YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#ሰበር ዜና

#የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩት የኢንጂነር ስመኘው በቀለን አሟሟት እና የሰኔ 16 የቦምብ ጥቃት ምርምራን በተመለከተ ሊሰጥ የነበረው ጋዜጣዊ #መግለጫ #ተሰረዘ

#መግለጫ የተሰረዘው የፌደራል ጠቅላይ ዋና አቃቤ ህግ አቶ #ብርሃኑ ጸጋዬ አስቸኳይ ስራ ስላጋጠማቸው ነው ተብሏል።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አንድ ባልደረባ ለዲ ደብሊው እንደተናገሩት ጠቅላይ አቃቤ ህጉ “አስቸኳይ ስራ ስላጋጠማቸው ወደ ሌላ ቦታ በመሄዳቸው መግለጫው ለሌላ ጊዜ ተላልፏል።” መግለጫው ለሌላ ጊዜ መተላለፉ ቢነገርም ቁርጥ ያለ ቀን ግን አልተነገረለትም።

#በዛሬው መግለጫ የኢንጂነር ስመኘው አሟሟት እና ከሰኔ አስራ ስድስቱ ቦምብ ፍንዳታ በተጨማሪ በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ማብራሪያ እንደሚሰጥ ተገልጾ ነበር።

#ዛሬ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ላይ በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት ሊሰጥ ታቅዶ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫው ጊዜ ሲዘዋወር የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። በነሐሴ 25 ቀን 2010 ዓ. ም. ይሰጣል ተብሎ የነበረው መግለጫ ወደ ዛሬ ጳጉሜ 1 መተላለፉ ይታወሳል።

ምንጭ ፦ DW
@YeneTube @Mycase27
#በዛሬው ዕለት ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባውን የኦሮሞ ነጻነት ግምባር ኦነግ አባላትና አመራር ቡድንን ለመቀበል ህዝቡ #በመስቀል አደባባይ ተሰባስቧል።

ከንጋቱ ጀምሮ ከአዲስ አበባ እና በዙሪያዋ ከሚገኙ ከተሞች ቁጥሩ ከፍ ያለ ነዋሪ ለአቀባበል ስነ ስርዓቱ መስቀል አደባባይ ተገኝቷል።
@yenetube @mycase27
#በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የሚገኘውና በሺዎች የሚቆጠሩ የክልሉ ንጹሀን ዜጎች #የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ይፈጸምበት ነበር የተባለውን ኦጋዴን ተብሎ የሚጠራው #ማእከላዊ ማረሚያ ቤት #በዛሬው እለት ተዘጋ ፡፡

የሶማሌ ክልል መንግስት በአሁኑ ጊዜ ትኩረት ሰጥቶ እየወሰደ ከሚገኘው የለውጥ እርምጃዎች መካከል ባለፉት አመታት በክልሉ ህዝብ ላይ ሲፈጸሙ የነበሩትን የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቅረፍ ዋነኛው ነው፡፡

📌የክልሉ መንግስት ካቢኔ ከትላንት ወዲያ ባካሄደው ስብሰባ በክልሉ ባለፉት አመታት በሺዎች የሚቆጠሩ የክልሉ ንጹሀን ዜጎች የሚታጎሩበትና በህዝቡ ላይ ከፍተኛ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች ይፈጸምበት የነበረ ነው በሚል በጅግጅጋ ከተማ የሚገኘውን ማእከላዊ ማረሚያ ቤት እንዲዘጋ ወስኗል፡፡

በዚህ መሰረት በዛሬው እለት በክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ የሚመራ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፤ ታዋቂ ግለሰቦች ፤ ሙሁራን እንዲሁም ለረጅም አመታት በተለያዩ የአለም ክፍሎች በመዟዟር በክልሉ የሚፈጸሙትን የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶችን ሲቃወሙና ሲታገሉ የቆዩት አክቲቪስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች አቶ #አብዱላሂ ሁሴንና አክቪስቲስት #አብዱረሺድ አሊ ሸአ በተገኙበት ማረሚያ ቤቱ በዛሬው እለት በይፋ #ተዘግቷል፡፡

በዛሬው እለት የተዘጋው የጅግጅጋ ከተማ ማእከላዊ ማረሚያ ቤት የሚገኙ እስረኞች ህጉን መሰረት በማድረግ እንደሚለቀቁም ከክሉ መንግስት ለኢቢሲ የተላከው መግለጫ ያለክታል፡፡

📌የኦጋዴን ነፃ አውጭ ግንባርም በትዊተር ገፁ እንዳስታወቀው የማሰቃያ ማዕከሉን መንግስት ለመዝጋት መወሰኑ መልካም እርምጃ ሲል በትዊተር ገፁ አወድሶታል፡፡
©ebc
@yenetube @mycase27