን በማግባትሽ ይቅርታ አደረገልሽ? አሁን ወደ ምድር ቤት መሄድ እንችላለን?”
ሰማያዊ አይኖቿ እንደገና ጥቁርና ችግር ያጠላባቸው ሆኑ፡ ከአባቷ ጋር የተሻለ መቀራረብ እንዳሳዩና በእግዚአብሔርና በህብረተሰቡ ላይ ለሰሯቸው ኃጢአቶች ይቅር እንዳላት ስትነግረን ድምጽዋ ላይ ምንም ደስታ አልነበረም
ከዚያ ልቤ ጉሮሮዬ ውስጥ እንድትወተፍ ያደረገ አንድ ነገር ተናገረች።
“በሚቀጥለው ሳምንት አባቴ ለጠበቃው እኔን ኑዛዜው ውስጥ እንዲያስገባኝ ሊያደርገው ነው ሁሉንም ነገር ሊሰጠኝ ነው። ይህም ቤት እንኳን እናቴ
ከሞተች በኋላ የኔ ይሆናል፡ እሷ ከእናቷና ከአባቷ የወረሰችው ሀብት ስላላት ምንም አይነት ገንዘብ ሊተውላት እቅድ የለውም" አለችን
ገንዘብ! ስለሱ ግድ አልነበረኝም፡ የምፈልገው ከዚህ መውጣት ብቻ ነው! እና ድንገት በጣም ተደሰትኩ፡ ደስ አለኝና እጆቼን እናቴ አንገት ላይ ጠምጥሜ
ጉንጯን ሳምኩና ጥብቅ አድርጌ አቀፍኳት አምላክ ሆይ! እዚህ ቤት ከመጣን ጀምሮ ካሉት ቀኖች ይሄ ምርጥ ቀን ነው . . . ድንገት ግን እናታችን ወደ ምድር ቤት መሄድ ስለመቻላችን ገና ምንም እንዳላለች አስታወስኩ ግን ግድ
የለም፣ ወደ ነፃነታችን አንድ እርምጃ ቀርበናል።
እናታችን አልጋ ላይ ተቀምጣ በአይኖቿ ሳይሆን በከንፈሮቿ እየሳቀች ነው:እኔና ክሪስ በምንናገራቸው ተራ ነገሮች እየሳቀች ነው፣ ሳቋ ግን የእሷ ሳቅ
ሳይሆን መራራ ሳቅ ነበር። “አምላኬ አሁን ወንድ አያትሽ የሚፈልጋት አይነት ቁምነገረኛና ታዛዥ ልጅ ሆኛለሁ፡ ይናገራል እታዘዛለሁ። ያዘኛል ዘልዬ አነሳለሁ። ቢያንስ ላስደስተው ችያለሁ፡” አለችና ድንገት ቆም አድርጋ መስኮቶቹና ባሻገር ወዳለው ደብዛዛ ብርሃን ተመለከተች። “በመሆኑም
ስላስደሰትኩት ዛሬ ማታ ግብዣ አዘጋጅቶ ከአካባቢው ሰዎችና ከድሮ ጓደኞቹ ጋር እንደገና ሊያስተዋውቀኝ ነው፡ ለወላጆቼ ነገሮችን በሰፊው በማድረግ
መደሰት ትልቅ ጉዳያቸው ነው፡ እነሱ አይጠጡም ነገር ግን ገሀነምን ለማይፈሩ ስዎች መጠጥ ለማቅረብ ግድ የላቸውም: ስለዚህ መጠጥ ይቀርባል ለዳንስ ደግሞ አነስ ያለ የሙዚቃ ባንድ ይኖራል” አለች “ግብዣ! የገና ግብዣ!
ለዳንስ የተዘጋጁ ሙዚቀኞች ምግብና መጠጥ! እና እናታችን ደግሞ አዲስ ኑዛዜ ላይ ልትገባ ነው! ከዚህ የበለጠ አስደሳች ቀን ይኖራል?
“ማየት እንችላለን?” እኔና ክሪስ አንድ ላይ ጠየቅን፡፡ “ድምፅ አናሰማም
“ማንም እንዳያየን እንደበቃለን፡”
“እባክሽ እማዬ እባክሽ ሌሎች ሰዎች ካየን ረጅም ጊዜያችን ነው: ደግሞ የገና ቀን ግብዣ ላይ ተገኝተን አናውቅም”
መጨረሻ ላይ መቋቋም እስከማትችል ድረስ ስለለመንናት፣ እኔንና ክሪስን መንትዮቹ ሊሰሙን ወደማይችሉበት ጥግ ወሰደችንና በሹክሹክታ ነገረችን።
“ሁለታችሁ ተደብቃችሁ ልታዩ የምትችሉበት አንድ ቦታ አለ መንትዮቹን ግን አደጋ ላይ መጣል አልችልም ለመታመን ገና ትንንሾች ናቸው እና አንድ ቦታ ላይ ከሁለት ሰከንድ በላይ እንደማይቆዩ ታውቃላችሁ። ኬሪ ደግሞ
ከደስታ ብዛት ልትጮህና የሰውን ሁሉ ትኩረት ልትስብ ትችላለች። ስለዚህ እንደማትነግሯቸው ማሉልኝ፡" አለችን፡
ቃል ገባን፡ ባታስምለንም እንኳን መንትዮቹን ስለምንወዳቸው ትተናቸው መሄዳችንንም እንዲያውቁ በማድረግ ስሜታቸውን መጉዳት ስለማንፈልግ አንነግራቸውም:
እናታችን ከሄደች በኋላ የገና መዝሙር ዘመርን በሽርሽር ቅርጫቱ ውስጥ ከማቀዝቀዣ የወጣና ከምስጋና ቀን የተረፈ ከሚመስል ምግብ በስተቀር
የተለየ ነገር አልነበረም፡ ነገር ግን ቀኑ በደስታ አለፈ ምሽቱ ሲመጣ ቁጭ ብዬ ኬሪና ኮሪ በደስታ የሚጫወቱበትን የአሻንጉሊት ቤት
ለረጅም ጊዜ እየተመለከትኩ ነበር አንዲት ትንሽ ልጅ በሆነ ወቅት ኖሯት እንድታየው እንጂ እንድትነካው ካልተፈቀደላት፣ ከዚያ ሌላ ትንሽ ልጅ መጥታ
የአሻንጉሊት ቤቱ ተሰጥቷትና ውስጡ ያሉትን ነገሮች መንካት እንድትችል የመስተዋት ሳጥኑ በመዶሻ ተሰብሮላት፣ ቀጥሎ የሆነ ነገር ከሰበረች ደግሞ
ልትቀማ ከምትችልበት ግዑዝ ነገር ምን ልትማር እንደምትችል ይገርማል።
የሚያንቀጠቅጥ ሀሳብ መጣብኝı ኬሪ ወይም ኮሪ የሆነ ነገር ሊሰብሩ ቢችሉ ቅጣቱ ምን ሊሆን እንደሚችል!.....

👍31❤3👏2
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
..."ባርባራ ” አለች ሚስዝ ሔር " " የዛሬ ቀን ደስ ማለቱን አየሺው ?”
