አቲዬ በዙሪያ ገጠም እጣፋንታዋ ዙራ ዘርፌ ቤት ገባች (ዞሮ ዞሮ መዝጊያው ጭራሮ እያለ
መንደሩ… እውር ቢሽፍት ጓር ድረስ ነው እያለ እሽሟጥጬ.) እንደገና ወተት ማለብ፣ እንደገና
አዛባ መዛቅ፣ እንደገና ጉልበቷን መገፍገፍ ሊያውም ቀጥ ብላ እመቤቷን በማታይበት የሞራል.
መዳሸቅ ተተብትቦ የበደሏትን ይቅርታ ጠይቃ፡፡ የዘርፌ ደግነት ግን በመንደሩ ተወራ::
"መልሳ ተቀበለቻት እኮ ዘርፌ ሆዷ ቂም አይቋጥር…” እየተባል፡፡
አቲዬ አባባ ያገኙላት የቆርቆሮ ቤት ውስጥ እየኖረች፣ ለመንደሩ ሰው ሁሉ የቀን ሥራ እየሰራች
ኑሮዋን ጀመረች፡፡ ዘርፌን በድላ በመመለሷ እንደተማረከ ባሪያ ጉልበቷን ትገፈገፍ ጀመረ፡፡
የመንደሩ ሰው ሁሉ ዳኛ ወንጀለኛው ሁሉ ፈራጅ ሆነ እናቴ ላይ!! የማያሰሯት ነገር አልነበረም።
እነዚህ ባሎቻቸው ከየመሸታ ቤቱ እያነሱ፣ በየመንገዱ እየለቃቀሙ፣ ከየገጠሩ እያመጡ ሰው
ያደረጓቸው…ጊዜ ያነሳቸው ቅሎች ለፍቶ በመኖር፤ አምላክን በማመን በእጆቿ ንፁህ ፍሬ የምትኖር እናቴን ብረት መንፈስ ሰበሩ፡፡
ጊዜ ያነሳው ቅል እንኳን ድንጋይ ብረት ይሰብራል!!
እጠላቸዋለሁ…!!
በባሎቻቸው ገንዘብ እድሜያቸውን የሚገፉ፣ ሰማኒያ ሚባል ህጋዊ ፈቃድ የባሎቻቸውን
ዳረጎት እየተቀበሉ የሚዘባነኑ የስማኒያ ለማኞች፡፡ ሰማኒያ የሚሉት፣ ፍቅር ሲያልፍ ያልነካው
የልመና ንግድ ፈቃዳቸው ሲቀደድ ከአቲ የባሰ አዘቅት ውስጥ የሚወድቁ ሁሉ ሚስኪን እናቴ
ላይ ተዘባነኑባት፡፡
ምነው ይሄ ምንጣፍ እንዳልረባ ነገር እዚህ ተጣለ?” ይላል አንዱ ጎረቤት ወደ አንዱ ጥግ
የዘመን ቆሻሻውን ተሸክሞ ወደ ተጣለ አሮጌ ምንጣፍ እያሳየ፡፡
አየ..አፈር ተሸክም በስብሶ ማን እሱን ይታገላል? ትላለች ባለቤት ተብዬዋ…ትላንት የከሰል ጆንያ ሳይቀር የምታጥብ የነበረች …ከሰራተኝነት ወደ ሚስትነት በአንድ ሌሊት የአልጋ ወለምታ
የተሸጋገረች መሆኗን አገር እያወቀ፡፡
“ግዴለሽም አፀደ ግማሽ ቀን ብትውልበት አባባ ይመስሳል ይላል መካሪው፡፡
አቲዬን ይጠሩና ያዟታል፡፡ ግማሽ ቀን ጭቃ ታጥባለች፡፡ እንዳሉትም አበባ ይመስላል ምንጣፉ፤
አቤት ቤት አያያዝ ! የምንጣፏ ንጣት ብቻ ለመርገጥ ያሳዝናል እኮ እከሊት ! የእሷ ባል
ሚስት አገባሁ ይበል…” ይባልላታል። ተወዝፋ አቲዬን ቁራሽ በማይገዛ ብር መንደር የሚያለብስ ምንጣፍ ያሳጠበች እከሊትን፣ በእናቴ ጉልበት የምስጋና ካባ ይደርቡላታል።
አፀደ በይ እችን ያዥ” ትልና ሶስት ብር ትሰጣታለች፡፡ አቲዬ ተቀብላ ወደ ማደሪያዋ ትመለሳለች
.አትከራከርም፡፡ ይሄንንም እንደብልጠት ይወስዱታል፡፡ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የደሀን
ጉልበት በነፃ በሚጠጋጋ ክፍያ መበዝበዝን እንደብልጠት ያዩታል፡፡
ቀናቸው የተዳረሰ እርጉዝ አሰሪዎች ስላሳ ትራስ ደልድለው በረንዳቸው ላይ ይቀመጡና ቀኗ
የደረሰ እናቴን፣ “በደንብ እሺው እንጂ" እያሉ ልብስ ያሳጥቧታል፡፡ ለዘመናት በስንፍናቸው
ቤታቸው የከመሩትን ቆሻሻ ሲያስፀዷት ይውላሉ፡፡ 'እንኳን ማሪያም ማረችሽ!' የሚል ጠያቂ
ቤታቸውን እንዳይታዘብ…የበከተ ቤታቸውን…ከቅዱስ ዮሐንስ እስከ ቅዱስ ዮሐንስ ውሀ ነክቶት
የማያውቅ መጋረጃቸውን ያሳጥቧታል !! ወይስ ከእርጉዝ እርጉዝ ይለያል፡፡ የደሀ እርግዝና
ቢጨነግፍም እዳው ገብስ ነው ዓይነት ፍዳዋን ያበሏት ነበር እናቴን፡፡
ለምን ላፋች አይደለም የምለው ! ግን የለፋችበትን የላቧን ዋጋ ከልከለዋታል። አፈር ያብላቸውና
የደም ገንዘብ የበሉ ናቸው:: ዳሌያቸውን እያገማሸሩ ወንድ የሚያሳድዱ ሴት ልጆቻቸው አቲዬ
ከእርግዝና ህመም ጋር እየታገለች ያጠበችውን ልብስ የለበሱ እርኩሳን ናቸው…፡፡ ሕፃናት
ልጆቻቸው በየሜዳው ሲንከባለሱ እናቶች በሳምንቱ መጨረሻ ስለሚደክመው የአቲዬ ጉልበት
ሳይሆን ስለሳሙናቸው ነበር የሚጨነቁት፣ 'አንተ ልጅ አረ የሳሙና ጡር አለው' እያሉ፡፡ አቲዬ
ቃል ሳትተነፍስ ማንንም ሳታማርር እስከ ወለደችበት ቀን ድረስ ስትሰራ ነበር፡፡....
✨አላለቀም✨

👍30❤14👎1
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
....ማሪየስ የሆነውን ሁሉ ከጣራ ላይ ተንጠልጥሎ አንድም ነገር ሳይቀረው ተመለከተ፡፡ ሆኖም ልቡ ያረፈው ክፍለ ውስጥ ከተፈፀመው ድርጊት ላይ
ሳይሆን ከወጣትዋ ላይ ነበር፡፡ ነፍስና ሥጋው ከልጅትዋ ላይ ነበር የተፈናጠጠው:: ከክፍሉ ስትወጣ የነበረው አሳብ አንድ ነበር፡፡ ይኸውም ከሄደችበት መከተልና አድራሻዋን ማየት ነው:: እንዲህ በድንገት በአጋጣሚ
አግኝቶአት ሁለተኛ እንድታመልጠው አልፈለገም:: ከነበረበት ቶሎ ብሎ ወርዶ ቆቡን አነሳ፡፡ በሩን ከፍቶ ሊወጣ ሲል አንድ ነገር ትዝ ብሎት ቆም
አለ፡፡ ሚስተር ዦንድሬ ለፍላፊ እንደመሆኑ ምናልባት በወሬ ይዟቸው ቶሎ ከዋናው መንገድ አይደርሱ ይሆናል ሲል አሰበ፡፡ ቀድመውት ሳይወጡ
ቀርተው ድንገት ቢተያዩ ጥሩ እንደማይሆን ገመተ:: ካዩት ምናልባት እንዳለፈው ጊዜ ዘዴ ፈጥረው እንዳይጠፉብት ልቡ ጠረጠረ፡፡ ታዲያ ምን ማድረግ ይሻላል? ትንሽ ከቤት ውስጥ መቆየት! ቢያመልጡኝስ! ማሪየስ
ግራ ገባው:: በመጨረሻ የሆነ ይሁን ብሎ በድፍረት ከክፍሉ ወጣ::
መንገድ ላይ ሰው አልነበረም፡፡ ወደ ውጭ እየሮጠ ወጣ፡፡ ወደ
ዋናው መንገድ እንደደረሰ አንድ ጋሪ ከኩርባው ላይ እጥፍ ሲል በሩቁ ተመለከተ፡፡
ማሪየስ ተመልሶ ከክፍሉ ውስጥ ገባ፡፡ በሩን ወደኋላ ወረወረው::
ሆኖም ገርበብ አለ እንጂ አልተቀረቀረም፡፡ በሩ ተዘግቶ እንደሆነ ለማየት ዞር ሲል የበሩ እጄታ ሲንቀሳቀስ ተመለከተ፡፡ በሩ በዝግታ ከውጭ ተገፋ፡፡
«ማነህ? ምንድነው የምትፈልጉት?» ሲል ጠየቀ፡፡
የሚስተር ዦንድሬ ልጅ ነበረች::
«አንቺ ነሽ እንዴ! ምነው እንደገና መጣሽ? አሁን ደግሞ ምን
ትፈልጊያለሽ?» በማለት ግሳፄ በተሞላበት አንደበት ጠየቃት፡፡
ልጅትዋ በመሽማቀቅ አቀረቀረች:: ጠዋት አሳይቶአት የነበረው
መልካም አቀባበል አሁን በመንፈጉ ግራ ተጋባች:: ከክፍሉ ውስጥ | እንደመግባት የበሩን እጀታ ይዛ እዚያው ከበራፍ ቀረች፡፡ በሩ በግማሽ ገርበብ ብሎአል፡፡
«ግቢያ ታዲያ! ምነው አሁን ተዘጋሽ? ከእኔ የምትፈልጊው ምንድነው?» ሲል በድጋሚ ጠየቃት::
አሳዛኝ ዓይንዋንና አንገትዋን ቀና አደረገቻቸው:: በተኮናፈዘ አንደበት
«መሴይ ማሪየስ፤ አሳብ የገባህና የአዘንህ ትመስላለህ፤ ክፉ ነገር አጋጠመህ እንዴ?» ስትል እየፈራች ጠየቀችው::
«እኔን ነው የምትዪው?»
«አዎን አንተን ነው::»
«ምንም አላጋጠመኝም፤ ምንም አልሆንኩም::»
«እውነትህን ነው?»
«አዎን፧ ምንም ነገር የለም::»
«አላምንህም፤ አንድ ነገር አለ፡፡»
ዝም ብል ይሻላል መሰለኝ::
ማሪየስ በሩን ሊዘጋባት ሞከረ፡፡ ግን እርስዋ አጥብቃ ይዛ ኣላዘጋም አለችው።
«ቆይ እስቲ አትቸኩል።» አለች «ዛሬ ጠዋት ደህና ነበርክ፡፡ በሀዘኔታ ነበር ያነጋገርከኝ፡፡ አሁን ግን ተለወጥክብኝ፡፡ እንደጠዋቱ ብትሆን ደስ ይለኛል የምረዳህ ነገር አለ? አንተን የመርዳት አቅም ካለኝ ያንን ከመፈጸም
ወደ ኋላ አልልም፡፡ ብቻ ምሥጢርህን ሁሉ አካፍለኝ ማለቴ አይደለም፡፡ሆኖም የምረዳው ነገር ካለ ንገረኝ፡፡ እቤት ውስጥ የምሠራው ወይም የምትልከኝ ነገር ቢኖር እዘዘኝ፤ እፈጽማለሁ፡፡»
ልጅትዋ ይህን ስትናገር ማሪየስ ጥሩ አሳብ መጣለት:: ሰው ሲሰምጥ ያገኘውን ሁሉ ለመጨበጥ እንደሚሞክር ሁሉ በመጣለት አሳብ ለመጠቀም
አላመነታም:: ወደ ልጅትዋ ጠጋ አለ፡፡
«ስሚ» ኣላት ጥቂት ፈገግ ብሎ፡፡
በጣም ደስ ብሉአት ጣልቃ ገብታ አሳቡን አቋረጠች፡፡
ምን «አዎን እንደዚህ ፈገግ እያልክ አናግረኝ፡፡ እንዲህ ስትሆን ደስ ይለኛል
«እሺ» ሲል ቀጠለ፡፡ «ከእናንተ ቤት መጥቶ የነበረውን ሽማግሌ ከነልጁ እየመራሽ ያመጣሻቸው አንቺ ነሽ? አይደል?»
«አዎን፤ እኔ ነኝ፡፡»
«ቤታቸውን ታውቂዋለሽ?»
«አላውቀውም፡፡»
«ማወቅ ትችያለሽ?»
«እሱን ነው የምትፈልገው?» በማለት እየተከዘች ጠየቀችው::
«አዎን እሱን ነው የምፈልገው» ሲል መለሰላት:: «ሰዎቹን
ታውቂያቸዋለሽ?»
«አላውቃቸውም፡፡»
«ማለቴ» አለ በችኮላ፤ «ልጅትዋን አታውቂያትም? ግን ከፈለግሽ
ለመተዋወቅ ትችያለሽ፤ አይደል?»
«እነርሱን» በማለት ፈንታ «እርስዋን» በማለቱ አንጀትዋ ተኮማተረ::
«ብረዳህ ምን ታደርግልኛለህ?»
«የፈለግሽውን!»
«የፈለግሁትን?»
«አዎን፤ የፈለግሽውን፡፡›
«ቤታቸውን አገኝልሃለሁ፡፡»
በመተከዝ ወደ መሬት አቀረቀረች፡፡ ወዲያው በሩን ዘግታ ሄደች::
ማሪየስ ብቻውን ሆነ፡፡ ወንበር ላይ ቁጭ እንዳለ ፊቱን በእጅ ሸፍኖ
ክርኑን ከአልጋው ላይ አስደገፈ:: በአሳብ ተውጦ ከዚያው ቀረ:: ቆይቶ ቆይቶ በድንገት ከአሳቡ ባነነ፡፡ የሚስተር ዦንድሬ ጎርናና ድምፅ ቀሰቀሰው::
«እርግጠኛ ነኝ አላልኳችሁም፧ አውቀዋለሁ ብዬ አልተናገርኩም?»
ሚስተር ዦንድሬ ስለማነው የሚያወራው? ማንን ነው ያወቀው?
አባባ ሸበቶን? ቀደም ሲል ያውቀዋል ማለት ነው? ያቺ ልቡን የሰለበችው ልጅና አባትዋ የታወቁ ሰዎች ናቸው ማለት ይሆን? እነማን እንደሆኑ
ድንገት ይፋ አውጥቶ ይነግረኝ ይሆን? እያለ ማሪየስ ተጨነቀ፡፡
ቀደም ሲል ከነበረበትና የእነሚስተር ዦንድሬን ክፍል ወደሚያሳየው ክፍት ቦታ አመራ:: ከላይ ሆኖ የሚስተር ዣንድሬን ቤተሰብ በድጋሚ ያስተውል ጀመር፡፡
የሚስተር ዣንድሬ ቤተሰብ የመጣላቸውን ስጦታ ሲከፍቱ ልብስ በማግኘታቸው እናትና ልጆች አዳዲስ ልብስ ለብሰዋል:: የሚያማምሩ የአልጋ ልብሶች ከወለሉ ላይ ተዘርግተው ተቀምጠዋል፡፡
ሚስተር ዦንድሬ ከውጭ ገባ፡፡ ሁለቱ ልጆች ከእሳት ማንደጃው
አጠገብ መሬት ላይ ቁጭ ብለዋል:: እናትየው መደብ ላይ ጋደም ብላለች።
ሚስተር ዦንድሬ እንደገባ መቀመጡን ትቶ ከወዲህ ወዲያ ተንቆራጠጠ፡፡ፊቱ ላይ የተለየ ገጽታ ይታያል፡፡ ባለቤቱ የሆነው ነገር እውነት ስላልመሰላት
በአንዴ ይህ እውነት ነው? እርግጠኛ ነህ?» ስትል ጠየቀችው::
«እርግጠኛ ነኝ! ከስምንት ዓመት በፊት ነው ያየሁት፧ መልኩ
አልጠፋኝም፤ ገና ሳየው ነው ያወቅሁት:: አንቺ ግን አልመሰለሽም?
«አልመሰለኝም::»
እኔ እኮ በሚገባ እንድታጤኒው ነግሬሽ ነበር፡፡ ቁመቱ መልኩ፧
እድሜው አንድ ነው፡፡ አንዳንድ ቶሎ የማያረጁ ሰዎች አሉ፡፡ ሰው እንዴት ላያረጅ እንደሚችል አይገባኝም፡፡ ድምፁ እንኳን አልተቀየረም፡፡ አለባበሱ
ግን በጣም ተሻሽሎአል፡፡ ሌላ ለውጥ የለውም፡፡ ይህ የጃጀ ርኩስ ሰይጣን፣አውቄበታለሁ!»
ገልመጥ ሲል ሁለቱን ልጆቹ ስላያቸው «ምን ታፈጣላችሁ፤ ውጡ ከዚህ! ዓይናችሁን ያውጣው» ሲል ጮኸባቸው::
ሁለቱ ልጆች ወጥተው ሊሄዱ ሲሉ የትልቅዋን ልጅ እጅ ይዞ «ልክ
በአሥራ አንድ ሰዓት እንድትመለሱ፤ ሁለታችሁንም እፈልጋችኋለሁ» በማለት አስጠነቀቃቸው::
ማሪየስ ኮስተር ብሉ ማጤኑን ቀጠለ፡፡ ሚስተር ዣንድሬና ባለቤቱ ብቻቸውን ቀሩ፡፡ ሚስተር ዣንድሬ ከተቀመጠበት ብድግ ብሎ መንቆራጠጥ ጀመረ፡፡ የተቀዳደደ ሸሚዙንና
ትሪውን አስተካክሎ ወደ ሚስቱ ዞር አለ፡፡
«ስለኮረዳዋ አንድ ነገር ላጫውትሽ?» ሲል ጠየቃት፡፡
«ኮረዳዋ አልክ! እስቲ ምን ይሆን ልስማዋ!» ስትል መለሰችለት።
የሚነጋገሩት ስለኮዜት እንደሆነ ማሪየስ አልተጠራጠረም:: በጉጉት ጆሮውን አቀና፡፡
ሚስተር ዦንድሬ ወደ ሚስቱ ጠጋ ብሉ በሹክሹክታ ለሚስቱ አንድ
ነገር ነገራት፡፡ ምን እንዳላት ማሪየስ አልሰማም፡፡ በመጨረሻ ግን ሰውነቱን ቀና አድርጎ «ይኸውልሽ እርስዋ ናት» ሲል ጎላ ባለድምፅ ተናገረ፡፡

👍25
“ያቺ ልጅ?» ስትል ሚስቱ ጠየቀች፡፡
“ያቺ ልጅ!» ሲል መለሰላት፡፡
ይህን ቃል ስትሰማ የሴትየዋ ፊት ተለዋወጠ፡፡ ቁጣዋ ገነፈለ፡፡
ጥላቻና ቁጣ ተመሰቃቀሉባት:: በጣም ተገረመች::
«ሊሆን አይችልም!» ስትል ጮኸች:: «የእኔ ልጆች የእግራቸው
መጫሚያ ሳይኖራቸው በባዶ እግር ራቁታቸውን እየሄዱ! እንዴት ተደርጎ የሀር ካባ፣ ባለወርቀ ዘቦ ቆብ፣ የአዞ ቆዳ ቡት ጫማ! እስከ ሁለት መቶ ፍራንክ የሚያወጣ ልብስ ለብሳ ልትሄድ! ያቺ ልጅ! ኧረ ተሳስተሃል፡እርስዋ ልትሆን አትችልም:: ይህቺ እንደሆነ ሲያይዋት ጨዋ የጨዋ ልጅ
ትመስላለች:: ምንዋም ዱርዬ አይመስል:: የለም፣ የለም ተሳስተሃል፡፡»
«መስሎሻል፤ ራስዋ ናት፤ ደግሞም ታያለሽ፡፡»
ባልዋ አረጋግጦ ሲነግራት ከተጋደመችበት ብድግ አለች፡፡ :
ያ ድቡልቡልና ግዙፍ አካልዋ የተቆጣች ነብር አመለካከት ያላት አሳማ አስመሰላት፡፡
«ምን!» በማለት ቀጠለች፡፡ «ይህቺ ልጆቼን ሀዘን በተሞላበት ዓይን እያየች ያነጋገረችው ቆንጆ ልጅ ያቺ ዱርዬ ልትሆን! የት አባትዋ፧ አንዴ በጥፊ ብላት ምንኛ አንጀቴ በራሰ!» በማለት ሰውነትዋ በንዴት እየተንቀጠቀጠ ተናገረች፡፡ ልጅትዋ ከአጠገብዋ ያለች ይመስል ልትመታት እጅዋን ዘረጋች፡፡ ሰውዬው ሚስቱ የምትለውን ብዙም ሳይሰማ ከወዲህ ወደ ወዲያ መንቆራጠጡን ቀጠለ፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች ዝምታ በኋላ ግን ተናገረ።
«ከፈለግሽ አሁንም አንድ ነገር ልነግርሽ እችላለሁ፡፡»
«ምን?» ስትል ጠየቀችው፡፡
ቶሎ ብሉ ዝግ ባለድምፅ ጨዋታውን ቀጠለ፡፡
«የእድላችን በር ተከፈተ፡፡»
ሴትዮዋ አፍጥጣ አየችው:: «ይኼ ሰውዬ አበደ እንዴ» ስትል
አሰበች፡፡ እርሱ ግን ንግግሩን ቀጠለ፡፡
«በደምብ አድምጪኝ፡፡ ይህን ተመጻዳቂ፣ ይህን ቱጃር ያዝኩት፡፡
ጥሩ ነው ጉዳዩ አልቆአል፡፡ ሁሉም ነገር በሚገባ ተስተካክሎ ታቅዷል፡፡ ሰዎች እንደሆነ አነጋግሬያቸዋለሁ:: ጀምበር ልትጠለቅ ስትል በአሥራ ሁለት
ሰዓት ገደማ ይመጣሉ፡፡ ይህ ወሮበላ! ስልሣውን ፍራንክ ይዞ ይመጣ የለ አየሽ ነገሩን እንዴት እንዴት አድርጌ እንዳቀናጀሁት? ስልሣ ፍራንካ የቤቱ ጌታ፣ የካቲት 4 የምን ስድስት ወር፣ ሦስት ወር እንኳን አይሞላም:: ብልህ ነኝ አይደል? አየሽ ሰውዬው በአሥራ ሁለት ሰዓት ይመጣል፡፡ በዚያ ሰዓት ጎረቤታችን እራቱን ፍለጋ ይወጣል፡፡ የቤት ጠባቂዎች
እንደሆነ በዚህ ሰዓት ሥራዋን ልትሠራ ወደ ከተማ ትወጣለች፡፡ ግቢያችን ውስጥ ከእኛ በስተቀር ማንም አይኖርም ማለት ነው:: ጎረቤታችን እንደሆነ ከአምስት ሰዓት በፊት ከቤቱ አይገባ! ልጆቻችን ከበር ላይ ቁመው ሰው
መምጣት አለመምጣቱን ይጠባበቃሉ፡፡ አንቺ ደግሞ ትረጂኛለሽ፡፡ ሰውዬው ግን በራሱ ይፈርዳል።»
«በራሱ ላይ ባይፈረድስ?» ስትል ምሽቲቱ ጠየቀች፡፡
ዦንድሬ በንቀት ዓይን እያየ መለሰላት::
«እኛ እንፈርድበታለን፡፡»
ይህን እንደመለሰ ከት ከት ብሎ ሳቀ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲስቅ ማሪየስ አየው፡፡ የፌዝ ሳቅ ስለነበር ማሪየስን አስፈራው::
ዦንድሬ ሳጥኑን ከፍቶ አንድ ያረጀ ቆብ ካወጣ በኋላ በለበሰው ልብስ እጅጌ ጠራረገው፡፡ ጠራርጎ ሲጨርስ አጠለቀው፡፡
«አሁን» አለ፤ «ወደ ውጭ መውጣቴ ነው:: የማነጋግራቸው ሰዎች ይቀሩኛል፡፡ ጥሩ ወዳጆች! ውጥኔ እንዴት እንደሚሠራ ታያለሽ፡ በተቻለ ፍጥነት ቶሎ እመለሳለሁ፤ ቤቱን ጠብቂ፡፡ የዛሬዋ ቀን ሌላ ናት፡፡»
ደረጃውን እያንኳኳ ቶሎ ቶሎ ሲሄድ ማሪየስ ኮቴውን ሰማ። በዚህም ወደ ውጭ መውጣቱን አረጋገጠ፡፡ ወዲያው በአካባቢው የሚገኝ ቤተክርስቲያን የስዓት ደወል ደውሎ ሰባት ሰዓት መሆኑን አበሰረ::.......
💫ይቀጥላል💫

