ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
✞✞✞ እንኩዋን ለካህኑ #ሰማዕት_አባ_ኦሪ ዓመታዊ
የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_ኦሪ_ቀሲስ "
ይህ ቅዱስ አባት የዘመነ ሰማዕታት ፍሬ ነው:: በዘመኑ
(በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን) #ክርስቲያን መሆን ብቻውን
ለሞት እንደሚያበቃ ወንጀል ይቆጠር ነበር:: በጊዜው
ክርስቲያን ከመሆን በባሰ መንገድ #እረኛ_ካህን ሆኖ
መገኘት በጣም ከባድ ነበር::
ከመነሻውም ያን ጊዜ ክህነት የሚሰጠው በሕዝቡና
በሊቀ ዻዻሱ ምርጫ ነበር እንጂ እንደ ዘንድሮ "እኔን ሹሙኝ" ማለት ልማድ አልነበረም:: ምዕመናንም
እረኛቸውን ሲመርጡ በጉቦ: በዝምድና አይደለም::
በርትቶ የሚያበረታቸውን: ለመንጋው ራሱን አሳልፎ
የሚሰጠውን ይመርጣሉ እንጂ::
ያልሆነ ሰው ለክህነት ቢመረጥ አንድም ክዶ ያስክዳል:
ሲቀጥልም ለሕዝቡ መሰናክል መሆኑ አይቀርም::
በጊዜው ( #በዘመነ_ሰማዕታት ) የነበሩ ካህናት የቤት
ሥራቸውም ማስተማር ብቻ አልነበረም:: በድፍረት
በምዕመናን ፊት አንገታቸውን ለሰይፍ መስጠት
ይጠበቅባቸው ነበር እንጂ::
ይህንን በገሃድ መፈጸም ከቻሉ አበው አንዱ ደግሞ አባ
ኦሪ ቀሲስ ናቸው:: ቅዱሱ ተወልደው ባደጉባት ሃገረ
#ስጥኑፍ (የግብጽ አውራጃ ናት) መጻሕፍትን የተማሩ:
ተወዳጅ እና ደግ ሰው ነበሩ::
አባ ኦሪ ገና ከወጣትነት ቀዳሚ ግብራቸው መንኖ
ጥሪት (ምናኔ) ነበር:: በንጽሕናቸው ደስ የተሰኙ
ምዕመናንም "ቅስና ተሹመህ ምራን: አስተምረን"
ቢሏቸው አበው ውዳሴ ከንቱን አይፈልጉምና "አይሆንም" አሉ::
ነገሩ ፈቃደ እግዚአብሔር ነበረና አባ ኦሪ ቅስናን ተሹመው ያገለግሉ ገቡ:: ሕዝቡን በማስተማር:
በመምከር: ደካማውን በማጽናት ብዙ ደክመዋል:: ከቅድስናቸው የተነሳ ቅዳሴ ሊቀድሱ ሲገቡ #ጌታችን በገሃድ ይገለጥላቸው ነበር:: ሠራዊተ መላእክትም
ከበው ይነጋገሯቸው ነበር::
#ሥጋውን_ደሙን በማቀበልም ተግተው ዘመናት
አለፉ:: ቆይቶ ግን ያ በዜና ይሰሙት የነበረ መከራ
( #ሰማዕትነት ) በደጃቸው ደረሰ:: በጊዜው ብዙ ሰው
በሰማዕትነት አለፈ:: አባ ኦሪም ወደ #ቤተ_እግዚአብሔር
ገብተው ስለ ራሳቸውና ሕዝቡ ጽናትን: ደኅንነትን ለመኑና
ከቤተ ክርስቲያን ወጡ::
በቀጥታ የሔዱትም ወደ #ዐውደ_ስምዕ (የምሥክርነት
አደባባይ) ነበር:: በመኮንኑ ፊት ቀርበው "#ክርስቶስ
አምላክ: ፈጣሪ: የሁሉ ጌታ ነው:: የእናንተ ጣዖት ግን
ጠፊ: ረጋፊ: ወርቅ: ብር: እንጨትና ድንጋይ ነው" ሲሉ
በድፍረት ተናገሩ:: መኮንኑም ከአነጋገራቸው የተነሳ ተቆጥቶ ሥቃይን አዘዘባቸው:: ወታደሮቹ ይሆናል ያሉትን ማሰቃያ ሁሉ
#አባ_ኦሪ ላይ ሞከሩ:: በሁዋላም ወደ ጨለማ እሥር
ቤት ወስደው ጣሏቸው:: በእሥር ቤት ውስጥም ድውያንን ፈወሱ: ተአምራትን ሠሩ:: ይሕንን ዜና የሰሙ አሕዛብ ብዙ ድውያንን ሰብስበው መጡ:: ቅዱሱም ሁሉን በጸሎታቸው ፈወሱ:: በዚህ
ምክንያትም ብዙ አሕዛብ ወደ ክርስትና መጥተዋል::
በክርስቶስ አምነውም ለክብር በቅተዋል:: ቅዱሱንም ከእሥር ቤት አውጥተው ብዙ ካሰቃዩዋቸው በሁዋላ በዚህች ቀን ገድለዋቸው ሰማዕትነትን
አግኝተዋል:: #በአክሊለ_ጽድቅ ላይ #አክሊለ_ካህናትን :
#በአክሊለ_ካህናትም ላይ #አክሊለ_ሰማዕታትን
ደርበዋል::
#አምላከ_ቅዱሳን_በአባቶቻችን_ጽናት_ያጽናን::_ጸጋ_በረከታቸውንም_ይክፈለን::
💚💛 ቅድስት ሣራ ብጽዕት💛❤️
አበው እናታችን ሣራን " #ቡርክተ_ማሕጸን " ይሏታል::
(የቅዱሱ ዘር የይስሐቅ እናት ናትና) በዚያውም ላይ የደጉ
ሰው የአብርሃም ሚስት ናት:: ልክ በዓለም ታሪክ "ከጠንካራና
ስኬታማ ወንዶች ጀርባ ጠንካራ ሴቶች አሉ" እንደሚባለው
ከአብርሃም አባታችን ስኬታማ የቅድስና ሕይወት ጀርባ
ብጽዕት ሣራ አለች::
ለአብርሃም አባታችን መጽሐፍ የተናገረው ክብር ሁሉ
ለቅድስት ሣራ ይገባታል:: አንድም ገንዘቧ ነው:: ቅድስቷ እናት
ደጉ አብርሃምን ያገባችው ገና በከላውዴዎን (በ2ቱ ወንዞች
መካከል) ሳለ ነው:: ገና ከልጅነቷ ጀምራ አብርሃምን "ጌታየ"
እያለች ታገለግለው እንደ ነበር ቅዱስ መጽሐፍ ይናገራል::
(1ዼጥ. 3:5)
በዚህም ከብራበታለች: ገናበታለች እንጂ አልተጐዳችበትም::
አብርሃም ወደ ካራን ሲወጣ "ለምን?" አላላችም:: እንዲሁ
ለፈቃደ እግዚአብሔር ታዘዘች እንጂ:: በካራን ታራን ቀብረው:
በፈጣሪ ትዕዛዝ ወደ #ከነዓን ሲፈልሱም ቅድስት ሣራ
አልተቃወመችም::
ለፈጣሪዋ ትዕዛዝና ለባሏ ስትል ርስቷን: ሃገሯን: ዘመዶቿን
ሁሉ ትታ ሔዳለች:: ይሔውም በጐ ምናኔ ነው:: እናታችን ሳራ
በከነዓን የተመቸ ነገር አልገጠማትም:: ከአንዴም ሁለቴ
በረሃብና በድርቅ ምክንያት ወደ ግብጽ እና #ጌራራ ተሰደዋል::
በዚያም ፈርዖን "እነካለሁ" ቢል እግዚአብሔር ተቆጥቶ:
ፈርኦንንና ግብጽን በደዌ መታ:: በዚህም ክብረ ሣራን
ተመለከትን:: ከስደት መልስም በኬብሮን (በተመሳቀለ
መንገድ ላይ) ድንኩዋን ሠርተው የወጣ የወረደውን ሲያበሉ:
እንግዳ ሲቀበሉ ኑረዋል::
(ልብ በሉልኝ ይህን ትጋትና ደግነት ያሳየችውን ቅድስት ሣራን
ልናከብራት ይገባል)
እድሜ ዘመኗን ያሳለፈችው እንግዳ በመቀበል:
እግዚአብሔርን በማምለክ ነው:: ምንም እንኩዋ ማሕጸኗ
ለጊዜው ቢዘጋ ተስፋ አልቆረጠችም:: ለአብርሃምም ከአጋር እንዲወልድ ፈቃድ ሰጥታለች:: ዕድሜዋ 89 ዓመት በሆነ ጊዜ ሰይጣን እንግዳ እንዳይመጣ ለ3 ቀናት ቢያስቀርባቸው እንደ ባሏ እርሷም 3 ቀናትን ያለ ምግብ አሣልፋለች:: በ3ኛው ቀን ሥላሴን በቤቷ
አስተናግዳለች:: ስለ ክብሯም ከ3 መሥፈሪያ ዱቄት ለውሳ
ያዘጋጀችውን እንጐቻ ሥላሴ በልተውላታል:: (ምንም ሥላሴ
ምግብን ባይመገቡም)
የሥላሴ በዚያች ድንኩዋን ውስጥ መስተናገድ ታላቅ
ምሥጢር አለው:: ከግብዣው በሁዋላም እግዚአብሔር አለ:-
"አመ ከመ ዮም እገብእ ኀቤከ . . . እንዲሁ ከርሞ
እመለሳለሁ: ሣራ ወንድ ልጅን ትወልድልሃለች" አለው::
ያን ጊዜ ሣራ በውሳጤ ሐይመት (በድኩዋኑ ውስጥ) ሆና
ሰምታ ሣቀች:: ለምን ሳቀች ቢሉ:- እጅግ ደስ ቢላት! አንድም
ቢገርማት:: ይሕስ በምን ይታወቃል ቢሉ:- ልጇ " #ይስሐቅ "
የተባለው "ለእናቱ ሣቅን: ደስታን ያመጣ" ለማለት ነውና::
ሥላሴም:- "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ: እንዘ ትብል
ዓዲየኑ እስከ ይእዜ: ወእግዚእየኑ ልሕቀ: ቦኑ ነገር ዘይሰዓኖ
ለእግዚአብሔር - ሣራን ምን አሳቃት? ለእግዚአብሔርስ
የሚሳነው ነገር አለን" ብለዋል::
ቅድስት ሣራ በ90 ዓመቷ ይስሐቅን ወልዳ በቀሪ ዘመኖቿ
በደስታ ኑራለች:: በዚህች ቀንም በመልካም ሽምግልና ዐርፋ:
አባታችን #አብርሃም ከታላቅ ሐዘን ጋር ቀብሯታል:: ሐዋርያው
#ቅዱስ_ዻውሎስ ብጽዕት ሣራን በበጐ ምሳሌ መስሏታል::
(ዕብ. 11:11)
💚💛ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር💛❤️
በቤተ ክርስቲያን ያሉ አበው ሊቃውንት እንደሚሉት
ከቅዱሳን በቁመቱ የአባ #አርሳኒን ያክል ረዥም አልነበረም::
እርሱ እንደ ዝግባ ቀጥ ያለ ነበር:: በዚያው ልክ ደግሞ የቅዱስ
ዮሐንስን (ዛሬ የምናከብረውን) ያህል አጭር አልነበረም::
በዚህ ምክንያት ይሔው ለዘለዓለም " #ዮሐንስ_ሐጺር -
አጭሩ አባ ዮሐንስ" ሲባል ይኖራል:: ሊቃውንትም ቁመቱንና ቅድስናውን በንጽጽር ሲገልጡ:-
"ሰላም ሰላም ዕብሎ በሕቁ:
ለዮሐንስ ሐጺር ዘነዊኅ ሒሩተ ጽድቁ" ይላሉ:: "ቁመቱ እጅግ
ያጠረ: ጽድቁ ግን ከሰማይ የደረሰ ቅዱስ ዮሐንስን ሰላም
ሰላም እንለዋለን" እንደ ማለት ነው::

