አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
576 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ያጠፋሁት_በዛ

የዘመኔን ጣርያ
እድሜዬን ላሰላ
ብደምር ብቀንስ
ባካፍል በበዛ
ካለማሁት ይልቅ
ያጠፋሁት በዛ።
#ይህች_አገር

በፀጋህ የባረካት ተቀደሺ ብለህ ያልካት
ይህች አገር !!
እንደ ባቢሎን እናዳትፈርስ
ፍሬዎቿ እንዳይደርቁባት
የባዘኑ በጐቿን እስኪ አንተው
ሰብስብላት
ጌታ ሆይ
ዝም አትበላት
ከማያልቀው ሰላም
በእጀጉ አብዝተህ ስጣት
አንድ መሆንን እንጂ
መከፋፈልን አርቅላት
ቀስትና ጦር ከሚይዙ
ጭካኔን ከሚያበዙ
የበግ ለምድ ከሚለብሱ
ከተኩላዎች ከልላት
አውሎ ነፋሱን ፀጥ አርግላት
የሰልፍ ሁካታን ገስጽላት
ምድርን በኃይልህ የፈጠርክ
ዓለምን በጥበብ የመሠረትክ
ሰማያትን በማስተዋል የዘረጋህ
ስለ ምሕረት የመጣህ
ጌታ ሆይ ዝም አትበላት
ይህች አገር !!
ቀኑ ያልደረሰ ምጥ ይዟታል
ጭንቀቷ በዝቶባታል
አምላክ ሆይ ተመልከታት
ከጥልቁ ሰላምህ ስጣት፡፡

🔘ሰላም ዘውዴ 🔘
#አትጠይቁኝ_በቃ

መቼ ማን እና እንዴት ከነማን ከወዴት
ጎጃም ነሽ ጎንደሬ ጉራጌ ወይ ትግራ
አማራ ኦሮሞ ከምባታ ሲዳም
ሐረር ነሽ ጂጂጋ ድሬ ወይ ወለጋ
አትከፋፍሉኝ በቃ በብሄር በጎሳ
ሚዛን አይደፋ ውሃም አያነሳ
ይህ አይነት ጥያቄ ምን ይሉት ብሂል ነው ?
ከየትነሽ ምንድን ነው
ከማንነሽ ምንድን ነው
በቃ አትጠይቁኝ መልስ ይቸግረኛል
ቃላቱ ሳይወጣ ካንደበቴ ሳይደርስ
ከጉሮሮዬ ላይ ስንቅር ይልብኛል
ውስጥ ውስጤን ያመኛል
አንጀቴን ቆፋፍሮ ያቆሳስለኛል
ልቤን ያደማኛል
ከሰው ደንብ አውጥቶ ትርጉም ያሳጣኛል
ከየትነሽ ምንድን ነው
ከማንነሽ ምንድን ነው
ከየትነሽ አትበሉኝ መልስ ይቸግረኛል
ምንም እንደሌለው ከሩቅ እንደመጣ ባዕድ ያደርገኛል
መቅኖ ያሳጣኛል
ከየትነሽ ?
አንድነትን ፈትሎ ፍቅር ካለበሰኝ
በፅናት ተጋድሎ ታሪክ ካወረሰኝ
በደሙ መሃተም ፅፎ ካስቀመጠኝ
በስስት ጠብቆ ለአደራ ከሰጠኝ
ከአትንኩኝ ንብረቱ ፅናት ምልክቱ
ከታላቅነቴ ከነፃነት ቤቴ
ከልበ ተራራ ሀውልትን ካነፀ አክሱምን ከስራ
ከጥበብ ጥልቅ ምንጭ ከጥንታዊ ማማ
ከታሪክ ማህደር ከስልጣኔ አርማ
ከኩሩ ማንነት ከማይነጥፍ እውነት
በህብር የታሰርኩ በአንድነት የከበርኩ
ከቃልኪዳን ምድር በመስዋዕትነት ጀግና የወለደኝ
ማነሽ አትበሉኝ በቃ #ኢትዮጵያዊት ነኝ፡፡

💚 💛 ❤️
#ፕ ! !

ያኔ እኔና አንተ ባልታሰበ ክስተት
ተገናኘንና ተያየን በድንገት
ያንተ ዐይን ከኔ ላይ የኔ ደግሞ ካንተ
ልቤ ከልብህ ጋር
ጨርቄን ማቄን ሳይል በባዶ ዘመተ
አጠፈ መረቡን አሳውን ለቀቀ
ባንተው ተሰደደ አንተኑ አጠመደ
ያኔ ስንገናኝ እንዲህ ነበር ውዴ
የእኔ አለም መውደዴ
ፐ!! የእነሱ አብሮነት እንከን የለሽ ጥምረት
ፍቅር የነገሰበት
ተብለን ነበረ
ዛሬ ያሁሉ አልፎ
ፍቅራችን ፈራርሶ ጠፍቶ መሠረቱ
ፐ ያሉን በሙሉ ፕ ብለው ዘበቱ፡፡

🔘ሰላም ዘውዴ🔘
እንኳን ለ 125ኛ ዓመት የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ።

#ኢትዮጵያ 💚 💛 ❤️
#ሚኒሊክ...💚 💛 ❤️

እንኳንስ...
ዘላለም ታሪክና ስምህ
የሚወደሰው ጎልቶ፣
ከጥቁር ሰማይ ስር
ሐውልትህ ይታያል
እንደ ወርቅ አብርቶ !!

🔘ሀብታሙ ወዳጅ🔘
👍1
#አድዋ

ዋ! ... ያቺ ዓድዋ
ዋ! ...
ዓድዋ ሩቋ፣
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ፣
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ።
ዓድዋ...
ባንቺ ብቻ ሕልውና፣
በትዝታሽ ብፅዕና፣
በመስዋዕት ክንድሽ ዜና፣
አበው ታደሙ እንደገና።
ዋ!
ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስቷ፣
የደም ትቢያ መቀነቷ።
በሞት ከባርነት ሥርየት፣
በደም በነፃነት ስለት፣
አበው የተሰውብሽ ለት።
ዓድዋ!
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ፣
የኢትዮጵያነት ምስክርዋ።
ዓድዋ
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ፣
ታድማ በመዘንበልዋ።
ዐፅምሽ በትንሳኤ ንፋስ፣
ደምሽ በነፃነት ሕዋስ።
ሲቀሰቀስ ትንሳኤዋ፣
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ፣
ብር ትር ሲል ጥሪዋ፣
ድው እልም ሲል ጋሻዋ፣
ሲያስተጋባ ከበሮዋ፣
ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ።
ያባ መቻል ያባ ዳኘው፣
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው፣
ያባ በለው በለው ሲለው፣
በለው በለው በለው በለው።
ዋ! ... ዓድዋ ...
ያንቺን ፅዋ ያንቺን አይጣል፣
ማስቻል ያለው አባ መቻል።
በዳኘው ልብ በአባ መላው፣
በገበየሁ በአባ ጎራው፣
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው፣
በለው ብሎ በለው በለው።
ዋ! ... ዓድዋ ...
ዓድዋ የትናንትናዋ፣
ይኸው ባንቺ ሕልውና፣
በትዝታሽ ብፅዕና፣
በመስዋዕት ክንድሽ ዝና፣
በነፃነት ቅርስሽ ዜና፣
አበው ተነሱ እንደገና።
ዋ! ... ያቺ ዓድዋ፣
ዓድዋ ሩቅዋ ፣
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ፣
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ።
ዓድዋ ...

