#እህቴን_ሸጥናት!!
፡
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
#በጥላሁን
ወደ ሀዋሳ ለመሄድ ያኮበኮበው ሚኒባስ ሞጆ መስቀለኛ ላይ ቆሟል።
ጋቢና ሁለት ወጣት ሴቶች ተቀምጠዋል ከጋቢና ጀርባ ባለው ወንበር ላይ እድሚያቸው ገፋ ያለ ባልና ሚስቶች ሲቀመጡ•••
መሀለኛው ወንበር ላይ የ 18 አመት ልደቷን ካከበረች ከሶስት አመት ብዙ ያልተሻገረች ።
ከልጅነት ወደ አቅመ ሂዋንነት ገብታ ያላበቃች ። ለመላ አካላቷ ከፈጣሪ የተቸራት ውበት ተገልጦ ያላለቀ በመሆኑ ከእለት ወደ እለት ወገባ እየቀጠነ ዳሌዋ እንደፅጌሬዳ አበባ እየፈነዳ እንኳን ወጣት ወንድ ስድስት ልጅ የወለደ ሽማግሌ ባጠገቧ ካለፈ ቡሀላ አንገቱን ጠምዝዞ ዞሮ ደግሞ ደጋግሞ ለማየት የሚያስቆመው ምንም አይነት ሀይል እንዳይኖር የሚያስገድ ምትሀታዊ የውበት ሀይል ተላብሷል ይህ ውብ ዳሌዋ በተመጠነ ርቀት ግራና ቀኝ ሲንገጫገጭ አገጩ አብሮ የማይንገጫገጭ ወንድ በፀሀይም በባትሪም ተፈልጎ አይገኝም።
አይን ውስጥ ለመግባት ተቸግረው የኖሩት ጡቶቿ ዳርና ዳር ተቀባብለው ሲታዩ እይታን የሚፈትን ህቡእ ጨረር ይተፉ ይመስል ድንገት ያያቸው ወንድ ሁሉ•••
ልቡ ስንጥቅ አፎቹ ሳያስቡት ሙልት በምራቅ እስከዛሬ ከነበሩት ምራቆች እሷን እንዳየ አፉ ውስጥ የመነጨው ይህ ምራቅ ብሎት ጥፍጥ አጣጥሞ የማይውጥ ወንድ ማግኘት አይቻልም ባይባልም ይከብዳል ። ፀጉሯን አንዴ ወደ ምስራቅ አንዴ ወደ ምእራብ እየበተነች በውብ ጥርሶቿ ፍልቅልቅ ስትል እንኳን ያያት ወንድና ሴት እራሷንም ሳያስደነግጣት አይቀርም።
የጠየቃት የለም እንጂ ስለውበቷ ምን እንደሚሰማት የጠየቃት ቢኖር እሷ እራሷ የቁም መስታወት ፊት ለፊት ቆማ የራሷን ውበት ስትመለከት ያ ሁሉ የውበት ዝናብ እሷ ላይ መርከፍረፉን ማመን እየተሳናት መስታወት ውስጥ ያየችውን እይታዋን ለማረጋገጥ በእጆቿ ከላይ ወደታች •••
በመጀመሪያ አይኖቿን ነካ •••ዝቅ ትልና ከንፈሮቿን በሁለት ጣቶቿ ከፈት •••አንገቷን ዳበስ••• ቀልቁል ወርዳ ጡቶቿን ያዝ ለቀቅ••• ደሞ ወደ ታች ፈቀቅ ዳሌዋን ነቅነቅ••• በጣቶቻ ጨበጥ ጨመቅ እያደረገች መስታወት ውስጥ ያየችው ውበት በአካል እሷ ላይ መኖሩን ሳታረጋግጥ እንደማትተኛ ትነግረው ነበር።
ይቺ ልእልት ነች እንግዲህ ወደ ሀዋሳ ለመሄድ ሰው እስኪሞላ በሚጠባበቀው ሚኒባስ ውስጥ መሀለኛው ወንበር ላይ ብቿዋን የተቀመጠችው።