👍18❤1🥰1
#ዶክተር_አሸብር
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
፡
፡
#አምስት
...እኔ የተወለድኩ ቀን ጠዋት አቲዬ አቃጣሪዋ ዘርፌ ቤት ወተት ስታልብ ነበር፡፡ ረፋዱ ላይ
የአንዲት ጎረቤት በርበሬ ስትቀነጥስ ዋለች፡፡ ውጋት ሲጀምራትና ምጡ ሲጫናት ከበርበሬ ቅንጠሳው በኋላ ልብስ ወደምታጥብበት ቤት ለመሄድ እየተዘጋጀች ነበር፡፡ ህመሙ ሲጀምራት ግን መንገዷን ቀይራ ወደ መንደር አዋላጅ አልማዝ ቤት ሄዳ እየፈራች፣ “እትዬ አልማዝ
እያመመኝ ነው፡: ምጥ ነው መሰለኝ…" አለቻት፡፡
“ውይ በሞትኩት መጣሁ ሂጂና ቤትሽ አረፍ በይ…" አለቻት፡፡
አቲዬ እንደታዘዘችው አደረገች፡፡ እዛች እሮጌ ፍራሽ ላይ ተኝታ ምጥ እየናጣት በር በሩን ማየት
ጀመረች፡፡ አልማዝ ግን ወደ አቲዬ አልሄደችላትም፡፡ ምክንያቱም እቲቲዬ ምጥ የተያዘች ቀን፣
ዘርፌ የምትባለዋ አቃጣሪ ባልቴት የአሜሪካ ላሟ ያልታወቀ ነገር በልታ ሆዷ ተቆዝሮና አረፋ
ደፍቃ እየጓጎረች ስለነበር፣ መንደርተኛው ሁሉ ወደዚያው ሄዶ ነበር፡፡ አዋላጇ ኣልማዝም
ቅድሚያ ለወርፌ ላም ሰጥታ ነበር፡፡
አንድ ግብርና የሚሰራ የእንስሳት ህክምና ባለሙያ ተጠርቶ እስከሪብቶ በሚመስል ነገር የላሟን ሆድ ወግቶ ካስተነፈሳት በኋላ ላሟ ነፍሷ መለስ በማለቱ የመንደሩ ሰው ደስታውን በእልልታ
ገለፀ፡፡
በዚህ መሐል እዋላጇ አልማዝ፣ “በሞትኩት ያች ሚስኪን ምን ደርሳ ይሆን?” ብላ ወደ ቤታችን
ተጣድፋ ብትደርስ አቲዩ እኔን አቅፋ አገኘቻት፡፡ የወርቅ ፍልቃቂ የመሰልኩ እኔ፣ በእሳት የተፈትንኩና የጥላቻ እሳት የምትፋ እኔ፣ አላፊ አግዳሚውን የምራገም እኔ በእናቴ እቅፍ ላይ ታሪክ ይወቀኝም አይወቀኝም፣ እናት የተባለች ታላቅ ሀገር ከስግብግብ፣ ከአስመሳይ፣ ከራስ
ወዳድ፣ ከአሽቃባጭ፣ ደሀ ከማይወድ፣ እምነት ከሌለው፣ ሆድ አምላኩ ከሆነ አመንዝራ እና
ጨካኝ ጎረቤት ቅኝ ግዛት የወጣሁ ጀግና እኔ ተወለድኩ !! አገሬ እናቴ አፀደ ናት ! ባንዲራዬም
የእናቴ ቀለም አልባ አሮጌ ቀሚስ !! ድምጿ መዝሙሬ ነው፣ ትዕዛዟ ሕገ መንግስቴ !! እናቴ
አፀደ ወይንም ሞት!! አቲዬ ትቅደም !! አቲዬ ለዘላለም ትኑር!
መዝመሬ፣
ተንቀሽ የኖርሽው ድሮ ከዚህ ቀደም፧
እናቴ አፀደ የደፈረሽ ይውደም !!
በሰሜን ስግብግብ የደሀ ደም መጣጭ ጎረቤቶች፣ በደቡብ ራስ ወዳድ በድሀ እምባ የሚዋኙ
እጋሰሶች፣ በምስራቅ የእናቴን ፀሐይ እንዳትወጣ የሚጋርዱ አስመሳይና ሆዳሞች፤ በምዕራብ
ሚስኪን ሴት ደፋሪዎች እና ትውልድ የሚነዱ ካፖርታሞች…፡፡ ከታች በባዶ እግሯ የምትረግጠው
ምድር፣ ከላይ እግዚአብሔር (የባህር በሯን የሚያዋስናት ሀገር አፀደ ትባላለች - የእኔ አገር እሷ
ናት !!
አፀደ ከሰማይ ዱብ እንዳለ ጉድ ዘመድ የላትም፡፡ እናት፣ አባት፣ አክስት፣ አጎት የላትም፡፡
አልተማረችም ገንዘብም የላትም፡፡ ግን ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ ለሆነ ባለፅጋ አግዚያብሔር እንብና ድፍን የኢትዮጲያ ሃምሳ ብር ያበደረች ልበ ሙሉ ሴት ናት፡፡ እግዚያብሔርም የማንም
ብድር በእጁ ይቆይ ዘንድ አይወድምና ብድሩን ይከፍል ዘንድ እኔን መንገድ አደረገ፡፡ በድፍን ሀያ አምስት ዓመታትም አነፀኝ ደለደለኝ።
እግዚኣብሔር ፈጠነም ዘገየም ወደ እያንዳንዱ ሰው ሕይወት ውስጥ ይመጣል፡፡ ሲመጣ የእግዜርን እርምጃ የእግሩንም ዳና የሚቋቋም መንገድ የሚሰራው መከራ በሚባል ኮንክሪት ነው :: ዙሪያህን የከበበህን ችግርና እልህ አስጨራሽ የሕይወት ፈተና ስታልፍ፣ የእግዜር የመጀመሪያ
እርምጃ ትጀምራለች፡፡ ያኔ ታዲያ ርሀብን ብቻ ሳይሆን ጥጋብንም የምትችል አድርጎ እንዳነፀህ ይገበሀል።
አሰራሩ እንደዛ ነው፤ ሳይሆንም እኔ እንደዛ ነው እላለሁ፡፡ አንተን ከድህነት ማውጣት ብቻ ሳይሆን መጭውን የጥጋብ ዘመንም የሚሸከም ትከሻ እንዲኖርህ አድርጎ ይሰራሀል ካለመንክ
እንደ የዕምነትህ መጽሀፍህን ግለጥ፣ አዱኒያን እንደ ምናምንቴ ንቀው ፈጣሪን ያመኑ፣ የተከተሉ
ሁሉ ሰፈርህ ሕንፃ አቁሞ እንደሚሸልለው እብሪተኛ ሃብታም ባንዴ ሰማይ ጥግ አልደረሱም፡፡
ፈጣሪ ሲሰራህ ቀስ ብሎ ነው፣ ግን መቼም እንዳትፈርስ አድርጎ፡፡ ያኔ ደስ ይልሃል ወደህ ነው ጎንበስ ብለህ ታመሰግናለህ በግድህ አንተ ላለማመስገን ብትጥር እንኳን ስጋህ ያማረ ፍራሸ ላይ ለሽ ሲል፣ በርሀብ የተንሰፈሰፈ አንጀትሀ ውስጥ የጣመ ምግብ ሲጎዘጎዝ፣ በላዩ ላይ ጥሩ ቡና ስትጨምርበት፣ ከምንም በላይ ደግሞ ራስህን ስትገዛና ልብህ በሰላም ሲሞላ፣ እግሲያብሔር ይመስገን ይልሀል አፍህ ከአንተ ትዕዛዝ ውጭ!!
አቲዬ እኔን ከወለደች በኋላ ትንሽ ተስፋ ልቧ ውስጥ አደረ፡፡ አባቱ በልጁ አይጨክንም መቼም
ብላ፡፡ ግን አባት በልጁ ጨከነ፡፡ ቀለመ ወርቅ አባት የመሆን ሞራሉም ብቃቱም የሌለው
ሴሰኛ ሽማግሌ መሆኑን የአቲዬ ልብ ያወቀው ብዙ ቆይቶ ነበር፡፡ ወንዶች ለአገር ዳር ድንበር
እየፎከሩና እየሸለሉ የመዝመታቸውን ያህል አባትነትን ለመቀበል፣ ትዳርንም አሜን! ብሎ
ለመኖር፣ ከነፍሳቸው ጋር የሚገጥሙት ጦርነት ቀላል አይደለም፡፡ ለመውለድ ወንድ መሆን በቂ ነው፡አባት መሆን ግን ታላቅ ጀግንነትን ይጠይቃል፡፡ ቀለመወርቅ ደግሞ ጀግና አልነበረም፡፡ስለዚህ እኔን ልጁን ዶሮ ሳይጮህ ሦስቴ ካደኝ፡፡
አቲዬ የእኔ ብርቱ ግን በሰባት ቀኗ ከአራስ ቤቷ ተነስታ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ ስራዋን
ጀመረች፡፡ “ኧረ ወገብሽ ይጥና” ያላት አልነበረም፡፡ የበሰበሰ ድሪቷቸውን ከምረው ጠበቋት
እንጂ ! 'የምትገርሚ ጠንካራ ልጅ እያሉ ፡፡ እርሳ ቐን ሙሉ አርባ ቀን ሙሉ ተዘፍዝፈው ሊጣቸውን ሲያሻምዱ ኑረው ሲወጡ እንኳን አራስነት ምን ያህል ከባድ መሆኑን እንደማያውቁ ሁሉ፥ አቲዩን በሥራ
ሲያጣድፏት ምንም አልከበዳቸው፡፡
ልጅ ይዛ ሥራ መሥራት ከባድ ነበር ለአቲዬ:: በየቤቱ በረንዳ ላይ እያስተኛች ሳለቅስባት እያጠባችኝ(ምናባቴ እንደሚያስለቅሰኝ እንጃ !)፡፡ አቲዬ እናቴ ብርቱ ሰው ከህይወት ጋር ትግሏን ቀጠለች.…አንድ.. ሁለት..ሦስት...አራት ወር ለአቃጣሪዋ ዘርፌ አቲዬ እየፈራች እንዲህ አለቻት፡
“አትዬ እኔ እንግዲህ እስካሁን ለልጁ አንድ ነገር ያደርጋሉ ብዩ ጠበቅኳቸው እሳቸው ግን
“ማናቸው ልጄ አለች ዘርፈ አካሄዱ አላምር ብሏት ፊቷን አጨፍግጋ፡፡
“ጋሽ ቀለመወርቅ" አለች አቲዬ፡፡
"እህ…ደም እሱ ምን ቤት ነው ባንች ልጅ”
"እትዬ ፈርቼ አልነገርኮትም እንጂ፣ እኔ ሌላም ወንድ ነክቶኝ አያውቅ ተሳቸው ነው :"
“ወዲያ ዝም በይ…ምን ትላለች
እቺ..የተከበረ ሰው አናት ዘሎ ፊጥ ማለት ምን ይሉት ብልግና
ነው?! ሁላተኛ እንዲህ ያለ ነውር ስትተነፍሽ ብሰማ ውርድ ከራሴ፡፡ ሂጂ አሁን ወዲያ ያው
ደሞዝሽ!"
ብላ አስር ብር ወረወረችላት፡፡ ስራዋ አስደንግጧት እንጂ ሳምንት ነው ገና ደሞዝ ለእቲ ከከፈለቻት፡፡
ቀለመወርቅ ይህችን ጭምጭምታ ሲሰማ ተንኮሉን ጀመረው:: አቲዬን ከመንደሩ ሊነቅል እንቅልፍ አጣ፡፡ አቲዬ ለአባ እስጢፋኖስ ሽምግልና ላከችበት፡፡
“ቀለመወርቅ መቼስ ዘር አይጣላም፡፡ ነገ የት እንደሚደርስ አንድ ፈጣሪ ነው የሚያውቀው፡፡
ሌላው ቢቀር የወተት መግዣ እንኳን ስጣት መቼስ እሷ ጋር እንዲህ ሠራህ፣ እንዲህ አደረግክ
ለማለት ባልደፍርም ልጁ ቆርጠው የጣሉት አንትን ነው…”

👍31❤1
“ምን ማለተዎ ነው አባ.…እኔን በእንዲህ ያለው ቅሌት እንዴት ይገምቱኛል?” ብሎ በአባ ከፉኛ
ተቆጣ፡፡ ቀለመወርቅ ሽምጥጥ አድርጎ ካደ !! መቸም ቁርጥ አድርገው የጣሉት ሰይጣን ነው፤
ይባስ ብሎ ከዘርፌ ጀምሮ መንደርተኛው ሁሉ አቲዬን ሥራ ማሠራቱን እንዲያቆም ተንኮል
ይሸርብ ጀመረ ተሳካለት፡፡ አንድ መንደር ሕዝብ አንዲት ደሀ ላይ እመፀ፡፡ ቀለመወርቅ እና
ዘርፌ ነበሩ የተንኮል ድሩ ፈታዮች፡፡
“ነገ ባልሸን ስሙን ብታጠፋውስ.. ሰው እንደሆነ አንች ቤት ልብስ ማጠቧን፣ ገባ ወጣ ማለቷን
ነው የሚያየው” ይሏታል ለአንዷ አሰሪ፡፡
አውነትዎትን ነው እትዬ ዘርፈ ለኣቶ ቀለምወርቅ ያልተመለሰች እች…" ትላለች፡፡ በቃ አቲዬን
በሰበብ አስባብ ታባርራታለች፣ “ውይ ትላንት ልጆቹ አጠቡት ልብሱን” በቃ !
አታዩ ግራ ገባት። እኔን አዝላ ስትንከራተት ትውልና የሚሠራ ሥራ አጥታ ማታ ቤት ትመሰላለች፡፡ቤት ውስጥ የነበረችው ርጋፊ በሶ ብቻ ነበረች፡፡ ወደ ማታውቀው መንደር እየሄደች፣ የሚታጠብ ልብስ አላችሁም ትላለች፡፡
"የለንም"
"ወፍጮ የሚሄድ እህል በርበሬ ካለ.”
“የለም…የለም” ይላሉ ያዘለችውን ልጅ እያዩ፡፡
እቲዬ ተንከራተተች፡፡ በመጨረሻም ያላት አማራጭ ልጇ በርሀብ ከሚሞት ቀለመወርቅ እግር
ላይ ወድቃ ይማሩኝ!” ማለት ነው፡፡ ቀለመወርቅ - ቀጣፊው ነብይ እሱ በመንደሩ “ይታሰር"
ያለውን ሥራ ሰይጣን በድፍን አዲስ አበባ ያስረዋል፡፡ አቲዬ ይቅር ይበሉኝ ልጁ የእርስዎ
አይደለም ሲቸግረኝ ነው ክፉ የተናገርኩት” ልትል ወደ ቀለመወርቅ ቤት ገሰገሰች፡፡
ለከፋቱ ደግሞ ዓይን የለ አፍንጫ፣ ፀጉር የለ ጆሮ እኔ ቁርጥ ቀለመወርቅን ነበር የምመሰሰው፡፡
ለክህደት የማልመች ጉድ፡፡ ቀለመወርቅ ብቻውን የወለደኝ ይመስል አቲዪን የሚመስል አንዲት ነገር የለኝም፡፡ የቀለመወርቅን የልጅነት ፎቶ ቁጭ!! ቢሆንም "ይቅር በለኝ ልጅህ አይደለሁም ስል በእናቴ ጀርባ ላይ ወደ ኣባቴ እየሄድኩ ነው -አባት ያሳጣውና፡፡ ይሄ የውሻ ልጅ !
ቀለመወርቅ የእድር ዳኛው ጋር ተነጋግሮ አቲዩን ከማደሪያዋ ሊያፈናቅላት ሲዶልት እንዳመሸ
የዘርፌ ሠራተኛ ለአቲዩ ሹክ ብላት ነበር፡፡ ለይቅርታ የባስ ያሮጣት አንዱ ጉዳይም ይሄ ነው፡፡
ጀግነት ጥግ እንደሌለው ሁሉ ከፋትም መጨረሻ የለውም፡፡ ይሄ ከፉ አቲዬን ማሳደዱን በትጋት
ተያይዞት ነበር፡፡ እናም አቲዬ ይቅርታ ልትጠይቅ፤ “ማረኝ ጌታዬ ልትለው ወደ ቤቱ ሄደች።
ወዳጄ እግዜር ይቅርታ ይወዳል ማለት 'ማንም ጥጋበኛ እግር ስር እየሄድክ እንድትደፋ ይሻል
ማለት አይደለም፡፡ አቲዬ የእኔን የልጄን ነፍስ ለማትረፍ ራሱን በፈጣሪ ቦታ አስቀምጦ ይቅርታ
ሲጠየቅ የታዘጋጀው ካፖርታሙ ቀለመወርቅ ቤት ልክ በሩ ላይ ስትደርስ እና የግቢውን በር
ልታንኳኳ እጇን ስታነሳ፣ እግዜር “ተመለሽ” አላት፡፡ ያው እንግዲህ እግዜር ሲናገር በሰው
አይደል…፡፡
የእድር ለፋፊው ጉልማው እሳት ጎርሶ እሳት ለብሶ አቲዬን ከኋላዋ በቁጣ ጠራት፡፡ በስሟ
አይደለም፣ "አንች..አንችን እኮ ነው፡፡ ምን ያለችው ናት ጃል” እያለ፡፡ አቲ እየተጣደፈ ወደ
እርሷ የሚመጣውን ለፋፊ ቁማ ጠበቀችው፡፡ እጠገቧ ሲደርስ፣ "ምን መሆንሽ ነው እንች ሴትዮ
የአዙሪት ቅጠል ረግጠሻል እንዴ?” አለ፡፡
“ምነው?” አለች ግራ ገብቷት፡፡
“ምነው ትለኛለች እንዴ በይ ነይ አሁን፡ እቃ ማስቀመወጫ ቤቱን ክፈችላቸው፡፡ ሰው ሞቶ ድንኳን ልናወጣ ብንል ቁልፍ ይዘሽ ጠፋሽ፡፡ አገር ተረፈ እንዴ፣ ያልኳተንኩበት የለም አንችን
ፍለጋ” አለ በማማረር፡፡ አቲዬ ቁልፍ ልትሰጠው አስባ አንድ እቃ ቢጠፋስ ብላ ሰለፈራች
የሰውየውን የማያቋርጥ ድንፋታ እየሰማች ይቅርታው ይቆየኝ ብላ ወደ እድሩ እቃ ማስቀመጫ
ቤት ተመለሱ፤ ሰፋፊው መንገዱን ሙሉ እየነተረካት ነበር አቲዬን፡፡
“እግር ተረፈኝ እንዴ ዘርፌ ቤት፣ ከዘርፌ ቤት ጀሚላ ቤት፣ ጀሚላ 'ወደ ላይ ሄደች ብትለኝ
ዝናሽ ቤት፣ ዝናሽ. አንዳንዱ ሰው አያባራም፡፡ ከእሱ ያነሰ ሰው ያገኘ ሲመስለው ሌሎች ያሉትን ሁሉ ይዘረግፋል፡፡ ሌሎች በናቁት ልክ ሊንቅ ይፍገመሞማል፡፡
እቃ ቤቱ ሲደርሱ ብዙ ሰዎች ተሰብስበው ነበር፡፡ ነጭ የእቃ መጫኛ መኪናም ቆማለች::
መኪናዋ ጎን ነጠላዋን ያዘቀዘቀች ሴት፣ ጀርባዋ ላይ ፎጣ ጣል ያደረጎች ፀጉሯን በሻሽ አስራ
ከቀሚሷ ስር ቱታ ሱሪ፣ የቱታውን ጫፍ ካልሲዋ ውስጥ ጠቅጥቃ ነጭ ሸራ ጫማ የተጫማች
ደልደል ያለች ቀይ ወይዘሮ ቆማለች፡፡ (የአዲስ አበባ ሴቶች ሀዘን ማካበድ ይችሉበታል።
ትጥቃቸው ሲታይ ዘመቻ የሚሄዱ እኮ ነው የሚመስሉት፣ የሟችን ነፍስ ሊያስመልሱ ያሰቡ
የከተማ አርበኞች)
እች ከራስ ሻሽዋ እስከ እግር ካልሲዎ የነገርኳችሁ ወይዘሮ እጥፍ ወርቅ ትባላለች፡፡ ዋናው
መንገድ ላይ ወደ ግራ ታጥፎ ከሹልቃ ክትፎ ቤት አጠገብ ያለው ባለ ሁለት ፎቅ ሆቴል የእርሶ
ነበር፡፡ ጋሪ መቆሚያው አጠገብ ነዳጅ ማደያው ኋላ ያለው ሰፊ ግቢ መኖሪያ ቤቷ ነው፡፡ እና
እች ሀብታም ሴት፣ አቲዬ ተጠርታ ከመድረሷ በፊት በወሬ ወሬ፣
“ዘበኛው ነው የጠፋው ?” ተላለች፡፡
“አይ እዚህ የምትኖረው ልጅ ናት” አላት የእድሩ ሊቀመንበር፡፡
“እዚህ መጋዘን ውስጥ ሰው ይኖራል ያውም ሴት ልጅ” እለች ከልቧ ደንግጣ፡፡
በቆርቆሮ ቤቱ ዙሪያ የሽንት መሽኝያ፡ ቆሻሻ መድፊያ ቦታ ሲሆን፣ እዛ አካባቢ ለደቂቃ መቆም እንኳን ከርፋቱ አይጣል ነበር፡፡ በቤቱ ጥግጥግ ሳርና ቅጠላቅጠል አብቅሎበት መቃብር ቤት አስመስሎታል፡፡ ጣሪያውም ላይ ሀረግ ተጎዝጉዟል፡፡ በቀንም የሚያስፈራ ቤት ነበር እንኳን በሌሊት፡፡
አቲዬ ስትደርስ የሴትዬዋ ድንጋጤ እና ሀዘን ጨመረ፡፡ ከጎኗ ለቆመው ሰው፣ “ጭራሽ ሕፃን ልጅም ይዛ ነው እዚህ የምትኖረው?" አለችው::
እዚሁ ነው እኮ የወለደችው¨ አላት የእድሩ ሊቀመንስሩ፡፡ ሴትዩዋ አንጀቷ ተንሰፈሰፈ፡፡ ቤቱ
ሲከፈት እች ሴት ጉዱን ልየው ብላ ወደ ውስጥ ተራመደች፡፡
አትዩ አጥናፍ ወርቅ አረ አቧራ ነው ጉንፋን ያስይዝሻል እያሉ ተንጫጩ ያእድሩ ሰዎች፡፡ አፍንጫ ያላት
ፍጥረት እቺ ሴት ብቻ ይመስል። ወይዘሮ እጥፍ ወርቅ ግን ወደ ውስጥ ገብታ የአትዬንና የእኔን መኝታ ተመለከተች። የተበሳሳውን የቤቱን ግድግግዳና ጣርያ በታላቅ ሀዘን ቃኘች በራሷ ዓይን ሳይሆን በእግዜር ዓይን፡፡ እናም ሁለት ጊዜ እስነጠሰችና አቲዩን እንዲህ አለቻት
አሁኑኑ የምትፈልጊውን እቃሸን መኪና ላይ ጫኝ፡፡ እኔ ቤት ትኖሪያለሽ፡ ማነህ ና አግዛት
አለችው የሕድሩን ሀላፊ፡፡ ዕቃችን የቆመችው መኪና ላይ ተጫነ፡፡ (ወጉ አይቀር ዕቃ ልበል
እንጂ) የእድር ለፋፊው ማውራቱን አላቋረጠም፣ ያንች ዕጣ ፋንታ እንደ መብራት ሊበራ እኔ
ካላምስት ሳንቲም እንዲህ መኳተን…ነገ ሰው ብትሆኝ አንድ ዋንጫ ጠላ አትይኝም፡፡ አውቀዋለሁ እጄ አመድ አፋሽ ነው፡፡ አገር ቀረኝ እንዴ፣ ዘርፌ ቤት የለችም ሲሉኝ. እንደ አዲስ ጀመረ፡፡...