🔘ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን🔘

💚 💛 ❤️
#ያንሰራራ_ነፍስ


#ክፍል_አንድ


#በእየሩስአሌም_ነጋ

ግን ለምን? ለምን ባሌ...እኔን ማሰብ ተሳነው? አሁን አሁን እስከመኖሬም ማወቁን እጠራጠራለሁ። ለስሙ አብረን ውለን እናድራለን፡፡ ለወገን ለዘመድ የሚተርፍ ፍቅር አለው፡፡ ለኔ ያልሆነበት ምክንያት ምንድነው? ምን አደረኩት? ልጆቼን ለማሳደግ ስል የሰው ደሃ እንደሆንኩ ያውቃል፡፡ የራሱን ፍላጎትና እርካታ በማዳመጥ ፈንታ የኔን ስሜት አንድ ቀን እንኳን አዳምጦልኝ
አያውቅም፡፡ ታዲያ እኔ ፍቅርን ብናፍቅ ማን ይፈርድብኛል? ማን ይከሰኛል?' ከራሷ ጋር እየተሟገተችና ሰው እንዳያያት ወደኋላዋ እየተገላመጠች ከቀጠሮው ቦታ ደረሰች፡፡
በጻፈላት መልዕክት መሰረት የተከራየበትን ሆቴል ለማግኘት ረዘም ያለ ጊዜ ወስዶባታል፡፡ በድካምና በፍርሃት የዛለ ሰውነቷን እየጎተተች የተከራየበት ሆቴል ስትደርስ እግሯ መንቀጥቀጥ ጀመረ።
ጆ ያረፈበትን ክፍል ስታይ ዛሬ የመጀመሪያ ቀኗ ነው፡፡ ስትገባ ጅቡቲያዊው ወጣት ሽርጡን እንዳሸረጠ
ከተቀመጠበት ምንጣፍ ላይ ተነሳ፡፡ “ኦ! ቢ ኦ! ቢ" እያለ ተጠጋት።
እሱ የሷን ፣ እሷ የሱን ስም መያዝ ስላልቻሉ ስማቸውን አሳጥረው በመጀመሪያው ፊደል ይጠራራሉ፡፡

ፍርሃት ያጠላበትን ፊቷን እንደምንም ደብቃ ፈገግ አለች፡፡እጆቹን በወገቧ ዙሪያ ጠምጥሞ አቀፋት። እንደገለባ ቀለላት፡፡
በእቅፏ የማይሞላ ደቃቃ ነገር ነው።
አጥንት እጆቹን ከላይዋ ላይ ሲያነሳ ተራ በተራ ቃኘቻቸው።በአካሉ ላይ ስጋ ያለው አይመስልም፡፡ በበለዘና በጠቆረ ቆዳ የተለበጠ እንጨት መሰላት፡፡ ከወገቡ በላይ እራቁቱን ነው።

ዐይኖቹን ስውነቷ ላይ እያንከባለለ በመጎምጀት አያት። ዛሬ እንደሌላው ሁሉ ቀን አልተሸፋፈነችም። የሰውነቷን ቅርጽ በውል ለይቶ የሚያሳይ ልብስ ለብሳለች። ፀጉሯንም ከተደበቀበት አውጥታ ነስንሳዋለች። ረጅም አንገቷንና ሰልካካ አፍንጫዋን ተራ በተራ ሳመና ጥርት ያለ ጠይም ቆዳዋን እየዳበስ ትላልቅ አይኖቿን በፍቅር ተመለከታቸው። “ኦ ቢ ቢዩቲፉል” አለ፡፡ በወገቧ ዙሪያ እጆቹን አቆላልፎ ቀጭን ወገቧን እየለካ።

ሹራብ፣ ሸሚዝ፣ ሱሪና ሌሎችም ልብሶች ተደበላልቀው በወንበር ላይ ተከምረዋል፡፡ አገልግሎታቸውን የጨረሱ የጁስ
ካርቶኖችና ቁርጥራጭ ቸኮሌቶች በአነስተኛ ጠረጴዛ ላይ ተበታትነዋል፡፡

ቢ እነዚህን ሁሉ ዝርክርኮች በተዝረከረከ መንፈሷ እየቃኘች ልትደብቀው ያልቻለችውን ፍርሐትና ድብርቷን ይዛ ከአልጋው ጫፍ ላይ ተቀመጠች፡፡
ጆ አጠገቧ ተቀመጠና ከንፈሮቿን እየተስገበገበ ጎረሳቸው፡፡
እፉ ውስጥ ያለው የጫት ድቃቂ ወደ አፏ ሲዘልቅ ምራቋን ልትተፋ ሞከረችና ይከፋዋል ብላ ስላሰበች በትግል እየተናነቃት ዋጠችው።

ከንፈሯን በማፈግፈግ ከከንፈሩ አላቃ ገፋ አደረገችው፡፡በአድናቆት ተመለከታት፡፡ “ኦ! ቢ ኦ! ቢ” ተመልሶ ወደ ከንፈሮቿ
ቀረበ።

በድጋሚ ገፋችውና “ኖ...እ... ዛሬ የመጣሁት ከአንተ ጋር ሻይ ለመጠጣት ነው እንጂ ለመቆየት አይደለም፡፡ አየህ መጀመሪያ መግባባት አለብን፡፡”

እጆቿን እያወራጨች ለማስረዳት ሞከረች፡፡ አልገባውም፡፡ትንሽ እንደመደናገር ብሎ፣
“አሌብን አለቢን?” አለና በመጨረሻ የተናገረችውን ቃል ደገመው፡፡ እንዳልገባው አወቀች፡፡ እንዴት እንደምታስረዳው ጨነቃት።

“ቺግር አለ? ቺግር አለ?” ካለ በኋላ ራሱን ነቀነቀና ወደ ኋላው አልጋ ላይ ተንጋለለ፡፡ አሻግራ ከፊት ለፊታቸው ያለውን ፎቅ
አየችና ሰዎች የሚመለከቷት ስለመሰላት ተነስታ መጋረጃውን ጋረደች፡፡

እዚያው መስኮቱ ጋር እንዳለች በእንግሊዝኛ በቀጣዩ ቀን እንደምትመጣ ነገረችው፡ በአዎንታ ራሱን ሲነቀንቅ ሀሳቧ የገባው መሰላት።

እተቀመጠችበት ትቷት ወደ መጸደጃ ቤት ገባ፡፡ የገላ መታጠቢያ ውሃ ሲለቀቅ አደመጠች፡፡ '
ተመስገን ሀሳቡን ቀይሯል፡፡ አለችና በፍርሐት የተሸማቀቀ ሰውነቷን ፈታ አደረገች፡፡

እየቆየች ስታስበው ለምን እንደመጣች ገረማት። ትናንት ጠዋት ገንዘብና ፍቅርን እለግስሻለሁ ነይ ብሎ በእንግሊዝኛ
በሞባይል መልእክት የጻፈላት ትዝ አላት፡፡ መልእክቱን የጻፈለት ሰው እንዳለ ተገንዝባለች፡፡ ምክንያቱም ከአረብኛና ከፈረንሳይኛ በስተቀር ለመግባቢያ የሚሆን ቋንቋ የለውም፡፡

ገንዘብና ፍቅር ባንድ ላይ የሚቸሩ ቁሶች ናቸው እንዴ?”እራሷን ጠየቀች፡፡ ግን ሁለቱንም ነገሮች ብትፈልጋቸውም
እንደፍቅር ግን የራባት ነገር የለም፡፡

የጆ ክፍል ምቾት የሚስጥ አይደለም፡፡ ሁለት ሻንጣዎች እዚህና እዚያ ወድቀዋል፡፡ የአልጋ ልብሱ መሬት ላይ ተዘርግቷል።እላዩ ላይ በአንድ ሳህን ላይ የተለነቀጠ ጎመን የሚመስል ነገር
ተቀምጧል። ምናልባት የታኘከ ጫት ይሆናል ብላ አሰበች፡፡

የክፍሉ ሽታ ከራሷ ሽቶ ጋር ተዳምሮ ውስጥን የሚያውክ ሽታ ፈጥሯል። “ጆ ትክክለኛ ፍቅር ይሰጠኛል?” ለሚለው ሀሳቧ እርግጠኛ አይደለችም፡፡
ግን በባሏ ተስፋ በቆረጠች አግኝታዋለች፡በተዋወቁበት ጥቂት ጊዜ ውስጥ እሷን ከማድነቅ የተቆጠበበት ደቂቃ አልነበረም፡፡

ከጆ የምትወድለት ነገር ቢኖር አድናቆቱን መግለጹና ለደቂቃ ከላይዋ ላይ የማይነሱ ዐይኖቹን ነው፡፡ ግን ፍቅር እንዳልያዛት
እርግጠኛ ነች፡፡የባሏን ቁመና አሰበች፡፡ ቆንጆ ነው! ቆንጆ! ታዲያ ምን ዋጋ
አለው? ግን ለምን ይሆን ስሜቴ የማይገባው? የምለብሰው፣
የምበላውና የምጠጣው፣ የማይገደው?”

