#የቅዳሜ_ማስታወሻ
ልባቸውን አይቶ
እግር የነሳቸው ፥ ቀርፋፋ ቀናቶች
ዘልዛላ ለሊቶች
እንደ ማቱ ሳላ ፥ እድሜ የሚያዘግሙ
ከሰኞ ተነስተው ፥ አርብ እስከሚያከትሙ
በስራ በትምህርት
በስብሰባ ብዛት
በሰበብ ባስባቡ ፥ ሲያቀጥኑኝ አክርረው
እንደ ጠቦት ቆዳ ፥ ሲሰቅሉኝ ወጥረው
በአማራሪ ቀኖች ፥ የማልማረረው
ለቅዳሜ ስል ነው።
#ዛሬ_ቅዳሜ_ነው !
አደረች አራዳ ፥ ዘፈን ይለቀቃል
አሳዳሪ አራዳ ፥ አልጋቤቱ ያልቃል
እንደጉድ ይጠጣል ፥ ይወደሳል ጠጪ
ነይና ላሳይሽ!
ቅዳሜ ከቀረሽ ፥ ዘላለም አትምጪ።
#ዛሬ_ቅዳሜ_ነው!
በየመጠጥ ቤቱ ፥ ገርበብ ያሉ ጭኖች
በየ ጎዳናው ላይ
ቆንጆ ሴት የጫኑ ፥ ጢኒኒጥ መኪኖች
በየ ፋርማሲ ቤት
ፅንስን የሚያመክኑ ፥ እንክብል ኪኒኖች
የሚያዘዋውረው
የሚመነዝረው
የሚያመነዝረው ፥ እንደጉድ ይበዛል
በደራ ገበያ
ጭን ከንፈር ጭንቅላት ፥ ይሸጣል ይገዛል
ሰክሮ
ተ
ን
ገ
ዳ
ጋ
ጅ
“ይህች ሀገር ወዴት ነው
የምትሔደው? " ; የሚል ጥያቄ ያባዛል።
ነይና ላሳይሽ!
“ጨዋ” የሚባል ህዝብ ፥ ጠፍቶት ትርጓሜ
“
ቀሚስ” የሚባለው
የት እንደሰረሰ ፥ አጥሮ እንደ ጳግሜ
የዝች ሀገር ጉዞ
ወዴት እንደሆነ ፥ መልስ አለው #ቅዳሜ።
ነይና ላሳይሽ
የአልኮል ባህር ላይ ፥ የመረብ አጣጣል
መንግስት አልወርድ ያለው
ውስኪ እያወረደ ፥ ሴት ከቦት ይጠጣል
የቢራ ያጣ ሰው
ስለውስኪ አጠጣጥ ፥ አቃቂር ያውጣል
ጭፈራው ለጉድ ነው ፣
ጨፋሪው ብዙ ነው ፥ አያስጥልም ጠጠር
ዝቅ ለሚሉት ጭን
ጎንበስ ላሉት ጡት ፥ ቀና ላሉት ከንፈር
ነፃ ይታደላል
ስካር አቅል ያሳጣው
“እቺ ሀገር ወዴት ነው ፥ የምትሔደው” ይላል?።
ሁሉ እየተነሳ
“ይቺ ሀገር ወዴት ነው
የምትሔደው” ብሎ ፥ መጠየቅ ቢወድም
ነይ መልሱን ላሳይሽ!
ወደ አልጋ ቤት እንጂ ፥ ወዴትም አትሔድም።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
ልባቸውን አይቶ
እግር የነሳቸው ፥ ቀርፋፋ ቀናቶች
ዘልዛላ ለሊቶች
እንደ ማቱ ሳላ ፥ እድሜ የሚያዘግሙ
ከሰኞ ተነስተው ፥ አርብ እስከሚያከትሙ
በስራ በትምህርት
በስብሰባ ብዛት
በሰበብ ባስባቡ ፥ ሲያቀጥኑኝ አክርረው
እንደ ጠቦት ቆዳ ፥ ሲሰቅሉኝ ወጥረው
በአማራሪ ቀኖች ፥ የማልማረረው
ለቅዳሜ ስል ነው።
#ዛሬ_ቅዳሜ_ነው !
አደረች አራዳ ፥ ዘፈን ይለቀቃል
አሳዳሪ አራዳ ፥ አልጋቤቱ ያልቃል
እንደጉድ ይጠጣል ፥ ይወደሳል ጠጪ
ነይና ላሳይሽ!
ቅዳሜ ከቀረሽ ፥ ዘላለም አትምጪ።
#ዛሬ_ቅዳሜ_ነው!