ቅዱሱ የተወለደው በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብጽ
ነው:: ወላጆቹ ምንም ከሥጋዊ ሃብት ድሆች ቢሆኑም ባለ
መልካም ክርስትና ነበሩና በጐውን ሕይወት አስተምረውታል::
ወደ ምናኔ የገባው ገና በ18 ዓመቱ ሲሆን የታላቁ አባ
ባይሞይ ደቀ መዝሙር ሆኖ ተጋድሎንና ትሕርምትን ተምሯል::
ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር በወቅቱ ከነበሩ ቅዱሳን ከቁመቱ ባሻገር
በትሕትናው: በትእግስቱና በመታዘዙ ይታወቅ ነበር:: አባ
ባይሞይ ይጠራውና ያለ ምንም ምክንያት ደብድቦ ያባርረው
ነበር:: እርሱ ግን "ምን አጠፋሁ?" ብሎ እንኩዋ ሳይጠይቅ
"አባቴ ሆይ! ማረኝ?" እያለ ከእግሩ ሥር ይወድቅ ነበር:: ለብዙ ጊዜ በተመሳሳይ ሲደበድበው: እርሱም እርሱው ተደብድቦ: እርሱው ይቅርታን ሲጠይቅ ኖረ:: አንድ ቀን ግን እንደ ልማዱ ሊገርፈው ሲሔድ 7ቱ ሊቃነ መላእክት ከበውት አይቶ ደንግጦ ተመልሷል::

#አባ_ባይሞይ ይሕንን ሁሉ የሚያደርገው ጠልቶት ወይ ክፉ
ሆኖ አይደለም:: አንድ ሰው የሌላኛውን ግፍ መቀበል ካልቻለ
ሰይጣንን ድል አይነሳም የሚል ትምሕርት ስለ ነበረ ነው እንጂ::

አንድ ቀን ቅዱስ ዮሐንስ ወደ መምሕሩ ቀርቦ "አባቴ ጅብ
ካገኘሁ ምን ላድርግ?" ሲል ጠየቀው:: (የአካባቢው ጅብ
መናጢ ነበር) አባ ባይሞይ ግን "ይዘህልኝ አምጣው" አለው:: ትዕዛዝ ነውና ቅዱሱ ወደ በርሃ ወርዶ: ጅብ አልምዶ ይዞለት መጥቷል:: ሌላ ቀን ደግሞ አባ ባይሞይ ቅዱስ ዮሐንስን ጠራውና
ተፈልጦ የወደቀ ደረቅ እንጨት ሠጠው:: "ምን ላድርገው
አባ?" አለው:: "ትከለውና እንዲያፈራ አድርገው:: ከዚያ
አምጥተህ አብላኝ" ሲል መለሰለት:: ይህ ነገር ከተፈጥሮ
ሥርዓት ውጪ መሆኑን እያወቀ ቅዱስ ዮሐንስ "እሺ" ብሎ
ወስዶ ተከለው:: ከዚያም ለ2 ዓመታት ሳይታክት ውሃ አጠጣው:: ውሃውን የሚያመጣበት ቦታ ደግሞ 10 ኪሎ ሜትር ያህል ከገዳሙ ይርቅ ነበር:: ቅዱሱ ላቡን እያፈሰሰ አሁንም ማጠጣቱን ቀጠለ:: በ3ኛው ዓመት ግን ለምልሞ አበበ: ደግሞም አፈራ:: ካፈራው
በኩረ ሎሚም ወስዶ ለመምሕሩ "አባቴ! እንካ ብላ" ብሎ
ሰጠው:: አባ ባይሞይ ግን ማመን አልቻለም:: እጅግ አደነቀ: አለቀሰም:: ወዲያው ያን ፍሬ ታቅፎ ወስዶ ለገዳሙ መነኮሳት አላቸው:- "ንሱ ብሉ: በረከትንም አግኙ:: ይህ የዛፍ ሳይሆን የመታዘዝ ፍሬ ነው::" ቅዱስ ዮሐንስ አባ ባይሞይ ቢታመም ለ12 ዓመት አስታሞታል::
መምሕሩ ከማረፉ በፊትም መነኮሳቱን ሰብስቦ የቅዱስ
ዮሐንስን እጅ አስጨበጣቸው:: "ይህ የያዛችሁት እጅ የሰው
ሳይሆን የመልአክ እጅ ነው" ብሏቸው ዐርፏል:: ቅዱስ
ዮሐንስም ከዓመታት ቆይታ በሁዋላ የገዳሙ አበ ምኔት ሆኖ
አገልግሏል:: ብዙ ነፍሳትንም ለቅድስና ማርኩዋል::
#መላእክት ንጽሕናው ደስ ስለሚያሰኛቸው አብረውት ይውሉ
ነበር:: ሲተኛም በተራ በተራ ክንፋቸውን ያለብሱት ነበር::
ምጽዋትን በጣም ስለሚወድ ሰፌድ እየሰፋ ይሸጥና ገንዘቡን
ለነዳያን ያን ያካፍል ነበር::
አንድ ቀን እንደ ልማዱ ወደ ገበያ ወጥቶ ሳለ ተደሞ
(ተመስጦ) መጣበት:: ሰማያት ተከፍተው: ቅዱሳን
#ሊቃነ_መላእክት #ሚካኤል እና #ገብርኤል በግርማ በጌታ
ፊት ቆመው ተመለከተ::
"እጹብ: እጹብ" እያለ ሲያደንቅ አንድ ገዢ መጥቶ "ባለ
እንቅብ ዋጋው ስንት ነው?" ቢለው "እኁየ ሚካኤልኑ የዓቢ
ወሚመ ገብርኤል - ከሚካኤልና ከገብርኤል ማን
ይበልጣል?" ብሎታል:: ገዢውም ደንግጦ "እብድ መነኩሴ" ብሎት ሔዷል:: ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ወደ #ባቢሎን (የአሁኗ ኢራቅ) ሒዶ
ከተመለሰ በሁዋላ በበርበሮች ምክንያት ከአስቄጥስ ወደ
#ቁልዝም ተሰዷል:: በዚያም በአባ እንጦንስ በዓት ውስጥ ዐርፏል:: ለ400 ዓመታት በዚያው ቆይቷል::
በ825 ዓ/ም ግን በአባ #ዮሐንስ_ፓትርያርክ ዘመን ክቡር
ሥጋው ወደ #ገዳመ_አስቄጥስ ተመልሷል:: ቅዱሱ ያረፈው
ጥቅምት 20 ቀን ሲሆን ዛሬ ሥጋው የፈለሠበት ነው:: በዚህ
ዕለትም የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርና የታላቁ #ቅዱስ_መቃርስ
ሥጋ በተገናኙ ጊዜ ግሩም ተአምር ተደርጉዋል:: ወደ ቤተ
ክርስቲያኑ ሲገባም ታላቅ የብርሃን ጐርፍ ሲፈስ ታይቷል:: ሰማያዊ መዓዛም አካባቢውን ሞልቶታል:: ከዻዻሳቱ አንዱ እባረካለሁ ብሎ የቅዱስ ዮሐንስን ሥጋ ቢገልጠው አካባቢው ተናወጠ:: መባርቅትም (መብረቆች) ተብለጨለጩ::
ደንግጠው ቶሎ ቢያለብሱት ጸጥታ ሆኗል:: በዚህ ሁሉ ደስ
ያላቸው አበው ቅዱሱን በዝማሬ ሲያወድሱት ውለዋል::
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
አምላከ ቅዱሳን የሐጺር ቅዱስ ዮሐንስን መታዘዙን: ትሕትናውን: ትእግስቱንና ቅንነቱን ያድለን::
በበረከቱም ይባርከን::
Dn yordanos abebe
🌼#ቅዱስ_ሚካኤል_ሊቀ_መላእክት🌼
#ቅዱሳት_መጻሕፍት እንደሚነግሩን የመላእክት ሁሉ
አለቃቸው በፈጣሪው ኃይል ብዙ ድንቆችን ሠርቷል::
ከመጀመሪያው ሰው #አዳም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ: አምነው
ለሚጠሩት ረዳት ነው:: ዘወትርም ያድናቸው ዘንድ በሚፈሩት
ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል:: (መዝ. 33:7)
¤እግራችን እንዳይሰናከል ዘወትር ይጠብቀናል:: (መዝ.
90:11)
¤የቅዱስ ሚካኤል ስሙ ድንቅ ነው:: (መሳ. 13:18)
¤ከእርሱ በቀርስ የሚያጸና ማን አለና! (ዳን. 10:21)
¤ለሕዝቡም የሚቆም ታዳጊ መልአክ ነው:: (ዳን. 12:1)
¤በፊቱ ሲቆምም ስለ ክብሩ ጫማ አውልቆ: ባጭር ታጥቆ
ነው:: (ኢያ. 5:13)

ይህ ድንቅ መልአክ ከሺህ ዓመታት በፊት በሮም ከተማ
ይህንን ድንቅ ተአምር በዚህች ዕለት መሥራቱን ቤተ ክርስቲያን
ትመሰክራለች:: በድሮው የሮም ግዛት ' #ሩፍምያ ' የምትባል
ከተማ ነበረች:: ይህች ከተማ ክርስቲያኖችም: ኢአማንያንም
ተቀላቅለው የሚኖሩባት ናት::
+በከተማዋ የክርስቲያኖች ቁጥር ትንሽ ቢሆንም በእምነት
ግን ጠንካሮች ነበሩ:: በተለይ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗ መጋቢ ባለ ፍጹም እምነት ሰው ነበር:: በቦታው የቅዱስ ሚካኤል ቤተ
ክርስቲያን በመኖሩም ብዙ ተአምራት ይደረጉ ነበር:: ተበለጥን
የሚል ስሜት የተሰማቸው አሕዛብ (ዮናናውያን) ግን ይሕንን ቤተ ክርስቲያን ለማጥፋት ተማማሉ::
+በቀጥታ ሔደው ቢያፈርሱት ወይም ቢያቃጥሉት በሕግ
እንደሚጠየቁ ያውቃሉና በሥጋዊ ጭንቅላታቸው ዘዴ ያሉትን
መከሩና ወሰኑ:: በከተማዋ ዳር የሚያልፍ አንድ ትልቅ ወንዝ
አለ:: በሞላ ጊዜ ያገኘውን ሁሉ ጠርጐ የሚወስድም ነበር::
+ታዲያ ክፋተኞቹ ሌሊት ሌሊት እየተነሱ የሚሔድበትን
መንገድ ዘግተው: ወደ ቤተ ክርስቲያኑ አቅጣጫ መንገድ ከፈቱለት:: ከቀናት በሁዋላ ከባድ ዝናብ በዚህች ቀን ጣለ:: ወንዙ ትልቅ ነውና ያገኘውን ሁሉ እያገላበጠ ደረሰ::

በወቅቱ በቅዱሱ መልአክ መቅደስ ውስጥ ከመጋቢው በቀር
ሰው አልነበረምና አስፈሪ ድምጽ ሰምቶ ቢወጣ ወንዙ እየደነፋ
ወደ ቤተ ክርስቲያኑ እየመጣ ነው:: አሰበው: ከደቂቃዎች
በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ እንዳልነበረ ሊሆን ነው::
+እርሱ አንድ ተስፋ ነበረውና ወደ ውስጥ ገብቶ ቅዱስ
ሚካኤልን ተማጸነ:: ከዚያ ላለመውጣትም ወሰነ:: ትንሽ ቆይቶ በታላቅ ኃይል ወንዙ ደረሰ:: በዚህ ጊዜ ግን ቅዱስ ሚካኤል
በግርማ ከሰማይ ወርዶ በወንዙ ፊት ቆመ::

