አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
575 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አንዳች የልብ ምት ነገር አለ፡፡ አንዲት የመንደራችን አሮጊት፣ ለሴት ልጃቸው የተመኙት ወንደላጤ ተከራያቸው አንዲት የገጠር ሴት ሲያገባ ተበሳጭተው “ሙታንቲው ላይ አስደግማበት ነው አሉ” ይሉ ነበር፡፡ ያኔ ያስቀኝ ነበር አሁን ግን “ይች ኢንስፔክተር መንበረ የራሷ ሙታንቲ ላይ አስደግማበት ይሆን እንዴ” እስክል ግራ ይገባኛል .ግን ማን ሊያየው ብላ እዛ ላይ ታስደግማለች ካስደገመች አገር የሚያየው ትከሻዋ ላይ ያለ ማዕረግ ላይ፣ከወገቧ የሚሻጥ ሽጉጧ ላይ አይሻልም ነበር? ..እንዲህና እንዲያ አስባለሁ፡፡ ሳስባት ልቤ ይደልቃል ዘወትር እንደሚደልቀው ዓይነት የልብ ምት አይደለም፣ ስልት ያለው የልብ
ምት፡፡ ያንን ትንፋሽ የሚያሳጥር…. ያንን ንዝረት የሚለቅ ትዝታ፤ ስንት ቦታ፣ ስንት
እንስቶች ላይ ፈለግሁት፤ የለም አልነበረም!!

ኢንስፔክተር መንበረ ሂድ! ተፈተሃል” ብላ ወደ ሰፊው ዓለም በፖሊስ ጣቢያው ሽንቁር ስትልከኝ፣ አእምሮዬ ውስጥ ግን ኃይለኛ ብርሃንና ሙቀት የሚያሾልክ አንዳች ቀዳዳ ሳይፈጠርብኝ አልቀረም፡፡ እንግዲህ ነፃነት ምንድነው?! .…የነፍስን ሽንቁር መድፈን አይደለምን? የጎን አጥንት ሲባልስ የጎን ሽንቁር አይደለም ማን አለ?.…ከሁለተኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርስቲ፣ ደግሞም ሥራ በሚሉት ስንክሳር በሕይወት ጎዳና ግራ ቀኝ ሳልል፣
አንዲት ለሌሎች የማትታይ የሐሳብ ሐዲድ ተከትየ ፣እሷን ሳላዛንፍ እየተከተልኩ ሠላሳ ዓመት ሞላኝ፡፡ ሴቶቹ ብዙ፣ ወሬው ብዙ፣ መልኩ ብዙ፣ አጋጣሚው ብዙ፣ መገናኛው ብዙ መለያያው ግን ብዙ የሚመስል አንድ አእምሮዬ ውስጥ የተሰነቀረ ቀለም ነበር፤
ቀይ ቀለም!!

አሥራ ስድስቱን ዓመት እስረኛ ነበርሁ ….ብዙ ፋሽን መጣ፤ ብዙ ፋሽን ሄደ፤ አንዱም ላይ ግን የውስጥ ሱሪን የሚያሳይ ሽንቁር ያለው የሴት ልብስ እስካሁን አላየሁም፡፡
እንግዲህ መንገድ ዳር ቆሜ “እስቲ ቀሚሳችሁን አውልቁ፣ እንደእሳት ፍም የቀላ፣ቀይ የውስጥ ሱሪ የለበሰችው የአገሬ ሴት እሷ የጎን አጥንቴ ናት” አልል ነገር ... ካቀፉትም ገላ በላይ የትዝታ ገላ ሙቀቱ አይጣል ነው …ሌላው ይበርዳል …በሽንቁር እንደሚገባ ኃይለኛ ነፋስ በቀስታ ቅዝቃዜና መንሰፍሰፍ ወደ ነፍሴ የሚያስገባ ሽንቁር ዛሬም አለ፡፡
“ውይ! እሱ ያያት ሁሉ ታምረዋለች …ወረተኛ ነው” ይሉኛል፡፡ ሲያሻቸው ለበጣም ይመርቁበታል

አቀፈን… ታቀፍንለት፣ ሳመን…ተሳምንለት፤ ዓመል ነው እንጂ ከእኛ ምን አጣ?! ሽንቁር ያው ሽንቁር ነዉ!” እያሉ፡፡

💫አለቀ💫
#ቢሆንም

በል ውረድ እምባዬ ስቃዬን አጣጥበው
ሀዘኔን አባብሰው
ይውጣልኝ የውስጤ
ነዲድ ረመጤ
አንዳችም ባይፈይድ
ወጥቶ ለቀረው ሰው
ይሁን ፍሰስልኝ አንጀቴን አርሰው።

🔘በሰላም ዘውዴ🔘
#በአፍ_ብቻ

ይህን እልፍ መውደድህን
የቃላት ክምርህን
እልቆ ቢስ ፍቅርህን
በአፍ የምትለኝን እንቶ ፈንቶ ወሬ
ተግብረህ አሳየኝ እባክህን ፍቅሬ።

🔘በሰላም ዘውዴ🔘
#በስንቱ_እንጨነቅ

በሰልፍ በሁካታው
በኑሮ ጫጫታው
በስንቱ እንጨነቅ በስንቱ እንምታታ
በርሀብ በጥማት በስቃይ መብዛቱ
በሌለ ነፃነት በውስጠ ባርነት
በስንቱ እንብሰልሰል
በየቱ እንማሰል
በስልጣን ሽኩቻ በኔነት ዘመቻ
በአብይ ሌጋሲ በስም ዲሞክራሲ
በእርስ በእርስ ግጭት ውል በሌለው ፍጭት
በሃይማኖት ተገን
ፍቅር ሲያጣ ወገን
ብዙ በሆነበት አንድ የማያደርገን
በየቱ እንጨነቅ በስንቱ እንቃጠል
በመንገድ በቤቱ
በሥራ ማጣቱ
በሌለ ኢኮኖሚ ባጣንበት ሰሚ
ደግሞ ምን እናስብ
በስንቱ እንብሰልሰል
በየቱ እንማሰል?

🔘ሰላም ዘውዴ🔘
#ማሙሼ


#ክፍል_አንድ


#በእየሩስአሌም_ነጋ

“ኤድያ እኔን ብሎ ንግሥት! አሁን ምኑ ታይቷቸው ነው ንግሥት ያሉኝ? ባዶ ምኞት!" አለችና ከአንደኛው መኖሪያ ቤት
ተጠራቅሞ የወጣውን ቆሻሻ ወደ ያዘችው ማዳበሪያ ገለበጠችው።

“አሁን አንቺ ንግሥት ለመባል ምን ያንስሻል? ዘውዱን እንደሁ ጭነሽዋል።” አለቻት ጓደኛዋ ጸአዳ ንግሥት ለፀሐይ
መከላከያ ራሷ ላይ የጠቀለለችውን ጨርቅ እያመለከተቻት፡፡ድምጻቸውን ጮክ አድርገው በሳቅ አወካኩ፡፡

“ምን ያንቺ ብቻ የኔንስ ስም አላስተዋልሽውም? ጸአዳ! አየ ጉድ! እንዴት ጸድቻለሁ እቴ! ጉድ!” አለች ራሷን ከእግሯ ጀምራ ወደ ላይ እየቃኘች በማሽሟጠጥ፡፡

“ይገርማልኮ! “መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ እንደ ሚሉት፤ ምናልባት የአሁኑ እጣ ፋንታችን ታይቷቸው ይሆናል” አለች
ንግሥት፡፡
“አይ እቴ እንደሱስ አይደለም። እንዲያው ጥሩ ነገር መመኘታቸው ነበር፡፡ ምን ዋጋ አለው ይኸው የሰው ቤት ቆሻሻ ገልባጭ ሆነን አረፍንላቸው!” አለችና በመታከት ከውስጧ የታመቀ የሚመስል ትንፋሽ ተነፈሰች።
ጸአዳ ማዳበሪያዋን እንደማስቀመጥ አድርጋ፣

“እኔ የምለው ይህን ስራ በመስራትሽ እግዚሐርን እንደማመስገን ታማርሬያለሽ?” አለቻትና ወገቧ ላይ ያሰረችውን መቀነት አጠበቀች።

“እ... ታዲያሳ አንቺስ ቅድም ምን ስትይ ነበር? ስታማርሪ አልነበረም?” አለቻት እርሷም እንደመቆም ብላ።

“እኔማ ልማድ ሆኖብኝ እንጂ ስራዬን መች ጠላሁ፡፡ እንዲያውም ጸአዳዬ ከዚህ ደግሞ ሻል ያለ ስራ ከሰሞኑ ሳናገኝ
አንቀርም።”