አዎን በጣም ደስ የሚል ቀን ነው እማማ "
“ ወጣ ብዬ ብመለስ የሚሻለኝ መሳለኝ "
“ በርግጥ ይሻልሻል እማማ !ቶሎ ቶሎ ብትወጭማ ኖሮ ጥቅሙን ታውቂው ነበር ቀኑ እንደ ዛሬ ጥሩ ሲሆን መውጣት ጥሩ ነው ”
“ አባትሽ ከጓሮ አለና እስኪ ይመቸው እንዶሆነ ጠይቂው "
ዳኛው ሔር ከፊት ለፊት የነበረውን አታክልት እየጎበኘ በትእዛዙ መሠረት ያልተሠራውን ለአትክልተኛው ለብንያም ያሳያል " ብንያም ሠረገላ ነጅ የፈሬሶቹ
ባልዶራስ ከመሆኑም ሌላ ከዚያ በሚተርፈው ጊዜም በአትክልተኝነት ይሠራል "
ትዳር አለው ማልዶ በመግባትና አምሽቶ በመጣት ከሠራበት እየተመግበ ! ከራሱ ቤት ይኖራል ጀስቲስ” ሔር ሰው ሠራሽ ጠጉር አጥልቆ የቤት ልብስ ለብሶ
በብንያም እየተቆጣ ሳለ ባርባራ ደረሰች " ከሦስት ልጆቹ ውስጥ አባቷን ደፈር የምትል እሷ ነበረች ሆኖም እንደ ሌሎቹ ባትርበተበትም አጠግቡ ደርሳ በአክብሮት ፍርሃት ቆመች "
“ አባባ ! ”
“ ምን ፈለግሽ ? አላት ግዙፍ ሰውነቱን በማዞር "
እማማ ወጣ ብላ ነፋስ ለመቀበል ትፈልጋለች " ሠረገላ ትፈቅድልናለህ ?”
ዳኛው መልስ ከመስጠቱ በፊት ሰማዩን ቀና ብሎ አየና “ወዴት ለመሔድ ትፈልጋለች ? አለ "
“ ወደ ሱቅ ብቅ ብለን አንዳንድ ነገችን ለመግዛት እንፈልጋለን ከዌስትሊን አንወጣም "
ሚስተር ሔር በሣሩ ውስጥ እየተንጐራደደ ወደ ምግብ ቤቱ ሔደና መስኮቱን ገፋ አድርጐ ከፍቶ ' ' ዛሬ ወደ ሱቅ ለመሔድ ፈለግሽ እንዴ አን ? አላት "
“ እኔ የግድ ዛሬ አላልኩም ” አለችው እየፈራች - “ምን ጊዜም ሊሆን ይችላል " ሠረገላውን የማትፈልገው ከሆነ ግን ፡ቀኑ ሞቃት ስለሆነ ትንሽ ወጣ ብዬ ልመለስ ፈልጌ ነበር " በዚያውም ባርባራ የበጋ ልብሷን ትገዛለች « ”
“ እሷ ሁልጊዜ ልብስ እንደ ገዛች ነው !” ብሎ አጉረመረመ "
“ ኧረ አባባ ! እኔ . . .
ዝም በይ እመቤቲቱ የሚያስፈልግሽ እጥፍ አለሽ ”
“ ምናልባት ሠረገላውን ካልፈቀድክልኝ በእግሬም ቢሆን ቀስ ብዬ ትንሽ ከሔድኩ በኋላ ሲደክመኝ መመለስ እችላለሁ " "
ከዚያ ሳምንት ሙሎ አልጋ ለመያዝ ነው !? በእግር ዌስትሊን ደርሶ መመለስ ? ዕብዶት ነው ” አለና እሺም እምቢም ሳይል መስኮቱን ዘግቶ ወደ ቤንጃሚን ተመለሰ "
" ባርባራ... አባትሽ ሠረገላውን ወዴት ሊሄድበት አስቧል? አለች ሚስስ ሔር
ማንንም መቃወም ዐመል ብሎት ነው እንጂ እሱስ የትም የሚሔድ አይመስለኝም " በእግርሽ መሔድ የምትችይ ይመስለኛልስንመለስ በኪራይ ሰረግላ እንመጣለን።
በርግጥ በእግሬ መሔድ እችላላሁ " አባትሽ ሳይፈቅድ ግን ለመሞከር
አልቃጣውም "
ባርባራ በመስኮት ስትመለከት ቤንጃሚን ያትክልት መሣሪያዎቹን ሰብስቦ አስቀምጦ ጋጦቹ ወደ ነበሩበት ወደ ቤቱ ጀርባ ሲያመራ አየችው " በዚህ ጊዜ በአቋራጭ ሮጣ ቀዶመችውና አባባ በሠረገላ እንድትወስዶን ያዘዘህ ነገር አለ ቤንጃሚን ? ” አለችው "
“ አዎን አንቺንና እሜቴን ዌስትሊን አድርሺ እንድመልሳችሁ ታዝዣለሁ
አላት " እንደገና ተመልሳ የደስ ደሱን ለናቷ ነገረቻት " ከዚያም እህል መሳሪይ አቅርባ ትንሽ አቀመስቻትና ተሣፍረው ሚስተር ሔር በነበረበት በኩል ሲያልፉ ምስጋናዋን በፈግታ ገለጸችላት እሱም “ ልብ በይ ለራት ሰዓት እንድትደርሱ ባርባራ ደግሞ ብዙ ገንዘብ እንዳታጠፉ ተጠንቀቁ ” አላት ከዚያ መንገዳቸውን ቀጠሉ
ዌስትሊን ደርሰው ከሚስተር ካርላይል ቢሮ ፊት ለፊት ከነበረው የጨርቃ ጨርቅ ሱቅ አጠግብ አቁመው ሠረገላውን ከዚያ ትተውት ገቡ "
ከሱቅ ገብተው ሲመርጡ ሲያገላብጡ ' ዋጋ ሲወጋወጉ አንድ ሰዓት ያህል ከቆዩ በኋላ ሚስዝ ሔር ቦርሳዋን አጣችው "
“ ከሠረገላው ውስጥ ትቸው ሳይሆን አይቀርም ... ባርባራ- ሔደሽ ብታመጭልኝሳ የኔ ልጅ ? የሐሩ ናሙናም ከውስጡ ነው ያለው "
ባርባራ ወጥታ ሔደች ሠረገላው ቤንጃሚና ጸጉረ ለስላሳው አሮጌ ፈረስ ፀጥ ብለው ይጠብቃሉ " ባርባራ በዐይኗ ፈልጋ ቦርሳውን ስታጣው አሽከርዮው አዘዘችው።
የእማማን ቦርሳ ፌልገው ቤንጃሚን ከሠረገላው ውስጥ አንዱ ጋ ተወሽቆ ይሆናል።
ቤንጃሚን ከመቀመጫው ወርዶ መፈለግ ጀመረ " ባርባራ በመንግዱ ቁልቁል እየተመለከተች ትጠብቃለች " ፀሐይዋ በጣም ደምቃለች " አንድ ሰውዬ በድንጋይ ንጣፉ መንገድ ይንሸራሸራል " በሰደሪያው የተጋደመው ወፍራም ሰንሰለትና
ከሱ ጋር የተያዙት ልዩ ልዩ ጌጦች hፀሐይዋ ጨረር ጋር ይንቦጋቦጋሉ የሸሚዙ የወርቅ ቁልፎችም ለብቻቸው ያበራሉ " ጓንቲ ባላጠለቀው እጁ ሪዙን ሲያሻሽ የእጁ ንጣት ከሩቅ ይታያል በተለይ ደግሞ ጣቱ ላይ የሰካው ያልማዝ ቀለበት ያንጸባርቃል ባርባራ ወንድሟ ሪቻርድ የነገራትን የዚያን ጌጣጌጥ ወዳድ ሰዬ ነገር ትውስ አላት።
ሲጓዝ ተመለከተችው " ዐይኑና ጸጉሩ ጥቁር ቀጠን ብሎ ረዘም ያለ ዕድው በኻያ ሰባትና ስምንት የሚገመት መልከ መልካም ጐበዝ ነበር ከፍል "ከፍየል ቆዳ የተሠሩ ብጫ ብጤ ጓንቲዎች አንዷን ከግራ እጁ አጥልቋል ሌውን ቀስ ብሎ እያፏጨ በመተከዝ ሲያወዛውዝ አየችው ደማቅ ፀሐይ ባይኖር ኖሮ ባርባራ የወርቁ
ጉጥ አታየውም ወይም ከዚያ አሳዛኝ ምስጢር ጋር በልቧ አታዛምደውም ነበር "
እንዴ ቶርን አንተነህ እንዴ ? እስቲ ወዲህ ተሻገር !
