የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.3K photos
132 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!

እኛ ጥያቄ አቅርበናል በህጋዊ መንገድ የይዞታ ማረጋገጫ ስለተሰጠን ቦታውን ላመስጠት ፍቃደኛ አይደለንም የሚል አካል ህጋዊ መሰረት የለውም።

ዶ/ር ኢያሱ ኤልያስ
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዝደንት
#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!

ኢትዮጵያ የሁላችን አገር ናት ስንል በምክንያት ነው፡፡ በህገ መንግስቱ የተሰጠንን መብታችንን ማንም ሊቆርስብንና ሲፈልግ ሊሰጠን ሲያሻው ደግሞ ሊከለክለን አይችልም፡፡ ካውንስሉ በህግ የተቃቋመ ተቋም እንደ መሆኑ መጠን ከሚወክላቸውን ቤተ እምነቶችና ሕብረቶች ቁጥር አንጻር ሲታይ ይህ ግዙፍ ተቋም መብቱ ሊከበርለትና ጥያቄው በህግ እና በአግባቡ ሊመለስለት ይገባል ብለንም እናምናለን፡፡

በዚህ ምክንያት መብታችንን ለመጠቀም የማንንም ደጅ መጥናት አስፈላጊ አይደለም።

መጋቢ ጌትነት ለማ
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጽ/ቤት ሐላፊ
#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!

ይሄንን ጉዳይ እኛ በካውንስሉ ውስጥ መሪዎች ብለን ለሰየምናቸው ሰዎች ብቻ የምንተወው ጉዳይ አይደለም። ምክንያቱም ሁላችንንም የሚወክል ካውንስል ስለሆነ ስለዚህ በቀዳሚነት በሚያስፈልግ ነገር ሁሉ ከካውንስሉ ጋር መቆም አለብን። በሌላ በኩል ምዕመናን በሙሉ በሚጠቀሙት የተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገጽ "ፍትህ ይሰጠን" "የተሰጠን ቦታ በህጋዊ ይመለስልን" በማለት በሰላማዊ መንገድ ሊጠይቁ ይገባል።

ቢሾፕ ዳዊት ሞላልኝ
የፌይዝባይብል ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን መሪ እና አገልጋይ
#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!

ስልጣን ላይ የተቀመጠው የትኛውም መንግስት በህዝብ የተሾመ ነው። የተሾመው ደግሞ ህዝብን ለማገልገል ነው። ይህን ለማስፈጸም የትኛውም የመንግስት መዋቅር ውስጥ የተቀመጡ ሃላፊዎች ህዝብን ያለ ምንም አድሎ በእኩልነት ማገልገል ይኖርባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ አባይ ሚዛን አጸያፊ ነው እንደሚል የትኛውም ነገር የእግዚያብሄርን መንግስት ተገዳድሮ ማስቆም አይችልም።

ሪቨረንድ አማኑኤል ቶማስ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስተ ክርስቲያናት ካውንስል ቦርድ አባል እና የኢትዮጵያ የፈቅር ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ጠቅላይ ጸሐፊ
#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!

ጊዜ ይወስድብናል እንጂ ይሄንን ነገር ከማግኘት አንጻር ምንም የሚያጠራጥረን ነገር የለም። ካውንስሉ በሀገር አቀፍ ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ይወክለናል ብለን በአዋጅ የተቋቋመ ተቋም ነው። ስለዚህ የተለያዩ አብያተክርቲያናት መሪዎች እና ምዕመናን የሚወክለን ተቋም እንደመሆኑ መጠን በተለያየ መንገድ ድምጻችንን ልናሰማ ይገባል።

መጋቢ ታምራት ታሪኩ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስተ ክርስቲያናት ካውንስል የቦርድ አባል እና የኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን ፕሬዝደንት
#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!

ነብይ መስፍን ገ/እግዚአብሔር
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል የቦርድ አባል

ሐዋሪያ ዳንኤል ጌታቸዉ
የሕያው ተስፋ ቤተክርስቲያን መስራች እና ባለራዕይ

ሐዋሪያ ሊዊ ጆይ
የኪንግደሞ ግሎሪያ መስራች እና ባለራዕይ
#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ሁላችንንም የሚወክል ጥላ ነው። ሁላችንም ከካውንስሉ ጎን ልንቆም እና ልንደግፍ ይገባል። ኢትዮጵያ ውስጥ የምትገኙ ሁላችሁም አንድ ሆነን የእግዚያብሄርን ስራ እየሰራን መብታችንን እናስከብራለን ግዴታችንንም እንወጣለን!!!

መጋቢ እሸቱ ወርቄ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስተ ክርስቲያናት ካውንስል የቦርድ አባል እና የኢትዮጵያ ፔንቴኮስታል አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዝደንት
#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!

ይህ በአጭሩ አድሎን ነው የሚያመልክተው። በቢሮ ሃላፊነት ላይ የሚገኙ ሰዎች ይሄንን ጉዳይ በአጭሩ መቋጨት የሚችሉት ነው ምክንያቱም በህግ የተፈቀደ እና የተወሰነ ነው

ደግሞም ይሄ የልመና ጉዳይ ሳይሆን ካውንስሉ የብዙ አብያተክርስቲያናት ተወካይ ስለሆነ ይሄ ቦታ የሚገባው ነው

ቢሾፕ ሂሩይ ጸጌ
የመከር የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ፕሬዝደንት
#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!