“ኧረ! እውነትሽን ነው?” አለች ጸአዳ በአግራሞት አፏን ከፍታ።

“እውነቴን ነው። ትንሽ ፍንጭ ቢጤ
አለ፣” አለች ንግሥት።

“ኤድያ! ገና ለገና ብለሽ ነው የምታጓጊኝ? እኔ ሌላ ስራ እስከማገኝ ዎሼ ቀንድ ታበቅላለች።”
“እንቺ ደግሞ ተስፋ የሚሉት ነገር ከግንባርሽም አልተጻፈም!” አለች ንግሥት።
“ኤድያ! ተስፋ ቢጋግሩት እንጎቻ አይሆን!” ጸአዳ ንግግሯ መረር ብሏል።

“ኧረ የኔውስ ተስፋ እንኳን እንጀራ ሌላም ይሆናል፡፡ ታያለሽ ያባቴ አምላክ ባያደርገው!” አለች የጣለችውን ማዳበሪያ
አንስታና በግንባሯ ላይ ኮለል ብሎ የወረደውን ላቧን ጠርጋ የጸአዳ ጥላ እንዲጋርዳት በጎን እየዞረች፡፡

“እስቲ በይ ተጠለይ! እኔን ጌታ ረጅም ባያረግልሽ ኖሮ በየትኛው ዛፍ ትጠለይ ነበር?” አለች እንደመኩራት እያለች፡፡
“አቤት! በዚችው ቁመትሽ እንዲህ የተመጻደቅሽ ሌላ ነገር ቢኖርሽ አለቅን!” አለችና ጸአዳን ወደ ኋላ ትታ በፍጥነት
ተራመደች፡ ወደ ሌላኛው ብረት በር ሲደርሱ በሩን አንኳኩ፡፡ በሩን በፍጥነት የከፈተ የለም፡፡

“እንዲያው ያንን የማሙሼን ነገር እንዴት አደረጋችሁለት?” አለች ጸአዳ በበሩ ቀዳዳ ወደ ውስጥ አጮልቃ እያየች።

“ውይ እንዲያውም እነግርሻለሁ እያልኩ ጸአዳዬ... የማሙሼ ነገርማ እያለቀለት ነው፡፡ ሁላችንም ቃላችንን ሰጥተናል።”

“እንዲያው ምን ብላችሁ ይሆን የመሰከራችሁት?”
“እናቱንና አባቱን ማጣቱን ድፍን የሚካኤል ሰፈር ሰው ያውቃል፡፡ ያው እውነቱን ነዋ የምንመሰክረው... ለማተባችን ስንል!” አለች ንግሥት ማተቧ ውስጥ ሌባ ጣቷን ከትታ ወደፊት ጎተት
እያደረገች፡፡

“ታዲያ አምነው ተቀበሏችሁ?”
“እንዴ... ለምን አያምኑንም?”
“እኛ እራሳችን መጤዎችና በሰው ማድቤት ተጠላልለን የምንኖር ነን፡፡ እንዳው አብረን ስላልኖርን...”

“እንዲህ ብሎ ነገርማ የለም፡፡ ትንሽ ጊዜም ቢሆን እኮ ከናቱ ጋር አብረን መአድ ቆርሰናል። ምስክርነት ደግሞ አብረው በኖሩ አይደለም፡፡”

“ስለዚህ አሳዳጊዎቹ ሊረከቡ ነው ማለት ነው?”
“ታዲያስ! ከሰሞኑ ሳይወስዱት አይቀሩም።”
“እስቲ ይለፍለት የኔ ከርታታ ገና በልጅነቱ አሳሩን አየ” አለች ጸአዳ፡፡
“አየ እንጂ፣ የሱ አሳር ደግሞ ይነገራል! ይቅር ብቻ!”
አሁንማ ለይቶለታል፡፡ የሚያዝንለትም ሰው ለአንዴ ሆይ! ሆይ! ብሎ ዝም አለ፡፡”
“ለዚያ ነው የገንዳ ምግብ የጀመረው?”
“ታዲያ ምን ያድርግ እራብ እንደው ክፉ ነው፡፡”
“ገንዳውንስ የሚያስጥለው ነገር ቢመጣ ጥሩ ነበር፡፡”
“ታዲያ ከኛ የቀረበ ማን ይመጣል? እኛ የምንበላውን ብናካፍለው...”

“እ... አሁን አስር ዓመቱ ሳይሆን ይቀራል ብለሽ ነው?" አለች ንግሥት የቆሙበት በር ሲከፈት ወደ ውስጥ እያየች፡፡

አንዲት ልጅ በማዳበሪ ውስጥ የተሞላውን ቆሻሻ እየጎተተች ወጣች፡፡ በግምት አባቷ የሚሆን ጎልማሳ
በፍጥነት መጥቶ ከእጇ ላይ እየተቀበለ “እናትሽ ይሄን ቆሻሻ አትንኪ ብላ ስንቴ አስጠንቅቃሽ ነበር!” አለና የቆሻሻውን ላስቲክ ንግሥት እግር ስር ወርውሮ
ተመልሶ ገባ፡፡ ንግሥት እስከ ማዳበሪው ተቀብላ ቆሻሻ ማዳበሪያ ውስጥ ከተተችው፡፡ ጸአዳ የቸኮለች ይመስል ፊት ፊት ፈንጠር ብላ የንግሥትን እጅ ጎተት አድርጋት ስትሄድ ንግሥት የሆነ ነገር
ልትነግራት እንደሆነ ገብቷታል። በፍጥነት ከተል ብላ በጥያቄ አስተያየት አየቻት፡፡

“ይኸውልሽ ይሄ ሰውዬ ባለፈው የነገርኩሽ..”
“የቱ ነው?” ግንባሯን አኮሳትራ ወደ እርሷ አሰገገች።
“ባለፈው ሰርግ ሄጄ ስመለስ...”
“እንዴ! ያ እንኳን በመኪና ካላሳፈርኩሽ ብሎ ያደረሰሽ?”
ጸአዳ በአዎንታ ራሷን ነቀነቀች፡፡
“አየሽ ልዩነታችንን! አየሽ! አሁን ሰላምታ እንኳን መች ሰጠን እግዚኦ ጌታዬ! የኛስ ነገር ምን ይሻለን ይሆን?” አለችና ወደ
ቀጣዩ በር እያመራች ንግግሯን ቀጠለች።
“አሁንማ ቆሻሻ መስዬ ቆሻሻ ለብሼ ስላገኘኝ ነው፡፡ የስርጉ እለት ደግሞ እግዚአብሄር ይስጣትና ዘመዴ ሰርጓ ላይ የምለብሰው እንዳላጣ ብላ ልባሽ ልብሶቿን እስከጫማዋ ሰታኝ ..”

“አቤት የፀጉርሽ ነገርማ አይነሳ! ጸዱ ሁልግዜ በቡቱቶ እየጠቀለልሽ ለካ እንደዛ አይነት ፀጉር ኖሮሻል? ኧረ ምነው አንዳንዴ ተሰሪው! የዛኔማ እንኳን እርሱን ለእኔስ ሌላ ሰው መስለሽኝ አልነበረም? አወይ ማማርሽ!” አለቻት ንግሥት ወደ ፀጉሯ እየተመለከተች።

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
ለወዳጆ #Share እያደረጉ
👍4
አትሮኖስ pinned «#ማሙሼ ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ ፡ #በእየሩስአሌም_ነጋ “ኤድያ እኔን ብሎ ንግሥት! አሁን ምኑ ታይቷቸው ነው ንግሥት ያሉኝ? ባዶ ምኞት!" አለችና ከአንደኛው መኖሪያ ቤት ተጠራቅሞ የወጣውን ቆሻሻ ወደ ያዘችው ማዳበሪያ ገለበጠችው። “አሁን አንቺ ንግሥት ለመባል ምን ያንስሻል? ዘውዱን እንደሁ ጭነሽዋል።” አለቻት ጓደኛዋ ጸአዳ ንግሥት ለፀሐይ መከላከያ ራሷ ላይ የጠቀለለችውን ጨርቅ እያመለከተቻት፡፡ድምጻቸውን…»
#ነፍስ_ይማር

