የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.68K subscribers
9.3K photos
132 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!

ሐዋሪያ ብስራት ብዙአየው
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል የቦርድ አባል እና ከኒው ክሬዬሽን አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን

ነብይ እዬብ
(ኦኘን ዶር አለምአቀፍ ቤ/ክ)
#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!

ነብይ እዩ ጩፋ
ከክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን

ሪቨረንድ ተዘራ ያሬድ
ከክብር ህይወት ቤተክርስቲያን
#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!

በካቢኔ ውሳኔ ተሰቷል ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ ሊሰጠን የሚገባ ቦታ ሁሉ በስም ቦታው ተጠቅሶ እስኪነገር ድረስ ግልጽ የሆነ ነበረ። ነገር ግን በበላይ እና በወሳኝ አካል ከተወሰነ በኋላ አስፈጻሚው አካል ጋር ሲደርስ የሚያስፈጽመው አካል በካውንስሉ ላይ መጉላላትን ፈጽሟል።

ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ም/ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዝደንት
#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ሁላችንም ደስ ብሎን በጋራ በ2012ዓ.ም ያቋቋምነው ተቋም ነው። በቅድሚያ ለዋና ጽ/ቤት እና ለተለያዩ አገልግሎቶች እንዲውል በካቢኔ 20ሺህ ካ.ሜ ስለተወሰነልን ከልብ እናመሰግናለን። ወደ አፈጻጸም ስንመጣ ግን ላለፉት ጊዜያት ስንጉላላ ነበር። መብት ልመና የለውም መብት መብት ነው።

መጋቢ ሰንበቶ ባሻ
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የስራ አመራር ቦርድ አባል እና የህይወት ብረሃን ቤተክርስቲያን ፕሬዝደንት
https://youtu.be/qqNYINkWlUo ውድ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ቤተሰቦች ካውንስሉ ከሰሞኑ ተሰቶት የነበረው 20ሺህ ካሬ ቦታ የሚመልከታቸው አካላት ሊያስረክቡን ፍቃደኛ እንዳልሆኑ አሳውቀን እንደነበር ይታወሳል።

ጉዳዩን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ም/ፕሬዝደንት ቄስ ዮናስ ይገዙ ጋር ቆይታ አድርገን ማብራሪያ እና ምላሽ ሰጥተውናል።
#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!

ይህ ካውንስል አብያተ ክርስቲያናትን ሁሉ የሚያቅፍ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ አባላትን የሚያገለግል ትልቅ ተቋም ነው። አገልግሎቱ ደግሞ ለሀገር ጭምር ሲሆን በህግም ለመጀመሪያ ጊዜ እውቅና ተሰጥቶታል። 20ሺህ ካ.ሜ የተሰጠውም ያለውን ትልቅ አገልግሎት ታይቶ ነው።

በሌላ መንገድ ደግሞ ይሄንኑ የተሰጠውን ቦታ ታሳቢ ተደርጎ የአምስት አመት እስትራቴጂ እቅድ ተዘጋጅቷል። በዚህ የአምስት አመት እቅድ ውስጥ ለሀገርም ለቤተእምነቶችም፤ ለህብረቶችም የሚያገለግል ትልልቅ የትኩረት መስኮች እና ግቦች የተለዩበት ነው።

ይሄንን ወደ ተግባር ለመቀየር የግድ እነዚህ የተሰጡ ቦታዎች ላይ ተቋማዊ የሆነ ግንባታ ማካሄድ ይኖርብናል።

በሌላ በኩል ይሄንን ታሳቢ ተደርጎ የተሰጠ ቦታን አናስረክብም ማለት ይሄ ከህግ ውጪ ነው ህጋዊ አይደለም መከልከልም አይችሉም ይጉም አይፈቅድላቸውም። ማጓተት ደግሞ የበለጠ ዋጋ ያስከፍላል።

ዶ/ር ጣሰው ገብሬ
የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ም/ፕሬዝደንት
#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!