መጋቢውንም "ጽና: አትፍራ" ብሎት በያዘው የብርሃን በትረ-
መስቀል መሬትን አንድ ጊዜ መታት:: በዚያች ቅጽበትም ትልቅ
ሸለቆ ተፈጠረ:: ወንዙም በሸለቆው ውስጥ አልፎ ሔደ::
የሚገርመው ሸለቆው የተፈጠረው በቤተ ክርስቲያኑ በታች
ነው:: ቅዱስ ሚካኤል ግን መጋቢውን ባርኮት በክብር ዐረገ::
በማግስቱ ክርስቲያኖቹ ይህንን አይተው ደስ አላቸው::
መልአኩንም አከበሩት:: አሕዛብ ግን አፈሩ::
Dn yordanos abebe
👉senkesar join us
🌼#ቅዱስ_ቢሶራ_ሰማዕት🌼
ታዲያስ በዘመነ ሰማዕታት ክርስቲያን መሆን የሚያስከፍለው ዋጋ ብዙ ነበር:: ከምንም በላይ መከራው የጸናባቸው ግን የቤተ
ክርስቲያን መሪዎች ነበሩ:: ክደው ያስክዳሉ በማለት አብዝተው
ያሰቃዩአቸው ነበር:: ቶሎም አይገድሏቸውም:: መከራውን
ከማራዘም በቀር::
ከእነዚህም አንዱ አባ ቢሶራ ነው:: እርሱ በምድረ ግብፅ
'መጺል' ለምትባል ሃገር ኤዺስ ቆዾስ ነበረ:: በእድሜው
አረጋዊ: በትምሕርቱ ምሑር: በምግባሩ ቅዱስና በእረኝነቱም
የተመሠከረለት በመሆኑ በምዕመናን ዘንድ ተወዳጅ ነበር::
+መከራው እየገፋ ሲመጣ ግን ቅዱሱ በመፍራት ፈንታ
የሰማዕትነት ፍቅር አደረበት:: ስለ ሃይማኖት መሞትን እና ቶሎ
ወደ #ክርስቶስ መሔድን ናፈቀ:: ነገር ግን መልካም እረኛ
ነውና በጐቹን (ምዕመናንን) እንዲሁ ሊተዋቸው አልወደደም::
ሰብስቦ ምን እንዳሰበ አማከራቸው:: የሰሙት ነገር ክርስቲያኖችን።አስለቀሳቸው::
"አቡነ ለመኑ ተኀድገነ-አባታችን ለማን ትተኸን ትሔዳለህ?"
ሲሉም ከእግሩ ወደቁ:: እርሱ ግን አስረድቷቸው: አጽናንቷቸውም
በእንባ ተሰናበታቸው:: አንዳንዶቹ ደግሞ "አብረንህ እንሞታለን"
ብለው ተከተሉት:: ቅዱስ አባ ቢሶራን ከብዙ ስቃይ በሁዋላ
አረማውያን ከነ ተከታዮቹ በዚህታዲያስ ቀን ገድለውታል::

🌼#ቅዱስ_ያሳይ_ንጉሥ
በቀደመው ዘመን መንግስታቸውን ትተው ከመነኑ ነገሥታት አንዱ ቅዱስ ያሳይ ነው:: ምናኔ በቁሙ ከባድ ነው::።መንግስትን: ዙፋንን: ክብርን ትቶ መመነንን ደግሞ ከማድነቅ በቀር እንዲህ ብለው ሊገልጹት ይከብዳል::
+ቅዱስ ያሳይም መንግስቱን ትቶታዲያስ ልምላሜ ወደሌለበት ደረቅ በርሃ ሔደ:: በዚያም ከአንዲት ዛፍ በቀር ምንም ነገር አላገኘም:: በዚያች ደረቅ ዛፍ ላይ ወጥቶ ለዓመታት በጾምና
በጸሎት ተጋደለ::
በዘመነ ተጋድሎው ከዛፏ አልወረደም: ሰውም አይቶ
አያውቅም:: በመጨረሻም ስለ ቅድስናው ዛፏ ለምልማለች::
እርሱም በዚህች ቀን ዐርፏል::
🌻🌻🌻🌻🌻አምላከ ቅዱሳን ተራዳኢ መልአክን ይዘዝልን:: ከወዳጆቹ
በረከትም አይለየን::
👉 @senkesar join sa
💚💛 #ቅዱስ_ቶማስ💛❤️
@senkesar

✞ ለነፍስ ማረፊያ የሚጠቅማትን ሰማያዊ ቤተ-መንግስት የገነባ ኢንጅነር!

ሐዋርያው ቶማስ ትንሳዔ ሙታን የለም ብለው ከሚያምኑ ከሰዱቃዊያን ወገን ነው፡፡ ሰዱቃዊያን በዘመነ ሥጋዌ በአይሁድ መካከል ከሚገኙት ትላልቅ ቡድኖች መካከል አንዱ ነው፡፡ ቀደም ሲል በፖለቲካው ውስጥ ከፍያለ ቦታ በመያዛቸው ሃብታሞች እንዲሁም የመሬት ባለአባቶች ነበሩ፡፡ በአይሁድ ሸንጎ ውስጥም ከፈሪሳዊያን ያልተናነሰ ቦታ ነበራቸው፡፡ ሐዋ 23፡6- 10 በትንሳዔ ሙታን ካለማመናቸው ባሻገር የኦሪትን መጽሐፍ ብቻ የሚቀበሉ ቀጥታ ትርጉምን የሚከተሉ ነበሩ፡፡ ሐዋርያው ቶማስም ከሰዱቃዊያን ወገን በመሆኑ ነበር ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሳቱን አሥሩ ሐዋርያት ሲነግሩት " የችንካሩን ምልክት በእጆቼ ካላየሁ ፣ ጣቴንም በችንካሩ ምልክት ካላገባሁ ፣ እጄንም በጎኑ ካላስገባሁ አላምንም " ያለው። ዮሐ 20 : 25 በኃላ ግን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቶማስ በእምነቱ እንዲጠነክር አስቀድሞ አሥሩ ባሉበት እንደተገለጠ ሁሉ ዳግመኛ ቶማስ ባለበት በዝግ ቤት ውስጥ ተገልጦ ቶማስ ያለው ሁሉ እንዲፈጸምለት አደረገ ፤ ቶማስም " ጌታዬ አምላኬ " ብሎ አምኖ መስክሯል።
፠፠፠፠፠፠
ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከሐዋርያት ሁሉ ርቆ ወደ ምሥራቅ የተጓዘ ሐዋርያ ነው ፤ በቅድሚያ ወደ ፐርሺያ (ያሁኗ ኢራን ስትሆን በዚህች ሀገር ኢትዮጲያዊው ጃንደረባ ‹ባኮስ› ወንጌልን አስተምሯል፡፡ በኮስ በሐዋርያው በፊልጶስ እጅ አምኖ ከተጠመቀ በኋላ በመጀመርያ ወደ ሀገሩ ተመልሶ ወንጌልን በመስበክ ንግስተ ሕንደኬ የቤተ-መንግስተ ሰዎች እና ሌሎች ሰዎች ከተጠመቁ በኋላ ወደ የመን ቀጥሎም ወደ ፐርሽያ ከዛ ወደ ሕንድ ተጉዞ በእነዚህ አከባቢ ወንጌልን አስተምሯል፡፡ የመጨረሻ ሀገረ ስብከቱ በጥንቷ ታፕሮባና በዛሬዋ ሲሎን በምትባለው ደሴት ሲሆን በዚህም ወንጌልን ሲያስተምር ቆይቶ በአረማዊያን እጅ በሰማዕትነት አርፏል፡፡) ከፐርሽያም ቀጥሎ ወደ ሕንድ ተጉዟል ፣ ቅዱስ ቶማስ ሕንድ የደረሰው በ46 ዓ.ም አካባቢ ነው።
፠፠፠፠፠፠
ቶማስ ወንጌልን በፐርሽያ ሰብኮ ወደ ሕንድ ለመውረድ ሲፈልግ አንድ ከንጉስ ዘንድ የተላከ ነጋዴ ከመንገድ ላይ ያገኘዋል፡፡ ነጋዴው ቶማስ ከኢየሩሳሌም መምጣቱን ሲሰማ እጅግ በጣም ደስ ይለዋል፡፡ ወደ ቶማስም ቀርቦ ከንጉስ ዘንድ እንደተላከ እና ንጉሱ የጠቢቡ ሰለሞንን አይነት ቤተ መንግስት ማሰራት እንደሚፈልግ ለዚህም ሃሳቡ ከኢየሩሳሌም የመጣ ጎበዝ ኢንጅነር እንደሚፈልግ አጫወተው ቶማስም የነጋዴውን ነገር ካዳመጠ በኋላ ሞያው እንደሆነ በዛም ይተዳደር እንደ ነበር ገልጾለት አብረው ወደ ንጉሱ አቀኑ፡፡ ንጉሱም በሰማው ነገር ተደስቶ ቶማስን አስከትሎ ቤተ-መንግስቱን ሊገነባበት ወዳሰበው ሳይት አመሩ በዚህም ስለግንባታው ከተወያዩ በኋላ ቶማስ እንዴት መሆን እንዳለበት ዲዛይኑን ለንጉሱ አስረዳው ንጉሱም በፕላኑ ተደስቶ ውሉን ከቶማስ ጋር ተዋዋለ፡፡ በትዕዛዙ መሰረት አስፈላጊውን ፈንድ ከንጉሱ ተለቆለት ወደ ሳይቱ ተመለሰ፡፡
@senkesar
ቶማስ ግን በተቀበለው ገንዘብ እንኳን ቤተ-ንግስት መሬት አላስቆፈረም፡፡ በሞያው ኢንጅነር ቢሆንም ጌታ ድንጋይ ለመገንባት ሳይሆን የሰውን ልብ ለመገንባት መርጦታል፡፡ ልክ ቅዱስ ጴጥሮስን አሳን ሳይሆን ሰው እምታጠም ድአደርግሀለው ብሎ ለትልቅ ክብር እንደጠራው ቶማስ ሰማያዊ ቤተ-መንግስት ለመገንባት የተመረጠ ሐዋርያ በሆኑ ከንጉሱ የተቀበለውን ገንዘብ የድሆችን ቤት በመስራት የተራቡትን በማብላት የተጠሙትን በማጠጣት የታመሙትን በመፈወስ ላይ አዋለው፡፡ ንጉሱ ግንባታው ምን ላይ እንደደረሰ ለማየት ሲመጣ ቤተ-መንግስት አይደለም ከዛፎቹ ውጪ ከፍ ብሎ የሚታይ ነገር አጣ፡፡ ኢ/ር ቶመስ በድሆች መንደር የተራቡትን በማብላት የተጠሙትን በማጠጣት የታመሙትን በመፈወስ ላይ እንደሚገኝ ሰማ አስጠርቶ ጠየቀው
‹‹ የታል ቤተ-መንግስቴ? ››
ቶማስ መለሰ ‹‹ በሚገባ ተሰርቶ ተጠናቋል ›› ንጉሱም ግራ በመጋባት ስሜት ‹‹ የታል የሚታየኝ?›› በዚህ ጊዜ ቶማስ ትልቁ ስራውን ገለጠ ‹‹ በእርግጥ በምድር ላይ የድንጋይ ቤተ መንግስት ላያዩ ይችላሉ እኔ ግን በሰማይ እርሶ ካሰቡት በላይ ቤተ-መንግስት ሰርቼሎታለው፡፡›› ንጉሱ በንዴት እሚያደርገውን አጣ እዛው ፍርዱን አስተላለፈ ‹‹ እጅ እና እግሩን ቆረጣችሁ ግደሉልኝ›› ንጉስ ተደመጠ ፍረዱ እስኪፈጸም ቶማስ በወይኒ ተጣለ፡፡ በዚህ ጊዜ የንጉሱ ወንድም በድንገተኛ በሽታ ሞተ ንጉሱ ተጠራ ተለቀሰ መላዕክት የልዑሉን ነፍሱን አጅበው ወደ ሰማይ አወጧት ‹‹ ከአብያተ መንግስታቱ ትኖሪበት ዘንድ ያማረሽን ምረጪ›› ተባለች ካሉት እሚያምረውን መረጠች ይሔ ያንቺ አይደለም ቶማስ ለውንድምሽ የሰራው ሰማያዊ ቤተ- መንግስት ነው ተባለች በዚህ ጊዜ የልዑሉ ነፍስ ከስጋው ተዋህዳ ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሳ ሁሉም ለቅሶውን አቆመ ልዑሉም የተመለከተውን መሰከረ ንጉሱም ቶማስ ላይ ስላደረሰው መከራ አለቀሰ ከእስር አስፈትቶም የሰማያዊ ቤተ-መንግስት መገንባቱን እንዲቀጥልለት ከቶማስ ጋር ውሉን አደሰ ሌሎች ባለሃብቶችም የንጉሱን አሰረ ፍኖት ተከትለው ‹የሰማይ ቤተ- መንግስት› መገንባትን ጀመሩ፡፡
@senkesar
ሐዋርያው ከዛም በመቀጠል ከማላባር ጀምሮ እስከ ቻይና በመዝለቅ ወንጌልን ሰብኳል ። በመጨረሻም በ66 ዓ.ም በሚላፖር ከተማ የሚገኙ አምላክያነ ጣኦት ቆዳውን ገፈው በቆዳው ስልቻ በመሥራት በሰውነቱ ላይ ጨው ነስንሰው በቆዳው አሸዋ በመሙላት አሸክመው በአሰቃቂ ሁኔታ እንደገደሉት ታሪኩ ይመሰክራል፡፡ ከዛም ፍልሰተ አጽሙ ከሚላፖር ወደ ኤዴሳ ተዛውሯል፡፡
ኤዴሳ ያሁኗ ታነሻ ኢስያ ፣ ዑር ናት ይህችን ሀገር ካነሳን አይቀር ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊን እናንሳ ቅዱስ ኤፍሬም በ393 ዓ.ም የነጽቢን ከተማ በወራሪዎች እጅ ስትወድቅ ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር ወደዚህች ሀገር ተሰዷል፡፡ ይህች ቦታ ቅዱስ ኤፍሬም ከመናፍቃን ጋር የተጋደለባት ፣ አብዛኞቹን ክህደት ትምህርቶች የሞገተበት ፣ አብዛኞቹን መጽሐፍት ያዘጋጀባት ቦታ ናት፡፡ ይህ ታላቅ አባት ‹ አቤቱ የጸጋህን ማዕበል ግታልኝ › እስከሚል ድረስ ድረሳናትን ደርሷል፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ 370 ዓ.ም ሐምሌ 15 አርፏል፡፡ በታላቅ አባትነቱም ሶሪያዊያን ‹ ጥዑመ ልሳን ፣ መምህረ ዓለም ፣ ዓምደ ቤተ-ክርስቲያን በማለት ይጠሩታል፡፡ በቁጥር ስንክሳራችን ሲገልፀው 14 ሺህ ድርሳናትን እና ተግሳጻትን መድረሱን ያስቀምጣል) ለእኔ ሐዋርያት ላይ ከደረሱት ስቃዮች የሐዋርያው ቶማስ ስቃይ የከፋ ነው የጽናቱን ቅንጣት በልባችን በአማልጅነቱ ያኑርልን፡፡ ግንቦት 26 መታሰቢያው ነው፡፡
ምንጭ፡- ስለ 12ቱ ሐዋርያት በዚሁ በቻናላችን ስም ካዘጋጀነው ጽሑፍ
@senkesar
Forwarded from ዐውደ ምሕረት
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

"የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል #ያድናቸውማል።" መዝ 33:7

👉 ይህን ኃይለ ቃል የተናገረው ልበ አምላክ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ነው። በግልጽ እንደነገረን የእግዚአብሔር የሆኑት ቅዱሳን መልአክት የሚያድኑ አዳኞች ናቸው። እነርሱን ከሚፈሯቸውና ከሚያምኗቸው ሰዎች አይለዩም። ከሚደርስባቸው መከራ እና ችግር ፈተና ሁሉ ያድኗቸዋል ይታደጓቸዋል። ቅዱሳን መልአክት የሰው ልጆችን የሚያድኑ አዳኞች መሆናቸውን ቅዱስ ያዕቆብ ዮሴፍንና ልጆቹን በባረከ ጊዜም እንዲህ ሲል መስክሯል። "ከታናሽነቴ ጀምሮ እኔን የመገበኝ እግዚአብሔር ከክፉ ነገር ሁሉ #ያዳነኝ_መልአክ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ።" ዘፍ 48:15

👉 እሱም ብቻ አይደለም የሰው ልጅ አምላክ በፈጸመለት የማዳን ተግባር ውስጥ የቅዱሳን መላእክት ሱታፌ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገልገል የሚላኩ የሚያግዙ መናፍስት አይደሉምን?" ብሎ የሰው ልጅ እንዲድን የቅዱሳን መላእክት አገልግሎት እና እገዛ የግድ እንደሚያስፈልገው ተናግሯል። ዕብ 1:14 እንዲሁም የሰው ልጅ የመዳኑ ነገር ለቅዱሳን መልአክት ታላቅ ደስታ መሆኑን ጌታ በወንጌል እንዲህ በማለት ተናግሯል። "እላችኋለሁ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።" ሉቃ 15: 7

👉 ቅዱሳን መልአክት በተጨነቅን እና በተቸገርን ጊዜ በጸሎት ስንጠራቸው መጥተው ያበረቱናል ያረጋጉናል። ጌታችን በመዋለ ሥጋዌው ለእኛ አርአያ አብነት ይሆነን ዘንድ በምሴተ ሐሙስ መከራን ከመቀበሉ በፊት ሲጸልይ "ከሰማይም መጥቶ የሚያበረታው መልአክ ታየው።" ይላል። ሉቃ 22:43 የመልአክት ፈጣሪያቸው እርሱ ሆኖ ሳለ የሚያበረታው መልአክ ታየው መባሉ ስለምንድን ነው ቢሉ እናንተም በጨነቃችሁ በጠበባችሁ መከራ ውስጥ በገባችሁ ጊዜ ብትጸልዩ ቅዱሳን መልአክት እናንተን ለማበርታት ይላካሉ ሲለን ነው።

👉 ቅዱሳን መልአክት ስለ ሰው ልጆች ዘውትር በአምላክ ፊት ያማልዳሉ። እግዚአብሔርም ምልጃቸውን ቸል አይልም። ዘካ 1:12–13 "የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ። አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ እነዚህ ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው? አለ። እግዚአብሔርም መልሶ ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረው መልአክ በመልካምና በሚያጽናና ቃል ተናገረው።" እንዲል። መልአኩ እግዚአብሔርን አሳዝነው 70 ዓመት ለተቆጡት እስራኤል ዘሥጋ ከለመነ፤ በቅዱሳን መልአክት ለታመንን እስራኤል ዘነፍስ ለሆንን ለኛ እንዴት አይማልዱልንም? እነርሱም ዘውትር በእግዚአብሔር ፊት ይቆማሉ፣ የእግዚአብሔርንም ፊት ያያሉ። ማቴ 18:10 ኢዮ 1:7 ሉቃ 1:9 "የእግዚአብሔር ዐይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸውና።" እንዲል የቅዱሳን መልአክትንም ምልጃቸውን ይቀበላል። መዝ 33(34):15

በተጨማሪም #ቅዱሳን_መልአክት

👉 አጽናኞቻችን ናቸው። ዳን 10:20
👉 ይረዱናል። ዳን 10:13
👉 ይጠብቁናል። መዝ 90:1
👉 እንሰግድላቸው ዘንድ ይገባል። ኢያ 5:14 ዘፍ 19:1 ራዕ 19:10 ራዕ 22:8

ሰኔ 12 በዚህች ቀን መልአኩ #ቅዱስ_ሚካኤል የተሾመበት፣ ቅድስት አፎምያን ከሰይጣን ያዳነበት፣ የባሕራንን የሞት ደብዳቤ ወደ ህይወት የቀየረበት ዕለት ነው።

ከመልአኩ ከቅዱስ ሚካኤል ረድኤት በረከት ያሳትፈን።

ይቆየን።

አዘጋጅ #አቤኔዘር

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit

..............+++++++++++............
እንድትከታተሉት የምንጋብዝዎ መንፈሳዊ ቻናል

ስንክሳር… @senkesar
💚💛ቅዱስ_ሚናስ ምዕመን ሰማዕት💛❤️

ቅዱስ ሚናስ ( #ማር_ሚና ) በምድረ ግብጽ ተወዳጅ ከሆኑ ሰማዕታት ዋነኛው ነው:: ልክ በሃገራችን #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ልዩ ቦታ እንዳለው ሁሉ ግብፃውያን
ማር ሚናስን ጠርተው አይጠግቡትም::

ምክንያቱም ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱ በመሆኑና ዛሬም ድረስ ለጆሮና ለዐይን ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ስለሚሠራ
ነው:: በተለይ ለታመመ: ለደከመና ለተጨነቀ ፈጥኖ ደራሽ: ባለ በጐ መድኃኒት ፈዋሽና አማላጅ ነው::

ግብጽ ውስጥ ቅዱሱን የማያውቅ ሰው ካገኛችሁ እርሱ ኦርርቶዶክሳዊ አይደለም ማለት ነው ሲባልም ሰምተናል:: በነገራችን ላይ ለቅዱሳን ተገቢውን ክብር በመስጠት: ታሪካቸውን በመጻፍ: በማጥናት: በመጽሔት: በፊልምና
በመሳሰሉት ለሕዝብ በማስተዋወቅ ግብጻውያኑ ከእኛ ብዙ ርቀት ሒደዋል:: ዛሬ እንኩዋ የምንጠቀምበትን ስንክሳር
80 ከመቶ እጁን ያዘጋጁት እነርሱ ናቸው::

አባቶቻችንና እናቶቻችን #ኢትዮዽያውያን_ቅዱሳን ግን አብዛኞቹ ተረስተው ቀርተዋል:: መጽሐፈ ገድላቸውንም ብል በልቶታል:: ዛሬም የቤት ሥራው የእኛ ብቻ ነው::

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ ሚናስ (ትርጉሙ ታማኝና ቡሩክ ማለት ነው):-

¤በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ የደጋግ ክርስቲያኖች ልጅ

¤በልጅነቱ የቅድስና ሕይወትን ያጣጣመ

¤በዘመኑ ሰው እጅግ ተወዳጅ የነበረ

¤ሃብትን: ክብርን: ሥልጣንን ንቆ በጾምና በጸሎት የተወሰነ

¤በመጨረሻም በክርስቶስ ስላመነ አላውያን የገደሉት ሰማዕት ነው::

እርሱ ሰማዕት ከሆነ ከበርካታ ዘመናት በሁዋላ ምዕመናን ክቡር አካሉን ፈልገው ያጡታል::

የሚገለጥበት ጊዜ ሲደርስ ግን እርሱ የተቀበረበት ምድረ በዳ የበጐችና የእረኞች መዋያ ነበርና ተአምራትን
አደረገ:: አንድ እረኛ በጐቹ ድውያን ሆኑበት:: በዚያ ሰሞን ከቅዱሱ መቃብር ላይ ጸበል ፈልቆ ነበርና እረኛው ተርታ
ውሃ ነው ብሎ በጎቹን ሲያጠጣቸው አንዱ ድውይ በግ ወደ ጸበሉ በመዘፈቁ ዳነ::

በዚህ የተገረመው እረኛ ሁሉንም የታመሙ በጐቹን አምጥቶ ነከራቸው:: እነርሱም ተፈወሱ:: ይህ ዜና በምድረ ግብፅ ሲሰማ ድውያን ሁሉ እየመጡ ይፈወሱ ገቡ:: ግን እነሱም ሆነ እረኛው ምክንያቱን ማወቅ አልቻሉም::

ነገሩ በሮም ንጉሥ ዘንድ ሲሰማ ሴት ልጁን ከሠራዊቱ ጋር ላካት:: ምክንያቱም እርሷ ከብዙ ዘመን ጀምራ መጻጉዕ ነበረችና ፈውስን አጥታ ነበር:: መጥታ
ተጠመቀች: ፈጥናም ተፈወሰች:: እርሷ ግን እንደ ሌሎች ያዳናትን ማንነት ሳታውቅ መሔድ አልፈለገችምና ሱባዔ ገባች::

#ቅዱስ_ሚናስ በሌሊት ራዕይ መጥቶ ሥጋው እንዳለ ነገራት:: እርሷም መሬቱን አስቆፍራ የቅዱሱን አካል በክብር አስወጣች:: ከዚያም በንጉሡ ትዕዛዝ ምድረ በዳው ከተማ እንዲሆን ተቀየረ:: ስሙም " #መርዩጥ " ተባለ:: ጸበሉ የነበረበት ቦታም ላይ የማር ሚናስ
#ቤተ_ክርስቲያን ታንጾበት በዚህች ዕለት ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል::