ረዳቱ ሚኒባሱ ሞልቶ እስከሚሄድ የቸኮለ ይመስላል ለሰከንዶች ሳያርፍ ይጣራል (ዝዋይ -ሻሸመኔ-ሀዋሳ የሞላ ነይ እሙዬ ሀዋሳ ግቢ ሞልቷል! አንዲት ቀጭን ጠቆር ያለች ሴት ገብታ የመጨረሻ ወንበር ጥግ ላይ እንደተቀመጠች ወድያው ሌሎች ሁለት ወንድ እና አንድ ሴት ባንድ ላይ መጥተው ተከታትለው ገቡ ።
ወንድ ቆንጂየዋን ልጅ ገና በመስታወት ውስጥ እንዳያት ነበር የደነገጠው አጠገቧ መቀመጥ ፈለገ ወደ ጫፍ ጠጋ አለች። ሆን ብሎ እየታከካት አልፎ ጥግ ላይ ተቀመጠ ።
ረዳቱ መጮሁን ቀጥሏል ። ከናዝሬት ወደ አዲስ አበባ የሚሄድ ዶልፊን እየተክለፈለፈ መጣና ቆሞ ሰው እሚጭነው ሚኒባስ አጠገብ እንደደረሰ ቆመ።
ሁለት ሴቶች ወረዱ ቀደም ብላ የወጣችው ሽቲ የለበሰች አይኗ ጎላ ጎላ ያለ መካከለኛ ቁመትና ውፍረት ያላት ሴት ስትሆን በቀኝ ጉንጯ የጫት ተርዚና እንደወጠረች ተከትላት ከወረደችው በዛ ያለ ጫት ከያዘች ጓደኛዋ ጋር መንገድ ላይ የጀመረችውን ወሬ እያወራችላት እና እየተሳሳቁ ወደ ሀዋሳ የሚሄደው ሚኒባስ ውስጥ ተያይዘው ገቡ ጫት የምትቅመው በፀጥታ የተሞላውን የዚህኛውን ሚኒባስ ድባብ ለመቀየር የፈጀባት ግዜ ተደላድላ እስክትቀመጥና አፏ ውስጥ ያለውን በውሃ ሉሉ አድርጋው ሌላ ጫት ቀንጥሳ እስክትጎርስ ብቻ ነበር።
"እዚህ ሚኒባስ ውስጥ የሚቅም ካለ ራብሳ መጠየቅ ይችላል ጫታችን ብዙ ነው !" አለች ሁሉም ወደሷ ተመለከቱና ተሳሳቁ። አብራት የመጣችው ሴት ረዳቱ በትርፍ ያስቀመጣት ቦታ አልመች ብሏት እየተቁነጠነጠች "ኧረ አንቺ ዝም በይ " የሚል መልክት በምልክት ስታሳያት
"ምን ችግር አለው የኛ ህዝብ ይሉኝታ ያጠቃዋል ጫቱን ሲያየው ለመቃም ተወስውሶ ፈርቶ ዝም ያለ አይጠፋም ብዬኮነው" ከማለቷ
"ልክ ብለሻል እንቅማለን ራብሽና ራብሽን " አሉ ከሴቷ ጋር የመጡት ሁለት ወጣት ወንዶች ። ባለጫቷ ፈጠን ብላ " እሄንን ነውኮ ያልኩት በሉ እንኩ" ብላ ስትሰጣቸው ሚኒባሱ ውስጥ ያልሳቀ ቢኖር ከሹፌሩ ጀርባ የተቀመጡት በድሜ ገፋ ያሉ ባልኖ ሚስቶችና በትርፍ ገብቶው አጠገባቸው ተንጠልጥለው የተቀመጡት ሙሉ ሽበት የወረሳቸው የድሜ ባለ ፀጋ አዛውንት ብቻ ናቸው። አዛውንቱ ሰውዬ ጫት የምትቅመውን ሴት ገልመጥ አደረጓት።
ፀጥ ብሎ የነበረው ሚኒባስ ተሟሟቀ ጫወታው ደራ ። ረዳቱ ገብቶ በር ዘጋ ሹፌሩ ቀበቶውን አስሮ ሞተር እንዳስነሳ ። አንድ ነጭ ላንድክሩዘር መኪና እያሽከረከረ የመጣ ፈረንጅ ወደ ሚኒባሱ እየተጠጋ እጁን በማውጣ ያዘው አትሂድ የሚል ምልክት ለሹፌሩ ስላሳየው ግራ በመጋባት ነዳጁ ላይ ያለውን እግሩን ሳይጫን ጠበቀው ።
