አትሮኖስ
280K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
472 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሸረኛ_እና_ደህና_በአንድ_ላይ #ሲሄዱ_በሸረኛው_በኩል_ተናደ #መንገዱ


#በአሌክስ_አብርሃም

#ሸረኛ

የዶክተር ደበጫ እርገጤ መዝገበ ቃላት ሸረኛ የሚለውን ቃል ሲያብራራው እንዲህ ይላል፡
ሸረኛ ስም፣ እንዳገባቡ 'ተውላጠ ስም፣ አንዳወጣጡ ግስ'፣ ሳይገባም ሳይወጣም ራሱን ችሎ
ዓረፍተ ነገር !

ትርጉሙ፡- (በተንኮል የሰው ማንነት፣ መልካም ስም፣ መልካም ሥራ፡ መልካም ግንኙነት
የሚሸረሸር፣ የሚሰረስር፣ የሚቦረቡር፣ የሚደረምስ፣ የሚያጠለሽ... ይለዋል። መዝገበ ቃላቱ ይሄን ሁሉ ነገር ከሚያንዛዛ በቀላሉ መግለፅ ይችል ነበር ልክ እንደዚህ፣

ሸረኛ፡- ሰው አቶ እጅጉ ! በቃ! አጭር ግልፅና ወቅታዊ ፍቺ !!

ምሳሌ፣ አቶ እጅጉ ሸረኛ ነው። ትክከል !! ይሄ ምሳሌ አይደለም፣ እጅጉ (እጅ እግሩን አስሮ
ሲኦል ይወርውረውና) 'ሸረኛ' ነው፡፡ ሸረኛ ብቻ አይደለም፣ ምቀኛም ነው፡፡ የሚቀናበት ነገር
ሲያጣ እኩል በተሰጠን 24 ስዓት ይቀናል፡፡ (“እንደው በየትኛው ጊዜ ብትማሩት ነው ይሄን ሁሉ ነገር ያወቃችሁት?” ይላል የማያውቀውን ነገር አውቀን ካገኘን፡፡ ለነገሩ እሱ ምንም
አያውቅም፡፡) ምን ይሄ ብቻ! እግዜር በፈጠረው አየር ሳይቀር ይቀናል፤ የቢሯችን መስኮት
ተከፍቶ እንደልብ አየር ሲገባ ብቅ ይልና፤ ይሄን አየር በነፃ ትሉታላችሁ” ይላል፡፡ እንከፈል?
ሸረኛም ምቀኛም ብቻ አይደለም መሰሪ ተንኮለኛም ነው:: አሟልቶ አይሰጥም' ይባላል አንጂ
ይሄው የተሟላ ክፉ ሰው፡፡

እንግዲህ ሸረኛ፣ ምቀኛ፣ መሰሪ ሆኖ ደግሞ አለቃዬም ነው፡፡ ጥሎበት አይወደኝም፡፡ እኔም
ሰለማልወደው ተመስገን ቢወደኝ ምን ይውጠኝ ነበር?' እላለሁ ሁልጊዜ፤ ለምወደው ሰው
ነው የምጨነቀው፡፡ አሁን በዚች ቅፅበት በሆነ አጋጣሚ ነገር ሎተሪ ምናምን ኣይነት እድል
ገጥሞኝ በድንገት የብዙ ኢ ቢሆን የመጀመሪያ ሥሪዬ ሁለት እጆቼን ኪስና ኪሴ ከትቼ በቀዳዳ ኪሴ ውስጥ በሾለኩ ጣቶቼ ራቁት ታፋዩን በማፏጨው ሙዚቃ 'ሪትም' እየተመተምኩ ጀነን ብዪ ወደ አለቃዬ ቢሮ ሄድና አንኳኳለሁ፣ ኖ..ኖ.አላንኳኳም፤ በሩን በእግሬ ገፋ አድርጌው እገባለሁ፡፡ (ካፈቀሩ ከነፍስ፣ ከጠሉም ከነፍስ ነው የምን ማስመሰል) ፊት ለፊት፣ ጉማሬ ፊቱ አለቃዬ ሁልጊዜ በሚደፈርሱ አስቀያሚ ደመኛ አይኖቹ ያፈጥብኛል። ቀጥሎ ኪሶቼ ውስጥ የወሸቅኳቸውን እጆቼን በቁጣ ያያል፤ (ደንግጨ
ከኪሲ እንዳወጣቸው እንድርበተቡት፡፡) ፀጥ ብዪ በትዕቢት ሳየው የኢትዮጵያን ሲጋራ ሁሉ ብቻውን ያጨሰ ከሚያስመስሉት አስቀያሚና ገጣባ ከንፈሮቹ ቃላት ደፈለፈላሉ፤ ሰው ሰው የማይሸቱ እብሪተኛ ቃላት፡፡