ገና ጨቅላ ሳለ በሕፃንነቱ
የት ልትደርስ እያሉ እያንገለታቱ
ደግሞ እየፎተቱ
ሊድህ ሲንገዳገድ
ለመቆም ሲሞክር
ለዳዴ ሲታትር
እየወዘወዙ ከምድር ይጥሉታል
አይበጅም እያሉ ይጨጸልቁታል
ሀሳቤ ተወልዶ ሳያድግ ይሞታል።

🔘ሰላም ዘውዴ🔘
#ማለቅያ

ዉል የሌለው ቁጭት እየተወሳሰበ
ልነጥልህ ስለው እየተሳሰረ
አንዱን ስመዝ ባንዱ እየተያያዘ እየተጋመደ
አልተወው ጨነቀኝ አልይዘው ከበደኝ
ጫፍ መድረሻው ጠፍቶኝ ይኼው እለፋለሁ
ለፍላጎቴ ጥግ ማለቅያ እየቃኘሁ።

🔘ሰላም ዘውዴ🔘
#አባሮሽ

አየሁሽ አየሁህ ስንጫወት አባሮሽ
ስትሸሸገኝ ሳገኝህ ስትሮጥብኝ ስከተልህ
አኩኩሉ ነግቷል ስልህ
የት ነህ የት ነሽ ስንባባል
ስንገናኝ በመሀል
እንቦርቃለን በደስታ
በልጅነት ጨዋታ
ያኔ መልካም ነበረ
ሳቅ ደስታና ፌሽታው
ችግሩ!!
ዛሬም ለአቅመ አዳም ሔዋን ደርሰን
ኑሮ ጎጆ መስርተን
እየኖርን የጋርዮሽ
ትዳር ጨዋታ መስሎህ
ለመደብህ ድብብቆሽህ፡፡

🔘ሰላም ዘውዱ🔘
👍1
#ማሙሼ


#ክፍል_ሁለት (የመጨረሻ ክፍል)


#በእየሩስአሌም_ነጋ
...
.
.

ጓደኛቸው ሐጎስ ሁልጊዜም
እንደሚያደርገው የሰበሰቡትን ቆሻሻ ወደ ጋሪው ገልብጦ ይዞላቸው ሄደ
ተረኛው በር ላይ እንደደረሱ የቆሙበትን
ያለማንኳኳታቸው ትዝ አላቸውና አንኳኩ አንዲት ሴትዮ አንድ ነገር ከፌስታል ውስጥ አውጥታ ከፊት ለፊታቸው ቁጭ አደረገች
ጸአዳ ጎንበስ ብላ አገላበጠችና፣ “በስመአብ ምንድነው?
ድመት! የሞተ ድመት! ምነው ይህንን
እንኳን ብትጥሉት.?”
በፍርሃት ገለጥ አድርጋ አየቻት ድመቷ ትተነፍሳለች
“ያውም እስከ ሕይወቷ! እኔ አልጥላትም፡፡ ራሳችሁ ጣሏት” መልሳ ከሴትየዋ እግር ስር አስቀመጠቻት
“ስራችሁ መሰለኝ እኮ!” ሴትየዋ በሁለት እጇ ወገቧን ይዛለች
“ይልቅስ ሌላ ነፍስ የሌለው ቆሻሻ የላችሁም?” አለች
ንግሥት ድመቷን በፍርኸት እያየች።”
ሴትየዋ ድመቷን እዚያው ጥላ በሩን በኃይል ዘግታ ገባች
“ዐይን የማያየው ነገር የለ! እንደው ይሄ ቆሻሻ ስንቱን ያሳየናል ንግሥቴ?”
“ጉድ ነዋ የሚያሳየን ከዚህ በፊት የሚገርመኝ ምን የመሰለውን ምግብ በፌስታል ጠቅልለው የሚጥሉት ነበሩ። ዛሬ ደግሞ.ይቅር በለን ጌታዬ!” ወደ ሰማይ አንጋጠጠች
“ምግብ የሚደፉት መቼም ባለቤቶች አይደሉም፡ ሠራተኞች የቀጣሪዎቻቸውን ትርፍራፊ መብላት ስለሚያስጠላቸው የተራረፈውን ምግብ ጠቅልለው ይጥሉና እነሱ እጅ ያልነካውን
ለመብላት ሲሉ ያንን ያደርጋሉ
“ወይ ጥጋብ! እግዚያብሄር የእጃቸውን ይስጣቸው ወይ እንጀራ ያስብላቸው ምነው ከሚጥሉት ለተራበ ቢሰጡት!”
“ግን ለደሃው በጅተዋል ለዚህ እኮ ነው እነማሙሼ ከገንዳ ላይ የማይጠፉት”

ከፊት ለፊታቸው የቤቱ በር ላይ የቆመ አንድ ልጅ ወደ ግቢው እየሮጠ ገብቶ ድምጹን ከፍ አድርጎ “ትርንጎ ትርንጎ ቆሻሾች መጡ” አለ ቆሻሻ የሚወስዱት የሚለውን አሳጥረው ለመናገር
ሲሞክሩ እንዲህ እንደሚሉ በመረዳት ንግሥትና ጸአዳ ተያዩና ፈገግ
አሉ ይህን ቋንቋ ለምደውታል
ትርንጎ የተባለችው ሴት የጠራትን ልጅ ወደ ውስጥ እንዲገባ ተቆጥታ ማዳበሪያዋን ይዛ ወደነሱ ቀረበች ከዚያም ወደ ግቢው ውስጥ እየተገላመጠች ከማዳበሪው ውስጥ አንድ ነገር ስባ አወጣችና
አየቻቸው፤ አዩዋት
“ይህንን ተጠቀሙበት” አለች የያዘችውን ወደነርሱ አቅርባ እያሳየቻቸው
“ኧረ! ... ምንድነው!” ጸአዳ በድንጋጤ ገፋ አደረገችው
“የሚያስፈራ ነገር አይደለም. ትንሽ ዱቄት ነው”
“እንዴ! እኛ እኮ ቆሻሻ ሰብሳቢዎች ነን!”
“ብትሆኑስ ታዲያ ይጠቅማችሁዋልኮ።” አለች ትርንጎ በሹክሹክታ
ይሔ እንደ ዝርፊያ ይቆጠራል፡፡ ስለዚህ ቢቀርብን ይሻላል።” አለች ንግሥት ግንባሯን አኮሳትራ፡
“ሴትየዋ እኮ የለችም፡”
“የቷ ሴትዮ?” አለች ንግሥት ከቅድሙ የበለጠ ደንገጥ ብላ
“የቤቱ ባለቤት” ትርንጎ አንሾካሾከች፡፡
“ኧረ ወግጂልኝ እህቴ! ምኑን ክፉ ስራ አመጣሽብኝ እኛን የጠቀምሽ መስሎሽ ከሆነ በጣም ተሳስተሻል!”

ጸአዳ ምንም ሳትናገር ፊቷን አዙራ ወደ ቀጣዩ ቤት አመራች
ንግሥት ትርንጎን እንደቆመች ትታት ጸአዳን ተከተለቻት ትርንጎ ወደ ቤትም አልገባችም፡፡ አፏን ይዛ በሳቅ
ትንተከተካለች

ሲጠራት የነበረው ልጅ ወደ ውጪ ወጣና ላስቲኩን ተመለከተ

“እንዴ አልሸወድ አሉሽ እንዴ?” አለና ትርንጎን አያት ትርንጎ ሳቋን አላቋረጠችም

“ኧረ እነሱ ከኔ የበለጡ ቆቆች ናቸው፡፡”
“አይ አመድ አንሸከምም ስለምትሉ
በሲስተም ልታስወስዳችሁ ነበር፡” አለና አመዱን በእርግጫ ጠለዘው አመዱ
ወደላይ ተበትኖ ትርንጎ ዐይን ውስጥ ሲገባና ዐይኗን ስታሽ ንግሥትና ጸአዳ በብሽቀት ጸጥ ብለው ጋሪያቸውን እየገፉ የቆሻሻ አሰሳቸውን ቀጠሉ
“ስራ አይናቅም ቢሆንም አንዳንድ ነገሮች ሲታዩ ግን ይህንን ስራ መስራትም አያስመኝ ይህቺ ማሰብ የተሳናት
ቀለደችብን አይደል እንዴ?” አለች ጸአዳ፡
“እንግዲህ መታገስ ነው እናቴ አለበለዚያ አንድም እርምጃ መሄድ አይቻልም!” አለችና አንዲት ዛፍ ስር ቁጭ አለች ንግስት
“እንዲያው የቆሻሻውን ክርፋትና ግማት ለምደነዋል፤ሽቷችን ሆኗል፡፡ የሰውን አመል፣ ክርፋት.”