“ቢ ካም! ቢ ካም!” አላት፡፡
በፍርሃት የመታጠቢያ ክፍሉን ከፍታ ጭንቅላቷን ወደ ውስጥ አስገብታ ተመለከተች፡፡ የተገመሱና የጠቆሩ ጥርሶቹን አሳያት፡፡ ደስ የሚልና ብሩህ ፈገግታ ከፊቱ ላይ አነበበች፡፡ እንደዚህ
አይነት አስደሳች ፈገግታ ከአስቀያሚ ጥርሶች መሐል ይፈጠራል ብላ አስባ አታውቅም፡፡

ካም! ካም!” አለና እጆቹን በገላው ላይ አሻሻቸው፡፡ ነይና እንታጠብ እንዳላት ገባትና ወደኋላ አፈግፍጋ ወደ ቀደመው ቦታ ተመልሳ ቁጭ አለች፡፡

ወጥታ ልትሄድ አሰኝቷት ወደ በሩ ተመለከተች፡፡ ምን ማድረግ እንዳለባት እርግጠኛ አልሆነችም፡፡

“ምን ፈልጌ መጣሁ?...f ለምን? ... ግን አይፈረድብኝም፡፡ በፍቅር ዐይኑ እያየ የሚንከባከበኝ እፈልጋለሁ፡፡ አምላኬ መጥፊያዬ ደረሰ ማለት ነው? እኔ አልቻልኩም፡፡ አንተ ከቻልክ ግን ከዚህ ብልግና አውጣኝ?” ፈጣሪዋን ተማጸነችዉ።

“እውነት ይሄ ሰው እውነተኛ ፍቅር ይለግሰኛል? እስቲ ለማንኛውም ልሞክረው፡፡ እኔ የምፈልገው ፍቅር ምን አይነት ነው? ግዚያዊ ፍላጎቱን የሚያረካብኝን ወንድ ወይስ...?”

ራሷ ለራሷ ጥያቄ ሆነች፡፡ ወደ ራሷ ድምዳሜ የደረሰች ሲመስላት ደግሞ፣ አሁን የኔን ነፍስ የሚያስጨንቃት ፍቅር
የማጣት ጉዳይ ነው ብላ ለሚጮኸው ውስጧ መለሰችለት።
እሰራልሀለሁ! እንዳስጠላሁህ እጠላሀለሁ!፡፡ አለቅህም! አሁን
በእርግጥ የምትለኝን ሆኛለሁ። እንኳን
ደስ ያለህ! ምንም የማላውቀዋን ጨዋ “አመንዝራ! ብለህ ትሰድበኝ ነበር፡፡
እግዚአብሔር ይይልህ፣ አመነዘርኩልህ... እንዴት አይነት ደካማ ሰው ነኝ!”

ግድግዳውን ቃኘች፤ ቀለሙ በያለበት ተፋፍቋል፡፡ በተፋቀው ቀለም ውስጥ ዝብርቅርቅ ስእሎች ታዩዋት፡፡ በስእሎቹ ውስጥ እርሷ አለች፡፡ ከባሏ ሊነጥላት የእርሷን ቀሚስ የሚጎትት ኮስማና ሰው
ታያት። አሁን በስስት እያየ የሚያደንቃት ትፈልጋለች። “እኔ አድናቆት ፈላጊ ሴት ሆኜ ነው? አይ ማንኛዋም ሴት ከማንም ወንድ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውን የተቃራኒ ጾታ እንክብካቤ ትወዳለች።
እኔ ብቻ አይደለሁም፡፡ ጆ ሲያየኝ ውሎ ሲያየኝ ሲያድር አይጠግብም፡፡ በርከት ላለ ግዜ ያደንቀኛል። ጥሩ ፍቅር ሊለግሰኝ ፍቃደኛ እንደሆነ ነግሮኛል። ምን ዋጋ አለው? በየትኛው ቋንቋችን
እንግባባ? የጭንቀት ትንፋሽ በረጅሙ
👍4
ተነፈሰች፡፡ የራሷ ትንፋሽ አቃጠላት።

የሽንት ቤቱ መቀመጫ ውሃ ሲለቀቅ አጠገቧ እንደሚመጣ እርግጠኛ ሆነች፡፡ ጆ እርቃነ ስጋውን እያሳየ ህፍረተ ስጋውን እንደ ጦር ወድሮ መጣ፡፡ ስታየው ጩሂ ጩሂ አሰኛት፡፡ “ አምላኬ ምን እንደምሰራ በእርግጥ አልገባኝም፡፡ አሁን ምናልባት ወደሞት መንገድ ጉዞ ሳልጀምር አልቀረሁም፡፡ በባል መጠላትና መገፋት ለምን ለኃጢአት ይዳርጋል? አቤቱ ይቅር በለኝ፡፡ የማረገውን የማውቅ አይመስለኝም፡፡ ጨዋነቴ የታለ? ታማኝነቴን ምን ዋጠው? እድሜ ላንተ! ልጆቼን ላሳድግ ብዬ ከሰውነት ተራ መውጣቴ ያስንቃል? ያስነውራል? ህሊና ቢስ ያደርጋል?”

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
👍1
#ርእስ_አልባ

የፍቅራችን ብሎን
በልፊያችን ላልቶ በሰው ከታሰረ
የቤታችን ሳሎን
በጎረቤት አይጥ ከተሰረሰረ
በኩርፊያችን ማግስት
ጓደኛ፣ ቤተሰብ፣ ዘመድ ቤት ከነቃን
ያንድ ቤትሽ ንግስት
ያንድ ቤቴ ንጉስ ለመሆን ካልበቃን
ልብቃሽ፣ ብቂኝ፣ በቃን፡፡
#ለብርሃኖች

አንተ ጧፍ ነኝ ብለኸኝ
አምኜኽ
እኔ መቅረዝ ነኝ ብዬህ
አቅፌኽ
“ጽልመት ጉድ ፈላበት ዛሬ!”
በማለት እኔ ፎክሬ
አብረኽኝ ሽልለህ አንተም
«የብርሃን ብቸኛ ምንጭ›
መሰኘትን በማለም
ከኖርንበት ጥጋጥግ
ከከረምንበት የጎጆ ዓለም
ብንወጣ ተንደርድረን
ያልጠበቅነው ትይንት ቆየን
አገር ሁሉ ፀሐይ ኾኖ
እየሣቀ ቁልቁል ዐየን፡፡
#ያንሰራራ_ነፍስ


#ክፍል_ሁለት(የመጨረሻ ክፍል)