አምላካችን ከቅዱሱ ሰማዕት በረከትን ይክፈለን::
from:- d/n yordanos abebe
@senkesar @senkesar
💚💛 ቅዱስ ሐናንያ ሐዋርያ 💛❤️

ሐናንያ ቁጥሩ ከ72ቱ አርድእት ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስማቸው ተመዝግቦ ከተቀመጠልን ከጥቂቶቹ ዋነኛው ነው:: ከነገደ እሥራኤል ተወልዶ : በሕገ ኦሪት አድጐ : ከወጣትነት ዕድሜው ትንሽ እልፍ ሲል ጌታችን ወንጌልን ማስተማር ጀምሯልና ጠራው:: እርሱም በበጐ ፈቃድ ተከትሎታልና ከ72ቱ አርድእት ደመረው::

ለ3 ዓመታት ከጌታ እግር ተምሮ : ከዕለተ ስቅለት በፊት ሀብተ ፈውስም ተሰጥቶት ነበር:: ምክንያቱም ቅዱስ ሉቃስ እንደ ጻፈልን ሰብዐው አርድእት "ጌታ ሆይ! አጋንንት በስምህ ተገዙልን" ማለታቸውን አስቀምጦልናል:: (ሉቃ. 10:17) ቅዱስ ሐናንያ በበዓለ ዕርገት ተባርኮ በ50ኛው ቀንም መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል::

በሚያስተምር ጊዜ የሶርያዋን ደማስቆን ማዕከል አድርጐ ነበር:: በሁዋላም አበው ሐዋርያት የዚህች ከተማ የመጀመሪያው ዻዻስ አድርገው ሹመውታል:: ጌታ ባረገ በ8ኛው ዓመት ክርስቲያኖችን ያሰቃይ የነበረው ሳውል (የሁዋላው ቅዱስ ዻውሎስ) ወደ ደማስቆ የተጉዋዘው ክርስቲያኖችን በተለይም ቅዱስ ሐናንያን ለማሠር ነበር::

ለእግዚአብሔር ምርጥ ዕቃ ይሆን ዘንድ መብረቅ ዐይኑን አጠፋው:: ወዲያውም ጌታችን ሳውልን ወደ ሐናንያ እንዲሔድ ነገረው:: ከ3 ቀናት በሁዋላ ጌታችን ለሐናንያ ተገልጦ አነጋግሮታል::

ሳውል (ዻውሎስ) ወደ ሐናንያ የደረሰው በመሪ ነበር:: 2ቱ እንደተገናኙ ቅዱስ ሐናንያ ሳውልን አስተማረው : ፈወሰው : አጠመቀው : በጐ መንገድንም መራው:: በዚህ ምክንያት ቅዱሱ ሐዋርያ የቅዱስ ዻውሎስ የንስሃ አባቱ ይሰኛል:: (ሐዋ. 9:1-19)

ከዚህ በሁዋላ ቅዱስ ሐናንያ ለብዙ ዓመታት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወንጌልን አስተማረ:: መከራንም ተቀበለ:: በመጨረሻም በዚህ ቀን ክፉዎች ከብዙ ስቃይ በሁዋላ በድንጋይ ወግረው ገድለውታል::

💚💛ቅዱስ ቶማስ ዘሰንደላት 💛❤️

በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ከነበሩ ሰማዕታት አንዱ የሆነው ቅዱስ ቶማስ ወደ ሰማዕትነት ሕይወት የገባው በ11 ዓመቱ በመላእክት መሪነት ነው:: ገና ወደ ምስክርነት አደባባይ እንደ ቀረበ መኮንኑ "ክርስቶስን ካድና ልሹምህ" ቢለው ሕጻኑ ቅዱስ ቶማስ ተቆጥቶ : "አንተ ሰነፍ መኮንን" ብሎ ገስጾ : በጐችን ይመልስባት በነበረችው ጅራፍ ገርፎታል:: ይሔም በዘመኑ የመጨረሻው የድፍረት ደረጃ ነበር::

በዚህም ምክንያት በሕጻን ገላው ላይ የተቀበለው መከራ ሊናገሩት ይከብዳል::

¤ግርፋት:
¤እሳት:
¤አራዊት በእርሱ ላይ አልፈዋል::

አካሉ ተቆራርጧል:: አንድ ጊዜም "ለጣዖታችሁ እንድሰግድ አምጡት" ብሏቸው ልክ ከፊቱ ሲደርሱ ወደ ጌታ ቢጸልይ መሬት ተከፍታ ውጣቸዋለች::

እሱን ያሰቃየው የነበረውን መኮንንም ከደዌው አድኖ ከነ ሠራዊቱ አሳምኖታል:: ሕጻኑን ቅዱስ ቶማስን ግን ያላመኑ አረማውያን በዚህች ቀን አንገቱን ሰይፈውት በሰማዕትነት ወደ ወደደው ክርስቶስ ሔዷል::

🌿 አምላከ ቅዱሳን ከሐዋርያው በረከት : ከሰማዕቱም ምልጃ አይለየን::🌿

💚💛ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ💛❤️

በቤተ_ክርስቲያን_ታሪክ በደራሲነታቸው: በወንጌል አገልግሎታቸውና በቅድስናቸው ከተመሠከረላቸው ዐበይት ሊቃውንት አንዱ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ነው::

ሊቁ የተወለደው መጋቢት 27 ቀን በ433 ዓ/ም ሲሆን ሃገሩ ሶርያ ነው:: ወላጆቹ ክርስቲያኖች ለዚያውም አባቱ ሊቀ ካህናት ነበር:: ቅዱስ ያዕቆብ ገና በልጅነቱ ጀምሮ ጸጋ እግዚአብሔር የጠራው ነውና በብዙ ነገሩ የተለየ ነበር::

አንድ ቀን በዕለተ ሰንበት ገና በ3 ዓመቱ እናቱ አቅፋ ወደ #ቤተ_መቅደስ ወሰደችው:: ምዕመናን #ቅዱስ_ሥጋውንና #ክቡር_ደሙን ሲቀበሉ ሕጻኑ ያዕቆብም ይቆርብ ዘንድ ቀረበ:: ሊቀ ዻዻሱ ደሙን በዕርፈ መስቀል ሊያቀብለው ሲል መልአኩ መጥቶ "በጽዋው ጋተው" አለው:: የጌታን ደም በጽዋ ቢጠጣ ምስጢር ተገለጸለትና "#አንሰ_እፈርሕ_ሠለስተ_ግብራተ-እኔስ 3 ነገሮች ያስፈሩኛል" ሲል አሰምቶ ተናገረ::

ዻዻሱና ሕዝቡ ወደ ሕጻኑ ያዕቆብ ቀርበው "ምን ምን?" አሉት:: እርሱም:-
1.ነፍሴ ከሥጋየ ስትለይ
2.ቅድመ እግዚአብሔር ለፍርድ ስቀርብ
3.ከፈጣሪየ የፍርድ ቃል ሲወጣ" አላቸው::
ያን ጊዜ ሕዝቡና ሊቀ ዻዻሳቱ "#እግዚአብሔር_በዚሕ_ሕጻን_አድሮ_ዘለፈን" እያሉ ለንስሃ በቅተዋል::

+ቅዱስ ያዕቆብ 7 ዓመት ሲሞላው ይማር ብለው ወደ ጉባዔ አስገቡት:: በ5 ዓመታት ብሉይ ከሐዲስ ጠንቅቆ በ12 ዓመቱ ሊቅ ሆኗል:: በዚህ ወቅት የነበሩ ታላላቅ ሊቃነ ዻዻሳት ወደ እርሱ ተሰበብስበው "እንግዳ ድርሰት ድረስልን: አዲስ ምሥጢር ንገረን" አሉት:: እርሱ ግን ሲቻለው ስለ ትሕትና "አልችልም" አላቸው::

"እንግዲያውስ #ትንቢተ_ሕዝቅኤልን ተርጉምልን" ቢሉት ባጭር ታጥቆ አመሥጥሮላቸው ተደስተዋል:: ፈጣሪንም አመስግነዋል::

ቅዱስ ያዕቆብ ከዚህ በሁዋላ ወደ ገዳም ገብቶ ትሕርምተ አበውን: ዕጸበ ገዳምን: ሕይወተ ቅዱሳንን በተግባር ተምሯል:: በድንግልናው ጸንቶ: #ጾምና_ጸሎትን እያዘወተረ ኑሯል:: በፈቃደ እግዚአብሔር የሥሩግ (በኤፍራጥስና ጤግሮስ ወንዞች መካከል የምትገኝ የሶርያ ግዛት ናት) ኤዺስ ቆዾስ ሆኖ ተሹሟል::

በዘመኑም:-
1.የ451ን የኬልቄዶን ጉባኤ አውግዟል

2.ብዙ መናፍቃንን ተከራክሮ ምላሽ አሳጥቷል

3.በወንጌል አገልግሎት መልካም እረኝነቱን አሳይቷል

4.ዛሬ የምንገለገልበትን መጽሐፈ ቅዳሴውን ጨምሮ በርካታ መንፈሳዊ ድርሰቶችን ደርሷል::

በመጨረሻም ከብዙ የተጋድሎና የቅድስና ዓመታት በሁዋላ በተወለደ በ72 ዓመቱ በ505 ዓ/ም በዚሕች ቀን አርፏል:: አንዳንድ ምንጮች ደግሞ ሰኔ 27 ቀን እንዳረፈ ይናገራሉ:: #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ ለቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ተወዳጅ ልጇ ነውና በእጅጉ ታከብረዋለች::

#አምላከ_ቅዱሳን ከታላቁ ሊቅ በረከት ይክፈለን::
From:-d/n yordanos abebe
ቀን:- 27/10/2011
@senkesar @senkesar
💚💛ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ 💛❤️
ቅዱስ ቄርሎስን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን " #ዓምደ_ሃይማኖት- የሃይማኖት ምሰሶ" ይሉታል:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

ሊቁ የተወለደው በእስክንድርያ (ግብጽ) በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: እናቱ የወቅቱ ፓትርያርክ #ቅዱስ_ቴዎፍሎስ እህቱ ነበረችና አጎቱ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ወስዶ አሳድጐታል:: ገና በልጅነቱ ወደ #አባ_ሰራብዮን ገዳም ገብቶ ቅዱሳት መጻሕፍትንና ገዳማዊ ሕይወትን ተምሯል:: በጾም: በጸሎትና በትሕትና የታሸ ነውና ሲማር አንድ ጊዜ ካነበበው በሕሊናው ተስሎ ይቀር ነበር::
ቅዱስ ቴዎፍሎስ "ምዕመናንን አስተምርልኝ" ብሎ ወደ ከተማ አመጣው:: #መንፈስ_ቅዱስ አድሮበታልና ሲያስተምር ወይ ደግሞ መጻሕፍትን ሲያነብ ከምዕመናን ወገን ስንኩዋን የሚያወራና የሚንቀሳቀስ ቀርቶ የሚቀመጥም አልነበረም:: ጣዕመ ስብከቱም ብዙዎችን ለወጠ::
ከዚያም በ412 ዓ/ም አጎቱ የነበረው ፓትርያርክ አባ ቴዎፍሎስ ሲያርፍ ዻዻሳትና ሊቃውንት በአንድነት ቅዱስ ቄርሎስን መረጡ:: የእስክንድርያም 24ኛ ሊቀ ዻዻሳት ሆኖ ተሾመ:: በዘመኑ #ቤተ_ክርስቲያን አበራች:: በቅድስናው: በሊቅነቱ: በስብከቱ: በድርሰቶቹና በትጋቱ በፍጹም አገለገላት::

በወቅቱ ስመ ክፉ መናፍቅ ንስጥሮስ ተነስቶ የእስያ አብያተ ክርስቲያናትን አወካቸው:: ትምሕርቱ ክርስቶስን "2 አካል: ባሕርይ ነው" (ሎቱ ስብሐት!) የሚል ነበር:: በእውነት እንየው ከተባለ ግን ጠቡና ጥላቻው ከድንግል ማርያም ጋር ነበር:: ምክንያቱም ጌታችንን ወደ 2 የከፈለው #እመቤታችንንየአምላክ እናት አይደለሽም ለማለት ነው:: (ላቲ ስብሐት!)
ነገሩን #ቅዱስ_ቄርሎስ በሰማ ጊዜ ወዳለበት ሒዶ ቢመክረውም ንስጥሮስ ሊሰማ አልፈለገም:: በዚህ ምክንያት በትንሹ ቴዎዶስዮስ (የቁስጥንጥንያ ንጉሥ) ትዕዛዝ በኤፌሶን ታላቅ ጉባኤ እንዲሰበሰብ ሆነ:: ይህ ጉባዔ በቤተ ክርስቲያናችን የመጨረሻው የተቀደሰ ጉባዔ ነው:: በ431 ዓ/ም #በኤፌሶን ከተማ የመናፍቃኑን ጥርቅም ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና 200 #ቅዱሳን_ሊቃውንት ተገኙ::

