የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.03K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት ካውንስል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የሸገር ከተማ አሰተዳደር ካውንስል ጽ/ቤት ምስረታ እየተካሄደ ይገኛል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/Evangelical MEDIA/Council
ዩትዩብ፦ https://youtu.be/gR3ahclodHM
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
1👍1
#ዜና_እረፍት
የቀድሞ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ማዕከላዊ ኮሚቴ አወያይ የነበሩት ዶ/ር አግነስ አቡኦም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ዜና እረፍታቸውን ተከትሎ #የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካውንስል እና የኢትዮጵያ_ወንጌላዊት_ቤተ_ክርስቲያን_መካነ_ኢየሱስ_ሀዘናቸውን_ገልፀዋል።

World Council Of Church "ተወዳጇ የሀይማኖት መሪ እና የማይታክቱ የሰላም ፈጣሪ ዶ/ር አግነስ አቡኦም ባደረባቸው ህመም ምክንያት በተወለዱ በ73 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ" ሲል ህልፈታቸውን አሳውቋል።

የዶ/ር አግነስ ሕልፈተ ህይወት ከተሰማ በኋላ ብዙዎች ሀዘናቸው የገለጹ ሲሆን የመካን ኢየሱስ ቤተክርስቲያንም ዶ/ር አግነስ ላለፉት አመታት በWCC ውስጥ ላበረከቱት አስተዋጽዖ ምስጋና አቅርበው እሷን ማጣት በአለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ኪሳራ ነው እና ከሁሉም በላይ ደግሞ አፍሪካ የአንድነት መገለጫዎቿን አጥታለች ሲሉ ሃዘናቸው በቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዝደንት ዶ/ር ቄስ ዮናስ ይገዙ አማካንኘት ገልጻለች።

በቅርብ ጊዜ ወደ ሃላፊነት የመጡት የአለም አብያተክርስቲያናት ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ ቄስ ፕሮፌሰር ዶ/ር ጄሪ ፒሌይ "ፍቅሯን፣ ጥበቧን፣ ደግነቷን፣ መተማመኗን፣ መነሳሳቷን እንናፍቃለን። እሷ አሁን በዘላለማዊ እቅፍ ውስጥ ተጠግታለች። እሷ ታላቅ ርህራሄ እና ጽኑ እምነት ያላት ሴት ነበረች። ሲሉ የተሰማቸው ሃዘን ገልጸዋል።

የመካከለኛው ምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት በምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ፕሮፌሰር ሚሼል ኢ አብስ በኩሉ ባስተላለፉት መልዕክት "በሞቱ ያዳነን ጌታ ኢየሱስ በትንሣኤው እንዲባርክና በሰማያት እንዲቀበላት እጸልያልሁ ብለዋል።

የሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የውጪ ቤተ ክርስቲያን ግንኙነት መምሪያ በበኩሉ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ወክለው የተሰማ
👍21
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካውንስል ጽ/ቤ ሃላፊ መጋቢ ጌትነትለማ #በአረንጉዴ_አሻራ_ዙሪያ ከካውንስሉ ክላስተር አመራሮች ጋር በዋናው ጽ/ቤ ተወያዩ፡፡