በየመጠጥ ቤቱ ፥ ገርበብ ያሉ ጭኖች
በየ ጎዳናው ላይ
ቆንጆ ሴት የጫኑ ፥ ጢኒኒጥ መኪኖች
በየ ፋርማሲ ቤት
ፅንስን የሚያመክኑ ፥ እንክብል ኪኒኖች
የሚያዘዋውረው
የሚመነዝረው
የሚያመነዝረው ፥ እንደጉድ ይበዛል
በደራ ገበያ
ጭን ከንፈር ጭንቅላት ፥ ይሸጣል ይገዛል
ሰክሮ
ተ
ን
ገ
ዳ
ጋ
ጅ
“ይህች ሀገር ወዴት ነው
የምትሔደው? " ; የሚል ጥያቄ ያባዛል።
ነይና ላሳይሽ!
“ጨዋ” የሚባል ህዝብ ፥ ጠፍቶት ትርጓሜ
“
ቀሚስ” የሚባለው
የት እንደሰረሰ ፥ አጥሮ እንደ ጳግሜ
የዝች ሀገር ጉዞ
ወዴት እንደሆነ ፥ መልስ አለው #ቅዳሜ።
ነይና ላሳይሽ
የአልኮል ባህር ላይ ፥ የመረብ አጣጣል
መንግስት አልወርድ ያለው
ውስኪ እያወረደ ፥ ሴት ከቦት ይጠጣል
የቢራ ያጣ ሰው
ስለውስኪ አጠጣጥ ፥ አቃቂር ያውጣል
ጭፈራው ለጉድ ነው ፣
ጨፋሪው ብዙ ነው ፥ አያስጥልም ጠጠር
ዝቅ ለሚሉት ጭን
ጎንበስ ላሉት ጡት ፥ ቀና ላሉት ከንፈር
ነፃ ይታደላል
ስካር አቅል ያሳጣው
“እቺ ሀገር ወዴት ነው ፥ የምትሔደው” ይላል?።
ሁሉ እየተነሳ
“ይቺ ሀገር ወዴት ነው
የምትሔደው” ብሎ ፥ መጠየቅ ቢወድም
ነይ መልሱን ላሳይሽ!
ወደ አልጋ ቤት እንጂ ፥ ወዴትም አትሔድም።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#እህቴን_ሸጥናት!
፡
፡
#ክፍል_ሶስት (የመጨረሻው ክፍል )
፡
፡
#በጥላሁን
ጫት ቃሚዋ ልታምነው አልፈቀደችም
"አቦ ዛሬ ደግሞ መቃም ሳይጀምር የሚመረቅን ሰው ነው እንዴ ያጋጠመኝ ! ወንድሜ ብላ ስላወራችው እህቱ የሆነች መሰለው እንዴ !
ኧረ ጓደኛዬ አምጪው እስቲ ያንቺን ስልክ የኔ ጨላ ስለለው ደውልላት ብዬ ቁጥሯን ብሰጠው ያጃጅለናል እንዴ! ባንቺ ልደውልላትና አጠገቧ የነበረው ልጅ ገና ፈረንጅ ከመጥበሷ እህቱ አርጓት እንዳረፈው ነግሬ ላስቃት በናትሽ አምጭው ስልክሽን !" አለች ሳቅ እየታገላት።
ሰጠቻት። ደወለች•••
"ሄሎ የኔ ቆንጆ እንዴት ነው ምቾቱ ?
ደሞ አጠገብሽ የነበረውን ልጅ ምን ብለሽው ነው? ባክሽ ! መጀመሪያ ቁጥርሽን ሰጥቼው ስልኩ ላይ እንደፃፈው ያባቴ ስም ወጣ ሲለን ምርቃና ነው ብለን አለፍነው ሲያዋራሽ ጭራሽ ብሶበት ያባቴ ልጅ እህቴ ነች ብሎ በሳቅ ሊገለኝ ፈረንጅ መጥበስ ወንድም ያበዛል አየሽ ኪኪኪ•••"
የልጅቷ ጥያቄ ሳቋን ባጭር ቀጨው•••
" ያባቱ ስም ማነው?አለቻት።
"እንዴ አንቺም ተጠራጠርሽ እንዴ ?"አለችና ልጁን ጠይቃ ነገረቻት
" አመሰግንሀለሁ አምላኬ ! ልክ ነው ወንድሜ ነው! በብቸኝነት ስሰቃይ አድጌ አባቴ ወንድም እንዳለኝ ከነገረኝ ጀምሮ ስንት አመት ሙሉ ነገ ዛሬ እያለ አሳቀቀኝ !ፈጣሪ ፍቃዱ ከሆነ ሰዎች ረድኑንም አልረዱንም በምክንያት ምኞታችንን እና ፍላጎታችንን ለማሳካት የማይታሰበውን አጋጣሚ እውነት ያደርገዋል ። ስሙ ዳግም ነው አይደል?"