#በእየሩስአሌም_ነጋ

ጆ በሐሳብ እርቃ የሄደችውን ቢ በዐይኗ የሞላውን እንባ አይቶ በርከክ አለና አገጯን ይዞ እየተመለከታት፡፡ “ቺግር አለ?” አለ።

“ችግር አለ” የሚለውን ቋንቋ ብቻ እንዴት እንደለመደው ደንቋታል። “ምናለ አማርኛ ቢስማና የልቤን በነገርኩት፡፡ ይሄኔ
አውቄ የምባልግ፣ በኃጢአት የወደኩ፣ አዳፋ አድርጎ ያየኝ ይሆናል፡፡
ምክንያቱም ባልና ልጆች እንዳሉኝ ነግሬዋለሁ። እሱንም ባስተርጓሚ።

ምን እንደምትፈልግ ግራ የገባው ይመስላል። ገፋ አድርጎ ወደ አልጋው አንጋለላት፤ እንደተኛች መላ አካሉን አየችው፡፡

ሀፍረተ ስጋው ከመላው አካሉ የሚበልጥ መሰላት። ደግሞ ከወደ ጫፉ ለምጽ የያዘዘው ይመስል ነጽቷል። ቀፈፋት፡፡ ዳበሳት፡፡ ዝም አለችው፡፡ እጇን ይዞ አካሉን እንድትዳብስለት በእጁ አስነካት።
እሷ ግን በተቃውሞ ወደ ነበረበት ቦት መለሰችው፡፡

ቀስ እያለ እላይዋ ላይ የተጋደመው ጆ አንዳች ኃይል የተመላ ይመስል ከብዶ ነፍስና ስጋዋን የሚለያይባት መሰላት፡፡
ያንን ሩህሩህና ኩሩ ባሏን በዐይነ ህሊናዋ አየችው። ሰፊና ግዙፍ ትከሻ ቢኖረውም ይህን ያክል አይከብዳትም፡ታከብረዋለች፣
ትወደዋለች ከሱ ሌላ ምንም አትፈልግም ነበር፡፡ እሱ ግን አንደ አንድ ግኡዝ ነገር መገልገያ አድርጓታል። እሱ ለብዙ ሰዎች ጉርስና ልብስ ነው፡፡ እሷ ግን በእርዛትና በጥማት ብትንገላታ ግድ የለውም፡፡

እኔ ገንዘብ ከሰው መጠበቅ የለብኝም፡፡ ምክንያቱም የመስራት አቅምና ችሎታ አለኝ፡፡ ስራ መስራት አለብኝ፡፡ ግፋ ቢል
ባሌን ላጣው እችላለሁ፡፡ ለገንዘብና ለፍቅር አሳልፌ ጨዋነቴን ልለውጠው አልፈልግም።ከነፍስና ስጋዋ ጋር ተሟገተች። ወዲያው ደግሞ ግን ደግሞ አይዞሽ እያለ የጎደለኝን እየፈለገ ሲከፋኝ እያባበለ ስሜቴን የሚያዳምጥ ወንድ እፈልጋለሁ፡፡ እኔ ለባሌ የማደርገውን
እሱም ለኔ ሊያደርግ ግድ ነው፡፡ አለበለዚያ ግን... አለች በትግሉ
መካከል እየተወራጨች።

ጆ ከንፈሯን የማላመጥ ያህል በአፉ ውስጥ ከቶ እያልመጠመጠ ነው። “ለምንድነው ከንፈሬን እንዲህ አድርጎ
የሚበላኝ?” አፏን ደም ደም አላት።

ከደረቱ ቀና ብሎ የለተቱና ከማስያዢያቸው ያመለጡ
ጡቶቿን ሊይዝ እጁን ሲስድ የጡት ማስያዢያ ስፖንጆች ውስጥ እጁ እያዋለለ የከሰሉ ደቃቃ ከንፈሮቹን አሞጥሙጦ ሊስማቸው ገሰገሰ፡፡

እጁን ከጡቷ ላይ መንጭቃ አወጣችው። መልሶ አስገባ፡፡ ይሄኔ እኮ ያጎጠጎጠ መስሎት ይሆናል፡፡ እንደ ለተተ ማን
በነገረው፡፡ ኮስተር ብላ እንደቀድሞ አፈጠጠች፡፡

“ቺግር አለ?” አለና በሚያሳዝንና በሚያባብል ዐይኑ አያት፡፡
“ችግር የለም!” አለች፡፡ እያቃተተች፡፡
“ኦ! ቢ ኦ! ቢ አይ ላቭ ዩ ሶ ማች፡፡” አለና ከላይዋ ላይ ተስፈንጥሮ ተነሳቶ አጠገቡ የተቀመጠች አነስተኛ እቃ ማስቀመጫ
ስር አጎነበሰ፡፡ ሰውነቱን ድጋሚ ተመለከተችው፡፡ ትንሽ፣ ደቃቃ
እራቁቱን ቁጢጥ ብሎ ብይ የሚጫወት መሰላት፡፡ እጆቹን ወደ ውስጥ ልኮ አንድ ነገር መዞ አወጣና ወደርሷ አመለከታት፡፡
የሚያመለክታትን ነገር አየችው። አውጥቶ አሳያትና አቀበላት፡፡ ተቀብላ አየችው፡፡ ኮንደም ነው፡፡

“እኔ ለዛሬ ዝግጁ አይደለሁም፡፡ በኮንደም እንጠቀም ማለትህ ጥሩ ነው” አለችው፡፡
“ቺግር አለ?” አላት፡፡
ችግር ያምጣብህ! ችግር አለ ከማለት በስተቀር የሚያቀው ንግግር የለም፡፡ አመዳም! አለች በውስጧ፡
ተነስቶ መሄድ እንደሚያዋጣት ገባትና ከመቀመጫዋ ስትነሳ በማባበል እያየ አስቀመጣትና ስልክ ደወለ፡፡

ሁለቱም በራሳቸው ሐሳብ ሲባዝኑ ከቆዩ በኋላ በር ተንኳኳ፡፡ ጆ ሽርጡን አገልድሞ ከፈተና በፈረንሳይኛ ድምጹን ከፍ
አድርጎ አንድ መልእክት አስተላለፈ።

አዲሱ ሰውዬ ወደ እርሷ እየተመለከተ፣
“ሀሳብሽ ምን እንደሆነ ማወቅ ይፈልጋል። ምክንያቱም እርሱ በጣም ይወድሻል። ልትረጂው ይገባል እኔ አብሬው የምሰራ
ጓደኛው ነኝ፡፡ ላንቺ ሲል እንግሊዘኛና አማርኛ ሊማር ዝግጅት ላይ ነው፡፡ ለብልግና ወይም ለጊዜያዊ ስሜት የሚፈልግሽ እንዳልሆነ ልትረጂ ይገባል።” አላት፡፡

ተመልሳ ተቀመጠች። ጆ አሁንም ፈገግ ለማለት ሞክሮ አስቀያሚ ጥርሶቹን አሳያት። አንዳች ነገር እንድትናገር በጥያቄ አስተያየት እያዩዋት ነው።
የመጣው ሰው ንግግሩን ቀጠለ፡፡

“በእርግጥ ምንም ባለመነጋገራችሁ ብዙ ነገሮች ላያግባቧችሁ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ለጊዜው ፍቅር ሊያግባባችሁ ይችላል፡፡ ወደፊት ግን በሚያደርገው ብርቱ ጥረት ቋንቋዉን ሊያዳብርና ልትግባቡ
ትችላላችሁ” አላት፡፡

ዛሬ እንደምትቸኩልና ለሌላ ጊዜ በረጅም ሰዓት በሰፊው እንደምታጫውተው ነገረችው። ጆ አስተርጓሚ ጓደኛውን
ቀና ብሎ አይቶ አመስግኖ ሸኘውና አጠገቧ ቁጭ ብሎ ጀርባዋን
እየደባበሰ በፍቅር ተመለከታት።