በጣም ነው የሚያሳዝነው ካቢኔ ወስኖ የተፈቀደን መሬት የተወሰኑ ግለሰቦች በየቢሮው በማመላለስ በወንጌላውያን አማኞች ላይ እየተደረገ ያለው ጫና በእውነት በእጅጉ የሚያሳዝን እና የሚይሳፍር ነው

የወንጌላውያን አማኝዕች ወደ 30ሚሊዮን የምንጠጋ ቁጥራችን ብዙ የሆንን ነን። የወንጌላውያን አማኞች ሁል ጊዜ እንደ ሁለተኛ ዜጋ መታየት የለባቸውም። አሁንም ቢሆን የጋራ ድምጽ ላይ ከልዩነት ይልቅ አንድነት ላይ መስራት ይጠበቅብናል።

ሐዋሪያ ታምራት ታረቀኝ
#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!

ቢሾፕ ፍጹም ወ/አረጋይ
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል የቦርድ አባል እና ከሬማ የእምነት አገልግሎት

ነብይ ምህረት
(የትንሳኤ ወንጌል አለምአቀፍ ቤ/ክ)
#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!
ነብይ ሄኖክ መንግስቱ
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል የቦርድ አባል
ነብይ ሄኖክ ግርማ
#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!

ሐዋሪያ ብስራት ብዙአየው
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል የቦርድ አባል እና ከኒው ክሬዬሽን አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን

ነብይ እዬብ
(ኦኘን ዶር አለምአቀፍ ቤ/ክ)
#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!

ነብይ እዩ ጩፋ
ከክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን

ሪቨረንድ ተዘራ ያሬድ
ከክብር ህይወት ቤተክርስቲያን
#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!

በካቢኔ ውሳኔ ተሰቷል ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ ሊሰጠን የሚገባ ቦታ ሁሉ በስም ቦታው ተጠቅሶ እስኪነገር ድረስ ግልጽ የሆነ ነበረ። ነገር ግን በበላይ እና በወሳኝ አካል ከተወሰነ በኋላ አስፈጻሚው አካል ጋር ሲደርስ የሚያስፈጽመው አካል በካውንስሉ ላይ መጉላላትን ፈጽሟል።

ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ም/ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዝደንት
#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ሁላችንም ደስ ብሎን በጋራ በ2012ዓ.ም ያቋቋምነው ተቋም ነው። በቅድሚያ ለዋና ጽ/ቤት እና ለተለያዩ አገልግሎቶች እንዲውል በካቢኔ 20ሺህ ካ.ሜ ስለተወሰነልን ከልብ እናመሰግናለን። ወደ አፈጻጸም ስንመጣ ግን ላለፉት ጊዜያት ስንጉላላ ነበር። መብት ልመና የለውም መብት መብት ነው

መጋቢ ሰንበቶ ባሻ
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የስራ አመራር ቦርድ አባል እና የህይወት ብረሃን ቤተክርስቲያን ፕሬዝደንት
#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!

ይህ ካውንስል አብያተ ክርስቲያናትን ሁሉ የሚያቅፍ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ አባላትን የሚያገለግል ትልቅ ተቋም ነው። አገልግሎቱ ደግሞ ለሀገር ጭምር ሲሆን በህግም ለመጀመሪያ ጊዜ እውቅና ተሰጥቶታል። 20ሺህ ካ.ሜ የተሰጠውም ያለውን ትልቅ አገልግሎት ታይቶ ነው

በሌላ መንገድ ደግሞ ይሄንኑ የተሰጠውን ቦታ ታሳቢ ተደርጎ የአምስት አመት እስትራቴጂ እቅድ ተዘጋጅቷል። በዚህ የአምስት አመት እቅድ ውስጥ ለሀገርም ለቤተእምነቶችም፤ ለህብረቶችም የሚያገለግል ትልልቅ የትኩረት መስኮች እና ግቦች የተለዩበት ነው

ይሄንን ወደ ተግባር ለመቀየር የግድ እነዚህ የተሰጡ ቦታዎች ላይ ተቋማዊ የሆነ ግንባታ ማካሄድ ይኖርብናል።

በሌላ በኩል ይሄንን ታሳቢ ተደርጎ የተሰጠ ቦታን አናስረክብም ማለት ይሄ ከህግ ውጪ ነው ህጋዊ አይደለም መከልከልም አይችሉም ይጉም አይፈቅድላቸውም። ማጓተት ደግሞ የበለጠ ዋጋ ያስከፍላል።

ዶ/ር ጣሰው ገብሬ
የኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ም/ፕሬዝደንት
#ካውንስሉ_የጋራ_ድምጽ_ነው!!!
#በካቢኔ_የተፈቀደልን_20ሺህ_ካ.ሜ
#የተወረሱ_የቤተእምነት_የጸሎት_ቦታዎች_ይመለስልን!!!

ይሄ ለኔ የሚያሳየኝ አሁንም ቢሆን የወንጌላውያን አማኞች ያላቸውን መብት እና ያላቸውን ነጻነት በአግባቡ እንዳይጠቀሙ ለመገደብ የሚፈልጉ አስፈጻሚ አካላት ያሉ ነው የሚመስለው።

መብታችሁ ነው ግን ይሄ ያልተወሰነው በዚህ ምክንያት ነው የሚል ምክንያት በግልጽነት መስጠት እንጂ እንዲሁ በደፈናው ጉዳዮችን ከቢሮ ቢሮ፤ ከሃላፊ ሃላፊ ማንከባለል እኔ የእምነት ነጻነትን ለመገድብ የሚደረግ ግልጽ ያልሆነ የአስፈጻሚዎች ድብቅ ሃሳብ ይመስለኛል።

ቄስ ዶ/ር አያሌው ተሰማ
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያን ካውንስል የስነ መለኮት ግብረ ሃይል መሪ