ንግሥት ጸአዳ አረፍተ ነገሩን እስክትቋጭ
አላስጨረሰቻትም በተናገረችው ንግግር በሳቅ ትንተከተክ ጀመር

“አንቺ ሳቂ !...ደግሞ ለምንድነው የተቀመጥሽው? ተነሽ ይልቅ ፀሐይ ሳይበረታ!” ጥላት ስትሔድ ተከተለቻት

ቆሻሽውን እየሠበሰቡ በየመንደሩ ከዞሩ በኋላ እነሱም የተቀረውን ለመዘርገፍ ወደ ቆሻሻ ገንዳ አመሩ

ከገንዳው ፊት ለፊት አስፋልት ዳር ላይ ሰዎች ይተራመሳሉ አንድ ልጅ እስከ ጉልበቱ የተተረተረውን ሱሪ እንደዳይጠልፈው ወደላይ ሰብስቦ እየሮጠ መጣ የንግሥት ጎረቤት
ልጅ ነው

“ምን አጋጠመህ አንተ?”
“እ .አ .ማሙሼ?” አለ መናገር አቅቶት በድካም እያለከለከ
“ማሙሼ ምን ሆነ?" አለች ጸአዳ በድንጋጤ
“እኔ እንጃ መሬት ላይ ወደቋል!...እ...እ...ሞቷል ሞቷል
መሰለኝ... እንጃ ብቻ ሰዎች ከበውት ያለቅሳሉ።”
“ወይኔ ልጄን ምን አገኘው ማሙሽዬን!”
“ምን እንዳገኝው አላቅም!” አለ የሚርገበገበው ድምጹ መለስ
ብሏል ንግሥትና ጸአዳ ወደተሰበሰበው ሰው እየሮጡ ሄደው እየተሽሎከሎኩ ማሙሼ ወዳለበት ተጠጉ
ማሙሼ እግሮቹንና እጆቹን ዘረጋግቷቸዋል በአፉ ዙሪያ
የሚታየው ነገር ቀደም ሲል አረፋ አስደፍቆት እንደነበር ያመለክታል ቀይ መልኩ ጠቁሯል አይኖቹ በከፊል ተከፍተዋል ንግሥት ሮጣ ልታነሳው ስትል ፖሊሶች ደርሰው የተዘረጋ
እጇን እንድትሰበስብ ወደ ኋላ ገፋ አደረጓት የማሙሼን ደረት ልብ
ብላ አየችው ትንፋሽ ያለው አይመስልም፡፡ የሷም ትንፋሽ ቀጥ
የሚል መሰላትና አምቃ የያዘችውን ትንፋሿን በረጅሙ ለቀቀችው፡እናቶች መቀነታቸውን በወገባቸው አስረው በለሆሳስ ያልጎመጉማሉ
ሮጦ የነገራቸው ልጅ የንግሥትን ልብስ ጎተት አደረገና፣ “አብረን እኮ ነበርን አሁን” አለ።

“ምን እያደረጋችሁ ነበር?” ጸአዳ ጠየቀች፡፡

“በአንድ እጁ ከላስቲክ ውስጥ እያወጣ ሲበላ አ

ገኘሁትና አላካፍልህም ብሎ ተጣላን፡፡ ከዚያ እሱን ተውኩና ወደ ገንዳው ሄጄ እኔም የተጣለ ነገር ስስበስብ ነበር፡፡ ትንሽ ቆያቶ እዚህ አፈር
ላይ መንከባለል ጀመረ፡፡”
“ውይ ልጄን አፈር ልብላልህ፡፡ ይህን የገንዳ ምግብ ተዉ ብንላቸው...”
“ታዲያ ሲርባቸው ምን ያድርጉ? እኛ እንደሁ አንዳንዴ ነው እንጂ ሁልግዜ አናስታውሳቸው፡፡ እነሱም እኮ የማያቁዋርጥ ሆድ አላቸው።”

ጸአዳ ንግግሯን ስትጨርስ ንግሥት መናገር አቅቷት በታፈነ ድምጽ እያልጎመጎመች እጥፍጥፍ ብላ ወደቀች።
ጸኣዳ “እህቴን!” ብላ ልታነሳት ጎንበስ አለች፡፡

ንግሥት ከአፏ አንድ ቃል ለማውጣት እየሞከረች ነው፡፡ ጸአዳ እየተርበተበተች “ኧረ ድረሱልኝ! ወይኔ እህቴን ምን አገኛት?” አለች።

ንግሥት መላ ሰውነቷ ቆፈን የወረደበት
ይመስል ይንቀጠቀጣል። ጥርሶቿ ይንገጫገጫሉ። እንደ ምንም አፏን በግድ አላቃ ጸአዳን እያየች “
ቀድሞ ከኛ በፊት... ሐጎስ የመጣውን
ሰውየው የጣለውን፣ ተጠንቀቁት ያለንን... የ..የአ........የአይጥ መርዝ...በልቶታል ማለት ነው።” ወዲያውኑ የጸአዳ ተደራራቢ ጩኸት አካባቢውን አናጋው።

አለቀ

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
👍2
#የሀጢአት_ፍሬ

ምኞቴ ሳላውቀው ሀጢአትን ፀንሳ
እንዲሁም  እነደዋዛ
ከሥጋዬ አርግዛ
በደል ተደግፋ
ሞት ወለደችብኝ
ሕይወት አጨናግፋ።

🔘ሰላም ዘውዴ🔘
#ከሆነው

ለምን ሆነ ብዬ ከማስጨንቅ ነፍሴን
ከምወቅስ ራሴን
ደግ ደጉን ላስብ ለበጐ ነው ብዬ
ከሆነው ባሻገር የሚሆነውን ስዬ፡፡

🔘ሰላም ዘውዴ🔘
#የማታ_እንጀራ

አባ ሲመርቁኝ እንዲህ አሉኝ
ውጥን ሀሳነብሽ ይሙላ
መንገድሽ ይሁን አላላ
እንከን ይራቅ ከስርሽ
ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሽ
እድሜ ከጤና ያድልሽ
ተገዢ ሚሆን ለአምላክሽ
ልጄ ንፁህ ልብ ይስጥሽ
ያድልሽ የማታ እንጀራ
ምሳሌ ያርግሽ የመልካም ሥራ አሉኝ፤
ምርቃቱን እነሆ ተቀብያለሁ
አሜን ይሁንልኝ ብያለሁ
ግን ግን አባ
ከዚህ ሁሉ ውስጥ ያልገባኝ
የሆነብኝ ወደ ግራ
ቀን አጥቼ ምን ሊሆነኝ የማታ እንጀራ፡፡

🔘ሰላም ዘውዴ🔘
#ያለ_ደንብ

ክበር የሐበሻ-ልጅ ዝም ብለህ አትኮፈስ
ይልቅ ወጉን ሰብረህ የኩራትን መንፈስ
በሕይወት ኑር እንጂ ተንኳሰስ ተወደስ
ጅቡን እረድና በልተኸው ተቀደስ፡፡😳
#አንተ_ሰዉ_ተመከር