ቢ አሁን ከቅድሙ ፍርሃቷ እየለቀቃት ሲሄድ ተሰማት፡፡ ፈገግታውን አሳያትና ሽርጡን ከላዩ ላይ ወደ መሬት ጣለው::
ቅድም ካየችው የተለየ ነገር የለም፡፡
ጭንቀቷን ለመርሳት ስትሞክር የፍትወት ፍላጎት በመላ ሰውነቷ የናኘ መሰላት። እጆቿን እሱ እንደፈለገው በገላው
ልታዟዙር ሞከረች።

ጆ አንዴ ከንፈሯን ስሞ ከፊት ለፊቷ ቁጭ አለ፡፡ ልትዳራ ፈልጋ የውጭው ጨለማ እየጠነከረ ሲመጣ ቤቷን አሰበች። ይህኔ
ባሏ ከንፈሩን ጥሎና አገጩን አስረዝሞ ይጠብቃታል፡፡ ልጆቿ በተቀመጡበት ያንጎላጃሉ። በፍጥነት ተነሳች፡፡ ጆ ዘሎ እጁን ሲይዛት የሚያስገድዳት መሰላት፡፡ አንስታ በመስኮት ልትወረውረው እንደምትችል፣ ጠንካራ እንደሆነች፣ እንኳን ይህን ኮስማና ቀርቶ በትግል
እንደማያሸንፋት ታውቃለች።

ጆ ከተዝረከረኩ እቃዎቹ መኸከል ሱሪውን ስቦ ከኪሱ በርከት ያሉ አረንጓዴ ብሮች አውጥቶ ሰጣት። ቢ በፈገግታ ያለ
አንዳች መግደርደር ተቀበለችውና ከእጁ አፈትልካ ወደበሩ አመራች፡፡
ቺግር አለ?” አላት።
ችግር ያጣድፍህ!' አለች በውስጧ፡፡ ወደ ውጭ ወጥታ በሩን በላዩ ላይ ዘጋችው:: የሰጣትን ብር ጨምድዳ ቦርሳዋ ውስጥ
ከተተች፡፡

“ደግሜ እመጣ ይሆን ጌታ ሆይ? እኔ ለመምጣት እፈልጋለሁ። አንተ ግን ኃጢአት እንዳልሰራ እርዳኝ፡፡

ዞራ ተመለከተች፡፡ ከፊል እርቃኑን ከክፍሉ ውስጥ አውጥቶ ይመለከታታል። ቅን የሚያስመስሉትን ዐይኖቹን አይታ እጇን
አርገበገበችለት፡፡ ሙሉ በሙሉ ወጥቶ ተመለከታት።

ፈገግታ ከፊቱ አልጠፋም፡፡ “ምስኪን!” አለችና አካባቢዋን ሳትቃኝ እንዳቀረቀረች አጎንብሳ ወጣች፡፡

አምላኬ ሌብነት እንዴት ያሳቅቃል? ምንድን ነው የማደርገው? ኦ ጌታ ሆይ! አንተ ምን እንደማደርግ ታውቃለህ? ምን
እንደሆንኩም ጭምር፡፡ አሁን ኃጢአት እያደረግሁ ነው ማለት ነው? ግን ማንን ነው የምጎዳው? ማንንስ ነው የምጠቅመው? ይሄ በእጄ
ጨምቄ የያዝኩት ብር የኃጢአት ገንዘብ ነው?”

ቀስ በቀስ ወደ ራሷ ተመለሰች። “አይሆንም እኔ ጨዋ ነኝ፡፡ አሁን ያደረግሁትን ሁሉ አላደረግሁም፡፡ በፍጹም! ይሄም ገንዘብ የኔ አይደለም! ጆም ቢሆን ከንፈሬን አልሳመም! ጆንን አላውቀውም፡፡ የማንንም እርቃነ ስጋ ተመልክቼ አላውቅም፤ ከባሌ በስተቀር፡፡”

ከደቂቃዎች በፊት የሰራችውን እውነት ሽምጥጥ አድርጋ ክዳ፣ በሩጫ ወደ ጆ ክፍል ደርሳ በሩን ስትገፋው ተከፈተ፡፡
ጆ አልጋው ላይ ተኝቶ ያቃስታል። ይህን የሚያቃስት ሰው አታውቀውም። ከሔደች በኋላም እንደሚያስቃስተው
አልገባትም፡፡ ግን የእርሱ ገንዘብ በእጇ አለ። ብሮቹን አልጋው ላይ በተነቻቸው፡፡
ጆ በድንጋጤ ከተንጋለለበት ተነስቶ ብሮቹን አያቸው ሐሳቧን እንደቀየረች ገባው፡፡ የተበተነውን ብር ከላዩ ላይ አራግፎ ወደ በሩ እሮጠ፡ የለችም፡፡
ተመልሶ በመስኮቱ በኩል ወደ ውጭ ሲመለከት
👍41🔥1
የሆቴሉ መውጫ ላይ በኩራት ትራመዳለች። ድምጹን ጮክ አድርጎ ተጣራ።
“ቢ! ቢ! ቺጊር አለ?” ድምጹ በአየሩ ውስጥ ተበትኖ ቀረ።

💫አለቀ💫
#እንዲህ_ነው

ሥራ አጡ በርክቶ
ሙስና አንሰራፍቶ
ቅጥ ስርዓት ጠፍቶ
ኑሮ ጣሪያ ነክቶ
በጠኔ ጠንዝቶ
ሕዝብ እየታመስ
ጥርስ እየነከሰ
ብሶት የወለደው
እንባ እያፈሰሰ
በዋይታ ተከቦ
ሳይጠፋ ተርቦ
ካንዱ ቤት ተክቦ
በስም ሀይበርኔሽን
በባዶ ኢንፎርሜሽን
በተስፋ ተመልቶ
ይኖራል ወገኔ
መጪውን አስቦ
ችግሩን ስብስቦ፡፡

🔘ሰላም ዘውዴ🔘
👍1
#ፈላጊና_ተፈላጊ

አንተ በዛኛው አፅናፍ
እኔ በዚህኛው ጠረፍ
አምሳያችንን ፍለጋ
ስንወርድ ስንወጣ
ስንባዝን ስንደክም
ሜዳ ገደሉን ስንቧጥጥ
ጫካ በረሀውን ስናቋርጥ
ከላይ ታች ስንዘክር
በዕድላችን ስናማርር
መንታ መንገድ ላይ ቆመን
ስንተላለፍ ተያየን
ፈላጊና ተፈላጊ ዛሬም ዳግም ተለያየን፡፡

🔘ሰላም ዘውዴ🔘
👍1
#ሸክም


#ክፍል_አንድ


#በእየሩስአሌም_ነጋ

“እናንተው ሰው የተፈጠረበትን ቀየ ትቶ ወዴት ይሰደዳል?” አለች ድምጿን አውጥታ ውስጥ ውስጧ የሚብላላውን ነገር ስታስታምም ቆይታ ልታጥብ ላወጣችው እንስራ ከቂጡ ስር የሳር
ጉዝጓዝ እያደረገችለት፡፡

አይኖቿን አጥብባ በርቀት እያየች አሰበች። ዛሬ ልንገራት?..ልንገራትና ምን እንደምትል ልስማ? እስከመቼ
እደብቀዋለሁ በዚያ ላይ ሰውየው እኔን ብቻ ሳይሆን የሰፈሩን ሴት ሁሉ ለማማገጥ ቆርጦ የተነሳ ነው የሚመስል...ወይ ልንገራትና የመጣው ይምጣ!” አጎንብሳ ማጠብ ጀመረች። ወዲያው ከነገረቻት በኋላ ልትል የምትችለውን አሰበች፡፡

