የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.05K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#ዜና_እረፍት

#ታላቁ_የወንጌል_ አርበኛ_ወንጌላዊ ዶ/ር #ገብሩ_ወልዱ_ወዳገለገለው_ጌታ_ሄደ:: ላለፉት 30 አመታት በላይ የእግዚአብሔርን መንግስት በወንጌል ያገለገለው ወንጌላዊ ገብሩ ወልዱ ወዳገለገለዉና ወደ ሚወደዉ አባቱ ወደሰማያዊ ቤቱ ሄዷል::
የኢቫንጀረልካል ቲቪ እግዚአብሔር ለመላዉ ቤተሰቦቹና ለወዳጆቹ እንዲሁም ለክርስቲያን ወገኖች መጽናናትን እንዲሰጥ ይመኛል።

መዝ 116 ፤ 15
የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC
ዩትዩብ፦ https://youtu.be/fFDM6J3MJK8
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
4👍1
#ዜና_እረፍት
የቀድሞ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ማዕከላዊ ኮሚቴ አወያይ የነበሩት ዶ/ር አግነስ አቡኦም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ዜና እረፍታቸውን ተከትሎ #የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካውንስል እና የኢትዮጵያ_ወንጌላዊት_ቤተ_ክርስቲያን_መካነ_ኢየሱስ_ሀዘናቸውን_ገልፀዋል።

World Council Of Church "ተወዳጇ የሀይማኖት መሪ እና የማይታክቱ የሰላም ፈጣሪ ዶ/ር አግነስ አቡኦም ባደረባቸው ህመም ምክንያት በተወለዱ በ73 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ" ሲል ህልፈታቸውን አሳውቋል።

የዶ/ር አግነስ ሕልፈተ ህይወት ከተሰማ በኋላ ብዙዎች ሀዘናቸው የገለጹ ሲሆን የመካን ኢየሱስ ቤተክርስቲያንም ዶ/ር አግነስ ላለፉት አመታት በWCC ውስጥ ላበረከቱት አስተዋጽዖ ምስጋና አቅርበው እሷን ማጣት በአለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ኪሳራ ነው እና ከሁሉም በላይ ደግሞ አፍሪካ የአንድነት መገለጫዎቿን አጥታለች ሲሉ ሃዘናቸው በቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዝደንት ዶ/ር ቄስ ዮናስ ይገዙ አማካንኘት ገልጻለች።

በቅርብ ጊዜ ወደ ሃላፊነት የመጡት የአለም አብያተክርስቲያናት ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ ቄስ ፕሮፌሰር ዶ/ር ጄሪ ፒሌይ "ፍቅሯን፣ ጥበቧን፣ ደግነቷን፣ መተማመኗን፣ መነሳሳቷን እንናፍቃለን። እሷ አሁን በዘላለማዊ እቅፍ ውስጥ ተጠግታለች። እሷ ታላቅ ርህራሄ እና ጽኑ እምነት ያላት ሴት ነበረች። ሲሉ የተሰማቸው ሃዘን ገልጸዋል።

የመካከለኛው ምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት በምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ፕሮፌሰር ሚሼል ኢ አብስ በኩሉ ባስተላለፉት መልዕክት "በሞቱ ያዳነን ጌታ ኢየሱስ በትንሣኤው እንዲባርክና በሰማያት እንዲቀበላት እጸልያልሁ ብለዋል።

የሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የውጪ ቤተ ክርስቲያን ግንኙነት መምሪያ በበኩሉ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ወክለው የተሰማ
👍21
#ዜና_እረፍት
#የኢትዮጵያ_ቃለ_ሕይወት_ቤተ_ክርስቲያን_አገልጋይ_መሪ_የነበሩት_አቶ_ወራቦ_መኑ_በ75_ዓመታቸው_ወደ_ጌታ_ሄዱ
አቶ ወራቦ በቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ብሔራዊ ቦርድ አባልነት፣ በዋና ጽሕፈት ቤት የሥራ ኃላፊነት ብሎም በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናቸው በተለይም በጌጃ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ለበርካታ ዓመታት በሽምግልና በማገልገል ቤተ ክርስቲያኒቱ ካፈራቻቸው አንጋፋ አገልጋይ መሪዎች መካከል አንዱ ነበሩ።
የአቶ ወራቦ ቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ ሐምሌ 14 ቀን 2015 ዓ.ም የሚፈጸም ሲሆን ከቀኑ በ7:30 ሳር ቤት በሚገኘው አይ ኢ ሲ (ኢንተርናሽናል ኢቫንጀሊካል ቤተ ክርስቲያን) የሽኝት መርሃ ግብር ከተካሄደ በኋላ ዊንጌት አደባባይ በሚገኘው ጴጥሮስ ወጳውሎስ የመቃብር ስፍራ ከቀኑ 9:30 ላይ ስርአተ ቀብራቸው ይፈጸማል።
ካውንስሉ ለቤተሰቦቻቸው እና ለውዳጅ ዘመዶቻቸው መፅፅናናትን ይመኛል
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/EGBCC
ዩትዩብ፡ -https://youtu.be/z4dg1y0ewBI
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍2
#ዜና_እረፍት
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረትን በዋና ጸሐፊነት የመሩት #ቄስ_ዓለሙ_ሼጣ ወደ ሚወዱትና ወዳገለገሉት አምላካቸው ተሰበሰቡ።
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስ የቲዮሎጂና ሚሽን መምሪያ ዳሬክተር እንዲሁም የቤተክርስቲያኒቱ የደቡብ ሲኖዶስ ፕሬዝዳንት በመሆን ያገለገሉት እንዲሁም የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት ህብረትን ከ1999 ዓ.ም እስከ ኅዳር 2008 ዓ.ም ለ9 አመታት በታማኝነትና በጥበብ በመምራት በብዙዎች ዘንድ ከበሬታን ያገኙት ቄስ አለሙ ሼጣ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
የእግዚአብሔር ቃል በ1ኛ ተሰሎንቄ 4:14፤ "ኢየሱስ እንደ ሞተና እንደ ተነሣ ካመንን፥ እንዲሁም በኢየሱስ ያንቀላፉቱን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋልና" እንደሚል በጌታ ቀን እንደምናገኛቸው ተስፋ አለን::
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል በወንድማችን እልፈት የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን እየገለጸ፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸውና ለመላው ወንጌላውያን አማኞች መጽናናትን ይመኛል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/JH8xh0nRv8I
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
4👍3