ከመንገድ ወዲያ ማዶ ሆኖ የተናገረው ኦትዌይ ቤተል ሲሆን የተጣራውም ያን በልዩ ልዩ ፈርጥ ያጌጠውን ጎበዝ ነበር » ሰውየው ግን በሐሳብ ተውጦ ስለ አልሰማው እንደገና ጮኽ ብሎ ጠራው ።
“ ካፒቴን ቶርን !
አሁን ሰማውና ራሱን በአዎንታ ነቅንቆ መንገዱን ተሻገረ ባርባራ ሕልም ውስጥ ያለች መሰላት አንጎሏ ' ልቧ ' ሐሳቧ ' አንድ ላይ ተቀላቀሎባት
“ ቦርሳው ይኸውና ሚስ ባርባራ " በሠረግላው የሥጋጃ እጥፋቶች | ውስጥ ገብቶ አገኘሁት " አለና ቤንጃሚን ወደሷ ሲዘረጋላት ልብ አላለችውም » የሆሊጆንን እውነተኛ ገዳይ ማየቷን ያለ ጥርጥር ስለ አረጋገጠች ከዚህ ጉዳይ ውጭ የሆነውን ነገር ሁሉ ረስታዋለች በሁለመናው ሪቻርድ ከነገራት ገለጻ ጋር ተስማማላት"
ረጅም ' በጣም ነጭ ያልሆነ መልከ መልካም ' እጀ ለስላሳ በጌጣ ጌጥ የተንቆጠቆጠና . . . ስሙ ደግሞ ካፒቴን ቶርን ! እሱ ለመሆኑ ምንም አልተጠራጠረችም ፊቷ ባንድ ጊዜ ተለዋወጠ " ልቧ ያለ መጠን ዘለለ
“ ቦርሳው ይኸው ሚስ ባርባራ !” ደገመ ብንጃሚን።
ባርባራ ቤንጃሚንን ከነቦርሳው ጥላው ሔደች » የቀዶ ጥገና ሐኪሙን ሚስተር ዌይንራይትን ከሩቅ አየችውና ወይሱ በረረች
ሚስተር ዌይንራይት . . . ያ ከኦትዌይ ቤተል ጋር የሚነጋግር ሰው ይታይዎታል . . . ማነው ?”
ሚስተር ዌይንራይት ' መልስ ከመስጠቱ በፊት መነጽሩን ከአፍንጫው ቁብ ማድረግ ነበረበት " ምክንያቱም ዐይኑ እሩቅ ነገር አስተካክሎ አያይለትም ነበር «ያ ነው? ካፔቴን ቶርን ይሉታል " የሔርበርትን ቤተሰብ ለማየት የመጣ መሰለኝ "
መኖሪያው የት ነው ? አሁንስ ከየት ነው የመጣው ?

👍16
“እንጃ? እኔም ያየሁት ዛሬ ጧት ነው " ስሚዝ አብሮት ነበርና እንደ ነገረኝዐየሔርበርት ቤተሰብ ወዳጅ ነው " ግን ምነው ፊትሽ ተለዋወጠ ደህናም አይደለሽ ?
ምንም ሳትመልስለት ዝም አለች ሚስተር ቤተልና ካፒቴን ቶርን ቁልቁል መጡና ቤተል ፡ “እንዴት ዋልሽ አላት " እሷ ግን ግራ ገብቷት ስለ ነበር አጾፋውን ለመመለስ እንኳን አልቻለችም እነሱም ዐልፈው ሔዱ እሷም ከዌይን ራይት ዘንድ ቀስ እያለች ወደ እናቷ ስትመለስ ከሱቅ ብቅ ስትል አገኘቻት "
“ምነው ቆየሽ ... የኔ ልጅ ? ቦርሳውን አጣሺው ?
“ሚስተር ዌይንራይትን ለማነጋገር ሔጄ ነው ቦርሳውን በደመ ነፍሷ ከቤንጃሚን እጅ ተቀብላ ' ለእናቷ እየሰጠች " ጠቅላላ ልቧና ዐይኖቿ
እየራቀ ከሔደው ሰው ጋር አብሪው ሔዴዋል
"እንዴ ምነው ፊትሽ ልውጥ አለ ? ደህናም አይደለሽ ?
አይ ደኅና ነኝ " አሁን ገበያችንን እንገብይ እማማ "
ባርባራ ቀድማ ከሱቅ ገባች ያ ሁሉ ፍላጎቷ ቶሎ ወደ ቤት ተመልሳ ብቻዋን ሁና
የምታስበትን ጊዜ ለማግኘት ነዉ" ሚስዝ ሔር ግን በልጇ ድንገተኛ
ለውጥ ማየቷ ለምን እንደሆነ ገርሟታል።
በይ እስኪ ልጄ ከነዚህ ሁለት ሐሮች የሚሻልሽን ምረጭ "
ከሁለቱ አንዱን የሆነውን ግዢ እማማ !
ባርባራ ዛሬ ምን ነካሽ?
"ደከመኝ መሰለኝ " እኔ አረንጓዴ አፌልግም ያኛውን ግዥው አለች
ባርባራ ቀልቧን ለመስብሰብ እየሞከሬች።
ወደ ቤት ከተመለሱ በኋለ ባርባራ ራት እስኪቀርብ ድረስ አምስት ደቂቃ ያህል ከክፍሏ ዘግታ ስታስብ ቆየችና በመጨረሻ ያየችውን ነገር ለሚስተር ካርላይል መንግር ቆረጠች " ለዚያውም እንደ ምንም ብላ የዚያኑ ለት ማታ አንድ ብልሃት ፈጥራ ወደ ኢስት ሊን መሻገር ፈለግች "
አሁን ሚስተር ካርላይል ዘንድ ለመሔድ እንዴት ያለ መላ ትፍጠር ? ጉዳዩ ጊዜ የሚሰጠው አይደለም " የዚያኑ ለት ማታ ኢስት ሊን ሳትዶርስ ማደር እንደማይኖርባት! እያውጠነጠነች ራት ለመብላት ወደ ምግብ ቤት ወረደች » በምግብ ላይ እንዳሉ ሚስዝ ሔር ለካባ ብላ ስለገዛችው ሐር ወግ ጀመረች ፍላጐቷ በሚስ
ካርይል ዐይነት ለማሰፋት ነው " ሚስ ካርላይል ስለ ዊልሰን ጠባይ ለመጠየቅ ባለፈሙ ጊዜ መጥታ ሳለ ሞዴሉን እንደምትሰጣት ነግራት ነበር - ሚስዝ ሔር"
ይኽንኑ ሞዴል የምታመጣላት ከሠራተኛቿ አንዷን ከራት በኋላ እልካለሁ ብላ እንደ ተለያዩ አንሥታ ተናገረች
"እማማ" አለች ባርባራ ጕጕት እየተናነቃት : “እኔ ልሒድ !” በኃይል በመናገሯ የሚጐርሰውን ሥጋ ሲቆርጥ የነበረው አባቷ አቋረጠና ያን ያህል ያስጨነቃት
ምን እንደሆነ ጠየቃት " ባርባራ መልሳ እንደ ማፈር አለችና ይቅርታ ጠየቀች።
የሷ ጥድፊያ እኮ የተፈጥሮ ነው በማንም ያለ ነው ...ሪቻርድ ሕፃኒቱን ሰረቅ አድርጋ ለማት ፈልጋ ይሆናል" ወጣቶች ሁሉ ሕፃን ማየት ደስ ይላቸዋል
አለችው ሚስቲቱ።
ባርባራ በናቷ ንግግር ፊቷ ደም ቢመስልም አላስተባበለችም " ባርባራ ሁለመናዋ በወንድሟ በሪቻርድ ሐሳብ ሞላና የቀረበላትን ምግብ እምብዛም ሳትበላለት መለሰችው
“እንዴ ምን ታርግ? ሐሳቧ እኮ እየመረጠች ስትገዛው ካመሸችው ልብስ ነው " ምኑን በላች ” አለ አባቷ በፌዝ።
ወደ ኢስት ሊን መሔድ ማንም አልከለከላትም » ልክ ራት እንዳበቃ ደረሰችና ሚስ ካርላይል ጠየቀች።
ሚስ ካርላይልን ጠየቀች ወደ
ውጭ እንደ ዋሉ አልገቡም" እሜቴም ዛሬ እንግዳ አይቀበሉም ” ተባለችና ሚስተር ካርላይልን ለማነጋገር እንደምትፈልግ ለፒተር ነግራ ከሳሎን አስግባት " ሚስተር ካርላይል ወደሷ መጣ።
“ስለ አስቸገርኩህ አዝናለሁ” ብላ ጀመረች " ከዓመት በፊት አንድ ቀን ማታ ሲሸኛት ካደረጉት ውይይት ወዲህ ምንም የመንፈስ መሸበር አሳይታው አታውቅም
ነበር የምታሳየው ጠባይም ረጋ ቀዝቀዝ ያለና አክብሮት የተምላበት ነበር እንደ ወትሮው “አርኪባልድ የሚለውን የቀረቤታ አጠራሯን ለውጣ እንደ ማንም
የውጭ ሰው ሚስተር ካርላይል ነበር የምትለው "
“ ቁጭ በይ ቁጭ በይ . . . ባርባራ ” አላት።
ሚስ ካርላይል ለናቴ እሰጥሻለሁ ያለቻትን የስፌት ምስል ለመውሰድ ነበር እሷን የጠየቅሁት ዋናው አመጣጤ ግን አንተን ፍለጋ ነው ሪቻርድ ሆሊጆን ግዳይ
ነው ያለው መቶ አለቃ ቶርን ትዝ ይልሃል ?