ምናልባትም፣ “ብላችሁ ብላችሁ ማንኳኳቱንም ተዋችሁት." ይል ይሆናል፡፡ (እግዜርና ሰይጣን
ለዚህች ቅፅበት እርቅ አውርደው ይሄን ድንጋይ ራስ ኣለቃዬን በመዶሻ ያንኳኩትና።) ወይም
“ኪስህ የወሸቅከውን እጅህን አውጣ!" ሊልም ይችላል፣ አላወጣም !(ኪሴ ቀዳዳ ሲሆን
ቀዳዳውን ተሻግሮ ያለም ወንድነት የራሴ ርስት ነው . ዘራፍ ! በቀዳዳ እኛነታችን ውስጥ እያለፈ ወንድነታችንን ያኮላሹን ክፉዎች ሁሉ ከዛሬ ጀምሮ አድርጉ ያሉትን አናደርግም፡፡

ኮራ ብዬ "እእእእ አቶ እጅጉ” እለዋለሁ፡፡ (“አቶ" በማሾፍ ሲጠራ እንዴት ያለ አሪፍ ስድብ ነው፡፡) ለምሳሌ፣ እኔ "አቶ” ከሚለው ቅፅል ይልቅ ከስሜ በፊት ሰሃራን የሚያህል ባዶ ምድረ በዳ ቢዘረጋ ይሻለኛል፡፡ በተለይ አለቃዬ "አቶ" ከሚለኝ ። ...አዎ ! እሱ "አቶ"
ሲለኝ በውስጡ “መቼም ለአቶነት አትበቃም በቸርነቴ 'ከቶ'ነት ልስጥህ እሰቲ” የሚል ይመስልበታል፡፡ አቷም።

እና አቶ እጅጉ ከዛሬ ጀምሮ ሥራ ለቅቄያለሁ” እለዋለሁ በኩራት፡፡ 'እእእእ' የምትለዋን ዘገምተኛ ቃል ማስቀደም አልረሳም፡፡ አራት ዓመት ሙሉ የሱን አስቀያሚ እእእ' ችዬ ኖሬ የለ ስለዚህ የምለው እንደዚህ ነው:: “እእእእ.አቶ እጅጉ ከዛሬ ጀምር...እእእእ ሥራ ለቅቄያለሁ !”

ይደነግጣል፣ አያምንም፡፡ እኔ ስፈጋ የዋልኩበትን ሥራ ሁሉ ለአለቆቹ እንዲህ ሠርቼው እንዲህ
አድርጌው እያለ በስልክ መወሽከቱ ሊቆም ሲሆነ ይደነግጣል እሰይ ! ወሽካቶች መደንገጥ አለባቸው።

ወዲያው የበሰበሰ የማኔጅመንት 'ሲስተሙን' እኔ ላይ ሊሞክራት ይፍገመገማል፣ “አትደነግጥ
የበታች ሠራተኛህ ፊት አዋቂ፣ ልብ ሙሉ ምንትስ ሆነህ ቅረብ፣ ባትሆንም ሁን…” የምትለዋን
ያስብና ጉሮሮውን ጠራርጎ፣ “እእእ….እዚህ መሥራቱ ራስህን ለማሳደግም ሆነ ቤተሰብህን ለመርዳት አይሻልህም? ይላል፡፡ ሥራ ብለቅ ቤተሰቦቼ በረሃብ ዛሬውኑ የሚያልቁ በሚያስመስል ሁኔታ 'ቤተሰብ የምትለዋ ቃል ላይ አፅንኦት ሰጥቶ፡፡

ከፉዎች መሳሪያ ልጅህ ላይ ባይደግኑም፡ እናትና አባትህን አፍነው ባይወስዱም፣ የነገን ጨለማነት እየነገሩ ያግቱUል፡፡ ስንቱ መሰለህ ቁራጭ ዳቦ እንዳይነሱት ፈርቶ ለማንም አጋሰስ ጉልበቱን የሚገፈግፈው፤ ስንቱስ ነው ' ከሥራ መባረር የሚባል የታንክ አፈ ሙዝ ልቡ ላይ ተደግኖበት ዘመናዊ ባርያ የሆነው !! ስንቷን ሚስኪን በፀሃፊነት ስም የጭን ገረዱ ያደረጋት ጋንጩር አለ ቢሮ ይቁጠረው !