❤17👍15
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_አራት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
....ደረጃውን እያንኳኳ ቶሎ ቶሎ ሲሄድ ማሪየስ ኮቴውን ሰማ። በዚህም ወደ ውጭ መውጣቱን አረጋገጠ፡፡ ወዲያው በአካባቢው የሚገኝ ቤተክርስቲያን የስዓት ደወል ደውሎ ሰባት ሰዓት መሆኑን አበሰረ::
ማሪየስ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሄዶ ተረኛ መኰንን እንዳለ ጠየቀ
መኮንኑ አለመግባታቸው ተገለጸለት:: ሆኖም አስቸኳይ ከሆነ ዋናውን አዛዥ ማነጋገር እንደሚችል ተነገረው፡፡
«አስቸኳይ ነው» አለ ማሪየስ፡፡
የቀኑ ዘበኛ ወደ ዋናው አዛዥ ቢሮ አመላከተው፡፡ ዋናው ኃላፊ
ከቁመቱ ዘለግ ያለ ጢማምና ቁጡ ሰው ነው: ሲያዩት ከሞት
ይበልጥ ያስፈራል ወፍራምና ረጅም ካፖርት ለብሷል ፊቱ ክብ ሆኖ ሪዙ ላይ ሽበት ጣል ጣል አድርጎበታል አፍጥጦ ሲያይ ወደ ውስጥ የገባውን ኪስ የሚገለብጥ ይመስላል:: ጠቅላላ ሁኔታው ከዦንድሬ የተለየ አልነበረም ሆኖም የሕግ ስው በመሆኑ ብቻ ከተኩላ ውሻን ማየት እንደሚሻል ዓይነት ትርኢት ነበር ለማሪየስ፡፡
«ጉዳይህ ምንድነው?» ሲል አክብሮት በተለየው አነጋገር ጠየቀው:
«እኔ እንኳን የፈለገሁት የእለቱን ተረኛ መኰንን ነበር፡፡»
«አልመጣም እሱ ፤በእርሱ ምትክ ጉዳይህን እኔ ልፈጽምልህ
እችላለሁ፡፡»
«ጌታዬ ትልቅ ምሥጢር ነው፡፡
«ተናገራ ታዲያ፡፡»
«እና ደግሞ በጣም አስቸኳይ ነው፡፡»
«ይሁና አሳብህን ቶሉ ልስማው፡፡»
ዋናው አዛዥ ይህን ተናግሮ ዝም አለ፡፡ ከጥቂት ጊዜ ጨዋታ በኋላ
ከማሪየስ ሳይሆን ከአሰረው ከረባት ጋር ይነጋገር ይመስል አዛዡ እንዳቀረቀ
«መቼስ መጠንቀቅ ያስፈልጋል» ብሎ ከተናገረ በኋላ መልሶ ዝም አለ:
«ቁጥር 50 52 ፤ ሰፈሩን አውቀዋለሁ፡፡»
‹‹ምን ማድረግ ይቻላል?» ሲል ማሪየስ ጠየቀ፡፡
«ያልካቸው ሰዎች ትልቁን በር የሚከፍቱበት ቁልፍ አላቸው! አንተስ አለህ?»
«እነሱም አላቸው፤ እኔም አለኝ፡:››
‹‹ቁልፉን አሁን ይዘኸዋል?»
«ይዤዋለሁ:፡»
«ስጠኝ» አለ ዋናው አዛዥ::
ማሪየስ ቁልፉን ከኪሱ አውጥቶ ሰጠው፡፡
«የነገርክዎት ነገር ካመኑበት ኃይል ይዘው ቢመጡ መልካም ነው፡፡
ዋናው አዛዥ እንደ መናደድ፧ እንደ መብሸቅ ብሎ ማሪየስን ቀና ብሎ
አየው፡፡ ‹‹ልጅ ለእናትዋ ምጥ አስተማረች» ዓይነት ሆነበት፡፡ ቢሆንም ነገሩ?
ናቅ አድርጎ በመተው ከካፖርቱ ግራና ቀኝ ኪስ ሁለት ሽጉጥ አወጣ:
ሁለቱንም በችኮላ ለማሪየስ ሰጠው።
«ያዛቸውና ወደ ቤትህ ተመለስ፡፡ ክፍልህ ውስጥ ተደበቅ፡፡ ስትገባ
ባያዩህ ጥሩ ነው ወደ ወጭ ወጥቷል ብለው እንዲያስቡ ድምፅህን አታሰማ፡፡ ሽጉጦቹ ጥይት አለባቸው:፡ እንደነከረከኝ ከሆነ የሁለታችሁን ክፍል የሚያገናኘው ግድግዳ ቀዳዳ አለው፡፡ ሰዎቹ መጥተው ከክፍሉ
ውስጥ ከገቡና ነገሩ አንተ ባልከው ዓይነት ሲጀመር አንድ ጊዜ ተኩስ ግን እንዳትፈጥን ወይም እንዳትዘገይ:: ጥሩ ሰዓት ነው በምትልበት ጊዜ ነው
የምትተኩሰው:: ከዚያ በኋላ የእኔ ጉዳይ ይሆናል፡፡»
ማሪየስ ሽጉጦቹን ይዞ ለመውጣት እጁን ከበሩ እጄታ ላይ እንዳሳረፈ ዋናው አዛዥ ያናግረዋል፡፡
«በነገራችን ላይ፣ ከአሁን ጀምሮ እስከ ማታ ብትፈልገኝ እኔ ከዚሁ
ስለምሆን ራስህ ልትመጣ ወይም ሰው ልትልክብኝ ትችላለህ፡፡ ከመጣህ ዣቬር ብለህ ጠይቅ::»
ማሪየስ እጅ ነስቶ ወጣ፡፡
የማይደርስ የለም ፤ ሰዓቱ ደረሰ፡፡ ደመና ስለነበረ ገና በአሥራ ሁለት
ለዓይን ያዝ ማድረግ ጀምሮአል፡፡ ማሪየስ ወደ 50 52 ተመለሰ፡፡ ትልቁ በር ክፍት ነበር፡፡ ቀስ ብሎ ድምፅ ሳያሰማና ማንም ሳያየው ከክፍሉ ገባ፡፡ካልጋው ጫፍ ላይ ተቀመጠ፡፡ ልቡ በኃይል ይመታ ጀመር፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ምን ሊሆን እንደሚችል ታወሰው፡፡ በአንድ በኩል የወንጀል
ሙከራ ሲደረግ በሌላ በኩል ፍትሕ ሲሰፍን ታየው:: ልቡ አልፈራም፡፡ የሕይወት አጋጣሚን መጋፈጥ ደስ እንደሚለው እንደማንኛውም ሰው እርሱም ደስ አለው:: የተወጠነው ነገር ሕልም እንጂ እውነት አልመሰለውም::
ጥቂት ደቂቃዎች አለፉ፡፡ ማሪየስ በር ሲከፈት ሰማ፡፡ ሁለት ልጆች
በር ከፍተው ሲገቡና አባታቸው ሲጮህባቸው አዳመጠ፡፡ ቀጥሎ የብዙ ሰዎች ድምፅ በሩቁ ተሰማ፡፡
«ስሙ ልጆች፤ አንዳችሁ በላይኛው አንዳችሁ በታችኛው በር በኩል ሆናችሁ የሚመጣ ሰው ካለ ተጠባበቁ፡፡»
«በዚህ ብርድ በባዶ እግራችን ከውጭ ልንቆም» በማለት ትልቅዋ
ልጅ አጉረመረመች::
«ነገ ምን የመሰለ ጫማ ትገዢያለሽ» ሲል አባትዋ መለሰላት፡፡
ማሪየስ ከለመደበት ሥፍራ ወጥቶ መጠባበቅ እንዳለበት ገመተ፡፡
ቀዳዳው ከነበረበት አካባቢ ወጥቶ ቁጭ አለ፡፡ ወደ እነሚስተር ዦንድሬ ክፍል ተመለከተ፡፡
ከክፍሉ ውስጥ ከሰል ተቀጣጠለ እንጂ ሌላ ብርሃን አልነበረም:: ከበሩ አጠገብ ረጅም ገመድና ሁለት ወፍራም የብረት ዱላዎች ተቀምጠዋል፡፡በኋላ ሻማ አያያዙ፡፡
ሚስተር ዦንድሬ ፒፓውን አያይዞ ከወንበር ላይ ቁጭ አለ፡፡ ባለቤቱ ዝግ ባለ ድምፅ ታናግረዋለች:: በድንገት ዦንድሬ ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ::
«በነገራችን ላይ በዚህ ብርድ ሰዎቹ በጋሪ እንጂ በእግራቸው
አይመጡም፡፡ ታዲያ አንቺ ምን ማድረግ ያለብሽ ይመስልሻል? ወዲያው የፈረስ ኮቴ እንደሰማሽ ቶሎ ብለሽ ትወጪና ለሰዎቹ ሰላምታ ሰጥተን በፍጥነት እቤት ይዘሻቸው ትመጫለሽ፡፡ ከዚያም «ቤት ለእንግዳ» በማለት
ካስገባሻቸው በኋላ ቶሎ ብለሽ ወደ ጋሪው በመመለስ ሂሣቡን ከፍለሽ ታሰናብቺዋለሽ:: እሺ?»
«የሚከፈለው ገንዘብ የት አለ?» ስትል ሴትዮዋ ጠየቀችው::
ዠንድሬ ኪሱን ዳበስ ፤ ዳበስ በማድረግ አምስት ፍራንክ ሰጣት::
«ምንድነው እርሱ?» ስትል ጠየቀች፡፡
ዛሬ ጠዋት ጎረቤታችን የሰጠን ገንዘብ ነዋ! አሁን እንግዲህ ቶሎ
ብለሽ ወደ በሩ ሄደሽ ብትጠባበቂ ይሻላል፡፡ የለም፤ አሁኑኑ ቶሎ ሂጂ፡፡»
ትእዛዙን ተቀብላ ቶሎ ወጥታ ሄደች:: ዦንድሬ ብቻውን ቀረ፡፡
የእሳት ማንደጃው፤ ጠረጴዛውና የቤቱ ሁለት ወንበሮች ማሪየስ
ከሚያይበት ቀዳዳ ትይዩ ነበሩ፡፡ አካባቢው በጣም ጭር ስላለ ማንኛውም ድምፅ በቀላሉ ከሩቅ ይሰማል፡፡
ዦንድሬ በአሳብ በመዋጡ ፒፓውን መማግ እንዳለበት ረስቶ እሳቱ ይጠፋል፡፡ እጁን ዘርግቶ የጠረጴዛውን ኪስ ሳበ፡፡ ከኪሱ ውስጥ የነበረውን ጩቤ አነሳ፡፡ ስለት እንዳለው በአውራጣቱ ሞከረው:: በኋላ መልሶ ከጠረጴዛው ኪስ ውስጥ አስቀመጠውና መሳቢያውን መልሶ ዘጋው::
ማሪየስ ደግሞ ከቀኝ ኪሱ ውስጥ የነበረውን ሽጉጥ አውጥቶ ቃታውን ስቦ ያዘው:: ቃታውን ሲስብ ሽጉጡ ድምፅ አሰማ፡፡
ዦንድሬ ደንግጦ ከተቀመጠበት ብድግ አለ፡፡
‹‹ማነህ?» ሲል ጮኸ፡፡
ማሪየስ ትንፋሹን ያዝ አደረገ፡፡ ዦንድሬ ጆሮውን አቅንቶ አዳመጠ፡፡ ከዚያም ብቻውን ይስቅ ጀመር፡፡
«ምን ጅል ነኝ! የኮርኒሱ እንጨት ድምፅ መሆኑን ማወቅ እንዴት
ተሳነኝ!» ሲል ዦንድሬ ራሱን ነቀፈ::
ማሪየስ ሽጉጡን እንደያዘ ቀረ
ልክ አሥራ ሁለት ሰዓት ስለሆነ በአካባቢው የሚገኘው ቤተክርስቲያን ደወል ተደወለ፡፡ ሚስተር ዦንድሬ የሚጠብቃቸው ሰዎች ከመጡ ብሎ የቤቱን በርና መስኮቶች ዘጋጋ፡፡ ይበራ የነበረውን ሻማ እየተመለከተ ከቤት ውስጥ ይንቆራጠጥ ጀመር፡፡ መንቆራጠጥ ሰልችቶት ከወንበር ላይ ቁጭ አለ፡፡ ወንበር ላይ እንደተቀመጠ የቤቱ በር ተከፈቱ:: የመጣችው ባለቤቱ

👍16❤1👏1
«ልግባ» ስትል ጠየቀችው::
«ምን ማለትሽ ነው? ግቢ እንጂ» ሲል መለሰላት::
አባባ ሸበቶ ተከትሉአት ገባ፡፡ አራት ልዋ ከጠረጴዛው ላይ አስቀመጠ፡፡
ዦንድራ ከጠየቀው ገንዘብ በጣም የላቀ ነበር::
«ይህን ገንዘብ ላልከው የቤት ኪራይና ለአንዳንድ ጉዳይ ይሆናችኋል፡፡
ወደፊትም ለሚሆነው ነገር እንረዳዳለን::»
«የሰማዩ ጌታ ዋጋዎን ይክፈልዎ፧ ባለውለታዎ ነን፡፡ ያልታሰበ
እንጀራ ይስጥዎት» አለ ሚስተር ዦንድሬ ሚስቱን በዓይኑ እየገሰጸ::
ቀደም ሲል የተነጋገሩትን እንድትፈጽም በዓይኑ እየገሰጻት ነበር፡፡
የተነጋገሩት ተገቢውን ሂሣብ ከፍላ ባለጋሪውን እንድትሽኝ ስለነበር ይህንኑ ለማድረግ ከክፍሉ ወጣች:: ብዙ አልቆየችም ቶሎ ተመለሰች::
ወደ ባለቤትዋ ጆሮ ጠጋ ብላ በሹክሹክታ ተሸኝቶአል» አለችው::
ኃይለኛ ዝናብ ይዘንብ ስለነበር ጋሪው ሊሄድ አልተሰማም::
እርስዋ ወጥታ ሳለ ዦንድሬ ለአባባ ሸበቶ ወንበር አቀረበለት ፤
እርሱም ከእንግዳው ትይዩ ተቀመጠ፡፡
በዝናቡ የተነሣ አካባቢው በጣም ጭር ብሎአል፤ ጊዜውም ጨልሞአል። አልፎ አልፎ ኃይለኛ መብረቅ ስለነበር በጣም ያስፈራል:: ሁለቱ ወንዶች
ገጽ ለገጽ እየተያዩ ተቀምጠዋል:: ሴትዮዋ ጥግ ይዛ ቆማለች : ሁለቱ
ሴቶች ልጆች ከውጭ ጥቂት ራቅ ብለው ጥግ ይዘው የሚመጣ ሰው ይጠባበቃሉ:: አባባ ሸበቶ በሥራው በጎ ተግባር ደስ ስላለው ፊቱን ፈካ ሲያደርግ ሚስተር ዦንድሬ ደግሞ ከአንገት በላይ ፈገግታ ተውቧአል፡ ማሪየስ ከመወጣጫ ላይ ወጥቶ በቀዳዳ ወደታች ያያቸዋል:: ሽጉጡን በእጁ
ይዞ ቃል ሳይተነፍስና ድምፅ ሳያሰማ ነው የተቀመጠው::
ተንኮል ቢያስቡ ወዲያው ጣልቃ በመግባት ይህን ደግ ሰው
አድነዋለሁ» የሚል እምነት ስላደረበት ደስ ብሎትና ጣቱን ከሽጉጥ ቃታ ላይ አሳርፎ ነው ያለው፡፡ የፖሊስ ኃይል በአካባቢው አድፍጦ እንደሚጠባበቅ
ያውቃል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለረጅም ጊዜ ሲያስጨንቀውና አንጀቱን ሲበላው የቆየው የኮዜት ጉዳይ በዚህ አጋጣሚ መልስ እንደሚያገኝ ይተማመናል::
ሚስተር ዦንድሬ አባባ ሸበቶን ሲያዋራ ቀደም ሲል ያላየው አንድ
ሰው ከወደ ጓዳ ውልብ ብሎ ሲያልፍ ማሪየስ ይመለከታል፡፡ ሰውዬው የሚራመደው ድምፅ እንዳያሰማ ፈርቶ በጥንቃቄ ነው:: ይህ ሰው እንደ ሚስተር ዦንድሬ ያረጀና የተቀዳደደ ልብስ ለብሷል:: ለእግሩ መጫሚያ አላደረገም፡፡ ክንዱ ላይ ንቅሳት አለው:: ፊቱን ከሰል ቀብቶ ሸለምጥማጥ
መስሎአል፡፡ ጓዳ ውስጥ ከነበረው በርጩማ መሳይ ነገር ላይ ሲቀመጥ ጨለማ በመሆኑ በግልጽ አይታይም:: ይህ ሰው የነበረው ልክ ከአባባ ሸበቶ
ጀርባ ነው::
አባባ ሸበቶ ጀርባውን ስለከበደው ልክ ማሪየስ ሰውዬውን ሲያይ
እርሱም ዞር ብሉ አየ::
«ማነው እርሱ?» ሲል ጠየቀ::
«እሱማ ጎረቤቴ ነው» ሲል ዦንድሬ መለሰለት::
በዚያ ሰፈር ንጥረ ነገሮችን ሠርተው የሚያወጡ ፋብሪካዎች ስለነበሩና ፋብሪካዎቹ ውስጥ የሚሠሩ ሰዎች ከዚያ ሲወጡ ፊታቸው ጥቀርሻ ለብሶ
መጥቆሩ የተለመደ ነገር ስለነበር የሰውዬው ፊት መጥቆር ኣባባ ሸበቶን አላስደነገጠውም:: ስለዚህ ወደ ጨዋታቸው በመመለስ «ይቅርታ ምን ነበር እያ
ያልከው?» ሲል ዦንድሬን ጠየቀው::
«እለውማ የነበረው ጌታዬ፧ ኣንድ ልሸጠው የምፈልግ ስእል አለ
እያልኩ ነበር የማጫውትዎት» ሲል ፈገግታ በተሞላበት ዓይን እያየ መለሰለት::
በር መከፈቱን የሚገልጽ ድምፅ ከወደ በሩ ተሰማ:: ሁለተኛው ሰው
ከቤቱ ውስጥ ገባ፡፡ ከሚስተር ዣንድሬ ባለቤት አጠገብ ከነበረው አልጋ ጫፍ ላይ ሄዶ ተቀመጠ፡፡ ይህም ሰው ፊቱን ጥላሸት ቀብቷል፡፡
ሰውዬው በጣም ዝግ ብሎ ድምፅ ሳያሰማ ቢገባም አባባ ሸበቶ
አይቶታል፡፡
«ከቁጥር አያስገቧቸው፤ እንደሌሉ ቆጥረዋቸው፤ እኛ እንጫወት፡፡
ዝም በሏቸው:: ይኸውልዎ ያንን ስእል ለመሽጥ ፈልጌ በማለት በጣቱ እያመለከተ እንግዳውን ለማዘናጋት» ሲል ዦንድሬ ብዙ ለፈለፈ፡፡
ዦንድሬ ብድግ ብሎ ተነስቶ ወደ ግድግዳው ሄደ:: አንድ ስእል
መሳይ ነገር ተሸፍኖ ነበረና ገለጠው:: የበራው ሻማ ብርሃን ደካማ ስለነበር አባባ ሽበቶ ስእሉን በጉልህ ለማየት አልቻለም:: ሰውዬው ምን ለማድረግ
እንደፈለገ ማሪየስ ሊገባው ስላልቻለ ግራ ተጋባ፡፡
«ታዲያ ይኼ ምንድነው?» ሲል አባባ ሸበቶ ጠየቀው:
«አገራችን ውስጥ ዝናው የገነነ ሰአሊ የሳለው ስእል ነዋ! ጌታዬ ልክ እንደ ልጆቼ ነው የማየውና የምወደው:: ብዙ ነገር ያስታውሰኛል፡፡ ሆኖም ችግር ስለጠናብኝ ከቤቴ ላኖረው አልችልም:: እንደነገርኮት ልሸጠው
እፈልጋለሁ» ሲል ዦንድሬ ጮክ እያለ በሀዘኔታ ተናገረ፡፡
በአጋጣሚ ይሁን በጥርጣሬ አባባ ሸበቶ ስእሉን እያየ ወደኋላ ቢመለከት አራት ሰዎች ጓዳ ውስጥ አሉ፡፡ ሦስቱ አልጋ ጫፍ ላይ ተቀምጠዋል፤
አንደኛው ቆሞአል፡፡ አራቱም ፊታቸውን ጥላሸት ቀብተዋል፡፡ አልጋ ጫፍ ላይ ከተቀመጡት መካከል አንደኛው ግድግዳ ተደግፎ ያሸለበው ይመስል
ዐይኑን ጨፍኖአል፡፡ ይህ ሰው በእድሜ ጠና ያለ ነው:: ፀጉሩ ሽብቶ ሳለ ፊቱን ጥላሸት ሲቀባ ጊዜ በጣም ያስፈራል፡፡ የተቀሩት ሁለቱ ልጅ እግሮች ሲሆኑ አንደኛው ጢሙን፣ ሌላው ፀጉሩን አሳድገዋል:: ማንኛቸውም
ቢሆኑ ጫማ አላደረጉም::
የአባባ ሸበቶ ዓይን ከእነዚህ ሰዎች ላይ መተከሉን ዠንድሬ ተገነዘበ፡፡
«ጓደኞቼ ከመሆናቸውም በላይ ጎረቤቴ ናቸው» አለ። «ፊታቸው
የጠቆረው ከሰል ማምረቻ ውስጥ ስለሚሠሩ ነው:: የእነርሱ ከዚህ መገኘት አያስጨንቅዎት:: ስእሉን ቢገዙኝ በጣም ደስ ይለኛል፡፡ ባይፈልጉት እንኳን ለእኔ ብለው ይግዙኝ:: እኔ ደግሞ እርስዎን ብዙ ገንዘብ አልጠይቅም::
ስንት የሚያወጣ ይመስልዎታል?»
«ነገር ግን» አለ አባባ ሸበቶ የዦንድሬን ዓይን እየጠበቀ፤ «መኝታ ቤት የሚሰቀል ዓይነት ስእል በመሆኑ ሦስት ፍራንክ ቢያወጣ ነው:: »
ዦንድሬ ረጋ ባለመንፈስ መልስ ሰጠ፡፡
«ገንዘብ ከያዙ አንድ ሺህ ክራውን ይበቃኛል::»
አባባ ሸበቶ ራመድ በማለት ጀርባውን ለግድግዳ ሰጠ፡፡ በግራው በኩል ዦንድሬ ቆሞአል:: የዦንድሬ ባለቤትና አራቱ ሰዎች በስተቀኙ ናቸው አሁንም ሰዎቹ ከነበሩበት አልተነቃነቁም:: እንዲያውም ከነአካቴው እርሱን አያዩትም:: ዦንድሬ መለፍለፉን ቀጠለ፡፡ በዚህ ጊዜ አባባ ሸበቶ
ይህ ሰው ችግር ያሳበደው ነው» ሲል አሰበ::
«የእኔ ጌታ፧ ስእሉን ካልገዙኝ» አለ ዦንድሬ፧ ‹‹ሌላ የገቢ ምንጭ
ስለሌለኝና ብዙ ችግር ስለገጠመኝ ወንዝ ውስጥ ገብቼ ራሴን አጠፋለሁ::»
ዦንድሬ ይህን የተናገረው አባባ ሸበቶን እያየ አልነበረም፡፡ የአባባ
ሸበቶ ዓይን ግን ከዦንድሬ ላይ ነው፡፡ ማሪየስ ከበላያቸው ሆኖ ተራ በተራ ዓይኑን ከሰዎቹ ላይ አሳረፈ፡፡ «ይህ ሰው አሁን በእውነት ሞኝ፤ ቂላቂል
ሰው ነው?» ሲል ራሱን ጠየቀ፡፡ ዠንድሬ «ራሴን ማጥፋት አለብኝ» ሲል ደጋግሞ ተናገረ::
የዦንድሬ ሰውነት በድንገት ተለዋወጠ፡፡ ፊቱ በደስታ ፈካ፡፡ ወደ
አባባ ሸበቶ ጠጋ ብሎ «አሁን ችግሩና ጥያቄው ይህ አይደለም! ለመሆኑ ታውቀኛለህ?» ሲል ጮኸ፡፡
የክፍሉ በር በድንገት ወለል ብሎ ተከፈተ፡፡ ፊታቸውን በምናምን
የሽፈኑ ሦስት ሰዎች ዘልለው ገቡ፡፡ አንደኛው ወፍራም የብረት ዱላ
ይዞአል፡፡ ሁለተኛው ትልቅ ቢላዋ፤ ሦስተኛው መጥረቢያና ትላልቅ ቁልፎችን ይዞኣል፡፡
ለካስ ዦንድሬ እነዚህን ሰዎች ነበር የሚጠባበቀው፡፡ ዦንድሬ የብረት
ዱላ ከያዘው ሰው ጋር ንግግር ቀጠለ፡፡