እኔ ምን አቅልሻለሁ ስምህ ዳግም ነው እንዴ? ስትለው በድንጋጤ እንደፈዘዘ በአውንታ ጭንቅላቱን ነቀነቀ።
ጫት ቃሚዋ ጩኸቷ ረገብ አለ። ቀዝቀዝ አለች። በረደች።
አዋ አለኮ ወንድምሽ ነው ማለት ነው" እያለቻት በመሀል ድንገት ፈረንጁና ልጅቷ መጨቃጨቅ ጀመሩ ።
ጫት ቃሚዋ ተደናግጣ "እንዴ ምን ሆኑ አሁን ባሁን!" እያለች ሁሉም እንዲሰሙ የስልኩን ድምፅ አጎላችው።
"ሄይ ኢት ኢዝ ኢነፍ ስቶፕ ቶኪንግ ኤንድ ጊቭ ሚ ዩር ፎን" አለ በቁጣ ፈረንጁ
" አቅርቢው እስቲ ላውራው•••
ምንድን ነው ምትለኝ ቆይ እስቲ በናትህ ወንድሜን ላዋራው " የልጅቷ መልስ ነበር እሄን ግዜ ፈረንጅ እንግሊዘኛውን አሽቀንጥሮ የኛኑ አማርኛ ያዥጎደጉደው ጀመር••
"ትሰሚያለሽ አንቺ ልጅ ካሁን ቡሀላ ማንንም ማዋራት አትችይም ወሬሽን ተይና ስልኩን ለኔ ስጪ!" አላት
ልጅቷም ሚኒባስ ውስጥ ያሉት ሰዎችም እኩል ደነገጡ።
ፈረንጁ መኪናውን ድንገት ፍሬን አንቆ ሲያቆመው ከፊት መስታወት ጋር ከመላተም ቀበቶው የታደጋት ልጅ ጮኸች!
"ስልኩን አምጪ!" ብሎ በጥፊ ከመታት ቡሀላ ስልኳን ተቀብሎ ዘጋው።
ሚኒባሱ ውስጥ ድምፅ ማጉያ ላይ የነበረው ስልክ ብቻ ሳይሆን ሁሉም በድንጋጤ ፀጥ አሉ።
ወንድምየው ወይኔ እህቴ ከሷ ፍላጎት በላይ እኛ ነን እህቴን ገፍትረን ላውሬ አሳልፈን የሸጥናት እባክህ ሹፌር አፍጥነው እና ሻሸመኔ ፖሊስ ጣብያ እናመልክት" አለ እየተርበተበተ።
ፖሊስ ጣብያ እንደደረሱ ልጅቷ ሞባይሏን ከነጠቃት ቡሀላ ከዋናው ሞባይላ ውጪ ቦርሳዋ ውስጥ አነስ አና ረከስ ያለች ሞባይል ይዛ ስለነበር መጀመሩያ ወንድሟ የደወለላት ግዜ የወንድሟን ቁጥር ያኛው ስልክ ላይ ያለው ሲም ካርዷ ሙሉ ስለነበር እዚቺኛዋ ስልኳ ላይ ባለው ሲም ላይ ሳያስተውላት ይዛው ነበርና ሳያያት ቀስ ብላ ከቦርሳዋ በማውጣት ስትነካካ ድምፅ እንዳይሰማ ፈጠን ብላ ዝም በዝምታ የሰጧትን እንድትቀበል አፋን ከዘጋቻት ቡሀላ ፈረንጁ በስልክ ከሌሎች ጋር የሚያወራውን እየሰማች ለወንድሟ ያለችበትን ሁኔታ የሚገልፅ የድረስልኝ መልክት ፅፋ ላከች•••
"ወንድሜ እባክህ ድረስልኝ ስልኩን ከቀማኝ ቡሀላ መኪናውን አዙሮ ራቅ ወዳለ አንድ ጫካ ይዞኝ እየገባ ነው ስልክ ሲያወራ እንደሰማሁት ችግሩ ከአባታችን ጋር ነው ስልክ ደወለና •••
"" እዛው ናችሁ አደል ልጅቷን ይዧት እየመጣሁ ነው ። እኔን መጠቀማችሁ ልክ ነበር በቀላሉ ነውኮ ሳር እንዳየ በግ የተከተለችኝ አሁኑኑ ላቧታ ደውሉና ሰነዱ ላይ እንዲፈርም ንገሩት አልፈርምም የሚል ከሆነ ልጁን አቃጥለን ይህን ውብ ገላ ወደ ከሰል ቀይረን በፎቶ እንደምንልክለት አስረዱት ካላመነ ድምፃን እንደደረስኩ ይሰማዋል ሲል ነበር ፈርቻለሁ ወንድሜ የማልተርፍ ከሆነና መሞቴ ግድ ከሆነ ግን ለብዙ ግዜ ላየው ስመኝ የነበረውን አንተን ወንድሜን አጠገቤ ተቀምጠህ አይቼህ ስለሞትኩ •••
