አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ለመንጋዎች_መንጋ_ግጥም

እኔ ሰው ስለሆንኩ
የግል አእምሮዬን ፥ አሳልፌ አልሰጥም
በመንጋ አስተሳሰብ ፥ ሀሳቤ አይዋጥም
ለመንጋዎችና
ለመንጋ አሳቢዎች ፥ አለኝ መንጋ ግጥም

#መንጋ_1
ብዙዎች ተስማምተው
በሔዱበት መንገድ
ትክክል ነው ብሎ ፥ አይነሳም እግሬ
ብዙዎች በህብረት
በጠሉት ነገር ላይ ፥ አይቀንስም ፍቅሬ
አመዛዝናለሁ
አስተሳስራለሁ
የግል አእምሮዬን ፥ ከደም ዝውውሬ።
ብዙዎች ሚወዱት
በጥላቻዬ ላይ ፥ ለውጥ አያመጡም
መንጋ አእምሮዎች
ሀሳብን አይወልዱም ፥ በግል አያምጡም
አንዱ የወለደውን
ይዘው ይጮሀሉ ፥ አይደማመጡም።

#መንጋ_2
መንጋ አሳቢዎች
በምላስ ነው እንጂ ፥ በአእምሮ አይቆሙም
ከእረኛቸው እንጂ
በራሳቸው መንገድ ፥ በድፍረት አይተሙም
በቀቀኖች ናቸው ፥ የገደል ማሚቶ
ተቀብሎ መጮህ
ያውቃል ምላሳቸው ፥ አእምሯቸው ሞቶ።

#መንጋ_3
አብሮ መኖር እንጂ
አብሮ ማሰብ ማላው ፥ ሀሳብን አውጠንጣኝ
አእምሮ የቸረኝ ፥ በምላስ ያልቀጣኝ
ፈጣሪ ይመሥገን!
ከባርነት በፊት
ከመንጋ አስተሳሰብ ፥ ነፃ ስላወጣኝ !!!

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