ፈረንጅ በፕላስቲክ መሰል ማሸጊያ የያዘውን ኢንጆሪ ይዞ በሚኒባሱ በር በኩል ሲመጣ የሚኒባሱ ረዳት በሩን ከፈተው። ከወጣትነት ወደ ጉልምስና ሊሸጋገር ድንበር ላይ የደረሰው መልከመልካም ፈረንጅ ጠጋ አለና ኢንጆሪውን በሁለት እጆቹ ይዞ ሚኒባሱ ውስጥ መሀለኛው ወንበር ላይ ወደተቀመጠችው ቆንጆ ሴት በመዘርጋት " ካን ዩ አክሴፕት ማይ ጊፍት ፕሪቲ ገርል ፕሊስ!" ልጅታ እጃን ዘርግታ ከመቀበል ተቆጠበች ሁሉም ግራ ተጋባ ። ጥያቄውን ደገመው ልጅቷ አሁንም እጇን አልዘረጋችም አልተቀበለችውም።
እሄን ግዜ " ታውቂዋለሽ የኔ ልጅ?" አሉ ሽበታሙ አዛውንት " ኧረ አላውቀውም እኔም ከናንተው ጋር አሁን ገና ነው ያየሁት" አለች
" እንዴ ባታውቂውስ ፈረንጅ እኮ ነው ይልቅ በጥዋት ያለሽበት ድረስ ሰተት ብሎ የመጣውን አሜሪካ ወደ ምትባል ገነት ወደሆነች ሀገር መግቢያ ቁልፍ የያዘ ሪስቅ አትግፊ ተቀበይው እዚ እንደሰርዲን ሚኒባስ ውስጥ ታጭቆ መሄድ አልሰለቸሽም እንዴ ይልቅ ተቀበይውና ወርደሽ መኪናው ውስጥ ግቢ እሄ እድል አያማጥሽ!" አለች የምትቅመዋ ሴት
💫ይቀጥላል💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏

👍5
#እህቴን_ሸጥናት!!
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
፡
#በጥላሁን
" እንዴ ባታውቂውስ ፈረንጅ እኮ ነው ይልቅ በጥዋት ያለሽበት ድረስ ሰተት ብሎ የመጣውን አሜሪካ ወደ ምትባል ገነት ወደሆነች ሀገር መግቢያ ቁልፍ የያዘ ሪስቅ አትግፊ ተቀበይው እዚ እንደሰርዲን ሚኒባስ ውስጥ ታጭቆ መሄድ አልሰለቸሽም እንዴ ይልቅ ተቀበይውና ወርደሽ መኪናው ውስጥ ግቢ ይሄ እድል አያማልጥሽ!" አለች የምትቅመዋ ሴት •••
እረ ልጄ ተይ ልጅቷን አታጣድፊያት በሰው ህይወት እንዲህ አቅልሎ መወሰን በጎም አይደል እናንተ ሰዎች እስቲ ቢያንስ በራሷ መንገድ ትወስን ይቺ ልጅ እኮ ሰው እንጂ እቃ አይደለችም !" አሉ አዛውንቱ ልጅቷ በመውረድና ባለመውረድ ስትወዛገብ ሲመለከቷት ሁኔታው አላምር ብሏቸው።
ሹፌሩ ተበሳጨ "ሰአት አትግደይብኝ እናቱ ወይ ተቀበይው ወይ ረዳቱ በሩን ይዝጋውና እንሂድ"
ከቦታዋ ላይ ሳትነሳ እንጆሪውን ተቀበለችው ፈረንጁም አመስግኖ ወደ መኪናው ሄደ።
የሚኒባሱ በር ተከረቸመ ።ጉዞ ወደ ሀዋሳ ተጀመረ።
ፈረንጁም ላንድክሩዘር መኪናውን ካቅም በታች እየነዳት ከሚኒባሷ ጀርባ በቅርብ ርቀት መከተል ጀመረ።
