የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.05K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካውንስል_በዋሽንግተን_ሲያትል_ቅርንጫፍ_ፅህፈት_ቤቱን_ከፈተ
የሲያትል ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ የካውንስሉ ምክትል ፕሬዝዳንት ሐዋርያው ዮሐንስ ግርማ እና የካዉንስሉ ጠቅላይ ፀሃፊ ቄስ ደረጄ ጀምበሩ በተገኙበት በይፋ ተቋቁሟል።
በምስረታ ስነስረአት ላይ የሲያትል ከተማ አብያተ ክርስቲያናት ህብረት መሪዎች እና ከካናዳ የተጋበዙ የቤተክርስቲያን መሪዎች በተገኙበት ይፋዊ ምስረታ ተካሂዷል።
ጌታ ረድቶንና አግዞን እዚህ ደርሰናል ለብዙ ጊዜ የለፋንበት ድካማችን ፍሬን አፍርቷል በስያትል ትልቅ ታሪክ ተሰርቷል።ደስ ብሎናል ከዚህ በኋላም እጅ ለእጅ ተያይዞን የሰማዩን ተልእኮ በጋራ ሆነን እናስፈጽማለን እግዚአብሔርም ይረዳናል በማለት መሪዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍2713