አልጨረሰውም ሞባይሉን ወርውሮ የፖሊስ ጣብያው ግርግዳ ላይ ለጠፈው እንክትክት አለ የእህቱን መልክት እጁ እየተንቀጠቀጠ ሲያነብ
እያዳመጡ የነበሩት ፖሊሶችና ሚኒባስ ውስጥ ለነበሩት ሰዎች ቆሌያቸው ተገፈፈ።
ጫት ቃሚዋ ሴት ሹልክ ብላ ካጠገባቸው ተሰወረች።
ጓደኛው ሌላ መልክት ብትልክስ ብሎ ስላሰበ ከተሰበረው ሞባይል ውስጥ ሲምካርዱን አወጣና እሱ ስልክ ውስጥ አደረገው።
ፖሊሶቹ በመደዋወል የፈረንጁ መኪና የት አከባቢ ላይ ሲደርስ ከዋናው መንገድ እንደወጣ ፍንጭ አገኙ።
ወንድሟ እና አብረውት የመጡት ሁለት ጓደኛቹ በመሆን ወደ ቦታው ሲንቀሳቀሱ ከጫት ቃሚዋ ሴት በስተቀር ሌሎቹ መልክም እድል ተመኝተውና ስልኩን ተቀብለው በመጡበት ሚኒባስ ወደ ሀዋሳ ሄዱ።
ፖሊሶቹ የመኪናውን ዳና እየተከተሉ መኪናውን አገኙት ነገር ግን ውስጡ ሰው አልነበረም የፖሊስ መኪናውም ከዛ በላይ የሚሄድበት መንገድ አልነበረምና
"ከዚህ ቡሀላ ያለው ስራ የኛ ብቻ ነው እናንተ እዚሁ ጠብቁን!"
በማለት ወንድሟን እና ጓደኛቹን እዛው ጥለዋቸው በተለያየ አቅስጣጫ በመሰማራት ጫካውን ወረሩት።
ከደቂቃዎች ቡሀላ የቶክስ ድምፅ ተሰማ ። ወድያው ከሻሸመኔ እየከነፈች የመጣችው አንቡላንስ በጭንቀት ወደ ሚፀልዩት ወንድሟ እና ጓደኛቹ ጋር ተጠግታ ቆመች ። ሁለት ፖሊሶች ተሸክመው ያመጧት ሴት ወደ አንቡላንሱ ሲያስገቧት ቀና አለችና ወንድሜ ብዙ አልተጎዳሁም እሺ ተርፊያለሁ አለችው።
💫ተፈፀመ💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏

👍3❤1
#ቢታነፅ_ቢወቀር
እኔም አንድ ሰሞን
ልክ እንደ ሰሎሞን
“ሁሉም ከንቱ ከንቱ ነፋስን መከተል”
ሳይጥሉ መታገል፣ ሳይከብሩ መባተል
አያልሁ አጨልሜ
በራሴ ለግሜ
እፈላሰፍ ነበር።
ከዚያ አንቺን አገኘሁ
በጓሮ በር በኩል፣ ሰሎሞኔን ሸኘሁ
መፈጠሬን ወደድሁ
ነፋስ አሳድጄ
አንድ ቆቅ አጠመድሁ
ከፀሐይዋ በቻች፣ ግልገል ፀሐይ ፈጠርሁ
ለኦናው አምፖሌ፣ ብርሃን አበደርሁ
ማቅ የነበረው ጨርቅ፣ ሸማ ሆኖ ቆየኝ
ከንቱ የነበረው፣ አንቱ ሆኖ ታየኝ።
ለካስ
ጠቢብ ሲያስተምረው፣ መከራ ቢመክረው
አካሉና ልቡ ቢታነፅ፣ ቢወቀር
ሰው አቅሙን አያውቅም፣ ካልወደደ በቀር።
🔘በዕውቀቱ ስዩም🔘
እኔም አንድ ሰሞን
ልክ እንደ ሰሎሞን
“ሁሉም ከንቱ ከንቱ ነፋስን መከተል”
ሳይጥሉ መታገል፣ ሳይከብሩ መባተል
አያልሁ አጨልሜ
በራሴ ለግሜ
እፈላሰፍ ነበር።
ከዚያ አንቺን አገኘሁ
በጓሮ በር በኩል፣ ሰሎሞኔን ሸኘሁ
መፈጠሬን ወደድሁ
ነፋስ አሳድጄ
አንድ ቆቅ አጠመድሁ
ከፀሐይዋ በቻች፣ ግልገል ፀሐይ ፈጠርሁ
ለኦናው አምፖሌ፣ ብርሃን አበደርሁ
