አትሮኖስ
286K subscribers
122 photos
3 videos
41 files
578 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ልውውጥ


#በእየሩስአሌም_ነጋ

በአስፋልቱ ግራና ቀኝ ያሉ ዛፎች የፀሐይዋን ሙቀት ለማብረድ በሚነፍሰው ነፋስ እየተቃኙ በእንቅስቃሴ ሲያዜሙ ስዓታት የቆሙ ካህናትን ይመስላሉ። የተንጣለለው ስፊ የእርሻ
መሬት በአትኩሮት ሲመለከቱት ነፍስን በሐሴት ያፍነከንካል፡፡

ተፈጥሮን ሳደንቅ ውዬ ባድር አይሰለቸኝም፡፡ ለወትሮው ቤቴ ደርሼ መኪናዬን ካቆምኩ በኋላ ነበር ወጣ ብዬ በዚህ መንገድ ብቻዬን የምጓዘው፡፡ በዚያን እለት ግን ከቤቴም አላዳርስ አለኝ፡፡
መኪናዬን ወደ ዳር አቆምኳትና የለበስኩትን ሹራብ በወገቤ ዙሪያ
አገልድሜ መልካም አየሩን እየሳብኩ ወደ ዛፎች ጥላ አመራሁ፡፡ አልፎ አልፎ ከሚታዩ ሰዎች በስተቀር በአካባቢው ሰው በብዛት ሲንቀሳቀስ አይታይም፡፡ ምናልባት ዐይንን ወርወር ቢያደርጉ እረኛ
የሌላቸው ከብቶችን በተንጣለለው መስክ ላይ ማየት ይቻላል፡፡

ከፊት ለፊቴ በማሳው መሐል የተዘረጋች ቀጭን መንገድ ትታያለች፡፡ በዚህች ቀጭን መንገድ እኔ ወዳለሁበት የመኪና
መንገድ ቁልቁል የሚወርድ ሰው ታየኝ፡፡ ወደታች እየመጣ እንደገና ተመልሶ ወደ ላይ ሲወጣ ስመለከት ነው፡፡በሚያደርገው ተደጋጋሚ እንቅስቃሴ ግራ ተጋባሁ፡፡ በግምት አስር እርምጃ የሚሆን ወደ ፊት ተራምዶ እንደገና ይመለሳል፡፡
ለጥቂት ደቂቃዎች ይህንን ድርጊት ሲደጋግም ዓይኔን ሳልነቅል ተከታተልኩት፡፡ መቼም ጤነኛ ሰው ይህን ያህል ምልልስ ሊያደርግ አይችልም ብዬ አስብኩ ምልልሱን አቁሞ እኔ ወዳለሁበት ሲመጣ ፍርሃትና ግርምት በተቀላቀለበት ስሜት አየሁት፡፡ በአንድ እጁ ሌዘር ኮት በትከሻው አንጠልጥሎ፣ በሌላኛው-
እጁ ያለቀች ሲጋራ ይዟል፡፡ የለበሰው ጥቁር ሽሚዝ አዝራሮች ያለቦታቸው ተሰካክተዉ ፣ ኮሌታው ተዛንፏል።

የሚናገረው ባይሰማኝም አንዳች ነገር እንደ ሚናገር የከንፈሩ እንቅስቃሴ ያስታውቃል፡፡ እኔ ከተቀመጥኩበት ትይዩ ጀርባውን ሰጥቶኝ ተቀምጦ ወደ አንድ አቅጣጫ አተኩሮ አየ። እንደገና
ከተቀመጠበት ተነስቶ ወደኔ ዞሮና ከወገቡ አጎንብሶ አንዳች ነገር ፈለገ
በፊት የጣላትን ሲጋራ አንስቶ ከተመለከታት በኋላ የቀረችውን ድጋሚ ለኮሰና እስኪበቃው ስቦ ወደኔ አቅጣጫ ወረወረው እኔ ወደቆምኩበት በቀስታ ሲጠጋ እንቅስቃሴውን መቃኘት አላቆምኩም፡ በግንባሩና በጉንጩ ላይ የተሰመሩ ጠባሳዎች ይታያሉ፤ ቁጭ ብዬ ስላየሁትም ይሁን እንጂ ስውየው እጅግ ገዝፎ ታየኝ፡፡ የሱሪው ቀበቶ በቦርጩ ተደብቋል። የቆዳው ቅላትና ወዝ
በምቾት ይኖር እንደነበር ጠቆመኝ፡፡ ድንገት ዐይኖቹን ዐይኖቼ ላይ
አሳረፋቸው፡፡ የዐይኑ ሽፋሽፍት የመርገብገብ ስራውን የቀነስና
በቁጣ የሚያይ ይመስላል፡፡