"አዎን"
"እሱ ዌስት ሊን ያለ መሰለኝ ”
“ ሰውየው ራሱ ? አለ ሚስተር ካርላይል በነግሩ ጓጉቶ"
“ምንም ሌላ ሰው ሊሆን አይችልም ” አለችና ያየችበትን ቦታኖ ሁኔታ መልኩን አለባበሱን ከማን ጋር እንደ ነበር ሚስተር ዌይንራይትን ጠይቃው ምን
እንዳላት በዝርዝር ነገረችው ቤተል “ካፒቴን” ሲለው መስማቷን ጠቅላ "ከአራት ዓመት በፊት መቶ አለቃ ከነበረ ፡ ዛሬ ካፒቴን ሊሆን ይችላል ” አለችው።
"በይ እንግዲህ ባርባራ
ከሁሉ በፊት እሱ መሆኑን ካረጋጥን በኋላ ወደፊት ምን ማድረግ እንደሚገባ አስቤበት ሳበቃ እነግርሻለሁ " "
ባርባራ ልትሔድ ተነሣች " ሚስተር ካርላይል ስለ አየችው ዝርዝር ነገር እየጠየቃትና እየተወያዩ እስተ መናፈሻው መጨረሻ ሸኛት " ሳቤላ ከመልበሻ ክፍሏ መስኮት ቁማ በቅናት ዐይኗ ትከተላቸው እንደ ነበር አላወቁም "
“ እና ኦትዌይ ቤተል ጋር” የቅርብ ወዳጅ ይመስላል አልሽኝ ?
“ ቅርብነቱን እንጃ!ሲጠራው ግን በደንብ እንደሚተዋወቁ አድርጎ ነበር ”
ከዚያ በኋላ ከሷ ጋር ተጨባብጦ ሊመለስ ሲል ቶም ሔርበትን ከአንድ ሌላ ሰው ጋር ሆኖ እሱ ወደ ነበረበት አቅጣጫ ሲመጡ አይቶ ጠበቃቸው
“ አንተን ማግኘታችን ጥሩ አጋጣሚ ነው ” አለ ሁልዜም ሲናገር ግልጽና ግድየለሽ የነበረው ቶም ሔርበርት " ቶም የሚስተር ሔር የሥራ ጓደኛ የነበረ የአንድ ዳኛ ሁለተኛ ልጅ ነበር “ ከዚያ የወይን ጠጅህ አንዳንድ ብትለን ትጸድቃለህ ካርላይል ቦሻ ዘንድ ሔደን ነበር ሁሉም ወጥተዋል አሉ » ውሃ ጥም
ግድል አድርጎኛል » ካፒቴን ቶርን ይባላል . . . ካርላይል” አለና አስተዋወቃቸው
ሚስተር ካርላይል ወደ ቤት ይዟቸው ገባ " ሔርበርት ከምቹ ወንበር ተቀምጦ አንድ ሲጋር አቀጣጠለና ለሚስተር ካርላይልም የሲጋሩን ባኮ ከዘረጋለት በኋላ '' ኦ ! ረስቸው ለካ ባመት አንድ እንኳን አታጤስም። ኧረ እመቤት ሳቤላስ እንዴት
ናት ?
“ ያማታል ' አልተሻላትም ” አለውና ሚስተር ካርላይል ወደ ካፒቴን ቶርን ዞረ።
“ይህን አካባቢ ደኅና አድርገህ ታውቀዋለህ ?
“ ኧረ የለም ዌስት ሊን ገና ትናንት መድረሴ ነው "
“ አየህ !.... እሱና ወንድሜ ጃክ በአንድ የጦር ክፍል ነው ያሉት አለ
ቶም ሔርበርት " አብረው ዓሳ እያጠመዱ እንዲሰነብቱ ጃክ ሲጠራው''መጣሁ እንኳል ሳይል ደረሰ ጃክ ደግሞ ለግዳጅ ወደ አየር ላንድ ትቶት ሔደ ስለዚህ እሱም ተመልሶ ሊሄድ እያሰበ ነው።
አሁን ርዕሱ ወዶ ዓሳ ማጥመድ ተለወጠ " ሞቅ ያለ ክርክር ተከፈት " በዚህ ጊዜ ቶርን ስለ አንድ ዓሣ የሞላበት ኩሬ አነሣ ሚስተር ካርሳይል ንግግሩን እንደ ዋዛ አድርጎ ልብ ብሎ አስተዋለው።
" የትኛውን ማለትህ ነው ? ረባዳ ኩሬ የሚባሉ ሁለት የተቀራረቡ ኩሬዎች አሉ።
"ባልሳሳት እስኳየር ቶርፕ መሬት ላይ ያለውን ማለቴ ነው» ምናልባት ከዚህ አምስት ኪሎ ሜትር ያህል ይሆን ይሆናል።
ሚስተር ካርላይል ሣቅ አለና ቦታውን ከዚህ በፊትም የምታውቀው መሰልከኝ ካፒቴን
እስኳየር ቶርፕ ሞቷል ንብረቱ ለሴት ልጁ ባል ተላልፏል ያ
ረባዳ ኰሬ ይባል የነበረውም የዛሬ ሦስት ዓመት ዐፈር ተሞልቷል " ..