ማቅ የነበረው ጨርቅ፣ ሸማ ሆኖ ቆየኝ
ከንቱ የነበረው፣ አንቱ ሆኖ ታየኝ።
ለካስ
ጠቢብ ሲያስተምረው፣ መከራ ቢመክረው
አካሉና ልቡ ቢታነፅ፣ ቢወቀር
ሰው አቅሙን አያውቅም፣ ካልወደደ በቀር።
🔘በዕውቀቱ ስዩም🔘
#ምነው_እመብርሃን
ማርያም ምስራቅ ናት ፥ የፀሐይ መውጫ በር
ይህ ዓለም ሰቅሎታል ፥ ልጇን እንደ ጀምበር ።
ከዓለም ተለይታ ፥ ስትጨልም ሃገሬ
ይነጋል እያልኩኝ ፥ተነገ ተዛሬ
መማፀኔን ሳልተው
ስምሽን እየጠራ
ጠዋት ማታ ምስራቅ ፥ ለሚመለከተው
በኢትዮጵያ ሰማይ ስር
ጨለማ ብቻ ነው ፥ የሚበረክተው፡፡
🔘በላይ በቀለም ወያ🔘
ማርያም ምስራቅ ናት ፥ የፀሐይ መውጫ በር
ይህ ዓለም ሰቅሎታል ፥ ልጇን እንደ ጀምበር ።
ከዓለም ተለይታ ፥ ስትጨልም ሃገሬ
ይነጋል እያልኩኝ ፥ተነገ ተዛሬ
መማፀኔን ሳልተው
ስምሽን እየጠራ
ጠዋት ማታ ምስራቅ ፥ ለሚመለከተው
በኢትዮጵያ ሰማይ ስር
ጨለማ ብቻ ነው ፥ የሚበረክተው፡፡
🔘በላይ በቀለም ወያ🔘
#እውነቱን_ተናግሮ_አሳደረኝ_ማጣት
“እውነቱን ተናግሮ ፥ የመሸበት ማደር"
እያለ ሲሰብከኝ ፥ የመሸበት ሃገር
ስሰማና ሳምን ፥ ቆይቼ ሰምቼ
በድንገት መሽቶብኝ
አንቺ ጋር ለማደር ፥ ከቤትሽ መጥቼ
እውነቱን ብናገር ፥ ባልሽ ግን ጠመደኝ
እንኳን ሊያሳድረኝ
መዋያ አሳጣኝ ቀን እያሳደደኝ ።
ዳሩ ብሳደድም
እውነት ተናጋሪ
ማደሪያ እንደሚያጣ ፥ ከእንግዲህ አልዘነጋም
እውነቴም አንቺው ነሽ!
ስትሄጂ መሽቷል ፥ ካልመጣሽ አይነጋም።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
“እውነቱን ተናግሮ ፥ የመሸበት ማደር"
እያለ ሲሰብከኝ ፥ የመሸበት ሃገር
ስሰማና ሳምን ፥ ቆይቼ ሰምቼ
በድንገት መሽቶብኝ
አንቺ ጋር ለማደር ፥ ከቤትሽ መጥቼ
እውነቱን ብናገር ፥ ባልሽ ግን ጠመደኝ
እንኳን ሊያሳድረኝ
መዋያ አሳጣኝ ቀን እያሳደደኝ ።
ዳሩ ብሳደድም
እውነት ተናጋሪ
ማደሪያ እንደሚያጣ ፥ ከእንግዲህ አልዘነጋም
እውነቴም አንቺው ነሽ!
ስትሄጂ መሽቷል ፥ ካልመጣሽ አይነጋም።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ሲቀርፁ_መዶልዶም
በጥይት እርሳስ ጫፍ
የተሳተ ስህተት ፥ በላጲስ ባይጠፋም
ቢቀርፁት መዶልዶም
በሆነ የእርሳስ ህግ ፥ ያጥራል እና ተስፋም
ሁለት ምርጫ የለም!
ጨለማ ብርሃኑን
ኑሮኖ አፈሩን ፥ ሰው እኩል አይገፋም፡፡
ዘጠኝ ሞት ቢመጣ ፥ ሰው አንዱን ይመርጣል
ሰው አንድ ሞት ሲመርጥ ፥ስምንት ሞት ያመልጣል
ሁለት ምርጫ የለም
መይ ወድቆ ማንሳት ነው ፥ ወይ ተነስቶ መጣል!
🔘በለይ በቀለ ወያ🔘
በጥይት እርሳስ ጫፍ
የተሳተ ስህተት ፥ በላጲስ ባይጠፋም
ቢቀርፁት መዶልዶም
በሆነ የእርሳስ ህግ ፥ ያጥራል እና ተስፋም
ሁለት ምርጫ የለም!