ዐይኔን ከእርሱ ላይ ነቅዬ ወደ መኪናዬ ለመግባት ስራመድ ረጅምና ግዙፍ ጥላው ሲከተለኝ አየሁና እጆቹን በአንገ ቴ ዙሪያ ሊያኖራቸው መስሎኝ ሽምቅቅ ብዬ ጭብጦ እንዳከልኩ ቀስ ብዬ ዞሬ
አየሁት። ፈገግ ለማለት ሙከራ ያደረገ ይመስላል። እኔም ግራ ገብቶኝ
ፈገግ፣ ኮስተር፣ ደግሞ ፊቴን ፈታ እያደረግሁ ተመለከትኩት፡፡ ባፈጠጠ ዐይኑ ወደታች ቁመናዬን ገረፍ አድርጎ
ቃኘኝና ዝም አለ፡፡ ወደመኪናዬ ልገባ አንድ እግሬን ሳነሳ፣

“ሃይ ዶክተር!” አለኝ፡፡ በድንጋጤ የሰላምታውን አጸፋ መለስኩና፣
“ይቅርታ እንተዋወቃለን?” አልኩት፡፡

“አንተ እንኳን አታውቀኝም፡፡ ነገር ግን አንድ ቀን በቤታችሁ በር ላይ ስናልፍ ባለቤትህን ከውጪ በር ላይ አገኘናትና ወደቤት ገብተን ቡና እንድንጠጣ
ጋበዘችን፡፡እናቴ እንኳን ፈቃደኛ አልነበረችም

ለምን?”
“አለ አይደል...እ... ልጄ አብዷል ብላ ስለምታስብ..." አለና ምላሽ እንድሰጠው ይሁን አይሁን አልገባኝም ዝም ብሎ
ተመለከተኝ፡፡ የምመልስለት ግራ ቢገባኝም አሰብ አደረኩና “ታዲያ
እኔ በቤት ውስጥ ነበርኩኝ...እ የዚያን እለት ...እ...ከዚህ በፊት አይቼህ የማውቅ አልመሰለኝም?”
“በቤት ውስጥ እንኳን አልነበርክም፡፡ ግን ፎቶዎችህን እንዴት ግሩም አድርጌ አይቼያቸዋለሁ መሰለህ! በተለይ በዚህ
በለበስከው ኮት የተነሳኸው ፎቶ ፓ! እንዴት እንደሚያምር!"
“አንድ ቀን ያውም በፎቶ አይተኸኝ አለመርሳትህ ይገርማል!"
“ታዲያ አሁን እንዴት እብድ ልባል እችላለሁ?
አይገርምህም? እየሰማኋቸው 'የጽጌ ልጅ አብዶ መጣ! ይላሉ።
ምነው የሀገሬ ሰው እፍረቱንና ይሉኝታውን ወዴት አደረሰው? እ?
ንገረኝ! ወዴት አደረሰው?” በንዴት እየተወራጨ እጁን ወደኋላው
ሰደድ ሲያደርግ ልቤ በጉሮሮዬ የተሸነቀረች ይመስል ትንፋሽ
አጠረኝ እንደምንም ለመረጋጋት ሞከርኩና “እ...ግዴለም
እንዳልሰማህ ማለፍ ነው” አልኩት፡፡
“እንዴት እንዳልሰማ ይታለፋል? አየህ! እኔ የሀገሬ ሰው፣ መንደሬና ተስማሚ አየሩ ቢናፍቀኝ ሁሉንም ነገር ትቼ መጣሁ፡፡
ሰው ግን አልገባውም፡፡ የሚገርመው ነገር አንተን ማግኘት እንዴት እፈልግ እንደነበር…ተካልኝ እባላለሁ” ጨበጠኝ፡፡ እጄ በመዳፉ እቅፍ ውስጥ ሲገባ ጣቶቹ ተንቋቁ፡፡ ከዚያም በብስጭት እንደ መቁነጥነጥ ብሎ፣ ሰው ብቻውን ሲቀመጥ፣ ከራሱ ጋር ሲማከር እብድ ይባላል ወይኔ ተካልኝ!" አለ።