👍20
«ሁሉም ነገር ዝግጁ ነው?» ሲል ዦንድሬን ጠየቀው፡ ፡
«አዎን» ሲል መለሰለት፡፡
«ታዲያ ሞንትፐርናሴ የት አለ?»
«ከልጅህ ጋር ውጭ ቆሞ ያወራል፡፡»
«ከየትኛዋ ጋር?»
«ከትልቅዋ፡፡»
«መንገድ ላይ የቆመ ጋሪ አለ?»
«አዎን፡፡»
«ሰረገላ ተዘጋጅቷል?»
«ተዘጋጅቷል፡፡‟
«ፈረሶቹስ፤ ብርቱዎች ናቸው?»
«በጣም፡፡»
«ሰረገላው እኔ እንዲቆም ካዘዝኩት ሥፍራ ነው የቆመው?»
«አዎን፡፡»
«በጣም ጥሩ» አለ ዦንድሬ::
አባባ ሸበቶ ቀልቡ ተገፈፈ:: ወጥመድ እንደገባች አይጥ ዓይኑ
ተቅበዘበዘ፡፡ የፍርሃት ምልክት ሳይታይበት ከነበረበት በዝግታ መነቃነቅ ጀመረ: ከጥቂት ደቂቃ በፊት ወገቡ የጎበጠ ሽማግሌ ይመስል የነበረው በድንገት ግስላ ሆነ::
ፊታቸውን ጥላሸት ከቀቡ ሰዎች መካከል ሦስቱ የብረት ቆመጥ
ይዘው ከበሩ ላይ ቆሙ፡፡ እንቅልፍ የወሰደው ሽማግሌ ግን አሁንም
አልጋው ላይ ነው፡፡ ግን ዓይኑን ገልጧል፡፡ የዦንድሬ ባለቤት አጠገቡ ተቀምጣለች።
ማሪየስ አሁን ጣልቃ መግባት አለብኝ በማለት እጁን ወደ ጣራ
አነሳ ሽጉጡን ለመተኰስ ተዘጋጀ:
ዦንድሬ የብረት ዱላ ከያዘው ሰውዬ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ወደ አባባ ሸበቶ ዞር አለ፡፡ ፊቱን አኮማትሮ የፌዝ ሳቅ እየሳቀ አናገረው፡
«አላወቅኸኝም?»
አባባ ሸበቶ ፊቱን አተኩሮ እየተመለከተ ‹የለም» ሲል መለሰለት፡፡
በዚህ ጊዜ ዦንድሬ ወደ ጠረጴዛው ጠጋ አለ፡፡ ግንባሩን ወደ አባባ ሸበቶ አስጠግቶ ልክ አውሬ ጠላቱን ነክሶ ለማጥቃት እንደሚያጓራ ሁሉ እሱም አጓራ፡፡
«የእኔ ስም ዦንድሬ አይደለም:፡ ስሜ ቴናድዬ ነው፡፡ እኔ እኮ
ሞንትፌርሜ ላይ ሆቴል የነበረኝ ሰው ነኝ፤ ገባህ? ቴናድዬ! አሁን አወቅኸኝ አይደል?››
በቃላት ሊገለጽ የማይቻል ቁጣ ከአባባ ሸበቶ ፊት ላይ ታየ፡፡
የመርበተበትና የመረበሽ ስሜት ሳያሳይ ቁጣውን ዋጥ አድርጎ ረጋ ብሎ ተናገረ፡፡
«ብዙም አልተለወጥህም፡፡»
ማሪየስ መልሱን አልሰማም በሰማው ነገር ክው ነው ያለው፡
ዦንድሬ ስሜ ቴናድዬ ነው» ብሎ ሲናገር ጉልበቱ ከድቶት የሚወድቅ መሰለው ግድግዳውን ተደገፈ ልቡ በጦር የተወጋ መሰለው ከዋተርሉ ጦር ሜዳ ላይ የአባቱን ሕይወት ማትረፉንና አባቱም ሲሞት ‹‹የዚህን ሰው
ነገር አደራ» ብሎ የተናዘዘው ትዝ አለው:: ሽጉጥ ለመተኰስ ወደ ጣራው አቅንቶት የነበረው ቀኝ እጁ በመዝለፍለፍ ፀሐይ እንደመታው ቅጠል አጎነበሰ
ገባህህ፧ «ቴናድዬ» ሲል ዦንድሬ በድጋሚ ተናገረ: ሽጉጡ ከማሪየስ እጅ ሊወድቅ ምንም ያህል አልቀረው.....

👍17
#ዶክተር_አሸብር
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
፡
፡
#ስድስት
፡
፡
አቲዬ ለመርገጥ የሚያስፈራው የወይዘሮ እጥፍወርቅ ግቢ ውስጥ አንዲት ቆንጆ ሠርቪስ ቤት
ተሰጠቻት፡፡ ያውም ከነሙሉ ዕቃው፡፡
“ማነው ስምሽ እናቱ?” አለቻት አቲዩን ወይዘሮ እጥፍወርቅ፡፡
“አፀደ"
"ውይ የኔ ድንቡሽቡሽ! ስንት ወሩ ነው” አለች እኔን እያያች፡፡
“አሁን የፊታችን ገብሬል መንፈቅ ይሞላዋል" እጇን ወደኔ ዘረጋች። ፈገግ ብዬ እጇን ለቀም፡፡ ሕፃናትን
መለይካው ይመራቸዋል የሚባለው እውነት ሳይሆን አይቀርም። ወይም ሴትዬዋ እጅ ላይ የተገጠገጠው የወርቅ ቀለበትና ጌጣጌጥ መጫወቻ መስሎኝ:: ወይዘሮ እጥፍወርቅ አቲዬን እንዲህ አለቻት፤
“ላንችና ለልጅሽ ሆድ አታስቢ.! እዚህ ተርፎ ለሚደፉ እህል የበላነውን ትበያለሽ፡፡ ብትወጅ እኛ ጋር እየሰራሽ፣ ከፈለግሽም የፈለክሽውን እየሰራሽ እዚሁ ኑሪ ቤትሽ ነው::
ኑሪ ኑረ ኑሪ ኑሪ…ኑሪ…በሕይወት ኑሪ፡፡ ሌሊት ኮሽ ባለ ቁጥር ሳትሰጊ ኑሪ፡፡ ልጅሸን
እንደፈለግሽ የምታጥቢበት፣ የሽንት ጨርቅ የምታጥቢበት ውሀ ሳያሳስብሽ ኑሪ፡፡ ልጅሽ የሚበላው
ነገር ሳይቸግረው ኑሬኑሪ.: እግዚርም ሲናገር ልክ እንዲህ ነበር፡ ያውላችሁ ምድር ኑሩበት፤
ውሀው ያው ምግቡ ያው፣ መኖሪያው ያው ይሄው ወይዘሮ እጥፍወርቅ ግቢ ዘፍጥረት
ራሱን ሲደግም፡፡
“በመጀመሪያ ምድር ባዶ ነበረ፡፡ ባዶው ላይ አንዲት የጨለመባት ሚስኪን ሴት ልጅ አዝላ ቆማ ነበረ፡፡ እግዜር ብርሃን ይሁን አለ፡፡ ቦግ !” ከእግዜር ብርሃን ጋር ሲወዳደር ቀለመወርቅ አብሪ ትል ማለት ነው፡፡ ዘርፌ ሀይሏን የጨረሰች የእጅ ባትሪ፡፡ ወይዘሮ እጥፍወርቅ ጨረቃ የእግዜርን ብርሃን የምታንፀባርቅ፡፡ እግዜር ግን ፀሐይ ከአድማስ እስከ አድማስ በብርሃን የሚያጥለቀልቅ እናም የሚምቅ !
አቲዩ በተሰጣት ምርጫ መሠረት እዛው ቤት ልትሰራ ወሰነች፡፡ በዕርግጥም የተሻለ ምርጫ
ነበረ፡፡ የማንንም ፊት ከማየት በእጅጉ የተሻለ፡፡ ለእኔ በተለይ ግቢው መቦረቂያዬ፣ የወይዘሮ
እጥፍወርቅ ፈገግታ ምቾቴ ሆነልኝ፡፡ በዛ ሰፊ ግቢ ውስጥ ወይዘሮ እጥፍወርቅ፣ ወጣት ተማሪ ልጃቸውና እኛ ብቻ ነበርን የምንኖረው፡፡ የወይዘሮ እጥፍወርቅ አምስት ልጆች ኑሯቸው ቀውጭ ሀገር ነበር፡፡
ወይዘሮ እጥፍወረቅ አስገራሚ ሴት ነበረች፡፡ እንኳን አቲዬ የድሮ እመቤቷ ዘርፌ ራሷ
የማታልመውን ከውጭ ሀገር የመጣ አንድ ሻንጣ ልብስ ለአቲዬ ሰጠቻት፡፡ ለእኔም ቆንጆ
ቆንጆ ልብስ ገዛችልኝ ዘነጥን !! እኔና እቲዬ ቂቅ ብለን ዘነጥን ደግሞ ስናምር!!
አቲዩ ከወይዘሮ እጥፍወርቅ የተሰጣትን ልብስ ለበሳ አበባ መስላ ብቅ ስትል ዘርፌ ዓይኗ ደም ለበሰ፣ ቀለመወርቅ ደም ግፊቱ ከፍ አለ፡፡ ክፉ አሳቢዎች ምን ሀብት ቢተርፋቸው የያዙት ነገር አያስደስታቸውም፡፡ ይልቅ የሚያጠሉት ሰው ጥቃቅን ለውጥ ያንገበግባቸዋል፡፡ ዘርፌና ቀለመወርቅ የምቀኛ ግንባር ፈጥረው ተንገበገቡ፡፡ የግንባሩ ጸሐፊ ሰይጣን!! እናም ሰይጣን ከቀለመወርቅ እና ዘርፌ ኋላ እግዜርም ከአቲዬ ፊት ቆመው ጦርነቱ ተጀመረ !! አሁን በኑሮ ማስፈራራት በክብር መንጠባረር የለም፡፡ ማንም ሆዱ ከሞላ ጀግና ነው፡፡ ማንም ቢመታ የሚወድቅበት፣ ሲቆስል የሚታከምበት ካለው ጀግና ነው፡፡ ማንም የሚያከብረው ሰው ከጎኑ ካለ ለሌሎች ንቀት ሞራሉ እንደደረቅ እንጨት አይሰበርም፡፡ ዋናው ስንቅና ትጥቅ ግን ማንም እግዚያብሄር ከኋላው እንዳለ ካመነ ልበ ሙሉ ነው !!
እቲዬ ይሄን ሁሉ ሆና ነው ወደ ጦርነቱ የገባችው !! እናም ጦርነቱ በታሪክ ወርቃማው ጦርነት በመባል ይታወቃል በእኔ በነፍሴ ዘገባ !! ወደፊት ልጆቼ “ለምን ወርቃማው ጦርነት ተባለ ?” ብለው ሲጠይቁኝ መልሴ አንድ እና አንድ ነው፤ “በቀለመወርቅ እና በእጥፍወርቅ መካከል በተደረገ ሰብዓዊ ጦርነት በእሳት የተፈተኑ ወርቆች ወደ ምቾት አገር ስለተሰደዱ” እላቸዋለሁ፡፡
የባርነት አስከፊ ገፅታ ያለው በባርነት መግዛቱ ላይ ሳይሆን በባርነት የተገዙበት መንገድ ላይ
ነው፡፡ በፍላጎት ለሌሎች ባሪያ መሆን ለራስ ህሊና የጌትነት ማዕረግ ሰለሚያጎናፅፍ፣ ለነፃነት
ትግል ሳይሆን ምስጋና ራስህን እንድታዘጋጅ ነው የሚያደርግህ:: እሰይ! እንኳንም ባሪያ ሆንኩ የሚባልለት ባርነት አለኮ፡፡ ሰዎች በፍቅር ለሀገራቸው ባሪያ ይሆናሉ፡፡ ለፈጣሪያቸው ይገዛሉ፡፡ ለሚወዷቸው ያገለግላሉ፡፡ ግን ደስተኞች ናቸው፡፡ ለምን ? መንገዱ ፍቅር ነዋ !
አቲዬ ዙሪያውን በረዥም የግንብ አጥር ወደተከበበው ግቢ ገብታ ብትከትምም ዕጣፋንታዋን ግን አላመለጠችውም፡፡ ዕጣፋንታ እኮ ጥላ ነው:: በዙሪያህ ያለውን ችግርና መከራ ፍንትው
አድርጎ የሚያሳይ ብርሃን ሲጠፋ፣ አብሮ የጠፋ ይመስለሃል እንጂ፣ ቀን የሚሉት ፀሐይ ወጋገኑን
ሲቀድ ከትላንቱ በላይ ደምቆ ካንተ በላይ ገዝፎ ከፊትህ ይመራሀል ከኋላህም ይከተልሀል፡፡
አትዬም ዕጣ ፋንታዋን ስንዝር አላመለጠችውም፡፡ ከባርነት ወደ ፍቅር ባርነት ተቀይሮ በትልቁ
ነፍስ ዘራችበት፡፡ ሰፊውን ግቢ ከጧት እስከ ማታ አፅድታ ትልቁን ቤት ውብት ትደፋበታለች፤
ግቢ ውስጥ ጠበቃት እንጂ፡፡ሰው አጥቶ፣ ውርማ ውጦት የነበረውን የወይዘሮ እጥፍወርቅ ግቢ
የወይዘሮ እጥፍወርቅን ሆቴልም ቀጥ አድርጋ የያዘችው አቲዬ ራሷ ነበረች፡፡
የሆቴሉን እንጀራ ሙሉ በሙሉ ትጋግራለች፡፡ የአልቤረጎዎቹን አንሶላዎች ታጥባለች፡፡ እንደዛም
ሆኖ በጣም ደስተኛ ነበረች፡፡ ወይዘሮ እጥፍወርቅ ደግ ሴት ነበረችና ምንም በደረግላት ይገባታል፤የአቲዬ ባርነት ጣፋጭ ነበር፡፡ መሀተመ ጋንዲ ወደ ወይዘሮ እጥፍወርቅ ግቢ ጎራ ቢሉ ኖሮ፣ "ነመስቴ…እኛም የታገልነው ለዚህች አይነቷ ባርነት ነበር በርቱ!” ብለው የሚሄዱ ይመስለኛል!
በእርግጥ ወይዘሮ እጥፍወርቅ አቲዬን እንጀራ ጋግሪ አላለቻትም፡፡ ራሷ አቲዬ ለሆቴሉ እንጀራ
ግዥ እየተባለ በቅን የሚወጣውን ብር ስትመለከት፣ “ምጣድ ግዙልኝ ሪሴ እጋግራለሁ" አለች እንጂ፡፡ የሆቴሉን አንሶላ፣ “እጠቢ ያላት ማንም አልነበረም፡፡ አጣቢዋ ስትጨማለቅ ስታያት አቲዬ የኔ የልብ ሰው፣ “ምነው እቴ ሰው የሚታኛበት እይደለም እንዴ” አለችና አጇን ሰቅስቃ
ገባችበት፡፡“አቦ የእጥፍወርቅ ቤርጎ እንሶላው ብትል ፎጣው እንዴት ይጸዳል” እስኪባል፡፡ የወይዘሮ እጥፍወርቅ ልብ አቲን በልጅነት መንበር ላይ ወስዶ አስቀመጣት፤ እኔንም የልጅ ልጅነት !!
ግቢው የእኔ ነበር፡፡ እንዳሻኝ የምሆንበት ግዛቴ፡፡ የሳሎኑ ዕቃ የእኔ ነበር፡፡ ጆሮ ጭው የሚያደርግ ዋጋ የተከሰከሰበት ሶፋ ላይ ሸንቼበታለሁ፣ ወተት ደፍቼበታለሁ፡ አቀርሽቼበታለሁ፡፡ ለዓይን የሚያሳሳውን የቡፌ ዕቃ እንኮታኩቼዋለሁ፡፡ የወደዘሮ አጥፍወርቅን ባለ አልማዝ ፈርጥ የአንገት ሀብል ከእንገቷ ላይ በጣጥሼዋለሁ፡፡ (የዚህ ሀገር ወርቅ አንጥረኛ አይሰራውም ተብሎ ተቀምጦ ቀረ…) የፋናዬን (እህቴ ማለት ናት - የወይዘሮ እጥፍወርቅ ልጅ) ቀይና ውብ ፊት ቦጫጭረዋለሁ፣ ፋኒዬን እንደ ህፃን ልጅ ነበር የማስለቅሳት፡፡
አትዬ ስትነግረኝ ፋናዬ ከትምህርት ቤት ስትመጣ ቦርሳዋን እንዳዘለች እኔ ላይ ትጠመጠምና ድበድብ ነው፡፡ ሱቅ የተሰቀለ አሻንጉሊት ካየች፣ የሕግን ልብስና መጫወቻ ዓይኗ ውስጥ ከገባ፡ ለእኔ ለመግዛት ከእናቷ ጋር ብር ስጭኝ አልሰጥም” ጦርነት ነው::
የእናቴ ንፁህ ልብ እንደስፖንጅ ፍራሽ በሕይወቴ መንገድ ላይ ተነጥፎ የዛች ቅፅበት የነበረ