“ አዎን አንድ ወዳጄ ሲናግር ስምቸዋለሁ "

👍11❤2
ሚስተር ካርላይል ቀስ በቀስ ንግግሩን ያ ሪቻርድ ሔር ካፒቴን ቶርን ይመጣበት ነበር ተብሎ ወደሚጠረጠረው ወደ ስዌንሰን አዞረው " ያሁኑ ካፒቴን ቶርን
ቦታውን ለአጭር ጊዜ ተቀምጦበት ስለነበር ትንሽ ትንሽ እንደሚያውቀው ነገረው
ይህ ቶርን አለባበስ አሳማሪነቱን የጣት ያንገትና የደረት ጌጥ ማድረጉንና ጠቅላላ አቋሙን ሁሉ ሲያየው ከሪቻርድ ሔር አገላለጽ ጋር ስለ ገጠመ ሚስተር ካርላይል የባርባራ ጥርጣሬ ትክክለኛ መሆኑን አመነበት ሚስተር ካርላይል ላንዳፍታ ትቷችው ወጣ አለና ጆይስን ጠራት።
“ ኧረ እሜቴ ሲጠይቁዎት ነበር ” ጌታዬ "
ለሷ ልክ ሰዎቹ እንደ ወጡ እመጣለሁ ብሏል በያትና አሁን አንቺ አንድ ምክንያት ፈጥረሽ ወደ ሳሎን ግቢ ከትንሹ ሔርበርት ጋር ያለውን ሰውዬ ከዚህ ቀደም አይተሺው ታውቂ እንደሆነ ለመለየት ደህና አድርገሽ አስተውለሽ ውጪ” አለና ጆይስ በትእዛዙ እንዶ ደነገጠች ትቷት ገባ።
ጆይስ ውሃ ይዛ ገባች " ጠርሙሶችን የምታደራጅ መስላ ትንሽ ቆይታ ካስተዋለች በኋላ ወጣች እንግዶቹ እንደ ወጡ ወደ ሚስቱ ከመሔዱ በፊት ጆይስን
ጠርቶ “ እናስ ... ዐወቅሺው ? ” አላት "
ኧረ አዲስ ሰው ነው!”
እንዲያው ዱሮ አይተሺው ታውቂ እንደሆነ ደኅና አድርሽ አስታውሺ
ጆይስ ነግሩ ግራ ገባት ቢሆንም ራሷን በአሉታ ነቀነቀች "
ያ አፊን ፍለጋ ከስዌንስ ይመጣ የነበረው አይመስልሽም ?ስሙ ያው ነው ስለዚህ ሰውየዉም አሱው ሊሆን ይችላል ብዬ ነው "
“ ኧረ እኔ እንጃ ጌታዬ እኔ ካፒቴን ቶርንን አንድ ጊዜ ብቻ ስለ ነበር ያየሁት አሁን ዐውቀዋለሁ ለማለት አልደፍርም " ይኸን ሰውዬ ላየውም ስለዚያኛው ሰውዬ የመጣልኝ ትዝታ የለም " ሰዉዬውን ሳየው ምንም አይቸው የማውቅም አልመሰለኝም "....

👍13
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አንድ
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
.....የሚያንቀጠቅጥ ሀሳብ መጣብኝı ኬሪ ወይም ኮሪ የሆነ ነገር ሊሰብሩ ቢችሉ ቅጣቱ ምን ሊሆን እንደሚችል!.
እናታችን ቃሏን በመጠበቅ መንትዮቹ ከተኙ በኋላ ወደ ክፍላችን መጣች::በጣም ቆንጆ ከመሆኗ የተነሳ ልቤ በኩራት፣ በአድናቆትና በትንሹ በቅናት
አበጠ የለበሰችው ልብስ ጆሮዎቿ ላይ በረጅሙ ከተንጠለጠሉትና ከሚያበሩት የአልማዝና ኤሜራልድ የጆሮ ጌጦች ጋር አብሮ ያንፀባርቃል። ጠረኗ
በምስራቅ ያለ በጨረቃ ብርሀን የደመቀ ሽቶ ሽቶ የሚሽት የአትክልት ስፍራን አስታወሰኝ፡፡ ክሪስ ፍዝዝ ብሎ እሷ ላይ ማፍጠጡ ምንም አያስገርምም::
በከባዱ ተነፈስኩ፡ አምላኬ እባክህ አንድ ቀን… እንደ እሷ እንድመስልና ወንዶች እጅግ የሚያደንቁት ገባ ያለ ወገብ እንዲኖረኝ አድርግ።
ስትራመድ ግራና ቀኝ ያለው የልብሷ ዘርፍ እንደ ክንፍ ከፍና ዝቅ እያለ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዚያ ደብዛዛ ብርሃን ካለው ክፍል ወጣን፡ የእናታችንን ኮቴ
እየተከተልን በሰሜን አቅጣጫ ባሉት ጨለማማ ሰፊ አዳራሾች በኩል መሄድ ጀመርን፡ “ልጅ እያለሁ ትልልቅ ሰዎች ሲደንሱ ለማየት ወላጆቼ ሳያውቁ
የምደበቅበት ቦታ ነበር” ስትል አንሾካሾከች: “ለሁለታችሁ ይጠባችኋል። ግን ተደብቃችሁ ልታዩ የምትችሉበት ቦታ ያ ብቻ ነው: በምንም አይነት ሁኔታ ቢሆን አንድም ድምፅ እንደማታሰሙ እንደገና ቃል እንድትገቡልኝ
እፈልጋለሁ እንቅልፋችሁ ከመጣ ቀስ ብላችሁ ሳትታዩ ወደ ክፍላችሁ ሂዱ እንዴት እዚያ እንደምትደርሱ አስታውሱ:” መንትዮቹ ድንገት ከእንቅልቻቸው ነቅተው ፍርሀት እንዳይስማቸው ከአንድ ሰዓት የበለጠ
እንዳንቆይ አስጠነቀቀችን፡ ምናልባትም እኛን ፍለጋ ሊወጡና አዳራሹ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ሊሉ ይችሉ ይሆናል። እንደዚያ ካደረጉ ምን ሊፈጠር
እንደሚችል እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያውቀው።
በሚስጥር ከስሩ በሮች ያሉት ትልቅ ጠረጴዛ ስር ገባን፡ የማይመችና በጣም ጠባብ ነው፡ ግን ከጀርባው ባለው መስኮት መስል ክፍተት በደንብ መመልከት
እንችላለን፡
እናታችን በፀጥታ ሹልክ አለች።
እኛ ካለንበት በታች ራቅ ብሎ በሚያምር ሁኔታ በሻማ ብርሀን ያጌጠ ክፍል ተመለከትን፡ በህይወቴ እንደዚህ የበዙ ሻማዎች አንድ ላይ ሲበሩ አይቼ
አላውቅም! የሻማዎቹ ሽታ እንዲሁም ብርሃኑ ሴቶቹ ያደረጓቸው ጌጣጌጦች
ላይ ሲያርፍ ያለው ማንፀባረቅ ምትሀታዊና ፊልም ላይ ሲንዴሬላና ልዑሉ የደነሱበትን ቦታ ይመስል ነበር።
በመቶ የሚቆጠሩ እንደ ሀብታም የለበሱ ሰዎች እየሳቁና እያወሩ ነው: ጥግ ላይ ደግሞ ለማመን የሚከብድ የገና ዛፍ ተቀምጧል እጅግ በጣም ትልቅ ሲሆን ባለቀለም ጌጣጌጦች ተደርገውበታል፡ ላዩ ላይ የተደረጉት በመቶዎች
የሚቆጠሩ ወርቃማ መብራቶች አይን ያፈዛሉ በዳንሱ ክፍል ውስጥ ወጣ ገባ እያሉ በትሪዎች ላይ ምግብ ይዘው ትልቅ ጠረጴዛ ላይ ይደረድራሉ፡ ሁሉም
ነገር ውብ፣ የሚያምርና የሚያስደንቅ ነበር ... እናም ከተቆለፈ በር ውጪ ደስተኛ ህይወት መኖሩን ማወቅ ጥሩ ነው።
"ካቲ…” ክሪስ በጆሮዬ እያንሾካሾከ “ከዚያ ጥርት ካለው መጠጥ አንድ ጊዜ ፉት ለማለት ነፍሴን ለሰይጣን እሸጣለሁ” አለ።
የእኔም ሀሳብ ነበር ...
