#የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል
#በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ
ካውንስሉ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ የተከሰተውን ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል፡፡
ካውንስሉ በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው የተጎጂ ቤተሰቦች እና ዘመድ ወዳጆች ሁሉ መፅናናትን ተመኝቷል።