👍24❤5
ልጅነቴን እንከን አልባ አድርጎልኛል፡፡ ጥፋቴን የሳቅ ምንጭ፣ ለቅሶዩ ለማባበል ለሚራወጡ ቤተሰቦቼ፣ “የማባበል ስራ ጀምሩ የሚል ደወል ነበር፡፡ የፍቅር እና የቤተሰብ ቅንጦት ቶምቦላ በጠዋቱ የወጣልኝ ጨቅላ !
ሦስተኛ ዓመቱን ልይዝ ሁለት ወራት ብቻ ሲቀሩ በእኔና በእቲዬ ሕይወት ላይ ድንገት ፀሐዬ ጠለቀች፡፡ ያች ፍልቅልቅ ፀሐይ ጠለቀች፡፡ ምንም ተራራ በሌለበት፣ ምንም ደመና በማይታይበት ንፁህ ሰማይ ፀሐይ ለወትሮው በእናት ትይዩ በምትሆንበት እኩለ ቀን ድንገት ድርግም አለችና እኔና አቲዩ ድቅድቅ ጨለማ ላይ ቆምን፡፡ ብርሃን ይሁን ያለ አምላከ በቁጣ "ጨለማ ይሁን ብሎ ያዘዘ ይመስል የዚህን ሁሉ ጊዜ ውብ ብርሃናችን በአንዲት ቅፅበት ድርግም አለ ! እንደማብሪያ ማጥፊያ ቀጭ አድርጎ ድርግም !!
ድቅድቅ ጨለማ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ በጠራራ ፀሐይ አይከሰትም ያለው ማን ነው? -የፀሐይ
ግርዶሽ፡፡ ማለትም ሳይንሱ ያሻውን ይበል እንጂ፣ እውነታው ወዲህ ነው፡፡ በምንወዳቸው
ሰዎችና በእኛ መካከል ሞት የሚባል ግርዶሽ ሲጋረጥ፣ 'የፀሐይ ግርዶሽ ይሻላል !!
ወይዘሮ እጥፍወርቅ በጓደኛዋ ልጅ ምርቃት ተጠርታ ወደ እዳማ ስትሄድ መንገድ ላይ አንድ
ከባድ መኪና ትንሽ ዲኤክስ መኪናዋ ላይ ወጣባት። ደግ አይበረከትም !! ተረት አውሪዎች
ደፋሮች ናቸው:: ቀለል አድርገው፣ “ሲኖሩ ሲኖሩ ሞቱ” ይላሉ፡፡ ሞት ከተረትም ከታሪክምና ከዛሬና ነገም በላይ የገዘፈ ሰቆቃ መሆኑን ማን በነገራቸው፡፡ “ወይዘሮ እጥፍወርቅ ደግ ሰው
ነበረች፣ ስትኖር ስትኖር በተወለደች በምናምን ዓመቷ በድንገተኛ እደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች ተባለ፡፡ በቃ!!
ስለ ወይዘሮ እጥፍወርቅ ሞት አቲዬ በማንም ምንም ስታወራ ሰምቻት አላውቅም፡፡ እግዜር
ስትደገፈው የሚወድቅ ምርኩዝ አቲዬ በማዋሱ ብዙ ዓመታት ቤተክስቲያን እየሄደች ወቅሳዋለች
“ስለምን ደግ ኑሮን እንቁልልጭ ትለኛለህ፣ ለተራበ ውሻ ቁራጭ ስጋ ይዞ ሲያጓጓ እንደቆየ ሰው
ከጠላቶቼ ዓይን በላይ ሰቅለህ አኖርከኝ፡፡ እንዲቦጫጭቁኝ ወደነሱ መልሰህ ጣልካኝ እያለች፡፡
እኔም ነፍስ ካወቅኩ በኋላ እግዜርን ወቅሼዋለሁ፡፡ “ዘርፌ ለመኪና ሞት ምን ይጎድላታል?
አዳማ መንገድ ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ ተጨፍልቆ ለመሞት ቀለመወርቅ ምን ያንሰው ነበር?”
ዘፋኞቹ እየተቀባበሉ፣
“መንገድ ዓይኑ ይፍለስ አይባልም ደርሶ፣
የወሰደውን ሰው ያመጣል መልሶ” ይላሉ፡፡
የታለ የአዳማ መንገድ ወይዘሮ እጥፍወርቅን የመለሰው? ቢሆንም እግዜር የለም አላልኩም፡፡
አቲዬ እግዜር አለ ካለች፣ ማንም ፈላስፋ ሀሳቤን ስንዝር አያናውጣትም፡፡ እግዜርን በድፍረት ልናገረው፣ ልነተርከው፣ ልነዘንዘውና ልነጫነጭበት እችላለሁ፡፡ በምድር ላይ ሰው ሁሉ ከእናቴ የተፋኝ እኔ፣ እግዜር የለም” ብዬ ማን ላይ ልነጫነጭ፣ ማን ላይ ልመናቸክ፣ ማንንስ ልነዝንዝ
በእርግጥ አይኑ ይፋሰስ የተባለው መንገድ ዘርፌንና ቀለመወርቅን ወስዶ ባይመልስም ባልከፋ፤
እግዜርስ ምኑ ሞኝ እነዚህን ጥራጊ ፍጥረቶች ወደ ሰማይ ቤት የሚጠራ፡፡ እዚሁ ይጨማለቁ እንጂ፤
ደሀ ላይ አፋቸውን ይከፈቱ፡፡ አስመሳይ መንደርተኛ፣ ግፋቸውን በአናቱ፤ ስማቸውን በምላሱ
ተሸክሞ ሲኖር እግዜር ለሲኦላቸው የሚሆን ማገዶ ይሰበስቡ ዘንድ እድሚ ይጨምርላቸው፡፡በየዓመቱ ልደታቸውን በፌሽታ ያክብሩ !!አንድ ቀን እንደልደት ሻማ እፍ! ተብለው እስኪጠፉ !
የአዳማ መንገድ አስጠላኝ፡፡ የአዳማ መንገድ ላይ ቀለመወርቅ ቀብረር ብሎ ሲራመድ ይታየኛል
ልክ እንደቤቱ ኮሪደር፡፡ ቀለምወርቅ የጣረሞትን ገጸ ባህሪ ወክሎ ድራማ የሚሰራ መሰለኝ፡፡ እንዴት ነው የሚዋጣለት፡፡
ደስ የሚለው ነገር አዳማ መንገድ ላይም ባይሆን በመኪና አደጋም ባይሆን ዘርፌና ቀለመወርቅ
ይሞታሉ !!!! (ሀሌሉያ) ያች አቃጣሪ ባልቴት ሽንሽን ቀሚሷን ጥላ እርቃኗን ትገንዛታለች፡፡
የአሜሪካ ላሞቿ አማላጅ ሆነው ገነት ያስገቧት እንደሆነ እናያለን !!
ይሄ ባለጌ ሽማግሌ ቀለመወርቅ ካፖርትና ኮፍያውን መልዕክት በር ላይ በክብር ይቀበሉትና፣
“እዚህም በከብር ልኖር ነው” እያለ ሲያስብ፣ ማጅራቱን ይዘው ወደ እሳት ጉድጓድ ውስጥ በእርግጫ ይገፈትሩታል። ታየኝ አየር ላይ እየተምዘገዘገ ሲወርድና ቦጭረቅ ብሎ ሲያርፍ፤ እሳቱ እንደውሀ ዙሪያውን ሽቅብ ሲረጭ ያኔ አሸብር ልጄ ነው” እያለ ሲቀባጥር እሳቱ ይበርድ እንደሆነ እናያለን ! እንዴ ፈላስፋዎች ምን ነካቸው ሲኦል የለም የሚሉት? ስለቱ
ካለ አፎቱን እንዴት የለም ይላሉ? ሲኦል መኖር አለበት። ቀለመወርቅና ዘርፌ እያሉ እንዴት ሲኦል አይኖርም !!....

👍16❤10
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_አምስት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
...ገባህህ፧ «ቴናድዬ» ሲል ዦንድሬ በድጋሚ ተናገረ: ሽጉጡ ከማሪየስ እጅ ሊወድቅ ምንም ያህል አልቀረው ዦንዴሬ ማን እንደሆነ ሲናገር ከአባባ ሸበቶ ይበልጥ ማሪየስን ነው የረበሸው:: ማሪየስ ገና ስሙን ሲሰማ
ይህ ሰው ማን እንደሆነ አወቀ፡፡ አባባ ሸበቶ ግን ቶሎ አላስታወሰውም::
የዚህ ሰው ስምና ሆቴል አባቱ ትቶለት ከሞተመ ወረቀት ላይ ተጽፎአል፡፡ የአባቱን አደራ ለመጠበቅ ሲያየውና ሊጠይቀው ብዙ ጊዜ ፈልጎ አልተሳካለትም:: በመጨረሻ ግን በዚህ ዓይነት ሁናቴ ተገናኘው፡፡ ለካስ
የአባቱን ሕይወት ያዳነው ሰውዬ ሽፍታ ነው! ምን የሚገርም ጉድ ነው ምን ዓይነት የሕይወት አጋጣሚ ነው? ሕይሀት ራስዋ ትቀልዳለች ሲል አሰበደ
ይህን ቴናድዬ የተባለውን ሰው ቢያገኘው እግሩ ላይ ወድቆና ጫማውን ስሞ ሊያመሰግነው ለራሱ ቃል ገብቶ ነበር፡፡ እርግጥ ነው አሁን አግኝቶታል፡፡
ነገር ግን ማመስገኑ ቀርቶ ለፍርድ አሳልፎ ሊሰጠው ነው:: ቀልድ
አይመስልም፤ ግን አይደለም::
ማሪየስ ሁኔታውን ሲያሰላስል አሳቡን መቋጨት አቃተው:: ድንገት በገጠመው ሁኔታ እንኳን አባባ ሸበቶን ሊረዳ ራሱን መቆጣጠር ተሳነው:: ነገሩ ራሱን አዞረው:: ሁኔታው እየተፋፋመ መጣ፡፡ እርሱ ግን ራሱን
ሊስት ሆነ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአሁን በኋላ ቴናድዩ እንጂ ዦንድሬ ብለን
የማንጠራው ሰው ከወዲህ ወዲያ ይንቆራጠጥ ጀመር፡፡ የኩራትና ድል የመምታት ስሜት አድሮበታል፡፡ በድንገት ወደ አባባ ሸበቶ ዞር ብሎ
«ተዘፈነ! ተበላ! ተጠጣ! ተተፋ!» ሲል ጮኸ፡፡
እንደገና መንቆራጠጥ ጀመረ::
«አይገርምም» ሲል ጩኸቱን ቀጠለ፡፡ ‹‹በመጨረሻ አገኘሁህ:: የእኛ ምፅዋተኛ፤ የእኛ አዛኝ ቅቤ አንጓች የእኛ ቱጃር! የእኛ አሻንጉሊት ለጋሽ አታውቀኝም? የለም ፧ ሞንት ፈርሜ ላይ ከሆቴል ቤቴ ውስጥ ገብተህ
ያደርህ አንተ አይደለህም፧ ከስምንት ዓመት በፊት የገና እለት፤ በ1823 ዓ.ም! የፋንቲንን ልጅ ከቤቴ የወሰድከው አንተ አይደለህም! የእኛ ቀጣፊ
ያን ጊዜ ለብሰኸው የነበረው ረጅም ብጫ ካፖርት ምን ደረሰ? አለቀ? እንደዛሬ ጠዋት ጠቅልለህ ይዘኸው የነበረውስ ጨርቅ! አሁን ውጣ ከዚህ፣ ዓይንህን ያውጣውና፡፡ አንተ ሰይጣን፤ የእኛ መጽዋች! አታውቀኝም፤ እ
ይሁና፤ እኔ ግን አውቅሃለሁ:: ከዚህች ቤት ውስጥ ገና ስትገባ ነው | የለየሁህ፤ ሞላጫ! ያን ጊዜ አታለልከኝ አሞኘኸኝ:: ለእድሌ መስበር ምክንያት የሆንከው አንተ ነህ:: አንድ ሺህ አምስት መቶ ፍራንክ ወርውረህልኝ ደህና ትረዳኝ፧ ታገለግለኝ የነበረችዋን ልጅ ወሰድክብኝ:: ልጅትዋ ይህን ጊዜ ብዙ ሀብት አስገኝታልኝ ነበር:: የሀብታም ወገን ስለነበረች በስምዋ ብዙ ሀብት ይመጣልኝ ነበር:: አንተ ግን ያንን ምንጭ አደረቅኸው:: ያቺን ሸቃባ ይዘክብኝ ስትጠፋ ድል ያደረገህ መስሎህ ነበር፡፡ ዛሬ ግን አታመልጠኝም፤አታሸንፈኝም:: አንተ ሽባ፤ በቀል ነው የሚታየኝ አሁን! ጻድቁ፣ ዛሬ አልቆልሃል፡፡ ደግሞ ገንዘብ ይዞልኝ መጣ እኮ! ቂል:: ዛሬ ጠዋት ሳይህ ፍዳህን እንደማስቆጥርክ ነው ለራሴ ቃል የገባሁት።
ቴናድዬ ንግግሩን አቋረጠ፡፡ ትንፋሽ አጠረው:: የሚያጨሰው ሲጃራ ፈላበት ፊቱ ግን እንደ ጠዋት ፀሐይ ፈካ፡፡ ሊዋጋ እንደሚዘል ፍየል ፈነጠዘ፡፡ አባባ ሸበቶን ከቀጥጥሩ ስር በማዋለ በጣም ደስ አለው:: ደስታው
የድንኮች ቀውሌን ጠልፎ የመጣል ፤ የቀበሮ የታመመ በሬን ዘንጥለ የመብላት ያህል ነበር፡፡ የታመመ በሬ እንዳይዋጋ አቅም ያንሰዋል፤ ዝም እንዳይል ነፍሰ አልወጣችምና ይንፈራገጣል::
ቴናድዬ ሲለፈልፍ አባባ ሸበቶ ሊያቋርጠው አልፈለገም:: ንግግሩን እስኪጨርስ ጠበቀው:: አሁን ግን ቆም ሲል እርሱ ተናገረ::
የምትለው ነገር አልገባኝም፤ ተሳስተሃል፡፡ እኔ ድሃ እንጂ ባለብዙ ብር ወይም ቱጃር አይደለሁም፡፡ አንተ ትላለህ እንጂ እኔ አንተን አላውቅህም::
ከሌላ ሰው ጋር ተምታትቼብህ ነው::
«እህ» ሲል ቴናድዬ ጮኸ፤ አሾፈ:: «አሁንም ታሾፋለህ፤ ትቀልዳለህ!
ጌታው ወጥመድ ውስጥ ነው የገባኸው:: አታስታውስማ፣ ማን እንደሆንኩ አልለየኸኝማ!
«ይቅርታህን» አለ አባባ ሸበቶ ተኮሳትሮ፧ «ሽፍታ መሆንህን እየለየሁ ነው»
ቴናድዬ የሰውዬው ድፍረት ከማስደንገጥ አልፎ በጣም አናደደው::ይዞት የነበረውን የወንበር ድጋፍ ንዴቱን የተወጣሰት ይመስል ጨምድዶ ያዘው:: ባለቤቱ «ሽፍታ» የሚለውን ቃል ስትሰማ ከአልጋ ጫፍ ተወረወረች፡፡ቴናድዬ «አትነቃነቂ» ሲል ባለቤቱን አስጠነቀቀ፡፡ ወደ አባባ ሸበቶ ዞር ብሎ ሽፍታ አልክ፤ እናንተ ሀብታሞች እኮ እኛን በዚህ ስም እንደምትጠሩን መቼ አጣነው›› ሲል በመጮህ ተናገረ::
«አዎን ተሸነፍኩልህ ፤ ይኸው ተደብቄና ተሰውሬ የሃፍረት ማቄን
ለብሼ እኖራለሁ፡፡ የምበላውና የምልሰው የለኝም:: ግን ሽፍታ ነኝ:: ይኸው ሶስት ቀኔ ነው እህል ከቀመስኩ:: አንተ ደራርበህ ለብሰሃልና ሞቆሃል::እኔን እዚህ ቆፈን ይዞ ያንቀጠቅጠኛል:: አሽከር ቀጥረህ ፎቅ ቤት ውስጥ
ትኖራለህ:: እኔ እንደ ከብት በረት አድራለሁ:: አንተ ሰሐምሌና በነሐሴ ምግብ ስታማርጥ እኛ የማሽላ ቂጣ አሮብናል:: ይህም አነሰና ሽፍታ ትለናለህ! የግሌ የሆነ ሥራ የነበረኝ ሰው ነኝ:: ከዚህም ደግሞ ይበልጥ ሁለታችንም ፈረንሳዮች በመሆናችን አስተዳዳሪ ለመምረጥ እኩል
እንሰለፋለን፡፡ በል አሁን ከላይህ ላይ ወጥተን ከመጨፈራችን በፊት
የምትናገረው ነገር ካለ ተናገር» ሲል አፈጠጠበት::
አባባ ሸበቶ ዝም አለ፡፡ በዝምታው
መካከል የፈረስ ድምፅ ስለተሰማ
ሁሉም ቀና አሉ።
«የሚፈለጥ እንጨት ካለ እኔ እፈረካክሰዋለሁ:::» መጥረቢያ በእጁ የያዘው ሰው ነበር።
«ለምንድነው ፊትህን የሸፈንክበትን ጨርቅ ያነሳኸው?» ሲል ቴናድዬ በቁጣ ጠየቀው
የያዘው ሰው ነበር-
በቁጣ ጠየቀው::
«ለመሳቅ» ሲል መለሰለት::
አባባ ሸበቶ ቁጣው ገንፍሉበት ይንቆራጠጥ የነበረውን ቴናድ።
በዓይኑ ይጠብቃል፡፡ በሩ ላይ ሦስት ዘበኞች ቆመጥ ስለሚጠብቁት ቴናድዬ በጣም ተዝናንቷል፡፡ ከዚህም በላይ ሴትዬዋ እንኳን ባትቆጠር
ዘጠኝ ለአንድ ናቸው:: ስለዚህ አባባ ሸበቶን ናቅ በማድረግ ቴናድዬ ፊቱ ወደ ባለ መጥረቢያው አዞረ፡፡
አባባ ሽበቶ በዚህች እድል ለመጠቀም ወንበሩን በእግሩ፣ ጠረጴዛው በእጁ አሽቀነጠረና በሚያስደንቅ ፍጥነት ተወርውር ለቴናድዬ ጊዜ ሳይሰጠው
ከመስኮቱ ደረሰ፡፡ መስኮቱን ለመክፈትና ለመፈናጠጥ ጊዜ አልወሰደበትም ሆኖም ገና ግማሽ ሰውነቱን እንዳስወጣ ስድስት ሰዎች ከኋላ ጉትተው ወደ
ክፍሉ መለሱት፡፡ ሦስቱ የከሰል ሠራተኞች ከላዩ ላይ ተረባረቡ፡፡ የቴናድዩ ባለቤት በወንበር ጭንቅላቱን አለችው::
ጫጫታ ሲሰሙ ጊዜ ሌሉች ውጭ ቆመው የነበሩት ሽፍቶች ወደ ውስጥ ገቡ፡፡ አልጋ ላይ ተጋድሞ የነበረው ሽማግሌ እንደሰከረ ሰው እየተንገዳገደ መዶሻ ይዞ መጣ፡፡
የሞትና የሽረት ትግል ቀጠለ:: አባባ ሸበቶ አንድ ጊዜ ደረቱ ላይ
በቡጢ ቢለው ሽማግሌው ከመሬት ላይ ተዘረረ: ሌሉች ሁለቱን ደግሞ አንዱን በእርግጫ ሌላውን በጡጫ ሲላቸው ጊዜ እነርሱም ከመሬት ተደፉ፡፡ ከዚያም ላያቸው ላይ ሲወጣ ጊዜ ልክ ድንጋይ እንደተጫነበት ሰው

👍16❤1
አጓሩ:: የተቀሩት አራት ሰዎች ግን ከኋላ መጥተው እጆቹንና ወገቡን
ጥርቅም አድርገው ያዘ፡፡ መሬት ላይ ተዘርረው ከነበሩት የከሰል ሠራተኞች ላይ ጣሉት:: አባባ ሸበቶ ከስር ያሉትን በሰውነቱ ሲያደቅቃቸው ከላዩ ላይ
የሰፈሩት ሰዎች ደግሞ እንደጥምብ አንሳ አሞራ አንዱ በዱላ ፧ አንዴ ደግሞ
በጡጫ ወረዱበት::
ተረዳድተው ከመስኮት አጠገብ ከነበረው አልጋ ላይ ወረወሩት:.
የቴናድዬ ባለቤት በወንበር ከመታችው በኋላ ከተቀመጠችበት ወንበር
አልተነቃነቀችም:: ሁለቱ የከሰል ሠራተኞች ሰካራሙን ሽማግሌ ገፍትረው ጥግ አስያዙት::
«ባቤት ይህን ሁሉ ሰው ለምንድነው ያመጣኸው?» ሲል ቴናድዬ ቆመጥ ዱላ የያዘውን ሽፍታ' ጠየቀው፡፡ «አያስፈልግም ነበር» አለ ቀጠለና፡፡
«ሁሉም ካልመጣን ብለው ስላስቸገሩኝ ነው፤ ጊዜው አጉል ስለሆነ ደግሞ ምንም ሥራ የላቸውም::»
አባባ ሸበቶ የተጣለበት አልጋ የሆስፒታል አልጋ ዓይነት ነበር፡
ከአልጋው ድጋፍ ጋር ጥፍር አድርገው አሠሩት፡፡ አባባ ሸበቶ ለመቋቋም ሆነ ለመከላከል አልቻለም:: በሚገባ ካሠሩት በኋላ ከነአልጋው በእግሩ አቆሙት
ቴናድዬ ወንበር አምጥቶ ከአፍንጫው ስር ተቀመጠ፡፡ አውራ ሆኖ የነበረው ቴናድዬ ትንሽ ቀዝቀዝ አለ:: ከንዴት ብዛት አረፋ ይደፍቅ የነበረው አፉ ለስለስ ብሎ ሲያየው ማሪየስ ማመን አቃተው፡፡ ለውጡ በጣም አስደነቀው:: ነብር የፍየል ጠበቃ ሲሆን ገረመው::
«ጌታው» አለ ቴናድዬ:: ይህን እንደተናገረ ከብበው የቆሙ ሰዎች ገለል እንዲሉ በዓይኑ ገረመማቸው::
«ትንሽ እስቲ ወደዚያች ፈቀቅ በሉና ጌቶችን ላነጋግራቸው::»
ሁሉም ወደ በሩ ሔዱ:: ቴናድዬ ቀጠለ::
«ጌታው፤ በመስኮት ዘልለህ ለማምለጥ መሞከርህ ስህተት ነው:: ባንይዝህ ኖሮ ወድቀህ ትሰባበር ነበር:: አሁን መልካም ፈቃድህ ከሆነ በጥሞና እንነጋገር፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ግን አሁን ስላየሁት የዓይን
ምስክርነቴን ብሰጥ እወዳለሁ:: ይኸውም እንደ ሴት እሪ ብለህ አለመጮህ ነው:: ሌባ ሌባ እያልክ ጥቂት መጮህ ይገባህ ነበር፡፡ ግን አላልክም::
ገደሉኝ፤ ኡኡ ፤ የሰው ያለህ የጎረቤት ያለህ' አላልክም፡፡ ልትጮህ ትችል ነበር፡፡ ግን ጨኸት አላሰማህም::ለዚህም አድናቆት ይገባሃል:: አለመጮሁ
ደግሞ ሳይበጅህ የሚቀር አይመስለኝም:: ይህንንም የምልበት ምክንያት አለኝ ጌታው እኔ እንደማውቀው አንድ ሰው ጨኸት ሲያሰማ ማነው
የሚመጣው? ፖሊስ፡: ከፖሊስ በኋላ ምን ይከተላል? ፍርድ ቤት:: ለመጮህ ያልፈለግከው ልክ እንደ እኛው ፖሊስ እንዲመጣና ፍርድ ቤት ለመቅረብ ስለማትፈልግ ነው:: ይኸው ነው የእኔ ጥርጣሬ:: ጥርጣሬዬ አንድ ለመደበቅ
የምትፈልገው ነገር መኖር አለበት የሚል ነው:: የእኛም ምኞትና ፍላጎት ከዚህ የራቀ አይደለም፡፡ ስለዚህ አሁን በመግባባት ለመነጋገር እንችላለን፡፡ »
ቴናድዪ ዝግ ብሉ ከመቀመጫው ተነሳ፡፡ ወደ እሳት ማንደጃው ሄደ፡፡
የከሰል እሳት ተያይዞ ነበር፡፡ ከዚያም ቴናድዩ ተመልሶ ከአባባ ሸበቶ አጠገብ ቁጭ አለ፡፡
«ብቀጥል ይሻላል» አለ፡፡ «አሁን የምንስማማ ይመስለኛል፡፡ ስምምነቱን ደግሞ በፍቅር ብናደርገው ይሻላል:: ቀደም ብሎ የእኔም እንደዚያ በቁጣ መገንፈል ስህተት ነው:: እኔም አበዛሁት፡፡ ከመጠን በላይ ለፈለፍኩ::
ለምሳሌ ቱጃር በመሆንህ ብዙ ገንዘብ እፈልጋለሁ ብዩ ተናግሬ ነበር፡፡ ይህ በሰውም ሆነ በእግዚአብሔር ፊት ትክክል አይሆንም:: እንደእውነቱ ከሆነ
ሀብታም ብትሆንም የራስህ የሆነ ወጪ ፤ የራስህ የሆነ እቅድ ሊኖርህ ይችላል፡፡ ማነው ለሀብቱ፤ ለገንዘቡ ውጥን የማይነድፍ? እኔ ደግሞ አንተን ጨርሶ ለማደህየት አልፈልግም፡፡ እኔ እንደ አንዳንድ ሰዎች መልካም እድል
ስለገጠመኝ ብቻ እጅግ አጸያፊ የሆነ ሥራ ለመሥራት አልፈልግም:: መሐል ቤት ለመገናኘት ብንችል የቀረውን ጥቅሜን ለመሰዋት ፈቃደኛ
ነኝ፡፡ አኔ አሁን የሚያስፈልገኝ ሁለት መቶ ሺህ ፍራንክ ነው:: ምናልባት ይህን ስልህ ኪሴ ውስጥ ይህን የመሰለ ገንዘብ የለም ትል ይሆናል:: እኔም
ሁለት መቶ ሺህ ፍራንክ ኪስህ ውስጥ ተሸክመህ ትዞራለህ ብዬ አልገምትም:: ነገር ግን አንድ ነገር እጠይቅሃለሁ:: እኔ በቃል የምነግርህን በእጅ ጽሑፍህ
እንድታሰፍር ነው::»
«እንዴት አድርጌ ነው ለመጻፍ የምችለው? ይኸው ተጠፍሬ ታስሬ የለ
«ልክ ነው፤ ይቅርታ» አለ ቴናድዬ:: «አልተሳሳትክም፧ ልክ ነህ፡፡»
የእስረኛውን ቀኝ እጅ ነፃ ካደረገ በኋላ ቴናድዬ መጻፊያ ሰጠው፡፡
አባባ ሸበቶ መጻፊያውን ተቀበለ፡፡ ቃሉን እንዲቀበለው ቴናድዬ መናገር ጀመረ::
«የምወድሽ ልጄ…»
እስረኛው ዘገነነውና ቴናድዬን ቀና ብሎ አየው::
«ተወዳጅ ልጄ ብለህ ጻፍ» አለ ቴናድዩ:: አባባ ሸበቶ ትእዛዙን
ተቀበለ፡፡ ቴናድዬ ቀጠለ፡፡
«ፈጥነሽ እንድትመጪ ፤ በጣም አስቸኳይ ለሆነ ጉዳይ እፈልግሻለሁ።
ይህን ማስታወሻ የሚሰጥሽ ሰው ካለሁበት ይዞሽ ይመጣልና እጠብቅሻለሁ። ሳታመነቺና ሳታወላውይ ቶሉ ድረሽ፡፡»
አባባ ሸበቶ ጽፎ እንደጨረሰ «አድራሻህን አክልበት» በማለት ቴናድዩ አዘዘው::
እስረኛው ጥቂት አሰበና አድራሻውን ጻፈ፡፡ ቴናድዬ ወረቀቱን አንስቶ ካየው በኋላ በደስታ ፈነደቀ፡፡
«ውድ ባለቤቴ!» ሲል ጮኸ፡፡
ባለቤቱ ብድግ ብላ ወደ እርሱ ተንደረደረች::
«ይኸውልሽ ደብዳቤው:: ከዚህ ቀጥሎ የምትሠሪውን ታውቂያለሽ:: ምድር ቤት ጋሪ ቆሞ ይጠብቅሻል፡፡ ፈጥነሽ ሂጂና ቶሎ ተመለሺልኝ፡፡»
አሁን ከክፍሉ ውስጥ ቀርተው የነበሩት አምስት ሽፍቶችና እስረኛው ነበሩ። ከዚያ በኋላ ፀጥታ ሰፈነ፡፡ ማሪየስ ከላይ ሆኖ ከአሁን በኋላስ ምን ይሆን እያለ በጉጉት ይጠባበቃል፡፡ ያ አስፈሪ ዝምታ ረጅም ጊዜ ወሰደ፡፡
ከአንድ ሰዓት በኋላ የወጭ በር ሲከፈትና ሲዘጋ ሰሙ:: እስረኛው ለመነቃነቅ ሞከረ።
«ሞጃዋ መጣች» አለ ቴናድዬ::
ይህን እንደተናገረ ሴትዮዋ ግስላ መስላ ገባች፡፡ ፊትዋ ተለዋውጧል፡፡በንዴት ግላለች፡፡ ትንፋሽዋ ቁርጥ ቁርጥ ይላል፡፡ ከንፈርዋን እየነከሰች ጭንዋን ትጠፈጥፋለች::
«ያልሆነ አድራሻ ነው የሰጠን፡፡»
አብሮዋት ሄዶ የነበረው ሽፍታ ቆመጡን እንደያዘ ተከትሉ ገባ።
አባባ ሸበቶን ካልዠለጥሁ በማለት ዳር ዳር ይላል::
«ያልሆነ አድራሻ?» ሲል ቴናድዬ ጠየቀ፡፡
ሴትዬዋ ንግግርዋን ቀጠለች::
«እርሱ የሰጠን አድራሻ ሰው የሚኖርበት አይደለም:: በዚያ አካባቢ እርሱነቱን የሚያውቅ ማንም የለም::»
ሴትዮዋ ትንፋሽዋን ለመሰብሰብ ቆም ካለች በኋላ እንደገና ቀጠለች፡፡
“ውድ ባለቤቴ፤ ይህ ሰው አሞኝቶሃል፡፡ አየህ ስላዘንከለት እኮ ነው እንዲህ የሚጫወትብህ:: መልከ ጥፉ ቢሆን እንኳን ከነነፍሱ እቀቅለው ነበር ያን ግዜ የሚለፈልፈውና ሳይደብቅ ልጅትዋ የት እንዳለች የሚያወጣው:: እኔ ብሆን፣ በዚህ መንገድ ነበር የማውጣጣው:: ወንዶች ከሴቶች ይበልጥ ሞኞች ናቸው' የሚባለው በከንቱ አይደለም::»
ባለቤቱ ስትለፈልፍ ቴናድዬ ቁና ቁና እየተነፈሰ ለጥቂት ደቂቃ ቃል
ሳይተነፍስ ዝም ብሎ ቁጭ አለ:: ቁጭ እንዳለ ግን በቀኝ እግሩ መሬቱን ዝም ብሎ ይደበድባል፡፡ ዓይኑን ከከሰሉ ፍም እሳት ላይ ተክሏል፡፡ በመጨረሻ ግን እስረኛውን በክፉ ዓይን እያየ «ያልሆነ አድራሻ! የሚያዋጣህ ይመስላሃል?» ሲል ይጮህበታል፡፡
«ጊዜ ለማግኘት ነው» ሲል እስረኛ በኃይል እየጮኸ ተናገረ፡፡
ወዲያው ሰውነቱን ለማላቀቅ ኣካለን ይነቀንቃል:: ለካስ ከአንድ
እግሩ በስተቀር ቀስ እያለ ሰውነቱን አላቅቆ ነበር::