“አይ እንዲህማ አይሆንም አንቺ ባልሽ የሞተ እንደሁ እኔም ባሌን ማጣት አለብኝ? እኔ እንደሆን ባሌን አምነዋለሁ፤ አንድ ማስረጃ ሳላገኝ ባሌን ልኮንን አልችልም' ትለኛለች ይቅርብኝ፡፡በእንስራ ውስጥ የከተተችውን ውሃና የግራዋ ቅጠል ደህና አድርጋ ስትደፍቀው አረፋው ተኩረፈረፈ፡፡ ወዲያው ከአንዳች ነገር ጋር
ትግል ስትገጥም የቆየች ይመስል በረጅሙ ተንፍሳ የምታጥበው እንስራ አጠገብ ተቀመጠችና በስንጥር ጥርሷን እየጎረጎረች ማሰብ ቀጠለች።
ከጎረቤቷ ከሸክም ጋራ ጥሩ ጓደኛሞች ናቸው፡፡ ሳይተያዩ። ውለው አያድሩም አሁን ግን የሸክም ባል እሷን ለማባለግ
በሚያደርገው ሙከራ በሀሳብ መብከንከን ከያዘች ዋል አደር አለች፡፡

ብዙ ጊዜ ውሃ ልትቀዳ ወደ ምንጭ ስትወርድ እየተከታተለ ጎነታትሏታል አመናጭቃ ገስጻዋለች። ቁጣዋ
ግን የገባው አይመስልም፡፡ በተደጋጋሚ ወደ ቤቷ ለመግባት ሙከራ ሲያደርግ
በር ዘግታ አባራዋለች። ጥሩሰው በር ላይ ብዙ ግዜ የታየው የሸክም ባል ጥሩሰውን በመንደሩ ሰው ጥርስ ውስጥ አድርጓታል ከሸክም ጋር ያላት ጥብቅ ፍቅር ደግም ይሄንን ለማስረዳት ድፍረት አልሰጣትም፡፡

ሐሳቧን ትሸሽው ይመስል የምታጥበውን እንስራ ትታ ከበረት ገብታ የተፈነቃቀሉ ድንጋዮችን ስታስተካክል ቆየች፡፡ የሸክም
ባለቤት እንደተለመደው ለጭቅጨቃ በር ድረስ መጥቷል። ሚስቱ ጥሩሰውን እየተጣራች ወደ ቤት ስትቀርብ ጥሩ ስው ከበረት መሆኗን አጢኖ በድንጋጤ ወደጥሩ ሰው ቤት ሰተት ብሎ ገባ፡፡
ሸክም እየቀረበች ስትመጣ ደመነፍሱን የጠላ እንስራዎች ወደሚቀመጡበት አነስተኛ ጨለማ ክፍል ውስጥ ከጋንና
ከእንስራዎች መኸከል ተዳበለ።

ሸክም በር ላይ ቆማ ስትጠራት ጥሩሰው እጇን በቀሚሷ እየጠራረገች ከበረት እንደወጣች ዐይኗ በበለዘው የሸክም ጉንጭ ላይ አረፈ።

“ከሳምንት አንድ ቀን የማይማታ ባል ምን ባል ይባላል?” አለች ሸክም የጠቆረ ፊቷ ጥሩሰውን እንዳስደነገጣት ልብ ብላ፡፡
“ኧረ ያንሳሽ ያባቴ አምላክ እቴ! ደሞ ብለሽ ብለሽ ዱላ ቀረብኝ ትይ አንቺ? ኧረ ይቦጭቅሽ! አህያ ይመስል ሰው ዱላ
ይወዳል እናንተዬ?”አለች ጥሩሰው የምታጥበውን እንስራ አቋርጣ፡፡

“ኤዲያ! በይማ ቁጣውን ትተሽ ከደጃፍ ላይ እንግባና ከሞላሽው አቅምሽኝ?” አለች። የያዘችውን ዋርማ እያቀበለቻት፡፡

“እና በጠዋት ባልሽን ወደ ስራ ትልኪያለሽ እንጂ የሚጠጣ
ጠላ በጠዋቱ...”
“ምን ላድርግ ብለሽ ነው? ይህችን ባይቀምስ አይደል ሰሞኑን ሸንቆጥ ሳያረገኝ የቀርቶ እናታለም፡፡”

“በይማ ቆይ፣ መቀነሻውን በወግ በወግ ሳላጥብ መተሺ...ኤዲያ... እንደው እኔስ በጠዋቱ ባትስጭው ነበር የምመርጥ?”
ሸክም የተኙትን የጥሩሰው ልጆች ከፊል እርቃን በነተበው ብርድ ልብስ ሸፈን እያደረገች ከመደቡ ላይ ቁጭ አለች፡፡ ልጆቹ የተኙበት ወዝ የጠገበ ቁርበት ተንሸራቶ ወደ መሬት ወድቋል፡፡
የወዳደቁ የበቆሎ ቆረቆንዳዎች በጥሩ ሰው እግር እየተነዱ በያሉበት
ይንገዋለላሉ።

ሸክም እጇን የሚልስ ነገር ተሰማት። ጥጃ እንደሆነ አላጣችውም፡፡ ጥጃውን ለማየት ዞር ከማለቷ አሻግራ በር የሌላትን ትንሽ ክፍል ተመለከተች። የሚላወስ ነገር የታያት መሰላት፡፡ እንደ መደንገጥ አለችና ለመጮህ አስባ፣ ምን አልባት ሰው ይሆን?' ብላ ጠረጠረች።

እፊያቸው ላይ የሽሮ ወጥ ነጠብጣቦች የደረቁባቸው የሸክላ ድስቶች በምድጃው ስር ተሰልፈዋል፡፡ ከበላይዋ ያለ መተኛ
የነበረ ቆጥ ላይ የሰፈሩ ዶሮዎች ያስካካሉ፡፡ “ብለሽ ብለሽ ይህንን
የዶሮ ማስፈሪያ አድርገሽው ታርፊ?...”
አለች ሸክም አንድ ዐይኗን ዝቅ አንድ ዐይኗን ከፍ አድርጋ አፏን ጠመም አድርጋ
በማሽሟጠጥ፡፡

“ኤዲያ ባሌን ከደፋ ወዲያ ወደ ላይ ወጥቼም አላውቅ፡፡ይኸው ደሮወችስ እርም ሆኖባቸው መች ጤና አላቸው?”

“እሱስ ልክ ነሽ፡፡” አለችና ያንን የሚንቀሳቀስ የመሰላትን ነገር አፍጣ አየች። አውጥታ ባትናገረውም አንዳች
ነገር ከንክኗታል። ወደ ጥሩስው እየተመለከተች፡
“እና ታቆይኛለሽ?” አለቻት። .
ኧረግ አንቺው! ምኒት ውጋት ሆንሽብኝ፤ መጥለቂያ እስካጥብ አጣደፈሽሳ! ይሄን ነገር ላንቺ ብለሽ ሳይሆን አይቀርም
አጅሪት...”
“ኧዲያ! ይልቅ ጥራሩ ውስጥ ብጣሽ ካለሽማ መች እጠላለሁ ብለሽ እንዲያው አንዳይደቃኝ?”
“ይኸው እኔስ መች አጣሁት? ለራስሽ ብላሽ ነው ስትክለፈለፈ የመተሸ ይኸው አያ ባንቲ መች ድምጹ ይሰማል?”
ሸክም አፏን በኩታዋ አፈን ኣድርጋ በሳቅ ተንተከተከች፡፡