የሚገባው ጸሎትና ሱባዔ ከተፈጸመ በሁዋላ ጉባዔው ተጀመረ:: አፈ ጉባዔው ሊቀ ማሕበር ማር (ቅዱስ) ቄርሎስ ነበርና በጉባዔ ፊት ንስጥሮስን ተከራክሮ ረታው:: ምላሽም አሳጣው:: ከቅዱሳት መጻሕፍት #ክርስቶስ አንድ ባሕርይ መሆኑን: #ድንግል_ማርያምም #ወላዲተ_አምላክ መሆኗን እየጠቀሰ: በምሳሌም እያሳየ አስረዳ::
የሰይጣን ማደሪያ ንስጥሮስ ግን እንቢ: አላምንም በማለቱ ተወግዞ ተለየ:: ቅዱሳን ሊቃውንቱም በቅዱስ ቄርሎስ አርቃቂነት 12 አንቀጾችን አዘጋጅተው ወደ ዓለም ሁሉ ላኩ:: እሊህ አንቀጾች ዛሬም በሊቃውንቱ እጅ አሉ:: ይነበባሉ: ይተረጎማሉ::

ከእነዚህም አንዱ ድንግል ማርያም " #ታኦዶኮስ(የእግዚአብሔር እናቱ) ናት" የሚል ነው:: እመቤታችንን:-
¤የአምላክ እናት:
¤ዘላለማዊት ድንግል:
¤ፍጽምት:
¤ንጽሕትና አማላጅ ብሎ ማመን ለሰማያዊ ርስት የሚያበቃ በጐ ሃይማኖት ነውና::
ጉባዔው ከተጠናቀቀ በሁዋላ ቅዱስ ቄርሎስ ንስጥሮስን ጠርቶ "በድንግል ማርያም እመን:: እርሷ ከልጇ ታስታርቅሃለች" ቢለው በድጋሚ "እንቢ" አለው:: ያን ጊዜ ሊቁ "ለአምላክ እናት ያልታዘዘ ምላስህ ላንተም አይታዘዝህ" ብሎ ረገመው:: ወዲያው ምላሱ ተጐልጉሎ ወጥቶ ደረቱ ላይ ወደቀ::
እንደ ውሻ እየተዝረከረከ ሒዶ ከወዳጆቹ ጋር ቁሞ ሳለ መሬት ተከፍታ ውጣዋለች::
ቅዱስ ቄርሎስ ግን ለ32 ዘመናት በመንበሩ ላይ አገልግሎ: ፍሬ ትሩፋት አፍርቶ: ብዙ ድርሰቶችንም ደርሶ በ444 ዓ/ም በዚህች ቀን ዐርፏል:: ከድርሰቶቹም ቅዳሴው: ድርሳነ ቄርሎስና ተረፈ ቄርሎስ ይጠቀሳሉ::

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአባቶቻችን ጸሎት ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን:: ከሊቁም በረከቱን ይክፈለን::
From:- d/n yordanos abebe

@senkesar @senkesar
💚💛ሐምሌ ፭💛❤️
✞እንኩዋን ለብርሃናተ ዓለም ቅዱሳን #ዼጥሮስ #ወዻውሎስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞

ፍጡር ቢከብር ከእመ ብርሃን ቀጥሎ የእነዚህን ቅዱሳን ያህል የሚከብር አይኖርም:: ለቤተ ክርስቲያን ያልሆኑላት ምንም ነገር የለምና እርሷም "ብርሃኖቼ:
ዐይኖቼ: ዕንቁዎቼ" ብላ ትጠራቸዋለች::

💚💛" ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት "💛❤️
የዮና ልጅ ስምዖን ዼጥሮስ (ኬፋ) የተባለው በጌታችን ንጹሕ አንደበት ነው:: ይሔውም ዓለት (መሰረት) እንደ ማለት ነው::

¤በቤተ ሳይዳ ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሳ በማጥመድ አድጐ

¤ሚስት አግብቶ ዕድሜው 56 ሲደርስ ነበር ጌታችን የተቀበለው:: በዕድሜውም ሆነ በቅንዐቱ: በአስተዋይነቱም መሠረተ ቤተ ክርስቲያን ተብሏል:: ለሐዋርያትም አለቃቸው ሆኗል:: (ማቴ. 16:17, ዮሐ.
21:15)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተያዘባት ሌሊት ለሰራው ስሕተት ንስሃ ገብቶ ምሳሌም ሆኗል:: ቅዱስ ዼጥሮስ
እንደ እረኝነቱ ሐዋርያትን ጠብቆ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ ሲያበቃ ከበዓለ ሃምሳ በሁዋላም ለሁሉም ሃገረ ስብከ አካፍሏል:: ምንም የርሱ ክፍል ሮሜ ብትሆንም አርድእትን ስለ ማጽናት በሁሉም አሕጉራት ዙሯል::

በስተእርጅናው ብዙ መከራዎችን ተቀብሏል:: አሕዛብ ግብራቸው እንደ እንስሳ ነውና በአባታችን ላይ ቀልደዋል::
እርሱ ግን ሁሉንም ታግሷል:: የቅዱሱን ታሪክ ለመናገር ከመብዛቱ የተነሳ ይከብዳልና ልቡና ያለው ሰው ሊቃውንትን ሊጠይቅ እንደሚገባ እመክራለሁ::

ቅዱስ ዼጥሮስ መልካሙን ገድል ተጋድሎ በ66 ዓ/ የኔሮን ቄሳር ወታደሮች ሲሰቅሉት ለመናቸው::."እባካችሁን? እኔ እንደ ጌታየ ሆኜ መሰቀል አይገባኝም"
አላቸው:: እነሱም ዘቅዝቀው ሰቅለው ገድለውታል:: በበጐ እረኝነቱም የማታልፈውን ርስት ከነመክፈቻዋ ተቀብሏል:: በሰማዕትነት ሲያርፍም ዕድሜው ወደ 88 አካባብ ደርሶ
ነበር::

#የቅዱስ_ዼጥሮስ መጠሪያዎች:-
1.ሊቀ ሐዋርያት
2.ሊቀ ኖሎት (የእረኞች / ሐዋርያት አለቃ)
3.መሠረተ ቤተ ክርስቲያን
4.ኰኩሐ ሃይማኖት (የሃይማኖት ዐለት)
5.አርሳይሮስ (የዓለም ሁሉ ፓትርያርክ)

💚💛#ቅዱስ_ዻውሎስ_ሐዋርያ 💛❤️
የቤተ ክርስቲያን መብራቷ ቅዱስ ዻውሎስን እንደ ምን ባለ ዐማርኛ እንገልጠዋለን?

¤ስለ እርሱ መናገርና መጻፍ የሚችልስ እንደ ምን ያለ ሰው ነው?

¤የዓለምን ነገር ሲጽፍ በኖረ እጄስ እንደ ምን እጽፈዋለሁ?

¤ይልቁኑስ የርሱን 14ቱን መልዕክታትና ግብረ ሐዋርያትን መመልከቱ ሳይሻል አይቀርም::

#ቅዱስ_ዻውሎስ ከነገደ ብንያም #ሳውል የሚባል የጠርሴስ ሰው ሲሆን ምሑረ ኦሪት: ቀናተኛና ፈሪሳዊ ነበር:: ጌታ በደማስቆ ጐዳና ጠርቶ በ3 ቀናት ልዩነት
ምርጥ ዕቃ አደረገው:: ይህ የሆነው በ42 ዓ/ም: ጌታ ባረገ በ8ኛው ዓመት ነበር:: ከዚያማ ብርሃን ሆኖ አበራ:: ጨው ሆኖ አጣፈጠ::

ከኢየሩሳሌም እስከ ሮም: ከእንግሊዝ እስከ እልዋሪቆን (የዓለም መጨረሻ) ወንጌልን ሰበከ:: ስለ ወንጌል ተደበደበ: ታሠረ: በእሳት ተቃጠለ:: በድንጋይ ተወገረ: በጦር ተወጋ:: ባፍም በመጣፍም ብሎ አገለገለ:: በየቦታውም ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ሠራ:: ለ25 ዓመታት ቀንና ሌሊት ያለ መታከት ወንጌልን ሰበከ::

እርሱን የመሰሉ: እርሱንም ያከሉ ብዙ አርድእትን አፍርቶ: በ67 ዓ/ም በኔሮን ቄሳር ትእዛዝ አንገቱ ተቆርጧል::.ከ14ቱ መልዕክታቱ ባሻገር ቅዱስ ሉቃስ ወንጌልን ሲጽፍ አግዞታል:: ልክ ቅዱስ ዼጥሮስ ማርቆስን እንዳገዘ ማለት ነው::

የቅዱስ ዻውሎስ መጠሪያዎች:-
1.ሳውል (ከእግዚአብሔር የተሰጠ)
2.#ልሳነ_ዕፍረት (አንደበቱ እንደ ሽቱ የሚጣፍጥ)
3.#ልሳነ_ክርስቶስ (የክርስቶስ አንደበቱ)
4.#ብርሃነ_ዓለም
5.#ማኅቶተ_ቤተ_ክርስቲያን (የቤተ ክርስቲያን መቅረዝ)
6.#የአሕዛብ_መምሕር
7.#መራሒ (ወደ መንግስተ ሰማያት የሚመራ)
8.#አእኩዋቲ (በምስጋና የተሞላ)
9.#ንዋይ_ኅሩይ (ምርጥ ዕቃ)
10.#መዶሻ (ለአጋንንትና መናፍቃን)
11.#መርስ (ወደብ)
12.#ዛኅን (ጸጥታ)
13.#ነቅዐ_ሕይወት (የሕይወት ትምሕርትን ከአንደበቱ
ያፈለቀ)
14.#ዐዘቅተ_ጥበብ (የጥበብ ምንጭ / ባሕር)
15.#ፈዋሴ_ዱያን (ድውያንን የፈወሰ) . . .