አፌን ለመናገር ከፍቻለሁ። ግን ቃል አልወጣኝም፡፡ እዚያው እንደቆመ አሻግሮ ወደ መንደሩ ተመለከተና

“መንደሬን እንዴት እወዳታለሁ መሰለህ አሁን ፊቱ ላይ ትንሽ ፈገግታ ብልጭ ሲል ታየኝ ።
“ስንት ግዜ ውጭ ሀገር ተቀመጥክ?” አልኩት፡፡
“ድፍን ሃያ አመት፡፡"
“ብዙ ቆይተኻል!”
“ምን ዋጋ አለው? ምንም አልሰራሁሰትም ፡፡ ታየዋለህ ያንን ቀይ ጥርያ ቆሮቆሮ ቤት ?"አለና ወደኔ ተመለከተ።በአወንታ መለስኩለት።

እናቴን ከዛ አላወጣኋትም።ድሮ አባቴ የሰራው ቤት ነው።ምንም ለውጥ አልተደረገበትም። ምንም!"
“እንግዲህ ምን ታደርገዋለህ? አንድ ግዜ ሆኗል።”
“አዎ! ምንም ላደርገው አልችልም! ምንም! ብዙዎች አሁን አንተ ያልከውን ነው የሚሉኝ፡፡ አባባሉ ተቀየረ እንጂ ያው
እንደነሱ!”
ዐይኖቹን ለመሸሽ ጥረት ባደርግም አላመለጥኩም፡፡
ዞርኩበት ዞሮ በኔ እይታ ፊት ለፊት ቆመና ወደኔ እየተጠጋ፣
“አንዴ ሆኗል! አንዴ ሆኗል! ለመሆኑ የሆነውን የመቀየር አሁንስ ጊዜ የለንም? የለንም ወይ?” ከፊት ለፊታችን ያለው ጋራ
አስፈሪ ድምጹን መልሶ አቀበለኝ፡፡ አምላክ የዛሬን እንዲያወጣኝ ደጋግሜ ተማጸንኩ፡፡
“ግን ለምን አበደ ይሉኛል? አሁን እኔ እብድ እመስላለሁ?"
የሚናገረው ሁሉ ያስጨንቀኝ ጀምሯል፡፡ ለጥቂት ደቂቃ ዝም አልኩ፡፡
“አሁን እኔ እብድ እመስላለሁ ወይ?”
“ኧረ አትመስልም፡፡ ምናልባት ቅድም እንዳልከው ብቻህን ስታወራ ያው እንደምታውቀው ብቻ ማውራት እብድ ያሰኛል።”
“እኔ ብቻ ነኝ ብቻዬን የማወራ? ድፍን የዓለም ህዝብ ብቻውን እያወራ እንደሚሄድ አታውቅም? አንተ ብቻህን
አታወራም? ቆይ አንተ እራስህ አሁን ለኔ ምን አይነት ስሜት ነው ያለህ? ሳትዋሽ ንገረኝ” አለኝ፡፡ ትንሽ ፈገግታ በፊቱ ላይ ብልጭ ያለ መሰለኝና እኔም ፈገግ ብዬ፣
“አንተን እብድ ነው የሚያስብል ምንም የተለየ ነገር አላየሁም” አልኩት፡፡
“ዋሽህ ዶክተር! ከውሸት ሁሉ የከፋው ደግሞ ምን አይነት ውሸት እንደሆነ ታውቃለህ?.. ራስን መዋሸት፡፡” አለና አሁንም አሻግሮ ማየት ጀመረ፡፡ ሁለተኛ በዚህ መንገድ ላለመምጣት በውስጤ
ማልኩ።
“አሁን ለምሳሌ ዋሸኸኝ አይደል?” አፈጠጠ፡፡
ፈራ ተባ እያልኩ፣
“በእርግጥ...” አልኩና ዝም አልኩ።
“በእርግጥ ምን?”
“እ..ብቻህን ስታወራ በማየቴ ትንሽ እንደመደንገጥ ብዬ ነበር፡፡ ግን ብቻ ማውራትህ ላንተ መልካም ከሆነ ጥሩ ነው። ግን በተቻለህ አቅም ከሰው ጋር ለመሆን ሞክር፡፡”
ለምን እንዲህ ብዬ እንደማወራ ግራ ገባኝ። የምናገረው አስቤበት ሳይሆን የሱ ስሜት
👍2