“ኧግ ያፍርስሽ እቴ! ምንኛ ነው እንዲህ የሚያስገለፍጥሽ?”
አለች ከጥራር ውስጥ ብጣሽ እንጀራ ቆርሳ እያቀበለቻት፡፡ያሳቃትን ነገር ሳትገልጽ፣ “ማዋዢያም የለሽ?” አለች ሸክም ደርቆ እግሩን የሰቀለውን እንጀራ በንቀት እያስተዋለች።
“እኔሳ እንዳንቺ አይነቷን አላስጠጣ፤ አላስበላ የምትል የተረገመች ሴት ከአጠገቤ ከማይ...” ወገቧን ይዛ ሰትውረገረግ እንጀራው ተደፋ። ሁለቱም የጀመሩትን ሳቅ አቁመው የተደፋውን
እንጀራ አዩት።

“በይ እሱንም እንጀራ አንስቼ እበላለሁ ብለሽ እንዳንጣላ!”
አለች። ጥሩሰው ልታነሳ እየተንደረደረች። ሸክም አንስታ ግማሹን
ስጨርቅ አድርጋ ወደ አፏ ሰደደች፡፡
“ኧረግ እንደው ያንቺስ ተፈጥሮ ምን አይነት ይሆን አያ!
ቆሻሻውን ትበይው? ደግሞ እኮ ቅድም ደርሰህ ተቀምጦበት በሽንት
በምናምን አትረክርኮት ነበር፡፡ አሁን በስሚዛ ጠራርጌ ነው የመተሽ፡፡
ኧረግ ያባቴ አምላክ..!” ደጋግማ ስትጎርስ በንቀት እያስተዋለች፣

አሁንም እየበላሽ ነው...? እንደው ትንሽም አይቀፍሽ?” አለችና በመጸየፍ አየቻት፡፡

“ይልቅ ማባያ ካለሽ ስጪኝ ኤዲያ!” አለችና አካባቢዋን ቃኘች፡፡ ጥሩሰው ድጋሚ ስለማባያ በመጠየቋ ዐይኗን እንደ
ማጉረጥረጥ አድርጋ ወደ ስራዋ ተመለሰች። ሸክም አካባቢዋን ስትቃኝ ትላንት ከገበያ መልስ የገዙትን እቃ ቅንባ ውስጥ እንደሞላ አስተዋለች፡፡
“አንደኛሽን ሰንፈሽ የለ፡፡ የገዛነውን እቃ እንኳን ቦታ ማስያዝ ያቅትሽ፡፡ አፍሽ እኔ ላይ ብቻ ነው የሚበረታ።” እጇን ወደ ቅምባው ከርስ ሰዳ በላስቲክ የተጠቀለለች ነገር አወጣች። ምን እንደሆነ ትዝ አላት።

ጥሩ ሰው ጀርባዋን ለሷ ሰጥታ ጠላ እየቀዳች ነው፡፡ ሸክም የተጠቀለለውን የበርበሬ ቋጠሮ ፈትታ የምትበላው እንጀራ ላይ በተን አደረገችው። ትላንት የገዙት አንድ ስኒ በርበሬ ነበር፡፡ እንደነበር
ቋጠረችና መልሳ ወደ ቅምባው ወርወር አደረገችው፡፡

ሽክም ጠላውን ቀድታ አቀብላት ዞር ልትል ስትል እንጀራ ላይ የተነሰነሰውን በርበሬ ተመለከተች፡፡
“አንቺ ያቺነ በርበሬ መኖሯን ብታውቂ ነስነሺያት? ኧረ ተይ አንቺ አውደልድል! ኧረ ተይ!”
“እንግዲያ ምን ላድርግ የረሳሽውን ላስታውስሽ ብዪ እንጂ...”
“ምን እረሳዋለሁ! ሳለሁን ሆዱን አሞብኝ ሀሳቤ ሁሉ ልጄጋ እንጂ የገዛሁትም ትዝ አላለኝ፡፡” አለችና እቃዎቹን ቦታ ቦታ
ማስያዝ ጀመረች፡፡
ሸክም እንጀራውን ጨርሳ ጠላውን መጠጣት ጀምራለች።
“አወይ እድሌ ጠላውን
👍5👎1
አጋመሽው እኮ?”
“እና ይህን ሁሉ አይጨርሰው፣ ልጠጣ እንጂ ብላ ዋርማውን መልሳ አስቀመጠችላት፡፡
“ኧረግ መበላሽት! እናንተው እንዴት ነው እንዲህ የሆንሺው
ባክሺ? ባንዴ ትጨልጪው፡፡ አንቺ ተበላሽተሻል፤ ለባልሽ ነው ብዬ
ሲገርመኝ አንቺው በጠዋቱ ጨልጠሽው ታርፊ! አንቺ የሀገር መሳቂያ ልትሆኚ ትንሺ ነው የቀረሽ፣ በጠዋቱ እስቲ፣ እረ በፈጣሪ እናንተው!”
ሸክም የጥሩስውን ንግግር ከምንም ሳትቆጥር አፏንእየጠራረገች፣
“ይልቁንስ አውቄ ነው አለ ያልኩሽ፡፡ እሱም የለ እኔም በቤት
መዋሌን እንጃ” አለቻት፡፡
“እረግ ያንሳሽ! አዙሪት እንደያዘው ሰው የሚያዞርሽ እንዳው ምኑን ቀምሰሽው ነው እናት አለም?”
ሸክም አሻግራ ያየችውን ነገር በደንብ ስትመለከተው ጥሩሰውም አሻግራ ሸክም ወደምታይበት ተመለከተችና ዐይኗን.....

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ
#ባላጋራ

አትችይም ይለኛል
መቻሌን ደብቆ
እንደሚሆን አውቆ
አትወጪም ይለኛል አቀብ ቁልቁለቱን
ሜዳና ዳገቱን
ቀድሞ ያዝለኛል እኔነቴን ይዞ
በአይሆንም አናውዞ
እየጠላለፈ ይተበትበኛል
እንዳልሄድ ያስረኛል ከቦ በዙሪያዬ
የእኔ ባላጋራ ይኼው ስንፍናዬ፡፡

🔘ሰላም ዘውዴ🔘
#መልስልኝ

ይቅር አይመቸው አይድላው ሥጋዬን
ከፍቶት ኅሊናዬን
አልመር አልታይ አጊጬ አብለጭልጩ
ማንነቴን ሸጬ
አልሻም ከእንግዲህ ይሄው ግሳንግስህ
ቅራቅንቦ ቁስህ
ልስማው ውስጠ ድምጹን
ላዳምጠው ሕመሜን
ንብረት ሐብቴን መልስ
ደስታና ሰላሜን፡፡
#ሸክም


#ክፍል_ሁለት (የመጨረሻ ክፍል)


#በእየሩስአሌም_ነጋ

ጥሩሰውም አሻግራ ሸክም ወደምታይበት ተመለከተችና ዐይኗን ሳታቆይ መለሰችው ሰው ያለበት ጨለማ ቦታ አሁን ባዶ መሰላትና ሸክም አፍጥጣ ወደ ጨለማው ተመለከተች።

“የጥሩሰው ባል ከሞተ በኋላ አንድ ሰው በድብቅ ወደ ጥሩሰው ቤት ሲገባ በተደጋጋሚ ታይቷል፡፡” የሚል ወሬ ስለነበር “ምናልባት በድንገት በመድረሴ በድንጋጤ ተደብቆ ይሆናል፡፡ ስትል
አሰበች፡፡ ደግሞ በዚህ ሀሳቧ እንዳትረጋ ያደረጋት ነገር የጥሩሰው መረጋጋትና ጨዋነት ነበር፡፡ እንደዚያ ቢሆን ኖሮ ጥሩሰውም እንዲህ ተረጋግታ አትጫወትም።