"እሄ ነጭ ፎንቃ ገብቶለታል የሚፋታሽ አይመስለኝ እየተከተለን ነው ሲል " ሁሉም ዞረው ተመለከቱ እውነትም ተጠግቶ እየተከተላቸው ነበር።
"ኧረ ተይ አንቺ ልጅ እሄ ፈረንጅ ትግስቱ አልቆ ካጠገባችን ከተሰወረ ቡሀል ቆጭቶሽ እንደ በረዶ ከምትማሚ አሁኑኑ ካይንሽ ሳይርቅ ወስኚ"
ልጅቷ ከውጪ እንደምታምረው ውስጣዊ ማንነታ ያን ያህል አልነበረም ምክንያቶቹ ደግሞ እድሜ ፣ አስተዳደግ እና አከባቢያዊ አመለካከት ያሳደሩባት ተፅእኖዎች ናቸው በዚህም ምክንያት ጫት ቃሚዋ ስታነሳሳት ለመሄድ ትነሳሳና ሽማግሌው ሲቃወሙ መልሳ በረድ ትላለች የራሷ የሆነ አቋም አልነበራትም ንፋሱ ወዳወዛወዛት ትወዛወዛለች።
ሁለቱ ከምትቅመው ላይ ጫት የተቀበሉት ወጣቶች እና ሴቷ ሂጂም አትሂጅም ቢሉ "ምናገባህ! ምናገባሽ! አናንተ ናችሁ እንዴ በኔ ሂወት ወሳኙ ብትለኝስ ብትለንስ " በሚል ሀሳብ ፈርተው ጥጋቸውን ይዘው ቢቆዩም ልጅቷ በውጪ ከሚታየው አስደንጋጭ ማራኪ ውበቷ ውስጥ ያለው ማንነቷ ገና ያልበሰለ መሆኑን ከሁኔታዋ ስለተረዱ የጫት ቃሚዋን ሀሳብ ደጋፊ ሆነው ክርክሩን ተቀላቀሉ።
ጫት እምትቅመው ወደአዛውንቱ ሰው እጇን እያወዛወዘች "አባባ እኔ በበኩሉ እሄ ወግ ባህል ስርአት እያላችሁ በማይመለከተው ቦታ ሁሉ እያስገባችሁ የራሳችሁን ግዜ ተጠቅማችሁ በኛ ግዜ እንደፈለግን እንዳንሆን በወግና ባህል ሰበብ በማይበጠስ ሰንሰለት እጅና እግራችንን አሳስራችሁ ቆማ ቀር ሴት የምታበረክቱበት አካሄዳችሁ በፍፁም አይመቸኝም አይገርሞትም።
በዚህ ግዜ! ሽበታሙ ሰውየ ብቻ ሳይሆኑ ከጎናቸው የተቀመጡት እስካሁን ያልተነፈሱት እድሜ ጠገብ ባልና ሚስቶች ተነሱባት ጫት ቃሚዋ ላይ ።
" ልጅሽ ብትሆን አንድም ቀን አይተሽው ለማታውቂው ሰው ይሁን አውሬ ላለየሽው ሰው አሳልፈሽ ትሰጫት ነበር ! ስላንቺ አይመለከተንም ልጅቷን ወደሳት ለመገፍተር? ምን አጣደፈሽ ?ሌላ አላማ አለሽ ? ተረባረቡባት•••
ፈረንጁ በዚህ መሀል ፍጥነት ጨመረና በሚንባሳ ጎን ትይዩ እየሄደ አንገቱን አውጥቶ በሚኒባሱ መስታወት ወደ ውስጥ ለልጅቷ ከንፈሮቹን የእጆቹ ጣቶች ላይ አስቀምጦ እፍፍፍ ብሎ ላከላትና እስም እንደንፋስ ካጠገባቸው እፍፍ ብሎ ጥሏቸው ሽምጥ ጋለበ ። የልጅቷ ፊት ተቀያየረ ።
በወጣቶቹ በኩል ጩኸት በረከተ •••
"አቦ ዝም ብላችሁ ነው እሄን የመሰለ እድል ያስመለጣቹሀት
አመት አወቀችው አንድ ቀን አወቀችው ምን ልዩነት አለው?