በገንዘብ አትኩራ
ገንዘብ ያልቃልና
በወገን አትመካ
ክፉ ሞት አለና
በጉልበት አትመካ
መሠበር አለና
ለወሬ አትቸኩል
አይጠቅምህምና
ለሥራህ ግን ድከም
ማደሪያህ ነዉና።
☞ ጃሎ እንበል……!
.
ዱብ ዱብ ባይ እንደበረዶ
በልጅነቱ በረሃ ለምዶ
እጥፍጥፍ እንደ ኩታ ልብስ
አተኳኮሱ አንጀት የሚያርስ
እዚህ አጉርሶ እዚያ ቢልከው
አንጀት ጉበቱን አዝለከለከው
ገና ወጣቱ የነበር ጣቱ
ያ ጎበዝ ጀግና ጠረፍ ነው ሞቱ።
አትንኩኝ! አትንኩኝ! አትንኩኝ እያለ ታልፋለች ህይወቱ።
.
.
.
ሞትን ያህል መከራ
ባሩድን ያህል መራራ
ጠጥቶ ሃገሩን ሊያኮራ
ቅንጣት ለነፍሱ ሳይፈራ
በሞቱ ታሪክ ሊሰራ
ይህ ነበር የጀግና ትውፊት ሃገር ትውልድን ያኮራ።
.
የሃገሩን ሞት ሞቶ የራሱን ነፍስ ሊሰጣት
የፍቅሩን ፅናት ፈትኖ በባሩድ በእቶን እሳት
ጠላቱን አይቀጡ ቀጥቶ የክብሩን ፀዳል ሊያለብሳት
ዘጠኝ ሞት ከፊቱ ቀርቦ ጨልጦ ዘጠኝኑም ሞት
ዘጠኙም ሳይገለው ቀርቶ በሺህ ልብ ህይወት ዘርቶ
ከዘላለም እስከ ዘላለም ጥግ ህያው ታሪክ ዘርቶ
እንዲህ ነበር አባት ሲያልፍ አኩሪ ስራውን ተክቶ።
.
ልጁም ያባቱን ወኔ ቆራጥ ተግባሩን ወርሶ
ለወገቡ ዘር መራራ ደሙን ከጀግና ልቡ ቀንሶ
እሱም ተክቶ ያልፋል ያገሩን ታሪክ አውርሶ
ይህ ነበር የኛ ታሪክ ድርሳኑን ላየው
ከግሉ ቅጦት ይልቅ ያገሩን ክብር ያሳየው
እንዲህ ለሀገር በመሞት ፈቃዷን እየፈፀምነ
ጎበዝ ሲያልፍ ጎበዝ ተክቶ ከዘንድሮ ላይ ደረስነ።
.
ዘንድሮስ! ዘንድሮስ! ዘንድሮማ ምን ይወራል
እድሜ ለስልጣኔ.....
ለለጋ ህፃናት ይብላኝ ለአገራዊ ሁሉ መጥኔ
ልጄ ኑርልኝ ስትል ሃገር በብርክ ቆማ
የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ ብሎ የእምዬን ተማፅኖ ላይሰማ
ወላጅ ለሞት ሲጣደፍ ጨቅላ ህፃናት በትኖ
እድሜ ባዛለው ጉልበቱ አያት ከልጅ ልጅ ታምኖ
አረጋዊነት ዘመኑ ማረፍ መጦሩ ቀረና
መውለድ እርግማን ሆነ ፀጋ መሆኑ አበቃና።
.
ሌጣ ሆኖ እንደበቀለ ሳያስብ ለእናት አባቱ
ለግሉ ደስታ ሲማስ ሲታደፍ ለእሳት ጉልበቱ
ወላጁን በሃዘን ማግዶ ሲሰበር በለጋነቱ
ወዴት አቤት ይባላል መጥኔ ለዚያች እናቱ
የልጇን መረታት አይታ ሰፍሳፋ ልቧ ሲባባ
አንጀቷ ሁለት ተከፍሎ ፊቷ ሲታጠብ በእምባ
ላፍታ እንኳ ይህ ቢታወሰው ዘሎ ከእሳቱ ባልገባ።
.
ጉድ ነው ጉድሽን ስሚ እማማ ከነእርምሽ መኖሩ ይብቃ
የጉድ ዘመን ትውልድሽ የአውሮፓ የላቲን መጢቃ
ክብሩን ሞራሉን ሸጦ እንኳን ለልጁ ሊተርፍ ለራሱም ገና ሳይበቃ
መች እንደአባቱ ሊያኖርሽ ለራሱም መኖር አቅቶት
20 30 ኬላውን አርባ መድፈን ተስኖት
በደዌ በትር ሲመታ ቡቃያው ጅምሩ ቀርቶ
ወፌ ቆመች እንዳላል የእምቦሳው ተስፋ ገርጥቶ
ጥናቱን ይስጥሽ እማማ አሳርሽ መከራሽ በዝቶ
እንደአሸን የፈላው ዘርሽ እንደአሸን ልርገፍ ካለ
ጎህ ሲቀድ የፈላው ዘርሽ ጀንበርን ማለፍ ካልቻለ
መገን ከማለት በቀር ከንግዲህ ሌላ ምን አ ለ።
……
ሽምግልና ላይገኝ ከእንግዲህ በተረት ይፃፍ
የእድሜ በረከት ስጦታው ሲዘጋ በደዌ ምዕራፍ
ጃሎ እንበል ጎበዝ እንፎክር የመኖር ገዳችን ቢመጣ
ወኔአችን ግሎ ተነስቶ ሞትን ካገሩ ሊያስወጣ
ያኔ ሃገር ስትጠራን በጭንቅ በጣር ተይዛ
ድረሱ አድኑኝ ስትል በጠላት አዝና ተክዛ።
.
በቀረርቶ ፍርሃትን ገድለን በሽለላ ሞትን ደፍረን
የሀገርን መደፈር ላናይ በፈቃዳችን ሞተን
ታንኩን መትረየስ መድፉን ጎራዴን ታጥቀን ማርከናል
ጠላትን አይቀጡ ቀጥተን ወደመጣበት ልከናል
አንዴ አይደል ደርዘን ተዋግተን የወንዱን ሱሪ ፈተናል።
ያኔም የነበር እኛ! አንሁን ያለን እኛ!
እንዴት ያን ሁሉ ወኔ ለደዌ ሰተን እንተኛ።
.
ጃሎ በል ጎበዝ እንፎክር የመኖር ገዳችን ይምጣ
ወኔአችን ግሎ ተነስቶ ሞትን ካገር ቢያስወጣ።
.
ዱብ ዱብ ባይ እንደበረዶ
በልጅነቱ በረሃ ለምዶ
እጥፍጥፍ እንደ ኩታ ልብስ
አተኳኮሱ አንጀት የሚያርስ
እዚህ አጉርሶ እዚያ ቢልከው
አንጀት ጉበቱን አዝለከለከው
ገና ወጣቱ የነበር ጣቱ
ያ ጎበዝ ጀግና ጠረፍ ነው ሞቱ።
አትንኩኝ! አትንኩኝ! አትንኩኝ እያለ ታልፋለች ህይወቱ።
አታታታታታታታታታታ እምምምምምምመምምምም…
===
ዘልአለማዊ ክብርና ሞገስ ለበረሃ ሲሳዮቹ!

🔘 በገጣሚ አበባው መላኩ 🔘
#ልውውጥ


#በእየሩስአሌም_ነጋ

በአስፋልቱ ግራና ቀኝ ያሉ ዛፎች የፀሐይዋን ሙቀት ለማብረድ በሚነፍሰው ነፋስ እየተቃኙ በእንቅስቃሴ ሲያዜሙ ስዓታት የቆሙ ካህናትን ይመስላሉ። የተንጣለለው ስፊ የእርሻ
መሬት በአትኩሮት ሲመለከቱት ነፍስን በሐሴት ያፍነከንካል፡፡

ተፈጥሮን ሳደንቅ ውዬ ባድር አይሰለቸኝም፡፡ ለወትሮው ቤቴ ደርሼ መኪናዬን ካቆምኩ በኋላ ነበር ወጣ ብዬ በዚህ መንገድ ብቻዬን የምጓዘው፡፡ በዚያን እለት ግን ከቤቴም አላዳርስ አለኝ፡፡
መኪናዬን ወደ ዳር አቆምኳትና የለበስኩትን ሹራብ በወገቤ ዙሪያ
አገልድሜ መልካም አየሩን እየሳብኩ ወደ ዛፎች ጥላ አመራሁ፡፡ አልፎ አልፎ ከሚታዩ ሰዎች በስተቀር በአካባቢው ሰው በብዛት ሲንቀሳቀስ አይታይም፡፡ ምናልባት ዐይንን ወርወር ቢያደርጉ እረኛ
የሌላቸው ከብቶችን በተንጣለለው መስክ ላይ ማየት ይቻላል፡፡