👍21
አንዳንድ ጊዜ በአጋጣሚ የሚሆን ነገር ለማመን ያስቸግራል፡፡ ዘወትር ምላጭ ተሸክሞ የማይሄደው ሰው ያን እለት እንዳጋጣሚ 'ጥፍሩን በምላጭ ከቆረጠ በኋላ ምክንያቱን ሳያውቀው ምላጩን እንደማስቀመጥ ከኪሱ ውስጥ
ይጨምረዋል፡፡ የኮዜትን አድራሻና መልእክት ለመጻፍ ቀኝ እጁን
ሊያላቅቁለት ቀስ ብሎ ሳይታይ ምላጩን ከኪሴ ያወጣል:: በምላጩ የታሰረበትን ገመድ ቀስ ብሎ ይቆርጣል:: ገመዱን በሙለ የቆረጠው እንደሆነ በአጉል ሰዓት እንዳይነቁበት የግራ እግሩ የታሰረበትን ገመድ ሳይቆርጥ ይተወዋል፡፡ ግን ለመንቀሳቀስ እንደሚችል ካረጋገጠ በኋላ ነበር
ሳይቆርጥ የተወው:: ሰዎቹ ኪሱን ሲፈትሹ ምናልባት ምላጩን በመዳፉ ጨብጦ ይዞት ይሆናል::
ከክፍሉ ውስጥ ሰዎቹ ከተሰባሰቡ በኋላ ሌሊቱ በጣም ይበርድ ስለነበር እሳት ያያይዛሉ:: ለምን እንደሆነ አይታወቅም ምናልባት እስረኛውን ለማጥቃት ብለው ያዘጋጁት ይሆናል፧ አንድ የእንጨት እጄታ ያለው ትልቅ ብረት ከእሳቱ ረመጥ ውስጥ ስለነበር በጣም ይግላል:: ሰባቱ ሰዎች
ጊዜ አግኝተው እርሱ ላይ ከመረባረባቸው በፊት አባባ ሸበቶ ተስቦ ሄዶ ያንን በረመጡ የቀላውን ብረት አንስቶ ይይዛል፡፡
ቴናድዬ፣ ባለቤቱና እንዲሁም የተቀሩት ሽፍቶች ፈርተወና
ተደናግጠው ከነበሩበት ወደኋላ ሽሽት ይላሉ:: የሚያደርጉትን አጥንተው ዓይናቸው ይቅበዘበዛል:: አባባ ሸበቶ ያንን የጋለውን ብረት ወደ ላይ አነሳ፡፡
ወደ ላይ ሲያነሳው ከዋክብት የመሰሉ ብልጭታዎች ከፍሙ ብረት ይንጠባጠቡ ጀመር፡፡ አሁን ቀስ ብሎ ግራ እግሩን አላቀቀ፡፡
ሌላው አስገራሚ ነገር ደግሞ ልክ በዚያቹ ሰዓት ፖሊሶች
ዝግጅታቸውን አጠናቅቀው ከክፍሉ ውስጥ ለመግባት ተሰናድተው ነበር፡፡
እስረኛው ድምፁን ከፍ አድርጎ የሚከተለውን ይናገራል፡፡
«ታሳዝናላች· ፧ የእኔ ሕይወት ግን እስከዚህም ተጨንቀውና
ተጠብበው የሚያድኑት ዓይነት አይደለም:: እናንተ እንደገመታችሁት እኔን
አስፈራርታችሁ የፈለጋችሁትን ለማወጣጣት ነበር፡፡ የፈለጋችሁትን
እንድጽፍላችሁም ተመኝታችኋል፡፡ ለማለት የማልፈልገውንም ለመናገር አስባችሁ ቃል ሳትገቡ አልቀራችሁም:: እንበል..» ካለ በኋላ ንግግሩን አቋረጠ
ከግራ ክንዱ ላይ ያረፈውን እጅጌ ወደ ላይ ሰበሰበ፡፡ ወደፊት አለው
ያንን በቀኝ እጁ ይዞት የነበረውን የጋለ ብረት ከሥጋው ላይ አሳረፈው ሰውነቱ ጩሰ፡፡ ሽታው ገለማቸው:: ማሪየስ የሚያየው ነገር ስላስደነገጠው ልቡ ቶሎ ቶሎ ይመታ ጀመር፡፡ ሽፍቶቹም በፍርሃት ተዋጡ የእስረኛው ፊት ግን ጭምድድ እንኳን አላለም::
ግራ እጁ ላይ የጋለ ብረት አርፎበት ሲጠበስና ሲጨስ ፊቱን ፈካ አድርጎ ወደ ቴናድዬ ዞረ:: ጭንቀቱንና ስቃዩን እንደ እንጀራ ውጦ በጥላቻ በፍቅር ዓይን አየው::
«የተረገማችሁ» አለ፤ «ራሳችሁን ፍሩ እንጂ እኔን አትፍሩኝ::»
የጋለውን ብረት ከሰውነቱ አንስቶ በመስኮት ወደ ውጭ ወረወረው::
ውሀ ላይ ስላረፈ ጭስ ሲወጣ በመስኮት ታየ:: እስረኛው ንግግሩን ቀጠለ፡፡
«አሁን የፈለጋችሁትን ልታደርጉኝ ትችላላችሁ:: »
ባዶ እጁን ነው የቆመው::
«በሉ ያዙት» ሲል ቴናድዬ ተናገረ::
ከሽፍቶቹ ሁለቱ ተግራ ተቀኝ ትከሻውን ያዙ ፊቱን የሸፈነ አንድ
ሰው ከፊቱ መጥቶ ቆመ::
ማሪየስ ከላይ ሆኖ በዝግታ የሚናገሩ ሰዎችን ድምፅ ሰማ፡፡
«አሁን ማድረግ ያለብን አንድ ነገር ብቻ ነው::
«ስውዬውን መግደል!»
«ይኸው ነው::
ባልና ሚስት ነበሩ ይህን የሚወያዩት፡፡
ቴናድዩ ዝግ እያለ ወደፊት ተራመደ:: የጠረጴዛውን ኪስ ከፈተ፡፡ ትልቁን ካራ አወጣ፡፡
ማሪየስ የሽጉጡን ቃታ ሳብ አደረገው:: ወደ መሬት ተመለከተ፡፡
አንድ ወረቀት ከራሱ ቤት ጠረጴዛ ላይ ተቀምጦ አየ:: ከወረቀቱ ላይ
«ሰዎቹ መጥተዋል» የሚል ቃል የተጻፈበት ለመሆኑ ተገነዘበ፡፡ ወረቀቱን የጣለችው) የተናድዩ ትልቅዋ ልጅ ነበረች::
አንድ አሳብ መጣለት:: ይህም አሳብ ተንጠልጥሎ ያለውን ችግር
የያኑን አruነበተ:: የሚፈታ
መሰለው:: አሳቡ ተበዳዩን ነፃ የሚያወጣና ወንጀለኞቹን የሚያድን መሆኑን አመነበት ቶሎ ብሎ ከነበረበት ወርዶ ወረቀቱን አነሳ ፤ ጠቀለለው
ሽፍቶቹና አባባ ሸበቶ ከነበሩበት ክፍል በቀዳዳ ወረወረው::
ቴናድዬ ፍርሃቱን ዋጥ አድርጎ በቆራጥነት ካራውን ይዞ ወደ እስረኛው ሲያመራ ነው ወረቀቱ ከመሬት ዱብ ያለው::
«አንድ ነገር ወደቀ» ስትል ሚስስ ቴናድዩ ጮኸች::
«ምንድነው እሱ?» ሲል ሚስተር ቴናድዩ ጠየቀ::
ሴትዬዋ ሮጣ ሄዳ ወረቀቱን አነሳች:: ለባልዋ ሰጠችው::
«ከየት መጣ? እንዴት ከዚህ ሊገባ ቻለ?» ሲል ጠየቀ::
«ሞኝ» አለች ሴትዮዋ:: «ከየት ሊመጣ ይችላል! በመስኮት ነዋ !
የሚገባው::
ቴናድዬ ቸኩሉ ወረቀቱን ገላለጠው:: ወደ ብርሃን ይዞት ሄደ፡፡ የልጁ የኢፓኒን የእጅ ጽሑፍ ነው::
‹‹የት ኣባትዋ፧ ሰይጣን!» አለ፡፡
ለባለቤቱ ምልክት ሲሰጣት ቶሎ ብለ" ብላ ወደ እርሱ መጣች:: ከወረቀቱ ላይ የተጻፈውን አሳያት፡፡ ከዚያም «ቶሎ በይ! መሰላሉን» አላት::
«የሰውዬውን አንገት ሳንቆርጥ?» ስትል ጠየቀች::
«አሁን ጊዜ የለንም::»
እስረኛውን ይዘው ቆመው የነበሩት ሽፍቶች ለቅቁት:: ከመቅጽበት
የገመድ መሰላል በመስኮት በኩል አንጠለጠሉ:: . መስኮቱ ላይ ከነበረው ወፍራም ማንጠልጠያ ጋር ጠፍረው አያያዙት:: እስረኛው ምን እንደሚሆን አላስተዋለም:: እርሱ ጸሎት ወይም ቅዠት ላይ ነበር፡፡
መሰላሉ በትክክል ከታሰረና ከተነጠለጠለ በኋላ «ጌታው፧ ና እስቲ!»ሲል ቴናድዬ ተናገረ:: ከዚያም ወደ መስኮቱ ሮጠ፡፡
«አይሆንም» አለ አንደኛው ሽፍታ ፤ «መጀመሪያ ማን እንደሚወጣ
እጣ እንጣል::»
«ጀሎች ናችሁ መሰለኝ! ለምን ጊዜ ታባክናላችሁ? ቶሎ ብላችሁ
ስማችንን ጻፉና ጠቅልሉዋ! የተጠቀለለትን ከቆብ ውስጥ ወርውሩአቸው በማለት ቴናድዬ ሲናገር «የእኔ ባርኔጣ አይሻላችሁም» ብሎ ጎርነን ያለ
ድምፅ ከበር ላይ ቆሞ ይናገራል:: ሁለም ወደ በሩ ፊታቸውን አዞሩ። )
ዣቬር ነበር፡፡ ዣቬር ባርኔጣውን አውልቆ በእጁ ይዞታል:: የእጣውን ! ቲኬት እንዲጨምሩበት ባርኔጣውን ገልብጦ ነው የያዘው፡፡....

👍23❤1
#ዶክተር_አሸብር
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
፡
፡
#ሰባት
ቁጥር ስፍር የሌለው ሕዝብ ለቅሶ ለመድረስ የወይዘሮ እጥፍወርቅን ግቢ አጥለቀለቀው:: ቀስ
በቀስ አስተዛዛኙ እየተመናመነ መጥቶ በመጨረሻ ግቢው ወደ ነበረው ገዝምታ ተመለሰ፡፡ ከሀዘኑ
በኋላ ነገሮች ህልም በሚመስል ሁኔታ ተቀያየሩ። ሀዘኑ ባበቃ በጥቂት ወራት ውስጥ ፋናዬን
ወንድሞቿ ሲዊዲን ወደሚባል ሀገር ወሰዷት፡፡
ፋኒ የእኔ እህት አቲዬን ስማ በተሰበረ ልብ ግቢውን ለቀቀች፡፡ አቲዬ በምድር ላይ ያሏትን ሁለት
ዘመዶች አጣች፡፡ ዛሬም ይሄን ስታወራኝ ዓይኗ ውስጥ ህመም ይንቀለቀላል። ነፍሷ ይቃትታል፣
ዝም ብላ ትቆይና፤
"አሹዋ” ትለኛለች፡፡
“አቤት አቲዩ!"
"ሱዲን የሚሎት ሀገር ወዴት ነው? ፡፡ ስዊዲን ሀገር ቤትና ሕዝብ ተቆጥሮ የሕንዘቡ ቁጥር
ምንትስ ሚሊዮን ደረሰ ሲባል አቲዬ አታምንም፡፡ የስዊዲን ህዝብ ቁጥር አንድ ብቻ ነው ፋናዬ ብቻ !! አቲዬ የዛችን ደግ ሴት ልጅ ፋናዬን እንደ እየሩሳሌም አንድ ቀን ልታያት ፅኑ መሻት ፊቷ ላይ ይንቀለቀላል፡፡
አንዲት እድሜዋ አርባ የሚሆን ሽቅርቅር፡ ሲበዛ ቆንጆ የሆነች ሴትዬ (የወይዘሮ እጥፍወርቅ እህት ናት ይላሉ) ከሁለት ጨምላቃ ሴት ልጆቿ ጋር፣
ወር ሳይሆን ጠብቂ ተብላ
እግዜር ይወቅ ብቻ ግቢውን ትኖርበት ጀመረ፡፡ ሆቴሉ ተሸጠ፡፡ እች ሴት አስቴር ትባላለች፡፡ ምኗም የማይጨበጥ ተልካሻ ሴት ! ከዕድሜዋ ጋር ጦርነት የገጠመች ማቶ !
አንዳንዴ በተረት የሚታወቀው አስማተኛ መስተዋት መኝታ ቤቷ ውስጥ የተቀመጠ ይመስል
ገብታ በወጣች ቁጥር ልብስ የምትቀይር፣ “የሆነ ቦታ በመልክ የምትበልጥሽ ውብ ሴት አለች
እያላት መስተዋቱ፡ ፊቷ ላይ የትራስ ሰንበር ከሚወጣ ኢትዮጲያ ላይ ከሰሜን እስከ ደቡብ
ጫፍ አዲስ ስምጥ ሸለቆ ሲፈጠር የምትመርጥ የውበት ስስታም " የዕለት እንጀራዋ የሰው
ዓይን የሆነ ከንቱ፣ የእጥፍወርቅን ግቢ በባለቤትነት ታስተዳድር ጀመር፡፡
አቲዬን እንደ ሰራተኛ ስለምታስባት ማመናጨቅ የጀመረቻት ገና የሀዘንተኛው እግር ጨርሶ ሳይወጣ ነበር፡፡ እኔንማ ግልገል ሰይጣን አድርጋ ነው የምታየኝ፡፡ በወይዘሮ እጥፍወርቅ የለመድኩትን መዘባነን ታጥቄ ወደ ሳሎን ዘው ስል በቲሸርቴ አንጠልጥላ መሬት ለመሬት እየጎተተች በረንዳው
ላይ የመወርወር ያህል ትጎትተኝና፣ “ማነሽ አንች ልጅ ነይ ወደዛ ውሰጅ ይሄን ልጅሽን !
እንዴ የምን መጨማለቅ ነው እሱ…ሁለተኛ እዚህ ምንጣፍ ሳይ ሲወጣ እንዳላይ!" ብላ እጇን
ታራግፋለች::
አቲዬ ነፍስና ስጋዋ እየተሟገተ መወልወያ ይዛ ትገባና ያበላሸሁት ነገር ካለ ትፈልጋለች። ብዙ
ጊዜ ግን የዚህች ከንቱ ጩኻት ምከንያት አልነበረውም፡፡ ምክንያቷ ሰው አለመፈለግ ነው።
ሰውን በማራቅ ሰላም ይገኝ ይመስል ! ሁካታ ነፍሷን ሀቅ አጉርሳ ዝም እንደማስባል የቀረባትን ሁሉ ታፍናለች፡፡
በዚያ ከወራት በፊት ምግብ ይልከሰከስበት በነበረ ግቢ ውስጥ ጣረሞት ራህብ ያንዣብብ
ጀመረ፤ በፊት ወተት የምትገዛልኝ እጥፍወርቅ ነበረች፡፡ መሶቧ መሶባችን፣ ድስቷም ድስታችን
ነበረ፡፡ እንዲህ ባጭር ጊዜ ከጓዳችን ቁራሽ ዳቦ፣ ንጣይ እንጀራ ይነጥፋል ብሎ ማን አስቦ !
አንዳንዴ ምቾት ያዘናጋል፡፡ ምቾት ስትኖርበት ዘላለማዊ ይመስላል፡፡ ሜዳ ላይ ጥሎህ እንደ
ጉም ሲተን ነው ፊቱ ላይ ቀዝቃዛ ውሀ እንደቸለሱሰት ሰው የምትበረግገው:: ስንቱ ቤተሰብ
ድንገት ከምቾቱ ችግር ተኮርኩሞ ነቅቷል፡፡ ስንቱ ባለስራ ስራውን ተደግፎ፣ ድጋፉ ሲከዳው
ወድቆ ቀርቷል፡፡ ሰንቷ ባለትዳር፣ የባሏ እጅ ሲነጥፍ አብሮ ቅስሟ ተሰብሯል፡፡ አግኝቶ ማጣት
ብሎ ህዝቡ የሚጠራው ይሄንን አይደል ተገኝቶ መጥፋት ቢሉት ይሻል ነበር !
አስቴር አቲየን ታዝዛታለች፣ ታመናጭቃታለች፣ ትልካታለች፣ ግን ብርም ሆነ ምግብ አትሰጣትም፤ የሚገርመው ደግሞ ቤቱ ውስጥ እንጀራ አይጋገርም ወጥም አይሰራም፡፡ እናትና ቦዘኔ ልጆቿ የታሸገ ነገር ይገዙና መኪናውም ውስጥ መንገድም ላይ ይበላሉ ማሸጊያውን ወዳገኙበት ይወረውሩታል፡፡ እነዛን ደማቅ ጽሑፍ ያላቸው የቸኮሌት ላስቲኮች በርሃብ እየተንሰፈሰፍኩ
ቀድጄ የላስኩባቸው ጊዚያት ብዙ ነበሩ ዛሬ ቸኮሌት እንደ መርዝ እጠላለሁ !! እነዛ ባዶ
የፍራፍሬ ጭማቂ ዕቃዎች ስይት ነበሩ ለኔ፡፡ ዘመናዊነት ያደነዘዛቸው እናትና ልጆች ምቾት
ውስጥ የመነኑ የስንፍናና የክፋት ቆብ የጫኑ ርኩሶች ነበሩ፡፡ እንኳን ግቢያቸው ውስጥ ለተጠጉ
ሚስኪኖች፣ እርስ በርሳቸውም የተለያዩ የሰው ከብቶች፡፡
መኝታ ቤታቸውን በየፊናቸው ዘግተው፣ ማንም አራት እግሩን ቢበላ አልሰማንም አላየንም
ብሎ የሚጮህ ጋግርታም የግለኝነት ባሕር ውስጥ የተጠመቁ፡፡ የምዕራባዊያኑን ቆሻሻ ግለኝነት የስልጣኔ አልፋ፣ የዕውቀት ኦሜጋ ያደረጉ ፉዙዎች፡፡ በእንግሊዝኛ እየተለፋደዱ፣ በአማርኛ
የአዕምሮ መቃወስ ውስጥ የተዘፈቁ የቤት ዕቃዎች፡፡ የሞራልም ይሁን የሀይማኖት፣ አልያም ከነፍስ ስልጣኔ የሚመነጭ ጠንካራ ስብዕና የሌለው ኢትዮጲያዊ፣ ውጭ ሀገር ደርሶ ሲመለስ ምን አይነት አስቃቂ ማቶንት ውስጥ እንደሚነከር የታዘብኩት በእነዚህ ከንቱዎት ነበር፡፡እናታቸው ሀያ ዓመት፣ ልጆቹ እየሄዱ እየመጡ ከአስር ዓመት በላይ አሜሪካ ኖረዋል፡፡ አስቴር
ታዲያ ለዓመታት ከኖረችበት አሜሪካ ምን ይዛ መጣች? ሰምቻታለሁ ለመጣ ለሄደው፣
“አበሻ ስራ አይወድም፣ ነጮቹ እኮ ለሰዓት ያላቸው ክብር ለስራ ያላቸው… "
“አበሻ የተመጣጠነ ምግብ አያውቅም ማድፋፋት፣ ጥሬ ከብስል ማጋበስ…"
“አበሻ መች ንፅህና ይወዳል ነጮቹ እኮ."
"ኤዲያ የሀበሻ ወንድ መች ሴት ያከብራል ነጮቹኮ”
“የአበሻ ልጅ አስተዳደግ.…
የአበሻ ሕክምና ደግሞ ራሱ በሽታ ነው፡፡ ነጮቹ እኮ”
አበሻ ገንዘብ ከመሬት የሚታፈስ ነው የሚመስለው፡፡ ዓይኑን በጨው አጥቦ፣ ዶላር ላኩ ነው
ነጮቹ እኮ አስራ ስምንት ዓመት ከሞላቸው… "
ነጭ የባርነት ቀንበር ጫንቃዋ ላይ ተሸክማ የምትደሰኩር ቱልቱላ፡ ከየትም የፈለፈለቻቸው ልጆቿ
በአስተዳደግ ይሁን የግል ባህሪ ምን ዓይነት እናት አንደሆነች ጮኸው እያወጁ፣ “ዓይናችሁን
ጨፍኑ ላሞኛችሁ” ትለናለች፡፡
የነጮቹ ፅንፍ የለሽ ውክቢያ ዕድሜዋን ሙሉ ያጨቀባት የታላቅነት አባዜ አበሻን በበጎ እንዳታይ እንደ ጋሪ ፈረስ ቀይዷት፣ ለእግዜር ሰላምታ የቀረባት ሁሉ የፈጋችበትን ዶላር የሚነጥቃት
እየመሰላት ስጋዋ ያልቃል፡፡ ልጆቿም በየአጥሩ ጥግ ከሚያናንቁት የአበሻ ወንድ ጋር ሲሳሳሙ እና በየመሸታ ቤቱ ሲዳሩ ከማምሸት ውጭ የፈየዱት ተዓምር የለም፡፡ በነፃይቱ ሀገር ኖረው ለመጡ የስልጣኔ ጥጎች፣ የከንፈር ዋጋው የዶላሩን ያህል ውድ አይደለም፡፡ እነዛ ወንበር ስበው በክብር ሴትን ልጅ የሚያስቀምጡ ነጫጭ ወንዶች የሴትነትን ክብር እየሰበኩ ሰብዓዊነታቸውን ከእግራቸው ስር እንደጨፈላለቁት ለመረዳት የጋረዳቸው ነጭ ደመና አይፈቅድላቸውም
ለእነዚህ የስልጣኔ ርዝራዦች የሰው ልጅ ስለክብሩ መኖር፣ ስለማተቡ ዓለማዊነትን በልክ ይሁን ማለቱ ተራ መኮፈስ ነው:: ቦርሳቸውን ከመከፈት፣ ለማንም አላፊ አግዳሚ እግራቸውን መከፈት ይቀላቸዋል፡፡ ምክንያቱም “ዶላር የተከበሩት የነጮች ውድ ቅርስ” ሲሆን ሰውነታቸው ግን
የርካሾቹ፣ የሰነፎቹ፣ ያልተማሩት፣ ሥራ የማይወዱት፣ ብር ከመሬት የሚታፈስ የሚመስላቸው
አበሾች ርካሽ ንብረት ነው፡፡
በዚህ ፍልስፍና አገሩን አጥምቀውት አገሬው ፈረንጅ ባል ፍለጋ ሲራኮት ሲታይ ምን ይገርማል !
አቲዬ አንድ ቀን እየፈራች ሴትየዋን አናገረቻት፤ “እትዬ ወጥቼ አንዳንድ ስራ ልሰራ ነበረ ምናልባት ከፈለጉኝ ብዩ ነው…"