እንደዛሬ ርሀብ፣ ጥማትና መከልከል ተሰምቶኝ አያውቅም: ሆኖም ግን ሁለታችንም ታላቅ ሀብት ሊገዛውና ሊያስገኘው በሚችለው ድምቀት ተገረምን፡ ጥንዶች የሚደንሱበት ወለል በሰም ተወልውሎ እንደ መስተዋት
ያንፀባርቃል፡ ትልልቅ ወርቃማ ፍሬሞች ያሏቸው በክፍሉ ውስጥ ያሉት መስታዎቶች የዳንሰኞቹን ምስል ሲያንፀባርቁ ሲታይ የትኛው እውነተኛ ምስል እንደሆነ እንኳ ለመለየት ያስቸግር ነበር።
እኔና ክሪስ ወጣትና ቆንጆ በሆኑት ጥንዶች ላይ አፍጥጠን ነበር፡ ስለ
ልብሳቸው፣ የፀጉር አሰራራቸውና ስላላቸው ግንኙነት በመገመት አስተያየት እንሰጥ ነበር ከሁሉም በላይ ግን የትኩረት ማዕከል የነበረችውን እናታችንን እያየን ነበር፡ በአብዛኛው ከአንድ ረጅም፣መልከመልካም፣ ጥቁር ፀጉርና ረጅም ፂም ካለው ሰው ጋር እየደነሰች ነበር: የምትበላውንና የምትጠጣውንም
ያመጣላት እሱ ነበር ምግቡን ይዛ ሶፋ ላይ ተቀምጠው መብላት ጀመሩ።በጣም ተጠጋግተው እንደተቀመጡ አሰብኩ። በፍጥነት አይኖቼን ከእነርሱ መልሼ ከትልልቆቹ ጠረጴዛዎች ኀላ ወደ ቆሙት ሶስት ምግብ አብሳዮች
አተኮርኩ አሁንም ምግብ እየሰሩ ነው የምግቦቹ ሽታ ወደኛ ደርሶ የምራቅ እጢዎቻችንን በኃይል እንዲሰሩ አደረጋቸው፡
ከጊዜ ወደ ጊዜ እናታችን ከዚያ ሰው ጋር ትሰወራለች የት ነው የሚሄዱት?ምንድነው የሚሰሩት? እየተሳሳሙ ነው? ፍቅር ይዟታል? ካለንበት ከዚያ ርቀት ላይ ሆነን እንኳ ሰውየው በእናታችን እንደተማረከ መናገር እችላለሁ:
አይኑን ከፊቷ ላይ መንቀል አልቻለም፧ እጆቹም እሷን ከመንካት መከልከል
አልቻለም::
ቀስ ባለ ሙዚቃ ሲደንሱ፣ ጉንጯ ጉንጩን እስኪነካ ድረስ አስጠግቶ ይዟት ነበር ዳንሱን ሲጨርሱ እጁን ትከሻዎቿ ወይም ወገቧ ላይ ያደርጋል። አንድ ጊዜ እንደውም ጡቷን እስከ መንካት ሳይቀር ደፍሯል።
አሁን ይህንን መልከ መልካም ፊቱን በጥፊ ትለዋለች ብዬ አሰብኩ። ምክንያቱም እኔ ብሆን እንደዚያ ነበር የማደርገው: እሷ ግን ዞር አለችና ሳቀች ከዚያ ገፋ አደረገችውና በአደባባይ እንደዚያ እንዳያደርግ ማስጠንቀቂያ
ሊሆን ይችላል የሆነ ነገር አለችው: እሱም ፈገግ ብሎ እጇን ያዘና ወደ ከንፈሩ አስጠጋው ከዚያ አይኖቻቸው ረጅምና ትርጉም ያለው እይታ ተለዋወጡ:
ወይም እንደዚያ እንደሆነ አሰብኩ
“ክሪስ እናታችንን ከዚያ ሰው ጋር አየሀት?”
“አዎ አይቻቸዋለሁ ልክ እንደ አባታችን ረጅም ነው።”
“አሁን ያደረገውን አይተሀል?”
“ልክ እንደሌሎቹ እየበሉና እየጠጡ፣ እየሳቁና እያወሩ እንዲሁም እየደነሱ ነው: አስቢው ካቲ… እናታችን ያንን ሁሉ ገንዘብ ስትወርስ እንደዚህ አይነት
ድግሶች ለገና እና ለልደቶቻችን እንደግሳለን፡ አሁን ያየናቸውን እንግዶች ወደፊት እናገኛቸው ይሆናል። ግላድስተን ላሉት ጓደኞቻችን የግብዣ ወረቀት
እንልክላቸዋለን፡ አቤት! የወረስነውን ሲመለከቱ በጣም ነው የሚገረሙት"አለ፡፡
ወዲያው አያታችን ወደ ዳንስ ክፍሉ ገባች: ወደ ግራም ወደ ቀኝም አልተመለከተችም ለማንምም ፈገግታ አላሳየችም
ቀሚሷ ግራጫ አልነበረም።
እኛን ለማስደነቅ ያ ብቻውን በቂ ነበር ፀጉሯ በሚገባ ተሰርቷል። አንገቷ፣ጆሮዎቿ ክንዶቿና ጣቶቿ በአልማዝና በሩቢ ጌጣጌጦች አሸብርቀዋል።ያቺ አስደናቂ ንጉሳዊ ግርማ ሞገስ ያላት ሴት በየቀኑ የምትጎበኘን አስፈሪ
አያታችን መሆኗን ማን ያምናል?
ፈቃደኛ ባንሆንም አሁንም አሁንም በሹክሹክታ “እጅግ አስደናቂ ሆናለች '' ብለን አመንን
“አዎ በጣም አስገራሚ”
የዚህን ጊዜ ነው የማናውቀውን ወንድ አያታችንን ያየነው!
ወደ ታች መመልከቴ ትንፋሼን ቀጥ አደረገው ያየሁት ሰው በጣም አባቴን ይመስላል አባታችን እስከሚያረጅ ድረስ በህይወት ቢኖር ኖሮ ይህን ሰው
እንደሚመስል ማየት ይቻላል በሚገፋ ወንበር ላይ ተቀምጦ ነበር። ቶክሲዶ ለብሷል። ሸሚዙ ጥቁር ቁልፍ ያለበት ነጭ ሸሚዝ ነበር፡ የሳሳው ወርቃማ ፀጉሩ ነጭ ወደ መሆን ሄዶ፣ በብርሃን ሲታይ ብርማ መስሎ ያንፀባርቃል።
ቆዳው ደግሞ የተደበቅንበት ቦታ ላይ ሆነን በሩቅ እያየነው ስለሆነ ሊሆን ይችላል፣ አልተጨማደደም: እኔና ክሪስ በመደንገጥና በመገረም አንድ ጊዜ ካየነው ጀምሮ አይኖችንን ወዴትም አላንቀሳቀስንም፡

👍37🥰2👏2
አቅመ ቢስ ቢመስልም፣ በስልሳ ሰባት አመት ዕድሜው እንኳን እጅግ ሲበዛ መልከ መልካም ነው: ወዲያውኑ በሚያስፈራራ አይነት ጭንቅላቱን ቀና አድርጎ ወደ ላይ… ቀጥታ እኛ ወደ ተደበቅንበት ተመለከተ: ለአንድ አስፈሪ
ቅፅበት እዚያ መሆናችንን ያወቀ ይመስል ነበር! ከንፈሩ ላይ ትንሽዬ ፈገግታ ይታያል። ጌታ ሆይ! ይሄ ፈገግታ ምን ማለት ይሆን?
እንደ ሴት አያታችን ጨካኝ አይመስልም፡ ነው ብለን እንደምንገምተው አይነት ጨካኝ ሊሆን ይችል ይሆን? ሰላም ሊሉትና ሊጨብጡት ትከሻውን
መታ መታ ሲያደርጉት ለሚመጡ ሰዎች ከሚያሳያቸው የደግነት ፈገግታ የተነሳ ገራገር ይመስል ነበር። የሚገፋ የተሽከርካሪ ወንበር ላይ የተቀመጠ
በጣም የታመመ የማይመስል ሽማግሌ ነበር። ይሁንና እናታችን እንድትገረፍ ያዘዘና ስትገረፍም ያየ ሰው ነው፡ ታዲያ እንዴት ነው ለዚያ ሰው ይቅርታ የምናደርግለት?