ይሄ ለኔ የሚያሳየኝ አሁንም ቢሆን የወንጌላውያን አማኞች ያላቸውን መብት እና ያላቸውን ነጻነት በአግባቡ እንዳይጠቀሙ ለመገደብ የሚፈልጉ አስፈጻሚ አካላት ያሉ ነው የሚመስለው።

መብታችሁ ነው ግን ይሄ ያልተወሰነው በዚህ ምክንያት ነው የሚል ምክንያት በግልጽነት መስጠት እንጂ እንዲሁ በደፈናው ጉዳዮችን ከቢሮ ቢሮ፤ ከሃላፊ ሃላፊ ማንከባለል እኔ የእምነት ነጻነትን ለመገድብ የሚደረግ ግልጽ ያልሆነ የአስፈጻሚዎች ድብቅ ሃሳብ ይመስለኛል።

ቄስ ዶ/ር አያሌው ተሰማ
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያን ካውንስል የስነ መለኮት ግብረ ሃይል መሪ
#መብት_ልመና_የለውም #የካውንስሉ_ቦታ_ይመለስ #ካውንስሉ_የጋራ_ድምጻችን_ነው!!!

ውድ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ቤተሰቦች ካውንስሉ ከሰሞኑ ተሰቶት የነበረው 20ሺህ ካሬ ቦታ የሚመልከታቸው አካላት ሊያስረክቡን ፍቃደኛ እንዳልሆኑ አሳውቀን እንደነበር ይታወሳል።

ጉዳዩን በተመለከተ የካውንስሉ የቦርድ አባላት እና የቤተክርስቲያን መሪዎች አነጋግረን
የነበረ ሲሆን ምላሻቸውን እንደሚከተለው ይዘንላችሁ ቀርበናል።
https://youtu.be/Fq8-DQAW6Lw
#ካውንስሉ_በሀዋሳ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ ካውንስሉ በአዋጅ መቋቋም አስመልክቶ ለቤተ እምነት መሪዎችና ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም አካሄደ።

በፕሮግራሙም የካውንስሉ አባል ቤተ እምነቶች የተገኙ ሲሆን ቀጣይ በጋራ የሚሰሩበትንም አደረጃጀት ፈጥረዋል።
#ካውንስሉ_ድጋፍ_አደረገ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያን ካውንስል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ ለስድስት የምገባ ማዕከላት እና በአማራ ክልል አጣዬ ከተማ ለሚገኙ ተረጂዎች የአልባሳት ደጋፍ አደረገ ።

ካውንስሉ አባል ቤተ እምነቶችን በማስተባበር ቀጣይ የድጋፍ ስራዎችን እንደሚያደርግም የተነገረ ሲሆን ተመሳሳይ ድጋፎችንም በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰበታ ከተማም አድርጓል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ካውንስሉ እና #ብልጽግና?????
ከሌላው የተለየ አልተደረገልንም ፤ የእኛም ጥያቄ የፍትህ ነው፡፡
#ፓስተር_ጌትነት_ለማ -የካውንስሉ ጽ/ቤት ሃላፊ
🔥2
#ካውንስሉ_በደቡብ_ኢትዮጵያ_በክልል_ደረጃ_ተዋቀረ
#ከጥር_12_ቀን_2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት በተደረገው የካውንስሉን የቅርንጫፍ ጽ/ቤት የማደራጀት መርሀ ግብር
1. የባቱ ዙሪያ
2. የዝዋይ ከተማ
3. ምዕራብ አርሲ
4. ሻሽመኔ ከተማ
5. የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
6. የሆሳዕና ከተማ
7. የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል
8. የወላይታ ዞን ከተማ ካውንስል
9. የጋሞ ዞን ካውንስል

10. የአርባምንጭ ከተማ ካውንስል የተደራጀ ሲሆን በሁሉም ስፍራዎች የካውንስሉ አባላት የተገኙ ሲሆን በአደረጃጀቱ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዚዳንት እና የካውንስሉ ስራ አስፈጻሚና ቦርድ አባል ፖስተር ጻዲቁ አብዶ እንዲሁም የካውንስሉ ጽ/ቤት ኋላፊ ፖስተር ጌትነት ለማና የካውንስሉ አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ፖስተር አሸብር ከተማ እና ከካውንስሉ አባል ቤተ እምነቶችና ሕብረቶች ተወካዮች በመርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል።

#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
4👍2