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ጽ/ቤ ሃላፊ መጋቢ ጌትነት ለማ ሃምሌ 6 ቀን 2015 ዓ/ም በአረንጉዴ አሻራ ዙሪያ ከካወንስሉ ክላስተር አመራሮች ጋር ሰኞ ሃምሌ 10 ቀን 2015 ዓ/ም 500ሚልዮን ችግኝ በአንድ ጀንበር በሃገር አቀፍ ደረጃ እንደሚተከል በታቀደው እቅድ መሰረት የክላስተር አመራሮች እና አባል ቤተ-እምነቶች በጉለሌ ህጽዋት ማእከል ተገኝተው አረንጓዴ አሻራቸውን ለማኖር እና የወንጌል አማኞች በዚሁ የሃገራዊ ጉዳይ ላይ መሳትፍ እንደሚገባቸው ተወያይተው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የካውንስሉ ጽ/ቤ ሃላፊ መጋቢ ጌትነት ለማ ችግኝ የምንተክለው የሃይማኖት ተቋማት ስለሆንን ብቻ ሳይሆን እንደ ዜጋ ለትውልድ የሚጠቅም ስራን መስራት ስለሚገባ ችግኝ መትከል ስላለብን እንተክላለን ብለዋል፡፡ በክላስተሩ የተዋቀሩ የወንጌል አማኞች በሙሉ በአረንጉዴ አሻራ መርሃ ግብር ሊሳተፋ እንደሚገባቸው መጋቢ ጌትነት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በስብሰባው የተገኙ ከአዲስ አበባ እና ከሸገር ከተማ የመጡ የክላስተር አመራሮች ከመንፈሳዊ አገላግሎት ባሻገር በሃገራዊ ጉዳይ ላይ ቀዳሚ ተሰላፊ መሆናቸውን ገልጸው የወንጌል አማኞች በዚህ ሃግራዊ ጉዳይ ላይ እንዲሳተፋ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ከአዲስ አበባ ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዩሃንስ ግርማ እንደገለጸው ሐምሌ 10 ቀን ለሚከናወነው አረንጉዴ አሻራ ቀን በጉለሌ የህጽዋት ማእከል ከሁሉም ሃይማኖት ተቀማት እንደሚሳተፉ ገልጾ በእለለቱ ከ4000 የሃይማኖት አባቶች 12000 ችግኝ ይተከላል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግሯል፡፡
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካውንስል_ድሬዳዋ_ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከሳልቬሽን ቮይስ የወንጌል አገልግሎት ጋር በመተባበር 120 ለሚጠጉ የቤተክርስቲያን መሪዎች እና አገልጋዮች #መንፈሳዊ_የአቅም_ግንባታ_ስልጠና ሰጠ።
በድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ማህበረ ምዕመናን አዳራሽ በተሰጠው በዚህ ስልጠና የእግዚአብሄር ራእይ በሚል ርእስ እግዚአብሔር የራእይ ባለቤት እንደሆነና አገልጋዮች የእርሱን ተልእኮ የመፈጸም አደራ እንዳለባቸው ትምህርት ቀርቧል ።
ስልጠናውን የሰጡት የሳልቬሽን ቮይስ ሚኒስትሪ መስራች እና መሪ የሆኑት ሐዋርያው መክብብ ሙላቱ ሲሆኑ በስልጠናው የተካተቱ ሐሳቦች ለጊዜው የሚያስፈልጉና ሕይወት ለዋጭ እንደነበሩም የስልጠናው ተሳታፊዎች ገልፀዋል።
በቀጣይም እንደዚህ አይነት ስልጠናዎች ቢበራከቱ የአካባቢው የወንጌል እንቅስቃሴ እንደሚያግዝ ተሳታፊዎቹ ተናግረዋል።
የድሬዳዋ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ቦርድ ሰብሳቢ ወንድም በላቸው ላምቦሮ ሳልቬሽን ቮይስ የወንጌል አገልግሎት እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ አድንቀው ሚኒስትሪው በድሬዳዋ ከተማ መንፈሳዊ ንቅናቄ የሚፈጥር እና በአይነቱ ልዩ የሆነ ከተማ አቀፍ ክሩሴድ ከጥቅምት 8- እስከ 11 ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።
‘ሁላችንም ስለወንጌል አንድ ሆነን እንደ ተማርነው እንደ አንድ የክርስቶስ አካል ተልእኮአችንን ልንፈጽም ይገባል’ም ብለዋል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/SHjyVAQRTzU
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍1🙏1
#የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አካሄደ።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ግንቦት 15 ቀን 2016ዓ/ም በመካነ ኢየሱስ ሴሚናሪየም የመሰብሰቢያ አዳራሽ አካሄደ። በጉባኤዉ የካዉንስሉ አባል ቤተ እምነቶች የአብያተክርስቲያናት መሪዎች የቤተ-እምነት መሪዎች ተካፍለዋል።

የካዉንስሉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጣሰዉ ገብሬ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዉ ጉባኤዉን አስጀምረዋል።

በጉባኤዉ የሰላም ሚንስቴር ተወካይ ዶ/ር አወቀ አጥናፋ መልእክት ያስተላለፋ ሲሆን በመልእክታቸዉም የወንጌል አማኞች ሰላምን ጠንቅቃችሁ ታዉቃላችሁ ከዚህ በበለጠ ለሰላም ስሩ ሲሉ ተናግረዋል።እንዲሁም የመፅሃፍ ቅዱስ ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ይልማ ጌታሁን ለጉባኤዉ ሰላምታ አቅርበዋል።በተለያየ የአለም ክፍል የሚገኙ የካዉንስሉ አባል በዙም አማካኝነት ለጉባኤዉ ሰላምታ ሰተዋል።