ሀላፊ ሲባል አርቲስት ነው፡፡ ወንበሩን መድረክ ያደረገ ተዋናይ፡፡ ያውም ድብን ያለ ትራጀዲ
የሚተውን፡፡ እና እኔ ምን እለዋለሁ ሃሳቤ ደስ ብሎኝ ሳምሰላስል፣ ዙፋን ዘው ብላ ወደ ቢሮዬ
ገባች፡፡ ጥሎባት ማንኳኳት አትወድም፡፡ 'እንኳኪ!' ብሏት የሚያውቅም የለም፡፡

"ብርሽዩ” ትለኛለች፡፡ (ስሟን ከነአያቷ ቄስ ይጥራትና) ! ሁልጊዜ ስትጠራኝ እንዲሁ ነው፡፡ ታዲያ አጠራርዋ ከማማሩ ብዛት እኔን ለጠራችኝ ሌሎቹ 'ወይዬ' ሊሏት ይዳዳቸዋል፡፡

እንዲህ በሀሳብ ጭልጥ ያልከው ወዴት ሄደህብኝ ነው?” ወዴትስ ብሄድ ምን አገባት፡፡ ጭራሽ
የምሄደውስ የምቀረውስ ለሷ ነው እንዴ? (ሄደህብኝ !! ጥርግ ብል እንትናዬ እያለች አንዱ ቢሮ ልትንኳተት፡፡

"እ..ምነው ጠፋሽ?” አልኩ እንደመጣልኝ፡፡ የምለው አጥቼ እንጂ ዙፋን ደግሞ መቼ ጠፍታ
ታወቅና፡፡ በአንድ ጊዜ ሰባት ቢሮ ውስጥ የምትገኘውን ዙፋንን ጠፋሽ ማለት መሬትን “ምነው
በዚህ ሳምንት መዞርሽን አቆምሽ?” ብሎ ከመጠየቅ አይተናነስም፡፡

ሆሆ ከየት ተገኘሽ፣ አሁን እንኳን ስመጣ አራተኛዬ ነው” አለችና ከጠረጴዛዬ ፊት ለፊት ወንበር
ስባ ተቀመጠች፡፡ ወንበሩ ተንጫጫ፡፡ ጉርድ ቀሚሷ ቀይ ታፋዋን ወለል አድርጎ ያሳያል…..
ኤጭጭጭጭጭ!!

“ቆንጆ ናት” ይባላል፡፡ “ትሁት ናትም” ይሏታል። “የሰለጠነች፣ ሰው አከባሪ" የሚሏትም ብዙ
ናቸው፤ እንደው ባጠቃላይ እዚህ ቢሮ ዙፋንን ለማናገር፣ ለማቅረብ፣ ሲመቸው ወደ ኣልጋው
ጎትቶ አብሯት ለመጋደም የማይመኝ ያለ አይመስለኝም፡፡

ዙፋን እኛ ቢሮ ሥራ ስትጀምር ከሥራ ልምዷ ጋር ከእግዜር የተላከ “ከዛሬ ጀምሮ ያየ አመነዘረ፤ የሚለው ጥቅስ ተሰርዟል” የሚል ደብዳቤ ይዛ የመጣች ይመስል፣ እዛ ፋይናንስ ከሚሠራው ዲያቆን ወልዱ ጀምሮ ሰው ሰላም ሲል እገጩ መሬት እስኪነካ የሚያጎነብሰው ጴንጤው ምክትል ኃላፊያችን የዙፋንን እግርና መቀመጫ አይተን እንሙት አሉ፡፡ ዙፋንም ታዲያ የዕለት እንጀራዋ የሰው አይን ይመስል ነገረ ሥራዋ ሁሉ የታይታ ነው፡፡ አቤት መታየት ስትወድ፡፡ ሰው ከኋላዋ እንደሚያያት ከጠረጠረች ለከፉ ቀን ያስቀመጠችውን መቆናጠር ሁሉ ትጠቀምበታለች፡፡
👍26🔥1
#ሸረኛ_እና_ደህና_በአንድ_ላይ
#ሲሄዱ_በሸረኛው_በኩል_ተናደ
#መንገዱ