ጌታችን እግዚአብሔር የአባቶቻችንን ብርሃን ያብራልን:: ከበረከታቸውም ያድለን::
From dn yordanos abebe

@senkesar @senkesar
💚💛 አቡነ ኪሮስ ጻድቅ 💛❤️
የጻድቁን ስም የሚጠራ አፍ ንዑድ ነው: ክቡር ነው:: በእውነት የቅዱሱን አባት ክብር ለማግኘት መፋጠን ይበጃል::
#አቡነ_ኪሮስ የተወለዱት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ወላጆቻቸው ነገሥታት ናቸው:: ተወልደው ባደጉባት ሃገር #ቁስጥንጥንያ ገና በልጅነት ምቾት ሳያሳሳቸው መጻሕፍትንና ትሕርምትን ተምረዋል:: ወንድማቸው (ታላቁ #ቴዎዶስዮስ) በነገሠባቸው የመጀመሪያ ዓመታት በቤተ መንግስቱ ዙሪያ ግፍ በዝቶ ነበርና አቡነ ኪሮስ ከኃጢአት ለመራቅና ለጌታ ለመገዛት ከከተማው ጠፍተው: አሕጉር አቋርጠው ወደ ግብፅ ( #ገዳመ_አስቄጥስ) መጡ::

እርሳቸውን ለመፈለግ የተደረገው ሙከራ አልተሳካም:: ይባስ ብሎ የንጉሡ ልጅ #ገብረ_ክርስቶስ ሙሽርነቱን ጥሎ ወደ ሌላ ሃገር መነነ:: "የቅኖች ትውልድ ይባረካል" እንዳለ #ቅዱስ_ዳዊት:: አቡነ ኪሮስ ለሙሽራው ገብረ ክርስቶስ አጎቱ ናቸው:: አቡነ ኪሮስ በገዳም ውስጥ የታላቁ #አቡነ_በብኑዳ ደቀ መዝሙር ሆነው ለዘመናት ቆይተዋል::

ቅዱስ በብኑዳን አንበሳ በበላው ጊዜ በጣም አዝነው "ለምን ጌታ ሆይ?" በሚል መሬት ላይ ወድቀው አለቀሱ:: "ምክንያቱ ካልተነገረኝ አልነሳም" ብለው ከወደቁበት መሬት ላይ ሳይነሱ ለ40 ዓመታት አልቅሰዋል:: በዚህ ምክንያት ግማሹ አካላቸው አፈር ሆኖ ሣር በቅሎበታል:: ጌታችን ተገልጦ ምክንያቱን ነግሯቸዋል:: አካላቸውንም እንደነበረ መልሶላቸዋል::
አንድ ቀን ጻድቁ ለቅዱስ በብኑዳ ሞት ምክንያት የሆነው መነኮስ ታንቆ መሞቱን ሰምተው በጣም አዘኑ:: ሱባዔ ገብተው: ፍጹም አልቅሰው: ከጌታም አማልደው: የዛን ኃጥእ ነፍስ ከሲዖል አውጥተዋል:: በሌላ ጊዜ ደግሞ ኃጥአን የሞሉበት አንድ ገዳም በግብጽ ነበርና መቅሰፍት ወርዶ ሁሉንም ባንድ ቀን ሲያጠፋቸው አዩ::

ጻድቁ በዚህም ምክንያት ለ30 ዓመታት አልቅሰው: ሙታኑን አስነስተው: ንስሃ ሰጥተው: ገዳሙን የጻድቃን: ሕይወታቸውንም የፍቅር አድርገውታል:: ጻድቁ #እመቤታችንን ከመውደዳቸው የተነሳ በስዕሏ ፊት አብዝተው ይሰግዱና ያለቅሱ ነበር:: እመ አምላክም ተገልጣ ትባርካቸው ነበር::

ከዚህ በሁዋላ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ሒደው ለ57 ዓመታት ማንንም ሳያዩ ተጋደሉ:: ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ (ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና) በየቀኑ ይጐበኛቸው: ቁጭ ብሎም ያወራቸው ነበር:: በመጨረሻም በዚህች ቀን ጌታ አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን: ድንግል እመቤታችንና ቅዱስ ዳዊትን አስከትሎ ወረደ::

#ቅዱስ_ዳዊት ቀርቦ እያጫወታቸው: በበገናው እየደረደረላቸው: ከዝማሬው ጣዕም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው በፍቅር ተለየች:: ጌታችንም ታቅፎ: ስሞ ይዟቸው አረገ:: ሥጋቸውን #አባ_ባውማ ቀበሩት:: የአቡነ ኪሮስ ቁመታቸው ቀጥ ያለ: ጽሕማቸውም የተንዠረገገ ነበር:: እድሜአቸውን ግን መገመት የሚቻል አይመስለኝም::
From d/n yordanos abebe
@senkesar @senkesar
💚💛ተአምረ ቅዱስ ሚካኤል💛❤️

ቅዱስ መጽሐፍ እንደ ነገረን በዚህች ዕለት የመላእክት ሁሉ አለቃቸው: የቅዱሳንም ረዳታቸው የሆነው ደጉ መልአክ #ቅዱስ_ሚካኤል ንጉሡን ሕዝቅያስን ግሩም.በሆነ ተአምር ከከተማው #ኢየሩሳሌም ጋር ታድጐታል:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

ከመድኃኒታችን #ክርስቶስ ልደት 700 ዓመታት በፊት #ሕዝቅያስ የሚባል ንጉሥ በይሁዳ ላይ ነግሦ ነበር:: ደጋጉ #ዳዊትና #ሰሎሞን ካረፉ በሁዋላ የሕዝቅያስን ያክል ቅን እና የእግዚአብሔር ሰው በእሥራኤል ላይ አልነገሰም:: ንጉሡ ጣዖት አምልኮን ነቃቅሎ አጥፍቶ ሕዝቡ እግዚአብሔርን ብቻ እንዲያመልክ አድርጐም ነበር::

ነገር ግን ቅዱስ ሕዝቅያስ በነገሠ በ14ኛው ዓመት የአሕዛብ (የአሦር) ንጉሥ ሰናክሬም በጠላትነት ተነሳበት:: ወደ አካባቢውም መጥቶ: ከቦ አስጨነቀው:: ሰናክሬም በጦር እጅግ ኃይለኛ ነበር:: በዚያውም ላይ ጦር የሚመዙ ከ185,000 በላይ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩትና ሕዝቅያስ እንደማይችለው ተረድቶ መልእክተኛ ላከበት::

"እገብርልሃለሁ:: የፈለግከውንም እሰጥሃለሁ:: ሃገሬን ግን አታጥፋ:: ኢየሩሳሌምን አታቃጥል:: ሕዝቤንም
አትግደል" በሚል ለመነው:: እጅ መንሻ ግብሩንም ከከተማዋ የተገኘውን ወርቅና ብር ሁሉ ጭኖ ላከለት::

ሰናክሬም ግን ሰይጣን ያደረበት ነውና የሕዝቅያስን ልመና ወደ ጐን ብሎ የእሥራኤልን አምላክ : ቅዱስ ስሙንም ተገዳደረ:: ለሕዝቅያስም "ከእኔ እጅ የሚያድንህ ማነው? ሕዝቡንም #እግዚአብሔር ያድናል ብለህ አታታልላቸው" ሲል ላከበት:: ቅዱስ ሕዝቅያስ በዚህ ጊዜ የፈጣሪው ስም ሲቃለል ሰምቷልና ፈጽሞ አዘነ::

መልእክተኞችን ወደ ነቢዩ #ቅዱስ_ኢሳይያስ ልኮ እርሱ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ:: በእግዚአብሔር ፊት ልብሱን ቀድዶ ማቅ ለበሰ:: ስለ ኢየሩሳሌምና ሕዝቡም ፈጽሞ አለቀሰ:: በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር የሰናክሬምን
መገዳደርና የሕዝቅያስን ልመና ሰምቷልና በኢሳይያስ አንደበት እንዲሕ አለ:- "ስለ ባሪያየ ስለ #ዳዊት ከተማዋን አድናታለሁ::"

በዚያች ሌሊትም ድንቅ መልአክ #ቅዱስ_ሚካኤል ከሰማያት በግርማ ወረደ:: ወደ ሰናክሬም የጦር ሠፈር ደርሶ አንድ ጊዜ የእሳት ሰይፉን መዝዞ ቢያሳያቸው ከአሕዛብ ሠራዊት 185 ሺ ኃያላን እንደ ቅጠል ረገፉ:: በለኪሶ የነበረው ሰናክሬም በጧት ቢነሳ ሠራዊቱ ሁሉ ወደ አስከሬን ክምር ተቀይሯል::

በድንጋጤ ወደ #ነነዌ ሒዶ ወደ ጣዖት ቤቱ ሲገባ የራሱ ልጆች (አድራማሌክና ሳራሳር) ገደሉት:: ትዕቢተኛው ሰናክሬም ለአሕዛብ ሁሉ መዘባበቻ ሆነ:: ቅዱስ ሕዝቅያስ ግን በፈጣሪው ታምኗልና ቅዱስ ሚካኤል ሞገስ ሆኖ የዓለም ነገሥታት ሁሉ ፈሩት:: (1ነገ. 18:13, 19:1)
From:- d/n yordanos abebe
@senkesar @senkesar
💚💛ቅዱስ ዮናስ ነቢይ💛❤️
በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ከ12ቱ #ደቂቀ_ነቢያት አንዱ የሆነው #ቅዱስ_ዮናስ ከክርስቶስ ልደት 800 ዓመታት በፊት እንደ ነበረ ይታመናል:: #ሊቃውንት እንዳስተማሩን ደግሞ እናቱ #ቅዱስ_ኤልያስን የመገበችው የሰራፕታዋ መበለት ናት:: ቅዱስ ዮናስ ገና ሕጻን ሳለ በእሥራኤል ምድር ዝናብ ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ተከልክሎ ነበር::

ይሕንንም ያደረገው ደጉ ነቢይ ኤልያስ ለአምልኮተ እግዚአብሔር ቀንቶ ነው:: በወቅቱ ኤልያስ በሰራፕታ ሳለ ሕጻኑ ዮናስ ታሞ ሞተ:: ልጇ የሞተባት መበለትም ኤልያስን ለመነችው:: ኤልያስም ወደ ፈጣሪው ማልዶ ሕጻኑን ዮናስን ከሞት አስነስቶታል:: ትንሽ ከፍ ባለ ጊዜም ከጉዋደኞቹ (ከነቢያቱ) #አብድዩና #ኤልሳዕ ጋር ሆነው ታላቁን ነቢይ ኤልያስን ተከትለውታል::

ኤልያስ ካረገ በሁዋላ ሁሉም በየተሰጣቸው አገልግሎት ተሠማርተዋል:: ቅዱስ ዮናስን #እግዚአብሔር "ወደ ነነዌ ሒደሕ ንስሃን ስበክ" አለው:: ዮናስ ግን የፈጣሪውን መሐሪነት ጠንቅቆ ያውቃልና አልሔድም አለ:: (ተመልከቱ የየዋሕነት ብዛት)

እግዚአብሔር እየደጋገመ እንዲሔድ ሲነግረው ነቢዩ "እንዲሕ የሚዘበዝበኝ ከፊቱ ብቀመጥ አይደል" ብሎ ሊኮበልል ወጣ:: ነገር ግን አልቀናውም:: በእርሱ ምክንያት ማዕበል ተነሳ:: ሕዝቡም ሊያልቁ ሆነ:: ከእንቅልፉ የነቃው ዮናስ ከመርከቡ ላሉት አሕዛብ አምልኮተ እግዚአብሔርን ሰብኮላቸው: በእርሱ ጠያቂነት ሐምሌ 15 ቀን ወደ ባሕር ጥለውታል::

አሣ አንበሪም ተቀብሎታል:: በግዙፉ አሣ ውስጥም ያለ እንቅልፍ በጾም: በጸሎትና በምስጋና 3 ለቀን ቆይቷል:: ሙስና ሳያገኘውም በዚህች ቀን አሣ አንበሪው #ነነዌ ዳር ላይ ተፍቶታል:: ቅዱስ ዮናስ እግዚአብሔር እንዳዘዘው "እስከ ሠሉስ ዕለት ትትገፈታእ ነነዌ ዓባይ ሃገር" /እስከ ሦስት ቀን ድረስ ነነዌ ትገለበጣለች (ዮናስ 3:4)/ ብሎ አሰምቶ ሰበከ::

የነነዌ ሰዎችም በስብከተ ዮናስ አምነው: ንስሃም ገብተው ድነዋል:: በዚህም ጌታችን በወንጌል ላይ አመስግኗቸዋል:: ቅዱስ ዮናስ መኮብለሉ #በሐዲስ_ኪዳን ለሚደረገው ምስጢረ ትንሳኤ ጥላ (ምሳሌ) ነውና ይደነቃል:: (ማቴ. 12:38) ነቢዩ ግን በተረፈ ሕይወቱ ሕዝቡን ሲያስተምር: ፈጣሪውን ሲያገለግል ኑሮ በመልካም ሽምግልና ዐርፏል::
From d/n yordanos abebe
@senkesar @senkesar
💚💛ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት 💛❤️
እናታችን ቅድስት ቴክላ በኒቆምድያ ተወልዳ ያደገች: ከአሕዛባዊ እምነት ወደ ክርስትና በሐዋርያው #ቅዱስ_ዻውሎስ አማካኝነት የመጣች እናት ናት:: እርሷ ክርስትናን ከልብ ለሚሹ ሴቶች ሁሉ መሪና ትልቅ ት/ቤት ናት:: ወንጌልን ከሐዋርያው ስትማር ምሥጢሩ እየመሰጣት አንዳንዴ ለ3 ቀናት ምግብ አትቀምስም ነበር::