“አባታችንን እንደሚመስል አላውቅም ነበር” አልኩት ለክሪስ
"አባታችን ከመወለዱ በፊት አያታችን ትልቅ ሰው ነበር ከሌላ ሴት የተወለደ ወንድም ከማግኘቱ በፊት አግብቶ የራሱ ሁለት ልጆች ወልዶ ነበር ወጣቷን የእንጀራ እናቱን ከትንሽ ልጇ ጋር ከቤቱ ያባረረው ማልኮም ኒል ፎክስወርዝ ያ ነው!”
ምስኪን እናታችን እንደ አባታችን ካለ ወጣት መልከመልካም አጎቷ ፍቅር ላይ በመውደቋ እንዴት እንወቅሳታለን? እሷ እንደገለፀችው ከእንደነዚህ አይነት
ወላጆች ጋር ስትኖር የምትወደውና እሱም የሚወዳት የሆነ ሰው ሊኖራት ግድ ነበር እሱም እንደዚያው፡
በተፅዕኖ ስር ያልወደቀ ፍቅር!
ከማን ጋር ፍቅር እንዲይዝህ መምረጥ አትችልም: ከዚያ ድንገት ሁለት ሰዎች ወደ ተደበቅንበት አካባቢ ሲመጡ ድምፃቸውንና የእግራቸውን ኮቴ ሰማን፡፡
“ኮሪን ምንም አልተወጠችም” አለ አንደኛው የማናየው ሰው፡ “በጣም ቆንጆና በጣም ሚስጥራዊ ከመሆኗ በስተቀር አሁንም በጣም ማራኪ ሴት ናት:”
“ምክንያቱም ሁልጊዜ ስለምትመኛት ነው፡" ስትል አብራው ያለችው ሴት መለሰችለት “ከክሪስቶፈር ፎክስወርዝ ይልቅ አይኖቿን አንተ ላይ አለመጣሏ
ያሳዝናል አሁን አንድ ደህና ሰው አላት ግን እነያ እዚያ ታች ያሉት
ጠባብ አእምሮ ያላቸው ሁለት አክራሪዎች ኮሪን አጎቷን በማግባቷ ይቅር ማለታቸው ተአምር ነው"
“ከሶስት ልጆች አንድ ብቻ ስትቀራቸው ይቅር ማለታቸው ግድ ነው:"
“ነገሮች የሆኑበት መንገድ ግን አይገርምም?” ጠየቀች ሴትዮዋ ከድምጿ ብዙ እንደጠጣች ያስታውቃል፡ “ሶስት ልጆች... ግን የተረገመችው፣ የተፀፀተችው
ብቻ ሁሉንም ለመውረስ በቃች”
በመጠኑ የሰከረው ሰው እንደገና ተናገረ “ኮሪን ሁልጊዜ የተጠላች አልነበረችም።ሽማግሌው እንዴት ይወዳት እንደነበር አታስታውሺም? ከክሪስቶፈር ጋር
እስክትኮበልል ድረስ በእሱ አይን ምንም ስህተት ሰርታ አታውቅም ነበር።ያቺ ተቆጪ እናቷ ለልጇ ምንም ትዕግስት አልነበራትም ምናልባትም ትመቀኝባት ይሆናል ግን በበርቶሎሚዮ ዊንስሎ እጅ ውስጥ ለመውደቅ እንዴት ጣፋጭና ውድ ነች የኔ ብትሆን ኖሮ ... " አለ የማይታየው ሰው በጉጉት
“ያንተ ብትሆን ኖሮ!” ሴትዮዋ ጠረጰዛው ላይ በረዶ ያለበት ብርጭቆ ነገር እያስቀመጠች በሽሙጥ ቀለደች። “ቆንጆ፣ ወጣትና ሀብታም ሴት በእርግጥም ለሁሉም ወንድ ውድ ናት ለእንዳንተ አይነት ሰነፍ ግን በጣም ከባድ ነው አልበርት ዶን፣ አሁንም ሆነ ወጣት ሳለህ ኮሪን ፎክስወርዝ አንተን አታይህም፡ በተጨማሪ አንተ ከእኔ ጋር ተጣብቀሀል” በማይረባ ነገር
እየተጣሉ የነበሩት ጥንዶች ከመሰማት ራቁ፡ ሌሎች ድምፆች ሲመጡና ሲሄዱ ረዥም ሰዓት አለፈ ወንድሜና እኔ ማየት ደከመን በዚያውም ሁለታችንም ወደ መታጠቢያ ቤት መሄድ ፈልገናል በተጨማሪ መኝታ
ክፍሉ ውስጥ ብቻቸውን ስለተኙት መንትዮች ተጨንቀናል አንዳንድ እንግዳ ወዲያ ወዲህ ሲል ድንገት ወደተከለከለ ክፍል ገብቶ የተገኙ መንትዮቹን ቢመለከትሰ? ከዚያ አለም ሁሉ… ወንድ አያታችን ጭምር እናታችን አራት ልጆች እንዳሏት ያውቃል።
በተደበቅንበት አካባቢ ዙሪያ ሰዎች ተሰብስበው ይስቃሉ፣ ያወራሉ፣ ይጠጣሉ
ከአካባቢው ዞር ብለው የመሳቢያውን በር በጣም በጥንቃቄ ለመክፈት ለእኛ
እድል ለመስጠት ዘመናት ወሰደባቸው ከዚያ ማንም ሳያየን ከተደበቅንበት ወጥተን በመጣንበት አቅጣጫ ተጣደፍን፡ ቁና ቁና እየተነፈስንና እያለከለክን
ፊኛዎቻችን ተወጥረው ሳንታይና ሳንሰማ ወደምንኖርበት ወደ ፀጥተኛው ክፍል ደረስን።
መንትዮቹ ልክ ትተናቸው እንደሄድነው በተለያየ አልጋ ላይ ጥልቅ እንቅልፍ ወስዷቸዋል። የደከማቸውና የገረጡ አንድ አይነት አሻንጉሊቶች᎓ ልክ ከረጅም
ጊዜ በፊት በታሪክ መፅሀፍ ውስጥ ያየናቸው የልጆች ስዕሎችን ይመስላሉ።ዛሬ የሚታዩት አይነት ልጆች አልነበሩም ግን ደግሞ እንደዚህ አይቀጥሉም ስል ማልኩ!
“እናታችን በርቶሎሚዮ ዊንስሎን ማግባት የምታስብ ይመስልሃል?” ብዬ ጠየቅኩት
“ምን አውቃለሁ?” መለሰ ክሪስ በግዴለሽነት። “ነገር ግን ሁሉም ሰው ያንን እንደምታደርግ ያስባል በእርግጥም እነሱ ያንን ነገሯን ከእኛ የበለጠ ያውቃሉ።”
ምን አይነት እንግዳ ነገር ነው የሚያወራው፡ እኛ ልጆቿ እናታችንን ከማንም የበለጠ አናውቃትም?
“ክሪስ... ምነው እንደዛ አልክ?”
“ምንም”
“ለምን እናታችንን እኛ ከምናውቃት የበለጠ ሌሎች ያውቋታል አልክ?”