👍31❤2
“ስራሽ ምንድን ነው?” አለች ሴትዮዋ አቲዬን ከታች እስከ ላይ እያየቻት፡፡
“እኔ እትዬ እጥፍወርቅ ጋ እንጀራም እጋግራለሁ ያው ለሆቴሉ፣ እዚሁ ነው ስራዬ ሌላ ምን ስራ አለኝ
“እኔ የማሰራሽ ነገር የለም፡፡ ውጭ ነው የምንበላው:: ልትሄጂ ትችያለሽ፡፡” እቲዬ ደነገጠች፡፡
“ቀን ቀን ስራ ሌላ ስፍራ እየሠራሁ፣ ለማደሪያዬ እዚሁ ቢፈቅዱልኝ፡፡ መሄጃም የለኝም፣ ከነልጇ ለነፍሴ ብለው እትዬ እጥፍወርቅ አስጠግተውኝ ነው "
“ኤጭ አበሻ ሲባል የነፃ ራት ካልበላ እንቅልፍ አይወስደውም፡፡ ጤነኛ ነሽ፣ እግር እጅ አለሽ፣
ሰርተሽ ሳትሳቀቂ ቤት ተከራይተሽ መኖር ስትይይ አስጠግተውኝ ቅብርጥሶ ማለት ምን አመጣው፤
ነጮቹ ቢሆኑ…“ ደሰኮረች፡፡ እቲዬን እዛ መቆየቷ ብዙም ደስ አላላትም፡፡ ቢሆንም አንዳንድ
ሥራ ማሠራቱ እንዳለ ልቧ አውቆታል፡፡ የነፃ ጉልበት የማይፈልግ የነጭ አድናቂ ማን አለና፡፡እናም አቲዩን እንዲህ አለቻት፣ “እንግዲያው ፀባይሽን አሳምረሽ ኑሪ፣ እኔ ጫጫታ ምናምን አልወድም፡፡ ቤቱን ከፈለግኩት በማንኛውም ጊዜ ትለቂያለሽ…"
አቲዬ እኔን አዝላ ወደረሳችው መንከራተት ተመለሰች:፡ አዲሳባ ውስጥ የምታውቀው መንደር
አንድ ነው እዛም ቀለመወርቅና ዘርፌ አሉ.. አሳ ነባሪዎቹ ሦስት ዓመት ፀሐይ ሳይነካት
ብርቱካን መስላ የወጣችውን አቲዬን ሲያዩ ጥርሳቸውን እፏጩ፡፡ ቀለመወርቅ ደፋሩ ምራቁን እየዋጠ እንደገና ተመኛት፡፡ ስላማረባት መንደርተኛው በሙሉ ጠላት፡፡ ዘርፌ የክፋት ልምጯን አዘጋጅታ ነበር የተቀበለቻት።
ከከፍታ እንደመውረድ ውርደት፣ ረግጠው ወዳለፉት ነገር እንደመመለስ ታላቅ ሰቆቃ የለም፤
የራስህ ወገኖች መብረር ስትጀምር እሰይ ከማለት ይልቅ ክንፍህ ተሰባብሮ እግራቸው ስር
ወድቀህ ስትፈጠፈጥ ለማየት ይጓጓሉ፡፡ እናም ስትወድቅ ይረካሉ፡፡ 'ብዬ ነበር፣ አያችሁ
እየተባባሉ የምቀኝነት ትንቢታቸው የሰመረላቸው ምቀኛ ነብያት ይንጫጫሉ፡፡ ብሔራዊ ምቀኝነት
የተጠናወተው ሕዝብ እንደኛ ይኖር ይሆን? “ ለምን በደፈናው እንሰደባለን?” ይልሀል ምቀኛ
ስትለው የተዳፈነበት አመክንዮ እየደረደረ፣ ሁሉም አንድ አይደለም ይልሀል፤ ግን ሁሉም አንድ
ነው፡፡ ሰጥቶታል እንደ ውሃ፣ በልቶታል እንደ እንጀራኛ ጥሬ ስጋው !! ቢማርም ቢያገኝም፣
ምቀኝነቱን ያዘምናታል እንጂ ቢሞት አይጥላትም፤ ማተቡ ናት፡፡
ከነዚህ ሰኋላ የሆነውን ዝርዝር ነገር ስናገር ማንንም ሳይሆን ራሴን እጠላለሁ፡፡ አቲዩ በስጋም
በነፍስም የቀለመወርቅ መጫወቻ፣ የዘርፌ ገረድ ሆና ኖረች፡፡ ለስንት ዓመት፡፡ ዘርፌ ቤት
የመደሀኒያለም ዝክር፣ እከሊት ቤት የኪዳነምህረት ዝክር፣ አሻሮ፣ የተበላ ቂጣ፣ ድፎ ዳቦ፡፡
የእከሊት ልጅ ልታገባ ነው ወጥ ስሪ፣ ጠላ ጠማቂ፡፡ ሲወልዱ - ልደት፣ ክርስትና እሳት በላት እናቴን፡፡
ውበቷን ጤናዋን ወጣትነቷን እሳት በላው። አቲዬ እንደብረት ምጣድ እሳት ላይ ተጥዳ እኔ የምባል ጣፉጭ ኬክ በላይዋ ላይ በሰልኩ፡፡ ይሄ ሁሉ ሥራ በዚህች ሚስኪን ሴት ላይ ተጭኖ፣
ማታ ወደ ማደሪያዋ ስትመለስ የአስቴር ጨምላቃ ሴት ልጆች የውስጥ ልብስ ላይቀር በየቦታው
ተወርውሮ ይጠብቃታል፡፡ ቀን እናትና ልጆች ሲወጡ ወንድ የሚራኮትላቸው ዘናጮች፣ ሽቷቸው ከሩቅ የሚጣራ ሽቅርቅሮች፣ የቤታቸውን ጉድ ወላድ አይየው! እነዚህ በየአደባባዩ ሽቅርቅር
የሚሉ ሰዎች ቤታቸው የዝርክርክነት ጥግ የሚሆነው ለምንድን ነው ግን ? ብዙ ሰው አየሁ ብዙ ሽቅርቅር !!
ሴት ልጅ ቢያንስ የውስጥ ልብሷን የራሷን ገመና እንዴት ሌላ ሰው እንዲያጥብላት ትፈልጋለች
ለዛውም በየካፍቴሪያው ተጎልተው ሲገለፍጥ የሚውሉ ስራፈት ሴቶች፡፡ አይቻለሁ በአስቴር
ልጆች ! እናታቸውም ያው ናት፡፡ የዘር ነው መቆሸሽ፡፡ ከማን ይማራሉ? ያኔ ነው ረጅም ጫማ
አድርጎ ከመቆነን በፊት፣ ፀጉር እየነሰነሱ አገር ይየን! ከማለት በፊት፤ 'ሴት' ሲባል ፊቴ የሚደቀነው ይሄው ፅንፍ አልባ ስንፍና ነው:: የሴት ልጅ ስንፍና እንዴት ይቀፋል? መንገድ ላይ ሰበር ሰካ የሚሉ ሴቶች ሁሉ ከውስታቸው በፊት መታጠቢያ ቤታቸው ነው ዓይኔ ላይ የሚደቀነው፡፡
ድንገተኛ ፍተሻ ይደረግ ቢባል፣ ከዝርከርኩ ወንደላጤ፣ ካልሲ በየቦታው ከሚጥለው ወንድ የባሰ
ስንት ጉድ ሴቶች አሉ፥ ስንትና ስንት ወር ሙሉ ሰው ሰራሽ ፀጉር እናታቸው ላይ ጀልቶ መሬት
ኣይንካን የሚሉ፡፡ በዛ የልጅነት እድሜዬ ተላላኪነትን በተማርኩባት፣ ለመኖር ስል የመሽቆጥቆጥን እርምጃ ዳዴ ባልኩባት በህይወት ውጣ ውረዴ ነበር “ሴትነት ደራሽ ንፋስ የሚከምረው፣ ደራሽ ንፋስ የሚበትነው የምድረ በዳ የአሸዋ ክምር ነው" ብዬ በሴት ተስፋ የቆረጥኩት። የአስቴር
ልጆች፣ ሴት መስለውኝ !! መቼስ በሕይወት ውስጥ ሕይወትን አጠናግረን እንድንመዝናት
የሚያደርጉን አባይ ሚዛኖች አይጠፉ፡፡...

👍34
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
ዣቬር ምልክት ሲሰጣቸው ብዙ መሣሪያ የያዙ ፖሊሶች ከክፍሉ
ውስጥ ገቡ፡፡ ሽፍቶቹን ያዝዋቸው: ክፍሉ ውስጥ በርቶ የነበረው ሻማ
አንድ ብቻ ስለነበር ክፍሉ ውስጥ ሰው ሲበዛ ጊዜ ብዙ ጥላ በማጥለሉ እየጨለመ ሄደ።
«ሁሉንም በብረት ሰንሰለት እጆቻቸውን እሰሩ» በማለት ዣቬር አዘዘ
«በሉ ወደዚህ ኑ» የሚል ቀጭን የሴት ድምፅ ተሰማ፡፡ ሚስስ
ቴናድዬ ነበረች፡፡ ባልዋ ከለበሰችው ሰፊ ካባ ስር ተሸሽጓል፡፡
ጠንቀቅ በሉ!» ስትል በመጮህ ተናገረች::
ሽፍቶቹ በሙሉ ያለማንገራገር እጆቻቸውን ሰጥተው ሲጠፈሩ
በማየትዋ «ፈሪ ሁሉ!» ስትል አጉረመረመች፡፡
ዣቬር ፈገግ አለ፡፡ ሚስስ ቴናድዬ ወደነበረችበት አመራ፡፡
«አይጠጉኝ፧ ከዚህ ቶሎ ቢወጡ ይሻላል» ስትል በማንጓጠጥ
ተናገረች::«እምቢ ካሉ ዋጋዎን ነው የምሰጥዎት::»
«ደፋር» አለ ዣቬር፡፡ «እመቤቴ እንደ ወንድ ጢም አብቅለዋል፤ እኔ
ደግሞ እንደ ሴት ጥፍር አሳድጌአለሁ» ሲል አሾፈባት።
ዣቬር እየተጠጋት መጣ፡፡ አጠገብዋ አንዳንዴ ልጆችዋ አንዳንዴም ራስዋ የምትቀመጥበት ድንጋይ ነበር፡፡ ዘልላ ሄዳ ያንን ድንጋይ አነሳችና
ዣቬርን ለመምታት ወረወረችው:: ዣቬር ጎንበስ በማለት ራሱን አዳነ፡፡ድንጋዩ ከግድግዳ ጋር ሄዶ ተላተመ:: የግድግዳው ቀለም ፈራርሶ ወለሉን ሞላው:: ድንጋዩ ሲመለስ እየተንከባለለ ከዣቬር እግር ስር ደረሰ።
ዣቬር ወደ ባልና ሚስቱ ሄደ:: በአንድ እጁ የሴትዮዋን፤ በሌላ እጁ የወንዱን ትከሻ ጨምድዶ ያዘ፡፡
«መሣሪያ አምጡ» ሲል ጮኸ፡፡
ወዲያው የብረት ማሠሪያ መጥቶ ሁለቱ ሰዎች ተቀፈደዱ። የራስዋና
የባልዋ እጆች መቀፍደዳቸውን ባየች ጊዜ «ወይኔ ልጆቼ» በማለት ከጮኸች ኋላ ከመሬት ላይ ተዘረረች፡፡
«በእድላቸው ያድጋሉ» ሲል አፌዘባት::
ሦስቱ ፊታቸውን በከሰል ያጠቆሩና ሦስቱ ፊታቸውን በጨርቅ የሸፈኑ ሽፍቶች እጃቸው ታስሮ ቆመዋል::
«ፊታችሁን እንደሽፈናችሁ ቆዩ» አለ ዣቬር፡-
እያንዳንዳቸውን በስም እየጠራ አንዱን «እንደምን አመሸህ»፣ ሌላውን ጤና ይስጥልኝ»፤ ሌላውን ደግሞ «ብርቱም አልሰነበትክ» በማለት
ሰላምታ ከሰጣቸው በኋላ ገና ከክፍሉ ሲገባ አንገቱን ደፍቶ ቆሞ
የነበረው እስረኛ ታወሰው::
«እስረኛውን ፍቱት» ሲል አዘዘ፡፡ «ከዚህ ቤት ደግሞ አንድ ሰው .
እንዳይወጣ?»
ይህን እንደተናገረ ከወንበሩ ላይ ሄዶ ቁጭ አለ፡፡ ከኪሱ ወረቀትና
ብዕር አውጥቶ ከጠረጴዛው ላይ አስቀመጠ፡፡ ቀና ብሉ «እያየ እስረኛውን ወደዚህ አምጡት» አለ፡፡
ፖሊሶቹ በዓይን ፈለጉት::
«ምነው፤ ምን ያንቀረፍፋችኋል? የት አለ ሰውዬው?» ሲል
ጮኸባቸው::
እስረኛው አባባ ሸበቶ ከዚያ አልነበረም፧ ወጥቶ ሄዷል፡፡
በሩ ላይ ፖሊስ ቆሞአል፡፡ የነበሩበት ክፍል ፎቅ ቤት ነው:: ታዲያ የት ሄደ? መስኮቱ አጠገብ ፖሊስ አልነበረም:: ትርምሱ ሲበዛ ቀደም ሲል እነቴናድዬ ለማምለጫ ባዘጋጁት የገመድ መሰላል አድርጎ ሾልኮአል። የፖሊሶቹ ዓይን አርፎ የነበረው ሽፍቶቹ ላይ ነበር፡፡
«ጋኔላም!» አለ ዣቬር በጥርሶቹ መሀል፤ «ጥሩ ምስክር ይሆነን
ነበር፡፡»
በሚቀጥለው ቀን ማታ አንድ ልጅ በኃይል እያፏጨና እየዘመረ
በመንገድ ላይ ሲጓዝ ከአንድ ነገር ጋር ይጋጫል፡፡ የተጋጨው ከሴት ጋር ነበር፡፡ ለመውደቅ እንደ መንገዳገድ ይልና ወደኋላ ዞር ብሎ ይመለከታል::
«ምነው! ትልቅ ውሻ መስሎኝ ነበር፡፡»
አሮጊትዋ ገንፍላ ከተኛችበት ብድግ አለች፡፡
«የተረገምክ» አለች ፤ «ከድካም ብዛት ሰውነቴ ባይከዳኝ ምን
እንደማደርግህ አውቅ ነበር፡፡»
ልጁ ኣሁን ትንሽ ራቅ ብሎ ነበር የቆመው፡፡
«ፕስ... ፕስ...» በማለት ካሽሟጠጣት በኋላ «በካልቾ ማቅመሴ አልተሳሳትኩም ፤ አበጀሁ፤ አበጀሁ» ሲል ተናገራት፡፡
ሴትየዋ ከተቀመጠችበት ብድግ አለች፡፡ ልጁ ሮጦ ሸሽ፡፡ እርሱን ለመያዝ ስትሮጥ መብራት ከነበረበት ደረሰች፡፡ የፊትዋ መሸብሸብና የወገብዋ መጉበጥ በግልጽ ታየ:: ልጁ ራቅ ብሎ ቆሞ አጤናት።
«እኔ የምወደው መልክ የለሽም» ብሎአት እያዜመ መንገዱን ቀጠለ፡፡ የቤት ቁጥር 50-52 ስለደረሰ ቆመ፡፡ በሩ መቆለፉን ሲያይ በእርግጫ መታው
አመታቱ የልጅ ሳይሆን የአዋቂ ነበር፡፡ ለካስ መንገድ ተኝታ
ያያት ሴት ትከተለው ኖሮ ከነበረበት ደረሰች::
ምንድነው ነገሩ እባካችሁ? ያ ከበሩ ላይ የቆመው ማነው? የእግዜር ያለህ በሩን እየሰበሩት ነው፤ ሌቦች ከቤቴ ሊገቡ ነው» ስትል ጮኸች፡፡
ልጁ በር መደብደቡን ቀጠለ፡፡ ሴትዬዋ ትንፋሽ አጥሮአት መተንፈስዋ በግድ ሆነ፡፡
«የአሁነስ ዘረፋ ዓይን በዓይን ሆነ እንዴ?» ብላ ከጠየቀች በኋላ ልጁን አተኩራ ስትመለከተው ማን እንደሆነ አወቀችው፡፡
«እንዴ! ያ ርኩስ፤ ያ ሰይጣን ነው እንዴ!»
«ጉድ ፈላ! አሮጊትዋ ናትና» አለ ልጁ ወደኋላ እየሸሸ፡፡ «ዘመዶቼን
መጠየቅ መጥቼ እኮ ነው::»
«ከዚህ ማንም የለም፤ አንተ ጋኔል» አለች ሴትዬዋ ጥላቻዋን ከፊትዋ ላይ ለማሳየት እየሞከረች::
«አይ ምን ይላሉ እርስዎ ደግሞ፤ ታዲያ አባቴ የት ሄደ?»
«ላ ፎርስ ከተባለ ሥፍራ፡፡»
«እናቴስ?»
«ሳን ላዛር፡፡»
«እሺ፧ እህቶቼስ?»
«ሌ ማደለኔ ሄደዋል፡፡»
ልጁ ጆሮውን አከክ እያደረገ ሴትዮዋን ቀና ብሎ አያት:: ሴትዮዋ እነቴናድዬ ይኖሩበት የነበረው ቤት ጠባቂ ነበረች፡፡
«እንዴት ይሆናል?» ሲል ራሱን ጠየቀ።
ከዚያም ፊቱን አዙሮ ቀደም ሲል ያዜመው የነበረውን ዜማ እያዜመ
መንገዱን ቀጠለ፡
ቅዱስ ዴኒስና ከፕሎሜ
ጎዳና ያስ ቤት
ኢፓኒን
ማሪየስ ባጠመደው ወጥመድ ፍርድ ሲገለባበጥ አየ:: የፖሊሱ
አዛዥ እስረኞቹን ይዞ ወጣ፡፡ ማሪየስም ከነበረበት ክፍል ወዲያው ሄደ፡፡ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ገደማ ሆኖአል፡፡ ወደ ጓደኛው ቤት አመራ፡፡ ከጓደኛ
ው ከኩርፌይራክ ቤት እንደደረሰም ከእርሱ ጋር ለማደር እንደመጣ ገለጸለት፡፡ ኩርፌይራክም ከመሬት ላይ ፍራሽ አነጠፈለት::
በሚቀጥለው ቀን በጠዋት ከቤቱ ተመልሶ ያለበትን ቤት ኪራይ
ክፍሎ ቤቱን ለቀቀ፡፡ እቃውን በጋሪ አስጭኖ ከኩርፌይራክ ሰፈር ሄደ፡፡
ዣቬር የልጁን ስም ረስቶ ከቤቱ አገኘው እንደሆነ ብሉ ቢመጣ
አጣው:: ማሪየስን ለማግኘት ብዙ ሞከረ ፤ ግን አልተሳካለትም:: ምናልባትም ልጁ የሚደርሰውን አደጋ ላለማየት ብሎ በመፍራት ከአገር የጠፋ መሰለው::
ማሪየስ ግን ባየውና በተሰጠው ፍርድ እጅግ ተረብሾ ነበር፡፡ ሁሉም
ነገር ጨለመበት:: የሚያየው የወደፊት ተስፋ ከፊቱ ራቀ፡፡ ልቡ የተሰቀለላት ልጅና አባትዋ ድንገት እንደ ብርሃን ብልጭታ ብቅ ብለው እንደገና ተሰወሩበት:: የእርሱ የወደፊት ተስፋ እነዚህ የማይታወቁ ፍጡሮች ነበሩ፡፡
ልቡ በልጅትዋ ፍቅር ታውሮአል፡፡ «ሂድና ፈልጋት» ብሎ ስሜቱን
ቢገፋፋውም ዓይኑ ማየት ስላልቻለ እንዲያው ዝም ብሎ መረበሽ፤ መጠበብ፤
መጨነቅ ሆነ፡፡ ቀቢጸ ተስፋ ተጠናወተው:: ተስፋ የተለየው ሕይወት ጨለማ ስለሆነ ፀሐይ ወጥቶ ሳለ ምድር ጨለመችበት:: ዓይኖቹ የፍቅር ረሃብተኞች ቢሆኑም ለማየት የፈለጉትን ባለማግኘታቸው ከማየት ተቆጠቡ::ጀሮዎቹ ለመስማት የፈለጉትን ድምፅ ባለመስማታቸው ሌላ ነገር ከመስማት አፈገፈጉ፡፡ ልቡ የፈለገውን ሳያገኝ ሲቀር የፍላጎቱ መጠንና ግለት እየጎላ

