አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ድል

መብትና ነጻነት
ክብርና ማንነት
የነሱ የሆነውን የሚሹ ለማግኘት
ሲገፉ ሲረገጡ
ቁብ እንኳ ሳይሰጡ
መቻል አጠንክሮ .
ጫንቃቸው ካበጡ
ታግለው የደከሙ
ጮኸው ሰሚ ያጡ
ግዜው ምን ቢነጉድ
ቢመሻሽ ሲጨልም
ከድል ደጃፍ ደርሰው
መንጋቱ አይቀርም፡፡
#ድል

ካሰቃቂ ጦርነት በኋላ
ከሚዘገንን እልቂት
ከሚጎመዝዝ ውድመት
የሰው ልጅ እራሱን ሲያታልል
አገኘሁ ይላል ጣፋጭ ድል
ጠባሳው በማይሽር ቁስል
መኮፈስ ይቻል ይመስል፡፡😏

🔘መንግስቱ በስር🔘
#ድል_እና_ዕድል

የ”የት ነህ ? የማነህ?” ነገር ጭጭ አለ
የ”እንምጣም የእንሂድ” ጥሪው አቆመ
መልእክት ጦማሩን ተወ–ከዙረት ተቀያየመ
ቅብዝብዝ ዓይኖቹ ተረጋጉ-ከአደባባዩ ተሠወረ
ስጋጃው ላይ ጋደም ብሎ -የቀኝ እጁን ወረወረ
ለብቻው ሱባኤ ገባ-ከዕድል ጋር መኖር ጀመረ
“ጉድ!” አለ የሀገሬው ሰው
“ጉድ!” አለ ባንድ ላይ ቆሞ
ጠየቀ መልስ ላያገኝ ጠየቀ ደግሞ ደጋግሞ
እሱ ግን ራሱን ገዝቷል-አደብ ከገዛች ጋራ
የሀገር መንደሩን ጉድጉድታ-ለምንስ ለራሱ ያውራ?
የተኛችበትን ስጋጃ-በወርቀዘቦ እያስጌጠ
እንደተኛች እያቀፋት -ሙሉ ፍቅሩን እየሰጠ
የቀኑ አልበቃ ሲለው ደግሞ ሌሊት ተቀመጠ
“ጉድ!” አለ የሀገሬው ሰው በአደባባይ ተሰልፎ
ድንገት ቢያየው የሱን ጐጆ - ያለወትሮው ተቆልፎ
የሱ ግን የተቆለፈው -የጐጆው መቃኑ ሳይሆን-የቀልቡ ደጃፍ ነበረ
የዚህ ልዩነት ያልገባዉ–አደባባይ ወቶ አደረ
“ጉድ!” የሚል የጉድ ጩኸቱም
እንደጉድ ለጉድ ከረረ
እርሱ ግን ከጉድ ተጣልቶ-በገዱ ከቀልቡ ታርቋል
ስጋጃው ላይ እንዳቀፋት-እድሉን “ገዴ” ይላታል
እያያትም አይጠግባትም–እያቀፋት ይስማታል
ይህን ጽድቀት ከሱ በላይ-የትኛው ሰው ያውቅለታል ?

🔘ሰለሞን ሳህለ🔘
👍10