#በአሌክስ_አብርሃም

...ፊታቸው በሀዘን አኮፍኩፎ በእድሜ እናቴን ይበልጣሉ፡፡ ከወንበሬ ተነስቼ ለሰላምታ እጄን ዘረጋሁላቸው፡
በሁለት እጆቻቸው አሁንም ጎንበስ ብለው ሰላም አሉኝ፣ እጃቸው ይሻክራል፡ ልክ እንደ እናቴ.
እነዚህ ሞረድ እጆች የስንቶቻችንን ባለ ለስላሳ እጆች ሆይወት እንደሞረዱ ፈጣሪ ይወቅ!

እንዲቀመጡ ወዳመለከትኳቸው ወንበር ቀስ ብለው ተቀመጡና የመጡበትን ጉዳይ ቀስ ብለው
እንደምታውቀው እዚህ ቤት ነገረ ሥራቸው ሁሉ ውስጥ ለውስጥ ነው:: ደከመኝ፣ ሰለቸኝ
አስረዱን፣ አቶ አብረሃም (አቤት አቶ በእሳቸው አንደበት እንዴት ክብር እንዳለው ) ያው እንደምታውቀው እዚህ ቤት ነገረ ስራቸው ሁሉ ውስጥ ለውስጥ ነው ደከመኝ ሰለችኝ ሳልል በሰራህ ለትንሽ ትልቁ 'እሺ' ብዬ ባደርኩ ድንገት ከሥራዬ ነቀሉኝ፡፡" አሉና እንባቸው ተዘረገፈ፡ እድሜ በሸነተረው የቆዳቸው እጥፋት ሽብሽብ ውስጥ እንባቸው ጎረፈ፡፡ በነጠላቸው ጫፍ እይናቸውን ጠረጉ፡፡ (እዚህች ባልቴት ውስጥ ይሄ ሁሉ እንባ እንዴት ሊኖር ቻለ? እድሜ ልካቸውን ያጠራቀሙት ይሆን?) እማማ መለኮት ከፅዳት የሥራ ገደብ ተነስተው በሀያ ዓመት የሰርክራሲ ባቡር ተጉዘው ፅሃፈ ለመሆን የበቁ ፅኑ ሴት ናቸው፡፡ ከልምድ እንዳየሁት ብዙ
ታላላቅ ድርጅቶች ሱፍ ለብሰው በሚኮፈሱት አለቆቻቸው ሳይሆን በሚስኪኖች ትከሻ ላይ
ተጭነው ነው የቆሙት፡፡ እማማ መለኮት የድርጅታችን ዋልታ ይሄው ተባረሩ፡፡

ከዛ በፊት፡ ከመባረራቸው በፊት፤ አሽሙር የሚመስል ስብሰባ ተደረገ፡፡ አንዲት ረዳት የሌላቸው
ሚስኪን ባልቴት ለማባረር ቱባ ቱባ ባለስልጣን፣ ከቱባው የተተረተሩ ክር አቃጣሪዎች እና እኛዎች" ውሃ ቡና ቀርቦ ስብሰባ ተደረገ፡፡የስብሰባው መሪ፣ "ሸረኛው" እጅጉ፣ ፀሃፊው “ሽረኛው"
አለሙ፣ ተላላኪው፣ ወሬ አቀባዩ (እንደ ሰው አልባ አውሮፕላን እያንዣበባ ሰላሉት አለቆቹ ወሬ ይቃርማል፡፡ “መታዘዝ ፅድቅ ነው” ሲባል የመታዘዝ ፅድቅነትን የማያመዛዝን አዕምሮ ተሸክሞ የሌሎች ባሪያ መሆን ማለት አይደለም፡፡ ሰብዓዊ ትዕዛዝ፣ ሰው መሆን ይቅርብሆ ተብለህ ሳይሆን፣ ለእኔ ማለት ይቆየኝ፣ ቅድሚያ ለሌሎች ከሚል በጎነት መነሳት ነው:: በጎነት በትዕዛዝ አይመጣም፡፡)