በጉባኤዉ የ2015ዓ/ም አመታዊ ሪፖርትእና የ2015ዓ/ም ኦዲት ሪፖርት በዉጪ ኦዲተሮች የቀረበ ሲሆን የ2016ዓ/ም እቅድ ለጉባኤዉ ቀርቧል።

በቀረበዉ እቅድ ከጉባኤዉ ለተነሱ ጥያቄዎች የካዉንስሉ ጠቅላይ ፀሃፊ ቄስ ደረጀ ጀንበሩ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰተዋል።

በጉባኤዉ ለኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አንድነት እና እርቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ መሪዎች ስጦታ እና ምስጋና ቀርቧል።

በመጨረሻም የካዉንስሉ ፅ/ቤ ሃላፊ መጋቢ ጌትነት ለማ ቃለ ጉባኤ አቅርበዉ የቀረበዉ ቃለ ጉባኤ በሙሉ ድምፅ ፀድቆ ጉባኤዉ በፀሎት ተጠናቋል።
6👍3
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካውንስል_በዋሽንግተን_ሲያትል_ቅርንጫፍ_ፅህፈት_ቤቱን_ከፈተ
የሲያትል ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ የካውንስሉ ምክትል ፕሬዝዳንት ሐዋርያው ዮሐንስ ግርማ እና የካዉንስሉ ጠቅላይ ፀሃፊ ቄስ ደረጄ ጀምበሩ በተገኙበት በይፋ ተቋቁሟል።
በምስረታ ስነስረአት ላይ የሲያትል ከተማ አብያተ ክርስቲያናት ህብረት መሪዎች እና ከካናዳ የተጋበዙ የቤተክርስቲያን መሪዎች በተገኙበት ይፋዊ ምስረታ ተካሂዷል።
ጌታ ረድቶንና አግዞን እዚህ ደርሰናል ለብዙ ጊዜ የለፋንበት ድካማችን ፍሬን አፍርቷል በስያትል ትልቅ ታሪክ ተሰርቷል።ደስ ብሎናል ከዚህ በኋላም እጅ ለእጅ ተያይዞን የሰማዩን ተልእኮ በጋራ ሆነን እናስፈጽማለን እግዚአብሔርም ይረዳናል በማለት መሪዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍2713
#የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል #በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ

ካውንስሉ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ የተከሰተውን ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል፡፡

ካውንስሉ በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው የተጎጂ ቤተሰቦች እና ዘመድ ወዳጆች ሁሉ መፅናናትን ተመኝቷል።
😢24👍5
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካውንስል_ከውሃና_ኢነርጂ_ሚንስትር_ጋር_የመግባቢያ_ስምምነት_ተፈራረሙ

ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ከውሃና ኢነርጂ ሚንስትር ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። በቀጣይ በማንኛቸውም በሚሰሩ ስራዎችን በመደገፍ ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ጋር በርካታ ስራዎችን በጋራ እንደሚሰሩ የውሃና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ገልጸዋል ።የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሃፈ ቄስ ደረጃ ጀምበሩ የውሃና ኢነርጂ ሚንስትር በማመስገን በመያያዝና በመከባበር በአንድነት ብንሰራ በሀገር ደረጀ በርካታ ስራዎች ላይ ውጤታማ መሆን እንችላለን ብለዋል።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍172
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካውንስል_10ኛው_የቦርድ_ስብሰባ_በኢትዮጵያ_ቃለ_ሕይወት_ቤተክርስቲያን_ኩሪፍቱ_ማዕከል_ቢሾፍቱ_ተካሄዷል

ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል 10ኛው የቦርድ ስብሰባ ፕሮገራም ላይ በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ዋና ፀሃፊ በዶ/ር ስምዖን ሙላቱ መሪነት የኩሪፍቱ ማዕከል ጉብኝት የተደረገ ሲሆን በማስከተልም በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ፀሃፊ ቄስ ደረጄ ጀምበሩ ጸሎት ተደርጎ በፓ/ር ታሪኩ ብርሃኑ በ2ኛዜና 20፣1፣25 ላይ የእግዚአብሔርን ቃል አካፍለዋል ።