“ሰዎች ብዙ መልክ አላቸው ካቲ፡ ለእኛ እናታችን እናታችን ብቻ ናት።
ለሌሎች ቆንጆ፣ እጅግ በጣም ብዙ ንብረት የመውረስ እድል ያላትና አማላይ ሴት ናት ደማቅ ነበልባል ሆና በምትታየው በእሷ ዙሪያ ብዙ የእሳት እራቶች ቢዞሩ የሚገርም አይደለም”
“ዋው! ይህንን ሁሉ የሚለው በግዴለሽነት ነበር፡ እንደሚሰማው ባውቅም እንኳን ልክ ምንም እንደማይሰማው ያስመስል ነበር
ወንድሜን በደንብ እንደማውቀው አስብ ነበር: ልክ እኔ እንደምሰቃየው ለካ እሱም በውስጡ እየተሰቃየ ነው፡ ምክንያቱም እሱም እናታችን እንደገና እንድታገባ
እንደማይፈልግ አውቃለሁ ጠርጣሪ አይኖቼን ወደሱ አዞርኩ ብቻውን እንደሆነ የተሰማው አይመስልም እናም ደስ አለኝ:
ልክ እንደሱ ለዘለዓለም መልካም ነገሮችን ብቻ የምመለከት መሆን ፈለግኩ።ሕይወት ሁልጊዜ እሳትና ውሀ ታቀርብልኝና አንዱን እንድመርጥ ትስጠኛለች:
ራሴን የተሻለና እንደ ክሪስ ዘለዓለም ደስተኛ ማድረግ አለብኝ። ስሰቃይ ስቃዬን መደበቅ መማር አለብኝ። ልክ እሱ እንደሚያደርገው ኮስተር ማለት
ሳይሆን ፈገግ ማለት መማር አለብኝ፡
እናታችን እንደገና የማግባቷን ጉዳይ ተወያየንበት: አንዳችንም ያ እንዲሆን አንፈልግም እሷ አሁንም የአባታችን ናት ለእሱ ትዝታና ለመጀመሪያ ፍቅሩ ታማኝ መሆን እንዳለባት እናስባለን፡ አዲሱስ ሰው ቢሆን የራሱ ያልሆንነውን አራት ልጆች ይፈልገናል?
“ካቲ!” ክሪስ ጮክ ብሎ ጠራኝ፡ “ይህንን ቤት ዙሪውን ለማየት አሪፍ ጊዜ አይመስልሽም? በራችን ክፍት ነው. አያቶቻችን ምድር ቤት ናቸው... እናታችን ከሰው ጋር ነች: ስለዚህ አሁን ስለ ቤቱ የምንችለውን ያህል
ለማወቅ አሪፍ እድል ነው:"
“አይሆንም!” በፍርሀት ጮህኩ፡ “ምናልባት አያታችን ካወቀችስ? ሁላችንንም ቆዳችን እስኪላጥ ትገርፈናለች።"
“እኔ ሄጄ ልየው አንቺ ባይሆን ከመንትዮቹ ጋር እዚሁ ቆይ፡ አይዞሽ አልያዝም፧ ከተያዝኩ ግን ግርፊያዎቹን ሁሉ የምቀበለው እኔ ነኝ በዚህ መንገድ አስቢው… አንድ ቀን ከዚህ ቤት ማምለጥ ያስፈልገን ይሆናል።
ስለዚህ ማየቴ ጥሩ ነው" የመደነቅ ፈገግታ ከንፈሮቹ ላይ ይታያል ከዚያ ቀጠለ፡፡ “ድንገት ከታየሁ ራሴን እለውጣለሁ::”
“እለውጣለሁ? እንዴት?”

👍34🔥2🥰2
ጣሪያው ስር ያሉትን ልብሶች ረስቻቸዋለሁ ወደዚያ ሄደና በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ብዙም ያልረዘመበትን አሮጌ ሙሉ ልብስ ለብሶ ተመለሰ ከእድሜው
በላይ ትልቅ ይመስላል፡ ሻንጣ ውስጥ ያገኘውን ጥቁር ዊግ በፀጉሩ ላይ አጠለቀ መብራቱ በጣም ከመደበዘዙ ጋር የሚያስቅ አለባበስ ያለው ትንሽ ሰውዬ ይመስላል
ከፊት ለፊቴ ተንጎራደደ ወደፊቱ ሳብ ብሎ የማይታይ ሲጋራ ያዘና መዟዟር ቀጠለ፡፡ በድንገት ፊት ለፊቴ ቆመና የማይታይ ኮፍያ ከጭንቅላቱ ላይ አንስቶ
በአክብሮት ዝቅ ብሎ እጅ ነሳኝ፡ ሳቅኩኝ እሱም ሳቀ። ከዚያ ቀና አለና አሁን የእውነትሽን ንገሪኝ ይህንን ትንሽ ሰውዬ የትልቁ የፎክስወርዝ ዝርያ ነው ብሎ ማን ይጠረጥራል?” “ማንም! ፎክስወርዝን ማን እንደሱ ያየዋል?
ጥቁር የወፍ ጎጆ የመሰለ ፀጉር ያለውና በእርሳስ የተሰመረ የሚመስል ፂም ያለው ገልጃጃ፣ ቀጫጫና ቀውላላ አድርጎ ማን ይጠብቀዋል?”
“እሺ ክሪስ፣ ድራማህን አቁመህ ሂድና የምትችለውን ያህል እይ፤ ግን ብዙ እንዳትቆይ! አንተ በሌለህበት እዚህ መሆን አልፈልግም:” አልኩት
ቀረብ ብሎ በጆሮዬ “ቶሎ እመለሳለሁ የኔ ቆንጆ ስመለስ የዚህን ትልቅ አሮጌ ቤት ሚስጥሮች ሁሉ ይዤ እመጣለሁ:" አለኝና ድንገት ጉንጬን ስሞ አስገረመኝ
ሚስጥሮች? ምን ነክቶታል? ሚስጥሮቹ እኛ መሆናችንን አላወቀም እንዴ?
ታጥቤና ለብሼ ለመኝታ ተዘጋጀሁ: ነጭ ሆኖ ረጅም እጅጌ ያለው የሚያምር ጋዋን ነው የለበስኩት። በጣም ድንቅ ሆኖ የተሰራ ስለሆነ ልክ ስለብሰው ዕፁብ ድንቅ እንደሆንኩ እንዲሰማኝ አደረገኝ
ክሪስ ከረጅሙ ጋዋን ውስጥ አልፎ እየተመለከተ ከላይ ከፀጉሬ ጀምሮ እስከ እግር ጥፍሬ ድረስ ቃኘኝ። ከዚህ በፊት ተናግሯቸው የማያውቁትን ነገሮች አይኖቹ ነገሩኝ፡ እስከ ወገቤ የወረደው ፀጉሬ ላይ አፈጠጠ በየቀኑ በደንብ ስለማበጥረው እንደሚያምር አውቄያለሁ: የተገረመና የፈዘዘ ይመስል ነበር።
እና ፈቅዶ ቢስመኝ ምንም አያስደንቅም: ልዕልት መስዬ ነበር።
“እንደገና እስክታገኚኝ ተጠንቀቂ” ሲል አንሾካሾከልኝ።
ክሪስቶፈር አሁን የሚያስፈልግህ ነጭ ፈረስና ጋሻ ብቻ ነው” አልኩት።
“ደህና ሁኚ፣ አትፍሪ አሁኑኑ እመለሳለሁ” አለኝ እየሳቅኩ አልጋዬ ላይ ወጣሁና ኬሪ አጠገብ ጋደም አልኩ፡ በዚያ ምሽት ስለእናቴና ስለዛ ሰውዬ፣ ስለ ክሪስ፣ ስለ ወንዶችና ስለፍቅር ሳስብ እንቅልፍ ከእኔ ራቀ ከታች የሚሰማውን ሙዚቃ እያዳመጥኩ ቀስ እያልኩ ወደ ህልም አለም ስገባ እጄ አባቴ ገና የሰባት አመት ልጅ ሳለሁ ጣቴ ላይ ያደረገልኝን
ቀለበት ለመንካት ተዘረጋ: ለረጅም ጊዜ አብሮኝ የኖረ ቀለበት… ስረ ነገሬ ከተባለ የወርቅ ሰንሰለት በበለጠ ዋጋ ያለው የእኔ አሸንክታብ፡
መልካም የገና በዓል አባዬ!....

👍19❤9