ከፊት ለፊቴ በማሳው መሐል የተዘረጋች ቀጭን መንገድ ትታያለች፡፡ በዚህች ቀጭን መንገድ እኔ ወዳለሁበት የመኪና
መንገድ ቁልቁል የሚወርድ ሰው ታየኝ፡፡ ወደታች እየመጣ እንደገና ተመልሶ ወደ ላይ ሲወጣ ስመለከት ነው፡፡በሚያደርገው ተደጋጋሚ እንቅስቃሴ ግራ ተጋባሁ፡፡ በግምት አስር እርምጃ የሚሆን ወደ ፊት ተራምዶ እንደገና ይመለሳል፡፡
ለጥቂት ደቂቃዎች ይህንን ድርጊት ሲደጋግም ዓይኔን ሳልነቅል ተከታተልኩት፡፡ መቼም ጤነኛ ሰው ይህን ያህል ምልልስ ሊያደርግ አይችልም ብዬ አስብኩ ምልልሱን አቁሞ እኔ ወዳለሁበት ሲመጣ ፍርሃትና ግርምት በተቀላቀለበት ስሜት አየሁት፡፡ በአንድ እጁ ሌዘር ኮት በትከሻው አንጠልጥሎ፣ በሌላኛው-
እጁ ያለቀች ሲጋራ ይዟል፡፡ የለበሰው ጥቁር ሽሚዝ አዝራሮች ያለቦታቸው ተሰካክተዉ ፣ ኮሌታው ተዛንፏል።

የሚናገረው ባይሰማኝም አንዳች ነገር እንደ ሚናገር የከንፈሩ እንቅስቃሴ ያስታውቃል፡፡ እኔ ከተቀመጥኩበት ትይዩ ጀርባውን ሰጥቶኝ ተቀምጦ ወደ አንድ አቅጣጫ አተኩሮ አየ። እንደገና
ከተቀመጠበት ተነስቶ ወደኔ ዞሮና ከወገቡ አጎንብሶ አንዳች ነገር ፈለገ
በፊት የጣላትን ሲጋራ አንስቶ ከተመለከታት በኋላ የቀረችውን ድጋሚ ለኮሰና እስኪበቃው ስቦ ወደኔ አቅጣጫ ወረወረው እኔ ወደቆምኩበት በቀስታ ሲጠጋ እንቅስቃሴውን መቃኘት አላቆምኩም፡ በግንባሩና በጉንጩ ላይ የተሰመሩ ጠባሳዎች ይታያሉ፤ ቁጭ ብዬ ስላየሁትም ይሁን እንጂ ስውየው እጅግ ገዝፎ ታየኝ፡፡ የሱሪው ቀበቶ በቦርጩ ተደብቋል። የቆዳው ቅላትና ወዝ
በምቾት ይኖር እንደነበር ጠቆመኝ፡፡ ድንገት ዐይኖቹን ዐይኖቼ ላይ
አሳረፋቸው፡፡ የዐይኑ ሽፋሽፍት የመርገብገብ ስራውን የቀነስና
በቁጣ የሚያይ ይመስላል፡፡

ዐይኔን ከእርሱ ላይ ነቅዬ ወደ መኪናዬ ለመግባት ስራመድ ረጅምና ግዙፍ ጥላው ሲከተለኝ አየሁና እጆቹን በአንገ ቴ ዙሪያ ሊያኖራቸው መስሎኝ ሽምቅቅ ብዬ ጭብጦ እንዳከልኩ ቀስ ብዬ ዞሬ
አየሁት። ፈገግ ለማለት ሙከራ ያደረገ ይመስላል። እኔም ግራ ገብቶኝ
ፈገግ፣ ኮስተር፣ ደግሞ ፊቴን ፈታ እያደረግሁ ተመለከትኩት፡፡ ባፈጠጠ ዐይኑ ወደታች ቁመናዬን ገረፍ አድርጎ
ቃኘኝና ዝም አለ፡፡ ወደመኪናዬ ልገባ አንድ እግሬን ሳነሳ፣

“ሃይ ዶክተር!” አለኝ፡፡ በድንጋጤ የሰላምታውን አጸፋ መለስኩና፣
“ይቅርታ እንተዋወቃለን?” አልኩት፡፡

“አንተ እንኳን አታውቀኝም፡፡ ነገር ግን አንድ ቀን በቤታችሁ በር ላይ ስናልፍ ባለቤትህን ከውጪ በር ላይ አገኘናትና ወደቤት ገብተን ቡና እንድንጠጣ
ጋበዘችን፡፡እናቴ እንኳን ፈቃደኛ አልነበረችም

ለምን?”
“አለ አይደል...እ... ልጄ አብዷል ብላ ስለምታስብ..." አለና ምላሽ እንድሰጠው ይሁን አይሁን አልገባኝም ዝም ብሎ
ተመለከተኝ፡፡ የምመልስለት ግራ ቢገባኝም አሰብ አደረኩና “ታዲያ
እኔ በቤት ውስጥ ነበርኩኝ...እ የዚያን እለት ...እ...ከዚህ በፊት አይቼህ የማውቅ አልመሰለኝም?”
“በቤት ውስጥ እንኳን አልነበርክም፡፡ ግን ፎቶዎችህን እንዴት ግሩም አድርጌ አይቼያቸዋለሁ መሰለህ! በተለይ በዚህ
በለበስከው ኮት የተነሳኸው ፎቶ ፓ! እንዴት እንደሚያምር!"
“አንድ ቀን ያውም በፎቶ አይተኸኝ አለመርሳትህ ይገርማል!"
“ታዲያ አሁን እንዴት እብድ ልባል እችላለሁ?
አይገርምህም? እየሰማኋቸው 'የጽጌ ልጅ አብዶ መጣ! ይላሉ።
ምነው የሀገሬ ሰው እፍረቱንና ይሉኝታውን ወዴት አደረሰው? እ?
ንገረኝ! ወዴት አደረሰው?” በንዴት እየተወራጨ እጁን ወደኋላው
ሰደድ ሲያደርግ ልቤ በጉሮሮዬ የተሸነቀረች ይመስል ትንፋሽ
አጠረኝ እንደምንም ለመረጋጋት ሞከርኩና “እ...ግዴለም
እንዳልሰማህ ማለፍ ነው” አልኩት፡፡
“እንዴት እንዳልሰማ ይታለፋል? አየህ! እኔ የሀገሬ ሰው፣ መንደሬና ተስማሚ አየሩ ቢናፍቀኝ ሁሉንም ነገር ትቼ መጣሁ፡፡
ሰው ግን አልገባውም፡፡ የሚገርመው ነገር አንተን ማግኘት እንዴት እፈልግ እንደነበር…ተካልኝ እባላለሁ” ጨበጠኝ፡፡ እጄ በመዳፉ እቅፍ ውስጥ ሲገባ ጣቶቹ ተንቋቁ፡፡ ከዚያም በብስጭት እንደ መቁነጥነጥ ብሎ፣ ሰው ብቻውን ሲቀመጥ፣ ከራሱ ጋር ሲማከር እብድ ይባላል ወይኔ ተካልኝ!" አለ።

አፌን ለመናገር ከፍቻለሁ። ግን ቃል አልወጣኝም፡፡ እዚያው እንደቆመ አሻግሮ ወደ መንደሩ ተመለከተና

“መንደሬን እንዴት እወዳታለሁ መሰለህ አሁን ፊቱ ላይ ትንሽ ፈገግታ ብልጭ ሲል ታየኝ ።
“ስንት ግዜ ውጭ ሀገር ተቀመጥክ?” አልኩት፡፡
“ድፍን ሃያ አመት፡፡"
“ብዙ ቆይተኻል!”
“ምን ዋጋ አለው? ምንም አልሰራሁሰትም ፡፡ ታየዋለህ ያንን ቀይ ጥርያ ቆሮቆሮ ቤት ?"አለና ወደኔ ተመለከተ።በአወንታ መለስኩለት።