ስለሚሄድና የፈለገውን ከመሻትና ከመመኘት ስለማይገታ ያንን ፍላጎቱን ለማሟላት ከመዋተት ወደኋላ እንደማይል ሁሉ የማሪየስ ልብም በምኞት ብዛት ራደ ፤ ተንሰፈሰፈ ፤ በፍላጎት ነደደ ፤ በፍቅር ጥም ተቃጠለ::
ማሪየስ ሥራውን መሥራት ስላልቻለ ሥራውን አቆመ:: የመኖር
ዋስትና ያለው ከሥራ ላይ ስለሆነ ደግሞ ሥራን ከማቆም የበለጠ አደጋ የለም:: ሥራ ለማቆም በጣም ቀላል ነው:: እንደገና ለመጀመር ግን እጅግ
ይከብዳል፡፡
ሰው በተፈጥሮው የምቾት ረሃብተኛና በቅዠት ዓለም የሚኖር
ፍጡር በመሆኑ ያንን ምቾት ለማግኘት ሲል ዘወትር በእጁ የያዘውን ይሰዋል:: ምቾት የተጠማ ሕይወት ጭንቅ አይችልም:: ክፋትና ደግነት
ይመሰቃቀሉበታል፣ ምክንያቱም ርህራሄ የሚጎዳ ሆኖ ሲታይ ክፋት ደግሞ የሚያጸድቅና ምግባረ ሠናይ ሆኖ የሚታይበት ጊዜ አለ::
ሥራ ከሌለ ምንጭ ደረቀ ማለት ነው:: የገቢ ምንጭ ከደረቀ ደግሞ ያልረኩ የእለት ፍላጎቶች ተከማችተው ያስጨንቃሉ። ይህም ወደ ወንጀል ወይም ራስን ወደማጥፋት ይገፋፋል፡፡ ማሪየስ ከዚህ ጎዳና ውስጥ ነበር
እየገባ ያለው:: በእውኑም ሆነ በሕልሙ በዓይነ ህሊናው የሚታየው አንጂ ነገር ብቻ ነበር ልጅትዋ::
ጭንቅላቱ ውስጥ የቀረውና ማር ማር የሚል አንድ አሳብ ብቻ
ተቀርጾበታል፡፡ ይኸውም «እርስዋም ትወደኛለች» የሚል ተስፋ ነበር መውደድዋን የገመተው በአመለካከትዋ ነበር፡፡ ገና ብቅ ሲል ዓይን
እንዳኰረፍዋት ፍቅረኛ ይንከራተታል፡፡ በዚህም የተነሣ የትም ትሁን የት እርሱን እንደምታሰላሰል ገምቷል፡፡ እርሱ ዘወትር በሕልሙ እንደሚያያት
ሁሉ ማን ያውቃል፤ እርስዋም በሕልምዋ ታየው ይሆናል፡፡ የሚገርመው አንዳንድ ጊዜ ያፈቀረ ከጭንቀቱና ከጥበቱ የሚወጣው በጎ ነገር በማሰብ ነው:: የእርስዋ አሳብ እኔን እንደሚያስጨንቀኝ ሁሉ እርስዋም በእኔ አሳብና ፍቅር ትጨነቃላች» እያለ ከጭንቀቱ መካከል ደስታ ይቸልስበታል።
«የእርስዎ አሳብ ምን እንደሆነ ጭንቅላቴ ውስጥ እየገባ እንደሚበጠብጠ ሁሉ የእርስዋም ጭንቅላት በእኔ አሳብ ይበጠበጣል» በማለት መንፈሱ
ያረካል፡፡
ብዙ ቀናት እያለፉ ሄዱ፡፡ ግን ምንም አዲስ ነገር አልተገኘም፡፡ ጊዜው እያለፈ ሲሄድ ፍቅረኛውን የማግኘት እድሉ እየመነመነና የተስፋ ጭላንጭ እየጠበበት ሄደ።
«እንዴት!» አለ አንድ ቀን እርስ በራሱ ሲነጋገር፤ «ሁለተኛ አላያትግል ማለት ነው?»
ፓሪስ ከተማ ውስጥ በውበቱ የሚደነቅ አንድ የአትክልትና የአበባ ሥፍራ ነበር፡፡ ከሜዳ መሃል እንደ ኩሬ ያለ ነገር ኣለው:: ወደዚህ ሥፍራ የሚወስደው መንገድ አመቺ ስላልነበረ ከሥፍራው ብዙ ሰው አይሄድም
አንድ ቀን ማሪየስ ብቸኝነት በጣም ስለተሰማው ዝም ብሎ ይጓዛል
ሳያውቀው ከዚህ ውብ ሥፍራ ሲደርስ አንድ ዓይነት አሳብ መጣበት ፍቅረኛዬ ወደ እዚህ ቦታ መምጣት አለባት» ሲል አመነ፡፡ ከዚያ ቀን ጀምሮ እርስዋን የሚያገኝ እየመሰለው በየቀኑ ተመላለሰ፡፡ ነገሩን በጥሞና
ሲያጠኑት የጀል አሳብ ይመስላል፤ ግን እርሱ ዘወትር ከመመላለስ አልቦዘነም
ዣቬር እዚች ቤት ውስጥ በፈጸመው ተግባር ድል ያደረገ ይመስላል፤ ግን አልነበረም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ እነዚያ ሽፍቶች ይዘውት የነበረው እስረኛ ባለመያዙ በጣም ተናዷል፡፡ ሽፍቶቹ እንደዚያ የፈለጉት ሰው
ካብ ምናልባት የበላይ ባለልጣኖችም የሚፈልጉት ሊሆን የሚችል ይሆን ነበር ብሎ ጠርጥሮአል፡፡ ስለዚህ ማምለጥ የሌለበት ሰው አምልጦናል በሚል
ተጸጽቶአል፡፡ ይህን ሰው ለመያዝ ሌላ እድል መጠባበቅ እንዳለበት አመነ፡፡ማሪየስን ሲፈልግ ኢፓሚን ያገኛል፡፡ ኢፓኒን እህትዋ አዜልማ ከነበረች ከሌማደሎኒ ተወስዳለች፡፡
ከተያዘት ሽፍቶች መካከል ደግሞ አንዱ መንገድ ላይ ይሰወራል፡፡
ፖሊሶቹም ሆኑ የፖሊስ መኰንኖች እንዴት ሊሰወር እንደቻለ አልገባቸውም። ከእስር ቤት ሲደርሱ ብቻ ነው እስረኛው ማምለጡ የታወቀው:: ዣቬር
በዚህ ደግሞ በጣም ይበሳጫል፡፡ የማሪየስ ጉዳይ ግን ብዙም አላስጨነቀውም::
«ግን በእርግጥ ማሪየስ ጠበቃ ነው ወይስ አይደለም?» ሲል ራሱን አዘውትሮ ይጠይቃል፡፡ ለማንኛውም የታሠሩ ሰዎች ጉዳይ በፍርድ ቤት መታየቱን
ቀጠለ፡፡
ማሪየስ ኣልፎ አልፎ ከመሴይ
ማብዩፍ ቤት በስተቀር ከማንም ሰው ቤት አይሄድም፡፡ ሁለቱ ሰዎች ኑሮ ስላልተሟላላቸው ሁለቱም ስሜታቸው እየቀዘቀዘና ለመኖር የነበራቸው ጉጉት እየደከመ ነበር። ሰውዬው ከማጣት ብዛት በቀን አንድ ጊዜ ብቻ እህል የሚቀምሱበት ጊዜ ነበር፡፡ ሳቅ ያበዙ የነበረው ሰውዬ ዛሬ ኩርፊያ ይቀናቸዋል፡፡ ወጣቱና ሽማግሌው ድንገት መንገድ ሲገናኙ እጅ ነስቶ ከመተላለፍ በስተቀር ቆም ብለው አይጫወቱም::ይኸው ነው፤ ችግር ሲበዛ የሚያፈቅሩት ባልንጀራ እንኳን ያስጠላል። ለዚህ ነበር ሁለቱ ጓደኛሞች በመነሳሳት የሚተላለፉት፡፡ ሁለቱም የየራሳቸው የሆነ ችግር ነበረባቸው፡፡
እኚያ የቀድሞው ጄኔራል የዛሬው የቤተክርስቲያን ሰው እድሜያቸው
ወደ ሰማንያ ቢጠጋም የሚተዳደሩት አበባ በመሸጥ ነበር፡፡ ሰሞኑን ዝናብ ጠፍቶ የአበባ ተክሎች እንደ መጠውለግ ብለዋል፡፡ ከጉድጓድ ውሃ ቀድቼ
ላጠጣ ቢሉም አቅም አነሳቸው፡፡
አንድ ቀን ማታ ከቤት ውጭ ቁጭ ብለው ሲተክዙ ወደ ሰማይ
ያንጋጥጣሉ፡፡ ምሽቱ ፀጥ ስላለ ቢያስፈራም ከዋክብት ደምቀው በመውጣቸው ልቦናን ይመስጣሉ፡፡
«ምነው ትንሽ እንኳን ቢዘንብ! ጤዛ እንኳን ይጥፋ! አትክልቴ መድረቁ ነው:: ከጉድጓድ ውሃ ቀድቶ ይህን ሁሉ ኣትክልት ማጠጣቱ የሚያደክም
ነወ» እያለ ሲያሰላስሉ ከአጠገባቸው ድምፅ ይሰማሉ፡፡
«አባታችን አትክልቱን ላጠጣልዎት?»
ቀና ቢሉ አንዲት ቀጭን መልከ መልካም ልጅ ከአጠገባቸው ቆማለች::
ልጅትዋ መልስ ሳትጠብቅ ባልዲ አንስታ ከጉድጓዱ ውሃ ማውጣት ጀመረች::
እየተመላለሰች ውሃ በመቅዳት አትክልቱን ሁሉ አጠጣችው:: ሰውዬው በጣም ደስ አላቸው:: ልጅትዋ አትክልቱን ስታጠጣ የተቀዳደው ቀሚስዋ
በውሃ ራሰ፡፡ አሳዝናቸው ብድግ ብለው ሄደው «እግዚአብሔር ይባርክሽ በማለት ግንባርዋን ሳምዋት:: ይህን ብለው አላቆሙም፡፡ «አንቺ የተባረክሽ
አበቦቼን እንዳጠጣሽ እንደ አበባ የሚያምር ነገር ይስጥሽ» በማለት መረቁዋት::
እርስዋ ግን «የለም፣ እኔ ሰይጣን እንጂ የተባረክህ ፍጡር
አይደለሁም:: ሆነም ቀረም ለእኔ ልዩነት የለውም» ስትል መለሰችላቸው::
«ምን ዓይነት እድል ነው! ምስኪን በመሆኔ ምንም ላደርግልሽ
አልችልም፡፡ ልረዳሽ ብችል ምንኛ ደስ ባለኝ!»
«ሊረዱኝ ከፈለጉ፣ ይችላሉ» አለች::
«እንዴት?»
‹ሚስተር ማሪየስ የሚኖርበትን አድራሻ ይንገሩኝ፡፡»
ሽማግሌው ስላልገባቸው «የቱ ማሪየስ?» በማለት ጠየቅዋት፡፡
«እዚህ እንኳን እርስዎ ቤት ይመላለስ የነበረው ወጣት፡፡
በዚህ ጊዜ ሽማግሌው ከቤታቸው ይመላለስ የነበረው ማሪየስ የተባለ ወጣት ማን እንደሆነ ለማስታወስ ሞከሩ፡፡
«እህ! አዎን፣ አስታወስኩት» ሲሉ ተናገሩ፡፡ «የማንን አድራሻ
እንደፈለግሽ ገባኝ:: ማሪየስ ፓንትመርሲን አይደለም የምትይው? አዎን እርሱ የሚኖረው... አይ ለካስ ከዚያ ቤት ለቅቋል:: እኔ እንጃ... አሁን የት
እንደሚኖር አላውቅም::»
ሰውዬው ከነበሩበት ሲነሱ ከኣጠገባቸው ሰው አልነበረም፡፡ ልጅትዋ ሄዳለች፡፡ ሽማግሌው ፍርሃት፣ ፍርሃት አላቸው:: ከአንድ ሰዓት በኋላ ከክፍላቸው ገብተው ተኙ::
አንድ ቀን ጠዋት ማሪየስ ከሽርሽር ሲመለስ የህሊና እረፍት አግኝቶ
ሥራ ለመሥራት የሚችል መስሎት ወደዚያ ይሄዳል:: በእለቱ ከእንቅልፉ እንደነቃ ከአልጋው ወርዶ የትርጉም ሥራ ለመሥራት ጥረት አድርጎ ሀሳቡ አልሰበሰብ ስላለው ነበር«ተነስቼ ከቤት ልውጣና ስመለስ ለመሥራት እሞክራለሁ።

👍15
ለመሄድ የተነሣው ቀደም ሲል ወደተጠቀሰው የሚያምር ግን መሄጃው መንገድ አስቸጋሪ ወደሆነው የአትክልት ሥፍራ ነበር፡፡ ከሥፍራው ሲደርስ
ልብስ አጣቢ ሴቶች ይንጫጫሉ፤ ወፎች ዝማሬያቸውን ያሰማሉ፡፡ ሴቶች ጉልበታቸውን ሲያፈሱ አእዋፍ በደስታ ያዜማሉ:: ሁለቱን ሲያነጻጽር ተገረመ።
ከወደኋላ የለመደውን ድምፅ ሰማ፡፡
«እህ! ያውና!»
ፊቱን ዞር ቢያደርግ ያቺ ያልታደለች አንድ ቀን ጠዋት ከቤቱ
የመጣችው ሴት ልጅ መሆንዋን አወቀ:: የእነሚስተር ቴናድዬ ትልቅ ልጅ ኢፓኒን ነበረች፡፡ ይህች ልጅ በይሰልጥ ብትጎሳቆልም ቁንጅናዋ በይበልጥ ጎልቶ ይታያል ፡፡ ሁለቴ ስትራመድ ብርሃን ከነበረበት ደረሰች:: ለእግርዋ
ጫማ አላደረገችም:: የተቦጫጨቀ ልብስ ነው የለበሰችው:: ከሁለት ወር
በፊት ከማሪየስ ክፍል ስትገባ የለበሰችውን ልብስ ነው የለበሰችው:: ልዩነቱ
ልብሱ አሁን በይበልጥ ተቀዳድዷል፤ በይበልጥ ቆሽሿል:: የድምፅዋ መጎርነን አልተለወጠም:: ፊትዋ በፀሐይ ብዛት ጠቋቁሮአል፡፡ አባ-ግድየለሽነትዋና የሚቅበዘበዝ ዓይንዋ ያው ነው:: ሆኖም የፍርሃት፣ የመረበሽና የሀዘን
መልክ ከበፊቱ ይበልጥ ፊትዋ ላይ ይነበባል:: ይህም ሆኖ ውበትዋ አልጠፋም:: እንደ ንጋት ኮከብ ወከትዋ ከዚያ ከተጎሳቆለ ሰውነትዋ ላይ ሲፍለቀለቅና ሲያንጸባርቅ ይታያል፡፡
ማሪየስ ከነበረበት ደርሳ ከፊቱ ቆመች:: ፊትዋን ፈካ ኣድርጋ በፈገግታ ይህን ተመለከተችው:: ልክ መናገር እንደማይችል ዱዳ ቃል ሳትተነፍስ ለአጭር ጊዜ ዝም ብላ ቆመች::
«ብመጨረሻ አገኘሁህ አይደል?» አለች፤ «አባታችን ማብዩፍ ልክ
ናቸው ማለት ነው:: ከዚህ ነዋ የተደበቅኸው፣ እንደመደበቅህ አልቀላህም::
ስንት ቀን ፈለግሁህ መሰለህ! ታውቃለህ ስንት ቦታ ዞርኩ፡፡ ለአስራ አምስት ቀን ካሠሩን በኋላ ምንም ወንጀል አለመሥሪቴን ሲደርሱበት ለቀቁኝ፡፡ እድሜዬ ደግሞ ለፍርድ የሚያስቀርብ አይደለም:: አሁን እንግዲህ
ከተለያየን ሁለት ወር መሆኑ ነው:: እንዴት ፈለግኩህ መሰለህ? ይኸው አንተን ስፈልግ ስድስት ሳምንት አለፈ:: ከድሮ ቤትህ አይደለም ያለኸው::
«የለም፧ ያንን ቤት ለቅቄአለሁ» አለ ማሪየስ:
ታዲያ አሁን የት ነው ያለኸዉ?
ማሪየስ መልስ አልሰጣትም::
«ወይ ጉድ! ሸሚዝህ ተቀዷል» ካለች በኋላ «ልስፋልህ» ስትል
ጠየቀችው::
ቀና ብላ ፊቱን አየች፡፡ ፊትዋን በማጠቋቆር ቋጠረችው::
«በእኔ መምጣት ደስ ያለህ አልመሰለኝም» አለች::
ማሪየስ አሁንም ዝም አለ፡፡ እርስዋ ለጥቂት ጊዜ ዝም አለችና በኋላ
ወሬዋን ቀጠለች::
«ግን እኮ ቢሆንልኝ አንተን ከማስደሰት ወደኋላ አልልም ነበር፡፡»
«እንዴት?» ሲል ጠየቃት አሳብዋን ለማወቅ ፈልጎ፡፡ «ምን ማለትሽ
ነው?»
«ምነው ተለወጥክ! ከዚህ ቀደም ከዚህ በተሻለ መንገድ ትህትናና
አክብሮት በታከለበት አንደበት ነበር የምታነጋግረኝ ስትል መለሰችለት::
«ግን ይሁንና ቅድም ምን ለማለት ፈልገሽ ነው እንደዚያ የተናገርሽው?»
ከንፈርዋን ነከሰች:: ለመናገር ፈልጋ አመነታች:: በውስጥዋ አንድ ዓይነት ትግል እንደሚካሄድ ያስታውቅባታል፡፡ በመጨረሻ ግን ከውሳኔ አሳብ ላይ ደረሰች::
«ምን አባቱ እንደፈለገው! ምንም ልዩነት አያመጣም» በማለት
አጉረመረመች፡፡ «የተከፋህ ትመስላለህ:: ግን እኔ ደስ ብሎህ እንዳይህ ነው የምፈልገው:: እንደምትስቅና ፈገግ እንደምትል ቃል ግባልኝና ልቀጥል፡፡
ስትስቅ ምን እንደምትመስል ማየት እፈልጋለሁ:: ጥሩ ነው ፤ እንደ እሱ
አየህ ሚስተር ማሪየስ፣ ታውቃለህ፤ የፈለግሁትን እንደምትሰጠኝ ቃል
ገብተህልኝ ነበር» ብላ ስትናገር ጣልቃ ገባ፡፡
«አዎን ብዬ ነበር፡፡ አሁን የምትፈልጊውን ንገሪኛ!»
ዓይን ዓይኑን እያየች ተናገረች::
«የምትፈልገውን አድራሻ አግኝቻለሁ፡፡»
ማሪየስ በአንድ ጊዜ ተለወጠ፡፡ የልቡ ትርታ ከፍ ሲል ፊቱ ወገግ
አለ::
«የምን አድራሻ?» ሲል ጠየቃት ያልገባው በመምሰል እየተግደረደረ፡፡
እንድፈልግልህ የጠየቅኸኝን አድራሻ ነዋ!»
«አዎን» አለ ማሪየስ በመንተባተብ፡፡
«የልጅትዋን አድራሻ እንደሆነ ገባህ አይደል?»
ማሪየስ ሳይታወቀው ከተቀመጠበት ብድግ አለ፡፡ ልጅትዋን እቅፍ አደረጋት::ኀ
«በይ ፤ ነይ እንሂድ፤ አድራሻዋን አሳዪኝ፡፡ የምትፈልጊውን ንገሪኝ፡፡
በኋላ ፈለግሽውን ነገር ጠይቂኝ፧ ይፈጸምልሻል፡፡ አድራሻዋን ብቻ አሳዪኝ ሲል ቀባጠረ::
«ተከተለኝ» ስትል መለሰችለት:: «የመንገዱን ስምና የቤቱን ቁጥር
በትክክል አላውቀውም:: ግን ቤቱን በትክክል አስታውሰዋለሁ:: መለየት አያቅተኝም:: ከዚህ ትንሽ ራቅ ይላል፡፡ ና እንሂድ አሳይሃለሁ፡፡»እጅዋን ይዞ ቆሞ ስለነበር መነጨቀችው:: የሚያይ ቢኖር እንደዚያ ስትመነጭቀው የጥል መስሉት ይደነግጥ ነበር:: ማሪየስ ግን ስሜት
አልሰጠውም::
«አቦ እንዴት ነው ደስ ያለህ!»
«ወሬውን ተይውና መንገዱን አሳዪኝ እባክሽ! »
«እሺ እንሂድ፡፡»
«አሁነኑ?»
«አዎን አሁኑኑ፡፡ ውይ እንዴት ደስ አለው!» አለች::
ጥቂት እንደተጓዙ ቆም አለች፡፡
«በነገራችን ላይ፣ አንድ ነገር ቃል እንደገባህልኝ ተስታውሳለህ?»
ማሪየስ ኪሱን ዳበስ፡፡ ያለችው አምስት ፍራንክ ብቻ ነበር፡፡ እንዳለች አውጥቶ ከኢፒኒን እጅ ውስጥ አስቀመጠው፡፡
ጣቶችዋን ዘርግታ ገንዘቡን ከመሬት ጣለችው፡፡ ቀና ብላ በማንቋሸሽ
ገንዘብህን አልፈልግም አለችው።