አመትም ቢሆን የሚጀምረው ባንድ ቀን ነው!
አንድ ብለው ሳይጀምሩ አመት የሞላቸው አሉ? እስቲ ንገሩን ?
"ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም ይላል የኛው አባባል እንዲህ ቢሆንስ እንዲያ ቢሆንስ ብሎ መጥፎ መጥፎውን ከማሰብ እሄ ሰውዬ እሷ ባታውቀውም እሱ ለብዙ ግዜ ሲከታተላት የቆየ አፍቃሪ ነው ብሎ ደግ ደጉን ማሰብስ አይቻልም ያለው ማነው?
በተለይ ጫት ቃሚዋ የፈረንጁ መሄድ እጅግ በሚገርም ሁኔታ ነበር ያንገበገባት ወደ ልጅታ ተነስታ ለመሄድ እየዳዳት •••
" ቆጨሽ አደል ፉትሽ ያስታውቃል አሁንም መጠቀም ከፈለግሽ እድሉ አለሽ ብዙ አራቀንም ሹፌር በናትህ በመጨረሻው ፍጥነት ንዳው እንድረስበት!" ስትል•••
"እንዴ ኧረ ልጆች አሳዳጊዎች ነን እንዳትገለብጠን !ቀስ ብለህ ንዳ ሹፌር ካበዱት ጋር አብረህ አትበድ የኔ ልጅ ቀስ እያልክ ንዳ!" አሉ ባልቴቷ
"እቦ መሞት ካለብን ሮጠም ቆመም መሞታችን አይቀርም " አለች ቃሚዋ በንዴት
ለደቂቃዎች ሁሉም በተከራከሩበት ሀሳብ ዙሪያ እያሰላሰሉ ፀጥታ ሰፈነ በመሀል አንድ ኩርባ መንገድ ላይ ሚኒባሱ እጥፍ እንዳለ ፈረንጁ መኪናውን ካንድ ዛፍ አጠገብ አቁሟት ጥቁር መነፀሩን እንደገረገደ እግሮቹን አጣሞሮ ዛፉን በመደገፍ የህንድ አክተር መስሎ ቆሟል ። ተቀወጠ ።
"ያውና!
ያውና!