እናቴን ከዛ አላወጣኋትም።ድሮ አባቴ የሰራው ቤት ነው።ምንም ለውጥ አልተደረገበትም። ምንም!"
“እንግዲህ ምን ታደርገዋለህ? አንድ ግዜ ሆኗል።”
“አዎ! ምንም ላደርገው አልችልም! ምንም! ብዙዎች አሁን አንተ ያልከውን ነው የሚሉኝ፡፡ አባባሉ ተቀየረ እንጂ ያው
እንደነሱ!”
ዐይኖቹን ለመሸሽ ጥረት ባደርግም አላመለጥኩም፡፡
ዞርኩበት ዞሮ በኔ እይታ ፊት ለፊት ቆመና ወደኔ እየተጠጋ፣
“አንዴ ሆኗል! አንዴ ሆኗል! ለመሆኑ የሆነውን የመቀየር አሁንስ ጊዜ የለንም? የለንም ወይ?” ከፊት ለፊታችን ያለው ጋራ
አስፈሪ ድምጹን መልሶ አቀበለኝ፡፡ አምላክ የዛሬን እንዲያወጣኝ ደጋግሜ ተማጸንኩ፡፡
“ግን ለምን አበደ ይሉኛል? አሁን እኔ እብድ እመስላለሁ?"
የሚናገረው ሁሉ ያስጨንቀኝ ጀምሯል፡፡ ለጥቂት ደቂቃ ዝም አልኩ፡፡
“አሁን እኔ እብድ እመስላለሁ ወይ?”
“ኧረ አትመስልም፡፡ ምናልባት ቅድም እንዳልከው ብቻህን ስታወራ ያው እንደምታውቀው ብቻ ማውራት እብድ ያሰኛል።”
“እኔ ብቻ ነኝ ብቻዬን የማወራ? ድፍን የዓለም ህዝብ ብቻውን እያወራ እንደሚሄድ አታውቅም? አንተ ብቻህን
አታወራም? ቆይ አንተ እራስህ አሁን ለኔ ምን አይነት ስሜት ነው ያለህ? ሳትዋሽ ንገረኝ” አለኝ፡፡ ትንሽ ፈገግታ በፊቱ ላይ ብልጭ ያለ መሰለኝና እኔም ፈገግ ብዬ፣
“አንተን እብድ ነው የሚያስብል ምንም የተለየ ነገር አላየሁም” አልኩት፡፡
“ዋሽህ ዶክተር! ከውሸት ሁሉ የከፋው ደግሞ ምን አይነት ውሸት እንደሆነ ታውቃለህ?.. ራስን መዋሸት፡፡” አለና አሁንም አሻግሮ ማየት ጀመረ፡፡ ሁለተኛ በዚህ መንገድ ላለመምጣት በውስጤ
ማልኩ።
“አሁን ለምሳሌ ዋሸኸኝ አይደል?” አፈጠጠ፡፡
ፈራ ተባ እያልኩ፣
“በእርግጥ...” አልኩና ዝም አልኩ።
“በእርግጥ ምን?”
“እ..ብቻህን ስታወራ በማየቴ ትንሽ እንደመደንገጥ ብዬ ነበር፡፡ ግን ብቻ ማውራትህ ላንተ መልካም ከሆነ ጥሩ ነው። ግን በተቻለህ አቅም ከሰው ጋር ለመሆን ሞክር፡፡”
ለምን እንዲህ ብዬ እንደማወራ ግራ ገባኝ። የምናገረው አስቤበት ሳይሆን የሱ ስሜት
👍2
እንዳይጎዳ በመጠንቀቅ ብቻ ነበር፡፡
አሁን ከዚህ ዓይነት ሰው ጋር ምን ዓይነት ወሬ ነው የማወራው?
ግራ ተጋባሁ። ተካልኝ የማስበውን ቀድሞ የሚያውቅ ይመስል፡፡
“ከኔ ጋር ምን ማውራት እንዳለብህ ሳይገባህ ቀርቶ ግራ የተጋባህ ትመስላለህ? የፈለከውን ነገር ማውራት ትችላለህ፡፡ ስለፈለከው ነገር፡፡” አለና በፈጣጣ አስተያየቱ ቃኘኝ፡፡
“ደክሞኛል” ብዬ ልሰናበተው ፈለግሁ፡፡ ያን ማድረግ ግን አልቻልኩም።
ፊት ለፊቱ ድንጋይ ላይ ቁጭ አልኩ።
“አየህ እብድ ነው ብለህ ገምተህ ፍራቻህን ውጠሃል፡፡ ምንም
የሚያስፈራ ነገር የለም፡፡” አለና እንደመተከዝ ብሎ በደከመ ድምጽ
አቃሰተ።
“ሰዎች ይህንን በመገመታቸው ቅር ሊልህ አይገባም:: ይልቁንም ጤነኛ እንደሆንክ የሚያስረዱ ነገሮችን...”
ተካልኝ የኮረኮሩትን ያህል ከት ብሎ ሳቀና፣
“ቅር አይለኝም፡፡ አለማችን ከተራራ የገዘፉ ቅሬታዎችን ታፈልቃለች፡፡ ታዲያ እኛ ለጥቃቅን ቅሬታዎች ስናዝን እገረማለሁ፡፡
ያልጨረሰውን ሳቁን እስኪጨርስ ዝም አልኩት፡፡

አሳዘነኝ፡፡ እንደፍራቴ ቢሆን ጥየው ለመሄድ በተገደድኩ፡፡
ግን ለነሱስ እኛ እንጂ ማን አላቸው? ልናዳምጣቸው ይገባል ብዬ ወሰንኩ፡፡ ይህ ሰው ደግሞ የሚተናኮልና የሌሎች ሰዎች እርዳታ የሚያስፈልገው አይደለም፡ የሚያወራውን ነገር ሲያዛንፍ ወይም
ክፉ ነገር ሲናገር እስካሁን አልሰማሁትም ስለዚህ በትግስት አናግሬው መሄድን መረጥኩ፡፡

“አብሬህ ብሄድ ደስ ይለኛል” አለና በቅሬታ የተሞላ ፊቴን በትዝብት ሲያጤን ተመለከትኩት፡፡
አበደ የተባለን ሰው ወደ ቤት ይዞ መሄድ ሊያሥፈራ እንደሚችል መቼም እሱም አውቋል፡፡ ከሀሳቤ ጋር እየተሟገትኩ
ሳለሁ “ግዴለም፡፡ ተወው ምንም ያህል ግዜ አትቆይም፡፡ እዚሁ ትንሽ ደቂቃ እንጫወትና ትሄዳለህ፡፡” ሲለኝ ቅሬታዬን እንዳያውቅብኝ ለመደበቅ እየሞከርኩ ወደ መቀመጫዬ ተመለስኩ። ለጥቂት ደቂቃ ወደ መሬት አተኮረና ቀና ብሎ ካየኝ በኋላ፣
“ይቅርታ ዶክተር ለመሆኑ በሽተኞችህን እንዴት ነው የምትንከባከባቸው?... ማለቴ የምታሳያቸው ፍቅር ርህራሄ?”
“በተቻለኝ አቅም ስሜታቸውን ለማወቅና ካለባቸው ችግር ለመገላገል እንደበሽታው ቅለትና ክብደት አስፈላጊውን ህክምና
አደርግላቸዋለሁ።”
“ይቅርታ ዶክተር ያንተን ሀሳብ መጋፋቴ አይደለም፡፡ በተለይ ደግሞ ሐኪሞች የአእምሮ ጭንቀት ያለባቸውን ሰዎች እናድናለን ሲሉ ይደንቀኛል፡፡ ስሜት እኮ ባለቤቱ ሊመራው የሚችል እንጂ
ማንም እንዳሰኘው የሚሾፍረው ባቡር አይደለም፡፡ መጀመሪያ የበሽተኛውን
ስሜት ሊያዳምጠው ግድ ነው፡፡ መድኃኒቱ እያንዳንዳችን የእያንዳንዳችንን ስሜት በማዳመጥ ላይ ይመሰረታል።
የሰው አስተሳሰብ ከተሰረዘ በኋላ ማንም ሰው ሊያስተካክለው የሚችል አይመስለኝም።”
የራሱን ስሜት እያዳመጠ የሚናገረውን ሰው በሀሳቡ ላይ ሌላ ተጨማሪ አስተያየት አክዬ ወይም ተቃራኒ ጉዳይ አንስቼ እንዳይሰሳጭብኝ ተጠንቅቄ ዝም አልኩ፡፡ ባለማቋረጥ ጉሮሮውን
ከጠረገ በኋላ፣
“ለህመምተኞችህ ያለህስ አክብሮት ምን አይነት ነው?” አለኝ፡፡
“በተቻለኝ አቅም እንከባከባቸዋለሁ፡፡
“አክብራቸው ዶክተር፡፡ ከበሬታህ ግን ራስን ለማከበር አይሁን። አባባሌ የሚገባህ ይመስለኛል።”
“እንዴት እንደዚህ ይሆናል? ይህ እንዲሆን የህክምና ስነ-ምግባር አይፈቅድም፡፡
“ዶክተር አትዋሸኝ! አለማችን ሁሉ በውሽት ተሞልታለች፡፡
ማንም ማንንም አይወድም፡፡ የሚወደው ቢኖር እራሱን ብቻ ነው።”
ዐይኑ እየፈጠጠ ድምጹ እየጨመረ ሲመጣ የፍርኸት ስሜቴም
እንዲሁ እየጨመረ ሄደ፡፡
“በእርግጥ ሰው ራሱን ይወዳል፡፡ ነገር ግን በተጨማሪ የሚወደው ሰው ይኖራል ባይ ነኝ” አልኩት፡፡ አሁን ደግሞ ግራ
የሚያጋባ ሳቅ ሳቀና “እዚህ ላይ ነው እኮ ፍሬ ነገሩ፡፡ በልባችን የመውደድ ሚዛን ቢኖር ኖሮ ሁሉን ሰው የመውደድ ችሎታ
በልባችን ይሸፍን ነበር፡፡ ስለሌለ ግን አንዱንም መውደድ አንችልም፡፡
መልሱ ያለው በተጨማሪ የምንወደው ሰው ይኖራል ባልከው ውስጥ
ነው፡፡ አንድ ሰው ያለምንም ለውጥ ወይም ያለ አንድ ልውውጥ
አንድን ሰው እወዳለሁ ሲል ትልቅ ውሸት ነው፡፡ ቆይ አንተ ሚስትህን ለምን አፈቀርካት?”
“ስለምወዳት።”
“ለምን ወደድካት?”
“እኔ የምፈልገው ሁሉ እሷ ጋር ስላለ።”
“አየህ ዶክተር የራስህ ፍላጎት ተሟልቶ ደስታና እርካታ
ፈልገህ ነው ያፈቀርካት፡፡ ታዲያ ወደድካት ይባላል?”
“እሷም አኮ በኔ ደስ ይላታል።”
“ታዲያስ! እዚህ ላይ አይደለ ምስጢሩ፡፡ ፍቅር አንድ ሰው ብቻ የሚለግሰው እኮ አይደለም ልውውጥ ነው።”
“አንድ ሰው ሰውን የሚወደው ለመወደድና በልውውጥ
የራስን ፍላጎት ለማሟላት ነው ካልክ ችግረኞችን ወይም ከአካል
ጉዳተኞች የምናገኘው አንዳችም ነገር የለም፡፡ ታዲያ እራስህን
ወደድክ ይባላል ወይም ከነሱ የምታገኘው ነገር አለ ማለት ነው?”