አሁን ዐይኗን አፍጣ ወደ ጨለማው በድፍረት ተመለከተች።
ጥሩሰው “ምነውሳ ወደዚያ አፈጠጥሽ?” አለች፡፡
“አይ እንደው ሰው ያየሁ መስሎኝ ነበር፤ ዞር ስል ደግሞ የለም፡፡” አለች በፍርሃት እየተመለከተቻት።
“ቅዠትሽን ሳትጨርሺ በጠዋቱ ተነስተሸ እዚሁ መቃዠት ጀመርሽ? ለመሆኑ ምን አይነት ሰው ነው ያየሽው? ጋኔል ይሆን?”
አሾፈችባት፡፡
“አይ እንግዲህ ወደ ጓዳ ጎራ ያለ ሰው ሊኖር ይችላል።” ብላ ፈገግ አለች፡፡

ጥሩሰው ሸክምን እንደመገላመጥ አድርጋ በገበቴ ላይ ያለውን እቃ ማጠብ ጀመረች፡፡ ወዲያው ሳቂታና ገራገር ፊቷ
ጨለማ አጠላበትና ዝም አለች፡፡

ሸክም ጥሩሰው ጥሩ ስሜት ውስጥ እንዳልሆነች ቢገባትም ምንም እንዳልተፈጠረ ጨዋታዋን ልትቀጥል ፈለገችና ምን ማውራት እንዳለባት ስታስብ፣ ጥሩሰው ቀና ብላ አፍጥጣባት
ቀረች፡፡

“ምነው?”
“እንዴት?”
“አፈጠጥሽሳ?”
“እንዲያው ገርመሽኝ ነውይ፡፡ እንደው ደርሰሽ ሰው አየሁ ስትይ...”
“ምን ላርግ እናት አለም? ያየሁትን ማለፍ አልወድ. አንቺስ አመሌን ታውቂው የለ?”
“ምን ታደርጊ አንቺማ ሲያወሩ የሰማሽውን ነው፡፡”
“ምኑን?” አለች ሸክም ደንገጥ ብላና መስማቷ ግምባሯ ላይ የሚታይ ይመስል አንገቷን ቀብራ፡፡
“እስቲ ይሁን፣ የወደቀ እንጨት ምሳር ይበዛበታል አሉ።ይሁን ግዴለም፡፡ እውነቱን ግዜ ያወጣዋል።” አለች በዐይኗ ሙሉ የሞላው እምባ እንዳይወርድ ወደ ላይ እያንጋጠጠች፡፡
“እና ለሰው ወሬ ብለሽ ልታለቅሺ ነው እናት አለሜ? ራስሽን የምታውቂው ራስሽ እንጂ ሌላ ሰው አይደለም፣” አለች የጠጣችበትን ዋርማ ቦታ እያስያዘች።
“ይሁና እንግዲህ ምን አድርጋለሁ? ያሉትን ይበሉ። የባሌ ሐዘን ከሆዴ ሳይወጣ አፋቸውን አልቻልኩትም፡፡ በነሱ ቤት ማጽናናታቸው ይሆን?” ጥሩሰው በረጅሙ ተነፈሰችና፣
“ይኸውልሽ ባለፈው ሰንበት ያቺ ምህዶ አፍ ያለችኝ ከሆዴም አይጠፋ። ያንን ሸውራራ ዐይኗን ይበልጥ አንሽዋራና
ድምጿን ጮክ አድርጋ እኔ እንድሰማላት ጓደኛዋን አሻግራ እያየች
ስሚ! ባልሽን ጠበቅ አድርገሽ ያዢ! ዛሬ ባልሽን ገድሎ አብሮሽ የሚተኛ ጎረቤትሽ ነው!' አለች። ሰምተሻታል አይደል?”
“በእርግጥ ሰምቻለሁ። ግን ገና ለገና አሽሙር ተናገረች ብለሽ መገመትሽ ጥሩ አይደለም።”
“እስቲ ይሁን ግዴለም” ብላ እንዳቀረቀረች ወደ ጓዳ ገብታ
አነስ ያለችውን የእንጨት መስኮት ከፍታ ዞር ስትል ባየችው ነገር
በድንጋጤ ደርቃ ቀረች፡፡
ፊት ለፊቷ እንደ ጅብራ ግርግዳውን ተደግፎ የቆመው ሰው አፉን እየተመተመ ዝም እንድትል ለመናት፡፡ ዝም ማለት
አልቻለችም፡፡
“ኧረግ ያባቴ አምላክ!” አለች፡፡
ሸክም የጠረጠረችው ሰው እውነት እንደሆነ አውቃ ወደ ጓዳ
ዘው ብላ ገባች፡፡

የቆመው ሰው ሸክምን በድንጋጤ እያየ፣ “አንቺ ቅንዳሻም! መተሽ የምታወሪውን ልሰማ ጥሩስው በረት እያለች ነው ቀድሜሽ መጥቸ የተሸሽኩኝ፡፡ እንዲያው የባለጌ ጓደኛ ያደረገሽ ምን ይሆን
አያ? ሞተሽ ባረፍሽ! አጅሪት አንቺንም ላንዱ ጎረቤት እንድትድርሽ ነው?” ዐይኑን እያጉረጠረጠ ሽመሉን እየወዘወዘ ወጣ፡፡

ጥሩሰው፣ “የተደፈርኩት ባሌ ሲሞት ነው ወይኔ!” አለችና ተስፋ ቆርጣና የሚብረከረክ ጉልበቷን በእጇ ይዛ ዐይኖቿን በመዳፏ እንደሸፈነች ከመደቧ ላይ ቁጭ አለች።

ሸክም ባለችበት ቆማ ተምዘግዝጎ እየዋጣ ያለውን ባሏን ግቢዉን ለቆ እስኪወጣ ተመለከተችና ጥሩሰውን ዞራ አየቻት። ጥሩሰው፣ ሸክም ወደ እርሷ እየተመለከተች እንደሆነ ገብቷት ፊቷን
ሸክም ከቆመችበት በተቃራኒው አቅጣጫ እያየች የሚወርደውን
እንባዋን ደጋግማ ትጠርጋለች፡፡
“አሁን ለምን እንደምታለቅሺ ብቻ ንገሪኝ?” አለቻት ሸክም፡፡
ለጠየቀቻት ጥያቄ መልስ ባለመስጠቷ ወደጥሩ ሰው ሄዳ በአንድ ጉልበቷ በርከክ አለችና፣
“ፊትሽ ምን እንደመሰለ ባየሽ? አታልቅሽ በቃ! ማንን ይመቸው ብለሽ ነው የምታለቅሽው? አንቺንም አውቅሻለሁ፣
ባሌንም አውቀዋለሁ።” አለቻት፡፡
ጥሩ ሰው ሸክም የምትለው አልገባ ብሏት ዐይን ዐይኗን በፍርሃት ስታያት፣ “ከዚህ በፊት ባሌ ሲያናግርሽና ደጋግመሽ
ስታመናጭቂው አይቻለሁ። ያንን ባላይ እንኳን ጨዋይቱን ጓደኛየን አምንሻለሁ... እመዬ አይክፋሽ... ተይው እናቴነሽ... ተይው አታልቅሽ ይሄ ድራሸ ቢስ ሁለተኝ ቀና ብሎም አያይሽ።እንኳንም እጄ ላይ ጣለልሽ”

ጥሩሰው ከሃዘኗ መኸከል አምልጦ የወጣውን ፈገግታዋን ለሸክም እየለገሰች እጇን ይዛ ከተንበረከከችበት እነድትነሳ
አደረገችና እንድትቀመጥ መደቡ ላይ ያለውን አጎዛ አራገፈችላት፡፡

💫አለቀ💫
👍1👎1