ጨለማ ብርሃኑን
ኑሮኖ አፈሩን ፥ ሰው እኩል አይገፋም፡፡
ዘጠኝ ሞት ቢመጣ ፥ ሰው አንዱን ይመርጣል
ሰው አንድ ሞት ሲመርጥ ፥ስምንት ሞት ያመልጣል
ሁለት ምርጫ የለም
መይ ወድቆ ማንሳት ነው ፥ ወይ ተነስቶ መጣል!
🔘በለይ በቀለ ወያ🔘
#ከእንጃ_ባሻገር
ተራራ የሚያህል ፥ ግዙፍ እምነት አለኝ
ለምንድነው ታዲያ
የሰናፍኝን ቅንጣት ፥ በመግፋት ያልተቻለኝ?
እንጃ!
ክሀሳብ የሰነፉ
ሰፊ መንገድ ኖሮኝ ፊቴ የተሰጣ
ከቶ ለመንድን ነው
ለመሔድ መጋፋው ፥ መርገጫ እስከማጣ ?
እንጃ!
በብርሐን ፍጥነት ፥ መፍጠን የምችል ሰው
ለወንድነው ታዲያ
ቀድሜ ወጥቼ ፥ አርፍጄ ምደርሰው ?
ከቶ ለምንድ ነው
ለጥያቄዬ መልስ ፣ እንጃ የማበዛው?
እንጃ !
ከቶ ለምንድን ነው
ለጥያቄዬ መልስ እንጃ የማበዛው?
እንጃ!
እሺ ለምንድነው ?
ነፃ ያደልኩትን ፣ በውድ የምገዛው ?
እንጃ!
ታድያ ለምን ይሆን
መልስ አልባ ጥያቄ የምፈለፍለው?
እንጃ !
እንጃ!
እንጃ!
ብቻ አንድ እውነት አለኝ እንጃ የማልለው
ከሙሉ ነገር ላይ መጉደል ነው ሚጎድለው።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
ተራራ የሚያህል ፥ ግዙፍ እምነት አለኝ
ለምንድነው ታዲያ
የሰናፍኝን ቅንጣት ፥ በመግፋት ያልተቻለኝ?
እንጃ!
ክሀሳብ የሰነፉ
ሰፊ መንገድ ኖሮኝ ፊቴ የተሰጣ
ከቶ ለመንድን ነው
ለመሔድ መጋፋው ፥ መርገጫ እስከማጣ ?
እንጃ!
በብርሐን ፍጥነት ፥ መፍጠን የምችል ሰው
ለወንድነው ታዲያ
ቀድሜ ወጥቼ ፥ አርፍጄ ምደርሰው ?
ከቶ ለምንድ ነው
ለጥያቄዬ መልስ ፣ እንጃ የማበዛው?
እንጃ !
ከቶ ለምንድን ነው
ለጥያቄዬ መልስ እንጃ የማበዛው?
እንጃ!
እሺ ለምንድነው ?
ነፃ ያደልኩትን ፣ በውድ የምገዛው ?
እንጃ!
ታድያ ለምን ይሆን
መልስ አልባ ጥያቄ የምፈለፍለው?
እንጃ !
እንጃ!
እንጃ!
ብቻ አንድ እውነት አለኝ እንጃ የማልለው
ከሙሉ ነገር ላይ መጉደል ነው ሚጎድለው።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#የሁለት_ጽንፍ_ዓለም
እጅግ ያስገርማል
የዓለም ልዩነት
አንደኛው በሃብቱ
አንዱ በድህነት
አንደኛው በህመም
አንዱ በጤንነት
አንደኛው በበጎ
አንደኛው በክፋት
አንደኛው ለመኖር
አንደኛው ለመጥፋት
ግን ለምን ተፈጠረች
ዓለም ሆና ሁለት ?
🔘ፋሲል ሃይሉ🔘
እጅግ ያስገርማል
የዓለም ልዩነት
አንደኛው በሃብቱ
አንዱ በድህነት
አንደኛው በህመም
አንዱ በጤንነት
አንደኛው በበጎ
አንደኛው በክፋት
አንደኛው ለመኖር
አንደኛው ለመጥፋት
ግን ለምን ተፈጠረች
ዓለም ሆና ሁለት ?