የስላቅ ሳቅ ሳቀብኝና አተኩሮ ካየኝ በኋላ “ከነሱ የምታገኘው
ነገርማ ከሌሎቹ ይልቅ የተሻለ ነገር ነው፡፡ አንድ ሰው በድህነት
ወድቆ ሲማቅቅ አንተ የተረፈህ ቱጃር ሆነህ በአጠገቡ ስታልፍ
እያየኸው ዝም ብለህ አታልፍም፡፡ ከህሊና ወቀሳ ለመዳን ስትል
ያለህን ትለግሳለህ፡፡ የህሊና ወቀሳው አያስቀምጥህማ፡”

እኔ ስስጥ ከህሊና ወቃሳ ለማምለጥ ብዬ አይደለም በእርግጥ በመስጠት የማገኘው እርካታ ይበልጣል አልኩት፡፡”
በትዝብት አመለካከት ተመለከተኝና “ዶክተር አሁንም ዋሸኸኝ፡፡”አለ።
ጉሮሮውን ሲጠርግ
እንደገና አስተዋልኩት፡፡
“ሃይማኖት አለህ?”
“አዎን!”
እርግጠኛ ነኝ የምታመልከው ...” አላስጨረስኩትም፡፡
“ልትል የፈለከው ገብቶኛል፡፡ የምታምነው ቅድስና ለማግኘት ነው እንጂ ለአምላክ ፍቅር ብቻ ሊሆን ኣይችልም
ልትለኝ ነው አይደል?
“አሁን እንደመሰለህ ውሰደው፡፡”
አነጋገሩ ደከም ያለ መሰለኝና አዘንኩለት። ላቡ በሶስት
መንታ ሲንቆረቆር “ተካልኝ
ፀሐይ ላይ ስለሆንክ አላስጨረሰኝም፡፡
“ፀሐይ ላይም ቁጭ ብዬ ይበርደኛል፡፡ ፍርሀት፣ ባዶነት፣
ብቸኝነት፣ ፍቅር የእነዚህ ሁሉ እጦት ፈሪ አድርጎኛል። ፍርኻት
ያጠመዳት ነፍስ ደግሞ ይበርዳታል።”
“ለምንስ ትፈራለህ? ለምንስ ብቸኝነት ያጠቃኸል?”
አልኩት፡፡
“የፍርሃቴን መነሻዎች ነገርኩህ እኮ። በዚያ ላይ ዓለም
የምትፈልገው ልውውጥ ነው፡፡ የልውውጥ ኑሮ ሰለቸኝ። ስለዚህ
ደግሞ ባዶነት ይሰማኛል፡፡ የሚገርመኝ እኮ ተፈጥሮም ያው ናት፡፡
እሷ ለአንተ ተፈጥሮዋን ስትለግስ አንተ ደግሞ ላብህ ጠብ እስኪል
ጉልበትህን ትገብርላታለህ፡፡ ከእርሷ ወዴት ይሸሻል? ሙታንንም
ኣትለቃቸውም የምትቀበላቸው ነገር
አለ፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ተፈጥሮ ብቸኛ ፍቅር ላጋሽ ማን ነው?”

አሁን አይኑን ማፍጠጥ ጥርሱን ማግጠጥ የጀመረ መሰለኝ፡፡ በዝምታ ላዳምጠው ፈለግሁ። ተካልኝ ግን ጥያቄዎችን በመኻል ስለሚሰነዝር ከማውራት አልዳንኩም፡፡ አሁንም ድመጹን ጮክ አድርጎ

“ለመሆኑ ሰው ምን ያህል እንደራበኝ ታውቃለህ?” አሁን በትክክል ተቆጥቷል፡፡ ከተቀመጠበት ተነስቶ አንዲት ተለቅ ያለች
የአፈር ጓል አነሳ፡ አፈሯን እንደጨበጠ፣

“ሰው፣ እውነተኛ ሰው! ሰውና በተፈጥሮ የማያላግጥ ፤ ሰውን ከልቡ የሚወድ። ምናልባት እንደ ዲዮጋን 'የሰው ያለህ!
እንዳልል እንኳ ተስፋ ቆርጫለሁ። ዲዮጋን ተስፋ ማድረጉ ውሸት ነበር፡፡ ውሽት! ሰው በሌለበት እንዴት ሰው ለማግኘት ጥረት
ይደረጋል?” የያዛትን አፈር አሻግሮ ፈጠፈጣት፡፡ የአፈሯ ጓል ተበታትና ዱቄት ሆነች። የተፈረካከሰችውን አፈር እያየ፣
“አየህ እኛ እንደዚች አፈር ነን፡፡ አፈሯ በአየሩ ላይ ተንሳፋ የቆየችበትን ያክል እድሜ ሳንኖር እልፍ የምንል፡፡ ግን ለዚሁም እድሜያችን ለራሳችን ብቻ የምንኖር! የልውውጥ ፍቅር
👍31
የምንወድ በፍቅር ስም የምናሾፍ! እህ!” ድንገተኛው የራሱ ትንፋሽ ንግግሩን ገታውና- ጎንበስ ብሎ ድንጋይ አነሳ የመጨረሻዋ ውርወራ ለኔ እንዳትሆን ፈርቻለሁ፡፡ ወዲያው የስንብት ሰላምታ ሳይሰጠኝ ወደ
መጣበት ሲመለስ በድንጋጤ አየሁት። በእርገጥም ታሟል። አዘንኩለት።
ተካልኝ እንዳለው ዓለም የልውውጥ ናት። ልውውጥ ከሌለ ዓለም የለም፡፡ ይህ የሕይወት እውነት ነው፡፡ ግን! ለምን ትክክል ነህ አላልኩትም? ቆጨኝ፡፡

💫አለቀ💫
👍2
#ደዌ

ስፍራ እንደምንሰጥ
ለሰውነታችነሸ
እንደምንሳሳ
ከላይ ለቆዳችን
እንደምንለፋው ውበት ለመጠበቅ
ለአዕምሮም ቦታ እንስጠጥ
እንከባከበው
መርዘኛ አስተሳሰብ ደዌ እንዳይበክለው።

🔘ሰላም ዘውዴ🔘