ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
💚💛ቅዱስ_ሚናስ ምዕመን ሰማዕት💛❤️

ቅዱስ ሚናስ ( #ማር_ሚና ) በምድረ ግብጽ ተወዳጅ ከሆኑ ሰማዕታት ዋነኛው ነው:: ልክ በሃገራችን #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ልዩ ቦታ እንዳለው ሁሉ ግብፃውያን
ማር ሚናስን ጠርተው አይጠግቡትም::

ምክንያቱም ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱ በመሆኑና ዛሬም ድረስ ለጆሮና ለዐይን ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ስለሚሠራ
ነው:: በተለይ ለታመመ: ለደከመና ለተጨነቀ ፈጥኖ ደራሽ: ባለ በጐ መድኃኒት ፈዋሽና አማላጅ ነው::

ግብጽ ውስጥ ቅዱሱን የማያውቅ ሰው ካገኛችሁ እርሱ ኦርርቶዶክሳዊ አይደለም ማለት ነው ሲባልም ሰምተናል:: በነገራችን ላይ ለቅዱሳን ተገቢውን ክብር በመስጠት: ታሪካቸውን በመጻፍ: በማጥናት: በመጽሔት: በፊልምና
በመሳሰሉት ለሕዝብ በማስተዋወቅ ግብጻውያኑ ከእኛ ብዙ ርቀት ሒደዋል:: ዛሬ እንኩዋ የምንጠቀምበትን ስንክሳር
80 ከመቶ እጁን ያዘጋጁት እነርሱ ናቸው::

አባቶቻችንና እናቶቻችን #ኢትዮዽያውያን_ቅዱሳን ግን አብዛኞቹ ተረስተው ቀርተዋል:: መጽሐፈ ገድላቸውንም ብል በልቶታል:: ዛሬም የቤት ሥራው የእኛ ብቻ ነው::

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ ሚናስ (ትርጉሙ ታማኝና ቡሩክ ማለት ነው):-

¤በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ የደጋግ ክርስቲያኖች ልጅ

¤በልጅነቱ የቅድስና ሕይወትን ያጣጣመ

¤በዘመኑ ሰው እጅግ ተወዳጅ የነበረ

¤ሃብትን: ክብርን: ሥልጣንን ንቆ በጾምና በጸሎት የተወሰነ

¤በመጨረሻም በክርስቶስ ስላመነ አላውያን የገደሉት ሰማዕት ነው::

እርሱ ሰማዕት ከሆነ ከበርካታ ዘመናት በሁዋላ ምዕመናን ክቡር አካሉን ፈልገው ያጡታል::

የሚገለጥበት ጊዜ ሲደርስ ግን እርሱ የተቀበረበት ምድረ በዳ የበጐችና የእረኞች መዋያ ነበርና ተአምራትን
አደረገ:: አንድ እረኛ በጐቹ ድውያን ሆኑበት:: በዚያ ሰሞን ከቅዱሱ መቃብር ላይ ጸበል ፈልቆ ነበርና እረኛው ተርታ
ውሃ ነው ብሎ በጎቹን ሲያጠጣቸው አንዱ ድውይ በግ ወደ ጸበሉ በመዘፈቁ ዳነ::

በዚህ የተገረመው እረኛ ሁሉንም የታመሙ በጐቹን አምጥቶ ነከራቸው:: እነርሱም ተፈወሱ:: ይህ ዜና በምድረ ግብፅ ሲሰማ ድውያን ሁሉ እየመጡ ይፈወሱ ገቡ:: ግን እነሱም ሆነ እረኛው ምክንያቱን ማወቅ አልቻሉም::

ነገሩ በሮም ንጉሥ ዘንድ ሲሰማ ሴት ልጁን ከሠራዊቱ ጋር ላካት:: ምክንያቱም እርሷ ከብዙ ዘመን ጀምራ መጻጉዕ ነበረችና ፈውስን አጥታ ነበር:: መጥታ
ተጠመቀች: ፈጥናም ተፈወሰች:: እርሷ ግን እንደ ሌሎች ያዳናትን ማንነት ሳታውቅ መሔድ አልፈለገችምና ሱባዔ ገባች::

#ቅዱስ_ሚናስ በሌሊት ራዕይ መጥቶ ሥጋው እንዳለ ነገራት:: እርሷም መሬቱን አስቆፍራ የቅዱሱን አካል በክብር አስወጣች:: ከዚያም በንጉሡ ትዕዛዝ ምድረ በዳው ከተማ እንዲሆን ተቀየረ:: ስሙም " #መርዩጥ " ተባለ:: ጸበሉ የነበረበት ቦታም ላይ የማር ሚናስ
#ቤተ_ክርስቲያን ታንጾበት በዚህች ዕለት ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል::

አምላካችን ከቅዱሱ ሰማዕት በረከትን ይክፈለን::
from:- d/n yordanos abebe
@senkesar @senkesar