ያውልሽ ያው ፈረንጅ "
ሚኒባሷን ሶስት እግሯን ሰቅለው ባንድ እግሯ አቆሟት ማለት ይችላል ።
ሚኒባሱ ፈረንጁን ሲያልፈው ተንጫጩ አቆመው ውረጂና ሂጅ ጨቀጨቋት አዛውንቱ ሰውዬ በሩን ተደግፈው አለቅ ሲሉ ጫት ቃሚዋ የሚኒባሷን የውሀላ በር ከፍታ ልጅታን በዛ በኩል አስወጧት
"ለማንኛውም ስልኳን ተቀበያት አለች ከወንዶቹ ጋር የመጣችው ሴት ጫት ቃሚዋን ።
ተቀበለቻት ።
ሚኒባሱ ፊት ፊት ፈሩንጅ እና አጠገቡ የተቀመጠችው ቆንጆ ሀበሻ ያሉበት መኪና ከውሃላ ሆኖ ጉዞ ቀጠለ።
" ግን በምን ይግባባሉ?" አለች ጋቢና ከተቀመጡት አንዷ
ጫት ቃሚዋ ዘወር ብላ ተመለከተችና " እሄው እየሳቀች እኮ ነው ባይግባቡ ትስቅ ነበር ደሞ የስ እና ኦኬ ማለት ምን ይከብዳል"
ፈረንጅ ከቆይታ ቡሀላ ያን ውሃ የመሰለ መኪና ባየር ላይ እያከነፈ ልጅቷን ይዞ ሚኒባሷን ጥሎ ከአይናቸው ተሰወረ። እሄን ግዜ ከልጅቷ አጠገብ የነበረው ወጣት•••
"እስቲ ለማንኛውም ስልኳን ስጪኝ ልደውልላት" አለ
"አዋ ደውልላት እስቲ በናትህ አልችና ስልኳን ሰጠችው ጫት የምትቅመዋ ሴት።
ቁጥሩን ስልኩ ላይ ከትቦ ሲደውል ያየውን ማመን አልቻለም ነበርና•••
" እንዴ ያባቴ ስም ወጣኮ ምንድን ነው እሄ ስልክ እስቲ ደግመሽ ንገሪኝ "
ደግማ ነገረችው ልክ ነው ያባቱ የድሮ ስልክ እየተርበተበተ ቁጥሩ ላይ ሲደውል ተነሳ
"ሄሎ " አለች ልጅቷ "
ያባቱን ስም በመጥራት ታውቀው እንደሆን ሲጠይቃት ።
"አዋ አባቴኮ ነው እንዴት አላውቀውም ምን አይነት ጥያቄ ነው !"አለችው •••
ስልኩን ከጆሮው ላይ ለቀቀውና "አባቴ ነው አለችኝ አባቴ ከናቴ ውጪ የወለዳት እህቴ ነች ማለት ነው ልጅቷ " አለ
ሹፌሩ በሰማው ነገር ደንግጦ ሲጢጢጢጥ አደረገና ሚኒባሷን ገተራት••

👍2
#እህቴን_ሸጥናት!
፡
፡
#ክፍል_ሶስት (የመጨረሻው ክፍል )
፡
፡
#በጥላሁን
ጫት ቃሚዋ ልታምነው አልፈቀደችም
"አቦ ዛሬ ደግሞ መቃም ሳይጀምር የሚመረቅን ሰው ነው እንዴ ያጋጠመኝ ! ወንድሜ ብላ ስላወራችው እህቱ የሆነች መሰለው እንዴ !
ኧረ ጓደኛዬ አምጪው እስቲ ያንቺን ስልክ የኔ ጨላ ስለለው ደውልላት ብዬ ቁጥሯን ብሰጠው ያጃጅለናል እንዴ! ባንቺ ልደውልላትና አጠገቧ የነበረው ልጅ ገና ፈረንጅ ከመጥበሷ እህቱ አርጓት እንዳረፈው ነግሬ ላስቃት በናትሽ አምጭው ስልክሽን !" አለች ሳቅ እየታገላት።
ሰጠቻት። ደወለች•••
"ሄሎ የኔ ቆንጆ እንዴት ነው ምቾቱ ?
ደሞ አጠገብሽ የነበረውን ልጅ ምን ብለሽው ነው? ባክሽ ! መጀመሪያ ቁጥርሽን ሰጥቼው ስልኩ ላይ እንደፃፈው ያባቴ ስም ወጣ ሲለን ምርቃና ነው ብለን አለፍነው ሲያዋራሽ ጭራሽ ብሶበት ያባቴ ልጅ እህቴ ነች ብሎ በሳቅ ሊገለኝ ፈረንጅ መጥበስ ወንድም ያበዛል አየሽ ኪኪኪ•••"
የልጅቷ ጥያቄ ሳቋን ባጭር ቀጨው•••
" ያባቱ ስም ማነው?አለቻት።
"እንዴ አንቺም ተጠራጠርሽ እንዴ ?"አለችና ልጁን ጠይቃ ነገረቻት
" አመሰግንሀለሁ አምላኬ ! ልክ ነው ወንድሜ ነው! በብቸኝነት ስሰቃይ አድጌ አባቴ ወንድም እንዳለኝ ከነገረኝ ጀምሮ ስንት አመት ሙሉ ነገ ዛሬ እያለ አሳቀቀኝ !ፈጣሪ ፍቃዱ ከሆነ ሰዎች ረድኑንም አልረዱንም በምክንያት ምኞታችንን እና ፍላጎታችንን ለማሳካት የማይታሰበውን አጋጣሚ እውነት ያደርገዋል ። ስሙ ዳግም ነው አይደል?"