ስብሰባው ተጀመረ፡፡ ለአንዲት ባልቴት ተሰበሰቡ እንዳይባል የማይረባ አርሲ ኩርሲ አጀንዳ
ጋር ተደምሮ የእማማ መለኮት መባረር መቀነስ” የሚል የዳቦ ስም ተሰጥቶት አጀንዳ ሆነ፡፡

“ባንድ ላይ ሲሄዱ” መዝገብ ቃላቱ በአንድ ላይ መሄድን በአንድ ላይ ከመታየት ነጥሎ አለማየቱ ትልቅ ጉድለት ነው::

የሸረኛ፣ “እና” ና “ደህና” ስብሰባው ላይ በአንድ ላይ ተገናኘን፣ በማንኛችን በኩል መንገዱ እንደሚናድ ልናይ - ቀድሞ የተናደውን፡፡

“ተናደ"

ስብሰባውን የጀመረው አለቃችን አቶ እጅጉ ነበር፡፡ ኩፍስ ብሎ የኮቱ አጥፋት ሸብዳዳ ትከሻው ላይ ተከምሮ (ከኮቱ ውስጥ ትንሽ የሶፋ ትራስ ያስቀመጠ ይመስለኛል)፡፡ ጨዋ ለመምሰል በሚዳዳው ድምፅ ስብሰባው መጀመሩን አረዳ (አበሰረ የሚሉም አሉ “ከሸረኞች ወገን ናቸው)

እ...ያው እንደምታውቁት…" አለ (ምንም በማናውቀው ነገር) ...መሥሪያ ቤታችን ያለውን
መልካም ሰምና ዝና ለማስቀጠል (ሂሂሂሂ ጉድ ፈላ በቀን የሚመጣው ባለጉዳይ ሁሉ እዩዬ እያለ ተራግሞ የሚሄድበት መሥሪያ ቤት መልካም ስምና ዝና ይሁና) ዘመናዊ የአሠራር ሲሰተም
ዘመን አፈራሽ መሳሪያዎች እንደሚያስፈልጉ በማመን የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ወስደን
እየተንቀሳቀሰን 'ያለበት ሁኔታ ነው ያለው….

እነዚህ ዘመናዊ መሳሪያዎች ደግሞ ብቻቸውን ጠብ የሚል ለውጥ እንደማያመጡ እሙን
ነው፣ ስለዚህ ቢሯችንን 'በአመለካከት በእውቀት እና በተግባር ከመሳሪያዎቹ ጋር አብሮ
በሚሄድ ወጣት የሰው ኃይል ማደራጀቱ ለነገ የማይባል አንገብጋቢ ተግባር ነውሸ

(እማማ መለኮት በኩል መንገዱ ተናደ:: ጨዋነትን የጫነው መኪና ገደል ገባ፡፡ ትህትና ተሽቀነጠረ፡፡ መንገድ ስለሌለ ወደኋላ ተመለስን፡፡ መንገድ አፍራሽ ሸረኞች ራእይ እንደ ህልም
ያያሉ፡፡ ከመድረስም ተጣልተዋል፡፡ መንገድ የለማ ...! ከአባይ ወዲያ ማዶ ያለ ዘመድ ሆነ የእማማ መለኮት ሥራ፣ እንባቸው በአይናቸው የሞላ እለት ዋይ ብለው ቀሩ፡፡

እንዲት በእድሜ የገፉ ሚስኪን አባሮ በየቢሮው እየዞረች ምስጋና የምትቀላውጥ ገልቱ
ለመቅጠር ምድረ ጉማሬ ሚስኪኑን ላብ አደር ሰብስቦ አላዘነ፡፡ ደግሞ ስላዘመናዊነት
ያወራሉ፣ እግዚኦ አለቆቻችን ስለዘመናዊነት አወሩ፡፡ስልካቸው ባትሪ ሲጨርስ ተበላሸ
ብለው ሠሪ ቤት የሚሮጡ አለቆቻችን ዘመናዊነትን ሰበኩ፡፡ ከፕሪንተር የሚወጣ ወረቀት ደመና ሰንጥቆ እንደሚወጣ መልአክ በግርምት የሚመለከቱ፡፡ (አይ ፈረንጅ ነፍስ መፍጠር እኮ ነው የቀረው!' እየተባባሉ፡፡) እለቆቻችን ዘመናዊ እንሁን አሉ፡፡