🔘ፋሲል ሃይሉ🔘
#የቀበቶ_ቅኔ
እንደ ብዙ ወንደች
ከብዙ ሴቶች ጋር ፥ ለዝሙት ተኝቶ
እንዲ እርኩ ማለት
ጀብዱ የሚመስለኝ ፥ እንጎለ ቀበቶ
ለስሜቴ ሳድር ፥ ነፍሴን አዝረክርኬ
ከቀበቶዬ ላይ
ተፅፎ አየሁት ፥ የህይወት ታሪክ።
እዩት ቀበቶዬን
በሴቶች ምሳሌ ፥ ቀዳዳ ተከቦ
እኔ ማለት ያ ነኝ
በቀዳዶች ውስጥ
ገብቶ የሚወጣ ; የቀበቶው ሽቦ፡፡
የማሰቤ ወገብ ፥ ሲቀጥን ሲወፍር
ካንዷ ቀዳዳ ጎን ፥ አንዷን የምቀይር፡፡
የማሰቤ ወገብ ፥ ሲከሳ ሲሰባ
ቀዳዶቹን ትቼ
ሌላ አዲስ ቀዳዳ ፥ ፈልጌ ምገባ።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
(መነሻ ሀሳብ ገጣሚ ደስታ ነጋሽ)
እንደ ብዙ ወንደች
ከብዙ ሴቶች ጋር ፥ ለዝሙት ተኝቶ
እንዲ እርኩ ማለት
ጀብዱ የሚመስለኝ ፥ እንጎለ ቀበቶ
ለስሜቴ ሳድር ፥ ነፍሴን አዝረክርኬ
ከቀበቶዬ ላይ
ተፅፎ አየሁት ፥ የህይወት ታሪክ።
እዩት ቀበቶዬን
በሴቶች ምሳሌ ፥ ቀዳዳ ተከቦ
እኔ ማለት ያ ነኝ
በቀዳዶች ውስጥ
ገብቶ የሚወጣ ; የቀበቶው ሽቦ፡፡
የማሰቤ ወገብ ፥ ሲቀጥን ሲወፍር
ካንዷ ቀዳዳ ጎን ፥ አንዷን የምቀይር፡፡
የማሰቤ ወገብ ፥ ሲከሳ ሲሰባ
ቀዳዶቹን ትቼ
ሌላ አዲስ ቀዳዳ ፥ ፈልጌ ምገባ።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
(መነሻ ሀሳብ ገጣሚ ደስታ ነጋሽ)
#ይህችን_አታሳጣኝ
የአዳም ዘር በሞላ ታድሞ ከእልፍኝ
ባለው ላይ ሲያተርፍ ካለው እጥፍ ሲመኝ
ከማዶ ሲያማትር አርቆ ከራሱ
ለልጅ ልጅ ሲለፋ ጠግባ አንድ ነፍሱ
ግራ ቀኝ ብፈልግ ውስጤ ፈጥሮ ቅናት
ሀበሻ ወገኔም ካፉ ሲል በአይኔ ልመለከት
መአዱን ሊቋደስ ተራው ከመድረሱ
እፍኝ ቆንጠር አርጎ ባዶ ሆኖ ኪሱ
ሊያመስግን'ሮጠ ሊቆም ከመቅደሱ።
🔘ፋሲል ሃይሉ🔘
የአዳም ዘር በሞላ ታድሞ ከእልፍኝ
ባለው ላይ ሲያተርፍ ካለው እጥፍ ሲመኝ
ከማዶ ሲያማትር አርቆ ከራሱ
ለልጅ ልጅ ሲለፋ ጠግባ አንድ ነፍሱ
ግራ ቀኝ ብፈልግ ውስጤ ፈጥሮ ቅናት
ሀበሻ ወገኔም ካፉ ሲል በአይኔ ልመለከት
መአዱን ሊቋደስ ተራው ከመድረሱ
እፍኝ ቆንጠር አርጎ ባዶ ሆኖ ኪሱ
ሊያመስግን'ሮጠ ሊቆም ከመቅደሱ።
🔘ፋሲል ሃይሉ🔘
#አረፍተ_ሀገር
“አበበ” ምንለው ፥ በሶ የሚበላ
ጩቤ እንደጨበጠ ፥ ለምናውቀው ጫላ
ጣሳ እያጠበ ፥ ለሚኖር ጨቡዴ
ሀገርሽ ሀገሬ
አረፍተ ነገርን ፥ ትመስላለች ውዴ።
*
ስልኬ አበበ ነው
በሶ ደሞ ካርዴ ፥ ስትገባኝ ሀገሬ
“ቴሌ ካርድ በላ።”
የሚል ትርጉም አለው ፣ አረፍተ ነገሬ።
*
ጫላ ባለ ስልጣን ፥ ስልጣን ደሞ ጩቤ
የጨበጡት ሁሉ
ሲያቆስሉት የኖሩ ፥ ስጋዬን ከልቤ።
***
ጨቡዴ ሙስና ፥ ጣሳ ደሞ ህዝቡ
እርቃን የሚያስቀሩት
በየ መሥሪያ ቤቱ ፥ ኪሱን እያሰቡ።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
“አበበ” ምንለው ፥ በሶ የሚበላ
ጩቤ እንደጨበጠ ፥ ለምናውቀው ጫላ