እኔ ምን አቅልሻለሁ ስምህ ዳግም ነው እንዴ? ስትለው በድንጋጤ እንደፈዘዘ በአውንታ ጭንቅላቱን ነቀነቀ።
ጫት ቃሚዋ ጩኸቷ ረገብ አለ። ቀዝቀዝ አለች። በረደች።
አዋ አለኮ ወንድምሽ ነው ማለት ነው" እያለቻት በመሀል ድንገት ፈረንጁና ልጅቷ መጨቃጨቅ ጀመሩ ።
ጫት ቃሚዋ ተደናግጣ "እንዴ ምን ሆኑ አሁን ባሁን!" እያለች ሁሉም እንዲሰሙ የስልኩን ድምፅ አጎላችው።
"ሄይ ኢት ኢዝ ኢነፍ ስቶፕ ቶኪንግ ኤንድ ጊቭ ሚ ዩር ፎን" አለ በቁጣ ፈረንጁ
" አቅርቢው እስቲ ላውራው•••
ምንድን ነው ምትለኝ ቆይ እስቲ በናትህ ወንድሜን ላዋራው " የልጅቷ መልስ ነበር እሄን ግዜ ፈረንጅ እንግሊዘኛውን አሽቀንጥሮ የኛኑ አማርኛ ያዥጎደጉደው ጀመር••
"ትሰሚያለሽ አንቺ ልጅ ካሁን ቡሀላ ማንንም ማዋራት አትችይም ወሬሽን ተይና ስልኩን ለኔ ስጪ!" አላት
ልጅቷም ሚኒባስ ውስጥ ያሉት ሰዎችም እኩል ደነገጡ።
ፈረንጁ መኪናውን ድንገት ፍሬን አንቆ ሲያቆመው ከፊት መስታወት ጋር ከመላተም ቀበቶው የታደጋት ልጅ ጮኸች!
"ስልኩን አምጪ!" ብሎ በጥፊ ከመታት ቡሀላ ስልኳን ተቀብሎ ዘጋው።
ሚኒባሱ ውስጥ ድምፅ ማጉያ ላይ የነበረው ስልክ ብቻ ሳይሆን ሁሉም በድንጋጤ ፀጥ አሉ።
ወንድምየው ወይኔ እህቴ ከሷ ፍላጎት በላይ እኛ ነን እህቴን ገፍትረን ላውሬ አሳልፈን የሸጥናት እባክህ ሹፌር አፍጥነው እና ሻሸመኔ ፖሊስ ጣብያ እናመልክት" አለ እየተርበተበተ።
ፖሊስ ጣብያ እንደደረሱ ልጅቷ ሞባይሏን ከነጠቃት ቡሀላ ከዋናው ሞባይላ ውጪ ቦርሳዋ ውስጥ አነስ አና ረከስ ያለች ሞባይል ይዛ ስለነበር መጀመሩያ ወንድሟ የደወለላት ግዜ የወንድሟን ቁጥር ያኛው ስልክ ላይ ያለው ሲም ካርዷ ሙሉ ስለነበር እዚቺኛዋ ስልኳ ላይ ባለው ሲም ላይ ሳያስተውላት ይዛው ነበርና ሳያያት ቀስ ብላ ከቦርሳዋ በማውጣት ስትነካካ ድምፅ እንዳይሰማ ፈጠን ብላ ዝም በዝምታ የሰጧትን እንድትቀበል አፋን ከዘጋቻት ቡሀላ ፈረንጁ በስልክ ከሌሎች ጋር የሚያወራውን እየሰማች ለወንድሟ ያለችበትን ሁኔታ የሚገልፅ የድረስልኝ መልክት ፅፋ ላከች•••