እጅግ ቆንጆ ወጣትና የሃብታሞች ልጅ ብትሆንም ስለ ክርስቶስ ሁሉን ለመናቅና መስቀሉን ለመሸከም አልተቸገረችም:: ከኒቆምድያ እስከ አንጾኪያ ወንጌልን ሰብካለች:: ወላጆቿን ጨምሮ ብዙ ነፍሳትን አድናለች:: በፈንታውም ብዙ መከራን ተቀብላ በዚህ ቀን ዐርፋለች:: ቤተ ክርስትያን " #ሐዋርያዊት" ብላ ታከብራታለች::
@senkesar @senkesar
💚💛ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ 💛❤️
ለቤተ ክርስቲያን በንጹሕ ሕይወታቸው ካበሩላት ዐበይት ቅዱሳን አንዱ #ቅዱስ_ዱማድዮስ ነው:: እርሱ ወደ ክርስትና የመጣው ከባዕድ አምልኮ ሲሆን መሪው #መንፈስ_ቅዱስ ነው:: ጣዕመ ሕይወቱን ሲሰሙት ዕዝነ ልቡናን ደስ ያሰኛል::

ገና በወጣትነቱ እንደ #ሐዋርያት ሰብኮ አሕዛብን አሳምኗል:: እንደ #ጻድቃን አካሉ አልቆ አጥንቶቹ እስኪታዩ ተጋድሏል:: እርሱ #ድንግል: #ንጹሕ: #መነኮስ: #ባሕታዊና #ካህን ነው:: ግን ውዳሴ ከንቱን አምርሮ ይጠላል:: በዚህ ምክንያት ካደረበት አይውልም: ከዋለበትም አያድርም::
እርሱ በጸሎቱ የተዘጉ ማሕጸኖችን ከፍቷል:: ዕውራንን አብርቷል:: ለምጻሞችን አንጽቷል:: አንካሶችን አርትቷል:: በፈጣሪው ኃይል ፈሳሽ ወንዝን አቁሟል:: እንደ ገናም እንደ ነበረው መልሶታል::

የቅዱስ ዱማድዮስ መጨረሻው ደግሞ #ሰማዕትነት ነው:: በበዓቱ ውስጥ ሳለ ከደቀ መዝሙሩ ጋር ክፉዎች በድንጋይ ወግረው ገድለውታል:: ድንጋዩም የኮረብታ ያህል ነበር:: ልክ በዓመቱ በዚህች ዕለት ምዕመናን ሥጋውን አፍልሠዋል::
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ቸር አምላክ ከነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃንና ሰማዕታት ክብርን ያሳትፈን::
From:- dn yordanos abebe
@senkesar @senkesar
ክፍል ፩
#የሰኞ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ
ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም እመቤታችን ከባረከችው በኋላ ምስጋናውን የጀመረው #“ፈቀደ እግዚእ…” ብሎ ነው፡፡
፩. በመቅድመ ወንጌል “ወአልቦቱ ካልእ ሕሊና ዘንበለ ብካይ ላዕለ ኃጢያቱ - በኃጢአቱ ከማዘን፣ ከማልቀስ በቀር ሌላ ግዳጅ አልነበረውም” እንዲል ጌታ ፭ ሺህ ከ፭፻ ዘመን በግብርናተ ዲያብሎስ ያዝን ይተክዝ የነበረ አዳምን ነጻ ያደርገው (ያድነው) ዘንድ ወደደ፡፡ ምድራዊ ንጉሥ የተጣላውን አሽከር “ሰናፊልህን (ልብስህን) አትታጠቅ፤ እንዲህ ካለ ቦታም አትውጣ” ብሎ ወስኖ ያግዘዋል፡፡ በታረቀው ጊዜ ግን ርስቱን፣ ጉልበቱን፣ ቤቱን፣ ንብረቱን እንደሚመልስለት ኹሉ ንጉሠ ሰማይ ወምድር እግዚአብሔርም “ጥንቱንም መሬት ነህና ወደ መሬት ተመለስ” /ዘፍ.፫፡፲፱/ ብሎ ፈርዶበት የነበረ አዳምን ይቅር ብሎ ወደ ቀደመ ቦታው ወደ ገነት፣ ወደ ቀደመ ክብሩ ወደ ልጅነት ይመልሰው ዘንድ ወደደ /ሉቃ.፳፫፡፵፫/፡፡
#ሊቁ (ቅዱስ ኤፍሬም) በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፱ ያለውን ኃይለ ቃል ሲተረጕምም እንዲህ ይላል፡- “ቸር ወዳጅ የኾነው እግዚአብሔር አዳምና ሔዋን ወዲያው እንደተሳሳቱ ፍርዱን አላስተላለፈባቸውም፤ ታገሣቸው እንጂ፡፡ ይኸውም ምኅረት ቸርነቱን ይለምኑት ዘንድ ነው፡፡ እነርሱ ግን አልለመኑትም፡፡ እግዚአብሔርም ምንም ሳይናገራቸው በገነት ውስጥ በእግር እንደሚመላለስ ሰው ኾኖ በድምፅ ብቻ መጥራቱን ቀጠለ፡፡ አዳምና ሔዋን ግን አሁንም አልመለስ አሉ፡፡ በመጨረሻም አምላክ ድምፁን ማሰማት ጀመር፡፡ ‘አዳምን ወዴት ነህ?’ ይላቸው ጀመር፡፡ አስቀድሞ በእግር እንደሚመላለስ ሰው ኾኖ በድምፅ ብቻ መጥራቱ መንገድ ጠራጊው ዮሐንስን እንደሚልክላቸው፣ ቀጥሎ ድምፅ አሰምቶ ወዴት ነህ ብሎ መፈለጉም ወልደ እግዚአብሔር ራሱ በተዋሕዶ ፍጹም ሰው ኾኖ ሊያድናቸው እንደ ፈቀደ ያጠይቃል” ይላል /St. Ephrem the Syrian, Commentary on Genesis/፡፡
#ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ኦሪት ዘልደትን በተረጐመበት በ፲፯ኛው ድርሳኑ ላይ፡- “በዚህ ንግግሩ የእግዚአብሔር ከአእምሮ የሚያልፈውን ፍቅሩን እንመለከታለን፡፡ አንድ አባት ልጁ የማይረባውን ነገር በማድረግ ከክብሩ ቢዋረድም አባቱ እጅግ እንዲወደውና ወደ ቀደመ ክብሩ ይመልሰው ዘንድ እንዲደክም፤ እግዚአብሔርም ከሰው ልጆች ጋር ይህን የመሰለ ፍቅር ሲያሳይ እናስተውላለን፡፡ አንድ ሐኪም ወደ ታማሚው አልጋ ጠጋ ብሎ በሽተኛውን እንዲጠይቀውና አስፈላጊውን ኹሉ እንደሚያደርግለት፣ ሰው ወዳጁ እግዚአብሔርም ወደ አዳም ጠጋ ብሎ ሲያነጋግረው እንመለከታለን” ይላል፡፡
ዳግመኛም #በሌላ አንቀጽ “አዳም ሆይ ወዴት ነህ” ማለቱ፣ ለአቅርቦት መኾኑን ሲገልጥ፡- “አዳም ሆይ! ምን ኾንክብኝ? በመልካም ቦታ አስቀምጬህ ነበር፤ አሁን ግን ቦታህ ተለወጠብኝ፡፡ ብርሃን ተጐናጽፈህ ነበር፤ አሁን ግን ጨለማ ውስጥ አይሃለሁ፡፡ ልጄ! ወዴት ነህ? ይህ ኹሉ እንደምን ደረሰብህ? በአንተ ውስጥ ያኖርኩት መልኬ ማን አበላሸብኝ? በዚህ ያህል ፍጥነት የጸጋ ልብስህን ገፎ የጽልመት ልብስ ያከናነበህ ማን ነው? ውዴ! ባለጸጋ አድርጌ ፈጥሬህ አልነበረምን? ታድያ አሁን ድኽነት ውስጥ የከተተህ ማን ነው? ያን የግርማ ልብስህን ሰርቆ ዕራቆትህ ትኾን ዘንድ ያደረገህ ማን ነው? እኮ የጸጋ ልብስህን እንድታጣ ያደረገህ ማን ነው? ይህን የመሰለ ቅጽበታዊ መለወጥ ከወዴት መጣብህ? የከበረ ዕንቁህን እንድትጥል ያደረገህ ምን ቢገጥምህ ነው? አክብሮ በተወደደ ቦታ ካስቀመጠህና ኹል ጊዜ በስስት ዐይን ሲያነጋግርህ ከነበረው አምላክህ ተደብቀህ እንድትሸሸግ ያደረገህ ምንድነው? ማንም የወቀሰህ ሳይኖር፣ እንዲህ እንዲህ አድርገህ በድለሃል ብሎ የመሰከረብህ ሳይኖር ይህን ያህል በፍርሐት መናጥ ከወዴት አገኘህ?” ይላል /Daily Readings of St. John Chrysostom/፡፡
#ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ሆይ! ፭ ሺሕ ከ፭፻ ዘመን በግብርናተ ዲያብሎስ የነበረ አዳምን ነፃ ካደረገው ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡ #“ቅድስት” ማለቱ ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት ልዩ ሲል ነው፡፡ ይኸውም፡-
· ሌሎች ሴቶች ከነቢብ ከገቢር ቢነጹ ከሐልዮ አይነጹም፡፡ እሷ ግን የዕንቆራው #ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ቴዎዶጦስ “ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ ድንግል በሕሊናሃ ወድንግል በሥጋሃ- ከፈጠራት ጀምሮ በምንም በምን (በሕሊናዋም በሥጋዋም) ከድንግልናዋ አልተለወጠችም” /ሃይ.አበ.፶፫፡፳፪/ እንዲል ከነቢብ፣ ከገቢር፣ ከሐልዮ ኃጢአት ንጽሕት ናትና፡፡
· #ጽንዕትም አለ፡፡ ሌሎች ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው፤ ኋላ ተፈትሖ አለባቸው፡፡ እሷ ግን ቅድመ ፀኒስ ጊዜ ፀኒስ፤ ቅድመ ወሊድ፣ ጊዜ ወሊድ፣ ድኅረ ወሊድ ጽንዕት (ወትረ ድንግል) ናትና፡፡
· #ክብርትም አለ፡፡ ሌሎችን ሴቶች ብናከብቸው ጻድቃንን፣ ሰማዕታትን፣ ጳጳሳትን፣ ሊቃውንትን ወለዱ ብለን ነው፡፡ እሷን ግን ወላዲተ አምላክ ወልዳልናለች ብለን ነውና፡፡
· #ልዩም አለ፡፡ እናትነትን ከድንግልና፣ አገልጋይነትን ከእናትነት፣ ወተትን ከድንግልና ጋር አስተባብራ የተገኘች፤ በድንግልናም እያለች ከጡቶቿ ወተት ተገኝተው በዝናም አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ የሚመግብ መጋቤ ፍጥረታት አምላክን የወለደች፤ እሳታውያን የሚኾኑ ኪሩቤል ሱራፌልም በፍርሐት በረዐድ ኹነው ዙፋኑን የሚሸከሙት እሳተ መለኮት ጌታን ፱ ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመች፣ በክንዷ የታቀፈች፣ በዠርባዋ ያዘለች ከእመቤታችን በቀር ሌላ ሴት የለችምና፡፡
#“ለምኚልን” ሲልም ልክ በዚህ ምድር እንደነበረው ዓይነት ልመና ከዚያ በኋላ ኖሮባት አይደለም፡፡ ስንኳን በሷና በሌሎችም የለባቸውም፡፡ በቀደመ ልመናዋ የምታስምር ስለ ኾነ እንዲህ አለ እንጂ፡፡ ይኸውም በቃል ኪዳኗ ማለት ነው፡፡ አንድም በቁሙ ይተረጐማል፡፡ ማዘከር (ማሳሰብ) አለና፡፡
#“ሰአሊ ለነ ቅድስት” የሚለው ቅዱስ ኤፍሬም የተናገረው አይደለም፡፡ “ታድያ ይህን የጨመረው ማን ነው?” በሚለው ላይም ኹለት ዓይነት አመለካከለት አለ፡፡ “ቅዱስ ያሬድ ለዜማ መከፈያ ተናግሮታል” የሚሉ አሉ፤ “የኋላ ሊቃውንት ተናግረውታል” የሚሉም አሉ፡፡
©ቅዳሴ ማርያም ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