እማማ መለኮት በጡረታ ስም ተባረሩ፡፡ (ተቀነሱ በል አቶ አብረሃም ተብያለሁ፡፡) ዙፋን
ተቀጠረች አሁን ድርጅቱ ዘመናዊ ሆነ፡፡ “እንደምን ዋላችሁ…”፣ “ሃይ ጋይስ” በሚል ሰላምታ .
በመተካቱ እልልል ቢሯችን ዘመናዊ ሆነ፡፡

ዙፋን የዘመናዊነት ፋና ወጊ፣ አንድ ገፅ ደብዳቤ ስትፅፍ አንድ ከግማሽ ገፅ ስህተት የምትዘራ
ጉድ፡፡ ወሬ ብቻ መሽኮርመም ብቻ፣ በየሰሙ ላይ “ዬ" መጨመር ብቻ (አብርሽዬ..ቶማስዬ.
ጋሽ ሰይድዬ ተፈራዬ... ሐጎስዬ.. ገኒዬ..እግዚያብሄርዬ..ጂሰስዬ_) እንደ ዬ ፈደል ትልቅ አፍ ብቻ
ያላት መርገምት፡፡ደህና ነገር ሲናገር ከንፈሩ እንደደረቀ ሰው በየደቂቃው ቻፕስቲክ እየተለቀለቀች በየቢሮው ማውራት !! (ውይ ጥርስ አታስከድንም፤ ተጫዋች ምናምን ይሏታል የሸረኛው መንጋ፡፡

ቆንጆ ብቻ መሆን እንዴት ይቃፋል፡፡ ሴት ብቻ በመሆን ከወንድ የሚቻር ወሲባዊ ክብር ምንኛ ውድቀት ነው?! ዕድሜ ከፍ ባለ ቁጥር የሚናድ የእንቧይ ካብ፡፡ እንዴት ሰውን ያህል ፍጥረት
ያውም እናትነትን ያሀል አደራ ትቀበል ዘንድ ተፈጥሮ የወከለቻት ሴት ስለጥፍር አንድ ሰዓት ሙሉ ታወራለች? ስለፀጉር ሁለት ሰአት፣ ስለጥፍር ቀለም ሙሉ ሸን፣ስለ ልብስ...

የመታየት ልክፍት (ኤግዝቢሽኒያም ይለዋል በሬቻ)፡፡ በፋሽን ስም ነጋቸው ላይ ውበት ሊዘሩለት ሚችሉትን ዛሬ አርሲ ኩርሲ የውበት ኮተት እያወሩ ይፈጁታል፡፡ ይሄ የሴት ውበት ነው የሴት ብክነት፡፡ ስለውበት የሚደሰኩር ሚዲያ ላይ አፍጥጣ የምትውል ዙፋን፣ ቆዳዋን በምናምን አደንድና ፍቅር እንዳይስርአት ራሷን ሳታዋድድ ትኖራለች። ሴት ከምልክ የተሻለ መወዳደሪያ በሌላት ውድድሩ ውስጥም የምትኖረው ቢበዛ ለጥቂት ዓመታት ነው፡፡ ባካና ! ዙፋን ባካና ናት፤ ስሟ ራሱ እሷ ላይ ሲደርስ 'ዙፋን' የሆነ፣ የመወዘፍ አይነት ደውል ነው፡፡ (ውዝፍ ከሚለው ስረወ ቃል የመጣ)

ከአለቃዬ ጋር በአይኗ ስትዳራ ስንት ጊዜ ታዘብኩ፡፡ እማማ መለኮትን ነቅላ ላትፀድቅ ነገር
ራሷን የተከለችበትን ቆሻሻ መንገዷን አይቻለሁ፡፡ ለፀሃፊነት ሥራ ውድድር መሰለፍ የማይችል
ባልጩት ጨንቅላቷ ላይ ሰው ሰራሽ ፀር ጎዝጉዛ ክቡር ሴትነቷን በየቢሮው ስትጎዘጉዝ ሳናይ
አላወራንም፤ “ጭስ ካለ እሳት አለ” ብለንም እይደለም፡፡ ቆይቶ የተደረገ ግምገማ ላይ የተገደደች
አስመስላ ቀባጠረችው እንጂ፡፡ (የሸረኞች መንገድ የተናደች" እለት)
👍191