#ቢታነፅ_ቢወቀር
እኔም አንድ ሰሞን
ልክ እንደ ሰሎሞን
“ሁሉም ከንቱ ከንቱ ነፋስን መከተል”
ሳይጥሉ መታገል፣ ሳይከብሩ መባተል
አያልሁ አጨልሜ
በራሴ ለግሜ
እፈላሰፍ ነበር።
ከዚያ አንቺን አገኘሁ
በጓሮ በር በኩል፣ ሰሎሞኔን ሸኘሁ
መፈጠሬን ወደድሁ
ነፋስ አሳድጄ
አንድ ቆቅ አጠመድሁ
ከፀሐይዋ በቻች፣ ግልገል ፀሐይ ፈጠርሁ
ለኦናው አምፖሌ፣ ብርሃን አበደርሁ
ማቅ የነበረው ጨርቅ፣ ሸማ ሆኖ ቆየኝ
ከንቱ የነበረው፣ አንቱ ሆኖ ታየኝ።
ለካስ
ጠቢብ ሲያስተምረው፣ መከራ ቢመክረው
አካሉና ልቡ ቢታነፅ፣ ቢወቀር
ሰው አቅሙን አያውቅም፣ ካልወደደ በቀር።
🔘በዕውቀቱ ስዩም🔘
እኔም አንድ ሰሞን
ልክ እንደ ሰሎሞን
“ሁሉም ከንቱ ከንቱ ነፋስን መከተል”
ሳይጥሉ መታገል፣ ሳይከብሩ መባተል
አያልሁ አጨልሜ
በራሴ ለግሜ
እፈላሰፍ ነበር።
ከዚያ አንቺን አገኘሁ
በጓሮ በር በኩል፣ ሰሎሞኔን ሸኘሁ
መፈጠሬን ወደድሁ
ነፋስ አሳድጄ
አንድ ቆቅ አጠመድሁ
ከፀሐይዋ በቻች፣ ግልገል ፀሐይ ፈጠርሁ
ለኦናው አምፖሌ፣ ብርሃን አበደርሁ
ማቅ የነበረው ጨርቅ፣ ሸማ ሆኖ ቆየኝ
ከንቱ የነበረው፣ አንቱ ሆኖ ታየኝ።
ለካስ
ጠቢብ ሲያስተምረው፣ መከራ ቢመክረው
አካሉና ልቡ ቢታነፅ፣ ቢወቀር
ሰው አቅሙን አያውቅም፣ ካልወደደ በቀር።
🔘በዕውቀቱ ስዩም🔘