በካውንስሉ ጽ/ቤት የስራ ሪፖርተር ቀርቦ አመታዊ መዋጮና የምዝገባ ክፍያን ሰለማሻሻል እና የካውንስሉን ዋና ጽ/ቤት ቦታ ግንባታን ሥራን በተመለከተ የውይይት እና የምክክር ጊዜ ተደረጎ የዕለቱን ቃለ ጉባዔ በማጽደቅና ቀጣይ የስብሰባ ቀን በቦርድ አባለት በመወሰን ስብሰባ ተጠናቋል።



#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካውንስል_ከቢሊግረሃም_አሶሴሽን_ጋር_በመተባበር_ለአገልጋይ_ሴቶች_ስልጠና_ተሰጠ

ህዳር 12 ቀን 2017ዓ/ም በዩጎ ቤተክርስቲያን በተሰጠዉ ስልጠና ከልዩ ልዩ ቤተ-ዕምነት እና ህብረቶች የተወጣጡ 260 የሚሆኑ ሴት አገልጋዮች በስልጠናዉ ተካፍለዋል።

የካዉንስሉ መንፈሳዊ ዘርፍ ዳይሬክተር ፓስተር ስንሻት ተካ እንደገለፁት የስልጠናዉ አላማ አገልጋይ ሴቶች ውጤታማ የወንጌል መስካሪዎች እንዲሆኑ ለማስታጠቅ መሆኑን በመግለፅ ይህ ፕሮግራም በተመሳሳይ ማክሰኞ ህዳር 17 ቀን 2017ዓ.ም. ከ2:30 ጀምሮ ልደታ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ በሚገኘው በናዛሪን ቤ/ክ የሚሰጥ መሆኑን አክለዉ ተናግረዋል።

ከቢሊግርሃም ኢቫንጀልስቲክ አሶሴሽን ስልጠናዉን የሰጡት ቄስ ፀጋነሽ በበኩላቸዉ እኔ እንድሪያስ ነኝ በሚል መሪ ሃሳብ በስልጠናዉ የተሳተፋ ሴት አገልጋዮች ወደመጡበት ሲመለሱ ወንጌልን በአካባቢያቸዉ መመስከር እንዲችሉ የሚያበቃ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል።

ከስልጠናዉ በኋላ የጋራ የዉይይት እና የምክክር እንዲሁም የትዉዉቅ ጊዜ ተከናዉኖ ስልጠናዉ ተጠናቋል።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍6
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካውንስል
#ከdynamic church planting international (DCPI) ጋር በመተባበር በሀዋሳ እና አዳማ ከተማ ስልጠና ተሰጠ።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ከDCPI ጋር በመተባበር በሀዋሳ እና አዳማ ከተማ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን የስልጠናው አላማ ቤተክርስቲያን በተሰጣት ብርቱ አላፊነት ላይ ትኩረት እንድትአደርግ የሚረዳ ስልጠና እንደሆነ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል የዓለም አቀፍ ግኑኝነት ዳይሬክተር ፓስተር አሸብር ከተማ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል የዓለም አቀፍ ግኑኝነት ዳይሬክተር ፓስተር አሸብር ከተማ የመጨረሻው ስልጠና በአምቦ ከተማ የሚደረግ መሆኑንና በ2025 በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በስፋት ስልጠናው የሚሰጥ መሆኑን አክለው ገልፀዋል።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍31
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካውንስል_ከኢትዮጵያ_መጸሐፍ_ቅዱስ_ማህበር_ጋር_በመተባበር_በኢትዮጵያ_ዘላቂ_ሰላም_ጉደይ_ላይ_የተዘጋጀ_አውደ_ጥናት_ተካሄደ

ጥር 16 ቀን 2017/ ዓ.ም የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ከኢትዮጵያ መጸሐፍ ቅዱስ ማህበር ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ጉደይ ላይ የተዘጋጀ አውደ ጥናት በስካይላይት ሆቴል የተካሄደ ሲሆን የካውንስሉ ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እስኪ መጣ ድረስ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ስራውን ይቀጥላል ሲሉ ገልፀው በሀገር ደረጃ የኢትዮጵያ መጸሐፍ ቅዱስ ማህበር እየሰራ ያለውን ስራ አድንቀው ልባዊ ምስጋናቸውን ገልጸዋል ።