"ወንድሜ እባክህ ድረስልኝ ስልኩን ከቀማኝ ቡሀላ መኪናውን አዙሮ ራቅ ወዳለ አንድ ጫካ ይዞኝ እየገባ ነው ስልክ ሲያወራ እንደሰማሁት ችግሩ ከአባታችን ጋር ነው ስልክ ደወለና •••
"" እዛው ናችሁ አደል ልጅቷን ይዧት እየመጣሁ ነው ። እኔን መጠቀማችሁ ልክ ነበር በቀላሉ ነውኮ ሳር እንዳየ በግ የተከተለችኝ አሁኑኑ ላቧታ ደውሉና ሰነዱ ላይ እንዲፈርም ንገሩት አልፈርምም የሚል ከሆነ ልጁን አቃጥለን ይህን ውብ ገላ ወደ ከሰል ቀይረን በፎቶ እንደምንልክለት አስረዱት ካላመነ ድምፃን እንደደረስኩ ይሰማዋል ሲል ነበር ፈርቻለሁ ወንድሜ የማልተርፍ ከሆነና መሞቴ ግድ ከሆነ ግን ለብዙ ግዜ ላየው ስመኝ የነበረውን አንተን ወንድሜን አጠገቤ ተቀምጠህ አይቼህ ስለሞትኩ •••
አልጨረሰውም ሞባይሉን ወርውሮ የፖሊስ ጣብያው ግርግዳ ላይ ለጠፈው እንክትክት አለ የእህቱን መልክት እጁ እየተንቀጠቀጠ ሲያነብ
እያዳመጡ የነበሩት ፖሊሶችና ሚኒባስ ውስጥ ለነበሩት ሰዎች ቆሌያቸው ተገፈፈ።
ጫት ቃሚዋ ሴት ሹልክ ብላ ካጠገባቸው ተሰወረች።
ጓደኛው ሌላ መልክት ብትልክስ ብሎ ስላሰበ ከተሰበረው ሞባይል ውስጥ ሲምካርዱን አወጣና እሱ ስልክ ውስጥ አደረገው።
ፖሊሶቹ በመደዋወል የፈረንጁ መኪና የት አከባቢ ላይ ሲደርስ ከዋናው መንገድ እንደወጣ ፍንጭ አገኙ።
ወንድሟ እና አብረውት የመጡት ሁለት ጓደኛቹ በመሆን ወደ ቦታው ሲንቀሳቀሱ ከጫት ቃሚዋ ሴት በስተቀር ሌሎቹ መልክም እድል ተመኝተውና ስልኩን ተቀብለው በመጡበት ሚኒባስ ወደ ሀዋሳ ሄዱ።
ፖሊሶቹ የመኪናውን ዳና እየተከተሉ መኪናውን አገኙት ነገር ግን ውስጡ ሰው አልነበረም የፖሊስ መኪናውም ከዛ በላይ የሚሄድበት መንገድ አልነበረምና
"ከዚህ ቡሀላ ያለው ስራ የኛ ብቻ ነው እናንተ እዚሁ ጠብቁን!"
በማለት ወንድሟን እና ጓደኛቹን እዛው ጥለዋቸው በተለያየ አቅስጣጫ በመሰማራት ጫካውን ወረሩት።
ከደቂቃዎች ቡሀላ የቶክስ ድምፅ ተሰማ ። ወድያው ከሻሸመኔ እየከነፈች የመጣችው አንቡላንስ በጭንቀት ወደ ሚፀልዩት ወንድሟ እና ጓደኛቹ ጋር ተጠግታ ቆመች ። ሁለት ፖሊሶች ተሸክመው ያመጧት ሴት ወደ አንቡላንሱ ሲያስገቧት ቀና አለችና ወንድሜ ብዙ አልተጎዳሁም እሺ ተርፊያለሁ አለችው።
💫ተፈፀመ💫

👍3❤1