ጣሳ እያጠበ ፥ ለሚኖር ጨቡዴ
ሀገርሽ ሀገሬ
አረፍተ ነገርን ፥ ትመስላለች ውዴ።
*
ስልኬ አበበ ነው
በሶ ደሞ ካርዴ ፥ ስትገባኝ ሀገሬ
“ቴሌ ካርድ በላ።”
የሚል ትርጉም አለው ፣ አረፍተ ነገሬ።
*
ጫላ ባለ ስልጣን ፥ ስልጣን ደሞ ጩቤ
የጨበጡት ሁሉ
ሲያቆስሉት የኖሩ ፥ ስጋዬን ከልቤ።
***
ጨቡዴ ሙስና ፥ ጣሳ ደሞ ህዝቡ
እርቃን የሚያስቀሩት
በየ መሥሪያ ቤቱ ፥ ኪሱን እያሰቡ።
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ለመንጋዎች_መንጋ_ግጥም
እኔ ሰው ስለሆንኩ
የግል አእምሮዬን ፥ አሳልፌ አልሰጥም
በመንጋ አስተሳሰብ ፥ ሀሳቤ አይዋጥም
ለመንጋዎችና
ለመንጋ አሳቢዎች ፥ አለኝ መንጋ ግጥም።
#መንጋ_1
ብዙዎች ተስማምተው
በሔዱበት መንገድ
ትክክል ነው ብሎ ፥ አይነሳም እግሬ
ብዙዎች በህብረት
በጠሉት ነገር ላይ ፥ አይቀንስም ፍቅሬ
አመዛዝናለሁ
አስተሳስራለሁ
የግል አእምሮዬን ፥ ከደም ዝውውሬ።
ብዙዎች ሚወዱት
በጥላቻዬ ላይ ፥ ለውጥ አያመጡም
መንጋ አእምሮዎች
ሀሳብን አይወልዱም ፥ በግል አያምጡም
አንዱ የወለደውን
ይዘው ይጮሀሉ ፥ አይደማመጡም።
#መንጋ_2
መንጋ አሳቢዎች
በምላስ ነው እንጂ ፥ በአእምሮ አይቆሙም
ከእረኛቸው እንጂ
በራሳቸው መንገድ ፥ በድፍረት አይተሙም
በቀቀኖች ናቸው ፥ የገደል ማሚቶ
ተቀብሎ መጮህ
ያውቃል ምላሳቸው ፥ አእምሯቸው ሞቶ።
#መንጋ_3
አብሮ መኖር እንጂ
አብሮ ማሰብ ማላው ፥ ሀሳብን አውጠንጣኝ
አእምሮ የቸረኝ ፥ በምላስ ያልቀጣኝ
ፈጣሪ ይመሥገን!
ከባርነት በፊት
ከመንጋ አስተሳሰብ ፥ ነፃ ስላወጣኝ !!!
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
እኔ ሰው ስለሆንኩ
የግል አእምሮዬን ፥ አሳልፌ አልሰጥም
በመንጋ አስተሳሰብ ፥ ሀሳቤ አይዋጥም
ለመንጋዎችና
ለመንጋ አሳቢዎች ፥ አለኝ መንጋ ግጥም።
#መንጋ_1
ብዙዎች ተስማምተው
በሔዱበት መንገድ
ትክክል ነው ብሎ ፥ አይነሳም እግሬ
ብዙዎች በህብረት
በጠሉት ነገር ላይ ፥ አይቀንስም ፍቅሬ
አመዛዝናለሁ
አስተሳስራለሁ
የግል አእምሮዬን ፥ ከደም ዝውውሬ።
ብዙዎች ሚወዱት
በጥላቻዬ ላይ ፥ ለውጥ አያመጡም
መንጋ አእምሮዎች
ሀሳብን አይወልዱም ፥ በግል አያምጡም
አንዱ የወለደውን
ይዘው ይጮሀሉ ፥ አይደማመጡም።
#መንጋ_2
መንጋ አሳቢዎች
በምላስ ነው እንጂ ፥ በአእምሮ አይቆሙም
ከእረኛቸው እንጂ
በራሳቸው መንገድ ፥ በድፍረት አይተሙም
በቀቀኖች ናቸው ፥ የገደል ማሚቶ
ተቀብሎ መጮህ
ያውቃል ምላሳቸው ፥ አእምሯቸው ሞቶ።
#መንጋ_3
አብሮ መኖር እንጂ
አብሮ ማሰብ ማላው ፥ ሀሳብን አውጠንጣኝ
አእምሮ የቸረኝ ፥ በምላስ ያልቀጣኝ
ፈጣሪ ይመሥገን!
ከባርነት በፊት
ከመንጋ አስተሳሰብ ፥ ነፃ ስላወጣኝ !!!
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