ቀሲስ ሊቅ ትጉዋን ይልማ ጌታሁን የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር በሀገር ደረጃ በሰላም ዙሪያ ምን አይነት ተጽእኖ እየፈጠረን ነው ብለን ልንጠይቅ ይገባል ሲሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል ።በዚህ መርሐግብር ላይ ከተለያዩ አብያተክርስቲያናት የተወከሉ መሪዎች በሰላም ዙሪያ ላይ እየሰራው የሚገኙት የልምድ ማካፈል ጊዜ አከናውነዋል።
በዶ/ር ሳምሶን እስጢፋኖስና በቄስ ዶ/ር ገለታ ሲሜሶ ቀጣይ አካሄዶችና እርምጃዎች ላይ ጠቃሚ አሳቦችን በማቅረብና ውይይት በማድረግ መርሐግብሩ በጸሎት ተጠናቋል ።



#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍43
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካውንስል_46ኛው_የሥራ_አስፈጻሚ_ኮሚቴ_ስብሰባ_በጉዲና_ቱምሳ_ሁለገብ_ማሰልጠኛ_ማዕከል_ተካሄደ
ጥር 22 ቀን 2017/ዓ.ም የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል 46ኛው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በጉዲና ቱምሳ ሁለገብ ማሰልጠኛ ማዕከል አካሄዶዋል። ቄስ ተሾመ አመኑ የአግዚአብሔር ቃል ያካፈሉ ሲሆን በካውንስሉ የተሰሩ የሥራ ሪፖርት ተደምጧል ።ከነዚህም መካከል የካውንስሉ የውጭ ግንኙነት መመሪያ ፣የታሪክ መጽሐፍ ዝግጅት ኮሚቴ ፣የመጽሐፍ ቅዱስ ይዘት ኮሚቴ እና የልጆች ፌሰቲሻል ፕሮግራምን በተመለከተ በነዚህ ርዕሰ ጉዳዬች ሪፖርት ቀርቦዋል።
የካቲት 29-30 ካውንስሉ ከቢሊግርሃም ኢሻንጀልስቲክ አሶሴሽን ጋር በመተባበር በመስቀል አደባባይ ያዘጋጀውን ፕሮግራም በሚመለከት አስካሁን የተሰሩትንና ልሰሩ በሚገባቸው ጉደይ ላይ ውይይት ተደርጓል ።የበዓለ ሃምሳ ቀን አከባበር በኢትዮጵያ ቅድመ ዝግጅትን አስመልክቶ ትልቅ የሆነ ውይይት እና አቅጣጫዎች ተቀምጦአል ።
በዚህ ስብሰባ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችና አሳቦች የተነሱ ሲሆን በካውንስሉ ፕሬዚዳንት ጣሰው ገብሬ(ዶ/ር) ፣በምክትል ፕሬዚዳንት ሐዋርያው ዮሐንስ ግርማ እና በካውንስሉ ጠቅላይ ጸሐፈ ደረጀ ጀምበሩ ምላሽ ተሰጥቶበታል ።ቀጣይ የቦርድ እና የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ ቀን በመወሰን ተጠናቋል ።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍2
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካውንስል_ከmission_of_hope_international_ጋር_ወይይት_አደረገ

ጥር 26 ቀን /2017 ዓ.ም mission of hope international በኬንያ መሰረት አድርጎ እየሰራ ያለ ተቋም ሲሆን በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ስራ ለመስራት በካውንስሉ ቢሮ በመገኘት የውይይትና የምክክር ጊዜ አድርጓል።

እ.ኤ.አ 2000 ዓ.ም 50 ሕፃናትን በመረዳት የትምህርት እድሎችን በማመቻቸት የጀመረ ሲሆን በአሁን ጊዜ በኬንያና በለቤሪያ ከ37 በላይ የሚሆኑ ትምርህት ቤቶችን እና በርካታ ሕፃናትን በመረዳት እያገለገለ ያለ ተቋም ነው።በተደረገው ወይይት ከኬንያና ከአሜሪካ የመጡ 18 የሉካን ቡድን ተገኝተዋል።የካውንስሉ የውጪ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ መጋቢ አሸብር ከተማ ካውንስሉ እየሰራ ስላለው ስራ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ውሰጥ ተመሳሳይ ስራዎችን ከካውንስሉ ጋር በመሆን ለመስራት ፍቃደኛ መሆናቸውንና የመጀመሪያውን ምዝገባ በካውንስሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።በሚቀጥሉት ጊዜያቶች የምክክሩ ወጤት ከምን እንደደረሰ የምን ገልጽ የሆናል ሲሉ የካውንስሉ የውጪ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ መጋቢ አሸብር ከተማ ለኢቫንጀሊካል ቴሌቬዥን ገልጸዋል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍114🙏1